You are on page 1of 19

የሁለተኛ ጴጥሮስ መልእክት እና የይሁዳ መጽሐፍ

የኤማሁስ ኢትዮጵያ ተልዕኮ ትምህርት ኮሌጅ

1. ጸሐፊው ማን ነው?

ብዙ የማብራሪያ መጻሕፍት ሐዋርዉ ጴጥሮስ እንደጻፈዉ ይህንን ለማድረግ በቂ ምክንት እንዳለዉ


ይነግረናል፤

 ጸሐፊዉ ስምኦን ጴጥሮስ እንደሆነ ተናግሯል (1፡1፣ዮሐንስ 1፡42)፤


 ራሱን የኢየሱስ ሐዋርያዉ ብሎ መጥራቱ (1፡1)፤
 ራሱ በመገለጡ ተራራ (በቅዱሱ ተራራ) ላይ አብሮ እንደነበር በመመስከር (1፡16-18፣ ማቴዎስ
17፡1-13)፤
 መጽሐፉ ሁለተኛ እንደሆነ ገልጾአል (3፡1)፡፡
ጴጥሮስ ከአስራ ሁለቱ ታዋቂ ሐዋርያት ዉስጥ አንዱ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ነዉ፤ በኢየሩሳሌም በተተከለችዉ
ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ተናጋሪ ቢሆንም እርሱ ግን በተለያዩ ከተሞች በሐዋርዉ ጳዉሎስ በተተከሉ
አብያተ ክርስቲያን ቤተክርስቲያነ በመዘዋወር ወንጌል ይሰብክ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ሁለት መልእክቶችን የጻፈ
ሲሆን መልዕክቶቹም በአምስት ትንሹ የእስያ አገሮች ተሰራጭቷል፤
መልእክቱ የሚጀምረዉ የጸሐፊዉን ስም በመጥቅስ ሲሆን ይኸዉም፤ ስምኦን ጴጥሮስ በማለት ነዉ፤ የአባቱ
ሰም ስምኦን ሲሆን ጌታ ያወጣለት ስም ደግሞ ጴጥሮስ ነዉ፤ (ዮሐንስ 1፡42)፤ ራሱን፤ የጌታ ባሪያ ይላል፤
ይህም የእርሱን ትህትና የሚያመለክት ቃል ነዉ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ፤ የሚያሳየዉ ተልእኮዉን
መረዳት ነዉ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ዉስጥ ታላቅ ማን ነዉ? ከሚል ክርክር ዉስጥ ወጥቶ እንዲህ
ማለቱ የሚገርም ነዉ፤ (ሉቃስ 22፡24-31)፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ምሳሌ ነዉ፤ በተሰጠን ስፍራ ላይ ሆነን
እንደ ባሪያ ነዉ ማሰብ ያለብን፡፤ በተልእኮአችን ሁሉ መታዘዝ ይኖርብናል፡፡
1
2. ለምን ጸፈ?
 በሁለተኛዉ መልእክቱ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ያሉ የስህተት አስተማሪዎችን ለማስጠንቀቅ ሲሆን
የእምነታቸዉ መሰረት በማስታወስ እና በመንፈሳዊ ሕይወታቸዉ እንዲያድጉ ለማበረታታት
ነዉ፡፡
 በመጀመሪያ መልእክቱ ጴጥሮስ ክርስቲያኖችን ሲያበረታታ እና ከውጭ በተቃዋሚዎች
ስለሚደርስባቸዉ ጉዳይ እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸዉ ሲጽፍ እንመለከታለን::
 በ 2 ኛ ጴጥሮስ ግን በዉስጥ ያሉ የሐሰተኛ አስተማሪዎችን እና አስተምህሮአቸዉን እንዴት
በቤተክርስቲያን ዉስጥ መቆጣጠር እንዳለባቸዉ ያመለክታል፤ እነዚህ የሐሰት አስተማሪዎች
ክርስቲያኖች ነን ብለዉ ያወራሉ ነገር ግን አይደሉም:: ጴጥሮስ እያስጠነቀቀ ያለዉ ነገር ቢኖር
ከእነዚህ የስህተት አስተማሪዎች አስተምህሮ እና የወንጌል እዉነት ከሚበርዙ ሰዎች አማኞች
መጠንቀቅ እንዳለባቸዉ ያስጠነቅቃል፡፡ በመልዕክቱ ዉስጥ አስተምህሮአቸዉን ለመለየት እና
ትክከለኛዉን አስተምህሮ ለመጠበቅ የሚያስችል መንገዱን ይጠቁማሉ፡፡

3. መቼ?

ጴጥሮስ ይህን መጽሐፍ የጻፈው በ 64 ዓ.ም ላይ ነዉ ተብሎ ይገመታል፤ ከዚያም ሰማእት የሆነዉ
በ 67 /68 ዓ.ም ላይ ተብሎ ይገመታል፤ በጽሑፉ ዉስጥ የሞቱ ቀን እንደቀረበ ይናገራል፤ (1፡14)፤

4. ለማን?
 2 ኛውን መልዕክት የጸፈላቸዉ የመጀመሪዉን ለጻፈላቸዉ ሰዎች ነዉ፤ (3፡1)፡፡
 እነዚህ አማኞች በአምስቱ የሮም ግዛት ዉስጥ ተበትነዉ ያሉ ናቸዉ:: (1 ጴጥሮስ 1፡1)፤
 ምናልባትም የአይሁድ እና የአሕዛብ አማኞች ድብልቅ ሕዝቦቸ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡
5. የት ሆኖ ጸፈ?
የመጀመሪያ መልዕክቱንም ሁለተኛውንም የጸፈው በሮም ሆኖ ነበር (1 ዼጥ 5:1)::
በቅርቡ እንደሚሞት ስለተረዳ (2 ዼጥ 1:14) ከመሞቱ በፊት ማስታወስ/ማስጠንቀቅ
ለሚፈልገው ነገር እንዲያውቁ ጽፎአል
6. ቁልፍ ጥቅስ 3:9 ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም የእርሱ ትዕግስት ማንም እንዳይጠፈ
ነው
7. የመልዕክቱ ጭብጥ ሐሳብ

<<ዕዉቀት>> በሶስቱ ምዕራፎች ዉስጥ ቁልፍ ሐሳብ ነዉ፤ የክርስቶስ ሙሉ እዉቀት ለመንፈሳዊ ሕይወት፤
ለሐይል እና እድገት ምክንያት ነዉ፡፡ 1:3-4 እግዚአብሔር በቅድስና እንድንኖር የሚያደርግ ሐይልን

2
ሰጥቶናል፤ ራሳችንን በመግዛት እና ክርስቶስን በማወቅ እርሱን በመምሰል እንድንኖር የሚያደርግ ነዉ፤
በጴጥሮስ ዘመን የስህተት አስተማሪዎች በእዉቀት ላይ ትኩረት ያደርጉ ነበር፤ ነገር ግን እዉቀት ያለ ሞራላዊ
ሃላፊነት ነበር፤ ክርስትና አስተምህሮዉ በክርስቶስ እዉቀት ስንኖር ዉጤቱ በሞራላዊ ሕይወታችን እርሱን
መምሰል ነዉ፡፡

8. ዋና ዋና ሀሳቦች
 እምነት ነፃ ስጦታ ሲሆን አማኞች በእሱ ላይ መጨመር አለባቸው
 እግዚ/ር ልጆቹን ለማዳን ታማኝ ነው
 ኢየሱስ የከበረ የፍጥረታት ንጉስ ነው

የየምእራፉ ማጠቃለያ ሐሳብ

8.1 በምዕራፍ 1 በመንፈሳዊ ሕይወታቸዉ እንዲያድጉ እና ነቢያት የመሰከሩለትን እዉነት መያዝ


እንዳለባቸዉ ያበረታታል::
 በእምነታቸው ማደግ እንዳያቆሙ ይሞግታቸዋል:: የክርስቲና ሕይወት
እያደገ የሚሄድ ነው:: እውነተኛ እምነት ሁሌም ይሰራል
 እግዚ/ር ሕዝቡን የጠራው መለኮታዊ ባህርዩን እንዲካፈሉ ነው:: ይህም
ዘላለማዊ ህይወትና ፍቅሩን ነው:: ይህም ድንቅ ስጦታ ሲሆን የዕድሜ ዘመን
ኃላፍነት የሚጠይቅ ነው::
 ይህን መለኮታዊ ስጦታ መቀበል መንፈሳዊውን ባህርይ ለማሳደግ ቃል
መግባት ነው፤ አማኞች በሰባት የሕይወት መፈርቶች ማደግ አለባቸዉ ይኸዉም፡
1) በበጎነት፤ ይህ ግብረ ገባዊ ልቀት ነው
2) እዉቀት፡ በአእምሮ፤
3) ራስን መግዛት፡ የሐጢአት ፈተና ሲመጣ፤(በስሜቶቻችን ስር እንዳንሆን ነገር ግን
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስር መሆን ነው)
4) ጽናት፡ በችግር ሰአት፤
5) እግዚአብሔርን መምሰል፡ አለምን ለመሳብ፤ (የየዕለት ተግባራችንን ከእግዚ/ር ጋር
ካለው ግንኙነት አንጸር ማድረግ ነው)
6) የወንድማማች መዋደድ፡ ለአማኞች ሁሉ፤ (አንዱ ሌላኘውን መንከባከብ)
ፍቅር፡ ለሁሉም ሰዉ፤ እንደ እየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ ፍቅር ማለት
ለሌሎች ብልጽግና መሰጠት ነው:: ፍቅር የፈቃድ ነው እንጂ የስሜት ጉዳይ
አይደለም
እነዚህን ነገሮች ስናደርግና ስናድግ ትልቅ ተጽእኖን መፍጠር እንችላለን፤
3
 የሐዋርያ ሰለአየሱስ ክርስቶስ ያለው ምስክርነት (1:16-21)
1) በተረት ተረት ላይ ወይንም በሰዎች ልምምድ ላይ የተመሰረተ አይደለም
2) በመገለጥ ተራራ ፊት ለፊት ክብሩንና ግርማውን አይተዋል (ማር 9:1-8)
3) ነቢያት ስለክርስቶስ ከተናገሩት ምስክርነት
8.2 በምዕራፍ ሁለት ላይ አማኞች ከስህተት አስተማሪዎችና ከትምህርታቸዉ እንዲጠበቁ
ያስጠነቅቃል::
 ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው የገቡ የሐሰት አስተማሪዎች ለቤ /ክ ከባድ አደጋ ናቸው::
እስራኤላውያንን ከእውነተኛ መንገድ እንዳስጣሉ ዛሬም ያደርጋሉ
 የሐሰት አስተማሪዎች በምስጥር አጥፊ ትምህርት ያስፋፋሉ ትክክለኛውን ትምህርት
ይቃወማሉ:: ቋንቋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርታቸው ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም
 በአስተምሮአቸው ጥፋት ሕዝቡን ወደ ልቅነት ይመራሉ
 ራስ ወዳዶቸ ናቸው:: ዝነኞች ናቸው አማኞችን ከእውነተኛ መንገድ በቀላሉ ይስባሉ
 የዝሙት ነጸነትን ያስተምራሉ
 በገንዘብ ፍቅር የተጠሙ ተከታዮቻቸውን በማተለል እየሸለቱ ሀብት የሚሰበስቡ ናቸው
 ሐዋርያ ዼጥሮስ እግዚ/ር አመጸኞችን እንደምፈርድ ከታሪክ ሶስት ምሳሌ ይጠቅሳል
1) የቀደሙት መላዕክት
2) በኖኅ ዘመን የነበረ የጥፋት ውሃ
3) ሰዶም ገሞራ

ሐዋርያው እነዚያን የጥንት ታሪኮች ከዘመኑ የሐሰት አስተማሪዎች የረከሰ የህይወት


ዘይቤ ጋር ያመሳስለል:: ገንዘብን የሚያሳድዱ፣ የረከሰ ግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተገብሩ፣
ስልጣናትን የሚያቃልሉ፣ እግዚ/ር እኛ ለሚናደርገው ግብረ ገባዊ ውሳኔ ግድ
እንደሌለው የሚያስተምሩ እና ክርስቲያኖች ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ነፃነት
አላቸው ብለው የነፃነት ሰርትፊኬት የሚሰጡ ናቸው:: ይህም ሐዋርያ ዸውሎስ
ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስላገኙት ነፃነት የፃፈውን (ሮሜ 6) አጠምመው
ማስተማራቸው ናቸው:: ነፃ እንደሆኑ ያስተምራሉ ነገር ግን ለስጋዊ ምኞቶቻቸው
ባሪያዎች መሆናቸውን አይገነዘቡም ምክንያቱም ሰው ለተሰሸነፈበት ለዚያ ነገር ባሪያ
ነው:: አነዚህ የሐሰት አስተማሪዎችን ፍርድ አስከፊ የሚያደርገው ክርስቶስን
አውቀው ክርስቲያኖች ሆነው ወደኋላ መመለሳቸው ነው::
የሐሰት አስተማሪዎችን የረከሰ የህይወት ዘይቤ ይሞግታቸዋል
 አመጸኞች ናቸው (ለቤተክርስቲያን የማይታዘዙ ነገር ግን አመጠን
የሚያስተምሩ)

4
 ኃጢአተኞች ናቸው (አእምሮ የሌላቸው እንስሳት የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ
የሚከተሉ የኃጢአት በሪያዎች)፤ የአመጸቸውን ዋጋ ይቀበላሉ
 አዋቂዎች እንደሆኑ ራሳቸውን ይቆጥራሉ ነገር ግን አይደሉም
 ምንዝር የሞለባቸው ናቸው
 ጥቅም ፈላጊዎች ናቸው:- ቅንን መንገድ ትተው የአመጸን ገንዘብ ፍለጋ
እንደ ባሶር ልጅ ነጎዱ ይላል
 አይረኩም:- ውሃ በሌላቸው ምንጮችና በአውሎ ነፋስ የተነዱ ደመናዎች
ተመስለዋል
 የሐሰት አስተማሪዎች መለያቸው ስራቸውና ስጋዊ ፍላጎታቸው ነው
 እግዚ/ር አመጸኞችን በመቅጣት ጸድቃንን እንደሚያድን ሁለት ምሳሌ ጠቅሶአል
1) የጽድቅ ሰባኪ ኖኅና ቤተሰቡ
2) ሎጥ

እኛሽ እግዚ/ር መጥቶ እስኪያድነን ድረስ መጽናት አለብን


8.3 በምዕራፍ ሶስት ላይ ግን አማኞች ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት አንጻር ከጌታ ጋር ያላቸዉን ህብረት
እንዲያጠናክሩ ይመክራል፡፡
ጸሐፊው የእግዚ/ርን ጽድቅና ፍትህ ያስታውሳቸዋል
 ኢየሱስ ይመጣል
 ፌዘኞች ታሪካዊ እውነታውን ዘንግተው የክርስቶስን መምጣት ይክዳሉ
 ይህ አለም ያልፋል
 ጌታ ስለመምጣቱ ዋስትና
 የጌታ የጊዜ ቀመር ከእኛ የጊዜ ቀመር ይለያል:: ጌታ በጊዜ እና በቦታ
አይወሰንም
 የጌታ የጊዜ ሰሌዳ በትዕግስቱና በምህረቱ ላይ የተመሰረተ ነው
የጌታ መምጣት የዘገየው ለመዳናችን ነው
 በቅድስና እና እግዚ/ርን በመምሰል የጌታን መምጣት እንዲጠበቁ
ያበረታታቸዋል
 በሐሰት ትምህርቶች እንዳይታለሉ በጌታ ፀጋና ዕውቀት በማደግ የክርስቶስን
መምጣት እንዲጠብቁ ይሞግታቸዋል

5
(ይሁዳ 1-4)
1. ማን ጸሐፊዉ? ይሁዳ

ይሁዳ ማን ነዉ? ራሱን የኢየሱስ ክርሰቶስ ባሪያ የያዕቆብ ወንድም ብሎ የገለጸ ሲሆን፤ ነገር ግን ያዕቆብ
ማን ነዉ? ከዘብዴዎስ ልጆች ዉስጥ አንዱ ያእቆብ ሲሆን ወንድምየዉ ዮየሐንስም እንዲሁ ከሐዋርቱ አንዱ
ነዉ፤ ይሁዳ ግን የእርሱ ወንድም አይደለም፤ ይህኛዉ ይሁዳ የኢየሱስ ወንድም ሳይሆን እንዳልቀረ
ይገመታል (ገላትያ 1፡19)፡፡ ያዕቆብ ማለት የኢየሩሳሌም ከተማ ዋና መሪ ሲሆን፤ (ሐዋ 15፡13-21,
ገላትያ 2፡9)፤ ይሁዳ የሚባል ወንድም አለዉ፡፡ ሁለቱም የተገለጹት፤ (በማርቆስ 6፡3) ላይ ነዉ፤ የዮሴፍ
እና የማርያም ልጆች ናቸዉ፤ ይህ ይሁዳ ማለት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋ ወንድሙ ነዉ፤ ወንድሞቹ
በኢየሱስ የአገልግሎት ዘመን ዉስጥ አላመኑበትም ነበር፤ (ዮሐንስ 7፡5፣ ማቴዎስ 12፡46)፤ ከትንሳኤዉ
በኋላ ኢየሱስ ለያእቆብ ተገለጠለት፤ (1 ቆሮንቶስ 15፡7)፤ ያእቆብና ወንድሙ ይሁዳም ሳይጠራጠሩ እርሱ
መሲህ መሆኑን ሊያምኑ ቻሉ፡፡ የያዕቆብ ወንድም ነኝ ብሎ ራሱን ሲገልጽ ለኢየሱስ ክርስቶስ ግን ባሪያ ነኝ
ይላል:: እውነተኛ መለወጥ እንዲህ ነው::

2. የይሁዳ መልእክት ተቀባዮች እነማን ናቸው?

የመልዕክቱ ተቀባዮች አልተገለጹም ጸሐፊና ተቀባዮቹ ይተዋወቃሉ :: መጽሐፉ ምናልባት ለአይሁድ


ክርስቲያኖች ሳይጻፍ አይቀርም ምክንያቱም ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ጋር ብዙ ይቀራረባል::

3. መቼ ተጸፈ?

ቀኑ ያልታወቀ ሲሆን ምናልባት ከኢየሩሳሌም መፍረስ ከ 70 ዓ.ም በኋላ ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል፤
ጴጥሮስ መልእክቱን ሲጽፍ ከ 60 ዓ.ም በኋላ ስለ ሐሰተኛ መምህራን በማስጠንቀቅ አጥፊ የሆነ የስህተት
ትምህርታቸዉን ይገስጻል (2 ጴጥሮስ 2፡1)፤ ይሁዳ ደግሞ መጥተዋል ይላል (ይሁዳ 4)፡፡ የተጻፈበት ጊዜ
ምናልባት በ 80 ዓ.ም ሳይሆን እንዳልቀረ ገመታል፤

4. ለምን ጸፈ?

ይሁዳ የጻፈዉ መልእክት ሐሳቡ የእምነትን መጋደል እንዲጋደሉ ነዉ (1:3) በዚእ ነጥብ ላይ ይሁዳ ርእሰ
ጉዳዩን በማንሳት መጀመሪያ ካለዉ አላማ የተለየ አላማ እንዳለዉ ይናገራል፤ ወዳጆች ሆይ፤
ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፤ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ
ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ፤ ከዚያም እቅዱን
በመቀየር ሁሉም አማኞች ስለሚካፈሉትን የጋራ ስለሆነዉ ስለድነት ሊጽፍ ቻለ፤ ስለሚመጡት
የሐሰት አስተማሪዎች ሲስማ ሐሳቡን በመቀየር ሊጽፍ ችሏል፡፡
6
የይሁዳ መጽሀፍ ሙሉ በሙሉ ስለስህተት አስተምህሮ ሲጽፍ ብቸኛዉ መጽሐፍ ነዉ፤ የመጨረሻዉ ዘመን
ምልክቱ አንዱ የስህተት አስተማሪዎችና ትምህርታቸዉ እንደ አሸን በዙሪያችን መፍላታቸዉ ነዉ (ቁ 4)፤
የአዲስ ኪዳን የመጨረሻዉ መጽሐፍ እንደመሆኑ መጠን የመጨረሻዉን መመሪያ ለቤተክርስቲያን
ይሰጣል፤

የሐሰት አስተማሪዎች

 አስመሳዮች ናቸዉ፤
 እዉነተኛ አማኞች እንደሆኑ ይናገራሉ፤ እዉነቱ ግን አልዳኑም፤
 እምነታቸዉን ትተዉ በስህተት የሚናገሩ ናቸዉ፤ የክርስቶስን መለኮትነት ይክዳሉ፡፡
 ድነት በእርሱ በኩል መሆኑን እና ትንሳኤዉን እና አስፈላጊ የሆኑ የክርስትናን አስተምህሮ
ይክዳሉ፤
 መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ለእነርሱ ትክክለኛ የአስተምህሮ መንገድ ሳይሆን አማራጭ መንገድ
ነዉ፤ (1 ጢሞቲዎስ 4፡1)፤ ከእምነት መንገድ የወደቁ፤ (2 ጢሞ 4፡3)፤ አጥፊ የሆነን
ትምህርት ያስተዋዉቃሉ፤ (2 ጴጥሮስ 2፡1)፤ የይሁዳ መጽሐፍ በግልጽ የሚያሰተምረዉ ስለ
ስህተት አስተማሪዎችና አስተምሮ ነዉ፤

በይሁዳ መልእክት ዉስጥ ሶስት በረከቶችን ስንመለከት ምህረት፤ ሰላም እና ፍቅር ይብዛላችሁ ይላል
(ቁ.2) አንባቢዎቹ እንዲያዉቁ የፈለገዉ ነገር በእነዚህ ሶስት በረከቶች እንዲደሰቱ ነዉ፡፡

1) ምህረት (ረዳት የሌላቸዉን መርዳት) ይህ ሁል-ጊዜ በነጻ የተዘጋጀ ሆኖ ይህንን


ለማግኘት(ወደ ጸጋዉ ዙፋን በመቅረብ መጠየቅ ያስፈልጋል (ዕብራዉያን 4፡16)፤
2) ሰላም እንፈልጋለን፤ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁን፤ አእምሮአችሁን፤ በክርስቶስ ይጠብቅ፤
የሚል ነዉ፤ (ፊሊጵስዮስ 4፡7)፤ የሰላም አምላክ ሰላምን በሁኔታዎች ላይ ሁሉ ይሰጠናል
(2 ተሰሎንቄ 3፡16፣ ዮሐንስ 14፡27)፡፡
3) ሶስተኛዉ በረከት የፍቅር በረከት ነዉ፤ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በልባችን ፈሰሰ፤
(ሮሜ 5፡5)፡፡ በእነዚህ በሶስቱ በረከቶች እያደግን ስንሔድ በዙሪያችን ከከበቡን ጠላቶች
ሁሉ ያድኑናል፡፡

እነዚህ ሶስቱ መንፈሳዊ በረከቶችን ምህረት፤ሰላምና ፍቅር ስንቀበል በዙሪችን ካሉ በጠላቶቻችን ላይ


እንድንዘጋጅ ያደርጉናል፡፡

አጥፊዎች እምነትን ይክዳሉ (ቁ.4) ፡-

7
የይሁዳ መጽሀፍ አንቂ ነዉ፤ ምክንያቱም ጥቂት ሰዎች ሾልከዉ በመግባት ሰዎችን ስለ ጎዱ
በራሳቸዉ መንገድ ሄደዉ ቤተክርስቲንን ይበጠብጣሉ፤ ጴጥሮስ ከጥቂት ዘመናት በፊት እንደሚመጡ
ተናግሮ ነበር፤ (2 ጴጥሮስ 2፡1-3)፤ ይሁዳ ሲጽፍ እነዚህ በዉስጥ ናቸዉ ሲል፤ ነገር ግን የስህተት
አስተማሪዎች መነሳት የሚያስደንቅ አይደለም፤ ከጥቂት አመታት በፊት ስለ እነርሱ ፍርድ ምን
እንደሆነ ተነግሮአል፡፡

እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደሚነሱና እንደሚፈርድባቸዉ ተናግሯል፤ የጥፋት ዉሃ ከመምጣቱ


በፊት፤ ሄኖክ ስለ ሚመጣዉ ፍርድ ተናግሯል (ይሁዳ 14-15)፤ ከዚያም በኋላ ነብዩ ኢሳይያስ
ትንቢቶች ከእግዚአብሔር ቃል የሚጻረረዉን ነገር ሲናገሩ በእነርሱ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ
እንደሚሆን ተናግሯል፤ ችግርና ጨለማ፤ (ኢሳይያስ 8፡19-22)፤ ጴጥሮስ ስለ ሐሰት አስተማሪዎች
ተናገረ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚመጣባቸዉ ነዉ አስረገጠ፤ (2 ጴጥሮስ 2፡9)፡፡

እነዚህን የስህተት ትምህረቶች እንዴት ገለጻቸዉ? በቁ.4 ላይ ይሁዳ በሶስት መንገድ ይገልጻቸዋል፤

1) በመጀመሪያ እግዚአብሔርን የማይመስሉ ናቸዉ ይላል፤ በልባቸዉ ዉስጥ እግዚአብሔር


የሚል ነገር የለም፤ በዉጫዊ ማንነታቸዉ የሐይማኖት መልክ አላቸዉ፤ በዉስጣቸዉ ግን
እግዚአብሔርን አይፈሩም፤
2) ሁለተኛዉ የእግዚአብሔርን ፀጋ ያጣጥላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ማንኛዉንም ሐጢአት
መሸፈን ይችላል ይላል፤ ኢሞራላዊ የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ ነጻ ናቸዉ፤ የእግዚአብሔርን
ፀጋ ወደ ሥጋዊ ፍላጎታቸዉ በመቀየር ይታወቃሉ፤ (ሮሜ 6፡15 እና ቲቶ 2፡11፣13)
ጋር አነጻጽሩ፡፡
3) ሦስተኛ አስተምህሮአቸዉ ክርስቲናዊ አይደለም፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸዉ፡፡
የግሪኩ ትርጉም ሲናገር ይሁዳ የሚጽፈዉ ለአንድ ሰዉ እንደሆነ ነዉ፤
 ጌታ አምላክ የሚለዉ ቃል የሚያመለክተዉ አገዛዙ ፍጹም መሆኑን ነዉ፤
የኢየሱስ ሉአላዊ ሐይል እርሱ የዓለማት ፈጣሪ እና መጋቢ ነዉ፤
 ሁለተኛዉ ጌታ፤ የሚለዉ ቃል በግሪኩ የተሰጠዉ ትርጉም አክብሮት እና
መታዘዝን የሚያሳይ ነዉ፤
 ሶስተኛዉ ርእስ ኢየሱስ ብሎ ራሱን ገልጧል፤ ኢየሱስ የሚለዉ ስም
እግዚአብሔር ያድናል ማለት ሲሆን በመጨረሻም ክርስቶስ ማለት ስለሚመጣዉ
ንጉሥ የተቀባ መሲህ ማለት ነዉ፡፡

የስህተት አስተማሪዎች ግን ይህንን ሁሉ የሚክዱ ናቸዉ፤ እርሱ ሉአላዊ፤ አዳኝ፤ ጌታ እና ክርስቶስ


ነዉ፡፡

8
ታሪካዊ የሆኑ የስህተት ትምህርቶች (ቁ.5-7) ፡-

በይሁዳ ዘመን የስህተት ትምህርት የተነሳዉ በመካከላቸዉ ነዉ፤ አንዴ ካወቁት በኋላ (ቁ.5)፤
ከእምነት ማፈግፈግ አዲስ ነገር አይደለም፤ ይሁዳ አንባቢዎቹን የሚስጠነቅቃቸዉ ነገር ቢኖር
እግዚአብሔር በቀደመዉን ዘመን የነበሩትን ሰዎች እንዴት እንደቀጣቸዉ በማስታወስ ነዉ፡፡
ከእዉነት በተመለሱ እና ባፈገፈጉ ሰዎች ላይ ሶስት ክስተቶችን በማስታወስ ይነግራቸዋል፡፡

 የመጀመሪያዉ ለተገለጠዉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እምቢ በማለታቸዉ ስለደረሰባቸዉ


ፈተና እና ቅጣት ሲሆን ስለዚህ በማስጠንቀቅ ይነግራቸዋል
 ስለ ሐሰት ትምህርትና አስተማሪዎች በተለይም ስለማታለላቸዉ እንዲጠነቀቁ
 ለማጽናናት እግዚአብሔር ክፉዎችን መቆጣጠር እንደሚችል እና ጠላቶቻቸዉን
እንደሚቀጣ ይናገራል፤ በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ጊዜ አንድ መፈክር አለ፤ ፒርል
ሃርበርን አስታዉሱ፤ ይህ ማስጠንቀቂያ ለአሜሪካኖች የተሰጠ ሲሆን ይኸዉም
በጠላቶቻቸዉ እንደገና እንዳይያዙ ለማስጠንቀቅ ነዉ፤ የይሁዳም ማስጠንቀቂያም እንዲሁ
አስታዉሱ በምድረበዳ የወደቁትን እስራኤላዉያንን ሐጢአት የሰሩትን መላእክት አስቡ
ሰዶምና ገሞራን አስቡ፡፡

እስራኤል በምድረ በዳ (ቁ.5) ፡-

በዘኁልቁ 14 እግዚአብሔር እንደተናገረዉ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ስላላመኑ በምድረ በዳ


ቀሩ፤ (ከሰላሳ ስምንት አመት በኋላ ማለት ነዉ) በምድረ በዳ ቀሩ፡፡

ሐጢአት የሰሩት መላእክት (ቁ.6)፡-

መኖሪያቸዉን የተዉትን እንጂ፤ ይህ ምናልባትም፤ (በዘፍጥረት 6፡1-7)፤ ላይ የተከሰተዉን ክስተት


ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች፤ (መላእክት በብሉይ ኪዳኑ የግሪክ መጽሐፍ)፤ ሰማያዊ
የሆነዉን ስፍራቸዉን በመተዉ ከሰዉ ልጆች ጋር ተጋቡ፤ ልጆቻቸዉ ግን ከሰዉ ኃይል በላይ ሆኑ
ማለት ነዉ፤ እነዚያ ሐጢአተኞች በጥፋት ዉሃ ጠፉ፤ ሞራላዊ ዉድቀት ዉስጥ ነበሩ፤ ልክ እንደ
ሶዶም ሰዎች ማለት ነዉ፤ ራሳቸዉን ለዝሙት አሳልፈዉ ሰጡ፤(ቁ.7)፡፡ ይሁዳ እንደሚነግረን
እነዚህ መላእክት ሲፈጠሩ በታላቅ ክብር ነበር፤ ነገርግን በእግዚአብሔር ላይ አመጹ፤ ተመለሱ፤
ከዚያም፤ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ በጨለማ ተፈርዶባቸዉ ተቀምዋል፡፡የመጨረሻን ፍርድ አስኪቀበሉ
ድረስ በጨለማ ተፈርዶባቸዉ ይቀመጣሉ፡፡

ሶዶምና ገሞራ (ቁ.7) ፡-

9
ሌላዉ እና ሶስተኛው ምሳሌ፤ የስህተት ትምህርት በሶዶምና ገሞራ እና አብርሃም በነበረበት ዘመን
በዙሪያዉ የተስፋፋዉ ሲሆን የእነርሱም ጥፋት (በዘፍጥረት 19) ላይ ተጽፏል፤ ልክ እንደ
እስራኤላዉያንና እንደ ወደቁት መላእክት የእግዚአብሔርን እዉነት አንቀበልም አሉ፤ እነዚህ
ኢሞራላዊ በሆነ ሕይወት ዉስጥ የኖሩ ስለነበሩ፤ የሥጋቸዉን ፈቃድ ተከተሉ፤ ይህ ማለት ከሴት
እና ወንድ ጋር እና የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሁሉ ያደርጉ ነበር፤ ሃያ ሶስት የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎች የሶዶም እና ገሞራን መጥፋት የሚናገሩ ናቸዉ፤ ይህ ጠንካራ የሆነ የሐጢአት ዉጤት
ማስጠንቀቂያ ነዉ፡፡

እግዚአብሔር እነዚያን ከተሞች በእሳት አጠፋ፤ የሶዶም በእሳት መጥፋት የዘላለማዊዉን እሳት
ጥፋት፤ (ሲኦልን)፤ የሚያመለክት ነዉ፡፡ ያም የሐሰት አስተማሪዎች የሚገቡበት ማለት ነዉ፤ ዋይ
ለዚያች ከተማ ዋይከእግዚአብሔር እዉነት ለሚመለሱ በሕያዉ እግዚአብሔር እጅ መዉደቅ፤ (ዕብ
10፡31)፡፡

ከታሪክ እንዳየነዉ ከእዉነተኛ መንገድ ስለሚመለሱ ይሁዳ ሶስት ባህርይዎችን ይጠቅሳል፤

1) ሥጋን ማርከስ፤ ልክ ሶዶማዉያን እንዳደረጉት ማለት ነዉ (ቁ.7)፤ ምን ያህል የስህተት


አስተማሪዎች ናቸዉ፡፡ ሞራላዊ ዉድቀት ዉስጥ ያሉት?፤ ስለ እግዚአብሔር ፀጋ
ይናገራሉ፤ ነገር ግን ስለ ሞራላዊ ሕይወት ቸልተኞች ናቸዉ፤ የሰህተት ቤተክርስቲያን
ፍቅርን ያበረታታሉ፤ እንደ ዉርጃ፤ ዝሙትን፤ እና ሰዶማዊነትን ይፈቅዳሉ፤ ስለዚህ ሶዶም
እንደገና ተመልሶመጣ ማለት ነዉ፡፡
2) ሁለተኛ ስልጣንን ማጣጣል የእግዚአብሔርን ሞራላዊ ሕግ መተላለፍ ብቻ ሳይሆን
ግትሮች ናቸዉ፤ ስልጣንን አይቀበሉም፤ (በቁ 6)፤ላይ የተገለጸዉ የወደቁት መላእክት
ሐጢአታቸዉ የእግዚአብሔርን ሕግ ያፈርሳሉ፤ ሁሉንም የስልጣን አይነቶች ቤተክርስቲያን
ይሁን በማህበረሰብ ወይም በመንፈሳዊ ስልጣን ላይ ያሉትን ሁሉ ያጣጥላሉ፤ ስልጣናትን
ሁሉ ሲቃወሙ የኢየሱስ ክርስቶስን ስልጣን ሁሉ አይቀበሉም፤ ስለዚህም ይፈረድባቸዋል፡፡
3) በመጨረሻም በባለሰልጣናት ላይ ክፉን ይናገራሉ፤ ይህንንም በምሳሌነት ስለ ሙሴ እና
አሮንእግዚአብሔር ተናግሯል፤ ጌትነትን ይጥላሉ፤ የእግዚአብሔርን ወይም የጌታን ሊሆን
ይችላል፡፡ የስህተት ትምህርት የድንግል መዉለድን አይቀበሉም፤ ስለቤዛ ሞቱ አይቀበሉም፤
ስለ ትንሳኤዉና ዳግም ምጽአቱ አይቀበሉም፤ከመለኮትነቱ ጋር በተገናኘ አይቀበሉም፡፡
4) ቸልተኞች ናቸዉ (ቁ.10) ፡-

እነዚህ የስህተት አስተማሪዎች ስለማያዉቁት ጉዳይ ክፉን ነገር ይናገራሉ፤ (ቁ 10)፤ እንደ ማያምኑ
ሰዎች አይናችዉ ድፍን ነው፤ ጆሮአቸዉም አይሰማም፤ (2 ጴጥሮስ 2፡12)፡፡ ስለመንፈሳዊ እዉነት
አይረዱም፤ ስለእነዚህ ሰዎች ይሁዳ ሲናገር፤ አእምሮ የሌላቸዉ እንስሶች ይላል፤ የሚያዉቁት ነገር
10
ቢኖር ዝም ብሎ በተፈጥሮ ያለው፤ እንጂ ከላይ የምትመጣዋን ጥበብ አይደለም፡፡ ምድራዊ ጥበብ
ያላቸዉ ናቸዉ፤ ይህም አጋንንታዊ ነዉ፤ (ያእቆብ 3፡15)፤ የሚያዉቁት ነገር ቢኖር ሆዳቸዉን
ለመሙላት በማሰብ ብቻ ነዉ፤ ሆዳቸዉን የሚወድዱ ናቸዉ፤ በመጨረሻ ግን ሁለቱም ጠፊዎች
ናቸዉ፡፡ በእዉቀት የበላይ ነን ብለዉ ያስባሉ፤ ነገር ግን ትእቢተኞች ናቸዉ፡፡ እግዚአብሔር አንድ
ቀን በጠላቶቹ ላይ ለመፍረድ ይመጣል፡፡

የሐሰተኞች የዉድቀት መንገድ (ቁ.11) ፡-

1) ከእውነት መንግድ የስህተትን መንገድ መረጡ:: ራሳቸዉን በማጽደቅ፣ እንደ ቃየን (ቁ.11) ፡-

ወደ ፍርድ የሚመጡባቸው ሶስት ደረጃዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያዉ በቃየን መንገድ ሄደዋልና በቃየን
መንገድ መሄድ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለበትን መንገድ መተዉ ማለት ነዉ፡፡
ቃየን የእግዚአብሔርን መንገድ በመተዉ በራሱ መንገድ በመሄድ መስዋእትን ማቅረብ ፈለገ፤ ይህም
የእርሻ ምርትን ነበር፤ በዚህም ላይ ያቀረበዉ ያለእምነት ነበር፤ ስለዚህም መስዋእቱ ተቀባይነትን
አጣ፤ (ዘፍጥረት 4፡1-5) ቃየል መስዋእቱ ተቀባይነትን ባጣ ጊዜ በቁጣ ተሞላ፡፡ ከዚም
ከእግዚአብሔር ጋር አልታረቅም ብሎ ሄደ፤ ወንድሙን ገደለዉ፤ (ዘፍጥረት 4፡5-8)፤ በመጨረሻም
ከእግዚአብሔር መገኘት ዉጭ ሆኖ ኖድ፤ (የመቅበዝበዝ ምድር)፤ መኖር ጀመረ፡፡ (ዘፍጥረት 4፡
16)፤ የስርየትን ድነት ማጣጣል ማለት የስህተት ትምህርት ነዉ፡፡

2) እንደ በለአም ስግብግቦች ናቸዉ (ቁ.11) ፡-

ሁለተኛዉ የስህተት ትምህርት ልክ እንደበለአም መስገብገብ ነዉ፤ በበለአም ምክር መሔድ ማለት
በገንዘብ ፍቅር ተነሳስቶ እዉነትን በማዳፈን የእግዚአብሔርን ሕዝብ መሳብ ማለት ነዉ፡፡
ምዋርተኛዉ በለአም ፒቶር ከሚባል ወንዝ በኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ የሚገኝ ሰዉ ነዉ፡፡

በይሁዳም ጊዜ በክርስትና ስም ብዙ ገንዘብን በመሰብሰብ ከሰማያዊዉ ኑሮ ይልቅ ልባቸዉን


በምድራዊዉ ላይ ያደረጉ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ በለአም በደንብ ያዉቃል፤ ነገር ግን እንደ ሌሎቹ
የስህተት ትምህርቶች ሕይወቱን አጣ፤ ሌሎችንም ሰዎች አጠፋ፡፡

3) እንደ ቆሬ ልጆች፤ አመጸኞች ናቸዉ (ቁ.11) ፡-

የሙሴን እና የአሮንን አመራር በመቃወም 250 ሰዎችን ያስተባበሩ ሲሆኑ እግዚአብሔር የሰጣቸዉን
የሙሴንና የአሮንን ስልጣን ተቃወሙ፤ቆሬ አደገኛ ሰዉ ሲሆን እግዚአብሔር ስልታን የሰጣቸዉን
ሰዎች በመቃወም እና በማስተባበር ይታወቃል፡፡ ይህን በማድረግ እግዚአብሔር የመሰረተዉን
የስልጣን መዋቅር ያጠፋል፤አመጸኝነታቸዉ ብዙ እንዲኖሩ አልፈቀደላቸዉም፤ እግዚአብሔር ምድር
11
ተከፍታ እንድትዉጣቸዉ አደረገ፤(ዘኍልቁ 16፡1-35)፡፡ የእግዚአብሔርን የስልጣን እርከን
መቃወም ማለት ቁጣዉን ማነሳሳት ማለት ነዉ፤ መጥፋት ሆነባቸዉ፤ ይህ የሚያስተምረን
በቤተክርስቲያን ዉስጥ የስህተት አስተማሪዎች ሾልከዉ በመግባት የእግዚአብሔርን ስልጣን
ያቃልላሉ፤ በዚህም የእግዚአብሔርን ቁጣ ያነሳሳሉ፡፡

የስህተት አስተማሪዎች ባሕርይ (ቁ.12-13) ፡-

ይሁዳ እነዚህን ሶስት የብሉይ ኪዳን ሰዎች እንደ ምሳሌ በማንሳት የሐሰት አስተማሪዎችን
ይገልጻቸዋል፡፡ እነዚህን የስህተት አስተማሪዎች አደገኛነታቸዉን ለመግለጽ ነዉ፤ በመደጋገም በምሳሌ
የሚያነሳዉ፤አደገኝነታቸዉ የማይኖሩትን ስለሚናገሩ ነዉ፤ ይህን በማድረግ ብዙዎችን እዉነተኛ
ክርስቲያኖች ያታልላሉ፤ግራ መጋባትን በመፍጠር ክፍፍልን ይፈጥራሉ፤ ይሁዳ እንደገና ከተፈጥሮ
ምሳሌን በመዉሰድ ድንጋዮችን፤ ደመናዎቸችን፤ ዛፎችን፤ ባህርን እና ከዋክብትን ያነሳል፤ እነዚህ
ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፡፡ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት
ራሳቸውን ይጠብቃሉ (ቁ.12) እንደ ጉድጓድ ሆነው ሰንጣቃ አለት ናቸዉ፤ የፍቅር ግብዣቸዉ፤
የሚለዉ ይህ በጥንት ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች ተሰባስበዉ በጋራ የሚመገቡት ምግብ ነዉ፤
ይህም ህብረትን የሚያሳይ ነዉ፤ የጌታ ራትን እንዲሁ በጋራ ይወስዱ ነበር፤የስህተት አስተማሪዎችም
ያለፍርሃት ከእነርሱ ጋር በመሆን ሕብረት ያደርጉ ነበር፤ ይህን የሚያደርጉት ስለራሳቸዉ ድብቅ
አላማ ነዉ፤ ያም አላማቸዉ ራሳቸዉን ማገልገል ነዉ፤ በመንፈሳዊ ስም የራሳቸዉን አላማ
ይፈጽማሉ፤ አደጋነቱ በእዉነተኛ ክርስቲያኖች ዘንድ እንኳ ስዉር መሆኑ ነዉ፤ ይህም በዚህ
የመጨረሻ ዘመንም ልክ ነዉ፤በሚደረጉት እዉነተኛ ሕብረቶች መካከል ሾልከዉ የሚገቡ ሐሰተኞች
ይኖረሉእና ተጠንቀቁ!!

ዉሃ የሌላቸዉ ደመና የስህተት አስተማሪዎች ማለት እንደ ደመና ናቸዉ፤ እንደሚዘንቡ ይናገራሉ፤
ነገር ግን አይዘንቡም፤ባዶ የሆነ ተስፋ የስህተት አስተማሪዎች ምልክት ነዉ፤ ምንም መንፈሳዊ ነገር
የላቸዉም፤ በንፋስ እንደሚወሰዱ አይነት ሚፍገመገሙ ናቸዉ፤መጽሐፈ ምሳሌ እንዲህ ብሎ
ይገልጸዋል፤ ስለ ስጦታው በሐሰት የሚመካ ሰው ዝናብ እንደማይከተለው ደመና ነፋስም ነው
(ምሳሌ 25፡14) ፡፡

ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች (ቁ.12)፤ ጌታ ኢየሱስ
ስለ እነርሱ ሲናገር እርሱ ግን መልሶ፤ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል ማቴ 15፡
13)፤ በአብ ስላልተተከሉ ፍሬ አይኖራቸዉም፤ ሁለት ጊዜ የሞቱ ናቸዉ፡፡በመጨረሻም
በእግዚአበሔር ይፈረድባቸዋል፤ ተነቅለዉ በእሳት ባህር ዉስጥ ይጣላሉ፡፡

12
በባህር ላይ እንዳሉ ማእበሎች እነዚህ የስህተት አስተማሪዎችም እንዲሁ ዕርጋታ እና ሰላም
የላቸዉም፤ ኢሳይያስ ስለ እነርሱ ከብዙ አመታት በፊት እንዲህ ብሎ ጻፈ ክፉዎች ግን
እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፡፡ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና፤
(ኢሳይያስ 57፡20) ፡፡

ሶስተኛ የሚጠብቃቸዉን ጥፋት ሲናገር፤ የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፤
ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው፤ የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው (ቁ.13)፡፡ እንደ
ተንከራች ከዋክብትከሰማይ ይወርዱና በምሽት ወዲያዉኑ ይጠፋሉ፤ ብርሃናቸዉ ሰዎችን ይማርክ
ይሆናል፤ ነገርግን ወዲያዉኑ ወደ ጨለማ ይለወጣል፡፡

ይሁዳ በቁ.12 እና 13 ላይ ከሚገልጻቸዉ ነገሮች መካካል አንዱ የስህተት አስተማሪዎችን አደገኛነት


ነዉ፡፡ የተደበቁ አለት የሚለዉ የማይታይን ነገር ግን አደገኛ የሆነ ማለት ሲሆን ባዶ ደመና
የሚለዉ የሚናገረዉ ባዶ የሆነ ተስፋቸዉን ነዉ፤ፍሬ የሌለዉ ዛፍ መካን ነዉ፤‹‹ጨካኝ የባህር
ማዕበል››፤ የሚለዉ ነዉረኝነታቸዉን ሲሆን የሚንከራተቱ ከዋክብት የሚለዉ ጊዜያዊ ብርሃናቸዉን
ነዉ፡፡አስመሳይ ናቸው፤ በመጨረሻ የዘላለም ጥፋት ይጠብቃቸዋል፡፡

የሔኖክ ትንቢት (ቁ.14-15) ፡-

ይሁዳ የሚመጣዉን ጥፋት የሚያሳየዉ የሄኖክን ትንቢት በመጥቀስ ሲሆን፤ ይህም የአዳም ሰባተኛ
ትዉልድ ነዉ፤ (ዘፍጥረት 5፡18)፡፡ እንዲህ አይነቱን ትንቢት ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
የሚደግፉት አይደለም፤ በአዋልድ መጽሐፍ ዉስጥ በመጽሐፈ ሔኖክ ዉስጥ ያለ ነዉ፤ ይህ መጽሐፍ
በእስትንፈሰ መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ባይካተትም በቀኖና መጽሐፍ ዉስጥ ባይገኝም ነገር ግን ይህቺ
አረፍተ ነገር በዚህ እስትንፋሰ እግዚአብሔር በሆነዉ መጽሐፍ ዉስጥ ተገልጣለች፤ ይህም
የሚያሳየዉ መረጃዉ እዉነት መሆኑን ነዉ፤የሔኖከ ትንቢት ከጥፋት ዉሃ በፊት የሆነ ነዉ፡፡
ትንቢቱም ከዘመናት በፊት ነዉ፤ ስለ ክርስቶስ ምጽአት ሲናገር የመጀመሪያዉ መጽሐፍ ነዉ
ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ቁ.14)፤የስህተት አስተማሪዎች
በታላቁ መከራ በኃይል የሚገለጡበት ጊዜ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ጋር አስቀድመዉ
ተነስተዉ የነበሩትን ቅዱሳን በመያዝ ወደዚህ ምድር እንደሚመጣ የሚያሰይ ነዉ (1 ተሰሎንቄ 4፡
13፣ ቆላስያ 3፡4 ዘካርያስ 14፡5)፡፡ ከዚያም ኢየሱስ በሙሉ ክብሩ ወደዚህ ምድር በመምጣት
ለ 1000 አመታት ይነግሣል፡፡ ከዚያም የመጨረሻዉ ፍርድ በሰዎች እና በመላእክት ላይ ይሆናል፡፡
በመጀሪያ የሔኖክ ትንቢት የሚያሳየዉ የፍርድ ትንቢትን ሲሆን የሰዉ ልጅ በክብሩ ሲመጣ፤
በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል (ማቴዎስ 25፡31-46)፡፡

13
ኢየሱስ ሲመጣ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ነዉ፤ አላማዉም እግዚአብሔርን በማይመስሉ ሰዎች ላይ
ለመፍረድ ነዉ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ጌታን በመቃወም የሚናገሩ ናቸዉ፤ ይሁዳ ለአራት ጊዜ
ያህል፤ ሐጢአተኞች፤ የሚል ቃል ተጠቅሟል፤ ይህ ማለት የሰዎቹን ስራ፤ ባህርይ ስለ ክርስቶስ
የሚያስቡትን ሐሳብ ጭምር ነዉ፡፡ ሐጢአተኝነታቸዉ፤ ክፉ ድርጊታቸዉ በእግዚአብሔር እና በልጁ
ላይ የሚደረገዉ ክፉ ንግግር ነዉ፤በዚያን ሰአት ይገመገማል፡፡

ይሁዳ አንባቢዎቹን ለማበረታታት እንዲህ ይላል፤ ሐጢአተኞች በጌታ ፊት ይገለጣሉ፤ ለሚናገሩት


ለእያንዳንዱ ከንቱ ቃላቸዉ ፊት ለፊት በመገናኘት መልስ ይሰጡበታል፤ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፤
ከእኔ ተለዩ፤ ወደ ተዛጋጀላችሁ የዘላለም እሳት (ማቴዎስ 25፡41) ሂዱ፡፡ ይሁዳ እነዚህን የስህተት
አስተማሪዎች በተመለከተ በሶስት ቃላት ያጠቃልላል፤ የመጀመሪያዉ አጉረምራሚዎች፤ ሁለተኛው
እንደ ምኞታቸዉ የሚሄዱ፤ ልክ እንደ ሶዶም ሰዎች ራሳቸዉን ለማስደሰት በራሳቸዉ ጎዳና የሚሄዱ
ናቸዉ፤ ሶስተኛ እንዲረባቸዉ በሰዉ ፊት እያደሉ፤ በትእቢት የሚናገሩናታላቅ ጥበብ እንዳላቸዉ
የሚቦሰትሩ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በስነ አእምሮ ትምህርት ወይም በማህበራዊ ስራ የሚቀይሩ
ናቸዉ፤ ባዶ ቃላት ናቸዉ፤ ቃል ብቻ ሆነዉ ምንም የማይገልጹ (ሼክስፒር)? ስለ መለኮታዊ ነገር
ብዙ ትኩረት የማይሰጥ ነገር ግን ለአደባባይ አስተያየት ለመስጠት ደስተኞች ናቸዉ፡፡

ይሁዳ እየተናገረ ያለዉ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ተነስተዉ ስለነበሩት የሐሰተኛ አስተማሪዎች
በማስጠንቀቅ ነዉ፤ የዘመናችን የስህተት ትምህርት ደግሞ ተመሳሳይ ባህርይ አለው ስለዚህ
ስለተሰጠን ማስጠንቀቂያ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይገባናል፡፡

ምዕራፍ አስር: የስህተት ትምርት እና ክርስቲያን፡-

ይሁዳ 17 ና 25
ለአማኞች የማስጠንቀቂያ ቃላት (ቁ.17) ፡-

እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
(ቁ.17)፤ ይሁዳ የጥንቱን ነብይ ሔኖክን እንድናስታዉስ ይነግሮናል፤ በመጨረሻዉ ዘመን የስህተት
አስተማሪዎች እንደሚነሱ ይናገራል፤ ሐዋርያት ይህንን በጽሑፍ እና በቃል አብራርተዋል፤ ይሁዳ
አንባቢዎቹን ብዙ መደነቅ እንደሌለባቸዉ ያሳስባቸዋል፡፡ እንዲያስታዉሱአቸዉ በማሳሰብ
ይነግራቸዋል፤ ምክንያቱም ሰዉ ስለሆኑ የመዘንጋት ጉዳይ አለና፡፡ ስለዚህም እኛ ከእነዚህ ነገሮች
ጋር በመላመድ የእነርሱን ነገር መረዳት እና ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ አብዛኛዉ የእግዚአብሔር ሕዝብ
አገልግሎት እዉነትን በማስታወስ እና ለሚያዉቁት ነገር ምላሽ እንዲሰጡም ለማሳሰብ ጭምር
ነዉ፡፡

14
ይሁዳ ለአማኞች ሲናገር፤ ቃሎችን፤ አስታዉሱ በማለት ሐዋርያቱ ስለ እስትንፋሰ ቃል ሲናገሩ፤
እያንዳንዱ ቃል እስትንፋሰ እግዚአብሔር እንዳለበት ይናገራሉ፤ ቅዱሳን ሰዎች በእግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ ተመርተዉ ጻፉት፤ (2 ጴጥሮስ 1፡21)፤ ጴጥሮስ ለአንባቢዎቹ ሲናገር፤ በቅዱሳን
ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን፤ የጌታንና የመድኃኒታችንን
ትእዛዝ እንድታስቡ፤ (2 ጴጥሮስ 2፡3)፤ መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ነዉ ሲል
ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣዉን የመጀመሪያዉን ቃል ነዉ፤ ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን
መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ፤ (1 ቆሮንቶስ 2፡13)፡፡

ከፌዘኞች መጠበቅ! (ቁ.18-19) ፡-

ፌዘኞች የሚለዉ ቃል ዘባቾች ከሚለዉ ከ 2 ኛ ጴጥሮስ ዉስጥ ከተጻፈዉ ጋር ተመሳሳይ


ነዉ፤የእግዚአብሔርን ቃል ያጣጥላሉ፤ሥጋን ያጎድፋሉ፤ ስልጣናትን ያጣጥላሉ፤ እና የከበረዉን ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስን ይሳደባሉ፤ (በቁ.8)፤ ሐዋርያቱ ሊመጣ ስላለዉ የስህተት ትምህርት አስጠንቅቀዉ
ነበር፤ (ሐዋርያት 20፡29፣30፣ 1 ጢሞቲዎስ 4፡1፣ 2 ጢሞቲዎስ 4፡3፣4 እና 1 ዮሐንስ 2፡18)፤
ይሁዳ እነዚህ ፌዘኞች ምን እንደሚያደርጉ በግልጽ አያብራራም፤ ግን በ 2 ጴጥሮስ 3 ዉስጥ ስለ
ጌታ ኢየሱስ ዳግመኛ መምጣት እና ተስፋ ያፌዛሉ፤ (2 ጴጥሮስ 3፡1-3)፤ ይሁዳ የአሮጌዉን
ሕይወት የሚያበረታቱ እና ባህርያቸዉ ግን ክርስትናን የማይገልጽ ሊሆን ይችላል (ቁ.19)፡፡

ክፍፍል (ቁ.19)፤ ራሳቸዉን ከተራዉ ክርስቲያን የበላይ አድርገዉ ያያሉ፤ በሚስጢር ገብተዉ
ልዩነትን ፈጣሪ ናቸዉ፤ 3 ዮሐንስ 9-11 ታዋቂዉ ከፋፋይ ሰዉ ዲዮጥራጢስ ይባላል፡፡ ሐዋርያው
ዮሐንስን አይቀበልም ነበር፤ እንደ ዮሐንስ ግምገማ በቁ 11 ላይ ዲዮጥራጢስ አማኝ አይደለም፡፡
ፌዘኞቹ ራሳቸዉን እንደ መንፈሳዊ ሰው አድርጎ ያያሉ፤ ይሁዳ ግን እንዲህ ይላቸዋል፤ ሥጋዉያን››
ይህ ማለት አምስቱ የስሜት ሕዋሳት የሚቆጣጠራቸዉ የተፈጥሮ ሰዎች ማለት ነዉ (1 ቆሮንቶስ 2፡
14)፤ ያልዳኑ ናቸዉ፤ መንፈሳዊ ሕይወት የላቸዉም፤ መንፈስ ቅዱስ የላቸዉም፤ ምክንያቱም በዳነ
ሕይወት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ይኖራልና (ሮሜ 8፡9)፤ ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ናቸዉ፡፡

ራስህን በእግዚአብሔር ፍቅር ጠብቅ (ቁ.20-21)፡-

ይሁዳ ከሐሰተኞች ጋር ያለዉ ተጋድሎ ምን እንደሚመስል ለአማኞች ሲጽፍ፤ እናንተ ግን ወዳጆች


ሆይ (ቁ.20) ይላል፤በመካከላቸዉ ስለተከሰቱት ስለ ሐሰተኛ መምህራን ይሁዳ ለእዉነተኛ
ክርስቲያኖች እምነታቸዉን እንዲጠብቁ እና መንፈሳዊ ሕይወታቸዉን እንዲከልሉ
ያሳስባቸዋል፤እንዲህ ብሎ ያሳስባቸዋል፤ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፍቅር ጠብቁ፤ ሌሎች ሶስት

15
ደረጃዎች (ቁ.20-21)፤ ይህንን ግብ ለመፈጸም የሚረዳዉ አሉ፤ ራሳችሁን ጠብቁ፤ እስኪ
በእያንዳንዱ ላይ እንመልከት፡-

በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ የሚለዉን ትእዛዝ መታዘዝ ነዉ፤ይህ ማለት
ድነታችንን የምንጠብቀዉ እኛ ነን ማለት አይደለም፤የእግዚአብሔር ፍቅር ማለት እንደ ጸሐይ
ነጸብራቅ እየተጨመረ እንደሚበራ ሁሉ የአማኞችም ፍቅር እንዲሁ ነዉ፤ሐጢአት ስንሰራ ከደስታዉ
እና ከፍቅሩ እንጎድላለን፤ ነገር ግን ከቤተሰቡ አባልነት አንሰረዝም ወይም ከድነታችን አንሰረዝም፡፡

ራሳችሁን አንጹ (ቁ.20) ፡-

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር እንዲህ አለ ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው፤


የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፡፡ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፡፡
ራሴንም እገልጥለታለሁ (ዮሐንስ 14፡21)፤ እዉነተኛ አማኞች ጌታን ለማሰደሰት እና ለአዳኙ
ለመታዘዝ ነዉ ፍላጎታቸዉ፡፡

በቁ.20 ላይ ይሁዳ እምነታቸዉን በቅዱሱ ላይ እንዲያደርጉና እንዲያንጹ ያድፋፋራል፤በሌላ ቃል


እዉቀታቸዉን በእግዚአብሔር ቃል እየጨመሩ እንዲሄዱ ይመክራል፤ አሁንም ለእግዚአብሔርና
ያነጻችሁ፤ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ
ሰጥቻችኋለሁ፤ (ሐዋ 20፡32)፤ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዛችን እና እድገታችን እየጨመረ ሲሄድ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት እየጠነከረ ይሄዳል፤በፈቃዳችን ሐጢአትን አንሰራም፤ በስህተት
ትምህርትም አንታለልም፡፡

በመንፈስ መጸለይ (ቁ.20)፡-

በመንፈስ ቅዱስ መጸለይ ማለት በመንፈስ እየተመሩ መጸለይ ማለት ነዉ፤ይህ ከጌታ ጋር ሕብረት
እንድናደርግ የሚያደርግ ነዉ፤በሥጋ ከመጸለይ ይልቅ በመንፈስ ስለመጸለይ ይነግረናል፡፡ ይህ ስለ
መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን መልካም እዉቀት እና ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ እንድናዉቅ የሚረዳን
ነዉ፤(1 ዮሐንስ 5፡14-15)፡፡ የጳዉሎስ ድምጽ ለኤፌሶን፤ ሁል-ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ጸልዩ፤
(ኤፌሶን 6፡18)፤ በመንፈስ መጸለይ ማለት በልሳን መጸለይ ማለት ግን አይደለም፤ ነገር ግን
በልባችን በመንፈስ አብርሆት መጸለይ ማለት ነዉ፡፡

የክርስቶስን መምጣት በመጠባበቅ (ቁ.21)፡-

ሶስተኛዉ የእግዚአብሔርን ፍቅር የምንለማመደዉ የሚመጣዉን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመጠባበቅ


ሲሆን፤ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደዉን የጌታችን የኢየሰስ ክርስቶስን ምህረት ስትጠባበቁ፤

16
(ቁ.21)፤ዮሐንስም ለአንባቢዎች የሚለዉ ነገር ቢኖር፤ በክርስቶስ ስንኖር እርሱ ሲገለጥበእርሱ ላይ
ድፍረት አለን፤ በመምጣቱም አናፍርም፤ (1 ዮሐንስ 2፡28)፤ ዮሐንስ እንዲህ ይላቸዋል፡፡ ይህ ተስፋ
ስላለን ራሳችንን እናንጻ (1 ዮሐንስ 3፡3)፤ ጳዉሎስ የኢየሱስን ተስፋ የሚያየዉ እንደ ‹‹ተባረከ
ተስፋ›› ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በቅድስና፤በጽድቅ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር
ያደርጋል(ቲቶ 2፡12-13)፤ ጌታ የመምጣቱ ተስፋ እዉነተኛ አማኞችን ከእርሱ ጋር ህብረት
እንዲያደርጉ ያነሳሳል ባህርያቸዉን በማንጻት ማለት ነዉ፡፡

ለጠፉት መመስከር (ቁ.22-23) ፡-

ይሁዳ ለአንባቢዎቹ የመጨረሻዉን ቃል ሲጠቀም ልክ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ወንጌልን እንዲሰሩ


እንዳዘዛቸዉ ሁሉ-ይሁዳ ደግሞ መንፈሳዊ ሕይወታቸዉን እንዲጠብቁ ይነግራቸዋል(ቁ.20-21)፡፡
ስለጠፉ ሰዎች ሐላፊነት እንዳለባቸዉ መከራቸዉ፤ያለክርስቶስ ላሉ ሰዎች ሁሉ ሰራ አለብን፤ ነገር
ግን የተለያዩ ሰዎችን ስንቀርብ ምን ማድረግ እንዳለብን መለየት ይጠበቅብናል፤እያንዳንዳቸው
የሐሰት ትምህርት አስተማሪዎች የተለያየ መነሻ ሐሳብ ስላላቸዉ ስንቀርባቸዉ በጥንቃቄ መሆን
ይኖርበታል፤በእነዚህ በሁለቱ ቁጥሮች ይሁዳ የሚነግረን ነገር እንዴት መቅረብ እንዳለብን ነው፤
በመጨረሻም አደገኛ የሆነ ፍርድ ይጠብቃቸዋል፡፡

ተጠራጣሪዎችን ማሩ (ቁ.22) ፡-

ለመጀመሪያዎች ቡድኖች እንዲህ ይላል፤ በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
እነዚህ የተለያዩ ክርክሮችን የሚያደርጉ የስህተት አስተማሪዎችንና ተከታዮቻቸዉንም ጭምር
ነዉ፤መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙትን ሰዎች መስማት ያስፈልጋል፤ለእነርሱ ማድረግ የሚገባዉ
ጉዳይ፤ ምህረትን ማድረግ ነዉ፤ለእነርሱ ጥርጣሬ እና ጥያቄ መልስ መስጠት ይገባል፤መልስን
ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል (1 ጴጥሮስ 3፡15)፡፡

ለእነዚህ ተጣራጣሪ እና ተከራካሪ ሰዎች መፍረድ እና ጨካኝ መሆን ስህተት ነዉ (1 ጴጥሮስ 3፡


15)፤ አንዱ የአማኞች የተባረከ ስራ ነፍሳትን ማዳን ሲሆን ምህረትንም ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
አንድን ሰዉ ከስህተት ትምህርት አዉጥቶ ወደ ትክክለኛዉ መንገድ ማምጣት ምንኛ
ያስደስታል፤እነርሱን ለማዳን ካልቻልን እነርሱ ተስፋ ወደ መቁረጥ ዉስጥ ይገባሉ፡፡

ከፍርድ ዉስጥ መንጠቅ (ቁ.23) ፡-

አንዳንዶችንም ከእለት አድኑ እነዚህ ሰዎች በሐሰት ትምህርት ተጽእኖ ዉስጥ ያሉ ሲሆን
መጨረሻቸዉም የእሳት ባህር ነዉ (ማቴዎስ 3፡10-12፣ራዕይ 21፡8)፡፡ ከሚሄዱበት አደገኛ
አቅጣጫ ሊጠነቀቁ ይገባል፤ በሕያዉ እግዚአብሔር ፊት መቆም እንዴት የሚያስፈራ ነዉ!
17
የእግዚአብሔርን እዉነት ከመናገር ወደ ኋላ ማለት አስፈላጊ አይደለም፤ከእሳት ዉስጥ መንጠቅ
ማለት ልክ እንደ ሎጥና ልጆቹን ከሶዶም ዉስጥ እንደማዳን ማለት ነዉ፤ይህ የሶዶም ዳራ ስለ
ክፉሞራላዊ ሕይወት ሕሊናቸዉ ደንዝዞ በሎጥ ላይ ግን ይስቁበትና ይሳለቁበት ነበር፡፡

ጠንካሮችን በመንከባከብ መያዝ (ቁ.23) ፡-

በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ፤ እንዲህ አይነት የማያምኑ ሰዎች ለአማኝ መስካሪዎች
እጅግ አደገኛ ናቸዉ፤ ስህተታቸዉን እያጠናከሩ ይሄዳሉ፤ሆነ ብለዉ ክፉን ነገር በመያዝ
የሚያራምዱ ናቸዉ፤ተስፋ አላቸዉ፤ ነገር ግን በሳልክርስቲያኖች ብቻ ናቸዉ እነረሱን ለማዳን
ሙከራ ማድረግ ያለባቸዉ፤ በሥጋ የረከሰ ልብስ፤ የሚለዉ ቃል ወደ ብሉይ ኪዳን ይወስደናል፤
ካህኑ ብቃት ያላቸዉን ሰዎች ይመረምራል፤ ምናልባትም በበሽታተይዞ እንደሆነ ለማወቅ
(ዘሌዋዉያን 13፡45-59)ይሁዳ (የዘካርያስ 3፡1-5)፤ ያለዉን ጥቅስ በአእምሮዉ ይዟል፡፡ኢያሱ
ሊቀካህኑ የአይሁድን ሐጢአት ተሸክሞ በሰይጣን ይከሰሳል፤ሰይጣን ኢያሱን ይከሰዋል፡፡
በእግዚአብሔርፊት ሊያቆምህ የሚችል መብት የለህም ይላል፤እግዚአብሔር ለሰይጣን ክስ መልስ
ይሰጣል፤ልክ ይሁዳም በዚህ ስፍራ ላይ ተመሳሳይ ቋንቋን ይጠቀማል፤ምህረቱ ከእሳትእና ከእድፋም
ልብስያድናል፡፡እግዚአብሔር ምህረትን ሊያደርግ መረጠ፡፡ ስለዚህም ከእሳት አዳናቸዉ፤ሶስተኛ
እንዲህ ይላል እድፋም ልብሱ ተወገደ፤ ንጹህ ልብስን አለበሰው፤የእግዚአብሔር ብዙ ፀጋ የስህተት
አስተማሪዎችን ሊነካ ይችላል፡፡ ነገር ግን ለእነርሱ ለመመስከር ታማኝ እና በተጠንቀቅ በጥንቃቄ
መመስከር ያሻል፡፡

ይሁዳ በምስጋና ይዘጋል (ቁ.24-25) ፡-

ይሁዳ መልእክቱን በምስጋና ይዘጋል፡፡ ምስጋናዉም ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትእና አማኞችን


በመጨረሻዉ ዘመን እንዲኖሩ ስለሚያደርገው ስለ በቂ ፀጋዉ ነዉ፤ የስህተት አስተማሪዎች ግፊት
ከታላቁ እግዚአብሔር ጋር አብሮ የማይሄድ መሆኑን ነዉ፤‹‹ከክፉ ሊጠብቃችሁ ለሚችለዉ››፤
ምስጋናዉ በእግዚአብሔር ላይ እና በአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ትኩረት ያደረገ ነዉ፡፡ ዕብራዉያን
7፡25 በእርሱ በኩል የሚመጡትን ሊያድናቸዉ ይችላልና፤ ‹‹ሊያድነን የሚችል ማለት
‹‹መጠበቅ›› ማለትነዉ፤ ክርስቶስ ከዉድቀት ሁሉ ይጠብቀናል፤

ሁለተኛ እኛንም ነዉር የሌለን አድርጎ ያቀርበናል፤ በእርሱ ክብር ፊት በደስታ እንገኝ ዘንድ በሰማይ
እስክንደርስ ድረስ ይጠብቀናል፤ (ኤፌሶን 5፡27)፤ በዚያን ሰአት የእርሱ ደስታ፤እንደ እኛ ብዙ ነዉ
ገለጻዉ፤ በ 1 ጴጥሮስ 4፡13 የሰማዩን ደስታ ነው የሚያሣየው ነገረ ግን አሁን በዚህ ምድር ላይ
እንለማመደዋለን፡፡

18
የመጨረሻዉ ቡራኬ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ
ዘላለምም ድረስ ለጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን፤
እርሱ ብቻዉን አምላክ የሆነ ፍጹም ጥበበኛ ነዉ፤ ከሰዎች ለእርሱ ክብር ሊሰጥ ይገባዋል፤ ክብር
የሚለዉ በዚህ አዉድ መሰረት ምስጋናን እና ትኩረት ማለት ነዉ፡፡ የእርሱን መብት እዉቅና
መስጠት እና በዓለማት ሁሉ ላይ ባለስልጣንና ገዢ ለሆነዉ እዉቅና መስጠት ነዉ፤ እርሱ
የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ለግርማዊነቱ ክብር ይገባዋል፡፡ በደስታ ለእርሱ ስልጣን እና ኃይል
መገዛት አለብን፡፡ ሁሉን ማድረግ ይችላልና፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሊቀበል ክብር ይገባዋል፤ ከዘመናት በፊት እዉነት ነዉ፤ አሁንም
እና ወደፊትም ለዘላለምም፤ የይሁዳን መጽሐፍ አጥንተን ስንጨርስ ስለ መጨረሻዉ ዘመን የስህተት
ትምህርት በማሰብ ድንቅ የሆነዉን ጌታ ማመስገን ይገባናል፤

19

You might also like