Professional Documents
Culture Documents
ክርሰትቶስ _እውነትና ሕ
ክርሰትቶስ _እውነትና ሕ
ስምዖን የቀሬና ሰው ነው። ቀሬና በአሁኒቷ ልብያ አካባቢ ያለች ሃገር ናት። በዘመኑ በተለያዩ አህጉር ያሉ አይሁዳውያን
በዓል ለማክበር ወደኢየሩሳሌም ይተምሙ ነበርና ነው ስምዖን የቀሬናው ሰው በአጋጣም ክርስቶስ በሚሰቀልበት ቀን
በዚያ የተገኘው።ጌታችን ከመስቀሉ ጽናት የተነሳ መሸከም ባቃተው ጊዜ ወታደሮቹ የሚያግዘውን ሰው በዓይናቸው
መፈለግ ጀመሩ። ቦታው በሮማውያን እና በዕብራውያን የተመላ ስለነበረ ሮማውያኑ ወታደሮች የክርስቶስን መስቀል
ከዚህ ጥቁር መጤ ሰው በቀር ሌላ ማንም እንዲሸከም አልፈለጉም። የቀሬናውን ስምዖን ንቀው አከበሩት። ተሳስተው
ለክብር ጠሩት። ለአንድ ምዕራፍ ያህል የክርስቶስን መስቀል በመሸከሙ በውስጠት አዋቂነት እግዚአብሔር ከመስቀሉ
በረከት እንደከፈለው እናውቃለን። የክርስቶስን መስቀል መሸከም ምንኛ መታደል ነው? እንግዳው አንገትህ ላይ ያሰርከው
ማተብ ክርስቶስ የተቀበለው መከራ ምልክት ነውና የተናቅኩ የተዋረድኩ ነኝ ብለህ አትሽሽ። ከዚያ ይልቅ ክዠጌታችን
'ሊከተለኝ የሚወድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ' ብሏልና መስቀሉን እንደቀሬናው ሰው ተሸክመህ ወደቀራንዮ
ተከተለው።
?ቨቨ