Professional Documents
Culture Documents
Final Exam
Final Exam
ማጠቃለያ ፈተና
ሀ. ትክክለኛውን መልስ እውነት ከሆነ እውነት ሐሰት ከሆነ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡
1. በብሉይ ኪዳን ለሌዋውያን ብቻ ይሰጥ የነበረው ስልጣነ ክህነት በሐዲስ ኪዳንም እንዲሁ ይፈጸማል።
2. ፊልጶስ የቁም ተዝካሩን አውጥቶ ጌታን የተከተለ ሐዋርያ ነው።
3. ቅ ማርቆስ የእስክንድርያ መንበር ሠስራች የነበረው ሐዋርያ ነው።
4. ቅ ጴጥርስና ቅ ጳውሎስ ሰማዕትነት የተቀበሉት በትራጃን ዘመነ መንግስት ነወ።
5. `` በሃይማኖት ላይ የሚጨምር ደፋር የሚቀንስ ደግሞ ሌባ ነው`` በማለት መናፍቃንን በመቃወም የሚታወቀው ቅ
ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።
በክርስቶስ ኢየሱስ የተመሰረተችው እምነት ክርስትና በመባል አማኞቹም ክርስቲያን በመባል እየተጠሩ እስከ 4 ኛው መቶ ክፍል ዘመን
ቆይቷል፡፡በ 325 ዓ.ም በተደረገው የኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት ሊቃውንት ኦርቶዶክስ ክርስትና በማለት እንደጠሯት እና በ 432 ዓ.ም
በኤፌሶን ጉባኤ ያደረጉ አባቶች “ተዋህዶን “ አስተምረው አክለዋል
1. ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል በወቅቱ ለማስተማር እና ለማከል ያበቃው ምክንያት ምን ነበር? በዚህስ ተጠቃሹ ከሃዲ ማን ነበር?
2. ኦርቶዶክስ የሚለው ሥያሜ ምንን ያመለክታል?
3. በወቅቱ ተዋህዶን ለማስተማር እና ለመጨመር ያበቃው ምክንያት ምን ነበር የነበረውስ ክህደቱስ ምን ነበር?
4. ተዋህዶ ስንል ምን ማለታችን ነው?
መ. ቦነስ
1. አያድርገውና ! ከመካከላችሁ አንዱ አባል የምንፍቅና ሀሳብ ይዞ ቢያስቸግር እና ይኸው ሀሳብ ሌሎች አባላት ላይ
ተጽዐኖ ማድረጉን ድንገት ብትሰሙ እርምጃ ለመውሰድ ምን አይነት ሂደት ትከተላላችሁ?
2. የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ከተማራችሁ በኋላ ምን እሴት ጨመራችሁ ምንስ ተሰማችሁ ?
3. ቤተክርስቲያንን በአሁኑ ጊዜ ይበልጡን እየፈተናት ያለው የውስጥ ጠላት ነው ወይስ ውጫዊ ጠላት ነው ?
አብራሩ