You are on page 1of 27

ምዕራፍ 1

፩.፩ መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )


ክፍል ፩
መጠይቃን ቃላት የምንላቸው ነገሮችን በፈለግነው መንገድ እንድንጠይቅ የሚያረጉን ናቸው። እነሱም የሚከተሉት
ናቸው።
• መኑ ➾ ማን | Who
• ምንት ➾ ምን | What
• ማእዜ ➾ መቼ | When
• አይቴ ➾ የት | Where
• አይ ➾ የቱ | Which
• እፎ ➾ እንዴት | How
• እስፍንቱ ➾ ስንት | How much
ክፍል ፪
፩. ለጠይቆተ ሰብእ (Who - Asking Person )
• መኑ ➾ ማን
• እለመኑ ➾ እነማን
ምሳሌ
➛ መኑ ውእቱ ስምከ? (ማን ነው ስምህ ?)
• ኤርምያስ ውእቱ ስምየ። (ስሜ ኤርምያስ ነው።)
➛ እለመኑ መጽኡ ትማልም? (ትናንት እነማን መጡ?)
• እለ አቤል መጽኡ። (ትናንት እነ አቤል መጡ።)
➛ መኑ ይእቲ እምከ? (እናትህ ማን ናት ?)
• ሐና ይእቲ እምየ። (እናቴ ሐና ናት።)
➛ መኑ መጽአ? (ማን መጣ ?)
• ክንፈ መጽአ። (ክንፈ መጣ።)
➛ እለመኑ አክበሩ አድዋ? (አድዋን አነማን አከበሩ?)
• ብዙኀኑ አክበሩ አድዋ። (አድዋን ብዙዎች አከበሩ።)
ክፍል ፫
፪ . ለጠይቆተ ነገራት (What - Asking things)
• ምንት ➾ ምን
• ምንተ ➾ ምንን

ምሳሌ
➛ ምንት መጽአ ናሁ? (አሁን ምን መጣ?)
• ከልብ መጽአ። (ውሻ መጣ።)
➛ ምንተ ታፈቅር ? (ምንን ትወዳለህ?)
• አነ አፈቅር ግብር ፡፡ (እኔ ሥራ እወዳለሁ፡፡)
➛ ምንት ገበርከ ናሁ ? (አሁን ምን ሠራኸ?)
• ግብረ ቤት ገበርኩ ፡፡ (የቤት ሥራ ሠራሁ፡፡)
➛ ምንት ገበርኪ ትማልም ? (ትናንት ምን ሰራሽ?)
• አንበብኩ መጽሐፍ ትማልም ፡፡ (ትናንት መጽሐፍ አነበብኩ፡፡)
➛ ምንት ተመሀርክሙ ትማልም? (ትናንት ምን ተማራችሁ?)
• በእንተ አድዋ ተማሀርነ ትማልም፡፡ (ትናንት ስለ አድዋ ተማርን፡፡)
➛ ምንተ ታፈቅሩ አርድእት ? (ተማሪዎች ምንን ትወዳላችሁ?)
• ንሕነ ናፈቅር ተውኔት ፡፡ (እኛ ጨዋታ እንወዳለን፡፡)
ክፍል ፬
፫ . ለጠይቆተ ጊዜ (When - Asking times)
• ማዕዜ - መቼ
• እስከ ማዕዜ - እስከ መቼ
ምሳሌ
➛ ማዕዜ ተወለድከ ? (መቼ ተወለድክ) • በወርኃ መስከረም ፡፡ (በመስከረም ወር)
➛ ማዕዜ ማዕዜ ውእቱ ትምህርተ ግእዝ? (የግእዝ ትምህርት መቼ መቼ ነው)
• ዕለተ ሐሙስ ወ ዕለተ ዓርብ ፡፡ (ዕለተ ሐሙስ ና ዕለተ ዓርብ)
➛ ማዕዜ ውእቱ ፈተና ? (ፈተና መቼ ነው)
• ጌሠም ውእቱ ፈተና ፡፡ (ፈተና ነገ ነው)
➛ ማዕዜ ተሐውሪ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ? (ወደ ቤተ ክርስቲያን መቼ ትሄጂያለሽ)
• በዕለተ ሰንበት ፡፡ (በዕለተ እሑድ)
➛ ማዕዜ ይመጽእ መምህር ? (መምህር መቼ ይመጣል)
• ጌሠም ይመጽእ መምህር ፡፡ (መምህር ነገ ይመጣል)
➛ እስከ ማዕዜ ውእቱ ዘትመጽእ ? (እስከ መቼ ነው የምትመጣው)
• እስከ ዘይመጽእ ወርኀ ፡፡ (እስከ ሚመጣው ወር)
ክፍል ፭
፬ . ለጠይቆተ መካን (ቦታ) (Where - Asking place)
• አይቴ ➾ የት
• ኅበ አይቴ ➾ ወዴት
• እም አይቴ ➾ ከየት
ምሳሌ
➛ አይቴ ውእቱ ቤተ ትምህርትከ ? (ትምህርት ቤትህ የት ነው)
• ጎንደር ውእቱ ፡፡ (ጎንደር ነው)
➛ አይቴ ይእቲ እምኪ ? (እናትሽ የት ናት)
• አክሱም ይእቲ እምየ ፡፡ (እናቴ አክሱም ናት)
➛ አይቴ ተወለድኪ ? (የት ተወለድሽ)
• አነ አዲስ አበባ ተወለድኩ፡፡ (እኔ አዲስ አበባ ተወልድኩ ፡፡)
➛ ኅበ አይቴ ተሐውሪ ? (ወዴት ትሄጂያለሽ)
• ኅበ ቤተ ትምህርት ፡፡ (ወደ ትምህርት ቤት)

➛ እም አይቴ መጻእከ ? (ከየት መጣኸ)


• እም ቤትየ መጻእኩ ፡፡ (ከቤቴ መጣኹ)
➛ ኅበ አይቴ ተሐውር መርድእ ? (ወዴት ትሄዳለህ ተማሪ)
• ኅበ ቤተ ትምህርት ፡፡ (ወደ ትምህርት ቤት)
ክፍል ፮
፭ . ለጠይቆተ ኲነት (How - Asking process)
• እፎ ➾ እንዴት
ምሳሌ
➛ እፎ ኃደርከ ? (እንዴት አደርክ)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ ፡፡ (እግዚአብሔር ይመስገን፡)
➛ እፎ ወአልክሙ አርድእት ? (እንዴት ዋላችሁ ተማሪዎች)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ መምህር ፡፡ (እግዚአብሔር ይመስገን መምህር፡)
➛ እፎ ኀደርኪ ኦ እምየ ? (እናቴ ሆይ እንዴት አደርሽ)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ ፡፡ (እግዚአብሔር ይመስገን)
➛ ትምህርት እፎ ውእቱ ? (ትምህርት እንዴት ነው)
• ሠናይ ውእቱ ፡፡ (ጥሩ ነው)
➛ ግብር እፎ ውእቱ ? (ሥራ እንዴት ነው)
• ጥቀ ሠናይ ውእቱ ፡፡ (በጣም ጥሩ ነው፡)
➛ እፎ አንተ ? (እንዴት ነኽ)
• ዳኅና አነ ፡፡ (ደኅና ነኝ)
➛ ሕይወት እፎ ውእቱ ወልድየ ? (ሕይወት እንዴት ነው ልጄ)
• አኮ ሠናይ አቡየ ፡፡ (መልካም አይደለም አባቴ)
ክፍል ፯
፮ . ለጠይቆተ ኁልቁ (How Many - asking quantity)
• ስፍን ➾ ስንት
• እስፍንቱ ➾ ስንት
• እስፍንተ ➾ ስንትን
ምሳሌ
➛ እስፍንቱ ውእቱ ዕድሜኪ ? (ዕድሜሽ ስንት ነው)
• እስራ ውእቱ ዕድሜየ ፡፡ (ዕድሜዬ ሃያ ነው)
➛ እስፍንቱ ውእቶሙ አኀዊከ ? (ወንድሞችህ ስንት ናቸው ?)
• ክልዔቱ ውእቶሙ ፡፡ (ሁለት ናቸው ፡፡)
➛ እስፍንቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ ? (አሁን ስንት ሰዓት ነው ?)
• ተስዓቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ ፡፡ (አሁን ዘጠኝ ሰዓት ነው ፡፡ )
➛ ስፍን ውእቱ ዝንቱ ? (ይኸ ስንተ ነው ?)
• ዐሠርቱ ብር ውእቱ ፡፡ (ዐሥር ብር ነው ፡፡)
➛ እስፍንቱ አርድእት መጽኡ ዮም ? (ዛሬ ስንቱ ተማሪዎች መጡ)
• ብዙኀኑ መጽኡ ፡፡ (ብዙዎቹ መጡ)
➛ እስፍንተ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ ? (ክርስቶስ ስንት ሐዋርያትን መረጠ)
• ዐሠርተ ወክልዔተ ሐዋርያተ ፡፡ (አሥራ ሁለት ሐዋርያትን፡)
፩.፩ ምልማድ
፩. ከመጠይቃን ቃላት ውስጥ የማይካተተው የቱ ነው?
ሀ. ስፍን
ለ. እፎ
ሐ. እስፍንቱ
መ. ውእቱ
ሠ. ሁሉም
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ቦታን ለመጠየቅ የሚያገለግለው የቱ ነው?
ሀ. መኑ
ለ. እፎ
ሐ. አይቴ
መ. ምነት
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ቁጥርን ለመጠየቅ የሚያገለግለው የቱ ነው?
ሀ. አይቴ
ለ. እስፍንቱ
ሐ. ማዕዜ
መ. መኑ
፬. "____ ተወለድከ?"
ሀ. አይቴ
ለ. ማዕዜ
ሐ. መኑ
መ. ሀ እና ለ

፭. "____ ውእቱ ስምከ?"


ሀ. መኑ
ለ. ምንት
ሐ. እፎ
፮. "እፎ ወአልክሙ ____?"
ሀ. አርድእት
ለ. አብርሃም
ሐ. መምህር
፯. "____ ሰዓት ውእቱ ናሁ?"
ሀ. እፎ
ለ. አይቴ
ሐ. እስፍንቱ
መ. መኑ
፰. "_____ ታፈቅሪ?"
ሀ. ምንተ
ለ. መኑ
ሐ. አይቴ
መ. ሀ እና ለ
፱. ማዕዜ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ስንት
ለ. እንዴት
ሐ. መቼ
መ. ማን

፲. "____ ውእቱ ቤተ ትምህርትከ?"


ሀ. ማዕዜ
ለ. መኑ
ሐ. አይቴ
መ. እስፍንቱ

፩.፪ ራስን በግእዝ ስለመግለጽ


• በአዳዲስ አጋጣሚዎች እና የዕለት ከዕለት ክንዋኔዎች ውስጥ ትውውቅ ትልቁን ቦታን ይወስዳል፡፡ ከዚህ በመቀጠል
በግእዝ ቋንቋ እንዴት ራስን ማስተዋወቅ እንደሚቻል እናያለን፡፡
➛ ዮሐንስ እትበሀል ወመኑ ስመዚአከ…
• (ዮሐንስ እባላለሁ ያንተስ ስም ማን ይባላል)
➛ ፍሡሕ አነ በተራክቦትነ ወእትበሀል ዮሐንስ….
• በመገናኘታችን ደስተኛ ነኝ ዮሐንስ እባላለሁ
➛ እፈቱ እትናገር በእንተርእስየ ወበቀዳሚ ዮሐንስ ስምየ……
• ስለራሴ መናገር እወዳለሁ በመጀመሪያም ስሜ ዮሐንስ ይባላል።
➛ሰላም ለክሙ ዮሐንስ ስምየ ወአነ ውዕቱ ዘተሰየምኩ ውስተ ዝንቱ አውደግብር በላዕሌክሙ....
• ሰላም ለናንተ ይሁን ስሜ ዮሐንስ ይባላል በዚህ ስራ መስክ በናንተ ላይ የተሾምኩት እኔ ነኝ።
➛ሰላም ለከ ሩት ስምየ ወፍሡሕ አነ በተራክቦትነ....
• ሰላም ላንተ ይሁን ስሜ ሩት ይባላል በመገናኘታችን ደስተኛ ነን።
➛ሰላም ለከ አብርሃም ሩት እትበሀል....
• ሰላም ላንተ ይሁነ አብርሃም ሩት እባላለሁ።

• ከትውውቅ በኋላ የሚሰጡ ምላሾች

➛ፍሡሕ አነ በተራክቦትነ…
• በመገናኘታችን ደስተኛ ነኝ።
➛ሰላም ለከ ወፍሡሕ አነ በአእምሮተ ኪያከ…
• ሰላም ላንተ ይሁን አንተን በማወቄ ደስተኛ ነኝ።
፩.፫ ምድብ ተውላጠ ስሞች መራሕያን
➛ መራሕያን : መርሐ = መራ መራሒ = የመራ መራሕያን = መሪዎች ወይም መርሖ = ቁልፍ መራሕያን =
ቁልፎች ማለት ነው፡፡
➛ ስፍን ውእቱ ? ስንት ናቸው ? = ዐሠርቱ ውእቱ፡፡ 10 ናቸው፡፡
➛ ባለቤት መራሕያን
ውእቱ = እርሱ ወንድ፣ ነጠላ ፣ሩቅ
አንተ = አንተ ወንድ፣ ነጠላ፣ቅርብ
ውእቶሙ = እነርሱ ወንዶች፣ብዙ፣ሩቅ
አንትሙ = እናንተ ወንዶች፣ቅርብ፣ብዙ
ይእቲ = እርሷ ሴት፣ነጠላ፣ሩቅ
አንቲ = አንቺ ሴት፣ ነጠላ፣ቅርብ
ውእቶን = እነርሱ ሴቶች፣ብዙ፣ሩቅ
አንትን = እናንተ ሴቶች፣ቅርብ፣ብዙ
አነ = እኔ ነጠላ
ንሕነ = እኛ ብዙ
➛ በመደብ ሲከፈሉ የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡
፩. አነ = እኔ
ንሕነ = እኛ
፪. አንተ = አንተ
አንትሙ = እናንተ
አንቲ = አንቺ
አንትን = እናንተ
፫. ውእቱ = እርሱ
ውእቶሙ = እነርሱ
ይእቲ = እርሷ
ውእቶን = እነርሱ
1ኛ መደብ ሩቅም ቅርብም አይደሉም፡፡ ምክንያቱም ሩቅ ቅርብ ለማለት ንጽጽር ያስፈልጋል። 2ተኛ መደብ
ቅርብ ናቸው፡፡ 3ተና መደብ ሩቅ ናቸው፡፡
፩. ፬ ነባር አንቀጽ ( የመሆን ግስ )
➛ ግስ : ድርጊትን የሚገልጡ ቃሎች ናቸው፡፡
ምሳሌ፦ ሞተ = ሞተ (የነፍስ ከሥጋ መለየትን)
መስየ = መሸ (መዓልቱ አልቆ ሌሊቱ የመተካቱ)
ሀበነ = ስጠን ( ልመናን )
ጸልዩ = ጸልዩ ( የአምላክ ትእዛዝን ያመለክታል )
ምሳሌ፦
ሰበከ፣ኀደገ፣መርሐ፣ቶስሐ፣ሴመ፣ሴጠ፣በርሀ፣አጸንሕሐ፣ተንበለ፣ጦመረ፣ዖደ፣ዐደመ(ቀጠረ)፣አደመ፣ሬመ
መለከ፣ነጸረ፣ዘመረ፣መነነ፣ረድአ፣ኀደፈ፣ሠረቀ፣ደፈነ፣ፈተለ፣ሰደደ፣ሰገደ፣ዐረበ፣ገብረ፣ወጽአ፣መስየ፣ኀረየ
ውህዘ፣ሴመ፣ሰተየ፣ሴሰየ፣መርሐ፣አኀዘ፣ቆመ፣ከብደ፡፡

➛ አዕማድ ማለት ምሰሶዎች ቋሚዎች ማለት ሲሆኑ አዕማድ የተባሉ 5 ናቸው፡፡

እነርሱም ፦ አድራጊ
አስደራጊ
አስደራራጊ
ተደራራጊ
ተደራጊ

➛ አንድ ግስ ብዙ ትርጉም ሊኖረው ይችላል፡፡


ምሳሌ፦ ሰብሐ = አመሰገነ “ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በቅዱሳኑ”
ሰብሐ = አበራ “ወተሰብሐ ገጹ ለሙሴ”
ሰብሐ = ገለጠ “ሰብሖ ለምሕረትከ”
ሰብሐ = አከበረ “አባ ሰብሐኒ”
ሰብሐ = ሰቀለ “በጽሐ ጊዜሁ ከመ ይሰባሕ ወልደ እጓለ እመሕያው”
ሰብሐ = አስመለሰ “አብ ሰብሖ ለወልዱ”

ምሳሌ፦ ባረከ = መረቀ “አድንኑ አርስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ”


ባረከ = ረገመ “ወባረከ ኢዮብ ዓመተ ልደቱ”
➛ ግስ የዓረፍተ ነገር መደምደምያ ነው፡፡
ምሳሌ፦ አምላክ አፍቀረ ሰብአ፡፡
ድንግል ወለደት አምላከ፡፡
ሐዋርያት አጥመቁ አሕዛበ፡፡
➛ ግስ በ ተሻጋሪ እና ኢ-ተሻጋሪ ግስ ተብሎ በ 2 ይከፈላል፡፡

፩. ተሸጋሪ ግሥ ምንን የሚል የሚያመጣ የሚስብ፡፡


ምሳሌ፦ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸለየ … ውዳሴ ማርያም፡፡
ኢዮብ ባረከ፡፡
ሐዋርያት አጥመቁ፡፡

፪. ኢተሻጋሪ ግሥ ምንን የሚል የማያመጣ የማይስብ፡፡


ምሳሌ፦ አዳም ሞተ፡፡
አምላክ ተሰቅለ፡፡
አኅዘነነ ለነ ዮሐንስ፡፡

➛ ሁሉም የግእዝ ግሶች ሥርወ ግስ (መነሻ ግስ) አላቸው፡፡ እነዚህም መነሻ ግሶች በ 7ቱም ሆሄ ሊጀምሩ
ይችላሉ የሚጨርሱት ግን በግእዝ ወይም በመጀመርያ ሆሄ ነው፡፡
ምሳሌ ፦ ሥርወ ግሥ ማለት ይበላል ይብላ ወ.ዘ.ተ ከማለቱ በፊት ሁሉም የመጡበት በላ የሚለው ቃል ነው፡፡
ይሄዳል ሄዶ ሲሄድ መሄድ አካሂዶ የሄደ የሄደች ………… ሄደ የሚለው ቃል ነው፡፡
በተመሳሳይ በግእዙም ሰገዱ ስግዱ ሰገድክሙ ሰገዳ ሰጊድ ስግደት ንስግድ …. ሰገደ የሚለው ቃል ነው፡፡
ቡሩክ ቡሩካን ቡርክት መባረክ ባራኪ ቡራኬ ባርኮ ….. ባረከ የሚለው ቃል ነው፡፡

፩.፭ አመልካች ቅጽል


በስሞች ወይም በነገሮች ላይ እየተጨመረ ትርጓሜያቸውን የሚገልጽ ቃል ሁሉ ቅጽል ይባላል። በዓረፍተ ነገር
ውስጥ አንዳች ነገር በተነገረ ጊዜ ምን ዓይነት የቱ ስንት የትኛው የሚል ጥያቄ ይገጥመን ይሆናል ይህን የጥያቄውን
ቃል ለመሙላትም ሌላ ቃል እንድንጨምርበት ግድ ይሆናል። በዚህ ጊዜ እየጨመርን የነገሩን ትርጓሜ የምንገልጽበት ቃል
ቅጽል ይባላል።
፩.፮ አመልካች ተውላጠ ስም

፩) ዝንቱ፣ዝ___ይህ
፪) ዛቲ፣ዛ_ይህች
፫) ዝኵ፣ዝስኵ፣ዝክቱ____ያ
፬) እንታክቲ፣ እንትኵ____ያች
፭) እሉ፣ እሎንቱ___እነዚህ
፮) እላ፣እሎን፣ እላንቱ፣__እነዚህ (ሴ)
፯) እልኰን፣ እልክቶን___እነዚያ(ሴ)
፰) እልኵ፣ እልክቱ____እነዚያ
በዓረፍተ ነገር ባለቤት ሆነው ሲያገለግሉ ለምሳሌ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።ትርጉሙ ለዘለዓለም ማረፊያየ ይች
ናት ማለት ነው። ቅጽል ሆነው ሲያገለግሉ ዳህንኑ ዝስኵ አቡክሙ ይላል። ትርጉሙ ያ አባታችሁ ደህና ነውን ማለት
ነው። ተሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ። አፍቅር ዛተ ቢል ያችን ውደዳት ማለት ነው።

የ"ዘ፣እለ፣እንተ" አስሩ ዝርዝርም ተናበው አመላካች የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ትርጉማቸውም እንደሚከተለው ነው።
፩) ዚኣሁ/እንቲኣሁ___የእርሱ
፪) ዚኣሆሙ/እንቲኣሆሙ__የእነርሱ
፫) ዚኣሃ/እንቲኣሃ___የእርሷ
፬) ዚኣሆን/እንቲኣሆን__የእነርሱ
፭) ዚኣከ/እንቲኣከ___የአንተ
፮) ዚኣክሙ/እንቲኣክሙ__የእናንተ
፯) ዚኣኪ/እንቲኣኪ___የአንቺ
፰) ዚኣክን/እንቲኣክን___የእናንተ
፱) ዚኣየ/እንቲኣየ____የእኔ
፲) ዚኣነ/እንቲኣነ_የእኛ
ሲናበቡ አመልካች ቅጽል ይሆናሉ። ለምሳሌ ሀገረ ዚኣነ ቢል ትርጉሙ የእኛ ሀገር ማለት ነው። ሕይወተ ዚአኪ ሲል
የአንቺ ሕይወት ተብሎ ይተረጎማል። የእኔ ሀገር ለማለት ዚኣየ ሀገር አይባልም። ከዚያ ይልቅ ሀገረ ዚኣየ ይላል እንጂ።
እንተ ለሴት ሲሆን፣ ዘ ደግሞ ለሴት ለወንድ ለአንድ ለብዙ ይሆናል። እለ ለብዙ ይሆናል።ሲዘረዘርም እንደሚከተለው
ነው።
፩) እሊኣሁ___የእርሱ
፪) እሊኣሆሙ__የእነርሱ
፫) እሊኣሃ____የእርሷ
፬) እሊኣሆን___የእነርሱ
፭) እሊኣከ____የአንተ
፮) እሊኣክሙ___የእናንተ
፯) እሊኣኪ____የአንቺ
፰) እሊኣክን___የእናንተ
፱) እሊኣየ____የእኔ
፲) እሊኣነ____የእኛ
ይላል። ለምሳሌ እልመክኑን ወረደ ውስተ ዓለም ወእሊኣሁ ሰቀልዎ ሲል ትርጉሙ ጌታ ወደ ዓለም ወረደ የእርሱ
ወገኖችም ሰቀሉት ተብሎ ይተረጎማል።

ምዕራፍ ፪
፪.፩ ሰላምታ አሰጣጥ በግእዝ
ሰላምታ
በግእዝ ቋንቋ ሰላምታ ለመለዋወጥ የምንጠቀማቸው ቃላት:-
ጠዋት ላይ:-
እፎ ኀደርከ__እንዴት አደርክ
እፎ ኀደርኪ__እንዴት አደርሽ
እፎ ኀደርክሙ__እንዴት አደራችሁ
እፎ ኀደርክን__እንዴት አደራችሁ
እፎ ኀደርክን የምንለው ሴቶች ብቻ ካሉ ነው። ሴቶችና ወንዶች ተቀላቅለው ካሉ በአንትሙ እፎ ኀደርክሙ ይሄዳል።
ከሰዓት ደግሞ:-
እፎ ወዐልከ___እንዴት ዋልክ
እፎ ወዐልኪ___እንዴት ዋልሽ
እፎ ወዐልክሙ__እንዴት ዋላችሁ
እፎ ወዐልክን___እንዴት ዋላችሁ
ምሽት ሲሆን ደግሞ እፎ አምሰይከ፣ እፎ አምሰይኪ፣ እፎ አምሰይክሙ፣ እፎ አምሰይክን ይላል ማለት ነው። ለዚህ ሁሉ
መላሹ "እግዚአብሔር ይሰባሕ" ይላል። እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው። ሌላ የሰላምታ ዓይነቶችም አሉ:-
ሰላም ለከ___ሰላም ለአንተ ይሁን
ሰላም ለክሙ_ሰላም ለእናንተ ይሁን
ስላም ለኪ__ሰላም ለአንቺ ይሁን
ሰላም ለክን__ሰላም ለእናንተ ይሁን
ይላል ማለት ነው። በተጨማሪም እንዴት አደርክ እንዴት ዋልክ ሰላም ነህ ወይ ለማለት አንድ ቃል አለ። ይኽውም:-

በሐከ_እንዴት ዋልክ/አደርክ፣ሰላም
በሐኪ_እንዴት ዋልሽ/አደርሽ፣ሰላም
በሐክሙ_እንዴት ዋላችሁ/አደራችሁ፣ ሰላም
በሐክን_እንዴት ዋላችሁ/አደራችሁ፣ ሰላም
፪.፪ ግእዝ ንባብ
ፍኖተ ንባብ ዘልሳነ ግእዝ
{የግእዝ ቋንቋ የንባብ መንገድ)
-ይህንን ማወቅ ግእዝ ቋንቋን ለመናገርና ለማንበብ ይጠቅማል
-ይህም የሚዳብረው ሕጉን ተምሮ መጻሕፍትን ሲያናብቡበት ነው
-ለዚህም ልምምድ ከመዝሙር ዳዊት ላይ በምልክት ስለተቀመጠ እርሱን መላልሶ ማንበብ ነው
-እነዚህ የተቀመጠው ጉልህ የሆነው ሕግ ነው
-ውስጣዊ ሕጎች በየትምህርቱ ይገኛሉ
ንባብ ግእዝ

ዓበይት ንባባት ንኡሳን ንባባት


ወዳቂ ዐራፊ/ቀዋሚ
ተነሽ ተናባቢ
ሰያፍ ቆጣሪ
ተጣይ ጠቅላይ
ጠባቂ
ልህሉህ
ጎራጅ
ጥያቄያዊ
ትርአስ ንባባት
-ንኡሳን ንባባት በዓበይት ንባባት ሥር ያሉ ናቸው
-እነዚህም -ግስን ከነርባታው ለማንበብ -ነባርን ለማንበብና
-በዐረፍተ ነገር ውስጥ የቃላትን አነባበብ ለመለየት ይረዳሉ
ዓበይት ንባባት
ወዳቂ - ይህ የሚሰበር ዕቃን ተጠንቅቆ እንደማስቀመጥ አኳኋን የሚነበብ ነው
-በሰባቱ ፊደላት ይጨርሳል(ይፈጽማል) -በሳድስ ግን ዝ በሚለው ነባር ብቻ ይገኛል
በግእዝ ሲጨርስ
አሐደ ፣ክልዔተ፣ሠለስተ አሐዝ ቅጽል ዘ ፣እንትኰ ፣ህየ -በግእዝ የሚጨርሱ አገባባት ብዙዎቹ
አምጣነ ፣እስመ ፣አመ፣ከመ -እነዚህ ከሌላ ጋር ይናበባሉ የራሳቸው ጠባይ ግን ወዳቂ መሆን ነው፡፡
-ይህ ወዳቂ ንባብ ሲነበብ መድረሻ ፊደሉን ያዝ ቆየት በማድረግ የሚነበብ የንባብ ሥርዓት ነው
በካዕብ ሲጨርስ
አሐዱ ፣ክልዔቱ ፣ሠለስቱ አሐዝ ቅጽል እሉ ፣ዝንቱ ፣እሙንቱ፣እማንቱ ኩሉ
በሣልስ ሲጨርስ አሐቲ ፣ክልዔቲ የሴት አኀዝ ቅጽል ዛቲ የሴት አማሪ ቅጽል ቀዳሲ ፣ኰናኒ ፣ቀታሊ ሣልስ ቅጽል
አረጋዊ ፣ኢትዮጲያዊ ወገን ቅጽል ብእሲ ፣ከይሲ ነገር ቅጽል
በራብዕ መና ደመና፣ዜና፣ዕዝራ፣ቤታ
በኀምሳ ፡- አውሴ፣ምናሴ፣ሙሴ፣ቅዳሰተ
በሳድስ ዝ፣ በእንተዝ ፣ከመዝ፣ ህየንተዝ፣ ፍዳዝ፣ተውላጠዝ
በሳብዕ ቀዲሶ ፣ቀቲሎ ፣ነቢሮ በዝ አንቀጽ መሰንቆ -ነባር ባረኮ ፣ሴስዮ ፣አእመሮ ውእቱ ለውእቱ (ዝርዝር) እፎ
-አገባብ
ተነሽ ንባብ
-እንደ ቁጣ ቃል ያለ ንግግር ነው -ተነባቢው ቀለም ቅድመ መድረሻው ነው -በአምስት ፊደላት ይጨርሳል
ግእዝ፣ካዕብ፣ሣልስ፣ራብዕ፣ሳብዕ ናቸው፡፡-አብዛኛዎቹ ከግሥና ከግሥ ክፍል የተመሠረቱ ናቸው
ግእዝ ቀተለ ፣ቀድ ፣ባረከ፣ማሕረከ ፣ሴስየ ፣ክህለ ፣ጠመረ ፣ተንበለ መሠረታዊ ግሥ በ፰ቱ የግሥ አርእስት
ቤተየ -የአለዝርዝር ቤተ -ተሳቢ
ካዕብ ሑሩ -በአንትሙ ትእዛዝ ቀተሉ -ውእቶሙ ገበርክሙ -አንትሙ
ሣልስ ሑሪ ፣ብልዒ ፣ሳአሊ ፣ንበሪ የአንቲ ትእዛዝ
ራብዕ ቀደሳ ፣ንበራ ውእቱ ንግራ ፣ርእያ የአንተን ትእዛዝ
ሳብዕ ሀቦ ፣ቅትሎ ፣ኰንኖ አንተ ለውእቱ ንወድሶ ፣አወድሶ ትወድሶ የዝርዝር እርባታ
ተጣይ ንባብ
-ቅድመ መድረሻውን ፊደል ያዝ አድርጎ ማንበብ ነው -በሳድስ ይጨርሳል
ምሳሌ ዮም ፣ጌሠም ዓለም አገባብ ሞት ፣ዖፍ ስም ቅዱስ ፣ቅቱል ፣ቡሩክ ፣ሲሉይ ቅ. ሳድ ሰው .ዘ ቅጽል
ከግሥ የሚገኙ ስሞች
አዳም ፣ክብር ፣ፍቅር ፣ጣዕም ፣ቀሳውስት ፣አርድእት የስም ብዜቶች
ሰያፍ ንባብ
-እንደ ተነሽ ንባብ ሆኖ መድረሻው ሳድስ ነው -የግሥና የተጸውዖ ስሞችን ያጠቃልላል
ምሳሌ
ዮሐንስ አማኑኤል ይቅትል/ይቀትል ማርቆስ ገብርኤል ይገብር/ይግበር ጤግሮስ አቤል አእመረት ትትሐነጽ
-እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ንባባት ለቅኔ ዜማ መጠባበቂያ አዋጅ አላቸው
-እነዚህ ንባባት ሕግን በማጥናት ብቻ አይታወቁም መጽሐፍት ሲነበቡ ለመስማት እንጂ
-ሕጉ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው እንጂ ንባብ ታወቀ ማለት አይደለም
ንኡሳን ንባባት
-ከዐበይት ንባብት የወጡ ናቸው
-በዐ.ነገር ውስጥ ቃላት እንዴት እንደሚነበቡ የሚያሳይ ነው፡፡
፩ ዐራፊ/ቀዋሚ ንባብ
-እያረፉ እየተነሱ ቃላትን ከቃላት ሳያያይዙ ማለት ነው
-አክብር አባከ ወእማከ ሑር ወብላዕ ስራረከ ኢትንበሩ በአሐዱ መካን እፎ ትጼእል አንተ ግዲ ኢበልዐ
-ብዙዎቹ የግእዝ ዐ.ነገች በዕራፊነት ይነበባሉ አስተውሉ
፪ ተናባቢ ንባብ
-ተናባቢ ንባብ ማለት አንዱ ቃል ከሌላው ጋር በስተመድረሻው ባለው ፊደል
ግእዝ ፣ራብዕ ፣ኃምሳ ሳብዕ ሆኖ የሚናበብበት ነው -ይህም ሳድስ --ግእዝ --ግእዝ --ግእዝ
ካዥብ --ሳብዕ ሣልስ --ኃምሳ ራብዕ --ራብዕ ኃምስ --ኃምሳ ሳብዕ --ሳብዕ
ምሳሌ በግእዝ በሳብዕ በኃምሳ
ዕፀ ሕይወት መሰንቆ ዳዊት ጽጌሃይማኖት
ሞተ ውሉድ ትክፎ ነግድ ውዳሴ አምላክ
በራብዕ
ደመና ሙሴ ደብተራ ኦሪት ሲለወጥ ዕፅ+ሕይወት --ዕፀሕይወት ሳድስ ግእዝ
መሰንቆ+ዳቂት --መሰንቆ ዳዊት ሳብዕ ሳብዕ
ጽጌ +ሃይማኖት --ጽጌ ሃይማኖት ኃምስ ኃምስ
ደመና +ሙሴ --ደመና +ሙሴ ራብዕ ራብዕ
ሁለትና ከዚያ በላይ ቃላት ሊናበቡ ይችላሉ
ባለ ሁለት ተናባቢ ባለሦስት ባለአራት
ዕፀ ሕይወት ከመ ጽጌ ገዳም ከመ ልገተ ዐቃቤ ቀምሕ
ባለ አምስ
ከመ እንተ ወላዴ ሃይማኖተ ክርስቲያን -ሌሎቹንም በዚሁ አስተውል
የሚናበቡ ቃላት
ዘ/አርእስት(ንኡስ አንቀጽ) -ይህ በግሥ እርባታ ስድስተኛ ረድፍ ላይ የሚገኝ ስም ነው
ምሳሌ ቀተለ --ይቀትል ፣ይቀትል ፣ይቅትል ፣ይቀትል፣ቀቲል/ቀቲሎት --አርእስት
ሲናበብ
ቀቲል +አርዌ --ቀቲለ አርዌ-አውሬን መግደል ቀድሶት+አምላክ --ቀድስተ አምላክ --አምላክን ማመስገን
ባርኮ -ባርኮ/ባርኮት፣ማሕረከ -ማሕርኮ/ማሕርኮት፣ሴስየ --ሴስዮ/ሴስዮት፣ክሕለ --ክሂል/ክሂሎት፣ጠመረ --ጠምሮ/ጠምሮት
፮. ዘመድ ዘር
-በአዛኛው በሳድስ ፊደል የሚፈጽም -ሌላ ፊደል በስተመነሻ ወይም በስተመድረሻ የሚጨመር ስም ነው
ምሳሌ
ጠበ/ጠበበ -ጥበብ፣ተሣሀለ -ሣሕል፣አፈቀረ -ፍቅር፣ይሕን የመሰለው ሁሉ
፯.ጥሬ ዘር
-በኃምስ
-በራብዕ
-በሳብዕ ፊደል የሚፈጽም -ያለፊደል ለውጥ ተሳቢ/ባለቤት) ተናባቢመሆን የሚችል ስም ነው
-ከግሥ እርባታ የሚገኝ
ምሳሌ
ቀደሰ --ቅዳሴ፣ባረከ --ቡራኬ/በረካ፣ተንበለ --ትንባሌ
፰.ሳቢ ዘር
-ከ ቀተለና ከክሕለ ቤት ብቻ የሚገኝ -በ ት ምንዕላድ የሚጨርስ አደራረግን የሚያመለክት
-ከግሥ እርባታ የሚገኝ ነው እነዚህ ከላይ የተገለጹት በቅጽልና በጋሥ እርባታ ሕጎች በስፋት የሚታዩ ስለሆነ ለማመልከት
ያህል ይህ ይበቃል
፫.ጠባቂ ንባብ
-የቀደሰ ቤት ከነ እርባታው
-ካልዓይ አንቀጽ ሱቱፉን ከሌሉበት (“ሀ”ወይም ኦ” ሐ” ዐ” ኅ”)
-በመሀል ያለውን ፊደል ያዝ ጠበቅ በማድረግ የሚነበብ ነው
፬.ልህሉህ ንባብ
-ከላይ በቁጥር አራት ከጠቀስናቸው በስተቀር ሌሎቹ ቃላት ላልተው ይነበባሉ
-ይህም መሀሉ ላልቶ የሚነበብ ማለት ነው፡፡
፭.ጎራጅ ንባብ
-ፊደል ከመነሻው ወይም ከመካከል ወይም ከመድረሻው የሚተው ንባብ ሲሆን
-ፊደል የመተው ምልክት -ከተወው ፊደል አጠገብ ያለው ይጠብቃል
በመነሻ ሲጎርድ
-“ተ” ን ተ፣ዘ፣ጠ፣ሳ፣ጸ ሲከተለው በሳልአይና በሣልሳይ አንቀጽ ይጎርዳል
ተተርአስ --ይተረአስ፣ተዘምዶ -ይዘመድ፣ተጠምቀ -ይጠመቅ ፣ተሰብኮ-ይሰበክ፣ ተጸምዶ -ይጻመድ በነሻ የነበረው “ተ
ቀርቷል
ከመካከል ሲጎርድ
-ከ “ቆመ ና“ሤመ ቤት
-ቀመመ -ቆመ “ወ ና “የተጎርደዋል ሠየመ -ሤመ -ከሳቢ ዘሩም ቅው መት --ቁመት ሥይ መት --ሢመት
-መድረሻው “ቀ ፣“ከ፣“ገ ፣“ነ የሆነ ግሥ በካልዓይና በቀዳማይ መደብ ይጎርዳል
ውእቱ አንተ አንቲ አንትሙ አንትን
ሰበከ ሰበከ ሰበኪ ሰበክሙ ሰበክን
ወረቀ ወረቀ ወረቂ ወረቅሙ ወረቅነ
ዖቀ ዖቀ ዖቂ ዐቅሙ ዖቅነ
በ “ቀ ፣“ከ፣“ገ፣“ነ የሚፈጽሙ ግሦች በዝርዝር ወቅት በቅርብ ያለውን ፊደል በማጥበቅ ፊደል ይተዋሉ
አነ አንተ አንቲ አንትሙ አንትን ውእቱ
አጥመቁ አጥመቀ አጥመቂ አጥመቅሙ አጥመቅን አጥመቆ
ሰበኩ ሰበከ ሰሰኪ ሰበክሙ ሰበክን ሰበካ
ዖቁ ዖቀ ዖቂ ዖቅሙ ዖቅን ዖቅ
ኀደጉ ኀደገ ኀደጊ ኀደግሙ ኀደግን ኀደጋ
በ “ነ”
አነ ንሕነ ውእቱ አመንኩ አመነ አምነ ድኀንኩ ድኅነ ድኅነ
ማስገንዘቢያ ሰበክኩ ይል የነበረውን ሰበኩ፣ዐቅከ ” ” ዖቀ፣ሰበክኪ ” ” ሰበኪ፣ጥመቅክሙ ” ”
አጥመቅሙ፣በክክን ” ” ሰበክን፣አመንነ ” ” አመነ፣እንዳሉ በዚህ አስተውል
በመድረሻ ላይ ያለ ፊደልን ሲተው
ት” ጥ”ን ት” -በሳድስ ውስጠዘ ቅጽል ዘ እንስት -በመድበል መድረሻ ስትመጣ ት”ትጎረዳለች
ይህም
ግሥ ዘእንሰት ሳድስ መድበል፣ውስጠ ዘ ቅጽል ውስጠ ዘ ቅጽል ፣ወለጠ ውስጠ ዘ ቅጽል ሞተ ምውት
መወት ወለደ ውልድ ወላድ
ማስገንዘቢያ/መክሥት፣ወለጥት ይል የነበረው ወለጥ፣ውልጥት ” ” ውልጥ፣መውትት ” ” መወት፣
ምውትት ” ” ምውት፣ወለድት ” ” ወላድ፣ውልድት ” ” ውልድ ብሎ ት”ን ማስቀረቱን
አስተውል
ጥያቄያዊ ንባብ
ይህ ኑ”ወይም ሁ” የተባሉ ፊደሎችን በመድረሻ እየጨመረ ወዳቂ የሚሆን የጥያቄ ንባብ ነው
ምሳሌ ይመጽእኑ/ሁ መጽአኑ/ሁ ይምጻእኑ/ሁ ትመጽእኑ/ሁ መጻእኦ/ሁ
ትርአስ ንባብት
ትራስ ፊደላት የሚባሉት፡-ወዳቂ የሚያደርጉ ተነሽ የሚያደርጉ፣ኬ -ከመዝኬ፣ሶ-አድኅንሶ፣ሂ -አድኅንሂ፣ኒ -አብርሃምኒ፣
ሰ-አንተሰ፣ዘ-ይብላዕአ፣መ -ሁ -
ማስገንዘቢያ ሰ”ወይም መ”ተነሽ የሚያደርጉት በ ወዳቂ” ንባብ መድረሻ ላይ ሲሆኑ ነው
ምሳሌ ይሁዳ(ወዳቂ) ይሁዳሰ (ተነሽ)፣ሙሴ (ወዳቂ) ሙሴሰ(ተነሽ) ኬ፣ሰ፣-ሥራቸው ግነት ነው
ሂ፣ኒ -ዋዌ ወይም ም”የሚል ትርጉም ያላቸው ናቸው
አ -የመልእክት ማመልከቻ ነው
፪.፫ የቃላት ጥናት
_ ስም____ትርጉም
1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ
2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ
3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ
4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር
17 ዲና፦ፈረደ
18 ማኑሄ፦እረፍት
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ
21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል
22 ሐና፦ ስጦታ
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ
25 ቶማስ፦ፀሐይ
26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ
27 ማትያስ፦ፀሐይ
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና
30 ኖኅ፦ደስታ
31 ሴም፦ተሾመ
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው
36 እሴይ፦ዋጋየ
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው
42 ዮናስ፦ርግብ
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ
44 ራኄል፦በግዕት
45 ዕዝራ፦ረዳቴ
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት
51 ሶምሶን፦ፀሐይ
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
53 ማርታ፦እመቤት
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር
59 ሄኖስ፦ሰው
60 ሰሎሜ፦ሰላም
61 ሩሐማ፦ምሕረት
62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል
63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ
65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ
66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል
67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል
68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ
70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል
71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል
72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር
73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ
74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!
75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል
76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት
77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ
79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ
80 ሣራ፦ልዕልት
81 ስምዖን፦ሰማ
82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል
85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል
86 አስቴር፦ኮከብ
87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው
89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ
90 አብራም፦ታላቅ አባት
91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት
92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው
93 አክዐብ፦የአባት ወንድም
94 ባሮክ፦ቡሩክ
95 አዳም፦መልካሙ
96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
97 ባርቅ፦መብረቅ
98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው
99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል
100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ
101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል
102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት
103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ
105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው
106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው
107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል
108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል
111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል
113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው
114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ
115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ
116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ
117 ኬብሮን፦ኅብረት
118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል
119 ኤደን፦ደስታ
120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል
122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ
123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ
124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው
125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው
126 ዮሴፍ፦ይጨምር
127 ዮናስ፦ርግብ
128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል
130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው
131 ምናሴ፦ማስረሻ
132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል
133 ዲቦራ፦ንብ
134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው
136 ጽዮን፦አምባ
137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሰባት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐለበ=አለበ
፪) ሐሰበ=አሰበ
፫) ሐበበ=ሀብ ሀብ አለ፣ ከዚያም ከዚያም ረገጠ፣ ወዳጅ ሆነ
፬) ሐብሐበ=ማለ
፭) ሐንበበ=አፈራ
፮) ሐንከበ=አሰፈረ
፯) ሐዘበ=ጠረጠረ
፰) ሔበ=ቀዳ፣ጠለቀ (የውሃ)
፱) ሐጠበ=ለቀመ (የእንጨት)
፲) ኀፀበ=አጠበ፣አጠራ፣አነጻ
፲፩) ልህበ=ወዛ፣ላበ፣ሞቀ፣ተኮሰ
፲፪) ለበበ=ሸበበ
፲፫) ለገበ=ሰፋ (የአቅማዳ)
፲፬) መረበ=ጣለ (የዓሣ)
፲፭) ማዕሰበ=ገለሞተ
፲፮) መገበ=ሾመ (የሹመት)
፲፯) ሰሐበ=ጎተተ፣ሳበ
፲፰) ሣህበበ=ሻገተ፣ተበላሸ
፲፱) ሰለበ=ሰለበ
፳) ሠረበ=ማገ፣መጠጠ፣ጠጣ
፳፩) ሰበ=ዞረ፣ከበበ፣ገጠመ (የሠራዊት)
፳፪) ሠብሠበ=ሕግ ሠራ
፳፫) ሠአበ=ተከተለ
፳፬) ሥእበ=ተዳደፈ፣ረከሰ
፳፭) ሰከበ=ተኛ
፳፮) ሤበ=ሸበተ (የሰው ብቻ)
፳፯) ርኅበ=ተራበ
፳፰) ረበ=ረበበ (የመልአክ የደመና ክንፍ ያለው ነገር ሁሉ)
፳፱) ረበበ=ዘረጋ
፴) ረከበ=አገኘ
፴፩) ረጥበ=ረጠበ
፴፪) ቀለበ=ዋጠ
፴፫) ቀረበ=ቆረበ
፴፬) ቄረበ=ቆረበ
፴፭) ቈረበ=ቆረበ
፴፮) ቀርበ=ቀረበ
፴፯) ቀቀበ=ሰፋ (የሰይፍ ማኅደር)
፴፰) ቀጸበ=ጠቀሰ (የጥቅሻ)
፴፱) ተሐዘበ=ታዘበ
፵) ተመንደበ=ተቸገረ፣ተጨነቀ፣ ተጠበበ
፵፩) ተማዕሰበ=ገለሞተ
፵፪) ተመገበ=በላ
፵፫) ተዐፅበ=ተጨነቀ፣ተደነቀ
፵፬) ተጥበበ=ብልሃተኛ ሆነ
፵፭) ነሀበ=ሠራ፣አነበ (የብረታ ብረት የንብ)
፵፮) ነቀበ=ለየ
፵፯) ነበበ=ተናገረ፣ነገረ
፵፰) ነጥበ=ነጠበ
፵፱) አመክዐበ=እጥፍ ድርብ አደረገ
፶) አማዕሰበ=ቤተ ፈት ሆነ (የሚስት)
፶፩) አማዕቀበ=አደራ አለ
፶፪) አማዕተበ=አመሳቀለ፣ አማተበ
፶፫) አስተርከበ=አስተዋለ
፶፬) አስተአዘበ=ሸና፣አፈሰሰ
፶፭) አስተዐፀበ=አደነቀ፣አስጨነቀ
፶፮) ዐሰበ=ሰጠ (የደመዎዝ)
፶፯) ዓሰበ=ፈታ፣ለቀቀ፣ተወ (የሚስት)
፶፰) ዐርበ=ገባ (የፀሐይ)
፶፱) ዐቀበ=ጠበቀ
፷) ዐተበ=ባረከ
፷፩) ዐንሰበ=አሟረተ
፷፪) አንበበ=አነበበ
፷፫) አንጠብጠበ=አንጠበጠበ፣ ተንጠበጠበ
፷፬) አውሰበ=አገባ
፷፭) አውገበ=አኮረፈ (የእንቅልፍ)
፷፮) አውጸበ=ሠራ (የቀለበት)
፷፯) ዐዘበ=ቆነነ፣ሠራ (የጭራ)
፷፰) አጠበ=ለቀመ (የእንጨት)
፷፱) ዐጸበ=አስጨነቀ
፸) አጽሐበ=ዘበዘበ፣ነዘነዘ፣ ጨቀጨቀ፣ ነገር አበዛ፣ አደከመ
፸፩) ከሰበ=ገረዘ፣ቆረጠ
፸፪) ከረበ=ለቀመ፣ሰበሰበ (የወይን)
፸፫) ኬረበ= አራት ዓይነት አድርጎ ጠረበ
፸፬) ኰረበ=ሰቀለ (የባጥ እንደ ዳስ ያለ ሁሉ)
፸፭) ከበበ=ከበበ (የማጀብ)
፸፮) ከብከበ=ሰርግ አደረገ
፸፯) ከተበ=ጻፈ
፸፰) ከዐበ=ሰደረ፣ካበ፣ደረደረ
፸፱) ወሀበ=ሰጠ
፹) ወከበ=ቸኰለ
፹፩) ወጸበ=ሠራ (የቀለበት)
፹፪) ዘረበ=መታ፣ቀጠቀጠ (የመዶሻ)
፹፫) ዘገበ=ሰበሰበ፣አከማቸ (የገንዘብ)
፹፬) የበበ=እልል እልል አለ፣ አመሰገነ፣ ዘመረ፣ ዘፈነ
፹፭) ደበበ=ዘረጋ (የጥላ የዝንቦ)
፹፮) ደብደበ=ነፋ (የሆድ)
፹፯) ደየበ=ወጣ፣አረገ
፹፰) ገለበ=ሸሸ፣ጋለበ፣ነዳ፣ አጠመደ
፹፱) ገልበበ=ሸፈነ፣ከደነ፣አለበሰ፣ አከናነበ
፺) ጠቀበ=ሰፋ፣ጠቀመ (የልብስ)
፺፩) ጠበ= ብልሃተኛ ሆነ
፺፪) ጠበጠበ=ጻፈ
፺፫) ጠብጠበ=ገረፈ
፺፬) ጤበ=ኮላ ኳለ፣ቀባ
፺፭) ጸለበ=ሰቀለ
፺፮) ጸረበ=ጠረበ
፺፯) ጸበ=ጠበበ
፺፰) ጾበ=ጨለጠ፣ጠጣ
፺፱) ጸግበ=ጠገበ
፩.፬ የአመልካቾች አካሄድ በግስ
፩) ዝንቱ፣ዝ___ይህ
፪) ዛቲ፣ዛ_ይህች
፫) ዝኵ፣ዝስኵ፣ዝክቱ____ያ
፬) እንታክቲ፣ እንትኵ____ያች
፭) እሉ፣ እሎንቱ___እነዚህ
፮) እላ፣እሎን፣ እላንቱ፣__እነዚህ (ሴ)
፯) እልኰን፣ እልክቶን___እነዚያ(ሴ)
፰) እልኵ፣ እልክቱ____እነዚያ
በዓረፍተ ነገር ባለቤት ሆነው ሲያገለግሉ ለምሳሌ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም።ትርጉሙ ለዘለዓለም ማረፊያየ ይች ናት
ማለት ነው። ቅጽል ሆነው ሲያገለግሉ ዳህንኑ ዝስኵ አቡክሙ ይላል። ትርጉሙ ያ አባታችሁ ደህና ነውን ማለት ነው።
ተሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ። አፍቅር ዛተ ቢል ያችን ውደዳት ማለት ነው።

የ"ዘ፣እለ፣እንተ" አስሩ ዝርዝርም ተናበው አመላካች የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ትርጉማቸውም እንደሚከተለው ነው።
፩) ዚኣሁ/እንቲኣሁ___የእርሱ
፪) ዚኣሆሙ/እንቲኣሆሙ__የእነርሱ
፫) ዚኣሃ/እንቲኣሃ___የእርሷ
፬) ዚኣሆን/እንቲኣሆን__የእነርሱ
፭) ዚኣከ/እንቲኣከ___የአንተ
፮) ዚኣክሙ/እንቲኣክሙ__የእናንተ
፯) ዚኣኪ/እንቲኣኪ___የአንቺ
፰) ዚኣክን/እንቲኣክን___የእናንተ
፱) ዚኣየ/እንቲኣየ____የእኔ
፲) ዚኣነ/እንቲኣነ_የእኛ
ሲናበቡ አመልካች ቅጽል ይሆናሉ። ለምሳሌ ሀገረ ዚኣነ ቢል ትርጉሙ የእኛ ሀገር ማለት ነው። ሕይወተ ዚአኪ ሲል
የአንቺ ሕይወት ተብሎ ይተረጎማል። የእኔ ሀገር ለማለት ዚኣየ ሀገር አይባልም። ከዚያ ይልቅ ሀገረ ዚኣየ ይላል እንጂ።
እንተ ለሴት ሲሆን፣ ዘ ደግሞ ለሴት ለወንድ ለአንድ ለብዙ ይሆናል። እለ ለብዙ ይሆናል።ሲዘረዘርም እንደሚከተለው
ነው።
፩) እሊኣሁ___የእርሱ
፪) እሊኣሆሙ__የእነርሱ
፫) እሊኣሃ____የእርሷ
፬) እሊኣሆን___የእነርሱ
፭) እሊኣከ____የአንተ
፮) እሊኣክሙ___የእናንተ
፯) እሊኣኪ____የአንቺ
፰) እሊኣክን___የእናንተ
፱) እሊኣየ____የእኔ
፲) እሊኣነ____የእኛ
#ተሳቢ #መራሕያን
ድርብ መራሕያን (Reflexive Pronouns) የሚባሉት በመራሕያን ላይ እየተደረቡ የሚመጡ አጽንዖት መስጫ ቃላት
ናቸው።እነዚህም ፲ ናቸው።
፩) ለሊሁ____ እርሱ ራሱ
፪) ለሊሆሙ_እነርሱ ራሳቸው
፫) ለሊሃ_እርሷ ራሷ
፬) ለሊሆን__እነርሱ ራሳቸው
፭) ለሊከ____አንተ ራስህ
፮) ለሊክሙ__እናንተ ራሳችሁ
፯) ለሊኪ____አንቺ ራስሽ
፰) ለሊክን___እናንተ ራሳችሁ
፱) ለልየ_እኔ ራሴ
፲) ለሊነ_እኛ ራሳችን
የሚሉት ናቸው። ለምሳሌ አነ ለልየ ሰማዕቱ ለዝንቱ ቢል። እኔ ራሴ ለዚህ ምስክር ነኝ ተብሎ ይተረጎማል። ለሊነ
ነአምር ኵሎ ዘኮነ ቢል የሆነውን ሁሉ እኛ ራሳችን እናውቃለን ተብሎ ይተረጎማል።
#ተሳቢ #መራሕያን
ተሳቢ መራሕያን የሚባሉት ደግሞ በተሳቢነት የሚያገለግሉ ናቸው። እነዚህም ቁጥራቸው ፲ ናቸው።
፩) ኪያሁ___እርሱን
፪) ኪያሆሙ__እነርሱን
፫) ኪያሃ____እርሷን
፬) ኪያሆን___እነርሱን
፭) ኪያከ____አንተን
፮) ኪያክሙ___እናንተን
፯) ኪያኪ____አንችን
፰) ኪያክን____እናንተን
፱) ኪያየ____እኔን
፲) ኪያነ_እኛን
የሚል ትርጉም ይኖራቸዋል። ለምሳሌ በቅዳሴ ጊዜ ኪያከ እግዚኦ ንሴብሐከ እንላለን።ትርጉሙ አቤቱ አንተን
እናመሰግንሃለን ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ተርጉሙ።
፩) ኪያሃ አፍቀረ
፪) ኪያክሙ ሠምረ
፫) ኪያየ ወደሰ

ምዕራፍ ፫
አገናዛቢ ዝርዝር
ተሳቢ መራሕያን አገናዛቢ መራሕያን
ኪያሁ = እርሱን ዚአሁ(ዘዚአሁ) = የእርሱ(ን)
ኪያከ = አንተን ዚአከ(ዘዚአከ) = ያንተ(ን)
ኪያሆሙ = እነርሱን ዚአሆሙ(ዘዚአሆሙ) = የእነርሱ(ን)
ኪያክሙ = እናንተን ዚአክሙ(ዘዚአክሙ) = የእናንተ(ን)
ኪያከሃ = እርሷን ዚአሃ(ዘዚአሃ) = የእርሷ(ን)
ኪያኪ = አንቺን ዚአኪ(ዘዚአኪ) = ያንቺ(ን)
ኪያሆን = እነርሱን ዚአሆን(ዘዚአሆን) = የእነርሱ(ን)
ኪያክን = እናንተን ዚአክን(ዘዚአክን) = የእናንተ(ን)
ኪያየ = እኔን ዚአየ(ዘዚአየ) = የእኔ(ን)
ኪያነ = አኛን ዚአነ(ዘዚአነ) = የእኛ(ን)
ሊተ = እኔን በ = በ
ለሊሁ = እርሱ እራሱ ቦቱ = በእርሱ
ለሊከ = አንተ እራሱ ብከ = ባንተ
ለሊሆሙ = እነርሱ ራሳቸው ቦሙ = በእነርሱ
ለሊክሙ = እናንተ ራሳችሁ ብክሙ = በእናንተ
ለሊሃ = እርሷ እራሷ ባቲ = በእርሷ
ለሊኪ = አንቺን ራስሽ ብኪ = በአንቺ
ለሊሆን = እነርሱ ራሳቸው ቦን = አላቸው
ለሊክን = እናንተ ራሳችሁ ብክን = በእናንተ
ለልየ = እኔ እራሴ ብየ = በእኔ
ለሊነ = አኛራሳችን ብነ = በእኛ
አልቦ = የለም በእንተ = ስለ
አልቦቱ = የለውም በእንቲአሁ = ስለእርሱ
አልብከ = የለህም በእንቲአከ = ስለአንተ
አልቦሙ = የላቸውም በእንቲአሆሙ = ስለእነርሱ
አልብክሙ = የላችሁም በእንቲአክሙ = ስለእናንተ
አልባቲ = የላትም በእንቲአሃ = ስለእርሷ
አልብኪ = የለብሽም በእንቲአኪ = ስለአንቺ
አልቦን = የላቸውም በእንቲአሆን = ስለእነርሱ
አልብክን = የላችሁም በእንቲአክን = ስለእናንተ
አልብየ = የለብኝም በእንቲአየ = ስለእኔ
አልብነ = የለብንም በእንቲአነ = ስለእኛ
እለ እንተ = የ ከመ = እንደ
እሊአሁ (እንቲአሁ) = የእርሱ ከማሁ = እንደ እርሱ
እሊአከ (እንቲአከ) = የአንተ ከማከ = እንደ አንተ
እሊአሆሙ (እንቲአሆሙ) = የእነርሱ ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
እሊአክሙ (እንቲአክሙ) = የእናንተ ከማክሙ = እንደ እናንተ
እሊአሃ (እንቲአሃ) = የእርሷ ከማሃ = እንደ እርሷ
እሊአኪ (እንቲአኪ) = ያንቺ ከማኪ = እንደ አንቺ
እሊአሆን (እንቲአሆን) = የእነርሱ ከማሆን = እንደ እነርሱ
እሊአክን (እንቲአክን) = የእናንተ ከማክን = እንደ እናንተ
እሊአየ (እንቲአየ) = የእኔ ከማየ = እንደ እኔ
እሊአነ (እንቲአነ) = የእኛ ከማነ = እንደ እኛ
ኀበ = ወደ እምነ = ከ
ኀቤሁ = ወደ እርሱ እምኔሁ = ከእርሱ
ኀቤከ = ወደ አንተ በእንቲአከ = ስለአንተ
ኀቤሆሙ = ወደ እነርሱ በእንቲአሆሙ = ስለእነርሱ
ኀቤክሙ = ወደ እናንተ በእንቲአክሙ = ስለእናንተ
ኀቤሃ = ወደ እርሷ በእንቲአሃ = ስለእርሷ
ኀቤኪ = ወደ አንቺ በእንቲአኪ = ስለአንቺ
ኀቤሆን = ወደ እነርሱ በእንቲአሆን = ስለእነርሱ
ኀቤክን = ወደ እናንተ በእንቲአክን = ስለእናንተ
ኀቤየ = ወደ እኔ በእንቲአየ = ስለእኔ
ኀቤነ = ወደ እኛ በእንቲአነ = ስለእኛ
እለ እንተ = የ ከመ = እንደ
እሊአሁ (እንቲአሁ) = የእርሱ ከማሁ = እንደ እርሱ
እሊአከ (እንቲአከ) = የአንተ ከማከ = እንደ አንተ
እሊአሆሙ (እንቲአሆሙ) = የእነርሱ ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
እሊአክሙ (እንቲአክሙ) = የእናንተ ከማክሙ = እንደ እናንተ
እሊአሃ (እንቲአሃ) = የእርሷ ከማሃ = እንደ እርሷ
እሊአኪ (እንቲአኪ) = ያንቺ ከማኪ = እንደ አንቺ
እሊአሆን (እንቲአሆን) = የእነርሱ ከማሆን = እንደ እነርሱ
እሊአክን (እንቲአክን) = የእናንተ ከማክን = እንደ እናንተ
እሊአየ (እንቲአየ) = የእኔ ከማየ = እንደ እኔ
እሊአነ (እንቲአነ) = የእኛ ከማነ = እንደ እኛ
መንገለ = ወደ ምስለ = ከ….ጋር
መንገሌሁ = ወደ እርሱ ምስሌሁ = ከእርሱ ጋር
መንገሌከ = ወደ አንተ ምስሌከ = ካንተ ጋር
መንገሌሆሙ = ወደ እነርሱ ምስሌሆሙ = ከእነርሱ ጋር
መንገሌክሙ = ወደ እናንተ ምስሌክሙ = ስለእናንተ
መንገሌሃ = ወደ እርሷ በእንቲአሃ = ስለእርሷ
መንገሌኪ = ወደ አንቺ በእንቲአኪ = ስለአንቺ
መንገሌሆን = ወደ እነርሱ በእንቲአሆን = ስለእነርሱ
መንገሌክን = ወደ እናንተ በእንቲአክን = ስለእናንተ
መንገሌየ = ወደ እኔ በእንቲአየ = ስለእኔ
መንገሌነ = ወደ እኛ በእንቲአነ = ስለእኛ
አልቦ = የለም ኅየንተ = ስለ
አልቦቱ = የለውም ኅየንቴሁ = ስለ እርሱ
አልብከ = የለህም ኅየንቴከ = ስለ አንተ
አልቦሙ = የላቸውም ኅየንቴሆሙ = ስለ እነርሱ
አልብክሙ = የላችሁም ኅየንቴክሙ = ስለ እናንተ
አልባቲ = የላትም ኅየንቴሃ = ስለ እርሷ
አልብኪ = የለብሽም ኅየንቴኪ = ስለ አንቺ
አልቦን = የላቸውም ኅየንቴሆን = ስለ እነርሱ
አልብክን = የላችሁም ኅየንቴክን = ስለ እናንተ
አልብየ = የለብኝም ኅየንቴየ = ስለ እኔ
አልብነ = የለብንም ኅየንቴነ = ስለእኛ
ሊተ = እኔን ኅየንተ = ስለ
ሎቱ = ለእርሱ ኅየንቴሁ = ስለ እርሱ
ለከ = ለእርሱ ኅየንቴከ = ስለ አንተ
አልቦሙ = የላቸውም ኅየንቴሆሙ = ስለ እነርሱ
አልብክሙ = የላችሁም ኅየንቴክሙ = ስለ እናንተ
አልባቲ = የላትም ኅየንቴሃ = ስለ እርሷ
አልብኪ = የለብሽም ኅየንቴኪ = ስለ አንቺ
አልቦን = የላቸውም ኅየንቴሆን = ስለ እነርሱ
አልብክን = የላችሁም ኅየንቴክን = ስለ እናንተ
አልብየ = የለብኝም ኅየንቴየ = ስለ እኔ
አልብነ = የለብንም ኅየንቴነ = ስለእኛ
፫.፪ አገናዛቢ ቅጽሎች
አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን (possessive adjective pronouns) ደግሞ ቅጽል (adjective) ሲሆኑ ከስም
በፊት እየመጡ የባለቤትነትን ወይም ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ሁልጊዜ ከስም በፊት ይገኛሉ።
እሱም የሚከተሉት ናቸው ፦
፩) ዘዚአየ=የእኔ=My
፪) ዘዚአነ=የእኛ=Our
፫) ዘዚአከ=የአንተ=Your
፬) ዘዚአኪ=የአንቺ=Your
፭) ዘዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Your
፮) ዘዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Your
፯) ዘዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዘዚአሃ=የእሷ=Her
፱) ዘዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Their
፲) ዘዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Their
ምሳሌ ፩፦ ወልድ=ልጅ (ስም)
ሀ) አነ ውእቱ #ዘዚአሃ ወልድ => እኔ #የእሷ ልጅ ነኝ፡፡
ለ) አንተ ውእቱ #ዘዚአየ ወልድ => አንተ #የእኔ ልጅ ነህ፡፡
ከምሳሌ ሀ) እንደምናየው "አነ ውእቱ ዘዚአሃ ወልድ".. ዘዚአሃ የሚለው አገናዛቢ መራሕያኑ "ወልድ" ከሚለው
ስም በፊት ነው የመጣው።
በምሳሌው መሠረት ሦስት ዓረፍተ ነገር ሥሩ።
የተሰጠን ስም፦ ብዕር = ብዕር (እስከብሪቶ)፣ መጽሐፍ = መጽሐፍ
የተሰጠን ግስ፦ ወሰደ = ወሰደ
ውእቱ ወሰደ #ዘዚአየ ብዕር => እርሱ #የኔን እስክብሪቶ ወሰደ።
አነ ወሰድኩ #ዘዚአከ መጽሐፍ => እኔ #የአንተን መጽሐፍ ወሰድሁ
እነዚህ መራሕያን ራሳቸው እንደ ስም ያገለግላሉ እንጅ ስም አይከተላቸውም፡፡

ምሳሌ
ሀ) ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአሃ ውእቱ፡፡
ይህ መጽሐፍ #የእርሷ ነው
This book is #Hers.

ዚአሃ የሚለው መጽሐፍ ከሚለው በኋላ ራሱን ችሎ እንደ ስም አገልግሏል

ለ) ስመ ዚአየ == #የኔ ስም
ሐ) ዝ ግብር #ዚአሁ ውእቱ፡፡
ይህ ሥራ #የሱ ነው፡፡
መ) አነ ውእቱ ወልደ #ዚአከ፡፡
እኔ የእንተ #ልጅ ነኝ።

የሁለቱን መራሕያን ልዩነት ተመልከቱ


ስመ #ዚአየ = የኔ ስም (አገናዛቢ ስም)
#ዘዚአየ ስም = የኔ ስም (አገናዛቢ ቅጽል)
ዝንቱ መጽሐፍ #ዚአየ ውእቱ (አገናዛቢ ስም)
ይህ መጽሐፍ #የኔ ነው
this book is #mine

ዝንቱ ውእቱ #ዘዚአየ መጽሐፍ (አገናዛቢ ቅጽል)


This is #my book
#የኔ መጽሐፍ ይህ ነው
የሁለቱን ልዩነት ትረዱ ዘንድ....
በዚህ መሠረት የሚከተለውን ጥያቄ በአገናዛቢ ቅጽል እና በአገናዛቢ ስም መራሕያን ሦስት ሦስት ዐ. ነገር ሥሩ።
ሀ) ደብተር = ደብተር
ምሳሌ፦
አገናዛቢ ቅጽል
ዝ ውእቱ ዘዚአሁ ደብተር
ይህ የእርሱ ደብተር ነው
አገናዛቢ ስም
ዝ ደብተር ዚአሁ ውእቱ
ይህ ደብተር የእርሱ ነው
፫.፫ መስተዋድዳን
መስተዋድዳን ቀለማት
በንግግርም ሆነ በጽሑፍ ጊዜ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩን/የጽሑፉን
ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት አሉ፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡አገባባት በሶስት
የሚከፈሉ ሲሆን ዐቢይ አገባብ፣ ንዑስ አገባብ፣ ደቂቅ አገባብ ይባላሉ፡፡ በግእዝ ሰዋስው ደቂቅ አገባብ የተባሉት
በአማርኛ መስተዋድዳን የሚባሉት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሶስቱም አገባባት የተውጣጡ ቃላት ከዚህ በታች
ተዘርዝረዋል፡፡
አገባብ የአማርኛ ፍቺ አገባብ
የአማርኛ ፍቺ
ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ በ _ ላይ ዝንቱ/ዝ ይህ
ታሕተ፣መትሕተ በ _ ታች ዛቲ
ይህች
ማዕከለ መካከል/በ _ መካከል እሉ
እኝህ
ውስተ ውስጥ/በ _ ውስጥ እላ
እኝህ
ቅድመ በፊት/በ _ ፊት ዘ፣እለ፣እንተ የ
ድኅረ በኋላ/በ _ ኋላ በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ስለ
እስከ(እስከነ) እስከ በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ስለዚህ
ኀበ ወደ/ዘንድ እምድኅረዝንቱ ከዚህ
በኋላ
መንገለ ወደ እስመ / አምጣነ / አኮኑ ና
አምሳለ እንደ መጠነ
ያህል
ከመ እንደ ዳዕሙ / ባህቱ
ነገር ግን
ምስለ ጋር አላ
እንጅ
እንበለ ያለ፣በቀር ወሚመ/አው
ወይም
እም/እምነ ከ ናሁ
እነሆ
እመ ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ እፎ
ንዴት
እንዘ እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ ጌሠም
ነገ
ሶበ/አመ በ _ ጊዜ ዮም/ይዕዜ ዛሬ
ጊዜ በጊዜ/በ _ ጊዜ ትማልም
ትላንት
ምሳሌ ፦ በሚከተሉት ዐ/ነገሮች ውስጥ መስተዋድዳን ቀለማቱን አስተውሉ
ሀ , አመ ተሰቅለ ክርስቶስ መልዕልተ መስቀል ፀሐይ ጸልመ፡፡
ለ , ናሁ ተወልደ ዮም ቤዛ ኵሉ ዓለም በከመተነበየ ኢሳይያስ ነቢይ።
ሐ , ነግሠ ሞት እምነ አዳም እስከ ሙሴ
መ , አመ ይመጽዕ ወልድኪ ምስለ አእላፍ መላእክቲሁ።
ሠ , ሰአሊ ለነ ማርያም በቅድሜሁ።
ረ , ተዐውቀ ዝንቱ ብእሲ በኀበ ሊቃውንትአምጣነ ምሁር ውእቱ።
የመስተዋድዳን ዝርዝር በመራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።(ስለ አገናዛቢ ቅጽል የስም
ዝርዝር በመራሕያን የሚለውን ክፍል አስታውሱ።) በሚዘረዘሩበት ጊዜም አብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ
ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ 1, መንገለ
መንገሌሁ =ወደ እርሱ መንገሌከ =ወደ አንተ
መንገሌየ =ወደ እኔ
መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ መንገሌክሙ =ወደ እናንተ
መንገሌነ = ወደ እኛ
መንገሌሃ=ወደ እሷ መንገሌኪ =ወደ አንቺ
መንገሌሆን=ወደ እነርሱ መንገሌክን =ወደ እናንተ
2, ቅድመ
ቅድሜሁ =በፊቱ ቅድሜከ =በፊትህ
ቅድሜየ = በፊቴ
ቅድሜሆሙ =በፊታቸው ቅድሜክሙ =በፊታችሁ
ቅድሜነ =በፊታችን
ቅድሜሃ =በፊቷ ቅድሜኪ =በፊትሽ
ቅድሜሆን =በፊታቸው ቅድሜክን=በፊታችሁ
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየርየሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ 1, ከመ
ከማሁ = እንደ እርሱ ከማከ = እንደ አንተ
ከማየ = እንደ እኔ
ከማሆሙ = እንደ እነርሱ ከማክሙ = እንደ እናንተ
ከማነ = እንደ እኛ
ከማሃ = እንደ እርሷ ከማኪ = እንደ አንቺ
ከማሆ = እንደ እነርሱ ከማክን = እንደ እናንተ
2, ውስተ
ውስቴቱ = በውስጡ ውስቴትከ = በውስህ ውስቴትየ
= በውስጤ
ውስቴቶሙ = በውስጣቸው ውስቴትክሙ = በውስጣችሁ ውስቴትነ =
በውስጣችን
ውስቴታ = በውስጧ ውስቴትኪ = በውስጥሽ
ውስቴቶን = በውስጣቸው ውስቴትክን = በውስጣችሁ
ምዕራፍ ፬
፬.፩ አገናዛቢ ተውላጠ ስም
(Possessive Nouns)

እነዚህ መራሕያን ባለንብረትነትን ይገልጣሉ። ከላይ ካየናቸው አገናዛቢ ቅጽል መራሕያን የሚለዩት ራሳቸውን ችለው
የሚቆሙ ከስም በኋላ የሚገኙ መሆናቸው ነው።

፩) ዚአየ=የእኔ=Mine
፪) ዚአነ=የእኛ=Ours
፫) ዚአከ=የአንተ=Yours
፬) ዚአኪ=የአንቺ=Yours
፭) ዚአክሙ=የእናንተ(ወ)=Yours
፮) ዚአክን=የእናንተ(ሴ)=Yours
፯) ዚአሁ=የእሱ=His
፰) ዚአሃ=የእሷ=Hers
፱) ዚአሆሙ=የእነሱ(ወ)=Theirs
፲) ዚአሆን=የእነሱ(ሴ)=Theirs

፬.፪ አገናዛቢ አጸፋዎችና ስሞች


ካልእ = ሌላ፣ ካልእከ / ሌላህ/፤ ካልእኪ የሌላሽን
ቀደምት =/የቀድሞ ሰዎች/፤ ቀደምትክሙ / የቀድሞ ሰዎች የሆኗችሁ ለእናንተ/
ክልኤ = ሁለት፣ ክልኤሆሙ / ሁለታቸው/፤ ክልኤነ / ሁለታችን /፤ ክልኤክሙ / ሁለታችሁ/

በበይናት = በመካከል እርስ በርስ፤ በበይናቲነ/ እርስ በርሳችን /፤ በበይናቲሆሙ / እርስ በርሳቸው/፤ በበይናቲክሙ / እርስ በርሳችሁ/

ኩሎ = ሁሉ፣ ኩሎሙ / ሁላችው/፤ ኩልክሙ / ሁላችሁ/፤ ኩልነ / ሁላችን/


ባሕቲት = ብቻ፣ ባሕቲቶሙ / ብቻቸውን/፤ ባሕቲትየ / ብቻየን/፤ ባሐቲታ / ብቻዋን/
አመ = ጊዜ፣ አሜሃ / በዚህ ጊዜ፣ በዚያ፣ ጊዜ፣ ወዲያው/
ሶበ = ጊዜ፣ ሶቤሃ / በዚህ ጊዜ፣ በዚያ ጊዜ፣ ወዲያው/
ጊዜ =ጊዜ፣ ጊዜሃ / በዚህ ጊዜ በዚያ ጊዜ ወዲያው/

ምሳሌ
ዘትፈቅድ ለርእስከ ግበር ለካልእከ = ለራስህ የምትፈልገውን ለሌላው አድርግ፡፡
ሰማእክሙ ዘተብህለ ለቀደምትክሙ / ተብህለ = ተባለ/
ቀደምትክሙ ሰገዱ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ
ክልኤሆሙ ሖሩ ወብልዑ ኅብስተክሙ
ተፋቀሩ በበይናቲክሙ
ተማከርነ በበይናቲነ
ተሰአሉ በበይናቲሆሙ / ተሰአለ፣ ተጠያየቀ/
ኩልነ አግብርተ እግዚአብሔር ንሕነ
መጽኡ ኩሎሙ ወሰአሉ በእንተ ንጉሦሙ
ሑሩ ኩልክሙ ኀበ ቤትክሙ ለክሙ
ኩሎሙ ነቢያት አስከ ዮሐንስ ተነበዩ
መጻእኩ እምብሔር ርኁቅ ባሕቲትየ
ዝንቱ ብእሲ ነበረ ውስተ ቤቱ ለባሕቲቱ
ዘበልዐ ባሕቲቶ ይመውት ባሕቲቶ

የንዑስ አንቀጽ ዝርዝር እንደ አገናዛቢ ሲያገለግል

ቀቲል/ ቀቲሎት/ –መግደል፤ ቀቲልየ = መግደሌ፤ ቀቲልክሙ = መግደላችሁ


ቀተለ = ገደለ፤ ቀቲሎትየ = መግደሌ፤ ቀቲሎትክሙ = መግደላችሁ
ቀደሰ = አመሰገነ፤ ቀድሶየ = ምስጋናየ፤ ቀደሶክሙ = ማመስገናችሁ
ቀድሶትየ = ምስጋናየ፤ ቀድሶትክሙ = ማመስገናችሁ
ገቢር/ ገቢሮት/ =መሥራት፤ ገቢርየ = ሥራየ፤ ገቢርክሙ = ሥራችሁ
ገብረ = ሥራ፤ ገቢሮትየ = ሥራየ፤ ገቢሮትክሙ = ሥራችሁ
1ዐ.3 ተጠቃሽ ተውላጠ ሥም

ነጠላ ብዙ
ሊተ = የእኔ ፣ ለእኔ ፣ ልኝ ለነ = ለእኛ
ለከ = ላንተ፣ ልህ ለክሙ = ለእናንተ ላቹሁ
ለኪ = ላንቺ፣ ልሽ ለክን = ለእናንተ / ለሴት/ ላቹሁ
ሎቱ/ሎ/ = ል፣እርሱ ሎቶ/ሎቶሙ/ሎሙ = ለእነርሱ / ለወንድ/
ብየ = በኔ፣ ብኝ፣ አለኝ ብነ = በእኛ ብን አለን
ብከ = በአንተ፣ አለህ ብክሙ = በእናንተ፣ ባችሁ ፣አላችሁ
ብኪ = በአንቺ አለሽ ብክን= በእናንተ፣ ባችሁ አላቹሁ/ለሴቶች/
ቦቱ/ ቦ/ = በት አለው ፣ በእርሱ ቦኑ/ ቦቶሙ/ = አላቸው፣ አላችሁ ባቸው/ለወንዶች/
ባቲ/ ባ/ = ባት ቦን / ቦቶን/ = አላቸው፣ አላችሁ፣ ባቸው /ለሴቶች/
ላቲ= ለእርሷ ሎሙ = ለእነርሱ / ለወንዶች/ ፣ባቸው

ምሳሌ

ፍታህ ሊተ እግዚኦ ወተበቀል በቀልየ


ልበ ንፁሐ ፍጥር ሊተ
ሰላም ለከ ኦ ሚካኤል መልአከ አድኅኖ
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ
ሎቱ ስብሐት
አምጽኡ ላቲ አምሐ ለድንግል
ብየ እግዚአብሔር ዘየዐቀበኒ
መጽአ ብየ ሞት አመ ነበርኩ በኃጢአት
ኦ ጎልያድ አይቴኑ ትበውእ እስመ በጽሐ ብከ ዳዊት
ብኪ ግርማ ራእይ ዘየዐቢ
ወተቀትለ ቦቱ ወልዱ ለአዳም
ወተሰቅለ ባቲ ወልዳ ለማርያም
ተአገሠ ለነ ኩሎ ኃጢአተነ
ሰአሊ ለነ ቅድስት
ሰላም ለክሙ
፬.፫ ተውላጠ ስሞች
፬.፬ ባለቤት ተውላጠ ስም
፬.፭ ተሳቢ
ምዕራፍ ፭
፭፩ የ ቦ ዝርዝር
፭፪ የ ለ ዝርዝር
፭፫ አሉታ
፭፬ የግእዝ አኃዝ
፭፮ አጫጭር ዓረፍተ ነገሮች ሠርቶ ማንበብ

ምዕራፍ ፮ መስተአምር

You might also like