You are on page 1of 9

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

#ፆም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሰረት ጾም የማህበርና የግል ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡

ፆም ምንድ ነው?

#ጾም ማለት ሰው ምግብ ወይም ሰውነት ከሚፈለጋቸው ነገሮች መካከል መወሰን ማለት ነው፡፡ ጾም በጥንተ ፍጥረት አትብላ ተበሎ የህግ
መጠበቅም ሆኖ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጾም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስርአት ስለሆነ ሃይማኖት በለበት ሁሉ አለ፡፡ ጾም ለተውሰነ
ጊዜ ከእህልና ውሀ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሰውነት የሚምረውን ለማየት እና ለመፈጸም የሚያስጎመጀውን ነገር ሁሉ መፈጸም ነው፡፡
በተግባራዊ ትርጉም የተረዱና የተጠቀሙበት ሰዎች ጾምን ‹‹ለፀሎት እናቷ፣ ለእንባ መፍለቂያዋ ለበጎ ስራ ሁሉ መሰረት ›› በማለት
ተርጉመውታል፡፡

#የፆም_አስፈላጊነት
ሃይማኖት መሰረት ነው ነገር ግን ቤት በመስራት ብቻ የተሟላ እንደማይሆን ሃይማኖትንም ፍጹም የሚያደርጉት በእርሱ መሰረትነት ነው
የመሚታነጹ ስነ ምግባራት ናቸው፡፡ ጾም፣ ጸሎት ምጽዋት ስግደትን የመሰሉት ምግባራት ሃይማኖትን እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡

ጾም የስጋን ምኞትን እናፈቃድን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ መዝ 34፡13፣ ሮሜ 8፡12-14፣ 1 ኛ ቆሮ 6፡12 ‹‹ ለሚጠፋ ምግብ አትስሩ
ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣቹህ የዘለዓለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ›› ዮሐ 6፡7 . ጾም በአምሮት በምኞትና በስስት ጸባዮች ላይ
የበላይነት ያስገኛል፡፡

#በፆም_የተጠቀሙ_ሰዎች

ሀ. #በብሉይ_ኪዳን

የሰማርያው ንጉስ አክአብ 1 ኛ ነገ 20፡27

የእስራኤል ሰዎች 2 ኛ ዜና 20፡1-23

በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች እዝ 8፡21

የነነዌ ሰዎች ዮናስ 3፡3

ነብዩ ነሕምያ ነህ 1፡2

ሀማ በተነሳ ጊዜ አስቴር 3፡9 የመሳሰሉት፡


ለ. #በሐዲስ_ኪዳን

በሐዲስ ኪዳን ጾም የጀመረው ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ ከጾም በኋላ 3 ነገሮችን ድል ነስቷል፡፡ 1. ስስት 2. ትእቢት 3. ፍቅረ
ነዋይ
መላእክትም ቀርበው አገልግለውታል፡፡ መዝ 90፡11 ፣ ማቴ 4፡1 ፣ ሮሜ 14፡1-6

#የአዋጅና_የግል_ጾም

፩.#የአዋጅ_ጾም
በአባቶቻችን የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡
፩ ዐብይ ጾም
፪.ጾመ ነብያት

፫.ሐዋርያት

፬.ፍልሰት

፭.ገሃድ

፮.ነነዌ

፯.ፆመ ድህነት

#ዐብይ_ጾም

ሙሴ በሲና ተራራ ህጉን ከማቅረቡ በፊት 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡ ጌታም ወንጌል ከመስበኩ በፊት በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀን 40
ሌሊት ጾሟል፡፡

. ይህ ጾም አብይ ወይም ሁዳዴ በመባል ይታወቃል፡፡ አብይ የሚሰኘው ዐብይ ነብያት የጾሙት በሐዲስ ኪዳንም ጌታም የኦሪተንና
የነቢያትን ህግ ለመጠበቅና ለመፈጸም ሲል የጾመው በጾሙ ፍጻሜ ከሰይጣን የመጣውን ፈተና ድል የነሳበት በመሆኑ ነው፡፡

. በአብይ ጾም ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሁድ ይገኛሉ፡፡ ይህም የጾሙን ጊዜ ስምንት ሳመንታት ያደርገዋል፡፡ የመጀመርያው ሳምንት ህርቃል
ተብሎ ይታወቃል ወደ ጾሙ መግቢያ መለማመጃ ማለት ነው፡፡ የመጨረሻው ሳምንት ሕማማት ነው ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቀን
በመሆኑ ነው፡፡
እንከኳን ለዐቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
የዐቢይ ጾም 10(አስር) ሌሎች መጠሪያ ስያሜዎች።

1. ዐቢይ ጾም ይባላል፤

2. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤

3. የካሣ ጾም ይባላል፤

4. የድል ጾም ይባላል፤
5. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፤

6. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፤

7. የቀድሶተ ገዳም ጾም ›› ፤

8. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፤

9. የሥራ መጀመሪያ ጾም ››፤

10. ጾመ አርብዓ ይባላል፡፡

..............

‹‹ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ›› ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፤ እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላምና


በጤና አደረሳችሁ፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት እና ሥርዓት መሠረት
በዘንድሮው ዓመት ከሰኞ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም. የሚጀመረውና መጋቢት፴
የሚፈሰከው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው ሲሆን፣ ጌታ
ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን
ምሳሌ ተከትለን እንጾመዋለን፡፡
ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ ይጠራል፡፡ እነርሱም፡-

1=> . ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡


ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች
(ዕብ.13፥7) ሲሆኑ ይኼኛው ግን የባሕርይ አምላክ በሆነው በጌታችን

በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡

የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል


የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡
2=> ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡
ሁዳድ ማለት የመንግሥት መሬት፣ የመንግሥት ርስት ማለት ነው፡፡ የመንግሥት
ሁዳድ በሚታረስበት ጊዜ፣ አዝመራው በሚሰበሰብበት ጊዜ ልጅ ዐዋቂ ሳይባል
የመንግሥቱ ዜጋ ሁሉ ለሥራ ታጥቆ እንደሚነሣ ይህንንም የጌታ ጾም ወይም
የጌታ ሁዳድ የክርስቶስ ዜጎች የሆኑ ምእመናን ሁሉ ይጾሙታልና ጾመ ሁዳዴ
ይባላል፡፡
3=> የካሣ ጾም ይባላል፡፡
አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት፥ ለሞት፥ ለሲዖል
ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነበር፡፡ በመብል የወደቀውን የሰውን ልጅ
ክርስቶስ በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠው እንዲሁም አዳም ከገነት ሲባረር ረሃበ
ጸጋ (መንፈሳዊ ረሃብ) ደርሶበት ነበርና ረሃቡን በረሃብ ካሠለት፡፡ የኛን ረሃብ እርሱ
ተራበ፡፡ ስለዚህም የካሣ ጾም ተባለ፡፡
‹‹ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ›› ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፤ እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላምና
በጤና አደረሳችሁ፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት እና ሥርዓት መሠረት
በዘንድሮው ዓመት ከሰኞ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም. የሚጀመረውና መጋቢት፴
የሚፈሰከው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው ሲሆን፣ ጌታ
ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን
ምሳሌ ተከትለን እንጾመዋለን፡፡
ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ ይጠራል፡፡ እነርሱም፡-

1. ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡
ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች
(ዕብ.13፥7) ሲሆኑ ይኼኛው ግን የባሕርይ አምላክ በሆነው በጌታችን

በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡

የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል


የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡
2. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡
ሁዳድ ማለት የመንግሥት መሬት፣ የመንግሥት ርስት ማለት ነው፡፡ የመንግሥት
ሁዳድ በሚታረስበት ጊዜ፣ አዝመራው በሚሰበሰብበት ጊዜ ልጅ ዐዋቂ ሳይባል
የመንግሥቱ ዜጋ ሁሉ ለሥራ ታጥቆ እንደሚነሣ ይህንንም የጌታ ጾም ወይም
የጌታ ሁዳድ የክርስቶስ ዜጎች የሆኑ ምእመናን ሁሉ ይጾሙታልና ጾመ ሁዳዴ
ይባላል፡፡
3=> የካሣ ጾም ይባላል፡፡
አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት፥ ለሞት፥ ለሲዖል
ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነበር፡፡ በመብል የወደቀውን የሰውን ልጅ
ክርስቶስ በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠው እንዲሁም አዳም ከገነት ሲባረር ረሃበ
ጸጋ (መንፈሳዊ ረሃብ) ደርሶበት ነበርና ረሃቡን በረሃብ ካሠለት፡፡ የኛን ረሃብ እርሱ
ተራበ፡፡ ስለዚህም የካሣ ጾም ተባለ፡፡
4. የድል ጾም ይባላል፡፡
ጌታችን ተጠምቆ ዕለቱን ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሔድ ከሰው ተለይቶ አርባ
መዓልትና አርባ ሌሊት በመጾም አዳምና ሔዋንን በመብል የረታቸውን
ዲያብሎስን እርሱ ድል አደረገላቸው፡፡ ዲያብሎስን ድል ያደርግ ዘንድ ከዚህ
ዓለም ርቆ ወደ ገዳም መሄዱ አዳም ከዚህ ዓለም ርቃ በምትገኘው ገነት ድል
ሆኖ ነበርና እርሱም ዲያቢሎስን በገዳም በዚህ ዓለም ርቆ ድል አደረገልን
ለእኛም ፈቃደ ሥጋችንን የምናሸንፍበተ ኃይል ሰጠን ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእንም
ድል ነሣልን፤ እነዚህም ሆድን መውደድ(ስስት) ተርእዮንና ክብርን መሻት

(ትዕቢት) ገንዘብን ያለልክ መውደድ (ፍቅረ ንዋይ) ናቸው፡፡ ጌታችን ስስትን

በትዕግሥት፣ ትዕቢትን በትሕትና፣ ፍቅረ ንዋይን በፀሊዓ ንዋይ (ገንዘብን

በመናቅና በመጥላት) ድል አድርጎ ድል እናደርግ ዘንድ ምሣሌ ትቶልናል፡፡ ይህ


ጾም ጠላት ዲያቢሎስ የተሸፈነበት አርእስተ ኃጣውእ ድል የተነሱበት ስለሆነ
የድል ጾም ይባላል፡፡
5=> መሸጋገሪያ ጾም ይባላል፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕዝቡን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት ሲያሸጋግር አርባ
መዓልትና አርባ ሌሊት በደብረ ሲና እንደ ጾመው ሁሉ ጌታችንም እኛን ከሕገ
ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሲያሸጋግረን አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡
ስለዚህም የመሸጋገሪያ ጾም እንለዋለን፡፡
6=> ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡
ሁሉን ነገር በቅጽበትና ያለ ድካም ማድረግ የሚችለው አምላክ እኛን ልጆቹን
ያስተምረን ዘንድ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ መልካም መምህር ተማሪዎቹ ይገባቸው
ዘንድ ዝቅ ብሎ በነርሱ ቋንቋ እየተናገረ በሚችሉት እየመሰለ እንዲያስረዳ
ጌታችንም እኛን ወደርሱ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እርሱ ወደ እኛ መጣ፡፡
ረሃባችንን ተራበ ፤ ድካማችንን ደከመ ፤ ፈተናችንን ተፈተነ ለእኛም አርአያ ሆኖ
ትሕትናን ፤ ትዕግሥትንና ፈተናን በጾም ማሸነፍን አስተማረን፡፡
7=> የቀድሶተ ገዳም ጾም ይባላል፡፡
እነ መጥምቁ ዮሐንስ እነ ነቢዩ ኤልያስ የኖሩትን የብሕትውና ኑሮ ጌታ ባርኮ
ሰጠን፡፡ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ርቆ በበረሃ ከአራዊት ጋር እየኖረ በዲያብሎስ
ተፈትኖ ድል አደረገ፡፡ ዛሬም ልጆቹ በየገዳማቱ ድምፀ አራዊትን፥ ጸብዓ
አጋንንትን፥ ግርማ ሌሊትን ፥ የሌሊት ቊሩን፥ የቀን ሐሩርን ታግሠው፤ ዳዋ
ጥሰው፥ ጤዛ ልሰው፥ መሬት ተንተርሰው፤ ዓለምን ንቀው ፤ ከሰው ርቀው በጾም
በጸሎት ከአጋንንት ጋር ይታገላሉ ድልም ያደርጋሉ፡፡
8=> የመዘጋጃ ጾም ይባላል፡፡
ለእሥራኤላውያን ስለ በዓለ ፋሲካ አከባበር ሲነገራቸው የፋሲካውን በግ ሥጋ
ከመራራ ቅጠል ጋር እንዲበሉት ታዘው ነበር (ዘጸ.12፤18)፡፡ ይኽም መራራ
ቅጠል በግብፅ ይኖሩት የነበረውን የመከራ ኑሮ የሚያሳስባችውና ዳግም ወደ
ግብፅ (ምድረ ፋይድ) እንዳይመለሱ ከኃጢአተ ይርቁ ዘንድ የሚያስተምራቸው

ነበር፡፡ ይህ ወቅትም በዓለ ትንሣኤን (የሐዲስ ኪዳን ፋሲካን) ለማክበር ቅዱስ


ሥጋንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ራሳችንን በጾም፥ በጸሎት፥ በስግደት
የምናዘጋጅበት ስለሆነ የመዘጋጃ ጾም ተብሏል(1 ቆሮ.11፤27)፡፡

9=> የሥራ መጀመሪያ ጾም ነው፡፡


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ሥራውን ከመጀመሩ
የመንግሥተ ሰማያትን አንቀጽ ከማስተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ
መዓልትና ሌሊት ጾመ፡፡ ይህም ለእኛ የማንኛውም ነገር መጀመሪያው ጾም
መሆኑን ሲያሰተምረን ነው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያት ጾምን የሥራቸው መጀመሪያ
ያደረጉት፡፡
10=> ፆመ አርብዓ
ስያሜው የተሰጠው በወንጌላት እንደተገለፀው ጌታችን ቀደምት ነቢያት አበው
(እነ ሙሴ፣ እነ ኤልያስ) በፆሙት አምሳል አርባ ቀንና ሌሊት መፆሙን
የሚያስታውስ መጠሪያ ነው፡፡ ይህ ስያሜ አሁን ከምንፆመው ፆም ከቅድስት
እስከ ሆሳዕና ያሉትን ብቻ የሚያመለክት ሲሆን ከዘወረደ እስከ ቅድስት ያለው
አንድ ሣምንት ፆመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ሕርቃል የተባለው ክርስቲያን ንጉሥ
በአመጻ ተነስቶ ንግስት እሌኒ ካስቀመጠችበት መቅደስ መስቀሉን የዘረፈውን
ዓላዊ ንጉሥ ተዋግቶ መስቀሉን ማስመለሱን በማሰብ እንዲጾም፤ እንዲሁም
ከሆሳዕና እስከ ትንሳኤ ያለውን አንድ ሣምንት ደግሞ ሰሙነ ሕማማት ተብሎ
የጌታ መከራና ስቃይ እንዲታሰብበትና እንዲጾም ቅዱሳን አባቶችን በሠሩት
ሥርዓት የተጨመሩ ናቸው፡፡
" አሜን ጾሙን አምላካችን ወዶ የሚቀበለው ፥ የኃጢአት መደምሰሻ ፤
የዲያብሎስ ድል መንሻ ፤ የመንግሥቱ መውረሻ ያድርግልን አገራችንን ሰላም
ያድርግልን።
ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
# የአበው # ጥንቃቄ
ምንም እንኳን ጾማችንና ሕይወታችን እንደ አባቶቻችን ባይሆንም ቢያንስ ግን
የአበውን ብርታትና ጥንቃቄ ማንሳትና ማሳወቅ ግን ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡
እንደሚታወቀው በበዓለ ሃምሳ ረቡዕና ዓርብን ጨምሮ ምንም ዓይነት ጾም
የለም
ይህን የምናደርገው ለበዓሉ ክብር ቢሆንም አበው ግን በዘመናት ሁሉ ለምግብ
ወይም ለሆድ ያልኖሩ በመሆናቸው አስቀድመው በበዓለ ሃምሳ ውስጥ የሚገኙ
የረቡዕና ዓርብን ጾም በዐቢዩ ጾም ውስጥ በጥንቃቄ እንዲካተት አድርገዋል፡፡
በዐቢይ ጾም ውስጥ ያሉት (ከሰኞ-ዓርብ) ያሉት ቀናት ብዛት፦ 8×5=40 ናቸው፡፡
በፍትሐ ነገሥት የተቀመጠው የዐቢይ ጾም የሰዓት ገደብ እንደሌሎቹ አጽዋማት
9:00 ላይ አይደለም፡፡

የሰሙነ ሕማማት አምስቱ ዕለታት ብቻ እስከ ምሽት 1:00 ወይም ኮከብ

እስከሚታይ ድረስ ሲሆን የሌሎቹ 35 ዕለታት እስከ 11:00 ድረስ ነው፡፡

አሁን ከተለመደው 9:00 በላይ የሆነበትን ምሥጢር እናንሳ፦

ከ 35 ቱ ዕለታት የ 3 ሰዓታት ልዩነቶችን ወስደን፦ 3×35=105 ሰዓታትን


እናገኛለን፡፡
ከሰሙነ ሕማማት 4 ሰዓታት ልዩነት ወስደን፦

4×5= 20 ሰዓታትን እናገኛለን፡፡

በጠቅላላው 105+20=125 ሰዓታትን እናገኛለን፡፡

በበዓለ-ሃምሳ ውስጥ ሰባት ረቡዖችንና ሰባት ዓርቦችን እናገኛለን ፤ እስከ ዘጠኝ

ሰዓት ድረስ በሚሆነው ጾም ሰዓቱን ስናሰላ፦ 7 ረቡዕ =7×9=63

7 ዓርብ =7×9=63

በድምሩ 63+63=126 ሰዓታት ይሆናሉ፡፡


ይህም በአንድ ሰዓት ልዩነት ብቻ በዐቢይ ጾም ከዘጠኝ ሰዓት አትርፈን እንድንጾም
ካዘዙን ሰዓት ጋር እኩል ነው፦Approximately 125 ~126 {~ን እንደ አቅራብ

ስሌት ምልክት በመጠቀም)

ስለዚህ 125 ቱ ሰዓቶች ለውጦች ናቸው ማለት ነው፡፡


ይህ ደግሞ የሚያሳየው፦
• የበዓለ ሃምሳዎቹ ረቡዕና ዓርብ አስቀድመው እንደተጾሙ

• አበው ስለ ጾም ያላቸውን ጥንቃቄ

• መናፍቃን በበዓል ምክንያት ጾምን ይሽራሉ ብለው ለመንቀፍ ምክንያት


እንዳያገኙ ነው፡፡
(የጽሑፍ ምንጭ፦ ፍትሐ ነገሥት አንድምታ ትርጓሜ የእጅ ጽሑፍ፤

የቃል ምንጭ ፡-አባ ደሳለኝ አራጌ ዘምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም )::
አባቶቻችን በእንደዚህ ዓይነት ጥንቃቄ ያቆዩልንን ሥርዓት እንድንጠብቅ
እግዚአብሔር ይርዳን!!!

አሜን!!!

ነቅዐ-ጥበብ

#ጾመ_ሐዋርያት
ጾመ ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወንጌልን ለሕዝብ ከማስተማራቸው አስቀድመው ጾመዋል፡፡ የሰኔ ጾም ይባላል፡፡
ይህ ጾም ከፍና ዝቅ ስለሚል የተወሰነ ቀን የለውም አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰላሳ ያንሳል፡፡

#ጾመ_ነብያት
ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ይጠብቁ የነበሩ ነብያት የጾሙት ነው፡፡ ነብያት ስለመሲህ መምጣት በናፍቆት ይጸልዩ ነበር፡፡

#ጾመ_ፍልሰታ
ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ የእመቤታችን የዕረፍት፣ ትንሳኤና ዕርገት ምስጢር ለሐዋርይት የተገለጠበት ታሪክ መታሰቢያ ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ከሐምሌ 1-14 ድረስ ጾመው ድንግል ማርያም ተገልጣላቸዋለች በ 16 ኛው ቀን አርጋለች፡፡

#ጾመ_ገሃድ
ገሃድ ማለት ግልጥ ይፋ፣ በገሃድ የሚታይ ማለት ነው፡፡ መለኮት የተገለጠበት ጌታ ልዩ የሆነ የአንድነትና የሶስትነት ምስጢር የተገለጠበት
ስለሆነ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ ማቴ 3፡16 ዮሐ 1፡29

#ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
ይህ የነነዌ ሰዎች የጾሙት ነው፡፡ የዚያች አገር ሰዎች የፈጸሙት በደል በእግዚአብሄር ፊት ታላቅ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት ታዝዞባቸው ነበር፡፡
የነነዌ ጾም ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ዕረቡ ሶስት ቀን ነው፡፡

#ጾመ_ድህነት (የዕረቡና የአርብ)

ከትንሳኤ በኋላ ከሚኖሩት 50 ቀኖች በቀር ዕረቡና አርብ ዓመቱን በሙሉ የጾም ቀኖች ናቸው፡፡ እንደጾሙአቸው የተደረገው አርብ እና
ዕሮብ፤ ዕሮብ የተፈረደበት አርብ የተሰቀለበት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ነው፡፡

፪. #የግል_ጾም
በሕግ የታወቁ አጽዋማት በግልጥ በማህበር ይጾማሉ፡፡ የግል ጾም ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በሰዎች የግል ፍላጎትና የሕሊና ውሳኔ ሚጾም
የፈቃድና የንስሐ ጾም ነው፡፡ ማቴ 5፡6 ማቴ 6፡18 ዳን 6፡10

🙏🙏🙏ለሌሎች ያካፍሉ

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

http://t.me/ortodoxtewahedo

You might also like