You are on page 1of 5

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን

✍”በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ”

📖መዝ 64፥11

ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

የወራት ስያሜ

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለውን
ይመልከቱ፡፡

፩. የወሩ ስም - መስከረም

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሴ እና ከረም

ትርጉም - መሴ-አለፈ ፣ ክረምቱ መሸ፤ ከረም- ክረምት፤ ክረምት አለፈ።

፪. የወሩ ስም - ጥቅምት

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ጠቀመ

ትርጉም - ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ።

፫. የወሩ ስም - ኅዳር

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ

ትርጉም - አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል።


፬. የወሩ ስም - ታኅሳስ

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀሠሠ

ትርጉም - መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን ያመለክታል ፤ ሰብዐ ሰገል በታኅሳስ ወር የተወለደውን
ጌታችንን ማሰሳቸውን ፣ መፈለጋቸውንም ያመለክታል።

፭. የወሩ ስም - ጥር

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ነጠረ ፣ አጥረየ

ትርጉም - ነጠረ - ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል ፤ አጥረየ - ገዛ (ከብቱም ምርቱም
የሚሸጥበት የሚገዛበት ወቅት)

፮. የወሩ ስም - የካቲት

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ከተተ ፣ ከቲት

ትርጉም - መክተቻ (እኅልን ወደ ጎተራ)

፯. የወሩ ስም - መጋቢት

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መገበ

ትርጉም - በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት)

፰. የወሩ ስም - ሚያዝያ

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሐዘ

ትርጉም - ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሠርግ መሆኑን ሲያጠይቅ)

፱. የወሩ ስም - ግንቦት

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ገነበ

ትርጉም - ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል)

፲. የወሩ ስም - ሰኔ

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሰነየ

ትርጉም - አማረ (አዝርዕቱ)


፲፩. የወሩ ስም - ሐምሌ

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሐመለ

ትርጉም - ለመለመ ፣ ሐመልማል ሆነ ፣ ለቀመ (ለጎመን)

፲፪. የወሩ ስም - ነሐሴ

የግእዝ ሥርወ ቃሉ - አናሕስየ

ትርጉም - አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለልን ያሳያል)

፲፫. የወሩ ስም - ጳጉሜ/ን

ሥርወ ቃሉ - ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ)

ትርጉም - ተጨማሪ ማለት ነው፡፡

📌 የኢትዮጵያ የዓመቱ ወራት ሥፍረ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን

፩. መስከረም .. የቀኑ ርዝመት ..12

የሌሊቱ ርዝመት ..12

፪. ጥቅምት ..የቀኑ ርዝመት ..11

የሌሊቱ ርዝመት ..13

፫. ህዳር ..የቀኑ ርዝመት ..10

የሌሊቱ ርዝመት ..14

፬. ታህሣሥ ..የቀኑ ርዝመት .. 09

የሌሊቱ ርዝመት ..15

፭. ጥር ...የቀኑ ርዝመት ..10

የሌሊቱ ርዝመት ..14

፮. የካቲት .. የቀኑ ርዝመት ..11

የሌሊቱ ርዝመት..13

፯. መጋቢት.. የቀኑ ርዝመት..12

የሌሊቱ ርዝመት..12
፰. ሚያዝያ.. የቀኑ ርዝመት.. 13

የሌሊቱ ርዝመት ..11

፱. ግንቦት .. የቀኑ ርዝመት ..14

የሌሊቱ ርዝመት ..10

፲. ሰኔ .. የቀኑ ርዝመት ..15

የሌሊቱ ርዝመት ..09

፲፩. ሐምሌ .. የቀኑ ርዝመት ..14

የሌሊቱ ርዝመት ..10

፲፪. ነሐሴ .. የቀኑ ርዝመት ..13

የሌሊቱ ርዝመት ..11

📌ምንጭ

📚 መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ (በመምህር አፈወርቅ ተክሌ የቅኔ መምህር)፤

📚ኅብረ አትዮጵያ (ዲያቆን ቴዎድሮስ በየነ 1999 ዓ.ም)፤

📚ከሊቃውንት አስተምህሮ

እንኳን ለ 2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

✍ “አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤
ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም
ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ
ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም
ትመራሃለች”

📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ይቆየን
Share

🇹🇪 🇼🇦 🇭🇪🇩🇴

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

✝ @Tewahedo12 ✝

✝ @OrthodoxTewahedo12 ✝

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

You might also like