You are on page 1of 70

መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

መሠረተ ሃይማኖት
ነገረ ማርያም
አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት


ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ 2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ያግኙን

Email
office@eotc-gssu.org
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCZl-
WxxCvV2UzcSz1Qxh6UAg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
Twitter
https://twitter.com/tibeb_felege

Copyright ©
2015 E.C

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ብጹዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ


ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ብጹዕ አቡነ አቡነ አብርሃም


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር
ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ
ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ
መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

መክሥተ ርዕስ (ማውጫ)

ምዕራፍ አንድ ነገረ ማርያም ፩


፩.፩ የድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜና የዘር ሐረገ
ትውልድ ፪
፩.፪ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደትና
ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ፭
፩.፫ እመቤታችን በቤተ መቅደስ እና ብሥራተ ገብርኤልን
መስማቷ ፯
፩.፬ እመቤታችን ጌታን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና
መውለድ ፲
፩.፭ የእመቤታችንና የጌታ ስደት በምድረ ግብፅ እና
በኢትዮጵያ ፲፪
፩.፮ የእመቤታችን ዕረፍት ፣ ትንሣኤና ዕርገት ፲፫

ምዕራፍ ሁለት የእመቤታችን ክብር እና ቅድስና ፲፯


፪.፩ የእመቤታችን ክብር ፲፯
፪.፪ የእመቤታችን ቅድስና ፳፪
፪.፫ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና ፳፭
፪.፬ እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ፴

ምዕራፍ ሦስት የእመቤታችን አማላጅነት ፴፫


፫.፩ ምልጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ፴፫
፫.፪ ስለ አማላጅነቷ ፴፮
፫.፫ የእመቤታችን ምልጃ በቃና ዘገሊላው ሰርግ ቤት ፴፱

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ምዕራፍ አራት የእመቤታችን ምሳሌዎች በብሉይ ኪዳን ፵፭
፬.፩ የማክሰኞ እርሻ ፵፭
፬.፪ የኖኅ መርከብ ፵፮
፬.፫ የኖኅ ቀስተ ደመና ፵፯
፬.፬ ዕፀ ሳቤቅ ፵፰
፬.፭ የያዕቆብ መሰላል ፵፱
፬.፮ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና ፶
፬.፯ የጌዴዎን ፀምር ፶፪
፬.፰ የአሮን በትር ፶፪
፬.፱ ጽላተ ሙሴ ፶፬
፬.፲ የሳሙኤል የሽቱ ቀንድና የናሆም መድኃኒት ፶፮
ዋቢ መጻሕፍት ፶፯

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማና ተማሪዎች ትምህርቱን ሲያጠቃልሉ፦

፩- የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ታሪክ ይናገራሉ።


፪- ድንግል ማርያም በፈጣሪና በሰው ዘንድ ያላትን ክብርና ልዕልና
ይረዳሉ፤ ይመሰክራሉ።
፫- በብሉይ ኪዳን የእመቤታችን ምሳሌዎችን ይዘረዝራሉ።
፬ እመቤታችንን ያመሰግናሉ፤ ያከብራሉ፤ ይወዳሉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ


የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
ነገረ ማርያም

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ ፤


የእመቤታችን ሐረገ ትውልድ፤የእመቤታችን ልደት፤ ወደ ቤተ
መቅደስ ስለመግባቷ፤ በቤተ መቅደስ ስለመኖሯ እና ብሥራተ
ገብርኤልን መስማቷ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና ፀንሳ
በድንግልና መውለዷን፤ ስደቷን፤ ዕረፍትና ትንሣኤዋን ይረዳሉ።

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

፩- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትና መቼ


ተወለደች?
፪- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተመቅደስ ስንት
ዓመት ኖረች?
፫- ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ምን ብሎ አበሠራት?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፩.፩ የድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜና የዘር ሐረገ ትውልድ


የድንግል ማርያም የስሟ ትርጓሜ

ማርያም የሚለው ስም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚርያም /ማሪሃም ሲሆን


ትርጉሙም ስጦታ ማለት ነው። ይህም ለጊዜው ለእናት ለአባቷ ኋላም
ለዓለም ሁሉ በእናትነት የተሰጠች በመሆኑ ነው። ሌላም ማርያም ማለት
እመ ብዙኃን የብዙዎች እናት ማለት ነው። ይህም አብርሃም የሚለው
ስም የብዙዎች አባት ማለት እንደሆነው ያለነው። ዘፍ፲፯፥፭
ማርያም ቃሉ የሁለት ቃለት ጥምር ሲሆን ማር ማለት በምድር ካሉ
ምግቦች በጣፋጭነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ጣዕሙ ወደር የሌለው ከንቦች
የሚገኝ ምግብ ነው። ያም ደግሞ በገነት የሚገኙ ቅዱሳን የሚመገቡት
ጣፋጭ ምግብ ነው። ታዲያ እናታችን ማርያምም በምድርና በሰማይ
የተመረጠችና የተወደደች፣ ርኅራኄዋ፣ ፍቅሯ፣ ትሕትናዋ፣ ንጽሕናዋ
ተወዳዳሪ የሌለው የተለየች ናትና ማርያም ተብላለች።
በተጨማሪም ማርያም የሚለውን ስም ያስገኙትን አራት ፊደላት አባቶች
እንደሚከተለው ተርጉመዋቸዋል።

ማ- ማኅደረ መለኮት (የመለኮት መደሪያ)


ር- ርግብዬ ይቤላ (ጠቢቡ ሰሎሞን ርግብዬ ይላታል) መኃ ፮፥፱
ያ- ያንቅዐዱ ኃቤኪ ኪሉ ፍጥረት (ፍጥረት ሁሉ ለምኝልን እያሉ ወደ
አንቺ ያንጋጥጣሉ (ያያሉ)
ም- ምስዐል ወምስጋድ ወመስተሥርይ ኃጢአት (መስገጃ መለመኛ
የኃጢአትም ማስተሥርያ ማለት ነው)

የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ማርያም የሚለውን ስም ከላይ ከተጠቀሱት


ትርጓሜዎች በተጨማሪ በምሥጢራዊ ዘይቤ እንደሚከተለው ይፈቱታል።
ማርያም ማለት፦


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሀ) መርሕ ለመንግሥትተ ሰማይ ወደ መንግሥትተ ሰማያት መርታ


የምታስገባ ማለት ነው።
በአዳም ስህተት ምክንያት የተዘጋው የገነት በር የተከፈተባት የጽድቅ በር
መክፈቻ ናትና።ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን የተወለደባት ናትና ወደ
መንግሥትተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ትባላለች።

ለ) ጸጋ ወሀብት ማለት ነው።


አዳም አጥቶት የነበረውን የቀደመ ክብሩን ከእመቤታችን በተወለደው
መድኃኔዓለም ተመልሷልና እመቤታችን ጸጋና ሀብት የተገኘባት ብፅዕት
እናት ትባላለች። ሉቃ፩፥ ፳፰ ‹‹ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር
ነውና ደስ ይበልሽ›› እንዳለ ቅዱስ ገብርኤል።

ሐ) መልዕልተ ፍጡሯን መትሕተ ፈጣሪ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች


ያለች ማለት ነው።ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረን መላእክት የማይችሉትን
መለኮት እርሷ በማኅፀኗ ተሸክማዋለች፣ ጡቷን አጥብታዋለች፣ በጀርባዋ
አዝላዋለች። መላእክት ሊያዩት ሊነኩት የማይቻላቸውን እርሷ በማኅፀኗ
ይዛዋለች እና ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች እንላታለን።

መ) የብዙኃን እናት /እመቤት/ እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው።


ሔዋን የሕያዋን ሁሉ እናት ተብላ ነበርና (ዘፍ.፫፥፳) በሔዋን ስህተት
ምክንያት የሰው ልጆች ሁሉ ከተፈረደባቸው ሞት ከዲያብሎስ ባርነት
ነፃ ያወጣቸው ዘንድ አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዷልና
የብዙዎች እመቤት እናት ትባላለች።

ሠ) ተላእኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ምህረት


የምታመጣ ለሰውም ወደ እግዚአብሔር የምታማልድ ማለት ነው።
ይህም ለአምላክ ሰው የመሆን ለሰውም የመዳን ምክንያት ስለሆነች እና
እያማለደች የእግዚአብሔርን ይቅርታ ስለምታሰጥ ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የእመቤታችን የዘር ሐረገ ትውልድ


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ትውልዷ በአባቷ በኩል ከንጉሥ
ዳዊት ወገን ነው። በእናቷ በኩል ከሊቀ ካህናቱ ከአሮን ወገን ነው።
የአባቷ ስም ቅዱስ ኢያቄም የእናቷ ደግሞ ቅድስት ሐና ነው። ይህንንም
በተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ላይ በግልፅ ተጽፎ እናገኛዋለን።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትውልድ ሐረጓም
እንደሚከተለው ነው።
*ከአዳም በሴት በኩል
*ከያሬድ በሄኖክ በኩል
*ከኖኅ በሴም በኩል
*ከአብርሃም በይስሐቅ በኩል
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ በኩል
*በይሁዳ በኩል በእሴይ በዳዊት በሰሎሞን…. በሕዝቅያስ በምናሴ ….
በአልዓዛር ከዛም ከልጁ ከቅሥራ የእመቤታችንን አባት ኢያቄም ተወለደ።

ማስታወሻ
አልዓዛር ከቅሥራ ሌላ ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን
ወለደ፤ያዕቆብም ክርስቶስ ኢየሱስን የወለደች የማርያምን ጠባቂ
ዘመዷን ዮሴፍን ወልዷል።

*በሌዊ በኩል ደግሞ በአሮን በአልዓዛር በፊንሐስ... በጴጥርቃና (በጥሪቃና)


በቴክታ (ባልና ሚስት ናቸው) በሄሜን በደርዴ በቶና በሲካር በሄርሜላ፤
ሄርሜላ ማጣትን አግብታ የእመቤታችንን እናት ሐናን ወልዳለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፩.፪ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት እና ወደ


ቤተ መቅደስ መግባት

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናትና አባቷ እግዚአብሔርን
የሚወዱና የሚያከብሩ ደጋጎችና በእምነታቸው የጸኑ ነበሩ። ነገር ግን ልጅ
አልነበራቸውም። በዚህም አዝነው ይኖሩ ነበር ሁል ጊዜም እግዚአብሔር
ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር እንዲህም ሲኖሩ ስእለት ተስለው
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነሐሴ ፯ ቀን ተፀነሰች።

እመቤታችንም ገና በቅድስት ሐና ማኅፀን እያለች ብዙ ተአምራትን


ታደርግ ነበር።ከነዚህም መካከል ለመጥቀስ ያህል የቅድስት ሐና ዘመድ
የሆነች አንዲት ስሟ ቤርሴባ (ቤርሳቤህ) የተባለች ዓይነ ስውር የቅድስት
ሐናን ሆድ ነክታ ዓይኗን ብትነካው ዓይኗ በርቶላታል። እንዲሁ ደግሞ
ቅድስት ሐና ፀንሳ ሳለች የሞተ ሰው (ሬሳ) ብትነካ የሞተው ሰው ሊነሣ
ችሏል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀን እያለች ብዙ
ተአምራትን ታደርግ ስለ ነበር አይሁዳውያን በዚህ ቀንተው ቅድስት
ሐናንና ቅዱስ ኢያቄምን ተቃወሟቸው፤ሊገድሏቸው ልጃቸውንም
ሊያጠፋ ስለነበር እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ወደ
ሊባኖስ ተራራ እንዲሸሹ ነገራቸው። እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ
ላይ ግንቦት አንድ ፩ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊወለድ ፲፭ ዓመት ሲቀረው
ተወለደች። “ከሊባኖስ...ነዪ” መኃ. ፬፥፰ እርሷም ለሰው ልጆች መዳን
ምክንያት ሆና የቀረችልን ነበረች። “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን
ባያስቀርልን ኖሮ ፥እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር”
ኢሳ ፩፥፱


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፩ ፡ በዓታ ለማርያም

የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመወለዷ በፊት ቀደም ብለን
እንዳየነው እናትና አባቷ በስእለት በብፅዓት ነበር ያገኟትና ስዕለታቸውንም
“ልጅ ከሰጠኸን የቤተክርስቲያን አገልጋይ እንዲሆን እናደርጋለን”
ብለው ስለተሳሉ እመቤታችን ከተሰጠቻቸው ከሦስት ዓመት በኋላ
ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ትሆን ዘንድ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዷት።
ዕለቱም ታህሣሥ ፫ ቀን ነበር። “በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን
ከንፈሮቼም ያሉትን ስእለቴን ለአንተ እፈጽማለሁ” እንዲል መዝ ፷፭፥፲፬
ቢሆንም በቤተ መቅደስ ወስዶ ማስረከብ ከባድ ነበረ።ምክንያቱም
እመቤታችን ገና ሦስት ዓመቷ ነበርና ምን ትበላለች? ምን ትጠጣለች?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የሚለው ፈታኝ ነበር። እናም ለዚህ መልስ እንዲሆን እመቤታችን ቤተ


መቅደስ ስትገባ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ይዞ
ከሰማይ ወረደ።
በሁኔታው ተገርመው ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ (የመጥምቁ ዮሐንስ አባት)
ለኔ የመጣ ነውና ልውሰድ ብሎ ሲጠጋ መልአኩ ወደ ሰማይ ከፍ አለበት
ራቀው። እንደገና ዝቅ ብሎ ሲወርድ ሌሎቹ ካህናትና አገልጋዮች ተራ
በተራ ለኔ ይሆናል ለእኔ ይሆናል ብለው ቢጠጉም እየደጋገመ ኅብስትና
ጽዋውን ሳይሰጥ ወደ ሰማይ ከፍ እያለ ወደ ምድር ዝቅ አለባቸው።
በመጨረሻም ሕፃኗ ትቅረብ ተብሎ እመቤታችንን ወደ መልአኩ
አቀረቧት፤መልአኩም ከያዘው ኅብስትና ጽዋ አብልቷት አጠጥቷት ወደ
ሰማይ አረገ።በዚህም ሁኔታ እመቤታችን በአምላክ እንደተመረጠች እና
ምግብና መጠጧም ሰማያዊ እንደሆነ ተገልፆላቸው፤ሊቀ ካህናቱም ሕፃኗን
ከእናትና ከአባቷ ተቀብሎ በቤተ መቅደስ እንድትቀመጥ አድርጓል።

ይህም በዓታ ለማርያም በመባል በየወሩ በ፫ኛው ቀን ይከበራል። “ልጄ


ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ”
እንዲል መዝ ፵፬፥፲

፩.፫ እመቤታችን በቤተ መቅደስ ሆና ብሥራተ ገብርኤልን መስማቷ


እመቤታችን በቤተ መቅደስ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ ከገባች በኋላ
በትሕትና ትታዘዝ ነበር።ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ
ሥራዋችንም ትሠራ ነበር።
ለምሳሌ፡- የቤተክርስቲያን ወለል መሬት ላይ የሚነጠፍ ምንጣፍ፣በርና
መስኮት የሚጋረድበት መጋረጃ በመፍተል ታገለግል ነበር። ሐርና
ወርቅም አስማምታ ተፈትል ነበር። የቤተክርስቲያኑ አገልጋዮችንም
እየታዘዘች፣ ቤተ መቅደሱን በማፅዳት እና እነዚህን የመሰሉ ሥራዋች
በመሥራት በቤተመቅደስ ለ፲፪ ዓመታት ኖራለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

እመቤታችን በቤተመቅደስ ለ፲፪ ዓመታት ኖራ ዕድሜዋ ፲፭ ዓመት


ሲሆን አይሁድ ለአቅመ ሔዋን ደርሳለችና (አንዲት ሴት ዕድሜዋ ፲፭
እና ከዛ በላይ ሲሆን ለአቅመ ሔዋን ደረሰች ይባላል) ቤተ መቅደሳችንን
ታሳድፍብናለች ታረክስብናለች በማለት ከቤተ መቅደስ እንድትወጣ
ስለፈለጉ ሊቀ ካህኑ በእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱ ተቀብሎ ስላሳደጋት
የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና ምን ማድረግ እንዳለበት ለማወቅ
ሲጸልይ ሚስቶቻቸው የሞቱ አረጋውያንን በትር እንዲሰበስብ በዚያም
ላይ እንዲጸልይ እና ምልክትን ጠባቂ በሚሆናት አረጋዊ በትር ላይ
እንደሚያሳየው በመልአኩ ነገረው።
እርሱም ይህን አድርጎ የዮሴፍ በትር ላይ ምልክት ስለታየ እመቤታችንን
በአደራነት እንዲጠብቃት ሰጠው። እርሱ አረጋዊ ዮሴፍ ዘመዷ ነውና
ወደ ዘመዷ ቤትም ገባች። እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን እግዚአብሔር
እመቤታችንን እንዴት እንደጠበቃት ነው። ከእናት ከአባቷ ብትለይም
በመላእክት እየመገበ እያጫወተ እየጎበኘ የዘመዷ ባለቤት በሆነው በሊቀ
ካህኑ ጥበቃ ሥር እንዴት አሳድጎ አሁንም ለዘመዷ እንዲጠብቃት
መስጠቱን ነው።

እመቤታችን ብሥራተ ገብርኤልን መስማቷ


ብሥራት ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን የምሥራች፣ደስታ መናገር ማለት
ነው። እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላክን እንደምትወልድ ስሙን
ኢየሱስ እንደምትለው በአምላክ ሰለ መመረጧ ያበሠራት መልአክ ቅዱስ
ገብርኤል ነው። እርሱም ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ሦስት
ጊዜ ነግሯታል።
• በመጀመሪያ ውኃ ስትቀዳ
• ቀጥሎ በቤቷ (በዮሴፍ ቤት)
• በሦስተኛ ደግሞ በቤተ መቅደስ አብሥሯታል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፪ ፡ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ሲያበሥራት

ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ናዝሬት ገሊላ በምትባል ቦታ


ተገኝቶ ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ በክብር በታላቅ ደስታ
አብሥሯታል። የምሥራቹን ስትሰማም በትሕትና ተቀብላለች። ይህም
ሉቃ.፩፥፳፰ ጀምሮ ተመዝግቧል።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጋቢት ፳፱ እሑድ ቀን ከጠዋቱ
በ፫ ሰዓት ላይ ቅዱስ ገብርኤል እንዳበሠራት በተአምረ ማርያም ፳፪ኛ
ተአምር ላይ እናገኘዋለን።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፩.፬ እመቤታችን ጌታን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ


ድንግል ማለት ንጹሕ፣ ያላገባች፣ ልጅ ያልወለደች፣ ዓለማዊውን ሐሳብ
ትታ ሰማያዊውን የምታስብ ማለት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያምም በሐሳቧም በሥጋዋም ንጹሕ ድንግል ቅድስት ነች። ይህንም
መጽሐፍ ቅዱስ፡
- “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?” ሉቃ.፩፥፴፬
- “ጸጋን የሞላብሽ ሆይ” ሉቃ. ፩፥፳፰ እና
- “ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም” መኃ. ፬፥፯
በማለት ይገልጸዋል። በዚህም ንጽሕናዋ አምላክን ካለወንድ ካለ አባት
ድንግል እንደሆነች በምድር ወልዳዋለች ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ እና
የተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ።
- “ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና” መዝ. ፵፬፥፲፩
- “እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው
ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤
መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ” መዝ ፻፴፩፥፲፫-፲፬
- “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥
ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ኢሳ
፯፥፲፬
- “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም
በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም
አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” ኢሳ ፱፥፮
- “የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ
በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች” ማቴ ፩፥፲፰

የእመቤታችን ቅድስና ንፅሕና አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና


መውለዷን በሐሙስ የውዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ ቅዱስ ኤፍሬም
እንዲህ ብሏል፡-
“ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረውን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ምን ልቡና ነው? መስማት የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? መናገር የሚቻለው
ምን አንደበት ነው?” ካለ በኋላ “... ድንግልናዋም አልተለወጠም” ብሎ
የእመቤታችንን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን መናገርና መግለፅ
የማይችል መሆኑን ለእርሱ መንፈስ ቅዱስ በገለፀለትና በተረዳው መጠን
ለእኛ ገልጦልናል።

ለዚህም ነው ነቢዩ ”ምልክት ይሰጣችኋል“ ያለው አይመረመርምና።


ኢሳ ፯፥፲፬ ስለሆነም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን
ኢየሱስ ክርስቶስን በንጽሕና በድንግልና ካለ ወንድ ዘር እግዚአብሔር
ባወቀ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፀንሳ በድንግልና ወልዳለች። ከላይ እንደ
ጠቀስነው ይህን ምሥጢር መርምረን ተናግረን የምንጨርሰው ስላልሆነ
በዚህ እንፈጽማለን። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልመና
ክብሯ ቸርነቷ ከኛ ጋር ይሁን።

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ሐሰት
በማለት መልሱ።

፩- የድንግል ማርያምን የስሟን ትርጓሜ የብዙሃን እናት ማለት ነው።


፪- እመቤታችን በቤተመቅደስ ሐርና ወርቅን እያስማማች ትፈትል ነበር።
፫- እመቤታችንን ያበሰራት መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
፬- እመቤታችን በስምንት ዓመቷ ወደ ቤተመቅደስ ገባች።
፭- እመቤታችንን ቅድስት ቤተክርስቲያን ንጽህትና ቅድስት እንዲሁም
ድንግል እያለች ትጠራታለች።

፲፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፩.፭ የእመቤታችንና የጌታ ስደት በምድረ ግብጽ እና በኢትዮጵያ


ወወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው የነገሥታት ንጉሥ የክርስቶስ
ኢየሱስ መወለድ (ማቴ ፪፥፲፩) ሥልጣናቸውን በሚወዱትና (ማቴ
፪፥፲፫) የዲያቢሎስ ማደሪያ በነበሩት ሄሮድሳውያን (ራእይ፲፪፥፬) ዘንድ
ስጋትን ፈጠረ። ይህን ሥጋትም ለማስቀረት በርከት ያለ ቁጥር ያለቸው
የቤተልሔም ሕፃናት በግፍ እንዲጨፈጨፉ ምክንያት ሆነ። (ማቴ.
፪፥፲፮) ከዚህም የተነሣ በፈቃደ እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል
መሪነት እመቤታችን የሰማይና የምድርን ፈጣሪ አዝላ ከምድረ እስራኤል
ወደ ምድረ ግብፅ በረሃ ተሰደደች።
በዚያም ሦስት ዓመት ከስድስት ወርም በመከራ እና በሐዘን
ቆይታለች።በስደታቸው ወቅትም ወደ ኢትዮጵያም ገብተው የኢትዮጵያን
ምድር ባርከው ወደ ሀገራቸው እስራኤል ተመልሰዋል። በኢትዮጵያም
በአክሱም፣ በዋልድባ፣ በጣና እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ዐርፈዋል።
በዚያን ጊዜም ሃገራችንን ጌታችን የዓሥራት አገር አድርጎ ለእመቤታችን
ማርያም ሰጥቷታል። ይህንም ሰቆቃወ ድንግል የተባለ መጽሐፍ በሰፊው
ያስረዳል።

እመቤታችን ከልጇ ጋር በዮሴፍና ሰሎሜም አገልጋይነት የተሰደዱበት


ምክንያት
ሀ. ትንቢቱ ይፈጽም ዘንድ
“እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት” ሆሴ
ዕ፲፩፥፩
ለ. ክርስቶስ ደሙን ያለ ጊዜው ስለማያፈስ
“ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም
እጁን አልጫነበትም” እንዲል ዮሐ. ፯፥፴
ሐ. ስደትን ለቅዱሳን ባርኮ ለመስጠት
እርሱ ተሰድዶ ነውና “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ
ሰማያት የእነርሱ ናትና። ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም
፲፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ” ማቴ
፭፥፲-፲፩ እና “እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና” ማቴ ፳፭፥፴፭ ያለውን
ማንሣት ይቻላል።

፩.፮ የእመቤታችን ዕረፍት ትንሣኤና ዕርገት

ሥዕል ፫ ፡ የእመቤታችን ዕረፍት


የእመቤታችን ዕረፍት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደች በ፷፬ ዓመቷ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ጥር ፳፩ ቀን አርፋለች። ይህም ፫ ዓመታትን
በእናት በአባቷ ቤት፣ ፲፪ ዓመታትን በቤተ መቅደስ፣ ጌታን ፀንሳ ሳለ
፱ወር ከ ፭ ቀን፣ ከጌታ ጋር ፴፫ ዓመታት ከ፫ወራት፣ በዮሐንስ ቤት
፲፭ ዓመታትን ባጠቃላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ ነው። ሥርዓተ
ቀብሯም በጌቴ ሴማኔ ሐዋርያት ሊፈጸም ሲል አይሁድ በምቀኝነት
ተነሣስተው በፈጠሩት ሁከት ሥጋዋን ሊያቃጥል የመጣን ታውፋንያ

፲፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የተባለ እጁን ቅዱስ ገብርኤል ቆርጦ በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት


ተቀጥሎ ተአምር ታይቶ የእመቤታችን ሥጋዋ ወደ ገነት ተሠወረ።በዕፀ
ሕይወት ሥርም ከቆየ በኋላ ሐዋርያት ለሁለት ሱባኤ (ይህም ከነሐሴ
፩-፲፬ ነው) ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን
ጌታችን ሰጥቶአቸው በጌቴ ሴማኒ ቀብረዋታል።

የእመቤታችን ትንሣኤ
ነቢዩ “አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት”መዝ
፻፪፩፥፰ በማለት በተነበየውም መሠረት እውነተኛዋ ታቦት የአምላክ
ማደሪያ ማህደረ መለኮት እመቤታችን ተነሥታለች።

የእመቤታችን ዕርገት
እመቤታችን ነሐሴ አሥራ ስድስት በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማለት
ነው ተነሥታ ዐርጋለች። (እዚህ ጋር እመቤታችን በእሁድ ዕለት በ14ት
ነው የተነሣችው ያረገችው የሚሉ መምህራንም አሉ። ምክንያታቸውም
ትንሣኤ ሙታን እሑድ ቀን ስለሚሆን፣ በእሑድ መነሳቷ ነው የልጇ
ትንሣኤ ጋር የሚያመሳስለው እና የ፲፮ቱ የማክሰኞው ሐዋርያት ሁለተኛ
ሱባዔ ከገቡ በኋላ ትንሣኤዋ የተገለጠበት ቀን ነው ይላሉ) ያም ሆነ ይህ
ግን ዕርገቷን በመጀመሪያ ያየው ቅዱስ ቶማስ ሲሆን እርሱም በደመና
ተጭኖ ከሕንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ መልአክ ሲያሳርጓት አይቷል
እርሷም ባርካው የመግነዟን ሰበን ሰጥታዋለች። ሌሎቹ ሐዋርያት ግን
ትንሣኤዋን አላዩም ነበርና የእመቤታችንን ነገር እንዴት ሆነች በማለት
ቅዱስ ቶማስ አውቆ ሲጠይቅ እርሷማ በጥር ሞታ በነሐሴ ቀበርናት
በማለት ስለመለሱለት። ይህማ አይሆንም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር
ስላላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ ድሮም ተጠራጥረህ ሰው ታጠራጥራለህ
ብሎ ቆፍሮ ሊያሳየው ቢሄዱ አካሏን አጡት። ቅዱስ ቶማስም የያዘውን
ይዞ ነበርና የጠየቃቸው፤ ማረጓንበሰበኗ አሳያቸው። እነሱም ተካፈሉት
ተአምራትም አደረጉበት (ዛሬ ካህናት መስቀል ሲይዙ ዲያቆናትም የመጾር
፲፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
መስቀሉን ይዘው አብሮ የሚታየው ጨርቅ የዚህ ምሳሌ ነው)። ኋላም
ቶማስ ያየውን ማየት አለብን ብለው ሱባዔ በቀጣዩ ዓመት ገቡ ጌታም
እመቤታችንም ተገለጡላቸው። እርሷም ባረከቻቸው። ይህን ትንሣኤዋን
ዳግምም መገለጧን ቤተክርስቲያናችን እንደ ልጇ ትንሣኤ አክብሩት
በማለት ታውጃለች። ከነሐሴ ፲፮-፳፩ም ይከብራል። በመሆኑም ነሐሴ
አሥራ ስድስት ቀን በየዓመቱ የትንሣኤዋ መታሰቢያ ሆኖ ይዘከራል።
ሐዋርያት የጾሙትን ጾምም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም በማለት እነሱን
አብነት አድርገን እንጾመዋለን።
ነቢዩ “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች”
መዝ ፫፬፥፱ ብሎ በተነበየው መሠረት አሁን እመቤታችን በሰማይ ስለኛ
ለልጇ በተቀበለችው ቃል ኪዳን እያሳሰበችል አለች።
-“በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት
በመቅደሱ ታየ” ራእይ ፲፩፥፲፱
- “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ
በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት
አንዲት ሴት ነበረች” ራእይ ፲፪-፩

፲፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ሐሰት
በማለት መልሱ።

፩- እመቤታችን ከቤተመቅደስ በ፲፪ ዓመቷ ወጣች።


፪- የእመቤታችን ምልጃ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠ ነው።
፫- እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ አረፈች።
፬- እመቤታችን ከልጇ ጋር የተሰደደችው ወደ እሥራኤል ሀገር ነው።

፲፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት
የእመቤታችን ክብር እና ቅድስና

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ፣ ቅድስና ፣


ንጽሕና እና ዘላለማዊ ድንግልና እንዲሁም በቅዱሳን ነቢያት ስለእርሷ
የተተነበዩ ትንቢቶችን አውቀው እመቤታችንን ያከብራሉ።

፪.፩ የእመቤታችን ክብር


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብርት ገናና ናት። ክብሯም
ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች ነው። ስለዚህም ቅዱሳን መላእክት
ቅዱሳን ሰዎች እና ትውልድ የሆኑ ሁሉ ያመሰግኗታል። (ሉቃ ፩፥፳፰/
፵፩-፵፭) የክብሯም ምንጭ የጌታ እናትነቷ ነው። “በመጀመሪያው ቃል
ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረይህ
በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም
አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም”ዮሐ ፩፥፩-፫ ተብሎ የተነገረለትን
ያለና የሚኖረውን አልፋና ኦሜጋ ሁሉን የፈጠረውን ስለወለደች “ቃል
ሥጋ ሆነ” ዮሐ ፩፥፲፬ ስላለን ይህን የእግዚአብሔር ቃል እናትነቷን
እንመሰክራለን። የአምላክ እናት ስለሆነችም እናከብራታለን። ለዚህም ነው
ቅድስት ኤልሳቤጥ ጻድቅ ለመሆኗ መጽሐፍ ቅዱስ የመሰከረላት እናት
(ሉቃ ፩፥፮) “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?”
፲፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሉቃ፩፥፵፫ ያለችው። ቅዱስ ገብርኤልም እንደ ዘካርያስ ሳይሆን እንደ


እመቤቱ እንደ ጌታው እናት እንደ ንግሥትነቷ ያመሰገናት ያናጋገራት
ክብሯን ስለተረዳ ማንነቷን ስላወቀ ነው።

በዚህ የአምላክ እናትነቷም ሰይጣን ሥራው ስለፈረሰ (፩ኛ ዮሐ ፫፥፱)


ጌታን ከወለደች ጀምሮ አሳድዷታል። እርሷ ስታርግም “ከዘሯ የቀሩ”
የተባልን፣ እናታችን የምንላትን ክርስቲያኖችን ይዋጋናል። (ራእይ ፲፪)
የእመቤታችን ክብሯ በመጽሐፍ ቅዱስ በንግሥት መልክ ተቀምጦልናል።
የዚህም ምክንያቱ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ (ራእይ ፲፯፥፲፬)
እናት ስለሆነች ነው። እኛም ንግሥት እንላታለን እመቤት እንላታለን።
“አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ
ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ” ራእይ ፲፪፥፭
- “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች”
መዝ ፵፬፥፱
- “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ
በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት
አንዲት ሴት ነበረች” ራእይ ፲፪፥፩

እመቤታችን ከፍጡራን ሁሉ የምትበልጥ ናት። ወንዶች አባት ቢሆኑ፣


ሴቶችንም የምናከብራቸው ነቢያትን ሐዋርያትን ጻድቃን ሰማዕታትን
ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ቀሳውስት ዲያቆናትን ነገሥታት መኳንንትን
ወለዱ በማለት እነሱም ቅዱሳን ሆኑ ብለን ነው።
እመቤታችንን ግን የምናከብራት
• እመ አምላክ (የአምላክ እናት - ታኦዶኮስ፣ቴዎቶኮስ
• እመብርሃን (የብርሃን ክርስቶስ እናት)፣
• ቤዛዊተ ዓለም (የዓለም ቤዛ መድኃኒዓለምን ያስገኘች ቤዛችን) በማለት
እናከብራታለን።
ክብር ለሚገባውም ክብር እንሰጣለን።(ሮሜ ፲፫፥፯) ስለዚህም እመቤታችን
፲፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ቅድስት ድንግል ማርያም ከከበሩ የከበረች ከተመረጡም የተመረጠች
መልዕልተ ፍጡራን (ከፍጡራን በላይ) መትሕተ ፈጣሪ (ከፈጣሪ በታች)
የሆነች ንዕድና ክብርት ናት። እንደ ርስዋ የከበረ የለም። ለአምላክ
እናትነት በተገባ ተገኝታለችና። የጌታ እናት ናትና። ሉቃ. ፩፥፵፫

እመቤታችንን ስለምን እናከብራታለን? ቢሉ


፩. የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነች፣ እግዚአብሔር ስለአከበራት የጸጋ
ስግደት እንሰግድላታለን።

፪. የጌታ እናት፣ የአምላክ እናት፣ ሰአሊተ ምሕረት፣ ድንግል፣ እመ


ብዙኃን፣ አቁራሪተ መዓት፣ የገብርኤል ብሥራት፣ ንጽሕተ ንጹሐን፣
ሀገረ እግዚአብሔር፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ማኅደረ ሰላም፣ መዓርገ
ሕይወት፣ ማኅደረ ስብሐት፣ ማኅደረ ትፍስሕት፣ ቤተ ሃይማኖት፣
ብጽዕት፣ ሕሪት፣ ክብርት፣ ልእልት፣ ውድስት፣ የሰማዕታት እናት፣
የመላእክት እህት፣ የነቢያት ትንቢት፣ የሐዋርያት ሞገስ፣ እመ
ብርሃን፣ ርሕርሕተ ልብ፣ የሲና ዕፀ ጳጦስ፣ የአዳም ተስፋ፣ የአቤል
የዋህት፣የሴት ቸርነት፣ የሔኖክ ደግነት፣ ሙጻአ ፀሐይ፣ ታቦት ዘዶር፣
እግዝትነ ማርያም፣ የቅዱስ ኤፍሬም ባራኪ፣ ምልዕተ ውዳሴ፣ ቡርክት፣
የደስታ መገኛ፣ ምእራግ፣ ጽርሕ ንጽሕት፣ ማሕደረ መለኮት፣ እኅቱ
ለሙሴ፣ ገራሕቱ ለአብርሃም፣ ወለቱ ለዳዊት፣እሙ ለአማኑኤል፣
ነያ ሰናይት፣ እምነ ጽዮን፣ መዝገበ ብርሃን፣ጽጌ ሃይማኖት፣ ደብተራ
ፍጽምት፣ ማርያም ቅድስት፣ አክሊለ ንጹሐን፣. ብርሃነ ቅዱሳን፣ ወለተ
ሐና ወኢያቄም፣ መድኃኒተ ይእቲ፣ሐመልማለ ገነት፣ ሙዳዬ መና፣
ርግበ ጸአዳ፣ ሐመልማላዊት፣ መንፈሳዊት ሃገር፣ የኖህ መርከብ፣
የሴም ምርቃቱ፣ የሴም እድል ፈንታዉ፣የአብርሃም ዘመድ፣ ሶልያና፣
እሙ ለፀሐይ ጽድቅ፣ ምስራቀ ምስራቃት፣በትረ አሮን፣ የይስሐቅ ሽቱ፣
የያዕቆብ መሰላል፣ የዮሴፍ አረጋጊ፣ቤዛዊተ ዓለም፣ የእሴይ ሥር፣
ወለተ ዳዊት፣ የሙሴ ጽላት፣የአሮን ካህን ጸናጽል፣ የኢያሱ የምስክር
፲፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሐውልት፣ የጌዴዎን ጸምር፣ የሳሙኤል ሽቱ፣ የአሚናዳብ ሰረገላ፣


የዳዊት መሰንቆ፣ የሰሎሞን ቀለበት፣የኤልያስ መሶበ ወርቅ፣ የኤልሳዕ
ልሕኩት፣ የኢሳይያስ ትንቢት፣የሕዝቅኤል አዳራሽ፣ ዕፀ ሕይወት፣
የሚኪያስ ኤፍራታ፣ የናሆም ፈዋሽ፣የዘካርያስ ደስታ፣ወለተ ጽዮን፣
ንጽሕት ጸምር፣ ደብተራ ዘትዕይንት፣ሀገረ ክርስቶስ፣ ኪዳነ ምሕረት፣
በዓታ፣ መሠረተ ሕይወት፣ ናዛዚተ ሕዙናን፣ አንቀጸ አድሕኖ፣ መዓዛ
እረፍት፣ ርግብ የሠናይት፣ሐረገ ወይን፣ አንቀጸ ብርሃን፣ ተቅዋም
ዘወርቅ፣ መቅደስ፣ሐመልማለ ወርቅ፣ ብርሃነ ሕይወት፣ ሆኅተ ምስራቅ፣
መዝገቡ ለቃል፣ ፍኖተ ሕይወት፣ ምስጢረ ስብሐት፣ መዝገበ ብርሃን፣
ምልእተ ክብር፣ ምልእተ ፍስሐ፣ ምልእተ ፀጋ፣ ጽላተ ኪዳን ፣ ጽላተ
ሕግ ፣ዳግሚት ሰማይ እያልን በክብር እንጠራታለን።

፫. ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፣ ቡርክት ነሽ፣ ብጽዕት ነሽ እያልን


በውዳሴ በቅዳሴ በጸሎት በመልክእ እናመሰግናታለን።
፬. ፴፫ቱን በዓላቷን እናከብራለን። እነርሱም
• ፩. ነሐሴ ፯ - እመቤታችን የተፀነሰችበት ዕለት።
• ፪. ነሐሴ ፲፮- ሥጋዋ የፈለሰበት/በልጇ ኃይል ከሞት ተለይታ
የተነሣችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ዕለት።
• ከ፫- ፯ ከነሐሴ ፲፯ እስከ ነሐሴ ፳፩ ድረስ ለ፭ ቀናት ትንሣኤዋ
እንደልጇ ትንሣኤ ይከበራል። የጌታ ትንሣኤ አንድ እሑድ ቀን መኾኗ
የታወቀ ቢሆንም የትንሳኤው መታሰቢያ እስከ ፶ቀናት ማክበራችንን
እናስታውስ የእመቤታችንም እንደዚሁ ነው።
• ፰. መስከረም ፲ ሥጋን የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራት
ታደርግ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል ፄዴንያ ወደተባለ አገር
ገብታ የተቀመጠችበትን ዕለት።
• ፱. መስከረም ፳፩ ትከብራለች። አርዮስን ለማውገዝ በ፵፻፳፮ ፫፻፳፮
ዓ.ም በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን ከሚያዝያ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን
ድረስ በመሆኑ የመስከረም ማርያም (ብዙኃን ማርያም) ተብሎ በዓሏ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ይከበራል። እንዲሁም ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል


ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በመስከረም ፳፩ ቀን ስላስገቡ ምእመናን
በዓሉን በግሸን ማርያም ያከብሩታል።
• ፲. ጥቅምት ፳፩- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው።
• ፲፩. ኅዳር ፮- ወደ ግብፅ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል
ሀገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት።
• ፲፪. ኅዳር ፳፩ ጽላተ ሙሴ አክሱም ቤተ መቅደስ ተሠርቶላት በክብር
ያረፈችበት ዕለት። ዳግመኛም ካህኑ ዘካርያስ የእመቤታችን ምሳሌ
የሆነውን የመቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት ነው።
• ፲፫. ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት።
• ፲፬. ታኅሣሥ ፳፩ ትከብራለች። የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው።
• ፲፭. ታኅሣሥ ፳፪- ብሥራተ ገብርኤል (ቅዱስ ደቅስዮስ እመቤታችን
ጌታን የፀነሰችበትን የመጋቢት ፳፱ ቀንን በዓል በዚህ ዕለት አከበረ)።
• ፲፮. ታኅሣሥ ፳፰- ጌታችንን የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል
• ፲፯. ታኅሣሥ ፳፱- ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት የመታሰቢያ
በዓል።
• ፲፰. ጥር ፳፩- እመቤታችን በ ፷፬ ዓመቷ ያረፈችበት ዕለት።
• ፲፱. የካቲት ፲፮ ከልጇ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ዕለት።
• ፳. የካቲት ፳፩ ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው።
• ፳፩. መጋቢት ፳፩ ትከብራለች/ የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው
• ፳፪. መጋቢት ፳፱ ትከብራለች/ጌታችንን የፀነሰበት ጥንተ በዓል።
• ፳፫. ሚያዝያ ፳፩ ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው።
• ፳፬. ግንቦት ፩- እመቤታችን የተወለደችበት ዕለት።
• ፳፭. ግንቦት ፳፩- በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር
ያደረገችበት።
• ፳፮ እስከ ፳፯ ግንቦት- ፳፪እስከ ፳፫ በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ
ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር
• ፳፰. ግንቦት ፳፬- እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና
፳፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት።


• ፳፱. ግንቦት ፳፭ ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት
ያለመለመበት ዕለት።
• ፴. ሰኔ ፰ ተወዳጅ ልጇ ከደረቅ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት።
• ፴፩. ሰኔ ፳- ጌታችን ተገልጦ ሐዋርያቱን ሰብስቦ በስሟ ቤተ
ክርስቲያን ሠራላት
• ፴፪. ሰኔ ፳፩ ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው።
• ፴፫. ሐምሌ ፳፩- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው።

፭. በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ስላላት፣ እናቱም ስለሆነች፣ በቀኙ የቆመች


ንግሥት ስለሆነች፣ ጸጋ የመላባት ስለሆነችም አማልጅን ብለን በትህትና
ወደ እርሷ እንቀርባለን።

፪.፪ የእመቤታችን ቅድስና


ቅዱስ ማለት ጽኑዕ፣ ንጹሕ፣ ክቡር፣ ልዩ፣ ምሥጉን ማለትነውና።
የእመቤታችን ቅድስና ስንል የእመቤታችን ጽንዕትነት፣የእመቤታችን
ንጽሕትነት፣ የእመቤታችን ክብርትነት፣ የእመቤታችን ልዩነት፣
የእመቤታችን ተመሥጋኝነት ማለታችን ነው።

ሀ) የእመቤታችን ጽንዕትነት
እመቤታችን ጽንዕት በድንግልና የጸናች ናት። ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ እስከ
ጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ (ድንግልናን ማጣት) አለባቸው። እመቤታችን
ግን ከመፅነሷ በፊት፣ በፀነሰች ጊዜ፣ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፣
በወለደች ጊዜ፣ ከወለደች በኋላ ጽንዕት ነችና በድንግልና የጸናች ናትና
ቅድስት እንላታለን። የጸናች ናትና ቅድስናዋን እንመሰክራለን።
ለ) የእመቤታችን ንጽሕትነት
እመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያልነካት፣ ነውር የሌለባት ንጽሕት
ናት። ሴቶች ቢነጹ፣ ሰዎች ቢነጹ፣ መላእክት እንኳን ቢነጹ ከነቢብ
፳፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
(ኃጢአትን ከመናገር)፣ ከገቢር (ኃጢአትን ከማድረግ) ነው እንጂ ከኀልዮ
(ኃጢአትን ከማሰብ) አይነጹም (ከመላእክት ዲያብሎስ እንኳን ሐሰትን
አስቦ፤ አስቦም ሳይቀር ፈጽሟልና)። እመቤታችን ግን ከነቢብ ከቃል
ከአንደበት፣ ከገቢር ከድርጊት፣ ከኀልዮ ከሐሳብ ኃጢአትና ነውር ሁሉ
ንጽሕት ናት። ስለዚህም ቅድስት እንላታለን።
ሐ) የእመቤታችን ልዩነት
እመቤታችን ልዩ ናት ከማንም ከማን አትመሳሰልም። ሴቶች እናት ቢሆኑ
ድንግል መሆን አይችሉም፤ ድንግል ቢሆኑ እናት መሆን አይችሉም።
እመቤታችን ግን እናትነትን ከድንግልና፣ ድንግልናን ከእናትነት ጋር
አስተባብራ (በአንድነት) ይዛ የተገኘች እርሷ ብቻ ስለሆነች፤ ከእርሷ
በቀር ስላልነበረ፣ ስለሌለ እና ስለማይኖር ልዩ እንላታለን። በዚህም ነቢዩ
እንዳለው ምልክታችን ሆናለች።

መ) የእመቤታችን ተመሥጋኝነት
እመቤታችን ከለይ በጠቀስናቸው ማንነቶቿ ሁሉ ትመሠገናለች።
ስለዚህም እራሷ እንዲህ በማለት መስክራለች።
“እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ
በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።”ሉቃ.፩፥፵፰-፵፱

ካመሰገኗት መካከልም
፩. የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ሌሎቹን ሊቃነ መላእክት፣ መላእክት
እና ሠራዊተ መላእክትን እንደ አለቃነቱ ወክሎ፡
- “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ
ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች
ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም
ማርያም ነበረ።መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ
ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ
አላት” ሉቃ ፩፥፳፮-፳፰ ይህ ጸሎት እመቤታችን ሆይ ብለን የምንጸልየው
፳፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

መሆኑን ልብ እንበል።
፪.ቅድስት ኤልሳቤጥ ጻድቃንን፣የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆኑ ሰዎችን
ወክላ
“ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ
ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ
እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ
የተባረከ ነው።የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ
ዘሎአልና።ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት”
ሉቃ ፩፥፵፩-፵፭
ጌታችንም እመቤታችን መመስገን እንዳለባት በወርቃማ ቃሉ ነግሮናል።
- “ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦
የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው።
እርሱ ግን፦ አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት
ናቸው አለ” ሉቃ ፲፩-፳፯-፳፰ ይህም በመልክአ ማርያም ማመስገን
እንዳለብን አስረጅ ነው።
ከዚህ ዓለም ቅዱሳንና ቅዱሳት መካከል እንደ እመቤታችን ያለ በእርሱዋ
መጠን ፀጋን የተመላ በንጽሕናና ቅድስና የተዋበ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ
የሆነና በልዑል ኃይልም የተጠበቀ ሰውነት ያለው የለም። (ሉቃ ፩፥፳፰)
ስለዚህም ቅድስት ብቻ ሳይሆን ቅድስተ ቅዱሳን (ከተለዩ የተለየች፣
ከተመሠገኑ የተመሠገነች፣ ከከበሩ የከበረች፣ ከጸኑ የጸናች)፣ ንጽሕት
ብቻ ሳይሆን ንጽሕተ ንጹሐን በማለት መለየቷ ከሌሎች ፍጡራን ሁሉ
መሆኑን እንመሰክራለን።ስለዚህም ትውልድ የአዳም ዘር፣ የሴም የካም
የያፌት ልጆች ቅዱስ ዳዊት ለልጁ ለሰለሞን እንደመከረው እንዳለው
ሰው የሆኑ (፩ኛ ነገ ፪፥፪-፫) ሁሉ “ቅድስት ብፅዕት” እያሉ ሲያመሰግኗት
ይኖራሉ።

፳፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
፪.፫ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና
ዘለዓለም ማለት መቼም መች ማለት ሲሆን ድንግል ማለት ግንኙነት
የማያውቅ የማታውቅ ማለት ነው። የእመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና
ስንልም መቼም መች ወንድ እንደማታውቅ የሚያሳይ ነው። ድንግል
የሚለው ቃል በርግጥ ቅድስናዋን ንፅሕናዋን ብቻ ሳይሆን ልዩ መሆንዋንም
ያመለክታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከተለዩ የተለየች
ከከበሩ የከበረች የሚያደርጋት ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ አምላክን
በድንግልና ጸንሳ በድንግልና መውለዷ ነው። ምክንያቱም ሌሎች ሴቶች
እናትም ድንግልም መሆን አይችሉምና ነው። በዓለም ከነበሩና ከሚኖሩ
ሴቶች እንደ እመቤታችን ድንግልናን ከእናትነት እናትነትን ከድንግልና
አስተባብረው የተገኙሴቶችየሉም አይኖሩምም።

እመቤታችን ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰች በኋላ ከመውለዷ


በፊት በወለደች ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት።እመቤታችን ከሌሎች
ሴቶች ተለይታ እግዚአብሔር ከመረጣት ጀምሮ በሐሳብ፣በመናገርና
በመስራት ንጽሀ ጠባይ ያላደፈባት ዘላለማዊት ንጽሕት ድንግል ናት።

እመቤታችን ጌታን ከመፅነሷ ከመውለዷ በፊት ንጽሕት ናት።


- “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ
ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች
ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም
ማርያም ነበረ” ሉቃ ፩፥፳፮-፳፯
- “ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?
አለችው” ሉቃ ፩፥፴፬ (ይህን ያለችው በታጨች ጊዜ መሆኑን አስተውሉ።)
በፀነሰች ጊዜ በወለደች ጊዜ ንጽሕት ናት
- “ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ
ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ኢሳ ፯፥፲፬
- “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል
፳፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል”


ሉቃ ፩፥፴፭
- “እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ
ተገኘች” ማቴ ፩፥፲፰
- “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው በመንፈስ ቅዱስ ነውና
እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ” ማቴ ፩፥፳
- “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል
ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው” ማቴ ፩፥፳፫
ከፀነሰች ከወለደችም በኋላ ንጽሕት ናት።
- “ወደ ምሥራቅም ወደ ሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ
መቅደሱ በር አመጣኝ፤ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፦ይህ በር
ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤የእስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሕዝ ፵፬፥፩-፪
እመቤታችን ሌሎች ልጆችን አልወለደችም።
- “ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም
ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤
ይሰናከሉበትም ነበር”ማር ፮፥፫
- “ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ
ባየ ጊዜ እናቱን፦ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ
መዝሙሩን፦ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀመዝሙሩ
ወደ ቤቱ ወሰዳት” ዮሐ ፲፱፥፳፮-፳፯

የወንድሞች ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ


ወንድሞች የሚለው ቃል በርካታ ትርጉሞች አሉት።
፩. የአባትና የእናት ልጅ
- “አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ
አለው።” ፪ሳሙ ፲፫፥፲፬
፳፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
፪. የሀገር ልጅ
- “በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ
ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው የወንድሞቹን
የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ።” ዘጸ ፪፥፲፩
፫.አንድ ነገድ
- “ንጉሡም ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ
አላቸው፦ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦የእስራኤል
ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶ አልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለምን
ዘገያችሁ? እናንተ ወንድሞቼ ፥የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ
ናችሁ፤ እናንተ ንጉሡን ከመመለስስ ለምን ዘገያችሁ?”፪ሳሙ ፲፱፥፲፩-፲፪
፬. በቤተሰብ ቤተ ዘመድ
- “ከብቱንም ሁሉ አስመለሰ፥ ደግሞም ወንድሙን ሎጥንና ከብቶቹን
ሴቶችንና ሕዝቡን ደግሞ መለሰ።” ዘፍ ፲፬፥፲፮
፭.በቃል ኪዳን
- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው
ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም
ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።”
አሞጽ ፩፥፱
፮. በቅርብ ዝምድና
- “ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ
ላከ፦ ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ
ታውቃለህ።” ዘኁ ፳፥፲፬
፯. በወዳጅነት
- “ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ በእኔ ዘንድ
ውድህ እጅግ የተለየ ነበረ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም
ነበረ።” ፪ኛ ሳሙ ፩፥፳፮

፳፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፰. በሥራ
- “የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ
ዘሩባቤል ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ
እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን
አምላክ መሠዊያ ሠሩ” ዕዝ ፫፥፪
፱. በሃይማኖት
- “ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ
አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን
እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።” ሮሜ ፩፥፲፫
፲. ከነዚህ የተለየ የክርስቶስ ወንድምነት ይህም ሰው መሆኑን ያሳያል።
- “ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር
ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን
ሊመስል ተገባው።” ዕብ ፪፥፲፯
ስለዚህ ወንድሞቹ እህቶቹ ተብለው የተጠቀሱት ከድንግል የተወለዱ
ሳይሆን ከዮሴፍ የተወለዱ ዘመዶቹ ናቸው።

የ “እስከ” ትርጉም በመጽሐፍ ቅዱስ


“ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤እጮኛውንም
ወሰደ፤ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም
ኢየሱስ አለው።” ማቴ ፩፥፳፬-፳፭
እስከ ፍጻሜ ያለው እስከ እና ፍጻሜ የሌለው እስከ በመባል በሁለት
ይፈታል። ከላይ የተመለከትነውም እስከ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው
ምክንያቱም እመቤታችን ሌላ ስላልወለደች ዮሴፍም የታጨው ሊጠብቃት፣
ዘመዷም ስለሆነ ነውና።
ፍጻሜ ያለው እስከ
- “ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች
በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ፤
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ” ኢያ ፯፥፮
፳፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
- “እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦
ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም
እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።”ማቴ ፪፥፲፬-፲፭
- “ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን
ድረስ በምድረ በዳ ኖረ”ሉቃ ፩፥፹
- “ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ
ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ
ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ”ሐዋ ፩፥፩-፪
- “በዚያም ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን ኤላትን ወደ ሶርያ መለሰ፥
አይሁድንም ከኤላት አሳደደ፤ ኤዶማውያንም ወደ ኤላት መጥተው እስከ
ዛሬ ድረስ በእርስዋ ተቀምጠዋል” ፪ኛ ነገ ፲፮፥፮
ፍጻሜ የሌለው እስከ
- “ቁራንም ሰደደው፤ እርሱም ወጣ፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ
ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር”ዘፍ ፰፥፯ ይህም ቁራ መቼም እንዳልተመለሰ
ያሳያል።
- “የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም”
፪ኛ ሳሙ ፮፥፳፫ ይህምሜልኮል ልጅን መቼም እንዳልወለደች ያሳያል
- “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”ማቴ
፳፰፥፳ ከዓለም ፍጻሜም በኋላ ከእነርሱ ጋር መሆኑን ያሳያል።
እንዲሁም መታጨት ሁሌ ለትዳር አይደለም።
- “በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል
እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና” ፪ኛ ቆሮ
፲፩፥፳፫

፳፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፪.፬ እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት


ትንቢት፡- ማለት ወደ ፊት ስለሚፈፀመው ስለሚሆነው ነገር መናገር
ምልክት መስጠት ወደ ፊት የሚሆነውን ማሳወቅ ማለት ነው።
ነቢያት፡- ማለት ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በገለፀላቸው
ባዘዛቸው መንገድ ትንቢትን የሚናገሩ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች
ናቸው።
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ነቢያት አምላክን
እንደምትወልድ፤ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ተንብየዋል
(ተናግረዋል)።
አምላካችን እግዚአብሔር አዳም ስቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ ሱባኤ ይዞ
ፆሞ ጸልዮ አምላኩ ይቅር እንዲለው ከለመነ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ
ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው ብሎቃል ገብቶለት ነበር። ይህም
ቃሉ ይፈጸም ዘንድ በተለያዩ ዘመናት በቅዱሳን ነብያት ላይ አድሮ
ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሚወለድ ያናገር ነበር።
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተነገሩት ትንቢቶች በጥቂቱ
እንመልከት፡-
አምላክ ኅሊና ታስባ ስለመኖሯ
- ዘፍ ፫፥፲፭ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል
ጠላትነትን አደርጋለሁ”
- ዘፍ ፫፥፳፪ “እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ
ሆነ”
- ኢሳ ፩፥፱ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ
ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።”
ስለ ልደቷ
- ኢሳ. ፲፩፥፩ “ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች አበባም ከግምዱ ይወጣል”
በዚህም ትንቢት ከእሴይ ልጅ ከቅዱስ ዳዊት ዘር እንደምተወልድ
ተናግሯል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
- መኃ ፬፥፰ “ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፤ ከሊባኖስ ከእኔ
ጋር ነዪ”
ስለ እድገቷ
- መዝ ፵፬፥፲ “ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን
ያባትሽንም ቤት እርሺ”
ጌታን ስለ መጽነሷና ስለመውለዷ
- ኢሳ. ፯፥፲፬ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋልእነሆ ድንግል
ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች”
ብሎ ነቢዩ ኢሳያስ በመንፈስ ቅዱስ ይህን ምሥጢር ተረድቶ ስለ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተናግሯል።
ስለ ስደቷ
- ሆሴዕ ፲፩፥፩ “ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።”
ስለ ሐዘኗ
- ሉቃ ፪፥፴፬-፴፭ “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል”
ስለሞቷ ትንሣኤዋና ዕርገቷ
- መዝ ፻፴፩፥፰ “አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።”
በሰማይ ስለመኖሯ
- መዝ ፵፬፥፱ “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ
ትቆማለች።”

፴፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክለኛውን መልስ መልሱ።
፩- እመቤታችንን ለምን እናከብራታለን?
፪- ከ፴፫ቱ የእመቤታችን ዐበይት በዓላት መካከል ቢያንስ አምስቱን
ጥቀሱ።
፫- ስለ እመቤታችን የተተነበዩ ትንቢቶችን ዘርዝሩ።
፬- በመጽሐፍ ቅዱስ የእስከ አገባብን አስረዱ።
፭- ወንድሞች የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ትርጉሞች ጻፉ።

፴፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ ሦስት
የእመቤታችን አማላጅነት

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• የምልጃን ምንነት ፣ የቅዱሳንን አማላጅነት ፣ የቅዱሳን መላእክትን


አማላጅነት እንዲሁም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን
አማላጅነት ፣ በቃና ዘገሊላ የተፈጸመውን የእመቤታችንን ምልጃ
አውቀው በአማላጅነቷ ይጠቀማሉ።

፫.፩ ምልጃ በመጽሐፍ ቅዱስ


ምልጃ ማለት መለመን፣ ልመና፣ ማስታረቅ ማለት ነው።እግዚአብሔር
አምላካችን በምድር በንጽሕና በቅድስና ያገለገሉትን የታመኑለትን ሥርዓቱን
ጠብቀው በሚገባ የፈፀሙትን ቅዱሳን ሰዎች ልመና ምልጃ ይሰማል
ይፈፅማል። ምክንያቱም እነኚህ ቅዱሳን ታማኝ አገልጋዮቹ ናቸውና፣
ትዕዛዙን ፈፅመዋልና፣ ንጹሕህ እና ቅዱስ ናቸውና፣እግዚአብሔርን
መርጠዋልና፣ በእርሱ አምነዋልና፣ የጠየቁትን እንደ ሚፈፅምላቸው
ያምናሉና፣ እግዚአብሔርም ቃል -ኪዳን ሰጥቷቸዋልና ነው።ቃል
ኪዳኑም በምልጃቸው አምኖ በቅዱሳኑ ስም የሚለመን ፀሎትን የሚሰማ
መሆኑ አንዱ ነው። እንዲሁም የቅዱሳንን ጸሎታቸውን እግዚአብሔር
ስለሚቀበለውና በጸሎታቸውም እጅግ ኃይል ስለሚያደርጉ ያማልዱናል።
“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን”
ዕብ ፲፪፥፩ እንዲያማልዱን እንጠይቃቸዋለን።
፴፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱሳን ሰዎች በዚህ ዓለም ሳሉም ከአረፉም


በኋላ እና ቅዱሳን መላእክት ምልጃን እንደሚፈጽሙት እንደሚማልዱ፤
እግዚአብሔርም ያዘዘው እንደሆነ ተመዝግቧል።
ቅዱሳን እንዲያማልዱ እግዚአብሔር ስለማዘዙ
- “ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ….. ስለ እናንተም ይፀልያል…
እኔም ፊቱን እቀበላለሁ”ኢዮብ ፵፰፥፩-፱
- “ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም”ዘፍ፳፥፯
- “የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው” ፪ቆሮ ፭፥፲፰
- “በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ” ፪ቆሮ ፭፥፲፱

ቅዱሳን በምድር እያሉ እንደሚያማልዱ


- “እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ
በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ” መዝ
፻፭፥፳፫
- “አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን
ሚስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ” ዘፍ ፳፥፲፯
- “ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ
በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል
አለው”ዘኁ ፳፰፥፰
- “እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን
እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።”ማቴ ፳፬፥፳፪

ቅዱሳን ከአረፉም በኋላ በሕይወት ስላሉ ሰዎች እንደ ሚያማልዱ


- “በዚያም ሌላ ራእይ አየሁ፤ የጻድቃንን ማደሪያቸውንና የቅዱሳንን
ማረፊያቸውን አየሁ። በዚያም ዐይኖቼ ከመላእክት ጋር ማደሪያቸውን
ከቅዱሳንም ጋር ማረፊያቸውን አዩ። ስለ ሰው ልጆች ይለምናሉ፥
ይማልዳሉ፥ ይጸልያሉም” ሄኖክ ፱፥፳፩-፳፫
- “አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና
፴፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች
አየሁ።በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ
መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ
አትበቀልም? አሉ። ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ
እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና
የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ
ተባለላቸው።” ራእይ ፮፥፱-፲፩

ቃል ኪዳንም እንደ ሰጣቸውና እንደሚያማልዱ


- “እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም
ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ”
ዘጸ፪፥፳፬
- “ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ
መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም”
ማቴ ፲፥፵፪
- “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት
ማልሁ” መዝ ፹፰፥፫
- “እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር
አቆማለሁ” ዘፍ ፱፥፱
- “የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” መዝ ፻፲፩፥፮
- “ስለ እኔም፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ
እጋርዳታለሁ”
፪ኛ ነገ ፲፱፥፴፬ ይህ ዳዊት ከሞተ በኋላ የተነገረ ነው።
- “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳ ፲፥፯

ቅዱሳን መላእክት እንደሚያማልዱ


- “ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ
ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ
፴፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ


፩፥፲፫-፲፬
- “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥
እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች
የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር
ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።” ዘካ
፩፥፲፪-፲፫
-“በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል
ይነሣል” ዳን ፲፪፥፩
- “መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል
ነኝ”ሉቃ ፩፥፲፱
- “ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው
በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ
እላችኋለሁና።”ማቴ ፲፰፥፲
- “የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፦ እነሆ፥ ከዚህች በለስ ፍሬ ልፈልግ
ሦስት ዓመት እየመጣሁ ምንም አላገኘሁም፤ ቍረጣት፤ ስለ ምን ደግሞ
መሬቱን ታጐሳቍላለች? አለው።እርሱ ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን
እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ
ተዋት።ወደ ፊትም ብታፈራ፥ ደኅና ነው፤ ያለዚያ ግን ትቈርጣታለህ
አለው” ሉቃ ፲፫፥፯-፱ የሚቆርጡ አጫጆች ቆራጮች ደግሞ መላእክት
እንደሆኑ ጌታችን ራሱ ነግሮናል “አጫጆችም መላእክት ናቸው” ማቴ
፲፫፥፴፱ ከዚህ በተጨማሪ የሚያምን ሁሉ ለሌላው አማኝ ይለምናል።
- “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር
እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና
አታግባን” ማቴ ፮፥፲፩-፲፫

፴፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
፫.፪ ስለ አማላጅነቷ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በክብር ከፍጡራን ሁሉ በላይ ናትና
አማለጅነቷ እውነተኛ እና እውን ነው። እመቤታችንን አምነው ለጠሯት
ሩህሩህ፤አዛኝ ናትና ከልጇ ከአምላካችን ታማልደናለች እንደ እናትነቷም
ለአምላካችን ቅርብ ናት። ስለዚህም ልመናችንን ታስፈፅምልናለች።
ምክንያቱም ልጅ እናቱን ሲጠይቅ የማይፈፀምለት የለምና። እርሷም
በዮሐንስ በኩል ለእኛ እናት ሆና ተሰጥታናለች።
- “እናትህ እነኋት አለው” ዮሐ ፲፱፥፳፯
- እኛም የአደራ የመስቀል ሥር ልጆቿ ነን “እነሆ ልጅሽ” ዮሐ ፲፱፥፳፮
በዚህም ላይ ዘርዋ ልጆቿ እንደሆን ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ “ዘንዶውም
በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም
ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ” ራእይ ፲፪፥፲፯ በማለት
ነግሮናል።
ስለ ምልጃዋም “የወርቅ ልብስ ተጐናፅፋ እና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ
ትቆማለች” በማለት መዝ ፵፬፥፩-፱ ላይ ነብዩ ዳዊት እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ንጽሕና ንገንዘብ አድርጋ ለአማላጅነት ከጎኑ በቀኙ በቅርብ
እንደምትቀመጥ አስረድቶናል። ይህም ንግሥቲቱ አስቴር እንዳደረገችው
ያለ ነው። እርሷ ወገኖቿን በምልጃዋ አትርፋለችና። መጽሐፈ አስቴር
፰፥፬-፮ “ንጉሡም የወርቁን ዘንግ ለአስቴር ዘረጋላት፤ አስቴርም ተነሥታ
በንጉሡ ፊት ቆመችና፦ ንጉሡን ደስ ቢያሰኘው፥ በፊቱም ሞገስ አግኝቼ
እንደሆነ፥ ይህም ነገር በፊቱ ቅን ቢሆን፥ እኔም በእርሱ ዘንድ ተወድጄ
እንደ ሆነ፥ አጋጋዊው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ በንጉሡ አገር ሁሉ ያሉትን
አይሁድ ለማጥፋት የጻፈው ተንኰል ይገለበጥ ዘንድ ይጻፍ።እኔ በሕዝቤ
ላይ የሚወርደውን ክፉ ነገር አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ? ወይስ
የዘመዶቼን ጥፋት አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ? አለች።”
መቆምም ምልጃን እንደሚያሳይ ራሱ ቅዱስ ዳዊት አስቀምጧል።
“እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት
ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ” መዝ ፻፭፥፳፫እንዲል።
፴፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

በመቀጠልም እመቤታችን አስቴር በንጉሡ ፊት ካላት የተሻለ የእናትነት


ሞገስ ጸጋ በእግዚአብሔር ፊት አላት።
- “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ” ሉቃ
፩፥፴ እንዲል። በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ጸጋ ያለው ደግሞ ለሌላው፣
ለኃጥኡ እንደሚማልድ አባታችን አብርሃምም ምሳሌ ሆኖ አሳይቶናል።
- “አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ
ብዬ እለምናለሁ” ዘፍ ፲፰፥፫ “አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት
ገና ቆሞ ነበር።አብርሃምም ቀረበ አለም፦ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ
ጋር ታጠፋለህን? አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ
ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን
አትምርምን?” ዘፍ ፲፰፥፳፪-፳፬
- ቅዱስ ዳዊትም ምልጃዋ ለመንግሥተ ሰማያት እንደሚያበቃን
“ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤ በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥
ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል” መዝ ፵፬፥፲፬-፲፭ በማለት
አረጋግጦልናል።
ከዚህም በተጨማሪም በመስቀሉ ሥር የተረከብናት እናታችን ድንግል
ማርያም በምልዕተ ፀጋነቷ (ፀጋን የተመላች) በመሆኗ እና በተሰጣት
የአማላጅነት ቃል ኪዳን መሠረት ለሚተማመኑ ሁሉ እንዲሁ ሳይሆን
የእናት አማላጃቸው ነች።
በዮሐ ፪፥፩-፭ በቃና ዘገሊላ በመጀመሪያው የክርስቶስ ተአምር የተደረገው
በእመቤታችን አማላጅነት ነው።
በተአምረ ማርያም ላይም በላኤ ሰብእ (የቀድሞው ስሙ ስምኦን) የተባለውን
ሰው በእመቤታችን ስም በሰጠው ውኃ ብቻ ነፍሱ ተምራለች። “ማንም
ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም
የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም” ማቴ ፲፥፵፪
በደብረ አሞር ለ፸ ዓመት እርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው እመቤታችንን
በመማፀን ከእርኩስ መንፈሱ እንዲወጣለት አድርጋለች። ምክንያቱም
ጸጋን የተመላች ናትና። (ሉቃ ፩፥፳፰) እንዲሁም ያመነችና ብጽዕት
፴፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ስለሆነች ሁሉን ማድረግ ስለምትችል። “ያመነች ብፅዕት ናት”ሉቃ
፩፥፵፭ “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል” ማር ፱፥፳፫ እነዚህን የመሳሰሉና
ሌሎች የአማላጅነት ሥራዎች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
እንደተፈፀመ በተአምረ ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ እና በተለያዩ
የቤተክርስቲያን መጻሕፍቶች ተገልጧል።
በአጠቃላይ አማላጅነት ለእመቤታችን ከተሰጧት ፀጋዎች መካከል ትንሿ
እና ጥቂቷ ናት። አመቤታችን ምልዕተ ፀጋ ናትና፣የአምላክ ማደሪያ
ናትና፣ የእመቤታችንን አማላጅነቷን ተናግረን ጽፈን የምንጨረሰው
አይደለም።

፫.፫ የእመቤታችን ምልጃ በቃና ዘገሊላው ሰርግ ቤት


ምልጃ ማለት ለሌላው መለመን ለሌላው መማጸን ሌላውን ማስታረቅ
ማለት ነው። አማላጅ ደግሞ ለሌላው የሚለምን፣ የሚጸልይ፣ የሚማጸን
ማለት ነው። አማለጅነት የሦስት አካላት ግንኙነትን ያመለክታል። ይህም
•ማላጅ- ምልጃ ላኪ፣ በደለኛ፣ ኃጥእ፣ በዳይ
•አማላጅ - የምልጃ መልእክተኛ፣ ምልጃ አቅራቢ፣ አስታራቂ፣ ሸምጋይ፤
እነዚህም ድንግል ማርያም፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን፣ ሰማዕታቱ
•ተማላጅ - ምልጃን ተቀባይ፣ የተበደለ፤ ይህም ልዑል እግዚአብሔር
ነው።
ልዑል እግዚአብሔር ለሰዎች በሚሰጠው ይቅርታ የቅዱሳንን አማላጅነት
እንዲጠቀሙ አዝዞአል።ስለዚህ አማላጅነት የሰዎች ስምምነት ጉዳይ
ሳይሆን፤ አምላካዊ ሥሪት መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው።ይህንንም በእነዚህ
ጥቅሶች እንረዳለን፦
-“ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም” ዘፍ ፳፥፯
- “ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥እኔም እንደ ስንፍናችሁ
እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ” ኢዮ ፵፪፥፰
- “ስለ እኔም ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ
እጋርዳታለሁ” ኢሳ ፴፯፥፴፭/፪ኛ ነገ ፳፥፮
፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

- “.. በእኛ የማስታረቅን ቃል አኖረ ” ፪ኛ ቆሮ ፭፥፲፱


- “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” ፪ኛ ቆሮ
፭፥፳
- “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል
ይነሣል” ዳን.፲፪፥፩
- “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥
እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች
የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር
ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ዘካ
፩፥፲፪-፲፫
- “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ሉቃ ፩ ፥ ፲፱
- “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም
መናፍስት አይደሉምን? ” ዕብ. ፩ ፥ ፲፬
- “ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤መላእክቶቻቸው
በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና”
ማቴ. ፲፰ ፥ ፲
- “እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ
በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ” መዝ
፻፭ ፥ ፳፫
- “ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም፦ አቤቱ፥ቍጣህ
በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ
ስለምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ፦ በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ከምድርም
ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለምን ይናገራሉ? ከመዓትህ
ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ
ከዋክብት አበዛለሁ፥ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ
እሰጣታለሁ፥ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን
ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ።” ዘጸ ፴፪ ፥
፲፩ - ፲፫

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
እመቤታችን ደግሞ በክብር ከፍጡራን ሁሉ በላይ ናትና አማላጅነትዋ
እውን ነው። አባቷ ዳዊትም በመዝሙር “ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና
ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ተቆማለች” (መዝ. ፴፬፥፱) ሲል መናገሩ
ንጽሕናን ገንዘብ አድርጋለ አማላጅነት ሰለ ሕዝብ ልጆች ሁሉ በቀኝ
እንደምትቆም የሚያስረዳ ነው።

ሥዕል ፬ የእመቤታችን ምልጃ በቃና ዘገሊላ

፵፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

የምልጃዋንም ግዳጅ ፈጻሚነት እዛው ላይ “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ


ይወስዳሉ፥ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤ በደስታና በሐሴት
ይወስዱአቸዋል፥ ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል” መዝ ፵፬፥፲፬-፲፭
በማለት መዝግቦታል።
እመቤታችን ምልጃዋ በግልጽ የታየውም ደግሞ በቃና ዘገሊላ ሰርግ
ቤት ነበር።የሙሽራው ዶኪማስ ጓዳ በበረከት የተትረፈረፈው በእርስዋ
አማለጅነት ነው። “የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦የወይን
ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ፦የሚላችሁን
ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።” (ዮሐ.፪፥፫-፭) “አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” ማለቱም አይሆንም ማለቱ እንዳልሆነ
ቀጥሎ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” በማለቷ እና እርሱም ውሃውን ወደ
ወይን በመቀየሩ ግልጽ ነው። (ዮሐ.፩፥፩-፲፩)

“አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” ያለበት


ምክንያትም በአይሁድ ልማድ ይህ አገላለጽ መስማማትን የሚያሳይ
ስለሆነ ጠብ እንደሌለ የሚናገር ስለሆነ ነው። ይህም የአነጋገር ልማድነቱ
ምስክር በሚቀጥሉት ታሪኮች እናያለን፦
- “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በምዋጋበት በሌላ ቤት
ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም” ፪ኛ ዜና፴፭፥፳፩
- “እርስዋም ኤልያስን፦ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?
ኃጢአቴን ስታሳስብ ዘንድ፥ልጄን ስትገድል ዘንድ ወደ እኔመጥተሃልን?
አለችው” ፩ኛ ነገ ፲፯፥፲፰
- “ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፦ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ
አባትህና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ አለው” ፪ኛ ነገ ፫፥፲፫
የጌታንግግሩ የንቀት ንግግር ያለመሆኑ ምስክር፦
- “በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ
ሆይ፥ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ
፵፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
አለ፤አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና” ማር ፭፥፯-፭
ሉቃ ፰፥፳፰
- “ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥አጋንንት ያደሩባቸው
ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤እነርሱም ሰው በዚያ
መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ። እነሆም፦ኢየሱስ
ሆይ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ
ልታሰቃየን ወደዚህ መጣህን? እያሉ ጮኹ” ማቴ ፰፥፳፰-፳፱ ማር ፩፥፳፬
ሉቃ ፬፥፴፬
አጋንንት የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ እግዚአብሔር የሆነውን ክርስቶስን
አይንቁትም ይልቁኑ በፊቱ ይንቀጠቀጣሉና ንግግሩ የማክበር ነው።
“አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል” ያዕ ፪፥፳፱ እንዲል።
“አንቺ ሴት” ማለቱም አጥንቴን ከአጥንትሽ የነሣሁ፣ ሥጋዬን ከሥጋሽ
ያገኘሁ እናቴ አካሌ ሆይ ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት ማለት “ይህች
አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት” ዘፍ ፪፥፳፫ ማለት ነውና።
“ጊዜዬ ገና አልደረሰም” ያለበት ምክንያቶችም
፩. ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለውና ሰዓቱ እስኪደርስ፣
፪. ወይኑ ሙጥጥ ብሎ እስኪያልቅ፤አልለወጠም አበረከተ እንጂ
እንዳይባል፣
፫. እውነተኛው ወይን ሥጋውን የሚቆርስበት ደሙን የማፈስበት ጊዜ
ገና ስለነበረ ነው።

ስለዚህ ጌታችን ከገዳም ከበረሃ ከተመለሰ በኋላ የመጀመሪያውን ተአምር


በእመቤታችን ምልጃ አድርጓል።አማላጅነትም ለእመቤታችን ከተሰጡአት
ጸጋዎች ትንሹ ነው። ምክንያቱም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ለሌላው “የዕለት
እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ
የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን”
ሉቃ ፲፩፥፫-፬ እያለ ዕለት ዕለት በጸሎቱ ይማልዳልና።

፵፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

እሷ ግን ጸጋ የመላባት ምንም ያልጎደላት የአምላክ እናት ናት። (ሉቃ


፩፥፩፰) እንዲሁም “ያመነች ብጽዕት ናት” ሉቃ ፩፥፵፭ እንደተባለላትም
“ለሚያምን ሁሉ ይቻላል”ና ማር ፱፥፳፫ብዙ ተአምራትን አስደርጋለች
አድርጋለች ወደ ፊትም ታደርጋለች በጌታ ቀኝ አለችና።

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክለኛውን መልስ መልሱ።
፩- ቅዱሳን በምድር እያሉ እንደሚያማልዱ የሚያስረዳ አንድ የመጽሐፍ
ቅዱስ ታሪክ ጥቀሱ።
፪- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቃና ዘገሊላ ያደረገችውን
ምልጃ ተናገሩ።
፫- ጌታችን በቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ ጊዜዬ ገና አልደረሰም ያለበትን
ምክንያት ዘርዝሩ።

፵፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት
የእመቤታችን ምሳሌዎች

ዓላማ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• በብሉይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌዎችን


አውቀው ይዘረዝራሉ።

፬.፩ የማክሰኞ እርሻ ዘፍ ፩፥፲፩- ፲፪


“እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ
እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤እንዲሁም
ሆነ።ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን
ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች።እግዚአብሔርም ያ መልካም
እንደሆነ አየ።”
• የማክሰኞ እርሻ የመጀመሪያዪቱ ምድር ገበሬ ሳይግርባት፣ዘር
ሳይዘራባት ውኃም ሳያስፈልጋት በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ለፍጥረት ሁሉ
ምግብ የሚሆነውን ዘር አስገኝታለች። እመቤታችን ድንግል ማርያምም
ያለ ወንድ ዘር መድኃኒዓለም ክርስቶስን አስገኝታለች (ወልዳለች) እርሱ
ክርስቶስም በዕለተ አርብ በቅዱስ መስቀል ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ
ብሉ ጠጡ ብሎ ዘለዓለማዊ ምግብ ሰጥቶናል።

፵፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፬.፪ የኖኅ መርከብ ዘፍ.፯፥፩-፬


“እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፦አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ
ወደ መርከብ ግባ…”
ኖህ ከጥፋት ውኃ የዳነበት መርከብ የእመቤታችን ምሳሌ ናት።በኖህ ጊዜ
የነበሩት ሰዎች (ሰብአ ትካት) በሰሩት የኃጢአት ሥራ እግዚአብሔርን
እጅግ አሳዘኑት እግዚአብሔርም ምድርን በውኃ ሊያጠፋት ሰያስብ በእርሱ
ፊት ፃድቅ ሆኖ የተገኘው ኖኅ ከነቤተሰቦቹ ከጥፋት ዉኃ የሚድኑበትን
መርከብ እንዲሠራ አዘዘው። ኖኅም መርከቡን እንደታዘዘው ሠርቶ
በውስጥ ገባ።እግዚአብሔርም ምድርን ለአርባ መዓልትና (ቀንና) ሌሊት
ውኃን በማዝነም በምድር ላይ የነበሩትን ሰዎች አጠፋቸው። ኖኅን ግን
በሠራው መርከብ እንዲድን አደረገው።
ነገር ግን ልናስተውል የሚገባን ኖኅ ሊድን የቻለው በሠራው መርከብ
ጥንካሬና ብቃት ብቻ ሳይሆን ዋንኛው በእግዚአብሔር ጥበቃ መርከብንም
ምክንያት አድርጎ ነዉ ያዳነዉ።
• ስለዚህ ክርስቶስ አዳምን ሊያድን ሊሻ እመቤታችንን ምክንያት
አድርጎ ከእርስዋ ተወለደ።
• ዳግመኛም የኖኅ መርከብ በዉስጥ ያሉትን ከመከራ ሥጋ እንዳዳነች
ሁሉ እመቤታችንንም በርስዋ ያመኑትን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ
እንደምታድን
• ከመርከብ ዉጭ ያሉት በንፍር ውኃ እንደጠፉ በእመቤታችን
ምልጃ ያላመኑትን በነፍስ በስጋ ዘለዓለም እንደሚጠፉ ምሳሌ ነው።
• በተጨማሪ መርከቧ ሦስት ክፍል እንዳላት (ዘፍ ፮፥፲፮)
እመቤታችን የሥላሴ ማደሪያ (አብ ለአጽንዖ ወልድ ለተዋሕዶ መንፈስ
ቅዱስ ለአንጽሆ) ለመሆኗ፣
• እንዲሁም ለንጽሐ ሥጋዋ፣ ለንጽሐ ነፍሷና ለንጽሐ ልቡናዋ
ምሳሌ ነው።

፵፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ሥዕል ፭ የኖህኅ መርከብ

፬.፫ የኖኅ ቀስተ ደመና ዘፍ፱፥፰-፯


“እግዚአብሔርም ለኖህ ከእርሱም ጋር ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተ ጋር ከእናንተም በኋላ ከዘራችሁ ጋር
አፀናሉ… የቃል ኪዳኔ ምልክት ይህ ነው ቀስቴን በደመና አኖራለሁ፡፡
የቃል ኪዳን ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል….”
እግዚአብሔር ዳግም ምድርን በውኃ እንደማያጠፋ ለኖኅ ፬ ኅብር ባለው
በቀስተ ደመና ቃል ኪዳን ገብቶለታል።
• ይህን የገባለትን ቃል ማፅናቱን ሊገልፅም ከአማናዊቷ ቀስተ
ደመና ከእመቤታችን ተወለደ። ኢሳ፩፥፱ “እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን
ኖሮ እንደ ሰዶም ቢሆንን እነደ ገሞራም በመሰልን ነበር” ሲል በትንቢት
የቅድስትን መትራፊያነት ነግሮናል። ስለሆነም እግዚአብሔር በኃጢአታችን
ተቆጥቶ እንዳያጠፋን የባሕርያችን መመኪያ የምትሆን እመቤታችን
፵፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ከጐኑ አደረገልን።
• ደመና የእመቤታችን፣ ፬ቱ ኅብር/ ቀለም ያለው ቀስተ ደመና
የ፬ቱ ባሕርያቷ ምሳሌ ሲሆን ከእርሷ በነሣው ሰውነት ሰውን ለማዳኑ
ማሳሌ ነው።

ሥዕል ፮ የኖኅ ቀስተ ደመና

፬.፬ ዕፀ ሳቤቅ ዘፍ ፳፪፥፩-፲፬


“አብርሃምም እጁን ዘረጋ ልጅንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አንሳ… አብርሃምም
ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ በኋላው እነሆ አንድ በግ ቀንዶቹ
በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ አብርሃምም ሄደ በጉን ወሰደው በልጁ በይስሐቅ
ፈንታም ሰዋው”
• እዚህ ቃለ- እግዚአብሔር ላይ ይስሐቅ የዚህ ዓለም፣ በግ የጌታ
ምሳሌ ነው።
• በጉ ለይስሐቅ ቤዛ በመሆን እንደተሰዋ ሁሉ ጌታችን ክርስቶስም
ለዓለም ቤዛ በመሆን ተሰውቷል።
• በጉ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ መገኘቱም የእመቤታችን ምሳሴ ነው።
፵፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
እርሷ ዓለምን ሁሉ ያዳነውን እውነተኛውን በግ ጌታችን ክርስቶስን
በማህፀኗ በድንግልና ዓሥራ (ይዛ) ተሸክማ ቤዛ መድኃኒት ለመሆን
አድርሳዋለችና።

ሥዕል ፯ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ የተያዘው በግ

፬.፭ የያዕቆብ መሰላል ዘፍ.፳፰፥፲-፳፪


- “... ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥
ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት
ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር...”
• እመቤታችን ያዕቆብ ሎዛ በተባለ ስፍራ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ
በራዕይ ያያትን መሰላልት መስላለች።
• በዚያችም መሰላል ላይ መላእክት ይወጡበትና የወረዱበት ነበር።
፵፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

እንዲሁም ጌታችን ሰው ከሆነ በኋላ መላእክት ለተልዕኮ መዳንን ለማውረስ


መውጣት መውረድ ጀምረዋል።ከጌታችን ልደት በፊት ግን ለተልዕኮ
(ሰው መዳንን ይወርስ ዘንድ) አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ለዚህም
ከእመቤታችን የነሣው ሥጋ ዋነኛ ምክንያት ነው።
• ሁለተኛም እመቤታችን ከሦስቱ አካላት ለአንዱ አካል ወልድ
ማደሪያ፣ እንዲሁም የድህነቱን ሥራ ጨርሶ ከእርሷ የነሣውን ሥጋ ይዞ
(እንደ ተዋሐደ) ነውና ያረገው።
• ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ያያው መሰላል በላዩ መላእክት
መውጣታቸውና መውረዳቸው ደግሞ በእመቤታችን አማላጅነት
መሰላልነት የሰው ሁሉ ልመና ወደ ባሕርይ አምላክ ወደ እግዚአብሔር
ይደርሳልና ነው። ያለ እመቤታችን አማላጅነት ፀሎት ወደ እግዚአብሔር
አይደርስምና። (አንቀጸ ብርሃን)

፬.፮ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና ዘጸ ፫፥፪


- “የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል
ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል
አየ”
ሙሴም በሲና ያያት በእሳት የተከበበችው ቁጥቋጦ በእመቤታችን
ትመሰላለች ሐመልማሉ ከነበልባሉም፣ ነበልባሉ ከሐመልማሉ ጋር
አንዱ አንዱን ሳያጠፋ ተዋህደው መታየታቸው ጊዜያዊና ፍፃሜያዊ
ምሳሌ አለው።
ለዚያን ጊዜ የነበረው ምሳሌ
• ሐመልማሉ የእስራኤል ነበልባሉ ደግሞ የሚደርስባቸው መከራ፣
• ሐመልማሉን ነበልባሉ ሳያቃጥለው ማየቱ በመከራቸው አዝነው
ንስሐ ገብተው ነፃ ከመውጣት የተዘጋጀ አለመሆናቸውንና በመከራ
ውስጥ የሚጓዙ መሆኑን፣
• ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥላት ማየቱ መከራው የሚፀናባቸው
ቢሆንም ጨርሶ የማያጠፋቸው መሆኑን ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
• ፍፃሜው ግን ነበልባል የመለኮት ሐመልማሉ የእመቤታችን
ምሳሌ ነው።

ሥዕል ፰ ዕፀ ጳጦስ

• የእሳቱ ነበልባል በአካባቢው የነበሩት ሌሎች ቁጥቋጦዎች


ሲያቃጥል አንዲቱን ብቻ ያላቃጠለ መሆኑ መለኮት የተባለ እግዚአብሔር
ወልድን ልትሸከም የተመረጠች መሆኗን፣አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ
ከእርሷ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን በነሣ ጊዜ የመለኮት ባሕርይ
አላቃጠላትምና።

፶፩
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

• እርሷን ሳያቃጥል ሌሎችን ቁጥቋጦዎች ማቃጠሉ ግን የመለኮትን


ባሕርይ ለመሸከም ሌሎች የማይችሉ መሆናቸውንና የመለኮት ባሕርይ
የሚያቃጥላቸው መሆኑን ያስረዳል።

፬.፯ የጌዴዎን ፀምር መሳ ፮፥፴፮-፵


- “ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንደተናገርህ የእስራኤል ልጆች በእኔ
እጅ ታድን እንደሆን በአውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ጠጉር አኖራለሁ
በጠጉሩም ላይ ብቻ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን እንደተናገርህ
የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንድታድናቸው አውቃለው እግዚአብሔርም
በዚያ ሌሊት እንዲሁ አደረገ”
• ፀምር የእመቤታችን፣ ጠል የጌታ ምሳሌ ነው።
• ጠል በፀምሩ ላይ መውረዱ ከሦስቱ አካል አንዱ እግዚአብሔር
ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ
ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በማህፀኗ ማደሩንና ሥጋን ተዋህዶ ሰው
መሆኑን ያስረዳል።
• ጠል በምድር ላይ አለመውረዱ ሌሎች ሴቶች ለዚህ ታላቅ ክብር
አለመብቃታቸውን የሚያሳይ ነው።
• በሁለተኛም ጠል በምድር ላይ ሆኖ በፀምሩ ላይ አልወረደም።
ይኸውም በሌሎች ሴቶች ላይ ያለ መርገምና ኃጢአት ያላረፈባት
እመቤታችን ከአንእስተ ዓለም (ዓለም ውስጥ ካሉ ከሌሎች ሴቶች)
የተለየች የተባረከች መሆኗን ያስረዳል።

፬.፰ የአሮን በትር ዘኁ ፲፯፥፩-፲


- “እንዲህም ሆነ በነጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ
ገቡ እነሆ ምለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቆጠቆጠች ለመለመች
አበባም አወጣች የበሰለለው ዝም አፈራች፡፡… እግዚአብሔርም ሙሴን
እንዲህ ብሎ ነገረው ‘ማጉረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም
እንዳይማቱ ለማይሰሙ ልጆችም ልክ ትሆናት ጠብቅ ዘንድ የአሮንን
፶፪
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
በትር በምስክሩ ፊት አኑር፡፡’ ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር ሙሴን
እንዳዘዘው አደሩ እንዲሁ አደረጉ”
በዚህ ቃለ- እግዚአብሔር ላይ የዓሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ተወካዮች
ከነበሩት በትሮች መካከል የአሮን በትር ብቻ ሳይተክሏት ተተክላ፣ ውኃ
ሳያጠጧት አቆጥቁጣ ለምልማና አብባ፣ የበሰለ ለውዝ አፍርታ መገኘቷ
ተገልጧል።
• የአሮን በትር የእመቤታችን፣ ለውዝ የጌታችን ምሳሌ ነው።
• የአሮን በትር ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት አብባና አፍርታ
እንደተገኘች፤ እመቤታችንም ያለ ወንድ ዘር በታላቅ በማይመረመር
ምስጢር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፍፁም ንጽሕና ፀንሳ በፍፁም
ንጽሕና ወልዳለች።

ሥዕል ፱ በትረ አሮን

፶፫
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ታላቁ የቤተ-ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም በእሁድ ውዳሴ ማርያም


ድርሰቱ ላይ “ክርስቶስ አምላካችንን የወለድሽልን አንቺ ሳይተክሏት እንደ
በቀለች ውኃ ሳያጠጡአት ለምልማና አብባ እንደ አፈራችው የአሮን በትር
ነሽ ”በማለት ምሳሴነቷን በሚገባ ገልጧል።

፬.፱ ጽላተሙሴ ዘጸ ፴፬፥፩


- “እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ
ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን
ቃሎች ዕፅፍባቸዋለሁ።”
ሙሴ እስራኤል የሚመሩበትን አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምበትን
የቃል ኪዳን ፅላት ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብሎ ከሲና ተራራ ሲወርድ
ህዝቡ እግዚአብሔርን ትተው የጥጃ ምስል ሠርተው ለዚያ ሲሰግዱ
አገኘናቸው። ፅላቱንም ከእጁ ጥሎ ሰበራቸው።ከዚህ በኋላ ሌሎች ፅላቶችን
በእግዚአብሔር ትዕዛዝ አዘጋጅቶ የእግዚአብሔርን ሕግ ፃፈበት ህዝቡም
በዚያ ይመሩ ጀመር።
• የተሠሩበት ፅላቶች የአዳም እና የሔዋን ምሳሌዎች ናቸው።
ፅላቱ በእስራኤል ኃጢአትና በደል ምክንያት እንደተሰበረ ሁሉ አዳምና
ሔዋንም በበደል ወድቀው ከእግዚአብሔርም እጅ ተጥለው ነበር።
• ሁለተኛው ፅላት ግን የእመቤታችን ምሳሌ ነው።በተሰበሩት ምትክ
ዳግመኛ መሠራቱ በሔዋን ምክንያት የሞተው የሰው ልጅ ዳግማዊ
አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ በተገኘባት በቅድስት ድንግል ማርያም ምክንያት
የመዳኑ ምሳሌ ነው።
• የቀደመው ጽላት የአዳም ሁለት መሆኑ የነፍስና የሥጋው፣
• ያ እም ኀበ አልቦ እንደተገኘ አዳምም ከኅቱም ምድር ያለ ዘር ያለ
አባት ያለ እናት የመገኘቱ ምሳሌ፣
• ያ በጣዖት ምክንያት እንደተሰበረ አዳምም በዲያብሎስ ምክንያት
ወደ ስሕተት ለመውደቁ ምሳሌ።
• ሁለተኛው በሙሴ እጅ እንደተቀረጸ እመቤታችንም በዘር በሩከቤ
፶፬
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል
ከሐና ከኢያቄም የመገኘቷ ምሳሌ፣
• የኋላዎቹ መሰበር መሰንጠር እንዳላገኛቸው እመቤታችንም ጽነተ
ሥጋ ጽነተ ነፍስ አላገኛትም።
• በላዩ የተጻፈ ቃል የአካላዊ ቃል፣
• ያ በግብር አምላካዊ እንደተገኘ አካላዊ ቃልም በዘር በሩካቤ
ከተገኘች ከእመቤታችን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የመወለዱ ምሳሌ።
• ዐሥሩ ቃላት አጻጻፋቸው ወደ ላይ ሳይተርፉ ወደታችም
ሳይሰጥሙ ነው ይህም አለመትረፉ ሥጋ ለሥላሴ አራተኛ፣ ለቃል
ሁለተኛ ያለመሆኑ ምሳሌ ነው።
• በተጨማሪም ያቺ ጽላት ያማረች እንደሆነች እመቤታችንንም
ባማረ ባማረ ነገር ይመስላታል፣ ያቺ ዐሥሩ ቃላት እንደተጻፉባት
እመቤታችንም ማኅደረ ቃለ አብ ናትና፣
• ያቺ ሕጓን የጠበቀውን ከመቅሠፍት እንደምትሰውር ቅድስት
ድንግል ማርያምም በቃል ኪዳኗ በምልጃዋ የሚታመነውን ከሞተ ነፍስ
ትታደጋለች፣
• ያች ጽላት አራት ማዕዘን እንዳላት እመቤታችንም በአራቱ
ማዕዘናት ቅድስት ሆይ ለምኝልን ሳይላት የሚውል የለምና።
• እንዲሁም ጽላቷ የመለኮት እሳት እንዳላቃጠላት እመቤታችን
አምላክን በማህጸኗ በያዘች ጊዜ አለመቃጠሏን፣
• ጽላቷ አሥሩን ቃል ፈጽማ እንደያዘች እመቤታችንም ዐሥሩን
ቃላት በሙሉ የፈጸመች ከሰው ወገን እርሷ ብቻ መሆኗን ማሳያ ምሳሌ
ናት።

፶፭
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፬.፲ የሳሙኤል የሽቱ ቀንድ የናሆም መድኃኒት ፩ኛ ሳሙ፲፮፥፲፫ /


፩ኛ ሳሙ ፲፥፩

- “ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው


የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል
መጣ።ሳሙኤልም ተነስቶ ወደ አርማቴም ሄደ”
ሳሙኤል ነገሥታትንና ካህናትን እየቀባ የሚሾምበት ሽቱ የሚይዝበት
የሽቱ ቀንድ ነበረው። ከቀንዲቱ የሚወጣው ሽቱ አራት ዓይነት
ነበር፤አምስተኛም ዘይት ይጨመርበታል።ከዚያ ከነገደ ሌዊ ካህናትን
ከነገደ ይሁዳ ነገሥታትን ይቀባበታል።

• እመቤታችን ደግሞ ሥልጣነ ክህነትንና ነገሥትን የሚሰጥ እንደ


አራቱ ሽቱ አራቱን ባሕርያተ ሥጋ እንደ አምስተኛ ዘይት ባሕርየ ነፍስን
ጌታ ከእርሷ ነሥቷል እና በሳሙኤል የሽቱ ቀንድ እንመስላታለን።

የመልመጃ ጥያቄዎች
ትክክለኛውን መልስ መልሱ።
፩- እመቤታችንን ለምን በኖኅ መርከብ ተመሰለች?
፪- ሙሴ ያያት ዕፀ ጳጦስ እንዴት የእመቤታችን ምሳሌ እንደምትሆን
አስረዱ።
፫- እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክት ቃል ኪዳን የገባለት ጻድቅ ማን
ይባላል?
፬- እመቤታችንን ለምን በአሮን በትር ተመሰለች?

፶፮
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

ዋቢ መጻሕፍት
• ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ
• ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ
• ውዳሴና ቅዳሴ ማርያም
• ተአምረ ማርያም

፶፯
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት አራተኛ ክፍል

፶፰
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
የሰንበት ት/ቤት አመራር እና መምህራን
እንዲሁም ተማሪዎችና ወላጆች በመጽሐፉ ላይ
ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት እና ግብዓት
በሚከተለው አድራሻ ላኩልን

office@eotc-gssu.org
https://t.me/GSSUCurricu-
lum_bot

You might also like