Professional Documents
Culture Documents
ጭውውት አንድ
ጭውውት አንድ
ራዲዮኑ ውስጥ ያለው ጋዜጠኛ - ይህ የአብዮታዊት ሶሻሊስት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ድምጽ ነው። ሊቀመንበር
ማኦ ዜዱንግ ከኩባው ፕሬዝደንት ጋር ባደረጉት ውይይት ምክንያት በሩስያዋ ዋና ከተማ በተፈጠረው የመንገድ መዘጋጋት
ነገ በመላው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የሶሻሊዝም እንቅስቃሴ በመደገፍና የአሜርካ መራሹን አቆርቋዥ ቡርዧ
ካፒታሊስት ሥርዓት ለማውገዝ አብዮት አደባባይ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለ
ማርያም አስታውቀዋል። በዕለቱም ከዩጎዝላቭያ፣ ከምስራቅ ጀርመን እና ኸሊብያ የሚመጡ የወንድም ሃገራት
ላባአደሮች ትርኢት እንደሚያሳዩ ይጠበቃል።
በተያያዘ ዜና አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ አህያ በር እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሕገ ወጥ መልኩ አህዮቻቸውን
ሲያደራጁ የነበሩ አህያ ነጂዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወሰደ። የአህያ በር ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ጓድ ማበሉ የትናየት
እንደተናገሩት አብዮታችን በማንም ፋንድያም ውርንጭላና አድሐሪ ምክንያት አይደናቀፍም። ይህንንም ለማረጋገጥ ሌት
ተቀን እንሰራለን ብለዋል።
ይህንን አብዮታዊ እርምጃ በማክመልከት 'የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት ያልታደለች ፍየል
ሁለት ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።' የሚለውን አብዮታዊ ዜማ አዳምጠን እንመለሳለን። "
ወይዘሮ - የሆነው ይሁን! እዚያ ነው የማይነካ ነካክተው ያፈነዱት! ይኸው ማን ይመልሰው! ቁጭ ብለው የሰቀሉት
ቆመው ማውረድ ይቸግራል ሰውዬ!
አቶ - ሆሆ በይ ሰው እንዳይሰማሽ