Sirate Bete Krstiyan Grade 4

You might also like

You are on page 1of 72

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

ለአራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት


ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ ፳፲፭ ዓ.ም
ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/
UC83LE1vp0FBsV2TEfcpSmUg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
Twitter
https://twitter.com/tibeb_felege

Copyright ©
፳፲፭
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ
አስኪያጅ እና የባህርዳር ሁገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ በሰንበት ትምህርት ቤቶች


ማደራጃ መምርያ የበላይ ሊቀጳጳስና የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ማውጫ
ምዕራፍ አንድ
ህንጻ ቤተክርስቲያን................... ፫
፩. የቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍሎች ............ ፱
፪ የቤተክርስቲያን ውጫዊ ክፍሎች እና አገልግሎቶቹ........ ፲፩
፫. በቤተክርስቲያን ማድረግ ስለ ሚገባን እና ስለ ማይገባን..... ፲፬

ምዕራፍ ሁለት
ሥርዓተ ቅዳሴ.................................. ፳
፩. ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ................................... ፳፩
፪. ለቅዳሴ የሚሰየሙ ካህናት ተግባራት.................... ፳፪
፫. ቅዳሴ በማስቀደስ የሚገኝ በረከት............................. ፳፪
፬. በቅዳሴ ወቅት ማድረግ ስለ ሚገባን እና ስለ ማይገባን...... ፳፬

ምዕራፍ ሦስት
፩. ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት.................................... ፳፰
፪. ከመቁረባችን በፊት ምን ማድረግ እንዳለብን.............. ፴፩
፫. ከቆረብን በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብን .................... ፴፬

ምዕራፍ አራት
፩. ወደ ገዳም ሂዶ የመሳለም ሥርዓት ............................ ፴፮
፪. ክርስቲያናዊ አለባበስ ሥርዓት...................................... ፴፰
፫. ሥርዓተ ስግደት......................................................... ፴፱
፬. ስለ ምጽዋት ሥርዓት.................................................. ፵፩

ምዕራፍ አምስት
፩. የጸሎትና መዝሙር ሥርዓት...................................... ፶፪
፪. የጸሎት ሥርዓት....................................................... ፶፫
፫. መዝሙር እንዴት መዘመር እንዳለብን........................ ፷


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

መግቢያ

የትምህርቱ ዓላማ በ፵ በ፹ ቀን ተጠምቀው ከእግዚአብሔር አምላክ


ልጅነትን ያገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ የቤተክርስቲያናቸውን ሥርዓት በሚገባ
አውቀውና ተረድተው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን
ያስተማረቻቸውን እና የምታዛቸውን ሥርዓት በቅጽረ ቤተክርስቲያንም
ሆነ ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ውጪ እንደ የአስፈላጊነቱ እንዲፈጸሙ ግንዛቤ
ማስጨበጥ ነው፡፡

ይህ የአራተኛ ክፍል የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት በአምስት


ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ ህንጻ ቤተክርስቲያን፤ ሥርዓተ
ቅዳሴ፣ ሥርዓተ ቁርባን፣ ሥርዓተ ገዳም፣ ሥርዓተ ጸሎት፣ ሥርዓተ
ምጽዋትንና ሥርዓተ መዝሙርን የሚያካትት ይሆናል፡፡ በእያንዳንዱ
ምዕራፍ የራሱ ማጠቃለያና መልጃዎችን አጠቃሏል፡፡ በዚህ ትምህርት
ተማሪዎች ትምህርቶችን ማወቅ ብቻ ሳይሆን በተግባር እንዲያውሉት
ይጠበቃል፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
ህንጻ ቤተ ክርስቲያን

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የቤተ ክርስቲያን ውስጣዊና ውጫዊ ክፍሎች እንዲሁም


አገልግሎቶቻቸውን ያዉቃሉ
• በቤተ ክርስቲያን ማድረግ ስለ ሚገባቸው እና ስለ ማይገባቸው
ሥርዓቶች ይገነዘባሉ
• ቤተክርስቲያንን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸውም ይረዳሉ

የመክፈቻ ጥያቄዎች

• ተማሪዎች ሥርዓት ማለት ምን ማለት ነው?


• ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ማለትስ ምን ማለት ይመስላችኋል?
• ቤተ ክርስቲያን ስንት ክፍሎች አሏት?
• ቤተ ክርስቲያን ስትመጡ ምን ምን ታደርጋላችሁ? ምንስ
አታደርጉም?
(እባክዎ መምህር የተማሪዎችን መልስ በቡድን ወይም በተናጠል
ይቀበሉልን)


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ስለ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ከማየታችን በፊት ሥርዓት ምን ማለት


እንደሆነ እንመልከት፡፡

፩.፩ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ‹ሥርዓት› እና ‹ቤተ ክርስቲያን› ከሚሉ
ሁለት የግእዝ ቃላት የተመሠረተ ነው፡፡ ትርጉማቸውን እንደሚከተለው
እንመለከታለን፡፡
፩.፩.፩ ሥርዓት፡- ሥርዓት ማለት ‹ሠርዐ› ሠራ ከሚለው የግእዝ ግሥ
የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር፣
መመሪያ ማለት ነው፡፡ ሥርዓት ለማንኛውም ሊከናወን ለሚችል ነገር
ቅደም ተከተል፣ መጀመሪያና መጨረሻ፣ ልክና መጠን ወይም ገደብ
ማዘጋጀት፣ ከዚህ ቢወርድ ይጎድላል፤ ቢያልፍ ይፈሳል፤ ወደ ቀኝ ሲዞር
ይዘጋል፤ ወደ ግራ ይከፈታል ወዘተ... በማለት መመሪያ ማውጣት፤
ውሳኔ መወሰን ማለት ሲሆን ስምምነቱ ትእዛዝ የአሠራሩ ስልት ውሳኔ
መመሪያ ወዘተ ማለት ነው፡፡ ሥርዓት በመንፈሳዊ ትርጉሙ (ቀደምት
አበው ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን የሠሩት ሕግ፣ ውሳኔ፣ ደንብ፣
መመሪያ ወይም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማለት ነው፡፡‹‹... ያለ ሥርዓት
የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች
ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።... ›› ፩ተሰ. ፭፥፲፬

፩.፩.፪ ሥርዓት ለምን ያስፈልጋል?

ሀ. ማንኛውንም ሥራ ዘላቂ እንዲሁም ወጥ በሆነ መልኩ በሥርዓት


ማስኬድ ያስችላል፡- ያለ ሥርዓት የሚሠራ ነገር ፍጻሜው አያምርም፤
እግዚአብሔር እንኳን ዓለሙን የፈጠረውንና የሚያስተዳድረው በሥርዓት
ነው፡፡ ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸሙ አገልግሎች ሁሉ ወጥና
አንድ ዓይነት በሆነ ሁኔታ እንዲፈጸሙ ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል ‹‹


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ሁሉ በአግባቡና በሥርዓት ይሁን›› እንደተባለ አንድ ሐሳብ አንድ ልብ
ለመሆን አንድ ዓይነት ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡ መዝ ፻፫፣፲፰-፳፰ ፣ ፩ኛ
ቆሮ ፲፬፣፵

ለ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጽናት ያስችላል፡- ያለ አንድ ዓይነት


ሥርዓት አንዱ ሲጀመር አንዱ የሚጨርስ አንዱ ሲዘምር ሌላው
የሚያስተምር ከሆነ መለያየትን ያመጣል፡፡ ስለሆነም በማኅበረ ምዕመናን
ሐዋርያው እንደተናገረ የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ አንድ ዓይነት
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ስንሆን አንድ ልብና አንድ
ሐሳብ የሚያደርገን ሥርዓት ነውና፡፡ ኤፌ ፬፤፫ ዮሐ፬፤፴፪ ሮሜ ፲፭፤፭-፮

ሐ. የቤተ ክርሰቲያን ምሥጢራትን በአግባቡ ለመፈጸም ይረዳል፡፡


ለምሳሌ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ጾም፣ ጸሎት ... ወዘተ በማመን
ብቻ የሚያበቁ ሳይሆኑ የአፈጻጸምና የአተገባበር መንገድ /ሥርዓት/
ያስፈልጋቸዋል፡፡ የእነዚህ ሁሉ ዝርዝር አፈጻጸም በሥርዓት ውስጥ
ይካተታል፡፡ ስለዚህ በአንዲት ርትዕትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን
እምነት ሥር ያለ ሁሉ ያቺን አንዲት እምነት የሚፈጽሙት በአንድ
ዓይነት ሥርዓት ነው፡፡

መ. የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጥልቅና ምጡቅ የሆነውን ቤተ


ክርስቲያን ትምህርት በመጠኑም ቢሆን ለመማርና ለማስተማር ለማወቅ
ሥርዓቱን ለመፈጸም የሚረዳ ነው፡፡

፩.፩.፫ የሥርዓት ዓይነት፡-


የሥርዓት ይዘት በልዩ ልዩ አገልግሎት ልዩ ልዩ ቢሆንም ሁለት ዓይነት
ዐበይት ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህም፡-
፩ የተፈጥሮ ሥርዓት፡- የተፈጥሮ ሥርዓት የሚባለው የሥነ ፍጥረት
ፈጣሪ እግዚአብሔር ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በነጻ ያደለው የእያንዳንዱ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

የግል ጸጋ መለያና የአስተሳሰብ እንዲሁም የአኗኗር ስልት ነው፡፡ ይህም


በመሆኑ ሁሉም አንድ ዓይነት ጸባይና የሕይወት ስልት የለውም፡፡ ሁሉም
የየራሱ የግል ጸባይ አለው፡፡ ለሰው ልዩ ሥርዓት አለው፡፡ የእንስሳትም
ሥርዓት ሌላ ነው፡፡ የአራዊትም ሥርዓት የተለየ ነው፡፡ ግዑዛኑ ፍጡራን
ሳይቀሩ በተፈጥሮ የተሰጣችው ሥርዓት አለ፡፡

፪. መንፈሳዊ ሥርዓት፡- ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ በእርሱ የሚዘጋጅ


የመንፈስ ቅዱስ ውጤት ነው፡፡ ይህም በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ
የተመሠረተ የመንፈሳዊ ሕይወት መመሪያ ነው፡፡ ሥጋዊ ሥርዓት
የሥጋዊ መሪዎች ለሥጋዊ ኑሮ መመሪያነት የተዘጋጀ ስለሆነ በስሩ ላሉ
ተስማሚ ካልሆነ በቀላሉ ሊሻሻልና ሊለወጥ ይችላል፡፡ ምንም ዓይነት ጊዜ
የሚወስድ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ሥርዓት የተሠራው በብዙ መንፈሳዊ
ጥረት ነው፡፡ ለሚደረገው ለውጥም ሆነ መሻሻል መንፈሳዊ አሠራርን
ይጠይቃል፡፡

መንፈሳዊ ሥርዓት ከሰበካ ሰበካ፤ ከሀገር ሀገር የሚለይ ሳይሆን አንድ


መሠረት ያለው ከአንድ ምንጭ የተቀዳ አንድ ወጥና የአንድ ዓይነት
አምልኮ መመሪያ ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤና የጋራ ውሳኔ እንጂ አንድ
ግለሰብ/አንድ ካህን/ አንድ ፓትርያሪክ ወይም ኤጲስቆጶስ፣ ቄስ፣ዲያቆን፣
ወዘተ... ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጨመር ወይም መቀነስ አይችሉም፡
፡ከጊዜውና ከምዕመኑ የኑሮ ደረጃ አንጻር ሲታይ መቀነስ መሻሻል
ወይም ፈጽሞ መለወጥ ያለበት ሆኖ ከተገኘ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ
በኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ አማካኝነት ይፈጸማል እንጂ እያንዳንዱ ካህንም
ሆነ ምዕመን እንደመሰለው የተጻፈውን መቀነስ ወይም ከእሱ እያወጣ
ሊጨምር አይችልም፡፡

፩. ፪ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?


በቀጥተኛ ትርጉም ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ቤተ እና ክርስቲያን


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ከሚሉት ሁለት የግእዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቲያኖች
መኖሪያ /ቤት/ ማለት ነው፡፡ ይህም የክርስቶስ ቤት፣ የክርስቲያኖች
መሰባሰቢያ ቤት የሚል ትርጉም አለው፡፡ በግሪክ አቅሌስያ ትባላለች፤
የምርጦች ጉባዔ ማለት ነው፡፡ ይህች የምርጦች ጉባዔ የእግዚአብሔር
ሕዝብ የነበሩት ጉባዔ እስራኤልን ያመለክታል፡፡

በዘይቤያዊ ፍቺ ቤተ ክርስቲያን ስንል ሦስት ትርጉም አለው ፡-


፩. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን:- ተሰባስበን የምናስቀድስባት፣ የምንማርባትና
ሌሎች ምሥጢራትን የምንፈጽምባት ናት፡፡ ይኽችም ቤት ጌታችን ኢየሱስ
ቤቴ ስላላት የክርስቶስ ቤት እንላታለን፡፡ “ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ
የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤እርሱም፦ ቤቴ የጸሎት ቤት
ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት
አላቸው።” ሉቃ. ፲፱ ፥ ፲፮ በዘመነ ሐዲስ የማርቆስ እናት የማርያም ቤት
የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ሐዋርያት በዚያች
ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ይጸልዩ ነበር፡፡ “ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ
ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት
አጥብቃ ታደረግ ነበር።” የሐዋ.፲፪፥፭

፪. የክርስቲያኖችን ስብስብ፡- በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖች


ሁለትና ከዚያ በላይ የሚኖራቸው ስብስብ ቤተ ክርስቲያን ይባላል፡፡
ምክንያቱም በዚያ የእምነት አንድነት ውስጥ እግዚአብሔር አለና፡፡ “ሁለት
ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”
ማቴ. ፲፰ ፥ ፳ እንደተባለ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የበደለንን መክረን አልሰማ ቢለን ለቤተ ክርስቲያን ንገራት ያለን ለዚህች
የአባቶች ካህናት እና የምእመናን ስብስብ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን
ነው፡፡ ማቴ. ፲፰ ፥ ፲፯ ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን በተለይም በሐዲስ
ኪዳን በተደጋጋሚ ተጽፏል፡፡ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ የሐዋ.
፲፩፥፳፪፣፲፫፥፩፣ሮሜ.፲፮፥፩፣ ፩ኛ.ቆሮ.፲፮፥፲፱፣ፊልሞ.፩፥፪፣ ፩ኛ.ጴጥ. ፭፥፲፫


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፫. እያንዳንዱ ክርስቲያን ፡- በእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት አምነው


የተጠመቁ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች፣ የክርስቶስ አካላት
ናቸውና ቤተ መቅደስ ይባላሉ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር
ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ
አታውቁምን?” ፩ኛ.ቆሮ. ፫፥ ፲፮ ብሎ የተናገረው፡፡ እንዲሁም በሌላ ቦታ
“ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣኦት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ
የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና ፪ኛ ቆሮ. ፮ ፥ ፲፮ እንዲሁም
እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም
እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”
እንደተባለ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ማደሪያ ነንና ቤተ ክርስቲያን ተብለን
እንጠራለን፡፡

፩. ፫ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አሰራር ሥርዓት

እግዚአብሔር በባሕርይ ምልዓቱ የተነሳ የሌለበት ቦታ ባይኖርም


ውስን ፍጥረታት እኛ ለሕሊናችን በሚስማማ ሁኔታ በውሱን ቦታ
እንድናመልከው አዝዞናል፡፡ ይህም ለእኛ መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን
እርሱም በእኛ በረድኤትና በጸጋ ላለመለየቱ የቃል ኪዳን ቦታ መሆኑ
ነው፡፡ እስራኤልን ‹‹ በመካከላችሁ አድር ዘንድ መቅደስን ሥሩልኝ››
ያላቸው ለዚህ ነው፡፡ ዘጸ ፳፤፱ ሰዎችም ምሕረትና ይቅርታ ረድኤትና
በረከት ሲፈልጉ ወደዚህ ቦታ ይመጣሉ፡፡

የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንም ያለሥርዓት አትተከልም ቅዱስ ጳውሎስ


‹‹ ... የኩነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ የጽድቅ አገልግሎት በክብር
አብዝቶ ይበልጣልና ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት
በዚሁ ነገር ክብሩን አጥቷልና ያ ይሻል የነበረው በክብር ከሆነ ጸንቶ
የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ይሆናል፡፡›› ብሎ እንደተናገረው
በሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የምትተካው ቤተመቅደስ ይህን ያህል


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ሥርዓት ከነበራት በሌላ የማትተካው በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው
ቤተክርስቲያን ይልቁንም እጅጉን ትከብራለችና በሥርዓት ትተከላለች
፪ቆሮ ፫፤፯-፲፩ ማንኛውም ቤተክርስቲያን በተለያየ ቅርጽ ቢሠራም
ሦስት ክፍል አለው፡፡ ይኸውም በሰሎሞን ቤተመቅደስ አምሳል ነው፡
፡ ምክንያቱም ለብዙ ክርስትና እምነት ሥርዓት መሠረቱና ምሳሌው
የብሉይ ኪዳን ሥርዓት ነውና፡፡

፩. ፬ የቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ ክፍሎች

መቅደስ

ቅድስት

ቅኔ ማህሌት

ሥዕል ፩ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችን የሚያሳይ

ቤተ ክርስቲያን ሦስት ክፍሎች አሏት፡፡ እነሱም፡- ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና


መቅደስ ይባላሉ፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሀ. ቅኔ ማኅሌት፡- ስያሜው ከግብሩ የተወረሰ ነው፡፡ ይህ ክፍል በቤተ


ክርስቲያን ከውጪ ወደ ውስጥ ስንገባ በመጀመሪያ የምናገኘው ክፍል ነው፡
፡ መዘምራን ስብሐት እግዚአብሔር ማኅሌተ እግዚአብሔር የሚዘምሩበት
ነውና፡፡ በዚሁ ክፍል በመስዕ/ሰሜን ምስራቅ/ በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት
በመንፈቀ ሌሊትና በነግህ ሰዓታት ይቆሙበታል፡፡ ኪዳን ያደርሱበታል፡፡
በጥንት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሥርዓተ ጥምቀት የሚፈፀመው በዚሁ
ክፍል ነበር፡፡በምዕራብ አቅጣጫ መዘምራን (ደባትራን ) የሚዘምሩበት፣
ቅኔ የሚቀኙበት፣ ማኅሌት ቆመው የሚያስቀድሱ ሲሆን ንፍቅ ዲያቆናት፣
አናጉንስጢስና መዘምራን በዚህ ሥፍራ ያስቀድሳሉ፡፡

በዚሁ ክፍል በሌብ/ ደቡብ ምስራቅ/ በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች


መቆሚያ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ወንድና ሴት አብረው
መቆም ስለማይችሉ በመጋረጃ ይጋረዳል፡፡ በምሥራቅ የካህናት፤ በሰሜን
የወንዶች፤ በደቡብ የሴቶች መግቢያ ይሆናል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ
ማዕዘናት አቅጣጫዎች አራት ወይም ሦስት በሮች አሉት፡፡

ለ. ቅድስት፡- ቅድስት ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ የተመረጠ፤ የተለየ


ማለት ነው፡፡ ይህ ክፍል የሚገኘው በቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ቦታ ነው
፡፡ በምዕራብ በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና
ዲያቆናት ሲሆኑ በሰሜን በኩል ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ
መነኮሳት፣ የሚቆርቡ ወንዶች ምእመናን ናቸው፡፡ በስተደቡብ በኩል
ቆመው ማስቀደስ የሚችሉት ደግሞ ንጽሕ ጠብቀው የኖሩ ደናግል
መነኮሳይያት እንዲሁም መአርገ ክህነት ያላቸው ቀሳውስትና ዲያቆናት
ምዕመናን ናቸው፡፡ በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያኑ በአራቱ ማዕዘናት
አቅጣጫ አራት በሮች አሉት፡፡ /ከወቅቱ የቤተክርስቲያን አሰራር ጋር
አገናዝቦ ማስተማር ይገባል።/
በቅዳሴ ጊዜ በስብከተ ወንጌል ሰዓት መምህራን ቆመው የሚያስተምሩበት
ክፍልም ነው፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ካህናት በድርገት ጊዜ ምዕመናንን የሚያቆርቡበት ቦታ ነው፡፡ በተክሊልና
በቁርባን ለሚጋቡ ሙሽሮች ሥርዓተ ተክሊል የሚፈጸምበት ነው፡፡ በስቅለት
ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፡፡ ካህናት ኪዳን ዘነግህ ያደርሱበታል፡፡
የማይቆርቡ ምዕመናን በዚህ ቦታ ቆመው ማስቀደስ አይችሉም፡፡

ሐ. መቅደስ፡- መቅደስ ስያሜው ከብሉይ ኪዳን ‹ቅድስተ ቅዱሳን›


አሰያየም ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በዚህ ውስጥ ኅብስቱ ወደ
አማናዊ ሥጋ መለኮት ወይኑም ወደ አማናዊ ደመ መለኮት በጸሎተ
ቅዳሴ የሚለወጥበት ሥርዓተ ቅዳሴው የሚመራበት ቅዱስ ሥጋውና
ክቡር ደሙ የሚፈተትበት ነው መንበረ ታቦቱና ሌሎችም ንዋያተ ቅድሳት
በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ክፍል ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ
ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ኤጶስቆጶሳት ያስቀድሱበታል፤ ቀሳውስትና
ዲያቆናትን ጨምሮ በዚህ ክፍል ሥጋወደሙንም ይቀበሉበታል፡፡ ወደዚህ
ክፍል ለመግባት የሚችሉት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣
ጳጳሳትና ኤጶስቆጶሳት፡ ቀሳውስትና ዲያቆናት ብቻ ናቸው፡፡

፩. ፭ የቤተክርስቲያን ውጫዊ ክፍሎች እና አገልግሎቶቹ

ሥዕል ፪፡- የቤተ ክርስቲያን ውጫዊ ክፍሎችን የሚያሳይ


፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሀ. ቤቴልሔም፡- ቤተልሔም ማለት የእንጀራ ቤት ማለት ነው፡፡


ቤተልሔም ከቤተ መቅደስ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚሠራ ቤት ነው፡
፡ ምሳሌነቱም ጌታችን መድኃ ኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት
ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ ቦታ መግባት የሚችሉት ዲያቆናትና ከዲቁና በላይ
ማዕረገ ክህነት ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ ቤት ለቅዳሴ የሚቀርበው
ኅብስትና ወይኑ ይዘጋጅበታል፡፡ ካህናትና ዲያቆናት ቅዳሴ በሚጀምሩበት
ጊዜ ኅብስቱን በመሶበ ወርቅ ወይኑን በጽዋ ከቤተልሔም ወደ ቤተ
መቅደስ ይዘው ይመጣሉ፡፡ ምሳሌነቱም ጌታችን በቤተልሔም ተወልዶ
በቀራኒዮ የመሰዋቱ ምሳሌ ነው፡፡ ሉቃ ፪ ፡፮-፲፪፤ ማቴ ፳፯፡፵፭-፶

ለ. ግብር ቤት ለመስዋእት የተመረጠ ስንዴ የሚሰየምበት ሲሆን ካህናት


ወይም መነኮሳይያት (ዲያቆናዊት) መስዋእቱን ይሰይማሉ።

ሐ. እቃ ቤት ንዋያተ ቅድሳት ማስቀመጫ ቤት ነው። ለቤተ መቅደስ


አገልግሎት የሚውሉ ንዋያተ ቅድሳት በክብር ሊቀመጡ ይገባል። ለሌላ
አገልግሎት ማዋል ቅጣትን ያመጣል። ትን ዳን ምዕ ፭፣ ፩-ፍጻሜ ፣ዘጸ
፴.፱

መ. ቤተ ምርፋቅ (ደጀ ሰላም)፡- ምርፋቅ ማለት ‹ረፈቀ› ከሚለው የግእዝ


ቃል የተገኘ ሲሆን የምግብ ቦታ ወይም ዳስ ማለት ነው፡፡ ይህ ቦታ ከቤተ
መቅደስ በስተ ምዕራብ ይሠራል፡፡ ምዕመናን ለካህናት የሚሆነውም
ምግበ ሥጋ ይዘው ሲመጡ የሚያስቀምጡበትና የሚመግቡበት ቦታ
ነው፡፡ እንዲሁም አገልጋዮች ከሌላ ሩቅ ደብር ሲመጡ የሚያርፉበት
ነው፡፡ የገነት ምሳሌ ነው፡፡

ሠ. ክርስትና ቤት፦ በ፵ና በ፹ ቀን ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና


ለመቀበል የሚመጡ ሕጻናት ከሌላ እምነት የተመለሱ ኢአማንያን
አምነው የሚጠመቁበት ነው።
ከላይ የተዘረዘሩት ቤቶች ቤተክርስቲያን ሲስራ አብረው መሰራት

፲፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ያለባቸው ናቸው።
በቤተክርስቲያን የሚሰሩ ማናቸውም ነገሮች ምሳሌነት ያላቸው
ቢመለከቷቸው በራሳቸው ቃለ እግዚአብሔርን የሚያስተምሩ ናቸው።
ጥቂቶቹም

ሀ. ቅፅሩ ወይም የግቢው አጥር (ከለላ)፡- የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ


ነው፡፡ ቅፅር ለቤተ መቅደስ ቤዛ፣አምባ፣ ከለላ ሆኖ እንዲጠብቅ በቤተ-
መቅደስ ለተመሠለ የሰው አካል ቤዛ አምባ ሆኖ ከጸበ አጋንንት የሚጠብቅ
ረድኤተ እግዚአብሔር ነውና፡፡

ለ. አጸድ (ዕጽዋት)፡- በቤተ መቅደስ ባለው ቅፅር ዙሪያ በብዛት ተተክለው


የሚገኙ እፅዋት አሉ፡፡ እነዚህ እፅዋት የሰውን ልጅ ከጥፋት የሚጠብቁ
አዕላፋት ወትልፊተ አእላፍ የሆኑ መላእክት ምሳሌ ናቸው፡፡ እፅዋት
በብዛት እንደሚታዩ ቅዱሳን መላእክትም በብዛት ሆነው ሰውንም
ሕንጻ ቤተክርስቲያኑንም ይጠብቃሉ፡፡ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ
ዘንድ መላእክቱን ስላንተ ያዝዛቸዋል፡፡ እግርህ በድንጋይ እንዳይሰናከል
በእጆቻቸው ያነሱሃል፡፡›› መዝ ፺፤፲፩

ሐ. ደወል (መጥቅዕ)፡- ደወል ለመንፈሳዊ አገልግሎት መዋል የጀመረው


በኖኅ ዘመን ነው።ደወል ካህናት ለአገልግሎት እንዲመጡ ለመጥሪያነት
ያገለግላል፡፡ ደወል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ራሱን የቻለ ሕንጻ ተሠርቶለት
የሚገኝ ሲሆን ይህም ደወል ቤት ይባላል፡፡ የደወል አገልግሎት ካህናትና
ምዕመናን ለአገልግሎት ይጠሩበታል፤ ቤተክርስቲያን አደጋ በሚደርስባት
ጊዜ ምዕመናን ትሰበስብበታለች፤ በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜም ቅዳሴ መጀመሩን
ለማሳወቅ፣ ጻኡ ንዑሰ ክርስቲያን በሚባልበት ጊዜ፣ በእግዚኦታ እና
ድርገት ሲወርዱ ይደወላል። በሰዓታት ፣በማኅሌት፣ በንግሥና ለሌሎች
የተለያዩ አገልግሎቶችም ይውላል፡፡ ምሳሌነቱም የመጥምቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ ስብከት ነው።

፲፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

እንደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅምና ስፋት ሰንበቴ ቤቶች፤ የሰንበት ትምህርት


ቤት አዳራሾች፤ የአስተዳደር ቢሮዎች፤ የአብነት ትምህርት ቤቶች
ይኖራሉ፡፡

ሥዕል ፫፡- በቤተ ክርስቲያን ነጭ ልብስ የለበሱ ሕጻናትን የሚያሳይ

ጥያቄ
ለተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትመጡ ምን ምን ታደረጋላችሀ?
(እባክዎ መምህር መልሶቻቸውን ይቀበሉ)

፩. ፮ በቤተ ክርስቲያን ማድረግ ስለ ሚገባን እና ስለ ማይገባን

፩. ፮.፩ በቤተ ክርስቲያን ማድረግ ስለ ማይገባን


ቤተ ክርስቲያን;- ቅዱስ አምልኮ የሚከናወንበት ቅድስት ቤት ናት፡፡
እግዚአብሔር ልጆቹን የሚጎበኝባት ሥፍራ ናት፡፡ እግዚአብሔር ወደ
ቤቱ በደስታ የሚመጡትን በበረከት ይጎበኛቸዋል፡፡ ልጆች ወደ ቤተ
ክርስsቲያን እንሂድ ሲሉን በደስታ መምጣት አለብን፡፡ ቅዱስ ዳዊት
በመዝሙሩ ‹‹ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ››
መዝ ፻፳፩፡፩

፲፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊት በመሆኗ መንፈሳዊ ሥርዓት አላት፡፡
ሥርዓተ አምልኮዋ በጸጥታ ስለሚከናወን የሥጋዊውን ዓለም ወሬና
ጫጫታ አታስተናግድም፡፡ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት ስለሆነች
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ ታከናውናለች፡፡ እግዚአብሔር የሥርዓት
አምላክ ነው፡፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ
በሥርዓት እንዲከናወኑ፤ አማኞችም በሥርዓትና በአግባብ እንዲመላለሱ
ይፈልጋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዓት
ይሁን›› ፩ቆሮ ፲፬፡፵ እናዳለ፡፡ ጌታችን ኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ቤተ
መቅደስ በመሄደ፤ በዚያም ሰዎች በሬ፣ በግ፣ ርግብ ሲሸጡ እና ገንዘብ
ሲለዋወጡ አገኛቸው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተ መቅደሱን ገበያ
ሲያይ አዘነ፡፡ ጌታችን ለምን የያዘነ ይመስላችኋል? ፈጣሪያችን ቤተ
መቅደሱን እዲያከብሩት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች
ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው፡
፡” ከቤተ መቅደሱም አውጥቶ መሸጫቸውንና ሸቀጣቸውን ጣለው፡፡
ልጆች እናንተም እግዚአብሔር እንዲያዝንባችሁ አትፈለጉም አይደል?
ስለዚህ በቤተ መቅደስ እንዴት መመላለስ አለብን ? ቤተ ክርስቲያን
የእግዚአብሔር ቤት የጸሎት ቤት ነው፡፡ ሉቃ. ፲፱ ፥ ፵፮ ልጆች ቤተ
ክርስቲያን የጸሎት ቤት ናት፡፡ ሥጋዊ ነገር ማከናወን አይፈቀድም፡፡
እግዚአብሔር በሞገስና በጥበብ በፊቱ እንዲያሳድገን የቤቱን ሥርዓት
ማክበር አለብን፡፡

በብሉይ ኪዳን በዘመነ መሳፍንት ነብዩ ሳሙኤል ከሕፃንነቱ ጀምሮ


የመቅደሱን ሥርዓት ያከብር እግዚአብሔርንም ይፈራ ነበር፡፡ አፍኒንና
ፊንሐስ ደግሞ ሥርዓተ አልበኞች፤ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር ሳሙኤልን
ለበለጠ ክብር አጨው፡፡ ሥርዓቱን ያላከበሩትን አፍኒንና ፊንሐስን ግን
በሞት ቀጣቸው፡፡ ፩ ሳሙ ፪፡፲፪
ልጆች የቤቱን ሕግ የማያከብሩትን እግዚአብሔር ይቀጣል፡፡ ስለዚህ
ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ ጫማ አድርጎ መግባት አይፈቀድም፡፡ ዘጸ ፫፡

፲፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፭፤ የሚበላና የሚጠጣ ነገር ይዞ መግባት ክልክል ነው፤ የቤተክርስቲያን


መገልገያ ንዋያተ ቅድሳትን ለግል ጥቅም ማዋልም ያስቀስፋል፡፡ ዘጸ ፴.፱
ት.ዳን ፭.፳፭፤ በቅፅረ ቤተ-ክርስቲያን ገበያ መገበያየት እግዚአብሔር
አይወደውም፣በማኀበር ጸሎት ወቅት የግል ፀሎት ማድረግ አይፈቀድም፡
፡ ማቴ ፳፩፡ ፲፫ ፤ከቤተ-መቅደስ ቅዳሴ አቋርጦ መውጣት አይገባም፡፡

፩. ፮ .፪ በቤተክርስቲያን ማድረግ ስለሚገባን


ልጆቸ የእግዚአብሔር ቤት የቅዱሱ እግዚአብሔር ቤት በመሆኑ ቅዱስ
ስለዚህ እኛም ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ፡-
የግል ንጽሕናችንን መጠበቅና ንጹሕ ልብስ መልበስ ይገባናል፡፡ ጎበዝ
ልጅ ንጽሕናውን ይጠብቃል፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ስትመጡ ንጹሕ
መሆን አለባችሁ፡፡ እግዚአብሔር ንጹሕ ስለሆነ ንጽሕናን ይወዳል፡፡
አቤል ንጹሕ መሥዋእት ስላቀረበ እግዚአብሔር ተቀብሎለታል፡፡ ዘፍ.፬
እኛም ንጽሕናችንን በሚገባ መጠበቅ አለብን፡፡

ነጠላ በመስቀል ምልክት አጣፍቶ መልበስ፡፡ በተለይም ለቅዳሴና ለቅዱስ


ቁርባን ስንመጣ፣ ነጠላችንን በመስቀል ምልክት እናደርጋለን፡፡ ይህም
ነጩን ልብስ ለብሰው ጌታቸውን የሚከተሉት የጻድቃንን መንገድ እና
እምነት ያመለክታል፡፡ ራዕ.፯፡፱ ጀምሮ ወደ ቤተ መቅደስ ስንመጣ
ማማተብ አለብን ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንገባ፣ ጸሎት ስንጀመርና
ስንፈጽም በመስቀል ምልክት ማማተብ አለብን፡፡ የመስቀል ምልክት
እንዴት እንደሚሠራና ለምን እንደምናማትብ ማወቅ አለብን፡፡

የቅዱሳን ሥዕላትን መሳለም፣ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት እና


ሰላምታ መስጠት ይገባናል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንገባ ‹በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፤ ብለን ካማተብን በኋላ፣ «
ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅደረ መለኮት አምሳለ ኢየሩሳሌም
ሰማያዊት- የመለኮት ማደሪያ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ቅድስት

፲፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ቤተ ክርስቲያን ሆይ ሰላም እልሻለሁ› እንላለን፡፡

ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባም ጫማችንን እናወልቃለን፡፡ እግዚአብሔር


ሙሴን ‹‹የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና፤ ጫማህን ከእግርህ
አውጣ ›› አለው፡፡ ሙሴም አወለቀ፡፡ ኢያሱም መልአኩ ሲገለጥለት
በተቀደሰው ስፍራ ጫማውን እንዲያወልቅ ተነግሮት ነበር፡፡ ዘጸ.፫፡፬፣
ኢያ.፭፡፭፣፡፡ እኛም ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ የተቀደሰ ስፋራ ስለሆነ
ጫማችንን ከእግራችን አውልቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንገባለን፡፡
ከዚያም መጸለይ፣ ትምህርት ማዳመጥ እና በምንሳተፍባቸው አልግሎቶች
ብቻ መሳተፍ፤ ለምሳሌ፤ በጸጥታ ቆሞ ማስቀደስ፣ መቁረብ፣ ሲዘመር
መዘመርና ማጨብጨብ፣ በቅዳሴው የምናውቀውን በዜማ መመለስ፤
ይገባል፡፡

መረጋጋትና ትኩረት መስጠት አለብን፡ አንዴ ወደ ቤተ ክርስቲያን


ከገባን በኋላ አገልግሎት እስኪፈጸም በጸጥታ ሆነን በአንድ ቦታ ልንቆም
ወይም ልንቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ካደረግን ጌታችን ይደሰትብናል
ይባርከናልም፡፡

፩.፰ የምዕራፋ ማጠቃለያ


• ሥርዓት፡- ሥርዓት ማለት ‹ሠርዐ› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል
ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መመርያ ማለት ነው፡፡ ሥርዓት
ማንኛውንም ሥራ ዘላቂ እንዲሁም ወጥ በሆነ መልኩ በሥርዓት
ለማስኬድ፤የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጽናት፤የቤተ ክርሰቲያን
ምሥጢራትን በአግባቡ ለመፈጸም፡ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት
ጥልቅና ምጡቅ የሆነውን ቤተ ክርስቲያን ትምህርት በመጠኑም ቢሆን
ለመማርና ለማስተማር ለማወቅ ሥርዓቱን ለመፈጸም ያስፈልጋል፡፡
• ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ቤት ማለት ነው፡፡ ዘይቤያዊ
ፍቺው ቤተክርስቲያን ስንል ሦስት ትርጉም አለው፡፡ ሕንጻ ቤተክርስቲያን

፲፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፤የክርስቲያኖችን ስብስብና እያንዳንዱ ክርስቲያንንም ያመለክታል፡፡


• ቤተ ክርስቲያን ውስጣዊና ውጫዊ ክፍሎች አሏት፡፡ ቤተ መቅደስ፣
ቅድስትና ቅኔ ማኅሌት ውስጣዊ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች ሲሆኑ
ቤቴልሔም ፣ ግብር ቤት ፣ እቃ ቤት ፣ ክርስትና ቤት ና ደጀሰላም
በቅጽረ ቤተክርስቲያን የሚሰሩ ቤቶች ናቸው፡፡
• ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ ውስጣዊና ውጫዊ ንጽሕናችንን
መጠበቅ፣ነጠላ ለብሶ መምጣት፣ ስንገባም ማማተብ ፣ ከገባን በኋላም
በሥርዓት ወዲያ ወዲህ ሳንል በእርጋታ ጸሎት ማድረግና የመሳሰሉት
መከወን አለብን፡፡ በተቃራኒው ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ መሯሯጥ፣
ሥጋዊ ምግብ መብላት፣ ከልብስ መራቆትና የመሳሰሉት ማድረግ
የለብንም፡፡

፩. ፱ የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ትእዛዝ አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ግን
ሐሰት በማለት መልሱ፡፡
፩. ሥርዓተ ቤተክርስቲያን መማር ለምንም አይጠቅምም፡፡
፪.ቤተክርስቲያን ስንመጣ ውስጣዊና ውጫዊ ንጽሕናችንን መጠበቅ
አለብን፡፡
፫. ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በዘይቤያዊ ትርጉም ሦስት ፍቺ አለው፡፡
፬. ምርፋቅ ከውስጠኛው የቤተክርስቲያን ክፍል አንዱ ነው፡፡
፭. ሥርዓተ ቤተክርስርስቲያንን ማወቅ ለዓለማዊ ሥራ ይጠቅማል።

ትእዛዝ ሁለት ፡-
ከተሰጡት አማራጮች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ውስጠኛው የቤተክርስቲያን ክፍል ያልሆነው የቱ
ነው፡
ሀ. ቤተ ምርፋቅ ለ. መቅደስ ሐ. ቅድስት መ. ቅኔ ማኅሌት

፲፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ከሚከተሉት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ ማድረግ ያለብን ነው
ሀ፣ ለታላላቆቻችን ክብር መስጠት ለ. በትዕምርተ መስቀል ነጠላ መልበስ
መ. ሁሉም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ የሥርዓት ትርጉም ያልሆነው የቱ ነው፤
ሀ. ቀኖና ለ. ደንብ ሐ. አሰራር መ. ሁሉም
፬. ቤተ ክርስርስቲያን የሚለው ቃል በዘይቤያዊ ፍቺው ምን ማለት
ነው፡፡
ሀ. የምዕመናን ሰውነት ለ. የክርስቲያኖች ስብስበ ሐ. ሕንጻ
ቤተክርስቲያን መ. ሁሉም
፭. ሥርዓት ለምን ያስፈልጋል
ሀ. ለማጽናት፤የቤተ ክርሰቲያን ምሥጢራትን በአግባቡ ለመፈጸም
ለ. ማንኛውንም ሥራ ዘላቂ እንዲሁም ወጥ በሆነ መልኩ በሥርዓት
ለማስኬድ
ሐ. ለመማርና ለማወቅ
መ. ሁሉም

ትእዛዝ ሦስት፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች አብራርታችሁ ጻፉ
፩. ሥርዓት ማለት ምን ማለት ነው?
፪. ሥርዓትን መማር ለምን አስፈለገ?
፫. ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ ምን ማድረግ አለብን?
፬. የህንጻ ቤተ ክርስቲያን ትርጉምና አሠራር አብራሩ?
፭.የቤተ ክርስቲያንን የውስጥ ክፍሎች ከውስጥ ወደ ውጭ በቅደም
ተከተል ጻፉ?

፲፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት
ሥርዓተ ቅዳሴ

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የሥርዓተ ቅዳሴን ምንነት ይረዳሉ


ለቅዳሴ የሚሰየሙ ካህናት ተግባራትን ያውቃሉ
ቅዳሴ በማስቀደስ የሚገኝ በረከት አውቀው በቅዳሴ ይሳተፋሉ
በቅዳሴ ወቅት ማድረግ ስለሚገባቸው እና ስለማይገባቸው አውቀው
ይተገብራሉ

የመክፈቻ ጥያቄዎች

• ተማሪዎች ቅዳሴ ታስቀድሳላችሁ አይደል? ቅዳሴ ማስቀደስ


ለምን ይጠቅማል? ስታስቀድሱ ምን ምን አደረጋችሁ? (እባክዎ
መምህር የተማሪዎችን መልስ ይቀበሉ)


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፬ ሥርዓተ ቅዳሴን የሚያሳይ

፪.፩. ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ


ቅዳሴ ማለት ቀደሰ፣ አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ
ሰጠ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን የቃሉም ትርጉም ማወደስ፣ መባረክ
፣ ማመስገን ማለት ነው፡፡ በጠቅላላ ሥርዓተ ቅዳሴ ማለት የምስጋና
መርሐ ግብር / የምስጋና ሥርዓት ማለት ነው፡፡

ቤተክርስቲያን ምስጢራት ከምትፈጽምባቸው፤ በረከቷን ከምታካፍልባቸው


አገልግሎቶች አንዱና ዋነኛው ቅዳሴ ነው፡፡ ቅዳሴ በጸሎት ለጥያቄያችን
መልስ የምናገኝበት፣ በዜማ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበትና በሥጋ
ወደሙ የምንታተምበት አገልግሎት ነው፡፡ ቅዳሴ ትምህርት፣ ጸሎት
አምልኮትና ባርኮትን ያካተተ የሥርዓተ አምልኮ ክፍል ነው፡፡ ቅዱስ
ቁርባን ለመቀበል ተዘጋጅተን ቅዳሴ ማስቀደስ አለብን፡፡ ስለ ተለያዩ ርእሰ
ጉዳዮች በጋራ የምንጸልየው፤ በነገር ሁሉ የረዳንን እግዚአብሔር በዜማ
የምናመሰግነው በቅዳሴ ነው፡፡
፳፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስራ አራት ቅዳሴያት
አሏት፡፡ እነሱም፡- ቅዳሴ እግዚእ፡ ቅዳሴ ማርያም፤ ቅዳሴ ሐዋርያት፣
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ፣ ቅዳሴ ባስሎስ፣ ቅዳሴ
አትናቴዎስ፣ ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት፣ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ፣ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
ካልዕ፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፣ ቅዳሴ ኤጲፋኒዮስ፣ ቅዳሴ ቄርሎስ፣
ቅዳሴ ያዕቆስ ዘስሩግ ናቸው ፡፡ እነዚህን አስራ አራቱን ቅዳሴያት በአንድ
ጊዜ በአንድ ቀን ለአገልግሎት እንጠቀማለን ማለት ሳይሆን ለዕለቱ
ከእነዚህ ቅዳሴያት በግጻዌ መሠረት በአንዱ ይቀደሳል፡፡

ሥርዓተ ቅዳሴ የሚጀምረው የዕለቱ ስዩማን/ሰሞነኛ አገልጋይ ካህናትና


ዲያቆናት ከቤተልሔም መስዋዕቱን ይዘው ሲመጡ ነው፡፡ ቅዳሴ ሦስት
ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህ የዝግጅት፣ የትምህርትና ፍሬ ቅዳሴ
ናቸው፡፡

፪.፪ ለቅዳሴ የሚሰየሙ አገልጋዮች


ቀዳስያን የሚባሉት የቅዳሴ ጸሎት በመሪነት የሚያካሄዱ የዲቁና የቅስና
ወይም የኤጲስ ቆጶስነት ሥልጣኑ ያላቸው ወንድሞችና አባቶች መሆን
አለባቸው፡፡ ቁጥራቸው ፭፣፯፣፲፪፣፳፬ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በዕለቱ ከአገልግሎታቸው አንጻር ሠራዒ ካህን፣ ንፍቅ ካህን፡ ሠራዒ
ዲያቆን፣ ንፍቅ ዲያቆንና ሰሞነኛ ተብለው ይሰየማሉ፡፡

፪.፫ ቅዳሴ በማስቀደስ የሚገኝ በረከት


ቅዳሴ ከምስጋናዎች ሁሉ የበለጠ ሰማያዊ አገልግሎት ነው፡፡ ከቅዳሴ
የበለጠ ምስጋናም ሆነ ጸሎት የለም፡፡ የምስጢራት ሁሉ ማሰሪያ ቅዱስ
ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት ታላቅ ጸሎት ነው፡፡ ቅዳሴ የጸጋዎች
ሁሉ ማግኛ የበረከት ግምጃ ቤት ነው፡፡
ቅዳሴ ከሚያሰገኛቸው በረከቶቸና ጸጋዎች ውስጥ፡-
ሀ. ከእግዚአብሔር በረከተ ሥጋ ወነፍስ እንድናገኝ ያደርገናል፡፡

፳፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ለ. ከቅዱሳን ጋር ኅብረት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡


ሐ. ምስጢራትን ለመካፈል ይጠቅማል፡፡

፪.፬. በቅዳሴ ወቅት ማድረግ ስለ ሚገባን እና ስለ ማይገባን

፪.፬.፩ በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ማድረግ ስለ ሚገባን

፩. ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ቀድሞ መገኘት


ቅዳሴ የሚጀመረው ካህናትና ዲያቆናት ወደ ቤተልሔም ሲወርዱ እና
ካህኑ ለህዝቡ የንስሐ ጸሎት ሲያደርስ ነው። ስለዚህ በቅዳሴ ጸሎቱ
የሚሳተፍም ሆነ በዕለቱ ክቡር ሥጋውንና ቅዱስ ደሙን የሚቀበል ሰው
ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት በቤተ መቅደስ መገኘት ይገበዋል፡፡

፪. ቀጥ ብሎ መቆም
በቅዳሴ ወቅት ከአገልጋዮች በስተቀር መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፡ ከአቅም
በላይ የሆነ ሕመም ከሌለ በስተቀርእና ሌሊቱን በአገልግሎት ከደከሙ
አገልጋዮች በስተቀር መቀመጥም አይፈቀድም፡፡

፫. በተፈቀደለን ቦታ መቆም
ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ሥርዓት ሠርታለች፡፡ በቅዳሴ ጊዜም ሁሉም
ሰው በተፈቀደለትና በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ቆሞ ማስቀደስ
ይገባል፡፡
፬. ባዶ እጅን አለመምጣት
« በእግዚአብሔር ፊት ራቁትህን አትቁም» እንዲል መጽሐፍ ወደ ቤተ
መቅደስ ስንመጣ አስራቱን፣ በኩራቱን፣ መባውን፣ እጣን፣ ጧፉን፣
ዘቢብን ወዘተ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚያስፈልጉ መስዋዕቶችንና
ንዋያተ ቅድሳትን ይዞ መምጣት ይገባል፡፡

፳፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
፭. በቁርባን ጊዜ ተራን ጠብቆ መቁረብ
በቤተክርስቲያን ሥርዓት ሁሉም በሥርዓት የሚፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ
ስንቆርብም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የሚቀድሙትን
በማስቀደም ተራችንን ጠብቀን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በትህትና
መቀበል ይገባናል፡፡

፮. ቅዱሳት መጻሕፍትን በማስተዋል መስማት ፦


በሥርዓተ ቅዳሴ ጸሎት የሚነበቡ መልዕክታትን፣ ምስባክን ጨምሮ
የዕለቱን ወንጌል ፣ለዕለቱ የተመረጠውን መልዕክት በአስተውሎት
መስማት ይገባል።

፪.፬.፪. በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች

፩ ቅዳሴ ከተጀመረ በኋላ መግባት እና መውጣት አይፈቀድም፡-


የቅዳሴ ጸሎት ጊዜ መላእክት እንደ ሻሽ ተነጥፈው የሚያዳምጡት
ሠማያዊ ሥርዓት ነውና ቅዳሴ ከተጀመረ በኋላ መግባትም ሆነ መውጣት
አይገባም፡፡ አቋርጦ መውጣት በምሴተ ሐሙስ ሐዋርያት መካከል ተነጥሎ
የወጣው የይሁዳ ምሳሌ ነው፡፡ በአሳማኝ ምክንያት ሥርዓተ ቅዳሴውን
አቋርጠን የምንወጣ ከሆነ ግን መጀመሪያውኑ መለየት ይገባል፡፡ (ፍት.
መን.አን ፲፪.፬፻፸፰)

፪ በቅዳሴ ወቅት የግል ጸሎትን ማድረግ አይቻልም


የቅዳሴ ጸሎት ከሁሉ የከበረ ታላቅ የማኅበር ጸሎት ነው፡፡ በዚህ ጸሎት
ቅዱስ ሥጋውንና እና ክቡር ደሙን የሚቀበሉና የማይቀበሉትም ሊሳተፉ
ይገባል፡፡ የግል ጸሎት ከቅዳሴ በፊት እና ከቅዳሴ በኋላ ባለው ጊዜ
መጸለይ ይገባል፡፡

፫. ተሰጥኦ በሥርዓት አለመመለስ


ተሰጥኦ (ቅብብል) በሥርዓተ ቅዳሴ ይ.ሕ (ይበል ሕዝብ) ተብሎ የተሰጠ

፳፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

የሕዝብ የምስጋና ድርሻ ነው፡፡ ተሰጥኦ ያላወቀ በአርምሞ ቅዳሴውን


ሊከታተል ይገባዋል፡፡ከመጠን በላይ ጮኾ መመለስ አይገባም፡፡ ይህም
የማኅበረ ጸሎትን ማወክ የሌላውን ኅሊና መረበሽ ነውና፡፡ ሌላው ደግሞ
እያወቁ አለመመለስም ተገቢ አይደለም፡፡ ›

፬. ዕትዉ በሠላም / በሰላም ግቡ ሳይባል ወደ ቤት አለመሄድ


ቅዳሴ አለቀ የሚባለው ሰርወተ ሕዝብ ሲከናወን ነው፡፡ ይህም የቅዳሴው
ሥርዓት ካለቀ በኋላ ሠራይ ዲያቆኑ ዕትው በሠላም ብሎ ሲያሰናብት
ነው፡፡ ስለዚህ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ ዕትው በሠላም ብሎ ሳያውጅ ወደ
ቤት መሄድ አይፈቀድም፡፡

፭. የግል ወሬ ማውራት ፈጽሞ ክልክል ነው፦


ቅዳሴ ከአምላካችን እግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት መገናኛ መንገዳችን
ነው።ሊባረከን ፈቅዶ በመካከላችን የተገኘ እግዚአብሔርን ቸል ብሎ
አጠገባችን የሚገኝ ሰውን እንዲሁም ምድራዊ ሃሳብን መነጋገር አይገባም።

የምዕራፉ ማጠቃለያ
• ቅዳሴ ማለት ቀደሰ፣ አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ
ሰጠ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን የቃሉም ትርጉም ማወደስ፣ መባረክ
፣ ማመስገን ማለት ነው፡፡
• ቀዳስያን የሚባሉት የቅዳሴ ጸሎት በመሪነት የሚያካሄዱ የኤጲስ
ቆጶስነት የቅስና እና የዲቁና ሥልጣኑ ያላቸው አባቶች ና ወንድሞች
መሆን አለባቸው፡፡ ቁጥራቸው ፭፣፯፣፲፪፣፳፬ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዲያቆናት
ብቻቸውን ቅዳሴ መቀደስ አይችሉም።
• ቅዳሴ ከእግዚአብሔር በረከተ ሥጋ ወነፍስ እንድናገኝ ያደርገናል፤
ከቅዱሳን ጋር ኅብረት እንዲኖረን ያደርገናል፤ ምስጢራትን ለመካፈል
ይጠቅማል፡፡
• በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ከተከለከሉ ነገሮች ውስጥ፡-ቅዳሴ ከተጀመረ

፳፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
በኋላ መግባት እና መውጣት አይፈቀድም፤ በቅዳሴ ወቅት የግል ጸሎትን
ማድረግ አይቻልም፣ ተሰጥኦ በሥርዓት አለመመለስ ይጠቀሳሉ፡፡
እንዲሁም፡- በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ማድረግ ከሚገባን ገነገሮች ውስጥ
ደግሞ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ቀድሞ መገኘት፤ ቀጥ ብሎ መቆም፣
በቅዳሴ ወቅት ከአገልጋዮች በስተቀር መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፤
በተፈቀደለን ቦታ መቆም፣ ባዶ እጅን አለመምጣት፣ በቁርባን ጊዜ ተራን
ጠብቆ መቁረብ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማስተዋል መስማት የሚሉት
ሥርዓቶች ይጠቀሳሉ፡፡

የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ትእዛዝ አንድ፡-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ውስጥ ትክክለኛውን
መልስ በመምረጥ መልሱ፡፡
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ቅዳሴ ትርጉም ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ማመስገን ለ.ማወደስ ሐ. ማክበር መ. ሁሉም
፪. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስንት ቅዳሴያት
አሏት?
ሀ. ፲፩ ለ.፲፪ ሐ. ፲፫ መ. ፲፬”
፫. ከሚከተሉት በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ከተከለከሉ ነገሮች ውስጥ
ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ተሰጥኦ መመለስ ለ. ቅዳሴ ከተጀመረ መግባት ሐ. ዕትዉ በሠላም
ሳይባል ወደ ቤት አለመሄድ መ. በቅዳሴ ወቅት የግል ጸሎትን ማድረግ
፬. ከሚከተሉት በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ማድረግ ከሚገባን ገነገሮች
ውስጥ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በቅዳሴ ቀጥ ብሎ መቆም ለ. ሥጋዊ ምግብ ቤተ መቅደስ ይዞ
አለመግባት ሐ.ባዶ እጅን አለመምጣት መ. ሁሉም
፭. በአንድ ቅዳሴ አገልግሎት በቁጥር ስንት ቀዳስያን ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡

፳፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሀ. ፭ ለ. ፯ ሐ. ፲፪ መ. ፳፬ ሠ. ሁሉም

ትእዛዝ ሁለት፡-
የሙከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ስሕተት ከሆኑ ሐሰት
በማለት መልሱ፡፡
፩. ቅዳሴ ከምስጋናዎች ሁሉ የበለጠ ሰማያዊ አገልግሎት ነው፡፡
፪. በቅዳሴ ጸሎት ወቅት የግል ጸሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
፫. ከቅዳሴ በረከተ ሥጋ ወነፍስ እናገኛለን።
፬. ቅዳሴ ሳይጀመር ቀድሞ ያልተገኘ ሰው በዕለቱ መቁረብ አይችልም።
፭. በቅዳሴ ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም አለብን።

፳፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሦስት
ሥርዓተ ቁርባን

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት ተረድተው እነሱም በሥርዓቱ ይቆርባሉ።


ከመቁረባቸው በፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይገነዘባሉ-ያደርጋሉም።
ከቆረቡ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አውቀው ይተገብራሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች
ተማሪዎች ቆርባችሁ ታውቃላችሁ አይደል? መቁረባችሁ
ምን ጥቅም አለው? ስትቆርቡ ከመቁረባችሁ በፊት ምን
ምን ታደርጋላችሁ? ስትቆርቡስ በቤተ ክርስቲያን ምን ምን
ታደርጋላችሁ? ከቆረባችሁ በኋላስ ምን ዓይነት ጥንቃቄ
ታደርጋላችሁ?

፳፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፭ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ


ለሐዋሪያት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙ ሲያቀብላቸው የሚያሳይ፡፡

የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት


ቍርባን፡ የሱርስት ቃል ሲሆን ለአምላክ የሚቀርብ ስጦታ የሚል
ቍርባን፡-
ትርጒም አለው፡፡ ጥንታውያኑ ግብጻውያን ኤውክሪስት ሲሉት “ምስጋና
ማቅረብ ” ማለት ነው ፡፡ ይኽው ቍርባን የተለያዩ ስሞች አሉት፡፡
አነርሱም፡- “የጌታ ራት” “ምስጢራዊው ራት ” “አንድ የመሆን ምስጢር
” “ክቡር ሥጋውና ቅዱስ ደሙ” ወ.ዘ.ተ…..ተብሎ ይጠራል፡፡

ቅዱሰ ቁርባን ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ቁርባን


ከሰባቱ የቤተ ክርስቲያን ምስጢራትም መካከል አንዱ ነው፡፡ ቤተ
ክርስቲያን ለአማኞቿ ምስጢራትን ትፈጽማለች፡፡ በሚታየው የምስጢራት
አፈጻጸም ሥርዓት የማይታየውን የእግዚአብሔር ጸጋ ታሰጣለች፡፡ ቅዱስ
ቁርባን በእግዚአብሔር አዳኝነት አምነው ለተጠመቁ ምእመናን የሚሰጥ

፳፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ከሚደገሙ ምስጢራት አንዱ ነው። ቅዱስ ቁርባን አምነን ከተጠመቅንበት
ከሕፃንነታችን ጊዜ ጀምሮ በዘመናችን ሁሉ የምንቀበለው አምላካዊ ስጦታ
ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርባቸው መሥዋዕቶች
ነበሩ፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግን ከእግዚአብሔር ለሰው ታላቅ ስጦታ ተሰጠ፤
ይህም ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ ቅዱስ ቁርባን የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ሰው ለኃጢአቱ
ስርየት እንስሳትን መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አያቀርብም፡፡
በሥጋ የተገለጠው አምላካችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው
ኃጢአት አንድ ጊዜ መሥዋዕት ሆኗል፤ ለዘላለምም ያድናል፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱንና


የተከተሉትን ሰዎች ሲያስተምር “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ አባቶቻችሁ
በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤ ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ
አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው፡፡ ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ
ነኝ፡፡ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡” አለ፡፡

ልጆች እስራኤል በምድረ በዳ መና ወርዶላቸው በልተዋል፤ ነገር ግን


በበረሐ ሞተው ቀርተዋል፤ የበሉት የሥጋ ምግብ ነውና፡፡ ክርስቶስ ግን
ሕያው እንጀራ ነው፤ ሕያውም ያደርጋል፡፡ እርሱን አምኖ በበረሐ መቅረት
የለም፡፡ ከእርሱ በልቶ መሞት የለም፡፡ ስለዚህ ሕያው የሚያደርገን
የሕይወት እንጀራ በቅዱስ ቁርባን ይሰጠናል፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “እውነት


እላችኋለሁ ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ
ሕይወት የላችሁም፡፡ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል
እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡ የሚበላኝ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል”
በማለት አስረግጦ ነገራቸው ዮሐ.፮፥፵፯—፶፩ ፡፡ እነርሱ ግን ፈቀቅ አሉ፤
ንግግሩ አስጨንቋቸው ነበርና፡፡ ያመኑት ደቀመዛሙርቱ “ካንተ ወደ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ” በማለት ከእርሱ


ጋር ኖሩ፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቃሉን


ለመፈጸም የጸሎተ ሐሙስ ሥርዓት ሠራ፡፡ ኅብስቱንም አንሥቶ ባረከ፤
ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” አለ፡
፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖም ባረከና ሰጣቸው፡፡ እንዲህም አለ
“ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ
የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” ማቴ. ፳፮÷፳፮፡፡ የቁርባንን ሥርዓት
የሠራው፤ ደቀመዛሙርቱንም ያስተማረው ራሱ የሥርዓቱ ባለቤት
ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን
አፍስሶ አድኖናል፡፡

ሥርዓተ ቁርባንን ከሥጋ ወደሙ ጋር በካህኑ ጸሎት በምስጢር ኅብረት


እንዲኖረው አድርጓል፡፡ ቅዱስ ሥጋውን እንድንበላ ክቡር ደሙንም
እንድንጠጣ ያዘዘን እርሱ ነው፡፡ ፩ኛ ቆሮ ፲ ÷ ፲፮ ስለዚህ ቅዱስ ቁርባንን
በደስታ ስንቀበል ለኃጢአታችን ይቅርታ እናገኛለን፡፡ የዘላለም ሕይወት
እናገኛለን፡፡ ከክርስቶስ ጋር በመንፈስ ኅብረት እናደርጋለን፡፡ ትእዛዙንም
በመፈጸማችን አምላካችን ደስ ይለዋል፡፡

፫.፩. ከመቁረባችን በፊት ምን ማድረግ አለብን?


ሥርዓተ ጥምቀት የተፈጸመላቸው ሕፃናት በዕለቱ ቅዱስ ቍርባን መቀበል
አለባቸው፡፡ ቅዱስ ቁርባን በክርስትና ዕለት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ
ተዘጋጅተን በንጽሕና የምንቀበለው ምሥጢር ነው፡፡ ስንቀበለውም
ከአምላካችን ጋር አንድ እንሆናለን፡፡ የዘላለምንም ሕይወት እናገኛለን፡፡
ከመቁረባችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች

፴፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ሀ. ሥጋዊ ንጽሕና
ማንም ሰው ወደ ቤተ መቅደስ ከመግባቱ በፊት ንጽሕናውን መጠበቅ
አለበት፡፡ የሚቀርባው ንጹሐ ባሕርይ ወደ ሆነው እግዚአብሔር
ነውና፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ንጹሕ ልብስ
መልበስ አለበት፡፡ ቅዱስ ሙሴን ‹‹ውረድና ዛሬና ነገ ራሳቸውን ያንጹ፣
ልብሳቸውንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝቡን እዘዛቸው፡፡›› ዘጸ. ፲፱፥፲ እንዳለው፡
፡ ይህም ልብሳችንን ብቻ ሳይሆን ሰውነታችንን መታጠብ እንዳለብንም
የሚያመለክትም ነው፡፡

ለ. መጾም
አንድ አማኝ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ከመቁረቡ በፊት
ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ (ፍትሕ መንፈሳዊ 13 /ረስጠብ
46) ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ እጅ
ከተያዘበት እስከ ተሰቀለበት ጊዜ ድረስ የደረሰበትን መከራ ለማዘከር ነው፡
፡ ሕጻናትም ቢሆን መጾም አለባቸው፡፡ በርግጥ ሕጻናት ለአስራ ስምንት
ሰዓት መጾም ስለማይችሉ በአቅማቸው እንደ እድሜያቸው መጠን መጾም
አለባቸው፡፡ በእድሜ በጣም ትንሽ የሆኑ ሕጻናት ቅዳሴው እስኪፈጸም
ድረስ የእናታቸውን ጡትም ቢሆን መጥባት የለባቸውም፡፡

ሐ. ንስሐ መግባት
ማንም ሰው ከመቁረቡ በፊት ንስሐ መግባት አለበት፡፡ ንስሐ ማለት
“ነስሐ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማዘን፣ መጸጸት፣
መቆጨት፣ የኃጢአት ካሳ ማለት ነው፡፡ አፈጻጸሙም ወደ ንስሐ አባት
በመሄድ የሰራውን ኃጢአት ለካህኑ በመናገር/በመናዘዝ ይከናወናል፡፡

መ. ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መገኘት

ማንም ሰው ቅዳሴ ከመገባቱ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን መገኘትና

፴፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

በሚገባው ቦታ ቆሞ ማስቀድስ አለበት፤፤ ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ


በመሀል ላይ ወይም መጨረሻ ላይ መጥቶ መቀበል አይቻልም፡፡ ኪዳን
ማደረስም ይገባዋል።

ሠ/ የአካል መደማት ካለ በዕለቱ መቁረብም ሆነ ቤተ መቅደስ ውስጥ


መግባት አይፈቀድም፡፡

ረ. በአራስነት ጊዜ
ሴቶች ወንድ ከወለዱ እስከ አርባኛው ቀንና ሴት ከወለዱ ደግሞ እስከ
ሰማንያ ቀን ድረስ ወ ደ ቤተ መቅደስ መግባት አይፈቀድም፡፡ ዘሌ፲፪፥፩-፭
ሴት “ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ አርባ ቀን ሴት ከወለደች ደግሞ
፹ ቀን ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ክልክል ነው”እንዳለው፡፡

፫∙፩ በቁርባን ጊዜ

ሀ. ሃሳብ ሰብስቦ እና በፈሪሀ እግዚአብሔር መቅረብ አለበት፡-


አለበት፡ «ቅዱስ
ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር» የሚለውን ጸሎት እየደገሙ በትህትና ሆኖ
በእግዚአብሔር ቸርነት ለዚህ ታላቅ ክብር መብቃትን እያሰቡ በፍጹም
ትህትና መሆን አለበት።
ለ. ተራን ጠብቆ መቁረብ፡- እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተቀመጠው
ቅደም ተከተል መሰረት መቁረብ አለብን፡፡ ይህም መጀመሪያ ጳጳስ፣
ቄስ፣ ዲያቆን ፣ በእለቱ ክርስትና የተነሱ ህጻናትና በመጨረሻ ታላላቆች
ይቆርባሉ፡፡
ሐ አፍን መሸፈን፡- እንደቆረቡ አፍን በነጠላ መያዝ ያስፈልጋል፡፡
መ. የቅዳሴ ጸበል መጠጣት፡- ሥጋ ወደሙን የተቀበለ ሰው እንደተቀበለ
ወዲያውኑ የቅዳሴ ጸበል መጠጣት ያስፈልጋል፡፡

፴፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
፫∙፪ ከቁርባን በኋላ

፩ አብዝቶ መብላት፣ መጠጣትማልቀስ ፤ ሩቅ መንገድ መሔድ፣


መስገድ፣ አይገባም፡፡
፪ ተላምጠው የሚተፉ ነገሮች እንደ ማስቲካ፣ የሸንኮራ አገዳ፣ የተለያዩ
ፍራፍሬና አትክልቶች መብላት አይገባም፡፡
፫ ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉር መላጨት፣ ከልብስ መራቆት አይገባም፤
በቆረብንበት እለት እጅን በአጠቃላይም ገላችንን መታጠብ አይገባም።

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ቍርባን፡- የሱርስት ቃል ሲሆን ለአምላክ የሚቀርብ ስጦታ የሚል
ትርጒም አለው፡፡ ቁርባን ሰማያዊ ማዕድ ነውና ሥርዓትና ክብር
ይገባዋል።
ቁርባን በእግዚአብሔር ቸርነት የበቃ ሰው ከመቁረብ በፊት፣ በቁርባን
ጊዜና ከቁርባን በኋላ ስለቁርባን ክብር ሲል ማድረግ ያለበት ጥንቃቄዎች
አሉ።
ከቁርባን በፊት መደረግ ካለባቸው ጥንቃቄዎች ውስጥ:- ሥጋዊ
ንጽህናን መጠበቅ፣ መጾም፣ ንስሐ መግባት፣ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት
መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
አካል መድማት ካለ በዕለቱ መቁረብም ሆነ ቤተ መቅደስ ውስጥ
መግባት አይፈቀድም፡፡
በቁርባን ጊዜ ሃሳብ ሰብስቦ እና በፈሪሃ እግዚአብሔር
መቅረብ አለብን፤ በእግዚአብሔር ቸርነት ለዚህ ታላቅ
ክብር መብቃትን እያሰቡ በፍጹም ትህትና መሆን አለብን።
ተራን ጠብቆ መቁረብ፡- እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተቀመጠው
ቅደም ተከተል መሰረት መቁረብ አለብን፡፡

አፍን መሸፈንና የቅዳሴ ጸበል መጠጣት ሥጋ ወደሙን የተቀበለ ሰው

፴፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

እንደተቀበለ ወዲያውኑ የሚያደርገው ተግባር ነው፡፡

ከቁርባን በኋላም ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካካል


ከልብስ አለመራቆት፣ አብዝቶ አለመብላት፣እጅንና በአጠቃላይ ገላን
መታጠብ አይፈቀደም።

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


ትእዛዝ አንድ፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል
ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልሱ።
፩. ቁርባን ማለት የአምላክ ሥጦታ ማለት ነው።
፪.የሚቆርብ ሰው ከቁርባን በፊት መጾም አለበት።
፫. አንድ ቆራቢ በሚቆርብበት ጊዜ ለሥጋወደሙ መስገድ አለበት።
፬, ለመቁረብ የተዘጋጀ ሰው ነጭ ነጠላ (ንጹህ ልብስ) ለብሶ መምጣት
አለበት።
፭. አንድ ለመቆረብ የተዘጋጀ ሰው ለመቁረብ ወደ ቤተ ክርስቲያን
እየመጣ እንቅፋት እግሩን መቶት ቢደማ በዕለቱ መቁረብ ይችላል።

ትእዛዝ ሁለት:- የሚከተሉትን ጥያቄዎች አብራርታችሁ ጻፉ።


፩. በተማራችሁ መሠረት ከቁርባን በፊት ማድረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ
ዘርዝራችሁ አብራሩ።
፪. በተማራችሁ መሠረት በቁርባን ጊዜ ማድረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ
ዘርዝራችሁ አብራሩ።
፫. በተማራችሁ መሠረት ከቁርባን በኋላ ማድረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ
ዘርዝራችሁ አብራሩ።

፴፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት
ሥርዓተ ገዳም፣ ስግደትና ምጽዋት

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

. ሥርዓተ ገዳም እና ገዳማትን መሳለም ተረድተው በሥርዓቱ


ይፈጽማሉ፡፡
. ክርስቲያናዊ የአለባበስ ሥርዓትን በማወቅ በሥርዓቱ ይለብሳሉ።
. ሥርዓተ ስግደትን አውቀው በሥርዓት ይሰግዳሉ።
. ስለ ምጽዋት ሥርዓት አውቀው ይመጸውታሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

ተማሪዎች ወደ ገዳም ሄዳችሁ ታውቃላችሁ? ማንን አገኛችሁ?


ምን ምን አያችሁ? ምንስ አግኝታችሁ ተመለሳችሁ?
(መምህር እባክዎ ከተማሪዎች መልሳቸውን ይቀበሉ)

፴፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፮፡- ገዳም መሳለምን የሚያሳይ

፬. ፩ ወደ ገዳም ሂዶ የመሳለም ሥርዓተ


ገዳም ማለት በቁሙ ደብር፣ የመነኮሳት ሰፈር፣ ምድረ በዳ፣ አባቶች ከሰው
ተለይተው የሚኖሩበት ቦታ ማለት ነው፡፡ ገዳማዊነት ‹‹እኔን መከተል
የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ››(ማቴ
፲፮ ፣፳፭ ) እንዳለ ጌታችን ይህንን አማናዊ ቃል መሠረት በማድረግ
ቅዱሳን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ ክርስቶስ በዕለተ አርብ ለሰዎች
ሲል የተቀበለውን መከራ እያሰቡ በማልቀስ መላ ሕይወትን ለክርስቶስ
የሚሰጥበት ሕይወት ነው፡፡

በእነዚህ መካናት የሚኖሩ ቅዱሳን አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር


ከማድረጋቸው የተነሳ ከእግዚአብሔር ለቦታዎቻቸው ቃል ኪዳን
የተገባላቸው የተቀደሱ ስለሆኑ ማንኛውም ሰው ወደ እነዚህ ገዳማት
ለመሳለም ሲሄድ ክርስቲያናዊ አለባበሱን መጠበቅ፣ የሚመገበውን

፴፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ምግብም የተመጠነና ከገዳሙ ሥርዓት ጋር የማይጋጭ፣ በዙሪያው
በስውር በጸሎት የሚኖሩ ቅዱሳንንም ላለመረበሽ በሚነጋገሩበት ጊዜ
ድምጽንም መቀነስና የመሳሰሉትን ትውፊታዊና ሥርዓታዊ ህግጋት
መጠበቅ ይገባል፡፡ ወደ ገዳም የሚሄድ ሰው ከተቻለው ጥሬ፣ ዳቦ ቆሎና
የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መሄድ ካልተቻለው ደግሞ እንጀራ ሊበላ
ይችላል፡፡

በመሆኑም ወደ ገዳም ለመሄድ የሚያስብ ሰው ሁሉ ማሰብ ያለበት ነገር


ቢኖር ወደ እነዚህ ቦታዎች የመጣው በቅዱሳን ቃል ኪዳን ተጠቅሞ
እግዚአብሔር ኃጢአቱን ይቅር እንዲለው መለመን፣ ከኃጢአት በቀር
እግዚአብሔር የልቡን መሻት እንዲሰጠው ሱባኤ የሚገባበት፣ ሥጋዊ
ድሎት ትቶ ለመንፈሳዊ ነገር ትኩረት የሚሰጥበት፣በአርምሞ፣ በተመስጦ
ከምግብና መጠጥ ተቆጦቦ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት፣ በስግደት፣
በምጽዋት የሚያሳልፍፈበት ከእግዚአብሔር የሚገናኝበት መሆኑን አምኖ
መሄድ ይኖርበታል፡፡

፬. ፪ ክርስቲያናዊ አለባበስ

ሥዕል ፯ ክርስቲያናዊ አለባበስ በቤተ ክርስቲያን የሚያሳይ

፴፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ቤተ ክርስቲያናችን ያስተማረችን ሰውነትን የሚሸፍን፤ ረጅም ቀሚስ እና


ነጠላ መልበስ ነው፡፡ ወንድ የሴትን፤ ሴት ደግሞ የወንድን ልብስ ማድረግ
ሕጉ ይከለክላል፤ (ዘዳ ፳፪፡ ፭)፡፡ “ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም
የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ
የተጠላ ነው፡፡” (ዘዳ.፳፪፡ ፭) እንደተባለ የአለባበስ ሥርዓትን ስንመለከት
ሥነምግባርን የሚገልፅ በመሆኑ ከክርስቲያናዊ አለባበስ ውጪ ከሆነ
ሰውነትን የሚያዋርድ ይሆናል፡፡

የሰው ልጅ በክብሩ በገነት ሲኖር፤ ልብሰ ብርሃንን /የፀጋ ልብሱን/


ሲገፈፍበትና ራቁቱን መሆኑን ሲያውቅ ሰውነቱን ለመሸፈን ቅጠል
ለብሷል፡፡ ሥልጣኔ ራቁት የሚያስኬድ ከሆነ የሰውን ልጅ ክብር
ይገፋል፡፡ ክርስቲያናዊ አለባበስን የሚጻረር ልብስ፤ይለብሳሉ፡፡ ይህ
ዓይነቱ አለባበስ የቤተክርስቲያንን ሥርዓትና ትምህርተ ሃይማኖትን
አለማወቅም ጭምር ነው እንደዚህ መልበስ አይገባም፡፡ እንኳን የተቀደሰ
የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሆነ የሰው ልጅ ሰውነት እንስሣት እንኳ
ሀፍረተ ሥጋቸውን ይሽፍናሉ። ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲሄዱ ቀርቶ
በዚህ ዓለም ሲኖሩ ለሥጋዊ ሥራ ባንክ፣ጤና ተቋም ና መሰል መስሪያ
ቤቶች የሚሰሩ ሁሉ ለአለባበስ ሥርዓት አላቸው።

፭. ፫ ሥርዓተ ስግደት

ሥዕል ፰ ምዕመናን ሲሰግዱ የሚያሳይ

፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ስግደት ሰው አምልኮቱንና ተገዢነቱን ለመግለጥ ራሱን ዝቅ አድርጎ
ግንባሩን መሬት በማስነካት ለፈጣሪው ተገዢነቱን የሚገልጽበት ተግባር
ነው። ስለዚህ ሥርዓተ ስግደትን ጠንቅቆ ማወቁ መቼና እንዴት የስግደት
ተግባር ማከናወን እንዳለብን ይረዳናል።

ለክርስቲያኖች ዋና መሠረታችን የእግዚአብሔር ቃል ነውና ስግደት


በመጽሐፍ ቅዱስ ምን መሆን እንዳለበት እስቲ እንመልከት፤ “……
ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ….» ማቴ ፬:፲ ።
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፣ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት
ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐንስ ፬: ፳፪-፳፬

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት የስግደት ዓይነቶች ሦስት


መሆናቸው በተለያዩ መጻሕፍት ተብራርቷል። እነርሱም ሰጊድ፣ ከመሬት
ወድቆ ግንባርን ምድርን አስነክቶ መነሣት፤ አስተብርኮ ጉልበትን ምድር
አስነክቶ መነሣት፤ አድንኖ ራስን ወደታች ዝቅ አድርጎ እጅ መንሳት
ናቸው። እንዲሁም ስግደት የአምልኮ፣ የፀጋና የአክብሮት ስግደት ተብሎ
ይለያል።

እኛም የአምልኮ ስግደትን ለእግዚአብሔር እናቀርባለን፣ የጸጋ ስግደትን


ደግሞ ለቅዱሳን የምናቀርብ ሲሆን የአክብሮት ስግደትን ደግሞ
ለታላላቆቻችንና ለሚገባቸው እናቀርባለን፡፡

ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፣ እርሱና የእስራኤል ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር


ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፣ በራሳቸውም ላይ
ትቢያ ነሰነሱ። ኢያሱ ፯: ፮። ይህንን ሕያው የሆነ የእግዚአብሔር
ቃል መሠረት በማድረግ በታቦተ ሕግ ፊት እንሰግዳለን ስለዚህ ልጆች
ከመሬት ላይ በግንባራችን ተደፍተን ለማን የት ማድረግ እንዳለብን
ጠንቅቀን እንወቅ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፭. ፬ ስለ ምጽዋት ሥርዓት

ምጽዋት የሚለው ሥርወ ቃል የግእዝ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም


ስጦታ፣ችሮታ፣ልግስና ማለት ነው፡፡ምጽዋት፡-
• ምሕረት ነው ( ፍት ነገ አንቀጽ ፲፮ : ፻፳፭ ) ማቴዎስ ወንጌል ፭ :
ትርጓሜ
• ለአምላክ የሚሰጥ ብድር ነው ( ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ
ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል፡፡ ምሳ ፲፱ :
፲፯ )፣ ( ምጽዋትን የሚመጸውት ሰው ለእግዚአብሔር በማበደሩ ነው
በእጁም የሚበቃ ገንዘብ ያለው ፈቃዱን ያደርጋል፡፡ ሲራ ፳፱ : ፩ )
• ብልሆች ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስቀምጡት አደራ ነው (
ሉቃ ፲፪ : ፴፫ )፣ ( ማቴ ፮ : ፲፱- ፳፩ )
• ሰው ለሰው ያለውን በጎ ፈቃድ የሚገልጥበት ክርስቲያናዊ የሥነ
ምግባር ዘርፍ ነው፡፡ ( ፪ኛ ቆሮ ፰ : ፪ )
• ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ መ.ምሳሌ ፳፭ : ፳፩
የምጽዋት አስፈላጊነትና ጥቅም
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን ለማግኘት
እንደምጽዋት የሚጠቅም ነገር የለም።” እንዳለ የምጽዋት ጥቅሙ በብዙ
ወገን ነው። ለአብነት የሚከተሉትን እናያለን።

፩, ምጽዋት ከኃጢአት ታነጻለች፦ ማር ይስሐቅ <<ነዳያንን ውደድ፣


እነሱን ስለወደድህ የልዑል እግዚአብሔርን ይቅርታውን ታገኛለህና”
እንዳለው ነቢዩ ዳንኤልም “የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደሆነ ምክሬ
ደስ ያሰኝህ፣ ኃጢአትህንም በጽድቅ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት
አስቀር”(ዳን ፬፥፳፯) በማለት እንደገለጸው ምጽዋት ኃጢአትን የምታስተስርይ
የእድፈ ነፍስ ሳሙና ናት።በትህትና መመጽወት በፍርድ ቀን ይቅርታን
ያስገኛል። ይህንንም ማር ይስሐቅ “ዝራዕ ምጽዋተ በትሕትና፤ ወተዓርር
፵፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ምሕረተ በጊዜ ፍዳ - ምጽዋትህን በትህትና መጽውት በፍርድ ቀን
ይቅርታን ታገኛለህ” በማለት አብራርቶታል። ሰው በቅርብ ላለው ጓደኛው
ከራራ እግዚአብሔር አምላክም ስለፍቅር ሲል እርሱን ከሠራው ኃጢአት
ይምረዋል።

፪, ምጽዋት በረከትን ታስገኛለች፦ ጠቢቡ ሰሎሞን “ለሚሰጥ ሰው በፍጻሜ


ዘመኑ እግዚአብሔር ዋጋውን ያስብለታል፤ በመከራም በተሰነካከለ
ጊዜ የሚድንበትን ረድኤት ያገኛል” እንዳለው ምጽዋት የሚሰጥ ሰው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ረድኤት በረከትን ያገኛል። ‘ስጥ ይሰጠሃል’
የሚባለውም ለዚህ ነው። “እስመ በረከት ትሄሉ ላዕለ ዘይሁብ ምጽዋት
- በረከት ምጽዋትን ከሚሰጥ ሰው ጋር ትኖራለች” እንደተባለው በረከት
በሚመጸውት ሰው ላይ እንደምድጃ እሳት ተዳፍና ትኖራለች። የተዳፈነ
እሳት እንዳይጠፋ በረከትም ከሚመጸውት ሰው አትጠፋም።

ብዙ ሰው በመመጽወቱ ምክንያት የሚደኸይ የሚጎልበት ይመስለዋል።


ምጽዋት ግን ገንዘቡን ይባርከዋል፤ ያበረክተዋል እንጂ አያሳንሰውም፤
አያጎድለውም። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ሰጥታችሁለት የተረፈውን
እግዚአብሔር ሊያበረክትላችሁ ይቻለዋል፤ ለሁሉም ታተርፋላችሁ፣
በጎነት በመሥራት ታበዙታችሁ” (፩ቆረ ፰÷፰-፱) በማለት ያስተማረው።
የሚያስተምር ሰው እውቀቱ ይበዛለታል፣ መልካም የሚያደርግ ሰውም
መልካምነት ይበዛለታል፣ የሚሰጥ ሰውም ገንዘብ ይበረክትለታል።
እኛ ያለንን ስንሰጥ እግዚአብሔር ያለንን አበርክቶ የሌለንንም ጨምሮ
ይሰጠናል።

፫, ምጽዋት ለሰማያዊ መንግሥት ታበቃለች፦ አምላካችን ኢየሱስ


ክርስቶስ በመጨረሻ ለፍርድ በመጣ ጊዜ የሚጠይቀንም የምጽዋት ጥያቄ
ነው።” የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን
መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም

፵፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ


በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤
ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ
ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥
ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ
ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ
አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ
አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ
አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ
ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት
ይላቸዋል።

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥


ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ
አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም
አልጠየቃችሁኝምና። እነርሱ ደግሞ ይመልሱና። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ
ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ
ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል። ያን ጊዜ።
እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት
ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል። እነዚያም ወደ
ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።” (ማቴ ፳፭፥
፵፮) ተብሎ ተመዝግቦልናል። ምግበ ሥጋን ብቻ ሳይሆን ምግበ ነፍስን
የተጠሙትን ቃለ እግዚአብሔር መመገብ፣ ስትየ ሥጋን ብቻ ሳይሆን
ጽዕመ ነፍስንም ማርካት... ምጽዋት ነው። ምጽዋት የሰማይ ቤትን
መሥሪያ ምድራዊ መሠረት ነው።

፵፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
፬, ጸሎታችንን ቅድመ እግዚአብሔር ያደርሳል፦ ጾምና ምጽዋት የማይለያዩ
አገልግሎቶች ናቸው። ጾም ያለ ምጽዋት ምሉዕ አይሆንም። በኢሳይያስ
ላይ አድሮ አምላካችን “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን?” (ኢሳ
፶፰፥ ፮) ብሎ እርሱ የመረጠውን ጾም ሲናገር ከዘረዘራቸው ውስጥ
“እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ” (ኢሳ ፶፰÷ ፯) በማለት የተነገረለት
አንዱ ምጽዋት ነው። ምጽዋትን አድርጎ የሚጾም ሰውም “የዚያን ጊዜ
ትጣራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፣ ትጮሃለህ እርሱም እነሆኝ
ይልሃል፤ “(ኢሳ ፶፰፥፰) በማለት ከምጽዋት ጋር የሚጾምና የሚጸልይ
ከእግዚአብሔር መልስ የሚያሰጥ እግዚአብሔርም የሚቀበለው ጾም
እንደሆነ ይናገራል።

፭, ምጽዋት መስጠት ለእግዚአብሔር መገዛት ነው:- ለስም አጠራሩ ክብር


ይግባውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ገንዘብ የሚገዛቸው
እንዳሉ ገልጦ አስተምሯል። “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም
የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ
አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት
አትችሉም።”(ሉቃ ፲፮:፲፫) ። በማለት አስተምሯል። እዚህ ላይ ጌታችን
በገንዘብ ጌታነት የሚያምኑ፣ ለገንዘብ ሲሉ የሚዋሹ፣ የሚያታልሉ፣
ሰውን ከሰው የሚያጣሉ፣ ሰውን የሚገድሉ አሉ። እነዚህ ሰዎች ገንዘብ
እስካገኙ ድረስ ማንንም ለመጉዳት አይመለሱም። ለገንዘብ ብለው
ሃይማኖታቸውንም የሚክዱ አሉ። ጌታችን ከላይ አተኩሮ የተናገረው
ለሁለቱም እንገዛለን የሚሉትን ነው። ለገንዘብ ሲሉ እየዋሹ ደግሞ
እግዚአብሔርን እናመልካለን ይላሉ፣ ለገንዘብ ሲሉ ሕንጻ እግዚአብሔርን
ክቡሩን ሰው እየገደሉ እግዚአብሔርን እናመልካለን ይላሉ፤ለእግዚአብሔር
እንገዛለን ይላሉ፤ ለገንዘብ ሲሉ የክብር መገለጫቸውን ድንግልናቸውን
እያጡ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፣ ለእርሱም እንገዛለን ይላሉ።
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ነው ለሁለት ጌቶች መገዛት
አትችሉም ያለው። እኔ ያዘዝኳችሁን ትታችሁ ለገንዘብ እየተገዛችሁ

፵፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ለእኔ ልትሆኑ አትችሉም፤ ሲለን ነው። በአንድ ጊዜ ጻድቅም ኃጥእም


መሆን አይቻልም። ብርሃንና ጨለማ በአንድ ላይ አይኖሩም።

የምጽዋት ዓይነቶች
ምጽዋት የሚለው ሲነገር ለሕሊና የሚታይን የገንዘብ የምግብ የቁሳቁስ
ስጦታ ነው፤ ነገር ግን ምጽዋት በገንዘብና በዓይነት ስጦታ ብቻ የሚወሰን
አይደለም፡፡ ምጽዋት ካለው ነገር የሌለውን ነገር መርዳት አስከሆነ
ድረስ በሚቆጠርና በሚሰፈር ብቻ አይወሰንም፡፡ ደካሞችን በጉልበት
ያልተማሩትን በዕውቀት የሙያ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በሙያ
መርዳት ምጽዋት ነው፡፡ (ሐዋ ፫: ፪-፲ ፣ (ማቴ ፳፭ : ፲፬-፴ )

የምጽዋት አፈጻጸም ሥርዓት


የምጽዋትን ምንነትና ጥቅም ተምረናል። ለማን እንደሚሰጥም ቀደም
ባለው ትምህርታችን አይተናል። የምጽዋት ምንነቱን ካወቅን፣ ጥቅሙን
ከተረዳን፣ ለማን እንደምንሰጥም ግንዛቤ ከወሰድን ቀሪው ትምህርታችን
‘እንዴት እንፈጽመው?’ የሚለው ነው።

ስለ ምጽዋት የተማርነው ትምህርትም ተምረን እንድናውቀው ብቻ ሳይሆን


ተግብረን እንድንኖረውም ጭምር ነው። ለመተግበርና ከበረከቱ ሱታፌ
ለማግኘት ደግሞ ‘እንዴት እንፈጽመው’ ብለን እንድንጠይቅ ያደርግናል።
ምክንያቱም ምጽዋት መስጠታችን ብቻ ሳይሆን ምጽዋታችንን ዋጋ
እንዲኖረው አድርገን መስጠታችንም አስፈላጊ ስለሆነ ነው። እንደ
አማኝ ምጽዋታችን ዋጋ እንዲኖረው አድርገን ካልሰጠን ስጦታችን እንደ
አንድ ዓለማዊ በጎ አድራጊ የሰብአዊ ድርጅት ለተቸገሩት መለገስ እንጂ
ሃይማኖታዊ ትሩፋት ሊያስገኝልን አይችልም። ይህም ማለት በምድር
የሰጠነው ምጽዋት ዋጋውም ምድራዊ ዋጋ የምንቀበልበት ይሆናል። ይህ
ደግሞ ጊዜያዊ ዋጋ ስለሆነ ዘለዓለማዊውን ሕይወት ለምንናፍቅ ለእኛ
አይጠቅመንም። ስለዚህ ምጽዋታችን ዘለዓለማዊ ዋጋን ያስገኝልን ዘንድ

፵፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
‘የምጽዋት አፈጻጸም’ የሚለውን መማር አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ከዚህ
ቀጥሎ የምጽዋትን አፈጻጸም እናያለን። እንዴት እንመጽውት፦

ሀ) ከውዳሴ ከንቱ በራቀና በስውር ፦ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና


ይግባውና ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ለሰዎች ትታዩ ዘንድ
ምጽዋታችሁን በሰዎች ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት
ባለው በአባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም”(ማቴ ፮÷፩) እንዳለው ምጽዋት
ስንሰጥ መስጠታችንን ሰው እንዲያውቅልንና፣ አውቆም <መጽዋቾች
ናቸው፣ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው፣ ቸርና ደግ ናቸው> ብሎ
እንዲያከብረን፤ እንዲያመሰግነን አስበን መስጠት የለብንም።ይህን
ካደረግን “ያለዚያ በሰማያት ባለው በአባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም”
እንደተባልነው የምንሰጠው ምጽዋት ምድራዊ ዋጋ እንጂ ሰማያዊ ዋጋ
አይኖረውም።

ለ) በትሕትና በንጽሕና መመጽወት፦ በእውነት ኃያልና ዘላለማዊ


የሆነ አምላክ ከሰው ምጽዋትን መውሰዱ ትሕትና ነው። ቅዱስ ዳዊት
“ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፤ ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ
“(፳፫፥፩) እንዳለው ሁሉ የእርሱ የሆነ አምላክ ነው። የምንሰጠውም
እርሱ የሰጠንን ነው። ስለዚህ “ከአንተ የተቀበልነውን ሰጠንህ”(፩ ዜና
፳፱፥፲፬) እንደተባለውከእኛ የሆነ ነገር እንደሌለ ማወቅ አለብን።

ሐ) በደስታና በልግስና መስጠት፦ “የሚሰጥ በልግስና ይስጥ”(ሮሜ


፲፪÷፰) እንደተባለው እግዚአብሔር በቸርነቱ ከሰጠን ነገር ላይ ለሌሎች
በማዘንና ስለእግዚአብሔር ብለን ስንመጸውት ያለ ኀዘን፣ያለ መከፋት
ያለ መጸጸት፣ በደስታ መስጠት አለብን።አንጋረ ፈላስፋ “እግዚአብሔር
ለአንተ እንደ ሰጠህ አንተም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ፍሡሕ በሆነ ልብ
ብሩህ በሆነ ዓይን ለጋስ በሆነ እጅ ለድሀው ስጥ መጽውት” ያለውም
ለዚህ ነው። “ አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ

፵፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፥ ልብህን አታጽና፥ በድሀው


ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ።”( ዘዳ ፲፭:፯) የተባለው በቸርነት
መስጠት እንዳለብን ያመለክታል። “ደስ ብሎት ደስ አሰኝቶ የሚሰጠውን
ሰው እግዚአብሔር ይወደዋል። እግዚአብሔር ከንቱ የሆነ ንፍገትን
ይጠላል። ንፉግ ሰው ቅር እያለው ይሰጣል። ከሰጠ በኋላም ያዝናል።”
(ሲራ ፪÷፮) በማለት ከሰጠን በኋላ ማዘን መተከዝ አግባብ እንዳልሆነ
የሚገልጽ ነው። እንዳውም የመጸወተ ሰው እግዚአብሔር ለዚህ ክብር
ለመመጽወት ያበቃውን አምላኩን ማመስገን ይገባዋል። ማር ይስሐቅ
እንዳለው “ብትመጸውትም ደስ ይበልህ አቤቱ ለአንተ ምስጋና ይገባል
ብለህ እግዚአብሔርን አመስግነው። ሰጥተህ እንድሰጥ አድርገኸኛልና
አመሰግንሃለሁ በለው። “ ይላል። ስለዚህ ስንመጸውት ሁልጊዜ በብሩህ
ገጽ ደስ እያለን መለገስ ይገባናል።

መ) ምጽዋት ለመስጠት አለመቅጠር፦ ምጽዋት ይሰጥ ዘንድ ያሰበ ሰው


ነገ ከነገ ወዲያ እሰጣለሁ እያለ መዘግየት የለበትም። “የመዳን ቀን
አሁን ነው” እንዲል መጽሐፍ ለመዳን ምክንያት የሆነውን ምጽዋት
የመስጠት ቀንም አሁን ነው። ከመስጠት ከዘገየን ለመዳንም እንዘገያለን።
በርሃብ ያሉ ሰዎችም በጉዳት ያልፋሉ። በርሃብ ይሞታሉ።ከመስጠት
በመዘግየታችንም እኛ በነፍስ ለመሞት ስንፈጥን ድሆች ደግሞ በርሃብ
ምክንያት በሥጋ ሞት ይፈጥናሉ። ስለዚሀ ለመመጽወት ጊዜ ቀጠሮ
አያስፈልግም። ሲራክ “ልመጸውት ብለህ ስታስብ ነገ ሣልስት አደርገዋለሁ
ብለህ አትዘናጋ እግዚአብሔር የምክንያትን ነገር አይቀበልምና”(ሲራ
፲፯÷፳፩) ሲል የተለያየ ምክንያት በመደርደር ምጽዋት ከመስጠት
መዘግየት እንደሌለብን አብራርቶታል። መጽሐፈ ምሳሌም “ለድሀም በጎ
መሥራትን ችላ አትበል። በእጅህ እንዳለ መጠን እርዳው እንጂ፤ ዛሬ
ሂድ ነገ እሰጥሀለሁና ተመለስ አትበለው መስጠቱ ሲቻልህ። ማግስት
የምትወልደውን አታውቅምና” (ምሳ ፫÷ ፳፯) በማለት አብራርቶታል።

፵፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ሠ) የበደሉንን ታግሶ መስጠት፦ ርኁሩኁ አምላካችን ፀሐይን ለኃጥአንም
ለጻድቃንም ያወጣል። ዝናቡንም እንዲሁ ለሁሉም ያዘንባል።
ለሚበድሉትም ህጉን ለማይጠብቁትም፣ ትእዛዙን ለማይፈጽሙትም
ለሁሉም ምግበ ሥጋን ይመግባል። ይህ የእግዚአብሔር ቸርነቱን
የሚያመለክት ነው። እኛም ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን
የበደሉንን ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን በማድረግ በመለገስ ማረጋገጥጠ
አለብን።ሰው የበደሉትን ይቅር ብሎ በሰጠ ጊዜ በልቦናው ጸጥታን
ጸጋ ክብርን ያገኛል። ላልበደሉት ከሚሰጠው ስጦታም በላይ ለበደሉት
በይቅርታ የሰጠው ስጦታ ዋጋው የበለጠ ዋጋ አለው። ስለዚህ ስንሰጥ
የበደሉንን ታግሰንና ይቅር ብለን መስጠት አለብን።

ረ) ለለመነ ሁሉ አስተካክሎ መመጽወት፦ ጠቢቡ ሰለሞን “ለተቸገረ


ሰው በጎ ነገርን ለማድረግ አትከልክል፤ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን”
(ምሳ ፫፥ ፳፯) እንዳለው ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “መጥቶ
ለለመነ ሁሉ ርኅራኄ ማድረግ፥ ደሀውን ከባለ ጸጋ፥ ባለ ጸጋውን ከደሀ፥
አረማዊን ከክርስቲያን፥ ክርስቲያኑን ከአረማዊ ሳይለዩ ለተቸገረው ሁሉ
ሁሉ መመጽወት ይገባል” በማለት ተቸግሮ ለለመነ ሁሉ መስጠት
እንዲገባ ያስረዳል። ስለዚህ ጉዳይ ማር ይስሐቅም እንዲህ ሲል
ያብራራል”በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለህ መጽውት እንጂ ይህ
ይገባዋል ይህ አይገባውም አትበል። ይህ አይሁዳዊ ነው ይህ ከሐዲ
ነው አትበል። ይህ ነፍስ ገዳይ ነው አትበል። በባሕርይ ወንድምህ ነውና
አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ። ፈረሰኛም ቢለምንህ በዚያን ጊዜ
ከነዳያን እንደ አንዱ ነውና ስጠው እንጂ አታሳፍረው። ከለመነህ አትርፈህ
ስጠው። ባለጸጋውን ለይተህ ለደሀ አትስጥ። አስተካክለህ በመስጠትህ
ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለህ። ከምጽዋት የተነሳ ስለሚገኝ ዋጋ
ባለመለያየት መስጠት ይገባል።” በማለት በዝርዝር አብራርቶታል።

፵፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምጽዋት ስንሰጥ በመልካም ንግግርና በማክበርም መሆን አለበት።


ሲራክ “ዝናም ዋዕይን እንዲያቀዘቅዘው እንዲሁ ምጽዋት ደሀውን ደስ
ያሰኘዋል። ክፉ ነገር ተናግሮ ከመስጠት በጎ ነገር ተናግሮ መንሳት
ይሻላልና። በምትሰጠው ሁሉ ክፉ ነገር አትናገር” በማለት የመልካም
ንግግር ምጽዋት ከገንዘብ ስለሚበልጥ የገንዘብ ምጽዋት ስለሰጠን
በክፉ ንግግር ነዳያንን ማቁሰል እንደማይገባን ያስረዳል። ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅም “ደሀ የዕለት ምግቡን እንጂ ሌላ አይሻምና። ስለዚህ ቢኖርህ
የምትሰጠውን ስጠው ባይኖርህ ስለምትሰድበው ፈንታ ከአለው ያድርስህ
ብለህ በፍቅር ስደደው” በማለት ይመክራል።

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ገዳም ማለት በቁሙ ምናኔ፣ ደብር፣ የመነኮሳት ሰፈር፣ ምድረ በዳ፣
አባቶች ከሰው ተለይተው የመኖሩበት ቦታ ማለት ነው፡፡

አማንያን ወደ ገዳማት ለመሳለም ሲሄዱ ክርስቲያናዊ አለባበስን መጠበቅ፣


የሚመገቡት ምግብም የተመጠነና ከገዳሙ ሥርዓት ጋር የማይጋጭ፣
በዙሪያው በስውር በጸሎት የሚኖሩ ቅዱሳንንም ላለመረበሽ በሚነጋገሩበት
ጊዜ ድምጽ መቀነስና የመሳሰሉትን ትውፊታዊና ሥርዓታዊ ህግጋት
መጠበቅ ይገባል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት ሦስት የስግደት ዓይነቶች


አሉ፡፡ እነርሱም ሰጊድ፣ ከመሬት ወድቆ ግንባርን ምድርን አስነክቶ
መነሣት፤ አስተብርኮ ፤ አድንኖ ናቸው። እንዲሁም ስግደት የአምልኮ፣
የፀጋና የአክብሮት ስግደት ተብሎ ይለያል።

ሰው ምጽዋት ሲሰጥ ከውዳሴ ከንቱ በራቀና በስውር፣በትሕትና በንጽሕና


፣በደስታና በልግስና፣ ለመስጠትም አለመቅጠር፦ወዘተ ይገባል፡፡

፵፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


ትእዛዝ አንድ፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆኑትን እውነት
ትክክል ያልሆኑትን ሐሰት በማለት መልሱ፡፡
፩. ሁሉም ሰው ወደ ገዳማት የሚሄደው ለቱሪስትነት ነው፡፡
፪. ክርስቲያናዊ አለባበስ ማለት ሴቶች በጣም አጭር ቀሚስ ወንዶችም
የተጣበቀ ሱሪ መልበስ ማለት ነው፡፡
፫. ምጽዋት ለለመነ ሁሉ የሚሰጥ ልግስና ነው፡፡
፬. ወደ ገዳም የሚሄድ ሰው አልኮል መጠጦችን መጠቀም ይችላል፡፡
፭. ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ስግደት የአምልኮ ስግደት ይባላል፡፡
ትእዛዝ ሁለት፡- የሚከተሉትን ጣያቄዎች አብራሩ
፩. ወደ ገዳማት መሄድ ምን ጥቅም አለው?
፪. ክስቲያናዊ አለባበስ ማለት ምን ማለት ነው?
፫. የስግደት ዓይነቶቸን ዘርዝራች አብራሩ?
፬. የምጽዋትን አስፈላጊነት ጻፉ?
፭. የምጽዋትን የአፈጻጸም ሥርዓት ዘርዝራችሁ አብራሩ ?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፶፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አምስት
ጸሎትና መዝሙር

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

. የመዝሙርና የጸሎት ሥርዓት ምን እንደሆነ አውቀው በሥርዓቱ


ይዘምራሉ፣ በሥርዓቱም ይጸልያሉ።
. መዝሙር እንዴት መዘመር እንዳለባቸው ይገነዘባሉ።
. የጸሎት ሥርዓቱንና የጸሎት ጊዜያትን ተረድተው ይጸልያሉ።

የመክፈቻ ጥያቄዎች

ተማሪዎች እንዴት ትዘምራላችሁ? ምንምንስ መዝሙሮችን


ታውቃላችሁ?
ጸሎትስ ታደርጋላችሁ? መቼ መቼ ? ለምን?

፶፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፱ ቅዱስ ዳዊት ለእግዚአብሔር ሲዘምር የሚያሳይ

፭. የመዝሙርና የጸሎት ሥርዓት

፭.፩. የጸሎት ሥርዓት፡-


ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው ሲሆን “ጸለየ” ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን
ጸሎት ማለት “ልመና” ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው ፣በአባታችን ሆይ
ጸሎታችን ስምህ ይቀደስ ስንል ምስጋና ነው፡፡ የዕለት ምግባችንን ዛሬ
ስጠን ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት ሰው ከልዑል
እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬ /

፭.፩.፩. ጸሎትን እንዴት መጸለይ ይገባል?

ሀ. በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል


በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡
እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡
፡ “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. ፳፩
፶፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
: ፳፪ እንደተባለ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብም በመልእክቱ ‹‹ ከእናንተ ማንም
ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን
ይለምን፣ ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፣
የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕር ማዕበል ይመስላል፡
፡ ሁሉት ሐሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ
ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው›› እንዳለው፡፡ያዕ ፩ : ፭-፰

ለ.ሀሳባችንን ሰብስበን አንድ ልብ በመሆን መጸለይ ይገባል


ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የጰራቅሊጦስ ዕለት አንድ ልብ ሆነው
ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ /የሐ. ሥራ ፪: ፩-፬ እኛም
ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያትን አብነት በማድረግ በአንድ ልብ ልንጸልይ
ይገባል፡፡

ሐ.በመፍራት ማለት ከልብ መጸለይ ይገባል


ነቢዩ ሕዝቅያስ በመፍራትና ከልብ በመጸጸት ሆኖ ስለጸለየ በዕድሜው
ላይ አሥራ አምስት ዓመት ተጨምሮለታል፡፡ /፪ኛ ነገሥት ፳: ፩ - ፮
/ኢሳ. ፴፰: ፩-፭ / /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬ ስለዚህ የሚጸልይ ሰው
በማን ፊት እንደቆመ በማሰብ በፍርሐትና በተመስጦ ከልብ በመሆን
መጸለይ ያስፈልጋል፡፡

መ. በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም
በጸሎት ጊዜ ቀጥ ብሎ መቆም እንደሚያስፈልግ ሥርዓት ተሠርቷል
“በጽባሕ እቀውም ቅድሜከ ወአስተርኢ ለከ” /በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ
እታይሀለሁም/ /መዝ.፭ : ፫ እንደተባለ፡፡

ሠ. ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ይገባል


ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ
ይገለጥ ዘንድ የተነገረለት ነውና ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ
ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬
፶፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ረ. በጸሎት ጊዜ መስገድ ይገባል


ይኸውም ጸሎቱን ስንጀምርና ስንጨርስ እንዲሁም በጸሎት ጊዜ ስግደትን
ከሚያነሳ አንቀጽ ስንደርስ መስገድ ይገባል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬

ሰ. በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ይገባል


ስናማትብም ከላይ ወደታች ከግራ ወደ ቀኝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ በማለት እንጀምራለን፡፡
በመስቀል አምሳል የምናማትብባቸው ጊዜያትም ጸሎት ሲጀመር፣ሲጨረስና
መስቀሉን ከሚያነሳ አንቀጽ ሲደረስ ይሆናል፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ
፲፬/

ሸ. ዐይኖቻችንን ወደላይ አቅንቶ መጸለይ ይገባል


“በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ “እንዲል ሰማይ ዙፋኔ ነው ያለን አምላክ
ጸሎታችንን በዘላለማዊ ዙፋኑ ለሚመለክ እግዚአብሔር የምናቀርበው
ልመና ጸሎት ነውና አይናችንን ወደ ላይ አቅንተን መጸለይ አለብን፡፡

ቀ. ለሌሎችም መጸለይ ይገባል


ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንና ለሌሎች ሰዎችም መጸለይ ይገባል፡
፡ ኤርምያስ ለሀገር ሰላም መጸለይ እንደሚገባ ‹‹በእርስዋ ሰላም ሰላም
ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ
ስለእርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ›› /ት.ኤር. ፳፱ : ፯ /፡፡ እንዳለ
እኛም ታመው በየሆስፒታሉ፣ በየቤቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን፣ በየማረሚያ
ቤቱ ላሉ በአጠቃላይ በተለያየ ችግር ለሚንገላቱ ሁሉ መጸለይ ይገባል፡
፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአገር መጸለይ ይገባል፡፡ “ትድኑም ዘንድ
እያንዳንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ” /ያዕ. ፭: ፲፮ /

፶፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

፭.፩.፪. የጸሎት ጊዜያት

ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት
ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ ፻፲፰ :፻፷፬ ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ
ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡
ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ. በ፲ቱ ወ ፪ቱ /በነግህ ሰዓት
ለ. በ፫ቱ (ሦስት) ሰዓት
ሐ. በ፮ቱ (ቀን ስድስት) ሰዓት
መ. በ፱ቱ (ዘጠኝ) ሰዓት
ሠ. በ፲ቱ ወ ፩ዱ (አስራ አንድ) ሰዓት /በሠርክ/
ረ. በ፫ቱ (ሦስት) ንዋም /በመኝታ ጊዜ
ሰ. በ፮ቱ (ሌሊት ስድስት ) በመንፈቀ ሌሊት

ሀ. ጸሎተ ነግህ (ጠዋት)


. ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ ፷፪
: ፲፩ እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው
የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት
እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡
. ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ
በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።
. የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን
እያሰብን እንጸልያለን፡፡
. ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል
በጲላጦስ አደባባይ ለፍርድ የቀረበበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን።

፶፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ለ. ጸሎተ ሠለስት (፫ቱ ሰዓት)


ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት)
ጸሎት ይባላል፡፡ ይህ የጸሎት ጊዜ
. ሔዋን የተፈጠረችበት
., እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት
የሰማችበት
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ
አደባባይ የቆመበትና ፮፻፷፮ ግርፋት የተቀበለበት፡፡

ሐ. ቀትር (፮ቱ ሰዓት)


በዕለቱ እኩሌታ ላይ የምናገኘው ይህ ሰዓትም እንደዚሁ የጸሎት ጊዜ
ነው፡፡
ይህም ጊዜ
. ሰይጣን አዳምን ያሳተበት
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀለበ፡
. የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም
የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው።

መ. ተሰዓተ ሰዓት (፱ቱ ሰዓት)


ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። በዚህ ጊዜ
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት
በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።
. ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱሰ ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ
በ፱ ሰዓት እንደሄዱበ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ሐዋ ፫: ፭

ሠ. ጸሎተ ሰርክ (በ፲ቱ ወ ፩ዱ ሰዓት)


. የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡”ጸሎቴን እንደ ዕጣን
በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን”
(መዝ ፻፵ : ፪

፶፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ
ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ቅዱስ ሥጋውን በአዲስ
መቃብር ያኖሩበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ. ፳፯ : ፶፯

ረ. ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)


. ይህ ጊዜ ቀኑን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ለዕረፍት የምንዘጋጅበት
ነው፡፡በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም አሳድረን ብለን ራሳችንን በእምነት
የምናስረክብበት ነው፡፡ እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን
የማያንቀላፋ ትጉኅ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል።
. ይህ ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን
በጌቴሴማኒ ጸሎት ያስተማረበት ሰዓት ነው፡፡

ሰ. መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)


እኩለ ሌሊትም እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት
። ቅዱሰ ዳዊት “መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ
ጽድቅከ” “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”
/መዝ ፻፲፰ :፷፪ በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት
እንደሆነ ገልጿል፡፡
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት
ሰዓት ነው።
. ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው።

፭.፩.፫. ጸሎት አይነቶች

ሀ. የግል ጸሎት
የግል ጸሎት ማንኛውም ሰው ለብቻው የሚያደርገው ጸሎት ነው፡፡ ይህም
በቤት፣ በት/ቤት፣ በቤተክርስቲያን እና በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብቻችን
ማድረግ ያለብን የጸሎት ዓይነት ነው፡፡

፶፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ለ. የቤተሰብ ጸሎት
ይህ የጸሎት አይነት የቤተሰቡ አባለት በጋራ ሆነው የሚያደርሱት ነው፡
፡ በዚህም ጸሎት ቤተሰባችንን እንዲጠብቅልን፣ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት
እንዲኖረን በቤታችን በኑሯችን እንዲሁም በልባችን ገብተህ ፍቅራችንን
ባርክልን እያልን ስለቤተሰባችን መንፈሳዊና ሥጋዊ ህይወት መሳካት
እንለምንበታለን ፡፡

ሐ. የማህበር ጸሎት
በማህበር የሚደረግ ነው፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ሆናችሁ በስሜ ብትሰበሰቡ
በመካከላችሁ እገኛለሁ በማለት የተሰጠንን ተስፋ ለመቀበል የምናደርገው
ጸሎት ነው::ማቴ ፲፰ : ለምሳሌ በሰንበት ትምህርት ቤት የምናደርገው ፤በ
ጸሎተ ቅዳሴ በሰርክ ጉባኤያት ብዙ ቦታዎች የሚደረግ ክርስቲያኖች
በኅብረት ሆነን የምንጸልየው በጣም አስፈላጊ ጸሎት ነው፡፡
ስለዚህ ዘወትር ለጸሎት መትጋት ይኖርብናል። ጸሎት ያልጸለየ ሰው
በባዶ ደብተር እንደማጥናት ቁጠሩት፣ ምንም አያገኝም ከእግዚአብሔር
ጋርም አይገናኝም ማለት ነው፡፡

ምግብ ስንመገብ ስለምጸልየው

ምግብ ከመመገባቸው በፊት ሲጸልዩ የሚያሳይ ምስል ቢደረግ

ምግብ ሲበላ ሁሉም ሰው መጸለይ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ የምንጸልየው


በቀን ሰባት ጊዜ ብቻ አይደለም እንደውም ከዛ በላይ ነው ማለት ነው።
ምግብ ሲበላ ደግሞ እራሱን የቻለ ጸሎት አለው፤ ምግብ ሲበሉ መጸለይ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን ጸሎት ነው፡፡

ምግብ ከመብላታችን በፊት የምንበላበትን እጅ እና ቁሳቁስ ማጽዳት


ይኖርብናል፡፡ ንጹህ ከሆነ በኋላ ለምግብ ተቀምጠን መጸለይ አለብን።
በመጀመሪያ በማማተብ እንጀምራለን፣ ከዚያም አማትበን እንደጨረስን
፶፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል
ለእኛ የምንመገብውን የሰጠንን ቸር አምላክ አመስግነን ላጡት
እንዲሰጥልን ለምነን አባታችን ሆይ ብለን እንጸልያለን፡፡ የአባታችን ሆይ
ጸሎት፡- ጌታችን ያስተማረን ማንም ቢሆን ሲቆምና ሲቀመጥ፣ ሲተኛና
ሲነሣ ፤ ሲበላም ሊጸልይ የሚችለው አጭር የኅሊና ጸሎት ነው፡፡

፭.፪ የመዝሙር ሥርዓት


መዝሙር የሚለው ቃል ‹‹ዘመረ›› አመሰገነ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ
ሲሆን ትርጓሜው ምስጋና ማለት ነው፡፡ መዝሙር በቤተ-ክርስቲያን
የዝማሬ ሥርዓት መሠረት በዜማ የሚቀርብ ምስጋና ነው፡፡ ምስጋና
የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ዓለማትን ከመፍጠሩ አስቀድሞ
ምስጋናው አልተጓደለበትም በባህርይው ይመስገን ነበር፡፡ ክብሩ በባሕርዩ
ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ስሙን እንዲቀድሱና ክብሩን እንዲወርሱ
መላዕክትና ሰውን አስተዋዮች(ለባውያን) እና አዋቂዎች(ነባብያን) አድርጎ
ፈጠራቸው፡፡

መዝሙር ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ በመሆኑ ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል


አለው፡፡ መዝሙር ሕሙማንን የመፈወስ የተጨነቁ ሰዎችን የማረጋጋት
ኃይል አለው፡፡ የእስራኤል ንጉስ የነበረው ሳኦል በታመመ ጊዜ ልበ
አምላክ ዳዊት ወደ እርሱ ዘንድ እየሔደ በገና እየደረደረ ሲዘምርለት
ሳኦል ከደዌው ይፈወስ ከጭንቀቱም ይረጋጋ እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ
ተጽፏል፡፡ 1፩ኛ.ሳሙ ፲፮ : ፳፩ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ በፊልጲስዮስ
ወኀኒ ቤቱ መሠረቱ እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ መንቀጥቀጥ አስከትሎ
የወኀኒ ቤቱን ደጆች አስከፍቷል ያንንም ታላቅ እሥራት አስፈትቷል፡፡
የሐዋ ሥራ ፲፮ : ፲፱- ፳፮

ሰዎች በገናንና መሰንቆን ለዝማሬ እንደሚቃኙ መንፈስ ቅዱስም


ዘማሪያንን ይቃኛል፡፡ ለሰዎች ዝማሬን ማስተማር የማይችሉ ለራሳቸው
ብቻ የሚዘምሩ ልዩ ሀብተ መዝሙር የተሰጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ መዝሙር


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

አስደሳች የድምጽ ቅላፄ የሚደመጥበት ጉባኤ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን


የምናመሰግንበት የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡

መዝምሩ ፈጣሪያችንን፥ ቅድስት ድንግል ማሪያምን እንዲሁም


ቅዱሳኑን የምናመሰግንበት በመሆኑ በሥርዓት ልናቀርበው ይገባ፤
ስንጀምርም በጸሎት ሊሆን ይገባዋል። በህብረትም ለአገልግሎት ዝማሬን
ስናቀርብ የድምጽ አወጣጣችን፥ የሽብሸባችን፥ እንቅስቃሴያችን ሥርዓተ
ቤተክርስቲያንን የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።

የምዕራፉ ማጠቃለያ
. ጸሎት ቃሉ ጸለየ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት ማለት
ልመና ፤ ምስጋናም ማለት ነው ።
. ጸሎት ስንጸልይ በፍጹም እምነት መጸለይ፤ ሀሳባችንን ሰብስበን በአንድ
ልብ በመሆን መጸለይ፤ከልብ መጸለይ ፤ በጸሎትም ጊዜ ቀጥ ብሎ
መቆም፤ ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መጸለይ ፤ መስገድ ፤ ጸሎት
ስንጀምር በትእምርተ መስቀል /በመስቀል ምልክት/ ማማተብ ፤ዐይኖችን
ወደላይ አቅንቶ መጸለይና ለሌሎችም መጸለይ ይገባል።
. ሰባት የጸሎት ጊዜያት አሉ። እነሱም:- ጸሎተ ነግህ፣ የቀን ሦስት ሰዓት
ጸሎት፣ የቀትር ጸሎት(ከቀኑ ፮ ሰዓት) ጸሎት፤ የሰርክ ጸሎት(ምሽት
፲ቱ ወ፩ዱ ሰዓት)፤ የምሽት ሦስት ሰዓት ጸሎተ ንዋም እና የመንፈቀ
ሌሊት ጸሎት ናቸው።
. ሦስት የጸሎት ዓይነቶች አሉ። እነሱም የግል ጸሎት፤ የቤተሰብ
ጸሎትና የማህበር ጸሎት ናቸው።
. ምግብ በምንመገበብት ጊዜ ጸሎት እናደርጋለን።
. መዝሙር የሚለው ቃል ‹‹ዘመረ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ
ሲሆን ትርጓሜው ምስጋና ማለት ነው፡፡

፷፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


ትእዛዝ አንድ :-
በ ‘’ሀ’’ የተዘረዘሩትን ቃላት በ’’ለ’’ ከተዘረዘሩ ትክክለኛ ሐሳቦች ጋር
አዛምዱ።
ሀ ለ
፩. ጸሎተ ነግህ ሀ. ምሽት ሦስት ሰዓት ጸሎት
፪. ጸሎተ ቀትር ለ. ሰማያዊ ምግብ
፫. የጸሎት ዓይነት ሐ. የጠዋት ፲፪ ሰዓት ጸሎት
፬. መዝሙር መ. የግል ጸሎት
፭. ጸሎተ ንዋም ሠ. የቀን ስድስት ሰዓት ጸሎት

ትእዛዝ ሁለት:-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ “እውነት” ትክክል ካልሆኑ
“ሐሰት” በማለት መልሱ።
፩. የጸሎት ጊዜያት አምስት ብቻ ናቸው።
፪, ቅዳሴ ከማኅበር የጸሎት ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው።
፫. መዝሙር ለመዘመር የአዘማመር ሥርዓት አለው።

ትእዛዝ ሦስት:-
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተማራችሁት መሠረት አብራርታችሁ ጻፉ።
፩. የጸሎት ጊዜያትን ዘርዝራችሁ አብራሩ ?
፪. መዝሙርና ሥርዓቱን አብራሩ ?
፫. ምግብ ስንበላ የምጸልይው እንዴት ነው ?

፷፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አራተኛ ክፍል

ዋቢ መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስ 81
ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ (1) -በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
ኆኅት ሰማይ
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን - በማኅበረ ቅዱሳን
ፍትሐ ነገስት
የቤተክርስቲያን ጸሎት መጽሐፍ
መርሐ ህይወት

፷፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት

You might also like