You are on page 1of 3

ክርስትያናዊ ስነጽሑፍ

ስነጽሑፍ ምንድነው?

በስነ ጽሑፍ ተመራማሪዎች ዘንድ ሥነጽሑፍ የሚለውን ቃል ለመተርጎም ከባድ ነው ይላሉ። ለዚህ ምክንያቱ
በሚሰጠው ሰፊ የትርጓሜ ዘውግ የተነሳ ነው። ለምሳሌ የተጻፈ ነገር በሙሉ ስነጽሑፍ ይባላል የሚሉ አሉ። ይህ ሰፊው
የስነጽሑፍ ትርጉም/ ብያኔ ይባላል። ለነዚህና ሰዎች የተጻፈ ነገር በሙሉ ስነ ጽሑፍ ነው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው
Litrature የሚለው ቃል አመጣጥ ነው። የእንግሊዘኛው ቃል የመጣው 'Littera፣ሊተራ' ከሚል የላቲን ቃል ሲሆን
ትርገሙ ፊደለ፣ ሆሄ፣ ጽሕፈት ማለት ነው። ስለዚህ የተጻፈ ነገር እስከተጻፈ ድረስ ብቻ ስነጽሑፍ ነው ይላሉ።
በተቃራኒው ደግሞ እንደፉከራና ቀረርቶ ያሉ ቃላዊ ሃብቶች እና ቅድመ ጽሕፈት የነበሩ ቃላዊ ባህሎች ደግሞ
አልተጻፉምና ከስነጽሑፍ ገብተው መቆጠር የለባቸውም። በዚህ ብያኔ ወሳኙ መስፈርት የመጻፍ እና ያለመጻፍ ጉዳይ
ነው።

በዚህ ሌላኛው ጽንፍ ያሉ ምሑራን ደግሞ ለስነ ጽሑፍ መስፈርት ሊሆን የሚገባው ውበት እንጂ መጻፍ አለመጻፍ መሆን
የለበትም ባይ ናቸው። ለነርሱ ነገረ ውበታዊ ልህቀት (Aesthetic Excellence) ወሳኝ ነገር ነው። Litrature ለሚለው ቃል
የአማርኛ አቻው ስነ ጽሑፍ መሆኑ ለዚህ የሚያመላክተው ነገር አለ። ሥን ማለት ያማረ የተስተካከለ ማለት ነውና።
ስለዚህየተጻፈ ነገር ከስነ ጽሑፍ ለመቆጠር አንዳች ዓይነት ውበት ሊኖራቸው ይገባል ይላሉ። ውበት ግን አንጻራዊ ነውና
ሊያግባባ የሚችል መስፈርት አልሆነም። ይህ ጠባብ ትርጉም/ብያኔ በዋናነት ልቦለድ፣ ቴአትር እና ሥነ ግጥም ላይ
ሲያተኩር አንዳንዴ ግን ደብዳቤዎቼ፣ ግለ ታሪኮች፣ ማስታወሻዎች(Memoirs) እና ዲያሪዎች እንደሥነጽሑፋዊ
ውበታቸው ታይተው ይካተታሉ።

በቅርብ ጊዜ የመጡ ትርጓሜዎች ደግሞ አፋዊ ስነ ቃሎችን አንድም በውበታቸው አንድም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
እየተሰበሰቡና እየተጻፉ በመምጣታቸው ምክንያት ከስነ ጽሑፍ ሲቆጥሯቸው ይታያሉ።

ለስነ ጽሑፍ እድገት ያበረከቱ መሰረታዊ ነገሮች

1. የጽሑፍ ብልሃት መመስረት

የቤተ ክርስቲያን ምሑራን የጽሑፍ ብልሃት የተጀመረው በአዳም የልጅ ልጅ በሄኖስ እንደሆነና እግዚአብሄር በጸፍጸፈ
ሰማይ ለሄኖስ አሌፋት የሚባሉትን ሃያ ሁለቱን ፊደላት ቀርጾ እንዳሳየው ያስተምራሉ። መዝ 118፤ ሰቆቃወ ኤርምያስ
በዚህም ቀጥቶ የመጀመሪያውን መጽሐፍ የጻፈው ሄኖክ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነበር። በዚህም ቋንቋ ና ስነ ጽሑፍ
ዘፈቀዳዊ ነው የሚለውን የሳይንሱን አመለካከት ይቃወማሉ።

በኋላ በባቢሎናውያን ዘመን ቋንቋ እስኪደበላለቅ ድረስ የነበረው ይህ የአጻጻፍ ስርዓት ሲሆን በኋላ ግን እንደየቋንቋው
የተለያየ ሆኗል።

በሳይንስ ግን የጽሑፍ ብልሃት የተጀመረው በባቢሎናውያን የንግድ ሥራ መቀላጠፍ እንደሆነ ይናገራሉ። በዚህም
ምክንያት ገቢና ወጪያቸውን በቃል መያዝ እየከበዳቸው ሲመጣ በሸክላ ሰሌዳ ላይ መጻፍ እንደጀመሩ ይተረካል።

2. የወረቀት መፈጠር

ከወረቀት በፊት እንደሸክላ ሰሌዳ፣ ፓፒረስ እና እንደብራና ያሉ መጻፊያ መሳሪያዎች ቢያገለጎሉም ጻይ ሉን(Cai lun)
የተባለ ቻይናዊ በ 3 መክዘ ቅልክ ወረቀትን እስኪፈበርክ ድረስ ግን ስነ ጽሑፍ አልተስፋፋም ነበር።

3. የማተሚያ ማሽን መፈጠር


በ 15 ኛው መክዘ ዮሐንስ ጉተንበርግ የተባለ ጀርመናዊ ዘመናዊ የማተሚያ ማሽን እስኪፈበርክ ድረስ መጻሕፍት በጥቂት
ባለሃብቶች ዘንድ ብቻ የሚገኝ ነገር ነበር።

*የስነ ጽሑፍ መነሻ ስነ ቃል ነው። አብዛኛዎቹ የተጻፉ ነገሮች አስቀድሞ በአፍ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፉ የተበሩ
ናቸው። ለምሳሌ የሆሜር ኢልያድ እና ኦዲሴ የአባ ዮሐንስ ከማ ገድለ ተክለሃይማኖት

በዓለም የሥነጽሑፍ ታሪክ ላይ የሃይማኖቶች ተጽዕኖ በተለይ ደግሞ የክርስትና ተጽዕኖ ትልቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን
በተለያየ ምክንያት እንደ ስነጽሑፍ ለመቀበል የሚቸግራቸው ሰዎች ቢኖሩም በዓለም ስነጽሑፍ ላይ ከባድ ተጽዕኖ
ያሳረፈው የመጽሐፍ ቅዱስ መታተም እንደሆነ ክርስቲያን ያልሆኑትም ጭምር ይመሰክራሉ።

ክርስትያናዊ ስነጽሑፍ - ክርስትያናዊ አስተምህሮዎች፣ ጭብጦች እና ማመሳከሪያዎች ያሉት መሆን አለበት።


በአብዛኛው አሊጎሪ ሲጠቀም መሰረታዊው ጉዳይ ግን ስነ ውበታዊ የሆነውን መንገድ ሳይለቅ ክርስቲያናዊ መልዕክቶች
ማስተላለፉ ነው። በአጠቃላይ በአራት ክፍል መክፈል ይቻላል።

ኢ- ልቦለድ

ይሄ በአብዛኛው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የስነ ጸሑፍ ዘውግ ሲሆን መልዕክቶችን(Letters)፣ የመጽሐፍ ቅዱስ
ማብራሪያ ትርጓሜዎችን(Commentaries)፣ መዝሙሮችን እና ጸሎቶችን(Hymns and Prayers)፣ ወደጽሑፍ
የተገለበጡ ስብከቶችን(የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ትምሀርቶች ማየቶ ይቻላል) ያካትታል።

ልቦለድ

ከኢልቦለድ አንጻር ሲታይ በቤተክርስቲያን ምንም ያልተሰራበት የስነ ጽሑፍ ዘውግ ቢኖር ልቦለድ ነው። የውጪ ሃገር
ደራስያን ክርስትያናዊ የሆኑ ጭብጦችን በልቦለዳቸው ውስጥ ቢያካትቱም መጻሕፍቱ ግን ለመንፈሳዊ ዓላማ ተብለው
የተጻፉ አይደሉም። እንደዚያም ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ልቦለዶች
እየታተሙ ነው። በዚህ ረገድ በኛ ቤተክርስቲያን የተሻለ ነገር ይታያል። ከስንት አንዴም ቢሆን ረዥም እና አጫጭር
መንፈሳዊ ልቦለዶች ይታተማሉ።

ግጥም

ውበትን እና ስልተ ምትን አስተባብሮ የያዘው ግጥም በቤተክርስቲያን ውስጥ አንዳንዴ ከዜማ ጋር አንዳንዴ ደግሞ
ለብቻው በስፋት ከተሰራባቸው ዘውጎች ውስጥ አንዱ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሞህራን ቡሉይ ኪዳንን በይዘቱ
ለአራት ሲከፍሉ አንደኛው የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት በሚል ነው። ከእነዚህ መካከል መዝሙረ ዳዊት፣ መጽሐፈ
ኢዮብ እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ያሉት መጻሕፍት ከዚህ ከሥነ ግጥም የሚመደቡ ናቸው። እንደ ጸሎተ ማርያም
እና ጸሎተ ስምዖን ያሉትም በግጥም መልክ የተጻፉ ናቸው። በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ክርስትያኖች የሚጠቀሙት
ሥርዓተ ቅዳሴ መዝሙር ነበረው። በካታኮምብ ውስጥ የነበሩ ክርስትያኖችን የተለያዩ መዝሙሮችን ደርሰው ይዘምሩ
ነበር። በቤተክርስቲያን ታሪክ ከሚታወቁ አባቶች መካከል እንደ ከተሰጣቸው ኤፍሬም ሶርያዊ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ
ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ዮሐንስ ዘደማስቆ ያሉት ገጣምያን ነበሩ። በውጪው ዓለም በቅርብ ጊዜ
እንደካሆሊል ጂብራን፣ እንደ ዊልያም ብሌክ፣ እንደኤሚሊ ብሮንት፣ እንደክርስቲና ሮዜቲ እና እንደ ቲኤስ ኢልየት ያሉት
አንጋፋ ገጣምያን መንፈሳዊነት ያጠቃቸዋል።በእኛም ሃገር ከጥንት ከቅዱስ ያሬድ ጀምሮ ለዝማሬ የሚደረሱ
መዝሙሮች፣ ቅዳሴው በራሱለጸሎት የሚያገለግሉት መልክኦች አርኬዎች ወዘተ በግጥም መልክ የሚቀርቡ ናቸው።

የግጥም ዓይነቶች

ተራኪ ግጥም - የራሱ ገጸ ባሕርያት ያሉትና በድርጊት የተሞላ


ምሳሌ ከበደ ሚካእል፣ ጸ.ገ.መ፣ ሼክስፒር፣ አሌክሳንደር ፖፕ፣ፑሽኪን

ሌሪክ - በአብዛኛው የግለሰብ ስሜትና አስተሳሰብ የሚወሳበት

ምሳሌ - አብዛኛዎቹ የዘመናችን ገጣምያን

ኤፒክ - ጀብዳዊና አፈታሪካዊ ረዣዥም ትረካዎች

ሆሜር(ኢልያድና ኦዲሴ)፣ ቨርጂል(ኤኖይድ)፣ The Epic of Gilgamesh

ቧልት (Satirical) እና ሙሾ ( Elegy) -ጎተ(Goethe)፣ ጆን ሚልተን

ተረት(Fable Verse) - ሰውኛ ዘይቤ የሚበዛው በአብዛኛው ለሥነምግባራዊ ጉዳይ የሚውል

ምሳሌ - ኤዞፕ፣ ከበደ ሚካኤል

ድራማ - ቃለ ተውኔቱ በግጥም የተጻፈ ወይ መዝሙር የሆነ ተውኔት

ምሳሌ - ኦፔራ፣ ጸ.ገ.መ

ነጻ ስንኝ

ቲያትር - በመካከለኛው ዘመን አውሮጳ በየቤተክርስቲያኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ይተወኑ ነበር። በ 16 ኛው መክዘ
ደግሞ ሥነ ምግባርን የሚያስተምሩ ተውኔቶች(Morality Plays) ተለመዱ። በ 16 ኛው እና በ 17 ኛው መክዘ ግን
የካቶሊክ ቤተክርስትያን በአውሮጳ ቲአትርን ስላወገዘች መሰራት ተተወ። በኋላ ፕሮቴስንቶቹ መጥተው እንደአዲስ
እስኪጀመሩ ድረስ በአውሮጳ አብያተክርስቲያናት ተውኔት ተከልክሎ ነበር።

በሃገራችን ተውኔት ከሰንበት ትምህርት ቤትና ከማኅበራት መመስረት አረ እየተስፋፋ መጥቷል።

You might also like