You are on page 1of 8

See discussions, stats, and author profiles for this publication at: https://www.researchgate.

net/publication/335911251

Foreword for Wedaje Libbe

Chapter · September 2007

CITATIONS READS
0 289

1 author:

Tewodros Gebre
Addis Ababa University
23 PUBLICATIONS 4 CITATIONS

SEE PROFILE

All content following this page was uploaded by Tewodros Gebre on 19 September 2019.

The user has requested enhancement of the downloaded file.


ማስተዋወቂያ

የሃያኛው ክፍሇ ዘመን የመጀመርያ አጋማሽ ቀዲሚ ምእራፍ፣ በተሇይ ከጦቢያ


(ሌብ ወሇዴ ታሪክ) መታተም እስከጣሉያን መግባት፣ 1900-1928 ያሇው ጊዜ ሇአማርኛ
ስነ ጽሐፍ የመሰረት መጣያ ዘመን ነው ተብል ይታመናሌ፡፡ በዚህ በተጠቀሰው ዘመን
ተነስተው የአማርኛን ስነ ጽሁፍ መሰረት ከጣለና ካጠበቁ ዯራስያን መሃሌ እውቁ
የፖሇቲካ ሰውና ዱፕልማት፣ ብሊቴን ጌታ ኅሩይ ወሌዯ ስሊሴ አንደ ናቸው፡፡ ብሊቴን
ጌታ በዚሁ ዘመን ውስጥ ባነሱት ሃሳብ፣ በተመሰረቱበት ዘውግና በመረጡት የአጻጻፍ
ቅጥ ሇየቅሌ የሆኑ በርካታ መጻሕፍትን -የሌብ ወሇዴ፣ የታሪክ፣ የሕይወት ታሪክ፣
የጉዞ ማስታወሻ፣ የስነቃሌ፣ የመጻሕፍት ዝርዝር፣ የተግሳጽና የምክር መጻሕፍትን-
አሳትመዋሌ፡፡

ከእነዚህ፣ ዯራሲው በሕይወት እያለ ካሳተሟቸው መጻሕፍት መሃከሌ ዯግሞ አዱስ


አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ “ወዲጄ ሌቤ”፣ “ሇሌጅ ምክር ሇአባት መታሰቢያ”፣ “ሱካርና
ወተት የሌጆች ማሳዯጊያ”፣ “የሌብ አሳብ፡ የብርሃኔና የጽዮን ሞገሳ ጋብቻ” እና “አዱስ
ዓሇም፡ የቅኖችና የዯግ አዴራጊዎች መኖርያ” የሚለትን አምስት ዴርሰቶች በአንዴ ቅጽ
ጠቅሌል አሳትሟሌ፡፡ ከአምስቱ ዴርሰቶች መሃሌ “ሇሌጅ ምክር ሇአባት መታሰቢያ” እና
“ሱካርና ወተት የሌጆች ማሳዯጊያ” ሇሌጆች ታስበው የተጻፉ የምክር-የተግሳጽ እና
የተረት መጻሕፍት ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሶስት ዴርሰቶች ዯግሞ የሌብ ወሇዴ ሙከራዎች
ናቸው፡፡ ይህ መግቢያም በዋናነት ሌብ ወሇድቹን የሚያስተዋውቅ ይሆናሌ፡፡ ሌብ
ወሇድቹን በተመሰረቱበት ሃሳብ እና በተከየኑበት መንገዴ፤ “የሌብ አሳብ”ን እና “አዱስ
ዓሇም”ን በአንዴ ወገን፣ “ወዲጄ ሌቤ”ን ዯግሞ በላሊ ወገን አዴርገን እንመሌከት፡፡

አንዯኛ፤ “የሌብ አሳብ” እና “አዱስ ዓሇም”፣ ማሕበራዊ ሌብ ወሇድች፤


እርግጥ ነው እነዚህን ከ75 ዓመት በፊት የተጻፉ ዴርሰቶች ዛሬ ሌብ ወሇዴን
በምንመዝንባቸው ኪናዊ መሇኪያዎች -- በአተራረክ ቴክኒክ፣ በመቼት አቀራረጽ፣ በገጸ
ባሕርይ አሳሳሌ ጥበብ ወዘተ. -- የምር እንመዝናችሁ ካሌን መቸገራችን አይቀርም (ገና
ከመነሻው “የሌብ ወሇዴ ሙከራዎች” መባሊቸውም ሇዚሁ ነው)፡፡ ዲሩ ግን፣ አንዴም
በኪናዊ እሴቶቻቸው የሳሱ ቢሆኑም እንዯምናባዊነት፣ ፈጠራዊነት ያለ መሰረታዊ

1
የስነጽሐፍ ባሕርያትን በማሟሊታቸው፤ አንዴም፣ ዯራሲው “አዱስ ዓሇም” ሇተባሇው
ዴርሰት በጻፉት መቅዴም በቀጥታ እንዯሚነግሩን (ገጽ 166-167) በትክክሌ ከተዯረጉና
ከሆኑ ገጠመኞች ይሌቅ በሰው ሌጅ ሕይወት ውስጥ ሉሆኑና ሉዯርሱ በሚችለ
እውነታዎች ሊይ በመመስረታቸው፤ በገቢር ከታዩና ከተሰሙ ጉዲዮች ይሌቅ ከአይነ
ኅሉናና ከእዝነ ሌቡና (በጥቅለ ከምናብ) የመነጩ ስሜታዊና ሃሳባዊ ገጠመኞችን
ምርጫቸው በማዴረጋቸው የዴርሰቶቹን ሌብ ወሇዲዊነት አምነን እንቀበሊሇን፡፡ ዴርሰቶቹ
የተጻፉበትን ዘመንና ሁኔታም ከግምት ማስገባቱ ተገቢ ይመስሇኛሌ፡፡

የሌብ ወሇድቹ አቢይ ትኩረት የማሕበረሰቡ የእሴት ስርዓት እና የገጸ ባሕርያቱ


ማሕበራዊ ማንነት ነው፡፡ በሌብ ወሇድቹ ውስጥ፣ የማህበረሰቡን ማህበራዊ ተቋማት፤
በተሇይም ጋብቻን፣ ቤተሰብን፣ ዝምዴናን ወዘተ. የሚመሇከቱ ቤተ ዘመዲዊ ተቋማት
(kinship institutions) እና ከሃይማኖት፣ ከትምህርትና ከእዯ ጥበብ ጋር ትስስር ያሊቸው
የባህሌ ተቋማት (cultural institutions) እንዯየአይነታቸው እና እርከናቸው የተነሱ
ሲሆን በተቋማቱ ውስጥም ይሁን በተቋማቱ መሃሌ ያሇ ትስስርም በመጠኑ
ተብልበታሌ፡፡ ግሇ ሰብ ገጸ ባህርያት ከተቋማቱ ጋር ካሎቸው ፈርጀ ብዙ መስተጋብሮች
የሚወሇደ ስምምነቶችና ይሌቁንም በአስተሳሰብ፣ በአመሇካከት፣ በአኗኗር ፈሉጥ ሌዩነት
ምክንያት የሚፈሇፈለ ግጭቶች፣ ግጭቶቹ ያስከተሎቸው ማህበራዊ ሇውጦች
(አንዲንዳም ቀውሶች) የእነዚህ ሌብ ወሇድች የትኩረት ነጥቦች ናቸው፡፡

ኅሩይ በእነዚህ ዴርሰቶቻቸው የማህበራቸውን ገበና በዴፍረት ይገሌጣለ፡፡ ከጽኑነታቸው


የተነሳ ዴርሰቶቹ ከተጻፉ ከ75 ዓመት በኋሊ፣ ዛሬን ጭምር የዘሇቁ አጓጉሌ ሌማድችን፣
ያሇእዴሜ ጋብቻን፣ በቤተሰብ የሚታቀዴና የሚቆረጥ ጋብቻን በዴፍረት (ጥበብና
ብሌሃት ባሇዘቡት ዴፍረት) ይተቻለ፡፡ ኅሩይ የገነቡት ምናባዊ ዓሇም ወሊጅና ሌጅ
ተቻችሇውና ተከባብረው የሚኖሩበት፣ የጾታ እኩሌነት የሰፈነበት ጭምርም ነው፡፡
በተሇይም በዘመኑ የነበረው የሴትነት እሴት ተነቅል የወዯቀ እስኪመስሌ ሚስት ከባሎ
እኩሌ በሌጇ እጣ ፈንታ ሊይ ትመክራሇች፡፡ ሴት ሌጅ ምርጫዋ ይከበራሌ፤ ፍሊጎቷን
ትፈጽማሇች፤ ፈቃዶን ትሞሊሇች፡፡

2
የኅሩይ ዴርሰቶች ማሕበራዊ ሇውጥ ነው ግባቸው፡፡ ሇውጥን ይናፍቃለ፤ ሇውጥን
ይጠራለ፤ ሇውጥን ያሰፍናለ፡፡ ሇአንደ ዴርሰታቸው በጻፉት መቅዴም “አንዲንዴ ሰዎች
ብዙ ዘመን የኖረውን ሌማዴ ማሻሻሌ ማዯስ እንዯነውር ይመስሊቸዋሌ፡፡ ይኸውም
የቀዴሞውንና የዛሬውን ታሪክ ካሇማንበባቸውና ካሇመረዲታቸው የተነሣ ነው---” (ገጽ
177) የሚለን ኅሩይ በሸንጎ፣ በሉቃውንቱ ፊት በሚዯረግ ሙግት አጓጉሌ ሌማዴ
በሇውጥ ሲረታ ያሳያለ፡፡ ዲሩ ግን፣ አዲዱስና ተራማጅ አስተሳሰቦች የሚመሰረቱት
ጠቃሚ በሆኑ ነባር የማህበሩ እሴቶች ሊይ በመሆኑ ይህ ሇውጥ ሙለና እንግዲ ነው
ሇማሇት አንችሌም፡፡ በዚህ አይነቱ ስርዓት የታነጹ፣ ወይም የዚህ ዓይነቱ እሴት ማዯርያ
(embodiment) የሆኑ ገጸ ባሕርያት፣ የምር ኢትዮጵያዊ ሆነው ነው የተቀረጹት፤ በአንዴ
በኩሌ ማህበራዊ ሇውጥ ይጠነስሳለ፤ በላሊ በኩሌ ዯግሞ ባህሌና ታሪክ ጠብቀው
ያኖራለ፡፡ በተጨማሪም ማህበራዊ ሇውጥ ማህበራዊው ስርዓት ሳይናጋ፣ ማሕበራዊ
ቀውስ ሳይፈጠር የሚመጣ ክስተት በመሆኑ ሌብ ወሇድቹ የዯራሲው በጎ ርእይ አዴሮ
የተገሇጠባቸው ዴርሰቶች ናቸው ብል ማጠቃሇሌ ይቻሊሌ፡፡

ሁሇተኛ፤ “ወዲጄ ሌቤ”፣ አሉጎሪያዊ ሌብ ወሇዴ፤


በሀገራችን የስነ ጽሁፍ ትምህርት ውስጥ ዛሬም ዴረስ ሇአላጎሪያዊ አጻጻፍ በምሳላነት
የሚጠቀሰው ወዲጄ ሌቤ በዋናነት በመንፈሳዊ ወይም ሀይማኖታዊ እና ስነ ምግባራዊ
እሴቶች ሊይ ተመስርቶ የተጻፈ ሌብ ወሇዴ ነው፡፡ የ“ወዲጄ ሌቤ”ን አይነት ሌብ ወሇድች
(ክርስትያናዊ አላጎሪ /Christian allegory/ በመባሌ ይጠራለ) አቢይ አሊማና ተግባር
የማህበራቸውን መንፈሳዊ እሴቶች አንስተው የስነ ምግባር ትምህርት መስጠት በመሆኑ
ብዙውን ጊዜ አንባቢያቸውን ሇመማረክና ሇማሸነፍ ይቸገራለ፡፡ ዲሩ ግን በ“ወዲጄ ሌቤ”፣
ዯራሲው እያፈራረቁ በተገሇገለባቸው ቴክኒኮች፣ እያሰባጠሩ በዘርዋቸው ፎክልራዊ
ቅርጾች፣ እንዱሁም የታሪኩን ፍሰት በተቆጣጠሩባቸው እንዯ “ጉዞ” እና “ፍሇጋ” ባለ
ነባር ሚታዊ መባያዎች (mythological motifs) አማካይነት ሌብ ወሇደን የታዯጉት
ይመስሇኛሌ፡፡

ሌብ ወሇደ ሲጀምር እንዱህ ይሊሌ፤ “በተወሇዴሁ በ፲፰ ዓመት ከዘመድቼ ተሇይሰቼ


ወዲጄ ሌቤን ብቻ አስከትዬ ከቤት ተነሣሁ፡፡ አሳቤም ይህን ዓሇም (መጻሕፍትን)
በምሥራቅና በምዕራብ፤ በሰሜንና በዯቡብ እየዞርሁ ሇማየት ነበር” (ገጽ 3፣ አጽንኦት

3
የእኔ)፡፡ በጥቅሱ ውስጥ ያሰመርኩባቸው አራት ሃሳቦች ሌብ ወሇደን በወጉ ሇማንበብ
(በተሇይም ሇሚታዊ ንባብ /mythological reading/) እጅግ ወሳኝ ይመስለኛሌ፡፡ በሌማዴ
እንዯምናውቀው 18 ዓመት፣ ሰው ከሌጅነት ወዯጎሌማሳነት፣ ወዯ ሙለ ሰውነት
የሚሸጋገርበት አካባቢውን ሇመረዲት፣ ማህበሩን ሇመመርመር፣ ራሱን ሇመፈተሸ፣
በጥቅለም የሰው ሌጅን የመኖር ምክንያት ፈሌጎ ሇማግኘት የሚቀሰቀስበት-የሚተጋበት
እዴሜ ነው፡፡ የ”ወዲጄ ሌቤ” ገጸ ባሕርይ ከሰሜን እስከዯቡብ፣ ከምስራቅ እስከምዕራብ
በተዘረጋው የመጻሕፍት ዓሇም ውስጥ እንዯ እውቀት፣ ጥበብ፣ እውነት ያለ ጸናን
ጉዲዮችን ፍሇጋ ነው የሚጓዘው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጉዞ በመመሰጥ፣ በማብሰሌሰሌ፣
በማሰሊሰሌ እና እነሱን በመሰለ ጥብቅ ዱሲፕሉኖች የሚካሄዴ በመሆኑ አካባቢን
በመንፈስ መሇየት፣ አካሌን መቆጣጠርና በስጋዊ ፍሊጎቶች ሊይ መሰሌጠን፣ ወዯውስጥም
ርቆ መጓዝ ይቻሊሌ፡፡ (ይህንን ነው እንግዱህ ገጸ ባሕርይው፣ “ከዘመድቼ ተሇይቼ ወዲጄ
ሌቤን ብቻ አስከትዬ ከቤት ተነሣሁ” የሚሇን፡፡)

በጉዞ ውስጥ ከመሇየት (departure) በኋሊ የሚከተሇው ምእራፍ ተጋዴል (adventure)


ነው፡፡ ሇረጅም ጉዞ የወጣ መንገዯኛ ብዙውን ጊዜ ሉወጣው ከሚከብዯው አስቸጋሪ ፈተና
ውስጥ ይጣሊሌ (ወይም ይገባሌ)፡፡ በምዴር ሊይ በሚፈጸም አካሊዊ ጉዞ (exterior
pilgrimage) ተጓዡ ከሰውና ከተፈጥሮ ክስተቶች ጋር ትንንቅ ይገጥማሌ፡፡ ከፍ ብዬ
እንዯጠቆምኩት፣ “ወዲጄ ሌቤ” የተመሰረተው በንባብ አማካይነት በሚካሄዴ አእምሯዊና
መንፈሳዊ ጉዞ (interior pilgrimage) ሊይ በመሆኑ ገጸ ባሕርይው በመሌክአ ምዴር
ትይዩ ያሇውን የመሌክኣ ሌቡናን (inner landscape) “ጫካ” የማቋረጥ፣ “ተራራ”
የመውጣት፣ “ባሕር” የመጥሇቅ ግዳታ ነው የሚጣሌበት፡፡ መሌክአ ሌቡና በትርጓሜ
ካሌሆነ በቀር በገሃዴ የማይዯረስበት የሰው ሌጅ ኅሉናዊ ዓሇም ነው፡፡ ይህ ዓሇም ዯግሞ
የሰው ሌጆች ስሜታዊ (emotional)፣ ምግባራዊ (moral) እና እውቀታዊ (intellectual)
ማንነት መኖርያ ወይም ማዯርያ ነው፡፡ ይህ ነው እንግዱህ የዴርሰቱ አቢይ ጉዲይ፡፡
ሌብ ወሇደ እንዯሚያሳየን የሰው ሌጅ ረቂቅ ባህርያት በአንዴ ሰው ሌቡና ውስጥ በአንዴ
ጊዜ ተቃርነው፣ ተቀያይጠው ይመጣለ፡፡ ትህትና የሚባሌ ጊዜ የጣሇው የጨዋ ሌጅ
እና ትዕቢት የሚባሌ ላባ ጌታ ዴንቁርና በሚባሌ አገር አብረው ይኖራለ (ገጽ 5)፡፡
ፍቅር ገርነትን አግብቶ፣ ቅንነትን አሽከር ቀጥሮ ከቅናትና ከምቀኝነት ጋር ተጎራብቶ
በአንዴ አገር ይኖራሌ (ገጽ 20)፡፡ ነጭ ሇባሹና ሳቂታው ተንኮሌ አቶ ፍቅር ቤት

4
በእንግዴነት ያዴራሌ (ገጽ 20)፡፡ ይህ ዓይነቱ የተጠፋፊዎችና የተቃራኒዎች መገጣጠምና
መቀያየጥ (coincidence and fusion of opposites) ነው የሰው ሌጅን ሰብእና
የሚያወሳስበው፤ ፀባዩን፣ ፍሊጎቱንና ምግባራዊ ማንነቱን እያዯበሊሇቀ፤ አንዴ ሰው ስሇገዛ
ራሱ፣ ሰው ስሇ ጥቅለ የሰው ሌጅ፣ ሰው ስሇአሇመ አሇማቱ፣ ሰው ስሇአምሊኩ ያሇውን
አመሇካከት፣ ፍሌስፍናና እምነት እያዛነቀ፣ ወዘተ.፡፡ የሌብ ወሇደ ማቀንቀኛ-ማጠንጠኛ
ጉዲዮች እነዚህ ናቸው፡፡ ጉዲዮቹ የሰውን ሌጅ አጠቃሊይ ኑባሬ (human existence)
የሚመሇከቱ ኅሉናዊ ክስተቶች በመሆናቸው እጅጉን ይረቅቃለ፤ ይጠሌቃለ፣
ይወሳሰባለ፡፡

ይህንን ጸናን እውነታ በመረዲት ይመስሇኛሌ ዯራሲው ሌብ ወሇዲቸውን ሙለ በሙለ


በአላጎሪያዊ የአጻጻፍ ቅጥ የከየኑት፡፡ በአላጎሪያዊ አጻጻፍ ሰው ያሌሆኑ ነገሮች፣ ረቂቅ
ሃሳቦችና ግብሮች የሰው ሌጅን ተግባርና ባህርይ ይወርሳለ፡፡ አንዯበት አውጥተው
ይናገራለ፤ አካሌ ገዝተው፣ ቅርጽ አበጅተው ይንቀሳቀሳለ፤ ስሜት ሉያግቱ--ሉያዝኑ፣
ሉዯሰቱ፣ ሉከፉ፣ ተስፋ ሉያዯርጉም ይችሊለ፡፡ “ምርምር” እና “ዴንቁርና” የአገር ስሞች
ናቸው፡፡ ትዕቢት አንበሳ፣ ንፍገት ዯግሞ አቦሸማኔ ነው (ገጽ 57)፡፡ ንፍገት ከርዝመቱ
የተነሳ “በጫፉ ሊይ የቆሙ እንዯሆነ ሰዉም፣ ከብቱም፣ ወርቁም፣ ብሩም --- ጥቂት
መስል” የሚታይበት ረጅም ተራራ ነው (ገጽ 9) ፡፡ በሰብዓዊ የእሴት ስርዓት ይመራለ፤
ይተዲዯራለ፡፡ ትሕትና ወንበር ዘርግቶ ያስተምራሌ (ገጽ 29)፤ “የበሇው ጌታ” ሇአቶ
ቅናት፣ “የፍጀው ጌታ” ሇአቶ ተንኮሌ የተሰጡ የፈረስ ስሞች ናቸው፡፡ ተንኮሌና ቅናት
በጦር ሌብሳቸው ዯምቀው በፈረስ ስማቸው ይፎክራለ፤ ይሸሌሊለ፤ ያቅራራለ (ገጽ 39-
40)፡፡ ረቂቆቹ ኅሉናዊ ክስተቶች በዚህ ሌብ ወሇዴ ውስጥ ሇዓይነ ሌቡና እጅግ ቅርብ
ሆነው ተስሇዋሌ፡፡ ሌብ ወሇደ የተከየነበት ቋንቋ ቅሇትና የአቀራረቡ ቀጥተኛነት ዯግሞ
ጽንሰ ሃሳቦቹን ጭምር ገር አዴርጓቸዋሌ፡፡

ከወገን በመሇየት የሚጀምረው “ወዲጄ ሌቤ” ገጸ ባሕርይውን ወዯተሇያቸው “ዘመድቹ”


በመመሇስ (return) ነው የሚቋጨው፡፡ በሚታዊ ጉዞ ውስጥ የገባ ገጸ ባሕርይ
ወዯመኖርያው የሚመሇሰው ሇተሇየው ዓሇሙ ከሚጠቅም አንዲች በረከት (boon) ጋር
ነው፡፡ በ“ወዲጄ ሌቤ” ውስጥ መሰረታዊው ጉዲይ በንባብ ምክንያት ወዯግጭት የሚገባ
ሌቡና ነው፡፡ ከፍ ብሇን እንዯተመሇከትነው በሌቡና ውስጥ የሚከሰተው የተቃራኒና

5
የተጠፋፊ ስሜቶች፣ ምግባሮችና አስተሳሰቦች መገጣጠምና መዯበሊሇቅ የሚፈጥረው
ሇባሇቤቱ እንግዲ የሆነ ቀውስ አሇ፡፡ ሰው ሇራሱም ጭምር ዴብቅና ሽሽግ ከሆነ ማንነት
(ክፉም ሆነ ዯግ) ጋር መተዋወቁ (self realization) ቀዲሚው በረከት ነው፡፡ (በስነ ሌቡና
ተራ እንናገር ከተባሇ ይህ ጉዞ ንቁ ከሆነው የሰው አእምሮ ወይም ማንነት "the
conscious self" በውሌ ወዯማይታወቀው፣ ሇባሇቤቱ ጭምር እንግዲ ወዯሆነው ማንነት
“unconscious self" የሚዯረግ ነው፡፡)

ከዚህ ዓይነቱ መገሇጥ፣ ከዚህ አይነቱ የራስ እውቀት በኋሊ ሕይወት እንዯወትሮዋ
አትሆንም፡፡ ተሇምዶዊው የኑሮ አዴማስ ያረጃሌ፡፡ ከነባር ጽንሰ ሏሳቦችና እሴቶች ፍቺ
ይታጣሌ፡፡ በዚህ ምክንያት ሰው ከገዛ ራሱ ጋር ትንንቅ ይገጥማሌ፤ ራሱን ያሸንፋሌ፤
ከራሱ ጋር (ወይም በራሱ መሃሌ) እርቅ ያወርዲሌ፡፡ በስነምግባር ዯንቦች ይታሻሌ፤
በስሜት ይበስሊሌ፤ በእውቀት፣ በግንዛቤ ይሌቃሌ፡፡ በአዱስ ማንነት ይወሇዲሌ፡፡ ሰው
በጥቅለ ሇሰብእና ሌእሌና (transfiguration of personality) ይበቃሌ፡፡ በተራዛሚው
ሇሰርክ ሕይወቱም ሇዘሇሇት ዓሇሙም መታዯስ ( renovation of the world) ምክንያት
ይሆናሌ፡፡ ይህ ነው ከረጅሙ ጉዞ በኋሊ ወዯተሇየው የሰርክ ሕይወት፣ ዘሇሇታዊ ማንነት
ይዞ የሚመሇሰው በረከት፡፡ ሇዚህም ይመስሇኛሌ በሌብ ወሇደ ማብቂያ በሚመጡ
ምእራፎች ውስጥ ከቀዲሚዎቹ ምእራፎች እጅግ በተሇየ እንዯ ትኅትና፣ ቸርነት፣ ይቅር
መባባሌ፣ ዴኅነት ወዘተ. ያለ በጎ እሴቶች የሚገኑት፡፡

ሇማሳረግ ያህሌ፤
እስካሁን በመግቢያነት ያስተዋወቅኋቸው የማንበቢያ አንጻሮች እነዚህን፣ በአንዴ ቅጽ
ተጠቃሇው የቀረቡ ሥራዎች ሇማንበብ ብቸኛ መንገድች አይዯለም፤ ፈጽሞ፡፡
ሥራዎቹን አናጥልም ይሁን አዲብል ሇማጣጣም የሚያስችለ በርካታ የማንበቢያ
አማራጮች (possibilities of reading) አለን፡፡ የዴርሰቶቹን ባሕርይ፣ ዴርሰቶቹ
የበቀለበትን ዘመንና ሥፍራ፤ እንዱሁም ከዘመኑና ከስፍራው ጋር የሚናበቡ
ማሕበራዊና ርእዮተ ዓሇማዊ አንዴምታዎችን ከግምት እስካስገባን ዴረስ በየትኛውም
የማንበቢያ አንጻር መገሌገሌ እንችሊሇን፡፡ ሁሊችንም እንዯምናውቀው፣ ጥሩ ሌብ ወሇዴ
በጥበባዊ ኃይለ ታግዞ ታሊሊቆቹን ሰብዓዊ እሴቶች ያነሳሌ፤ ሕይወትን ይመረምራሌ፤
ሕይወትን ይተረጉማሌ፤ የዯረሰበትንም ግኝት በቋንቋው ሀይሌ ይስሊሌ፡፡ ወይም በላሊ

6
አነጋገር ስነ ጽሐፍ ከፍ ብዬ በዘረዘርኳቸው ጉዲዮች ሊይ በዯራሲው የሚሰጥ
አስተያየትና ትችት ነው፡፡ አንዴን ሌብ ወሇዴ ስናነብ ምናሌባት--ምናሌባት አስተያየቱና
ትችቱ ሉጎረብጠን፣ ትርጓሜው ሊይስማማን ይችሌ ይሆናሌ፡፡ የምናነበው ዴርሰት
ስነጽሐፋዊ ሥራ እስከሆነ ዴረስ ግን ቅዴምና የምንሰጠው ጉዲይ (determining factor
of the work) አከያየኑ መሆን አሇበት፡፡ ስሇዚህ ምናሌባት ስብከቱ ያሌጣመው፣
አስተምሕሮቱ ያሌተዋጠሇት ቢኖር እንኳ ቢያንስ ቢያንስ አሇም የታየችበትንና
የተተቸበትን፣ ሕይወት የተተረጎመበትን፣ የሰው ሌጅነት የተበየነበትን ጥበባዊ መንገዴ
አዴንቆ ይሇፍ፡፡ መሌካም ንባብ፡፡

ቴዎዴሮስ ገብሬ

View publication stats

You might also like