Professional Documents
Culture Documents
Introduction To Patristic
Introduction To Patristic
አበው የሚባሉት የቤተክርስቲያን አባቶች ከሐዋርያት በኋላ የተነሱ፣ የጌታችንን እና የመድኀኒታችንን የማዳን
ሥራ ከሐዋርያት በመቀጠል በትምህርቶቻቸው እና በስራዎቻቸው ያስቀጠሉ፣ በማዕረጋቸው እና በቅድስናቸው
ሐዋርያትን የሚያክሉ፣ ወንጌልን አንደ ዘመናቸው ሁኔታ እያብራሩ ክርስትና እና የክርስትና ሕይወት እዚህ
እንዲደርስ ያደረጉ መሰረት የጣሉ የቤተ ክርስቲያን ጸሀፊዎች፣ አባቶች ቅዱሳን ናቸው
ሐዋርያነ አበው፣ ነገስታትን ተቃውመው ስለ ክርስትና ጥብቅና የጻፉ አበው፣ የግኖስቲኮችን እና ፍልስፍናን
አስተምህሮ ተቃውመው የክርስትናን ትክክለኛነት የጻፉ አባቶች፣ ከዘመነ ሰማዕታት በኋላ የተነሱ ቅዱሳን
አባቶች፣ ገዳማውያን አባቶችን ያጠቃልላል፡፡
እነዚህ አባቶች በተለያየ ዘመን የተነሱ፣ ከተለያየ ቦታ የተገኙ፣ እንዲሁም የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ፣
በዘመናቸውም የተለያየ ዓይነት ፈተና እና ጥያቄን የተጋፈጡ፣ በወቅቱም ተገቢውን መልስ እና ትምህርት
አስተምረው ያለፉ፣ የቤተክርስቲያን ሕይወት የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዶግማ እና ሥርዓት (ትውፊት)
ያዘጋጁ እናም ተጠብቆ እንዲቆይ ስርዓት የሰሩ በግልም በሕብረትም ሆነው ቤተክርስቲያን በዘመናቸው
የነበረውን ፈተና እንድትሻገር ያደረጉ ናቸው፡፡
የሩቅ ምስራቅ የታናሽ ኢሲያ፣ የሶርያ አባቶች፣ ከወደ ሮም የተነሱ አባቶች፣ ከአፍሪካ (ሊቢያ፣ እስክንድርያ፣
ኢትዮጵያ) የግሪክ ቋንቋ፣ የላቲን ቋንቋ፣ የሶርያ ቋንቋ፣ የግዕዝ ቋንቋ ለምሳሌ (በቅዱስ ቀሌምንጦስ
እንደተጻፈ የሚነገረው ኢትዮጵያዊው መጽሐፈ ቀሌምንጦስ፣ የእመቤታችንን ሞት፣ ትንሣኤና እርገት)
የሚናገሩ ስራዎች፣ መጽሐፈ ሄኖክ …
የዶሴቲስቶች፣ የኢቢዮናይቶች፣ አስተምህሮ ችግር መንስኤ ግኖስቲካውያን ለምን ቁሱን ዓለም ሌላ ፈጣሪ
ፈጠረው ይላሉ፣ ከፊል ግኖስቲካዊ ይዘት ያላቸው በሐዋርያት ስም የተጻፉ ጽሑፎች ውስጥ ያለውን እውነት
እንዴት መለየት ይቻላል፣ በአርጌንስ አስተምህሮ ውስጥ ያለው ስህተት የፍልስፍና ተጽእኖ ያመጣው እንደሆነ፣
የአቡሊናርዮስ፣ የንስጥሮስ፣ የአውጣኪ
ከዛ ባሸገር የቤተክርስቲያን አባቶች ያሳለፉዋቸውን ውጣ ውረዶች፣ የቤተክርስቲያን አባቶች ሆነው ቆይተው
ስለ ቤተክርስቲያን ከነገስታት ጋር ሲታገሉ ቆይተው፣ በዘመናቸው ካሉ ማናፍቃን ጋር ቤተክርስቲያንን ወግነው
ሲከራከሩላት ቆይተው በኋላም ወደ ምንፍቅና የሄዱትን የቤተክርስቲያን ሰዎች ማንነት እና ትምህርት
እንመለከታለን፡፡
አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን ሰዎች፣ መናፍቃንን ጨምሮ በተለይ ከኒቂያ ጉባኤ በፊት የነበሩት አባቶች
ሕይወታቸውን በሰማዕትነት እንዳሳለፉ፡፡ በተለይ ከቤተክርስቲያን የተለዩት በቤተክርስቲያን ውስጥ በነበሩበት
ዘመን ያበረከቱት ኦርቶዶክሳዊ ስራዎች እንዳላቸው፣ ከፊሎቹ አሁን ድረስ በሀሰት እንደተወነጁሉ የሚጠቀሱ
ይገኙባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ታቲያን፣ ጠርጡለስ፣ አርጌንስ፣ አቡሊናርዮስ፣ አውሳቢዮስ፣ ንስጥሮስ፣ …
ለምሳሌ የአርጌንስ የትርጓሜ ስራዎች በተለይ የዮንስ ወንጌል እስከአሁንም አቻ የማይገኝለት፣ የቅዱስ
ኤፍሬም፣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ፣ የቅዱስ ቄርሎስ፣ የቅዱስ አትናቴዎስ
ትርጓሜዎች፣ እንዲሁም በየጉባኤው እና በየ አባቶች የተደረጉ ቀኖናዎች፣ ለምሳሌ የቅ.አትናቴዎስ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ቀኖና፣ የኒቂያ ጉባኤ ጳጳሳትን ስለመሾም የሚናገረውን ቀኖና መረዳት ዛሬ በቤተክርስቲያናችን
የተፈጠረው ጉድ እንዳይፈጠር ያደርግ ነበር፡፡ ከሀገር ስብከት ሀገረ ስብከት መቀየር፣ ያለ ሲኖዶስ ፈቃድ
ጳጳስ መሾም የተከለከለ መሆኑን
የዶግማ እና የቀኖና መምህራንም፣ በቤተክርስቲያን ያለውን የዶግማ አስተምህሮ ዕድገት፣ ጅማሮ እና አሁን
የደረሰበትን አገላለጽ፣ በየጊዜው ዶግማውን እና የቤተክርስቲያን አስተዳደር እና ሕይወትን ለመጠበቅ
የተደረጉ ቀኖናዊ አስተምህሮዎችን እና ውሳኔዎችን ከአበው ትምህርት መፈተሸ ያስፈልጋል
ዋና ዋና የሚባሉት የቤተክርስቲያን ዶግማዎች በተለይ ሚስጢረ ሥላሤ እና ሚስጢረ ሥጋዌ ለነገረ ድኅነት
ያላቸው ትልቅ ቦታ እና ለመንፈሳዊ ዕድገት ያላቸው ቦታ
ዛሬ ጥያቄ ለሚያነሱ መናፍቃን በተለይ አርዮሳውያን መልስ የሚሆን ስራዎች በ1ኛ እና በ2ኛው ጉባኤ
ጥንቅቅ ብለው መሰራታቸው (የቅዱስ አትናቴዎስ፣ የቀጶዶቂያ አባቶች)
የቤተክርስቲያን ሚስጢራትን፣ ምግባራትንም የምናስተምር ሰዎች፣ የቤተክርስቲያን አባቶችን ሕይወት
መረዳት፣ ወደደረሱበት ማንነት ለማደግ ምን ዐይነት መንፈሳዊ ልምምድ ሲያደርጉ እንደነበር፣ ለእኛም
በዚህ ዘመን እንመራበት ዘንድ እንደምሳሌ ያቆዩልን ስራዎቻቸውን ማየት ተገቢ ነው፡፡
ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እንዴት ይፈጸሙ እንደነበር፣ እንዴት እንደተሻሻሉ፣
በሚሰጢራተ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚገኘው ጸጋ፣ ለመንፈሳዊ ዕድገት ያላቸው አስፈላጊነት እና አስተዋጽኦ
በዲድስቅልያ፣ በጠርጡለስ፣ በዮስጢኖስ፣ በቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ስራዎች እና በቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ
ስራዎች ውስጥ ይታያሉ
የሙሴ ሕይወት፣ መሀልይ መሀልይ እና የአቡነ ዘበዘማያት ጸሎቶች ትርጓሜዎች፣ የሐዋርያነ አበው ሕይወት
እና አሟሟት፣ የነ ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ፣ የነ ቅዱስ ኤፍሬም፣ የነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእነ
አባ እንጦንስ እና የሎሎች መነኮሳት አባቶች የአርጌንስ ሕይወት ጭምር ለመንፈሳዊነት ያለውን ምሳሌነት
ያስተምራሉ
ባጠቃላይ በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እስከዚህ ዘመን ድረስ የተነሱ የቤተክርስቲያን አባቶችን መለስ
ብለን ማየት ለእራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሰዎች ጭምር ሊተርፍ በሚችል መንገድ አልፎ ተርፎ በኛ
ዘመን ስለ አበው እና ሥራዎቻቸው የተጻፉ ስራዎችን ማየት ማንበብ ተገቢ ነው፡፡
ነገረ/ትምህርተ አበው
ትምህርቱን በ3/4 ዘመን ከፍለን ለማየት እንሞክራን
ምዕመናንን ማጽናናት፣ ነገስታትን መቃወም፣ እና በወቅቱ ለነበሩ መናፍቃን ተገቢውን መልስ መስጠት
ቤተክርስቲያን በቀጣይ በተመሳሳይ ችግር እንዳትረበሽ ስርዓት መዘርጋት ዋና ኃላፊነተቻው ነበር፡፡ በመሆኑም
ክርስትና ከዚህ ዘመን ጀምሮ በብዙ ነገሩ ተወልዶ እንደሚያድግ ህጻን የሚድህበት ዘመን ነው ማለት ነው፡፡
የሐዋርያት ደቀመዝሙር የነበሩ 7 አባቶች ሲሆኑ በአብዛኛው የጴጥሮስ የዮሐንስ እና የጳውሎስ ደቀመዛሙርት
ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ አባቶች ሌሎች ሐዋርያትን እንዳዩ ይመሰክራሉ፡፡
ዲዲስቅልያ
አመክንዮ ዘሐዋርያት
ቅዱስ አግናጢዎስ
ቅዱስ ቀሌምንጦስ
ቅዱስ ፓሊካርፕ
ኖላዊ ሔርማስ
ቅዱስ በርናባስ
ፓፕያስ
ሰማዕቱ ጁስቲኒያን
ታትያስ
ጠርጡለስ
ቅዱስ ሔሬኔዎስ
አርጌንስ
አውሳቢዮስ ዘቂሳርያ