You are on page 1of 24

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

2013 ዓ.ም
1
ምዕራፍ አራት

ሥርዓተ ጸሎት

2
1ጸሎት ምንድን ነው
ሀ /ጸለየ ለመነ ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርገሙ ልመና
እና ምስጋና ማለት ነው

‹‹ ጌታ ቅርብ ነው በነገር ሁሉ በጸሎት እና ምልጃ ከምስጋና ጋር


በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች
አትጨነቁ ›› ፊል 4፡-6
‹‹ እሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኃል ደጅ ምቱ ይከፈትላችኃል ›› ማቴ 7፡-7

3
ለ/ ጸሎት ንግግር ነው
‹‹ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርባት መንገድ ናት››

ፍትሐ ነገስት 14

‹‹ ልጅ ከአባቱ ጋር እንደሚጫወት አንተም በጸሎት ከልዑል


እግዚአብሔር ጋር ተጫወት ››

ማር ይስሐቅ

4
ሐ/ ቅጽር ነው

‹‹ የማይጸልይ ሰው ቅጽር የሌላትን ሀገር ይመስላል ››

ፊልክዮስ

መ/ እስትንፋስ ነው
‹‹ መተንፈስ ያቆመ ሰው የሞተ እንደሆነ መጸለይ ያቆመ ሰውም
እንደዛ ነው ›› ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ

‹‹ ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ ›› 1ተሰ 5፡-6


5
ሠ/ መንገድ መሪ ነው
- ምርኩዙን የጣለ ዓይነ ሰውር እና የማይጸልይ ሰው መጨረሻ
አንድ ነው (ፍኖተ አእምሮ )

- ነፍስ የረቂቁን ዓለም እውነታ እንድትረዳ የጸሎት ብርሃንነት


ያስፈልጋታል ( ቅ.ኤፍሬም )

6
2 ለመጸለይ ምን ያስፈልጋል

ሀ/ እምነት

‹‹ አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ ››


ማቴ 21፡-21

‹‹ ከእናንተም አስቀድሞ የነበሩትን እዩ በእግዚአብሔር አምኖ


ያፈረ ማን ነው አብርሐም ነውን ኢዮብ ? ዳዊት? ማን ነው ?››
ሲራ 2፡-10
7
ለ / ንጹሕ ልቦና

‹‹ ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገድህን ይውደዱ›› ምሳ


22፤24

‹‹ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ነው ይቀርባል ከንፈሮቹም ያከብሩኛል


ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው ›› ኢሳ 29፡-11

ሐ/ ይቅር ባይነት
‹‹ የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካከል እንደወደቀ ዘር ነው ›› መጽሐፈ መነኮሳት

‹‹ ቂመኛ ሰው ሥጋ የለበሰ ሠይጣን ነው ›› አረጋዊ መንፈሳዊ


8
3 ሥርዓተ ጸሎት

3.1/ የጸሎት ዓይቶች


ሀ/ የማህበር ጸሎት ፡-ሰዓት አክብረን ፣ በተመጠነ ድምጽ ፣ የህብረት ጸሎቱን
ማድረስ

ለ/ የግል ጸሎት ፡- ለራስ በሚሰማ ድምጽ የሌላውን ሀሳብ ሳይሰርቁ እና


ሳይረብሹ

9
3.2 በጸሎት ጊዜ
ሀ/ ብርሃን ባለበት ቦታ መቆም ወይም ማብራት

ለ/ መቆም
‹‹ በማለዳ በፊትህ እቆማለው እታይህማለው ›› መዝ 5፡-3

- በቤተ ክርስቲያን ወይም በቅዱሳት ሥዕላት ፊት

- ቀጥ ብሎ መቆም

- ወደ ምሥራቅ መቆም

10
ሐ/ እጅን መዘርጋት
‹‹ በለሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ
እግዚአብሔርን ባርኩ ›› መዝ 133፡-2

መ/ ዐይንን ወደ ሰማይ በማቅናት


‹‹ በሰማይ የምትኖር አቤቱ ሆይ ዓይነ ልቦናችንን ወደ አንተ
እንመልሳለን ›› መዝ 122፡-2

ሠ/ ከዕንባ እና ስግደት ጋር
11
4 የጸሎት ክፍሎች
ሀ/ስዕለት
- የተቀበሉትን የጸጋ ሥጦታ ላለማጣት

- የተቀበሉትን ጸጋ ለዓለማው በሥርአት ለመጠቀም

- ያጡትን ለማግኘት

- ከክፉ ነገር ለመዳን መለመን ነው

12
ለ/ አስተብቁዓት
- ስለ ኃጢአት ስለ በደል የሚጸለይ ጸሎት
- ስለ ሞቱ ሰዎች ፣በአካለ ስጋ ስላሉ ሰዎች እና ስለ ራስ ሊጸልዩት
ሊያጸልዩት ይችላሉ

ለምሳሌ ጸሎተ ፍትሐት

ዲድስቅልያ አንቀጽ 341

13
ሐ/ ምስጋና

- ከእናታችን ማሕጸን ጀምሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ጠብቆ


ላቆያን አምላክ

- ስለ ተሰጠን ስጦታ

- የተፈጠርንለት ዓላማ ማመስገን ነው

14
5 የጸሎት ጊዜያት
- ሰባት የጸሎት ጊዜያት አሉን
‹‹ ስለ ጽድቅህም ፍርድ ሰባት ጊዜ አመሰገንከው ››
መዝ 118፡-6
1 ነግህ
- ጠዋት 12 ሰዓት

- ለሊቱን ጠብቆ የማለዳውን ብርሃን እንድናይ ስለረዳን

- አዳም የተፈጠረበት ሰዓት ነውና

- ጌታ በጲላጦስ ዘንድ የተመረመረበት ሰዓት ነውና


15
2 ሠልስት
- ጠዋት 3 ሰዓት

- ሔዋን የተፈጠረችበት

- ዳንኤል ይጸልይበት የነበረ ሰዓት ነው ዳን 6፡-10

- እመቤታችን የመልአኩን የብሥራት ቃል የሰማችበት ሰዓት ነው

- ጌታችን የተገረፈበት ሰዓት ነው

- መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበት ሰዓት ነው

16
3 ቀትር (የስድስት ሰዓት ጸሎት)
- ጸሐይ የምትበረታበት እኛም የምንዝልበት ሰዓት ነውና ለመበርታት

- አዳም ዕጸ በለስን በልቶ የሳተበት ነውና ወደ ፈተና አታግባን ብለን

- ጌታችን የተሰቀለበት ሰዓት ነው

4 ተሰዓት (የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት)


- መላእክት የሰውን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያሳርጉበት ሰዓት ነው

- ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው የለየበት ሰዓት ነው

- ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት


ሰዓት ነው ሐዋ 3፡-1 17
5 ሠርክ ( የ11 ሰዓት ጸሎት )
- ሲሰራ የዋለ ሠራተኛ ሁሉ ዋጋውን ደምወዙን የሚቀበልበት ሰዓት ነውና
በዳግም ምጽአትህ ጊዜ ያለ ዋጋ አታስቀረን ስንል
- ኤልያስ ያቀረበው መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘበት
ሰዓት ነው 1ነገ 18 ፡-36
- ጌታችን ሥጋው ወደ መቃብር የወረደበት ሠዓት ነው
6 ንዋም ( የመኝታ ሰዓት )
- በሰላም ያዋልከን አምላክ በሰላም አሳድረን

- ጌታ በጌቴሴማኔ ሥርዓተ ጸሎትን ያስተማረበት ጊዜ ነው

- የዚህ ዓለም ድካም በሚያበቃበት ጊዜ የዕረፍት ሥፍራ ወደ ሆነች መንግስተ


ሰማያት አስገባን ስንል
18
7 መንፈቀ ለሊት
- ጌታ በከብቶች በረት የተወለደበት

- ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት

- ዓለምን ለማሳለፍ የሚመጣበት ሰዓት ነው

19
ምን እንጸልይ
- ቀኖና ሎዶቅያ አንቀጽ 19

ጸሎተ ዳንኤል እና ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ

- መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ 22

በቀን ቢቻል 30 ዳዊት ባይቻል 10 ጸልዩ

የት እንጸልይ
በመኖሪያ ቤት ፡- የሠልስት የቀትር የተሰዓት የንዋም እና የመንፈቅ

3ቀሌምንጦስ አንቀጽ 47

በቤተ ክርስቲያን ፡- የነግህ እና የሠርክ ጸሎት ( ዲድስቅልያ አንቀጽ 12 20


6 የጸሎት ፈተናዎች
ለምን እንፈተናለን
- ናፍቆታችንን የምናገኝበት መንገድ ነው

‹‹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፈቅ አቤቱ ነፍሴ ወደ አንተ


ትናፍቃለች ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች መቼ እደርሳለሁ
የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ ›› መዝ 41፡-1

- ጸሎት የሌሎች ፈተናዎች መውጫ በር ነው

- አለ መጸለይን የመሠለ ፈተና ለክርስቲያን የለውም


21
ዐበይት ፈተናዎች

1 የጸሎትን ዓለማ አለመረዳት

- ለችግር ጊዜ ብቻ መጸለይ

- የእኛ ፍቃድ ብቻ እንዲሆን መፈለገ

‹‹ ነገሮች ሁሉ አንተ እንደ ምትፈልጋቸው እንዲሆኑ አትመኝ


እግዚአብሔርን እንደሚያስደስቱተ እንጂ ››

22
2 የሀሳብ መበትን

ሀ/ አዘውትሮ መጸለይ

‹‹ በጸሎት ደስ ይበላችሁ በመከራ ታገሡ በጸሎት ትጉ ›› ሮሜ 12፡-12

ለ/ አለመቸኮል
‹‹ በጸለይክ ጊዜ አትቸኩል ›› ሲራ 7፡-10

‹‹ እግዚአብሔር በሰማይ አንተ በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን በእግዚአብሔር


ፊት ቃልን የናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል ›› መክ 3፡-2

23
ሐ /ከማስተዋል ጋር መጸለይ

‹‹ አፍ ቃላትን ሲደግም ልብ እየተረጎመ መሆን አለበት


በእግዚአብሔር ፊት ቃላትን ለመቁጠር ብቻ ቆሜአለሁ ይበል ››
ማር ይስሐቅ

መ/ ዲያቢሎስን መቃወም

‹‹ ዲያቢሎስን ተቃወሙት ከእናንተ ይሸሻል ››

ሠ/ ተስፋ አለመቁረጥ

ረ/ የግል የጸሎት ልምድን ማዳበር 24

You might also like