Professional Documents
Culture Documents
አይደሉም!
የአገራችንን ታሪክ ያላነበቡ አንዳንድ ግልቦች ባንዳንነትና አርበኛነትን በነገድ፣ በአካባቢና በሃይማኖት ሲወስኑት
ማየት የተለመደ ሆኗል። በመሰረቱ አርበኛነት የግለሰብ ውሳኔ፣ ብርታትና ጥንካሬ ውጤት እንጂ አንድ ሰው
የአንድ ነገድ አባል ስለሆነ፤ ከአንድ አካባቢ ስለተወለደና የሆነ ሃይማኖት ተከታይ ስለሆነ የሚሰፍርበት ዛር
አይደለም። ባንዳነትም እንዲሁ ነው። አንድ ሰው የአንድ ነገድ አባል፣ የአንድ አካባቢ ተወላጅ ወይም የአንድ
ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ ባንዳ አያደርገውም ወይም ባንዳ እንዳይሆን አያግደውም።
የአገራችን ባንዶች ከሁሉም የአገራችን ነገዶች፣ አካባቢዎችና ሃይማኖቶች ይመዘዛሉ። ጸረ ፋሽስቶቹን አርበኛ
አባቶቻችንን በዱር በገደሉ እያሳደዱ የወጓቸው ከሮም የመጡ ነጭ የጣሊያን ወታደሮች አይደሉም። ጀግኖች
አባቶቻችን በብዛት የወጓቸው ባንዶች አጎቶቻችን ናቸው።
የአገራችን ባንዶች በነገድ፣ በአካባቢና በሃይማኖት ሳይወሰኑ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ያገለግሎ እንደነበር ለግንዛቤ
ያህል ለማሳየት በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት ፋሽስት ጣሊያንን እስኪያልባቸው ድረስ ያገለገሉና
ጀግኖች አርበኞቻችንን እያሳሰዱ የፈጁ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ዋናዋና ባንዶችን ስም ዝርዝር
እንደሚከተለው አቀርባለሁ፤
የአማራ ባንዶች
የትግሬ ባንዶች
የኦሮሞ ባንዶች
ልብ በሉ! እነዚህ ባንዶች ዋና ዋናዎቹና ከዋናዋናዎቹም በጣት የሚቆጠሩት ናቸው እንጂ በየነገዱ፣
በየአካባቢውና በየሃይማኖቱ የፈላው የባንዳ ቁጥር እልቆ ቢስ ነው። የሆነው ሆኖ ይህ የአገራችን ዋና ዋና
ባንዶች ማንነትና ስብጥር የሚያሳየን ነገር ቢኖር ጀግኖች አባቶቻችንን ሲያሳድዱ የነበሩት ባንዶችአጎቶቻችን
በነገድ፣ በአካባቢና በሃይማኖት ያልተወሰኑ በሁሉም ነገዶች፣ አካባቢዎችና ሃይማኖቶች ውስጥ የፈሉ ጉዶች
መሆናቸውን ብቻ ነው።
ባጭሩ ባንዳ የሌለበት ነገድ፣ አካባቢና ሃይማኖት እንደሌለ ሁሉ አርበኞም የሌለበት የኢትዮጵያ ነገድ፣ አካባቢና
ሃይማኖት የለም። ስለዚህ እያንዳንዱ ያገራችን ነገድ፣ አካባቢና ሃይማኖት አርበኛ እንዳለው ሁሉ እልቆ
መሳፍርስት ባንዳም አፍልቷልና ባንዳነትን በነገድ፣ በአካባቢና በሃይማኖት በመወሰን የሚደረገው የአላማቂዎች
መመጻደቅ የእውቀት ጾመኛነታቸውን ከማስመስከር ባለፈ ቁምነገር የለውም።
የኢትዮጵያ ባንዶች በነገድ፣ ባካባቢና በሃይማኖት ያልተወሰኑ፤ ብሔር፣ ብሔረሰብ ከሚባሉት በሚሉ
የተውጣጡና በየአካባቢው የነበሩ ባንዶች ቁጥራቸው ከአርበኞቻችን እጅጉን ይልቅ እንደነበር ከነማንነታቸው
ማወቅ የሚሻ ቢኖር፤
10 ኛ. የአቶ ግብረ ወልድ እንግዳ ወርቅን “ማይጨው፤ የማይጨው ዘመቻና የጉዞ ታሪክ”፣
15 ኛ. የኮሎኔል ዳዊት ገብሩን “ከንቲባ ገብሩ ደስታ የኢትዮጵያ ቅርስ” መጽሐፍ ያንብብ!