You are on page 1of 7

✝✨💠✨✝✨💠✨✝✨💠✨✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን

☑️#ሊቀ #ዲያቆናት #ወቀዳሜ #ሰማዕት #ቅዱስ #እስጢፋኖስ

🎚በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው::

🎚ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር::

❓ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ

🎚የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ፤ (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ
የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤት ገባ::

🎚የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር፤ ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

🎚በትውፊት ትምህርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን ዻውሎስን ናትናኤልን ኒቆዲሞስን . . .)
አስተምሯል::

🎚በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር፤ በፍጻሜውም
አምኗል::

🎚ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ::

🎚ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::
🎚በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን
መረመረ::

🎚ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ፤ ለ 6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

🎚ለ 6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተጠመቀ::

🎚በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

🎚"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው፤ ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ እጅ ነስቶ ተማረ::

📖ሉቃ 7፥18

🎚በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ፤ ጌታም ከ 72 ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው፤ አጋንንትም

ተገዙለት::

📖ሉቃ 10፥17

🎚ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔዓለም ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን

ተማረ፤ ምሥጢር አስተረጐመ::

🎚ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ

ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ

ባርኳል፤ በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን

(ዽዽስናን) ተሹሟል::

🎚በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ 72 ቱ

አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት የለም፤ በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::
🎚በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት

ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7

ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር፤ አልፎም የ 6 ቱ ዲያቆናት

አለቃ እና የ 8 ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::

🎚8 ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው::

🎚አንድን ሰው ተቆጣጥሮ

ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው፤ መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ማሕደረ እግዚአብሔር'

ነውና ለእርሱ ተቻለው::

📖ሐዋ 6፥5

🎚አንዳንዶቻችን ቅዱስ

እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን

ይሆናል፤ እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው፤ ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ
አይደለም::

🎚ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለ 1 ዓመት ያህል 8 ሺውን ማኅበር እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት
'እጠፋ እጠፋ' ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ' አለች::

🎚በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው
ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

🎚እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ

ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው::

🎚በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት፤ ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ

ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::


☑️#ፍልሠት

🎚ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ 300 ዓመታት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር፤ ስሙም ሉክያኖስ ይባል
ነበር።

🎚በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው፤ ዻዻሱም ደስ ብሎት

ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል (የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ፤ ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ
ሆነ::

🎚መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ፤ ዝማሬ መላእክትም

ተሰማ ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው በታላቅ

ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው:

🎚በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው

ቤት) አኖሩት፤ እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት::

🎚ከ 5 ዓመታት በኋላም እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን ስለ ፍቅሩ አኖሩት፤ ሚስቱ ወደ ሃገሯ
ቁስጥንጥንያ ስትመለስ የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው፤ መንገድ ላይ
ከሳጥኑ ውስጥ

ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው::

🎚እጅግ ደስ አላት አምላክ ለዚህ አድሏታልና፤ እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች::

🎚በከተማውም ታላቅ ሐሴት ተደረገ ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ
ማረፊያውን አሳወቀች::

🎚በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል፤ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲመቱ ጥቅምት 17 ዕረፍቱ ጥር 1 ፍልሠቱ ደግሞ
መስከረም 15 ቀን ነው::
☑️#ሰማዕታተ #አክሚም

🎚በቤተክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ አሰቃቂ ጭፍጨፋ

ከተካሔደባቸው አካባቢዎች አንዷ ሃገረ አክሚም ናት::

🎚አክሚም ማለት የቀድሞ የግብጽ አውራጃ ናት፤ በተለይ በ 3 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በፍቅር ይኖሩባት

ነበር፤ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቡዓን ታማኞች ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉና ዘወትር ቅዱስ ቃሉን
ለመስማት

የሚተጉ ነበሩ::

🎚ለዚህም ደግሞ ከሊቀ ዻዻሱ አባ ብኑድያስ ጀምሮ ካህናቱ ዲያቆናቱ ንፍቅ ዲያቆናቱ መጋቢዎቹ አናጉንስጢሶቹ
(አንባቢዎቹ) መምሕራኑ መሣፍንቱም ሳይቀር ለክርስቶስ ፍቅር የተጉ መሆናቸው አስተዋጽኦ ነበረው፤ በተለይ ግን 2
ወንድማማቾች የነበራቸው ቅድስና ብዙዎችን ስቧል::

🎚እኒህ ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ይባላሉ፤ ከባለ ጸጋና ባለ ስልጣን ቤተሰብ ቢወለዱም ክርስትናቸው
አልቀዘቀዘም::

🎚የወጣትነት ስሜት ሳያሸንፋቸውም ወደ በርሃ ተጓዙ፤ በዚያም በቅድስና ኑረው ለክህነት ማዕረግ በቅተዋል::

🎚ቅዱሳኑ በገዳም ሳሉም መድኃኒታችን ክርስቶስ ተገልጦ

"ወደ ትውልድ ሃገራችሁ አክሚም ተመለሱ፤ ክብረ ሰማዕታት

ይጠብቃቹሃል" አላቸው::

🎚እነርሱም ደስ እያላቸው

በፍጥነት ወደ አክሚም ወጡ፤ በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ

የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ በጠላት ሠራዊት ተከበቡ::

🎚ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው፤ ዋናው ተልዕኮው ክርስቲያኖችን
ለጣዖት ማሰገድ እንቢ ካሉ ደግሞ መግደል ነው::
🎚ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቀ አልፈሩም፤ ታኅሳስ 29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን
ተሰበሰቡ፤ በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን አደረሱ::

🎚ሁሉም በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ

በገሃድ ተገለጠላቸው፤ በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን

አቀበላቸው::

🎚ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው

ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው፤ ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ::

🎚እነርሱ ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ፤ በዚያን ጊዜ

ወታደሮቹ በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ፤ በተራ

አሰልፈው ዻዻሱን ካህናቱን ዲያቆናቱን አንባቢዎችን መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ 16,000 በላይ ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ::

🎚የቤተክርስቲያኑ ቅጥር

ሞልቶ ደም ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ፤ በክርስቲያኖች ላይ

ግፍ ተፈጸመ፤ አካባቢውም ያለ ወሬ ነጋሪ ቀረ፤ ግድያው

ለ 3 ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና

ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ::

በረከታቸው ረድኤታቸው ይደርብን

#መልካም #እለተ #ዕረቡ #ይሁንልን

✝✨💠✨✝✨💠✨✝✨💠✨✝

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

@Tewahedo12

@Tewahedo12

@Tewahedo12

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

You might also like