You are on page 1of 432

ጥቋቁር አናብስት

ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው እና ኤፍሬም ጀማል አብዱ እንደመለሱት


ጥቋቁር አናብስት

የዘመናዊት ኢትዮጵያ ዐበይት ደራሲያንና የጥበብ ሕይወታቸው

“መቅድም”

ማለፊያ ሥነ ጽሑፍ፣ የአንድ ህዝብ ህይወት እና መንፈስ መልክ ነው። ደራሲዎች፣ ህዝቡራሱን
የሚያይበት መስታወቶች ናቸው። አንድ ማህበረሰብ በደራሲዎቹ ውስጥ ራሱን ያየዋል፤ በዚህም
መንገድ እያንዳንዱ ሕብረተሰብ በሥነ ጽሑፍ ስራዎቹ ውስጥ እጁ አለበት ብሎ አፍን ሞልቶ
መናገር ይቻላል። የፀሀፊዎችን ህይወት ማጥናት ጥበባቸውን ወይም ጥበበኛ ያደረጋቸውን ነገር
አይገልጽም። ነገር ግን እንደዚህ ያለ መረጃ፣ ደራሲዎች የሚጽፉትን ለምን እንደሚጽፉ ያስረዳል።
የሚኖሩበት ማህበረሰብ፣ አካባቢ እና ዘመን የሚጽፉበትን ጭብጥ እና ይበልጡንም
አመለካከታቸውን ይወስናል። ነገር ግን ማህበረሰብ፣ አካባቢም ሆነ ዘመን ጥበብንም ሆነ ጥበበኛ
እንዴት እንደሚፈጠር ሊገልፁ አይቻላቸውም (አንዳንድ ዘመናት በርካታ ጥበበኞችን
ማፍራታቸው የታመነ ሀቅ ቢሆንም ቅሉ።

የደራሲዎች የሕይወት ታሪክ ስብስብ፣ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍን አጠቃሎ ያስረዳል ብዬ ራሴን


አልሸነግልም ። ነገር ግን እነዚህ ታሪኮች ተደማምረው ሥነ ጽሑፉ በተወለደበት እና
በፋፋበትዘመን የነበረውን ማህበረሰብ፣ አካባቢ እና ወቅት አጉልተው ያሳያሉ። የኢትዮጵያን ሥነ
ጽሑፍ የተመለከተ Tradition and Change in Ethiopia: Social and Cultural
Life as Reflected in Amharic Fictional Litrature ca. 1930-1974 የተሰኘ ሌላ
መጽሐፌን ያነበቡ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ ደራሲያን ዙሪያ ጠብሰቅ ያለ መጽሐፍ እንድጽፍ
ይጎተጉቱኝ ነበር። በ1973ዓምበተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ እየሰራሁ፣ ለዚህ መጽሀፍ
የሚሆን ግብአት ማሰባሰብ ጀመርኩ። ይህ ስራ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ግዜ ያደረግኩት ረዘም ያለ
ቆይታ ባበቃበት 1981ዓምተጠናቀቀ። ከባለታሪኮቹ ጋር ያደረግኳቸው ቃለመጠይቆች ከተጠናቀቁ
በኋላ ትኩረቴን የሚስብ አንዳች መረጃ ሲደርሰኝ በመጽሐፉ ውስጥ እንደ አመቺነቱ
ጨምሬያለሁ። በ1982በኢትዮጵያ ተጨማሪ አጭር ቆይታ ያደረግኩ ጊዜ፣ ያገኘኋቸው መረጃዎች
በአግባቡ የተሰደሩ ባለመሆናቸው በመጽሐፉ ውስጥ አላካተትኳቸውም ። እስከቅርብ ጊዜ ድረስ፣
አንዳንድ አግባብነት ያላቸው መረጃዎች ከኢትዮጵያ በጽሑፍ ይደርሱኝ ስለነበር፣በየታሪኮቹ
ማብቂያ ላይ ጨምሬያቸዋለሁ።

መረጃ በምሰበስብበት ወቅት ብዙ ደራሲያን በፈቃደኝነት ተባብረውኛል። እነዚህ የቃላት ንድፎች፣


ስለ ኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ህይወት ከመግለፃቸውም ባሻገር ስለ ተውኔት እና የፕሬስ እድገት
እንዲሁም በኢትዮጵያ ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ታሪክ ውስጥ አንዳች ምስል ይፈጥራሉ።
ደራሲዎች ለቃለመጠይቅ በማይገኙበት ወቅት፣ በተለያዩ ቦታዎች የሰፈሩ የጽሑፍ
መረጃዎችን(በቀላሉ የማይገኙ ወይም በአማርኛ የተፃፉ) ተጠቅሜያለሁ ፤እነዚህን መረጃዎች
የተጠቀምኩት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው። መረጃዎቼን በሕይወት ያሉ ምስክሮች ከነገሩኝ ጋር
ሳስተያየው ብዙ ስህተት አግኝቼያለሁ። ሁለት ደራሲዎችን በተመለከተ ከተማሪዎች የጥናት
ወረቀቶች የተገኘ መረጃ ( ምንም እንኳን የመረጃ ምንጮቹ ጥሩ የነበሩ ቢሆንም)፣ በብዙ ረገድ
በስህተት የተሞላ ሆኖ ተገኝቷል። ነገር ግን ከሌላ ምንጭ መረጃ ማግኘት በማልችልበት ወቅት
እነዚህን ምንጮች ተጠቅሜያለሁ።

በሕይወት ያሉ ደራሲዎችን ታሪክ ከሌላ ምንጭ ጋር ሳላመሳክር እንደተነገረኝ አቅርቤያለሁ።


አብዛኛዎቹ ቃለመጠይቅ ያደረግኩላቸው ደራሲዎች ስለ ሕይወታቸው በልበ–ሙሉነት፣ በትክክል
መልሰዋል ፤ አንዳንዶቹ ግን ቀኖችን፣ ቦታዎችን እና ስሞችን በትክክል ማስታወስ አልቻሉም።
በደራሲዎቹ በራሳቸው የተዘጋጀ ግለታሪክ አንዳንዴ ከእውነትነቱ ይልቅ ፈጠራነቱ ይጎላል። ይሄ
የምንጮቼ እውነተኝነት ምን ያህል ድረስ እንደሆነ እንድጠራጠር ያደርገኛል። (በአንድ አባትና ልጅ
ጉዳይ ላይ ከእውነታው ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ መረጃዎችን አንብቤያለሁ ፤ በዚህ ረገድ አብዛኛዎቹ
የፈጠራ ታሪኮች የተፈበረኩት ከልጁ ዘንድ ነው ፤ ይኼም ገና ያልታተመውን የአባቱን ግለታሪክ
መጽሀፍ እየጠቀሰ በሚናገርበት ወቅት ነው።) ይሁን እንጂ ደራሲዎች ራሳቸውን እንዴት
እንደሚያዩ ወይም እንዴት መታወስ እንደሚፈልጉ ማወቅ ፍላጎትን የሚጭር ነው።

የአማርኛ እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ቋንቋው ስለሚገድባቸው፣


የተተረጎሙትም ጥቂት ስለሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ውጪ በአንጻራዊነት አይታወቁም። ከልቡ አፍሪካዊ
የሆነና፣ የማደግም ተስፋ ያለው (በቅኝ ገዢዎች ቋንቋ የሰፈረ የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ የትም
አይደርስም)?፣በብሔራዊ አፍሪካዊ ቋንቋ የተፃፈሥነ ጽሑፍ ነው።ይህንን ሥነ ጽሑፍ
ማወቅየወለደውን ማኅበረሰብ በአግባቡ ለመረዳት ይጠቅማል፤ ምክንያቱም በሥነ ጽሑፍ እና ሥነ
ጥበብ ውስጥ አንድን ማህበረሰብ “ነፍስያውን” ይገልጣልና።

ይህንን የኢትዮጵያ ደራሲያን የሕይወት ታሪክ ስብስብ እንዲሳካ ለረዱኝ ሁሉ ከባድ ውለታ
አለብኝ። መጽሀፉ የተፃፈው የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በደንብ
እንዲታወቅ ለማድረግ በሚል አላማ ነው።
እነኚህ ሁሉ የደራስያን ምስሎች የተከተቡት፣መንግስቱ ኃይለማርያም ገና ስልጣን ላይ በነበረበት
ግዜ ላይ መሆኑ መታወቅ አለበት። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ደራሲዎች ስለ ሕይወታቸው እና ሥራቸው
ከልብ እንዳያወሩ አግዶ ይሆናል።

በመጽሑፉ ውስጥ ለሰፈሩት ታሪኮች ሁሉ ሐላፊነቱ የእኔ እንደሆነ መጥቀሱ መቼም ያን ያህል
አያስፈልግ ይሆናል።አንዳንዴ የመረጃ ምንጮቼን በአግባቡ ሳልረዳ ቀርቼ ይሆናል ፤ ወይ ደግሞ
በስማ በለው የተሳሳተ መረጃ ደርሶኝ ይሆናል። ለተፈጠሩ ስህተቶች እየተፀፀትኩ ይቅርታ
እጠይቃለሁ። ይህ መጽሀፍ የተፃፈው የአማርኛንሥነ ጽሑፍ እና ፈጣሪዎቹን ከልብ በማድነቅ
እንዲሁም በሌሎች ? እንዲታወቅ እናእንዲደነቅ በመሻት ነው።

ሬዱልፍ ኬ. ሞልቬር

ኢትዮጵያ ለክፍለ ዘመናት የኖረ የጽሑፍ ባህል አላት። ከክርስትና ?በፊት ጀምሮ በድንጋይ ላይ
የተቀረጹ ጽሁፎች ነበሩ። ነገር ግን ክርስትና በመንግስት ደረጃ እና በሕዝቡም ዘንድ በ4ተኛው
ክፍለ ዘመን ቅቡል ከሆነ በኋላ በተለይ የሐይማኖት መጽሀፍት እየተተረጎሙ መቅረብ ጀመሩ።
መጽሐፍቱ በዘመኑ መግባቢያ በነበረው በግእዝ ቋንቋ የተዘጋጁ ሲሆን ። በየክፍለ ዘመኑ እድገት
ከታየ በኋላ መቀዛቀዝ በመከተሉ እስከ መካከለኛው ዘመን ድረስ የተዘጋጁት አዳዲስ መጽሀፍት
ጥቂት ነበሩ። ግዕዝ የንግግር ቋንቋ መሆኑ ካበቃ በኋላ ከ14ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የግዕዝ ሥነ
ጽሑፍ እያንሰራራ መጣ።

ከ1000 ዓ ም አካባቢ ጀምሮ ግዕዝ በሌሎች የንግግር ቅጦች ወይም ቋንቋዎች እየተተካ መጣ።
ጥንታዊው አማርኛ እራሱን ችሎ እንደቋንቋ ያቆጠቆጠው በዚህ ግዜ ሳይሆን አይቀርም። ነገር ግን
የሰለሞናዊ ስርወ መንግስት በ1270 ወደ መንበረ ስልጣን ከተመለሰ ከጥቂት ግዜ በኋላ ገዢዎችን
የሚያወድሱ እስከአሁን ተጠብቀው ከቆዩ ንጉሣዊ መወድሶች በስተቀር አማርኛ ለሥነ ጽሑፍ
(ፋይዳ) እምብዛም ጥቅም ላይ አልዋለም። በጽሑፍ አልሰፈሩም እንጂ ተረቶች፣ መዝሙሮች እና
ሌሎችም ሥነ ቃሎች በአማርኛ ይሰናዱ ነበር።

በ16ተኛው ክፍለዘመን የካቶሊክ ሚሽነሪዎች (መልእክተኞች) የሐይማኖት ትምህርታቸውን ሰፊው


ህዝብ ዘንድ ለማድረስ በራሪ ወረቀቶችን በጊዜው የቤተመንግስት እልፍኝና የደጋው ቋንቋ በነበረው
በአማርኛ ቋንቋ ያትሙ ነበር። ነባሯ የኦርቶዶክስ ቤተ ክህነት ግዕዝን ስትጠቀም ብትቆይም (ግዕዝ
ቅዱስ ቋንቋ የሚል ማዕረግ አግኝቷል)እሷም የአማርኛ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ምላሽ ሰጠች።
ነገር ግን በዚህ አጭር የቅራኔ ወቅትካልሆነ በቀር እስከ 19ኛው ክፍለዘመን ሁለተኛአጋማሽ ድረስ
አማርኛ ለሥነ ጽሑፍ ፈጠራ ተግባር አልዋለም። ያኔ አፄ ቴዎድሮስ አማርኛን የቤተመንግስት ቋንቋ
አደረጉት ፤ በዚህ የተነሳም ሶስት ዜና መዋዕሎቻቸው በአማርኛ ቋንቋ ተጽፈዋል። ከዛ በፊት ዜና
መዋዕል የሚፃፈው በግዕዝ ነበር። ከነዚህ ፀሀፊዎቻቸው አንዱ አለቃ ዘነብ "መጽሐፈ ጨዋታ ስጋዊ
ወመንፈሳዊ"ን ጽፈዋል። ይህ መጽሀፍ አንባቢዎችን ለማዝናናት እና ለማስተማር ያለመ ነበር።

በ20ኛው ክፍለዘመን መግቢያ የመጀመሪያውን ሳምንታዊ ጋዜጣ "አእምሮ"ን በሰፊው ለማዳረስ


መንግስት የመጀመሪያውን የህትመት ማሽን አስመጣ። "አእምሮ" መታተም የጀመረው በ1902
ሲሆን በእጅ እየተገለበጠ በ24 ቅጂዎች ይዘጋጅ ነበር ፤ ቀጥሎ በማባዣ ማሽን በ200 ቅጂዎች
መዘጋጀቱን ቀጥሏል። በመጀመሪያ የቤተመንግስት ጋዜጣ ነበር ፤ የጀመረውም አንድ ግሪካዊ ሲሆን
፤ ምኒልክም ይህን ጅማሮ ወደዱት። የህትመት ሁኔታው ከግዜ ወደግዜ እየተሻሻለ፣ ጋዜጦች
ለብዙዎች መድረስ ቻሉ። አዳዲስ የማተሚያ ቤቶችም ተቋቁመው እየተፃፉ ያሉትን አዳዲስ
መጽሀፍት ህትመት አፋጥነዋል።

በኢትዮጵያ መጀመሪያ የታተመው የአማርኛ ልብወለድ "ጦቢያ" ሲሆን፤ደራሲውም ኢጣሊያ


የተማረው አፈወርቅ ገብረእየሱስ ነው። ኢጣሊያውያን መምህሮቹ ብዙ አማርኛ ጽሑፍ እንዲኖር
ስለፈለጉ አፈወርቅ ይህንን መጽሐፍ እንዲጽፍ አነሳስተውታል። በመሆኑም መጽሐፉ በ1900
ለመጀመሪያ ግዜ የታተመው ኢጣልያ፣ ሮም ውስጥ ነበር። ልብ በሚነካ ታሪኩ እና በሥነ ጽሑፋዊ
ውበቱ አሁን ድረስ ይወደሳል ፤ ነገር ግን ሌሎች ደራሲዎች ላይ ስላሳረፈው ተጽእኖ በውል መናገር
አይቻልም። ካናገርኳቸው ደራሲዎች ውስጥ በአፃፃፍ ዘዬአቸውምሆነ በአስተሳሰባቸው እድገት ላይ
ትርጉም ካላቸው መጻሕፍት መካከል እንደ አንዱ የጠቀሱት ጥቂቶች ናቸው።

የመጀመሪያው የአማርኛ ተውኔት5 ከጥቂት አመታት በኋላ እንደተፃፈ ይነገራል። ምናልባትም


ከ1905–08 በነገሱት ልጅ (አቤቱ) እያሱ ዘመን ሳይሆን አይቀርም። ተውኔቱ "ፋቡላ የአውሬዎች
ኮሜዲ" የተፃፈው በተክለሀዋርያት ተክለማሪያም6 ነበር። ተክለሐዋርያትን ያሳደጓቸው የቀዳማዊ
ኃይለሥላሴ አባት ራስ መኮንን7 ሲሆኑ የተማሩት ሩስያ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ነው። ተውኔቱ
በግጥም መልክ የተፃፈ ሲሆን ከኢትዮጵያ ተረት፣ ከኤዞጵ፣ ከላፎንቴይን እና ከሌሎችም ተረቶች
ተውጣጥቶ የተዘጋጀ ሲሆን ለየት የሚያደርገው ፖለቲካውን ለመንቀፍ ስለተጠቀሙበት ነው።
ንጉሱ እና ባለሟሎቻቸው ሐላፊነት የጎደላቸው እና ብልሹ ሆነዋል ብለው ያስቡ ነበር ፤ ስለዚህ
ሊያስተምሯቸውና ሊያስጠነቅቋቸው አስበው ይህንን ተውኔት ፃፉ። ተውኔቱ ከነጭራሹ
አልታተመም።(አንዳንድ ምንጮች ተውኔቱ የተፃፈው በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን 1908–23
መሆኑን ይገልፃሉ። በዚህ መጽሐፍ የተካተተውን የተክለሃዋርያትን የሕይወት ታሪክ ይመልከቷል)
ከኢጣሊያ ወረራ በፊት ዝነኛ የኢትዮጵያ ደራሲ የነበሩት ሕሩይ ወልደሥላሴ ነበሩ። ኢትዮጵያን
እና ሕዝቦቿን “ለማሻሻል” ልብወለዶች፣ የሐይማኖት መጽሐፍት፣ ታሪክ፣ የጉዞ ማስታወሻዎች
የመሳሰሉትን ሁሉ በትርፍ ግዜያቸው አዘጋጅተዋል ( በደራሲነታቸው ዘመን ሁሉ ከፍተኛ የፖለቲካ
ስልጣን ነበራቸው።)

መምህር የነበሩት ዮፍታሔ ንጉሴም በዚህ ጊዜ ተውኔቶችን ይጽፉና በትምህርት ቤት ውስጥ


ለመድረክ ያቀርቡ ነበር። ይሁን እንጂ አንድም ተውኔታቸው የታተመላቸው አይመስልም።በደንብ
የሚታወቅ ተውኔታቸው "አፋጀሺኝ" ነው።

***

ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ ከበደ ሚካኤል የኢትዮጵያ ቀዳሚ ገጣሚ እና ፀሀፊ ተውኔት ሆነው ብቅ
አሉ። ተውኔቶቻቸው የተፃፉት ቤት በሚመቱ ጥንድ ስንኞች ሲሆን ቋንቋቸው ሊኮርጁት
የማይቻል መሆኑን ብዙ ኢትዮጵያውያን እያደነቁ ይናገራሉ። የአውሮፓን ዘመን ተሻጋሪ የሥነ
ጽሁፍ ስራዎች አዛምደው ከመተርጎማቸውም ሌላ ብዙ የታሪክ መጽሀፍት ጽፈዋል።

ወደ በኋላ ሹመታቸው በጋዜጣ የሚታወጅላቸው የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆኑት


መኮንን እንዳልካቸውም በዚህ ግዜ ንቁ ፀሀፊ ነበሩ ፤ በእርግጥ ወግ አጥባቂ ድምፀት ነበራቸው።
የቋንቋቸው ውበት ሀሳባቸውን በማይጋሯቸው ሰዎች ዘንድ እንኳን መደነቁ አልቀረም።
የስራዎቻቸው ብዛት ይበል አሰኝቷቸዋል፡፡

በእርግጥ ሐዲስ አለማየሁ መፃፍ የጀመሩት ከጠላት ወረራ በፊት ሲሆን በኢጣሊያ በጦር
እስረኝነት ጥቂት ግዜ አሳልፈዋል። በሰዎች ዘንድ የሚታወቁት ግን ከጦርነቱ በኋላ በሰሯቸው
ስራዎች በተለይ በታላቁ "ፍቅር እስከ መቃብር" ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎች ሁለት ትልልቅ
መጽሀፍትን አስከትለዋል። ይህ ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ያበረከቱት ትልቁ አስተዋጽኦ እንጂ ብቸኛ
አይደለም።

ከነኚህ ፋና ወጊዎች በኋላ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሥነ ጽሑፍ ስራዎችን ያበረከቱ ደራሲያን ቁጥር
ያለማቋረጥ ጨምሯል። አቤ ጉበኛ ብዙ ቢጽፍም ቅሉ ከምርጦቹ አንዱ ግን አልነበረም። ብርሀኑ
ዘርይሁን እና በአሉ ግርማ ከዘመናዊ ፀሀፊዎች መሀል ተጠቃሾች ናቸው። ነገር ግን ወዲያውኑ
ሌሎች እንደ ማሞ ውድነህ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ መንግስቱ ለማ፣ ፀጋዬ ገብረመድህን የመሳሰሉት
ደራሲዎች ብቅ ብለዋል፦ የደራሲዎችን ስም እዚህጋ መዘርዘሩ የተለየ ዓላማ የለውም ፤ ይልቁንም
መጠቀስ የሚገባቸው ሁሉ የሕይወት ታሪካቸው ከዚህ ቀጥሎ ሰፍሯል።የቲያትር ተመልካቾች
ጥቂት ከመሆናቸውም ባሻገርተውኔቶቻቸውባለመታተማቸው ("ሰዎች ተውኔቶችን አያነቡም"
በሚል ምክንያት) ፤ነጥረው ከወጡጥቂቶች በስተቀር ፀሀፌ ተውኔቶች በብዛት አልተቃኙም።

በ1953 ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላይ ከተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኋላ በጥብቅ ሳንሱር
ማድረግ ተጀመረ። ነገር ግን በተመሳሳይ ወቅት እውነታዊነት እና ዘመናዊነት ወደ አማርኛ ሥነ
ጽሑፍ እየመጣ ነበር። እስከ 1966ቱ አብዮት ድረስ የቀረቡልብወለዶች እና ተውኔቶች ይህ
መንፈስ የዘለቃቸው ነበሩ።ደራሲዎችም ማህበራዊ ችግሮች ላይ፣ በተለይ ዘውዳዊ ክብር፣ መንግስት
እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ትችቶችን ለመሰንዘር የሚያመች ልዩ አይነት አፃፃፍ
ፈጠሩ ።

ከአብዮቱ በኋላቅድመ–አብዮት ምርጥ ደራሲዎች መፃፋቸውን እና የአንባቢዎቻቸውን ቀልብ


መግዛታቸውን ቀጥለዋል። የሥነ ጽሑፉን አለም ገና የተቀላቀሉ አዳዲስ ደራሲዎችም ነበሩ።8አያሌ
የውጪ ሶሻሊስታዊ ስራዎች ተተርጉመዋል ፤ አንባቢዎችን ግራ ያጋቡ ብዙ አዳዲስ የአማርኛ
ቃላትም ተፈልስፈዋል።9መጀመሪያ አካባቢ ብቻላላተደርጎየነበረው ሳንሱር ከአብዮቱ በኋላ
ይበልጥ ጠበቀ። በተለይ የበአሉ ግርማ የመጨረሻ መጽሀፍ "ኦሮማይ" ከሰው እጅ እየተቀማ
ከተወገደና ደራሲውም ከጠፋ በኋላ ማንኛውንም መጽሐፍ በአዲሱ የሳንሱር ሹም በኩል ማሳለፍ
በጣም አዳጋች ሆነ። ይህ ሹም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የሥነ ጽሑፍ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ
ለማፈን ቆርጦ የተነሳ መሰለ። ነገር ግን ከ1978 በኋላ አዲስ የሳንሱር ክፍል ሀላፊ በመሾሙ
እንደገና መጽሐፍትን ማተም ቀለል ያለ ተግባር ሆነ ብዙ አዳዲስ መጽሐፍትም ብቅ ብቅ አሉ።

ከ1966 አብዮት በኋላ ሊያከናውኗቸው የሚችሏቸው ተግባሮች እጅግ በጣም ውስን ስለነበሩ
ሰዎች ከበፊቱ የበለጠ ያነባሉ። በንጉሳዊው ዘመን ከነበረው በላቀ ቁጥር መጻሕፍት አሁን መታተም
ጀመሩ። የሐዲስ አለማየሁ ሶስተኛ ልብወለድ "የልምዣት" 50,000 ቅጂዎች ታትሞ ወዲያው
ተሽጦ በማለቁ እንደገና ታትሟል10። የቴአትር ተመልካች ቁጥርም ከአብዮት በኋላ በማደጉ፤
ለወራት ብሎም ለአመታት የሚታዩ ተውኔቶች ነበሩ። ይህ አዲስና ነባርደራሲዎችንም አበረታቷል።

በእንግሊዘኛ የነበሩ የመማሪያ መጻሕፍት ቀስ በቀስ እየተተኩ፣ አማርኛም በትምህርት ቤቶች


ውስጥ በይበልጥ ጥቅም ላይ እየዋለመጣ።ነገር ግን እንግሊዘኛ በሁለተኛ ደረጃና በዩኒርስቲ ውስጥ
ጥቅም ላይ መዋሉን ቀጥሏል።
ሌሎች አፍሪካዊ ሃገሮች ያልታደሉት፣ ሀገር በቀል ብሄራዊ ቋንቋመኖሩና ጥቅም ላይ የመዋሉ
በረከት በመኖሩ፣ ሥነ ጽሁፍ በፍጥነት መብሰል ችሏል።ሶሻሊስቶችአጓጉል ቢይዙትም፣ የአማርኛ
ቋንቋን በሐገር አቀፍ አውድ፣በትምህርት ቤት እና በሥነ ጽሑፍ ውስጥ መጠቀም በመጨመሩ፣
ቋንቋው በፍጥነት አድጓል። የተለያዩ ዘይቤዎች ተበራክተዋል፤ የነጠሩ እና በሳል የሥነ ጽሑፍ
ስራዎች መታየት ጀምረዋል። የቤተክርስቲያን ቋንቋነቱ ጠቃሚ ተጽእኖ ቢሆንም፤
የኢትዮጵያውያንን መንፈስ የሚያነሳሳው ግን ይህ ብቻ አለመሆኑ ይበልጥ ጠቃሚ ነው። የውጪ
ሥነ ጽሑፍ ተጽእኖዎች እና መንደርኛ ዘዬዎች በዘመናዊ አማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ቦታቸውን
እያገኙ መጡ ፤ አንባቢዎችም ለዚህ ተገቢ ዋጋ የሰጡ ይመስላሉ።

ማተሚያ ቤቶች ለአመታት በስራ በመወጠራቸው፣ ደራሲዎች መጽሐፍቶቻቸው ከመታተማቸው


በፊት ለረዥም ግዜ መጠበቅ ይጠበቅባቸው ነበር። በአብዮቱ ዘመን ሁለት አሳታሚዎች
መኖራቸው ( የመንግስት ማተሚያ ቤቱ ኩራዝና የአዲስአበባውን ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ
የተካው የኢትዮጵያ መጽሐፍት ማዕከል) በንጉሱ ዘመን ደራሲዎች መጽሀፎቻቸውን ለማሳተም
ከኪሳቸው ማውጣት የሚጠበቅባቸውን በማስቀረት የደራሲዎችን ሸክም አቃልሏል። እነዚህ
አሳታሚዎች ከህትመት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ሁሉ ተሸካሚ ነበሩ። ይሁን እንጂ ደራሲዎች
አሁንም ቢሆን ረቂቃቸውን ይዘው በቀጥታ አታሚዎች ጋር መውሰድ ችለዋል።

ከልብወለድ ደራሲያን ባሻገር እንደ ማህተመሥላሴ ወልደመስቀልና ተክለፃድቅ መኩሪያ ያሉ


በአማርኛ የሚጽፉ ምሁራን ለኢትዮጵያ ባህል እና ታሪክ ጥናት ብዙ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ነገር
ግን ስለነሱ መፃፍ ከዚህ መጽሀፍ አላማ ውጪ ነው። ይሁን እንጂ የሶስት መዝገበ ቃላት
አዘጋጂዎችን አጭር ታሪክ አካትቻለሁ። እነኚህ ሰዎች ከመዝገበቃላት ውጪ ያሉ ሌሎች
መጽሀፍትንም ደርሰዋል። በተጨማሪም በቋንቋው ላይ የሰሩት ስራ የአማርኛን እድገትና ብሔራዊ
ቋንቋዎችን ለማጥናት ያለውን ፍላጎት ያንፀባርቃል። መቼም ቢሆን የመዝገበ ቃላት ዝግጅትና ሥነ
ጽሑፍ እርስ በእርስ እየተመጋገቡ ተያይዘው የሚያድጉ ናቸው።12

የአማርኛ መጽሀፍት ሕትመት በፍጥነት እያደገ ቢመጣም ለማሳተም ያልሞከሩ ወይንም ያላሳተሙ
ግን አሉ። ይህምከነበረው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻርችግር ውስጥ ላለመግባት ከመፈለግ ወይንም
በራስ ችሎታ ባለመተማመን ሊሆን ይችላል።12አርታኢዎች አይተዋቸው ለህትመት ተቀባይነትን
ካገኙና ለአሳታሚዎች ከተሰጡ በኋላ፣ ባለቤቶቻቸው መልሰው የወሰዷቸውም ስራዎች አሉ።

አንዳንድ ደራሲዎች በተለይ አዲሶቹ ከሌሎች ደራሲዎች ዘንድ ምክር ይጠይቃሉ። ነገር ግን ሁሌም
ምክሮቹን ተቀብለው ተግባራዊ ስለማያደርጉ መጽሐፍቶቻቸውን ለማሳተም ብዙ ስቃይ ያያሉ፡፡
ያውም ከታተመላቸው ነው። በዚህ መጽሐፍ የተካተተ አንድ ደራሲ ለምሳሌ፣ የፃፋቸው ብዙ
ረቂቆች ከአብዮቱ በፊትም ሆነ በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊታተሙ እንደማይችሉ ተረድቶ ነበር።
በእርግጥ ቃለምልልስ ካደረግኩለት ጥቂት ግዜ በኋላ አንድ የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ ማሳተም
ችሏል።

ከኢትዮጵያ ውጪ በመላው አለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። እነኚህ


ኢትዮጵያውያንየትውልድ ሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ሥነ ጽሑፍ በይበልጥ ለማወቅ ይሻሉ። ይህ
አጋጣሚ ለአማርኛ መጽሐፍት ገበያ ይከፍታል። ዳያስፖራው እራሱ "የስደት ሥነ ጽሑፍ"
የማይፈጥርበት ምክንያት የለም። በዚህ ዘውግ ሊመደብ የሚችል ፖለቲካዊ ያልሆነ መጽሀፍ
በ1979 በጀርመን ታትሟል።

***

የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ በጥሩ አጀማመር ከመነሳቱም በላይ በፈጠራ ጉልበትም ሆነ ፍላጎት


እየጨመረ መጥቷል። ስለ ለጋው ትውልድ ደራሲዎች እዚህ አልፃፍኩም። ነገር ግን የነገ የሥነ
ጽሑፍ አውራዎች መጽሐፍትን በማሳተም ( ወይም ጽፈው ለራሳቸው በማስቀረት)ወይም ተውኔት
በመፃፍ እጃቸውን አፍታተዋል። የኢትዮጵያ ደራሲዎች ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩባቸውም ሊዳፈን
የማይችል የፈጠራ መንፈስ እንዳለ ግን ግልጽ ነው።

ከእነኚህ ስብስቦች መሀል የማካትተው አንዲት ሴት ደራሲ እንኳን ባለማግኘቴ አዝናለሁ። የሕሩይ
ወልደሥላሴ ልጅ የሆኑት ላቀች ሕሩይ ለወጣቶች የሚሆን ምክር በብእር ስም ጽፈው ነበር፡፡ ነገር
ግን ልጣቸው የራሰ፣ መቃብራቸው የተማሰ እንደሆነ ተነገረኝ። ሌላዋ ስንዱ ገብሩ (የከንቲባ ገብሩ
ደስታ ልጅ) ብዙ ጽፈዋል፡፡የታተመላቸው አንድ መጽሐፍ ብቻ ሲሆን ሌላው በኢትዮጵያ ጥናት
ኢንስቲትዩት አዲስ አበባ ይገኛል። ነገር ግን እኔ ስለእርሳቸው የፃፍኩትን አልተቀበሉትም ፤
ስለራሳቸው ለመፃፍ የገቡትንም ቃል አልጠበቁም። አሮጌው አየር ማረፊያ አካባቢ በሚገኘው
ቤታቸው ብዙ የወዳጅነት ጨዋታዎች ብናደርግም ለቃለመጠይቅ ፈቃደኛ አልነበሩም።

በኢትዮጵያ ውስጥ የበሳል ሥነ ጽሑፍ ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱ ደራሲዎች ወደፊት የተሻለ
ህይወት እንደሚኖራቸው ተስፋ ሰጪ ነው ፤አንባቢዎችም አማርጠው የሚያነቡት ሰፊ መስክ
ይኖራቸዋል። ምናልባት ደራሲዎች ለጥበብ ብቻ ብለው የሚኖሩበት እና በዚያ ብቻ
የሚተዳደሩበት ጊዜም እየመጣ ይሆናል።

ማስታወሻዎች

1) የስብሀት ገብረእግዚአብሔር የመጀመሪያ የአጭር ልብወለዶች ስብስብ "አምስት ስድስት ሰባት"


ቃለምልልስ ካደረግኩለት በኋላ ታትሟል። በ1983 ያየኋቸው አዳዲስ መጽሀፍት (አብዛኛዎቹ
በድጋሚ የታተሙ) የማሞ ውድነህ እና የአማረ ማሞን ስም ይዘው አይቻለሁ። ይልማ ሀብተየስም
ሁለት ስራዎቹ ገበያ ላይ ነበሩ። ከቃለምልልሳችን በኋላ ሁለት ደራሲዎች ( ተስፋዬ ገሰሰ እና ታደሰ
ሊበን)የመፃፍ ግዴታ እና ፍላጎታቸው እየጨመረ እንደመጣ ነግረውኛል። መንግስቱ ለማ
ቃለመጠይቅ ካደረግኩለት ጥቂት ግዜ በኋላ ስለሞተ በሕይወት እያለ እንዲፃፉ የማይፈልጋቸውን
ነገሮች በተጨማሪ መረጃነት ከህይወት ታሪኩ መጨረሻ ላይ አስፍሬዋለሁ።

2) ይህ ለምሳሌ የራስ እምሩን የሕይወት ታሪክ ይመለከታል ፤ መረጃውን ያገኘሁት ከባለታሪኩ


ሳይሆን በልጃቸው ሚካኤል በኩል ካልታተመው የእምሩ የግል ሕይወት ታሪክ ነው። ቅር
የሚያሰኘኝ፣ ታሪኳን እዚህ ላካትትላት ስለነበረችው ብቸኛ ሴት ደራሲ( የታተሙት የደራሲዋ
ስራዎች ጥቂት፣ በጥራትያን ያህል ባይሆኑም)ማስታወሻ የወሰድኩት ለደራሲዋ ቃለመጠይቅ
ካደረገች ተማሪ የጥናት ወረቀት የነበር ቢሆንም፣ የያዝኩት ማስታወሻ በደራሲዋ ስህተተኛና
የማያጠግብ ተብሎ ውድቅ የተደረገ መሆኑ ነው።።

3) ለአማርኛው ትርጉም አንባቢዎች የማያስፈልግ በመሆኑ የተዘለለ ማስታወ

5) ይህ ተውኔት የመጀመሪያው ተውኔት ብሎ ለመደምደም እንደ አወሳሰዳችን ይወሰናል። የሕሩይ


ወልደሥላሴ "ወዳጄ ልቤ" የመጀመሪያው ነው። ነገር ግን ተውኔትን እኛ በምንረዳበት መንገድ
ሁለቱም ተውኔት አይደሉም።

6) በመኳንንት ቤተሰብ ውስጥ ልጅ የሚለው ቅጥያ ምንም ማዕረግ ለሌላቸው ሰዎች ይሰጣል።
እያሱ ኢትዮጵያን በመሩበት ወቅት አቤቶ ተብለው ይጠሩ ነበር ፤ ንጉስ ተብለው አልተቀቡም።

7) ከንጉሥ ቀጥሎ ከፍተኛው ማዕረግ ራስ ነው።

8) አንዳንዶቹ ከ1966ቱ አብዮት በፊት እንኳን ሳያውቁት ምን ያህልአብዮታዊ፣ ተራማጅ እና


ሶሻሊስታዊ እንደነበሩ ሲታዘቡ ተደንቀዋል

9) ሶሻሊስታዊ መዝገበ ቃላቶች ታትመው ነበር ፤ ይህ ችግሩን ቢያቃልለውም እስከ መጨረሻው


አልቀረፈውም

10) መጽሀፉ ልክ እንደ ኦሮማይ ከሰው እጅ እየተቀማ ይሰበስባል ብለው በመስጋታቸው ሁለትም
ሶስትም ቅጂዎች የገዙ ነበሩ።
11) የሳንሱረኞቹ ማህተም ካላረፈበት ግን ምንም ነገር ሊታተም አይችልም ነበር። የታተሙ
መጽሀፍት እራሳቸው ከተፈቀደው ውጪ ሌላ ነገር አለማካተታቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ሳንሱር
ይደረጋሉ ። አንዳንዴ ሳንሱር አድራጊዎቹ በአንደኛው ዙር የፈቀዱትን በሚቀጥለው ዙር
ይከለክሉና በደራሲውእና በአሳታሚው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያደርሳሉ።

12)አስተዋፆዎቻቸው ከሥነ ጽሑፍ ይልቅ ለተረት የሚቀርብ የአንድ ታላቅ ደራሲና ሊቅ ታሪክም
አካትቻለሁ። ለተረት መቅረባቸው በስማቸው ብዙ ስለሚባልና ስለሚፃፍ ነው።

13) ወታደራዊው መንግስት ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ፣ የበአሉ ግርማ እጣ፣ ለብዙዎች
የማስጠንቀቂያ ደወል ነበር።

የተርጓሚዎቹ ማስታወሻ

በመጽሐፉ ውስጥ የተቀመጡ የአመተ ምህረት አቆጣጠሮች እንደተለዩበት ግዜ ማለትም እ.አ.አ


ከሆነ በጎርጎሮሳዊው ሌጣቸውን ከተቀመጡ ደግሞ በኛው አገር አቆጣጠር መሰረት እንደሰፈሩ
እንዲታወቅልን ይሁን፡፡ሌላው የአንቱታ ጉዳይ ሲሆን በተቻለ አብይ የሃገራችን ክስተት እና የብዙ
ለውጦች ጅማሮ ነው ብለን የምናስበውን የ53ቱን ግርግር ተከትሎ የመጡት ጸሐፍት ደራስያንን
"አንተ" ቀደምቱን "አንቱ" ብለን ከግዜ አንጻር ልንጠራቸው ወደናል፡፡ከዚህ በተጨማሪም እንደ
ተጠቀሱበት የታሪክ ሁኔታ(ልጅነት፤ከሹመት አስቀድሞ ባሉ ግዜያት) ለይተን የተለያያ አጠራርን
ተጠቅመናል፡፡በተጨማሪ አንተ ወይም አንቱ የማክበር ያለማክበር ጉዳይ ብቻም ሳይሆን
የቀረቤታም ጭምር እንደሆነ ስለምናምንም በግዜያችን የነበሩትን ደራስያንን በተለምዶ ስናወሳቸው
የምንጠቀምበትን የ"አንተን"አጠራር ልንጠቀምበት ወስነናል፡፡ እንጂማ ከጋሽ ማሞ፤ ከስብሐት እና
ከበዓሉ በላይ የሚከበሩ የስነጽሑፍ አድባራት በአገሪቱ ከወደ የት ተገኝቶ?

በተረፈ ለበርካታ አመታት ከጎናችን ሳትለዩ በፌስቡክ የንባብ ቡድናችን አብራችሁን ለነበራችሁ
የመላው የBOOK FOR ALL የፌስቡክ ቡድንና የBOOK FOR ALL ETHIOPIA ገጽ
ተከታታዮች በሙሉ ምንም እንኳን ለእናንተ ፍቅርና አክብሮት ብታንስም ይህችን እጅ መንሻ
በመታሰብያ አምሐነት ስናቅርብ እጅግ የላቀ ደስታ እየተሰማን መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

እናመሰግናለን

ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው

ኤፍሬም ጀማል አብዱ


ማውጫ

1 ሐዲስ አለማየሁ...................................................................................................... ......1

2 ኅሩይ ወልደሥላሴ…………………………………………………………………………………..26

3 አቤ ጎበኛ……………………………………………………………………………………………..55

4 ተክለሐዋርያት……………………………………………………………………………………….60

5 በእምነት ገብረአምላክ………………………………………………………………………………88

6 ማሞ ውድነህ………………………………………………………………………………………..94

7 ይልማ ሐብተየስ…………………………………………..………………………………………114

8 ነጋሽ ገብረማርያም እና ወንድሙ አሰፋ ገብረማርያም………………………………………….124

9 መኮንን እንዳልካቸው……………………………………………………………………………..141

10 ዳኛቸው ወርቁ…………………………………………………………………………………..152

11 እምሩ ኃይለሥላሴ………………………………………………………………………………167

12 አማረማሞ……………………………………………………………………………………….210

13 ወልደ ግዮርጊስ ወልደ ዮሃንስ………………………………………………………………….222

14 ሶስቱ የመዛግብተ ቃላት አዘጋጆች……………………………………………………………..238

15 ብርሀኑ ዘርይሁን………………………………………………………………………………...249

16 ስብሐትገብረእግዚአብሔር……………………………………………………………………..265
17 አሰፋገብረማርያም ተሰማ……………………………………………………………………….275

18 ፀጋዬ ገብረመድህን………………………………………………………………………………291

19 መንግስቱለማ…………………………………………………………………………………….297

20 ታደለ ገብረሕይወት……………………………………………………………………………..313

21 አለቃ ገብረሃና……………………………………………………………………………………321

22 አበራ ለማ………………………………………………………………………………………..328

23 ተስፋዬ ገሠሠ……………………………………………………………………………………335

24 ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም……………………………………………………………………..361

25 ታደሰ ሊበን………………………………………………………………………………………380

26 ሲራክ ኅሩይወልደሥላሴ………………………………………………………………………..392

27 በዓሉ ግርማ……………………………………………………………………………………..397

28 ከበደሚካኤል …………………………………………………………………………………………………………………….410
ጥቋቁር አናብስት

ሐዲስ አለማየሁ
የፖለቲካ ሰው እና ቁንጮ ኢትዮጵያዊ ደራሲሐዲስ አለማየሁን
ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋቸው በጎርጎሳውያኑ 1970 አካባቢ ነው።
ቦታውም ከአዲስ አበባ100 ኪሜ አካባቢ በምትርቀው ዝነኛ
የመዝናኛ ቦታ ሶደሬ ነበር። በወቅቱ አንዱንም መጽሀፋቸውን
አላነበብኩም፤ ስለእርሳቸው የማውቀውም አንዳች ነገር አልነበረም።
ነገር ግን "ዝነኛው የኢትዮጵያ ደራሲ" መሆናቸው ተነግሮኛል ።
ቀጥዬ በ1978 ዓ.ም እስከማገኛቸው ድረስ፣ የፃፏቸውን ሁሉንም
መጽሀፍት ከማንበቤ ባሻገር ስለ ፖለቲካ ሰውነታቸው በብዛት
ሰምቻለሁ። ከዚህ ቀደም ብዬ እ.ኤ.አ በ1980 ስለ ኢትዮጵያ ሥነ
ጽሑፍ አንድ መጽሐፍ ጽፌ ነበር። በመጽሐፉ የሐዲስ አለማየሁ ሥራዎችን በሰፊው ዳስሼያለሁ።
በወቅቱ መጽሐፉን ልኬላቸው ስለነበር ሀዲስ አለማየሁ ስለእርሳቸው የፃፍኩትን አንብበው
እንደወደዱት ኋላ ነግረውኛል። “ሙገሳው ቢበዛም በደስታ ተቀብዬዋለሁ” ነበር ያሉኝ። በ1978
ዓ.ም ሊያገኙኝ ተስማሙ፤ በእርግጥ ይጽፉት የነበረውን መጽሐፋቸውን ረቂቅ ለማረም፣
ለመጨረስና ለአታሚዎቹ መላክ ይፈልጉ ስለነበር የቀጠሮአችንን ቀን፣ማስተላለፍ መረጡ። ሁሉም
ተሳክቶ በመጨረሻ በህዳር 1978 ስንገናኝ የደከሙና የተሰላቹ መስለው አገኘኀቸው፤ረዥም
ቃለመጠይቅ ለማድረግም አመነቱ። ነገር ግን አንዴ በቀላል ጥያቄዎች ካስጀመርኳቸው በኋላ፣
ሁለታችንም ጨዋታውን ለማቆም ቸገረን። እያንዳንዳቸው ረዥም ሰአት የፈጁ ብዙ
ቃለመጠይቆችን አደረግን።በቆይታችን ወቅት ሁሉ ሐዲስ ግልጽ፣ ሰው ወዳድ፣ ቀጥተኛና ተግባቢ
ነበሩ።

ሐዲስ አለማየሁ አዲስ አበባ1 ውስጥ አስመራ መንገድ ላይ ከቡልጋሪያ ኤምባሲ አጠገብ፣ በግንብ
በታጠረ ና በእጽዋት በተሞላ ደስ የሚል ግቢና ቤት ውስጥ ።ከሶስት ዘመዶቻቸው ጋር አብረው
ይኖሩ ነበር። ሁሌም የምንገናኘው ማረፊያ ክፍላቸው ውስጥ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምንጣፍና
ሁለት ሶፋዎች ክፍሉን አሳምረውታል። ግድግዳው ላይ ያለው ብቸኛ ጌጥ፣ በእሳት ማንደጃው
ትክክል የተሰቀለው የጢስ አባይ ፏፏቴ ቅብ ስእል ብቻ ነው። አቶ ሀዲስ አቅም እንደሚያንሳቸውና
እንደሚደክማቸው ቢናገሩም ጤነኛ ይመስሉ ነበር። የጤናቸውን ሁኔታ ለመከታተል ሀኪም ጋር
ሄደውፀረ–ሕዋስ መድኀኒት ታዞላቸው ነበር። መድኀኒቱ እንደውም ድካማቸውን አባባሰባቸው።
በጭንቅላታቸው ጎን፣ በግራና በቀኝ፣ ፀጉራቸው እንደ መሸበት ብሏል፤ ግን ከዚህ ይልቅ ጎላ ብሎ
የሚታየው ከግንባራቸው ገለጥ ያለ በራቸው ነው። ከላይ የፊት ፍንጭታቸውበቀር ጥርሳቸው
ሙሉ ነው። ደግሞም በደንብ ይሰማሉ፣ ያያሉ፣ ያወራሉ። አእምሮአቸው ንቁ ነው፣ የማስታወስ
1
ጥቋቁር አናብስት

ችሎታቸውም እንዲሁ። ሀሳባቸውን ለመግለጽና ለማብራራት ችግር የለባቸውም።


በቃለመጠይቃችን ወቅት በኢትዮጵያርካሽ ነው የሚባለውን ኒያላ ሲጋራ ያጨሱ ነበር።

****

ሐዲስ አለማየሁ የተወለዱት በ1902 ዓ.ም አካባቢ ሳይሆን አይቀርም። በዛኔይቱ ኢትዮጵያ ልደት
አይመዘገብም ነበር፤ ስለዚህ የትውልድ ዘመናቸውን በግምት 1906 ዓ.ም ብለው በሕጋዊ ሰነዶች
ላይ አስፍረዋል። ኋላ ግን አንድ ነገር ጥርት ብሎ ታወሳቸው። እናታቸው በልጅነታቸው “ሰዎች
እድሜህን ከጠየቁህ፣ በሰገሌ ጦርነት ጊዜ ሰባት አመቴ ነበር ብለህ መልስ”ያሉት ትዝ አላቸው። ይህ
ጦርነት በ1909 ዓ.ም እንደመካሄዱ የሐዲስን የትውልድ ዘመን 1902 ዓ.ምያደርገዋል።
እንደውም ቀኑ እራሱ የሰገሌ ጦርነት በተካሄደበት የጥቅምት ወር እና ቀን ሳይሆን አይቀርም።
ሐዲስ የተወለዱት በጎጃም ክፍለ ሐገር፣በደብረ ማርቆስ አውራጃ፣ በጎዛምን ወረዳ፣ እንዶዳም2
በምትባል ትንሽ መንደር ነበር። በመንደሩ አጠቃላይ የሚኖሩ ቤተሰቦች ከ100 ያንሳሉ፤ እንደውም
ግፋ ቢል ከ50 ወይ 60 አይበልጡም።

አባታቸው አቶ አለማየሁ ሰለሞን ቅድሚያ ካህን፣ ከዚያም አለቃ ሆነዋል። ትውልዳቸው ኤልያስ
ቢሆንም አግብተው የወለዱት እንዶዳም ነው። ቢሆንም ሐዲስ ገና ሁለት ዓመታቸው እያለ
ጨቅላውንና እናቱን ጥለው ወደ ኢሊባቦር ተሻገሩ፤ በቅስናው ለመቀጠል ሳይሆን አይቀርም።
አለቃ የሚለውን ማእረግ ያገኙትም እዛው ኢሉባቡር እያገለገሉ ሳለ ነው3። እናታቸው ደስታ
አለሙ የእንዶዳም ተወላጅ ሲሆኑ በ16ተኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ ግማሽ በአህመድ ግራኝ
ወረራ ወቅት በነበረው የኦሮሞ እና የአማራ ጋብቻዎች የተነሳ በደማቸው ውስጥ የኦሮሞ ዝርያ አለ።
አባቷ የዜማ መምህር እና መራቂ ሲሆኑ ይኸም ተማሪዎች ዜማ ካጠኑ በኋላ የሚፈትን ሊቅ ማለት
ነው። ሐዲስ በእናቶቹ ወላጆች፣ በአያቶቹ ቤት፣ በእናቱ እጅ አደገ። ለእናቱ እና አባቱ ብቸኛ ልጅ
ቢሆንም፣እናቱ ከሁለተኛ ጋብቻቸው ሁለት ወንድ እና ሶስት ሴቶች ልጆች ወልደዋል። ከነዚህ
መሐል አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት ልጆች፣ እስከ 1978 ዓ.ም ድረስ በሕይወት የነበሩ ሲሆን
ሐዲስ ወንድሜ እና እህቶቼ እያሉ በአክብሮት ይጠሯቸዋል። አባታቸው ዳግመኛ ቢያገቡም ሌላ
ልጅ አልወለዱም። ሐዲስ ከእናታቸው አባት ዘንድየዜማ ትምህርታቸውን በ6 ዓመታቸው
ጀምረው እስከ 15 ዓመታቸው ድረስ ቀጠሉ። ፆመ ድጓን አጠናቀው ጨርሰዋል ፤ አሁንም ቢሆን
ጥሩ የዜማ አዋቂ አድርገው እራሳቸውን ይቆጥራሉ። ከዚያም ወደ አባታቸው ሐገር ኤልያስ
አቅንተው ቅኔ ተማሩ። ቀጥሎም ወደ ደብረወርቅ ከዚያ ዲማ በመሄድ የቅኔ ትምህርታቸውን በ17

2
ጥቋቁር አናብስት

ወይም 18 ዓመታቸው አጠናቀቁ። የቅኔ ትምህርታቸው ከተለመደው ሁለት ዓመት ወይም ትንሽ
በለጥ የሚል ጊዜ ወስዶባቸዋል። ሀዲስ ያደጉበት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርአት ቅባት በመባል
ሲታወቅ፣ በጎጃም ስር የሰደደ ነው።

ሐዲስ ደስ የሚል የልጅነት ጊዜ ያሳለፉ ሲሆን፣ በተለይ የእንዶዳሙ የተለየ ነበር። በዚያች ትንሽ
መንደር ከብቶችን እያገዱ፣ ከወንድ እና ሴት ልጆች ጋር በመጫወት ጣፋጭ ጊዜ ያሳልፉ ነበር።
ከእኩያዎቹ ጋር መጫወት በመውደዳቸው ሃላፊነታቸውን አልተወጡም፣ ጨዋታ እና ቧልት
አብዝተዋልበሚል ይደርስባቸው የነበረውን ግሳፄና ቅጣትያስታውሳሉ።እንዲህም ሆኖ ሐዲስ
ደስተኛ ህፃን ነበሩ፤ጥሩ የልጅነት ትዝታዎችም አሏቸው። ከተማሪነት ሕይወታቸው ይልቅ
በመንደር ሕይወታቸው ሀሴት አድርገዋል። ትምህርታቸውን በቁምነገር ጉዳዬ ብለው የያዙት፣
አዲስ አበባ መጥተው ዘመናዊ ትምህርት ከጀመሩ በኋላ ነው። እዚህ ፈተናዎች ስለሚኖሩ፣
በርትተው መማርና ማጥናት ይጠበቅባቸው ነበር።የደብረወርቅና የዲማ4 ትዝታዎቻቸው
የሚያጠነጥኑት በቤተ ክርስቲያን እና በትምህርታቸው ዙሪያ ነው።ቅኔ ቢወዱም፣ በዚህ ዐይነት
የሥነ ግጥም ዘርፍ አልገፉበትም፤ምንም የቅኔ መጽሐፍም አላሳተሙም።

በቅኔ ከተመረቁ በኋላ፣ ሐዲስ በ1918 ዓ.ም በዋና ከተማዋ በሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል
ቤተክርስቲያን የአለቃነት ማእረግ ከተሰጣቸው የቀድሞ መምህራቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ መጡ፡
፡ሐዲስ በመካነ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ በሚገኘው የስዊድን ሚስዮን ትምህርት ቤት
ገቡ።ትምህርት ቤቱ የአምስት ኪሎ አደባባይ ከሚገኘው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅርብ
ነበር። ሐዲስ እዚህ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን ከአንደኛ ክፍል ለመጀመር ተገደዱ።
ምክንያቱም እስካሁን ከባህላዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ፈቅ አላሉም፤ከግዕዝና አማርኛ ቋንቋ
በስተቀር አያውቁም።አዲሱ ትምህርት ቤታቸው ደግሞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነበር የሚያስተምረው።
ርእሰ መምህራቸው ፔር ሶጆርን ሲባሉ መምራኖቻቸው ደግሞ ኤሪክሰን እና ኒልሰን ነበሩ።ሁሉም
ቄሶች ነበሩ። ሐዲስ ትምህርት ቤቱንም ሆነ መምህሮቻቸውን ወደዋቸው ለሁለት ዓመት ያህል
ቆዩ። ከዚያም የሶስተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለመቀጠል ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብተው
የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እስከሚጨርሱ በዚያው ቆዩ። ከዚህ በኋላ በምኒልክ ትምህርት
ቤት የሚሰጠውን የመምህራን ማሰልጠኛ ትምህርት ከ6–8 ወር ለሚሆን ጊዜ ተከታተሉ። በ23
ወይም 24 ዓመታቸው ቀድሞ በተማሩበት የስዊድን ሚስዮን ትምህርት ቤት 1 ዓመት (8 ወይም
9 ወር) ለሚሆን ጊዜ በደስታ አስተማሩ።

ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በነበራቸው ቆይታ፣ ተውኔቶች፣ ትወና እና ድርሰት ላይ ፍላጎት


አሳይተዋል።ሼክስፒርንና ሌሎች ጸሐፌተውኔቶችንም አንብበዋል። በየዓመቱ የትምህርት
ማጠናቀቂያ ላይ ተማሪዎች በግርማዊቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት ተውኔቶችን ያቀርቡ ስለ ነበር፤

3
ጥቋቁር አናብስት

ሐዲስም የዘወትር ተሳታፊ ነበሩ። እሳቸው እንደሚሉት ተማሪዎችም፣ መምህራንም ትወናቸውን


ወደውላቸዋል። እንግዲህ እዚያእያሉ ነበር የመጀመሪያ ተውኔታቸውን የፃፉት፤ ርእሱም "የሀበሻና
የወደኋላ ጋብቻ" ይሰኛል። ከዚህም ባሻገር፣ የተውኔቱን መዝሙር የደረሱት እራሳቸው ነበሩ።
ተውኔቱ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሴት“ኋላቀር” የተሰኘ ሰው አግብታ ስለወለደቻቸው ልጆቿ
ይተርካል። ልጆቹ ስለራሳቸው ምቾት እና ደስታ እንጂ ስለእናታቸው ኢትዮጵያ አያስቡም።
በዚህም የኢትዮጵያ ታላቅነትና ክብር አደጋ ላይ ይወድቃል። ብሎም ኢትዮጵያ ትደኸያለች፣
ትታመማለች። የአይን በሽታ ያጠቃትና ትታወራለች፣ ማየት ይሳናታል።ኑሮዋም የስቃይ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ለወንድና ለሴትም ልጆቿ ለዚህ ያበቃለት የነሱ አመል መሆኑንም ሳትደብቅ
ትነግራቸዋለች። በመጨረሻ ትንሹ ልጇ ኃይለሥላሴ ይወለድና ሁኔታዎችን ይቀይራል፤ ቤተሰቡን
ወደብልጽግና እና ደኅንነትይመራል። እናቱ ኢትዮጵያም ተገቢውን ህክምና ታደርግና ትታከማለች
፤ የአይን ብርሀኗም ይመለስላታል።

በ1921 ዓ.ም የትምህርት መዝጊያ ወቅት፣ተማሪዎቹ ይህንን ተውኔት ማሳየት ቢፈልጉም


የትምህርት ሚኒስትሩ ብላቴንጌታ ሳህሌ ፀዳሉ ተቃወሙ። ተማሪዎቹ ግን ተውኔቱን በሚስጥር
አጠኑና ግርማዊነታቸውን ፈቃድ ጠየቁ። ግርማዊነታቸውም መልካም ፍቃዳቸው ሆነና ተውኔቱ
በማጀስቲክ ሆቴል ታይቶ የከተማው መነጋገሪያ ሆነ።

ከኢጣሊያ ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት፣ አቶ ሐዲስ ይህንንና ሌሎች ንብረቶቻቸውን ሸክፈው


ከእናታቸው ዘንድ አስቀመጡ። ነገር ግን በጦርነቱ ወቅት ጠፍቶ ቀረ፤ ዳግመኛም አልተገኘም።

ይህ ተውኔት ሀዲስ አለማየሁን ከቀደምት የኢትዮጵያ ፀሐፌ ተውኔቶች አንዱ ያደርጋቸዋል። ነገር
ግን ሐዲስ በተማሪነታቸው ወቅት፣ የብላቴንጌታ ኅሩይወልደሥላሴን “ወዳጄ ልቤን” ስላነበቡ፣
“ኅሩይ ቀዳሚ ነው” ይላሉ5።በተጨማሪም ዮፍታሔ ንጉሴ ከእርሳቸው ቀደም ብለው ተውኔት
ይጽፉ እንደነበር ይናገራሉ። ሐዲስ ይህንን ተውኔት ከፃፉ በኋላ መላኩ በጎሰው6 የተባሉ ፀሐፊ፣
ተውኔት መፃፍ ጀመሩ። በ1922 ዓ.ም የታተመው የብርሀንና ሰላም ጋዜጣ የሐዲስን ተውኔት
ጠቅሶጽፏል።

ኃይለሥላሴ በፍፁም የሐዲስን ተውኔት አልተመለከቱም።“ምክንያቱም ” ይላሉ ሀዲስ“ንጉሦች ወደ


ሆቴል ቤት አይሄዱም”። ነገር ግን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩን ቢትወደድ ወልደፃዲቅን ወደ
ማጀስቲክ ሆቴል ሄደው ቲያትሩን ይመለከቱ ዘንድ አዘዋል። ቲያትሩም ጥቅጥቅ ብሎ በሞላ ትልቅ
አዳራሽ ውስጥ ነበር የታየው። በኋላም ኃይለሥላሴ ተዋናዮቹ ተውኔቱን በቤተመንግሥት
ተገኝተው ይጫወቱ ዘንድ ጋበዟቸው፤ ነገር ግን ይህ ሳይሳካ ቀረ። ከዛ በ1923 ዓ.ም ልዑል አልጋ

4
ጥቋቁር አናብስት

ወራሽ ከራስ ስዩም ልጅ ጋር ሲጋቡ ተውኔቱን በቤተመንግሥት እንዲያቀርቡ ታዘዙ። ነገር ግን


ሶስት ሰአት በሚፈጀው በዚህ ተውኔት ውስጥ ሐዘንና ለቅሶ የሚበዛባቸው ገቢሮች ስለነበሩ፣
በሰርግ ላይ ለማቅረብ አመቺ አይደለም ተባለ። በምትኩም ሌላ ተውኔት ተፃፈ። ሆድ አምላኩ
የተሰኘውን አዲሱን ተውኔት ሲያዘጋጁ፣ሐዲስ ብቻቸውን አልነበሩም።በጅሮንድ ሰብስቤና ሐዲስ
ስሙን አሁን ሊያስታውሱት ያልቻሉት አንድ ሰው ረድተዋቸዋል።

ይህም አስቂኝ ትእይንቶች፣ ብዙ ዐይነት ጭፈራዎች፣ ጨዋታዎች፣ብቻ በአጠቃላይ ሳቅና ደስታን


በሰርጉ ላይ ለመጫር ያለመ ተውኔት ነበር። የፃፉት ተውኔት በሶስት በአንጓ ተከፋፍሎ ሲታይ፣
ኃይለሥላሴም በመጨረሻ ለተውኔቱ ጸሐፊዎችና ለተዋናዮቹ ሽልማት ሰጡ። ሐዲስ የንጉሱ ምስል
ከጀርባው ያለበትን ሰአትና 50 ብር ሲሸለሙ ተዋናዮቹ እያንዳንዳቸው 50 ብር ደረሳቸው።

***

በ1924 ዓ.ም ሐዲስ ወደ ጎጃም ተመለሱ።ከ1918 እስከ 1924 ዓ.ምድረስ ያለፈው ጊዜ፣ ሐዲስ
ከሰሯቸው ስራዎች አንፃር አጭር ነበር። ቀኖቹን ያስቀመጥኩላችሁ ግን እሳቸው እንደነገሩኝ ነው።
1925 ዓ.ም ግንቀጥሎ ከሚሆነው ሁነት ጋር ይበልጥ የሚጣጣም ይመስለኛል።በመጀመሪያ
በዳንግላ የጉምሩክ ጽህፈት ቤት ጸሐፊ ሆነው ለ ሁለት ዓመትሰሩ።በዳንግላ የእንግሊዝ ቆንስላ
ጽህፈት ቤት ነበር። ነገር ግን ጽህፈት ቤቱ ተዘግቶ ቆንስሉ ወደ ሀገሩ ሲመለስ፣ ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ
ወደ ትምህርት ቤትነት ተቀየረ። ሐዲስም ትምህርት ቤቱን ስራውን እንዲያስጀምሩና በርእሰ
መምህርነት እንዲያስተዳድሩ ተመረጡ። ከ1ኛ―3ኛ ክፍል የሚያስተምር አንደኛ ደረጃ
የመንግስት ትምህርት ቤት ነበር።ሐዲስ በዚህ የስራ ቦታ የቆዩት ለአንድ ዓመት ብቻ (ከ1926–
1927) ሲሆን።በአብዛኛው ሥራቸው መቆጣጠር እና ማስተዳደር ቢሆንም አልፎ አልፎ
እንግሊዝኛ ያስተምራሉ፤ለተማሪዎች የሚሆን መዝሙርም አዘጋጅተዋል።

ከዚያም በ1927 ዓ.ም ወደ ጎጃም ዋና ከተማ ደብረማርቆስ ተዘዋውረው በርእሰ መምህርነት ፈንታ
እንግሊዝኛ እና ሂሳብ ለሦስትና አራተኛ ክፍሎች ማስተማር ጀመሩ።ይኼም በወልወል ግጭት
ወቅት ሲሆን፤ እዚያ በቆዩበት አንድ ዓመት ከጣሊያን ጋር ጦርነት ሊኖር እንደሚችል ብዙ ይወራ
ነበር። በዚህ መሐል "የሀበሻና የወደኋላ ጋብቻ" የተባለ ተውኔታቸው ማስተካከያ ተደርጎበት፣
በደብረ ማርቆስ ለመድረክ በቃ። አስተዳዳሪው ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ ሐዲስን ለአርበኝነት
የሚያነሳሳ አጭር ተውኔት እንዲጽፉ ጠየቋቸው።አዲስ የተጠየቁትን ከማድረጋቸውም ባሻገር
"የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በአድዋ" የሚል መነባንብም ጨምረው አዘጋጁ። ትርኢቱ
የተዘጋጀውየሕዝቡን መንፈስ በወታደሮች ፉከራ ለማነቃቃት ሲሆን በአጠቃላይ ቀስቃሽና

5
ጥቋቁር አናብስት

ስሜታዊነት የሚንፀባረቅበት ነበር። ይኼ ሁሉ የሆነው በ1927 ዓ.ም ሲሆን፣ በወቅቱ"የኢትዮጵያ


እና የወደኋላ ጋብቻ" ተውኔትን አብሮ ሲከታተል የነበረው የኢጣሊያ ቆንስላበመልእክቱ ጥሩ
ስሜት ስላልተሰማው አቋርጦ መውጣት ፈልጎ ነበር ፤ እስከመጨረሻው እንዲያየው ተገደደ እንጂ።

***

ይህ የመጨረሻ ተውኔት፣ ሐዲስ የጦር ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ ያስወሰናቸው ምክንያት ሆነ።


ሀሳባቸው ልክም ይሁን ስህተት፣ የጦር ሰራዊቱ ሊፈልገኝ ይችላል ብለው ስላሰቡ ። ተቀላቀሉና
በተራ ወታደርነት ወደ ትግራይ ዘመቱ።በምእራብ በኩል በሽሬ ስር ዋና ግንባር በሆነው ሰለቅለቃ
ላይ በራስ እምሩ ስር ሆነው ጣሊያኖችን ወጉ። ተሸንፈው ሲያፈገፍጉ ራስ እምሩ ሐዲስን ወደ
ሱዳን ሄደው የጦር መሳሪያ፣ትጥቅ፣ድንኳንና የመሳሰሉትን እንዲሸምቱ ላኳቸው። ሀሳባቸው
በአርበኝነት (በጉሬላ ስልት) ጦርነቱን መቀጠል ነበር። ሀዲስ ምንም እንኳን ተራ ወታደር የነበሩ
ቢሆንም፣ በትምህርት ደረጃቸው የተነሳ ነው ከበድ፣ ከበድ ያሉ ሀላፊነቶች የተሰጧቸው። ከዛም
ተከዜ ወንዝ ሲደርሱ ከዋናው ሰራዊት ተገነጠሉና ወደ ሱዳን ገሰገሱ። ዮሐንስ አብዱ7 እና ሌሎች
50 ወታደሮች ሐዲስን ሱዳን ገዳሪፍ አደረሷቸውና ተመለሱ። ሐዲስ በግንቦት ካርቱም ደርሰው
እስከ ነሐሴ 1928 ዓ.ም ድረስ በዚያው ቆዩ። በዚያ እያሉም ራስ እምሩ በዚያው ወደ እንግሊዝ
እየተሻገሩ በነበሩትበብላቴንጌታ ኅሩይ ሁለት ልጆች (ፈቃደስላሴ እና ሲራክ) አማካኝነት በፊት
በነበሩበት በተከዜ ፈንታ አሁን ባሉበት በኢሊባቡር በኩል፣ ጎሬ ይገናኟቸው ዘንድ ለሐዲስ
መልእክት ላኩ። ይህ ደብዳቤ በነሐሴ ደረሰ። ሐዲስም ነጭ አባይንና ከፊል ኢሊባቦርን ተሻግረው
ጎሬ ደረሱ። በመጨረሻም በመስከረም 1929 ዓ.ምከራስ እምሩ ጋር ተገናኙ።

ከዚያም አርበኞቹን ተቀላቅለው ጣሊያኖችን በጎሬላ ጦርነት መውጋት ያዙ። የመጀመሪያውውጊያ


ለኢጣልያ አድረው የገዛ ወንድሞቻቸውን ከሚወጉትከወለጋው ገዢ በደጃዝማች ሀብተማርያም
ገብረእግዚአብሔር ስር ካሉ ኢትዮጲያውያን ጋር ሆነ።ደጃዝማቹ አስካሪ እና ባንዳ ከኤርትራ
አስመጥተው ሰራዊታቸውን አጠናክረው ነበር። በሆለታ የጦር ትምህርት ቤት ውስጥ በስዊድኖች
የሰለጠኑ መኮንኖች በመጀመሪያ ከሀብተማርያም ጦር ጋር የተሰለፉ ቢሆንም ተታለው ለጣልያኖቹ
እንዳደሩ በተረዱ ጊዜ ሰልፋቸውን ቀይረው ከራስ እምሩ ወታደሮች ጋር ተቀላቅለው
ሀብተማርያምን መውጋት ያዙ። ዋናው ጦርነት በቡናያ ተካሄዶ በሁለቱም ወገን ብዙ ሰው አለቀ።
ለሐዲስ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያንን ሲገድሉ ማየት አሰቃቂ ነበር። በዚህ የቡናያ ጦርነት፣
የራስ እምሩ ሐይሎች በለስ ቀናቸው። የእምሩ ጦር ከዚህ ተነስቶ ወደ ጅማ ገሰገሰ።ከጅማ ብዙም
በማትርቀው ቡኖ ሲደርሱ፣ጅማ ከሁለት ሳምንት በፊት በጣሊያኖች እጅ እንደወደቀች ሰሙ።
በቡኖ8 ሌሎች የነፃነት ተዋጊዎችን አገኙና ተቀላቅለው በሕብረት ወደ ከፋ አቀኑ። በዚህም የሸዋው

6
ጥቋቁር አናብስት

ንጉሥ የልጅ ልጅ የሆኑት ደጃዝማች ታዬ ጉልላት ሀገረ ገዢ ነበሩ። ኢጣሊያኖች ይህንን


እንቅስቃሴያቸውን ስለሚያውቁ ይከታተሏቸው ነበር።በጅማ አባ ጅፋር አውራጃ ስር
በነበረቸውጌራ ጣሊያኖችን ገጠሙና ተሸነፉ፤ ተመልሰው ወደ ከፋ ሸሹ።ነገር ግን የከፋ ዋና ከተማ
ቦንጋ በጣሊያኖች እጅ ስለወደቀች ታዬ ጉልላትም ተማረኩ። በመጀመሪያም የኢጣሊያ ወታደሮች
ሲከታተሏቸው ነበርና፣ በጅማ እና ከፋ ድንበር ላይ በሚገኘው ጎጀብ ወንዝ ላይ በሁለቱም
አቅጣጫ ተከበቡ፤ እጃቸውን ሰጥተው ሁሉም ታሰሩ።9

እስረኞቹ ወደ ቦንጋ ተወሰዱ፤ሐዲስም በዚያ ለሶስት ሳምንት ቆዩ።ደጃዝማች ታዬ እና ራስ እምሩ፣


በአውሮፕላን ሆነው ወደ ኢጣሊያ ከተላኩት የመጀመሪያ ሆኑ። ሐዲስ እና የተቀሩት፣ አብዛኛዎቹ
ተሸናፊ ወታደሮች ወደታጎሩበት ጅማ ተወሰዱ። ሐዲስ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደረገና
ብዙም ሳይቆይ ከአንድ አራት ቀን በኋላ ከይልማ ደሬሳ እና ሌሎች ጋር ሆነው፣ ወደ ኢጣሊያ
ተጋዙና ራስ እምሩን እና አብረዋቸው የነበሩትን እንዲቀላቀሉ ሆነ። ኢጣሊያ ውስጥ በመጀመሪያ
የቆዩት በምእራብ ሜዲትራኒያን በምትገኝ ፖንዛ በተባለች ደሴት ሲሆን ሐዲስ እዚህ ለ2 ዓመት
ከ1010 ወር ቆይተዋል። በኋላም ከሳርዲኒያ አጠገብ ወደምትገኘው ሊፓሪ ደሴት ተዛወሩ። ይሁንና
ይልማ ደሬሳ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ሲደረግ ሐዲስና ራስ እምሩ በዚሁ ሊፓሪ ደሴት
ለሁለት ዓመት ከአስር ወር ቆዩ። በዚያም ሐዲስ በብሮንካይተስ በጠና ታመሙ፤ በዶክተር ትእዛዝ
ወደ የብሱ ካላብሪያ ግዛት እንዲሄዱ በመደረጋቸው ራስ እምሩን በሊፓሪ ደሴት ትተዋቸው መሄድ
ግድ ሆነባቸው። በካላብሪያ ሉንጎ ቡሌ ሐዲስ፣ ግርማቸው ተክለሀዋርያትን11 እና ሌሎች አስራ
ዘጠኝ ኢትዮጲያውያንን አገኙ። ሐዲስ እና ሌሎች እስረኞችን የእንግሊዝ እና ካናዳ ወታደሮች
በዛች የጣሊያን ከተማ ካገኟቸው በኋላ ነፃ ያወጧቸዋል―ጊዜው 1936 ዓ.ም።እነ ሐዲስም
ግርማዊነታቸው ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ከሶስት ዓመት በኋላ ለሃገራቸው አፈር በቁ። ሐዲስ
በኢጣሊያ ቆይታቸው ወቅት፣ ወታደሮቹ ምንም ዐይነት የማሰቃያ መንገድ አልተጠቀሙባቸውም ፤
ወይም በሌላው ላይ ሲጠቀሙ አልተመለከቱም።አያያዛቸውም እንደ እስረኛ ሳይሆን የማቆያ
መጠለያ ውስጥ እንዳሉ ሰዎች ነበር። ማቆያቸው በተከለከለ ስፍራ ሲሆን፣ ከመጠለያው መውጫና
መመለሻ ቋሚ ሰአት አላቸው።ይሁንና የአካባቢው ተራ ዜጎች ለነዚህ የሰው ሐገር ሰዎች
ከማዘናቸውም ባሻገር፣ እነሱን በመደገፍ ከመጠለያው መኮንኖች ጋር ይጣሉ ነበር።

***

ሐዲስ በኢጣሊያም ሆነው ቆይታቸውን በተመለከተ ግጥም ጽፈዋል ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣


ግርማዊነታቸው ግጥሞቹን እንዲያሳትሙ ሊረዷቸው ተስማሙ።በዚህም ምክንያት ግጥሞቹ
በጊዜው የፍትህ ሚኒስትር ለነበሩት ዘውዴ ገብረየስ እንዲያስቀምጡ በአደራ ተሰጠ። ታዲያ አቶ

7
ጥቋቁር አናብስት

ዘውዴ በችኮላ ወደ ውጭ ሐገር ለሥራ ሲሄዱ አቶ ኦሊቨር ስኮት ለሚባሉ ግለሰብ ሰጧቸው።
ሐዲስ እንደሚሉት እነዛ ግጥሞች ከዛ በኋላ ዳግመኛ አልታዩም ፤ ጠፍተው ቀሩ።

ወደ አዲስ አበባ በተመለሱ ቀን ግርማዊነታቸው እራሳቸው ተቀበሏቸው።በዋና ከተማዋ ዘመድ


የሌላቸው ተመላሾች፣የመንግሥት እንግዳ ተብለው አሁን የእርሻ ሚኒስቴር ከሚገኝበት ቦታ
ማደሪያ እንዲሰጣቸው ተደረገ።12

ሐዲስ ወዲያውኑ በፕሬስ እና ፕሮፓጋንዳ መስሪያ ቤት (ወይም የጋዜጣ እና መረጃ መስሪያ ቤት፣
በመጨረሻ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በተደረገው) ስራ ተሰጣቸው፤ እዚያም ለ5 ወይም 6 ወር ሰሩ።
ከዚያም ለጥቂት ወራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሩ።ሁለቱም ቦታ የሰሩበት ጊዜ ባንድነት
ቢቆጠር ከዓመት አይበልጥም።ከዚያም በየካቲት 1937 ዓ.ም በጊዜው በእንግሊዝ አስተዳደር ስር
በነበረችው በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቆንሲል ሆነው ለሁለት ዓመት ሰሩ።በዚህ ወቅት ምንም
አልፃፉም።ነገር ግን እዚያው እየሩሳሌም ያደጉትንና እዚያው የሚኖሩትን ክበበ–ፀሐይ በላይን
አገቡ።

ከእየሩሳሌም በቀጥታ የተላኩት የኢትዮጵያ ዋና እና ብቸኛ የመገናኛ ተወካይ ሆነው፣ በአለም አቀፉ
የቴሌኮሙኒኬሽን ጉባኤ ለመካፈል ወደ አትላንቲክ ሲቲ፣ ሰሜን አሜሪካ ነበር። በጦርነቱ ጊዜ
እንዲህ ዐይነት ጉባኤ ስላልነበርና፣ ነገሮች ስርአት ባለመያዛቸው የሚሰራ ብዙ ስራ በመኖሩ
ከሃገራቸው ብቸኛ ተወካይ በመሆን ሁሉንም ስብሰባዎች(የፍሪክዌንሲ፣የአስተዳደርና የዲፕሎማቲክ
ጉባኤዎች)በአንድ ላይ መካፈል ነበረባቸው። ይህም ለአምስት ወራት ያህል ቆየ።

ይህ ጉባኤ ከተጠናቀቀም በኋላ፣ በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ሌጋስዮን ውስጥ፣ በራስ እምሩ


ሚኒስትርነት ስር፣ ዋና ፀሐፊ ሆነው በሰሜን አሜሪካ ቆዩ። ሐዲስ እንደሚሉት ከራስ እምሩ ጋር
“በጥሩ ስምምነት” አብረው ሰርተዋል።በዚሁ ጊዜ፣ ሐዲስ በለጋሲዮኑ ውስጥ ካላቸው ስራ ባሻገር፣
በተባበሩት መንግስታት ንዑስ ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው መስራት ጀመሩ። ስለዚህ
ባልተጠበቁ ጊዜያት ስብሰባዎች ስለሚጠሩ፣ በተደጋጋሚ ወደ ኒውዮርክ እየተጓዙ አንድ ሳምንት
13
ለሚሆን ጊዜ ቆይተው ይመለሱ ነበር። ሐዲስ በዋሺንግተን ከ1939–1945 ዓ.ም ድረስ ቆዩ።
በዚህ ወቅት መጨረሻ በተባበሩት መንግሥታት የነበራቸውን ስራም አቆሙ። ሐዲስ ከሁለቱ
ስራዎቻቸው ባሻገር፣ ዋሺንግተን በሚገኘው አሜሪካን ዩኒቨርስቲ በማታ የትምህርት ክፍለ ጊዜ፣
አለም አቀፍ የህግ ትምህርትን፣ ለሁለት ዓመታት ተከታትለዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ከ1943–1949 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ቅድሚያ


በዳይሬክተርነት፣ ኋላም በምክትል ሚኒስቴርነት ለስድስት ዓመታት አገልግለዋል።
8
ጥቋቁር አናብስት

ከ1949–1953 ዓ.ም ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ለሁለት


ዓመት ከአምስት ወር ኒውዮርክ ውስጥ ሰርተዋል።

በተባበሩት መንግሥታት አምባሳደርነታቸው የነበራቸው ጊዜ አስደሳች እንደነበር ሐዲስ ይናገራሉ።


በአንዳንድ አሳሳቢ ጉዳዮች የኢትዮጵያን አቋም ለመቀየር ንቁ ተሳትፎም አድርገዋል። ለምሳሌ
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት፣ደቡብ አፍሪካን መደገፏን እንድትቀጥል አልፈለጉም።
የቀድሞው ድጋፍ ኢትዮጵያ ከኢጣሊያ ጋር በነበራት ጦርነት ወቅት፡ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች
ድጋፍ ስላደረጉ ውለታ የመክፈል ግዴታ እንዳለባት ከማሰብ በመነጨ ብቻ የሚደረግ ነበረ።
በተጨማሪም ፈረንሳይ በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያን የረዳች ቢሆንም፣ በአልጄሪያ ላይ ላላት ቅኝ
ገዢነት ድጋፍ እየሰጡ መቀጠል አልፈለጉም።ቀደም ያሉ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከአዲስ አበባ
የሚተላለፍላቸውን ትእዛዝ ምንም ሳይጠይቁ የሚያስፈጽሙ ነበሩ፤ሐዲስ ግን ይህን አካሄድ
መቀየር ፈለጉ። በሀገራቸው ስም በነፃ አቋም ለመመራት ወሰኑ።ነገር ግን ኢትዮጵያ በእንዲህ ዐይነት
አለምአቀፍ ሽኩቻዎች ረገድ ያላት ልምድ አነስተኛ በመሆኑ፣ ገና ብዙ መማር እንዳለባቸው
ተገንዝበዋል። ሐዲስ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካየኢኮኖሚ ኮሚሽን በአፍሪካ እንዲቋቋም
ረድተዋል፡፡

በኒውዮርክ በነበራቸው አስደሳች ጊዜ፣ ሐዲስ በተለይ ከማይረሷቸው ሁነቶች አንዱ፣ “የኢትዮጵያ
ቁርጥ ሀሳብ” ዋነኛው ነው። ከአዲስ አበባ ባለሥልጣኖች ጋር ብዙ አለመግባባት ውስጥ የዶላቸው
ይህ “ቁርጥ ውሳኔ” የኔውክሌር ሀይልን ለጦር መሳሪያነት መጠቀምን የሚከለክል ነው። ይኼም
በሁለት ክፍል የተከፋፈለ ነበር። የመጀመሪያው ክፍል በጠቅላላ ጉባኤው የኒውክሌር መሳሪያን
ለጦርነት እንዳይውል መግለጫ ማወጅ ነው፤ይህንን ተላልፎ መገኘት አለምአቀፍ ወንጀል ሲሆን፣
ተሳታፊዎቹም አለምአቀፍ ወንጀለኛ ይሆናሉ ማለት ነው።ይህ መግለጫ ህጋዊ ሀይል አይኖረውም።
የቁርጥ ውሳኔው ሁለተኛ ክፍል ጠቅላላ ጉባኤው ይህን ጉዳይ በተመለከተ አባላቱን ስብሰባ
እንዲጠራ ይጠይቃል።ይህ መግለጫ በዚያን ጊዜ በስምምነት ከተፈረመ፣አስገዳጅነት ይኖረዋል።
ብሪታኒያ፣ሰሜን አሜሪካናፈረንሳይ፣ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያሳየቸውን አቋም ለመቃወም በአዲስ
አበባ ተወካዮቻቸውን አስቀመጡ።ይህም ሩስያ ብዙ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በማከማቸቷ፣
ምእራብያውያን ተመጣጣኝ መሳሪያ ከማከማቸት በስተቀር ሩስያ መሳሪያዎቿን እንዳትጠቀም
ለማገድ ሌላ የመከላከያ አማራጭ የሌላቸው መሆኑን በመግለጽ ነው።ስለዚህ ሐዲስ ከገዛ
መንግስታቸው ይህንን ቁርጥ ውሳኔ እንዲያቆሙ ብዙ ግፊት ተደርጎባቸዋል፤ሀዲስ ግን ቁርጥ
ውሳኔን እንደ ቀላል ማቅረብና መተው እንደማይችሉ ገለፁ። የዚህ ሁሉ እሰጥ አገባ መጨረሻ፣ጉዳዩ
ለድምጽ አሰጣጥ ይቅረብ የሚለው ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ ሀዲስ ድምፀ ተዐቅቦን መምረጣቸው
ሆነ።

9
ጥቋቁር አናብስት

ከሁለት ዓመት በኋላ በ1953 ዓ.ም፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ብራዚልን ጎበኙ።ይህም በአዲስ አበባ
መፈንቅለ መንግሥት የተሞከረባቸው ዓመትማለት ነው።ሐዲስ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ
በተባበሩት መንግሥታት የነበራቸውን ስራ ለቀው ነበር፤ አሁን ግን ለጠቅላላ ጉባኤው ምክትል
ተወካይ ሆነው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደግሞ ዋና ተወካይ ሆነው ላጭር ጊዜወደ የተባበሩት
መንግስታት ተመልሰዋል።ከግርማዊነታቸው ጋር አብሮ የሚጓዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ
በቅድሚያ ወደ ኒውዮርክ አቀና።ሐዲስም በጠቅላላ ጉባኤው የነበሩትን የኢትዮጵያ አባላት
ከመምራታቸው ባሻገር ከሚኒስትሩ ጋር በመሆን "የኢትዮጵያ ቁርጥ ውሳኔ" ሃሳብ ዳግም
እንዲያንሰራራ አደረጉ። ይህንንም ለማስፈፀም ሚኒስትሩ ፈቃደኛበመሆን በጠቅላላ ጉባኤው ፊት
ንግግር አደረጉ። ሐዲስም እንደውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ቁርጥ ውሳኔው ፣ በጠቅላላ
ጉባኤው በከፍተኛ ድምጽ ፀደቀ። በጊዜው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ዳግ ሀመርስክጆልድ
የምክር ቤቱ አባላት በሸንጎ ተሰባስበው ቁርጥ ውሳኔውን እንዲፈርሙ እንዲጠሩ ተጠየቁ።
ጸሐፊውም ለሁሉም አባላት ተዘዋዋሪ ደብዳቤ በመላክ፣በተቆረጠ ቀን በሸንጎው ላይ ለመገኘት
ፍላጎት እንዳላቸው ጠየቁ። ከአባላቱ ሶስት አራተኛዎቹ ቢስማሙ፣ ይህንን ዐይነት ሸንጎ ማድረግ
ይቻላል። ለሁለት ወይም ሶስት ዓመታት ለሚሆን ጊዜ ከአባል ሀገራቱ የተገኘው አዎንታዊ ምላሽ
ሦስት አራተኛ አልሞላም። ስለዚህ ጉዳዩ ቀርቶ ሸንጎውም ሳይካሄድ ቀረ።

ግን በጠቅላላ ጉባኤው የፀደቀው መግለጫ አሁንም እንደፀና ነው። በዚህም የተነሳ አየርላንድ
የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በፍጥነት መስፋፋትን የሚቃወም የቁርጥ ውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ቻለች።
ይህ ውሳኔ በብዙ አባል አገራት ቢፈረምም ለማስፀደቅ የሚሆን ሸንጎ አልተካሄደም ይላሉ ሐዲስ።
የጦር መሳሪያ ቅነሳ ጉባኤው ከቁርጥ ውሳኔው ጀርባ የነበሩ ኢትዮጲያውያንን በሙሉ በአባልነት
ሲያሳትፍ ሐዲስም በዋና ተወካይነት ተመረጡ። ይህን ሀላፊነትም በለንደን አምባሳደር ሆነው
በቆዩበት ጊዜም ይዘውት ቀጥለዋል።

ሐዲስ በዚህ የተነሳ በታህሳስ 1953ቱ መፈንቅለ መንግሥትሙከራ ወቅት በኒውዮርክ ነበሩ።
ስለዚህተገደውም እንኳን ቢሆን ጎራ ለመለየት በሚያበቃቸው ስፍራ አልነበሩም።። ይልቁንም
ሁነቱን፣ንጉሡን ካስወገደውና የመንግሥት ለውጥ ካስከተለው የ66ቱ አብዮት ፍፁም
የተለየየህዝቡ ተሳትፎ ወይም ድጋፍ ያልነበረው “የቤተ መንግሥት ብጥብጥ” አድርገው
ይቆጥሩታል።

***

የተባበሩት መንግስታትን በ1953 ከለቀቁ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታነት
ተሾሙ።ነገር ግን ይህን ሐላፊነት ይዘው ፍፁም አልሰሩም ምክንያቱም ወዲያው የትምህርት

10
ጥቋቁር አናብስት

ሚኒስቴር “ይፋዊ ያልሆነ”ሚኒስትር ሆነው እንዲሰሩ ተዘዋወሩ።በእርግጥ ይህ የስራ ድርሻ


የግርማዊነታቸው (ይህ ሐዲስ ንጉሡን ለመጥራት ከሚጠቀሙባቸው ስሞች ሁሉ የሚመርጡት
ነው) ነበር።ሐዲስ እንደሚያስታውሱት ግርማዊነታቸው በትምህርት ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ፍላጎት
እንዳላቸው “መስለው መታየት” ይወዳሉ።ሐዲስ በዚህ ስራ ላይ የቆዩት ለአምስት ወራት ብቻ
ነው።

በነኚህ ወራት ንጉሠ ነገሥቱን በተደጋጋሚ በማግኘት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በዚህን
ጊዜ ነበር ሐዲስ ከጓደኞቻቸው በተሻለ ኃይለሥላሴን በቅርቡ የማወቅ እድል ያገኙት። ኃይለሥላሴ
ከሰዎች ጋር ብቻቸውን ሲሆኑ ልክ እንደ ተራ ሰው ተጫዋችና ፍልቅልቅ ሲሆኑ። እራሳቸውን
ለመግለጽ የሚጠቀሙት ተውላጠ ስምም “እኛ” ሳይሆን “እኔ” ነበር። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች
ሲገቡ፣ በፍጥነት ይለወጡና አንድ እራሳቸውን “እኛ” ብለው በመጥራት ግርማዊነታቸውን
ይላበሳሉ።በግል ሲጫወቱ ስለ ግል ሕይወታቸው ያወራሉ፤ ስለ ሌሎች የግል ጠባይም ይጠይቃሉ።
ሁለገብና አስገራሚ ሰብእና ያላቸው ሰው ናቸው።ከአንድ ማንነት ወደሌላ ማንነት በቀላሉ
ይሸጋገራሉ።ሐዲስ እንደሚያስታውሱት መልካቸው ሳይቀር በተመሳሳይ ጊዜ በተወሰዱ የተለያዩ
ፎቶዎች ላይ ይቀያየራል።

ሐዲስ አለማየሁ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጣቸውን ስራ ተረክበው ብዙም ሳይቆዩ፣ሁሉንም


የአፍሪካ የትምህርት ሚኒስትሮችን ያሳተፈ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ።በዚህ አጋጣሚ
ሚኒስትሮቹ መሀይምነትን ከአፍሪካ በ25 ዓመት ጠራርገው ለማስወጣት ቃል ገቡ።እያንዳንዱ
ሚኒስትርም ይህንን ግብ ለማስፈፀም የሚጠቅም እቅድና ዝግጅት እንዲያደርግ ተጠየቀ።
በኢትዮጵያም ትምህርት ቤት ለመገንባት፣ልጆችን ለመመዝገብና መምህራንን ለማሰልጠን ወዘተ
እቅዶች ተዘጋጁ።ሐዲስም ከኢትዮጵያ መሀይምነትን ለማጥፋት የሚጠቅም እቅድ አዘጋጅተው
ለመንግሥት አቀረቡ።

የቀድሞው የትምህርት ስርዓት ‘መጥፎና የማያጠግብ’ ተብሎ ስለተፈረጀ፣ የሀገሪቱን የትምህርት


ስርዓት ለመከለስ ሃሳብ ቀረበ።ብዙም ከማያወላዳው በጀት 75% የሚሆነው ለአስተዳደር እና
ውጣ ውረድ ለሚበዛው የስራ ሂደት የሚውል ነው። ሐዲስ ይኼንን ሁኔታ መለወጥ ፈለጉ―
አስተዳደሩን ከማእከላዊነት አሰራር አላቆ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅዶችን በማዘጋጀት የትምህርት
ስርአቱን በማደራጀት እና በመምራት ብቻ እንዲወሰን አድርጎ ለእያንዳንዱ ንኡስ ክፍል ይህንን
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያወጣውን እቅድ እንዲያስፈጽሙሥልጣን እና ሐላፊነት በመስጠት
ለመለወጥ ፈለጉ። በዚህ መንገድ አብዛኛው ገንዘብ ሳይባክን ትምህርትን ለማስፋፋት ሊውል

11
ጥቋቁር አናብስት

ይችላል። ነገር ግን የቀረበውን ማሻሻያ ብዙዎች ተቃወሙት―ዋንኛ ተቃዋሚዎቹ ምንም ሳይሰሩ


ደሞዛቸውን ብቻ የሚቀበሉት ኃላፊዎች ነበሩ።

ሐዲስ ያቀረቡት ማሻሻያ ብዙ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ አልነበረም ፤ ገንዘቡ የሚወጣበት


መንገድ እንዲቀየር ብቻ ነበር የፈለጉት። በመጀመሪያው ዓመት የጠየቁት ተጨማሪ በጀት ሁለት
ወይም ሶስት ሚሊየን ብቻ ነው። በመጨረሻ ግን የቀድሞ በጀታቸው ራሱ ተቆራርጦ ሶስት
አራተኛው ብቻ ተሰጥቷቸው በዚያ ብቻ እንዲሰሩ ተገደዱ። ሐዲስ ጠንካራ ሠራተኛ እንደሆኑ
በሰፊው ይታወቃል።ስለዚህ የስራ ባልደረቦቻቸው ሐዲስን ዝም ብለው ለማባረር
አልተመቻቸውም። አስቸጋሪ የስራ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዝውውር ወይም መልቀቂያ እንዲጠይቁ
መገፋፋቱ የተሻለ አማራጭ አድርገው ወሰዱት። አሁን "ዘዴያቸው" ሐዲስ የቀደመ እቅዳቸውን
በሶስት አራተኛው በጀት ብቻ እንዲያስፈጽሙ መጠየቅ ነበር። በዚህን ጊዜ አማራጭ ያልነበራቸው
ሐዲስ የስራ መልቀቂያ አስገቡ።

ቀጥሎ በ1953 ዓ.ም መጨረሻ ሐዲስ የታላቋ ብሪታኒያ እና የኔዘርላንድ አምባሳደር ሆነው ወደ
ለንደን ተጓዙ። በዚያም ወደ ኢትዮጵያ እስከተጠሩበት 1958 ዓ.ም ድረስ ቆዩ። ይህ ቆይታቸው
ለሀዲስ አለማየሁ በጣም ጥሩ ጊዜ ነበር። እንግሊዝንና ለንደንን ወደዋቸዋል፤ኔዘርላንድንም
እንዲሁ―እንደውም ዘ ሄግንም በተደጋጋሚ ጎብኝተዋል ።

ንግስት ጁሊያና አስደሳች እና የምትቀል ሰው ነበረች። ሐዲስ ስራቸውን ሲለቁ ንግስቲቱን


ለመሰናበት ከዘ ሔግ ከ30―45 ደቂቃ ወደምትርቀው የክረምት ቤታቸው ብቅ ብለው ነበር።
በእርግጥ ንግስቲቱ አምባሳደሮችን እዚህ ተቀብለው የማነጋገር ልምድ የላቸውም። ይህንን ስራም
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ትተውላቸዋል።ሆኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሐዲስን በኒውዮርክ
የተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅት ተወዳጅተዋቸው ስለነበር ይህንን ልዩ የመገናኛ
አጋጣሚ አዘጋጁላቸው።ንግስቲቱን ይረብሻል ተብሎ ሞተረኞቹ እንኳን ራቅ ብለው ከንግስቲቱ
ጊቢ በር ላይ ቆመውላቸው ሀዲስ ብቻቸውን ያለአጃቢ፣ ወደ አንድ ክፍል ሲገቡ፣ ተራ ቀሚስ
የለበሰች ሴት፣ በኮሪደሩ እያንጎራጎረች መጥታ ተቀበለቻቸው። ወደ ክፍሏ እንዲገቡ ስታሳያቸው
ያቺ´ተራ ሴት´ የቤት ውስጥ ሠራተኛ ሳትሆን ንግስት ጁሊያና እራሷ መሆኗን ሲረዱ ሃፍረት ቢጤ
ተሰማቸው። ንግስቷ እራሷ ያቀራረቡትን ሻይ ጠጡ።ንግስቲቱ ጥሩ አንባቢ ስለነበሩ እና በቂ መረጃ
ስለነበራቸው ስለሀዲስ የቀድሞ ስራ በደንብ ያውቁ ነበር። የተባበሩት መንግስታት ስላለበት ሁኔታና
እንዴት ሊሻሻል እንደሚችል ጠየቁ። ስለትምህርት ጉዳዮችም ተነጋገሩ። በመጨረሻም በዜጎቻቸው
እገዛ ስለሚተዳደረው የወንጂ ስኳር እርሻ እና ፋብሪካ ጠየቁ።ሀዲስም ከዚህ ቆይታ በኋላ
ተሰናብተው ወጡ።

12
ጥቋቁር አናብስት

ነገር ግን ሐዲስ በለንደን የገጠማቸው ችግሮችና ቅር የተሰኙባቸው ነገሮች ነበሩ።ሚስታቸው


እዚያው እያሉ ሞቱ። ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ደግሞ ከዩኒቨርስቲው አቅራቢያ የሚገኘውን የድሮ
ቤታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለሚተዳደር የልጆች ማሳደጊያ በስጦታ ሰጡ።
አብዛኛዎቹ ልጆች ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሲሆን የተወሰኑት በጉዲፈቻ ስዊድንን ወደመሳሰሉ
ሀገሮች ተወስደዋል። ከወ/ሮ ክበበ ፀሐይ ጋር ምንም ልጆች አላፈሩም ነበርና ይህ የበጎ አድራጎት
ስራ ለልጆች ያደረጉት ታላቅ ነገር ነው። ከሚስታቸው ሞት በኋላ ዳግመኛ አላገቡም።

ከእንግሊዝ ሲመለሱ ሀዲስ ጤንነት እየተሰማቸው አልነበረምና፤ሌላ የመንግሥት ሹመት በፍጹም


አልፈለጉም።ከእንግሊዝ ሀገር በዶክተር የተፃፈ ለአንድ ወይም ለሁለት ዓመት እረፍት
እንደሚያስፈልጋቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ይዘው መጥተዋል። ነገር ግን በኢትዮጵያ መንግሥት
ውስጥ ለውጦች እየተካሄዱ ነበር። ሐዲስ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ "አንዳንድ ማሻሻያዎች"
እንደሚደረጉ ተነገረ―በዚህም መሰረት ንጉሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲሾሙ፣ሌሎች
ሚኒስትሮችን የመሾሙን ጉዳይ ግን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚተዉላቸው ተለፈፈ። ጠቅላይ
ሚኒስትሩ አክሊሉ ሀብተወልድ ሐዲስን የሚኒስትሮች ምክር ቤትን እንዲቀላቀሉ ጠየቋቸው።
ሐዲስ በመጀመሪያ እምቢ ቢሉም ጓደኞቻቸው ለዚህ አዲስ ሀሳብ እንቅፋት መሆን
እንደሌለባቸው፣ ሃገሪቷን ሊለውጥ ለሚችለው ለዚህ አጋጣሚ እድል እንዲሰጡ ግፊት
አድርገውባቸው ተስማሙ። በመሆኑም በ1958 ዓ.ም ከለንደን ከተመለሱ ከሶስት ወራት
በኋላየእቅድና እድገት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። በዚህም እስከ 1961ዓ.ም ድረስ ቆዩ።
እንደተለመደው ስራ የለቀቁት ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ነው።
በሚመሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከዋናው የኢንቨስትመንት በጀት ለሐገር ውስጥ እቅድ
ማስፈፀሚያ የሚመደበው መጠን በግማሽ መታጠፉን ሊቀበሉት አልቻሉም።

በ1961 ዓ.ም ሐዲስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሆኑ። በዚያም የ’66ቱ አብዮት እስኪፈነዳ
ድረስ አገልግለዋል። ከዚያ በኋላ ግን ጡረታ የወጡ ቢሆንም በጡረታ ላይ ግን ከሁለት ወይም
ከሶስት ወር በላይ አልቆዩም። ምክንያቱም ደርግ እንዲበተን የተደረገውን የቀድሞ ፓርላማን
ለመተካት ባቋቋመው የመማክርት ሸንጎ አባል እንዲሆኑ ስለተመረጡ ነው። እርሳቸው እንዴት
እንደተመረጡ ባያውቁም ´የጎጃም ህዝብ´ በዚህ ሸንጎ እንዲወክሉት እንደመረጣቸው ተነገራቸው።
ሐዲስ በመጀመሪያ እንዳረጁ፣ ጡረታም እንደወጡ በመግለጽ ራሳቸውን ለማግለል ሞከሩ። ደርግ
ግን በምትካቸው ሌላ ሰው እስኪገኝ ድረስ በሸንጎው እንዲቀመጡ አስገደዳቸው። ነገር ግን ምንም
ተተኪ ስላልተቀመጠ፣ ሐዲስ የሸንጎው አባል ሆነው ለሁለት ዓመት መቆየት ግድ ሆነባቸው።
ከሁለት ዓመት በኋላ ግን ሸንጎው ተበተነ። ሐዲስም ዳግመኛ ወደጡረታ ተመለሱ። ከዚያን ጊዜ
ጀምረው ቋሚ ጡረተኛ ሲሆኑ የሚኖሩትም በጡረታ ድርጎአቸው እና ከመጽሐፍቶቻቸው በሚገኝ

13
ጥቋቁር አናብስት

ገቢ ነው። እንደ እርሳቸው ሀሳብ ከሆነ በመጨረሻ ያገለገሉበት ሸንጎ አንዳች ጠቃሚ ስራ
አልሰራም።

ነገር ግን ቀጣይ አመቶቻቸው ፍፁም የተለዩ ሊሆኑ ይችሉ ነበር። በ1966 ዓ.ም ሐምሌ ወይም
ነሐሴ አካባቢ፣ ሐዲስ አለማየሁ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ተጠየቁ14። የድሮው
ስርአት የካቲት 1966ቱ ከፈረሰ በኋላ ግርማዊነታቸው ለዚህ ሐላፊነት፣እንዳልካቸው መኮንንን
መረጡ።ደርግ ግን ሐዲስ አለማየሁን ፈለገ።ሐዲስም ደርግ ከእርሳቸው ምን እንደሚፈልግና
ከደርግ ጋር ያላቸው የስራ ግንኙነት ምን እንደሚሆን ጠየቁ። እንዳልካቸው መኮንን
በመንግስታቸው ውስጥ አዲስ ሰው በሾሙ ቁጥር፣ ደርግ ይወስድና ያን ሰው ያስረዋል። ሐዲስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ይህ ነገር በእርሳቸው ላይም ይደገም እንደሆን ጠየቁ―እንዲያ ከሆነ
ምንም የማከናውነው ነገር አይኖርም ብለው ቁርጥ አድርገው ተናገሩ። ደርግ በራሱ እና
በሚኒስትሮች ምክር ቤት መሀል ሆኖ እንደ አገናኝ የሚሰራ አንድ ቡድን አዋቅሮ ነበር። ሐዲስ
ደርጎች በዚህ ቡድን በኩል ትእዛዛቸውን እየላኩ በማስፈፀም ምኞታቸውን ማሳካት ነው
የሚፈልጉት የሚል እምነት ነበራቸው። ማንኛውንም ነገር ለማስፈፀም የደርግመልካም ፈቃድ
መገኘት አለበት። ደርጎች የሚመሩበት እቅድ ካላቸውና ይህ እቅድ ምን እንደሚመስል ሐዲስ
ጠየቁ፤ አክለውም እርሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ የደርግ ስራ ምን እንደሚሆን ለማወቅ
ፈለጉ። ሁሉም “ለውጥ ያስፈልጋል” በሚለው ሀሳብ ተስማሙ።ሀዲስ ቀላልና ተግባራዊ የሚሆን
የመንግሥት ስርአት እንዲመሰረት ሀሳብ አቀረቡ።ነገር ግን ምንም ዐይነት እቅድ ስላልነበረ፣ እቅድ
እንዲዘጋጅ አሳሰቡ። ያለ እቅድ ግን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሹመት እንደማይቀበሉ አስታወቁ።
ደርግ እና ሌሎች የጦር ሰራዊት አባላት ወደ የጦር ሰፈራቸው ተመልሰው ህዝብ እና መንግስት
የጣሉባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ጠየቁ። አለበለዚያ ማንኛውም ዐይነት መንግሥት
ስራውን በአግባቡ ሊወጣና ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል አውቀዋል፤ ተናግረዋልም። ሌላው
ደግሞ በመንግሥት ስራ ላይ ልምድ ያላቸው ሰዎች/ግለሰቦች ሁሉ እስር ላይ መሆናቸውን
ተቃውመው የመንግሥትን ስራ በአግባቡ ለመከወን የስራ ልምዳቸው እንደሚያስፈልግ ጠቆሙ፤
ከነሱ መሐል ወንጀል የፈፀሙ በአግባቡ ለፍርድ እንዲቀርቡ ተደርጎ ሌሎቹ ነፃ መውጣት
እንዳለባቸው ሀሳብ አቀረቡ።

ደርግ በበኩሉ በቅርቡ የታዩ ለውጦች ሁሉ ምክንያት ራሱ መሆኑን በመግለጽ መመሪያውንም ራሱ


እንደሚሰጥ የሐዲስን እቅድ ለመተግበር አይደለም ለውጡን ያመጣነው" በማለት ገለጸ።
በኋላምየራሱን እቅድ እንደሚነድፍ አስታወቀ። ሐዲስ እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች መስራት
እንደማይችሉ በመግለጽ ሹመቱ እንዲያልፋቸው ጠየቁ― “ደርግ የሃገሪቷን እጣ ፈንታ በተመለከተ
የራሱ እቅድ ስለሚኖረው”15 እንዲህ ባለ አስመሳይ መንግሥት ውስጥ መስራት አይችሉም። ደርግ

14
ጥቋቁር አናብስት

ቀጥሎ ወደ ግርማዊነታቸው በመሄድ ያለውን ሁኔታ ከገለፀላቸው በኋላ ስልጣን እንደሚይዝ


ተናገረ። ሐዲስ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ተቀብለውት ቢሆን ኖሮ፣ ሚካኤል እምሩ ( የራስ እምሩ
ኃይለሥላሴ ልጅ) እና ዘውዴ ገብረስላሴ ለምክትልና ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ታጭተው
ነበር። ነገር ግን ሐዲስ ሹመቱን ስላልተቀበሉ በጊዜው ለተባበሩት መንግስታት በጄኔቭ ይሰሩ
ለነበሩት ሚካኤል እምሩ ጥያቄው ቀረበላቸው። ጉዳዩን ለማጤን ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም
ደርግ አይሆንም አለ። ደርግ ስልጣን ያዘና ሚካኤል እምሩን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሾመ
ለግርማዊነታቸው እና ለሚካኤል እምሩ ገለፀ። ሐዲስ እንደሚሉት ይህ ሁሉ የሆነው ሚካኤል
እምሩ ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡና በሐሳቡ መስማማታቸውን ሳይገልፁ ነበር። ይሁንና ሚካኤል
እምሩ ለአጭር ጊዜ ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ካገለገሉ በኋላ የደርግ የፖለቲካ አማካሪ ሆኑ።
በመጨረሻ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሆነው ሰሩና ጡረታ ወጡ።

****

የሐዲስ አለማየሁ የሥነ ጽሑፍ ሰውነታቸው የተጀመረው ገና ትምህርት ቤት እያሉ፣ ወደ ስራ


አለም ከመግባታቸውም በፊት ነበር፤ደግሞም ከጡረታ በኋላም ለረጅም ጊዜ መጻፋቸውን
ቀጥለዋል―ሶስተኛውን ረዥም ልብወለዳቸውን ገና በ1976 ዓ.ም ጥር ወር አጠናቀዋል ። ይህ
የመጨረሻ ታላቁ ሥራቸው ቢሆንም፣በአእምሮአቸው አንዳንድ ትንንሽ ሀሳቦች ነበሯቸው።በ75
ዓመታቸው እንኳን የፈጠራ ችሎታቸው አልነጠፈም ነበር።

ከኢጣሊያ እስኪመለሱ የነበራቸው የሥነ ጽሑፍ እንቅስቃሴ ቀደም ብሎ ተጠቅሷል።16 ከዚያ


በኋላ ወደ ፈጠራ ጽሑፍ ለመመለስ የተወሰነ ጊዜ ወስዶባቸዋል። ስራዎቻቸው እንደገና
እስኪታተሙ ድረስ ደግሞ ሌላ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዷል።

በ1958 ዓመት የታተመው የመጀመሪያ ትልቁ ልብወለዳቸውን ፍቅር እስከ መቃብርን መፃፍ
የጀመሩት በግምት ከ20 ዓመት በፊት በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋና ፀሐፊ እያሉ
(ከ1939–1943) ነበር። መጀመሪያ የፃፉት በእንግሊዝኛ ሲሆን ተጽፎ ሳያልቅኒውዮርክ ለሚገኝ
አሳታሚ ልከውት ለማሳተም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ከዚያ በአማርኛ ይጽፉ ጀመር። የተፃፈው
በረዥም ጊዜ ሂደት ሲሆን በየመሀሉ ለረዥም ጊዜ ተቋርጧል። በእንግሊዝ አምባሳደር ሳሉ
(1953–1958) ሚስታቸው ከሞቱ በኋላ መፃፉን እርግፍ አድርገው ተዉት፤ከአንድ ዓመት
የሐዘን እረፍት በኋላ መፃፉን እንደገና ቀጠሉ። ከስራ ወደስራ በተዛወሩ ቁጥር ሌሎችም ረዣዥም
መቆራረጦች ነበሩ። ሲጨርሱት ግን ጥሩ መጽሐፍ መስሎ አልታያቸውም።ብዙ ጊዜ እያቋረጡ
ስለጻፉት ያልተስተካከለ ሆኖ ተሰማቸው።

15
ጥቋቁር አናብስት

ያለምንም ማቋረጥ ሲጽፉ፣ ፍሰቱ ጥሩ እንደሚሆን፣ ነገር ግን የሚያቋርጣቸው ነገር ሲኖር እንደገና
ካቆሙበት ለመቀጠል ሀሳባቸው ስለሚበታተን፣ ፍሰቱን እንደነበር ለመቀጠል እንደሚያዳግታቸው
ያስረዳሉ። ስለዚህ መጽሐፉ በአስቸጋሪ ወራቶች የታጀቡ ብዙ ቅጥልጥል ደስተኛ የድርሰት ወቅቶች
ውጤት ነው።ይህ አለመመጣጠን ባለቀው መጽሐፍ ላይ በጉልህ ይታያል ባይ ናቸው። ነገር ግን
መጽሀፉን ጽፎ ለመጨረስ ብዙ ጥረት ስለጠየቀ፣ መጽሐፉን ለማሳተም መሞከር ትክክለኛ ውሳኔ
ሆኖ ታያቸው። መጽሀፉን ለማሳተም ገንዘብ መበደር ነበረባቸውና፤17ታትሞ እንደወጣ በጥሩ
ሁኔታ በመሸጡ ተደስተውም ተገርመውም ነበር። በመጀመሪያ ህትመት 5,000 ቅጂዎች ብቻ ነበር
የታተሙት። በሚቀጥለው ጊዜ 7,000 ቅጂዎች ታተሙ። እስከ 1978 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ
ስድስት ጊዜ ተደጋግሞ ታትሟል። መጽሐፉ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ ከታተመ
ከጥቂት ዓመታት በኋላም በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ውስጥ ገብቶ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
የማስተማሪያ መጽሐፍ ሆነ።

በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ ብዙ ክፍሎች ከደራሲው ሕይወት የተቀዱ ናቸው። በጎጃም
ደብረወርቅ እና ዲማ ያሉት ታሪኮች ደራሲው በቅኔ ተማሪነታቸው ያሳለፉት ሕይወት ግልባጭ
ነው። በዛብህ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣና በከተማው ውስጥ የሚያጋጥሙት ሁነቶች፣ሐዲስ
እራሳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1918 ዓ.ምከጎጃም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የታዘቡት ገጠመኝ
ጥርቅም ነው። በአጠቃላይ ሀዲስ ልብወለዱ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ገፀ ባህሪያት ውስጥ
እራሳቸውን በተወሰነ መልኩ እንደሚያዩ ይናገራሉ።የመጀመሪያው ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱ
በፊት የቤተክርስቲያን ትምህርት የቀመሰው እና እንደ ሐዲስ ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ የሆነው
የልብወለዱ ዋና ገፀ ባህሪ በዛብህ ሲሆን፣ሌላው ደግሞ በማህበረሰቡ ሳይሆን በራሱ ሀሳብ
የሚመራው፣ ይኼም ዘወትር ከራሱ ወገኖች እና ከመደብ ፍላጎቶቹ ጋር ቅራኔ ውስጥ የሚያስገባው
´ጠቢቡ ሞኝ´፣ ጉዱ ካሳ ነበር።

የልብወለዱ መቼት ከሐዲስ የልጅነትና ወጣትነት ሕይወት ጋር በተወሰነ ደረጃ ይገጥማል(


የተወለዱት በ1902 ነበር)፤ በእርግጥ ልብወለዱ ከዚህ ትንሽ ቀደም ብሎ ይጀምራል።
የልብወለዱን መቼት በሀያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ ወደ ኃይለሥላሴ የግዛት ዘመን
የመጀመሪያ ዓመታት (ስልጣን የያዙት በ1923 ዓ.ም ነው) ማስጠጋት አሳማኝ ነው። ከሀዲስ ጋር
ይህንን የጊዜ ሰሌዳ አውጥተን ነበር፤ነገር ግን ሐዲስ በልብወለዱ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ
ልማድና ስርአቶች የጥንት እንደነበሩ አንዳንዶቹም እስከ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘመን (1847–
1861) ወደኋላ እንደሚለጠጡ ነግረውኛል።

16
ጥቋቁር አናብስት

ሌላ አንድ ልብወለዱን ልዩ የሚያደርገው ነገር ሐዲስ አዲስ የጽሕፈት ስርአት ማስተዋወቃቸው


ነው።ይህም በድምጽ የሚመሳሰሉ መንታ ወይም ሶስት ሆሄዎችን በማስወገድ በአንዱ ብቻ
እየተጠቀሙ ከመፃፋቸውም ባሻገር፣ሁለት ሆሄዎችን በማጣበቅ በአንድ ሆሄ ተክተዋል።ይህን
“አዲስ የጽሕፈት ስርአት” ጥቂት ውይይት ቢኖርም፣ ስር ሰዶ ቋሚ ስርአት አልሆነም። ነገር ግን ከዛ
በኋላ ለመጡ ሌሎች የሆሄ ክለሳዎች መንገድ ከመጥረጉ ባሻገር ይህ ሀሳብ በቀላሉ ተቀባይነት
እንዲኖረው መነቃቃትን ፈጥሯል።

***

ፍቅር እስከ መቃብር ከመታተሙ ከ10 ዓመት በፊት፣ ሐዲስ ሌሎች ሁለት መጽሀፍትን ለገበያ
አቅርበው ነበር። አንደኛው በተረት መልክ የቀረቡ 12 ታሪኮችን የያዘ ሲሆን የታተመው በ1948
ዓ.ም ነው። ከነዚህ ተረቶች መሐል አንዱ ብቻ በከፊል ነባር ሲሆን ሌሎቹ የራሳቸው ፈጠራ
ናቸው።መጽሐፉ ተረት ተረት የመሰረት18 ይሰኛል።ይህም በኢትዮጵያ ባሕልተረት መንገር
ሲጀመር እንደ መግቢያ የሚያገለግል ነው።በዚያው ዓመት ሀዲስ በኢትዮጵያ የትምህርትና
የትምህርት ቤቶች ስርዓት እንዴት መደራጀት አለበት በሚለው ላይ ያላቸውን አስተሳሰብ
“የትምህርትና የትምህርት ቤት ትርጉም” በሚል ርእስ ባሳተሙት መጽሐፍ ውስጥ ገልጸዋል።

ሀዲስ የትምህርት ሚኒስቴርን ለቀው፤በለንደን ገና አምባሳደርነቱን በጀመሩበት ወቅት (1953–


1958) ኢትዮጵያ ምን ዐይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል? የሚል መጽሀፍ ፃፉ። ይህ መጽሀፍ
የተፃፈው የ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ግለት ብዙም ሳይበርድ ነበር። ስለዚህ ሀዲስ አንዳንድ
ለውጦች እንዲያደርጉ ለንጉሡ ለማሳሰብ ጥሩ ጊዜ መሆኑ ተሰምቷቸዋል። ንጉሡ በሐገር ውስጥም
ሆነ በውጪ ያተረፉትን ክብር ሀገራቸውን እና ህዝቦቿን ለመለወጥ መጠቀም ይችሉ ነበር። ይህንን
ቢያደርጉት ኖሮ ንጉሡ ክብራቸውን ባስጠበቁ፤መጪው ጊዜም የተለየ በሆነ ነበር ብለው ሐዲስ
ያስባሉ። ነገር ግን ሐዲስ ያቀረቡት ሐሳብ ክብደት ኖሮት ግርማዊነታቸው እንዲቀበሉት፣
ጓደኞቻቸውን እንደ ተባባሪ ደራሲ ማካተት ፈለጉ።ስለዚህ የእርሻ ሚኒስትሩ አበበ ረታን፣
የመከላከያ ሚኒስትሩን፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩን እና ሌሎችንም ተባባሪ ደራሲ እንዲሆኑ
ጠየቁ ፤ በህብረት ሆነውም ለንጉሡ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ፈለጉ። ከንጉሡ ጋር በትብብር
መስራታቸው እንዲቀጥል እነዚህ ማሻሻያዎች መተግበር አለባቸው የሚል አቋም እንዲወስዱ
ፈለጉ። ሀዲስ ለእቅዳቸው ድጋፍ ለማሰባሰብ የጓደኞቻቸውን እርዳታ ቢፈልጉም፣ ተባባሪ ደራሲ
እንዲሆኑ የመረጧቸው ሰዎች አልተስማሙም ፤ አንዳንዶች ንጉሡ ሀሳቡን እንደማይቀበሉ ሲገልፁ
፣ሌሎች ደግሞ የንጉሡ የጥቃት ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ፍርሃታቸውን ገለፁ። ስለዚህ
“እናለሳልሰው!”የሚል ሀሳብ ሲያቀርቡ፣ ሀዲስ ተቃውመው ረቂቁን ቆልፈው አስቀመጡት።
17
ጥቋቁር አናብስት

መጽሀፉ በመጨረሻ የታተመውም ከ1966ቱ አብዮት በኋላ ነበር፤ምክንያቱም በወቅቱ አዲሱ


መንግስት የተዘጋጀ እቅድ አልነበረውም።አሮጌውን ስርአት አጥፍቶ ለውጥ ከማምጣት የዘለለ
የተደራጀ ሀሳብ አልወጠነም። ስለዚህ ምን ዐይነት ለውጥ እንደሚፈለግ ወይም መምጣት
እንዳለበት የሚያውቅ አልነበረም።ለጥናትና ለውይይት የሚሆኑ ጽሑፎች አልነበሩም።አዲሶቹ
“ንጉሶች”የሚፈልጉት ምንም የሚተካ ነገር ሳያዘጋጁ የድሮውን ሙልጭ አድርገው ማጥፋት ነበር።
ሀዲስ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ብዙ አማራጮችን አቅርበዋል፤አማራጮቹ ለህዝቡ ቀርበው፣
በሪፈረንደም ሊወሰንባቸው ይገባል ይላሉ።

ሐዲስ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት “ኢዝም” የሚባል ነገር አይጠቅምም ይላሉ። እድገት ለማምጣት
የሚያስፈልገው እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ትራንስፖርት፣ ኢንደስትሪ፣ መገናኛ እና በመሳሰሉት ዘርፎች
ተጨባጭ ስራ መስራት ነው። እያንዳንዱ "ኢዝም" ከእድገት አኳያ ምን ማለት እንደሆነ ይጠይቁና
“ኢዝም” በማደግ ላይ ያሉ ሐገራት ሊተገብሩት የማይቻላቸው ቅንጦት እንደሆነ ይቆጥሩታል፤
ወደእዛ ለመሸጋገር ሀገራት ቢያንስ መሰረታዊ የሆነ እድገት ማምጣት አለባቸው። ምን ዐይነት
አላማ እንደሚያሻና ያንን አላማ ለማሳካት የሚነደፈው እቅድ―ለምሳሌ የአስር ዓመት የግብርና፣
የኢንዱስትሪ፣ የትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ መገናኛ እቅድ―ምን መምሰል እንዳለበት ያስቀምጣሉ።
ለ“ኢዝም” እና ለሌሎች የማይጨበጡ ሃሳቦች ዋጋ አይሰጡም። ማንኛውም ዐይነት መንግስት
ህዝቡን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ተጨባጭ የሆኑ እቅዶች ያስፈልጉታል። ህዝቡ ወደ አንድ
ዐይነት የእድገት ደረጃ ከደረሰ በኋላ፣ከተለያዩ የ”ኢዝም” ዐይነቶች የፈለገውን እንዲመርጥ ምርጫ
ከተሰጠው በኋላ ሕገመንግሥት ቀርቦ ህዝቡ በሪፈረንደም ሊወሰን ይችላል። ሐዲስ ይህንን ሀሳብ
ስለ አስተዳደር ወይም መንግስት በፃፉት መጽሀፍ አቅርበዋል ፤ እስካሁን ድረስ (በቃለመጠይቁ
ወቅት) በመጽሀፉ መልእክት ያምናሉ። ይሁን እንጂ ከአብዮቱ በኋላ አዳዲስ ሀሳቦች
በመምጣታቸው መጽሐፉ ወደጎን እንደተገፋ ይናገራሉ።19

***

ፍቅር እስከ መቃብር ከመጠናቀቁ በፊት፣ ሐዲስ ገና ለንደን እያሉ፣ሁለተኛ ልብወለዳቸውን


"ወንጀለኛው ዳኛ"ን መፃፍ ጀምረው ነበር ፤ መጽሐፉ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1974 ሲታተም፣
በ1978 ለሶስተኛ ጊዜ ታትሟል። የመጀመሪያው እትም ብዙ የህትመት ግድፈቶች ሲኖሩት፣
ተቀባይነቱም የመጀመሪያውን ልብወለድ ያህል አልነበረም። በኋላ የታተሙት ስህተቶቹ
ተነቅሶላቸዋል። "ፍቅር እስከ መቃብር" ከደራሲው ሕይወት የሚጨልፈውን ያህል "ወንጀለኛው

18
ጥቋቁር አናብስት

ዳኛ" አይደግምም። የ"ወንጀለኛው ዳኛ" መቼት ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ ይጀምርና አብዮቱ
ከመፈንዳቱ በፊት ይጠናቀቃል።

የመጨረሻ መጽሐፋቸው "የልምዣት" የተጠናቀቀው በ1976 ታህሳስ ወር ላይ ነበር። ብዙዎች


የርእሱ ትርጉም ስላልገባቸው፣ አንባቢዎችን ለመርዳት ሲሉ ቃሉን ለሁለት ሰንጥቀው በሚቀጥሉት
እትሞቻቸው ላይ "የልም እዣት" ብለው ተጠቅመዋል ፤ ይሁን እንጂ አብዛኛው አንባቢ አሁንም
ትርጉሙ አልገባውም።በ1977 ዓ.ም ሳገኛቸው የመጽሀፉን የመጨረሻ ምእራፍ በማረምስራ ላይ
ተጠምደው ነበር ፤ ስለዚህ ከአንድ ወር በኋላ እርማቱን ሲጨርሱ ላገኛቸው እንደምችል
ጠቆሙኝ። ከአንድ ወራት በኋላ ሳገኛቸው፣ በእጃቸው የፃፉትን ረቂቅ የቀደመ መጽሀፎቻቸውን
ላሳተሙላቸው የመንግስት ማተሚያ ቤት (ኩራዝ) ሰጥተው፣በሶስት ቅጂዎች፣ አንዱ ለደራሲው፣
ሁለቱ ደግሞ ለሳንሱር ክፍል፣እየተተየበ ነበር። ስለዚህ መጽሐፉ ይታተም እንደሆነ፣ ከታተመስ
መቼ የሚለውን አያውቁም ነበር። "የልምዣት" ማለት "በህልም ውስጥ ብቻ ያለ መትረፍረፍ"
ነው። ቃሉን ለሁለት ስንሰነጥቀው "የልም" ( የህልም) እና "እዣት" (ብዙ)የሚል ይሆናል።
ትርጉሙ በህልሙ ውስጥ ሲኮን የተትረፈረፈ ከእንቅልፍ ሲነቃ ግን በኖ የሚጠፋ ብዙ ሐብት
ለማለት ነው። እንደውም ይሄ አንድ የአማርኛ አባባልን ያስታውሳል፦"ላም አለኝ በሰማይ
ወተቷንም አላይ"።ሐዲስ ይህ ልብወለድ የዘመኑን ኢትዮጵያ የሚገልጽ ሀተታ አይደለም ይላሉ።
በጊዜ ቅደም ተከተል መሰረት ቢቀመጥ ""የልምዣት" ከ"ወንጀለኛው ዳኛ" በፊት መውጣት
ነበረበት።ምክንያቱምበመቼቱ መሰረት "የእልምዣት"፣ "ፍቅር እስከ መቃብር"ከሚያልቅበት ጊዜ
ይጀምርና(ኃይለሥላሴ ንጉስ ከሆኑ ከሁለት ዓመት በኋላ እና ከጣሊያን ወረራ ሁለት ዓመት በፊት)
ጣሊያን በወረራ እስከያዘችበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎ "ወንጀለኛው ዳኛ" እስከሚጀምርበት ጊዜ ድረስ፣
ማለትም ኢትዮጵያ ነፃ ከወጣች ከጥቂት ዓመት በኋላይዘልቃል።

ሶስቱ መጽሐፍት በጭብጥ ባይመሳሰሉም፣ ከጊዜ መቼት አንፃር ተለጣጣቂ (trilogy)ናቸው


ማለት ይቻላል። ነገር ግን እያንዳንዱ መጽሐፍ ከቀሩት ሁለቶቹ ተነጥሎ መነበብ ይችላል።

***

ሀዲስ ህዝብን ማህበረሰቡን እንደሚወክል ተዋናይ አድርገው ይቆጥራሉ። ስለዚህ በልቦለዳቸው


ውስጥ ግለሰቦችን አይወቅሱም።ለምሳሌ አንዳንዶች እንደሚያምኑት በ"ፍቅር እስከ መቃብር"
ኃይለሥላሴን በተዘዋዋሪ ያብጠለጥላሉ የሚባለው እውነትነት የለውም። ሰዎች የማህበረሰቡ

19
ጥቋቁር አናብስት

ውጤት ናቸው፤ንጉሡም እንደማንኛውምሰው የእዚህ ውጤት ናቸው። “ልብወለዶቼ በጊዜው


የነበረውን ስርአት የሚያሳዩ እንጂ ስለ ግለሰቦች የተፃፉ አይደሉም” ይላሉ።

ሐዲስ አለማየሁ ከ"የልምዣት" በኋላ ትልቅ የሚባል የሥነ ጽሑፍ ስራ የሚሰሩ አልመሰላቸውም፤
ሆኖም ትውስታቸውን በተለይ ስለ ጦርነቱና ስለተዋጉበት ግንባር ትዝታቸውን መፃፍ እንደሚፈልጉ
ይናገራሉ። ግለታሪካቸውን እንዲጽፉ ቢጠየቁም መጻፍ አለመጻፋቸውን እርግጠኛ አይደሉም።
የመጨረሻ የፈጠራ ስራቸው ተለጥጦ የተዘጋጀው "ተረት ተረት የመሰረት" ሊሆን ይችላል።
በ1977 ኩራዝ አሳታሚ ለሁለተኛው እትም ተጨማሪ ታሪኮችን እንዲያዘጋጁ ስለጠየቃቸው ያንኑ
በመስራት ላይ ነበሩ። አንድ ታሪክ ጨርሰው ሌሎች ሁለት ታሪኮችን ደግሞ አጽመ-ታሪካቸውን
አዘጋጅተዋል። በአጠቃላይ ለዚህ እትም አምስት አዳዲስ ታሪኮች ለማዘጋጀት አስበዋል።ሐዲስ
በልቦለዶቻቸው በከፊል እንጂ ሙሉ በሙሉ እንዳልረኩ ይናገራሉ። መንፈሳቸው ሲነቃቃ መፃፍ
ያስደስታቸዋል፤ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜየተበጣጠሱ ታሪኮችን ገጣጥሞ ማቀናጀቱ፣ የተፃፈው
ታሪክ ስህተቶች ካሉት ያንን ለመንቀስ ደጋግሞ ማንበቡ እና የመሳሰሉት ከባድና አሰልቺ ስራ
ናቸው።ይሁን እንጂ ሐዲስ የሰዎችን አስተያየት ተንተርሶ እርማት ማድረግን አይወዱም፤
ምክንያቱም ከሰዎች ማሻሻያ ከተቀበሉ ሙሉ በሙሉ የራሳቸው ስራ መሆኑ ቀርቶ በከፊል የሌላ
ሰው ስራም ጭምር ይሆናል የሚል እምነት ነበራቸው።የመጽሐፍቶቻቸው ህትመት፣ ለምሳሌ
የየልምዣት ህትመት፣ ከሌሎች የሚቀበሉትን ማሻሻያ ማካተት የሚኖርበት ቢሆን ኖሮ ረቂቁን
ቁምሳጥናቸው ውስጥ ቆልፈውበት ሳይታተም ቢቀር ይመርጡ ነበር።20

***

በአፃፃፋቸው ላይ ተጽዕኖ ያሳረፋባቸውን ደራሲዎች ሀዲስ የሚገለፁት በደፈናው ነው።


የሚያደንቋቸው ደራሲዎች ቢኖሩም፣ እነሱን ለመምሰል አልሞከሩም። በቶልስቶይ ስራዎች ውስጥ
የቤተሰብ ሕይወት የመሳሰሉት ነገሮች የተገለፀበት ዝርዝር ሁኔታ ይማርካቸዋል። ነገር ግን ያንን
አስመስለው መስራት አይችሉም፤ እንደዚያዝርዝር የመጻፍ ተሰጥኦ የተቸራቸው አይመስላቸውም።
የቪክቶር ሁጎን የገለፃ ብቃትም ያደንቃሉ። ከበደ ሚካኤል ጥሩ ገጣሚ፣ምናልባት ኢትዮጵያ
ካፈራቻቸው መሀል ምርጡ ገጣሚ እንደሆነ ያስባሉ።"ከይቅርታ በላይ" ("Beyond Pardon")
የሚለው የትርጉም ስራቸው ምግሩም ስራ እንደሆነ ያስባሉ።

ምንም እንኳን ከበደን በአካል ያወቋቸው ከጣሊያን ከተመለሱ በኋላ ቢሆንም፣ ጣሊያን፣ ፖንዛ
ውስጥ እያሉ ግጥሞቻቸውን በጋዜጣ ላይ እያነበቡ ይደነቁ ነበር። ገና ተማሪ እያሉ የብላቴንጌታ
ሕሩይን መጽሀፍ ያነበቡ፣ በአካልም አንድ ሁለት ጊዜ ያገኟቸው ቢሆንም፣ ኅሩይ ጥልቅ ተጽእኖ
ያሳደሩባቸው ግን አይመስልም።
20
ጥቋቁር አናብስት

ሐዲስ መጽሐፍቶቻቸው መጥቀማቸውን፣ ወይም ተጽእኖ ማሳደራቸውን አፋቸውን ሞልተው


ባይናገሩም፣ለሀገራቸው ግን በጎ ስራ መሆናቸውን ተስፋ ያደርጋሉ። ሐዲስ መጽሐፍቶቻቸው
በተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ረክተዋል፤ሰዎች መጽሐፍቶቻቸውን እንደወደዱላቸው ሲሰሙም
ደስ ተሰኝተዋል። በነሱ ስኬት ባይኮፈሱም፣በሥነ ጽሁፍ ስራዎቻቸው እርካታ ይሰማቸዋል።

ምናልባት ህዝብን ባገለገሉበት የፖለቲካ ሕይወታቸው የበለጠ እርካታ ሳይሰማቸው አይቀርም፤


“እንደዚያ ይመስለኛል” ይላሉ ሐዲስ። ውጤቶቹ ከጠበቁት በታች በሚሆኑበት ጊዜ እንኳን
የተቻላቸውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም። ወደኋላ ዞረው የስራ ሕይወታቸውንሲመለከቱ፣
አንድም የሚፀፀቱበት ነገር የለም።

****

በውይይታችን መጨረሻ፣የቀደመውን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመለከት አስተያየት ሰነዘሩ። ዳግማዊ


ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ አራተኛ እና ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ በማድረግ ላይተጠምደው ነበር
፤ ይህ ትግል በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመንም (1923–1966)ቀጥሏል ፤ኃይለሥላሴከ1916
ጀምሮ አልጋ ወራሽ መሆናቸው ሳይዘነጋ። በአንዳች መልኩ ዘመናዊው የብሔርተኝነት መንፈስ
የተጠነሰሰው በዳግማዊ ቴዎድሮስ ነበር፤ይሁን እንጂ በጦርነት መርታት የተሳካላቸውን ያህል
በሰላም መምራቱን አልቻሉበትም። ምኒልክ በጦርነትም፣ በሰላምም ወቅት ጥሩ መሪ ነበሩ። ነገር
ግን ጠንካራ ዘመናዊ ስርአት መገንባት የጀመረው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጊዜ ነው። በኃይለሥላሴ
ዘመን ሁሉንም ዐይነት ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ። ዘመናዊ ትምህርት፣ የጤና
አገልግሎት፣ የኢኮኖሚ እድገት እቅዶች ሁሉ የተጀመሩት በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ነበር። የጀመሩት
ስራ በኢጣሊያ ወረራ ተቋረጠ። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን የማዘመኑ ነገር ላይ ጣሊያኖችም ሀይል
ጨምረውበታል፤ ምንም እንኳን የሚከውኗቸው እንደ መንገድ ግንባታ የመሳሰለው በሐገሪቱ
ውስጥ የዘረጉትንወታደራዊ ተልእኮ ለማሳካት ቢሆንም አላማቸው ኢትዮጵያውያንን አንድ በአንድ
ጨርሰው የራሳቸውን ህዝብ ለማስፈር መሆኑን የሚገልጥ ወረቀት በኋላ ተገኝቷል። ይሁን እንጂ
በኢትዮጵያ መሻሻል የመጣው በከፊል በእነሱ ቆይታ በተለይ ደግሞ በ1933 ከለቀቁ በኋላ
እንደሆነ ሀዲስ ያብራራሉ።

ሌላው ደግሞ ከ1933–1966 ባለው ጊዜ በመላው ሀገሩ ሰላም በመስፈኑ ለኢትዮጵያ እድገት
ረድቷል። ከዚህ ውጪ ባለው ዘመን፣ ኢትዮጵያ ከጦርነት ተላቅቃ ስለማታውቅ ሰዎች የሚኖሩት
ድንኳን ውስጥ ወይም ወዲያውኑ ሊፈርሱ በሚችሉ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ነበር። ለዚህ ነው
ኢትዮጵያውያን ከተማን በስርአት መገንባት ሳይችሉ ቀርተው በዘፈቀደ ያለ እቅድ የሚሰሩት።
ሐዲስ የድሮውንም አዲሱንም አይተውት ከ1933 ወዲህ የመጣው ለውጥ ትልቅ መሆኑን

21
ጥቋቁር አናብስት

ይመሰክራሉ። ምንም እንኳን ስህተቶች ቢሰሩም፣ እንከኖች ባይጠፉም፣ ከአብዮቱ በፊት ኢትዮጵያ
በእድገት ጎዳና እየተንደረደረች ነበር።

የኃይለሥላሴ ትልቁ ችግር ገንዘብና ስልጣን አለመጠን መውደዳቸው ነበር። (“እንደ ኃይለሥላሴ
ገንዘብ የሚወድ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም”)፤ሌላ ሰው ሲሳካለት ወይም ክብር ሲያገኝ ማየት
አይወዱም።“የትኛውም ኢትዮጵያዊ ዶክተር እንኳ ውጤታማ ሲሆን ማየትአይፈልጉም”።ደህና
አድርጎ የሚሰራውን ሁሉ ወይ ያባርሩታል አልያም ያዛውሩታል። ስለ ሁሉም ነገር ማወቅና
መቆጣጠር ስለሚፈልጉ ነገሮች እንዲዘገዩ ያደርጉ ነበር። ሲያረጁ ሁሉንም ልጓሞች መጨበጥ
ስላልቻሉ፣ ነገሮች ከቁጥጥራቸው ውጪ ሆኑ። ሐዲስ ከኃይለሥላሴ ጋር ጠንካራ ቅራኔ የነበራቸው
ቢሆንም፣ ለሀገሪቱ ያመጡትን እድገትና መሻሻል አይክዱም። ሐዲስ ኃይለሥላሴ አንዳንድ
እምነቶቻቸውን እና አመለካከቶቻቸውን፣ በተለይ የመጨረሻዎቹ ዓመታት ላይ ቢለውጡ ኖሮ ፤
በዛ ላይ በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ክብር ቢጠቀሙት ኖሮ ለሳቸውም ለሀገራቸውም በረከት በሆነ
ነበር ብለው ያምናሉ። ነገር ግን እሳቸውም አልተለወጡም ፤ ለሀገሪቱም አልበጀም። ይሁን እንጂ
ሀዲስ በኃይለሥላሴ ጊዜ የመጣውን ትልቅ እድገት መካድና፣ ሀገሪቱ የደረሰባትን ክፉ ነገር ሁሉ
እሳቸው ላይ ማላከክ ተገቢ ሆኖ አይታያቸውም።ሐዲስ የመንግሥት ባለሥልጣን ሆነው
አገራቸውን ያገለገሉት በኃይለሥላሴ ዘመን ሲሆን ረዥም ሕይወታቸውን ወደ ኋላ ዞር ብለው
ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ማድረግ የቻሉትን ነገር ሲመለከቱት፣ በደስተኝነትናበምስጋናስሜት
ነው።

የደራሲው ማስታወሻ፡ በቅርቡ የተለጠጠው "ተረት ተረት የመሰረት" እና የጦርነት ማስታወሻቸው


"ትዝታ" (1985) መታተሙን ሰማሁ። በ1987 ዶክተር ዴቪድ አፕልያልድ "ፍቅር እስከ
መቃብር"ን ወደ እንግሊዝኛ ተርጉመው ጨርሰዋል።

የተርጓሚ ማስታወሻ-ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የክብር ዶክትሬታቸውን በነሀሴ 27

1991 ዓ.ም የተቀበሉ ሲሆን፡በተወለዱ በ90 አመታቸው አካባቢ በሞት ተለይተዋል፡፡

ማስታወሻዎች

1) የማውቃቸው ኢትዮጵያዊ ደራሲያን ሁሉ የሚኖሩት አዲስ አበባ ውስጥ ነው።

2) በዚያ ያለው ቤተክርስቲያን ኪዳነምህረት ስለነበር፣ መንደሩ እንዶዳም ኪዳነምህረት ተብሎ


ይጠራል።
22
ጥቋቁር አናብስት

3) ቀሳውስት የመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ከጎጃም ተነስተው ኦሮሞዎችን አማርኛና፣ ክርስትናን


ለማስተማር ይሄዱ ነበር። ያን ጊዜ በአመዛኙ ኦሮሞዎቹ አርብቶ አደር ነበሩ ይላሉ ሐዲስ።

4)እነዚህ ስሞች በልብወለዳቸው ውስጥም ብቅ ይላሉ።

5) የኅሩይ ተውኔት ግብረገብን በሚያስተምሩ ንግግሮች የተሞላና ድርጊት አልባ ሲሆን ለመድረክ
የሚመች አይደለም። ለተመልካች በቀጥታ ቀርቦ የሚያውቅ አይመስልም።

6) ዮፍታሔ እና መላኩ ሁለቱም የዳግማዊ ምኒልክ መምህራንና ቀሳውስት ወይም ደባትር ነበሩ ፤
ሁለቱም የመጡት ከጎጃም፣ ኤልያስ ነው። ኤልያስ የሐዲስ አባት የትውልድ ስፍራ ሲሆን
በተጨማሪም ሐዲስ የቅኔ ትምህርታቸውን የጀመሩት እዚህ ነው።

7) የኢትዮጵያና የኬንያ የድንበር ከተማ በሆነችው ሞያሌ ላይ ለብሪታኒያው ቆንስላ አስተርጓሚ


ነበር።

8) ቡና መጠሪያውን ያገኘው ከዚህ ከተማ ስያሜ እንደሆነ ሐዲስ ሀሳባቸውን ያካፍላሉ።

9) እነኚህ ሁለቱም ግዛቶች በቀደመው ጊዜየየራሳቸው ነገስታት ነበራቸው። አባ ጅፋር የጅማ


ንጉሥ ነበሩ። የጎጃሙ ተክለሃይማኖት የከፋውን ንጉስ ማርከው ለጥቂት ጊዜ የጎጃምም፣ የከፋም
ንጉሥ ነበሩ። በኋላ ምኒልክ ከፋን ተቆጣጠሩ።

10)በዚህ ጊዜ ጣሊያኖች የመኳንንት ዘር ለሆነው ታዬ ጉልላት ምህረት አደረጉለት። ሮም


አቅራቢያ በምትገኘው አቬሊኖ ከራስ ከበደና ሌሎችም ጋር ታስሮ ነበር። ሙሶሎኒን እንዲያገኝ
ከዚያ ከመጣ በኋላ በመጨረሻ ለአንድ ዓመት ያህል ከቆዩበት ኢጣሊያ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።

11) የእምሩ እና የግርማቸው አባቶች የቅርብ ጓደኞች ስለሆኑ ግርማቸው ከእምሩ ጋር አብሯቸው
እንዲሆን ሲጠየቅ ተስማማ። ነገር ግን ጣሊያንን የሚወጉ ሃይሎች ሞሮኮ ሲደርሱ፣ እምሩ እና
ግርማቸው ከሌሎቹ ጋር ሉንጎ ቡኮ ውስጥ ተቀመጡ።

12) ካሳንቺስ የሚገኘው ይህ ህንፃ ያኔ ባዶ ነበር። በመጀመሪያ አዲስ ለተቋቋመው ፓርላማ


ከጠቅላይ ግዛት የሚመጡ አባላቱ መቆያ ስፍራ ለማግኘት ጊዜ ስላልነበራቸው ይህ ህንፃ እንደ
ጊዜያዊ ማረፊያ ያገለግል ነበር። ያኔ ግን መኖሪያቸውን ስላመቻቹ ጊዜያዊ ማረፊያውን ለቀውታል

23
ጥቋቁር አናብስት

13) የተባበሩት መንግስታቱ ንዑስ ጉባዔ አሁን ህልውናው አክትሟል። ይህ ንዑስ ጉባዔ እንደ
ጠቅላላ ጉባዔው ሁሉንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላትን ይዟል። የሚሰበሰበውም
ጠቅላላ ጉባዔው በሚያርፍበት ጊዜ ነበር። በመሆኑም በጠቅላላ ጉባኤው ተከታታይ ስብሰባዎች
መሀል ያለውን ክፍተት ይሞላል።

14) ለዚህኛው የሕይወታቸው ክፍል የተለየ ግምት ይሰጡ እንደሆነ አላውቅም። ምክንያቱም
የሕይወት ታሪካቸውን እርሳቸው በሚፈልት መንገድ ከተረኩልኝ በኋላ እኔ እራሴ ነጥዬ ስለዛ
ወቅት እስከምጠይቃቸው ድረስ ምንም አልነገሩኝም ነበር።

15) ከደርግ ጋር ለመተባበር አሻፈረኝ ካሉ በኋላ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ሊታሰሩ ይችሉ


እንደነበር ያምናሉ። ነገር ግን ይላሉ ሀዲስ፣ “ጠቅላይ ሚኒስትራቸው እንዲሆን የጠየቁትን ሰው
ማሰሩ ሳያሳፍራቸው አልቀረም።”

16) አጭር ማጠቃለያ፦ የመጀመሪያ ተውኔታቸው “የኢትዮጵያና የወደኋላ ጋብቻ” የተፈሪ


መኮንን ተማሪ እያሉ በ1921/22 ተፃፈ። በ1922 በጋዜጣ ላይ ቅኝት ተሰራለት። ( ተፈሪ
መኮንን ትምህርት ቤት የቆዩት ከ1920/21–1924፣ ከ3ኛ–6ኛ ክፍል ነበር) ወዲያውኑ በ1923
ለአልጋ ወራሹ ሰርግ ሶስት ርእሳቸው ያልታወቀ ተውኔቶችን ደርሰዋል። በ1927 ደብረ ማርቆስ
ሲያስተምሩ አንድ አጭር ተውኔት ጽፈዋል። ይህ ተውኔት በጣሊያን ወረራ ወቅት ብሔራዊ
ስሜትን ለማነሳሳት የተፃፈ ሲሆን ለተውኔቶቻቸው መዝሙሮችን እራሳቸው ይጽፉ ነበር ፤ ከዚህ
በተጨማሪ በ1926/27 በዳንግላ ርዕሰ መምህር እያሉ ለተማሪዎቻቸው ግጥም ጽፈዋል ።
ከ1929–36 በጣሊያን የጦር እስረኛ እያሉ የራሳቸውን እና አብረዋቸው የታሰሩ ጓደኞቻቸውን
ገጠመኝ በግጥም አስፍረው ነበር። እነዚህ ሁሉ የተደከመባቸው ስራዎች ጠፍተው ሳይታተሙ
ቀርተዋል።

17) በጊዜው ደራሲዎች ምንም ነገር ከማሳተማቸው በፊት የሕትመቱን ወጪ መክፈል


ይጠበቅባቸው ነበር።

18) "Socialization and Social Control in Ethiopia" የሚለውን መጽሐፌን


ይመልከቱ።

በዚያ ውስጥ ስለ ልጅ አስተዳደግ አንድ ወግ አለ ፤ በዛ ስር ተረት ስለመንገር አንድ ምዕራፍ አለ።

24
ጥቋቁር አናብስት

19) በመጨረሻው ውይይታችንላይ፣ ሐዲስ አለማየሁ ማርክሳዊው መንግስት አምባገነናዊ ባህሪ


እንዳለው ተናገሩ። ማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቀው በመግባት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ
እንኳን ሳይቀር የራሳቸውን ሰዎች በመሰግሰግ አኮላሽተውታልይላሉ።( በእርግጥ እርሳቸውብዙም
ሀይማኖተኛ ባይሆኑም ይሄ ያሳዝናቸዋል፤ሀዲስ ቤተክርስቲያንን እንደ አንድ የኢትዮጵያ የባህል
መገለጫ አድርገው የሚያዩ ፤ ወደ ቤተክርስቲያንም እንደ ጥምቀት፣ ሰርግ ወይም ቀብር ያለ ትልቅ
ስርአት ሲኖር ብቻ የሚሄዱ ሰው ነበሩ።

20) መጽሐፉ በመጽሐፍት መደብሮች በ1980 ታየ። ከመውጣቱ በፊት በኢሠፓ ማእከላዊ
ኮሚቴ በጥንቃቄ ምርመራ ተደርጎበት በርዕዮተ አለም ጠበብቶች ተገምግሟል።በ1979 መጨረሻ
አካባቢ ታተመ ፤ ኩራዝ ለህትመት እንደሚያልፍ እርግጠኛ ስ ለነበር 50,000 ቅጂዎች
እንዲታተሙ አዘዘ ። በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ህትመቱ በዚህን ያህል
ቅጂዎች ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህ ሁሉ ቅጂ በጥቂት ወራቶች ውስጥ ተሽጦ አለቀ (
አንዶንዶች በኦሮማይ ጊዜ የደረሰውን በማሰብ ሁለት እና ከዚያ በላይ ቅጂዎችን ገዝተዋል)
ወዲያውኑ ለድጋሚ ህትመት ገብቶ አሁንም 50,000 ቅጂዎች ታትሟል።

25
ጥቋቁር አናብስት

ኅሩይ ወልደሥላሴ
የአማርኛ ስነጽሁፍ አባትየአማርኛ ስነ-ጽሁፍ ቅርጽ በሚይዝበትወቅት
የኅሩይ ወልደሥላሴ ሚና በጣም ከፍ ያለመሆኑ ስለታወቀላቸው ከዚህ
ቀደም ብዙ ሰዎችስለ እሳቸው ጽፈዋል::ከኅሩይ የልጅ ልጆች አንዱ
ግርማሥላሴ አስፋው1ለተወሰኑ አመታት ግለታሪካቸውን ለመጻፍ ተነሳስቶ
የነበረ ቢሆንም በቅጡ ስራውን ሳይጀምረው እ.ኤ.አ በመስከረም 1987
በአስመራ ከተማ አቅራቢያ የአውሮፕላን አደጋ ቀደመው፡፡ በ1970ዎቹ ግርማ ኅሩይ የጻፉትን
የግል ማስታወሻዎች ላይ ምንባቦችንና ማጠቃለያዎችን አሳይቶኝ ነበር፡፡እስካሁን ድረስ ስለ ኅሩይ
ህይወት ስለእሳቸው ማወቅ በሚፈልው ህዝብ ዘንድ ብዙ ያልተሰሙ ነገሮች እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡
ስለኅሩይ ብዙ ጭምጭምታዎችን የሰማሁ ቢሆንም የተሻለ የተጨባጭ መረጃ እጥረት ግን አለ፡፡2

የተወሰኑ የቤተሰብ ማስታወሻዎችንማግኘት ችዬ ነበር፡፡ ስለሳቸው ከተወላጆቹ ጋር መነጋገር


ችያለሁ፡፡ከአንድ ለማ ወልደ ማርያም በተባሉ ሰው ስላእሳቸው በአማርኛ የተጻፈና ካልታተመ
ጽሁፍ ላይ(ዩንቨርሲቲው ውስጥ ይገኛል) ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁ፡፡እኚህ ጸሃፊ ስለኅሩይ ብዙ
ያውቁ ከነበሩና ማስታወሻዎቹን በይዞታቸው አኑረው ከነበሩት ከኅሩይ የመጨረሻ ልጅ ከብላታ
ሲራክ3 ጋር ረዘም ያሉ ቆይታዎችን ማድረግ የቻሉ ጸሃፊ ነበሩ፡፡በተጨማሪም ሲራክ የኅሩይ
“የስነጽሁፍ አስፈጻሚ ነበሩ” ከዚህ ሌላ ለማ በርካታ ሰዎችን ቃለመጠይቅ አድርገውላቸው የነበረ
ሲሆን እነዚህ ሰዎች ከኅሩይ ጋር ይቀራረባሉ፡፡ ስለ እሳቸው የተጻፉ አስደሳች ነገሮችን
የሚያገኙባቸውን በርካታ የመንግስት መዛግብትንም የማገላበጥ እድሉ ነበራቸው፡፡ይህ ጥራዝ
የመታተምም ሆነ የመገኘት እድሉ ጠባብ ስለሆነ ብዙ ነገሮችን በውሰት ልወስድ ችያለሁ፡፡
በተጨማሪም ከሌሎች ምንጮችም ግብአቶችን ተጠቅሜያለሁ፡፡ያነበብኩትን ከሚያውቋቸው
ሰዎች ከሰማሁት ጋር ለማብላላት በመሞከር ስለ ኅሩይ ሃሳብና ስሜት ልጠቅስ የምችልበት
አጋጣሚ ሊኖርም ይችላል፡፡ይሄ ደግሞ በሁሉም አጋጣሚዎች ላይ የሚታይ ነው፡፡ምንም እንኳን
ብዙ መረጃዎች ከእኔ ጥናት በኋላ ቢወጡም ኅሩይ በአማርኛ ስነጽሁፍ ውስጥ ካላቸው ትልቅ ቦታ
አኳያ ቀደምት ጥናቴን ማሳተሙ ዋጋ ያለው መስሎ ታይቶኛል፡፡

***

የኅሩይ አባት አቶ ወልደሥላሴ በሸዋ፤መርሃቤቴ ሃገሪት በተሰኘ ስፍራ ነው የተወለዱት፡፡ነገር ግን


ያደጉት መንዝ ውስጥ ነው፡፡ቤተሰባቸው ከወሎ አምሃራ ሳይንት4 ነው የመጡት ይላል
በቤተሰባቸው ውስጥ የሚነገረው አፈታሪክ፡፡የኅሩይ እናት ወይዘሮ አመተ ማርያም ዜና ይባላሉ፡
26
ጥቋቁር አናብስት

አባታቸውም5 (የኅሩይ) ያገቧቸው በ40 አመታቸው ነበር፡፡ከማደረ ቤተሰብ ከመንዝ ጠል ነው


የተገኙት፡፡ከሸዋው ንጉስ ሳህለሥላሴ እናት ወይዘሮ ዘነበ ወርቅ ጋር የሩቅ ዝምድና አላቸው፡፡

ወይዘሮ ባፈና6የዳግማዊ ሚኒሊክ የመጀመርያ ሚስት ሲሆኑ በ1975 እስከሚፋቱበት ድረስ


(ያሴሩባቸውም ነበር) ባፈና የደን አቦ ገዳም አለቃ ነበሩ፡፡7 የኅሩይንም አባት ወልደ ሥላሴ
ያልተማሩ ቢሆንም ለአስተዳደር ችሎታቸው ሲሉ በገዳሙ ላይ እልቅና ሾሟቸው፡፡የኅሩይ አባት
እሳቸው ማግኘት ያልቻሉትን ዐይነት ትምህርት ልጃቸው እንዲያገኙ ይፈልጉ ነበር፡፡

ኅሩይ ግንቦት 1 ቀን 1871 አ.ም ተወለዱ፡፡የቤተሰቦቻቸው የበኩር ልጅ ሲሆኑ ከሳቸው በታች


ሁለት ሴቶች አሉ፡፡ሌሎች ልጆችም በቤተሰቡ ውስጥ አልነበሩም፡፡ኅሩይ (ትክክለኛው ስማቸው
አይደለም)ስመ ጥምቀታቸው ገብረ መስቀል ነው፡፡ወልደ ሥላሴ ልጃቸውን ለማስተማር የተጣደፉ
ይመስላል፡፡ኅሩይም ከቤተሰባቸው ጋር ያደጉት እስከ 7 አመት ሲሆን ከዚያ ወደ ቤተክህነት
ትምህርት ተላኩ፡፡8የመጀመርያ መምህራቸውም ደብተራ ስነግዮርጊስ ነበሩ፡፡ ግዕዝ ማንበብና
መድገምን ለመልመድ ሁለት አመት ፈጀባቸው ፡፡ይህም አጭር የሚባል ጊዜ ሲሆን የጽህፈት
ትምህርት ግን አልተማሩም ነበር፡፡9

በችሎታቸው የመጣ ኅሩይ ለአባታቸው ጠቃሚ ለመሆን ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ይህ ደግሞ


ይበልጥ እንዲማሩ ገፋፋቸው፡፡10አባታቸው ጥሩ ወደተባሉ የቤተክህነት ትምህርት ቤቶች
እንዲሄዱ (በወቅቱ የነበሩት እነሱ ስለነበሩ)ይፈልጋሉ፡፡አስር አመት ሲሞላቸው አባታቸው
ቀዬአቸውን ለቀው ወደ ስሬ ቤት ይዘዋቸው በመሄድ መድሐኔዓለም ደብር ውስጥ በሚገኘው
ትምህርት ቤት አስገቧቸው፡፡ አባትየው በልጃቸው ውጤታማነት ክብር ለማግኘት ፈልገው ነበር፡፡
ስለዚህ እዚያው አብረዋቸው እያዩና እየተቆጣጠሯቸው ቆዩ፡፡የልጃቸውንም መሻሻል በየቀኑ
ይከታተላሉ፡፡ውዳሴ ማርያምን በሁለት ወር ተወጡ፡፡አባት በዚህ ተደሰቱ ኅሩይም ፈጣን እድገት
ያሳዩ ጀመር፡፡

በወቅቱ ማንበብ፤በቃል ማነብነብና መድገም እንጂ መጻፍ ብዙም ትኩረት አይሰጠውም ነበር፡፡
የቤተክህነት ምሁር መለኪያም አልነበረም፡፡ቢሆንም ኅሩይ ከረቂቆች ላይ ደብዳቤዎችን በመገልበጥ
እራሳቸውን ጽህፈት ማስተማር ችለዋል፡፡ቀለም ከእንጀራ ምጣድ ጥላሸት ያዘጋጁ ነበር፡፡ብእርም
ከሸምበቆ ይቀርጻሉ፤መጻፍያም ከበሬ ቆዳ በለፋ ብራና፡፡13

27
ጥቋቁር አናብስት

አባትና ልጅ በዚህ ወቅት በስሬ መድሃኒዓለም በችግር ነበር የቆዩት፡፡በኋላ ግን የስሬ መድሃኒዓለም
አለቃ የነበሩት ወይዘሮ ጸሃይ ወርቅ ዳርጌ 14ትንሽም ብትሆን የማትቆራረጥ የምግብ እርዳታና
አመታዊ ተቆራጭ አደረጉላቸው፡፡

እንዲህ ባለ ሁኔታ ለሁለት አመታት ከዘለቁ በኋላ ወልደሥላሴ በ53 አመታቸው ደብረ ሊባኖስ
ገዳም ገብተው መንኩሰው ወደ ልጃቸው ተመለሱ፡፡ሚስትየው(የኅሩይ ወይም የገብረመስቀል
እናት) ልጃቸው ስለናፈቃቸው እሚማሩበት ድረስ ሄደው ለአንድ ወር ቆይተው ጎበኟቸው፡፡

የአባታቸው ጤንነት ግን በዚህ ወቅት እየተዳከመ መጥቶ ነበር፡፡ወደ ደብረ ሊባኖስም በተደጋጋሚ
ለጠበል ተመላለሱ፡፡ነገር ግን ሳይሻላቸው ቀርቶ ገብረመስቀል(ኅሩይ) የ13 አመት ታዳጊ ሳሉ
አባታቸው ሞተው በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ፡፡አንድ ወቅት ኅሩይ(በወቅቱና ከዛ በኋላ ለረዥም ጊዜ
በዚሁ ስም ይጠሩ ነበር)የአባታቸውን መቃብር ለመጎብኘት ሄደዋል፡፡በዚያ ወቅትም የገዳሙ
አስተዳደር የነገሯቸው የአባታቸው የመጨረሻ ቃላትና ምክር እንዲህ የምትል ነበረች “ገብረ
መሰቀል የሚወርሰው ነገር የለም፡፡ወደ ቤቱ የሚመለስበት ጉዳይም የለም እዚያው ትምህርቱን ግን
ሳያቋርጥ መቀጠል ነው ያለበት፡፡“

በኢትዮጵያ በ1881 አ.ም ብዙ ከብት ካለቀ በኋላ15በሃገሩ ላይ ርሃብ ጸንቶ ስለነበር ወይዘሮ ጸሃይ
ወርቅ ለገብረ መስቀል ቀለብ መስፈር ስላቆሙ እራሳቸውን መቻል ነበረባቸው፡፡ድቁናቸውን
ለመቀበል በሚማሩበት ወቅት አንድ ገበሬ የየ በተባለ ስፍራ የቤተክህነትን መሬት ያርስ ስለነበር
እሱን እያገዙ እንዲቆዩ ሆነ፡፡በሂደት ጥሩ ለመኖር ቻሉ፡፡ለእራሳቸውም ትንሽ መሬት ማረስ ችለው
ነበር፡፡ምንም እንኳን ጥሩ ጋላቢ ባይሆኑም ገቢያቸው ከፍ ስላለ ፈረስ እስከመግዛት ደረሱ፡፡በክፍያ
ለሰዎች እየጸፉም ትርፋማ ሆኑ፡፡ዝናቸው እየናኘ ስለመጣ የሰላሌው ገዢ ደጃች በሻህ ጸሃፊ
ባስፈለጋቸው ወቅት ገብረ መስቀል መጻፍ እንደሚችሉ ስላወቁ ቀጠሯቸው16፡፡ከበሻህ ጋር ግን
ብዙም አልቆዩም፡፡ወድያውኑ ለራስ 17መኮንን ታማኝ ሎሌዎች ከነበሩት ለአንዱ ቀኛዝማች
መቅረጭ ሲሞ የሚባል አካባቢ አዳአ በርጋ ላይ ተቀጠሩ፡፡የተቀጠሩት በጽሁፍ ችሎታቸው ስላሆነ
ከጊዜ በኋላ ችሎታቸውን ያወቁት ቀጣሪያቸው ቀርበው ችሎታቸውን እንዲያስመሰክሩ ጠየቋቸው

፡18መቅረጭም በውጤቱ ተደስተው "የሆነው ፍሬ" ሲሉ የቅጽል ስም ሰጧቸው፡፡በዚህ ስምም


ለተወሰነ ጊዜ ተጠርተውበታል፡፡ገብረመስቀል የሚለው ስመ ክርስትናቸው ከዚህ በኋላ
ለመጠርያነት አልዋለም፡፡ነገር ግን በኅሩይ እስከሚለወጥ ጥቂት ጊዜ ቆይቷል፡፡

28
ጥቋቁር አናብስት

ኅሩይ ለቀኛዝማች መቅረጭ በተለይ በግብር ስብሰባ ወቅት መመዝገብ በሚያስፈልግበት ጊዜ


በጣም ይጠቅማሉ፡፡ከአበ-ንስሃቸውም ጋር ተግባብተው በቅዱስ ግዮርጊስ ቤተክርስትያን
19
መቀደስ ጀምረው ነበር፡፡ሆኖም ግን ቄሱ በኅሩይ የተፋጠነ ስኬት ቀንተው ግንኙነታቸው ሊሻክር
ቻለ፡፡ቄሱ ደጃች መቅረጭ ኅሩይን ፊት እንዲነሷቸው ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ፡፡

ኅሩይ ከደጃች መቅረጭ ጋር ደህና በቆዩበት ወቅት ነገሮች በኢጣልያና በኢትዮጵያ መሃል እየሻከሩ
ነበር፡፡በሰኔ 1887 ዓ.ም ዳግማዊ ሚኒልክ ለአድዋ ጦርነት እንዲከተት “ታቦታችሁን ይዛችሁ
ስንቃችሁን ሰንቃችሁ እንድትመጡ ይሁን ”ሲሉ አዋጅ አስነገሩ፡፡ ወታደሩንና መሪውን የጎሳ
ግጭታችሁን ትታችሁ እንደ ኢትዮጵያዊነታችሁ ሁኑ ሲሉ መከሩ፡፡ቀኛዝማች መቅረጭ ዘመቻውን
በመስከረም 1888 ዓ.ም ተቀላቀሉ፡፡ኅሩይም በልማዱ መሰረት ከሜታ በቾ አቅራቢያ እስከ
አዋሽ ወንዝ ድረስ ተከትለዋቸው ወደ አሳዳሪያቸው ቤት ተመለሱ፡፡ኅሩይ ወድያውኑ ከአዲስ
አበባ እንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስትያን ከመጡት አራት ደባትር ጋር በመሆን እንጦጦ
ራጉኤል ቤተክርስትያንን ማገልገል ጀመሩ፡፡ከነሱ መሃልም አለቃ (መምህር) ወልደግዮርጊስ እና
አቶ ማህደር ይገኙበታል፡፡20ኅሩይ ቅዳሴን በሚያቆሙበት መንገድ ተመስጠው ስለነበር ቅዳሴው
ካለቀ በኋላ አቶ ማህደርን ቀርበው ትምህርታቸውን እነሱ ዘንድ መቀጠል ይችሉ እንደሆን ጠየቁ፡፡
ጥያቄው በአራቱም ተቀባይነት ስላገኘ ኅሩይም ለአሳዳሪያቸው ቤተሰብ የት እንደሚሄዱና
መሄዳቸውንም21 ጭምር ሳይናገሩ ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡ወደ አዲስ አበባ በእግር እየመጡ ሳለ
ከሰዎቹ ጋር ይበልጥ ተቀራረቡ፡፡

'የሆነው ፍሬ' ለምን እንደተባሉም ጠየቋቸው፡፡እሳቸውም ለምን እንደዛ እነደተባሉ ሲናገሩ አለቃ
ወልደግዮርጊስ ጎንደር ሳሉ ኅሩይ (የተመረጠው) ተብለው ይጠሩ እንደነበርና የሆነው ፍሬም
ይህንን ስም መውሰድ እንደሚገባቸው ተናገሩ፡፡'የሆነው ፍሬ' የተባለው ስማቸው ግን ኅሩይ
በህይወታቸው የላቀ ስኬት እስከተቀዳጁበት ወቅት ድረስ ለመጠርያነት ይውል ነበር፡፡

ምን መማር እንዳለባቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ከመከሩ በኋላ ኅሩይ ቅኔንና የእንጦጦ ትርጓሜ


ለመቀጸል ወሰኑ፡፡ቅኔን በታህሳስ 1 1888 አ.ም ማጥናት ጀምረው ለ9 ወር ቀጸሉ፡፡ከትንሽ ጊዜ
በኋላም መምህር ወልደ ግዮርጊስ ከእሳቸው ጋር መዐድ እንዲቆርሱ ፈቀዱላቸው፡፡ይህም ከዚያ
በፊት በጥሬ ብቻ ሲኖሩ ለነበረውና በሆድ ህመም ሲሰቃዩ ለኖሩት ኅሩይ ጤና መሻሻል መልካም
ሆነ፡፡ስነመለኮታዊ እውቀትን ብቻም ሳይሆን የእጅ ሙያም ለመልመድ ፍላጎት ነበራቸው፡፡

በአጓጉል ሰዓታት ስለሚያጠኑም ተገልለው ለማጥናት እንዲመቻቸው በመምህር ወልደ ግዮርጊስ


ግቢ ውስጥ አነስተኛ ጎጆ ቀለሱ፡፡22ሁለት ጓደኞቻቸው ጎጆዋን ተጋርተው አብረውም መኖርና
29
ጥቋቁር አናብስት

በኩራዝ ማጥናት ቀጠሉ፡፡በወቅቱ ዳግማዊ ሚኒሊክ ትንሽ ዳረጎት ለቀሳውስቱ ቤት መስርያ ችረው
ነበር፡፡ገንዘቡ እንደ ቤቱ መጠን በመከፋፈሉ ኅሩይ የደረሳቸው እስከ 15 ብር ድረስ ያነሰ እንደነበር
አንዳንዶች በግምት ይናገራሉ፡፡23ኅሩይ በሆድ ህመም ይሰቃዩ ስለነበር ወደ ደብረ ሊባኖስ ለጠበል
ይመላለሳሉ፡፡24

የአጼ ሚኒሊክ የግል ጸሃፊ ጸሃፌትእዛዝ ገብረ ሥላሴ25የእንጦጦ ራጉኤል አለቃም ስለነበሩ
ከጊዜጊዜ ብቅ እያሉ ነገሮችን ይቃኙ ነበር፡፡በመስከረም 1989 አ.ም የቅዱስ ራጉኤል ቀን የኅሩይን
ለመልአኩ የተቀኘ ቅኔ መወድስ ሰምተው በጣም ተደሰቱ፡፡ከድግሱም በኋላ ኅሩይ አዲስ አበባ
እንዲመጡና እንዲያዩዋቸው ነገሯቸው፡፡ጃኖ ሸልመው ፡ቁና እህል (5ኪሎ)እንዲሰፈርላቸው
አምስት ብር ወርሃዊ የመንግስት ደሞዝም26 እንዲቆረጥላቸው አዘው ከሳቸው ጋር ለመኳንንቱ
በሚሾመው መሶበ ወርቅ ቅዱስ ራጉኤልን በጎበኙበት ወቅት ሁሉ አብረዋቸው እንዲቆርሱ ፈቀዱ፡
፡ወደ ቤተመንግስትም ለጉብኝት በፈቀዱበት ወቅት ሁሉ እንዲመጡ ታዘዘላቸው፡፡ይህ ታላቅ
ክብር ነበር፡፡

ለሁለት አመታት ኅሩይ የአዲስ ኪዳን 27 መጻህፍት አንደምታ ሲያጠኑ ቆዩ፡፡ይህም የመጻህፍቱን
ሀይለቃላትን ሆነ ትርጓሜ በልቦና ማጥናትን ይጠቀልላል፡፡27ይህንን ትምህርት ሲያጠናቅቁ
እሳቸውና ሌሎች አራት ሰዎች ከአጤ ሚኒሊክ ካባ በሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ ኅሩይ በመምህር
ወልደ ግዮርጊስና በሌሎች ስር በአጠቃላይ ለ12 አመታት ተምረዋል፡፡የብሉይን አንደምታ
ቢሞክሩም ያን ያህል አልተራቀቁበትም፡፡ቆይቶ ፍትሐ ነገስቱን አጠኑ ወደ ቤተመንግስቱም
እግራቸውን ማዘውተር ቀጠሉ፡፡በዛም ሆነ ሌላ ቦታም ላይ ከተለያዩ ጠቃሚ ሰዎች ጋር መተዋወቅ
ጀመሩ፡፡በኢትዮጵያ እንጀራ መጋገርያው ብቸኛ መንገድ ጠቃሚ ሰዎችን ማወቅ ነውና፡፡

አንድ ወቅት በገብረ ሥላሴ ቢሮ ሳሉ ኅሩይ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስትያን አለቃን መልክዐፀሃይ
አፈወርቅን አገኙ፡፡

ጸሃፌትእዛዝ ገብረሥላሴም ካህኑን ኅሩይን ያውቁ እንደሆነ ጠየቋቸው፡፡መልሳቸውም “ይህ ትንሽ


ልጅ በአዲስኪዳን ምሁርነቱ የታወቀ ደብተራ ነው”28 ሲሉ ተናገሩ፡፡ገብረሥላሴም ተቀብለው
ትንሽ መባል አይገባውም ሲሉ ስለ ቅዱስ ግዮርጊስ በግእዙ ከተጻፉት የኢትዮጵያ መጻሐፍት
በአንዱ ያለውን ጠቀሱ “ከልጅነት ጀምሮ(ኅሩይ)የተመረጥክ ነህ” አሏቸው ለኅሩይ፡፡በወቅቱ ኅሩይ
በዚያ ስም ባይታወቁም ገብረሥላሴ ኅሩይ ሲሉ ሰየሟቸው፡፡

30
ጥቋቁር አናብስት

ኅሩይ ለትምህርት ወደ እንጦጦ ሲመለሱ ደጃች(ኋላ ፊት አውራሪ) የመቅረጭን ወደ አድዋ


መዝመት ተከትሎ ለመቅረጭ ቤት ማገልገላቸውን ትተው ነበር፡፡ከጦርነቱ በኋላ መቅረጭ ኅሩይን
ፍለጋ እንጦጦ ድረስ መጡ፡፡ሲያገኟቸውም ትምህርታቸውን እንዲገፉበት መክረው ላም
ሸለሟቸው፡፡29ኅሩይም ደስተኛ የነበሩ ሲሆን፤በኋላ ተጽዕኖ የሚፈጥሩበት አቅም ላይ ሲደርሱ
አዲስ አበባ ላይ ለልጆቻቸው ስራ አፈላልገው አስቀጥረዋቸዋል፡፡

ኅሩይ በተማሪ ቤት ሳሉ ቁና እህልና 5 ብር ደመወዝ በየወሩ ከመንግስት ይሰጣቸው ነበር፡፡


በቁምና እንዲሁም በተራ ጸሃፊነትም ለብዙ ሰዎች ያገለግላሉ፡፡ለዚህም በየወሩ 7 ብር ያገኛሉ፡፡ይህ
ሁሉ ሲደማመር በጊዜው ጥሩ የሚባል ክፍያ ነበር፡፡

***

ትምህርታቸውን አጠናቀው ስራ ሲጀምሩና ቋሚ ደመወዝ ሲያገኙ ማግባት ፈለጉ፡፡የጸሃፌ ትእዛዝ


ገብረ ሥላሴን ልጅ እንዲያገቡ እቅድ የነበር ቢሆንም እጅ አጠር ከመሆናቸው የተነሳ ሳይሳካ ቀረ፡፡
ወደ ደን አቦ የትውልዳቸው ስፍራ ሚስት ለማጨት ሄዱ፡፡እዝያም አልቀናቸውም፡፡ ፈለጋቸውን
ቀጥለውበት አባታቸው ወዳደጉበት ወደ ሃገሪት አመሩ፡፡ፍሬያማ ካልሆነ ሃሰሳ በኋላ የቀኛዝማች
እሸቴ ልጅ30መኖሯን ሰሙ፡፡ስለፈቀዷትም ሽማግሌ ልከው በመጀመርያ አባት በድህነታቸው ሳብያ
ቢያንገራግሩም በእናትየው እርዳታ ሊያገኟት በቁ፡፡31በግንቦት 17 1985 ተጋቡ፡፡32በወቅቱ ኅሩይ
የ24 አመት ከ 17 ቀን ወጣት ሲሆኑ ሐመረ እሸቴ33 የ16 አመት ኮረዳ ነበረች፡፡በኢትዮጵያ ድል
ያለ ሰርግ ነው የሚባለው በምግብና መጠጡ ዐይነት ሲሆን የኅሩይ በዚያ ሚዛን ለክፉ የማይሰጥ
ሊባል ይችላል፡፡ጓደኞቻቸው ከብትና በግ ስጦታ ይዘው መጥተው ነበር፡፡ጸሃፌትእዛዝ አንድ በሬ
10 ብር 10 ዳውላ እህልና አንዲት ባርያ ለሰራተኝነት ሰጧቸው፡፡አጼ ሚኒሊክ በጸሃፌትእዛዝ
በኩል አንድ ጋሻ መሬት(40 ሄክታር) ስለሰጡ የሙሽሪት አባት ቅሬታቸውን አነሱ፡፡በኋላም
የአዲስ አበባ ቤታቸው እየመጡ ይጎበኟቸው ነበር፡፡እንደጊዜው ልማድ ኅሩይ ወጣት ውሽሞች
ቢኖሯቸውም34ጥሩ የሚባል ዐይነት ትዳር ነበር፡፡ይህ ወቅቱን በሚያስታውሱ ወይንም ኅሩይን
በሚያውቁ ሰዎች የተለመደ ነበር፡፡የወሲብ ስሜት አብሮን እስከተፈጠረ ድረስ ይህንን ስሜት
ለማስታገስ ብቸኛው ወይም ጥሩው ምርጫ ሚስት ብቻ ላትሆን ትችላለች ተብሎ እንደሚታመን
ተነግሮኛል፡፡ ይህም አስተሳሰብ የቤተክህነትን ሰዎች ይጨምር ነበር፡፡35ለማንኛውም የሚታወቀው
የኅሩይ ልጆች ሁሉም ከሐመረ የተወለዱ ህጋዊ እንደነበሩ ነው፡፡በ1896 እና 1897 ሁለት ሴት
ልጆችን አገኙ፡፡36በ1900 እና 1903 ወንዶቹ ልጆቻቸው ፍቃደ ሥላሴና ሲራክ ተወለዱ፡፡
37
ተከትለውም ሁለት ሴቶች ልጆች አገኙ፡፡38
31
ጥቋቁር አናብስት

ኅሩይ ካገቡ በኋላም ከተማሪዎች ጋር ይበልጥ ለመማርና ያወቁትንም ላለመርሳት አንደታዛቢም


እየሆኑ ከቆሎ ተማሪዎች ጋር መቀመጥ ያዘወትራሉ፡፡የውጭ ቋንቋዎችንም የማወቅ በመጀመርያም
እንግሊዘኛን የመካን ፍላጎት አደረባቸው፡፡በባዶ እግራቸው (በተለምዶ እንደዛ ነው የሚሄዱት)
ከሚሰሩበት የካ ወደ ራጉኤል ለስራ ሲያቀኑ በስውድሽ ሚስዮን ትምህርት ቤትና ከዳይሬክተሩ
ካርል ሴደርቪስትጋር ለመግባባት በቁ፡፡ወድያው ከ10 እስከ 11 ሰአት ባለው ክፍለ ጊዜ
እንግሊዘኛን መማር ጀመረው ለስድስት ወር ገፉበት፡፡ነገር ግን ሰዎች በተለይ የቤተ ክህነቶቹ
"የሚማሩት ካቶሊክ ለመሆን ነው" ሲሉ ስላስወሩ አቆሙት፡፡39ከዚያ በኋላ ግን እንግሊዘኛን
በራሳቸው ይበልጥ ማንበብ ስለጀመሩ በዚያም መክንያት ነው የኋላ ኋላ በህይወታቸው የተወሰነ
እንግሊዘኛ መጻፍና ማንበብ እንደሚችሉ የሚነገረው፡፡የተወሰነ ፈረንሳይኛና አረቢኛንም
ተምረዋል፡፡ አረቢኛውም ሰዎች “ከመጽሃፍ ቅዱስ ይልቅ ቅዱስ ቁርአንን ይመርጣል” መባልን
ሲሰሙ ተውት ፡፡ልባቸው እንደከበደም የውጪ ቋንቋ ጥናታቸውን ገትተውታል፡፡

****

ካገቡና ስኬታማ መሆን ከጀመሩ በኋላ ብዙ ሰዎች እርዳታቸውን በመሻት መምጣት ጀመሩ፡፡
እሳቸው ደግሞ ሁሌም ለጋስ ነበሩ፡ይሄ ደግሞ ለእሳቸውና ለቤተሰቡ ችግርን አመጣ፡፡ሚስታቸው
ጠንካራ ሰራተኛ ነበረች፡፡ወደ መስክ በመውጣት ለማገዶነት የሚውል ኩበት ስትለቅም ውላ
መለስ ብላ ቀኑን ሙሉ በቤት ስራ ተጠምዳ ትውል ነበር፡፡

1881 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ ገብቶ ብዙ ከብት አለቀ፡፡ፈረንሳይ ሶስት የእንስሳት ሃኪሞችን
ላከች፡፡ጉለሌ አካባቢ ያለው የቀድሞ የንጉስ ተክለሃይማኖት ቤት ለስራቸው ተለቀቀላቸው፡፡
በከንቲባ (በኋላም ቢትወደድ )ወልደ ጻዲቅ ስር ሆነው በእርሻ ሚንስቴር መስራት ጀመሩ፡፡ከንቲባ
ወልደጻዲቅ ትሰሜ ዳርጌን ያገቡ ሲሆን ፈረንሳዮቹ ወደ ሃገራቸው የመሄጃ ጊዜያቸው ሲደርስ
እነሱን የመተካት እቅድ ነበራቸው፡፡ስለዚህ በፈረንሳዮቹ የሚሰለጥን ተማሪ ያስፈልጋል፡፡ሚኒልክ
የፈረንሳዮቹ መሄጃ ሲቃረብ ለወልደ ጻዲቅ ስራውን አስቀጥሎ ምትክ የሚሆን ሰው እንዲፈልጉ
ነገሯቸው፡፡እሳቸውም ኅሩይን ጠቆሙ፡፡ይሄ አደራ ሲጣልባቸው ከአጤ ሚኒሊክ ጋር በስራው
መክንያት በተደጋጋሚ የመገናኘት እድል ገጥሟቸው ነበር፡፡ኅሩይ የአንድ ደብር አለቃ እንጂ የከብት
ሃኪም መሆን አይፈልጉም፡፡ነገር ግን ስራውን ሊሰሩ ተስማሙ፡፡እንደ ጸኃፊ በሚሰሩበት ወቅት 10
ብር የሚከፈላቸው ሲሆን በየቀኑ ባዶ እግራቸውን ከስራ ቦታቸው እንጦጦ እስከ ጉለሌ ድረስ
ይሄዱ ነበር፡፡ሲቆይ ግን ይሄ አድካሚ እየሆነ መጣ፡፡ከሶስተኛው ልጃቸው መወለድ በኋላ
መድሃኔአለም ትምህርት ቤት አካባቢ አንዲት በሳር ወደ ተሰራች ቤት ተዛወሩ፡፡በወቅቱ ሰላሳ አንድ
አመት ከ4 ወራቸው ነበር፡፡ብላታ ሲራክ ሁለተኛው ልጃቸው በ1903 የተወለደው እዚህ ነበር፡፡

32
ጥቋቁር አናብስት

አንዳንድ የእድሜ ባለጸጎች ከዚህ ቤት የሚያስታውሱት ነገር ቢኖር ከበሩ ትይዩ በግልጽ በሚታይ
ሁኔታ በተቀመጠች ወንበር ላይ የሚቀመጥ ጠርሙስ ሙሉ ውሃና ብርጭቆ ነበር፡፡

በአንድ ወቅት የእንስሳት ህክምና ሆስፒታል ውስጥ በሚሰሩበት ወቅት በአቡነ ማቴዎስና40 በአፈ
ንጉስ እስጢፋኖስ41 መሃል በነበረ የተጭበረበረ ደብዳቤ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው
ተወንጅለው ታስረው በእግረ ሙቅ ገብተው ስስ ፍራሽ ላይ ለአንድ ወር ተኝተው አሳልፈዋል፡፡
በኋላ ነገሩ ጠራ እሳቸውም ተለቀው ወደስራቸው ተመለሱ፡፡

***

ኅሩይ ትንሽ እንግሊዘኛ እንደቻሉ ወደ አውሮጳ ስለመሄድ ማለም ጀመሩ ፡፡ከአደዋ ጦርነት በፊት
ኢትዮጵያውያን ከግብጽና እየሩሳሌም ውጪ ስለውጪው አለም የሚያውቁት ትንሽ ነበር፡፡ከጥቂት
አመታት በኋላ ግን ዶክተር ወርቅነህ እሸቴ (ወይም ዶክተር ማርቲን) አንድ የጂኦግራፊ መጽሃፍ
ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ መለሱ፡፡አማርኛቸው ብዙም ስለማያወላዳ በትርጉሙ ወቅት ኅሩይና
ሌላ አንድ ሰው አግዘዋቸዋል፡፡እዚህ መጽሐፍ ላይ መስራታቸው የውጪውን አለም የሚያዩበት
አይናቸውን ከፈተላቸው፡፡መጽሐፉ በ1904 ተዘጋጅቶ ያለቀ ቢሆንም በገንዘብና ሌሎች ችግሮች
ምክንያት(በአንደኛ የአለም ጦርነትም) ሳይታተም ለብዙ አመታት ቆየ፡፡ የኅሩይን መሄድ ፍላጎት
ግን ቀሰቀሰው፡፡ወደ ውጭ የመሄድ አድል የመጣላቸው ለጆርጅ አምስተኛ የዘውድ ክብረበአል
በሰኔ 15 1903 ነበር፡፡

ልጅ(አቤቶ)እያሱ ደጃች (በኋላ ራስ) ካሳን (የወይዘሮ ትሰሜን ልጅ) ጨምረው ልኡካኑን
እንዲመክሩ ላኳቸው፡፡ኅሩይም በጸሃፊነት ተከተሉ፡፡ወደ ድሬዳዋ ባቡር ለመሳፈር ሄዱ፡፡በጊዜው
የባቡሩ መንገድ ማለቂያው እዚያ በመሆኑ ኅሩይ ወደ አውሮጳ በመሄዱ ጉዳይ በጣም ተሳክረው
ስለነበር ምንአልባት አንዳች የሚያድዳቸው ነገር እንዳይፈጠር በመስጋት እስከ ሞጆ(በግምት 75
ኪ.ሜ) ከሌሎች ተነጥለው ሔደው እዚያ ሲደርሱ ከዋናው ቡድን ጋር ተቀላቀሉ፡፡

ሃረር ላይ ሶስት ቀን ከደጃዝማች ተፈሪ ዘንድ ቆዩ፡፡ቀጥለው ወደ ድሬዳዋ በመዝለቅ ወደ ጅቡቲ


በባቡር ተሳፈሩ፡፡በባቡር መጓዝ ለሁሉም አዲስ ነበር፡፡ከሎንዶን የዘውዱ በአል በኋላ ወደ
ኦክስፎርድ ሄዱ፡፡(እዛም ዩንቨርሲቲውን ጎበኙ)ፓሪስ ሮም አሌክሳንድሪያ፤ካይሮ፤እየሩሳሌም
ቆይተው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡በድጋሚ ደጃዝማች ተፈሪ ጋር ለ3 ቀን በመቆየት ወደ
አዲስ አበባ ጉዞ ሆነ፡፡ተፈሪ በጊዜው ለኅሩይ 50 ብር ሰጥተዋቸው ነበር፡፡(ምንአልባትም ለምግብ
ይሆናል)ይህ ጉዞ ለኅሩይ ደጃች ተፈሪን ለማግኘት በር ከፍቷል፡፡ወደአዲስ አበባ ሲመለሱም ደጃች
33
ጥቋቁር አናብስት

ካሳ ኅሩይን ለመጀመርያ ጊዜ ከአቤቶ እያሱ ጋር “አብሮኝ የሄደ ሰው ነው”በማለት


አስተዋወቋቸው፡፡ሲመለሱም የኅሩይ ወርኀዊ ደሞዝ የሁለት ብር ጭማሪ ተደረገለት፡፡ወድያው
የፈረንሳዮቹ ዶክተሮች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡ከዛ በኋላ ግን ኅሩይ ወደ ሆስፒታሉ ለስራ
አልተመለሱም፡፡ደሞዛቸውን ግን መቀበል ቀጠሉ፡፡

ነጋድራስ በኋላ (ቢትወደድ)ኀይለ ግዮርጊስ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሲሆኑ ኅሩይንና አንድ
ገብረክርስቶስ የሚባል ግለሰብን ፍትሐነገስቱን እንዲያስተረጉሙላቸው ጠየቁ፡፡ ለዚህም
እያንዳንዳቸው 200 ብር ተከፈላቸው፡፡ይህ የሆነው ኅሩይ እንጦጦ እያሉ ነበር፡፡ከዚህ በኋላ
በኀይለዮርጊስና በኅሩይ መሃል ወዳጅነት ተፈጠረ፡፡ወደኋላም ለኅሩይ ይሄ ጓደኝነት ረድቷቸዋል፡፡
ኀይለግዮርጊስ ጠቅላይ ሚንስትርነትን በአቤቶ እያሱ ተሾሙ፡፡ይሄም ለኅሩይ ጥሩ በር
ከፈተላቸው፡፡የኀይለግዮርጊስ ሚስት ስህን ሚካኤል ይባላሉ፡፡(የራስ ሚካኤል ልጅ)ኀይለ ግዮርጊስ
የከተማ መስተዳደር ቢሮ አዲስ አበባ ላይ መሰረቱ፡፡ኅሩይም ይሄን ቢሮ እንዲመሩ በ1907
ተሾሙ፡፡ሌሎች አቤቶ እያሱን ለምነው የነበር ቢሆንም ኅሩይ ግን በወር 50 ብር ሊቀጠሩ ቻሉ፡፡
ኀይለ ግዮርጊስ እና ኅሩይ አብረው መስራትና መቀራረብ ቻሉ፡፡አቤቶ እያሱም ኅሩይ ቢሮ

ከጊዜ ጊዜ የመዘጋጃ ቤቱን ስራ ሊቆጣጠሩ ይመጡ ነበር፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን አቤቶ በአዲስ አበባ የሚያሳልፉት ጊዜ እያጠረ መጣ፡፡መኳንንቶቹ


መስተዳድሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቆጣጠሩት መጥተው ለኅሩይና ለቢሮው ትኩረት ነፈጓቸው፡፡
ለመስራትም በመናገሻው የሰላም እጦት ስለነበር ቦታው አዳጋች ሆነ ፡፡ኅሩይ በዚህ የተነሳ ወደ
ቢሮው መሄድ ለጥቂት ጊዜ አቁመው ነበር፡፡ኅሩይ ወደ ቢትወደድ ኀይለ ግዮርጊስ ቤት በመስከረም
17 1909 ለመስቀል በአል እንኳን አደረስዎ ለማለት ሲሄዱ አቤቶ እያሱን ከስልጣን አፈናቅሎ
ዘውዲቱን ስለመተካት የታቀደ ሴራ ሰሙ፡፡ኅሩይ ወደ ቤት ሲጣደፉ መንገድ ላይ ተኩስና
ፉከራው ቀለጠ፡፡42ምሽት ላይ ኅሩይ ወደ ኀይለ ግዮርጊስ ቤት ተመልሰው ሲሄዱ፤ቢትወደድም
የመፈንቅለ መንግስት ጭምጭምታውን እውነታነት አረጋገጡ፡፡

ከዛ በኋላ ኅሩይ ለሶስት ቀናት ከቤት ሳይወጡ ቀሩ፡፡

ኅሩይ ለለውጡ የነበራቸውን አቋም ማወቅ ይከብዳል፡፡ስለ ልጅ እያሱ ብዙ ጭምጭምታዎች


ይሰሙ ነበር፡፡ነገር ግን ኅሩይ በነሱ ተቀይረዋል ማለት አይቻልም፡፡ተራው ህዝብ እያሱን
ይወዳቸዋል፤መኳንንቱ ግን በተቃራኒው ይጠላቸዋል ፡፡ይህም በትእቢትና በማንቋሸሽ
ስለሚመለከቷቸውም ነው፡፡አንድ ሰው ከሞተ “እያሱ ነው የገደለው” የሚል ሃሜት ይናፈሳል፡፡

34
ጥቋቁር አናብስት

ሃይማኖታቸውንም ወደ እስልምና እንደቀየሩም አሉባልታ ይናፈሳል፡፡አንዳንድ የውጪ ዜጎች


ኅሩይ እያሱን ክደው አሳልፈው እንደሰጧቸው ቢናገሩም ይሄ ትርጉም የለሽ ነው፡፡43

ቢትወደድ ኀይለግዮርጊስ የልጅ/አቤቶ እያሱን እህት ወይዘሮ ስህንን ስላገቡ (የኀይለሥላሴ


ባለቤትና የእቴጌ መነን እናት) ሁለቱም እያሱና ተፈሪ ቤታቸው አልፎ አልፎ መምጣት ነበረባቸው፡
፡ኅሩይም እዚያ ስለሚያዘወትሩ የመገናኘታቸው እድል ሰፊ ነው፡፡አንዳንዶችም ተፈሪ ኅሩይን
በእያሱ ደጋፊነት ይጠረጥሯቸው እንደነበር ይናገራሉ፡፡በአንድ ወቅት እያሱና ተፈሪ አንድ ላይ
ኅሩይ ቢሮ ማዘጋጃ መጡ፡፡እያሱም “ኅሩይን ታውቀዋለህ?”ብለው ተፈሪን በመጠየቃቸው ተፈሪ
ይሄንን አስታውሰው ስልጣን ከያዙ በኋላ ይጠረጥሩኝ ይሆን ብለው ይሰጉ ነበር ሲሉ በግል የውሎ
መዘከርያቸው ጽፈዋል፡፡ይህንን ተከትሎ ኅሩይ በብጥብጡ ወቅት ከቤት ሳይወጡ ቆዩ፡፡በኋላም
በመስከረም 20 1909 ከመፈንቅለ መንግስቱ 3 ቀናት በኋላ መልእክተኛ መጥቶ “አልጋ ወራሽ
ይፈልጎዎታል” ተብለው ተጠሩ፡፡ቤተመንግስቱ ውስጥ ተፈሪ“ለምን እስካዛሬ
አልመጣህም?”ብለው ጠየቋቸው፡፡ኅሩይም “ፈርቼ ነበር” ሲሉ መለሱ፡፡ይህ ምላሽ በተፈሪ
ጭንቅላት ውስጥ ተቀርጾ ቀርቶ የነበር ይመስላል በሌላ ቀን ለምን እንደፈሩ ጠየቋቸው ህሩይም
“ከአቤቶ እያሱ ጋር አብረን ስላዩኝ ምናልባት ታማኝ ሰራተኛቸው መስዬዎት ያሳስሩኝ ይሆናል
ብዬ”43 ነው ካሉ በኋላ በማከልም የአልጋወራሽ ታማኝና ደጋፊ እንደሆኑ ተናገሩ፡፡ተፈሪ ቀጥለውም
“በስራህ ምክንያት ነው ታማኝነትህ፤ለሃገርህ በትጋት ከሰራህም ሽልማትህን አታጣም” አሏቸው
ከዚያ በኋላ ኅሩይ ከስጋት አረፍ አሉ፡፡

***

በ1909 ኅሩይ የመዘጋጃ ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡ይህም ከአልጋ ወራሹና ከንግስቲቱ


ጋር አቀራረባቸው፡፡ሁለቱም በተለያዩ አጋጣሚዎች በቀጥታ ጽፈውላቸዋል፡፡ከአንደኛው የአለም
ጦርነት በኋላ ሶስት የተለያዩ የልኡካን ቡድኖች የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው ወደ ውጪ
ተልከው ነበር፡፡(እንኳን ደስ አላችሁ ለማለትና ወዳጅነትን ዳግም ለመመስረት)አንዱ ቡድን ወደ
ጣልያን ሌላው ወደ ፈረንሳይ ኅሩይ ያሉበት ደግሞ በደጃዝማች በኋላ (በራስ ናደው መሪነት)ወደ
እንግሊዝና አሜሪካ አቀኑ፡፡ ከንቲባ ገብሩ ደስታም ቡድኑ ውስጥ ነበሩ፡፡በዚህ ወቅት የባቡር
መስመሩ አዲስ አበባ ደርሶ ነበር፡፡በእንግሊዝ ንጉስ ጆርጅ ለልኡካኑ በአየር ላይ ሎንዶንን
የማስጎብኘት ግብዣ አቀረቡላቸው፡፡አውሮጵላን ላይ ተሳፍረው ባያውቁም እያቅማሙ ተስማሙ፡፡
44
የኢትዮጵያ ልኡካኑ የቆሰሉ ወታደሮችን በሎንዶን በሚገኙ ሆስፒታሎች ጎበኙ፡፡ በአሜሪካ

35
ጥቋቁር አናብስት

የመጀመርያ ጉብኝታቸው ደግሞ የተቀበሏቸው ፕሬዝደንት ውድሮው ዊልሰን ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ


በ1913 ዋሽንግተንንም ከአየር ላይ ሆነው አዩ፡፡ኒውዮርክንም አይተው ታካሚ ቁስለኞችን
በሆስፒታል ጎበኙ፡፡ከዚህ ጉብኝት በኋላ ፓሪስ ደርሰው ከ1918 መጨረሻ በፊት ወደ አዲስ አበባ
መመለሳቸው ይነገራል፡፡

ሰዎች “የማዘጋጃ ቤቱ ስራ ቅርጽ የያዘው ኅሩይ በነበሩበት ወቅት ነው ”ይላሉ፡፡የአዲስ አበባ


ካርታና የመዘጋጃ ቤት ግብር ተቋቋመ፡፡በስራም ጫና የተነሳ ሊሆን ይችላል የኅሩይ ጤና እየተጓደለ
መጣ፡፡ጥቅምት 13 በ1913 አ.ም ቀንም ስላዞራቸው በበቅሎ ወደ ቤት መመለስ ነበረባቸው፡፡
ከተወሰኑ ቀናት በኋላ መንቀሳቀስ አቃታቸው፡፡አልጋ ወራሹ ወደ አውሮጳ ለህክምና ሊልኳቸው
ቢያስቡም ልጅ እያሱ (በወቅቱ ከስልጣን ተወግደው በነጻነት ይንቀሳቀሱ ነበር)ወደ ትግራይ የሄዱት
ጦርነት ሊያነሱ ነው መባልን ሲሰሙ ተፈሪ ወደ ወሎ ሄዱ፡፡በሰኔ 1913 አንድ ልኡክ ወደ
እየሩሳሌም በኢትዮጵያ ገዳማት ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ተላከ፡፡ ኅሩይም የዚህ ልኡክ አባል ነበሩ፡፡
ካይሮ ሲደርሱ ኅሩይ ለህክምና ጉዟቸውን አቋረጡ፡፡በኋላም እየሩሳሌም ላይ ከሌሎቹ ጋር
ተቀላቀሉ፡፡ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት በጥሩ የጤና ሁኔታ ነበር፡፡ነገር ግን ሌሎች ችግሮች ተነሱ፡፡
ማዘጋጃ ካሉት አለቃቸው ጋር መስማማት ስላልቻሉ ስራቸውን መቀጠል አልፈለጉም ነበርና
መልቀቂያ አስገቡ፡፡

ከሁለት ወራት እረፍት በኋላ በ1914 የብላታነትን መዐረግ ተቀዳጁ፡፡በመቋቋም ላይ በነበረው


ከፍተኛው ፍርድ ቤትም የኢትዮጵያና የውጪ ዜጎችን ጉዳይ በሚያየው ሸንጎ ላይ በዋና ዳኝነት
ተሾሙ፡፡በወቅቱ እድሜያቸው 43 አመት ከ6 ወር ነበር፡፡በተጨማሪም ለልዩ ስራዎች ወደ
ቤተመንግስት ይመላለሳሉ፡፡እንደ ዳኛ በፍትሐ ነገስቱና በልማዳዊ ህጎቹ ላይ ያላቸው እውቀት
ጠቃሚ ነበር፡፡ስራዎቻቸውንም በቀላልና በቅልጥፍና ይፈጽማሉ፡፡በዚህም ምስጉን ነበሩ፡፡ስራው
ግን አስቸጋሪ ስለነበር በድጋሚ ታመው ለህክምና ወደ ውጪ መሄድ ነበረባቸው፡፡የወደፊቷን
እቴጌ መነንን አጅበው ወደ እየሩሳሌም ለመሳለም ሲሄዱ አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች መሃል ነበሩ፡፡
የኅሩይ ሚስት ወይዘሮ ሐመረም ከቡድኑ መሃል ነበረች፡፡ከእየሩሳሌም ቆይታቸው በኋላ ወደ
አሌክሳንድርያ ሄደው ታላቅ አቀባበል በፓትርያርኩ አቡነ ዮሐንስ ተደረገላቸው፡፡ኅሩይ የምስጋና
ንግግር እዛው ከተማ ቪክቶርያ ኮሌጅ በሚማረው ልጃቸው ፍቃደ ሥላሴ እያስተረጎሙ ተናገሩ፡፡
ለልጁ ለዚህ የትርጁማንነት ስራው እቴጌ መነን የወርቅ ሰአት ሸልመውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ዋናው ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ፡፡ኅሩይ ግን ወደ አውሮጳ ለህክምና ሄዱ፡፡


ለሁለት ወራትም ኦስትርያ ውስጥ ታከሙ፡፡ከዛ በኋላ ወደ ቡዳፔስትና ስውድን ሄዱ፡፡ብቻቸውን
ቢጓዙም አንዳንድ የመንግስት ሹመኞችን በጉብኝታቸው ላይ አግኝተው ለመነጋገር በቁ፡፡አውሮጳ
ሳሉም ኢትዮጵያን በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ለማስመዝገብ ከተላከው ቡድን ጋር እንዲቆዩ ተጠይቀዋል፡፡
36
ጥቋቁር አናብስት

ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም ኅሩይ በጣም እረፍት አስፈልጓቸው ስለነበር ተፈሪም ፈቀዱላቸው፡፡


አልፎ አልፎ ብቻ ነበር ወደ ቢሯቸውና ወደ ቤተመንግስት የሚሄዱት፡፡

አንዳንድ የቤተክህነት ሰዎች ኅሩይን ተቃውመው ተወዳጅነታቸው እንዲቀንስ ለንግስት ዘውዲቱ


የኦርቶዶክስ ሃይማኖታቸውን እንደተው ቢነግሯቸውም ማስረጃ ስላልተገኘ ንግስቲቱ ነገሩን
ትተውታል፡፡45

ኅሩይ ጤናቸው መለስ ብሎላቸው ወደ ስራቸው ሲመለሱ ደሞዛቸው በወር ወደ 200 ብር


አደገላቸው፡፡46 ጭማሬውም ከየካቲት 1916 ጀምሮ ከድሬዳዋ መዘጋጃ ቤት እንዲከፈል ሆነ፡፡
ለዚህ ደግሞ ማህተማቸውን ለድሬዳዋ መዘጋጃ ቤት ሃላፊ መስጠት ነበረባቸው፡፡

***

ኢትዮጵያ ሊግ ኦፍ ኔሽንስን ስትቀላቀል ሃገሪቱ በአውሮጳ በይበልጥ ለመታወቅ ቻለች፡፡ከዛ በፊት


ተፈሪ በአውሮጳ የጉብኝት ጥሪ ተደርጎላቸው ስለበርካታ ምክንያቶች ሲባል ግን መቀበል
አልቻሉም፡፡አሁን ግን ለመሄድ ዝግጁ ሆኑ በሚያዝያ 1916 ዓ.ም ተፈሪ ወደ አውሮጳ ሲሄዱ
ብላታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አብረዋቸው ነበሩ፡፡ሁለቱን ልጆቻቸውንም ሲራክና ፍቃደ ሥላሴን
በአሌክሳንድርያ ለመጎብኘት ቻሉ፡፡በዚህ ከአልጋ ወራሽ ጋር በተደረገ ጉዞ ግብጽን ፤እየሩሳሌምን፤
ፓሪስን፤ ቤልጅየምን፤ እንግሊዝን፤ ጣልያንን ፤ስቶክሆልምን፤ ጄኔቫን ፡እንዲሁም ሌሎች የአውሮጳ
ከተሞችንና ሃገራትን ጎብኝተዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ግን ኅሩይን አሁንም ጤናቸው
አስቸገራቸው፡፡ በመስከረም 1917 ሰዎች የአእምሯቸውን በጤንነት መቀጠል
እስከሚጠራጠሩበት ደረጃ ድረስ በጽኑ ታመው ደከሙ፡፡ በወቅቱ ላምቤ እሚባለው ሆስፒታል
ገብተው 47ለአርባ ቀን ቆይተው መለስ አለላቸው፡፡በሚቀጥለው በልዑክነት በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ላይ
እንዲሳተፉ ጄኔቫ ሲላኩ የህክምና ዶክተሮችን ለማየት እድሉን ተጠቀሙበት፡፡በዚያው ጉዞ
(ሃገራቸውን የሚጠቅም አንዳች ለመፈለግ)ብዙ ሃገራትን ጎብኝተዋል፡፡ተፈሪ የኅሩይን የጤና
ሁኔታ አሳስቧቸው ስለነበር በሚነጋገሩበት ወቅት ሁሉ ስለጤናቸው እንዲጽፉላቸው ይነግሯቸው
ነበር፡፡በዚህ ወቅት በርካታ የጽሁፍ ልውውጦችን በቋሚነት በሳምንት አንዴ አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ ላይም የተፈሪና የኅሩይ ወዳጅነት እንደቀጠለ ነበር፡፡ኅሩይ ከተለያዩ የመንግስት መስርያ
ቤቶች ባደረጓቸው ግንኙነቶች መጨረሻ ላይም (ይህ የአልጋ ወራሽ ትእዛዝ ነው) የሚሉ ቃላት
ይገኙባቸው ነበር፡፡የኅሩይ ቢሮ ከቤታቸው ይርቃል፡፡እናም ወደ ቢሯቸው ለመሄድ የሚያደርጉትን
ጉዞ ጫና ለማካካስ ያህል በ1919 የልኡል አልጋ ወራሽ ልዩ አማካሪ ሆኑ፡፡ያም ቢሆን ግን

37
ጥቋቁር አናብስት

ስራቸውን የሚሰሩት በንግስቲቱ ቀጥተኛ ትእዛዝ ነበር፡፡ከንግስት ዘውዲቱም የተጻፉ በቀጥታ


ኅሩይን የሚያዙ ብዙ ደብዳቤዎችም አሉ፡፡

ብላታ ኅሩይ ልዩ አማካሪ ከሆኑ ከአንድ አመት በኋላ የብላቴን ጌታ መአረግ ተሰጥቷቸው በ1920
የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጠቅላይ ዳይሬክተር ሆኑ፡፡ደሞዛቸው በወር 300 ብር ሲሆን ውጪ
ጉዳይ ሚንስቴሩ እራሳቸው ተፈሪ ነበሩ፡፡የኅሩይን ትጋትና ታማኝነት ካዩ በኋላ ግን ሚንስትርነቱን
ተውላቸው፡፡ስራ ሲበዛባቸው በበቅሎ ወደ ቤት ለምሳ የሚሄዱት ኅሩይም ሰአት ላለማባከን
መኪና መከራየት አስፈለጋቸው፡፡ይህም ወጪ የሚሆነው ከሚንስትሩ ነበር፡፡የተመደበለት መጠን
ግን በወር50 ብር ነበር፡፡የኅሩይ ስራና አስተዋጽኦ እውቅና ያገኘና የተመሰገነ በጽህፈት ሚንስትርም
የተመዘገበ ነበር፡፡ብዙ ክብርንም ተቀዳጅተዋል፡፡

***

ንግስት ዘውዲቱ በድንገት ታመው በመጋቢት 24 1922 አረፉ፡፡አልጋ ወራሽ ተፈሪም ቀዳማዊ
ኀይለሥላሤ ተብለው ተቀቡ፡፡የዚህ ዝግጅት ሃላፊነትም በብላታ ኅሩይ ትከሻ ላይ ወደቀ፡፡
ተጨማሪ ስራ ቢጠይቅም ኅሩይ በትጋት ሊወጡት ችለዋል፡፡ኅሩይ ከኀይለሥላሴ በዐለ ሲመት
በኋላ በውጪ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተርነታቸው አልቆዩም፤በሚያዝያ 12 የውጪ ጉዳይ ሚንስትር
ሆነው ሲሾሙ ደሞዛቸው 1000 ብር ደረሰ መኪናም ተሰጣቸው፡፡48 ወደ ጉለሌ ቤታቸው
መዳረሻም መንገድ ተሰራ፡፡በጊዜው ለእንደዚህ አይነት ክብር የመጀመርያው ነበሩ፤49በህይወታቸው
ሙሉ አንድ ሹፌር ብቻ ሲሆን የነበራቸው እ.ኤ.አ በ1987 እንደተነገረኝ ከሆነ ይህ ሹፌራቸው
ከጥቂት አመታት በፊት ነበር ያረፈው፡፡

በ1920 ዓ. ም ኢትዮጵያና ጃፓን የወዳጅነትና የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ኀይለሥላሴም


ይህንን ውል ለማደስና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ከጃፓን ጋር መመስረት ፈለጉ፡፡ኅሩይ ነበሩ
ለዚህ ስራ የተመረጡት፡፡ጃፓንን ሌላ ኢትዮጵያዊ ጎብኝቷት ስለማያውቅ ኅሩይ በመመረጣቸው
በጣም ተደሰቱ፡፡በመስከረም 21 1924 ዓ.ም ቡድኑን እየመሩ ከአዲስ አበባ ተንቀሳቀሱ፡፡50
በጃፓንእንደ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ነበር የተያዙት፡፡በብዙ ትእይንቶችም በተሞላ ሁኔታ ኅሩይ the
order of the rising sun(የፀሃይ ፍልቀት ኒሻን) ከነጥብጣቡ ተቀበሉ፡፡በርካታ ከተሞችን
ታሪካዊ ቦታዎችን ዩንቨርሲቲዎችን ቤተ እምነቶችንም ጎበኙ፡፡በጉብኝታቸው ማጠናቀቅያ ወደ
ኢትዮጵያ የተመለሱት በመርከብ ነበር፡፡በወቅቱ ኅሩይ በእንግዳ ተቀባይነትና ለውጪ ዜጎች
ወዳጅነትን በማሳየት ጃፓንን የሚስተካከል ሃገር እንደሌለ ተሰምቷቸው ነበር፡፡51

38
ጥቋቁር አናብስት

ከጥቂት ወራት በኋላ ኀይለሥላሴን ለአንድ ወር የአውሮጳ ጉዞ ፍቃድ ጠይቀው ተፈቀደላቸው፡፡


ከእቴጌ መነን ጋር ነበር የሄዱት፡፡እሳቸውም ወደ እየሩሳሌም ያሰሩትን ቤተክርስትያን ለማስመረቅና
ታቦቱን ለማስገባት በ1926 ዓ.ም አቀኑ፡፡ኅሩይ ከእቴጌይቱ ጋር አንድ ወር አሳለፉ፡፡እቴጌ መነን
ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም ወደ ግሪክ እሳቸው ወደ ግሪክ ጉዞዋቸውን ቀጠሉ፡፡ምንም እንኳን በግል
ቢሄዱም እንደ መንግስት ልዑክ ነበር አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ እዚያም የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን
እና ድርጅቶችን ለመጎብኘት ችለዋል፡፡የክብር ሜዳይ የግሪክ ጄኔራል የደንብ ልብስና ሻምላ
ተበረከተላቸው፡፡

***

ኅሩይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደነበሩ በኢትዮጵያና በጣልያን መሃል የነበረው ግንኙነት
እየሻከረ መጣ ፡፡በውጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጦች ኢትዮጵያን አስመልክቶ ብዙ አሉታዊ ጽሁፎችን
ማውጣት በመጀመራቸው በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ይህንን ማስተባበል አስፈላጊ ሆነ፡፡ይህንን
የኢትዮጵያ እይታ ለማስረገጥም የአጥብያ ኮከብ የተሰኘ ጋዜጣ በ1926 ዓ. ም በጎሃ ጽዮን
ማተምያ መታተም ጀመረ፡፡ሳምንታዊ የስምንት ገጽ ጋዜጣ ሲሆን በአማርኛና በፈረንሳይኛ
የሚታተም በኅሩይ ሰብሳቢነት እና ፕሬዝዳንትነት የሚመራ የአርትኦት ቦርድ ነበረው፡፡ሰዎች
“የብላቴን ጌታ ኅሩይ ጋዜጣ ”ብለው ይጠሩት ነበር፡፡ኅሩይ ከዚህ ቀደም ብሎ የብርሃንና ሰላም
ጋዜጣን ከቤተክህነት ምሁራን ጋር በመሆን እንዲቋቋምም እርዳታ አድርገዋል፡፡ ከህዝቡ ጋር
ለመተዋወቅ ገና ድክድክ በሚልበት ወቅትም በጦርነቱ ሳብያ ተቋረጠ፡፡ለጦርነቱ ዝግጅትም
ኢትዮጵያ ከውጪ የጦር መሳርያ በብዛት በመግዛት ላይ ነበረች፡፡ኅሩይም ከደመወዛቸው አንድ
አምስተኛውን ለዚሁ ግዢ አውለው ነበር፡፡የውጪ ሃይሎች ለኢትዮጵያ ባላቸው አመለካከት
በአብዛኛው ግድየለሽና ጠብ አጫሪ ነበሩ፡፡ምንም እንኳን በርካታ መንግስታት ኢትዮጵያን በጦር
መሳርያና በወታደር ሊረዱ ቢፈልጉም የቤልጅየም መንግስት ግን ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩትን
ጭነቶችና ሽያጮችን ለማከላከል ሞከረ፡፡በዚህም ኅሩይ የኢትዮጵያን ቅር መሰኘት ገልጸዋል፡፡
በሮም የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢጣልያ ወደ ጦርነት አታመራም ብለው አስበው ነበር፡፡በአጠቃላይ
ኢትዮጵያ ውሱን የውጭ ድጋፍ ነበር ያገኘችው፡፡ኅሩይ በ1929 መስከረም 22 ዓ.ም በተጻፈ
ደብዳቤያቸው በአዲስ አበባ የሚገኘውን የኢጣልያንን ልዑክ ቴሌግራም ወደ ጣልያን ከመላክ
እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡በስተመጨረሻም ከጣልያን ጋር ያለው ግጭት በሰላማዊ ሁኔታ ያለ
ጦርነት ይፈታል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ግን “ያለን ብቸኛ
ተስፋ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ነው” ብለዋል፡፡

በዚህ ቀውጢ ሰአት ውስጥ እንኳን (የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በጄኔሬተር ሃይል እያገኘ
በሚሰራበት ወቅት) ኅሩይ በሃምሌ 27 ለተቋቋመው የቀይ መስቀል ማህበር የመጀመርያው
39
ጥቋቁር አናብስት

ፕሬዝደንት እንዲሆኑ ተጠይቀው ተስማምተዋል፡፡ለቤተሰባቸውም የተሻለ ጥሩ ቤት መስራት


ጀመሩ፡፡ተጨማሪ መሬት በመግዛት ለራሳቸውና ለሶስት ልጆቻቸው ቤት ገነቡ፡፡ሁሉም ልጆቻቸው
አግብተው በዙርያቸው ይኖሩ ነበር፡፡በመንግስት ስልጣን ከፍ እያሉ ሲሄዱ በግልም ሆነ
ከባለስልጣናቱ ብዙ ሰዎች እሳቸው ዘንድ ደጅ ጥናት ጀመሩ፡፡52ኅሩይ ግን የሰሩትን አዲስ ቤት
ብዙም አልኖሩበትም፡፡ጣልያን ጦርነት ስለጀመረች በህዳር 1928 ዓ.ም ኃይለሥላሴ ለማይጨው
ጦርነት ለመዘጋጀት ወደ ደሴ አቀኑ፡፡የውጪ ጉዳዩን ነገር ለኅሩይና ኤቨሬት ኮልሰን ለተባሉ
አሜሪካዊ አማካሪ አደራ ሰጥተው ነበር የሄዱት፡፡ጣልያኖች በማይጨው ድል ሲቀናቸው
ኃይለሥላሴ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ ነገር ግን እሳቸው ሳይደርሱ ሚንስትሮቹ መናገሻውን ወደ
ጎሬ ኢሉ አባቦራ ወስድው በሽምቅ ለመዋጋት መክረው ነበር፡፡ኅሩይና ቤተሰቦቻቸው በአዲሱ
ቤታቸው ለ 8 ወራት ብቻ ከቆዩ በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ወደ ሜታ ላኩ፡፡ጣልያኖች ወደ አዲስ
አበባ ሲቃረቡ ዋናዋና መንገዶችን ዘጉ፡፡ንጉሱም በፍቼ በኩል አሳብረው ነበር ወደ ዋና ከተማው
መግባት የቻሉት፡፡ከመድረሳቸው በፊት ግን በእርሳቸውና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት
ለተወሰነ ወቅት ስለተቋረጠ ሚንስትሮቹ በመጨረሻ በህይወት ሲያገኟቸው እፎይታ ተሰማቸው፡፡

ጣልያን ደብረብርሃን ሲደርስ ሚንስትሮቹ ተሰብስበው ንጉሱ ወደ ጅቡቲ እንዲሄዱ መከሯቸው፡፡


ሃያ አንዱ ይህንን ሃሳብ ሲደግፉ ሶስት ተቃውሞ ተሰነዘረበት ፡፡ከተቃዋሚዎቹም መሃል ኅሩይ
አንዱ ነበሩ፡፡ሶስቱ ኃይለሥላሴ በሃገር ውስጥ ቆይተው የአርበኝነት ትግሉን እንዲመሩ ይፈልጉ
ነበር፡፡ የመጀመርያው መናገሻውን ወደ ጎሬ የማዛወር ሃሳብም ውድቅ ተደረገ፡፡ነገር ግን አብሮ
በእዛው ጊዜያዊ መንግስት በወልደ ጻዲቅ መሪነት እንዲቋቋም ተወሰነ፡፡ይህ ቢሆንም ኅሩይ
በጃንሜዳ በተደረገው ስብሰባ ላይ ንጉሴን አልተውም አሉ፡፡ቤተሰባቸውን ለማየትም ጊዜ
ስላልነበረ ንጉሱ ተቃውሟቸውን በጄኔቭ ለማቅረብ በሚያዝያ 24 (1928) ሲነሱ ኅሩይም
በውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ተከተሏቸው፡፡

የኅሩይ ስደት የታወቀ የስነ ጽሁፍ ሙያቸው ማሳረግያ ነበር፡፡ከ1904 ጀምሮ እስከ ጣልያን ወረራ
ወቅት ድረስ ኅሩይ ፍሬያማ የነበሩ ሲሆን ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ነበሩ የሳቸው መሳ ሆነው ያን
ያህል መጻፍ የቻሉት፡፡አንድ ግዜ በ1903 ኅሩይ በባቡር ከኦክስፎርድ ወደ ሎንዶን እየተጓዙ ሳለ
ነበር አንድ ስኮትላንዳዊ አልፍሬድ ጆን የሚባል ሰው ተዋውቀው በኢትዮጵያ ምን መጻሕፍት
እንዳሉ የጠየቃቸው፡፡ኅሩይ ከሃዲስና ብሉያት መጻሕፍት ውጪ ሌላ ዝርዝር እንደሌለ ተናገሩ፡፡
አልፍሬድ ጆን ኅሩይን በኢትዮጵያ ያሉ የመጻሕፍትን ዝርዝር እንዲጽፉለት ጠየቃቸው፡፡ወደ
ሃገራቸው ሲመለሱም ከሊቃውንቱ የሰሟቸውን በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የተጻፉ መጽሐፍት
በ9 ገጽ ዝርዝር ይዘው መጥተው በኢትዮጵያ ማተምያ ቤት በ1904 ዓ.ም ሊታተም በቅቷል፡፡

40
ጥቋቁር አናብስት

ከዚያ ቀደም ግን የመጀመርያና በአዲስ አበባ የታወቀውን በ1904 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤቱ ማባዣ
የተባዛና (በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተውን) ወዳጄ ልቤ የተሰኘውን ጽሁፍ አበርክተዋል፡፡ነገር ግን
እስከ 1915 ዓ.ም ድረስ በወጉ አልታተመም፡፡በነጻ ነበር ያከፋፈሉት፡፡በዝርዝሩ ከተካተቱ መሃል
የራሳቸው ስራና ሳይታተም የቀረው ወይዘሮ ጥበብና የለቅሶ ዜማ ግጥም ይገኙበታል፡፡

በ1904 እና በ1927 መሃል በርካታ መጻህፍትን ጽፈዋል፡፡በትክክል ምን ያህል እንደጻፉ ማካተት


ባይቻልም 26 መጻሕፍትን መጻፋቸውን መናገር ይቻላል፤ምንም እንኳን አንዳንዶች 28
ቢያደርሱትም፡፡አንድ ጋዜጣም በአንድ ወቅት 42 መጽሐፍ መጻፋቸውን ቢያትትም

የአርእስታቸውን ዝርዝር ግን አላካተተም ነበር፡፡

በተከታዮቹ መጻሕፍት ላይ ግን ከሞላ ጎደል እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡

1በኢትዮጵያ የሚገኙ የመጻህፍት ቁጥር 1904 የ318 መጻህፍትን ዝርዝር አካቷል፡፡

2ኢትዮጵያና መተማ 1910 ስለ አጤ ዮሃንስ አራተኛ ነው

3ለልጅ ምክር ለአባት መታሰብያ 1910 ለበኩር ልጃቸው ተጻፈ ምከር

4ወዳጄ ልቤ ቢታተምም ከበርካታ አመታት በፊት የተጻፈ ምንአልባት በ1904 አ.ም


በሃይማኖታዊ እሳቤዎች የበለጻገና ከጆን ቡንያን pilgrim´s progress ከተባለው ተተርጉሞ
ብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ ተጽእኖ ካሳደረው መጽሐፍ ጋር ተመሳስሎ ያለው፡፡

5የልእልት ወይዘሮ መነን መንገድ በእየሩሳሌምና በምስር 1915

6የህይወት ታሪክ 1915 የብዙ ታዋቂ ሰዎችን ታሪክ የሚናገር

7ደስታና ክብር 1916

8ስለአውሮጳ መንገድ የምክር ቃል 1916

9መጽሃፈ ቅኔ 1918

41
ጥቋቁር አናብስት

10 ጎህ ጸባ 1919

11 የለቅሶ ዜማ 1919

12 ዋዜማ 1921

13ስኳርና ወተት 1922 ከእንግሊዘኛው ወጥ ስራ የተመለሰ

14የልብ ሃሳብ 1923

15ጥሩ ምንጭ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች በተለዋጭ አቀራረብ 1923

16 ማህደረ ብርሃን በሃገረ ጃፓን 1923

17 አዲስ አለም ወይም አወቀ በመባል ይጠራል ስለ ኢትዮጵያ ዘመናዊነት ነው

18 በእድሜ ልሰንብት ሁሉን ለማየት1926

19 እኔና ወዳጆቼ 1927

20 የኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ ቀኑ ያልታወቀ

21 የአጼ ኀይለሥላሴ አጭር ታሪክ ጊዜው ያልታወቀ

ያልታተሙ

22ወይዘሮ ጥበብና የልቅሶ ዜማ ግጥም

23የሰማይ መንገድ ካርታ

24 የአጼ ኀይለሥላሴ ሙሉ ታሪክ

25 ከሳቴ ብርሃን

42
ጥቋቁር አናብስት

26እንደ ግጥም ያለ ምሳሌ

አንዳንዶች የሚቀጥሉትንም ጽፈዋል ይላሉ

27 አዲስ አበባ

28የአማርኛ ስዋሰው

ይህን በማየት ኅሩይ በአመት አንድ መጽሐፍ እየጻፉ ለብዙ አመታት አሳትመዋል ማለት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ያልታተሙ መጽሐፍትንም ጽፈዋል፡፡በ1911 እና በ1914 መሃል የጤና እክል


ስለተፈጠረባቸው ለምን እንዳልጻፉ ማመላከቻ ይሆናል፡፡አብዛኞቹ መጽሐፍቶቻቸው ከ 1915
እስከ 1927 ባለው ጊዜ ውስጥ የታተሙ ናቸው፡፡ይህ ምናልባትም ከብርሃንና ሰላም ማተምያ ቤት
በ1914 መቋቋም ጋር ተቆራኝቶ የማሳተም እድሉ መሻሻል ስላሳየ ሊሆን ይችላል፡፡ብዙም ሳይቆይ
´የሳቸው´ ማተምያ ቤት ጎህጸባህ ተቋቋመና የመጀመርያው በዚህ ማተምያ ቤት የታተመው
መጻሐፋቸው በ1921 ዓ.ም ተለቀቀ፡፡በመዘጋጃ ቤት ሳሉ የህትመቱን ስራ በኢትዮጵያ
ለማቀላጠፍ ጉጉት አድሮባቸው ነበር፡፡መሳርያዎቹ እ.ኤ.አ በ1906 ለመጡለት መርሐጥበብ
ማተምያ ቤት እድገትም በጣም ለፍተዋል፡፡

ኅሩይ በሚጽፉበት ወቅት ሳንሱር አልነበረም፡፡ከመጽሀፎቻቸው አንዱ የሆነውና የቤተክህነትን


አላግባብ ስራዎች የሚተቸው መጻህፋቸው ብዙ ነቀፌታን ከቤተክህነቱ ሰዎች ያሳደረባቸው ሲሆን
ምንአልባትም የቤተ ክህነቱ ሰዎች ሳንሱር አድራጊ በነበሩበት የኋለኛው ዘመን ቢሆን ለህትመት
ላያልፍ ይችል ነበር፡፡ኅሩይ ሁሉንም መጽሐፍቶቻቸውን በመንግስት ስራ ተጠምደው ሳለ
በነበራቸው ትርፍ ግዜ ነው የጻፏቸው፡፡አንዳንዴ በስራ ከመዳከማቸው የተነሳ እራት እንኳን
ሳይበሉ ነበር የሚተኙት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከእንቅልፋቸው በመንቃት ግቢያቸው ውስጥ
መዟዟርና ወደ ጥናት ክፍላቸው በመሄድ ያነባሉ ይጽፋሉ፡፡በጥቅምት 1915 ዓ.ም ኢትዮጵያ ወደ
ሊግ ኦፍ ኔሽንስ እንድትገባ ተደራድረው ከተመለሱ በኋላ በተሰጣቸው የህመም ፍቃድ ነበር
ከሌላው ጊዜ በላቀ ሁኔታ የጻፉ የሚመስለው፡፡በቀጣይ “ስሜ በጻፍኳቸው መጻህፍቶቼ ይነሳል”
ሲሉ ያስቡ የነበር ሲሆን ብዕርና ወረቀት በአካባቢያቸው አዘጋጅተው ድንገተኛ ሃሳብ ሲመጣ
ለመክተብ ይዘጋጃሉ፡፡ ሁሌም ንቁ ይመስላሉ፡፤ምንም እንኳን በጊዜው የአንዳንድ ጸሀፍት ስራዎችን
እንደወሰዱ በጭምጭምታ ደረጃ ቢነገርም ካለፍ አገደም የሌሎችን እርዳታ ረቂቃቸውን ለህትመት
ለማዘጋጀት ይጠቀሙ ነበር፡፡ በታሪክ ፤ጉዞ፤ሃይማኖት፤ልብወለድ፤ስነ ግጥም፤ ተግሳጽና ምክር

43
ጥቋቁር አናብስት

ዙርያ ሰርተዋል፡፡ከሌሎች ትውፊቶችን በመልቀም የራሳቸውን አሻራ በማኖር አሳትመዋቸዋል፡፡


አማርኛን የተሻለ የስነ ጽሁፍ አውታር ለማድረግ በጣም ለፍተዋል፡፡ የአማርኛ ስነጽሁፍ አባት
(ይገባቸዋልም) ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡የተወሰኑ ከእሳቸው በፊት የጻፉ ቢኖሩም የአማርኛ ስነጽሀፍ
ግን ወግ ያየው በእርሳቸው ነበር ማለት ይቻላል፡፡ዝናቸው እስከ አውሮጳ ናኝቶ የጀርመኑ
ኦርየንታል ማህበር የክብር አባል ሆነዋል፡፡

የጣልያን ወረራ የኅሩይን የስነጽሁፍ ጉዞ ቢገታውም በእንግሊዝ ሳሉ የንጉሱን ግለ ህይወት ታሪክ


መጽሐፍ በቅርጽ ደረጃ ያዋቀሩ እሳቸው ነበሩ፡፡

……

ኅሩይ ወልደሥላሴ ምን ዐይነት ሰው ነበሩ? የድሮ ባህሎችን የሚሰብሩ አዲስ ሃሳብ አመንጪ
ዐይነት ሰው ነበሩ (ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያውያን የሚወደደውን ጥሬ ስጋ ከምላስና ሰንበር ውጪ
ሳይበስል የማይመገቡ ሲሆን የበሰለና የተጠበሰ ስጋ ግን ምርጫቸው ነበር)ክርክር የማይወዱ ሲሆን
የጸብ መነሳት አዝማምያ ካዩ ዝምታን ይመርጣሉ፡፡በትርፍ ጊዜያቸው ያነባሉ ይጽፋሉ፡፡ጋዜጣን
በንቃት የሚከታተሉ ሲሆን ያልተመቻቸው ነገር ባገኙበት ጊዜ ሁሉ ምላሽ ለጋዜጣው ከመጻፍ
አይቆጠቡም፡፡በዚህ የተነሳም የአንድ ክፍለ ሃገር አስተዳደር በመስተዳድሩ ውስጥ እየተዟዟረ
በሚጎበኝበት ወቅት ሃገሬው ለእሱና ለ500 ሰዎቹ ምግብና መኝታ ብሎም ለአፍራሳትና
በቅሎዎቻቸው ጥሬ የማቅረብ ግዴታ መግባታቸውን ነቅፈው ገበሬው ላይ ሸክም የሚሆንና
ምንም ፋይዳ የሌለው የበፊት ልማድ ቢሆንም መደረግ ያለበት ከሆነም ደግሞ በገበሬዎቹ ጥያቄና
ወጪው በመንግስት ተሸፍኖ ነው መሆን ያለበት ሲሉ ጽፈዋል፡፡ኅሩይ እንዲህ ባለ ይዘት በብዛት
የመንግስት ሹሞችን እንኳን የሚያስጠይቅ ጽሁፍ ይጽፉ ነበር፡፡

ኅሩይ ቀጥተኛና ሃሜት የማይወዱ ሰው ነበሩ ይባላል፡፡ በስልጣናቸው የማይታበዩ ትሁት ሰው


እንደነበሩ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ከላይ የመጣ ትእዛዝን ሳይጠይቁ ማስፈጸም የሚችሉ ሲሆን
ኀይለሥላሴም ይህንን ይወዳሉ፡፡በኅሩይ ላይ ያላቸውም አመኔታ የጸና ነበር፡፡ይህም በተወሰነ
መልኩ ኅሩይ ለበላዮቻቸው ያላቸው አመለካከት እምን ድረስ እንደሆነ የሚመሰክር ሲሆን ኅሩይም
ለዚህ ታማኝነታቸው በብዙ መንገዶች ተሸልመውበታል፡፡ከነዚህ ማሳያዎች መሃል አንዱ
ትእምርታዊ በሆነ መልኩ ካባቸውን በቤተመንግስት ውስጥ እንዲለብሱ መፍቀድ ሲሆን ሌሎች ግን
ካባቸውን አውልቀውት ሸማ ነበር የሚለብሱት፡፡ከ1909 ጀምሮ በንጉሱ የዙፋን ችሎት ፊትም
ከአንድ እስከ ሶስት ሰአት ድረስ ሁልጊዜ ማለዳ የሚቀርቡትን ጉዳዮች ሁለቱም (ንጉሱና
እራሳቸው) ከሃገር እስከ ሸሹበት ጊዜ ድረስ ሳያበላልጡ እንዲያሰናዱ ፈቅደውላቸዋል፡፡ይህም

44
ጥቋቁር አናብስት

የሆነው ከአድልዎ በጸዳው ባህርያቸው የተነሳ ነው፡፡ ሁልጊዜ ጠዋት ጉዳያቸውን ለንጉስ
እንዲያቀርቡላቸው አቤት በሚሉ ባለጉዳዮች የቤታቸው በረንዳ ይጨናነቃል፡፡

በትህትና ተቀብለው የሚያናግሩ ቢሆንም ሰው የሚያዙትን እንዲሰማና የተባለውን በፍጥነት


እንዲያደርግ ይፈልጋሉ፡፡ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ባልተለመደ መልኩ ቀጠሮ
የሚያከብሩ ሲሆን ሌላኛው ወገንም እንዲያከብር ይፈልጋሉ፡፡በዚህ ረገድ የማይዋዥቅ አቋም
እንዳላቸው ቢታመንም በብዙዎች ዘንድ ግን የሚታወሰው ቸርነታቸውና የነበራቸውን ስልጣን
ለዘመድ አዝማድ ለመጥቀም ባለማዋላቸው ነበር፡፡ይህም ሌላው የባለስልጣን ኢትዮጵያውያን
መገለጫ ነበር፡፡ከመንግስት መሬት ቢጠይቁም( የህግ ክርክር በመሬቱ ዙርያ ነበራቸው) እጅ መንሻ
አይቀበሉም፡፡ደግ ይቅር ባይና በቀልን የማያውቁ ነበሩ፡፡በአንድ ወቅት አለመሥላሴ ሃብተሚካኤል
የተባለ ሰው እሳቸውንና ንጉሱን የሚዘልፍ ግጥም ከጻፈ በኋላ በነጻ እንዲለቀቅ አድርገውታል፡፡
(ተፈሪ ንጉሱና ኅሩይ ጳጳሱ ሃይማኖታችንን አጠፏት የምትል፡፡)53

ኅሩይ ሲበዛ ዝምተኛና ገለል ያሉ ነበሩ፡፡ወደ ድግስ ቦታዎች አይሄዱም፡፡ግን ጥሩ ቀልደኛ የሚባሉ
ዐይነት ሰው ሲሆኑ ቀልድ ማውራትና የመልስ ምት መስማት የሚያስደስታቸው ሰው ነበሩ፡፡
54
በጊዜው አብዛኛው ሰው እንደሚያደርገው ሰው ሲከተላቸው ወይም ሲያጅባቸው አይወዱም ፡፡
በእርግጥ ግን ኦፊሴላዊ ከሆነ ወይም የልዑክ ቡድን ከሆኑ ወዘተ ይስማማሉ፡፡

ዋና አትኩሮታቸው እውቀት፤ትምህርት፤ጥናቶች ፤ትምህርት ቤትና ተማሪዎች ነበር፡፡ገንዘብ ያን


ያህል የሚወዱም አይመስሉም ፡፡በጣም ሃብታምም ሆነው አያውቁም ፡፡ምንም እንኳን ደህና ቤትና
የተወሰኑ ንብረቶች ቢኖሯቸውም እነዚህን ንብረቶች በዛን ጊዜ ለማፍራት ያን ያህል የሚከብዱ
ዐይነት አልነበሩም፡፡ልጆቻቸው ከሳቸው የወረሱት አንድ ጋሻ መሬትና የየግላቸውን መኖርያ ቤት
ብቻ ነበር፡፡ወደ ስደት ሲሄዱ ምንም ውድ ጌጥ ይዘው አልሄዱም ምንአልባት ላይኖራቸው ሁሉ
ይችላል፡፡ስለሰዎች ማወቅ ቢፈልጉም ስለራሳቸው ግን የሚናገሩት ውስን ነበር፡፡ስለ ቤተሰባዊ
ዳራቸው ግን በፍጹም አይናገሩም፡፡ለዚህም ይሆናል ለረጅም ጊዜ በመነሾዋቸው ላይ ክርክር
የሚነሳው፡፡ኅሩይ በተክለ ሰውነታቸው አነስ ይላሉ፡፡ምንአልባትም ከኃይለሥላሴ ብዙም አይለዩም
(ብቻ ንጉሱ ከፍ ያለ ጫማ ስለሚጫሙ ረዘም ያሉ መስለው ይታያሉ)55አፋቸውም ጠበብ ያለ
ነበር፡፡ በመጠጥና በሴቶች ጉዳይ ከሳቸው በላይ ጠንቃቃ ናቸው የሚባሉት ንጉሱ ነበሩ፡፡ 56የጤና
እክል የነበረባቸው ሲሆን ምንአልባትም የጨጓራ አልሰር ይሆናል፡፡ወደ ስዊድናዊው ሚስዮናዊ
ካርል ሴደርቪስትና መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን በዚሁ የጤና ጉዳይ ለአመታት ተመላልሰዋል፡፡57
ሁለቱ የሚቀራረቡም ይመስላል፡፡በአንድ ወቅት ኅሩይ ወደ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስትያን ቅጥር
መጥተው ሴደርቪስትን ጉድጓድ ሲቆፍር ያገኙበት ቀን እንደ ታሪክ ይነገራል፡፡ ቀኑን ሙሉ አብረው
ቆይተው በምሳ የእረፍት ጊዜም ምሳቸውን አስቋጥረው ወደ ጉድጓዱ እያስወረዱላቸው

45
ጥቋቁር አናብስት

አብረዋቸው ውለዋል፡፡በዚህ ቀን ሲጨዋወቱ የዋሉት ሴደርክቪስት ጉድጓድ ውስጥ እንዳሉ ነበር፡፡


ጉድጓዱ ተቆፍሮ ካለቀ በኋላ ሴደርቪስት “ክርስቶስ እስኪመለስ በዚህ ጉድጓድ ውስጥ ውሃ
ይኖራል ” አሏቸው፡፡ሴደርቪስት በ1919 ሞተው ብዙ ከቆዩ በኋላ ኅሩይ ወደ እዚህ ግቢ እየሄዱ
በግቢው ውስጥ የሚኖሩትን ኗሪዎች ይጎበኟቸው ነበር፡፡በመጀመርያም ከጉድጓዱ አጠገብ ቆም
ብለው እጆቻቸውን ለጸሎት በሚመስል ሁኔታ አጣምረው ቁልቁል ወደ ጉድጓዱ እየተመለከቱ
ረጅም ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡ምናልባትም ጓደኛቸውን ለማስታወስ ይመስላል፡፡ስዊድኖቹ ኅሩይን እንደ
ራሳቸው ነበር የሚያዩዋቸው ለችግርም እሳቸው ጋር ነበር የሚሄዱት፡፡

እንግሊዘኛን ያን ያህል ያቀላጥፋሉ ባይባልም ጥሩ ይረዳሉ፡፡አንዳንዶች“እንግሊዘኛ ይናገራሉ”


ይላሉ፡፡በአንድ ወቅት አንድ እንግሊዛዊ “ክቡርነትዎ”ብሎ ሲጠራቸው በእንግሊዘኛ ከንጉሳውያን
ወገን እንዳልተወለዱና በዚህ አግባብ መጠራት እነደሌለባቸው ነግረውታል፡፡በመጽሐፍ ቅዱስ
አስተምህሮት መሰረት መኖር ሲሆን የሚፈልጉት ወደ ቤተክርስትያንም ሰርክ ያቀኑ ነበር፡፡

ሚስታቸውም እንደሳቸው በተክለ ሰውነት አነስ ያሉ ነበሩ፡፡ዝምተኛና የቤት ውስጥ ስራዎችን


ለመከወን ሲባትሉ ይውላሉ፡፡ልጆቻቸውገነት፤አጸደ፤አምሳለናላቀች ሲሆኑወንዶቹ ደግሞ ፍቃደ
ሥላሴና ሲራክ ናቸው፡፡የሴት ልጃቸው አጸደ ልጅ ሀይሉ እሳቸው ጋር ያደገ ሲሆን አብሯቸው ነበር
ወደ ስደት የሄደው፡፡በአባቱ አስፋው ገብረ ዮሃንስ በመጠራት ፋንታ በዚህ ምክንያት ሃይሉ ኅሩይ
ተባለ፡፡የፍቃደ ሥላሴም ልጅ አለምሰገድ ኅሩይ ብላ እራሷን ትጠራ ነበር፡፡

ኅሩይ ቀጥ ብለው ነበር የሚሄዱት እቃ ቢወድቅባቸው እንኳን ጎንበስ ብለው ማንሳት አይችሉም፡፡
የጀርባ ችግር ሳይኖርባቸው አይቀርም፡፡ሁሌም በደንብ የሚለብሱ ሲሆን የሃገር ባህል ልብስ ነበር
የሚለብሱት፡፡(ሻውል ቶጋ እጀጠባብ ከላይ ካባ)ወደ ውጪ አገር ሲሄዱ ግን የአውሮጳውያንን
አልባሳትን ይለብሳሉ፡፡ንግግራቸው ግልጽ የማይጮሁ ነገር አዋቂ ሲሆኑ ለብዙዎች መልካም
እርዳታ አድርገው ስራ አስገብተዋቸዋል፡፡ በምላሹም ምንም ነገር አይጠብቁም፡፡መጽሐፍቶቻቸው
የወጡበትን ጊዜ የሚያስታውሱ ሰዎች መጻሕፍቱ በጥሩ ሁኔታ እንደተሸጡ ይናገራሉ፡፡የኅሩይ
ማህተም በግራና ቀኝ የንብ ምስል አለው፡፡መፈክሩም "መልአክ ያልሆነ" የሚል ሲሆን እንደ
መልአክ ባይኮንም እንደ ንብ በታታሪነት መስራት እንዳለበት ለማጠየቅ ነው ይላሉ ልጃቸው ብላታ
ሲራክ፡፡

ጣልያኖች በወራራው ወቅት በአዲስ አበባ ውስጥ ለወረሷቸው ንብረቶች ካሳ ከፍለው ነበር፡፡አንድ
ኢጣልያዊ በአስመራ ለጋዜጣ እንደተናገረውና እውነት እንደሚመስለውም መኳንንቶቹ ሁሉ
“ከንጉሱ ከንግስቲቱና ከራስ እምሩ ውጪ” ካሳ ተቀብለው ነበር፡፡ይህ ቢሆንም የካቶሊክ ቤተ
ክርስትያን የበላይ ሃላፊን ሞንሲኞር ካስቴሌኒን እስካገኙበት ድረስ የኅሩይ ባለቤት ወይዘሮ ሐመረ

46
ጥቋቁር አናብስት

ምንም ያገኙት ነገር አልነበረም(ኅሩይ በወረራው ወቅት ነበር የሞቱት) ፡፡እናም በየወሩ የተወሰነ
ሊሬ እንዲያገኙ አደረጉ፡፡በስደት ወቅት ኅሩይ ኀይለሥላሴ ስለ ኢትዮጵያ እንዲናገሩ እስከ
እለተሞታቸው ድረስ ይገፋፉ ነበር፡፡ነገር ግን የስደትን ስራ አስፈቺነት አድካሚ ሆኖ ሳያገኙት
አልቀሩም፡፡በሎንዶን የኦርየንታል ጥናት (አሁን የኦርየንታልና አፍሪቃዊ ጥናት ትምህርት
ቤት)አማርኛና ግእዝን ማስተማር ጀመሩ፡፡ኅሩይ በሎንዶን በሚኖሩበት ወቅት ኀይለሥላሴ
በፌርፊልድ ባዝ በመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡58

ኅሩይ በጣልያን ኢትዮጵያን መውረር አእምሯቸው ተጎድቶ ነበር፡፡በተለይ በሃገሪቱን መጻኤ እድልና
የነጻነት አለመታወጅ ሲብሰከሰኩ በስተመጨረሻ ታመሙ፡፡ኀይለሥላሴ በመንግስት ቤቱ ግቢ
ውስጥ ክፍል ተሰጥቷቸው እንዲኖሩ ወደ ባዝ ጠሯቸው፡፡ጤናቸው መጓደል ጀመረ፡፡
በመጨረሻም መንቀሳቀስ አቅቷቸው በባለጎማ ተሸከርካሪ ወንበር ነበር የሚሄዱት፡፡
እንደጠበቁትም በጣልያንና ጀርመን ሽንፈት ለኢትዮጵያ የነጻነት ተስፋ ፈንጣቂ ሊሆን ስለሚችል
በማለት ሁለቱ ሃገራ በፈረሙት ስምምነት ተደስተው ነበር፡፡የጤናቸው ጉዳይ ግን ባሰበት፡፡
በመስከረም 9 በ60ኛ አመታቸው በ1931 ዓ.ም አረፉ፡፡ልጃቸው ሲራክና አባ ገብረሃና ጂማ
ምናልባትም ሌሎች ጥቂቶች በመሞቻቸው ሰአት ከጎናቸው ነበሩ፡፡

አጼ ኀይለሥላሴ በሉክዘምበርግ ቀብራቸው ላይ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ከነጻነት በኋላ አጽመ


ቅሪታቸው ለሃገራቸው አፈር በቅቷል፡፡ በጢያራ ተጓጉዞ 4 ሰአት አካባቢ ደርሶ መስከረም 11 ቀን
በ1940 አ.ም በከፍተኛ ክብር ተቀብሯል፡፡የዚህም ጊዜ ኀይለሥላሴና ተጠባባቂ ጠቅላይ
ሚንስትሩ ራስ አበበ አረጋይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በህይወታቸው ሶስት የኢትዮጵያ የክብር ሽልማቶችን አግኝተዋል እንዲሁም፤በእንግሊዝ፡ ፈረንሳይ፤


ቤልጅየም፤ጣልያን፤ቫቲካን፡ስዊድን፤ግሪክ፤አውስትራሊያ(ምንጮቼ ከኦስትሪያ ጋር ካላምታቱት
በስተቀር)፤እየሩሳሌም፡እና በግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ የክብር ሜዳይ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት(ወመዘክር) ውስጥ አንድ ክፍል የተሰየመላቸው ሲሆን
ጉለሌ በሚገኘው ቤታቸው የሚያቋርጠው መንገድም በስማቸው የተሰየመ ነው፡፡

ከመሞታቸው ጥቂት ቀናት በፊት ኅሩይ ልጃቸውን ሲራክ ስነጽሁፋዊ ስራዎቻቸውን ወይም
ቅርሶቻቸውን እንዲንከባከብ አደራ ብለውት ነበር፡፡ኀይለሥላሴ “ካገዷቸው” መጻሕፍት በስተቀር
አሁንም በመደበኛ መጻህፍት መደብሮ መጻህፍቶቻቸውን ማግኘት ቢከብድም በአዲስ አበባ
መንገዶች ላይ መጽሐፍቶቻቸው ይሸጣሉ፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብላቴንጌታ ኅሩይ በሚለው
ስማቸው የሚያውቃቸው ሲሆን ተወዳጅም ነበሩ፡፡

47
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻ

1 የኅሩይ ሴት ልጅ አፀደ ማርያም ልጅ ና የአስፋው ገብረ ዮሃንስ ልጅ ነው፡፡

2 ምሳሌ 1 ታዋቂው የስነ-ሰብ ምሁር ሲ.ኩን በአንድ ወቅት የኅሩይን የራስ ቅል መጠን ለመለካት
ሞክሮ ነበር፡፡ኅሩይ ግን በሳቸው ምትክ አንዱ ሰራተኛቸውን ላኩ፡፡(2)አንድ ዘመዳቸው ጠንካራ
መጠጥ (ውስኪ)ይወዱ ነበር ብለዋል፡፡ ይህ አባባል ግን በቅርበት በሚያውቋቸው ሰዎች ተቃውሞ
ገጥሞታል፡፡ (3)በቤተሰቦቻቸው ዘንድና በሚተዋወቋቸው መሃል ስጠይቅ ወጣት ሴቶችን የሚወዱ
መሆኑንና ብዙ እቁባቶች በከተማው ውስጥ እንዳሏቸው ነግረውኛል፡፡ከህጋዊ ጋብቻ ውጭ ግን
የተወለዱ የታወቁ ልጆች የሉም፡፡(4)ብዙዎች ትምህርት ይገልጻል ብለው የሚያስቡትን አብሾ
እንደጠጡ ያምናሉ

3ብላታ ከብላቴን ጌታ አነስ ያለ ለምሁራንና ለንጉሱ ውለታ ለዋሉ የሚሰጥ ሹመት ነው

4ዋነኛ የአምሃራ አካባቢ ከሚባሉት አንዱ ነው

5በህግ ሲሆን ያገቧት ይህ ማለት ከዚያ በኋላ ትዳርን መፍታት አይቻልም፡፡በህይወት ያለ ቀሪ


የትዳር አጋርም ማግባት አይችልም

6 ከሸዋ መርሃቤቴ ነች

7ሴቶች በአንዳንድ ገዳማት አለቃ መሆን ይችላሉ፡፡ወንዶች ብቻ ይሁን የሚለው ለሌሎች ገዳማት
ነው የሚሰራው በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ መነኮሳት ይሾማሉ አለቃ ለብዙ አግባቦች የሚያገለግል
ቢሆንምትክክለኛው ስራቸው ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡

(ምናልባት እመምኔት ለማለት ይሆናል)

8በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የቤተክህነት ትምህርት የመጀመርያ የተለመደ ጊዜ ነው፡፡በከተማና በዋና


አድባራት አካባቢ ግን ቀደም ብሎ (ምንአልባት ከ5 አመት እድሜያቸው ጀምሮ)ይጀምራሉ

9ጽህፈት በተለይ የቁም ጽህፈት በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ የሚሰጥ የተለየ ጥበብ ነው፡፡
መጻፍና ማንበብ አብረው አይሰጡም፡፡ አብዛኞቹ ማንበብ የተማሩ ሰዎችም መጻፍ አልተማሩም

48
ጥቋቁር አናብስት

10የኅሩይ አባት በሳቸው ስልጣን ደረጃ ሆነው ማንበብ ስለማይችሉ ተሰድበው ያውቃሉ፡፡በአንድ
ወቅት ኅሩይ አባታቸው እንዲህ ባለ ሁኔታ ሲሰደቡ ሰምተው ነበር፡፡የዚህ ትዝታ ደግሞ
በአእምሯቸው ተቀርጾ ቀርቷል፡፡(ምንም እንኳን ሰዳቢውን በኋለኛ ዘመኑ አግኝተው ይቅር
ቢሉትም)ይህ ሁኔታ አባትየው እሳቸው እንዲማሩ የመፈለጋቸውን ቁርጠኝነት ሳይወልድ
አልቀረም፡፡

11የአምናውን አዝመራ ቃርሚያ ወስደው ነበር፡፡

12 ሰው እንዳይከለክላቸው በለሊት ነበር የወጡ

13 የእጅ ጽሁፋቸው በተለመደው መልኩ በትምህርት ቤት አስተምህሮት ተምረው እንዳላዳበሩት


ያስታውቃል፡፡

14 በጊዜው ከኀይለኞች ሴቶች መካከል አንዷ ስትሆን በአቤቶ እያሱ የስልጣን ሽሚያ ዙርያ
የራስዋን ሚና ተጫውታለች

15እ.ኤ.አ ከ1888 እስከ 1892 ድረስ በአካባቢው የተዛመተ ድርቅ ነበር፡፡አንበጦችና አረም
ኢትዮጵያና አካባቢውን አጠቁ፡፡የሪቻርድ ፓንክረስትና የዲ.ኤች ጆህንሰን "the great
drought and famine of 1888-1892 ገጽ 44-70 ጆህንሶን እና ዲ.አንደርሰን the
ecology of survival case studies from northeast African history London
1988 ኢትዮጵያውያን ይህንን ጊዜ "ክፉ ቀን " ሲሉ ይጠሩታል፡፡የ ጎጃሙ አለቃ ተክለኢየሱስ
የኢትዮጵያ ያልታተመ ታሪክ፡፡

16ኅሩይ ሰርክ ስለዚህ ጉዳይ ያመሰግኑ ነበር፡፡በኋላ ለበሻህ ልጆች ጊዜው ሲከብድባቸው መሬት
ገዝተውላቸውም ነበር፡፡

17ራስ ከንጉስ ቀጥሎ ያለ ታላቅ መአረግ ነው፡፡ራስ መኮንን የአጤ ምኒሊክ ጠንካራ ደጋፊና
የሃረርጌ ገዢ ነበሩ፡፡

18ይሄ በቤተክህነት ምሁራን መሃል የእጅ ጽሁፍ ችሎታ ምን ያህል ከባድ እንደነበር ያሳያል፡፡

49
ጥቋቁር አናብስት

19ይህ ያልተለመደ ነበር፡፡ኅሩይ በድቁና ተመርቀው ነበር፡፡ስላላገቡ ግን በሙሉ ድቁና ማገልገል


አይችሉም፡፡እስካላገቡ ድረስ ዲያቆናት በለጋ እድሜያቸው ብቻ ነው ማገልገል የሚችሉት፡፡ከአስራ
አምስት አመት በታች ሆነው፡፡ወይንም እድሜያቸው በደንብ ከገፋ በኋላ ከወሲብ ፍላጎት በፊትና
በኋላ ማለት ነው፡፡

20ጎንደር ተምረው የቅኔና አንደምታ መምህር ሆነዋል፡፡

21 በጊዜው ይህ የኢትዮጵያውያን ዐይነተኛ መገለጫ ነው

22በቅዱስ ራጉኤል ያሉ ቀሳውስት ከቤተክርስትያኒቱ አቅራቢያ ቤቱ የነበረበትን ቦታ ያሳያሉ እንጂ


በአሁን ወቅት የለም፡፡

23 ብር በወቅቱ አባባል የማርያ ቴሬዛ ዶላር ማለት ነው፡፡በወቅቱ እንደ መገበያያ የሚጠቅም
ሲሆን ጥሩ የመግዣ አቅም ነበረው፡፡

24 የኅሩይ የረዥም ጊዜ ባለሟል ኅሩይ ”አስማት“ ይሰሩ እንደነበር ይናገራል፡፡ አብዛኞቹ


የቤተክህነት ቀሳውስት በዛም አነሰ ይሰሩት ነበር በወቅቱ፡፡ለማንኛውም የምእራቡን አስተሳሰብ
መከተል ከጀመሩ በኋላ ትተውታል፡፡

25የዳግማዊ ሚንሊክ ዜና መዋእል ጸኃፊ የነበሩ

26ለተለያዩ ሰዎች በጸሃፊነት በመስራት ተጨማሪ ደመወዝ ያገኙ ነበር፡፡

27ትርጓሜዎቹ ከመምህር ወደ መምህር እየተወራረዱ የሚሄዱ ነበሩ፡፡

28ኅሩይ በቁመት በጣም አጭር ከንጉሱ ሁሉ ያነሱ ነበሩ፡፡

29እንደ ኅሩይ ቤተሰቦች አነጋገር ከሆነ ከዚህች ላም የሚወለዱ ዝርያዎች ይህ መጽሐፍ እስከ
ተጻፈበት ጊዜ ድረስ ነበሩ፡፡

30 ኅሩይ መጀመርያ እንጦጦ ልምጣ ብለው ከጠየቋቸው ቤትም ከተጋሯቸው አቶ ማህደሩ


የምትወለድ ነች፡፡ጥሩ ጓደኛማማቾች ናቸው፡፡

31ቤተሰቦቿና ኅሩይ ለጥቂት ጊዜያት ይገናኙ ነበር፡፡


50
ጥቋቁር አናብስት

32 በምንጮቼ የተሰጠኝ መረጃ ይኸው ነው፡፡ይሄ ግን ለብዙዎቹ አስገራሚ ነው፡፡አብዛኛው


ክርስትያን በወርሃ ግንቦት አይጋባም፡፡ኅሩይ ግን ይሄን ምልኪ አይጋሩም ይሆናል፡፡

33እንደአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ልማድ ሁሉ በሁለት ስም ነበር የምትጠራው፡፡እሷንና ቤተሰቡን


የሚያስታውሱ ሁሉ ልጆቹ ”እምወድሽ“ ብለው ይጠሯት እንደነበር ይናገራሉ፡፡

34 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣት ሴቶች በተቀረው አለም የወጣት እድሜ ግንዛቤ መሰረት ያሉ
አይደሉም፡፡እሳቸውም የጋብቻ የእድሜ ጠለሉ አስር አመት እንዲሆን በኋለኛ እድሜያቸው
ታግለዋል፡፡ከዛ ቀደም በሳባትና በስምንት አመታቸው ሴቶችን ለጋብቻ ማጨት የተለመደ ነበር፡፡

35 አንድ ምንጭ እንደነገረኝ ከሆነይህ የቤተክርስትያኒቱ ኦፊሴላዊ አቋም አይደለም፡፡ ነገር ግን


ይህ የተስፋፋው ወሲባዊ አስተምህሮቶች ባለፉት አራትና አምስት ክፍለ ዘመናት ልቅ እየሆኑ
ከመምጣታቸው አኳያ ነው፡፡ከ16ኛው ክ.ዘ የግራኝና የኦሮሞ ወረራ በኋላ የክርስትና እምነት
ተከታይ ኢትዮጵያውያን ሲሸነፉ፡አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደ ሙስሊሞቹ ከአንድ በላይ
ሚስት በማግባት ወረራውን መቋቋም አለብን በማለት ሃሳብ አቀረቡ፡፡ምንም እንኳን ይህ
መከራከርያ በቤተክርስትያኗ ተቀባይነትን ባያገኝም፡፡አብዛኞቹ ከአንድ በላይ ሚስት ወይም
እቁባትን መያዝ ጀመሩ፡፡ በዘመነ መሳፍንትና በዳግማዊ ሚኒልክ ጊዜ እየባሰበት መጣ፡፡"ምንሊክ
ብዙም አጥባቂ ሃይማኖተኛ ስላልነበሩ" ሁኔታው እየተስፋፋ መጣ፡፡ቀጥሎ አዲስ በተገኘው
ነጻነትና በወረራው ወቅት እሰስካሁንም በቆየ ሁኔታ ከተሜው ወደ አመንዝራነት ጉዞውን
ተያያዘው፡፡

36 ጸመኔ ዳርጌ የታላቂቱ ልጅ የክርስትና እናት ነበሩ፡፡

37 ፍቃደ ሥላሴ “ጆርጅ”በሚለውም ስም ይጠራል፡፡የኋላ ኋላ በአሌክሳንድርያ ተምሮ ወደ


ካምብሪጅ አቅንቷል፡፡ሲራክ ደግሞ ከአሌክሳንድርያ ወደ ኦክስፎርድ ሄዷል፡፡ፍቃደ ሥላሴ ከዋነኛ
ስራው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ ነበር፡፡በጣልያን ወረራ
ወቅት የነጻነት ታጋይና የጥቋቁር አናብስት ማህበር ተባባሪ መስራች ነበር፡፡በየካቲት 12ቱ
ጭፍጨፋ የተገደለ ሲሆን፡፡የትሰሜ ዳርጌ ልጅ የእንጀራ አባቱ ነበር፡፡

38 እ.ኤ.አ በ1988 በህይወት የቀረው ልጃቸው አንድ ብቻ ነበር፡፡ታሪካቸውን ለማጥናት


በሞከርኩበት ወቅት የነበረችው ላቀች ብቻ ነበረች፡፡ህመምተኛና ከአልጋ የዋለች ነበረች ሲል
ከሚያውቋትና መሃልና እሷ ጋር ይዞኝ የሄደው ሰው ነግሮኛል፡፡በዚህ መጽሐፍ ማስታወሻ

51
ጥቋቁር አናብስት

ልጽፍላቸው ከምችላቸው ሁለት ሴቶች አንዷ ነበረች፡፡ነገር ግን የሚያስተማምን መረጃ ላገኝ


አልቻልኩም፡፡ላቀች በወጣትነቷ በብእር ስም ለወጣቶች ምክር አዘል ትንሽ መጽሐፍ ጽፋ ነበር፡፡

39 ስዊድኖቹ ሉተራን ፕሮቴስታንቶች ነበሩ፡፡ በጊዜው ግን በካቶሊኮችና በፕሮቴስታንቶች መሃል


ልዩነት አይደረግም ነበር፡፡

40 አቡን የኢትዮጵያ ቤተክህነት ታላቁ ሹመት ነበር፡፡እስከ 1951 አ.ም ድረስ ከእስክንድርያ
እናት ቤተ ክርስትያን ነበር የሚሾመው፡፡ከዚያ ወዲህ ግን ቤተክርስትያኒቷ እራስዋ ነች
የምትሾመው

41 አፈ ንጉስ የዙፋን አዋጅ ለፋፊ

42 የተወሰኑ ሰዎች እንደ አንዳንድ ሪፖርቶች ደግሞ 3 ወይንም 4 ሰዎች ሞተዋል፡፡

43 ትክክለኛው መጠርያቸው አቤቶ እያሱ የሚለው ሲሆን ከስልጣን በኋላና በፊት ግን ልጅ


በሚለው ይጠራሉ፡፤

44 ኢትዮጵያ የመጀመርያ አውሮፕላኗን በነሃሴ 2 1921 ዓ.ም በእጇ አስገባች፡፡በወቅቱ ግን


አስፈሪ ታሪኮች ተሰራጭተውበት ነበር፡፡

45 ኅሩይን የሚያስታውሱ ሰዎች «ቤታቸው ሁልጊዜም በካህናት ቀሳውስቶች የተሞላ ነበር»ይላሉ


ስለዚህ ክሱ መሰረተ ቢስ ነበር ማለት ነው፡፡እንደውም መጽሀፎቻቸው የተጻፉት በነዚህ ቀሳውስት
የታተሙት ግን በስማቸው ነበር የሚል ጭምጭምታ አለ፡፡ከኦርቶዶክስ አስተምህሮ ትንሽ ፈንገጥ
ያለው በአንዱ መጽሐፋቸው የተገለጸው ነገር ነው ፡፡እሱም ተኮናኞች ለዘለአለም አይጣሉም
ቅጣታቸውን ጨርሰው በመጨረሻ ይማራሉ የሚል ሲሆን ፡፡ምንም እንኳን በኦፊሴል
ባያስተምሩትም፡፡በኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት በብዛት የሚታመንበት ነው፡፡

46የጽሁፍ ማስረጃ በወር 200 ብር ቢልም ይህ ግን የተሳሳተ ሳይሆን አይቀርም፡፡በ1907


የመዘጋጃ ቤቱ ሃላፊ ሲሆኑ ወርሃዊ 50 ብር ደመወዝ ነበራቸው፡፡በ1920 የውጪ ጉዳይ
ዳይሬክተር ሲሆኑ ደሞዛቸው 300 ብር ሆነ፡፡

47ይህ በኋላ የፓስተር ኢንስትትዩት ቆይቶ ደግሞ የብሄራዊ ጤና ምርምር ተቋም ሆኗል፡፡

52
ጥቋቁር አናብስት

48አንዳንዶች የጣልያን ባሊላ ነው ሲሉ አንዳንዶች በጊዜው የጣልያን ባሊላ የለም በማለት


የፈረንሳይ ሲትሮይን ነው ይላሉ፡፡

49ቆይቶ ሁሉም ሚንስትሮች ባለመኪና ሆኑ፡፡ከዚያ በፊት ባለመኪና ከነበሩት መሃል ራስ ሃይሉና
የተወሰኑ አርመኖች ይገኙበታል፡፡አብዛኞቹ መኪናዎች የጣልያን ስሪት ነበሩ፡፡እናም በአብዛኛው
በታክሲነት ከባቡር ጣብያ በማመላስ ይሰሩ ነበር፡፡

50 በሳቸው የልኡካን ቡድን ውስጥ ከነበሩት ሌሎች በተጨማሪ ዳባ ብሩና አርአያ አበበ
ነበሩበት፡፡

51ኅሩይ ስለዚህ ጉዞ የ192 ገጽ መጽሐፍ ጽፈው በ1924 አ.ም ታትሟል፡፡

52 በኢትዮጵያ በግልና በጋራ መሃል ያለው መስመር ቀጭን ነው፡፡እሱም በብዙ ሁናቴ ውስጥ
ከተገኘ ነው፡፡ውለታ በብዙ ግንኙነቶች መሃል ጠቃሚ ነው፡፡

53ይሄ ጉዳይ በአንዳንዶች ከሚባለው በላይ ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡ ስለ ወንጀለኛው መረጃ
አቅራቢ እና የተወሰኑ ሰዎች በጽሁፉ ውስጥ እንደጠቀሱት ከሆነ አቶ አለመ ሥላሴ ሃብተ መስቀል
የጉምሩክ ተቀጣሪ ነበሩ፡፡እሳቸው አንድ ስሙ አቶ ሃዲስ የሚባል ግለሰብ እና ሌላ አንድ ሰው
ተፈሪ እነሱ ወደ ሚሰሩበት ከመጡ ለመግደል ተስማምተው ነበር፡፡አቶ ሃዲስ በኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ነበር የሚሰሩት፡፡ሶስተኛው ሰው የተፈራረሙበትን ሰነድ ለተፈሪ አሳያቸው ፡፡ ሌሎቹ ሁለቱ
በቁጥጥር ስር ውለው እንዲገረፉ ተፈረደባቸው፡፡ነገር ግን አቡነ ማቴዎስ ጣልቃ ገብተው ቅጣቱ
ወደ እስራት ተለወጠ፡፡ሌሎች ሁለት ሰዎች አንዱ አጋፋሪ በቀለ አቦዬ የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክን
የጻፉትና (ያልታተመ ሲሆን በዙፋን ቤተመዝገብ የነበረ ሲሆን የተሰረቀም ሊሆን ይችላል)
ቀኛዝማች ድፋባቸው የአቡነ ማቴዎስ ዳኛ በሴራው እንዲሳተፉ ተጠይቀው ፍቃደኛ የነበሩ ሲሆን
በጉዳዩ ተስማምተው የደገፉ ቢሆንም አንፈርምም ብለዋል፡፡ጉዳዩን ባጋለጠው ሰው ስማቸው ሲነሳ
ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረው ካዱ፡፡ተፈሪም ነገሩን አለፉት፡፡አለመ ሥላሴ በሰላ ድንጋይ
ሲታሰር ሃዲስ ደግሞ ሙሎ ሰላሌ ውስጥ ታሰሩ፡፡ቆይቶ ሁለቱም ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡አለመ
ሥላሴ ሚስቱ የግብጽ ዝርያ ስላለባትና ከአቡነ ማቴዎስ ጋር ስለሚዛመዱም እሳቸው ቤት
በሰራተኞች አዛዥነት ቆይቶ ንጉሱ ከስደት ተመልሰው ጎጃም ላይ ሲደርሱ ህይወቱ አልፏል፡፡ሃዲስ
ግን ብዙ ቆይተው እ.ኤ.አ በ1960 አካባቢ ህይወታቸው አልፏል፡፡

54የኢትዮጵያ አዝናኝ ታሪኮች ባለ ሁለት አጽቅ ምላሾችን ያካተቱ ናቸው፡፡ይህ የሃበሻ ቋንቋ
ተወዳጅ አጠቃቀም ነው፡፡

53
ጥቋቁር አናብስት

55ኀይለሥላሴ የሰዎችን አይን ለማየት ቀና ማለት አይወዱም

56ኀይለሥላሴ በልጅነታቸው ታላቅ ጉጉት እንደነበራቸው ይነገራል፡፡መሳሳትን ይፈሩ ነበር፡፡


ስለዚህ እራሳቸውን አርቀው ስማቸውን ጠብቀው መቆየት ነበረባቸው፡፡

57ሴደርክቪስት የተወሰኑ የህክምና ስልጠናዎች ያገኘ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥም በዶክተርነት


አገልግሏል፡፡

58 አንድ የቅርጻ ቅርጽ ሻጭ እኚህ ትንሽ ሰው ሱቁን እንደሚጎበኙና ለማስቀነስም ይከራከሩ


እንደነበር ይናገራል፡፡

54
ጥቋቁር አናብስት

አቤ ጎበኛ
ብቸኛው የሙሉጊዜ ደራሲ/እንጀራውን በመጻሕፍቱ
የጋገረብቸኛው ኢትዮጵያዊ ደራሲከብዙ ዓመታት በፊት በአማርኛ
ሥነጽሑፍ ላይ ፍላጐት ማሳደር ስጀምር ፣ብዙ ወጣት
ኢትዮጵያውያን "የአቤ ጉበኛን መጽሐፍት አንብበሀል?" እያሉ
ይጠይቁኝ ነበር።ወዲያውኑ አንዳንዶቹን ማንበብ ጀመርኩ፤ቀስ
በቀስ ሁሉንም አንብቤ ጨረስኩ።ነገር ግን የጠበቅኩትን ነገር
አላገኘሁም። ይሁን እንጂ መጪው ጊዜ ብሩህ እንደሚሆን፣እነሱም
ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ለሚጠብቁ ወጣት (በተለይ በፖለቲካ
ረገድ)እና ገና በመማር ላይ ላይ ያሉ ያልበሰሉ አንባቢዎች፣አቤ ለምን ማራኪ ሊሆን እንደቻለ
መረዳት አይከብድም፡አቤ በአንድ ታታሪ መሪ የሕይወት ዘመን ውስጥ ሐገሪቱ ከፍተኛ የእድገት
ማማ ላይ መውጣት እንደምትችል የሚያሳይ አስደሳች ምስል መቅረጽ ችሏል።ሁሉም ነገር
ቀላልነው፤ይሁን እንጂ መሰናክሎችን ሁሉ ችሎ ለማለፍ አንድን ሰው "ከባድ ስራ" ይጠይቀዋል።
ሐብት እና "ስልጣኔ" ሃገሪቱን ያጥለቀልቃታል፤ ባህል ያብባል።ይህ ሁላችንም መኖር
የምንፈልግበት የምኞት አለም ነው።ይህ ነበር አቤ ጉበኛ ለወጣቶች ቃል የገባላቸው ፍፁም አለም።

አቤን ስለሥነጽሑፍ ስራዎቹ ሳላነጋግረው በፊት በ1972 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።አቤ
ሁለገብ ነበር፤ልብወለድ፣ተውኔት፣ወግ፣አጭርልብወለድ፣ባህላዊ እና ዘመናዊ ሥነግጥም ይጽፍ
ነበር። ከመሞቱ ከአስር ዓመታት በፊት የኢትዮጵያውያንን የንባብ ልምድና ምርጫ በተመለከተ
በተደረገ ጥናት፣አቤ ቁጥር አንድ ተነባቢ ደራሲ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አቤ ጉበኛ የተወለደው በሰኔ 25ቀን 1925 ዓ.ም ወይም በሰኔ 19ቀን 1926 ዓ.ም (ከሁለት
የተለያዩ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሰረት) በጎጃም ክፍለሀገር፣በባህርዳር አውራጃ፣በአቸፈርወረዳ፣
ቆረንጭ (ቆረንጭ አቦ) በምትባል መንደር ነበር።ወላጆቹ ጉበኛ አምባዬ እና ይጋርዱ በላይ
ይባላሉ። “በጠራ” የአማራ ሀገር የተወለደውና ያደገው።1

አቤ ቅድሚያ ፊደል የቆጠረው በቄስ ትምህርት ቤት ሲሆን፣ በስድስት ዓመቱ ማንበብ ቻለ።ከዚያ
ወደ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ገብቶ፣በዚያ የሚሰጠውን ባህላዊ ትምህርት ተከታትሏል።
የቤተክርስቲያን ዜማ እና ወረብ እንዲሁም ቅኔ ተማረ።በተለይ ቅኔ አዋቂነቱ የተመሰከረለት ሲሆን
"ሊቅ" የሚል ማዕረግ አሰጥቶታል።በቤተክርስቲያን ውስጥ አባቶች "የልጆችን አእምሮ ለመክፈት"
፣ይበልጥ ብሩህ ለማድረግ፣ትምህርት እንዲቀበሉ እና ቅዱስ መጽሐፍትን በቃላቸው እንዲያውቁ፣
55
ጥቋቁር አናብስት

አብሾ የተባለ አንዳች መድሐኒት ያቀምሷቸው ነበር።በተለይ ደግሞ የአቤ አባት ልጃቸው የተሻለ
ተማሪ እንዲሆን ይህንኑ "መድሃኒት" እንደሰጡትይነገራል።ይህ ጉዳይ እውነትም ይሁን ውሸት፣አቤ
ጎበዝ ተማሪ እንደነበር ያስታውቃል።

የቤተክርስቲያኑን ትምህርት ከጨረሰ ከሦስት ዓመታትበኋላ፣ወደ ዳንግላ ሄዶ ቢትወደድ መንገሻ


ጀምበሬ ትምህርት ቤትገባ።ተማሪዎች ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ሲገቡ፣የቀድሞ የቤተክርስቲያን
ትምህርት ከምንም ሳይቆጠር፣ትምህርታቸውን ከ1ኛ ክፍል መጀመራቸው የተለመደ ነበር።አቤም
በዚሁ ትምህርት ቤት እስከ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ማብቂያ (8ተኛክፍል) ድረስ ተማረ።እዚህም
ጥሩ ውጤት ስላመጣ፣አዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለመከታተል እድል አገኘ።መደበኛ
ትምህርቱን 12ተኛ ክፍል ሲያጠናቅቅ ወደ ዩኒቨርስቲ ወይም ሌላ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም
መግባቱን ትቶ "ራሱን በራሱ አስተማረ"ብዙዎች እንደሚሉት አቤ "በሚገባ የተማረ" አልነበረም።

ከትምህርት ቤት ከወጣ በኋላ የመንግሥት ስራ አገኘ፤በቅድሚያበማስታወቂያ ሚኒስቴር


በጋዜጠኝነት፣ኋላም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር።በአጠቃላይ በመንግሥት ስራ ለስድስት ዓመት ከቆየ
በኋላ ዳግመኛ ላይመለስ ተሰናብቶ በጽሑፍ ስራው ብቻ ለመተዳደር ወሰነ።ይህ ከባድ ትግል ነበር፣
ምክንያቱም በኢትዮጵያ ለመንግሥት ጋዜጦች ከሚሰሩ ጋዜጠኞች በስተቀር በሥነጽሑፍ ስራ ብቻ
የሚተዳደር ማንም አልነበረም።ገበያው ሳቢ አይደለም፤መጽሐፍት በብዛት እንዲሸጡ ዋጋቸው ዝቅ
ማለት ነበረበት። አቤ ለብዙ ዓመታት በመጠኑ ቢሳካለትም በከባድ እዳ ውስጥተዘፍቆ ነበር።

አቤ ጉበኛ በመጽሐፍቶቹ "የሀሳባዊነት" አቀንቃኝ ሆኖ ብቅ አለ። ጭቆናን፣ ብዝበዛን፣ ጉቦኛነትን፣


ኋላቀርነትን፣ድንቁርናን እና ሌሎችንም በሐገሪቱ ያሉ የተበላሹ አሰራሮች ሁሉ ተቃዋሚ ሆነ።
በእንዲህ ዐይነት ጉዳዮች ዙሪያ ከሚያጠነጥኑት መጻሕፍቱ መካከል አንዱ በሆነው በአልወለድም
ጦስ፣ አቤ ለሶስት ዓመታት ታስሯል።“በዚህም ምክንያት ሳይሆን አይቀርም አቤ ከመጽሐፍቶቹ
ሁሉ አብልጦ ይህንን ይወደው ነበር” ትላለች የሶስት ልጆቹ እናት እና የተለያት ሚስቱ። ለፍትህ፣
ለእድገት እና ለመላው ኢትዮጵያውያን የተሻለ ሕይወት የታገለው አቤ ለሀሳቡና ህልሙ
ተሰቃይቷል።

አቤ መፃፉን “እንዲያቆም” ብዙ ጥረት ተደርጓል።ለምሳሌ መፃፉን እንዲተውና የደብረ ብርሃን


አውራጃ አስተዳዳሪ እንዲሆን ስልጣን ተሰጥቶት ነበር።ይህንን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆኑ እና
መፃፉን በመቀጠሉ፣እሱን ለመግታት ሌሎች ዘዴዎች ተሞከሩ።በአጠቃላይ አቤ በኢሊባቡር እና
አዲስአበባ እስር ቤቶች ውስጥ ለአምስት ዓመት ከግማሽ ቆይቷል።

56
ጥቋቁር አናብስት

አቤጉበኛበአማርኛ ከ20 በላይ መጽሐፍትን ሲጽፍ፣ ሌሎች ሁለት ደግሞ በእንግሊዝኛ አሳትሟል።
ብዙ ከፃፉ ኢትዮጵያዊ ደራሲያን መሐል አንዱ ነው።ሁለት ተውኔቶቹ በአዲስአበባ ለመድረክ
በቅተውለታል።አባቱ እንደሚሉት አቤ ትምህርት በጣም መውደዱ ብቻ ሳይሆን ገና ከለጋነቱ
ጀምሮ ብእርና ወረቀት ከእጁ እንደማይለይ ይናገራሉ።አቤ በጫካ ውስጥ ብቻውን መዘዋወር
መውደዱ ከልጅነቱ ጀምሮ "ህልመኛ"ሳይሆን እንዳልቀረ ያሳያል።ለድሆች ሀዘኔታ እንደሚሰማው
መግለጽ የጀመረው በለጋነቱ ነው፤በተለይ ውሀ ቀድተው ሩቅ መንገድ ለሚሸከሙና ሌላ ከባድ ስራ
ለሚሰሩ ሴቶች ያዝናል።በተጨማሪም በደንብ የሚያውቁት ሰዎች "ለሴቶች የተለ የፍቅር ነበረው"
ይላሉ።

አቤ ጉበኛ የሚያልመው አዲስ ህብረተሰብ፣ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ መሰል አልነበረውም፤


በመጽሐፍቱ የተገለፁት የለውጥ ሂደቶች በታሪክ ተሰምተው አይታወቁም። የ1966ቱ አብዮት
በኢትዮጵያ ሲፈነዳ፣ለውጥ ይመጣል በሚል ተስፋ ተሸንግሎ ነበር።ነገር ግን መጨረሻ ላይ
አቧራው ሲሰክንና፣ተጨባጭ ማሻሻያዎች እና ለውጦች መተግበር ሲጀምሩ፣አቤ ያልጠበቀው ነገር
በመከሰቱ ብስጭት ላይ ወደቀ።በመጀመሪያ አዲሱን አብዮታዊ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ሰዎችን
ያበረታታ ነበር።በጊዜው እሱ አሜሪካ ውስጥ የነበረ ቢሆንም፣ህዝቡ ግን አዲሶቹን መሪዎች
እንዲከተል ሳያቋርጥ እየጻፈ ይጎተጉት ነበር።ነገር ግን ቀስበቀስ ቅሬታው ስር ሲሰድ፣ጥልቅ ሐዘን
ስላደረበት መፃፉን አቆመ፤መጠጥ መጠጣትም ጀመረ።ከቀደምት መጽሐፍቶቹ ብዙም ትርፍ
ስላላገኘ እንደነገሩ የፃፋቸውን ሁለት ትንንሽ መጽሐፍት “በብድር” አሳተመ። በሕይወት ዘመኑ
ሁሉ ከፍሎ የማይጨርሰው እዳ ውስጥ ተዘፈቀ። ሲሞት የአታሚዎች ብዙ እዳ ነበረበት።

ሁለት መጽሐፍቱ በሚገባ እንደሚሸጡ በመተማመን ከቁጥር በላይ አሳትሞ ሽያጩ በውስኑ
የኢትዮጵያ ገበያ ምክንያት እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀረ። በሕይወቱ የመጨረሻ ወራት ላይ፣ነፍስና
ስጋውን ለማቆየት ከጓደኞቹ ገንዘብ እስከመበደር ደረሰ።ከዚህ ጥቂት ቀደም ብሎ ከባህርዳር
ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ የፋብሪካው ምርቶችን በእርካሽ እንዲያገኛቸው ተደርጐ፣ይህንን እየሸጠ
የተወሰነ ትርፍ ማግኘት ቻለ።ነገር ግን ለኑሮ፣ ለምግብ እና ለልጆች የትምህርት ወጪ በቂ
አልነበረም። ትንሿ የመጽሐፍትና የጽሕፈት መሳሪያዎች መደብሩ ሙሉ ለሙሉ ልጆቻቸውን
የማሳደግ ሃላፊነቱን በተረከበችው በቀድሞ ባለቤቱ እጅ ነበር።

አቤ ጉበኛ በሕይወት የነበረበት የመጨረሻውወር ጥር 1972ዓም ነበር። በዚሁ ወር አቤ ከባህር


ዳር ወደ አዲስአበባ ሲመጣ አዲስ መጽሐፍ ለማሳተምና ከነበረበት ችግር ለመውጣት በተስፋ
ተሞልቶ ነበር፤ ነገር ግን ነገሮች እንደተጠበቁትአልተሳኩም።በሕይወት በነበረበት የመጨረሻ ቀን
ከጠዋቱ እንጂ ጀምሮ እየጠጣ እንደነበር አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ፤የቀድሞሚስቱ ግን "ግራ
ተጋብቶ ነበር አልሰከረም ነበር" ብላ ታስተባብላለች። እኩለ ሌሊት ላይ አንድ መጠጥቤት
57
ጥቋቁር አናብስት

ለመግባት ይሞክራል፤ መጠጥ ቤቱ ግን ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ አስራ አንድ ሰአት2 ድረስ
በሚዘልቀው ሰአት እላፊ ምክንያት ሊዘጋ ነበር። ጠባቂዎች መግባት ቢከለክሉትም3 ነገሩ ተጋግሎ
ወደ ጠብ በማምራቱ አቤ ጭንቅላቱን ተመቶ ራሱን ሳተ። ይህ የሆነው አዲስ አበባ ውስጥ ጎጃም
በረንዳ በሚባለው አካባቢ ነው።

የቀበሌ ታጣቂዎች አቤን ሆስፒታል ማድረስ ከመቻላቸው በፊት ሞተ።አስከሬኑ በጥር 30 ቀን


1972 ዓ.ም ከቀዳማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ ባህርዳር ተወሰደና ጥቂት ጓደኞቹ እና
ዘመዶቹ በተገኙበት ተቀበረ።ሌላ ምንጭ ደግሞ የሞተው የካቲት2 የተቀበረው ደግሞ የካቲት 5
መሆኑን ይናገራል። አቤ ጉበኛ ሲሞት የ45 ዓመት ሰውነበር።

አቤ ጉበኛ ባህርዳር ውስጥ ለክብሩ ሐውልት ቆሞለታል፤ኢፍትሃዊነትን፣ ጭቆናን ብልሹ አሰራርን


ለመታገል የቆመ የነፃነት፣የፍትህ እና የሰላም ዘብ ነበር ተብሎለታል።መጽሐፍቱ አሁንም ድረስ
ይሸጣሉ፤ህልሞቹ እውን ባይሆኑም እስከዛሬ በሰዎች ልብ ውስጥ መኖራቸውን ቀጥለዋል።

አቤ ጉበኛ “ኃይል ያላቸው”እና በሚገባ የደረጁ ምንባቦችን ጽፏል፤ነገር ግን የነበረውን ጉልበት


ወይም ትዕግስት ወይም መነቃቃት ያጣና ወደ “ተራ ዝርው ጽሑፍ”ይወርዳል።ችሎታ እንደነበረው
አያጠያይቅም፤ነገር ግን ይህ ችሎታ ጎልምሶ ሙሉ አልሆነም። ላመነበት ነገር ግን በሙሉ ልብ
ታግሏል።አቤ በመጽሐፍቱ ውስጥ የፈጠራቸው ገፀ ባህሪዎች ነፀብራቅ ሊሆን ይችላል፤እነዚህ
ገፀባህሪያት በርካታ ጥልቅ ምኞቶች አሏቸው፤ይሁን እንጂ ምኞታቸውን ሊተገብሩት ወይም ወደ
ድርጊት ሊተረጉሙት አልተቻላቸውም።

የተርጓሚው ማስታወሻ

የአቤ ድርሰቶች በተለያዩ ወቅቶች ተለያይተውም ሆነ በአንድነት በድጋሚ ታትመዋል፡፡የህይወት


ታሪኩም ተጽፎ ለንባብ በቅቷል፡፡

ማስታወሻዎች

1) ዋና ዋናዎቹ ምንጮቼ የቀድሞ ሚስቱ፣ ልጆቹ፣ ጓደኞቹ፣ ባልደረቦቹ እና ሌሎች የሚያውቁት


ሰዎች እንዲሁምስለሱየተፃፉ የጋዜጣና የመጽሄት መጣጥፎች ናቸው።

2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከአብዮቱ ፍንዳታ ጊዜ ጀምሮ የሰአት እላፊ ነበር።

58
ጥቋቁር አናብስት

3) እነዚህ ጥበቃዎች የመጠጥ ቤቱ ዘበኞች ወይስ የቀበሌ ጠባቂዎች ነበሩ በሚለው ላይ


ባነጋገርኳቸው ሰዎች መካከል አለመግባባት አለ።

59
ጥቋቁር አናብስት

ተክለሐዋርያት
ተክለማርያም እና ግርማቸው ተክለሐዋርያት የተረት አባትና ተራኪ
ግርማቸው ተ/ሐዋርያት ስለ ሕይወቱ ላነጋግረው በተገናኘንበት
አጋጣሚ በጸና ታሞ ነበር፡፡በአብዮታዊው መንግስት ለ8 አመታት
ከታሰረ በኋላ የተለቀቀውም በዚሁ እያስቸገረው በመጣው የጤና
መጓደል መንስኤ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ልጆቹ በሙሉ የሚኖሩት ከሃገር
ውጪ ነበር፡፡ አንዱ ልጁ

ዶክተር ሆኖ ከሚሰራበት ጀርመን ቦን ከመሞቱ በፊት ለህክምና


አቅንቷል፡፡ለጥቂት ጊዜያት መለስ ያለለት ቢመስልም ዳግም
አገረሸበት፡፡ምን አልባትም በህዳር 1980 በስተመጨረሻ ለህልፈት
ያበቃው የነቀርሳ በሽታ ይመስለኛል፡፡አዲስ አበባ 6 ኪሎ ከሚገኘው
የየካቲት 12 መታሰቢያ ሆስፒታል 105 ቁጥር ክፍሉ ውስጥ ሳገኘው
የደም ዝውውር ስለተደረገለት ደህና ይመስል ነበር፡፡ ስለሕይወቱ
ሊያጫውተኝ ጓጉቶ ስለነበረ አንዳንዴ እያስቆምኩ እንዳይደክመው
ስል አረጋጋዋለሁ። በዝርዝር ታሪኩን ሊያጫውተኝ ቢፈልግም ብዙም ሳይቆይ እየደከመ መጣ፡፡
ከሆስፒታል ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡በድጋሚ ተመልሶም የሕይወቱን የመጨረሻ ቀናት ወዳሳለፈበት
ሆስፒታል ተመልሶ ገባ፡፡ በህዳር መጀመርያ ወደ ኖርዌይ ሄጄ ስመለስ አርፏል፡፡ስለእርሱና አባቱ
የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ብጠቆምም ምን አልባት ስህተት እንኳን ቢኖር ብዬ የያዝኳቸውን
ማስታወሻዎች ማመሳከርን ነበር የመረጥኩት። የሆኖ ሆኖ ለዚህ የሚበቃ ጊዜ አልነበረንም።

በእርሱና በአባቱ ዙርያ የተሰሩ ታሪኮች የተወሰነ አስቸጋሪነት አላቸው። በጦርነቱ ወቅት ጣልያን
ስለነበረበት ጊዜያት የነገረኝ ሃዲስ አለማየሁም ሆነ ሚካኤል እምሩ(ትውስታዎቻቸው ላይ
ተመስርተን)ካወጉኝ ጋር አይጣጣምም፤ሶስቱም ደግሞ በዚያን ወቅት አብረው ነበሩ። ግርማቸው
ለእውነታው በቂ ትኩረት ሳይሰጠው "ሞቅ ያለ ታሪክ" ሊነግረኝ ስለፈለገ በአበይትም ሆነ ጥቃቅን
በሆኑ ጉዳዮች እውነታዎችን ሳይዘረዝር ያጫወተኝን ነገሮች ሙሉ በሙሉ አልተቀበልኳቸውም፡፡¹

የግርማቸው አባት ተክለሐዋርያት ተክለማርያም ግለ ታሪካቸውን በሁለት ቅጽ ጽፈውት ስለነበር


ግርማቸው እነሱን ለማሳተም ሙከራ አድርጓል፡፡ ከመሞቱ በፊት ግን ሊያሳየኝ አልቻለም።ነገር ግን
በሃሰን አሊ የተሰራ በግለ ታሪኩ ላይ የተመሰረተና በግርማቸው የንግግር እና የጽሁፍ
ማስታወሻዎች የዳበረ(ከግታሪኩ በርካታ ክፍሎችን የወሰደ)ዲማጽና በማሞ ውድነህ፣በስብሃት

60
ጥቋቁር አናብስት

ገብረእግዚአብሔር እንዲሁም በመንገሻ ገሠሠ የተደረጉ የተክለሐዋርያትን ቃለ መጠይቆች ማየት


ችዬ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎ የልጅ(አቤቶ) ኢያሱን ታሪክ ለማጥናት እድሉ ስለገጠመኝ ስለእያሱ
ካነበብኩት፣ከሚያስታውሱ ሰዎች ጠይቄም ከተረዳሁት ታሪክ ጋር የተክለሐዋርያትን ታሪክ
በጥንቃቄ ሳነጻጽረው በርካታ እውነት የማይመስሉ ድምዳሜዎችን ስላገኘሁ ብዙም ባላምንበት
የሚያስፈርድብኝ አይመስለኝም፡፡ተክለሐዋርያት የራሳቸውን ሚና የማጋነንና ጥፋቶቻቸውን
በሌሎች የማላከክ ሙከራ ሳያደርጉ አልቀሩም፡፡አሁን ግን በተቻለ የተክለሐዋርያትንና
የግርማቸውን ታሪክ ዳግም ለማዋቀር ሙከራ አድርጌያለሁ፡፡

***

በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ የተክለሐዋርያት ፋይዳ ምንአልባትም የመጀመርያውን


ተውኔት በአማርኛ ስለጻፉና ምንአልባትም በግርማቸው ታዋቂ ድርሰት አርአያ ላይ የዋናው
ገጸባሕርይ ሞዴል ሆነው በመቅረባቸው ጭምር ነው፡፡ ²

ተክለሐዋርያት ተ/ማርያም ለተወሰነ ጊዜ በበጅሮንድነት ማዕረግ የገንዘብ ሚኒስትር (አቃቤ ነዋይ)


በመሆን አገልግለዋል፡፡ ምን አልባትም በዚያ አጠራር መቀጠሉ ሳይሻል አይቀርም፡፡ በተለምዶ ግን
ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት በሚለው ማዕረግ ይጠራሉ፡፡መቼና በእርግጥም ተሰጥቷቸው እንደነበር
ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም፡፡ ³

ከበርካታ የአውሮጳ የትምህርት ቆይታ በኋላ የዘር ሀረጋቸውን የማወቅ ፍላጎት አድሮባቸው ይህንኑ
የቤተሰቦቻቸውን ትውልድ አመጣጥ ከሚያውቁ አእሩግ ጠይቀው ይዘው የነበር ቢሆንም
ከ1928-1933 ዓ.ም በነበረው የጣልያን ወረራ ወቅት ጠፍቶ ቀርቷል፡፡ግለታሪካቸውን መጻፍ
በጀመሩበት ወቅትም ማስታወስ የቻሉት ከአያቶቻቸው ፈቅ አይልም፡፡አያቶቻቸው ዋየህ እና
ይጠይቁሽ 6 ሴት ልጆች የነበራቸው ሲሆን (ስማቸው አይታወቅም) ሁለት ወንድ ልጆችም
አሏቸው። አብዬ (ትንሽ ጊዜያት የሚፈልገውን መሰረታዊ ትምህርት አጥንቶ ቀሰሰ)ተክለማርያም
ደግሞ ከሚስታቸው በለጥሻቸው አራት ልጆችን መውለድ ችለዋል፡፡ ገብረ ጻዲቅ፣ገብረ መድህን፣
ሃብተ ማርያም እና ተክለሐዋርያት።ተክለሐዋርያት የወልደማርያምን ልጅ ሳህለ ማርያምን አገቡ፡፡
ሳህለማርያም በእንጀራ አባቷ ስም ሳህለማርያም ንጋቱ ተብላ ነው የምትጠራው፡፡የተክለሐዋርያት
ዘሮች ኦሮሞ ፈረሰኞች ሲሆኑ ወደ መንዝ ተሻግረው ኑሯቸውን እዚያው የመሰረቱ(የቤተክርስቲያን
ሰዎችም የሆኑ)ቤተ ክርስቲያንም ጭምር ያነጹ ነበሩ።ዋየህ”ትልቅ ሰው”ለመሆን በቅቶ በአካባቢው
ቤተ ክርስቲያን ለመታወቅ በቃ፡፡⁴

61
ጥቋቁር አናብስት

ተክለሐዋርያት በ1876 አካባቢ ሳያደብር በምትባል(በአንኮበርና ደብረብርሃን በስተምስራቅ


ደብረሊባኖስ በስተምእራብ የሚያዋስኗት)ቦታተወለዱ፡፡አምስት ዓመት እስኪሞላቸውም
በእናታቸው እቅፍ ነው ያደጉት፡፡ በኋላ በአለቃ አቢዬ ጥበቃ ስር ቢቆዩም ከትንሽ ጊዜ በኋላ ዝናህ
አያልቅ ከተባለ ካህን ዘንድ የአብነት ትምህርት ቤት ሞተለሚ የተባለ አካባቢ አስገቧቸው። ይህ
ሲሆን 6 አመታቸው ነበር፡፡በ9 አመታቸው ወደ ስርዐተ ቤተ ክርስቲያን ለማለፍ በቅተዋል፡፡
ብዙም ሳይቆይ እ.ኤ.አ (1884-1886) ወደ አዲስ አበባ ትምህርታቸውን ለማስቀጸል አቀኑ፡፡
ከአቡነ ማቴዎስ ጋርም እንደተዋወቁና ለትንሽ ጊዜም በእንግድነት ቤታቸው ማረፋቸውን ጽፈዋል፡፡
ተክለሐዋርያት አዲስ አበባ ከደረሱ ጥቂት ጊዜያት በኋላ አጎታቸው አለቃ አብዬ ለራሳቸው
ለተክለሐዋርያት ታላቅ ወንድም ለሆኑት ገብረ ጻዲቅ በአደራ አስረከቧቸው፡፡ገብረ ጸዲቅ በጊዜው
በተማሩት ዘንድ እንኳን የማይቻለውን መጻፍም ሆነ ማንበብ በሚገባ ይችል ነበር፡፡ ገብረ ጻዲቅ
ወደ ሃረር5 ለራስ መኮንን በጸሃፊነት ተሹሞ ሲሄድም አስከትሏቸው ሄዶ ትምህርታቸውን እዚያው
ቀጥለዋል፡፡የራስ መኮንን ባለቤት ወ/ሮ የሺመቤት ለተክለሐዋርያት“እንደ እናት” የሚቆጠሩ ሲሆኑ
እሳቸውም በቤት ውስጥ ለሚያድጉ ህጻናት እንደ ታላቅ ወንድም“ጋሼ”ይታያሉ፡፡በቤቱ ከነበሩት
ልጆች መሃል ተፈሪ (ኃይለሥላሴ)እና ታዋቂው ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ ይገኙባቸዋል፡፡የሁለቱም
እናቶች በልጅነታቸው ነበር የሞቱት(የተፈሪ እናት የሞቱት የተፈሪን ታናሽ ሲወልዱ ሲሆን ለአቅመ
አዳም የደረሰ ልጃቸው ተፈሪ ብቻ ነበር) ተክለሐዋርያት ጥሩ ተስፋ ያላቸው ተማሪ ስለነበሩ ራስ
መኮንን የዛኔም ሆነ ወደ ፊት ይደግፏቸው ነበር፡፡

ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ሚኒሊክ ሃገር አቀፍ የጦር ጥሪና ንቅናቄ ባደረጉበት
1888 ዓ..ም ራስ መኮንን ወደ ጦርነቱ የሄዱት የያኔውን የ12 ዓመት ልጅ ተክለሐዋርያትን (በጉዞ
ወቅት በእርሳቸው ፈረስ ላይ ለመሄድ አንዳንዴም ከጀርባቸው ለመፈናጠጥ በቅተዋል)6እና ገብረ
ጻዲቅን ይዘው ነበር፡፡ራስ መኮንን ባሸነፉበት የመቀሌው የህዳር 28 1888 አ.ም ጦርነት
ባለቅኔው፣ ምሁሩና በቀጥታ በመናገር ባሕርይው የሚታወቀው ገብረጻዲቅ ተገደለ፡፡

የገብረጻዲቅ ሞት ያብከነከናቸው ራስ መኮንን አንድ የተለየ ነገር ለተክለሐዋርያት ለማድረግ ፈለጉ፡


፡ንጉሰነገስቱን አስፈቅደው በ1889እና1890 ዓ.ም መሃል ለትምህርት ወደ ሩስያ ላኳቸው፡፡ ወደ
ሩስያ ከመላካቸው በፊት ግን ቁልቢ ላይ ከሚኖሩ ሁለት የመስኮብ የጦር አማካሪዎች ጋር
አስተዋውቀዋቸዋል፡፡ሊዎንቲየቭ በኢትዮጵያዊው ማዕረጉ ደጃዝማች፣ባቢቼቭ በፊታውራሪ
ማዕረግ ነበሩ። የጉዞውን አጠቃላይ ሁኔታ ያመቻቹትም እነኚህ ሁለት ሰዎች ናቸው።

62
ጥቋቁር አናብስት

በጅቡቲና በአሌክሳንድሪያ አድርገው ተክለሐዋርያት ወደ ፒተርስበርግ ሲሄዱ የ13 ዓመት ጉብል


ነበሩ፡፡ እዚያም ሲደርሱ የምኒሊክ ልዑካን ጻር ኒኮላስ ዘንድ አቅርበዋቸው ከኮኖሬል ማልቻኖቭ
ቤተሰብ ዘንድ በማደጎ ተሰጡ፡፡ የኮነሬሉንም እናት"አያቴ"7 ሲሉ ነበር የሚጠሯቸው።
ፒተርስበርግ የጦር ማሰልጠኛም ለመግባት እንዲያግዛቸው የግል አስጠኚም ተቀጥሮላቸው ሩስኪ፣
ሒሳብ (አርቲሜቲክ)፣ስነጽሑፍ፣ታሪክ፣ስነ-ጥበብን አጠኑ፡፡በ1892 እዚሁ ማሰልጠኛ እንዲገቡ
ተፈቅዶላቸው ለእጩ ካዴቶች የሚሰጡትን የዝግጅት ኮርሶችን ወሰዱ፡፡8ራሳቸው እንደ ጻፉትም
ስማቸውን ለማሳጠር ሲባል ተክሌ ዋዬህ1፟ ተብለው በቀጣይነት ትምህርታቸውን
8
ሚካይሎቭስካያ መድፈኛ ማሰልጠኛ ተመዝግበው እ.ኤ.አ ከ1904-1907 ድረስ በመከታተል
በዲፕሎም ተመርቀው በሩስያ ጦር ውስጥ በመኮንንነት ተቀጠሩ፡፡

ከትምህርታቸው ውጪ በሩስያ በጊዜው ይካሄዱ በነበሩ ምሁራዊ ክርከሮች በፍላጎት ይከታተሉ


ነበር፡፡እንደ ልዕልት ቮልኮንስኪይ ካሉ ተራማጆች(አያቷ "በዲሴምበርሰት" አባልነትና እና
በተመሳሳይ ስያሜ የሚታወቁ)እንደ ኩቹቤይ ካሉ ታዳጊ ብሄርተኛ መሪዎችና ሊዎ ቶልስቶይንም
ጨምሮ በርካታ ሰዎችን የመተዋወቅ እድል አጋጥሟቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ካሳደጓቸው
ቤተሰብ ጋር በዝምድና ይተሳሰራሉ፡፡

የሩስያ“ አያታቸው” ባመቻቹላቸው ታላቅ የጉብኝት እድል ተጠቅመው ፈረንሳይ ፣ጀርመንና፣


እንግሊዝን ብቻቸውን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ወደ ሃገራቸው እ.ኤ.አ በ1908 ተመልሰዋል፡፡
ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ እድሜያቸው 24 አመታት አካባቢ ሲሆን ከሃገራቸው በወጡ በ12
አመታቸው ነበር የተመለሱት፡፡በቀድሞው ጊዜያት በአብዛኛው ከውጪ ተምረው ለሚመጡ
ኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ስራ ከተማሩበት ትምህርትና ከሙያቸው አንጻር እዚህ ግባ የማይባል
ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም የተክለሐዋርያት ግን የተለየ ነበር፡፡ዶክተር ጆሴፍ ቪታልየን የአጼ
ሚኒሊክ የግል ሀኪም ተክለሐዋርያት በቀኛዝማች ማእረግ በጦር ሚንስትሩ በፊትአውራሪ
ሃብተግዮርጊስ ስር በተማሩት ሙያ የመድፈኛ ክፍሉን እንዲያዋቅሩ ሃሳብ በማቅረቡ ይሄ ሃሳብ
በንጉሱ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ፡፡ነገርግን በሕይወታቸው የኋለኛ ክፍል ተደጋግሞ እንደሚታየው
ተክለሐዋርያት አልተስማሙም9።በምትኩም ወደ እንግሊዝና ፈረንሳይ በመሄድ ለኢትዮጵያ
ከ“ማርሻል አርት” ይበልጥ ያስፈልጋታል የሚሉትን የእርሻ ትምህርት በሁለቱም ሃገራት አጠኑ፡፡
ከንጉሱ ፍቃድን ካገኙ በኋላ 23000 ብር¹10ይዘው እ.ኤ.አ በ1908 ወይም በ1909 የሄዱት ወደ
ፓሪስ ነበር፡፡ እዚያ በትርፍ ጊዜያቸው በሃገሪቱ የሚኖሩ የሩስያ ልጆችን ሩስኪ ያስጠናሉ፡፡ ቀጥሎ
ወደ ሎንዶን አቀኑ እዚያም በግል አስተማሪ ሲያጠኑ ቀይተው ከሶስት አመታት በኋላ በ1911

63
ጥቋቁር አናብስት

ወይም በ1912 በጅቡቲ አድርገው ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡ይህ ጊዜ ማለት ተፈሪ መኮንን


ከሲዳሞ ወደ ሃረር በሃገረ ገዢነት በተዘዋወሩ በአመቱ ማለት ነው፡፡ ራስ መኮንንም በዚሁ ወቅት
ከሞቱ ጥቂት አመታትን አስቆጥረዋል፡፡

ተፈሪ ወድያውኑ ነበር በሃረርጌ አስተዳደር ላይ አብረዋቸው እንዲሰሩ የጠየቋቸው። ግን


ተክለሐዋርያት በድጋሚ ባለመቀበል በጨርጨር አካባቢ በእርሻ መሰማራትን መረጡ፡፡ ከውጪ
በተመለሱ በአመቱ ማለትም እ.ኤ.አ በ 19012 ና በ1913 አካባቢ የ28 ወይም የ29 ዓመት
ወጣት በነበሩበት በዚህ ጊዜ ወደ ሂርና ሄደው በአንዲት መቃኞ ቤት ውስጥ ለ11 ወራት ያህል
በመኖርና ለአካባቢው ኗሪዎች የህክምና እርዳታ በማድረግ ተወዳጅነት ለማትረፍ ችለዋል፡፡
የሚኖሩበት አካባቢም የራስ መኮንን ርስት ማለትም የተፈሪ ቤተሰቦች ይዞታ ቢሆንም ተፈሪ ያለ
ኪራይ እንዲቆዩ ፈቅዱ፡፡ይሄ ተግባር ብዙ የአማራ መልከኞችንና የቀድሞ ወታደሮችን ያፈናቀለ
ቢሆንም ተፈሪ ቅሬታዎቹ እንዲዳፈኑ ረድተዋቸዋል፡፡ተክለ ሐዋርያት አዲስ የንግድ ግንኙነት
በሂርናና በድሬዳዋ መሃል በመክፈት ንግዱ እንዲቀላጠፍ አበረታቱ፡፡ በውጤቱም አዳዲስ ሸቀጦች
ወደ ሂርና ገበያ መምጣት ጀመሩ፡፡ የስልክ መስመርም በጥረታቸው ተዘረጋ፡፡በዚህ ወቅት
የመስተዳድሩ መናገሻ ቁኔ ነበረች፡፡

ሚኒሊክ በዚህ ወቅት ከአልጋ ውለዋል፡፡ለውጥ ማምጣት የሚችለው ሃይልም በልጅ ልጃቸው
በእያሱ (የወሎው ራስ ሚካኤልና የምኒሊክ ሴት ልጅ ወ/ሮ ሸዋረጋ ልጅ)እጅ ላይ ነበር፡፡
ተክለሐዋርያት የኋላኋላ በሕይወታቸው ቆይታ ከእያሱ ጋር ለመግባባት ስለፈለጉ የላፎንቴይንን እና
የክሪሎቭን ተረቶች በመተርጎምና በማላመድ በ1913 እ.ኤ.አ አካባቢ ወደ አሰማርኛ እንደመለሱ
ጽፈዋል፡፡ እንዳንዶች ግን የሃገረሰብ ተረቶችንም እንደተጠቀሙ ይናገራሉ፡፡ይህን ይህን አድርገው
የተሰናሰለ ታሪክ በመፍጠር ልጅ እያሱን በምሳሌ ለማስተማር ነበር ያልታተመ ረቂቁን ፋቡላ
የአውሬዎች ኮመድያ11ሲሉ ሰይመው በግምት በ1913 የጻፉት፡፡እሳቸው እንደ ኢትዮጵያውን
አቆጣጠር በ1904 ና በ1906 በአውሮጳውያን አቆጣጠር በ(1911/2 እና በ1913/4)ቢሉም
በልማድ ደረጃ ግን በብዛት የሚታመነው በንግስት ዘውዲቱ የአገዛዝ ዘመን እ.ኤ.አ (1916-
1930) እንደተጻፈ ነው፡፡ እኔም በዚሁ ትክክለኛነት ወደማመን አደላለሁ።¹²በእያሱ ዘመን
(1913-916) እንደተመደረከ ቢጽፉም እውነቱ ግን ይኀው ተውኔት በዘውዲቱ ዘመን ለመድረክ
በቅቶ መልሶ መታገዱ ነው፡፡ንግስቲቱ በአጠቃላዩ በንቅዘት በሚታሙና በችሎታ ባልበቁ
ባለስልጣናት ላይ እንደ ተሰነዘረ ሂስ ነበር የቆጠሩት፡፡ተውኔቱ በድጋሚ በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመን
ለመድረክ ቢበቃም በህትመት መልክ ግን ወጥቶ የማያውቅና ለማግኘትም አስቸጋሪ ነው፡፡ 13

64
ጥቋቁር አናብስት

በተመሳሳይ ወቅት ተክለሐዋርያት በጽሁፋቸው"መልካም ስነ ምግባራትንና ግብረገብን ለልጅ እያሱ


ለማስተማር የታለመች የአጫጭር ታሪኮች መድብል አሳትሜያለሁ"ቢሉም መጽሐፉ ሙሉ ለሙሉ
ጠፍቶ (ቢኖር እራሱ) ሊገኝ አልቻለም።

ስለ ተውኔቱ በጻፏቸው እያንዳንዱ ማጣቀሻዎች ላይ ተክለሐዋርያት የልጅ እያሱን አስተዳደር


መኳንንትና እራሳቸውን እያሱን ጭምር ለመተቸት በማሰብ እንደጻፉ እንደልባቸው ከልጅ እያሱ
ጋር ለመገናኘት ባለመቻላቸውም“ለማስጠንቀቅ” በዚህ መልኩ መጻፋቸውን በአጽንኦት ያትታሉ፡፡
ልጃቸው ግርማቸውም ይህንኑ ደግሞ ያስረግጣል፡፡በግለ ታሪካቸው ላይም ተክለሐዋርያት ልጅ
እያሱ የሳቸውን ስራዎች እንደሚያከብሯቸውና ዋጋ እንደሚሰጧቸው ይሔም ከእርሳቸው ጋር
እንዳቀራረባቸው ይናገራሉ።እንደ ልጃቸው ግርማቸው አባባል ከሆነ እንደውም በተጨማሪ
“የሃገሪቱን ማስተዳደርያ ደንብ”ለማርቀቅ ፍቃድ ጠይቀው እንደተፈቀደላቸውና ያረቀቋቸው
“ህግጋት” በቢትወደድ ሃይለግዮርጊስ፤ፊትአውራሪ ስራህብዙ እና በቀኛዝማች ወልደአማኑኤል
ቢነበቡም ደንቦቹ ተረስተው በጭቃ ውስጥ ተቀብረው ቀርተዋል ይለናል ግርማቸው አባቱን
በመጥቀስ፡፡

በ1914 እ.ኤ.አ ተክለሐዋርያት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ
ዘንድ እንዲሰሩ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው በ1915 እ.ኤ.አ ከእንግሊዝ አሳሾች ጋር ወደ
ጣና አቅንተዋል፡፡ እንደእሳቸው ከሆነ በዚያው ዓመት የምድር ባቡርተቆጣጣሪ ሆነው ቢሾሙም
ልጅ እያሱ በሃገር አስተዳደር እርዳታቸውን ስለሚፈልጉ እንዳስጠሯቸው ፤በዚያን ወቅትም የእያሱ
የቅርብ አማካሪ እንደነበሩ፤ከቅርብ ወዳጃቸው ከተሰማ እሸቴ(ዘመዳቸውን ጸሃይ ወርቅ ዳርጌን
ከዳሩላቸው)ሳይቀር እንሚያስበልጧቸው ያስቀምጣሉ፡፡በዚሁ ግለ ታሪካቸው ላይ በተጨማሪም
ከልጅ እያሱ ጋር የፈረንሳዊውን ገዢ ሙሴ ሳይመንን ለማግኘት ወደ ጂቡቲ አብረው ባደረጉት ጉዞ
የተገለጸልኝ ነገር ቢኖር "እያሱ ኢትዮጵያን የመምራት ክህሎት እንደሌላቸው ነው"ሲሉ ያክላሉ፡፡
እያሱ ለውሳኔዎች ፈጣን፤ሰዎችን ለመሾም ለመሻር የማይጠበቁና ሃላፊነት የማይታይባቸው
ብያኔዎች እንደሚሰጡ ለእርሳቸውም ይሄን ጉዞ ተከትሎ ከፍተኛ ሃላፊነት በሐረርጌ እንደሰጧቸው
(ተፈሪ አስተዳዳሪ በሆኑበት)ጽፈዋል የሚታመን ከሆነ፡፡እያሱ በርካታ ሰዎችን መሾማቸውን
ቀጠሉበት በርካቶቹም ሙስሊሞች መሆናቸው ተክለሐዋርያት እያሱ ሙስሊም¹4መሆናቸውንና
ሃገሪቱን ወደ እስልምና15 የመቀየር ፍላጎት እንዳላቸው እንዲጠራጠሩ አደረጋቸው፡፡እያሱ
ተክለሐዋርያትን “እንደ ቅርብ አማካሪያቸው” ቆጥረዋቸው ሳለ መልሰው ደግሞ ከኔ ይልቅ ከተፈሪ
ጋር ይቀራረባል ሲሉ እንደሚጠረጥሯቸውም ጭምር ቀጥለውም በእያሱ ያለመብሰል፤ችሎታ ማነስ

65
ጥቋቁር አናብስት

፤ከሁሉ በላይ ወደ እስልምና በማጋደላቸው የተነሳ ከሚዶልቱባቸው የሸዋ መኳንንት


መግጠማቸውን እያሱን በቅርበት እንደሚያውቋቸው አመላቸውንም ለማረቅ ፍሬቢስ አመታትን
ማሳለፋቸውን በሪፖርት መልክ ማስታወቃቸውን ጽፈዋል፡፡በእያሱ ላይ የጻፉትም ይህ ሪፖርት
ሸዌዎቹ በእያሱ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያሳልፉ ማድረጉን ይናገራሉ፡፡ በመስከረም 27(በ20
መሆን ሲገባው)1916 እ.ኤ.አ ተገናኝተውም በከንቲባ ወልደ ጻዲቅ መሪነት በጅሮንድ ይገዙ፣
ቀኛዝማች መኮንን፣ፊትአውራሪ ሃብተግዮርጊስ፣በተገኙበት በበጅሮንድ ይገዙ ጠቋሚነት የአቡነ
ማቴዎስ ግዝት ተፈቶ ዘውዲቱ በንግስትነት ተፈሪ መኮንን በአልጋ ወራሸነት እንደተቀቡ ይገልጻሉ፡፡
በጅሮንድ ይገዙ በመስከረም 29(በ27 መሆን ሲገባው)እያሱ ሃረር እያሉ ከአልጋ መውረዳቸውንና
በአዲሱ መንግስት መተካታቸውን ሲናገሩ ተክለሐዋርያት እንደ ራስ ዳምጠው፣ደጃዝማች ባልቻ፣
ራስ ወልደ ግዮርጊስ፣ በጊዜው ንጉስ የነበሩት ራስ ሚካኤል (የእያሱ አባት) እና ራስ ሃይሉን
የመሳሰሉ መኳንንት መፈንቅለ መንግስቱን ይቃወማሉ ሲሉ ፈርተው ነበር፡፡ እንደፈሩትም አመጽ
ተቀሰቀሰ “አስቀድሞ ታይቶኝ” ባሉት ተቃውሞ ተክለሐዋርያት እራሳቸው የልጅ እያሱ ወገን
የሆኑትን (በጉግሳ አሊዮ የሚመራ)ሃይሎች ጥቅምት 6 1916 መኢሶ ላይ ገጥመው ድል
ማድረጋቸውን ይናገራሉ፡፡ እያሱ ወደ አፋር አመለጡ፡፡ ተክለሐዋርያት ቆይተው እያሱ በደቢኒ
ከሚባል የአፋር ጎሳ ዘንድ መኖራቸውን(ቁኒ እያሉ)ሰምተው ወደ እዚያው በመዝመት እያሱን
ባያገኙም (ከሺህ በላይ)ከብት ለራሳቸው ዘርፈው ከአፍደም 20 ኪ.ሜ ርቀት ለነበረው የከብት
ርቢያቸው ዋነኛ ምንጭ አድርገውታል፡፡

በእያሱ ታሪክ ላይ ፍላጎት አሳድሬ በእርሳቸው ዘመን የነበሩ እኩዮቻቸውን ጠይቄ ነበር ፡፡ በተለይ
እርግጠኝነቱን ያመንኩበት አንድ (ምስክር)“እንኳን በነዚህ ነገሮች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ቀርቶ
ተክለ ሐዋርያት ከማእከላዊው ስልጣን የራቁና እየሆነ ያለውን የማያውቁ ናቸው16 ”ብሎ ነግሮኛል፡
፡በዚህ ወቅት የነበራቸውን ሚና አጋነው ለማቅረባቸው እርግጠና ነኝ፡፡እራሳቸውን ሲያዋድዱ
አልያም ስልጣኑ ወዳጋደለበት ሊጠጉ ሲፈልጉ ካልሆነም የልጅ እያሱ ወገን ስለነበሩ እራሳቸውን
ሊያድኑ ወይም አፋሮቹን ወርረው ለዘረፉባቸው ከብትና እድሜ ልካቸውን ለከበሩበት ዘመቻ
ማስተባበያ ፍለጋ ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተክለሐዋርያት ከቀርሳ ሃረርጌ የተገኘቸውን ከራስ መኮንን ወታደሮች መሃል
የአንዱ ልጅ የሆነችውን ወ/ሮ ሳህለ ማርያምን በተክሊል አገቡ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ
ክርስቲያን ህግጋት መሰረትም ጋብቻው መፍረስ አይችልም፡፡ብዙ መከራ ባዩባቸው የስልጣን
ሽግግሮች ቢቸገሩም በደስታ የተሞላ “ከሚመስል” የትዳር ኑሮ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች
ልጆችን አፍርተው ኖረው ወ/ሮ ሳህለ እ.ኤ.አ በ1959 አርፋለች፡፡ልጆቻቸው ግርማቸው፤ላቀች፤

66
ጥቋቁር አናብስት

ወይንሸት፤ተስፋቸው፤ከልላቸው፤መራ፤አልማዝ(ቆይታ የሚካኤል እምሩ ባለቤት የሆነች እና)፤


አስቴር የበኩር ልጃቸው የሆነችውን ግርማቸውን በሂርና ጨርጨር ወረዳ ሃረርጌ አውራጃ ህዳር
12 ሲወልዱ የመጨረሻ ልጃቸውን ከ20 ዓመት በኋላ ነው ያገኙት፡፡

****

እ.ኤ.አ በ1918 ተክለሃዋርያት የጅጅጋና አካባቢዋ ገዢ ሆነው ተሾሙ፡፡ አካባቢውን ለስድስት


ንኡሳን ክልሎች በመክፈል እራሱ የጅጅጋን ከተማን እ.ኤ.አ በ1918 ቀረቆሩ፡፡ ወህኒ ቤት፤ግምጃ
ቤት አቋቋሙ ቋሚ ዘቦችን ሾሙ የቀረጥ ማሻሻያም ደነቡ፡፡ አርብቶ አደሩን የሱማሌ ሰውንም ወደ
አካባቢው በማምጣት መሬት እንዲያለማ ሞከሩ፡፡ወዲያውኑ በዘካ(አስራ በአይነት) መልክ ቀድሞ
ከሚሰበሰበው ብልጫ ያለው(900000 ኪ.ግ እ.ኤ.አ በ 1920) ጥራጥሬ ለመንግስት ለመሰብሰብ
ቻሉ፡፡አስተዳደሩንም ለማሻሻል በስራቸው ደስ አያሰኙም ያሏቸውን ሰራተኞች ቢነቅሉም ተፈሪ
ጋር ሄደው አቤት በማለታቸው ወደ ቀደመ ስራቸው ቀሚስ እየለበሱ(ተሹመው) በስራቸው
ስለተመለሱ ይሄ ያናደዳቸው ተክለሐዋርያት እራሳቸውን ከስራ አሰናብተው ወደ ሂርና ተመለሱ፡፡

በ1923 መጀመርያ አካባቢ ተፈሪ ወደ አዲስ አበባ አስጠርተዋቸው (ሂርናን ጨምሮ) ጨርጨር
ላይ በገዢነት ሾሟቸው፡፡ ሹመቱን ግን ከመቀበላቸው በፊት ተክለሓዋርያት ቅድመ ሁኔታዎችን
አስቀመጡ፡፡በመንግስት መሬት ተተክለው ጭሰኞችን ክራይ እየተቀበሉ ያሉ መልከኞች ተነስተው
በምትካቸው ችሎታ ያላቸው ሰዎች እንዲተኩ፤የአዳል መሬት በእርሳቸው ስር(ወደ ጨርጨር)
እንዲጠቃለል፤አዲስ ህግ ለአካባቢው ወጥቶ በስራ ላይ እንዲውል ሲሆን የዚህ ቅድመ ሁኔታ
ግልባጭም ለሃረሩ አውራጃ እንደራሴ ለእምሩ ኃይለሥላሴ እንዲደርስ ጠየቁ፡፡ በተፈሪ ሂርናን
መናገሻ የማድረግ ፍላጎታቸውን ከተከለከሉ በኋላ መስተዳድሩን ከቁኔ ይመቻል ብለው ወዳሰቡት
በ1923 እ.ኤ.አ መስርተውት አልጋወራሽ ተፈሪ አሰበተፈሪ ተብሎ እንዲሰየም ወደወሰኑት ጭሮ
አዞሩት፡፡17ከተማዋም በፍጥነት ተገንብታ ለሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ሞዴል እንድትሆን
ታስባ ነበር።18 ተክለሐዋርያት ጨርጨርን ለ7 አመታት አስተዳደሩ፡፡ በድጋሚም አውራጃውን
ለማሻሻል ሲሉ ለ10 ንኡስ ወረዳዎች ከፈሉት፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ አዲስ በሆነው አሰራር ቋሚ
ደሞዝ ለሰራተኞች መክፈልና የዓመት ግብርን (ህጉ እስከዚያ ግዜ ድረስ እንደተደነገገው)በገንዘብ
መሰብሰብን አስጀመሩ፡፡ ቀረጥ የሚተመነው በመሬት ስፋትና ጥራት ተዋረድ ልክ ስለነበር ይሄም
የተለመደውን የገባሮችን የኩዳድ ስራ የሚያስቀር ነው፡፡ተፈሪ ግን በተሰበሰበው ግብር ስላልረኩ
በህዝቡ ላይ ግብሩን እጥፍ እንዲተምኑባቸው አዘዟቸው፡፡ተክለሐዋርያት ግን ድልድይ በማስገንባት

67
ጥቋቁር አናብስት

አሰበተፈሪንና (በአጠቃላይ ጨርጨርን) ከመኢሶና ከሂርና ጋር በማገናኘት ለውጪ ገበያ መውጪያ


ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች እህል ገበያ በመፈለግና ከውጪም ሸቀጥ እንዲገባ አመቻቹ፡፡ የህግ
ስርአቱንም ላይ ማሻሻያ በማድረግ እንዲፋጠንና ፍትሃዊ እንዲሆን ረድተዋል፡፡ ሰዎች እስካሁን
ድረስ ፍትሐዊ ዳኛ እንደነበሩ ይመሰክሩላቸዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የቡና ችግኞችን
በማስተከልና በሙስሊሙ ዘንድ በሚዘወተረው ጫት ላይ ከባድ ግብር በመጣል ለማስቀረት
ሙከራ አድርገዋል፡፡ባይዘልቁበትም ዘመናዊ ትምህርትም አስጀምረው ነበር፡፡የደን ውድመትንም
ለማስቀረት ጥረት አድርገዋል፡፡አፋር ግብር አልከፍልም ብሎ ሲያምጽባቸው ጦራቸውን ይዘው
በመዝመት እስከ ዛሬ በሚታወስ ዘመቻ ብዙ አፋሮችን ገድለው በርካታ ምርኮ ወስደዋል፡፡ ይሄም
ቅሬታ አስከተለ፤ ከከበርቴ ባለመሬቶች ያገኙትን ትርፍ መሬትም በመሸጥ እንዲገበርለት አድርገው
በየወሩ ለክቡር ዘበኛ የሚሆን የደሞዝ ብር 11.000 ይልኩ ነበር፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ
ከሚኒሊክ ለስራቸው ዋጋ መሬት የተሰጣቸው መልከኞች(አብዛኛው የአማራ ወታደሮች) ግን በዚህ
ግብር ቅሬታ ተሰምቷቸው ጠላት ሆኗቸው፡፡ አዲስ አበባ ላለው እንደራሴ በልጅ በለው መሪነት
ስለ ግብር ፖሊሲዎቹና ጫት ላይ ስለተጣለው ግብር ወዘተ ቅሬታ በማቅረባቸውእ.ኤ.አ በ1927
በ11 ክሶች እራሳቸውን ለመከላከል ተክለሐዋርያት በዙፋን ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተጠሩ፡፡ተፈሪ
የማሻሻያውን ነገር ለይስሙላ የወደዱት ቢመስሉም በልጅ በለው ወገን አድረው 10000 ብር
መቀጮ ተክለሐዋርያት ላይ ወደቀባቸው፡፡

ይህ ካጋጠሟቸው ችግሮች የመጀመርያው ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1929 የተለያዩ ታዋቂ ባላባቶች


አብረው በሌሉበት ከሰሷቸው፡፡ወደ መናገሻው በመጣደፍ የመጡት ተክለሐዋርያት ከሳሾቻቸው
ለተፈሪ ክሳቸውን አቅርበው ከተደመጠላቸው በኋላ ነበር፡፡ይህ የርሳቸው ወደ አዲስ አበባ
መምጣት በወቅቱ ወደ ድሬዳዋ በባቡር የመጡትን የተፈሪን ባለቤት ወ/ሮ መነንን እንዳይቀበሉ
ስላደረጋቸው ተፈሪ ቅር ተሰኙባቸው፡፡ ይህ ይሄ ተደማምሮ ለተክለሐዋርያት መባረርና እስር በር
ከፈተ፡፡ የጥሉ አይነተኛ መንስኤ ግልጽ አይደለም፡፡ተክለሐዋርያት “የታሰርኩት የንጉሳዊውን
ቤተሰቦች እና የበላይ መኳንንቱን ባለማክበሬ ነው”(ለሚስቴ ሰላምታ አልሰጠኅም ተብየ) ቢሉም
ሌሎች ደግሞ የታሰሩት “ከቦልሼቭክ መረብ በኢትዮጵያ”ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው
ስለተጠረጠሩ ነው ይላሉ። አንድ ሰራተኛቸው መድፍ አምጥቼላቸው ነበር ስላለ ያንን ለማጣራት
በተደረገ ፍተሻ የወፍጮ መለዋወጫ ክፍሎች ነበር የተገኙት፡፡የታሰሩት አዲስ አበባ ውስጥ
በፊትአውራሪ ገብረማርያም ጥበቃ ስር ነበር፡፡ በአሰበ ተፈሪና በሂርና የሚገኙ ቤቶቻቸው
ተፈተሹ። የቤተሰባቸው አባላት ታሰሩ፤ተንገላቱም፡፡ እሳቸውም ስድስት ወራትን በእስር አሳለፉ።
በዚህም ወቅት በእርሻ ላይ ጽሑፍ የጻፉ ሲሆን(ትንሽ መፈተኛ ስለእርሻ ትምህርት) 2፟አሁንም

68
ጥቋቁር አናብስት

አንዳንዴ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይሸጣል፡፡ ከእስር ከተፈቱ በኋላ እንቅስቃሴያቸው ሂርና ላይ
ባለው እርሻቸው ተገደበ፡፡

***

ብዙም ሳይቆይ ግን ወዲያውኑ በ1930 እ.ኤ.አ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተብለው በተቀቡት ንጉስ
ለአዲስ ስራ ተፈለጉ፡፡ኃይለ ሥላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማያውቀውን ሕገመንግስት
እንዲቆም ፈለጉ፡፡ተክለሐዋርያት ለመንገሻ ገሠሡ በመስከረም 1963 በሰጡት ቃለ መጠይቅ
“ሕገመንግስቱ ያስፈለገበት ምክንያት ለውጪ መንግስታት ኢትዮጵያ ህገመንግስት እንዳላት፤
መንግስቷም ህገመንግስታዊ እንደሆነ፤በስርአት አልበኝነት ላይ የሚነሱ ውንጀላዎች፤ የፊውዳል
ህጎችን፤ ያልተብራሩ የአስተዳደር ቅደም ተከተሎችንና፤ ትርምስምስ መንግስታቸው ላይ የሚሰነዘሩ
ውንጀላዎችን ለመመከት እንዲመቻቸው ነበር” ብለዋል፡፡ ሲጀመር ባለ 55 አንቀጹ ሕገመንግስት
የህዝቡን ጸጥታናየሃገሪቷን አንድነትና የንጉሱን ሃይል ለማጋፈር ነው የተቀረጸው፡፡ ተክለሐዋርያት
የተለያዩ ሕገመንግስታትን ቢመረምሩም (የጣልያን፤ጀርመንና፤የእንግሊዝ) የተመቻቸውን “ደብዛ”
ግን ያገኙት ከጃፓኑ የ1889 ህገመንግስት ነበር፡፡በመጀመርያ ይህ ስራ ካቅሜ በላይ ነው ብለው
ስላሰቡ ቢያንገራግሩም በኃይለሥላሴ ግፊት ተቀብለዋል፡፡ ከጃፓኑ ሕገመንግስት ጋር ካሉት
ልዩነቶች መሃል ለምሳሌ(በኢትዮጵያው ህገመንግስት ላይ የንጉሱ ስልጣን መላቅ)የመናገር፤
የመሰብሰብና የሃይማኖት ነጻነት(ጭርሱን በሳቸው ህገመንግስት ውስጥ አልተነሱም) ይገኛሉ፡፡(ስለ
ውጪ ግንኙነት በህገ መንግስቱ ያለው ነገር“ዋጋ የሌለው”ነበር ሲሉ እራሳቸው ተናግረዋል )
በታላቁ3፟ ቤተመንግስት ከቤተሰባቸው ጋር አብረው ተቀምጠው ሕገ መንግስቱን እያረቀቁ የጻፉት
ተክለሐዋርያት “ኃይለሥላሴ የእርሳቸውን ፍላጎት ያማከለ ሕገመንግስት እንዲረቅ ይሻሉ፡፡ሰርቼ
በጨረስኩ ጊዜ ንጉሱ ከባለሟሎቻቸው ራስ ካሳ፤ብላቴንጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ እየተማከሩ
የሚስማማቸውን ማሻሻያዎች ካገቡበት በኋላ ጸድቆ ተፈረመ፡፡መብትና ስልጣናቸው
በሕገመንግስቱ እውቅና ስላልተሰጠው ሰነዱን በጣም የተቃወሙት መኳንንቱ ናቸው”ሲሉ
ይጽፋሉ፡፡ተክለሐዋርያት ቆይተው ስለ ሕገመንግስቱ የሚያብራራ (ስልጣኑ በሕግ
ያልተረጋገጠ)ዲስኩር አዘጋጁ፡፡ በዲስኩሩም(በፓርላማ በማህተመሥላሴ ወልደ መስቀል የተነበበና
በዝክረ ነገር ድጋሚ የወጣ ነው)ስለ “መተካካት ህግና”ስለ ፓርላማው ስልጣን (ሕገመንግስቱ
ከሚለው በላይ እንደሚሆን“ ቃልበመግባት”)አውስተዋል፡፡ሕገመንግስቱን እንዲቀበሉ
ለማስተማመን ሲባል አንዳንድ መብቶች ለመኳንንቱ ተሰጥተዋል፡፡ ተክለሐዋርያት እንደጻፉት
ኃይለሥላሴ ህገመንግስቱ በምንም አይነት ከሳቸው በላይ እንደሆነ እንደማያምኑና “የቤተሰባቸውን
69
ጥቋቁር አናብስት

የመተካካት ሂደት እንዲያረጋግጥላቸው”ብቻ ነበር የፈለጉት፡፡ይህ ህገመንግስት እስከሚከለስ ድረስ


“በስልጣን ላይ” እስከ 1955 ቆይቷል፡፡

ይሄ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ኃይለሥላሴ ለተክለሐዋርያት የእርሻ ሚኒስትርነትን ቦታ ሊሰጧቸው


ቢፈልጉም(በአውሮጳ ለ3 አመታት የተማሩበትንና ለኢትዮጵያ ከጦርነት ሃይልና ስልት በላይ
ያስፈልጋታል ለሚሉት)አሻፈረኝ አሉ፡፡ጥቂት ጊዜያትን በእርሻቸው ላይ ካሳለፉ በኋላ በደጃች ይገዙ
አሳሳቢነት በበጅሮንድ ማዕረግ በፋይናንስ ሚኒስትርነት (በመንግስት አቃቤ ነዋይነት) ተሾሙ፡፡
በሁለት የውጪ አማካሪዎች በኤቨርት ኮልሰንና ፤በሜትረ ጃኪ ኦበርሰን እርዳታ አዳዲስ
መመርያዎችንና ደንቦችን ለሚንስትር መስሪያ ቤቱ ነደፉ፡፡ረቂቁ ለኃይለሥላሴ ቀርቦ ደጃዝማች
ይገዙን፤ቢትወደድ ገብረ ጻዲቅን ደጃዝማች ወዳጄን በመምረጥ እንዲመረምሩት በኮሚሽንነት
መደቧቸው፡፡ነገር ግን (ያለምንም ድርጊትና ለውጥ) ሃሳቡ የተረሳ መሰለ፡፡ተመሳሳይ እጣም
ተክለሓዋርያት ባስተዋወቁት በአዲሱ የባንክ ህግጋት (የባንኩ ስራ አከናዋኝነት የተሰናዳ ሰነድ)ላይ
ደረሰ፡፡በርካታ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ጠቁመዋል፡፡ለምሳሌ ባርያዎች ስለሚኖሩበት ሁኔታ መሻሻል፤
ለመንግስት ሚኒስትር መስርያ ቤቶች በአግባቡ ታቅዶ የጸደቀ ባጀት ስለማግኘት ወዘተ ከመንግስት
የተበደሩ ሃያላን ሰዎች ብድራቸውን እንዲመልሱ፤የንጉሱ የግል ወረትና የሃገሪቱ ሀብት እንዲለያይ
የሚሉ ሀሳቦችን አንስተዋል በባንክ ላይም ያጠኑት ጥናትና የሰሩት ስራ የደረሱበት ውሳኔ ተመሳሳይ
ነበር፡፡ይሄ ከስራ አጋሮቻቸው ጋር ቅራኔ ውስጥ ሲያስገባቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማያውቅ
ሁኔታ በተለይ ፍርድ ቤቶችን በፍርድ ሸንጎ “ዲሞክራታይዝ” ለማድረግ መፈለጋቸው “ጥርጣሬ”
ውስጥ እንዲወድቁ አስችሏቸዋል፡፡ በወቅቱ የስራ ሚኒስትር የነበሩት ፊትአውራሪ ታፈሰ
ለቤተመንግስት ቅጥያ ስራ ከግምዣቤት እንዲከፈል ሃሳብ በማቅረባቸው (ሌሎችም እንደ ወጪዎች
ለራስ ካሳ የተሰጠ 20000 ብር 5000 ለአንዲት እመቤት የሽቶ የመሳሰሉትን )ከግምጃ ቤት
ለመክፈል በመከልከላቸው በኃይለ ሥላሴ ዘንድ ተቀባይነታቸውን አወረደው፡፡ራስ ካሳም "ወደ
ውጪ በመላክ ገለል እናድርገው"ሲሉ ሃሳብ ስለአቀረቡ ተቀማጭነታቸውን ጄኔቭ አድርገው
ለስዊዘርላንድ፤እንግሊዝና ፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሆኑ ተሾሙ፡፡እንደ ልጃቸው ግርማቸው
አባባል ከሆነ ደግሞ ስልጣናቸው ለጄኔቭ ሊግ ኦፍ ኔሽንስም ልኡክነት ነበር፡፡

የጄኔቩ ስራ ለእርሳቸው ጥሩ እና ተስማሚ መሆን ነበረበት፡፡እንደ ግርማቸው አባባል ከረጅም ግዜ


በፊት እያሱንና ተፈሪን ለአለም አቀፍ ግንኙነት ጥያቄዎች ትኩረት እንዲሰጡ በተለይ ከአንደኛው
የአለም ጦርነት በኋላ ለራስ ተፈሪ ስለ ሊግ ኦፍ ኔሽነስ እንዳስረዷቸው ይናገራል፡፡የዚያን ጊዜም
በአባልነት ለመመዝገብ እንዲያመለክቱ ለመገፋፋት ሞክረዋል፡፡ በግለ ታሪካቸው ውስጥም ሲጽፉ
ተፈሪ ሃሳቡን ቢደግፉም ከራሳቸው አንድ ሰው(ተክለሐዋርያትን)ከዘውዲቱ(ደጃዝማች ሺበሺን)

70
ጥቋቁር አናብስት

በማድረግ ለመላክ በማሰባቸው ይሄ ደግሞ በተክለሐዋርያት ዘንድ “ተገቢ” እንዳይደለ ለኢትዮጵያ


አንድ ልኡክ ብቻ እንደሚያስፈልጋት በመታሰቡ ይሄ ተፈሪን አናዷቸው በሁለቱ መሃል ቅራኔን
ብሎም መለያየትን ሊያስከትል ችሏል፡፡ተፈሪም አቅማቸውን አውቀው እንደራሴውን የሚያከብር
ሰራተኛ እንዲሆኑ አስጠነቀቋቸቸው፡፡ይህንንም ተክለሐዋርያት አልተቀበልኩትም ሲሉ ይተርካሉ፡፡
ከዚህ አለመግባባት በኋላ ኢትዮጵያም የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ሳትሆን ተክለሐዋርያት ወደ ሂርና
ተመልሰው የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው እስኪሾሙ ድረስ ተቀመጡ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍኔሽንስ አባል ሆነች፡፡ተክለሐዋርያት ግን


"በአምባሳደርነት"ማእረግ ወደ ውጭ ከሄዱ በኋላ ነው ከሊጉ ጋራ በቅርበት መሳተፍ የቻሉት።
ይህን ወቅት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በመተንኮስ ለመውረር የምታቅድበት አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፡፡
ተክለሐዋርያት ሀገር ውስጥ በነበሩበት ወቅትም ሃገሪቱ በዘመናዊ መሳርያ እራሷን እንድታጠናክር
መንግስትንና ንጉሱን ጎትጉተዋል፡፡ ይህንንም ሃሳቤን ካዋየሁዋቸው መሃል ራስ ደስታ፤ብላቴን ጌታ
ህሩይ፤ከንቲባ ነሲቡ፤ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው ነበሩበት ይላሉ፡፡ ወደ ፓሪስ ለሁለት ዓመት
በልኡክነት ሲላኩ ለሌጋሲዎን ስራ ማስኬጃ 220000 ብር ይዘው ሄዱ፡፡

ተክለ ሐዋርያት ስለ እ.ኤ.አ 1934ቱ የወልወል ግጭት ከንጉሱ በመስማታቸው በሊጉ ውስጥ
ነገሩን በማንሳት ኢትዮጵያ ነገሩን በሰላም ለመፍታት እንደምትሻ ተናግረዋል፡፡እንግሊዝና ፈረንሳይ
ከጣልያን ጋር በማበር ኢትዮጲያ አንዳንድ ነገሮችን እንድታለሳልስና ነገሩ እንዲራዘም ለሊጉ አጀንዳ
ሳታስይዝ በሽምግልናው እንድትስማማ የመሳሰሉ ግፊቶችን አደረጉ፡፡ የሊጉ ዋና ጸሃፊ ጆሴፍ
አቬኖል፤ፒየር ላቫል እና አንቶኒ ኤደን የእንግሊዝና የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በቀጥታ
ከተክለ ሐዋርያት ጋር ተገናኙ፡፡እሳቸው በዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ ልምድ ከማጣታቸው የተነሳ
ነገሩ ሲጓተት ጣልያን ሁኔታዋን ለማጠናከር ክፍተት ስታገኝ ኢትዮጵያ ከተጣለባት ማእቀብ አኳያ
መሳርያ ማስገባትም ሆነ ራሷን ለመከላከል አልቻለችም፡፡ ተክለ ሐዋርያት ከዚህ በኋላ “ተስፋ
ቆርጠውና ተማረው”ንጉሱን ወደ ሃገርቤት እንዲመልሷቸውና ጣልያንን በመከላከሉ ስራ ለማገዝ
ጠየቁ፡፡በጥር 1935 ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ታዘዙ፡፡ እርሳቸው እንደጻፉት ከሆነ ነገሮች
የአድዋ ጊዜ በ1988 እንደነበሩ ባለመሆናቸው ኢጣልያንም ባላት የተሻለ መሳርያ አማካኝነት ፊት
ለፊት መጋፈጥን በማስወገዷ ለመከላከል የሽምቅ፤የጋዱ፤የፋኖ(የጌርያ) ስልት ተመራጭ መሆኑን
ለዘውድ አማካሪዎች ተናግሬያለሁ ብለዋል፡፡ይህ ሃሳብ(ኢትዮጵያ ከተሸነፈች ኋላ የብዬ ነበር
ካልሆነ በቀር) አማካሪዎቹ የኢትዮጵያን መሸነፍ ይፈልጉ ይመስል ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ግርማቸው እንደሚለው ከሆነ ጦርነቱ ሲጀመር ንጉሱ በሃገሪቷ ካሉ በከፍተኛ ደረጃ በጦርነት
ከሰለጠኑ ባለሙያዎች አንዱ ስለሆኑ አብረዋቸው ወደ ሰሜን እንዲሄዱ ፈልገው የነበረ ሲሆን

71
ጥቋቁር አናብስት

እሳቸው ግን (ጨርጨር) ሄደው ለመዋጋት መርጠው እምቢታቸውን ገልጸዋል፡፡የራሳቸውን ጦር


በማሰልጠንም በሽምቅ ውጊያ ለመዋጋት ከሂርና ወደ አፍደም ተንቀሳቀሱ፡፡ንጉሱ ማይጨው ላይ
ተሸንፈው ንጉሱ ሃገር ጥለው እየሸሹ ወደ ጀቡቲ በባቡር ሲሄዱ አግኟቸው፡፡ አፍደም ጣቢያ ላይ
እቴጌ በባር ስሚያልፉ እንዲቀበሉ በኃይለስላሴ ታዘው ነበር፡፡ ባቡሩ ላይ በመሳፈር አስከ ድሬ ዳዋ
ድረስ አብረው ሄደው ንጉሱን እዚህ ቀርተው የአርበኝነት ትግሉን እንዲመሩ ወይም( ካልሆነ)አንድ
ልጃቸውን ለእንቅስቃሴው በመሪነት እንዲሾሙ ቢነግሯቸው የኋለኛው ሃሳብ ንጉሱን እንደ
ግርማቸው አባባል አስቆጣቸው ንጉሱ ይላል ግርማቸው ራስ ካሳ ጄኔቭ ሄደው ስለኢትዮጵያ
እንዲሟገቱ እስከሚያሳምኗቸው ድረስ ሁለት ልብ ነበሩ፡፡ይሄም ሆኖተክለሐዋርያት "በጠመንጃ
ንጉሱን እንዲቀሩ አስፈራሩ" የሚለው ታሪክእንደ ምራታቸው የራስ እምሩ ልጅ ሚካኤል እምሩ
አባባል የተሳሳተ ሲሆን ባቡሩ ላይ መኖራቸውን እንኳን አላወቁም፡፡ እንደ ተክለሐዋርያት እምነት
የንጉሱ መሸሽ የአርበኝነት ትግሉን ያዳፍነዋል በእርግጥም ውድቀቱን አጣድፎታል፡፡ለማንኛውም
ተክለ ሐዋርያት በጦርነቱ እንዲቀጥሉ ታዘዙ፡፡እሳቸውም ለተወሰነ ጊዜ ከቀጠሉ በኋላ
"በምክትሎቼ" እንደተመከርኩት ይላሉ፡- ወደ ድሬዳዋ ሄደው(እርሻቸውን በአደራ አስጠብቀው)4፟
ፈረንሳዮችን እገዛ ቢጠይቁም19 ገለልተኛነታቸውን ገልጸው እርዳታቸውን ነፍገዋቸዋል፡፡

በዚህ ጊዜ ጣልያኖቹ ሃረርን ስለተቆጣጠሩ እንደሳቸው ወይም ሌሎች ሹመኞች አመለካከት


ተክለሐዋርያት ምንም ማድረግ የሚችሉት ነገር አልነበረም፡፡ በዚህ ምክንያት በከበባ አደጋ ውስጥ
ስለነበሩ ሃገሩን ለመልቀቅ ተገደዱ ይላል ግርማቸው፡፡የኢትዮጵያ ደጋፊ የሆነ አንድ የሱዳን
ኮማንዳስ ታሪስ ቤይ የሚባል መኮንን ሊያቆማቸው ሞክሮ መልሶ ግን ለቋቸዋል፡፡ከዚያ ሁለት
ቀናት ቀደም ብሎ ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው፤ፊትአውራሪ ተሰማ በንቲ፤ደጃዝማች አመዴ፤
ደጃዝማች ነሲቡና ጄኔራል ውሂብ ፓሻ በተመሳሳይ መስመር ሸሽተው ጅቡቲ ገብተዋል ሲል
ልጃቸው ግርማቸው ይናገራል፡፡

እዚያም ተክለ ሐዋርያት ልጅ አንዳርጋቸውን ለሚመጡት ስደተኞች ማረፊያ እንዲያዘጋጁ


ሲረዷቸው ነበር፡፡

ቆይቶም ኃይለ ሥላሴ ተክለሐዋርያትን ወደ አውሮጳ መጥተው የቀድሞ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክርክር
ላይ ያላቸውን እውቀት እንዲያካፍሏቸው በእውቀታቸውም እዚያ ያለውን የኢትዮጵያ አላማ
እንዲረዱ ቢልኩባቸው ተክለሐዋርያት ሃገራቸውን ለማገልገል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው በጅቡቲ
(ኦቦክ)ለአንድ ዓመት ተቀመጡ፡፡

እንደ ግርማቸው ከሆነ ስደተኞቹን የማስተባበሩ ስራ አመርቂ አልሆነም፡፡ወደ ኤደንም ተሻገሩ፡፡


በዛም "የዘይት ኩባንያ"ቢያቋቁሙም (ከሃገር ቤት ገንዘብ ይዘው ሳይወጡ አልቀረም)አረቦቹ ሴራ

72
ጥቋቁር አናብስት

ስላደረጉባቸው ውጤታማ አልሆኑም፡፡በኪሳራ ወደ ጅቡቲ ተመልሰው መለስተኛ የጨርቃጨርቅ


ንግድ ጀምረው እሱም አልተሳካላቸውም፡፡እዚያም ሳሉ ፈረንሳዮች ቀርበዋቸው እያሱ ሚኒሊክን20
በኢትዮጵያ ስለማንገስ አንስተውባቸው የነበረ ቢሆንም ተክለሐዋርያት ይህ ሊሆን የማይችልበትን
ምክንያት ገልጸው ስለነገሯቸው እቅዱ በዚሁ ቀረ፡፡ ተክለ ሐዋርያት ከአርበኞች ጋር አስከ 1939
ድረስ ሲገናኙ ቆዩ፡፡በዚህም ግንኙነት ወቅት ለበርካታ ፖለቲካዊ ስህተቶች ተወቃሽ አድርገው
በተደጋጋሚ ኃይለሥላሴን ይተቹ፤ራስ አበበ አረጋይንና ደጃች ገረሱ ዱኪን ንጉሱ ወደ አልጋቸው
እንዳይመለሱ እንዲቃወሙ ይገፋፉ ነበር ይላል ልጃቸው ግርማቸው፡፡ 21የጣልያን መንግስትም
ለፈረንሳዮች በላከው ጥያቄ የተከለሐዋርያትና የአንድአርጋቸው እጅ ተላልፎ እንዲሰጠው አልያም
ከጅቡቲ እንዲባረሩ በመጠየቁ ተከለ ሐዋርያት (የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ወደ ነበረችው)ማዳጋስካር
ሸሽተው አመለጡ፡፡ እዚያም በገበሬነት ሳይሳካላቸው በችግር ማዚንጋ በምትባል ከተማ እስከ
1952 እ.ኤ.አ ድረስ ቆዩ።²²በኋላ በስቶኮልም በአምባሳደርነት(ወይም የጉዳይ አስፈጻሚ ሳይሻል
አይቀርም) ለነበረው ልጃቸው ግርማቸው ደብዳቤ ላኩ።²³በግርማቸው ጥረትም ፓስፖርት
አግኝተው ወደ ጅቡቲ ለመመለስ ቢበቁም²4 አሁንም ችግር አጋጥሟቸው በኢትጵያዊው ቆንሲል
አሰፋ ለማ ጥበቃ ስር ወደወደቁባት ኤደን ሄዱ፡፡በዚያም ችግር አልለቀቃቸውም።

ግለታሪካቸውን የጻፉትም በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሳሉ ነበር ።25

***

በ1955 በአፈ ንጉስ ዘውዴ ሸምጋይነት ከንጉሱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አስፈቅደውና ቃል


ተቀብለው አዲስ አበባ ውስጥ ተገልለው መኖር ጀመሩ፡፡ራስ አበበ ብዙ ጊዜ በተክለሐዋርያትና
በንጉሱ መሃል ሰላም ለማስፈን ቢጥሩም በልኡል ራስ ካሳ በኩል ጥረቱ (የራስ አስራተ ካሳ አባትና
የ(እውቀት ብርሃን መጽሃፍ ደራሲ1962))ተቃውሞ ገጠመው፡፡ብዙም ሳይቆይ ግን ራስ ካሳ
ስለሞቱ(1965)ተክለሐዋርያት“ መንግስትዎ በተመለሰ ግዜ እንኳን ለአልጋዎ አበቃዎ ስላላልኩዎ
ይቅርታ ያድርጉልኝ”የሚል መልእክት አስይዘው ሽማግሌ ልከው ከንጉሱ ጋር ታረቁ፡፡ወደ ሂርና
እርሻቸው ተመልሰውም በማረስ፤በ1960ዎቹ በቀላዳቸው የነበረውን "የጢሰኝነት አሰራር
ማጥፋት" ጀመሩ፤ነገር ግን የመሬት ከበርቴ መሆንን ይሹ ስለነበር በሐረርጌ 50 ጋሻ መሬት
(2000)ሄክታር ነበራቸው፡፡ይህንም በማከራየት እና ገቢውን በመሰብሰብ ቆዩ፡፡ በኢትዮጵያ አዲስ
የሆነውንም የአቮካዶ ችግኝን መትከል ጀመሩ፡፡ተክለ ሐዋርያት ግብርናን ማዘመን ይፈልጉ ነበር፡፡
ጠንክረው እየሰሩ ቀለል ያለ ምቾት የሌለው ሕይወትን ይገፉ በነበረበት በስተርጅናቸው ወቅት
73
ጥቋቁር አናብስት

ብዙ እንግዶችን በቤታቸው ለማስተናገድ በቅተዋል።ከነዚህም መሃል ለምሳሌ የሌዎ ቶልስቶይን


የልጅ ልጅ ተቀብለዋል ንጉሱ ለቅዱስ ገብርኤል ንግስ ወደ ቁሉቢ ሲያልፉም በ1970 እ.ኤ.አ
ለአንድ ቀን እንግድነት ቤታቸው ጎራ ብለው ነበር፡፡በዛም ወቅት ተክለሐዋርያት ስልጣኑን ለወጣቱ
ትውልድ እንዲያስተላልፉ ሲመክሯቸው ንጉሱ (በምጸት ፈገግታ)ነበር እንደ ግርማቸውና በ22
ዓመት የሚበልጣት ታናሽ እህቱ አልማዝ አባባል፡፡

***

በ1974 እ.ኤ.አ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም በጽኑ ታመው ወደ ድሬዳዋ ሆስፒታል ለህክምና


በልጃቸው ላቀች ተወሰዱ፡፡ተሽሏቸውም ለጥቂት አመታት መኖር ቻሉ።በዚህም ወቅት የሳቸው
እርዳታ ታክሎበት በርካታ ጋዜጠኞች ቃለመጠይቅ አድርገውላቸው እንደ ጀግና ሊስሏቸው ጥረት
አድርገዋል፡፡ልጃቸውም ሆነ እሳቸው ለማሳተም ባልቻሉት ግለታሪካቸውም ተመሳሳዩን ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡በ1977 በድጋሚ ታመሙ።ከአጭር ቆይታ በኋላ በሚያዝያ ወር በእለተ ረቡዕ ወይም
ሃሙስ ህማማት ላይ አረፉ፡፡ምንም እንኳ በሚወዷት ሂርና ቀርተው እዚያው መቀበርን ቢፈልጉም
በድሬ ዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ፡፡

ተክለ ሐዋርያት ግብርና ከንግድም ሆነ ከኢንዱስትሪ በላይ የኢትዮጵያ መሰረት ነው ብለው ያምኑ
ነበር፡፡ይህንንም ለመነን መጽሔት ከስብሃት ገብረአግዚአብሄር ጋር ባደረጉት የግንቦት 1967 ቃለ
-መጠይቃቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን እስከ 90 አመታቸው ድረስ እርሻቸው ላይ ይሰሩ ነበር፡፡ ራስ
እምሩ ከማሞ ውድነህ ጋር በ1966 ባደረጉት ቃለመጠይቅ ተክለሐዋርያት የማይለሳለስ ተፈጥሮ
ይዘው በርካታ ጠላት ፈጥረው ከፖለቲካው ቢገለሉም “የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ወደኋላ
መቅረት”ያሳዝናቸው እንደነበር አይነተኛ ፍላጎታቸውም የኢትዮጵያ አንድነት እንደነበርተናግረዋል፡
፡ተክለሐዋርያትአማርኛ፤ኦሮሚፋ፤አፋር፤ሶማሊ፤ሩስኪ፤ፈረንሳይኛ፤እንግሊዘኛ፤አረብኛና ማላጋሲ
ቋንቋዎችን ይችላሉ።

በርካታ ጽሑፎችንም የጻፉ ሲሆን፤የታተሙት ግን ጥቂት ናቸው፡፡ከላይ ከተጠቀሱት መሃል በእርሻ


ላይ ያዘጋጁት ጥናት ነው ለብቻው መታተም የቻለው፡፡በ1931 ህገመንግስት ላይ ያዘጋጁት
ንግግርም በዝክረ ነገር ላይ በብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ታትሟል፡፡በእርግጥ
ህገመንግስቱ(ከሌሎች ሰዎች ማሻሻያ ጋር)በርካታ ጊዜያት ታትሟል፡፡በአስተዳደር ላይ(በጄኔቭ ሳሉ
የተጻፈ በራሳቸውና በልጃቸው ግርማቸው ይሁንታ)በ(ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ) በ(ማዳጋስካር ሳሉ
74
ጥቋቁር አናብስት

የተጻፈ የመጀመርያው ክፍል በእጄ አለ ይላል ግርማቸው)፤ባለ ሁለት ቅጽ(መንቶችና ምድራዊ ኑሮ


የተባሉ በስደት ሳሉ ጽፈው ለኃይለሥላሴ የላኩላቸው)ሳይታተሙ ቀርተዋል፡፡ምን አልባትም
በግርማቸው እጅ ካሉት ውጪ የቀሩት ጠፍተውም ሊሆን ይችላል፡፡ግርማቸው ግለ ታሪካቸውን
የያዘ ባለ ሁለት ቅጽ መጽሃፍ በተደጋጋሚ የማሳተም ሙከራ ቢያደርግም ሳይሳካለት ሞት
ቀድሞታል፡፡ቤተሰባቸውም የማሳተም ጥረቱን ቀጥለዋል፡፡ምንአልባትም ሃሰን አሊ እንደሚለው
ተክለሐዋርያት “ኑሮዋቸውን ቅር በመሰኘትና በብስጭት ነው የገፉት” ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ
የተመኙትና ሊሰሩት የሞከሩት ነገር ሁሉ ስላልተሳካ ይመስላል፡፡ ለዚህ መወቀስ ካለበት ደግሞ
የሚወቅሱት እራሳቸውን ነው፡፡

***

ግርማቸው ተክለሐዋርያት - ያደገው በ“ስነ ጽሑፋዊ ባህል” በተቃኘ ቤተሰብ ውስጥ ነበር፡፡ከአባቱ
ሌላ አጎቱ ገብረጻዲቅም26የአያቱ ወንድም (ምንአልባትም የአንድ ቤተ ክርስተያን አለቃ)የሆኑት
አብዬም ነበሩ፡፡የግርማቸው የድርሰት ዝና በሁለት መጻህፍት ህትመት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
በአንድ ተውኔትና በአንድ ልብ ወለድ ላይ፡፡በተለይ ልብ ወለዱ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች እንደ አማርኛ ማስተማርያ ተደርጎ ከ 1966 አብዮት በፊት ይቆጠር ስለነበር ተጽእኖው
ይጎላል፡፡በሕይወቱ የመጨረሻ ጊዜያት ግርማቸው እስከ ዛሬ ከሰራቸው በጥራትም ሆነ በብዛት
ይበልጥ በተሻለ ለመጻፍ እንደሚመኝ ነግሮኝ ነበር፡፡የራሱን ስራዎች ጨምሮ ለአማርኛ ስነ ጽሑፍ
ያለው አመለካከት እምብዛም ነው፡፡

***

ግርማቸው ተክለሐዋርያት የተወለደው ሂርና ውስጥ ህዳር 21 1915 ሲሆን አድጎ ለትምህርት
ወደ ድሬዳዋ እስከሚሄድበት የዘጠኝ አመት እድሜው ድረስ እዛው ቆይቷል፡፡አባቱ ተክለሐዋርያት
ከመጀመርያ ወንድ ልጃቸው ብዙ ስለሚጠብቁ ይመስላል ግርማቸው በልጅ አእምሮው
ሲያስታውሳቸው ቆፍጣና፤ሀይለኛ፤ለልጅ ጭንቅላቱ የሚከብድ የጭቆና ቀንበር እንደጫኑበት ሆኖ
ይሰማዋል፡፡ይሄ በአባትና ልጅ መሃል ምንአልባት እድሜ ልካቸውን የዘለቀ ቅራኔ ያስነሳ
ይመስላል።ምንአልባትም ግርማቸው የሟች አባቱን መልካም ዝና ለማናኘት ደፋ ቀና ቢልም ይሄ
ቅሬታ ግን ፈጽሞ የተፋቀለት አይመስልም፡፡ከሌሎች ጋር ሲሆን ተግባቢና ጨዋታ ወዳድ
ቢመስልም የአባቱ ጥብቅነት እሳቸው ባሉበት ቦታ አይናፋር እንዲሆን አስገድዶታል፡፡ከሌሎች
ሰዎች ጋር ግን ቀጥተኛና ሃይለኛ አንዳንዴም ምንአልባትም ከአባቱ የወረሰው የግትርነት ባሕርይ
ይታይበታል፡፡ተክለሐዋርያት የሚታወቁት በጭምትነት ሲሆን ግርማቸው ግን ቀልደኛና ተጫዋች
ነበር፡፡ ²⁷ሃይለኝነቱና ጠበኝነቱ ከአባቱ ጨቋኝ ባሕርይ የተነሳ የመጣ የቅሬታው መግለጫ ሊሆን
75
ጥቋቁር አናብስት

ይችላል፡፡በአዳሪ ትምህርት ቤት ፈረንሳይኛ ለማጥናት በ1917 ዓ.ም ወደ ድሬ ዳዋ እስከሄደበት


ጊዜ ይሄው የአይናፋርነት ባሕርይው ሊለቀው አልቻለም፡፡ ሁለት አመታት በዚያ ካሳለፈ በኋላ
1919 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በአሊያንስ ፍራንሴዝ ለአምስት አመታት የምስክር ወረቀቱን
በ1924 ዓ.ም እስኪያገኝ ድረስ የማታ ትምህርት መርሐ ግብር ተከታተለ፡፡በአብዛኛው ወቅት
ከተማሪዎች የሚልቅ ጎበዝ ሲሆን የፈረንሳይኛ ድርሰቶቹም መምህራኑን ሳይቀር የሚያስደምሙ
ነበሩ፡፡ ከተማሪ ጓደኞቹና ከአስተማሪዎቹ ጋር መወያየት ይወዳል፡፡ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያውቁት
ወልደግዮርጊስ ወልደ ዮሃንስ እንደ ሚናገሩት ግርማቸው መጻፍም ሆነ መናገር ከጀመረ ያለ
መደነቃቀፍ በፍሰት ቃላት የሚጎርፍለት ሲሆን ሃሳቡን ለማረምም ሆነ ለማብራራት አያቆምም፡፡
ይህንን መጽሐፍቶቹን በሚጽፍበት ወቅት ስላለው ፍጥነት ከነገረኝ ጋር ሳነጻጽረውም ሆነ
ስለህይወቱ ባጫወተኝ ወቅት በነበረው ፍሰት ለመታዘብ ችያለሁ፡፡

ከማህተመ ስላሴ ታደሰ የተዋስኩት መጣጥፍ ግርማቸው ትምህርቱን በ1924 ዓ.ም ሲጨርስ
ያቀናው አባቱ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ወደሚያገለግሉበት በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲነው፡፡
የተክለሐዋርያት ግለ ታሪክ የሄዱት በአምባሳደርነት ነው ያስቀምጣል፡፡በፈረንሳይ ሳለም
በስታኒስላስ²⁸ ትምህርተ መለኮት በማጥናት የባችለር ድግሪ (ባካሎርያ)አግኝቷል፡፡ የሚወዳቸውና
የሚልቅባቸው የትምህርት አይነቶች ግን ፈረንሳይኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ነበሩ፡፡”ኃይለሥላሴ ሁለት
(የወርቅ ሜዳልያ)ለጥረቴ እና ኣካዴሚክ ውጤታማነቴ አበርክተውልኝ ነበር፡፡የተለያዩ
መጣጥፎችን መጻፍ የጀመርሁት በዛን ወቅት ነው የሕይወት ታሪኬንም እንዲሁ (በዛ የልጅነት
ወቅት የቀን ውሎ ማስታወሻዎቹን ሳይሆን አይቀርም)”ሲል ይናገራል ግርማቸው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ሃያ ዓመት ከመሙላቱ በፊት 1928አ.ም መጀመርያ ነበር፡፡በወቅቱ


የኢትዮ-ጣልያን ጦርነት መነሻው አካባቢ ሲሆን ግርማቸው በዚህ ወከባ ወቅት የስነጽሑፍ
ስራዎቹን ከፈረንሳይ አጥቷቸዋል፡፡በዚህ ወቅት ግርማቸው ፈረንሳይኛ ቋንቋን በጥሩ ሁኔታ
ያቀላጥፋል፡፡ቆይቶም የጣልያንኛንና የእንግሊዘኛን ቋንቋንም ሊካ በቅቷል፡፡ልክ ሩስኪ ለአባቱ
(በጥልቀት ሳሰላስል ቋንቋዬ ሩስኪ ነው እንደሚሉት) ፈረንሳይኛ ለግርማቸው የመጀመርያ ቀዳሚ
እና ተወዳጅ የውጭ ቋንቋው እንደሆነ ዘልቋል፡፡

ግርማቸው ወደ ደሴ²9 ንጉሱን ተከትሎ ቢዘምትም ገና የ20 ዓመት ልጅ ነው ተብሎ ከአልጋ ወራሽ
መርእድ አዝማች አስፋ ወሰን ጋር ንጉሱ መልሰውታል፡፡ከመመለሱ በፊት ለ3 ወራት ለስዊድናዊው
የጦር አሰልጣኝ በአስተርጓሚነት አግልግሏል፡፡ጣልያኖች ጦርነቱን አሸንፈው አዲስ አበባን
ሲቆጣጠሩ ግርማቸው ጅቡቲ አባቱ ዘንድ ሄደ፡፡እዚያም ብዙም አልቆየም፡፡ከሙቀቱ አንጻር
76
ጥቋቁር አናብስት

(አስምም ስላለበት) ከአባቱ ጋር የህክምና ወጪውን ለመክፈል ባለመስማማታቸው ምክንያት


ስላልተግባቡ ይማረርና ይበሳጭባቸው፤መሰላቸቱንም ይገልጽ ነበር።30ከስድስት ወር በኋላ ወደ
አዲስ አበባ በ1929 ዓ.ም ተመለሰ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ብዙም አልቆየ ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ የካቲት 12 ቀን በግራዝያኒ
ላይ ቦምብ ጥለው ስላቆሰሉት በዚህ ምክንያት በተደረገው አሰሳ ተይዞ ወደ ጣልያን ለ7 አመታት
ግዞት ተላከ፡፡ይህም ከኢትዮ-ኢጣልያ ግጭት በላይ ለሆነ ጊዜ ሲሆን መጀመርያ በሰሜን ሳርዲንያ
አሲናራ ቆየ ፤ቀጥሎ በሃዲስ አለማየሁ ጥያቄ መጥቶ ራስ እምሩን ጨምሮ ሶስቱ በሊፓሪ የሚገኝ
በመሃከለኛው ዘመን በመስቀል ጦረኞች በተሰራ የግምብ ቤት አብረው ተቀመጡ፡፡³¹

ከጥቂት አመታት በኋላ ወደ ትንሽ ካላብርያ ወደ ምትባል መንደር ተወስደው በአንድ ሳጅንና በ10
ወታደሮች እየተጠበቁ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ተቀመጡ። በሊፓሪ ውደ ውጭ መውጣት
ባይፈቀድላቸውም ቢያንስ በግምብ ቤቱ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ይፈቀድላቸዋል፡፡እዚህ አዲሱ
መንደር ላይ ግን እንደዚህ አይነት ነጻነት አይሰጣቸውም፡፡³²

ጣልያን ከኢትዮጵያ ከወጣ ከብዙ ቆይታ በኋላ ጣልያን ውስጥ በነበረው በ(ጄኔራል ዊልሰን
በሚታዘዝና በሞንት ጎምሪ በሚመራው የ8ኛው የብሪታንያ ጦር)ነጻ እንደወጣ ግርማቸው
ያስታውሳል፡፡ወደ ኢትዮጵያ በሰሜን አፍሪካ በካይሮ በምጽዋ አድርጎ አስመራ ሲደርስ
በአውቶቢስ ወደ አዲስ አበባ ተወሰደ፡፡ይህ የሆነው ጣልያን ከኢትዮጵያ ከተባረረች ከ2 ዓመት
በኋላ በ1935 አ.ም ነው፡፡

ልክ እንደ አባቱ ሁሉ ግርማቸው የኢትዮጵያ ነጻነትና አንድነት ያስጨንቀዋል፡፡ በኢጣልያ ያለ


ውዴታ በቆየበት ጊዜያት ሳይቀር የሃገርና የነጻነት ፍቅሩ ይበልጥ ጎልብቶ ነበር፡፡የተወረርነው
አንድነት ስለሌለን መተማመን ስለጠፋ ህዝባችን መሃል የትምህርት አናሳነት ስለነበር ነው ይላል፡፡

***

ከግዞት ከተመለሰ በኋላ የኢትዮጵያን መንግስት እስከ 1966ቱ የመንግስት ግልበጣ ድረስ
አገልግሏል፡፡ የመጀመርያ ስራው በግዜው ትልቅ ስልጣን በሆነው ጋዜጦችና በመረጃ ቢሮ ውስጥ
በድሬክተር ጄኔራልነት ነበር፡፡በነዛ ቀናት ጋዜጦቹ ውስን ሲሆኑ የሚወጡት በሳምንት አንዴ
የሚያነባቸውም ሰው ጥቂት ነበር፡፡ይህ ቢሮ ከጊዜ በኋላ በውጭ ጉዳይ ስር ሆኖ የዜና

77
ጥቋቁር አናብስት

ሪፖርተሮችም በዋና ዋና የክፍለ ሃገር ከተሞች ለዜና ዘገባ ተልከዋል፡፡ በተጨማሪም ሬድዮ
ፕሮግራሞቹን ለማሻሻል ጥረቶች ይደረጉ ነበር፡፡ በ1937 ዓ.ም ግርማቸው በውጪ ጉዳይ
ሚኒስቴር የአውሮጳ ቢሮ ዳይሬክተር ሆኖ ተሾመ፡፡

በመቀጠል ግርማቸው ተክለሐዋርያት ዲፕሎማሲ የስራ መስክ መጓዝ ጀመረ፡፡ከ1942-1947


በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ኤምበሲ ጉዳይ አስፈጻሚ ነበር፡፡ቀጥሎ በብራዚል በተመሳሳይ ስልጣን
ለሶስት አመታት (1947 አስከ 1950 ዓ.ም) በመቀጠል በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን
ለሁለት አመታት (1950-1952 በኢትዮጵያ አቆጣጠር)ቀጥሎ በብላታ ማዕረግ በምስራቅ
ጀርመን ለአንድ ዓመት (1952-1953ዓ.ም) ካገለገለ በኋላ ይህ የዲፕሎማቲክ ስራው ፍጻሜ ሆኖ
ወደአዲስ አበባ ተመልሶ ተጠርቷል፡፡

ወደ አትዮጵያ ተመልሶ የማስታወቅያ ሚኒስትር በመሆን ለ4 አመታት በያዘው ስልጣን ጋዜጦቹን


ወደ እለታዊነት አውርዷቸዋል፡፡አንባቢዎች አስተያየታቸውን የሚገልጹበት አምድም አዘጋጅቶ
ነበር፡፡የሬድዮ ስርጭት ሞገዶችን በማስተካከል የመወያያ መርሐግብራትን ከፈተ፡፡በዚህ ቢሮ
ስራው ማብቂያ አካባቢ በ1957ዓ.ም ደጃዝማች ተሰኝቶ ለአንድ አመት የቆየ ቢሆንም
በአስተዳዳሪነት ወደ ኢሉባቡር በገዢነት ተላከ፡፡

ግርማቸው እንደ አባቱ ብርቱ ሰራተኛ ቢሆንም ቅንጦትና ምቾትን ስለሚወድ በኢሉባቡር ቆይታው
“ተሰቃይቷል”፡፡³³

ግርማቸው በመቀጠል የእርሻ ሚኒስትር ሆነ፡፡ 1958-1960 ዓ.ም ኋላቀሩን ባህላዊ ዘዴዎችን
የሚጠቀመውን(አሁንም ይጠቀማል) ግብርና ለማሻሻል ጠንክሮ ሰራ፡፡ ³4

በመቀጠል የጤና ሚኒስትር በመሆን ከ1960-1962 ዓ.ም ለሁለት አመታት ሲሰራ ሃምሳ አዳዲስ
ክሊኒኮች ሲያስገነባ የነጻ ህክምናንም ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጓል፡፡

በ1962 ዓ.ም የንጉሱ “ልዩ አማካሪ”በመሆን ተሾመ፡፡ደርግ መጥቶ በ1967 እሰከሚያስወግደው፤


ንጉሱ እስኪታሰሩፐ፤ግዛታቸውም አስኪያበቃ ድረስ ቆይቶ በዚያው የስራ ሕይወቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡

***

78
ጥቋቁር አናብስት

ከግዞት ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ግርማቸው በ1938 ዓ.ም በአባቱ መልካም ፍቃድ እሱም
ተስማምቶበት ሽማግሌዎችን በባህሉ መሰረት በመላክ ወ/ሮ ምንትዋብ ሃይለሚካኤልን አገባ፡፡
(ጋብቻ የሃገር መሰረት ነው ብሎ ያምናል)ስኬታማ ያልሆነ ትዳርም እንዲሁ የትዳርን አባላትንም
ሆነ ሃገርን ይጎዳል ሲል ያምን ነበር፡፡ቤተሰቦቹ እሱ በሚፈልገው ሁኔታ አቻው የሆነች ሴትን
ስላጩለትና ስለዳሩት ደስተኛ ነበር፡፡ትዳርን ያህል ውስብስብ ነገርን በዚህ መልኩ በመፈጸሙ
ይደሰታል፡፡መልካም ባሕርይን ከተላበሰችው ባለቤቱም ጋር በጋራ አምስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡
በለጥሻቸው፤(ከተጋቡ ከሶስት ዓመት በኋላ) ዘውዴ፤ወንዱ፤ጉስታቭ(ግርማቸው በስዊድን
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ በተሾመ ቀን ስለተወለደ በስዊድን ንጉስ ስም የተጠራ)
እና መቅደላ ናቸው(ግርማቸው የንጉስ ቴዎድሮስን ለማስታወስ ነው ቢልም የእህቱ ባል የሆነው
ሚካኤል እምሩ ግን የመጽሐፍ ቅዱሷን ማርያም መቅደላዊትን ተከትሎ የተሰጠ ነው ይላል)፡፡
ግርማቸው ልጆቼን መትቼም ሆነ ተቆጥቻቸው አላውቅም ይላል፡፡መልካም ዜጎች እንዲሆኑለት
ይልቁን በምሳሌ ማስተማር እንደሚሻል ሚስቱንና ልጆቹን በጣም እንደሚወድ (ልጆቹም
እንደሚያከብሩት እንጂ እንደማይፈሩት ስሙን ሲጠሩትም በአማርኛ የ(የ እንግሊዘኛው´ዳዲ´አቻ
ቃል ተጠቅመው) እንደሆነ ይናገራል ሚስቱም በሌጣው ስሙ ብቻ ነው የምትጠራው።ይህም በሱ
ደረጃ ላሉ ሰዎች ያልተለመደ ነው።³5እሱም በቁልምጫ ስም ነበር የሚጠራት።ግርማቸው ልጆቹ
ለሃገራቸው ጠቃሚ እንዲሆኑ ለፈርጀ ብዙ ችግሮቿም መፍትሄ በማፈላጉ እንዲረዷት ይመኛል፡፡
³6

ወጣቱ ግርማቸው ስፖርት ይወድ ነበር፡፡ በአብዛኛው በንጉሳውያኑ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትን አደን፤
ግልቢያ ፤ገናና፤ኳስ ጨዋታ ወደኋላ ላይም ቤተሰቦቹን ይዞ ለበአል ከአዲስ አበባ ወጣ ወዳሉ
መናፈሻዎች ይሄዳል፡፡ በአትክልት ስፍራውን በመንከባከብ ራሱን በስራ መጥመድ ስለሚወድም
"ጥቂት ጓደኞች" ብቻ ነበሩት፡፡³7ለዋሾ፣ለቀጣፊ፣ለሰነፍ፣ለስስታም ሰዎች ትእግስት አልነበረውም፡፡
በተጨማሪም የራሳቸው (ፍልስፍና) የሌላቸውን (ፍልስፍና ሲል ለማለት የፈለገው የራሳቸው
አቋም ለማለት ይመስላል) ይጠላ ነበር።ከልጅነቱ ጀምሮ "መምራት "ነው እንጂ "መከተልን"
አይወድም፡፡ አብሯቸው የሰራ የስራ ጉዋዶቹ ብርቱ፤ሰው የሚረዳና ሩህሩህ ሲሆን ሰዎች የመንፈስ
ልዕልና እንዳለው ይመሰክራሉ፡፡ግርማቸው ከቀልደኛነቱ የተነሳ ሰዎች ቻርሊ ቻፕሊን³8 ሲሉ
ይጠሩት ነበር፡፡የዛኑ ያህልም የበታቾቹ እንዲታዘዙት ይጠብቃል፡፡ያሰበውን በነጻነት የሚናገር
ቀጥተኛ ሰው ነበር፡፡ከእርሱ ጋር በማስታወቅያ ሚንስትር አብረውት የሰሩት ሰዎች በፍቅር
የሚያስታውሱትና (በቅርቡ አመታት ከመጡ ምርጡ የማስታወቅያ ሚኒስትር የሚሉት )ሰው ነው፡

79
ጥቋቁር አናብስት

፡ሰራተኞች በስራ ሰአት ለስራ ካልወጡ በስተቀር በቢሯቸው ውስጥ እንዲገኙ ይፈልጋል፡፡ይሄ
ደግሞ በኢትዮጵያ ያልተለመደ ነው፡፡

ግርማቸው ተክለሐዋርያት በኢትዮጵያም ሆነ ፈረንሳይ ተማሪ ሳለ ሁሌም በማንበብና በመጻፍ


ፍቅር እንደተለከፈ ነበር የኖረው፡፡በኢጣልያ በእስር ሳለም ብዙ አንብቧል፡፡የጣልያን
መጻሕፍትንም ለማንበብ ሲል ጣልያንኛንም ተምሯል፡፡ደራሲ ለመሆን የበቃው በንባብና በጠንካራ
ስራው ነው፡፡ በፈረንሳይኛ ችሎታውና በሚጽፋቸውም ድርሰቶች በትምህርት ቤት ሳለ መወደስን
ይወድ ነበር፡፡ ጣልያን ሳለ ከጠቀስነው (የስነ-ማስተማር) መጽሐፍ ውጪ የፍልስፍናና አና የታሪክ
መጻሐፍትን ተርጉሟል፡፡ረቂቆቹ ራሱ ጋር ቢኖሩም ታትመው አያውቁም፡፡እስር ላይ ሳለ
የኮርኒየል፤ራሲን፤ሞሊየር፤ላሮሽፎክ፤ቪክቶርሂውጎ፤ሼክስፒር፤ቶልስቶይና ሌሎችም ካነበባቸው
መጻሕፍት መሃል ናቸው፡፡መጽሐፍ ቅዱስንም አጥንቷል፡፡

***

ግርማቸው ሲጽፍ በፍጥነት ነው፡፡ለማረም ተመልሶም አያውቅም፡፡ቴዎድሮስ የሚለውን ቴአትሩን


ለመጻፍ ከአንድ ወር ያነሰ ግዜ እንደፈጀበት የሚጽፈው ከተፈጥሮ በተሰጠው ስጦታ በቀላሉና
በፍጥነት እንደሆነ፤ይሀም ምናልባት መሰስ አድርገው ከሚጽፉት አባቱ የተወረሰ ሊሆን ይችላል
ይላል ግርማቸው፡፡ሁለቱንም የታተሙ ስራዎቹን ልብ ወለዱን አርአያንም ሆነ ተውኔቱን
ቴዎድሮስን የጻፈው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮጳ ጉዳዮች ሃላፊ ሳለ በ1939 ዓ.ም ነው፡፡
መጻሐፍቱ በተማሩባቸውም ተማሪዎች ሆነ በጠቅላላው አንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅነት አላቸው፡፡
በ"አርአያ" መጽሐፉ ውስጥ ያሉ ድርጊቶች(የአቀንቃኝ ገጸ ባሕርይውም ስም ነው) በውጥረትና
በግጭት ባይሞሉም መቼቱ በከፊል በኢትዮጵያ እና ጣልያን ጦርነት ላይ እና የትግል ወቅት ላይ
ነበር የተመሰረተው፡፡መጽሐፉ ግን እሚደነቅበት ጎኖች አሉት።እነዚህም ቋንቋውና የሚያነሳቸው
ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ገጸ ባሕርይ ማድበብ ላይ ጥልቀት ቢጎለውም ግርማቸው በዚህ መጽሐፉ
ሁሌም እንደሚጓጓለት ለኢትዮጵያ ትምህርት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ችሏል፡፡በአርአያ
በብላቴን ጌታ ኅሩይ የተጀመረውን ከውጭ የተመለሰ የዋና ገጸ ባሕርይ ተማሪና ኢትዮጵያን
የማገልገል የማዘመን ፍላጎታቸውንና የሚገጥማቸውን የተለመደ ተስፋ አስቆራጭ ችግር
የመሳሰሉትን የገለጻ “መሳርያ” ገፍቶበታል።³9በአርአያ ውስጥ አንባቢው የግርማቸውን አባት ተክለ
ሐዋርያትን የሚያስታውሱ ገጽታዎች ማግኘት ይችላል፡፡አባቱ ለመጽሐፉእሳቤዎች ሞዴል ነበሩ፡፡

ተውኔቱ ቴዎድሮስ ግርማቸው ካልከዷቸው ጥቂት ወታደሮች ጋር በ1868 ተዋግተው በጄኔራል


ሰር ሮበርት ናፕየር ሃይል በቁጥር በመበለጣቸው እራሳቸውን በስተመጨረሻ ላጠፉት ጀግና ንጉስ
የነበረውን አድናቆት ያንጸባረቀበት ነው፡፡ተውኔቱ አንድ ጸሐፊ በመነን መጽሄት ላይ በ1966

80
ጥቋቁር አናብስት

እንዳሰፈረው (በውብ አማርኛ የተሰናኘ)ነው፡፡ግርማቸው ቴዎድሮስን ለኢትዮጵያውያን የጻፍኩት


ስለ ነጻነት ለማስተማር ለብሔራዊ አንድነት ትኩረት እንዲሰጡና ሃገራቸውን እንዲወዱ ነው
ይላል።በአርአያ ውስጥም ተመሳሳይ ሃሳቦች አሉ፡፡በግዞት ኢጣልያ ውስጥ እያለ ነው እነዚህ ሃሳቦች
በግርማቸው ውስጥ ስር የሰደዱት፡፡

እንደ እሱ አስተሳሰብ አንድ ደራሲ የሞራል ግዴታዎች ያሉበት ሲሆን ለሃገሩና ለህዝቡ ጠቃሚ
ነው ያለውን መጻፍ፤ጎጂ ነው የሚለውን ደግሞ ማስወገድ ይገባዋል፡፡ሳንሱሩም ቢሆን በጊዜ ሂደት
እየላላ ይምጣ እንጂ አስፈላጊ ነው ባይ ነው፡፡ የፈረንሳይ ባህልና ታሪክን ያደንቃል፡፡ ከፈረንሳይ ስለ
ነጻነት እኩልነት ወዘተ የሚሰነዘሩ የተራማጅ እና የቡርዡዋ በርካታ ሃሳቦችን አምጥቷል፡፡ ከነዚህ
ውስጥ የተወሰኑት በአርአያ ተንጸባርቀዋል፡፡ለባህሉ ያለው ስሜትና መኖርያ ቤቱ ሳይቀር ከፈረንሳይ
እና ከተቀረው አውሮጳ ጋር ያለውን ቁርኝት ያሳብቃሉ፡፡

ከ1966 አብዮት በኋላ ግርማቸው ያለ ምንም ወንጀል ወይንም ጸረ አብዮት እንቅስቃሴ ለ8


አመታት ታስሮ ቆየ፡፡እንዲወጣ የተፈቀደለትም በጤና እክሉ ምክንያት ነው፡፡በሃገር ውስጥና
በውጪ የህክምና እርዳታ ሊያገኝ ሞከረ፡፡ የጉበት ወይም ኩላሊት ነቀርሳ ነበረበት፡፡ ይሄም
በጥቅምት 25 ቀን 1980 ዓ.ም ለሞት ዳረገው፡፡ ሲሞት ወደ 72 አመቱ ይጠጋ ነበር፡፡

ባይታደልም በመስከረም 1980 ግርማቸው ከህመሙ አገግሞ ስለ መጻፍ ያስብ ነበር፡፡ ጽሑፉ
በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ውስጥ የራሱን አሻራ ትቶ አልፏል ፡፡በደራሲነቱም ከፍተኛ አስተዋጽኦን
ካደረጉ ቀደምት የአማርኛ የልብወለድ ጸሐፍት ስር ይጠቃለላል፡፡

***

የግርማቸው ቴዎድሮስ ቴአትር መጀመርያ በመዘጋጃ ቤት ውስጥ በ1939 አ.ም ለመድረክ በቃ፡፡
ቴዎድሮስን ወክሎ የሚጫወተው መኮንን አበበ ሲሆን በቴዎድሮስ 120ኛ የሙት ዓመት
መታሰብያ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 14 1988 በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ያለው ራስ መኮንን አዳራሽ
አግኝቼው እንደነገረኝ ወደገነተ ልኡል ተዘዋውሮ በሚመደረክበት ወቅት ንጉሱና መኳንንቱ
በተገኙበት ሊታይ በቅቷል፡፡በመቀጠልም ወደ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር(ያሁኑብሔራዊ)
ቴአትር ተዘዋውሯል፡፡በመጀመርያ አካባቢ በተደጋጋሚ ቢታይም በቀጣዮቹ አመታት ለአጫጭር
ግዜያት በየአመቱ ይታይ ነበር፡፡የመጨረሻው ግዜ በ1952 በመፈንቅለ መንግስቱ አካባቢ ነው፡፡
በክፍላተሃገራት በበጌምድር፤ ትግራይ፤በወሎ፤በሃረርጌ፤እስከ ጂጂጋ ድረስም ታይቷል፡፡ከቴዎድሮስ
120 ዓመት የሞት መታሰቢያ ጋር በማገናኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል አዳራሽ ለመድረክ

81
ጥቋቁር አናብስት

ለማብቃት ታስቦ የነበረ ቢሆንም “ሳንሱሮች” ጣልቃ በመግባት አስቁመውታል፡፡የታተሙት


የተውኔቱ ኮፒዎች ግን እስካሁን ስለሚሸጡ ማንበብ ይቻላል፡፡በብዙ መኖርያ ቤቶችም ይገኛል፡፡

የተርጓሚ ማስታወሻ

የፊትአውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም ግለታሪክ በ2004

ዓ.ም ታትሞ የወጣ ሲሆን በዚህ መድብል ከተጻፉ ታሪኮች ጋር በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ልዩነት
አግኝተንባቸዋል፡፡
1----
፟ ተክለ ዋዬህ ሳይሆን በግለ ታሪካቸው ተክለ አብዬ ነው የሚለው ገጽ 111

2----
፟ በ1922 ዓ.ም በ179 ገጾች ለህትመት በቅቷል ኦቶባዮግራፊ ገጽ 395
3-----
፟ ባለ አንድ ፎቅ ቤት በፍልውሃ አካባ ባለ መሬታቸው ላይ ሰርተው እንደተቀመጡ ይናገራሉ
ገጽ 401

4-----
፟ ወደ ድሬ ዳዋ በሄዱበት ወቅት ሞልቪየር የሚለው መሬታቸውን አደራ ያሉ እነደሆነ ነው፤
በእርሳቸው ኦቶባዮግራፊ ላይ ግን ንብረትና ሀብታቸውን ወታደሮቻቸው እንዲወስዱ መናገራቸው
ተጽፏል፡፡ መግቢያ xxvi

ማስታወሻ

1)ሌሎች ቆይተው ይሄንን ስለግርማቸውና አባቱ ያደረብኝን ስሜት ተጋርተውኛል

2)ቀኑ ያከራክራል፡፡ የህሩይ ወልደ ስላሴ ወዳጄ ልቤ ከዚያ በፊት ተጽፎ ነበርና የተክለሐዋርያት
ተውኔት ያህል በተውኔትነት ሊወሰድ ይችላል፡፡

3)አማቻቸው ልጅ ሚካኤል እምሩም እንደሚያስቡት ከሆነ ተክለሐዋርያት ከጣልያኑ ጦርነት


በፊት ተሹመው ነበር፡፡ ህሩይ ወልደ ስላሴ በ የሕይወት ታሪክ (ገጽ 56) ላይ ተክለ ሐዋርያት
የጂግጂጋ አስተዳዳሪ ሲሆኑ ተፈሪ አልጋ ወራሽ ሳሉ(1916-1930) ፊትአውራሪነትን ተሹመው

82
ጥቋቁር አናብስት

ነበር ይላሉ፡፡ ለዚህ አይነት ጠቃሚ ላልሆነ ቦታ ያልተለመደ ቢሆንም፡፡ (ምንአልባት ተፈሪ በታላቅ
ወንድምነት ሊረዷቸው አስበው ይሆናል)

4)እንደማስበው ከሆነ የቤተሰባቸው ወደ ክርስትና መምጣትና የመጀመርያው ካህን “ማደግ”


ቆይቶ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ምንአልባትም በዋየህ እና በአብዬ የጀመረ ሊሆንም ይችላል፡፡
ክርስትያን ኢትዮጵያኖች ከዚያ የቀረቡ ዘመዶችን ማግባት ስለማይቻል በእናትና አባታቸው በኩል
እስከ ሰባት ዝርያቸው ድረስ ማጥናት አለባቸው፡፡ የዋየህ ክርስትና የይስሙላ ካልሆነ በቀር
ለልጆቹና ለልጅ ልጆቹ የወላጆቹን ታሪክ እስከሚያቀው ድረስ ይነግራቸው ነበር፡፡ ተክለሐዋርያት
እስከ ሃያታቸው ድረስ በማስታወሳቸው የሆነ የሚደበቅ ጉዳይ እንደአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን
ይኖረው ይሆናል፡፡ከህግ ውጪ መወለድ፤መጣል፤አሳፋሪ ርሃብ፤አብዛኞቹ ያሳፍራል እንደሚሉት
አይነት ወይም ምንአልባት ከነገስታቱ መዋል ከጀመሩ በኋላ የቤተሰቡ የዘር ግንድ ያን ያህል ጥሩ
አይደለም ብለው ስለሰጉ ሊሆንም ይችላል፡፡

5)ሃረርጌና ሃረር በአጼ ምኒሊክ ነበር የተያዙት፡፡ (ወይም በራስ መኮንን ለምንሊክ ) እ.ኤ.አ
በ1887 መስከረም ላይ

6)የአድዋው እልቂት በህጻን አእምሮዋቸው ላይ የፈጠረው ጫናን ተክለሐዋርያት ስለ ጉዳዩ ምንም


ባለመናገራቸው መገመት ይቻላል፡፡

7)ተክለሐዋርያት ሊያገኟት የነበረ የሊዎ ቶልስቶይ የአክስት ልጅ ነበረች በግለ ታሪካቸው


እንደጻፉት

8)ከመደበኛው እድሜ ከፍ ያሉ ቢሆንም ልዩ አስተያየት ተደርጎላቸዋል

9)በባህላዊው የጦርነት ስልት ተዋግተው ያለፉ ወታደሮችን ለማሰልጠን ሞክረው ሳይሳካላቸው


ቀርቶ ይሆናል፡፡

10)ከነዚህ መሃል ከምኒሊክ 3000 ከወንድማቸው ሃብተማርያም 5000 ከሩስያዊቷ አያታቸው


ደግሞ 15000 ሲሆን ገንዘቡ ምንአልባት በማርያ ቴሬዛ ነው የሚሆነው

11)የዚህ ኮሜዲ ስራ በርካታ አርእስት ለማየት ችያለሁ 1.ፋቡላ2. የአንስሶች ኮመድያ


3.የአውሬዎች ኮመድያ 4.የአውሬዎች ፋቡላ5.ፋቡላ የአውሬዎች ኮመድያ 6.ፋቡላ የእንስሶች
ኮመድያ
83
ጥቋቁር አናብስት

12)የዚህ አይነት ስነጽሀፍ ለመጻፍ የመጀመርያ የመሆን ፍላጎት አድሮባቸው ሊሆን ይችላል፡፡
ወይም እያሱ ከስልጣን ሲወርዱ መክሬው ነበር ለማለትም ሊሆን ይችላል፡፡

13)በኢትዮጵያ ጥናት ማእከል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በድጋሚ የታተሙ ስራዎቸቸውን ነው


ለመመልከት የቻልኩት፡፡ ሙሉው የተውኔቱ ጽሑፍ በላፍራንኮ ሪቺ እጅ ይገኛል ይባላል፡፡

14)ከነሱ መሃል አብዱላሂ ሳዲቅ፤ስራህ ብዙ ፤አቡበከር ወዘተ ይገኛሉ

15)ይህ እያሱ በጊዜው ለምን እንደወረዱ የተነሳውን ክርክር መልሶ የሚያሳይ ይሆናል፡፡ በ1916
እያሱን ከስልጣን ለማስወገድ የህዝቡንና የቤተክህነትን ሰዎች ድጋፍ ማግኘት ነበረባቸው፡፡ ክሶቹ
ቢጋነኑም የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች ስም እና ቀናቱ ግን ትክክለኛ አይመስሉም፡፡

16)የገብረእግዚአብሔር ኤልያስ እና የሩዲልፍ ኬ. ሞልቬርን "Prowess, Piety and


Politics. The Chronicle of Abeto Eyasu and Empress Zewditu of
Ethiopia(1909–1930, Cologne 1994"ይመልከቱ።

17)ተክለሐዋርያት ከተማዋ ጭሮ ወይንም ሞቴ ተብላ እንድትጠራ ይፈልጉ ነበር፡፡

18)ዛሬ ላይ ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ገጽታዋ ብዙም አይለይም፡፡ ትኩረት የማትስብና


በድህነት የቆረቆዘች እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች አይነት ናት፡፡

19)ፈረንሳዮች እዚያም ሆነ በሌላው የከተማው ክፍል በባቡር መስመሩ ላይ ተቆጣጣሪ ነበሩ፡፡


የንጉሱን ቤተመንግስት ንጉሱ ሲሸሹ ወርሰውት ነበር፡፡

20)የልጅ እያሱ ሙስሊም እና (እንደ ኢትዮጵያውያን)አባባል የልጅ እያሱ ዘር እንዳይቀጥል ታስቦ


የተኮላሸ ሃረር የሚገኘው ወንድ ልጃቸው

21)የእያሱ ልጅ መልአከ ጸሃይ በጦርነቱ ወቅት በንግስና ተቀብቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከበአለ ሲመቱ
ከአንድ ዓመት አለፍ እንዳለ ሊሞት በቅቷል፡፡ (በኃይለሥላሴ ወኪሎች ተገድሎ ነው ሲሉ ብዙዎች
ያምናሉ)፡፡

84
ጥቋቁር አናብስት

22)በምን ላይ ተመስርተው እንደሆነ ባላውቅም አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ እንግሊዞች


ከጣልያን ወረራ በኋላ ተክለሐዋርያትን ለማንገስ አስበው ነበር ይላሉ፡፡ እንደዛም ከሆነ ያሉበትን
ስለማያውቁ ሊያገኟቸው አይችሉም ነበር፡፡ ተክለ ሐዋርያት በሽሽት ማደጋስካር ነበሩ በወቅቱ፡፡

23)ይሄ ለእሳቸው አሳፋሪ መሆን አለበት፡፡ እንደ ግርማቸው አባባል ከሆነ ጅቡቲ አብረው
በነበሩበት ወቅት ግርማቸው እንዲታከም ሳይፈቅዱ ቀርተዋል፡፡ በተክለሐዋርያት እምቢታ የመጣ
ግርማቸው ወደ አዲስ አበባ ሊመለሱ ችለዋል፡፡ እዚም ሲደርሱ በኢጣልያኖች ተይዘው ለ7 ዓመት
ግዞት ወደ ኢጣልያ ተልከዋል፡፡

24)ከልጆቻቸው አንዱ ማደጋስካር የነበረ ሲሆን እዚያው ቀርቷል፡፡ የማደጋስካር ዜግነት ወስዶ
ማላጋሲ ሚስት አግብቶ በገበሬነት ይኖር ነበር፡፡ ቢያንስ እስከ ጎሪጎሮሳውያን 1988 ድረስ፡፡

25)በግለ ታሪካቸው የራሳቸውን ሚና ማጉላት ብቻም ሳይሆን ለድክመቶቻቸው ማምለጫ


መንገድ ይፈልጉ ነበር በተለይ የጥላቻቸው መጀመርያ ንጉሱ ናቸው፡፡

26)የቤተ ክህነት ትምህርት ነበር የተማረው፡፡ ለቤተክህነት ሰዎች እድሜ ልካቸውን በማንበብ
በቃል በመያዝና በመድገም ለሚማሩት ያልተለመደ ነው) በባህላዊው ዘመን እንደ ባለቅኔ ነበረ፡፡

27)የማስታወቅያ ሚንስትር እያለ የሚነገረው ታሪክ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ቀን ወደ ሚኒስትር


ጽህፈት ቤቱ ሲገባ በጊዜው ልማድ እንደነበረው ሰራተኞቹ ለጥ ብለው እጅ ይነሱታል፡፡ ከነሱ
መሃል አንድ ተቀጣሪ ግን የነሱን ያህል ሳያጎነብስ እጅ ይነሳል፡፡ ግርማቸው አንድ ሰራተኛ ወደ
ቢሮው ጠርቶ ሰውየው ማን እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ በሚኒስትር መስርያ ቤት ውስጥም ቅጥር
እንዳልሆነ ተነገረው፡፡ “ቅጠሩትና 100 ብር ቅጡት” ሲል ግርማቸው ጮኸ፡፡ምንም እንኳን ይሄ
ታሪክ አብሮት በሚሰራው ብርሃኑ ዘርይሁን ቢነገረኝም የፈጠራ ወሬ ሊሆን ይችላል፡፡ ግርማቸው
ላይ እንደዛ አይነት ነገሮች በብዛት ስለሚወሩና ወጣ ባሉት ቀልዶቹ ተወዳጅ ስለነበር

28)በደቡባዊ ፈረንሳይ ከኒስ ብዙም ሳይርቅ የነበረ ሲሆን አሁን ግን የለም

29)እንደ ደስታ ተክለወልድ መዝገበ―ቃላት ከሆነ ትክክለኛው አጠራር ደሴ ነው።

30)ግርማቸው ከአባቱ ጋር የነበረውን ግንኙነት ያማርሩ የነበር ሲሆን በተቻለ ከራሱ ልጆች ጋር
ያለውን ግንኙነት ጥሩ እንዲሆንና እሱ ከአባቱ ጋር የነበረው አይነት በጥላቻ የተሞላ እንዳይሆን
ይጥር ነበር፡፡ቤተሰብ ሲመሰርት ለጤናና ትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው በፍቅር ላይ የተመሰረተ
85
ጥቋቁር አናብስት

ግንኙነት እንዲኖረው ይፈልግ ነበር፡፡ በጣልያን በግዞት ሳለ 3 መጻህፍት በማስተማር ጥበብ


(ስነማስተማር) ዙርያ እንደተረጎመና አባቱ እሱን እንዳንገላቱት እሱም ልጆቹን እንዳያንገላታ
በማሰብ ነው፡፡

31)ግርማቸው ስለዝውውሩ መራር ስሜት ይሰማው የነበር ሲሆን ሃዲስ አለማየሁን ለዚህ ጉዳይ
ይወነጅላል፡፡

32)ያሳለፉትን ትውስታ ባልዘግብ እመርጣለሁ፡፡ በጣም አምርሮ ስለ ሁኔታው መጥፎ ስሜትን


ይዞ ነበር፡፡ ብዙ ክልከላ ለበዛበት ለዚህ ቦታ ሃዲስ አለማየሁን ይወቅስ ነበር፡፡ ራስ እምሩንና
ሃዲስን ከማግኘቴ በፊት በነጻነቱ የላቀ አያያዝ(እስር) ነበረ ይላል፡፡ የነገሩኝ ሃዲስ ከነገሩኝ ወይም
ራስ እምሩ ከጻፉት ጋር ይጣረሳል፡፡ የግርማቸው ታሪክ እውነት ነው ለማለት አይዳዳኝም ፡፡ እንደ
አባቱ ሁሉ ግርማቸውም ሞቅ ያለ ድራማ መሰል ታሪክ የመንገር አዝማሚያ አለው፡፡

33)በአዲስ አበባ ያለው ቤታቸውን ጎብኝቼው የነበር ሲሆን ጥሩና ምቹ ነው፡፡ መናፈሻው በአበባና
እጽዋት ያጌጠ ሲሆን ሳሎኑ በጥሩ እቃዎች ያመረ አውሮጳዊ ዘዬን ተከትሎ የተጌጠ ነው፡፡ በእንግዳ
ክፍሉ እንደ ጎበኘሁት እንደሌሎች የኢትዮጵያ ታላላቅ ሰዎች ቤት ሳይሆን አንዳችም ኢትዮጵያዊ
የእደጥበብም ውጠትም ሆነ ቁሳቁስ አላየሁም ፡፡

34)ምንም እንኳን ማረሻ ለብዙ ክፍለዘመናት በኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉት ሃገራት በላይ
ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ቢውልም አሁንም ተራ ስሪት ያለው ነው

35)ሚካኤል እምሩ ስለ አባቱ ታሪክ ሲያጫውተኝ ትክክለኛውን የስራ መደብ ከትክክለኛው


ሹመት ጋር እያሰናሰለ ነበር፡፡

36)በ1987 ከመሞቱ በፊት ሁሉም ልጆቹ ውጪ ሃገር ነበሩ

37)ከነሱ መሃል አንዱ ጄኔራል አብይ አበበ ነበሩ(ልዕልት ጸሃይን ያገቡ ሲሆን እሳቸው በ1948
ሲሞቱ ለረዥም ጊዜ የጦር ሚኒስትር የነበሩት የሴኔቱ ፕሬዝደንት እና በተለያዩ ቦታዎች ተሹመው
የነበሩትና በደርጉ ህዳር 23 ቀን 1974 ዓ.ም የተገደሉት የደጃዝማች ነሲቡን ልጅ አማረችን አገቡ)

38)አጭር ተክለ ሰውነቱ የአባቱን ያህል ባያጥርም ቅጽል ስሙን ተገቢ ያደርገዋል

86
ጥቋቁር አናብስት

39)ራስ እምሩ ተመሳሳይ ቴክኒክን በወረራው ዘመን ጣልያን ሳሉ በጻፉት መጽሐፋቸው


ተጠቅመውበታል፡፡ ነገር ግን ይሄ መጽሃፍ ብዙ ቆይቶ ነበር የታተመው እንደጎርጎርሳውያኑ
በ1974፡፡ ሚካኤል እምሩ አንድ ጊዜ ከእኔ ጋር አብሮ ሳለ እሱ ሃዲስና ግርማቸው በሊፓሪ ደሴት
አብረው ሳሉ ይህን ቴክኒክና ጥያቄ አንስተው ተወያይተው ይሆናል፡፡ ምንአልባትም ግርማቸው
በእምሩ ሃሳብ ተጽእኖ ስር ወድቆ ሊሆን ይችላል፡፡

87
ጥቋቁር አናብስት

በእምነት ገብረአምላክ
ብስጭት ምኞቱን በአጭር የቀጨበት ደራሲ በእምነት ገብረአምላክ
በ1967ዓ.ም ሲሞት፣በኢትዮጵያ ውስጥ ነበርኩ። ነገር ግን የመተዋወቅ
እድሉ አልገጠመኝም። በዚያን ወቅት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች አማርኛ
የሚማሩበትን"ልጅነት ተመልሶ አይመጣም" የሚለውን መጽሐፉን እዚህም
እዚያም አየው ነበር። ነገር ግን ወዲያውኑ አላነበብኩትም። ይህ መጽሀፍ
በተለይ ለኢትዮጵያውያን ተብለው ከተጻፉ መጽሐፍት መሀል ያነበብኩት
የመጀመሪያው መጽሀፍ ነው። ለውጪ ሀገር ሰዎች አማርኛ ማስተማሪያ ተብለው የሚዘጋጁ
መጻሕፍት፣ ጋዜጣ እና መጽሄትን ከማንበብ አንድ ደረጃ ከፍ ብዬ "ሥነ ጽሑፍ" ወደ ማንበብ
ያደግኩበት አጋጣሚ ነው ። ነገር ግን በ1950ዎቹ መጀመሪያበአንድ የፕሮቴስታንት ቄስ እጅ
በጥብቅ ክርስቲያናዊ ስርአት አድጎ በገዛ እጁ ሕይወቱን ስላጠፋ አንድ ደራሲ አዲስአበባ ውስጥ
ሰዉየሚቀባበላቸውን አሉባልታዎች ሰምቼያለሁ።1

በእምነት ራሱ ከፃፋቸው ይልቅ የተረጎማቸው መጽሐፍት ቢልቁም፣ መጽሀፍቱ በመላው


አዲስአበባም ሆነ በየክፍለ ሀገሩ ተሽጠዋል። ከመጽሐፍት መደብሮች ባሻገር መጽሐፍቱን እንድገዛ
በጉራጌ የጎዳና ላይ መጽሐፍት ሻጮች ግፊት ተደርጎብኛል።2 ስለዚህ ደራሲ ብዙም አልተፃፈም፤
እኔም ታሪኩን ለመፃፍ የተጠቀምኩትን መረጃ ያገኘሁት ከቤተሰቡ ነው።3 ነገር ግን በ1975
በተድላ ወልደሥላሴ ስለደራሲው የተፃፈ አጭር፣ ያልተጠናቀቀ እና አንዳንድ ስህተቶች ያሉት
አንድ ጽሑፍም አንብቤያለሁ።

በእምነት ገብረአምላክ በኤርትራ ሐማሴን ውስጥ አማድር በምትባል መንደር ወይም በአቅራቢያ
በምትገኝ አዲ ኡግሪበተባለች ከተማ በጥቅምት 16 1913 ዓ.ም ተወለደ። አባቱ አማድርን
የለቀቁት በዚህ ጊዜ አካባቢ ነው። አቶ ገብረአምላክ ሩፋኤል እና ወይዘሮ ጋብሬላ ወልደአብ እዝጊ
ከወለዷቸው አስራ ሁለት ልጆች መሀል በእምነት ሁለተኛ ልጅ ነው። የመጀመሪያ አምስቱ ልጆች
ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ የተወለዱት ኤርትራ ውስጥ ነው፣ የተቀሩት (ሶስቱ ሴቶች ናቸው)
የተወለዱት አዲስአበባ ነው።4 ገብረአምላክ ድሀ ገበሬ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ቄስ ነበሩ።5 ልጆቻቸውን ለማሳደግና ለማስተማር ያሉበት አካባቢ ብዙም
ስለማይመች፣ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ አዲስአበባ ለመሄድ ወሰኑ። መጀመሪያ ለብቻቸው ሄደው ስራ
ከያዙ በኋላ ለሚስታቸው ሃብት፣ ንብረታቸውን (እርሻ እና ከብቶቹን) ሸጠው፣ ልጆቻቸውን

88
ጥቋቁር አናብስት

ይዘው እንዲመጡ መልእክት ላኩባቸው። በቃ ካሁን በኋላ ቤታቸው አዲስአበባ ሊሆን ነው።
ገብረአምላክ ሩፋኤል ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ1977 ዓ.ም ነበር።ከመጠን ያለፈ

ጥብቅነታቸውን ወንዶቹ ልጆች አይወዱላቸውም፤ሴቶቹ ግን በትእግስት ከመቀበላቸውም ባሻገር፣


ጥቅሙ እንደሚበልጥ ከእህትማማቾቹ አንዷ ተናግራለች።

በእምነት የተወለደው ገጠር ውስጥ ሲሆን ልጅነቱንም ያሳለፈው እዚያ ነው፣ ትምህርት የጀመረው
ግን ወደ አዲስአበባ ከመጣ በኋላ ነው። አዲስአበባ ከመጡ ወዲህ አባቱ በተፈሪ መኮንን ትምህርት
ቤት የግብረገብ መምህር ሆኑ። ነገር ግን ከትንሽ ጊዜ በኋላ በአንድ የስዊድን ሚሲዮን ውስጥ
ፓስተር ወይም ሰባኪ ሆኑ። አንደኛው ልጃቸው እንደነገረኝ ኤርትራ እያሉም ከነዚህ የስዊድኖች
ሚስዮን ወይም ቤተክርስቲያን ጋር ቅርበት ነበራቸው።በዚሁ መሰረት በአምላክ፣ምናልባትም
ከሚማርበት የዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ወጥቶ ከታላቅ ወንድሙ እና ከሁለት ታናናሾቹ ጋር
በሚስዮኑ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገባ።ነገር ግን ከሶስት ዓመት በኋላ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን
በመውረሯ ትምህርት ቤቱ ተዘጋ።በወረራው ወቅት ትምህርታቸውን በቤት ውስጥ ቀጠሉ ፤
እህታቸው እንደነገረችኝ ልጆቹ ለማወቅና ለማንበብ ጉጉ ስለነበሩ ለማጥናት ብዙም ገፋፊ
አያስፈልጋቸውም ነበር። ነገር ግን ከትንሽ ጊዜ በኋላ በእምነት ራስ ደስታ ሆስፒታል አቅራቢያ
ከሚገኘው የኢጣሊያ ኮንሶላታ ትምህርት ቤት ገባ፤በመጀመሪያ ግን ኢጣሊያንኛ ቋንቋ መማር
ነበረበት። በዚህ ትምህርት ቤት ለሶስት ዓመት ከተማረ በኋላ ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገደደ ፤
ምክንያቱም ይሄንን ትልቅ ቤተሰብ ለማስተዳደር ስራ ይዞ አባቱን ማገዝ ነበረበት። ለአንድ
ጣሊያናዊ ፎቶ አንሺ ተቀጠረና ስለ ፎቶ ማንሳት ጥበብ ተማረ።

የኢጣሊያ ወረራ በ1933 ዓ.ም ካበቃ በኋላ፣ በእምነት በአዲስ አበባ የፖሊስ ሀይልን ተቀላቅሎ
ለስድስት ዓመት ሰራ፤እስከ ሻምበልነት ማዕረግም ደርሷል። ከፖሊስ ሀይል እንደለቀቀ በ1939
ዓ.ም ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ሰሜን አሜሪካ አቀና።ነገር ግን የነብራስካ አየር ሁኔታ
ስላልተስማማው ታመመ።ዶክተሩም ወደ ሀገሩ ቢመለስ እንደሚሻል ነገረው፤እንደተመከረው
በሰሜን አሜሪካ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለአንድ ዓመት ብቻ ከተከታተለ በኋላ ወደ ሀገሩ
መጣ። በ1940 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተመፃህፍት (ከብሔራዊ ሙዝየም ጋር የተያያዘ) ውስጥ
መስራት ጀመሮ ለአምስት ዓመታት ቆየ። ቀጥሎ አስመራ ውስጥ በሚገኘው ባህር ሀይል አገናኝ
መኮንን ሆኖ ለአምስት ዓመት ሰራ። ከዚህም ለቀቀና የላይብረሪ ሳይንስ ለመማር ወደ
አውስትራሊያ ሄደ። ይሄ የሆነው በ1950 ዓ.ም ነበር። አውስትራሊያ ለሁለት ዓመት ቆይቶ
ሲመለስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ገባ። በዛም አማርኛን በዋነኛነት ተማረ። ከዛ ለአምስት
ዓመታት አማርኛ እያስተማረ፣ ማታ ማታ ደግሞ ይማራል። እንደገና ደርቦ ቤተመፃሕፍት ውስጥ
ቀን ቀን ይሰራል። ቤተሰብ ስለመሰረተ ይህ ሁሉ ጫና ከብዶት ነበር።

89
ጥቋቁር አናብስት

ትዳር የመሰረተው ጥር 7 1942 ዓ.ም ሲሆን ባለቤቱ ውህበት ተወልደብርሃን (ራሷን ውቢት ብላ
መጥራት ትወዳለች)ትባላለች።ሶስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆች ስለወለዱ፣ ልጅ ማሳደግና
ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ይጠበቅበት ነበር። ሚስቱ የቤት ውስጥ ስራ እና ልጅ ማሳደግ
እንዲያው በአጠቃላይ የቤተሰብ ሕይወት አትወድም ብለው የሱ ቤተሰቦች ያስባሉ። ስለዚህ
በእምነት ከማንኛውም አባወራ በበለጠ ብዙ ሃላፊነት መሸከም ነበረበት። የሆነው ሆኖ በእምነት
ትምህርቱ ላይ ጎበዝ ነው። በ1958 ዓ.ም በማዕረግ ሲመረቅ ከመጠን በላይ ተደሰተ። በኢትዮጵያ
ቋንቋዎች እና ሥነ ጽሑፍ የትምህርት ክፍል ያገኘው የመጀመሪያ ዲግሪ በፈጠረለት ደስታ የተነሳ
ያን ሌት እንቅልፍ ባይኑ ዝር ሳይል እንዳደረ ቤተሰቦቹ ያስታውሳሉ።

ከተመረቀ በኋላ በተማረበት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር ሆኖ ተመደበ።


የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ወደ ሰሜን አሜሪካ ሄዶ ሁለተኛ ዲግሪውን ከያዘ እድገትና የተሻለ ደሞዝ
እንደሚያገኝ ስለመከሩት በዚሁ መሰረት በ1959 ዓ.ም ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ ወደ ሰሜን
አሜሪካ ሄደ።

ነገር ግን ሁለተኛ ዲግሪ የመያዙ ነገር ሳይሳካ ቀረ። በሰሜን አሜሪካ አንድ ዓመት እንኳን
ሳይሞላው በተፈጠረ የቤተሰብ ችግር ምክንያት ልጆቹን ለማሳደግ ወደ ሀገር ቤት ተመለሰ።
እንደተነገረኝ ከሆነ ሚስቱ ልጆቹን ለብቻዋ ማሳደግ አልቻለችም ወይም አልፈለገችም። ስለዚህ
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ትምህርቱን ሊቀጥል የሚችልበት መንገድ አልነበረም። በሕይወቱ ውስጥ
ሊያሳካቸው ከሚፈልጋቸው ነገሮች መሀል አንዱ በመምከኑ ድብርት ውስጥ ወደቀ። ይህ
“ውድቀት”፣ከቤተሰብ ችግሮቹ ጋር ተደራርቦ ከአቅሙ በላይ ሆነበት፤ ከዚህ በላይ ሊሸከመውም
አልቻለም። ስለዚህ በህዳር 19 1960 ገና በ47 ዓመቱ ሕይወቱን በገዛ እጁ አጠፋ። አዲስ አበባ
ጉለሌ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ እና የቅዱስ ጴጥሮስ (ጳውሎስ ወጴጥሮስ)
የፕሮቴስታንቶች የመቃብር ስፍራ ተቀበረ። ለቤተሰቦቹ ሕይወቱ በዚህ ዐይነት መንገድ ማለፉን
መቀበል ከባድ ሆኖባቸዋል።በሰንበት እስከ መስበክ የደረሰ "ጥሩ ክርስቲያን" ነበር ፤ ደግሞም እንደ
እህትና ወንድሞቹ ብሩህ አእምሮ እንደነበረው ተነግሮኛል።

***

በእምነትን የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ በአንድ አፍ የሚስማሙበት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ለመጽሀፍት


ጥልቅ ፍቅር እንደነበረውና በጣም ታታሪ አንባቢ መሆኑን ነው። ስለዚህ በሰፊው ለማጥናትም ሆነ
ራሱን ለደራሲነት ለማዘጋጀት፣ደመነፍሱ በቀላሉ ወደ ሥነ ጽሑፍ ተሳበ። ዩኒቨርስቲ ውስጥም
ይሁን ሌላ ቦታ፣ ቤተመፃሕፍት ውስጥ ብዙ ጊዜ ያጠፋል። መፃፍ የጀመረው ወደ አውስትራሊያ
ከመሄዱ ከብዙ ዓመታት በፊት ሲሆን።እጁን ያፍታታው በትርጉም ስራ እና በማዛመድ ነበር።
90
ጥቋቁር አናብስት

በሄንሪ ድረሞንድ የተፃፈውን "The Greatest Thing in the World"፣ በ1946


ዓ.ም"በአለም ካለው ሁሉ ትልቁ ነገር" ብሎ ወደ አማርኛ መልሶታል።55 ገፆች ብቻ ያሏት ይህቺ
የግብረገብ መጽሀፍ፣ ከመጽሀፍ ይልቅ በራሪ ወረቀት ለመባል ትቀርባለች። የሚቀጥለው"የአንድ
ቋንቋ እድገት ወይም አማርኛ እንዴት ተስፋፋ" ተብሎ የተዘጋጀው መጽሐፉ መጀመሪያየተዘጋጀው
በጣሊያንኛ ነበር።የታተመው በ1947 ዓ.ም ነው። በ1948 "የልጆች ሁኔታ በቤትና በትምህርት
ቤት" ተከተለ።

በ1949በእምነት ራሱ ፈጥሮ፣ከምናቡ አፍልቆ የፃፈው ብቸኛ የልብወለድ ስራው "ልጅነት ተመልሶ


አይመጣም" ታተመ።ይህ መጽሐፍ በትምህርት ቤት ለማስተማሪያነት ስለዋለ፣ ትምህርት
ሚኒስቴር ደጋግሞ አሳትሞታል።ከፃፋቸው፣ ከተረጎማቸው ወይም ካዛመዳቸው መጽሀፍት ሁሉ
ይህንን አብልጦ መውደዱ ብዙ የሚያስገርም አይደለም። ወዲያውም በሰፊው በመነበቡ፣
በሕዝቡም ዘንድ ይሁን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት አገኘ። ወደፊት ደራሲ
የሚሆኑ ወጣት አንባቢዎች ላይ ተጽዕኖ ሳያሳርፍ አይቀርም።

ከላይ የተጠቀሱት መጽሐፍትን ካዘጋጀ በኋላ በእምነት እረፍት ቢጤ ወሰደ። ከዚያ መልስ የሉዊጂ
ፒራንዴሎ ስራዎችን ተረጎመ፤ይህ መጽሀፍ የታተመው በ1960 ከተርጓሚው ሞት በኋላ ሲሆን
አሳታሚው የኢጣሊያ ባህል ተቋም ነው።ሌሎች ስራዎቹን በተመለከተ በ1955 ዓ.ም በታተመው
በ"The Ethiopian Observer" ቁጥር ሶስት፣ ቅጽ ሁለት ላይ በታተመ "Foreign
Borrowings in Amharic" የተሰኘ መጣጥፍ የአማርኛ ቋንቋ እድገት ላይ ለመስራት ትልቅ
ፍላጎት እንደነበረው ያሳያል።

በእምነት ገብረአምላክ አንባቢ እና ጸሐፊ ብቻ አልነበረም። በትርፍ ጊዜው አናጢነት ይሞካክራል።


“ስለዚህ እያነበበ ወይም እየፃፈ ካልሆነ፣ መዶሻና መጋዝ ይዞ ከእንጨት ጋር እየታገለ ነው ማለት
ነው።” ቅን እና ትጉህ በመሆኑ በጓደኞቹም በስራ ባልደረቦቹም የሚወደድና የሚከበር ሰው ነበር።
በእምነት የሚናገረውን ነገር “ሰዎች ወደዱት አልወደዱት ብሎ ሳይጨነቅ የሚሰማውን ፊትለፊት”
እንደሚነገር ይወራለታል።“ልጆች በጥቂት ውሀ ንጽህናቸውን እንዲጠብቁና አዘውትረውም
እግራቸውን እንዲታጠቡ ይመክራል። ቤተክርስቲያን ውስጥ እየሰበከ እንኳን ስለሚሸት ጫማ
አስጸያፊነትበግልጽ ይናገራል።”8"ኢትዮጵያውያን ምክር አይወዱም"፤ስለዚህ በደንብ
የሚታወቅበት የንጽህና ጉዳይ ላይ ያለው የማያወላዳ አቋም "ሀይለኛ" የሚል ቅጽል አሰጥቶታል።
በእምነት “ሀሜት እና ስራ መፍታት አይወድም ነበር።” ጥቂት ጥሩ ጓደኞች ቢኖሩትም መጠጣት
91
ጥቋቁር አናብስት

(በተለይ ቢራ)፣ “መረጃ መለዋወጥ” (ሀሜትና አሉባልታ) እንዲሁም “ሴት ማሳደድ”


እንደሚወድዱ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን “ከሰዎች ጋር መቀላቀል” አያዘወትርም።

በእምነት መጽሐፍቱን በሚጽፍበት ወቅት ጠንክሮ ስለሚሰራ፣ ሲታተሙ የድካሙን ውጤት ማየት
በጣም ደስ ይለዋል። ለመጽሐፍቱም ሆነ ለሕይወት ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን የሚያገኘው
ከመጽሐፍት በመሆኑ፣ ሰዎች እንዲያነቡ ዘወትር ይመክራል። ሰዎች ግን “በራሳችን ጊዜና ሕይወት
ስለምናደርገው ነገር አያገባህም ”ብለው እንደሚመልሱለት ተነግሮኛል። እሱም ራሱ፣ በሕይወት
ዘመኑ በርካታ መጻሕፍትን የሰበሰበ ሲሆን፣ ለሰበሰባቸው መጽሐፍት ትልቅ ቦታ ይሰጥ ነበር።

ጥልቅ ምኞት ስላለው፣ ጠንካራ ሰራተኛ ስለሆነ፣ ሀሳባዊነት ስለሚያጠቃው፣ ምናልባት ደግሞ
ጥብቅ አስተዳደግ ስለነበረው ሳይሆን አይቀርም ሽንፈትንና ውድቀትን መቀበል ይከብደው ነበር።
በመጨረሻ ከሕይወት ቤት በገዛ እጁ ሕይወቱን በማጥፋት ወጣ። ነገር ግን ወደ መጨረሻ አካባቢ
ጭንቅላቱ በትክክል መስራቱ አጠራጣሪ ነው ይላሉ ቤተሰቦችና ወዳጆቹ ፦ ልጆቹን ለመንከባከብ
ሲል ስራውን አደጋ ላይ ጥሎ ትምህርቱን ከአሜሪካ አቋርጦ የተመለሰ ሰው፣ እንዴት ሕይወቱን
በማጥፋት ልጆቹን ያለ አባት ያስቀራል?

ከ1966 ዓ.ም አብዮት በፊት በመላው ኢትዮጵያ በስፋት የተሰራጨው አንድ ልብወለዱ አንድዬ
ትውልድ ላይ ተጽዕኖ ሳያሳርፍ አይቀርም፤ በእርግጥ ይህ ልብወለድ አሁን አንባቢ የለውም።
ከ1966 በኋላ ታትሞ አያውቅም፤ ከዚህ ወዲህም ላይታተም ይችላል። ነገር ግን መጽሐፉ አሁንም
በጎዳና ላይ ወይም በትናንሽ የግል መጽሐፍት መደብሮች ይገኛል። የትርጉም ስራዎቹም ዳግም
ላይታተሙ ይችላሉ። ወደፊት በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ እድገት ውስጥ "ልጅነት ተመልሶ አይመጣም"
በሚለው ልብወለዱ ሲታወስ ይኖራል።

ማስታወሻዎች

1) የበእምነት ወንድምም ራሱ ከሁለት ዓመት በኋላ ራሱን ሲያጠፋ ሀሜት በረከተ። የበእምነት
ልጅና (የኔም የቀድሞ የስራ ባልደረባዬ) ከፍቅረኛው ጋር በተፈጠረ ግጭት እሷን ተኩሶ ገድሎ
ራሱንም በማጥፋቱ ሰዎች እዚህ ቤተሰብ ላይ በወረደው መአት ተሳቀቁ።

2)ይህ ከ66ቱ አብዮት በኋላም ቀጥሎ ነበር። በ1970ዎቹ በሙሉ የመጽሐፉ ቅጂዎች
በአዲስአበባ አውራጎዳናዎች ላይ ለሽያጭ ይቀርቡልኝ ነበር።

92
ጥቋቁር አናብስት

3)አብዛኛውን እርዳታ ያገኘሁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምትሰራው የበእምነት እህት ነበር ፤ ነገር
ግን እሷም ቢሆን ጥያቄዎቼን ከመመለሷ በፊት ሌሎች የቤተሰብ አባላትን ታማክር ነበር።

4)አዲስአበባ ከመጡ ወዲህ የወለዷትን የመጀመሪያ ሴትልጅ"ኤርትራ" ብለው ሰየሟት፤ ይህም


ወላጆቿ ለትውልድ ቦታቸው ያደረባቸውን ናፍቆት ለመግለጽ ነው። ነገር ግን ከወንዶች ልጆቻቸው
መሀል አንዱን "ቴዎድሮስ" ብለው በጀግናው፣ ጦረኛ ንጉሥ ሲሰይሙ ኢትዮጵያዊ
አርበኝነታቸውም ተገልጧል።

5)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቄሶች የሚቀበሉት ትምህርት መጻፍና ማንበብን እንዲሁም


ጥቂት የፀሎት መጽሀፍትን በቃል ለመያዝ የሚያስችላቸውን፣በዋናነትም የግእዝ
ድርሳናትንናሃይማኖታዊ መጽሐፍትን ለመረዳት የሚያስችላቸውን ትምህርት ነው። እነዚህም
መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴማርያም የመሳሰሉት ናቸው። ብዙዎቹ ኑሮአቸውን የሚመሩት በግብርና
ነበር ፤ ይህም አንድም በራሳቸው መሬት አሊያም በ1967 ትርፍ መሬት በአዋጅ ከመወረሱ በፊት
በጣም የተለመደ በነበረው በቤተክርስቲያን መሬት ላይ ነበር።

6)ይህ አባባሉ የሚያመለክተው፣ ህሊናው ውስጥ የኖረ ጉዳይ መኖሩን የሚገልጥልን ፍሩይዳዊ
ምሁር ማግኘታችንን እንጃ፤ ምናልባት በልጅነቱ ሳያደርገው ቀርቶ የሚፀጽተው ነገር ነበር ማለት
ይሆን?

93
ጥቋቁር አናብስት

ማሞ ውድነህ
የስለላ የስነ ማህበረሰብዊ ታሪኮችና ልብወለዶች ደራሲ ተርጓሚ
የኢትዮጵያ ጸኃፍትን አጫጭር ግለታሪኮች የያዘ መድበል
ለማዘጋጀት ሳስብ ገና ከመጀመርያው ቃለመጠይቅ
ካደረኩላቸው ደራሲያን መሃል ማሞ አንዱ ነበር፡፡እንደ እውነቱ
ከሆነ ማሞ የምሰራውን ሲሰማ እራሱ መጥቶ ነበር ለበርካታ
ጊዜያት ስለ ህይወቱና ስራዎቹ ለመጨዋወት የበቃነው፡፡

ማሞ ውድነህ ቲላላ በምትባል አካባቢ ዲሃና ወረዳ ውስጥ በዋግ


አውራጃ ወሎ በግምት በ1927 ዓ.ም አካባቢ በጥቅምት 12
ተወለደ፡፡ ስለ ተወለደበት ቀንም ስመ ክርስትናው
ገብረሚካኤል ተሰኘ፡፡እናቱ አለማየሁ ብላ ትጠራው የነበር ቢሆንም እስከ አሁን የሚጠራው
ግን አባቱ ባወጡለት ስም ማሞ ነው፡፡እንዳጨወተኝ ከሆነ አባቱ የሞቱት ማሞ የአምስት አመት
ልጅ ሳለ ነው፡፡ (ከጣልያን ጋር በተደረገ ጦርነት ቆስለው የነበረ ቢሆንም እስከ ጦርነቱ ማብቂያ
ድረስ አልሞቱም ነበር፡፡በግሪጎርያን አቆጣጠር በ1934 ከተወለደ ይህ ማለት ማሞ ቀደም ብሎ
ነው የተወለደው አልያም አባቱ ሲሞቱ ትንሽ ተለቅ ያለ ነበር ማለት ነው)እናቱ ደግሞ በ9 አመቱ
ሞተችበት፡፡ የእናቱ አባት ከሰቆጣ እስከ ትግራይ በበቅሎ በመመላስ ብሎም እስከ አስመራ ድረስ
የሚዘልቁ ሃብታም ነጋዴ ነበሩ፡፡የማሞ እናት መጀመርያ ገበሬ ብታገባም በአመታቸው
ሳይወልዱ ተለያይተዋል፡፡በመቀጠል 'ነፍጠኛውን' የማሞን አባት አገባች፡፡ገበሬና ወታደር
ነበሩ፡፡መጀመርያ ከበለሳ አካባቢ ነበር የመጡት፡፡በጣልያን ወረራ ወቅት አርበኛ የነበሩ ሲሆን
ከነሱ ጋር በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ መቁሰላቸውን ማሞ ይናገራል፡፡የማሞ የእናቱ አባት
ጣልያን ሰቆጣን ሲደበድብ ገድሏቸው ንብረታቸውንም (ሶስት ወይም አራት ቤት
ነበራቸው)አጥፍቶታል፡፡አባቱ አባት ቀኛዝማች ተፈሪ ደግሞ በለሳ ሳሉ በጣልያን ተገድለዋል፡፡
ቤተሰባቸውም ተበታትኖ በየመንደሩ ተዘራ፡፡ማሞ አባቴ ጣልያንን ለአምስት አመታት ያህል
ተዋግተው ነው የሞቱት ይላል፡፡የጊዜ ክፍተቱ ግን ቀጥሎ ስለ እሳቸው ከመሞታቸው በፊት
በወረራው ወቅት የመንደሩ የጎበዝ አለቃና ዳኛ ለመሆን ፍላጎት ስለማሳደራቸውና በመንደሩ
ባለ የጣልያን አፈቀላጤ ድጋፍን ለማግኘት በበተነው የማርያ ትሬዛ ጠገራ ብር ሃይል ነው
የተሸነፉ ብሎ ከሚናገረው ታሪክ ወቅት ጋር ለማጣጣም ትንሽ ያስቸግራል፡፡ይሄ በማሞ አባትና
በተመረጠው ዳኛ መካከል ቅሬታ በማስነሳቱ የተመረጠው ዳኛ ተከታዮች የማሞን አባት
በመንደሩ ገላጣ ስፍራ ላይ ሳይታጠቁ ገደሏቸው ፡፡

94
ጥቋቁር አናብስት

ማሞ የቄስ ትምህርቱን አምደ ወርቅ በምትባል የወረዳው ዋና ከተማ ጀመረ፡፡መጻፍ ማንበብና


ጸሎት መድገም የጀመረው እዚያ ሳለ ነበር፡፡“እንደ ወላጄ ነበረች” ከሚላት ከአባቱ እህት ጋር
ነበር የቆየው፡፡አባቱ “ቄስ ትምህርት ቤት አይገባም ፈሪ ይሆናል ተኳሽ አይሆንም”ብለው
ያከላክሉ ነበር፡፡ከአባቱ ትዝ የሚለው ነገር ቢኖር መሳርያ እንዲተኩስ ተሰጥቶት ተኩሶ በመሳቱ
በጥፊ መመታቱን ነው፡፡ትምህርት በጀመረበት ወቅት አባቱ ከሞቱ ጥቂት አመታትን አስቆጥረው
ነበር፡፡ ልክ ዘጠኝ አመት ሲሞላው አክስቱ የራሷን ልጅ ለእረኝነት አስቀርታ እሱን ግን ጎበዝ
ነው ጸሃፊ መሆን ይችላል ብላ ስላሰበች ወደ ትምህርት ቤት ላከችው፡፡

ማሞ በቄስ ትምህርት ቤት ለአራት ወይም አምስት አመታት ቆየ፡፡አስራ ሶስት ወይም አስራ
አራት አመቱ አካባቢ ሲደርስ መዝሙረ ዳዊትን በቃሉ መውጣት ጀመረ፡፡ህይወት በቄስ
ትምህርት ቤት ከባድ ነበር ደበሎ ለብሶ አኩፋዳ ተሸክሞ በቀፈፋ ለሁለት አመታት ቆይቷል፡፡
አክስቱ ይህንን በመጥላት ከትምህርት አስወጣችው፡፡ማሞ ግን ይሄ ነገር “አስተማሪ”ነበር
ይላል፡፡ “በአካል ከማጠንከሩም በላይ ከሰው ያግባባል፤ ችግር ያስተምራል ፤ ምግብ ማግኘቱም
ያን ያህል አያስቸግርም፡፡ ቀፈፋ ራስን ለመስዋእትነት ማቅረብን ያስተምራል መንደርተኛውንም
የቆሎ ተማሪዎችን እንዲደግፉ ያስለምዳል፡፡ተማሪን መርዳት (ለነፍስ እንደማደር)ይቆጠራል
ተብሎ ስለሚማሩና ቤተክርስትያንም ሲመጡ ልዩ መስተንግዶ እንዲደረግላቸው ስለሚሹ እኛን
ለመዘከር ይገደዳሉ፡፡የእለት እንጀራችንን ማግኘትን መካፈልን ያስተምራል፡፡እንደ አውነቱ ከሆነ
ትምህርቱን ወድጄው ነበር ስነ ምግባራዊ ሃላፊነቶችን ግብረ ገባዊ ህግጋትን ለሰው ዘር ሁሉ
መልካም መሆንን የመሳሰሉ በዘመናዊ ትምህርት ቤቶች የማይገኙ ነገሮችን ያስጨብጣል፡፡
አማርኛ በትክክል መጻፍ ማንበብን፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እንዴት ሃገሪቷን
እንዳገለገለች ያየሁበት ቀሪ ህይወቴ ላይም ተጽእኖ ያሳደረ፤መጸለይ ለቤተሰብም ሆነ ለሃገር
የሃላፊነት ስሜት ማሳደርን፤ ታማኝነትን፤ ሰው ማክበርን፤ የተማርኩበት ብቸኛ ስፍራ ነው”
ይላል ማሞ፡፡

በትምህርት ቤት ሳለም ሆነ ከወጣ በኋላ በአንድ ዘመዱን ባገባ የወረዳ ገዢ ይበልጥ መጻፍና
ማንበብ እንዲችል ይረዳው እንደነበር ያክላል፡፡

በ1939 ወይም በ1940 ዓ.ም አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ሰቆጣንና አካባቢውን ሲጎበኙ 20
የሚጠጉ ልጆችን ደሴ ወስደው እንዲያስተምሩ ተሰጣቸው፡፡የተሰጡት ልጆች የተሰዉ የአርበኞች
ልጆች ሆነው አባቶቻቸው በጦርነት የሞቱ ናቸው፡፡የማሞ መንደር 20 ኪ.ሜ አካባቢ ይርቅ
ስለነበር የመመረጥ እድል አላገኘም፡፡አክስቱ ግን ይህን ወሬ ሰምታ ኖሮ ሰዎችን እዚህ ከቆየ
ሰውም አይሆን ይልቅ ለራሱም ለዘመድም እንዲያገለግል ደሴ ከልዑል አልጋ ወራሽ ጋር
ውሰዱልኝ ስትል እንዲረዱት ለመነችለት፡፡ከላይ የጠቀስነው ዳኛ ዘመዱ ግን ደሴ ገብቶ ልዑል

95
ጥቋቁር አናብስት

አልጋ ወራሽ ጋር ላይሳካለት ይችላል ካልተሳካለት ደግሞ ዱርዬ ይሆናል ይልቁን እዚህ እኔ ዘንድ
ጸኃፊ ቢሆን ይሻላል ሲል አከላከለ፡፡ ስለዚህ ማሞ እሱ ዘንድ ቆየ ከከተማ ከተማ በመዘዋወር
ራቅ ሲል እስከ ኮረም ድረስ ለስራ ይሄዳሉ፡፡ ዳኛው ለማሞ እንደ ጽህፈት አስተማሪ በመሆን
የጸሃፊነትን ስራ አስለመደው፡፡

አንዴ ገበያ ቦታ ደረሱ እኚህ ዳኛ ማሞን በመጥራት ከሰንደቅ አላማችን ጋዜጣ ላይ ስለ


´መልካሙ ገበሬ´ግጥም እንዲያነብ ነግረውት ሶስቴ በማንበቡ ከሰዎች አድናቆትን"ሊቁ"የሚል
ሙገሳን አገኘ፡፡ይህ ማበረታቻ ማሞን ይበልጥ እንዲጽፍ እንዲያነብ አተጋው፡፡የድርሰት
ህይወትን ለመጀመርያ ጊዜ እንዲመርጥ መነሾው፤በጋዜጦችም ላይ ፍላጎት እንዲያሳድር ገፊ
መክንያቱ ሆነ፡፡ ጋዜጣን በጊዜው ከዳኛና ከአስተዳደሪው ውጪ ማግኘት ብርቅ ነበር፡፡
በነጋዴዎች በአህያ ተጭኖ ከኮረምና ሰቆጣ በሶስት በአራት አልያም በስድስት ወር ቢመጣ ነው፡፡
ማሞ በሩጫ በመሄድ በሳምንት ሁለቴ የሚታተመውን ሰንደቅ አላማችን አልያም ሳምንታዊውን
አዲስ ዘመን ካለ ይጠይቃል፡፡በዚህ ጊዜ ነበር የጋዜጠኝነት ፍላጎት በውስጡ እየተጸነሰ
የመጣው፡፡

ከእለታት በአንዱ ቀን ማሞ ማንንም ሳይሰናበት ብን ብሎ ከአምደ ወርቅ ወደ ሰቆጣ ብሎም


እስከ ኮረም ከሚዘልቁ ነጋዴዎች ጋር ጠፋ፡፡ኮረም ላይ (የዋጉ ገዢ የዋግ ሹም ወሰን መቀመጫ)
የአስመራ ወይም የትግራይ ጳጳስ እዚያ መሆናቸውንና ለጥቂት ቀናት እንደሚቆዩ ሰማ፡፡ማሞ
ኮረም በደረሰ በነጋታው ደግሞ ጳጳሱ ተማሪዎችን በመባረክ ለዲያቆንነት እንደሚያበቁ ሰምቶ
ማሞ ቡራኬውን ተቀብሎ ለመዛቆን ተሰለፈ፡፡ግን ሊደርሰው አራት ወይም አምስት ሰው
ሲቀረው ዝናብ መዝነብ ጀመረና ጳጳሱ ለመጠለል ወደ አንድ ታዛ አቀኑ፡፡ዝናቡ የሚያባራ
ዐይነት ስላልነበር ተማሪዎቹ ወደ የቤታቸው ሄዱ ማሞም ቡራኬውን ሳያገኝ ቀረ፡፡ ጳጳሱም
ኮረምን ለቀው ወጡ ማሞ መዛቆኑን ለእኔ ባይለው ይሆናል በማለት ተስፋ ቆርጦ ተወው፡፡

አንድ ሁለት ሳምንት በኮረም ከጓደኞቹ ጋር ከቆየ በሁዋላ የአውራጃው አስተዳዳሪ ዋግሹሙን
የማየት ሃሳብ ብልጭ አለለት፡፡ጠባቂዎችን ማለፍ አልቻለም፡፡ስለዚህ ዋግሹሙ ወደ ቢሮው
ለመሄድ ከቤታቸው ሲወጡ እስኪያገኛቸው ድረስ ጠበቆ እራሱን የአቶ ውድነህ ልጅ ነኝ ሲል
አስተዋወቀ፡፡ግን የተጠቀመው በታወቀው ስም ውዱ ተፈሪ ብሎ ነበር፡፡አባቱን የሚያውቁት
ዋግሹም በጣም ተገርመው እዚያ ምን እንደሚያደርግ ጠየቁት፡፡ 2 ማሞ አልጋ ወራሽን
ቢያገናኙኝ ትምህርቴን እንድቀጥል እንዲረዱኝ እፈልጋለሁ ቢልም አልጋ ወራሽ በወቅቱ አዲስ
አበባ ሄደው ስለነበር ዋግሹም እንደማይቻል ነገሩት፡፡ይልቁንም ማሞ አብሯቸው እየሰራ
ከተቻለም እየተማረ እንዲቆይ ነገሩት፡፡ከዚህ በኋላ (እንደ ተወዳጅ የቤት ልጅ)ከዋግሹም ጋር
በየቦታው አብሮ መዞር ጀመረ፡፡ትምህርቱን ግን መቀጠል አልቻለም፡፡ትምህርቱን መቀጠል

96
ጥቋቁር አናብስት

እንደሚፈልግ ለዋግሹሙ ሲናገር ዋግሹሙ አዲስ አበባ ካለች ሚስታቸው ዘንድ ለቤት ልጅነት
ላኩት ፡፡ማሞም በዚህ አድል ተደሰተ አዲስ አበባም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት፡፡

ከትንሽ ወራት ቆይታ በኋላ ልኡል አልጋ ወራሽ የት እንደሚኖሩ አጣርቶ የአስተምሩኝ
ተማጽኖውን አስገባ፡፡የዋግሹሙ ሚስት ይህንን ከትንሽ ወራት በኋላ ስትሰማ ለስራ ነው እንጂ
ለመማር እንዳልመጣ ነግራው በጣም ተናደደችበት፡፡ማሞ አብሮ ለመቆየት ቃል ቢገባም
በሳምንቱ አካባቢ ቆይቶ ጠፍቶ ሄደ፡፡

የቀጨኔ መድሃኔአለም ሊቀ ካህን ጋር ሄዶ ማረፍያ ተሰጠው፡፡እዚህ አካባቢ ከዋግ የመጡ ሰዎች


በብዛት ይገኙ ነበር፡፡አንድ ቀን ከላስታ አውራጃ የመጡ ሴት አንዲትን(በመሃከለኛ እድሜ ላይ)
ያለች ሴት ሊጎበኙ ሲሄዱ አስከትለውት ሄዱ፡፡ሴትይዋ ለማሞ ዘመዱ ሆና ተገኘች፡፡ወደ
ደጃዝማች አድማሱ ወሰን (በጣም የታወቁ ወደ ኋላም ዋግሹም የሆኑ ግለሰብ) ዘንድ ይዛው
ሄደች፡፡

ማሞ ለጥቂት ጊዜ አብሯቸው ከዘለቀ በኋላ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲያስገቡት ጠየቀ፡፡ቃል


ቢገባለትም ዳሩ እርዳታቸውን ግን አላገኘም፡፡ልኡል አልጋ ወራሽም ዘንድ አላቀረቡትም፡፡ማሞ
እኚህ ሰውዬ ቤት እያለ ለማጥናት ቢሞክርም ተጠግቶ የሚኖር ብዙ ዘመድ አዝማድ ስለነበር
የሚቻል አልሆነም፡፡

ማሞ ከዚያም ጠፍቶ ወደ ቀጨኔ መድሃኒአለም ተመለሰ፡፡ እዚያም ሊቀ ካህኑ መጀመርያ


ካስተዋወቁት ሴትዮ ጋር ሰነበተ፡፡በዚህ ጊዜ ለንጉሱ እርዳታቸውን በመፈለግ ተስፋ የቆረጡ
ሰዎች በጊዜው እንደሚያደርጉት መኪናቸው ሲያልፍ በመስኮት በኩል በወረቀት ጽፎ
በመወርወር ለማመልከት ቢሞክርም አልተሳካም ነበር፡፡

ከአንድ አመት ትግል በኋላ ቀንቶት ልኡል አልጋ ወራሽ ዘንድ ቀርቦ ማመልከት ቻለ፡፡በዛ ወቅት
15 አመቴ ነበር ይላል ማሞ(ምን አልባትም ሳይሳሳት አይቀርም ከሌሎቹ ከላይ ከተሰጡት ቀናት
ጋር በቄስ ትምህርት ቤት እስከ 13 ወይም 14 ድረስ ቆየሁ ካለበት ጊዜ ጋር ተጨምሮ በሌላ
ጉዳይ የሚያሳልፈው ጥቂት ጊዜ ተደማምሮበት ብናሰላው ይጣረሳል) ልዑል አልጋ ወራሽ
ሊረዱት ተስማምተው መልእክት አስይዘው ወደ ደሴ ቤተመንግስታቸው ሰደዱት፡፡“ያ ነበር
የመጀመርያ ድሌ” ሲል ያስታውሳል ማሞ፡፡ደብደቤውን ይዞ ደሴ ቤተመንግስት ተመለሰ ዋና
አስተዳደሩ አቶ አለባቸው ገሰሰ የሚፈልገውን ሁሉ አሟሉለት፡፡የሰቆጣ ልጆች ወዳሉበት የንጉስ
ሚካኤል ትምህርት ቤትም መልእክት ተልኮለት ማሞ ተመዘገበ፡፡

97
ጥቋቁር አናብስት

ከአንደኛ ክፍል የጀመረ ቢሆንም አማርኛና ግዕዝ በቤተክህነት ትምህረት ቤት በመቻሉ በነዚህ
ትምህርቶች የ4ኛ ክፍልን ትምህርት መከታተል ቻለ፡፡ወድያውኑ ወደ 2ኛ ክፍል አደገ፡፡አዚያም
ሁሉንም የትምህርት አይነቶች አማርኛና ግዕዝን ጨምሮ ከመከታተሉም በላይ በአማርኛና ግዕዝ
የትምህርት ዐይነት ሁልጊዜ የበላይ ነበር፡፡አንዳንዴ መምህራኑን በማስተማር ሂደቱ ያግዛቸዋል፡
፡ በአማርኛ መምህሩ መምህር አለማየሁ ዘንድ ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ ወደ መምህራን
ማሰልጠኛ ገብቶ አማርኛ አስተማሪ እንዲሆን መከሩት፡፡ የሂሳብና አማርኛ መምህራኑ አቶ
አለማየሁና አቶ አበራ አለማየሁ በተለይ በአማርኛ ትምህርት እንዲታትር ይገፋፉታል፡፡እስከ
6ኛ ክፍል ማብቂያ ድረስ በዚህ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ማሞ በጣም ረዥም ልጅ ስለነበር 3(ልኡል
አልጋ ወራሽ እራሳቸው ከእድሜው በላይ ነው ይላሉ) በትምህርት ቤት ሰልፍ ላይ ሰንደቅ አላማ
የሚይዘው እርሱ ነበር፡፡

ስድስተኛ ክፍል በዲሬክተሩ ህንዳዊው አቶ ዳንኤል ለቦይ ስካውት አባልነት ተመረጠ፡፡እንደ


አንድ የስልጠናው አካል አቶ ዳንኤል ወደ ገጠራማው ክፍል ለሽርሽር ይዟቸው ይወጣል፡፡በዚህ
ወቅት እንደ ማሞ አባባል በሁለተኛው ቀን ታመመ ከፊል አካሉ ልምሻ (ፓራላይዝድ) ሆነ፡፡
እንደነገረኝ ከሆነ የግራ ጉንጩ እስካሁን ድረስ(ከ35 ወይም 40 አመታት በኋላ) እንደተጎዳ
ነው፡፡(ቀናቱን ብናወዳድር አሁንም ግነት ያለው ይመስለኛል)ሲጀማምረው ግን ፊቱ ግራ ጎንና
በተወሰነ በአካሉ ክፍል ብድናት ነበር፡፡በዚህ የተነሳ ማሞ ትምህርቱን መቀጠል ተሳነው፡፡ለሶስት
ወራት ሆስፒታል ውስጥ ከቆየ በኋላ ቤተሰቦቹ ወደ ጸበል ወሰዱት፡፡ሁሉም አልረዱትም፡፡ማሞ
ለ8 ወራት ከታመመ በኋላ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ፡፡ትምህርት ቤቱ ግን ሊቀበለው ፍቃደኛ
አልሆነም፡፡አቶ ዳንኤል ከሶስት ወራት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ስላልመጣ 4 እንደ ቅጣት
ከአራተኛ ክፍል እንዲጀምር ነገረው፡፡ማሞ በዚህ ጊዜ ትእግስቱ አልቆ አቶ ዳንኤልን “ጨቋኝ”
ሲል ጠራው፡፡ለዚህ ስድቡ ቅጣትም በተጨማሪ በአይበሉባው በኩል አልጠበጠብም ሲል
አሻፈረኝ አለ፡፡ከፈለገ በመዳፉ በኩል ሊመታው እንደሚችል ሲናገር “መጥፎ” ብሎም
ጨመረለት፡፡ትምህርት ቤቱንም ለቆ ወደ ቤተ መንግስቱ ተመለሰ፡፡የቤተመንግስቱ አስተዳዳሪ
የትምህርት ቤቱን አስተዳዳሪውን አቶ ጎበዜ ጣፈጠን 5 በማናገር ድጋሚ እንዲገባ ጥረት አደረጉ
አቶ ዳንኤልንም ተጭነውም ቢሆን ልጁ እንዲመለስ ቢያግባቡም አቶ ዳንኤል በእምቢታው
ስለጸና ሊሳካ አልቻለም፡፡

በሚቀጥለው አመት በወ/ሮ ስህን የመጀመር እድል የነበረው ቢሆንም ማሞ ታሞ ስለነበር


ለመሄድ ሳይችል ቀረ፡፡በቤተመንግስቱ የጽህፈት ስራ ሲሰራና ሲያነብ ቆይቶ ወደ አዲስ አበባ

98
ጥቋቁር አናብስት

ተመልሶ ሄደ፡፡ከረጅም ጊዜ በኋላ ለህክምና 30 ብር አገኘ፡፡ብሯ ብታንስም የልዑል አልጋ


ወራሽ የአዲስ አበባ ቤተመንግስቱ አስተዳደር ሻምበል ሃይሉ ወ/ማርያም(ተክለ ማርያም መሆን
አይገባውምን?) ለጊዜው በቂህ ነው አሉት፡፡ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ማሞ የተወሰነ በቤተመንግስቱ
ስራ ስላገኘ በወር 15 ብር መኝታው ከነሱ ሆኖ ተቀጠረ፡፡

ለአመት ከሶስት ወር ከቆየ በኋላ ማሞ እንደገና ትምህርቱን የመቀጠል ፍላጎት አደረበት፡፡


ከቤተመንግስቱ ምንም እርዳታ ባለማግኘቱም አምልጦ ከአንድ ዘመዱ ከሆኑ ከትግራይ
ተዘዋውረው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከሆኑ ከፊትአውራሪ ኃይለማርያም ብጡል ጋር ተጠጋ፡፡
እኚህ ዘመዱ ግን ሳያስፈቅድ በመውጣቱ እንዳጠፋና ቅጣት እንደሚጠብቀው ነገሩት፡፡ማሞ
ህክምና እንደሚሻ ትምርቱንም መቀጠል እንደሚፈልግ ተናገረ፡አኚህ ዘመዱም
እንደሚያስጠልሉት ነግረውት ከቤተመንግስት ሹማምንት የሚመጣውንም ቁጣ ለማቀዝቀዝ
ተስፋ ሰጡት፡፡የተለያዩ ሰራዎችን ለዳኛው እየሰራ የማታ ትምህርቱን ለመቀጠል ብርሃነ ዛሬ
አዲስ ትምህርት ቤት ተመዘገበ፡፡የዚህ ትምህርት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዴቪድ ታልቦት ነው፡፡እዚያ
ስድስተኛና ሰባተኛ ክፍልን ተማረ፡፡

ማሞ ደሴ አብሮት የተማረ ጓደኛውን ከማሁ እሙንን እዛ አግኝቶ ስለነበር በትምህርት ቤቱ


ውስጥም በአማርኛና በግብረገብ አስተማሪነት ክፍት የስራ ቦታ መኖሩን ለማሞ ነገረው፡፡ማሞ
ትምህርት ሚኒስትር ያዘጋጀውን ፈተና በማለፍ ስራውን አገኘ፡፡ለስምንት ወራትም ደሞዙን
ሳይቀበል በዚህ የሙያ ትምህርት ቤት አስተማረ፡፡ይህም የሆነው አስተዳደራዊው ውሳኔ
መገኘት ስለነበረበት በጀቱ እንዲጸድቅ የማህበሩ ሃላፊዎች በበቂ ቁጥር በማህበራት አመራሮች
ስብሰባ ላይ ስላልተገኙና ምልዐተ ጉባኤው ስላልተሟላ ነበር፡፡ማሞ እያስተማረ ጎንለጎንም
የምሽት ትምህርቱን እየተማረ 10ኛ ክፍል ደረሰ፡፡በትምህርት ምንስትር የተዘጋጁ የክረምት
ኮርሶችን በምኒሊክና በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤቶችም ተከታትሏል፡፡

***

በዚህ ጊዜ “ተአምር ተፈጠረ”ይላል ማሞ ፡፡የአሜሪካ የመረጃ አገልግሎት USIS የተወሰኑ


የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያላቸው ሰዎችን ለስራ ፈለገ፡፡ማሞ በፈተናው ሁለተኛ ደረጃን ስላገኘ
በፊልም ማከፋፈያ ቢሮ ውስጥ(የተወሰነ ጊዜ የፊልም ማሳያ ፕሮጄክተሮች አጠቃቀምን ለሰዎች
እያሳየ ከቆየ በኋላ) በ25 አመቱ አካባቢ ተቀጠረ፡፡

በዚህ ጊዜ ነበር በአስተማሪነቱ አልፎ አልፎ ጀምሮት የነበረውን ለጋዜጦች የመጻፍ ልማድ
በተከታታይነት አጠንክሮ የገፋበት፡፡ለአዲስዘመን፤የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ሰንደቅ አላማችን፤
የኤርትራ ድምጽ ላይ በመጻፉ ጥረቱ ፍሬ አፍርቶለት ሌላ ምእራፍ በህይወቱ ለመጀመር በቃ፡፡
99
ጥቋቁር አናብስት

ጥሩ ከመከፈልና ራሱን ከመቻሉ ውጪ ሰዎች በሚጽፋቸው ነገሮች እንደሚያውቁትና


አንደሚያደንቁት ተረዳ፡፡በጽሁፎቹ ላይ ከሪደር ዳይጀስት እና ከሌሎች የውጭ ቋንቋ
የተተረጎመ በማለት ሲፈርም የብእር ስም አይጠቀምም፡፡

ማሞ በወቅቱ ለአዲስ ዘመን ሲጽፍ አርታኢው ብላታ ወልደ ግዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ነበሩ፡፡
ታዋቂ ጸኃፊ ሲሆኑ 6“ጋዜጠኛ እንድሆን አሰለጠኑኝ”ይላል ማሞ “ለእሳቸው ነበር የምጽፈው
ተቀራረብንም” ከጻፋቸው ታሪኮች መሃል ግን አንዱ ችግር አስከተለ፡፡የ “የአስራ ሁለት ልጆች
አባት”የሚል ከሪደርስ ዳይጀስት የተተረጎመ የአረብ ታሪክ ሲሆን በከፊል ታትሞ ነበር፡፡ቀጣዩ
ክፍልስ ብሎ ማሞ ሲጠይቅ“ብዙ ባለስልጣኖች አልወደዱትም”ተብሎ ተነገረው “አጼ
ኃይለሥላሴንና አስራሁለቱን ሚንስትሮችን ለመንካት ተብሎ የተጻፈ” እንደሆነ አስበው
ስለነገሩት ትንሽ ተደናገጦ ከዚያ በኋላ መጻፉን ባያቆምም ይበልጥ ተጠነቀቀ፡፡

ከአመታት በኋላ በአንድ ወቅት በ(USIS)የዜና ጥንቅር እየሰራ አንድ ማሽን በእሳት ስለተያያዘ
ማሞና ጓደኛው በመስኮት በማምለጥ ለእርዳታ ተጣሩ፡፡እሳቱ ´ምንም ጉዳት´ ሳያደርስ ጠፋ፡፡
ማሞ ግን ተጎድቶ ነበር በግራ ክንዱ ላይም እስካሁን የቆየ ጠባሳ አለው፡፡ለጥቂት ቀናት
በኢምባሲው ወጪ በሆስፒታል ጭምር ታክሞ ወደ ስራ ሲመለስ አለቃው አቶ ሊሊኮ በአደጋው
ወንጅለውት ከስራ እንደሚባረር ነገሩት ፡፡ማሞ ይህንን ቢቃወምም ስራውን ግን ለቀቀ ፡፡ብዙም
ሳይቆይ በሩስያ ቋሚ አውደርዕይ ሃላፊ ጋር ተዋውቆ በፊልም እና በላይብረሪ ክፍል ውስጥ
ተቀጠረ፡፡ 7

በዚህ ወቅት ማሞ ለ/ከ ዊንስተን ቸርችል በሩዝቬልት፤ሰታሊን፤ሂትለር (እናም ከሙሶሎኒ


የተላኩ ) በሁለትቅጽ የተጠረዙ ደብዳቤዎችን መተርጎም ጀመረ፡፡እኒህን መጻሕፍት በሶቭየት
ቤተመጻሕፍት ነበር ያገኛቸው፡፡ እነዚህ ደብዳቤዎች መጀመርያ በጋዜጣ ላይ ወጥተው ሰፊ
ተቀባይነትን በማግኘታቸው በደብዳቤ፤በስልክ ፤በአካል ሰዎች አናገሩት፡፡

ትንሽ ቆይቶ ማሞ ከሩስኪ አለቃው ጋር ተጋጨ፡፡አለቅየው ማሞን በአንድ አሮጌ ፊልም መጉዳት
ሲወነጅለው፤መጨረሻው የሁለቱ ሰዎች መጯጯህ ሆነ፡፡ማሞ ክፍሉን ለቆ ሲወጣ ውጪ አንድ
ሌላ ሩስኪ የካሜራ ቀራጭ ድሃና አካል ጉዳተኛ ኢትዮጵያውያንን ሲቀርጽ አግኝቶት ለምን
ደህናውንስ አትቀርጽም በማለት ዙርያውን ለከበቡት ሰዎች “የሚቀርጻችሁ ሀገሩ ወስዶ
መሳለቅያ ሊያደርጋችሁ ነው ”ብሎ በመናገሩ ለጸብ ተጋበዙ አለቅየውም በእዚህ ነገር ውስጥ
ገባ፡፡ማሞም አውደርዕዩን ለቀቀ አልተመለሰምም፡፡ቤቱ ተቀምጦም ስለ ሁለተኛው የአለም
ጦርነት መጣጥፎቹን መጻፍ ቀጠለ፡፡

100
ጥቋቁር አናብስት

አንድ ቀን ላንድ ሮቨር መኪና ቤቱ በር ላይ ቆሞ ሹፌሩ ማሞን ሊያዩት ወደሚፈልጉት ምክትል


ማስታወቂያ ሚንስትሩ ለመውሰድ እንደመጣ ተናገረ፡፡ ምክትል ሚንስትሩ አቶ አምደ ሚካኤል
ደሳለኝ መጣጥፎቹን እንደወደዷቸውና ዋና ቅጂዎቹን ማግኘት እንደሚፈልጉ ነግረውት
አገኘላቸው፡፡ከትንሽ ቀናት በኋላ እንዲመለስ ተነግሮት ሲመጣ ንጉሱ መጣጥፎቹን እንደ
ወደዷቸውና በመጽሐፍ መልክ በአማርኛ እንዲታተም መፈለጋቸውን ተነገረው፡፡የማሞ ከስራ
መውጣት ከታሪኩ ከሰሙ በኋላ በፊታቸው ማመልከቻ እንዲጽፍ ነግረውት እዚያው ጽፎ
ሲሰጣቸው ደብዳቤውን መሩለት፡፡ ምክትል ሚንስትሩ ከዛን ቀን ጀምሮ የአዲስ ዘመን ከፍተኛ
ሪፖርተር ሆኖ እንዲያገለግል መቀጠሩንና ለአርታኢው ብላታ ወልደግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ስለ
አዲሱ አባል ነገሯቸው፡፡ይህ የሆነው ፋሲካ በዋለበት ሚያዝያ ውስጥ 1951 ዓ.ም ነው፡፡
(የትውልድ ቀኑ ትክክል ቢሆን ኖሮ በዛን ጊዜ 25ኛ አመቱ ነበር ነገርግን ከ USIS ጋር ስራ
ሲጀምር 25 አመቴ ነው ብሎ አስቀድሞ ተናግሯል)

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሶስት እንግሊዛውያን ዜጎችን እየተከተለ በኢትዮጵያ ዙርያ የሚጎበኙትን
በሪፖርት መልክ እንደመጣጥፍ እንዲዘግብ ታዘዘ፡፡ይህ ለማሞ ሃገሩን ይበልጥ እንዲያውቅ
እድል ፈጠረለት፡፡አብሯቸው ከሚሰራቸው የእንግሊዝ ኤክስፐርቶች ብዙ ነገርን ተማረ፡፡ወደ
ምእራብ ቀጥሎም ምስራቅ በኋላም ወደ ኤርትራ ተጓዙ፡፡ማሞ በኤርትራውያን ምድር ላይ ሆኖ
ኤርትራውያንን ሲያገኝ ለመጀመርያ ጊዜው ነው፡፡ኤርትራውያን አማርኛ መናገር ያን ያህልም
ባለመፈለጋቸው ለመግባባት እንግሊዘኛን መጠቀም ግድ ነበር፡፡ (ጣልያንኛ ስለማይችል ነው
እንጂ ይቀለው ነበር)

ከአንድ ወር ጉዞ በኋላ ወደአዲስ ሲመለሱ ማሞ ብዙ ልምድ ቀስሞ ነበር፡፡ከሶሰቱ የጉዞ ጓደኞቹ


ልምድ በመነሳት እንግሊዞችን ማድነቅ ጀምሯል፡፡ቤቱ ጋብዟቸው ከባለቤቱ ጋር (ከስድስት
ወይም ከሰባት ወራት በፊት ካገባት)አስተዋወቃቸው፡፡

(ጋብቻቸው ብዙም ከበርቻቻ በሌለበት በጥቂት ውስን ጓደኞች ኑባሬ የተፈጸመ ነበር)ስለዚህ
ጉዞ የጻፋቸው መጣጥፎች ተወዳጅ ነበሩ፡፡ስለኤርትራዊያን እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የጻፈውም
በኤርትራውያን ተደንቆ ነበር ይላል ማሞ፡፡

***

በመስከረም 1953(ከኩዴታው ሶስት ወራት በፊት አካባቢ)ማሞ ወደ ፖሊስ ዋና መስርያ ቤት


ተዘዋውሮ ለፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ በመስራች አርታኢነት እንዲሰራ ተመደበ፡፡የዚህ ጋዜጣ
ምስረታ ሃሳብ የመጣው ከጄኔራል ጽጌ ዲቡ ነበር፡፡ነገር ግን በሰራዊቱ አባላት ሳይሆን በባለሙያ
እንዲመራ በመፈለጋቸው ሃሳባቸውን ለንጉሱ አቀረቡ፡፡ንጉሱም የማስታወቂያ ምክትል
101
ጥቋቁር አናብስት

ሚንስትሩን የጠየቀውን ሰው እንዲሰጠው አዘዙለት፡፡ምክትል ሚንስትሩ የማሞን ስም ሲያነሱ


ማሞን እንዲሰጡ ታዘዙ፡፡ማሞ በመጀመርያ ሲሰማ ተቃወመ፡፡ምክንያቱ ደግሞ ሰዎች “ሰላይ
ሆነ” እንዳይሉኝ ፈርቼ ስለነበር ይላል፡፡ምክትል ሚንስትሩ “የቤተመንግስት ትእዛዝ
አይቃወሙትም ላንተም ለወደፊቱ ጥሩ አይደለም” ብለውት ትእዛዛቸውን ተቀብሎ ለአርትአት
ስራ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እውቅናን ወደተጎናጸፈው ፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ አምርቶ ሰራዊቱን
ተቀላቀለ፡፡

ይህ ዝውውር በማሞ ውድነህ ህይወት ውስጥ አዲስ ምእራፍ ከፈተ፡፡አዲስ ጋዜጣ ማቋቋም
ታላቅ እድልም ተግዳሮትም ነበር፡፡ለሃገሪቱ ጥሩም ጠቃሚምም እንዲሆን ፍላጎት ነበረው፡፡
ስራው በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በጋዜጠኛነት ስለሚወስደው (በተለይ የኦጋዴን አካባቢ
መስጦት ነበር)ከከተማ ውጪ ያሉ የጦር ሰራዊትና የፖሊስ አባላት እንዴት እንደሚኖሩና
እንደሚሰሩ የማየት እድል አጋጠመው፡፡እዚህ እየሰራ ሳለ ነበር በሁለተኛው የአለም ጦርነት
ዙርያ የሚያጠነጥኑት መጻሐፍቱ የመጀመርያው በ1954 ዓ.ም ሁለተኛው ከአምስት አመታት
ገደማ በኋላ በ1958 ዓ.ም መታተም የጀመሩት፡፡

የመጀመርያው የፖሊስና እርምጃው እትም ጥቅምት 23 በ 1953 ዓ.ም ነው የወጣው፡፡


መሸጫውም .10 ሳንቲም ነበር፡፡ትኩረት የሳበውም በጥር 15 የወጣው የፖሊስ መኮንን
ቃለመጠይቅ ሲሆን በቀዳሚው ወራት በመፈንቅለ መንግስት የተሳተፉትን መሪዎች የማደን
ዘመቻውን የመራ ሰው ነበር፡፡ስለግርማሜን ንዋይ ሞትና የወንድሙን የመንግስቱ ንዋይን ቆስሎ
መያዝ ያትታል፡፡

በዚህ ጊዜ ነው ማሞ በስለላ ጉዳዮች ላይ ፍላጎትን ያሳደረው፡፡ ከዚያ ጊዜም አንስቶ የኢትዮጵያ


ባለብዙ መጽሐፍት ጸሀፊና የስለላ ስራዎች ተርጓሚ ሆነ፡፡የመጀመርያ መጽሐፉ የሴትዋን ፈተና
በ1954 ዓ.ም ወጣ፡፡“በመምህራን የክረምት ስልጠና እየተከታተልኩ ሳለሁ ተማሪዎች
የየራሳቸውን የምርጫ ድርሰት እንዲጽፉ ሲጠየቁ በብሉይ ኪዳኑ ስላለው ህልመኛ ዮሴፍ
የጻፍኩት ነው” ይላል፡፡ በተውኔት መልክ የተጻፈ ሲሆን ተመድርኮ ግን አያውቅም፡፡ያም ቢሆን
በ1954 ዓ.ም ታትሟል፡፡ቀጣዩ መጽሐፉ በማርቲን ቦርማን ላይ የተጻፈው ከወንጀለኞች አንዱ
ይሰኛል፡፡በተወሰነ መልኩ የትርጉም ስራ ሲሆን የራሴንም ምርምር አክዬበታለሁ ሲል
ያብራራል፡፡ በ1956 ዓ.ም ለገበያ ቀረበ፡፡ቀጣዩ መጽሐፉ ቬኒቶ ሙሶሎኒ ሲሆን በተመሳሳይ
አመት ወጣ፡፡ይሄም የትርጉምና የምርመራ ጥምረት ነው ይላል ማሞ፡፡ቀጥሎ የገባር ልጅ የተሰኘ
የልብ ወለድ ስራው የራሱ ፈጠራ ሲሆን ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሚያወሳ ነበር፡፡የፊውዳል
የመሬት ስሪት ከተጻፈ ቢቆይም በ1956 ዓ.ም ነበር የወጣው፡፡ይህ መጽሐፍ ለማሞ ችግር

102
ጥቋቁር አናብስት

ይዞበት መጣ፡፡መክንያቱ ደግሞ በባለመሬትና በባለስልጣናቱ ዘንድ በመልካም አመለካከት


ስላልታየ ነበር፡፡ከመፈንቅለ መንግስቱ 8 በፊት በኢትዮጵያ አንድ የሳንሱር ሰራተኛ ብቻ ነበር፡፡
እሱም በእድሜ የገፋ ሲሆን ረቂቁ እንዲታተም ከፈቀደ በኋላ በማሞ ላይ ጥፋቱን ለማላከክ
ሞከረ፡፡

እስካሁን ካየናቸው መጻሕፍት የማሞን ብርታት መለየት እንችላለን፡፡በ1954 ዓ.ም ሁለት


መጻህፍት በ1956 ዓ.ም ሶስት በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር 1985 ቃለ መጠይቅ
እስካደረግንበት 9 ጊዜ ድረስ ከ30 በላይ መጻሐፍቶችን በስሙ አስመዝግቦ ነበር፡፡አብዛኛው
የምእራቡ አለም ትርጓሜ መሆናቸው ይሄን መገለጫውን አይቀንስበትም፡፡

ከመጀመርያዎቹ የሁለተኛው አለም ጦርነት መጻሕፍቱ ህትመት በኋላ ማሞ ንጉሱን እንዲያገኝ


በፖሊስ ኮሚሽነሩ ድረሴ ዱባለ ተወሰደ፡፡ ንጉሱ ለምን ሊያዩት እንደፈለጉ ባለማወቁ
እየተጠራጠረ ነበር የሄደው፡፡ሲደርሱ ንጉሱ በእጃቸው የሱን መጽሐፍ ይዘዋል፡፡የተለያዩ የግል
ጥያቄዎችን የት እንደተወለደ ስለቤተሰቡ፤ስለ ትምህርቱ ወዘተ ከጠያየቁት በኋላ የመጽሐፉን
መጣጥፎች ማንበባቸውና ተሰብስቦ እንዲጠረዝ ማዘዛቸውን አስታውሰው በትምህርቱና
በጽሁፉ እንዲቀጥልበት አበረታቱት፡፡ማሞ ከዚህ በኋላ የግቢ ፍቃድ እንዳገኘና ልጁና ሚስቱን
መደጎምያ እንደተረጠበው ይናገራል፡፡ 10

ማሞ ለአምስት አመታት በፖሊስና እርምጃው ከሰራ በኋላ ከአለቃው ኮሎኔል በረከት(ከአብዮቱ


መጀመር በኋላ የተገደለ) ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ወደማስታወቂያ ሚኒስትር ተመለሰ፡፡
በዚህ የአምስት አመት ቆይታ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተጉዟል፡፡ኤርትራ ብቻ ሶስት ጊዜ
ተመላልሶ ከጎዳና ህጻናት እስከ ልዑል ራስ አስራተ ካሳ(በቃለ መጠይቅ ሪፖርቶቹ ተደስተው
ወደሚያስተዳድሩበት ኤርትራ ተመልሶ እንዲመጣ ጠይቀውታል) በአንድ ወቅትም ልዑል ራስ
አስራተ ካሳ የአውሮፕላን ትኬት የላኩለት ሲሆን ይህም ከውህደቱ(እ.ኤ.አ 1962)በኋላ
በኤርትራ በንቃት የሚንቀሳቀስ ፕሬስ እንዲኖር ስለፈለጉና ማሞ አብሯቸው በፕሬስ መኮንንነት
እንዲሰራ ለመጋበዝ ስለፈለጉ ነበር፡፡ማሞ በኤርትራ ጠቃሚ(ታሪካዊ፤ማህበራዊና፤
ፖለቲካዊ)ስራዎችን መስራት እንደሚችል፤በተጨማሪም ከ70 አመታት ቅኝ ግዛት በኋላ
ኤርትራ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥመቅ በሃገሪቱ የተከፈተ አዲስ ምእራፍ ነው ብሎ ስላሰበ
ተስማማ፡፡ በተጨማሪም የኤርትራ ጸረቅኝ ግዛት ትግልን ለማጥናት እድሉን ስለሚከፍትለት
ጭምርም ነው፡፡ የማስታወቂያ ሚንስትሩ ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ እኔን መልቀቁን ባይፈልጉም
የግዳቸውን ተስማሙ ይላል፡፡ማሞ ወደ ኤርትራ በ1957 አ.ም መጨረሻ ገደማ አቀና፡፡እዚያም
በፕሬስ መኮንንነት በሳምንት አንዴ ለሚወጡት ሁሉም የአማርኛ ጋዜጦች ሃላፊ ሆኖ መስራት
103
ጥቋቁር አናብስት

ጀመረ፡፡በዚያን ወቅት ሳምንታዊ ኢትዮጵያ የሚል አማርኛ ጋዜጣ፤የኢትዮጵያ ህብረት


በትግርኛ፤የአረቢኛው አልዋሂዳ፤የጣልያንኛው ኮትዲያኖ ኤርትሪኦ በየቀኑ የሚታተሙ ነበሩ፡፡
ማሞ ለእነዚህ ጋዜጦች ይጽፋል መጣጥፎቹና ሃቲቶቹ እየተተረጎሙ ይቀርባሉ፡፡እንደሱ
እንደሚለው ከዚያ በኋላ ሽያጩ በአንድ ጊዜ ተተኮሰ ለምሳሌ ህብረት ከ2000 ወደ 3000 እና
4000 ብዙም ሳይቆይ 8000 ኮፒ በየቀኑ መታተም ጀመረ፡፡የራሱ የአማርኛ ጋዜጣ ኢትዮጵያ
ከ1500 እና 2000 ወደ 4000እና 6000 በማደግ በመጨረሻ 10000 ሊደርስ ቻለ፡፡

ማሞ በኤርትራ ለ9 አመታት ቆየ፡፡በዚህ ወቅትም በዚያ ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ከመቶ የበለጡ
ጽሁፎችን ጻፈ፡፡“(ስለ ኤርትራ ችግርና ያለጦር መሳርያ ግርግር የሚፈታበት ዘዴ) በመጻፌ
ኤርትራውያን ጽሁፌን ያውቁት ነበር ብዙዎች ከእኔ ሃሳቦች ጋር የሚስማሙም ነበሩ ሌላው
ቀርቶ አማጽያኑ እራሳቸው የኔን መጣጥፎች በገንቢነት ይወስዷቸው ነበር ”ይላል፡፡የኤርትራው
ገዢ ራስ ካሳ በችግሩ አፈታት ላይ በኔ ሃሳብ ቢስማሙም “በተቃዋሚዎች መኖር አናምንም”
ብለው መኖራቸውን ከሚክዱት የአዲስ አበባ ባለስልጣናት ተቃውሞ መጣ፡፡ማሞ ጌታቸው
መካሻ፤ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ፤ዶ/ር ተስፋዬ ገ/እግዚ ከመሳሰሉ የማስታወቂያ ሚንስትሮች
ባለስልጣናት ጋር በዚህ ጉዳይ የከረረ አለመግባባቶች ውስጥ ገባ፡፡በመጨረሻም ማሞ ሃሳቡን
በረጅም ጽሁፍ ለንጉሱ አቀረበ፡፡ንጉሱም በሃሳቤ ተስማምተው በወቅቱ ለኤርትራ ጠቅላይ ገዥ
ለነበሩት ጄኔራል ደበበ ኀይለማርያም “በጽህፈት ሚንስትር በኩል (ትእዛዝ የሆነ)የኤርትራ
ጉዳይ ከማሞ ሃሳብ አንጻር ተጠንቶ ድርድር እንዲጀመርና ከባለጉዳዮቹ ጋር በንግግር
እንዲፈታ” የሚል ደብዳቤ አስጽፈው ላኩ፡፡ማሞ ለኤርትራ በሰራው ስራ ኩራት እንደሚሰማው
ይናገራል፡፡የኤርትራታሪክ መጽሐፉን በ1962 ዓ.ም ጻፈ፡፡ስለታዋቂው ጀግና ራስ አሉላ አባ
ነጋም ተውኔት ደርሶ አሉላ አባ ነጋ ተብሎ በ1966 ዓ.ም ለመድረክ በቃ፡፡ቃለመጠይቅ
በምናደርግበት ወቅትም የመንግስት አሳታሚ የሆነው 11 ኩራዝ ማተምያ ቤት ስለ ራስ አሉላ አባ
ነጋ የጻፈው መጽሐፍ ለመታተም ገብቶ የነበረ ሲሆን 10 አመታትን የአሉላን ታሪክ በማጥናት
አሳልፌያለሁ ይላል፡፡

ማሞ አስራሁለት መጻሕፍትን ኤርትራ ሳለ ጻፈ፡፡ሶስቱ ወጥ የፈጠራ ስራዎች ሲሆኑ "ዲግሪ


ያሳበደው"ና ፤"ካርቱም ሄዶ ቀረ"፤በአንድ ተጠርዘው በ1959 ዓ.ም ለገበያ ቀረቡ፡፡"ብዕር
እንደዋዛ" በ1960 ዓ.ም የወጣ የግጥም መድብሉ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የኤርትራ ታሪክ
መጽሐፉም በ1962 ወጥቷል፡፡ቀሪዎቹ ዘጠኝ መጻሕፍት ትርጉም ሲሆኑ ሳይታተሙ የቀሩ ብዙ
ረቂቆች በዚህ ጊዜ እንደነበሩት ይናገራል፡፡ከነዚህ መሃል አንዱ" የአሮጊት አውታታ" ሲሆን
ኤርትራም ሆነ ኢትዮጵያ ባሉ ሳንሱሮች ታግዶ ነበር፡፡ስለዚህ ማሞ አንድ ኮፒ ለንጉሱ ሰጣቸው፡
104
ጥቋቁር አናብስት

፡እሳቸው በተራቸው (ያጎታቸውን ልጅ)ራስ እምሩ አንብበው አስተያየት እንዲሰጡበት


ሰጧቸው፡፡እምሩ“ታሪኩ ኣሳዛኝ ቢሆንም የመከልከሉ መክንያት አልገባኝም”አሉ፡፡ንጉሱም
ለ“መጨረሻ ፍርድ” ወደ መረጃ ሚንስትር ላኩት፡፡እነሱ በሰጡት መልስ መታተም
እንደሌለበትና በጊዜው ስላለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በአሽሙር የሚናገር እንደሆነ ገለጹ፡፡ንጉሱ
ማሞን ስለ መጽሐፉ ጠየቁት ማሞም ስለ አንዲት ብዙ ወንዶችን አግብታ በርካታ ልጆችን
ስላፈራች አሮጊት እንደሆነና ልጆችዋም ለንብረቷ እየተጣሉ እንደሆነ መለሰ፡፡ንጉሱም
“ገብቶናል ሚኒስትር መስርያ ቤቱ እንዲታተም ፍቃደኛ አልሆነም ፡፡አሸሙረህ እንደጻፍከው
ነግረውናል፡፡ስለዚህ ለጊዜው እሱን ትተህ ሌላ መጽሐፍ ጻፍ” አሉት መጻሐፉም ሳይታተም
ቀረ፡፡

***

የኤርትራ የ9 አመታት ቆይታው ለማሞ ከራሱም ፤ከባለስልጣናቱም ፤ከቃኘው የጦር ሰፈር ጋር


ግንኙነት ካላቸው አሜሪካኖች ጋር ቅራኔ ውስጥ የገባበት ወቅት ነው፡፡

ከአሜሪካኖቹ ጋር የነበረው ቅራኔ በጋዜጦች ላይ ይንጸባረቅ ነበር፡፡በአንድ ወቅት አንድ


የአሜሪካን ወታደር ኤርትራዊ ጋሪ ነጂን ገደለ፡፡አሜሪካዊ ዳኞች (ከቱርክ)ተጠርተው ጉዳዩን
እንዲያዩ ተደረገ፡፡አምስት ኢትዮጵያዊ ምስክሮችም ነበሩ፡፡ከመሃላቸው ሁለቱ አሜሪካዊው
የጋሪ ነጂውን ጭንቅላት ከመሬት ጋር አጋጭቶ ገደለው ሲሉ ቀሪዎቹ ሶስቱ ደግሞ ባለጋሪውን
ከግድግዳ ጋር አጋጭቶ ነው የገደለው አሉ፡፡ምስክሮቹ እርስ በእርስ በመቃረናቸው ተከሳሹ በነጻ
ተለቀቀ፡፡ማሞ ይህንን ፍርድ በመቃወም ረጅምና ጠንካራ ጽሁፍ በጋዜጣ ላይ ጻፈ፡፡የመረጃ
ሚንስትር ነገሩን ከመረመረ በኋላ ከማሞ ተቃራኒ አቋም ያዘ፡፡“በዚህ ወቅት ልኡል ራስ አስራተ
ካሳ ግን ከጎኔ ቆመው ድጋፋቸውን ሰጥተውኛል” ይላል ማሞ፡፡ለማንኛውም የዚህ ጉዳይ መቋጫ
ዳግም እንዲጻፍ የሆነው የአሜሪካና የኢትዮጵያ መንግስታት የስምምነት ፊርማ ነው፡፡
የአሜሪካኖቹም ባለሙሉ ስልጣንነት ሊታጠፍ በቃ ይላል ማሞ፡፡

ማሞ ኢትዮጵያውያኑን እንኳን አንዳንዴ በገዛ ሃገራቸው የነጻነት ስሜት እንዳይሰማቸው


ስለሚያደርጓቸው የአሜሪካ ወታደራዊ ፖሊሶች ባህርይም በመተቸት ጽፏል፡፡በማከልም
ኢትዮጵያውያን ዳኞች ከዚያ በኋላ የአሜሪካን ወታደሮችን በተመለከተ በማንኛውም
የፍትሐብሄርም ሆነ የወንጀል ጉዳይ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ ይለናል፡፡

ከባለጋሪው ገዳይ መለቀቅ በኋላ ማሞ የተወሰኑ ኤርትራውያን ወጣቶችን በማሰባሰብ


የአሜሪካኖቹን መኪኖች በማታ ጠብቀው እንዲሰብሩ አደራጃቸው “የወሮበሎች መሪ

105
ጥቋቁር አናብስት

ነበርኩ”ሲል ያስታውሳል፡፡ በስተመጨረሻም ማሞ ጋር ሽማግሌዎች ተልከው ነገሩ


የሚቋጭበትን መንገድ ጠየቁ፡፡

በወቅቱ በአስመራ ጸረ አሜሪካ ስሜት ተስፋፍቶ ነበር፡፡የጋሪ ነጂውን ቤተሰብ ለማገዝ


መፈለጉንና 10000 ብር እንዲያዋጡ አሜሪካኖቹ ላይ ስለተፈረደ ከሳምንት በኋላ አምጥተው
ከፈሉ፡፡ከሌሎች ኤርትራውያን ደግሞ 1000 ብር አካባቢ ተዋጥቶ ነበር፡፡ሁሉም ኤርትራዊ
ይህንን እንደሚያስታውስ ማሞ ይናገራል፡፡

ማሞ አስከ 1966 አብዮት ዋዜማ ድረስ “ውጤታማ አመታትን” በኤርትራ አሳልፏል፡፡ብዙ


ጠላቶችንም ስለኤርትራ ባለኝ አቋሜና ድፍረት በተሞሉት ጽሁፎቼ መክንያት አፍርቻለሁ ሲል
ያስባል፡፡ኤርትራውያንን በሃቀኝነታቸው ይወዳቸዋል፡፡ክርስትያኖቹም እውነተኛ ክርስትያን
ሙስሊሞቹም እውነተኛ ሙስሊም የሆኑ ቅን ህዝቦች በመሆናቸው ልወዳቸው በቅቻለሁ ይላል፡
፡(በገጠሩም ሆነ በከተማ የኤርትራ ቤቶች ባህሉ ኢትዮጵያዊ ነው ከጣልያንነት ይልቅ)

***

በግርግሩ መጀመርያ በ1965 ዓ.ም ማሞ ወደዋናው የጦር ጣብያ ፎርቶ የጉዳዩን “ግልጽ
ምስል ለማግኘት” ሄደ፡፡በዚህ ጊዜ ማሞ “የህብረት እዝ” የሚባል ወይም ጂ5 የሚባል ቡድን
አመራር ነበር፡፡የተዋቀሩትም ከ ባህር ሃይል ፤ፖሊስ፡ከምድር ጦር፤ ከአየር ሃይል እና ከሲቪል
ሰርቪስ ነው፡፡ከዚያ በፊት እነዚህ ቡድኖች በማሞ አማካኝነት ለአንድ ስራ ተገናኘተው የነበሩ
ሲሆን ከዚህ በኋላ ግን አንድ እዝ አቋቁመው ከሽኩቻና ከፉክክር ይልቅ በትብብር ለመስራት
በመፈለጋቸው ይህ ሃሳብ በ ልዑል አስራተ ካሳ ተወዳጅ ሆነ፡፡ይህ የጂ5 ጅማሮ ሲሆን ማሞም
“አዛዡ” ሆኖ ነበር፡፡ ስለዚህም በጸጥታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከ ፎርቶ መሪዎች ጋር
ለመወያየት ወደ እዚያው አቀና፡፡እዚያም ደርሶ ላሉት ሰዎች ሃሳቡን አቀረበ፡፡ የፖሊስ ጄኔራሉ
እጅ ለመስጠት ሳይስማማ ቀርቶ ፈጥኖ ደራሽ ኮማንዶዎችን 12ለጥበቃ ሲጠራ ማሞ ሃይል
እንዳይጠቀሙ መከረ፡፡በመጨረሻም ንጉሱ አስማሚ ሽማግሌ በመላክ ነገሮችን ሊረጋጉ
ችለዋል፡፡

ማሞ “ተጠቂ”ሆነ በኤርትራ ባለስልጣናት “ጦሩ እንዲያምጽ በመርዳትና የሬድዮ ማስታወቂያ


ለአማጺያኖቹ በመናገር”13 ስለወነጀሉት የአስመራ ቆይታው አደጋ አንዣበበበት፡፡ከእስር
የተለቀቁት ጠቅላይ ገዢ ደበበ ኀይለማርያም ንጉሱ ማሞን ከኤርትራ እንዲያስወጡ መከሯቸው፡
፡ 14ከንጉሱ ለማስታወቅያ ሚንስትር በተላከ ትእዛዝ ማሞ ወደ አዲስ አበባ ተጠራ፡፡

106
ጥቋቁር አናብስት

ወደ አዲስ አበባም ተመልሶ ማሞ “ለአዲሱ መንግስት እንዴት የኤርትራን ችግር መፍታት


እንደሚቻል ”መጻፉን ቀጠለ፡፡እሱ እንደሚያስቀምጠው ይሄ በኢትዮጵያ ፕሬስ ስለ ኤርትራ
ጉዳይ ተነስቶ ክርክር ሲቀርብበት ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ 15ማሞ በአዲሱ ጠቅላይ
ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን ተጠርቶ ጊዜ ወስደው ስለ ኤርትራ ተነጋገሩ፡፡ ስለ ኤርትራም
የተጻፈ ከ1933-1964 ዓ.ም ያለውን ታሪክ የሚናገር 70 ገጽ ረቂቅ ሰጡት(ይህ ሰነድ
የኢጣልያ ከኢትዮጵያ መውጣት እንዲሁም ከኤርትራ ቅኝ መገዛት ማብቃት ጀምሮ እስከ አጼው
አገዛዝ ማብቂያ መዳረሻ ሁለት አመት ድረስ ያለውን ያካትታል በኤርትራ ስላለው ፖለቲካዊ
ሁኔታ ይዳስሳል ታትሞም አያውቅም )ማሞ እንደሚያስበው ግን የዩንቨርሲቲው የፖለቲካ
ሳይንስ ተማሪዎች በቆይታችን ወቅት እየሰሩበት እንደሆነ ነው፡፡ለእንዳልካቸው የኤርትራ ችግር
እንዴት እንደተጀመረ፤ማን እንደጀመረው፤ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያንቀሳቅሰው፤እንዴት
መፍታት እንደሚቻል በተጨማሪም የኤርትራን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ በዋናነት የመፍቻ ጊዜ
እንደሆነ ነገራቸው፡፡የኤርትራን ችግር “የኢትዮጵያ ዋነኛ ነቀርሳ” ሲልም ይጠራው ነበር፡፡
እንዳልካቸው በማሞ ሃሳቦች “ተደምመው” የሃገር ውስጥ ሚንስትሩ ዘውዴ ገብረ ሥላሴ ጋር
ደውለው ከማሞ ጋር እንዲገናኙና አብረው እንዲሰሩ በጋራም ችግሩ የሚፈታበትን አቋም
አጥንተው እንዲያቀርቡላቸው ነገሯቸው፡፡ዘውዴ ማሞን እንዲያገኛቸው ጠየቁት፡፡ተገናኝተውም
ተነጋገሩበት ዘውዴ ነገሩን በሰላማዊ መልክ ለመፍታት ፈልገዋል ሀይለኛ ሰው አይደሉም፡፡
ወድያው ግን እንዳልካቸው ወርደው ልጅ ሚካኤል እምሩ በቦታቸው ተተኩ፡፡ማሞ ከሚካኤል
ጋር በዘውዴ አማካኝነት ተዋወቀ፡፡“ሚካኤልም በኤርትራ ጉዳይ ላይ ተከትለው ለመስራት
በጣም ጉጉት ነበራቸው ሌላው ቀርቶ በኤርትራ ስለሚካሄዱ ሹመቶች አማክራቸው ነበር
”16ይላል ማሞ፡፡

በዚህ የተነሳ ከአብዮቱ በፊትም ሆነ በኋላ ስለ ኤርትራ ከመጻፍ ውጪ ማሞ በንቃት ስለ


(ኤርትራ ጥያቄዎች )ለንጉሱም ሆነ ለምንስትሮቻቸው ሀሳብና ጥያቄዎችን በማቅረብ ይሳተፍ
ነበር፡፡

ንጉሱ ወርደው ደርግ ስልጣኑን በ1966 ከያዘ በኋላም ማሞ ጥያቄውን ለአዲሱ መንግስት
ማቅረቡን አላቋረጠም፡፡“ደርጎች ሃሰቤን ቢሰሙም በመሃላቸው አለመግባባት ስለነበር
በተለመደ መልኩ ስራቸውን ሊከውኑ አልቻሉም”ይላል፡፡ማሞ ጄኔራል አማን አንዶምን
(ኤርትራዊ ጄኔራልና ለተወሰነ ጊዜ የኢትዮጵያ መራሄ መንግስት የነበሩትን)“ከሃይ ሃይ በስተቀር
በቁም ነገር አማጺያኑን ለማናገር ዝግጁ አልነበረም”ሲል ይተቻቸዋል፡፡

107
ጥቋቁር አናብስት

በቀጣዩ መሪ በተፈሪ በንቲ ጊዜ ማሞ ፖለቲካዊ ኮሚቴ በኤርትራ ላይ እንዲያዋቅር ተጠየቀ፡፡ 17


ኮሚቴው ለችግሩ መላ ይሆናሉ ያላቸውን ሃሳቦች ቢያቀርብም “ለስልጣን የተራበ አንድ ቡድን”
የነሱን ሃሳቦች ወደ ጎን ብሎ ´ርዕዮተ አለማዊ መፍትሄ´ ለጉዳዩ ለመሰጠት ፈለገ፡፡ማሞ ከነሱ
ጋር ባይስማማም ወደ መረጃ ሚንስትር በመሄድ “እንደ ራሴ መርህ” በማለት ስለ ኤርትራ
መጻፉን ቀጠለ ከብዙ ነገሮች መሃል በትናንሽ ቅንጣቶች ቢወቀስም 18ማሞን የሚቆጨው
የሃገሪቱ ጠላት የሚባሉትን የሰላም ጠላቶች በንግግር ያለማግባባቱ ነው አሁንም ግን “በዚህ
ወይም በሚመጣው ትውልድ ሰላማዊ መፍትሄ ያገኛል”ሲል ተስፋ ያደርጋል፡፡ተገናኝተን
ባወጋንበት ወቅትም ቢሆን ኤርትራ የኢትዮጵያ ግዛት አካል መሆኗን ፤የኤርትራ ህዝቦችም
ትክክለኛ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን በእያንዳንዱ የኤርትራዊ ልብ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰንደቅ
እንደተሰቀለ በማንኛውም ኤርትራዊ ወጣት ፍቅረ ኢትዮጵያ እንዳለ በጽኑ ያምናል፡፡

***

በኤርትራ ችግር ላይ ያለው ጠንካራ ተሳትፎ ሃሳቡን በሙሉ ሰርቆት ነበር በነዚህ አመታት፡፡
በርካታ ሰዎችም “ትክክለኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል”ይሉኛል ሲል በዚህ ወቅት ግን እነዚህን
የትርጉምና የራሱ ስራዎችን ለመጻፍ ግዜ ማግኘቱ ያስገርማል፡፡በንግግራችን ወቅትም ስለ
ስነጽሁፍ ስራዎቹ በአጭሩና እንደማጠቃለያ አድርጎ ከኤርትራ ፖለቲካ ተሳትፎው በኋላ
ማንሳቱም ስነ ጽሁፍ በሃሳቡ ተከታይ ቦታ መያዟንና አልያም ተቀዳሚ ከሆነችም በፖለቲካዊ
ክርክር ውስጥ እንደ አንገት ማስገቢያ መላ የመሆንዋን ሃቅ ያጠይቃል፡፡ለማንኛውም ከኤርትራ
በኋላ ስላለው አበርክቶት ስናነሳ ከ20 በላይ መጻህፍት ተርጉሟል፡፡ከነዚህም መሃል ወደ አስሩ
በቃለመጠይቃችን ወቅት ለህትመት በቅተዋል፡፡አስራ አንድ ያህሉ ደግሞ በሳንሱር ታንቀዋል፡፡
ከነሱ መሃልም የ ኤም.ኤች ሃይካል THE ROAD TO RAMADAN እና ስለ ሳይኪክ እውቀት
የተጻፈው IS DEATH THE END ?ይገኙበታል፡፡ስለ ሲአይ ኤ ዩፎ ወዘተ›..የተጻፉም አሉ፡፡

አብዛኞቹ መጻሕፍቶቹ ´እንደመከልከላቸው´ ምን ማድረግ እንደሚችል ባለማወቅ ውዥንብር


ውስጥ ነው፡፡ለመጻፍና ለትየባ ብዙ ገንዘብና ጊዜ አባክኗል፡፡ከ25 የትርጉም አመታት በኋላ
በሰራው ላይ እንዲያክልበት"ጎሽ"መባልን ሲጠብቅ የግርምቢጥ ተስፋ አስቆራጭ ነገር
አጋጠመው፡፡ምን አልባት ጭብጦቹ ከምእራቡ አለም ስለሆኑና ከወቅታዊው የህብረተሰባዊት
ኢትዮጵያ ከነበረው ሁኔታ ጋር ስምም ስላልሆኑ ይሆናል፡፡ይህ ተስፋ መቁረጥ ግን ለበጎ ሆኖለት

108
ጥቋቁር አናብስት

በማሞ የስነ ጽሁፍ ታሪክ ውሥጥ መጀመርያው ምንም ያህል ያልተጤነ ቢሆንም አዲስ በርን
መክፈት ችሏል፡፡

ወዲህ ነው ነገሩ፡፡ማሞ አንድ ቀን ከጓደኛውን ጋር ጋራዥ ውስጥ ተገናኘ፡፡ ጓደኛው በጣም


ተናዶ ነበር፡፡አንድ ወርሃዊ እቁብ እንደሚጠጣና ዳኛው የተጣለውን ብር ሰብስቦ እንደተሰወረ
ነገረው፡፡ይህ ክስተት ማሞን አነሳስቶት በዚህ ዐይነት የኢትዮጵያ ማህበራት ላይ ወደ መስክ
በመውጣትም ሆነ በቤተ መጻሕፍት ውስጥ ጥናት ማድረግ ጀመረ፡፡ከጥልቅ ጥናትና ምርምር
በኋላ ስለማህበራቱና አባሎቻቸው መጻፍ ጀመሮ ውጤቱም በታህሳስ 1976 ዓ.ም
የታተመው" እቁብተኞቹ" ሆነ፡፡

ሌላው የእርስበእርስ መረዳጃ የሆነው የኢትዮጵያ የማህበር ዐይነት ደግሞ እድር ነው፡፡ማሞ
ደግሞ በነዚህ ማህበራት ላይ የተመረኮዙ ስነ ማህበራዊ ልብወለዶችን መጻፍ በመጀመሩ
እድርተኞቹን ጻፈ፡፡እኛ በምንጨዋወትበትም ወቅት በህትመት ላይ ነበር፡፡ቀጥሎ ደግሞ
ስለሌላው የማህበር ዐይነት"ማህበርተኞቹ" የሚል መጽሐፍ እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር
1985 ላይ ጽፎ አጠናቀቀ፡፡

እነዚህን ሶስት ማህበራት “የአዲስ አበባ አእማድ” ሲል ይጠራቸዋል፡፡ እናም “ማንኛውም ሰው


የእነዚህ ማህበራት የአንዱ አባል መሆን ይኖርበታል”ይላል 19፡፡ማሞ እንደነገረኝ ከሶስቱ
ተለጣጣቂ ስራዎቹ መሃል ሁለተኛውን የገመገመው ሴንሰርና አርታኢ መጽሐፉን "የአዲስ
አበባን ህይወት ያንጸባረቀ መስታወት"ሲል ጠርቶታል፡፡ 20በዚህ በመበረታታት ሶስተኛውን
ስራውን በፍጥነት አጠናቀቀ፡፡ሶስቱ መጻሕፍት በመጠናቸው እየተለቁ ነበር የሚሄዱት ለነሱ
የሚሆን ግብአት ለማግኘት ማሞ ታላላቆችን ዳኞችን ወጣትና አዕሩግ አባላቶችን አነጋግሯል፡፡
አብዛኛው አለመግባባቶች በህግ ስለሚዳኙ የፖሊስና የፍርድ ቤት ፋይሎችን አገላብጧል፡፡
በቤተ መጻሕፍትና አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አካባቢ ከመፈተሹም በላይ የራሱን ልምድም
ገንብቷል፡፡“በእነዚህ መጻሕፍት የተነገሩት ታሪኮች ለገሃዱ አለምና አውነታ የቀረቡ ታሪኮቹ
ቦታዎቹና ሰዎቹ ከእውነተኛው አለም ጋር የተጠጋጉ ናቸው፡፡ነገር ግን የገጻባህርያቱ ስምና
ቦታዎች ተቀይረዋል” ሲል በኢትዮጵያ ጉዳዮችም ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳደረ መምጣቱንም
ከእቁብ እድርና ማህበር ጥናቶቹ በኋላ አክሎ ነግሮኛል፡፡

ማሞ ከአስመራ ከተመለሰ በኋላ ´በኤርትራው ችግር መንስኤ´ ምንም ዐይነት የመንግስት ስራ


አልተሰጠውም ያችኑ የማትቀየር የ700 ብር ደሞዙን ይዞ ነበር ለነዚህ ሁሉ አመታት
የቀጠለው፡፡ተጨማሪ ገንዘብ ከሚጽፋቸው መጣጥፎችና ከመጻሕፍቱ ያገኛል፡፡ስድስት ልጆች
ሲኖሩት ሁለቱ ከአዲስ አበባው ህንጻ ኮሌጅ ተምረው መሐንዲስ ሲሆኑ ሌላው አንድ ልጁ
109
ጥቋቁር አናብስት

ከጎንደር ዩንቨርሲቲ ተመርቆ የህክምና ዶክተር ሆኗል አንዱ በ 1978 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ
የመጨረሻ አመት ተማሪ ሲሆን አንድ ወንድና ሴት ልጆቹ ግን ገና ህጻናት ናቸው፡፡

ማሞ እስከ 1978 ዓ.ም ከ2000 በላይ መጣጥፎችን ከ27 አመታት በላይ ለተለያዩ ጋዜጦች
አበርክቷል፡፡በእንግሊዘኛ (ሌላው የሀገሪቱ ኦፊሴል ቋንቋ) ግን ብዙም አልጻፈም፡፡

እንደ የአሮጊት አውታታ ያሉ በበፊቱ ስርአት በሳንሱር የተያዙ ረቂቆቹን ኣሳትሞ ለማውጣት
ይፈልጋል፡፡ ትርጉሞቹን ጨምሮ በዚህ ጊዜ ከ30 በላይ መጻሕፍትን በስሙ ሰርቶ አውጥቷል፡፡

በጥር መጀመርያ 1965 ከመጣሁ ጀምሮ የማሞን ስም በየመጻሕፍት መሸጫ ሱቆች ባሉ


መጽሐፍቶቹ ላይ አየዋለሁ፡፡ትጉህ ሰራተኛ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡መጽሐፍቶቹ ይሸጡለታል፡፡
አብዛኞቹም ከአንድ ጊዜ በላይ ታትመዋል፡፡ጠቃሚ ገቢን ከመጽሐፍቶቹ ከሚያገኙ ጥቂት
ጸሃፍት መሃል አንዱ ይመስላል፡፡በኢትዮጵያ ገበያ ግን ከውስንነቱም አንጻር ከአንባቢውም
አቅም አኳያ ማንም በመጽሐፍቶቹ ባለመብትነት በሚያገኘው ገቢ መዝለቅ አይቻለውም፡፡አንድ
መጽሐፍ አንድ ጥሩ ምግብ ቤት ገብተን ለምግብ ከሚወጣው ወጪ ወይም ኢትዮጵያውያንን
ወንዶች ለቢራ ከሚያወጡት በብዙ ያነሰ ነው የሚሸጠው፡፡ቢሆንም ቅሉ ለመጽሐፍ ገንዘብ
ለማውጣት የሚፈልጉት ጥቂቶች ናቸው፡፡ 21ትምህርት እየተስፋፋ ሲሄድ ምንአልባት
የመጽሐፍት ፍላጎትም እየጨመረ ይመጣ ይሆናል በ80ዎቹ በእርግጠኝነት እንደሚታየው
የጸሃፍት የወደፊት ተስፋ የዚያን ያህል ጨለማ ላይሆን ይችላል፡፡

***

ማሞን ወደ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ስመጣ በተደጋጋሚ አግኝቼው ነበር፡፡በጥንካሬ ከመጻፉ


ውጪ ያን ያህል ለውጥ በህይወቱ አልተከሰተም ነበር፡፡ነገር ግን በ1980 ዓ.ም ስንገናኝ
በ1979 ስለ አጼ ዮሐንስ አራተኛ ልብ ወለድ ጽፎ መጨረሱን ነገረኝ፡፡

በዚያን ወቅት በሳንሱር አድራጊዎችን እጅ ነበር ለመጽሐፉም ´የድራማ ቅጽ´ እየሰራለት ነበር፡፡
ጎን ለጎን በተጓዳኝ ጊዜም የማጠናቀቅያ ስራዎች እየሰራለት የሚገኘው በአንድ ኢትዮጵያ ውስጥ
ያደገ የመናዊ አረብ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ልብወለድ ስራው ነበር፡፡ወደ የመን ከተመለሰ በኋላ
አንዲት ኢትዮጵያዊትን አግብቶ አሜሪካን ሃገር አንድ ልጅ ከወለዱ በኋላ ተፋቱ፡፡ መጽሐፉን
የደጎመውም እራሱ ይሄው ሰው ነው፡፡ተመልሼ በ1982 ዓ.ም ስመጣም የማሞ አዳዲስና ዳግም
የታተሙ መጻሕፍትን ብመለከትም እሱን ግን አላገኘሁትም ፡፡

110
ጥቋቁር አናብስት

የተርጓሚው ማስታወሻ ደራሲ እና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ ከዚህ ጥንቅር በኋላ ህይወቱ


እስካለፈበት ግዜ ድረስ እና ከዛም በኋላ የሰራቸው የሰላዩ ካሜራን፤ሰላይ ነኝ፤በዘመናችን
ከታወቁ ሰዎች፤ሾተላዩ ሰላይ፤የበረሃው ማእበል፤ኬ.ጂ.ቢ፤የሲ.አይ.ኤጥልፍልፍ፤መጪው ግዜ፤
ዮሐንስ፤እኔ እና እኔ፤ኤርትራና ኤርትራውያን፤የደረስኩበት 1 እና2(ግለ ታሪክ) መጽዐተ
እስራኤል (በተደጋጋሚ) ታትመውለታል፡፡

ማስታወሻ

1ኢትዮጵያ ውስጥ ስሞች ቋሚ አይደሉም፡፡ብዙ ሰዎችም ሰማቸውን ከጊዜ በኋላ ይቀይራሉ፡፡


የክርስትና ስሞች ቋሚ ቢሆኑም አብዛኛው ሰው ግን የሚጠቀምበት እንደ ጋብቻ ለቤተ ክርስትያን
አገልግሎት ብቻ ነው፡፡

2ማሞ ከአክስቱና ከሌሎች አርበኞች እንደሰማው ከሆነ አባቱ የአርበኞች መሪ ከነበረው ዋግሹሙ
ጋር ቅርበት ነበራቸው፡፡ ከጣልያኖች ጋር የሚተባበሩ ባንዳዎች ዋግሹሙን በቁጥጥር ስር ለማዋል
ጓጉተው ነበር፡፡አንድ ቀን ተሳክቶላቸው በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ተቃርበው የነበር ቢሆንም
የማሞ አባት ተኩሰው ከማሃከላቸው አንዱን ጥለው የተቀሩትን ስላባረሩ ላይሳካ ችሏል፡፡ዋግሹሙ
ለዚህ ስራቸው ወሮታ አንድ ረጅም የጣልያን ሽጉጥ ሸልሟቸዋል፡፡እስከመጨረሻውም
ባለውለታቸው ሆነው ዘልቀዋል

3አሁን ረጅም ሰው ሆኗል

4ማሞ እንደሚለው ከሆነ አቶ ዳንኤል ወደ ጠበል እንደሄድኩ የቀረበለትን ማብራርያ


አልተቀበለውም

5“ከሃይሌ ፊዳ ቀጥሎ ሁለተኛ የመኢሶን ሰው የነበረው የዶክተር ነገደ ጎበዜ አባት ነበሩ”ሲል ማሞ
ያብራራል

6የወልደ ግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ታሪክ በዚህ መድብል ተካቷል

7ከዚያ ቀደም ብሎ ማሞ ከቤተ መጻሕፍታቸው መጽሐፍ ይዋስ ነበር፡፡

8ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በኋላ የሳንሱር ሂደቱ እየጠበቀ መጣ

111
ጥቋቁር አናብስት

9ከጨዋታችንም በኋላ ቢሆን መጻሕፍትን ከመጻፍና ከሳንሱር ክፍሉ እንዲያልፍ ከመታገል


አልተቆጠበም፡፡ከንግግራችን በኋላ በቆየሁባቸው አራት አመታትም ሆነ ዳግም ኢትዮጵያን
በጎበኘሁበት እ.ኤ.አ በ1990 ላይ በአዳዲስ ስራዎች ላይ ስሙን አስተውያለሁ

10በወቅቱ አንድ ልጅ ነበርየነበራቸው፡፡አንዳርጋቸው፤ቃለመጠየቅ ባደረግንበት አመት እ.ኤ.አ


በ1985 አ.ም በ24 አመት እድሜው ከጎንደር ሜዲካል ኮሌጅ በሜዲካል ዶክተርነት ሊመረቅ
ከጫፍ ደርሶ ነበር

11 ይሄ የ412 ገጽ ታሪካዊ ልብወለድ በመስከረም 26 አሉላ በመሩት የዶጋሊ ድል መታሰብያ


በአል እለት እ.ኤ.አ በ1987 ወጣ፡፡በማሞ ውድነህ ተጽፎ በአባተ መኩርያ የተዘጋጀው ስለ አሉላ
የተጻፈው ተውኔትም በተመሳሳይ ወቅት በብሄራዊ ትያትር በመድረክ ላይ ውሎ ለበርካታ ወራት
ታይቷል፡፡

12በዚህ ወቅት የኤርትራ ክፍለሃገር አስተዳዳሪ የነበሩት ጄኔራል ደበበ ሀይለማርያም በቁጥጥር ስር
ውለው በጦር ካምፕ ውስጥ ታስረው ነበር፡፡

13አማጺው ሃይል የሬድዮኑን ጣብያ ተቆጣጥሮት ነበር

14ማሞ እንደሚለው ከሆነ ደበበ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንንን ስለጉዳዩ
ለማናገር ቢደውልላቸውም እሳቸው በተራቸው በወቅቱ የማስታወቂያ ሚንስትር ለነበሩት ታዋቂው
ጋዜጠኛ አሃዱ ሳቡሬ ሳይነግሯቸው ቀርተዋል

15ማሞ በአብዛኛው ለፖሊስና እርምጃው ላይ ቢጽፍም አንዳንድ ጊዜ ለአዲስ ዘመንም ይጽፋል

16ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ማሞ በኤርትራ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪነት እንዲመረጡ ከሚፈልጋቸው


ሰዎች መሃል አማኑኤል አምደ ሚካኤል በንግግራችን ወቅት የፖሊት ቢሮው አባል ነበሩ፡፤የማሞ
ሁለተኛ እጩ ደጃዝማች ተስፋ ዮሃንስ ናቸው፡፡የኤርትራ ክፍለሃገር ምክትል አስተዳዳሪ በመሆን
ለበርካታ አመታ ያገለገሉ ሲሆን በንግግራችን ወቅት የማአድን ሚንስትር ነበሩ፡፡ማሞ ሚካኤል
እምሩ ሃሳቡን ወደውለት እንደነበር ያስታውሳል

17እዚህ ኮሚቴ እያለ ማሞ በተፈሪ በንቲ ቢሮ ይሰራ የነበር ሲሆን ተጠሪነቱ ለሱ ነበር

112
ጥቋቁር አናብስት

18ከክሶቹ መሃል ሰዎች እንዳሏቸው ከሚያስታውሳቸው(1)ምንም እንኳን ሚስቱ ከኦሮሞ አባትና


ከአማራ እናት የተገኘች የደብረብርሃን ሰው ብትሆንም ኤርትራዊ እንደሆነች(2)ኤርትራ ውስጥ
ባለድርሻ ነው(3)ደጋፊያቸው እንዲሆን ከኤርትራ ተቃዋሚዎች ገንዘብ ተቀብሏል(4)በኤርትራ
ውስጣዊ ቁርቁስ ውስጥ ታዋቂነትን ለማትረፍ ይንቀሳቀሳል(5)ለኤርትራውያኑ ጥሩ መስሎ
ለመታየት ይሞክራል የመሳሰሉ ሲሆኑ ሁሉንም እርባና ቢስ ሲል ያጣጥላቸዋል

19ማሞ እራሱ በአንድ ወቅት እቁብ ይጠጣ ነበር፡፡ያልተመቸው አንድ ነገር ስለነበር እቁቡን ጥሎ
ወጥቶ የእድር አባል ሆነ፡፡“ያለ እድርማ መኖር አይቻልም”ሲል ያክላል

20ማሞ ስለሱ ሲያነሳ“የዩንቨርሲቲ ምሩቁ አቶ ስብሐት ”በማለት ነበር

21 በአንድ ወቅት አዳማ ላይ በተደረገ የጤናና የንጽህና ኮንፍረንስ ላይ ከተሳታፊዎቹ መሃል


ስሜን አይተው በለዩኝ ጋዜጠኞች ከስብሰባው መኃል ተጠርቼ ነበር፡፡traditiion and
change in ETHIOPIA የሚለውን መጽሐፌን ስለሚያውቁት ሊያናግሩኝ ነበር፡፡ሊነግሩኝ
ያመጡት ትልቁ ዜና መጽሐፌን በአንድ የመጽሐፍ መደብር ጓደኛቸው እንዳየው ለመንገር ሲሆን
(በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት በሽያጭ ላይ አይገኝም)ወድያውኑ በወቅቱ የሳምንት ደሞዙን
የሚሆን ዋጋውን መቶ ብር አውጥቶ እንደገዛው ነገሩኝ፡፡ለመጽሐፍ እንዲህ ያለ መሰጠት ብዙም
የማይታይና አስደናቂ ነበር፡፡ከመጻሕፍት መደብር ከመግዛት እድሉን ሲያገኙ በፎቶኮፒ የሚያባዙት
ሰዎች ችግርም ምን እንደሆነ ይገባኛል

113
ጥቋቁር አናብስት

ይልማሐብተየስ
በኢትዮጵያ ቀደምት የወንጀል ክትትል ታሪክ ጸሐፊ
ከኃይለሥላሴ ጊዜ ጀምሮ የይልማ ሐብተየስን ስም አዲስ
አበባ መጽሀፍት መደብር ውስጥ ያሉ መጽሀፍት ሽፋን ላይ
አየዋለሁ። ከመጽሀፍቱ መሀል አንዳንዶቹን ላነብባቸው
ከመቻሌ በፊት ሁሉ እንዲሁ ገዝቼ አስቀምጪያቸው ነበር።
በጊዜው በወንጀል ነክ ድርሰቶች ቢታወቅም፣ የሚጽፈው
ያንን ብቻ አልነበረም። ወንጀል ነክ ታሪኮች እንደ "ደንበኛ
ሥነ ጽሑፍ" አይቆጠሩም ነበር፤ይልማ ሐብተየስም
መጽሀፎቹን የሚያያቸው በተመሳሳይ መነጽር ነበር።አላማው አንባቢዎቹን ማመራመር ሳይሆን
ማዝናናት ነው።ነገር ግን በቋንቋው ውበት እና በአፃፃፍ ዘይቤው ስለሚደነቅ ላነጋግረው ወሰንኩ።
መጀመሪያ ያገኘሁት በ1979 አጋማሽ ሲሆን ወዲያውኑ የሕይወት ታሪኩን ነገረኝ።

ቤተሰቦቹ ከመራህቤቴ ናቸው። እነሱም እንደ አብዛኛዎቹ የመራህቤቴ ሰዎች የእጅ ጥበብ ባለሙያ
ናቸው።መራህቤቴዎች በብዛት ሸክላ ሰሪ፣ ቀጥቃጭ፣ ሸማኔ የመሳሰሉት ናቸው። ነገር ግን አባቱ
ከሌላው የበለጠ የቤተክርስቲያን ትምህርት በማግኘታቸው ዲያቆን ብሎም ነጋዴ ነበሩ። አባቱ
በ75 ዓመታቸው በ1978 ሲሞቱ፣ያልተማሩት ባለቤታቸው ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ በ70
ዓመታቸው አርፈዋል። በይልማ ቤተሰብ ውስጥም እንዲህ ዐይነት ሰዎች አሉ።ቤተሰቡ ወደ አዲስ
አበባ መጥተው በቀጨኔ መድሐኒአለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሰፈሩ። ይህ አካባቢ መርሀቤቴዎች
በተለይ ሸማኔዎች የሚኖሩበት ነው።

ይልማ ሐብተየስ የተወለደው በአዲስአበባ በ1930ዓም ነበር። እስከ ሰባት ዓመቱ“በጨዋታ ብቻ”
አደገ። አምስት ዓመት ሲሆነው አባቱ የይልማን እናት ፈትተው ቀሪውን ዘመን በድጋሚ ሳያገቡ
ኖረዋል። በዚህ ጋብቻ ውስጥ የተፈጠረው ብቸኛ ልጅ ይልማ ነበር፤ይሁን እንጂ አባቱ
ከውሽማቸው ሴት ልጅ ወልደዋል።አብራቸው ግን አልኖረችም።እናቱ ደግመው ካገቡ በኋላ
እየሄደ ይጠይቃቸው ነበር። እናቱ “በጣም ደግ” ሲሆኑ አባቱ “ግትር እና“አክራሪ ሀይማኖተኛ”
ነበሩ። ዘወትር ወደ መርካቶ ለስራ ጉዳይ ከመሄዳቸው በፊት የሐይማኖት መጻሕፍትን ይደግማሉ ፤
ዘወትር እሁድ ደግሞ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ።

ሰባት ዓመት ሲሆነው “በራስ ደስታ ሆስፒታል መንገድ ላይ” በሚገኘው የዮሐንስ ቤተክርስቲያን
ትምህርት ቤት ገባ።በዚያ ዳዊት እና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን መድገም፣መፆምና ቤተክርስቲያን
መሄድ ተማረ።እንዲህ ያሉ ነገሮች ወላጆች በቤት ውስጥ ለልጆቻቸው የሚያስተምሩት ነገር
114
ጥቋቁር አናብስት

አልነበረም።ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩ ወላጆች እንኳን አንዳንዴ ካልሆነ በቀር ይህንን


አያደርጉም።መኳንንቶች ዘንድ ግን የሐይማኖት አስተማሪዎች ቀጥረው ልጆቻቸውን በቤት
እንዲያስተምሩ ማድረግ የተለመደ ነበር። ይልማ የፊደል ገበታን፣መልእክተ ሐዋርያን እንዲሁም
አባታችን ሆይን ተምሯል ፤ በትምህርቱ ይዘቱን ከመረዳት ይልቅ ቃሉትን ማስታወስ ላይ ትኩረት
ይደረጋል።እነኚህን ነገሮች ሙሉ ለሙሉ በቃል ማጥናቱ ሲረጋገጥ ከሶስት ዓመት በኋላ
“ተመረቀ”።ይህ ትምህርት ቤት አሰልቺና "ዘዴ/መላ? ቢስ" ሆኖ አገኘው። ምንም እንኳን
ትምህርቱ የግእዝ ምንባቦችን ደጋግሞ ማነብነብ ቢሆንም፣ ይልማ አሁንም ምንም የግዕዝ ቋንቋ
እውቀት የለውም።ንባብ የሚከወነው በጩኸት(ድምጽ በማውጣት)ሲሆን ቄሱ
የሚያነበውን(ተማሪዎቹን በአይኑ እየተቆጣጠረ)፣ተማሪዎቹ በህብረት ይደግማሉ።ወይም ሁሉም
በአንድነት እየጮሁ ያነባሉ።

የጎረቤት ጓደኛው አዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ትምህርት ቤት ሊሴ ገብረማርያም ገባ።


ይልማም ፈረንሳይኛ ባይችልም(በቤተሰቡ ውስጥ የፈረንሳይ ቋንቋ ወይም ባህል እውቀት
አልነበረም) በ10 ወይም 11 ዓመቱ እዚሁ ትምህርት ቤት ገባ።አባቱ ምንም እንኳን አክራሪ
የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቢሆኑም“የውጪ”ትምህርት ቤት ጥሩ ነው ብለው ያስብ ስለነበር፤ እንደ
ብዙ ኢትዮጵያውያን በትምህርት ቤቱ የነበረውንየካቶሊክ ተጽእኖ አልፈራውም።ለውጪ ቋንቋ
እውቀት እና ትምህርት ዋጋ ይሰጥ ነበር።ይልማ በዚያ ትምህርት ቤት እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ
ተማረ፤ጥሩ ትምህርት ቤት ነውም ይላል። መምህራኑ ከአማርኛ መምህሩ በስተቀር ሁሉም
ፈረንሳዊ ነበሩ። ለአንድ ዓመት የፈረንሳይኛ ቋንቋ ካጠና በኋላ ሌሎች ትምህርቶችን በፈረንሳይኛ
በሚገባ መከታተል ጀመረ፤የፈረንሳይ ቋንቋ እና ባህል በጣም ማረከው፤ሂሳብ ትምህርትን ቢወድም
“የሂሳብ ሊቅ አይደለሁም” ይላል። በሥነ ጽሑፉ ግን ገና አልተሳበም ነበር።

ይልማ በሊሴ አምስት ዓመት ከቆየ በኋላ፣ፓስተር ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖችን


ለማሰልጠን ኮርስ እንደሚሰጥ ሰማ።ይህ ኮርስ በዐይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን ዳይሬክተሩ ቻቦን
ይባል ነበር።ይልማ፣የጎረቤቶቹ ልጆች እንዲሁም ሌሎችን ጨምሮ 12 የሚሆኑ ልጆች ለዚህ ኮርስ
በ1948 ዓ.ም ተመዘገቡ።ትምህርቱ የሚሰጠው በፈረንሳይኛ ቋንቋ ነበር።ይህ ስልጠና የይልማን
የሕይወት አቅጣጫ የወሰነ ሲሆን፤እስከ አሁን ድረስ የላቦራቶሪ ቴክኒሺያን ነው።ጓደኛው ግን
ፈተናውን ስለወደቀ ለመድህን ድርጅት ይሰራ ነበር።

አንድ ዓመት ከፈጀው ስልጠና በኋላ በ1949 ይልማ በራስ ደስታ ሆስፒታል1እንዲሰራ ተመደበ።
በዚያ ለአንድ ዓመት ተኩል ከሰራ በኋላ በጎንደር የህብረተሰብ ጤና ኮሌጅ በከፍተኛ ላቦራቶሪ
ቴክኒሺያንነት ለመሰልጠን ገባ።ይህ ኮርስ በአይነቱ የመጀመሪያ ቢሆንም የጤና ጥበቃ መኮንነት

115
ጥቋቁር አናብስት

ስልጠና ከጀመረ ግን ሁለት ዓመት አስቆጥሮ ነበር።ይህ በUSAID የሚሰጠው ኮርስ ሁለት ዓመት
ይፈጃል።ትምህርቱ የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነበር። ነገር ግን በሊሴ ይህንን ቋንቋ ከመማሩም
በላይ በአርበኞች ትምህርት ቤት ለአምስት ዓመታት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ስለተከታተለ፣
ትምህርቱንለመረዳት ምንም አልከበደውም።ትምህርቱ ለላቦራቶሪ ቴክኒሺያኖች የሚሰጥ
“አጠቃላይ” የሚባል ስልጠና ሲሆን በክፍሉ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ ተመሳሳይ ኮርስ
ይወስዳሉ።

ይልማ ጎንደርን ወዶት ነበር። ከተማውን እንዲሁም የፋሲልን ግንብ ቢጎበኝም በኢትዮጵያ ታሪክ
ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አልነበረውም። ኮሌጁ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች የተሟሉለት ሲሆን
“በአሜሪካኖች የሚሰናዳው ምግብ በየቀኑ ስጋን ያካተተ ነበር”ጎንደር እያለ የፈጠራ ሥነ ጽሑፍን
ለማንበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍላጎት አደረበት። ይህ መነቃቃት የተፈጠረው ዙሪያውን ከከበቡት
ተማሪዎች ሲሆን በዚህ በኩል መምህራኑ ምንም ግፊት አላሳደሩበትም። በዚህ ጊዜ ካነበባቸው
ኢትዮጵያዊ ደራሲያንን መካከል እንዳልካቸው መኮንንን ይጠቅሳል፤"ጥሩ እና ሀይማኖተኛ ጸሐፊ"
ነው ይለዋል። ካነበባቸው የደራሲው ስራዎች መካከል "አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም"፣ "ጸሐይ
መስፍን" እና "የደም ዘመን" ይገኙበታል። ከከበደ ሚካኤል ስራዎች መሀል "ሮሚዮ እና ጁልየት"
(ከሼክስፒር የተዛመደ)፣"ታሪክና ምሳሌ"፣ "ከይቅርታ በላይ" (Beyond Pardon)፣"አቶ
በላይነህ" (Faustንመነሻ ያደረገ) እና"ታላላቅ ሰዎች"ን አንብቧል። ከውጪ ደራሲዎች አጋታ
ክሪስቲን፣ኧርል ስታንሌይ ጋርድነር፣ፒተር ቼኒይ ካነበባቸው መሀል ናቸው።እነዚህ ሶስት ደራሲዎች
ይብዛም ይነስምይልማ በኋላ መፃፍ ሲጀምር የሚከተለው የሥነ ጽሑፍ “ዘውግ” ተከታይ
ጸሐፊዎች ናቸው። ቀስ በቀስ ይልማ እንደ ዶስቶቭስኪ፣ ቶልስቶይ፣ ጎርኪ፣ ዲክንስ፣ ሔሚንግዌይ
ያሉትን“ደንበኛ ጸሐፍት”ማንበብ ጀመረ፤ይህ ዐይነቱ ንባብ ግን “ቀስ በቀስ፣ ዘግየት ብሎ”
የተጀመረ ነው።

የጎንደር ቆይታው ሲጠናቀቅ አንዳችም ነገር አልፃፈም፤“ለትምህርት ቤት የሚሆን ድርሰት እንኳን።


”በ1953 ወደ አዲስአበባ ተመለሰና በመጠን ትንሽ ቢሆንም በመሳሪያዎች በተሟላው የኢትዮ
ስዊድሽ የልጆች2 ክሊኒክ ተቀጠረ። ይልማ በዚህ ክሊኒክ ለሶስት ዓመት ሰርቷል።

ወደ መዲናይቱ ከመጣ በኋላ ይልማ “በመጠጥ ቤትና በልጃገረዶች ዙሪያ የማንዣበብ” ሕይወት
ይበልጥ እየሳበው መጣ። ነፃ ጊዜውን ሁሉ እዚህ ማጥፋት ጀመረ።

116
ጥቋቁር አናብስት

ቀጥሎ የልጆች የሥነ ምግብ ጥናት ክፍል(በኋላ የኢትዮጵያ የሥነ ምግብ ጥናት ኢንስቲትዩት)
ተቀላቅሎ እስከአሁን ድረስ እዛው ይሰራል። በስዊድናዊ ዳይሬክተር ስር የላቦራቶሪ ቴክኒሺያን ሆኖ
ስራ ጀመረ። በ1956 መጨረሻ ወደ ስዊድን አቅንቶ በኡፕሳላ ኬሚካል ኢኒስቲትዩት ለሁለት
ዓመት ያህል ከተማረ በኋላ ወደ ድሮው የስራ ቦታው ተመለሰ። ስዊድን ቢበርድም ወዶት ነበር፤
እዚያ ሀገር ብዙ ጓደኞች ሲኖሩት፣ ከፊሎቹ አዲስአበባ እያለ የሚያውቃቸው ናቸው። ስዊድናውያን
ቀዝቃዛ እና ከሰው የማይቀላቀሉ ቢሆንም እነሱንም ወዷቸው ነበር፤“ግለኝነት የሚያጠቃቸው ግን
ማንንም የማይጎዱ” ናቸው ይላል። በስዊድን“ጥሩ ጊዜ”ሲያሳልፍ ቋንቋቸውንም ለምዶት ነበር
የተመለሰው።ነገር ግን በስዊድን ለመቆየት አላሰበም። ምናልባት ዳግመኛ የመጎብኘትና በዚያው
የመቅረት ፍላጎት ሳይኖረው አልቀረም(ይህን ያለው መንግስቱ ሐይለማሪያም ገና በሥልጣን ላይ
እያለ ነው)።

በ1959 ወደ ሀገሩ ተመልሶ በኢትዮጵያ ሥነ ምግብ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ቴክኒሺያን ሆኖ


እስከአሁን ድረስ በዚህ ማእረግ ይጠራል።ይህ መስሪያ ቤት ጥሩ የስራ ቦታ ቢሆንም፣ “ሁኔታዎች
ከመሻሻል ይልቅ እየባሰባቸው ነበር።”

***

ይልማ ሀብተየስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመፃፍ የሞከረው ከጎንደር የማህበረሰብ ጤና ማእከል


እንደተመለሰ በ1953 ነበር። የመጀመሪያ መጽሐፉ ከሁለት ዓመት በኋላ ታተመ።የፃፈው በኢትዮ
ስዊዲሽ የህፃናት ክሊኒክ በሚሰራበት ወቅት ሲሆን ረቂቁን ወደ ማተሚያ ቤት ወስዶ በቅድሚያ
500 ብር፣መጽሀፉ ታትሞ ዝግጁ ሲሆን ደግሞ ሌላ 500 ብር ከፍሎ፣ ለመጽሐፍት መደብሮች
ራሱ እያዞረ ማከፋፈል ነበረበት።በ1955 "ያልታደለች በሰው ሰርግ ተዳረች" በሶስት ሺህ ቅጂዎች
ታትሞ ለገበያ ቀረበ።ታሪኩ“ማህበራዊ ችግሮችን”የሚዳስስ ሲሆን፣ ልጃገረዶችና ሴቶች
በማህበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ቦታ “ከፍቅር ይልቅ” ቁሳዊ ዋስትናቸውን የሚያረጋግጥላቸውን ባል
ለመፈለግ እንደሚገፋፉ ያስረዳል። ይልማ "መጽሐፉ ጥሩ አልነበረም" ይላል።2,500 ቅጂዎች
ከተሸጡለት በኋላ የቀሩትን ቅጂዎች መርካቶ ወስዶ ለጉራጌ መጽሐፍት ሻጮች በርካሽ ዋጋ
አስረከባቸው።

ይልማ ሐብተየስ መፃፍ የጀመረው “መፃፍ እንደሚችል ስለተሰማው” ነው።እንዲጽፍ


የሚያበረታቱትም አሉ።ለጓደኞቹ ረዣዥም ደብዳቤዎች ይጽፍላቸው ነበር። ከነዚህ መሀል በጎንደር

117
ጥቋቁር አናብስት

የሚገኝ አንዱ እንደ ቀልድ "እንደዚህ መፃፍ ከቻልክ ለምን ደራሲ አትሆንም?"ይለዋል።ይህ ጥያቄ
አብሮት ቀረ፤ጊዜውን በከንቱ ከማባከን እንደ መዝናኛ መፃፍ ጀመረ።የመጀመሪያውን መጽሀፍ
ሲጽፍ“ደስታ ተሰማው”፤ገና መፃፍ ሲጀምር “የገንዘብ ኪሳራ ቢደርስበትም ለመንፈሱ የሚያረካ
ነበር።” የኢትዮጵያ ደራሲያንን ሁኔታ ስለሚያውቀው፣ ከድርሰት ስራ ገንዘብ አተርፋለሁ ብሎ
አልተነሳም።የሚጽፈው ሁሌም በአማርኛ ነበር፤በሌላ ቋንቋ የመፃፍ ሀሳብ ተከስቶለትም አያውቅ።

የመጀመሪያ መፃፉ በደንብ ባይሸጥም፣ መፃፉን አላቋረጠም ነበር፤ሁለተኛው የተሻለ አቀባበል


አገኘ። የታተመው ከመጀመሪያው መጽሐፍ አንድ ዓመት በኋላ ሲሆንመጻፍ የጀመረው
ደግሞበቀደመውዓመትነው። ርዕሱ "እትዬ ላድርስሽ" ሲሆን አንድ ወንድ የማያውቃትን ሴት
ለወሲባዊ ጉድኝት የሚጠይቅበት የተለመደ አባባል ነው። አነስተኛ መጽሀፍ ብትሆንም፣ ይልማ
“በደንብ ተወደደች” ይላል። ታሪኩ “ልጃገረዶችን ከመንገድ ዳር ጠርተው ወደ መኪናቸው
አስገብተው እንደፈለጉ ከተጫወቱባቸው በኋላ እንደ ቆሻሻ ስለሚጥሏቸው ሀብታም ወንዶች ነው።
” መጽሀፉ “ግብረገብነትን የሚሰብክ ነው፤ በሃይማኖት አንጻርም ቢታይ” እንዲህ ዐይነት ነገር
በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ዘወትር ማየቱ ቅር ስለሚያሰኘው፣መጽሐፉ የስሜቱ ማስተንፈሻ
ነበር። መጽሀፉ በሁለት ወር ውስጥ 3,000 ቅጂዎች መሸጡ ጥሩ ነው ብሎ ያስባል።ይህ መጽሐፍ
በድጋሚ አልታተመም፤ነገር ግን ከህዝቡ ያገኘው ምላሽ ስላስደሰተው በዛው ዓመት (1956)
የሚቀጥለውን መጽሀፍ መፃፍ ጀመረ።

ይህም "ለአርባስምንት ሰአት ተጋቡ" የተሰኘው መጽሐፍ በ1957 ዓ.ም ታተመ። ታሪኩ ስለ
አንዲት የታጨች ሙሽሪት ነው። ሙሽራው ሰርጉ ላይ ሳይገኝ ቀረ። የቤተሰቡ ጓደኛ የሚያገባት
ሌላ ወንድ ቢያገኝላትም የደረሰች እርጉዝ ስለነበረች በሰርጉ ምሽት ምጥ ያዛት። የሰርጉ ቬሎ
እርግዝናዋን ደብቆላታል።ሙሽራውና ሙሽሪት ጭራሽ አይተዋወቁም፤በጊዜው በኢትዮጵያ ይህ
የተለመደ ነበር። ባል የህመሙን መንስኤ ሳያውቅ ሚስትን ወደ ሆስፒታል ይዟት ይሄዳል። ዶክተሩ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልየው የተወለደው ልጅ አባት መስሎት "እንኳን ደስ አለህ!" ሲለውክው
ይላል። ጋብቻው ለ48 ሰአታት ብቻ የቆየው በዚህ ምክንያት ነው።መጽሐፉ “አዝናኝ” ሲሆን
ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቶ የታተሙት 3,000 ቅጂዎች ወዲያው ተሽጠውለታል። ከካናዳ ማክጊል
ዩኒቨርስቲ ዲግሪ ያገኘው መብራህቱ ዮሐንስ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለዚህ መጽሀፍ ቅኝት
ሰርቶለት ነበር። በቅኝቱ መጽሐፉ ጥሩ እንደሆነና ፀሐፊው ተሰጥኦ እንዳለው፣ እንዲሁም የተሻለ
መፃፍ እንዳለበት መፃፉን ይልማ ያስታውሳል።

118
ጥቋቁር አናብስት

በሚቀጥለው መጽሀፉ ይልማ በሰፊው የሚታወቅበትን የወንጀል ታሪክ ፃፈ።ይህ "እሱን ተይው"
የተባለ መጽሐፍ በ1958 ዓ.ም ጀምሮ ከአንድ ዓመት በኋላ ተጠናቀቀ።ታሪኩ ባልፈፀመው
ወንጀል፣ አባቱን በመግደል ስለተከሰሰ ሰው ነው። እውነታኛው ገዳይ በመጨረሻ ሲያዝ ተከሳሹ ነፃ
ይወጣል።

በጊዜው የወንጀል ታሪኮች ለኢትዮጵያ አዲስ ነበሩ፤ማንም እንደዚህ ዐይነት መጽሀፍ ለመፃፍ ሞክሮ
አያውቅም ይላል ይልማ። ይሁን እንጂ በቃለመጠይቃችን ወቅት ጥሩ መጽሐፍ እንዳልነበር
ተሰምቶታል፤ተቀባይነትን ያገኘው “አዲስ ዐይነት መጽሀፍ በመሆኑ ብቻ ነው” ይላል።እንደዚህ
ዐይነት “ልብ አንጠልጣይ” ታሪኮችን ለመፃፍ ተበረታታ። መጽሀፉ በሰባት ወይም በስምንት ወር
ውስጥ 3,000 ቅጂዎች ተሸጠ።ነገር ግን እርሱ ራሱ በመጽሐፉ ስላልረካ ከቃለመጠይቃችን ጥቂት
ቀደም ብሎ "ሶስተኛው ሰው" በሚል ርዕስ አሻሽሎ ጽፎታል።

እንደ ወንጀል ታሪክ ፀሐፊነቱ አጋታ ክሪስቲ እና ኧርል ስታንሌይ ጋርድነር ተጽእኖ አሳድረውብኛል
ይላል።

የሚቀጥለው መጽሀፉ ነጥሮ የወጣበትና፣ የአንባቢዎቹንመጠን የጨመረለት ነበር፤ ምንም እንኳን


ይህ ሁኔታ ዝግ ብሎ የተከሰተ ቢሆንም። መጽሐፉ "ከቀብር መልስ"ሲሰኝ የታተመው በ1960
ነው። በ1974ዓም ይህ መጽሀፍ ለቴሌቪዥን እንዲመች ተደርጎ "ያልተከፈለ እዳ" በሚል ርዕስ
እንደገና ተጽፎ በሁለት ክፍል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ነበር።በኋላ በህዝብ ጥያቄ ይደገም
ተባለ። ከዚያ በኋላ እየተደጋገመ አራት ጊዜ ታይቷል። አዘጋጁ አፈወርቅ መና ሲሆን፣ “በጣም ዝነኛ
ሆኖ” ነበር። በዚህ መንገድ መጽሀፉን ማንበብ የማይችሉ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያኖች ጋር
በመድረሱ “እውቅናው” የተረጋገጠ ሆነ። ከዚህ በኋላ ታሪኩን በልብወለድ መልክ የድራማውን
ርዕስ ተጠቅሞ እንደገና ጽፎት፣በ1978ዓም በኢትዮጵያ መጽሐፍት ማእከል አማካይነት
በ10,000 ቅጂዎች ታተመ። ሁለተኛው እትምም ተመሳሳይ ቁጥር ነበረው።

የሚቀጥለው መጽሐፉ"ሳይናገር ሞተ"ነበር።በ1961 ተጀምሮ በ1962 ወይም 63 ታተመ።


የታተመው 3,000 ቅጂዎች ብቻ ሲሆን ወዲያውኑ ተሽጦ አለቀ።ታሪኩ ፍቅረኛው የነበረችን ሴት
አስክሬንን ከአልጋው ስር ስለሚያገኝ የሴት-አቃጣሪ ነው።የገደላት ቀናተኛው ባሏ ሲሆን፣ለወንጀሉ
ውሽማዋ ተጠያቂ እንዲሆን አድርጎ አቀነባበረው።ነገር ግን ገዳዩ በመጨረሻ ይገኝና አቃጣሪው ነፃ
ይወጣል።

119
ጥቋቁር አናብስት

"ደስ ያለው ሀዘንተኛ" ደግሞ በ1964 ወጣ። ታሪኩ 5,000 ብር ሰርቆ ከሚወዳት ባለትዳር
ፍቅረኛው ጋር ስለሚኮበልል ሰው ነው። ከዚያ ሞቶ ይገኛል። በመጨረሻ ግን ሞቶ የተገኘው ሰው
የወንጀለኛው መንታ ወንድም ሆኖ ይገኛል። ወንድሙን የገደለው ወንጀለኛ ራሱ ሲሆን፣
አላማውም እሱ ላይ የሚደረገውን ክትትልለማስቆም ነበር። በመጨረሻ፣ ፍትህ ይሰፍናል።

****

ይልማ ገና ጀማሪ ጸሐፊ እያለ፣ በጊዜው እንደነበሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ደራሲያን መጽሀፎቹን ራሱ
ማሳተም ነበረበት። ለማስተየብ፣ ሳንሱር ለማስደረግ፣ ለማተም ራሱ ወጪውን ይሸፍንና ለመጽሀፍ
ሻጮች ራሱ ያከፋፍላል። ከመጽሀፍ ሻጮች የድርሻውን እየዞረ የሚሰበስበውም ራሱ ነው። ይህ
ስራ ከባድና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው፤“ምንም ትርፍም የለውም”። በዚህ የተነሳ ይልማ ለተወሰነ
ጊዜ መፃፍ አቁሞ ነበር። ይሁን እንጂ ለ"ጸደይ" መጽሔት ሁለት አጫጭር ታሪኮችን ጽፏል።
አንደኛው "የአብየቅየለሽ ኑዛዜ" ሁለተኛው ደግሞ "ደም የነካው እጅ" ይሰኛሉ። ይሄ ሁሉ
ከ1966ቱ አብዮት በፊት ነበር።

አብዮቱ ሲፈነዳ ይልማ ለሁለት ዓመት ያህል ሙሉ ለሙሉ መፃፍ አቆመ።ፖለቲካ ውስጥ ገብቶም
ሆነ ለመግባት ፍላጐት ኖሮት አያውቅም።በአብዮቱ የመጀመሪያ ደረጃ ወቅት ብዙ ግራ መጋባት/
ውዥንብር ስለነበረ እሰከናካቴው መፃፉን ተወው።

አብዮቱ ከፈነዳ ከሁለት ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚሰራ አዘጋጅ የቴሌቪዥን ድራማ
እንዲጽፍ ሲጠይቀው ተስማማ። ይልማ ለ"ጸደይ" መጽሔት የፃፈውን አጭር ታሪክ "ደም የነካው
ጎጆ" ለቲቪ ድራማ እንዲመች አድርጎ ፃፈው። በተመሳሳይ ርእስ በ1968 ተዘጋጀ።

በሚቀጥለው ዓመት ሌላ የቴሌቪዥን አዘጋጅ፣ ሌላ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲጽፍ ጠየቀው። በዚህ


መሰረት የመጀመሪያውን የወንጀል ታሪክ መጽሀፉን "እሱን ተይው"ን ወደ ድራማ ለውጦት "ቁጭ
ብለው አይሞቱም" በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በቴሌቪዥን ቀረበ።

ከዚያ በኋላ ቀይ ሽብር መጣ። የፖለቲካ ባለጋራዎች ጠላቶቻቸውን መግደል ሲጀምሩ የአዲስ አበባ
ጎዳናዎች በሬሳ ተሞሉ። በዚህ የተነሳ ይልማ “የመፃፍ ፍላጎቱ ለሶስት ዓመት ጠፋ።” ከዚህ በኋላ
"ያልተከፈለ እዳ" የተሰኘውን ከዚህ በፊት የተጠቀሰውን የቴሌቪዥን ድራማ መሰረት አድርጎ
ልብወለድ ፃፈ።

120
ጥቋቁር አናብስት

ብዙም ሳይቆይ "አጋጣሚ" የተሰኘ ልብወለድ ጽፎ"ያልተከፈለ እዳ"በታተመበት የኢትዮጵያ


መጽሐፍ ማዕከል በዚያው አመት በ1978 ዓ.ም ታተመ። ሁለቱም በደንብ ተሽጠው በዚያው
ዓመት በድጋሚ ታተሙ። በሚቀጥለው ዓመት "የአብየቅየለሽ ኑዛዜ" ወደ ልብወለድ ተለውጦ
በተመሳሳይ አሳታሚ በ10,000 ቅጂዎች ታተመ።የሚቀጥለው ልብወለዱ "ሌላው እጅ" በ1979
ዓ.ም በ15,000 ቅጂዎች ታተሟል። "ሶስተኛው ሰው" ደግሞ በ1980 ታተመ።

***

በቃለመጠይቃችን ወቅት ይልማ በደንብ የሚታወቅ ደራሲ ሲሆን፣ ከጽሑፍ ስራውም ጥሩ ገቢ


ያገኛል።ይሁን እንጂ ለመኖር “ከመደበኛ” ስራው የሚያገኘው ደሞዝ ያስፈልገው ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከድርሰቶቹ ብቻ በሚያገኘው የሚተዳደር ጸሐፊ የለም ይላል ይልማ፤"አቤ
ጉበኛ ሞክሮ ነበር፤ ግን አልተሳካለትም" ሲል ጨምሮበታል። የመጽሐፍት ገበያ ውሱን ነው፤
ኢትዮጵያውያን ደግሞ የማንበብ ልማድ የላቸውም ይላል። ነገር ግን ሁኔታዎች ከጊዜ ወደጊዜ
እየተሻሻሉ ነው ፤ ምክንያቱም፣“ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የመዝናኛ አማራጭ የለም፤ የሚኬድበትም
ቦታ የለም።” ኢትዮጵያውያን ከጊዜ ወደጊዜ ፊታቸውን ወደ ንባብ ይመልሳሉ ብሎ ያስባል፤ይህ
ደግሞ ደራሲያንን ይጠቅማል።በተጨማሪም “አሁን ለመፃፍ ጥሩ ጊዜነው” የሚል ስሜት
ይሰማዋል፤ሌላም ምክንያት አለ፦ ጥሩ እንቅስቃሴ ያላቸው አሳታሚ ድርጅቶች አሉ። እነዚህም
የመንግሥት አሳታሚው ኩራዝ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬስን ተክቶ ጥሩ ስራ እየሰራ
የሚገኘው የኢትዮጵያ መጽሀፍት ማእከል ናቸው። እነኚህ አሳታሚዎች ደራሲዎች መጽሀፎቻቸውን
ለማውጣት ያለባቸውን ጭንቅ ከፍለውላቸዋል፤ረቂቃቸውን ለሳንሱር ክፍል በማቅረብ፣
ለአታሚዎቹ ቀብድ በመክፈል፣ መጽሐፍቶቻቸውን በማከፋፈል፣ የተሸጡ መጽሀፍትን ክፍያ
በመሰብሰብ እና “በማስተዋወቅ”ብዙ ጫና ቀንሰውላቸዋል።ይህ አዲስ ሁኔታ ደራሲዎችን ረድቷል፤
አበረታቷልቷል።

ይልማ ሐብተየስ ከመፃፍ ብዙ እርካታ እንዳገኘ ይናገራል። መፃፍ “ሀሳቡ እንዳይከፈል”አድርጎታል


፤“መጠጥ ቤት ከመሄድ መፃፍ ይሻላል” ይላል። ብቸኝነትን እንደሚመርጥና ለማንበብና ለመፃፍ
ሰላምና ፀጥታ እንደሚፈልግ ይናገራል።ብዙ አንብቧል፤በዋነኛነት የሚያነበውም “ቁምነገር የተሞሉ
መጽሐፍትን ”እንጂ የሚጽፋቸውን ዐይነት የወንጀል ታሪኮችን አይደለም። በቃለመጠይቃችን
ወቅት የኧርቪንግ ዋላስ መጽሀፍትን እያነበበ ነበር። መጽሀፍ መሰብሰብ ስለሚወድም ቤቱ ውስጥ
ደህና ክምችት አለው።
121
ጥቋቁር አናብስት

ይልማ እኔ እስካነጋገርኩት ጊዜ ድረስ አላገባም፣ወደፊትም ማግባት አይፈልግም። ጋብቻ ብዙ ችግር


ይጎትታል ብሎ ያስባል። በጋብቻ ውስጥ ያሉ ጓደኞቹ ሁሌ ሲያማርሩ ይሰማል፤ስለ ሚስታቸው
ሳይሆን ስለ "ተቀጥላው ቤተሰብ"፣―የሚስታቸው ዘመዶች እና የወንዱ የራሱ ቤተሰቦች ብዙ
ዐይነት እርዳታ ይጠይቃሉ። አንድ ደራሲ ለመፃፍ የአእምሮ ሰላም ይፈልጋል፤ነገር ግን ትዳር ውስጥ
ብዙ አትኩሮትን የሚሰርቁ ነገሮች አሉ፤ ለምሳሌ ክርስትና፣ ቀብር፣ለቅሶ መቀመጥ፣ ለቅሶ መድረስ፣
ግብዣ የመሳሰሉት። በዚሁ ምክንያት“ቋሚ የሴት ጓደኛ” አይፈልግም፤ አልነበረውምም።
ከ1962ዓም በፊት የሴት ጓደኛ ነበረችው፤ነገር ግን በዚያው ዓመት ወደ ሰሜን አሜሪካ ሄደች።
እዚያ ካለ ኢትዮጵያዊ ጋር ጋብቻ ስለፈፀመች ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለች ብሎ አይገምትም።
በሕይወቱ በጣም የቀረባት ሴት ይቺ ብቻ ነበረች። ወሲብ ሲያስፈልገው ወደ ሴተኛ አዳሪዎች
በመሄድ ከሴቶች ጋር የሚፈጠር አላስፈላጊ የስሜት ቁርኝትን ያስወግዳል።

በፈጠራ ስራው፣ ረዥም ልብወለድን ይመርጣል። በተውኔት መልክ የፃፈውን ብቸኛ መጽሀፍ፣
ባህል ሚኒስቴር ውስጥ ለሚገኝ ኮሚቴ ለግምገማ ልኮታል።እነሱም “አሳለፉትና” መርካቶ አካባቢ
ወደሚገኘው ራስ ቲያትር እንዲዘጋጅ “ላኩት”። ነገር ግን ይልማ “ቲያትር ቤቱን ስላልወደደው
አስወጥቶ ወሰደው።” ከዚያ በልብወለድ መልክ እንደአዲስ ፃፈውና በ1978 "አጋጣሚ" በሚል
ርዕስ ታተመ። ይልማ የፃፋቸው አጫጭር ልብወለዶች ጥቂት ናቸው።

በቃለመጠይቃችን ወቅት ሌላ መጽሀፉ “ሳንሱር ክፍሉ አሳልፎት” ለመታተም ዝግጁ ሆኖ ነበር።


የኢትዮጵያ መጽሀፍት ማእከል "ደላላው"3

በሚል ርእሰ እንዲያሳተምለት ይፈልጋል።

ይልማ "የምጽፈው ለማዝናናት ነው" ይላል። ለአንባቢዎቹ አንዳችም “ጥልቅ መልእክት”


ለማስተላለፍ አይፈልግም ፤ ነገር ግን ጥሩ የንባብ ጊዜ አሳልፈው ከተዝናኑ እርካታ ያገኛል።

***

በ1981መጨረሻ እና በ1982 ወደ ኢትዮጵያ በተመለስኩ ጊዜ፣ በመጽሀፍት መደብሮች ውስጥ


የይልማ ሐብተየስን አዳዲስ መጽሀሐፍት ማየት ችዬ ነበር። በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ካሉ
ታዋቂ "አዝናኞች" መሀል ያለጥርጥር አንዱ ነው። በጣም ያነበቡ እና የተማሩ ሰዎች የይልማ ቋንቋ
“በጣም ጥሩ” ስለሆነ በራሱ ዘይቤ እንደሚጽፍ ደራሲ መጽሐፍቶቹ በቁምነገር መወሰድ
እንዳለባቸው ይነግሩኛል።
122
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻዎች

1) የተሰየመው በራስ ደስታ ዳምጠው ስም ነው። ራስ ደስታ ዳምጠው ከኃይለስላሴ የበኩር ልጅ


ከልእልት ተናኘወርቅ ባሎች መሀል አንዱ እና የእስክንድር ደስታ አባት ናቸው። እስክንድር አብዮቱ
ሲፈነዳ የባህር ሀይል ሃላፊነቱን ጥሎ መፈርጠጡ ብልህ ውሳኔ ሳይሆን አይቀርም።

2) በጊዜው ፕሮፌሰር ኤድጋር ማንሀይመር የተቋሙ ዳይሬክተር ነበሩ። ኋላ ኡጋንዳ ውስጥ


በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፏል።

3) መጽሐፉ ግንቦት 1980ዓም ገበያ ላይ ውሏል።

123
ጥቋቁር አናብስት

ነጋሽ ገብረማርያም እና ወንድሙ አሰፋ ገብረማርያም


ባይተዋር ግን ባለተሰጥኦ ደራሲ እና ጋዜጠኛ
ነጋሽ ገብረማርያም የሚታወቀው ሆነ በብዛት የሚሞገሰው በአንድ
መጽሐፉ ነው "ሴተኛ አዳሪ"፡፡ ከዚህ ውጪ ሌሎች በርካታ
ጽሁፎችን ጽፏል፡፡እንደ ጋዜጣ አርታኢነቱም በርካታ በጎ
ተጽእኖዎችን በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ላይ አሳድሯል፡፡

ነጋሽ በአንድ ትንሽ ገጠራማ በሆነች በጨርጨር አውራጃ ሃረርጌ


ሃብሮ ውስጥ በምትገኝ መቻራ በተባለች ቦታ ተወለደ፡፡በቅርብ
ከሚገኘው ከተማ አሰበ ተፈሪ ይርቃል፡፡መቻራን ምንም አይነት
መንገድ አያቋርጥም፡፡ነጋሽ የሶስት አመት ልጅ ሳለ ዳኛ
ማግባታቸውን በነገሩት የእናቱ ግምት ላይ ተንተርሶ በ1917 ዓ.ም
እንደተወለደ ይገምታል፡፡የጋብቻ ቀኑም ይታወቃል፡፡የበፊት
ባላቸው 1የነጋሽ አባት ነጋሽ በተወለደበት ተመሳሳይ ወቅት ነበር
ያረፉት፡፡2

አባቱ ገበሬ ሲሆኑ ነጋሽ አብሯቸው ለጥቂት አመታት የኖረው የእንጀራ አባቱ ደግሞ ዳኛ ነበሩ፡፡
በኋላ ነጋሽ የእናቱ አባት ከሆኑት ከወሎ ከመጡት ከእስልምና ወደ ክርስትና ወደተጠመቁት
ከፊትአውራሪ አሊ ቡሊ ዘንድ ለመኖር ሄደ፡፡እኚህ አያቱ በገበሬነት ከወሎ ወደ ሃረርጌ የሄዱት
በራስ መኮንን ዘመነ ግዛት ነው፡፡በሳቸው ጊዜ የፊትአውራሪነትን ትልቅ መዕረግ ቢያገኙም ቅሉ
ለመኮንን ሳይሆን ለሌላ ጌታ ነበር ያደሩት፡፡አሊ ቡሊ በርካታ መሬት ማግኘት ችለው የነበር ሲሆን
ከአዲስ አበባ የጎጃም ሴት በሚስትነት አስመጥተው ከሷም ሶስት ልጆችን ሲወልዱ የነጋሽ እናት
ሁለተኛዋ ነበረች፡፡

በአንድ ወቅት ፊት አውራሪ አሊ ቡሊ ለአስተዳዳሪነት ቢታጩም ባለመማራቸው መክንያት እድሉ


ለሌላ ሰው ተላልፎ ተሰጠ፡፡ይሄ አበሳጭቷቸው ሁሉም ልጆቻቸውነ የልጅ ልጆቻቸው መማር
እንደሚገባቸው ወሰኑ፡፡“ቢያንስ ዳዊት መድገም አለባቸው”….ቄስ ወደ ቤታቸው በማስመጣትም
ልጆችና ሰራተኞችን ማስተማር ያዙ፡፡በርካታ ዘመድ አዝማድ ስለሰበሰቡም በዙርያቸው ብዙ
ቤተሰብ ነበራቸው፡፡ነጋሽም ለመማር እሳቸው ጋር ነበር የሄደው፡፡እዛም 14 ወይም 15 አመት
እስኪሞላው ድረስ ቆየ፡፡እ.ኤ.አ1939 ከጣልያን ወረራ ጥቂት ጊዜ በኋላ ከታላቅ ወንድሙ አሰፋ

124
ጥቋቁር አናብስት

ጋር ለመኖር ሄደ፡፡አሰፋ በወቅቱ ለጣልያኖች ትርጁማን የነበረ ሲሆን መጀመርያ እንግሊዘኛውን


ቀጥሎ ጣልያንኛውን ነበር የለመደው፡፡

ነጋሽ በአያቱ ቤት በኖረበት ወቅት የቤተ ክህነት ትምህርት ለተወሰኑ አመታት ተምሯል ወንድሙ
አሰፋ ግን በአምስት አመት ከነጋሽ የሚበልጥ ሲሆን3ነጋሽ እዚያ በሚማርበት ወቅት ዘመናዊ
ትምህርት የማግኘት እድል አጋጥሞታል፡፡መክንያቱም ካናዳውያን ሚስዮኖች በቃጠሎው የኢብሳ
ክልል አካባቢ“አረማውያንንና ዘላኖችን አስተምሮ ለመለወጥ” በሚል የሚስዮን ጣብያና ትምህርት
ቤት በመቻራ ስላቋቋሙ ነበር፡፡ከአሊ ቡሊ መኖርያ እስከ ሚስዮኑ በበቅሎ ወይም በእግር የግማሽ
ቀን መንገድ ነበር፡፡አሊ ቡሊ ነጫጮቹን ቤቶች ሲመለከቱ የማወቅ ጉጉት አድሮባቸው ወደእዚያው
አቀኑ፡፡የውጪ ሃገር ዜጎቹ አርብቶ አደሮቹን ለማስተማር ቢመጡም እንደ ልባቸው እነሱን
ለማግኘት ከእንቅስቃሴያቸው አኳያ መቸገራቸው ተነገራቸው፡፡ስለዚህም አሊ ቡሊ ስድስት ወይም
ሰባት የቤት ልጆቻቸውን ቤተሰቦቻቸውን ጨምረው ለመላክ ተስማሙ፡፡የነጋሽ ወንድም አሰፋም
ከተላኩት መሃል ነበር፡፡የነጋሽ ግን ምን አልባትም በእድሜው ማነስ መክንያት አልተላከም ፡፡

ከላይ እንደጠቀስነው እ.ኤ.አ በ1939 የጣልያን ወረራ ከማብቃቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነጋሽ
ከታላቅ ወንድሙ ጋር ለመኖር ሄደ፡፡4ከስድስት ወራት በኋላ ነጋሽ በአካባቢው በተጀመረው
የጣልያን ትምህርት ቤት ትምህርቱን ሲጀምር አሰፋ5 ግን ከአንድ ወር በኋላ ግን እዚያው ሃረርጌ
ውስጥ ወዳለው ወደ መሰላ ተዛወረ፡፡ሌላ የጣልያን ትምህርት ቤት በአካባቢው ስላልነበረ ነጋሽ
ወደ ቄስ ትምህርት ቤት መመለስ ነበረበት፡፡በቄስ ትምህርት ቤቱም ወንጌል፤ዳዊትና ዜማን አጠና፡፡
የኔታው ችሎታቸው እስከዚህም ስለነበር ነጋሽ ግዕዝን በአግባቡ አላጠናም፡፡6 እንደነገረኝ ከሆነ
አሁን ምንም ግዕዝ አያውቅም ፡፡ተማሪዎቹ ምንም ሳይገባቸው እንዲሁ በደመነፍስ ነበር የሚማሩት
ብሎኛል፡፡ነጋሽም ከጊዜያት በኋላ የቄስ ትምህርቱን ሲያስታውስ እንደባከነ ጊዜ ነበር የሚሰማው፡፡

በ1933 ዓ.ም የጣልያን ሃይሎች ተሸንፈው ኢትዮጵያን ለቀቁ፡፡ነገር ግን ብዙ ጣልያኖች ሃገር


ውስጥ ቀሩ፡፡አሰፋ ስራውን ቢያጣም ከጣልያኖቹ ጋር አብረህ ሰርተሃል ተብሎ በተባባሪነት
አለመታሰሩም እድለኛ የሚያሰኘው ነበር፡፡7ወንድማማቾቹ ማሳላን ለቀው ወደ አሰበ ተፈሪ አቀኑ፡፡

ከጣልያን መውጣት በኋላ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ጎልቶ መታየት ጣልያኖቹንም በሲጋራ ማጨስ
፤ስኳር መጠቀምና ሴተኛ አዳሪነትን በማስተማር መወንጀል የጊዜው ፋሽን ሆነ፡፡ይህ የሴተኛ
አዳሪዎቹ ሃሳብ ጣልያኖቹ የአርበኞቹን ሚስቶች እነሱ ዱር ቤቴ ብለው በወጡበት ወሽመው
በመተዋቸው የተስፋፋ ነው፡፡ነጋሽ እንደሚለው ከሆነም “እነዚህ ሴቶች ከዛ በኋላ ቡና ቤቶችን
ከፍተው ስራዬ ብለው ሴተኛ አዳሪነቱን ተያያዙት በዛም የተነሳ ሽርሙጥና ተስፋፋ ሴተኛ አዳሪነት
ከዚያ በፊትም የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ በፊትም ሆነ አሁን እንዝህላል ናቸው”
125
ጥቋቁር አናብስት

ይላል፡፡ነገር ግን የጣልያኑ ጊዜ ነገሩን በይፋ ስላወጣው ጣልያኖቹ ይህን ነገር (በስህተትም


ቢሆን)በኢትዮጵያ ውስጥ በማስተዋወቅ ይተቻሉ፡፡

አሰፋ ገብረማርያም በጣልያን ጊዜም ሆነ በኋላ ስለነበረው የሴተኛ አዳሪነት ችግር የጻፈው መጽሐፍ
ነበር፡፡ይህ መጽሐፉ ለሴት ልጃገረዶች ሞራላዊ ይዘት ያለው የሴተኛ አዳሪነት ህይወትን መጥፎነት
ለሴት ልጆች የሚሰብክ እነሱንም በሚያስጠነቅቅ ሁኔታ የተጻፈ ነበር፡፡ነጋሽ ወንድሙ አሰፋ
ከጣልያኖች ጋር የነበረውን የቅርርብ ኃጥያቱን በዚህ ብቸኛ ስራው ከትከሻው የማውረድ ስርየትን
ለመፈጸም ያደረገው እንዳልሆነ ነው የሚያስበው፡፡ከወንደሙ ጋር ስለ ብቸኛ ልብ ወለዱ "እንደ
ወጣች ቀረች" ተነጋግረው ስለማያውቁ እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡

አሰበ ተፈሪ ላይ አሰፋ ለክፍለ ሃገሩ አስተዳደር በጸሃፊነት ተቀጠረ፡፡ይህንን ስራም ከ 7 ወር እስከ
አንድ አመት ለሚደርስ ግዜ እዚያው አሰበ ተፈሪ ላይ ሆኖ ሰርቶታል፡፡8 ነጋሽ ደግሞ ለመጀመርያ
ጊዜ በእንግሊዘኛ ትምህርት ወደ ሚሰጥበት ትምህርት ቤት ሲገባ በዚያም እንደ አዲስ ሆሄያቱን
በእንግዳ ቅደም ተከተል ተምሮ ሌሎች ላይ መድረስ ተቸገረ፡፡ነገር ግን እንግሊዘኛን ለመማር
ስለጓጓ ውጤታማ ሆኗል፡፡ታፈሰ አስራትና አንድ ሌላ ጥላሁን የሚባሉ መምህራንን በተለይ
ያስታውሳል፡፡

በአሰበ ተፈሪ ቆይታው ማሳረግያ ላይ ነጋሽ ወባ ይዛው ለህክምና ወደ ሃረር ከወንድሙ ጋር ሄደ፡፡
ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላ ወደ አዲሳ አበባ ተጉዘው ከአጎታቸው ኮሎኔል አባተ አሊ ዘንድ
ተቀመጡ፡፡9አጎታቸው ኮሎኔል አባተ የፖሊስ መኮንን ሲሆን በኋላም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ
ሆኖ ነበር፡፡መኖርያው አሜሪካ ኤምበሲ አካባቢ ከአምሐ ደስታ ትምህርት ቤት ትይዩ ነበር፡፡አሰፋ
በጸሃፊነት በጦር ሚንስቴር ውስጥ ሲቀጠር ነጋሽ ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገባ፡፡ከሶስተኛ
ወይም አራተኛ ክፍል ቢጀምርም መምህራኑ ጥሩ የእንግሊዘኛ እውቀት አልነበራቸውም፡፡
አንዳንዶቹ በኬንያ በስደት በወረራው ወቅት የለቃቀሟት ስለነበረች ነጋሽ ጥሩ ውጤት ለማግኘት
ቀሎታል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከፍ ወዳሉ ክፍሎች ተዘዋወረ፡፡እዛም መምህራኑ የተሻሉ ሲሆኑ
አንዳንዶቹ እንግሊዛውያን አብዛኞቹ ሃበሾች ነበሩ፡፡ከትምህርት መማርያ መጽሐፍቶች መሃል
የሚያስታውሰው አንዱ መጻሐፍ Ethiopian lives ይሰኛል፡፡

ከተወሰኑ አመታት በኋላ ከብሪቲሽ ካውንስል የመጣች ወይዘሮ ቡከር የተባለች እንግሊዛዊ ሴት
የመምህራን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት እንደምትጀምር ጥሩ የተባሉ ተማሪዎችም ወደ አውሮጳ
ተጉዘው የመማር እድል እንደሚያገኙ ገለጸች፡፡እሱ ከሚማርበት ክፍል አራት ወይም አምስት
ተማሪዎች የመምህራን ማሰልጠኛውን በ1944 እ.ኤ.አ ተቀላቀሉ፡፡ነጋሽም ከነሱ መሃል አንዱ
ነበር፡፡እስከ 1946 እ.ኤ.አ አቆጣጠር እዚያው አጠና፡፡ የሁለት አመቱ ኮርስ ለአንደኛ ደረጃ
126
ጥቋቁር አናብስት

መምህራን ለማሰልጠን የሚሰጥ ነበር፡፡በመጀመርያ ተማሪዎቹ በጣልያኖች ወታደራዊ ካምፕ


ውስጥ ከንግድ ትምህርት ቤት አጠገብ ባለው በዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ነበር
የቆዩትም ሆነ የተማሩት፡፡ አብዛኞቹ ተማሪዎች አዳሪዎች ነበሩ፡፡የማደርያና የትምህርት ክፍያም
አይጠየቁም፡፡አንዳንዴ እንደውም ልብስም ጭምር ይሰጣቸው ነበር፡፡በሁለተኛ አመቱ የመምህራን
ማሰልጠኛው ራስ ደስታ አካባቢ ወደ ሚገኘው የፖሊስ ክበብ ተዛወረ፡፡ነጋሽ ይህኛውን ትምህርት
ቤትተስማሚ ሆኖ አገኘው፡፡አብዛኞቹ መምህራን አውሮጳውያን ሲሆኑ የአውሮጳውያንን
የእንግሊዘኛ ቅላጼ መረዳት ጀመረ፡፡አንዳንዶቹ መምህራን ከምርጡ ጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት
የመጡ ነበሩ፡፡ዋና ዋና ትምህርቶቹም ታሪክ ጂኦግራፊ፤አማርኛና ፤ስነ ትምህርት ነበሩ፡፡የተወሰነ
ሳይንስም ይሰጥ ነበር እንደ ነጋሽ አባባል፡፡

በወቅቱ ጥቂት የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስራዎች ነበር ማግኘት የሚቻለው፡፡ነጋሽ ደግሞ ከዛ ውስጥ
የተወሰኑትን አንብቧል፡፡በዚህ ወቅት ነበር ከከበደ ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ ጋር ለመተዋወቅ ፤
የተክለ ጻዲቅ ታሪክ መጻሕፍትን ለማንበብ የበቃው፡፡(እኚህ ደራሲ እንደውም አንድ ክፍል
አስተምረዋቸው ነበር፡፡መጻሐፎቻቸው በግሩም አማርኛ የተጻፉ ሲሆኑ አንዳንዶች ከታሪካዊ
ይዘታቸው በተጨማሪ ባላቸው ስነጽሁፋዊ ጥራት ይመዝኗቸዋል፡፡)የአለቃ ታዬ የኢትዮጵያ ታሪክ
(እንደ ነጋሽ ትውስታ ከሆነ አለቃ ታዬ ለኦሮሞ የነበራቸው አመለካከት የወረደ ነበር) እና ታዋቂው
አማርኛ ስዋሰው መማርያ የሆነው የመርስኤ ሀዘን ወልደቂርቆስ ኢትዮጵያውያን በወቅቱ ማግኘት
የሚችሏቸው መጻሕፍት ነበሩ፡፡ነጋሽ ስለ አማርኛ ጽሁፎቹ እስከዚህም ስለሆነ ፈተናን ለማለፍ
እንጂ ለመዝናናት አልነበረም የሚያነባቸው፡፡

ከመምህራን ማሰልጠኛ እ.ኤ.አ በ1946 ዓ.ም ከተመረቀ በኋላ ነጋሽ ጅማ ወደ ሚገኘው (the
sudan interior mission missionaries) ትምህርት ቤት ተልኮ ለማስተማር እንዲችል
ሚስዮናውያኑን በመጠየቅ ማመልከቻ አስገባ፡፡ይህንን ስራ የፈለገበት መክንያት የተሻለ እንግሊዘኛ
ለመማርና በእነሱ በኩል የሚመጣ የውጪ እድል ካለ ለማግኘት ሲል ነበር፡፡ስራው ተሰጥቶት 24
ተማሪዎች የነበሩበትን ክፍል ለአንድ አመት አስተማረ፡፡ሚስዮናውያኑ ጥሩና ሃይማኖተኛ ሆነው
አገኛቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በየቀኑ ማንበብ በትርፍ ሰአቱም የስብከት ዘዴዎችን ማጥናት ጀመረ፡፡
ይህ ለነጋሽ አይከብድም፡፡(ሃይማኖተኛና ከቤቱ አጠገብ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤትክርስትያን የሚሄድ ቢሆንም ያን ያህል ጠንካራ አማኝ አይደለሁም ይላል፡፡በንፋስ ስልክ
አካባቢም ከቪላ ቨርዴ አጠገብ የያሬድ ትምህርት ቤትን ለማሰራት የተቋቋመው ኮሚቴም
ሊቀመንበር ስለነበር ትንሽም ብትሆን የሃይማኖተኝነት እርሾ ውስጡ ሳትኖር አትቀርም)

ከአንድ አመት የጅማ ቆይታ በኋላ ነጋሽ ለስራው ተስማሚው ሰው እንዳልሆነ እየተሰማው መጣ ፡፡
ስለዚህ ኮተቤ ለሚገኘው ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልክቶ
127
ጥቋቁር አናብስት

(በወንድሙ አሰፋ ተጽእኖ) የመግቢያ ፈተናውን አለፎ ለመግባት ቻለ፡፡በዚያ ከ 1948 እ.ኤ.አ
ጀምሮ እስከ 1950 መጨረሻ ድረስ ለሶስት አመታት 10ኛና 11ኛ ክፍልን እየተከታተለ ቆየ10
አስተማሪዎቹ በአብዛኛው ስዊድናዊያን ሲሆኑ የተወሰኑ ካናዳውያን ነበሩ ይላል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ሳለ ነጋሽ ድርሰቶችን መጻፍ ጀመረ፡፡አንዳንድ አስተማሪዎችም እንዲጽፍ


አበረታቱት የሚጽፋቸውም ድርሰቶች በክፍል ውስጥ ይነበባሉ፡፡ትምህርት ቤቱ ትንሽ ቤተ
መጻሕፍት የነበረው ሲሆን ነጋሽ የሚነበቡ ቀደምት የእንግሊዘኛ ስራዎችን እንደ ዲከንስ አር.ኤል
ስቲቨንሰንን የመሳሰሉትን አነበበ፡፡የማንበብ ልማዱን ያዳበረው በእዚያ ሳለ ነበር፡፡ንባብን
ለመዝናናት መዝናናትንም በማንበብ ተማረ፡፡

ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ በ1950 እ.ኤ.አ የተመሰረተውን የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅን ተቀላቀለ፡
፡ ከኮተቤው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ ከጄኔራል ዊንጌት፤ ከተፈሪ መኮንን ከነበሩ ተማሪዎች
ተመርጠው ነበር እዚህ ኮሌጅ የገቡት፡፡በካናዳውያን ጀዝዊቶች የሚመራና ሁሉም ሰራተኞችም
ካናዳዊያን ጀዝዊቶች ነበሩ፡፡ዳይሬክተሩ ደግሞ ከንጉሱ ጋር ቅርበት የነበራቸው የተከበሩት ሉሲየን
ማት ነበሩ፡፡(ማት በቅርብ ግዜ እንደሞቱ ይናገራል)አንድ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሌላው የጥበብ እውቀት
ጥናት በዩንቨርሲቲ ኮሌጁ ሁለት ፋከልቲዎች ነበሩ፡፡ በንግግራችን ወቅት ግን ምርጫዬ “ስህተት
ነበር” የሚለውን ለጥበብ እውቀት ጥናት ፋከልቲ ለመቀላቀል ነበር ነጋሽ የመረጠው፡፡ ሙያ
መልመድ ይሻላል በማለት፡፡በመጀመርያው አመት ኢኮኖሚክስ፤የአፍሪቃቅኝት(ታሪክና ጂኦግራፊ)፤
ፍልስፍና፤ስነአእምሮ፤አጠቃላይ ሳይንስ ወዘተ ወሰዱ፡፡

ነጋሽ ከመጀመርያው አመት በኋላ አልዘለቀበትም፡፡እንግሊዞች ምጽዋን ለቀው እየወጡ ስለነበር


የኢትዮጵያ መንግስት በምጽዋ ወደብ የሚሰሩ የተማሩ ወደብ አስተዳዳሪዎችን መተካት ስለነበረበት
13 ያህል ተማሪዎች ተመርጠው የወደብ አስተዳደርን እንዲአጠኑ ስለታሰበ ነጋሽም ከነሱ መኃል
አንዱ ሆነ፡፡ አስተማሪዎቹ ቤልጂጎች ነበሩ፡፡ለአመት ያህል አዲስ አበባ ውስጥ በተዘጋጀ ክፍል
ውስጥ የወደብ አስተዳደርን ተማሩ፡፡በዚህ ወቅት ወደ ምጽዋ ኤደንና ጂቡቲ የመሄድ እድል
አጋጥሞታል፡፡ይህን እሱ በማእረግ የተመረቀበትን ትምህርት ሲያጠናቀቁ ከእሱ በስተቀር ሁሉም
እዛው ስራ ላይ ተቀጠሩ፡፡ነጋሽ የምጽዋን የአየር ንብረት ስለሚያውቀውና ስላልወደደው ወደእዚያ
መሄድ አልፈለገም፡፡በምትኩ ለስድስት ወራት የሰራበት አውራ ጎዳና መስርያ ቤት በእቃ ግምዣ
ቤት ጸሃፊነት በጊዜው ብዙ በሚባል ደሞዝ በብር 200 ስራ ተቀጠረ፡፡ ስራው አሰልቺ ስለሆነበት
በአመቱ ለቆ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገባ፡፡

128
ጥቋቁር አናብስት

ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአሜሪካን የማስታወቅያ አገልግሎት(usis)በአዲስ አበባ አስተርጓሚና


የቤተመጻሕፍት ባለሙያ ለመቅጠር በሚሰጠው ፈተና ተፈተኖ የመጀመርያ ተመራጭ በመሆንም
ቦታውን ለሁለት አመታት በወርሃዊ 300 ብር ደሞዝ ያዘው፡፡ ከሁለት የዚህ አመታት ስራ ቆይታ
በኋላ ሁለት አማራጮች ቀረቡለት በደሞዙ ላይ የ25 ብር ጭማሪ ወይም ወደ አሜሪካ ለትምህርት
መላክ፡፡ወደ አሜሪካ ለትምህርት መላኩን በመምረጥ በUSIS ዝግጅት መሰረት እ.ኤ.አ በ1955
ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ በUSIS የሰራበት ወቅት ለአሜሪካ ቆይታው መለማመጃ ሆኖታል፡፡ብዙ
መጻሕፍትን በቤተ መጻሕፍቱ ማንበብ፤በተጋባዥ እንግዶችም የሚሰጡትን ትምህርቶች መከታተል
ስላቻለ አብዝቶ ማትረፉን ይናገራል፡፡ብቃት ካላቸው ሰዎች ጋር መስራቱም በስራው
ውጤታማነትን ሲማር ለባህርይውም ጥሩ ተጫዋችነትን አትርፎለታል ሰዎች እዛ ሳለ ምን እንደሰራ
ያስታውሳሉ፡፡ከኢትዮጵያ ስራው በተቃራኒ ምንም መጥፎ ገጠመኝ በUSIS ስራ ላይ በነበረበት
ወቅት አልገጠመውም፡፡በስሩ ሰራተኞች የነበሩበት የመጀመርያው የነጋሽ አጋጣሚ ሲሆን በወቅቱ
ግን ብዙ አነበብኩ እንጂ አልጻፍኩም ይላል፡፡

***

ከዚያ በኋላ ወደ አሜሪካን ተልኮ በሞንታና ግዛት ዩንቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤትን
ተቀላቀለ፡፡ለዚህም መክንያቱ ለመጻፍ በመፈለጉ ነበር፡፡ትምህርት ቤት ሳለ በድርሰቶቹ ይሞገስ
ነበር፡፡ላነበባቸውም ደራስያን አድናቆት ይሰማዋል፡፡“ምንም እንኳ ሰነፍ ብሆንና ግፊት ብፈልግም
በአግባቡ ከተከፈለኝ ቀበቶዬን አጥብቄ ለመጻፍ ዝግጁ ነኝ መጻፍ በራሱ ጠቃሚ የሆነ የመማር
ሂደት ነው”ይላል፡፡በዛ ረገድም ተሰጥኦው እንዳለው ስለሚያምን ነበር ጋዜጠኝነትን ማጥናት
የጀመረው፡፡በመጀመርያ በቋንቋው እና ነገሮች በሚጓዙበት ፍጥነት የተነሳ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ግር
ቢሰኝም እርዳታ ግን አገኘ፡፡ሰዎች መልካም እንደነበሩለትም ያምናል፡፡የውጪ የትምህርቱ እድሉ
ለሁለት አመታት ቢቆይም ነጋሽ ከዛም በላይ ለመቀጠል ፈለገ፡፡ለኢትዮጵያ መንግስት ስለ ጉዳዩ
ጻፈ፡፡ወንድሙ አሰፋም ጉዳዩን በወቅቱ ትምህርት ሚኒስቴር ከነበሩት ከበደ ሚካኤል ዘንድ
እያስጨረሰ ቆየ፡፡መንግስት በጉዳዩ ቢስማማም ለድርጊቱ ግን ቀሰስተኛ ስለነበር ነጋሽ ከሁለት
አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ መመለስ ነበረበት፡፡በማስታወቅያ ሚንስቴርም ስራ ጀመረ፡፡

በወቅቱ ልማድ እንደነበረው ከውጪ ተመላሽ ተማሪዎች ንጉሱን እጅ ለመንሳት ይሄዳሉ፡፡ ለንጉሱ
በተነገራቸው መሰረት ከበደ ሚካኤል ነጋሽን ጨምረው ሌሎች ተማሪዎችን አቀረቡ፡፡በዚህ
ስነስርአት ላይ ነበር ከበደ ሚካኤል ለንጉሱ ከተማረው ትምህርትና ከስራው አንጻር ለዚህ ተማሪ
ተጨማሪ የትምህርት እድል እንዲሰጠው ሲሉ ለነጋሽ የጠየቁለት፡፡ንጉሱ ከተወሰነ ማቅማማት
በኋላ 2 አመት እንዲጨመርለት ስለወሰኑ ነጋሽ ከ 4 ወራት በኋላ ወደ አሜሪካ ሲራኩስ

129
ጥቋቁር አናብስት

ዩንቨርሲቲ ኒውዮርክ ለተጨማሪ ሁለት አመታት የጋዜጠኝነት ትምህርትን ለመከታተል ተመልሶ


ሄደ፡፡ በዚህኛው ወቅት ትምህርቱን አስደሳች ሆኖለት፡፡አማካይ የሚባል ዐይነት ተማሪ የነበረ
ሲሆን ዘገባን ለመጻፍና ለማንበብ ፍጥነት ከማስፈለጉ አንጻር ከብዶት ነበር፡፡ከዚህ የተነሳ በስነ
ማህበረሰብና ኢኮኖሚክ ጥናቶች ላይ የተደገፉ ሃቲቶችን መጻፍ ጊዜ ስለሚሰጠው ተስማሚ
ሆነለት፡፡አሜሪካ በነበረበት ወቅት ከተማረ ሃገርና ሰው መሃል መሆኑ ይሰማው ነበር፡፡በርካታ
ጠቃሚ መረጃዎችም ወደ ህዝቡ በሳንሱር ሳይታነቁ እንደሚተላለፉ ይናገራል፡፡ልምዱን
በማምጣት በኢትዮጵያ ትክክለኛ መረጃ አቀባይ የመገኛኛ ብዙኃንን ለመፍጠር ተንቀሳቅሷል፡፡
አሜሪካ እያለ ምንም እንኳን በማስታወቂያዎች እጁ ሊጠመዘዝ ቢሞክርም ሚዲያው በብዙ
መንገድ ተአማኒ ለመሆን እንደሚጥር ከዚህ ውጪ ግን በሃቅ ላይ የተመሰረተ ለውይይት በሩን
የከፈተና ግልጽ እንደሆነ ይናገራል፡፡

በ1959 ወይም በ1960 እ.ኤ.አ ወደ ሃገሩ ተመልሶ በኢትዮጵያ ሄራልድ ላይ መስራት ጀመረ፡፡
በወቅቱ ዶ/ር ታልቦት ነበር በማስታወቂያ ሚንስቴር ስር የሚታተመው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ
አርታኢ፡፡ዶ/ር ታልቦት በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ አመታትን የቆየ አፍሪቃ አሜሪካዊ ሲሆን በብዙ
መልኩ ደግ የሆነ ሰው ሲሆን ነጋሽ ግን አሜሪካን ካየው ጋር ሲያነጻጽረው ታልቦት ያን ህልም ጥሩ
የሚባል ጋዜጠኛ ባይሆንም በባለስልጣናቱ ዘንድ ጠቀሜታው የጎላ፤ተጽእኖ ፈጣሪ፤ደግ፤ ሁልጊዜም
ለእርዳታ በሩ ክፍት የሆነ ነበር ይላል፡፡

ብዙም ሳይቆይ ግርማቸው ተክለሐዋርያት የማስታወቂያ ሚንስትር ስለሆኑ የአማርኛ ጋዜጦቹን


ማሻሻል ፈለጉ፡፡ነጋሽ ገብረማርያምንም ከደራሲና ምሁሩ ወልደግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ስር(በወቅቱ
እንደ ጋዜጣው አማካሪ ስለነበሩ በይዘቱ ላይ የነበራቸው ተጽእኖ ፈጣሪነት ከመቀነሱ አኳያ
በሹመትም በሽረትም ለማለት በማያስችል መንገድ)የአማርኛው ጋዜጣ የአዲስ ዘመን አርታኢ
እንዲሆን ጠየቁት፡፡“ወልደ ግዮርጊስ ለትናንሹ ነገር ሁሉ ግርግር ያበዙ ስለነበር ከሳቸው ጋር
በአርትኦት ጉዳዮች ላይ ሁሌ እንጋጫለን” ሲል አስተያየቱን ይሰጣል፡፡ነጋሽ በተጨማሪም
የጋዜጣውን አቀራረብ ለመቀየር ፈለገ፡፡በወልደግዮርጊስ ስር ሙሉው የፊት ገጽ ስለ ንጉሱ
የሚያወራ ስለነበር ሌላ ምንም ዜና በዚህ ገጽ ላይ የለም፡፡በአንድ ወቅት ነጋሽ በፊት ለፊት ገጽ ላይ
ከኬንያ ስለመጡ አዲስ የላም ዝርያዎች ጻፈ፡፡ይህንንም ያደረገው ጠቃሚ ነው ብሎ ስላሰበ ነበር፡፡
ወልደ ግዮርጊስ ግን የንጉሱ ፎቶ ባለበት ተመሳሳይ ገጽ ላይ የላም ፎቶ አብሮ መውጣቱ ላይ ቅሬታ
ገባቸው፡፡ሚንስትሩ ግርማቸው ተክለሐዋርያት ግን የነጋሽ ደጋፊ ነበሩ፡፡ቀስ በቀስ ይሄ የፊት ለፊት
ገጹ ላይ ዜና የማውጣት ነገር እየተለመደ ችግሩም እየተቀረፈ ስለመጣ በውጤቱም ጋዜጣው
መሻሻሉን ነጋሽ ያምናል፡፡ግርማቸው'በጣም የተገለጠላቸው'የማስታወቂያ ሚንስትር ነበሩ እንደ
ነጋሽ አባባል ቀልድ አዋቂ አንዳንዴም አሽሙረኛ ባስፈለጋቸው ጊዜም ንጉሱን የሚተቹ ስርአቱ
ላይም ያሉትን ችግሮች በግልጽ የሚናገሩ ሲሆን ሃያሲና የተሻለ ፕሬስ እንዲኖርም ይፈልጋሉ፡፡ ነገር
130
ጥቋቁር አናብስት

ግን በንጉሱ ላይና በመንግስት መስርያ ቤቶች ላይ የሚሰነዘር ትችት ስለሚከለከል ሰዎች ወደ ንጉሱ
በመሄድ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ንጉሱ በመሃል ጣልቃ ይገባሉ፡፡እንደ ነጋሽ አባባል ከሆነ
ግርማቸው ተክለሐዋርያትና አሃዱ ሳቡሬ የፕሬስን መሻሻል የሚፈልጉ ምርጦቹ የማስታወቂያ
ሚንስትሮች ነበሩ፡፡ነጋሽ በስዩም ሃረጎት (ጊዜያዊ) እና ማሞ ታደሰ ስርም ሆኖ ሰርቷል፡፡ ያኔ
ዲፕሎማቶች በጊዜያዊ ማስታወቂያ ሚንስትርነት ይሾሙ ነበር፡፡ ለአብነትም ተስፋዬ
ገብረእግዚ11የመጨረሻው የኃይለሥላሴ ጊዜ ሚንስትር ሲሆኑ ነጋሽም በእሳቸው ስር ሰርቷል፡፡

ነጋሽ ገብረማርያም ለኢትዮጵያ ሄራልድ ለበርካታ ወራት ለአዲስ ዘመን ደግሞ ለጥቂት አመታት
ከሰራ በኋላ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የሶማሊያ ክፍል አደራጀ፡፡ የአምስት ወይም ስድስት ሰዎች
ቡድን አዋቅሮ ስለ ሱማልያ የተጻፈውን ሁሉ እንዲያጠኑ ተደረገ፡፡12 ነጋሽ በቡድኑ ውስጥ
´የሚድያ ወኪል´ በመሆን ተመረጠ፡፡ቡድኑ በተጠኑት ግብአቶች ላይ ተመስርቶ ጥቆማዎችን
እንዲሰጥ እንዲያማክር ሪፖርቶቹ ደግሞ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲልክ ንጉሱም ዘንድ
እንዲቀርቡ ነበር የተፈለገው፡፡ነገር ግን በወቅቱ ሚኒስቴር የነበሩት ስዩም ሃረጎት ነጋሽን ወደ
ማስታወቂያ ሚንስቴር እንዲመለስ በመፈለጋቸው ለአመት ጥቂት ፈሪ ሲሆን ተመለሰ፡፡በደመወዙ
ላይም 200 ብር ጭማሪ ተደረገለት፡፡ በዚህም ወቅት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየተመሰረተ
ቢሆንም ነጋሽ ግን ለቴሌቪዥን ሳይሆን በሬድዮ ላይ ነበር የሚሰራው፡፡ለራድዮ ስራ አስኪያጁ
ረዳት ሆኖ በንጉሴ ሃብተ ወልድ ስር በማስታወቂያ ሚንስትሩ ውስጥ ይሰራል፡፡በዚህ ቦታ ነጋሽ
የፕሮግራም አስፈጻሚ ሲሆን በተጨማሪም በሚንስቴሩ ለውስጥ ሰራተኞች የአዘጋገብ ስልጠናን
ይሰጣል፡፡ነጋሽ በዚህ ስራ ላይ ከሶስት እስከ አራት አመታትን ቆየ፡፡ጌታቸው መካሻ በዚህ ወቅት
አዲሱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ፡፡13ነጋሽንም ዳግም ወደ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
መልሰው ላኩት፡፡

***

ነጋሽ ገብረ ማርያም የስነ ጽሁፍ ስራውን የጀመረው 1956 በታተመው በታዋቂው እና በወጉ
በተጻፈው ልብወለዱ ሴተኛ አዳሪ ነው፡፡ለአዲስ ዘመን በሚሰራበት ወቅት ግን መጣጥፎችና
ግጥሞችን (በስሙ)ይጽፋል14፡፡እዚያው እየሰራ ባለበት ወቅት ነበር ይህንን መጽሐፍም የጻፈው፡፡
የመጀመርያ ሙከራው ሲሆን ወድያውኑ ነበር የታተመለት፡፡

***

131
ጥቋቁር አናብስት

እዚህች ላይ አረፍ ብለን ስለ ወንድሙ እንቃኛለን፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ወንድሙ አሰፋ
በ1956/7 ዓ.ም አካባቢ ብቸኛ ስራውን "እንደወጣች ቀረች"ን አበረከተ፡፡ከዚያ በኋላ ዳግመኛ
ልብወለድ የመጻፍ ሙከራ አላደረገም፡፡ይህም ምናልባት መጽሐፉ ከታተመ በኋላ በተጫነበት
የስራ ሸክም ይሆናል፡፡በሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር የበላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከጥቂት
ግዜ በኋላ ሙሉ ምክትል ሚንስቴርነቱን ተሾመ፡፡በስተመጨረሻም በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር
ሆኖ በኒው ዴልሂ ህንድ ለሁለት አመታት ቆየ፡፡እዚያ በነበረበት ወቅት በድባቴ ህመም ክፉኛ
ይሰቃይ ስለነበር የህክምና እርዳታ ህንድ ውስጥ ለማግኘት ሞክሯል፡፡ወደ እየሩሳሌምም በ1959
ዓ.ም አካባቢ ለመሄድና ለመፈወስ ቢሞክርም ሁሉም ውጤት አልባ ሲሆኑ ለምክክር በወንድሙ
ነጋሽ ወደ ኢትዮጵያ ተጠርቶ በ1960 ዓ.ም አካባቢ ተመልሶ መጣ፡፡ነጋሽ አብሮት ቆየ፡፡ ወደ
አማኑኤል ሆስፒታል አብረው ሄዱ፡፡ቤተሰቦቹም ከነበረበት ሁኔታ እንዲወጣ በጸበል ቢሞከሩም
ምንም ሳይረዳው ቆይቶ አሰፋ ገብረ ማርያም በጥቅምት 21 1961 ዓ.ም እራሱን በመሳርያ ተኩሶ
አጠፋ፡፡

***

በ1964/65 ዓ.ም አካባቢ ነጋሽ በኢትዮጵያ ሬድዮ በሚሰራበት ወቅት "የድል አጥቢያ አርበኛ"
የሚል ተውኔት ጽፎ ነበር፡፡ጭብጡ በጣልያን ወረራ ማብቂያ አካባቢ ወደ አርበኞች ጎራ
ስለተቀላቀሉ አርበኞች ሲሆን በተውኔቱ የተሳለውን አርበኛ ቆንጆ ሚስት አንድ የጣልያን ወታደር
ይመኛታል፡፡ባል ቢጎሳቆልም ግን ጣልያኑ ስለተገደለ ባልየው አምልጦ ጣልያኖቹ እጅ
ከመስጠታቸው በፊት ኢትዮጵያንም ሳይለቁ ወደ አርበኞቹ ጎራ ተቀላቀለ፡፡ሚስቱ ከጣልያኑ ልጅ
አርግዛ ስለነበር ወለደች፡፡ልጁንም ባልየው በጉዲፈቻ መልክ ወሰደው፡፡ይህ ቴአትር በቀዳማዊ
ኃይለሥላሴ ቴአትር(አሁን ብሔራዊ ቴአትር) ለመድረክ በቃ፡፡

ነጋሽ በዚህ ወቅት ነበር በዋርሳው በአሰፋ ሚስት የወንድሙን ሃሳብ ሰርቋል የሚል ክስ የቀረበበት፡
፡ነጋሽ የዚህ ክስ መነሾ ወንድሙ የተናዘዘለትን የ20000 ብር ኑዛዜ ስለፈለገችው ነበር ይላል፡፡ነገሩ
ፍርድ ቤት ደርሶ ብዙም ተቀባይነትን ሳያገኝ የተጣጣለ ሲሆን እሷም ተሸነፈች፡፡ ምንም እንኳን
ቢረታም ነጋሽ 20000 ብሩን አላገኘም፡፡የኔ "ጀግኖች" በወንድሜ መጽሐፍ ላይ ከተሳሉት ይለያሉ
ሲል የሃሳብ ስርቆት ክሱን ያስተባብላል፡፡

***

132
ጥቋቁር አናብስት

ከራዲዮ ወደ አዲስ ዘመን ከተመለሰ በኋላ ከአለቆቹ ጋር መስማማት አቃተው፡፡ከነሱም መሃል


ወልደግዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ እና ያሬድ ገብረ ሚካኤል ይገኙበታል፡፡“የቄስ ተማሪዎች” ሲል
ይጠራቸዋል፡፡በዚህ መክንያት ወደ ሬድዮ ተመልሶ ለ3 አመታት 1966ቱ አብዮት አልፎ አንድ
አመት ድረስ እስኪሞላው ድረስ ቆይቶ ሰራ፡፡ በድጋሚ በአቶ ንጉሴ ሀብተ ወልድ ስር የመርሃ
ግብርና አስተዳደር ክፍል ምክትል የአስተዳደር ስራ አስኪያጅ በመሆን ሰራ፡፡ ከአብዮቱ በኋላ
የማስታወቂያ ሚንስትሩ ተስፋዬ ገብረእግዚ እና ተገኝ የተሻወርቅ ሲገደሉ ንጉሴ ሃብተወልድ
ታሰሩ፡፡ሚካኤል እምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቆይተው በኋላ የደርጉ ፖለቲካ አማካሪ ሆኑ፡፡
በኋላም የማስታወቂያ ሚንስትር ቦታን (ከዚህ በፊት ለአንድ አመት ያህል የአለቃ ገብረ
እግዚአብሔር ልጅ የአቤቶ እያሱና የንግስት ዘውዲቱ አፈ ቀላጤ ልጅ በነበሩት በያእቆብ ገብረ
እግዚአብሔር የተያዘ ነበር)ሚካኤል እምሩ ሲይዙት ነጋሽን ተጠባባቂ የኢትዮጵያ ስርጭት ስራ
አስኪያጅ አድርገው በሬድዮና ቴሌቭዥን ላይ ሾሙት፡፡ነገር ግን ነጋሽ አስተዳደር መሆን
ስላልፈለገ ሹመቱን ተቃወመ፡፡ስለዚህ በምትኩ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ
ሆኗል፡፡በሰባት ወራት ቆይታው በአሉ ግርማን በአርታኢነት ከሚሰራበት አዲስ ዘመን ከነበሩ ሰዎች
ጋር ሊግባባ ስላልቻለ ምክትሉ እንዲሆን አስመጣው፡፡ከዚያ በኋላ በአሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆን
ነጋሽ ወደ ሃገር ግዛት ሚንስቴር የሹመት ደብዳቤ ደርሶት ቢላክም ደሞዙን የሚከፍል በጀት
ባለመመደቡ እዛ ሳይሰራ ቀርቷል፡፡ስለዚህ ወደ ቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መስርያ ቤት
የህዝብ ግንኙነት የበላይ ሃላፊ በመሆን ተላከ፡፡ለሁለት አመታት ወይም ትንሽ በለጥ ላለ ጊዜ እዚያ
ሰራ፡፡በ1970 ዓ.ም እሱን ጨምሮ 130 ያህል ሰዎች በጡረታ እንዲወጡ ´ሲጠየቁ´ እድሜው 52
አመት ገደማ ነበር፡፡

***

ነጋሽ ጡረታ ሲወጣ ለመጻፍ የተሻለ ጊዜን አገኘ፡፡እንደ ጡረተኛ ሽማግሌ በተቆጠረበት ወቅት ነበር
በአዲሱ ችግሩ ላይ ባተኮረውና በብሄራዊ ቴአትር ለመድረክ በበቃው ተውኔት ብቅ ያለው፡፡
ተውኔቱ በኢትዮጵያ ልኬት የአመቱ ምርጥ ተውኔት ሊባል ይችላል፡፡ሃሳቡን ያገኘው ከእውነተኛ
የጡረታ ህይወት ተሞክሮ ነበር፡፡ከእሱ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያዘወትሩባት
ቡና ቤት ውስጥ እየተገናኙ እንደ ምሁርነታቸው ምን ማበርከት እንደሚችሉ ሲወያዩ አብዛኛው
ተስፋ አስቆራጭ ሃሳቦችን በህይወትና በጊዜያቸው ምን ለመስራት በሚያደርጉት ውይይት ዙርያ
ቢሰነዝሩም አንዳንዶች ግን ካፌ ወይንም ክለብ ከፍተው ተጋባዥ እንግዶችን የመጋበዝ ዐይነት
ሃሳብ ነበራቸው፡፡ ቢሆንም በተለይ የኢትዮጵያ ባንኮች በጡረታ ለወጡ ሰዎች ማበደር
ስለማይችሉ ያለ ገንዘብ መስራት አስቸጋሪ ነበር፡፡ከመሃላቸው ካለ አንድ ሃብታም ሰው ለመበደር
ቢጠይቁ እሱም አሻፈረኝ አለ፡፡ከዛ በኋላ አንዲትን ጥሩ ቤት ያላትን አሮጊት ሴትዮ ሌላ ቤት ያለው
ሽማግሌ አግብቶ የእሷን ቤት ለቡድኑ የመገናኛ ቦታ የማድረግ ሃሳብ መጣ 15ተውኔቱ በቡና ቤቱ
133
ጥቋቁር አናብስት

ይህ ሃሳብ በሚውጠነጠንበት ሁኔታ ነበር የተወለደው፡፡ታዋቂ ኮመዲም ለመሆን በቃ፡፡ሰዎች


ሙሉውን የሶስት ሰአት ጊዜ በሳቅ እንዳውካኩ ያልቃል፡፡ለቴያትር ቤቱም ማለፍያ የሆነ ለነጋሽም
ጥሩ የሚባል የ30000 ብር ገቢን አስገኘ፡፡ይህም ለመጀመርያ ተውኔቱ ካገኘው 3000 አንጻር
እጅግ ጥሩ የሚባል ገቢ ነበር፡፡ለዚህም ምክንያት ሲያስረዳ ብዙ ሰዎች ወደ ትያትሩ እየመጡ
ስለነበርና ከበፊቱ የላቀ የማጣጣም ችሎታ እያዳበሩ ስለነበር ነው ብሏል፡፡በአዲስ አበባም የትወና
ትምህርት ቤት ስለተከፈተ ትወናው እየተሻሻለ ስለመጣም ጭምር ነው፡፡

ነጋሽ ገብረ ማርያም በተውኔት ጽሁፍ ላይም ሆነ በቴአትር ምንም ትምህርት አልነበረውም፡፡
እንደሱ እምነት ከሆነ ግን የሰዎችን ልማድና ጸባይን ማወቁ ተውኔቱን ለመጻፍ ጠቃሚ እንደሆነለት
ይናገራል፡፡በተለይም በትውልድ ቦታው ሃረርጌ ከተለያዩ ብሄር የተገኙ ሰዎችን በአንድ ቦታ ሲኖሩ
አስተውሏል፡፡ይህንንም በመመንዘር ለጽሁፍ ስራው ግብአትነት ተጠቅሞበታል፡፡በቴክኒኩ ረገድ
ድክመቶች እንዳሉበት ያውቃል፡፡በአብዮታዊት ኢትዮጵያ ለመጻፍ ያየው ችግር ይሄ ብቻም
አልነበረም፡፡ሌላ ከባድ ተግዳሮትም ነበር፡፡በሚቀጥለው "ሐመልማል" በተሰኘ ተውኔቱ
የጠበቀው፡፡

በመንግስቱ ለማ ስር ተምረው ከዩንቨርሲቲ ተመርቀው የወጡ ወጣቶች እንደ ሁለተኛ ሳንሱር


አድራጊዎች ከመንግስት ሳንሱር አድራጊዎች ስር ተቀመጡ፡፡እነዚህም ወጣት ተማሪዎች ስለ አጻጻፍ
እናውቃለን ባዮች ሲሆኑ ሁሉን ነገር የሚያዩት ከሶሻሊዝም ርእዮተ አለም ጥግ እና ቴክኒክ አንጻር
ነበር፡፡እነዚህ በባህል ሚኒስቴሩ ውስጥ የተቀመጡ ርእዮተ አለማውያን ወጣቶች ተውኔቱን
ሐመልማል በአንዳንድ ቦታዎች እንዲቀይርና እንዲቆርጠው ነገሩት፡፡ነጋሽ ግን ተውኔቱን
ለመንግስቱ ለማ ወስዶላቸው ጥቂት መሻሻሎችን ከማድረግና በመርዘሙ እንዲቆረጥ አስተያየት
ከመስጠት በስተቀር ተውኔቱን«ጥሩ ነው»በማለት እንዲያልፍ ፈቀዱለት፡፡ነጋሽ እንደሚለው
ከሆነም መንግስቱ “ከትረካ በላይ ድርጊት ቢበዛ እንደሚመርጡ” አስተያየት ሰጥተውኛል ብሏል፡፡
ወጣቶቹ ግን በዚህ አልረኩም፡፡

ተውኔቱ ስለ ቤተሰብ ችግሮች ነበር ፡፡ሀመልማል 18 አመት ሲሞላት ወጣት ስትሆን እናቷ አንድ
የመንዝ ፊትአውራሪ ለማግባት የታጨች ወይዘሮ ነገር ግን ሃብታም ጉራጌ ያገባች ነበረች፡፡
የሐመልማል ወላጆች ሌሎችን ልጆችንም አላፈሩም፡፡ ከሐመልማል ገጽታ መመሳሰል ጋር ተደርቦ
የሐመልማል እናት የአሁኑ በሏ መሃን መሆኑንና ልጇ ከበፊት ወዳጇ የተወለደች እንደሆነች
ባወቀች ጊዜ ህመም ላይ ስለነበረች ትክከለኛ አባቷ ማን እንደሆነ ለመንገር ታሪኩን ለልጇ
ሐመልማል በጀመረችበት ወቅት ባልየው ቢገባም መናገሩን አላቋረጠችም፡፡16ባልየው በሚሰማው
ነገር ተቆጣ፡፡ከዚያ በኋላ ሚስትየው ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ዳነች፡፡በቁርባን በቤተክርስቲያን
ስለተጋቡም መለያየት አልቻሉምና በምትኩ ባልየው ሐመልማልን ከቤት አስወጥቶ አባሯት

134
ጥቋቁር አናብስት

ተቸገረች፡፡ነገር ግን በመጨረሻ የአባቷ ነብስ አባት የሆኑ አንድ ቄስ ባልና ሚስቱን በማስታረቃቸው
ባልየው ይቅርታ አድርጎ የእንጀራ ልጁን ይቀበላል፡፡ሰላምም ወደ ቤታቸው ይመለሳል፡፡

የርእዮተ አለም ወጣቶቹ ኮሚቴ ትያትሩን ከገመገሙ በኋላ የቄሱን ክፍል ቆርጦ እንዲያወጣ
ይነግሩታል ነጋሽ ግን ጠቃሚ በመሆኑ አይሆንም አለ፡፡ቀጥለው ቄሱ እንደ ቂላቂል ገጸ ባህርይ ሆኖ
በማርክሲስት ሌኒኒስት አስተሳሰብ አራማጅነት እንዲወከል ፈለጉ፡፡ነጋሽ ግን ቄሱ ጠቃሚ ሚና
በተውኔቱ ውስጥ እንዳላቸው ከከባድ ቁምነገሮች ዙርያ የሚገኙና መቀየር የማይችሉ መሆናቸውን
ተናገረ፡፡የመጨረሻውን እርቀ ሰላም የማያወርዱ ከመሆናቸው ሌላ እርሱ እራሱ የማርክሲስት
ሌኒኒስት ርእዮት አራማጅ ባለመሆኑ ከነሱ ጋር እንደማይስማማ ነገራቸው፡፡

ተውኔቱ እንዲታይ ሲል ብቻም ከነሱ ለመመሳሰል አልፈቀደም፡፡በምንነጋገርበት ወቅትም በነጋሽና


በነሱ መሃል ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡“እነኚህ ናቸው እንግዲህ ልምድ በሌላቸው ወጣቶች
የሚመራው የሃገሪቱ አብዮት የተፈጠሩት ችግሮች” ሲል ይናገራል፡፡(እንደ ሌሎች የዚህ መድብል
ቃለ መጠይቆች ሁሉ አብዮቱ በጊዜው በጥንካሬ የቀጠለ ቢመስልም አንዳንዶች ግን ከጅማሮው
እንደሚወድቅ ገምተው ነበር)

እ.ኤ.አ በ1990 የጻፈው አዲሱ ተውኔት "አስመሳይ ሃኪሞች" ይሰኛል፡፡ስለኤድስ በሽታ የተጻፈ
ሲሆን በሽታው ገና አፍላ በነበረበት ወቅት ወይም በታወቀ ሰሞን ሁሉን እናድናለን ስለሚሉ የባህል
ህክምና አዋቂዎች ነበር የጻፈው፡፡በተውኔቱ የባህል ሃኪሙ ወጣት ልጅ17እና ጓደኞቹ ኤች.አይ.ቪ
ኤድስን እናድናለን በማለት ክሊኒክ ይከፍታሉ፡፡18ምንም ላቦራቶሪም ሆነ ሌላ ቁሳቁስ አልነበረም፡፡
አንድ ዶክተር እንዲሁም የወንጀል ፍርድ ቤት አማካሪ የነበረ ሰው ህመምተኛ ተመስሎ ይሄዳል፡፡
በክሊኒኩ ያሉ ወጣቶች ትክክለኛ ያልሆነ መድሃኒት ለሰዎች እንደሚሰጡ ይደረስበትና ለጤና
ጥበቃ ሚኒስቴር ሪፖርት ይደረጋል፡፡ተከሰውም ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡ ዶክተሩም
ይመሰክርባቸዋል፡፡ምንም እንኳን በባህላዊ ህክምና ቤተ ሙከራ የሚባል እንደሌለ በማስረዳት
ለመከራከር ቢሞክሩም ሃሳዊ ሃኪሞቹ ተቀጥተው ይታሰራሉ፡፡ነጋሽ መልእክት ያለው ኮመዲ ነው
ይለዋል፡፡

ተውኔቱ በማስታወቂያ ሚንስቴር ህዝባዊ አመራር ስር ባሉ ሴንሰሮች ምንም ችግር አልገጠመውም፡


፡ነገር ግን አሁንም ወጣቶቹ የባህል ሚንስቴር ርእዮተ አለማዊያን የፍርድ ቤቱን ጉዳይ ያለበትን
ክፍል እንዲቆረጥ ነጋሽን ጠየቁት፡፡ነጋሽ ይህ ዋነኛ የተውኔቱ መልእክት የተላለፈበት ነው በሃገሪቱ
ስላሉ ጉዳዮችም የሚናገር ክፍል ነው በማለት ተከራከረ፡፡ይሄኛውም ግጭት በቃለመጠይቃችን
ወቅት ስላልተፈታ ተውኔቱም ለመድረከ አልበቃም፡፡

135
ጥቋቁር አናብስት

በአሁኑ ወቅት(በቃለመጠይቁ) ነጋሽ ገብረማርያም አንድ ልብወለድን ለመጻፍ እየጠነሰሰ ሲሆን


ሃሰቡም ቅርጽ እየያዘ መጥቷል፡፡ከጨረስው በኋላ ሌላ ልብወለድ“ጊዜ ካገኘሁ”በማለት ለመጻፍ
እቅድ ይዟል፡፡አንዳንድ ሰዎች ግለታሪኩን እንዲጽፍ ሃሳብ ቢያቀርቡለትም “ምን ልጽፍ
እችላለሁ?”በማለት ለዚህ የሚሆን በቂ ግብአት የማግኘቱ ጉዳይ ይጠራጠራል፡፡

ስለዚህ በአሁን ሰአት በአእምሮው ከሚብላሉት ሁለት የልብወለድ ሃሳቦች ውጪ ሌላ የተለየ እቅድ
የለውም፡፡

በኢትዮጵያውያን መስፈርት አኳያ መጻፍ እችላለሁ ብሎ ቢያስብም የውጪዎቹን ሲመለከት ግን


ተስፋ ይቆርጣል፡፡“የእነሱ እድገትና ዘዬ ላይ መድረስ አንችልም”ሲል ሃሳቡን ይናገራል፡፡
“ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን መቼት የሚመጥን ጽሁፍ ሊያወጡ ይችላሉ፡፡”በማከልም “ህይወት
አጭር ናት ስለዚህ ማንኛውም ስው የሚችለውን ማበርከት አለበት፡፡እዚህች ሃገር ላይ ሳንሱርና
ወቅታዊ ሁኔታዎች ቢኖሩም ብዙ የሚጻፉ ነገሮች አሉ፡፡”በሚጽፍበት ወቅት እራሱን በራሱ ሳንሱር
እንደሚያደርግ እና ሳንሱሮች በሚፈልጉት መጠን እያሰቡ መጻፍ መጥፎ እንደሆነና የጽህፈትን ስራ
በጣም እንደሚያጣምመው ይናገራል፡፡ነጋሽ የፈጠራ ጽሁፍ እጥረት ያሳስበዋል፡፡የአንባቢዎችና
ጸኃፍት ክበቦች ሲመሰረቱ ለማየትም ይፈልጋል፡፡በ1987 መስከረም ጣልያን ላይ ባህላዊ
ኮንፈረንስ እንዲሳተፍ ጥሪ ሲደርሰው የደራስያን ማህበር ወረቀቱን በጊዜው ማስጨረስ አልቻለም
ነበር ምንም እንኳን የጣልያን ባህል ማእከልና መንግስት በተቃራኒው ተባባሪ ሆነው
ቢጨርሱለትም ቅሉ፡፡ ስለዚህም በማህበሩ ላይ ብስጭት አድሮበት ነበር፡፡

ነጋሽ ገብረማርያም እድሜ ልኩን ወንደላጤ ነበር፡፡ነገር ግን ከ1982 እ.ኤ.አ ጀምሮ ከአንዲት ሴት
ጋር መኖር ጀመረ፡፡በ1986 አቆጣጠር የመጀመርያ አጋማሽ ላይም ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡ከዛ ቀደም
ወደ ሌሎች ሴቶች ቢሄድም ሌላ ልጅ ግን እንዳለው አያውቅም፡፡ቢያረግዙ እንኳን ከኑሮዋቸው
አንጻር ሃላፊነትን ወስዶ ይቀበል ነበር ለማለት ያዳግታል፡፡“ተራ ህይወት”ነበር የኖርኩት ይላል፡፡

ነጋሽ ከእናት አባት ወንድሙ አሰፋ ጋር በጣም ይቀራረቡ ነበር፡፡ከሱም ብቻ ሳይሆን ከእናቱ
ከሚወለዱት ኤልያስ (ጋብቻውና ጊዜው ደራሲ)እና ከአቶ በሻህና ከነሱ እናት ከሚወለዱ ሁለት
እህቶቹ ጋርም ቅርርብ አለው፡፡የነጋሽ የመጀመርያ ስራው ሴተኛ አዳሪ ሲሆን እናኑ "አጎናፍር"
በሚል የብእር ስም የተጻፈና በጥልቀት ስለ ሴተኛ አዳሪ ህይወት የሚዳስስ ነበር፡፡በተለይ
ስለምታዘወትራቸው የወሲብ ስልቶችና ከደንበኞች ስለምትማራቸው ወይም ከሌሎች ሴተኛ
አዳሪዎች አልያም ከመጻሕፍት (እንግሊዘኛንም ሆነ አማርኛ ማንበብ ትችላለች)ስለምታገኛቸው

136
ጥቋቁር አናብስት

በተለይ ይገልጻል፡፡ያምአለያ መጀመርያ መጻሐፉን እንደ ድብቅ የወሲብ መመርያ ነበር


የተመለከትኩት (ግልጽ የሆነ ወሲብ መመርያ በጊዜው ግን ሳንሱሩን ስለማያልፍ በመጽሓፉ ላይ
ሲተገበሩ ያየናቸው የወሲብ ስልቶችን የፈጻሚውን መጨረሻ ሳያሳምሩ ማቅረብ ያስፈልግ ነበር
በልብ ወለዱ ውስጥ የነበረችውንም ገጸ ባህርይም ፍጻሜዋ እንዲሁ ነበር)ምንም እንኳን በአንደኛ
መደብ እኔ ተብሎ በሴተኛ አዳሪዋ በዋና ገጸ ባኅርይዋ ቢተረክም የአጻጻፍ ዘዬው የወንድ መሆኑን
እንደሚያሳጣ እፈራለሁ፡፡ነጋሽ እራሱ እንደ ወሲብ መመርያ አስቦ እንዳልጻፈው ይናገራል፡፡
በልጅነቱ ወቅት እሱና ጓደኞቹ በውቤ በርሃ ያሳለፉትን ልምድ ነጸብራቅ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ጓደኞቹ ገንዘባቸውን ካፈሰሱ በኋላ መልሰው ሴተኛ አዳሪዎቹን ይወቅሱ ነበር፡፡ነጋሽ ከዚህ የተለየ
አመለካከት ነበረው፡፡ገንዘቡን ካጠፋ መወቀስ ያለበት እሱ እራሱ መሆን እንዳለበት ያምናል፡፡
ከዚህም ሌላ ሴተኛ አዳሪዎቹን ለመረዳትና ከነሱ ጥግ ሆኖ ነገሮችን ለማጤን ይሞክራል፡፡በልብ
ወለዱም ይህንኑ እይታውን እነሱን ለመወከል ሲል ለማቅረብ ሞክሯል፡፡አንድ ሃሳባዊ ሴተኛ አዳሪ
ታሪኳን እንድትናገር አድርጓል፡፡ትምህርት ቤት ገብታ አማርኛና እንግሊዘኛን ስለተማረች ብዙ
የፍቅር ታሪኮችና የወሲብ አተገባበር መመርያዎችን አንብባለች፡፡ነጋሽ እንደሚለው ከሆነ ከምእራቡ
አለም በተቃራኒ ሴተኛ አዳሪዎች በኢትዮጵያ በደንብ አልተጠኑም የሚረዳቸውም የለም፡፡
በማስከተልም ሽርሙጥና በኢትዮጵያ ሳይታዩ የታለፉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘቶች አሉት
ይለናል፡፡ብዙ የሚናገሩት አላቸው ስለሚልም በመጽኃፉ ላይ እድል ሰጥቷቸዋል፡፡አብዛኞቹ ሴተኛ
አዳሪዎች ከአማካዩ የኢትዮጵያ ሴቶች በተሻለ የተማሩ ነበሩ፡፡ በትምህርት ቤት ብቻም
አይደል(አብዛኞቹ ትምህርት አቋርጠው የወጡ ሙያ የሌላቸው በሌላ ስራ ላይም መሰማራት
የማይፈልጉ ነበሩ)ብዙ ሰው ስለሚያገኙ አጠቃላይ እውቀታቸው የሰፋ ነበር፡፡19 በመጽሐፉ
የተወከለችውም ጀግና ሴት ከዚህ የተለየ አልነበረችም፡፡ነጋሽ ሰዎች የሴተኛ አዳሪዎችን ችግር
እንዲረዱ ሁኔታቸውንም እንዲያገናዝቡና ብልህነታቸውን እንዲያውቁላቸው ይፈልጋል፡፡ እንደ እሱ
አባባል ስለተለያዩ የወሲብ ስልቶች ማውራት በሴተኛ አዳሪዎች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ ወንዶች
ሴቶችን የሚያበላልጡበትን መንገድ ማወቅ ስለሚፈልጉም ጭምር ነው ይህን የሚያደርጉት፡፡
በመልክ ብቻም ሳይሆን አንዳንዶች ጥሩ ጓደኛና አጫዋች ይፈልጋሉ፡፡ሌሎች ደግሞ ´የቴክኒክ´
ችሎታ ወዳላቸው ያደላሉ፡፡የወሲብ ቴክኒኮች በኢትዮጵያ በሴተኛ አዳሪው ዘንድ ብቻ ሳይሆን
በሌላውም ህዝብ ዘንድ እየታወቀ መጥቷል፡፡በመጽሐፉሊያነሳቸው ያሰባቸውን ጥያቄዎችም እነኚሁ
ናቸው፡፡እንደ ነጋሽ አመለካከት ከሆነ በኢትዮጵያ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች ከሴተኛ አዳሪዎቹ እኩል
ለመስፋፋቱ ተጠያቂ ናቸው፡፡

ተውኔቶች በኢትዮጵያ በብዛት ስለማይታተሙ ጋዜጠኝነቱም ጊዜያዊ ስለሆነ ነጋሽ ምንአልባት


የሚታወሰው በደንብ በተጻፈውና ለማንበብ በሚያስደስተው በሴተኛ አዳሪ ልብወለዱ ነው፡፡
በአሁን ወቅት የሚያስባቸውን ልብ-ወለዶች ከጻፈና ሌሎችንም ከጨማመረ የተሻሉ የብእሩን
ምርቶች ማግኘት ይቻል ይሆናል፡፡
137
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻ

1ከመንዝ ሲሆን በሐረርጌና ቆይቶም በወለጋ የአውራጃ አስተዳደር የነበሩት የቀኝ አዝማች ተስፋ
ልጅ ነው፡፡

2እዚህ ጋር ነጋሽ በቀን ማስታወሱ በኩል ጥሩ እንዳይደለ ለማክል እፈልጋለሁ፡፡በነገረኝ ታሪኩ


ውስጥ ያሉ ቀናትን ለማስታረቅ እክል ገጥሞኛል፡፡ለማንኛውም በማለት እራሱ እንደነገረኝ
አስቀምጫቸዋለሁ፡፡በኔ ጎትጓችነት ባይሆን ብዙ ቀናትንም ባልጠቀሰልኝ ነበር፡፡«መቼ
ነው?»በግልጽ የተከናወነበትን ቀን እንደማያስታውሰውና ሊሳሳትም እንደሚችል ያስባል

3 በግምት እ.ኤ.አ በ1919 ወይም በ1920 ሲሆን የተወለደው እለተ እረፍቱ ጥቅምት 21 1961
ነው፡፡

4 የነጋሽ ታናሽ የሆነ ሌላም ወንድም አላቸው

5በዚህም ወቅት ለጣልያኖቹ በአስተርጓሚነት ይሰራ ነበር

6 በቤተክርስትያኒቱ የአብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ድሮም ሆነ አሁን በትምህርትነት የሚሰጠው


ቋንቋ ይሄው ሲሆን አብዛኛው የማስተማር ሂደቱ በድግግሞሽ በማጥናት የሚተገበር ነው፡፡

7አሰፋ ጣልያኖቹን በተስፋ ነበር የሚመለከታቸው፡፡በርካታ የጣልያን መጻህፍትንም አንብቧል፡፡


ከነዚህም ውስጥ በርካታ ታሪኮችን ለነጋሽ ይነግረው እንደ ነበር ነጋሽ ያስታውሳል፡፡

8ነጋሽ እንደሚናገረው አሰበተፈሪ(ጭሮ) በተክለሐዋርያት ተክለማርያም እና በዶክተር ማርቲን


ወርቅነህ ነው የተቋቋመችው፡፡ ሹማምንቶቿ ከእቃ ይልቅ በብር የሚከፈሉባት ቀጥ ያሉ መንገዶች
ከተማዋን የሚያቋርጡባት ወዘተ ከተማ ስትሆን በዘመናዊ አስተዳደር ማሳያነት መንስኤ ነበር
የታቀደችው፡፡እሱ ከመምጣቱ በፊት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የነበረውና ወደ ኋላ በሐይለሥላሴ
መንግስት ሚንስትር እና በኢትዮጵያ የመካነ ኢየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት የሆነው
አማኑኤል አብርሃም ከሱ በፊት በአስተማሪነት እዛ ሰርቷል፡፡

9ይሄኛው አጎታቸው ከሴት አያታቸው ውጪ ሌላ ከሆነች የተወለደ የአያታቸው አሊ ቡሊ ልጅ


ነው፡፡ፊትአውራሪ አሊ ቡሊ ከተለያዩ ሴቶች ወደ ሀያ የሚጠጉ ልጆች ሲኖሯቸው በክርስትና

138
ጥቋቁር አናብስት

ቢጠመቁም «በዚህ ረገድ ግን እንደ ሙስሊም »ነበር የሚኖሩት፡፡ሐረርጌ ከመስፈራቸው በፊት


ለተወሰነ ወቅት የጊሚራ ገዥሆነው ሰርተዋል ይላል ነጋሽ፡፡

10ከእሱ ጋር አብረው ከተማሩት መሃል በህይወት ጎዳና የተሳካላቸው እንደ በትሩ አድማሱ ያሉ
የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ስራአስኪያጅን የመሳሰሉ ስኬታማ ሰዎች ይገኙባቸዋል፡፡
በጨዋታችን ወራትም በኬንያ የሚገኘው አለምአቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ነበር፡፡ነገር ግን
ይህንን ስራ የተረከበው ከስልሳ ስድስቱ አብዮት መፈንዳት በኋላ አምስት ወይም የስድስት አመታት
እስርን ተከትሎ ነበር፡፡ሌላኛው አብረውት ከተማሩት መሃል የተሳካለት ሰው የሚባለው ከበደ
አካለ ወልድ ሲሆን የአሰብ ማጣርያ ሃላፊ ነበር፡፡እንዲሁም ሌሎች አሉ፡፡

11እዚህ ላይ በግርማ ታደሰ የተጻፈ የግጥም ስብስብ የሆነው "ተናገር አንተ ሐውልት" እንዴት
በተስፋይ ገብረእግዚ እንደታገደ እገልጻለሁ፡፡በገበያ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ከቆየ በኋላ መድበሉ
መጠርያ የሆነው ግጥም እኔ የስርጭት አርታኢ ሆኜ በምሰራበት ራድዮ ላይ በኔ ፍቃድ ተነበበ፡፡
ተስፋዬ ገብረእግዚ ቅሬታውን ለማሰማት መልእክተኛ ላከ፡፡እኔም መጽሐፉ በኢትዮጵያ የሳንሱር
ክፍሎች ታይቶ ይለፍ እንደተሰጠውና በገበያ ላይ እንደሚገኝ ሳንሱር አድራጊዎችን ሳንሱር
የማድረግ ስራ የኔ እንዳልሆነም አያይዤ ተናገርኩ፡፡ወድያውኑ መጽሐፉ ታገደ ከመጻህፍት መሸጫ
ቤቶችም ተለቀመ፡፡ተስፋዬ የግጥሙ ትርጉም እንደተረዳውና ለንጉሱ እንደተሰነዘረ ስድብ ነው
የቆጠረው፡፡በግጥሙ ውስጥ ያለው ሰው የረጀና ብዙ ያየ የአክሱምን ሃውልት ብልሃት
እንዲስተምረው የሚጠይቀው ኃይለሥላሴን ለማለት ነው ይሄ ደግሞ ንጉሱን ደደብ ለማለትና
የተሻለ ብልሃት እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል እንደማለት ነው የታሰበው (ይሄ ሁሉ በተስፋዬ
መልእክተኛ ነበር የሚገለጽልኝ)«ብልሁ»ተስፋዬ በዶክትሬት ዲግሪው የሚኮራና በክብር
ስሙ«ዶክተር»ካልተባለ ሰዎችን የማያናግር ሰው ከሌሎች በተሻለ ስውር ትርጉሞችን የማወቅ
ችሎታ እንዳለው ለማሳየት ፈለገ፡፡ስለዚህ በራድዮው በተላለፈ ሌላ መንደራችን በተሰኘ ግጥምም
መናደዱን ነገሩኝ፡፡ከመንግስታዊው ጋዜጣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ መወሰዱን ስናገር ምንስትሩ
ከጋዜጣው አርታኢ ጋር መጋጨታቸውን ተነገረኝ፡፡በመሃከላቸው ያለውን ችግር እራሳቸው
እንዲፈቱ እና እኔ ጋር ለዳኝነት እንዳይመጡ ነገርኳቸው፡፡ተስፋዬ ገብረ እግዚ ትግሬ ሲሆን
በ1966 ተገድሏል፡፡

12)የቡድኑ ሊቀመንበር በፍቃዱ ታደሰ ልእልት ብላ እራሷን(ግን ልእልት ያልሆነችው)


የምትጠራውና የማስታወቅያ ሚንስትሩ የማሞ ታደሰ እህት የሆነችው የሜሮን ታደሰ ባለቤት ነው፡
፡በትሩ ኪዳነ ማርያምም የቡድኑ አባል ነበር

139
ጥቋቁር አናብስት

13)ከዛ ቀደም ብሎ በካይሮ አምባሳደር ነበር፡፡በውይይታችን ወቅት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ


ይኖራል፡፡

14)ነጋሽ የጻፋቸውን ሃተታዎችን እና ግጥሞችን በቀላሉ ማስታወስ አይችልም፡፡አረጀው መሰለኝ


የምትል አንዲት በአዲስ ዘመን ላይ የወጣች ግጥምን ግን ያስታውሳል

15)በወቅቱ ማንም ተጋቢ ጥንዶች ሁለት ቤቶች እንዲኖራቸው አይፈቀድም ነበር፡፡ስለዚህ


ከመጋባታቸው ቸበፊት ሁለቱም ቤት ከነበራቸው አንዳቸው ቤታቸውን ሊለቁት ግድ ነው፡፡

16)እንዲህ ያሉ የአልጋ ላይ የመጨረሻ ኑዛዜዎች የተለመዱና ሟቹ ወደ ፈጣሪ እየሄደ ስለሆነ


በምድር ላይ ላደረገው ሁሉ ስለሚዳኝበት እንደ እውነተኛ የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

17)ባህላዊ ህክምና ከአባት ወደ ልጅ እየተወራረሰ የሚሄድ ነው

18)ያን ያህል በኢትዮጵያ ሩቅ የሚባል አይደለም ፡፡ምንአልባትም ሶስት አራተኛው ህዝብ በባህላዊ
ህክምና የሚያምንና አድርግ የተባለውንም የሚያደርግ ነው

19)ይሄ ሊሆን የሚችል ነው፡፡አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ለወሲብ ብቻ ወደ ሴተኛ አዳሪዎች


አይሄዱም፡፡ሙሉ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ እንደጓደኛም ያወራሉ፡፡

140
ጥቋቁር አናብስት

መኮንን እንዳልካቸው
መሳፍንታዊው ፖለቲከኛና፣ ወግ አጥባቂው ፀሀፊ
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸውእኔ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቴ
ከሁለት አመታት በፊት ስለሞቱ የመገናኘት እድል አልነበረንም፡፡
ከመጣሁም በኋላ በአማርኛ ስነጽሁፍ እስክሳብ ድረስም ጥቂት
አመታትን ወስዶብኝ ስለነበር እዚህ በነበርኩባቸው የመጀመርያዎቹ
አመታ ለእሳቸው ቃለ-መጤቅ ለማድረግ እንኳን ምናልባት
ባላሰብኩም ነበር፡፡ስለሆነም እዚህ ያሰፈርኳቸው ማስታወሻዎችና
በሌሎች ሰዎች ማስታወሻዎችና ትውስታዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡
፡ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች በጭምጭምታ ደረጃ ስለሳቸው የሚነገሩና የተጻፉ ነገሮች ቢኖሩም
እዚህ በአማርኛ የተጻፉና በቀላል ሊገኙ የማይችሉ ምንጮችን መጠቀም ነው የፈለግሁት፡፡ዋቢ
ምንጮቼ ለአርባ ቀን መታሰብያቸው የታተመች ማስታወሻና በደምሰው በቀለ የተሰራ ያልታተመ
ጽሁፍ ነው፡፡መኮንንም በመጽሐፍቶቻቸው ስለራሳቸው የተወሰኑ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡የልብወለድ
ስራዎቻቸውም በእራሳቸው የህይወት ልምድና ታሪክ ዙርያ የተከተቡ ናቸው፡፡1

ንጉስ ወይም አጼ ሳይሆኑ በስልጣን መሰላሉ መውጣት እስከሚቻልበት ጫፍ ደርሰዋል፡፡ይህም


በብልጣብልጥነት ወይም እድል አልያም በስሌት ወይም በአምቻ ካልሆነም በሁሉም ድብልቅ
ሊሆን ይችላል2፡፡አንድ የሩቅ ዘመድ ከንጉሱ የበኩር ልጅ ጋር ተጋባ ሌላው ደግሞ ከመነን
ከምትወለደው ትልቋ ልጅ ጋር ተጋባ፡፡በተጨማሪም አንድ ዘመዱ የአቤቶ እያሱን እህት ያገባል፡፡
የራሱ የመኮንን ሁለተኛ ሚስትም የንጉሱ በአባት በኩል ወንድማቸው ከሆነው ሰው የምትወለድ
ልጅ ነበረች፡፡ከዚህ ሁለተኛ ጋብቻው በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ከፍታ የመጡት፡፡
አንዳንዶች ሁለተኛ ጋብቻቸውን ለስኬት ታስቦ እንደተወሰደ እርምጃ ቢቆጥሩትም ለልዕልቲቷ
ከነበራቸው የልጅነት የፍቅር ስሜትም እንደመነጨ አመላካች ሁኔታዎች አሉ፡፡

የመኮንን እንዳልካቸው በ1916 ከስልጣን ስለተወገዱት ከልጅ እያሱ ጋር የነበራቸው ግንኙነት


በጅማሮው በድጋፍ የተሞላ ነበር፡፡ የኋላኋላ ግን ወደ ከርሞው ንጉስ ኃይለሥላሴ አዘነበለ፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ(ወደ ሃረር በጊዜው ገዢ ወደነበሩት የተጓዙት)በሃይል ጫወታው
ወደፊት ያሸንፋሉ ብሎ ስለገመቱ ተፈሪ መኮንንን ለማግኘት እንደሄዱ ይናገራሉ፡፡ይሄ
እንኳንያጋጣሚ ጉዳይ እንጂ ታሪካዊ ይዘት ያለው አይመስልም፡፡ተፈሪም ሆነ መኮንን በወቅቱ
አልጋውን ለመገልበጥ ስለመሴሩ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ለማንኛውም በቀሪው የህይወት
ዘመናቸው ባለስልጣናትን የመደገፍ ባህርይ ነበራቸው፡፡

141
ጥቋቁር አናብስት

መኮንን በጻፏቸው መጽሐፍቶቻቸው እራሳቸውን እንደ ሩህሩህ፤ሃይማኖተኛና ደግ አድርጎ


የማቅረብ አባዜ ነበረባቸው፡፡ይህ እውነተኛ የእርሳቸው ምስል ሊሆን ቢችልም በመጠኑም ቢሆን
ማስመሰል አለበት፡፡ ለምን ግን አንድ በባለጠግነት የሚኖር ሰው በስንክሳሩ የችሮታን መልካምነትና
የሃብት ጉዳቶችን መዘብዘብ አስፈለገው?እንደ ገጸባህርያቶቻቸውም ሃብታቸውን የማከፋፈል
ፍንጭ እንኳን አላሳዩ፡፡በመጽሐፍቱ ስለ ሃብት ችሮታ ከሚዘከዝኩት በተቃራኒው በስደት ሳሉ ስለ
አጋጠሟቸው ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ቅሬታ አሰምተዋል፡፡እንደውም አንዳንዶች ሃይማኖትን
በመጠቀም ስለ አለም ቁሳቁሶች አላስፈላጊነት በመስበክ ለመጠቀምና በኢትየጵያ ፖለቲካ ውስጥ
እውቅናን ለመትረፍ እንዳሰቡ ይናገራሉ፡፡

መኮንን እንደ ወግ አጥባቂ መስፍን የኖሩ ሲሆን ለገጽታቸው ይጨነቃሉ፡፡ይሄ ልማዳቸው


ከልጅነት ጀምሮ አብሯቸው አርጅቷል፡፡እድሜ ልካቸውን በሴቶች ስለመወደዳቸው በመኩራራት
ያወሩ ነበር ይላሉ በቅርበት የሚያውቋቸው፡፡የሚነገሩት ወሬዎች ሁሉ እውነት ሊሆኑ አልያም
ከንቱ አሉባልታዎች፤የምቀኝነት ወሬም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡እውነቱ ምንም ይሁን ምን ሰብእናቸው
የሚስብና ሰው ሲሆኑ ተወዳጅ ዘዬ ያላቸውን መጻሕፍት ደርሰዋል፡፡ስለሳቸው የመጻፌም ዋነኛ
መክንያቴም ይሄ ነው፡፡ምናልባት ኢትዮጵያውያን የሚወዷቸው እንደ ደራሲ ከአብዛኛው
ኢትዮጵያዊ አኗኗር ጋር የሚመሳሰል አሳዛኝ አቋም ስላላቸው ሊሆን ይችላል፡፡እንድ አንባቢ “ፀሀየ
መስፍን”የሚለውን መጽሓፋቸውን አንብቦ “ደስ የሚል አሳዛኝ ታሪክ ነው” ብሏል፡፡
መጸሐፍቶቻቸው ታዋቂነትን ለማግኘት ችለዋል፡፡የተወሰኑትም እንደ ማስተማርያ ያገለግሉ ነበር፡፡
በነገራችን ላይ ከቤተክርስትያን ሰዎች ጽሁፎችን ገዝተው በስማቸው እንደሚያሳትሙ የሚወራ
ጭምጭምታም አለ፡፡ተመሳሳይ ወሬዎች ስለ ብላቴን ጌታ ኅሩይም ስለሚነገሩ እውነተኛነቱን
እጠራጠረዋለሁ፡፡

***

መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ ተጉለት ውስጥ አዲስጌ ላይ የካቲት10 1883 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
አባታቸው ባላምባራስ እንዳልካቸው አብሪቅ ይባላሉ፡፡የታወቁ ጦረኛ፤ፈረስ ጋላቢና አዳኝ ሲሆኑ
በምኒሊክ የግዛት ማስፋት ጦርነቶች መሃል መኮንን በተወለዱበት አመት1883 ወደ ወላይታ
ዘምተው በ30 አመታቸው በዚያው ጦርነት ሞተዋል፡፡መጀመርያ እዚያው ቢቀበሩም በ7 አመቱ
አጽማቸው ተሰብስቦ ወደ ታዋቂው ደብረ ሊባኖስ ገዳም ተዛውሯል፡፡

የመኮንን እናት ወይዘሮ አቦነሽ ተክለማርያም ከንጉሳውያን ቤተሰብ ነበሩ ባላምባራስ ከሞቱ ከብዙ
አመታት በኋላም ደጃዝማች ተሰማ ዳርጌን አግብተው ነበር፡፡እሳቸው ሲሞቱ ደግሞ ራስ ደምሰው
ነሲቡን አገቡ፡፡ራስ ደምሰው ወይዘሮዋን ያገቡት የራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው እህት በመሆናቸው

142
ጥቋቁር አናብስት

ነው ይባላል፡፡ ተሰማ ናደው በምኒሊክ ጊዜ ሃያል ሰው የነበሩ ሲሆን የአቤቶ እያሱ ሞግዚትና
እንደራሴ ነበሩ፡፡ተሰማ ናደው ሲሞቱ ደምሰው አቦነሽን ፈትተው የአቤቶ እያሱን እህት የሆነችውን
ወይዘሮ ስህንን ለማግባት ጠየቁ፡፡ እሷ ግን ስሌቱን ተረድታ በጣም ጠላቻቸው፡፡ ሌላው ምክንያት
ደግሞ ሟቹ ባሏ ደጃች ብሩ ኃይለማርያም የወይዘሮ አቦነሽ ወንድም ስለነበሩ ነው፡፡ወድያው
ደምሰው እንደፈቷት አቦነሽ ሞተች፡፡

ከአባታቸው ሞት በኋላ እናታቸው መኮንንን ከመምሬ አካሉ ኪዳነ ማርያም ዘንድ ሰላ ድንጋይ
አምጥተው እንዲያስተምሯቸው ጠየቁ፡፡በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር ሲሉ መምህሩ ለዘመዶቻቸው
ይናገራሉ፡፡ቆይቶም መኮንን ከአያታቸው ወይዘሮ ቆንጂት ጋር በአዲስጌ ለተወሰኑ አመታት መኖር
ጀመሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ደብረ ሊባኖስ ተልከው ተጨማሪ የቤተክህነት ትምህርትን ቀስመዋል፡፡
ከመምህሮቻው አንዱ ወልደ ጻዲቅ ወልደ ሃዋርያት የሴት ሃያታቸው ሰራተኛ ነበር3፡፡በሃገርኛ
እውቀቱም የበለጸገ እሙር እንደነበር ሰዎች ይናገሩለታል፡፡

በ1891 እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር አጎቱ ተሰማ ናደው ራስ ሆነው ዘመዶቻቸውን


ለመጎብኘት ሄዱ፡፡በመኳንንቱ ቤት በወቅቱ እንደተለመደው ብላቴናውን መኮንንን ሲያዩ ወደ
ንጉሱ ቤተ መንግስት ለመውሰድ ፈለጉ፡፡በኋላም ወይዘሮ ቆንጂት ወደ መናገሻ ከተማው በ1892
ዓ.ም ይዘዋቸው መጥተው በጥቅምት 12 ቀን ሲደርሱ አጎታቸው ራስ ተሰማ ከምኒሊክና ከጣይቱ
ጋር አስተዋወቁዋቸው፡፡በቤተመንግስቱም ለጥቂት ጊዜያት ተቀመጡ፡፡ነገር ግን በቤተመንግስቱ
የነበሩት ልጆች ስለሚያሾፉባቸው(በዛን ጊዜ እንኳ በመልከመልካምነቴ የመጣ ነው ብለው ያስቡ
ነበር) እዚያ መኖሩን አልወደዱትም፡፡በዚህ የመጣ ወደ አዲስጌ እንዲመልሷቸው ለመኑ፡፡አዲስጌ
ጥሩ ጊዜ ቢያሳልፉም በአጭሩ ነበር የተቋጨው፡፡የቤተመንግስቱ ልጆች ስርአተ ቤተመንግስትን
መማር ስለነበረባቸው በመስከረም 6 ቀን 1895 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ዋነኛ ስራቸው
የታላላቆቹን እጅ ማስታጠብ ሲሆን በዚሁ ወቅት ነበር እናታቸው ደጃች ተሰማ ዳርጌን አግብተው
ወደ አዲስ አበባ የመጡት፡፡መኮንን አብረዋቸው መቆየት ችለዋል፡፡4ነገር ግን የእንጀራ አባታቸው
ወድያውኑ ስለሞቱ እናታቸው ወደ አዲስጌ፤መኮንን ደግሞ ወደ ቤተመንግስት ኑሮዋቸው
ተመልሰዋል፡፡

የዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት በ1899 ዓ.ም ሲከፈት መኮንን ፈረንሳይኛ እንዲያጠኑ


(ከደጃዝማች ተፈሪ መኮንን፤ ልጅ ብሩ ሃብተ ማርያም፤ ልጅ እምሩ ኃይለሥላሴ፤ልጅ ዘውዴ ጎበና፤
ልጅ አስፋው በንቲና ከሌሎችም ጋር አብረው)ተመረጡ፡፡በአንድ መጽሐፋቸው ውስጥ
እንደተገለጸው ከሆነ እስከ 1901 ድረስ በትምህርት ቤቱ ቆይተው ነበር፡፡ዘመዶቻቸው በእዚያ

143
ጥቋቁር አናብስት

ትምህርት ቤት የተማሩ ሰዎች ለስድስት ወራት ብቻ እንደቆዩ ይናገራሉ (ከተማሩት በላይ ሆኖ


ለመገኘት ሳያጋንኑ አልቀረም)፡፡

በ1901 አጎታቸው ልጅ እንጥሌ ስለታመሙ የመኮንን ሴት አያትና እናቱ ሊያስታምሟቸው ወደ


አዲስ አበባ መጡ፡፡ በተመሳሳይ ወቅትም አጼ ምንሊክ ታመው ስለነበር በደጃች ወርቅነህና በአንድ
እንግሊዛዊ ዶክተር ዌክማን የህክምና ክትትል ይደረግላቸው ነበር፡፡ሚኒሊክ ከእንጥሊ ጋር ቅርብ
ስለነበሩ ሃኪሞቻቸው እሳቸውንም እንዲያዩዋቸው ፈቀዱ፡፡እንጥሌ ግን ህመሙ ብሶባቸው አረፉ፡፡
መኮንን አዲስ አበባ ያለውን ቤታቸውን ወርሰው በምላሹም የአርባ፤የሰማንያ ቀንና ሙት
አመታቸውን ዘከሩ፡፡

መኮንን የአጎታቸው ሬሳ በወጣበት ቤት መኖሩን አልወደዱትም፡፡ ስለዚህ ቤቱ ለራስ ቢትወደድ


ተሰማ ልጅ ለደጃዝማች ደበበ ተሰማ ተሰጠ፡፡በምትኩም ሌላ መሬት ለመኮንን ተሰጣቸው፡፡ነገር
ግን እቴጌ ጣይቱ ይህ መሬት የቤተክርስትያን ነው በማለት መኮንንን ወደ ደጃች እንጥሊ ቤት
መለሷቸው፡፡5

መኮንን ሰፋ ያለ ቤት ስላገኙ ከጓደኞቻቸው ጋር አብረው በመኖር ጠዋት በ11 ሰአት ተነስተው


አብረዋቸው ከሚኖሩት ከአለቃ ገብረሚካኤል ስር ሆነው ዳዊትና ሃዲስ ኪዳኑን ማጥናት ጀመሩ፡፡
መኮንን የግዕዝ ሰዋሰውን ከአለቃ አርአያ ሥላሴ ወሮታ ዘንድ ሲማሩ እርሳቸውም እዚያው
አብረዋቸው ነበር የሚኖሩት፡፡ በነዚህ ትምህርቶች ጥሩ የነበሩ ሲሆን በተጨማሪም በዳግማዊ
መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸው ይከታተላሉ፡፡

ምኒሊክ ህመሙ እየጠናባቸው ስለሄደ በደጃች ተሰማ ናደው እንደራሴነት አልጋውን ለልጅ
ልጃቸው አቤቶ እያሱ አወረሱ፡፡ተሰማ ሚያዝያ 11 በ1903 ዓ.ም ወድያውኑ አረፉ፡፡መኮንንም
አቤቶ እያሱን በቀብሩ ጊዜ የተመለከቷቸው ሲሆን በሌላ ብዙ ሁኔታዎች ውስጥም ሰፊ የመገናኘት
እድል ነበራቸው፡፡6

የራስ ተሰማ መሞት ሃገሪቱን ለውዥንብር ዳረጋት፡፡የሸዋ መኳንንት እያሱን ከሃላፊነት አስወግደው
የምኒሊክን ሴት ልጅ ዘውዲቱን በምትኩ ወደ አልጋው ለማምጣት ፈለጉ፡፡የእያሱም ደጋፊዎች
የዋዛ አልነበሩም፡፡ ከነሱም መሃል አንዱ መኮንን እንዳልካቸው ነበሩ በአንድ መጽሐፋቸው ላይ
እንዳሰፈሩት፡፡ራስ አባተ (የመኮንንን አክስት የሚያገቡ) ለአቤቶ እያሱ ጠባቂ ለመሆን ቢሞክሩም
አልቻሉም፡፡ቆይቶ ራስ አባተ ተይዘው ለእስር ወደ ደሴ ተላኩ7 መኮንን አባተ ወደ ደሴ ሊያቀኑ
ሲሉ ሄደው ተሰናበቷቸው፡፡በዚህ ወቅት ነበር ከአባተ ጋር ሆኖው ሳሉ እያሱ ሊያዩዋቸው የቻሉት፡
፡ ከዚህች ክስተት በኋላ ብዙ አዳዲስ ሰዎች ተሾሙ፡፡መኮንን ግን እያሱን መደገፋቸውን ቢቀጥሉም
144
ጥቋቁር አናብስት

አበረታች8 ሽልማት ወይንም ስልጣን ማግኘት ግን አልተቻላቸውም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት


መኮንን የJHON BUNYAN ስራ በሆነው PILGRIM´S PROGRESS እያነበቡ ይጽናኑ
ነበር፡፡9 በዚህ ወቅት ራስ ደምሰው ነሲቡ የሳቸውን እናት ፈትተው የእያሱን እህት ለጋብቻ ጠየቁ፡፡
ያልተሳካ የጥቅም ግንኙነትን ፍለጋ ነበር፡፡የመኮንን እናታቸውና የሴት አያታቸው ታላቅ እህት
ወይዘሮ መድፈርያሽ ወርቅ ድብነህ በዚህ ወቅት ሞቱ፡፡

በ1907 ዓ.ም መኮንን የራስ ቢትወደድ መንገሻን ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱ መንገሻን አገቡ፡፡ጎበዝና
ታጋሽ ሴት የነበረች ቢሆንም10 መኮንን ግን በመጀመርያ ትዳራቸው ብዙም ደስተኛ አልነበሩም፡፡
የልጅነት ፍቅራቸውን (የመጨረሻውን የግርጌ ማስታወሻን ይመለከቷል)ሳያስታውሱ አይቀርም፡፡
የወለዷቸው በርካታ ልጆችም ሞቱባቸው፡፡ከተወለዱላቸው አስራስድስቱ ሁለቱ ብቻ ነበሩ
ሊተርፉ የቻሉት፡፡ልጅ እንዳልካቸው መኮንንና ወይዘሮ ብርሃኔ መኮንን፡፡ሚስታቸው ዘውዲቱ
በትዩበርክሎሲስ ታማ በፍልውሃ ሆስፒታል ታክማለች፡፡በዚህ መክንያት በሀኪሞች ትዕዛዝ
አብረው እንዳይተኙ ተከልክለው ነበር፡፡ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ መኮንን በ20 ህዳር
1928 ዓ.ም ወደ ጦር ግንባር ሲዘምቱ ሚስታቸው በጠና ታማ ነበር፡፡ወደ ድሬዳዋ ከመሄዳቸው
በፊትም በጣም ሊቀርቧት ቢሞክሩም ወድያውኑ ወደ ሃረር ሄዱ፡፡እዚያም እያሉ በታህሳስ19 ቀን
መሞቷን ተረዱ፡፡ ለጊዜው ግን መኮንን ካገቡ በኋላ ወዳሉበት ጊዜ እንመለስ፡፡

የንጉሳዊ ቤተሰብ ልጆች በኦፊሴል ባይሰጣቸውም በክብር ስም “ልጅ” ተብለው ነው የሚጠሩት፡፡


የመኮንን እንዳልካቸውም እንዲሁ ነበር፡፡ነገር ግን በ1909 ዓ.ም በአፊሴል የልጅነትን ማዕረግ
ተቀብለው ለአስር አመት ተጠርተውበታል፡፡በ1919 ዓ.ም ተፈሪ መኮንን አልጋ ወራሽ በሆኑበት
አመት አካባቢ እሳቸውም የወምበሮ አብቹና ማሴት ገዢ ሆኑ፡፡ከዚያ በኋላ ለበርካታ አመታትም
የፍራንኮ ኢትዮጵያ የባቡር ኩባንያ ዋና ኢንስፔክተር በመሆን ተሹመው በስራ ጉዳይ እስከ ፓሪስ
ድረስ ተጉዘዋል፡፡12

ተፈሪ መኮንን ወደ አውሮጳ ሲሄዱ የአልጋ ወራሽ ልዩ አማካሪ በመሆን አብረዋቸው ተጉዘዋል፡፡
በ1919 ዓ.ም መኮንን በነጋድራስነት ማዕረግ የንግድ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ፡፡ወደ ሎንደንም
ኢትዮጵያን ወክለው እንዲሁም በሚንስትርነት ተጉዘዋል፡፡

ልዕልት የሻሽወርቅ ይልማ የተፈሪ የእህት ልጅ ታማ ለማሳከም ወደ ጣልያን በ1921 ዓ.ም


አብረው ሄዱ፡፡በባለቤታቸውም ፍቃድም ነጋድራስ መኮንን የተወሰነ ወቅት እሳቸውን አጅበዋቸው
ነበር፡፡ ከትንሽ ወቅት በኋላም በፓሪስ ተገናኙ፡፡ለሚስጥራዊ የፍቅር የሽርሽር ጉዞዎችም በጀርመንና
145
ጥቋቁር አናብስት

ፓሪስ አካባቢዎች ተዘዋውረዋል፡፡የሻሽወርቅ የመኮንን የመጀመርያዋ እውነተኛዋ ፍቅረኛቸው


እንደነበሩ በግልጽ በአንዱ መጸሐፋቸው ላይ ተመላክቷል፡፡

አብረው በአጓጉል ቦታዎች ከተነሷቸው ፎቶዎች መሃል አንዱን ለባልየው ራስ ጉግሳ አርአያ
በመላኩ እሳቸው ለንጉሱ አሳዩዋቸው፡፡ንጉሱ መኮንንን በጥድፊያ “ታስረው” እንዲመጡ ካስደረጉ
በኋላ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ታግደው አቃቂ ባለ መኖርያቸው በጥበቃ ቆዩ፡፡ልዕልት የሻሽወርቅም
ሆለታ እናታቸው ወይዘሮ አሰለፈች ወንዴ ዘንድ (የጣይቱ አባት የብጡል ውላጅ ናቸው )እንዲቆዩ
ተደረገ፡፡እናታቸውም ንጉሱን ለምነው ወደ አዲስ አበባ አስመጧቸው፡፡ከመኮንን ጋር በሚስጥር
መገናኘታቸውን ቀጥለው በተወሰነ መልኩ ሊረዷቸው ቻሉ፡፡በመጨረሻም በብላቴን ጌታ ኅሩይ
ወልደሥላሴ አማላጅነት መኮንን ከንጉሱ ይቅርታን ቢያገኙም የሻሽ ወርቅን እንዳያዩ ተከለከሉ፡፡
የሻሽወርቅና ራስ ጉግሳም ቢሆን ተፋቱ፡፡ግን ከዚያ በኋላ ለቢትወደድ መኮንን ደምሰው እንዲዳሩ
ተወሰነ፡፡

ከሶስት አመታት በኋላ ነጋድራስ መኮንን በ1924 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆኑ፡፡ከአንድ
አመት በኋላ በ1925 ዓ.ም የሃገር ግዛት ሚንስቴር ምክትል ወይም ተጠባባቂ ሚንስትር ሆነው
ተሾሙ፡፡የሲቡ፤ጉዳያ እና የገንጂ ገዢም የሆኑት በዚህ ወቅት ነበር፡፡ በ1927 ዓ.ም በደጃዝማች
ማዕረግ የኢሉባቡር ገዢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ቀጣዩ 1928 የነውጥ አመት ነበር፡፡ጣልያኖቹ ኢትዮጵያን ለመውረር በሚዘጋጁበት ወቅት መኮንን
ወደ አዲስ አበባ ጣልያን ልትወረን ስለምትችል ሃገሬውን ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብለው መልእክት
ቢልኩም ጣልያን የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ስለሆነች አትወረንም የሚል ምላሽ ደረሳቸው፡፡
በግትርነት አቋማቸውን ገፍተውበት በሚቀጥለው የኃይለሥላሴ ልደት ሲከበር ኢሉባቡር ጎሬ ላይ
ሰብስበው የጣልያንን የወረራ ፍላጎት ለህዝቡ ነገሩ፡፡ እንደተነበዩትም በዚያው አመት በ1928
ጣልያን ኢትዮጵያን ወረረች፡፡

መኮንን ከኢሉባቡር በርካታ ጦር አሰባስበው ወደ አዲስ አበባ ሄዱ፡፡እዚያም በኢሉባቡር ጦር ላይ


በይፋ ጄኔራል ሆነው ተሾሙ፡፡ከሃገሪቷ ደቡብ ምስራቅ የተቃጣውን የጣልያን ወረራ ለመመከት
ዘመቱ፡፡መጀመርያ በድሬዳዋ13 አጠገብ ወደ ምትገኘው ቀርሳ ደረሰው ከሁለት ሳምንታት በኋላ
ወደ አባከር ተንቀሳቀሱ፡፡ከሶስት ቀናትም በኋላ በሃረር በኩል ወደ ጅጅጋ አለፉ፡፡በአምስተኛው ቀን
ካራማራ ላይ ሰፈር አደረጉ፡፡እዚያ ለሁለት ወራት ያህል ስለቆዩ ለመዋጋት በመጣው ጦር ላይ
ቅሬታን ፈጠረ፡፡

146
ጥቋቁር አናብስት

በጀኔራል ነሲቡ ስር የጦርነት አቅድ ተዘጋጀ፡፡የመኮንን ጦርም መንገዱን ተከትሎ ሄደ፡፡ወድያው


ጦርነት ገጥመው በሚያዝያ 2 ቀን በ11 ሰአት ተጀምሮ እስከ ምሽት 6 ሰአት ድረስ በቆየው
የእሁድ ጦርነት የጠላትን ጦር በብዙ የህይወት መስዋትነት ለ5 ጊዜያት ያህል ለመመለስ ተቻለ፡፡
የመኮንን ጦር ቀለብና ስንቅ ባስፈለጋቸው ሰአት ወደ ጠላት ሰፈር በወረራ በመሄድ ይዘርፉ ነበር፡፡
በመጨረሻ ግን ወደ ሃረር አፈገፈጉ፡፡ሃረር ከመድረሳቸው በፊት የመኮንን ሃሰተኛ ሞት ወሬ ተነዝቶ
ቀድሟቸው ሃረር ደርሶ አገኙ፡፡ይህም በ“አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” መጻሕፋቸው ጭብጥነት
ተነስቷል፡፡

ከሐረር ጋር የቀጥታ ግንኙነት እድል ሲፈጠርላቸው የጦሩን በጥንካሬ የመቀጠል ዜና ቢያቀርቡም


የኃይለሥላሴ የመሸሽ እቅድ ተነገራቸው፡፡ለምክርም ወደ ሃረር ተጠርተው በዛ መስመር ያሉ የጦር
መሪዎች አብረው ወደ አውሮጳ እንዲጓዙ ስለተወሰነ ወደ ጅቡቲ አቀኑ፡፡መኮንን እዚያ የደረሱት
በሚያዝያ 26 ሲሆን ኃይለሥላሴ ኢንተርፕራይዝ በተሰኘችው መርከብ ሲሳፈሩ ከትንሽ ቀን ቆይታ
በኋላ መኮንን የማሲጌሪ ማርታይም ንብረት በሆነች መርከብ ተሳፍረው በፖርት ሳይድ በማድረግ
ወደ እየሩሳሌም አቀኑ፡፡የመሄጃ ፍቃዳቸውን አስኪያገኙም ስለቆዩ እዚያ የደረሱት ንጉሱ ወደ
እንግሊዝ በተሳፈሩበት ግንቦት 1 ቀን ነበር፡፡

ጅቡቲን ከመልቀቃቸው በፊት መኮንን ዋና ጸሃፊያቸውን ቀኛዝማች መንግስቱ ሮባን የአለም


ወረተኛ የሚለውን አቃቂ ቤታቸው ትተውት የሄዱትን ባለምስል መጽሓፋቸውን ረቂቅ አደራ
ብለዋቸው ነበር፡፡የስነጽሁፍ ስራቸውን ያስቀድማሉ ማለት ነው፡፡

***

በእየሩሳሌም መኮንን የሻሽወርቅ ይልማን በድጋሚ አገኙዋቸው፡፡ ባለቤታቸው ቢትወደድ መኮንን


ደምሰው በማይጨው በጥቅምት 1928 ዓ.ም ላይ በተደረገው ጦርነት ሞተው ነበር፡፡መኮንንና
የሻሽወርቅ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው ሥላሴ ቤተክርስትያን በ1928 ዓ.ም ጋብቻቸውን
ፈጸመው በሆቴል ዴቪድም የተወሰነ ግብዣ አደረጉ፡፡በሰኔ 23 ወደ ካይሮ ሄዱ፡፡የሄዱበትም
ምክንያት በሱዳን አድርገው በቀይ መስቀል አውሮጵላን ወደ ጎሬ የመግባት ተስፋን ሰንቀው
ስለነበር ነው፡፡ግን የሱዳን መንግስት ከለከለን ሲሉ ታሪካቸውን ይናገራሉ፡፡14

መኮንንና የሻሽወርቅ ወደ ፍልስጤም ተመለሱ፡፡በኃይለሥላሴ እርዳታም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትንሽ


ቤት በእያሪኮ ገዙ፡፡የጓሮ አትክልት እየተከሉና ስእል እየሳሉ ለመሸጥ ቢሞክሩም ኑሮ ከብዶባቸው
ነበር፡፡

147
ጥቋቁር አናብስት

በስደት እያሉ መኮንን ሁለት መጻህፍትን ጽፈዋል፡፡why was the lion of Juda
defeated እና አትፍሩ ስጋችሁን ለሚበድሉ ይሰኛሉ፡፡(ማቴዎስ 10፤28 )በስደት ወቅት
መኮንን የኢትዮጵያን ስደተኞች ፍላጎት ለማሟላት የተቋቋመ ቆንስላ ፕሬዝደንት ነበሩ፡፡ ይህ
ቆንስላ የንግስት ዘውዲቱን 92 ክፍል ያለው ቤተመንግስት የሚጠቀም ሲሆን ኢጣልያም ለረዥም
ጊዜ የይገባኛል ክርክር አንስታበታለች ፡፡

በ1929ዓ.ም መኮንን እንግሊዝን ለንጉስ ጆርጅ 6ኛ የዘውድ በአል ላይ ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡


በ1932 ወደ ሱዳን በመሄድ ዘመናዊ የጦርነት ትምህርትን በሶቦር አካዳሚ ለመማር ፈልገው
ካርቱም ደረሱ፡፡መኮንን ኀይለሥላሴ ኦሜድላ ላይ ሰንደቁን ጥር 23 1933 ዓ.ምበተከሉበት
ወቅት በቦታው ላይ ተገኝተዋል፡፡ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ በተደረገው ረዥም መልስ ጉዞ ላይ እንደ
ንጉሱ ወኪል ሆነው የሚያዝያ 27 1933 ቱን የድል አከባበር ለማሰናዳት ሲባል ከንጉሱ ቀድመው
ነበር የገቡት፡፡

***

ከነጻነት በኋላ መኮንን እንዳልካቸው በስልጣን ወንበር ከፍ ከፍ እያሉ መሄድ ጀመሩ፡፡በግንቦት 1


1933 ዓ.ም የሚንስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው ሲሾሙ የአገር ግዛት ሚንስትርም ሆነው
ከብሪታንያ ጋር የሉአላዊነት ስምምነትን ተፈራረሙ፡፡ በየካቲት 12 የሰማእታት መታሰብያ ቀንም
የክብር ንግግር እንዲያደርጉ ታዘው ነበር፡፡በ1935 የቢትወደድነት ማዕረግን አግኝተው በ1942
ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትርና የዘውድ አማካሪ ሆኑ፡፡ ከአጎታቸው ተሰማ ናደው በተሰጣቸውም ረጲ
ባለ ቦታ ላይ የመድሃኒያለም ቤተክርስትያንን አስገነቡ፡፡በታህሳስ10 1937 ዓ.ም በኢትዮጰያና
በታላቋብሪቴን መሃከል ስለ ኢትዮጵያ ሉዐላዊነት በተደረገው ዳግም ስምምነት ላይ መማክርቱን
በመምራት መደራደር ችለዋል፡፡በ1938 የተመድ ቻርተር ላይ በሳንፍራንሲስኮ ኢትዮጵያን
ወክለው ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ከተመድ ስብሰባ መልስ በእየሩሳሌም ከባለቤታቸው ጋር
ተገኝተው ስለኢትዮጵያ ነጻነት ምስጋናን አቅርበዋል፡፡በ1938 አዲስ አበባ ውስጥ ቤት የሰሩ
ሲሆን ረጲ ደግሞ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት መኖርያና ትምህርት ቤት አሳንጸው ተቆጣጣሪነቱን
ለሚስታቸው ሰጥተዋል፡፡አብረውም ባልና ሚስቱ አቃቂ ላይ እግዚሃርአብ ቤተ ክርስትያንን
አሳነጹ፡፡ከስደት ከተመለሱ በኋለም ብዙ የስእል የቅብ ስራዎችን ሰርተው አጠናቀዋል፡፡

በ1950 ራስ ቢትወደድ በመባል በኢትዮጵያ የሚሰጠውን ታላቅ ክብር ተጎናጸፉ፡፡15ከዚያም ጋር


አብሮ የራስ ወርቅ አክሊል የማድረግ ክብር ይሰጣል፡፡የሴኔቱ ፕሬዝዳንት ሆኑ፡፡
148
ጥቋቁር አናብስት

መኮንን እንዳልካቸው ወደኋላ የአይናቸው ብርሃን አስቸገራቸው፡፡ንጉሱን በግል ቢያማክሩም


ከማህበራዊና ከፖለቲካ ህይወትም እራሳቸውን አገለሉ፡፡ረጲ ባለው መኖርያ ቤታቸው በ72
አመታቸው በስኳርና ደም ግፊት መንስኤ አረፉ፡፡

በሚቀጥለው ቀን አስክሬናቸው አዋሬ ወዳለው ቤታቸው ተወስዶ ለቀስተኞች ሃዘናቸውን ሲገልጹ


ዋሉ፡፡ከነሱም መሃል ንጉስና አልጋ ወራሽ ልኡላን ልእልቶች መኳንንቱና ባለስልጣናቱ እንዲሁም
አቡነ ቴዎፍሎስ ይገኙበታል፡፡የመኮንን እንዳልካቸው አስክሬን በሙሉ ጄኔራል አልባሳት የሬሳ
ሳጥኑ ደግሞ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ተሸልሞ ነበር፡፡ቀጥሎ ፍታት ተጀመረ፡፡ሁሉም ለቀስተኞች በእግር
ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴሄደው ተመልሰው ደግሞ ወደ ረጲ ሄደው ቀበሩ፡፡

ስለ መኮንን የሚያውቁ ሰዎች ስለ ባህርያቸው ቀጥተኛነት ቀልደኛነት ክፋትን አለማወቅና ትህትና


ግብረገባዊ ተጨዋችነት ያወሳሉ፡፡የውጭ ሃገር "ጨዋ ሰው" እና "መስፍን" ይመስላሉ ይሏቸውም
ነበር፡፡ተፈጥሮን የሚወዱ ክላሲካል ሙዚቃን የሚያደምጡ፤ማንበብን የሚወዱ ሲሆን አንዳንዶች
ግን በመልካቸው ይኩራራሉ ይሏቸዋል፡፡ስሌታዊ አካሄድም አላቸው ሲሉ ይናገራሉ፡፡የነበሩባቸው
የስልጣን ቦታዎች መልካም ባህርያቸውን አጉልተው አሳይተውላቸው ነበር፡፡

መጻሕፍቶቻውከአለም ስለመገለል ብዙም በጥልቀት ወደማያውቁት አለም መሄድ


ስለመፈለጋቸው፤ አለምን፤ገንዘብን፤ስልጣንን ስለመካድ እራስን መስዋት ስለማድረግ ይሰብካሉ፡፡
ሌላው ቀርቶ ርሃብ እንኳን (በምርጫ ከሆነ) በአስጎምጂነት ተስሏል፡፡መጻሕፍቱ የቤተሰብን
ህይወትና ደስታን ያሞጋግሳሉ፡፡ነገር ግን በሌላ በኩል ደግሞ ለንጉሳዊ ቤተሰቦች እሴት ያላቸውን
በትእቢት የተሞላ አስተያየት ያንጸባርቃሉ፡፡ንጉሳውያን ቤተሰቦቹ ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መሪ
ሆነው ነው የሚታዩዋቸው፡፡አንድ ችግር ቢፈጠር ለእነሱ ጸጥ ለጥ ብለው ባልተገዙ ሰዎች ጦስ
የመጣ ነው ብለው ያምናሉ፡፡በዳግማዊ ቴዎድሮስ ላይ በጻፉት መጽሐፋቸው "ጣይቱ ብጡል"
አጼ ቴዎድሮስን ከመጠን በላይ በማግዘፋቸው ምክንያት በሚያደንቋቸው አንባብያን ብዙ ሂስ
አስከትሎባቸዋል፡፡መኮንን ከአብዮቱ በኋላ ብዙም ተወዳጅነት የላቸውም ይሄ ብዙም
አያስገርምም፡፡ የመጻሕፍቶቻቸውን ቅጂዎች ከመጻሕፍት አዟሪዎች የተወሰኑ ኮፒዎችን ማግኘት
ችያለሁ፡፡ቀድሞ ላገኛቸው ያልቻልኹትን አንዳንድ ጽሑፎች ጭምር ከአብዮቱ በኋላ ላገኛቸው
ችያለሁ፡፡

የመኮንን ስነጽሁፋዊ ዘዬ አስደሳች ነው፡፡በበርካታ አንባቢዎች ዘንድም ይወደዳል፡፡ቴክኒኮቹ


የአማተር ቢሆኑም ታሪክ የመንገር ተፈጥሯዊ ችሎታ ተችረዋል፡፡የህይወት ልምዶቻቸውም
በመጻሕፍቱ ውስጥ ይንጸባረቃሉ፡፡መጪው ትውልድ የመኮንን ስራዎችን በርህራሄ አይን
ተመልክቶ ለኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ የዋሉትን ውለታ ይዘክር ይሆናል፡፡ታላቅ ጸሃፊ ባይሆኑም ቀደም
ያለ ውለታን ውለዋል፡፡

149
ጥቋቁር አናብስት

የግርጌ ማስታወሻ

1)ኢትዮጵያ ውስጥ ከበአሉ ሌላ የራሱንና የሌሎችን የገሃድ አለም ልምዶች በግብአትነት


የሚጠቀም ደራሲ ላስብ አልቻልኩም፡፡

2)አንዳንዶች እንደሚያስቡት መልካም ገጽታው በተለይ በቤተ መንግስቱ አካባቢ ጥቅም


አላስገኘላቸውም አይባልም ይላሉ፡፡

3)የመኳንንት ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩላቸው የቤተክህነት ሊቃውንትን


በቤታቸው ያኖሩ ነበር

4)ከዚያ በፊት ከራስ ተሰማ ናደውና ከአንድ አጎቱ ማለትም ልጅ እንጥሊ ተክለ ማርያም ከሚባል
የእናቱ ወንድም ጋር ለአጭር ጊዜ ቆይቶ ነበር፡፡ከአጤ ምኒሊክ ጋርም ቅርበት ነበራቸው፡፡የቆንጂት
እህት የሆኑት የሴት አያቱ መድፈርያሽ ወርቅ ዘሮቻቸው የንጉሳውያን ቤተሰቦችን ያገቡ ሲሆን
መኮንንንም በማሳደጉ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

5)ቆይተው ራስ ቢትወደድ ተሰማ ይህንን ቀልብሰውታል

6)መኮንን በተሰማ ቤት አንደመቆየታቸው ልጅ እያሱን እዚያ የማግኘት እድላቸው የሰፋ ነው፡፡


ሌላው አጎታቸው ደጃዝማች ብሩ ኀይለማርያም በአንድ ወቅት የእያሱን እህት አግብተዋል፡፡ስለዚህ
የመኮንንና የእያሱ የመገናኘት ጉዳይ እውን ይመስላል፡፡ምናልባትም አብረው ዳግማዊ ሚንሊክ
ተምረውም ሊሆን ይችላል፡፡

.7)የዚህ መጽሃፍ አባዜ እስከ ህይወቱ መጨረሻ ተከትሎት ሊቆይ ይችላል፡፡ በብዙ የድርሰት
ስራዎቻቸውም ላይ ተንጸባርቆ ይታያል፡፡በአንድ ወቅት በጣም የሚያምረውን የእሳቸው የነበረ
ያልተለመደ የክርስትናና የድግምት ቅልቅል የሆነ መጸሀፍ እንድገዛ ተጠይቄ ነበር፡፡በወቅቱ ግን
አቅሜ አልፈቀደም ነበር፡፡(ምንም እንኳን ዋጋው ፍትሃዊ የነበር ቢሆንም)ምንአልባት የይምሰል
ሀይማኖተኛ የመምሰል ነገር ሳይኖርበት አይቀርም፡፡

8)ከሁለት አመታት በፊት በ1905 መኮንን የተፈሪ መኮንን ወንድም (በኣባታቸው በኩል ) ሴት
ልጅ ጎብኝቶ ነበር፡፡(ማለትም የይልማ መኮንንን)የሻሽ ወርቅ ይልማን፡፡በታመመችበት ወቅት፡፡
በወቅቱ በፍቅሯ ወድቆ ነበር፡፡ከብዙ አመታት ውጣ ውረድ በኋላ ግን ሁለተኛ ሚስቱ ልትሆን

150
ጥቋቁር አናብስት

በቃች፡፡ ከመጀመርያ ግንኙነታቸው በኋላ ወድያውኑ አንድ ሰው አግብታ አዲስ አበባን ለቃ


ሄዳለች፡፡

9)ተፈሪ እንደራሴ ነበሩ ወይስ አልጋወራሽ የሚለው የሹመታቸው ሁኔታ ላይ ያከራክር ነበር፡፡
ወይም ይሄ በቆይታ ይከሰት የሚለውን ለማየት

በመጻህፍቶቹ ውስጥ ጠንካራ የፈረንሳይ ተጽእኖ ይነበባል፡፡ይህ ከአስተዳደጉ ትምህርቱና


ካደረጋቸው ጉዞዎች የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡les misreables በቪክቶር ሁጎ በበርካታ
መጻህፎቹ ላይ የመነሳት እድል ገጥሞታል፡፡በአንዳንድ ወቅቶች ገጸባህርያቱ ህይወት ላይ ጠንካራ
ክፍል እንደሚጫወት ተደርጎ ይቀርባል፡፡ከዚህም ተነስተን መኮንን ላይ ተጽእኖ ያሳደረ መጸሀፍ
እንደሆነ እንገምታለን፡፡

10)ወደ ከተማው ብዙ ሰራዊት ይዘው መግባቱን አልፈለጉም ነበር፡፡

በዚህ ወቅት የ800 ተመላሽ ወታደሮቹ ቤት በራስ እምሩ ወታደሮች መያዙን ሰማ፡፡ለመልቀቅም
አሻፈረኝ አሉ፡፡መኮንንን ለእርዳታ ቢጠይቁትም ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡

11)ተፈሪ እንደራሴ ነበሩ ወይስ አልጋወራሽ የሚለው የሹመታቸው ሁኔታ ላይ ያከራክር ነበር፡፡
ወይም ይሄ በቆይታ ይከሰት የሚለውን ለማየት

12)በመጻህፍቶቹ ውስጥ ጠንካራ የፈረንሳይ ተጽእኖ ይነበባል፡፡ይህ ከአስተዳደጉ ትምህርቱና


ካደረጋቸው ጉዞዎች የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡les misreables በቪክቶር ሁጎ በበርካታ
መጻህፎቹ ላይ የመነሳት እድል ገጥሞታል፡፡በአንዳንድ ወቅቶች ገጸባህርያቱ ህይወት ላይ ጠንካራ
ክፍል እንደሚጫወት ተደርጎ ይቀርባል፡፡ከዚህም ተነስተን መኮንን ላይ ተጽእኖ ያሳደረ መጻህፍ
እንደሆነ እንገምታለን፡፡

13)ወደ ከተማው ብዙ ሰራዊት ይዘው መግባቱን አልፈለጉም ነበር፡፡

14)በዚህ ወቅት የ800 ተመላሽ ወታደሮቹ ቤት በራስ እምሩ ወታደሮች መያዙን ሰማ፡፡
ለመልቀቅም አሻፈረኝ አሉ፡፡መኮንንን ለእርዳታ ቢጠይቁትም ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡

15)የንጉሳዊ ዝርያ ያላቸው መኳንንት ልኡል ራስ ተብለው ሲሾሙ ከነሱ በላይ ንጉሱ ብቻ ነበር
ያሉት

151
ጥቋቁር አናብስት

ዳኛቸው ወርቁ
በአጻጻፍ ዘይቤ እና ቋንቋ ተመራማሪናፈልሳፊ የዳኛቸው ወርቁ ታሪክ
ከማንም በበለጠ መልኩ ከአባቱ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነበር።
ዳኛቸው ራሱ እንደነገረኝ፣ አባቱ ወርቁ በዛብህ በወጣትነታቸው
ጀብደኛ እና በብዙ መለኪያም ለየት ያሉ ሰው ነበሩ።በ1906
በድሬዳዋ በኩል ጅቡቲ ገብተው ወደ ፈረንሳይበመሻገር፣በአንደኛው
የአለም ጦርነት ላይ በፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ተመልምለው ጀርመንን
ወግተዋል። ሶስት ጊዜ ያክል በቀላሉ ቢቆስሉም እስከ ጦርነቱ
መጨረሻ ድረስ በፓሪስ፣ ማርሴይና ቤልጂየም ውስጥ እየተዘዋወሩ ተዋግተዋል። በውጪ
ቆይታቸውም ፈረንሳይኛን አቀላጥፈው መናገር ችለዋል።ከተራ የገበሬ ቤተሰብ የተገኙ በመሆናቸው
ምንም ዐይነት መደበኛ ትምሕርት አልተከታተሉም ነበር። አማርኛ ማንበብና መጻፍ የተማሩት
እዚያው ፓሪስ ሲሆን ፈረንሳይኛንም መጻፍና ማንበብ ጨምረው ተምረዋል።የተወለዱት
በ1889ዓ.ም ይፋት፣አጋም በር ውስጥ ነበር። ፈረንሳይና ቤልጂየም ውስጥ ማዕድን ማውጫ እና
የመጠጥ ፋብሪካ ውስጥ ሰርተዋል።ቀጥለውም የሆቴል ቤት አስተናጋጅ ሆኑ። ራስ ተፈሪ(በኋላ
ቀዳማዊ ሀይለስላሴ)ልዑል እና እንደራሤ ሆነው ፓሪስን ሊጎበኙ ሲመጡ፣ ባጋጣሚ አቶ ወርቁ
ከዋና አስተናጋጆቹ አንዱ ሆነው ከሚሰሩበት ሆቴል ያርፋሉ።በወቅቱ ልዑሉ እና አጃቢዎቻቸው
ከረባት ማሰር ስለማይችሉ ከአቶ ወርቁ ከሀላፊነቶች መሀል አንዱ የእንግዶቻቸውን ከረባት ማሰር
ነበር። ዳኛቸው እንደነገረኝ ከረባት ካሰሩ የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጲያውያን መሀል አቶ ወርቁ አንዱ
ናቸው። ከልዑል ተፈሪ ጉብኝት በፊት ወርቁ በማርሴይ እየሰራ ሳለ አስፋው ወልደጊዮርጊስ ከተባለ
ኢትዮጵያዊ ጋር ተገናኘ።አስፋውና ወርቁ የተገናኙት አስፋውን ወደ ፈረንሳይ በቤት ሠራተኝነት
ካመጡት ፈረንሳውያን ጥንዶች ጋር ተጣልቶ ከቤት ሲወጣ ነው። ወርቁ አስፋውን ወደ መኖሪያው
ወስዶ አብረው መኖር ጀመሩ። በጣም የሚዋደዱ ባልንጀሮች ሆኑ። በኋላም ወደ ፓሪስ አብረው
ተጓዙ።ልዑል ተፈሪ ለጉብኝት ወደ ፓሪስ ሲመጡ ወርቁና አስፋውም እዚያው ነበሩ።ራስ ተፈሪ
አቶ ወርቁን "እንድናስተምርህ ትፈልጋለህ?"ብለው ቢጠይቋቸው "እኔ እንኳን አልፈልግም፤
ባልንጀራዬን በኔ ምትክ ያስተምሩልኝ" አላቸው።ልዑሉም አስፋው የሚማርበትን ሁኔታ አመቻቹ።
አስፋው ወልደጊዮርጊስ ወደ ጦር ትምህርት ቤት ገብተው፣ ኋላ ላይ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው
ጀነራል ሆኑ።ከፍዬ ላስተምርህ ቢባሉ አሻፈረኝ ያሉት ወርቁ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ፤ ሹመትም
ሊሰጧቸው ቃል ሲገቡላቸው አቶ ወርቁ ይህንንም ተቃወሙ።በኢትዮጲያ ባህል መሰረትም ይህ
እንደ ታላቅ ብልግና/ነውር የሚቆጠር ነበር። በዚህም ምክንያት አቶ ወርቁ ዘይግተው ወደ
ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ብዙ እንግልት ደርሶባቸዋል። ብዙዎች ራስ ተፈሪን እንደዚያ
ካሳፈሯቸው በኋላ ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ በጥብቅ መክረዋቸው ነበር። ወርቁ ምክሩን ወደ

152
ጥቋቁር አናብስት

ጎን ትተው በመጨረሻ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ግንወደ ገጠሩ ገለል ብለው “ከራስ ተፈሪ መደበቅ”
ነበረባቸው።በ1918 በደጃዝማች ወዳጄ፣ኋላ ሊጋባ(ወደ ንጉሱ ለመቅረብ ደጅ ተጠንቶ ፍቃደኝነቱ
የሚጠየቅ ባለማእረግ)እና የክቡር ዘበኛ ኃላፊ እርዳታ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።ሊጋባ ወዳጄ፣ወርቁ
ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆዩቢመርጡም፣እሳቸው ግን ወደ ፈረንሳይ መመለስ ፈለጉ። ስለዚህ
በ1919 ዓ.ም ዳግም ወደ ፈረንሳይ“ኮበለሉ”። ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ አሸሼ ገዳሜ እያሉ
ብራቸውን ሁሉ ጨርሰዋል። ከሁለት ዓመት በኋላ በ1921/22 ዳግም ፈረንሳይን ላለመርገጥ
ቆርጠው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣1000 የማርትሬዛ ጠገራ ብር ይዘው ነበር። አሁንም ወደ
ገጠርገቡ። በ1922 ውሀ–ጠገብ በምትባል መንደር ጠቅልለው ገብተው፣ዘመናዊ ልብሳቸውን
"አሽቀንጥረው ጣሉና"፣ "በባዶ እግሩ የሚያርስ ገበሬ" ሆኑ። ውሀ–ጠገብ በአብዲላቅ ወረዳ፣
ከደብረሲና በደቡብ በኩል 20 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ መንደር ነች። "እንደ ደብረሲና
ብርዳማ አልነበረችም (ደብረሲና በኢትዮጵያ በጣም ብርዳማ ከሆኑ ቦታዎች አንዷ ናት)።ውሀ–
ጠገብ ጥሩ፣ሞቃትወይናደጋ የአየር ንብረት አላት። ውሀ–ጠገብ ላይ ከአሰገደች ሀብተወልድ ጋር
ተገናኝተው በ1926/27 ዓ.ም ተጋቡ። ከብዙ ዓመት የፈረንሳይ ቆይታው በኋላ ወርቁ ሃይማኖቱን
የተወ ወይም "የኮተለከ" (ካቶሊክ የሆነ) ስለመሰላቸው ዳግም እንዲጠመቅ ወይም በሌላ አነጋገር
"እንዲነፃ" ይገፋፉት ጀመር።አሰገደችን ከማግባቱ በፊት የተለመደውን "የቄደር" ወይም
"የመንፃት"ስርአት መፈፀም ነበረበት። አሰገደች ያልተማረች፣የአካባቢው ገበሬ ልጅ ነበረች።
በቃለመጠይቃችን ወቅት በ1979 ዓ.ም አሰገደች በደብረሲና ትኖር ነበር።

የዳኛቸው ቤተሰቦች እስከ 1932 ዓ.ም ድረስ በውሃ–ጠገብ ይኖሩ ነበር።ነገር ግን ዳኛቸውን
ለማስተማር ወደ ደብረሲና ተዛወሩ።ዳኛቸው የተወለደው በየካቲት 16 ቀን 1928 ዓ.ም ነበር።
ከ40 ቀን በኋላ ሲጠመቅ የክርስትና ስሙ ኪዳነ ማርያም ተባለ።አቶ ወርቁ በከተማው ትንሽ ሱቅ
ከፍተው ጨው፣ልብስ የመሳሰሉትን መነገድ ጀመሩ።

ገና መንደር ውስጥ እያሉ፣ ዳኛቸው በጊዜው ኢትዮጵያን ወረው የነበሩት ጣሊያኖችን (1928–
1933) ያስታውሳል።አባቱ በ"መንግሥት ሰላይነት" ተጠርጥረው ደብረሲና ቢታሰሩም ኋላ
ተፈተዋል። ያኔ ቤተሰባቸውን ይዘው ደብረሲና ከተሙ። ዳኛቸው አስቸጋሪ እና ቀዥቃዣ ልጅ
ነበር። አንዴ አንድ ጣሊያን እየጋለበወደ ሰሜን ሲመጣ፣ዳኛቸው ተንቀዥቅዦ መሀል መንገድ
ይገባል።ጣሊያኑም ዳኛቸውን አፈፍ አድርጎበማንሳት በፈረስ ከመረገጥ ለጥቂት ያድነዋል።
አባትየው ተጠርተው ይመጡና ልጃቸውን በአግባቡ ስላልጠበቁ ዱላ ይቀምሳሉ።ዳኛቸው አባቱ
153
ጥቋቁር አናብስት

ሲገረፉ በልጅ አዕምሮው ተመልክቷል።ልጃቸው ከእይታቸው ተሰውሮ መንገድ ድረስ እስኪገባ


ባለማስተዋላቸው እናቱም ጉሸማ አልቀረላቸውም። በዚህ ወቅት ቤተሰቡ ሁሉ ከአንድ ልኳንዳ
ቤት ጎን ያለች አንዲት ክፍል ቤት ውስጥ ታጉረው ይኖሩ ነበር። ኢጣልያኖች ካንገላቷቸው በኋላ
አቶ ወርቁ ቤተሰባቸውን ደብረሲና ትተው ለአንድ ዓመት ያህልዳግም ወደ ገጠሩ ገለል አሉ።
በዳኛቸው አብይ ስራ "አደፍርስ" ውስጥ፣ አቶ ወልዱ የተባሉት ገፀ ባህሪ፣ ነገረ–ስራቸው ሁሉ
ከአቶ ወርቁ ጋር በጣም ይመሳሰላል።

ዳኛቸው ለወላጆቹ የበኩር ልጅ ነው―ቀጣይ ታናሽ እህት፣ ሁለት ወንድሞችና የሁሉም ታናሽ ሌላ
እህት ነበሩት። በአራት ዓመቱ ወደ ከተማ ከመግባቱ በፊት ለአጭር ጊዜ በገጠር እረኛ ነበር።
ደብረሲና እንደመጣ ያለምንም ሀሳብ “እንደልቡ ይጫወት” ነበር።ስድስት ወይም ሰባት ዓመት
ሲሆነው ትምህርት ቤት ገባ። እንደሌሎች ልጆች ማንበብና መፃፍ ለመማር የቄስ ትምህርት ቤት
ደጃፍ ሳይረግጥ ቀጥታ የመንግሥት ትምህርት ቤት ገባ።አባትየው ለቤተክርስቲያንብዙም ቦታ
ስለማይሰጡ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ወሰዱት። እናትየው ግን ማታ ማታ ወደ ቤተክርስቲያን
ስትሄድ አብራ ትወስደውና ግዕዝ እንዲማር ታደርገዋለች።ይሁን እንጂ አባትየው ካህናትን
እምብዛም ስለማይወዱ ይህንን ጉዳይ ስራዬ ብሎ የነገራቸው የለም።የቀሳውስቶች ነገረ–ስራ
አይጥማቸውም። እስከ ስድስተኛ ክፍል ደብረሲና በሚገኘው የመንግስት ትምህርት ቤት ከተማረ
በኋላ፣ ኮተቤ በሚገኘው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰባተኛን ዘሎ
ስምንተኛ ክፍል ገባ።

ከዚያ በፊትም ቢሆን፣ ለጥቂት ወራት በሀገሪቱ መናገሻ ቆይቷል።ገና ሶስተኛ ወይም አራተኛ ክፍል
እያለ፣ ጄነራል አስፋው ወልደጊዮርጊስ አቶ ወርቁ በፈረንሳይ ለዋሉላቸው ውለታ ብድር
ለመመለስ፣ዳኛቸውን ወደ አዲስአበባ ይዘውት መጥተው ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት
አስገቡት።ነገር ግን ማዕድ ከሰራተኞች ጋር እንዲቋደስ ስለሚደረግ፣ዳኛቸው የአቶ አስፋው ቤት
“የአኗኗር ሁኔታ” ስላልተመቸው፣ በግምት ከአምስት ወራት በኋላ ጠፍቶ ወደ ደብረሲና ተመልሶ፣
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ በዚያው ቆየ።

ዳኛቸው ለተጨማሪ ትምህርት እስኪለያቸው ድረስ ወላጆቹ ለ12 ዓመታት ያህል ብርቱ ተጽዕኖ
አሳርፈውበታል። አባት በጣም ስራ ወዳድ ሲሆኑ ዘወትር ጠዋት 12፡30 ከእንቅልፋቸው ይነቁና
ዳኛቸውንም ይቀሰቅሱታል። እናቱም እቤት ውስጥ እስካለድረስ ለልጃቸው ተረት መንገር የዘውትር
ስራቸው ነበር።ዳኛቸው በልጅነቱ ግጥም መጻፍ የጀመረው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ገና የአንደኛ
ደረጃ ተማሪ እያለ፣ በርካታ ግጥሞችንጽፏል።እናቱ የነገሩትን ተረቶች እንዳሉ በጽሑፍያሰፍርና
ፍጻሜያቸውን ብቻ ምናቡ እንደመራው አድርጎ ይቀይራቸዋል።ተረቶቹን ለማሳተም አሳታሚ
ሲያፈላልግ የነበረ ቢሆንም በኋላ "ይኼንን ሀሳቡን ተወው"።ግጥሞቹን ለክፍል ጓደኞቹ

154
ጥቋቁር አናብስት

ቢያነብላቸውም ለመታተም ግን አልበቁም።ንጉሱ ወደ ደብረሲና ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ


ባይሰረዝ ኖሮ፣ዳኛቸው እርሳቸው በተገኙበት ግጥም እንዲያነብ ተመርጦ ነበር።

ዳኛቸው ገና የ13 ዓመት ጉብል ሳለ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፌዴሬሽን ሊዋሀዱ ነው የሚል ወሬ


ናኘ።ዳኛቸውም ይህንን ተመርኩዞ "ያላቻ ጋብቻ ትርፉ ሐዘን ብቻ" የተሰኘ ተውኔት ፃፈ።ብዙ
ግጥሞች የነበሩት ይህ ተውኔት በደብረሲና ለአንድ ጊዜ ብቻ ታየ።ዳኛቸውም "አንድ ወይ ሁለት
ገፀ ባህሪያትን" ወክሎ ተጫውቷል። "ሰዎች ወደውት ነበር" ይላል ዳኛቸው። የመድረክ ቁሳቁሱን፣
መጋረጃ የመሳሰለውን የገዙት አባቱ ነበሩ።

በተማሪ ቤት እያለ ከሚያነባቸው እና ከሚወዳቸው መሐል ከበደ ሚካኤል ("ታሪክና ምሳሌን"


በቃሉ ይወጣው ነበር)፣ መኮንን እንዳልካቸው እና ሕሩይ ወልደስላሴ1ይገኙበታል።እነዚህ
ደራሲዎች ከሥነ ጽሑፍ ጋር በፍቅር እንዲወድቅ ቢያደርጉትም “ደራሲነቴ ላይ ግን ተጽእኖ
አላሳደሩብኝም” ይላል፤ "የተወለድኩት ለመፃፍ ነው ፤ በልጅነቴ መፃፍ የጀመርኩትም ለዚህ ነው"
ይል ነበር ደጋግሞ። ቤተሰቦቹ ራሱን እንዲሆን ያበረታቱት ነበር እንጂ፤ በማይገባ መልኩ፣
በማይፈልገው አቅጣጫ ገፍተዉት አያውቁም።

የዳኛቸው ቤተሰቦች ጥሩ የኑሮ ደረጃ ቢኖራቸውም፣ በእሱና በሌሎች ልጆች መሐል ለምን ልዩነት
እንዳለ አይገባውም።ጓደኞቹ አብረውት እንዲኖሩ ይፈልግ ነበር። አንድ ጓደኛው ከ3 እስከ 4
ሳምንት አብሯቸው ሲቆይ ሌላኛው ደግሞ ከ6 እስከ 7 ወር ከርሟል።አባቱ ግን ይህንን
የሚፈቅዱት የዳኛቸው ጓደኞች በስራ በማገዝ ቆይታቸውን ከደጎሙ ብቻ ነበር። ልጆቹ ግን ሰነፍ፣
በዚያ ላይ ሌባ ሆነው፣ዳኛቸው ላይ ክፉ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ዐይነት ሲሆኑ፣ የዳኛቸው አባት
ቆይታቸውን በብርቱ ይቃወማሉ። በዚህ ምክንያት ዳኛቸው ተቀይሞ "ከነዚሁ ልጆች" ጋር ጠፍቶ
ደብረብርሃን ለስድስት ወር ከረመ። አባቱ ለነዚህ ልጆች ያላቸው መጥፎ አመለካከት ምንም ግልጽ
አልሆነለትም። ይህንን ገጠመኙን በኋላ "ሰው አለ ብዬ" በተሰኘ ተውኔቱ ተንጸባርቆሊሆን
ይችላል። በተቀረ ወላጆቹ “ነጻ አስተሳሰብ የነበራቸውና ታጋሽ” ነበሩ። በቤት ውስጥ ውሻ እና
ድመት እንዲያሳድግም ይፈቀድለት ነበር። ዳኛቸው ከለማዳ ድመቶች ይልቅ የዱሮቹ ይበልጥ
ይስቡታል።እናቱ “የማይከብዱ እና ቤተሰባቸውን ወዳድ” ናቸው። አባቱ በቤታቸው
የዘፈን/የሙዚቃ ሸክላማጫወቻ ስለነበራቸው ሙዚቃ ከፍተው ከልጃቸው ጋር ይደንሱ ነበር፤
“ዳንስ አዋቂም ናቸው።”ቤተሰቡ “መበታተን እስከጀመረበት”ጊዜ ድረስ በጋራ ተደስቶ ይኖር
ነበር።ዳኛቸውትምህርት መማር እንዳለበት አባትየው አበክረው ስለሚያስቡ፣ደብተሩን ዘወትር

155
ጥቋቁር አናብስት

እየተመለከቱለውጡን ይከታተላሉ። አስተማሪው ልጃቸውን በዱላ መቅጣቱን እናቱ በጥብቅ


ይቃወሙ ነበር። “አስተማሪው ግን ግድ አልነበረውም።”እንደዳኛቸው አስተያየት የአባቱ ብርቱ
ጥረትና ክትትል ባይታከልበት ኖሮ ምናልባት “ዛሬየሆነውን ዐይነት ሰው ላይሆን ይችል ነበር።
”አባቱ አቶ ወርቁ እስከ 78 ዓመታቸው ድረስ ኖረው፣ ኃይለሥላሴ ከሥልጣን ከተወገዱ ከሦስት
ወይም አራት ወራት በኃላ አረፉ። ሆስፒታል ውስጥ ለስድስት ወር ቆይተው ወደ ቤት ባመጧቸው
በአራተኛ ቀናቸው አረፉ።የሕይወት ፍልስፍናቸው "የራስህ አገልጋይ ካልሆንክ፣ የሌሎች አገልጋይ
ሆነህ ትቀራለህ" የሚል ነበር።

****

ዳኛቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እስከ 11ኛ ክፍል ድረስ በኮተቤ ተከታተለ። በኮተቤ
ቆይታው ስለ ትምህርት ቤት ሕይወት ግጥሞች ይጽፍ ነበር።ልክ ስምንተኛ ክፍልን እንደጨረሰ
እረፍቱንበተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አሳለፈ። በነዚያ ሶስት ወራት "ሰው አለ ብዬ"ን ፃፈ።
ተውኔቱ በ1950 ታትሞ ሲወጣ “ብዙም አልተለወጠም።”ይሁን እንጂ በመድረክ ላይ አንዴም
ቢሆን ለእይታ አልበቃም።

ዳኛቸው ልክ አስራ አንደኛ ክፍልን ከመጨረሱ በፊት ከባድ የጉሮሮ ህመም ያጋጥመውና ለሶስት
ወር በጽኑ ይታመማል።ወደ ዳግማዊ ምኒልክ ትምሕርት ቤት ክሊኒክ ይዘውት ቢመጡም
ሊፈውሰው የሚችል መድሐኒት አልነበራቸውም። ጉሮሮው ፍጹም ተዘግቶ ምግብ እንኳን መመገብ
አይችልም ነበር።ወላጆቹ ተጠርተው ለአንድ ወር ከግማሽ ያህል ከዛሬ ነገ ይሞታል ተብሎ ሲጠበቅ
ቆየ።ራሱም ሞቱን እየጠበቀ ነበር። እንደሚሞት ”ያውቅ“ ነበር፤ ይህም በቀረው ሕይወቱ የማይፋቅ
አሻራ አትሞበት አልፏል። ወላጆቹን ጨምሮ ማንም እንዳይጠጋው የተከለከለ ስለነበር፣ ከተቀረው
አለም ጋር የነበረው ግንኙነት በመስታወቱ መስኮት አሻግሮ በማየት ብቻ ተወሰነ። ከዚያም እንደ
እድል ሆኖ አዳዲስ መድሀኒቶች ተገኙ፤ በጠና የታመሙ በሽተኞች ላይም ይሞከሩ ጀመር። ከነዚህ
አንዱ ዳኛቸውን ፈወሰው፤ ከሞትም ተረፈ።ዳኛቸው አሁን ያንን ጊዜ ሲያስታውስ ”ከመቃብር
የመውጣት፤ እንደገና የመወለድ ያክል ነበር“ ይላል።ከተሻለው በኋላ ለሁለት ሳምንት ያህል በኮተቤ
በክትትል ከአልጋ ሳይወርድ ከቆየ በኋላ ወደ ወላጆቹ ሀገር ወደ ደብረሲና ሄደ። ከዚህ ክፉ
አጋጣሚ በኋላ ወደ ኮተቤ መመለስ አልፈለገም። ይልቁንም አቶ ካራማይክል የተባለ ግለሰብ
በኮከበጽባህ (የሚገኘው ኮተቤ መንገድ ላይ ነው) ባቋቋመው የመምህራን ማሰልጠኛ ለአንድ
ዓመት ሰለጠነ። በዓመቱ መጨረሻ ለሁለት ፈተና ተቀመጠ፦ ለመምህራን ስልጠና ፈተናውና
ለአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና። ይሄም ሳይበቃው በእንግሊዝ የለንደንን

156
ጥቋቁር አናብስት

መልቀቂያ ፈተና ተፈትኖ ሦስቱንም አለፈ።የመምህርነት ስልጠናውን የፈለገው በቶሎ ስራ


ለመቀጠር ነበርና፣ በሐረር መድኃኔዓለም ትምህርት ቤት በአማርኛ ቋንቋ አስተማሪነት በ225 ብር
ደምወዝ ተቀጠረ። መደበኛ ክፍያው 180 ብር ብቻ ሲሆን በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ተማሪዎቹ
ሁሌም በአማርኛ “ከፍተኛ ውጤት” ያስመዘግቡ ነበር። በዚህ ወቅት "ሰቀቀንሽ እሳት" የተሰኘ
ተውኔት ፃፈ።በዚያው በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ለመድረክ እንዲበቃ ከማድረጉም በላይ
"በጣም ውጤታማ" ነበር ይላል። ይኼው ተውኔት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት አማርኛ ባስተማረበት
የአዲስ አበባ ቴክኒካል ትምህርት ቤትም ለእይታ በቅቷል። በኋላ በ1951 ዓ.ም ደግሞ በቀድሞው
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር ቤት ተመድርኳል። ከዚህ ተውኔት ባገኘው ገቢ የቀደመው ተውኔቱን
"ሰው አለ ብዬ" ቢያሳትምም "ሰቀቀንሽ እሳት" ግን ጭራሽ የመታተም እድልአላገኘም።

ለእለታዊው አዲስ ዘመንና ለሳምንታዊው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ መፃፍ የጀመረውም በዚህ ወቅት
ነበር። በብዛት ይጽፍ የነበረው ስለ ሥነ ጽሑፍ፣ ስላነበባቸው መጽሀፍት፣ ስላያቸው ተውኔቶች፣
ስለተመለከታቸው ፊልሞች ነው። በዚሁ ወቅት አወዛጋቢ ርእስ ስለነበረው የፀሐፊዎችገቢ ማነስ
ለመፃፍም ብዕሩን አንስቶ ነበር።ፀሐፊዎችየተሻለ ገቢ ማግኘት አለባቸው ብሎ ሽንጡን ገትሮ
ተከራክሯል።በጊዜውየነበረው አሰራር ግን ትያትር ቤቶች አብዛኛውን ትርፍ ለራሳቸው
የሚያስቀሩበት ነበር።

ጥሩ ስራ ቢኖረውም አግብቶ፣ የቤተሰብን ኃላፊነት ለመሸከም ገና ዝግጁ አልነበረም።ይልቁንም


በትምህርቱ መግፋት ይፈልግ ነበር።የወሲብ ፍላጎቱን ለሟሟላት ጋብቻ መመስረት
አይጠበቅበትም።እንደውም ዳኛቸው ፍቅር መስራት የጀመረው ከእድሜው ቀድሞ ነው።በ12
ዓመቱ ከ14 አመቷ ሞግዚቱ ጋር ቢቀብጥም ሁለቱም ወሲብ እንዴት እንደሚደረግ ግንዛቤው
ስለሌላቸው ከመተሻሸት ያለፈ ነገር አላደረጉም።እርሷ ግን እንዲያስረግዛት ሁሉ ፈልጋ "ለፍሬ
በለው" እያለች በለሆሳስ ትናገር ነበር።በነገሩ ካለው አነስተኛ እውቀት የተነሳ 14 ዓመት
እስኪሞላው ድረስ ከወሲብ የሚገኘውን ደስታ በአግባቡ ማጣጣም አልጀመረም ነበር።ለብዙ
ኢትዮጵያውያን ይህ እድሜ ፍቅር ለመስራት፣ያን ያህል ባይሆንም፣ ገና የሚባል ነበር።

በ1953 ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገባ። ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ የተመሰረተው በ1943 ሲሆን በ1953 ቀዳማዊ
ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ተሰየመ።ከአራት ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኘ።
ለሁለት ዓመት የተማረው አጠቃላይ ማህበራዊ እውቀት የሚያስጨብጡ ትምህርቶችን ብቻ ነበር።
በኋላ ግን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ሥነ ጽሑፍን ማስተማር በመጀመራቸው፣ ግዕዝ እና
አረብኛንም ጨምሮ ለሁለት ዓመት ተማረ።"ምኞቴን ያሳካሁባቸው" ስለሆኑ በሚል
የመጨረሻዎቹን ሁለት ዓመታት እንደሚወዳቸው ይናገራል። በዩኒቨርስቲ ቆይታው የተቃውሞ
157
ጥቋቁር አናብስት

ግጥሞችን መፃፍ ጀመረ። "እምቧ በሉ" በሚለው የግጥም መድብሉ ውስጥ የተካተቱት አብዛኛዎቹ
ግጥሞች በነዚህ አራት ዓመታት የተፃፉ ነበሩ።"ሁሉም የተቃውሞ ግጥሞች ነበሩ" ይላል።
እንደውም የተቃውሞ ግጥም መፃፍ ፋሽን ሆኖ ሁሉም ይጽፍ ነበር። ይህ የተቃውሞ ግጥም
መበራከት መንግስትን እጅግ ስላስጨነቀው “አጼው” ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው “እንዳያድሩ”
ከለከሉ። ለወጪያቸው መሸፈኛ ገንዘብ እየተቆረጠላቸው ቀን ቀን ብቻ እንዲማሩ ተደረገ።
ግጥሞቹ ከሚዳስሷቸው "ማሕበራዊ ጉዳዮች" መሐል የመሬት ስሪት ለውጥ ("መሬት ላራሹ")፣
"ፍትህ ለደሀው"፣ "ለተመሳሳይ ስራ ተመሳሳይ ደሞዝ"፣ "በመንግሥት ስራ እኩል ተቀጣሪነት"
―በአጠቃላይ ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል እድል እንዲሰጥ የሚጠይቁ ነበሩ።2ዳኛቸው
“ይፋት ውስጥ ከሁሉም ብሔረሰቦች ጋር ተቀላቅሎ” በማደጉ “የብሔርተኝነት ስሜት የለኝም”
ይላል። በኢትዮጲያ ውስጥም የጠራ/የነጠረ ጎሳ አለ ብሎ አያምንም—ካለም የጎሳ ማንነት
የሚገለጸው “በቋንቋ” ነው ብሎነው የሚያስበው።ቤተሰቡ በብዛት “አማራ ይመስላሉ።”ነገር ግን
የአባቱ እናት ኦሮምኛን አቀላጥፈው ይናገራሉ ፤ ያደጉት ጋሞ ጎፋ ቢሆንም በከፊል ወይም በሙሉ
ኦሮሞ ሳይሆኑ አይቀርም።

የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች "የሶስት ሺህ ዓመት ታሪክ" እየተባለ በባለስላጣናቱ የሚለፈፈው "ምንም


ለውጥ ያልታየበት" ባዶ ጉራ ነው እያሉይቃወሙት ጀመር። የተቃውሞ ግጥሞቹ "ከአብዮታዊነት"
ይልቅ "ተራማጅነት" እና "ለውጥ ናፋቂ" ነበሩ ባይ ነው።

ዳኛቸው ዩኒቨርሲቲ እያለ የሥነ ጽሑፍ እንቅስቃሴዎቹ ግጥም በመፃፍ ብቻ የተወሰኑ ነበሩ።
የግእዝ ቅኔን በተመለከተ ብዙ ጥናት አድርጎ፣ የአራተኛ ዓመት ተማሪ እያለ በኋላ ደግሞ
የዩኒቨርስቲው ሰራተኛሲሆን በስፋት ጽፎበታል። ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ስላጠናቀቀ
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መጀመሪያ ተመራቂ ረዳት፣ ከዚያም ረዳት ሌክቸረር፣ ኋላም ሌክቸረር
ሆኗል።

በ1960 ዓ.ም፣ ከተመረቀ ከሶስት ዓመታት በኃላ "ትበልጭ"(ትበልጪያለሽ ለሚለው የልጃገረዶች


ስም ቁልምጫ ነው)የተሰኘ ተውኔት ጽፎ ለመድረክ አበቃ፤ትበልጪያለሽ የተውኔቱ መሪ ገፀ ባህሪ
ናት።ተውኔቱ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቲያትር ቤት ሁለት ጊዜ ለመታየት በቃ።ዳኛቸው
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ገና የአራተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ማስተማር ጀምሮ ነበር።ከተመረቀም በኋላ
ማስተማሩን ለአራት ወይንም አምስት ዓመት እስከ 1961 ዓ.ም ድረስ ቀጠለ። ለመድረክ የበቁት

158
ጥቋቁር አናብስት

ሁለቱ ተውኔቶቹ "ሰቀቅንሽ እሳት" እና "ትበልጭ"፣በመዲናዋ በሚታተሙ ትላልቅ ጋዜጣዎች


ተቃኝተዋል።

***

በ1962 መጀመሪያ ዳኛቸው ለሶስት ዓመትሥነ -ጽሑፍን “በአለም አቀፍ ጸሐፍት አውደጥናት”
ላይ ለመማር ሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው አዮዋ ዩኒቨርስቲ ነጻ የትምህርት እድል አግኝቶ ወደዚያው
አመራ።ትምህርቱየመምህራን አቅም ማጎልበቻ ሳይሆን ብቁ የወደፊት ደራስያንን ለማፍራት ያለመ
ነው። ለአብዛኛዎቹ ተማሪዎች እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው፤ ለጥቂቶች ሁለተኛ ቋንቋቸው
ሲሆን ዳኛቸውም ከነዚህኞቹ የሚመደብ ነበር። አስከትሎም በሥነ ጥበባት ሁለተኛ ዲግሪውን
በመስራቱ፣ትምህርቱን ለማጠናቀቅእንደ ቅድመ ሁኔታ ከተቀመጡ መስፈርቶች መሀል ሊታተም
የሚችል ወጥ የሆነ ድርሰት ማዘጋጀት አንዱ ነበር። ዳኛቸው የፈጠራ ጽሑፍ ፕሮግራምን
ከመቀላቀሉ በፊት፣በእንግሊዝኛ ቋንቋ የትምህርት ክፍል ለሁለት ዓመት ተምሮ የሁለተኛ
ዲግሪውን መያዝ ይጠበቅበት ነበር።ትምህርቱን በ1964 ዓ.ም ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ሀገሩ
ተመለሰ። በዚህ ወቅት ሁለት ታሪኮችን ("ማሚቴ" እና አንድ ሌላ ርዕሱ ያልታወቀ) ያሳተመ ደራሲ
ሆኗል። የመመረቂያ ጽሑፉ በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ ስምንት ታሪኮች ስብስብ ነበር። ነገር ግን ሌሎች
ታሪኮችን መጨመር ስለሚፈልግ ቃለ መጠይቃችንን እስካደረግንበት ጊዜ ድረስ አላሳተማቸውም።
እነዚህ ታሪኮች "በማንኛውም ጊዜ" ሊታተሙ የሚችሉ ናቸው ብሎ ያምናል።

ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ ዓመት ያህል ሲያስተምር ቆይቶ
"ከዩኒቨርስቲው ሹመኞች ጋር ተጋጨ"።"ችግሩ" የጀመረውየዳኛቸው ለአራተኛ ዓመት ተማሪዎች
የሚሰጠውን ጨምሮ፣ ክፍል ገብቶ ምንም ትምህርት ተከታትሎ የማያውቅ ልጅ "22 ክሬዲት
ሰአት" እንደወሰደ ተደርጎ መያዙን ሲቃወም ነው።ሹመኞቹ "ነገሩን አለባብሰው፣ ተማሪው
የተወሰኑ ትምህርቶችን በዚያ ሴሚስተር እንደማይወስድ አድርገው ፎርም አስሞልተው ለማለፍ
ቢሞክሩም" ዳኛቸው በጄ አላለም። ስለዚህ ዳኛቸውን "የዩኒቨርስቲውን ስም በማጥፋት" ከሰሱትና
በህጉ መሰረት "የስድስት ወር ቅድመ ማስታወቂያ" ተሰጥቶት በዘዴ እንዲለቅ ተደረገ። የተባለው
ተማሪ "ትልቅ ስልጣን ያለው የታዋቂ ቤተሰብ ልጅ" ቢሆንም ከዚህ ሁሉ ግርግር በኋላ "በስርአቱ
አጥንቶ" “ከሁለት ዓመት” በኃላ ዲግሪውንአግኝቷል።"ይህንን ሁሉ የሚያደርገው የዩኒቨርስቲው
ፕሬዚዳንት የነበረው አክሊሉ ሀብቴ ነው" ይላል ዳኛቸው፤"ከአብዮቱ በኋላ ስለፈራኝ ሀገር ጥሎ
ፈረጠጠ፤ አሁን ዩናይትድ ስቴትስ፣ በአለም ባንክ ውስጥ ጥሩ ስራ አለው" ይላል ጨምሮ።ከአራት

159
ጥቋቁር አናብስት

ዓመት በፊት ወደ ሀገሩ ሲመለስ፣"ኢትዮጵያ ብድር ስለምትፈልግ ብቻ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው


ተቀበሉት" ይላል ሲያጠቃልል።

ዳኛቸው ዳግም የመንግሥት ስራ ከመያዙ በፊት አራት ዓመት ተኩል አልፎት ነበር። ከአራት ወይ
አምስት ወራት በኋላ ስራፈትነቱን ተለማመደው። ያኔነው አንድ ዓመት ተኩል ያህል የፈጀበትን
ታላቁን ስራውን "አደፍርስ"ን የፃፈው።ዳኛቸው ራሱን "የአንድ መጽሐፍ ደራሲ" ብቻ አድርጎ ነው
የሚቆጥረው። ምንም እንኳን ዳኛቸው ሌሎች ሥነ ጽሑፋዊ ስራዎች ቢኖሩትም፣ ለ"አደፍርስ"
የሚሰጠው ግምት ምን ያህል ላቅ ያለ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም። ቀደምት ስራዎቹን፣ ለዚህ
መጽሀፍ እንደ መንደርደሪያ ወይም መዘጋጃ አድርጎ ሳይቆጥራቸው አይቀርም። አደፍርስ የተፃፈው
በጣም በተወሳሰበ አማርኛ ቢሆንም፣ ዳኛቸው በትውልድ ቀዬው የሚነገረውና እየተነገረም ያለው
አማርኛ እንዲህ ያለ መሆኑን ይናገራል። ለማሳተሚያ የሚሆነውን ገንዘብ ያገኘው ከቤተሰቦቹና
ከጓደኞቹ ሲሆን እርማቱን፣ አርትኦቱንና የመሳሰለውን የሰራው እርሱ ራሱ ነው። አደፍርስ
10,0003 ቅጂዎች ታትሞ በደንብ በመሸጡ አሁን እንኳን አዲስ፣ አሮጌውን ራሱ ለማግኘት
በጣም ከባድ ነው።

ቀጣይ መጽሐፉ የተፃፈው በእንግሊዝኛ ርዕሱም "The Thirteenth Sun"4 ይሰኛል።መጽሐፉ


የኢትዮጵያን ማሕበረሰብ ባህላዊ ስርአት አንዳንድ እሴቶችአጥብቆ የሚተች በመሆኑ በኢትዮጵያ
ውስጥ በአማርኛ ለማሳተም የሚሆን ስላይደለ በእንግሊዘኛ እንደታተመ ዳኛቸው ይናገራልመጽሀፉ
ለሔይንማን አሳታሚዎች እንደተላከ ወዲያውኑ ተቀብለውት እ.አ.አ በ1973 ታተመ። ከዚያም
በኋላ ተደጋግሞ ታትሟል። ወደ ጀርመንኛም ሁለቴ ተመልሷል፦ በምእራብ ጀርመን በጠንካራ
ልባድ እንዲሁም በምስራቅ ጀርመን በስስ ልባድ።ወደ በፖርቱጋልኛ እና “እንደሰማሁት” ወደ
ቻይንኛም ተተርጉሟል።ወደ ቻይንኛየተተረጎመውን ቅጂ ማግኘት አልቻለም።

ከዚህ በኋላ በሐገሪቱ ለሚገኙት ሁሉምጋዜጦች በአማርኛና በእንግሊዘኛ መፃፍ ጀመረ።ስለ ቅኔ፣
ስለልብወለድ የአጻጻፍ ዘዴ5፣እንዲሁም በብዛት የ“ቤሳ ልብወለድ” መጽሀፍትን ቅኝት ይጽፍ ነበር።

ቀጥሎ በEcole Normal Superieure/ከተወረሰ በኋላ ጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት በሆነው/ "ሥነ ጽሑፍ እና ሥነ ግጥም"ን ለአንድ ዓመት ተኩል አስተማረ።ሁለተኛ ደረጃ
ተማሪ እያለ በፈረንሳይኛ ማንበብ ቢሞካክርም፣አሁን ግን የፈረንሣይኛ ቋንቋ ችሎታው ብዙ
እንደማያወላዳ ይናገራል።እንኳን ፈረንሳይኛዬ የተሻለ የማውቀው እንግሊዝኛ እንኳን “አዘውትሬ
ስለማልጠቀመው፣ዝጓል/እየጠፋኝ ነው”ይላል።ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በትርፍ ጊዜው በኢትዮጵያ

160
ጥቋቁር አናብስት

የደረጃዎች ድርጅት መስራት ጀመረ፤በቃለመጠይቃችን ወቅትም እዚያው ይሰራ ነበር። በ1966


ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አግኝቼው"አደፍርስ"ን የሰጠኝም እዚያው መስሪያ ቤት ውስጥነበር።
አደፍርስን አንብቦ ለመረዳት በጣም ብዙ ወራት ሲወስድብኝ፣ በማንኛውም ቋንቋ የተፃፈ መጽሀፍ
ሳነብ ያንን ያህል መዝገበ ቃላት ማገላበጥ አስፈልጎኝ አላውቅም።6

****

አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ በሚያዝያ 1966ዓም፣ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ድርጅት የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ
ሆኗል። በዚያው ዓመት ለአንደኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ከአራት ዓመትበኋላ ደግሞ ለሁለተኛ ዲግሪ
ተማሪዎች ፈታኝ ሆኖ እስከ 1977 ዓ.ም ድረስ ሰርቷል። (በመጀመሪያው ዓመት አንድ ተማሪ ብቻ
ነበር የፈተነው።)

ዳኛቸው ወርቁ በአብዮቱ ወቅት"ከአይን ራቅ ብዬ ቆየሁ" ብሎ ነግሮኛል።ዳኛቸው


ወርቁ“የአብዮቱን ወቅት ድምጼን አጥፍቼ አሳለፍኩት” ሲል አጫውቶኛል።/ጥቂት የልጆች
መጽሐፍ ጽፎ፣ ሁለቱ በ1970/71 በልጆች ቀን በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት
ታትመውለታል።የአርትኦት ስራ የሰራባቸው ሁለት መጻሕፍትም በዚያው እለት ታትመዋል።
በ1977 ደግሞበከባድ አማርኛ የፃፈውን"የጽሁፍ ጥበብ መማሪያ" አሳተመ። ከዶክተር አምሳሉ
አክሊሉ ጋር በመሆን ያዘጋጀው "የአማርኛ ፈሊጣዊ አነጋገሮች" ከቃለመጠይቃችን ከሁለት ወራት
በኋላ ይወጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ነግሮኛል። (ታትሞ የወጣው ግን ከብዙ ወራት በኋላ በ1979
ዓ.ም ሐምሌ ላይ ነበር) በኢትዮጵያ ደረጃ አውጪዎች ድርጅት ስር የሳይንሳዊ እና ቴክኒካል
ቃላቶች መዝገበ ቃላት ዝግጅትና አርትኦት ሰርቷል ምንም እንኳን ገበያ ላይ ባይውልም።

በቃለመጠይቃችን ወቅት ዳኛቸው መፃፉን ባያቆምም "አሁንም ሆነ ወደፊት ለማሳተም"


አላቀደም። የአብዮቱ እርምጃ "ከብዕሬ ፈጥኗል" ይላል። አብዮቱ "ከልብወለድ የበለጠ ቅዠት"
ሆኗል ብሎም ይጨምራል። እየፃፈ የነበረውን ለማሳተም ጥሩ ወቅት አልነበረም ብሎአስቧል።
የሚጽፈው ሁሉ በቶሎ እውነት እየሆነ፣የሚከሰቱት ኩነቶች የፈጠራ ምናቡን እየተጫኑት፣ ጊዜ
እየቀደመው መጣ።ያልታተሙት ጽሑፎቹ "ከአብዮቱ በኋላ የታሪክ ሰነዶች“ ሆነው
እንደሚያገለግሉ እርግጠኝነት ይሰማዋል። መፃፉን ግን መቼም አያቋርጥም። "አንዴ መፃፍ የጀመረ
መቼም አያቆምም" ይላል፤“መፃፍ እንዲሁ እንደዋዛ የሚተዉት ነገር አይደለም።”በዚያን ወቅት
ፖለቲካውን ወደጎን አድርጎ ሰብአዊ ለውጦች ላይ ይበልጥ በማተኮር፣ ስለ ማኅበረሰብ በጥልቅ
161
ጥቋቁር አናብስት

ጥናት እያደረገ ነበር።አንድ ማኅበረሰብ እንዴት አምባገነናዊ እየሆነ እንደሚመጣ ይታዘባል። በፊት
ህልሞቹ ሁሉ "ለውጥ፣ ለውጥ" የሚሸቱ ነበሩ።አሁን ግን "ሰዎችን ባሉበት፣ በሚያስቡበት
በሚኖሩበት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ መረዳት" ነው የሚፈልገው። በቃለ -መጠይቃችን ወቅት
"ለሰው ልጅ ከፖለቲካ የሚልቁ እውነቶች እንዳሉት፤ሰው ፖለቲካዊ እንስሳ ከመሆን የሚሻሉ
መሻቶች እንዳሉት" መረዳት የጀመርኩበት ወቅት ነውብሎኛል።

እንደ ዳኛቸው አባባል በመጽሀፎቹ ማስተላለፍ የሚፈልገው መልእክት “የጋራ ሀገር እንዳለን፣
ልዩነቶች ቢኖሩንም አብሮነታችንን ሊያስቀጥሉልንየሚችሉት ብቸኛዎቹ ነገሮች ለዘመናት በጋራ
ያፈራናቸው እሴቶች መሆናቸውን ነው። እነዚህ እሴቶች እንደ አሮጌ እቃ በአንድ ቀን አውጥተን
የምንጥላቸው አይደሉም። ሕይወታችንን ሙሉ የኖርንባቸውን እሴቶች በአንድ ጊዜ የምንተካቸው
አይደሉም።ወደፊት የሚገፉን ሃይሎች እነዚህ በዘመናት ጥረት የተገነቡት እሴቶች ናቸው። አዳዲስ
የግፊት ሃይሎችን ከስሜታችን እና ከልምዳችን ጋር ለማዋሃድ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል። የሥነ
ጽሑፍ ስራዎቼ ማዕከላዊ ማጠንጠኛ ሴማ ይኸው ነው።”

ጎሳ፣ነገድ፣ ዘር የሚባሉ ነገሮች ለእሱ ዋጋ የላቸውም። "ብዙ እሴቶች ያሉት ማኅበረሰብ ፈጥረናል።
ለዚህ ማህበረሰብ እና እሴቶቹ መጎልበት ሁሉም አስተዋጽኦ አድርጓል―የአንድ ወይም የሁለት
ጎሳዎች ብቻ ሳይሆን የሁሉም አስተዋጽኦ ድምር ውጤት ነው።ልቤ መምታቱን እንዲቀጥል
የሚያደርገው ይሄ ነው።ያለዚህ ሕይወት ለኔ ትርጉም የላትም። ይህ የያንዳንዳችን የግል ሕይወት
አካል እስኪሆን ብዙ ጊዜ ፈጅቷል፤በአንድ ቀንም የሚፈርስ አይደለም።እሴቶች በአንድ ቀን
ቢገነቡና ቢፈርሱ ምኞቴ ነበር፤እውነታው ግን ከዚህ ይለያል።ገና ኋላ ቀር እና በማደግ ላይ ያለን
ስለሆንን ለውጥ ያስፈልገናል፤ነገር ግን በ3,000 ዘመን የገነባነው ሁሉ በቀላሉ አይፈርስም።
የበለፀግነው በመንፈስ ብቻ ነው። በኪነ–ጥበብና በሥነ –ውበት ረገድ አይናችንን ገና
አልገለጥንም። በየቀኑ አዳዲስ ሀሳቦችን ከሕይወታችን ጋር እያዋሃድን፣ የሕይወታችን አካል
ልናደርጋቸው ይገባል። ሰዎች እንዲያስተውሉና እንዲማሩ ማድረግ እንችላለን ፤ ነገር ግን ስሜት
ካልሰጣቸው በስተቀር የተማሩትን ጥቅም ላይ አያውሉትም።

ስለ አብይ የሥነ ጽሑፍ ስራው አደፍርስ ደግሞ እንዲህ ይላል (የልብወለዱ ዋና ገፀባህሪም
አደፍርስ ይባላል)፦ "አደፍርስ ተራማጅ ወጣት ነው―ነገር ግን ከሕዝቡ ተለይቶ ብቻውን ነው።
ሁሉን ነገር በብርቱ አመክንዮ ለመተንተን ይሻል።የተግባር ሰው አይደለም። ከተግባር ይልቅ ልፈፋ
ያበዛል።አመክንዮ ጥሩ ቢሆንም ሁሉም ነገር በልኩ መሆን አለበት።አደፍርስ ዛሬ በመሃከላችን
እንደምናያቸው ሰዎች ያለ ነው።አብዮቱ ሰዎችን በአንድ ሌት አንቅቶ ለማደር ይቋምጣል፤ያ ግን
የሚቻል አይደለም―ቢቻል ምኞቴ ነበር።የብኄርተኝነት ስሜት7እንኳን ለማዳበር ሕዝብን ማመን
162
ጥቋቁር አናብስት

የግድ ይላል ይባላል።ይህ ምን ማለት ነው? ሕዝቡ ባንድ ሌት ተለውጦ ማደር ይችላል ለማለት
ነው?ሕዝባችን ለውጥን መቋቋም ቢችልም በዚህ ፍጥነት መለወጥ ግን አይችልም። ለአደፍርስ ግን
ከሞት ውጪ ከዚህ ቅዠት መውጫ በር የለውም―ብዙ መብሰል ይቀረዋል፤ ጥራዝ ነጠቅ ነው።
ዙሪያውን የከበበውን እውነታ ማስተዋል አልቻለም―እሱ የሚናገረው አንድ ቋንቋ፣ ሀገሪቱን
መለወጥ የሚችለው ይህ ሕዝብ ደግሞ የሚያወራው ሌላ። አብዮቱ ያልተሳካው ለዚህ
ነው―ሁላችንም እንደ አደፍርስ ዐይነቶች ነን። አደፍርስ በ1950ዎቹ ሳይፈለጉ እንደ አሸን
የፈሉትን ዐይነት ሰዎች ይወክላል።የድሮ ሰዎች እሴቶች ነበሯቸው― ለሃይማኖታቸው፣
ለመሬታቸው፣ለሃገራቸው ሞተዋል።እኛ ግን አሁንምንም እሴቶች የሉንም። እነዚህን እሴቶች ንቀን
ከተውናቸው፣ ምን ይቀረናል? የሰዎች ሕይወት አካል የሆነ ምንም ነገር አይቀርም።"

ዳኛቸው በአደፍርስ ውስጥ ባህላዊዋንና ዘመናዊዋን ኢትዮጵያ ለማሳየት ይሞክራል።“ሁለቱ


የሕይወት ዘዬዎች ዘወትር እርስ በእርስ እንደተጣረሱ ነው” ይላል።“የድሮዎቹ ሰዎች የግፊት ኃይል
ያላቸው እሴቶች ስለነበሯቸው መኖር ይሻሉ።መኖርን እንድንፈልግ የሚያደርጉን ነገሮች
ምንድናቸው?እኛ አንደኛ እንደዚህ ዐይነት እሴቶች የሉንም ወይም ከሕይወታችን ጋር
አላዋሃድናቸውም፣ ሁለተኛየሕይወታችን የግፊት ኃይል ምሁርነት ብቻ ነው።ስለዚህ አደፍርስ
ይሞታል―ምሉዕ አልነበረም፣ውስጡ የተከፋፈለ/ሃሳቡ የተበተነ እና
ከማህበረሰቡ/ከማኅበረሰባዊው እውነታ/ የተፋታ ነው። አባቶቻችን በተግባር የተጠመዱ ነበሩ።
ዋናዋ የሴት ገፀባህሪ ፂዎኔ፣ የባህላዊት ኢትዮጵያ ወኪል ናት። አደፍርስ ፂዎኔን ቢወዳትም ሮማንን
(ሁለተኛዋ ዋና የሴት ገፀባህሪ) አብልጦ ይወዳታል። ሮማን ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ከተወረረችበኋላ
(1928—1934) ብቅ ብቅ ያሉትን ሴቶች ትመስላለች።ለራሷ በገባት መንገድ "ተራማጅ" ናት።
ሴተኛ አዳሪ ብትሆንም እንኳን፣ እሷን መርጦ ውሽማው ትሆናለች። በፂዎኔ ድንግልነት እና ንጽህና
ቢሳብም በሮማን የተወከለው ሥጋዊ ዘመናዊነት ስለሚያማልለው በሁለቱ መሀል ተወጥሯል።
ሁለቱንም ባንድነት ማግኘት ካልቻለ መኖር አይችልም። ስለዚህ አደፍርስ አሳዛኝ ሰው ነው።
ሁለቱንም ፍላጎቶች በአንድ ሰው ውስጥአንድ ላይ ለማጣመርየሚፈቅድ ጊዜአልነበረም።
”በአደፍርስ ውስጥ የሚገኘው ሌላው ገጸ ባሕሪ ወልዱ፣“መጪውን ጊዜየሚናፍቅ ነጋዴ ነው።
የፊውዳል ስርአቱን እንደ ኋላ ቀር ያየዋል። አዲስ ነገር ለመቀበል እና ለመመሳሰል ፈጣን ነው።
የሰዎችን ድክመት ያውቃል፤ አደፍርስ ያለበትንም አሳዛኝ ሁኔታ የሚረዳ ቢሆንም ሃሳቦቹ በአንድ
ሌት እውን እንደማይሆኑግን አሳምሮያውቃል።ወልዱ የሁለቱንም አለሞች እውነታ አይቶ፣ ተረድቶ
ለማዋሃድ የሚያደርገው ሙከራ ይሳካለታል። ምሉዕ ሰብእና ቢኖረውም፣ለለውጥ

163
ጥቋቁር አናብስት

የሚያንደረድረው ሀይል ግን የለውም። ማርክሲስት―ሌኒኒስቶች ወልዱን ይጠሉታል።” ዳኛቸው


“ማርክሲስት ስላልሆንኩ፣ የወልዱን ስሜት እረዳዋለሁ” ባይ ነው።

ዳኛቸው ከላይ ስለጠቃቀሳቸው ችግሮች ሲያወራ፣ በብርቱ ስሜትናተመስጦ ውስጥ ሆኖ ነበር።ነገር


ግን ሃሳቦቹን (ሲደጋግማቸው እንኳን) በተቻለኝ አቅም ልክ እንደነገረኝ አድርጌ አስፍሬያቸዋለሁ።
ለእሱ እና ለጽሑፉ ማዕከላዊ ስለሆኑ ጉዳዮች የሚያነሳቸው ነጥቦች በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አውራ
ስለሆነው ልብወለድ ፍንጭ ይሰጣሉ። ዳኛቸው ወርቁ በአንድ ወቅት የኩራዝ አሳታሚ ድርጅት
የቦርድ ሰብሳቢ/ሊቀመንበር ነበረ። የበአሉ ግርማንኦሮማይተከትሎ በተነሳው“ግርግር”(በዚሁ
መጽሀፍ የደራሲው የሕይወት ታሪክ ስር በዝርዝር ተገልጿል)እሱን ጨምሮ ሙሉ ቦርዱ ተበተነ።
በመጽሐፉ ውስጥ ብዙ ለውጦችን እንዲያደርግ በአሉን ቢያማክረውም አብዛኛዎቹ አስተያየቶች
ተቀባይነት ባለማግኘታቸው፣ ፍፃሜውም አሳዛኝ እንደሆነ ዳኛቸው ይናገራል።(በአሉ ከጥቂት
ወራት በኋላ ጠፋ)ዳኛቸው ጨምሮም፣ በአሉ ግርማን ተስፋውን በመጨረሻም የሚፈራውን ነገር
ያጣ "አደፍርስ"አድርጌ እቆጥረዋለሁ ይላል።በጊዜው በአዲስ አበባ "ሁሉም የሚያውቀውን ነገር
ነው የፃፈው። ታትሞ ሲወጣ የሚያስከትለውን ጣጣ ግን አልተረዳም" ብሎ ያስረዳል።

ዳኛቸው ወርቁ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት(ሰይፉ እና አለምሸት)ቢሆንም ብቸኝነትን


ይመርጣል፤ጓደኞቹም ጥቂት ናቸው። ሰዎችን" አላምንም" ይላል። መንግስቱ ለማ ከቅርብ ጓደኞቹ
መሐል አንዱ ናቸው። የፈጠራ ስራ የብቻ ሕይወት ነው።

ማስታወሻ

፦ በቅርቡ ዳኛቸው ወርቁ ከመንግስት ስራ በ1983 ዓ.ም በጡረታ እንደተገለለ ሰማሁ።ከ1981


መጨረሻ ወይም ከ1982 መጀመሪያ ጀምሮ እስከ 1983 ድረስ በራሱ ትርፍ በሚተዳደረውእና
የመንግስት በጀት በማይመደብለት Industrial Project Service የተሰኘየመንግስት የምክር
አገልግሎት ስራ ድርጅት ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል።ድርጅቱ የሚተዳደረው በአገልግሎቶቹ ሽያጭ
ሲሆን፣ ዳኛቸውም የተሻለ ደሞዝ እና የጡረታ ዋስትና የሚያገኝበት ሁኔታ ተመቻችቶለት ነበር።
ነገር ግን ዳኛቸው በህዳር 22 ቀን፣ 1987 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:30 በየካቲት 12 ሆስፒታል በምግብ
መመረዝ ሞተ። ከሁለት ቀን በፊት የታሸገ አሳ በልቶ በዚያው ሆስፒታል ህክምና ተደርጎለት "ቀላል
የምግብ መመረዝ ስለሆነ ብዙም አያሳስብም" ተብሎ ወደቤቱ ተመልሶ ነበር። በሚቀጥለው ቀን
ብሶበት ቢመለስ አንጀቱ መሸንቆሩን ሃኪሞች ደረሱበት። በሚቀጥለው ቀን ቀዶ ጥገና

164
ጥቋቁር አናብስት

ቢደረግለትም በሶስተኛው ቀን አረፈ። ህዳር 23 ቀን ደብረሲና በሚገኘው መድኃኔዓለም


ቤተክርስቲያን ተቀበረ። 650 ገጽ ተተይቦ ያለቀ "Shout It From the Mountain Top"
የሚል ረቂቅና( በልጁ አስተያየት መሰረት “ከሁሉ የሚበልጠው” መጽሀፉ ይህ ነው)ሌላ አንድ
ሊጠናቀቅ ጥቂት የቀረው ረቂቅም ትቶልን አልፏል።

የተርጓሚው ማስታወሻ የዳኛቸው ወርቁና የአምሳሉ አክሊሉ ፈሊጣዊ አነጋገር መጽሐፍ ታትሞ
ለንባብ የቀረበ ሲሆን፤፤አጫጭር ታሪኮቹም ጭጋግና ጠል ላይ ወጥተዋል፡፡

ማስታወሻዎች

1) የአፈወርቅ ገብረእየሱስን "ጦቢያ" ራሱ ያነበበው ቆይቶ ነው።

2) በጊዜው የነበረው የዘር ጭቆና አማራዎችን የሚጠቅም ነበር። ስለዚህ የሌላ ጎሳ አባላት
የመንግስት ስራ ለማግኘት ሲሉ ስማቸውን ይቀይራሉ። በንጉሱ ዘመን የመንግሥቱ ኃይለማርያም
አባት የጦር ሰራዊቱ አባል ለመሆን ስማቸውን ቀይረዋል ፤ በክርስትና ተጠምቀዋል።

3) በጊዜው ይሄ ብዙ የሚባል ነበር። "ሰው አለ ብዬ" በ5,000 ቅጂዎች ሲታተም "እምቧ በሉ"
ደግሞ በ2,000 ቅጂዎች ታትሟል። ( "አደፍርስ" የታተመው በ1962 ስለሆነ የዳኛቸው ወርቁ
የቀኖች ትውስታ የተሳሳተ ሳይሆን አይቀርም)

4) የመጽሀፉ ርዕስ የኢትዮጵያ ቱሪስት ድርጅት "የአስራ ሶስት ወር ፀጋ" ብሎ ከሚጠቀምበት


ማስታወቂያ ጋር ይመሳሰላል።

5) ከብዙ ጊዜ በኋላ ስለ ልብወለድ አፃፃፍ ዘዴ የተወሳሰበ መመሪያ የያዘ መጽሀፍ ይጽፋል።

6) ያነበብኩት ለዶክትሬት ዲግሪዬ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ላይ የተመሰረተ የጥናት ወረቀቴን ስሰራ


ነው። መዝገበቃላት በተደጋጋሚ አገላብጬ ቃላቶቹን ብረዳቸውም እንኳን፣( አብዛኛዎቹን ቃላቶች
ለማግኘት የቻልኩት በደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት ውስጥ ብቻ ነበር) ያልተረዳኋቸው ሀሳቦች
ነበሩ። አንዳንዶቹ ቃላት እሱ የፈጠራቸው ናቸው ለምሳሌ "ፊደሳ" ማለት "ፕሮፓጋንዳ" ማለት
ነው ብሎ ያስረዳል። በጊዜው በለንደን ዩኒቨርስቲ የምስራቅ እና የአፍሪካ ጥናት ክፍል የጥናት

165
ጥቋቁር አናብስት

ተባባሪ የነበረው ግርማሥላሴ አስፋው መጽሀፉን ሲያነበው ምንም አልገባውም ነበር። የማይታወቁ
ቃላትን ትርጉም ስሰጠው ግን የከበዱኝን ምንባቦች ከማህበራዊ እና ባህላዊ አንደምታቸው አንፃር
አብራራልኝ። ሌሎቹን ለጥናት ወረቀቴን የመረጥኳቸውን መጽሀፍት ለመረዳት ችዬ ነበር።
አደፍርስ ግን፣ እኔና ግርማሥላሴ አስፋው መተባበር ባንችል ኖሮ፣ሚስጥር ሆኖብኝ በቀረ ነበር።
ሌሎች ኢትዮጵያውያንም መጽሀፉን ለመረዳት ችግር እንደገጠማቸው ነግረውኛል።

7) "አብዮታዊ"፣ ማርክሲስት ወይም ሶሻሊስት የሚለው ለአውዱ የሚገጥም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

8) ከላይ እንደተገለፀው ወልዱ ከዳኛቸው አባት የተኮረጀ ገጸባህሪ ነው።

166
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ኃይለሥላሴ
እምሩ ኃይለሥላሴ የለውጥ

አቀንቃኝ ፖለቲከኛና ደራሲ

እ.ኤ.አ በ1987 አጋማሽ የተባበሩት መንግስታት በአማካሪነት ወክዬ አዲስ


አበባ በሚገኘው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በሆነው የቀድሞ
የራስ እምሩ ቤት ቢሮ ተሰጥቶኝ ሄድኩ።ቦታውን አብጠርጥሬ ለማወቅ
ቻልኩ።አንዳንድ የራስ እምሩ1የበፊት ተቀጣሪ የነበሩ ሰዎች
እስካሁንም(እስከተጻፈበት ወቅት) አሉ።እምሩ አዲስ አበባ ሲሆኑ
ለማረፍያነት የሚመርጡት ቤት ሲሆን ልጆቹም ቤታችን ሲሉ
የሚያስታውሱት ይህንን ቦታ ነው።እንደእውነቱ ከሆነ ቤቱ የሚስታቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ብዙ
አማራጮች ቢኖሯቸውም በደሳሳ ጎጆዎች በተከበበው አነስተኛ ቤት መቆየቱን መርጠዋል ሰፈሩ
ወደ ጉለሌ መውጫ አባኮራን አካባቢ ነው።ግቢው ፈረስ ባያስጋልብም ስፋቱ በቂ ነው ማለት
ይቻላል ።ቤቶቹ ምቹ አይደሉም፡፡ግቢው አጥር የለውም፤የጎረቤት ልጆች እንደፈለጉ
እንዲጫወቱበት ተብሎ የተሰራና ልጆቹም “እንደፈለጉ የቦረቁበት ግቢ ነው”ይላል ልጃቸው
ሚካኤል።በመጨረሻም ንጉሱ (የእናቱ የመጀመርያ የአክስት ልጅ)ቤቱን ጎብኝተው አጥሩን
እንዲያሳጥሩ ስለመከሯቸው አሳጥረውታል ።ይህ እምሩ ምን ያህል ቀላል ሰው የመሆናቸው ማሳያ
ምሳሌ ይመስለኛል።እራሳቸውን ከሌሎች የማይለዩ ለክብርና ለልታይ ባይነት“ያልተጋለጡ”ሰው
ነበሩ።

እምሩ በኢትዮጵያውያን ታሪክ ውስጥ ታዋቂ ሰው ናቸው።

ከምንሊክ ጊዜ ጀምሮ በልጅ እያሱና ዘውዲቱ ብሎም ከኃይለሥላሴ እስከ አብዮቱ ጊዜያት
በሕይወት የቆዩ ሲሆን፤በቆዩ ቁጥር ደግሞ ይህንን እውቅና የማንበር ጥሩ እድል አጋጥሟቸዋል።

እምሩ ከዚህ በተጨማሪም ሶስት ልብወለዶችን አሳትመዋል።

እዚህች መድብል ላይ ግለታሪካቸው የተጠቃለለበትም መንስኤ ይሄው ነው ።ብቸኛ ወንድ


ልጃቸው ልጅ ሚካኤል እምሩ ታሪካቸውን ሊነግረኝ የተስማማው አባቱ ከነገሩት ትውስታና
በሁለት ጥራዝ ከተዘጋጀው የግል ታሪካቸው በመነሳት ነበር።2ስለእሳቸው በተወሰነ መልኩ መጻፍ
መቻሌ አስደስቶኛል።ምንም እንኳ የሳቸው ጠቀሜታ በፖለቲካው በዲፕሎማሲና በውትድርናው

167
ጥቋቁር አናብስት

ቢሆንም ከስነ ጽሑፋቸው በላይ እዚህ የፃፍኩት በእርሳቸው ዙርያ በሌሎች ቦታዎች ከሚነገሩ
የተወሰኑ ታሪኮች ጥቂቱን “ያስተካክላሉ” ብዬ አምናለሁ።3

ሌሎች የፃፉትን ግን የማሳቀል ስራ አልሰራሁም።ቀጥሎ የማቀርበው ታሪክ የእምሩ ኃይለሥላሴ


ታሪክ ልጃቸው ሚካኤል እምሩ እንደነገረኝ ነው።4ከሌሎች ምንጮች ያገኘሁትን አካትቻለሁ።5
ሚካኤል እምሩ አባቱ ተሳታፊ የነበሩበትን የኢትዮጵያ የታሪክ ወቅት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አለው።
ይህንንም በግሉ ለማመዛዘን የሚያበቃ የፖለቲካ ስራዎች በዚህ ወቅት ሰርቷል።6

ስለ ራስ እምሩ የሰበሰብኩት ግብአት ከመብዛቱ የተነሳ የተወሰኑ ክፍሎችን ጨምቄ ለማቅረብ


ተገድጃለሁ።

***

እምሩ ኃይለሥላሴ በጉርሱም ሃረርጌ በህዳር 15 1885 ዓ.ም ተወለዱ።ይሄም ከቀዳማዊ


ኃይለሥላሴ ልደት ሃምሌ 16 1884 ዓ.ም አራት ወራት በኋላ ነው።የእምሩ እናት
መዝለቅያ7እምሩ የጥቂት ወራት ጨቅላ ሳሉ ነበር የሞቱባቸው እሳቸውም በሕይወት የተረፉ ብቸኛ
ልጃቸው ነበሩ።አባታቸው ኃይለሥላሴ አባይነህ 8ዳግም ያገቡት ከብዙ አመታት ቆይታ በኋላ
ነበር።ስለዚህም ነው የእምሩ ታናሽ እህት የሆነችው የአባታቸው ልጅ በ20 ዓመት ከእርሳቸው
የምታንሰው።

እምሩ ለተወሰኑ አመታት በጉርሱም ቆዩ።አራት ዓመት ከሞላቸው በኋላ ብዙ ሳይቆይ ከሌሎች
የመኳንንት ልጆች ጋር አብረው ትምህርታቸውን እንዲቀስሙ ወደ ኃይለሥላሴ አባት ወደ ራስ
መኮንን ተላኩ።እዚያ የነበሩት የመኳንንት ልጆች ኃይለ ሥላሴን(ተፈሪን) ጨምሮ (እናታቸው
በወሊድ ጦስ የሁለት ዓመት ልጅ ሳሉ አርፈዋል)፡፡10በአብዛኛው እናቶቻቸው የሞቱባቸው ነበሩ።
በመኮንን ቤት ያሉ ህፃናት ለቤተክህነት ትምህርት የ5 ሰአት መንገድ ያህል ጉዞ ወደ ምታስኬደው
ጃርሶ ተልከው ዳዊትንና ሌሎች ሃይማኖታዊ መፃሕፍትን ይደግማሉ፤ያጠናሉ።አለቃ ወልደ ኪዳንና
አባ ወልደስላሴ ነበሩ በአብዛኛው በግዕዝ የሚያስተምሯቸው።

ወደየቤተሰዋቸው መለስ ቀለስ ሳያበዙ በጠባቂዎችና በአሳዳጊ ሞግዚቶች ተንከብክበው ነበር


ያደጉት።11 ከክፍል ትምህርታቸው ውጭ ከባለሟሎቻቸው ጋር የመኳንንቱን ጨዋታ ሁሉ
ይጫወታሉ።እምሩ በፈረስ ግልቢያ በአደንና በውሃ ዋና ጥሩ ሆኑ።መለስ ያሉትንም ሰላማዊ
ጨዋታዎችም እንደ ጊጤ፣ገበጣ፣ሰንጠረዥ ባሉትም ተካኑ።
168
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ዘመናዊ ትምህርታቸውን ከአንድ ኢጣልያዊ ዶክተር ዘንድ፤ፈረንሳይኛን ከአንድ ከማርትኒክ


ከመጣ ሰው ጋር በአምስት ወይም በስድስት ዓመት እድሜያቸው ማጥናት ጀመሩ።በ1903 ራስ
መኮንን ለኤድዋርድ 7ኛ በዓለ ሲመት ወደ እንግሊዝ ምንሊክን ወክለው ለመገኘት ባቀኑበት ዘመን
ነበር እምሩ በስርአት የተዋቀረ በካቶሊክ መምህራን የሚሰጥ ትምህርት መማር የጀመሩት።
ምንአልባት ያደረጓቸው ጉዞዎች (ራስ መኮንንን) በዘመናዊ ትምህርት ላይ ፍላጎት እንዲያሳድሩ
ሳያደርጋቸው አይቀርም ።ለዚህ ደግሞ ከሚስዮናውያኑ ውጪ እርዳታ ማግኘት አይታሰብም፡፡

የውጭ ሚስዮናውያን መኮንን እራሳቸው ትምህርትን እንዲወዱ በካቶሊክነት እንዲታሙ (እውነት


ባይሆንም) መንስኤ ሆነዋል ቢባልም መኮንን ሚስዮናውያኑ ወደ ሃረር ከመዝለቃቸው በፊትም
በትምህርት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው ።12

ሁነኛ የካቶሊክ መምህራቸው ደግሞ አባ ሳሙኤል ነበሩ።13ተፈሪና እምሩ ከሌሎች ጋር አብረው


ነው ትምህርትን የጀመሩት።ከነበሩት መሃልም እንደ ይልማ መኮንን14፤አሰገደች ብሩና15 ተፈራ
በለው 16ይገኙባቸዋል።

እምሩ ራስ መኮንን ሲያርፉ የ13 ዓመት ታዳጊ ሲሆኑ ልጆቹ ወደ አዲስ አበባ ምንሊክ
ቤተመንግስት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ተጠሩ።እዚህ ነበር በዙፋን ጉዳዮች እየሰለጠኑ ከነበሩት
ከሚኒሊክ የልጅልጅ እያሱ ጋር የተገናኙት።17

የዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እ.ኤ.አ በ190818 ሲከፈት እዚያ ገቡ፡፡ በአንድ ዓመት
ቆይታቸውም ከሌሎች ልጆች ቀድመው ከሃረር ቀለም ቆጥረው ስለመጡ ልዩ ክፍል 'ከሀረርጌ
ለመጡት' ልጆች ተከፍቶ ስለነበር በስርአተ ትምህርቱ ያሉትን አራት ትምህርቶችን ፈረንሳይኛ፤

እንግሊዘኛ ፤ስፖርትና ፤ግብረገብ መከታተል ጀመሩ።

በሚያዝያ 1901 አ.ም ተፈሪ የደራሳ(ግማሽ ሲዳሞ) ገዥ ሆነው ተሾሙ።19እምሩ አብረዋቸው


ነበር የሄዱት፡፡ለራሳቸው የሚያስተዳድሩት ንኡስ ግዛትም ተሰጣቸው።ይህ የተፈሪ የመጀመሪያው
ኃላፊነት ሲሆን በወቅቱ 17 አመታቸው ነበር።ከሁለት ዓመት በኋላ በ1903 አ.ም ተፈሪ የሃረርጌ
ገዢ ሆኑ።20እዚያም እስከ 1908 አ.ም ልጅ እያሱ እስከሚወርዱበት ጊዜ ድረስ ቆይተዋል።እምሩ
ከተፈሪ ጋር ሀረርም አብረው ሄደዋል።

169
ጥቋቁር አናብስት

ሲዳሞ እያሉ እምሩ የግራዝማችነት ሹመት ተሰጣቸው።

ቆይቶ በሃረርጌ ቀኛዝማች ተብለው የጃርሶ ገዥ ሆኑ። በጀግንነቱ ከታወቀው "የባሩድ


ቤት"በሚባለው በማእከላዊ መንግስት የጦር ሚኒስትር ፊትአውራሪ ሃብተጊዮርጊስ የሚመራው
ክፍል አመራር በመሆን የመጀመሪያ የመድፍ ስልጠናቸውን ወስደዋል።

በሰኔ 1903 ከሲዳሞ ወደ ሀረር እንደተመለሱ ተፈሪ የልጅ እያሱ የእህት ልጅ የሆኑትን21 ወ/ሮ
መነንን አገቡ እያሱ በአምቻ አመኻኝተው ሊዛመዱ ይፈልጉ ነበር።ራስ ተሰማ የእያሱ ሞግዚት
የነበሩ ሲሆን በሚያዝያ 1903 ስላረፉ እያሱ ሌላ ሞግዚት አልቀበልም አሉ።ራስ አባቴ አዲሱ
ሞግዚት ለመሆን በቤተመንግስት ስልጣንን ለመውሰድ በሃይል ፈልገው የነበሩ እንደውም የተወሰኑ
ሃይሎችን ይዘው ከቤተመንግስቱ ገብተው የነበሩ ቢሆንም በፊትአውራሪ ሃብተጊዮርጊስ እና በራስ
ሚካኤል (የኢያሱ አባት) እርዳታ የእያሱ ስልጣን ከእጃቸዉ እንዳትወጣ አደረጉ።22እያሱን
በግንቦት 1901 አልጋወራሼ ነው ብለው ሚኒሊክ አዋጅ ስለስነገሩላቸው ምኒልክም በቂጥኝ
በሽታ ተይዘው ከአልጋ ከዋሉ23 ስለሰነበቱ እያሱና ሞግዚታቸው ከምንሊክ የየጎርጎሮሳውያም
አቆጣጠር የታህሳስ 13 1913 ሞት24 በፊትም ቢሆን ሃገሪቱን ማስተዳደር ችለዋል።በዚህ
አስቸጋሪ ወቅት እያሱ የተፈሪንና የእህታቸውን ልጅ መነንን ጋብቻ አዘጋጅተው ሰለነበር እምሩ
መነንን ከአዲሳባ ወደ ሃረር የማምጣት ስራ ተሰጣቸው።በቤተመንግስቱ ከተከተሏቸው የሰራዊቱ
አባላት ጋር በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ በመግባት ተጠርጥረው ቢቆዩም በመጨረሻ ተሳክቶላቸው
መነንን ከአዲስአበባ አስወጥተው ተፈሪን ወዳገቡበት ሃረርጌ ይዘዋቸው ሄዱ።

ከጥቂት አመታት በኋላም 21ኛ አመታቸውን ሲይዙ በአባታቸውና በሚስታቸው አባት በተመከረ
ትዳር እምሩ ራሳቸው አገቡ።ሚስታቸው ጽጌ ማርያም ሲሰኙ የልጅ ገብረ ሩፋኤልና የወይዘሮ
ላቀች(የራስ መንገሻ አቲከም የዳሞት ቡሬው)25 ልጅ ናቸው።እምሩና ጽጌ ማርያም ያላቸው አንድ
ወንድ ልጅ አምስተኛው ልጃቸው ሚካኤል ሲሆን የተቀሩት በሙሉ ሴቶች ናቸው።ይህ መጽሐፍ
በተጻፈበት ወቅት እ.ኤ.አ በ1988 ሁሉም በሕይወት ነበሩ።እናታቸውም በ90 አመታቸው
በህይወት ነበሩ፡፡(ራስ እምሩ በ1980 ቢሞቱም)26

የእያሱ ዘመን በተቃርኖዎች የተሞላ ነበር።ችኩልና የሚያደርጉት ነገር የማይታወቅ ሲሆኑ ግን


ደግሞ በተቃራኒው ሃገር ወዳድ ናቸው።ለእንደዚህ አይነት ሃላፊነት እድሜያቸው ገና ለጋ ነበር።
ምንአልባትም በሕይወት የተረፉና ታናሹ የንጉስ ሚካኤል ልጅ ናቸው።27በእያሱ አገዛዝ
ያለመደሰት ጉርምርምታዎች በሸዌ መኳንንት መሃል ተነሳ።እ.ኤ.አ በሰኔ 28 1916 ይህን በአዲስ

170
ጥቋቁር አናብስት

አበባ የተፈጠረ አለመረጋጋት ንቀው ወደ ሃረር ወረዱ።ከስልጣን የተወገዱት ግን በመስከረም 17


1916 ነው።28ይህም የሆነው አቡነ ማቴዎስ ከመኳንንቱ ላይ ግዝታቸውን ከፈቱ (እንደ አንዳንዶች
አባባል ያለፍቃዳቸው)በኋላ ነበረ።እምሩ በዚህ የሃይል ጥልፍልፍ ውስጥ እንዴት እንደተሳተፉ
በቆይታ እምናየው ይሆናል።ለማንኛውም እያሱ ከሃረር አምልጠው ወደ ደንከል በረሃ ሸሹ።
ቀጥለውም ከአመታት በኋላ በቁጥጥር ስር ወደ ዋሉበት ትግራይ አቀኑ።29

እያሱ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ የምንሊክ ልጅ የሆኑት ዘውዲቱ በየካቲት 1 1917 ተፈሪ መኮንንን
በአልጋ ወራሽነት30 አስከትላ ነገሱ።ተፈሪ የግልበጣውን ሴራ ቀደም ብለው ሳያውቁ አይቀሩም ነገር
ግን ከጅማሮው አልነበረም ቀንደኛ ተሳታፊም ሳይሆኑ እንደ አጃቢ ነበሩ።

አዲሲቱ ንግስት ዘውዲቱ31 ሃይላቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጡ በአንጻሩ ደግሞ የተፈሪ እየፈረጠመ
መጣ።ከእያሱ መወገድ በኋላ ለተፈሪ ፍላጎታቸውን ያሳዩ የተፈሪ ታማኝ ተከታዮች እምሩን ጨምሮ
እያበቡ መጡ።

ተፈሪ ከሃረር በእያሱ ትእዛዝ ከመነሳታቸው በፊት ሃረር የሚገኘውን የተፈሪ ቤተሰብ በእምሩ
ጥበቃ ስር ነበሩ፡፡32

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የተፈሪን ሚስትና ሁለት ልጆች ይዘው(አንዷ ትልቋ ልእልት ተናኜ ወርቅ
ስትሆን ሁለተኛው ልኡል አልጋ ወራሽ ትልቁ ወንድ ልጃቸው በወቅቱ 40 ቀን ሞልቶት ክርስትና
እንደተነሳ ነበር)33ወደ አዲስ አበባ ተፈሪን እንዲያገኙ ይዘዋቸው መጡ።ልክ አዲስአበባ ደርሰው
ከተፈሪ ጋር ሲገናኙ ነበር እምሩ ልጅ እያሱን ከስልጣን ስለማስወገድ እና ስለአዲስ መንግስት
የማቋቋም ሴራ ሊሰሙ የበቁት።እያሱ የሆነ ተንኮል እየተጠነሰሰ እንደሆነ ስለጠረጠሩ ይመስላል
ተፈሪን ወደ ከፋ ለመላክ የተፋጠኑት።

የእያሱ ከስልጣን ከመውረዳቸው ጥቂት ግዜ ቀደም ብሎ እምሩ ወደ ሃረር ተመልሰው ለመፈንቅለ


መንግስቱ "ታማኞች" ስለሚመጣው ለውጥ እንዲነግሩ ታዘዙ።

34
እያሱም እምሩ ወደ ሃረር በፍጥነት በመመለሳቸው ስለገነገኑ ከተፈሪ በወሰዱት ቤተመንግስት35
ውሥጥ በሰንሰለት አስገብተው በእስር አቆራኟቸው።36 እምሩ ቤተመንግስቱን አብጠርጥረው
ሲለሚያውቁ37ሲመሽ በጨለማ አመለጡ።ሰንሰለታቸውም የተፈታው ከሀረር ግንብ ወጥተው
ነው።38

171
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ነፃ ሆነው የግልበጣው ታማኝ ወታደሮችን ሲያገኙ ሁሉም የሀረር በሮች ተዘግተው
እንዲጠበቁ አዘዙ።መልሰው ወደ ሀረር ለመግባት ሲችሉ በእያሱ የታሰሩ ሰዎችን ከእስር
አስፈትተው አስታጠቁ።በእነርሱም እርዳታ ሁኔታውን ለማረጋጋት ቻሉ።ከዚያም በአብዛኛው
(የሱማሌ ወታደሮች) የነበሩበትን የልጅ እያሱ ታጣቂ ተከታዮቻቸውን የማደን ስራ ተጀመረ ።39

እምሩ በሃረርጌ የራስ መኮንን ደጋፊዎች የነበሩትን ሰዎች ስም በዝርዝር ይዘው ነበር።ለምሳሌ
ፊትአውራሪ ባንቲ፤ደጃዝማች ገብሬና ደጃዝማች ወልደስላሴ የነበሩባቸው ሲሆን ቆይቶም ወደ
ሃረር ከእያሱ ጋር አብረው የመጡት ደጃዝማች ባልቻም አዲስ አበባ ካሉት ከአዲሱ መንግስት
(ከመፈንቅለ መንግስት ሴረኞቹ ጋር) ተቀላቀሉ፡፡ከመነሾው እምሩ ከአዲስ አበባ ትእዛዝ
ስላልመጣላቸው የመንግስት ግልበጣው ጊዜ ያልተነገራቸው ሲሆን የራሳቸው ፈጠራ ተጠቅመው
ለመንቀሳቀስ የተገደዱ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ህግና ስርአትን ለማስፈን ችለዋል።

እምሩ አሁን ለሀረር ሰው ስለመንግስት ለውጡ ሊነግሩ ፈለጉ።ስለዚህም ከሀረርጌ ዳኞች


የተወሰኑትን ሰብስበው በሚቀጥለው ቀን ወደ የገበያ ቦታዎች በታትነው በመላክ አዲሱን
የመንግስት አዋጅ ስለመንግስት መለወጥና እነሱም ስልጣን ስለመያዛቸው አዋጅ አስነገሩ።በዚህ
ወቅት ባልቻ ከሃኪም ጋራ ወደ ሃረር ተመልሰው ሰለነበር አዋጁ ሲለፈፍ በገበያው ቦታ በአካል
ተገኝተዋል።40

እምሩ በቦታው በመገኘታቸውም እያሱ ከቦታው ከማምለጣቸው በፊት እንዳስገደሏቸው


የሚወራውን አሉባልታ ለማክሰም ችለዋል።እንደእውነቱም ከሆነ እያሱ ከተከታዮቻቸው ጋር
ሲያመልጡ ማንንም አልገደሉም ነበር።

***

ለእምሩ ከተፈሪና ከአዲሱ መንግስትጎን መሰለፍ ግን ያን ያህል ቀላልና ቀጥተኛ ውሳኔ


ነበርን?በወቅቱ ወጣትና በፖለቲካው ብዙም ተፈላጊነት የሌላቸው ሰው ነበሩ ።የተፈሪን ቤተሰብ
ከሃረር እስካመጡበት ጊዜ ድረስም በውሳኔዎች ላይ ያልተሳተፉ ሲሆን እየሆነ ስላለውም ነገር
የማወቅ ምንም እድል አልተሰጣቸውም።በሚኒልክ ቤተመንግስት ከእያሱና ከኃይለ ሥላሴ ጋር
አብረው ያደጉ ቢሆንም ከኃይለሥላሴ ጋር የነበራቸው እውቅያ ዘለግ ያለና ከልጅነታቸው የጀመረ
ነበር።እያሱ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነገሮች ከቁጥጥር እየወጡ ሲመጡ ተመልክተዋል። እያሱ
ሀገሪቱን እያካለሉ ሳለ በመናገሻው ግን ሃይላቸው እየተመናመነ መጣ።ብዙዎች ጊዜያቸውን
በአዲስአበባ እንዲያሳልፉ ለመንግስቱ ስራም ቀረብ እንዲሉ መክረዋቸው የነበር ቢሆንም
ከልጅነትም ልምድም ከማጣት ሊያዳምጡ አልፈልጉም።

172
ጥቋቁር አናብስት

ከውድቀታቸው በፊት እምሩ ከእያሱ ጋር ተገናኝተው የመምከር እድሉ አጋጥሟቸዋል። ይህም


በመሃላቸው የነበረውን ቅርርብ ያሳያል።የሆነው እንዲህ ነው።የድሬዳዋ ጉምሩክ ስራአስኪያጅ
ነጋድራስ ሃቢብ ይድሊቢ የሚባሉ ስመጥር የአስተዳደር ባለሙያ ነበሩ።ሶርያዊው ሹም በእያሱ
ዘንድ ተወዳጅ ሲሆኑ(ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የጎማ ልዩ መብት ተሰጥቷቸዋል)።በጉሙሩክ
ውስጥ የንቅዘት ችግር ያለባቸውን ሰራተኞች አስወገዱ።እነሱ ግን በወቅቱ የሃረርጌ አስተዳዳሪ
ለነበሩት ለተፈሪ ይግባኝ በማለታቸው ነገሩ አስቸጋሪ የሆነባቸው ተፈሪ በወቅቱ ወሎ አባታቸውን
ሊጎበኙ ሄደው ወደነበሩት እያሱ ዘንድ ጉዳዩን ለመመካከር እምሩን መላክ ግድ ሆኖባቸው ነበር።
ይህ የሆነው እያሱ ከስልጣን ከመውረዳቸው 9 ወራት በፊት በ1915 መጨረሻ ወይም በ1916
መጀመሪያ አካባቢ ነው።ደሴ ውስጥ ለአንድ ወር ያህል አብረው ሰነበቱ።በዚህ ጊዜ ውስጥ እምሩ
እያሱን በመንግሥት ስራ ላይ በቅርበት እንዲሳተፉ መከረዋቸው የነበር ቢሆንም እያሱ ግን
አካሄዳቸውን ለመለወጥ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ።ነገሮች ከእሳቸው በተፃራሪ መንገድ ምን ያህል
እየሄዱ እንደሆኑም አልተረዱም።እምሩ ለኢያሱ ያላቸው ድጋፍ በዚህ ወቅት እየተሟጠጠ ቢሆንም
ክህደትን ግን እንደአማራጭ አልወሰዱም።

በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት እያሱ ራስ (ዋግሹምም)አባተን ለማግኘት ቻሉ።እሳቸው የቧያለው ልጅ


ሲሆኑ የትውልድ ቦታቸው ዶባ መንዝ(የራስ መኮንን ቤተሰብ መገኛ አካባቢ ነው) በምንሊክ ጊዜ
የታወቁ ጦረኛና በተለይ በሁለት የጀብዱ ሙያቸው የታወቁ ነበሩ።በአድዋዉ ጦርነትም ላይ
ተሳትፈዋል።በእያሱ ጊዜ ደግሞ እያሱ አባተ ደጃች አብርሃን ተክተው በትግራይ እንዲያስተዳድሩ
ስለፈለጉ ደጃች አብርሃ ደግሞ ይህን ስለተቃወሙ ደጃዝማች አብርሃን በትግራይ ወግተው አሸነፉ።
አባተ በእያሱ ባህሪይና አመራር ስላልተደሰቱ እራሳቸውን በሃይል የኢያሱ እንደራሴ ለማድረግ
ፈልገው ነበር።ሃብተግዮርጊስ ለእያሱ ወግነው ከአባተ በተቃራኒ ቆሙ።አባተ ለባለጋራቸው(የእያሱ
ወገን) ተሸንፈው ምንም እንደማይደረጉ የተገባላቸውን ቃል ይዘው የጦር ሃሳባቸውንም ወደ ጎን
በመተው ወደ መናገሻው ንጉስ ሚካኤልን ሊጎበኙ ቢሄዱ በቁጥጥር ስር ውለው ለቁም እስር
በንጉስ ሚካኤል ትእዛዝ ወደ ወሎ ተወሰዱ ።እምሩ አባተን በአንድ ወቅት ደሴ ከተማ 41ላይ የውሃ
መስመር ዝርጋታ ወይም ጥገና ላይ ለመስራት ከነበሩበት እስር ሲወጡ ተመልክተዋል።በሌላ ወቅት
ደግሞ በአንድ ትልቅ ግብዣ ላይ እስረኛ ሆነው ሳለ 42የክብር እንግዳው ሆነው አይተዋቸዋል።
ዘውዲቱ በቤተመንግስቱ በስልጣን ፉክክሩ ከአባተ ጎን ነበሩ(ወይም እንደነበሩ ይገመታል)።
ምናልባትም ከቤተመንግስቱና ከአዲስ አበባም ጭምር በልጅ እያሱ የተባረሩበት እና እስከ ምኒልክ
ሞት ድረስ በፋሌ መድሃኒአለም ቤተክርስትያን የቆዩበት ምክንያት ይኽው ሊሆን ይችላል።43

****

173
ጥቋቁር አናብስት

መፈንቅለ መንግስቱ ተከናውኖ እያሱ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ እምሩ በቀድሞ መንግስት አገዛዝ
ደስተኛ እንዳልነበሩ ሆነው የአዲሱ መንግስት ደጋፊ በመሆን በታማኝነት ብቅ አሉ።ሙሉ በሙሉ
በኢያሱ ተስፋ ባይቆርጡም "የቅሬታ ስሜት"ነበራቸው።እምሩ ልጅ እያሱ ለሃላፊነት ብስለት
ይጎድላቸዋል ብለው ቢያስቡም ከስልጣን ማስወገዱ ግን ሌላ አስከፊ እርምጃ ነው።እምሩ ልጅ
እያሱን ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንደሚያስታውሷቸው ስልጣን ላይ ካልቆዩባቸው ምክንያቶች
መካከል ፈር የለቀቁ ቁጥጥር በጎደለው ሁኔታ በምንሊክ ቤተመንግስትና በዳግማዊ ምንሊክ
ትምህርትቤት ለአስተማሪዎቹም አስቸጋሪና44 "የተበላሹ" ልጅ ስለነበሩ ነው።እያሱ እዩኝ እዩኝ ባይ
ከመፃህፍቱ ወደ እስፖርቱ የሚያዳሉ ለዲስፕሊን ተግዥ ያልሆኑ ሰው ናቸው።ወደ ስልጣን
ሲመጡ ራስ ተሰማ ናደውን ለሞግዚትነትና ለእንደራሴነት ተሰጥቷቸው የነበር ቢሆንም ተሰማ ግን
ደካማ በመሆናቸው እያሱን መምራት ተሳናቸው።እንደ እምሩ አስተሳሰብ በራስ ተሰማ ፈንታ
ፊትአውራሪ ሃብተግዮርጊስ ሆነው ቢሆን ኖሮ ውጤቱ ለእያሱ የተለየ ይሆን ነበር።ሃብተጊዮርጊስ
ብልህና ጠንካራ ሰው ስለነበሩ እያሱን ወደ ትክክለኛው የንግስና አቅጣጫ ይመሯቸው ነበር ሲሉ
ይገምታሉ።

በመፈንቅለ መንግስቱ ጊዜ ተፈሪ ከሃረርጌ እምሩ ደግሞ ከጅግጅጋ ገዥነት ስልጣናቸው ተነስተው
ነበር።እምሩ ከተፈሪ ጋር ወደ ከፋ መሄድ ነበረባቸው።ምንም እንኳን በህግ የታወቀ ትእዛዝ
ባይሰጥም ቅሉ…. እምሩ ግን “የተፈሪ ሰው”ተባሉ።45 እያሱ ወደ ሃረርጌ ከመመለሳቸው
ከመንግስት ግልበጣው አንድ ወይም ሁለት ወር በፊት ተፈሪ ወደ አዲስ አበባ መጡ።እያሱ
ከስልጣን ሲወርዱ ሀረር የነበሩ ሲሆን ተፈሪ ግን አዲስ አበባ ነበሩ።

የምንሊክ ልጅ የነበሩት ዘውዲቱ ሊታሰሩ ቀርበው ከነበሩበት እያሱ ሲወርዱ ወደ ንግስትነት


መጡ።እያሱና ሞግዚታቸው ራስ ተሰማ ዘውዲቱን በፋሌ መድሃኒአለም ገዳም እንድትኖር ልከዋት
ነበር።በተመሳሳይ ወቅትም ጣይቱን ለኑሮ ወደ እንጦጦ ማርያም ልከዋቸው ነበር።ጣይቱን
የማይወዱት ተሰማ እና እያሱ ዘውዲቱን ከመጨረሻ ባላቸው ራስ ጉግሳ ወሌ የለያዩበትም
መክንያት የጣይቱ የወንድም ልጅ ሰለሆኑ ነው።ተሰማ በመጀመርያ ጉግሳን አሳሰሩ።ቀጥለው
ከመናገሻው ራቅ ያለ ቦታ ገዥነት ሾሟቸው።ተመሳሳይ እጣም ለጣይቱ የእህት ልጅ ባለቤት
ለሆኑት ለደጃዝማች ታዬ ጉልላቴ ገጠማቸው ።ይሄ ሁሉ የተደረገው የጣይቱን በመናገሻው ላይ
ያላቸውን ተፅእኖ ለማኮሰስ ሲባል ነው ።ጣይቱም የሀይላቸውን መሰረት በቤተሰባዊ ግንኙነት ላይ
ገንብተውት ነበር።ከራስ አባተ ያልተሳካ ሙከራ በኋላ ብዙዎች የቀድሞው ጥበቃዎች
ከቤተመንግስቱ ተባረሩ።ይሄ ሁሉ ግን የተከሰተው ተፈሪ በቤተመንግስቱ የፖለቲካ ውስብስብ
ከመዘፈቃቸው አስቀድሞ ነው።ሰለዚህ ተፈሪን በሆነው ጉዳይ መውቀሱ አላግባብ ይሆናል ።
(ለምሳሌ የራስ ጉግሳና የዘውዲቱን መፋታት በመሰሉ) እስከናካቴውም አዲስ አበባም አልነበሩም፡፡
ፖለቲካዊ ሚናም የላቸውም ።

174
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ሀረርን ካረጋጉ ከአዲስ አበባም ሃይል ከመጣላቸው በኋላ ሃረርን ኋላ ገዥ ለሆኑት
ለደጃዝማች ገብሬ ጥለው ወደ መናገሻው ተመለሱ ።የእያሱ አባት የወሎው ንጉስ ሚካኤል
አልጋውን ለልጃቸው ለመመለስ ተንቀሳቀሱ።ራስ ልዑልሰገድም ከደጃዝማች ተሰማ ገዝሙና
ከአሳላፊ አብዬ እና ከሌሎች ጋር በመሆን ንጉስ ሚካኤልን ለመግጠም ሄዱ።ልኡል ሰገድ እና
ተሰማ ቶራ መስክ ላይ ቃፊር አንኮበር አካባቢ እ.ኤ.አ በጥቅምት 13 1916 በተደረገው ጦርነት
ተሸንፈው ተገደሉ።እምሩ በዚህ ወቅት ከሀረር ጦራቸውን ይዘው ሳይንቀሳቀሱ አልቀረም ሚካኤል
ግን ለዘመቻ ከደሴ እስኪንቀሳቀሱ ድረስ ሀረር ውስጥ ነበሩ።

ንጉስ ሚካኤል ጦሩ ገበሬውን እንዲዘርፍ በመፍቀዳቸው ከህዝቡ ተቃቃሩ።ይሄ ከዘመቻው ላይም


ጥቂት ጊዜ አባከነ።በተጨማሪም ለእያሱና ለንጉስ ሚካኤል ታማኝ በመሰሉት ብልሃታቸውም
በያዘላቸው በሃብተግዮርጊስ ተታለው የተወሰነ ጊዜ አጠፉ።ይህ ሚካኤልን በጅምር ድላቸው ላይ
ተደግፈው እንዳይቀጥሉ ሲያዘናጋቸው የሸዋን ጦር(የአዲሱን መንግስት)እንዲፋጠኑ ረዳቸው።
በጥቅምት 25 1916 በተደረገው የሰገሌ ጦርነት ሚካኤል ተሸንፈው ተማረኩ ።ከዚህ ጥቂት
ቀናት ቀደም ብሎ እምሩ ከሃረር ጦራቸውን እየመሩ በታላቅ ፍጥነት ሌሎች ወደ ጦርነቱ የሚያቀኑ
የመንግስት ወታደሮችን አካተው ደርሰው የመንግስት ጦሩን ለሚመሩት ተፈሪና ሃብተጊዮርጊስን
ተጨማሪ የማጠናከሪያ ጦር እየመጣ እንደሆነ አበሰሩ።ከዚህ ድል በኋላም እምሩ ነበሩ ንጉስ
ሚካኤልን አስረው ወደ አዲስ አበባ ያመጧቸው ።(የወሎው ንጉስ ሚካኤል ብዙም ሳይቆዩ
በ1918 አርፈዋል)

እያሱ ከአዳል ተነስተው በአንኮበር አሳብረው ወደ ወሎ ሲመጡም የአባታቸውን ሽንፈት ስለሰሙ


ወደ መቅደላ ሸሽተው በሃብተግዮርጊስ ተሳደዱ።ተራራው ተከበበ።እያሱ ግን ከዚያም አምልጠው
ለአዲሱ መንግስት የጎን ውጋት በመሆን እስከተያዙበት 1921 ድረስ ቆዩ።

እምሩ ለተፈሪና ለዘውዲቱ ስር ነበሩ፡፡በ1917 ዓ.ም በደጃዝማችነትን መአረግ ሀረርጌን እንዲገዙ


ተሾሙ።ይህም ተከታትለው ከመጡ የገዥነት ሹመቶች አንዱና የመጀመርያው ሲሆን
በተራማጅነትና በማሻሻያ ፖሊሲዎቻቸው የታወቁ ነበሩ።የእምሩ አባትም በተመሳሳይ ዓመት
አነስተኛዋን ጨርጨርን ለጥቂት አመታት ካስተዳደሩ በኋላ በደጃዝማች ማዕረግ የባሌ ገዥ ሆነው
ተሾሙ ።46

ለእምሩ ሹመት መነሻ እርሾው በአዲስ አበባ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ ነበር።ሃይላቸውን አጥተውና
የኢያሱ ጊዜ ስልጣናቸውን ተነጥቀው የነበሩ ነባር ወገኖች ቦታቸውን ለማስመለስ ንግስቲቱን
የሚደግፉ በማስመሰል እንደራሴውን ተፈሪን ለመቃወም ተጣጥረው ነበር።ይህ ደግሞ ከጦር
ምኒስትሩ ሃብተግዮርጊስ ውጭ ያሉት በ1918 እንዲባረሩ ምክንያት ሆነ።በወቅቱ የሀረርጌ ገዥ
175
ጥቋቁር አናብስት

የነበሩት ደጃዝማች ገብሬ የንግድ ሚኒስትር በሆኑት የደጃዝማች ይገዙ ወንድም ነጋድራስ አሰበ
እየታገዙ በዚሁ ጥልፍልፍ ውስጥ ገቡ።47ገብሬ በዚሁ የተነሳ ተባረው በግዛታቸው ውስጥ በቁም
እስር ስር ዋሉ።ተመሳሳይ እጣ ለሌሎች ሚንስትሮች ገጥሟቸዋል።ሌሎቹም ታሰሩ።ሰለዚህ የሀረርጌ
የአስተዳደሪነት ቦታ ክፍት ሆነ።እምሩም ሀረርን ከአባታቸው የባሌ ሹመት ጋር በተመሳሳይ ወቅት
ተሾሙ።

እምሩ የሀረርጌ ገዥ ሆነው ከ1918 እስከ 1929 ድረስ ለ 11 አመታት ቆዩ።በፊት በሀረርጌ
በውትድርና ሃላፊነቶች ነበር የቆዩት።ከዚያ ቀደም ብሎም የጃርሶና የጅግጅጋ ገዥ ነበሩ።ተወልደው
ስላደጉበትም አካባቢውን በደንብ ያውቁታል።የተፈሪን ተራማጅ ፖሊሲዎችን ይደግፋሉ። እንደ
ገዥነታቸውም ሀረርጌ ላይ ለውጥን ለማምጣት ጥረዋል።ህግ ላይ አትኩሮታቸውን ስላሳረፉ
በአካባቢያቸው “የፍትህ ሰው”በመባል ይታወቁ ነበር።አንዳንዴ ጥብቅና ጨከን ያሉ ውሳኔ
ያሳልፋሉ።የግብር አጣጣል ስሪቱን ለገበሬው በሚመች መልኩ ለመለወጥ ቢሞክሩም እራሱ
ገበሬው የለመደውን ላለመልቀቅ ሲል ተቃወመው።ቀስ በቀስ ግን በዝባዥ ከነበረው
ስሪትአላቀቁት።

ከዚህ ጊዜ በፊት ታላላቆቹ ደሚኖችና ገራዳዎች የፈለጉትን ያህል ክፍያ በገንዘብም በጉልበትም
መልክ ሲቀበሉ፡ ማንም ኃይ ባይ አልነበረባቸውም። ይሄ ደግሞ ለገባር ትከሻ ሌላ ሸክም
ይደርባል።በዚህ ላይ የፈለገውን የሚቀለብ እና የሚወስድ ወታደር ይታዘዝላቸዋል።ይሄ ደግሞ
ሁኔታውን ያባብሳል።በተጨማሪም ለመንግስት የሚከፈለው ትንሽ ቢሆንም አመታዊ የአንድ ብር
ክፍያ ነበር።እምሩ ይህንን ሁሉ ቁርጥ አመታዊ የገንዘብ ክፍያ ለማስቀየር በማሰብ ወደ 300
የሚጠጉ አርሶ አደሮችን በተወካይነት በመውሰድ ሰበሰቡ።ስለ አዲሱ የግብር ስሪት ማሻሻያ
እቅዳቸው ባዋዩዋቸው ወቅትም ከዚህ በፊት ለበለጠ ግብር ተታለው ይሁን ወይም ከአንዳንድ
ጉልተኞች ማስፈራሪያና ጉቦ ወስደው ይሁን ባልታወቀ ሁኔታ ነገሩን በተጣመመ መልክ ነበር
የተረዱት።48በውጤቱም የእምሩ ሃሳብ በውስን ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ሆኖ እሳቸውም
ሀሳቡን ለጥቂት ጊዜ ለመተው ተገደዱ።ቆይቶ ግን በተፈሪ ይሁንታ ገበሬዎቹን ሳያማክሩ
በጨርጨር እና በሌሎችም የሀረርጌ ክፍሎች ስሪቱን ስራ ላይ አዋሉት።

በአዲሱ ስሪት ሁሉም ግብር በመንግስት ሰብሳቢዎች ተሰብስቦ በዓመት ቁርጥ ለመንግስት ገቢ
የሚሆን ሲሆን በፊት ለሚቆርጡት ለወታደር ወይም ለጉልተኛ አይሰጥም።49 የዚህ ስሪት አንዱ
መዘዝ ለወታደር የሚሰጥ ቋሚ ደመወዝ ሲሆን እምሩ ከጀመሩት በኋላ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል
ሊሰራበት ቻለ።ይህ በመንግስትም ወይም በክልሉ ገዥዎች (የራሳቸው ጦር ስላላቸው) የሚተገበር
ነበር።ከግብር ስሪቱ ጋር አብሮ የጉልበት ስራም ተከለከለ።ተክለሐዋርያትም ሆነ ዶ/ር ወርቅነህ
ማርቲን በእምሩ ስር ሆነው ነው የጨርጨር ገዥ የሆኑት።አዲሱን ስሪትም ለአርሶአደሩ
176
ጥቋቁር አናብስት

ለማብራራት ይተጋሉ።ከዚህ የመጀመሪያ ሙከራ በኋላ ጨርጨር ለሌሎች የሀረርጌ ክፍሎች


እንደማሳያ ሞዴል ተደርጋ ልትወሰድ ችላለች።50

ከተፈሪ ፖሊሲዎች ትይዩ ሆነው እምሩ በአስተዳደራቸው ማዕከላዊነትን ለመጨመር በሃረርጌም


ሆነ ቀጥለው ባስተዳደሯቸው ክፍለሃገራት ሰርተዋል፡፡ይህ የታችኛው መደብ ከላይኛው ክፍል ጋር
ያለው መስተጋብር ያሻሽላል ብለው ያምናሉ።እምሩ ዘመናዊ ትምህርትንም ይደግፋሉ።ይህም
የፈረንሳይ ካፑችን ሚስዮናውያን ከሸዋ በተባረሩበት ዓመት በ1880 ሀረር ላይ የጀመሩት ነበር።
ለዚህም ሁነኛ ረዳታቸው የነበሩት አባ እንድርያስ ነበሩ፡፡እምሩ ትምህርት ቤቶችን በመስራት
ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ የማስገደድ ልማድ የነበራቸው ሲሆን ይህንንም
በገዥነታቸው ጊዜ ሁሉ በወሎና በጎጃም ጨምሮ ከጦርነቱ በኋላም በበጌምድር ገፍተውበታል።

በእምሩ የሀረርጌ ገዥነት ጊዜ ነበር እያሱ በመጀመርያ እ.ኤ.አ 1921 የተያዙት።ለራስ ካሳም
ተላልፈው ተሰጡ።እሳቸውም ልጃቸው ደጃዝማች አበራ ፍቼ ሰላሌ ውስጥ እንዲያስቀምጧቸው
አደረጉ።ከፍቼ እስር በ1932 አምልጠው በድጋሚ ሽመሎ ገቦ ጎጃም ላይ አባይን ተሻግረው
51
በፊትአውራሪ ገሠሠ በተያዙበት ወቅትና በሀረርጌ ጋራ ሙለታ52ለመታሰርያ ወደ ተዘጋጀላቸው
ቦታ ተወሰዱ፡፡እምሩ ግን ከዚህ ጊዜ ቀደም ብሎ ከሀረርጌ ወደ ወሎ እ.ኤ.አ በ1929 ሄደው ነበር።
በዛን ወቅትም ደጃዝማች ገብረማሪያም ነበሩ እምሩን ተከትለው የሀረርጌ ገዥ የሆኑት።

የእምሩ የመጀመሪያ አራት ሴት ልጆች ሀረርጌ ገዥ ሳሉ ነበር የተወለዱት ።የበኩሯ የጅግጅጋ ገዥ


ሳሉ ክርስትና ያስነሷት በገዥነት ጊዜያቸው ባሳነፁዋት የጃርሶ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያን ነበር።
ምንም እንኳ ስራ የሚበዛባቸው ቢሆንም እምሩ የቤተሰብ ሕይወትን የሚወዱና ለልጆቻቸው
ቅርብ ለመሆን የሚሞክሩ አባት ነበሩ።ይህ ግን በተለያዩ የስራ ውጥረቶች በየወቅቱ እንደልብ
ለማሟላት የሚቻል አልነበረም።ሀረርን ለቀው የወሎን አስተዳደር ከመሾማቸው ከህዳር 1929
በፊት አዲስ አበባ ሳሉ ብቸኛውን ወንድ ልጃቸውን ሚካኤልን አገኙ ።53

***

እምሩ በመስከረም ወይም ጥቅምት እ.ኤ.አ 1929 ወደ ወሎ ሄዱ፡፡ ተፈሪ በሚስታቸውና


በእናታቸው መነሾ ክፍለሃገሩ ላይ የተለየ ፍላጎት ያሳድራሉ፡፡በተለይ በሚስታቸው በእቴጌ
መነን(የንጉስ ሚካኤል ልጅ ከሆኑት ስህን የሚወለዱት) እናም አባታቸው ወለዬ በሆኑት እናታቸው
መክንያት አጼ ኃይለስላሴ ተብለው ተቀብተው ግዛታቸውን ቢያጠናከሩም “የቤተሰብ መሬት”
ብለው በሚጠሯቸው ሀረርና ወሎ ላይ የተለየ ምናልባትም አጨቃጫቂ54 የሆነ ትኩረትን በወሎ
177
ጥቋቁር አናብስት

እና በሃረር ላይ ያሳድሩ ነበር፡፡ዘመዳቸውን ደጃዝማች ስዩምን ከእምሩ በፊት ወሎ ላይ ሹመው


የነበሩ ቢሆንም በችሎታ ማነስ ምክንያት አንስተዋቸዋል፡፡55ወሎ ውስጥ ድርቅና የአንበጣ ወረርሽኝ
በኤ.አ 1928 ተከስቶ ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ በወሎም ሆነ በመላው ሃገሪቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች
ነበሩ፡፡ ተፈሪ እ.ኤ.አ በ1928 ተቀብተው ነገሱ፡፡ ከዚያ ቀደም ብዙ ሃያላን ሰዎች ተፈሪ የወሎን
ግዛት እንዲያስተዳደሩ (ሌሎች ደግሞ ወደ ጎንደር በንጉስነት መአረግ እንዲሄዱ) እግረ
መንገዳቸውንም በታሪክ ተቀዳሚ የሌለውን የተፈሪ እና የዘውዲቱን በአንድ ላይ በአዲስ አበባ
መሆንን የማከላከል የኦፊሴል ሽፋን በተሰጠውስራ56 አሳበው ተፈሪን ከስልጣን ምህዋሩ በማራቅ
እንዳይነግሱ የማከላከል ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ብዙዎች እያሱን በቂ ቅጣት ተቀጥተው ትምህርት
ተምረዋል ብለው ወደ አልጋ እንዲመለሱ ይፈልጉ ነበር፡፡

ከድርቁ በኋላ በወሎ ውስጥ አለመረጋጋት ነበር፡፡ ደጃዝማች ስዩምና ራስ ጉግሳ አርአያ(የዮሐንስ
አራተኛ የልጅ ልጅ)አመጹን እንዲያበርዱ በተለይ የራያና አዘቦ የኦሮሞ ነዋሪዎች በአዳል አካባቢ
የሚያደርጉትን ወረራ እንዲያስቆሙ ሲሆን በውድባን እየቀጡ እምቢኝ ያለ እንደሆን እንዲወጉ
ቢታዘዙም አልተሳካላቸውም፡፡57እምሩ ወሎ ሲደርሱ ግን የወሎ ጦር መሪ በሆኑት በፊትአውራሪ
(በኋላም ደጃዝማች)ፍቅረ ማርያም እየታገዙ ህግን ማስፈን ቻሉ፡፡58 ወሎ ውስጥ ወሳኞቹ
ጦርነቶች የተደረጉት እ.ኤ.አ በመጋቢትና በሚያዝያ 1930 ሲሆን እምሩ ራሳቸው ጦሩሜዳ መሃል
ገብተው አልተዋጉም፡፡ነገር ግን የዘውዲቱ የቀድሞ ባለቤት የነበሩትን የራስ ጉግሳ ወሌን ጦር
ለመመከት እንዲረዳ ጦር በማደራጀትና (ሶስት?)ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ለዚሁ ስራ የተላኩ
አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጦሩን ያሰለሉ ነበር፡፡ጦርነቱን የመሩት የወቅቱ አዲስ የጦር ሚንስትር
ራስ ሙሉጌታ ነበሩ፡፡እምሩ እዚያም በተደረገው ጦርነት ላይ አልተሳተፉም፡፡ጉግሳ በጦርነቱ
ተገደሉ፡፡ ዘውዲቱም ብዙም ሳይቆዩ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2 1930 አረፉ፡፡ ተፈሪም አጼ ኃይለሥላሴ
ተብለው ነገሱ፡፡

ከጦርነቱ መስክ ካሉ ችግሮች ውጪ ባህሉን ተከታይ በሆኑት ቡድኖች በተለይ በሰሜነኞቹ


ዘመናዊነትን ያለመቀበል ችግርም በወሎ ውስጥ ነበር፡፡እምሩ ከነሱ ጋር የነበረውን ሁኔታ
እንዲያስተካሉ ተልከው ሃይልን በመጠቀም ሁኔታውን አረጋግተውታል፡፡ትምህርት ቤቶችን
በመስራት እና መስተዳድሩን መልሶ በማዋቅር ፤በተለምዶ ከሚታወቁት ቤተሰቦች ውጪ የሆኑ
የራሳቸውን ባለሙያዎች በመመደብ የተጋረጠባቸውን ተቃውሞ አሸንፈው የማዘመኑን ሂደት
ተያያዙት፡፡መንገዶችና ድልድዮችንም በተጨማሪ አሰርተዋል፡፡ወሎን ከማእከላዊው መንግስት ጋር
የማቀናጀቱንም ስራ አስጀመሩ፡፡ ጉግሳ ወሌ ራሳቸው ተፈሪ እምሩን ወደ ወሎ ለአስተዳዳር
መላካቸውን ሲሰሙ “አሁን ገና ተፈሪ አመረረ” ብለዋል ይባላል፡፡ወሎ ከኋለኛው ጊዜ ይልቅ

178
ጥቋቁር አናብስት

በእምሩ የአስተዳዳሪነት ዘመን ማእከላዊ ወሎን (ሰባት ቤት ወሎንና) ወደ አዳል የሚያመራውን


መተላለፍያ ያጠቃለለች በስፋትም አነስተኛ ነበረች፡፡ 59

እምሩ ወሎ ላይ ያመጡትን ማሻሻያ ለማስጀመር ከምንም መነሳት ነበረባቸው፡፡ ሀይለኛ ወታደራዊ


መሪ ቢሆኑም ለሚያስተዳድሯቸው ህዝቦች ሃላፊነት ይሰማቸዋል፡፡ አፋሮች በድርቅና በዝርፍያ
ሳብያ ተከታታይ ጉዳት ሲደርስባቸው እምሩ ከሌሎች ዘመቻዎች በምርኮ ያገኙትን ከብቶች
በመስጠት ተክተውላቸዋል፡፡በዚህ ምክንያት ነው እምሩ በአፋሮች ዘንድ እስከ አሁን ድረስ
ተወዳጅ የሆኑት፡፡

እንደ ልጃቸው ሚካኤል አመለካከትም ምንአልባት በራስ መኮንን ቤት ያደጉበት ከአክራሪነት ይልቅ
በክርስትያናዊ ወግ የታሸው ባህል ሊሆን ይችላል ለዚህና ለተቀሩት የሕይወት እንዲሁም የፖለቲካ
አመለካከቶቻቸው አስተዋጽኦ ያደረገው፡፡ እምሩ ከመኮንን ችሎት የወረሱት እድሜ ልካቸውን ልክ
የሆነውን ካልሆነው ለይተው የሚመሩበት የፍትህ መርሆ ነበራቸው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም
እምሩ ከልጃቸውም ከተፈሪም በላይ የመኮንን ጸባይ ወርሰዋል፤ምሳሌያቸውንም ተከትለዋል ይላሉ፡
፡ (መኮንን ፍትሐዊ የሆኑ ገዢ ሲሆኑ ለምሳሌ ለሀረር ኦሮሞዎች ጥቅም የሰሩ ሀቀኛ አስተዳዳሪ
ነበሩ) በፍትሕም ረገድ በንጉስ ሚካኤል ተደንግጎ የነበረውን የሽፍታ ቤተሰቦችን ለሽፍታው ጥፋት
የመቅጣት ህግ አስወግደው በድርጊቱ ተባባሪ ከሆኑ ብቻ እንደሚቀጡ ደነገጉ፡፡

***

ለተወሰነ ወቅት እምሩ በጉረሮ ቁስለትና በሆድ ህመም ታመው ተሰቃዩ። የወሎ ገዥነታቸው ልክ
እንዳበቃ እ.ኤ.አ በ1932 ወደ አውሮጳ ለህክምና የመጀመሪያውን የውጭ ጉዞዋቸው አደረጉ።
60
ቀዶ ጥገና ወደ ተደረገላቸው ወደ ፓሪስ አቀኑ ቀጥሎ ወደ ጄኔቭ ተጉዘው ኢትዮጵያ በቅርብ ወደ
ተቀላቀለችው (የተባበሩት መንግስታት)የሊግ ኦፍ ኔሽንስን ቢሮዎች ጎብኝተው የኢትዮጵያ ተወካይ
ዘለቀን አግኝተው ጥሩ ጊዜን በአውሮጳ አሳለፉ፡፡እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት የባቡር
መስመር ስለሆነና ከጅቡቲ የሚነሳው ባቡር በድሬዳዋ ስለሚያልፍ ሐረር ሳሉ የተዋወቋቸውን
ሰዎች አገኙ። እምሩ ስለአውሮፓ ለማወቅ ፍላጎት አድሮባቸው ለመጎብኘት ይፈልጉ ነበርና ጉብኝቱ
ያሳደረባቸው ስሜት በጣም አዎንታዊና አስደሳች ሆነላቸው፡

***

የእምሩ ቀጣይ ሹመት ጎጃም ሲሆን የተሾሙት እ.ኤ.አ በህዳር 1932 ነበር።ራስ ሃይሉ
ተክለሃይማኖት የሚያስተዳድሩት ግዛት የነበረ ቢሆንም እሳቸው ግን ከግንቦት 1932 ጀምሮ
179
ጥቋቁር አናብስት

በማጭበርበርና ልጅ እያሱን እንዲያመልጡ በመርዳት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።ከህዳር


እስከ ግንቦት ድረስ ጎጃም በከንቲባ ማተቤ ጊዜያዊ አስተዳዳሪነት ስር ነበረች ።ከንቲባ ማተቤ
በጎጃም 61ብዙ ተግዳሮት አጋጥሟቸዋል።ከደጃዝማች የፃዲቅ ጀምሮ ያስተዳደርነው የአባቶቻችን
ርስት ነው ብለው ያስቡ ስለነበር የንጉስ ተክለሃይማኖት ተወላጅ ባላባቶች አካባቢውን የመግዛት
ፍላጎት ነበራቸው ።62ንጉስ ተክለሃይማኖት ግዛታቸውን ለማስፋፋት ቢፈልጉም በምንሊክ
ውጤታማ መከላከል ስለተደረገ አልቻሉም63።ሃገሬው የጎጃም ሰውም የሃገራቸው ሰው
ከመሃላቸው እንዲሾምለት ይፈልጋል ።ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ማተቤ ላይ ከባድ ችግርን ፈጠረ።
በተለይ የራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖት ልጅ ፊትአውራሪ አድማሱ እና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት እንደ
የንግስት (የተክለሃይማኖት ልጅ)64 ልጆች ያሉት አወኳቸው።እንደ አስተዳዳሪ ራስ ሃይሉ በህግና
ስርአት ጉዳይ ላይ ቸለልተኛ ነበሩ።

ሌሎች አስተዳዳሪዎች እንደሚያደርጉትም በሹመታቸው ወቅት ብዙ ሃብት ያከማቹ ሲሆን ይህን


ልማድ ያስቀሩ እምሩ ናቸው።65ራስ ሃይሉ ከሹመታቸው ሲነሱ ልጆቻቸው እንደ ህጋዊ ውርሳቸው
ቆጥረው ንብረታቸው ይገባናል ብለው አምባጓሮ ፈጥረዋል።

ይሄ ሁሉ ችግር ተንከባሎ ያረፈው እምሩ ጫንቃ ላይ ነበር።ሚስታቸው በከፊል ከጎጃም የአቲከም


ቤተሰብ ሆነው ከቡሬ ዳሞት66 አካባቢ ቢገኙም እምሩ ግን እንደባይተዋር ነበር የሚታዩት።በርካታ
ችግሮችንም አሳልፈዋል።

አንጋፋዎቹ ቤተሰቦች የሳቸውን መሾም እንደ ስድብ ነበር የቆጠሩት።እምሩ በተደጋጋሚ “ጎጃም
ጉልበቴን ጨረሰው” ሲሉ ይሰሙ ነበር።ከታወቁ ችግር ፈጣሪ መኳንንት መሃል ማሞ
ሃይለሚካኤል (ቆይቶ ወደ ኢጣልያ የገባውና ከጦርነቱ በኋላ በስቅላት የተቀጣው)እና አድማሱ
መስፍን ይገኙበታል።ከዚህ ውጭ በርካታ ትናንሽ አመፆች ነበሩ።

እምሩ በሃምሌ 1932 ወደጎጃም ሲመጡ እንደሌሎች በቀደሙት የግዛቶቻቸው ወቅቶች


እንዳደረጉት ሁሉ ማሻሻያና ዘመናዊነት ለማምጣት ቆርጠው ነው።ትምህርትን የአስተዳደርና የህግ
ጅማሮዎች ላይ የተደረጉትን አዳዲስ ሃሳቦች ከሚቃወሙት ውጭ ከሽፍትነትና ከህግ የለሽነት ጋር
መታገል ነበረባቸው።ራስ ሃይሉ የውጭ ነጋዴዎች ወደ ደብረማርቆስ እንዳይገቡ የከለከሉ ሲሆን
በየቦታው የግብር መቅረጫ ቦታዎችን አቋቁመዋል።እምሩ ለውጭ ነጋዴዎች ቦታውን ክፍት
በማድረግ መቅረጫ ቦታዎችን በማንሳት ጎጃምን ለዚህ ንግድ ምቹ አደረጓት ።ራስ ሃይሉ አውሮጳ
ላይ በ1924 የገዙትንና ያልተጠቀሙበትን የሃይል ማመንጫ ጄኔሬተር ለመጠቀም ደብረማርቆስ
ላይ የመጀመሪያው ሰው ነበሩ።የመጀመሪያውን ሬድዮም ጎጃም ላይ አምጥተዋል።ኃይለሥላሴ

180
ጥቋቁር አናብስት

ከቀደምት ቤተሰቦች እንዲቀጥሯቸው ከሚነግሯቸው ውጭ በራሳቸው ምርጫ ነበር ሹመኞችን


የሚቀጥሩት67። እምሩ በርካታ ወጣት ተራማጅ መምህራን ወደአስገነቧቸው ትምህርት ቤቶች
አስመጡ ።ከነሱም መሃል አንዱ ሀዲስ አለማየሁ ነበሩ ።ሌሎች ደግሞ ገብረመስቀል ክፍልእግዚ
68
ገብረመስቀል ሀብተማርያም፤ ወልደጊዮርጊስ ተድላ፣ዮሐንስ አብዱ69 ነበሩ፡፡ ደብረ ማርቆስ
ባለው ትምህርት ቤት ግጥም ንባብ ቴአትር ዘፈን ዳንስ የመሳሰሉ ህዝባዊ ትእይንቶች ይካሄዱ
ነበር። በአንዳንዶች ሀገራዊ ስሜት ባላቸው ምሽቶች ላይ የጣልያን ቆንስላ ይመጣል (መምጣትም
ነበረበት) እንደ ፋሽስት ደግሞ ለእምሩ ሌላ ችግር ነበር።ቆንስላው በጎጃም ያለው የአስተዳደር
ሁኔታ ላይ ቅሬታ ያላቸው ወገኖችን በጉቦ በመደለልና በማበረታታት ካህናትን ሳይቀር ይገፋፋ
ነበር።ከህግ ከለላ ለማግኘት ስለሚሹ በርካታ ጀውሶችና ወስላቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ይከለላሉ።
ካህናቱ ደግሞ አቅም ስለሌላቸው ወይም ስለሚስማሙ በዚህ ጉዳይ ምንም ማድረግ
አልተቻላቸውም።ይህ እምሩን ከካህናቱ ጋር እንዲጋጩ በር ከፋች ሆነ።70

እምሩ የጎጃም ገዥነት ስልጣን ሲሰጣቸው በራስነት ማዕረግ ነበር።ንጉሱን ሳያማክሩም


(ከሁለተኛው ዓመት ጀምሮ እንደተፈቀደላቸው) የሞት ቅጣትንም ማስፈፀም ከሚችሉ ውስን ሃያል
ባለስልጣናት መሃል አንዱ ነበሩ።ይሄንን መብታቸውንም ጎጃምን ለማረጋጋት ተጠቅመውበታል።
የሽፍታ አለቆቹን እየያዙ ወደ መናገሻ ለፍርድ ይልኩ ነበር።አስቸጋሪ ሊሆኑ ቢችሉም ለፍትህ
ባላቸው ቀናኢነት ይወደዳሉ።71 ራስ ሃይሉ ለመቆጣጠር ችላያሉትን ዝርፍያንና ሌሎች የወንጀል
አይነቶችን በከባድ እርምጃዎች ተቆጣጥረው ሰላምን አሰፈኑ።72የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎችን መልሶ
ለማከፋፈል ያደረጉት ጥረት ባይሳካም እንደ የቤተክርስቲያን የልዩ ጥቅም መብት ፤ግብር
መሰብሰብ፤ የራሳቸውን ፍርድ ቤት ማቋቋምና በአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ መግባት የመሳሰሉትን
ማገድ ችለዋል ።የጎጃም ስራቸው መገባደጃ ጊዜ ሲደርስ ያሰለጠኗቸውን ሰራተኞች ይዘው ከመሄድ
ይልቅ እዚያው ትተዋቸው መውጣትን መርጠዋል።73

***

ራስ እምሩ ጎጃምን የለቀቁት በሌላ ቦታ ስራ ለመስራት አይደለም። እ.ኤ.አ በ1935 ጣልያን


ኢትዮጵያን ወረረች።እምሩም ከዋነኞቹ የአርበኞች ተዋጊዎች መሃል ለመሆን የታጩ ሲሆን ይህም
በ1936 ተይዘው በግዞት ጣልያን እስከተላኩበት ጊዜ ነው።ጦራቸውን በመስከረም አስከትተው
በጥቅምት 1935 ወደ ግንባር ተንቀሳቀሱ።ምንአልባት ለማስተዳደር አስቸጋሪ የሆነውን በባህላዊ
ልምድ የተኮደኮደውን ክፍለሃገር ከዚህ በፊት ከሰሩባቸው ክፍለሃገራት የማይጣጣም ስለነበር
በመልቀቃቸው ሳይደሰቱ አልቀሩም።

181
ጥቋቁር አናብስት

ከጣልያን ጋር በነበረው ጦርነት ራስ ስዩም መንገሻ የሰሜኑን ግንባር ሲይዙ ከ1930 ጀምሮ የበጌ
ምድር ገዥ የነበሩት ራስ ካሳ ሃይሉ እና ራስ ሙልጌታ የጦር ሚኒስትሩ ወድያውኑ ተቀላቀሏቸው ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኃይለሥላሴ ራስ ካሳን የሰሜን እዙ ጠቅላይ አዛዥ አደረጓቸው።ይሄ ውሳኔ
አንዳንዴ የጦር ሚኒስትሩን ለምን ጠቅላይ አዛዥ አላደረጓቸውም? በሚል ይተቻል።

የእምሩ ምድብ ከራስ ስዩም እና ከሌሎቹ ጋር መገናኘት ሳይሆን በስተሰሜን ምእራብ በማቅናት እና
በመመሸግ ጣልያኖች መቀሌን ያጠቁበታል ተብሎ በሚገመተው በሰቲት ኦም ሀጃር ወይም ራስ ካሳ
ያሉበትን አካባቢ ካልሆነም እስከ ተከዜ እና የራሳቸውን የእምሩን አካባቢ መሽገው መጠበቅ ነበር።
እምሩ በስራቸው ወደ 40000 የሚገመት ጦር የነበራቸው ሲሆን 20000 ከጎጃም ከ3000 እስከ
4000 የራሳቸው ሰው ሲሆን በመከዳት ስሜት ውስጥ እየዋለሉ ቢሆንም ግን ጣልያንን ለመውጋት
የላይላዩንም ቢሆን 74በመጡት የንግስት ጣይቱ የቅርብ ዘመድ በደጃዝማች አያሌው ብሩ
የሚመራው የጎንደር ጦር ጠቅላይ አዛዥም እሳቸው ነበሩ።አያሌው ቢዋጉም ያን ያህልም በፍላጎት
አልነበረም ሲሉ አንዳንዶች ይገልጻሉ፡፡ጣልያኖች እንደተጠበቁት በሰቲቱ (በእምሩ) ግንባር በኩል
አላጠቁም።እምሩም እራሳቸውን በምሽግ አጥረው የጣልያንን ይዞታዎች ማጥቃት ችለዋል።

የእምሩ ጦር ከተዋጋባቸው ዋነኛ ቦታዎች አንዱ ጣልያኖቹ በመሸጉበትና በተከዜ ቁልቁለቶች


የሚገኘው ደብረ ቁና አንዱ ነው።ከታዋቂ አርበኞችና(ከአያሌው ሰዎች መሃል የሆነው) ከጎንደሬ
አዛዦች መሃል አንዱ ፊታውራሪ ሽፈራው በደብረ ቁና ያሉትን ጣልያኖች ለማስለቀቅ እንዲያጠቁ
እምሩም ሆነ አያሌው ባልተካፈሉበት ጦርነት በእምሩ ታዘው ድል ቀንቷቸው በርካታ ታንክ
ከጣልያን ወገን የማረኩ ቢሆንም ፊታውራሪ ሽፈራው ግን ሕይወታቸውን ከፈሉ።ጣልያኖች ከዚህ
በኋላ ነው በኢትዮጵያውያን ጦር ላይ የመርዝ ጋዝ መርጨት የጀመሩት።አንድ ግሪካዊ ዶክተር
ከእምሩ ጦር ጋር በሙሉ ዘመቻው ውስጥ ተሳትፎ የነበረው ጦሩን በሙስታርድ ጋዙ ዙርያ
ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለመምከር ሞክሯል።ነገር ግን ጋዙ ተስፋ የማስቆረጥ ሃይል ነበረው።ያም ሆኖ
ግን ጣልያኖች ወደ አክሱም አፈገፈጉ ።እምሩም ጣልያኖች መልሰው ለማስለቀቅ በከበዳቸው
እንደስላሴ ጥሩ ቦታ ለማግኘት ቻሉ።

ተከዜ ላይ እምሩ የመጀመሪያው የመከዳት እጣ ደረሳቸው።የንጉስ ተክለሃይማኖት የልጅ ልጅ


የሆኑት ደጃዝማች ገሠሠ በለው በራስ እምሩ ስር ከነበሩት የጎጃም ጦር አዛዦች መሃል አንዱ ነው።
በተከዜ ወንዝ አካባቢ ከዳባት አቅራቢያ ሊማሊሞ ላይ በተደረገው ጦርነት ጣልያኖች
የመጀመሪያውን ቦምባቸውን በእምሩ ጦር ላይ ጣሉ።75እምሩ ከቦንቡ ለምማለጥ ሲሉ በለሊት
ከሚከተሏቸው 20000 ጦር ጋር ተዳፋቱን ለመውረድ በሚንደረደሩበት ወቅት በገሠሠ ስር ያለው
የጎጃም ጦር ተከትሎ ለመዋጋት አልፈለገም ነበርና ወደ ጎጃም ተመለሰ።ቆራጡ ታማኙና ሀገር
ወዳዱ ብቻ ተለይቶ እምሩን ተከተለ።ይሄ ምናልባትም ለወደፊቱ በቆይታ ሳይረዳቸው አልቀረም።
182
ጥቋቁር አናብስት

አንዳንዶቹ ገሠሠን ለማሳደድ ቢፈልጉም እምሩ ግን በኢትዮጵያውያን መሃል ውስጣዊ ግጭትን


ባለመፈለጋቸው ከለከሉ።ገሰሰ ደብረማርቆስ ሲደርስ ለከተማ ጥበቃ የቀሩ የእምሩ ጦረኞች
አባረሩት።ነገር ግን አምልጦ ከራስ መስፍን ልጆች ጋር ጦርነት ገጥሞ አሸንፎ ገደላቸው ።(የአጎቱ
ልጆች ሲሆኑ እነሱም እንደሱ የንጉሥ ተክለሃይማኖት የልጅ ልጆች ናቸው።ንግስት
የተክለሃይማኖት ልጅ የራስ መስፍን ባለቤት ነበሩ) እነኚህ የአገው ምድር ገዥዎች ነበሩ።እሱም
የእነሱን አካባቢ ተቆጣጥሮ መግዛት ጀመረ።ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስ በእሱና ሊከተሉት በሚፈልጉ ላይ
ግዝት አውርደው ነበር፡፡ገሠሠ እንደ ህገወጥ የቆቅ ኑሮ መኖር ነበረበት፡፡

እምሩ የራሳቸውን ግንባር በሽሬ አደረጉ።ነገር ግን ካሳ በሰሜን የጠቅላይ ጦሩ አዛዥ ሲሆኑ


በእርሳቸው ስር ለመሆን ተገደዱ።በሁለቱ መሃል ግንኙነት ለማድረግ ከባድ ነበር።ከአንዱ ወደ
ሌላው የሚላክ መልእክት ቀናት ሊወስድ ይችላል።ሰለዚህ እምሩ ብዙውን ጊዜ የራሳቸውን ውሳኔ
ማሳለፍ ነበረባቸው።ሰለዚህ በሰሜን የነበረው ውግያ ያልተቀናጀና ውጤታማ ያልሆነ ነበር።ለዚህ
አንደኛው መክንያት የኃይለሥላሴ ግልፅ ትእዛዝ ያለመስጠት ነው።ሙሉጌታንም እንዲያጠቁ ላያዙ
ይችላሉ። የዚህ ምንጭ "የቃል ብቻ "ቢሆንም ከዚህ ማመንታት ጀርባ ያለው የንጉሱ ምክንያት
1888 የአድዋ ጦርነት እንደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ወደ ግንባር እራሳቸው በመሄድ የጀግንነት አክሊል
ለመድፋት በማሰብ ይሆን ወይንም ለውሳኔ ተቸግረው? ትክክለኛው መልስ ለማግኘት አዳጋች
ወይንም የማይቻል ነው ።

ሽሬ ካሉበት ሆነው እምሩ የሽምቅ ተዋጊዎች እስከ ኤርትራ ድረስ ይልካሉ።ጣልያኖች የእምሩ ጦር
እንደ መንገድ ሰራተኛ ያለውን ያልታጠቀውን ዜጋ ሁሉ እያጠቃ እንደሆነ በመናገር ቅሬታ አሰሙ።
እንዳስላሴ ላይ ያሉት እምሩ አብዲ አዲ ላይ ካሉት ካሳና ስዩም አምባ አራዶም ላይ ካሉት
ሙልጌታ ጋር ተርራቀዋል።ጣልያኖች ካሳን በማስለቀቅ ከሙሉጌታ ጋር እንዳይገናኝ ለመቁረጥ
አሰቡ።ከተለያዩ ጦርነቶች በኋላ አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያውያኖች ሲያሸንፉ 76ሌላ ጊዜ ጣልያኖቹ
ድል ሲቀናቸው ቆይቶ ካሳ ቦታቸውን ለቀው ወደ ደቡብ አፈገፈጉ።ሙሉጌታ በተለያዩ ጥቃቶች
ተሸንፈው ሲሸሹ ሳለ በኢትዮጵያውያን የራያና አዘቦ የጎሳ ሰዎች ተገደሉ።

***

እንደሚገመተው ከሆነ ካሳና ሙሉጌታ የተሸነፉት እርዳታ ስላልደረሰላቸው ነበር።እምሩ


እንደሚናገሩት ከሆነ ከካሳ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ካደረጉ ረዥም ጊዜ ሆኗቸዋል።እምሩ ሰላዮችን
ወደ አክሱም በማስረግ ከተማዋን ለማጥቃት አሰቡ።ሽምቅ ተዋጊዎቻቸው77 በተለያዩ ወቅቶች
የጦር መጋዘኖች ላይ ጥቃት አደረሱ።በኋላ እምሩ ከካሳ የእርዳታ ጥያቄ ደረሳቸው።መልእክቱ
እስኪመጣ ግን ረዥም ጊዜ ወሰዶ ስለነበር መልእክቱ ሲደርስ ካሳ ተሸንፈው እያፈገፈጉ ነበር።
183
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ይህንን አላወቁም።እምሩ ከእንዳስላሴ ጠንካራ ይዞታቸው ለመልቀቅ አመነቱ።ነገር ግን ካሳ


ከእምሩ እርዳታ ካልደረሰላቸው የተንቤኑን ግንባር እንደሚያጡት መልእክት በመስደዳቸው እምሩ
ጦርነቱ ምን ያህል ለኢትዮጵያውያን እንደከፋባቸው ተረዱ።አያሌው ብሩን ጨምሮ ከሌሎች የጦር
አለቆቻቸው ጋር ከመከሩ በኋላ እያመነቱ ወደ ተንቤን ለመንቀሳቀስ ቆርጠው እንደስላሴን
በጥድፍያ ለቀቁ።ነገር ግን ካሳም ሆነ ሙሉጌታ በጦርነቱ ስለተሸነፉ እምሩ ብቻቸውን ከጣልያኖች
ጋር መፋጠጥ ግድ ሆነባቸው። ታላቁ ወሳኝ ጦርነት ልክ በአድዋ 40ኛ ዓመት እ.ኤ.አ መጋቢት 2
1936 ሰለክላካ ላይ ተደረገ።ጦርነቱ ቀኑን ሙሉ ዋለ።በውግያው መሃልም እምሩ በፀሃፊያቸው
ቢተው አያሌው ተመስጥሮ የነበረና የተፈታ መልእክት ከኃይለሥላሴ ተልኮ ደረሳቸው። መልእክቱ
ጣልያኖች እምሩን ለመክበብ ጥረት እያደረጉ እንደሆኑ የሚናገር ሲሆን ትክክለኛ ግን አልነበረም።
ጣልያኖች ጎንደርን ለመውሰድ በሰሜን በኩል ግንባር ከፍተው ነበር። ኃይለሥላሴ ግን በስህተት
ይህ እምሩን በመክበብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጦር ለመቁረጥ የተደረገ ሙከራ ነው ብለው ነበር
ያሰቡት።78ኃይለ ሥላሴ በዚህ ደብዳቤ እምሩ በተከዜ ዙርያ መሽገው ወደ በጌምድር እንዲያፈገፍጉ
አዘዟቸው ።መጋቢት 2 አመሻሹ ላይ እምሩ የጦር ምክር መክረው ስልታዊ ማፈግፈግ ለማድረግ
ተስማሙ። በወሳኝ ቦታዎችም መትረየስ በማስጠመድ የማፈግፈጉ ሂደት ሰላማዊ መሆኑን
ለማረጋገጥ ሞከሩ በእርግጥ ሰላማዊም ነበር። እምሩ በኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ አፈገፈጉ።በዚህ ትእዛዝ
ምክንያት ባይሆን ኖሮ ወደ ተንቤን በሄዱና 79ከተንቤን ደግሞ ወደ ማይጨው በመቀጠል ንጉሱን
ማግኘት በቻሉ ነበር። በዚህ ፈንታ ግን ከጎጃም እና ከጎንደር (እነዚህኞቹ በአያሌው ብሩ ስር
ነበሩ)ከመጡት ዘማቾች ጋር ወደ ጎንደር ተመለሱ።በዚህም መክንያት እምሩ በመጨረሻው ንጉሱ
መርተውት በተሸነፉበት ወሳኙ የማይጨው ጦርነት ሳይሳተፉ ቀሩ።ወደ ማይጨው እንዲመጡም
አልታዘዙም።በዚህ ጊዜ ግን በምንም ረገድ ከበጌምድር ወደ ማይጨው መሻገር አይቻልም።

ከሰለክላካ ጦርነት በኋላ እምሩ ማንኛውንም ግንኙነት ከኃይለሥላሴ ጋር ሃገሪቱን ለቀው በስደት
እስኪሄዱ ድረስ ማድረግ አልቻሉም።

በበጌምድር አያሌው ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሌላ ግንባር ሳይፈጥሩ ጦርነቱን ለመተው አስበው


ነበር።80ብዙዎች በመርዝ ጋዙ እና በሌሎችም ጉዳዮች ተሰላችተውና ተስፋ ቆርጠው
ወደየቤታቸው እየተበተኑ ነበር።81

እምሩ በመቀጠል ወደ ደብረማርቆስ ጎጃም በመሄድ ሁለተኛ ግንባር ለመፍጠር አሰቡ።እምሩ


በግንባሩ ላይ ምንም ሬድዮ አልነበራቸውም ።በደብረ ማርቆስ የነበራቸው ሬድዮ ገብረመስቀል
ሃብተማርያም በተባለ ከትግራይ በመጣ ሰው ነበር የሚሰራው እናም እሱ ነው ኃይለሥላሴ ጅቡቲ
እንዳሉ የነገራቸው።82እምሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለንጉሱ መሰደድ የሰሙት በዚህ ወቅት

184
ጥቋቁር አናብስት

ደብረማርቆስ ሳሉ ነው። ወደ ሸዋ ለመሄድ ወሰኑ።መኳንንቱን ሰብስበውም እሳቸው በሌሉበት ማን


ተክቷቸው ጎጃምን እንደሚያስተዳድር ምክር አድርገው እምሩ እሳቸው ደጃዝማችነትን
የሾሙዋቸው ደጃዝማች ነጋሽ በዛብህ ተመረጡ።83የጎጃም አመራሮች ከእምሩ ጋር በመሆን እስከ
አባይ ድረስ ሲሄዱ እሳቸውም አባይን ግንደበረት ላይ አቋረጡ።በወንዙ የሸዋ መዳረሻ ሲደርሱ
እምሩ ለተከተሏቸው ጥቂት በሺህ የሚቆጠሩ የግል ወታደሮች ኃይለስላሴ ሀገሩን መልቀቃቸውን
ነገሯቸው ።ጣልያኖቹ እምሩ እዚያው በጌምድር እያሉ ነው የጎንደር ከተማን የያዙት ።ጎጃምንም
እንደለቀቁ ወድያውኑ ደብረማርቆስን ያዙ።

***

ኃይለሥላሴ ሀገር ከመልቀቃቸው በፊት በራስ ካሳ የተጠራ ሸንጎ ንጉሱ ምን አይነት አካሄድ
መምረጥ እንዳለባቸው ለመምከር ተሰበሰበ። አንዳንዶች መናገሻው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ
ከሌላ ቦታ ሆኖ ጦርነቱን ለመቀጠል ሃሳብ ሲያቀርቡ ጎሬ የአዲሱ የመንግስት መቀመጫ እንድትሆን
ሃሳብ ቀረበ።የሀገር ውስጥ ሚንስትርና የሴኔት ፕሬዝዳንት የነበሩት ቢትወደድ ወልደፃድቅ
84
ለመዋጋት ቢያረጁም መኮንን እንዳልካቸው ኢሉባቡርን ለቀው ወደ ግንባር ሲሄዱ እሳቸውን
ተክተው ጎሬ መናገሻዋ የሆነችው የኢሉባቡር ገዥ ስለሆኑ ኢሉባቡር ደግሞ የወልደፃድቅ ግዛት
እንደመሆኗ አዲሱ መንግስትንም እንዲመሩ የታጩት እሳቸው ነበሩ።ኃይለ ሥላሴ እንደእምሩ ያሉ
አርበኞችን ተቀላቅለው በመሪነት እንዲዋጉና እንዲያዋጉ የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት አጥቶ ወደ
ውጭ በመሄድ ለሊግ ኦፍ ኔሽን አቤት እንዲሉ ተመከረ።እሳቸውም አቤቱታቸውን ያጠናክር
ይመስል በእርሳቸውም ትዕዛዝ ሀገሪቱ እየተዋጋች እንደሆነች ለማጠየቅ ሲባል ምንም ቢሆን
የአርበኝነት ትግሉ እንዳይቋረጥ አዘዙ። ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው ፣ራስ ጌታቸው አባተ
የዋግሹም አባተ ልጅ እምሩን ተቀላቅለው ጦርነቱን እንዲቀጥሉ ታዘዙ።እነሱ ግን አሻፈረኝ ብለው
ሀገሪቱን ጥለው ሸሹ፡፡ 85

86
"ሽቅርቅሩ መልከመልካሙ፣ግዙፉና፣ልፍስፍሱ"መኮንን ወደ እየሩሳሌም ራስ ጌታቸው ደግሞ
ካይሮ ገብተው ቆይተው ከጣልያኖቹ ጋር አበሩ።

እምሩ በአዲስ አበባ ስለነበረው ምክክር የሚያውቁት ነገር አልነበረም።ነጋድራስ (በኋላ ደጃዝማች)
ይገዙ በሃብቴ 87ኃይለሥላሴ ጦር ግንባር ላይ ሳሉ መንግስቱን በአደራ ተረክበው ያስተዳድሩ ነበር።
ኃይለሥላሴ ግንባር ሳሉ ቢሸነፉ ወይንም ቢሞቱ የመጠባበቂያ እቅዶችን የሚያዘጋጀው ቡድን
ሊቀመንበር ነበሩ።ንጉሱ ሃገር እንዲለቁ ከተመከረ በኋላ የወልደ ፃዲቅ እጣፈንታ ግልፅ አልሆነም።
የታቀደው በኢትዮጵያ እየተዋጉ እንዲቆዩ ነበር።ይህም እቅድ ቀረ።በጎሬ የመንግስቱ መሪ የነበሩት
ወልደፃዲቅ በጦርነቱ መግፋት ባይፈልጉም በአርበኝነት ለመቀጠል ለሚፈልጉት የሽንገላ ይሁንታ

185
ጥቋቁር አናብስት

እያሳዩ በውስጣቸው ግን ከጣሊያኖቹ ጋር ለመስማማት ቢክሞሩ እንደሚሻል ያምኑ ነበር፡፡እምሩና


ሰዎቻቸው በኢትዮጵያውያን ሽንፈት እና በንጉሱ ሽሽት ተስፋ ቢቆርጡም በጦርነቱ ለመቀጠል
ፈለጉ።የእምሩ ሃሳብ ቢያሸንፍም የወልደፃዲቅ የመንግስት መሪነት (ከነበረም) እስከምን ድረስ
እንደነበር ወይም እምሩ እንደነበሩ ግልፅ አይደለም።(ኃይለ ሥላሴ በግለታሪክቸው እምሩ
እንደነበሩ ሲፅፉ ይሄ ምናልባትም እምሩን በሾምኩት ኖሮ የሚል ቁጭት የመነጨ መሆኑን
የሚያጠይቅ ሊሆን ይችላል ። ስለዚህ እምሩ እዚህ የመሪነት ቦታ ላይ በንጉሱ ተሹመው ነበር
እንዲባል )

እምሩ ጎሬ እንደደረሱ ለመጀመርያ ጊዜ ከሰለክላካ ጦርነት በኋላ ከንጉሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት


ፈጠሩ። ካውንት ቮን ሮሴንም በራሳቸው አውሮፕላን ጎሬ ድረስ መጥተው ከንጉሱ የተላከ
መልእክት ሰጧቸው። ኢሉባቦር የኦሮሞ ሀገር ነው። ኦሮሞዎች ደግሞ በጦርነቱ ለመሳተፍ ያን
ያህል ጉጉ አይደሉም ። ቢሆንም እምሩ ጦራቸውን እንደገና አደራጅተው ጦርነቱን ማስቀጠል
ነበረባቸው ።ወደ ጎሬ በሚወስደው መንገድ ላይ ትልቋን ልጃቸውን የምስራችን ከባለቤቷ ፍቃደ
ስላሴ ህሩይ ከልጃቸው አለም ሰገድ (ህሩይ) ጋር ሆነው አገኟት ።በንጉሱ ትእዛዝ አረጋውያን
ሴቶች ወደ ካርቱም ሄደው ስለነበር (የምስራች እና አለምሰገድ ከነዚህ መሃል ነበሩ)፡፡ፍቃደስላሴ
ግን አባቱ ወደ ነበሩበት እንግሊዝ አቅንቶ ከንጉሱ ወደ እምሩ መልእክት ይዞ መጣ።እምሩ ጎሬ ሳሉ
ከካርቱም ብዙ አቅርቦት ይደርሳቸው ነበር።ሃዲስ አለማየሁም ተልከውላቸው ተቀላቀሏቸው።88
እምሩ በጎሬ እ.ኤ.አ ከሰኔ እስከ መስከረም 1936 ድረስ ቆዩ።ጣልያኖቹ ከተማዋን ከጥቂት ጊዜ
በኋላ ተቆጣጠሩ ።እምሩን የሆለታ ወታደራዊ ካዴቶች ጨምሮ ከስደት ተመላሾችና ሌሎች የነፃነት
ታጋዮች ተቀላቀሏቸው።89 የጥቁር አንበሳ የሀገር ፍቅር ማህበርም በአያሌው አግዘዋቸል።90እምሩ
በአዲስ አበባ ስለሚካሄደው ጉዳይ የሚያሳውቋቸው ሰላዮች ነበሯቸው።

በርካታ የጦር መሪዎች ኃይለሥላሴ በሽሽት ሲሄዱም ሆነ በዚያው አካባቢ አብረው ለቀቁ።
የምስራቅ እዙም አመራር እንዲሁ።ፊትአውራሪ ተክለሐዋርያት እቴጌይቱ ከነ ልጆቻቸው ጋር ወደ
ጅቡቲ በባቡር በማቅናት ላይ መሆናቸው ተነግሯቸው በአፍደም ጣብያ ላይ እንዲያገኟቸው
ተጠይቀው ወደ ባቡሩ ሲገቡ ንጉሱን በማግኘታቸው ተደነቁ።ንጉሱ በሽሽት ላይ መሆናቸውን
አላወቁም።(ይህ አንዳንድ ፀሃፍት ባቡሩን አስቁመው ኃይለ ሥላሴን እንዳይሄዱ ለማስገደድ ሞከሩ
ከሚሉት በተቃራኒ ነው)ንጉሱ በባቡር ወደ ውጭ በመውጣትላይ እንዳሉ ሲሰሙ በውሳኔያቸው
አልተደሰቱም።ሁለቱ ወደ ድሬዳዋ እየሄዱም በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ተወያዩበት። ንጉሱ ግን
በአማካሪዎቻቸው ምክር ፀንተው(21ለ3 በሆነ ድምጽ በተወሰነው)ወደ ጅቡቲ አቀኑ ምንም እንኳ
አርበኞቹ ቆይተው በጦርነቱ እንዲቀጥሉ ፈልገው ቢስማሙም።ድሬደዋ ላይ ተክለሐዋርያት ከባቡር
ወርደው ወደ ጦር መሪዎቹ በመመለስ ጦርነቱን እንዲቀጥሉበት ለማደፋፈር ሞከሩ።ነገር ግን ሀረር
186
ጥቋቁር አናብስት

እና በድሬዳዋ በተካሄደው ጦርነት የሚሸሸውን ህዝብ ቀልብ መሳብ ሳይችሉ ቀርተው ንጉሱ ቢኖሩ
ግን ይህን ስደት ለማስቆም በተቻለ ነበር ብለው እያሰቡ በስተመጨረሻም እሳቸውም ወደ ጅቡቲ
አመለጡ።

****

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ እምሩ ውጊያውን ቀጠሉ።ብላታ ታከለ ወልደሐዋርያት ሌላኛው የጦር
መሪ ወዲያውኑ እምሩን ትተው ከበርካታ ጦር ጋር ወደ ጎንደር (በጌምድር) አቀኑ።ጣልያኖቹ ጅማን
ሲይዙ እዚያ የነበረው መሪ አባጆቢር አባዱላም ለጣልያኖቹ አደረ።91 ሰለዚህ እምሩ ወደ ጅማ
መግባት አልቻሉም።ከዚያ የመጡ ብዙ ስደተኞች የሳቸውንናየጥቁር አንበሳ ተዋጊዎች ጥበቃን
ሽተው መጡ። ከስደተኞቹ መምጣት በፊት በእምሩና በጣልያኖች መሃል አጋሮ ላይ ሀይለኛ ጦርነት
ተደረገ ።ከዚህ ጦርነት በኋላ የተወሰኑ የጦሩ አባላት ወደ ጅማ ገፍተው የነበር ቢሆንም ነገር ግን
ከስደተኞቹ ጋር ተገናኙ ።ከመሃላቸውም ታቦት የያዙ ካህናት ነበሩ ።እነዚህ ተሰዳጆች የጦሩን ጉዞ
ገቱት።እምሩ ከፋ ቦንጋ ለነበሩት ለደጃዝማች ታዬ ጉልላቴ ሊልኳቸው በማሰብ ወደ አጋሮ
ተመልሰው የጎጀብን ወንዝ አቋረጡ።ጌራ ሲደርሱ ጣልያኖች ደረሱባቸው። እዚያም በጣም ከባዱ
ውግያ ተደረገ።ከሁሉ የከፋው ጦርነት ቀኑን ሙሉ ዋለ።92ጣልያኖች በአየር ቢታገዙም ውሃ
አግኝተው መትረይሶቻቸውን እንዳያቀዘቅዙ ከውሃው በመቆረጣቸው ተቸግረው እየተዋጉ ውለው
ቢያሸንፉም ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰው አለቀ።ጣልያኖች ጦርነቱን ቢያሸንፉም ኢትዮጵያኖቹን
በዝግታና ባልተቀናጀ መልክ ለማሳደድ ችለዋል።93እምሩ ከነጦራቸው ጎጀብ ሲደርሱ ከማዶ
የደጃዝማች ጉልላቴ ግዛት ላይ ጣልያኖችን አሻግረው መመልከት ቻሉ። የዛን ጊዜ ነበር ደጃዝማች
ታዬ እጃቸውን ሰጥተው ሊሆን እንደሚችል ምንአልባትም ከጣልያኖች ጋርም ተባብረው እየሰሩ
ሊሆን እንደሚችል ያወቁት።ታዬ በዘመቻው ወቅት ከጣልያኖች ጋር ተገናኝተው በሀሰት
ጣልያኖችን እየወጉ እንደሆኑ ከጣልያኖች ጋር ካበሩ በኋላ ለእምሩ እንደፃፉላቸው ነው የተነገረኝ።
ቅዳሜ ላይ እምሩ ሰፈራ አደረጉ።ከፊታቸው ያልተዋጋ ትኩስ ከከፋ የመጣ የጣልያን ጦር
ከጀርባቸው እያነከሰ የሚከተላቸው የጅማ ትርፍራፊ ጦር አጣብቋቸዋል፡፡ነገር ግን ምንም ጦርነት
አልተካሄደም።በምትኩም ድርድሮች ተካሄዱ።እምሩ በጦርነቱ ህፃናት፣ሴቶች፣አእሩግ፣ የቤተክህነት
ንብረት የያዙ ካህናት ስለነበሩበት ለማይዋጉት ከጅማ ለመጡት ስደተኞች ደህንነት ፈለጉ።ለጊዜው
በዚህ በኩል መስማማት ላይ የተደረሰ መሰለ ።ስደተኞቹም ወደ ከፋ ወንዙን ማቋረጥ ጀመሩ።
በኋላ በቦታው ላይ የነበረው ባለስልጣኑ ኮለኔል እምሩ ስድተኞቹን ከራሳቸው ካወረዱ በኋላ
ከተዋጊዎች ጋር ሲቀሩ እንደገና መዋጋት ለመጀመር አስበው ነው በማለት ስደተኞቹን ወደ እምሩ
ሰፈር (ኮረብታ ላይ ያለ ነበር) መለሳቸው።ከዚያ በኋላ እምሩ እጅ እስኪሰጡ ድረስ ድርድሩ ለ3
ቀናት ቀጠለ።በዚህ ወቅት ጥይት እያለቀባቸው ነበር።ጣልያኖች ግን ይህንን አላወቁም ።በእጅ

187
ጥቋቁር አናብስት

መስጠቱ ድርድር ጣልያኖች ለህፃናት ፣ሴቶችና፣ቀሳውስት እና ላከበሯቸው ታቦታት መጠለያ


ለመስጠት ቃል ገቡ።

***

ራስ እምሩ እ.ኤ.አ በታህሳስ 1936 እጅ ሰጥተው ወደ ከፋ ቦንጋ ተወሰዱ።95በዚያው በታህሳስ


ወር ሌሎች ሀገር ወዳድ አርበኞችም እጅ ሰጡ ለምሳሌ ደጃዝማች አበራ ካሳ በማይጨው ከነባልቻ
ጋር አብረው የተዋጉ በኋላም ወደ ሰላሌ ያፈገፈጉ እ.ኤ.አ በሰኔ 1936ም ወደ መናገሻዋ የዘመቱ
ሲሆኑ ከሳቸው ጋር የሆለታ ሚልታሪ ካዴቱ ሙልጌታ ቡሊ፣መንግሥቱ ንዋይ፣አበበ ተፈሪ96እና
አክሊሉ ዳዲ ይገኙባቸዋል።እጅ ከመስጠታቸው በፊት ግን ከጣልያኖች ጋር የወዳጅነት ንግግር
እያደረጉ ነው በማለት ከድተዋቸው የሄዱም በርካታ ነበሩ።የአበራ አማች ደጃዝማች ስዩምና
በተለይም ሃይሉ ተክለሃይማኖት በጣልያን በኩል ሆነው አበራ ካሳ እንዲቀሏቀላቸው ሲገፋፏቸው
ነበር።ነገር ግን አበራ ያለጦርነት እጃቸውን ሲሰጡ ከወንድማቸው አስፋ ወሰን ጋር በታህሳስ 21
1936 በጣልያን ተገደሉ።

የተወሰኑ ቀናት በቦንጋ ቆይታ አድርገው እምሩ ታዬ ጉልላቴን ጨምረው ወደ ጅማ ቀጥለው ወደ


አዲስአበባ ተላኩ ።ቀጥሎ ወደ አስመራ በአውሮፕላን ተልከው ወደ ምፅዋ ተወሰዱ ።ከምፅዋ
በመርከብ (ኮሎምቦ) ወደ ኔፕልስ ብሎም ወደ ፖንዛ ከትንሽ ጊዜ በኋላም በርካታ አመታትን
ወደአሳለፉባት ሊፓሪ(ከሰርዲንያ በስተስሜን የምትገኘው) ወደ ዋናው መሬት ከመመለሳቸው
በፊት በእስር ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።

ግራዝያኒ ኢጣልያ ውስጥ ጓደኛ ማንን ላምጣሎት ቢላቸው ሃዲስ አለማየሁን (ረዳታቸውን) ታዬ
ጉልላቴን ፣ይልማ ደሬሳን ቢሉም ከጥቂት አመታት በኋላ ታዬ ጉልላቴና ይልማ ወደ ኢትዮጵያ
እንዲመለሱ ጠየቁ ። በተለይ ታዬ ከጣልያን ጋር እንዳልተዋጉ በማስመስል የንግስና ዝርያ
ስላላቸው ጣልያኖቹ ቢያነግሱኝ ብለው ተመኝተው ነበር።እነሱ ከለቀቁ በኋላም እምሩ ግርማቸው
ተክለሐዋርያትን አገኙ።በዚህኛው የአብሮነት ቆይታቸው እምሩ እንደፃፉት ከሆነ ግርማቸው
ተክለሐዋርያት ከነገረኝ በተቃራኒው በተወሰነ ደረጃ የመንቀሳቀስ ነፃነት ተሰጥቷቸዋል።እምሩ
እሁድ ሲሆን ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ደሴቷ ላይ የካቶሊክ ቄስ ያነጋግራሉ፡፡የተወሰነ
ጣልያንኛም ያውቃሉ።ሊፓሪ ላይ ሳሉም የጣልያንኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት አዘጋጅተው ሁሉ
ነበር።የደሴቲቱን ነዋሪዎችንም ሌሎችንም ታሳሪዎችንም መግባባት ችለው ነበር።አብዛኞቹ
ጣልያኖች ሲሆኑ አፍቃሪ ሶሻሊስት ወይም ማርክሲስት ነበሩ።የተወሰኑ የዩጎዝላቪያ ዜጎችም ነበሩ
።97 በምን ያህል እንደሆነ መናገር ባይቻልም ርዕዮታቸው በእምሩ ላይ ተፅእኖ አሳድሮ ሊሆን

188
ጥቋቁር አናብስት

ይችላል።ልጃቸው እንደሚናገረው ከሆነ የእምሩ ሶሻሊዝም ወደ "ክርስትና ማህበራዊ እሳቤ


"ያጋደለ ነው ።

እምሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ካላቸው ከፍተኛ ቦታ አንፃር በስነ ፅሁፍ ሊሰጣቸው ከሚገባው
ቦታ በላይ በዚህች መድብል ላይ ተሰጥቷቸዋል ።ጣልያን በሊፓሪ ደሴት በግዞት ሳሉ ነበር
የስነፀሑፍ ስራቸውን የጀመሩት የመጀመሪያ ልብወለድ ስራቸውን በንፁህና በሚነበብ የእጅ
ፅህፈት የፃፉት በ1933 "የአለም ትግል"የሚል ርዕስ ነበረ።98የመፅሐፉ ታሪክ አንድ ውጭ ቆይቶ
በመጣ ተራማጅ እና በባህል ተጽእኖ በታሰሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ያለ በእድገት እና ስልጣኔ
ዙርያ የሚደረግ ውይይት ነው።99ምንም እንኳ ይህ የእምሩ የመጀመሪያው መፅሐፍ ቢሆንም
የታተመው መጨረሻ ላይ ነበር።(በሕይወት ሳሉ ከታተሙት ለማለት ነው ።ግለታሪካቸው ለምሳሌ
በሕይወት እያሉ አልታተመም፡፡ምንአልባት በኋላ ሊታተም ይችላል) ኃይለሥላሴ ረቂቁን እምሩ
ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አንብበውት ለመታተም ጊዜው ገና እንደሆነ አሰቡ። ስለዚህ የታተመው
በ1967 አብዮቱ ሲፈነዳ እና ኢትዮጵያ ለአዳዲስ ሃሳቦች በሯን ክፍት ባደረገችበት የመንግስት
ለውጥ የመጀመሪያው ዓመት ነው።“አለማዊ ትግል” በሚል ርእስ ነበር የወጣው ።ከዚህ መፅሐፍ
በፊት እምሩ ግጥሞችን ጽፈው ቤት ውስጥም ለቤተሰቦቻቸው ያነቡላቸው፤ በሚሰበሰቡበት
ስብሰባዎች ማስታወሻ እየያዙ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙርያ ፅሁፎችን ይፅፉ ነበር።ታትመው ግን
አያውቁም ።እምሩ ከትውስታቸው ባለ ሁለት ቅፅ የግልታሪካቸውን የመጀመርያ ክፍል በሊፓሪ
ደሴት ላይ ሳሉ ፅፈዋል።100

በአንድነት ሀይሎች ግስገሳ ምክንያት እምሩ ወደ ደቡብ ጣልያን ካሊብራ ውስጥ ወዳለችው ሉንጎ
ቡኮ ተዘዋውረው ለመጨረሻዎቹ የ6 ወራት የጣሊያን ቆይታቸው በግዞት ተቀመጡ።101በጣልያን
ቆይታቸው በጥሩ ሁኔታ እንደተያዙ ይናገራሉ።በአንድነት ሀይሎች ከእስር ነፃ ወጥተው እ.ኤ.አ
በጥቅምት 1943 ንጉሱ ወደ ኢትዮጵያ በተመለሱ በሁለት ዓመት ከግማሹ እ.ኤ.አ በግንቦት 5
1941 ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በጦርነቱ ወቅት የእምሩ ቤተሰብ መጀመርያ አዲስአበባ ውስጥ ነበሩ።በኋላም ወደ ሀገረሕይወት


(አምቦ) ቆይቶም ከንጉሱ ጋር አብረው ወደ ጅቡቲ ሄዱ።እዚያም በበጅሮንድ ተክለሐዋርያት
አስተናጋጅነት ቆዩ።ከአዲስ አበባ በባቡር እ.ኤ.አ በግንቦት 30 1936 አ.ም ተንቀሳቅሰው
በሚያዝያ 12 ጅቡቲ ደረሱ።ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ኤደን ተሻገሩ።እዚያ ሳሉ የእምሩ ታላቋ
ሴት ልጃቸው ተቀላቀለቻቸው።በኋላም መልሳ ወደ ካርቱም ሄደች።ስድስት ወራትን በኤደን

189
ጥቋቁር አናብስት

ካሳለፉ በኋላ ወደ እየሩሳሌም ሄደው ቆዩ።ህፃናቱም ለስድስት አመታት እስከ ህዳር 1942 ድረስ
ትምህርት ቤት ገቡ።የእምሩ ባለቤት፤ የታላቅ ሴት ልጃቸው ሴት ልጅ፤ የጉዲፈቻ ልጃቸው፤
(ጫማሽ ወርቅ ሀዋዝ )እና የተወሰኑ ጥቂቶች በሻህ ጊራህ ይህን ወቅት አሳልፈዋል።102

***

አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ እምሩ በመናገሻ ከተማዋ ለጥቂት ወራት ተቀመጡ ።ምንም እንኳ
ለሌላ የገዥነት ሹመት ፍላጎት ባይኖራቸውና ለወጣቶች እድል መስጠት ቢፈልጉም ምንአልባትም
በንጉሱ ግፊት ለበጌምድር ገዥነት ተሹመው እ.ኤ.አ በግንቦት 1944 ለ10 ወራት በሹመት ወደ
ቆዩበት ጎንደር ሄዱ።ጎንደር ላይ አመፃዎችና ሌሎች ችግሮች ነበሩ።ነዋሪዎቹም ለመተዳደር
ያዳግታሉ።እምሩ ጨከን ያሉ እርምጃዎችን በመውሰድ ህግና መረጋጋትን አሰፈኑ።ወደ ክፍለሀገሩ
ለመግባት እራሱ የራሳቸውን ጦር ይዘው መሄድ ነበረባቸው።

ወደ በጌምድር ሲመጡ ከወረራው በፊት ሲደክሙላቸው የነበሩ ማሻሻያዎች በጣሊያኖች ቀጥለው


አገኟቸው።ስልጣን ተማክሏል።የቀረጥ መቅረጫዎችና የፊውዳል ተቋማት ተወግደዋል።ግብር ወጥ
ሆኗል።ይሄ ዘመናዊ መዋቅር ከተዘረጋ ማስተዳደሩ ለእምሩ ቀላል ነበር።በዚህ ወቅት የነበረው
ችግር ከበፊቱ የተለየ ነበር።ለዚህም ነበር ወጣት ልጆችን የየክፍላተሃገሩን መስተዳድር እንዲይዙ
ሲፈልጉ የነበሩት ።

***

እምሩ ወደ ጎንደር ከመሄዳቸው በፊት ንጉሱ ምልከታቸውን እንዲያጋሯቸው ከጊዜ ጊዜ ይጠሯቸው


ነበር።ከጎንደር ሲመለሱም ተመሳሳይ ነገር ቀጠለ።ኃይለሥላሴ የሚመርጧቸውን ጥቂት ሰዎች
ለዚህ አይነት ስብሰባ የመጥራት ልምድ አላቸው ።ሀሳብ በነፃነት ይንሸራሸራል።ኃይለሥላሴ ሀሳብን
የሚቀበሉ ሲሆን መዋቅራቸው (በወቅቱ)ዝግ አልነበረም።በነዚህ ስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች
በአብዛኛው ምንም አይነት ኦፊሴላዊ የአማካሪነት ስልጣን አልነበራቸውም።እምሩም በወቅቱ
የዘውድ ምክር ቤትም ሆነ የሌላ ተመሳሳይ አካል አባል አልነበሩም።103ያለቀጠሮ እንኳ ታዋቂ
ሰዎች በሳምንት ሁለት ሶስቴ ወደ ቤተመንግስቱ ይመጡ ነበር።የተወሰኑ ቀናት መቅረት እንደ
ህመም አይነት ችግር መፈጠሩን ማመላከቻ ነበር።ከቤተመንግስቱ መላዕክተኛ ተልኮ ምን ችግር
እንዳለ ይጠይቃል።እምሩ ወደቤተመንግስት በየጊዜው ይመላለሳሉ። ከሰዎችም የተፈረሙ
አቤቱታዎን ለንጉሱ ያቀርባሉ።በስብሰባ ወቅትም እንደመሬት ስሪት ላሉት የበፊት ስሪቶች በዘመናዊ
ኢትዮጵያ ስራ ላይ ማዋል አይቻልም በማለት ይናገሩ ነበር ።

190
ጥቋቁር አናብስት

የእምሩ በመሬት ስሪቱ ላይ ያለውን ጥያቄ የመመለስ ፍላጎት ከሀረር የጀመረ ነበር።የጎሳ የመሬት
አጠቃቀም ጥያቄዎች በመጡበት ጊዜያት የመሬት ጥያቄዎች በድጋሚ በወሎ መነሳት ጀመረ።
በባለይዞታ ገበሬዎችና በዘላኖች መካከል ተነስቶ እስከ ዘመቻ እና ዝርፍያ የደረሰ ችግር አስከተለ፡፡
በጎጃም የነበሩ ፊውዳል ጌችቶም መሬት ለሌለውና ተከራይቶዋቸው በሚያርሰው በገበሬው ላይ
ኑሮውን አክበዱበት።በጦርነቱ ወቅት የመሬት ጉዳይ ቀደም ብሎ አንድ መፍትሄ ቢያገኝ ኖሮ
የመከላከል ጦርነቱ የተሻለ እንደሚሆን ያስባሉ።በእስር ላይ እያሉም በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም
አስበውበታል።ስርነቀል የመሬት ማሻሻያ ሀሳቦቻቸው እንደ ራስ ካሳ ቤተሰብ፤ ራስ መስፍን
ስለሺ(አርበኛና ቀጥለው የሸዋ ገዥ)ምንም እንኳ ከቤተክህነት ጋር ቅርበት ቢኖራቸውም ቅሉ
ቤተክርስቲያኗን ጨምሮ የሀብታም ባለመሬት ከበርቴዎችን ጠላትነት ገዝቶላቸዋል። የመሬት
ማሻሻያ ሀሳባቸውን የሚደግፍ አላገኙም።የግላቸውን መሬት ማደል ጀመሩ።(በተለይ በአርሲና
በሌሎቹ ቦታዎች) ለድሀ ገበሬዎች ለጭሰኞች ለራሳቸውም ቤተሰብ ጭምር አከፋፈሉ።እምሩ
በመሬት ባለይዞታነት ወሰን መጠን እንዲበጅለት፤ብዝበዛን ለማስቀረት ሲባል ከጭሰኞች
በሚሰበሰበው የግብር መጠን ላይ ወሰን እንዲበጅም ይፈልጋሉ።104

ከጦርነቱ በፊት ኃይለሥላሴ ስለመሬት ባለይዞታነት የነበራቸው ሃሳብ ከእምሩ ከተክለሐዋርያትና


ከሌሎቹ ጋር ያን ያህል አይራራቅም ነበር።ከጦርነቱ በኋላ ይዞታዎች ጠንክረው በውስን እጆች ላይ
እየወደቁ መጡ።እምሩ በቂ ገቢ ባላቸው ባለመሬት ከበርቴዎች እጅ የሚገኙ ያለልማት የተቀመጡ
መሬቶችን በተለይ ለመከልከል ፈለጉ። ኃይለስላሴ ከጦርነቱ በኋላ ይበልጥ ወግ አጥባቂ ሆኑ።ይሄ
በእሳቸውና በእምሩ መካከል አለመግባባት ፈጠረ።የሀብት ክፍፍሉ ከጦርነቱ በኋላ ለእምሩ ቅሬታን
ያሳደረ ያልተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ቀጠለ።ማህበራዊ ማሻሻዮች እንዲኖሩ የሚፈልጉት ፍትሐዊም
ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እድገትን የሚያቀናጅ እንደሆኑ እንደሚጠቅሙም
ስላሚያምኑበትም ጭምር ነው።ቢሮክራሲውም በአንጻሩ በእምሩ ላይ ቅሬታ አሳደረ።ምክንያቱም
ፊርማ እያሰባሰቡ በቢሮክራቶቹ ላይ ቅሬታ ለንጉሱ የሚያቀርቡት እሳቸው ስለነበሩ ነው።ንጉሱ
እምሩ የጎን ውጋት እንደሆኑባቸው እያሰቡ መጡ።እስካሁን ድረስ ግን እምሩ የንጉሱ ተቃዋሚ
አልሆኑም ። የሚፈልጉት በንጉሱ በኩል ለውጥ እንዲመጣ ነበር።ንጉሱ የተቃርኖ ሀሳብ ካለው
አካል ይቅርና እንዲሁም ከማንኛውም ተቃራኒ ሃሳብ ካለው ሰው ጋር ተፈጥሯዊ የመቃረን ስሜት
አላቸው ። የሚያቀርቧቸውን እንኳን በምቀኝነት ማናከስ ይፈልጋሉ።ሰዎችን ሹመት ይሁን ሽረት
በማያሳውቅ ሁኔታ ወደ ሌላ ቦታ ያዘዋውራሉ።በደግነት የሚሰጡት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ነው።
ስጦታቸውን የማይቀበል ሰውም አይወዱም።ገንዘብንም ስለሚወዱ ያለአንዳች ፖለቲካዊ ምክንያት
አያወጡም ።ገንዘብ አጠራቅመው ነበር።ነገር ግን በአግባቡ በውጭ ሀገር ሳይሆን በእርሳቸው ጊዜ
በቤተመንግስቱ ውስጥ ባሉ ስውር ቦታዎች ሊያስቀምጡ ይችላሉ።ይህ ግን በጉብዝናቸው ወራት
አልነበረም ።105

191
ጥቋቁር አናብስት

***

ምንአልባትም ንጉሱ ካሉበት አጣብቂኝ ሁኔታ ለመገላገልም ፈልገው ይሆናል በዲፕሎማሲ ተልእኮ
ከሀገር ውጭ የላኳቸው።እ.ኤ.አ በሚያዝያ 1946 እምሩ በአምባሳደርነት ማእረግ ወደ አሜሪካ
ተልከው እስከ የካቲት 1954 ድረስ ቆዩ።አሜሪካ እያሉ እምሩ ሁለተኛ ልብወለዳቸውን ፃፉ።
ርእሱ "ፊትአዉራሪ በላይ" ሲሆን የመጀመሪያው የታተመው መፅሀፋቸው ነው ።በ1948 አ.ም
ታትሞ ወጣ።በ1956 አ.ም በድጋሚ ታተመ።ቀጥሎም በ1976 አ.ም ለሶስተኛ ግዜ ሲታተም ወደ
እንግሊዘኛ ቋንቋም ተተርጉሟል ።

እምሩ ከኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር አሜሪካ ሳሉ ይገናኙ ነበር ።የተማሪዎች ህብረት ሁለተኛ


ፕሬዝደንት የሆነውን በ53ቱ መፈንቅለ መንግስት ዋነኛ የርእዮተ አለም አቀንቃኝ ገርማሜ ንዋይን
አገኙት።ግርማሜ በዚህ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ህይወቱን አጣ፡ንጉሰ ነገስቱም በዙፋናቸው
ቆዩ፡፡እምሩ የግለታሪካቸውን ሁለተኛ ክፍል መፃፍ የጀመሩት አሜሪካ ሆነው ነው ።እስከ እለት
ሞታቸውም መፃፋቸውን ቀጥለውበታል። ሁለተኛው ቅፅ ቤተሰቦቻቸው ጋር የለም አላነበቡትምም
የት እንዳለም አያውቁም ግን በደህና ቦታ አስቀምጠውታል ብለው ይገምታሉ።

***

ከአሜሪካ ሲመለሱ ለእሳቸውና ለሚስታቸው ልኡልና ልእልት የሚል መአረግ ተሰጣቸው ። እነዚህ
በጊዜው አዳዲስ መአረጋት ሲሆኑ የነገሥታት ዘር ላላቸው በዘውዲቱ ጊዜ ለነበሩ የሚሰጡ ናቸው
።106 ቢሆንም ከተመለሱ በኋላ ምንም አይነት የመንግስት ስልጣን አልተሰጣቸውም።
ምልከታቸውን የማይጋሩ ሰዎች ይህ እንዳይሆንና በተቻለ ትንሽ ተፅዕኖ እንዲኖራቸው ከመታተር
አልቦዘኑም። አብዛኞቹ መሬታቸውን መስጠት ሲጀምሩ ስጋት ቢገባቸውም በተራማጆች እና
በህዝቡ ዘንድ ታዋቂነትን አትርፎላቸዋል።

የእምሩ ቀጣይ ሹመት የህንድ አምባሳደርነት ነው።ይህም እ.አ.አ ከግንቦት 1954 እስከ 1959
አጋማሽ ለአምስት አመታት ያህል ነው።ሌሎች ሹመቶችንም ለምሳሌ እንደ ኤርትራ ገዥነት ያሉ
ወይንም ጠቅላይ ሚንስትር በመሆን ሁሌ የሚያወዛግበውን የህገመንግስት ጉዳይ ለመከለስ
ቢፈልጉም ንጉሱ አልተቀበሏቸውም። ምንአልባት ብዙ ማሻሻያዎችን ፈልገው ሊሆን ይችላል።
በወቅቱ ባለው ህገመንግስት ስር በሚኒስትርነት መስራት አለመፈለጋቸውም ኃይለሥላሴን
አስቆጣቸው።እምሩ ስለ ዘውድ መማክርቱ ያላቸው ምልከታ ዝቅተኛ የነበረ ሲሆን አባልም መሆን
አይፈልጉም።ሰለዚህ ወደ ህንድ ተላኩ፡፡ህንድና ባህሏን ወደዷት ኔህሩንና የኮንግረስ ፓርቲውንም
አደነቁ።
192
ጥቋቁር አናብስት

እምሩ ሶስተኛውን ልብወለድ (ለመታተም ሁለተኛ የሆነውን)ኒው ዴልሂ ሳሉ በ1947 ፅፈው


በ1952 ታትሟል።"ሰውና እውቀት" ይሰኛል ርእሱ።

****

ከህንድ ወደኢትዮጵያ ሲመለሱም ወደ ሞስኮ በአምባሳደርነት ተላኩ።በተለምዶው ንጉሱ ሰዎችን


ከመሾማቸው በፊት ጠርተው ያናግራሉ።ሰለዚህም በእምሩም ጉዳይ እንደዛ ሳይሆን አይቀርም።
የእምሩም ምርጫ ሊሆን ይችላል።ሹመቱ እ.ኤ.አ በ1960ቹ አጋማሽ የተደረገ ቢሆንም እምሩ ግን
አዲሱን የሞስኮ ስራ አልሰሩም።107

በ1953 ታዋቂው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በግርማሜ ንዋይ በወንድሙ መንግሥቱ ንዋይ እና
በወርቅነህ ገበየሁ መሪነት ተካሄደ።ገርማሜ በአሜሪካ ቆይታው እምሩን ኮለምብያ ዩንቨርስቲ
ከመግባቱ በፊት በዋሽንግተን ጎብኝቷቸዋል።እምሩ መንግስቱን ከርቀት ወርቅነህን ግን በተሻለ
ያውቁታል።108እምሩ ስለመፈንቅለ መንግስቱ እቅድ የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም።
አላማከሯቸውምም፡፡በመፈንቅለ መንግስቱ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መታጨታቸውን
በሬድዮ ሲነገርም አልሰሙም።እምሩ ለለውጥ የቆሙ አረጋዊ የፖለቲካ ሰው ናቸዉ ።በመስተዳድሩ
ውስጥ ያሉ ወጣት ተራማጆች ለመሪነት የሚመለከቷቸው ሰው ነበሩ። አሮጌውን ቡድን እንዲሻሻል
የሚጥሩ በቢሮክራቶችና በባለስልጣኖች ለተበደሉ ገበሬዎች የሚያዝኑ ሰው ናቸው።በዚህም
መክንያት ሳይሆን አይቀርም አማፅያኑ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾሟቸው።

እምሩ የአጼው መዋቅር እንዲገረሰስ ባይፈልጉም በፖለቲካው ተሳትፎ የሌለውና ለኢትዮጵያ


አንድነት በትእምርትነት የሚቀመጥ ህገመንግስታዊ የንጉስ አገዛዝ እንዲኖር ይሻሉ፡፡ የራሱን ካቢኔ
የሚያዋቅርና ሚንስትሮቹን የሚሾም፤ የማስፈጸም ሃይል ያለው፤ለፓርላማውም ተጠያቂና በህዝቡ
እምነት የተጣለበት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡

በመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች መካከል እንኳን የቀኝና ግራ ዘመም ክፍፍሎች ነበሩ፡፡ ወርቅነህ ወግ
አጥባቂ የነበሩ ሲሆን ግርማሜ ስርነቀል ለውጥን የሚፈልጉ አምባገነናዊ ሌኒናዊ እንዲያውም
ስታሊናዊ ጸባይ ያላቸው ናቸው ዲሞክራትም አልነበሩም፡፡109ጠንካራ ሰራተኛ፤ ጥሩ ተናጋሪ እና
በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ጥንቁቅ በስልጣን መባለግንም የሚቃወሙ ነበሩ፡፡ መዋቅሩ ሚስጥራዊ
ስላደረጋቸው እሳቸውን አውቆ ለመገምገም አዳጋች ነው፡፡ 110መፈንቅለ መንግስቱ የተለየ ጉዳይ
ስለሆነ እዚህ አናነሳውም፡፡111እምሩ ንጉሱ ከተመለሱ መፈንቅለ መንግሰቱም ከከሸፈ በኋላ ዳግም
ከንጉሱ ጋር ሊቀራረቡ ቻሉ፡፡

193
ጥቋቁር አናብስት

***

ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በኋላ በኢትዮጵያ ይደረጉ የነበሩ የፖለቲካ ክርክሮች ቆሙ፡፡ ነገሮች
በብዙ መልኩ እየጠበቁ መጡ፡፡ለአብነትም መገናኛ ብዙሃን ይበልጥ ጫና ተደረገባቸው፤ታፈኑ፡፡
የመጽሐፍ ሳንሱርም እየጠበቀ እና አዳዲስ ሃሳቦችን የማያሳልፍ እየሆነ መጣ፡፡ ከብዙሃኑ አይንና
ጆሮ ቢርቅም ቅሉ የኢኮኖሚው ክርክር ግን እንደቀጠለ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1965 ወይም 1966 አካባቢ ኃይለሥላሴ የመሬት ማሻሻያ ጥያቄውን የሚመለከት
ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡ በፓርላማው ስልጣን ዙርያ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሌሎች ሚንስትሮችን ይሹም
ተጠሪነታቸው ለሱ ይሁን ወይም ለንጉሱ በሚሉትም ዙርያም ክርክር ተካሄደ፡፡ አብዛ,ኞቹ ጉዳዮች
የተነሱት እ.ኤ.አ በ1965 አካባቢ ነው፡፡ እምሩም በነዚህ ጉዳዮች ላይ በንቃት ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡
ንጉሱ ለሙከራ ያህል ሶስት እጩዎችን አቅርበው በፓርላማው አብዛኛውን ድምጽ የሚያገኘውን
እንዲሾሙ ፤ጠቅላይ ሚንስትሩም እራሱ ሚኒስትሮቹን እንዲሾም ፤በሃገሪቱ ስላለውም የአስተዳደር
ሁኔታ ተጠያቂ እንዲሆን የሚል ሃሳብ አቀረቡ፡፡ በነዚህ ድርድሮች ዙርያ ለመከራከር ታላላቅ
ጉባኤያት ቢደረጉም በመጨረሻ ንጉሱ ግን ሁሉንም አልተቀበሉም፡፡112ነገር ግን እ.ኤ.አ በ1966
ሃሳባቸውን ቀይረው አክሊሉ ሃብተወልድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመሾም የራሳቸውን
ሚንስትሮች እንዲሾሙና ለመንግስቱ ስራ ሃላፊ እንዲሆኑ አደረጉ፡፡ይህ የወረቀት ውሳኔ ብቻ ሆኖ
እውነታው ግን ነገሮች ባሉበት መቀጠላቸው ነው፡፡ ሁሉንም ነገር እራሳቸው ይወስናሉ እያረጁም
ሲሄዱ በነገሮች ላይ ያላቸው ቁጥጥር እየላላ ሄደ፡፡

ልኡል ራስ እመሩ ኃይለሥላሴ በፖለቲካ ክርክሮች ውስጥ ቢሳተፉም ቀስ በቀስ ወደ ቤታቸውና


ወደ ቤተሰባቸው አዘነበሉ፡፡ የመጨረሻዎቹን የሕይወት ዘመናቸውን የባለቤታቸው በሆነው
በአባኮራን ሰፈር በሚገኘው “የራስ እምሩ ግቢ” አሳለፉ፡፡ አዲስ አበባ ሲሆኑም ሆነ በፊትም ብዙ
ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በዚያ ቤት ማረፍ ይወዱ ነበር፡፡ በነሃሴ 11 1972 አ.ም ከሌሊቱ
113
በዘጠኝ ሰአት ያረፉትም እዚያው ነው፡፡ ከሁለት ቀናት በኋላ በፍልሰታ ጾም በደብረታቦር
114
እለት ተቀበሩ፡፡ በመጨረሻ የሕይወት ቀናቶቻቸው ትንሽ ህመም የተሰማቸው ሲሆን ምግብም
ከልክሏቸው ነበር፡፡አልጋ ላይ ብዙም አልዋሉም፡፡ባረፉበት ቀን በሰባት ሰአት አካባቢ
ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲያወሩ የነበረ ሲሆን ከሁለት ሰአታት በኋላ ነበር ያረፉት፡፡

የእምሩ ኃይለሥላሴን ያህል ፈርጀ ብዙ ስኬት የተጎናጸፉ ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡ ከደህና ቤተሰብ
የመጡና ሲጀመር ጀምሮ ጥሩ እውቂያ የነበራቸው ናቸው፡፡ ይሄም ወደ ስልጣን ማእከሉ እንዲጠጉ
የእድሜ ልክ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ነገር ግን የራሳቸው አስተሳሰብ ያላቸው ሰው ስለነበሩ ይሄ
በስልጣን ላይ ከነበሩት ጋር ባመጣው መቃቃር፤የበጎ አድራጎት ስራቸውም በህዝቡ ዘንድ ታዋቂ
194
ጥቋቁር አናብስት

አድርጓቸዋል፡፡ሰዎች እራሳቸውን እንዲችሉ ለመርዳት ስለሚፈልጉ ሰርተው የሚያተርፉበትን


መሬት ለግሰዋቸዋል፡፡ ተመጽዋቹን ሲያልቅ ወደ ችግሩ ስለሚመልስ ኃይለሥላሴ እንደሚያደርጉት
ገንዘብ መስጠት ግን እምብዛም አይወዱም፡፡ 115

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ለእምሩ ያላቸው ከበሬታ ከፍ ያለ
ነው፡፡ክብራቸውን የጠበቁ ጌታ፤ዝነኛ ጦረኛ፤አስተዳዳሪና ፖለቲከኛ ነበሩ፡፡ ይሄ በጠላቶቻቸው
ሰፈር እንኳን ክብርን እንዲቀዳጁ አስችሏቸዋል፡፡ ቁጥብ ፤ልታይ ልታይ የሚል ባሕርይ
ያልነበራቸው ቢሆንም በቅርብ ጓደኞቻቸው ዘንድ ተግባቢና የሚከበሩ ሰው ናቸው፡፡116
እርዳታቸውን ለሚሻ ቅርብ ላገኙት ሁሉ መልካም ነበሩ፡፡ ባስተዳደሯቸው ግዛቶች ከሳቸው ቀደም
ብለው ይሰሩባቸው የነበሩ የደም ካሳና ላለመታሰር የሚፈጸም ክፍያን አስቀርተዋል፡፡አንዳንዶች
በዚህ ምክንያት ጨካኝና ምህረት የለሽ ቢያደርጓቸውም ሁሉንም በእኩል አይን እንደሚያዩና
ፍትሐዊ እንደሆኑ ያምናሉ፡፡እያሱ በተወገዱበት ጦርነት ብዙ ሙስሊሞችን ሀረር ላይ
ጨፍጭፈዋል ብለው የሚወነጅሏዋቸው ሙስሊሞች እራሳቸው«የፍትህ ሰው»ነበሩ ሲሉ
ቃላቸውን ይሰጣሉ፡፡ልጃቸው ሚካኤል እንደሚያምነው ተገቢ ያልሆኑ የጭካኔ ድርጊቶች
ተፈጽመዋል የሚለውን ውንጀላ የተጋነነ እንደሆነና ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው እንደሆነ
ይገልጻል፡፡ 117 ምንም ይሁን ምን ግን እነዚህ ውንጀላዎች የእኒህን ሰው ምስል እና ዝና
ሊያደበዝዙት አልቻሉም፡፡ከንጉሳዊ ቤተሰብ ስለመወለዳቸው ተኩራርተው ሲናገሩ አይደመጡም
ትሁት ናቸው፡፡ ለሰራተኞቻቸው፤ለተከታዮቻቸውናለረዳቶቻቸው በጣም ጥሩ ሰው ነበሩ፡፡
118
ፍትሕ የተጓደለች መስሎ ከተሰማቸው በጣም ሊናደዱ ይችላሉ፡፡ከዚህ ባለፈ ከልጃቸው ጋር
ደግሞ ቼዝ ሲጫወቱ መሸነፍን ይጠላሉ፡፡

በሳቸውም ሆነ በሚስታቸው የዘር ግንድ ውስጥ ታዋቂ ስሞችን ማግኘት ይቻላል፡፡ ንጉስ
ሳህለሥላሴ፤ራስ መኮንን፤ኃይለሥላሴ፤ራስ ጎበና አቲከም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ልጃቸው ሚካኤልን
ለምን የእምሩን የአባት ዘር አልተከታተላችሁም ብዬ ጠይቄው ለምን እንደሆነ አያውቅም ፡፡
የእምሩ ቅምአያት እርገጤቃል መንዝ ውስጥ በመሬት ተጣልተው ሰው ገድለው በቀል እና ከገደሉት
ሰው ቤተሰቦች ጋር የሚካሄደውን እሰጥ አገባ ለመሸሽ ሊሆን ይችላል ወደ ተጉለት ሄዱ፡፡ ሚካኤል
ይህን አያውቅም፡፡ታሪኩን ስነግረው ቤተሰቡ በሃይለኝነታቸው በጦረኝነትና በአደን ስለሚታወቅ
ሊሆን እንደሚችል ያምናል፡፡ እምሩም የዘር ሆኖባቸው ይሄን መንፈስ ይጋሩታል፡፡ አጎታቸው
ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ በፊትአውራሪ ገበየሁ ይታዘዙ ከነበሩት ሁለት የጦር ምክትል አዝማቾች
አንዱ ሆኖ በአጼ ምኒሊክ ስር አድዋ ላይ ሲዋጋ ሞቷል፡፡ አባቱ ቀኛዝማች አባይነህ እርገጤቃልም
በጦርነቱ ሞተዋል፡፡እምሩ ስለዚህ የዘር ግንዳቸው የማይናገሩበት ምክንያት አይታወቅም
ምናልባትም የእርገጤቃል ትዝታ ያሳፍራቸው ይሆናል፡፡ ቤተሰባቸው ግን ቀድሞም ሆነ አሁን
መንዝ ካሉት ዘመዶቻቸው ጋር በጥሩ ሁኔታ ይገናኛሉ፡፡

195
ጥቋቁር አናብስት

እምሩምንም እንቅፋት ቢያጋጥማቸው መዘዙ ቢከፋም ላመኑበት ነገር የሚቆሙ የማይናወጥ አቋም
ያላቸው ሰው ናቸው፡፡የልጅነት የሃያል ጦረኝነታቸውና ጥብቅ ገዢነታቸው ምስል በተራማጅ
ለውጦቻቸውና በፍትሓዊ አስተሳሰባቸው ተሸርሽሮ ጠፍቷል፡፡ ቆይቶ «ከጊዜያቸው የቀደሙ»
የሚያስብላቸውን ሀገርን የማዘመን ትግል በሁኔታዎች ለመርጋት ፍላጎት ካላቸው ሃያላን በስተቀር
በተቀሩት ዘንድ ሁሉ ይበልጥ ታዋቂ አድርጓቸዋል፡፡ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ተነስተው ለውጦች
ሲመጡ እንደ 1967 የመሬት አዋጅ ያሉ እምሩ ከገመቷቸውም በላይ ነበሩ፡፡ ቢያንስ በአብዮቱ
ለጋ አመታት በአንዳንዶቹ ለውጦች ሳይደሰቱ አይቀሩም፡፡ በአብዮቱ መሪዎች ሳይቀር እስከእለተ
ሞታቸው ድረስ ተከብረው ነው የኖሩት፡፡

የተርጓሚ ማስታወሻ-የልዑል ራስ እምሩ እኔበእንተእኔ ካየሁት ከማስታውሰው በሚል ርእስ


ለህትመት በቅቷል፡፡

ማስታወሻ

1)ሙሉ ሕይወታቸውን ራስ አልነበሩም በእርግጥ ሌሎችምሹመቶች ነበሯቸው፡፡ በመጨረሻም


የንጉሳውያን ቤተሰቦች ብቻ ማግኘት የሚችሉት ማአረግ ልኡል ራስ ሆኑ፡፡ ያም ቢሆን በተለምዶ
ራስ እምሩ በሚባለው መጠሪያቸው ይታወቃሉ፡፡

2)ከግለታሪካቸው ለቤተሰባቸው የሰጡት የመጀመርያውን ጥራዝ ብቻ ነበር፡፡ ሌሎቹ ቅጂዎች ግን


ቤተሰቡ ከማያውቃቸው ሰዎች ዘንድ(በደህና ቦታ ተቀምጠው ነበር) በአብዮታዊት ኢትዮጵያ ራስን
ለማቆየት ዋነኛ ዘዴው ሚሥጥራዊ መሆን ነበር፡፡

3)ምንም እንኳን ምንጬ በታሪኮቹ ውስጥ ሸሪክ የነበረና ለማሰማመር ቤተሰባዊ ፍላጎት
ቢኖረውም፡፡ቀጥተኛ እውነታዎቹን ለማጣመም የሚያበቃ ነጥብ ያለ አይመስለኝም፡፡ ግምት ግላዊ
ነው፡፡ የአንድ ሰው እይታ ደግሞ የሌላውን ያህል ዋጋ ሊኖረው ይችላል፡፡

4)ሚካኤል እምሩ የኔን የታሪኩን ክፍል አላነበበውም፡፡ የነገረኝን ታሪክም እና በእራሴ ቃላት
በድጋሚ የተናገርኳቸው አህጽሮት ነው፡፡ ምንአልባትም የተወሰነውን መቀየር ፈልጎ ሊሆን ይችላል፡

5)ጥናቴን የጀመርኩት በቀድሞ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪ ጥናት በማንበብ ነው፡፡ተማሪው
መረጃዎቹን ያገኘው ከተለያዩ ምንጮች ሲሆን ሚካኤል እምሩንና ራሳቸውን እምሩ ጨምሮ

196
ጥቋቁር አናብስት

ልጆቻቸውን ለማግኘት ይችል የነበር ቢሆንም ጥናቱ ግን በስህተት የተሞላና ለታሪካዊ ሰነድነት
መብቃትም የማይችል ነበር፡፡ ይሄ መሆኑ የሚያሳዝን ነበር፡፡

6)ኦክስፎርድ የተማሩት ሚካኤል እምሩ ከዚያ በፊት በተለያዩ ሹመቶች ላይ የሰሩ ቢሆንም
በUNCTAD የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ሳለ ነበር ወታደራዊው መንግስት ኃይለሥላሴን ገልብጦ
ስልጣን የያዘው፡፡ አዳዲሶቹ መሪዎች ከጄኔቫ ጠርተውት ለተወሰነ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር
ቀጥሎም የፖለቲካ አማካሪ ሆኖ ሳለ ነበር ራስ እምሩ እ.ኤ.አ በ1980 ያረፉት

7)የአጼ ኃይለ ሥላሴ የመጀመርያ የአክስት ልጅ ነች፡፡ እናቷ እህተ ማርያም የራስ መኮንን እህት
ነበረች፡፡ እናታቸው ተናኜ ወርቅ የሸዋው ንጉስ የሣህለሥላሴ ልጅ ነበረች፡፡

8)አባቱ (የእምሩ አያት)ቀኛዝማች አባይነህ ከመንዝ ተጉለት የተገኙ የንጉስ ሚኒሊክ ታዋቂ ጭፍራ
ናቸው፡፡ኃይለሥላሴ ተወዳጁ ልጃቸውም ፈጣን አእምሮ የነበራቸው ጠንካራ ነበሩ፡፡

9)እናቷ ወለተየስ ሃይሌ ስትሆን ከባለጠጋ የተጉለት ቤተሰብ የተገኘች ነች፡፡

10)ራስ መኮንን በኋላ የጣይቱን ወንድም ሴት ልጅ የሆነችውን ምንትዋብ ወሌን በጣይቱ ምክር
አገቡ፡፡“ምክንያቱም የመኮንንን ዝምድና ስለሚፈልጉ” ምንትዋብ በጣም ወጣት ነበረች ምንአልባት
13 ወይም 14 አመት መኮንንም ከመጋባታቸው በፊት ጥቂት መጠበቅ ፈለጉ፡፡ ይሄ ጣይቱን
አስከፋቸው፡፡ እንዲፋቱም አስገደዱ፡፡ ምንአልባት ምንትዋብ ቅሬታዋን ነግራቸው ሊሆን ይችላል፡፡
(በኋላ ራስ ከበደ መንገሻን ያገባች ሲሆን ሳትወልድ በልጅነቷ ነው የሞተችው)

11)አባቶቻቸው ባለስልጣኖች ሲሆኑ ስራ ይበዛባቸዋል፡፡ለጉዞም ይወጣሉ፡፡

12)ሃረር ከባቡር መንገዷ ከተማ ድሬ ዳዋ አቅራቢያ የምትገኝሞቅ ያለች ከተማ ስትሆን ከአዲስ
አበባ የተሻለች ዘመናዊ ከተማ ነበረች፡፡ የካቶሊክ ሚስዮኖች ከአዲስ አበባ በ1979 ተባረው ሀረር
ላይ በ1980 ስራቸውን ሲጀምሩ መኮንን የትምህርታዊ እንቅስቃሴያቸው ደጋፊ ነበሩ፡፡ ተፈሪን
(ከመጀመርያ ጋብቻቸው የተገኘ ብቸኛ ልጃቸውንና)እምሩን እንዲማሩ ላኩ፡፡ እነዚህ ሁለቱ
በትምህርት ቆይታ ዘመናቸው እኩል ትምህርት ነው ያገኙት፡፡

13)በኋላ በሀሮማያ ሀይቅ ከተፈሪና ከሌሎች ሶስት ሰዎች ጋር የሚጓዝበት መርከብ ሲሰምጥ
የሞተ፡፡ በዚያ ጉዞ ላይ ተፈሪ ሚስታቸውን ይዘው በቅርብ የሞተ ዘመዳቸውን ለመቅበር ወደ
197
ጥቋቁር አናብስት

አለማያ እያመሩ ነበር፡፡ ተፈሪ ለጥቂት ከሞት የተረፉ ሲሆን ግሪካዊው ዶክተር ዜርቮስ ሙሉ
በሙሉ ተዳክመው የውሃው ዳርቻ ሲደርስ ነፍስ እንዲዘሩ አግዟቸዋል፡፡

14)ይልማ መኮንን በልማድ ጋብቻ ወይም በመሳሰሉት የሚወለዱ የተፈሪ በአባት በኩል የሚገናኙ
ወንድም ናቸው፡፡ በጥቅምት 12 1907 ከአባታቸው ሞት በኋላ የሃረር ገዢ በሆኑ (መስከረም
1906)ከአንድ አመት በኋላ ሞቱ፡፡

15)የራስ መኮንን የወንድም ልጅ ሴት ልጅ ነች

16)የንጉስ ሳህለ ስላሴ ውላጅ ነው

17)ከዚያ በፊት ጀርመናዊ አስጠኚ ለተወሰነ ወቅት ነበረው

18)መጀመርያ በኢንጅነር ኢልግ ቤት ውስጥ እሪ በከንቱ አካባቢ ነው የተገኘው፡፡ ቀጥሎበራስ


ወይም ንጉስ ሚካኤል መኖርያ (ከአብዮቱ በኋላ የፖለቲካ ትምህርት ቤት የሆነው) ወደ አሁኑ
ቦታው ከመዛወሩ በፊት፡፡የመጀመርያዎቹ መምህራን ግብጻውያን ኮፕቲኮች ነበሩ

19)ሌላው እኩሌታ -አለታ- ለራስ ናደው አባ ወሎ እንዲያስተዳድሩት ተሰጣቸው፡፡

20)ከይልማ ሞት በኋላ የአካባቢው ገዢ ከሆኑት ባልቻ ቀጥሎ

21)የእያሱ እህት ስህነና የአምባሰሉ ዣንጥራር አስፋው ልጅ ነች፡፡ በእድሜ በብዙ ከሚበልጥዋት
ራስ ልኡል ሰገድ ጋር ልታደርገው የነበረውን ጋብቻዋን እያሱ ከሰረዙባት በኋላ ነበር ለተፈሪ
የተሰጠችው

22)አባተ ከድርድር በኋላ እጃቸውን ሰጡ፡፡ እያሱና ደጋፊዎቹ እንደማይነኳቸው ቃል


ገብተውላቸው የነበር ቢሆንም ቃላቸውን ግን አልጠበቁም፡፡ሃብተ ግዮርጊስ ከጥቂት ማመንታት
በኋላ ከእያሱ ጎን ተሰልፈዋል፡፡

23)ሚኒሊክ መጀመርያ የአንጎል ምት መቋረጥ የደረሰባቸው እ.ኤ.አ በ1906 ነበር፡፡

198
ጥቋቁር አናብስት

24)እያሱ ወደ ስልጣን ያደረጉት ጉዞ አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ ንግስት ጣይቱም ከሃይል አሰላለፉ
ተወግደው በእንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስትያን እስከተቀመጡበት ጊዜ ድረስ ስልጣኑን ለማግኘት
ይፈልጉ ነበር፡፡ ወደ እንጦጦ የሄዱበት መንገድ ሰላማዊና ምንም ደም ያላፋሰሰ ነበር፡፡

25)በተጉለት ገዢ የነበረና የታዋቂው የምኒሊክ ጄኔራልና የሸዋና የኦሮሞ ህብረት መሀንዲስ የራስ
ጎበና ልጅ ነበር፡፡

26)ታላቋ ሴት ልጃቸው የምስራች መጀመርያ የብላቴን ጌታ ኅሩይን ልጅ ፍቃደ ስላሴን አገባች፡፡


ከሱም ሴት ልጅ ወልዳ ነበር፡፡ አለም ሰገድ(በ1970ቹና 80ቹ በኢትዮጵያ ታዋቂ ጋዜጠኛ የነበረች
ሲሆን ያገባችውም ልጅ አባተ የራስ አባተ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ከሁለቱ የምትወለደው ሴት ልጅ
በአሁን ወቅት ዶክተር ሆና ታገለግላለች፡፡ ፍቃደ ስላሴ የካቲት 12 1929 በጣልያኖች ተገደለ፡፡
የምስራች ቆይታ ታዋቂውን ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ትእዛዝን አገባች፡፡ እኚህ ሰው የመጀመርያው
የኢትዮጵያ ሴት ጸሃፊ እና በሌሎችም መስኮች የሚታወቁት የታዋቂው የከንቲባ ገብሩ ደስታ ልጅ
የስንዱ ገብሩ የመጀመርያ ባለቤት ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን ቃል ብትገባልኝም ስንዱ ግለ ታሪኳን
እንድታጫውተኝ ወይንም እንድትጽፍልኝ ማድረግ ሳልችል ኢትዮጵያን ለቀቅኩ፡፡ ከሌሎቹ የራስ
እምሩ ልጆች መሃል ማርታ የበጌ ምድር ገዥ የነበሩትንና በአብዮቱ ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር
የተገደሉትን ኮነሬል ታምራት ይገዙን አገባች፡፡ ሂሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር ስትሆን ዮዲት ደግሞ
ሚኒስትር ሆነች፡፡ እሌኒ የጎንደር ህብረተሰብ ጤና ኮሌጅ ዲን የሆነ አንድ ዶክተር አገባች፡፡ሩፋኤል
ተመራማሪ ሆነች፡፡ ማምዬ የንድፍ ባለሙያ ሆነች ፡፡ አራቱ ሴት ልጆች አላገቡም፡፡ ብቸኛ ወንድ
ልጅ የሆነው ሚካኤል ከኦክስፎርድ ተመረቀ፡፡ የፊት አውራሪ ተክለሐዋርያት ልጅና የግርማቸው
እህት የሆነችውን ወይዘሮ አልማዝን አገባ፡፡ ሚካኤል አንድ ሴትና አንድ ወንድ ልጆች አሉት፡፡

27)በወሎ የሚገኘው ሚካኤል ከሁለተኛ ሚስታቸው እና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የተቀበሩበት


ተንታ ሚካኤል አለቃ እንደነገሩኝ ከሆነ የእያሱ ወላጆች ሌላም በ12 አመቱ የተቀጨ እና እዚያው
አቅራቢያ ጫጫ ላይ የተቀበረ ልጅ አላቸው፡፡ ይሄ ግን ትክክል ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ (ጫጫ
ላይ ለማረጋገጥ ሞክሬ የሚያውቅ ሰው አላገኘሁም)የእያሱ እናት (የምኒሊክ ልጅ )ሸዋ ረጋ
ከደጃዝማች ወዳጆ የወለደችው ሌላ ታላቅ ልጅ አላት፡፡ በቤተመንግስቱ የተወሰነ ዓመት ከቆየና
ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ለተወሰኑ አመታት ከተማረ በኋላ በለጋ እድሜው አርፎ በስላሴ
ቤተክርስትያን ተቀብሯል፡፡ ከዚያ በኋላ ነበር የምኒሊክ ምርጫ እያሱ ላይ ያረፈው

28(የተነገረኝ ቀን መስከረም 16 ነው፡፡ ያ ቀን ግን በእምሩ ማስታወሻዎች ላይ ይገኝ ወይም


በልጃቸው ስህተት 17ኛው ተብሎ ይነገረኝ አላውቅም፡፡ እምሩ ከፖለቲካ ሕይወት ውስጥ

199
ጥቋቁር አናብስት

በቅርበት ተሳትፎ ስለነበራቸው አብዛኛው በዚህ ምእራፍ ላይ የሚገኘው መረጃ በተዘዋዋሪ ስለ


እምሩ ብቻ ነው፡፡ምናልባትም እምሩ ስለ እነዚህ ክስተቶች የጻፉባቸው እውነተኛ መዘከርያዎች
ናቸው፡፡ ምንም ነገርን ለማስተካከል አልሞከርኩም አቀራረቡ ላይም ጥያቄ አላነሳሁም፡፡
ስለፖለቲካ የቀረቡ ግምቶች ካሉ የእምሩ ናቸው፡፡ (በራሳቸው ልጅ ሚካኤል የተነገረና
ማስታወሻቸው ላይ ያለ ነው)የራሴን ግምቶች እራሴው ጋር አስቀርቻቸዋለሁ።

29)በወቅቱ በልጅ በኋላ ራስ ደስታ ትግራይ ውስጥ ነበር የተያዙት፡፡ በራስ ካሳ አማካኝነትም ፍቼ
ላይ እ.ኤ.አ በ1921 ታሰሩ፡፡ አምልጠው ጎጃም ውስጥ በ1932 ተያዙ፡፡ ቀሪውን የእድሜ
ዘመናቸውን በእስር አሳልፈው በ1936 ምናልባትም በግድያ በኢጣልያ ወረራ ዋዜማ ሞቱ፡፡
ምንአልባትም ብዙዎች እንደሚገምቱት ጋራ ሙለታ ሳይሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው የተገደሉት፡፡

30) አንዳንዶች ነበር ብለው ቢከራከሩም ይሄ ከመጀመርያውም በግልጽ ያልተቀመጠና


ያልታቀደበትም ነበር፡፡ ተፈሪ «የስልጣን ቴክኒሻኑ » እ.ኤ.አበ1928 እስከተቀቡበትና በ1930
አጼ ተብለው እስከነገሱበት ጊዜ ድረስ በስልጣን ከፍ ከፍ እያሉ የመጡት በዘውዲቱ ዘመነ ግዛት
ነበር፡፡

31)መጀመርያ ለ ንጉስ ዮሃንስ ልጅ ለራስ አርአያ የተዳረች ሲሆን ነገር ግን እሳቸው እ.ኤ.አ
በ1888 ሞቱ፡፡ (ያልተወለደው ልጃቸው አንዳንዶች የጨነገፈ ልጅ ወልዳለች ቢሉም እንደዚያ
ከሆነ ብቸኛው የዘውዲቱ እርግዝና ይሆናል)የምንሊክን አልጋ ሊወርስ የታሰበ ነበር ማለት ነወ፡፡
በርካታ ባሎች የነበሯት ቢሆንም ግን ንግስት ስለሆነች ግን አሁን አልቻለችም፡፡ ስለዚህም ለዙፋኑ
አልጋ ወራሽ ወይንም እንደራሴ ተመደበላት፡፡

32)ተፈሪ ሀረርን እንዲለቁ በእያሱ ተነግሯቸው ነበር፡፡ ቆይቶም አዲስ አበባንም እንዲሁ ለቀው
ወደ ከፋ በፍጥነት እንዲሄዱ ተነገራቸው፡፡ መነን ግን በእምሩ አማላጅነት ቆይታ ልጇን
እንድትገላገልና እንድታስጠምቅ ተፈቀደላት፡፡ እያሱ ሃረርን በቀጥታ ተቆጣጠሩ፡፡ ይህም
አካባቢውን በማእከላዊ መንግስት ስር በቀጥተኛ ቁጥጥር ስር የዋለ “መአድ ቤት ”አደረገው፡፡

33)ከጥርጣሬያቸው የተነሳም ከተከታዮቻቸው መሃል ደጃዝማች ወልደ አማኑኤልን


(1960ቹና 70 መጀመርያ የሃረር ገዢ የነበሩት የደጃዝማች ወርቅነህ አባት) ወደ አለማያ ምን
እየተደረገ እንደሆነ እንዲያዩላቸው ላኳቸው፡፡ ወልደ አማኑኤል ከሃረር ለእያሱ ደውለው ከአዲስ
አበባ የመጣ ጦር ሃረርን እየከበበ እንደሆነ ተናገሩ፡፡ እነሱም ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋና
ከጨርጨር የመጡ ሲሆን ተከታዮቻቸውም ነበሩ፡፡ደጃዝማች ገብሬ ከአዲስ አበባ ከመጡት
200
ጥቋቁር አናብስት

ሃይሎች ጋር አንድነት ሲገቡ እያሱ በታጠቁ ሶማሌ የሀረሪና የኦሮሞ ሃይሎች መከላከያ ሀይላቸውን
ገንብተው ነበር፡፡ ነገር ግን በጦርነት ምንም የድል ተስፋ እንደሌለ ገብቷቸው ነበር፡፡ ስለዚህ
ለማምለጥ ሞከሩ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን እምሩ በእጀ ሙቅ ተቀፍድደው ነበር፡፡

35በባህሉ መሰረት በእጀ ሙቅ የተቆራኙት ከአንድ ታማኝ ተከታያቸው ጋር ነበር፡፡ አበበ ወልዴ
ይባላል፡፡

36)እያሱ ተፈሪን የከፋ ገዢ አድርገው ሾመዋቸው ነበር፡፡ ተፈሪ ደግሞ በጊዜው አዲስ አበባ
ውስጥ ሆነው ወደ ከፋ ለመሄድ በመዘጋጀት ላይ ነበሩ፡፡ ነገር ግን የሴራው ዋና ጠንሳሽና የጦር
ሚንስትሩ ሃብተግዮርጊስ አዘገዩዋቸው

37)እዚያ ስላደጉ በጀርባ ያለች በር በሌሊትም የተከፈተ በር አግኝተው ሰንሰለቱን እንዳያንቃጭል


በጨርቅ ጠቅልለው እንዳይሰማ በማድረግ የሀረር በሮች በሌሊት የሚዘጉ ቢሆንም ከቅጥሩ ውጪ
መውጣት ችለዋል፡፡ ያን ያህልም ረዥም ስላልሆኑ ምንአልባትም በአጥሩ ላይ ተንጠላጥሎ
በመውጣትም ሊሆን ይችላል፡፡ የተወሰኑ ቤቶችም ተጠጋግተው ከአጥሩ ጋር ተሰርተዋል፡፡(ይህም
ከውጭ የሚመጣውን ለመከላከል እንጂ ወደ ውጪ የሚወጣውን ለማገድ አልነበረም)

38)በመጀመርያ የሄዱት ወደ አንድ ታማኝ በቅርብ ያለ ወዳጃቸው ቤት ሲሆን (እሳቸውንና


የተቆራኙትን ሰው ካላቀቋቸው በኋላ) ትንሽ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው መድሃኒያለም ደብር አለቃ
ዘንድ ወሰዷቸው፡፡ እኚህን አለቃ ያምኗቸውም ይተዋወቁም ነበር፡፡ በመልስ ጉዞዋቸው ላይ ወደ
ሃረር ብቅ ብለው ማንም ተቆጣጣሪ እንደሌለና መረጋጋት ካልሰፈነ በማንኛውም ሰአት አመጻ ሊነሳ
እንደሚችል ዘገቡ፡፡ እያሱ በዚህ ጊዜ ከቤተመንግስቱና ከከተማው ተሰደው ወደ አዳል በየረር በር
በኩል አምልጠዋል፡፡

39)የሀረር ሃደሬ ህዝቦች በምንም አይነት በጦር እንደማይስተካከሉ በማመን እጅ ሰጥተው


መሳርያቸውን አስረከቡ፡፡ የአብዱላሂ አሊ ሳዲቅ ዘመድ እንደነገረኝ የሶማሌ መሪዎች የተረፉት
በአብዱላሂ ቤት በመሸሸግ ነበር፡፡ ነግር ግን መንገድ ላይ የሚገኙ በመቶዎች አንዳንዶች በሺዎች
የሚቆጠሩ የሱማሌ ዜጎች ተገድለዋል ቢሉም የእምሩ ቤተሰቦች ትንሽ ሰዎች ናቸው የሞቱት ብለው
ያሳንሱታል

40)ከዚህ በኋላ ጦራቸው ወዳለበት ጨርጨር ሲመለሱ ባልቻ በእያሱ ደስተኛ አልነበሩም

201
ጥቋቁር አናብስት

41)አባተ የብዙ ችሎታዎች ባለቤት ነበር። ሀገር ወዳድና አርበኛ ከመሆናቸውም በተጨማሪ
ለምኒሊክ እንደ መሃንዲስም ነበሩ፡፡ እራሳቸውን በራሳቸው ያስተማሩ ተወዳጅ ሰው ነበሩ፡፡

42)አባተ በእያሱ የመውደቂያ ጊዜ ተለቀቁ፡፡ ለአጭር ወቅት በ1917 እስከ ሚሞቱም ድረስ
የወሎ ገዢ ሆኑ፡፡ ደብረ ሊባኖስም ተቀበሩ

43)ቤተክርስቲያኑ በራስ ጎበና የተሰራ ሲሆን ንግስት ዘውዲቱ ከንግስናዋ በኋላ አሳድሳዋለች

44)ይሄ ለሁሉም ሳይሆን የመጀመርያው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክትር ማርቆስ ሃና የግብጽ


ኦርቶዶክስ ተከታይ ሲሆኑ ኢትዮጵያዊ ሚስት የነበራቸው ሲሆን የልጅ ልጆቻቸው በሕይወት
ነበሩ፡፡ አንዱ ልጅም የኃይለሥላሴ ሚኒስትር ነበር

45)በመኮንን ቤትና በሚኒሊክ ቤተመንግስት አብሯቸው ባደገውና በ 10ዓመት አካባቢ


የሚበልጣቸው ተክለሐዋርያት ጋር ግን እንደዚህ አልነበረም፡፡ ከራስ መኮንን ጀርባ ተፈናጦ ከራስ
መኮንን ጸሃፊ ለሆነው እዚያው ከሞተው ታላቅ ወንድማቸው ጋር በአድዋ ጦርነት ላይ ተገኝተው
ነበር፡፡ ቆይቶ ወታደራዊ ስልጠናዎችን በሩስያ የግብርና ስልጠናዎችን በእንግሊዝና ፈረንሳይ
ከተከታተሉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡

46)በእርግጥ እምሩ ነበሩ ለአባታቸው ይሄንን ነገር ያዘጋጁት፡፡ እምሩ ደጃዝማችነትን ሲሾሙ ገና
ወጣት ነበሩ፡፡ በመጀመርያ ከሳቸው በእድሜ የሚበልጡ ስላሉ ላለመሾምም አመነቱ፡፡ እምሩ «የኔ
ታላቅ የሆኑ ይህ ስልጣን የሚገባቸው ብዙ ሰዎች አሉ»ሲሉ ተናገሩ፡፡ ለተፈሪ ጠባቂ የነበሩትና
የተፈሪ ታላቅ ወንድም ይልማ በሃረር ገዢነት ሲላኩ እንደ አማካሪያቸው የነበሩትቀኛዝማች ቆለጭ
አንዱ ነበሩ፡፡ እምሩ በተጨማሪም ከአባታቸው የሚበልጥ ክብርን ላለማግኘትም ፈልገው ነበር፡፡
ይህ ችግር ሁለቱንም አባቱንና ቆለጭን ወደ ደጃዝማችነት በማሳደግ ሊፈታ ችሏል፡፡

47)እንደ ነባር ሚኒስትርነታቸው ይገዙ በወቅቱ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር ጋር


ይተካከሉ ነበር፡፡

48)እኒህ ሃሳቦች በኦሮምኛ መቅረብ ነበረባቸው፡፡ እምሩ ደግሞ አይረዱትም

49)ጡረታ የወጡ ወይም ባስፈለገው ጊዜ የሚጠሩ ወታደሮች ለመተዳደርያ እንዲረዳቸው መሬት


ይሰጣቸው ነበር፡፡ መሬቱ ላይ ያሉት ጭሰኞች ሆነው በመጨረሻም ወደ መንግስት የሚዘዋወሩ
ሲሆን ለነሱ ገባር ሆነው ይቀጥላሉ
202
ጥቋቁር አናብስት

50)ደጃች ነሲቡ በ1932 የባሌ ገዢ ሳሉ ተመሳሳይ ስሪት አስተዋውቀው ነበር

51)የራስ ሃይሉ በለው ታላቅ ወንድም ሲሆኑ የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት የልጅ ልጆች ነበሩ

52)ራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖት (ቀደም ብለው ስዩም በሚለው መጠርያ ይታወቁ የነበሩ ሲሆን
በምልኪ ምክንያት ስማቸውን ቀይረዋል)የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት ልጅ ሲሆኑ እ.ኤ.አ
በግንቦት 27 1932 ተይዘው ታስረዋል፡፡ እያሱ እንዲያመልጡ ረድተዋቸዋል ተብለው ተከሰሱ፡፡
ወደ ሃረርጌም በእስረኝነት ተላኩ፡፡ ነገር ግን እሳቸውና እያሱ በአንድ ቦታ አልታሰሩም ነበር፡፡
የሃይሉ ልጅ ሰብለ ወንጌል ከእያሱሚስቶች መሃልና የአለም ጸሃይ እናት ነበሩ፡፡አለም ጸሃይን
በ1988 ጉለሌ ያለው ቤቷ አግኝቻት ነበር

53)የእምሩ ቀጣይ ሁለት ልጆች አዲስ አበባ ውስጥየተወለዱ ሲሆን የመጨረሻው እምሩ ጦር
ግንባር ላይ እያሉ በጦርነቱ ወቅት አምቦ ነው የተወለደው፡፡

54) እንደ ንጉስነታቸው ሙሉ ኢትዮጵያ የሳቸው ግዛት ነች፡፡ የበፊት ነገስታት ማንኛውም ሰው
እንደሚኖረው አይነት የግል መሬት አልነበራቸውም፡፡

55)ከዚያ ቀደም ብሎ በ1926 ተፈሪ ከበደ መንገሻ አቲከምን ከተመሳሳይ ገዚነት ስልጣን ላይ
አንስተዋቸው ነበር

56)እንደዚህ ያሉ ነገሮች እንግዳ አይደሉም፡፡ ዳግማዊ ቴዎድሮስ በነገሱበት ዘመን ከስልጣናቸው


የወረዱ የቀድሞ ገዢዎች የነበሩ ሲሆን ንጉሱ በማሾፍ መልክ «አጼ» ብለው ይጠሯቸው ነበር፡፡

57)የዘውዲቱ የመጨረሻ ባል ራስ ጉግሳ ወሌ የአባታቸውን ሀገር የጁን በገዢነት ለማስተዳደር


እንደ ቅድመ ሁኔታአመጹን እንዲያፍኑት ተነግሯቸው ነበር፡፡እሳቸው ግን በፋንታው ከአማጺያኑ
ጋር አብረው ማእከላዊውን መንግስት ለመውጋት ተዘጋጁ፡፡ ይህ ደግሞ በአንቺም ላይ በተደረገው
ጦርነት እ.ኤ.አ በመጋቢት 13 1930 ለሽንፈት ዳረጋቸው፡፡

58)ሌሎች ከየጁ የመጡ ሰራዊቶች ደግሞ በአበበ ዳምጠው ይታዘዛሉ(የፊት አውራሪ ዳምጠው
ልጅና በሩስያ ቅዱስ ፒተርስበርግ የሚኒሊክ ወኪል የራስ ደስታ ዳምጠው ታላቅ ወንድምና የኃይለ
ሥላሴ ታላቅ ልጅ ተናኜ ወርቅ ባል)አበበ በኋላ በነሲቡ ስር ሆነው ጣልያኖቹን በሃረርጌ ወግተው
በኋላ ወደ ስደት ሄዱ ፡፡ ወደ ወረራው ማብቂያ ላይ ካርቱም ያሉትን የጌድዮን ሃይሎችን ተቀላቀሉ
203
ጥቋቁር አናብስት

59)ልኡል አልጋ ወራሽ የወሎ ገዢ በሆኑበት የ1932ወቅት የወሎአካባቢ ላስታንና ምንአልባትም


ወረኢሉን ጨመረ፡፡ በፊት ሚኒሊክ የጁንና ምስራቃዊ የአማራውን ክፍል ለሚካኤል የዘሮቹ
መሬት ነው በማለት መርቀውለት የነበር ቢሆንም ከሰገሌ ጦርነት በኋላ ሚካኤል ሲሸነፉ ወሎ
የተወሰነ መሬት አጣች

60)ከዚያ በፊት ወደ ውጭ ሃገር ወጣ ብለው የነበር ሲሆን እሳቸው ተፈሪና ሌሎች ሆነው እያሱ
ጅቡቲን ሊጎበኙ በ1915 በሄዱበት ወቅት አጅበዋቸው ሄደው ነበር

61)ከዚያ ቀደም የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን ቆይተው ደጃዝማች ሆኑ፡፡ ደብረታቦር
ተወልደው በ1947 አ.ም ጎንደር ሞቱ

62)በውልደታቸው ብቻ የጎጃም ገዢ መሆን ሲችሉ የነገስታት ዘር የሆኑት የእቴጌ ምንትዋብ ሶስት


ልጆች መሃል አንዷየሆነችውን ወይዘሮ ወለተ እስራኤልን በማግባት የንግስና ዝርያ ለልጆቻቸው
ትተው አልፈዋል፡፡በዘመነ መሳፍንቱ (ጀምስ ብሩስ ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ከአንዷ ልጅ አስቴር ጋር
የቀረበ መግባባት ነበራቸው)

63)ሚኒሊክ ተክለሃይማኖት በከፋ ላይ የነበራቸውን የይገባኛል ጥያቄ በድል አድራጊነት


ተወጥተውታል፡፡ እንደ ወሎ ሁሉ ከጎጃም አንዳንድ ክፍሎችን የወሰዱ ሲሆን ጎጃም የተረጋጋ
ድንበር አልነበራትም

64)ከጎጃሙ ራስ መስፍን ጋር ተጋብታ ነበር

65)የእምሩ አብዛኛው መሬት እሳቸው ባላስተዳደሩበት አሩሲ ይገኛል፡፡ ሃረርጌ ውስጥም የከተማና
የገጠር ቦታ አላቸው፡፡ ድሬ ዳዋም እንዲሁ ቤቶችና መሬት አላቸው፡፡ ጉደር አምቦ አቅራቢያ ለድሃ
ጭሰኞችና ገበሬዎች የሰጡት ቦታ ከራስ መኮንን የወረሱት ነበር፡፡ የተወሰነውን ክፍል ለእርሻ
ትምህርት ቤት ሲሰጡገሚሱን የወይን መሬት ለሴት ልጆቻቸው ሰጥተዋል

66)ይህ አካባቢ በጎጃም አካልነት ስለማይታወቅ እንደ ጎጃም ክፍል አይቆጠርም

67)ኃይለ ሥላሴ የድሮና የአሁኑን ለማዛነቅ ይሞክሩ ነበር

68)በሎንዶን የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን በ1960ዎቹ የመጨረሻ የሹመት ዘመናቸውን


አሳልፈዋል
204
ጥቋቁር አናብስት

69)የሆለታ አይነት ወታደር ነበር

70)የጎጃም ቤተክርስትያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አካል ቢሆንምበክርስቶስ ባሕርይ ላይ የተለየ


ቀኖና የሚያራምዱ የተገነጠሉ አካላት ናቸው

71)በኢትዮጵያ ያሉ የውጪ ሃገር ዜጎች ካዩት የቆየ ቢሆንም ግኮቹና ፈረንሳዮቹ የሃረርጌ ገዢ ሳሉ
ሸልመዋቸዋል፡፡

72)ከአዲስ አበባ ባመጡትልምድ ባለው ትንሽ ጦር እየተረዱ ነው ይህንን ያደረጉት

73)ኋለኛው የተለመደ ድርጊት ሲሆን ገዢው የለቀቀበት ክፍለ ሃገር ውዥንብር ውስጥ የሚገባበት
ልምድ አለ

74)ከጦርነቱ በፊት ኤርትራ ካሉ ጣልያኖች ጋር ግንኙነት ነበረው የሚል ጥርጣሬ አለ

75)የስለላ አውሮፕላኖችን የጠላት መገኛን ለማወቅ ተጠቅመዋል

76)ደጃዝማች ሃይሉ ከበደ የዋግ ሹም ከበደ ልጅ ሲሆኑሌላው ቢትወደድ መኮንን ደምሰው በዚህ
ጦርነት መልካምጀብድ ፈጽመዋል

77)ዋናው የሽምቅ ውግያ መሪ ሻለቃ ዮሃንስ አብዱ ነበር

78)ኃይለ ሥላሴ በዚህ ወቅት ካሳ የት እንዳለ አያውቁም ፡፡ ካሳ እምሩን ወደ ተምቤን እንዲመጣ


ማዘዛቸውንም እንዲሁም አያውቁም ፡፡ ኃይለ ሥላሴ እምሩ እንዳስላሴ ያሉ መስሏቸው ነበር፡፡

79)ካሳን ግን እዚያ ማግኘት አልቻለም፡፤ዋነኛ ተልእኮው እሱ ነበር

80)ቆይቶ ከጣልያኖች ገብቶ በራስነት መአረግ ሹመውታል

81)የሃዲስ አለማየሁ ወንድም በመርዝ ጋዙ ጥቃት ሞቷል፡፡ ሃዲስ እራሳቸው ከእምሩ ጦር ጋር


ዘምተው የነበር ሲሆን ወደ ሱዳን ለተጨማሪ መሳርያ እስከተላኩበት ጊዜ አብረው ነበሩ

205
ጥቋቁር አናብስት

82)ደብረ ማርቆስ እያሉ አድርገውት ሊሆን ይችላል ወይንም እምሩን ለማግኘት መጥተው ከተማ
ከመግባታቸው በፊት ሊሆንም ይችላል

83)በራሳቸው ፍቃድ ከሾሟቸው ሹመቶች አንዱ ይሄ ሊሆን ይችላል፡፡ ነጋሽ በዛብህ ብዙውን ጊዜ
የንጉስ ተክለሃይማኖት ልጅ በመባል ይታወቃል ፡፡ እውነቱ ግን የበዛብህ ሴት ልጅ ልጅና
የፊትአውራሪ ወልደ ማርያም ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ለማንኛውም ግን ያደገው በበዛብህ በራስ ሃይሉ
ታላቅ ወንድም በአያቱ ቤት ውስጥ ሲሆን ስሙንም ያገኘው ከዚያ ነው፡፡ ነጋሽ በነሃሴ 1964
አ.ምአርፏል

84)ትሰሜ ዳርጌን ማለትም የሚኒሊክ የአጎት ልጅን የገባ ሲሆን የራስ ካሳ ሃይሉ የእንጀራ አባት
ነበር

85)በመኮንን እንዳልካቸው የሚነገረውን የተቃርኖ ታሪክ በግለ ታሪካቸው ላይ ይመለከቷል

86)እምሩ እንደተነገራቸው ከሆነ መኮንን እንዳልካቸው በኋላ በካይሮ አድርገውበካርቱም ወደ


ኢትዮጵያ ለመግባት ቢሞክሩምበእንግሊዞች እንደተከለከሉ ሲሆን፡፡ ለማንኛውም ለምሳሌ በልሁ
ኃይለ ሥላሴ ረዳት መኮንን እና ፍቃደ ስላሴ ህሩይ የብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ስላሴ ልጅ ከእንግሊዝ
ተመልሰዋል፡፡የመኮንንታሪክ የማይመስልነበር፡፡ እንደተነገረኝም መኮንን የጦርነቱን ጊዜ
በእየሩሳሌም ቀጥሎም በእያሪኮ አሳልፈዋል

87)የነጋድራስ በሃብቴ ልጅና የታምራት ይገዙ የልጅ ልጅ ሲሆን ከእምሩ ልጆች መሃል አንዷን
ሊያገባ የታጨ ነበር

88)በጋምቤላ በኩል ያለው መንገድ እስከ እ.ኤ.አ ታህሳስ 1936 ድረስ ክፍት ነበር

89)ከእነሱ መሃል ሻለቃ በኋላ ቀኛዝማች በልሁ የነበረበት ሲሆን በኃላ በየካቲት 12ቱ ጭፍጨፋ
ሞቷል፡፡

90)ፍቃደስላሴ ህሩይ ከጥቁር አናብስት ተዋጊዎች መሃል የነበረ ሲሆን፡፡ ደራሲዋ ስንዱ ገብሩ
ደግሞ ከጥቁር አንበሳ ተዋጊዎች ነርሶች መሃል ነበሩ

91)ከጦርነቱ በፊት በኃይለ ሥላሴ ታስሮ የነበር ሲሆን በኋላ በጣልያኖቹ ነጻ ወጥቷል፡፡

206
ጥቋቁር አናብስት

92)ስንዱ ገብሩ በጦርነቱ ወቅት ተማርከዋል

93)ወደ እምሩ ማረፍያ አካባቢ ለመድረስ በርካታ ጥረቶችን በረግረጉ በኩል ቢያደርጉም
በመትረየስ ተኩስ ተመልሰዋል

94)ከጅማ የመጡትን ሃይሎች የመራው ጄኔራል ፐሪንስቫሊን ባናደደ መልኩ ጄኔራል የተደረገው
የእምሩን የእጅ መስጠት ስላደራደረ ነው፡፡

95)የእዚያ እለት ያየሁት ፎቶላይ ታህሳስ201936 የተነሳ ሲሆን ፎቶው ከጀርባው ቀን አለው

96)የአበራ ካሳ ጸሃፊ ሲሆን በኋላ ጄኔራል ሆኗል

97)ከመሃላቸው አንዱ በኢትዮጵያ የዩጎስላቭ አምባሳደር ሆኗል፡፡ እምሩንም ጎብኝቷል

98)መጻፍን ያስተማሩት የሃረሩ አባ ሳሙኤል ወልደ ካህን ናቸው፡፡ የዚህ መጽሃፍ ዋናው ቅጂ
በልጁ እጅ ይገኛል

99)ይሄ ግርማቸው ተክለሐዋርያት አርአያ ላይ የተጠቀሙበት ቴክኒክ እንደመሆኑ መጠን


ምናልባትም እምሩና ግርማቸው በአብሮነት ቆይታቸውበስነጽሑፋዊ መልኩ አንዱ በሌላው ላይ
ተጽእኖ ያሳድሩ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የሚሰሩትንም የመነጋገር እድላቸው ሰፊ ይሆን ይሆናል፡፡
ከሶስቱ የሊፓሪ ሰዎች መካከል ሌላው ሰው ሃዲስ አለማየሁ ከሁለቱ የላቀ ደራሲ ሆኗል፡፡
ምንአልባት በመሃላቸው ያለ የጋራ ስነጽሑፋዊ መብሰል ይኖራል፡፡

100)ይህንን እና ሁለተኛውን ክፍል የማሳተም ሙከራዎች ይኖራሉ

101)እምሩ እስር ቤት ብለው ሲጠሩት ግርማቸው ተክለሐዋርያት ግን ደርዘን በሚሆኑ ወታደሮች


ሌት ተቀን የሚጠበቅ ሆቴል ነው ብለው ነግረውኛል፡፡

102)ከአመታት በኋላ የእምሩ ልጅ ሚካኤል አባቱን ወደ እየሩሳሌም ወስዶ ቤተሰቡ የት እንደነበር


ለማሳየት ፈልጎ ነበር

103)ይሄ በምኒሊክ ጊዜ ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ አማካሪዎችንም


ይጠቀሙ ነበር

207
ጥቋቁር አናብስት

104)እስከዚህ ጊዜ ድረስ በመሬቱ ወይም መብት ባለው የመንግስት ግብር ላይ ከጭሰኞች


ስለሚገኝ ግብር የሚወስነው ባላባቱ ብቻ ነበር፡፡ ቀጥተኛ ባለመሬትነት ተጠቃሚነትን የመጠየቅ
ባለሙሉ መብት አያደርግም

105በዚህ ከራስ ሃይሉ በጣም ይለዩ ነበር ራስ ሃይሉ ለምሳሌ ያህል የብር ማርያ ቴሬዛ ማየቱ ብቻ
ያረካቸው ነበር፡፤

106)በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመርያዋ ልእልት ለመባል የበቃችው ሴት የኃይለ ሥላሴ ልጅ


ተናኜ ወርቅ ነች

107)በዚያ ዓመት ፋሲካ ላይ ልጃቸው ሚካኤል ከእምሩና ከራስ አበበ አረጋይ ጋር በመሆን ወደ
እየሩሳሌም ለስድስት አመታት የቆዩበትን ቦታ ለማሳየት ሄዶ ነበር፡፡ ወድያውኑ እንደተመለሱ
የእምሩ ሹመት ተነገረ

108)ወርቅነህ እምሩ የህንድ አምባሳደር በነበሩበት ጊዜ የንጉሱ ረዳት በመሆን አብረዋቸው


ሄደዋል

109)ግርማሜ ከታላቅ የሸዋ ቤተሰብ ነበር የመጣው፡፡ አያቱ (የእሳቸውም ስም ግርማሜ ነዋይ
ነው)የሚንሊክ ታማኝ ተከታይ ሲሆኑ የሸዌ ያልሆኑ መኳንንት ከስልጣኑ ተነስተው ራቅ ወዳለ
ገጠራማ አካባቢ የመላኩንና የሸዌ መኳንንት ወደ ስልጣን ከፍ ከፍ የማስደረግእቅድ ተካፋይና
አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ እስከ ኃይለ ሥላሴጊዜ መጨረሻ ድረስ ቆይቷል፡፡

110)ምን ያህሉ የእምሩ ምን ያህሉ ደግሞ የልጁ ምዘና እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

111)የምእራቡ ወይም የውጪው አለም ሪፖርቶች የተጋነኑና የተጣመሙ ናቸው፡፡ እንደ ሚካኤል
እምሩሃሳብ ያልታተሙ የኢትዮጵያ ምንጮች ያሉ ሲሆን ተአማኒም ናቸው፡፡ ለምሳሌ እንደዱብ
እዳ ያሉ በታዋቂው ጦማሪ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ቅጂው ያለኝ ሲሆን፡፡ ለnortheast
African studies በማጠቃለልአቅርቤዋለሁ

112)ማህተመ ስላሴ ወልደመስቀል አባል የነበሩበትንና ንጉሱ የሚታደሙበትን የራሱን በዙፋን


ምክርቤትያሉትን ቆይታዎች ጽፈዋል፡፡ ታትሞ ባያውቅም፡፡ ከነሱም መሃል (ያገኘሁዋቸው
የማህተመ ስላሴን ያልታተሙ ረቂቆችን ከያዘው ከወንድሙ ሲሆን )እንዳየነው ከሆነ እምሩ

208
ጥቋቁር አናብስት

ቢኖሩም የዙፋን መማክርቱ አባል ሳይሆኑ በጊዜ ውም ያለ ጊዜውም ስለ ህገመንግስታዊ የዘውድ


አገዛዝ ደጋግመው ይናገሩ ነበር፡፡ የህገመንግስታዊ የዘውድ አገዛዝ አጀንዳ የተያዘከሆነ ሃሳባቸውን
በስሜት ይገልጻሉ፡፡ አጀንዳው በሌላ ጉዳይ ላይ ከሆነም ጣልቃ በመግባት ንጉሱ
ብቻቸውንእንደሚወስኑ እየታወቀ ስለ ጉዳዩ መነጋገር ዋጋቢስ ነው ይላሉ፡፡ በስብሰባው ወቅት ወግ
አጥባቂው ራስ ካሳ ከንጉሱ አጠገብ ይቀመጣሉ፡፡ ፓትርያርኩ ደግሞ ከራስ ካሳ ቀጥለው
ይቀመጣሉ፡፡ በእምሩ ሃሳቦች የቤተክርስትያኒቱ ጥቅም የሚነካ መስሎ ከታያቸው ተነስተው
ቆመው ከንጉሱ ጋር ለብቻቸው ለመነጋገር ይጠይቃሉ፡፡ አብረው ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ፡፡ ንጉሱ
ታላቅ ከበሬታ አላቸው ፓትርያርኩ ለራስ ካሳም እንዲሁ፡፡ በሌሎች የዙፋን ምክርቤት ስብሰባዎች
ደግሞ ንጉሱ ራስ እምሩ በተናገሩት ነገር ቅያሜ ሲገባቸው እምር ብለው ተነስተው ቃል ትንፍሽ
ሳይሉ ይወጣሉ ተመልሰውም አይመጡም፡፡ ይመለሱ አልያም የውሃ ሽታ ሆነው ይቅሩ ማንም
ስለማያውቅ ሌሎቹ ለግማሽ ሰአት ያህል እየተጨዋወቱ ይጠብቁና ከቀሩ ቀስ ብለው ይበታተናሉ

113)ለነገሩ ኢትዮጵያውያኑ ነሐሴ 12 ብለው ነው የሚቆጥሩት

114 ድንግል ማርያም ወደ ሰማየሰማያት የተጠራችበት ክብረ በአል

115)ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳ ትርፍ የሌለው ቢሆንም እንደዚህ አይነት ትእምርታዊ


ድርጊቶችን ይወዳሉ፡፡ እምሩ ለእንደዚህ አይነት ነገር ፍላጎቱ ስለሌላቸው ቆጥቋጣ ይሏቸው ነበር፡፡

116)ከባልንጀሮቻቸው አንዱ ታዋቂው ስውዲናዊ ቮን ሮሰን ነበር፡፡ በአንድ ወቅት (በ1970)


አካባቢ በናይጄሪያ ስለተደረገው የቢያፍራ ጦርነት ለተወሰኑ እንግዶች በስላይድ የታገዘ መግለጫ
ሲሰጥ እምሩ ተገኝተው ነበር፡፡ እሳቸውን የማግኘት እድል ጥቂት ቀናት ገጥሞኝ ያውቃል አንዱም
ይሄ ነበር፡፡

117)ኃይለስላሴ በጎጃም ውስጥ የወንጀለኞች ስቅላትን እንዲያሻሽል ጠይቀውታል የሚሉ አሉ፡፡

118በእሳቸው ወቅትና አሁንም አባ ኮራን ግቢ ውስጥ የሚሰሩ አዛውንት አትክልተኛ


አመስግነዋቸው አይጠግቡም «እንደ እምሩ ያለ ማንም የለም!» ይላሉ

209
ጥቋቁር አናብስት

አማረማሞ
ለሥነ ጽሑፍ የተሰጠ ሕይወት አማረ ማሞ በሲዳሞ ክፍለሀገር፣
በደራሳ አውራጃ (አሁን ጌዴኦ አውራጃ)፣ በዲላና ሀገረማርያም
መሀል በምትገኝ፣ ፍስሀገነት በምትባል ትንሽ ከተማ በህዳር 12ቀን
1931ዓም ተወለደ። አባቱ በአካባቢው ገዢዎች መሬት የተሰጣቸው
ከሌላ ቦታ የመጡ ሰፋሪ ነበሩ።የሞቱት አማረ ገና የሰባት ዓመት ልጅ
እያለ ነው።ስማቸው ጐዳና አሚሮ ሲባል በትውልዳቸው ሶዶ ጉራጌ
ናቸው።1አማረ እንደደንቡ በአባቱ ስም ከመጠራት ይልቅ
ከሚስታቸው ጋር ሆነው ባሳደጉት ልብስ ሰፊ የክርስትና አባቱ ማሞ
ደበላ ስም ተጠራ።አማረ ንፁህ የመንዝ አማራ በሆኑት በእናቱ ሰልፍየለሽ ወልደሚካኤል እጅ
አላደገም። አማረ ባደገበት የደራሳ አካባቢ የሚነገረው የጉጂ ኦሮምኛ ስለነበረ፣ምንም እንኳን ቤቱ
ውስጥ አማርኛ ይነገር የነበረ ቢሆንም፣ አማረ አፉን የፈታው በኦሮምኛ ነው። የክርስትና አባቱ
የሚኖሩት በዲላ እና ይርጋለም መሀል በምትገኘው አለታ ወንዶ(ወንዶ ብቻ ተብሎም
ይጠራል)ሲሆን ከይርጋለም በስተደቡብ 30 ኪሜ ላይ ትገኛለች።አማረ ወደ አለታ ወንዶ ከመጣ
በኋላ ሲዳምኛ ቋንቋንም ለመደ፤አሁን ድረስ ከአማርኛ ቋንቋ ቀጥሎ አቀላጥፎ የሚናገረው ቋንቋ
ነው።

አማረ በሰባት ዓመቱ ወደ አለታ ወንዶ እንደመጣ ወዲያውኑ የቄስ ትምህርት ቤት ገብቶ ለሶስት
ዓመት ያህል ማንበብና ዳዊት መድገም ተማረ።ከዚያ በኋላ ወደ የመንግሥት ትምህርት ቤት ገብቶ
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በጊዜው እንደነበረው ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ስምንተኛ ክፍል
ድረስ አጠናቀቀ።አሁን የአስራ ስምንት ዓመት ጎረምሳ ሆኗል። ጥሩ ውጤት ቢያመጣም ትምህርት
ግንአይወድም ነበር።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 20 ጎበዝ ተማሪዎች ተመርጠው ይርጋለም የመምህራን


ማሰልጠኛ ሲገቡ አማረ ከመካከላቸው ይገኝ ነበር፤ ለዚህ ስልጠና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን
ማጠናቀቅ አልተጠበቅባቸውም።ይህ ሀሳብ የሲዳሞ ትምህርት ቤቶች ኃላፊ የሆነው የዋለሉ ቦጋለ
ሲሆን፣ ስልጠናው አንድ ዓመት ያህል ይረዝማል።ነገር ግን ገና በስድስተኛው ወር ከትምህርት
ሚኒስቴር ተቃውሞ ስለገጠመው መቀጠል አልቻለም።“በኢትዮጵያውያን እና በህንዳውያን
መምህራን የሚሰጠው ትምህርት በጣም ግሩም ነበር” ይላል አማረ።

210
ጥቋቁር አናብስት

ስልጠናው በፍጥነት ከተቋረጠ በኋላ፣ ለተማሪዎቹ በየወሩ ይሰጣቸው የነበረውየ12.50 ብር አበል


አብሮ ስለቆመ አማረ ምንም ገንዘብ አልነበረውም። ይሁን እንጂ በይርጋለም ለጥቂት ጊዜ ቆየ።
በይርጋለም የኖርዌጂያን ሉተራን ሚስዮን የሆነውን በሰሙ ጊዜ የራሳቸውን የመምህራን ማሰልጠኛ
አቋቋሙና አማረን ጨምሮ አብዛኛዎቹን ከበፊቱ ስልጠና የተፈናቀሉትን ተማሪዎች ተቀበሉ።
ለሁለት ዓመት የቆየውን ስልጠና አማረ በጣም ወደደው።ከክርስቲያን ሚስዮን ጋር ሲገናኝ
የመጀመሪያው ነበር፣ከአንድ ዓመት በኋላ እሱም ሉተራን ክርስቲያን ሆነ። መጀመሪያ የኦርቶዶክስ
ክርስቲያን የነበረ ቢሆንም፣ በሚስዮኖቹ "ጠንካራ ግፊት"የተነሳ ወደ ሉተራን ሲለወጥ፣በዚያውም
የፆም ልምዱንም እርግፍ አድርጎ ተወዉ።

ትምህርት ቤቱን ስለወደደው እና በርትቶ ስላጠና፣አንደኛ ሆኖ በከፍተኛ ውጤት ተመረቀ።


የሚስዮኑ ቤተመፃሕፍት ጥሩ ስለነበር ብዙ አንብቧል።በተለይ በቋንቋ―አማርኛ እና እንግሊዝኛ
ጎበዝ ነበር፤ታሪክ እና ጂኦግራፊም እንደዛው፤ሂሳብ እና ሳይንስ ላይ ግን ያን ያህል አልነበረም። ብዙ
ታሪክ ያላቸውን መጽሐፍት ከማንበቡም በላይ የቋንቋ መምህራቸው ክሪስቲን ስክጄስሊየን ታሪክ
ታነብላቸውና በራሳቸው ገለፃ ታሪኩን ደግመው እንዲናገሩ ታደርጋቸዋለች።ይህ በኖርዌይ
ትምህርት ቤቶች የተለመደ አሰራር ሲሆን "gjenfortelling" ወይም“መልሶ መተረክ” ይባላል።
አማረ ይህንን ስልት አስደሳችና የቋንቋ ችሎታን ለማዳበር በጣም ጠቃሚ ሆኖ አገኘው።

ይርጋለም እያለ ካነበባቸው ታሪኮች በተጨማሪ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ያነበው የአማርኛ ሥነ
ጽሑፍ ተጽዕኖ አሳድሮበታል።በተለይ ሁለት ርእሶችን ያስታውሳል።የመጀመሪያው “የእንስሳት
አገልግሎት ለህፃናት በረከት” ነው።ደራሲው ያሬድ ገብረሚካኤል2 ሲሆን በግጥም መልክ የቀረበ
የእንስሳት ታሪክ ነው።አማረ አሁን ደረስ ለልጆች ከተፃፉ ታሪኮች ሁሉ የሚበልጥ ምርጥ ነው
ይላል።ታሪኮቹ የደራሲው ፈጠራ ናቸው፣ አንዳንዶቹ ተረት የሚመስል ገጽታ ቢኖራቸውም
መጽሐፉ ወጥ የፈጠራ ስራ ነው።አማረ ከአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ጋር ሲተዋወቅ ይህ የመጀመሪያው
ነው።ሌላኛው የጠቀሰው ተከታታይ መጽሐፍ የከበደ ሚካኤል "ታሪክ እና ምሳሌ" ነው፤ይህ
መጽሐፍ በከፊል በከበደ ሚካኤል የተፃፉ ታሪኮችንና ግጥሞችን ይዟል። በተጨማሪ ሌላኛው
የከበደ ሚካኤል መጽሐፍ፣"የእውቀት ብልጭታ"አስደንቆታል።የተክለፃዲቅ መኩሪያ የታሪክ
መጽሐፍትንም ወዷቸው ነበር።

በይርጋለም የመምህራን ማሰልጠኛ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በኖርዌጂያን ሉተራን ሚስዮን


በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች በፍጥነት እየተዘዋወረ አስተምሯል።ለምን እንደሆነ ባያውቅም
በጊዶሌ ለሶስት ወር፣ በሜጋ ለሶስት ወይም አራት ወር፣ በሀገረማርያም ለአራት ወር ተዘዋውሮ
አስተምሯል። ሚስዮኖቹ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት ቤት ሲከፍቱ፣ በዚያም ለአንድ ዓመት
አስተማረ። የሚያስተምረው እንደ አማርኛ፣ ሂሳብ፣ ጂኦግራፊ ያሉ "አለማዊ" የትምህርት
211
ጥቋቁር አናብስት

ዐይነቶችን ሲሆን፣ በትምህርት ቤቱ ለሚያስተምሩ የውጪ ሀገር ዜጎችም አስተርጓሚ ሆኖ


ይሰራል። አማረ ማስተርጎሙ በራሱ እንደ መማር ነው ይላል፤በኋላ በተርጓሚነት ለሚሰራው ስራ
መሰረቱ የተጣለው ያኔ ሳይሆን አይቀርም።አማረ ብዙ የእንግሊዝኛ እና የኖርዌጂያን መጽሐፍትን
ተርጉሟል። ኦሙንድ ሊንድትጆርንን ተዋውቆ የጋለ ስሜቱንና ሀቀኛነቱን ለማድነቅ የበቃውም
እዚያው ነው። ዲላ ውስጥ በሚስዮኑ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ከሆነችው ምንትዋብ
አየለ ጋር ተዋውቆም እዚያው ተጋቡ።

ከዲላ ወደ አዲስአበባ ተዘዋውሮ፣ ወደ ባንክ ቤቶች፣ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጽህፈት ቤቶች


እየሄደ የሚስዮኑን ጉዳይ ያስፈጽም ነበር። ዘወትር እሁድ ደግሞ በቤተክርስቲያኗ በማስተርጎም
ያገለግላል።በአዲሳባ ለአንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ሚስዮኑ ወደ ኖርዌይ ላከው።ለመጀመሪያ ጊዜ
ከሚስዮኑ ውጪ በባንክ ቤት ውስጥ በጥሩ ክፍያ እየሰራ ነበር።በኢትዮጵያ ሉተራን ቤተክርስቲያን
ውስጥ ተደማጭ የሆኑት አማኑኤል ገብረሥላሴ ከሁለት ሳምንት በኋላ ስራውን እንዲለቅ አሳመኑት
፤በምትኩም ወደፊት በኖርዌይ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚያስገኙለት ቃል ገቡለት።ሚስዮኑ ወደ
ኖርዌይ ለምን እንደላከው አልገባውም፤ምናልባት ለፕሮፖጋንዳ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ
ግን አለው።ምክንያቱም በየቦታው ሚስዮኑ "አረማውያንን"ወደ ክርስትና ለመለወጥ የደረገው
ጥረት "ያፈራቸው ፍሬዎች"ማሳያ ተደርጎ በተደጋጋሚ ይቀርብ ነበር። ነገር ግን ምንም እንኳን
ኦርቶዶክስ ቢሆንም፣ አንዳቸውም ቢሆኑ የክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ እንደተወለደ፣ ያደገውም
በክርስቲያናዊ ስርአት ውስጥ እንደሆነ ለመግለጽ አልተጨነቁም።ኖርዌይ ውስጥ ሁለት ዓመት
ሲቆይ በዚህ አጭር ጊዜ የኖርዌጂያን ቋንቋ አቀላጥፎ መናገር ቻለ።3 ኖርዌይ ውስጥ በስፋት
ተጉዟል፤ይህንን ቢወደውም በየሄደበት የሚስዮኑ ታላቅ ስራ ውጤት እየተባለ በየቦታው
"መቅረቡ" ያበሽቀው ነበር።

***

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ የውጪ ሀገር ሰዎች ጋር ከነበረው ጉድኝት ውጭ፣ ወደ
ኖርዌይ ያደረገው ጉዞ ከውጪው አለም ጋር የፈጠረው የመጀመሪያው ትልቁ ግንኙነት ነው።
በኖርዌይ ቆይታው ለሥነ ጽሑፍ ያለው ፍላጎት ይበልጥ ጠነከረ፤የኖርዌጂያን ቋንቋ እውቀቱም
በኋላ ወደ አማርኝ ቋንቋ ለሚተረጉማቸው መጽሐፍት ጠቃሚ ሆኖ አግኝቶታል።ኖርዌጂያኖቹ
የሚወደዱ ሰዎች ሆነው አግኝቷቸዋል።"ደግ እና ቅን ሰዎች"ናቸው ይላል፤እነሱም በሚገባ
ተንከባክበውታል።በአጠቃላይ በኖርዌይ ጥሩ ቆይታ ነበረው።

ሌላው በኖርዌይ ቆይታው ያጋጠመው ያልተጠበቀ ነገር፣ በሕይወቱ ለመጀመሪያ በሀገሩ ኢትዮጵያ
ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳደሩ ነው።ሀገሩን ከመልቀቁ በፊት ስለ ኢትዮጵያ ብዙ አላነበበም
ነበር።ኖርዌጂያኖች ስለ ኢትዮጵያ ለሚጠይቁት ጥያቄዎች ለመመለስ ሲሞክርና ኖርዌጂያኖች ስለ
212
ጥቋቁር አናብስት

ኢትዮጵያ የፃፉትን መጽሐፍ(በብዛት በሚስዮኖች የተፃፉ እና ስለኢትዮጵያ ብዙ የሚናገሩ)


ሲያነብ፣በሀገሩ ጉዳይ ላይ አዲስና ጠንካራ ፍላጎት ማሳደር ጀመረ።የውጪ ሀገር ሰዎች ስለ
ኢትዮጵያ የፃፉትን ወዶታል።

በ1960 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰና በኢትዮጵያ ወንጌላዊት አብያተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ
የብዙሃን መገናኛ ማእከል ውስጥ መስራት ጀመረ።ማእከሉ“የምስራች ድምጽ” በመባል
ይታወቃል። ለአምስት ዓመት በዚያ ስራ ቆይቷል። በዚህ መሀል፣ በ1963 የየምስራች ድምጽ የሥነ
ጽሑፍ ዝግጅት ዋና አዘጋጅነትን ደርቦበ1965 ወደ ዛምቢያ እስከሚሄድበት ጊዜ ድረስ ሰርቷል።

ዛምቢያ ኪትዌ ውስጥ፣ በአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ማእከል "የኢልብወለድ እና ልብወለድ አፃፃፍ"


ለስድስት ወር4 ተከታትሎ ስልጠናውን “በጣም ጠቃሚ” ሆኖ አገኘው።ይህ መደበኛ የአፃፃፍ
ስልቶችን በተመለከተ የመጀመሪያው ስልጠና ያገኘበት ገጠመኙ ነው።በጊዜው ብዙ አጫጭር
ልብወለዶችን ጽፏል። አማረ ይህ ስልጠና5"ወደ ፈጠራ ጽሑፍ የገፋኝ" አጋጣሚ ነው ይላል።

ሲመለስ የየምስራች ድምጽ የሥነ ጽሑፍ ክፍል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ተሾመ። በ1970 ዓ.ም ወደ
ሰሜን አሜሪካ እስኪሄድ ድረስም በዚሁ ስራ ቆየ። ስራውን በጣም አስደሳች ሆኖ አገኘው።
ከሀይማኖታዊ እና አስተማሪ ጽሑፎች ባሻገር የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት አብያተ ክሪስቲያናት፣
መሀይምነትን ለማጥፋት ከሚያደርጉት ዘመቻ ጋር በቅንጅት መሰረታዊ የትምህርት መርጃ
መሳሪያዎችን ያዘጋጁ ነበር።በቤተክርስቲያን ፖለቲካ ውስጥም እጁን አስገባ።

በ1961 ከኖርዌይ እንደተመለሰ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ ረዳት ዋና


ፀሐፊ ሆኖ ተመረጠ።በዚህ ሃላፊነት እያንዳንዳቸው አራት ዓመት ለሆኑ ሁለት ወቅቶች
አገልግሏል( በዚህ ወቅት ከፊሉን ከሀገር ውጭ ነው ያሳለፈው)ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆኖ በሰራባቸው
በነዚህ ስምንት ዓመታት ውስጥ ብዙዎቹ የቤተክርስቲያኗ ተቋሞች አገልግሎት ተጀምረዋል፤
ለምሳሌ፦ የምስራች ድምጽ ብዙሃን መገናኛ ማእከል (የሬዲዮ ስቱዲዮ እና የሥነ ጽሑፍ ክፍል) ፣
የወንጌል ድምጽ አለማቀፍ ሬዲዮ፣የመካነ እየሱስ ማሰልጠኛ ማዕከል፣የመካነእየሱስ የወጣቶች
ማረፊያ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊ ኮሌጅ በደብረዘይት (የዚህ የሁለተኛ ደረጃና የአስተማሪ ማሰልጠኛ
ኮሌጅ የቦርድ አባል ነበር)።በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሀጎስ ለገሰና እዝራ ገብረመድህን በተከታታይ
ዋና ጸሐፊ ሆነው፣ አማኑኤል ገብረሥላሴ ደግሞ የመጀመሪያው የመካነእየሱስ ቤተክርስቲያን
ፕሬዚዳንት ሆነው አብረው ሰርተዋል።“ወቅቱ ስራ የበዛበት አስደሳች እና ጥሩ ጊዜ ነበር” ይላል
አማረ።ቤተክርስቲያኗን እና ህዝቡን ለማገልገል ጥሩ እድል አግኝቷል፤በቤተክርስቲያን ውስጥ
213
ጥቋቁር አናብስት

ያለው ትብብርም አስደሳች በመሆኑ።ስራው ላይ አምሽቶ ስለሚቆይ ቤት የሚገባው ዘግይቶ ነበር።


ይህ ደግሞ በትዳሩ ላይ ችግር ፈጠረ።በመጨረሻ ከባለቤቱ ጋር በ1968 ህጋዊ ፍቺ ፈፀሙ።6

***

በ1970 ከሉተራን የአለም ፌዴሬሽን የአራት ዓመት ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ ሎስ አንጀለስ
በሚገኘው የካሊፎርኒያ ሉተራን ኮሌጅ ሥነ ጽሑፍ ለመማር ወደ ሰሜን አሜሪካ ሄደ። ከሁለት
ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ዲግሪውን በማእረግ ተቀበለ። የነፃ የትምህርት እድሉን ቀሪ ሁለት
ዓመታት ሁለተኛ ዲግሪውን በመስራት መጠቀም ፈለገ ፤ እንደውም በካሊፎርኒያ የሎስ አንጀለስ
ዩኒቨርሲቲ(UCLA) የአፍሪካንሥነ ጽሑፍ ለመማር ቦታ አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ
የሚሰራበት ቤተክርስቲያን ጥሪ ስላደረገችለት በ1972 ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። በድሮው ስራ
ላይም እስከ 1978 ድረስ ቆየ።

አማረ ኖርዌይ እያለ ሚስቱ ቦታ ተከራይታ ከኖርዌጂያን ሉተራን ሚስዮን ያገኘችው እርዳታ
ተጨምሮበት ካዛንቺስ ላይ እስከ 1967ዓም የኖሩበትን ቤት ሰርታ ነበር።ይኼኔ ኃይለሥላሴን
በመስከረም 1966 ከዙፋናቸው አሰውግዶ በምትኩ የሶሻሊስት ስርአት ያሰፈነው አብዮት አንድ
ዓመት ሞልቶታል።አማረ ደግሞ ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመሄዱ በፊት ቦሌ መንገድ ላይ በገዛው ቦታ
በ1967 ዓም ቤት ሰርቷል። በ1967 አጋማሽ ቤቱ አልቆ ዝግጁ ሆኗል። ነገር ግን ቤቱን ለመስራት
ሲል ከመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን የወሰደውን ብድር ለመመለስ ቤቱን አከራየው። በሐምሌ
1967ትርፍ ቤቶችንና መሬትን የመንግስት ንብረት የሚያደርገው አዋጅ ወጣ። ይህ ማለት አማረ
ተከራዮችን ማስወጣት አይችልም ማለት ነው። በነሐሴ1967 ዓም ላይ ቤተክርስቲያኗ የአማረን
ደሞዝ በ300ብር ቀነሰች። የቤት ኪራዩን ገንዘብ ደግሞ መንግስት ይወስደዋል። ስለዚህ በጠባቧ
የካዛንቺስ ቤቱ ውስጥ ተጨናንቆ መኖር ግድ ሆነበት። የቤቱ ተከራዮች ከ16 ወራት በኋላ ሲለቁ
አማረ ገባበት። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ በ1969 መጨረሻ ላይ የነበረበትን የመካነእየሱስ
ቤተክርስቲያን7 እዳ ለመክፈል ሲል ሸጠው። ከዚያ አብዮት አደባባይ(መስቀል አደባባይ)ጀርባ
ወዳለ የቀበሌ ቤት ገብቶ እኔ ኢትዮጵያን እስከ ለቀቅኩበት እስከ 1981 ድረስ በዚያው ይኖር
ነበር።

እነኚህ የግል ጉዳዮች እዚህ የሰፈሩት በሕይወቱ ውስጥ ፈታኝ የነበሩትን ወቅቶች ለመግለጽ ነው ፤
እንጂከገንዘብ ጋር በተያያዘ የገጠመውን ችግር ብቻ ለመዘገብ አይደለም። አማረም የደረሰበትን
መከራ የገለፀው እንዲህ ነው።
214
ጥቋቁር አናብስት

በዚህ ወቅት ብዙዎች ከቤተክርስቲያኗ እየተለዩ ነበር፤ምክንያቱም ነገሮች ፖለቲካዊ እና ጎሰኛ ቅርጽ
እየያዙ መጥተው ተመሳሳይ ወገንተኝነት እና ጎሳ (አብዛኛው በኋላ ደግሞ ሁሉም መሪዎች
ኦሮሞዎች ነበሩ)―የሌላቸውን ሁሉ ማስወገድተፈለገ።አማረ እንዳስቀመጠው፣ማስወገድ
የፈለጓቸውን ሰዎች ደሞዝ መቁረጣቸው ይህንኑ ሁኔታ ያስረዳል።የደሞዛቸው መቆረጥ ህገወጥ
ድርጊት ነበር። አማረ የምስራች ድምጽየመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ቦርድን ደሞዙን በመቁረጣቸው
ፍርድ ቤት ከሰሳቸውናረታቸው። ነገር ግን “በዚህ ሂደት የሰው ልጅ ክፋት―በመካነ እየሱስ
ቤተክርስቲያን እንዲሁም በከፊል በሌሎች ሚስዮኖች ውስጥ―የት ድረስ እንደሆነ
ተመለከትኩበት”8 ይላል አማረ። መጀመሪያ ላይ የምስራች ድምጽ መገናኛ ብዙኃን ማዕከል ቦርድ
ጉዳዩን ጠምዝዞ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተፈጸመ ጥቃት አስመሰለው።

አማረበፍርድ ቤት ከረታቸው በኋላ ከስራው ተባሮ በዚያውም ለሀያ ዓመት ያህል የሰራበትን
የጡረታ መብት አጣ። በመጀመሪያ ግን ውሳኔው ላይ ይግባኝ ብለው፣ ከረጅም ክርክር በኋላ አማረ
ዳግመኛ አሸነፈ። እንደገናም ይግባኝ ብለው፣አሁንም ለአማረ ተፈረደ። በአጠቃላይ የፍርድ ቤት
ክርክሩ ሁለት ዓመት ተኩል ሲወስድ፣ቤተክርስቲያኗ ለጠበቃ በየወሩ 750 ትከፍል ነበር ፤ በአማረ
በኩል ግን እንደነገረኝ ከሆነ ጉዳዩን የተከታተለው ራሱ ነው። ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ራሷ
የተከሰሰች ይመስል ጉዳዩን ስትከታተል ብትቆይም (አማረበፍፁም ቤተክርስቲያኗን አልከሰሰም) ፣
የአማረን የሁለት ዓመት ተኩል ደሞዝ ከነወለዱ መክፈል ያለበት የምስራች ድምጽ ነው አለች፤ ነገር
ግን ክሱ በሂደት ላይ እያለ የምስራች ድምጽ በመንግስት ተወርሶ ነበር። ቤተክርስቲያኗ አማረ
ገንዘቡን አሁን የመንግስት ንብረት ከሆነው የየምስራች ድምጽ እንዲቀበል ላኩት! ይሁን እንጂ
አማረ በየምስራች ድምጽ ስም በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ እንዳለ በማወቁ፣ ፍርድ ቤቱ ገንዘቡን
እንዲከፍለው ባንኩን አዘዘው፤ነገር ግን የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ የያዘው ደብዳቤ ባንክ ከመድረሱ
በፊት ገንዘቡ ወጥቷል።“እንደ አጋጣሚ የባንኩ ስራ አስኪያጅ፣ የመካነእየሱስ ዋና ጸሐፊ የሆነው
የጉዲና ቱምሳ ዘመድ ነበር” ይላል አማረ።ከዚህ በኋላ አማረ ወደ መገናኛ ሚኒስቴር ሄዶ
በየምስራች ድምጽስም የተመዘገበ ተሽከርካሪ እንዳለ ሲያጣራ፣ ሁለት መኪኖችን አገኘ። ይሄ
ለፍርድቤቱ እንደተነገረ፤ወዲያውኑ እርምጃ ተወሰደ። አንደኛው ለፍርድቤቱ ገቢ ተደረገና አማረ
በመጨረሻ ገንዘቡን አገኘ።

ከዚያ በመላው ሀገሪቱ ያሉ የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን አባላት ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስቸኳይ
ስብሰባ ተጠሩ። አማረ ቤተክርስቲያኗን (አሁን ደግሞ የተከሰሰችው ቤተክርስቲያኗእንጂ የምስራች
ድምጽ አይደለም እየተባለ ነው!) በመክሰሱ፣ ስራውን ለመልቀቅ 24 ሰአት ተሰጠው (ቀደም ብሎ
ከዚህ ስራ ተባሮ ነበር―ፍርድቤቱ ደግሞ መባረሩን ህገወጥ ነው ብሎታል)።አማረእንደሚለው፣

215
ጥቋቁር አናብስት

በአንድ በኩል ቤተክርስቲያኗ የጡረታ ክፍያውን የከፈልከው ለኖርዌጂያን ሉተራን ሚስዮን ነው


ስትለው፣ ሚስዮኖቹ በበኩላቸው በመንግስት ሲወረሱ ሁሉንም የጡረታ ገንዘብ ለቤተክርስቲያኗ
እንዳስተላለፉ ነገሩት።በዚህ የተነሳ አማረ ማሞ ለ20 ዓመት ካገለገለበት እና ጡረታ ከከፈለበት
ቤተክርስቲያን ያለምንም ጡረታ መሰናበት ግድ ሆኖበታል።

የኢትዮጵያ መንግስት ሰራተኞችን ከስራ ማባረርን ህገወጥ አድርጎ ስለሚቆጥር፣ አማረ


ቤተክርስቲያኗን ፍርድ ቤት ቢገትራት፣ እንደሚረታ ጥርጥር የለውም።ይሁን እንጂ በተመሳሳይ
ሁኔታ ውስጥ ማለፉን ስለጠላው ያንን ማድረግ አልፈለገም።በቅቶት ነበር፤ከዛ ወዲህ
ቤተክርስቲያን ደጃፍ ድርሽ ብሎ አለማወቁ የሚያስገርም አይደለም። በኢትዮጵያ የሚታተሙ
ጋዜጦች ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ ዘግበውታል።የኖርዌጂያን ሉተራን ሚስዮን ጋዜጣ "ኡትስይን"ግን
ስግብግብና ሌሎችንም ስሞች በመስጠት አወገዘው።በጉዳዩ ላይ ፍትህ ወይም ዳኝነት (እርቅ
ወይም ስምምነት) ለማስፈን እጁን ያነሳ ወይም ሊያነጋግረው የሞከረ ቤተክርስቲያንም ሆነ ሚስዮን
አልነበረም።9

ከዚህ በኋላ ለስድስት ወር ያህል አማረ ስራ አልነበረውም። የሱዳን ቤተክርስቲያን ምክር ቤት ጁባ


ላይ የህትመት ድርጅት እንዲያቋቁምና ሱዳናዊ ጸሐፊዎችን እንዲያሰለጥን ጠይቆት ነበር። ነገር ግን
በዚሁ ወቅት ላይ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ በአዲስ አበባ ያላቸውን ማተሚያ ቤት
በመዝጋታቸው፣ የድርጅቱ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ተስፋዬ ዳባ ንብረታቸውን ገዝቶ
የራሱን አሳታሚ ድርጅት መሰረተ፤አማረንም አብሮት እንዲሰራ ሲጠይቀው ፈቃደኛ ሆነ።ድርጅቱ
የኢትዮጵያ መጽሀፍት ማእከል ሲሰኝ አማረ የህትመት ክፍል ሀላፊ ሆኖ ተሾመ፤ከሁለት ዓመት
በኋላ ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነ።ስራ የጀመሩት በ1972 ዓም ሲሆን ከዛን ጊዜ
ጀምሮ በኢትዮጵያ ከታተሙት ምርጥ መጽሐፍት መሀል ብዙዎቹ የታተሙት እዚህ ነው፤በሀገሪቱ
ውስጥ ካሉ ሌሎች አሳታሚዎች ሁሉ ለደራሲዎችየተሻለ አማራጭ ያላቸው እነሱ ነበሩ።
የኢትዮጵያ መጽሐፍት ማእከል በአዲስ አበባ ውስጥ የራሳቸው የመጽሐፍት መደብሮችም
ነበሯቸው።

***

አማረ የራሱን የሥነ ጽሑፍ ስራ የጀመረው ገና በዲላ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት ቤት ውስጥ
እያለ ነበር። የመጀመሪያ መጽሐፉ "ማርቲን ሉተር"55 ገጽ ብቻ ነበረው።ሁለተኛ መጽሀፉ "የስጋ
አርነት"ም የተፃፈው ዲላ እያለ ነበር።ቃለመጠይቃችን እስከተካሄደበት ድረስ በነበረው ጊዜ፣ 25
ያህል መጽሐፍትን በመፃፍ፣ በማዛመድ ወይም በመተርጎም አሳትሟል።ሕይወቱን በሙሉ የራሱን
መጽሐፍት በመፃፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎችን መጽሐፍት አርትኦት በመስራትና በማሳተም ሕይወቱን
216
ጥቋቁር አናብስት

ለሥነ ጽሑፍ ስራ በመስጠቱ አማረ የተለየ ነው። ከየምስራች ድምጽ መገናኛ ብዙኃን መእከል ጋር
በሚሰራበት ወቅት 150 የሚሆኑ የልብወለድ፣የባህል፣የሐይማኖትና የትምህርት ህትመቶች ውስጥ
ተሳትፎ ነበረው። አማረ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የአርትኦት እና የእርማት ስራ ከሚሰሩ ሰዎች ሁሉ
በጣም ጠንቃቃውና የካበተ ልምድ ያለው ሆነ።ብዙ መጽሐፍት በእጁ የሚያልፉት ደራሲዎች
መጽሐፍቶቻቸው በብዙ ጥንቃቄ እና ያለ ብዙ እንከንእንደሚታተሙ ስለሚያምኑ ነው።ብዙ
ደራሲዎች አማረ ማሞ የመጽሐፍቶቻቸውን የህትመት ሂደት እንዲከታተል የሚፈልጉት ውጤቱ
ያማረ እንደሆነ ስለሚያውቁ ነው። ከዚህም በላይ ወጣት ጸሐፍትን ማማከርና መርዳት ችሏል፤
ይህም እርካታ ፈጥሮለታል። ብዙ ደራሲዎችም ደራሲ ያደረጋቸው አማረ እንደሆነ በመግለጽ
ያመሰግኑታል፤ ለእኔም ይህንኑ ነግረውኛል።

የምስራች ድምጽ የመገናኛ ብዙሀን ማእከልም መካነእየሱስ እና ሌሎችም አብያተ


ክርስቲያናትከአብዮቱ በፊት ሲያካሂዷቸው የነበሩትን የመሰረታዊ የትምህርት ዘመቻዎች፣
ለመደገፍ ያዘጋጃቸው መጻሕፍት የመጀመሪያው የንባብ ቅጽበ500,000 ቅጂዎች ተሸጧል።
መጻሕፍቱ ዝነኛ ነበሩ። አማረ የልጆች ሥነ ጽሑፍም ለማዘጋጀት ሞክሮ፣ ሰባት ያህል መጻሕፍት
ማሳተም ችሏል።በዚህ መስክ በሰፊው ለመስራት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣በ19969 መንግሥት
የምስራች ድምጽን በመውረሱ በሀሳብ ቀረ።

አማረ ከራሱ ፈጠራዎች ውስጥ "የልብወለድ ድርሰት አፃፃፍ"ን ይጠቅሳል። የታተመው በ1968
ሲሆን በደንብ ተሽጧል።በሁለት የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋሟት የመማሪያ መጽሀፍ ሆኖ
ሲያገለግል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ የፈጠራ ጽሑፍን ለማስተማሪያ ይጠቀሙበታል።
እነኚሁ ተቋማት "የቀለም ጠብታ" የተሰኘ መጽሐፉን ኢልብወለድ አፃፃፍን ለማስተማር
ይጠቀሙበታል።በጊዜው በዘመናዊ የኢትዮጵያ ደራሲዎች ዘንድ የአጻጻፍ ስርአት መልክ የያዘ
ስላልነበረ እና በዘርፉ ከፍተኛ ፍላጎት ያሟላሉ ብሎ ስለታሰበ ሁለቱን መጽሐፍት ሲያዘጋጅ
በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በትጋት ነበር።

የአማረ ማሞ የአጭር ታሪኮች ስብስብ ውስጥ የተካተቱ አንዳንድ አጫጭር ልቦለዶች፣ በአዲስ
አበባ ዩኒቨርስቲ የፈጠራ ጽሑፍ ትምህርቶች ውስጥ እንደ ጥሩ ምሳሌዎች ተጠቅሰው ጥቅም ላይ
ይውላሉ።

ከመጽሐፍቶቹ ውስጥ በአለን ፓተንን Cry the Beloved Country ወይም "እሪ በይ አገሬ"ን
እና Martyrs of the Catacombs ወይም "የካታኮምብ ሰማእታት"የተሰኙትን የትርጉም
ስራዎች፣ታላቅ ስራዎቹ እንደሆኑ ይገልፃል።ሁለቱም መጽሐፎቹ በሰፊው ከመነበባቸውም ባሻገር፣
በሬዲዮ በተከታታይ ተተርከዋል።

217
ጥቋቁር አናብስት

Cry the Beloved Countryን ለማንበብ እና ለመተርጎም የተነሳሳው ኖርዌይ እያለ ነበር፤
በጊዜው የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ሞቅ ያለ የመዋያያ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ አማረ፣ ከደቡብ አፍሪካ
ከመጣ አንድ ስደተኛ ጋር ስለ ሀገሩ ሲወያዩ እጅግ ተደንቆ ነበር (ከዚህ ሰው ጋር በኋላ ላይ
ኢትዮጵያም ውስጥ ተገናኝተዋል)።በጊዜው ኢትዮጵያውያን ስለ ተቀረው አፍሪካ ብዙም
አያውቁም፤ስለዚህ የደቡብ አፍሪካንም ሁኔታ በደንብ አይገነዘቡም ነበር።አሁን ግን ይህ ሁኔታ
ተለውጧል፤ አማረየለውጡ ከፊል ምክንያትየተረጎመው መጽሐፍ ተጽእኖ መሆኑን ያምናል።
10
ምንም እንኳን የትርጉም ስራ ቢሆንም፣አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የመጀመሪያ
ዲግሪዋን የመመረቂያ ጽሑፍ "እሪ በይ ሐገሬ" ላይ ሰርታለች።ወደ ኢትዮጵያ ባህላዊ አውድ
ስለተዛመደከቃል በቃል ትርጉም በላይ ነው፤እንዲሁም የቋንቋ ውበት አለው በማለት
አድንቃዋለች።

"Martyrs of the Catacombs"ን ያገኘው ኖርዌይ ነበር።ነገር ግን ሮም ውስጥ (ወይም


ከሮም ውጪ) የሚገኙትን ዋሻዎች ከጎበኘ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እስኪመለስ ድረስ አላነበበውም
ነበር። የአማርኛ ትርጉሙ ሲወጣ ተወዳጅነትን አተረፈ።

የዋልተር ትሮቢሽን ሁለት መጽሀፍትም ተርጉሟል፤I Loved a Girl እናI loved a Young
Man። አላማው ለወጣቶች የወሲብ ጉዳይ ትምህርት ለመስጠት ነው።በኢትዮጵያ ይሄ
በትምህርት አይሰጥም።ብዙ ሰዎች ስለጉዳዩ ያላቸውን እውቀት የሚያገኙት ከመጠጥ ቤት ወሬ
ወይም በሙከራ ነው።በዚህም የተነሳ ያልተፈለገ እርግዝና እና በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ
በሽታዎች ይከተላሉ።ብዙ ሠዎች ስለዚህ ጉዳይ በማንበባቸው ቢደነግጡም 11መጻሕፍቱ በሬዲዮ
መነበባቸው አልቀረም።

ከትርጉም ስራዎቹ መሀል፣ በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ በቤተክርስቲያን የተገኘው ባለ አንድ


ገጽ የጥበብ መግለጫ Desiderata አንዱ ነው።የአማርኛው ትርጉም "ዴዝዴራታ" በ10,00
ቅጂዎች በጠንካራ ክርታስ ላይ ተዘጋጅቶ በሁለት ወር ውስጥ ተሽጦ አልቋል። ትርፉ በ1966
ለእርዳታ ማስተባበሪያ ተሰጥቶ የድርቁን ሰለባዎች ለመርዳት ውሏል።ይህ ከአብዮቱ በፊት
የተከሰተ ነበር ፤ ነገር ግን አብዮቱ እንዲሳካ ድርቁ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ
"ዴዝዴራታ" ከ20 ጊዜ በላይ ሲታተም በ100,000ዎች የሚቆጠሩ እትሞች ተቸብችበዋል።

የአማረ ማሞ መጽሀፍት በኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው ተነበዋል። ጆን ኮናቸርበ1961 ባካሄደው


ጥናት መሰረት በጣም ተነባቢ የኢትዮጵያ ደራሲዎች፣ በቅደም ተከተል እነኚህ ናቸው፡
218
ጥቋቁር አናብስት

1)አቤ ጉበኛ

2)አማረ ማሞ

3) መኮንን እንዳልካቸው

4) ሀዲስ አለማየሁ

ከዚያ ወዲህ በእርግጥ ሁኔታዎች ተለዋውጠዋል። ቢሆንም እነዚህ ደራሲዎች አሁንም በደንብ
የሚታወቁና የሚነበቡ ናቸው።

አማረ ማሞ በጣም ተነባቢ ደራሲ ቢሆንም፣ኑሮ ለኢትዮጵያ ጸሐፍት ከባድ እንደሆነ ይናገራል።
ከመጽሀፎቻቸው የሚገኘው የመብት ክፍያ በጣም ትንሽ ስለሆነ ለአንድ ደራሲ፣በተለይ ቤተሰብ
ላለው በቂ አይደለም።ከመጽሐፉ በሚገኝ ገቢ ብቻ ለመኖር የሞከረው አቤ ጉበኛ እንኳን ሲሞት
የማተሚያ ቤቱ 100,000 ብር እዳ ነበረበት። አቤ በጊዜው ከማንኛውም የኢትዮጵያ ደራሲ በላይ
የፃፈ እና የሸጠ ነበር።ታዲያ ደራሲዎች በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ መፃፋቸውን ለምን
ይቀጥላሉ?ኢትዮጵያዊ ደራሲዎች የሚጽፉት ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ የሚሉት ነገር ስላላቸው ነው።
አማረ የምጽፈው ማለት የምፈልገውን ለመግለጽ ነው ይላል። በመጽሐፉ አማካይነት ህዝቡ
ያላወቀውን በማሳወቅ ለመርዳት ከመፈለግ ነው።

አማረ ማሞ ከብዙ ኢትዮጵያውያን ደራሲዎች ጋር አብሮ የመስራት እድሉን አግኝቷል።ለምሳሌ


ከበአሉ ግርማ፣ብርሀኑ ዘርይሁን፣ደበበ ሰይፉ(በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጽሑፍ እና ተውኔት
መምህር እና ገጣሚ)እና ሌሎችም ጋር ሰርቷል።አሁንም መፃፉን ባያቆምም ብዙ ጊዜውን
የሚያጠፋው በማንበብ፣ አሻሽሎ በመፃፍ፣የሌሎች ደራሲያን ስራ ላይ የአርትኦት እና የእርማት ስራ
በመስራትነው፤ኑሮውን የሚገፋውም ከነዚህ በሚያገኘው ገቢ ነው።

በቅርቡ ከዶክተር እዝራ ገብረመድህን ጋር የአዲስ ኪዳንን ዘመናዊ እና የተሻሻለ ትርጉም "ህያው
ቃል" ን ሰርተዋል። ከመንግሥቱ ለማ ጋር ደግሞ ብሉይ ኪዳንን በከፊል ወደ አማርኝ መልሰዋል።

አማረ ማሞ ስለ አማርኛሥነ ጽሑፍ በሚገባ ከሚያውቁም ሰዎች መሀል አንዱ ነው።

ደራሲ አማረ ማሞ የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ስራ አስፈጻሚ በመሆን የሰራ ሲሆን

ከሁለት አመት በፊት ተሸላሚ ሆኗል፡፡


219
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻዎች

1)እነኚህ ከሰባት ቤት ጉራጌ ውጪ ያሉ ሌሎች ጉራጌዎች ናቸው። ሶዶ ጉራጌዎች እራሳቸውን


ክስታኔ ("ክሪስቲያኖች") ብለው ይጠራሉ።ትግራይ ውስጥ ጉራዕ ከምትባል ቦታ እንደመጡ
በመግለፅ እራሳቸውን የጉራጌ ቁንጮዎች አድርገው ይቆጥራሉ።

2)በደንብ የሚታወቅ ገጣሚ እና ደራሲ ሲሆን የሞተው በ1975 ነው።

3)አማረን ለመጀመሪያ ግዜ ያገኘሁት በዚህን ወቅት ነበር። በኖርዌጂያን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን


ቃለመጠይቅ ሲደረግለት አስታውሳለሁ፤ በኖርዌጂያን ቋንቋ ችሎታው ሁላችንንም ነበር ያስደነቀን።
አፉን የፈታበትን ቋንቋ የሚናገር ነበር የሚመስለው።

4)በዚያ ከጥር 1957 እስከዚያው አመት ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ቆይቷል።

5)የሚያስተዳድሩት የተለያየ እምነት ያላቸው የቤተክርስቲያናት ስብስብ ነው።

6)ወዲያውኑ ሌላ ትዳር መስርታለች፤ በቃለመጠይቁ ወቅት አዲስአበባ ውስጥ እየኖረች ነበር።


አማረ አሁንም ድረስ የቀድሞ ሚስቱና አዲሱባሏ ጓደኛ ሲሆን በፍፁም በጠላትነት አይተያዩም።
ምንም ልጅ አልነበራቸውም፤ ነገርግን ፍሬህይወት የተባለች አንዲትልጅእናቷ ከ22 አመት በፊት
በይርጋለም ሆስፒታል ሲገላገሏትበመሞታቸውና የልጅቷ አባት ስላልታወቀ በማደጎ ወስደው
አሳድገዋታል።ፍሬሕይወት ወደ ጀርመን እስከ ሄደችበት ግዜ ደረስ ከአማረ ጋር መኖሯን
ብትቀጥልም እናቷን በየግዜው ትጠይቅ ነበር። በቃለመጠይቁ ግዜ የአማረ የቀድሞ ሚስት ሁለተኛ
ባሏ ኮለኔልነበር። ከኢትዮጵያ እስከተለየሁበት ግዜ ድረስ አማረ ዳግመኛ አላገባምነበር።

7) በግዜው ቤት ለመስራት ከቤተክርስቲያኗ ገንዘብ ተበድረው ከነበሩ ብዙ የቤተክርስቲያኗ


ባለሥልጣኖች መሀል እዳውን በመክፈል ከጥቂቶቹ አንዱ ወይም ብቸኛ ሳይሆን አይቀርም።

8)በግዜው ቄስ ጉዲና ቱምሳ የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን ዋና ፀሐፊ ነበሩ።አቶ አማኑኤልአብርሃ


ም/ፕሬዚዳንት ሲሆኑ አቶባይሳ ጃሞ ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ።ሶስቱም ከአንድ
የኦሮሞዎች አካባቢ፣ ወለጋ ሲሆኑበዚህወቅት ሁሉም በጣም ሀብታም መሆን ችለው እንደነበረ
አማረ ይናገራል።

220
ጥቋቁር አናብስት

9)በመካነእየሱስ ውስጥ ትልቅ ስልጣን የነበራቸውን ሰው በተፈጠረው ጉዳይ ላይ አማረ


የተናገረውን ታሪክ እውነትነት ስጠይቃቸው አንድም ነገር አልካዱም።

10)ብርሀኑ ዘርይሁንስለ ደቡብ አፍሪካ የሻርፕቪል እልቂት የፃፈው መፅሀፍ "ድል ከሞት በኋላ"
በዚህ ረገድ ተፅእኖ ፈጣሪ ነበር።የብርሃኑ ዘርይሁንን የሕይወት ታሪክ እዚሁ መፅሀፍ ውስጥ
ታገኙታላችሁ።

11)አንድት ተያቢ የሴቶች ብልት በወሲባዊ እርካታ ወቅት እርጥብ ይሆናል የሚል ጽሑፍ
ስላጋጠማት ስራዋን

221
ጥቋቁር አናብስት

ወልደ ግዮርጊስ ወልደ ዮሃንስ


የኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት አባትምንም እንኳን አብዛኛው
መጻሕፍቶቻቸው የሚታወቁት በመንፈሳዊ ይዘታቸው አልያም
በንጉሱ እና ቤተሰቦቻቸው ውዳሴ ላይ ቢሆንም ከነዚህ መጻሕፍት
አንባቢዎችም ባሻገር ወልደግዮርጊስ የሚታወቁበት በዋነኛነት በአንድ
መጽሐፍ ነው―በአግአዚ።ከስልሳ ስድስቱ የመንግስት ለውጥ በፊት
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደ አማርኛ ማስተማርያነት
ያገለግል ነበር፡፡እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም በድጋሚ ባይታተምም
በአሮጌ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ሲሸጥ አስተውያለሁ፡፡ስለ ወልደ
ግዮርጊስ የማቀርበው ቀጣዩ ገለጻ ከቤተሰባቸው በተገኘው መረጃና
አቶ ፍቃደ አደራ ከጻፉት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ቤተ
መዛግብት ባገኘሁት ጥናት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ወልደ ግዮርጊስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ምንጃር ወረዳ ጉብሌ ውስጥ በ1887 ዓ.ም
ተወለዱ፡፡ለአባታቸው ወልደ ዮሃንስ ደባልቄ እና ለእናታቸው ያድንቁሽ መኩርያ የበኩር ፍሬያቸው
ሲሆኑ ወላጆቻቸው ከመኳንንት ዘር የተገኙ ቢሆኑም ያልተማሩ አርሶ አደሮች ነበሩ፡፡
እንደማንኛውም የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በልጅነታቸው ከጥጃና ፍየሎች ጀምሮ ከብት አግደዋል፡፡
ለአባታቸውም ከእርሻ ቦታ ምሳ አድርሰዋል፡፡ለእናታቸውም የማገዶ እንጨት ለቅመዋል ውሃ
ቀድተዋል፡፡ብዙም ሳይቆይ አባታቸውን በእርሻ ማገዝ ጀመሩ፡፡

ወላጆቻቸው ከሳቸው ሌላ ሁለት ወንድ ልጆች ቢኖሯቸውም ሴት ልጅ ግን አልነበራቸውም፡፡አንድ


ቀን አባታቸው ከልጆቻቸው መሃል አንዱን ማስተማር እንዳለባቸው ለሚስትየው ተናገሩ።
ሚስትየውም ተስማሙ፡፡በዚህም መሰረት ወልደ ግዮርጊስ ወደ ዋናው የአጥብያ ደብር ቅዱስ
ሚካኤል ለቤተ ክህነት ትምህርት ተላኩ፡፡መምህራቸውም ደብተራ ምንዋልኩት ነበሩ፡፡በሁለት
ሳምንት ውስጥ ወልደ ግዮርጊስ ፊደል አጠናቀው ጨረሱ፡፡በአንድ አመታቸው ደግሞ ዳዊቱን
በግዕዝ ልቅም አድርገው በቃላቸው አጥንተው ጨረሱ፡፡ይሄ ለቤተሰቡ ትልቅ ክስተት ነበር፡፡ የደስ
ደስ ተብሎ ጊደርም ተሸለሙ፡፡

የልጅነት የደስታ ወራታቸው ያበቃው በ8 አመት እድሜያቸው እናታቸው ሲያርፉ ነበር፡፡


አባታቸው ሁለተኛ ሚስት አገቡ ፡፡የእንጀራ እናታቸው ሀይለኛ ስለነበሩ በወልደ ግዮርጊስ ቆዳ
ስስነት ተወዳጅተው መቀጠል አልሆን አላቸው፡፡በመሃላቸው ብዙ አለመግባባቶች ተነሱ፡፡
አባታቸው እራሳቸው ይሄ ለልጃቸው ጥሩ አለመሆኑን አስተውለው ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ሌላ
ቦታ እንዲሄዱ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ሌላው ለመሄድ የገፋፋቸው ነገር ደግሞ በቀዬው የተከሰተው

222
ጥቋቁር አናብስት

ድርቅና የከብቶች እልቂት ነው፡፡ውሳኔው የተወሰነው በአንዲት ቀን ነበር ፡፡ታናሽ ወንድማቸው


ከሚጠብቃቸው አንዲቷ ከብት በጨዋታ ተዘናግቶ ሳለ ወደ ሜዳ በማምራቷ የእንጀራ እናቱ
አባታቸውን በስራ በማገዝ ላይ የነበሩትን ወልደ ግዮርጊስን ያለጥፋታቸው ክፉኛ ስለመቷቸው
ነበር፡፡ምንም ስንቅና ቅያሪ ልብስ እንኳን ሳይዙ በሚቀጥለው ቀን በዶባ አህያ ፈጅ አድርገው
(የኃይለሥላሤ ቤተሰቦች መገኛና የመጡበት ስፍራ ነው) ወደ ወረኢሉ አቀኑ፡፡ብርዱና ረሃቡ
ለትንሽ ጊዜያት ቢያስቸግራቸውም ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ የሚመለሱ ሙስሊም ነጋዴዎች
አግኝተው ምግብ ሰጧቸው፡፡ሲመሽ ግን ካደረጉት ጥብቆና ነጠላ ሌላ ልብስ ስላልነበራቸው ብርዱ
አንዘፈዘፋቸው፡፡

ወረኢሉ ደርሰው እንደምንም ትምህርት ቤት አገኙ፡፡ከታወቁት የዜማና ድጓ መምህር ከአለቃ ጸጋ


ዘንድ ትምህርታቸውን ጀመሩ፡፡ተማሪዎቹ ከወሎ ሸዋና በጌምድር የመጡ ሲሆን እሚተዳደሩት
በየቤቱ በልመና ከሚያገኙት እህል ነው፡፡ወልደግዮርጊስ ዜማና ድጓን ለሁለት አመታት ያህል አለቃ
ጸጋ ጋር አጠኑ፡፡ጎበዝ ተማሪ በመሆናቸው አዳዲስ ተማሪዎችን ያስጠናሉ ብዙም ቀለም
የማይዘልቀው የአስተማሪያቸውን ልጅም ጭምር ይረዳሉ፡፡በተለይ በድጓው በኩል ጎበዝ ነበሩ፡፡
መምህራቸው ወልደግዮርጊስ እዛው እያስተማሩ እንዲቀሩ ቢፈልጉም ነገር ግን ድምጻቸው ለዜማ
ስለማይሆን ትምህርታቸውን ወደ ቅኔ ቀየሩ፡፡ቅኔ መማር የጀመሩት ከነበሩበት ብዙም
ከማይርቅው ከስመ ጥሩው አለቃ ገብረሚካኤል የአብነት ትምህርት ቤት ነው፡፡ቅኔ በተለይ
ለተሻሉት ተማሪ ወጣቶች የሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡ወልደግዮርጊስ ወጣት የነበሩ ቢሆንም ከ9
ወራት ቆይታ በኋላ የመጀመርያ ቅኔያቸውን ተቀኙ፡፡በቅኔ ጥናት ውስጥ ሁለት ደረጃዎች ሲኖሩ
የመጀመርያው ቅኔ የመቀኘቱን የማቀናበሩን ህግ የምንማርበት በተጨማሪም የሰምና ወርቅ
(ተለዋዋጭ ዘዬን) የምንቀስምበት ስለ ጻድቃን ሰማእታት ገድሎች የምናውቅበት ሲሆን በዚህ ደረጃ
ያለ ተማሪ በተራ ደረጃ ቅኔን የሚቀኝ ሲሆን ቀጣዩ ደረጃ ግን የግእዝ ሰዋሰውን በጥልቀት
የምንማርበት ነው፡፡በዚህ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከነሱ በታች ያሉትን ያስተምራሉ፤ ጥያቄዎቻቸውን
ይመልሳሉ፡፡አንድ ተማሪ ወደ እዚህ ደረጃ ለማደግም ከታችኛው ክፍል በጥሩ ውጤት ተመርጦ
መምጣት ያለበት ሲሆን አብዛኛዎቹም እራሳቸው የቅኔ መምህር ይሆናሉ፡፡ወልደ ግዮርጊስ ይሄንን
ሁለተኛውን ደረጃ ካጠናቀቁ በኋላ ዜማን ለመቀጸል ወደ አለቃ ጸጋ ተመለሱ፡፡አለቃ ጸጋ ቆይተው
እንዲተኳቸው ፈልገው የነበር ቢሆንም ወልደ ግዮርጊስ ግን ይህንን አልተቀበሉም፡፡ወደ ዋድላና
ደላንታ በመሄድ ከአለቃ ተሰማ ዘንድ አኩፋዳቸውን ይዘው፤ ደበሎዋቸውን ለብሰው፤ቁራሽ
እየለመኑ ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ከስድስት ወራት በኋላ የአካባቢው ሁኔታ ስላልተመቻቸው ወደ
ጉራምባ ደብር በጌምድር ሄዱ፡፡ብዙም አልቆዩ ከሶስት ወራት የዜማ ጥናት በኋላ በበርበሬ ምርቷ
ወደ ታወቀችው ደምቢያ አቀኑ፡፡ለአንድ አመት በርበሬ ቀንጥሰው 30 የማርያ ቴሬዛ ብር አገኙ፡፡
በዚህ ገንዘብም ወደ ጎንደር ከተማ አምርተው ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡በዚህ ጊዜ ግን የአዲስ
ኪዳን አንድምታንና የጎንደር ቅኔን ከአለቃ ኅሩይ ፋንታ፤ደግሞ ፍትሐ ነገስቱን ከአለቃ ዘዮሃንስ ስር

223
ጥቋቁር አናብስት

ሆነው ተማሩ፡፡በዚያ ለአራት አመታት(ከ1909-1913 ድረስ) ዓ.ም ተምረው የ16 አመት


የትምህርት ቆይታቸውም በዚሁ ተደመደመ፡፡

***

በ1913 ዓ.ም አለቃ ኅሩይ ወደ አዲስ አበባ በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተጠሩ፡፡የተጠሩበት
ምክንያትም በግዕዝ የተጻፉ መፃህፍትን ወደ አማርኛ እንዲመልሱ ተፈልገው ነበር፡፡1አለቃ ኅሩይ
ወልደግዮርጊስን ጨምሮ ሌሎችንም ወደ አዲስ አበባ አስመጡ፡፡ወልደግዮርጊስ ከመጡም በኋላ
አለቃ ኅሩይ ወልደግዮርጊስን ይሄ ምርጡ ተማርዬ ነው ብለው ከታዋቂው ፖለቲከኛና ምሁር
ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ጋር አስተዋወቋቸው፡፡ኅሩይ በተራቸው ደግሞ ወልደ ግዮርጊስን ከልኡል አልጋ
ወራሽ ጋር አስተዋወቋቸው፡፡የግእዝ ቅኔያቸውም ላቅ ያለ ሆኖ ስለተገኘ በተለያዩ
አብያተክርስትያናት ቅኔ እንዲቀኙ ሆኖ ገቢያቸውን ከእንጦጦ ቁስቋምና ቅዱስ ማርቆስ እና
ከሌሎች ቦታዎች እያገኙ ቆዩ፡፡ቀጥሎ ማስተማር ጀመሩ፡፡ደሞዛቸውም በቀን አንድ እንጀራና አንድ
ብርጭቆ ጠላ ተቆረጠላቸው፡፡በተጨማሪም ከጎንደር ከመጡ ከ1913 ጀምሮ እስከ 1917 ድረስ
ለኅሩይ ወልደሥላሴ በመንግስት ግምዣ ቤት ጸሃፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ለዚህ ስራቸው ደግሞ
በወር የአምስት የማርያ ትሬዛ ብር ምንዳ ይከፈላቸዋል፡፡

በ1917 ዓ.ም የግዕዝ መጻሕፍቱን ወደ አማርኛ በመመለስ ስራ ተቀጠሩ፡፡ለሚቀጥሉት ሁለት


አመታትም (ከ1917 -1919)በተፈሪ መኮንን ትእዛዝ ከሌሎች አምስት ምሁራን ጋር በመሆን
መጽሐፈ ቄርሎስን አስተረጎሙ።2ወልደ ግዮርጊስ በዚህ ቡድን ውስጥ ጸሃፊ ነበሩ፡፡ለሚቀጥሉት
አመታትም እስከ 1920 ዓ.ም ድረስ ከአለቃ በዛብህ ጋር በመሆን ተመሳሳይ ስራ እየሰሩ ሰቆዩ
ለዚህ ስራቸው ደግሞ ደመወዛቸው በወር 10 የማርያ ቴሬዛ ጠገራ ብር ነበር፡፡በተጨማሪም
ለቤተሳይዳ ሆስፒታል ማተምያ ቤት እየሰሩ በወር 20 የማርያ ቴሬዛ ጠገራ ብር ተጨማሪ
ደመወዝም ያገኛሉ፡፡

ብርሃንና ሰላም ማተምያ ቤት በ1920 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ጋዜጣውም በተመሳሳይ ስም ማውጣት


በጀመረ ወቅት ወልደ ግዮርጊስ ከአቶ ገብረ ክርስቶስ ተክለሃይማኖትና ከአቶ ወልደ ግዮርጊስ
ደሳለኝ ጋር በመሆን በረዳት አርታኢነት ተቀላቀሉ፡፡ ህይወታቸውን በጋዜጠኝነት ላሳለፉት ወልደ
ግዮርጊስ ወልደ ዮሃንስ ይህ ጠቃሚ እመርታ ነበር፡፡ጎን ለጎንም ከሳቴ ብርሃን ለልበ ጠቢባን የተሰኘ
ወርሃዊ መጽሄት ከታወቁት ምሁር አቶ ማህተመ ወርቅ እሸቴ ጋር በማቋቋምና በረዳት
አርታኢነትም ይሰሩ ነበር፡፡ወልደግዮርጊስ በኋላ ሙሉ አርታኢ ሲሆኑ ወርሃዊ ደመወዛቸው በየወሩ
50 ጠገራ ብር ደረሰ፡፡ለተለያዩ የህትመት ድርጅቶችም የማረጋገጫ ንባብ ስራ ያካሂዳሉ።
224
ጥቋቁር አናብስት

ስራዎቻቸው በንጉሱ ዘንድም ውዴታን ስላስገኙላቸው በ1926 ዓ.ም የወርቅ ሜዳልያና


ለክብራቸው የሚመጥኑ አልባሳትን ተሸልመዋል፡፡

የኢትዮጵያን ጋዜጠኝነት በመመስረትና በማሳደጉ በኩል እስከ ፋሺስት ጣልያን መምጫ 1928
ዓ.ም ድረስ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡የጦርነቱ ነገር እርግጥ እየሆነ ሲመጣ ሃገራዊ ስሜትን ያዘሉ
በራሪ ወረቀቶችን የጋዜጣ መጣጥፎችን መጻፍ ጀመሩ፡፡በ1927 ዓ.ም በግላቸው መጀመርያ
ያሳተሙትየወንድ ልጅ ኩራት ስለ ሃገር ልጅ መሞትን ሲሆን ሙያ በልብ ደግሞ ብዙም ሳይቆይ
ተከተለ። በ1928 ዓ.ም ጀግና ሰው ተጋዳይ ለጠላት አልሞት ባይ ወጣ፡፡

በ1927 ዓ.ም አቶ መኮንን ሃብተወልድ እና የአዲስ አበባ መስተዳድር የሃገር ፍቅር ማህበርን
መሰረቱ፡፡ወልደግዮርጊስ ደግሞ በመክፈቻው ዝግጅት ጽሁፋቸውን እንዲያቀርቡ ከተጋበዙ
ደራስያን መሃል አንዱ ነበሩ፡፡እንደሚባለው ከሆን በሚነበብበት ወቅት ሰዎች ጎራዴያቸውን
አውጥተው ቀረርቶና ሽለላውን ተያያዙት በጠላት ላይም መፎከር ጀመሩ፡፡

ጣልያን በ1928 ዓ.ም ሃገሪቷን በወረረበት ጊዜ ወልደግዮርጊስን ጨምሮ ሌሎችም ጋዜጠኞች


በወራሪው ሃይል በኩል ለፕሮፖጋንዳ ስራ ተፈለጉ፡፡ከተያዙ ቅጣቱ ሞት የነበር ቢሆንም
ወልደግዮርጊስ ተደበቁ፡፡ከሁለት አመታት በኋላ ግን አንድ ሰው ያሉበትን መርቶ በወራሪዎቹ
ቁጥጥር ስር ለመውደቅና ከመገደል ጫፍ ለመድረስ በቁ፡፡በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ከወንድ
ልጆቻቸው አንዱ አያሌው እጆቹን አንገታቸው ላይ ጥምጥም አድርጎ በማቀፉና ሚስታቸውም
በቦታው እየተመለከተች በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ ችለዋል፡፡በምትኩም አሁን የአዲስ አበባ
ዩንቨርስቲ ከሚገኝበት ቦታ በስተጀርባ ተወስደው ለአንድ አመት ያህል ታሰሩ፡፡የወራሪው ፋሺስት
ሃይል ጋዜጣ ለነበረችው "የቄሳር መንግስት መልእክተኛ" እንዲሰሩም አስገደዷቸው፡፡እዚህ እየሰሩ
ሳለ ግን ከውስጥ አርበኞች ጋር በመገናኘትም ሊያስጠረጥር በማይችል መልኩ ውስጠ ወይራነት
ያላቸውን የተመሰጠሩ ግጥሞች በበራሪ ወረቀት እያሳተሙ መልእክት ያስተላለፉ እንደነበረ
ይነገራል፡፡ ከእነዚህ ግጥሞች መሃል አንዷ በማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ዝክረ ነገር ውስጥ
ተካታ የታተመች ሲሆን በወቅቱ ለአርበኞች ትልቅ ተጽእኖ ፈጣሪና እንደ መጻህፍ ቅዱስ የምትታይ
ሰዎች በጣልያን መንግስት ላይ እንዲያምጹ ያነሳሳች ስትሆን ወልደ ግዮርጊስ ወልደዮሃንስም እንደ
ምስጥር የውስጥ አርበኛ ይቆጠሩ ነበር፡፡3

***

ጣልያን ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ እንግሊዞች ኃይለሥላሴ ከመመለሳቸውም አስቀድሞ የጋዜጣውን


ነገር ለማንሳቀሳቀስ ሞክሩ፡፡አንድ የብሪታንያ መኮንን ጋዜጠኞችን ከያሉበት አፈላለገ።ከነሱም
225
ጥቋቁር አናብስት

መሃል ወልደ ግዮርጊስ ወልደ ዮሃንስና አቶ ሰሎሞን ዮሐንስ ይገኙበታል፡፡ምንም ያህል ሳይቆይ
በአቶ ይልማ ደሬሳ አደራዳሪነት ወደ ጋዜጠኝነቱ ተመለሱ፡፡አዳዲስ ጋዜጦች ለመጀመር ስለታሰበም
ወልደ ግዮርጊስ የአማርኛው ጋዜጣ አዲስ ዘመን ተብሎ እንዲሰየም ሃሳብ አቀረቡ፡፡ ኃይለሥላሴም
ቆይተው አርእስቱን አጸደቁት፡፡በግንቦት 1933 ዓ.ም ተጀመረ፡፡በሚቀጥለው ወር ሰኔ 14 1933
ዓ.ም ይዞት በወጣው ጽሁፍ ላይ ኃይለሥላሴ ከስደት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ በሚያዝያ
27 1933 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር “ይህ ቀን ለአዲስቷ ኢትዮጵያ የአዲስ ዘመን ጅማሮ ነው” ስላሉ
አንዳንዶች የጋዜጣው ስያሜ ከዚህ የመጣ ነው ይላሉ፡፡ለ18 አመታትም ሳምንታዊ ሆኖ ከቆየ
በኋላ በታህሳስ 11 1951 ዓ.ም ከጅማሮው አንስቶ በአርታኢነት የሰሩበት ወልደግዮርጊስ ስለ
ለውጡና ተገቢነቱ መክረው ወደ እለታዊነት እንዲቀየር ተወሰነ፡፡ ወልደግዮርጊስ ከብርሃንና ሰላም
ለጣቂ ነው በሚባለው አዲስ ዘመንና ባንዲራችን (በኋላ ሰንደቅ አላማችን) በተከታታይ በየቀኑ
መጻፋቸውን ቀጠሉ፡፡ የነዚህ ሁለት ጋዜጦች ዳይሬክተር በመሆን ከ1952-1954 ዓ.ም ድረስ
ቆይተው፤በረዳት ሚንስትርነት መአረግ ለሁሉም ጋዜጦች ሃላፊና ተጠሪ በመሆን ሲሾሙ በ1952
ዓ.ም ለታዋቂ ምሁራንና የንጉስ አማካሪዎች የሚሰጠውን የብላቴንነት ማዕረግን አገኙ፡፡አዲስ ዘመን
25ኛ ልደቱን ባከበረበት 1958 ዓ.ም ወልደግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ይፋዊ “የኢትዮጵያ ጋዜጦች
አባት”የሚል ማዕረግም በማስታወቂያ ሚንስትር ተሰጥቷቸዋል፡፡ይሄ በህይወታቸው የሚልቀውና
እንደ ጀግንነት መታሰብያ የሚቆጥሩት ክብር ነበር፡፡እንደ ቤተሰቡ አባባልም ከሆነ ከዚህ ሌላ ብዙ
ማዕረጎችን ቢቀዳጁም የሚያስበልጡት ይሄንን ነበር፡፡በሚቀጥለው አመት በ1959 ዓ.ም
ለማስታወቂያ ሚንስትር አማካሪ ሆነው በምክትል ሚንስትርነት ማዕረግ እስከ 1964 ዓ.ም ድረስ
ቆዩ፡፡

ለኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ያደረጉት አስተዋጽኦ የላቀ ነው፡፡በብዙ ሚንስትሮች ስር የሰሩ ሲሆን


ለምሳሌ እንደ መኮንን ሃብተወልድ፤አምደ ሚካኤል፤ግርማቸው ተክለሃዋርያት ይገኙበታል፡፡
ለአዲስ ሃሳቦችም በራቸው ክፍት ስለነበር ሁሉም የበላዮቻቸው ለሳቸው የነበራቸው ግምት ላቅ
ያለ ነበር፡፡ግርማቸው እንደውም የልጃቸው ዮሐንስ የክርስትና አባት ነበሩ፡፡ከእስራኤል ግሪክና
ዩጎስላቪያ ጣልያን እንዲሁም ግብጽ ጉብኝታቸው በኋላ ይበልጥ ተራማጅ ሆነው "ብልጽግና
በግብርናን" ጻፉ፡፡በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንና በሃገሪቱ ኋላ ቀርነት ይናደዱ
ነበር፡፡

በህይወታቸው ሙሉ በትምህርት ላይ የማይነቃነቅ ጽኑ እምነት ነበራቸው፡፡እንደ ቤተሰቡ አባባል


ከሆነ ሃብታም ሰው አልነበሩም ያገኙዋትን በሙሉ ግን በልጆቻቸው ትምህርት ላይ ነበር

226
ጥቋቁር አናብስት

የሚያጠፏት፡፡በአንድ ወቅት ንጉሱ ለሰሩት ስራ እንደ ሽልማት የተለመደውን “ምን ላድርግልህ?”


ጥያቄ ቢጠይቋቸው ወልደግዮርጊስ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩላቸው እርዳታቸውን ጠየቁ፡፡
በውጤቱም በወቅቱ ተወልደው የነበሩትና በህይወት የሚገኙት ሁለቱ ታላላቅ ልጆቻቸው (ሁለተኛ
የተወለደው ልጃቸው አርፎ ነበር)በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በአዳሪ ተማሪነት ቦታ
ስለተገኘላቸው ገቡ፡፡ምንም እንኳን ወልደ ግዮርጊስ እንግሊዘኛንም ሆነ ሌላ የውጪ ቋንቋን
ባያውቁም ልጆቻቸው ዘመናዊ ትምህርትን እንዲቀስሙላቸው ይፈልጋሉ፡፡በመጀመርያ ለተወሰነ
ጊዜ ወደ ቤተክህነት ትምህርትቤት ቢሰዷቸውም ቅሉ፡፡

ወደ ውጪ ባደረጉት አንድ ጉዞ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሃገርን ለማዘመን ያለውን ፋይዳ ታዝበዋል4።


በተለይ እስራኤል እንዴት በረሃውን ወደ ምድረ ገነትነት እንደቀየረችው ሲያዩ ተማረኩ፡፡ካዩት
በተጨማሪም ከንባብና እንደ ጋዜጠኛ ባላቸው ውሎ ብዙ ነገሮችን ተረዱ፡፡ከዚህ ሁሉ በኋላ
ማጠቃለያ ያደረጉት ኢትዮጵያ በኣላስፈላጊ ወግ አጥባቂነት ተጠፍራ መታሰሯን ነው፡፡
የቤተክርስትያኗን መሰረታዊ አቋም ለመቀየር ባይፈልጉም ቤተክርስትያኒቷ ፍልስፍናዋን
እንድታዘምን ይፈልጉ ነበር፡፡5ምክንያቱም በበርካታ መንገዶች በትምህርት በስብከት በአገልግሎት
ኋላ ቀርነት ስለሚታይባት ነው ብለው ስለሚያስቡ ነበር እንደ ልጃቸው አያሌው አባባል፡፡ግን
ምንም ያህል ስለ ቤተክርስትያኒቷ ቅሬታ ቢኖራቸውም ጠንካራ አማኝና ለቤተክርስትያኗም
ተቆርቋሪ ነበሩ፡፡ኢትዮጵያ በሃይማኖት የትክክለኛው ትግበራ የስልጣኔ ምንጭ እንድትሆን
ይፈልጉነበር፡፡በተራማጅነታቸውና ከቀደምት የንባብ ልምዳቸውም ይህ እንደሚመጣ አስቀድመው
ስለተረዱ ሌሎች በቤተክርስትያን አካባቢ ያሉ ሰዎች የተደነቁባቸው እንደ የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ
መውጣት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች አላስገረሟቸውም ፡፡ልጆቻቸው ለሃገር የሚጠቅም ትምህርት
ብለው የሚያስቡትን እንደ ህክምናና ምህንድስና ያሉትን እንዲማሩላቸው ስለሚፈልጉ
ከልጆቻቸው አንዱ ዳዊት ወልደግዮርጊስ አየር ሃይልን ለመቀላቀል ሲያስብ ተቃውመዋል፡፡

ወልደ ግዮርጊስ ለኃይለሥላሴ ታማኝ ባለሟል በመሆን ከዘመነ ተፈሪ መኮንን የአልጋ ወራሽነት
ጊዜያቸው ጀምሮ እስከ ንግስና አገዛዛቸው ጊዜያት በታማኝነት ለበርካታ አመታት በጥቅሉ
አገልግለዋል፡፡ በአገልግሎታቸውም ይኮራሉ፡፡ሃገሪቱን በማዘመኑና በማሸጋገሩ ላይም የበኩላቸውን
እንዳደረጉ ያምናሉ፡፡ይሄም እድገትም ለመጭው ብሩህ ጊዜያት መምጣት ትክክለኛው መንገድ
እንደሆነ፡ የንጉሱ አመራር ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪቃ ትክክለኛው አመራር
እንደሆነ ያምናሉ፡፡ወልደ ግዮርጊስ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ ጊዜያቸውን የቀደሙ ነበሩ። ሌላው
ኢትዮጵያዊ “ስልጣኔ ፤ክርስትና በአጠቃላይ ማንኛውም ነገር ኢትዮጵያ ነች” ብሎ በሚያስብበት፣
የአፍሪካን መኖር በማያውቅበት ወቅት የአፍሪካ ግንዛቤ የነበራቸው ሰው ነበሩ፡፡ ስለዚህም ወደ
ሌሎች አፍሪካውያን በመሄዳቸውና ቡድን ፈጥረው ለኋለኛው የአፍሪካ ህብረት መሰረት ስላስጣሉ

227
ጥቋቁር አናብስት

ኀይለሥላሴን ታላቅ የመሪነት ብቃት አሳይተዋል ባይ ናቸው፡፡የአፍሪካ ህብረት የመጀመርያው


ስብሰባም ለሳቸው ጠቃሚ ሲሆን የህልማቸውን እውነታነት አረጋግጠውበታል፡፡

እንደቤተሰቦቻቸው አባባል ከሆነ ወልደግዮርጊስ ብዙዎቹ እንደሚያስቡት ሳይሆን ለንጉሱ ስለሰሩት


ስራ ብዙ ሽልማትና እድገት ቢሰጧቸውም ንጉሱን አያመልኳቸውም፡፡በልደታቸውና በዘውድ
በአላቸው ላይ ፈልገውም ታዘውም ተቀኝተውላቸዋል፡፡በተወሰነ መልኩም ለሁለተኛው ቅጽ
ግለታሪካቸው ግብአቶችን ማሰባሰብ ጀምረው ነበር፡፡ ምናልባትም ራሱን የቻለ ቅጽም እንዲሆን
ለተፈለገው ስራ ´ገድል´ የሚል የግዕዝኛውን ቃል ለመጠቀም አስበው “ገድለ ኃይለሥላሴ”
ለማለት ፈልገው ነበር፡፡ይህን በመመልከትና "ገድል" የሚለው ቃል ለቅዱሳን መጠቀሚያ ብቻ
ማገልገሉን በመታዘብ አንዳንዶቹ ለንጉሱ የቅድስና መዕረግ ሊሰጧቸው አስበዋል ይሏቸዋል፡፡
ቤተሰቦቻቸው ግን ይሄ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ምንም እንኳን ኃይለሥላሴን እንደ
ቤተክርስትያኗ አስተዳዳሪ እና ሃይማኖታዊ መሪ እንዲሁም የእምነቱ ጠበቃ አድርገው
ቢያይዋቸውም ሰው እንደሆኑና የራሳቸው ሰብአዊ ጉድለቶች እንዳሉባቸው በእርግጠኝነትም
ቅድስና እንደሌላቸው ያውቃሉ ይላሉ፡፡በውጤቱም “ገድለ ኃይለሥላሴ” የወልደግዮርጊስ ሃሳብ
እውን ሆኖ ሳይጀመር ሳይጻፍ ሳይጠናቀቅም ቀረ፡፡የንጉሱን ግለታሪክ ለመጻፍ ከዛ በፊት ከበደ
ሚካኤል፣መርስዔሃዘን ወልደቂርቆስ እና ተክለጻዲቅ መኩርያ የሚገኙበት ኮሚቴ ተዋቅሮ
ግብአቶችን እያሰባሰቡ ነበር፡፡ ከመጋቢት 1964-ዓ.ም እስከጡረታ መውጪያቸው ግንቦት 1966
ዓ.ም 6ድረስም ወልደግዮርጊስ የዚህ ኮሚቴ የሁለት አመታት አባል ነበሩ፡፡እንደ ከበደ ሚካኤል
ሁሉ ወልደግዮርጊስም ንጉሱ በዚህ ግለታሪካቸው አውነተኛውን ክስተት እንዲናገሩ እንጂ በሌሎች
ህትመቶች ስለንጉሳዊ ቤተሰቦች ተጽፎ የታየውን እንዲደጋግሙ አይፈልጉም፡፡“በወቅቱ
በኃይለሥላሴ አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነው በግለታሪኩ ውስጥ አልተነገረም” ሲሉ
ወልደግዮርጊስ ለቤተሰባቸው ነግረዋቸው ነበር፡፡

***

ወልደግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ከንጉሱ በቀጨኔ መድሃኒያለም ቤክርስትያን አካባቢ በተሰጣቸው


ብቸኛ መሬት ላይ ቤታቸውን ገንብተው ነበር፡፡7እንደ ሁለት የተለያዩ ምንጮች ከሆነ 9 ወይንም
11 ልጆች አሏቸው፡፡( ቤተሰቦቻቸውም አጥርተው መንገር አልቻሉም) ነገር ግን እ.ኤ.አ በ1988
ቤተሰቡን ቃለ መጠይቅ ባደረግሁበት ወቅት 5 ወንድና 2 ሴት ልጆች በህይወት ይገኙ ነበር።
ከዋካ ድንቄ ጋር በ1919 ተጋቡ። እሷም የታወቂው ደራሲና ዲፕሎማት የብርሃኑ ድንቄ እህት ነች፡
፡አባታቸውም አለቃ ድንቄ የእንጦጦው ራጉኤልና ሰበታ የሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ ያስተከሉት
ወጨጫ ማርያም ቤተክርስትያን አለቃ ነበሩ፡፡
228
ጥቋቁር አናብስት

ወልደግዮርጊስ የትርፍ ጊዜያቸው ተጠቅመው24 መጻህፍትን ጽፈዋል።ነገር ግን በገንዘብ በኩል


ያገኙት ውስን ነው፡፡ብዙ አንብበዋል።የጽህፈት ስራቸውንም የሚከውኑት ለሶስትና አራት ሰኣታት
በቢሯቸው ከስራ ሰአት በኋላ በመቆየት ነው፡፡በዚህ የተነሳ ወደ ቤት ሲመጡ ብዙ ጊዜ ይዳከማሉ፡
፡የሚጽፉትም ሳያረቁ ቀጥታ እንደመጣላቸው ነው።በኋላ ማስተካከያዎችን በዛው ጽሁፍ ላይ
ያደርጋሉ፡፡የእጅ ጽሁፉም(በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም አዲስ አበባ ውስጥ እንዳየሁት)
ማራኪና ለመነበብ የሚመች አልነበረም፡፡እራሳቸውን ከብራና መጻህፍት በመገልበጥ ጽህፈት
እንዳስተማሩ ግልጽ ነው፡፡ስለ መጻሕፍቶቹ ሲናገሩም ንጉሱም ሆነ ሌላው ህዝብ አግአዚን
ቢመርጡም እኔ ግን ዋጋ የምሰጠው (ብልጽግና በግብርናን)ነው ይላሉ፡፡

ከነጻነት በኋላ በ1941 እ.ኤ.አ እንደገና መጻህፍትን መጻፍ ሲጀምሩ ስለንጉሳውያን ቤተሰቦችና
ንጉሱን ለማወደስ በዝርው እና በግጥም መልክ መጻፋቸውን ቀጠሉ፡፡እነሱም 1ኛ ገራ መንግስት ዘ
ኢትዮጵያ በ23 ጥቅምት 1937 ዓ.ም የታተመው ረዥም ግጥም ስለ ዘውድ አከባበሩ የተጻፈ
ሲሆን ንጉሱን የሚያወድስ የፋሺስትን ወረራንም የሚኮንን ነበር፡፡2ኛ ክብረ ነገስት 1938 የዘውድ
በኣል የተጻፈ ረዥም ግጥም ነው፡፡3ኛ ታሪክ ያለው አይሞትም ለ1939 የዘውድ በአል የተጻፈ
ሲሆን ይሄኛው በተለይ ረዘም ያለ የመታሰብያ መጽሐፍ ሲሆን ከርእሱ ጋርም የሰመረ ነበር።
በግራኝ አህመድ ስለደረሱት ውድመቶች ስለቴዎድሮስ ጀግንነት ፣የራስ አሉላ አባ ነጋ ጀብዱ፣
የአንዳንድ አርበኞች የጀግንነት ስራዎች(ዘርአይ ድረስ፤አብርሃ ደቦጭ ፣እና ሞገስ አስገዶም
በግርያዝያኒ ላይ ፈንጂ የጣሉት) ታሪክ ያካተተ በምስልም የዳበረ ነበር፡፡(ከላይ የተጠቀሱት ሁለት
መጻህፍት መጀመርያ በጋዜጣ ተከታታይ መጣጥፎች መልክ የታተሙ ነበሩ)4ኛ አምሐ ፍቅር ወ
ሰላም ለንጉሱ ልደት በሃምሌ 16 1939 የቀረበና ኃይለሥላሴን ለህዝቡ ስላላቸው ፍቅር
ስላመጡት ሰላም የሚያወድስ ነው፡፡5ኛ ሌላ ተመሳሳይ መጽሐፍ በ1942 ለ ንጉሱ 58ኛ
ልደታቸው የተጻፈና ለመሪነት በእግዚአብሔር መቀባታቸውን አንስቶ የሚያሞካሽ ነው፡፡6ኛ
በጥቅምት 23 1949 ዓ.ም የታተመው አምሐ ንጉስ ለንጉሱ 25ኛ የዘውድ በአል የተጻፈና
ከልጅነት እስከ ዘውድ ክብረ በኣል የተነሷቸውን ፎቶዎች ይዟል፡፡7ኛ ዘርዐ ብሩክ 37 ግጥሞችን
ያካተተው ስለ ኃይለሥላሴ ህይወትና እድገትን በኢትዮጵያ ለማምጣት ስለሰሩት ስራ ሲሆን
ለ38ኛው የዘውድ ክብረበኣል በ1961 ዓ.ም የታተመ ነው፡፡፣ምንአልባትም ሌሎች ሁለት ወይም
ሶስት መጻህፍት አሉ፡፡የድል ኮከብ ፤ገጸ በረከት ታሪክና ስራ በዚሁ ዘርፍ ስለንጉሳውያኑ ቤተሰብ
የሚያትቱ ናቸው፡፡

229
ጥቋቁር አናብስት

ምንም እንኳን እነዚህ መጻሕፍቶቻው ለተወሰኑ የታሪክ ድርሳኖቻው ሲባል ተፈላጊ ሲሆኑ በሌሎች
ሴማዎች ላይ የሰሯቸው ስራዎች ለመጪው ግዜ የሚፈለጉና የሚዘከሩ ናቸው፡፡መክንያቱም
ከኪናዊ ዋጋቸው ይልቅ ከጻፏቸው መሃል ምንአልባትም የተወሰኑት በቀደመው እና ፋናወጊ
በሆነው የስነጽሁፍ አጻጻፍ ባሕል የተጻፉ ስለነበሩ ነው፡፡በጦርነቱ በፊትና መሃል ከጻፏቸው
ትናንሽ የግጥም መጻሕፍት በኋላ በውጪ ጉዞዋቸው ባደረባቸው ተጽእኖ ለሃገራቸው እድገት
በሰነቁት ራእይ ተነሳስተዋል፡፡ወድያው እንደተመለሱም ብልጽግና በግብርናን ጽፈው በ1941 ዓ.ም
ታተመ፡፡ወልደግዮርጊስ ስለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አስተያየት ከፍተኛ ነው፡፡ስለእርሻና እንስሳት
ርቢ ስለኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክና ስለመጻኤ እድገቷ እምቅ ችሎታ የሚያነሳ ነው፡፡በመጽሐፉ መሃል
ግጥሞችም ተቃይጠውበታል፡፡ በቀጣዩ አመት ሌላ ስለንጉሳውያን ቤተሰቦች ከጻፉት መጽሐፍ
ውጪ ስለ ንጉሳውያን ቤተሰቦች(ከ1948 እና ከ1961 በስተቀር)ሌላ ስራ አልሰሩም፡፡ በ1941
ከስራ በኋላ ስትፈቱ እንቆቅልሽ ተጫወቱ የሚል የእንቆቅልሽ ስብስብ መጽሐፍ አሳተሙ፡፡
በስብስቡ ውስጥ የተካተቱት ጥቂት እንቆቅልሾች ቢሆኑም ተብራርቶ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በተመሳሳይ አመትም የአለም ጸባይ እና ስነምግባር የተባሉ ሁለት መጻሕፍትን በማሳተም በዝያን
አመት ያሳተሙትን የመጽሐፍ ብዛት ሶስት አድርሰዋል፡፡ስነምግባር ትልቅ ግምት ከሚሰጧቸው
መጻሕፍቶቻቸው መሃል አንዱ ነው፡፡በክርስትያናዊ ህግጋትና ስነምግባራት እንዴት መኖር
እንደሚቻል ምክር ይለግሳል፡፡ ወልደግዮርጊስ በርካታ ምሳሌዎችንም ይሰጣሉ፡፡በ1948 ዓ.ም
በድጋሚ ታትሟል፡፡ሌላው በኢትዮጵያና ኤርትራ ቅልቅል ዙርያ በ1945 ዓ.ም የታተመው
ስራቸው አዲሲቱ ኢትዮጵያ ነው፡፡8በ1949 ዓ.ም የባልና ሚስት ጭውውት በእንካ ሰላንትያን
አሳተሙ፡፡መጽሐፉ በኢትዮጵያ አይነተኛ የስነቃል ጨዋታ ዙርያ ያጠነጥናል፡፡ወልደ ግዮርጊስ
በእንካ ሰላንትያ የሚነሱትን መረን የለቀቁና ጽርፈት የተሞላባቸውን ምልልሶች በመግደፍ ደገኛ
ምሳሌዎችን አካተዋል፡፡ቀጣዩ መጽሓፋቸው በ1954 ዓ.ም ከአምስት አመት በኋላ ነው
የታተመው፡፡አምስት መንገደኞች ይሰኛል፡፡9 (በዝርው የተጻፈ ሲሆን)ገጸ ባህርያቱ ”አጠቃላይ
የዚህን አለም ሰዎች“ን በትዕምርታዊ መልኩ ይወክላሉ፡፡ ጉዞዋቸው በአጠቃላይ የተሰጠው
ለመጽሐፍ ቅዱስና ለሳይንስ ነው፡፡ቀጥሎ በ1957 ዓ.ም ግብረገባዊ የሆነው መጽሐፋቸው
አትስረቅ ወጣ፡፡እንደ ስርቆት፡ማመንዘር፤ምንፍቅና፤እብለት፡የሌሎችን ንብረት ማውደም
የመሳሰሉትን ወንጀሎች በመንቀፍ የተጻፈ ነው፡፡በዝርው እና በግጥም መልክ ተዛንቆ በመልካም
ቋንቋ የተጻፈው ዝርዋዊ ትረካ የሆነው ታሪክ አይሙት እንዲያጫውት የኢትዮጵያን እድገት ዘጋቢ
በሆነ መልኩ በተመሳሳይ አመት ታተመ፡፡ቀጣዩ መጽሐፍ የእስማኤል ቁጥቋጦ ነው፡፡ሀይማኖታዊ
ይዘት ያለው ሲሆን የደግነት ትሩፋትን የመሳሰሉትን ያነሳል፡፡(በመጽሐፍ ቅዱስና በቅዱስ ቁርአኑ
ስለተጠቀሱት)በእስማኤል በእናቱ ሃጋር እና በአባቱ አብርሐም መካከል ስላለው ግንኙነት ያትታል፡

230
ጥቋቁር አናብስት

፡የተወሰኑ ግጥሞች በዝርው መሃል ተዘርተው ይገኙበታል፡፡በ1957 ወይም በ1959 ዓ.ም ነበር
የወጣው፡፡(ልዩነቱ የመጣው በደራሲው መጻህፍት የተጠቀሱ የተለያዩ ቀኖች መሰረት ነው)

ከሁሉ የታወቀውና የተነበበው መጽሓፋቸው አግአዚ በመጽሐፍ መልክ የታተመው በ1961 ዓ.ም
ነው፡፡የተጻፈው ግን ከዚያ በፊት ነበር፡፡ከ1938 ሀምሌ 27 አንስቶ በተለያዩ ወቅቶች አዲስ ዘመን
ጋዜጣ ላይ የወጡ አስራ ሰባት ያህል ተከታታይ ስራዎች ስብስብ ነው፡፡በዚህ መጽሐፍ
ወልደግዮርጊስ ኢትዮጵያውያን ለልብወለድ ጽሁፍ ፍላጎት እንዲያሳድሩ ጥረዋል፡፡ በግል
ማስታወሻቸውም ላይ እንዳሰፈሩት ከሆነ ግርማቸው ተክለሐዋርያት አርአያን10ከመጻፉ በፊት
ጽፈውት ነበር፡፡ወልደግዮርጊስ በዚህ መጽሐፍ ኢትዮጵያ “ለውጪው አለም በሯን ስለመክፈቷ”
የጻፉ ሲሆን ብዙ ነገሮች በትንቢት መልክ ተዘርዝረውበታል፡፡በ1961 ዓ.ም በታተመበት ግዜ
መጽሐፉ ሲጻፍ ከተተነቡት በርካታ ነገሮች ውስጥ አብኛዎቹ ይዘዋል፡፡አግአዚን በመጽሐፍ መልክ
ያሳተሙት ሌሎች ስለገፏፏቸው ነበር፡፡መጽሐፉ ስለ ዘመናዊ እድገት፤እና ስለኢትዮጵያ የባህር በር
ፍላጎት እንዲሁም በባህል እና በዘመናዊነት መካከል ስላለው ቅራኔ ነው የሚያነሳው፡፡

ወልደ ግዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ በአሁኑ ወቅት ብዙም ተነባቢነት ባይኖራቸውም በተለይ በአግአዚ
መጽሐፍ ለአማርኛ ስነጽሁፍ እድገት ይበልጡኑ በሁለት እግሩ ለመቆም ድክ ድክ በሚልበት
የልጅነት ዘመኑ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

አንዳንዶች ለመንግስት ጥቅም መጠበቅ የቆሙ ወግ አጥባቂ አደርገው ያስታውሷቸዋል፡፡


በስተመጨረሻ አካባቢ ሳንሱር እንደአንድ የስራቸው ክፍል ነበር፡፡በዚህም መክንያት ወጣቱ
የጋዜጠኛ ትውልድ እንደእድገት ማነቆ ቢቆጥራቸው የሚገርም አይደለም፡፡ያም ሆኖ ግን ያሉበትን
ሁኔታ እና በሁለት ወገን የሚያሳደሩትን ፍላጎት(ለመንግስትም ለጋዜጠኞችም) ሳያደንቁ አያልፉም፡
፡ብርሃኑ ዘርይሁን ስለእሳቸው ሲናገር“ የመንግስትን ፖሊሲዎች መፈጸማቸውን እየተቆጣጠሩ
አብረዋቸው የሚሰሩ ሰራተኞችን እንደ አባት የሚመክሩ ነበሩ ”ይላል፡፡አንድ ልጃቸውም “እንደ
ምክትል የማስታወቅያ ምንስትርነታቸው የመንግስት ፖሊሲዎች በመንግስት ጋዜጦች ላይ
መንጸባረቃቸውን እርግጠኛ መሆን ነበረባቸው” ብሏል፡፡

በግል ባህርያቸው በማንበብ እና መጻፍ የተጠመዱ፤ከምስኪን ቤተሰብ የመጡና ይህንንም


ያልዘነጉ፤መክሊታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙበት ባመቻቸላቸው የስራ ሁኔታ በመስራታቸው
አመስጋኝ ሲሆኑ ስማቸውንም ወልደግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ታላቁ የጽህፈት ሚንስትር የንጉሱ
ቅርብ ሰውና ዜና መዋዕል መዝጋቢ ተብሎ በአንድ ትንፋሽ መጠራቱን ለቤተሰዋቸው ማስረዳት

231
ጥቋቁር አናብስት

ይፈልጋሉ፡፡ስኬታቸው ግን አላስታበያቸውም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ችሎታቸውን የሚመጥን ስራ


እንዲያገኙና ጥረታቸው ወይም የስራ አፈጻጸማቸው ታይቶ እንዲሾሙ ይፈልጋሉ፡፡

በሁሉም ረገድ ታማኝ ነበሩ፡፡በመታመንም ያምናሉ፡፡ እንደሚነገርላቸውም ይህንን ታማኝነት


በህይወታቸው ሙሉ ሲከተሉት ኖረዋል።ለንጉሱም ሆነ ለሚንስትሮቻቸው በሚያማክሩበት ወቅት
ሃቀኝነትን ተላብሰው ለራሳቸውም እድገትንም ሳይፈልጉ ነው፡፡ከፍ ያሉ ስልጣናት ሆነ ኃላፊነቶች
በንጉሱ ሲሰጣቸው አመስጋኝ ሲሆኑ የንጉሱ ፖሊሲዎችም ለሃገሪቱ ጠቃሚ እንደነበሩ ያምናሉ።

በተለያዩ አርእስቶች ላይ ከጓደኞቻቸው ከዘመዶቻቸውና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር መወያየትን


ይወዳሉ፡፡ሰፊ ሰአትም በታሪካዊ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይም በመከራከር ያሳልፋሉ፡፡ በራሳቸውና
በሌሎች ሰዎች መጻህፍት ላይ በቅዱሳን ገድል ላይ የቃላትና የሃረጋትን ትርጉም በማስተንተን
የፓትርያርኩን ንግግር እና የንጉሱን መግለጫዎች በመሳሰሉ ጉዳዮች ወዘተ በርካታ ጊዜያትን
ይወያያሉ፡፡

ንቁ አእምሮ የነበራቸው በመንፈሳዊ ህይወታቸው የጠነከሩ ፤ኢትዮጵያ በፍልስፍና፤በሃይማኖታዊ


አስተሳሰብና፤ ሃገሪቱ በቁሳዊ ነገሮች በተመለከተ ቁርጠኛ የሆነ አቋም የምታድግበትን፤ ንጉሳዊው
አገዛዝ የሚሻሻልበትን መንገድ የሚያልሙ ሰው ነበሩ፡፡ በአመለካከታቸውም የኢትዮጵያ እድገት
በዚህ በኩል የተደራጀ መሰረት ያለውና እስካሁን በነበሩት ታሪካዊ እድገቶች ላይ የተመሰረተ
እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡በሃሳቡ ትክክለኛነት እራሳቸውን ያሳመኑ ሲሆን ሃሳባቸውንም በመጻሕፍትና
በጋዜጦች ላይ በጻፏቸው ጽሁፎች ገልጸዋል። እንዲያው ተጽዕኖ ለመፍጠር ያህል ብለውም ጽፈው
አያውቁም¹¹፡፡

የአልኮል መጠጦችን አይጠጡም፡፡ጠላ እንኳን ቢሆን፡፡የስራ ባልደረቦቻቸው በሆኑት ጋዜጠኞች


የተለመደውን የመጠጣት ልማድ አልነበራቸውም፡፡ይልቁን ከመጠጡ እንዲቀንሱ ይመክሯቸዋል፡፡
በተለይ ብርሃኑ ዘርይሁንና ያሬድ ገብረ ሚካኤልን12፡፡መጠጥ የተቀደሰውን የሰው ልጅ ያረክሳል
ብለው ያስባሉ፡፡13

ወልደግዮርጊሰ ከኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ፈር ቀዳጆች መሃል ስማቸው ቢጠራም በዚያን ጊዜ


ከነበሩት መሃል ለምሳሌ ያሬድ ገብረ ሚካኤል14፤ሮማነ ወርቅ ካሳሁን፤መኮንን ወርቅ አገኘሁ15
ይገኙበታል፡፡ ከሁሉም ልቆ የሚታየው ግን የእርሳቸው ቀዳሚ አስተዋጽኦ ነው፡፡

በትምህርት ላይ ያላቸው እምነት ልጆቻቸውን በሚገባ እንዲያስተምሩ አድርጓቸዋል፡፡በ1980


ዓ.ም በህይወት ከነበሩት ውስጥ የበኩር ልጃቸው ሙሉጌታ አታሚ ሆኖ ለ32 አመታት በኖረባትና
ዜግነትን ባገኘባት ስዊድን በቋሚነት ይኖራል፡፡ቀጣዩ አያሌው ጋዜጠኛና የእንግሊዘኛ ጋዜጣ
232
ጥቋቁር አናብስት

ለሆነው voice of Ethiopia በአርታኢነት ያገለግላል ይህም(ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያ ድምጽ


ላይ አርትኦት ይሰራ በነበረበት ወቅት)ሲሆን እሱና ዮሃንስ ገብረማርያም የሞስኮ አማርኛ
ሬድዮ አገልግሎትን አስጀምረዋል፡፡ (በዛም ወቅት ነው የጋጋሪንን ወደ ህዋ መጓዝ ያወቁት)ቀጥሎም
ለንጉሱና ለረዳት ሚንስትሩ በካቢኔው የግል ጸኃፊ ሆነ፡፡በዚህ ስራቸውም ከኃይለሥላሴ ጋር ብዙ
ቦታዎች ሄዷል፡፡ከአብዮቱ በኋላ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆንም ለ8 አመታት
አገልግሎ ጡረታ ወጣ ፡፡የግል ትውስታውን ተመርኩዞ አንድ ልብ ወለድ ለመጻፍ ቢሞክርም
በጋዜጠኝነት ከሰራቸው ስራዎች ውጪ ምንም አላሳተመም፡፡ሴት ልጃቸው ተቋመች ትባላለች ።
ከመጀመርያው የኢትዮጵያ የነርስ ምሩቃን መሃል ስትሆን ለተጨማሪ ትምህርትም ወደ ታላቋ
ብርታንያ ሄዳለች፡፡የበርካታ ሆስፒታሎች አስተዳዳሪ ነበረች(ጥቁር አንበሳ፣ልእልተ ፀሃይ፣ቅዱስ
ጳውሎስ፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ)እቴጌ መነንን እስኪያርፉ ድረስ ያስታመመቻቸውም እሷ ነበረች፡፡
በባህርይዋ ችሎታ ያላት ብልህ፣ፊትለፊት የምትናገርና ኀይለኛ ስሜቷን ገላጭ እንደሆነች ይነገራል፡
፡ቀጣዩ ልጅ ዳዊት ከሃረር አካዳሚ ተመርቆ በኤርትራ ረዳት በመሆን ለአስተዳዳሪው ይሰራ ነበር፡፡
ቆይቶም ወደ አሜሪካ በማቅናት በህግ የማስተርስ ዲግሪውን በስኮላርሺፕ አግኝቷል፡፡ከአብዮቱ
በኋላ የእድገት በህብረት ምክትል አመራር ሆነ፡፡በኋላ በሽመልስ አዱኛ ስር ምክትል ሆኖ (relief
and rehabilitation commission) የእርዳታ ማስተባበርያ መቋቋሚያ ኮሚሽን ውስጥ
ሰራ፡፡ቆይቶም በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ውስጥ በቋሚ ጸሃፊነት ተቀጠረ፡፡ቀጥሎ በኤርትራ ክፍለ
ሃገር በኢሰፓኮ(COPWE)በልዩ ልኡክነት ማገልገል ጀመረ፡፡ወደ አሜሪካ ሃገር ከመሸሹ በፊት
የመጨረሻው የኢትዮጵያ ስራው የእርዳታ ማስተባበርያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን ዋና ስራ አስኪያጅነት
ነበር፡፡እዚያ እያለ በአብዮቱ ዙርያ Red tears የተሰኘ መጽሐፍ ጽፏል፡፡16ቀጣዩ ልጅ ጌትነት
ከሁሉም ልጆቻቸው ብሩህ ጭንቅላትን የታደለ ነው ይባላል፡፡አዲስ አበባ ከሚገኘው የህንጻ ኮሌጅ
በምህንድስና ተመርቆ አሜሪካን ሃገር በመሄድ ማስተርሱን አግኝቷል፡፡ በኢንዱስትሪ ሚንስትር
የፕሮጀክቶች ማዕከል የበላይ በመሆን ሲሰራ ቆይቶ በኋላ የቆዳና ሌጦ ኮርፖሬሽን አስተዳዳሪ ሆነ፡
፡ቀጥሎ ለኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ አስተዳደር በመሆን በእቅድ ኮሚሽን ስር ሰራ፡፡
በ1980 ዓ.ም ከዋና ኢንጂነሩ ስር ምክትል በመሆን በአሜሪካን ለኒው ጀርሲ ከተማ ምክር ቤት
ያገልግል ነበር፡፡ቀጣዩ ልጅ ዮሐንስ በትምህርቱ ጎበዝ የነበረ ሲሆን በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ማህበር ጸሃፊ ሆኖ ነበር፡፡ነገር ግን በተማሪዎች መሃል በነበረው አለመረጋጋት
ወደ ውጪ መውጣትን እንደ አማራጭ ይዞ ወደ አሜሪካ አቀና(ያመለጠው ልክ የንግስት ሳራ
የልኡል መኮንን ሚስት ልጃቸው?? (እዚህ ጋር ወንድማቸው መሆን አይገባውምን?)በተገደለበት
ወቅት ነው)በባልቲሞር ዩንቨርሲቲ ሜርላንድ አጥንቶ ኦክላንድ ዩንቨርሲቲ ካሊፎርንያ በፍልስፍና፤
ፖለቲካ ሳይንስና በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ተመርቋል፡፡ በ1980 ዓ.ም በካሊፎርንያ ከውጪ

233
ጥቋቁር አናብስት

የመጡ ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር ሆኗል፡፡ቀጣይዋ ልጃቸው ኤልሳቤጥ በቢዝነስ


አድሚንስትሬሽን ከዋሽንግተን ዩንቨርሲቲ ተመርቃ በ1980 ዓ.ም በካሊፎርንያ የአንድ ባንክ ስራ
አስኪያጅ ነበረች ፡፡

***

ወልደግዮርጊስ የመሞቻቸው ጊዜ ሲደርስ ቤተሰባቸውን ሰብስበው ምንም የሚያወርሷቸው ሃብት


እንደሌለ ነገር ግን በሚችሉት ሁሉ እነሱን ለማስተማር እንደጣሩ ነገሯቸው፡፡በልጆቻቸው እርስ
በእርስ መፈቃቀር ደስተኛ እንደሆኑና በዚሁ ቀጥለው እናታቸውን (በወቅቱ በህይወት ነበሩ)
እንዲንከባከቡ አደራ አሏቸው፡፡ይሄን የመጨረሻ ኑዛዜያቸውን በወረቀት ላይ ያሰፈሩት ሲሆን
ሁሉም ልጆቻቸው ቀሪው አላቸው፡፡

ወልደ ግዮርጊስ ወልደዮሐንስ ሙሉ ህይወታቸውን ጠንካራ ነበሩ፡፡የእግር ጉዞ ማድረግም


ይወዳሉ፡፡ነገር ግን ለረዥም ጊዜ የቆየ የሆድ ህመም ምን አልባትም አልሰር ስለነበረባቸው ምግብ
ይመርጣሉ፡፡ይሄ ምንአልባት በጠንካራ ስራ መንስኤ የመጣ ሊሆን ይችላል “ሁሌ መጻፍ እንጂ
አርፈው አያውቁም” ይላል ልጃቸው አያሌው፡፡

ምንም እንኳን ከ25 የስራ አመታት በኋላ በ1958 አ.ም ጡረታ ለመውጣት ቢፈልጉም (1933
ጀምሮ እስከ ግንቦት 33 1966 ድረስ) የመንግስት ለውጡ 3 ወራት እስኪቀረው ድረስ
አልቻሉም፡፡ ወልደግዮርጊስ በአዲሱ መንግስትም ጊዜ በሰላም ለመኖር ቻሉ፡፡ጡረታ ከወጡ በኋላ
ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በትጋት መጽሐፍ መጻፍ ጀምረው የነበር ሲሆን በጽሁፋቸውም ያላቸውን
ተስፋ ገልጸው እንዲታተም ቢፈልጉም ሳይታተም ቀርቷል፡፡ወልደ ግዮርጊስ ጽፈው የጨረሱት
በሰባዎቹ ማገባደጃ ነበር፡፡መጨረሻ ላይ ከቤተሰባቸው ውስጥ አንድ ሰው ረቂቁን ችግር ይፈጥራል
ብሎ በቤት ከማኖር አቃጠለው፡፡17

በ1972 ዓ.ም አይናቸው ማየት ተሳነው፡፡ይህ ክስተት በሳቸው ላይ ታላቅ ጭንቀትን ፈጠረ፡፡
እድሜ ልካቸውን ሲጽፉና ሲያነቡ ኖረው በዚህ ሰአት ፈጣሪ ለምን ብርሃኑን ነሳቸው?ይሄን
ስነልቦናዊ ቅራኔ የማስታረቅ ችግር ደረሰባቸው፡፡የፈጣሪ ፍቃድ ነው ብለው ለመቀበል ቢሞክሩም
መልሶ ግን በፈጣሪ የመማረር ስሜት ይመጣባቸዋል፡፡ቤተሰቦቻቸው እንደሚያስቡት ችግራቸውን
ተቀብለው አዕምሯቸው ከመረጋጋት ይልቅ እንደውም እያገረሸበት እንደተናወጠ የመጨረሻዎቹን
እድሜያቸውን ገፍተዋል፡፡መጻፍም ሆነ ማንበብ እንዲሁም መራመድ አቃታቸው፡፡ስለዚህ የመኖር
ትርጉም ምንድን ነው?በአካልም ሆነ በመንፈስ ድቅቅ አሉ፡፡ ለ2 አመታት አልጋ ላይ ዋሉ፡፡

234
ጥቋቁር አናብስት

በስተመጨረሻ ከሚደሰቱበት ነገሮች መሃል ግን የልጆቻቸው ደህንነት አንዱ ነበር፡፡ጤናቸው


እየደከመ ሲሄድ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብተው ነበር፡፡ሆስፒታሉ ውስጥ ሳሉ ምናልባት
በውስጥ ድማት ምክንያት በታህሳስ 10 1974 አ.ምበ87 አመታቸው አረፉ፡፡

ያገለገሉባቸው የነበሩ አድባራት ቀሳውስት የደብረ ሊባኖስን አፈር መቅመስ አለባቸው ስላሉ
ከቤተመቅደሱ አቅራቢያ ቤተሰቡን በሚያኮራ ሁኔታ ታላላቅ ባለስልጣናት፤የቤተ ክህነት ሰዎችና
በርካታ ሀዘንተኛ በተገኘበት ልጃቸው አምባሳደር አያሌውም ከሎንደን በራሱ ወጪ ተሳፍሮ
በመጣበት ስርዐተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ቤተሰቦቻቸውም በተገኙበት ተገቢው ስርአተ ዝክር በተለያየ ጊዜ የተፈጸመላቸው ሲሆን


ልጆቻቸው ግን አባታቸው እንድታድግበትከሚመኙላት መንገድ ያፈነገጠች ሃገራቸው ላይ መኖሩ
ከብዷቸው ነበርና ወደ ውጪ ሃገር ተሰደዱ፡፡

ማስታወሻ

1)አለቃ ህሩይ የታወቁ የቤተልሄም በጌ ምድር ምሁር ነበሩ፡፡መስከረም 15 1855 ዓ.ም ሲሆን
የተወለዱት አመተ እረፍታቸው በ1948 ዓ.ም ነው፡፡

2)እነሱም መምህር ሃይለማርያም በኋላ አቡነ ጴጥሮስ የሆኑት አቶ ሊቄ በኋላ አፈ ንጉስ ገብረ
ክርስቶስ የሆኑት አለቃ ለማና መልዐከ ገነትክፍሌ ናቸው፡፡

3)ሌላ ታዋቂ ድራሲ ሆነው ለኢጣልያ መንግስት “በውብ አማርኛቸው መክንያት” በስርጭት ስራ
የተሳተፉት ደግሞ ከበደ ሚካኤል ሲሆኑ በዚህ ስራ ላይ የሰሩበት ሁኔታ በፍቃደኝነት ይሁን
አይሁን አይታወቅም፡፡አንዳንድ“ተባባሪዎች” እጃቸውን ተጠምዝዘው ከወራሪው ጋር እንደሰሩ
ይናገራሉ፡፡ ምናልባትም እንዲረሳላቸው ፈልገው ይሆናል፡፡

4)በዚህ ጉዞ ብርሃኑ ዘርይሁን በአሉ ግርማ ጳውሎስ ኞኞ እና አንድ ሌላ ጋዜጠኛ አብሯቸው ነበር፡

5) እንደሚያስቡት ከሆነ የራሳቸው ቤተክርስትያን የክርስቶስን ደቀመዛሙራት ዋነኛና ጠቃሚ


መልእክት እንደያዘች ያስባሉ፡፡እንደ ልጃቸው አያሌው አባባል አስተምህሮቶቿም በንጽህና ጠብቃ
የኖረች ነች፡፡

235
ጥቋቁር አናብስት

6)ይህ የኋለኛው ቀን በጣም የረፈደና ለዚህ ስራ ተስማሚው ቀን አይመስልም፡፡አብዮቱ በዚህ


ወቅት ጎምርቶ ነበርና፡፡ሁለተኛው የግለታሪክ ቅጽ በ1965 ዓ.ም ሲታተም ከበደ ሚካኤል
ለሚፈልጉት ሰነዶች ሁሉ ሙሉ የማግኘት ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ከንጉሱ ጋርም በርካታ ቃለ
መጠይቆችን አድርገዋል፡፡በኋላ ግን እራሳቸውን ከስራው አገለሉ፡፡ምንአልባትም በህመማቸው
ጅማሮ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ወይም ምናልባት በሚጻፍበት ሁኔታ ከንጉሱ ጋር
ባለመስማማታቸው ይሆናል፡፡(ይሄ የኋለኛው መክንያት ከበደ ለኔ የነገሩኝ ነው)

7)ንጉሱ በቤተመንግስቱ ውስጥ ለሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ለሚሰሩ ቀሳውስት መሬት ይሰጡ ነበር፡
፡ወልደ ግዮርጊስ በልጅ እያሱ ከተሰራው ቀጨኔ መድሃኒያለም ከመስራታቸው በፊት አሁን
ዩንቨርሲቲው አጠገብ ከሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ያገለግሉ ነበር፡፡

8)ይህ መጽሐፍ በሌላ ቆየት ብሎ በወጣ መጽሃፍ አትስረቅ የሳቸው ለመሆኑ ከጀርባው ተጠቅሷል፡
፡መጽሐፉ ራሱ ግን የደራሲውን ስም አይጠቅስም፡፡

9)ሙሉ ርእሱ አምስት መንገደኞች በጉዞ ምእራፍ ላይ ይሰኛል፡፡

10)ሁለቱም መጻህፍት ከውጪ ትምህርት ስለተመለሱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዙርያ


ያጠነጥናሉ፡፡ለነገሩ የግርማቸው መጽሐፍ የተጻፈው የወልደ ግዮርጊስ የመጀመርያዎቹ ተከታታይ
ህትመቶች በአዲስ ዘመን ብቅ ማለት ከጀመሩ ከአንድ አመት በኋላ ሲሆን የታተመውም ቆይቶ
ነበር፡፡ስለዚህ ምንም እንኳን ወልደ ግዮርጊስ በመጀመርያ ቢጽፉም እርስ በእራሳቸው አንዱ
በሌላው ተጽእኖ ስር የመውደቅ ሁኔታቸው አናሳ ነው፡፡ሁለቱም መጻሕፍት ብቅ ያሉት ህሩይ
ተመሳሳይ ቴክኒክ ተጠቅመው አዲስ አለምን ከጻፉ በኋላ ነው፡፡እራስ እምሩም የአለም ትግልን
ከዚህ በፊት በ1933 ጽፈው የነበሩ ቢሆንም ሊታተም የበቃው ግን በ1966ዓ.ም ነው፡፡

11)ለማንኛውም ´ከእውነቱ ያነሰ ነገርን´እንዲናገሩ የተገደዱባቸው ተልእኮዎች ተስጥቷቸዋል፡፡


ለምሳሌ ለልኡል መኮንን ሞት የሃዘን መግለጫ ማስታወሻ መጽሐፍ እንዲሰሩ ሲነገራቸው መቼም
መገመት እንደሚቻለው ስለነበሯቸውን እቁባት እና ከህግ ውጪ ስለተወለዱ ልጆችን ማንሳት
አይችሉም ፡፡ወይንም ከሚስቱ ጋር ሲወሰልቱ የያዛቸው አንድ የአየር ሃይል መኮንን በመሳርያ
ተኩሶባቸው የመሞታቸውን ዜና በመኪና አደጋ ወደ ደቡብ ሲሄዱ በአደጋ እንደሞቱ ለማድረግ
መሞከሩን መጻፍ አይችሉም፡፡

12)የያሬድ ገብረ ሚካኤል እናት የወልደግዮርጊስ የአባታቸው እናት ነበረች ወይም እንደዚህ
አይነት ዝምድና ነበራቸው፡፡የያሬድ ልጆች ወልደግዮርጊስን አጎት በማለት ይጠሯቸዋል፡፡ያሬድ
236
ጥቋቁር አናብስት

ከ20 በላይ መጻህፍትን ጽፈዋል፡፡አብዛኞቹ ስለ ንጉሳዊው ቤተሰብ ነበሩ፡፡በተለይ ስለሚወዷቸው


ልኡል

13)የብርሃኑ ዘርይሁንና የያሬድ ገብረ ሚካኤል እንዲሁም የሌሎች ጋዜጠኞች እድሜ ያጠረው
በመጠጥ ጦስ ነው ብለው ወልደ ግዮርጊስ መገመታቸው አይቀርም ነበር፡፡

14)(የሰንደቅ አላማችን)ጋዜጣ ጥሩ አርታኢ ጥሩ ዘጋቢና ጋዜጠኛ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ለምሳሌ


ኃይለሥላሴ ከፌዴርሽኑ በኋላ ወደ አስመራ ሲሄዱና ከዛ ቀደም ብሎ ወደ አዲስ አበባ በነጻነት
ወቅት ሲመለሱ ዘግቧል

15)(የንጉሳዊው ቤተሰብ ጥሩ ጋዜጠኛና ቤሳ መጻሕፍት ጸኃፊ)ተብሎ ተፈርጇል፡፡ከያሬድ ገብረ


ሚካኤል ጋርም ይቀራረባሉ፡፡የወልደ ግዮርጊስን ታሪክ በማጠናበት ወቅት በህይወት ነበር በ1980
ዓ.ም

16)በርካታ የግል ጽሁፎችና ምስሎች ከንጉሱ ግዜ በኋላ ባለው የድህረ አብዮት ግዜ በካድሬዎችና
ለደህንነታቸው ፍርሃት ባደረባቸው ሰዎች ወድመዋል፡፡

17)አንዳንድ ኢትዮጵያኖች በዚህ ርእስ ቅኔያዊ ይዘት አለው ይላሉ፡፡በኮምዩንስት አገዛዝ የፈሰሱ
የእንባ ዘለላዎችን በአጽንኦት ለማንሳትና ሌላ መራር ሃዘንንም ለመግለጽ ዘይቤያዊ ስልትን
ተጠቅሟል በማለት (መጽሐፉ ከማርክሳዊው አገዛዝ ውድቀት በኋላ ዳዊትም ወደ ሃገሩ
በተመለሰበት ወቅት ወደ አማርኛ ተመልሷል)

18)ደብረ ሊባኖስ ገዳም ስለሆነና ቤተክርስትያኒቱም የዛ አካል ስለሆነች ወዳጆቹ የሆኑት ካህናት
በቀብሩ ስነ ስርአት ሊካፈሉ አልቻሉም፡፡ባህታዊዎች ብቻ ናቸው በሃይማኖታዊ ስርአቶች መሳተፍ
የሚችሉት በደብረ ሊባኖስ ፡፡ያላገቡ ንቁ ወጣት ዲያቆናት ግን ማገዝ ይችላሉ፡፡በጣም ወጣት
አልያም በጣም የሸመገሉ መሆን አለባቸው፡፡(የወሲብ ስሜት እንዳይኖራቸው ተብሎ)ይህ የቅድስና
መገለጫ ነው፡፡(ዲያቆናት የወሲብ ስሜት ባደረባቸውም ወቅት በአገልግሎት ላይ እስካላገቡ
መሳተፍ አይችሉም)፡፡

237
ጥቋቁር አናብስት

ሶስቱ የመዛግብተ ቃላት አዘጋጆች


የአንድ ሃገር ስነጽሁፍ ሲያብብ ቋንቋውም አብሮ ያድጋል፡፡የውጪ ቋንቋ የመግለጫ መንገድ ሲሆን
ግን አግባቡ ይሄ አይደለም፡፡የተለመደ ድህረ ቅኝ ግዛት ክስትተ ነው፡፡በሃገራዊ ቋንቋ የተጻፈ
ሃገራዊ ስነ ጽሁፍ የማደግ እምቅነት ይኖረዋል፡፡ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት አማርኛ ቋንቋ
በፍጥነት አድጓል፡፡ይህ የሆነው በአዳዲስ ወጥ ቃላት መምጣት ሳይሆን (ከተለያዩ ዘዬዎች ፤ዘመናዊ
ቋንቋዎች፤ከውጪ በመበደር፡በአዳዲስ ፈጠራዎች ለምሳሌ በአማርኛ እንደተለመደው ደግሞ ወደ
ግእዝ በመመለስ)ነገር ግን ከተረሱ ወይም ሊረሱ ከተቃረቡ ቃላትን በማዳን ምንአልባትም
በአረጋውያን ወይንም ከጥንት ድርሳናትን በመጠቀም ደራሲዎችና ምሁራን ቋንቋቸውን
ሊያሳድጉበት ይችላሉ፡፡

ይህ የቃላት አደን ጠቀሜታ ያለው ባህላዊ ስራ የሚሆነው ሃገራዊ ስነጽሁፉ በፍጥነት ሲስፋፋ
ነው፡፡የዚህ ስራ አንዱ ውጤት ደግሞ አዳዲስና የተሻሻሉ መዛግብተቃላት መዘጋጀት ነው፡፡ባለፉት
ጥቂት አስርት አመታት የተዘጋጁ መዛግብተቃላት ደግሞ ታላቅ አስተዋጽኦን ለአማርኛ(ለትግርኛና
ኦሮምኛ ቋንቋዎች) አበርክተዋል፡፡ ጠቀሜታው ለነዚህ ቋንቋ ተማሪዎችና በነዚህ ቋንቋዎች
በተለያዩ መንገድ ለሚጠቀሙባቸው ሁሉ ነው፡፡ መዝገበ ቃላትን እያነበቡ የቃላት እውቀታቸውን
ለማስፋትና ትክክለኛውን ትርጓሜ ለማግኘት ለሚፈልጉ ደራስያንም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ፡፡ስለ
ባህላዊ እሴቶችና ያለፉ ልማዶችም የምናውቅባቸው አስተማሪ መዛግብተ ቃላት ናቸው፡፡ቃላቱን
ብቻ ስለማይፈቱና ከአውድ አንጻር ስለሚያዩት እንዴት ባለና በምን ሁኔታ ውስጥ መጠቀም
እንደምንችል ስለሚያሳዩ ታሪካዊ መረጃዎችንም ማግኘት ይቻላል፡፡እምነቶች እደ ጥበባዊ ቅርሶች
አባባሎች ትውፊት ሁሉ ከሞላ ጎደል በጥሩ መዝገበ ቃላት ውስጥ ይካተታሉ፡፡በሌላ መንገድ
እነርሱ እራሳቸው ለአያያዝ የሚመቹ ኢንሳይክሎፔድያ ናቸው ማለት እንችላለን፡፡

እዚህ እገዛቸውን ካገኘሁባቸው ሁለት መዛግብተቃላት አዘጋጆችን አጭር የህይወት ታሪክና አንድ
በትግርኛ ተማሪዎች ስሙ የሚመሰገን የትግርኛ መዝገበ ቃላት አዘጋጅን ለማካተት ሞክሬያለሁ፡

238
ጥቋቁር አናብስት

ተሰማ ሀብተሚካኤል
በመዝገበ–ቃላቱ የተነሳ "ብርሃን ፈንጣቂ" ተብሎ የሚጠራ

ለበርካታ አመታት ከሳቴብርሃን(ከፋች፤ከሳች፤ገላጭ) ገበያ ላይብቸኛና


ጥሩ የሚባለው መዝገበ ቃላት ነበር:: በአንድ ቃል ዙርያ ክርክር ከተነሳ
ወይም የቃሉ አቻ ትርጉም ለማወቅ ከተፈለገ ወደ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ
ሃብተሚካኤልን ማየት ግድ ይላል::ይግባኝ የማይባልበት ዳኛ ነበር፡፡ብዙ
ሰዎች እንዲሁ እያገላበጡ በመመልከት አማርኛን በተሻለ ለማወቅ ጥረት
ያደርጉ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ቤተመፃሕፍት የተጎሳቆለ መጽሐፍ
ካያችሁ እሱ ከሳቴብርሃን ነው:: ለተማሪዎች የቃላት የገለጻ ቋት ነው ለአንባቢና ለምሁሩም
እንዲሁ::ለመጀመርያ ጊዜ መዝገበ ቃላት ማግኘት ስፈልግ የተሰማ ዐይነት ለማግኘት
ተቸግሬያለሁ::ቆይቶ አሮጌውን በውድ ዋጋ አግኝቼ ገዛሁ:: ምንአልባት ዛሬ ዛሬ ሌሎችም
ስለታተሙ በምርጫ ማግኘት ይቻል ይሆናል:: በተለይ መርካቶ አካባቢ ካሉ መጻሕፍት
መሸጫዎች እጅግ በናረ ዋጋ ማግኘት ይቻላል አቅም ከፈቀደ::

የመዝገበ ቃላት አሰናጂው ተሰማሃብተሚካኤል¹የተወለደው ጎሃጽዮን በሚባል አካባቢ በጃርሶ


ወረዳ በሰላሌ አውራጃ ሸዋ ውሰጥበ1882 ዓ.ም ሲሆን ወላጆቹም አቶ ሃብተሚካኤል ትእዛዙና
ወይዘሮ ወለተየስ ወልዴ ይባላሉ፡፡

ተሰማ በልጅነቱ ነው ትምህርት የጀመረው በአቅራቢያው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው ትምህርት


ቤት ለመድረስ አባይን ማቋረጥ ነበረበት፡፡ጽዋትወ ዜማን ቅኔን ትርጓሜን በተለያዩ አብያተ
ክርስትያናትና ገዳማት አጠና፡፡ለቅኔና ዜማ ግን ወደ ታዋቂው ዲማ ነበር ያቀናው፡፡

ከፍ ያለ የቤተክርስትያን ትምህርቱን ከቀሰመ በኋላ ሃረር የመጀመርያ ስራውን በፀኃፊነት ተቀጠረ፡


፡ለዚህ ስራው ወርሃዊ ምንዳው 9ብር ነበር፡፡ይሄ የሆነው በ29 አመቱ በ1911 ዓ.ም ነው፡፡በዚህ
ጊዜ በወረቀት መጻፍ እየተለመደና ጊዜ የሚፈጀውን ብራናን እየተካ ነበር፡፡(ብራናን ማልፋትና
ለጽሁፍ እንዲስማማ ማድረግ በቤተክርስትያን ከቁምጽሁፍ ጋር ከሚሰጡት ትምህርቶች አንዱ
ሆኖ ሳለ አብዛኛው ሰው ግን በቃል በማንበብና በቃል በማጥናት ይወሰን ነበር)በሃገሪቱ በክብር
እሚታይና በትልቅ ጥበብነት የሚወሰደውን የቁም ጽሁፍ ተሰማ በየዐይነቱ በመጻፍ ችሎታው
የተመሰገነ ነበር።ስራው ላይም ብዙ መንፈሳዊ መጻሕፍት እንዲገለብጥ ይታዘዛል፡፡ከነዚህም መሃል

239
ጥቋቁር አናብስት

አንዱ ግጽው² ይሰኛል፡፡ተሰማም የዚህን መጻሐፍ ገልብጦ መጨረስን ተከትሎ በመከተል (ግጽው)
ተብሎ ይጠራ ጀመር፡፡

ከ1922 እስከ1927 አ.ም ለሃረርጌ የመሳርያ ግምዣ ቤት ሃላፊ ነበር፡፡ጣልያን ኢትዮጵያን


በወረረችበት ወቅትም በዚሁ ሃላፊነት ላይ ነበር፡፡ከወረራው በኋላ እዛው ሃረርጌ ለሚሰራጩት
ጋዜጦችና መረጃ ሃላፊ ለሆነው ለጋዜጦችና ፕሮፖጋንዳ ቢሮ በፀሃፊነት ተቀጠረ፡፡

ቆይቶ መምህር መሆን ፈለገ፡፡ በማመልከቻውም መሰረት ወደ ትምህርትና ስነጽሁፍ ሚንስትር


ተዘዋወረ፡፡መጀመርያ በሃረር ማስተማር ጀመረ፡፡ጎንለጎን የአርትኦት ስራን ለሚንስትር ቢሮው ሃረር
እያለ ይሰራ ጀመረ፡፡ አዲስአበባም ከመጣ በኋላ መምህራን ማሰልጠኛ ይህንን የአርትኦት ስራ
ቀጠለበት፡፡

በመቀጠል በህብረተሰቡ ዘንድ እንደ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚቆጠርለትን ተልእኮ ትምህርት


ሚንስትር ተሰጠው፡፡ የአማርኛ መዝገበቃላትን ማዘጋጀት፡፡በ1954 ዓ.ም በጡረታ እስከተገለለበት
ጊዜ ድረስም በዚህ ስራ ላይ አብዛኛው የስራ ጊዜውን ሰውቶ ሰርቷል፡፡ ከሳቴብርሃን ላይ መስራት
ታላቁ ስኬቱና አድምቶ የተጓዘበት መንገድ ነበር፡፡በተለይከ1937-1947 ዓ.ም፡፡ ይህን
መዝገበቃላት እውን ለማድረግ ሲንቀሳቀስ ብዙ ችግርና መሰናክል አልፏል፡፡ በሚሰራበት መስርያ
ቤት ሊያግዘው የሚችል የስራ ባልደረባ ወይም ሊያማክረው የሚችለው ሰው እንኳን አልነበረም፡፡
አባቱ ለበርካታ አመታት ውጪ ቆይተው በመመለሳቸው እንግሊዘኛን ፈረንሳይኛን አስተማሩት፡፡
የውጭ ቋንቋዎችን መማሩም ለመዝገበቃላት ዝግጅቱ ጠቅሞታል፡፡በተጨማሪም ሃረርጌ ሳለ ተሰማ
አረቢኛን ኦሮምኛን ሀደርኛን ተምሯል፡፡አማርኛ አፍ የፈታበት ቋንቋ ሲሆን ግእዝንም
በቤተክርስትያን ቆይታው ቀስሟል፡፡ይህንን እወቀት ለበጎጉዳይ በማዋል ለከሳቴብርሃን እውንነት
ታትሯል፡፡ተሰማ ይህንን መዝገበቃላት ያሰናዳበት ዐይነተኛ መክንያት በመምህራን ማሰልጠኛ
መምህር ሳለ ባጋጠመው የማጣቀሻ መጽሐፍት እጦት መንስኤ ነው፡፡እዚያ ያሉት ተማሪዎች
ትክክለኛ የአማርኛ ቃላትን የመፍታትና በአግባቡ የመጠቀም ችግር ነበረባቸው፡፡ በሌላም በኩል
አብዛኛው የአማርኛቋንቋ ቱባ ቃላት በተለይ በከተማ አካባቢ ባሉ ተናጋሪዎች እየጠፋ ስለሆነ
የአማርኛ መዝገበቃላትን የማዘጋጀት ራእይ ጸንሶ ተንቀሳቀሰ፡፡የዚህን ቋንቋ ውርስ ለትውልድ
ለማስተላለፍ መዝገበቃላቱን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ አምኖበት ነበር፡፡ከ10 አልህ አስጨራሽ
የድካም አመታት በኋላ ለ1398 ገጽ መዝገበቃላት የሚበቃ ግብአት ሰበሰበ፡፡ይህም 33000ያህል
የቃላት ፍቺዎችና 1278 ያክል ምስሎችን ያካተተ ነበር፡፡በተጀመረ በ12 አመቱ ተጠናቆ ለገበያ
በቃ፡፡መዝገበቃላቱ ለተሰማ ክብር ሲባል ተሰማ ተብሎ እንዲሰየም በመዝገበቃላቱ ዙርያ
በትምሀርትና እደጥበባት ሚንስትር የተዋቀረው ቦርድ ፈቀደ፡፡በተለይ ብቻውን በአነስተኛ ደመወዝ
ሰርቶ ከማጠናቀቁ አኳያ ይህ ለተሰማ እንደ ትልቅ ሽልማትየሚቆጠር ነበር፡፡በአንድ ወቅት ተሰማ
240
ጥቋቁር አናብስት

ከደመወዙ ማነስ የተነሳ ከስራ የመልቀቅያ ደብዳቤ አስገብቶ የነበረቢሆንም መዝገበ ቃላቱ
በቀዳማዊ ኀይለሥላሴ በመፈለጉ ምክንያት ተቀባይነት አጥቷል፡፡

አቶ ተሰማ ጡረታ ሲወጣ አድካሚ የሆነ ደምግፊት አስቸግሮት ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ከፍተኛ
ድካም ይሰማው ነበር፡፡በ80 አመቱ በመስከረም 30 1962 አ.ም ከማረፉ ከስድስት ቀናት በፊት
በጥልቅ የምርምር ስራ³ የቀዳማዊ ኀይለሥላሴን ሽልማት እንዳሸነፈ ተነግሮታል፡፡ በአዲስ አበባ
ውስጥ በቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተቀበረ። ካረፈ ከ23 ቀናት በኋላ ልጁ ሰላማዊት
ተሰማ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ሽልማት በአባቷ ስም ተቀብላለች።

ተሰማ ሀብተሚካኤል እስከአሁን ያልታተሙና በልጆቻቸው እጅ የሚገኙ ሌሎች መፅሀፍትንም


ጽፈዋል።

241
ጥቋቁር አናብስት

ደስታ ተክለወልድ

ምርጡ የአማርኛ መዝገበ–ቃላት አዘጋጅ

TRADITION AND CHANGE IN ETHIOPIA .SOCIAL AND


CULTURAL LIFE AS REFELECTED IN AMHARIC FICTIONAL
PLAN OF ACTION CA .1930-1974⁴

የተሰኘውን ስለ አማርኛ ስነጽሁፍ የተዘጋጀ

መጽሐፌን ሳዘጋጅ ጥሩ ፈሊጣዊ አነጋገርን የሚያስረዳ የአማርኛ


መዝገበ-ቃላትን ፈለግሁ፡፡ በአውሮጳ ትርጓሜ ካላቸው ብሎም
በከሳቴብ ርሃን መዝገበቃላት ብዙ ፍሬቢስ ሀሰሳዎችን አደረኩ፡፡
የፈለኩትን ያገኘሁት ግን በደስታ ተክለወልድ አዲስ መዝገበ ቃላትነው፡፡አብዛኛዎቹ መዝገበ
ቃላት የምፈልጋቸውን ቃላቶች አልያዙም፡፡አልያም ፈሊጣዊ አጠቃቀማቸውን አያካትቱም፡፡
ከሞላጎደል በአብዛኛው የምፈልገውን ከደስታ ተክለወልድ አገኘሁ፡፡ከመዝገበቃላቱ ጋር ለረጅም
አመታት እስካሁንም የዘለቀ ቁርኝት አለን፡፡በደስታ ተክለወልድ ውስጥ ተፈልገው የታጡ
ቃላትን በሌላ መዝገበ-ቃላት ውስጥ የማገኘው ከስንት አንዴ በሚያስብል ሁናቴ ውስጥ ሲሆን
የግርምቢጥ በሌላ መዛግብተቃላት ውስጥ የጠፉትን ግን ደስታ ተክለወልድ ጋር ለቁጥር
በሚያታክቱ ጊዜያት ለማግኘት ችያለሁ፡፡ የቃላቱን ትርጉም ከመፍታቱ ውጪ ደስታ የቃላትን
የገለጻዎችን ትውፊታዊና ታሪካዊመረጃ ስለሚያቀብለኝ እንደ ወርቅ ጉድጓድ ነው የምቆጥረው፡፡

ደስታ ተክለወልድ በመዝገበቃላቱ የሚጠቀመው የቀደመውን የአቡጊዳ ፊደል አደራደርን


(ኪዳነወልድ ክፍሌ ጀምረውት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ)ደስታ ተክለወልድ ከዳር
ያደረሰው መዝገበ ቃላት ላይ ያለውም ይሄ አጠቃቀም ነው፡፡ለአንዳንድ ሰዎች አጠቃቀሙ
ያደናግራል፡፡ የሱ የዚህ ሆሄያት አጠቃቀም ግን በአዲሱ የሀሁ ሆሄያት አደራደር ለተማሩ
ተማሪዎች ተግዳሮት አልነበረም፡፡ረዥሙን የፊደላት ድርድር በአእምሮው ላልሸመደደ ሰው ወደ
መጨረሻ ወይም በሚታየው መልኩ ማስቀመጥ ይችላል፡፡በአማርኛ ቋንቋ ላይ ተመስርተው
ከተሰሩ መዛግብተቃላት ደሰታ ተክለወልድን ለየት የሚያደርገው የፊደል አደራደሩ ቀላልና
አሳማኝ በሆነ መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ሌሎቹ ሰአት አባካኝና የተንዛዙ ናቸው፡፡ ቃላትን በመሰተሩ
242
ጥቋቁር አናብስት

ደስታ ተክለወልድን በሚበልጥ መልኩ የቀረበ የለም፡፡የእሱ ዘዴም ለዘመናዊው አደራደር


ሊሰራበት ይችላል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1985 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ስመጣ ደስታተክለወልድን መጎብኘት


ፈለኩ፡፡የአንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁር ልጅ የሆነ ወደጄ በመጀመርያ ቆይታዬ (ከ1965-
1974) ወቅት እንዳገኘው ቢጠይቀኝም በየጊዜው ቀጠሯችን እየተላለፈ ሳላየው ቀረሁ፡፡ እንደ
እድል ሆኖ በቀጣዩ ቆይታዬ ግን ትውፊታዊውን የግዕዝ ንባብን እንዲያስተምረኝ የቀጠርኩት
የግል አሥጠኚዬ መዝገበቃላቱ የታተመበት ከደስታ ጋር አብረው በአርቲስቲክ ማተምያ አብረው
ይሰሩ ስለ ነበር ይተዋወቃሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ የግል አስጠኚዬ ስም እንኳን ለመዝገበቃላቱ
አንዳንድ ፍቺዎችን በማዋጣቱ ተጠቅሷል፡፡ደስታ ተክለወልድ በጊዜው ጤናው እምብዛም ቢሆን
ወስዶ እንደሚያሳየኝ ቃል ገባልኝ፡፡

አለቃ ደስታ ተክለወልድ በሽልማት መልክ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጅት ስለ


መዝገበ ቃላት ስራው መጠናቀቅ 10000 ብር ተከፍሎታል፡፡በዚህ የሽልማት ገንዘብ ከሥላሴ
ቤተክርስትያን ጀርባ ጥሩ ቤት ሰርቶ ስለነበር ልንጎበኘው የሄድነው እዚያ ነው፡፡በጣም ጥሩ
አቀባበል ቢደረግልንም ደስታ ስለታመመ ወደ እንግዳ ክፍል መጥቶ ማናገር ስለማይችል ማናገር
ከፈለግን ወደ መኝታ ክፍሉ መግባትና ማናገር እንደምንችል ተነግሮን ዘለቅን፡፡ብርድ ብርድ
ብሎት በብርድ ልብስ ተሸፋፍኖ ነበር የሚያናግረን፡፡ደረቱን ያመዋል፤ያስለዋል፡፡የግዕዝ
መምህሬ በእደማርያም ማንነቴንና ስለ ኢትዮጵያ ስነጽሁፍ መጽሐፍ መጻፌን ነገረው፡፡ደስታ
ትምህርት በኢትዮጵያ ስለማሽቆልቆሉ በአውሮጳ ግን እያበበ ስለ መሄዱ አንስቶ በቁጭት
አማረረ፡፡ በጨዋታችን መሃል የደስታ የማስታወስ ችሎታ እየደከመ መሄዱን ግልጽ እየሆነልን
መጣ፡፡በጣም ተዳክሟል፡፡ወደ እንግዳ ክፍሉም በቶሎ ተመልሰን በእጅ የተጻፈውን የታዋቂውን
የመዝገበቃላት ረቂቅ ሌላውን በቤተክርስትያን ታሪክና ትውፊት ላይተጽፎ በፍሮቤንየስ ተቋም
ጀርመን የታተመውን ሃይማኖተ አበውን ሌሎችንም ስራዎቹን አየናቸው፡፡ጥሩና ግልፅ የእጅ
ጽህፈት ነበረው፡፡ሚስቱ (እድሜ ልኩን በጥናት ስለኖረ ጓደኛ የለውም ጓደኞቹ መጻህፍቱ
ናቸው) አለችን፡፡ ሻል ሲለው ለመመለስ ወጣን ነገር ግን ከሶስት ቀናት በኋላ አረፈ፡፡ይህንን
የተረዳሁት ከጥቂት ቀናት በኋላ (ምንአልባትም በዶክተር ብርሃኑ አበበ የተጻፈ የሃዘን
መግለጫ)በጋዜጣ ወጥቶ ስላየሁትነው፡፡

ደስታ ተክለወልድ በሃምሌ 1893 ዓ.ም ሸዋ ተጉለት ውስጥ በቡልጋ አውራጃ ከአባታቸው አቶ
ተክለወልድና ከወይዘሮ ወለተማርያም ጎሽውሃ ወግዳ ውስጥ ተወለደ፡፡በአቅራቢያው ካለ
ቄስትምህርት ቤት ገባ፡፡ቀጥሎም በደብረሊባኖስ ገዳም ከአለቃ ኪዳነማርያምና ከመምህር
ገብረኢየሱስ ስር ቅኔና ዜማን ቀጽሏል፡፡ደስታ በጊዜ ነበር ተለይቶ መውጣት ያስቻለው ተቀባይ
243
ጥቋቁር አናብስት

ጭንቅላትም ነበረው፡፡የመጽሐፍ ቅዱስ አንድምታንም ተምሯል፡፡ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ


ደስታ በብርሃንና ሰላም ማተምያ ቤት በአርታኢነትና ለሚታተሙ ሃይማኖታዊ መጻሕፍት
በማማከር ተቀጠረ፡፡ይሄን ስራ በጥንቃቄና በሃላፊነት ከ1916- 1920 ዓ.ም ድረስ ሲከውን
ቀየ፡፡በንግስት ዘውዲቱ አበረታችነትብዙ የሃይማኖት መፅሐፍት በዚህ ጊዜ ታትመው
ወጥተዋል፡፡

ቀጥሎ በአላዛር(ላዛሪስት)ማተምያ ቤት በተመሳሳይ ስራ ተቀጠረ፡፡ይህንን ስራ አብሯቸው


እንዲሰራ የጠየቁት ታዋቂው ና የተከበሩት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ናቸው፡፡ኪዳነ ወልድ ደስታን
የጠየቁበት መክንያት በብርሃንና ሰላም ጉብኝታቸው ግዕዙን ጮክ ብሎ ሲያነበንብ አይተውት
ነው ይባላል፡፡ ደስታ በዚህ ስራ ለ16 አመታት ድሬዳዋ ቆየ፡፡ከዚህ ስራ ለቅቆ ወደ አዲስአበባ
ከተመለሰ በኃላ ለብርሃንና ሰላም ለአርቲስቲክ ማተምያዎች ሰርቷል፡፡አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
በመምህራቸው መምህር ክፍለግዮርጊስ የተጀመረውን መዝገበ ቃላት እንዲፈጽሙ አደራ
ተቀብለው ነበር፡፡ኪዳነ ወልድ አስካሁን እንደታገሉትና መጨረስ እንዳቃታቸው ካሁን በኋላ
እሱ እንዲቀጥልበትና ጨርሶ እንዲያሳትመው ነገሩት፡፡⁵ ከረዥምና አታካች ስራ በኋላ ደስታ
ትልቁን የግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለህትመት አዘጋጀው፡፡በ1948 ዓ.ም በኪዳነ ወልድ
ክፍሌ ብቸኛ ደራሲነትም ነበር የወጣው፡፡በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታላላቅ ምሁራዊ ስራዎች መሃል
እንደ አንዱ ይታወቃል።

አለቃ ደስታ ተክለወልድ ታላቅ ምሁርና በባህልና ትውፊት ዙርያ እንዲሁም ስለ ሁለቱ
ሆሄያትም ሰፊ እውቀት የነበረውና የጻፈም ሰው ነበር፡፡⁶ መዝገበ ፊደልና አቡጊዳ ፤ገበታ ሃዋርያ
፤ረብሃ ስም (ታላቅ ስም) የሚሉ ሌሎች ስራዎችን ቢሰራም ተለይቶ እሚታወቀው ግን በልጨኛ
የ1283 ገጽ በ523 ምስል በረዥም የስዋሰው መግቢያውና በአማርኛ ፊደላትና ቋንቋ ታሪክን
ባቀፈው መዝገበ ቃላት አበርክቶቱ ነው፡፡እዚህ መዝገበ ቃላት ላይ ከ1921 -1950 ዓ.ም
ድረስ ደክሞበታል፡፡ የታተመው በአርቲስቲክ ማተምያ ቤት በ1962 ነው፡፡ትልቅ ስኬት
ቢሆንም ለመስፋፋትና ለማሻሻል እያሰበ በነበረበት እ.ኤ.አ በ1977 ዓ.ም በ84 አመቱ
አርፏል፡፡

ለማተምያ ቤቶች ለ46 አመታት ሰርቷል ግን ስሙ ሲጠቀስ የሚኖረው በመዝገበ ቃላቱ ነው፡፡
ከሌሎች መዛግብተ ቃላት በላይ ባቆራቸው ቃላትም ብቻ ሳይሆን በባህላዊ እውቀትና እምነቶች
አፈታሪኮች(አንዳንዶቹ እምነቶች በታሪክ ብቻ እንጂ በሳይንስ ባይረጋገጡም) በፈሊጥ የዳበረ

244
ጥቋቁር አናብስት

ነው፡፡ይህ ሁሉ ለመጪው ትውልድ ያለፈውን ታሪክ ባህል ወግ ትውፊቱን እንዲያውቅ


ያደርጋል፡፡በዘመናዊ ስነጽሁፍ ያለ እነዚህ ቀደምት ማጣቀሻዎች ለመገንዘብ አይችሉም፡፡

አንድ ሚስቱ ያሳየችኝ የመጽሐፍ ረቂቅ (ሃይማኖተ አበው) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ቤተክርስትያንን እምነት ለማብራራት በጣም ታላቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ከሞቱ በኋላም ታትሟል፡
፡የደስታ ተክለ ወልድ ቀብር የተፈጸመው አዲስ አበባ በሚገኘው በሥላሴ ካቴድራል ጳጉሜ 1
1977 ዓ.ም ነበር፡፡

245
ጥቋቁር አናብስት

ግርማ–ጽዮን መብራህቱ

የትልቁ ትግርኛ መዝገበ ቃላት አዘጋጅ

በ1985 ሁለተኛው አጋማሽ አንድ ዳጎስ ያለ የትግርኛ መዝገበ


ቃላት በኢትዮጵያ መጻህፍት መደብሮች ታየ፡፡የታተመው በዶጋሊ
ማተምያ ቤት አስመራ ፤ አሰናጁም ግርማጺዮን መብራህቱ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በብዛት እንደሚዘወተረው ደራሲው መጽሃፉን እራሱ
ማሳተም ነበረበት፡፡ትግሪኛ የዚህ መጽሐፍ ዋና ማጠንጠኛ
ባይሆንም የደራሲውን አጭር ምስል ለማስቀመጥና መዝገበ ቃላቱ
የሃገሪቱን ብሄሮች ለማጥናትና የቋንቋ ቅርስ ተጠብቆ ለትውልድ
እንዲተላለፍ በመሻት እንዲጠቃለል ሆኗል፡፡የተለያዩ የትግሪኛ
መዝገበ ቃላት በሃገር ውስጥና በውጪ የታተሙ ቢሆንም ይህ ግን በመጠኑ ከሁሉም የዳጎሰ ሲሆን
አርእስቱ ልሳነ-አግአዚ ዘ’እም ግርማ ይሰኛል፡፡

***

ግርማ ጽዮን መብራህቱ በሲፋጉላ ወረዳ በሰራዬ አውራጃ ኤርትራ ውስጥ በ1919 ዓ.ም ነው
የተወለደው፡፡ በመጀመርያ ትምህርት የጀመረው ከአቅራቢያው ካለ የቄስ ትምህርት ቤት ነው፡፡
በጊዜው ባልተለመደ መልኩ (በባህላዊ መንገድ የቤተ ክርስትያን ትምህርት)የተማሩ እናት
ስለነበሩት ግርማጽዮንን በትምህርቱ ይረዱት ነበር፡፡የቁም ጽህፈት መጻፍና ከቆዳ ብራና ማሰናዳትን
የተማረው ከእርሳቸው ነው፡፡ስማቸውም እማሆይ አምለሰት ማሉ ይሰኛል፡፡በመቀጠል ግርማጽዮን
በአቅራቢያው ወደሚገኙ ገዳማት በመሄድ ተጨማሪ ትምህርትን በተለይ የጽዋትወ ዜማን ቀሰመ፡፡
በመቀጠል ትምህርቱን ለማስቀጸል ወደ ጎንደር በማቅናት የሙሉ ደብተራነትን አገኘ፡፡ ዜማን፤
አቋቋምን፤ተምሮ ወደ ሃገሩ ተመለሰ፡፡እዚያም ከተመለሰ በኋላ በርካታ የብራና ጽሁፎችን ጽፏል፤
ቅጂዎችን ገልብጧል፡፡ለዚህ ስራ የበግ ፤ የፍየል ወይም የላም ቆዳን ማግኘት እንደ ብራና
እንዲያገለግሉ ማልፋት ወደ መጽሐፍትነት መጠረዝ፤የቀስም ብእርና ቀለም ማዘጋጀት ይጠይቃል፡፡

ጎንደር ሄዶ ስለማጥናቱ(ጎንደር የቤተክርስቲያን ትምህርት ከፍተኛ መማርያ ቦታ ስለሆነ)የመሪ


ጌትነት(የዜማ እና የአቋቋም መሪ)ማዕረግ አገኘ፡፡ በዚህ ወቅት ግርማ ´የሃይማኖት ጋሻ ለጠላት
መመለሻ´የሚል መጽሐፍ ጻፈ፡፡

246
ጥቋቁር አናብስት

በሀይማኖት ትምህርት ብቻ መቀጠልን ያልፈለገው ግርማጽዮን ወደ ዘመናዊ ትምህርት በመግባት


እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ተማረ፡፡በመቀጠል ወሎ የመምህራን ማሰልጠኛን በመቀላቀል ለአማርኛ
መምህርነት ብቁ ሆነ፡፡ከተመረቀ በኋላ ትምህርት ሚንስትር ውስጥ ተቀጠረ፡፡ከ1948-52 ዓ.ም
አሬንቱ ውስጥ አንድ የአንደኛ ደረጃን ትምህርት ቤት ሲመራ ቆየ፡፡በመቀጠል 7ኛና 8ኛ ክፍሎችን
በአግአዚ መለስተኛ ሁለተኛ አስመራ ውስጥ ለጥቆም አስመራና በደቀመሃሪ ውስጥ ከፍተኛ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማረ፡፡በ1967 አብዮት ሊፈነዳ ሲል ወደ አዲስ አበባ መጥቶ
አዲስ ስርአተ ትምህርት ለሚዘረጋው ኮሚቴ አባል እንዲሆን ተጠራ፡፡ግርማጽዮን መብርሃቱ
ከትምህርቱና ከፍላጎቱ አንጻር ወደ ቋንቋ የማድላት ዝንባሌ አለው፡፡የእናቱ ቋንቋ ትግርኛ ነው፡፡
ቤተክርስትያን ትምህርት ቤቶች ገብቶ ደግሞ አማርኛና ግዕዝን አጠና፡፡ በተማረባቸው ዘመናዊ
ትምህርት ቤቶችም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ስለሚሰጥና በሁለተኛ ደረጃ ሆነ የመማርያ ቋንቋም
ስለሆነ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ቀስሟል፡፡ ግርማጽዮን መዝገበ ቃላትን ለማሰናዳት ፍላጎት ያሳደረው
ከብዙ አመታት በፊት ነው፡፡በትግራይ ብዙ መንደሮችን በማሰስ የሰዎችን ንግግር መስማት በተለይ
አረጋውያንን፤ንጹኁን ትግርኛ (በአማርኛ ወይም ጣልያንኛ ጋር አንዳንዴም ከእንግሊዘኛ ጋር
ያተባረዘውን)የሚናገሩትን በመስማት 25 አመታትን በዚህ ስራ አሳልፏል፡፡መዝገበ ቃላቱን
ከማዘጋጀቱ በፊትም ግርማጽዮን በትግርኛ ቋንቋና ችሎታና በቋንቋው ላይ በሰራው ስራ
ይታወቃል፡፡በ1974 በአስመራ ዩንቨርስቲ በአፍሪካ የጥናት ተቋም በተካሄደው ብሄራዊ ሴምናር
ላይ በትግርኛ ቋንቋ ላይ ጥናት አቅርቦ ነበር፡፡ባለ 650 ጥራዝ መዝገበ ቃላቱ በ250 ገላጭ
ምስሎች የዳበረ ሲሆን በትግርኛ ቋንቋ መነሻና ታሪክ ላይ ያተኮረ ምእራፍ አለው፡፡አዲስ የስነ ልሳን
ማብራርያ በማስተዋወቅም ለትግርኛ ቋንቋ አነጋገር እንደ መማርያ ሰርቷል፡፡ብዙ የትግርኛ ቋንቋ
ተናጋሪዎችንና ተማሪዎችን የዚህ መዝገበ ቃላት መገኘት አስደስቷቸዋል፡፡በመጀመርያ የታተመው
5000 ኮፒ ሲሆን ዋጋው የኪዳነ ወልድ ክፍሌን ግእዝ አማርኛን እና የደስታ ተክለወልድን አማርኛ
ወደ አማርኛን መዛግብተ ቃላትን በአንድነት የመግዣ ዋጋ ቢያጥፍም አሰናጂው (ለመዝገበ ቃላቱ
ትልቅ ፍላጎት አለ)ይላል፡፡ብቻውንም ይህን ለመከወን ያሳለፈው እልህ አስጨራሽ ትግል ይህን
ውጤት ሊያስገኝ ችሏል፡፡

ማስታወሻ

1)አጭር የህይወቱ ታሪክ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ነበር፡፡ብርሃኑ ገብረ ጻዲቅ የሚባል የአዲስ
አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪም መመረቂያ ዲማጹን በሱ ላይ ሰርቷል፡፡

247
ጥቋቁር አናብስት

2)ግጽው የሚባለው መጽሐፍ ግማሽ ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ የሚናገርና በቤተክርስትያን
የሚነበብ የሚዜምበት ነው፡፡

3)ይህንን ሽልማት ለማሸነፍ የበቁት ሁለት የመዝገበቃላት አዘጋጆች ሲሆኑ ተሰማ ሀብተ ሚካኤልና
ደስታ ተክለወልድ ናቸው

4)ሆላንድ ውስጥ በ ኢ.ጄ.ጅብሪል 1980 ላይ ታትሟል

5)በአጼ ዮሐንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት በቦሩ ሜዳ ላይ በተደረገው ክርክር በወግ አጥባቂ
ቀሳውስት ለዳተኛ ተብለው ተከሰው ያውቃሉ፡፡ሚኒሊክ ወደ ሚያስተዳድሩት ሸዋም አምልጠው
እንዲሄዱ ተመክረው ነበር፡፡ኪዳነ ወልድ ያኔውኑ በሱዳን አድርገው በግብጽ አቆራርጠው ወደ
ጣልያን አቀኑ፡፡ለኢግናዝዮ ጉዊዲ እና ሌሎች ሰዎች ግዕዝና አማርኛን ማስተማር ጀመሩ፡፡
ቀጥለውም ወደ እየሩሳሌም ሄደው ሳለ ወደ ኢትዮጵያ ተጠርተው በስነጽሁፍ ላይ እንዲሰሩ ጥሪ
ሲቀርብላቸው ተቀብለው መጥተው እስከ እለተ ሞታቸው በዚሁ ዘርፍ አገልግለዋል፡፡

6)ከዘመናዊው አደራደር ይልቅ የበፊቱን የአቡጊዳን ይመርጡ ነበር፡፡ስለ ሃሁ አደራደር ከሚነገሩት


ትውፊቶች መሃል አንዱ ከሳቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ በአራተኛው ክ.ዘ ከሌሎች ምሁራን ጋር በመሆን
የሀሁን አደራደር እንደፈጠረ የሚነገር ሲሆን ይህም መተተኞች የአቡጊዳን አደራደር
ስለሚጠቀሙበት ቁጥሮችንም በክፍልፋይ ከሆሄያቱ ጋር እያያዙ ስለሚጠነቁሉ እነሱን ለማሸነፍ
የተወጠነ ሴራ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ፍሪምናጦስና በአስራ አምስተኛው ክ.ዘ የኖረው አጼ
ዘርዐያእቆብ «ታላላቆቹ የመተተኛ ጠላቶች»ተብለው ይታወቃሉ

248
ጥቋቁር አናብስት

ብርሀኑ ዘርይሁን
የልብወለድ ደራሲ፣ጸሐፊ ተውኔት፣ጋዜጠኛ እና የአዳዲስ አጻጻፍ
ዘዴ ፈርቀዳጅ ብርሀኑ ዘርይሁንን ታሪኩን ለመፃፍ ከማሰቤ በፊት
ጀምሮ ለዓመታት አውቀዋለሁ። ለቃለመጠይቅ ስጠይቀው
ወዲያውኑ ቢስማማም ሰፋ ላለ ጊዜ ተገናኝተን እንድናወራ ስፈልግ
ግን ጭራው አልያዝ አለኝ። እረፍት ማጣት የከያኒያን ጣጣ ሳይሆን
አይቀርም። ወይም ሌሎች የበለጡ ጉዳዮች አእምሮውን
አጨናንቀውት ይሆናል። ይህ ቃለመጠይቅ ከመካሄዱ በፊት
ብርሀኑ ለዓመታት በርካታ ጠቃሚ የሥነ ጽሑፍ ስራዎችን ሲያበረክት ቆይቷል። ምናልባት በንጉሱ
መጨረሻ ዘመናት ለዓመታት ታፍኖ የቆየውን ድምፁን በማሰማት፣ ከዛ በፊት በከንቱ የጠፋውን
ጊዜ እያካካሰ ይሆናል።

ብርሀኑ ዘርይሁን በ1926 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደተወለደ ነግሮኛል። ነገር ግን ዜና እረፍቱና
አንዳንድ የመንግስት መዛግብት በ1925 ዓ.ም እንደተወለደ ይጠቁማሉ።አባቱ ዘሪሁን መርሻ
"የቤተክርስቲያን ሰው" ሲሆኑ፣ የአካባቢውን የቤተክርስቲያን የዝማሬ እና የወረብ ቡድን ይመሩ
ነበር። ከዚህም ባሻገር ብራና እያዘጋጁ ቅዱስ ድርሳናትን ይገለብጣሉ። የብርሀኑ እናት አልጣሽ
አግደህ የቤት እመቤት ቢሆኑም፣ ጌሾ እየሸጡ ትንሽ ገቢ ያገኛሉ። ብርሀኑ ከቤተሰቡ ስድስት ልጆች
መሀል የመጨረሻ ነው። ቃለመጠይቃችንን ባደረግንበት በ1979 ዓ.ም ከአንዲት እህታቸው በቀር
ሁሉም በሕይወት ነበሩ። ብርሀኑ በወላጆቹ እንክብካቤ ነው ያደገው። ስድስት ወይም ሰባት ዓመት
ሲሆነው የቤተክርስቲያን ትምህርት መማር ጀምሮ እስከ አስራሁለት ዓመቱ ቀጠለ። ያን ጊዜ ግዕዝ
ቢማሩም ብርሀኑ ፍላጎት ኖሮት በደንብ ስላልተከታተለ፣ የግእዝ እውቀቱ የሚያወላዳ አይደለም።
ነገር ግን ከአማርኛ መጽሐፍት ጋር መላመድ ጀምሮ ነበር። ከአፈወርቅ ገብረየሱስ "ዋህድ" ( በኋላ
"ጦቢያ") እንዲሁም ከደብተራ ዘነብ "መጽሀፈ–ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ" ጋር ተዋወቀ።
መጽሐፍቱን ያመጣለት አዲስአበባ የሚኖር አጎቱ ሲሆን፣ በተለይ የአፈወርቅን ልብወለድ ታሪክ
ወደደው። ሁለተኛው መጽሐፍ ጥቅሶችና ምክሮች ያሉት የግብረገብ መጽሐፍ ነበር። ብርሀኑ
እነኚህን መጽሐፍት ሲያነብ የ10፣ ግፋ ቢል የ11 ዓመት ልጅ ቢሆን ነው።

ብርሀኑ በወግ አጥባቂ ስርአት ቢያድግምደስተኛ የልጅነት ጊዜ አሳልፏል። ቤተሰቦቹም ቢሆን


ደስተኛ የሚባሉ ዐይነት ናቸው። ትምህርቱን እየተከታተለ፣ ቤተሰቦቹን እንጨት በመልቀምና
ከብት በማገድ ይረዳል፤ አባቱ አንድ ላም፣ አንድ አህያ እና ጥቂት በጎች ነበሯቸው።

249
ጥቋቁር አናብስት

የቤተክርስቲያን ትምህርቱ ወደመጠናቀቅ ሲደርስ የብርሀኑን የሕይወት ጉዞ የሚለውጥ ክስተት


ተፈጠረ። ንጉሱ ወደ ጎንደር ለጉብኝት በመጡ ጊዜ፣ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች
ዩኒፎርም ለብሰው በዝማሬ ተቀበሏቸው። ብርሀኑ ልጆቹ በዩኒፎርም ተውበው ሲያያቸው ቅናት
ቢጤ ተሰማውና የመንግስት ትምህርት ቤት ለመግባት ፈለገ። ነገር ግን እነኚህ ትምህርት ቤቶች
ብዙ የውጪ ተጽእኖ ያለባቸው "ፀረ–ማርያም" ትምህርት ቤቶች ስለሆኑ ወላጆቹ በጄ አላሉም።
ስለዚህ ብርሀኑ ከቤት ጠፍቶ አላማውን ከዳር ለማድረስ ወሰነ።.50 ሳንቲም ይዞ በእግሩ ጉዞ
ጀመረ። ባህርዳር ከተማ ሲደርስ በጣም ስለደከመው ከአንድ ቤተክርስቲያን ተጠጋ።በዚያው
የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተከታተለ ለአራት ወራት ቆየ። እድሜው ወደ 12 ዓመት ይገመታል።
ከጉዞው ለማገገም፣ እንዲሁም በቆይታው ወቅት እንደ ሌሎች የቆሎ ተማሪዎች ቁራሽ እየለመነ
ረሃቡን ያስታግስ ነበር። ነገር ግን ቀዳሚ አላማው የነበረው ወደ መንግስት ትምህርት ቤት
የመግባቱ ነገር አልተሳካም።በዚያ ላይ የቤተሰቡና የቀዬው ናፍቆት ስለበረታበት ወደቤት ተመለሰ።

ቤት ሲደርስ እናቱ በጠና ታመዋል። ብርሀኑ ሞቷል ብለው ስለደመደሙ ልባቸው ተሰብሮ፣
በጭንቀት ተዳክመዋል።ብዙም ሳይቆዩ አረፉ።ብርሀኑ ራሱን ለዚህ ሁሉ ጥፋተኛ አድርጎ
ስለቆጠረ፣ ፀፀቱ አሁን ድረስ ይለበልበዋል። ነገር ግን ጠፍቶ መሄዱ አባቱን ጠልቆ ስለተሰማቸው፣
ብርሀኑ የመንግስት ትምህርት ቤት እንዲገባ ተፈቀደለት።አሁን ብርሀኑ ታታሪ አንባቢ ሆነ፤ በተለይ
ታላቅ ወንድሙ የሚያመጣለትን ጋዜጦች በፍቅር ያነብ ጀመር።በዚሁ ወቅት የከበደ ሚካኤል
መጽሐፍት ታትመው መውጣት ጀምረው ነበርና እነኚህ መጽሐፍት ያለመጠን አስደነቁት።

በደንብ ማንበብ ስለሚችል ትምህርቱን ከሁለተኛ ክፍል ጀመረ።አንድ ሁለት ክፍሎችን እንዲያልፍ
ስለተደረገም በአራት ዓመት ውስጥ ስምንተኛ ክፍል ደረሰ።የመጀመሪያ ግጥሙን የፃፈው
የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለ ነው።ግጥሙ አቶ ብሩ ስለተባለ ጉቦኛ ዳኛ ሲሆን፣በ"የዛሬይቱ
ኢትዮጵያ" ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል።ግጥሙ መታተሙ ብርሀኑ ላይ ጥልቅ ስሜት
ስለፈጠረበት፣አንዳንድ ሁነቶችን ተመርኩዞ አዘውትሮ መፃፍ ጀመረ።በመጀመሪያ ዓመት በብዛት
የሚጽፈው ግጥሞችን ሲሆን።ግጥሞቹ ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ነበሩ፤ ስለ ፍቅር መፃፍ
የጀመረው ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ነው። ከ1940—44 ዓ.ም ድረስ በጎንደር የአንደኛ
ደረጃ ትምህርቱን ሲከታተል ያበረታታው ወይም በአፃፃፍ ተጽእኖ ያሳደረበት አንድም መምህር
የለም። በ1945 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን እንዲከታተል ነፃ እድል አገኘ።

በመዲናይቱ ለአንድ ዓመት ወደ መምህራን ማሰልጠኛ እንዲገባ ጥያቄ ቢቀርብለትም የሱ ፍላጎት


ግን ከፍተኛ ትምህርት መከታተል ነበር። ፍላጎቱ ታይቶ በአዲስ አበባ ቴክኒካል ትምህርት ቤት
(በጊዜው ጎንድራድ ተብሎ ይጠራ ነበር) እንዲገባ ተፈቀደለት።በትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የአራት

250
ጥቋቁር አናብስት

ዓመት ትምህርት ከሁለተኛ ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ ነው። ትምህርት ቤቱ የአሜሪካኖች፣ አብዛኛዎቹ


መምህራንም አሜሪካውያን ሲሆኑ አንድ ወይም ሁለት ሕንዳውያን መምህራንም ይገኙበታል።

የአዲስ አበባ ኑሮው ከድሮው ሲነጻጸር ለብርሀኑ ትልቅ ለውጥ ነበረው። በትምህርት ቤቱ በዋነኛነት
"ሬዲዮ መካኒክስ" አጠና። በቋንቋ ጥሩ ችሎታ ስላለው ኢራናዊው የእንግሊዝኛ መምህሩ
እያበረታታው ጭምር ከእንግሊዝኛ እና ከአውሮፓ ሥነ ጽሑፍ ጋር አስተዋወቀው። ከነዚህም
መሀል ሼክስፒር እና አሌክሳንደር ዱማ በጣም ማረኩት።የብሮንት እህትማማች (የትኛዋን እንደሆነ
ግልጽ አላደረገም)፣ ኤፍ. ስኮት ፊትዝጄራልድ፣ ዲክንስ፣ ፍሉቤር የመሳሰሉትን ጨምሮ ሁሉንም
ቀለል ባለ እንግሊዝኛ የተዘጋጁትን አነበበ። የስፖርት መምህራቸው "ቴክኒ–ኤኮ" የሚል መጽሔት
ማሳተም ሲጀምር ብርሀኑን ለማበረታታት ዋና አዘጋጅ አደረገው። መጽሔቱ በሁለት ቋንቋ
የሚዘጋጅ ስለሆነ፣ ብርሀኑ በአማርኛም በእንግሊዝኛም ይጽፍ ነበር፤ነገር ግን "የእንግሊዝኛው
ጽሑፍ" በመምህራኑ ነው አርትኦት የሚሰራበት። መጽሔቱ ወርሀዊ በመሆኑ ብዙ ጊዜውን
የሚሻማ አልነበረም።ከዚህ በተጨማሪ ለአዲስ ዘመን፣ለየዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ድምጽ
ጋዜጣዎች ላይ ይጽፍ ነበር።የኤርትራ ድምጽ የሚታተመው አስመራ ሲሆን፣አዲስ አበባ ውስጥ
ቢሮ አላቸው። በ1947 ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚመለከት አንድ አጭር ተውኔት ፃፈ፤ርእሱን
አያስታውሰውም። ተውኔቱ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ታይቶ፤ ተመልካቾች
በጣም ወደዱት። "ይህን ተውኔት የፃፍኩት ያለምንም የድራማ አጻጻፍ እውቀት፣ስሜቴን ብቻ
ተከትዬ ነው"ይላል። በዚህ ተውኔት ላይ አልተወነም፤ ነገር ግን ገና ወደ አዲስ አበባ ሳይመጣ
ጎንደር እያለ የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር በፃፉት የአማርኛ ተውኔት ላይ ረዳት ተዋናይ ሆኖ
ተውኗል።ከዚህ በተጨማሪ የክፍል ጓደኞቹ ለፍቅረኞቻቸው የፍቅር ግጥም ያስጽፉትና፣እጅ
መንሻ፣ለእያንዳንዱ ግጥም የእንቁላል ጥብስ ይጋበዛል።

ብርሀኑ ከቴክኒክ ትምህርት ቤቱ በ1948 ዓ.ም ተመረቀ። በመጀመሪያ ስራው በዛው የቴክኒክ
ትምህርት ቤት የሰርቶ ማሳያ ክፍል ረዳት ኃላፊ ሆኖ ሰራ።የተመረቀው ከክፍሉ ተማሪዎች አንደኛ
ወጥቶ ስለነበር፣ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚያገኝ ጠብቆ ነበር። ነገር ግን እድሉ እሱን ተላልፎ
ከክፍሉ አራተኛ ለወጣው ልጅ ተሰጠ።ብርሀኑ በዚህ በጣም ስለተናደደ፣በትምህርት ቤቱ
የጀመረውን ስራ ጥሎ ወጣ።በወቅቱ ምክትል የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ከበደ ሚካኤል
እንደነበሩ ብርሀኑ ያስታውሳል።ዋና ሚኒስትሩም ለስሙ ያህል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ይሁኑ እንጂ፣
በተግባር ግን ያው ከበደ ሚካኤል ናቸው። ከበደ ሚካኤል ካቶሊክ ስለነበሩ ነፃ የትምህርት እድሉን
አግኝቶ ወደ ውጭ ሀገር የሄደው ልጅ የተመረጠው ካቶሊክ ስለሆነ መሆን አለበት ብሎ ብርሀኑ
ይጠረጥራል።

251
ጥቋቁር አናብስት

ብርሀኑ በትምህርት ሚኒስቴር ስር የነበረውን የመጀመሪያ ስራ ከለቀቀ በኋላ በአዲስ አበባ


ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኘው ካርታ ስራና ጂኦግራፊ ተቋም ተቀጠረ።በዚያም በኋላ በጣም ታዋቂ
ጸሐፊ እና የጂኦግራፊ መምህር ከሆኑት መስፍን ወልደማርያም እና ካላዌይ ከተባለ አሜሪካዊ ጋር
እስከ 1951 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ሰራ። ቀጥሎ የተሻለ ክፍያ ስላገኘ በመከላከያ ሚኒስቴር
አስተርጓሚ ሆኖ ተቀጠረ ፤ ነገር ግን በስራው ላይ የቆየው ለሁለት ወይም ለሶስት ወር ብቻ ነው።

ትምህርት ቤቱን ከለቀቀም በኋላም ቢሆን ለአዲስ ዘመን እና ለየዛሬይቱ ኢትዮጵያ መፃፉን
አላቋረጠም።መጣጥፎቹን የሚልከው በፖስታ ቤት ነበር።ይሁን እንጂ ለጽሑፎቹ ተከፍሎት
ስለማያውቅ የራሱን አድራሻ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አልታየውም።አንድ ቀን ግን ጽሑፉን ይዞ
በአካል ተገኝቶ ለማስረከብ ወደ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ቢሮ ሲሄድ ዋና አዘጋጁን አቶ አሃዱ ሳቡሬን
አገኛቸው። በጊዜው አሃዱ ሳቡሬ በጣም ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነበሩ። በወቅቱ በተባበሩት
መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) ዋና ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ እየተቋቋመ
ስለነበር፣አዲስ ዘመንን እና ኢትዮጵያን ሔራልድ እለታዊ ጋዜጣዎች ለማድረግ ተፍ ተፍ እየተባለ
ነበር። ስለዚህ አዘጋጆቹ ተሰጥኦ ያላቸውን ጸሐፍትን በማፈላለግ ላይ ናቸው። በዚህ መሰረት አሃዱ
ሳቡሬ1ብርሀኑን እያፈላለጉት የነበረ ቢሆንም፣አድራሻውን ጽፎ ስለማያውቅ፣ እሱን
ለማግኘትአዳጋች ሆኖባቸው እንደነበር ነገሩት። በመጨረሻ ተገኝቶ በማስታወቂያ ሚኒስቴር
ከፍተኛ ሪፖርተር ሆኖ እንዲሰራ ጥያቄ ሲቀርብለት ያለምንም ማወላወል ተቀበለ። በ1952 ዓ.ም
ስራውን ሲጀመር የቅጥር ደብዳቤ ወይም የቅጥር ውል እንኳን አልነበረውም።ብርሀኑ በመጀመሪያ
በሁሉም የሐገሪቱ ጋዜጦች ላይ ቢጽፍም በኋላ ጽሑፎቹ በየዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ተወሰኑ።
በዚህ መሰረት "መሞነጫጨር የሙሉ ጊዜው ስራው" ሆነ።የስራው ሃላፊነት በሚጠይቀው መልኩ
ነፃ አስተያየቶችን፣ትርጉሞችን እና ሪፖርታዥ መስራት ቀጠለ።ወርሃዊ ደሞዙ 347 ብር ሲሆን
በካርታ ስራና ጂኦግራፊ ተቋም ያንኑ ያህልነበር የሚያገኘው።ብርሀኑ የሙሉ ጊዜጸሐፊ ሲሆን ደርቦ
ጠገግ ያሉ የሥነ ጽሑፍስራዎችንም መፃፍ ጀመረ።በደቡብ አፍሪካው የሻርፕቪል እልቂት አነሳሽነት
የከተባቸው ተከታታይ መጣጥፎች በኋላ በሁለተኛው መጽሀፉ "ድል ከሞት በኋላ" በሚል ርዕስ
ሁለተኛ መጽሐፉ ታተመ።ነገር ግን ይህ ተከታታይ ታሪክ ተጽፎ ከማለቁ በፊት ብርሀኑ "የእንባ
ደብዳቤዎች" የሚል መጽሀፍ ጽፏል።ርእሱ የተገኘው መጽሀፉ ውስጥ ከተካተቱ ሁለት ደብዳቤዎች
ነው። ይህ አሳዛኝ ታሪክ ስለ አንዲት ሴት ያወራል። ሴቲቱ ባለትዳርና የልጆች እናት ስትሆን፣
ትዳሯን በትና አንዱን "ሽቅርቅር" ተከትላ አዲስአበባ ትመጣለች። ፍቅራቸው ካለቀ በኋላ ጥሏት
እብስ ሲል ርካሽ ሴተኛ አዳሪ ሆና በስቃይ ኖራ በስቃይ ትሞታለች።ይህ መጽሀፍ በ3,000
ቅጂዎች ታትሞ ቀስ በቀስ ተሽጦ አለቀ። በጊዜው የመጽሀፍት ቅኝት የሚሰራ አልነበረም፤ስለዚህ
ብርሀኑ አንባብያን ስለ መጽሀፉ ያላቸውን አስተያየት የሚያውቅበት መንገድ አልነበረውም። ነገር

252
ጥቋቁር አናብስት

ግን ምክትል የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደሳለኝ መጽሀፉን አንብበው ስለወደዱት ለብርሀኑ


የፓርከር ብእር ሸልመውታል።

"ድል ከሞት በኋላ" በጋዜጣ ላይ በተከታታይ ተጽፎ አልተደመደመም። ይልቁንም ሙሉ ረቂቁ


ተዘጋጅቶ በ1955 ዓ.ም በመጽሐፍ መልክ ብቅ አለ። የታተመው በ2,000 ቅጂዎች ሲሆን ሽያጩ
የሚያረካ አልነበረም።ኢትዮጵያውያን ስለ ደቡብ አፍሪካ የተጻፈ ታሪክ ለማንበብ ፍላጎት
አልነበራቸውም፤ይህም በወቅቱ ኢትዮጵያ ከቀሪው አፍሪካ ተነጥላ እንደነበር ያሳያል። የሆነው ሆኖ
መጽሐፉን ላነበቡት ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ድንበር ባሻገር ስላለው አፍሪካ መጠነኛ ግንዛቤ
እንዲያገኙ ረድቷል።

ቀጣይ መጽሀፉ "የበደል ፍፃሜ" በ1956 ዓ.ም ታተመ። ይህም መጽሐፍ እንደ "የእንባ
ደብዳቤዎች" ሁሉ መነሻው "አስደንጋጩ የሽርሙጥና ሕይወት" ነው።ብርሀኑ በተማሪነት ዘመኑ
በቀይ መብራት ወደተንቆጠቆጠችው ውቤ በረሀ ብቅ ይል ነበር። ሴቶቹ ወጣት እና ቆንጆ እያሉ
ፈላጊያቸው ብዙ ቢሆንም ካረጁ በኋላ ምን ይውጣቸው ይሆን ብሎ ይጨነቃል።እራሱም
በወጣትነታቸው ቢደሰትባቸውም፣የሕይወታቸው መጨረሻ ያሳዝነዋል።በቃለመጠይቃችን ወቅት
እንኳን አንዳንዶቹን በመንገድ ላይ ያያቸው ነበር፤ከመሃከላቸው ተጠቅመው እንደጣሉት እቃ
ያለቁ፣የጨረጨሱ ብሎም “ነካ ያደረጋቸው” የሚመስሉ ነበሩባቸው።

"አማኑኤል ደርሶ መልስ" የሚለው ቀጣይ መጽሐፉም በተመሳሳይ የታሪክ ጭብጥ፣ በተመሳሳይ
ዓመት ታተመ።የሴተኛአዳሪነት ሕይወት2 በሁለት ምክንያቶች በብርቱ ያሳስበዋል፦ አንድም በዚህ
የሕይወት መስመር የሚጓዙ ሴቶች ያሳዝኑታል፤ሁለትም ከለመደውና ከሚወደው የቤተሰብ
ሕይወት ጋር ሲያወዳድረው አፉን በእጁ ያስጭነዋል። እድገቱ በጎንደር በተለመደው ዐይነት
የቤተሰብ ስርአት ውስጥ ሲሆን ከዘመዶቹ መሀል በፍቺ የተለያየ አንድ እንኳን አያስታውስም። እሱ
ራሱ ጥሩ የትዳር ሕይወት ተደግሶ እየጠበቀው ነው። ብርሀኑ እና የሺ ፍስሐ የተገናኙት ሁለቱም
ለ"Voice of Ethiopia" በሚሰሩበት ወቅት ሲሆን ፤እሷ ለእንግሊዝኛው ዴስክ ስትሰራ
ተጫጩና በ1958 ዓ.ም ተጋቡ። ጥንዶቹ ሁለት ወንድና አንድ ሴት ልጅ ሲያፈሩ፣ ብርሀኑም
በትዳሩ ደስተኛ ነበር።

በዚህ ወቅት ብርሀኑ ከመጽሀፍቱ ሽያጭ እዚህ ግባ የሚባል ገቢ ማግኘት ገና አልጀመረም።


የሚተዳደረው ከመደበኛ ስራው በሚያገኘው ደሞዝ ነው።ከ1952–1954 በ"የዛሬይቱ
ኢትዮጵያ" ከፍተኛ ሪፖርተር እና ምክትል አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።በ1954 ዓ.ም "Voice of
Ethiopia" ("የኢትዮጵያ ድምጽ"ን)በዋና አዘጋጅነት ተቀላቀለ።ያኔ የ1953ቱ"የታህሳሱ ግርግር"
253
ጥቋቁር አናብስት

ገና ጋብ ማለቱ ሲሆን ከዚያ ወዲህ የሳንሱር ህጉ መጥበቅ ጀመረ።በ1956/57 ብርሀኑ የአዲስ


ዘመን ዋና አዘጋጅ ሆነ። በመሐል ለአራት ወራት ከማቋረጡ በስተቀር በዚሁ ስራ እስከ 1959
ዓ.ም ድረስ ቆየ። በ’59 ዓ.ም ግን ከስራ ተባሮ እስከ አብዮቱ ማግስት፣ 1967 ዓ.ም ድረስ ደሞዙን
ብቻ እየተቀበለ ያለስራ ከረመ።

የአዲስ ዘመን አዘጋጅነቱን “በ1957 ዓ.ም አካባቢ” እንደተረከበ ሐገር አቀፍ የኢትዮጵያ ቁንጅና
ውድድር እየተዘጋጀ ነበር። በተመሳሳይ ወቅት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተማሪዎች እንቅስቃሴ
እየተቀጣጠለ ነው። ብርሀኑ እና ያዕቆብ ወልደማርያምን የመሳሰሉ ሌሎች ጋዜጠኞች የቁንጅናው
ውድድር የሀገሪቱ አንገብጋቢ ጉዳይ እንዳልሆነ ይልቁንም ትኩረት የሚሹ ሌሎች ችግሮች እንዳሉ
በማስተጋባት ውድድሩን ተቃወሙ።ቢሆንም "ብሔራዊ አነሳሽ ኮሚቴ" ተቋቁሞ የንጉሱን ድጋፍ
አግኝቶ ሁሉም ጋዜጦች ለሁሉም እጩ ተወዳዳሪዎች እናለውድድሩ ድጋፍ ለሚያደርጉ ድርጅቶች
የፊት ገጽ ሽፋን እንዲሰጧቸው ታዘዙ። ብርሀኑ ይህንን ትእዛዝ ተላልፎየቁንጅና ውድድሩን
የሚመለከት ዘገባ በገጽ 3 ላይ አሰፈረ። የአነሳሽ ኮሚቴው ሊቀመንበር አቶ ተገኝ ይህንን ይዘው
ለማስታወቂያ ሚኒስትሩ ዶክተር ምናሴ ሐይሌ ስሞታ አቀረቡ።በዚሁ ወቅት ብርሀኑ በደቡብ
አፍሪካ ስለሚደረገው የእንቁራሪቶች የቁንጅና ውድድር (የዝላይ ሳይሆን) ዜና ደረሰው። ይህ ዜና
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ ወጣ ( ብርሀኑ ይህንን ተንኮል ቢጤ አሁን ድረስ በፈገግታ
ያስታውሰዋል)። ይህ ጥፋት የመጨረሻውነበር። በማግስቱ ብርሀኑ ከጋዜጣው አዘጋጅነት መነሳቱን
የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰው፤ይሁን እንጂ ደሞዙን አልተከለከለም። የቁንጅና ውድድሩ እስኪጠናቀቅ
ለአራት ወር ያህል፣ ስራፈት ሆነ ቆየ።

ብርሀኑ ዳግም ከስራ የታገደው በ1959 ዓ.ም ነበር። እገዳው አሁንም ደሞዙን ባይጨምርም
ለስምንት ዓመትያለ ስራ ቆይቷል። አሁን ደግሞ ምክንያታቸው ለአቤ ጉበኛ የረዥም ልብወለድ
መጽሀፍ "አንድ ለናቱ" የሰራው የመጽሀፍ ቅኝት ነበር። አቤ በመጽሀፉ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ
ዘራቸው ከንጉሥ ሰለሞን እና ከንግስት ሳባ እንደሚመዘዝ፣ እውነትም የይሁዳ አንበሳ እና የንጉስ
ዘር መሆናቸውን በማጋነን አቀንቅኗል።መጽሐፉን የቃኘው ሰው ቴዎድሮስ ለእንደዚህ ዐይነት ርካሽ
ነገር እንደማይጨነቅ በመግለጽ አቤን ያብጠለጥላል፤ዋናው ጉዳይ የንጉስ ዘር አለው ወይስ የለውም
የሚለው ሳይሆን ጥሩ ንጉሰ ነገስት መሆን አለመሆኑ ነው ብሎ ይጨምራል። አጼ ኃይለሥላሴ
ይህንን ባነበቡ ጊዜ በጣም ተቆጡ። ብርሃኑ ይህንን ቅኝት አይቶታል፤ነገር ግን ሕገመንግሥታዊ
አንደምታውን በቅጡ አልተረዳውም።እንደ ህገመንግስቱ ከሆነ አንድ ንጉሰነገስት ዝርያውን ከንጉሥ
ሰለሞን እና ከንግስት ሳባ መምዘዝ አለበት።ወዲያውኑ ይህንን ጉዳይ የሚመረምር ኮሚቴ
ተቋቋመ።አንዳንድ የኮሚቴው አባላት ብርሀኑ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሊፈረድበት ይገባል እስከማለት

254
ጥቋቁር አናብስት

ደረሱ።ነገር ግን አብዛኛዎቹ አባላቶች 400 ብር ተቀጥቶ ከጋዜጣው አዘጋጅነት እንዲነሳ ብቻ


በመስማማታቸው ይኼው ተፈፃሚ ሆነ።ደሞዙ ስላልተነካበት እና በሬዲዮው ክንፍ ቢሮ
ስለተሰጠው(በእርግጥ ምንም ነገር ማስተላለፍ ባይችልም)በቀላሉ እንዳለፉት ተሰምቶታል። በአሉ
ግርማ የ"መነን" መጽሔት ዋና አዘጋጅ እያለ ብርሀኑ እዚያ ላይ አልፎ አልፎ ይጽፍ ነበር፤ አንዴ
ሳት አለውና ሴቶች ስለፖለቲካ ምንም እንደማያውቁና፣እንደውም የፖለቲካ ጉዳዮችን አንስቶ
ከመወያየት ይልቅ ስለ ኮስሜቲክስ መቀበጣጠር እንደሚመርጡ ፃፈ።አሁንም ወደ ቤተመንግሥት
ተጠርቶ መጣና ከንጉሰ ነገስቱ ፊት ቀርቦ እንደዚያ ብሎ ለመፃፍ ምን እንዳነሳሳው ጠየቁት።
ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ሴቶች ሕይወታቸው ከድሮው እንደተሻሻለላቸው በመግለጽ የፖለቲካ
ጉዳይ ውስጥ መግባት ምንም እንደማይሰራላቸው ተናገረ።3 ከዚህ ንግግር በኋላ፣ብርሀኑ ዳግም
ብዕሩን አንስቶ የትም፣ አንዳች ነገር እንዳይጽፍ ተከለከለ። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ጌታቸው መካሻ
ከአሁን በኋላ ጭራሽ ባይጽፍ እንደሚሻል ብርሀኑን መከሩት።ይሁን እንጂ ይህ "ትእዛዝ" እንጂ
"ምክር" አልነበረም።ከዚህ በኋላ ብርሃኑ ለብዙ ዓመታት ምንም ሳይሰራ ቆየ፤ በእርግጥ በአጫጭር
ልብወለድ ረገድ እጁን ለማፍታታት ሞክሮ ነበር (በነገራችን ላይ ይህ ብቸኛው የብርሀኑ የአጭር
ልብወለዶች ስብስብ ነው)።

የብርሀኑ ዘርይሁን ቅድመ–አብዮት ረዥም ልብወለዶች ሁሉ የተፃፉት ከ1959 ዓ.ም በፊት


መሆኑን ልብ ይሏል።

እስቲ ወደ ልብወለዶቹ እንመለስ።"የበደል ፍፃሜ" የወንጀል ታሪክ ነው። አንድ ስራ ተቋራጭ


ረቂቁን ከብርሀኑ ላይ በ4,000 ብር ቁርጥ ክፍያ ገዛውና 10,000 ቅጂዎች አሳተመ።ሽያጩ
አስደሳች አልነበረም፤እንዲያውም አሁን ድረስ ሳይሸጡ የቆዩ ቅጂዎች በየመጽሐፍት መደብሩ
ሳይኖሩ አይቀርም። ነገር ግን አዲስ ዘመን ጋዜጣ አዎንታዊ ቅኝት ስላወጣ በዚህ ተጽናንቷል
(ይህ መጽሐፉ ቅኝት የተሰራለት የመጀመሪያ መጽሐፉ ነበር) ብርሀኑ በጋዜጠኝነቱም በደራሲነቱም
አዲስ የአጻጻፍ ስልት እየቀየሰ።የሚጽፋቸው አረፍተ ነገሮች አጭር እና ግልጽ ነበሩ። አንዳንድ
የዩኒቨርስቲ መምህራን ይህንን አዲስ ቋንቋ "ብርሀኑኛ" እያሉ ይጠሩት ጀመር።"አማኑኤል ደርሶ
መልስ" ከ2,500–3,000 ቅጂዎች አካባቢ ቢታተምም በደንብ አልተሸጠም።ጭብጡ ከ"የእንባ
ደብዳቤዎች"ጋር ተቀራራቢ ነው፤ይሁን እንጂ አሁን በታሪኩ ውስጥ "የሚበላሸው"እና ሚስቱ
"የምታድነው" ወንድ ነው።

255
ጥቋቁር አናብስት

"የቴዎድሮስ እምባ" በ1958 ዓ.ም ታትሞ ጥሩ ተቀባይነት አገኘ። መጽሀፉ በሶስት ጋዜጣዎች
(አዲስ ዘመን፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ድምጽ) ቅኝት እንደተሰራለት ደራሲው
ያስታውሳል።ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ጀግና በጠማቸው ወቅት ነበር ይህ መጽሐፍ የወጣው።
ቴዎድሮስ ይህንን ጥማት ለማርካት ይቻለዋል። ቴዎድሮስ ወደሞተበት መቅደላ ዘመቻ ለማድረግ
30 ሰዎች ያሉት ቡድን መንቀሳቀስ ጀመረ። አቤ ጉበኛ ስለ ቴዎድሮስ የፃፈው ትልቅ መጽሐፍም
በዚሁ ጊዜ ወጣ።4 የወቅቱ አየርም የብርሀኑ መጽሀፍ ጥሩ ምላሽ እንዲያገኝ ረድቷል።የመጽሐፉ
5,000 ቅጂዎች ወዲያውኑ ተሸጡ። በሃያስያን ዘንድም ጥሩ ተቀባይነት አግኝቷል። ከልጅነቱ
ጀምሮ የቴዎድሮስ ታሪክ እንደሚማርከው፣ አሁንም ድረስ ጀግናው እንደሆነ ብርሀኑ ነግሮኛል።
“ከጎንደር እንደመምጣቴ፣ ጀግናው የኔም ነው” የሚለው ብርሀኑ ይህንን ልቦለድ የፃፈው ስለ
ቴዎድሮስ የነበረውን የተጣመሙ አመለካከቶች ለማቃናት ነው። መኮንን እንዳልካቸው "ጣይቱ
ብጡል" በተሰኘ ተውኔታቸው፣ ቴዎድሮስን የሳሉበት መንገድ አናዶት ነበር።ታዋቂው የታሪክ
ጸሐፊ ተክለፃድቅ መኩሪያ ራሳቸው፣ ቴዎድሮስን ጨካኝ እና ቁጡ አድርገው ቀርፀውታል ይላል።

የሚቀጥለው መጽሀፉ "ጨረቃስትወጣ" በሶስት ሺህ ቅጂዎች ተዘጋጅቶ ለገበያ ቢቀርብም፣


በፍጥነት አልተሸጠም።

ሁሉም ቅድመ–አብዮት ልብወለዶቹ የታተሙት ከ1952―1959 ዓ.ም ሲሆን፣ የአጭር


ልብወለድ ስብስቡ "ብር አምባር ሰበረልዎ" ከዓመት በኋላ ታተመ።

የደራሲ ስራ ቀላል አይደለም ይላል ብርሀኑ። የሳንሱር ክፍሉ እንዲቀበለው ስራውን ማመቻቸት፣
አሳታሚ መፈለግ እንዲሁም ለህትመቱ በቅድሚያ መክፈል ይጠበቅበታል። ከዚያ ቅጂዎቹን ይዞ
በየመጽሐፍት መደብሩ እየዞሩ ማከፋፈል፣ ሲሸጡም በሽያጩ ልክ ገንዘቡን መሰብሰብ የራሱ ስራ
ነው።

የብርሀኑ ዘርይሁን ልብወለዶች የራሱ ገጠመኞችና ልምዶች ውጤት ናቸው። የሙሉ ጊዜ ስራ


ሲያገኝ ለመፃፍ ጊዜውንም፣ መነሳሳቱንም አግኝቷል። በኋላ ስራ ፈት ሆኖ ለመፃፍ ጊዜውንም፣
ገንዘቡንም ሲያገኝ ደግሞ የማሳተም ፍላጎቱ ቀዘቀዘ። ያለጊዜው ጡረታ በወጣበት በዚህ ወቅት፣
የፃፈው አንድ መጽሐፍ ብቻ ነበር። ይህ "ብር አምባር ሰበረልዎ" የተሰኘ መጽሐፍ ብቸኛው
የአጭር ልብወለድ ስብስቡ ነው። መጽሐፉ ከግል ገጠመኙ ይልቅ የኢትዮጵያ ጎሳዎችን
መተጫጨት፣ ጋብቻ እና ፍቺ በተመለከተ ባደረገው ጥናት ላይ የተመሰረተ ነው።

256
ጥቋቁር አናብስት

ስራ ከለቀቀ በኋላ ራሱን በተለያዩ ጉዳዮች ለመጥመድ ሞክሮ ከ1960–61 አፄ ዮሐንስ አራተኛ
የተሰዉበትን መተማን፣ ሱዳን ድንበር ድረስ ሄዶ ጎበኘ። ወንድሞቹ በዚያ ትልቅ የእርሻ መሬት
ስለነበራቸው ከፍለው ሰጥተውት እርሻ ቢጤ ቢሞክርም የግብርና ዝንባሌ ስለሌለው፣ ከአራት
ወራት በኋላ ወደ አዲስአበባ ተመለሰ።

በዚህ "ረዥም እረፍት" የከወነው ጥቂት ነበር።ብዙ ጊዜውን እንዲሁ በዋዛ በፈዛዛ አባክኗል፤
የፃፈው በጣም ጥቂት ከመሆኑም በላይ፣ አብዝቶ መጠጣት ጀመረ (ይህ ልምድ እስከ እለተሞቱ
ቀጥሏል)። ነገር ግን ምሬት አልተሰማውም፤እንዲያውም ምንም ሳይሰራ ሙሉ ደሞዙ
ስለሚከፈለው ቅሬታ አልነበረውም።ብዙ መፃፍ በቻለ ነበር፤ነገር ግን “ግራ ሳይገባው አልቀረም”፤
ስለዚህ ምንም መፃፍ አልቻለም።

****

በነዚህ ስራ በፈታባቸው ዓመታት መጨረሻ አካባቢ አንድ ክስተት ትኩረቱን ሳበውና፣ ዳግም
ሀገሪቱ ውስጥ በዋነኛነት ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንዲያጤን አሳሰበው። ይህ ክስተት የ1965–
66 ቱ ድርቅ እና ረሀብ ነው።የረሀቡ ሰለባዎች መናገሻ እና ለገዳዲ ላይ ቢኮለኮሉም ወደ አዲስ
አበባ እንዲገቡ ግን አልተፈቀደላቸውም። ስለዚህ እሱ ሊጎበኛቸው ሄደ፤ ከጎበኛቸው በኋላ ብዕሩን
አንስቶ ድህረ–አብዮት ለጻፋቸው ሶስት ጥንድ ልብወለዶች ማስታወሻ መውሰድ ጀመረ። በጊዜው
መጽሀፉ የጎላ ፖለቲካዊ አንደምታ ይኖረዋል ብሎ አላቀደም ወይም አላሰበም።በ1965 ዓ.ም
ለመጽሀፉ ማስታወሻ እየወሰደ ቅርፁን ቢያወጣም፣ገና በስርአቱ ዝርዝሩን ቁጭ ብሎ መፃፉን
አልጀመረም። በመጀመሪያ መጽሐፉን ሲያዋቅር ያሰበው ስለ ረሀቡ ብቻ እንደነበር ይናገራል።
ስለዚህ ስለ መሬት ባለቤትነት ስርአት፣ስለ መደብ ልዩነት እና ለረሀቡ እንደ መንስኤ ሊሆኑ
ስለሚችሉ ማህበራዊ ቀውሶች የመሳሰሉ ጉዶዮችን ጭራሽ አላሰበም።ቢያስብ እንኳን ያን መሰል
ጉዳዮችን የያዘ መጽሐፍ በድሮው ስርአት ሊታተም አይችልም ነበር።በጊዜው አንድ ደራሲ የፃፈው
ነገር መታተም እንዲችል፣ ሳንሱሩን ማለፍ እንደሚችል የግድ መጨነቅ ነበረበት። ነገር ግን ስለ
ማህበራዊ ችግሮች ያውቃል፤በ1959 ዓ.ም ልክ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነቱ ከመነሳቱ
በፊት፣ ወደ ሞስኮ5 በተጓዘበት ወቅት የካርል ማርክስን "ካፒታል" ስላነበበ ስለ መደብ ልዩነት
በጥቂቱ ያውቃል፤ ቢሆንም ከአብዮቱ በፊት ይህንን አንስቶ መፃፍ አይችልም።

በሰኔ 1966 ብርሀኑ ወደ ወሎ ለመጓዝ ሲነሳ፣ አብዮቱ መፋፋም ጀምሯል። ወሎ በተለይ በድርቅና
በረሐብ ክፉኛ ተመቶ ነበር፤ሐይቅ እና ዙሪያውን ከጎበኘ በኋላ ከሐይቅ የአንድ ቀን መንገድ በኋላ
ወደምትገኘው ወርጠያ ተጉዞ በገበሬዎች መንደር ለሁለት ወራት ቆየ።በቆይታው ከአካባቢው
257
ጥቋቁር አናብስት

ገበሬዎች ጋር ረዣዥም ውይይቶች በማድረግ የረሀቡ መነሻ የጉልት (የጭሰኛ) ስርአቱና


የአስተዳዳሪዎቹ ቸልተኝነት መሆኑን ተረዳ።

ብርሀኑ በጊዜው በኢትዮጵያ 40 ዐይነት የጭሰኛ ስርአቶች ነበሩ ይላል። ነገር ግን በወሎ የነበረው
ስርአት ከተቀረው የሀገሩ ስርአት ይለያል።ከአልጋወራሹ ጀምሮ፣ የወሎ ገዢ እና ሌሎች ሹመኞች፣
ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ የገበሬውን ምርት በመቀራመት በክፉ የሚታወቁ ናቸው። ለሁሉም ገበሬዎች
ስርአቱ ክፉ ቢሆንም፣ "ከደቡብ ኢትዮጵያ ይልቅ ወሎዎች ላይ ይብሳል"።በደቡብ ጭሰኛው
"የሚከፍለው ቁርጥ ብሎ" ይታወቃል፤በወሎ ግን ልክ የቤተሰብ ንብረት ይመስል ሁሉም እየመጣ
የአቅሙን ያነሳል።መሬቱ ሁሉ በአልጋወራሹ፣በሌሎች የንጉሳዊ ቤተሰቡ አባላት ወይም በአካባቢው
ሹመኞች እጅ ነው።ብርሀኑ ሁሌም የንጉሡ ተቃዋሚ ቢሆንም የንጉሡ ቤተሰቦቻቸው ግን ግድ
አይሰጡትም ነበር።ስለ ኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ከተለያዩ መጽሀፍት የቃረመው እውቀት አለው።
ለምሳሌ በጽህፈት ሚኒስትሩ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ተጽፎ በ1935 ዓ.ም የታተመው
"የመሬት ስሪት በኢትዮጵያ" እና በማህተመሥላሴ ወልደመስቀል ተጽፎበ1942 ዓ.ም የታተመው
"ዝክረ–ነገር"ይገኙበታል። ወሎ ሄዶ የነበረውን ሁኔታ በአይኑ ሲመለከት፤የገበሬዎቹን የጭሰኞቹን
ችግር ከአፋቸው ሲሰማ፣ያነበበው ሁሉ ግልጽ እና ልዩ ሆኖ ታየው። ከሁሉም የበለጠውን ጉዳት
ያደረሱት የመንደሩ ተራ ሹመኞች (የዋና ሹመኞቹ እንደራሴዎች እና የመንደሩ መሪዎች)ናቸው
ብሎ ያምናል።ገበሬዎቹ የመከላከል አቅም የላቸውም።በጊዜው ምንም የፖለቲካ ንቃትም
አልነበራቸውም።

ብርሃኑ በዛው ዓመት ነሐሴ ላይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ፣ነገሮች "ተጋግለው" ጠበቁት።


ሚኒስትሮቹ እና መኳንንቱ ተለቅመው እየታሰሩ፣ንጉሰ ነገስቱ ደግሞ ገለል እየተደረጉ ነበር። በየቀኑ
አዳዲስ ነገር ይፈጠራል። በመስከረም 2 ንጉሰ ነገስቱ ከሥልጣን ተወግደው ታሰሩ።

በዚህ ወቅት ብርሀኑ የሰበሰበውን መረጃና ጭብጥ በምን ዐይነት መንፈስ መጠቀም እንዳለበት
እያወጣ እና እያወረደ በራሱ በራሱ ጭንቅላት ውስጥ መጽሐፉ ኋላ ላይ የሚኖረው ቅርጽ አልቆ
ሳይታየው በፊት አብዮቱ አዲስ የአመለካከት ፈር አመላከተው። በህዳር 1966 ዓ.ምየአዲስ ዘመን
ጋዜጣ ዋና አዘጋጅነቱ ተመልሶለት ዳግም ተቆናጠጠው። አሁን በቢሮው እስከ ምሽቱ 5 ሰአት
ድረስ እየቆየ ስለሚሰራ ለመፃፍ ምንም ጊዜ አልነበረውም። ለጊዜው የመጽሐፉን ነገር ወደ ጎን
አድርጎ ቢተወውም፣ ስለመጽሀፉ ማሰላሰሉን ግን አላቋረጠም። ነገር ግን በ1970 ዓ.ም ብርሀኑ
ለሶስተኛ ጊዜ ከአዲስ ዘመን አዘጋጅነቱ ተነሳ። “ምክንያቱ ፖለቲካ ሳይሆን አይቀርም።” ብርሀኑ እና
ጌታቸው አብዲ( በቃለመጠይቃችን ወቅት የብሔራዊ ቲያትር ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ)
258
ጥቋቁር አናብስት

የመኢሶንን አመለካከት የሚያንጸባርቅ ጽሁፍ በጋዜጣው ላይ ፃፉ። ነገር ግን መኢሶንና ደርግ


በነሐሴ 1969 ዓ.ም"ተለያይተው" ስለነበር በመኢሶን፣በብርሀኑና በጌታቸው መሀል ግንኙነት
ሳይኖር አይቀርም ተብለው “እንደተጠረጠሩ” ብርሀኑ በዝርዝር ያስታውሳል። በዚህ ወቅት
የኢሕአፓ አባላትም “ከያሉበት እየታደኑ” ነበር።ብርሀኑ እና ጌታቸው ለዘጠኝ ወራት ታሰሩ
(ብርሀኑ በከፍተኛ 15 ጌታቸው ደግሞ በከፍተኛ 4 ታስረዋል)። እነኚህ የእስር ወራት እንዳለቁ
ብርሀኑ እና ጌታቸው ወደ ደርግ “የምርመራ ክፍል” ተወስደው “አንዳንድ ጥያቄዎችን” ተጠየቁና
“ወደቤታቸው ተሸኙ።” ከዚህ በኋላ ብርሀኑ የአማርኛው የካቲት መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሆነ።

ብርሀኑ በከፍተኛ 15 ታስሮ ሳለ፣ እንዲጽፍ ተፈቅዶለት ስለነበር፣የ"ማዕበል"ን ሲሶ ያህል


አጠናቀቀ። የየካቲት መጽሔት ዋና አዘጋጅነቱ ብዙ ጊዜ የሚፈልግ ባለመሆኑ፣ይህንኑ እየሰራ
የመጀመሪያውን የ"ማዕበል" ክፍል ጽፎ ጨረሰ። ነገር ግን ረቂቁን ወደ ማተሚያ ቤት ከመላኩ
በፊት፣ የአንድ ወር ፍቃድ ወስዶ ተመልሶ ወደ ወሎ ሄደ።ባያቸው አዳዲስ ለውጦች ላይ ተመርኩዞ
ማሻሻያ ካደረገ በኋላ፣መጽሀፉን ሳንሱር ክፍሉ ተመልክቶ ያለ ምንም ለውጥ ታተመ።6ብርሀኑ
ዘርይሁን በዚህ መጽሐፉ ከበኩር አብዮታዊ ልብወለድ ደራሲዎች መሀል አንዱ ሆኖ ታወቀ።
"ማዕበል" በመጀመሪያው ህትመት ብቻ 10,000 ቅጂዎች ታተመ።መጽሐፉ በሃያስያን ዘንድም
ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል። ብርሀኑ ዘርይሁን፣በአሉግርማ እና ታደለ ገብረሕይወት በተመሳሳይ
ጊዜ አብዮቱን የሚመለከቱ አብዮታዊ ልብወለዶች አሳተሙ። ሶስቱም ደራሲዎች ይህንን በማድረግ
ቀዳሚ ሲሆኑ ሶስቱም ከፍተኛ ሙገሳ እና ተቀባይነትን አገኙ።የባህል ሚኒስቴር በሶስቱ ደራሲዎች
ስም እና ክብር የኮክቴል ግብዣ አዘጋጀ፣በዝግጅቱም ላይ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ሸዋዬ ተገኝተው
ንግግር አደረጉ። በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ደረጃ ለመጽሐፍት እንዲህ ያለ እውቅና ሲሰጥ
ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ሶስቱም ደራሲዎች በሁኔታው ተበረታቱ።ብርሀኑ አሁንም የየካቲት ዋና
አዘጋጅ እያለ ሁለተኛውን ማዕበል መፃፍ ጀመረ። ነገር ግን በዚህ መሀል በ1972 ዓ.ም አዲስ ስራ
ተሰጠው። ስራውም የአለም አቀፉ "World Marxist Review" አማርኛ እትም ዋና አዘጋጅነት
ነው። ጽሑፎቹ የሚላኩት ከፕራግ ሲሆን መጽሔቱ በወር አንዴ የሚታተም ነው። የብርሀኑ ስራ
ከፕራግ የሚላኩትን ጽሑፎች እየመረጠ ወደ አማርኛ መተርጎም ነበር ( በቃለመጠይቃችን ወቅት
ይህንኑ ስራነበር የሚሰራው)። ስራው ብዙ ጊዜ እና አቅም የሚሻማ አልነበረም ፤ ነገር ግን በጎን
ብዙ የኮሚቴ ስራ እንዲሰራይጠየቃል። ትንሽ ትንሽ መፃፍ ቢችልም፣ በብዛት የሚጽፈው ከሌሊቱ
አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ እስከጠዋቱ አንድ ሰአት ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ነበር። የ"ማዕበል"ን
ሁለተኛ ክፍል ከማጠናቀቁ በፊት "ሞረሽ"7 የተሰኘ ተውኔት ፃፈ። በ1972 ዓ.ም ተጽፎ በተስፋዬ

259
ጥቋቁር አናብስት

ገሠሠ አዘጋጅነት በዚያው ዓመት መጨረሻ በብሔራዊ ቲያትር ቀረበ። በጣም ስኬታማ እና ጥሩ
ተቀባይነት አግኝቶ ለሁለት ወር ያህል ታየ።

በተመሳሳይ ወቅት፣ የ"ማዕበል"ን ሁለተኛ ቅጽ እየፃፈ ነበር። ይህንን መጽሐፍ በሚጽፍበት ወቅት
ስለ ማህበራዊ እና አብዮታዊ ችግሮች የነበረው ንቃተ ህሊና እየጎለበተ መጣ። ነገር ግን፣ ይላል
ብርሀኑ “አቢዮት እንዴት መካሄድ እንዳለበት ወይም እንደሚኖርበት የራሴ አመለካከት ነበረኝ።
በሶሻሊዝም አምናለሁ ግን ኢትዮጵያዊ ሶሻሊዝም ማዳበር አለብን። እዚህም፣ እዚያም ስህተቶች
ተሰርተዋል። ነገር ግን ሶሻሊዝም ብቸኛው መንገድ ነው። ያለ ምንም ምክንያት ቢሆንም ዘጠኝ ወር
መታሰሬ ፀረ–አብዮተኛ ሊያደርገኝ አይችልም።” ለሱ ሶሻሊዝም “ሀይማኖት” ሳይሆን ለማህበራዊ
እድገት መፍትሔ ነው።8

በ1973 ዓ.ም ሁለተኛው ክፍል የ"ማዕበል"በ10,000 ቅጂዎች ታትሞ ሲሰራጭ እንደ


መጀመሪያው ሁሉ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠበቀው።በዚህ ወቅት የመጀመሪያው "ማዕበል" በሬዲዮ
እየተተረከ ነበር (ቅጽ ሁለት እና ሶስትም ዘግየት ብለው ተተርከዋል )

ብርሀኑ ሶስተኛውን ቅጽ መፃፍ ከመጀመሩ በፊት ለዚሁ ለመጽሀፉ ሲል ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ወሎ


ለመጓዝ ተነሳ።ኩታበር እያለ አንዳንድ ፀረ–አብዮታዊ እንቅስቃሴዎች ይካሄዱ ጀምረዋል።
መሆነኛም ላይ እንደዚህ ያለ እንቅስቃሴ ነበር። እንቅስቃሴዎቹ በቀድሞ ባለስልጣናት የሚመሩ
ሲሆን 20,000 ያህል ሰዎች ተሳትፈውበታል።“ትልቅ ጦርነት ነበር” ይላል ፤ እሱም ሁኔታዎችን
እየታዘበ በኩታበር ለአንድ ወር ያህል ቆየ። ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ "ማዕበል" ቅጽ ሶስትን
አጠናቀቀና በ1974 ዓ.ም ታተመ።ልክ እንደ ሁለቱ ቀደምት ቅፆቹ ሁሉ ይኼኛውም ደህና
ተቀባይነት አገኘ።

የብርሀኑ ቀደምት ልብወለድ "የቴዎድሮስ እንባ" በመስፍን አለማየሁ አማካኝነት ወደ ተውኔት


ተለውጦ በ1973 ዓ.ም በራስ ቲአትር ይታይ ነበር። “ቦታው ለቲያትር ባይመችም”፣ተውኔቱ
ተወዳጅ ሆኖ ለሁለት ወራት ታየ።

ብርሀኑ በ1975 ዓ.ም "ጣጠኛው ተዋናይ" የሚል ተውኔት ጽፎ በሐገር ፍቅር ቲያትር ቤት
ለመድረክ አበቃ።9 “ከምርጥ ስራዎቼ አንዱ ነው” ይላል በኩራት። በዚህ ተውኔት አዳዲስ የአጻጻፍ
ስልቶችን ሞክሯል። ይህ ስራ በተውኔት ውስጥ ሌላ ተውኔት የያዘ ሲሆን ጭብጡ አንድ ተውኔት
ለማዘጋጀት ያለውን ጣጣ ይዳስሳል።ይህ ደግሞ ልምምዶችን እና ዋናው ተውኔቱን፣ ሁለቱንም

260
ጥቋቁር አናብስት

በአንድ ላይ መድረክ ላይ ማሳየትን ይጠይቃል። ነገር ግን ይህ ለብዙ ሰዎች ውስብስብ በመሆኑ


ሊረዱት እና ሊደነቁበትአልቻሉም።በመሆኑምከስድስት ወይም ሰባት ሳምንታት በኋላ በኪሳራ
ተዘጋ። በእርግጥ ጌታቸው አብዲ ግሩም አድርጎ አዘጋጅቶት ነበር ብሎ ብርሀኑ ይጨምራል።

በቀጣዩ 1977 ዓ.ም ዝነኛውን ተውኔት "አባ ነፍሶ"ንደረሰ። "አባ ነፍሶ" የዝነኛው ጦረኛ
የደጃዝማች ባልቻ የፈረስ ስም ነው። ተውኔቱ በተፃፈበት ዓመት ለመድረክ በቅቶ ለረዥም ጊዜ
ታይቷል(እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ መታየቱን ቀጥሎ ነበር)። ከብርሀኑ ተውኔቶች ሁሉ የበለጠ ሆነ።
10
ተውኔቱ ሶስት ሰአት የሚፈጅ ሲሆን ።ሰዎች ወደ ቲያትር ቤቱ ገብተው ተውኔቱን ለመመልከት
ረዥም ሰአት ተሰልፈው ይጠብቁ ነበር። እኔ ግን ብርሀኑ ዘርይሁን እና የተውኔቱ አዘጋጅ በነፃ
ስለጋበዙኝ ከመሰለፍ ድኜአለሁ።

ይህ ቃለመጠይቅ በሚካሄድበት ወቅት፣ ብርሀኑ አዲስ ልብወለድ መፃፍ ጀምሮ ነበር።ልብወለዱ


“የቴውድሮስ እምባ" ከተሰኘው መጽሐፉ መነሻ ሀሳብ ቢወስድም ታሪኩ ግን ፍፁም አዲስ ነው።
”ባለ 300 ገጽ ትልቅ ልብወለድ እንደሚወጣው ነው።"የታንጉት ሚስጥር" የተሰኘው ይህ
ልብወለድ በ1978 ይጠናቀቃል ብሎ ገምቷል።11

****

"የታንጉት ሚስጥር" እንደታተመ፣ ብርሀኑ ታሞ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገባ።ጉበቱ፣ጨጓራውና


አንጀቱ ታሞ ተዳክሞ ነበር።ልጎበኘው ሆስፒታል ስሄድ መንምኗል፤ያስለዋል።ከስድስት ሳምንት
በኋላ ከሆስፒታል ወጣ።አዲሱ መጽሀፉ ባገኘው ተቀባይነት ደስተሰኘ። ነገር ግን ሶስቱ የ"ማዕበል"
መጽሐፍቱ ተሰብስበው ያለፍቃዱ ወደ ሩስኪ በመተርጎማቸው ተበሳጭቶ ነበር። ደግሞም
መተርጎማቸው ሳይንስ ማግኘት ያለበትን ክፍያ ከለከሉት።ሩስያዊ አሳታሚዎቹ የሰጡት ምክንያት
ኢትዮጵያ በቅጂ መብት ላይ የበርሊንን ስምምነት አልፈረመችም የሚል ነበር።

በዚህ ወቅት ብርሀኑ አዲስ ልብወለድ ለመፃፍ እየተዘጋጀ ነው። ልብወለዱ የዘመኑን “ማህበራዊ
ችግሮች” ይዳስሳል። መጽሐፉን ገና መፃፍ እየጀመረ ነበር፣ ነገር ግን ወደ ጎጃም ሄዶ ለሶስት ወር
ያህል የልብወለዱን ዳራ እና የማህበረሰቡን ዘዬ ማጥናት ያስፈልገዋል።

ገበያ ላይ ያሉ አስራ አንድ መጽሐፍት ሲኖሩት፣ ተውኔቶችንም ጽፏል።ገና በሕይወት እያለ


ከታላላቅ የኢትዮጵያ ደራሲዎች መሀል አንዱ ሆኗል።

****
261
ጥቋቁር አናብስት

ከሆስፒታል ወጥቶ ብዙም ሳይቆይ ድጋሚ ታመመና ተመልሶ ገባ። አርብ ሚያዝያ 16 1979
ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑትን ዶክተር ብርሀኑ አበበን አግኝቼያቸው ብርሀኑን
ከአንድ ቀን በፊት እንደጠየቁት ነገሩኝ። በጊዜው በጣም ከመዳከሙ የተነሳ መናገር እንኳን
ስለማይችልና ብዙ ቀን ይቆያል ብለው አልገመቱም።በቅርቡ እጠይቀዋለሁ ብዬ ባስብም፣ ብርሀኑ
በዚያው ምሽት(ምናልባትም በጉበት ካንሰር) ከዚህ አለም በሞት ተለየ።በማግስቱ ቅዳሜ ሚያዝያ
17 ቀን 1979 ዓም በሥላሴ ቤተክርስቲያን ተቀበረ።በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፖለቲካ
ባለሥልጣኖች፣ ደራሲዎች(ሊቀመንበር ሆኖ ባገለገለበት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር እና ዋና
ጸሐፊ ሆኖ ባገለገለበት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አባል የሆኑ)፣ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹን
ጨምሮ ብዙ ህዝብ ተገኝቷል። "The Ethiopian Herald" በሚያዝያ 18 ቀን 1979 ዓ.ም
እትሙ በጎንደር ከተማ በ1926 ዓ.ም ተወልዶ በ55 ዓመቱ መሞቱን ጽፏል።እነኚህ ቁጥሮች
ብርሀኑ ከነገረኝ ጋር አይጣጣሙም። እሱ በነገረኝ መሰረት ሲሞት 53 ወይም 54 ዓመት ቢሆነው
ነው።

***

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብርሀኑ ዘርይሁንን የሚያውቅ አንድ ሰው፣መንግስት ለተጨማሪ ህክምና


ወደውጭ ሊልከው ፈቃደኛ ባለመሆኑ መከፋቱን ነገረኝ።በሕይወቱ የመጨረሻ ቀናት ፀሎት
እንዲደረግለትና እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሞት እንደሚፈልግ ተናግሮ ነበር።የተቀበረውም
እንደምኞቱ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ደንብ መሰረት ነው። አርባው ሲወጣ በሥነ ስርአቱ ላይ
ሶስት ጳጳሶች ተገኝተዋል።ነገር ግን ቀኑ ቅዳሜ ላይ እንዲውል ስለተፈለገ፣ ጥቂት ቀናት ተገፍቶ
ነበር። መቃብሩ ላይ ምንም ዐይነት የሶሻሊስት አርማ አልተደረገም።

የተርጓሚው ማስታወሻ ከብርሃኑ ዘርይሁን(1925-79)ሞት በኋላ አንዳንድ ስራዎቹ ተደጋግመው


ታትመዋል፡፡

ማስታወሻዎች

1) ብርሀኑ ዘርይሁን፣ አሀዱ ሳቡሬን ያሳደጋቸው አንድ ፈረንሳዊ ስለነበርሁለተኛ ፈረንሣዊ ስም


እንደነበራቸው ፤ ይሁን እንጂ ከሐረር የመጡ ፍፁም ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ ይናገራል።

262
ጥቋቁር አናብስት

2) በኢትዮጵያ ውስጥ "የቆየ ማሕበራዊ ስርዓት" ብሎ ይጠራዋል። በዘመነ መሣፍንት ከ18ተኛው


ክፍለ ዘመን አጋማሽ እስከ 19ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ድረስ በጎንደር ውስጥ “የሴተኛ አዳሪዎች”
ሰፈር ነበሩ ስለሚባሉ ቦታዎች ተነግሮታል።

3) ሌላው ደራሲና በኃይለሥላሴ ዘመን ሚኒስትር የነበሩት ሐዲስ አለማየሁ ኃይለሥላሴ ተራው
ህዝብ የፖለቲካ ፍላጎት እንዲያድርበት አይፈልጉ እንደነበር እና ይህንን የሚቆጣጠሩላቸው
የራሳቸው ፖለቲከኞች እንደነበሯቸው አጫውተውኛል። ይህ ሁኔታ የ66ቱ አብዮተኞች በቀላሉ
ሊሞሉት ያስቻላቸውን ክፍተት መፍጠሩን ጨምረው ነግረውኛል።

4) "አንድ ለናቱ" ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ታትሟል ፤ ጥሩ ምላሽም አግኝቷል። ይሁን እንጂ ብርሀኑ


የአቤ ጉበኛ ምርጥ መጽሀፍ ይሄ አይደለም ፤ "የረገፉ አበቦች" የሚለውና መጽሐፉናግጥሞቹየበለጠ
ሊደነቁ ይገባል ይላል።

5) ወደዚያ የሄደው የአፍሮ–እስያዊ ደራሲዎች ማህበርን ስብሰባ ለመካፈል ነው። ከዚያ ቀደም
ብሎ ለመንግስት የስራ ጉዳይ ወደ ግሪክ፣ ዩጎስላቪያ፣ ጀርመን እናአሜሪካ ተጉዟል ፤ በዚያውም
መጠነኛ የዘገባ ስራ ሰርቷል።

6) ሳንሱረኞቹ ብዙ ለውጥ ማድረግ ፈልገው ነበር ፤ ነገር ግን ከዚያ በፊት ረቂቁ ለማስታወቂያ
ሚኒስትሩ ግርማ ይልማ ቀረበ። እርሳቸው ግን ሳንሱረኞቹ መለወጥ ወይም ማስወገድ የፈለጉትን
አብዛኛውን ነገር እንዳለ አሳለፉት። የተደረገው ንዑስ የቃላት ለውጥ ብቻ ነው።

7)ቃሉ የመጣው ከግሪኩ "Moreshi" ሲሆን ትርጉሙም “የሚስጥር ቃል” ማለት ነው።
በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ካመሸ፣ ዘመድ ወዳጆቹ ሲፈልጉት
ወይም ምን እንደደረሰበት ለማወቅ ሲሞክሩ፣ በእውነተኛ ስሙ አይጠሩትም። ምክንያቱም ጠላቶቹ
አውቀው ጉዳት እንዳያደርሱበት በሚስጥር ስሙወይም "ሞረሽ" ይጠሩታል።

8) ብርሀኑ ዘርይሁን ከጎንደር ተማሪነቱ ጊዜ ጀምሮ ለሀይማኖት አሉታዊ አመለካከት ነበረው።


ፀጉሩን በዘመናዊ መንገድ አሳጥሮ ይቆረጥ ነበር። አንድ ቀን ሻይ ቤት ቁጭ ብሎ ዳቦ በሻይ እየነከረ
እየበላ የቤተክርስቲያኑ ሀላፊ መጣ። ሃላፊው ግን እንቊላል እየበላ መሰለው ፤ ቀኑ ረቡዕ የጾም
ቀን በመሆኑ እንቁላል መብላት አይፈቀድም ነበር። ይሄ ቄስ ለሁሉም ሰው ብርሃኑ ጴንጤ ሆኗል ፤
የማርያም ጠላት ነው እያለ መናገር ጀመረ። በሚቀጥለው ቀን ብርሀኑ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ፣
አውጥተው አባረሩት። ከዚያ በኋላ ለሀይማኖት ያለው አመለካከት እየቀዘቀዘ መጣ። ቤተሰቡን
ለማስጠመቅ፣ለቀብር ወይ እንዲያው መሄድ ሲፈልጉ ለማድረስ ካልሆነም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ
263
ጥቋቁር አናብስት

አያውቅም። ሚስቱ ግን የቤተክርስቲያን ሰው ነበረች ፤ እሱም የሷንና የቀረውን ቤተሰቡን ነፃነት


ያከብር ነበር። ብርሀኑ ቤተክርስቲያንን እንደ ባህል ተቋም ነው የሚመለከተው፤በተያያዘም
ተግባራቸውን በመጠኑ ያከብራል።

9) ይህ የብርሀኑ የራሱ ትርጉም ነው። ነገር ግን "ጣጠኛ" የሚለው ቃል ፍቺ "ችግር ፈጣሪ"


እንጂ"የተቸገረ" የሚለው አይመስልም።

10) " ሀብታም አላደረገኝም። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ሕክምና ወደ እንግሊዝ ሀገር የምትሄደውን
ሚስቴን ወጪ ለመሸፈን ረድቶኛል" ይላል።

11) ይህ ልብወለድ በ1979 ታህሳስ፣ ወይ ጥር ላይ "የታንጉት ሚስጥር" በሚል ርዕስ ታትሟል።


በወራት ውስጥ 30,000 ቅጂዎች ተሽጦለታል። መጽሐፉ ሲወጣ፣ በጎንደር ብቻ የሚታወቁ
ቃላቶች እና አገላለፆች ስላሉት አንብቤ ለመረዳት ሊከብደኝ እንደሚችል ነግሮኛል።

264
ጥቋቁር አናብስት

ስብሐትገብረእግዚአብሔር
"ሊታተም የማይችለው" የደራሲዎች "ደራሲ" የበአሉ ግርማ
መጽሐፍትን ካወቅኳቸውና ካነበብኳቸው በኋላ ብዙ ዘግይቼ፣
ከነዚህ መጽሐፍቱ መሐል"ደራሲው" በተሰኘው ውስጥ፣ በአሉ
በሌሎች ልብወለዶቹ ላይ ከተለመደው በላይ አብዝቶ በሕይወት ያለ
አንድን ሰው መሰረት አድርጎ መሳሉን ተረዳሁ። ለደራሲው ሞዴል
የሆነው ሰው፣ በአሉ ምን እየሰራ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል ፤
በአሉም መጽሐፉን ከማሳተሙ በፊት "ለሞዴሉ" ረቂቁን ደጋግሞ አንብቦለታል። ይህንን ሰው
ማግኘት ፈለግኩ ፤ ቀጥሎ የምታነቡት የዚህ ሰው ምስል ነው። ምንም እንኳን ይህንን ሰው ማግኘት
የፈለግኩት በበአሉ ታሪክ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የነበረ ቢሆንም፣ ስለሕይወቱ ብዙ
ሲነግረኝ ግን፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በራሱ አስገራሚ ሰው መሆኑን ተረዳሁ። የፃፋቸው
ጥቂት መጽሐፍት እኔ ቃለ መጠይቅ እስካደረግኩለት ጊዜ ባለመታተማቸው፣ እዚህ ለማካተት
የሚያበቃ ጠንካራ መሰረት አልነበረውም።ሆኖም ይህ ቃለ መጠይቅ ከተደረገ በኋላ የአጭር
ልብወለዶች ስብስብ የሆነውን የመጀመሪያ መጽሐፉን "አምስት ስድስት ሰባት"ን አሳተመ። እ.ኤ.አ
በ19901 ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ፣ በመጽሐፍት መደብሮች ለሽያጭ የቀረበው ይህ መጽሐፉ ብቻ
ነበር። በዚህ መጽሐፍ ከቀረበው የበአሉ ግርማ የሕይወት ታሪክ ጋር ሲነፃፀር ይህ የስብሀት ምስል
ስብሀት ስለራሱ ባለው አመለካከት፣በአሉ ግርማ ለ"ደራሲው" የተጠቀመበት ህያው ሞዴል እና
የበአሉን መጽሐፍ ያነበቡት ሰዎች በምናባቸው በሚቀርፁት ምስል መሐል ያለውን ልዩነት ፍንትው
አድርጎ ያሳያል።

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የተወለደው ትግራይ ውስጥ፣አድዋ አጠገብ በምትገኝ ርባገረድ


በምትባል ትንሽ መንደር በሚያዝያ 27፣ 1928 ዓ.ም ነበር። ወላጆቹ ገብረእግዚአብሔር ዮሐንስ
እና መአዛ ተወልደመድህን ከወለዷቸው 11 ልጆች መሐል ስብሐት 7ተኛ ልጅ ነው። አባቱ ቄስ
እና ገበሬ ሲሆኑ እናቱ የቤት እመቤት ናቸው። ስብሐት እንደማንኛውም የገጠር ልጅ ከብት ጠብቆ
ነው ያደገው፤ ታዲያ እረኝነቱን ቢወደውም ሁሌ በሌት መነሳቱ ያማርረው ነበር። ወላጆቹ
ልጆቻቸው ላይ ዱላ ሰንዝረው ስለማያውቁ፣ያደገው ደስተኛ ሆኖ ነው፤ ይሁን እንጂ በጣም ድሆች
በመሆናቸው ፣ ነፍሳቸውን ለማቆየት ልጆቹ ከለጋነታቸው ጀምሮ፣ ጠንክረው መስራት
ነበረባቸው። አባቱ ማስመሰል የማያውቁ ቀጥተኛ ሰው ነበሩ። በአንድ ጊዜሩህሩህ እና ቶሎ
የሚቆጡ ሲሆኑ፣ በስብሐት አማርኛ "ሰብአዊ" ነበሩ ይላል ስብሀት። በገጠር እንደተለመደው
ቤተሰቡ ቤተክርስቲያን ይስማል፤ በቤት ውስጥ ግን አባቱ "አባት ብቻ" ናቸው፤ማታ ማታ
ለልጆቻቸው የግእዝ ፀሎት በማስተማራቸው ብቻ ይለያሉ።
265
ጥቋቁር አናብስት

በኋላ ስብሀት ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው፣ በአባቱ መምህርነት "የቄስ ትምህርት ቤት" ገብቶ ግእዝን
መናገር ሳይሆን ማንበብ ብቻተማረ። በተረፈ ግእዝን የሚረዳው፣ አፉን ለፈታበት ትግርኛ ባለው
ቅርበት ነው። እናቱ "ጠንካራ ሠራተኛ"፣ "ረጋ ያሉ" እና "ፍቅር የማይሰስቱ" ናቸው።

በ10 ዓመቱ፣ በታላቅ ወንድሙ እርዳታ፣ ስብሐት ወደ አዲስ አበባ መጣ። ስዊዲሽ ሚስዮን
ትምህርት ቤት ስቬን ሩቢንሰን ርእሰ መምህር እያሉ፣ አንድ ዓመት ጥሩ የአዳሪ ተማሪነት ጊዜ
አሳለፈ። ከዚያም አጎቱ ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በአዳሪነት እንዲገባ ረድተውት፣ 2ተኛ
ክፍልን መማር ሳያስፈልገው፣ ከ3ተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ድረስ
ተማረ።ይህ ጀዝዊቶች የሚያስተዳድሩት "በጣም ጥሩ የሚባል ትምህርት ቤት" ነበረ።
አስተማሪዎቹ "ቅጥ ያጣ የሥነ ስርአት ቁጥጥር የሚያበዙ " ከመሆኑም በላይ፣ "ፍልስፍናቸው
በፍልስፍና ቃላት የተለወሰ ሥነ ―መለኮት" ሲሆን፣ "ይህንንም ፍልስፍና ብለን እንድንጠራው
ቢያስገድዱንም"፣እንዲሁም "ከተማሪዎች መሀል ሰላዮችን መልምለው የሚሰልሉን መሆኑ
ቢደብረንም" ጎበዝ አስተማሪዎች ነበሩ። ስብሐት አብዛኞቹ የትምህርት ዐይነቶችን ቢወዳቸውም፣
ለጂኦሜትሪ ልዩ ፍቅር ነበረው፤ የአብዛኛዎቹ ትምህርቶች ውጤቱም ጥሩ ናቸው ። “ትምህርት
በጣም ቀላል ነበር” ይላል ስብሐት። ከ10ኛ ክፍል ጀምሮ ሎንግማን በቀላል እንግሊዝኛ
የሚያሳትማቸውን መጽሐፍት እያነበበ ይደሰት ነበር። በትምህርት ቤትቲያትሮች ማዘጋጀት
የተለመደ ሲሆን፣ ስብሐትም 11ደኛ ክፍል ላይ በአንድ ቲያትር ላይ ተሳትፏል። በዛው ዓመት
የትምህርት ቤቱ መጽሔት አዘጋጅ እንዲሆን በእንግሊዝኛ መምህሩ ተመረጠ። በትምህርት ቤቱ
የአማርኛ ትምህርት በሚገባ ካለመሰጠቱም በላይ፣ ስብሐት በግሉ የግርማቸው ተክለሐዋርያትን
"አርአያ" ከ30 ገጽ በላይ አላነበበም ፤ በእርግጥ የከበደ ሚካኤልን "ታሪክና ምሳሌ" አንድ ዙር
ሳይሄድበት አልቀረም። በተጨማሪም ራሳቸው ከበደ ሚካኤል የተረጎሙትን "Beyond
Pardon" (ከይቅርታ በላይ) የተሰኘ ተውኔት ተመልክቷል ። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ለአማርኛ
ቋንቋ ከሚሰጠው ዝቅተኛ ግምት የተነሳ፣ ስብሀት በመንገዱ የገጠሙት የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ
ፍሬዎች ብዙም አልማረኩትም ፤ የከበደ ሚካኤል ስራም ቀልቡን አልያዘውም። በአማርኛ ክፍለ
ጊዜ በክፍሉ ከሚነበብ ምንባብ የበለጠ ቦታ ሰጥቶት አያውቅም ነበር። ተማሪዎቹ ጭራሽ ከበደ
ሚካኤልን እንደ ደራሲ እንኳን አይቆጥሯቸውም። በጊዜ ሂደት በእርግጥ የስብሐት አመለካከት
ይቀየራል። በኋላ ላይ ከበደ ሚካኤል በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ "ጉልህ የታሪክ ድርሻ"
እንዳላቸው ቢገነዘብም “እኔን ግን አሁንም አይማርኩኝም” ይላል። “አንዳንድ ሥራዎቻቸውን

266
ጥቋቁር አናብስት

ባነብላቸውም፣ ጨምሬ ሌሎች መጽሐፍቶቻቸውን እንዳነብ አይገፋፉኝም" ይላል አስከትሎ፤ በግል


ዝንባሌ እንጂ በግድ አላነብምና!”

የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተናን "ደህና" በሚባል ውጤት ካለፈ በኋላ፣ እዚህም ጀዝዊቶች
በሚያስተዳድሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገባ። እንደ ስብሐት ግምት ከሆነ፣ በጊዜው 19
ዓመት ይሆነዋል። ያጠናው የመምህርነት ሞያን ሲሆን፣ በተለይ የሰለጠነው "የሁለተኛ ደረጃ
የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር" ለመሆን ነው። ከአራት ዓመት በኋላ ተመረቀ። በኮሌጅ ቆይታው
ብዙም የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አላነበበም፤ ያነበባት ትንሿም ብትሆን ማራኪ ሆና አላገኛትም።
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ፣ የሚወዳቸው ደራሲዎች ሪደር ሀጋርድ፣ ሉዊስ ስቴቨንሰን እና አንቶኒ
ሆፕ የመሳሰሉት ነበሩ። በኮሌጅ ውስጥ "ዶስቶቭስኪ መስኮት ከፈተለት" ― " አለምን፣
ሕይወትን" የሚያሳይ መስኮት! ከዶስቶቭስኪ ሌላ ሶመርሴት ሞም፣ ዞላ፣ ሞፓሳ፣ ቼኮቭ እንዲሁም
ከሁሉ የሚያስበልጠው፣ ይህንን ቃለ መጠይቅ እስካደረግኩለት ጊዜ ድረስ የሚያደንቀው ሌዊስ
ካሮል ምርጫዎቹ ነበሩ። ረዥም እና አጭር ልብወለድ ከሌሎች የሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ይልቅ
ይማርኩታል። በኮሌጅ እያለ ኋላራሳቸው ታዋቂ ደራሲያን ከሚሆኑት ተስፋዬ ገሰሰ እና ሰለሞን
ደሬሳ ጋር ሞቅ ያለ ጓደኝነት መስርቷል። ሁሉም "አንድ ባች" ተማሪዎች ከመሆናቸው ባሻገር፣
"ተመሳሳይ መጽሀፍ ማንበብ የሚያዘወትሩ"፣ "ውቤ በረሀ ወረድ ብለው በሕብረት የሚዝናኑ"፣
ደግሞ ስለ "ህዋ፣ እግዚአብሔር፣ እጣ ፈንታ፣ ደግነት፣ ክፋት " ሳያቋርጡ፣ ሳይሰለቹ የሚወያዩ
ነበሩ።

ኮሌጅ እያለ እጅ እያጠረው፣ኪሱ እየጎደለ እንደልቡና እንደሚፈልገው "ሲኒማ ባይገባም፣ ውቤ


በረሀ ባይወርድም " ደስተኛ ነበር፤"ቤተመፃሕፍቱ በሚገባ የተደራጀና የተሟላ በመሆኑ " ጥሩ ጊዜ
አሳልፏል። "አንድ ሺህ አንድ ሌሊት"ንም ያነበበው እዚህ ነበር። ለዛው፣ ምትሀቱ እንዲሁም እሱ
ባነበበው የሰር ሪቻርድ በርተን ትርጉም ውስጥ ጎላ ብሎ የሚስተዋለው የቤት ዓመታቱ“ጠንካራ
ተጽእኖም አሳድሮብኛል” ይላል2። እነዚህ ትረካዎች ስብሐት ከሚወዳቸውና አሻራቸውን
ካሳረፉበት የኢትዮጵያ ተረቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው።

ኮሌጅ እያለ ከአንዲት ልጅ ጋር በፍቅር ቢወድቅም አይናፋርነቱ አሸነፈውና ሳይነግራት ቀረ፤


ቢሆንም ከሁለት ዓመት በኋላ ዋሺንግተን ተገናኝተው ቢነግራት እሷ ራሷ በፍቅሩ ስትማቅቅ
እንደነበረች፣ ካሁን አሁን ይጠይቀኛል በማለት ተስፋ አድርጋ እንደነበር በመግለጽ ወቀሰችው።

267
ጥቋቁር አናብስት

ነገር ግን ያ እድል አልፏቸዋል፤ስሜታቸውም ቀዝቅዟል። አሁን የፍቅር ሕይወቱ አዲስ መስመር


ሊይዝ ነው።

ኮሌጅ ላይ ሌላ ቀልቡን የሳበው በሩስያዊው ሚስተር ሶሎዱሂን " ህያው እየሆነ" በማራኪ
አቀራረብ ይማሩት የነበረው ጥንታዊ ታሪክ ነበር። በተረፈ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት
ስለማያምንና ስለማይፈልግ፣ኮሌጅ ለሱ "በጣም ቀላል" ሆኖለት አልፏል።

ከኮሌጅ እንደተመረቀ፣ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ለስምንት ወራት እንግሊዝኛ ቋንቋን


አስተማረ። ቀጥሎ በትምህርት ሚኒስቴር፣ የነፃ ትምህርት እድል ክፍል ሰራ። ከተመረቀ ከሁለት
ዓመት በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጓዘ። ስብሐት ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናው፣በፊትየሁለተኛ
ደረጃ ርእሰ መምህሩ በነበሩት፣ ኋላ የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ዲን የሆኑት ባለሙያ፣ ላይብረሪ ሳይንስ“
የሰውን ልጅ እውቀት ሁሉ የምታይበት በር ይከፍትልሃል”ብለው መክረውት፣ ይህንኑ የትምህርት
መስክ ለማጥናት ነበር። ይሁን እንጂ ስብሐት ላይብረሪ ሳይንስን እንደጠበቀው አላገኘውም ፤
የትምህርት መስኩ እንዲቀየርለት በተደጋጋሚ ቢያመለክትም ሰሚ አላገኘም።ስለዚህ ስብሐት
ለስድስት ወር ሁሉን እርግፍ አድርጎ ትቶ፣ ክፍል መሄዱን አቁሞ፣ ዘወትር ከሰአት "የአሜሪካ
ፊልሞችንና፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ረቂቅ ሙዚቃ እያጣጣመ"፣ እንዲሁም ማስታወቂያ የሚበዛበትን
የቴሌቪዥን ፕሮግራም እየተመለከተ ጊዜውን አሳለፈው። በመጨረሻ ግን "ፋካልቲ እንዲቀይር"
ተፈቀደለት። “ይሁን እንጂ” ይላል ስብሀት “በጣም ረፍዶ ነበር”―አሁን የሚፈልገው ወደ ቤት
መሄድ ብቻ ነው፤ ወደ ሀገሩ ቢሄድም ቅሉ አሜሪካንንና ህዝቦቿን በጣም ወዷቸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት ለሁለት ዓመት እንግሊዝኛ ካስተማረ በኋላ
ተሰላቸ። እንደ እድል ሆኖ በዩኔስኮ በኩል የፍልስፍና እና የሶሲዮሎጂ ትምህርት ነጻ እድል አግኝቶ
ወደ ፈረንሳይ አመራ። በኤክስ―ኤን―ፕሮቫንስ ለ22 ወራት ቆየ። ስብሐት ከፈረንሳይ ተመልሶ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የዶክተር ክላውድ ሰምነር ረዳት ሆኖ ሊሰራ ተስማምቷል።
ሰምነርሲልኩትም ይህንኑ አስበው ነበር። ሰምነር እነ ስብሀትን በኮሌጅ ለአራት ዓመት ፍልስፍና
ወይም "ፍልስፍና ነው ብለው ያሰቡትን" አስተምረዋል። በስብሀት አስተሳሰብ ግን "ያ ፍልስፍና
አልነበረም"! "በፍልስፍና መመራመር፣ መጠየቅ ትጀምራለህ። ምን ዐይነት መልስ እንደምታገኝ ግን
አታውቅም። ነገሩ የሀሳብ ጉዞ ነው። ነገር ግን እኛ በተማርነው ፍልስፍና የጥያቄዎቹ መልሶች
አስቀድመው ይታወቃሉ፤ ክርክሮቹም ቀድሞ የሚታወቀውን ውጤት እንዲያስገኙ ተብለው
የሚቀናበሩ ናቸው። ልክ የማርክሲዝም ፍልስፍና ከሚሉት ጋር አንድ ነው። መልሶቹን አስቀድመህ
ታውቃለህ ፤ አመክንዮውም ከአንተ መልስ ጋር እንዲገጥም ታረገዋለህ።እንደዚያ አድርገህ ነው
የምታወናብደው።"
268
ጥቋቁር አናብስት

ስብሐት ከሁለት ሳምንት በኋላ ፍልስፍና እና ሶሲዮሎጂን አይናችሁ ላፈር ብሎ፣ልብወለድ መፃፉን
ተያያዘው። ይህ "ሌቱም ዐይነጋልኝ" የተሰኘ ልብወለዱ፣ በአዲስ አበባ የውቤ በረሀ፣ በቀይ
መብራት ቀጠናን፣ የማታ ሕይወት ይዳስሳል። ርእሱም ከአንድ የአማርኛመጽሀፍ የተወሰደነው።
ይህንን ልብወለዱን በእንግሊዝኛ 65 ገጽ ያህል የፃፈው በሰሜን አሜሪካ እያለ ነበር። ነገር ግን
"በባእድ ቋንቋ የትርጓሜዎችን ረቂቅ ልዩነት ማጉላትና፣ ለዛውን ጠብቆ መፃፍ ስለማይቻል"
ፈረንሳይ ውስጥ እንደ አዲስ በአማርኛ ይጽፈው ጀመረ። የውቤ በረሀን ሕይወት
"እንደወረደ―ሳያሞግስም፣ ሳይነቅፍም" ፃፈ። "በአዲስ አበባ በጊዜው የነበረውን የማታ ሕይወት
እውነተኛ ምስል አቀረበ"። ይህ መጽሀፍ እስከአሁን አልታተመም፤“በዚህ የንቃት ደረጃችን
ሊታተምም አይችልም ” ይላል ስብሐት ጨምሮ። በፈረንሳይ ትምህርቱን ባይከታተልም፣ በነፃ
የትምህርት እድሉ ሁለት ዓመት ቆየ።

ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ፣ በትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ዓመት ስራ ተሰጠው። ከዚያም የመነን


ጋዜጣ አዘጋጅ ለነበረው በአሉ ግርማ ረዳት ሆኖ፣ ለሁለት ዓመትያክል ሰራ። ስብሐት በመነን
ጋዜጣ ላይ በበአሉ ግርማ ኃላፊነቱ እየተሰጠው በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሁሉም ቅጾች ላይ ይጽፍ
ነበር።ዜና፣ አመለካከትና እይታ እንዲሁም፣ ምርጥ ስራዎቼ ነበሩ በሚላቸው ―አውደ ሰብ (
ከነዚህም መሐል ሰአሊው አፈወርቅ ተክሌ፣ ታሪኩ በዚሁ መጽሀፍ የተነገረለት ተስፋዬ ገሰሰ፣
ሌላው ዝነኛ ሰአሊ እስክንድር ቦጎሲያንን አነጋግሮ የሕይወት ታሪካቸውን ያቀረበበት) የመሳሰሉትን
ጽፏል።

ቅርርብ ባይኖራቸውምስብሐትና በአሉ ግርማ ከኮሌጅ ጊዜ ጀምሮይተዋወቃሉ። ይህ ስራ ዳግመኛ


ሲያገናኛቸው በአሉ ባልደረቦቹን የሚያበረታታ ሆኖ አገኘው ፤ ስብሐት ስራው በጣም
ተስማማው። በጣም የሚያስደስት የስራ ግንኙነት ነበራቸው። በዚሁ ወቅት ፈረንሳይ ሳለ
ስለሚያውቀው አንድ ኢራናዊ ወጣት ልብወለድ መፃፍ ጀመረ፤ልብወለዱ ርእሱ "ትኩሳት" ሲሆን፣
የተፃፈበት ቋንቋ አማርኛ ነው። ኢራናዊው የተደላደለ ኑሮውን "ለአብዮታዊ አላማ" ብሎ ጥሎ
ይሰደዳል ፤ ከሀገሩ እና ከቤተሰቡ ጋር ተቆራርጦ ቀርቷል። ልብወለዱ "ለፍትወት ወይም በአካል
ለሚገለጽ ፍቅር የቀረበ የውዳሴ ዜማ" ነው። ስብሐት ይህንን አብዮተኛ "እንደ ተራ ሰው"
ቢያቀርበውም፣በሱ እምነት "የጀግኖች መስፈሪያ/ልኬት/ልክ" ነው። ስብሐት እንደሚያስበው
ከሆነ በፍፁም ሊታተም የሚችል ዐይነት መጽሐፍ አይደለም።

ምናልባትም ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ልብወለዶቹ ታተሙ አልታተሙ ግድ የሚሰጠው ሰው


አልነበረም። እንደነገረኝ ከሆነ ልብወለዶቹን የሚጽፋቸው ለራሱ ደስታ ነው፤አንዴም እንኳን

269
ጥቋቁር አናብስት

ሊያሳትማቸው ሞክሮ አያውቅም። ለራሱ ደጋግሞ አንብቧቸዋል ፤ ለጓደኞቹም ያነብላቸዋል።


ከነዚህ መሐል አንዳንድ ስራዎቹን በእጅ ገልብጠዋቸዋል። የሚጽፍበት አብይ ምክንያት መፃፍ
ስለሚያስደስተው ነው። ሕይወትን እንደሚያየውና እንደሚያውቀው መግለጽ ይፈልጋል ፤ ለዚህም
ታሪኩ እስካስፈለገውና ልብወለዱን እውነት እስካስመሰለ ድረስ ብዙ "ስድ" ቃላትን (በተለይም
ወሲብን በተመለከተ) ይጠቀማል ፤ ይህ የ"ተፈጥሮአዊነት" የአጻጻፍ ዘይቤ ሲሆን የተማረው
ከሚወደው ነገር ግን ልብወለዶቹን ለብዙ ዓመታት ሳያነብለት ከቆየው ፈረንሳዊው ኤሚል ዞላ
ነው። ስብሐት በሁለት ልብወለዶቹ (ሌቱም ዐይነጋልኝ እና ትኩሳት)ደስተኛ ነው ፤ ነገር ግን ርእስ
እንኳን ያልሰጣቸውን፣ ረቂቃቸው ጠፍተው የቀሩ ሌሎችሁለት ልብወለዶቹን እንደ ደካማ
ይቆጥራቸዋል።

መነን ላይ ለሁለት ዓመት ከሰራ በኋላ የንግድ ችሎታ ከነበረው ደረጄ ደሬሳ ጋር በመሆን የህዝብ
ግንኙነት ድርጅት አቋቋሙ። ደረጀ ከድርጅቱ የንግድ ስራ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን
ሲቆጣጠርስብሐት ደግሞ የድርጅቱን ሁለት የሕትመት ውጤቶች ይከታተላል። የመጀመሪያው
መጽሔት ከኢጣሊያዊው ኦስካር ራምፕተን የተረከቡትና በየሶስት ወሩ የሚታተመው
እንግሊዝኛው "ኢትዮጵያ ሚረር" ሲሆን ሁለተኛው በየወሩ የሚታተመው የአማርኛው መነን
ነበር። ደረጄ የሰለሞን ደሬሳ ታናሽ ወንድም ሲሆን ፣ በሐይለስላሴ ጊዜ የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት
ይልማ ደሬሳ ደግሞ አጎታቸው ናቸው። ስብሀት በዚህ ድርጅት ውስጥ ለስድስት ወይም ሰባት
ዓመታት (ቀኖችን በጉልህ አያስታውስም)ከሰራ በኋላ ድርጀቱበአብዮታዊው መንግሥት ትእዛዝ
ተዘጋ።3

የህዝብ ግንኙነት ድርጅቱን ከመሰረቱ ከሁለት ዓመት በኋላ፣ ስብሐት በደረጄ ደሬሳ በኩል ግብዣ
ላይ የተዋወቃትን የአቶ ይልማ ደሬሳን ልጅ፣ ሐና ይልማን አገባ። “በጣም ቆንጆ ነበረች” ይላል
ስብሐት “ገና እንዳየኋት ነው የወደድኳት”። ቤተሰቦቿ ስብሐትን ለመቀበል ብዙ ዓመታት
ወስዶባቸዋል። አማችነቱን በመጨረሻ ሲቀበሉ፣ስብሐትና ሐና ተጋቡ። ከሁለት ዓመት በኋላ
ብቸኛ ልጃቸውን እያሱን ወለዱ።

ከላይ የተጠቀሰው ድርጅት ለሚያሳትማቸው መጽሔቶች በሚጽፍበት ወቅት፣ አጫጭር


ልብወለዶችን በመፃፍ እጁን አሟሸ፤ ከዚያ በፊት አጭር ልብወለዶችን ቢጽፍም "ለራስ ብቻ
የሚሆኑ" ነበሩ። ስብሐት “የትውልዱ ቁጥር አንድ ምርጫ” ነበሩ የሚላቸውን "ስለ ግልጽ ወሲብ"
የፃፋቸውን ታሪኮች ማሳተም አልቻለም። የሱም ፍላጎት ለራሱ መጻፍ ስለነበር፣በጉዳዩላይ
የጻፋቸውን ስራዎች ለግሉ ብቻይዞአቆይቷቸዋል።“ ወጣትና ጤነኛ ከሆንክ፣ ሀገሩም ሰላም ከሆነ፣
ለሀያ ዓመት ልጅ ከወሲብ በላይ አስደሳች ነገር የለም" ይላል ስብሐት” ነገር ግን ለ50 ዓመት
270
ጥቋቁር አናብስት

ጎልማሳ ጉዳዩ የተለየ ነው፤ በግለሰቡና በማህበረሰቡ መካከል ያለው ግንኙነት ነው ይበልጥ
የሚያስጨንቅህ "ከዚህም ባሻገር ልጆች፣ሥነ ጥበብና ምንነቱ― "በተለይ በቃላት የሚገለጽ
ጥበብ" ያስደስቱታል። በሕይወቱ ውበትን ተመልክቷል ፤ “መኖር የሚያስደስት ነገር ነው” ይላል፤
“መኖር አይጠገብም ” ይላል ጨምሮ። "በጣም እድለኛ ነኝ" ብሎ ከማሰቡም በላይ “
በእግዚአብሔር ባምን ኖሮ ነገሮችን ሁሉ በምክንያት ሰራው ብዬ አስብ ነበር።”―ነገር ግን በተለይ
ዶስቶቭስኪን ካነበበ በኋላ በፈጣሪ እምነቱን እያጣ መጣ፤ የዶስቶቭስኪ በእግዚአብሔር የማያምኑ
ገፀ ባህሪያት ከሚያምኑት ይልቅ አሳማኝ ነበሩ። በሕይወቱ ወደኋላ ተመልክቶ፣ ሊለውጠው
የሚፈልገው አንዳች ነገር የለም። በወላጆቹ፣ በትምህርቱ፣ በስራው፣ በሀና፣ በሁሉም ደስተኛ ነው።
ሐና “ውበትን፣ ደግነትን፣ ሩህሩህነትን፣ መልካምነትን ” አጣምራ የያዘች ሴት ነበረች። “የሷን ያህል
ጥሩ ሰው መፈለግም እችላለሁ ብዬ አላስብም ” ካለ በኋላ “በሳል ያደረገችኝ እሷ ነበረች” ብሎ
ይጨምራል። ኢያሱ ገና የሶስት ዓመት ተኩል ልጅ እያለ፣ሐና እና ደረጄ ተከታትለው ሀገር ጥለው
በመሰደዳቸው እንኳን ምንም ቅያሜ የተሰማው አይመስልም። ቆየት ብሎ ስብሐት ከሌላ ሴት ጋር
ግንኙነት ጀመረ።

የህዝብ ግንኙነት ድርጅቱ ከመዘጋቱ በፊት፣ ታዋቂው ተዋናይ ደበበ እሸቱ ለሚያዘጋጀውና በየወሩ
ለሚታተመው ቁምነገር መጽሔት በትርፍ ሰአት እንዲያግዘው ሲጠይቀው ስብሐት ደስተኛ ነበር።
ስለዚህ የደረጄ እና የስብሐት ድርጅት ሲዘጋ፣ ምንም እንኳንየሙሉ ጊዜ ስራ ባይሆንም ከደበበ ጋር
ከአንድ ዓመት በላይ ሰራ። ደበበ እሸቱ ጋር መስራቱን ወዶት ነበር፤"ምርጥ አለቃና" ፤“የሚሰጡትን
ገንቢ አስተያየቶች ሁሉ የሚቀበል ነው”ይላል። ስብሀት በየወሩ ለቁምነገር መጽሔት የሚሆን አንድ
አጭር ልብወለድ እና "ሌሎች ነገሮችንም " ይጽፍ ነበር። በተለይ"ሞትን ፈርተው ዘወትር
ስለሚሸሹ ባላባት " የፃፈው አንድ ታሪክ በተከታታይ መቅረብ ጀመረ ፤ ነገር ግን ይህ አስቂኝ ታሪክ
ከመጠናቀቁ በፊት ሳንሱር ክፍሉ "የሠራተኛውን መደብ ልእልና የሚያሳይ ካልሆነ በቀር ቀልድ
ማቅረብ አይቻልም" በማለቱ ስብሐት ስራውን ለቀቀ። ነገር ግን በዚህ ቃለመጠይቅ ወቅት የዚህን
ባላባት ታሪክ (በግምት 150 ገጽ) ያህል በሚስጥር መፃፉን አጧጡፎታል። እኚህ ገፀ ባህሪ፣
በበአሉ ግርማ "ደራሲው" ልብወለድ ላይ አጋፋሪ እንደሻው ተብለው በመጽሀፉ ውስጥ
ለተጠቀሰው "ደራሲ" ምጥ ሆነው ሲያስጨንቁት እናነባለን።

ቁምነገርን ከለቀቀ በኋላ ስብሐት ለ11 ወራት ስራ አጥ ሆነ ። ከዚያ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውሉ


በየስድስት ወሩ የሚታደስ፣ የሁለት ዓመትጊዜያዊ ስራ አገኘ። እዚያም ከበአሉ ግርማ ጋርዳግም
ተገናኙ። ስብሐት የበአሉን የበኩር ልብወለድ "ከአድማስ ባሻገርን" አንብቦት ከመውደዱ የተነሳ
271
ጥቋቁር አናብስት

መጽሐፉ ላይ እያሰመረ ብዙ ማስታወሻዎችን በመውሰዱ ይህንኑ ለበአሉ አሳይቶት ለረጅም


ውይይት መነሻሆናቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቀን በቀን ውቤ በረሀ ከ"መዲና ግሮሰሪ" ፊትለፊት
መኪናቸውን አቁመው እየጠጡ ስለ "ሥነ ጽሑፍ እና ሕይወት " ይጨዋወቱ ጀመር። በአሉ
በአካባቢው ከነበሩ ለማኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበረው ሲሆን፣ ዘወትርም ሳንቲም ይሰጣቸዋል።
መሐመድ የተባለ አስተናጋጅ ዘወትር "በጣም እንደ ክቡር ሰው" ይንከባከበው ስለነበር፣በአሉም
አስተናጋጁንያቀርበዋል። በአሉና ስብሐት በጥልቅ ጨዋታ ተመስጠው እንኳን በአሉ ሁሌም
በንቃት አካባቢውን ይከታተላል ፤ በአንድ ጊዜ ሁለት ስራ ላይ የማተኮር ችሎታ ነበረው።“ በአሉ
"የቀይ ኮከብ ጥሪን" ሲጽፍ ረቂቁን ለስብሐት ያሥነብበዋል፤ስብሐት አንዳንዴ አስተያየት
ቢሰነዘርም ይበልጡኑ "ልብወለዱን በዝምታ ያጣጥም " ነበር። ስብሐትም በበኩሉ ለበአሉ ግርማ
የራሱን ልብወለዶች ረቂቅ ሰጠው፤ "በአሉ ልብወለዶቹን ቢወዳቸውም በፍጹም እዚህ ሊታተሙ
አይችሉም ይል ነበር።" ስብሐት ጨምሮም " የእብዱን ባላባት" ታሪክ ለበአሉ አነበበለት። እናም
አንድ ቀን በአሉ ስብሐትን እንደ ሞዴል አድርጎ የልብወለድ ታሪክ መፃፍ ይቻል እንደሆን
ቢጠይቅ፣ ስብሐት"በደስታ ተስማማ"።

ስብሐት እንደሚለው " በአሉ ሲጽፍ ፈጣን ነው ።""በቀይ ኮከብ ጥሪ" ልብወለዱ ውስጥ
እማእላፍ (ከሺህ አንድ ማለት ነው) የሚባል ገፀ ባህሪ አለ ፤ ይኼም ገፀ ባህሪ ከስብሐት
ከራሱየተቀዳ እንደሆነነግሮኛል። በአሉ ለስብሐት ይህንን ገፀ ባህሪ በተመለከተ የፃፈውን ካነበበለት
በኋላ"ገፀባህሪው ሁለቱንም እያዝናናቸው ይስቁ ነበር።" ከዚያ በኋላ በአሉ ስለ ደራሲ ሕይወት
የሚያወራ ሙሉ መጽሀፍ ለመፃፍ አስቦ "ደራሲውን" ፃፈ። “በአሉ ሁሌም በሕይወት ያሉ ሰዎችን
ለገፀ ባህሪነት ይጠቀማል፤ ስለዚህ በቅርቡ የነበርኩትን እኔን ለልብወለዱ መጠቀሙ ተፈጥሮአዊና
የማያስገርም ነው።”

ከዚህ በኋላ ስብሐት በኢትዮጵያ መጽሐፍት ድርጅት ስራ አገኘ፤ ቢሆንም ስራው የጽሑፍ ረቂቅ
አርታኢነት በመሆኑ፣ ስራውን እንደጠበቀው አስደሳች ሆኖ አላገኘውም። ስለዚህ ከአንድ ዓመት
ትንሽ በለጥ ከሚል ጊዜ በኋላ የቱሪዝም ኮሚሽንን ተቀላቅሎ “የህትመት ውጤቶቻቸውን
እናአጠቃላይ የቱሪዝም ማስታወቂያዎቻቸው” ላይ መስራቱን ተያያዘ። ከአንድ ዓመት በኋላ የካርል
ማርክስን "ዳስ ካፒታል" ወደ አማርኛ ከሚተረጉመው ቡድን ጋር እንዲሰራ ተመርጦ ለአንድ
ዓመት አካባቢ ሰራ። በ1985 አጋማሽ ላይ ወደ ኩራዝ አሳታሚዎች ድርጅት ተዘዋውሮ እኔ
እስካነጋገርኩት ጊዜ ድረስ አርታኢ ሆኖ ሰርቷል ።

272
ጥቋቁር አናብስት

ስብሐት ለአማርኛውም፣ ለእንግሊዝኛውም “የካቲት” እስከ 1985 መጨረሻ ድረስ ይጽፍ ነበር።
በእንግሊዝኛው እትም ላይ "የደጋ ጨዋታዎች" የሚል ቋሚ አምድ ነበረው። እነኚህ ጨዋታዎች፣
የኢትዮጵያ ተረቶችን ስለሚያካትቱ፣ “ሥነ ቃላችን ደግሞ ከሥነ ጽሑፋችን ይበልጥ ስለሚጥም”
መጣጥፎቹን ማራኪ ሆነው ላገኛቸው እንደምችል ነገረኝ።

ስብሐት "ከአብዮቱ በኋላ ሕይወት ቢከብድም፤እንደሁልጊዜውም ተወዳጅ እንደነበረ" ይሰማዋል።


ግላዊነት ስለሚያጠቃው፣ ርእዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካ አይጥመውም። "የአውሮፓ ስልጣኔ"
በቴክኖሎጂ ጫፍ ላይ ደርሷል፤"ህንዳውያንም በመንፈስ በልጽገዋል"፤ "ስካንዴኔቪያውያንም
ዜጎቻቸው ከሌላው የበለጠ ነፃነትን ስለተጎናጸፉ በማህበራዊ ምህንድስና ተራቀዋል"፤ ነገር ግን
ከልምዱ እንደተማረው "ሁሉም ነገር ዞሮ ዞሮ ወደ ሰው ልጅ ይመጣል፤የነገሮች ሁሉ መለኪያ
የሰው ልጅ ነው" እናም"በዚያ መለኪያ መሰረት ማንም ሀገር ከሌላው አይበልጥም"፤"አቢሲኒያም
ከሌላ ከማንኛውም ሀገር ጋር መወዳደር ትችላለች"።

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሀገሩንናባህሉን ይወዳል። ለማግባት ወይ ለመውለድ እቅድ


አልነበረውም። "ከቆንጆ ሴቶች ጋር ፍቅር መስራት ያስደስተዋል ፤ቆንጆ ሴቶች የተፈጠሩትም
ለፍቅር ነው" ነገር ግን ከሐና ጋር ተዋወቁ ፤ እያሱም ተወለደ ፤ ይህም ልጅ ሕይወቱን ሞላው።
ሐና ከሄደች በኋላ ደግሞ፣ "ከሌላ ሴት ጋር ተዋወቀ" እናም "አብረው መኖር ጀመሩ "―"
በአጋጣሚ በሕይወቴ እንደተከሰተች ሁሉ በአጋጣሚ በሕይወቷ ተከሰትኩ"። በዚህ ቃለ መጠይቅ
ወቅት ስብሐት ከሁለተኛዋሴት ጋር ሁለት ሴት ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ ወልደው ነበር፤ ነገር ግን
ወንድ ልጁ ገና በአስር ወሩ የማጅራት ገትር በሽታ አጠቃውና እጅግ በሽተኛ ሆነ። የመጀመሪያ ሴት
ልጁን እንደ ወንዱ የበኩር ልጁ እንደሚወዳት ይናገራል። ሁለተኛዋን ሴት ልጁ የአስመራ
ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የነበረው ታናሽ ወንድሙ ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር እና
እንግሊዛዊት ሚስቱ ልጅ ስላልነበራቸው፣ ለነሱ ተሰጠች።

ቃለ መጠይቅ ባደረግኩለት ወቅት ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በሕይወቱ ደስተኛ፣ አብዝቶ


የሚያነብ ("ከጸሐፊ ይልቅ አንባቢ ነኝ")፤ ምንም ባይታተሙም እንኳን አልፎ አልፎ የሚጽፍ ሰው
ነበር።ካነበባቸው ደራሲዎች ሁሉ ፕሮስትን ያስበልጣል፤ከሐገር ውስጥ ደግሞ ብዙም
ለማይታወቀው ፀሐፌ–ተውኔት ስዩም ተፈራ ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል።ስዩም ከፃፋቸው
ተውኔቶች መሐል ስለ የኔቢጤዎች የተፃፈ "ድሆች" እና በብሔራዊ ቲያትር ለአንድ ዓመት ብቻ

273
ጥቋቁር አናብስት

ታይቶ የታገደው "ሐሙስ" ይገኙበታል። ስዩም ተፈራን "ባለተሰጥኦ/talented/ታላቁ


ኢትዮጵያዊ ደራሲ" ነው ይለዋል ስብሐት።

****

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን ከመልቀቄ በፊት፣ ስብሐትን ለጥቂት ጊዜያት በተደጋጋሚ አግኝቼዋለሁ።
ሁሌም በእጁ መጽሐፍ ይዞ የሚታየው ስብሐት ፈገግታ ከፊቱ አይለየውም። በኢትዮጵያ ሊታተም
የሚችል መጽሐፍ ቢጽፍ የሚል ምኞት ነበረኝ ፤ በ1981 ጥቅምት የመጀመሪያው መጽሐፉ
ታትሞ በአዲስአበባ የመጽሐፍት መደብሮች ለገበያ በቃ። ይህም መጽሀፉ"አምስት ስድስት ሰባት"
የተሰኘው የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ ነበር።

የተርጓሚ ማስታወሻ

ስብሐትለአብ ገብረእግዚአብሔር(1928-2004) በወቅቱ ከታተመለት አጭር ልብወለድ ስብስቡ


(አምስት ስድስት ሰባት)ውጭ እንደ ትኩሳት፡(ቴዎድሮስ፤ታከለ ታገለ በመጽሔት የወጡ
መጣጥፎችን ጨምሮ በደቦ፤በእፍታ፡ጭጋግና ጠል ስብስብ ስራዎች መድብላት ውስጥ ያሉ
አጫጭር ድርሰቶች) ሌቱም አይነጋልኝ፤ሰባተኛው መልዐክ፤እግረመንገድ፤እነሆ ጀግና፤ዛዚ፤የፍቅር
ሻማዎች፤ ቦርጨቅ ያሉ ስራዎች በተዳጋጋሚ በአርትኦት ለዝበውም ሆነ እርቃናቸውን (እንደወረዱ)
ህዝብ ጋር ደርሰዋል፡፡

ማስታወሻዎች

1) ሐገሪቱን በ1989 ለቅቄ የሄድኩት የነበረኝ ሁለተኛው ረዥም ቆይታ ሲያበቃ ነበር። አሁን
የቆየሁት ለ4 ዓመት ሲሆን ይህ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የነበረኝን ቆይታ ወደ 14 ዓመት
ያደርሰዋል። በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ላይ ፍላጎት ማሳደር የጀመርኩት ከ20 ዓመት በፊት ሀገሪቷ
ውስጥ በ1965 ታህሳስ ላይ ከደረስኩኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።

2) “ምቱ” ለማለት ፈልጎ ሳይሆን አይቀርም።

3) ደረጀ ደሬሳ አብዮቱ ፈንድቶ በኋላ ሁለት ዓመት ሳይሞላው ሀገር ጥሎ ኮብልሏል።

274
ጥቋቁር አናብስት

አሰፋገብረማርያም ተሰማ
የአብዮታዊት ኢትዮጵያ የህዝብ መዝሙር ደራሲ
አሰፋ ገብረማርያም የሚባሉ ሁለት ደራሲዎች አሉ ፤ ስለዚህ ራሱን አሰፋ
ገ/ማ/ተ ብሎ የሚጠራው ደራሲ፣ ለመለየት በስሙ ላይ የአያቱን ስም ተሰማን
ጨምሯል። ከቃለመጠይቃችን ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ በባህል ሚኒስቴር
ውስጥ ነበር የሚሰራው፤ በ1980 ቃለምልልስ ከማድረጋችን በፊት
ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁትም እዚያ ነው። በጊዜው በተረት ጥናት ላይ ተጠምዶ
ነበር። በዚህ መስክ ላዘጋጃቸው ብዙ ስብስቦች የተጠናቀረ ወፍራም ጥራዝም
ደርሶኛል።የዚያኑ ያህል ስለ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ የማወቅ ፍላጎት
ነበረኝ።ይህ አካዳሚ በኃይለሥላሴ ዘመን በሌላ ቅርጽ የነበረ ቢሆንም ብዙም ተግባር
አላከናወነም። አሁን ግን ወደ ስራ የገቡ ይመስላሉ፤አሰፋም በአካዳሚው ውስጥ ቁልፍ ሰው ነበር።
ይህ አካዳሚ የአማርኛ ቋንቋ ፊደላት ተመሳሳይ አፃፃፍ እንዲኖራቸው በመስራት በዛውም
ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆኑየሚያስችል ስራ ሰርቷል1፤ በ1980 የሳይንሳዊ መዛግብተ ቃላትን
በተከታታይ አሳትመዋል፣ በተመሳሳይ ዓመት የግዕዝ ቅኔ ስብስብ፣ ከነአማርኛ ፍቺያቸው፣
ከምስጢርና ትርጉማቸው ጋር እንዲሁም ከቅኔው ዳራ ጋር አብሮ ታትሟል።መንግስቱ ለማ ለቅኔ
መጽሐፋቸው ብዙ ዓመት የፈጀ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፤መጽሐፉም የወጣውበ1980 በጠና
ታሞ ሆስፒታል ከመግባቱ ጥቂት ጊዜ በፊት ነው።
***

አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ በመስከረም 16 ቀን 1928ዓም ተወለደ። ቀኑ ደመራ የሚበራበት


እለት፣ የመስቀል ዋዜማ ነው። የትውልድ ቦታው ዘበኛ ሰፈር ሲባል ቀጨኔ ጫፍ አካባቢ፣አዲስ
አበባ ውስጥ ይገኛል። አባቱ ገብረማርያም ተሰማ የመጡት ከወሎ ሲሆን መርካቶ አካባቢ የሚሰሩ
ድሀ ነጋዴ እና ልብስ ሰፊ ናቸው። እናቱ ተዋበች ብርቄ የሸዋ ጅሩዬ ናቸው። አሰፋ ወላጆቹ
ከመጡበት አካባቢ ካሉ ዘመዶቹ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። አባቱ አሰፋ ገና የስምንት ዓመት
ልጅ እያለ ሞቱ። እናቱ እንደ ብዙ አማራዎች፣ አንድ ልጅ በእንጀራ አባት እጅ ማደግ የለበትም
ብላበጥብቅ ታምናለች ፤ ስለዚህ ዳግመኛ አላገባችም። አንድ ታላቅ ወንድሙ ገና በልጅነቱ
ቢሞትም፣ ወላጆቹ ሰለሱ ብዙም አያወሩም። ስለዚህ ሁለተኛ ልጅ የነበረው አሰፋ ታላቅ ሆኖ
አደገ። ተከትሎ ሌላው ወንድሙ ሞገስየተወለደ ቢሆንም አሰፋ ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ
በነበረበት ወቅት ሞቷል። የመጨረሻዋ ልጅ የውብዳር የተባለች ሴት ናት።

አሰፋ ገና ትንሽ ልጅ እያለ፣ ቤተሰቦቹ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን እና ራስ ደስታ ሆስፒታል


አቅራቢያ ይኖሩ ነበር። ይሁን እንጂ በቋሚነት አንድ ቦታ አልኖሩም። በተለያየ ጊዜእዚያው አካባቢ
የተለያዩቦታዎች ላይ ኖረዋል።ለምሳሌ ያህል፣ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወይም ካቴድራል፣
275
ጥቋቁር አናብስት

ቀጨኔ የሚገኘው የመድሀኒአለም ቤተክርስቲያን እና የካቶሊክ ካቴድራል አካባቢ ይገኙበታል።


አሰፋ ገና በልጅነቱ ስለ አንድ ምሁር ይሰማ ነበር። ይህ ምሁር በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰራው
ታዋቂው የታሪክ አጥኚ አቶ አርአያ ወሮታው ነው። በኋለኛው ሕይወቱ አሰፋ አቶ አርአያያን
በቅርብ የማወቅ እድል ያገኛል።3አሰፋ በዙሪያው ያሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚያሰሙት ቅዳሴ
እና በቅርቡ ያለው የመስጊድ ማማ ላይ ወጥተው የሚያሰሙትየአዛን ዜማስሜቱን
ያነሳሱት/ይነሽጡት/ይኮረኩሩት እንደነበር ይናገራል። በአራት ወይም አምስት ዓመቱ
የቤተክርስቲያን ትምህርት ጀመረ። በሁለት ዓመት ቆይታው፣ማንበብና ዳዊት መድገም፣“እንደ
በቀቀን ማነብነብ እንጂ መረዳት አይደለም”፣ ቻለ።ይሁን እንጂ እየተማረ በጎን እናቱን በስራ
መርዳት ነበረበት። በተለይ አባቱ ከሞቱ በኋላ በመላላክ እና በሌላም ስራ ስለሚያግዝ ለጨዋታ
የሚሆን ጊዜ አልነበረውም። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እናቱን መርዳትና መንከባከብ የሞራል
ግዴታው መሆኑን ያምን ነበር፤እናቱ ከቃለምልልሳችን ትንሽ ቀደም ብሎ አርፈዋል። አሰፋ በሁለት
ምክንያቶች ትምህርት ቤቱን አልወደደውም።አንደኛ ተማሪዎቹ የአስተማሪውን እግር እንዲስሙ
ይገደዱ ነበር። ይህ ሳይበቃ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ስለሚገረፉ ለዚህ ዐይነት ትምህርት ምንም
ዐይነት ፍላጎት ሊኖረው አልቻለም።

በቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ሁለት ዓመት ከቆየ በኋላ፣ የስዊድን ሚስዮን ትምህርት ቤት ገባ።
የትምህርት ቤቱ ስም ቢ.ቪ. ይባላል( ይህም በሰዊድንኛ የመጽሀፍ ቅዱስ ታማኝ ጓደኞች የሚለው
በአጭሩ ሲፃፍ ነው)። ትምህርት ቤቱ ራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ከተከፈተ ብዙም አልቆየም።
ከአስተማሪዎቹ መሀል አንዱ፣ የደራሲ በእምነት ገብረአምላክ አባት የሆኑት፣ ቄስ ገብረአምላክ
ሩፋኤል ነበሩ።4
አሰፋ በዚህ የስዊድን ቢ ቪ ሚስዮን ትምህርት ቤት ለሁለት ዓመታት ቆየ። አብዛኛዎቹ መምህራን
ወጣት ስዊድናውያን ሲሆኑ በትንሿ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ፒያኖ እየተጫወቱ ይዘምሩላቸው
ነበር።አስተማሪዎቹ ጥሩናቸው፤ ነገር ግን በንጽህና ጉዳይ ላይ ጥብቅ ነበሩ። ይሁን እንጂ አሰፋ
በድህነቱ ምክንያት ንጽህናውን ሁሌ ለመጠበቅ አልቻለም።ስለዚህ ከሁለት ዓመት በኋላ
የመንግስት ትምህርት ቤት ገባ። የገባበት ትምህርት ቤት የአርበኞች ትምህርት ቤት ሲባል ሰፈሩ
ውስጥ የሚያውቃቸውወንድ ልጆች ሁሉ የሚማሩት እዚህ ነው።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን
በዚያ ጨረሰ።እዚያ ተማሪ እያለ በማዘጋጃቤት የቲያትር አዳራሽ ተውኔቶችን ይመለከት ነበር ፤
ቲያትር ቤቱ ያኔ ይገኝ የነበረው አሁን የዳግማዊ ምኒልክ ፈረሰኛ ሐውልት አጠገብ የፍርድ ቤቱ
ህንፃ ላይ ነው። ዘወትር እሁድም ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ይሄዳል፤ ልጆች በነፃ እንዲገቡና ማእዘን
ላይ ወይም ግድግዳውን ተደግፈው እንዲታደሙ ይፈቀድላቸው ነበር። ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት

ተውኔት ከመቅረቡ በፊት፣ ከመስራቾቹ አንዱ የሆኑት መኮንን ሀብተወልድ ንግግር ያደርጋሉ።
አሰፋ አንዳንዶቹን ተውኔቶች በደንብ ቢያስታውሳቸውም፣ ርዕሳቸውን ወይም ደራሲያቸውን
276
ጥቋቁር አናብስት

ረስቶአቸዋል። ብዙዎቹ ተውኔቶች ቧልታይ ናቸው ፤ በብዛት የባልና ሚስትን ግጭት የሚመለከቱ
ናቸው። የአሰፋ እናት ደሀ ናቸው። ቢሆንም ጠላ ጠምቀው፣ ልብስ ሸምነው በሚያገኙት ገንዘብ
ልጆቻቸውን ያስተምራሉ። በተለይ ሴት ልጃቸውን በደንብ ይንከባከቧት ነበር።
ከስዊድን ትምህርት ቤት ከለቀቀ በኋላ፣አሰፋ ሠፈራቸው ከሚኖሩ አንድ አሮጊት ጋር መኖር
ጀመረ። አሮጊቷ የአቶ ድንቁ ልጅ ናቸው (አቶ ድንቁ ከድሬዳዋ የመጡ በደንብ የሚታወቁ ካቶሊክ
ናቸው።) አሮጊቷ ለአሰፋ ደግ ሴት ነበሩ። አሰፋ በትምህርቱ ጎበዝ ነበር። ከስድስተኛ ክፍል በኋላ
አባ ዲና ኮሌጅ መግባትፈለገ። አባ ዲና የፖሊስ መኮንኖች ማሰልጠኛ ነው። ስልጠናው ሁለት
ወይም ሶስት ዓመት ይወስዳል። አሰፋን ያማለለው 150 ብር (75$) ወርሃዊ ክፍያው ነበር።
አብረውት የተማሩት አብዛኛዎቹ የክፍል ጓደኞቹ ኮሌጁን ተቀላቀሉ። በአርበኞች ትምህርት ቤት
ያሉ መምህራኖችም የቃል ፈተናውን እንዲያልፉ ይረዷቸው ነበር። እንዲሸመድዱ ካደረጓቸው
መልሶች ውስጥ "ሀገሬንና ንጉሴን መጠበቅ እፈልጋለሁ፣ወንጀልን መዋጋት እፈልጋለሁ"
የመሳሰሉት ይገኙበታል። አሰፋ የመግቢያ እና የቃል ፈተናውን ቢያልፍም የሰውነት አቋምህ ጥሩ
አይደለም ብለው መለሱት።( እኔ ሳገኘው ግን በተቃራኒው ጥሩ ቁመና ነበረው)። ከሶስት ዓመት
በኋላ እንዲያመለክትና ያለምንም ፈተና እንደሚቀበሉት ተነግሮት ነበር። ይሁን እንጂ ተመልሶ
ወደዚያ አልሄደም። ይልቁንም ጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ገባ። ዊንጌት ብዙዎች ለመግባት
የሚንሰፈሰፉለት “የልሂቃን ትምህርት ቤት” ነው። ትምህርት ቤቱ ከሰባተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ
ክፍል የሚያስተምር ነፃ የአዳሪ ትምህርት ቤት ነው(አሰፋ እዚህ የተማረው ለአምስት ዓመታት
ከመስከረም 1943 እስከ ሐምሌ 1948 ነው)። እንደዚያ ከሆነ አንድ ክፍል ሳይዘልል አልቀረም።
በቆይታው ጎበዝ የሚባል ተማሪ ነበር፤“በክፍሉ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ካመጡት ተማሪዎች
መሀል አንዱ” ሲሆን ትምህርት ቤቱ “በጥብቅ የእንግሊዝ ስርአት የተቃኘ” ነበር። ስርአቱ አሰፋ
ላይ ተጽዕኖ አድርጎበታል―ተጽእኖው“ድብልቅ ጥቅም ነበረው”ይላል። “ሥነ ስርአቱ ለተማሪዎች
ጠቃሚ ነበር”፤በጠዋት እንዲነሱ፣እንዲተጣጠቡ፣ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም ራሳቸውን
እንዲችሉ ያደርጋል ይላል። አስተማሪዎቹን በደንብ ያስታውሳል ፤ ይሁን እንጂ በሥነ ጽሑፋዊ
ሰውነቱ ላይ የተለየ ተጽዕኖ ያሳረፈበት የለም። የመጀመሪያ ርዕሰ መምህሩ ሚስተር ሄሪንግ ይባላሉ
፤"ጥብቅ እና ወግ አጥባቂ" ነበሩ። በቃለምልልሱ ወቅት የብሪቲሽ ካውንስል ሀላፊ የነበረው
ሚስተር ሀድሰን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሥነ ጽሑፍ አስተማሪ የነበረ ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርት
ቤቱ ውስጥ የሚገኘውን የተደራጀ ቤተ መጽሀፍት እንዲጠቀሙ ያበረታታ ነበር። በጊዜው ዊንጌት
ውስጥ “ልብወለድ ማንበብ ፋሽን ስለነበር” አሰፋም “እነ ዲክንስን፣አሌክሳንደር ዱማን” አነበበ።
የሚስተር ሀድሰን ባለቤት ታሪክ አስተማሪ ነበረች። ጂም ማርሻል (አሁን የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ
መምህር) ደግሞ ሒሳብ ያስተምር ነበር። ሚስተር ሮበርትስ(በኋላ የሚንሊክ ትምህርት ቤት
277
ጥቋቁር አናብስት

ዳይሬክተር)የጂኦግራፊ መምህር ነበር(በቃለምልልሱ ወቅት የብሪታኒያውያን–ኢትዮጵያውያን


ወዳጅነት ማህበር ፕሬዚዳንት ነበር)።
ከመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች ወደ ዊንጌት ስለሚመጡ አሰፋ “ሰፋ ያለ ትውውቅ” መፍጠር ቻለ።
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቲያትር (አሁን ብሔራዊ ቲያትር) ያኔ አልተከፈተም ፤ በጊዜው የዊንጌት
ትምህርት ቤት የቲያትር አዳራሽ እና መድረክ ምናልባትም በሐገሪቱውስጥ ከሚገኙት ሁሉ ምርጡ
ነበር ይላል አሰፋ። ለገና በእድሜ ከፍ ያሉት ተማሪዎች በጂም ማርሻል እየተመሩ፣ አዲሳባ
ከሚገኘው የእንግሊዝ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መምህራን ጋር በመተባበር፣ ተውኔት ያቀርቡ
ነበር።5 በየዓመቱ የትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ደግሞ፣ ተመራቂ ተማሪዎች ተውኔት ያሳያሉ።
በትምህርት ቤቱ ውስጥ ደግሞ የቲያትር ማህበር ነበር ፤ አሰፋ ለሁለት ዓመት (11ደኛ እና 12ተኛ
ክፍል ተማሪ እያለ) የዚህ ማህበር ፕሬዚዳንት ሆኗል። በትምህርት ቤቱ ውስጥ በጣም ጎበዝ ጎበዝ
ተማሪዎች ነበሩ ይላል አሰፋ፤ ለምሳሌ፣ በቃለምልልሱ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት
ብርሀኑ ባየህ፣ እንዲሁም በዚያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምክትል ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጥበቡ
ይገኙበታል (በእርግጥ ከአሰፋ ጋር በአንድ ክፍል አልነበሩም)። በትምህርት ቤቱ ውስጥ በየዓመቱ
አንዴ የሚታተም መጽሔት ሲኖር፤ አሰፋም ለዚህ መጽሔት ግጥሞች ያበረክት ነበር። አሰፋ ሒሳብ
ላይ ጎበዝ ስለሆ መሐንዲስ ለመሆን ይመኝ ነበር (ምህንድስና የአብዛኛዎቹ ባለተሰጥኦ ኢትዮጵያዊ
ተማሪዎች ምኞት ነበር) ፤ ነገር ግን “ሥነ ጽሑፋዊ ዝንባሌዎችም” ነበሩት።
አስራ አንደኛ ክፍል እያሉ ሼክስፒርን ማንበብ ጀመሩ።እዚህ ደረጃላይ እንዲያነቧቸው
ከተመደቡላቸው መጻሕፍት አንዱ "ጁልየስ ቄሳር" ነበር።አሰፋ ተውኔቱን ስለወደደው ወደ
አማርኛሊተረጉመው ጀመረ፤ ለአንድ ዓመት ተኩልም በዚሁ ተግባር ተጠመደ። አስራ ሁለተኛ
ክፍል ጨርሶ ሲመረቅ ተማሪዎቹ የሚጫወቱት ተውኔት ይሆናል ብሎ ሳያስብ አልቀረም። በእጅ
የተፃፈ ቢሆንም፣አስራሁለተኛ ክፍልን ሲጨርሱ ተውኔቱ ደርሶ ነበር። ነገርግን ልክ ከዚያ በፊት
በሼክስፒር ተጽፎ በከበደ ሚካኤል የተመለሰው ታዋቂ የትርጉም ስራ"ሮሚዮ እና ጁልየት" ወጣ።
ተውኔቱ ወዲያውኑ ዝነኛ ስለሆነ፣ ክፍሉ በሙሉ የዓመቱ የምረቃ በዓል ተውኔት እንዲሆን በአንድ
ድምጽ መረጠው። ስለዚህ የአሰፋ ተውኔት (የጁሊየስ ቄሳር ትርጉም) ለመድረክ ሳይበቃ ቀረ።
የተሰማው ስሜት ግን በከበደ ሚካኤል ቂም ከመያዝ በጣም የራቀ ነው ፤ እንደውም ከበደ
ሚካኤል ተጽእኖ አሳድረውበታል―በተለይ "ሮሚዮ እና ዡልየት በአማርኛ እጅግ ውብ ነው”
ይላል። የከበደ ሚካኤልን "ታሪክ እና ምሳሌ" አንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለ አንብቦታል ፤ በጊዜው
መማሪያ መጽሐፍ ነበር። የከበደ ሚካኤልን መፃሕፍት ከዚያ በኋላም ቢሆን እንደወጡ
እየተከታተለ ማንበቡን ቀጥሏል ፤ በተለይ ባህል ሚኒስቴር እያለ "ጃፓን እንደምን ሰለጠነች?"

278
ጥቋቁር አናብስት

የመሳሰሉ ኢልብወለድ ሥራዎቻቸውን ጨምሮ አንብቧል።ነገር ግን ኋላ የወጡትን "ሀይማኖታዊ


ተውኔታቸውን" አላነበበም። እንደውም የከበደ ሚካኤልን ግጥም በቃሉ አጥንቶ ይወጣቸው ነበር።
አሰፋ ሌሎች ብዙ ኢትዮጵያዊ ደራሲያንን አላነበበም፤ይሁን እንጂ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ
የግርማቸው ተክለሐዋርያትን "አርአያ" በግል ዝንባሌው የተነሳ አንብቧል―መጽሀፉ በዊንጌት
የትምህርት ስርአት ውስጥ አልተካተተም ነበር።

አሰፋ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርቱን ሲጨርስ ለሁለት ፈተናዎች ተቀመጠ ፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ
መልቀቂያ ፈተና እና የብሪቲሽ GCE ፈተና ተፈትኖ በሰባት ትምህርቶች፡በእንግሊዝኛ፣ በሥነ
ጽሑፍ፣ በሂሳብ፣ በአማርኛ፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ እና በጠቅላላ ሳይንስ አልፏል።
አሰፋ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ፣ ደሀ እናቱን መርዳት ስለነበረበት ወዲያውኑ ወደ
ዩኒቨርስቲ አልገባም። ዊንጌት እያለ ቤተሰቡ ውስጥ የተከሰተ አንድ ነገር ጥቁር ጠባሳ ጥሎበት
አልፏል፦ትንሽ ወንድሙ ሞገስ ይታመምና፣ምናልባትም በድህነታቸው የተነሳ ሆስፒታል ሊወስዱት
ስላልቻሉ፣ ሞተ። ዝነኛው የራስ ደስታ ሆስፒታል በአቅራቢያቸው መኖሩ ሁኔታውን የበለጠ
መራር ያደርገዋል። በነዚህ ዓመታት አሰፋ ስለ ማህበራዊ ችግሮች ያለው ግንዛቤ እየጨመረ መጣ ፤
ስለዚህ አሰፋ ስለ ሶሻሊዝም “በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የተቀመጠ እውቀት ሳይኖረው”፣ ከራሱ ሁኔታ
በመነሳት ሶሻሊስታዊ ዝንባሌ እያሳደረ፣ ብዙዎችን ለአላስፈላጊ ስቃይና ለድህነት እየዳረገ ስላለው
የፊውዳል ስርአት እየተረዳ ነበር።
በ1949ዓም በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በትምህርት ስርአት ክፍል ውስጥ መስራት ጀመረ።
በእዚያ በጊዜው ተራማጅ ዲሞክራቶች ብሎ የሚጠራቸውን ብዙ ሰዎች አገኘ። ለይቶ ከጠቀሳቸው
መሐል የትምህርት ስርአት ክፍል ዋና ሐላፊና የአሰፋ አለቃ 6የነበረው ሚሊዮን ነቅንቅ፣ ከሲዳሞ
ድረስ እነ ሚሊዮንን ለመጠየቅ የሚመጣው የ1953ቱ የመፈንቅለ መንግስት የርዕዮተ አለም መሪ
የነበረው ግርማሜ ነዋይ ይገኙበታል። በወቅቱ ከበደ ሚካኤል የትምህርት ሚኒስትር ዋና
ዳይሬክተር እና የሚሊዮን አለቃ ሲሆኑ፣ አሰፋ “በቅርብም ባይሆን” ያውቃቸው ነበር። ሚሊዮን
ነቅንቅ ራሱ ገጣሚ ነበር፤እንደውም "ሮሚዮ እና ዡልየት"ን ከከበደ ሚካኤል በፊት "ካለቁ ታረቁ"
በሚል ርዕስ ተርጉሟል። አሰፋንም ያበረታታው ነበር ፤ በዚህ መሰረት የአሰፋን የ"ጁሊየስ ቄሳር"
ትርጉም ስህተቱን አርሞ ለማተሚያ ቤት ዝግጁ አድርጎለታል።7 ሚሊዮን አማርኛን በመላው
ኢትዮጵያ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመማሪያ ቋንቋ እንዲሆን በማድረግ
የመጀመሪያው የትምህርት ስርአት ሀላፊ ነበር(ከዛ በፊት አውሮፓዊ ቋንቋዎች በተለይ እንግሊዝኛ

ቀደም ብሎ ደግሞ ፈረንሳይኛ ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር)አሰፋ በዚህ ወቅት የተዋወቃቸው


ዲሞክራቶች ተጽእኖ እየፈጠሩበትእንዲሁም፣ለወደፊቱ ሙያዊ ሕይወቱ ሁኔታዎችን እያመቻቸ
279
ጥቋቁር አናብስት

ነበር።የብሪታኒያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው አንድ ውይም ሁለትየA


ደረጃፈተናዎችን ማለፍ ነው። በዝነኛው የለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ
ኢኮኖሚክስ ወይም ስታትስቲክስ ማጥናት ይፈልጋል። ስለዚህ በሒሳብ እና ስታትስቲክስ ጎበዝ
ስለሆነ፣ ሒሳብ እና ኢኮኖሚክስ በA ደረጃ፣ በርቀት ትምህርት መውሰድ ጀመረ።

ጊዜው ኢትዮጵያ በታላቅ ተስፋ የተሞላችበት ጊዜ ነበር። ንጉሱ የብር ኢዮቤልዩ በአላቸውን
በ1948 ሲያከብሩ አዲስ ህገ መንግስት አስረቅቀዋል(የ1923 ህገ መንግስት ማሻሻያ ተደርጎበት)።
ይህ አዲስ ህገ መንግስት የፕሬስ ነፃነት፣ የንግግር ነፃነት እና ሌሎችም ደስ ደስ የሚሉ ሀሳቦችን
ይዟል። “ሁሉም ሰው የሚያወራው ስለዚህ ነበር”፤እነሆ በመጨረሻ “ያለ ሳንሱር” መናገር፣ መፃፍ
እና ማተም ሊችሉ ነው። ስለዚህ አሰፋ "የጁልየስ ቄሳር" ትርጉሙን ለህትመት አዘጋጀና ወደ ተስፋ
ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት ይዞት ሄደ።ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት በግእዝና በአማርኛ
የሐይማኖት መጽሀፍትን፣ የፀሎት መጽሐፍትን፣የቅዱሳን ገድሎችን፣የመሳሰሉትን እያተመ እስካሁን
ያለ ማተሚያ ቤት ነው።የግእዝ እና የአማርኛ ምንባቦችን በትይዩ የሚያቀርቡበት መንገድ በተለይ
ለግእዝ ተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው። በጊዜው በኢትዮጵያ የሚታተሙ መጽሀፍት በፊት ገፃቸው
የንጉሱን ምስል መያዛቸው ደንብ ነበር።አሰፋ ግን ከዚህ ደንብ ወጥቶ፣ የንጉሱን ተወዳጅ ልጅ
የሀረሩን መስፍን የልኡል መኮንንን ምስል በምትኩ አስገባ። ልዑሉም የሞቱት በዚሁ ዓመት ነበር።
አሰፋ መጽሀፉ በሙሉ ከመታተሙ በፊት ነበርይህን ያደረገው።በተጨማሪ መኳንንቱ ላይ በምፀት
የሚያፌዝ ግጥም ጣል አድርጎ ነበር ፤ ነገር ግን ድብቅ ስለሆነ ማንም አይደርስበትም። (አሁን ላይ
ይህንን ድርጊቱን ሲያስበው የሞኝ ስራ እንደነበር ተረድቷል)።አሳታሚዎች ጋር እየሄደ
የተስተካከሉትን ቅጂዎች ያነብ ነበር።የመጨረሻው ትእይንት ሲታተም ሳንሱር አድራጊዎቹ
እየፈለጉት እንደነበርሰማ። የንጉሱን ፎቶ ሳያስገባ መጽሀፍ ለማተምመሞከር “ከደንብ ውጪ”
መሆኑን ሳንሱረኞቹ ነገሩት። (በየቦታው “ሰላዮችና”ጆሮ ጠቢዎች ስለነበሯቸው፣ በማተሚያ ቤት
ውስጥ የሚሰራ አንድ ሰው “የንጉሱ ፎቶ መቅረቱን” ነግሯቸው መሆን አለበት)። ኢትዮጵያ ግዛት
ስለሆነች፣ንጉሠ ነገሥቷ በዚህ ዐይነት መንገድ"መሞት" እንደሌለበት ተነገረው። ስለዚህ መጽሀፉ
ከታተመ በኋላ ሳይከፋፈል እንዲወረስ ተደረገ። አሰፋ ጥቂት ቅጂዎች ብቻ ደርሰውታል። በጊዜው
ደራሲዎች ለአታሚዎች በቅድሚያ መክፈላቸው እንደ ህግ ነበር። ነገር ግን የአሰፋ ጓደኞች በጊዜው
ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ተማሪ የነበረውን የአታሚውን ልጅ ያውቁት ነበር። አሰፋ እና ልጁ ከተዋወቁ
በኋላ በሱ በኩል ለህትመት በቅድሚያ ሳይከፍል መጽሀፉ መታተም ቻለ። ስለዚህ አሰፋ ሰባራ
ሳንቲም አልከሰረም። የሀይለስላሴ “የፕሬስ ነፃነት” እዚህ ድረስ ነበር ይላል አሰፋ። ( ሰዎች ግን
እስከ 1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ድረስ ሳንሱሩ የላላ ነበር ፤ ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ግን
ዳግም ጠበቀ ይላሉ።)
280
ጥቋቁር አናብስት

በዚህ መጥፎ አጋጣሚ የተነሳ፣ ይህ መጽሀፍ የስራ መስኩን ሙሉ ለሙሉ እንዳስለወጠው አሰፋ
ይናገራል።ተስፋ መቁረጥ ስለወረሰው፣ ብዙም ሳይቆይ ስራውን ለቀቀ። በመጽሀፉ መግቢያ ላይ
እሳቸውን ሳያማክራቸው ከከበደ ሚካኤል ስራዎች ላይ ቀንጭቦየጠቀሰው ጥቅስ ስለነበረ፣
ስማቸውን በመጥቀሱ ብቻ ለሳቸውም ችግር ፈጠረባቸው። ምናልባትም ሳንሱረኞቹ ከበደ
ሚካኤል ስለጉዳዩ ቅድሚያ ሳያውቁአይቀርም የሚል ጥርጣሬ ሳያድርባቸው አልቀረም። አሰፋ የA
ደረጃ ፈተናውን ካለፈ ከበደ ወደ ለንደን ዩኒቨርስቲ እንደሚልኩት ቃል ገብተው ነበር። አሁን ግን
ቃላቸውን በማጠፋቸው፣አሰፋን ለተጨማሪ ብስጭት ዳረገው።

አሰፋ ከትምህርት ሚኒስቴር ከለቀቀ በኋላ፣ወደ ጅማ ሄዶ በጅማ ሁለተኛ ደረጃ የእርሻ ትምህርት
ቤት ማስተማር ጀመረ። ትምህርት ቤቱ የሚተዳደረው በአሜሪካኖችና በእርሻ ሚኒስቴር ትብብር
ነው። ይህ አጋጣሚ አሰፋ ከአዲስ አበባ ውጪ ለረዥም ጊዜየቆየበት የመጀመሪያው አጋጣሚ
ነበር። በ1949 መጨረሻ አካባቢ ወደ ጅማ የሄደ፣ የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ሊደረግ ትንሽ
ጊዜእስኪቀረው ድረስ ቆይቷል። በመስከረም/ጥቅምት 1953 በዴሞክራት ጓደኞቹ ሚሊዮን
ነቅንቅ እና ታደሰ ተፈራ እርዳታ፣ ዳግመኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ተቀላቀለ (በቃለምልልሱ ወቅት
ታደሰ የጀርመን አምባሳደር ነበር)።

በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መሀል የመጀመሪያው የባህል ስምምነት ተፈረመ። አሰፋ እና
ሌሎች ስድስት ኢትዮጵያውያን ተመርጠው ሩስያ ውስጥ የተለያየ ስራ ተሰጣቸው። የአሰፋ ስራ
በሌኒንግራድ ዩኒቨርስቲ አማርኛ ማስተማር ነበር።
***
ሌኒንግራድ ውስጥ አሰፋ ራሱን ሙሉ ለሙሉ ለሥነ ጽሑፍ ሰጠ። የሩስያን ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ
ለማጥናት በማታ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ተመዘገበ፤በዚያ የነበረውን አብዛኛውን ጊዜ ለዚሁ
አውሎት ነበር። ወደ ሩስያ የሄደው ታህሳስ 1953 ሲሆን የቆየው እስከ ሐምሌ 1957 ድረስ
ነበር። በቆይታው የሩስኪ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገር ችሏል። በቃለምልልሱ ወቅት የሩስያን ሥነ
ጽሑፍ ቢወድም አሁን አሁን ብዙም እያነበበውአልነበረም። ሌኒንግራድን ወዶት ነበር፤
ምክንያቱም በባህል የበለፀገ ቦታ ነው። የአሮጌውንና የአዲሱን ስልጣኔ ህብር በሥነ ህንፃውና፣
በየሙዚየሙ ማየት ይቻል ነበር። ከኢትዮጵያ ውጭ የባእድ ባህል ሲያይ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው
ነው ( በኋላ ወደ 20 የሚደርሱ የውጪ ሃገራትን መጎብኘት ችሏል)።

አሰፋ ጅማ እና ሌኒንግራድ እያለ ብዙ ግጥሞችን ጽፏል። የመንግሥቱ ለማ "የግጥም ጉባኤ" እና


ገብረክርስቶስ ደስታ ተጽእኖ እንዳሳረፉበት ይናገራል። "የግጥም ጉባኤ"ን መንግስቱ ገና ከእንግሊዝ
እንደመጣ በወረቀት ተባዝቶ ብቻ በሚገኝበት ወቅት በ1949ለማንበብ ችሎ ነበር።
281
ጥቋቁር አናብስት

ከገብረክርስቶስ ደስታ ጋር ደግሞ፣ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን እና በራስ ደስታ ሆስፒታል


መሀል አንድ ቤት ተጋርተው ኖረዋል። የገብረክርስቶስ ስቱዲዮም8 እዛው ነበር። አሰፋና
ገብረክርስቶስ ከዚህ በፊት በትምህርት ሚኒስቴር አብረው ሰርተዋል።
አሰፋ ግጥሞቹን ከ1966ቱ አብዮት በፊት አላሳተመም፤ ነገር ግን አልፎ አልፎ አውሮፓ ውስጥ
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ስብሰባ ላይ ግጥሞቹን እንዲያነብ ይጋበዝ ነበር፤እነዚህ ተማሪዎች ግጥሞቹን
በደንብ እንደሚያውቋቸው ይናገራል። በጊዜው ከሚያውቃቸው ሌሎች ገጣሚዎች ሰለሞን ደሬሳን
ይጠቅሳል።አሰፋ ዊንጌት ሲገባ፣ ሰለሞን እዚያው ነበር። በክፍል ቢበልጠውም ኋላ ለመቀራረብ
ችለዋል።ሰለሞን ገና በዊንጌት እያለ በሥነ ጽሑፍ ይሳብ ነበር። ኋላ "ልጅነት"ን ሲያሳትም፣ ራሱ
ታዋቂ ገጣሚ ሆነ። አሰፋ ዳኛቸው ወርቁንም በሚገባ ያውቀው ነበር። ስለ ዳኛቸው ሲናገር "ለሥነ
ጽሑፍ የጋለ ስሜት ነበረው። ባህሪው ግን አስቸጋሪና ሕይወትን ዘወትር የሚያማርር ነበር"
ይለዋል።
አሰፋ በሌኒንግራድ ብዙ ዓመት ቢቆይም ወደ መጀመሪያ አካባቢ ብቸኝነት ያጠቃው ስለነበር
ማግባት ፈለገ። ስለዚህ ከአንድ ዓመት በኋላ ሚስት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።ወዲያውኑ
አልማዝ በቀለን አገኛትና ብዙም ሳይተዋወቁ በፍጥነት ተጫጩ―አሰፋ "ድንገተኛ አጋጣሚ" ብሎ
ይጠራዋል። በየካቲት 19549 ተጋቡና ወደ ሌኒንግራድ ሄዱ። በ1955 ወንድ ልጅ ወለዱ።
በሌኒንግራድም ኋላ አዲስአበባ ከመጡም በኋላ ጥሩ ጊዜ አሳለፉ። አሰፋ ጋብቻ “መልካም ነገር
ነው” ብሎያስባል።ነገር ግን ከአብዮቱ በኋላ የማይስማሙበት ነገር እየበዛ በመምጣቱ ተፋቱ።
አሰፋ የሀሳቡ ተቃዋሚ ባይሆንም ዳግመኛ አላገባም። ይሁን እንጂየቤት ውስጥ ስራ የሚሰሩ
ሠራተኞች በርካሽ ስለሚገኙ ፤ ወሲባዊ ፍላጎትን ለማርካት ሴቶችን በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል፣
ዳግመኛ ማግባት አላስፈለገውም። አሁን ግን ጥልቅ እና ከበፊቱ ጋብቻው የበለጠ የመንፈስ ቁርኝት
ያለው ግንኙነት ይፈልጋል።
ሌኒንግራድ ውስጥ ከጎጎል "The Inspector General" ("The Government
Inspector" ተብሎም ይጠራል) ጋር ተዋወቀ።። ይህንን ኮሜዱ ወዲያውኑ መተርጎም ጀመረ።
ይሁን እንጂ በአብዮቱ ማግስት በ1967 ድረስ እንኳን ተርጉሞ አልጨረሰም ነበር።
“የቢሮክራቶችን ማህበራዊ ንቅዘት” የሚተች ስላቅ ስለሆነ ከአብዮቱ በፊት ሊታተም አይችልም
ነበር ይላል። ይህ የአሰፋ ትርጉም ብሔራዊ ቲያትር መድረክ ላይ ቀርቦ “በጣም ተወዳጅ” መሆን

ችሏል። በተጨማሪ ሌኒንግራድ ውስጥ የሩስያ ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ የሥነ ጽሑፍ ስራዎችን
አንብቧል። በእርግጥ የሚማረው ትምህርት እንዲያነባቸው ያስገድደዋል። ከነዚህ መሀል ቶልስቶይ፣
ፑሽኪን እና ዶስቶቭስኪ በተለይ ስበውት ነበር።ነገር ግን ከዚህም በላይ ብዙ አንብቧል ፤ከጎርኪ
ጀምሮ ያሉትን የሶቪየት ደራሲዎች ሌሎችንም አንብቧል።
282
ጥቋቁር አናብስት

ከሌኒንግራድ በኋላ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ የውጪ ተማሪ ሆኖ በሥነ ትምህርት


የመጀመሪያ ዲግሪውን በሐምሌ 1962 ተቀብሏል። በጥቅምት 1963 በሥነ –ልሳን ሁለተኛ
ዲግሪውን ለመስራት ወደ ኤደንብራ ሄዶ ነበር፤ ነገር ግን በመጋቢት 1963 ዲግሪውን ሳይቀበል
ወደ ሀገሩ ተመልሷል። በሌኒንግራድ እያለም በፍልስፍና የማስተርስ ትምህርት ተከታትሏል፤
ለፈተና ግን አልተቀመጠም።

አሰፋ ገብረማርያም ሶሻሊስታዊ ዝንባሌዎችን ማሳደር የጀመረው ከልጅነት ገጠመኞቹ ተነስቶ እንጂ
በጽንሰ–ሀሳብ ደረጃ ወይም መጽሐፍ በማንበብ አይደለም። ድህነት ምን እንደሆነ በሚገባ
ያውቃል፤የሚፈልገው እናቱን እና ቤተሰቡን ለመርዳት የሚበቃውን ያህል ሰርቶ ለማግኘት
የሚችልበት አጋጣሚ እንዲመቻችለት ነው። ሀብታም ለመሆን ተመኝቶ አያውቅም። ሌኒንግራድ
እያለ ሶሻሊስታዊ ስርአት እንዴት እንደሚሰራ አስተውሏል። ወደ ሀገሩ ሲመለስ ኢትዮጵያ “የተሻለ
ዲሞክራሲያዊ ስርአት” ያስፈልጋታል የሚለውን “ጽኑ እምነት” እንደያዘ ነበር ፤ ነገር ግን ኋላ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (የዛኔ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ)ተማሪ ሲሆን፣ “የተማሪዎች
እንቅስቃሴ ግንባር ቀዳሚ ተሳታፊ የሚሆንበት ሁኔታ ላይ አልነበረም።” ነገር ግን “ፖለቲካዊ ንቃተ
ሕሊናው ከፍ ያለ” ነበር። “የፊውዳል ስርአት በጅማ እና ሌሎች ቦታዎች እንዴት እንደሚሰራ”
አስተውሏል ፤ “ስርአቱን” በተመለከተም ከብዙ ምሁራን ጋር ተወያይቷል።
አሰፋ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ አሰፋ ዳግመኛ ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ መስራት ጀመሮ
እስከ 1967 ድረስ በዚያ ቆየ። በ1967 የባህል ሚኒስቴር ሲቋቋም በዛ መስራት ጀመረ በመሐል
ለአጫጭር ጊዜ ውጪ ከመሄዱ በቀር እስከ ቃለምልልሳችን ጊዜ ድረስ እዚያውነበር የሚሰራው።
በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በሥነ ጥበብ ክፍል ይሰራ ነበር። የክፍሉ ሀላፊ የነበረችው ሜሪ
ታደሰ ለአጭር ጊዜ ነበርበዚህ ሃላፊነት የቆየችው። ይህ ክፍል በ1967 ከአብዮቱ በኋላ 10ወደ
ባህል ሚኒስቴር ሲዘዋወር “ወይ በጡረታወይ በሌላመንገድከስራ ተገልላለች።” በዚህ ጊዜ አሰፋ
“ወጣቶች የሚበዙባቸውን ቦታዎች ይጎበኝ” ነበር ፤ ለምሳሌ አሮጌው አየር ማረፊያ አጠገብ ያለው
አባዲና ኮሌጅ(በአብዮቱ ጊዜየደህንነት ክፍሉ እዚህ ነበር)፣ ደብረዘይት የሚገኘው አየር ሀይል
የመሳሰሉት። በዚያ ከወጣቶች ጋር እየተገናኘ በብዙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ሥነ ልሳንእና ሥነ
ጽሑፍ ሲያስተምር ከቋንቋ እና ባህል ጉዳይ ተነስቶ እንደ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ፖለቲካንም ጨምሮ
ወደ ሌሎችም ጉዳዮች መሄዱን ቀላል ሆኖ አግኝቶታል። ሌኒንግራድ እያለ ያዳበረውን ልምድ
ለተማሪዎቹ በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጪ ያካፍል ነበር።
ሜሪ ታደሰ ከባህል ሚኒስቴር ስትለቅ፣ አሰፋ እሷን ተክቶ የሥነ ጥበብ ክፍሉን መምራት ጀመረ ፤
የሾመው ወታደራዊው መንግስት ደርግ ነበር። በጊዜው የባህል ሚኒስቴር የነበሩት ዶክተር አክሊሉ

283
ጥቋቁር አናብስት

ሀብቴ11 ነበሩ። ፀጋዬ ገብረመድህን ከ1967 ጀምሮ ለአጭር ጊዜ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና


ጸሐፊ ነበሩ።
በ1967 የሀይለስላሴ መንግስት ከተገረሰሰና ንጉሡምበኋላ፣ አዲስ ብሔራዊ መዝሙር ለመምረጥ
ውድድር ተደርጎ አሰፋ በመጨረሻ ሰአት ተወዳድሮ አሸነፈ። ወቅቱ ከአብዮቱ በኋላ ከፍተኛ
መነቃቃት የነበረበት ጊዜ ነበር፤በየጋዜጣው ብዙ ይጻፋል፣ብዙ ተውኔቶች በመድረክ ይቀርባሉ፣
ብዙ ግጥሞች ይፃፋሉ። አሰፋ እንደሚያስታውሰው፣ ይህ መንፈስ በ1966 ተቀስቅሶ፣ 1967
ከርሞ እስከ 1968 ድረስ ሁሉ ተሻግሮ ነበር። “አብዮቱ ተንቀሳቅሶ የጎመራው” በነዚህ
ዓመታትነው። እንደ “ጎህ” ያሉ ብዙ ጋዜጣዎች እና መጽሔቶች መታተም ጀምረው ነበር።ይሁን
እንጂ ይህ መጽሔት የሚታተመው መንግስትን በሚቃወመው ኢሕአፓ (ኢትዮጵያ ሕዝቦች
አብዮታዊ ፓርቲ)መሆኑ በኋላ ተደረሰበት። እነዚህን በመሳሰሉ መጽሔቶች ላይ ጥሩ ነገሮች ይፃፉ
ነበር ይላል። አሰፋ በተለይ አዲስ ዘመን ላይነበር የሚጽፈው። አዲስ ዘመን ያኔ በብርሀኑ
ዘርይሁን12 አዘጋጅነት "ትኩስ እና ለሃሳብ ክፍት" ነበር። ሌላኛው የዊንጌት ተማሪ በአሉ ግርማም
በዚህወቅት ብዙ በመፃፍ ተጠምዷል ፤ “ምናልባትም እስከ መጨረሻው ድረስ የሚሰራውን ያውቅ
ነበር።” በአሉ ፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ “ንቃቱ ከፍ ያለ” ስለነበር፣ ሕይወቱን ያሳጣውን
13
የመጨረሻ መጽሀፋን ኦሮማይን “ያለ አንድ ትልቅ ባለስልጣን አይዞህ ባይነት” አይጽፈውም ነበር
ብሎ አሰፋ ያስባል።
አሰፋ በ1967 በባህል ሚኒስቴር የሥነ ጥበብ ክፍል ሀላፊ ሆኖ ለሁለት ዓመት ቆየ (“ማንኛችንም
አንድ የሐላፊነት ቦታ ይዘን ብዙ አንቆይም ነበር” ይላል አሰፋ)። ይህንን ሐላፊነት በተረከበበት
ዓመት የኒኮላይ ጎጎል "ዋናው ተቆጣጣሪ" በብሔራዊ ትያትር መታየት ጀመረ። ነገር ግን በትያትር
ቤቱ ውስጥ “ከጸጋዬ ገብረመድህን ስራ ጋር በተያያዘ” አድማ ተነሳ። በዚሁ የተነሳ በተውኔቱ ላይ
ዋናውን ገፀባህሪ ወክሎ የሚጫወተው “የሀገሪቱ ኮከብ ተዋናይ” ወጋየሁ ንጋቱ ታሰረ። ወጋየሁ
በ1968 ሲፈታ ተውኔቱም መታየቱን ቀጠለ።
በ1971 አሰፋ ከአብዮቱ በፊትም እና በኋላ የፃፋቸው ግጥሞች ስብስብ "የመስከረም ጮራ"
በሚል ርእስ ታተሙ። ከግጥሞቹ መሀል የመጽሀፉን ርዕስ የያዘ ሰለ 66ቱ አብዮት የተፃፈ ግጥም
አለ። አሰፋ ሙሉ ለሙሉ የራሱ ፈጠራ የሆነ ስራ ሲያሳትም ይህ የመጀመሪያውነው። በሚቀጥለው
ዓመት በ1972 በእንግሊዝኛ የፃፋቸውን ግጥሞች "The Voice" በሚል ርዕስ አሳተመ።
የብሔራዊ መዝሙሩ የእንግሊዝኛው ትርጉምም በዚሁ ስብስብ ውስጥ ታትሟል።14
በ1969 ከላይ የተጠቀሱትን መጽሀፍት ከማሳተሙ በፊት አንድ "ለንደን–አዲስአበባ" የተሰኘ
284
ጥቋቁር አናብስት

ተውኔት ጽፎ ነበር፤ቢሆንም ለመድረክ አልበቃም። የግጥም ስብስቦቹን ካሳተመ በኋላ በአማርኛም


በእንግሊዝኛም መፃፍ ቀጥሎ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚን በማስተዳደር የስራ
ሐላፊነት ስለሚደራረብበት የሚፈልገውን ያህል መፃፍ አልቻለም። ስለዚህ እስከአሁን ሌላ የግጥም
መድብል አላሳተመም። ስራውን በመልቀቅ15 ሙሉ ጊዜውን ለሥነ ጽሑፍ ለመስጠት እንዳሰበ ያኔ
ነግሮኛል።

በባህል ሚኒስቴር የሥነ ጥበብ ክፍል ውስጥ ከነበረው ቆይታ በኋላ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት
ቤትና በአዲስአበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት አማርኛን እና "ባህልን ማክበር"ን ከ1968–70
አስተምሯል። ከዚህ ቀደም ብሎ በ1967/68 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ምክር ቤት አባል
ሆኖ ተመርጧል። በ1970 የአካዳሚውን ጽህፈት ቤት ተቀላቅሎ የሥነ ቃል ክፍል ዋና ሀላፊ ሆኖ
ለሁለት ዓመት ሰርቷል። በዚሁ ወቅት ትልቅ የሥነ ቃል አውደጥናት አዘጋጅቶ ብዙ የጥናት
ወረቀቶች ቀርበዋል። በ1973 የአካዳሚው ጊዜያዊ ዋና ጸሐፊ ሆነ ፤ በ1977 ሐላፊነቱ ቋሚ
ሆኖለት እስከ ከቃለምልልሳችን ጊዜ ድረስ ይሰራ ነበር። አሰፋ በሐላፊነት እያለ የኢትዮጵያ
ቋንቋዎች አካዳሚ ያከናወናቸው ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡(1)የአማርኛ እና ሌሎች
ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ፊደላት አንድ ወጥ የሆሄ ስርአት እንዲኖራቸው መደረጉ (2) የአማርኛ
ቅኔዎች ተሰብስበው በመቶ የሚቆጠሩት ምሳሌዎች ተመርጠው በ1980 በመጽሀፍ መልክ
መታተማቸው(3)ተከታታይ የቴክኒካዊ እና ሳይንሳዊ መዛግብተ ቃላት በዚያው ዓመት በ1980
መታተማቸው።
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ የጥቂት አስርት ዓመታት ታሪክ ያለው ቢሆንም፣ እስከ 66ቱ
አብዮት ድረስ ግን ብዙም ተግባር አላከናወነም። አካዳሚው እንዲቋቋም የታዘዘው በ1934 ነበር፤
ነገር ግን እስከ 1964 ድረስ ትእዛዙ ተፈፃሚነት ካለማግኘቱም በላይ፣ ለብዙ ዓመታትምጥቂት
ተጨባጭስራዎችን ነበር ያከናወነው። የቀድሞው የአማርኛ ቋንቋ ብሔራዊ አካዳሚ፣ በአማርኛ
ሥነ ጽሑፍወይም በቋንቋው ጥናትና አጠቃቀም ከፍተኛ ዝና ያተረፉ አባላት ነበሩት፤ ( ሁሉም
አባላት በቀዳማዊ ኃይለስላሴ የተሾሙ ናቸው) ከነዚህ መሀል ከበደ ሚካኤል፣ ግርማቸው
ተክለሀዋርያት፣ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ማህተመሥላሴ
ወልደመስቀል፣ መርስዔሀዘን ወልደቂርቆስ፣ ተክለፃድቅ መኩሪያ፣ ዶክተር አብርሃም ደሞዝ፣
ዶክተር አክሊሉ ሀብቴ፣ ዶክተር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶክተር ኃይሉ ፉላስ፣ ዶክተር ስርግው
ሀብለሥላሴ ወዘተ ይገኙበታል። በ1967 አካዳሚው ስሙን ወደ “የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ”
ሲቀይር የቀድሞ አባላቱ አዲሶቹን አባላት መረጡ።እነዚህም ሐዲስ አለማየሁ፣መንግሥቱ ለማ፣
ዳኛቸው ወርቁ፣ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ፣ ተክለፃድቅ መኩሪያ (የታሪክ ሊቅ) ፣ አፈወርቅ

285
ጥቋቁር አናብስት

ተክሌ (ሰአሊ)፣ አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ፣ ዶክተር ብርሀኑ አበበ (የታሪክ ሊቅ) ፣ ዶክተር
አክሊሉ ሀብቴ (የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት)፣ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ (የቋንቋ ሊቅ)፣
ዶክተር ፈቃዱ ገዳሙ (የሥነ ሰብዕ ተመራማሪ)፣ ዶክተር ጌታቸው ኃይሌ ( የቋንቋ ሊቅ)፣ ዶክተር
ኃይሉ ፉላስ (የቋንቋ ሊቅ) ፣ ዶክተር ኃይሉ አርአያ (የቋንቋ ሊቅ) ፣ ዶክተር መርእድ ወልደአረጋይ
( የታሪክ ሊቅ)፣ ዶክተር ታደሰ በየነ (የቋንቋ ሊቅ)፣ ዶክተር ታደሰ ታምራት ( የታሪክ ሊቅ)፣
ዶክተር ስርግው ሀብለሥላሴ ( የታሪክ ሊቅ) እና ሌሎችም ይገኙበታል።16 በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ
ላይ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በ1980 አካዳሚው ያሳተመው የአማርኛ ቅኔዎች ስብስብ
ሳይማርካቸው አይቀርም። ይህን ስብስብ በማዘጋጀት ብዙ ጸሐፊዎችና ምሁራን ተሳትፈዋል፤
ለምሳሌ መንግስቱ ለማ (አርታኢ)፣ ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ እና ዶክተር
ኃይሉ አርአያ ይገኙበታል።የመጽሐፉ ርዕሰ "የግዕዝ ቅኔያት" ሲባል 337 ያህል ቅኔዎችን ይዟል።
ቅኔዎቹ ቀድሞ ከነበሩ ስብስቦች የተወሰዱ ሲሆን በዚህ መጽሀፍ ላይ ግን ወደ አማርኛ ቋንቋ
ተተርጉመው ከጠቃሚ ማብራሪያዎች ጋር ቀርበዋል።በዚህ ወቅት ሌላው ይህ አካዳሚ ያከናወነው
ታላቅ ተግባር የሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊመዛግብተ ቃላት በተመሳሳይ ዓመት ማሳተሙ ነው።
ከተዳሰሱት የእውቀት ዘርፎች መሀል ህክምና፣ሥነ –እንስሳት፣ሥነ –እጽዋት፣ እርሻ፣ ጂኦግራፊ፣ሥነ
–ምድር፣ ሂሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ኤሌክትሮመካኒክስ ይገኙበታል። የሥነ ምግብ፣
ስታትስቲክስ እና የህንፃ ግንባታ መስኮችን የሚመለከትመዛግብተ ቃላት በኋላ ተከትለው
ወጥተዋል። አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት ትርጉም ፕሮጀክት (መዛግብተ
ቃላቱን ያዘጋጀው አካል)ዳይሬክተር ነበር። ዝግጅቱ የጀመረው በ1973 ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ
እና ከኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሲሆን የተባበሩት መንግስታት
የልማት ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ አድርጎላቸዋል።

አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ በተጨማሪም፣ ለብዙ ዓመታት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አባል
የነበረ ሲሆን የማህበሩ ዋና ፀሐፊም ሆኖ ሰርቷል። በቃለምልልሳችን ወቅት የማህበሩን ስራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበር።በማህበሩ ውስጥ“ጥሩ የመተባበር መንፈስ” ነበር ይላል።አብረውት
ከሰሩ ደራሲዎች መሀል ብርሀኑ ዘርይሁን፣መንግስቱ ለማ፣ ተስፋዬ ገሰሰ፣አማረ ማሞ እና ሌሎችም
ይገኙበታል።ከላይ ከተጠቀሱት ስራዎች ባሻገር አሰፋ የአማርኛ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍን
በሚመለከት በተለያዩ መድረኮች ላይ ብዙ ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርቧል። በመላው አለም በሰፊው
ተዘዋውሯል። በ1979 በሌኒንግራድ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪውን ለመከታተል የውጪ ተማሪ
ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። በስራው እጅግ በርካታ ሽልማትን ተቀብሏል። የተመረጡ ግጥሞቹ ወደ
አረብኛ፣ እንግሊዝኛ ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ሩስያኛ እና ቡልጋሪያኛ ተተርጉመው

286
ጥቋቁር አናብስት

ታትመዋል ብሏል። ምንም እንኳን የግጥም ስብስቦቹ ትልልቅ ቅጽ ባይሞሉም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ
በደንብ የሚታወቅ ገጣሚ ነው። በግንባር ቀደምትነት የሚታወቅበት ነገር ግን በአብዮቱ ዘመን
የብሔራዊ መዝሙሩን ግጥም በመድረሱ ነው።

የተርጓሚ ማስታወሻ አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ እሚኖርበት አሜሪካ ላስቬጋስ ውስጥ በቅርቡ
ህይወቱ አልፋለች፡፡

ማስታወሻዎች

1) ይህ ቀላል የፊደል ገበታ፣ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸውን ተደጋጋሚ ፊደሎች ቢያስወግድም


ሊለመድ አልቻለም። ሰዎች ወጥነት በሌለው መንገድ እንደበፊቱ መፃፍ ቀጥለዋል።

2) መንግስቱ ለማ ከህመሙ አላገገመም። የሕይወት ታሪኩን በዚህ መጽሀፍ ውስጥ


ታገኙታላችሁ።

3) አቶ አርአያ በ1940ዎቹና በ1950ዎቹ የትምህርት ሚኒስቴር ዋና ጸሐፊ ሆነው ለረዥም ጊዜ


ከሰሩት አቶ አለም-ሥላሴ ጎላ ጋር የቅርብ ወዳጅ እንደነበሩ አሰፋ ይናገራል። የመንግሥቱ ለማ
የቅርብ ጓደኛና፣ የአባቱም ተማሪ ነበሩ። ከሌላው ወዳጃቸው የታሪክ ሊቁ ተክለፃድቅ መኩሪያ ጋር
ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ በጣሊያን አብረው ታስረው ነበር።

4) በአቅራቢያው ስለሚኖሩ አሰፋ ሁሉንምየገብረአምላክን ልጆች ያውቃቸው ነበር። በእምነት


በኋላ ራሱን ወደአጠፋበት አሮጌው አየር ማረፊያ አጠገብ ወደሚገኘው ቤቱ ተዛውሯል።ከልጆቹ
መሀል ጥቂቶቹ ከአሰፋ ጋር አብረው በአንድ ትምህርት ቤት ተምረዋል። ከልጆቹ መሀል መዝገበ
ከሚባለው ጋር ጥሩ ጓደኞች ነበሩ። አብዛኛዎቹ ልጆች ጥሩ የሚባል ትምህርት አግኝተዋል ፤
ፍፃሜያቸው ግን አላማረም። ሁለቱ ( በእምነት እና ቴዎድሮስ) ራሳቸውን ሲያጠፉ ሌላኛው ከባድ
የአእምሮ ህመም ነበረበት።በእምነት ራሱ አንዴ የፈለጋትን ሴት የወሰደበት ሰው ፊት ላይ ነዳጅ
አርከፍክፎ በማቃጠል መልኩን አጥፍቶታል። አንዳንዶቹ ልጆች ጥሩ ስራ ነበራቸው። አባታቸው
“በጣም ጥብቅና ሀይለኛ” የነበሩ ሲሆን እናትየው ለሰፈሩ ልጆች ሁሉ አንባሻ የሚሰጡ ደግ ሴት
ነበሩ። ገብረአምላክ ከጸሐዩ ለመከለል ባርኔጣ አጥልቀው ቀጥ ብለው ይራመዳሉ ፤ “የህፃናት
ንጽህና ጉዳይም ሁሌም ያሳስባቸው ነበር።”

5) ዊንጌት ውስጥ ከአሰፋ ጋር መማር ከጀመሩ ተማሪዎች መሀል በኋላ ታላቅ ጸሐፊ ተውኔት
ለመሆን የበቃው ፀጋዬ ገብረመድህን አንዱ ነው። ነገር ግን ሁለተኛው ዓመት ላይ ከዊንጌት ወጥቶ

287
ጥቋቁር አናብስት

የንግድ ስራ ትምህርት ቤትገባ። (ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ የሚወጡት በደካማ ውጤት ብቻ


ሳይሆን በሌሎችም ምክንያቶችም ሊሆን እንደሚችል አሰፋ ይናገራል።

6) በኋላ የጃፓን አምባሳደር ሲሆን በዚህ ቃለመጠይቅ ወቅት በሰሜን አሜሪካ ውስጥ “ስደተኛ”
ነበር።

7) ሚሊየን ነቅንቅ ዊንጌት ውስጥ ከነአሰፋ ዘመን በፊት አማርኛ አስተምሯል። ከዚያም ወደ
ዩናይትድ ኪንግደም ሄዶ በሥነ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ይዞ ተመልሷል። ሚሊየን ዌልስ
ውስጥ እየተማረ በነበረበት በዚህ ሰአት ሚካኤል እምሩ ኦክስፎርድ ውስጥ፣ መንግሥቱ ለማ ደግሞ
ለንደንየኢኮኖሚክስና የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ይማሩ ነበር። ሶስቱ በደንብ
ይተዋወቁ እንደነበር አሰፋ ይመሰክራል።

8) ገብረክርስቶስ ደስታ በዋነኛነት የሚታወቀው በሰአሊነቱ ነው። ነገር ግን አሰፋ ገማተ፣ ሚካኤል
እምሩ እና ሌሎችም እንደ ገጣሚም ትልቅ ቦታ ይሰጡታል። ገብረክርስቶስ ደስታ በሰሜን አሜሪካ
በ1972 አርፏል። በአሳሳል ስልቱ ተማሪዎቹ ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳድሮባቸዋል። ኢትዮጵያ
በቆየሁባቸው ዓመታት ስሙ ገኖ የወጣና፣ ስእሎቹም በተደጋጋሚ የሚጎበኙለትሰአሊገብረክርስቶስ
ደስታ ነበር።

9)ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በ1949፣ 1951፣ 1957 ሶስት ሴት ልጆችን ወልደዋል።

10) ሜሪ ታደሰ “በኢትዮጵያ ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ የተማሩ ሴቶች መሀል አንዷ ነች።”
“ፈረንሳዊት ሴት ያገባው” ወንድሟ ማሞ ታደሰ፣ በአንድ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር ነበር። "በጠራ
ጨረቃ" የሚለው የመንግስቱ ለማ ግጥም ለእሷ እንደተፃፈ “ሰዎች እንደሚያወሩ” አሰፋ ይናገራል
፤ “እርግጠኛ ግን አይደለም” ( እኔም ብሆን ለመንግስቱ ጉዳዩን አላነሳሁበትም)። ጨምሮ “ቆንጆ
ሳትሆን እንደማትቀር” ይናገራል ፤ አብረዋት የሚማሩ ወንዶች ያደንቋት ነበር ፤ በእጃቸው
ለማስገባትም “ብዙ መላ” ሞክረዋል።(መንግስቱ ለማን የሚያውቅ አንድ ሌላ ሰው ከሜሪ ጋር
ስለነበረ ግንኙነት ምንም ባያውቅም፣ ነገር ግን አልማዝ ከምትባል አንዲት ሴት ጋር ድብን ያለ
ፍቅር ውስጥ እንደነበር ፤ እርሷ ግን ሐይለማሪያም ከበደን በማግባቷ መንግስቱ በጠና እንደታመመ
“በእርግጠኝነት” ያውቃል። ሐይለማሪያም ከበደ የግርማሜ ነዋይ ዘመድ በመሆኑ ይህ ጋብቻ
በመንግስቱናበግርማሜ መሀል ያለውን ፍጭት ጨመረው። በኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤትም ሁለቱ አብረው ተምረዋል ፤ ከ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ በፊት ኋላ የስዊዲሽ

288
ጥቋቁር አናብስት

ትምህርት ቤት በሆነው በራስ እምሩ ቤት ውስጥ ስለ ለውጥ ይከራከሩ ነበር ፤ “ስለ አብዮት ግን
በፍጹም አውርተው አያውቁም”፤ አንድ ምሽት ከሞቀ ክርክር በኋላ መንግስቱ በግርማሜ እና
በአጃቢዎቻቸው ከመደብደብ ለጥቂት ነው የዳኑት)

11) ዶክተር አክሊሉ ሀብቴ የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ነበሩ። በቃለመጠይቁ
ወቅት ከዩኒቨርስቲው ተሰናብተው አለም ባንክ ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ዶክተር ደምሴ
ሀብቴ የተባሉ ታናሽ ወንድማቸው የህክምና ፕሮፌሰር እና ታዋቂ የህፃናት ሀኪም ነበሩ። ሌላ ታናሽ
እህታቸው ፈረንሳይ ውስጥ ሥነ ልቦና ያጠናች፣ ቁንጅናዋ የተመሰከረለት ሲሆን አንድ ናይጄሪያዊ
አግብታለች ፤ ይህ ድርጊት በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደ “ተራማጅነት” ይቆጠራል።

12) ብርሀኑ ዘርይሁን የመንግስት ደጋፊ ለነበረው የመኢሶን ፓርቲ ቅርብ ወይም አባል እንደነበር
አሰፋ ይናገራል። ብርሀኑ ዘርይሁን ከስራ በኋላ እንደ ልማዱ ለመጠጣት ወደ መጠጥ ቤት ጎራ ሲል
ኢሕአፓዎች አዲስ ዘመን ላይ ለሚጽፈው ፕሮፓጋንዳ እንደ “ቅጣት” ጣቶቹን ሊቆርጡለት ይችሉ
እንደነበር ነገር ግን “ለሥነ ጽሑፍ ሲሉ” እጆቹን እንደማይነኳቸው ይነግሩት ነበር። የብርሃኑን
መጽሀፍ የማያደንቅ የለም፤ እነሱን ጨምሮ።

13) የሞተው አዲስአበባ ውስጥ ካሉ የቀበሌ እስር ቤቶች በአንደኛው ሳይሆን አይቀርም።

14) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕድሪ) በ1979 ኃይለሥላሴ ከሥልጣን


ከተወገዱ ከ13 ዓመት በኋላ ሲመሰረት፣ መንግስት አዲስ ብሔራዊ መዝሙር ፈለገ። የቀደመውን
መዝሙር የደረሰው አሰፋ፣ ይህንኑ መዝሙር ብዙ ተሳታፊዎች ለነበሩበት ውድድር በድጋሚ
አስገባው። በውጤቱም አሰፋ በዚህ መዝሙር በድጋሚ በአንደኝነት አሸነፈ ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የሕዝብ መዝሙር መሆኑንም ቀጠለ። የመዝሙሩ ግጥም በነጋሪት ጋዜጣ ላይ በመስከረም 7 ቀን
1979ዓም ወጥቷል።

15) በሱ አቅም ማድረግ የሚችለው “የመልቀቂያ ፍቃድ” መጠየቅ ነው። ነገር ግን መልቀቂያው
ተቀባይነት ካላገኘ በ"ዲሞራሲያዊቷ" ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ማድረግ የሚችለው ነገር
አልነበረም።

289
ጥቋቁር አናብስት

16) በ1978 ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ አባል ነበሩ፦ አፈወርቅ፣ መንግስቱ፣ ብርሃኑ፣ ዳኛቸው፣
ፍቃዱ፣ ሐይሉ አርአያ፣ መርዕድ፣ ታደሰ ታምራት፣ ተክለፃድቅ ወዘተ። አሰፋ፣ መንግስቱ፣ ብርሃኑ፣
ሐይሉ አርአያ እና ሌሎችም የአካዳሚው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጭምር ነበሩ።

290
ጥቋቁር አናብስት

ፀጋዬ ገብረመድህን
"ባለቅኔ፣ ጸሐፌ–ተውኔት፣ አዘጋጅ፣ የታሪክ ሥነ –ጽሑፍ
ተመራማሪ፣የጥቁር ኢትዮ–ግብፃውያን ጥንታዊየኪነጥበብ እሴት
የሥነ –ሰብዕ ባለሙያ"ፀጋዬ ገብረመድህንን ለመጀመሪያ ጊዜ
ያገኘሁትበ1965ዓም፣ በአዲስ አበባ "የፓን–አፍሪካኒስቶች"
ጉባኤ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ሲያቀርብ ነው።በጊዜው፣ ከዚያ
በኋላም በተደጋጋሚም ረጅም ሰአት የፈጀ ቆይታ ኖሮን
ቢያውቅም፣ ሁሌም ሲያናግረኝ ገና ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተገናኘን አድርጎ ነው።ለዚህ መጽሐፍ
ቃለ መጠይቅ ላደርግለት ቢሮው ስገኝም የገጠመኝ ይኼው ነው። ለቃለ–መጠይቁ ፍላጎት
ያደረበት ይመስላል፤ እኔም እቅዴን በሚገባ ከዘረዘርኩኝ በኋላ ሥነ –ጽሑፋዊ እንጂ ፖለቲካዊ
ዝንባሌ እንደሌለኝ ግልጽ አደረግኩኝ (በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በነበሩት"ከሌሎች የበለጡ አንዳንድ
ሰዎች" ዘንድ ይህንን ማድረጉን ጠቃሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ)።"ፕሮጀክቴን" በተመለከተ ከሚገባው
በላይ ገለፃ በአንክሮ የሚሰማኝ ለመሰለኝ አድማጭ(በአትኩሮት ይመለከተኝ ስለነበር) ሳደርግ
ከቆየሁ በኋላ ከጨዋታችን ጋር ምንም በማይገናኝ መልኩ፣ "ግንኮ ስካንዲኔቪያዊ አትመስልም!"
የሚል አስተያየት ሰነዘረ። የጥበባዊ ሰብእናው መገለጥ ሳይሆን አይቀርም ብዬ ካሰብኩ በኋላ
የሕዝቦችን ብሔራዊ ባህርያት በተመለከተ ሚስጢራዊ በሚመስሉ ቃላት ተነጋገርን። ከተውኔቶቹ
በአንደኛው ውስጥ፣ ገፀ–ባህሪ ሆኜ ብቅ ሳልል አልቀርም የሚል ስጋት ስላደረብኝ፣ በሕይወቱ
ታሪክ ላይ ያሳደርኩትን ፍላጎት ያህል በስካንዲኔቪያዊ ነፍስያም ላይ እንዳሳደርኩ መስዬ ለመታየት
ጣርኩ። ነገር ግን ስለራሱ ከማውራት ይልቅ ስለ ኢብሰን ማውራት አሰኘው።ዋናውን ጉዳይ ትተን
ብዙ ስናንዣብብ ከቆየን በኋላ፣ የትምህርት መረጃውን በአግባቡ በዝርዝርመዝግቦ እንደሚያቆየኝና
ያ ጥሬ መረጃ ("እውነታ")፣ስለሱ አንዳች ምስል ለመቅረጽ እንደሚረዳኝ ቃል ገባ።በአማርኛ
የታተሙ ከእሱ ጋር የተደረጉ ሁለት ቃለ–መጠይቆችንም ጠቆመኝ።ካሁን በፊት ስለ ሕይወቱ እና
ሥነ–ጽሑፋዊ ሰውነቱ "ጉዞ" ለሌሎች ሰዎች ያጫወተውን ለእኔ እንዳይደግም፣"ስራ በጣም
ይበዛበታል"።

የአውሮፓና የአፍሪካ ሥነ –ጥበብ፣ ተውኔት፣ሀይማኖት ወዘተ መሰረቱ ግብጽ እንደሆነ


ያቀረባቸውን ምሁራዊ ግምቶች ከመስማቴ በላይ ግጥሞቹን የማንበብ፣ ተወኔቶቹን ደግሞ
በመድረክ የመመልከትና የማንበብ እድሉ አጋጥሞኝ ነበር። በአንድ አጋጣሚ በአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት እየሰጠ ሳለ ለምን "በከባድ" ቋንቋ እንደሚጽፍ
291
ጥቋቁር አናብስት

ሲጠየቅ ቋንቋን ማስፋትና ማበልጸግ የአንድ ደራሲ ሙያዊ ግዴታ እና ሐላፊነት መሆኑን
እንደሚያምን፣ ይህም ለዘመኑና ለዘመናዊው ሥነ ጽሑፍ የሚሆን ቋንቋ መፍጠርን እንደሚጨምር
ተናግሯል። ፀጋዬ ገብረመድህን በቀላሉ የሚያነቡት ወይም ሊለው የፈለገው በቀላሉ የሚገባ ደራሲ
አይደለም። ፀጋዬ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ደራሲያን፣ ከግዕዝ ቋንቋ በመነሳት አዳዲስ ሀሳቦችን
ለማጎልበት፤ ሀገር በቀል ትርጉሞችን ለማመንጨት፣ ወይም ቃላት አቀናጅቶ አዲስ ሀሳብ
ለመፍጠርአይሞክርም ፤ ይልቁንም አዳዲስ የፈጠራቸውን ቃላት እየሰነጣጠቅኩ ወደ
እንግሊዝኛስመልሳቸው ትርጉማቸውን ለመገመት አስችሎኛል፦ ፀጋዬ አብዛኛውን ጊዜ፣
በእንግሊዝኛ እያሰበ ወይም ቃል በቃል ትርጉም እየፈለገ (ሀሳቡን በመተርጎም ፈንታ ቃሉን ቀጥታ
እየተረጎመ)የፈጠራቸው ይመስላል። እንግሊዝኛ "በፈሊጣዊ አነጋገሮች" የበለፀገ እንደመሆኑ
መጠን፣ በቀላሉ "በቀጥታ" ሊተረጎሙ የማይችሉ ቃላቱና ሀሳቦቹ ብዙ በመሆናቸው፣ እነዚህ
ቃላትና ሃሳቦች በአማርኛ ቋንቋ እንደገና ሲፈጠሩለጆሮ እንግዳ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ፣
በነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለኝ ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ፣ የኔን "አስተያየቶች" ማንም ከቁምነገር
ሊጥፋቸው አይገባም። ያም ሆነ ይህ ብዙ ኢትዮጵያውያን ፀጋዬ የፈጠራቸውን ቃላቶቹን ትርጉም
ለመረዳት ይታገላሉ። አንዳንዶች እንደሚሉት የፀጋዬ ተውኔቶች በመድረክ ተመልክተዋቸው
ካልሆነ አንብበዋቸው አይገቡም። ይሄ የግጥሞቹም ባህሪ ነው፦ አንባቢው ለብቻው ሆኖ
ከሚያነባቸው ይልቅ ፀጋዬ ራሱ ሲያነባቸው ህያው ይሆናሉ።

በመድረክ ያየኋቸው የፀጋዬ ተውኔቶች ሁሉ ተውበው የተከወኑ ናቸው፦ትወናው፣ የመድረክ


ስራው፣ ሙዚቃው―ሁሉም በሚገባ ተከናውነዋል። ያለጥርጥር ፀጋዬ ከዝነኛ የኢትዮጵያ ጸሐፌ–
ተውኔቶች መሐል አንዱ ነው።በማዘጋጃ ቲያትር ቤት/የአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ/ ለብዙ
ዓመታት ሲታዩ ከኖሩት ቲያትሮቹ መሐል አብዛኛዎቹ የፀጋዬ የራሱ ፈጠራዎች ወይም የትርጉም
ስራዎቹ ናቸው።ይህም በሌሎች የኢትዮጵያ ጸሐፌ–ተውኔቶች ዘንድ ቅናት ቢጤ አሳድሯል።ይህንን
በተመለከተ አንድ ምጸታዊ ጽሑፍ በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በአዲስአበባ "በስውር"
ይዘዋወር ነበር።

ፀጋዬ ገብረመድህን የተወለደው በ19281፣ነሐሴ 11 በሸዋ ክፍለሀገር፣በጅባትና ሜጫ


አውራጃከአምቦ (ሐገረ ሕይወት)30 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቦዳ በምትባል መንደር ነው።
የቀድሞው ዘመንታዋቂ የጦር መሪ እና የፖለቲካ ሰው ፊታውራሪ ሀብቴጊዮርጊስ ዲነግዴም
የተወለደው (በ1918 ሞቷል)እዚሁ መሆኑን ሲገልጽ በኩራት ነው። ፀጋዬ ሲወለድ ከሜጫ
"ነገድ" የሆኑትአባቱ አቶ ገብረመድህን ሮባ ቀዌሳ በቦታው አልነበሩም፤ ጣሊያኖችን ሊዋጉ
በሐይለስላሴ የሚመራውን ጦርተከትለው ማይጨው ዘምተዋል―ጣሊያኖች ወሳኝ የሚባለውን

292
ጥቋቁር አናብስት

ድል ያስመዘገቡት እዚሁ ነው። ይህንን ተከትሎ ባንዳዎች የአቶ ገብረመድህን ቤት ላይ


አባወራውበሌሉበትእሳት ሲለቁ፣ የፀጋዬ እናት፣ የአንኮበሯ ወይዘሮ ፈለቀች ዳና፣ ፀጋዬን እና ታላቅ
እህቱን ይዘው ጎረምቲ ወደተባለች ሌላ መንደር ሸሽተው ከዘመድ ተጠጉ።

እናቱ ቤታቸው ሲቃጠል ከእሳቱ ስላዳናቸው ለቦዳ አቦ ፀጋዬን ተሳሉ። በዚህ ስለት መሰረት ፀጋዬ
ቄስ ወይም መነኩሴ መሆን ነበረበት።2 ነገር ግን አባቱ ከዘመቻው ተመልሰው ቤተሰቦቻቸውን
ሲቀላቀሉ፣ ፀጋዬን በተመለከተ ሌላ እቅድ ነበራቸው፦ፀጋዬ ተምሮ የመንግሥት ሠራተኛ እንዲሆን
ፈለጉ።

ፀጋዬየመጀመሪያ ትምህርቱን የቀሰመው ከእናቱ ዘመዶች ነው―ግእዝ፣ ዜማ እና ቅኔ ለሶስት


ዓመታት (ከ1937–1940) አስተማሩት። መዝሙረ ዳዊትን ከአለቃ ብስራት እና ከአባ
ወልደማርያም ዘንድ አጠና። ነገር ግን እንደ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ልጆች በለጋ እድሜ እረኛ ሆኖ
ስራ በመጀመር ከብት ጠብቋል።

ከ1940–1944 ድረስ በአምቦ ከተማ አስኳላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል።


በ19413ዓ.ም ፀጋዬ የ13 ዓመት ልጅ እያለ ቤተሰቡን በተመለከተ ደስ የማይል ነገር
ገጠመው―ቤተሰቦቹ በፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር ጉቦ መክፈል ስላልቻሉ "ፍትህ ተነፈጉ"።
ይህ ፀጋዬን ስላስከፋው "የዳዮኒሰስ ፍርድ" የተሰኘውን ተውኔት ወደ አማርኛ ለመመለስ ተነሳሳ።
በዚህ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ "ደራሲ" ተብሎ ተጠራ። በትምህርት ቤት
እያለ ሌሎች ሶስት ተውኔቶችን ፃፈ፦ "የደም አዝመራ"፣ "እኔም ሰው ነኝ" እና "የእድገት
መስዋእት" ይሰኛሉ።

አንደኛ ደረጃን በ16 ዓመቱ በጥሩ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ "በዝነኛው"
ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገባ። ነገር ግን የፀጋዬ ምኞት "የቲያትር ጥበባት" ማጥናት
ነበር፤ይሁን እንጂ እንደዚህ ዐይነት ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት ገብቶ፣
ቲያትር ቤት ለማስተዳደር የሚያበቃውን የአስተዳደር ትምህርት ለመማር ፈለገ። ርእሰ መምህሩን
"ጨቅጭቆ" አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ፣ ሁለተኛ ደረጃ የንግድ ትምህርት ቤት ገባ። ከዚያ
ከተመረቀ ከአንድ ዓመት በኋላ በ1948 ዓ.ም "በልግ" የተሰኘውን ተውኔት በቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴ ትያትር ቤት (ኋላ ብሔራዊ ቲያትር) አቀረበ። በተመሳሳይ ዓመት "የሾህ አክሊል" የተሰኘ
ሌላ ተውኔት ጽፎ ከአንድ ዓመት በኋላ በዚሁ ትያትር ቤት አቀረበ ፤በ1951ዓም ደግሞ ታተመ።

293
ጥቋቁር አናብስት

ፀጋዬ ገብረመድህን በከፍተኛ ትጋት፣ በአማርኛም በእንግሊዝኛም ተውኔቶችን መፃፍ ቀጠለ።


ከውጪም የሼክስፒርን ብዙ፣ የሞሊየርን ሁለት፣ የብሬሽትን አንድ ተውኔቶች ተርጉሟል።
በተጨማሪ ግጥሞችን በእንግሊዝኛም በአማርኛም አሳትሟል። በውጪ ሀገር ስራዎቹን
ከማሳተሙም ባሻገር፣ ለሥነ ጽሑፋዊ አስተዋፆኦው ብዙ ሽልማቶችን ተቀብሏል። በመላው አለም፣
በተለይ በአፍሪካ ብዙ ተዘዋውሮ አለም አቀፍ እውቅና አግኝቷል። በ1978 ከኬንያዊ ደራሲ ጋር
በመተባበር የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ብሔራዊ መዝሙር ደርሷል። ፀጋዬ ከተለመደው በላይ
ታታሪ በመሆኑ ብዙ ጽፏል ፤ የስራዎቹን ሙሉ ዝርዝር (የአማርኛ ርእሶቹን በእንግሊዝኛ
እየተረጎመ ጭምር) ቢሰጠኝም እዚህ መዘርዘሩ ጥቅሙ አልታየኝም። እዚህ ላይ "የከርሞ ሰው" (
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትያትር ከታየ ከአንድ ዓመት በኋላ በ1959 ዓ.ም የታተመ)የተሰኘ
ተውኔቱን ወደ እንግሊዝኛ "The Seasoned (One)" ብሎ በመተርጎሙ ብዙ ሰዎች
የአማርኛው ርእስ እቅጭ ትርጉም ምን እንደነበር እንደገና እንዲያስቡበት መሆናቸውን
ያስታውሷል።

ፀጋዬ ገብረመድህን በአማርኛ እንደሚጽፉ ሌሎች ደራሲዎች በኢትዮጵያ ብቻ የሚታወቅ


አይደለም። የእንግሊዝኛ ተውኔቶቹ በአፍሪካ፣ በአውሮጳ ብሎምበአሜሪካ ለመድረክ በቅተዋል።

በ1951 ዓ.ም ፀጋዬ በቺካጎ ከሚገኘው ብላክስቶን የህግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪውን
ተቀብሏል።ከዚህ በቀደመ ወቅት በኢትዮጵያ አለመኖሩን ወይም ጉዞ ማድረጉን ባለመጥቀሱ
ትምህርቱን የተከታተለው በርቀት ሳይሆን አይቀርም፤የሚያውቁት ሰዎችም ይህንን ሀሳብ
ያጠናክራሉ።ከዚያ የዩኔስኮን ነፃ የትምህርት እድል በማግኘቱ ከ1951–1952 ዓ.ም የለንደን
ሮያል ቲያትርና የፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴን ጎብኝቷል፤ወደ ዊንድሶር ሮያል ቲያትርና የሮም ኦፔራ
አዳርሽም አጭር ጉብኝት አድርጓል። የዚህ ሁሉ ጉዞ አላማ "ኤክስፐርመንታል" ቲያትር ለመማር
ነው።

ፀጋዬ ገብረመድህን ስሙ ከአፍሪካ የነፃነት እንቅስቃሴ ጋር ብዙ ጊዜ ተያይዞ ይነሳል። ስለዚህ ኬንያ


በ1955 ዓ.ም የነፃነት በአሏን ስታከብር የኢትዮጵያ ልኡክ መሪ ነበር። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት
በ1955 ሲመሰረትም በአካል ተገኝቷል፤የኢትዮጵያ አብዮትን ለመደገፍም ብዙ አስተዋጽኦ
አድርጓል።

ፀጋዬ ብዙ ትልልቅ የሚባሉ ስራዎች ነበሩት። ከ1953–1963ዓም ድረስ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ቲያትር (ኋላ ብሔራዊ ቲያትር) ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን፣ ከ1959–1966ዓም (የአብዮቱ ፍንዳታ
ድረስ) ደግሞ የዚሁ ቲያትር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሰርቷል። ከ1967–1968 ድረስ
294
ጥቋቁር አናብስት

በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቋሚ ፀሐፊ ነበር። በ1969 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ክፍል
ተባባሪ ፕሮፌሰር ነበር። በዚህ ውይይታችን ወቅት (1980 ዓ.ም)የባህል ሚኒስቴር አማካሪ ነበር።

ከ1966ቱ አብዮት በኋላ ፀጋዬ አብዮታዊ ለውጡን የሚደግፉ ብዙ ተውኔቶችን ፃፈ ፤ ከዚህም


ባሻገር በቀድሞ ስራዎቹ ውስጥ አብዮታዊ ወይም "ቅድመ–አብዮታዊ" ባህሪያትን “አግኝቷል”፤
ነገር ግን እነዚህ ባህሪያት በሚገባ በመደበቃቸው፣በ1958 ዓ.ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን
አለምአቀፍ ሽለማት፣ በሥነ ጽሑፍዘርፍ ለማሸነፍ በቅቷል።

በፀጋዬ ተውኔት ድርሰቶቹ፣ በግጥም ጽሑፎቹ፣ በአፍሪካ ባህል ጥናትና ምርምሩ ሙሉ ለሙሉ
የተዋጠ ይመስላል።የሚያውቁት ሰዎች ሲናገሩ፣ በጨዋታ ወቅት "ከመስኩ" ውጪ ያሉ አርእስቶች
ሲነሱ የመጫወት ፍላጎቱ ይጠፋል።የሥነ ጽሑፍ ውጤቶቹ ብዛት አስደናቂ ነው፤ ይሁን እንጂ
የአፍሪካ ቅድመታሪክ ጥናቶቹ ግምታዊ ስለሚሆኑብኝየማያሳምኑ ሆነው ባገኛቸውም፣
የሚያነሳሱትን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ፣ የእሱን አመለካከት መስማት ግን ደስ ይላል።

ፀጋዬ ገብረመድህን ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ነው። ረዥም፣ በራው ከፊቱ ገለጥ ያለ፣ ቀጭንና
የስኳር ህመም ታማሚ ነው። ብዙ የሥነ ጽሑፍ ስብስቦችወይም የደራሲያን ማኅበሮች አባል ነው።
በብዛት የፃፈ፣በእጅጉ የተጓዘ ደራሲ ሲሆን ለሥነ ጽሑፋዊ አስተዋጽኦው ተመጣጣኝ የሆኑ ዳጎስ፣
ዳጎስ ያሉ በርካታ ሽልማቶችን ተቀብሏል።ከአውራ ኢትዮጵያዊ ደራሲያን አንዱ ነው።

እዚህ ልገልፀው ከሞከርኩት በላይ አስደናቂ ሕይወት እንደነበረው እርግጠኛ ነኝ ፤ ነገር ግን


ስለራሱ በደንብ አድርጎ አልነገረኝም። ስለራሱ ብዙ "ደረቅ" መረጃዎችን (የስራዎቹን ዝርዝር፣
የሽልማቶቹን ዝርዝር፣ የጉዞ ዝርዝር፣ አባል የሆነባቸውን ማህበሮች ዝርዝር ወዘተ)ሰጥቶኛል። ፀጋዬ
ገብረመድህን እንደ ሰው ምን ይመስላል የሚለውን ማወቅ የሚፈልጉ አሁንም ጥቂት ጊዜ መጠበቅ
ይኖርባቸዋል። "ጥንቁቅነቱን" አንድ ቀን ቀነስ እንደሚያደርገው ተስፋ አደርጋለሁ። እስከዛው
ድረስ ግን፣ በዚሁ መጽሀፍ ላይ ሕይወታቸው ከተዳሰሰላቸው ጓደኞቹ ማህደር፣ ስለ ስራው
አንዳንድ ጠቃሚ እውነቶችን ማግኘት ይቻላል። ፀጋዬየራሱ የሕይወት ታሪክ "አላስፈላጊ" መስሎ
ሊታየው ይችላል፤ "መጽሀፎቼን አንብቡ"፣ "ቲያትሮቼን ተመልከቱ" ከሚሉት ወገንም ይሆን
ይሆናል። ከዚህ በተረፈግን ዝምታን መርጧል―ቢያንስ ለጊዜው።

295
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻ(የደራሲው)

፡- በ1987 ሌላ ኢትዮጵያዊ ደራሲ፣ ፀጋዬ ገብረመድህን ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ እንደታሰረ


ነገረኝ።

የተርጓሚ ማስታወሻ የብላቴንጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን (1929-93) ዓ.ም የተላያዩ ስራዎቹ
ደጋግመው የታተሙ ሲሆን የተላያዩ ጸሐፍት ግለታሪኩን ጽፈውታል፡፡

ማስታወሻዎች

1) ቀኑን የነገረኝ ፀጋዬ ራሱ ነው። ነገር ግን በሌላ አጋጣሚ የተወለደው በ1929 ዓ.ም እንደሆነ
ተናግሯል፣ ጽፏልም። ይህ ግን እንግዳ ነገር ነው። በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከተቀመጠው ቀን
ጋር ይጋጫል። አንድ ምንጭ ፀጋዬ የተወለደው ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ከወረረች ከስድስት ወር በኋላ
መሆኑን ገልፆ ነበር።

2) ፀጋዬ ይህን ታሪኩን ሲናገር ቃልኪዳኑ በሀዲስ አለማየሁ "ፍቅር እስከ መቃብር" ውስጥ ዋና ገፀ
ባህሪው ላይ ከሚደርስበት ነገር ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስተውሏል።

3) ይህ ከፀጋዬ አፍ የሰማሁት ቀን፣ በፊት እንደተባለው በ1929 ሳይሆን በ1928 እንደተወለደ


ያመለክታል።

296
ጥቋቁር አናብስት

መንግስቱለማ
የቧልታይ ተውኔት ፋና ወጊ፣ ፀሐፌ–ተውኔት እና
ገጣሚ በንጉሱ ዘመን ተማሪዎች በተደጋጋሚ የአቤ ጉበኛን
ስራዎች ማንበቤን ይጠይቁኝ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን
የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ እንደምከታተል የሚያውቁ
ኢትዮጵያውያን የሚጠይቁኝ የመንግሥቱ ለማ ስራዎችን
ማንበቤን ነው። መንግስቱ ከ1966ቱ አብዮት በፊትም ሆነ በኋላ በግጥምም ሆነ በተውኔት በደንብ
ከሚታወቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲያን መሀል አንዱ ነው። ብዙዎች ቅኔን ለማብራራትና ለማሳተም
ያደረገውን ጥረት ያደንቃሉ።

የመንግሥቱ ለማ ሁለት ቀደምት ተውኔቶች ቧልታይ ነበሩ። ይህ የሥነ ጽሑፍ ዘውግ በኢትዮጵያ
የተለመደ አይደለም ። እነዚህ ሁለት ተውኔቶች “ላይ ላዩን” ሲታዩ ስለ ጋብቻ ይመስላሉ።
ርእሳቸውም (“ጠልፎ በኪሴ” እና “ያላቻ ጋብቻ”) ይህንን አመላካች ነው። ነገር ግን ተውኔቶቹ
ከጋብቻ ባሻገር ጥልቅ ጉዳዮችንም ይዳስሳሉ። ሁለተኛው ተውኔት በመደብ ልዩነት ውስጥ
የሚፈጠር ጋብቻን የሚያሳይ ነው፦ ከተለያየ መደብ የመጡ ጥንዶች ጋብቻ “ተቀባይነት” አለው?
እነሱስ ደስተኛ ይሆናሉ? ስለ“መደብ ልዩነት” በግልጽና በቀጥታ ማውራት በማይቻልበት ወቅት
መንግስቱ ለማ ቧልትን ተጠቅመው ጥያቄውን በተዘዋዋሪ መንገድ አንስተዋል።በነፃነት
የማይነገረውን፣ የማይተቸውንና ማህበረሰቡን ውስጥ ውስጡን ያኘከውን እውነታ የሳቅና የመዝናኛ
ምንጭ አድርጎታል። መንግስቱ ይህንን ለማድረግ ባህላዊውን የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ አብጠርጥሮ
ማወቁ እጅጉን ጠቅሞታል። ተውኔቱ ብዙ ትርጉም እንዲሰጥ አድርጎ መፃፉን ተክኖበታል። ፍፁም
ቀልድ መስሎ የሚታየው የተሰወረ “ጥልቅ” ትርጉም ነበረው። ቀጥተኛውም ትርጉምም ቢሆን ያንኑ
ያህል አስፈላጊ ነው። የዘመኑ ወጣቶች ማንን፣ እንዴት ባለ ሁኔታ ማግባት እንዳለባቸው ሞቅ ያለ
ክርክር አካሂደዋል ።ተምረናል የሚሉት አንዳንዶች “ዘመናዊ” ሚስቶችን ሲመርጡ፣ መንግስቱ
ለማን ጨምሮ ሌሎቹ፣ ከ“ባእድ ባህል” ይልቅ ኢትዮጵያዊ ስርአትን ያስበለጡትን ይመርጡ ነበር።
ለነገሩ “ባእድ ባህል” የተባለውም ቢሆን፣ ያን ያህል ሥልጣኔ የዘለቀው አልነበረም።
መንግስቱ“ለማህበረሰቡ ታይታ” ሲባል የሚደረገውን የተንቀላጠጠውን የኢትዮጵያ የሰርግ ሥነ
ስርዓት፣ ከሚቃወሙት መሀል አንዱ ነበር።

297
ጥቋቁር አናብስት

ይህ በባህላዊነት እና ዘመናዊነት መሀል ያለ ክርክር የመንግሥቱ ለማ ሥነ ጽሑፋዊ እና ምሁራዊ


ስራዎች ቋሚ ባህርይይመስላል። ብዙ የውጪ ሀገሮችን ተዘዋውሮ ቢያይም፣ በዩኒቨርስቲዎቻቸው
ቢያጠናም፣ በመላው አለም ብዙ ወዳጆች ቢያፈራም፣ መንግስቱ እስከመጨረሻው ድረስ ከሀገሩ
ባህል እና ታሪክ ጋር በጥልቅ የተሳሰረና የተቆራኘ ነበር። ስራዎቹ ሁሉ ለሀገሩና ለባህሏ ያለውን
ጥልቅ ፍቅር ይመሰክራሉ። የሀገሩን ታሪክ፣ እውቀት እና ሥነ ጥበባዊ ቅርስ ገና በለጋነቱ ያሰረፁበት
ገናናው አባቱ ለዚህ ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም።

****

መንግሥቱ ለማ የተወለደው ሰኔ 1 1928 በአዲስ አበባ ቢሆንም፣ ገና በልጅነቱ ሐረር ሄዶ


እዚያው አደገ። ወደ ሐረር የተጓዘው አባቱ ሐረር ውስጥ የሚገኝ ትልቅ ደብር አለቃ ሆነው
በመሾማቸው ነው። መንግሥቱ ከወላጆቹ ስምንት ልጆች (6 ወንዶች እና 2 ሴቶች)መሐል
የመጨረሻው ነው። አባቱ አለቃ ለማ ከላስታ፣መቄት ሲሆኑ እናቱ ወይዘሮ አበበች ይልማ ከሰሜን
ሸዋ፣ ተጉለት ናቸው። አባቱ “ተራ ቄስ” አልነበሩም።አለቃ ለማበወቅቱ በቤተክህነት የሚሰጠውን
ጥንታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ከፍ ባለ ደረጃ የሚያስተምሩ ባለቅኔና ሊቅ ነበሩ። መንግስቱም
ጥልቅ እና ዘለአለማዊ ተጽእኖ ያሳደሩበትንየአባቱን ንግግር ቀርጾ ”መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ”
የተሰኘ መጽሐፍ በጎልማሳነቱ ጽፎላቸዋል። ይህ ማስታወሻ አባቱ ለዘመናት ያለፉበትን የሕይወት
ውጣ ውረድ ከመከተቡም በላይ የኢትዮጵያን ባህል እና ታሪክ በተመለከተም ብዙ ጠቃሚ
መረጃዎች አሉት። የተፃፈበት ቋንቋም ከንግግር የተቀዳ በመሆኑ፣ የተዋበ እና “ተፈጥሮአዊ” ፍሰትን
የጠበቀ ነው።መጽሐፉ መታሰቢያነቱ ለአለቃ ለማ ብቻ አይደለም። ይልቁንም ጠብቀው እና
አበልጽገው ያቆዩት ባህል ከዘመን ዘመን ተሸጋግሮ አሁን ድረስ እንዲዘልቅ ላደረጉት
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት መዘክርም ጭምር ነው።

መንግስቱ ለማን ሕይወቱን በተመለከተ ቃለመጠይቅ ላደርግለት እንደምፈልግ ስገልጽለት አንድ


ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ልማድን አስታወሰኝ፦ ደራሲዎች ስለራሳቸው እንዲያወሩ ወይም እንዲጽፉ
የሚያበረታታ ልማድ የለም፤እንዲያውም ብዙ ጥንታዊ ድርሳናት የተጻፉት ደራሲዎቻቸው ጭራሽ
ሳይገለጹ ነው።መንግሥቱም ይህንን ስለሚያምንበት ሕይወቱን በተመለከተ ጠለቅ ብሎ ለማውራት
ፈቃደኛ እንዳልሆነ ነግሮኛል።1 በሌላ በኩል ደግሞ ካሁን በፊት ስለሱ ለፃፉ ሰዎች የነገራቸውን
ለኔም ለመድገም አልፈለገም።ስለዚህ ቃለመጠይቁን ከማድረጋችን በፊት ላነባቸው የሚገባኝን
ጥቂት ጽሁፎች አመላከተኝ።እኔም ካሁን በፊት ስለሱ የተባለውንና የተፃፈውን መድገም
እንደማልፈልግና አዲስ ነገር ለማቅረብ እንደምሻ ተናገርኩ። ስለዚህ ከዚህ በታች የምታነቡት
ከራሱ አፍ የሰማሁት፣እንዲሁም ከሌሎች ያልታተሙና በአማርኛ ብቻ ታትመው ከሚገኙ
ህትመቶች የተውጣጡ ናቸው።2
298
ጥቋቁር አናብስት

መንግስቱ በሐረር ትምህርቱን የጀመረው በቤት ውስጥ፣ብሎም በጣም ታዋቂ በሆነውአባቱ


በሚያገለግሉበት ደብር በመካነሥላሴ ቤተክርስቲያን ነበር። በዚያም ዜማን እስከ ድጓ፣ ቅኔእና
የቅዱሳት መጽሐፍትን ትርጓሜ ተማረ። በተለይ የቅኔ መምህሩ በመንግሥቱ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ
አሳድረውበታል። ከዚህ በኋላ "ዘመናዊ" ትምህርት ቤት ገብቶ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን
ተከታተለ፤ሁሉንም ትምህርቶች ቢወዳቸውም "የጂምናስቲክ" ክፍለጊዜግን የጊዜ ብክነት እንደሆነ
ይቆጥረው ነበር።

በሥነ ጽሑፋዊ እና ሥነ ጥበባዊ ስራዎቹ ላይ ተጽእኖአቸው ጎላ ብለው ከሚታዩት መሀል የግእዝና


የአማርኛ ቅኔ፣የአዲስ ኪዳን ትርጓሜ፣ ውዳሴ ማርያም፣ የቤተክርስቲያን ዝማሬ(ግጥሙም፣
ዜማውም) ይገኙበታል። ከዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ትሩፋቶች መሀል ደግሞ፣የከበደ ሚካኤል
እና የኅሩይ ወልደሥላሴ ስራዎች ጉልህ አሻራቸውን አሳርፈውበታል።

በትርፍ ጊዜው በሸክላ አፈር የተለያዩ እንስሳትን፣የአእዋፍን እና የሰዎችን ምስል መቅረጽ፣ በውሃ
ቀለምም ሆነ በባለቀለም እርሳሶች ምስሎችን የመንደፍ ሥነ ጥበባዊ ዝንባሌዎች ነበሩት።

በሐረር የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ኮተቤ በሚገኘው
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ የለንደን ኮሌጅ
መግቢያ ፈተና ተፈትኖ አለፈ። ከዚያ ወደ እንግሊዝ ተሻግሮ የሥነ ማህበረሰብ፣ የፖለቲካ ሳይንስ
እና ኢኮኖሚክስ ትምህርቱን በለንደን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስና የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ቤት
ተከታተለ። መንግስቱ ዩኒቨርስቲው በጊዜው “የስርነቀል ምሁራን ማፍሪያ” ነበር ይላል። ለአንድ
ዓመት ያህል በለንደን ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የታዋቂው ፖለቲካል ሳይንቲስት እና የሶሻሊስት
ሀሮልድ ላስኪ ተማሪ ነበር። ላስኪ ተማሪዎቹ ላይ ጉልህ ተጽእኖ በማሳረፍ ይታወቃል።
መንግስቱም ስርነቀል ዝንባሌዎችን የወሰደው ከዚህ አስተማሪው እንደሆነ ይናገራል።

መንግስቱ ከተማሪነቱ ባሻገር በታላቋ ብሪታንያ፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር ውስጥ ንቁ አባል
እና የማኅበሩ ጋዜጣ The Lion Cub አዘጋጅ ነበር። ኋላ የማህበሩ ፀሐፊ ብሎም ፕሬዚዳንት
እስከመሆን ደርሷል። የውጪ ሀገር ቆይታው እና ተሞክሮዎቹ በ1955 የግጥም ጉባኤ በሚል ርእስ
በታተመው መጽሐፉ በሥነ ግጥም መልክ ተከስተዋል።ከስድስት ዓመት የውጪ ሀገር ቆይታው
በኋላ መንግስቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ሀገሩን ለማገልገል ተዘጋጀ።

****

የመጀመሪያ ስራው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን፣ የስታትስቲክስ ክፍል ሐላፊነት ነበር። ከዚያ
በኋላ ለብዙ ዓመታት የሰራው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ሲሆን፣ በመጀመሪያ ስራው ሕንድ፣
299
ጥቋቁር አናብስት

ኒው ደልሂ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋና ፀሐፊ ሆኖ ለአምስት ዓመት አገልግሏል። ቀጥሎ


በዚያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ የጥናት ክፍል ዋና ሀላፊ ሆኖ ሰራ። በመጨረሻ በውጭ ጉዳይ
ሚኒስቴር የተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክንፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሆነ።

ከዚያ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ተዛወረና የአማርኛ ቋንቋ አካዳሚ ዋና ፀሐፊ ሆነ። ከ1966
አብዮት በኋላ የባህል ሚኒስቴር ሲቋቋም የአማርኛ ቋንቋ አካዳሚ ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች
አካዳሚ እንደገና በዚሁ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስር ሆነ። መንግስቱም የዚሁ አካዳሚ ዋና ፀሐፊ
ሆነ። ከዚህ ባሻገር ጊዜያዊ ወታደራዊ የደርግ አስተዳደር ባቋቋመው ጊዜያዊ የመማክርት ሸንጎ
ውስጥ እንዲያገለግል በባህል ሚኒስቴር ሰራተኞች ተመርጦ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወር አገለገለ።
በኋላ በሥነ ጽሑፍ ጉዳዮች ኤክስፐርትነት ወደ ባህል ሚኒስቴር ተመለሰ።

መንግሥቱ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጡረታ የሚወጡበት እድሜ ላይ ቢደርስም የኢትዮጵያ ሥነ


ጽሁፍና ቋንቋዎችን በተመለከተ ባለው ልምድና የላቀ ችሎታ ምክንያት ሁለት የስራ መደቦችን
ደርቦ ይሰራ ነበር፦ በባህል ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት
እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የድራማ ትምህርት ክፍል የተውኔት አጻጻፍ ቴክኒኮች
መምህርነት ናቸው።

መንግስቱ ለማ ከሁሉም አብልጦ ይፈልገው የነበረው በባህል ከሚመስሉት የሀገሩ ሕዝቦች ጋር


መነጋገርን ነው። ለዚያም ነው ሳያቋርጥ በአማርኛ ቋንቋ የሚጽፈው።ይህንን በቋንቋ ላይ ያለውን
አመለካከት "የህዝብ ቋንቋ እንደ ሥነ ጽሑፍ ቋንቋ" በተሰኘ የ1975 መጣጥፉ ግልጽ አድርጎታል።
ይህ ክርክር ያኔም፣ እስከ መንግሥቱ የሕይወት ፍፃሜ፣ ከሞተም በኋላ የቀጠለ በኢትዮጵያውያን
ደራሲዎች ዘንድ ያለ ክርክር ነው። ይሁን እንጂ ተውኔቶቹ ወደሌሎች ቋንቋዎች እንዳይተረጎሙ
በፍጹም አልተከላከለም። እንደውም ከአብዮቱ በፊት የፃፋቸውን ሁለት ተውኔቶች ራሱ ወደ
እንግሊዝኛ ተርጉሟል። ከነዚህ መሀል"ያላቻ ጋብቻ" የተሰኘውን ተውኔት ወደ ሩስያ ቋንቋ
ተተርጉሟል። ከነዚህ ስራዎቹ በተጨማሪ ከአብዮቱ በፊት በግጥም መልክ የተዘጋጁ ተረቶችን
ሰብስቦ "የአባቶች ጨዋታ" በሚል ርእስ አሰናድቷል። በዚህ ወቅት በአፃፃፍ ቴክኒክ፣ በአማርኛ ሥነ
ጽሑፍና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ብዙ መጣጥፎችን ከትቧል ፤ እነዚህን የመሳሰሉ የጥናት
ወረቀቶቹን በአለምአቀፍ ጉባኤዎች ለምሳሌ በሩስያ፣ ስዊድን፣ ኢትዮጵያ በተዘጋጁ መድረኮች ላይ
አቅርቧል። ለዚህ አስተዋጽኦው ሀገራዊውን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሽልማት ድርጅትን ሽልማት
በ1960 ሲቀበል፣ በ1961 ደግሞ አለምአቀፋዊ (አፍሪካዊ) የሆነውን በካሊፎርኒያ ሎስአንጀለስ
ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ጥናት ማእከል የሚዘጋጀው የአፍሪካ ሥነ ጥበብ መጽሔት የሚሰጠውን፣
የመላው አፍሪካ የድራማ ሽልማት አሸንፏል። መንግስቱ ለማ ዘመናዊ ድራማን ለማህበራዊ
ትችት/ሂስበማዋል ፈር ቀዳጅ ነው።3

300
ጥቋቁር አናብስት

ከዚህ በፊት እንደተቀመጠው የመንግሥቱ ቀደምት ተውኔቶች ቧልት ቀመስ ናቸው።ሆኖም “ቁም
ነገር አዘል” ቀልዶች እንጂ ስላቅ/ሽሙጥ አልነበሩም።ምፀትን ወይም ግነትን ሳይጠቀም የኑሮን
እውነተኛ ገጽታ ለማሳየት እንደሞከረ ይናገራል። እንዲያውም ራሱን በህልም ሳይሆን በማህበራዊ
ሂስ እንደተጠመደ “ሪያሊስት” አድርጎ ይቆጥራል። በቴክኒክ ረገድ ተጽእኖ ያሳረፋበት ሞሊየር፣
ጎጎል፣ ኢብሰን እና ጆርጅ በርናርድ ሾው ናቸው ይላል። ቧልታይ ተውኔቶቹ ማህበራዊ እንከኖችን
ነቅሶ ለማውጣት የሚታትሩ ተራማጅና ለውጥ ናፋቂ ናቸው። የተውኔቶቹ ነገረ–ጉዳይ ጋብቻ
ቢሆንም፣ ጭብጣቸው ግን ከዚያም ላቅ ያለ መሆኑን ከአብዮቱ በኋላ ተናግሯል።

ከውጪ እንደተመለሰ፣ የጋብቻ ጉዳይ ችግር ሆኖ ጠበቀው። አንዳንዶች ለፍቅር ብለው ቢያገቡም፣
አብዛኛዎቹ ወንዶች ግን ሃብትና የኑሮ ደረጃን ለጋብቻ እንደ ቅድመሁኔታ ያስቀምጣሉ። መንግስቱ
በሁለቱ ተውኔቶቹ የኑሮ ደረጃን ወደጎን ብለው ለፍቅር ያገቡትን ያገናቸዋል።በወቅቱ ይህ እንደ
“አብዮታዊ” የሚባል አቋም ነበር ይላል። በመንግስቱ አመለካከት እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ
የእውነተኛ ጋብቻፋና ወጊዎች ነበሩ። ከእንደዚህ ዐይነት ሰዎች መሀል አንዱ ባህሩ ነው። ባህሩ
ከመኳንንት ወገን የተወለደ፣ "ያላቻ ጋብቻ" የተሰኘ ተውኔቱ ዋና ገፀባህሪ ነው። ባህሩ በሚስጥር
የቤት ሰራተኛውን ማግባቱን ተከትሎ የሚመጣውን ማህበራዊ ጣጣ በጀግንነት ሲታገል ይታያል።
ደራሲው እንደሚለው በተውኔቱ ለማስተላለፍ የተፈለገው “ጥልቅ” መልእክት “በነባሩና በአዲሱ፣
በልማዳዊውናአዲስ በሚፈጠረው እሳቤ መሀል ያለው የማያቋርጥ ግጭት የሚወልደውን
ማህበረሰብ አቀፍ ለውጥ አስፈላጊነት ማሳየት ነው”ይላሉ፡፡

መንግስቱ በጊዜው በኢትዮጵያ ያልተለመደውን ቧልትን በተደጋጋሚ መጠቀሙን በተመለከተ


"ኮሚክ ድራማ ለመጻፍ ሁኔታዎች ረድተውኛል" ይላል። “የወቅቱ የፖለቲካ አየር ትራጀዲ ለመፃፍ
የተመቻቸ አልነበረም። ትራጀዲ የህዝቡ ምሬት የሚገለጽበት መንገድ በመሆኑ፣ አመጽ ይቀሰቅሳል
ተብሎ ስለሚፈራ ይታፈን ነበር። ኮሜዲ ግን እንደ ማደንዘዣ ስለሚቆጠር በቀላሉ ተቀባይነትን
ያገኛል። ስለዚህ ማህበራዊ ትችቴን ለመግለጽ ቧልትን ምቹ ሆኖ አገኘሁት። ተውኔቱቹ አንድ
ልማድን የሚጥስ ዋና ገፀ ባህሪያት አይጠፋቸውም። መኮንን እንዳልካቸው እና መሰል ቀደምት
ፀሐፊ–ተውኔቶች የገዢው መደብ አባል በመሆናቸው መሰረታዊ ለውጥ የሚያቀነቅኑ ማህበራዊ
ሂሶችን ለመፃፍ አልተቻላቸውም። ስለዚህ የነበረውን ስርአት የሚደግፉ፣ ግብረገባዊ ተውኔቶችን
ጻፉ።እኔ ከተለያዩ ሀገራት የሥነ ጽሁፍ ባህል ጋር የነበረኝ ትውውቅ በኢትዮጵያ የሥነ ጽሁፍ ባህል
ውስጥ ከተለመደው ሁኔታ ገንቢ በሆነመልኩ እንዳፈነግጥ ረድቶኛል። በጊዜው ከነበሩ የኢትዮጵያ
ፀሐፌ ተውኔቶች ምንም አዲስ ነገር ልማር አልቻልኩም ፤ ምክንያቱም እነሱ ስለ ቴክኒክ
አስፈላጊነት የሚያውቁትነገር አልነበረም።"

301
ጥቋቁር አናብስት

"ጠልፎ በኪሴ" የተሰኘው ተውኔት ያልተለመደ ባይሆንም፣ ትንሽ ወጣ በማለት ሚስት ለማግኘት
በሚደረግ ድርጊት፣ ማለትም በጠለፋ ዙሪያ የሚያተኩር ነው። ጠለፋ በኢትዮጵያ ባህል አዲስ ነገር
ባይሆንም ተውኔቱ ግን አዳዲስ ነገሮችን አካቷል። ጠላፊው፣ ጓደኞቹና ተጠላፊዋ ሁሉም ከተማ
ያደጉ፣ የተማሩ ወጣቶች ናቸው። ደራሲው በተውኔቱ “ተምረው ከወሬ ያለፈ ጠብ የማይል፣
ስርነቀል ለውጥ ሊያመጡ ያልቻሉ ወጣቶችን” ይተቻል። የተውኔቱ ዋና ገፀባህሪ በዛብህ ለማሳካት
ያለመው ነገር መና ሆኖ ቢቀርም “ሙከራው መደነቅ አለበት ፤ ቢወድቅም ለተከበረ አላማ ነው”
ጨምሮም መንግስቱ “ ዋና ገፀባህሪዬ ሁሌም ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት የሚታትር ነው”
ይላል። ስለ ሁለቱ ተውኔቶቹ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ "በዛብህ እና ባህሩ ( የሁለቱ ተውኔቶች ዋና
ገፀባህሪያት)ፍፁም እኔነቴን የሚገልጡ ናቸው፤መሰረታዊ አመለካከቴ በነሱ አማካይነት ስጋ ለብሶ
ይታያል። ሁለቱም ተውኔቶች በአንድ ጭብጥ ዙሪያ/ይሽከረከራሉ//ላይ/ያተኩራሉ፦ በነባር እና
መጤ መሀል ስላለው የማያቋርጥ ግጭት።"

የአጻጻፍ ዘዬውን በተመለከተ ሁለቱን ዋና ተነጻጻሪ የቅኔ ዘውጎችን ካወዳደረ በኋላ የበለጠ የሳበውን
መንገድ እንደመረጠ ይናገራል። የዋድላ ቅኔ አስተምህሮ በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት ቅኔ ብዙም
ረብ የለውም ይላል። የዚህ ዐይነቱ ቅኔ ወዳጅ ፍልሱፋን"የቅኔ ውበቱ ስውርነቱ" መሆኑን
በመግለጽ ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። ሌላኛው የቅኔ ዘውግ (የጎንደሩ)የዚህ ፍፁም ተቃራኒ
ነው። ለነሱ ጥሩ ቅኔ የሚባለው “ቀላል ሆኖ ረቂቅ፣ ግልጽ ሆኖ ድንቅ ሲሆን ነው። በዚያው ልክ
ጥልቅና ቁምነገር ያዘለ መሆን አለበት ባይ ናቸው።” መንግስቱም ሆነ አባቱ ይህንን የጎንደር ዘውግ
ተከትለዋል፤ለዚህም ግጥሞቹ እና ተውኔቶቹ ምስክር ናቸው። የአባቱን የንግግር ለዛ “ግልጽና
የአድማጮቻቸውን ቀልብ በቀላሉ የሚገዛ በመሆኑ” ይወደዋል። “ቀላልና የነጠረ ሃሳብ እና ቋንቋ
ማዳበር መቼም ጠንክሮ መስራትን ይፈልጋል፤ የተሰወረ ሁሉ በቀላሉ እንዲታይ አልተለፋበትም”
ስለዚህ መንግስቱ የግዕዝ ቃላትን በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ አለቅጥ በመጠቀም እዩኝ እዩኝ
የማለት አባዜ አይዋጥላቸውም። የአንድ ፀሐፌተውኔት ቀዳሚ አላማ ተደራሲያኑ በቀላሉ
እንዲረዱት ማድረግ ነው። ተውኔት እንደ ሥነ ጥበብ ዘርፍ ለሽሽግነት አይመችም። ስለዚህ
የተውኔት ቋንቋ ረቂቅ፣ ግን ለመረዳት ቀላልመሆን አለበት።” በተውኔት ውስጥ ሴራው እና
ቀልዳቀልዱ“የተሰጥኦ ጉዳይ” ቢሆንም መንግስቱ ይህንን ተሰጥኦ የታላላቆቹን ከያኒያን ስራ
በማጥናት ማበልፀግ ይቻላል ብሎ ያምናል። በቴክኒኩ ውስጥ ስሌት፣በኪነጥበብ ውስጥ ደግሞ
ሙያ አለ። ( መንግስቱ ይህንን አመለካከቱን የገለፀው ከ1966ቱ አብዮት በኋላ በጣም ቆይቶ
በመሆኑ፣ እነዚያ ቅድመ–አብዮት ሁለት ቧልታይ ተውኔቶቹን በፃፈበት ወቅት እነዚህ ሀሳቦች ምን
302
ጥቋቁር አናብስት

ያህል ጥርት ብለው አእምሮው ውስጥ እንደነበሩ አላውቅም። እነኚህ አመለካከቶች ለ"አዲሱ
ዘመን" በልኩ የተሰፉ በመሆናቸው፣ የሰዎች ሕይወት በፃፉት ነገር ምክንያት አደጋ ላይ
በሚወድቅበት ዘመን ጠቅመውታል)

ከ1966ቱ አብዮት በኋላ መንግስቱ ኮስተር ያሉ ጽሑፎችን ወደማሳተም ተሸጋገረ። ጽሑፎቹ


ግጥምም፣ ተውኔቶችም ሲሆኑ ግጥሞቹ የራሱ፣ ከተውኔቶቹ ደግሞ ከፊል የራሱ፣ ከፊል ደግሞ
የተተረጎሙ አጫጭር ተውኔቶች ( ከአብዮቱ በፊት ተዘጋጅተው የተቀመጡ ነበሩ ይላል) ናቸው።
የመጀመሪያው "ባሻ አሸብር በአሜሪካ" ነው። ይህ የግጥሞች ስብስብ ከአብዮቱ በፊት የተፃፈ
ቢሆንም "ተራማጅ አስተሳሰብ ያጠላበት በመሆኑ የሳንሱር ክፍሉን ፍቃድ ለማግኘት ብዙም እድል
አልነበረውም።" በእርግጥ ለርእስ የተጠቀሙበት ግጥም በንጉሱ ዘመን ሳይቀር በብሔራዊ የሬዲዮ
ጣቢያ በስፋት ይሰራጭ ነበር።ቃለመጠይቃችንን እስካደረግንበት ጊዜ ድረስም "ቀልድ ቀመስ ነገር
ግን ቁምነገረኛ መልእክት ካላቸው በስፋት ከሚታወቁት ግጥሞቹ" መሀል "ባሻ አሸብር በአሜሪካ"
ዝነኛው ነበር። ከዚያም "ባለካባ እና ባለዳባ"ን ፃፈ። ከአብዮቱ በፊት የተተረጎሙ ሁለት ባለ አንድ
ገቢር ተውኔቶች ለህዝቡ እይታ የበቁት ከአብዮቱ በኋላ ነበር። የአንቷን ቼኾቭ "The Bear"
(ዳንዴው ጨቡዴ) እና የግብፃዊው ጸሐፌ ተውኔት፣ የወግ እና ልብወለድ ጸሐፊ፣ እንዲሁም
አብዮተኛ ቶፊቅ አል–ሀኪም (ከተለያዩ ምንጮች እንደተገኘው በአሌክሳንድሪያ እ.አ.አ በ1898
ወይም 1903 ተወልዶ በካይሮ በ1987 የሞተ) "Lust to Kill" (ግደይ ግደይ አለኝ) ናቸው።
እነኚህ ሁለቱም ተውኔቶች በቴሌቪዥን ለሕዝብ ቀረቡ። መንግስቱ ገና በእንግሊዝ እያለ
በአማተሮች የተከናወውን የጄ ቢ ፕሪስትሊን "An Inspector Calls" ተከታትሎ በጣም
ወዶታል። ይህ ተውኔት የተተረጎመው ፖለቲካ ቀመስ ተውኔቶችን እንድጽፍ የሚፈልጉ ሰዎችን
ፍላጎት ለማሟላት ነበር።"ጠያቂ" በሚል ርእስ መድረክ ላይ ለሕዝብ ቀረበ። ከዚህ በኋላ ሌሎች
ሁለት ተጨማሪ ተውኔቶችን ፃፈ። ትራጀዲ የሆነው "ፀረ ኮሎኒያሊስት" (ርእሱን የመረጠው
የሳንሱር ክፍሉን አማክሮ ነው) እና ምፀታዊ ኮሜዲ የሆነው እና በቀድሞው አስተዳደር በከፍተኛ
ሹመኞች መሀል ተንሰራፍቶ የነበረውን ንቅዘት የሚዳስሰው፣ በ1975 የተፃፈው "ሽሚያ" ነው።
ከአብዮቱ በኋላ የፃፋቸው ሶስት ኮስታራ ተውኔቶቹ ተሰብስበው "የተውኔት ጉባኤ" በሚል ርእስ
ታትመዋል። የመንግስቱ ተውኔቶች በሙሉ ከአንዱ በስተቀር በብሔራዊ ቲያትር ሲታዩ፣ "ባለካባና
ባለዳባ" ብቻ በሀገር ፍቅር ቲያትር ተከፍቷል።

303
ጥቋቁር አናብስት

***

መንግስቱ “ተውኔትና ግጥም በተፈጥሮ የተቆራኙ ስለሆኑ ሁለቱ የሥነ ጽሑፍ ዘርፎች አብረው
ይሄዳሉ፤ድራማ የሚጽፍ ደራሲ ግጥምንም ሆነ ተውኔትን በስንኝ መሰደር ይችላል” ብሎ ያምናል።

መንግስቱ ለማ በትርፍ ጊዜው ሁሉ ያነባል ወይም ድርሰት ይጽፋል። ልክ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ


ደራሲዎች ሁሉ እንጀራ ለመብላት ሌላ ስራ ያስፈልገዋል። በቃለመጠይቃችን ወቅት እንዳባቱ ገና
ለረዥም ጊዜ ለመፃፍ ይመኛል።“አባቴ በ97 ዓመታቸው ቅኔ ይዘርፉ ነበር፤እኔም ቢያንስ እስከ 87
አመቴ እጽፋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብሏል።

መንግስቱ ለማ ቁመቱ አጠር ያለ፣ ፀጉሩም ገባ ያለ ሲሆን፣ ስለዚህም አብዝቶ መቀለድ


ይወዳል―ሆኖም መላጣው ላይ ጣል የሚያደርጋት ኮፍያ በተለይ ወደ ሕይወቱ ማብቂያ አካባቢ
ከእጁ አትለየውም ነበር። ተግባቢ ፊቱ ዘወትር ደማቅ ፈገግታን ይለግሳል።

የሕይወቱ የመጨረሻ ዓመታት ላይ ሪህ እያሰቃየው ስለነበር ዱላ ይዞ ይንቀሳቀስ ነበር።ይሁን እንጂ


በሕይወቱ የመጨረሻ ዓመታት እንኳን እንዲህም ሆኖ ዩኒቨርስቲ መመላለሱን አልተወም ፤
ከደራሲዎች እና ምሁራን ጋር መገናኘቱንም አላቆመም። አንዳንዶች ብቸኝነትን እና ጠንክሮ
መስራትን ያዘወትር ነበር ይላሉ። በጣም ታዋቂ ሲሆን በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ላይ የነበሩት
አስተያየቶች ተፈልገው የሚደመጡ ነበሩ። በዚሁ ወቅት ከብዙ ታዋቂ ደራሲዎች ጋር በመተባበር
የግእዝ ቅኔን በማሰባሰብ፣ ወደ አማርኛ በመተርጎም፣ ሰምና ወርቃቸውን በመተንተን ለብዙ
ዓመታት ሰርቷል። ይሄም በ1979 በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ታትሟል። ከመሞቱ በፊት ግለ
ታሪኩን በተመለከተ መጽሀፍ እየፃፈ እንደሆነ ባይነግረኝም፣ ታሪኩን በዚሁ መጽሀፍ የዳሰስኩለት
አማረ ማሞ ግን መንግስቱ ለማ በእርግጥም የግለ ታሪኩን ዐይነት ረቂቅ እንዳሳየው አውግቶኛል።

***

በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ተውኔቶች የቀረቡት በትምህርት ቤት ውስጥ ነበር። ዮፍታሔ ንጉሴ4፣


መላኩ በጎሰው እንዲሁም "የጎንደሬው ገብረማርያም ጀብዱዎች"ን የፃፈው ሙዚቀኛው ካፕቴን
ናልባንዲያን በዚህ ረገድ ፋናወጊዎች ነበሩ። የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በ1927 ሲከፈት፣ የአዲስ
አበባ ማዘጋጃ ቤት ደግሞ በ1940ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ስራ ጀመረ። በኢትዮጵያ ትልቁ ትያትር
ቤት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቲያትር ቤት(ኋላ ብሔራዊ ቲያትር) የተመሰረተው በ1948 ዓ.ም
ነበር። ይህ ቲያትር ቤት ከተከፈተ በኋላ ግብረገባዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ይዘት ያላቸው

304
ጥቋቁር አናብስት

ተውኔቶች የሰላ ማህበራዊ ሂስ በሚያወርዱ ተተኩ።5ይሄንን አዲሱን የተውኔት ነፋስ ተከትለው


"አዲስ የቲያትር ዘዬ"ከፈጠሩት መሀል መንግስቱ ለማ፣ ፀጋዬ ገብረመድህን፣ ተስፋዬ ገሰሰ እና
ሌሎችም ይገኙበታል። ከአብዮቱ በኋላ "አዲሶቹ ፋና ወጊዎች" ተከተሉ። ለምሳሌ ብርሀኑ
ዘርይሁን፣ አያልነህ ሙላትእና ሌሎችም።

መንግስቱ ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ስላበረከተው አሰተዋጽኦ እና ስለፈጠረው ተጽእኖ ከማስተጋባት


የተቆጠበ ቢሆንም፣ በጊዜው ግን በሐገሪቱ ውስጥ ከሚታወቁ፣ ከሚከበሩ እና ከሚደነቁ ጸሐፊዎች
መሀል ዋነኛው ነበር። የሚጽፈው“ሥነ ጽሑፍ ልፋቱ ፍሬ ያለውና አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው”
ብሎ ስለሚያምን ነው።

***

ከቃለመጠይቃችን በኋላም ቢሆን መንግስቱን ሳገኘው ሁሌም ፈገግታ ከፊቱ የማይጠፋ እና


ተጫወች ሲሆን ። ሪሁ እየባሰበት ስለመጣ፣ ዱላዋ አትለየውም ነበር። ድንገት ግን በግንቦት
1980 በጣም ታሞ ሆስፒታል መግባቱን ሰማሁ። መጀመሪያ የገባው ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል
ቢሆንም ከሁለት ሳምንት በኋላ የተሻለ ምቾትና አገልግሎት ወዳለው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
ተዛወረ። ሰኔ ላይ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ልጠይቀው ስሄድ የጠናባቸው ህመምተኞች
በሚታከሙበት ክፍል ተኝቶ አገኘሁት ።ለብዙ ሳምንታት ምግብ የሚወስደው በደምስሩ በኩል
ነበር። እኔ ስጎበኘውና ለመጀመሪያ ጊዜ ምግብ ሲመገብ አንድ ሆነ። በጣም ከስቷል፤ደግሞም
በጣም የተዳከመ ይመስላል፤ነገር ግን እየተሻለው እንደመጣ ይናገራል ፤ ወዳጆቹም በቅርቡ
ከሆስፒታል እንደሚወጣ ጠብቀዋል።እየደከመውም ቢሆን ሲያናግረኝ ደስተኛና ጨዋታ በጣም
ይወድ ነበር ( ጓደኞቹ እንደነገሩኝ አንዴ ጨዋታ ከጀመረ ብዙ ጉዳዮችን መነካካት ስለሚወድ ለሱ
ከመደወላቸው በፊት ሰፊ ጊዜ እንዳላቸው እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ) ይሁን እንጂ ሳይተርፍ
ቀረ።

መንግስቱ ለማ ሐምሌ 27 1980 ዓ.ም ልክ ከቀኑ 12:00 ሰአት ላይ ሞተ። እንደወዳጆቹ ከሆነ
ላለፉት 15 ዓመታት በሪህ በሽታ ተሰቃይቷል፤ለዚህ ህመሙ ማስታገሻ ከባድ መድሀኒቶችን
ይወስድ እንደነበርም ጨምረው ይናገራሉ።ስለዚህ እነኚህ ህመም ማስታገሻዎች ጉበቱንና ኩላሊቱን
ሳይነኩት እንዳልቀረ ይገምታሉ።እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ የቤት ሠራተኛ እንኳን
አልነበረውም፤ ስለምግቡ እና ጤንነቱ መጨነቅም አቁሞ ነበር። በተጨማሪም ከመሞቱ ከሶስት
ዓመት በፊት አቆመው እንጂ በጣም ይጠጣ እንደነበርም ሰምቻለሁ።መንግስቱ እያገገመ እያለ
ኬንያ ነበርኩ ፤ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ህመሙ አገረሸበትና ስመለስ መሞቱ ተነገረኝ። በሞተበት

305
ጥቋቁር አናብስት

ቀን በአስር ሰአት አካባቢ ጠያቂዎች አነጋግረውታል፤ነገር ግን ከሁለት ሰአት በኋላ ሐኪሙ ሁሉም
ነገር እንዳበቃለት ተናገረ። እንደ ኤድዋርድ ኡለንዶርፍ እና ሪቻርድ ፓንክረስት ያሉ ጓደኞቹ ወደ
እንግሊዝ ሄዶ ኩላሊቱ የሚቀየርበትን ሁኔታ ቢያመቻቹለትም፤በጥቁር አንበሳ በቂ የኩላሊት
እጥበት ባለመኖሩና ኩላሊት የሚሰጥ ሰው ባለመገኘቱ ሳይሳካ ቀረ።

መሞቱ በይፋ የተገለፀው ከሁለት ቀን በኋላ በመሆኑ ብዙ ሰዎች በሀምሌ 29 የሞተ


ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሐምሌ 29 1980 መንግስቱ ለማ ቀጨኔ በሚገኘው መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የተቀበረበት ቀን ነው።

***

የመንግሥቱ ለማን የሕይወት ታሪክ ስጽፍ፣ገና ከመገናኘታችን በፊት በሌላኛው መጽሐፌ ላይ


ስለፃፈኩት ጉዳይ በሰፊው የተጫወትነውን እዚህ ውስጥ አላካተትኩትም። "Tradition and
Change in Ethiopia" በሚለው መጽሐፌ የመንግሥቱን "መኖር መላ አገኘ" የሚለውን
ግጥም ፀረ–ማርክሳዊ ትርጓሜ ሰጥቼው ነበር። በጊዜው ኢትዮጵያ ማርክሳዊ ስለነበረች፣ ፀረ–
ማርክሳዊ አመለካከቶች ማንፀባረቅ አደገኛ ነበር። ስለዚህ መንግሥቱየኔን ትርጓሜ በጠንካራ
ቃላትየሚቃወም መልስ በታህሳስ 17 1980 በኢትዮጵያን ሄራልድ ፃፈ። ከዚያ በኋላ
"ይጠራጠረኝ" ነበር። በፃፈው ነገር ባልስማማም፣ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ችግር
እንዳልፈጥርበት ብዬ ነገሩን ተውኩት። ከብዙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ አማርኛ ሥነ ጽሑፍ
አውርቻለሁ ፤ መንግስቱን የሚያውቁት ሁሉ የሚነግሩኝ ከላይ በተጠቀሰው ግጥም ውስጥ
"መስኩ" ተብሎ የተገለፀው የሞስኮ ከተማን በተመለከተ ሌላ ትርጉም የሚሰጥ ነው ይላሉ፤
እንደውም መንግስቱ ራሱ ስለዚህ ፍንጭ ሰጥቷል ብለውም ይጨምራሉ። በነበረው የፖለቲካ
ሁኔታ ምክንያት ሃሳቤን በይፋ መደገፍ ባይቻላቸውም የኔ ትርጓሜ ከመንግሥቱ ወጥ ሀሳብ
እንደተቀዳ ወደማመኑ ተቃርቤያለሁ። ነገር ግን የተጻፈ ማስረጃ ስለሌለኝ፣ትርጓሜው የራሴ
እንደሆነ አድርጌ ለማቅረብ ተገድጄያለሁ። አንዳንድ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች በትርጉሙ
ባይስማሙም፣ ኢትዮጵያውያኑም ነገሩ ቅኔ አዘል ሊሆን እንደሚችል ቢያምኑም፣ እርግጠኛ
ባለመሆናቸው፣ ግጥሙ ላይ ያለኝን አስተያየት አሳጥሬዋለሁ። ከመንግሥቱ ጋር በተገናኘሁ ጊዜ
ግጥሙ በፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት በ"ግምት" የታጠረ ባይሆን፣ በደንብ አብራርቼ ልጽፍበት
እንደነበረ ነገርኩት። ሙሉ ትርጓሜዬ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። በመጽሀፌ ውስጥ መንግስቱ
ብኄርተኛም፣ ተራማጅም ሆኖ ተስሏል። ግጥሙ ፀረ ማርክሳዊ ወይም ፀረ ሶሻሊስታዊ ከመሰለ፣
የኔ ትርጉም እነኚህን ሁለቱን አመለካከቶቹን ከግምት ውስጥ ሊያስገባ ይችላል።በ1953ዓም
መፈንቅለ መንግስቱ በማርክሳዊ አቀንቃኞች በተሞከረበት ጊዜ ወይም ከዛ በፊት ኢትዮጵያ
306
ጥቋቁር አናብስት

የነበሯት "የነቁ" ማርክሲስቶች በጣም ጥቂት ነበሩ። በጊዜው የተሳካ መፈንቅለ መንግስት ወይም
አብዮት ቢካሄድ፣ ስልጣን ላይ የሚወጡት ሰዎች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ያላቸው ብቸኛ
አማራጭ የኮሚኒስታዊ ሀገሮችን እርዳታ መሻት ነው ፤ በወቅቱ ይህንን ዐይነት ድጋፍ ማድረግ
የምትችለው ብቸኛ ሀገር ደግሞ ሩስያ ወይም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን እንደሚጠሯት "መስኮብ"
ነበረች። መንግስቱ የሶሻሊስት ርእዮተ አለምን ሳይቃወም፣ እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ብኄርተኛ፣
ትንሽ የሶሻሊስቶች ጥርቅም፣ ከውጪ ትእዛዝ እየተቀበሉ ሀገሪቱን ማስተዳደራቸው ላይዋጥለት
ይችላል። ይሄ ሁሉ የራሴ ግምት ብቻ ባይሆን በወረቀት ሳላሰፍረው አልቀርም ነበር። ይህንን
ለመንግስቱ ስገልጥለት፣ “በትክክል!” ብሎ ስለመለሰለኝ የኔን ትርጓሜ መቀበሉን አረጋገጠልኝ።ይህ
ታዲያ መጽሀፌ ላይ የፃፍኩትን ከመደገፉም በላይ በወቅቱ መንግስቱጋዜጣው ላይ ይህ ተራ የፍቅር
ግጥም ከመሆኑ የዘለለ ሚና የለውም ብሎ የፃፈውን ያፈርሳል።7 ስለዚህ እሱ የፃፈውን ከቁምነገር
እንዳልቆጥረውና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ8 በነበረው ሁኔታ ምክንያት ሕይወቱንና ደህንነቱን
ለማስጠበቅ ሲል የፃፈው መሆኑን ገለፀልኝ። አሁን ሳያምነኝ አልቀረም፤አለበለዚያ ይህንን ሁሉ
ባልነገረኝ ነበር። መንግስቱ ጠንቃቃ እና ተጠራጣሪ ሰው ነበር።ከእኔ ጋር ቃለመጠይቅ ለማድረግ
ከመስማማቱ በፊት በስልክ ብዙ አውርተናል። ልጠይቀው ያሰብኩትን ጥያቄዎች በወረቀት ላይ
እንድጽፋቸው አደረገና በሌላ ሰው አማካኝነት ላኩለት። በኋላ በኢትዮጵያ እንደ ትልቅ የወዳጅነት
መግለጫ የሚቆጠረውን አብሮ ማዕድ የመቁረስ ሥነ ስርዓት ስንካፈል አሁን በመተማመን በጋራ
ጉዳዮች ላይ ከልብ እንደምናወራ እርግጠኛ ሆንኩ። ነገር ግን ጥርጣሬውን ዳግም ሊያነሳሱ
የሚችሉ "ስሜትን የሚነኩ" ጥያቄዎችን ማንሳት አስፈራኝ። የግል ጉዳዮችን የሚመለከቱ ብዙ
ጥያቄዎችን ብጠይቀው ደስ ባለኝ ነበር፤ ለምሳሌ ስለ አስተሳሰብ ለውጡ፣ የሚወዳቸውና
የሚጠላቸው ነገሮች፣ በተለያየ ጉዳዮች ላይ ስላለው አመለካከት ወዘተ። ነገር ግን ይህ የሚሆን
አልነበረም።

በሁለት ቀደምት ቧልታይ ተውኔቶቹ መንግስቱ የጋብቻን ጉዳይ ያነሳል። ሌላ ሰው እንደነገረኝ፣


መንግስቱ እንደሌሎች የተማሩ ወጣቶች ሳይሆን፣ ባህሏን የምታከብር ሴት ማግባት ይፈልግ ነበር።
ያገባውም እንደዚህ ያለች ሴትን ነው።በእርግጥ ዘመነኛ ከሚባሉ ጥቂት ሴቶች ጋር
(ከመሀከላቸውም አንዷን ወይም ሌላዋን ለማግባት እስከመፈለግ ያደረሰ) ፍቅር ይዞት እንደነበር
ስለሚወራው አሉባልታ መጠየቁ ተገቢ አይደለም። ነገር ግን ከእንግሊዝ እንደተመለሰና ከመሞቱ
23 ዓመት ቀደም ብሎአንድ ወንድ እና ሴት ልጅ ያፈራ ጋብቻውን ሲበትን ስለ ጋብቻ ተመሳሳይ
አቋም ይኑረው አይኑረው መጠየቅ ብፈልግም ስሜቱን ይነካል ብዬ ተውኩት።

መንግስቱ ለማ በባለስልጣናቱም ሆነ በሌሎች ዘንድ ጥሩ ሶሻሊስት ተደርጎ ይቆጠራል። በኢትዮጵያ


ባህል በተለይ በሥነ ጽሑፉ እና ተውኔት ዝንባሌ ለሚያሳዩ ማርክሲስት ወጣቶችም እንደ አርአያ

307
ጥቋቁር አናብስት

ይወሰዳል። ነገር ግን አንዳንድ የቅርብ ጓደኞቹ "ክርስቲያን ሶሻሊስት" እንደሆነ ነው የሚያውቁት፤


ክርስቲያን የምትለው ተቀጥላ፣ነገር ውስጥ እንዳትዶለው በሚስጥር ይዟታል። አስተዳደጉ እንደ
ክርስቲያን ቢሆንም በእንግሊዝ ቆይታው 9ለሶሻሊስታዊ እና ሌሎች ዘመናዊ ሀሳቦች በመጋለጡ
ክርስቲያናዊው መሰረቱ “እንደሸሸ” ወዳጆቹ አጫውተውኛል። ነገር ግን ከ1966ቱ ሶሻሊስታዊ
አብዮት በኋላ መንግስቱ ወደቀድሞው የክርስቲያን መሰረቱ ተመልሷል። እንዲያውም በ Living
Bible International አማካኝነት ለሚዘጋጀው የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም የቋንቋ አማካሪ ሆኖ
ይሰራ ነበር። መንግስቱን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባው ሒልተን ያገኘሁትም የመጽሐፉ ኮሜቴ
አንድ ስብሰባ ሲጠናቀቅ ነው።

አማረ ማሞም መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ዘመናዊ አማርኛ የሚተረጉመው የዚህ ኮሚቴ አባል ነበር።
ለረጅም ጊዜ መንግስቱ ጀምሮት የነበረውን የግል ግለ ታሪኩን መጽሀፍ እንዲጨርስ ጎትጉቶታል ።
ለመጨረሻ ጊዜ ሆስፒታል ከመግባቱ ሁለት ወር ቀደም ብሎ መንግስቱ አማረን ቤቱ ምሳ
ይጋብዘውና ያለቀውን ረቂቅ ያሳየዋል።አማረ ይህ ረቂቅ በግምት ከ300–400 ገጽ ይሆናል ይላል።
(የአማረ ማሞን የሕይወት ታሪክ በዚሁ መጽሀፍ ታገኙታላችሁ) መንግስቱ መጽሐፉ አልቋል ነገር
ግን አንዳንድ ነገሮችን መከለስና ማስዋብ ይቀረኛል ብሎ ነበር። ይህ ረቂቅ መንግስቱ ከሞተ በኋላ
ቤተሰቦቹ ( ልጆቹን እና የጥንት ሚስቱን ጨምሮ) ከሚጣሉበት ነገሮች መሐል ጠፍቶ እንደማይቀር
ተስፋ አደርጋለሁ።10ስለ ኢትዮጵያ ባህል እና ሥነ ጽሑፍ ብዙ የሚያስደስቱ ጨዋታዎች አካቶ
ሊሆን የሚችል ይመስለኛል። በሌላ በኩል በሌላ ቦታ እንደነገሩ የተገለፁ ነገሮች ተደባብሰው
ይቀራሉ። መንግስቱ ከዳግማዊ ሚኒልክ ጋር ዝምድና እንዳላቸው ጠቀስ አድርጓል፤ሌሎች ሰዎች
ይህንኑ ቢያረጋግጡልኝም መረጃው ግን አስተማማኝ አልነበረም። የጉራጌ ዘር እንዳለበት ተናግሮ
ካለማወቁም በላይ ስለዚህ የነገረኝ ዘመዱ ጭራሽ እንዳላነሳበት አሳሳበኝ። አለበለዚያ ሊከፋና ይህ
ዘመዱ ሆን ብሎ እሱን ለመጉዳት አስቦ እንደነገረኝ ሊያስብ ይችላል። ነገር ግን ለጓደኛው ሚካኤል
እምሩ ይህን ጉዳይ ሳነሳበት፣ መንግስቱ የዘር ጉዳይ ብዙም እንደማያስጨንቀው አረጋገጠልኝ ፤
እኔም በዚህ ሀሳብ እስማማለሁ። ስለዚህ ዘመዱ የነገሩኝን ነገር መንግስቱን ለመጉዳት ሳልሞክር
እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

***

የመንግሥቱ ቅድመ አያቶች ወሎ ውስጥ በላስታ ሸደሆ፣ አቡነ አሮን ቤተክርስቲያን አካባቢ
በምትገኝ መቄት11 በምትባል ትንሽ መንደር ገበሬዎች ነበሩ። አያቱ አቶ ሐይሉ ወልደታሪክ እዚህ
ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲኖሩ በቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ፊደል ቢቆጥሩም ገፍተው
ሳይሄዱበት ገበሬ ሆነው ቀሩ። ከሀይሉ ልጆች መሀል አንዱ ለማ ከሀይሉ በቤተክርስቲያን ትምህርት
308
ጥቋቁር አናብስት

መጀመሪያ በአቡነ አሮን፣ ቀጥሎ በጎንደርና በጎጃም ዲማ ተማረ (የሀይሉ ዝርያ ከጎጃም ሁሉ
ይመዘዛል) ቀጥሎ ለማ የአንኮበሩ አለቃ ሀይለማርያም ዘንድ ይማራል። ከዚያ ሐይለማሪያም
የአንጎለላ ኪዳነምህረት አለቃ ሆነው ሲሾሙ እርሳቸውን ተከትሎ ሄደ።12 ለማ ትምህርታቸውን
ከጨረሱ በኋላ ወይዘሪት አበበችን አገቡ። የአበበች አባት ተጉለቴ ሲሆኑ፣ እናቷ የባሻ ተጎዳ ልጅ
ናቸው። ባሻ ተጎዳ ጉራጌ ሲሆኑ ስራቸው ኮርቻ ማበጀት ኋላም ለዳግማዊ ምኒልክ ኮርቻ የሚሰሩ
ሰዎችን መቆጣጠር ነበር። ለማ እና አበበች ስምንት ልጆች ሲያፈሩ ከነዚህ መሀል ስድስቱ ወንድ
ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ነበሩ። ነገር ግን ሁሉም መንግስቱን ቀድመው ሞተዋል። ወንዶች ልጆቹ
የሚከተሉት ናቸው፦ መአዛ–ክርስቶስ የተባለው ብልህ እና ዝምተኛ ሲሆን በጽሕፈት ሚኒስቴር
ይሰራ ነበር ፤ ጥቂት መጽሐፍትንም ጽፏል ፤ ሁለት ጊዜ አግብቷል ( ከመጀመሪያዋ ሚስቱ ጋር
በፍቺ ሲለያዩ ሁለተኛዋ እስከ 1980 ድረስ በሕይወት ነበረች)፤የሞተው በስኳር በሽታ ነበር ፤
ከሁለቱም ሚስቶቹ ልጆች ወልዷል። ልሳነ–ክርስቶስ እስከለተ ሞቱ በሐረር ኖሯል።መርሐ–
ክርስቶስ በአዲስ አበባ የተማረ የሥነ ህንጻ ባለሙያ ሲሆን፤አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ፈረንሳይኛ፣
ጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ይናገራል ፤ የሞተው ከአብዮቱ በፊት በመጠጥ ጠንቅ ነው።13 ገብረ–
ክርስቶስ ከአብዮቱ በፊት ሞቷል። ቀጥሎ የተወለደው መንግስቱ ሲሆን ትክክለኛ ስሙ መንግስተ–
ክርስቶስ ነበር። የቀረውን አንድ ወንድ ልጅና የሴቶቹን ስም ለማወቅ አልቻልኩም። ከሁሉም
ረዥም እድሜ የኖረው መንግስቱ ነው።

የመንግስቱ ዘመድ አባቱ አለቃ ለማ ሀይሉ ስለፃፉት አንድ ግጥም አጫውቶኝ ነበር። በአንድ
አጋጣሚ አለቃ ሀይሉ አዳልጧቸው ይዘውት የነበረው ባለ እንጨት ክርታስ ዳዊትላይ ይወድቁና
ጎድናቸውን ክፉኛ ይጎዳሉ። ከዚያም የሚቀጥለውን ስንኝ ደረደሩ፦

ከጎልያድ እንኳ ዝምድና የለኝ

አሁን በምን ነገር ዳዊት ገደለኝ

መንግስቱ ለማ ዝነኛ ሰው ቢሆንም፣ ጓደኞቹ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ። እነዚህ ጥቂት ጓደኞቹ፣
ለጓደኝነታቸው ትልቅ ግምት የሚሰጡ ነበሩ።

የተርጓሚው ማስታወሻ-የመንግስቱ ለማ ግለ-ታሪክ(ደማሙ ብዕረኛ) መጽሐፍ ታትሞ ለገበያ


ቀርቧል፡፡

309
ጥቋቁር አናብስት

ማስታወሻዎች

1) ይኼንን እንኳን ያለው እንደቀልድ ሳይሆን አይቀርም ምክንያቱም መንግስቱ ብዙ መቶ ገፆች


ያሉትን ግለ ታሪኩን እየፃፈ እንደሆነ ከቅርብ ሰዎቹተረድቼያለሁ ፤ ይህ ረቂቅ ከመሞቱ ከጥቂት ጊዜ
በፊት ተጠናቋል።

2) በጽሑፍ ካገኘኋቸው መረጃዎች ጠብሰቅ ያለው መንግስቱ ለአካሉ ጌታነህ ሰጥተውት በማባዣ
የተዘጋጀቃለመጠይቅ ነው( ይህንን ቃለምልልስ ከመንግስቱ ጋር በማደርግበት ወቅት አካሉ በአዲስ
አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ነበር) ሆኖም ከዚህ ምንጭ አንዳንድ ማስታወሻዎችን ከወሰድኩ በኋላ
መንግስቱ የኔን ማስታወሻ ማየት ፈለገ። ከዚያም አንዳንዶቹን ሲያርም፣ ሌሎችን ደግሞ በአዳዲስ
ቃላት ተክቶፃፋቸው። ስለዚህ ከአካሉ ጌታነህ ከተዋስኳቸው ላይ ጭምር ከማስታወሻዎቼ ላይ
ትእምርተ ጥቅሶችን አስወግጄያለሁ። (የኔን ማስታወሻ ተመልክቶ ካፀደቀልኝ በኋላ ትእምርተ
ጥቅሶቹን እንዳስወግዳቸው ሐሳብ ያቀረበልኝ ራሱ መንግስቱ ነው፤ ምክንያቱም አካሉ የእርሱን
ሀሳብ ቃል በቃል እንዳሰፈረ ተደርጎ እንዳይወሰድ ስለፈለገነበር።እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳቦቹ እንደ
አዲስ ተጽፈዋል ባይ ነው።ነገር ግን የመንግስቱ ከአካሉን ጽሑፍም ሆነ የኔን ማስታወሻ ሲያርም
እንዳሉ እንዲተዉ የፈለጋቸው አንዳንድ ገለፃዎች በትእምርተ ጥቅስ መካከል እንዳሉ
ትቼያቸዋለሁ። ስለዚህ አንዳንዶቹ አስተያየቶች የመንግሥቱ የራሱ እንጂ የእኔ አለመሆናቸውን
ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ)። ሌሎች የመረጃ ምንጮችም ተጠቅሜያለሁ፤ በይበልጥ ከራሱ ከአብዬ
መንግስቱ ጋር ያደረግኳቸው ጨዋታዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

3)በተክለሐዋርያት ተክለማርያም የተፃፈው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ተውኔት "የእንስሳቶች


ኮሜዲ ወይም ፋቡላ" በተመሳሳይ የሚጠቀስ ነው። ደራሲው ተውኔቱን ከፃፉት ከብዙ ዓመታት
በኋላ "ተውኔቱን የፃፍኩት በጊዜዬ የነበሩትን ብልሹ ባለሥልጣኖችን በጠንካራ ትችት ለማስደንገጥ
ነበር" ብለዋል። ደራሲው የተፃፈው ለእያሱ ነው ብለው ቢያስረግጡም የተፃፈው በእያሱ ዘመን
(1905–1908) ነው ወይስ በዘውዲቱ (1908–1923) የሚለው አከራካሪ ነው።

4) አንዳንዶች "የአማርኛ ተውኔት አባት" ነው ይሉታል። ለምሳሌ "አፋጀሺኝ" የተባለውን ተውኔት


ጽፏል። ብዙ ደብዳቤዎቹና ታሪኩን የሚያስረዱ ሌሎች ሰነዶች በኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት፣
በአዲስአበባ ይገኛሉ።

310
ጥቋቁር አናብስት

5) እንደ የብርሀኑ ዘርይሁን "ባልቻ አባ ነፍሶ" እና የማሞ ውድነህ "አሉላ አባነጋ" የመሳሰሉ
ተውኔቶች ብዙ ተመልካች ሲስቡና ለረዥም ጊዜ ሲታዩ ማህበራዊ ሂስ ያዘሉ ታሪካዊ ተውኔቶች
በ1980ዎቹ መጨረሻላይ እንደገና ዝነኛ ሆኑ።

6) በተመሳሳይ መድበል ወስጥ በሚገኝ አንድ ሌላ ግጥም ላይ መንግስቱ በአማርኛው "ኪስ"፣


“ክስ” በሚሉት የአማርኛ እና "kiss" በሚለው የእንግሊዝኛ ቃል መካከል ድርብ ትርጉም
ሊሰጠው የሚችል ሁኔታን በመቅረጽ በቃላቶቹ ይጫወትባቸዋል። kiss ከአማርኛው ቃል ከ“ክስ”
በጣም በተለየ አነባበብ የሚባል ቃል ነው። በሁለቱ ቃላት መሀል ያለው የአነባበብ ልዩነት
በ"መስኮብ" እና "ሞስኮ" መሐል ያለውን ልዩነት ያህል ይሆናል።

7) መንግሥቱ ስለ ስጋዊ ፍቅር ጽፏል ነገር ግን በስሜ ስለሚገለጽ ፍቅር ለመፃፍ ብእሩን አንስቶ
ስንኝ አልደረደረም።ስለንጹህ ፍቅር ብቻየተጻፈግጥም እኔ ራሴበእጄ ጽፌያለሁ ቢለኝ እንኳን፣
እውን የእሱ አይመስለኝም ነበር፤ ከባህሪው ጋር አይገጥምምና። "መኖር መላ አገኘ"ም ሙሉ
በሙሉ የፍቅር ግጥም ነው ብዬ አላስብም። ከዚህ ቀደም ለዚህ ግጥም የሰጠሁትን ፀረ ማርክሲሳዊ
ትርጓሜ በይፋ እንዳነሳለት ይፈልግ እንደሆን ስጠይቀው፣ ያን እንዳደርግ እንደማይፈልግ በግልጽ
ነግሮኛል።

8) የኔ ትርጓሜበስራው ላይ ችግር እንዳይፈጥርበት በጣም ስለተጨነቀ የራሱን መጣጥፍ


የመንግስት ርእዮተ አለም ክፍል ሐላፊዎች ጋር እስከ መውሰድ እንደደረሰ ነግሮኛል። በጊዜው
በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው ስርአት የተነሳ ራሱን መከላከልና እኔን ማጣጣል ነበረበት። ሁሌም
ጠንቃቃ ሰው ነበር። ስለራሳቸው የፈለጉትን ከነገሩኝ በኋላ ምን እንደፃፍኩ እንዳሳያቸው ከጠየቁኝ
ሁለት ሰዎች መሀል አንደኛው መንግስቱ ለማ ነው። ከዚያም በጥንቃቄ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
በኋላ ግን የራሴ ረቂቅ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች አከልኩበት።( ከመንግስቱ ሌላ ስለሱ የፃፍኩትን
ለማየት የጠየቀኝ ሌላው ደራሲ ታደሰ ሊበን ነው)

9) ምንም እንኳን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ቢማርም ዲግሪውን እንዳልተቀበለ ጓደኞቹ ነግረውኛል።

10) መንግስቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍ ብሎ ተከራይቶ የሚኖርበትን ቤት ኪራይ ለረዥም


ጊዜ ስላልከፈለ እንደሞተ የቀበሌው ባለሥልጣኖች ቤቱን በማሸግ ማንም ሰው የመንግሥቱ
ንብረት ላይ እንዳይደርስ አድርገዋል። ቀበሌው አንዳንድ የመንግሥቱን ንብረቶች በመሸጥ ገንዘቡን
ለማስመለስ ሳይሞክር አልቀረም። በዚህ ሂደት ውስጥ የመንግሥቱ ረቂቅ ግለ ታሪክ እንዳልጠፋ
ተስፋ እናደርጋለን።የአብዮቱ “አገልጋዮች” ከአብዮቱ በኋላ ከቤተመንግሥቱ ቁሳቁስ ከመስረቅ
311
ጥቋቁር አናብስት

ወይም ቄሶችና መነኩሴዎች ከቤተክርስቲያን ወይም ገዳም የወርቅ ዋንጫ ወይም ሌላ ጠቃሚ
ንብረት መስረቅ ካልከበዳቸው፣ የቀበሌው ሰራተኞች ንብረቶቹን ለግል ጥቅም ለማዋል መስረቅ
የበለጠ አይከብዳቸውም። ከአብዮቱ በኋላ ብዙ ረቂቆች አዲስአበባ ላይ በሕገወጥ መንገድ
ሲቸበቸቡ ነበር። የራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው የፀሎት መጽሀፍ እንድገዛ ቀርቦልኝ ነበር
፤ ነገር ግን ይሄ የተሰረቀ ሳይሆን መኮንን ሊሞቱ ሲሉ ለቀድሞው ሾፌራቸው እንደ ስጦታ
ሰጥተውት አሁን ችግር ውስጥ በመውደቁ ለሽያጭ ሰላቀረበው ነው።

11) ጎጃም ውስጥም መቄት የሚባል ቦታ አለ። በዛ ስም የሚጠሩ ከአንድ በላይ ቦታዎች ሊኖሩ
ይችላሉ።

12) አለቃ ኃይለማርያም በ“እብድ አይጥ” ተነክሰው በኋላ ሞቱ። አንድ ደብተራ እንዲገድላቸው
አይጡን የላከው ጠንቋይ ነው ብሏል።

13) በኢትዮጵያ ውስጥ “አልኮል” ተብለው የሚታወቁት ከቢራና ወይን ውጪ ያሉ ብርቱ


መጠጦች ናቸው።

312
ጥቋቁር አናብስት

ታደለ ገብረሕይወት
አብዮተኛና የድሆች አፈቀላጤ

ታደለ ገብረሕይወት በሚያዝያ 15 ቀን 1939 ዓ.ም በሸዋ ክፍለሀገር፣ ወሊሶ


ጨቦ እና ጉራጌ አውራጃ ግዮን ውስጥ ተወለደ። አባቱ ገብረሕይወት በየነ
የመጡት ከጋሞጎፋ ሲሆን አባታቸው ከሸዋ መጥተው የሰፈሩ ነፍጠኛ
ናቸው።ገብረሕይወት ጣሊያኖችን በጀግንነት ተዋግተዋል፤ በመቀጠልም
ፖሊስ ሆኑ። መጨረሻ ላይ ገበሬ የነበሩ ቢሆንም ንብረታቸውን ሁሉ
አጥተው፣ ደህይተው በ1957 ዓ.ም ታደለ የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለ አረፉ።
የታደለ እናት ወይዘሮ አበበች ገዳ በአባታቸው በኩል ግማሽ ጉራጌ፣ግማሽ ኦሮሞ ናቸው (ራቅ ብሎ
የሚቆጠር የትግሬ ዝርያም አላቸው) ታደለ የጉራግኛ ቋንቋን አልለመደም። ይልቁንም እሱ
በተወለደበት አካባቢ በስፋት የሚነገረውን የኦሮምኛ ቋንቋ እየተናገረ አደገ። አራት ዓመት ሲሞላው
ወደ አዲስአበባ መጥቶ ከእናቱ አክስት እና ከባላቸው ጋር መኖር ጀመረ።ባልየው የመጣው “ምርጥ
አማርኛ ከሚነገርበት” ከመንዝነው ይላል ታደለ። ከዚህ ቤተሰብ ጋር ብዙ በቆየ ቁጥር፣ ኦሮምኛ
እየረሳ፣ አማርኛ እየለመደ መጣ። 1

ታደለን ያሳደጉት ጥንዶች በዚያን ጊዜ በጣም አርጅተዋል። ባልየው ጡረታ የወጡ የመንግስት
ባለሥልጣን ሲሆኑ፣ በስራቸው ምክንያት ብዙ ተጉዘዋል ፤ አሁንም ቤተሰቡ አልፎ አልፎ
ስለሚጓዝ አንዳንዴ ታደለን ይዘውት ይሄዳሉ።በቤታቸው "ባሪያዎችና አገልጋዮች" ስለነበሯቸው፣
ለታደለ የድሮ ስርአትን እንዲረዳ አድርጎታል። ሀብታምና ባህላቸውን የሚያውቁ “የሰለጠኑ” ሰዎች
ነበሩ። ልጆቹም እንዲሁ የተማሩና ለታደለም ደግ ናቸው፤በተለይ ከልጆቹ አንደኛው በኢትዮጵያ
አውራጎዳና መስሪያ ቤት የሚሰራ እና በስራው ምክንያት ከሀገር ሀገር የሚዞረው የበለጠ ደግ ነበር።
ለታደለ ይህ ቤተሰብ ተስማምቶታል፤አንዳች ችግር ገጥሞት አያውቅም። ለቤተሰቡ ልብስ እያጠበና
እየተኮሰ፣ ትምህርቱንም አብሮ በጎን ያስኬዳል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ
እስከሚያገኝ ድረስ እዚሁ ቆየ።

በዚያ ወቅት ኢትዮጵያውያን የፊደል ዘር መለየት የሚጀምሩት ቄስ ትምህርት ቢሆንም ታደለ ግን


ወደነዚህ ትምህርት ቤቶች ዝርም አላለ። ትምህርቱን የጀመረው የእንግሊዞች በሆነው ኮከበ ጽባህ
ትምህርት ቤት ነበር (ትምህርት ቤቱ የሚገኘው አስመራ መንገድ፣ የሩስያ ኢምባሲ አካባቢ ነው)።
የመጀመሪያ አስተማሪው አሜሪካዊት ነበረች።ምንም እንግሊዝኛለማይሰማው ታደለ፣
የመጀመሪያው ዓመት “በጣም ከባድ” ነበር። ነገር ግን አራተኛ ክፍል ሲደርስ እንግሊዘኛውን
313
ጥቋቁር አናብስት

ማቀላጠፍ ስለቻለ፤ ከዚያ በኋላ ትምህርት አስደሳች ሆነ። በዚሁ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ
ክፍል ተምሮ አጠናቀቀ። በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት እሱና ሌሎች ከአንድ ደርዘን የሚበልጡ
ተማሪዎች የጥናት ቡድን አቋቁመው ስለወደፊት እቅዳቸው ይነጋገራሉ። በዚህ ውይይት ወቅት
ታደለ ደራሲ መሆን እንደሚፈልግ ይገልፃል። የመጀመሪያ የፈጠራ ጽሑፉን በመፃፍ እጁን
ያፍታታውም ይሄኔ ነው። የሼክስፒርን "የቬኒሱ ነጋዴ"ለተማሪዎች በሚገባ ቀላል እንግሊዘኛ
እንደገና ፃፈው። ተውኔቱን ለመድረክ ከማብቃቱም በላይ፣ እራሱም ተውኖበታል። ተውኔቱ
ትምህርት ቤት ውስጥ በሚገኘው ትልቅ አዳራሽ ታየ፤“እስከ10,0002የሚደርሱ ሰዎች
ተመልክተውታል” ይላል ታደለ። "ይህ አጋጣሚ ነው ቃጭሎ) ወደ ሥነ ጽሑፍ ጎዳና የመራኝ"
ይላል።

ከኮከበ ጽባህ በኋላ፣ታደለ አዲስ አበባ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት ገብቶ የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርቱን አጠናቀቀ። ዘጠነኛ ክፍል ላይ ቀለል አድርጎ የተረጎመውን "የቬኒሱ ነጋዴ " ዳግም
ለመድረክ አበቃው። ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከብዙ ደራሲያን ጋር የመገናኘቱን እድል አገኘ፤ እነሱም
ደራሲ መሆን እንዳለበት መከሩት። መምህራኑም አበረታቱት። ከዝነኛው ገጣሚ እና ፀሐፊ
ተውኔት ከጸጋዬ ገብረ መድህን እና በሙያው ኢኮኖሚስት ሆኖ ለሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ ዝንባሌ
ካለው ከአስፋው ዳምጤ ጋር ተዋወቀ።ብሪትሽ ካውንስል ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራትም ጋር
ለመተዋወቅ ቻለ። ታደለ እየበሰለ የመጣበት ጊዜ ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ግጥሞችን
በእንግሊዝኛ ይጽፍና ሰኞ ለአስተማሪዎቹ አሳይቶ አስተያየት እንዲሰጡት ይጠይቃል። ብዙዎች
ሙከራውን ሲያደንቁለት፣ ግጥም የመፃፍ ተሰጥኦ እንዳለው እያመነ መጣ። ከዚያም ስፖርትና
ሌሎች መዝናኛዎችን ቀነስ አድርጎ ብዙ ጊዜውን መጽሐፍት ቤት ያሳልፍ ጀመር። በጊዜው
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቲያትር ቤት ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት እና በቲያትር ቤት ውስጥ
የሚታዩትን አብዛኛዎቹን ተውኔቶች የደረሱት ፀጋዬ ገብረመድህን ያበረታቱት ነበር ፤ ዘወትር
በየሁለት ሳምንቱም ፊልም እንዲመለከት ነፃ ትኬት ይሰጡታል፤ በጊዜው በቲያትር ቤቱ ውስጥ
ከተውኔቶች ይልቅ ፊልሞች በብዛት ይታዩ ነበር። ታደለ አሁን በተውኔቶች ውስጥ መሳተፍ
ጀምሯል ፤ ለምሳሌ በትምህርት ቤቱ ውስጥ በእንግሊዝኛው "ኦቴሎ" ውሰጥ እንዲሁም በቀዳማዊ
ኃይለ ሥላሴ ቲያትር ቤት በቀረበው የፀጋዬ ገብረ መድህን "ሀምሌት" ትርጉም ውስጥ ተውኗል።
ይሁን እንጂ በጊዜው የቲያትር ተመልካቾች በጣም ጥቂት ነበሩ፤ አንዳንዴ በአዳራሹ ውስጥ
የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ላይበልጥ ይችላል።

ታደለ የንግድ ስራ ትምህርቱ አልጣመውም፤ይልቁንም ተውኔት አና ሌሎችም ሥነ ጽሑፍ ዐይነቶች


ማንበብና መፃፍ መረጠ። እንዲያውም ዋና ትምህርቱን እርግፍ አድርጎ ትቶ “ወደ መፃፍ በመሳቡ”
ከራሱ ጋር ግጭት ውስጥ ገባ። ግጥም መፃፍ ይወዳል፤ከሕይወት ጋርም በፍቅር ወድቋል ፤“ከሴቶች

314
ጥቋቁር አናብስት

ጋር መሆን እና እነሱን ማፍቀርም ያስደስተዋል”፤ይህ ዐይነት ሕይወት “ከንግድ ስራ ይልቅ ኪናዊ


ውበት የሞላበት” ሕይወት መስሎ ተሰምቶታል።

በ1959 ዓ.ም የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን በንግድ ስራ ትምህርት ቤት ጨረሰ። ጽሑፉን
በተመለከተ እርዳታና ማበረታቻ የሰጡትን የእንሊዝኛ ቋንቋ መምህራኑን፣ በተለይ እንግሊዛዊው
ኪይዝ ጆንስን እና ስኮትላንዳዊቷ ሚስ ብራይድን፣ ይወዳቸዋል።በተለይ ኪይዝ ጆንስ በሥነ ጽሑፍ
ረገድ ለታደለ “እንደ አባት ያለ” ሲሆን፤በንግድ ስራ ትምህርት ቤት ውስጥ በቆየበት አራቱም
ዓመታት ያስተማረው ሰው ነው። ታደለ እዛ በነበረበት ወቅት ከፃፋቸው ግጥሞች መሀል
የተወሰኑት በማባዣ ወረቀት ተባዝቶ በሚዘጋጀው በትምህርት ቤቱ ጋዜጣ ላይ ታትመዋል፤ ነገር
ግን የትኞቹም በሌላመንገድ ታትመው አያውቁም።

ከንግድ ስራ ትምህርት ቤት ከወጣ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት
ጀመረ። በዚህ የመጀመሪያ ስራው በማህበረሰባዊ ስራዎች የትምህርት ክፍል ውስጥ፣ ለዲኑ ጸሐፊ
ሆኖ ለሶስት ዓመት ሰራ። ነገር ግን "ማነው ኢትዮጲያዊው" የሚለው መጽሐፉ በ1963 ታትሞ
ሲወጣ የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ሀብቴ በመጽሐፉ የተነሳ የእርሳቸው ጸሐፊ
እንዲሆን ጠየቁት፤ታደለም በሐሳቡ ተስማምቶ እስከ 1967 ድረስ በዚሁ ስራ ቆየ።

ታደለ ገብረሕይወት ከንግድ ስራ ትምህርት ቤት ከተመረቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ጸሐይ ተገኝን
አገባ።በመጀመሪያ እይታ የተፈጠረ ፍቅር ሲሆን፣ ከሦስት ወራት በኋላ ተጫጩ። ከአንድ ዓመት
በኋላ ሕጋዊ ጋብቻ ሳይፈጽሙ አብረው መኖር ጀመሩ። ጸሐይ የትምህርት ቤት ፎቶዎችን፣
የምስክር ወረቀቶችን ስታይ የፃፋቸውን ነገሮች ስታነብ ተማረከችና ጨምሮ እና አስፍቶ እንዲጽፍ
ትጨቀጭቀው ጀመር። "ማነው ኢትዮጲያዊው" የተፃፈው እና የታተመው በዚህ ዐይነት ሁኔታ
ነበር። ከሚስቱ ማበረታቻ ባሻገርም ዩኒቨርስቲው ገና እያበበ ላለ ጀማሪ ደራሲ አመቺ ቦታ ሆኖ
አገኘው።በዚያም ከጨዋና፣ ከትላልቅ ሰዎች ጋር መዋል ጀመረ፤አንዳንዶቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣
ሌሎቹ ደግሞ የውጭ ሀገር ሰዎች ነበሩ።ከነዚህ መሀል የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ንጉሴ አየለ፣
የሥነ ትምህርት ባለሙያው ፕሮፌሰር አባይነህ ወርቄ፣የታሪክ ተመራማሪዎቹ ፕሮፌሰር ስቬን
ሩቤንሰንና ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፣የኪነጥበብ ታሪክ አጥኚው ፕሮፌሰር ቾጅናኪ፣ የአማርኛ
ቋንቋው ሊቅ ዶክተር ሐይሉ ፉላሰ፣ ዶክተር ስዩም ገብረስላሴ (ጥልቅ መረዳት እና ሰብአዊነት
ያለው ሶሺዮሎጂስት) እና ሌሎችም ብዙ ይገኙበታል።እነኚህ የተማሩ ሰዎች ታደለ የተሻለ ሰው
እንዲሆን ያነሳሱትና ሞራል ይሰጡት ነበር።

ታደለ ዩኒቨርስቲ በሚሰራበት ወቅት የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶችን ጨምሮ ተምሮ አንድ
የፖለቲካ ሳይንስና፣ አንድየማህበራዊ ስራ፣ ሁለት ዲፕሎማዎችን ተቀብሏል።
315
ጥቋቁር አናብስት

በ1967 ዓ.ም ማስታወቂያ ሚኒስቴርን ተቀላቅሎ፣ የዛሬይቱ ጋዜጣ አዘጋጅ፣ ረዳት ሆኖ መስራት
ጀመረ። በዚህ ዐይነት ስራ ውስጥ፣ በየቀኑ የመፃፍ ባህል ስለሚዳብር፣ በታደለ ገብረሕይወት
ውስጥ ወሳኝ የሆነ ጊዜ ነበር። በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወረ የተለያዩ የሕይወት ገጽታዎችን
እንደተገነዘበው፣ ራሱ ያየውንና ከሌሎች የሰማውን ጽፏል፤ በጋዜጣው ላይ ያልተፃፈለት እና ርዕስ
ያልሆነ የሀገሪቱ አካባቢ የለም። ይህ አጋጣሚ ስለራሱ ህዝቦች በደንብ የማወቅ እድል ሰጠው።
በጣም ራቅ ወዳሉ የሀገሪቱ ክፍሎች ተጉዞ ብዙ ነገር ስለተማረ፤ለሀገሩ ህዝብና በጊዜው ለፈነዳው
አብዮት ፍቅርና ወገንተኝነት ይሰማው ጀመር። በዚህ የተነሳ "የኢትዮጵያን ሀብትና ድህነት"
መረዳት ቻለ። ያየውንና ሁሉ መዝግቦ ጋዜጣው ላይ፣ ብሎም ወደኋላ በሚጽፋቸው መጽሐፍት
ላይ ያንፀባርቃል።

በየካቲት 1966 የታደለ እጣ ፈንታ ከአብዮቱ ጋር ተቆራኘ። አብዮቱን ሙሉ ለሙሉ ለመደገፍ እና


ስለ አብዮቱ ለመፃፍ ማለ። በአብዮቱ ላይ ተስፋ እንዲጥል ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ፣የራሱ
የሕይወት ልምድና፣ምንም መሬት ያልነበራቸው አባቱ፣ በድህነት ልጆቻቸውን እንዴት እንዳሳደጉ
ስላስታወሰ ነበር።የአባቱ መከራ በዚህ ብቻ አያበቃም፤አባቱ እህል የጫነ መኪናላይ ተጭነው
ሲጓዙ፣መኪናው ተገልብጦ፣ ቋሚ የጀርባ ህመም አትርፈዋል። ማህበራዊ ስርአቱ ሌላ ቢሆን፣
የሱም፣ የቤተሰቡም ሕይወት የተሻለ ይሆን እንደነበረ አመነ።

ታደለ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተቀጣጠለ የመጣውን አብዮት ድምጽ ገና በጊዜ ሲሰማ እና ሲያጠና
ነበር። ወዲያውኑ ስለ አብዮቱ መፃፍ ጀመረ። ስለዚህ የሁለተኛ መጽሐፉን ርዕስ በዘመኑ ከሚሰሙ
መፈክሮች3መሀል መርጦ "ኢትዮጵያ ትቅደም" አለው። ይህንን መጽሐፍ በየካቲት 1966 ጀምሮት
በዛው ዓመት ሐምሌ ላይ ታተመ። ሲታተም “እንደጋዜጣ ነበር የተቸበቸበው”፤በአንድ ሳምንት
ጊዜ4 ብቻ 5,000 ቅጂዎች ተሸጠ። በመጀመሪያ ላይ ደርግ ይህንን መጽሐፍ በዐይነቁራኛ ነበር
የሚከታተለው።መጽሐፉን የሚያጠና ኮሚቴ ከተቋቀመ በኋላ መንግስት ለታደለ ምስጋና
አቀረበለት። መጽሐፉ የወጣው የአሮጌውም፣ የአዲሱም ስርአት ወኪሎች ገና ስልጣን ላይ እንዳሉ
ነበር፤ ገና ኃይለ ሥላሴንጉሥ እንዳሉ፤ እንዳልካቸው መኮንንም ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ፤
የዚያኑ ያህል ወታደሮቹም (አዲሶቹ) የስልጣኑን ልጓም እንደጨበጡ። የታደለ ገብረሕይወት
መጽሐፍ ተቀባይነት ያገኘው ግን እንደ አብዮታዊ ስራ ነው።

አብዮቱ እንደጀማመረ ሰሞን፣ የአብዮቱን መልካም ዜና ለሁሉም ሊያበስሩ ተማሪዎች በመላው


ኢትዮጵያ ይዘምታሉ።የታደለ ሶስተኛ መጽሀፍ ስለ ዘመቻው እና ከጀርባ ስላነገባቸው ሀሳቦች
ሲሆን ርዕሱም "ከርሞ ዘመቻ"ይሰኛል።እንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ካሁን በፊት ያልገጠማት ኢትዮጵያ
በመጽሐፉ ውስጥ እንደ"ድንግል"ተመስላለች። ታደለ በዚህ መጽሐፉ አብዮቱ “የሁሉም ህዝቦች

316
ጥቋቁር አናብስት

የስራ ውጤት በመሆኑ፣ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን በፍቅር ማገልገል እንዳለባቸው"


ይሰብካል።መጽሐፉ ሁለት ትይዩ ታሪኮች አሉት፤አንደኛው ታሪክ መቼቱ ገዳም ውስጥ ሲሆን
በንጽጽር ደግሞ ከአብዮቱ ጋር የባተውን አዲሱን ዘመን የተመለከተ ታሪክ ቀርቧል፤በተጨማሪም
መጽሐፉ የፍቅር ታሪክ አለው።መጽሐፉ በታህሣሥ 1967ዓም ታትሞ፣ 5,000 ቅጂዎቹ ተሸጡ።
“የመጀመሪያው ዙር ዘማቾች ሲንቀሳቀሱ በእጃቸው ይህንን መጽሐፍ ይዘው ነበር” ብሏል ታደለ።

አብዮቱ በታደለ የስራ ጠባይም ላይ ለውጥ አምጥቷል። ከየካቲት 19665 ዓ.ም ጀምሮ፣ታደለ
ዘወትር ከሌሊቱ 8 ሰአት ይነቃና እስከ ሌሊቱ 11 ሰአት ድረስ መጻፍና ማንበብ ልምዱ ሆነ።
ያቋረጠውን እንቅልፉን ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይይቀጥላል።ይህ ልምድ እስከአሁንም ድረስ
ቀጥሏል። እነኚህን የማታ ማታ የስራ ሰዓታት ዋጋ ይሰጣቸዋል፤ ይደሰትባቸዋልም።

ከ1967 ጀምሮ እስከ ጥር 1971 ድረሰ ታደለ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ሰርቷል። የለቀቀው
ደግሞ ደሞዙ አነስተኛ ስለሆነ ነበር፤ታደለ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሚከፈላቸው በቂ አይደለም
ይላል። በዛ ላይ የቤተሰቡ ቁጥር በጣም እየጨመረ ነበር፤አራት ልጆች አሉት፤በቃለምልልሳችን
ወቅት ደግሞ አምስተኛው በመንገድ ላይ ነበረ። ስለዚህ የመንግስት ድርጅት በነበረው የኢትዮጵያ
ችርቻሮ ንግድ ኮርፖሬሽን ተቀጠረ። እስከ 1978 ዓ.ም እዚሁ ሰርቷል። ስራ መቀያየሩ “ለመፃፍ
ብዙ ጊዜ ሰጥቶታል”፤ጊዜ ብቻ ሳይሆን “የፈጠራ ነፃነትም” አግኝቷል። ማስታወቂያ ሚኒስቴር
ውስጥ በሚሰራበት ወቅት "የዛሬይቱ ኢትዮጵያ"አብዛኛውን ጊዜ እና ጉልበቱን ይጨርስበት ነበር።
ከጋዜጣው ስራው ጎን ለጎን እንደምንም ብሎ የሊቀመንበር ማኦን"ትንሿን ቀይ መጽሐፍ"
ተርጉሟል። ነገር ግን ማስታወቂያ ሚኒስቴር ብዙ በቆየ ቁጥር፣ ጊዜ ይበልጥ እያጠረው መጣ።
አሁን አዲሱን ስራ ከጀመረ ወዲህ ግን፣ መጻፍ የሚፈልገውን ለመጻፍ ብዙ ጊዜ አገኘ።

***

በአሉ ግርማ፣ ብርሀኑ ዘርይሁን እና ታደለ ገብረሕይወት በኢትዮጵያ ውስጥ ፈር ቀዳጅ አብዮታዊ
ደራሲያን ሆነው ይቆጠራሉ። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ልምድ ያላቸው፣ የታወቁ እና በስራቸው
የተከበሩ ጸሐፊዎች ነበሩ። ስለዚህ በ1972 ዓ.ም የታደለ "ለቀይ አበባ"፣ ከበአሉ "የቀይ ኮከብ
ጥሪ"፣ እንዲሁም ከብርሃኑ "ማዕበል" ጋር በተመሳሳይ ጊዜ በመውጣቱ እና ልብወለዱ ከነሱ
ልብወለዶች ጋር ፈር ቀዳጅ ተብሎ መጠራቱ የራስ መተማመኑን ጨመረለት።እነኚህ ሶስት
መጽሐፍት እውነተኛ ፋናወጊ አብዮታዊ ልብወለዶች ተደርገው ይወሰዳሉ። ይሁን እንጂ

317
ጥቋቁር አናብስት

"ኢትዮጵያ ትቅደም" የተሰኘው ቀደምት መጽሐፉ ከዚህ በኋላ እንደ አብዮታዊ ልብወለድ
መወሰዱ ቀረ።

ታደለ እስከአሁን ድረስ የፃፋቸው መጽሐፍት የየራሳቸው ድክመት እንዳለባቸው ተሰምቶታል።


"ለቀይ አበባ" ከቀደሙት ቢሻልም እንከን አላጣውም። እንደ ፍቅር ስላሉ የሰዎች ስሜት ከመፃፍ
ይልቅ የፖለቲካ እንቶ ፈንቶ እንደበዛበት ተሰምቶታል።መጽሐፉ የተፃፈው የአብዮቱ ሁኔታ በርካታ
ግርታ በፈጠረበት፤የቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር በተፋፋመበት፣ ከሶማሊያ ጋር የሚደረገው ጦርነት
በተጋጋለበት፤ሞቅ ያለ የፖለቲካ ክርክር በሚደረግበት ወቅት ነበር። ስለዚህ በዚህ ሁሉ ውክቢያ
መሀል፣ ልቦለዱ እንደሚገባው አልበለፀገም ይላል ታደለ።

ከዚህ መጽሐፍ በኋላ ታደለ፣ ለብዛት ሳይሆን ለጥራት ዋጋ ለመስጠት ወሰነ። ይህንን የፈጠራ ስራ
እንደ ቁምነገር ወስዶ በጥልቀት መጻፍና ማንበብ ጀመረ። ይህ ሰባት ዓመታት የወሰደው የጽሞና
ጊዜ አዲስ ልብወለድ ወለደ።ልቦለዱ "1996" የሚል ስያሜ ሲኖረው በ1977 የተጠናቀቀውን
ረቂቅ በእጁ ይዞ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ "1996" ከተባለው የሳይንሳዊ ልብወለድእረፍት
ለመውሰድ የሜሪ ኮሬሊን "Vendetta"6 ወደ አማርኝ "ብቀላ" ብሎ ተረጎመ። ለማሰብ እና
ለማንበብ ስለፈለገ ወደ ስምጥ ሸለቆ ወረደ። ረቂቁን ደግሞ ደጋግሞ ይጽፋል፤አንብበው አስተያየት
እንዲሰጡት ለብዙ ሰዎች ይሰጣል፤የፃፈውን ቀዳዶ ይጥለውና እንደገ "ሀ" ብሎ መፃፍ ይጀምራል።
“ከፃፍኳቸው ልብወለዶች ሁሉ የበለጠ ምርጥ መጽሀፍ ነው፤እንደውም ዘመን ተሻጋሪ ሊሆን
ይችላል” ብሎ ያስባል። ሀሳቡ ትልቅ፣ገፀ ባህሪያቱ ሰው ሰው የሚሸቱ፣ ታሪኩ ደግሞኢትዮጵያን እና
ህዝቦቿን የሚገልጽ ጥሩ የሚባል ነው፤ልብወለዱ በአጭሩ የሚገልፀው ታደለ የወደፊቱ ኢትዮጵያዊ
ሰው ምን ሊመስል እንደሚችል ያለውን ምኞት ነው።ምኞቱ አብዮቱ ፍሬ አፍርቶ፣ በጎዳናው ላይ
ቁስላቸውን እያሳዩ የሚለምኑ የኔብጤዎች ጠፍተው ንፁህ ሰዎች፣ንፁህ ቤቶችብቻ ማየት ነበር።
ይህም ደራሲው፣ ኢትዮጵያ ነፃ ሆና ህዝቦቿም ደስተኛ ሆነው―ክብራቸው ተጠብቆ―ለማየት
ያለውን ተስፋ ያንፀባርቃል።

ይህ መጽሀፍ የተፃፈው ማርክሳዊ―ሌኒናዊ የሆነው የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ከተቋቋመ በኋላ


ሲሆን ይህ ፓርቲም በኢትዮጵያ ውስጥ ሶሻሊስታዊ ሪፐብሊክ ለመመስረት እየተንደረደረ እያለ
ነው።7“አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመስረት ድልድዩ ላይ ነበርን”ይላል ታደለ።በዚህ የሽግግር ወቅት፣
“ሳንሱር ክፍሉ ይለሳለሳል ተብሎ አይጠበቀም፤ስለዚህ መጽሐፉ “በጠንካራ የሳንሱር ሂደት ውስጥ
አልፏል”፤ በቃለመጠይቃችን ወቅት እንኳን እንዲታተም ገና አልተፈቀደለትም ። ታደለ ግን
ይታተማል የሚል እርግጠኝነት ነበረው። ሙሉ ለሙሉ የረካበት የመጀመሪያ መጽሐፉ ነበር።

318
ጥቋቁር አናብስት

“ፀጉሬን ያሸበተው ይህ መጽሐፍ ነው” ይላል። ልብወለዱን ለመጨረስ ቤት ውስጥ ለረዥም ሰአት
መቀመጥ ስለነበረበት፣ ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ተቆራርጧል። ነገር ግን “ካገኘሁበት እርካታ አንፃር
ይበል የሚያሰኝ ነው” ብሏል።8

***

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ታደለ ወደ ፖላንድ ሄዶ የእንግሊዝኛ ሥነ ጽሑፍ እንዲያጠና ከመንግሥት


እርዳታ/ልገሳ ተደረገለት፤ፖላንድ ጥሩ እንደሚያስተምሩ ሰምቷል። በአማርኛም፣ በእንግሊዝኛም
ጥሩ ጸሐፊ ለመሆን ጉጉት ነበረው። ከመጽሐፍት በሚያገኘው ገቢ ብቻ ለመኖር ይመኝ ነበር።
“አዲሱ መንግሥት”ቃሉን ጠብቆ ወጣት ደራሲያንን እንደሚያበረታታ፣የእርሱም ምኞት
እንደሚሟላ አምኗል። ወደፊት የ"1996 ዐይነት"ልቦለዶችን ብቻ ለመፃፍ ተስፋ ያደርጋል።
የበፊቶቹ ብዙ ሥነ ጽሑፋዊ ግድፈት ያለባቸው፣ “በጉልበት” የተፃፉ ነበሩ። አሁን ታላላቅ የሥነ
ጽሑፍ ስራዎችን ለማምረት ዝግጁ እንደሆነይናገራል።

***

ታደለ በ1979 ዓም መጨረሻ ላይ ትምህርት ለመማር ወደ ፖላንድ ሄደ። ሁለት ጊዜ ያህል


ከፖላንድ ሆኖ ከፃፈልኝ በኋላ ለረጅም ጊዜ ግንኙነታችን ተቋረጠ።

በ1987 ዓም በድጋሚ ፃፈልኝ። በዋርሶው ዩኒቨርስቲ እየተማረ ያስተምራል። ቤተሰቡም


አብረውት እዚያው ፖላንድ ነበሩ። ሶስት ልጆቹ እዛው ይማራሉ። ወደ ፖላንድ ከመጣ ወዲህ
መፃፉን እርግጠኛ ባልሆንም በአማርኛ ቋንቋ ያሳተመው አንድም መጽሐፍ ግን የለም።

ማስታወሻዎች

1) ታደለ ወደ ዋና ከተማዋ ሲያመራ ቤተሰቡ ለስራ “ወደ ክፍለሀገር” ሄደው ነበር። ነገር ግን “12
ወይም 14 ዓመት ሲሞላው” ወደ ታደለ የትውልድ ቦታ ተመለሱ።ለበአል እየሄደ ይጠይቃቸዋል።
እናቱ አማርኛ ስለማይናገሩ ከእርሳቸው ጋር ለመነጋገር ሲሞክር ኦሮምኛመለማመድ ጀመረ።
ቃለምልልሳችን እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ፣ እናቱ በሕይወት ነበሩ።

2) ይህ ቁጥር የተጋነነ ሊሆን ይችላል።

319
ጥቋቁር አናብስት

3) ይህ ሀረግ "Ethiopia First" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። "May Ethiopia Progress"


ወይም "Let Ethiopia Take the Lead" ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። የመጀመሪያው
ትርጉም ከሶሻሊስታዊ ይልቅ ልሂቃዊ ስርአትን የሚደግፍ ይመስላል። እነኚህ ሶሻሊስታዊ
አብዮተኞች ለሰው ልጆች እኩልነት የቆመ ርዕዮተአለም ደጋፊ ነን የሚሉኝ ከዚህ ጋር
ስለሚጣረስብኝ እወቅሳቸው ነበር። ይህንን መፈክር የተካው "አብዮታዊት እናት ሀገር ወይም
ሞት" የሚለው መከራን የሚናፍቅ ድምፀት ያለው መፈክር ሆነ።

4)መጽሐፉ ገና ማተሚያ ቤት ሳለ በስምምነት ተሽጧል።

5) ወሩ በአክሊሉ ሀብተወልድ የሚመራው የኃይለሥላሴ መንግስት (ካቢኔ?) አብዮታዊው


እንቅስቃሴ ባሳደረበት ግፊት ስራ የለቀቀበት ነው።

6)ይህ የትርጉም ስራ እስከ 1985 ድረስ አራት ጊዜታትሞ በአጠቃላይ 50,000 ቅጂዎች
ተሸጧል።

7) የተመሰረተው በ1987 ነው።

8)ከታደለ ገብረሕይወት ጋር ይህንን ቃለመጠይቅ በማደርግበት ጊዜ አሳታሚዎቹ አይታተምም


ብለው አንድ ጊዜ መልሰውት ነበር። ዳኛቸው ወርቁ የኩራዝ ቦርድ ሊቀመንበር እያለ እንዳይታተም
ሲል ወስኗል። ታደለ ይግባኝ ጠይቆ፣ መጽሐፉ ዳግመኛ ሊታይ ቀረበ። ቃለመጠይቃችን
ከተጠናቀቀ በኋላ በ1985 መጨረሻ ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይታተም ተብሎ ተመለሰ።ረቂቁን ያነበቡ
አንዳንዶች(ጥቂቶቹን እኔም አናግሬያቸው ነበር)፣ፍጹም ምናባዊና ተጨባጭ ያልሆነ ነው ብለው
ያሰቡ ይመስላል።

320
ጥቋቁር አናብስት

አለቃ ገብረሃና
ቀልድአዋቂ፣ ሊቅ እና ዝነኛ
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በጣም ከመታወቃቸው የተነሳ በመጀመሪያ
ስማቸው ብቻ ይጠራሉ። ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያ ስማቸው፣
እውነተኛ የግል መጠሪያቸው ሲሆን የአባት ስምና ማዕረግ አብሮ
ይጠቀሳል። በመጀመሪያ ስማቸው ብቻ እጅግ ከሚታወቁ
ኢትዮጵያውያን መሀል ብላቴን ጌታ ኅሩይ፣ ራስ እምሩ እና አለቃ
ገብረሃና ተጠቃሽ ናቸው። ሕሩይ በሁሉም ዘንድ እንደ ቅዱስ
የሚቆጠሩ ናቸው። የገብረሃና ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ፤ገብረሃና
በስማቸው ስድ የሆኑ ወሲብ ነክ ታሪኮች1 እና ሌላም ብዙ
ቀልዳቀልዶች ይነገራሉ። ከሞቱ ከብዙ ዓመት በኋላ እንኳን በስማቸው ትኩስ ቀልዶች
ይፈበረካሉ። ታሪኮቹ ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ ፈጠራ ቢሆኑም፣ሰዎች ስለእሳቸው ካላቸው
አመለካከት―በትዳራቸው ደስተኛ አለመሆናቸው፣ሴት አውል እንደሆኑ፣በአማርኛ ሊቅ
መሆናቸው፣ከመሳሰሉት―ጋር መግጠማቸው ብቻ ሳይሆን ይህንን አመለካከት ጠብቀውም
አቆይተዋል። የኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን ሊቆች ቅኔ በመናገር የተካኑ ናቸው፤እናም አለቃ
ገብረሃናም እንዲህ ካሉ፣ ብዙ ቅኔ ጠገብ ታሪኮች ጋር ስማቸው አብሮ ይነሳል።

አለቃ እንዲህ ስማቸው ይግነን እንጂ፣ ብዙ ሰዎች በሕይወት የኖሩ ሰው መሆናቸውን ሁሉ


ይጠራጠራሉ።ነገር ግን ስለሕይወታቸው ብዙ መረጃ ማግኘት ተችሏል።አንድ ጊዜ በ1890 ዓ.ም
መሴ. ሙንሮስ2 (ሜርኖስ) የተባለ ግለሰብ ፎቶ አንስቷቸዋል።እውነቱ እና አፈ–ታሪኩ ግን ሁሌም
አይገጥምም።ለምሳሌ በአፄ ምኒልክ አደባባይ ተቀምጠው፣እንደ ተራ አዝማሪ ወይም አረሆ እየዘፈኑ
መንገደኞችን በውስጠ ወይራ ንግግር፣ በምሳሌና በሰምና ወርቅ መተረባቸውን ወይም በአሽሙር
መሳደባቸውን ማረጋገጥ አይቻልም።

አለቃ ገብረሃናን ከኢትዮጵያ ስመጥር ደራሲዎች የሕይወት ታሪክ ጋር እዚህ ያካተትኳቸው በቋንቋ
አጠቃቀማቸው ጥበበኛ ስለሆኑ ነው።በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ሌሎች ደራሲዎች ጽሑፍ
ውስጥም እንደ ተረታዊ ገፀባህሪ ብቅ ብቅ ይላሉ።በተጨማሪ ራሳቸው የፃፏቸው የሃይማኖት
መጽሐፍትም አሉ፤ይሁን እንጂ ሳይታተሙ ቀርተዋል። እዚህ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱት
ደራሲዎች የተቀመጡበት ቅደም ተከተል በኖሩበት ዘመን መሰረት ቢሆን፣አለቃ ገብረሃና የመጽሐፉ
መጀመሪያ ላይ መቀመጥ ነበረባቸው። ነገር ግን ስለሳቸው ለመፃፍ ያነሳሳኝ ከሰዎች እና ደራሲዎች

321
ጥቋቁር አናብስት

አፍ እና ጽሑፍ ስለማይጠፉ ስለሆነ፣ ከመዝገበ ቃላት አዘጋጆቹ ቀጥሎ በሚገኘው "አሻሚ" ቦታ


ላይ አስቀምጬያቸዋለሁ።3

***

አለቃ ገብረሃና ገብረማርያም የተወለዱት በ1797 ዓ.ም በበጌምድር(ጎንደር) ክፍለሀገር፣


በደብረታቦር አውራጃ፣ በፎገራ ወረዳ፣ናበጋ–ጊዮርጊስ በሚባል ቦታ ነው። አባታቸው መምህር
ገብረማርያም መጠኑ የቤተክህነት ሰው ሲሆኑ፣እናታቸው ወይዘሮ ሳህሊቱ ተክሌ ይባላሉ።
ከቤታቸው አቅራቢያ በሚገኘው ደብር፣ ትምህርታቸውን ጀምረው ዳዊት መድገም፣ ጽዋትወ ዜማ
መውጣት ተማሩ። አለቃ በተለይ በዜማና በቅኔ ጎበዝ ነበሩ።እቴጌ መነን(የስመጥሩ ራስ አሊ እናት)
ናበጋ ወደሚገኘው ደብር ደብዳቤ ጽፈው፣ ዳዊትና ውዳሴ ማርያም የሚያስጠናቸው ሰው
እንደሚፈልጉ ሲያሳውቁ፣ አለቃ ገና የመሐፍት ትርጓሜ እየተማሩ ነበር።እነኚህ ዝነኛ የፀሎት
መጽሐፍት፣ በጥብቅ ሃይማኖተኞች ዘንድ የሚደገሙት፣ በግዕዝ ነው።ግዕዝ የቤተክህነት ቋንቋ
ስለሆነ፣አለቃ በቄስ ትምህርት ቤት ተምረውታል። ስለዚህ ለዚህ ስራ ከአለቃ የበለጠ የሚመጥን
ሰው ስላልተገኘ፣ እቴጌ መነን በጠየቁት መሰረት ፀሎት ለማስተማር ወደ ሕሩይ–ጊዮርጊስ ተላኩ።

አለቃ፣እቴጌ መነንን አስጠንተው ከጨረሱ በኋላ በእቴጌይቱ ትዕዛዝ ከፍተኛ ትምህርት ለመማር
ወደ ጎንደር ሄዱ። በአታ ላይ ሀዲስ እና ብሉይ ኪዳንን ተማሩ።እቴጌ መነን ለአለቃ መምህር ክፍያ
ምግብና ልብስ ይልኩላቸው ነበር።ይህንን ትምርታቸውን ከጨረሱ በኋላ እቴጌ መነን “አለቃ”
የሚለውን ማዕረግ ሰጧቸው። "አለቃ" የሚለው ማዕረግ የቤተክርስቲያን/ገዳም ሃላፊ ወይም
ደግሞ በአንድ የቤተክርስቲያን የእውቀት መስክ አዋቂ/ሊቅ ወይም መምህር የሆነ ማለት ሊሆን
ይችላል። ከዚህ በኋላ በጎንደር ያሉ አብያተክርስቲያንን በብቃት ማስተዳደር ጀመሩ።ሊቅነታቸው
በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ሲሆን በተለይ ፍትሃ ነገስትን በመተርጎም “የሚወዳደራቸው
አልነበረም”። ፍትሐ ነገሥት አለማዊ እንዲሁም መንፈሳዊ ጉዳዮች ባንድ ተጣምረው የሚገኙበት
የህግ መጽሐፍ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያ የምትዳኘውም በዚሁ መጽሐፍ ነበር።

የቋራው ካሳ የእቴጌ መነንን የልጅ ልጅ ቢያገባም፣ የሚስቱን አባት ራስ አሊን ካሸነፈ በኋላ፣ እቴጌ
መነንን ራሳቸውን ማርኮ አሰራቸው። በኢትዮጵያ ትልቁን ስልጣን ከያዘ በኋላ ዳግማዊ ቴዎድሮስ
ተብሎ ተቀብቶ ነገሰ። ከዛ በኋላ አለቃ ገብረሃና ከቴዎድሮስ ጎን ተለይተው አያውቁም። በፍጹም
አይለያዩም ነበር ይባላል። በተለይ በፍትሐ ነገሥት(መጽሐፍ ቅዱሳዊ ህግጋትን ተመርኩዞ የተፃፈ
ነው)እየተመሩ ፍትህን ለማድረስ ደክመዋል።በጊዜው በኢትዮጵያ የፍትሓ ብሄርም ሆነየወንጀለኞች

322
ጥቋቁር አናብስት

ወይም የሃይማኖት መቅጫ ህግ ስላልነበረ ሁሉም የሚዳኘው በፍትሐ ነገሥት ነበር። አለቃ በተለይ
በዘመነ መሳፍንት ፍትህ አጥቶ ለነበረው ደሃው ህዝብ ህግና ስርአትን ለማስከበር፣ ጓግተውም፣
ቆርጠውም ነበር። ቴዎድሮስ ተናዶ በሚቆጣበት ጊዜ፣ ማረጋጋቱ የአለቃ ስራ ነበር።

አፄ ቴዎድሮስ ደብረታቦር ላይ የመድሀኒአለምን ቤተክርስቲያን አሳነፁና አለቃን ጠርተዋቸው"ይህ


ቤተክርስቲያን ትልቅ ነው ትንሽ?" ብለው ቢጠይቋቸው፣ አለቃም እንዲህ ብለው መለሱ፦

"ትልቅ ነው እንጂ! ለሁለት ቄሶችና ለሶስት ዲያቆናት(ለአምስት ሰሞነኛ) በደንብ ይበቃል!"


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርአት እና ቀኖና መሰረት ቅዳሴን ለመቀደስ
የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የካህናት ቁጥር፣ ቢያንስ ሁለት ቄሶችና ሶስት ዲያቆናት ነው።
ኢትዮጵያውያን እንደዚህ ዐይነት አሻሚ የሆነ መልስ መስጠት ይወዳሉ―ውስጠ ወይራ ብለው
ይጠሩታል።4

ቴዎድሮስ ከቤተክህነት ጋር አይስማሙም፤በተቃራኒው አለቃ ደግሞ ስምም ናቸው። በዚህ የተነሳ


አለቃ አልተሳካላቸውም እንጂ ቴዎድሮስን እና ቄሶችን ለማስታረቅ ብዙ ጊዜአጥፍተዋል።እንደውም
አንድ ጊዜ ቴዎድሮስ በአለቃ ተናድደው ስልጣናቸው ከማይደርስበት ቦታ ሄደው እንዲሸሸጉ
ያዟቸዋል።አለቃ ንብረታቸውን ናበጋ አስቀምጠው ቆራጣ ወለተ ጴጥሮስ በሚባል ገዳም ገብተው
ተደበቁ። በገዳም ቆይታቸው እዛው ካለ ተማሪ ጋር ይጣላሉ፤ተማሪውም ቴዎድሮስ ከግዛታቸው
ውጭ እንዲሄዱ ያዘዟቸውን ትዕዛዝ እያነሳ ያስፈራራቸው ጀመር። ሌሎቹ ለማስታረቅ ሞከሩ ፤
ለተማሪው አፍ ማስዘጊያ ገንዘብ እንስጥህ እስከማለት ደረሱ፤ተማሪው ግን አልደለልም ብሎ
አሻፈረኝ አለ። አለቃ ግን በመጨረሻ ባለጋራቸውን ማባበል እንዲተዉ ነገሯቸውና ራሳቸው
ቴዎድሮስን ለማግኘት ሄዱ። ቴዎድሮስ አለቃን ሲያዩዋቸው በጣም ተደስተው አቀፏቸውና
ጉንጫቸውን ሳሟቸው። “እስከአሁን የት ነበርክ?” ብለውም ጠየቋቸው።አለቃም “ከግዛትዎ ውጪ
እንድሄድ አዘውኝ ነበር። የግዛትዎ መጨረሻ ደግሞ ከውሃው ባሻገር ነው፤ነገር ግን የሚያሻግረኝ
መርከብ ስላላገኘሁ ቆራጣ ወለተ ጴጥሮስ ገዳም5 ተደብቄ ቆየሁ። በዚያ አንድ ተማሪ እየነዘነዘ
አስቸገረኝ ....” ብለው መለሱ። አለቃ ከሄዱ በኋላ ፍትህ ስለጠፋና ስለመነመነ፣ ቴዎድሮስ አለቃን
የሚቃረነውን ልጅ ከግዛታቸው እንዲጠፋ አዘዙ።አለቃ ግን እስከ መቀደላው ጦርነት ጅማሬ ድረስ
ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር ቆዩ።እስከ ነፋስ መውጫ ድረስ ቴዎድሮስን ካጀቡ በኋላ ጤነነት
ስላልተሰማቸው ፊታቸውን አዙረው ወደ ትውልድ ቦታቸው ናበጋ ተመለሱ።

በመቅደላ ጦርነት ቴዎድሮስ እጄን ለአሸናፊዎቹ እንግሊዛውያን አልሰጥም ብለው ራሳቸውን


አጠፉ። ከዚህ በኋላ ዙፋኑን ለመቆጣጠር በአዲሱ ንጉስ ተክለጊዮርጊስ እና በደጃዝማች ካሳ(በኋላ
ዮሐንስ አራተኛ) መካከል ጦርነት ተጀመረ።ዮሐንስ አራተኛ ተክለጊዮርጊስን በጦርነት ካሸነፉ በኋላ
323
ጥቋቁር አናብስት

አለቃ ገብረሃና በሰሜን ወደሚገኘው ትግራይ እንዲመጡና በፍትሐነገስት መሰረት እንዲዳኙ


ተጠሩ።በዚህ ወቅት ጥቂት መጽሐፍትን በብራና ላይ ጽፈዋል።መጽሐፍቱም አክሱም (በኢትዮጵያ
ዋነኛው ቅዱስ ቦታ)በሚገኘው የጽዮን ደብር እስካሁን ድረስ ከነስማቸው ተጠብቀው ይገኛሉ
ተብሎ ይነገራል።

አለቃ ገብረሃና ዝናቸው የናኘው በዳግማዊ ምኒልክ ችሎት ነው። ዮሐንስ አራተኛ በ1881 ዓ.ም
መተማ ላይ በተደረገው ጦርነት ከተሰዉ በኋላ አለቃ ወደ ትውልድ መንደራቸው ናበጋ ተመለሱ።
ነገር ግን አለቃ በጊዜው ሊቆች በተለይ በአለቃ ገብረማርያም እና በጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ (ኋላ
የምኒልክ ጸሐፌ ዜና መዋዕል) በደንብ ስለሚታወቁ ወደ ምኒልክ ችሎት እንዲቀርቡ ተጠሩ።
ከምኒልክ እና ከጣይቱ ጋር በመወዳጀታቸው ዝናቸው በፍጥነት ተስፋፋ። በመጀመሪያ አለቃ
እንጦጦ ላይ በሚገኘው ቤተመንግስት፤በኋላ ደግሞ በኡራኤል እና ራጉኤል ቤተክርስቲያን፣
እንዲሰነብቱ ምርጫ ተሰጣቸው። ነገር ግን አለቃ የሚናፍቃቸው የትውልድ መንደራቸው ናበጋ
ጊዮርጊስ ነበር። ስለዚህ መናገሻው ወደ አዲስ አበባ ሲዘዋወርእስከመጨረሻው በዚያ ለመቆየት
አሻፈረኝ ብለው ወደ ትውልድ መንደራቸው ተመለሱ። ነገር ግን የአዲሳባ ቆይታቸው፣ የጎንደር እና
የአክሱምን ያህል አለቃን “አይረሴ” ለማድረግ የሚያበቃ ነበር። አፄ ምኒልክና አለቃ ገብረሃና
በአንድ ላይ ፎቶ ተነስተው ነበር ይባላል። ፎቶውም ብላቴንጌታ ሕሩይ ቤት ተቀምጦ እያለ ሌባ
ገብቶ ስለዘረፈው ጠፍቶ ቀረ። ካርዲናል ማስጃ እና ሌሎች 12 የውጭ ሀገር ሰዎች፣ እንደሚሉት
መነኩሴ ሳይሆኑ ሰላይ መሆናቸውን በቅኔ ለምኒልክ ነግረው ያሳወቁት ራሳቸው አለቃ ነበሩ ፤
አለቃ ለሃገራቸው ያላቸውን ተቆርቋሪነት እና ፍቅር በዚህ አጋጣሚ አስመስክረዋል።

አለቃ ገብረሃናየምድር አለቆቻቸውን ብቻ ሳይሆን የሰማይ ጌታቸውንም ጭምር ይገዳደሩ ነበር።


ለአብነት እግዚአብሔርን እንዲህ ይሉታል፦“ሀጢያተኞችን ወደ ገሃነም ልከህ ማሰቃየት የለብህም።
ጠላቶችህን እንደራስህ ውደድ ብለህ ትእዛዝ የሰጠኸን ራስህ ነህና”። በእንደዚህ ዐይነቱ ቅኔ ውስጥ
"ዘለአለማዊ እውነቶች" ስለሚመረመሩ "የምርምር ቅኔ" ይባላል።

አለቃ ገብረሃና ብሉይ እና ሀዲስ ኪዳንን በመተርጎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ


ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል።ግን ያደረጉት ዋና አስተዋጽኦ በህግ እና በቤተክርስቲያን ዜማና ወረብ
ረገድ ነው። ከዚህም በላይ አለቃ አዲስ የሆነ የአቋቋም ስልት ፈልስፈዋል። ይህ የአቋቋም ስልት
መነሻው ደብረታቦር ሲሆን ወደ ሸዋ እና ትግራይም ተሰራጭቷል። ስልቱንም በብቸኛ ወንድ
ልጃቸው ስም "ተክሌ" ብለውታል።በጣም የሚያስደስትና መንፈስን የሚይዝ የአቋቋም ስልት ነው
ይባልለታል።

324
ጥቋቁር አናብስት

የአለቃ ገብረሃናን የጨዋታ ለዛ ለመረዳት ሁለት ምሳሌዎችን ጣል ማድረግ ይጠቅማል። እነዚህ


አብነቶች እውነት የአለቃ ገብረሃና መሆናቸውን እርግጠኛ አይደለሁም።ምናልባት በስማቸው
ከሚነገሩ እልፍ አእላፍ ቀልዶች መሀል ይሆናሉ።

በአንድ ወቅት "ትላልቅ ሰዎች" ሱረት የመማግ፣ ትምባሆ የማጨስ፟ ልምድ ነበራቸው።
ቤተክርስቲያን ግን ይህንን ልምድ በጽኑ ታወግዘው ነበር። አንድ ቀን አለቃ ሱረት ሲምጉ፣ አንድ
ቄስ አያቸውና ለምን ይሄንን እንደሚያደርጉ ጠየቃቸው። አለቃም "ለምን አላጨስም?" አሉ።
"ምክንያቱም" አለ ቄሱ "ምክንያቱም ሲጋራ የሰይጣን ንብረት ነው"

"እንግዲያውስ ከሰይጣን ስትወለድ ጠይቀኝ"

ይህ ላይ ላዩን ሲታይ ትርጉም የለሽ የሚመስል መልስ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው። አለቃ ይህን
ቄስ የሰይጣን ንብረት የሆነውን "ሲጋራ" ለምን ተጠቀምክ ብሎ ለመጠየቅ የሴይጣን ዘመድ/ወራሽ
መሆን አለብህ እያሉት ነው።እንዲህ ያለ መልስ የባለጋራን አፍ የሚያስዘጋ ነው።አለቃም
የሚታወቁበት "ፈጣን ምላሽ" እንዲህ ያለ ነው።

አለቃ አንዲት በቅሎ ነበረቻቸው፤ይቺ በቅሎ በአንድ በኩል ያሉትን እግሮቿን በትይዩ፣በቅንጅት
በማንቀሳቀስ፣ ያለመንገጫገጭ እንድትራመድ የሰለጠነች ናት።ስለዚህ እንደውሃ የምትፈስ ነች
ማለት ይቻላል።6 ታዲያ ባለቤታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ይህቺ በቅሎ በተደጋጋሚ አንዲት ሴት
ከምትኖርበት ራቅ ያለ ቤት ታስራ ይመለከታሉ። ስለዚህ ወደባለቤታቸው አንድ ሽማግሌ ልከው
እሳቸውን ችላ ብለው ለምን ሌላ ሴቶችን እንደሚያማግጡ⁷ እንዲጠይቁላቸው ያረጋሉ። በቅሎዋን
ሴትየዋ ቤት ታስራ ስላዩ “ምስክሬ”ነችአሉ (በቃል አቀባያቸው በኩል)። አለቃም ለምስክርነት እንደ
በሬ እና ላም ያሉ ሰላማዊ እንስሳት ይቅረቡብኝ እንጂ ይቺ በቅሎ እኔን በጥላቻ ስለምትመለከተኝ
ምስክር ልትሆን አይገባትም።በቅሎዋን በዳገት በቁልቁለት ስለምነዳት ቂም ሳትይዝብኝ አይቀርም።
ስለዚህ የእሷ ምስክርነት ተቀባይነት አይኖረውም።ኢትዮጵያውያን ሙግት እንደ መውደዳቸው ስለ
ችሎት ደንብ ስለሚያውቁ የአለቃን ብልሃት የሚያስደንቅ ሆነው እንደሚያገኙት አይጠረጠርም።

በህዝቡ ዘንድ ብዙ የጫወታ ለዛዎች በብዛት እና በስህተት የአለቃ ገብረሃና እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
የሆነው ሆኖ አለቃ ፈጣን መልስ በመስጠት፣ ቃላትን በመሰንጠቅ፣ ቅኔ በመናገር፣ በቃላት
በመጫወት፣ላይ ላዩን ሲታዩ ከሚሰጡት ትርጉም የጠለቀ ሌላ ትርጉም ያለው፤ ትርጉሙን ፈልጎ
ለማግኘትም ቃላቱ ላይ ብዙ ማሰብና መመራመር የሚያስፈልገው ዐይነት ንግግር በመናገር የተካኑ
ናቸው ይባላል።አለቃ፣ በኢትዮጵያ የልሂቃን ሰማይ ላይ እንደ "ደማቅ የማለዳ/የአጥቢያ ኮከብ"
የፈለቁ ናቸው ይሏቸዋል። በብዙ ታላላቅ ነገሥታት ዘመን ኖረው፣ ሁሉንም በቅርብ ማወቅ
325
ጥቋቁር አናብስት

ችለዋል።አለቃ ጽፈዋቸዋል ተብሎ ከሚነገርላቸው መጽሐፍት ባሻገር፣ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ


ውስጥ ያላቸው ስፍራ በእርሳቸው ምክንያት ጠንካራ እና ልዩ የሆነው በሰምና ወርቅ ራስን በራስ
የመግለጽ ልማድ በቀጣይነት እያንሰራራ በመሄዱ፣እንዲሁም በስማቸው አዳዲስ ፈጠራዎች
በየጊዜው እየታከሉ በመምጣታቸው ሊረጋገጥ ይችላል።

አለቃ ገብረሃና ከሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ ጋር ተክሌ የተባለ ወንድ ልጅ፣ ጥሩወርቅ እና
ሲኔ/ሥነ ?? የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆች ነበሯቸው።

አለቃ በሰኔ 5 ቀን 1894ዓም በ97 ዓመታቸው አረፉ።

የተርጓሚ ማስታወሻ
ስለ አለቃ ህይወት የሚተርኩ መጻህፍት የወጡ ሲሆን የሙሴ ሜርኖስን ፎቶ በጉልህ ባይታይም
ማስቀመጣችንን ልብ ይሏል ስለ ጥራቱም ይቅርታን እንጠይቃለን

፟በእንግሊዝ አፉ smoke tobacco ቢልም እንደ ሃገራችን የወቅቱ ባህል ከማጨስ ይልቅ
ማመንዠክ ወደ ሚለው የሚቀርብ ይመስለናል፡፡

ማስታወሻዎች

1) መጨረሻ የሰማሁት ታሪክ ይህን ይመስላል። አንድ ምሽት አለቃ ከሰራተኛቸው ጋር ፍቅር
ይሰራሉ (ኢትዮጵያውያን ይህ ዓይነቱ ድርጊት የተለመደ እንደሆነ ነግረውኛል) በኋላ ሌሊት ላይ
በራሳቸው አልጋ ከሚስታቸው ጋር ተኝተው ከሰራተኛቸው ጋር ሌላ የፍቅር ጨዋታ ማድረግ
ያምራቸዋል። ከአልጋቸው ተነስተው ወደ ሰራተኛቸው ጋር ሊሄዱ ሲሉ ሚስታቸው "አለቃ ወዴት
ነው?" ሲሏቸው "ልደግም ነዋ" ብለው መለሱ። አለቃ ፀሎት ሊደግሙ ያሉ ያስመስሉ እንጂ
እሳቸውስ ከሰራተኛቸው ጋር የፍቅር ጨዋታ ሊደግሙ ነበር።

3) ይህንን የአለቃ ታሪክ ከፃፍኩ በኋላ አረፈአይኔ ሐጎስበ1979ዓም "አለቃ ገብረሃና እና


ቀልዶቻቸው" የሚል ትንሽ መጽሀፍ አሳትሟል። ነገር ግን በዚህች መጽሐፍ ላይ አልተመሰረትኩም
ምክንያቱም ጊዜያዊ ከሆኑ እንደ ጋዜጦች ካሉ ምንጮች በስተቀር ሌሎች የህትመት ውጤቶችን
ለግብአት አልጠቀምም። በቀላሉ የማይገኘውን መረጃ ሳሳድድ ከርሜያለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ
ከደራሲዎቹ ከራሳቸው መረጃ ለማግኘት እሞክራለሁ ፤ ያ በማይቻልበት ጊዜ የቅርብ ዘመድ ወይም
ጓደኛ እጠይቃለሁ። ነገር ግን ከሌላ ምንጭ መረጃ በማይገኝበት ወቅት በኢትዮጵያ ያሉ ያልታተሙ

326
ጥቋቁር አናብስት

ጽሑፎችና የጥናት ወረቀቶች ( አንዳንዴም በጋዜጣ ወይም በመጽሔት በአማርኛ የሰፈሩ


መጣጥፎች) ጠቃሚ ሆነው ተገኝተዋል። አለቃ ገብረሃናን በተመለከተ የቃል ጨዋታዎችን ፤
ከኢትዮጵያዊ ምሁራን ጋር የተደረጉ ንግግሮችን፣ እንደሁም ጸሐፊው የማይታወቅአንድ የጋዜጣ
ጽሑፍ ተጠቅሜያለሁ። የጋዜጣ ጽሑፉ የአረፈአይኔ ሐጎስ ሳይሆን እንደማይቀር ባምንም እርግጠኛ
ግን አይደለሁም።

4) ውስጠ ወይራ እስከ ስምንት የሚሆኑ አገባቦች ያሉት የሥነ ግጥም ዐይነት ነው። ከነዚህ ሁሉ
ድንገቴነቱ ዋናው ባህሪው ነው። (መጠሪያውን ያገኘውጋቢ ውስጥ በተደበቀ የወይራ ሽመል
በድንገት ከመመታት ይመስላል)

5)ቤተክርስቲያኖች እና ገዳሞች የምድራዊ ገዢዎች ስልጣን ሊደርስባቸው እንደማይችሉ ምቹ


የመሸሸጊያያ ስፍራ ይቆጠራሉ።

6)በቅሎዎች በአንድ ጎን በኩል ያሉ እግሮቻቸውን ከዱላ ጋር በማሰር፣ በሚጓዙበት ወቅት እነኚህን


እግሮቻቸውን እኩል እንዲያነሱ ይሰለጥናሉ። እንደዚህ የሰለጠነ በቅሎ ሰጋር በቅሎ ይባላል። በዚህ
የተነሳ የሰጋር በቅሎ ግልቢያ ቀላል እና የሚያስደስት ነው ፤ ጋላቢውም ሲቀመጥ አይንገጫገጭም።
ፈረሶች፣ ግመሎችና ሲናር አህያ ተብለው የሚጠሩ ትላልቅ አህዮችም እንደዚህ እንዲጋልቡ
ይሰለጥናሉ ፤ በዚህ መልኩ የሰለጠኑት ሁሉም ሰጋር ተብለው ይጠራሉ።

7) "ማገት" የሚለው ግስ ከሴቶቹ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ግልጽ


የሚያደርግ ነው።

327
ጥቋቁር አናብስት

አበራ ለማ
በርካታ የአጻጻፍ ቅርጾችን የሞከረ ደራሲ አበራ ለማ በሸዋ ክፍለሀገር፣
ሰላሌ አውራጃ፣ ፍቼ በምትባል ከተማ ግንቦት 1ቀን 1943 ዓ.ም ተወለደ።
አባቱ ለማ ደግፌ1 ከሰላሌ ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ አውራ ጎዳና ባለሥልጣን
በመጀመሪያ በጥበቃ ኋላ ደግሞ በፀሐፊነት ሰርተዋል። እናቱ ወይዘሮ
ማጫሽወርቅ ተከተል ከመርሃቤቴ የመጡ "ንፁህ የሸዋ አማራ" ናቸው።
አበራ በአማራም፣በኦሮሞም ባህል ውስጥ ሁለቱንም ቋንቋዎች እያቀላጠፈ
አደገ። በጊዜ ከሁለት ቋንቋዎች ጋር መተዋወቁ የምናብ ነፃነት እንደሰጠው ይናገራል።ሁለቱን
ባህሎች መረዳት ብሎም ልዩነታቸውን ማወቅ በመቻሉ ደስተኛ ነው።አሁን ድረስ ሁለቱንም
ቋንቋዎች መናገር ይችላል።ልጅ እያለ በሁለቱ ባህሎች መሃል አንዳንድ “ባህላዊ ግጭቶች” ይፈጠሩ
ነበር፤ብዙውን ጊዜ አማራዎች "የበለጡ" እንደሆኑ ተደርጎ በራሳቸውም፣በሌሎች ሰዎችም
ይቆጠራሉ። አበራ ከአማራ ልጆች ይልቅ አብረውት ከብት ከሚያግዱት ከኦሮሞዎቹ ጋርይውል
ነበር። የልጅነት ጓደኞቹ አሁን ድረስ ገበሬ ሆነው ቀርተዋል።

አበራ በልጅነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር አደገ። ትምህርት የጀመረው በ1952 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ በፊት
ለሁለት ዓመት የቄስ ትምህርት ተከታትሏል። በአበራ እና በአስፋ ወሰን አንደኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት ከአንደኛ ክፍል እስከ ስምንተኛ ለሰባት ዓመትተማረ። ስምንት ክፍል ለመጨረስ ሰባት ዓመት
ብቻ የወሰደበት ከሁለተኛ ክፍል ወደ አራተኛ ክፍል በአንድ ዓመት በመዘዋወር ሶስተኛ ክፍልን
በመዝለሉ ነው።በገንዘብ ችግርናበትምህርቱ መክበድ ምክንያት፣በአንደኛ ደረጃም ሆነ በሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደስተኛ አልነበረም።ቤተሰቦቹ የሚኖሩት ገርበ ጉራቻ2 ሲሆን፤ እሱ
ደግሞ ለትምህርት ቤቱ እንዲመቸው ከአጎቱና ሌሎች ዘመዶቹ ጋር ፍቼ ይኖራል። አጎቱ ደግሞ
ንግድና ገንዘብ እንጂ ትምህርት እና የትምህርት ጉዳይ ብዙም አያስጨንቀውም። አበራ ከአጎቱ ይህ
ነው የሚባል እርዳታ ካለማግኘቱም ባሻገር፣ብዙ ብዙ ስራዎችን እንዲያከናውን ይጠበቅበት ነበር።
ለምሳሌ በጎችን እና ፍየሎችን በየቀኑ ማገድ እና አመሻሽ ላይ ወደማደሪያቸው መመለስ ነበረበት።
አበራ ከአጎቱ ልጆች ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለነበረው አብሯቸው ማዕድ የመቅረብና ትምህርት ቤት
የመሄድ እድል አግኝቷል። አንድ ጊዜ ፈተና እያለው አጎቱ አብሮት መጥቶ ስራ እንዲያግዘው
አዘዘው። አበራ ግን ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ስላልሆነ ከአጎቱ ቤት ጠፍቶ፣ለሶስት ወር ያህል
በየሱቁ በረንዳ እያደረ ፈተናውን እስኪፈተን ድረስ ቆየ።

አበራ አምስተኛ ክፍል እያለ ለአስተማሪዎቹ “ስለ ሕይወት የሚሰማውን” በተመለከተ ግጥሞች
ይጽፍላቸው ነበር፤ግጥሞቹን የሚጽፈው ደብተር ላይ ሲሆን እያንዳንዳቸው ሁለት ገጽ ያህል

328
ጥቋቁር አናብስት

ይፈጃሉ። አስተማሪዎቹ በሚጽፈው ነገር “ደስተኞች” ነበሩ።በግጥሞቹ ትምህርት ቤት ውስጥ


ታዋቂ እየሆነ ሲመጣ ሰልፍ ላይ ለሁሉም ተማሪዎች ማንበብ ጀመረ።በተለይ ከሰባተኛ ክፍል
ጀምሮ ብዙ ምስጋና እና ሙገሳ ይደርሰው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት ቤቱ ውስጥ
የስካውት አባል እንዲሁም የሙዚቃ፣ ድራማ እና ግጥም ክበቦች አባል ነበር።

አበራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ወሊሶ ( ግዮን ወሊሶ ተብሎም ይጠራል) ሄዶ
ጎበና ዳጨ (በእርሱ አጠራር ጎበና ዳጨው) አባ ጥጉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ
9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማረ። የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን ደግሞ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተለ። በዚያም ጥሩ ጊዜ አሳልፏል፤በተለይ ከተለያዩ ክበቦች እና
ሥነ ጽሑፍ ጋር የተገናኙ እንቅስቃሴዎቹ ያስደስቱት ነበር።በየወሩ መጽሔት የሚያሳትመው፣
የመጽሄት ክበብም ወስጥንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ክበቡን በገንዘብ የሚደግፈው አንድ መምህር
ሲሆን፣አበራም በሁለተኛ ደረጃ ተማሪነቱ የመጨረሻ ሁለት ዓመታት የክበቡ ፕሬዚዳንት ነበር።

አበራ ገና ፍቼ እያለ፣ አጫጭር ታሪኮች፣ ተረቶች እና ግጥሞች ያነብ ነበር። ከነዚህ መሀል ዋናው
በተለይ ለትምህርት ቤቶች የተዘጋጀው የከበደ ሚካኤል"ተረትና ምሳሌ"ነው።በተጨማሪ
የማህተመሥላሴ ወልደመስቀል እና የመኮንን እንዳልካቸውን መጽሐፍት አንብቧል።ስሜት የሚነኩ
ሆነው ስላገኛቸው ደራሲ እንድሆን ገፋፍተውኛል ይላል።ከነዚህ መጽሀፍት የጨዋታ ለዛ ተምሯል፤
ነገር ግን በነዚህ ሳይወሰን የወንጀል እና ልብ አንጠልጣይ ታሪኮችንም አንብቧል። በእንግሊዝኛ
እንደ"Arabian Nights"("አንድ ሺህ አንድ ሌሊት")ያሉ መጽሀፍትን ሲያነብ፣በአማርኛ ደግሞ
ለቁጥር የሚያታክቱ ቤሳ–ልብወለዶችን አንብቧል፤ርዕሳቸውን ግን አያስታውስም። የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ወሊሶ ከመጣም ወዲህ በብዛት ያነብ ነበር።በዚያ ሶስት ወይም አራት
ልጆች በአንድነት ሆነው የጥናት ወይም የንባብ ቡድን ይፈጥሩና ሰለ መጽሀፍት ይወያያሉ። የከበደ
ሚካኤል መጽሐፍት በተለይ ግጥሞቹ ይማርኩት ነበር። የአቤ ጉበኛን መጽሀፍትም አንብቧል።

ወሊሶ እያለ የአማርኛ መምህሩ አቶ ወንድሙ ተጫኔ እና የእንግሊዝኛ መምህሩ ህንዳዊው ሚስተር
ቭሬንድራ ኩማር ባሲል፣ በዝርውም ሆነ በግጥም እንዲጽፍ ያበረታቱት ነበር።እነኚህ ሁለት
መምህራን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቆይታው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አስተምረውታል
፤በተለይ ህንዳዊው የእንግሊዝኛ መምህሩ ግሩም እና ልዩ ሰው ነበር። አበራ የ11ኛ ክፍል ተማሪ
እያለ በደብተር ላይ የጻፈውን 200 ገጽ ያለው የልብ-ወለድ ታሪክ ጨምሮ የፈጠራ ስራዎቹን
እርማት የሰሩለት እነኚህ መምህራን ናቸው።ምንም እንኳን መጽሐፉ ከነጭራሹ ባይታተምም፣
አበራ ግን ጥሩ ጅማሮ መሆኑ ተሰምቶት ነበር።ወንድሙ ተጫኔ ይህንን ረቂቅ ሙከራ ተመለከቱና
ለአበራ አፃፃፍን በተመለከተ አንዳንድ ምክሮች ለገሱት፤የተለያየ የአጻጻፍ ዘዬ ያላቸውን መጽሐፍት

329
ጥቋቁር አናብስት

እንዲያነብ መከሩት። ረቂቁ "ለመቃብር በቃ"ይሰኛል። መጽሐፉን ለማሳተም አንድ ግለሰብ ወደ


አንድ "ትልቅ ሰው" ይዞት ሄደ።አበራም ረቂቁን እንዲያይለት እዚህ ሰውዬ ዘንድ ትቶት ሄደ፤ነገር
ግን ከሁለት ወይም ሶስት ወር በኋላ ተመልሶ የህትመቱ ጉዳይ ምን እንደደረሰ ለመጠየቅ ሲመጣ፣
ረቂቁ እንደጠፋ ተነገረው።3

ከዚህ አጋጣሚ በኋላ፣ አበራ ሳያቋርጥ ግጥም መጻፉን ገፋበት።አስራ ሁለተኛ ክፍልን ከጨረሰ
በኋላ፣ አዲስ አበባ ኮተቤ በሚገኘው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ገብቶ
ለአንድ ዓመት ተማረ።ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት አንደኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ እዛው
በተማረበት ትምህርት ቤት እንዲያስተምር ይቀጠራል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን አበራ
ግጥሞቹን ማሳተም ፈለገ፤ይህንን ለማድረግ ደግሞ ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ለአታሚዎቹ በቅድሚያ
መክፈል ይጠበቅበታል።ስለዚህ የተሻለ ክፍያ አግኝቶ ተርፎት የሚቆጥብበት ቦታ እንዲመደብ
ጠየቀ።በዚህ መሰረት ጎንደር በሚገኘው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
መምህር ሆኖ ተመደበ። ከጎንደር ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ በወር ሁለት ብርቤት ተከራየ። ከጓደኛው
ጋር በተከራየው በዚህ ቤት ውስጥ፣ ቤቱን ለምትጠብቅላቸው፣ ለምታፀዳላቸው እና ምግብ
ለምታበስልላቸው የቤት ሰራተኛ በወር አምስት ብር ይከፍሏታል። ለምግብ በየወሩ ከ25–30 ብር
ወጪ እያደረገ በወር ከሚያገኘው የ230 ብር ደሞዝ ላይ በዓመት 1500 ብር አካባቢ መቆጠብ
ቻለ። ይህንን ቋጥሮ ክረምት ላይ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰና 76 ግጥሞችን አሰባሰበ፤ ሁሉም
የሳንሱር ክፍሉን ይሁንታ አግኝተው ማለፍ ቻሉ። እነኚህ ግጥሞች በ1967 ዓ.ም ቀዳማዊ
ኃይለሥላሴ ከሥልጣን በተወገዱበት የመስከረም ወር "ኩል ወይስ ጥላሸት" በሚል ርዕስ ስር
ታተመ። ግጥሞቹ “ድብልቅ” ናቸው፤ስለ ፍቅር፣ ተፈጥሮ፣ ፖለቲካ፣ የሕይወት ፍልስፍና፣ የሰው
ልጅ ሥነ-ልቦና የመሳሰሉትን ከማካተታቸውም በላይ “አብዛኛዎቹ ሕይወትን ከተለያየ አቅጣጫ
ለማየት የሚሞክሩ ናቸው።” የታተሙት 2,000 ቅጂዎች በስድስት ወር ተሽጠው አለቁ።
አበራንየሚያውቁት ሰዎች ግጥሞቹን እንደወደዷቸው ነግረውታል።የአብዛኛዎቹ ግጥሞች
ማስታወሻነታቸው ለጓደኞቹ፣ ዘመዶቹ እና መምህሮቹ ነበር።አገሪቷ እረፍት አጥታ በማያቋርጥ
ለውጥ ውስጥ ስለነበረች ጊዜው የሚፈልገው የተለዩ ግጥሞችን እንደሆነ ሰዎች ይነግሩት ነበር።
ግጥሞቹ ዘመናዊውንም ልማዳዊውንም የአማርኛ አፃፃፍ የተከተሉናቸው።አንዳንድ ቦታ ቤት
የማይመቱ ስንኞችን መጠቀሙን ጥቂት ሰዎችአልወደዱለትም፤ስንኞቹ ሁሉ ቤት እንዲመቱ
ፈልገው ነበር።አበራ ይህ ልቅ ግጥም የተለመደው ባህር ማዶ እንደሆነ፣በኢትዮጵያ ውስጥ ድግሞ
ሰለሞን ደሬሳ ራሱ ይህንን ልማድ እንደጣሰው ያስታውሳል።የሆነው ሆኖ፣የተሰነዘረበት ትችት
እምብዛም እንዳልነበረ አበራ ይናገራል።

330
ጥቋቁር አናብስት

ከመጽሀፉ ህትመት በኋላ፣ አበራ ወደ ጎንደር ተመልሶ ለአንድ ዓመት ያህል አስተማረ። ከዚያ ወደ
አዲስ አበባ መጥቶ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገባ።መጀመሪያ ሬዲዮ ላይ ለአምስት ዓመት ከሰራ በኋላ
ወደ ህትመት ክፍል ተዛውሮ ለሁለት ዓመት ሰራ።በዚያም የእለታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ
የዝግጅት ቦርድ አባል ሆኖ ርዕሰ አንቀጽ እና ሌሎች አስተያየቶችንም መፃፍ ጀመረ። የበአሉ ግርማ፣
ብርሀኑ ዘርይሁን እና ታደለ ገብረሕይወት ዝነኛ አብዮታዊ መጽሀፍት ታትመው ሲወጡ፣ አበራ
የጋዜጣው "የባህል መድረክ" የተሰኘ ገጽ አዘጋጅ ነበር። በዚሁ ወቅት አበራ እና አለቃው ትልቅ
ግጭት ውስጥ ገቡ።4አበራ በባህል ገፁ ላይ የበአሉ ግርማን "የቀይ ኮከብ ጥሪ"ን የተመለከቱ
የተለያዩ አመለካከቶችን ያንፀባርቃል። አለቃው ይህንን አልወደዱትም ፤ “ሰውዬው ደራሲዎች ላይ
ችግር በመፍጠር የሚታወቁ አደገኛ በመሆናቸው” የበአሉ ጎላ ብሎ መታየት አላስደሰታቸውም ፤
"በአሉ ለአብዮቱ የማይበጅ አደገኛ ሰው ነው" ብለው ማስወራትም ጀመሩ።አበራ ግን መጽሀፉ
ከመታተሙ በፊት በሳንሱር ክፍል ስላለፈ ጣልቃ እንዳይገቡ ነገራቸው።አለቃውም ለአበራ
"የመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ" ፃፉለት። አበራ ምላሽ ሰጠ፤ ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት
አለቃው ዳግም የባህል ገፁን ለማየት ጠየቁ። ግጥሞቹን ካዩ በኋላ አሁንም ለአብዮቱ እንደማይበጅ
በመግለጽ ለአበራ ሌላ ደብዳቤ ጻፉለት።አሁንም ምላሽ ሰጠ። ግጥሞቹ ግን የእነተስፋዬ ገሰሰ፣
የአለማየሁ ሞገስና የዮፍታሔ ንጉሴስሜትን የሚገልፁ ዐይነት ግጥሞች ነበሩ።አለቃው እነዚህ ፀረ–
አብዮት ግጥሞች ናቸው በማለት “ሁለተኛ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ” ጻፉለት።በወር ውስጥአበራ
ሶስተኛ “ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ” ሲደርሰው፣ስራውን ለቆ፣ ቀይ መስቀል ማህበርን ተቀላቀለ። ይህ
የሆነው በ1974 ዓ.ም ነበር። በተፈጠረው ነገር የተነሳ በጋዜጠኞች መሀል ትልቅ ግጭት ሆነ።
አበራ ለማ ከኤርትራ ተገንጣዮች ጋር የሚካሄደውን ጦርነት ለመዘገብ በፍቃደኝነት ወደ ጦር ሜዳ
ከዘመቱ ጋዜጠኞች የመጀመሪያው ነበር። ነገር ግን “ድምፁን አጥፍቶ”፣ “ያለምንም ተቃውሞ
በታዛዥነት” የማይሰራ ከሆነ፣ እነሱ ፀጥ እንደሚያሰኙት (ወደ እስር ቤት በመወርወር ወይም በባሰ
መንገድ) በመግለጽ አስጠነቀቁት።ሶስት የአበራ ረቂቆች(አንድ የልብወለዶች ስብስብ፣ አንድ
የግጥሞች ስብስብ እና በቲያትር ቤት ውስጥ ሊቀርብ እየተጠና ያለ አንድ አጭር ተውኔት) ሳንሱር
ክፍል በሚሰሩት በዚሁ አለቃው ታገዱ።አበራ በ1977 ዓ.ም"ሕይወት ለደራሲዎች ከባድ እና
አስጨናቂ ነው" ብሎኝ ነበር (አለቃው ያን ጊዜ ድረስ የሳንሱር ክፍሉ ሃላፊ ነበሩ።)

አበራ ለማ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በሚሰራበት ወቅት አንድም መጽሀፍ አላሳተመም ፤ ነገር ግን


በዚሁ ወቅት በግጥሞቹ ሰበብ ሁለት ጊዜ ያህል ተሸልሞ ነበር።በመጽሔት("የካቲት" እና "ጸደይ")
እና በጋዜጣ ("አዲስ ዘመን" እና "የዛሬይቱ ኢትዮጵያ") የታተሙ ብዙ ግጥሞችን ጽፏል። ልዩ

331
ጥቋቁር አናብስት

ጉዳዮችን የተመለከቱ መጣጥፎችን እና ነፃ አስተያየቶችን ይጽፋል። በራሱ አገላለጽ በዚያን ጊዜ


"ለአብዮቱ የቆምኩ ጥሩ ቀስቃሽ ነበርኩ" ይላል። አበራ በ1974 ወደ ቀይ መስቀል ማህበር
በመግባቱ ራሱን እንደ እድለኛ አድርጎ ይቆጥራል ፤ ምክንያቱም ማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ
ቢቆይ ኖሮ፣ “ሊገደል ይችል ነበር”።በተጨማሪ ብዙ ነፃ ጊዜ በማግኘቱ እንደልቡ መፃፍ ስለቻለ
ቀይ መስቀል ማህበር ውስጥ በቆየበት አንድ ዓመት ሁለት መጽሐፍትን ጽፎ
አዘጋጀ―"ሽበት"እና"ሕይወትና ሞት"። የመጀመሪያው በነሃሴ 1974 ሲታተም ሁለተኛው
በታህሳስ 1975 ታትሟል። በየካቲት 17 ቀን 1975ዓም ወደ ሩስኪ የተተረጎሙ የትላልቅ
ገጣሚዎች መድብል ታተመ፤ስራዎቻቸው ከተካተቱላቸው ገጣሚዎች መሀል ከበደ ሚካኤል፣
ፀጋዬ ገብረመድህን፣ መንግሥቱ ለማ፣ሰይፉ መታፈሪያ፣አየለ ሙላት፣አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ፣
ተስፋዬ ገሠሠ እና አበራ ለማ(“ወደ ስድስት”ግጥሞቹ ተካተውለታል)ምናልባትም ሌሎችም
ይገኙበታል።

አበራ "ሽበት"ን ራሱ በ2,000 ቅጂ አሳትሞት፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ከገበያ ጠፋ። "ሕይወት እና
ሞት" በ5,000 ቅጂዎች ታተመ። ሁለተኛው ህትመት ከቃለመጠይቃችን በኋላ ለገበያ ይቀርባል
ተብሎ ይጠበቃል።በ1975 አበራ ሌላ ሽልማት ተሸለመ።የግጥም ውድድሩን ያዘጋጀው ኢሠፓአኮ
(የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ አደራጅ? ኮሚቴ)ሲሆን አበራ፣ሽልማቱ ደግሞ 800 ብር፣ ሜዳሊያ
እና የምስክር ወረቀት ነበር።

በ1975 የመንግሥት ተቋም ወደሆነው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ድርጅት ገባ። ለቃለመጠይቅ


በ1977 ሳገኘው እዛው እየሰራ ነበር። ስራው የህዝብ ግንኙነት መኮንንነት ነው። እዚህ እየሰራ
ለአብዮቱ ምስረታ 10ኛ ዓመትበዓል አከባበር፣ በአማረ ማሞ አርታኢነት የ17 ኢትዮጵያዊ
ገጣሚዎች ስራ ተሰብስቦ ሲታተም፣አበራ ስምንት ግጥሞቹ ተካተውለታል። ስብስቡ "ጽጌረዳ
ብዕር" በሚል ርዕስ በመስከረም 1977 ታትሞ ወጣ። ከዚህም ሌላ የስድስት አጫጭር ልብወለድ
ደራሲዎች ስራ"አባደፋር"በሚል ርዕስ ነሐሴ 1977 በኩራዝ አሳታሚ ሲታተም፣
ከተካተቱትራሲዎች አንዱ አበራ ነበር። እዚህ ስብስብ ውስጥ አበራ የተጠቀመው የአጻጻፍ ዘዬ፣
ከበፊት ስራዎቹ ፍፁም የተለየ ነበር። ይሄ “ለሁሉም አንባቢ እንግዳ”ሆነ። አበራ ግን በጉዳዩ ጥልቅ
እውቀት የነበራቸው ሰዎች ይህንን ሙከራውን “እንደተቀበሉት” ተሰምቶታል።

አበራ ከሳንሱር ክፍሉ ጋር ሁሌም ችግር እንደገጠመው ነው፤በተለይ ኋላፊው ጠምደው ይዘውት
የሚጽፈውን ነገር ሁሉ ውድቅ ሊያደርጉበት የተዘጋጁ እንደነበሩ ይሰማዋል። በአንፃራዊነት ኩራዞች
332
ጥቋቁር አናብስት

ጋር ማሳተም ይቀላል ፤ እነሱ የራሳቸው የሳንሱር ስርአት ስላላቸው መጽሐፋቸውን ለማሳተም


ከዋና ሳንሱር አድራጊዎቹ ፍቃድ ማግኘት አይጠበቅባቸውም ነበር። ስለዚህ አበራ ስራዎቹን ወደ
ኩራዝ ይዞ መሄድ ጀመረ።በ1977 እኔ ሳነጋግረው፣አንድ 45 ግጥሞችን እና 10 አጭር
ልብወለዶችን የያዘ ስብስብ "የማለዳ ስንቅ" በሚል ርዕስ በኩራዝ አሳታሚዎች አማካኝነት
“ለመታተም በሂደት ላይ” ነበር። በጎንም ሌሎች ግጥሞችን እና አጫጭር ታሪኮችን እያዘጋጀ ነው።
በዚሁ ወቅት የበፊት አጭር ልብወለዶቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋን ለማስተማር
እንደ “ምሳሌ” እየተጠቀሱ ጥቅም ላይእየዋሉ ነበር።

በኢትዮጵያ የሳንሱር ጉዳይ ለደራሲያን የሚዋጋ እሾህ ሆኖባቸው ስለነበር፣ በተገናኙበት መድረክ
ሁሉ የሚያነሱት ጉዳይ ነው። ደራሲዎች መጽሀፉቸውን ወደ ኩራዝ ይወስዱ ዘንድ“ይገደዱ”ነበር፤
ይሁን እንጂ ኩራዝ ራሱ ብዙ ረቂቆችን አይታተሙም ብሎ መመለሱ አልቀረም።አበራ “የሳንሱር
ክፍሉ ውድቅ ያደረገበትን” ሶስት ረቂቆች ይታተሙለት እንደሆን ወደ ኩራዝ ለመውሰድ እያሰበ
ነበር። በተለይ አራት መለስተኛ ልብወለዶቹን የያዘውን ስብስቡን ለማሳተምጓጉቷል። አንደኛው
ልብወለድ ስለ የመን ሲሆን ወደዛ ጉዞ አድርጎ ሲመለስ የፃፈው ነው።ሁለተኛው ማህበረሰቡ ውስጥ
ስላለው ንቅዘት ነው። ሦስተኛው ሽፍታዎችን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ አንድ የጥበቃ ቡድን፣
ከአንድ ሽፍታ ጋር ሲፋጠጡ ስለሚያጋጥማቸው አሳዛኝ አደጋ ነው። የመጨረሻው ስለ ፍትህ ጥያቄ
ነው። የመድብሉ ርዕሰ "ነፍስ ይማር" ሲሰኝ የተፃፈው በ1975 ነበር።

ሁለተኛው የታገደው ተውኔት የተፃፈው በ1976 ዓ.ም ነው።ይህ ተውኔት በትውልዶች መካከል
ስላለ ግጭት ነው። የድሮው ትውልድ ያደገው አብሽ ጠጥቶ ሲሆን አዲሱ ትውልድ ደግሞ
በዘመናዊው እና የተሟላ ምግብ ፋፋ ነው።የተውኔቱ ስም "አብሽና ፋፋ" ይሰኛል።

ሶስተኛው የታገደው መጽሀፍ "ጸሐይቱ" የግጥሞች ስብስብ ሲሆን ከ1976–77 ዓ.ም በኢትዮጵያ
የነበረውን ድርቅ እና ረሀብ ይዳስሳል። የታገደው በርዕሱ ምክንያት ነው። "ሳንሱር ክፍሉ
ኃይለሥላሴ ‘ፀሐዩ ንጉሥ’ በመባል ስለሚታወቁ ጸሐይ የሚል ቃል ለርዕሱ መጠቀም
እንደማልችል ነግሮኝ ውድቅ አደረገብኝ" ይላል አበራ።

በዚህ ዐይነት አበራ በሥነ ጽሑፍ እንቅስቃሴዎቹ ተስፋ ቢቆርጥ ምንም አያስደንቅም፤ እርግፍ
አድርጎ ሊተወው ግን አልቻለም። ከቃለመጠይቃችን በኋላም ቢሆን አበራን ዘወትር አገኘው ነበር።
መፃፉን ባያቋርጥም፣ በሕይወት ታሪኩ ላይ ሊጨምር የሚፈልገው ምንም ነገር አልነበረም።

333
ጥቋቁር አናብስት

በ1977 አበራ አብዮቱ እንደጠበቀው ባለመሆኑ ተስፋ ቆርጦ ነበር።ጀርባ መስጠቱ ከ1977 ዓ.ም
ወዲህ በየዓመቱ እየጎላ መጣ እንጂ አልቀነሰም። ነገር ግን በጊዜው ከዚህ በላይ በይፋ መናገር
“አደገኛ” ስለነበረ ተጨማሪ ዝርዝር ውስጥ ላስገባው አልፈለግኩም።

አንዳንድ አንባቢዎች አበራ ገና ለጋ ጸሐፊ በነበረበት ወቅት እንኳን ኢትዮጵያ በጊዜው ከነበሯት
ታላላቅ ጸሐፊዎች አንዱ አድርገው ይቆጥሩት ነበር።

ማስታወሻ፡ በ1987 የመንግስት ለውጥ መጥቶ ሁኔታዎች በመቀያየራቸው አበራ ከነበረው ጥሩ


ስራ ተፈናቅሎ፣ አዲስ አበባ ላይ በአንጻራዊ ስራ ፈትነት በሚባል ደረጃ ውስጥ እንደሚገኝ ሰማሁ።

የተርጓሚ ማስታወሻ-እ.አ.አ (2005) ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድሕን፤ስዊድናዊ ኤርትራዊ


የሆነውን የአስመራውን እስረኛ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ እ.ኤ.አ (2009)ሃሳብን በነጻ
የመግለጽ ሽልማት እንዲሸለሙ ከፍተኛ አስተዋጥጽ አድርጓል፡፡

ማስታወሻዎች

1) የለማ ደግፌ አባት የመንዝ አማራ ሲሆኑ እናቱ ኦሮሞ ናቸው።

2) ገብረ ጉራቻ ማለት "የጥቁሩ ባህር አገልጋይ" ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ጉራቻ
ከሚባለው ወንዝ መሆኑን አበራ ለማ ይናገራል።

3)ከቃለመጠይቃችን ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ አበራ ያን የ"ትልቁን ሰው"የቀድሞ አገልጋይ


አግኝቷቸው ነበር ፤ ሰውዬው ስለ ረቂቁ እንደሚያስታውሱና አሁን ድረስ በእጃቸው እንደሚገኝ
ነገሩት። አበራም ረቂቁን አስመልሶ በድጋሚ ቢያነበው ጥሩ ታሪክ ሆኖ አላገኘውም። ስለዚህ
አለመታተሙ ለበጎ ነበር ብሎ እንዳሰበ አጫውቶኛል።

4) አለቃው የፕሬስ ክፍል ሐላፊ ነበሩ። እስከ 1978 ድረስም የሳንሱር ክፍል ዋና ሀላፊ ነበሩ።
አበራ ሥነ ጥበባዊ ውበት ያልገባቸውና ሁሉም ደራስያን ላይ ችግር በመፍጠር የሚታወቁ ነበሩ
ይላል። እንደውም ይላል “ችግር የሚፈጥሩት ሆን ብለው ነው ፤ የኢሕአፓ ደጋፊ ስለነበሩ
መንግስትን ማስጠላት ስራዬ ብለው ተያይዘውት ነበር ይባላል።”

334
ጥቋቁር አናብስት

ተስፋዬ ገሠሠ
ለቴአትር የተሰጠ ህይወት ተስፋዬን ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘሁት የግል
ችግሮች ተጋርጠውበት ነበር፡፡በመጀመርያ ትዳሩ፤ በስራው፤በገንዘብ…
የአብዮቱ መሳፍንት ይኖሩበታል ተብሎ በሚወራለት በቦሌ መንገድ
ላሰራው ቤት እዳውን ለመክፈል ተስኖት ነበር፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን
ብእረኞች የመጻፍ ሃሳቤን ሲሰማ ደስተኛ ሆኖ ለቃለመጠይቅ መጣ፡፡
ተረጋግቶ ቃለመጠይቁን ለመስጠት ግን ጥቂት ጊዜ ፈጅቶበታል፡፡
በስተመጨረሻ ለነዚህ ቃለመጠይቆች ስንገናኝ አዲስ ህይወት ጀምሮ በአዲስ ሚስት በአዲስ
ኑሮ…..ቤቱንም የማስቀረት እድል ገጥሞት ነበር፡፡(ፔጆውን ሽጦና መስዋእትነትን ከፍሎ ቢሆንም)

ተስፋዬ ገሠሠ መስከረም 17 ቀን 1930 ዓ.ም የመስቀል እለት ነበር የተወለደው፡፡የተወለደው


በአነስተኛዋ የሃረርጌ ጉሮ ጉቱ በተባለች መንደር ነው፡፡ያደገው ግን በዋና የክልሉ ከተማ በሆነችው
ደደር ሲሆን በአቦ ቤተክርስትያን ተጠመቀ (የክርስትና ስሙም ተስፋ ህይወት ሲባል በቅዱሱ
በመታሰቢያነት ይጠራል)አካባቢው ቱሎ የሚባል በልጅነቱ ወቅት በአመት ሁለቴ ይሄድበት የነበረ
የእናቱ ቤተሰቦች በሙሉ የተጠመቁበት አካባቢ ነው፡፡እናቱ ተስፋዬ የ8 ወር ልጅ ሳለ፤አባቱ ደግሞ
የሁለት አመት ልጅ እያለ ነበር ያረፉት፡፡ተስፋዬም ስለነሱ የሚያስታውሰው ምንም ነገር የለም፡፡
ከሌላው የቤተሰቦቹ አባላት ተገልሎ በውርስ ባገኘው መሬት ላይ በቤተሰቦቹ ጭሰኞች እጅ ነበር
ያደገው፡፡አእምሮው ወደ ኋላ ማስታወስ የሚችለው ደደር በኢጣልያ ጦር እስከተራቆተችበት እና
በኤርትራ ባንዶች እስከተዘረፈችበት ጊዜ ድረስ ነው፡፡ በወቅቱ ተስፋዬ 3 አመቱ አካባቢ ነበር፡፡
ቆይቶ ያክስቱ ልጅ ሊጎበኘው እንደጋሻ ጃግሬ ሊጠብቅውም መጣ፡፡ከአክስቱ ዘንድም ወደ አዲስ
አበባ መጥቶ ትምህርት እንዲገባ መልእክት ይዞለት ነበር የመጣው፡፡ተስፋዬ ስለዚህ በ1938
መባቻ ወራት በባቡር ሄደ፡፡በዚህ ወቅት 7 አመቱ ነበር፡፡ከዛ በፊት ግን ተስፋዬና ሌሎች የመንደሩ
ልጆች የቤተ ክህነት ትምህርት በጭሰኞች በተያዘው የተስፋዬ መሬት ላይ በተቀጠሩ ቄስ ይማራሉ፡
፡ብቸኛ የነበረው ዘመድ አንድ በአካባቢው ያለ አጎቱ ሲሆን እሱም ወደ ደደር እግር አያበዛም፡፡

አዲስ አበባ ተስፋዬ የእናቱ ታላቅ እህት ጋር አረፈ፡፡ጉሮ ጉቱ ባለው ቤትዋ ነበር ባለቤቷ
የአካባቢው አስተዳዳሪ እያለ ተስፋዬ የተወለደው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ተስፋዬ ማህበራዊ ቀውስ
ገጠመው፡፡ይህንንም ክልስ እንደሆነ በጠየቅሁት ጊዜ ባሳየኝ አጸግብሮት ይታይ ነበር፡፡ከአግራሞቱ
መለስ ካለ በኋላ “የሚስማሩን አናት የሚመታ”ጥየቄ እንደ ጠየኩት ለሙሉ ህይወቱና ስራው እርሾ
የሆነው ይሄ ነገር እንደሆነ ነገረኝ፡፡ሰዎች በአዲስ አበባና በትምህርት ቤት ዘመዶቹ መሃል ሲሆኑ
ስለ ተስፋዬ ገጽታው አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ነጣ ያለ መልክና ሉጫ ጸጉር
335
ጥቋቁር አናብስት

የነበረው ሲሆን ሌሎች ሰዎች ባይነግሩኝ እኔ ልዩነቱን አላስተውለውም ነበር፡፡ይህ አዲስ አትኩሮት
ተስፋዬን ረብሾት ታሞ ሆስፒታል ሊገባ በቅቶ ነበር፡፡ተስፋዬ ሰዎች እንደሚጠቁሙት አክስቱን
ትክክለኛ አባቱ ጣልያናዊ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እስከጠየቀበት ጊዜ ድረስ የአእምሮ እረፍት
ማግኘት አልቻለም፡፡ክልሶች በኢትዮጵያ ብዙም የሉም ነበር በዚያ ወቅት1፡፡ጣልያኖችም ጠላት
ስለነበሩ ከጣልያን ወታደር አባት መወለዱ ለሱ አሳፋሪ ነበር፡፡ሌላው ቀርቶ የተስፋዬ አባት
ዘመዶች እንኳን የዘመዳቸው ልጅ እንዳልሆነ ይናገሩ ነበር፡፡"ይቺ እንኳን አባቴ ያወረሰኝን መሬት
ስለፈለጉ የተናገሯት ነች" ይላል ተስፋዬ፡ጥያቄው ለተስፋዬ አንገብጋቢ ሆነበት፡፡በአካል
በሚያስብል ደረጃም ራስ ምታት ይታመምየነበረ ሲሆን በኋላ ነበር የተወገደለት፡፡

ተስፋዬ አክስቱን ሲጠይቃት በመሞቻዋ ሰአት ከእሷና(ከእናቱ) ከባሏ ጋር እንደነበረች ነገረችው፡፡


እናትየው በመሞቻዋ ሰአት የተስፋዬንና የአክስቱን(የእሷን)አውራ ጣት በትእምርታዊ መልኩ
አያይዛ አደራውን በእግዚአብሔር ፊት ሰጠቻት፡፡ የተስፋዬ እናት ስትሞት ታላቂቱ ስለተስፋዬ
አባት የሚወራውን ስለሰማች በመጨረሻው ሰአት ስለ ተስፋዬ ትክክለኛ የአባት ጉዳይ አነሳችባት፡፡
ተስፋዬ የአክስቱን ቃላት(ስለ እናቱ የነገረችውን) ያስታውሳል..“በህልሜም ሆነ በእውኔ ከነጭ
ወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም ተስፋዬን ከባሌ የወለድኩት ልጅ ነው”የሟች ኑዛዜ በሃገሪቱ
ስለሚከበር ባልየው (የተስፋዬ አባት) አምኖ ተቀበለ፡፡ያለውንም ሙሉ ንብረት ለተስፋዬ
አወረሰው፡፡ተስፋዬ በዛን ወቅት የ2 አመት ልጅ ነበር፡፡ተስፋዬ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት
ወቅት አባትና እናቱ በተጋቡ በ16ኛው አመት ነው የተወለደው፡፡ምንአልባትም ከአባቴ በኩል ባሉ
ዝርያዎች ይሆናል ይሄን ገጽታ የወረስኩት ያስባለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ደደር ለጉብኝት ሲሄድ
በአባቱ በኩል የሆነች አንዲት በእድሜ የገፋች አንዲት ሴትዮን ካየ በኋላ ነው፡፡ነጣ ያለ ገጽታና
ሉጫ ጸጉር የነበራት ሲሆን አባቷ ጎንደሬ ነበሩ፡፡እንደተነገራት ከሆነ አጼ ቴዎድሮስ (በኦሮሞ ስም
በሚጠሩበት ወቅት)ሰዎችን በመንደር ሰብስበው እንዴት መንደሩን እንዳቃጠሉ ታስታውሳለች፡፡
ተስፋዬ በገጽታ ዘመዶችህን ትመስላለህ ያለችው ዘመዱ እንደነገረችው ከሆነ በዛን ወቅት ከነበሩ
ዘሮቿ መሃል አንዱ ነጭ ነበር፡፡አክስቱ ስለ ትክክለኛው ውልደቱ ከነገረችው በኋላ ዳግመኛ
ጥቄውን ባያነሳም፡፡በምንነጋገርበት ወቅት የታዘብኩት በዚህ ጥያቄ ስሜቱ በጥልቀት እንደሚነካ
ነው፡፡

ተስፋዬ በአባቱ ገሠሠ ቆለጭነት ተማመነ2 እናቱ ከተጉለት የተገኘችው በለጠች ያየህይራድ
የሚኒሊክ ቅርብ የነበሩት የደጃዝማች ግርማሜ ነዋይም ዘመድ ነበረች3፡፡ተስፋዬ በእናቴ በኩል
ከግርማሜ አራተኛ ትውልድ ነኝ ይላል፡፡ገሠሠ ቆለጭ የፊትአውራሪ ቆለጭ ልጅ ነው፡፡(ፊት

336
ጥቋቁር አናብስት

አውራሪ ቆለጭ እንደ ጓደኛቸው ደጃች በንቲ ሁሉ የኃይለሥላሴ አባት የራስ መኮንን ጦር አዛዥ
ነበሩ) ፊትአውራሪ ቆለጭ ከጉራጌ አንዲት ሴት አግብተው ገሠሠን ወለዱ፡፡4 ራስ መኮንን የሃረርጌን
ግዛት በአስተዳዳሪነት ሲሾሙ ቆለጭና በንቲ አብረዋቸው ነበር የሄዱት፡፡በአካባቢው የነበሩትን
የሃረር ሙስሊም ገዢዎች አሸንፈው አካባቢውን በጠንካራ የመንግስት ቁጥጥር ስር አዋሉት፡፡

ቆለጭ ከራስ መኮንን ጋር በተመሳሳይ ቀን ወንድ ልጅ አገኙ፡፡የሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ


የልጃቸው የክርስትና ስሞች ኃይለሥላሴ ነበር ፡፡የቆለጭ ልጅ በዛው ወቅት (ተፈሪ በጃርሶ/ኢጃርሶ
ጎሮ ሲወለዱ የቆለጭ ልጅም ሃረር ውስጥ ሳይወለዱ አይቀርም) ግራዝማች ሃይሌ ሲሆኑ የቆለጭም
ልጆች ከኃይለሥላሴ ጋር ቢቀራረቡም አብረው ግን አላደጉም፡፡የተስፋዬ አባት ገሠሠ ከታላቅ
ወንድማቸው ከኃይለሥላሴ (ሃይሌ) (በ76 አመታቸው ነበር ያረፉ) ቀጥሎ ከሁለት አመት በኋላ
ነበር የተወለዱት፡፡ቀዳማይ ኃይለሥላሴ በአንድ ወቅት ተስፋዬ በተፈሪ መኮንን5ተማሪ ሳለ
ስለቤተሰቦቹ ጠይቀውት ነግሯቸው አስታውሰዋቸው ነበር፡፡

ገሠሠ ቆለጭ በቃፊርነት ከጣልያኖች ጋር የተዋጉ ሲሆን ዋነኛውን የሽምቅ ተዋጊ ቡድን
አልተቀላቀሉም፡፡ጣልያኖቹ ገሠሠንና ሌሎችን ገበሬዎች ይቅርታ ለማድረግ ቃል ስለገቡላቸው
በይቅርታ ገብተው በገበሬነት መኖር ቀጠሉ፡፡ነገር ግን ኢትዮጵያ ከወረራው ነጻ ከመውጣቷ በፊት
ነው የሞቱ፡፡ፊትአውራሪ ቆለጭና ደጃች በንቲ ግን ለረዥም ጊዜ በህይወት ቆይተዋል፡፡ለተፈሪም
በሃረር ግዛት አስተዳዳሪ ሳሉ አማካሪ ሆነዋል፡፡

ተስፋዬ የወረሰውን መሬት ልጅነት ይዞት አልያም በትምህርቱ መንስኤነት ብዙም ሊቆጣጠረው
አልቻለም፡፡አክስቱም መሬቱን ብታስተዳድረውም ርቀት ባለው ስፍራ ስለምትኖር በሌለችበት
ስለምትቆጣጠር መሬቱን በስነ ስርአቱ መያዝ አልተቻለም፡፡ ተስፋዬ ውጪ ትምህርቱን ጨርሶ
ሲመጣ ነው መሬቱን ማቅናት የተቻለው፡፡

***

በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የአርበኞች ልጆች በአዳሪነት ሲማሩ ተስፋዬ ከነሱ አንዱ ነበር፡፡ነገር
ግን እንደ ሌሎች ልጆች ዐይነት ስሜት ሳይሰማው (እንደ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ሳይቆጠር)እንደ
ባይተዋር እራሱን እያየ ነበር ለበርካታ አመታት የዘለቀው ፡፡እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን እንጂ
ማንበብን አይወድም፡፡እስከ 9ኛ ክፍል መጨረሻ ድረስ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ሳያመጣ ነበር
የቀጠለው፡፡ ከዛ በኋላ ግን እየተሻሻለ መጣ፡፡በወቅቱ የትምህርት ጠቀሜታ አልታየውም፡፡በአንድ
ወቅት በትያትር ውስጥ ሚና ተሰጠው ሚናውም እንደ ህጻን ልጅ መጮህ ነበር፡፡ይህቺ ጥቂት
የቴአትር ክፍል ልቡን ለትያትር ሳታነሳሳው አትቀርም፡፡አንደኛ ደረጃ ሳለ የትንቢት ቀጠሮን

337
ጥቋቁር አናብስት

በከበደ ሚካኤል ተደርሶ ሲመደረክ ለማየት በቅቷል፡፡ ለአመታትም ያስታውሰዋል፡፡6ተስፋዬ


beyond pardon የተሰኘውን መጽሐፍ ውርስ ትርጉም በከበደ ሚካአል ተጽፎ አንብቧል፡፡
እንደ አብዛኞቹ የወቅቱ ተማሪዎችም የከበደ ሚካኤልን ሃገርኛ እሮሮ ግጥም በልቡ አነብንቧል፡፡7

እነዚህ አፍላ ተጽእኖዎች ልቦናውን ወደ ስነ ጽሁፍና ቴአትር መልሰውት ይሆናል ትወና ግን ለሱ


በሌላም መንገድ ሳትጋብዘው አትቀርም፡፡ተስፋዬ በተለምዶ ነገሮችን የሚሰራው ሌሎች
ስለሰሯቸው እንጂ ስለሚፈልግ አልነበረም፡፡ለትምህርት ግድየለሽ የነበረ ሲሆን የሚያነበውም
ከሌሎች ጋር ለመስተካከል ነበር፡፡ፈተናዎቹንም እንዲሁ በተመሳሳይ ምክንያት ነበር የሚያልፈው
እንጂ ለትምህርት ዐይነቱ በተለየ የሚያሳድረው ፍቅር አልነበረም፡፡10 ኛ ክፍል ሲደርስ ነበር
የትምህርቱን ጉዳይ አሻሽሎ ከክፍሉም በላይ ለመሆን የበቃው፡፡ በቀጣዮቹም ሁለት
አመታት(11ኛ 12ኛ ክፍል)አንደኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃን ማግኘት ጀመረ፡፡በዚህም ወቅት ቢሆን
እውቀትን ፈልጎ ሳይሆን መብለጥ እንደሚቻል ለማሳየት ሲል ነበር ፡፡

የትአትር መድረኩ ይህንን ለማስረገጥ ምቹ ምህዳር ፈጠረለት፡፡ የበታችነት ስሜቴን ለመግደል


የጫወታ ሜዳዎችም እንዲሁ ናቸው ሲል ያስባል፡፡ለዚህም ነበር ጨዋታዎችን የሚወደው፡፡
በክፍል ውስጥ የሚደረጉ የድርሰትንም ስራዎች አስፈላጊ ሆነው አግኝቷቸዋል፡፡ጥሩዎቹ
ተመርጠው ክፍል ውስጥ ስለሚነበቡ እሱም ስራዎቹ ሲነበቡ ለማየት ፈለገ፡፡ይህንን ለማሳካት
አእምሮውን መወጠር በተብራራ እንግሊዘኛ የተጻፉ ታሪኮችን ማንበብ ጀመረ፡፡ይህ ሁሉ ግን
እውቅናን በመሻት እንጂ ለእውቀቱ ፍቅር ኖሮት አልነበረም፡፡ፊልም ለመመልከት የሚሄደውም
ከውዴታ በመነጨ ሳይሆን ሌሎች ስለሚመለከቱ ነበር፡፡ ከጓደኞቹ መሃል አንዱ ስብሃት ገብረ
እግዚአብሔር ነበር፡ተስፋዬ ባህርይውን ሲገልጸው “ከስፖርት በላይ የመጻሕፍት ቀበኛ የሆነ
ዝምተኛና ጴንጤ ”ይለዋል ፡፡ተስፋዬ ስለራሱ ሲናገር ግን ልታይ ልታይ የማበዛ በቀላሉ ነገር
የምጣላ ነበርኩ ይላል፡፡ምንም እንኳን አንዳንድ ወቅት ላይ ታጋሽ ሊሆን ቢችልም ሁሌ መለፍለፍ
የማይሰለቸው ሲናገርም ጯሂ ነበር፡፡

አንደኛ ክፍል እያለ ተስፋዬ ታሞ የተወሰነ ጊዜ በሆስፒታል ካሳለፈው ውጪ ግን 15 አመቱን


በሙሉ በአዳሪነት በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ውስጥ ነው ያሳለፈው በወር 15 ብር እየከፈለ (አክስቱ
ናቸው የሚሸፍኑት) አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታተለ፡፡መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃው(ከ7ኛ
ጀምሮ) ግን ለሁሉም ነጻ ነበር፡፡በዚህ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ እያለ በሚመደረኩት ተውኔቶች
ላይ ሁሉ ተሳትፎ ነበረው፡፡ይህም በአመት አንዴ ይደረጋል፡፡ስካውትም ስለነበር ለሽርሽር ብዙ ጊዜ
ይወጣል፡፡በሚቀጣጠለው እሳት ዙርያ ይዘፍናል ይተውናል፡፡ በስካውቶች ዋና መሰባሰብያ
በሆነው የግቢው አካል ሳምንታዊ የመዝናኛ መርሃ ግብር ነበር፡፡ተስፋዬም በመለፍለፍና እንደ
338
ጥቋቁር አናብስት

ሌሎቹ መሆኑን ለማስገንዘብ በመጣር ሁሌም ይሳተፋል፡፡ሁሌም ባይሆን ወደ ሃገር ፍቅር ቴአትር
ቤት ገንዘብ ባለው ወቅት ጎራ ማለትን ያዘወትራል፡፡ራዲዮንም በብዛት ይከታተላል፡፡

በ1948 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ቀጥታ ወደ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ገባ፡፡
ለአራት አመታትም ዋነኛ ትምህርቱን ህግ በማድረግ ተማረ፡፡ኮሌጅ እያለ ነበር ተዋናይ የመሆን
ፍላጎት ያደረበት፡፡በፊልሙም ሆነ በመድረክ…በተጨማሪ ደግሞ (ወይም) በተወሰነ መልኩ ለሱ
እንደትወና ስለሚቆጠር በተጓዳኝ ጠበቃ የመሆን ፍላጎትን አሳደረ ምንም እንኳን እነዚህ ሃሳቦች
ከውጥኑ ቅርጽ ባይዙለትም ቅሉ፡፡ለሱ ኮሌጅ ከጨረሰ በኋላ (የሆነ መልካም ነገር ብቻ
እንደሚመጣ) እርግጠኛ እየሆነ መጣ፡፡“መዝናናትንና ትፍስህት ያለው ህይወትን እፈልግ ነበር
ትርጉሙ ባይገባኝም ምንአልባት ስራ ማለት ይሆናል፤ ሚስት ፡ መኪና÷ ብቻ ከፖለቲካ ጋር
አይነካካ”

ሁለተኛ ደረጃ እያለ ልጃገረዶች መቃኘት ጀመረ፡፡በፍቅር ወደቀ (እንበለ ጾታዊ እሳቤ ወይም
ፍትወት ነበር፡፡አቅም ሳላበጅ ምንም ነገርን ከሴት ጋር አልፈጸምኩም) ይላል ባለ ረጅም ፀጉሯ
ፍዮሬላ ግን ሁሉንም በፍቅር ለማንበርከክ ጉልበት የነበራት “እንደኔው ክልስ” ነበረች ይላል፡፡
ቀጨኔ መድሃኒያለም አካባቢ ሄዶ እየሰረቀ ቆነጃጅቶቹን ይመለከታል፡፡ምንአልባት ከነሱ መሃል
አንዷ ሚስቴ ብትሆን እያለ ይከጅላል፡፡ገና ብቅ ሳይሉ ግን እየተቀለቡ ተቸግሮ በትምህርት ቤትም
ሆነ በኮሌጅ ትክክለኛ የሴት ጓደኛ ሳይኖረው ነበር ግዜውን የገፋው፡፡ሲበዛ አይናፋር ነበር፡፡በኋላ
ወደ በቀይ መብራት ወዳበደው የውቤ በርሐ ለዳንስና እንዳንዴም እጁ ከረጠበ አቅፎ ለማደር ጎራ
ማለቱን ተያያዘው፡፡ይህም የሴት ጓደኛ ከመያዝ ይቀላል፡፡ስለዚህ ሲመሻሽ ስብሃት ገብረ
እግዚአብሔርን ጨምሮ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ለመዝናናት ወደዚያ ይሄዳሉ፡፡

ተስፋዬ እንደሚናገረው ከሆነ በልጅነቱም ሆነ በብስለቱ ለመጻፍና ለመተወን ያለው ፍላጎት


የሌሎችን አድናቆት ከመሻት የመጣ ነው፡፡ጭብጨባ እንዴት እንደሚያስደስተው ያስታውሳል፡፡
ምን ያህል ጥኡም ዜማ እንደሆነ አስራ አንደኛ ክፍል እያለ አራት ኪሎ ካምቦኒ ሲኒማ ዩንቨርስቲ
ኮሌጁ የነበረበት ቦታ በተወነው ትወና ያስታውሳል፡፡ትውኔቱን8ተጋባዥ እንግዶች ብቻ ነበር
የተከታተሉት፡፡አብረውት ከተወኑት መሃልም መኮንን ዶሪ እና ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
ይገኙበታል፡፡

ኮሌጅ ውስጥ በስነ ጽሁፍና ክርክር ክበቦችም ይሳተፋል፡፡ ይህም ለሰዎች በአንድ በማንኛውም
አርእስት ላይ ማውራት መጻፍ እንደሚችል ለማሳየት ያህል ነው እንጂ ትወና ነበር ዐይነተኛ
ፍላጎቱ፡፡በተጨማሪም ቅርጫት ኳስ የጠረጴዛና የሜዳ ቴኒስ እና ሶፍትቦል የሚዝናናባቸውና

339
ጥቋቁር አናብስት

በንቃት የሚሳተፍባቸው ስፖርቶች ነበሩ፡፡መጽሐፍ መግለፅ ግን አስቸጋሪ ግብር ይሆንበታል፡፡


ቢሆንም ግን ጥሩ ውጤት አምጥቶ የውጪ የትምህርት እድል አገኘ፡፡በህላዌነት ላይ የሰራው
አንብሮ ጥሩ ስላነበረ እንጂ በማዕረግ ሊመረቅ ይችል ነበር፡፡በቀላሉ የሚገባው ሲሆን ከፈተና በኋላ
ግን በፍጥነት ይረሳዋል እስከአሁንም ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንደሌለው ይናገራል፡፡ በኮሌጁ
ውስጥ ሳለ የሳሙኤል ቤኬት waiting for godot የተሰኘው ስራ በጊዜው ተወዳጅ ቢሆንም
ተስፋዬ ሊገባው እንዳልቻለ ያታውሳል፡፡

***

ከዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በ1951 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ አጠናቆ ወጣ፡፡በ1952 ወደ አሜሪካ በነጻ
የትምህርት እድል ተጓዘ፡፡እዚያ ለሁለት አመታት ያህል እስከ 1953 መጨረሻ ድረስ ቆየ፡፡ይህም
በአይዘንሃወር እና በኬኔዲ የስልጣን ዘመን ነበር፡፡በቺካጎው ኖርዝ ዌስተርን ዩንቨርስቲ ነበር
ያጠናው፡፡በሰሜኑ መሆን ከ ደቡቡ የሃገሪቱ ግዛቶች ይልቅ ለአፍርቃውያን ተማሪዎች ይሻላል፡፡
በአሜሪካ ውስጥ እያለ የቀረው አለም ምን ያህል እንደሰለጠነ አይቶ የማህበራዊ ቀውስ ተጽእኖ
አድሮበታል፡፡አሜሪካንን ከሃገሩ ጋር ማነጻጸር ወደ ጥልቅ መሬት የመስመጥ ያህል ሆነበት፡፡
ዘረኝነትንም በዚያ አየው፡፡ጥቁሮች በሚገባ አይስተናገዱም፡፡የመኝታ አገልግሎት በፈለገባቸው
አንዳንድ ቡና ቤቶች እንዳይገለገል ጥቁር በመሆኑ ብቻ ተከልክሏል፡፡ይህን ከነሱ ቁሳዊ ሃብት ጋር
በማናጸር (ትናንሽ አእምሮዎች ታላላቅ ህንጻዎችን ገነቡ)ሲል ደምድሟል፡፡“ለዚህ ይሆናል
ኢትዮጵያ መዘመን ስትፈልግ ፊቷን ወደ ምስራቅ የመለሰችው”ይላል፡፡ተስፋዬ በትምህርቱ በኩል
“የምፈልገውን አግኝቻለሁ” ስለሚል በአሜሪካን ያሳለፈው ጊዜ መልካም እንደሆነ ያስባል፡፡
በአሜሪካ በነበረው ቆይታ ለሃገሩ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት በመወሰን በቴአትሩ ዘርፍ
እውቀቱን ለማበርከት ተነሳ፡፡

በአሜሪካ የመማሩ ሂደትም ፈትኖታል፡፡እሱም ራሱን ለትምህርት አስገዝቶ በማስቀጠል ማንንም


ጓደኛ ሳያደርግ በብቸኝነት ነበር የጨረሰው፡፡ሌሎቹ ተማሪዎች ቴአትሩን ቀደም ብለው ተምረውት
በተግባርም ሆነ በቃላቸው ስለተቆራኙት እዚያ ከነበሩት ተማሪዎችም (የቴአትር ኮርሶችን
ባለመውሰዱ የበታችነት ስሜት፤ በአነጋገር ቅላጼውም እፍረት ይሰማው ነበር፡፡ከኮሌጅ ውጪ
ኮርያዊ ናይጄርያዊ ፤ከደቡብ የመጣ ጥቁር አሜሪካዊ ጓደኞች ቢኖሩትም አብዛኛውን በራሱ አለም
ውስጥ ነበር የሚዋኘው፡፡

የመጀመርያው አመት የመሰናድኦ ሲሆን የሚቀጥለውን አመት በቴአትር ጥበብ የማስትሬት ዲግሪ
የምረቃ ስራዎችን በመስራት ነበር ያሳለፈው፡፡ለመድረክ የበቃ ተውኔት ጻፈ፡፡ በአንድ የጣልያን

340
ጥቋቁር አናብስት

ተውኔት ላይ ተሳተፈ (six man in search of character)ይሰኛል የሎኔስኮን


rhinoceros ዳይሬክት አደረገ፡፡አንብሮውን በተውኔት ላይ ሰራ፡፡

***

ተስፋዬ በዚህ ዘርፍ መሰረቱ ደካማ ሆኖ ሳለ ለምን የቴአትር ጥበብን ለማጥናት ፈለገ ?በተወነበት
"እዮብ" በተባለው ተውኔት የተነሳ እንደሆነ ይናገራል፡፡ስለ መጸሐፍ ቅዱሱ እዮብ የተጻፈ ነው፡፡
ይህም የተፈጸመው ኮሌጅ አራተኛ አመት እያለ አዲስ አበባ ሆኖ ነበር ፡፡ሚናው እርሱ ራሱን እንደ
እዮብ የተበደልኩ ነኝ ብሎ አስቦ ተጫወተው፡፡ከገጸ ባኅርይው ጋር ተዋወቀ፡፡ ህመሙ ለማንነቱና
ለክብሩ ባለው ትግል ተስማማው፡፡ እግዚአብሔርም ለእዮብ “እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን
ታጠቅ እጠይቅሃለሁ አንተም ተናገረኝ”አለው፡፡ተስፋዬ ራሱ የተውኔቱን ጠቃሚ ነጥቦች ማሰባሰብ
ጀመረ፡፡በግል አስተሳሰቡን ሁሉ ተገዳደረው፡፡እሱ እንዳለው ከሆነ ሰዎች “በተሰጥኦ የተተወነ”
ተውኔት ነው ይላሉ፡፡“ይህ የሆነው እዮብን ስላወቅሁት ነው ለመኖር የሚደረግ ፍትግያን
እንድጋፈጥ አደፋፈረኝ፡፡የመጀመርያው ምሽት ውብ እንደነበር ተሰምቶኛል፡፡ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ
ሁለተኛውን ምሽት ተከታትሉት”ተስፋዬም በዚህ ወቅት“ትንሽ ትወናውን ስላጋነንሁት ድምጼ
ቢሰልም ንጉሱ ግን በተውኔቱ ተመስጠው ነበር ጠንካራ ስራ በመስራቴ በተውኔቱ ላይ የነበሩ
ግድፈቶችን እንዳጠራ ረድቶኛል ስለዚህም ጭምር ነው የተውኔቱ ´እንከኖች´ ሳይቀሩ መልካም
የነበሩት” ይላል፡፡

ኃይለሥላሴ ተውኔቱን ባዩ ማግስት አሁን ዩንቨርሲቲ ከሆነው ቤተመንግስት ጠርተው የእጃቸውን


ሰአት ሸለሙት፡፡ ቀጥሎም ወደ ንጉሱ ቢሮ እንዲሄድ ተነግሮት የትምህርት ምክትል ሚንስትሩን
እንዳልካቸው መኮንንን (እራሳቸው ኃይለሥላሴ ነበሩ የትምህርት ሚንስትር) አገኛቸው፡፡ተስፋዬ
ምን መሆን እንደሚፈልግ ተጠየቀ፡፡ህግ ማጥናት እፈልጋለሁ ሲል መለሰ፡፡ነገር ግን ንጉሱ ቴአትር
እንዲያጠና መፈለጋቸውን በዚህ መንስኤም ወደ ውጪ ሊልኩት ማሰባቸውን ተነገረው፡፡ የቀዳማዊ
ኃይለሥላሴ ቴአትር ቤት ከጥቂት አመታት በፊት ስለተከፈተ ተስፋዬ እድሉን በይሁንታ
ተቀበለው፡፡የሚማርበት ቦታም ይፈለግለት ጀመር፡፡እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው ወደ ትያትር የመጣው፤
ወደ አሜሪካ ሄዶ የትያትር ጥበባትን ሊያጠና የበቃው፡፡ተስፋዬ ኃይሥላሴን በጣም ያከብራቸው
ነበር፡፡በወቅቱ ለሌላው እንደሚሰማው ሁሉ ለሱም ´የኢትዮጵያ አንድ አካል´ እንደሆኑ ያስባል፡፡
ተስፋዬ በእግዚአብሔር እንደሚረዳ ፡ለማሳካት የቆመለትም ተልእኮ እንዳለው ይሰማዋል፡፡
አቅሙንም አሳምሮ ያውቃል፡፡እርሱ እራሱም ቢሆን በተውኔት፤በጸሃፊ ተውኔትነት፤ በመራሔ
ተውኔትነት እና በትያትር የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ሞከሯል፡፡ ተልእኮና የግዴታ ስሜቱ አብሮት
341
ጥቋቁር አናብስት

ዘልቋል፡፡“በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን በዘርፉ ውስጥ ያለሁት ለዚህ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ጥሩ


ልሆን ከማልችልባቸው ሳይንስና ሂሳብ ውጪ በየትኛውም ሙያ ልሳተፍ እችል ነበር የእዮብ
ታሪክና ተውኔቱ ግን በህይወቴ ላይ ለውጥን አመጡ” ይላል፡፡

***

በ1954 ዓ.ም ከአሜሪካ የትወና፤ዳይሬክቲንግና የገጸመድረክ ግንባታን ተምሮ ወደ አዲስ አበባ


ከመጣ በኋላ ተስፋዬ በ1954 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር ቤት ወድያውኑ ተቀጥሮ
መስራት ጀመረ፡፡ይህም የሆነው በትምህርት ሚንስትር ውስጥ በጥበባት ክፍሉ የቢሮ ስራን
“ቢሮክራት መሆን አልፈልግም”ብሎ አሻፈረኝ ካለ በኋላ ነበር፡፡የቀረበለትና የተቀበለው ስራ9
የተውኔት ዳይሬክተርነትና የመድረክ ተቆጣጣሪነት ነበር፡፡ለሁለት አመታትም በዚህ ስራ ላይ ቆየ፡፡
በዚህ ሁለት አመታት ውስጥ የጸጋዬ ገብረመድህን ድርሰት የሆነውን የእሾህ አክሊል ተውኔት
በዳይሬክተርነትና በመሪ ተዋናይነት አስኪዶታል፡፡ይህ ´በእሳት የተጠመቀበት ´የመጀመርያ ስራው
ነበር፡፡ቀጠሎ የመላኩ አሻግሬን"አለም ጊዜና ገንዘብ"ን ሰራ፡፡ነገር ግን ከአንድ ምሽት በላይ መታየት
ሳይችል ቀርቶ በባለስልጣናቱ ´ፖለቲካዊ ይዘት አለው´ተብሎ ተዘጋ፡፡ተስፋዬም ከቢሮው ተይዞ
እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ በፖሊስ ጣብያ የቆየ ሲሆን በአንድ ወገን ጣልቃ ገብነት ከእስሩ
ተለቋል፡፡ቀጥሎ የራሱን የሺ የተባለ ሁለተኛ ተውኔቱን ዳይሬክት በማድረግ በትወናውም ተሳተፈ፡፡

"Laqech and her pot" የተሰኘው በእንግሊዘኛ ለመጀመርያ ጊዜ በ 1953 የደረሰው


ተውኔት በመንግስት ግልበጣው ሙከራ ወቅት ነበር በአሜሪካ የተጻፈውና ፕሮዲውስ የተደረገው፡፡
የተወጠነው ግን አዲስ አበባ ኮሌጅ ውስጥ ሳለ በአጭር ታሪክነት ነበር፡፡ከአሜሪካ ሲመለስ
በ1954 ዓ.ም ወደ አማርኛ መለሰው፡፡ይህ እጁን ያሟሸበት የስነጽሁፍ ስራው ነው፡፡ባለ አንድ
ገቢር ተውኔቱ ላይ ላቀች የጭሰኛ ልጅ ስትሆን የአባቷ ባለጉልት የሆኑት ወይዘሮ ቤት ነበር
ያደገችው፡፡ የድርጊቱ ቦታ አዲስ አበባ ይህም በአካል ያልተገኙት ባለጉልት ይኖሩበት የነበር ቦታ
ነው፡፡ ላቀች አንዲት የላንቲካ ማንቆርቆርያ ይዛ ጭቃ ላይ ተቀምጣ መጫወት ስለምትወድ
የተውኔቱ ርእስ ከዚያ መነጨ፡፡ይህ ተውኔት ተስፋዬ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ትያትር
እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ አልታየም፡፡

በኢትዮጵያ ለመመድረክ "የሺ" የመጀመርያ ተውኔቱ ነበር፡፡ባለሙሉ ጊዜ ተውኔቱን የጻፈው


በ1954 እና 55 ዓ.ም ለእቴጌ መነን ሞት ሲባል በታወጀው የሃዘን ጊዜ ነው፡፡በወቅቱ ሁሉም
ቴአትሮች ተዘግተዋል፡፡በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር የሃዘኑ ጊዜ ልክ እንዳለቀ ለእይታ በቃ፡፡
የተውኔቱ መቼት በሁዳዴ ጦም ጀምሮ በፋሲካ የሚጠቃለል ሲሆን የሺ ውዳቂ ሰብእና ያላት ትንሽ
342
ጥቋቁር አናብስት

የሽርሙጥና ክዮስክ ከፍታ እራሷ ብቻ የምትሰራበት ሴት ነበረች፡፡የዚህን አለም ክፋት የሚኮንን


ነገር ግን ከሱ ርቆ መራቅ ያልቻለ አንድ ሃሳባዊ ሰው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከየሺ ጋር በፍቅር
ይወድቃል፡፡ከተለያዩ ትንቅንቆች በኋላ የሺ ባልዋለበት በወንጀል ከሳው በቁጥጥር ስር ይውላል፡፡
ተውኔቱ በየሺም ባህርይ ላይ ሆነ በፖሊስ ሃይሉ ላይ የኩናኔ ጅራፉን የሚያወርድ ነበር ፡፡ በጎ የሆነ
ገንቢ ዳሰሳ በ voice of Ethiopia ጋዜጣ ላይ ምን አልባትም ተስፋዬ እንደሚያስበው በረዳት
አርታኢው መንግስቱ ገሠሠ የተጻፈ አገኘ፡፡

ተስፋዬ በሚተውንበት ትያትር ላይ ዘመዶቹን እንዲታደሙ ሲጋብዛቸው እነሱ ያሰቡት


በ´አለቃነት እንደየሚያስተዳድር ነበር፡፡ እርሱ ግን መድረኩ ላይ ዝቅተኛ ደረጃ አላቸው ብለው
ከሚያስቧቸው ´አዝማሪዎች´ጋር አብሮ ሲተውን አይተው ተሰቀቁ፡፡ ይህን ክብር የለሽ ስራም
በመስራቱ እንዲንኳሰስ ምክንያት ሆነ፡፡ከድቅል ኢትዮጵያዊ´ ገጽታው ጋር የተደማመረ ቢሆንም
“በወኔ ተጋፈጥኩት” ይላል ተስፋዬ፡፡በመደረክ ላይ የተወሰኑ ዘመዶቹ ሲተውን ያዩበት ተውኔት
"የእሾህ አክሊል" ነበር፡፡በኋላ ግን በተዋናይነቱም በዳይሬክተርነቱም በተለያዩ ተውኔቶች ላይ
አይተውት ሙያውን ተቀብለውለታል፡፡ይህ ግን የሴቶቹን አቀባበል አያጠቃልልም፡፡ከተከበሩ
ቤተሰቦች የመጡት ሴቶች ፊት ነሱት፡፡በአዝማሪነት ተመደበ፡፡ተስፋዬ ከነሱ ክበብ በመገፋቱ
ምንም ያልተማረች የቡና ቤት ሴትን በ1955 ዓ.ም መተዋወቅ ቻለ፡፡አብረው መኖር ጀምረው
አምስት አመት ሞልቷቸው ሁለት ልጆችን እስኪወልዱ ድረስም ህጋዊ ጋብቻ አልፈጸሙም ነበር፡፡

እነዚህ ከእሾህ አክሊል ተውኔት በኋላ በአዝማሪነት የመመደብ ፤የጨዋ ቤተሰብ ልጆችን እንዳለ
ማግኘት ያሉ ችግሮች በተጨማሪም ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በቀጣዩ ተውኔት የገባው እሰጥ አገባ
አስጨናቂ ነበሩ፡፡11ጥንቃቄን መውሰድ ቢጀምርም ወጣትና ስሜታዊ ነበር፡፡ከጸጥታው ክፍል ጋር
ያለውም ልምድ መጥፎ ነበር፡፡12 ነገሩም የስራ ባልደረቦቹ መወያያ በመሆኑ“ያው ታውቀዋለህ ይሄ
እኮ አቢሲንያ ነው” በማለት እንደዚህ ያለ ነገር እንደሚጠበቅ ነገሩት፡፡

***

በእነዚያ ጊዜያት ተዋንያን ቢጠሉም ጸሃፍት ግን ይከበራሉ፡፡ምንም እንኳን በመተወኑ ጥቂት


ልምጭ ቢያርፍበትም "የሺ"ን በመጻፉና ዳይሬክት በማድረጉ ያጣውን ክብር በተወሰነ መልኩ
ማስመለስ ቻለ፡፡ የቴአትር ሰውነት የመሰማት ስሜት እያሳደረ መጣ፡፡ትምህርቱን የተማረው
እንደው በከንቱ እንዳልሆነ ለአንድ ነገር እንደተወጠነ አንዳች ትርጉም እንዳዘለ ይሰማው ጀመረ፡፡
የሺ ለአምስት ወይም ስድስት ጊዜ ለመታየት በቃ፡፡ይሄ ማለት በወቅቱ ትልቅ ነገር ነበር፡፡
በቴአትር ውስጥ የሚያገኘው ደሞዝ ጥሩ ቢሆንም ተዋንያንና ጸሃፍት ደህና አይከፈላቸውም፡፡
343
ጥቋቁር አናብስት

ተስፋዬ የሺን በመጻፉ ተጨማሪ 1500 ብር ገደማ አገኘ፡፡ በዚሁ ተጠቃሎ እንደ ተዋናይነትና
ዳይሬክተርነቱ ግን የተጨመረለት ነገር የለም፡፡ብዙ ጊዜ የሚተውነው በወቅቱ የሰለጠነ የሰው
ሃይል እጥረት ስለነበር ነው፡፡

በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ቴአትር ተስፋዬ ከስራ አስኪያጁና ከጸጋዬ ገብረመድህን ስር ሲሆን ጸጋዬ
እሱ ከመግባቱ ከጥቂት ወራት በፊት እንደ ቋሚ ጸሃፊና በትያትር ክፍሉ ሃላፊ በመሆን ነበር
የተቀጠረው፡፡ተስፋዬ እንደሚለው ጸጋዬ ገንዘብ ያስፈልገው ስለነበረ ጽሁፉ ላይ አድምቶ
ይሰራል፡፡ጭምትና ከሰው የማይግባባ ሲሆን ቁጭ ብሎ መጻፍ ብቻ ነበር ስራው፡፡በአንጻሩ
ተስፋዬ ግን (ከመሬቱ በሚያገኛት ገቢ) እየታገዘ ከጽህፈቱ ቀንሶ ከተግባቦቱ አብዝቶ ችሮታል፡፡
ሁለቱ ግን የማይነጣጠሉ ሲሆኑ ለቴአትሩ እድገት አብረው አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ጸጋዬ
ተስፋዬን ለተውኔትና ዳይሬክተርነት ስራው ሲፈልገው ተስፋዬ ደግሞ የጸጋዬ ቃለ ተውኔቶች
ያስፈልጉታል፡፡ አብረው በደስታ ሰሩ፡፡ቴአትሩ እመርታን እንዲያሳይ በመግፋትም በጥራቱ ረገድ
ሊያሻሽሉት በቅተዋል፡፡“እርስ በራሳችን የምንፈላለግና አንዳችን የሌላችን ጥገኛ ነበርን ”ሲል
አስተያየቱን ይሰጣል ተስፋዬ|፡፡

ተስፋዬ የመንግስቱ ለማን የመጀመርያ ተውኔትም ለእይታ ያበቃ ሰው ነበር፡፡መንግስቱ በጓደኛቸው


በኩል የጉዳይ አስፈጻሚ ከነበሩበት በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በላኩት ተውኔት "ጠልፎ በኪሴ"
ላይ በትወናና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል፡፡ጸጋዬ ገብረመድህን "በእሾህ አክሊል" መንግስቱ ደግሞ
በ"ጠልፎ በኪሴ" ህዝቡ ዘንድ ሲደርሱ ተውኔታቸውን ለመድረከ በማብቃት ተስፋዬ እውቅናን
አገኘ፡፡ አዳዲስ ጸሃፊ ተውኔቶችን እድል እየሰጠ ፈጠራን በቴአትር ላይ ለመጨመር ይሞክራል፡፡
ከእሱ በፊት የነበሩት ዳይሬክተሮች የውጪ ዜጎች ሲሆኑ የቀደምት ጸሐፌተውኔቶችን
ስራዎች(ተክለ ሃዋርያት፤ መኮንን እንዳልካቸው፤ዮፍታሄ ንጉሴ) ብቻ ነበር የሚያቀርቡት፡፡ “ይህ
ለደካማ ቴአትር በር ከፋች ነው” ይላል ተስፋዬ፡፡ሌላው ችግር ደግሞ እነዚህ የውጭ ዳይሬክተሮች
ቋንቋውን አለማወቃቸው ነበር ፡፡ተስፋዬ አዲሱን የተውኔት ጸኃፊ ትውልድ እንዲያቆጠቁጥ
በመርዳት ጠገነው፡፡

እነዚያ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር ቤት የመጀመርያ ሁለት አመታት ለተስፋዬ ውጭ ሄዶ


የማጥናቱን ጠቀሜታ ያሳወቁበት ለሱም ሆነ ለሃገሪቱ የቴአትር ታሪክ ጠቃሚ ነበሩ፡፡ተስፋዬ
የሚያሰራቸው ተዋንያን ምንም ዐይነት መደበኛ ስልጠና አልተሰጣቸውም፡፡13አንዳንዶቹ እንደውም
ያልተማሩ ስለነበሩ መሰመሮቹ እንዲነገራቸው ይፈልጋሉ አልያም በልጆቻቸው ማስነበብ
ነበረባቸው እነዚህ ቀደምት ባለሙያዎች በቴአትር በኦፔራ አከል የተጋነነ ትወና በውጪ ዜጋ

344
ጥቋቁር አናብስት

ዳይሬክተሮቹ ስር በመሆን ያቀርባሉ፡፡ተስፋዬ እኔ ግን እውነተኛ ትወናንና ዳይሬክተርነትን


ለኢትዮጵያ አስተዋውቄያለሁ ይላል፡፡

በሃምሌ 1955 ዓ.ም ተስፋዬ በረዳት ዳይሬክተርነትና በትወናም ጭምር የጸጋዬ "ቴዎድሮስ
"የተሰኘው ተውኔት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ሲቀርብ ለመሳተፍ
በቃ፡፡ወቅቱ የትምህርት አመቱ መዝጊያ ሲሆን ንጉሱም ታድመዋል፡፡ተስፋዬ መልእከተኛ ሆኖ
የተራኪውን ገጸ ባህርይ ወክሎ ተጫወተ፡፡በተጨማሪም ከቀዳማይ ኃይለሥላሴ ቴአትር የተገኙ
ተዋንያን ከዩንቨርስቲውም ከውጪም የመጡ አማተርና ፕሮፌሽናል የሃገር ውስጥና የውጪ
ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡

***

ከዚሀ በኋላ ነበር ተስፋዬ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የባህል ማዕከልን በ1955 ዓ.ም መስከረም
ወይም ጥቅምት ወር ላይ የተቀላቀለው፡፡እዚያም እስከ ኢትዮጵያውኑ 1960 ቆየ፡፡ በመጀመርያ
ከአሜሪካዊው ዶክተር ፊሊፕ ካፕላን ጋር በቅርበት ሰራ፡፡የጸጋዬ ገብረመድህን ቴዎድሮስ ግሩም
አፈጻጸም ነበር ዩንቨርሲቲውን የባህል ማዕከል እንዲከፍት የገፋፋው ፡፡ባህል ማዕከሉ
በሚቀጥለው የትምህርት አመት 1956 ዓ.ም ተከፈተ፡፡ካፕላን ዳይሬክተር ሲሆኑ በአሜሪካ የብዙ
አመት የስራ ልምድ ያላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ በምርምር ላይ የነበሩ ሰው ነበሩ ፡፡ተስፋዬ
የአማርኛ ቴአትር ዳይሬክተር ሲሆን ለካፕላን ረዳትም ነበር፡፡ካፕላን በነሃሴ 1956 ዓ.ም ለቀው
ሲሄዱ ተስፋዬ የባህል ማእከሉ ዳይሬክተር ሆነ፡፡በማዕከሉ የመጀመርያ አመት ኦርኬስትራ
ኢትዮጵያ ሊመሰረት በቃ፡፡ የመጀመርያው ዳይሬክተሩም ሐኪም ኤል-ዳብ ዋነኛ የሙዚቃ
ዳይሬክተርና የውዝዋዜ አስተባባሪ (ኬሮግራፈር) ሆኑ፡፡14ከኦርኬስትራው ምስረታ ብዙም ሳይቆይ
ተስፋዬ ለማ በተስፋዬ ገሠሠ ተቀጥሮ ተቀላቀለ፡፡በኋላም ከሐኪም ኤል-ዳብ ተከትሎ ዳይሬክተር
ሆኗል፡፡

ባህል ማዕከሉ የስእል ቅብንም ያስተምራል፡፡ከታዋቂ የጊዜው መምህራን መካከልም ገብረክርስቶስ


ደስታ እና (እ.ኤ.አ በ1980 አርፏል)እስክንድር ቦጎስያን (ከአርመን ወላጆቹ የተገኘና አባቱ
የአሜሪካ ዜጋ ሆነው ድብልቅ ደም ቢኖረውም ቅሉ እጅግ ኢትዮጵያዊ ስሜት የነበረው በፈረንሳይ
የተማረ) ይገኙበታል፡፡በኋላ ታዋቂ ሰአሊና መምህር የሆነው ዘሪሁን የትም ጌታም እዚያ ነበር
የተማረው፡፡የስነጥበብ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አለፈለገ ሰላምና ቀራጺ ዳንኤል ጧፌም
አውደርዕያቸውን አሳይተውበታል፡፡15

345
ጥቋቁር አናብስት

ተስፋዬ ገሠሠ ካስተማራቸውና በኋላ ታዋቂ ከሆኑት ተዋንያን መሃል ወንድወሰን ገብረኢየሱስ
ቆይቶ የራስ ቴአትር ስራ አስኪያጅ በኋላም የብሔራዊ ቴአትር የኪነጥበብ ዳይሬከተር የሆነ ተስፋዬ
እራሱ ዳይሬክት ባደረገው የብርሃኑ ዘርይሁን "ሞረሽ" ትያትር ላይ እየተወነ እዚያው መድረክ ላይ
ህይወቱ ያለፈች፤ወጋየሁ ንጋቱ ፤ደበበ እሸቱ ሃገር ፍቀር ትያትር ቤት እ.ኤ.አ በ1987 ለመድረክ
በዋለው በሼክስፒር የቬንሱ ነጋዴ ላይ እንደ ሻይሎክ የተጫወተ እና ሌሎችም ስራዎችን የሰራ፤
አባተ መኩርያ፤ተፈሪ ብዙአየሁ ይገኙባቸዋል፡፡ከተስፋዬ ታዋቂ ፕሮዳክሽኖች መሃል የመንግስቱ
ለማ "ያላቻ ጋብቻ" ፤የከበደ ሚካኤል "ሮምዮና ዡልየት"፤የራሱ የተስፋዬ አባትና ልጆች፡"oda
oak oracle" በጸጋዬ በእንግሊዘኛ የተደረሰ የመሳሰሉ ይገኙባቸዋል፡፡እነዚህ ሁሉ ተውኔቶች
በተስፋዬ ዳይሬክተርነት በባህል ማዕከል የቀረቡ ነበሩ፡፡“ቦታው በወቅቱ የተጨናነቀ ሲሆን
አማርኛም ሆነ እንግሊዘኛ ተውኔቶች ለእይታ ይበቁ ነበር ”ይላል ተስፋዬ፡፡ ከውጪዎቹ ተስፋዬ
የኢዮንስኮን rhinoceroes,who´s afraid of virginia wolf በኤድዋርድ አልቢ
waiting for godot የሳሙኤል ቤኬት ይገኙባቸዋል፡፡አብዛኞቹ አዲስ ዐይነት ለሙከራ
የሚሰሩ ቴአትሮች በኢትዮጵውያንና በውጪ ዜጎች የቀረቡ አውደ ርእዮችና የኦርኬስትራው
የሙዚቃ ድግሶችም ነበሩ፡፡

***

ከስራው በተጨማሪ ተስፋዬ በዚህ ወቅት የተጣበበ የቤተሰብ ህይወትም ነበረው፡፡ሁለት ልጆችንም
አፍርቷል፡፡መለስ ብሎ ያን ጊዜ ሲያስታውስ “ ጥሩ ይመስላል አስከፊ ጊዜ አልነበረም” ሲል
ይገልጸዋል፡፡የደሞዝ ጭማሪ ባይደረግለትም ንቁ ነበር፡፡ከመሬቱም ገቢ ነበረው፡፡የሚያከራያቸው
ቤቶችም ነበሩት፡፡የልጅነት ጉልበትም ሀይለኛ ስሜትም ነበረው፡፡ይህን የህይወቱን ጊዜ
“ኤልዛቤታዊ ዘመን”እና “አስደሳቹ ወቅት” ሲል ይጠራዋል፡፡ከትእይንቶች በኋላ ያመሻሻል፡፡
“ገንዘብ በኪሴ ሞልቼ ከተማዋን አስስ ነበር” ልጆቹ ተረሱ፡፡ምንም እንኳን ቁሳዊ ፍላጎታቸው
ቢሟላም የሱን በቂ ትኩረትን ማግኘት አልቻሉም፡፡ “ደንበኛ አባት ለመሆን አልተዘጋጀሁም እኔ
እራሴ ተገቢውን አስተዳደግ ስላላደገሁ” ይላል፡፡ሚስቱ ገጠሬ ናት ታጋሽና ቅር የማይላት፡፡
የተስፋዬ ወጣት ደስተኝነት አሞኛት፡፡ የተስፋዬ ቤተሰቡን ቸል የማለት ባህርይው ግን ጎልቶ
የወጣው ከአብዮቱ በኋላ ነበር፡፡ባይሰክርም ቀን በቀን መጠጣት ጀመረ፡፡አራት አምስት ቢራ አንድ
መለኪያ ውስኪ ከዚያ ያቆማል፡፡ ሞቅ ብሎት ነበር በወደ ቤት የሚመጣው፡፡ነገር ግን አይሰክርም፡
ከስምንት እስከ አስር ሰአት ባለው ጊዜ መሓል ነበር ቤቱ የሚመጣው፡፡በወቅቱ ባል የሚስቱ የበላይ
ነው የሚል ፊውዳላዊ ግንዛቤ ነበር፡፡ከአብዮቱ በኋላ ግን ይሄ ሊቀየር ችሏል፡፡የተስፋዬ አጠጣጥ
እየፈጠነ ይህም ከሚስቱ ጋር ችግሮቹን እያባባሳቸው መጣ፡፡በፊት ብዙ የምትችለው አሁን መታገስ
346
ጥቋቁር አናብስት

አቃታት፡፡በማስከተልም በነዛ አስፈሪ የድህረ አብዮት ቀናት “ሞትን የመፍራት አባዜዬን


ለማባረር”ስል ይበልጥ መጠጣት ጀመርኩ ይላል፡፡

ሶስተኛው በተስፋዬ ተጽፎ ለመድረክ የበቃው ተውኔት (መጀመርያ በባህል ማእከል በ1959
አካባቢ በኋላ ከአመት በኋላ ደግሞ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር የቀረበው)" አባትና ልጆች"
ይሰኛል፡፡የቱርጌኔቭ ታዋቂ ርእስ በሃሳቤ ነበር መሰል ርእሱን ሳወጣ የተውኔቱ ሃሳብ ግን
“በስነጽሁፍ ትውልድ መሃል ያለው ክፍተት መጽሐፍ” ብሎ ከሚያስቀምጠው ከዲ.ኤች ላውረንስ
sons and lovers ጋር ቅርርብ ነበረው ሲል ያስቀምጣል፡፡ምንም እንኳን የውጪ ተጽእኖዎች
ቢኖሩም ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አስቦ ነበር የጻፈው፡፡ስለ አንድ አባትና ሁለት ልጆቹ
የሚያወሳ ነበር፡፡ታላቅየው (ሃላፊና ሁሉ በእጁ የሚባል ) አይነት ባህርይ ሲኖረው የክብር ዘበኛ
አባልም ነበር፡፡ታናሽየው ደግሞ ራሱን የሚያዳምጥ ሃሳቡን የሚያመናትል አይነት ባህርይ ያለው
የኮሌጅ ተማሪ ነበር፡፡ታናሹ ማንነቱን የህይወትን ትርጉም በመፈለግ ወዘተ በመሳሰሉት ሲጠመድ
እነዚህ ዐይነት ጥያቄዎች ግን በታላቅየው ጭርሱኑ አይታሰቡም፡፡ተስፋዬ በዚህ ለማመልከት
የሞከረው ወጣቱ ትውልድ የራሱን እሴት በመፈለግ ስራ መጠመዱን ይህን ሲያደርግ ግን ከታላቆቹ
ምንም እርዳታ አለማግኘቱን ማሳየት ነው፡፡ባህላዊ እሴቶች (እንደ ሃይማኖት፤ባህል ወዘተ)ከይዘቱ
አንጻር በሂደት ለፈተና ይቀርባሉ፡፡ትያትሩ በተጋጋለ ፍላጎት የተሞላ በተወሰነ መልኩ ቁምነገራም
ስለመጻኤ አመላካች ግን ለስነምግባር አስተምህሮ እምብዛም የሆነ ነው ይለዋል፡፡

በ1957 ዓ.ም ተስፋዬ ከአመት እስከ አመት የሚሄድ በጥበባት ላይ ያተኮረ (ምንአልባትም ለ52
ክፍል የሄደ)ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ጀመረ፡፡የኪነጥበባት ጉዞ የተሰኘ ፕሮግራሙ ለ30
ደቂቃ የሚደመጥ ሲሆን ይህ መርሐግብር በአዲስ አርእስትና በሌሎች ፕሮዲውሰሮች
በጭውውታችን ወቅትም አየር ላይ ይውል ነበር፡፡ተስፋዬ እንደሚለው ከሆነ ይህ ፕሮግራም
ከመድረክ በላይ ብዙ ህዝብ ጋር የመድረስ አቅም ነበረው፡፡“በጊዜው ኪነጥበባቱን ለህዝቡ
አስተዋውቋል አላማውም ለጥበብ ያለንን ንቃተ ህሊና ማዳበር” ነው፡፡ለተስፋዬ ይህ የትርፍ ጊዜ
ስራው ሲሆን በፕሮግራም 60 ብር ብቻ ነበር የሚያገኝበት፡፡በሱ እግር የተተካው ወንድወሰን
ገብረኢየሱስ ግን እንደ ሙሉ ጊዜ ስራ ለበርካታ አመታት ይዞታል፡፡

ቀጣይ የተስፋዬ ተውኔት ለአባትና ልጆች እንደ´ተቀጥላ´ ተውኔት ተደርጎ የተጻፈ ነው፡፡"ኡኡኡኡ"
ወይም "በገላጋይ"ስለ ገበሬ ባልና ሚስት የተደረሰ አጭር ተውኔት ሲሆን መጀመርያ በባህል
ማዕከል ቀጥሎ በራድዮ ነበር የቀረበው፡፡በአባትና ልጆች ላይ ያለው አባት በዚህኛው ትአትር ላይ

347
ጥቋቁር አናብስት

መጥቶ በተጣሉት ሁለቱ ባለትዳሮች መሃል እርቀ ሰላምን ያወርዳል፡፡ የገጠሩን ህይወት ለማሳየት
የጻፍኩት ተውኔት ሲሆን “በቀላል ህይወት ውስጥ ያውን የፍቅር ገጽታ ያሳያል” ይላል፡፡16

የመጨረሻው በባህል ማዕከል ሳለ የጻፈው ቴአትር "ሲዳዳን" ነው፡፡“ባለአንድ ገቢር ህልም አስተኔ”
ተውኔት ሲል ይጠራዋል፡፡ በ1959ዓ.ም ነው የተጻፈው ሲል ያስባል፡ በሬድዮ ብቻ ነበር
የተላለፈው፡፡ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ምንአልባት በ1960ዓ.ም አካባቢ ተስፋዬ መልሶ አነሳው ይህም
የሆነበት መክንያት የገጸ ባህርያቱ ወለፈንዴነት ነው፡፡ከባሻገር ነው የሚመጡ፡፡የሚያወሩት
የሚጨዋወቱት ሁሉ ግራ በሚያጋባ የድምጽ ቅላጼ ሲሆን ይነጋገሩና ተነው ይጠፋሉ፡፡ታሪኩ
በህልም አለም የሚታይ ዐይነት በተመሳሳይ ወቅትም እውን የሆነ ነው፡፡ “ሁሌም ጥላ ስለሆነው
ሞት፤ስላቅ፣ስስት” ነበር ተውኔቱ፡፡ ተስፋዬ የሬድዮ አድማጩ እንዴት እንደተቀበለው
የሚያውቀው ነገር የለም፡፡በዚያ ላይ ደግሞ ስለ ሰዎች አስተያየት በማመንታት የሚሰነዘር ስለሆኑ
በማለት ብዙም ጠቀሜታ እነደሌላቸው በማሰብ አይጨነቅም፡፡ነገር ግን የራሱን ተውኔቶች ከሞላ
ጎደል በተጻፉበት ሁኔታ ሲተወኑ ማየት ለሱ ያሳፍረዋል፡፡እሱ የሚፈልገው ተውኔቱን ከተዋንያኑ
ጋር ተጫውቶ እዚያው እያለ የክለሳ ማሻሻያዎችን ማድረግ ነበር፡፡በገሃዱ አለም ግን የዚህ ዐይነት
ለውጥን ለማድረግ ትንሽ እድል ብቻ ነው ያለው፡፡

ተስፋዬ ገሠሠ በ1960 ዓ.ም መጨረሻ የባህል መዕከልን ለቀቀ፡፡ ለማዕከሉ የሚመደቡ በጀቶች
መቆራረጥና የሱ በተለይ ለኦርኬስትራው ይህን ለሟሟላት መዳከር አሰለቸው፡፡አንዳንድ
ሙዚቀኞች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ለቀቁ፡፡በመጨረሻ ተስፋዬ እራሱ ለቅቆ እጥፍ ደሞዝ ወዳገኘበት
የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽንን በህዝብ ግንኙነት ሰራተኛነት ተቀላቀለ፡፡ ከ1961 መጀመርያ
አንስቶ እስከ 1965 ድረስ በዚህ ስራ ቆየ፡፡ ከስራዎቹ መሃል አንዱ የድርጅቱን መጽሄት ቴሌ
ነጋሪት ላይ በአርትኦት መሳተፍ ነበር፡፡እሱ ነበር ለእውቅና ያበቃውና እስከ ቃለመጠይቃችን
ወቅት እንዲዘልቅ ያስቻለው፡፡በዚህ ስራ ላይ እያለ ኢትዮጵያን በደምብ እንዲያውቅ ያስቻለውን
ጉዞ ተጉዟል፡፡በትርፍ ግዜው ደግሞ በተለያዩ ተውኔቶች ላይ ይሳተፋል፡፡ ለምሳሌ ግራዝያኒን
በመወከል በጸጋዬ ገብረ መድህን ጴጥሮስ ላይ፤እንደ ሃምሌት በመሆን በጸጋዬ ገብረ መድህን
የሼክስፒር ትርጉም ስራ ላይ፤እንዲሁም እራሱ ዳይሬክት ባደረገው የነጋሽ ገብረ ማርያም የድል
አጥቢያ አርበኛ ላይ የጣልያን ወታደር በመሆን፤ወደ አልጄርያ በማቅናትም የአፍሪካውያን የጥበብ
ፌስቲቫል ላይ ጴጥሮስን ደግሞ ተጫውቷል፡፡

ቴሌኮሚዩንኬሽን በገባ በመጀመርያው አመት እስካሁን ድረስ የታተመለት ብቸኛ የተውኔት ስራው
የሆነውን "እቃው" የተሰኘው ተውኔት ደረሠ፡፡እንደ እቃ ለአገልግሎት ስለሚውሉና እንደ እቃ
ስለሚቆጠሩ ሰዎች ነው፡፡ከዚህች መጽሐፍ ህትመት በኋላ እንዲህ ያሉ ልግመኞችን “እቃው”ብሎ
348
ጥቋቁር አናብስት

መጥራት የተለመደ ሆነ፡፡ተስፋዬ ይህንን ተውኔት ይወደዋል ከምመርጣቸው መሃል ነው ይለዋል፡፡


2000 ኮፒ ታትሞ ቀስ እያለ ነበር የተሸጠው፡፡የተውኔት ጽሁፎች ብዙም በኢትዮጵያ አይሸጡም
የታተመው ቅጽ ከወጡ ስራ ያንስ ነበር፡፡ይሄም አንዳንድ ወለፈንዴ ቃላት ስለወጡለት ነበር፡፡

ተስፋዬ እንደሚለው ተውኔትን ለመጻፍ ዝግጅቱ ረዥም ጊዜ ይፈጅበታል፡፡ይህ የመዘጋጀት ጊዜ


ሲሆን ዋናው ጽሁፍ ግን ብዙም አያዘገየውም፡፡ ባለ አንድ ገቢር ተውኔት በፍጥነት ጽፎ የጨረሰ
እንደሆን ለተወሰኑ ወራት ትቶት ተመልሶ ደግሞ ያነሳዋል፡፡ የእቃውን የመጨረሻ ገቢር የጻፈው
አልጀርስ እያለ ነበር፡፡“የድርሰትን ስራ በቁምነገር ይዤ ሳይሆን በያዝ ለቀቅ ነገሮችን ሳላጠብቅ ነው
የምጽፈው፡፡ለዲሲፕሊን የተገዛሁ አይደለሁም ይህም ለተማርኩት ትምህርት እንደስድብ ይቆጠራል
”ይላል፡፡

እቃው መቼቱን በደቡባዊ አፍሪቃ ነው ያደረገው፡፡(የዚያኔ ሮድኤዝያ የነበረችውን ዝምባቡዌ ሲሆን


እሱ ግን የመረጠው ዝምባብዌ የሚለውን ስም ነበር) ደቡብ አፍሪቃና ዝምባብዌ ´በአንድ
ተጨፍልቀው´ነው በተውኔቱ ላይ የቀረቡት፡፡ሰው እንደ እቃ የሚቆጠርበት የአፓርታይድ፤
የዘረኝነትን፤የቶታልሊታራኒዝም ስርአቶችን ተቃውማ የተጻፈች ድርሰት ነበረች፡፡በተውኔቱ ላይ ያለ
ታሳሪ ለእናቱ ወደ ኢትዮጵያ ለማምለጥ ማሰቡን ይነግራታል፡፡እዛ(ኢትዮጵያ ውስጥ) ክብርና ነጻነት
አገኛለሁ ብሎ ያስባል፡፡ይህ ግን በሀገሪቱ ያለውን ሙስናና መድልኦ አንስቶ ለመጎሽመጥ ታስቦ
የተሰነዘረ ሽሙጥ ሲሆን ከአፓርታይድ ባልተለየ ሁኔታ የሚተገበረውን ሙስናና የዘር መድልኦውን
ላይ ተመስርቶ ነው የተጻፈው፡፡እንደ ተስፋዬ ከሆነ ይህ ተውኔት ከአብዮቱ በፊት ታይቶ
ባያውቅም እንዲታተም ግን ተፈቅዷል፡፡ለማንኛውም በ1968 ዓ.ም ለመድረክ በቃ፡፡ ከአብዮቱ
መባቻ በኋላ መንግስት ስለምን እንደተጻፈ ባወቀ ጊዜ ከሁለት ወይም ከሶስት ትርኢቶች በኋላ
አስቆመው፡፡ተስፋዬ ለተወሰኑ ወራት በእስራት ያለ ስራ ደግሞ ለተጨማሪ ጥቂት ወራት ቆየ፡፡

ለቴሌኮሙኒኬሽን ለበርካታ አመታት ከሰራ በኋላ ማረፍያው ንግድ ምክር ቤት ሆነ፡፡በህዝብ


ግንኙነት ባለሙያነት፡፡ለ8 ወራት ያህል ነበር የዘለቀው፡፡አብዮቱ እስኪፈነዳ ድረስ፡፡ለንግድ ምክር
ቤት Ethiopian trade journal የተሰኘ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የሚታተም ጋዜጣቸው ላይ
በአርታኢነት አገለገለ፡፡

እዚህ እንደ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሆኖ ነበር የሚሰራው፡፡የመጀመርያው የላይኛው ቢሮን ጣእም
ማጣጣም ጀመረ፡፡ጠቃሚ ስብሰባዎችን ከጠቃሚ ሰዎች ጋር አካሄደ፡፡ በሆቴሎች ከስብሰባ በኋላ
ከነዚህ ጠቃሚ ሰዎች ጋር ይጠጣል፡፡ደሞዙም ጥሩ ሆነለት፡፡ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን አግኝቶ
ተቃበጠ፡፡ከተወሰኑት ጋር ወሲብ ቢፈጽምም እንደ ጓደኞቹ ግን ለሊቱን ሙሉ አይቆይም፡፡ከግዜ

349
ጥቋቁር አናብስት

ወደ ግዜ በአባላዘር በሽታ ቢያስይዛትም ሚስቱ ይሄንንም በትእግስት አለፈችው፡፡ጉዱን ሁሉ


ታውቅ የነበር ሲሆን የኋላ ኋላ ግን አመጽዋ የከፋ ነበር፡፡

ተስፋዬ መጻፉን ቀጥሎ በርካታ አጫጭር ታሪኮችን ጨረሰ፡፡በባህል ማዕከል ጊዜው ሲያደርገው
እንደነበር ሁሉ በጥበብ ዙርያ ለተለያዩ ጋዜጦች መጻፍ ጀመረ፡፡በወቅቱ ለጥበብ እንደ አስተዋዋቂዋ
ነበር፡፡የአጫጭር ታሪኮቹ ስብስብና የግጥሞቹ መድበል "መተከዣ" ተብላ በ1967 ዓ.ም
ለህትመት በቃች፡፡ንጉሱ ከስልጣን ከመወገዳቸው በፊት ለአታሚዎቹ ተልኮ የነበር ቢሆንም ያለ
ምንም ስራ ለ6 ወር ተቀመጧል፡፡ከአብዮቱ በኋላ ነበር ብቅ ያለችው፡፡ከእቃው ውጪ የታተመች
ብቸኛ ስራው ነች፡፡ሁለቱ ታሪኮች ከትምህርት ቤት ዘመኑ ሲሆኑ ጓደኞቹን ሞዴል በማድረግ
ተጠቅሞባቸዋል፡፡እነዚህ ታሪኮች ስለተማሪ ህይወት የሚያነሱ እንጂ ፖለቲካዊ ይዘት
አልነበራቸውም፡፡አንዱ ታሪክ ስለ አንዲት አማራ ሴተኛ አዳሪና ስለሚያዘወትራት ጋናዊ ደንበኛዋ
ነው፡፡“በቀደመውም አሁን በምንኖርበት ዘመን እንደሚታየው ሁሉ የተወሰነ ዘረኝነት
ተንጸባርቆበታል”18ተስፋዬ የሚወደው ሌላው ታሪክ ሽልንጌ (የ ኦ .ሄንሪ ዐይነት ታሪክ ነው)በባቡር
ወደ ሃረር ሲሄድ ያገኘውን ልምድ የሚያካፍልበት ታሪክ አንዳንዶች “ይሄ ምርጡ ስራው ነው”
ይላሉ፡፡ተስፋዬ“የሆነ ዐይነት የቼኾቭ ነጸብራቅ በታሪኮቹ ውስጥ አለ፡፡አብዮተኛ ባይሆኑም
ያለመርካት ስሜት ግን ይነበብባቸዋል ቆስቋሽ የምባል ዐይነት ሰው አይደለሁም፡፡ ወሬኛ እንጂ
አሳቢ ዐይነትም አይደለሁም” ይላል፡፡ስለግጥሞቹ (አንዱ ለእናቴ የሚለው ለእናቱ መታሰብያ
የተደረገ ነበር ከንግግራችን ጥቂት ጊዜ በፊት በሬድዮ ሄዷል) ሲናገርም ግጥሞቹ የግል ልምዱ
ነጸብራቆች የሆኑ ማህበራዊ ትችቶች ያዘሉ በሞትና ህይወት ግንዛቤዎች ላይ የተንተራሱ ናቸው
ይላል፡፡የበሰሉ ሌሎች ተጨማሪ ስራዎችን ማሳተም ቢፈልግም ሳይቻል ቀርቷል፡፡

***

በአብዮቱ አመት በሚያዝያ 1966 ተስፋዬ የሃገር ፍቅር ቴአትር ስራ አስኪያጅ ሆነ፡፡19 ቀጣዩ
ሙዚቃዊ ተውኔቱ "ማነው ኢትዮጵያዊው?" በ1966 ዓ.ም የተጻፈውም ሆነ ለመድረክ የበቃው
የሃገር ፍቅር ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት በመስከረም 67 ነው፡፡"ማነው ኢትዮጵያዊው?"
የሚለው ርእስ ከታደለ ገብረ ህይወት መጽሐፍ የተወሰደ ሲሆን ተስፋዬ ገጸባህርያቱን ቢጠቀምም
የታሪኩ ፍሰት ግን የተለየ ነበር፡፡“ከፕርል ኤስ በክ the good earth ከሚለው መጽሀፍ በርካታ
ክፍሎችን ተከትሎ ወደ ሀገርኛ በመመለስ ራስን ለማወቅ የተደረገ ጠንካራ ሙከራ ነው” ይላል
ተስፋዬ፡፡በተውኔቱ ላይ ያሉት ግጥሞች በሙዚቃ መልክ የቀረቡ እንጂ ራሳቸውን ችለው
በግጥምነት መልክ ሊቀርቡ የሚችሉ ዐይነት አልነበሩም፡፡“እንደ ኦክሎሃማ ሙዚቃዊ ትእይነት
350
ጥቋቁር አናብስት

የመሰለ ሆኖ ሙዚቃና ውዝዋዜን በመጨመር ወደ ኢትዮጵያዊ መቼት የተመለሰ ነው” ሙዚቃዊ


ትያትሩ ያልተሳካና አስከፊ ነበር አንዳንዶች በዚህ ነገር ሲያማርሩት ነበር፡፡እሱም ሲናገር
“ይገባኛል” ብሏል፡፡ተውኔቱ የሚሰብከው “ኢትዮጵያ ወደ ምስራቅም ሆነ ምእራብ መሄድ ሳይሆን
የራሷን ፍልስፍና ማዳበር እንደሚገባት ነው ኢትዮጵያ ትቅደም”20ስር ነቀሎቹ ወደ ምስራቅ
ተራማጆቹ ወደ ምእራቡ ስለሚያዘነብሉ ይሆናል አንዳንዶች ያልወደዱት፡፡ተስፋዬ ስለ እራሱ ስር
ነቀል ለውጥ አቀንቃኝም ተራማጅም ሳይሆን የዘውድ አገዛዝን የሚደግፍ ወግ አጥባቂ እንደሆነ
ነው የሚያስበው፡፡(ይህንንም ያለው ወታደራዊው ጁንታ በስልጣን ላይ እያለ ነበር) ሙዚቃዊ
ድራማው ለወር ያህል ሄደ፡፡በሃገር ፍቅር ቴአትር ተስፋዬ የ የአቤ ጉበኛን "የደካሞች ወጥመድ"
ለመድረክ አበቃው፡፡የተስፋዬ አበበንም አንድ ስራ አቀረበ፡፡ የመንግስቱ ለማን "ባለካባና ባለዳባ"ን
ለመድረክ አውሎ እራሱም ተወነበት፡፡(በኋላ በመዘጋጃ ቤትም ታይቷል)

ትያትሮችን ለመድረክ ከማዋል ሌላ አስተያየት ለሚጠይቁት ወጣኒያን የተውኔት አጻጻፍና


አስተያየቶችን ይሰጣል፡፡እራሱን ሳይክብ ጀማሪ ቃለ ተውኔት ጸኃፍትን ለማሰልጠንም ፈልጎ ነበር፡፡
መላኩ አሻግሬን ጨምሮ ከሌሎች ጋር ሰርቷል፡፡

በወቅቱ ቴአትሮች የሚቀርቡት እሁድ ቀን ሲሆን ተመልካቹም ብዙ ቤቱም የሞላ ነበር፡፡


21
መድረኩንም አሳድሶታል፡፡አርዝሞታል፡፡የእድምተኞቹን መቀመጫ ተዳፋት አስደረገ፡፡መብራት
መቆጣጠርያ ኪዮስክ በስተጀርባ አሰራ፡፡እስከዚያ ጊዜ ድረስ የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት
የሚታወቅባቸው ተለምዶአዊ ቴአትሮች እርካሽና በኪናዊ ጥራት የወረዱ ነበሩ፡፡ተስፋዬ ግን እሱና
ጸጋዬ አብረው በብሄራዊ ቴአትር የሰሩትን እዚህ ብቻውን ሰራው፡፡ከተለመደው የቴአትር ትወናና
አጻጻፍ ወደ እዚህ ዐይነት ታላቅ ጥበባዊ አብዮት እመርታን ማምጣቱ በሁሉም ዘንድ በበጎ
አልታየም፡፡በርካታ የበፊት ቅጥረኞች ያልተደሰቱበት ምክንያት ለተስፋዬ የመታሰር መነሾም ሊሆን
ይችላል፡፡ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል የቴአትር ቤቱ ዳይሬክተር የነበረው እዮኤል ዮሃንስ አንዱ
ነው፡፡ተስፋዬ በምክትልነት አስቀምጦት የነበር ሲሆን በምንነጋገርበት ወቅት በዚህ ነገር
ይጸጸትበታል፡፡አቶ አዩኤል በተስፋዬ መምጣት ከስልጣኑ ተነስቶ የነበረ ሲሆን በዛም ቂም
ቋጥሮበታል፡፡ተስፋዬ የዚህን ዐይነት ተቃውሞ ስለለመደ ችሎ ተወው፡፡በኋላ ሲያስበው ይህም
ሌላ ስህተት ነበር፡፡"እቃው"ለመድረክ በዋለበት ወቅት እዩኤል ተስፋዬን ለማስወገድ እድል አገኘ፡፡
“ስራዬን ሊያገኝ ፈልጎ ነበር” ይላል ተስፋዬ፡፡ከበፊት ሰራተኞችና ከደርጉ አባላት ጋር ተመሳጥሮ
እንድታሰርና እንድገደል ሴራ ጠንስሷል ሲል ያስባል፡፡በመጨረሻ ተስፋዬ ከተከሰሰበት 17 ክሶች
ነጻ ወጥቶ ሊያመልጥ ቻለ፡፡ ከክሶቹ ውስጥ በዘመድ መስራት፤መልካም አስተዳደርን ማሳጣት፤
ንቅዘት(ሙስና)፤ጸረ አብዮት እንስቃሴዎች፤ከልኡል አልጋ ወራሽና ከመንገሻ ስዩም (ከትግራይ

351
ጥቋቁር አናብስት

ባላባቱ)ጋር ግንኙነት መፍጠር፤በውጪ ምንዛሪ ማጭበርበር፤ለቴአትር ቤቱ መኪና ሲገዛ ለራሱ


ጥቅም በማስያዝ፤ከኢንሹራንስ ጥቅም በማግኘት፡ደርጉን በመዝለፍ፤(ከተውኔቱ ላይ ተጠቅሶ
ሰዎችን እንደ እቃ ይጠቀማል በማለት)ተስፋዬ ከመኳንንቱ ወገን ባይሆንም ባለርስት ስለነበረ ይህ
ወድያውኑ የጸረ-ደርግነት፤ጸረ-አብዮታዊነት ስም በአንዳንዶች ዘንድ ያሰጠው ስለነበር በነዚህ
ሊወነጀል በቃ፡፡ነገር ግን በህይወት ሊያልፈው ቻለ፡፡በእስር ለሁለት ወራት ከሰባት ቀናት ቆየ፡፡
የመጀመርያዎቹ ሁለት ሳምንታት በጣም አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ከዛ ቀጥለው አስቸጋሪ የሁለት ሳምንታት
ግዜያት ተከተሉ፡፡እንደ ፖለቲካዊ እስረኛ የታየበት የመጨረሻዎቹ ሳምንታት የተረጋጋ ወቅት ነበር፡
፡እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ በቅርበት ታይተው ጥፋተኛ ስላልሆነ በነጻ ተለቀቀ፡፡

***

ከሶስት ወራት በኋላ በሬድዮ ሞስኮ የስራ እድል ቢሰጠውም መንግስት የመውጫ ቪዛ ከለከለው፡፡
በምትኩ ወደ ትምህርት መገናኛ ማእከል ተልኮ ለወራት ቆየ፡፡

ተስፋዬ በእስር ቤት ሳለሁ “በብሄራዊ ቴአትር የነበሩ ተዋንያን በጸጋዬ ገ/መድህን ላይ አመጹ”
ይላል፡ጸጋዬ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይሰራ በነበረው በካሳዬ ዳመና ተተካ፡፡ከትምህርት መገናኛ
የተወሰነ ቆይታው በኋላ ተስፋዬ ገሠሠ ደግሞ የብሄራዊ ቴአትር ስራ አስኪያጅ ሆነ፡፡ካሳዬ ደግሞ
ወደ ትምህርት መገናኛ ከሄደ በኋላ ኬንያ ዋና መስርያ ቤቱን ወደአደረገው አለም አቀፉ የስርጭት
አገልግሎት URTNA ያመራው፡፡22

ሁለተኛው የብሄራዊ ትያትር ቆይታው እስከ 1976 ዓ.ም ለስምንት አመታት የዘለቀ ሲሆን
ለተስፋዬ አስደሳች አልነበረም፡፡ግፊት የበዛበት ወቅት ነበር፡፡“ለጥበብ ለመቆም የጥበብን ዋጋ ፊት
ለፊት ለማስገንዘብ” አዳጋች የነበረበት ፤ምንም እንኳን ከፖለቲከኞቹ ጋር መወዳደር ቢከብድም23
በአንጻሩ በሌላ በኩል ደግሞ ታላቅ ወቅትም ነበር፡፡እራሱ የተወነበትን የመንግስቱ ለማን "ጸረ-
ኮሎንያሊስት" ለመድረክ አበቃ፡፡ cherchez la femme የተሰኘ ተውኔቱንም ጽፎ በ1972
ዓ.ም ቢጨርስም በብሔራዊ ቴአትር ሳይታይ በሃገር ፍቅርና ራስ ቴአትር ለመድረክ በቃ፡፡የተውኔቱ
ርእስ ምጸታዊ ሲሆን ዋናው አላማው በወቅቱ የነበሩትን ነጭና ቀይ ሽብር ለመንካት ነበር፡፡24
በአለቆቹ ግን አልታወቀም፡፡ተውኔቱ ለዚህ ሁሉ ሽብርና ተያያዥ ክፋቶች ማን ሃላፊነቱን
እንደሚወስድ ይጠይቃል፡፡ ድርጊቱ የሴተኛ አዳሪነት ንግድ በሚካሄድበትና መጠጥ
በሚሸጥበትበሴቶች ቡና ቤት ውስጥ የሚፈጸም ሲሆን (ይህ ደግሞ በቁምነገር እንዳይወሰድ
አድርጎታል) በምሽት አንድ የታክሲ ነጂ ከቤቱ ተወስዶ እንደ ሽብሩ አካል ይገደላል፡፡ይህ ሰውዬ
352
ጥቋቁር አናብስት

የሚሾፍራት ታክሲ ባለቤትም የሆነው ሃብታምም ይገደላል፡፡አለቃው ከሽብሩ ጀርባ ባሉት


አብዮተኞች ቡድን እንደ አድሃሪ ተቆጥሮ ተገቢውን ቀብርም ያገኛል፡፡25 የድሃው ጉዳይ ግን በዚህ
መልኩ አላለቀም፡፡አብዮቱ በዚህ ረገድ ምንም ነገር አልለወጠም፡፡ የሃብታሙ ሰው ሚስት በሃብት
ቆየች የድሃው ሰው ቤተሰብ ግን በችጋር እንደ ተቆራመደ ቀረ፡፡እህቱማ ጭርሱኑ ከሞቱ በኋላ
ባሰባት፡፡ስለዚህ ምንድነው የተቀየረው?ይህ ተውኔት የታየው “ለአጭር ጊዜም ቢሆን አዝጋሚ
ስኬት ነበረው” ይላል ተስፋዬ፡፡

በተመሳሳይ አመት 1972 ዓ.ም "ተሃድሶ" የተሰኘውን ባለ ሁለት ገቢር ተውኔት ለአምስተኛ
የአብዮቱ ክብረ በአል ጻፈ፡፡ይህ ፖለቲካዊ ተውኔት ሲሆን ተስፋዬ በወቅቱ “ከመንግስት ጋር አብሮ
ነበር ”ምንም እንኳን በግለኝነት እራሱን ከምንም በአብዮቱ መነሾ ከነበሩ ፓርቲዎች ጋር
ባያቆራኝም ተስፋዬ ለወደፊቱ ተስፋን የሰነቀበት ጊዜ ነበር፡፡ዋነኛ የተውኔቱ ገጸ ባህርይ የደርግ
አባል የሆነ ሰው ሲሆን የመጀመርያው ገቢር (ብሬችቲያን ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ሲዘዋወር
ያሳያል) ሁለተኛው የህዝቡን ሸንጎ ያሳያል፡፡ህዝቡ የተያዙ ካሃዲዎችን ዝርዝር ያሳያል፡፡የአብዮቱ
መነሾ በፍቅር ግለት የተሞላና በዲሞክራሲ ስም የተፈጸመ ነበር፡፡ነገር ግን ከመሃል አንድ ሰው
ተነስቶ በስመ ዴሞክራሲ ፓርቲ ልመስርት ቢል እስር ቤት ይወረወራል፡፡ይሄ ደግሞ በአብዮቱ
እንደሚፈጸሙ ቃል የተገቡ ነገሮች ላይ ጥርጣሬን ያጭራል፡፡ተስፋዬ ተውኔቱ በቅርጽ ደካማ
ቢሆንም የድራማ ተጽእኖዎችን ተጠቅሟል ይላል፡፡ለምሳሌ ተፈጽመው የሚያውቁና
ላለመደገማቸው ምንም ዋስትና የሌላቸው የሆኑ ድርጊቶችን በማስመሰል ተዋንያኑ ከህዝቡ መሃል
ገብተው መሳርያ በመደገን እጅ ወደ ላይ! ብለው ህዝቡን የሚያስደነግጡበት ትእይንቶች የመሳሰሉ
ሲሆን ከእውነታዊ ተውኔት ጋር ተቀራርቦ ነበር፡፡

በዚህ የብሔራዊ ትአትር ቆይታው ትአትርን ወደ ህዝቡ ማድረስ የሚወደው ተስፋዬ ቴአትር
ቤቶችን በክፍለሃገራት ለመጀመር ቅርንጫፍ ለመክፈት አስቦ በ1971 ዓ.ም የላሊበላ ትአትር
ቡድንን በወሎ ቴአትር አዳራሽ ከደሴ ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር መሰረተ፡፡26 ተውኔቶቻቸውን
ሲያቀርቡ ሲዘፍኑና ሲወዛወዙ እንደ ሃገር ፍቅር ቴአትር ነበር፡፡ነገር ግን ይህ የማስፋፋት ሃሳብ
ከባህል ሚንስትር ችግር ይዞ መጣ ፡፡ በወቅቱ ሚንስትሩ በአሉ ግርማ ነበር፡፡ ቢሆንም ተስፋዬ
በሃሳቡ ገፍቶበት በባህር ዳርና በጎንደር ተመሳሳይ ቡድኖችን አቋቋመ፡፡ጅማም ሄዶ ተመሳሳይ ስራ
ሊጀምር በነበረበት ወቅት ነበር ካራቸውን የሻጡበት፡፡ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ነው በሚል ስሜት
አርፎ እንዲቀመጥ በማሰብ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አማካሪ እንዲሆን አደረጉት፡፡እንደዚህ ዐይነት
ስራዎች ለብርሃኑ ዘርይሁንና ለጸጋዬ ገብረ መድህንም የተሰጡ ማግለያዎች ነበሩ፡፡

353
ጥቋቁር አናብስት

ተስፋዬ እንዲህ ባለ ሁናቴ በኢትዮጵያ ትያትር ተጽእኖ ፈጣሪ ከነበረበት ስልጣን ዳግም ተወገደ፡፡
ነገር ግን በርካታ ባለሙያዎችን በዩንቨርሲቲ ባህል ማእከልም ሆነ በብሄራዊ ቴአትር አሰልጥኖ
የሱን አላማ አንግበው ተልእኮውን እስከዳር የሚያደርሱ ሰዎችን አፍርቷል፡፡በግሉ ለኢትዮጵያ
ቴአትር የበኩሉን ማበርከቱን ከዚህ በኋላም እራሱን ችሎ እንደሚቀጥልም ያምናል፡፡

ከብሄራዊ ቴአትር በለቀቀበት ተመሳሳይ አመት 1976 አንድ "ፍርዱን ለእናንተ" የምትል ተውኔት
ጽፏል፡፡night of January 19th በተሰኘ የአንዲት አሜሪካዊት ሴት ድርሰት ላይ የተመረኮዘ
ነው፡፡ወጥ ስራውን በቅርበት ተከታትሎ እንደውም አንዳንድ ክፍሎች ቃል በቃል መልሶ ያቀረበው
ቢሆንም ነገር ግን አጨራረሱን ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል፡፡የተስፋዬ ተውኔት የሚያጠነጥነው
በአንድ የሞተ ኢትዮጵያዊ ላይ ሲሆን ሌላ የሞተ ገጸ ባህርይም ከመካከለኛው ምስራቅ ያመጣል፡፡
ተስፋዬ ተውኔቱ በጥሩ ሁናቴ እንደተዋቀረ ያስባል፡፡በተውኔቱ መሃል ሰዎች በሚፈጠሩት ክስተቶች
ላይ ፍርድ እንዲሰጡ ይጠየቁ ነበር፡፡ያ ነበር የተውኔቱ ርእስ መነሾ፡፡27 ተስፋዬን ብዙዎች ስለ
ፈጠራው አሞገሱት፡፡ ለመጀመርያ ደራሲዋ እውቅናን አልሰጠሁም ስሟንም አላነሳሁም ይላል
በአሁን(በንግግራችን ወቅት)ስሟንም ረስቶታል፡፡

መጀመርያ በብሄራዊ ቴአትር ታይቶ ከወር በኋላ እንዲቆም ተደረገ፡፡ተስፋዬ ለባለስልጣኖች አቤት
ካለ በኋላ በብሄራዊ ቴአትር መታየት ቢጀምርም ተመልሶ በባህል ሚንስትር ትእዛዝ ከሶስት
ትርኢት ቆይታ በኋላ እንዲታገድ ሆነ፡፡ ሳንሱሩ ቢያሳልፈውም ደርጎቹ በእነሱ ላይ እንደተሰነዘረ
ሽሙጥ ቆጠሩት፡፡በ1979 ዓ. ም አንድ ጊዜ በድጋሚ በባህል ማዕከል ለመታየት ግን ችሏል፡፡

***

ተስፋዬ ይህን ግዜ በድጋሚ ብሄራዊ ቴአትር ስባረር ሚስቴ የህይወታችን አለመቀየርና ድግግሞሽ
አታክቷት ከቤት አባረረችኝ ሲል ታሪኩን ያስታውሳል፡፡28ይህ የሆነው በ1976 ዓ.ም ነበር፡፡
በ1977 ተለያይተው በ1979 ፍቺ ፈጸሙ፡፡በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ነበር ከተስፋዬ ጋር ልገናኝ
የቻልኩት፡፡ አንድ ነገር እየረበሸው እንደሆነም ግልጽ ነበር፡፡ከቤተሰቡ ችግር ውጪ እሱና ባለቤቱ
ለከፈቷት የሃገር ባህል ምግብ ቤትም ሃላፊነት ነበረበት፡፡ነገር ግን በፍቺያቸው ወቅት ይህን ምግብ
ቤት እንድትወስደው በፍቺ ስምምነቱ ለሚስቱ ተፈረደላት፡፡በተመሳሳይ ወቅትም በቦሌ መንገድ
ለሚገኘው ቤቱ ወጪ ለመሸፈን መቻሉ እያጠራጠረው ነበር፡፡በአማካሪነትም የሚሰራው ስራ
(እሱም አለቃውም እንደነገሩኝ)ከምንም የማይሻል ሲሆን፡እንደ እድል ሆኖለት በ1979 ዓ.ም
በባህል ማእከል ዳይሬክተርነት አዲስ ስራ አገኘ፡፡አዲስ ሚስትም አገባ፡፡ቤቱንም ይዞ መቀጠል
የሚችል ይመስል ነበር፡፡እኔ እስከማውቀው ጊዜ ድረስ ቢጠጣም ከመጠጡ ቀንሷል፡፡“እንዴት

354
ጥቋቁር አናብስት

መጠጥ ማቆም እችላለሁ? አዲሷን ሚስቴን ጤነኛ ብሆን ኖሮኮ አግቢኝ ብዬ ደፍሬ ባልጠየቅኋት
ነበር!”ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሃኪሙ መጠጥ ቢቻል ለ 6 ወራት እንዲያቆም ካልሆነ እንደሚሞት
ነግሮታል፡፡ አሁን ውሃ ብቻ ነው የሚጠጣው፡፡

ተስፋዬ ገሠሠ አዲሱን ስራዬን ወድጄዋለሁ ሲል ተናግሯል፡፡29በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የጥበባት


ፋከልቲ የድራማ ክፍሉ በ1978 ዓ.ም ገደማ ሲቋቋም እሱ ደግሞ በትርፍ ግዜ ከ 1971 ዓ.ም
ጀምሮ እዚያ ያስተምር ነበር፡፡ነገር ግን የማስተማር ስራው የማእከሉ ዳይሬክተር ከሆነ ጀምሮ
ጨምሮ ነበር፡፡በትያትር ታሪክ ፤ስነጽሁፍና ፤የፈጠራ አጻጻፍ ላይ ኮርሶችን ይሰጣል፡፡ይህን በራሱ
ለሙያው አንድ አስተዋጽኦ እንደ ማድረግ ይቆጥረዋል፡፡በዛ ላይ ከተለያዩ የድራማ ተማሪዎች ጋር
በባህል ማእከሉ የመስራት እድል ገጥሞታል፡፡በዚህ ስራ ላይ እያለ ብዙ ጊዜ አግኝቼዋለሁ፡፡
ተረጋግቶ በስራው ደስተኛ እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡በኢትዮጵያ የጡረታ መውጫ እድሜ ጣርያ
ላይ የደረሰ ይመስላል፡፡30በጡረታው ምን እነደሚያደርግበት እያቀደ ይገኛል፡፡ ለመንግስት 25
አመት አገልግሎ በ1980 አ.ም 50ኛ እድሜውን ስላስቆጠረ ጡረታ ለመውጣት ከፈለገ ይችላል፡

ምን አልባት ቦዝኖ ከመዋል በችግሩ ወቅትም ቢሆን መጻፉን ቢቀጥልም ወይም ችግር የሚያነሳሳው
እንደሆነ ቢገምትም በ1979 "መንገደኞች" የተባለውን ኮመድያ ጻፈ፡፡“በጥሩ ሁኔታ የተዋቀረው
ድርሰቴ” ሲል ይናገርለታል፡፡በገብርኤል ንግስ ወደ ሐረር ቁልቢ ገብርኤል ልጅ ለማግኘት ለበረከት
ለመልካም እድል ለጥምቀት ወዘተ ስለሚሄዱ ሰዎች ነው የተጻፈው፡፡ የክርስትያኖች ቤተ
ክርስትያን ቢሆንም ሙስሊሞችም በገብርኤል “ስለሚያምኑ” ይሄዳሉ፡፡ዋናው የተውኔቱ ገጸ
ባህርይም አንድ ሙስሊም ሽማግሌና ያስኮበለላት ሴት እንዲሁም ስለነሱ በቀድሞ ውሽማዋ በኩል
ስለሰማች “እውነተኛ ሚስቱ” ነው፡፡ኮመዲው የሚመነጨው ከተከታታይ ትንቅንቆቹ ነው፡፡
በምንነጋገርበት ወቅትም ለመድረክ አልበቃም፡፡

ከጥቂት አመታት በኋላ "ሰኔና ሰኞ" የተሰኘ ተውኔት ደረሰ፡፡በሰኔና ሰኞ ግጥምጥሞሽ መጥፎ ገድ
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡አስደሳች ነው የሚለው ታሪክ መቼቱ ከአብዮቱ በፊት በነበረችው አስመራ
ውስጥ ሰኔ 1 ቀን ነው፡፡አንድ ሰው ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ከሚዋጉት ነጻ አውጪዎች 10000
ብር የሚጠይቅ ደብዳቤ ይደርሰዋል፡፡ ይህ ካልሆነም እንደሚገድሉት ይነግሩታል፡፡ወደ ፖሊስ
ጣብያ ደብዳቤውን ይዞ ሄዶ ለመኮንኑ እያሳየው ሳለ ሌላ ተመሳሳይ ደብዳቤ የደረሰው ሰው መጣ፡
፡በተውኔቱ የተሳለው መጥፎ ገድ ታድያ ይሄ ከመክፈል ውጪ አማራጭ የሌለው ችግር ነው፡፡
ለተገንጣዮቹ ገንዘቡ ተሰጣቸው፡፡ገጸባኅርያቱ ኤርትራዊ ሲሆኑ በባህል ማእከል ለመድረክ በቅቷል፡

355
ጥቋቁር አናብስት

ከተውኔቶቹ በተጨማሪ ተስፋዬ በርካታ አጫጭር ታሪኮችን ጽፏል፡፡ለአምስተኛው የአብዮታዊ


በአል ክብረ በአል መዝግያ ንግግር አዘጋጅቷል፡፡ለ10ኛውም እንዲሁ፤ለኢሰፓ ምስረታም
በተመሳሳይ መልኩ፡፡ለዚህ የመጨረሻ አድራጎቱም ሶስተኛ ደረጃን በማግኘት ተሸልሞበታል፡፡
ሁለቱ አጫጭር ታሪኮቹና 8 ግጥሞቹ ወደ ሩስኪ ተተርጉመው በሩስያ ታትመዋል፡፡በጠረጴዛው
ላይ የግጥም ስብስቦችና መንገደኞች የሚለው ተውኔቱ በንግግራችን ወቅት ነበሩ፡፡ሁሉም
አልታተሙም ፡፡ከጡረታ በኋላ ጊዜ ስለሚያገኝ ለመጻፍ ይችል ይሆናል፡፡ ወይም ከመንግስት ስራ
ውጪ ሌላ ስራ ያፈላልግ ይሆናል፡፡

ከመጀመርያ ሚስቱ የሚወለደው ልጁ በንግግራችን ወቅት አሜሪካ ነበር፡፡ ሴት ልጃቸው ግን አዲስ


አበባ ነች፡፡በርካታ የስራ አመታት ከፊቱ እንደሚኖሩ ይጠብቃል፡፡ምንአልባት ለኢትዮጵያ ቴአትር
አሁንም የበኩሉን ያበረክት ይሆናል፡፡

***

ተስፋዬን ከዚህ ቆይታችን በኋላ በተደጋጋሚ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከሌሎች ሃላፊነቶቹ በተጨማሪ በኤ.አ
1988 በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የድራማ ክፍሉ የበላይ እንደተደረገ ነግሮኛል፡፡ ኢትዮጵያን በ
1989 እ.ኤ.አ ከመልቀቄ በፊት አንዴ ለአጭር ቆይታ ተገናኝተን በእንግሊዘኛ የጻፈው ረቂቅ
እንዳለውና አንብቤ አስተያየት እንድሰጠው ጠይቆኝ የነበር ቢሆንምበኢትዮጵያ የምሰራውን ስራ
ለመቋጨት በጥድፊያ ላይ ስለነበርኩ ልቀበለው አልቻልኩም ፡፡ለእነዚህ ገጾች መጻፍ መክንያት
ከሆኑ ንግግሮቻችን በኋላ የመጻፍ ጉጉት እንዳደረበት ነግሮኛል፡፡አንድ ሰው በሱ ስራዎች ከተደሰተ
በተሻለ ለመጻፍ ግዴታ ውስጥ እንደሚገባና በፊት ከሰራው ሳይቀር በተሻለ ለመስራት ጊዜውንና
ተሰጥኦውን መጠቀም እንዳለበት አጫወተኝ ፡፡ከሁለተኛው የኢትዮጵያ ጉብኝቴ እ.ኤ.አ 1989
በኋላ ዳግመኛ ላገኘው ባልችልም ለኢትዮጵያ ቴአትር አንድ ጉልህ መዳረሻ ማስቀመጡን
አምናለሁ፡፡

የደራሲው ማስታወሻ
በቅርቡ የኦማር ኻያምን ሩባያቶች ተርጉሞ ማሳተሙ ተነግሮኛል፡፡

የተርጓሚው ማስታወሻ

ተስፋዬ ገሠሠ ከዚህ ጽሁፍ ጥንቅር በኋላ የተለያዩ ስራዎችን አሳትሞ ለገበያ አቅርቧል፡፡

ማስታወሻ

356
ጥቋቁር አናብስት

1)አንዳንድ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያውያንን በሚስትነት አስቀምጠዋል፡፡ክልሶችም ብቻውን ከኖረ


ህብረተሰብ ጋር ለመቀላቀል ካለባቸው ችግር በተጨማሪ በዚህም ግንኙነት እንደተወለዱ ተደርገው
ይጠረጠሩ ነበር፡፡

2)ቆለጭ በጎንደር አካባቢ የታወቀ ስም ሲሆን በጣና ሃይቅ ካለ ብርማ አንጸባራቂ መልክ ያለው
አሳ መጠርያ ነው፡፡ከሌላው መጠርያ ስም ቁልጭልጭ ጋር ተመሳሳይነት አመጣጥ ሊኖረው
ይችላል፡፡

3)ተስፋዬ እንደሚለው ከሆነ የምንሊክ ባለሟል የነበሩት የግርማሜ ዘር ነች፡፡ግርማሜ የምኒሊክን


እናት በጀርባቸው አዝለው ከተራራም ሲወርዱ እግራቸውን ሰብረው ከመቅደላ ያመለጡ ናቸው
ይባላል፡፡በዚሁ ምክንያትም በጦርነት ላይ መሳተፍ አልቻሉም፡፡አንድ እግራቸውም እንደተሰበረ
ቀረ፡፡ሚኒሊክና እናታቸው በአጼ ቴዎድሮስ ቤት በእስር ቆይተው ነበር፡፡ግርማሜ አጼ ምንሊክ
ወደ አድዋ በዘመቱበት ወቅት ሃገር ለመጠበቅ ቀርተው ነበር፡፡(ሸዌዎች እንደሚሉት ግርማሜ
አጼውን በሚከተሉት ላይ ቅናት በማሳደራቸው በዚህ ተነሳስተው ለምኒሊክ ከሌላ ቦታ
የሚመጡት ሰዎች የማይታመኑ እንደሆኑና ከሸዋ የተገኙት ብቻ ታማኝ እንደሚሆኑላቸው
ነገሯቸው፡፡ምኒሊክም ሲመልሱላቸው“እኔ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ነኝ ፡፡በእኩልነት ነው ሁሉን
ማየት ያለብኝ እንደዚህ ካልሆነ ወደ ጦርነት ይመራናል” አሉ፡፡ግርማሜ ቀጥለው ለመኳንንቶቻው
ማእረግ እየሰጡ ወደ ትግራይ ፡በጌምድር፡ጎጃም እንዲልኳቸውና በታማኝ አዛዦች ስር ሆነው
እንዲያገለግሉ ነገሯቸው፡፡ቀጥለውም ወልደግዮርጊስንና መኮንንን ራስ ብለው ሾመው ወደ ከፋና
ሃረር መኳንንት አስከትለው እንዲሰዱ መከሯቸው፡፡በኋላም ግርማሜ ከተጉለት እና መንዝ
እንዲሁም ሌሎች አካባቢ ምኒሊክን እንዲያገለግሉ ሸዌዎቹን አስመጡ፡፡ይሄ የሸዋ የስልጣን
ቁጥጥር መጀመርያ ነበር፡፡የቴዎድሮስ ታማኝ አገልጋይ የነበረው በዛብህ በሚኒሊክ ላይ ሲያምጽ
ሊያድኑት ሚኒሊክ ቢፈልጉም በግርማሜ ትእዛዝ ነበር በጥይት የተገደለው፡፡የበዛብህ ሁለት
ፈረሶች ጥልፌና ቦራ ለግርማሜ ተሰጡ፡፡ዘፈንም ተዘፈነላቸው

ቦራና ጥልፌ እንዴት ይግረማቸው

አንካሳው ግርማ ሲቀመጥባቸው

ደጃዝማች ግርማሜ የየ53ቱ መፈንቅለ መንግስት ርእዮተ አለማዊ መሪ ግርማሜ ንዋይም አያት
ናቸው፡፡

4) ኢትዮጵያውያን በመነኩሴዎች በሚነገር ንግርት ያምናሉ፡፡በንጉስ ሳህለ ሥላሴ ዘመን ከጉራጌ


እናት ስለሚወለዱ ንጉስ አንድ ንግርት ይዘዋወር ነበር፡፡ንጉስ ሣህለሥላሴ ወደ ጉራጌ ምድር
357
ጥቋቁር አናብስት

ወርደው ረገን የምትባል ውሽማ ያዙ፡፡ከሷም ራስ ዳርጌን ወለዱ፡፡ዳግማዊ ምኒሊክም ከጉራጌ


ሚስት የሚወልዷቸው ልጆች አሏቸው፡፡የራ ስ መኮንን እናት እና የኃይለሥላሤ አያትም ከጉራጌ
ብሄር ተወላጅ ናቸው፡፡እነዚህ ሁሉ ሴቶች በዘመቻ ወቅት የተማረኩ ናቸው፡፡

5)ተስፋዬ በዚያን ወቅት ´ግራጫ´ በሚል ግራጫ ቀለም ባላቸው የአህያና የበቅሎ ለመጠርያ
በሚያገለግል ስም እንደሚጠራ ያስታውሳል፡፡ይህ ስምም ለክልሶች እንደ ቅጽል በመሆን ያገለግል
ነበር፡፡

6)የተወሰኑትን ተዋንያን አሁንም ያስታውሳቸዋል፡፡ለምሳሌ ያህል እንደ ሴት ሆኖ በሚስትነት


የተወነውን ልዑልሰገድ በለጠን ያስታውሳል፡፡አሰፋ ክፈተውም አለ አየር ሃይልን የተቀላቀለ ተዋናይ
ሲሆን በቃለመጠይቃችን ወቅት ጡረታ ወጥቶ ነበር፡፡

7)በዚህ ግጥም ባይበዛም ይናደዳል፡፡በግጥሙ ላይ ´ጩሊ´ የሚለው ከበደ የተጠቀሙበት ቃል


ከእርሱ ቅጽል አስማት አንዱ ነበር፡፡

8)እንደሚናገረው ከሆነ የካናዳ ፈረንሳዊ በሆነው አቶ ፕሬቮ ከእንግሊዘኛው ተተርጉሟል፡፡´ሳቂታና


ፎልፏላ ´የሆነው ይህ ሰው ተጽእኖ ሳያሳድርብኝ አይቀርም ይላል፡፡ሃይማኖተኛ ደግ ተባባሪና
የጀዝዊቶች አባል የነበረ ነው፡፡ተስፋዬ እራሱ በሁለተኛ ደረጃ ሳለ ወደ ሃይማኖት ያዘነብል
እንደነበር ይናገራል፡፡ያኔም ሆነ አሁን ለሃገሩና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን
ታላቅ ፍቅር ያለው ሲሆን የመገለል ስሜት ከሚያሳድሩብኝ የበታችነት ስሜትና ብቸኝነትን
እንደሚያረክሱልኝ መድሃኒት ነው የምመለከታቸው ይላል፡፡በተጨማሪም አማርኛ ለሱ ጠቃሚ
እንደነበርና ማንነቱን ለማግኘት እንደረዳው ይናገራል፡፡በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ቅናት እንዳሳደረና
በየትኛውም የሃገሪቱ ክልል አማርኛን እንዲተካ አይፈልግም፡፡አቶ ማርሻል የሚባሉ የእንግሊዘኛ
መምህር እንግሊዘኛ ቋንቋ ለሁለተኛ ደረጃ መጠቀሚያነት እንዲውል ሃሳብ ሲያቀርቡ ተናድጄ ነበር
ይላል፡፡ለነገሩ አሁንም መጠቀሚያ ነው፡፡

9)ቆይቶ በተመሳሳይ ቴአትር ቤት በስራ አስኪያጅነት በተሾመው ሰይፉ እነሱ የቀረበለት ሲሆን
በወቅቱ በዳይሬክተርነት መአረግ ያለ ሰው እንዳልነበረ ተስፋዬ ይናገራል፡፡

10)ተስፋዬ በመላኩ ተውኔት ያን ያህል አልተደሰተም፡፡ መላኩንም ከአቤ ጉበኛ ጋር ተመሳሳይ


በሆነ ደረጃ የ(ቢ ክፍል ደራሲ)(እንደ ሁለተኛ ደረጃ) ሲል ይጠራዋል፡፡

11)ከአብዮቱ በኋላ ምንም ያህል መጥፎ ጊዜም ቢመጣ ወደ ኋላ የሚነገርም ቢሆን ወታደራዊው
መንግስት ገና ስልጣን ላይ ሳለ ነበር ተስፋዬ በድፍረት ያጫወተኝ፡፡
358
ጥቋቁር አናብስት

12)ኋላ ከኢምፔሪያሊዝም ውድቀት በኋላ ማድረግ እንደ ጀመሩት ሳይሆን ባለስልጣኖቹ በዛን
ወቅት መግደል አይፈልጉም ነበር፡፡

13)ከሚያስታውሳቸው ተዋንያን መሃል አንዱ መኮንን አበበ ሲሆን በግርማቸው ተክለሐዋርያት


አጼ ቴዎድሮስ ላይ አጼ ቴዎድሮስን ሆኖ የተጫወተ ሲሆን ተስፋዬ ሲያታውሰውም በአድናቆት
ነው፡፡ቆይቶ በተስፋዬ ስር ሆኖ የ´ እሾህ አክሊልን ´ ተጫውቷል፡፡

14)ተስፋዬ የባህል ማእከሉን ከለቀቀ በርካታ አመታት በኋላ አንድ አሜሪካዊ ኦርኬስትራ
ኢትዮጵያን ተቀላቀለ፡፡ቻርለስ ሳተን የተባለው ይህ አሜሪካዊ ባህላዊውን የሙዚቃ መሳርያ
መሰንቆን በዝቅተኛ ደረጃ ከሚጫወቱ ሰዎች ተምሮ የመጣ ሲሆን ከዛ በኋላ በኦርኬስትራው
ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ጀመረ፡፡ከውጪ ዜጎች ጥቂቶቹ ናቸው የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለምደው
ለመጫወት የሚበቁት፡፡

15)ታዋቂው ሰአሊ አፈወርቅ ተክሌ በማእከሉ አላስተማረም፡፡ነገር ግን በጸጋዬ ገብረመድህን


´ቴዎድሮስ´ ላይ የተውኔቱ ማስታወቂያ ብሮሸር ላይ ያለውን የጀርባ ምስል ሰርቷል፡፡

16)ተስፋዬ የዚህ ተውኔት የእራሱ ቅጂ ጠፍቶበታል፡፡ነገር ግን የተቀዱ የራድዮ ቅጾች ይኖራሉ


ብሎ ያስባል፡፡

17)ዮሀንስ አድማሱ በሬድዮ ላይ ተውኔቱን የገመገመው ሲሆን አሞግሶትም ነበር፡፡በጋዜጣ ግን


አልተገመገመም፡፡

18)ጋና ከአፍሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በቀደምትነት ከተወዳጁት ሃገራት መሃል ስለሆነች በተለምዶ


´ጋና´ ለሌሎች አፍሪካውያን በተለይ ጠቆር ያለ ቆዳ ላላቸው መጥርያነት የሚውል ክብረ ነክ ስያሜ
ነበር፡፡

19)በተመሳሳይ ወቅት ጸጋዬ ገብረመድህን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ ሆነ

20)´ኢትዮጵያ ትቅደም!´ሲሆን የመጀመርያው የአብዮታዊው መንግስት መፈክር ወደ ኋላ


´አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት!´ በሚለው ተቀይሯል

21)በቃለመጠይቃችን ወቅት በሳምንት ሶስት ጊዜ ይታይ የነበረ ሲሆን ሁሉም የሚታዩት ከሰአት
በኋላ ነበር፡፡በኢትዮጵያ የምሽት መርሐግብራት ብዙም አልተለመዱም፡፡
359
ጥቋቁር አናብስት

22)ትምህርት በሬድዮ ቢቆይ ኖሮ ተስፋዬ የተሻለ ክፍያ ያለውን በዝና ከፍም ያለውን የURTNA
ስራ እንደሚያገኝ አይገምትም፡፡ እዛው በነበረበት ስራ ላይም ይቆይ ነበር፡፡

23)ከመሃከላቸው በወቅቱ ተጽእኖ ማሳደር የሚችለው የመኢሶን ፓርቲ የሚቃወሙት ደርጎቹ


“ጀማሪ አብዮተኞቹ” የመሳሰሉ ነበሩ

24)በቀላሉ ለመናገር ያህል ኢ.ህ.አ.ፓ በመጀመርያ መንግስት ላይ ነጭ ሽብርን አወጀ፡፡ደርጉ


ደግሞ መኢሶንን በመጠቀም በቀይ ሽብር ኢ.ህ.አ.ፓ.ን ለማጥፋት ቻለ፡፡እርስ በራሳቸውም
ሊጠፋፉ በቁ፡፡ሁለቱንም ያስወገደው ደርግ ተደላድሎ ስልጣን ላይ ለመቀመጥ በቃ፡፡

25)በኢትዮጵያ ለቀብር ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል

26)የወሎው ርሃብ በአንድ መልኩ ለአብዮቱ መቀጣጠል አስተዋጽኦ ስላደረገ ወደ ወሎ ፊትን


መልሶ አብዮታዊ ቴአትር መቅረብ እንደነበረበት ተስፋዬ ይናገራል፡፡

27)ወጡ የአሜሪካው ስራ ሸንጎ የነበረው ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ፍርድ ሸንጎ ስለሌለ ዳኞቹን
መጠቀም ግድ ሆኖበታል፡፡

28)እሱንና ሚስቱን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እሱ ሳይሆን አይቀርም ያባረራት ይላሉ

29)አንዳንዶቹ ቃለመጠይቆቻችን በስራ ቦታው ነው የተደረጉት፡፡

30)በወቅቱ አንድ ሰው 25 አመታትን ካገለገለ በ50ኛ አመቱ ላይ ጡረታ ይወጣል፡፡ወይም በ


55ኛው አመት እድሜው ከዛ በፊት ምንም ያህል ይስራ ጡረታ ይወጣል፡፡

31)ይህ ተውኔት መጀመርያ ´ቁሉቢ´ ተብሎ ነበር የሚጠራው፡፡ሳንሱር አድራጊዎቹ አርእስቱን


እንዲቀይር ሲነግሩት ግን ለወጠው፡፡በዚያ ወቅት ግን በሳንሱር ክፍል እንዲያልፍ ተፈቅዶ እነደነበር
ይናገራል፡፡

360
ጥቋቁር አናብስት

ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም
በሶስት ቋንቋ የሚጽፉ ሁለገብ ደራሲሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም
የተወለዱት በቀድሞው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ጨቦ እና ጉራጌ ወረዳ፣
ሲስ በተባለች መንደርነው።ትውልዳቸው ከሰባት ቤት ጉራጌ ውስጥ
አንዱ በሆነው ቸሃ ነው።የሚኖሩት ከአርሶአደር እና አርብቶአደር
አባታቸው፣ ከቤት እመቤት እናታቸው እንዲሁም ከወንድምና
እህቶቻቸው ጋር ነበር። በጉራጌ ባህል "ሴቶች ብዙም ቦታ
አይሰጣቸውም"፤ስለዚህ ገና የአስረኛ ክፍል ተማሪ ሳሉ አባታቸው ሲሞቱ፣ ምንም እንኳን
እናታቸው ያኔም ሆነ አሁን ይህንን ቃለመጠይቅ ባደረግንበት 1977 ዓ.ም በሕይወት የነበሩ
ቢሆንም፣ታላላቅ እህቶች ቢኖራቸውም፣የቤተሰብ ሃላፊነቱን ተቀብለው እርሻውንና ቤተሰቡን
የማስተዳደር ኃላፊነቱን ተረክበዋል።ይህ አዲስ ሃላፊነት ሳህለሥላሴ ትምህርታቸውን አቋርጠው
ጊዜያቸውን ሁሉ ቤተሰቡንና እርሻውን መንከባከብ ላይ እንዲያውሉ አስገደዳቸው።ነገር ግን
የአባታቸው ጓደኛ የነበሩት በሳቸውም ሕይወት ውስጥ ሚና የነበራቸው አባ ፍራንሷ ማርቆስ
የተባሉ የካቶሊክ ቄስ፣ ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እና ቤተሰቡንና እርሻውን በትርፍ ሰአታቸው
እንዲንከባከባቸው አሳመኗቸው።ትምህርት ቤት በሚሆኑባቸው ወቅት አጎታቸው ተክተው በስራ
እያገዟቸውት፣ ምክራቸውን ተቀብለው ተግባራዊ አደረጉ።

አባ ፍራንሷ የሳህለሥላሴ ቤተሰቦች በሚያመልኩበት የአካባቢው ቤተክርስቲያን ቄስ


ከመሆናቸውም ባሻገር እምድብር በሚገኘው፣ ሳህለሥላሴ በተማሩበት የመጀመሪያው የመንግሥት
ትምህርት ቤት መምህር እና ርእሰ መምህር ነበሩ።የላቲን ፊደላትን በፈረንሳይኛ ዘዬ መማር
ጀምረው የነበር ቢሆንም፣ኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ቋንቋን ብሔራዊ የትምህርት ቋንቋ አድርጋ
በመቀበሏ ፊደላቱን እንደገና በእንግሊዝኛ ዘዬ ማጥናት ግድ ሆነባቸው።በተመሳሳይ ጊዜ የሐገሪቱ
ብሔራዊ ቋንቋ የሆነውን አማርኛ መማር ጀመሩ። አፋቸውን በፈቱበት ጉራግኛ ትምህርት
አይሰጥም። ሳህለሥላሴ በትምህርት ቤቱ በቆዩበት ሶስት ዓመታት፣ አባ ፍራንሷ በብዙ መንገድ
ሳህለስላሴ ላይ አሻራቸውን ከማሳረፋቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪዎች ወደሚላኩበት አዲሳባ
እንዲሄዱ አመቻቹላቸው።በዋና ከተማው ሳህለሥላሴ አብዛኛውን ጊዜ በላዛሪስት ሚስዮን
ተቀምጠው፣ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ከአራተኛ ክፍል ጀምረውው እስከ
ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ አስራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ተከታተሉ።ሁለተኛ ትምህርት ቤታቸውንም
መውደዳቸውን ገልጸውልኝ፣በተለይ የፈረንሳይ ካናዳዊ የነበረ ጋሮ1 የተባለ መምህራቸውን
እያመሰገኑት ጭምር እንደሚያስታውሱት ነገሩኝ።ይህ መምህር በቀላል እንግሊዝኛ የተፃፉ
መጽሐፍት ዝርዝር አዘጋጅቶ ተማሪዎቹ እንዲያነቡ ያበረታታ ነበር።ከነዚህ መጽሐፍት መሐል

361
ጥቋቁር አናብስት

ሳህለሥላሴ ቀሎ እና አጥሮ አንብበውት በኋላ ወደ አማርኛ የተረጎሙት የቻርልስ ዲክንስ "የሁለት


ከተሞች ወግ" ይገኝበታል።

ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እያሉ ሳህለሥላሴ በክርክር ክበብ ውስጥ ሆነውየንግግር ጥበብ
ይማርካቸው ነበር፡፡ምንም እንኳን "አንደበተ ርቱእ" ባይሆኑም አድማጮቻቸውን በንግግራቸው
ይዘው ለመንጎድ ያኔም ሆነ በኋላ ይመኙ ነበር―ያ ምኞት ግን አሁን ሞቷል።በሕይወታቸው
ለመጀመሪያ የፃፉት መጣጥፍ ለትምህርት ቤታቸው መጽሔት ሲሆን ስለ ምኞት መሆኑን
ከማስታወሳቸው በስተቀር ዝርዝሩን ረስተውታል።2

በዚህ ወቅት አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በላዛሪስት ሚስዮን ነበር። እዛ በተለይ


የሳባቸው ሰው አልነበረም፤ቢሆንም ቤተ መጽሐፍቱን እንዲቆጣጠሩ ሐላፊነት ስለተሰጣቸው ብዙ
ጊዜያቸውን እዚያ በማሳለፍ የቅዱሳንን ሕይወት እና ተረቶችን በቀላል ቋንቋ በማንበብ ተማረኩ።
እዚያ በነበሩበት ወቅት ቄስ እንዲሆኑ ብዙ ግፊት ቢደረግባቸውም ቤተሰባቸውን መንከባከብ
ስላለባቸው ሀሳቡን አልተቀበሉትም።አስራ አንደኛ ክፍል እያሉ ከላዛሪስት ሚስዮን እንዲለቁ
የተደረገውም በዚህ ምክንያት ነው፤ነገር ግን ምክንያቱን ስለተረዱ አላዘኑባቸውም።

ከዚያ በኋላ ዘመድ ቤት ለአንድ ዓመት ኖሩ።ነገር ግን መጀመሪያ ሊያገኟቸው ስላዳገታቸው ተፈሪ
መኮንንን ለቀው የሐረር መምህራን ማሰልጠኛን ለመቀላቀል አስበው ነበር።ነገር ግን ሳህለሥላሴ
ከትምህርት ቤቱ ምርጥ አምስት ተማሪዎች አንዱ በመሆናቸው የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር
በተፈሪ መኮንን እንዲቆዩ ፈለጉ፤ከብዙ ጥረት በኋላ ሳህለሥላሴ ዘመዶቻቸውን ማግኘት ቻሉ።

ሳህለሥላሴ በላዛሪስት ሚስዮን ቆይታቸው ለበዛ የካቶሊክ ቀኖና ቢጋለጡም ከልባቸው ሊቀበሉት
ግን አልቻሉም።በጣም ጥብቅ እና ከሰብአዊ ባህሪ የራቀ ሆኖ ይሰማቸው ነበር።ሕይወት እና
ቀኖናው የሚጣጣሙ አልሆኑም።ስለዚህ አመፁ፤ይሁን እንጂ ስለቄሶቹ ብዙ ጥሩ ትዝታዎች
አሏቸው።በሚስዮኑ ለነበሩት ተማሪዎች እንደ ወላጅ አባቶች ነበሩ።በቆይታቸው መጨረሻ ከነበሩት
አለመስማማቶች መሐል ሀጢያትን በተለይ ደግሞ የፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ያላቸው ሕግጋት
ነበሩ።ቤተክርስቲያን መሄዳቸውን ባያቋርጡም በውስጣቸው ግን አመፁ።ቀኖናቸው የሰውን
ምክንያታዊነት ይቃረናል።በቃለ መጠይቃችን ወቅት ቤተክርስቲያን መሄዳቸውን አቁመዋል፤
እንደውም ረዥም ጊዜ ሆኗቸዋል።ይሁን እንጂ ኢአማኒ አይደለሁም― “ነፃ አሳቢ” እንጂ ይላሉ።

ሳህለሥላሴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው ዩኒቨርስቲ
ኮሌጅ ገቡ።ይህ እንግዲህ የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የአሁኑ አዲስአበባ
ዩኒቨርስቲ ከመቋቋሙ በፊት ነበር። በዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ለአራት ዓመት ማለትም ከመስከረም
1948 እስከ ሐምሌ 1951 ዓ.ም ድረስ ቆይተው በሥነ ጥበብ ፋካልቲ ውስጥዲግሪያቸውን
362
ጥቋቁር አናብስት

ተቀበሉ። የትምህርት ዐይነቶቹ ህግ፣ የማህበራዊ ሳይንስ፣የፖለቲካ ሳይንስ፣ፍልስፍና፣ታሪክ፣


ጂኦግራፊ፣ሥነ ጽሑፍ እና ቋንቋን የመሳሰሉ ሁሉን አቀፍ ነበሩ። የህግ ትምህርት አልማረካቸውም፤
ነገር ግን ፍልስፍና እና የፖለቲካ ሳይንስን ከመውደዳቸውም በተጨማሪ፣በትምህርታቸው
ከሚጠበቅባቸው በላይ በትርፍ ጊዜያቸው ሁሉ መጻህፍትን እያሳደዱ ያነባሉ። በዚህ ወቅት ነበር
የሥነ ጽሑፍ ስራዎችን በገፍ ያነበቡት።በሁለተኛ ደረጃ እና በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ያነበቧቸው
መጽሐፍት፦ ሮበርት ሉዊስ ስቴቨንሰን(Travel with a Donkey)፣ ቻርልስ ዲክንስ (A Tale
of Two Cities,David Copperfield,Oliver Twist,A Christmas Carol).She
Stoops to Conquer,The Black Stallion, The Mill on the Floss,Silas
Marner ወዘተርፈ ይገኙበታል።ጆሴፍ ኮንራድን አግኝተው ቢያነቡትም ያኔም ሆነ አሁን
ሊገባቸው አልቻለም።የጆን ፓድሞር"ፓን አፍሪካኒዝም ወይስ ኮምዩኒዝም" አስደንቋቸዋል።

ደራሲው ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበቡት ጥቁር ደራሲ መሆኑ አድናቆታቸውን


ጨምሮታል። የክዋሜ ንክሩማን The Story of My Life ንም ጨምረው አንብበዋል።
ከፍልስፍና መምህሮቻቸው አንዱ ክላውድ ሰምነር ነበሩ።ሳህለሥላሴ የሚከብዱ ጥያቄዎችን
ስለሚጠይቋቸው "ይናደዳሉ"፤የሚያስተምሯቸው ስለነ ቶማስ አኩዊና ሲሆን ፍልስፍና እና
ቶሚዝም አንድ ናቸው ብለው ተማሪዎቻቸውን ሊያሳምኑ ይደርሱ ነበር ይላሉ ሳህለሥላሴ። በኋላ
ሚኬላይደስ የተባለ ሌላ ጀዝዊት የፍልስፍና መምህር ተመደበላቸው። እኚህ መምህር ተማሪዎችን
ከዘመናዊ ፈላስፋዎች ጋር አስተዋወቋቸው ―ኪርክጋርድ፣ ዴካርት፣ ካሙ፣ሳርትር ከመሳሰሉት
ጋር። ደግሞም ከካርል ማርክስ ጋር አስተዋወቋቸው።እኚህ መምህር ሳህለሥላሴ ላይ ጉልህ አሻራ
ከማሳረፋቸውም ባሻገር ለፍልስፍና ፍላጎት እንዲያድርባቸው አደረጉ፤የተማሪዎቹን አይን ከፍተው
በራሳቸው ብዙ እንዲያነቡ አደረጓቸው።"ታላቅ ሰው ነበሩ"። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ቀኖና ላይ
እንዳመጹ ሁሉ፣ በሳምነር ትምህርትም ላይም በተመሳሳይ ምክንያት እንዲሁ አደረጉ፤ይህ ትምህርት
ከአመክንዮ ጋር ሊታረቅላቸው አልቻለም።4ካሙ፣ሳርትር እና ሩሶ ያኔም የሚያነቧቸው አሁንም
የሚያደንቋቸው ናቸው፤በተለይ ሩሶን በፖለቲካው ፍልስፍና ያደንቁት ነበር፦"የሰው ልጅ በነፃነት
ቢወለድም ባለበት ሁሉ እስረኛ ነው፡፡"እነኚህ ፈላስፋዎች የሥነ ጽሑፍ ሰዎችም ጭምር
መሆናቸው ለሳህለሥላሴ ትልቅ ቦታ ነበረው፤ሥነ-ጽሑፋቸው በፍልስፍናቸው ላይ የተመሰረተ
ነበር። ዶስቶቭስኪን ከመውደዳቸውም ባሻገር፣ካሙ እና ሳርትርን ለመሳሰሉ ፈላስፋዎች መምጣት
ምክንያት ነበር ብለው ያስባሉ።በተጨማሪም የኤፒክቲተስን The Moral and
Philosophical Discourses of Epictetus እንደ መጽሀፍ ቅዱስ አብጠርጥረው
እንዳነበቡት ይናገራሉ፤ቢያንስ በየዓመቱ አንዴ።የስቶይክ ፈላስፋው ኤፒክቲተስ፣ዶስቶቭስኪ እና

363
ጥቋቁር አናብስት

ሳርትር እንደሚመሳሰሉ መገንዘብም ችለው ነበር።ኤፒክቲተስ እንደሚያስተምረው ሰው በመሰረቱ


ነፃፍጥረት ስለሆነ ይመርጣል―የሚመርጠው በሱ ምርጫ ውስጥ ካሉ ነገሮች መሐል ብቻ ነው፤
ከሱ ምርጫ ውጪ ያሉት ነገሮች አይመለከቱትም፤ ለሚመርጣቸው ነገሮች ግን ኃላፊነቱን ራሱ
ይወስዳል። እነኚህ ሀሳቦች በኤግዚስቴንሺያሊዝም በተለይም በሳርትር ፍልስፍና ውስጥም ይገኛሉ።
ለምንመጣቸው እና ለምናደርጋቸው ነገሮች ሃላፊዎች የገዛ ራሳችን መሆናችንን የሚገልፀው
አመለካከት በሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳርፏል፤ይሁን እንጂ ነጻነታችን
የተገደበ እስር ቤት ውሰጥ ካለው ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ገብቷቸዋል።

ሳህለሥላሴ በፍልስፍና፣ፖለቲካ እና ሥነ-ጽሑፍ ጭብጦች መሐል ጠንካራ ግንኙነት እንዳለ


ደርሰውበታል ሕይወታቸውን ሙሉም በእያንዳንዱ መስክ ብዙ አንብበዋል።

በውይይታችን ወቅት እየፃፉ ያሉት "ከሕይወት አመለካከታቸው"ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣እንደ


ችሎታቸው "ያገኙትን ይሞነጫጭራሉ"።መፃፍ ሲጀምሩ ያለ ጥልቅ ማሰላሰል የነበረ ቢሆንም
እየበሰሉ ሲመጡ ከግላዊ ፍላጎታቸው፣ አለምን ከሚመለከቱበት መነጽር አንፃር መፃፋቸው
እየበረታ መጣ።መጀመሪያ የሚጽፉት ያለምንም ፍልስፍናዊ ደጀን ወይም እውቀት የነበረ ቢሆንም፣
ኋላ ግን አዎንታዊ አመለካከት እያዳበሩ በመምጣታቸው፣ ለአንባቢዎቻቸው ማለት የፈለጉትን
መንፈስ ለማስረጽ ፈለጉ።

ከኮሌጅ ጊዜያቸው "የግል" ትዝታዎቻቸው መሐል የክርክር ክበብ አባል መሆናቸው፣ የቅርጫት
ኳስ መጫወታቸው(በረዥም ቁመታቸው ምክንያት እና ምንም እንኳን "ሶፍትቦል" መጫወት
የበለጠ ቢወዱም፤የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ እግር ኳስ መጫወታቸው ይገኝበታል)።
ከልጅነታቸው ጀምሮ ዋና በጣም ይወዱ ነበር።ኮሌጅ እያሉ በጣም ይመገባሉ፤ጓደኞቻቸው
ከሚበሉት እጥፍ ያሻምዱ ነበር። ዳንስም ይወዳሉ“በዳንስ አብጃለሁ ―ነፃነትን ይሰጠኝ ነበር
መሰለኝ”ይላሉ።ደግሞም ከጓደኞቻቸው ጋር "ሁሉንም ዐይነት መጥፎ የሚባሉ ድርጊቶች"
ይፈጽሙ ነበር፤ምሳሌ በአዲስ አበባ ዝነኛው የቀይ መብራት ሰፈር፣ውቤ በረሀ ወርደው ሴተኛ
አዳሪዎችንመጎብኘት የመሳሰሉት፤ከነዚህ ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ጥሩ ትዝታዎች አሏቸው ምክንያቱም
መልካም ሰዎች ነበሩ፤ደግሞም “በጣም ይወዱን ብሎም ያፈቅሩን ነበር” ብለዋል፤ታዲያ ይህ
አመለካከታቸው ከአውሮፓ እና አሜሪካ ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ኋላ ከነበራቸው ልምድ ጋር
ተጣርሶባቸዋል። ደግሞ በሌላ ጊዜ ለተማሪዎች ህብረት ፀሐፊነት ቢወዳደሩም፣ኋላ ላይ በካናዳ
ፕሮፌሰር በሆኑትና "አክራሪ" የፖለቲካ አመለካከት በነበራቸው ሐጎስ ገብረእየሱስ ተሸንፈዋል።
ሳህለሥላሴ አላገቡም፤ነገር ግን ፍቅር ይዟቸው ያውቃል። ኮሌጅ እያሉ ገና ስምንተኛ ክፍል
በነበረች ልጅ ፍቅር ከንፈው ነበር።ገና እንዳይዋትት ነበር የወደዷት፤ጠንካራ ዱካ ጥሎ ያለፈ
364
ጥቋቁር አናብስት

አጋጣሚ ነበር።ምንም እንኳን ልጅቷ መልሳ ባትወዳቸውም፣ጠብ ያለላቸውም ነገር ባይኖር፣


በጊዜው "ከባድ ሥነ ልቦናዊ ተጽእኖ" አሳድሮባቸዋል። ከልጅቷ ጋር ተገናኝተው አውርተው
እንኳን አያውቁም፤ምክንያቱም "ልጅቷ ሁልጊዜ በተቆጣጣሪዋ እንደታጀበች ነበር"፤በመጨረሻ ግን
ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ስትመለስ ጠብቀው ሊያናግሯት ቻሉ።የመጀመሪያ ፍቅራቸው ነበረች ፤
እናም የፍቅር ስሜቱን ቢወዱትም፣ "ስቃዩን" ግን ጠሉት፤ስለዚህ በእርሳቸው ላይ "አዎንታዊም፣
አሉታዊም ተጽእኖ "ነበረው።ለምን እንዳፈቀሯት ባያውቁም ቅሉጥልቅ ስሜቱ ግን ተሰምቷቸዋል።
በጊዜው "ኩሩ እና እብሪተኛ" ስለነበሩ፣ ከልጅቷ ጋር ምንም ባለመፈጠሩ ተጎድተው ነበር።

***

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ዲግሪያቸውን ከተቀበሉ ከሁለት ወር በኋላ ወደ ፈረንሳይ አቀኑ።
ማጥናት የፈለጉት የፖለቲካ ሳይንስን ቢሆንም ይሄ ምርጫ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያስደስት
አልነበረም፤ስለዚህ ኮሌጅ አብረዋቸው የነበሩት አብዛኛዎቹ ጓደኞቻቸው በውጪ ሀገራት ነፃ
የትምህርት እድል ሲያገኙ እሳቸው ምንም ሳያገኙ ቀሩ። ምክትል የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት
እንዳልካቸው መኮንን (የደራሲውና ፖለቲከኛው ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ልጅ)
በሣህለሥላሴ ምርጫ ተሳለቁ። "ከዚህ ሁሉ ለፓርላማ ለምን አትወዳደርም?" ብለው
ስላላገጡባቸው ሳህለሥላሴ በፖለቲካ ሳይንስ ምንም ነፃ የትምህርት እድል ሳያገኙ ቀሩ። ይሁን
እንጂ ከዚያ በኋላ አንድ ፈረንሳያዊ መምህር አዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኢምባሲ
ተሯርጠው በፈረንሳይ ህግ ማጥናት የሚያስችላቸውን ነፃ የትምህርት እድል አገኙላቸው።ስለዚህ
በመስከረም 1952 ዓ.ም እርሳቸው እና ሌሎች ጥቂት ተማሪዎች እድሉን በመጠቀም ወደ ፈረንሳይ
አቀኑ። በዚህ ወቅት በሳህለሥላሴ ሕይወት አንድ ለውጥ ተከሰተ።እንዳልካቸው መኮንን
ጥያቄያቸውን አጣጥለው ስለሳቁባቸው የመኳንንትን ዘር አምርረው ጠሉ፤የገዢው መደብ አባል
ቢሆኑ ኖሮ እንደዚያ እንደማይሳቅባቸው እርግጠኛ ነበሩ።

በመጀመሪያ በፈረንሳይ ግሬኖብል የፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሁለት ወር ተማሩ። በኋላ


በኤክስ―ኤን―ፕሮቫንስ የሕግ ትምህርታቸውን ጀመሩ። በፈረንሳይ የህግ ትምህርታቸው
እጅግም ውጤታማ አልነበሩም፤ ምንም በሌሎቹ ቢያልፉም፣ በሮማውያን ህግና ሌላ አንድ
ትምህርታቸው ወደቁ። እነዚህን ሁሉ ትምህርት መስኮች በፈረንሳይኛ መማራቸው ለመውደቃቸው
ምክንያት እንደነበረ ይገምታሉ፤ነገር ግን የወደቁባቸውን የትምህርት ዐይነቶች ደግሞ ለመውሰድ
አሻፈረኝ አሉ። በምትኩ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሄደው የፖለቲካ ሳይንስን ለማጥናት ፈለጉ።

በትምህርት ቢወድቁም፣ሳህለሥላሴ በዚህ የአንድ ዓመት ተኩል የፈረንሳይ ቆይታቸው ብዙ


ተምረዋል።ፈረንሳዮችን በሰብአዊነታቸው ያደንቋቸዋል።በፈረንሳይ የዘረኝነት አድልኦ ደርሶባቸው
365
ጥቋቁር አናብስት

አያውቅም፤የፈረንሳይ ባህልም ያስደንቃቸው ነበር።የፈረንሳይ ሥነ-ጽሑፍን አግበስብሰው


በማንበባቸው፣ አዲስ አድማስ ከፈተላቸው።The Moral and Philosophical
Discourses of Epictetus የተሰኘውን መጽሀፍ ያገኙትም እዚሁ ፈረንሳይ ነው።መጽሐፉን
ያገኙበት ታሪክም እንደሚከተለው ነው፦ሳህለሥላሴ የሥነ-ልቦና ነፃነት ስለማይሰማቸው ከነፃ
ትምህርቱ ሚጢጢ ድርጎ፣ከምግብ በጀታቸው ላይ ቀንሰው "ሜቶድ ቦርባ" የተሰኘ የሥነ ልቦና
ትምህርት በርቀት ይከታተሉ ነበር። በትምህርታቸው መሐል እያሉ ይህንን የኤፒክቲተስ መጽሐፍ
ከመደበኛ የሥነ ልቦና ማስተማሪያ መጽሐፍት ይልቅ ይሻላቸዋል ብለው ላኩላቸው፤እናም ልክ
ነበሩ።አሁንም በይዞታቸው ስር እንደሆነና ደጋግመው እንደሚያነቡት የነገሩኝን ይህንን መጽሐፍ
ካገኙ በኋላ፣የሥነ ልቦና ትምህርቱ እንደማያስፈልጋቸው ተረድተው መውሰዱን ተዉት።

በፈረንሳይ ሳርትርና ካሙን በብዛት አነበቡ። ሳርትር የካሙን ሞት አስመልክተው ሞቱ


“ትርጉምየለሽ” መሆኑን የገለፁበትን መጣጥፍ አንብበው አስደነቃቸው። ገና በአስራስምንት አመቷ
ታዋቂ የሆነችው ፍራንሷ ሳጋንንም አነበቡ። የስቶይክ ፍልስፍናን ከማንበባቸው ባሻገር፣ሙዝየምና
ጋለሪዎችን ጎብኝተዋል "ብዙ ነገር የማወቅ ጉጉት" ነበራቸው። ከዚያ አሁንም ድረስ የሚያደንቁትን
ጋንዲን አነበቡ፤ ሰብአዊ ፍልስፍና የሆነው ሰላማዊ ተቃውሞአቸው እንደማረካቸው አይደብቁም።
(በርትራንድ ራስልም ተጽእኖ እንዳሳረፈባቸው አልሸሽጉም።ያ ግን ገና በኋላ ላይ ነው፤ወደ ሰሜን
አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት አያውቁትም)

አንዴ ማርሴይ እያሉ ወደሻቱ ዲፍ የሚደረግ ጉዞ ሲተዋወቅ ሲሰሙ፣ ስለ ቦታው በመጽሐፍ


ስላነበቡ ብቻ ዘለው መርከብ ላይ ወጡ6፤ከዚያ ጉብኝታቸው የሰበሰቧቸው ጠጠሮች አሁንም
አብረዋቸው አሉ። ሌላ ፈረንሳይን "በፍቅር"እንዲያስታውሱ የሚያደርጋቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ
ገና ተማሪ ሳሉ ያነበቧቸው እንደ አሌክሳንደር ዱማ (The Three Musketeers የተሰኘውን
ልብወለዱን በፍቅር ይወዱታል) ያሉ ደራሲዎች ነበሩ።

ሳህለሥላሴ በዚህ ወቅት ዝንባሌያቸው ስራ መስራትና ያሻቸውን ማንበብ እንጂ የክፍል ፈተናዎችን
ማለፍ አልነበረም፦ የዩኒቨርስቲ የመማሪያ መጽሐፍትን አሁን ድረስ ይጠላሉ። ይህ የማንበብ
ፍላጎት ሳይቀንስ ባይቀርም አሁን በቃለ መጠይቃችን ወቅትራሱ በሰፊው ያነባሉ፤ አሁን በእድሜ
እንደመግፋታቸው፣የበሰሉ፣ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍትን ይመርጣሉ―ደግሞ ተወዳጅ ዘመናዊ
መጽሐፍትን(አጥረው የሚዘጋጁትን ማንበብ ትተዋል)፣እናም "ሁሉንም አቀፍ" መጽሐፍትን፣
ማለትም ሀሳብ፣ ፍልስፍና፣ የራሳቸው ሥነ ጽሑፋዊ ዘዬ እና የአጻጻፍ ተውህቦ ባንድነት ያሏቸው
መጽሐፍት ምርጫዎቻቸው ናቸው። አሁን የመጀመሪያ ምርጫቸው ረዥም ልብወለድ ቢሆንም
366
ጥቋቁር አናብስት

አጭር ልብወለድ፣ወግ፣ሒሳዊ ሥነ ጽሑፍ "እና ሥነ ግጥምን በመጠኑ" ያነባሉ። አንዳንዴ ቲያትር


ቤት ቢሄዱም "ጉጉታቸው ያን ያህል የበረታ" አይደለም።

ፈረንሳይ ውስጥ/እያሉሥነ ጽሑፍ የምታጠና ፈረንሳዊት ፍቅረኛ ነበረቻቸው። አንድ ቀን


ከኢትዮጵያ ውጪ የሚታወቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲ መኖሩን ጠየቀቻቸው፤ነገር ግን መልስ ሊሰጧት
ስላልቻሉ ሃፍረት ጠቅ አደረጋቸው―አንድም አያውቁም ነበርና።ምንም እንኳን የአፈወርቅ
ገብረእየሱስን “ጦቢያ” በማባዣ ተባዝቶ ቢያነቡትም፣እንዲሁም የከበደ ሚካኤል ግጥሞችን
አጥንተው በቃል ቢያውቋቸውም፣ኢትዮጵያዊ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች የአማርኛ ሥነ ጽሑፍን
ወይም ኢትዮጵያዊ ደራሲዎችን እንዲያነቡ አይበረታቱም። ፤ይህ ሁሉ ግን የአማርኛ ትምህርት
ማሟያ ብቻ ነበር፤የፍቅረኛቸው ያልተመለሰ ጥያቄ―ከኢትዮጵያ ውጪ የሚታወቅ ኢትዮጵያዊ
ደራሲ መኖር አለመኖሩ―አብሯቸውከመቅረቱ ባሻገር በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲጽፉ ተጽእኖ
ሳያሳድርባቸው አልቀረም።

ሳህለሥላሴ ወደ ፈረንሳይ የሄዱት በዚያው ወደ አሜሪካ የመሻገር ምኞት ስለነበራቸው ነው። በዚህ
ወቅት ዝነኛው የኢትዮጵያ ቋንቋ አጥኚ ዎልፍ ሌስላው ረዷቸው።ሳህለሥላሴ ሌስላውን
የሚያውቋቸው ገና እምድብር እያሉ እሳቸው እና የክፍል ጓደኞቻቸው እያንዳንዳቸው
አስርየጉራግኛ ቋንቋ ምሳሌያዊ አነጋገሮችንእንዲሰበስቡ በጠየቋቸው ጊዜ ነው―ለዚህ ጥረታቸው
ልጆቹ የየራሳቸውን ፎቶግራፍ ተሸልመዋል።በኋላም ሌስላው ሳህለሥላሴን በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ
ሲያገኟቸው ስለ ጉራግኛ ቋንቋ "ያልጠየቋቸው ጥያቄ" አልነበረም። በኋላ እዚያው በአዲስአበባ
ኮሌጅ ውስጥ እያሉ ሳህለሥላሴ ለሌስላው በፖለቲካ ሳይንስ የነፃ ትምህርት እድል ያገኙ ዘንድ
እንዲረዷቸው ሲጽፉላቸው፣ ሌስላው ይህ በስድስት ወር ሊሳካ ይችላል ብለው
መለሱላቸው―ይህንን በልባቸው ይዘው ወደ ፈረንሳይ ተሻገሩ።ፈረንሳይ እያሉ በደብዳቤ
መገናኘታቸውን ቀጥለው፣ በመጨረሻ በቆይታቸው ማብቂያ ሌስላው ነፃ የትምህርት እድሉን
እንዳገኙላቸው ነገሯቸው። ከዚያም ፓሪስ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመሄድ
ፓስፖርታቸው የአሜሪካ ቪዛ ለማስመታት እንዲቻል ተደርጎ እንዲስተካከል ቢጠይቁ አምባሳደሩ
አካለወርቅ ሀብተወልድ ወደ ውጪ የመጣኸው ህግ እንጂ ፖለቲካ ሳይንስ ለማጥናት አይደለም
በማለት ከለከሏቸው።ይህ የሆነው ከ1953ቱ ያልተሳካው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ በፊት
ነበር። በዚህ ሙከራ ወቅት፣የአምባሳደሩ ወንድም መኮንን ሀብተወልድ በመሞታቸው፣ አምባሳደሩ
ለቀብር ወደ አዲስአበባ ሄዱ። ሳህለሥላሴ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም፣ ዳግመኛ ወደ ፓሪስ
አቅንተው (ይህንን ጉዞ ለማድረግ ገንዘብ መበደር ጭምር አስፈልጓቸው ነበር)ሁለተኛ ጸሐፊውን
ቢያገኙት በትህትና ከማስተናገዱም በላይ ወደ አንደኛ ፀሐፊው ሄዶ ፓስፖርቱ ተስተካከለላቸው፡፡
―ነገር ግን ከአምባሳደሩ ፍቃድ ውጪ በመሆኑ በሚስጥር እንዲይዙት ተነገራቸው። ሳህለሥላሴ

367
ጥቋቁር አናብስት

ፓስፖርታቸው በመስተካከሉ በጣም ደስተኛ ሆኑ፤ምክንያቱም ቪዛውን አግኝተው ወደ ሰሜን


አሜሪካ ለመሄድ አለዚያ ግን "ሁከት ቢጤ ለመፍጠር " ቁርጥ ውሳኔ አድርገው ስለነበረ ነው።

ከዚያም ሳህለሥላሴ ወደ ካሊፎርኒያ ሄደው፣ በካሊፎርኒያ የሎስአንጀለስ ዩኒቨርሲቲ(UCLA)


ፖለቲካ ሳይንስን ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ አጠኑ። ነፃ የትምህርት እድሉ ለአንድ ሴሚስተር ብቻ
የነበር ቢሆንም የተቀረውን ጊዜ ባገኙት መጠነኛ ድጎማና ለሌስላው እየሰሩ በሚያገኙትገቢ
ሸፈኑት። ወደ ኢትዮጵያ በ1955 ዓ.ም ከመመለሳቸው በፊት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አገኙ―እኔ
ከኢትዮጵያ እስከወጣሁበት 1981 ዓ.ም ድረስ ወደውጭ አገር አጭር ጉብኝት ከማድረጋቸው
በስተቀር በሃገራቸው ይኖሩ እና ይሰሩ ነበር።ነገር ግን ዲግሪያቸውን ባገኙበት የፖለቲካ ሳይንስ
ብዙም አልሰሩም።

አሜሪካ እያሉ The Bland of Noble Wood የሚል፤በአፍሪካዊ ፀሐፊ በእንግሊዘኛተጽፎ


ያነበቡት የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ነበር። የጋዜጠኝነትን የአጻጻፍ ዘዬ የተከተለ ነው ብለው
አስበዋል። ሳህለሥላሴ ይህንን መጽሐፍ ካነበቡ በኋላ መጽሐፍ መፃፍ እችል ይሆን ብለው
እራሳቸውን ጠየቁ። ከዚያም ሌስላው ስለ ጉራጌዎች የዕለተለትሕይወት በጉራግኛ እንዲጽፉ
ጠየቋቸው። ምንም የሚያመሳክሩበት የጉራግኛ መጽሐፍ ሳይኖራቸው፣በክረምት እረፍታቸው፣
በቀን አንድ ወይም ሁለት ገጽ የሚችሉትን ያህል አሳምረው ፃፉ።የዚህ ጥረታቸው ፍሬ "የሺነጋ
ቃያ" ("የሺነጋ መንደር") የሚል መጽሀፍ ሆነ። የተፃፈው ለፕሮፌሰር ሌስላው ነበር። በሳህለሥላሴ
እርዳታ ሌስላው መጽሐፉን በቀጥታ ትርጉም ወደ እንግሊዝኛ መለሱት፤ሌስላውም ሳህለሥላሴ
ሳያውቁ ትርጉሙን ለካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ አሳዩት፤እነርሱም ቃል በቃል ሳይሆን በነፃ
ትርጉም እንዲታተም ፈቀዱ። ሳህለሥላሴም ከአርታኢ ጋር በመሆን ነፃ ትርጉሙን አዘጋጁ።
ለህትመት የሚበቃ ነገር መፃፋቸውን ማመን አልቻሉም።ይህ አጋጣሚ በሕይወታቸው ወሳኝ
ለውጥ ፈጠረ።ፍላጎታቸው ተነቃቅቶ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው መጽሐፍ መፃፍ አይችሉ እንደሁ
ጠየቁ።ስለ አጻጻፍ ዘዴ የሚያወራ መጽሐፍ አላነበቡም ወይም ትምህርት አልወሰዱም፤
በደመነፍሳቸው እየተመሩ፣ ስሜታቸውን እየተከተሉ ይህንን መጽሐፍ ለሌስላኡ ከፃፉ በኋላ
ተነባቢ መጽሐፍ ወጣው ይላሉ። ምንም እንኳን በቃለ መጠይቃችን ወቅት ራሳቸውን እንደ "ሙሉ
ደራሲ" ባይቆጥሩትም፣ ይህ አጋጣሚ ሳህለሥላሴን አስፈንጥሮ እስከ አሁን ድረስ ወደሚጓዙበት
የሥነ ጽሑፍ አውራጎዳና መራቸው።አሁንም በውስጣቸው በምሉእነት እና በነፃነት ሊገልፃቸው
ያልቻሏቸው ነገሮች እንዳሉ ይሰማቸዋል።

***

368
ጥቋቁር አናብስት

ወደ ኢትዮጵያ በ1955 ከተመለሱ በኋላ በHVA ኢትዮጵያ(ኋላ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን)


የበጎ አድራጎትና የማስታወቅያ ስራ ("በብዛት የህዝብ ግንኙነት ስራ") ከአዲስ አበባ በስተደቡብ
85 ኪሜ በምትርቀው እና ለናዝሬት ቅርብ በሆነችው ወንጂ ከተማ አገኙ።በዚያም ለሰራተኞቹ
"ዜና ሸንኮራ" የሚል ጋዜጣ ማዘጋጀት በመጀመራቸው በዚሁ ስራ ተጠመዱ። ይህንን ጋዜጣ
ለናዝሬት አካባቢ፣ የማህበረሰብ ጋዜጣ ለማድረግ ቢፈልጉም ይህን የኔዘርላንድና የኢትዮጵያ
ኩባንያ አምስት ዓመት ቆይተው ከለቀቁ በኋላ ጋዜጣውም ተቋረጠ።

ወንጂ እያሉ በሰሜን አሜሪካ ጀምረውት የነበረውን የመጀመሪያ የአማርኛ ልብወለዳቸውን


አጠናቀቁት። "ወጣት ይፍረደው" ብለው የሰየሙት ልብወለድ በደራሲው በቅድሚያ በተከፈለ
ወጪ በ1,500 ቅጂ ተዘጋጀ።“መፃፌን ማቆም አልቻልኩም” የሚሉት ሳህለሥላሴማሳተማቸው
ግን እንደሚፀጽታቸው ይናገራሉ።በመጀመሪያ ቋንቋው ጥሩ አልነበረም፤ይህ ሳያንስ ሳንሱረኞቹ
ቆራርጠው ለወጡት።የፈለጉትን ያህል አልተዋጣላቸውም፤ውጤቱም ያማረ አልነበረም።እንደገና
ጽፈው ሊያሻሽሉት አልፈለጉም፤ምክንያቱም የራሳቸውን አንድስራ ደጋግሞ መስራት አልፈለጉም።

ሳህለሥላሴ በወንጂ ሰፊ "ቁምነገር ያላቸው መጻሕፍትን በሰፊው አንብበዋል። በአፃፃፍ ዘዴዎች


ዙሪያ የሚያተኩሩ መጽሐፍትን ማንበብ የጀመሩት በዚያው ነው―በቃለ መጠይቃችን ወቅት
በዚህ ርእስ ዙሪያ ከ40 ያላነሱ መጽሐፍት ሰብስበዋል።"ከመጽሐፍት ጀርባ ስላለው ፍልስፍና"
ማጥናትና መረዳት የጀመሩትም ያኔ ነው። ወንጂ በቆዩበት አምስት ዓመት ውስጥ የንባብ
ጥማቸውን ማርካት ችለው ነበር። እዚያው ሳሉ ለ"ኢትዮጵያን ሔራልድ" አንድ መጣጥፍ ልከው
ቢታተምላቸውም አሁን ርእሱንም ሆነ ጭብጡን አያስታውሱትም።

ወንጂ ለሥራ ጥሩ ቢሆንም፣የተገለለ ስፍራ በመሆኑ ጸሐፊን የሚያነቃቃ አይደለም። ከመነሻው


የመንግስት ሰራተኛ ለመሆንፈልገው የነበረ ቢሆንም፣ነገሩ ቀላል አልሆነላቸውም። ሁለተኛ ዲግሪ
ስላላቸው የ550 ብር ደሞዝ ማግኘት ቢገባቸውም፣ከመጀመሪያ ባለዲግሪዎች እኩል የ450 ብር
ደሞዝእየተከፈላቸውይሰሩ እንደሁ ተጠይቀው ነበር።ምናልባት መንግስት የተማሩትን የፖለቲካ
ሳይንስ ትምህርት አልወደደው ይሆናል፤ምናልባት እንደ ተራማጅ ተቆጥረው ይሆናል፤ በመንግስት
"የጥቁር መዝገብ" ውስጥ ሳልኖርበት አልቀርም ብለው ያስባሉ። ከሰሜን አሜሪካ ለመመለስ
ሲዘጋጁ የመልስ ጉዞውን ወጪ መንግሥት አልከፍልም ብሎ፣ የአሜሪካ መንግስት በበኩሉ
አስገድዶ እንደሚልካቸው ሲያስፈራራቸው ቆይቶ ከአራት ወራት በኋላ በመጨረሻ የኢትዮጵያ
መንግሥት ትኬት ላከላቸው። ሳህለሥላሴ በዚህ ምሬት ተሰምቷቸው ነበር። ሕይወታቸውን
ለማቆየት ከጓደኛቸው ከሐይሉ ፉላስ(በቃለመጠይቃችን ወቅት በአሜሪካ ፕሮፌሰር የነበሩ) 100$

369
ጥቋቁር አናብስት

መበደር ነበረባቸው―ይቺም ቶሎ አለቀች።ሲመለሱ ወንጂ የስኳር ኩባንያ ውስጥ በመቀጠራቸው


መንግሥት ሁለተኛ ዲግሪ ላላቸው ተመራቂዎች ከሚከፍለው የተሻለ ደሞዝ ተከፋይ ሆኑ።

"The Afersata" የተሰኘውን የመጀመሪያ የእንግሊዝኛ ልብወለዳቸውን መፃፍ የጀመሩትም


ወንጂ ሲሆን፣ በ1960 ዓ.ም ለሁለተኛ ቀጣሪዎቻቸው ሚሸል ኮትስ አሰልጣኝ መኮንን ሆነው
በሚሰሩበት ጊዜ ታተመ። ይህንን መጽሐፍ በእንግሊዝኛ የፃፉት የአማርኛ መጽሐፍት የሚያልፉበት
የሳንሱር ሂደት ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ እና እንዳሰቡት ሳይሆን በመቅረቱ ነበር። የአፍሪካ
ደራሲዎች በእንግሊዝኛ የሚጽፏቸው መጽሐፍት ስላስደነቋቸው፣ በመስኩ የሚችሉትን ያህል
እያሳደዱ አንብበዋል። ከዚያም በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ጓደኛቸው እንግሊዝ ውስጥ
የአፍሪካንሥነ ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያሳትሙ አሳታሚዎች መኖራቸውን ፃፉላቸው።
"The Afersata" በ1960 እንደተጠናቀቀ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማሳተም አስበው የሳንሱር ክፍል
ዋና ሃላፊውን ሲያነጋግሩት በአማርኛ አለመፃፉ አስከፋው፤ይሁን እንጂ ስለህትመቱ በአንድ ወር
ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ላይ እንደሚደርሱ አስታወቋቸው።ነገር ግን ሳህለሥላሴ በሳንሱር ክፍል ውስጥ
ለሚሰራ ጓደኛቸው መጽሐፉን ቢሰጡት፣ ይህንን መጽሐፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማሳተም መሞከር
ከንቱ እንደሆነገለፀላቸው―ሳንሱር አድራጊዎቹ አያሳልፉትም።ስለዚህ ሳህለሥላሴ መጽሀፉን
የአፍሪካ ጸሐፍትን ለሚያሳትመው ሔይንማን አሳታሚዎች ልከውላቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ከትንሽ የአርትኦት ማሻሻያ ጋር መታተም እንደሚችል ገልፀው መልሰው ፃፉላቸው።አርትኦቱን
በሔይንማን አሳሳቢነት የሰራው በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የሚሰራ እንግሊዛዊ ሲሆን
ሳህለሥላሴ አንዳንዶቹን ማስተካከያዎች ሲቀበሉ ሌሎችን ውድቅ አድርገዋል። መጽሐፉም ተጠናቆ
ለሔይንማን በተላከ በዓመቱ በ1961 ዓ.ም ታተመ።

በዚህ ወቅት ሳህለሥላሴ ሶስት መጽሐፍትን በሶስት ቋንቋዎች ጽፈዋል፦ "የሺነጋ መንደር" በአፍ
መፍቻቸው በጉራግኛ (ኋላ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ የታተመ)፣ "ወጣት ይፍረደው" በአማርኛ
እንዲሁም "አፈርሳታ" በእንግሊዝኛ። እነዚህን ሶስት መጽሀፍት "እንደሙከራ" ይቆጥሯቸዋል።
ከዚህ ሁሉ በኋላም እንደ ደራሲእንዴት መቀጠል እንዳለባቸው አያውቁም። "የመጻፍ ዝንባሌ"
በውስጣቸው እንዳለ በደመነፍስ ቢያውቁም በአፃፃፍ ዘዴና ቋንቋ ገና ሙከራ እያደረጉ ነበር።
ከመጀመሪያ መጽሐፋቸው በኋላ በጉራግኛ ለመፃፍ አልሞከሩም ፤ ለዚህም በቂ ምክንያት አለኝ
ብለው ያስባሉ ፦አንደኛ አንባቢዎቹ በጣም ጥቂት ናቸው (ምንም እንኳን በመላ ሐገሪቱ ከ1.5
ሚሊዮን ጉራጌዎች በላይ ቢኖሩም)፣ ይሸጣል ብሎ ስለማይገምት የትኛውም አሳታሚ በጉራግኛ
ለማተም አይደፍርም፣ ከ1966 አብዮት በፊት አማርኛ ብቸኛው የመፃፊያ ቋንቋ ተደርጎ
ስለሚወሰድ ሳንሱር ክፍሎች የጉራግኛ መጽሀፍ ሐሳቡራሱ ሳያስቃቸው አይቀርም።በነዚህ

370
ጥቋቁር አናብስት

ምክንያቶች ዳግመኛ በጉራግኛ ለመፃፍ ብእሩን ማንሳት አልተከሰተላቸውም፤ነገር ግን


እስከሚያውቁት ድረስ ሌላ ፀሐፊ በጉራግኛ ባለመፃፉ እና የመጀመሪያ መጽሐፋቸው በቋንቋቸው
በመሆኑ ደስተኛ ናቸው። የጉራጌዎች ሥነ –ቃል ብቻ ነበር ያላቸው፤ነገር ግን የህዝቡ ቁጥር
ሲጨምር፣ ትምህርት ሲስፋፋ፣ ወደፊት ለጉራጌ ጸሐፊዎች ገበያ ይኖራል ብለው ያስባሉ። ሌሎች
በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እየፃፉ "ቋንቋውን ያራምዱታል" የሚል ተስፋ አላቸው።

"የሺነጋ መንደር" በ1956 በ5,000 ቅጂዎች ታትሞ፣በሙሉ ተሽጦ ቢያልቅም ዳግም


አልታተመም። ብዙ አስተያየቶች የተሰጡበት ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ጥሩ አስተያየቶች ናቸው።
"ወጣት ይፍረደው" በ1,500 ቅጂዎች ታትሞ በደንብ ካለመሸጡም በላይ ጥሩ ተቀባይነት
አላገኘም። "አፈርሳታ" ሁለት ጊዜ ታትሞ 15,000 ቅጂዎች ተሽጠውለታል።"አፈርሳታ" ከሶስቱ
መጽሐፍት የበለጠ ቢሸጥም ከ"ሺነጋ መንደር" የበለጠ ትችት አጋጥሞታል። አንዳንድ ሂሰኞች
የመሬት ይዞታ ለውጥን የተመለከተ የፖለቲካ ክርክር በልብወለድ ውስጥ ቦታ የለውም ብለው
ጽፈዋል። ሌሎች የአጻጻፍ ስልቱን ድክመቶች ነቅሰው አውጥተዋል። ሳህለሥላሴ አንዳንድ ሂሰኞች
ጠቃሚ ነጥብ እንዳነሱ ቢሰማቸውም፣ሌሎች ግን ምክንያታዊ ባለመሆናቸው እና ሀሳባቸውን
ስላላገኙት ቅሬታ አድሮባቸዋል፤ነገር ግን ለትችቶቹ መልስ ሰጥተው አያውቁም። በጣም
የተማሩባቸውን ጠቃሚ አስተያየቶች ያገኙት፣ገና መጽሐፉ ከመታተሙ በፊት ረቂቁን ከሚያነቡት
የአሳታሚዎቹ ሠራተኞች ነው።ሔይንማንን ለበሳል አመራራቸው፣የያኔው አርታኢአቸውን ጀምስ
ከሬን ደግሞ ለቴክኒካል ድጋፋቸው ያመሰግናሉ። ከነዚህ የተማሩት ትምህርት ከመጽሀፍት
ካነበቧቸው ወይም መጽሀፉ ከታተመ በኋላ ከሀያስያን ካገኟቸው አስተያየቶች ይልቃል።

በእንግሊዝኛ ሲጽፉ አንዳንዴ የሀገራቸውን"ባህላዊ እሴቶች" ለመግለጽ ይከብዳቸው ወይም


ይቸግራቸው ነበር፤ነገር ግን እነዚህ እሴቶች የግድ መገለጽ ነበረባቸው ፤አለበለዚያ ግን መጽሐፉን
አንባቢዎች ሊረዱት አይችሉም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝኛ ለመፃፍ አሁንም በቂ
ምክንያት አላቸው ብለው ያስባሉ። አማርኛ መጽሀፍት መታተም የሚችሉት በኢትዮጵያ ብቻ ነው
፤እዚህ ከታገዱ ደግሞ ሳይታተሙ ይቀራሉ። ነገር ግን በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሀፍ በኢትዮጵያ
ቢታገድም ከሀገር ውጪ ገበያ ይኖረዋል። በተጨማሪም ሳህለሥላሴ እንደሚሉት እሳቸው ራሳቸው
ስለኢትዮጵያ ያላቸውን እውቀት ያገኙት በውጪ ፀሐፍት የተፃፉ የእንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ
መጽሐፍትን በማንበብ ነው። ኢትዮጵያውያንም ስለራሳቸው ለውጪዎቹ የሚሆን እውቀት
ማዋጣት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፤ በተጨማሪም የተማሩ ኢትዮጵያዊያን እንግሊዝኛን
ስለሚረዱ፣ በእንግሊዝኛ ቢጻፍ ኢትዮጵያውያንንም ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ አንባብያንንም መድረስ
ይችላል።ሳህለሥላሴ አንድ መጽሐፍ ጨርሰው ገበያ ላይ ሲውል ትልቅ ደስታ ይሰማቸዋል፤ያ
ደስታም መጽሀፍ እንደመፃፍ ላለ ከባድ ስራ ተገቢ ሽልማት እንደሆነ ይሰማቸዋል።ነገር ግን አንድ
መጽሐፋቸው ለገበያ እንደበቃ ቀጥለው ስለሚጽፉት መጽሐፍ ማሰብ ይጀምራሉ።ትልቁ
371
ጥቋቁር አናብስት

ችግራቸው ለመፃፊያ የሚሆን ርእስ ማግኘት ነው።መጽሐፍ ሲያነቡ አንድ ሐሳብ ካገኙ ማስታወሻ
ይይዛሉ። ከሚያዘወትሩበት መጠጥ ቤት ፊትለፊት መኪናቸው ውስጥ ብቻቸውን ቁጭ ብለው
ሲጠጡ ብዙ ጊዜ ሐሳብ ይመጣላቸዋል።9 በዚህ መንገድ ሁለት መጽሐፍት "በሃሳባቸው"
ጽፈዋል፤—የሁለት መጽሐፍት ሴራ፣ ቅርጽና አርእስት በዚህ በሚወዱት መጠጥ ቤት ፊት ለፊት
መኪናቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ተከስተውላቸዋል።በሌላ በኩል፣ምንም እንኳን ባህላዊውን
የምርመራ መንገድ "አፈርሳታን" በተመለከተ በመጽሐፉ ከአንድ አንቀጽ በላይ ባይጠቀስም፣
ለ"አፈርሳታ" የሚሆነውን መነሻ ሀሳብ እና ርእስ ያገኙት በማህተመሥላሴ ወልደመስቀል በተፃፈው
"ዝክረ ነገር" ከተሰኘ ዝነኛ መጽሐፍ ነው።ሐሳቡ በአእምሮአቸው ስር ከሰደደ በኋላ በጉዳዩላይ ገፀ
ባህሪያቱንና ሴራውን ለማበልፀግ የሚያስችላቸውን ሰፊ ምርምር እና ጥናት አደረጉ።ያኔ ነው ቁጭ
ብለው ለልብወለዱ ቅርጽ ለመስጠትዝግጁ የሆኑት።

ቀጥለው የፃፉት መጽሀፍ Warrior Kingን ሲሆን ይህንን መፃፍ የጀመሩት The Afersataን
ከጨረሱ በግምት ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።በመሀሉ አጫጭር መጣጥፎችንና የመጽሐፍት
ቅኝቶችን ጽፈዋል።“ምንም እንኳን በኋላ ወርውሬ ብጥለውም፣ ብቀዳድደውም፣ ሁሌም የሆነ ነገር
መፃፍ አለብኝ” ይላሉ። በዚህ መሰረት የሐዲስ አለማየሁ10 "ፍቅር እስከ መቃብር" ላይ ሰፋ ያለ
ቅኝት አደረጉ―ይህንን በማድረግም የመጀመሪያው ናቸው። ከዚያ በኋላ ደግሞ በአፈወርቅ
ገብረእየሱስ "ጦቢያ"11 ላይDialogue ለተሰኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህትመት ሂስ አዘጋጁ።
ገና ወንጂ እያሉ ለአማርኛው እለታዊ ህትመት “አዲስ ዘመን” የፈጠራ ጽሑፍን በተመለከተ አንድ
መጣጥፍ ጽፈዋል።

ሳህለሥላሴ ለ"Warrior King" የሚሆን ሀሳብ ለማግኘት ጥቂት ጊዜ ወስዶባቸዋል።ዳግማዊ


ቴዎድሮስን ከኮሌጅ ዘመናቸው ጀምሮ ከማድነቃቸውም በላይ በርሳቸው ዙሪያ ብዙ መጽሐፍትን
አንብበዋል፤ታዲያ ድንገት አንድ ቀን ሀሳቡ ተከሰተላቸው፦"ለምን በርሳቸው ዙሪያ ታሪካዊ
ልብወለድ አልጽፍም?" ከዚያም መፃፉን ከመጀመራቸው በፊት ሰፋ ያለ ጥናት አደረጉ―
በቴዎድሮስ ዙሪያ የተፃፉ ታሪካዊም፣ልብወለዳዊም መጽሐፍትን አነበቡ። ይህ ብዙ ጊዜ ስለወሰደ
"Warrior King" የተጠናቀቀው "The Afersata" ከታተመ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ልብወለድ ቴዎድሮስ እንዴት ወደ ስልጣን እንደወጡ ብቻ ለመተረክ
ወሥነ ው ይህ ውጤታማ ከሆነ አወዳደቃቸውን በሌላ ልብወለድ ሊመሰሉበት አሰቡ። ምንም
እንኳን የአቤ ጉበኛ "አንድ ለናቱ" ከዚህ ቀድሞ የታተመ ቢሆንም (ሳህለሥላሴም ጥሩ መጽሀፍ
እንደሆነ ያስባሉ) መጽሀፉ ብዙ ቴክኒካል ግድፈቶች ስላሉት እና የማይስማሙባቸው ጉዳዮች

372
ጥቋቁር አናብስት

ስላሉት ተጽእኖ አላሳደረብኝም ይላሉ። ስለዚህ "Warrior King"ን ሲጽፉ ከዚያ በፊት ማንም
ያልተጠቀመውን ሴማ በመምረጥ፣ ወጥ የሆነ ነገር እንደፈጠሩ ነው የሚሰማቸው።

Warrior King ቀደም ብለው እሳቸው ከፃፏቸው መጽሐፍት ሁሉ የላቀ እንደሆነ ይሰማቸዋል።
በሃያሲያን ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት ከማግኘቱም በላይ "በአንድ ዩኒቨርስቲ የወሩ ምርጥ
መጽሐፍ ተብሎ ተመርጧል" የአጻጻፍ ዘዴዎችን የሚመለከቱ መጽሐፍትን ጎንለጎን ማንበባቸው
ተጨምሮ በዚህ መጽሐፍ እንደ ደራሲ መመንደጋቸው ቢሰማቸውም መጽሐፉ እንደ "The
Afersata" በደንብ አልተሸጠም።በእርግጥ በቃለ መጠይቃችን ወቅት አንዴ በድጋሚ ታትሞ
ነበር።ሁለተኛውን የቴዎድሮስ መጽሐፍ በተመለከተ ስለ አወዳደቃቸው "አጭርመጣጥፍ" ጽፈው
ነበር።ነገር ግን ይህ የኢትዮጵያ የታሪክ ወቅት ብዙ የተጠናና የተፃፈበት በመሆኑ፣ወጥ የሆነ ነገር
ማበርከት እንደማይል ተሰምቷቸዋል።በዚህ የተነሳ ለመፃፍ የታቀደው ሁለተኛ መጽሐፍ በጭራሽ
ላይሳካ ይችላል። "Warrior King"ን ከፃፉበኋላ በሳል ደራሲ እየሆኑ መምጣታቸው
ተሰምቷቸው ነበር፤በራስ መተማመናቸውም ጨምሯል።ነገር ግን ያኔም ሆነ አሁንበ1985
"ጥንቅቅያሉደራሲ" እንደሆኑ አይሰማቸውም።

መጽሐፉ የወጣው በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ነበር፤ይሄም በመጀመሪያ ከተፃፈ ከአንድ
ሁለት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው―ይህ የሆነበት ምክንያት አሳታሚው ሔይንማን መጽሐፉን
በአፍሪካ ፀሐፊዎች ተከታታይ መጽሐፍት የሚካተቱት አንዳንድ ነገሮች ከተስተካከሉ በኋላ ነው
በማለታቸው ነበር።በዚህ መሰረት በከፊል በድጋሚ ከተፃፈ በኋላ ተቀባይነትን አግኝቷል።በ1971
ሳህለሥላሴ የሚሼል ኮትስ ኮርፖሬሽንን ለቀው ወጡ። "Warrior King" የተፃፈው በብሔራዊ
ሀብቶች ልማት ኩባንያ ውስጥ የአስተዳደር መኮንን ሆነው እስከ 1974 በሰሩበት ወቅት ሲሆን
በዛው ዓመት በአዲስአበባ የእንግሊዝ ኢምባሲ በአስተርጓሚነት ተቀጠሩ።እስከ 1988
ድረስምሰርተዋል ።ከ1966 ወዲህ ድርሰትን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው አድርገው በዚሁ ለመተዳደር
ያልሙ ነበር።በኢትዮጵያ እስከቆየሁበት እ.ኤ.አ 1989 ድረስ ግን ይህ ህልም እውን አልሆነም።
ነገር ግን የእንግሊዝ ኢምባሲን ከተቀላቀሉ በኋላ ጊዜያቸውን ለፈጠራ በአግባቡ ከመጠቀማቸውም
በላይ "አራት እጥፍ ውጤታማ" ሆነዋል።በእንግሊዝ ኤምባሲ ውስጥ የነበራቸውን ስራ
ወደውታል፤ምክንያቱም ነፃነት ሰጥቷቸዋል፤በተጨማሪ የትርጉሙ ስራ―ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ
እና በተገላቢጦሹ―ከመፃፍ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሚያስደስት ልምድ ሆኖላቸዋል።የመፃፍን
አካላዊም ሆነ የፈጠራ ገጽታውን እንደሚወዱት ይናገራሉ።እስከማውቃቸው ድረስ አላገቡም።

373
ጥቋቁር አናብስት

ይህም ቤታቸው ውስጥ በነፃነት እንዲሰሩ ሰፊ ጊዜ ሰጥቷቸዋል።ቀጣዩ መጽሐፋቸው


"Firebrands" ከሌሎቹ መጽሕፍቶቻቸው ሁሉ የበለጠ ጊዜ ወስዷል።የታተመው በ1979
ነበር።በመጀመሪያ ለሄይንማን አሳታሚ ሁለት የተለያዩ ረቂቆች ንላኩ።ይሁን እንጂ ሁለቱም
ተቀባይነት አላገኙም።ከዚህ በኋላ ሁለቱንም መጽሐፍ አዋህደው ሴራውን እንደ አዲስ አዋቅረው
በድጋሚ ፃፉት፤ሙሉ ለሙሉ አዲስ እና የተለየ መጽሐፍ ነበር።ሔይንማን አሳታሚ አሁንም የዚህ
መጽሐፍ ረቂቅ ደረሳቸው፤ነገርግንከቀደሙት ረቂቆች ጋር ሲወዳደር ፍፁም አዲስ በመሆኑ
አልለዩትም።ይሁን እንጂ አሁንም አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረግ ጠየቁ።ተጨማሪ ማሻሻያዎች
ከተደረጉ በኋላ የሄይንማን አሳታሚ ኤዲ ተርጀምስከሪ እንዲህ ከሚልማስታወሻ ጋር እየተቆጨ
መለሰላቸው፦"ለመታተም የቀረበ፣ያንኑ ያህል ደሞ የራቀ" ማለቱን ሳህለሥላሴ ቃልበቃል
ያስታውሱታል።እንደገና ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ አስተካክለው ከጻፉት ሊቀበሉት እንደሚችሉ ገለፁ፤
ነገር ግን ሳህለሥላሴ ጉልበታቸውን ሁሉ አሟጠው ስለሰሩ እና ቶሎ እንዲታተም ስለፈለጉ ተስፋ
መቁረጥ ጀምረውነበር። "ከ"The Afersata“ በጣም የተሻለ ነበር ነገር ግን ሰዎቹ ሊያሳትሙት
አልፈለጉም!” ከዚህ በኋላ አንድም ቃል ሳይጨምሩ፣ሳይቀንሱ ለሌላ አሳታሚ ለመስጠት ወሰኑ።
ሎንግማን አሳታሚ "Drumbeat" የተሰኘ ተከታታይ ህትመት ስለጀመረ ረቂቁን ለነሱ
ላኩላቸው።ከአምስት ረዣዥም የስቃይ ወራት በኋላ በመጨረሻ ሎንግማን አሳታሚ ያለ ትልቅ
ለውጥ―አምስት ቃላት ብቻ ነው የተቀየሩት―መጽሐፉን ለማሳተም ተስማማ። በተጨማሪ
ከሄይንማን የተሻለ ክፍያ አቅርቦላቸዋል።በጣምተደሰቱ፦ "ያ ደብዳቤ በሕይወቴ ሙሉ ከደረሱኝ
ደብዳቤዎች ሁሉ የላቀ ነው።"Firebrands" በሽያጭም ሆነ በሃያሲያን አስተያየት እጅግ
ስኬታማው መጽሐፋቸው ሆነ።የሃያስያን አቀባበል ጥሩ ነበር ይላሉ።መጽሐፉ በአንድ ወር 3,000
ቅጂ ከመሸጡምበላይእስከ 1985 ድረስ 10,000 ቅጂዎች ተቸብችቧል።በእርግጥ መጽሐፉ
በሀገር ውስጥ እንዲሸጥ አልተፈቀደም፤ይሁን እንጂ በባህርማዶ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል።
አንድ ናይጄሪያዊ ደራሲ ወደ ተውኔት ሊቀይረው ፈልጎ ነበር፤ነገር ግን ሎንግማን አሳታሚ ወደ
ናይጄሪያዊ ቋንቋ ካልተተረጎመ በስተቀር አሻፈረኝ አለ።ስለዚህ ሳይሳካ ቀረ። በሞዛምቢክ ውስጥ
የሚገኝ አንድ አሳታሚ በፖርቱጋልኛ ሊያሳትመው ቢፈልግም ቀብድ ከከፈሉ በኋላ ውሉን
አቋርጠውታል። እነዚህ ሁሉ ፍላጎቶች የስኬቱ ምልክት እንደሆኑ ሳህለሥላሴ ያስባሉ። በ1984
ዚምባቡዌ ውስጥ የተሰራ ቅኝት መጽሐፉ አሁንም ላለ አንባቢ ጠቃሚ መሆኑን ጽፏል―በተለይ
ስለ ሙስና የተፃፈው።በአጠቃላይ ከሁሉም መጽሐፍቶቻቸው የላቀ ተቀባይነት አግኝቷል።

ሳህለ ስላሴ firebrands ን ከ66ቱ አብዮት ጅማሮ በኃላ ነው መጻፍ የጀመሩት፡፡ካልሆነም


በ1965 ዓ.ም አካባቢ ይሆናል፡፡ መጽሐፉ ግን የሚያወራው ከአብዮቱ ሶስት ዓመታት ቀደም ብሎ
ከባተ አንድ ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ያለውን ጊዜያካትታል፡፡
374
ጥቋቁር አናብስት

በወቅቱ አፍሪካ ዳር እስከ ዳር በአብዮት እየታመሰች ነበር፡፡ሳህለስላሴ ግን በወቅቱ በኢትዮጵያ


ውስጥ የተከሰተውን (የተማሪዎችና የምሁራን እንቅስቃሴ)ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል ከጀርባ
ያለውም ገፊ ሃይል እሱ እንደሆነም ነው ምልከታቸው፡፡ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ስለሚደረጉት
የለውጥ እንቅስቃሴዎች ግን የሚያውቁት ምንም ነገር አልነበረም፡፡

"Firebrands"ን ሲጽፉለማሳየትየፈለጉት በዚህ ውስን የታሪክ ወቅትየሐገሪቱንመንፈስምን


እንሚመስል መግለጽ ነው፤ይህ ወቅት የአብዮቱን ማግስት ተከትለው እስከመጡት ለውጦች
ይለጠጣል።መጽሐፉ የታገደው በመጨረሻዎቹ 10 ገጾች ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ብለው
ያስባሉ።በነዛ ገጾች ውስጥ አብዮቱ ገና ሊመጣ እንደሆነ ተጽፏል።አንዳንድ ተንታኞች አብዮቱ
በጀመረ በአንድ ዓመት ማብቃቱንይናገራሉ።ሌሎቹ ደግሞ መጽሐፉ ትሮትስካዊ አመለካከቶችን
ያንፀባርቃል ይላሉ።አንድ አስተያየት ሰጪ በመጽሐፉ ውስጥ የኃይለሥላሴ መንግሥት ያለ ምንም
ደም መፋሰስ እንደ ተገለበጠ መፃፋቸውን ይተቻል―ሳህለሥላሴግን በመጽሐፉ መቼት ምንም
ደም አለመፍሰሱን ይናገራሉ።12እነዚህን ትችቶች የተሳሳቱ፣አስቂኝ ብሎም "የማይረቡ" ሆነው
አግኝተዋቸዋል።

----

ከ FIREBRANDS መታተም በኋላ ሳህለስላሴ ምንም እንኳን በግልጽ ባያሳውቁም እራሳቸውን


እንደ ደራሲ መቁጠር ጀመሩ፡፡ ሰዎች በዚህ ስምም ሲጠሯቸው መሳቀቅ አቆሙ፡፡

ቀጣዩ ስራቸው አጠር ብላ የተዘጋጀችው የቻርልስ ድክንስ A tale of two cities የሁለት
ከተሞች ወግ በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ መመለስ ነው፡፡በአጭሩ የተዘጋጀውን የመጽሐፉን ቅጽ
በትምህርት ቤት ቆይታቸው ያነበቡት ሲሆን ያላጠረውን ሙሉውን ክፍል የኋላኋላ በተደጋጋሚ
አንብበውታል፡፡ ዋናው ገጸባህርይም በአእምሮአቸው ተቀርጾ ቀርቷል፡፡ሃገራቸውም በተመሳሳይ
የአብዮት ጉዞ ላይ በመሆኗ በወቅቱ በአስተርጓሚነት ይሰሩት ከነበረው ስራ በላይ ይሄንን የሚስብ
ሆኖ አግኝተውታል፡፡ ነገር ግን ያለ ጥሩ አሳታሚም እንደማይሰሩት ወሰነው የነበር ቢሆንም
የኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት (ኋላ ወደ ኩራዝ በሄዱት አስፋው ዳምጤ በኩል)ዘላቂነት ያላቸው
የውጪ ስራዎችን የማሳተም ፍላጎቱ እንዳለ ስለተነገራቸው የትርጉም ስራውን መስራት ጀመሩ፡፡

ሳህለስላሴ ብርሃነ ማርያም የመጀመርያው መጽሐፋቸው በአማርኛው በኩል የነበረበትን ጉድለት


ለማካካስ አማርናቸውንም ለማሻሻል ሲሉ ጠንክረው ሰርተዋል ይህ የመጀመርያ መጻሐፋቸውም
ምንም ዐይነት ዳሰሳ አልተደረገለትም፡፡ሰዎችም ለምን በአማርኛ እንደማይጽፉ ይጠይቋቸው ነበር፡፡
የትርጉም ስራ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሆነ ስለሚያምኑ በደስታ ተክለወልድ

375
ጥቋቁር አናብስት

የተዘጋጀውን አዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላትን ገዙ፡፡The tale of two cities መተርጎምም
ጀመሩ፡፡ ጥሩ ተቀባይነትንም አገኘ፡፡ በthe Ethiopian herald ላይም ጥሩ ዳሰሳ ተደረገለት፡፡
ድጋሚ በሌላ ሃገራዊ ዳሰሳ ቢቃኝም ያን ያህል ጥሩ የሚባል ግን አልነበረም፡፡አንድ ጓደኛቸው
ደውሎ በትርጉሙ እንደተደሰተና ጨምረው እንዲሰሩ አንደሚፈልግ ነገራቸው፡፡በኢትዮጵያ
የትርጉም ስራ ውስጥ በብዛት በማቅረብ የሚታወቁት ደራሲ የሚባሉት ማሞ ወድነህ ደውለው
እንኳን ደስ ያለህ አሏቸው፡፡ የኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዳባ ከቢቢሲ
ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለስራው መልካም ጎን እያነሱ አወደሱት፡፡ሌሎችም በበጎ አወሱት፡፡ሳንሱር
አድራጊዎቹም ያለ ምንም ማስተካከያስለተቀበሉላቸው ደስተኛ ሆነዋል፡፡

የሚቀጥለው መጽሐፋቸው "ባሻ ቅጣው" ሌላው የአማርኛ መጽሐፋቸው ቢሆንም መጀመሪያ


የፃፉት በእንግሊዝኛ ነበር።በዚህ ጊዜ ሳህለሥላሴ፣ አፍሪካዊ ደራሲዎች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ
በራሳቸው ቋንቋ መፃፍ አለባቸው ወይስ በውጪ በሚለው ክርክርመሃል ያለውዴታቸው
ተወጥረው ነበር።13 ስለዚህ ጥያቄው ይህንን መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ላሳትመው ወይስ ወደ አማርኛ
ልቀይረው የሚል ነበር። ከገጣሚው እና ፀሐፌ ተውኔቱ መንግስቱ ለማ ጋር በእንግሊዝኛው
“የካቲት” መጽሄት ላይ ግልጽ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በመንግሥቱ ለማ ሀሳብ በመጠኑ
በመስማማታቸው "ባሻ ቅጣውን" ወደ አማርኛ መለሱት። ከዚህም ባሻገር"የሁለት ከተሞች ወግ"
የተሰኘውን የበፊቱን መጽሐፋቸውን በተመለከተ ከሳንሱር ክፍሉ ጋር የነበራቸው መልካም
ግንኙነት፣ መጽሐፉን በአማርኛ ለማውጣት ይበልጥ አበረታታቸው።

ባሻ ቅጣው በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያ መካከል ከ1927–1928 ድረስ ስለነበረው ጦርነትና፣


ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ተይዛ ስለነበረበት ከ1928–1933 ስላለው ጊዜ ታሪክ የሚያወሳ ታሪካዊ
ልብወለድ ነው። ረቂቁ ለሳንሱር ክፍሉ ተሰጥቶ፣ እንዲያሻሽሉ ከተጠየቁት መሐል የሚችሉትን እና
የሚቀበሉትን አሻሽለው ሲያበቁ ሳንሱር ክፍሉ እንዲታተም ፍቃደኛ ሆነ። በደንቡ መሰረት
የሚቀጥለው ተግባር የታተመው መጽሐፍ ለሳንሱር ክፍሉ በድጋሚ ተልኮ እንዲሻሻሉ የጠየቋቸው
ነገሮች ሁሉ መሻሻላቸውን ማረጋገጥ ነው። ደራሲው እና አሳታሚዎቹ ሌላ ችግር ይገጥመናል
ብለው አላሰቡም። የመጽሐፉ ቅጂዎች በብዛት ታትመው ተዘጋጅተዋል። ነገር ግን ነገሮች "ወደ
አልታሰበ አቅጣጫ" መሄድ ጀመሩ። ሳንሱር ክፍሉ ባያግደውም ለሽያጭ መልቀቅን ግን አሻፈረኝ
አለ። ይሄ የሆነው የአብዮቱ አስረኛ ዓመት ሊከበር ሶስት ወር ብቻ ሲቀረው በ1976 ዓ.ም ስለሆነ
ምናልባት የሰዎችን አትኩሮት የሚሰርቅ ሌላ ነገር እንዳይኖር ከመፈለግ የመነጨ ሊሆን ይችላል
ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን ከበአሉም በኋላም ቢሆን መጽሐፉ አልተለቀቀም ―በዚህ
ቃለመጠይቅ ወቅት በ1985ዓ.ም ራሱ መጽሐፉ ለሽያጭ አልዋለም። "ሌሎች ምንም ይበሉ ምን"

376
ጥቋቁር አናብስት

ሳህለሥላሴ ይህን መጽሀፍ ትልቅ ሥነ ጽሑፋዊ ዋጋ ይሰጡታል። ይህ አጋጣሚ የጠበቁት


ባለመሆኑ ቅሬታ አሳደረባቸው፤"በፈጠራ ስሜቴ ላይ የተደፋ ቀዝቃዛ ውሀ" ነው ይላሉ።
መፃፋቸውን ቢቀጥሉም የበፊቱን ያህል አልነበረም።መጽሀፉ ተለቆ ቢሆን ኖሮ፣ በቀድሞው
ፍጥነታቸው በአማርኛ መጻፍ ይቀጥሉ ነበር። አለበለዚያ፣ "አንዳንዶች የአፍሪካ ጸሐፍት
በእንግሊዝኛ ሲጽፉ እውነታን በቀለመ መነጽር እየተመለከቱ ነው ብለው ቢቃወሙም"፣
ፊታቸውን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ አዙረው በዚያ ለመፃፍ ይገደዳሉ።ይህንን የመንግሥቱ ለማ እና
ሌሎችም መከራከሪያ ሀሳብ ሊቀበሉ ይሉና በአማርኛ ማሳተም ከባድና የሚገጥመው ውጣ ውረድ
መገመት የማይቻል ሲሆን አማራጩ ምንድነው? ብለው ይጠይቃሉ።14

ለማንኛውም በቃለመጠይቃችን ወቅት ሳህለሥላሴ የፐርል ኤስ በክ ድርሰት የሆነውን "The


Mother" የተሰኘ መጽሀፍ ተርጉመው ጨርሰዋል፤ ነገር ግን በባሻ ቅጣው ምክንያት የደረሰባቸው
ውጣ ውረድ እንዳይደገም በመሳቢያቸው ውስጥ ቆልፈው አስቀምጠውት ነበር።15

ሳህለሥላሴ የፈጠራ ጽሑፍ በሚያነቡ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለውጥ ያመጣል ብለው ያምናሉ።
የለውጥ መሳሪያ ነው ብለው ያምናሉ። አብዮቱም የተቀሰቀሰው በኋላ "ሰለባ" በሆኑት ምሁራን
እንጂ ሌሎች እንደሚሉት በሌሎች ሀይለኞች እንዳልሆነም ያስባሉ። ያለ ምሁራን ተሳትፎ ለሀገሪቱ
"መጪው ጊዜ" ብሩህ ይሆናል ብለው አያስቡም ፤ ምክንያቱም "ማህበረሰቡ መሀል ንቃት ያላቸው
እነሱ ናቸው"። ስለዚህ የህዝቡን ባህል፣ሥነ ጽሑፍና አስተሳሰብ ለማበልፀግ የሚችሉትን
አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን መቀጠል ይፈልጋሉ።

የተርጓሚው ማስታወሻ

ደራሲና ተርጓሚ ሳህለሥላሴ ብርሀነማርያም ከዚህች መድብል ጥንቅር በኋላ እንደ ሹክታ፤
መከረኞች፤እምቢ ባዮች፡ዕጣ ፈንታ፡እምዩ(የተጠቀሰው)የእየሱስ ህይወት፡ፍኖተ ህይወት(ግለ
ታሪክ) መሳሰሉትን መጻሕፍት ያሳተሙ ሲሆን በስነጽሁፍ ዘርፍ የ1994 ዓ.ም የህይወት ዘመን
ሽልማትና፤ በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ በስነ-ጽሑፍ ዘርፍ የክብር ዶክትሬት ተሸላሚም ሆነዋል፡፡

የግርጌ ማስታወሻዎች

1) ሳህለሥላሴ ትምህርት ቤት በነበሩበት ዓመታት ሁሉ አብረዋቸው ነበሩ ፤ ከዚያም ባሻገር


አብዮቱ ከፈነዳም በኋላ አብሯቸው ሳይሆኑ አልቀሩም።

377
ጥቋቁር አናብስት

2) ለዚህ መጣጥፍ የሚሆን ስዕል የሰራው ቴዎድሮስ ጽጌ ስራዎቹን በአዲስ አበባና በናይሮቢ
ማሳየት የቻለ አማተር ሰአሊ ለመሆን በቅቷል። የአዲስ አበባው ኤግዚቢሽን "የቀለም ቋንቋ"
ተብሎ መሰየሙ ተገቢ ነው ምክንያቱም የቀረቡት ስእሎች በቀለም የተንቆጠቆጡ ነበር ይላሉ
ሳህለሥላሴ። ሰአሊውን በትርፍ ጊዜያቸው ያሰለጠኑት ዝነኛው አርቲስት እስክንድር ቦጎሲያን
ናቸው።

3) በኋላ ከጀዝዊትነት ተለይቶ፣ አግብቶ ፈረንሳይ ውስጥ እንደሚኖር ሳህለሥላሴ ይናገራሉ።

4) ሳህለሥላሴ የኋለኞቹንም የሳምነርን መጽሕፍት ማንበብ አልቻሉም ፤ ጥቂት ገፆችን ካነበቡ


በኋላ መቀጠሉ ጊዜን ማባከን ሆኖ ይሰማቸዋል። ዶክተር ሰምነር ከማርክሳዊው አብዮት በኋላም
እንኳንበአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍና ማስተማራቸውን ቀጥለዋል።

5) ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያበረታታቸው ወንድማቸው እርሳቸው ወደ ውጭ ከሄዱ


በኋላ እርሻውንና ቤተሰቡን የማስተዳደርሐላፊነት ተረክቧል። ሳህለሥላሴ ይሄ የራሳቸው ጊዜ ጌታ
እንዲሆኑ እንዳስቻላቸው ይገልፃሉ።

6) የአሌክሳንደር ዱማስን "የሞንቴክሪስቶው እንደራሴ" አስታውሰው መሆን አለበት።

7) ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ጊዜው ለኢትዮጵያውያን የመረጋጋት መንፈስ አልነበረውም።


በመፈንቅለ መንግስቱ ወቅት በፓሪስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስዊድን ለሚገኙት የኢትዮጵያ
አምባሳደር ተፈሪ ሻረው መፈንቅለ መንግስቱን በመደገፍ ደብዳቤ ፃፉ ነገር ግን ደብዳቤውን
ከመላካቸው በፊት መፈንቅለ መንግሥቱ ከሸፈ። ይሁን እንጂ የተፈጠረው ስሜት አልበረደም ፤
ሳህለሥላሴም በጊዜው ስር ነቀል አቋም እንደነበራቸውይናገራሉ።

8) ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም ከፕሮፌሰር ዎልፍ ሌስላው ጋር ለሰሩት ስራ ዋጋ ይሰጣሉ። ነገር ግን


ሌስላው “ስሜን እንኳን አስተካክለው መጥራት አልሆነላቸውም ነበር” ይላሉ።

9) ብዙ ጊዜ መጠጣት የሚወዱት ደብረዘይት መንገድ ላይ በሚገኝ ከቤታቸው ብዙም በማይርቅ


አንድ መጠጥ ቤት ደጃፉ ላይ ሆነው ነው። ሳህለሥላሴ ከራሳቸው ጋር ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉ ብቸኛ
እንደሆኑ ይታወቃል። ማታ ማታ እንደ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ቢራ በመጠጣት ያሳልፋሉ፤
ልዩነታቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲጠጡ ሳህለሥላሴ መኪናቸው ውስጥ
ብቻቸውን ሆነው መጠጣት ይመርጣሉ። ሳህለሥላሴ ለቃለመጠይቅ በቀላሉ የሚገኙ ሰው
አይደሉም ፤ ካሁን በፊት የሕይወት ታሪካቸውን እንዲያካፍሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ሁሉን

378
ጥቋቁር አናብስት

ተቃውመው መልሰዋል። ከእኔ ጋር ይህንን ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሲስማሙ እድለኛ እና ልዩ


ተጠቃሚ የመሆን ስሜት ተሰምቶኛል። ቃለመጠይቁ የተካሄደው በተለያዩ አጋጣሚዎች ነበር።

10) ይህ መጽሐፍ ለረዥም ጊዜ ምናልባት እስከ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ በብዛት የተሸጠ
መጽሀፍ ነው።

11) ይህ መጽሐፍ በአማርኛ የተፃፈ( ወይም በእርግጠኝነት የታተመ) የመጀመሪያው ልብወለድ


ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው ሮም ውስጥ በ1900 ነበር።

12) በዚህ መሰረት በመጽሐፉ መቼት ውስጥ የተካተተው የአብዮቱ የመጀመሪያ ዓመት አማን
አንዶምና ስልሳዎቹ በህዳር 1967 ከመገደላቸው በፊት ያበቃል።

13) ብሔር ብሔረሰቦች በራሳቸው ቋንቋ መጻፍ አለባቸው የሚለው አቋም ኢትዮጵያ ውስጥ
በሚገባ ድጋፍ አላገኘም። ብሔራዊ ቋንቋ ሲባል የምንረዳው የጎሳዎች ቋንቋ ሳይሆን የመንግስት
ይፋዊ ቋንቋ መሆኑን ነው።

14)ያልተለቀቁት የ"ባሻ ቅጣው" ቅጂዎች መንግስት ከቆለፈበት መጋዘን ተሰርቀው ለገበያ ውለው፣
በመጋቢት 1978 መርካቶ ውስጥ ለእኔም እንድገዛቸው ቀርበውልኝ ነበር። በኋላ መጽሀፉ ብዙ
ማስተካከያ ተደርጎበት በሰኔ 1978 ከመለቀቁ በፊት አሳታሚውን የኢትዮጵያ መጽሐፍት
ማእከልን ብዙ ወጪ አስወጥቶታል። ይህንን የተከለሰ ቅጂ እኔም ለመግዛት ችያለሁ።

15) "ባሻ ቅጣው" ከታተመ በኋላ ሌሎቹንም መጽሐፍት ማውጣት ጀመረ ፤ በዚህ መሰረት
"እምዩ" በ1979 ታትሟል። የታተመውም ከሌሎች አሳታሚዎች ይልቅ የሳንሱር ሂደቱ ለዘብ
በሚለው የመንግስት ኣሳታሚ፣ ኩራዝ ዘንድ ነው።

379
ጥቋቁር አናብስት

ታደሰ ሊበን
የአማርኛ አጭር ልብወለድ ፋናወጊ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው
ምርጥ የአጭር ልብወለድ ጥበበኞች ውስጥ ታደሰ ሊበን
አንዱ ነው፤ነገር ግን ስራዎቹ ጥቂት ናቸው። እስካገኘሁት ጊዜ
ድረስ ያሳተማቸው መጽሐፍት ሁለት ቀጫጭን ቅፆችን ብቻ
ነው። እነዚህ ቅፆች ግን በአገር ውስጥም በውጪም ያሉ
አንባቢዎችን ( ከነዚህ መሀል መንግስቱ ለማ እና ላንፍራንኮ
ሪቺ ይገኙበታል) አድናቆት ለማግኘት በቂ ነበሩ። ላገኘው
ስሞክር የሚያውቁት ደራሲዎች ወይም ከመጻሕፍቱ ባሻገር ስለእሱ የሚያውቁ ሰዎች በጣም ጥቂት
ነበሩ። የደራሲያን ማህበርም ሆነ ሌሎች ደራሲዎችን ማዕከል ያደረጉ ስብስቦች አባል አልነበረም።
ደራሲ ጓደኞችም አልነበሩትም። ቀደም ብዬ የሚሰራው ባንክ ውስጥ እንደሆነ አውቄያለሁ። አንድ
ጊዜ ኬንያ እያለሁ፣ ለትልቅ ስብሰባ ወደ ሀገሪቱ ከሚመጡ ከፍተኛ የባንክና የገንዘብ ባለሙያዎች
መሀል ስሙበጋዜጣ ላይ ተጠቅሶ አይቼዋለሁ።የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሆኑን
በኋላ ላይ ለመረዳት ችያለሁ።ነገር ግን ከተወሰነ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ፣
ከጠየቅኳቸው መሀል የት እንደማገኘው ሊነግረኝ የሚችል አንድምሰው አልነበረም። ነግር ግን
በአፍሪካ አዳራሽ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች በሚጠቀሙበት ባንክ ቼኬን
ለሚመነዝርልኝ ባለሙያ ስሙን ስጠቅስለት ወዲያውኑ ቢሮው የት እንደሚገኝ ነገረኝ። ቢሮው
በቸርችል ጎዳና ከራስ ሆቴል ተሻግሮ በሚገኘው በአዲሱ የንግድ ባንክ ህንፃ ላይ፣ነው። በተነገረኝ
አድራሻ መሰረት ቢሮው ስሄድ ታደሰ ሊበንን አገኘሁት።ታደሰ የብድር ክፍል ሀላፊ ነበር። በትህትና
ከተቀበለኝ በኋላ የመጣሁበትን ጉዳይ ነገርኩት። እሱም በሌላ ቀን ስለ ሕይወቱና ስራው
እንደሚያጫውተኝ ቃል ገባ። እኔም "Tradition and Change in Ethiopia" የሚለውን
መጽሐፌን ሰጠሁት። በመጽሐፉ ውስጥ ስለሱ ስራዎችም ስለጠቀስኩ ለቃለመጠይቁ ዝግጅት
ይረዳዋል።

ታደሰ እድሜው እየገፋ ነው። ቢሆንም ከእድሜው አንፃር ቢሸብትም ገና ወጣት ይመስላል።
በአግባቡ ለመተዋወቅ ያህል ጥቂት ካወራንና ስልክ ቁጥር ከተለዋወጥን በኋላ፣ አሮጌው አየር
ማረፊያ አካባቢ በሚገኘው ቤቴ ገና ባልወሰንነው ቀን ለመገናኘት ተቀጣጥረን ተለያየን።

***

የታደሰ ወላጆች ሁለቱም ወሎዬዎች ነበሩ። አባቱ ሊበን ጣፈጠ በመጀመሪያ ገበሬ ኋላ ደግሞ ነጋዴ
ነበሩ። የተወለዱት ከኮምቦልቻ አቅራቢያ ጎሴ ውስጥ በጀቢል ነው። በሰገሌ ጦርነትላይ በንጉሥ
ሚካኤል በኩል ሆነው ልጃቸውን አቤቶ (ልጅ) እያሱን ከሥልጣን ያስወገደውን አዲሱን መንግስት
380
ጥቋቁር አናብስት

ተዋግተዋል። ንጉስ ሚካኤል በተፈሪ መኮንን (ኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ) ሲሸነፉ፣ አቶ ሊበን
በግዞት ወደ ወለጋ ተልከው ደምቢዶሎ ላይ ሰፈሩ። ከዚያ ከደምቢዶሎ ተነስተው፣ በጭነት
እንስሳት አዲሳባን እያቋረጡ እስከ ወሎ፣ደሴ ድረስ መነገድ ጀመሩ።አቶ ሊበን የታደሰን እናት
ጀማነሽ ወልደሚካኤልን ሲያገቡ ጎልማሳ ነበሩ። ወይዘሮ ጀማነሽ ከወሎ፣ አምባሰል ቢሆኑም
ቤተሰቦቻቸው ቡኖ በደሌ፣ ወለጋ ላይ የሰፈሩ ነፍጠኞች ነበሩ። ሊበን እና ጀማነሽ የተገናኙት
ደምቢ ዶሎ ሲሆን፣ ብቸኛው ልጃቸው ታደሰ ንግስት ዘውዲቱ ከሞተች ከጥቂት ቀናት
በኋላበ1923 ዓ.ም እዚያው ተወለደ። ታደሰ ሰድስት ዓመት ሲሆነው አባቱ ሞቱ፤እናቱ ከዚህ
በኋላ ሁለት ጊዜ አግብተው፣ ከሁለቱም ትዳር ልጆች አፍርተዋል። ነገር ግን ታደሰ ገና የሁለት
ዓመት ልጅ እያለ፣ ቤተሰቡ ወደ አዲስአበባ መጥቶነበር።ታደሰ ሲወለድ ሽማግሌ ስለነበሩት አባቱ
ምንም አያስታውስም፤እናቱ ግን ገና ወጣት ነበረች።ወለጋ እያሉ ከታደሰ ቤተሰብ ተጠግተው
የሚኖሩ ሁለት ዘመዶች ነበሩ ፤ አቶ ሊበን በንግዳቸው ምክንያት ሲከብሩ ሁለት ወንድሞቻቸው
ወደ ቤታቸው መጡ። ደምቢ ዶሎውስጥ አንደኛው የአሜሪካ ሚስዮን ትምህርት ቤት ሌላኛው
ደግሞ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ገቡ።ቤተሰቡ ወደ አዲስአበባ ሲመጣ
ወንድማማቾቹ እዚያው ቀሩ።

ከታደሰ አባት ሞት ጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በአሜሪካ ሚስዮን ትምህርት ቤት የነበረው ጎበዜ ጣፈጠ
የተሰኘ አጎቱ፣ ታደሰን ከእናቱ እቅፍ ወስዶ፣ ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት አቃቂ ላይ በሚገኘው
አድቬንቲስት ሚስዮን ትምህርት ቤት አስገባው። ታደሰ እዚህ ትምህርት ቤት ሲገባ 10 ዓመቱ
ሲሆን አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እስኪጨርስ በዚያው ቆይቷል።በጣም የሚወዳት እናቱ
ትናፍቀዋለች፤፣ እሷም አቃቂ እየመጣች ትጠይቀው ነበር። ጥሩ ታሪክ ተራኪ ነበረች ፤ ታደሰም
ልብወለድ የመፃፍ ተሰጥኦውን ከእሷ እንዳገኘ ያምናል። ቤት ውስጥ ብዙ ታሪክ ታወራላቸዋለች ፤
ከነዚህ መሀል ታደሰ ሁለቱን መርጦ ነግሮኛል ፤ እኔም ባጭሩ መልሼ እነግራችኋለሁ፤(በአጭሩ
የምነግራችሁ ታደሰ ወደፊት እንደገና መፃፍ ሲጀምር ሊጠቀማቸው ስለሚፈልግ እንዳልሰርቀው
በሚል ነው)።1

የመጀመሪያውን ታሪክ የነገረችው በእሷ በኩል ብቻ ከሚዛመዳቸው ወንድሞቹ እና እህቶቹ ጋር


አብሮ ባለማደጉ ብሎም መጀመሪያ ላይ ከነጭራሹ ስለማይቀርባቸው ነበር። ብዙ ጊዜውን
የሚያሳልፈው ከጓደኞቹ ጋር በትምህርት ቤት ውስጥ እየተጫወተ ነው።ስለዚህ ከወንድሞቹ ይልቅ
ከጓደኞቹ ጋር መዋል ስለሚመርጥ አንድ ሀብታም ሰው ነገረችው።ታዲያ እውነተኛ ጓደኞቹ እነማን
እንደሆኑ ለማወቅ አንድ በግ ካረደ በኋላ በነጭ አንሶላ ሸፈነው።በጉ የታረደበት አንገቱ አካባቢ
አንሶላው በደም ጨቀየ። ከዚያ ሁሉንም ጓደኞቹን ጠርቶ ሰው እንደገደለ ሲነግራቸው ችግር ውስጥ
ላለመግባት ፈርተው ሁሉም ጥለውት ሄዱ። ከዚያ ወንድሙን ጠርቶ ተመሳሳይ ነገር ሲነግረው፣
ከገባበት ችግር የሚወጣበትን መፍትሔ በመፈለግ ሊረዳው ሞከረ። ሀብታሙ የሰው ልጅ

381
ጥቋቁር አናብስት

እውነተኛ ጓደኞች የስጋ ዘመዶቹ መሆናቸውን በዚህ ዘዴ አወቀ። ታደሰም በዚህ ታሪክ የተነሳ
ከእናቱ ትምህርት ተማረ።

እናቱ ለታደሰ የነገረችው ሌላኛው ታሪክ፣ ለሞት ካላት ቋሚ ፍርሀት የመነጨ ነው። ከነሕይወቷ
እንዳትቀበር ስለምትሰጋ ( ተመሳሳይ ታሪኮችን ሰምታስለምታውቅ) የሬሳ ሳጥን ውስጥ ከመግባቷ
በፊት ለአንድ ሙሉ ቀን በድኗ እንዲሁ እንዲቀመጥ ትሻለች።2 በዚህ የተነሳ የታደሰ እናት በ83
ዓመታቸው በ19877/78 አ.ም በእርግጥ ሲሞቱ የተቀበሩት ዘግይተው ነበር። ኢትዮጵያ ውስጥ
ለቀብር የሚመጡ ሰዎች ብዛት ትልቅ ግምት ስለሚሰጠው፣ የታደሰ እናት ለቀብራቸው
የሚመጣው የሰው ብዛት እና ማን ማን ይመጣ ይሆን የሚለው ያስጨንቃቸው ነበር። ታደሰ ገና
ልጅ እያለ ይህ ጉዳይ ምንኛ እንደሚያሳስባቸው የሚገልጥ ታሪክ ነግረውታል። ታሪኩ እንዲህ
ነው፦

አንዲት መሀን ሴት፣ብዙ ልጆች ካሏት ሴት ጋር ተጎራብታ ትኖራለች። እናትየው በእርጅናዋ ወራት
በልጆቿ እየተጦረች ደስተኛ ሕይወት እንደምታሳልፍ ተስፋ ስታደርግ፣ መሀኗ ግን “ቀባሪ በፈጣሪ”
እያለች ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋለች። እናታቸው ስታረጅ፣ በማያልቀው ፍላጎቷ
የተሰላቹት ልጆች በጅብ እንድትበላ ገላጣ ቦታ ላይ ከጣሏት በኋላ ጥርጣሬ ለማዳፈን መሀኗን ሴት
እንደ እናታቸው አድርገው ተቀበሏት። አንዳንድ ጥርጣሬዎች ሲፈጠሩ፣ በሰፈሩ
አውጫጪኝ/አፈርሳታ ላይ ተገኝተው እናታቸው እንደሆነች አስረግጠው ተናገሩ። መሀኗም
ሚስጥራቸውን ጠበቀች፤እነሱም በአግባቡ ተንከባከቧት።እስከ ሕይወቷ ፍፃሜ ድረስ በደስታ ኖረች
፤የተቀበረችውም በታላቅ ክብር ነበር። የእውነተኛ እናታቸው ፍፃሜ ግን በጅቦች በመበላቷ
አላማረም ።የተገኘው ቀሪ አካሏ እጆቿና እግሮቿ ብቻ ናቸው፤ኢትዮጵያውያን ጅቦች እነኚህን
የሰውነት ክፍሎች አይበሉም ብለው ያምናሉ።

በ1949 በታተመው የመጀመሪያ መጽሐፉ "መስከረም" መግቢያ ላይ፣ ታደሰ ሊበን በአጭር
ልብወለድ ጥበብ ችሎታቸውን ማሻሸል የሚፈልጉ እንዲያነቧቸው ብዙ ታዋቂ የአጭር ልብወለድ
ጸሐፍትን ይጠቁማል። በመስኩ በሚገባ እንዳነበበ ግልጽ ነው። ነገር ግን ራሱን በተመለከተ
ችሎታውን ለማዳበር ከነዚህ ደራሲዎች ይልቅ የእናቱ አስተዋጽኦ እንደሚበልጥ ይናገራል። ገና ልጅ
እያለ ከእናቱ ጋር ስለሚተኛ ብዙ ታሪኮች ይነግሩት ነበር። እናቱ ጥብቅ የሥነ ስርዓት ቁጥጥር
የሚያደርጉ ቢሆኑም ለልጆቻቸው ደግ ነበሩ። በባህሪያቸው ያሰቡትን ሳይደብቁ ለሁሉም
ይናገራሉ። “በአካል ግዙፍ እና መልከመልካም” ሲሆኑ ። አባቱ ከሞተ በኋላ ታደሰ ከእርሳቸው ጋር
ይኖር ነበር። ሁለተኛ ባል ካገቡም በኋላ ለተወሰነ ጊዜ አብሯቸው ኖሯል ። በኋላ ቤቱን ጥሎ ሄደ።
በጣም ብቸኛ ልጅ እንደነበር ይናገራል። ምናልባት እንደልቡ ጓደኞችን ለመምረጥ አልቻለም
ይሆናል። አንዴ ሶስተኛ ሀብታም ባላባት ባል ያገቡትን እናቱን ለመጠየቅ ከአዲስአበባ 75 ኪሜ
382
ጥቋቁር አናብስት

ወደምትርቀው ሸኖ ሲሄድ ጎረቤት ካለች ልጅ ጋር ጓደኝነት ይመሰርታል። እናቱ ግን ይቺ ልጅ ቡዳ


ናት ብለው አስጠነቀቁት። ይህ አጋጣሚ "ጅብ ነች" ለተሰኘው አጭር ታሪኩ መነሻ ሆነ። በታሪኩ
ቡዳዎች ማታ ማታ ሰው ወደሚበሉ ጅቦች እንደሚቀየሩ በህበረተሰቡ ዘንድ ያለውን እምነት
ያንፀባርቃል። ታሪኩም "መስከረም" ላይ ተካቷል።

***

ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያለ ለጋነቱ ታይቶ የቀበና የልጃገረዶች አድቬንቲስት ሚስዮን ትምህርት
ቤት እንዲገባ ተፈቀደለት። ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር፣ የሚያሳድገው አጎቱ አሁንም ድረስ ከደሴ
ወጣ ብለው የሚኖሩ ሁለት የአባቱ ወንድሞች ጋር ሊያስተዋውቀው ወደ ወሎ ይዞት ሄደ።
አጎትየው ወደ ወሎ የሄደው፣ እንግሊዝኛ ስለሚችል በጣሊያኖች እየታደነ ስለነበር ነው። ለአራት
ዓመት ያህል ወሎ ውስጥ ተደብቆ ቆየ። ታደሰ ግን ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አዲስአበባ ተመለሰ።
ሌላኛው አጎቱ ደምቢዶሎ ውስጥ ሲሞት፣ አብሮት የነበረው አጎቱ ለቀብር ወደዚያው ሄደ። የታደሰ
እናት ግን አዲስ አበባ እንዲቆይ አልፈለጉም ምክንያቱም ባሊላ(ታደሰ ስያሜውን ያገኙት ባሊላ
ከሚባሉ የኢጣሊያ መኪናዎች ነው ይላል―በሕሩይ የሕይወት ታሪክ ስር የግርጌ ማስታወሻውን
ይመልከቱ) ስለሚባሉ ዩኒፎርም ተሰጥቷቸው ሙሶሎኒን የሚያሞግሱ መዝሙሮችን ስለሚዘምሩ
ልጆች ሰምተው ስለነበር ታደሰም እንደነሱ ለመሆን ይገፋፋል ብለው በመፍራታቸው ነበር።
ስለዚህ ከነበረበት ጃንሜዳ ( ጣሊያኖች አዘውትረው ኳስ የሚጫወቱበት አካባቢ ነበር)
አስወጥተው ከአዲስአበባ 40 ኪሜ በምትርቀው ሰንዳፋ ውስጥ አንድ ባለ ጠጅ ቤት የሩቅ
ዝምድና ካላቸውና ጓደኛቸው ከሆኑ ወይዘሮ ዘንድወስደው “ሰጡት”። እንደዚህ ርቆ ከተቀመጠ
"ባሊላዎችን" ለመሆን አይጎመዥም። ሂሳብ መቀበል ላይ ጎበዝ ስለነበር ጠጅ በማሳለፍ ያግዛቸው
ነበር። በጣም ብዙ የኢጣሊያ ጦር ሰራዊት በቤቱ በኩል ሲያልፍ እንዴት እንደነበረ እስከ አሁን
ድረስ ያስታውሳል።

አጎቱ ጎበዜ ከደምቢዶሎ ሲመለስ የሰባት ዓመቱን ታደሰን ሊያገኘው አልቻለም ፤እናቱም ወዴት
እንዳለ አልናገር አለች። ስለዚህ በታደሰ እናት እነደተናደደ ወደ ደሴ ሄደ። ታደሰ መጠጥ ቤት
ውስጥ ለሁለት ዓመት ከሰራ በኋላ ወደ አዲስአበባ መጣ። ከጦርነቱ በኋላ አቃቂ አድቬንቲስት
ሚስዮን ማስተማር የጀመረው አጎቱ፣3 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጣና የአስር ዓመቱን
ታደሰ እዛው አቃቂ ሚስዮን ወስዶ አስገባው። ይህ አጎቱ በአቃቂ ለትንሽ ጊዜ ካስተማረ በኋላ ወደ
ደሴ አድቬንቲስት ትምህርት ቤት ተዛወረ ፤ በመጨረሻም የመንግሥት ትምህርት ቤት ገባ። ይህ
አጎቱ በአድቬንቲስት ሚስዮኑ በነበረው ቦታ ምክንያት ታደሰ ለትምህርት ቤት ወይም ለምግብና

383
ጥቋቁር አናብስት

ለመኝታ መክፈል አይጠበቅበትም ።ነገር ግን በክፍያ ፋንታ በየቀኑ ለአራት ሰአታት በአትክልት
ስፍራው መስራት ይጠበቅበት ነበር፤ክፍያ የሚከፍሉት ተማሪዎች ለሁለት ሰአታት ብቻ ይሰራሉ።

በዚህ ትምህርት ቤት በቆየባቸው አራት ዓመታት፣ ስድስተኛ ክፍልን አጠናቀቀ።ነገር ግን


የትምህርት ቤቱ ደረጃ ከፍተኛ ስለሆነ ይህ ቆይታው ከመንግስት ትምህርት ቤት አንጻር ሲመዘን
ከዘጠነኛ ክፍል ጋር ተመጣጣኝ ነበር።ከዚህ በኋላ ኮተቤ በሚገኘው በቀዳማዊ ኃይለስላሴ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገባ።ስለዚህ የታደሰ የክፍል ጓደኞች አስረኛ ክፍል ሲገቡ ታደሰ ግን
በቁመቱና ልጅነቱ የተነሳ ዘጠነኛ ክፍል ገባ።

በዚህ ትምህርት ቤት ከመንግስቱ ለማ ጋር አንድ የመኝታ ክፍል ተጋርተዋል። ይሁን እንጂ


መንግስቱ በትምህርት ክፍሉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነበር። መንግስቱ የለንደንን የኮሌጅ መግቢያ
ፈተና ያለፉ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ ታደሰይናገራል።መንግስቱ የሮበርት ሉዊስ
ስቴቨንሰንን "ዶክተር ጄኪል እና ሚስተር ሀይድ"ን ስላነበበ የመኝታ ክፍሉን ለሚጋሩ ጓደኞቹ
ዘወትር ማታ ከእንቅልፍ በፊት ይተርክላቸዋል። ታደሰም ታሪኩን በጉጉት እየተከታተለ፣
የሚቀጥለውን ክፍል በናፍቆት ይጠብቃል። ምንም እንኳን ታደሰ ሌሎቹ ትልልቅ ልጆች መንግስቱ
ታሪኩን በምሽት መንገሩን መቃወማቸው ቢያናድደውም፣4መንግስቱ ግን ትረካውን እንደምንም
ጨረሰ።ታደሰ አሁን እነዚያ የትረካ ጊዜያቶች ለሥነ ጽሑፍ ያለው ፍላጎት እንዲዳብር አስተዋጽኦ
እንዳደረጉ ያምናል። ታደሰ መፃፍ ከጀመረ በኋላ ከመንግስቱ ጋር መገናኘት የጀመረሲሆን ፤
መንግስቱም በታደሰ ከመተማመኑም በላይ ያበረታታው እና ይመክረው ነበር። ሁለት መጽሐፍት
ብቻ አሳትሞ በማቆሙ ግን መንግስቱ በጣም ተናዶበታል። ከዚያ በኋላ ግንኙነታቸው መቋረጡ፣
መንግስቱ ታደሰን ለማግኘት አለመፈለጉ በዚህ ምክንያት እንደሆነ ያስባል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጽእኖ ያሳረፈበት የአማርኛም ሆነ የእንግሊዝኛ መምህር


”ባይኖርም፣ታደሰ ግን በራሱ የእንግሊዝኛ ሥነ ጽሑፍን ያነብ ነበር። ለምሳሌ አርተር ኮናን ዶይል፣
የሞፓሳ የመሳሰሉትን።

ሁለተኛ ደረጃን እ.ኤ.አ 1949 ካጠናቀቀ በኋላ፣ ልክ ፈተናውን እንደጨረሰ ደሴ የሚገኙ አጎቱ ጋር
ተደብቆ ቆየ። ምክንያቱም በግድ የአየር ኃይል አባል እንዲሆን ተመልምሎ ስለነበር ነው፤ እሱ
ደግሞ እዚያ መስራት አልፈለገም።5ጠፍተው የተደበቁ ልጆችን መፈለጉ ሲያበቃ፣ታደሰ ወደ
አዲስአበባ ተመለሰ። ከዚያም የግል የሙስሊም ትምህርት ቤት በሆነውና ከአንዋር መስጊድ ቀጥሎ
በሚገኘው ደጃዝማች ኡመር ሰመተር ትምህርት ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ለሁለት ዓመት አስተማረ።
ጥሩ አስተማሪ ሳይሆን አይቀርም፤ ምክንያቱምተማሪዎቹ ስምንተኛ ክፍልን (የመለስተኛ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት ማጠናቀቂያ)በጥሩ ውጤት አልፈዋል።

384
ጥቋቁር አናብስት

ታደሰ ማስተማሩን ቢወደውም፣ ለዚያ ብቁ የሚያደርግ ትምህርት አልነበረውም፤ስለዚህ


የኢትዮጵያ መንግስት ባንክ የተሻለ ክፍያ ስላቀረቡለት እነሱን ተቀላቀለ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባንክ
ውስጥ ነው የሰራው።

የባንክ ተቀጣሪ ከሆነ በኋላ ለዚህ አዲስ የስራ ዘርፍ የሚሆን ትምህርት ለማግኘት ሞከረ።
መጀመሪያ ቢሮው ካይሮ ከሚገኘው የብሪቲሽ ትምህርት ቤት በርቀት የሒሳብ ስራ፣የቢዝነስ
እንግሊዝኛእና የቢዝነስ አርቲሜቲክ መማር ጀመረ። ከሁለት ዓመት በኋላ ቢያቋርጠውም፣
እስከተማረበት ድረስ ላለው የምስክር ወረቀት ተቀብሏል ፤ በስራውም ረገድ ትምህርቱ በጣም
እንደረዳው ይናገራል።ትምህርቱን ቢጨርሰው ኖሮ፣የተመዘገበ/የተመሰከረለት የሒሳብ ሰራተኛ
መሆን ይችል ነበር። ነገር ግን ርቆ ከመሄዱ በፊት በሥነ ጽሑፉ ተሳበ። በግሉ ብዙ ካነበበ በኋላ፣
የፃፋቸው ታሪኮች በኋላ "መስከረም" በሚል የአጭር ታሪኮች መድብል ታተሙ። መስከረም
የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ከመሆኑ ባሻገር፣አዲስ ጅማሬ፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ቃልኪዳንን
ያመለክታል።

ይህ መጽሐፍ ዝግጁ ከመሆኑ በፊት እ.ኤ.አ 1948 አገባ፤ቀኑን እርግጠኛ ለመሆን ቀለበቱን
አውልቆ የታተመውን ቀን ማየት አስፈልጎት ነበር―26/6/48 ይላል (ኢትዮጵያውያን የደስታ
ቀኖችን እንደ ምእራብያውያን በየዓመቱ አያከብሩም፤ይልቁንም ሙት አመቶችን እስከ ሰባት ዓመት
ድረስ ያከብራሉ) ሚስቱ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት ምሩቅ ስትሆን የተገናኙት ባንክ
ቤት ውስጥ በፀሐፊነት ስትሰራ ነው። የአዲስአበባ ልጅ ስትሆን ሁለት ልጆቻቸውንም የወለዱት
እዚሁ ነው።የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ ስትሆን አግብታና ሁለት ልጅ ወልዳ በሰሜን አሜሪካ
ትኖራለች፤ሁለተኛው ወንድ ልጅ ቆይቶ በ1966/67 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ከእህቱ ጋር ይኖራል።
የታደሰ ሚስት ጤናዋ አስተማማኝ ስላልነበረ፣የወለዱት እነዚህን ሁለት ልጆች ብቻ ነው።

ከጋብቻው በኋላ ብዙም ሳይቆይ በ1949/50 ዓ.ም ታደሰ በ"መስከረም" ውስጥ የተካተቱ
አብዛኛዎቹ ታሪኮችን ፃፈ፤ነገር ግን አንዳንዶቹን የፃፋቸው ከዛ በፊት ሳያገባ በፊት ብቸኛ እያለ
ሲሆን፣ ታሪኮቹ በጊዜው የነበረውን ልምድ እና አስተውሎት ያንፀባርቃሉ። የባንክ ቤቱንም ሆነ
የመምህራንነት ስራውን ለማግኘት ተቸግሮ ነበር።

በ1952 የታተመው የሚቀጥለው የአጭር ታሪኮች ስብስቡ "ሌላው መንገድ" ም በግሉ


ካስተዋለው የተቀዳ ነው። "የተበጠሰች ፍሬ" የተሰኘው አንዱ ታሪክ ለትምህርት ከሄደችበት ሰሜን
አሜሪካ ወደ ሀገሯ ተመልሳ ከማህበረሰብ ጋር መቀላቀል ስለከበዳት አንዲት ኢትዮጵያዊት
ይተርካል።ይህ በጊዜው የተለመደ ችግር ነበር፤ ግን ታደሰ ያለርህራሄ አንጥሮ ጽፎታል።
በመጽሐፍቱ ውስጥ በሚቀያየር ማህበረሰብ ውስጥ ስለሚኖሩ ሰዎች ጉዳይ ያነሳል።
385
ጥቋቁር አናብስት

ከማግባቱ በፊት ባሳለፈው የብቸኝነት ሕይወት ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ከልጅነቱ አንድ
አጋጣሚ አስታወሰ። በአጋጣሚው ታደሰ የገና ጨዋታ ከአንዲት ቆንጆ ልጅ ደጅ ላይ ሲጫወት
እናቱ ቡዳ ናት ወላጆቿም ቆማጣ ናቸው ብለው ያስጠነቅቁታል። (በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ
በኦሮሞ ባህል ውስጥ የወንድና ሴት ልጅ የቅርብ ግንኙነት በጊዜ ሊጀምር ይችላል)።
እንደተጠቀሰው ታደሰ ከዚህ አጋጣሚ ተነስቶ የፃፈውን "ጅብ ነች" የተሰኘ ታሪክ ለመጀመሪያ
መድብሉ"መስከረም" የመክፈቻ ታሪክ አድርጎታል። ስለዚህ የግል ገጠመኞችና በአካባቢው
የሚያስተውላቸው ነገሮች የታሪኮቹን ጭብጦች የሚያገኝባቸው ቦታዎች ናቸው።ሁለቱም
መጽሐፍቶቹ በ5,000 ቅጂዎች የታተሙ ሲሆን በጊዜው እንደተለመደው ራሱ ሳንሱር ጋር
መውሰድ፣ ለማተሚያ ቤት ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ነበረበት። ቅጂዎቹን እንዲሸጡለት ለጓደኞቹ
ካከፋፈለ በኋላ “እንደ ትኩስ ኬክ” ወዲያውኑ ተሸጡ ይላል።ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ በድጋሚ
አልታተመም።እስካሁን ባያደርገውም በተደጋጋሚ ለሚያሳትመው ይችል እንደነበር ፤አሁን ቢሆን
ወደፊት ሊያደርገው እንደሚችል ይናገራል።

ታደሰ ሊበን የተሳካለት ጸሐፊ ሆኖ እያለ፣ ከየአቅጣጫው የሚያበረታቱ አስተያየቶች እየተሰጡት


እያለ መፃፉን ለምን አቆመ? "ሌላው መንገድ" ላይ ግብረሶዶማዊ ገጠመኝ ስላገኘው አንድ ሰው
የተፃፈ ታሪክ አለ። ይህ በኢትዮጵያ እንግዳና ያልተለመደ ነው። የተለመደው የተቃራኒ ፆታ
ጉድኝትበቀላሉ በሚፈጸምበትና፤ ወጣት እና አዋቂ ወንዶች ከልጅነታቸው ጀምሮ በተለያየ ደረጃ
እንዲህ ያለ ልምድ ለማግኘት በማይቸገሩበት በኢትዮጵያ፣ ይህ ፈጽሞ ያልተለመደና “እንግዳ” ነገር
ነው። ግብረሶዶማዊነት እና ግብረሶዶማዊ እንቅስቃሴዎች በኢትዮጵያ “በፍፁም የማይታሰቡ”
ናቸው ይላል ታደሰ።ይሁን እንጂ ይህ ታሪክ በሚያውቀው ሰው እውነተኛ ገጠመኝ ላይ የተመሰረተ
ነው። አንድ የስራ ባልደረባው የባንኩ ደንበኛ የሆኑ ግብረሶዶማዊ ቤት ይጋበዛል፤ነገር ግን
ግብረሶዶማዊ እንደሆኑ አያውቅም። ይሁን እንጂ ወደ ቤታቸው በሄደ ጊዜ የሰውዬውን እውነተኛ
አላማ ተረዳ።የታደሰ ባልደረባ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ በመስኮት ዘሎ አመለጠ። የደረሰበትን
ሁሉ ለታደሰ ነገረው። ታደሰም ከዚህ ተነስቶ ታሪኩን ፃፈ።“ነገር ግን ይህ የግብረሶዶማዊነት ታሪክ
ገደለኝ፤ለምን እንደዚህ ዐይነት እንቶ ፈንቶ ፃፍኩ? ለምን እንዲህ ዐይነት ባዕድ ነገር ወደ ሐገሬ ሥነ
ጽሑፍ አመጣሁ? ይህ በጣም ጎድቶኛል" ይላል። ስለዚህ “የተሻለ ነገር መፃፍ ካልቻልኩ ባቆም
ይሻለኛል” ብሎ ይደመድማል።እናም እንዳሰበው አቆመ ፤በእርግጥ በታሪኩ የተነሳ የወቀሰው
ወይም አንስቶ ያወያየው ሰው የለም።ውሳኔው ስለ ጉዳዩ ካሰበበት በኋላ በራሱ የደረሰበት ነው።
ምናልባት አንባቢዎቹ አልተረዱት ይሆናል፤ሳንሱር ክፍሉ ቢረዳው ኖሮ አያሳልፈውም ነበር። ታደሰ
የተማረው በሚሲዮን ትምህርት ቤት ሲሆን አሁን ድረስ ክሪስቲያን ነው። እነኚህ ግብረገባዊ
አስተውሎቶች ከሀይማኖታዊ አስተዳደጉና እምነቱ የመነጩ ሊሆኑ ይችላሉ።ይህን ችግር ለመፍታት
386
ጥቋቁር አናብስት

ረዥም ጊዜ ቢወስድም አሁን በቃለመጠይቃችን ወቅት ግን መላ አበጅቶለታል። አሁን መፃፍ


ይጀምራል ፤ አፃፃፉ ግን ለየት ያለ ይሆናል።

ወደፊት ታደሰ "በአላማ" ይጽፋል። እንደሚናገረው፣ መፃፉን ማቋረጡ ስህተት ሊሆን ይችላል፤
ነገር ግን ይህንን የተረዳው ከጥልቅ ማሰላሰል በኋላ ሲሆን እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው
የነበረበትን ግብረገባዊ ግራ መጋባትን ካጠራ በኋላ ነው። ያኔ “አልበሰለም” ነበር ከአሁን በኋላ ግን
የትኛውም ያሳተማቸውም ሆኑ ሌሎች ታሪኮቹ አያሳፍሩም። ነገር ግን የተሻሉ
ታሪኮችን―የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጡ እና የኑሮውንም መንገድ የሚያሳዩ
ታሪኮችን―የሚጽፍበትን ችሎታ እንዲሰጠው ይፀልያል።“ስብከት መሰል” ወይም ግብረገባዊ
ታሪኮችን መጻፍ ከጀመረ አንባቢዎች ይበረክቱልኛል ብሎ በማመን ይሆን ?“አንባቢዎች እንዴት
መኖር እንዳለባቸው የመምከር ፍላጎት”እንደሌlው፣ነገር ግን “ሰዎችን በመንፈስ ከፍ የሚያደርግ
ነገር”እጽፋለሁ ብሏል። ይሁን እንጂ ይህንንም ራሱ ቢሆን በግልጽ አያደርግም። ከድሮም ቢሆን
ታሪኮቹ ከዋናው የታሪክ መስመር ወጣ ብለው የተደበቁ ጥልቅ ትርጉሞች አሉት። በዚህ መሰረት
አንደኛው የታተመው ታሪኩ "ትንሽ ልጅ" ስለ አንድ ልጅ ያወራል። ይህ ልጅ አንድ እንግዳ
ቤታቸው መጥቶ ለሚጠይቃቸውእንደ―ስምህ ማነው? ወላጆችህን ትወዳቸዋለህ? ለመሳሰሉት
ጥያቄዎች―መልስ መስጠት ይፈራል። "ትንሹ ልጅ" በኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበረው፣ የመናገር እና
ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት እጦት መሆኑን አሁን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ራሱ ገና አሁን ነው የተረዱት።
በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ባህል እንዲህ ያለ ነበር ይላል ታደሰ። በታሪኩ ውስጥ ልጁ እናቱንና
አባቱን ስለመውደዱ የተጠየቀው "አገርህንና ንጉስህን ትወዳለህ ወይ?" ለማለት ነው።ሰዎች
አገራቸውን እና ገዢዎቿን እንደሚወዱ በግልጽ ለመናገር እንኳን ይፈራሉ። ነገር ግን በሚስጥር
ያወሩታል።ይሄም ልክ ልጁ እንግዳው ከቤት እስኪርቅ ጠብቆ፣ ከአባቱ እና ከእናቱ አይን ተሰውሮ
የእንግዳውን ጥያቄዎች ሁሉ እንደሚመልስለት ማለት ነው።6

ታደሰ ንጉሡን ሁሌም ቢወዳቸውም ነገር ግን ይህን ለመናገር የሚያመነታበት ጊዜ ነበር። “የእሱ
ትውልድ ሰዎች ንጉሱንም ንግስቷንም ስለሚወዱ ስለነሱ አንዳች መጥፎ ነገር አይተነፍሱም ነበር”
ይላል።

ኃይለሥላሴ በቤተመንግሥቱ ኩሽና የተዘጋጀ ምግብ ራሳቸው ይዘው ኮተቤ ወደሚገኘው ቀዳማዊ
ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይዘው ዘወትር ሃሙስ እንደሚመጡ በተለይ
ያስታውሳል ፤በሁዳዴ ደግሞ ዘወትር አርብ የፆም ምግብ ይዘው ይመጣሉ።በገበታ ወቅት ንጉሡም
ከተማሪዎቹ ጋር ተቀምጠው ይበላሉ።ምግቡይጣፍጥ እንደሆነም ተማሪዎቹን ይጠይቃሉ―አዎን!
387
ጥቋቁር አናብስት

ጣፋጭ ነበር። አንድ ቀን እንደውም፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ጥሩ ምግብ ያቀርቡላቸው እንደሆነ


ጠየቁ።አንድ ደፋር ተማሪ ተነስቶ ጥሩ ምግብ የሚቀርብላቸው ንጉሡ በሚመጡበት ሐሙስ ቀን
ብቻ መሆኑን ተናገረ።ንጉሡ ይህንን ሲሰሙ የምግብ ቤቱ ሀላፊ እንዲባረር ትእዛዝ ሰጡ፤በትእዛዙ
መሰረትም ወዲያውኑ ተባረረ።ንጉሱ ከምግቡ በተጨማሪ ተማሪዎች ክብራቸውን መጠበቅ
እንዲማሩ ይፈልጋሉ።ስለዚህ ተማሪዎቹ ምግባቸውን በሚበሉ ሰአት እየተዘዋወሩ ተደፍተው
የሚበሉትን ጀርባቸውን ነካ በማድረግ ቀና ብለው እንዲቀመጡ ይነግሯቸው ነበር።

ተማሪዎቹ ስለ ንጉሳቸው ያላቸው ትዝታ እንዲህ ያለ ነበር፤ስለዚህ በዚያው በንጉሱ ዘመን የንጉሱን
ስም በፍቅር መጥራት “የሚያስጠረጥርበት” ዘመን ላይ መድረስ ያሳዝናል። ነገር ግን ታደሰ ለንጉሱ
ያለው ፍቅር አልቀነሰም። በመንግሥቱ ሐይለማሪያም አምባገነናዊ ማርክሳዊ አገዛዝ ወቅት እንኳን
ለኃይለሥላሴ ያለውን ውዴታ ለመግለጽ አያፍርም ወይም አይፈራም።

***

ታደሰ በኢትዮጵያ መንግስት ባንክ በ1951 ዓ.ም የዴስክ ጸሐፊ ሆኖ ስራ ጀመረ። ከአንድ ዓመት
በኋላ መዝገብ ያዥ ሆነ። በዚህ ስራ ለሁለት ዓመት ከቆየ በኋላ ምክትል መርማሪ ሆነ። ከአንድ
ዓመት በኋላ መዝገብ ያዥ ሆኖ በመጀመሪያው የባንኩ ቅርንጫፍ በአዲስ ከተማ (የዛኔ ቁጨራ
ተብሎ ይጠራ ነበር) ከአንዋር መስጊድ በቅርብ ርቀት ይሰራ ነበር። በኋላ የባንኩ ረዳት ስራ
አስኪያጅ ሆኖ ለሶስት ዓመት ሰራ። ከዚህ በኋላ ስለ ባንክ ስራ እንዲማር ወደ ጣሊያን፣ ሮም
እ.ኤ.አ በ19647ተልኮ በክሬዲቶ ኢታሊያኖ ለዘጠኝ ወራት ትምህርት ተከታተለ። ይህንን በውጪ
ሀገር ያደረገውን የመጀመሪያ ቆይታ ወዶት ነበር።

በ1965 እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር እንደተመለሰ በኢትዮጵያ መንግስት ባንክ ዋና ሂሳብ


መርማሪ ሆነ። ነገር ይህ ባንክ ብሔራዊ ባንክ እና ንግድ ባንክ ተብሎ፣ለሁለት ተከፈለ።የመንግስት
ባንኩ ዋና ቅርንጫፍ ፒያሳ ላይ ነበር። ስለዚህ ለንግድ ባንኩ ከመከላከያ ሚኒስትር ፊትለፊት አዲስ
ህንፃ መገንባት ተጀመረ።

ታደሰ የተሰጠው ስራ የንግድ ባንክን (በ1965 ባንኩ ለሁለት ከተሰነጠቀ በኋላ እነሱን ተቀላቅሏል)
የአራዳ ቅርንጫፍ ማደራጀት ነበር። ይህ ስራ የተሰጠው ባንኩ ውስጥ ሁሉን ስራ በሚመለከት
ልምድ ስለነበረው ነው። ለስድስት ወር የሰራበት ይህ ቅርንጫፍ በጊዜው ትልቁ ቅርንጫፍ ነበር።
ከዚያ መከላከያ ሚኒስትር ፊትለፊት ወደሚገኘው ዋና ቅርንጫፍ ተዛወረና የብድር ክፍል ዋና ሀላፊ
ሆነ።ከዚህ በኃላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ቼዝ ማንሃተን ባንክ ተልኮ ስለ "ብድር ጉዳዮች" እያጠና
ለአምስት ወራት ቆየ። በጊዜው የብድር ክፍል ሃላፊነቱን እንደያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቼዝ
388
ጥቋቁር አናብስት

ማንሀተን ባንክ ምክር መሰረት የብድር ትንተና ትምህርት በርቀት ወስዶ በ1960 ዓ.ም የምስክር
ወረቀት ተቀበለ። ከኒውዮርክ እንደተመለሰ የብድር ክፍል ረዳት ስራ አስኪያጅ ሆኖ ከ1961–
1966 ዓ.ም አብዮቱ እስከሚፈነዳ ሰራ።እስከዚህ ወቅት ድረስ በንግድ ባንክ ለስምንት ዓመት
ሰርቷል።

አብዮቱ በ1966 ከፈነዳ በኋላ፣ ታደሰ አድሃሪ ተብሎ፣ ከነበረው ደረጃ ዝቅ ተደርጎ ከዘጠኝ ዓመት
በፊት ራሱ ባደራጀው የንግድ ባንክ የአራዳ ቅርንጫፍ እንደገና ስራ አስኪያጅ ሆነ። በዚያ ለሁለት
ዓመት ከሰራ በኋላ፣ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነ። ይሄ ቅርንጫፍ ከአራዳው
ቅርንጫፍ ስለሚተልቅ እንደ እድገት የሚቆጠር ነበር።

ከዚያ የባንኩ የሰሜን ክፍል (ትግራይ እና ኤርትራ)ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ለስድስት ዓመትሲሰራ።


ቢሮው አስመራ ነበር። አስመራ “ጥሩ ቦታ” ነበር፤ ነገር ግን በጊዜው ብዙ ችግሮች ነበሩ። በ1975
በአስመራ ቆይታው ማብቂያ ከጣሊያን የባንከኝነት የምስክር ወረቀት ተቀበለ። የአስመራ ንግድ
ምክር ቤት ፕሬዚዳንትም ሆነ። ከዚያ ቀጥሎ ለሁለት ዓመት ተኩል የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት
ፕሬዚዳንት ሆነ። ይህንን ስልጣን ያገኘው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የሁሉም ከተሞች ንግድ ምክር
ቤቶች መርጠዉት ነው።በዚህ የስልጣን ዘመኑ ታደሰ ወደ ብዙ ሀገራት ተጉዟል። ገና አስመራ እያለ
ደግሞ ወደ ብራስልስ ለአንድ ወር ስልጠና ተጉዞ ነበር።

በ1976/77 ዓ.ም ወደ አዲስአበባ ተመልሶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ክፍል ሐላፊ ሆነ።
በቃለመጠይቃችን ወቅት በዚሁ የስራ መደብ ላይ ነበር። ታደሰ ሊበን የጡረታ መብቱ ተከብሮለት
በ1978 ዓ.ም መጨረሻ ጡረታ እንደሚወጣ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም፤ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት
ስራውን እንዲቀጥል ጥያቄ ቀርቦለታል።

የባንክ ቤት ስራ አድካሚ በመሆኑ፤ ታደሰ ሁሌ ቤት ሲደርስ አቅሙ ተሟጦ እንደነበር ይናገራል።


የደረሰበት የኃላፊነት ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ድካም እና የስራ ፍቅር ጠይቋታል። ይሁን እንጂ
ስራው “ድርሰትን ለመፃፍ የሚያበረታታ” አይደለም። ነገር ግን ስለመፃፍ “በየቀኑ አስብ ነበር”
ይላል። አብልጦ ስላልፃፈ “የጥፋተኝነት ስሜት” ይሰማው ነበርና፤ይህንን በተመለከተ ወደ
እግዚአብሔር ይፀልይ ነበር። ጡረታ ከወጣ በኋላ መፃፉን ለመቀጠል ያስባል። "ካልፃፍኩ
በሕይወቴ እንዳልተሳካልኝ እቆጥረዋለሁ። ለኢትዮጵያ የመፃፍ እዳ አለብኝ" ብሎ ይጨምራል።
ለጊዜው ሥነ ጽሑፍን በተመለከተ ሊያደርገው የሚችለው ነገር “ጥሩ መጽሐፍትን ማንበብ ነው።
ወደ ሥነ ጽሑፍ የመመለሱ ነገር ብዙም የሚከብደው አይመስለውም። ከዛሬ ሐያ ዓመት በፊት

389
ጥቋቁር አናብስት

የወጠናቸውን/የጠነሰሳቸውን ታሪኮች ዛሬም ያስታውሳል። “አብረውኝ ነው የሚኖሩት” ይላል።


ራሱን መግዛት ከቻለ መፃፍ እንደሚችል ይሰማዋል፤ይህንን ለማድረግ እንዲቻለው ይፀልያል። ነገር
ግን ነገሮችን ለረዥም ጊዜ እያስተላለፈ መቆየቱ ወደ አእምሮው እየመጣ ያስጨንቀዋል ፤ ከዚህ ጋር
በተገናኘ የሚወደው ደራሲ ሶመርሴት ሞም የአለምን ታሪክ ለመፃፍ ስለፈለገ አንድ ሰው የፃፈውን
አጭር ታሪክ ይጠቅሳል። ይህ ሰውየተንዛዛና ረዥም ዝግጅት አደረገ ፤ ጣሊያን ውስጥ ካፕሪ ላይ
ቤት ገዛ ፤ አሁን ለመፃፍ ዝግጁ ሆነ፤ይሁን እንጂ በሚቀጥለው ቀን ሞቶ ተገኘ። "ይሄ በኔ ላይ
እንዳይደርስ የዘወትር ፀሎቴ ነው"። አንድ ሰው ለመፃፍ የሚያስፈልገው ነገሮች ሁሉ እንዳሉት
ይሰማዋል―ሐሳብ፣ ተሰጥኦ፣ መነሳሳት፣ ግዴታን ማወቅ፣ ከጡረታ ሲገለል ደግሞ ጊዜውን
ያገኛል። ያለበት አንድ ጭንቀት የአይኑ ጉዳይ ነው። ደግሞም "ባለመፃፌ ጓደኞቼ ይጠሉኛል"
ይላል።

በአንድ ወቅት ብርሀኑ ዘርይሁን በሬዲዮ ቀርቦ ታደሰ ሊበን ሥነ ጽሑፍን የከዳው ለገንዘብ ብሎ
ነው ፤ ስለዚህ ባንክ ቤት መስራት ጀመረ ማለቱን ያስታውሳል፤ "ብዙዎች ባለመፃፌ ይወቅሱኛል"።
አንዳንድ ታሪኮቹ ከአብዮቱ በፊት ወደ ሩስኪ ተተርጉመዋል።አሁን ድረስ እንኳን ታደሰ ሊበን
መኖሩን ወይም መሞቱን ለማወቅ የሚፈልጉ ሩስያውያን አሉ። በ1964 ጣሊያን ውስጥ ፕሮፌሰር
ላንፍራኖ ሪቺ ስለሚተማመኑበት ወደ ኔፕልስ ወስደውት በጋዜጣቸው ላይ ስለ ታደሰ እና አፃፃፉ
ማስፈራቸውን ያስታውሳል።

በታደሰ ሊበን የቀደመ አፃፃፍ የሚደነቁ ሞልተዋል ፤ የመፃፍ ሀይሉ ከመዳከሙ ወይም ተሟጦ
ከማለቁ በፊት ዳግመኛ ብእሩን አንስቶ እንዲጽፍ የሚመኙም ብዙ ናቸው።

***

የሕይወት ታሪኩን ከላይ እንደተጠቀሰው ከነገረኝ ከብዙ ወራት በኋላ ለመፃፍ የበለጠ ጥድፊያ
እንዳደረበት ገለፀ። ስለ ሕይወቱና አላማው ከነገረኝ በኋላ ለመፃፍ የበለጠ ሳይነሳሳ፣ እንዲሁም
ህሊናው ይበልጥ ሳይቆረቁረው አልቀረም።

የተርጓሚው ማስታወሻ

ታደሰ ሊበን “መስከረምና፤ ሌላው መንገድ” በቅርቡ በድጋሚ የታተሙ ሲሆን የአጭር ልብወለድ
በመጻፍ ግን የተመስገን ገብሬ የጉለሌው ሰካራም ይቀድማል የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡

ማስታወሻዎች

390
ጥቋቁር አናብስት

1) በኢትዮጵያ ውስጥ ልጅ በማሳደግ በኩል ተረቶች ያላቸውን ሚና ለመገንዘብ


"Socialization and Social Control in Ethiopia" የሚለውን መጽሐፌን ተመልከቱ።

2) በኢትዮጵያ ደንብ መሰረት ሰዎች በሞቱበት ቀን ይቀበራሉ ፤ ወይም አመሻሽ ላይ ከሞቱ


በሚቀጥለው ቀን በጊዜ ይቀበራሉ።

3) ታደሰ የተወለደው በ1930ዎቹ የመጀመሪያ አጋማሽ ቢሆን ትምህርቱን የጀመረው ደግሞ


በአስር ዓመቱ በ1940/41 ቢሆን፣ ከሚያዝያ/ግንቦት 1941 በፊት 11 ዓመት ስለማይሞላው፣
በዚህ ወቅት የኢጣሊያ ወረራ አብቅቷል ማለት ይቻላል።

4) ኮተቤ አብሯቸው ከነበሩትና መንግስቱ ታሪኮችን ማታ ማታ እንዲያወራ ከማይፈልጉት መሀል


ኋላ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ሰርተው በኃይለሥላሴ መንግስት ውስጥ ሚኒስትር የሆኑት ምናሴ
ሐይሌ ይገኙበታል። “እንደ መንግስቱ የሐረር ሰው ሲሆኑ አብሮ አደጎች ነበሩ” ይላል ታደሰ።

5) በንጉሡ ዘመን ጎበዝ ተማሪዎችን ለአየር ኃይል መመልመል የተለመደ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ
ተማሪዎች የአየር ሀይልን ሊቀላቀሉም፣ ላይቀላቀሉም እንደሚችሉ ቃል ይገባላቸውና በፈቃደኝነት
የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ነገር ግን ያለፉትን እንዲቀላቀሉ ያስገድዷቸው ነበር።

6) በኢትዮጵያ ባህል መሰረት አዋቂዎች ሲጫወቱ፣ ህፃናት ዝም ብለው መስማት አለባቸው። ይህ


ልጅ ይህንን ህግ ለመተላለፍ መፍራቱ ቢጋነንም፣ ወላጆቹ በማይሰሙበት ወቅት ግን ለእንግዳው
ግልጽ ያደርግለታል።

7) የገለፀላቸው የስራ ቆይታዎች ተደማምረው ከ1951 እስከ 1964 መሀል ካሉት ዓመታት
ጋርልክ አይመጡም። አንዳንድ ስራዎች ላይ ከተባለው ጊዜ በላይ ቆይቶ ይሆናል። ይሁን እንጂ
ቀኖቹን እንደተነገረኝ አስፍሬያቸዋለሁ።

391
ጥቋቁር አናብስት

ሲራክ ኅሩይወልደሥላሴ
የአባቱ ልጅ እና አንድ መጽሐፍ ብቻተርጓሚ ብላታ ሲራክ በኢትዮጵያ
ወግና ደንብ መሰረት በአባቱ ስም በ“ኅሩይ” ብቻመጠራት ይበቃው ነበር።
ነገር ግን በራሱ ስም ላይየአባቱንና የአያቱን ስም ጨምሮ ሲራክ ኅሩይ
ወልደሥላሴ ተብሎ መጠራቱን መረጠ። ስመጥር አባት ሲኖሩህ ፣ደንብ
መሻር ይፈቀድልሃል። ከሲራክ መገለጽ የሚያሻው አስፈላጊ ነገር የአባቱ
ልጅ መሆኑ ነው። ሲራክ ከአባቱ የወረሳቸውን የሥነጽሑፍ ስራዎች ቅርስ
ጠብቆ በማቆየት፣ ከዳር በማድረስና በማሳተም፣ የአባቱ “የጽሁፍስራአስፈጻሚ” ሆኗል። የአባቱን
የኅሩይ ወልደሥላሴን ታሪክ ስጽፍ አብዛኛዎቹን መረጃዎች ያገኘሁት ሲራክ በጥንቃቄ
ካስቀመጠው ካልታተመው የአባቱ የቀን ውሎ ዘገባዎችና ማስታወሻዎች ሲሆን ሌሎች
ማስታወሻዎቹ በአደባባይ ቢታወቁም፣ ይሄኛው ግን ከሕዝብ አይን ተሰውሮ የተቀመጠነበር።1

ከአለቃገብረሃና ወዲህ እንደ ሲራክ በቀልደኝነቱ የሚታወቅ አንድም ኢትዮጵያዊ ደራሲ የለም።
ሁለት ቀልዶቹን ለአብነት ያህል እነሆ፦

አንድ ጊዜ ሲራክ በንጉሳዊ ቤተመንግሥት በተዘጋጀ ግብዣ በእንግድነት ተጋበዘ። ነገር ግን


በስርአቱና በደንቡ መሰረት ለብሶ ስላልመጣ በር ላይ እንዲገባ አልፈቀዱለትም። ስለዚህ ወደ ቤቱ
ተመለሰና ተሽቀርቅሮ መጣ። አሁን በሩ ወለል ብሎ ተከፍቶለት ገባ። ግብዣው ላይ ምግቡን
አንስቶ ልብሱ ላይ መለቅለቅና በየኪሶቹ መሞጀር ያዘ። ሰዎች ይህንን ሲያዩ መሳቅ ጀመሩ፤ ምን
እያደረገ እንደሆነም ጠየቁት። ሲራክም ተራ ልብስ ለብሶ ቢመጣ አናስገባህም እንደተባለ፣ ልብስ
ከቀየረ ወዲህ ግን በቀላሉ ስለተፈቀደለት፣ የተጋበዘው እርሱ ሳይሆን ልብሱ መሆኑን አስረዳ።
“ስለዚህ የተጋበዘውን ልብስ ከምግቡና ከመጠጡ እያቋደስኩ ነው” ብሎመልሷል።

በሌላ ጊዜ ደግሞ ንጉስ ኃይለሥላሴ እሱ በሚኖርበት የከተማ አካባቢ አቋርጠው እንደሚያልፉ


ሰምቶ ይጠባበቃል።በጌዜው የኢትዮጵያ መንግሥት 12 ሚኒስትሮች ነበሩት። ኃይለሥላሴ ሲደርሱ
ሲራክ 12 አህዮች ይዞ በመንገዱ ነዳ። ኃይለሥላሴ ይህንን ሲመለከቱ ቆሙና ሰላምታ ከሰጡት
በኋላ ምን እየሰራ እንደሆነ ጠየቁት።2ሲራክንጉሡ 12 አህያዎች ( ሚኒስትሮቹ) ስላሏቸው
የእርሳቸውን ፈለግ በመከተል12 አህያዎች እንዳሉት ለማሳየት መሆኑን ተናገረ ይባላል።

እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ታሪኮች አሉ። በሲራክ ስም የሚነገሩ ቀልዶች በሙሉ በትክክል የሱ


ባይሆኑም "ዋዘኛእናብልህ" በመሆኑ ከሰብዕናው ጋርይገጥማሉ።

392
ጥቋቁር አናብስት

ሲራክ ከወጣትነቱ ጀምሮ በተለይ ደግሞ ኦክስፎርድ ተምሮ ከመጣ ወዲህ አፈንጋጭ ነበር። ከዛ
በፊት በግብጽ፣አሌክሳንድሪያ ተምሯል።

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ሲራክን ያገኘው ስዊድናዊ ጸሐፊ “ሲራክ
በራሱ ህዝብ ኋላቀርነት ላይ የሚሳለቅ ግብዝ ነው” ሲል ትንሽ ቆይቶ ባሳተመው መጽሐፉ
አስፍሯል።ይኸው ጸሐፊ ሲራክ በራሱ ህዝብ መሳለቁና መዘባበቱ ልክ እንዳይደለና፣ ይህን
አመለካከቱን እስካልቀየረ ድረስ፣ ለቁምነገር አይበቃም የሚል አስተያየት ጨምሯል።

ብላቴንጌታ ኅሩይ ሁለት ወንድ ልጆች ነበሯቸው፤ ፈቃደስላሴ እና ሲራክ። ሲራክ በመጀመሪያ
ግዕዝ ለመማር ወደ ታላቁ የደብረሊባኖስ ገዳም ሄደ። ከዚያ በኋላ ወደ አዲስአበባ ተመልሶ
ሚስዮን ትምህርት ቤት ገባ። ቀጥሎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለመከታተል ከወንድሙ ጋር
አሌክሳንድሪያ ወደሚገኘው ቪክቶሪያ ኮሌጅ ሄደ።ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር ኅሩይ ወደ
እንግሊዝ ተሰደዱ። ሁለቱም ልጆቻቸው ወደ እንግሊዝ ቢከተሏቸውም የነሱ ምክንያት ግን
ለትምህርት ነበር።የሄዱትበ1928 ዓ.ም በሱዳን በኩል ሲሆን፣ ፈቃደስላሴ በካምብሪጅ ምህንድስና
ሲማር፣ ሲራክ ደግሞ በኦክስፎርድ ፍልስፍናን አጥንቷል።

ኢትዮጵያ በ1933 ዓ.ም ነፃ ስትወጣ ከንጉሡ ጋር ወደ ኢትዮጵያተመለሰ። ከጦርነቱ በፊት


ከተለያቸው ሚስትና ልጁ ጋርም ተገናኘ። ሚስቱ ወይዘሮ ወይንሸት በየነ፣ የተጉለት፣ የሞጃ ሰው
ናቸው። አባቷ የመራቤቴው አዣዥ በየነ፣ ከጥሩ ቤተሰብ የተገኙ ቢሆኑም የንጉስ ዘር ይቅርና
ከመኳንንት ወገን እንኳን አልነበሩም። ሰዎች ይህንን የሚሉት አንድ በተለምዶ የሚነገር አሉባልታን
ለማስተባበል ነው። ይህም አሉባልታ የሕሩይ እናት፣ ከሸዋው ንጉሥ ሳህለሥላሴ እናት ጋር
ዝምድና አላቸው የሚልነበር።

ኃይለሥላሴ በ1933 ዓ.ም ከእንግሊዝ እንደተመለሱ፣ ሲራክ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና
ጸሐፊ ሆኖ ተሾመ። በሹመኝነቱ ወቅት፣ ከብዙ ሚኒስትሮች በተለይም ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ
ከራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ጋር አይጣጣምም ነበር። ጉቦ መብላታቸውን፣ ጉዳዮችን
በቀጠሮ እያሳደሩ ሰው ማጉላላታቸውን፣ ለሰዎች ቀጥተኛ ውሳኔ እና መልስ በመስጠት ፋንታ
በኢትዮጵያ አሁን ድረስ እንደተለመደው “ነገ፣ተመለስ!” እያሉ የሰዎችን ጊዜ ማቃጠላቸውን ፣ሁሉ
ይጠላል።

ከጊዜ በኋላ ሲራክ ከመንግስት ስራ እንዲሰናበት በጠየቀው መሰረት ተፈቀደለት። ከዚያ በኋላ
ይተዳደር የነበረው እሱም፣ ሚስቱም ከወላጆቻቸው በወረሱት መሬት እና ከሚያከራያቸው ቤቶች
በሚገኘው ገቢ ነበር።

393
ጥቋቁር አናብስት

ከኢትዮጵያ ድንበር ባሻገር ሁለተኛው የአለም ጦርነት አሁንም ገና እየተቀጣጠለ በነበረበት ወቅት
ሲራክ የእንግሊዝ ኢምባሲ የፕሬስ መኮንን ከነበሩት ሚስተር ዱልፍስ ሞልስዎርዝ ጋር ተዋወቀ።
ይህ ቢሮ በኢትዮጵያ“ ወደ ድል ጎዳና” የሚል ህትመት ማዘጋጀት ጀመረ። ሲራክ በሚስተር
ሞልስዎርዝ3 ስር ሆኖ፣ መጣጥፎችን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ይተረጉም ነበር። ሌላው
ኢትዮጵያዊ አቶ በዕደማርያም ደግሞ ለሲራክ ጸሐፊ ወይም ረዳት፣ ለሚስተር ሞልስዎርዝ ደግሞ
አስተርጓሚ እንዲሆን ተቀጠረ። አቶ በእደማርያም የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የአስረኛ ክፍል
ምሩቅ እና ብዙ የቤተክርስቲያን ትምህርት የነበራቸው ሰው ነበሩ። አቶ በእደማርያም የሲራክን
ግርድፍ ረቂቆች በእጅ ገልብጠው፣ ቋንቋውን አቃንተው ወደ ማተሚያ ቤት ይልካሉ። የሳሙኤል
ጆንሰንን ራሴላስ ወደ አማርኛ ቋንቋ እንዲተረጉም ሲራክን የገፋፉት ራሳቸው ሚስተርሞልስዎርዝ
ሲሆኑ፣ በዚህ መሰረትትርጉሙ በመፃፍ መልክ ከመውጣቱ በፊት፣ በዚሁ መጽሔት ላይ
በተከታታይ ይወጣ ጀመር። እንደተለመደው ሲራክ በግርድፉ ተርጉሞ ረቂቁን ካዘጋጀ በኋላ አቶ
በዕደማርያም ለህትመት እንደሚሆን አድርገው ያስውቡታል። መጽሐፉ ጀርመንና ኢጣሊያ
ከተሸነፉ በኋላም ተተርጉሞ በጋዜጣው መቅረቡ አልቀረም፤ ብቻ የጋዜጣው ስም ተቀይሮ “ጊዜ
የወለደው” ተባለ።ጋዜጣው የሚታተመው ከተቀረው ኤርትራ ጋር በእንግሊዝ ስር በነበረችው
አስመራ ነበር።

ሙሉ መጽሐፉ በጋዜጣው ላይ በተከታታይነት ሲተረክ ቆየ በኋላ፣ ሲራክ እያንዳንዱን ክፍል


ሰብስቦ በመጽሐፍ መልክ ጠርዞት በአዲስአበባ ታተመ።

ሚስተር ሞልስዎርዝ “ራሴላስ” እንዲተረጎም በማድረግ ብቻ ሳይወሰን በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ላይ


ፍላጎት አሳደረ። እንደ "ክብረነገስት" ያሉ ጥራዞችንና ሌሎችንም እንዲባዙ እያደረገ ያሰባስብ ነበር።
ሁለተኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ትንሽ ቆይቶ ሚስተር ሞልስዎርዝ ወደ ሀገሩ
ተመለሰ። እሱ ከሄደ በኋላ ሲራክ ወደ ድሮ ስራው ተመልሶ የቤተሰቡን ንብረት እያስተዳደረ፣
ኑሮውን ከዚያ በሚያገኘው ገቢ መምራቱን ቀጠለ። ሕይወቱ እስከሚያልፍም በዚሁ ግብር ቆየ።
ነገር ግን ከ 1966 አብዮት በኋላ መንግስት ባለቤቶቹ የማይጠቀሙበትንና የማይኖሩበትን ትርፍ
ቦታ በመውረሱ፣ ሲራክ ያለ ምንም ስራና የገቢ ምንጭ ቀረ።

ሚስተርሞልስዎርዝ ወደ ሀገሩ ከመመለሱ በፊት ሌላኛውን ረዳቱ አቶ በዕደማርያም በብሪቲሽ


ካውንስል ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ቢያስቀጥረውም ኋላ ላይ በዐደማርያም በኢትዮጵያ ፖለቲካ
በመበሳጨቱ የግራ ዘመም የፖለቲካ ክንፍን ተቀላቀለ። ያኔ ይህ የፖለቲካ መስመር ፋሽን ሊሆን
ይቅርና ገና በቅጡ እንኳን አይታወቅም። በዚሁ ጦስ አስራ ሁለት4 ዓመት ሲታሰር5፣ ከግራ
ዘመምነቱም ሙሉ ለሙሉ ተፈወሰ። ሲለቀቅ ሲራክን ሊጠይቀው መጣ። ሲራክም 50 ብር
ሰጠውና ደግሞ እንዲጠይቀው አሳሰበው። በዕደማርያምም በተደጋጋሚ እየመጣ ሲራክን የጠየቀው
394
ጥቋቁር አናብስት

ሲሆን ሲራክም ዘወትር እንዲህ እያለ ይመክረው ነበር፦“አፍህን ያዝ፤ሁለተኛ ፖለቲካ ውስጥ
እንዳትገባ!” በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ሲራክ የሚታወቀው የሳሙኤል ጆንሰንን "ራሴላስ"
ወደ አማርኛ ቋንቋ በመተርጎሙ እና የአባቱን አንዳንድ ስራዎች በማሳተሙ ነው። በነገራችን ላይ
ሳሙኤል ጆንሰን "ራሴላስ"ን በ1751 ዓ.ም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የፃፈው የእናቱን ቀብር
ወጪ ለመሸፈን ነበር።አንዳንዶች ሲራክን እንደ ፈላስፋ ይቆጥሩታል። ነገር ግን በሀገሩ ባህል እና
ፖለቲካ ላይ ይህ ነው የሚባል ተጽእኖ አልፈጠረም።

ሲራክ በ1980ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ሞተ። ስለ ሲራክ ብዙ ያውቃል ተብሎ የሚገመት


ባለሥልጣን ስለ ሲራክ ብጠይቀው “ሲራክ ምንም ረብ ያለው ሰው አልነበረም” ብሎ
መልሶልኛል። ሲራክ ያለውን እምቅ ችሎታ አልተገነዘብውም ይሆናል። ወይም ደግሞ አውቆት
ለሀገሩ በሚበጅ መልኩ አልተጠቀመውም። ሲራክን የሚያውቁት አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ግን
“ሀሳባዊ” እና “እጅግ ቅን” ሰው ነበር፤ ለዚያም ነው ከኃይለሥላሴ ባለሥልጣኖች ጋር የፖለቲካ
ቁማር መጫወትያልቻለው።እንደውም ለንጉሡ አገዛዛቸውን ካልቀየሩ አብዮት እንደሚነሳ ሁሉ
ነግሯቸው ነበር ይባላል። የመንግሥት ስልጣኑን የለቀቀውም ለዚህ ዐይነቱ ፍፃሜ ሰለባ ላለመሆን
ነው ተብሎ ይነገራል። ይህ በእርግጥ አርቆ አስተዋይነት ነው፣ ጀግንነት መሆኑን ግን እንጃ።

ማስታወሻዎች

1) የኅሩይን ታሪክ ከፃፍኩ በኋላ የሕይወት ታሪካቸው ታትሞ ወጣ። ደራሲው ይህንን ማስታወሻ
አግኝቶት ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ እኔ መጽሀፉን አላነበብኩትም።

2) ኃይለሥላሴንም ሕሩይንም ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎችሕሩይ ለእርሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው


በሰጡት ግልጋሎት ኃይለሥላሴ የሕሩይ ቤተሰብ እዳ እንዳለባቸው ሁሌም ይሰማቸው ነበር
ይላሉ።

3) የተወለደው ተጉለት ውስጥ በወደራና ሞጆ ወረዳ ነው። አባቱ አለቃ ሲሆኑ ያሳደጉት አጉቱ
ተጉለት ውስጥ ኤጲስ ቆጶስ በኋላ ደግሞ የወለጋ ጳጳስ ሆነዋል። ምሁር፣ጸሐፊ እና ሰአሊ የነበሩ
ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ እንደ ቅዱስ ሰው ይቆጥሯቸዋል።

4)አብዛኛውን ጊዜ የኖረው ተንታ፣ ወሎ ውስጥ ገረድም፣ ውሽማም ቢጤ ከሆነች ሴት ጋር በጎጆ


ውስጥ ነው።ኑሮው "የቁም እስር" ዐይነት ሆኖ የሚኖርበትን ቦታ የወሰነለትም መንግስት ሲሆን፤
ለፖሊስም በየጊዜው እየሄደ አለሁ ማለት ይጠበቅበት ነበር።

395
ጥቋቁር አናብስት

5) ፖሊስ እሱ የነበረበት ስብስብ ላይ ደርሶ እጅ እንዲሰጡ ሲያስጠነቅቅ እጁን ሰጠ። አብዛኛዎቹ


ሲያመልጡ፣ በዕደማርያም ብቻ ተማረከ። ኃይለሥላሴ ሌሎቹ ቀደምት ነገሥታቶች ያደርጉት
እንደነበረው ስላላስገደሉት ሰብአዊነት የሚሰማቸው ሰው ናቸው ተብሎላቸዋል ። ተቀጥሮ
እንዳይሰራ ቢከለከልክም በኋላ ስሙን ቀይሮ ብዙ ስራ እየቀያየረ ሰርቷል። ያልታተሙ ግጥሞችና
ለትምህርት ሚኒስትር የሚሆኑ ጥቂት መጽሀፍትንም ጽፏል።

396
ጥቋቁር አናብስት

በዓሉ ግርማ
"የሥነ –ጽሑፍ አድባር" "ለመፃፍ የተወለደ" እና "ለፃፈው
የተሰዋ" ደራሲ፣ ጋዜጠኛ እና ሰማዕት

በ1982ዓ.ም በዓሉን አግኝቼው ስራዎቹንና ሕይወቱን የበለጠ


እንድረዳቸው የሚያስችለኝ መረጃ ለማግኘትቃለ መጠይቅ
ላደርግለት እንደምፈልግ ስገልጽለት በቀላሉ ተስማማ ፤ ታዲያ
ምንም እንኳን በወቅቱ ጥቂት ብንነጋገርም፣ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ስመጣ (በጊዜው ኬንያ ኗሪ
ነበርኩኝ) ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ብናደርግ እንደምመርጥ ነገርኩት። በጊዜው ሁለት ረቂቆች ላይ
ጠንክሮ እየሰራ እንደነበር ስለማውቅ፣እስካገኘው ድረስ ሌሎች ብዙ ጥሩ መጽሀፍት ይሰጠናል
የሚል እምነት ነበረኝ። ይሁን እንጂ "መዘግየቴ" ፀፀተኝ ፦ ምክንያቱም በ1984 ተመልሼ ስመጣ
በአሉ ጠፍቷል ፤ እምጥ ይግባ ስምጥ የሚያውቅ አንድ ሰው እንኳን አልተገኘም። በአሉን ደህና
አድርገው የሚያውቁት ሰዎች እንኳን ስለሱ ለመናገር ፈቃደኛ አልነበሩም፤ ጉዳዩ ትልቅ "የፖለቲካ
ጉዳይ" ነው። ስለዚህ ስለበአሉ ከራሱ አንደበት ተረድቼ በምፈልገው መጠን እና ስፋት እዚህ
ልገልጽ አልችልም። ከአፉ የለቃቀምኩት ጥቂት ነገሮች ሙሉ "ምስል" አይሰጡንም፤በተቀረ ስለሱ
ከዚህም ከዚያም የሰበሰብኳቸው ቁርጥራጭ መረጃዎች ከብዙ አቅጣጫዎች የመጡ ናቸው (
አብዛኞቹ በ1986 ሌሎቹም በኋላ―በ1991 እና በ1995 የተገኙ)

በብዙዎች አስተያየት በአሉ ግርማየኢትዮጵያ ቁንጮ ደራሲ ነው። ሌሎች ደራሲዎች የትኛውንም
የበአሉን "ነጠላ ስራ" የሚያስከነዳ አንድ "ነጠላ ስራ" ደርሰው ይሆናል ፤ ነገር ግን በአጠቃላይ
ሲታይ ኢትዮጵያ እንደ በአሉ በተከታታይ አቅሙን ያስመሰከረ ድንቅ ደራሲ አላፈራችም። ሌሎች
ደግሞ በአሉን ከሌሎች ጸሐፊዎች ጋር ያስተካክሉታልወይም አንድ ወይም ሁለት ከእሱ የተሻሉ
ደራሲዎች እንደሚኖሩ ያስባሉ። የሆነው ሆኖ የኔ አላማ ስራዎቹን መመዘን ሳይሆን የምችለውን
ያህል ስለ ሕይወቱ መረጃ መስጠት ነው።

***

በአሉ ግርማ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ፣ በኢሉባቡር ክፍለሀገር ውስጥ በምትገኝ ሱጴ የተባለች
ትንሽ ከተማ ተወለደ ( ሱጴ የበአሉ ሁለተኛ ልብወለድ መቼት ነች።) የበአሉ እናት "የአካባቢው
ተወላጅ፣ ምናልባት ኦሮሞ" ሳይሆኑ አይቀርም። አባቱ በሕንድ የጉጂራት ተወላጅ ሲሆኑ፣ ወደ
397
ጥቋቁር አናብስት

ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት እዚያው ሕንድ አግብተው የወለዱ አናፂ ነበሩ። አባትየው
የሒንዱ እምነት ተከታይ እንደመሆናቸው ከጋብቻውጪ ልጅ መውለዳቸው"በሃይማኖቱ
የሚፈቀድ" አልነበረም፤የበአሉ መወለድም እንደ "ክፉ አጋጣሚ" ይቆጠር ጀመር። የአባቱ ስም ባቡ
ይሰኛል። ከቤተሰቡ ተለይቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ገና ወጣት የነበረ ሲሆን በአሉ ነፍስ ሳያውቅ
ወደ ህንድ ተመልሷል።

በአሉ ስሙን እንዴት እንዳገኘ በውል ባይታወቅም፣ ከአባቱ ስያሜ ጋር ተዛምዶ ሳይኖረው
አይቀርም። ከብዙ ዓመታት በኋላ በአሉ ለስራ ሕንድን ሲረግጥ፣ አባቱን ለማግኘት ወይም ስለአባቱ
ለማወቅ ቢሞክርም አልተሳካለትም።

በአሉ ለእናቱና አባቱ ብቸኛ ልጅ ነው። በኢትዮጵያ ባህል መሰረት በአሉ ግርማ ሳይሆን በአሉ ባቡ
ተብሎ መጠራት ነበረበት። ግርማ ያሳደጉት አያቱ፣ የቅርብ ዘመዱ ወይም እንጀራ አባቱ ሊሆኑ
ይችላሉ። እንደዚህ ዐይነት ነገሮች ያልተለመዱ አይደሉም። በአሉ በእናቱ በኩል ብዙ ወንድሞች
ስላሉት (እነ መሰለ ግርማ) አቶ ግርማ የእናቱ ሁለተኛ ባል፣ የእንጀራ አባቱ መሆናቸው ብዙም
አያጠራጥርም። ስለዚህ በአሉ በእንጀራ አባቱ እጅ አድጓል።

በአሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በኢሊባቡር1 ከተከታተለ በኋላየሁለተኛ ደረጃ


ትምህርቱንበአዲስ አበባ ጥሩ በሚባለው ዊንጌት ትምህርት ቤት ስለገባ ጎበዝ ተማሪ ነበር ለማለት
ያስደፍራል። በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አራት ዓመት አጥንቶ የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኘ።
ቀጥሎ ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዞ በጋዜጠኝነት የሁለተኛ ዲግሪውን ካገኘ በኋላ፣ በማስታወቂያ
ሚኒስቴር በ1984 እ.ኤ.አ "እስከጠፋበት ጊዜ"ድረስ አገልግሏል።

በ1960 ዓ.ም በአሉ ግርማ ከኃይለሥላሴ መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ ነበር። በዚህ
ምክንያትለስድስት ወራት ያህል ከስራ "ታገደ"። በጋዜጠኝነት ሙያው ግን ብርቱ በመሆኑ
ከአብዮቱ ፍንዳታ2 ከ1966 በፊት የመነን፣ የአዲስ ሪፖርተር፣ እንዲሁም የአማርኛው አዲስ ዘመን
አዘጋጅ ሆኖሰርቷል። በአሉ በሶስቱም ጋዜጦች ቅርጽ እና ይዘት ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣቱ
ይነገርለታል።

በአሉ ሁለት ዝነኛ ልብወለዶቹ “ከአድማስ ባሻገር” እና “የሕሊና ደወል” የፃፈው ገና ከአብዮቱ
በፊት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አዘጋጅ እያለ፣ነው።ሁለተኛው ልብወለድ "ተራማጅ" እና "አብዮት
ናፋቂ" ሴማዎች ስላሉት ከ1966 የአብዮት ነፋስ ጋር በደንብ እንዲነፍስ አስችሎታል። በእርግጥ
ከአብዮቱ በፊት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እያለ፣ በጋዜጣው የሚወጡ መንግስትን

398
ጥቋቁር አናብስት

የሚደግፉ ርእሰ አንቀፆች ፀሐፊ እርሱ ነው ተብሎ በመታመኑ፣ "አፍቃሪ አፄ" ነው ተብሎ ይታማ
ነበር። ነገር ግን እንደሚባለው፣ በአሉ እንደዚህ ዐይነት ርእሰ አንቀጾችን አልፃፈም ፤ እንደውም
አፄውንና አስተዳደራቸውን በግልጽ በመቃወሙ ከላይ እንደተገለፀው ከስራ ታግዷል። ይሁን
እንጂብዙዎች ስለ ፖለቲካ ዝንባሌዎቹ ያላቸው "ጥርጣሬዎች" በዩኒሸርስቲም ሆነ ሌሎች
አካባቢዎች በጥርጣሬ እንዲታይ ምክንያት ሆነውበታል። በሌላ በኩል ደግሞበአሉ ሥልጣን
ያላቸው ጓደኞችና ወዳጆች ነበሩት።

ከአብዮቱ በኋላ በአሉ ከወቅቱ የሃገሪቱ መሪመንግስቱ ሐይለማሪያም ጋር ቅርበት ፈጠረ።


"የሊቀመንበሩን" ንግግሮችና የፖሊሲ ሀተታዎችን ለእሳቸው መፃፍ፣ ከስራዎቹ ዝርዝር መሐል
ይገኙበታል። የኤርትራው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዕስከሚፈጸም ድረስም የቅርብ አማካሪያቸው ነበር።
በዚህ ዘመቻ ወቅት ሊቀመንበሩ በአሉን ከሚኒስትሮቻቸውና ከአማካሪዎቻቸው ጋር ወደ ኤርትራ
ይዘውት ሄዱ። በአሉ "የቀይ ኮከብ ጥሪ" የተሰኘ ልብወለዱን የፃፈው ከዚህ ዘመቻ በፊት ሲሆን፣
ዘመቻውም ስያሜውን ያገኘው ከዚህ ልብወለድ ነው። በኤርትራ ቆይታቸው ወቅት፣ በአሉ እና
ሊቀመንበሩ በየለቱ ይገናኛሉ ። በአሉ የመጨረሻው ልብወለዱን "ኦሮማይ"ን የፃፈው በዚሁ ዘመቻ
ወቅት ነው ። ኦሮማይ ቃሉ የኤርትራ ጣሊያንኛ ሲሆን ትርጉሙም "ተፈፀመ" ማለት ሳይሆን
አይቀርም።

ከዚህ በፊት በአሉ በስራው የላቀ ደረጃ ላይ ደርሷል። በ1974 እ.ኤ.አ አዲስ ዘመንን ለቆ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነ። በ1969 ዓ.ም የወቅቱ ርእሰ–ብሔር
ተፈሪ በንቲ ከተወገዱ በኋላ፣በማስታወቂያ ሚኒስቴር ቋሚ ፀሐፊ/ተጠሪ?/ሆኖ፤ነበር።ተፈሪ በንቲ
በተወገዱ ጊዜ ቋሚ ፀሐፊ/ተጠሪ/ የነበረው ሰው ለብዙ ዓመታት እስር ተዳረገ።4 ከእሱ በኋላበዓሉ
የኃላፊነቱን ስፍራ ተረከበ።በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ባለመኖሩም፣ በዓሉ ሥልጣኑንም፣
ተግባሩንም በመረከብ የማስታወቂያ ሚኒስቴርን የአስተዳደርና የፖለቲካውን ስራ ደርቦ መስራት
ያዘ።ትልቅ ስልጣንና ሐላፊነት ስለነበረው በዚያው ልክ ብዙ ጠላት አፈራ፤ከነዚህ መሐል ጎሹ ሞገስ
(እስከ 1986 የሳንሱር ሀላፊ የነበረ)፣ እምሩ ወርቁ ( በኋላ የአዲስ ዘመን ዋና አዘጋጅ የሆነ)፣ ፀሐይ
ደባልቀው (በኋላ የኢሠፓአኮ ዋና ፀሐፊ የሆነና ቀጥሎ ም "እስር ቤት የተወረወረ")፣ ገዳሙ
አብርሃ ( የማስታወቂያ ሚኒስትር አማካሪየሆነ፣ ስልጣኑን ውጭ ሀገር ሄዶ እንኳን ያስጠበቀ፤
የበአሉ ጠላቶች "አስተባባሪ" እንደሆነ የሚወራለት፤የበአሉ ተቃዋሚዎች "ፊታውራሪ")5 ገዳሙ
አብርሃ በግልጽም፣ በስውርም የኤርትራ ነፃነት ግንባርን በመደገፍም ይታማል፤በአሉም ይህን
ያውቃል። የሳንሱር ክፍል ኃላፊነቱን ገዳሙ አብርሃ የተሾመው ጎሹ ሞገስ የኢሕአፓ አባል መሆኑ
ይወራል። እምሩ ወርቁ በሌላው ህቡ ዕቡድን በ"ኢጭአት" አባልነት ይጠረጠራል። በአሉ "ከነዚህ
399
ጥቋቁር አናብስት

ሰዎች ጋር ከባድ ግጭት ውስጥ ነበር" በአሉ እንደ ሊቀመንበሩ የሰደድ አባል ሲሆን ( በደርግ ጊዜ
ሚኒስትር የነበሩ ሰው እንደነገሩኝ ሊቀመንበሩ ሰደድን ሲመሰርቱ በአሉ ተባባሪ ነበር)። ከላይ
የተጠቀሱት የበአሉ ጠላቶች ኋላ ሰደድን ቢቀላቀሉም፣ "በአሉ እንደ እውነተኛ የሰደድ አባላት
ስላልተቀበላቸው"፣ እርስ በእርስ ይጣሉ ጀመር። በአሉ ብዙ ጠላቶች ለማፍራት እስከመድፈር
ያደረሰው ከሊቀመንበሩ ጋር ያለውን ቅርበት ተማምኖ፣ እሳቸው ይጠብቁኛል ብሎ ገምቶ ነው
ተብሎ ይታመናል። ከላይ የጠቀስኳቸው ሚኒስትር ጨምረው እንደነገሩኝ፣ በአሉ በፖለቲካ
ሰውነቱ ይበልጥ የማደግ ብርቱ ምኞት ነበረው።

በአሉ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ እያለ፣ግርማ ይልማ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው፣ ጠላቶቹ
ከሳቸው ጀርባ ተሰባሰቡ፤ስለዚህ በዚህ መስሪያ ቤት በአሉ ብቻውን ጠላቶቹን ለመጋፈጥ ተገደደ።
6
በዚህ ወቅት ነበር በአሉ ስልጣኑን እና ክብሩን ለማስጠበቅ፣ በልብወለዶቹ አማካይነት መታገል
የጀመረው። በ"የቀይ ኮከብ ጥሪ" ልብወለዱ በማስታወቂያ ሚኒስትር የሚገኙ "የቤቱ ውስጥ
ጠላቶቹን"ታግሏል፤የመጽሐፉ አብዛኛዎቹ ገፀ ባህሪያትምበማስታወቂያ ሚኒስቴር ከሚገኙ ሰዎች
የተቀዱ ናቸው። ከዚህ በኋላ በቀጣይ"ሐዲስ"፣በኃላ "የሕሊና ደወል" የተሰኘ ልብወለዱን
አስፋፍቶና አሳድጎ መጣ። ብዙዎች እንደሚስማሙበት"ሐዲስ" የበአሉ ግርማ ቁንጮ ስራ ነው።
በመጀመሪያው ስድስት ወር ብቻ 10,000 ቅጂዎች ሲሸጥ፣ይሄም በኢትዮጵያ ገበያ ትልቅ የሚባል
ነው።

"ደራሲው" በተሰኘው ተከታይ ልብወለዱ በአሉ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የተንሰራፋውን ንቅዘት


ተዋግቷል። የመጽሐፉ ዋና ገፀ ባህሪ ደራሲ ሲሆን በብዙ ንቅዘትና ሸፍጥ የተተበተበ አለም ውስጥ
እንደሚኖር ሆኖ ተቀርጾአል።ልብወለዱ በሥነ ጽሑፍ አለምም ሆነ፣ በንግድ፣በመኖሪያ ቤት
እጦትም ሆነ ( በጊዜው መንግስት ይህንን ሁሉ ይቆጣጠር ስለነበር)―በሌላም ረገድ አብዮቱን
ተከትለው እየተንሰራፉ የመጡትን እኩይ ሁኔታዎችን አንጸባርቋል።

እንደውም የልብወለዱ ዋና ገፀ ባህሪ ሲራክ በእውኑ አለም ያለ ሰው ነው፦ የበአሉ ጓደኛ፣ራሱም


ደራሲ የሆነው ስብሃት ገብረእግዚአብሔር የሚባለው የበዓሉ ጓደኛ ነው7። በመጽሐፉ ውስጥ
በአብዮቱ ግራ የተጋባ እና የተሸበረ ሰው ሆኖ ተገልጿል። በእውኑ አለም ስብሐት ከኃይለሥላሴ
የገንዘብ ሚኒስትር ከይልማ ደሬሳ ልጅ ከሆነችው፣ከሀና ጋር ተጋብቶ ይኖራል። አብዮቱ ሲፈነዳ ሀና
አንድ ልጃቸውን ይዛ መሰደዷ ስብሐት ላይ ከባድ ተጽእኖ እንዳሳረፈ ይወራል። ከዚህ በኋላ
የስብሐት ንብረት በመንግስት ሲወረስ፣ እንደተነገረኝ ከሆነ፣ ስብሐት አንዲት ተራ “ሴተኛ አዳሪ”
“አግብቶ” ሶስት ልጆችን ወለደ። ስብሐት ጫት አብዝቶ የሚቅም፣ ለአለባበሱም ብዙ የማይጨነቅ
400
ጥቋቁር አናብስት

ሆነ ።8 ይህንን ማስታወሻ በምጽፍበት በ1978 ዓ.ም የመንግሥት ንብረት በነበረው ኩራዝ


አሳታሚ ድርጅት በአርታኢነት ተቀጥሮ በወር ከ1,000 ብር በላይ ደምወዝ ያገኝ እንደነበረ
የሚያውቁ ሰዎች ነግረውኛል። በአሉ ስብሐትንም ሆነ፣ ሕይወቱን አበጥሮ ያውቅ ነበር።
የ"ደራሲው" ታሪክ መጀመሪያ ሚስቱ ጥላው ከሄደች በኋ ላይ ጀምርና ከዚያ በኋላ የሚገጥመውን
የተመሰቃቀለ ሕይወት ያሳያል። ስብሐት እንደዚህ ሆኖ በመቀረፁ በመቀየም ፈንታ፣ ጭራሽ በአሉን
"እስከማምለክ" ይደርስ ነበር ይባላል፣ ምንም እንኳን ቃሉ ጓደኝነታቸውን ከልክ በላይ ያጋነነ
ቢመስልም። በአሉ ይህንን መጽሐፍ የፃፈው የሚያከብረው እና የሚያደንቀው ጓደኛውን ለመርዳት
ነው ተብሎ ይወራል፤ስብሐትን ከስቃይ ሕይወቱና ከአፈንጋጭ የኑሮ ዘይቤ የሚያላቅቀውን
የሞራል ድጋፍ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ ነው ይባላል። ስብሐት በዚህ ልብወለድ "ደራሲው"
ቢሆንም በወቅቱ አንድም መጽሐፍ አላሳተመም፤በእርግጥ በመጽሔቶች ላይ ይጽፋል፤ እንዲሁም
በአንድ ወቅትም የመነን9 ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።ቁም ነገር መጽሔት በአብዮታዊው መንግሥት
ከመታገዱ በፊት በዝግጅትና በፀሐፊነት ይሰራ ነበር።ብዙ ልብወለዶችን ቢጽፍም፣ "ወሲብ
ቀስቃሽ" ተብለው በመፈረጃቸው አንዳቸውም በኢትዮጵያ ሊታተሙ አልቻሉም። በአሉ
አስተያየቱን ለመስማት የድርሰቶቹን ረቂቅ ለስብሃት ይሰጥ ነበር። አንዳንዶች ስብሐትን
"ባለተሰጥኦ" ነው ቢሉትም፣ ሌሎች ደግሞ በስራ ረገድ "ተስፋ የለውም" ይላሉ (ከቀጣሪዎቹ
አንዱን ማነጋገር ችዬ ነበር)። በጣም ያነባል ፤ ደሞዝ ከተቀበለ በኋላ ግን ስራውን እርግፍ አድርጎ
ይተውና ብሩን የትም ይበትናል ይላሉ አንዳንድ ሰዎች። ነገር ግን "በጣም ግሩም ሰው መሆኑም"
ይነገራል። እነኚህን መረጃዎች ያሰባሰብኩት ስብሐት ራሱን በአካል አግኝቼ ከማነጋገሬ በፊት
ከሌሎች ሰዎች ባገኘሁት መረጃ ላይ ተመስርቼ ነው። በስብሐት አይኖች ሲታይ ታሪኩ ሌላ መልክ
ይይዛል ( ስለ ስብሐት የሕይወት ታሪክ በዚህ መጽሐፍ የፃፍኩትን ይመልከቱ)

***

ለሕይወቱ መጥፋት ምክንያት የሆነውየበአሉ የመጨረሻ መጽሐፍ፣ "ኦሮማይ" ነው። ኦሮማይ


የሚለው ቃል "ሀዲስ" በተሰኘው ቀደምት የበአሉ መጽሐፍ ላይ በአንድ ኤርትራዊ አፍ ይነገራል።
ብዙ ኦሮማይ ውስጥ የሚገኙ ሀሳቦች "ሀዲስ" ላይ ተነስተዋል።

ኦሮማይ የተፃፈው በቀይ ኮከብ ጥሪ ዘመቻ ወቅት በአሉ ከሊቀመንበሩ ጋር በቅርበት እየሰራና
በተደጋጋሚ እያገኛቸው ኤርትራ ውስጥ በቆየባቸው ሶስት ወራትነው። ስለዚህ ሊቀመንበሩ ስለ
መጽሐፉ መነሻ ይዘት በጥቂቱ ከማወቃቸው ባሻገር እንዲያውም የመጽሐፉን ሀሳብ ተቀብለውትም

401
ጥቋቁር አናብስት

ሊሆን ይችላል፤ባይስማሙበት ኖሮ በአሉ መጽሐፉን ማሳተም ባልቻለ ወይም እንዲያሳትም


ባልተፈቀደለት ነበር።መጽሐፉ ከታተመ ሊበቀሉት ወደኋላ የማይሉ ብርቱ ጠላቶችን እንደሚያፈራ
ሳያውቅ መቼም አይቀርም። ምናልባትም በመጽሐፉ ውስጥ "ሰውዬው" እያለ የሚጠራቸው
ሊቀመንበሩ መከታ ይሆኑኛል ብሎ አስቦ ይሆናል። በአሉ በቀደሙት መጻሕፍቱ ጠላቶቹን ተንኩሶ
በሰላም ማምለጥ ችሎ ነበር ፤ከዚህም የተነሳ“ኦሮማይ”ን በጻፈበት ወቅት፣ የወታደራዊ ደርግን
አመራር አባላት ሳይቀር እስከማጥቃት የደረሰ በራስ መተማመን አድሮ በት ሊሆን ይችላል።10

በአሉ ግርማ ካሁን ቀደም መጽሐፍቱን የግል አሳታሚ በሆነው በኢትዮጵያ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ
ፕሬስ ይዞታን በወረሰው የኢትዮጵያ መጽሐፍት ማእከል አሳትሟል። የኦሮማይን ረቂቅ መጀመሪያ
የሰጠው ለነሱ ነበር። ነገር ግን በአሉ እንደሚለው ረቂቁን የሰጠው አንድ አርታኢ ከነሱ ይልቅ
የመንግሥት ንብረት ለሆነው ኩራዝ አሳታሚዎች11 እንዲያሳይ መከረው ፤ በአሉም ምክሩን
ተግባራዊ አደረገ። የኩራዝ ስራ አስኪያጅ ረቂቁን ገና በለጋነቱ አስመራ ላይ አንብቦታል። ኩራዞች
ረቂቁን እንዳገኙ፣ ቦርዳቸውን እንኳን ሳያማክሩ በችኮላ ወደ ማተሚያ ቤት ወሰዱት። በተለመደው
አሰራር መሰረት አንድ መጽሐፍ ከመታተሙ በፊት የቦርዱን ይሁንታ ማግኘት አለበት።12 ከቦርድ
አባላቱ መሐል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ የነበሩት አቶ ደበበ ሰይፉ መጽሐፉ እየታተመ
መሆኑን ሰምተው፣ ስርአቱን ያልተከተለውን አካሄድ ተቃውሙ።ስለዚህ እኚሁ የቦርድ አባል፣
መጽሐፉን አንብበው፣ አስተያየታቸውን እንዲሰጡና፣ መጽሐፉም ለቦርዱ እንዲቀርብ ተወሰነ። አቶ
ደበበ ረቂቁን ካነበቡ በኋላ በተለይ ይዘቱ ላይ መሰረታዊ "ስህተቶች" እንዳሉበት በመግለጽ፣ ኩራዝ
መጽሐፉን ከማሳተሙ በፊት ስህተቶቹ መስተካከል እንዳለባቸው ገልፀው አስተያየታቸውን ለቦርዱ
ፃፉ።የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ ዳኛቸው ወርቁ በዚህ አስተያየት ከመናደዳቸውም በላይ(
እንደተነገረኝ ከሆነ) እነዚህ አስተያየቶች ግምት ውስጥ ከገቡ፣የበዓሉ መጽሐፍ እንዳይታተም
ውድቅ ሊያስደርጉት ይችላሉ ብለው ተናገሩ።13ከዚያም ቦርዱ፣ ሊቀመንበሩ ረቂቁን እንዲያነቡ
ጥያቄ አቀረበ፤ሊቀመንበሩም አንብበው አስራ አምስት ገጽ ሪፖርትፃፉ። ከበአሉ ጋር ከተነጋገሩበት
በኋላ በአሉ አንዳንድ ለውጦችን ለማድረግ ተስማማ ፤ ሌሎች ማሸሻያዎችን ውድቅ ያደረገበት
ምክንያት ግን የፃፋቸው ፍሬ ነገሮች "በአደባባይ የሚታወቁ" ናቸው ብሎ በመገመቱ ነበር።
ከአሉባልታ ጋር ሲወዳደር ተጽፎ የታተመን ነገር የላቀ ኃይል አሳንሶ በማየት ስህተት ሳይሰራ
አልቀረም።

ከዚያ በኋላ መጽሐፉ ታትሞ ተሰራጨ ፤ በአንድ ሳምንት ብቻ 5,000 ቅጂዎች ተሸጡ። ነገር ግን
ብዙም ሳይቆይ መጽሐፉ ከገበያ እንዲወጣ ተደረገ።የደኅንነት አባላትም፣መጽሐፉን ከያለበት
ማደንና ከሰው እጅ ሳይቀር መቀማቱን ተያያዙት።14መጽሐፉ የታገደበት ምክንያት በይፋ

402
ጥቋቁር አናብስት

ካለመገለፁም በላይ፣ መጽሐፉ እንዲታተም በመፍቀዳቸው፣የኩራዝ ቦርድ አባላት "እንዲበተኑ"


ተደርጐ በኢሰፓአኮ ርእዮተ አለም ክፍል በኩል ተወቀሱ።ወዲያውኑ አዲስ ቦርድ ተቋቋመ፤
ከድሮዎቹ አባላት መሐል አንዳቸውም አልነበሩበትም። ምናልባት መጽሐፉ እንዲታገድ የተደረገበት
ዋነኛ ምክንያት፣ብዙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የትኛውም አንባቢ በቀላሉ ሊለያቸው15
በሚችል መንገድ በመጽሐፉ ውስጥ ገፀ ባህሪያት ሆነው በመቅረባቸው ነው ተብሎ ይገመታል።

ቀድሞውኑም ብዙ ጠላቶች የነበሩት በአሉ ግርማ፣ አሁን ደግሞ ይበልጥ ሀይለኛ የሆኑ ጠላቶችን
ጨምሮ አፈራ። አንዳንድ ሰዎችወደ መጨረሻው አካባቢ በአሉ ትእቢተኛ፣ ኩራተኛና ጉረኛ እየሆነ
መጥቶ ነበር ይላሉ። በሊቀመንበር መንግሥቱ ያለቅጥ ተመክቶ ይሆናል፤16የነበረችው ስልጣን
እንደጠበቀው አስተማማኝ አለመሆኗን አልተገነዘበም። ወይንም ደግሞ በቀደምት መጽሐፍቱ
“በህዝብ” ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት በማግኘቱ፣ ስለሚጽፈው ነገር ብዙ መጨነቅ ሳያቆም
አልቀረም። በሌላ በኩል ደግሞ የሚገጥመውን ፈተና ከወዲሁ ጠንቅቆ አውቆትም ሊሆን ይችላል
የጻፈው።ወይም በቀደመ መጻሐፍቱ ዝና ተመምኖ ሊሆን ይችላል፡፡17ለፖለቲካዊ መሻቱ
መረማመጃ እንዲሆነው፣ እንዲሁ በድፍረት የፃፈው ሊሆንም ይችላል። ወይም አብዮቱ እየሄደበት
ያለበትን ጎዳና ወደ መቃወም ደርሶም ሊሆን ይችላል።በአንድ ወቅት ለጥቂት ጓደኞቹ
እንደነገራቸው ከሁሉም በላይ የሚፈልገው በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘትና ህዝብ ልብና
አእምሮውስጥ መግባቱን ነው፤እንደምኞቱ መጻሕፍቱ እሱ ከጠፋ ከረጅም ጊዜ በኋላ ራሱ፣ ከሊቅ
እስከ ደቂቅ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ሆነዋል። ስለዚህ በአሉ ላመነበት ዓላማ ሲል ሕይወቱን ጭምር
አደጋ ላይ ለመጣል እስከመድፈር ሳይደርስ አይቀርም።18

በአሉ ግርማ ኦሮማይን በሚጽፍበት ወቅት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ዋና ፀሐፊ ሲሆን የሀገሪቱ
ፕሮፖጋንዳ ክፍል በሱ ቁጥጥር ስር ነበር።ነገር ግን መጽሐፉ ከወጣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በመጽሐፉ
ምክንያት ከስራ ታገደ። ይህየሆነው በነሐሴ 1975 ዓ.ም ነበር። ለ6 ወይም7 ወራት ያህል ሳይሰራ
እንዲሁ“ተንሳፍፎ” ከረመ። ከፊት ለፊቱ ምን እንደሚገጥመው ያላወቀው በአሉ በ1976 የካቲት
ድንገት "ጠፋ"። በአሉ ከስራ በታገደበት ወቅት ምኞቱ "የህዝብ ተቀባይነት እና የሌሎች ደራሲያን
አክብሮት ማግኘት ብቻ እንደሆነ" ተናግሮ ነበር።

በአሉ በመጨረሻው "የነፃነት" ቀኑ አንድ ጓደኛው ከቤቱ መጥቶ ሻይ ቡና እያሉ እንዲጫወቱ


ጥያቄ አቀረበለት።የበአሉ ሚስት ግን ቀልቧ አንዳች ክፉ ነገር ሊመጣ እንደሆነ ነግሯት፣ በአሉ
ከቤት መውጣት እንደሌለበት በመቃወም ተናገረች፤በመጨረሻ ግን ተሸንፋ እጇን በመስጠቷ በአሉ
ከጓደኛው ጋር ተያይዞ ወጣ። ሁለቱም ወደሚያዘወትሩበት መጠጥ ቤት አመሩ። ከበአሉ ቤት
የወጡት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ ሲሆን፣ በአሉ ሳይመለስ ቀረ። የበአሉ ሚስት ይዞት የወጣው
403
ጥቋቁር አናብስት

ጓደኛው ጋር ስትደውል በጊዜ እንደተለያዩ፣ ከዚያ በኋላ ግን በአሉ የት እንደሄደ ወይም ምን


እንደተፈጠረ እንደማያውቅ ነገራት። ለሌሎች ሰዎች ግን በአሉ ከመጥፋቱ በፊት ጭራሽ ለሁለት
ሳምንት እንዳላየው በመናገሩ፣ የበዓሉ ሚስት ከተናገረችው ጋር የተፈጠረው መጣረስ ብዙዎችን
አስገረመ። በኋላ ጓደኛ ተብዬው ለአብዮቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ የኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ስራ
አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ።የበአሉ መኪና ከአንድ ሳምንት በኋላ ደብረዘይት መንገድ፣ ቃሊቲ አካባቢ
ተገኘች። ከዚያ በኋላ የበአሉ ግርማ ወሬ የውሃ ሽታ ሆኖቀረ።19

በአሉ ግርማ ከጠፋ በኋላ መንግስት በአሉ የኛ ወገን ነበረ፤አሁን ግን በአድሃሪነት ከድቶን ተሰወረ
የሚል ወረቀት በመላ ሐገሪቱ በተነ። ያለበትን የሚያውቅ ለመንግስት ማሳወቅ እንዳለበት ተገለፀ።
ይህ ሁሉ ሽርጉድ መንግሥት በአሉ የት እንዳለ እንደማያውቅ ወይም እጁ እንደሌለበት
"ለማስመሰል" የተደረገ ነበር።

***

ስለበአሉ ግርማ ሰብዕና ለማውራት የሚያስችል ቀረቤታ የለኝም።ባገኘሁት ወቅት ተግባቢ ቢሆንም
የተጨናነቀ ይመስል ነበር። ብዙ ውዝግብ ማሥነ ሳቱ የጠንካራ አመለካከቶች ባለቤት መሆኑን
ይመሰክራል። የስራዎቹ ውጤታማነት ብቃቱን ያስረዳሉ። ብዙም መልከመልካም ባይሆንም ሴቶች
በቀላሉ ይረቱለታል።ለአንድ ዓመት ያህል ከኢትዮጵያ ቁንጮ ዘፋኞች መሐል የአንዷ "ፍቅረኛ"
ነበር።ነገር ግን ትዳር የመሰረተው ከሌላ ሴት ጋር ነው።ደብዛው ድንገት በጠፋበት ወቅት
ከኢትዮጵያ ቆነጃጅት መሐል ግንባር ቀደም ከሆኑት ወይዘሮ አልማዝ ጋር ሐያ ዓመት በጋብቻ
ተሳስሮ አንድ ሴትና ሁለት ወንድ ልጆች አፍርቷል።የበአሉ ሚስት እሱን ከማግባቷ በፊት
ባለትዳርና የአምስት ወይ ስድስት ልጆች እናት ነበረች።20 ባሏ አቶ ከበደ ሐይሌ በአዲስ አበባ
ማዘጋጃ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣን ሲሆን አባቱ ሐይሌ አባ መርሳ ስመጥር አርበኛ ነበሩ። አልማዝ
በውበቷ ምክንያት በአርሲ ገዢ ዳንኤል አበበ (የራስ አበበ ዳምጤ ልጅ)21 እስከመጠለፍ ሁሉ
ደርሳለች።ባሏ አቶ ከበደ ለግርማዊነታቸው አቤት ብሎ ነበር ሚስቱን ለማስመለስ የቻለው።
የአልማዝ ወንድም ከበአሉ ጋር በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰርቷል። በወንድሟ ምክንያት በዓሉና
አልማዝ ተዋወቁና "ከባሏ አለያይቶ የራሱ አደረጋት"። ከባሏ ጋር ከተፋታች በኋላ በልጃገረድ ወግ
አገባት።ቅልጥ ያለ ሰርግ ተደግሶ በወግ ማእረግ ተዳሩ። እስከመጨረሻው ድረስ እጅግ የሚቀራረቡ
ጥንዶች ነበሩ።

በአሉ እንደ ጸሐፊስ እንዴት ያለ ነበር? በኦሮማይ ምክንያት ዝናው ጫፍ ደርሷል፤ነገር ግን ስለዚህ
መጽሐፍ እርስ በእርስ የሚቃረኑ አስተያየቶች ተደምጠዋል።ብዙዎች ከዚህ የተሻሉ መጽሐፍት
ቀደም ብሎ እንደፃፈ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ኦሮማይ ከሁሉም የበለጠ ታላቅ ስራው ነው፤የመፃፍ
404
ጥቋቁር አናብስት

ችሎታው ጣራ የነካበት "እንደ ደራሲ ራሱን ያገኘበት ስራው" ነው ይላሉ።በአፃፃፍ ይሁን በጭብጥ
ቁንጮ ስራው ነው ብለው ይጨምራሉ፦ በመጽሐፉ"ሙሉ ለሙሉ ራሱን ለእውነት አስገዝቷል፤
አላማውንም አሳክቷል"ይላሉ"በገፀ ባህሪይ አሳሳል፣ በልብ ሰቀላ፣ በአፃፃፍ ዘዬ፣ በጭብጥ፣ በጥሩ
አጀማመር እና አጨራረስ"―በአጠቃላይ በሁሉም መስክ ኦሮማይ ታላቅ ስራ ነው። አንድ ጎላ
ብሎ የሚሰማ አስተያየት "በአፃፃፍ ዘዬ፣ በሥነ ጽሑፍ ውበት እና በጭብጦቹ ትልቅነት በአሉን
የሚተካከል አንድም ደራሲ የለም" ይላል። አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች የኢትዮጵያ ደራሲዎች ጋር
እንዲህ ያወዳድሩታል፦ ከበደ ሚካኤል ጥሩ ገጣሚ፣ በሳል ተርጓሚ በመሆን የበለጡ ናቸው ፤
ሀዲስ አለማየሁ የበለጡ ነጠላ መጻሕፍትን ጽፈው ሊሆን ይችላል፤ነገር ግን በአጠቃላይ ሲታይ
በአሉ ግርማ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ደራሲዎች ሁሉ ምርጡ ነው፤በአሉ ከአንድ መጽሐፍ ወደ ሌላ
መጽሐፍ እየተካነ የመጣ፣ በመጽሐፉ ላመነበት ነገር ራሱን ያስገዛ፣ በመጨረሻም ለእውነትና
ለመርሁ ሲል ራሱን እስከ ሰማዕትነት ድረስ የሰጠ ነበር።

***

ከዚህ በታች ከሌሎች የቃረምኩትን አንዳንድ መረጃዎች እጨምራለሁ። አንዳንዴ ከሰዎች ወይም
ከጽሑፍ ያገኘኋቸውን መረጃዎች ሲያጎሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ በከፊል ይቃረናሉ ወይም ያርማሉ።

በአሉ ግርማ የተወለደው በ1930 ወይም 1931 ዓ.ም ነው። አፉን የፈታው በኦሮምኛ ቋንቋ
ነበር። አስር ዓመት ሲሞላው ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ልእልት ዘነበወርቅ ትምህርት ቤት ገባ።
በዚህ ትምህርት ቤት የአማርኛ መምህሩ የነበሩትን አለቃ ዳዊትን ያደንቅ ነበር።ወንዶችና ሴቶች
ተቀላቅለው የሚማሩበት ትምህርት ቤት ስለነበር ልጃገረዶችን በቀላሉ እና በነፃነት ይግባባል።
የወንዶች ብቻ ወደሆነው ዊንጌት ሲገባ ጥሩ ቤተ መጽሐፍት እና ብቃት ያላቸው መምህራን
ስለገጠሙት በማንበብ ተጠመደ። በዊንጌት አራት ዓመት ከቆየ በኋላ፣ በ1950 አዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገብቶ ለአራት ዓመታት ማህበራዊ ሳይንስና ጋዜጠኝነት አጥንቶ የመጀመሪያ
ዲግሪውን ተቀበለ።መፃፍ የጀመረው በተማሪነት ዘመኑ ሲሆን፣ ለዩኒቨርስቲ ኮሌጁ መጽሔት
(News and Views) ጽሑፎች ያዋጣ ነበር።ኋላም የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።
አብዛኞቹ መጣጥፎቹ ዘመናዊ ሕይወትን ( ለስራ ያለን ግድየለሽነት የመሳሰሉትን ) ይተቻል።
ይህንን ጭብጥ በመጀመሪያ ልብወለዱም ዳስሶታል።

ከዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በኋላ በኢትዮጵያ ሬድዮ ሪፖርተር ሆነ። በሰሜን አሜሪካ የፖለቲካ ሳይንስ እና
ጋዜጠኝነት አጥንቷል። ከተመለሰ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የመነን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና፤ቀጥሎ
ደግሞ በጊዜው ዝነኛ የነበረው አዲስ ሪፖርተር ዋና አዘጋጅ ሆነ። ነገር ግን በመጽሔቱብዙ "ለውጥ
405
ጥቋቁር አናብስት

ናፋቂ" ጽሑፎች መበርከታቸው ብዙ ባለሥልጣናትን "ስላስከፋ" በአሉ ከስራ "እንዲለቅ" ተደረገ።


ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስራ አጥ በመሆኑ፣የመጀመሪያ ልብወለዱን ለመፃፍ በቂ ጊዜ አገኘ።
ከዚያ የአማርኛው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ተሾመ። ቀጥሎ የእንግሊዝኛው
The Ethiopian Herald ዋና አዘጋጅ ሆነ። በኋላ በ1963 ደግሞ የአማርኛው አዲስ ዘመን
ዋና አዘጋጅ ነበረ።በ1965 አጋማሽ ሁለተኛውን ልብወለዱን መፃፍ ጀምሮ በሚቀጥለው ዓመት
ታተመለት። ከዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነ። በ1969
በማስታወቂያ ሚኒስቴር ቋሚ ፀሐፊ ሆነ።

በአሉ ግርማ ከሚወዳቸውና ተጽእኖ ካሳረፉበት ደራሲያን መሐል ሄሚንግዌይ፣ ግራሃም ግሪን፣
ዶስቶቭስኪ ሲገኙበት የዳኒሽ ተወላጁን እና ፈላስፋውን ሶረን ኪርክጋርድንም ያደንቀው ነበር።

የተርጓሚው ማስታወሻ

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ “በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ስራዎቹ ”መሰለ የእንጀራ አባቱ ልጅ እንደሆነ፤
እሱ ብቻም ሳይሆን ሌሎች የእንጀራ አባት ልጆች እንደነበሩ፤ በግርማ ስም መጠቀሳቸውን ፤ግርማ
የያኔ ሁለተኛ ባል ስለመሆኑ የተጻፈውን ፈጽሞ ሐሰትና የተሳሳተ መረጃ ነው ሲሉን በአሉ ከእናቱ
የሚወለዱ ወንድምም እህትም እንደሌለው እናቱም ከህንዳዊ ባላቸው ሲለያዩ ያገቡት አበበን እንጂ
ግርማን ያለመሆኑን ጽፈዋል፡፡(ገጽ23)

ማስታወሻዎች

1) አንዱ ምንጭ ወደ አዲስ አበባ በአስር ዓመቱ መጥቶ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በዘነበወርቅ
ተከታትሎ እንደጨረሰ ይናገራል።

2) የወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ቤተሰቦች እንደነገሩኝ ከሆነ በአሉ ግርማ ገና "አዲስዘመን"


መስራት እንደጀመረ እየታመመ ብዙ ጊዜ ከስራ ስለሚቀር ወልደጊዮርጊስ ያማርሩ ነበር።

3) የምስራች ድምጽ ሬዲዮ ላይ ስለ ልብወለዶቹ የሰጠውን ቃለምልልስ ሰምቼያለሁ።


በቃለመጠይቁ በአሉ ሁለተኛው ልብወለድ ከመጀመሪያው የተሻለ እንደሆነ አመለካከቱን ሲገልጽ
በውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩት መሀል ጥቂቶቹ የመጀመሪያውን እንደሚመርጡ ገልጸዋል።

4) ይሁን እንጂ ስለ በአሉ ግርማ መረጃ በማሰባስብበት ወቅት በዓሉ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ
ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበር።

406
ጥቋቁር አናብስት

5) "የቀይ ኮከብ ጥሪ" የተሰኘው የበአሉ መጽሀፍ ውስጥ ከማስታወቂያ ሚኒስትር ባልደረቦቹ ጋር
ጌታቸው የሸዋሉል በሚል ስም ሰካራም እና የነቀዘ “ብልሹ ገፀባህሪ” ሆኖ ተቀርፇል። በአሉ
ለልብወለዶቹ ሰዎችን፣ ቦታዎችን እና ድርጊቶችን ከሕይወት ልምዱና ከአካባቢው መውሰዱ
የሚታወቅበት ባህሪ ነው።

6) ይህን መረጃ ያገኘሁት ለበአሉ ቅርብ ከነበሩ ሰዎች ነው። ይሁን እንጂ፣ ግርማ ይልማ ሀቀኛ እና
እንደተፈለገ የሚጠመዘዝ ሰው እንዳልሆነ ሁሉም ይስማማሉ።

7) እሱንም ቃለምልልስ ስላደረግኩለት በዚሁ መጽሀፍ የሕይወት ታሪኩን ይመልከቱ።

8) ሁሌም ሳየው ሰማያዊውን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ካኪ ዩኒፎርም ለብሶ ነው። አብዛኛዎቹ
ፓርቲውን የተቀላቀሉት ከስራ እንዳይባረሩ “ተገድደው” ነው። የፓርቲው ዩኒፎርም የተስማማው
ይመስላል።

9) በጊዜው ይህ መጽሔት የሚሰራጨው የይልማ ደሬሳ ቤተሰብ በሚቆጣጠረው በአለም አሳታሚ


ድርጅት ነበር። ከአብዮቱ በፊት በአሉም፣ ስብሐትም እዚህ ሰርተዋል። አብዮታዊው መንግስት ግን
የመጽሔቱ ህትመት እንዲቆም አድርጓል።( መነን የእቴጌይቱ ስም ነበር)

10) አንባቢያን በመጽሀፉ ውስጥ ያሉ ብዙ ገፀባህሪያትን በቀላሉ መለየት ችለዋል። ስማቸውን


እዚህ መዘርዘሩ ምን ዐይነት ህጋዊ መዘዞችን ሊያስከትል እንደሚችል ስላላወቅኩ ከመጥቀስ
ታቅቤያለሁ።

11) አርታኢው ይህን ያደረገው ለቀጣሪዎቹ ሳያሳውቅ ነው። በ1977 ከሱ ጋር ከተደረገው


የጋዜጣቃለምልልስ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ካሁን በፊትም ተመሳሳይ ነገር አድርጎ ያውቃል።
ከዚህ ቀደም ከነበረበት የመንግስት ስራ ስለተባረረ፣ በግል ስራ ላይ ለመቀጠር ልዩ ፍቃድ
ያስፈልገዋል። ለኢትዮጵያ መጽሀፍት ማዕከል ይህ ፍቃድ ተሰጥቶት፣ ስራ አስኪያጁም ሊረዳው
ፈልጎ ነበር።ግን በኋላ ላይ ኩራዝ አሳታሚ ዘንድ ተቀጠረ።

12) የመንግስት ማተሚያ ቤቶች ረቂቅ ጽሁፎችን ለማተምሌሎች እንደሚያደርጉት የመንግስት


ሳንሱረኞች ጋር ይዘው መሄድ አይጠበቅባቸውም። ሌሎቹ አሳታሚዎች/አታሚዎች ግን
ረቂቃቸውን ለማሳተም/ለማተምፈቃድ ማግኘት አለባቸው ፤የታተመ መጽሀፋቸውን ገበያ ላይ
ከማዋላቸው በፊት ራሱ ከረቂቁ ምንም ያህል እንዳልተቀየረ መረጋገጥ አለበት፤ያኔ ብቻ ነው ለገበያ

407
ጥቋቁር አናብስት

መቅረብ የሚችለው። አንዳንዴ ረቂቁ ተቀባይነት አግኝቶ መጽሀፉ ከታተመ በኋላ ሳንሱረኞቹ
ሀሳባቸውን በመለወጣቸውመጽሐፉ ለገበያእንዳይቀርብ የሚታገድበት ጊዜ አለ ፤ ኪሳራው ሙሉ
በሙሉ የአሳታሚዎች ነው።

13) ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ ተቃውሞ ያነሳው አባል በ"ኦሮማይ" ጉዳይ በተፈጠረው
አለመግባባት ከቦርድ አባልነቱ ራሱን አግልሏል።

14) የቀሩት የ"ኦሮማይ" ቅጂዎች በወንጂ ስኳር ፋብሪካ ተቆራርጠውተፈጩ። እነዚህን ቅጂዎች
ማሰባሰቡና ወደ ወንጂ የመላኩ ሂደት የቀሩ ወይም የተደበቁ ቅጂዎች እንዳይኖሩጥብቅ የደህንነት
ቁጥጥር ተደርጎበታ ይሁን እንጂ መርካቶ አካባቢ መጽሀፉን ማግኘት ችዬ ነበር ፤ በእርግጥ ውድ
ዋጋ (50 ብር) መክፈል ነበረብኝ። ከዚያ በፊትናይሮቢእያለሁፎቶኮፒውን አግኝቼ እኔም ለራሴ
ፎቶኮፒ ለማድረግ ችዬ ነበር። መጽሀፉን ከልባቸው ማንበብ ለፈለጉ፣ ቅጂዎችን ማግኘት ያን ያህል
ከባድ አልነበረም።

15) ይህ በመጽሀፉ ውስጥሱስሎቭ እየተባለ የሚጠራውን የፓርቲውንቀንደኛ አይዲሊጂስት


ይጨምራል። ተቀጥላ ስሙን ያገኘው በስታሊን ዘመን የፓርቲ ፖለቲከኛ ከነበረው ማይክል
ሱስሎቭ ነው።ሰዎች በዙሪያው እንደ ቅጠል ሲረግፉ ምንም ስሜት ሳይሰጠው፣ ማርክሳዊ
መጽሀፍቱን በማንበብ ብቻ የሚጠመድ አንዳች ርህራሄ የሌለው ሰው ነበር። ከዚህም ሌላ
የፖለቲካ፣ የርዕዮተ አለም እና የወታደራዊ መሪዎች እንዲሁም የደህንነት ሰዎች በሚገባ ሳይደበቁ
በመጽሀፉ ውስጥ ተካተዋል።

16) በ"ኦሮማይ" ውስጥ መንግስቱ የተፃፈላቸውን ከሚያነቡ ይልቅ በራሳቸው ንግግር ሲያደርጉ
እንደሚሻሉ የጠቀሰው ሳያስቆጣቸው እንዳልቀረ አንዳንዶች ይናገራሉ። ይሄ መንግሥቱ ማንበብ
አይችልም ወይም በደንብ አልተማረም የሚል ድብቅ ስድብ የያዘ ነው ይላሉ። ይህ እውነት ከሆነ
መንግስቱ ለበአሉ የሚያደርጉለትን ጥበቃ ለማቆም በቂ ምክንያት ይሆናቸዋል።

17) ጽሑፉን በታማኝነት እና በቆራጥነት በማስፈሩ ይመሰገናል።

18) አብዮቱ በ66 ከፈነዳ በኋላ ሁሌም አደጋ ውስጥ እንደነበር ሳያውቅ አይቀርም። ለምሳሌ
በአብዮቱ የመጀመሪያ ዓመታት መኢሶን “ስልጣን በነበረው” ወቅት በማስታወቂያ ሚኒስትር
ውስጥ ሊያጠፋቸው ከሚፈልጋቸው ከ30 ከሚበልጡ ሰዎች መሐከል በ3ተኛ ተራ ቁጥር ላይ
ስሙ ሰፍሮ እንደነበር በቂ መረጃየነበራቸው ሰዎች ይናገራሉ።

408
ጥቋቁር አናብስት

19) በ1979 አንድ የቀበሌ ታጣቂ በአሉ በእነሱ ቀበሌ ውስጥ እንደተገደለ ማውራቱን የሰማ ሰው
ነገረኝ( በ1987 በደርግ ባለስልጣኖች ላይ የቀረበ ክስ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ይመስላል።)

20) ያኔ አዲስአበባ ውስጥ ካዛንቺስ አካባቢ ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖር ነበር።

21) የተነገረኝ እንደዛ ነው። ነገር ግን ዳንኤል አበበ የራስ አበበ አረጋይ ልጅ ሳይሆን አይቀርም።(
ደጃዝማች አበበ ዳምጠው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የመጀመሪያ ልጅ የነበሩት የልዕልት ተናኘወርቅ
የመጀመሪያ ባል የራስ ደስታ ዳምጠው ወንድም ነበሩ)

409
ጥቋቁር አናብስት

ከበደሚካኤል
የአማርኛ ስነፅሁፍ ታላቁ ሰው ከበደሚካኤልን ለበርካታ ጊዜ
ባገኛቸውም በዚያ ላይ ብቻ ተመስርቼ ግን ታሪካቸውን ማስቀመጥ
አልወደድኩም፡፡ጓደኞቼን ቃለመጠይቅ ላደርግላቸው እፈልጋለሁ
ስላቸው ተስፋ አስቆርጠውኝ ነበር፡፡“አእምሯቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ
አይደለም የማያውቁትን ጠያቂ እንኳን በጥሩ መንፈስ አይቀበሉም ፤
ነገር ግን ለውጭ ሃገር እንግዶችያላቸው ጥርጣሬ እንደሃበሾቹ
አይደለም”ሲሉ ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ፈነጠቁልኝ፡፡ አማረ ማሞ የግጥም መድበል ማዘጋጀት
ፈልጎ የሳቸውን ግጥም ለማካተት ሊጠይቃቸው ቤታቸው በሄደበት (የደርግ ሰላይ ነህ)ብለው በሩን
ፊቱ ላይ ደርግመውበታል፡፡

ሌሎችንም ያጋጠማቸው ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡ ከበደ ሚካኤል በአብዮቱ ጉልበተኞች


የደረሰባቸው እንግልት በጤንነት ከመቆየት በላይ ሆኖባቸው ይሆናል፡፡እውቅናና ሃገር አቀፍ ዝና
አሁን ምንም አይፈይዱም፡፡የነበራቸው ትልቅ ስልጣን በደርጉ በጥርጣሬ እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡
ቤታቸው ተወርሶባቸዋል፡፡¹ በግዮን ሆቴልና ገነት ሆቴል ኖረዋል እኔ ሳገኛቸው ግን ፒያሳ አካባቢ
ባለው አውራሪስ ሆቴል²ነበር የሚኖሩት።ቀጥሎ አራት ኪሎ አካባቢ ወደሚገኘው ጥንታዊው
የቱሪስት ሆቴል ተዘዋወሩ፡፡በመንግስት ከሚተዳደሩት ውስጥ ርካሹ ሆቴል ሲሆን መታጠቢያ
ቤቱም ሆነ መጸዳጃው³ የጋራ ነበር። በ1980 አ.ም አንዲት ባልቴት ሊንከባከቧቸው እንደ ተጧሪ
እንደወሰዷቸው ሰማሁ፡፡የደራሲያን ማህበር ነገሮች እንዲሻሻሉላቸው ቢጥርም አልተሳካለትም፡፡
በኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ደራሲ የሚቆጥሯቸው እንኳን መንግስት ከበደ ሚካኤልን የያዘበት
መንገድ ያሳፍራቸውና ያሳዝናቸው ነበር፡፡እንደ ደራሲነታቸው በግል ባይሆንም ከሌሎች ደራሲዎች
ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ምክንያቱም ከበደ በጣም ጥቂት(እነሱም ካሉ )ጓደኞች ነበሯቸው ከዘመዶቻቸው
ጋር ግንኙነት የላቸውም ልጅም አልወለዱም ባለቤታቸውም ለረጅም አመታት አእምሯቸው ጤነኛ
አልነበረም፡፡

በ1978 መባቻ አንድ እሁድ ጠዋት ነው ከበደን ለማየት የሄድኩት፡፡እስኪገርመኝ ድረስ በሞቀ
አቀባበል አውራሪስ ሆቴል ወደነበረው ክፍላቸው እንድገባ በመጋበዝ ነበር የተቀበሉኝ፡፡የሚኖሩት
በዋናው ህንጻ ሆኖ በላይኛው ፎቅ አንድ ሰፊ ክፍል ውስጥ እንደማረፊያና እንደ እንግዳ ቤት
ይገለገሉበት ነበር፡፡ የግል መጸዳጃና መታጠቢያ የሆኑ ከጎን የተያያዙ አንድ ወይም ሁለት ክፍሎች
አሉ፡ ዋናው ክፍል በመጻሕፍትና በሻንጣዎች የተጨናነቀ ነበር፡፡ከበደ በጋወን ሲሆኑ ግዜው ቀትር
አካባቢ ቢደርስም አልጋው አልተነጠፈም፡፡ትኩስ ፍራፍሬ በትሪ ሆኖ ከአልጋው አጠገብ
ተቀምጦላቸዋል፡፡አንድ ያልተማረ የሚመስል ትንሽ ሰው ብቅ እያለ ትእዛዛቸውን ይቀበላል፡፡ከዚያ
410
ጥቋቁር አናብስት

በኋላ በየጊዜው አገኛቸው ጀመር ለከበደ በመሰረታዊነት የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት


የሚያግዛቸው፡፡እኔም ለጥቂት ጊዜ ወደ አውራሪስ ሆቴል ተዘዋውሬ ስለነበር ባገኘሁት ቁጥር ስለ
ደህንነታቸው ስጠይቀው ሁሉም ሰላም ነው በማለት ይመልስልኛል፡፡

በመጀመርያ ግንኙነታችን ለከበደ ስለ አማርኛ ስነጽሁፍ አንድ መጽሐፍ መጻፌን


ነግሬያቸው(Tradition and change in Etthiopia)አሁን ስለ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን
ብእረኞች ደግሞ መጽሐፍ ለመጻፍ ማሰቤን ስነግራቸው ደስተኛ ሆነው ነበር፡፡ነገር ግን የራሳቸውን
ግለ ታሪክ በሁለት ጥራዝ አዘጋጅተው ረቂቁ ለመታተም ኒውዮርክ እንደሚገኝ አጫወቱኝ፡፡
የራሳቸውን ታሪክ ቢያወጉኝም ከራሳቸው ጋር መፎካከር እንደሚሆንባቸው ሽያጩንም
እንደሚቀንሰው ገለጹልኝ፡፡የራሳቸውን ግለ ታሪክ ግን አንብቤ ጥያቄ ወይም ጎደለ የምለው ካለ
ተመልሼ በመምጣት መጠየቅ እንደምችል ነገሩኝ፡፡አስከትሎም ሃያ ሁለት መጻሕፍቶቻቸው
እንደታተሙላቸውና በአጠቃላይ ከመቶ በላይ መጻሕፍትን እንደጻፉ አብዛኞቹም በማህበራዊ
ጉዳዮችና ስለ አጤ ቴዎድሮስ በርከት ያሉ ከመሃላቸውም እንዳሉባቸውም ነገሩኝ፡፡ጥቂት
ጋዜጠኞች ከዚህ በፊት ጠይቀዋቸው ተመሳሳይ ታሪክ ነገረዋቸው አምነዋቸው አትመውት ነበር፡፡
እኔም ላምናቸው ዳድቶኝ ነበር ጤነኛና ተአማኒም ይመስላሉ፡፡
ምንም እንኳን ጥያቄ ከመጠየቄ በፊት ግለታሪካቸውን እንድጠብቅ ቢነገረኝም በትንሹ
ስለማውቀውና እንዲብራራልኝ ስለምፈልገው ነገር እንዲነግሩኝ ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ ስለዚህ የንጉሱ
ግለታሪክ ሲጻፍ(ህይወቴና የኢትዮጵያ እድገት) ለምን ለማገዝ እንዳልፈለጉ ጠየቅሁ፡እሳቸውም
“ኃይለሥላሴን እንደ አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ መሪ እንዲሁም እንደ ትእምርት እራሳቸውን
ወስደው ከውስጥ ጥቃቅን ጉዳዮች በዘለለ ስለ አለም አቀፍ ጉዳይ እንዲጽፉ መክሬያቸው ነበር”
ይላሉ፡፡ሌላ ሰው ደግሞ በተቃራኒው መክሯቸው የሱን ሃሳብ ተቀበሉ፡ስለዚህ ከበደ ሚካኤል
ለንጉሱ ስራውን መስራት እንደማይፈልጉ ተናገሩ፡፡እንደነገሩኝ ከሆነ አንድ ነገር ሲሰራ ፍጹም
እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ የስነ-ቅሪተ አካል ምርመራ ተቋም ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ
የሚኮራበት እንዲሆን ይሻሉ፡፡ከንጉሱ ግለታሪክ ስራ ራሳቸውን ሲያገሉ በእግራቸው ሌሎች ተተኩ
ብላቴን ጌታ ኅሩይ በመጀመርያውም ጥራዝ በመንደፍ አግዘው የነበረ ሲሆን ለሁለተኛው ጥራዝ
ደግሞ ተክለ ጻዲቅ መኩርያ እገዛቸውን አበርክተዋል ሲሉ ነግረውኛል፡፡(ከማለቃቸውም በፊት
የሚመረምራቸውም ኮሚቴ ነበር)ሌሎች ጥያቄዎችንም ለከበደ አንስቼ ሁሉንም አስተዋይነት
በሞላበት ሁኔታ መለሱልኝ፡፡ቀጥሎም መጻሕፍቶቻቸውን በመረዳት እንዳነበብኳቸው ጠየቁኝ፡፡
ማርሴል ኮህንና ዎልፍ ሌስሎውን እንደሚያውቋቸው አማርኛ በትንሹ እንደሚናገሩ የሳቸውንም
መጻሕፍት በአግባቡ አንብበው ተረድተውም ማድነቅ እንደማይችሉም ነገሩኝ፡፡ለጥያቄው መልስ
ሳልሰጥ የራሳቸውን ፍርድ እንዲፈርዱ በአማርኛ ማናገር ጀመርኩ፡፡(ምንም አስተያየት አልሰጡም)
አስከዚያ ድረስ በእንግሊዘኛ ሲሆን እናወራ የነበረው እንግሊዘኛ ቋንቋን እንደዚያ ማቀላጠፋቸው
411
ጥቋቁር አናብስት

ፈረንሳይኛ የመጀመርያ የውጪ ቋንቋቸው ከመሆኑ አንጻር አስገርሞኛል፡፡ሌሎች ሰዎች የነገሩኝ


ስህተት መሆኑን ያረጋገጥኩት ነገር እንግሊዘኛ ቋንቋን በደንብ የመቻላቸውን ጉዳይ ነበረ፡፡
ለማንኛውም ስለታተሙ ስራዎቻቸው በደንብ ለማናገር እድሉን አላገኘሁም፡፡
እንግሊዘኛ በደንብ ቢችሉም በኒውዮርክ ካለ ታዋቂ ግን ስሙን ለመጥራት ፍቃደኛ ካልሆኑት
አሳታሚ ጋር ስለሚገኙትና ወደ ደርዘን ስለሚጠጉ (በራሳቸው ወጪ ስለሚታተሙት አሳታሚው
የተሻለ የባለቤትነት ክፍያ የሚሰጠኝ ያሏቸው)መጻሕፍቶቻቸው የነገሩኝን በተለይም ስለ
ግለታሪካቸው ያወጉኝን እየተጠራጠርኩ መጣሁ፡፡ስለ ግለታሪካቸውም መጽሐፍም የነገሩኝ
ተመሳሳይ የማሞኛ ታሪክ እንደሆነ እየገባኝ መጣ፡፡በሌላ ግንኙነታችን ወቅት ደግሞ ሼክስፒርና
በርናንድ ሾው በአንድነት ከጻፉት በላይ እንደጻፉ (ታላቅ ነኝ በማለት) አጋንነው ሲያወሩልኝ ቆዩ፡፡
ስለ እሳቸው ግለታሪክ መጻፍና ማውጣትም እርባና ቢስ እንደሆነ መጻሕፍቶቻቸው ሁሉ
በእንግሊዘኛ ተተርጉመው ሲወጡ አለም ሁሉ ስለእሳቸው እንደሚያውቅ የከበደን ማንነት
እንደሚረዳ ነገሩኝ፡፡ምንም ማስታወቂያ አያስፈልግም፡፡እንዲህ ያ ታላቅ ሆነው ሳሉ ለምን ከእኔ ጋር
እንደሚያወሩ ግራ እንደገባቸውም ሆኑ፡፡ስለ ምን ታላቅ የስነ ጽሁፍ ሰው ሆነው ሳሉ ያነጋግሩኛል
ማን ነኝ እኔ? ግጥምም ሆነ ተውኔት አልጻፍኩም ወይም ታዋቂ መጽሐፍ የለኝ ስለ ስነ መለኮት ሆነ
ምጣኔ ሃብት ጥናት ምን አውቃለሁ? ደራሲ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚስትና የነገረ መለኮት አዋቂም
ጭምር እንደሆኑ፡፡በእነዚህ መስኮች ባለሙያ ካልሆንኩ እንደ ሰው በተለያየ መደብ ላይ መሆናችን
ስለሆነ ምንም የሚያናግሩኝ ነገር እንደሌለ ገለጹልኝ፡፡“ስለምን ላናግርህ እችላለሁ?” በእነዚህ
ደቂቃዎች ውስጥ በከበደ አይኖች የእብደት እሳት ስለሚንቀለቀል አእምሯቸው ጤናማ እንዳልሆነ
መገመት አያስቸግርም፡፡⁴

ምናልባት ስለማደንቃቸው ደራሲ የሕይወት ታሪክ የመጨረሻው የውድቀት ጊዜያት እንደዚህ


ባልጽፍ ይመረጥ ነበር፡፡ምንም ቢሆን ግን በፉከራዎቻቸው ውስጥ አንድ የሚደንቅ ነገርም አለ፡፡
በህይወታቸው ስለ ተሾሙባቸው ታላላቅ ስራዎች ወይም በኃይለሥላሴ መንግስት ስለነበራቸው
ስልጣን አውርተው አያውቁም ፡፡ከቁጥጥር ውጪ በወጣው ቅዠታቸው ግን የድርሰት ስራቸው
ብቻ ነበር ትውስ የሚላቸው፡፡ከሁሉም በማስቀደም የሚፈልጉት ደራሲ መሆንን ነው መዘከርም
የሚፈልጉት በደራሲነታቸው ብቻ ነው፡፡ይሄ ለሳቸው በጣም ጠቃሚ ከመሆኑ የተነሳ ከእውነታው
አራርቋቸው (ከ100 በላይ)የጻፏቸው መጻሕፍት የሚገኙት በዐይነ ህሊናቸው ብቻ ነበር፡፡5

በአንድ የግንኙነታችን ወቅት ግጥም በልጅነታቸው ለሳቸው በጣም ጠቃሚ እንደነበር አሁን ግን
በተውኔት ላይ የበለጠ ፍቅር እያሳደሩ መምጣታቸውን ነገሩኝ፡፡ኢትዮጵያውያን አንባቢዎች
የከበደን “ግጥሞች” “አቻ የለሽ” ሲሉ ያወድሷቸዋል፡፡ግጥምን በትምህርተ ጥቅስ ያስቀመጥኩበት
መክንያት ሁሉም ሰዎች ተውኔቶቻውን እንደ ግጥሞቻው አካል ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ሁሉም
412
ጥቋቁር አናብስት

የተጻፉት በስንኝ ወይም በድርደራ መልክ ነው፡፡ቋንቋቸው ሌላ አቻ የአማርኛ ደራሲ


እስከሚጠፋለት ድረስ“ምትሃታዊ” ነው፡፡ይሄ የወል እይታና ግምት ነው እንግዲህ፡፡

ከገናና ስራዎቻቸው መሃል ከውጪ ተውኔት የተመለሱ ይገኙባቸዋል፡፡እንደ አብዛኞቹ ግምት


የሼክስፕር የሮሜዮና ጁልየት ምልሰት ታላቁ ስራቸው ነው፡፡ከፈረንሳይኛው ትርጉም ላይ
ተመስርተው የሰሩት ቢመስልም፤ከወጡ ስራ ያልተተረጎመ ቢሆንም ይሄ ብዙም ለውጥ
አያመጣም፡፡ ውርስ ስራዎቻቸው ፍትሐዊ እና ባለሙያ ባልሆኑ የአማርኛ ስነጽሁፋዊ እይታ ላይ
የተወሰነ እውቀት ባላቸው የውጭ ዜጎች ነበር የተገመገሙት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅነትን
እንዲያገኙ የገት ፎውስት የውርስ ትርጓሜ ስራቸው ሙሉበሙሉ መቀየር ነበረበት ፡፡አንድ
የትርጉም ስራ በሰፊው ለመነበብ ወይም ወደ ህዝብ ለመድረስ ዋናውን ማእከላዊ ጭብጥን
መንተራሱ ብቻ ይበቃል፡፡ማንኛውም ጠና ያለ ኢትዮጵያዊ ወንድ ከደናግላት መሃል የማማረጥና
እንደ እቁባቶቹ የመያዝ መብት እንዳለው ፡ሴትን ልጅ እንደ እቃ የመቁጠር ልማድ (በኢትዮጵያ
ጥንታዊ ልማድ መሰረት ጠና ያለ እድሜ ያለው ሰው ቅድሚያ ይሰጠው ነበር) በተንሰራፋበት
ባህል ይህ ጭብጥ የፎውስት ድርሰት ውስጥ መኖሩ ለኢትዮጵያዊው ተመልካች ምንም ትርጉም
አይኖረውም፡፡6የሃይልና የገንዘቡ መንስኤ እንኳን በቀላሉ ለማንኛውም ሰው የሚገባ ነው፡፡ከበደ
በአጽንኦት የሚያተኩሩባቸው የሞራል ጉዳዮች ግን ቀድመውም የተተከሉ ነበሩ፡፡በራሳቸው
ትርጉም ላይ ከበደ ከምትሃት ጋር የተገናኙ ቅንጣቶችን ሙሉ በሙሉ በሚያስብል መልኩ
አውጥተዋቸዋል፡፡ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ በከበደ ላይ ሒስን የሰጡት ሰዎች ግን ንፉግ ተመጻዳቂ
ትችታቸውን ያወርዱባቸዋል፡፡በከበደ ላይ የልጅ በሚመስል ሁኔታ መለኮታዊ እርዳታን
ተጠቅመው የዋና ገጸ ባኅርዩን ረዳት በተውኔቱ መጨረሻ አቀንቃኝ ገጸባህርይውን ገደል
እንደከተተው አድርገው ቀርጸውታል ሲሉ ይተቿቸዋል፡፡ የዚህን ዐይነት መስፈርት ለገት ወይም
ሼክስፒር ብናስቀምጥ ማነው እስከአሁን ተውኔቶቻቸውን የሚያነብና የሚያየው? እንዳለመታደል
ሆኖ አፍሪቃ ከምእራቡ አለም ብዙ መጥፎ የስለጽሁፍ ሃሳቦችን ስለተቀበለች የነዚህ ተጽዕኖ
ዘመናዊ ስነጽሁፎቿ ላይ አርፎባታል፡፡7

***

የማውቃቸው በድርሰቱ አለም ውስጥ ያሉም የሌሉም ኢትዮጵያውያን የከበደን የፈጠራ ስራዎች
ልቅም አድርገው ያውቋቸዋል፡፡በርካታ ጸኃፍት የሳቸው ተጽዕኖ እንዳደረባቸው ይናገራሉ፡፡ሁሉም
ወደ ትምህርት ቤት ከጣልያን ወረራ በኋላ የገቡ ልጆች ከስራዎቻቸው አንዱን ሳያነቡ አይቀሩም፡፡
የከበደን ግጥሞች በቃላቸው ተወጥተው እርስ በእርስ ይደጋገሙ እንደነበር ያጫወቱኝ ሰዎች አሉ፡፡
ወደ ኋላ ዘመናቸው አብዮታዊ የነበሩ አንዳንዶች ሳይቀሩ በከበደ ግጥሞች ውስጥ ባሉ ሃገራዊ

413
ጥቋቁር አናብስት

ስሜቶች ተነሳስተዋል፡፡ቋንቋው ቀላልና ግልጽ ሆኖ ሳለ ማንበብ ስንጀመር ወድያው የሚሰወር


ጥልቀት አለው፡፡ለሚያነቡት ሁሉ አጻጻፍ ስልቱ የራሱ ውበትና ሙዚቃ አለው፡፡

በ1970ቹ ሁለተኛ አጋማሽ ከበደ ሚካኤል በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ሲዘዋወሩ ይታዩ ነበር፡፡
በተለይ በፒያሳ አካባቢ ሁሌም እንደባላባት በደንብ ለብሰው ጥቁር መለዮና ካፖርት ደርበው ትንሽ
ሳምሶናይት ይዘው ነበር የሚወጡት፡፡አጭርና በዝግታ የሚጓዙ ቢሆንም ቀጥ ብለው በኩራት ነበር
የሚያዘግሙት ፡፡ፈገግ ሲሉ አይቻቸው አላውቅም::ቢሉ እንኳ ከሳቸው የማይጠበቅ እንግዳ ነገር
ይመስለኛል፡፡ እንደ እደሜያቸው ሳይሆን ገና ይመስላሉ፡፡መጀመርያ ያየሁዋቸው ጊዜ ከልጅነት
ፎቶዋቸው ጋር ያላቸው መመሳሰል ያስገርም ነበር፡፡በራሳቸው የሚተማመኑ ስለእራሳቸው ብቻ
የሚያስቡና አንዳንዴም ግትር ሰው እንደ ሆኑ ነው የኋላ ኋላ የተሰማኝ፡፡አንድ የካቶሊክ ቄስ
አዘወትሮ እንደሚጎበኛቸው ተነግሮኛል፡፡
ከበደ ሚካኤል በርካታ ሰዎችን በህይወት አጋጣሚ አስከፍተዋል፡፡ስለወታደራዊው መንግስት
በግልጽ የተቃውሞ ንግግር በማድረጋቸው ለ6 ወራትም ታስረው ነበር፡፡በተቃራኒው በብዙዎች
የሚከበሩ ብዙዎችም ሊያግዟቸው የሚፈልጉ ሲሆን ከብዶ የሚታያቸው ግን ተቀራርቦ ግላዊ
ግንኙነት መፍጠሩ ነው፡፡አንዳንድ ደራሲዎች ልዩው ደራሲያችን ለሚሏቸው ለእኚህ ሰው (የተለየ
ነገርን ለማድረግ )እየተነጋገሩ ይገኛሉ፡፡

***

የከበደን ምስል ክሱት ለማድረግ የሚያስችል በቂ መረጃ ባለማግኘቴ ከሌሎች ጥናት ያገኘሁትን
ጨምሬ አቀርባለሁ፡፡

በመስከረም 1973 ዓ.ም ለየካቲት መጽሄት የተጻፈ አንድ መጣጥፍ ከበደ 65 አመታቸው
መሆኑን ይናገራል፡፡ይሄ ትክክል ከሆነ የተወለዱት በ1908 ነው ማለት ነው፡፡ቅዳሴን ለመማር ወደ
ቤተክህነት ትምህርት ቤት ነው በመጀመርያ ያቀኑት፡፡ቆይተው ፈረንሳይኛ ጣልያንኛና እንግሊዘኛን
ያጠኑ ሲሆን በስነ ግጥምና በተውኔት ድርሰት አጻጻፍ ላይ ግን ዘመናዊ ትምህርትን አልቀሰሙም፡፡
የቅኔ ትምህርቱ ግን ያለጥርጥር ተጽእኖ አሳድሮባቸዋል፡፡ዋነኛ መምህሮቼ የሚሏቸው ደጋግመው
ያነበቧቸው ከ3000 በላይ መጻሕፍት ናቸው ይላሉ፡፡

አብዛኛው ህብረተሰብ ስለ ከበደ ሚካኤል የግል ህይወት የሚያውቀው ነገር ውሱን ነው፡፡
በጽሁፎቻቸው መቅድም ላይ ባሉት ጥቂት ቃላትም ተንተርሶ፡ ብዙሃኑ ከጽሁፎቻቸው ሌላ
ስለሳቸው የሚያወቀው ቁንጽል ነው፡፡ሆኖም በ1975 ወይም 76 አስፋው አጽማት የተባለ ተማሪ
414
ጥቋቁር አናብስት

ቃለመጠይቅ አድርጎላቸዋል፡፡ይህ ተጨማሪ ተጨባጭ መረጃዎችን ስለ ከበደሊሰጥ ችሏል፡፡ሌላው


ቀርቶ ያልታተሙ የከበደ መጻሕፍትን ታሪክ ለማወቅና አርእስቶች ሁሉ ማግኘት ችሎ ነበር፡፡
የበለጠ ትኩረትን የሚስበው ግን ስለ ከበደ ታሪክ ያገኘው መረጃ ነው፡፡ሌላ ማነጻጸርያ ስለሌለ
በአማርኛም ስለተጻፈ ከቃለ መጠይቁ የተወሰኑ የማረኩኝን ክፍሎች

----

ከበደ ሚካኤል ለአስፋው እንደነገሩት ከሆነ የተወለዱት በ1907 ህዳር ነው፡፡አንኮበር ከተማ፡፡
የአባታቸው ስም አይታገድ ሲሆን የእናታቸው ደግሞ አጸደ ሚካኤል ነው፡፡በጽድአምባ ግዮርጊስ
ክርስትና የተነሱ ሲሆን ስመ ክርስትናቸው ቀጸላ ግዮርጊስ ነው፡፡ከበደ ተወልደው ብዙም ሳይቆዩ
አባታቸው እናታቸውን ጥለው ስለሄዱ ከበደ አባታቸውን አይተው አያውቁም ፡፡ለዛም ነው
በተለመደው መልክ ሳይሆን የእናታቸውን አባት ስም ለመጠርያነት የወሰዱት፡፡ከበደ
ትምህርታቸውን በአራት አመታቸው ሲጀምሩ ከሴት አያታቸው ጋር ነበር የሚኖሩት፡፡አያታቸው
የጣራውዷ ወይዘሮ ወለተ ገብርኤል ይሰኛሉ ፡፡ከአለቃ ተክለ ግዮርጊስ ስር በወንድ ሃያታቸው
ደጃች መኩርያ በተተከለው ገርብ ገብርኤል ነበር ዳዊት የደገሙት፡፡ግዕዝንም በደንብ
አስተምረውኛል ይላሉ፡፡

በ 9 አመታቸው እናታቸውና ሴት አያታቸው ወደ አሩሲ ሄዱ፡፡በዚህ መክንያትም ከበደን አዲስ


አበባ በካቶሊክ ሚሲዮን ካቴድራል አስገቧቸው ፡፡አዲስ አበባ ምንም ዘመድ ስለሌላቸው
በአልያንስ ፈረንሳይኛ ሲማሩ በካቶሊክ ሚስዮኑ ዳረጎት መቆየት ነበረባቸው ፡፡አምስት አመታትን
በዚህ ትምህርት ቤት ከገፉ በኋላ እናታቸው ከአርሲ ስለመጡ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡መምህራኑ
ስለሚመቷቸው ከበደ አሌያንስን አልወደዱትም፡፡ስለዚህም ወደ ላዛሪስት ሚሲዮን ተዛወሩ፡፡በኋላ
ግን ወደ አልያንስ ተመልሰዋል፡፡ዳይሬክተሩ(ሚስተር ማህላቢ እሱን ጨምሮ ሌሎቹም
ሊባኖሳውያን ነበሩ)የልብወለድ አጻጻፍ ስልትን(እራሱም ይጽፍ ስለነበር)ማስተማር ጀመረ፡፡ከበደ
ሚካኤልን ጨምሮ እዛ ቡድን ውስጥ ባሉ ስድስት ልጆች ላይ የልብ ወለድ ፍቅርን መትከል ቻለ፡፡
ከበደ ፈረንሳይኛ አስተማሪውንም በጽሁፎቹ የተነሳ ይወዱት ስለነበር ከ12 ሰአት በኋላ በግል
እሳቸውን ማስጠናት በመጀመሩ ከበደ ፈረንሳይኛን አቀላጥፈው ከመናገራቸውም በላይ
በትምህርታቸው በጣም ጥሩ ውጤት ማምጣት ጀመሩ፡፡ትጉህም ብሩህም ስለነበሩ የትምህርት
ቤቱ አስተዳዳሪዎች ለንጉስ ኃይለሥላሴ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ በተጨማሪ እንዲማሩ ጥያቄ አቀረቡ፡፡
ንጉሱ ቢስማሙም ከበደ ስለታመሙ መሄድ አልቻሉም፡፡በዚያ ወቅት ሁለት መምህራን ከፈረንሳይ
ልዑል አልጋ ወራሽን ሊያስተምሩ ስለመጡ ከበደም ሶስተኛ መምህር ሆነው ተቀላቀሉ፡፡ይሄ
ጤናቸው እስከሚሻሻል የተያዘ አዲስ እቅድ ቢሆንም የጣልያን ወረራና የንጉሱ መሸሽ ነገሩን ሁሉ
አበላሸው፡፡ቢሆንም ከበደ በልኡል አልጋ ወራሽ መምህር አቶ ሌሞይን በተቋቋመው ትንሽ

415
ጥቋቁር አናብስት

ቤተመጻሕፍት የሚነበብ ነገር አላጡም፡፡ካነበቧቸው መጻሕፍት መሃል የናፖሌዎን ግለታሪክን ነበር


በጣም የሚወዱት ለሶስት ጊዜያት ያህል ደግመው አንብበውታል፡፡
በከበደ ላይ የልብ ወለድ ፍቅርን ካሳደሩት ሌሎች ሰዎች መሃል የልዑል አልጋ ወራሽ የግዕዝ
መምህር የነበሩት አለቃ ወልደ ጻዲቅ ናቸው፡፡እኚህ ሰው በጊዜው የትምህርት ምኒስትር የነበሩት
ሳህለ ሳድሉ የልብ ወዳጅ ስለሆኑ ከዚያ መጻሕፍት ሲላክላቸው ለከበደ ይሰጧቸው ነበር ከበደም
በተራቸው ፈረንሳይኛ ያስተምሯቸዋል፡፡
በጣልያን ወረራው ጊዜ ከበደ ጣልያንኛን አጥንተው ብዙ በጣልያንኛ የተጻፉም ሆነ ትርጉም
መጻሕፍትን የማንበብ እድል አጋጥሟቸዋል፡፡ከበደ ጣልያን ሃገሪቱን ሲያጠቃ እድሜያቸው 20
አመት አካባቢ ነበር፡፡በጣልያን ይዞታ ስር ሃገሪቱ በነበረችበት ወቅትም ብርሃነ ህሊናን ጻፉ ጣልያን
ሃገሪቱን በወረረችበት አመታትም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጨረሱ፡፡

ብዙ መጻሕፍት ከወረራው በኋላ ተቃጥለው ስለነበር ታሪክና ምሳሌን ጻፉ፡፡ቀጥለው የቢ.ክሌይን


beyond pardon ሃሳቡን በመውሰድ ወደ አማርኛ በግጥም መልክ አዋረሱት፡፡ከበደ አሁንም
የጤና ችግር ስላለባቸው የሚኖሩት የጨርጨር ምክትል ገዢ ከሆኑት አጎታቸው ሰይፉ ሚካኤል
ጋር ተጠግተው ነው፡፡ከአጎታቸው ቤት አቅራቢያ የመማርያ ቋንቋው እንግሊዘኛ የሆነ ትምህርት
ቤት ስላለ ከበደ እንግሊዘኛ ትምህርታቸውን እዚያ ጀመሩ፡፡የአጎታቸው ሚስትም እንግሊዘኛ
ቋንቋን ትችል ስለነበር ከእሷ ጋር ለመለማመድ እና beyond pardon ለማንበብ ለመተርጎም
በቁ፡፡በዚህ ጊዜ የቴአትር ፍላጎትም በማሳደር ከታላላቅ የአውሮጳ ተውኔቶች ጋር ተዋወቁ፡፡
ሼክስፒርን ለማድነቅ ብሎም ሮሜዮና ዡልየትን ወደ አማርኛ ለመመለስ ቻሉ፡፡በዚህ መጽሃፉ ላይ
ያለው የአማርኛ ዘዬው የከበደ ምርጡ ነው፡፡ የbeyond pardon ወደ አማርኛ የመመለስ
ስራውን ከከወኑ በኋላ የራሳቸውን ተውኔት የትንቢት ቀጠሮን ደረሱ፡፡

በጣልያን ወረራ ወቅት ለጣልያኖቹ የስርጭት ሰራተኛ የነበሩ መሆኑን ግን አንስተው አያውቁም፡፡
ተገደው ይሁን ወደው ያደረጉት እንደሆንም አይታወቅም፡፡

ከነጻነት በኋላ ከበደሚካኤል ለማንበብ ለመጻፍና መጻሕፍትን ለማሳተም ፍላጎት አደረባቸው፡፡


በተከታታይነትም ያደረጉት ይህንኑ ነበር፡፡በሺዎች የሚቆጠሩ መጻህፍትን አንብቤያለሁ ይላሉ፡፡
በትምህርት ሚንስትር በተቆጣጣሪነት ተቀጠሩ፡፡ቀጥሎም ለአምስት አመታት ወደሰሩበት ውጭ
ጉዳይ ሚንስትር ተዘዋወሩ፡፡ልጅ አርአያ ሃይሌ ከለቀቁም በኋላ የብሄራዊ ቤተመጽሐፍት ስራ
አስኪያጅ ሆኑ፡፡ከበደ የስነቅሪት ቤተመዘክርንም አቋቁመዋል፡፡ከዚያም በመቀጠል በትምህርት
ሚንስትር ለአራት አመታት በተጠባባቂ ሚንስትርነት ሰሩ፡፡በዚህ ጊዜ በርካታ ትምህርት ቤቶች
ታንጸዋል፡፡ቀጥሎ ወደ ፖሰታ ተዘዋውረው በምክትል ሚንስትር ሹመት ብሎም ወደ

416
ጥቋቁር አናብስት

ግርማዊነታቸው ካቢኔና ወደ ዙፋን ቤተመጻህፍት ተወሰዱ፡፡እንደኔ ግምት ከዛ በኋላ እስከ አብዮቱ


ድረስ በጡረታ እንደቆዩ ነው፡፡ከበደ የሚጽፉት በትርፍ ጊዜያቸው ሲሆን ታሪኮችን በ15
አመታቸው ግጥምን በ18 አመታቸው መጻፍ እንደጀመሩ ይናገራሉ፡፡የአማርኛ ስነጽሁፍ በከበደ
አንድ እመርታን አሳይቷል፡፡

የተርጓሚ ማስታወሻ -ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል በጥቅምት 26 ቀን 1990 የክብር ዶክትሬት
ማዕረግ ሲበረከትላቸው ህዳር 3 1991 አርፈዋል፡፡ከመጻሕፍቶቻቸው መሃል የእውቀት
ብልጭታ፤ የመጀመርያ እርምጃ፤ታሪክና ምሳሌ፤ታላላቅ ሰዎች፤የኣለም ታሪክ፤ብርሃነ ሕሊና፤የቅኔ
አዝመራ፤ የቅኔ ውበት፤ጃፓን እንዴት ሰለጠነች፤የትንቢት ቀጠሮ፤አኒባል፤በላይነህ(የቅጣት
ማእበል)፤ ካሌብ፤ አክዐብ፤ቅዱስ ገብርኤል በምድረ ገነት እና የመሳሰሉት ሲገኙ ከእረፍታቸው
በኋላም ለህትመት የበቁ በርካታ ስራዎች አሉ፡፡

ማስታወሻ

1)አዲስ አበባና ቢሾፍቱ ከተማ ስለሚገኙት ቤታቸው ብዙም ቅር አይሰኙም፡፡በግቢያቸው


የሚገኘውን የጽህፈት ቤታቸውን ሲወስዱባቸው ግን ባሰባቸው፡፡ውድ ውድ መጻህፎቻቸውንና
ሰነዶቻቸውን ሰብስበው አቃጠሉ፡፡

2)መጀመርያ እቴጌ ሆቴል ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ኋላ ስሙ ወደ አውራሪስ ተቀየረ፡፡አብዮተኞቹ


በምኒሊክ ጊዜ እንደተሰራና በኃይለሥላሤ ሚስት ስም መሰየም እንደማይችል ሲያውቁት ወደ
ቀድሞ መጠርያው-ጣይቱ መለሱት፡፡

3)በወቅቱ ጫት ለሚቅሙና መጠጥ ለመጠጣት ለሚፈልጉት አረቦች ተመራጭ ቦታ ነበር፡፡

4)በሆቴሉ የሚሰሩ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ አንዳንዴ በንዴት ብው የሚሉበት ወቅቶች አሉ፡፡
ይህንን ለመመስከር ባልበቃም አንዳንዴ ባህርያቸው ላይ አንድ ጥላ ሲያጠላ ይታየኝ ነበር፡፡

5)ተውኔት፤ልብወለድ፤ግጥም፤ማህበራዊና ታሪካዊ ስራዎች ብለው ከፋፍለዋቸው ከነአርእስታቸው


ይዘዋቸው ነበር፡፡ይሄ ነገር ሊታወቅ የቻለው ምስጢር ያጋለጡ በመሰላቸው ጋዜጠኞች ነው፡፡

6.ነገሮች እየተለዋወጡ ነው፡፡ዘመናዊ ተመልካቾች አሁን አሁን ፎውስት ተተርጉሞ


ቢቀርብላቸውም የማጣጣም ብቃቱ ይኖራቸዋል፡፡

417
ጥቋቁር አናብስት

7.አንድ ጠቃሚ የምእራባውያን ነጥብ ክስተቶችን በተውኔት መሃል መፍጠር ሲሆን ቀደምት
የኢትዮጵያና የአፍሪካ ስራዎች ግን ይህ ያጥራቸው ነበር፡፡ኢትዮጵያውያን ምንአልባትም ህይወትን
እንደማትለወጥ ድንገቴ ክስተት የሌላት አድርገው ያዩዋት ይሆናል፡፡በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ
ታድያ እንዴት ነው የምእራባውያን ተጽእኖ ሊያርፍ የሚችለው?የኢትዮጵያና የተቀረው የአፍሪካ
ጸሃፊዎችም ችግራቸውን በራሳቸው እንዲፈቱት መተዉ የተሻለ ነው፡፡

418

You might also like