Professional Documents
Culture Documents
የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን
በቅድሚያ ከሁሉ አስቀድሜ የአማራ ፋኖ እስክንድር ንጋና መላው ይፋኖ ታጋዮች ለእናንተ
የላኩትን የከበረ ሰላምታ ለማቅረብ እወዳለሁ። ጀግናው የነጻነት ታጋይ፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ
ቀን ልጅ፣ የድሆች ጠበቃ፣ የነጻነት ታጋይ፣ እስክንድር ነጋ በውጪ ሃገር ሆናችሁ በተለያዬ
መንገድ የፋኖን ትግል ለምትደግፉ ሁሉ በአማራ ፋኖ ታጋዮች ስም ምስጋናው ብዙ አድናቆቱ
እጥፍ ድርብ እንደሆነ ገልጿልና በዚህ አጋጣሚ ይህንን መልዕክት እንድትቀበሉ በአክብሮት
እጠይቃለሁ።
ውድ ወገኖቼ
እዚያ አካባቢ በተንቀሳቀስኩ ቁጥር ይህንን መርህ ስመለከት ለአማራ ወገናችን ለኢትዮጵያ
አገራችን ፋኖ የገባውን ቃለ ምህላ ዘወትር የምናስታውስበት የምናድስበት እንዲሆን እውቀትና
ንቃት እንዲስጠን እፀልያለሁ:: The Spirit of Amhara The Spirit of Ethiopia : Live Free
or Die ወይም የአማራነት መንፈሥ ከኢትዮጵያ መንፈስ አይለይም እላለሁ፣ ነጻ ሆነን ለመኖር
እስከ ሞት መስዋዕትነትን እንከፍላለን። እንግዲህ ለነጻነት የሚታገለውን ፋኖን እግዚአብሄር
ያጠናክርልን:: መስዋእትነቱን ቀንሶ ህዝባችን በነፃነት የሚኖርበትን ጊዜ ያቅርብልን እላልሁ::
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ
እውነት ነው። የሰው ልጅ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ህይወቱ ነጻ ይሆን ዘንድ
አጥብቆ ይሻል። ይህ ነጻነቱ ሲገሰስ ሙሉነት አይሰማውም። የነጻነት እጦቱ ለከት የሌለው
ሲሆን ደግሞ ለነጻነት ትግል እስከ ሞት ይታገላል። live free or die ወይም በነጻነት ኑር አለያ
ብትሞት ይሻላል ብሎ ታጥቆ በነጻነት አውድማ ላይ ህይወቱን እንኳን ሲሰጥ ከቶውንም ትንሽ
አይሰስትም።
አማሮች በተለይ ባላፉት ዓመታት በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር እጦት እንደ ሌላው
ኢትዮጵያዊ ሁሉ እየተሰቃዩ መኖራቸው ሳያንስ በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ሌላ ጥቃት ሰለባ
ሆኑ። አማሮች ብዙ ዋጋ በከፈሉላት ሃገራቸው፣ በሞቱላት ኢትዮጵያ ውስጥ ጎጆ ቀልሰው
ለመኖር ያልቻሉበት ሁኔታ በምድሪቱ ተፈጠረ። ከጉራ ፋርዳ የጀመረው ብሄር ተኮር ጥቃት
በተለይ በአብይ አህመድ ዘመን የደረሰውን የአማሮች ስደት፣ ግድያና የንብረት ዝርፊያ ከቶ ምን
ሃይለ ቃል፣ ከቶ ምን አንደበት ይገልጸዋል?። አማራ ምን ያልሆነው ነገር አለ?
እንግዲህ መቼም፣ አንድ ህዝብ ግፍን ተሸክሞ የሚኖርበት የሆነ ልክ ይኖረዋል አይደለም?
የአማራ ልጆች እጅግ የሚሳሱላት ሃገራችው ኢትዮጵያ በህገ መንግስት ፈራሽ ናት ተብላ
የተፈረደባት ሀገር ስለሆነች አገሪቱ በቋፍ ሆናለችና እኛን አማሮችን ነጥሎ የሚያጠቃን ስርዓት
ቢኖርም፣ ግፍ ቢበዛም፣ በአማራ ስም አንደራጅም፣ የከፈልነውን ዋጋ ከፍለን በኢትዮጵያዊነት
ጥላ ስር ሆነን ትግላችንን መቀጠል አለብን በሚል በየእለቱና በየወሩ፣ በማንነቱ ለሚጠቃው
አማራ ተገቢ መከታና ጋሻ ሳይሆኑለት ቆዩ። አማሮች በብሄራቸው፣ በማንነታቸው
መደራጀታቸው ለሃገራዊ አንድነት አይጠቅምም፣ እስቲ ጊዜ ያልፍ ይሆናል እያሉ ቢጠብቁም
በአማሮች ላይ የሚደርሰው የማንነት ተኮር የጥቃት ጦር ከቶውንም አልበርድም አለ። ይባስ
ብሎ ማንነት ተኮር ጥቃቱ እየተሻለ ሳይሆን እያደር እየከፋ.... እየከፋ.... እየከፋ መጣ። አሁን
አማሮች ማንነት ተኮር የሆነውን ጥቃት ለመመከት በማንነት ከመደራጀት ውጪ ሌላ አማራጭ
የጠፋበት ደረጃ ላይ ደረሱ። እነሆ ተደራጁ፣ ከእንግዲህ ምንም ዓለማዊ ሀይል ይሁንን ትግል
ወደ ኋላ አይመልሰውም::
እስከ ዛሬ ድረስ በአንድ በኩል ከክልሉ ውጪ የሚሆነው አማራ በማንነቱ ሲፈናቀል፣ ሲገደልና
ሲዘረፍ በሌላ በኩል በክልሉ ውስጥ የሚኖረው አማራ ደግሞ በመልካም አስተዳደርና በድህነት
የሚቀጣው ክፉ አስተዳደር እንደ መዥገር በላዩ ላይ ተጣብቆበት ቆይቷል። አማራ በክልሉ
ውስጥም ከክልሉ ውጪም ሳይመቸው ኖረ። ይህ ህዝብ ህወሃት የተከለው ደካማ አስተዳደር
ከዛሬ ነገ ይሻል ይሆናል ብሎ በጀርባው አዝሎ ቢቆይም ይህ አስተዳደር ለአማሮችም ሆነ
ለኢትዮጵያ ተስፋ የማይሆን እንደሆነ በተግባር ታዬ። ስለሆነም አማሮች ይህንን አስተዳደር
በቃኝ አንተን የማዝልበት ማንገቻዬ ተበጥሷል ብለው እነሆ ዛሬ ከባድ ትግል ላይ ናቸው።
በቅርቡ እንደምታስታውሱት የአማራ ህዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ በይልቃል ከፋለ ይመራ የነበረውን
የብልጽግና ካቢኔ አፍርሶ እንደነበር ታውቃላችሁ። ይሁን እንጂ ትንሽ ትምህርት
የማይወስደው የአብይ አህመድ አስተዳደር ከይልቃል ከፋለ ካቢኔ የባሰ ሌላ የብልጽግና ካቢኔ
አቋቁሜ አማሮችን አስተዳድራለሁ ብሎ ተነሳ። የአብይ መንግስት ይህንን በማሰቡ በአማሮች
ዘንድ የተደረገውን ትግል መናቅ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መራራ ትግል
ላይ ይገኛል።
ዛሬ የአማሮች ትግል ህዝባዊነቱ አድጎ ባህላዊ የአማሮች የክተት ጥሪ ታውጆ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣
ሸዋ፣ ወሎ ድረስ ያስተጋባ መለከት ተነፍቷል። የአራቱም ክፍሎች የፋኖ መሪዎች አጠቃላይ
እዝ እየመሰረቱ ናቸው:: የአማራን ማንነት በተግባር እያሳዩ ነው:: አማራ ማለት ትርጓሜው ነጻ
ህዝብ ማለት ነውና በሃገራችን በነጻነት መኖር ካልቻልን ለነጻነት እየታገልን ልንሞት መርጠናል
ብለው የአማራ ልጆች በአጭር ታጥቀው እየታገሉ ነው። live free or die ብለው ፋኖዎች
በነጻነት፣ የመኖር መብታቸውን ለማስከበር ለእኩልነትና ለፍትህ ቤዛ ለመሆን በተዋጊነት ስልት
ተደራጅተውና በአጭር ታጥቀው እነሆ የአብይ አህመድን አገዛዝ እያርገበገቡት ይገኛሉ።
በክልሉ ውስጥ ከፋኖ የቅርብ ርቀት ቁጥጥር ውጭ የሆነ ከተማም ሆነ ገጠር የለም። ፋኖ
በየትኛውም ጊዜ የትኞቹንም ቦታዎች ተቆጣጥሮ እያሰላ ወደፊት እየተራመደ ነው።
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ
1. ሀይማኖት
2. ታሪክና እሴት
እዚህ ላይ የሚነሳ ጥያቄ ይኖራል። ታዲያ አማራነትና ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የተሳሰሩ ከሆኑ
የአማራ ፋኖ ትግል ምንድን ነው? የአማራ ጥያቄስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና የአማራን ትግል ዓላማ በሚገባ ማጥራት ተገቢ ነው።
አማሮች ከፍ ሲል እንደገለጽነው የብሄርተኝነት ትግል ላይ አይደሉም። ብሄርተኝነት
(ethnonationalism) የሚባለው አስተሳሰብ ፖለቲካው ሁሉ በብሄር ይሁን፣ እኔም አንድ
የአማራ ፖለቲካ ፓርቲ ይኑረኝ፣ የፌደራል ስርዓቱ በብሄር ላይ ተከልሎ ይቆይ፣ በእኔ ክልል
መስተዳደር ውስጥ ከአማራ ሌላ የሌላ ብሄር ሰው አይሾምብኝ፣ ወዘተ አይደለም። አማሮች
ለመዋቅራዊ ለውጥ እንታገላለን ሲሉ አንዱ የሚታገሉት ነገር ይህንን ለእኔ ለእኔ የሚባል የስስት
ፖለቲካ ነው።
ታዲያ በዚህ ወቅት አማሮችን ያደራጃቸውና መራራ ትግል ውስጥ የከተታቸው ምንድን ነው?
ብለን ከጠየቅን የአማሮች ጥያቄዎችና በአማራነት ተደራጅተው የሚታገሉላቸው አንኳር
ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው።
4. ትጥቅ አንፈታም
ውድ ወገኖቼ
ውድ ወገኖቼ