You are on page 1of 14

See discussions, stats, and author profiles for this publication at: https://www.researchgate.

net/publication/360491804

Book · May 2022

CITATIONS READS

0 589

1 author:

Habtamu Demiessie
Jijiga University
126 PUBLICATIONS   8 CITATIONS   

SEE PROFILE

Some of the authors of this publication are also working on these related projects:

View project

: (1850-1960 ) View project

All content following this page was uploaded by Habtamu Demiessie on 10 May 2022.

The user has requested enhancement of the downloaded file.


የሥነ ጽሑፍ ሰዎች እና ሥራዎቻቸው

ልቦለድ፣ የተውኔት ድርሠት እና ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ (ከ1850-1960ዎቹ)

ሀብታሙ ግርማ ደምሴ

መስከረም 2011 ዓ.ም


ጅግጅጋ፤ ኢትዮጵያ

1
የደራሲው መብት በህግ የተጠበቀ ነው

ISBN: 978-0-359-12352-0

2
ስለ መጽሐፉ አዘጋጅ

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ሀብታሙ ግርማ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ2001 ዓ.ም በኢኮኖሚክስ እንዲሁም፣ በ2005
ዓ.ም የሁለተኛ ዲግሪውን በኢኮኖሚክ ፖሊሲ አናሊሲስ (Economic Policy Analysis) ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተቀጥሮ
በማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በማማከር እየሠራ ይገኛል። በተለያዩ
አገራዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አድማስ ፣ The Reporter Ethiopia እና Addis Fortune ጋዜጦች
ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ በኢ-መደበኛነት ይጽፋል። አንባቢያን በመጽሐፉ ላይ ለሚያነሷቸው
ሀሳቦች ወይም አስተያየቶች በኢሜይል አድራሻዎቹ፦ ruhe215@gmail.com ወይም hab200517@yahoo.com
ደራሲውን ማግኘት ይችላሉ።

3
ማውጫ
ማውጫ

ምስጋና

መቅድም

መግቢያ

ክፍል አንድ: ሥነ ጽሁፍ በኢትዮጵያ

1.1. የኢ-ልቦለድ እና ልቦለድ ሥነ ጽሑፍ በኢትዮጵያ

1.2. የተውኔት ድርሰት በኢትዮጵያ

1.3. ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ

1.3.1. የህትመት ሚዲያ አጭር ቅኝት

1.3.2. የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ አጭር ቅኝት

1.4. የአማርኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ጥናት በኢትዮጵያ

1.5. የኢትዮጵያ መሪዎችና መጻህፍቶቻቸው

ክፍል ሁለት

ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን የስነ ጽሁፍ ሰዎች አጫጭር የህይወት ታሪክ

1. አለቃ ታዬ ገብረ ማርያም

2. ነጋድርራስ ገ/ህይወት ባይከዳኝ

3. ፊት አውራሪ ተክለ ሀዋርያት ተክለ ማርያም

4. ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ

5. ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል

6. አሀዱ ሳቡሬ
4
7. መንግስቱ ለማ

8. ጳውሎስ ኞኞ

9. አቤ ጉበኛ

10. ነጋድራስ አፍወርቅ ገ/ኢየሱስ

11. ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው

12. ሮማነ ወርቅ ካሳሁን

13. ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ስላሴ

14. ኢዩኤል ዮሀንስ

15. ነጋሽ ገብረ ማርያም

16. ብላቴን ጌታ መርስኤ ሀዘን ወልደ ቂርቆስ

17. ክቡር ዶ/ር ስንዱ ገብሩ

18. ክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ

19. መስፍን ሀብተ ማርያም

20. ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን

21. ብርሃኑ ዘሪሁን

22. ዳኛቸው ወርቁ

23. በዓሉ ግርማ

24. አያልነህ ሙላት

25. ስብሐት ገብረ እግዘአብሄር

26. ገብረ ክርስቶስ ደስታ

27. ደበበ ሰይፉ

28. ማሞ ውድነህ

29. ተክለ ጻድቅ መኩሪያ

30. ሀይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው)

5
ዋቢ ስራዎች

መጽሃፍት

የጥናት ስራዎች

መጽሄቶች

ጋዜጦች

ድረ ገጾች (websites)

አባሪዎች

አባሪ አንድ የቤተ መንግስት እና ሌሎች የሲቪል ማዕረጎች

አባሪ ሁለት ወታደራዊ ማዕረጎች

አባሪ ሶስት በኢትዮጵያ ከ1933 ዓ.ም በፊት ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች

አባሪ አራት በኢትዮጵያ ከ1933-1966 ዓ.ም ድረስ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች

6
የዚህች መጽሐፍ ማስታወሻነቷ ለምወዳት ልጄ ሩህ ሀብታሙ ትሁንልኝ።

7
የ ቅንነ ትን ኃይል ያስገ ነ ዘብከኝ፤ በምክሮችህ እና በተግሳጾችህ የ ማይነ ጥፍ የ መንፈስ ጥሪት ያወረስከኝ ግርማደምሴ

(1951-2009)

የ አባትነ ት አርዓያዬ ነ ህ !

8
ምስጋና

ከሁሉ አስቀድሜ ይህ ስራ ከዳር እንዲደርስ ለፈቀደ ለልዑል እግዚአብሄር ክብሩ ይስፋ!

መጽሀፉን ለማዘጋጀት በተነሳሁበት ቅጽበት ሀሳቤን አማክሬው ጥሩ የሞራል እርሾ የጣለልኝና ያበረታኝ ወንድሜን

አዲስአለም ግርማ አመሰግነዋለሁ።

በህይወት ጉዞዬ ሁሉ ለስኬት እንድበቃ ያለመታከት ለደከምከው ውድ ወንድሜ ተመስገን ግርማ ምስጋናዬ ካለህበት

ይድረስህ።

መጽሀፉን በማዘጋጀት ሂደት ባሳለፍኳቸው ውጣ ውረዶች ሁሉ አብሮነትህ ያልተለየኝ ወዳጄ ውብሸት ገዛኸኝ ልፋትህ

ፍሬ አፍርቷልና እንኳን ደስ አለህ።

9
መቅድም

ሥነ ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ literature የሚለው አቻ የአማርኛ ቃል ነው። የተጻፈ ነገር ሁሉ ሥነ ጽሑፍ ነው

ማለት አይቻልም። ሥነ ጽሑፍ የገሃዱን ወይም የምናባዊውን አለም ሁነቶችን በጽሑፍ ወይም ሥነ ቃል በጥበብ

መግለጽ ማለት ነው። ሥነ ጽሑፍ ልቦለድ፣ ሥነ ግጥም፣ የተውኔት ጽሁፍ እና ኢ-ልቦለድ በሚል በአራት ዘርፎች

ይከፈላል። ምናባዊ ትርክት (Imaginative Literature) ልቦለድ፣ ሥነ ግጥም እና የተውኔት ድርሰት ያካትታል።

በኢ-ልቦለድ (Non-fiction) ዘርፍ የሚካተቱ የሥነ ጽሁፍ ውጤቶች የዜና ዘገባ (News Reports)፣ የዳሰሳ

ጽሁፍ (feature article) ፣ የግለ ታሪክ (biography) ፣ የታሪክ ዘገባ (historical accounts) ሊሆኑ ይችላሉ።

ሥነ ጽሑፍ ከጥበባዊ ፋይዳዋ ባለፈ በየዘመኑ የህዝብን አኗኗር፣ አስተሳሰብ፣ ባህልና ወግ፣ በአጠቃላይ የማህበረ

ፖለቲካ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ሁነቶችን ከትባ ለትውልድ የምታስተላልፍ የታሪክ ማህደር ጭምር ናት።

በአጠቃላይ ሥነ ጽሑፍ ህዝብን ከማሳወቅና ከማንቃት የማይተካ ሚና አላት።

ስለሆነም መንግስት የሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ልማት ከሌሎች ልማቶች እኩል ትኩረት መስጠት ያሻዋል። ከዚህ አንጻር

ህዝብ የመጻፍና የማንበብ ክህሎት ብቻ ሳይሆን ልምድም ጭምር እንዲያዳብር ምቹ ሁኔታዎች መፈጠር

አለባቸው። ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ <መንግስትና የህዝብ አስተዳደር> በተሰኘው መጽሀፋቸው እንደጻፉት

ህዝብ እንዲያውቅና እንዲነቃ ማድረግ ጥቅሙ ለህዝቡ ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለመንግስትም ጭምር ነው፡-

ለአስተዳደር የሚመችና አርነት ያለው ህዝብ ጤናማ የህዝብና መንግስት ግንኙነት እንዲኖር መሰረት ነው:፤

ያልሰለጠነ ህዝብ መብትና ግዴታውን ስለማያውቅ ለማስተዳደር አይመችም፤ምክንያቱም ከንግግርና


ውይይት ይልቅ ጦርነት ይቀናዋልና ነው።ስለሆነም የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን የሚገባው ህዝቡ
እንዲነቃና እንዲሰለጥን ማድረግ ነው።

በተለያዩ መስኮች ታሪካቸው ሊወሳ፣ ገድላቸው ሊነገር ከሚገቡ የአገርና ህዝብ ባለውለታዎች መካከል

ኢትዮጵያዊያን ጸሀፍት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተለያዩ የዘመን ማዕቀፍ ብቅ ያሉ ጸሀፊያን የቀደመውን ትውልድ

የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ከፍታና ዝቅታ መዝግበው ያቆዩ፣ የዛሬን ዕውነቶችን ከትበው ለቀጣይ

ትውልድ ያኖሩ የታሪክ ነጋሪዎችም ጭምር ናቸው።

ጸሀፊያኑ በስራዎቻቸው ህዝብን ለማስተማርና ለማንቃት ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ ራሳቸው እንደ ሻማ ቀልጠው

ለህዝብ ብርሃን ሆነዋል። ታዲያ እነዚህን የሲቪል ጀግኖቻችንን ምስጋና መንፈግ አሉታዊ ተጽዕኖው ትውልድ
10
ተሻጋሪ ነው፤ ዛሬ ላይ ሆነው ነገን እየሰሩ ያሉ ተተኪ ጸሀፍት ተነሳሽነት የሚጎዳም ጭምር ነው፤ የነገውን ትውልድ

መሰረት ማሳጣት ነው፤ ይህም በታሪክ የሚያስወቅስ፣ ከሞራል አኳያም ወንጀል ነው።

ስለሆነም የአገርና የህዝብ ባለውታ ለሆኑ ጸሀፊያንና ስራዎቻቸው እውቅና ከመስጠት ባለፈ መጪው ትውልድ

እነዚህን ጀግኖች እንዲያውቅ ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታ ነው፡፡ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም

እንዲሉ በዚህች መጽሀፌ በስነ ጽሁፍ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር ያደረግሁት ጥረት ይህን

የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት እንጂ ልዩ የሥነ ጽሁፍ ችሎታ ኖሮኝ እንዳልሆነ አንባቢያን እንዲገነዘቡልኝ

እፈልጋለሁ፡፡

11
መግቢያ

በዚህ መጽሀፍ በልቦለድና ኢ-ልቦለድ ሥነ ጽሑፍ ፈር ቀዳጅ የሆኑ፣ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለዘርፉ

እድገት የራሳቸውን ሚና የተጫወቱ የሠላሳ አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን የህይወት ታሪክና ስራዎቻቸው በአጭሩ

ቀርቧል። በመጽሀፉ የተካተቱት የሥነ ጽሁፍ ሰዎች በርካታ የሚያመሳስላቸው ጉዳዮች አሉ፤ ከዚህ አንጻር

የልቦለድና የተውኔት ድርሰት እንዲሁም ጋዜጠኝነትን በሁለገብነት የሚከውኑ መሆናቸው ዋነኛው ነው።

ይህን መጽሀፍ ለማዘጋጀት በርካታ መጽሄቶችና ጋዜጦች፣ መጽሀፍት፣ የጥናት ውጤቶችና ጆርናሎች፣

የቴሌቭዥንና የሬዲዮ ፕሮግራሞች፣ ድረ ገጽ መረጃዎችን እንዲሁም ሌሎች የህትመት ውጤቶችን እንደ ማጣቀሻ

ወስጄአለሁ። ከእነዚህ የህትመት ውጤቶች ጸሀፊያኑ ራሳቸው ስለ ስራዎቻቸውና የህይወት ጉዟቸው በተለያዩ

ጊዜያት ያደረጓቸውን ቃለ መጠይቆች፣ ሌሎች ጸሀፊያን በስራዎቻቸው ዙሪያ ያጠናቀሯቸው ትንታኔዎች ለማየት

ሞክሬአለሁ። በግሌ ያነበብኳቸውን መጻህፍት ይዘት በራሴ አረዳድ በጥቂቱም ቢሆን ለመጻፍ ጥረት ባደርግም

ቴክኒካዊና ጥንቃቄ ማድረግ ስለሚያሻ በአብዛኛው ግን የስነ ጽሁፍ ባለሙያዎች የሰጧቸውን ሂሶችና ትንታኔዎችን

ማካተትን መርጫለሁ። ለዚህም ምክንያቴ አንደኛ ሁሉም መጻህፍትና ተውኔቶችን የማንበብና የማግኘት ዕድሉ

አልነበረኝም፤ ሁለተኛና ዋናው ጉዳይ ይህን ለማድረግ ራሱ የሀያሲነት ሙያን ይጠይቃልና በማላውቀው ሙያ ገብቼ

አንባቢን ማሳሳት ስለሌለብኝ ነው።

የመጽሀፉን ጠቀሜታና አስፈላጊነት አንባቢያን የሚመዝኑት ቢሆንም እኔ ግን ይህን መጽሀፍ የማሰናዳት አስፈላጊነት

ቢያንስ ከአራት አቅጣጫዎች ለማየት ችዬአለሁ። በቅድሚያ ትናንትን ያሳዩንና ለዛሬ መሰረት የጣሉ ፈር ቀዳጅ

ደራሲያንና ጋዜጠኞችን የህይወት ታሪክ እንዲህ ማዘጋጀቴ በትንሹም ቢሆን ለስነ ጽሁፍ አለም ዕድገት ላበረከቱት

ውለታ ማስታወሻ እንዲሆን በማሰብ ነው። ሁለተኛ የኢትዮጵያን ጸሀፍትን የግል የህይወትና የስራ ጉዞ መርምሮ

እንደዚህ ማዘጋጀቱ አንባቢያን ከጸሀፍቱ የግልና የስራ ህይወት ሊማሩ የሚችሏቸው በርካታ ፍሬ ነገሮች አሉ ብዬ

ስለማምን ነው። ሌላው ጉዳይ በተለያዩ ጊዜያት የጸሀፊያንን የስራና የህይወት ታሪክ በጋዜጦች፣ በመጽሄቶችና

በመጽሀፍት ለመዘከር በተደረጉ አንዳንድ ጥረቶች የመረጃዎች መጣረስና መዛባት በስፋት ይስተዋላል። በዚህ

መጽሀፍ እነዚህን ጉድለቶች ለመሙላት ተሞክሯል። ከሁሉ በላይ ግን ይህ መጽሀፍ የደራሲያኑን ስራዎችን ይዘትና

ጥልቀት፣ እንዲሁም የህይወት ጉዞ በስፋት ለመዳሰስ ለሚፈልጉ ሌሎች ጸሀፊያን ምናልባትም እንደመነሻ ይሆናል

የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።

12
ስለ ደራሲያንና ስራዎቻቸው ከማንሳት በፊት በተለያዩ የጊዜ ማዕቀፎች የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ከባቢን ማሳየት ተገቢነቱ

አያጠራጥርም። ይህም መጽሀፉን ምሉዕ ከማድረግ ባለፈ የዘርፉን ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች በማሳየት

ጸሀፊያኑ ያለፉበትን መንገድ ሊጠቁመን ይችላል፡፡ በዚህም በመጽሀፉ የመጀመሪያ ክፍል በዋናነት ከ1850ዎቹ እስከ

1960ዎቹ መጨረሻ ባለው የዘመን ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የልቦለድና ኢ-ልቦለድ ስራዎች፣ የተውኔት ድርሰትና

ጋዜጠኝነት ዙሪያ አጭር ቅኝት ለማቅረብ ሞክሬአሁ፡፡

ሠናይ ንባብ!

ሀምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም

ጅግጅጋ፤ ኢትዮጵያ

13

View publication stats

You might also like