You are on page 1of 4

የዋቢ ጽሁፎች አጻጻፍ(Reference Citation)

አራት አይነት የአጻጻፍ ስልቶች አሉ፡-

1. የሀርቫርድ አጻጻፍ ስልት (Harvard System of Reference)


2. የ “APA” አጻጻፍ ስልት(APA format - American Psychological Association)
3. የ “MLA” አጻጻፍ ስልት (MLA style – Modern Language Association)
4. የቺካጎ ማንዋል(The Chicago Manual of style)

ምሳሌዎች፡-

1. የሀርቫርድ አጻጻፍ ስልት (Harvard System of Reference)


- አለም እሸቱ (1992) መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አጻጻፍ፡፡ አዲስ አበባ፣ የቅድስተ
ማርያም ኮሌጅ የሊበራል አርትስ ፋካሊቲ ህትመት፡፡
- Seyler, Dotothy U. (1993) Doing Research: The Complete Research
Paper Guide. New York: McGraw-Hall,Inc.

2. የ “APA” አጻጻፍ ስልት(APA format - American Psychological Association)


- አለም እሸቱ፡፡(1992)፡፡መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አጻጻፍ፡፡ አዲስ አበባ፣ የቅድስተ
ማርያም ኮሌጅ የሊበራል አርትስ ፋካሊቲ ህትመት፡፡
- Seyler, Dotothy U. .(1993). Doing Research: The Complete Research
Paper Guide. New York: McGraw-Hall,Inc.

3. የ “MLA” አጻጻፍ ስልት (MLA style – Modern Language Association)


- አለም እሸቱ፡፡ መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አጻጻፍ፡፡ አዲስ አበባ፣ የቅድስተ ማርያም
ኮሌጅ የሊበራል አርትስ ፋካሊቲ ህትመት፣1992፡፡
- Seyler, Dotothy U. Doing Research: The Complete Research Paper
Guide. New York: McGraw-Hall,Inc.,1993.

4. የቺካጎ ማንዋል(The Chicago Manual of style)


- አለም እሸቱ፡፡1992፡፡መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አጻጻፍ፡፡ አዲስ አበባ፣ የቅድስተ
ማርያም ኮሌጅ የሊበራል አርትስ ፋካሊቲ ህትመት፡፡
- Seyler, Dotothy U. .1993. Doing Research: The Complete Research
Paper Guide. New York: McGraw-Hall,Inc.

1
በዋቢ ጽሁፍ አጻጻፍ ጊዜ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች

ሀ. መጻህፍት

- ሁለት የውጪ ሀገር ደራስያን ከሆኑ መጽሐፉን የጻፉት የሁለተኛው ደራሲ ስም


በመጽሐፉ ላይ በተቀመጠው መልኩ ይሰፍራል፡፡
- ሶስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ደራስያን ከሆኑ መጽሐፉን የጻፉት የመጀመሪያው ሰው
ስም ብቻ ከተጻፈ በኋላ ኮማ(,) ተደርጎ ‘et al’ ተብሎ ይጻፋል፡፡ መጽሐፉ አማርኛ
ከሆነ ደግሞ “… እና ሌሎች” ተብሎ ይሰፍራል፡፡
- በአንድ ደራሲ የተጻፉ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መጻሕፍት ሲጠቀሱ
ከመጀመሪያው ውጪ ያሉት መጸሕፍት በሚሰፍሩበት ጊዜ የደራሲው ስም ቦታ ላይ
“ዳሽ” ተደርጎ ይተዋል እንጂ ስሙ አይጻፍም፡፡
- ተተርጉሞ የቀረበ መጽሐፍ በመዘርዝር ላይ ሲሰፍር ከመጽሐፉ ርዕስ ቀጥሎ በቅንፍ
ውስጥ የተርጓሚው ስም ይጻፋል፤ ትርጉም መሆኑንም ይገለጻል፡፡

ምሳሌ፡- ቤላዬቭ አሌክሳንደር (1986) ኢህቲአንድር፡፡ (ተርጓሚ ተስፋዬ ለማ) ሞስኮ፣


ራዱጋ አሳታሚ ድርጅት፡፡
 መጽሐፉ በእንግሊዝኛ የቀረበ ከሆነ የተርጓሚው ስም ከተጻፈ በኋላ
“Full stop(.)” ተደርጎ “Trans.” ተብሎ ይጻፋል፡፡
- በአርታኢ(ኤዲተር) ስም የታተመ መጽሐፍ ወይም መድበል በመዘርዝር ላይ ሲሰፍር
የአርታኢው ስም ከተጻፈ በኋላ በቅንፍ ውስጥ “ዓኢ” ወይም ደግሞ በእንግዚእኛ
የቀረበ ከሆነ “Ed./Esd.” ተብሎ ይጻፋል፡፡

ለ. በመድበል ውስጥ የተጠቃለለ መጣጥፍ(Article) አጻጻፍ

ምሳሌ፡- Espin, Ch. A. (1998) “Curriculum Based Measurement for Secondary


Students” In Mark, R. Shinn (Ed.), Advanced Application of
Curriculum-Based Measurement. (pp 214 – 253). New York: The
Guilford press.

ማስታወሻ፡- አንዳንድ ጊዜ መድበሉ የተጠናቀቀበትና መጣጥፉ የተጻፈበት ዓመተምህረት


ሊለያይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱም ዓመተምህረቶች መየስፍራው መጻፍ
አለባቸው፡፡

ሐ. የጥናታዊ መጽሔት ወይም የጆርናል መታጥፎች


ምሳሌ፡- Philphot, P. (1990) “Two Observation Charts.” The Teacher Trainer. Vol.4,
No. 3, 21-22.
ፈቃደ አዘዘ (1984) “አፋዊ ኪነተቃል” የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ መጽሔጽ፡፡
ቅጽ 1፣ ቁጥር 2፣ 3-25፡፡

2
መ. የመጽሔት መጣጥፎች
ምሳሌ፡- ኃይሉ ገ/ዮሃንስ ፡፡1992፣ ጥር፡፡ “አማራው ክርስቶስ” ፡፡ ኢትኦጵ፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 8፣
ገጽ 33- 36፡፡
 የመጽሔቱ ስም ከመጣጥፉ አቅራቢ ስም የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ
ከተገኘ ወይም ርዕሰ አንቀጹን ብቻ ከተጠቀምን እንደሚከተለው
ባጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል፤
ኢትኦጵ፡፡ 1992፡፡ ጥር፡፡

ሠ. የጋዜጣ መጣጥፎች
ምሳሌ፡- ጌታቸው ሰናይ፡፡ 1994፣ መስከረም 1፡፡ “ህይወታዊ ሀብትን መንከባከብ ለባህላዊ
እሴት ጥበቃ”፡፡ አዲስ ዘመን፣ ገጽ 14፡፡
ወይም ባጭሩ፡-
አዲስ ዘመን፡፡1994፡፡ መስከረም 1

ረ. አውደ ጥበባት(Encyclopaedia)

ምሳሌ፡- Language. 1967ed. The World Book of Encyclopaedia.

ሰ. የደራሲ ስም ያልተጠቀሰባቸው መጻሕፍትና መጣጥፎች

- ርዕሱ በደራሲው ቦታ ይጻፋል፡፡


ምሳሌ፡- ሙዚቃ፣ ውዝዋዜና ተውኔት በኢትዮጵያ፡፡ 1968፡፡ አዲስ አበባ፣ ንግድ
ማተሚያ ቤት
የአመት በዓል ገበያ፡፡ 1994፣ መስከረም 1፡፡ አዲስ ዘመን፣ ገጽ 1፡፡

ሸ. ዓመተ ምህረት ያልተጠቀሰባቸው መጻሕፍት

ምሳሌ፡- ዳዊት ወልደጊዮርጊስ(ዓ.ም ያልተጠቀሰ)፡፡ የደም እንባ፡፡ (ተርጓሚ ደበበ እሸቱ)፣ አዲስ
አበባ፣ ቦሌ ማተሚያ ቤት፡፡
 መጽሐፉ በእንግሊዝኛ የቀረበ ከሆነ ከደራሲው ስም ቀጥሎ በቅንፍ
ውስጥ “undated” ተብሎ ይጻፋል፡፡

ቀ. ያልታተሙ ጽሁፎች እና መጣጥፎች


- የመጽሐፉ ርዕስ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ይቀመጣል እንጂ ከስሩ አይሰመርበትም
ምሳሌ፡- ዮናስ አድማሱ እና ሌሎች (1966) “አማርኛ ለኮሌጅ ደረጃ የተዘጋጀ”፡፡ አዲስ
አበባ፣ ቀ.ኃ.ሥ. ዩኒቨርሲቲ፡፡

3
በ. የዲግሪ ማሟያ ጽሁፎች

ምሳሌ፡- ታሪኩ ፋንታዬ (1988) “ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ያላቸው


አመለካከት” ያልታተመ የአርትስ ማስተርስ ዲግሪ ማሟያ ጽሑፍ፣ አ.አ.ዩ፡፡
 ጽሁፉ የቀረበው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከሆነ፡-
‘Unpublished M.A Thesis’ ተብሎ ይጻፋል፡፡

You might also like