You are on page 1of 18

በአማራ ተማሪዎች ማህበር ( )

አተማ

የተዘጋጀ

“ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን”

“ሰብአዊነትና ፍትሐዊነት ይጠበቁ”

“አማራ ታሪክ ሰሪ እንጅ ታሪክ አጥፊ ሆኖ አያውቅም”

“የነጻነት ትግልና የፍትሐዊነት ጥያቄ የትርፍ ጊዜ ሥራ ሳይሆን የሰብአዊነት ትግል ነው”

“የኢትዮጵያውያን ህብረት ለቀጠናው ዋስትና ነው”

“ በአማራ ላይ ያነጣጠረ የውሸት ትርክት በአርበኛ ፋኖ ትግል ይከሽፋል(ይቆማል)

1
1. መግቢያ

ለፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ትግል መነሻ የሆኑ ምክንያቶች በጥቅል የእኩልነት ፤የፍትህና ነጻነት እጦት በፋኖ
አርበኞች ግንባር ጥቅል ምክንያት ተደርገው የሚወሰዱ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ይዘት
ያላቸው ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ የተሳሳቱ ትርክቶችና ከዚህ በመነሳት በተጨባጭ የሚደርሱ
ጥቃቶችና በደሎች እንዲሁም የወደፊት ከባድ ሥጋቶችና የሥጋት አቅሞች መነሻ ሁኔታ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

በመሠረታዊነት ኢትዮጵያን በማፍረስና በመበታተን ታሪክ አልባ ሕዝብና ሀገር ለመፍጠር የሚኳትኑ የውስጥ
ደካማ ፖለቲከኞችና የውጭ ኃይሎች በተናጠልና በጋራ የአማራን ሰፊ ሕዝብ የማዳከም ስትራቴጅ ቀርጸው
የመንቀሳቀሳቸው ጉዳይ ውሎ ያደረ እውነት ነው፡፡ ይህ ያልሰለጠነ ፖለቲካዊ አስተሳሰብና እኩይ ዓላማ እንደዚህ
ቀደሙ ተችሎና በለሆሳስ ሊታለፍ የማይገባው በመሆኑ ለግንባሩ ወቅታዊ መነሳሳትና እንደገና መደራጀት መነሻ
ምክንያት ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኢትየጵያውያን እህትና ወንድሞች ጋር በኢትየጵያ የነፀነትና የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ
የአኩሪ ገድል ባለቤት ነው፡፡ የአማራ ሰፊ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵይውያን ጋር አጥንቱን ከስክሶ፤ ደሙን አፍሶ፤
ሥጋውን ቆርሶ በእየድንበሩ እንደኮለን ተቀብሮ በመሰረታት ሀገር ውስጥ መብቱንና ነጻነቱን የሚቀፈድድ፤
ሰብአዊነቱን የሚያዋርድ የመንደርና የጎጥ ህጎች እየወጡ በገዛ ሀገሩ ውስጥ የከፋ በደል ደርሶበታል፡፡
እየደረሰበትም ይገኛል፡፡ ይህ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት ህዝብ መብትና ነጻነቱን ክብሩን ተገፏል፡፡ በአብዛኛው የሀገሪቱ
ክፍል ውስጥ የዳር ተሳታፊና የሁለተኛ ዜግነት እድልና እጣ ፈንታ እየገጠመው ይገኛል፡፡ ይባስ ብሎ በራሱ
አስተዳደራዊ ክልል ውስጥ እንኳን በተጫነበት ኢ አማራ የመድሎ ህጎችና አሰራሮችና ውሳኔዎች ለከፋ
አስተዳደራዊ በደልና ፖለቲካዊ ጉስቁልና ተደርጓል ፤፤በመሆኑም ይህንን የከፋ መከራና ሶቆቃ ለማስተካከል
የተደራጀና በሳል ፖለቲካዊ ትግልና ፋኖአዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ግድ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የሰው ልጆች በተገቢው ክብር ለመኖር በመጀመሪያ ነጻነትና ፍትህ
መሆኑን ያለተገዳዳሪነት ተቀባይነት እያገኘ የመጣ ሀሳብ ሆኗል፤፤ ይህ መሪ ሀሳብ ከአማራ ህዝብ ወቅታዊ
ጥያቄና መብት ሁኔታ አንፃር ሲመዘን ይህ ጉዳይ በአንክሮ እንድንመለከተው ያስገድደናል፡፡ ሰፊው የአማራ ህዝብ
በመሰረታትና መስዋዕትነት ከፍሎ አስከብሮ ባቆያት ሀገር ውስጥ የመኖር መብቱና ነጻነቱ ተገፍዋል፡፡ በሀገሪቱ
ጠረፍ እንደወታደር ድንበር አስከባሪ ሆኖ ተሰማርቶ ያፈራውን ሀብትና ንብረት በጠባብ ፖለቲከኞች የተደራጁ
ህገወጥ ኃይሎች ለዓመታት ተቃጥሎአውል፤ ተዘርፍዋል፤ ይህ አሁንም ያለ ሀይባይ ተጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል፡፡
በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ የአማራ ህዝብ እንዲገደል ፤እንዲሰደድ ሀገር አልባ እንዲሆንና ለአሰቃቂ በደልና
መከራ እየተዳረገ ያለበት ወቅት ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር ለ 27 ዓመታት አጀንዳ ተደርጎ በተሰራ የውሸት ትርክት የአማራን ታሪክና ገጽታ የሚያጠለሹ እንቅስቃሴዎች
ተደርገዋል፡፡ ሰፊው የአማራ ህዝብ ባደረገው አስተዋጽኦ ልክ ተጠቃሚ መሆኑ ይቅርና ህልውናውን የሚፈታተኑ
ጸረ አማራና ኢት ዯ ጵ ያ እንዲሁ ም ጸረ ኦርቶዶክስ የሆኑ እንቅስቃሴዎ ች ና ህገወጥ ተግባሮች እየተፈጸሙ
ይገኛሉ፡፡ በዚህም ሰፊው የአማራ ህዝብ በማንነቱና በእምነቱ፤ በኢትጵያዊነቱ ዯጵያዊነ ቱ እንዲሁም

2
በባንዴራው ላይ ባለው ጽኑና የማይናወጥ አቅዋም ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በአሰቃቂ ሁኔታ
እየሞተና እየተሳደደ ይገኛል፡፡

በዚህ ወቅት እነዚህ አሰቃቂ በደሎች በከፋ ደረጃ ላይ የደረሱ በመሆናቸው እነዚህን መመከት የአማራና
የሌሎች የኢትዮጵያዎያን መሰባሰቢያ አጀንዳና የትውልዱ ብቸኛ አማራጭ እንጅ በቁዘማና በለቅሶ
የሚታለፍበት ዘመን የደረስንበት ጊዜ አሁን መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

የአማራ ህዝብ አስተሳሰቡና እድገቱ ኢትጵያዊ


ዯየ ሆነና ከሌሎች ኢትጵያጵውያን
ዯህ ዝቦች ጋር በጋራ መኖር
የሚችል ሰብአዊነትን መሠረት ያደረገ ሥልጡን ህዝብ ቢሆንም የኢትጵያውያንዯታ ሪክና እውነታ በማይመጥን
መንገድ በተቀየሠው የፌደራሊዝም የአደረጃጀት ስልትና ፍርደ ገምድል አሰራርና አደረጃጀት ክብርና ታሪክ
ያላትን ሀገር እየቆራረሱና እያፈራረሱ ያሉ ኃይሎች አማራው በደሙ በመሰረታት ሀገር ውስጥ በብዙ መልኩ
የሚገለጽ የከፋ በደልና ችግር እያደረሱበት የሚገኙ ከመሆኑ ባሻገር በተለይ ተወልዶ ባደገበት ቀየና ርስቱ
በሆኑት ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ መተከል፤ ራያና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ሀገር አልባ እንዲሆን በመደረጉ ይህ
ህገወጥና አሳፋሪ ተግባር በመሆኑ ይህ ጉዳይ የፋኖ አርበኞች ግንባር የትግል ዘውግና መነሻ ተግባር ነው፡።

በአሁኑ ወቅት በግልጽ ከሚንቀሳቀሱ ጸረ አማራና ኢት ዯ ጵያ ግንባሮችና ፖለቲካኞች እንዲሁም ድርጅቶች


ባሻገር ከአማራ ጉያ የወጡ አመራሮችና ድርጅቶችም ቢሆን በተዳከመ አደረጃጀትና በተፅዕኖ ውስጥ ያሉ
ከመሆናቸው ባሻገር በግልፅ የተጠለፉና አጀንዳ ፈፃሚ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለለየላቸው ፀረ አማራና ፀረ
ኢትጵያ
ዯኃ ይሎች ሰርጎ ገብነት ምቹ መደላድል ሆኖ የሚገኝ በመሆኑ በመላ ህዝቡ ውስጥ በግልፅ አቅዋም
ይህንን የሚያስተካክልና የሚታገል፤ ይህንን አፍራሽ አካል ወደ በጎ አቅምነት የሚቀይር ኃይልና ግንባር እጅ
አስፈላጊ በመሆኑ ሌላው የግንባሩ መነሻ ነጥብ ነው፡፡

በመጨረሻ የኢትጵያ
ዯህ ዝብና የኢትጵያ
ዯታ ሪክ እንከን ባጋጠመው ጊዜ የክፉ ዘመን የትግል አቅምና
አደረጃጀት ፋኖአዊ የአርበኝነት ትግል ማድረግ በመሆኑ በዚህ ወቅት የዚህ ግንባር እንቅስቃሴ ዘመኑን
የሚመጥን፤ የአማራንና የኢትጵያን
ዯህ ዝብ ወቅታዊ ችግሮች የሚፈታ፤ ተግዳሮቶችን የሚመክት የትግል
ሥልት በመሆኑ በቀዳሚ አማራጭነት መወሰዱ እጅግ ተቀባይነት ያለው መሆኑ ሊጤንና ከግንዛቤ ሊወሰድ
የሚገባው ነው፡፡

2. የአተማ የትግል መነሻዎች

ድርጅቱ ወይም ግንባሩ ሲመሰረት የትግል መነሻ ያደረጋቸው የተለያዩ የውስትና የውጭ ፖለቲካዊና ማህበራዊ፤
አኮኖሚዊና ባህለዊ፤ ክልላዊና ሀገራዊ እንዲሁም አህገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታዎች ሲኖሩ እነዚህ የፍላጎት፤
የበደልና የችግር ይዘት ያላቸው ሆነው መሰረታቸው ሰብአዊነት፤ ህዝባዊነት፤ ሰላም፤ የልማት ፍትሀዊና ዘላቂ
ተጠቃሚነት፤ የህግ የበላይነት ናቸው፤፤

2.1. የሰብአዊ ክብር የትግል መነሻዎች፡-

የተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግማሽ አካል የሆነው መላው የአማራ ህዝብ ካለው ታሪክ፤ ከከፈለው
መስዋእትነት፤ ካበረከተውና እያበረከተው ካለው አስተዋጽኦ አኳያ ሊከበርና ተገቢ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ
ቢሆንም ላለፉት 27 አመታት በተገነባው የውሸት ትርክት ምክንያት አማራ ጠል የሆኑ ድርጅቶችና ቡድኖች

3
እየተፈጠሩ ፤ በየወቅቱ የተጠና አጀንዳ እየተሰጣቸው አማራው ላይ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችና በራሱ ቀየና
መንደር ውስጥ እየተገደለ፤ አየተሳደደ፤ እየተሰቃየ፤ ሀብት ንብረቱ እየወደመና እየተዘረፈ ለከፋ ሰብአዊ ቀውስ
ተዳርጓል፤፤ ይህ ህዝብ እየደረሰበት የለው አሰቃቂ ግፍና በደል፤ መዋቅራዊ ጭቆና በየትናውም የአለም ክፍል
የሚገወገዝና የርብርብ ማእክል ቢሆንም በዚች አገር ውስጥ ተጠናክሮ ቀጥሎ ይገኛል፡፤

በመሆኑም ይህ ፈረጀ ብዙ ግፍና በደል በቸልታ ሊታይ የማይገባው ከመሆኑ ባሻገር የዲሞክራሲ ትግል
አጀንዳዎች ቁንጮ በመሆኑ ይህ የሰብአዊነት አጀንዳ የትግል መነሻ ተደርጎ ሲወሰድ የአማራ መብት ሊከበር
ይገባል ከሚል ጥብቅ መስፈርትና ሞራላዊና ሰብአዊ መብትና ግዴታ አንጻር ነው ፡፡ ከዚህ በላይ ግን ይህ
የህልውናና እንደ አማራ የመቀጠልና ያለመቀጠል እንዲሁም እንደሀገር ከተገባበት አጣብቂኝ የመላቀቅ ጉዳይ
ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

2.2. ፖለቲካዊ የትግል መነሻዎች፡-

የማነኛውም የፍትህ፤ የነጸነትና የእኩልነት ጥያቄ ወይም ትግል መነሻዎች በአብዛኛው ፖለቲካዊ መሆናቸው
ይታወቃል፡፡ ከአማራና ከኢትዮጵያ ህዝብ በአበዛኛው የሚነሱ ጉዳዮችም ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡ በዚህ ረገድ
በአሁኑ ወቅት የሚነሱና በጉልህ የትግል አጀንዳ ከሆኑት መካከል የሚከተሉት በዋናነት የሚታዩ ናቸው፡፡

እንደሚታወቀው በአማራ ክልል ሁሉም ህዝቦች በእኩል ህዝባዊና መንግስታዊ እውቅና ያላቸውና
በኢትዮጵውያዊነታቸውና በሰብአዊነታቸው ተከብረው የሚኖሩ ቢሆኑም በተቃራኒው ግን የአማራ ህዝብ
በሌሎች ክልሎችና የሀገሪቱ አካባቢዎች ሰፊ በደሎች እየደረሱበትና ስቃይ ውስጥ ይገኛል፡፡በተለይ ሆን ተብሎ
በተገነባው ሀሰተኛ ታሪክና ትርክት በአማራ ላይ ያነጣጠሩ በደሎች እንዲደርሱ ተደርጓዋል፡፡ በየትኛዉም የአለም
ክፍል ባልታየ መንገድ የማንነቱ መሰረትና ምንጭ ከሆኑ ግዛቶቹ እነዲሳደድና ተላልፈው እንዲሰጡ የተደረገ
ከመሆኑ በላይ በቀሩትም የሀገሪቱ አካባቢዎች የቤ ተመልካችና የፖለቲካዊ ባይታወርነት እጣ ፈንታ እየገጠመው
ይገኛል፡፡ በራሱ ክልል ውስጥም ቢሆን በሰርጎ ገቦች እነዲከፋፈል እና ከመሰረታዊ አጀንዳው ወጥቶ እርሰ በእረሱ
እነዲበላላ እየተደረገ የሚገኝበት ወቅት ነው፡፡ በከፋ ሁኔታም ከራሱ አብራክ የወጡ ገዥዎችም ለውጭ ሀይሎች
የሚመቹ እንጂ የመያዳምጡትና ጥያቄውን የሚፈቱለት አልሆኑም፡፡ እነዚህ የውስጥና የውጭ ሀይሎችም
ከእነሱ ጥቅም በመነሳት የአማራን እዝብ ጥያቄ የሚሸከሙ ሀይሎች እንዳይፈጠሩ በሚሰራ ደባና ፖለቲካዊ
ሸር የአማራ አብራክ በቀጥተኛ ጥቃትና በመዋቅራዊ ስልት እንዲመክን እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህም የአማራ ህዝብ በተጋድሎና መስዋእትነት ከፍሎ ባቆያት ሀገር ውስጥ እኩል ተሳታፊ፤ ወሳኝና ተጠቃሚ
ሊሆን ይቅርና የሚደርሱበት በደሎች እየተጠናከሩና የሚያነሳቸውም ዙርያ መለስ ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው
ባሉበት ቀጥለዋል፡፡ ከህዋሀት መዳከምና ወደመቀሌ መመሸግ በኋላም ቢሆን በተረኛ አሰተሳሰብና ዝንባሌ
በደሎቹና ችግሮች ተጠናክረው ከመቀጠል ባሸገር ለዚህ ህዝብ የመጣ ለውጥ የለም፡፡ ለዚህ ሁሉ ገዥ
ምክንያትና ምንጭ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ህጎች በመውጣታቸውና በመተግበራቸው ነው፡፡
በተለይ ለዚህ በሀገሪቱ ህገ መንግስት በግልጽ የተደነገጉ ጉዳዮች ማሳያ ናቸው፡፡ እንዲሁም አማራና
ኢትዮጵያውያን ባልተቀበሉት የፌደራል አደረጃጀትና የጭቆና ስልት የሶስተኛ ዜግነት እድልና እጣፈንታ ገጥሞት
ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በላይ ከብዙ በጥቂቱ የተነሱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የዚህ ግንባር የትግል መነሻ
ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡

2.3. ኢኮኖሚያዊ የትግል መነሻዎች፡-

የአማራ ህዝብ ታታሪ ህዝብና በአገር ግንባታ ውስጥ ሰፊና ጉልህ ድርሻ ያለው ና ያበረከተ ብቻ ሳይሆን የሰፊ
ጸጋ ባለቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለአብነት በአገሪቱ የምግብ አህል አቅርቦት ውስጥ ከራሱ ክልል ብቻ ከ 37
በመቶ በላይ ድረሻ ያለው እንዲሁም እነደህዝብ ሲታይ ከ 63 በመቶ በላይ አበርክቶ ያለው ህዝብ ነው፡፡
በተጨማሪም ከግማሽ በላይ የሆነው የሀገሪቱ የሀይል አቅርቦት ክልል ተብሎ ከተሰጠው ቦታና አካባቢ
የሚመነጭ ነው፡፡ በሀይል ከተነጠቁት ግዛቶቹ ባሻገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው አካባቢዎች

4
ባለቤትም ነው፡፡ ይሁን አነጂ ባለው ጸጋ ልክ ሊጠቀም ይቅርና በእጁ ያለው ሀብትም በተጠና መንገድ በተዘረጋ
ስርአት ለህገወጥ ተጠቃሚዎች ተላልፎ እየተወሰደበት ይገኛል፡፡

ከዚህ በላይ በተዘረጋው ህጋዊ የኢኮኖሚ ስሪትም ቢሆን ፍትሀዊ ተጠቃሚ አይደለም፡፡ በተለይ በታሰበ መንገድ
በተጠለፉ ተቋዋማዊ አሰራሮች በገቢና ታክስ፤ በውጭ ኢነቨስትመንትና ኢክስፖርት ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ
እንዳይኖረው በማድረግ የበይ ተመልካችና ጥሬ ሀብት አቀባይ ሆኖ ይገኛል፡፡ በመሰረተ ልማትና በኢንዱሰትሪ
ዘርፍም ወደ ኋላ የቀረ ክልልና ህዝብ ሆኖ ይገኛል፡፡የክልሉ ኢኮኖሚና ልማትም የተዳከመና ከጥገናዊ ለውጥና
ድጎማ በወጣ መንገድ መሰረታዊ የፖሊሲና የእይታ ለውጥ የሚፈልግ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የአማራ ህዝብ
የኢኮኖሚና የፍትሀዊ ልማት ጥያቄ በተገቢው መመለስ ያለበት በመሆኑ የዚህ ግንባር አንዱ የትግል ዘውግ
ተደርጎ ተወስዷል፡፡

2.4. ማህበራዊ፤ባህላዊና ታሪካዊ የትግል መነሻዎች፡-

የአማራ እዝብ በኢትዮጵያ የነጻነት ተጋድሎ ውስጥ ትልቅና አኩሪ ድርሻ ያለው መሆኑ ቢታወቅም ይህንን
ታሪካዊ እውነታ በመደፍጠጥና በመትኩ የውሸት ትርክት በማቅረብ ጥቃት እንዲደርስበት ከመደረጉ ባሻገር ይህ
ታሪኩ እየተበተነና ሌሎች በተሳሳተ መንገድ እንዲረዱትና አንዲነጠል ብሎም መልካመነቱንና ተቀባይነቱን
እንዲያጣ በውስጥና በውጭ ሀይሎች ትስሰሰር እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአማራ ህዝብ በባህሉና ማህበራዊ ትውፍቱና እሴቶቹ ውስጥ በዘመናዊ የመንግስት አሰራር ላይ እምነት ያለውና
ለዚህ አስተዋጽዎ ያደረገ፤ አቃፊ፤ ለሰብአዊነትና ለሌሎች ማንነቶች ክብር ያለው መልካም ህዝብ ቢሆንም
ሆን ተብሎ በሚጠነሰሱና ተግባራዊ በሚደረጉ እኩይ ተግባራት ከሌሎች ህዝቦች ጋር በጥርጣሬ እንዲተያይ፤
በተለይ በመንደር ፖለቲከኞች ሴራ በመሰረታት ሀገር ውስጥ በባይታወርነትና በቁዘማ ህይወቱን እንዲመራ
እየተደረገ ይገኛል፡፡ የጀግንነት ታሪኩን በመናድም የሚሳካ ባይሆንም በምትኩ የተሸናፊነት ስነ ልቦና እንዲላበስ
ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የማይቻል ግን በዝምታ የማይታለፍ ታሪካዊ ስህተት በአርበኝነት ሊከሽፍ ይገባል፡፡

በሌላ በኩል የባህሉ ፤ የማንነቱ ምንጭ የታሪኩ አስኳል የሆኑት መተከል፤ ራያና ወልቃይት;ሸዋ/ሰላሌና ደራ/
ከክልሉ ተገንጥለው በወቅቱ በጉልበተኞች ከተወሰዱ ውለው አድረዋል፡፡ ይህንን በሰለጠነ መንገድ ፤ በድርድርና
በውይይት ለመፍታት ጥረት ቢደረገም በህጋዊ መንገድና በኢትዮጵያውይነት መንፈስ መፍታት አልተቻለም፡፡
ይህም ሌሎች አማራጮችን መሻትና መጠቀም አስገዳጅ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በመሆኑም በፋኖ አርበኞች ግንባር
ይህ አንዱ የትግል አውድ ሆኖ ተወሰወዷል፡፡

እንዲሁም የአማራን ህዝብ ከውስጥና ከውጭ ሆነው ከዋና ጉዳዩ እንዲወጣ፤እርስ በእርሱ እነዲናከስ ከሌሎች
ጋርም እንዲጠራጠርና እንዲጋጭ የሚሰሩ ሀይሎች ተሳክቶላቸው ብዙ እኩይ ተግባሮች እንዲሳኩ ሆኗል፡፡ በዚህ
ከተከሰተው ሰብአዊ ኪሳራ ባሻገር የክልሉ ልማት እንዲሰናከል ሆኗል፡፡ በዚህም ብዙ አማራ ስራ አጥ እንዲሆንና
ስደትና የከፋ ድህነት የአማራ ህዘብ መገለጫና ወርስ በሚመስል ደረጃ ተንሰራፍቶ ይጋኛል፡፡ ይህም በየደረጃው
በተባበረና በተጠና አግባብ ሊመከትና ለዚህ ዋና ምክንያት በሆነው አማራ ተኮር መዋቅራዊ ጭቆናና የመድሎ
አሰራር ላይ ያተኮረ ትግል ማድረግና በዚህ ላይም ህዝቡን በማነቃትና በማደራጀት መንቀሳቀስ ይገባል፡፡

2.5. የወደፊት ሁኔታ እንደ ትግል መነሻ፡-

ባለፉት አመታት እየተደማመሩ የመጡ በደሎችና ጭቆናዎች የአማራውን ህዝብ በከፋ የድህነት አዙሪት ውስጥ
የከተቱት ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ ፈጥነው በእዝባዊ ትግል እንዲቆሙ ካልተደረገ የመላ አማራው ህዝብ የወደፊት
እጣ ፈንታ እጅግ እስከፊ እየሆነ እንደሚሄድ የሚያከራክር አይሆንም፡፡ በተለይ ጸረ አማራና ኢትዮጵያ የሆኑ
የውስጥና የውጭ ሀይሎች ትስስርና ቅንጅት መመከት የሚገባ በመሆኑ እንዲሁም አማራውን ከወደቀበት

5
ስነልቦናዊ ጫናና ከቁዘማ አዘቅት ውስጥ ማውጥት እጅግ አንገብጋቢ የወቅቱ ጥያቄ እየሆነ
በመምጣቱ፤የተበታተነውን የኣማራ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያውያን ጋር በማስተሳሰር ተገቢነት ወደአለው
ፍትሀዊ ትግል ውስጥ ማስገባትም እጅግ አስገዳጅ እየሆነ የመጣበት ወቅት ነው፡፡

በሌላ በኩል ታሪክ አልባ ህዝብ ይዞ መቀጠል የማይገባና ይህንን ለመቀልበስም ዙርያ መለስ ትግል ማድረግ
የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት የአማራው ህዝብ በተበተታነ መንገድ የሚያደርገው ትግል
መሪ የሚያስፈልገው በመሆኑ ይህ አንዱ የትግል መነሻ ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በተለይ አማራ ተደራጅቶ
በኢትዮጵያዊ መልክና ቁመና እንዲንቀሳቀስ ፋኖአዊ አደረጃጀትና ስልት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እየሆነ
መጥቷል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ይህ ህዝብ የተበተነነና መሪ አልባ ሆኖ ወደ ሰፋ ቀውስ ውስጥ እየገባ ሊሄድ የሚችል
መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በአሁኑ ሰአት የሚታዩ የትግል እንቅስቃሴዎችም በተገቢ ሁኔታ ሊመሩ ይገባል፡፡

አሁናዊ የአማራ ሕዝብ የደኅንነት የሁኔታ ትንታኔዎች

የአማራን ደኅንነት ጉዳይ ስናነሳ በሦስት መልኩ ክፍለን ልናየው እንችላለን፡፡ እነሱም የፖለቲካ ደኅንነት፣

የማሕበራዊ ጉዳዮች ደኅንነትና የኢኮኖሚ ደኅንነት ሲሆኑ የአማራ ሕዝብ እንዴት እነዚህን የዜግነት መብቶች

እንዳላገኘ ዝርዝር ማሳያዎቹም እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡

የፖለቲካ ደኅንነት ጉዳዮች


ዛሬ ላይ ዓለም በፖለቲካ ፍክክር ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት ለማስነሳት አዳዲስና ዘመናዊ መሳሪያዎችን

በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኀያላኑ ሀገራት የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ አንዱ በአንዱ ላይ ከብሮና ከፍ ብሎ

የበታቹን ቀጥቅጦ ለመግዛት የሚያደርጉትን እሽቅድድም እውን የሚያደርጉት በአፍሪካ ሀገራት ላይ ነው፡፡

በተለይም በዚህ ዘመን ደግሞ ኢትዮጵያን የዚህ ፍክክራቸው ሰለባ ለማድረግ ይልቁንም የአማራን ሕዝብ

ከምድረ ገጽ ማጥፋት አዋጭ መሆኑን አምነውና አቅደው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

እንደ ሀገር በተለይ በዚህ ዐራት ዓመታት በፖሊቲካው ዘርፍ ያለንበት ሁኔታ

 ጠንካራና ሀገርን ሊያስቀጥል የሚችል ሀገራዊ የፖሊቲካ ፓርቲ አለመኖር

 ሀገሪቷ በሰፈርተኞችና በተረኞች መውደቅና የመበተን አደጋ ላይ መድረስ

 ሀገራዊ እና ክልላዊ ሉዓላዊነት ተጥሷል

 ሀገሪቷን ሊታደግ የሚችል ሀገራዊና ሕዝባዊ ወታደር አለመኖርና ወታደሩ ከሙያው ይልቅ
የባለስልጣናቱ ፖሊቲካ ማስፈጸሚያ መሆን
 የተለያዩ የሀገራችን እና የክልላችን ክፍሎች በአሸባሪ ቡድኖች ተወረዋል

 ድንበራችን በውጭ ወረራ (ሱዳን) መዳፍ ስር ወድቋል፣ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት መካከል
መዳከምና በመካከልም መተማመንና ማመን እንዲሁም መታመን መጥፋት
 ሀገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ የሽብርና የወከባ እንዲሁም የውሸትና የክህደት መዲና መሆን፣

 የሕዝብን አሁናዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ፖለቲካ በሁሉም ፓርቲዎች መጋባት

6
 የብሔራዊ ደኅንነት መዋቀሩ የይስሙላ መሆን፣ የሳይበር ደኅንነት እና ሌሎችም ክፍሎች ሕዝብን
ከመጎዳቱ በፊት ማዳን አለመቻል
 በፌደራልና በክልል ም/ቤቶች ትክክለኛ የፖለቲካ ውክልና አለመኖር፣

 የዜግነት መብት አለመኖር (በሕገ መንግሥቱ እንደዜጋ አለመታወቅ)

 የግለሰብና የቡድን መብቶች መጣስ፣ መደበላልቅ እና መካድ

 የሕግ የበላይነት አለመከበር (በመንግሥት የዜጎች መታፈን፣ መሰወር፣ የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለመከበር
ወይም ፍትሕ ነፋጊ የፍ/ቤት ቀጠሮ መብዛት ወዘተ)
 ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበር

 የፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ጉዳዮች አላግባብ ጣልቃ ገብነት

 የኃያላን ሀገራት እና ዓለም አቀፋዊ የተራድኦ ተቋማት ጣልቃ ገብነት

የማኅበራዊ ደኅንነት ጉዳዮች


 እንደ ሀገር ሀገሬ የሚል ማኅበረሰብ አለመኖርና በተሰጠው ክልል የእርስ በርስ ግድያና ወከባ መባባስ

 ማኅበራዊ አንድነት ፈጽሞ መጥፋትና አንዱ አሳዳጅ ሌላው ተሳዳጅ መሆን

 በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እና በክልሉ ጭምር መፈናቀል፣ መሳደድና የማህበራዊ ቀውስ ሰለባ መሆን

 የማህበረሰብ እሴቶች መጥፋት (ሌብነት፣ አለመተማመን፣ ፆታዊ ጥቃት እና ሌሎችም)

 አቅመ ደካሞች፣ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም ድጎማ የሚሹ ዜጎች እጣ ፈንታ
በአሸባሪዎች እና መንግሥት መር በሆኑ ጉልበተኞች እጅ መውደቃቸው

የኢኮኖሚ ደኅንነት ጉዳዮች


 እኩል የሀገር ሀብት ክፍፍል አለመኖር

 ከፍተኛ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር

 የፌደራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እጥረት (ትክክለኛ የሕዝብ ቁጥርን መሠረት ያላደረገ
ስለሆነ)
 ዜጎች በወደዱት የሀገራችን ክፍሎች ሐብት አፍርቶ የመኖርን መብት መነፈግ እና
ያፈሩትም ንብረት በጉልበተኞች መልካም ፈቃድ ላይ መውደቅ
 የመሬት ባለቤትነት መብት አለመኖር (መሬት የመንግሥትና የዜጎች ሳይሆን የብሔር
መሆኑ)
 የልማት ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት እና ኢኮኖሚውን የሚደግፉ ልዩ ልዩ ተቋማትን
መገድብ፣ ማጓተት እና እንዳይመሰረቱ ማድረግ
 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መውደም፣ መወረር ወይም በኃይል አቅርቦት ችግር በሚፈለገው
መጠን አለመስፋፋት ወይም መቆም

7
 የሥራ ፈጠራ አለመበረታታት

 የብድር አቅርቦት እጥረት

 የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት አለመኖር እና የቴክኖሎጂ መሃይምነት መስፋፋት (ግብርና፣


ኢንዱስትሪው፣ የትምህርት ተቋማት፣ የጤና ተቋማት፣ እና ሌሎችም በቴክኖሎጂ
አለመበለጸግ)
 ሚዛናዊ ያልሆነ የታክስ ሥርዓት መፈጠር

 አግላይ የንግድ ሥርዓት መወለድ (የምንዛሬ አቅርቦት አለመኖር፣ የድጎማ ሥርዓቱ፣ ከገበያ
የማስወጣት አሻጥሩ ወዘተ)
 ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የገበያ ሥርዓት መፈጠር

 የምግብ ዋስትናን አለመቻል

የአማራ ጠል ኃይሎች አሁናዊ አሰላለፍ


 ብልፅግና ፓርቲ

በአማራ ደምና አጥንት ተረማምዶ ሥልጣን የያዘው የኦነግ መንግሥት በአፉ ኢትዮጵያን አጣፍጦ እየጠራ
በተግባር ሀገርን የማፍረስ ተግባራቱን አጠናክሮ መስራቱ ራሱን ብልፅግና ብሎ ከሰየመ በኋላም የአማራ
ጠሉ ሃይል ሁሉ በአማራው ሕዝብ ላይ የቻለውን ዓይነት እኩይ እና አደገኛ ነገር ለማድረግ የሚሰንፍ
ባይሆንም ሁሉም አማራ ጠል ሃይሎች ይህን የማድረግ ጉልበትም ሆነ አቅማቸው ግን በእኩል ደረጃ ላይ
ያለ አይደለም፡፡ በአማራው ላይ ያሰበውን አደገኛ ጥፋት ከመፈጠም አንፃር በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ
ያለው ብልፅግና ፓርቲ ከሁሉም አማራ ጠል ሃይሎች የበለጠ ጉልበትም፣ ዝግጁነትም፣ ፍላጎትም አለው፡፡
ስለዚህ በፌደራል ስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና መንግስት/ፓርቲ በግንባር ቀደምነት ልንታገለው የሚገባው
አማራ-ጠል አካል ነው ማለት ነው፡፡

በስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና ፓርቲ ያቀፋቸው የሃገራችንን ክልሎች የሚመሩ ንዑስ የብልፅግና ፓርቲ
አባላት ሁሉ ሕዝባችንን በጨቋኝነት ፈርጀው በቻሉት ሁሉ እያሳደዱት ይገኛሉ፡፡

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ/ክልላዊ መንግሥትን በግንባር ቀደምትንት የምንታገልበት ዋነኛ ምክንያት


በሕዝባችን ስም ስልጣን ይዞ በተግባር ግን የአማራ ጠሉን ጎራ ፍላጎት በመንግሥታዊ ጠንካራ ጉልበት
እያስፈፀመ ያለሕዝባችን ለነፃነቱ እንዳይታገል በማፈን፣ በአንድነት እንዳይቆም በጎጥ በመከፋፈል በኩልም
ዓይነተኛውን ሚና እየተጫወተ ያለ አካል ስለሆነ ነው፡፡ ይህን ቡድን መታገልና ማሸነፍ ከተቻለ ቀሪውን
አማራ ጠል ሃይል ማሸነፉ እጅግ ቀላል ይሆናል፡፡

8
 በዘውግ የተደራጁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች

ጣሊያን ወደ ሃገራችን ለቅኝ ግዛት በመጣችበት ጊዜ በአድዋ ድል አፍራ እንድትመለስ ያደረገውን የጦርነት
ገድል የመሩት አፄ ምኒልክ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ሽንፈት ለጣሊያን እጅግ አሳፋሪ በመሆኑ ይህን
ሽንፈቷን እንድትከናነብ ባደረጉት አፄ ምኒልክ ላይ ከፍተኛ የሆነ የበቀል ስሜት በማሳደሯ ለሁለተኛ ጊዜ
ሃገራችንን ለመውረር በማጨው ጦርነት ለመመለስ ተገዳለች፡፡ በዚህ ወቅት በጦርነት ኢትዮጵያን
ከመውጋት ባሻገር በፕሮፖጋንዳ ሽንፈት ያከናነቧት የሸዋው ምኒልክ በመሆናቸው ምኒልክን እና መላውን
አማራ በጠላትነት ፈርጃ የኢትዮጵያን ህዝቦች ሁሉ አማራውን እንዲያሳድዱ መቀስቀስ ጀመረች፡፡

በዚህ መልኩ በፋሽስት ጣሊያን ጀማሪነት የተጠነሰሰው የአማራ ጥላቻ በ 1960 ዎቹ የተማሪዎች
እንቅስቃሴ በስታሊኒስት ርዕዮት ተቀመረ፡፡ ውሎ አድሮም በህወሃት፣ ኦነግ፣ ኦብነግ በመሳሰሉ እና ሌሎች
የዘውግ ፓርቲዎች በኩል አማራን ማክፋፋት፣ ማሳደድ፣ ሃገር አልቦ ማድረግ የብሄረሰቦች እኩልነት ትግል
ዋነኛ አላማ ተደርጎ ተወሰደ፡፡ በዚህም ሳቢያ በሃገራችን የተመሰረቱ የዘውግ ፓርቲዎች ሁሉ ትግላቸውን
የሚጀምሩት አማራውን በጠላትነት በመፈረጅ ሆነ፡፡ ህወሃት በለስ ቀንቶት ስልጣን ላይ ሲወጣም እነዚሁኑ
አማራን በጠላትነት የፈረጁ የዘውግ ፓርቲዎችን ሰብስቦ አማራውን የሚያሳድዱበትን ህመንግስት አማራው
ባልተሳተፈበት ፃፈ፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ከ 1983 ጀምሮ በተመሰረተው የዘውግ ፖለቲካ ውስጥ
የሚንቀሳቀሱ የዘውግ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቸቸው ሁሉ አማራውን በጠላትነት ፈርጀው መንቀሳቀሳቸው፣
በአደባባይ አማራውን ለዘር ማጥፋት ጭምር የሚያጋልጥ የጥላቻ ንግግር መናገራቸው ህገመንግስታዊ
ድጋፍ ያለው “ተገቢ ነገር” ሆኖ ቀጠለ፡፡

በአጠቃላይ በሃገራችን የሚንቀሳቀሱ ስልጣን የያዙትም ሆኑ ለስልጣን የሚወዳደሩ የዘውግ ፓርቲዎች


በሙሉ አማራውን በጠላትነት የፈረጁ ናቸው፡፡ በመሆኑም ስልጣን ሲይዙ በተግባር፣ ስልጣን ሳይዙ
በፕሮፖጋንዳ አማራውን ለዘር ማጥፋት አደጋ ሳይቀር የሚያጋልጥ አደገኛ ፖለቲካዊ አቋም ያራምዳሉ፡፡
እነዚህ የዘውግ ፓርቲዎች ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ ባለው ሁኔታ ያለምንም ከልካይ ለረዥም ዘመን በየዘውግ
ማህበረሰባቸው ዘንድ አማራ-ጠልነትን ሲሰብኩ የኖሩ በመሆናቸው ሳቢያ በህዝባችን ላይ የጋረጡት አደጋ
በጅምላ ተገድሎ በስካቫተር የመቀበርን ያህል እጅግ ከፍ ያለና አሰቃቂ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ የዘውግ
ፓርቲዎች በጥብቅ ከምንታገላቸው አካላት ውስጥ ናቸው፡፡

 አማራ-ጠልነትን በኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ስር የተደበቁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች

9
በሃገራችን ከ 1983 ወዲህ እውን የሆነው የፖለቲካ ዘይቤ የቆመው በዘውግ ብሄርተኝነት ላይ ቢሆንም ከህገ-
መንግስታዊው ዘይቤ ባፈነገጠ መንገድ “በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ለማራመድ”
በሚል ዘውግ ዘለል ፓርቲ መስርተው በፖለቲካው የሚሳተፉ አካላት አሉ፡፡ በቅርቡ ከተመሰረቱት ባልደራስ
እና እናት ፓርቲ በቀር ለረዥም ጊዜ በፖለቲካ ተሳትፎ የቆዩት ቅንጅት ለአንድነት እና ዲሞክራሲ፣አንድነት
፣ሰማያዊ እና ሌሎች በተለያየ ስም የሚጠሩ ፓርቲዎች በአማራው ህዝብ ላይ በዘውጋዊ ማንነቱ ምክንያት
የሚደርስበትን አሰቃቂ ግድያና መሳደድ በሆነው ልክ ጠቅሰው ታግለው ሊታደጉት አልቻሉም፡፡ በምትኩ
በአማራው ላይ በማንነቱ ሳቢያ የሚደርሰውን የተለየ የሚደርስበትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለሳለሰ
ስም በመጥራት ብሎም በመካድ በሌላው ዘውግም ላይ የሚደርስ ቀላል ጉዳይ እንደሆነ አድርገው
በማቅረብ የአማራውን ጥቃት በዝምታ ወይም በማደናገር ሲደግፉ ኖረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአማራው
ህዝብ ላይ የተቃጣውን ግልፅ የዘር ማፅዳት እና ዘር ማፅዳት ዘመቻ በመካድ ላይ ተጠምደው ታይተዋል፡፡
ይህ የሆነበት በርካታ ምክንያት ቢኖርም ዋነኛው ምክንያት ግን እነዚህ ፓርቲዎች ዘውግ ዘለል ነን ቢሉም
በሃገሪቱ የረበበውን አማራ ጠል የፖለቲካ ዘይቤ በግልፅም በስውርም የሚጋሩ መሆናቸው ነው፡፡

ስለሆነም በዘውግ የተዋቀሩ ክልሎችና ፓርቲዎች የየራሳቸውን በቂ ኀይል እያደራጁ ያሉ ሲሆን በዚህ ሰአት
በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ፍጅት የሚደግፉ እንጅ የሚቃወሙ አይደሉም፡፡ ይልቁንም
በመንግሥት በጀት አማራን ከሁሉም ቦታ የዘር ማጥፋት ፍጅትን እያደረገ ካለው የፌደራል መንግሥትና
የኦርሚያ ክልል ጎን ተሰልፈው የሚገኙ ክልሎችም አልጠፉም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ፓርቲዎች ከምንታገለው
አማራ-ጠል ጎራ የሚመደቡ ናቸው፡፡

የምንታገለው አካል ከመገኛ አድራሻው አንፃር

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አማራ-ጠሉ ሃይል እንደ አጠቃላይ ሲታይ እጅግ ግዝፈት ያለው የፖለቲካ
አካል ነው፡፡ ስለሆነም የሚገኝበት አድራሻ አንድ ውስን ቦታ አይደለም፡፡ ይህ ሃይል ስልጣን የያዘ መሆኑ
ደግሞ የመገኛ ቦታው ውስን እንዳይሆን አድርጓል፡፡ በመሆኑም ይህ አማራ-ጠል ሃይል በትውልድ አማራ
በሆኑ ፣በአማራው ስም በተቋቋሙ አካላት ዘንድም ያለምንም ችግር ህልውናውን እንዲያገኝ አድርጓል፡፡
በወቅታዊው የሃገራችን ፖለቲካ ሰፌድ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው አማራ-ጠሉ ሃይል ከሞላ ጎደል በሁሉም
ቦታ የሚገኝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለትግላችን ይቀል ዘንድ የመገኛ አድራሻውን “የውስጥ” እና
“የውጭ” በሚል በሁለት ሰፋፊ ክፍሎች መክፈል ይቻላል፡፡

10
ለትግላችን ዓላማ የውስጥ አማራ ጠሎች ምንላቸው ሃይሎች በአጠቃላይ ወለልኛዊ ባህሪ
የተጠናወታቸውን፣ከአማራው ህዝብ የተወለዱ እንደሆኑ እየተናገሩ ነገር ግን አማራ ጠሉን ጎራ ፖለቲካዊ
ትርክቶች የሚጋሩ፣ በአደባባይም የአማራን ህዝብ የሚያዋርዱና ህዝባችንን ለአደጋ የሚያጋልጡትን
ይሆናል፡፡ ከዚህ ተርታ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚመጣው በአማራው ስም ተደራጅቶ ስልጣን የያዘው
አማራ ብልፅግና መንግስት/ፓርቲ እና በተለያየ ሁኔታ በአማራው ስም ያደራጃቸው ድርጅቶችን፣ የሙያ
ማህበራትን፣ የምሁራን መማክርቶችን ፣እንደ አሚኮ ያሉ መገናኛ ብዙሃንን፣ አማራው በአማራነቱ
የተቃጣበትን ጥቃት በአማራነቱ ተደራጅቶ እንዳይመክት የሚያደርጉ የመንደር/የጎጥ ስውርም ሆነ ግልጽ
ህብረቶችን/ ቡድኖችን ያካትታል፡፡ እነዚህ የጎጥ/የመንደር ስውርም ሆኑ ግልፅ አደረጃጀቶች አማራው
በአንድነት ቆሞ ሰብዓዊ ክብሩን እንዳያስመልስ የተለያየ የቤት ስራ እየሰጡ ጉልበቱን እንዲያዝሉ በአማራ
ብልፅግና መንግስት/ፓርቲ አዝማችን የተሰማሩ አደገኛ ሃይሎች በመሆናቸው እንደ ኦነግ/ህወሃት ካሉት
በአማራው ላይ ሞት ካወጁ ጠላቶቹ በማይተናነስ መንገድ ልንታገላቸው የሚገቡ አካላት ናቸው፡፡

የውስጥ በምንለው አማራ-ጠል ሃይል ውስጥ በሁለተኛ ተርታ የሚሰለፉት በአሁኑ ወቅት የፓርቲ መዋቅር
ውስጥ የማይገኙ ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በዋናነት ከኢህዴን እስከ አማራ ብልፅግና በነበረው
ዘመን በአማራ ህዝብ ስም በያዙት የስልጣን ሰንሰለት ላይ ተሰይመው ህዝባችንን በግልፅ ተሳድበው
ለተሳዳቢ ሲሰጡ የነበሩ፣ በዚህ ስራቸውም በግልጽ ህዝቡም ይቅርታ ያልጠየቁ ፣ይባስ ብለው እስከ ዛሬ
ድረስ አማራ የለም ከማለት ጀምሮ በተለያየ መንገድ ወጣንበት የሚሉትን የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ
ላይ የሚጥል ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ፣ በግልፅም ሆነ በስውር የትህነግ ጠበቃ ሆነው በገዛ ህዝባቸው
መከራ ላይ የሚዘባበቱ ጡረተኛ የኢህዴን/ብአዴን ባለስልጣናትን ያካትታል፡፡ በህብረብሄራዊ ተቃዋሚ
ድርጅቶች ውስጥ መሽገው ራሳቸውን በአማራነት እየገለፁ ግን ደግሞ ከአማራ ህዝብ ችግር ይልቅ
የአሳዳጆቹን የትህነግን/ኦነግን በደል አጉልተው የሚያቀርቡ ጭራሽ ሰለባ የሆነውን የአማራ ህዝብ
የሚወቅሱ አማራ ነኝ ባዮችንም ያጠቃልላል፡፡

ከፖለቲካዊ አድራሻው አንፃር በሁለተኝነት ረድፍ ሊገለፅ የሚችለው ከአማራው ዘውግ ውጭ የሆነው
“የውጭ ጠላት” ተብሎ ሊገለፅ የሚችለው የአማራ ጠል ሃይሎች ጎራ ነው፡፡ በዚህ ጎራ አባለት በዘውግ
ማንነታቸው አማራ ያልሆኑና አማራውን በጠላትነት ፈርጀው በአደባባይ የሚሰብኩ የዘውግ ፓርቲዎች፣
የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ የብዙሃን መገናኛዎች፣ የጥናት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች ወዘተ ናቸው፡፡ እነዚህ

11
አካላት በጥቅል ባህሪያቸው የጣሊያንን ፈለግ ተከትለው አማራውን በጠላትነት እና በጨቋኝነት የፈረጁ
አካላት ናቸው፡፡

 የምንታገለው አካል ከዓላማው አንፃር

አማራ-ጠሉ ሃይል በአማራው ህዝብ ላይ ማለቂያ የሌለው መከራን የሚያወርደው የተለያየ አላማ ይዞ
ነው፡፡ እንደ ትህነግ፣ ኦነግ፣ ብልፅግና ፓርቲ፣ ሁሉም የዘውግ ፓርቲዎች የአማራን ህዝብ የሚያሳድዱት ፣
በሕይወት የመኖር መብቱን ጨምር ሰብዓዊ መብቱን የሚረግጡት/የሚያስረግጡት አማራው የፖለቲካ
ስልጣን የሚጠይቅበትን ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዳያገኝ በማድረግ እነሱ እየተፈራረቁ ስልጣን የሚይዙበትን
ሁኔታ ለማመቻቸት ነው፡፡ እነዚህ የዘውግ ፓርቲዎች አማራውን በኮሰሰ መንገድ ማየት ስለሚፈልጉ
ታሪካዊ ርስቶቹን ነጥቀው እንደ ዘውግ ገዝፎ እንዳይታይ ያደርጋሉ፡፡ አማራው ግዛቶቹ እንዲመለሱለትና
በዘውግ ፖለቲካው ቀመር መሰረት ገዝፎ ያለ የህዝብ ቁጥር ይዞ ዋና ተደራዳሪ እንዲሆን አይፈልጉም፡፡
ስለዘሊህ በአማራነቱ ተደራጅቶ ለመታገል ሲሞክር በርስት አስመላሽነት፣ከኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት
በማነስና እየከሰሱ ማሳደዳቸውን የሚቀጥሉ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት አማራው በትክክለኛ ወኪሎቹ
ከተገለጠና በሚገባው ግዝፈት ላይ ከተቀመጠ በሐሰት ትርክት አማራውን እየወቀሱ የያዙት ስልጣን ረዥም
እድሜ እንደማይቆይ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ አማራው በትክክለኛ ወኪሎቹ እንዳይገለጥ እና በሚገባው ግዝፈት
እንዳይቆም በማድረግ ስልጣን ላይ ያሉት የስልጣን ዘመናቸውን ማራዘም ይፈልጋሉ፡፡ ስልጣን ያልያዙት
የዘውግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ የአማራው ተጠናክሮ ለሚያደርጉት የስልለጣን ሩጫ ብርቱ ተፎካካሪ
እንዳይሆናቸው ይፈልጋሉ፡፡

 የክልሎች አሰላለፍ
1. የኦሮሞ ክልል

ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ሀገር፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚለው ብሂል ቀርቶ የእኔ ብሔር የእኔ ቋንቋ የእኔ ክልል
በሚለው ከተቀየረ 50 ዓመትን ለመድፈን እየገሰገሰ ይገኛል፡፡ በዚህ የገድሎ ማደግ ስሌት ወደፊት የመጣው
የኦነግ ኀይል የ 16 ኛው ክ/ዘመን ትርክቱን ለመድገም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ባንክና ታንክ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡
የኦሮሞ መሪዎች የኢትዮጵያ የሆነ ሁሉ የኦሮሞ ጠላት ነው በማለት በሀገሪቱ የሚገኙ ከሕያው እስከ ቅርስ
እያጠፉ የራሳቸውን አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ሀገር፣ አዲስ እምነት፣ አዲስ ሰው ለመፍጠር ከግማሽ በላይ
እቅዳቸውን አሳክተዋል፡፡ ለዚህም በክልላቸው የሚገኘውን አማራ በመግደል፣ በማሳደድ፣ ከክልላቸው

12
አጎራባች እንደ ግሙዝ ዓይነት ክልሎችን የራሳቸው የነገ ግዛት አድርገው በማሰብ በዛ ክልል ውስጥ የሚገኙ
አማራዎችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያለምንም ፍርሃትና መሸማቀቅ በግልፅ በመዝረፍ
የራሳቸውን ገዳይ ቡድን በማሰልጠን ትግበራ ላይ ይገኛሉ፡፡

2. የትግራይ ክልል

የትግራይ ክልል እንደ ፓርቲም ሳይሆን እንደ ሕዝብ አማራ ጠላቴ ነው ብሎ በመፈረጅ ትናንት ካደረሰው
ዘግናኝ ጭፍጨፋና ሰቆቃ በላይ ነገም ከማንኛውም አማራ ጠል ጋር በመሰለፍ የአማራን ሕዝብ ከምደረገጽ
አጥፍተን እኛም እንጠፋለን አቋም እያራመዱ ብቻ ሳይሆን እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የተማረ ያልተማረ
ሴት ወነድ ወጣት ሽማግሌ ሳይል አቅማቸውን የቻለውን ያህል አማራውን ገድለው ለመሞት አማራን
ባንገድል ገደሉ ይናድብን፣ መሬቱ ይንሸራተትብን፣ ሰማይ ይቆረስብን የሚል መዝሙር ይዘምራሉ፡፡
ስለሆነም ትግራይ ያለርህራሔ ከኦነግ ጋር የጋብቻ ቃል ኪዳን በማሰር ላትመለስ ተሰልፋለች፡፡

3. ሌሎች ክልሎች

በሀገሪቱ የሚገኙ ሌሎች ክልሎች አንዳንዶቹ የኅልውና እና የመዋጥ አደጋ ያንዣበበባቸው ቢሆንም በግልፅ
ወሃጢውን መንግሥታዊ ቡድን ለመቃወም ግን ስንኩላን ሁነው እናያቸዋለን፡፡ ይልቁንም ለገዳዩ ቡድን
ምሽግ በመሆን የአማራ ሕዝብ እንዲገደል፣ እንዲፈናቀልና እንዲታረድ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ
ነው፡፡

 የአማራው አሁናዊ አሰላለፍ

አማራው ባለፉት ዘመናት አብዛኛው ሰው ቁሞ እየተመለከተ ውስን ሰው ደግሞ ፊት ለፊት በመጋፈጥ


ከአካላዊ ስቃይ እስከ አንድያ ሕይወቱን እስከመስጠት ደርሷል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ የገዳይ አስገዳይ በመሆን በሆዱ
በማያዝበት ስልጣን እየጠገዛ አማራውን ሲገዘግዘው ነበር፡፡ አንዳንዱ ደግሞ በጎጥና በሰፈር ተቧድኖ የአማራን
ሕዝብ መከራ ዛሬ ድረስ ያባብሳል፡፡ ይህ ሁሉ ተደምሮ ዛሬ ሁለት እጃችን ወደ ላይ ብለን ለመስጠት
የተገደድንበት ሰአት ላይ ደርሰናል፡፡

በፖሊቲካዊ ሁናቴ፡ የአማራ ሕዝብ ለ 40 ዓመታት በላይ ያለማቋረጥ ቢገደልም ያለማቋረጥ የሚታገሉ ጀግኖችም ነበሩት
ዛሬ ድረስም አሉት፡፡ በዚህ 40 ዓመታት ውስጥ የአማራ 53 የፖሊቲካና የሲቪክ ማኅበራት አደረጃጀቶችና
ፓርቲዎች ፈርሰውበታል፡፡ በዚህ 40 ዓመታት አንዳቸውም ውጤታማ አልሆኑም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ጠላት
ከአማራው ሕዝብ በርትቶ እና ንቃተ ኅሊናው መጥቆ ሳይሆን፡

13
 በአማራ ስም በሚሰገሰጉ አማረኛ ተናጋሪ ዲቃላዎች አማካኝነት ሁለተኛ በራሱ በአማራው አልጠግብ ባይ
ስግብግብ ባንዳዎች አማካኝነት ነው፡፡ በአጥቂነቱ የሚታወቀው አማራ ከቤተመንግሥት ተገፍቶ የወጣው
የፖሊቲካ ብልጫ ተወስዶበት ነው፡፡
 አማራው በተለይም ከተማሪዎች እንቅስቃሴ መጀመር ጋር ተያይዞ ትክክለኛ አሳቢና አቅም የነበራቸው
ምሁራን ከቤተክህነት እስከ ቤተመንግሥት እየተለቀሙ በድብቅና በአደባባይ በመረሸናቸው የዛሬው
የአማራ የፖሊቲካ ውድቀት መንስኤ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከሞትና ከስደት የተረፉት አማራ ምሁራን
አንድም በኢትዮጵያዊነት አቋም አንድም በተስፋ መቁረጥ ከአማራነት ራሳቸውን ማግለላቸው ሌላኛው
የአማራ ፖለቲካ ውድቀት መንስኤ ነው፡፡
 በቅርቡ የወጡ ምሁራንና ፖለቲከኛች ደግሞ ጥገኛ እና ፈሪ እንዲሁም ሰፈርተኝነት የሚያጠቃቸው
በመሆናቸው ትግሉን ያለመዝገብ እንዲመለስ አድርጎታል፡፡ በቦታውም የአማራ ሕዝብ ከአንዱ ገዳይ ወደ
ሌላኛው ገዳይ እንዲሸጋገር አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ ዛሬ ላይ ለምናደርገውና ለወደፊት ልናደርገው
ለምንፈልገው የነጻነት ትግል በእርግጠኝነት ይመራናል የምንለው የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ የለም፡፡
 ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ

ለአንድ ሕዝብም ሆነ ለአንድ ሀገር ጠንካራ ኀይል ለመመስረት ተቀዳሚ ጉዳዩ ኢኮኖሚ ነው፡፡ ህውሃት አማራ
ጠል ማኒፌስቶውን ይዞ ብቅ ካለበት ዘመን ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ከመሬት ነጠቃ ጀምሮ እስከ ንግድ
አውታሮች ዛሬም መስመር ተዘግቶበታል፡፡ በሀገር ደረጃ ያፈራው ንብረት ከተቻለ ተነጥቋል ለመንጠቅ አመች
ያልሆነው በእሳት ጋይቷል፡፡ አማራው ከገበሬ እስከ ሙህር ከነጋዴ እስከ ቀን ሰራተኛ በኢኮኖሚ አቅመቢስ
እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አማራው በሀገር ደረጃ በውስጥም ሆነ በውጭም በኢኮኖሚ አቅመ ቢስ
እንዲሆን ተደርጎ ተሰርቷል፡፡

 በማኅበራዊ ንቃተ ኅሊና


አማራው የማያቋርጥ ሰቆቃ ከማስተናገዱ በላይ ዛሬ ላይ እየጠባባሰ የመጣው ማኅበራዊ ቀውስ እጅጉን
ዘርፈ ብዙ ሁኖ ቀዳዳው በዝቶ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡ ልጆቻችን፣ አሽከርካሪ ሹፌሮቻችን፣ ተንቀሳቃሽ ነጋዴ
ልጆቻችን፣ በተዘዋዋሪ ሰርቶ አደር ሕዝባችን ላይ ከክልሉ ውስጥም ሆነ ከክልሉ ውጭ ማዋከቡና
ማሳደዱ ተጠናክሮና ቅጥ አጥቶ መቀጠሉ ሕዝባችን ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ አድርሶታል፡፡ በዚህ በደል ላይ
ገዳዩን ለመግደል አሳዳጁን ለማሳደድ ቆርጦ ሕይወቱን ሰጥቶ ለመታገል የተነሳው ወጣት አማራ ተስፋ
በተጣለባቸውና ዋጋ በተከፈለባቸው አደረጃጀቶች እና ፓርቲዎች መፈረካከስ የበለጠውን መደራጀት
መታገል የሚለውን ስም እስከመጥላት የሚደረስበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

 ለትግሉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎች


 የአማራ ሕዝብ በሁሉም አቅጣጫ በሕይወት የመኖር እድል መቀማቱና መሳደዱ
 በቂ የሰው ኀይል መኖሩ
 የወጣቱ ንቃተ ኅሊና የተሻለ መሆን

 የትግሉ እንቅፋቶች

14
 የአንድነት እጦት
 ስግብግብነት(ባንዳነት)
 ያልሰሩትን ጀብድ መፈለግ
 ተስፋ መቁረጥ
 ጠንካራ መሪና ፓርቲ አለመኖር
 ጠባቂነት
 እውነታን አለመረዳት
 አጉል ተስፈኝነት
 የፋይናንስ ችግር

፨ የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የሚመራባቸው የሥነ_ምግባር መርሆዎች

ሀ. ምክንያታዊነት

በድርጅቱ የሚወሰዱ እርምጃዎችና የሚደረጉ የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እንቅስቃሴዎች ከስሜታዊነት


የወጡና በበቂ ምክንያታዊነት የተደገፉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለ. ገለልተኝነት

የድርጅቱ አላማዎችና እንቅስቃሴዎች ከሌሎች አካላት ተፅዕኖ ነፃ የሆኑና ድርጅቱ ከራሱ የውስጥ ሁኔታ ተነስቶ
የሚወስዳቸው ሲሆኑ ይገባል፤ያለማዳላትና የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ያለ በቂ ምክንያትና መነሻ የማይፈፀመውና
ከአድሎአዊነት የፀዱ ይሆናሉ

ሐ. ታማኝነትና ጠንካራ አቋም

 የአርበኝነት ተጋድሎና አሁን ያሉ ፈርጀ ብዙና ድርብርብ በደሎችን ለመቀልበስ ጠንካራ አቋም
መውሰድና ይህንን በበቂ ምክንያት ማስደገፍ ይገባል
 የድርጅቱ ተልዕኮ ዓላማዎችና ግቦች ለከፍተኛ ሁኔታ የአባላትንና የአመራሩን ታማኝነት የሚጠይቁ
በመሆናቸው ይህ በግንባሩ አመራሮችና አባላት በእምነት የሚያዝና የሚተገበር ነው

መ. ፍትሐዊነት

_ የድርጅቱ ግብ በአማራና በኢትዮጵያውያን ላይ የተጫነውን ኢ ፍትሐዊ አሰራር በመቀልበስ በሚደረጉ


እንቅስቃሴዎች ውስጥ የፍትሐዊነት አሰራር ቁልፍ መርሆ ተደርጎ ይወሰዳል

15
_ የድርጅቱ የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እንቅስቃሴዎች በክልሉ ውስጥና በኢትዮጵ ያ ደረጃ ፍትሐዊነትን
ማረጋገጥ ነው

ረ. ድፍረትና ትጋት

 የድርጅቱ አባላትና አመራሮች የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በሙሉ አቅሙ በድፍረት የሚፈጽማቸው


ይሆናል
 የወቅቱ የትግል ሁኔታ እጅግ ያደገ ትጋትን የሚፈልግ በመሆኑ ከድርጅቱ አባላትና አመራሮች ይህ
ይጠበቃል

ሰ. ተጠያቂነትንና ኃላፊነትን መውሰድ

 በድርጅቱ የሚወሰዱ ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችና እርምጃዎች ግለሰባዊ ድርጅታዊና


ማህበራዊ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ለዚህም በየደረጃው ኃላፊነትን መውሰድ ይገባል

ሸ. አካታችነት

 ይህ ትግል የህዝብና የሰብአዊነት የፍትሐዊነት የነፃነትና የዲሞክራሲን መርሆ የተከተለ በመሆኑ ይህንን
በፅኑ የሚቀበሉ አካላት በትግሉ ውስጥ መሳተፍና አጋር ሆነው ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ
 በዚህ የትግል ምእራፍ ውስጥ በሁሉም የትምህርት ደረጃ ጾታና ማህበራዊ መሰረት ውስጥ ያሉ
አማራዎችና የአማራ ጥያቄ አጋር አካላት ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ

ቀ. ዘላቂነት

 ይህ የትግል ምእራፍ በአጭር ጊዜ የአማራን ጥያቄ ለመመለስና በደሎችን ለመቀልበስ ፤አድሎአዊ


አሰራሮችን ለማስተካከል እንዲሁም የአማራን ግዛቶች ለማስመለስ ያለመ ቢሆንም ዋና ግቡ በሀገሪቱ
ፍትሐዊ ሥርአት ማስፈንና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት በሰላም የሚኖሩበት የተረጋጋ ሥርዓት
መዘርጋትነው
 ትግሉ በአጭር ጊዜ ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ሲሆን በእየ ምዕራፉ የራሱ የሆነ ሀገራዊና ህዝባዊ
ተልዕኮዎች ያሉትና ሀገሪቱን ዲሞክራሲዊና ፍትሐዊ በሆነ አሰራር በመምራት ተከታታይ ተመጋጋቢ
የትግል ምዕራፍ የሚከተል ነው

በ. በጎ ተፅዕኖ

ይህ የትግል ምዕራፍ ከዚህ በፊት እንደታየው ትግል በጠመንጃና በወታደራዊ ኃል ብቻ ሚመራ ሳይሆን ይህን
እንደመጨረሻ አማራጭ በመውሰድ በመጀመሪያ ደረጃ በሰለጠነ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ መግባባትንና ትብብርን
የማጎልበት አቅጣጫ የተከተለ ነው

ተ. በጎ ሥነ ምግባር

የድርጅቱ አባላትና አመራሮች እንዲሁም አጋር አካላት ከሚታገሉለት የነፃነትና ፍትህ ዓላማ አንፃር በጎ
ሥነምግባርን የተላበሱ ሊሆኑ ይገባል ፡፡ በዚህ ድርጅት ውስጥም በጎ ሥነምግባር የአባላቱና የአመራሩ መገለጫ
ሊሆን ይገባል፡፡

ቸ. የዳበረ ባህልና ታሪክ

16
የግንባሩ የትግል መርህ ከህወሀት ሥርዓት በፊት የነበረውን የአማራና ኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት የተጋድሎ ታሪክና
መልካም ባህል እንዲሁም አብሮነትን የሚስቀጥልና የሚያደብር ሲሆን በአንፃሩም ዛሬ ላይ ህዝብን ከህዝብ
የሚያነጣጥልነና እያጋደለና ደም እያቃባ ሀገሪቱ በርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገብታ እንድትማቅቅና የጦርነት
ቀጠና እንድትሆን ያደረጋትን ጎጠኝነትንና ሰፈርተንነትና ሰብአዊነትን ያላካተተ አሰራርን የሚያወግዝ ነው

ነ. ለዕቅድ መገዛት

የድርጅቱ አሰራርና እንቅስቃሴ በጠንካራ የዕቅድ ዲሲፕሊን የሚመራ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዕቅዶችም በበቂ
ቅድመ ዝግጅትና ጥናት የታገዙና በጥንቃ የሚዘጋጅ መሆን ይኖርበታል ፡፡ እያንዳንዱ አመራርና አባል በዕቅዱ
ላይ ግልጽና ቀጥተኛ ተሳታፊ ሊሆን ይችላል

ኘ. ሞራላዊና ሀይማኖታዊ ሥነምግባር

በአሁኑ ወቅት ያለው ስርአት ፀረ አማራና ጸረ ኢትየጰያ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ግቡ ያደረገው ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያንን በሸፍጥና በመከፋፋል እንዲሁም በሰርጎገብነት በማዳክምና በማጥፋት አረባውያንን ለማግዘፍ
የሚታገል ነው፡፡ የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲን ለኢትዮጵያ መመስረትና ታሪክ በመስራት መሰረት ያጣለች
መሆኑ የግንባር ሥጋ ሆኖ እያለ ይህንን የሀገሪቱንና የአማራን ታሪክ ከመሰረቱ ላማጥፋት ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያንን ማጥፋት ነው ብሎ ተነሳውን ኃይል በመቃወም ይህ ድርጅት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የአቅምና
የማሸነፍ ምንጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡ በሌላ በኩል ቅዱስ የሆነው የእስልምና ሀይማኖት ከባእዳን ተጽእኖ ነጻ በሆነ
አግባብ እነዲሁም የኢተዮጵያውያንን እስላማዊ አሰተምሮና ትውፊት የተከተለ እነዲሆን ይሰራል፡፡ በእስልምናና
ክርስትና መካከል መከባበር፤ መቻቻል እንዲኖር መስራትይገባል፡፡

አ. ኅቡእነትና ምስጢር ጠባቂነት

ድርጅቱ ያየዘው የትግል አውድና ምዕራፍ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ድርጅቱ በሰው ኃይልና በገንዘብ
እስኪጎለብት ድረስ ለተወሰነ ጊዜ የኅቡእነት መርህ የሚከተል ይሆናል፡፡ ለዚህም የድርጅቱ አመራሮች ፤አባላትና
አጋር አካላት የድርጅቱን እንቅስቃሴዎችና መረጃዎች በምስጢርነት መያዝና መጠበቅ ይገባቸዋል

6. የትግል ስልት

 የህዝብ ፍላጎትን መሰረት የደረገ ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ መስራት


 ቀደምት ታሪክን መሰረት ያደረገ ስልት መከተል

17
 ሰላማዊ የትግል አማራጭን መጠቀም
 አዋጭ የሆነ ወታደረዊ የትግል ስልት መከተል፤ ማጎልበት
 የውስጥና የውጭ አቅምን አቀናጅቶ መጠቀም
 በጎ ተፅዕኖ ስልትን መከተል
 መረጃን በአግባቡ ማደራጀትና መተንተን
 በተጠናና ስውራዊ በሆነ መንገድ የጠላትን ኢኮኖሚ አቅም መቆጣጠር
 የህዝብ ፍላጎት ላይ መመስረት/ በደልና ችግር ፤ ፍላጎት ያለባቸው አካባቢዎች በተለየ ሁኔታ ይታያሉ
 በተጠና ሁኔታ የአጋርነት አሰራርን ከውጭና ከውስጥ ሀይሎች ጋር መፍጠር
 የተሳካ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ተግባር መፈጸም
 የመንግስትን ሀብት በትግሉ ውስጥ መጠቀም/በመንንግት ስራ፤ በመንግሥት ሎጅስቲክ መጠቀም
 የጎሬላ ትግል ስልትን መጠቀም
 ከውስጥ ወደ ውጭ የሚመለከት ስልትና እንቅስቃሴ መከተል
 የየስራ ዘርፉ የራሱ ስልቶችና ታክቲኮች ይኖራሉ

7. አጋር አካላት

 በአማራ ሕዝብ ፍላጎትና እንዲሁም በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ የተመሰረቱ የፖለቲካ፤


የሲቪክና ቤተ እምነቶች እንዲሁም ቡድኖች ና ተቋማት በአጋርነት ይመዘገባሉ
 ከእነዚህ አካላት ጋር በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የአጋርነት ስርአት ይዘረጋል
 በሀገር ውስጥ ተቋማት ላይ ትኩረት ያደርጋል
 ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
 የኢትዮጵ እስልምና ተቋም
 የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ)
 የአማራ ርስቶች አስመላሽ ኮሚቴዎች
 አብን
 አዴኃን
 ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
 አሻራ፣ ታዛቢ ሚዲያ
 አማራ ቴሌቪዥን
 ግዮን የአማራ በጎ አድራጎት ማህበር
 አማራ ሚዲያ ማዕከል ወዘተ

18

You might also like