You are on page 1of 3

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን የየረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የፈለገ ሕይወት

ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል የ 2015 ዓ.ም የ 8 ኛ ሀ ክፍል

የክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ማጠቃለያ ፈተና

ስም ክፍል ቁጥር ______

ትዕዛዝ ፩

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ሀሰት በማለት መልሱ፡፡

1. አንድ ክርስቲያን ሕሊናን የሚነካ ልብን የሚያሳዝን እና ከክብር የሚያሳንስ ክፉ ስድብ የሚሳደብ ከሆነ የነፍሰ ገዳይ ፍርድ
ይጠብቀዋል፡፡

2. በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረ የሰው ልጅ ሕይወቱን ማኖር፣መግደልና ማዳን ከአምላኩ የተሰጠው ስልጣን ነው፡፡

3. ሰው ዝሙትን በተገቢው በመፈፀሙ ብቻ የሚፈረድበት አይደለም፡፡

4. ምህረት መንፈሳዊ ማለት ሰውን ክፉ ሃይማኖት በጎ ሃይማኖት መስሎት ይዞት ሲኖር ክፉውን ሃይማኖት አስትቶ በጎውን
ሃይማኖት ማሳያዝ ነው፡፡

5. የሰው ፍቅር ሁሉን አስተካክሎ መውደድ ነው፡፡

6. ፍትወት የባህርይ ፆር የዝሙት፣የስስት ጠባይ የኃጢያት ጦስ ነው፡፡

7. ዝሙት ከሰው አልፎ ምድርን የሚያረክስና የሚያስረግም ክፉ በደል ነው፡፡

ትዕዛዝ ፪

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡

1----------ሰው ክፉውን ምግባር በጎ ምግባር መስሎት ይዞት ሲኖር መክሮ አስተምሮ ክፉውን ምግባር አስትቶ በጎውን ሃይማት
ማስያዝ ነው?

ሀ. ምህረት ነፍሳዊ ለ. ምህረት ስጋዊ ሐ. ምህረት መንፈሳዊ መ. ሀእና ሐ መልስ ናቸው

2.---------ሰውን ወደ መግደል ከሚያደርሱ መካከል አንዱ ምክኒያት ምንድ ነው?

ሀ. ስድብ ለ. ጥላቻ ሐ. ቁጣ መ. ሁሉም

3.--------ከሚከተሉት ውስጥ የሐዲስ ኪዳን ሕግጋትን ያስተማረው ማነው?

ሀ. ቅዱስ ማቴዎስ ለ. ቅዱስ ጴጥሮስ ሐ. ቅዱስ ዮሐንስ መ. መልስ የለም

4.-------ከሚከተሉት ውስጥ ወደ ዝሙት ኃጢያት ከሚገፋፉ ነገሮች የማይካተተው የትኛው ነው?

ሀ.ማየት ለ. ክፉ ባልጀርነት ሐ. አለባበስ መ. ምልስ የለም

5.-------ማለጥ የአእምሮ ሀሳብ እና ፈቃድ ማለት ነው?


ሀ. ጽድቅ ለ. ልብ ሐ. ተስፋ መ.ሁሉም

ትእዛዝ ፫

የሚከተሉትን በ" ሀ" ስር የተዘረዘሩትን በ"ለ" ስር ከተዘረዘሩት ጋር ተስማሚውን እየመረጣችሁ አዛምዱ ፡፡

ሀ ለ

1. በሐሰት አትማል ሀ. ምህረት ስጋዊ

2. ኦሪት ለ. በከንቱ አትቆጣ፣አትሳደብ

3. አትግደል ሐ. አንቀጸ ብጹአን

4. ዓይን በዓይን ጥርስን በጥርስ መ. መጽሔት(መስታወት)

5. ባልጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ ሠ.አነጋር

6. ሚስቱን የሚፈታት የፍችውን ጽህፈት ይስጣት ረ. ክፉውን በክፉ አትቃወም

7.ውጫዊ ሥነ-ምግባር ሰ.ወደ ሴት በማየት አትመኝ

8. አታመንዝር ሸ. አባ መባ ጽዮን

9. ውስጣዊ ሥነ-ምግባር ቀ. በፍፁም አትግደል

10.የሚገባ ሀዘን በ. ጠላትህን ውደድ

ተ. የመንግስት ሰማያት ምሳሌ

ቸ. ሚስትህን አትፍታ

ነ. እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው ትዕዛዝ

ትእዛዝ ፬

ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች በተጠየቀው መሰረት መልስ ስጡ፡፡

1. የእግዚአብሔር ሕግ በጹሁፍ መቅረብ እስካልቻለበት ጊዜ ድረስ ሰዎች የእግዚአሔርን ሕግ እንዴት ያውቁ ነበር?

2. ሕገ ትሩፋት ፣ አንቀጸ ብጹአንን ዘርዝሩ?

3. ስድስቱ ቃላተ ወንጌል የሚባሉት እናማናቸው? በአጭሩ አብራሩ

4. ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር መማርህ/ሽ የሰጠህ/ሽ ጥቅም በአጭር ግለፅ/ጪ?

5. የብጹአን ማዕረግ ስንት ናቸው? አብራሩ

ዳረንጎት

1.አንድ ልጅ ትናትና እናንተ የቤተክርስቲያን ልጆች አይደላችሁም? ኃጢያት ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ስያሜ ለምን
ተሰጠው ብሎ ጠየቀኝ ምን በዬ ላስረዳው?

You might also like