You are on page 1of 10

ኦርቶዶክሳዊ መምህር፣ ዕውቀቱ እና ክሂሎቱ

ማስተማር ምንድን ነው?

ጌታችን ሐዋርያትን ሲልካቸው የሰጣቸው የመጨረሻው መመርያ ለመምህራን ሁሉ መሠረት ነው፡፡ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣
በሰማርያ፣ እስከ ዓለም ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ» /የሐዋ 1÷8/ ይህ ቃል የአንድ ሐዋርያ ተግባር ፍጻሜ እንደሌለው
ያስረዳናል፡፡ ሊቃውንቱ ይህንን መመርያ በሁለት መንገድ ተርጉመውታል፡፡ (Arch bishop Anthonios Marqos, The
Theology of mission and missionary.)

1/ ከቅርብ እስከ ሩቅ፡- የአንድ ሐዋርያ ተግባር አጠገቡ ካለው ማኅበረሰብ ጀምሮ አይቶት እና ሰምቶት እስከማያውቀው ሕዝብ
ሊደርስ እንደሚችል

2/ ከቀላል ወደ ከባድ፡- ለአገልግሎቱ ቀላል ከሆነው አንሥቶ ውስብስብ እና አስቸጋሪ ወደሆነው አገልግሎት፤ መሥዋዕትነት
ከማይጠይቀው አገልግሎት መሥዋዕትነት እስከ ሚጠይቀው አገልግሎት እንደሚደርስ ያስረዳል፡፡

በዚህ ተግባሩ የሚፈጽማቸው አገልግሎቶች በሁለት ዋና ዋና ተልዕኮዎች እና በአምስት ዝርዝር ተልዕኮዎች ይጠቃለላሉ፡፡

ዋና ዋና ተልዕኮዎች

1. ያመኑትን ማጽናት፡- በወንጌል አምነው፣ በቤተ ክርስቲያን በረት ውስጥ ያሉ ምእመናን በመናፍቃን፣ በከሃድያን እና
በኢአማንያን እንዳይነጠቁ መጠበቅ

2. ያላመኑትን ማሳመን፡- ወደ ወንጌል ማዕድ ያልቀረቡ የአዳም ልጆችን ወደ ወንጌል ማዕድ ቀርበው የመዳንን መንገድ ዐውቀው
እንዲጓዙ ማድረግ

ዝርዝር ተልዕኮዎች

መመስከር፡- ወንጌልን ማስተማር

መምራት፡- ሕዝቡን በሕይወት፣ በዕውቀት እና በአሠራር አርአያ መሆን

ማሠልጠን፡- ቤተ ክርስቲያንን ሊመሩ፣ ሊያስተዳድሩ፣ ጉባኤያትን ሊያስተምሩ፣ ለሕዝቡ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሪዎችን
ማሠልጠን

ማደራጀት፡- ጉባኤያትን፣ ማኅበራትን፣ ሰንበት ት/ቤቶችን፣ አጥቢያዎችን፣ ማደራጀት


መትከል፡- አጥቢያዎችን፣ ገዳማትን፣ ማሠልጠኛዎችን፣ የአብነት ት/ቤቶችን ወዘተ መትከል

እነዚህ ነገሮች የመምህራን ሥራ መድረክ ላይ ወጥቶ ከማስተማር በላይ መሆኑን ያስረዱናል፡፡ በሐዋርያት ሥራ ላይ የአበው
ሐዋርያትን ተግባር ብንመለከት እነዚህን አምስት ተግባራት በጉዞዎቻቸው ውስጥ እናገኛለን፡፡

አንዳንድ ሊቃውንት አንድ የወንጌል መምህር ሦስት ነገሮች ሊኖሩት ይገባል ይላሉ፡፡ እነዚህም

የማስተማር   ቀደምት አበው ጉባኤ ዘርግተው፣ተዘዋውረው አስተምረዋል፡፡ ትምህርቶቻቸው በዘመኑ የግሪክ ፍልስፍና የሚዋጅ፤
እንደ ዲዮናስዮስ ያሉ የአርዮስፋጎስ ሊቃውንትን የማረከ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከናዝሬት ወደ ገሊላ ሄደ የሚል ሳይሆን አዳዲስ ዕው
ቀት በየዕለቱ የሚገኝበት ነበር፡፡

ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቁስጥንጥንያ ሐጊያ ሶፍያ ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ የሠርክ ጉባኤ ነበረው፡፡ ትምህርቶቹን
ተከታትለው ይጽፉ የነበሩ ደቀ መዛሙርትም ነበሩት፡፡ እርሱም ትምህርቶቹን አስቀድሞ ይጽፋቸው ነበር፡፡ ባስልዮስ ዘቂሳርያም
በቂሳርያ ከተማ በመሠረተው ገዳም አያሌ ሕዝብ ያስተምር ነበር፡፡ በተለይም ዓምደኞች እየተባሉ ይጠሩ የነበሩ መምህራን
ሕዝቡን ሌሊትና ቀን ያስተምሩት ነበር፡፡ ስምዖን ዘዓምድ ከቆመበት ዓምድ ሳይወርድ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ይመጡ የነበሩትን
ሁሉ አስተምሯል፡፡

የመጻፍ    በሐዋርያውያን አበው እና ከእነርሱ በኋላ በተነሡ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ዘንድ እነዚህን ሦስቱን ነገሮች
እናገኛለን፡፡ ዛሬ በየድርሳኖቻቸው እና በሃይማኖተ አበው የምናገኛቸውን ጽሑፎች እና መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡ ትርጓሜያትን
አዘጋጅተዋል፡፡ እንዲያውም በሃይማኖተ አበው ላይ የምናገኛቸውን ድርሰቶቻቸውን ስናይ አበው እርስ በርሳቸው በመልእክት
ትምህርት ይለዋወጡ እንደ ነበር፣ጥያቄ ይጠያየቁ እንደነበር እንረዳለን፡፡

ከትምህርት መጻሕፍት በተጨማሪ እስከ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጡ የጸሎት፣ቅዳሴ፣የመዝሙር፣የሥርዓት


መጻሕፍትን አዘጋጅተዋል፡፡ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ባስልዮስ፣ ዲዮስቆሮስ፣ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እና ሌሎች ቅዳሴ አዘጋጅተዋል፡፡ እነ አባ
ሄሮኒመስ እና ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ ጽፈዋል፡፡ እነ ሄሬኔዎስ እና አቡሊዲስ ዘሮም ለዘመኑ መናፍቃን ምላሽ ጽፈዋል፡፡ እነ
ባስልዮስ እና አባ ኤፍሬም የጸሎት መጻሕፍት ደርሰዋል፡፡ እነ አውሳብዮስ ዘቂሳርያ፣ ሶቅራጥስ እና ሩፊኖስ ታሪከን
አደራጅተዋል፡፡ እነ አውግስጢኖስ የሕይወት ታሪካቸውን ጽፈዋል፡፡ እነ ቅዱስ አትናቴ ዎስ የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍትን እና
የአበውን ታሪክ ጽፈዋል፡፡

የመመራመር ተሰጥኦ  ቀደምት አበው ዘመናቸውን ለመዋጀት ይችሉ ዘንድ የግሪክን እና የሮምን ፍልስፍናዎች፣ የብሉይ ኪዳንን
ትምህርቶች እና ባህሎች፣ የዘመን አቆጣጠር እና የመልክዐ ምድራዊ ሥራዎች መርምረዋል፡፡ አቡሊዲስ ዘሮም ለብሉይ ኪዳን
እንደ ዋና መክፈቻ ቁልፍ የሚነገረውን የዘመን አቆጣጠር ትንተና አቅርቧል፡፡ ኤጲፋንዮስ ስለ ሥነ ፍጥረት አክሲማሮስ የተሰኘ
መጽሐፍ አቅርቦልናል፡፡ አውሳብዮስ ዘቂሳርያ የመጽሐፍ ቅዱስን መልክዐ ምድር አጥንቷል፡፡
የዕውቀት ምንጮች

አንድ መምህር ሊያስተምራቸው የሚችሉ ነገሮችን የሚያገኝባቸው ምንጮች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም

መሠረታውያን እና ተጨማሪዎች ይባላሉ

የዕውቀት መሠረታውያን

የዕውቀት መሠረታውያን የምንላቸው የምእመናንን ሕይወት እና እምነት፣ የቤተ ክርስቲያንን አካሄድ እና አሠራር የሚወስኑ
ናቸው፡፡ እነዚህ ምንጮች የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመመስከር እና ለማረጋገጥ የምናውላቸው ናቸው፡፡

የጌታችን ትምህርቶች  ወደ ኋላ ሄደን ብሉይን ፣ወደፊት ተጉዘን ሐዲስን የምንተረጉመው የቤተ ክርስቲያን መሠረቷ የሆነው
ጌታችን በሰጠን መሠረት ላይ ሆነን ነው፡፡

የሐዋርያት ትምህርቶች፡ በወንጌል ተጽፎ የምናገኘው የጌታችን ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን መሠረቷ ነው፡፡ጌታችን ከዋለበት
ውለው ካደረበት አድረው፣ ትምህርት ተአምራት ሳይከፈልባቸው የተማሩ፣ የመጀመርያዋን ቤተ ክርስቲያን የመሠረቱ፣ እንደ
ቅዱስ ጳውሎስ በልዩ ሁኔታ የተጠሩ ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን ያስቀመ ጧቸው ትምህሮች፣ ሥርዓቶች እና አሠራሮች የቤተ
ክርስቲያንን አስተምህሮ እና አካሄድ ይወስናሉ፡

የቤተ ክርስቲያን አባቶች ትምህርቶች፡   ከሐዋርያት የተቀበሉትን ትምህርት፣ሕይወት እና ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አደራጅተው
እና አብራርተው፣ያስረከቡ አበው ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ጉዞ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ አንድን
አባት የቤተ ክርስቲያን አባት የሚያደርገው አራት ነገሮችን ሲያሟላ ነው፡፡

1. ርቱዕ የሆነውን ኦርቶዶክሳዊ እምነት አምኖ ሲያስተምር

2. ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የሚረዳ መጽሐፍ ሲጽፍ እና

3. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈጸም ሲችል

4. ለሌሎች አርአያ የሚሆን የቅድስና ሕይወትን ሲኖር (H.G. Bishop Moussa, The Characteristics of
Orthodox Teaching. P ,85)

አንድ ኦርቶዶክሳዊ መምህር የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በተመለከተ ሊከተላቸው የሚገቡት መርሖች አሉ፡

1 የአባቶችን ሕይወት ማጥናት


የአባቶችን ሕይወት ማጥናት ለተሻለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚያበረታ፣ የሚያተጋ እና የሚያበረታታ ነገር ይገኝበታል፡፡

መንፈሳዊ ልምዳችንን ይጨምርልናል፡፡ ለተለያዩ ችግሮች እና ሁኔታዎች ምን ማድረግ እንዳለብን ተግባራዊ ልምድ እናገኛለን፡፡

የተለያዩ እሴቶችን እንማርበታለን፡፡ የተለያዩ አበው ልዩ ልዩ ጸጋ፣ ተሰጥኦ እና ደረጃ አላቸው፡፡ የልዩ ልዩ አበውን ሕይወት ስናጠና
እነዚህን ነገሮች እናገኛለን፡፡ ከአትናቴዎስ ለሃይማኖት መጽናትን፣ ከእንጦንስ ራስን መግዛትን፣ ከአርሳንዮስ ትኅትናን፣
ከዲዮስቆሮስ ሃይማኖትን በድፍረት እና በእውነት መመስከርን፣ ከአባ ቢሾይ ጸሎት እና ፍቅርን፣ እንማራለን፡፡

በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም ያደርገናል፡፡

2 የአባቶችን ትምህርት እና አባባል ማጥናት

አንዳንዶች ያለፈውን መጥቀስ እና ካለፈው መነሳት ትውፊታዊነት ወይንም ያለፈውን ብቻ የማድነቅ አባዜ ያደርጉታል፡፡ ግን
አይደለም፡፡ ክርስትና በኛ አልተጀመረም፤ እኛ ለክርስትና ተቀባዮች እንጂ ጀማሪዎች አይደለንም፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት
እንደሚነግሩን ደግሞ ዘመናት በጨመሩ ቁጥር የቅድስና ሕይወት እየደከመ እንጂ እየበረታ አይሄድም፡፡ ስለዚህም በእምነት ረገድ
ያለፉት ከኛ ይሻላሉ፡፡

በመሆኑም አንድ ኦርቶዶክሳዊ መምህር የአባቶችን ትምህርት አጥንቶ ትምህርቱን በእነርሱ መሥመር ማድረግና በትምህርቱም
እነርሱን መጥቀስ ይኖርበታል፡፡

3 ሕይወቱን እና ትምህርቱን በአባቶች ሕይወት እና ትምህርት መሠረት ማድረግ (Ibid, p. 78 )

እኛ አባቶች ፈጽመው አይሳሳቱም infallible ብለን አናምንም፡፡ ሰው የመሆን ስሕተቶችን ሊሠሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የዶግማ
እና የሥነ ምግባር ጥፋቶችን አይሠሩም፡፡ በትንታኔያቸው አና በትርጓሜያቸው አንዱ ከሌላው ሊለዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን
በኦርቶዶክሳዊ እምነታቸው እና ሕይወታቸው አንድ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሊቅነታቸው የምናደንቃቸው ቢሆንም እነዚያን
አራት ነገሮች ካላሟሉ ግን «የቤተ ክርስቲያን አባት» አንላቸውም፡፡ ለምሳሌ አርጌንስ በኑሮው እና በድርሰቱ የሚደነቅ ቢሆንም
ክርስትናን ከግሪክ ፍልስፍና በመቀላቀሉ «የቤተ ክርስቲያን አባት» አይባልም፡፡

እንዴት እናንባቸው ?

አበውን በአጠቃላይ ማንበብ አለብን፡፡ ምክንያቱም አንዱ በሌላው ይሟላሉና፡፡ ሃሳባቸውን፣ የተነሡበትን ምክንያትና ሌሎች
ነገሮችን ተተን አንድን ሃሳብ ብቻ ለራሳችን መደገፊያ መጠቀም የለብንም፡፡ በርግጥ እንደ ተሰጥኦዋቸው ልዩነት ቢኖርም የሁሉም
አንድ ማዕከላዊ ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ እምነት እና ሕይወት ነው፡፡
የነበሩበትን ዘመን፣ ሁኔታ እና ለነማን እንደ ጻፉት መረዳት አለብን፡፡ መጀመርያ የተጻፈበትን ቋንቋ፤ በዘመናቸው የነበረውን
የሃይማኖት እና የሥነ ምግባር ችግር ማጤን አለብን፡፡

የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በሁለት ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡፡ ይህ አከፋፈል በአብዛኞቹ ሊቃውንት ዘንድ የተለመደ ነው፡፡
እንደ መክፈያ ዘመን የሚጠቀሙትም የመጀመርያውን ዓለም አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ የሆነውን ኒቂያን ነው፡፡

ቅድመ ኒቂያውያን /pre Nicene /

እነዚህ አባቶች በአብዛኛው ከፈላስፎች እና ከግኖስቲኮች ጋር የተከራከሩ፤ የመጀመርያዎቹ አበው ናቸው፡፡ ጽሑፎቻቸውም
በአብዛኛው አልተገኙም፡፡ ዮስጢኖስ ሰማዕት፣ ሄሬኔዎስ፣ ሄርማን፣ ታትያን፣ አቴናጎራስ፣ ቀሌምንጦስ ዘሮም፣
ፓፒያን፣ዲዮናስዮስ፣አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፣ወዘተ

ድኅረ ኒቂያውያን  /post Nicene/ እነዚህኞቹ አበው ከመናፍቃን ጋር የተከራከሩ ናቸው፡፡ በተለይም አርዮሳውያንን፣
ንስጥሮሳውያንን፣ አቡሊናርዮሳውያንን ተከራክረዋል፡፡ በአብዛኛው ካለፉት በተሻለ ጽሑፎቻቸውን እናገኛለን፡፡ አውግስጢኖስ፣
ዮሐንስ አፈወርቅ፣ አትናቴዎስ፣ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፣ ባስልዮስ፣ ቄርሎስ፣ ኤፍሬም ሶርያዊ፣ ዲዮስቆሮስ፣
ወዘተ ናቸው፡፡

ከዘመናቸውም በተጨማሪ በጻፉበት እና ባስተማሩበት ቋንቋ ምክንያትም በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነዚሀም

በግሪክ ቋንቋ የጻፉ፡ በአብዛኛው በግብጽ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ሶርያ፣ አርመንያ፣ አንጾኪያ የነበሩ

በላቲን ቋንቋ የጻፉ፡ በአብዛኛው በምዕራብ አውሮፓና በሰሜን አፍሪካ የነበሩ፡፡

በሌላም በኩል ባስተማሩበት ሀገርም ይከፈላሉ፡

ሮማውያን፡ በሮም እና የሮም ሀገረ ስብከት በነበሩት ቦታዎች ያስተማሩና የጻፉ፡፡ እነ አውግስጢኖስ፣ ዲዮናስዮስ፣ ቀሌምንጦስ
ዘሮም፣ ሄሮኒመስ፣ ወዘተ

ግብፃውያን፡ በግብጽ እና በሀገረ ስብከቷ የጻፉ፣ ያስተማሩ፡፡ ለምሳሌ አትናቴዎስ፣ ዲዮናስዮስ፣ ዲዮስቆሮስ፣ ቄርሎስ፣ ወዘተ

አንጾኪያውያን/ቀጰዶቅያውያን/፡ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፣ ባስልዮስ፣ ወዘተ

አርመናውያን፡ ለምሳሌ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ

ሶርያውያን፡ ለምሳሌ ኤፍሬም ሶርያዊ


ኢትዮጵያውያን፡ ቅዱስ ያሬድ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ርቱዐ ሃይማኖት፣ ወዘተ

የአበውን ትምህርቶች ለማጥናት እንድንችል ጽሑፎቻቸውን በይዘታቸው መከፋፈልም ይቻላል፡

• ትርጓሜያት /Exegetics/ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመተርጎም የተጻፉ

• የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት መጠበቅ /Apologetics/ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለማስረዳትና ከብረዛ ለመጠበቅ የተጻፉ

• ትምህርቶች /Sermons and Essays/ ስለ ሕይወት፣ስለ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ስለ ሥነ ምግባር፣ስለ ልዩ ልዩ


በዓላት፣ወዘተ የሚያብራሩ ጽሑፎች

• መልእክታት/Epistles/ ወደ ልዩ ልዩ ቦታዎች የተላኩ መልእክታት

• ቅዳሴያት/liturgies/

• መዝሙራት እና ጸሎቶች/ Poetry and Hymns of Praise/

• ክርክሮች /Dialogues/ በልዩ ልዩ ጊዜ ስለ ሃይማት ጉዳዮች የተደረጉ ክርክሮች

• ምናኔያውያን / Ascetics/ ስለ ምንኩስና፣ብሕትውና እና የምናኔ ሕይወት የተጻፉ

• ሕግጋት እና ሥርዓታት/Church Law/ ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸውን ልዩ ልዩ ሥርዓቶች እና አሠራሮች የደነገጉባቸው


ጽሑፎች

የታሪክ መጻሕፍት/Ecclesiastical history/ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በተመለከተ የተጻፉ (Fr.Tadros Yacoub
Malaty. An Introduction of Patrology.)

ኢትዮጵያውያን አባቶች

ለቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት፣ የመዝሙር፣ የቅኔ፣ የቅዳሴ እና የሥርዓተ መጻሕፍትን የጻፉ ኢትዮጵያውያን አበው
«ኢትዮጵያውያን አበው» ይባላሉ፡፡

እነዚህ አባቶች በሦስት ይከፈላሉ፡፡


የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና የቤተ ክርስቲያን መምህራን

የቤተ ክርስቲያን አባቶች፡  የምንላቸው ከፍ ብለን ያየናቸውን አራቱን መመዘኛዎች ያሟሉትን ነው፡፡እነዚህ አበው በቀኖና ቤተ
ክርስቲያን ገብተው ቅዱሳን ተብለዋል፡፡ እነርሱም ቅዱስ ያሬድ፣ ርቱዐ ሃይማኖት፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣እነ አባ ጽጌ
ድንግል፣እጨጌ ዕንባቆም፣ ወዘተ ናቸው

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፡  የምንላቸው በሁሉም ነገር ተሟልቶላቸው ቅዱሳን ለመባል ግን የቤተ ክርስቲያንን ውሳኔ ያላገኙትን
ነው፡፡ ከጥንቶቹ የመልክዐ ሥላሴን ደራሲ መምህር ስብሐት ለአብን፣ እነ መምህር ኤስድሮስን፤ እነ መምህር አካለ ወልድን፣
ወዘተ፣ ከአሁኖቹ እነ መልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬን ያካትታል፡፡

የቤተ ክርስቲያን መምህራን   በየቤተ ክርስቲያን መምህራን የምንላቸው በማስተማር እና በድርሰት በርትተው በሕይወታቸው
ምክንያት የቅድስና ማዕረግ ያላገኙትን ነው፡፡ እነ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ፣ እነ ንግሥት ዕሌኒ፣ እነ ዐፄ ናዖድ፣ ፡በትምህርት፣በድርሰት
አና በልዩ ልዩ አገልግሎት ቢበረቱም በኑሮ ዐንቅፋት ገጥሟቸዋል፡፡፡
                                                  

                                                                      ይቀጥላል

Posted by danielkibret at 5/04/2010 11:01:00 PM

10 comments:

Anonymous said...

ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል

እግዚአብሔር የበለጠ ፀጋ ይስጥህ፤ ከፈተና ይጠብቅህ፤ በጎ ጅማሬህን እስከመጨረሻው ያጽናልህ።

May 5, 2010 2:21 AM

Anonymous said...

thanks dani ,

May 5, 2010 3:11 PM


Anonymous said...

ዲ/ን ዳንኤል
Egziabher yestelen. Gena bizu enemaralen (enetebikalen).

Berta

May 5, 2010 3:59 PM

kindu said...

the Sprit of aba Giorgis the gascha be apon you D.Daniel

May 5, 2010 6:53 PM

Anonymous said...

Dn. Daniel,
You are so diversifying and every aspect of your articles touches everybody
in many respects.

This teaches, the teachers, students, and Administrators, and historians


too.

Bertana Tsaf...We need more ... Sew Mechem tegebku Ayilm.

May 5, 2010 6:59 PM

Anonymous said...

"Kale hiwot yasemah"--- I don't like to wonder u b/s if I wonder u I will b


your first and dangerous enemy but I will b trying to pray.
our brother Daniel!!
May god bless u. U carry many problems in your personality---but not
u...that is the secret behind your mother saint virgin marry and her
son,our GOD Jesus Christ.U are Trying to search a big and unforeseen fish
deep in to the sea in my opinion this is to get RELIEF. The way u r going is
what we and the church needs.D/N Daniel try to explore the problems of
our hearts -MONASTRIES. Then as much as u can post fruits of your hands in
what way the believers can help them and give great attention.
pray more and more. Your payment(salary)is not on the mouth of the
believers like those "preachers" of the TIME but at the time of ... from
JESUS CHRIST.
YOUR BROTHER YOSEPH FROM MEKELLE UNIVERSITY ENDAYESUS GIBI
GUBAE
MAY GOD B WITH US

May 5, 2010 11:45 PM

Anonymous said...

Kalehiwot Yasemalen

May 6, 2010 12:54 AM

Aklilu said...

ዳኒ!
ይሄ ነገር በቤተክርስቲያን መምህራንና ሰባክያን ለሚባሉት ሰዎች ራስን መመርመሪያ መነጽር ነው፡፡
መሆን/መባል ሳይገባን የሆንን ስንቶች እንሆን እግዚአብሔር ይወቅ፡፡
ያበርታልን

May 6, 2010 8:17 AM

ኤልሮኢ said...

ለኔ እንደሚገባኝ መ/ር ለመሆን ጥሩ ተማሪ መሆኑ የግድ ነው መማርም አጣርቶ መሆን አለበት ለዚህም
ይመስለኛል ቤ/ክ አወደ ምህረት ላይ አስተምረው መናፍቃን አዳራሽ፣ወደ ዓለም ና ወደመሳሰሉት አልባሌ
ቦታ የት ይደረሳሉ ሲባል የነበሩ መምህራን፡፡ ይህ ሁሉ የመምህርን ምንነትና መምህር ሊኖሩት የሚገባውን
ካለመረዳት ጭምር፡፡
እሰቲ እናስተውል ስንቱ ጉባዔያት ፍሬ አፈሩ ብዙ ወጪ ወጥቶባቸው ትልልቅ ድምጽ ማጉያዎች ተሰቅለው
ምን ያህል ሰው ትምህረቱን ተረዳው ይሆን?

ትዝ ይለኛል ያልተጋነኑ ብዙ ብር ያልወጣባቸው ነገር ግን ብዙዎችን እስከ ዛሬ ያጸኑ እና ምዕመናንን


ከመናፍቃን የጠበቁ መምህራን እና ጉባዔያት፡፡

መቼም በህይወት ዘመኔ የማልረሳው አንድ ሰው አለ ብዙ የኢሉባቦር ሰዎችን በአርአያነት ያስተማሩ


በሕይወቱምበትምህርቱመ በዚህ ዞን ውስጥ ያለማጋነን ከ 100 በላይ ሰ/ት/ቤት የቆረቆሩ ከዚህ ቁጥር
በላይ ቤ/ክ በየገጠር እንዲተከሉ ምዕመናንን በማስተማር በትጋት ያለ ዺ.ን ዳዊት አንዳርጌን የመሰሉ
መምህራን ሲያስተምሩ ድምፃቸው ሳይሰማ ቤ/ክ ሲተከል ና ምዕመናን ሲጸኑ እናይ ነበር፡፡

ዛሬን ግን አይወራ ይቅር ዛሬ ምላሹን ባንተ ጽሁፍ ማግኘት ችያለሁ ምክንያቱም ክ/ሀገር ለማስተማር
ሲመጣ ብሩ ነው የሚሰላው እንጂ የተሸከሙትን አደራ አይደለምና፡፡

ለማንኛውም ሁሉንም በአንድ መፈረጅ አይቻልም በቀና ልቦና ተምራችሁ ለማስተማር የምትጣጣሩ
ሁላችሁ መውደቅ እንዳለ ሁልግዜ አስባችሁ ራሳችሁን አዋርዱ እግዚአብሔር እንዲያለነሳችሁ፡፡

በትዕቢት እንቅልፍ ያንቀላፋችሁ ስም ብቻ የተሸከማችሁ ንቁ ብሎናል ዳንኤል በተባው ብዕሩ፡፡

እግዚአብሔር ለሁላችንም ልብ ይስጠን፡፡

May 6, 2010 2:33 PM

Tigistu Tefera said...

Daniel, yalehin motive weyim wistawi menesasat egziabeher abezito


yibarkileh. Egziabher lehulachinem eyaderek yalewin agelgelot medagna
yadergeline amen.

May 6, 2010 3:15 PM

You might also like