You are on page 1of 21

የመስቀል ዓይነቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የዳበረ የዕይታ ባህል ያላት ሲሆን፤ ለዚህ ማሳያ ከሆኑት መካከል
ቅዱሳት ሥዕላት፣ መስቀል፣ የበዓላት አከባበር፣ የካህናት የአለባበስ ሥርዓት፣ የኪነሕንጻ አሠራር፣ ደስታ አሊያም ሐዘን
የሚገለጽበት ሥርዓት ወዘተ. . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ በሙሉ የተቀደሱ ሕይወትን፣ የክርስትና መሠረታዊ ዶግማ
እንዲሁም ቀኖና መመልከት ለሚችሉ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፡፡ ከሥዕል መገለጫ ባሕርያት መካከል አንዱ የሚታይ
መሆን ሲሆን ከላይ ለአብነት የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ቅዱስ የሆነ አገልግሎትን በግልጥ ተመልካቹ አዕምሮ ላይ ሥዕል
በመፍጠር ያሳያሉ፡፡ በተመልካች ዘንድ የሚፈጠረው ሥዕልም ቤተክርስቲያን በምታደርጋቸው መንፈሳዊ ምስጢራት
ትርጉሞችን ከመረዳት ይመነጫል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ምስጢሩን ያልተረዳ የሚመለከተውም ሆነ የሚፈጥርበት ሥዕል
ከቤተክርስቲያን ቅዱስ ሀሳብ አንጻር ላይገጥም ይችላል፡፡

በመሆኑም የቤተክርስቲያን ድንቅ የሥዕል ጥበብ ከሚታይባቸው አንዱ የሆነው የመስቀል አሠራር ጥበብን ማወቅ
ይገባል፡፡ ቀርበን ስናውቅ ደግሞ የቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ጥልቀትን የሠዓሊያን ደግሞ መራቀቅን እንረዳለን፡፡
ይህም የተገለጠው መስቀልን በአንድ ንድፍ ብቻ ሳይወስኑ ልዩ ልዩ የንድፍ ዓይነቶች በመሥራት፣ ስያሜም በመስጠት
እንዲሁም የሚሠሩበትን ቁስ ጭምር በመምረጥ እንጂ፡፡የዚህን ድንቅ ምስጢር በማስተዋል ስንረዳ በልባችን ላይ
ክርስቶስ ይሣልብናል እንደ ገላቲያ ሰዎችም ከመወቀስ እንድናለን፡፡ ገላ 3፡1

በዚህ አጭር ጽሑፍም ምእመናን የቤተክርስቲያን የመስቀል ዓይነቶች በአሠራር ንድፋቸውና በተሠሩበት ቁስ
ትርጉማቸውን ከናሙና መስቀሎች ጋር ከሥር ቀርቧል፡፡ ይህንን ምስጢር ሁሉም ሰው አውቆ የመስቀሉን ነገር
በልቦናችን እንዲሣል በማስተዋል መስቆሎችን እንመልከት፡፡ የቤተክርስቲያን ሠዓሊያን የሠሯቸውን መስቀሎች ሌሎች
እንዲመለከቱ በማጋራት ክርቲያናዊግዴታችንን እንወጣ፡፡

1. የእንጨት መስቀል ጌታችን የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ምሳሌ

2. የብረት መስቀል ጌታችን ከብረት ከተሠሩ አምስት ችንካሮች ተቸንክሮ የመሰቀሉ ምሳሌ

3. የብር መስቀል ጌታችንን ይሁዳ ጌታን ለ፴ ብር አሳልፎ የመስጠቱ ምሳሌ

4. የወርቅ መስቀል ጌታችን ንጹሐ ባሕርይ ለመሆኑ ምሳሌ፡፡

5. የመዳብ መስቀል መዳብ ቀለሙ ቀይ እንደሆነ የወርቀ ደሙ ምሳሌ

የመስቀልዓይነቶች /በንድፍአሠራር/

1. አርዌ ብርት መስቀል ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለው የናስ እባብ ምሳሌ


2. ሐዋርያ መስቀል ሐዋርያት ዓለምን ዞረው የማስተማራቸው ምሳሌ

3. ቀርነ በግዕ መስቀል ጌታችን የዓለምን ኃጢአት የሚያስተርይ የእግዚአብሔር በግ ለመሆኑ ምሳሌ

4. ዓውደ ዓለም መስቀል በክብ ቅርጽ የተዘጋጀ መስቀል ሲሆን የዓለም ሕዝብ በመስቀሉ የመዳኑ ምሳሌ

5. ሌንጊኖስ መስቀል ለንጊንስ ጌታችንን ጎኑን የወጋው የጦር ምሳሌ

6. ቀራንዮ መስቀል ጌታችን በቀራንዮ የተሰቀለበት መስቀል ምሳሌ

7. ልሳነከለባት ውሻ የጌታውን ቤት እንደሚጠብቅ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በትምህርታቸው የመጠበቃቸው


ምሳሌ

8. ትእምርተንትፊትመስቀል ጌታችን ጎኑን የመወጋቱ፣በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል የመድፋቱና የተበሳ አካሉ ምሳሌ

9. ዕፀ ሳቤቅ መስቀል የጌታችን ምሳሌ የሆነው በይስሐቅ ፈንታ የታረደው በግ የተያዘበት የሳቤቅ ቅጠል ምሳሌ

10. እስተግቡዕ መስቀል ከተለያዩ የመስቀል ያሉትን ንድፎች በማስተባበር የሚሣል መስቀል
የመስቀል በዓል ታሪካዊ አመጣጥ

መስከረም , 2016

የመስቀልበዓልስናከብርልናጤነውየሚገባንዐቢይቁምነገርአይሁድክርስቶስየተሰቀለበትንመስቀልቆሻሻማጠራቀሚያቦታበ
መቅበርእንዲረሳለማድረግቢሞክሩምበንግሥትዕሌኒአማካኝነትእንዴትእንደተገኘናየቀኝእጁየተቸነገረበትክፋይወይምግ
ማድእንዴትወደሀገራችንእንደመጣእንቃኛለን፡፡ መልካምየመስቀልበዓልይሁንላችሁ!

የመስቀል በዓል ታሪካዊ አመጣጥ

ጌታችንኢየሱስክርስቶስየሰውልጆችንለማዳንየተሰቀለበትቅዱስመስቀልሕሙማንንበመፈወሱምክንያትበርካታአሕዛብክ
ርስቲያንእንዲሆኑአስችሏል፡፡
በተአምራዊነቱናበክርስቲያኖችዘንድከፍተኛክብርየተሰጠውበመሆኑናይህንየተመለከቱአይሁድቅዱስመስቀሉንበአንድየቆ
ሻሻማጠራቀሚያቦታእንዲቀበርአደረጉ፡፡የአካባቢውነዋሪዎችበየቀኑቆሻሻስለሚጥሉበትቦታውወደተራራነትተቀየረ፡፡
ምንምእንኳንመስቀሉንለማውጣትባይችሉምበኢየሩሳሌምየነበሩክርስቲያኖችቦታውንያውቁትነበር፡፡
በሰባዓመተምሕረትበጥጦስወረራኢየሩሳሌምስለጠፋችበዚያየነበሩክርስቲያኖችተሰደዱ፡፡
የተቀበረበትንቦታየሚያውቅባለመገኘቱመስቀሉከ 300 ዓመታትበላይተዳፍኖተቀብሮኖረ፡፡

በ 326 ዓ.ም.የንጉሥቆስጠንጢኖስእናትንግሥትዕሌኒቅዱስመስቀሉንለመፈለግወደኢየሩሳሌምጉዞአደረገች፡፡
እዚያምደርሳጉብታየሆነውንሁሉብታስቆፍርመስቀሉያለበትንቦታማግኘትአልቻለችም፤ሰውምብትጠይቅየሚያውቅአል
ተገኘም፡፡
በመጨረሻምየመስቀሉመገኘትየእግዚአብሔርፈቀድነበርናአንድይሁድአረጋዊየታሪክአዋቂናሽማግሌአግኝታቅዱስመስቀ
ሉየተቀበረበትንናየተጣለበትንአካባቢያውቅዘንድጠየቀችው፡፡ሽማግሌውም አንቺምበከንቱአትድከሚሰውንምአታድክሚ
እንጨትአሰብስበሽእጣንአፍሽበትበእሳትምአያይዢውየእጣኑጢስወደላይወጥቶወደታችሲመለስአቅጣጫውንአይተሽአ
ስቆፍሪውበዚህምልክትታገኚዋለሽ አላትእርሷምያላትንሁሉአደረገች።እንጨትደምራበዚያላይምዕጣንጨምራበእሳትለ
ኮሰችው፤የዕጣኑጢስወደላይወጥቶወደታችሲመለስመስቀሉያለበትንቦታበጣትጠቅሶእንደማሳየትያህልአመለከተ፡፡
ንግሥትዕሌኒምጢሱያረፈበትቦታቅዱስመስቀሉየተቀበረበትእንደሆነአመነች፡፡
ይህይሁድአረጋዊየታሪክአዋቂናሽማግሌበኋላበክርስቶስአምኖተጠምቋል፤ስሙምኪርያኮስተብሏል፡፡

በዚህምመሠረትከመስከረም 17 ቀንአስጀምራእስከመጋቢት 10
ቀንሌሊትናቀንለሰባትወራትያህልየጉድፍንኮረብታቆፍረውቆሻሻውንምካስወገዱበኋላሦስትመስቀሎችተገኙ፡፡
የጌታምመስቀልሙትበማስነሣቱተለይቶታውቋል፡፡መስቀሉየተገኘውመጋቢት 10 ቀን 326 ዓ. ም. ነበር፡፡
ቅድስትዕሌኒይህንተአምርበማየቷእጅግደስአላት፡፡
ሕዝቡምሁሉመስቀሉንእየዳሰሱኪርያላይሶንእያሉምበመዘመርደስታናሐሴትአደረጉ፡፡
ቀኑመሽቶጨለማበሆነጊዜምየኢየሩሳሌምጳጳስብፁዕአቡነመቃርዮስናንግሥትዕሌኒ፣ሠራዊቱናሕዝቡበሰልፍበችቦመብራ
ትመዝሙርእየዘመሩቅዱስመስቀሉንወደቤተክርስቲያንወስደውበአንድየጸሎትቤትአኖሩት፡፡
በኋላምበንጉሥቆስጠንጢኖስዕብነመሠረትወይምየመሠረትድንጋይተቀምጦለመሰቀሉመታሰቢያቤተክርስቲያንተሠርቶ
ተመርቆየገባው (ቅዳሴቤቱ) የተከበረውመስከረም 17 ቀን 327 ዓ.ምነው፡፡
በቤተክርስቲያናችንሁለቱምዕለታትይከበራሉ፤በደማቅሁኔታናበመጀመሪያደረጃየሚከበረውግንመስከረም 17 ነው፡፡
ይህምየሆነበትምክንያትመጋቢት 10
ቀንሁልጊዜምበዐቢይጾምወቅትየሚውልመሆኑናለመስቀሉየተሠራውቤተመቅደስየከበረውመስከረም 17 በመሆኑነው፡፡

ይህዕለትከ 300
ዓመታትበላይጠፍቶየነበረውንቅዱስመስቀልበንግሥትዕሌኒአማካኝነትመገኘቱንየምንዘክርበትበዚህምደስየምንሰኝበትዕለ
ትነው፡፡ይህንመነሻበማድረግበኢትዮጵያቤተክርስቲያንደመራበመደመርየመስቀልበዓልበታላቅመንፈሳዊሥነ-
ሥርዓትይከበራል።

የደመራ ትርጉም

ደመራየሚለውቃልደመረ፣ጨመረ፣አንድአደረገ፤ከሚለውየግእዝቃልየተወረሰሲሆንመቀላቀልን፣መገናኘትን፣መሰብሰብን፣
መጣመርን፣መዋሐድንበአጠቃላይሱታፌን፣አንድነትንእናኅብረትንያመለክታል፡፡
ቅዱስመስቀሉበተገኘበትቦታምስለሆነምደመራእንጨቶችየሚደመሩበትየበዓለመስቀልዋዜማነው፡፡
ቤተክርስቲያናችንከምታከብራቸውዘጠኙየጌታችንንዑሳንበዓላትአንዱበዓልነው፡፡
መስቀልየሰላማችንናየድኅነታችንየመቀደሳችንዓርማ፣ኢየሱስክርስቶስየሰውንልጆችለማዳን፥የዘላለምሕይወትንለመስጠ
ትመስዋዕትነትየከፈለበትቅዱስሥጋውንክቡርደሙንያፈሰሰበትመንበር፥ሲሆንአምላካችንንየምንመለከትበትመስታወትነ
ው።

በሀገራችንበኢትዮጵያየመስቀልንበዓልደመራበመደመርናችቦበማብራት፥ቅዳሴበመቀደስናማኅሌትበመቆምየምናከብረው
ለዚህነው።በዚሁምላይይህንታላቅዕፀመስቀልበወቅቱየነበሩታላላቅነገሥታትየሚያደርጋቸውንተዓምራትበማየትለእያንዳ
ንዳቸውይደርሳቸውዘንድከአራትክፍልሲከፍሉትከአራቱአንዱየቀኝእጁያረፈበትግማድ
(ክፋይ)ብቻበደብረከርቤግሸንማርያምሲገኝሌሎችሦስቱግንየትእንደደረሱአይታወቅም።

መስቀሉእንዴትወደሀገራችንመጣ?

የጌታችንቅዱስመስቀልወደሀገራችንሊመጣየቻለበት 1394
ዓ.ም.ዐፄዳዊትሁለተኛበነገሡበ 29 ኛዓመታቸውየእስክንድርያቤተክርስቲያንሊቀጳጳስብፁዕአቡነሚካኤል
47 ኛበወቅቱየነበረውየግብጽመሪ(ከሊፋ)አሠራቸውክርስቲያንየሆኑዜጎቹን የእኔንሃይማኖትካልተከተላችሁበግብጽመኖር
አትችሉም ብሎከአቅማቸውበላይግብርጣለባቸው፡፡መከራውየጸናባቸውየግብጽክርስቲያኖች ከደረሰብንመከራ ታላቅቀን
ሊቀጳጳሳችንንታስፈታልንዘንድበእግዚአብሔርስምተማጽነናል” ሲሉለዐፄዳዊትመልእክትላኩባቸው፡፡

አፄዳዊት “ክተትሠራዊትምታነጋሪት” ብለውአዋጅበማወጅጦርነትለማካሔድወስነውወደካርቱምጦራቸውንአዘመቱ፡፡


ካርቱምደርሰውሁኔታውንሲያዩጦርነትከማካሔድለምንየዐባይንወንዝአልገድብምብለውወሰኑ፡፡
ይህንንምተግባራዊለማድረግእንቅስቃሴማድረግጀመሩ፡፡
ይህንየሰሙየወቅቱየግብጽመሪመርዋንእልጋዴንመኳንቱንሰብስበው “ምንይሻለናልብለውምክርያዙ” የዐባይንወንዝከምና
ጣ “ሊቀጳጳሱንአቡነሚካኤልንእንፈታለንበክርስቲያኖችምላይመከራአናደርስም” ብለውቃልበመግባትብፁዕአቡነሚካኤ
ልንሁለትእልፍወቂትወርቅእጅመንሻአስይዘውለዐፄዳዊትአማላጅላኩ፡፡

ንጉሡዐፄዳዊትም “ብርናወርቅአልፈልግምጌታዬኢየሱስክርስቶስየተሰቀለበትንመስቀልነውየምፈልገው” አሏቸው፡፡


የሀገራችንሕዝብበውኃጥምከሚያልቅብንስማማይሻለናልብለውመስከረም 10 ቀን 1395
ዓ.ም.ከመስቀሉጋርቅዱስሉቃስየሳላትየእመቤታችንሥዕልጨምረውሰጧቸው፡፡በየዓመቱመስከረም 10
ቀንየተቀጸልጽጌየዐፄመስቀልእየተባለየሚከበረውይህንመነሻበማድረግነው፡፡

የታላቋንንግሥትዕሌኒንታሪክበማስታወስመስከረም 17 የመስቀልበዓልንካከበሩበኋላ “መስቀልየይነብርበዲበመስቀል


/መስቀሌበመስቀልላይይኖራል/” የሚልራእይታያቸው፡፡ “ይሔነገርምሥጢሩምንድንነው?” እያሉበድንገትሲናርላይአርፈ
ውአጽማቸውዳጋእስጢፋኖስዐርፏል፡፡

በእሳቸውእግርየተተኩትልጃቸውዐፄዘርዓያዕቆብ “አንብርመስቀልየበዲበመስቀል
/መስቀሌንበመስቀልያስፍራአስቀምጥ/” የሚልራእይበተደጋጋሚእግዚአብሔርአሳያቸው፡፡
በኢትዮጵያካሉትመልከዐምድርውስጥየመስቀልቅርጽያለውየቀራንዮአምሳልየሆነቦታከፈለጉትናካጠኑበኋላጌታችንኢየሱ
ስክርስቶሰበቀራንዮየተሰቀለበትቀኝእጁያረፈበትግማደመስቀልአሁንግሼአምባበሚባለውሥፍራላይመስከረም 21 ቀን
1446 ዓ.ምደብረከርቤአሁንእግዚአብሔርአብቤተክርስቲያንየታነጸበትቦታላይእንዲያርፍአደረጉ፡፡

ግሸንደብረከርቤማርያምገዳም

የግሸንደብረከርቤማርያምገዳምወሎክፍለሃገር፣አምባሰልወረዳውስጥግሸንተራራአናትላይየምትገኝቤተክርስቲያንናት።ለ
ዚችቤተክርስቲያንመግቢያአንድመንገድብቻነው።እንደየኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያንትውፊትይህችቤተክ
ርስቲያንበየዘመኑየተለያየስያሜንአግኝታለች።

የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም መጠሪያ ስሞች

ግሸንደብረከርቤማርያምገዳምመጠሪያስሞችበተለያዩዘመናትየተለያዩእንደነበርየታሪክድርሳናትይነግሩናል፡፡
ከዐፄድልናአድዘመን /866 ዓ.ም/ እስከ 11 ኛውክፍለዘመንበአሁኑስያሜ /ደብረከርቤ/ ትታወቅነበር።

በ 11 ኛውክፍለዘመንአጼላሊበላከቋጥኝድንጋይፈልፍለውእግዚአብሔርአብየተሰኘቤተክርስቲያንበዚሁቦታሲያሰሩደብረእ
ግዚአብሔርበሚልስምታወቀች።ብዙሳይቆይግንደብረነገሥትተባለች።

በ 1446 ዐፄዘርዓያዕቆብግማደመስቀሉንበዚህስፍራሲያርፍደብረነገሥትመባሏቀርቶደብረከርቤተባለች።

ዐፄዘርዓያዕቆብግማደመስቀሉንይዘውእየገሰገስገሱስለመጡበግዕዙ “ገሰ” ወይምበአማርኛው “ገሰገሰ”


የሚለውቃልለቦታውስያሜሆነ።በዘመናትሂደትገስወደግሸንየሚለውስያሜተቀየረ።አካባቢውበዚህስምእንደተጠራየግሸን
ደብረከርቤገዳምታሪክየጻፉትየመሪጌታየማነብርሃንአዲሴመጽሐፍበስፋትይነግረናል፡፡
የግሸንደብረከርቤገዳምታሪክበስፋትለማወቅየምትፈልጉወገኖቻችንመጽሐፋቸውንብታነቡተጨማሪመረጃማግኘትትች
ላላችሁእያልበዚሁእንሰናበት፡፡በቸርያገናኘን!

ወስብሃት ወእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

ተአምረ መስቀል
በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ
የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተክርስቲያንም ገባ።
መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን
አቃጠለችው።
ከክርስቲያንበቀርማንም ሊነካው እንደማይችልየመስቀልንየክብሩንነገርሰዎችነገሩት።ሁለትዲያቆናትንም ይዞየከበረ
መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው ከኢየሩሳሌም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።
የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉንእንደወስዱ
የሮም ንጉስህርቃልበሰማ ጊዜእጅግአዘነ።ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንንአዝዞወደፋርስዘምቶወጋቸው
ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረእፀመስቀልንም እየፈለገበሀገራቸው ሁሉዞረግንአላገኘውም።
ያዲያቆናቱናመስቀሉንየወሰደመኰንንከቦታዎችበቤቱአነፃርባለበአንድቦታላይወስዷቸው ጥልቅጉድጓድ
እንዲቆፍሩአዝዞበዚያየከበረመስቀልንአስቀበረእነዚያንም ዲያቆናትገደላቸው።
ነገርግንያመኰንንየማረካትየካህናትወገንየሆነችበእርሱቤትየምትኖርአንዲትብላቴናነበረች።እርሷም የከበረ
መስቀልንሲያስቀብርናሁለቱንዲያቆናትሲገድላቸው በቤቱውስጥ ሁናበመስኮትትመለከትነበርወደንጉስሀርቃልም
ሂዳመኰንኑያደረገውንሁሉነገረችው።
ይህንንም ንጉስሰምቶእጅግደስአለው ያቺብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራብዙሰራዊትሆኖኤጲስቆጶሳትና
ካህናትም ነበሩ።ወደቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺንልጅተከተሏትቅፍረውም የከበረእፀመስቀልንአገኙት
ከአዘቅቱም አወጡትንጉሱናሰራዊቱም ሰገዱለት።
በልብሰመንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወክብርንም አከበረው እጅግም ደስአለው ከሰራዊቱጋር።የዚህም መስቀል
ሁለተኛየተገለጠበትናየተገኘበትበዚችቀንበመጋቢትአስርነው፡፡ከዚህበኃላንጉሱየከበረእፀመስቀልንተሸክሞ ወደ
ቁስጥንጥንያከተማ ወሰደው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
የመድኃኒታችንየመስቀሉበረከትከሁላችንየክርስቲያንወገኖችጋራይኑርለዘላለሙ አሜን።

You might also like