You are on page 1of 119

መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ትምህርት (መጽሐፍ

ሁለት)

የደቀመዝሙር ትምህርት

በቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ትምህርት ተምረውና ስርዓተ


ጥምቀት ወስደው ለደቀመዝሙር ምርቃት የሚቀርቡትን አማኞች ለሚያስተምሩ
የተዘጋጀ ማስተማሪያ መጽሐፍ

“እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን


ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው” ቆላ. 1፥28

ከተለያየ መጽሐፍ ተወጣጥቶ በወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ትምህርት


ክፍል የተዘጋጀ
አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ, 2014 ዓ.ም.

ምስጋና
የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ከገጠሟት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መካከል ዋንኛው የእምነታችን ዋነኛ መሠረት የሆነው መጽሐፍ
ቅዱሳዊ የክርስትና አስተምህሮ በአግባብ አለመሰጠቱ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ለአባላቶቿ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትናን

1
አስተምህሮ ማስተማር አለባት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለአባላቶቿ ለማስተምር ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትና አስተምህሮ
በአግባቡ ተዘጋጅቶና በጥራት ተጠርዞ መቅረብ አለበት፡፡ ስለዚህ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክርስትና ትምህርት ከወንጌላዊያን ሥነ
መለኮት አንጻር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ አነሳስቶ ላስጀመረን፣ አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና
ይሁን፡፡
ከጌታ ቀጥሎ ይህ ማስተማሪያ መጽሐፍ እንዲዘጋጅ በአንድም በሌላም መንገድ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ሰዎች ሁሉ መዘርዘር
የማይቻል ሲሆን፤ ነገር ግን መጽሐፉን በማዘጋጀት፣ ረቂቁን በማረም፣ ሀሳብ በመስጠት፣ በኮምፒዩተር በመጻፍ፣ ዲዛይን
በማድረግ፣ የሽፋን ገጽ በመስራት፣ የተለያዩ መጻሕፍት ያዋሳቹሁን፣ በጸሎትና በምክር የደገፋቹሁን፣ ለህትመት እና ተያያጅ
ወጪዎች ገንዘባችሁን የለገሳቹሁ በሙሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቹሁ ማለት እንወዳለን፡፡
ይህ መጽሐፍ በሚዘጋጅበት ጊዜ ውድ ጊዜያቸውን መሥዋዕት በማድረግ ያዘጋጁ እንዲሁም ከመጽሐፋቸው ላይ ሙሉ በሙሉ
እንድንጠቀም የፈቀዱልን ሰዎችን ማመስገን እንወዳለን እንዲያም ሆኖ በመጽሐፉ ላይ ስሕተት ቢገኝ የስሕተቱ ተወቃሽ
የትምህርት ክፍሉ አዘጋጆች እንጂ እነዚህ ሰዎች አይደሉም ምክንያቱም የነሱ ጹሑፍ ሙሉ ለሙሉ አልተካተተም ወይም
አንዳንድ የተቀየሩ ቃላት እና አረፍተ ነገሮች አሉ፡፡

“ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና” (2 ቆሮ. 13*8)

ማስታወሻ
ይህ የደቀመዝሙር ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍ የተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት፣ ሚኒስትሪዎችና ግለሰቦች እንዲጠቀሙበት
ከወንጌላዊያን ሥነ መለኮት አንጻር ታስቦ የተዘጋጀ እንጂ ለሽያጭ በገበያ ላይ የሚውል መጽሐፍ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከተለያየ
መጽሐፍት እና ማህበራዊ (ሶሻል) ሚዲያ የወሰድናቸውን ጹሑፎች (አሳቦች) ካለን የቦታ ጥበትና ለገበያ የሚቀርብ መጽሐፍ
ስላይደለ፤ በግርጌ ማስታወሻ (footnote) ላይ ሳይሆን በዋቢ መጻሕፍት (Bibliography) ላይ የጠቀስን መሆኑን በታላቅ ትህትና
እንገልጻለን፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጠቀሱት ትምህርቶች ከተለያየ መጽሐፍ ላይ የተወሰዱ ስለሆነ ከላይ እንደተገለጸው በግርጌ
ማስታወሻ (footnote) ላይ ስላልተገለጸ፤ ይህን መጽሐፍ ወይም ማንኛውንም የመጽሐፉን ክፍል ለማባዛት፣ ለመግልበጥ፣
2
ለመቅረጽ ወይም በሌላ መጽሐፍ በስፋት ለመጥቀስ አይቻልም፡፡ ሆኖም ግን ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ቤተ ክርስቲያን
ከዚህ መጽሐፍ ለመጥቀስ ቢፈልግ የመጽሐፉን ስም፣ የደራሲውን ስምና መጽሐፉ የተጻፈበትን ዓ.ም. ከዚህ ማስተማሪያ
ሳይሆን ከዋናው መጽሐፍ የመጥቀስ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ የደቀመዝሙር ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍ የተለያዩ ቤተ
ክርስቲያናት፣ ሚኒስትሪዎችና ግለሰቦች እንዲጠቀሙበት ታስቦ የተዘጋጀ እንጂ ለሽያጭ በገበያ ላይ የሚውል መጽሐፍ
አለመሆኑን በድጋሚ እየገለጽን ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ቤተ ክርስቲያን ለግል ጥናት፣ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣
ለማስተማሪያነት ለማሳሰሉት ዓላማዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቅም ይችላል፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ
የምትኖሩ ይህንን መጽሐፍ በሶፍት ኮፒ (Soft Copy) ሆነ በመጽሐፍ (Hard Copy) የምትፈልጉ በአድራሻችን ብትልኩልን በነጻ
የምንልክላቹሁ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡

አድራሻ
ወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን
የመ. ሣ. ቁ. 371፣ ኮድ 1110 አዲስ አበባ
ስልክ፡- (011) 8693233 ሞባይል፡- 0911364451
Email: - shalomsel@gmail.com
Website: - www. gospellightintchurch. com

ይህ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ምክንያት የሆኑን ነገሮች


ወንጌላዊውን ክርስትና ከሌሎች ቤተ እምነቶች የተለየ ያደረገን፤ እንታመንበታለን የምንላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ

አስተምህሮዎች (ዶክትሪኖች) የእምነታችን ዋነኛ መሠረት መሆናቸው ነው፡፡ የዘመናችን ወንጌላዊ ክርስትና አቅፎ

ለያዛቸው ምእመናን ብቻ ሳይሆን በውጭ ላሉትም የሚከብድ ብዙ ችግሮች ውስጥ እንደምንገኝ የአደባባይ

ሚስጥር ነው። ለብዙ ችግሮቻችን መነሻ ሆኖ ያገኘነው መሠረታዊ ችግር የቅዱሳት መጻሕፍት ስልጣናዊ

ማዕከልነት መጣስ እና የአስተምህሮ ብልሽት (መዛነፍ) እንደ ሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ የክርስትና ሕይወታችን

የሚመራው ትክክል ብለን ባመንበት አስተምህሮ (ዶክትሪን) ነው፡፡ የአንድ ክርስቲያን ዘላለማዊ ዕጣ ፈንታ

የሚወሰነው ወይም እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጉዳይ የሚታየው፤ መጽሐፍ

ቅዱሳዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) ላይ ባለው እምነት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆኑ ወይም ቤተ ክርስቲያን
3
በመመላለሱ አይደለም፡፡ ያለ ትክክለኛ ዶክትሪን ትክክለኛና ውጤታማ የክርስትና ሕይወት ሊኖር አይችልም፡፡

ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) ወደ ስሕተትና ጥፋት እንዳንሄድ በመርዳት ወደ ትክክለኛ

ሕይወት ይመራናል፡፡ በዚሁ ተቃራኒ ደግሞ የተሳሰተ አስተምህሮ (ዶክትሪን) ደግሞ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ

በመምራት ከእውነት ዞር እንድንል በማድረግ ሌላ ኢየሱስ፣ ልዩ መንፈስ ወይም ልዩ ወንጌል እንድንቀበል

ያደርገናል፡፡ (2ቆሮ. 11*4፤ ገላ. 1*6) ትምህርታችን ከተበላሸ የክርስትና ሕይወታችን እንደሚበላሽ ግልጽ ነው፤
አስተምህሮ ሲበረዝ ወይም ሲሸቃቀጥ ወይም ባዕድ አስተሳሰብ ሲጫነው ሕይወታችንን በማነጽ ፈንታ ያፈርሳል፡፡

ትክክለኛ የክርስትና ሕይወት የሚኖረን ጤናማ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) የያዝን እንደሆነ

ነው፤ ለዚህ ነው ይህ የትምህርት አጋዥ መጽሐፍ የተዘጋጀው፡፡ አንድ ሰው “ክርስቲያን መሆኔ በቂ ነው፤ እውነተኛ

የክርስቲያን አስተምህሮዎች የትኞቹም የመሆናቸው ጉዳይ አያሳስበኝም” ሊል አይችልም፡፡ አስተምህሮ

(ዶክትሪን) የክርስትያን እምነትና ሕይወት ያለመናወጥ የሚቆምበት ዐምድ ነው፡፡ አስተምህሮ (ዶክትሪን)

መለወጥ፤ አንድ ሰው በዚህም ዓለም ይሁን በመጪው ዓለም የሚኖረውን የመጨረሻ ውጤት ይወስነዋል፡፡

“መሠረቱ ከተናደ ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል” አ.መ.ት (መዝ. 11*3)

ትምህርት አንድ:- ደቀ መዝሙር

ምዕራፍ አንድ፡- የደቀ መዝሙር መሠረታዊ ግንዛቤ


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28*19-20 በሰጠው በታላቁ ተልዕኮ ትዕዛዝ ሁለት ዋና ዋና ትዕዛዞች
እንመለከታለን፡፡ አንደኛው ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ መስበክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በወንጌል በማመን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ
ተወልደው የዳኑትን የኢየሱሰ ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሚወራረሱና ተነጣጥለው የማይታዩ አንዱን ከአንዱ

ሳናበላልጥ የምንፈጽማቸው ትዕዛዛት ናቸው፡፡ “ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው” ከሚለው የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ

እንደምንማረው በወንጌል በማመን ጌታ ኢየሱስን የሕይወቱ አዳኝና ጌታ ያደረገ ሁሉ ደቀ መዝሙር ለመሆን ጥሪ የቀረበለት

መሆኑን ነው፡፡ ይህ ጥሪ የማይመለከተው ማንም የለም፡፡

1.1 ደቀ መዝሙር ምንድን ነው?


4
ደቀ መዝሙር በላቲን “ዲሳይፕሎስ” ሲሆን ትርጉሙም ተማሪ፣ የሚማር፣ ተከታይ ማለት ነው፡፡ በግሪክ ደግሞ “ማቴቴስ”
ማለት ሲሆን መሰረታዊ ትርጉሙ አስተማሪውን የሚከተል ተማሪ (የአስተማሪው እውነተኛ ተማሪ) ማለት ነው፡፡ በዚህም

ግንኙነት መሰረት አስተማሪው በቃልና በአኗኗሩ እውነተኛ ክርስትናን በደቀ መዝሙሩ ሕይወት እንዲመሰረት ያደርጋል፡፡ (ዮሐ.
8*31)

1.2 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ደቀ መዝሙር ምን ይላል?

ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በብዛት የሚገኝ ቃል ባይሆንም በአዲስ ኪዳን ግን በብዛት ጥቅም ላይ
ውሎ እናገኘዋለን፡፡

1.2.1 ብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን ደቀ መዝሙር በማፍራት በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ፡- ኢያሱ

የሙሴ ደቀ መዝሙር ነበረ። (ዘኁ. 11*28፤ ዘጸ. 24*13፤ ዘዳ. 3*28) ካሌብ የሙሴ ደቀ መዝሙር ነበረ። (ኢያሱ 14*6-7)

ዳዊት የሳሙኤል ደቀ መዝሙር ነበረ። (1 ሳሙ. 19*18) ኤልሳዕ የኤልያስ ደቀ መዝሙር ነበረ። (1 ነገ. 19*16-21፤ 2 ነገ. 3*11)

ባሮክ የኤርሚያስ ደቀ መዝሙር ነበረ። (ኤር. 36*5-8)

1.2.2 አዲስ ኪዳን


ሀ/ ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ዘመን ፈሪሳውያን የራሳቸው ተከታዮችና ተማሪዎች ነበሩአቸው
እነዚህም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ይባሉ ነበር፡፡ ፈሪሳውያን ራሳቸውን የሙሴ ደቀ መዛሙርት በማለት ይጠሩ ነበር፡፡ (ማር.
2*18፤ ዮሐ. 9*28)
ለ/ ልክ እንደ ፈሪሳውያውያን የመጥምቁ ዮሐንስም ተከታዮች የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ተብለው ይጠራሉ፡፡ (ዮሐ. 1*35፣
3*25) እነዚህም ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው በጸሎትና በጾም እንደ ዮሐንስ ትዕዛዝ የሚተጉ ነበሩ፡፡
(ሉቃ. 11*1) ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምራቸው የነበረው ስለ ኢየሱስ ስለነበር ኢየሱስን ባገኙ ጊዜ የኢየሱስ ደቀ
መዝሙር ሆነዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል እንድርያስ አንዱ ነበር፡፡ (ዮሐ. 1*35-41)
ሐ/ ኢየሱስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ መምህር (ረቢ) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ (ማር. 9*5፤ 11*21* ዮሐ. 3*2፤ 20*16) ከእርሱ ጋር
ደግሞ የቀረበ ግንኙነት የነበራቸው ሁሉ ደቀ ሙዝሙር ተብለው ተጠርተዋል፡፡ በተለይ ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል ከኢየሱስ
ጋር የተያያዘው የእርሱን መልዕክት ሰምተው ምላሽ ለሰጡ ሰዎች ነው፡፡ (ማቴ. 5*1፤ ሉቃ. 6*17፤ 19*37) ብዙ ጊዜ ደቀ
መዝሙር ተብለው የተጠሩት ከእርሱ ጋር የነበሩና ከቦታ ቦታ አብረውት ይጓዙ የነበሩት ናቸው፡፡ (ማር. 6*45፤ ሉቃ. 8*2፤ 10*1፤
ዮሐ. 6*66፣ 21*8) ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ሴቶች ነበሩ (ሉቃ. 8*2-3) ከዚህ በበለጠ ጠበቅ አድርገን ስንመለከት ብዙ ጊዜ
ደቀ መዛሙርት ተብለው የተጠሩት አስራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው፡፡ (ማቴ. 10*1-5፤ ማር. 6*7) የመጀመሪያዎቹ ደቀ
መዛሙርት እነዚህ ሐዋርያት ሲሆኑ ከዚህም በኋላ ጌታ ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩት አሁንም አሉት፡፡ (ዮሐ. 4*1)
መ/ ከኢየሱስ በኃላ የደቀ መዝሙር ሕይወት በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ቀጥሎ ነበር፡፡ (ሐዋ. 6*1፣ 6*7) በበአዲስ ኪዳን ደቀ

መዝሙር በማፍራት በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ፡- ጳውሎስ የአናንያና የበርናባስ

ደቀ መዝሙር ነበረ። (ሐዋ. 9*17-20፤ 9*26-27፤ 11*21-26) አቂላና ጵርስቅላ የጳውሎስ ደቀ መዝሙር ነበሩ። (ሐዋ. 18*1-

3) አጵሎስ የጵርስቅላና አቂላ ደቀ መዝሙር ነበረ። (ሐዋ. 18*24-28) ጢሞቴዎስ እና ቲቶ የጳውሎስ ደቀ መዝሙር ነበሩ።
5
(ሐዋ 16፥1-3፤ ሮሜ 16*21፤ 1 ቆሮ. 4*17፤ 2 ቆሮ. 8*23፤ 1 ጢሞ. 1*2፤ 2 ጢሞ. 1*2፤ ቲቶ 1*4) ማርቆስ የጴጥሮስ ደቀ

መዝሙር ነበረ። (1 ጴጥ. 5*13) አናሲሞስ የጳውሎስ ደቀ መዝሙር ነበረ። (ፊልሞና 1*10-11)

1.3 ደቀ መዝሙር የማድረግ ጥቅም

ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ስታደርግ በአማኞች ሕይወት የምትፈጽማቸውን አምስት አብይት ሃሳቦች እንደሚከተለው
እንመለከታለን፡፡
ሀ/ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑትን ደቀ መዛሙርት በማድረግ ራሳቸውን መመገብ የሚችሉ ክርስቲያኖች እናደርጋቸዋለን፡፡
የጌታ ደቀ ሙዝሙር የሆነ አማኝ የጌታን ቃል የሚጠብቅና በቃሉ የሚኖር ሰው ነው፡፡ (ዮሐ. 8*31፤ ሐዋ 17*11)
ለ/ ሌላው ደቀ መዝሙር ማድረግ የሚጠቅመው በአማኞች ሕይወት የጠነከረ የፀሎት ሕይወት እንዲኖር ማድረጉ ነው፡፡ ጌታችን
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከአስተማረው ትምህርት አንደኛው ስለ ጸሎት ኃይል ነው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከትምህርቱ ብቻ ሳይሆን
ከሕይወቱ ይማሩ ነበር፡፡ (ማቴ. 6*7-8፤ ሉቃ. 11*1፤ 18*1-8፤ ሐዋ 1*12-14፣ 2*5፣ 8*2፣ 22*12)
ሐ/ ቤተ ክርስቲያን አማኞችን ደቀ መዝሙር በማድረግ አማኙ የተሰጠውን የአገልግሎት ስጦታ እንዲያውቅና እነዲገነባ
ታደርገዋለች፤ ይህም አማኙ በተሰጠው ስጦታ ለእግዚብሔር መንግስት ፍሬ እንዲያፈራ ያደርገዋል፡፡ (ማር. 4*20፤ ዮሐ. 15*8፣
16፤ 1 ጢሞ. 4*13-14፤ 2 ጢሞ. 1*6)
መ/ አንድ አማኝ የደቀ መዝሙር ሕይወት ውስጥ በማለፍ መንፈሳዊ ባህሪያትን በመላበስ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ የክርስትና
መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሳይሆኑ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፡፡ (1 ቆሮ. 11*1፤ 1 ተሰ. 1*6፤ 1 ጢሞ. 6*6፤ ሮሜ
8*29፤ ገላ. 5*22)
ሠ/ ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርት በማድረግ የወንጌል አደራን የሚቀበሉ ሰዎችን ታገኛለች፡፡ የአንድ ቤተ ክርስቲያን እድገት
ከሚመዘንበት መንገድ አንደኛው የአገልግሎት ኃላፊነት የሚቀበሉ ሰዎችን በማፍራቷ ነው፡፡ (ሉቃ. 9*1-2፤ 2 ጢሞ. 2*1-2)

ምዕራፍ ሁለት፡- የደቀ መዝሙር መለያ ባሕርያት

እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ተለይቶ የሚታወቅበት ዓይነተኛ ባሕሪያት አሉት፡፡ ይህም በግላዊና ማኅበራዊ ሕይወት

ይንጸባረቃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ›› ብሎናል፡፡ (ማቴ. 7*16) ፍሬ የማንነት መግለጫ ነው፡፡

እውነተኛ ደቀ መዝሙር የሚከተሉት ባሕሪያት አሉት፡-

ሀ/ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ነው፡፡ (ዮሐ. 8*31፤ ሐዋ. 2*42)


ለ/ በፍቅር የተሞላ ነው፡፡ (ዮሐ. 13*34-35)
ሐ/ መልካም ነገርን የሚያደርግና ፍሬያማ የሆነ ነው፡፡ (ዮሐ. 15*8፤ ሐዋ. 9*36)
መ/ በፍጹም ልቡና ነፍሱ ክርስቶስን የሚከተል ነው፡፡ (ማር. 12*33)
ሠ/ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ጌታን የሚያገልገል ነው፡፡ (ሐዋ. 9*10-17፣ 13*52)
ረ/ በቅድስና ሕይወት የሚመላለስ ነው፡፡ (1 ጴጥ. 1*15-16)

2.1 ወደ ደቀመዝሙር የሚደረግ የእድገት ሂደት

6
በእኔ ኑሩ
ዮሐ. 15*4
ኑ ከእኔ ጋር ሁኑ
ማር. 3*13-15

ኑና ተከተሉኝ

ማር. 1*16-20

ኑና እዩ

ዮሐ. 1*40

ወደ እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ለማደግ የሚረዱ ደረጃወች አሉ፡፡ ሂደቱ ከሕጻንነት ይጀምራል በ 1 ዮሐንስ ምዕራፍ 2*12-14
መሰረት (ልጆች፣ ጐበዞች፣ አባቶች) በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ በዮሐንስ 21*15-17 መሰረት ደግሞ (ግልገል፣ ጠቦት፣ በግ)
በማለት ያስቀምጠዋል፡፡
ሀ/ የመጀመሪያው የእድገት ደረጃ የሕፃንነት (የልጅነት) ወይም የግልገልነት ደረጃ ሲሆን፤ በዚህ የእድገት ደረጃ ያለ ክርስቲያን
የደቀ መዝሙር አድራጊው ጥብቅ ክትትል ያስፈልገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፍቅርና መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት
ያስፈልገዋል፡፡ (1 ጴጥ. 2*2-3)
ለ/ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ የጐልማሳነት (ጐበዞች) ወይም የጠቦት ደረጃ ሲሆን በዚህ የእድገት ደረጃ አማኙ የሚያስፈልገው
ጠንከር ያለ ትምህርት ሲሆን፤ አማኙ በግሉ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና እና መጸለይ የሚጀመርበት ወቅት ሲሆን ደቀ
መዝሙር አድራጊው እንደ አባት ማበረታታትና ማሰልጠን ይገባዋል፡፡ (1 ተሰ. 2*9-12)
ሐ/ የመጨረሻው ደረጃ ደግሞ የአባትነት ወይም በግ ወደ መሆን የሚደረግ ደረጃ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ አማኙ ሙሉ ሰው ወደ
መሆን ያድጋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኖርበታል በግሉ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ሕብረት በማድረግ ሌሎችን ደቀ
መዝሙር ወደ ማድረግ ሂደት ይሸጋገራል፡፡ (ኤፌ. 4*11-13)

ምዕራፍ ሦስት፡- የደቀ መዝሙር ጥሪ

ደቀ መዝሙርን ወደ እርሱ የሚጠራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ (ማቴ. 10*1፤ ሉቃ. 9*1) ይሁንና አንድ ደቀ መዝሙር
ለምን እንደተጠራ በደንብ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ አንድ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ሲሆን ምን ዓይነት ጥሪ መቀበሉ እንደ
ሆነ እንመለከታለን፡፡

3.1 ቀንበር ለመሸከም ተጠርቷል

የደቀ መዝሙር ምልክቶች መስቀልና ቀንበር ናቸው፡፡ ኢየሱስ ወደ ራሱ ሲጠራን ዓለም፣ ኃጢአት፣ ዲያቢሎስ የጫነብንን ቀንበር
አውርዶ የራሱን ቀንበር ጫነብን፡፡ የኢየሱስ ቀንበር ቀላል ነው፡፡ (ማቴ. 11*28-30) ቀንበር በእንስሳት ላይ የሚጫን ከእንጨት
የተሰራ መሣሪያ ነው፡፡ ቀንበር የተጫነ እንስሳ የራሱ ፈቃድ የለውም መሄድ ወደ ፈለገበት መሄድ አይችልም፤ ቀንበሩ
ወደሚያዘው ብቻ ነው የሚሄደው፡፡ ቀንበር መታዘዝንና የራስን ፈቃድ መጣልን ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ የደቀ መዝሙር ጥሪ ቀንበር
የመሸከም ጥሪ ነው ስንል፤ ቀንበር መሸከም ኢየሱስን የሕይወት ጌታ በማድረግ ይጀምርና በሕይወት ዘመን ሁሉ ኢየሱስን

7
በመታዘዝ ይቀጥላል፡፡ ደቀ መዝሙር ስንሆን የራሳችንን ፈቃድና ፍላጎት ትተን ለጌታ ፈቃድ መኖር እንጀምራለን፡፡ (ሐዋ.
13*22፤ ገላ. 2*20፤ 1 ጴጥ. 4*2፤ 1 ዮሐ. 2*17)

3.2 መስቀል ለመሸከም ተጠርቷል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት በጣም የሚያስደንቀው ሰዎች እንዲከተሉት ሲጠራቸው አጉል ተስፋ
የተሞላበት አነጋገር አለመናገሩና እርሱን በመከተል የሚደርስባቸውን መከራና ስደት ግልጽ አድርጐ ማስታወቁ ነው፡፡ (ማቴ.
10*34-39፤ ማር. 8*34-35) ተከታዮችን ማፍራት የሚፈልግ ማንም ፈላስፋ ወይም የኃይማኖት መሪ እንዲህ ዓይነቱን ንግግር
አይናገርም፡፡ መስቀል ስንል በአንገታችን ላይ የምናንጠለጥለውን በብር፣ በወርቅ ወይም በእንጨት የሚሰራውን አይደለም፡፡
መስቀል ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተላችንና በቅድስና ሕይወት በመኖራችን ምክንያት ከሰዎች የሚደርስብን መጠላት፣
መገፋት፣ ከስራ መባረር፣ መሰቃየት፣ መራብና መጠማት እንዲሁም መታሰር ማለት ነው፡፡ (ሮሜ. 8*35-36፤ 2 ቆሮ. 11*24-
27) የክርስትና ሕይወት የመስቀል ሕይወት መሆኑን ባለመገንዘብ አንዳንድ ክርስቲያኖች አንዳንድ መከራ በሕይወታቸው ሲመጣ
በእግዚአብሔር በማዘን ወደ ኋላ የሚመለሱ አሉ፡፡ ደቀ መዝሙር ለየትኛውም ዓይነት መከራ መዘጋጀት አለበት፡፡ ደቀ መዝሙር
ስደት የሚቀበለው ከውጭ ከሚመጣ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም ከሚመጣ ችግር ነው፡፡ ክርስትናን ከመስቀሉ መለየት
አይቻልም፡፡ (ሉቃ. 14*27፤ ሮሜ 8*17፤ 2 ጢሞ. 1*8፤ ዕብ. 11*35-38፤ 1 ጴጥ. 3*13-17)

3.3 ሁሉን ትቶ ኢየሱስን ለመከተል ተጠርቷል

ጌታ የመረጣቸው ደቀ መዛሙርት ሁሉን ትተው ተከትለውታል፡፡ (ማቴ. 19*27፤ ማር. 1*16-20) እውነተኛ ደቀ መዝሙር

ለመሆን ስንጠራ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ትተን ጌታን እንድንከተል ነው፡፡ ለምሳሌ አስፈላጊ ሲሆን
እንኳን (ሁሌም ላይሆን ይችላል) የቅርብ ቤተሰባችንን፣ ሀብታችንን፣ ምቾቶቻችን፣ የፍቅር ጓደኛ (እጮኛ) እንኳን ሳይቀር
ለመተው የተዘጋጀን መሆን አለብን፡፡ (ሉቃ. 14*26) የጌታ ደቀ መዝሙር የሆነው ሰው የተቀበለውን የጌታን ፍቅር ከምንም ነገር
ጋር ማወዳደር የለበትም፡፡

3.4 ራስን ለማዋረድ ተጠርቷል

ጌታ ደቀ መዛሙርቱ ደጋግሞ ካስተማረው ትምህርት አንዱ ትህትና ነው፡፡ ትዕቢት እግዚአብሔር የሚጸየፈው ኃጢአት ነው፡፡
(ምሳ. 11*2፤ 16*18፤ ሮሜ 12*16) ደቀ መዝሙር የተጠራው ራሱን ለማዋረድ ነው፤ በዚህም ሕይወት ውስጥ ጌታ ከፍ
ማለትን ይሰጠዋል፡፡ (ምሳ. 3*34፤ 11*2፤ ሉቃ. 1*52፤ ያዕ. 4*6) ደቀ መዝሙር በእግዚአብሔር ቃል ለመሞላት በጠቅላላው
ጌታ ባዘጋጀው በረከቶች ለመሞላት አስቀድሞ ራሱን ከብዙ ነገሮች ማንጻትና ባዶ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ (ማቴ. 20*27-28፤
ሉቃ. 22*25-26፤ ቆላ. 3*12)

8
3.5 ለመታዘዝ ተጠርቷል

ለደቀ መዝሙር ትልቁ ምልክት የመታዘዝ ሕይወቱ ነው፡፡ መታዘዙን የሚገልጸው በሁለት አቅጣጫ ነው የመጀመሪያው
ለእግዚአብሔርና ለቃሉ መታዘዝ ነው፤ ሌላው አቅጣጫ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን መታዘዝ ነው፡፡ (1 ሳሙ. 15*22፤ ሐዋ. 5*29፤
ማቴ. 18*17፤ ገላ. 2*1-2)
3.6 ለመመስከር ተጠርቷል

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ምስክር ስለ መሆን ሲያስተምራቸው “እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ” በማለት
በአጭርና ቀጥተኛ በሆነ ቃል ይናገራል፡፡ (ሉቃ. 24*48) ለደቀ መዝሙር መመስከር ከጌታ የተሰጠው ተልዕኮና ኃላፊነት ነው፡፡
(ዮሐ. 20*21፤ ሐዋ.1*8፤ 1 ዮሐ. 1*1) ስለዚህ አንዲት ቤተ ክርስቲያን በነፍሳት ልትበለጽግ የምትችለው ሰዎችን ደቀ
መዝሙር በማድረግ ለመላክ ስትዘጋጅ ነው፡፡

ምዕራፍ አራት፡- የደቀ መዝሙር ሕይወት ግንኙነት

የደቀ መዝሙር ሕይወት በምንመለከትበት ጊዜ የሕይወቱ ግንኙነት ከእግዚአብሔር፣ ከቤተክርስቲያንና እንዲሁም ከዓለም ጋር
ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አስራ ሰባት ለደቀ መዛሙርቱ በጸለየው ጸሎት እነዚህን
ሦስት የግንኙነት አቅጣጫዎች አስመልክቶ እንደ ጸለየ እንመለከታለን፡፡ (ዮሐ. 17*1-26)
4.1 ደቀ መዝሙርና እግዚአብሔር

የደቀ መዝሙር ሕይወት የሚመዘነው በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ነው፡፡ የዚህ ግንኙነት መስመር

አውታሮች የእግዚአብሔር ቃልና ጸሎት ናቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠው ትዕዛዝ ውስጥ ጉልህ ሆኖ የወጣው መመሪያ

‹‹ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዝሙር አድርጓቸው›› የሚለው ነው፡፡ (ማቴ. 28*19-20)

ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት (ከመጽሐፍ ቅዱስ) ውጪ ደቀ መዝሙር መሆን አይቻልም፡፡

እንግዲህ ደቀ መዝሙር በቃሉ በመኖር የጌታን ማንነት ያውቃል፣ ውስጣዊ ሕይወቱን ይገነባል፣ እንደ ጌታ ፈቃድ ይመላለሳል፣
ጌታ ለሰጠው አገልግሎት የተዘጋጀ ይሆናል፡፡ በደቀ መዛሙርት ሕይወት የእግዚአብሔር ቃል ከፍተኛ ስፍራ አለው፡፡ ሌላው ደቀ
መዝሙር ከጌታ ጋር ያለው ግንኙነት የመገናኛው መስመር ጸሎት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ለደቀ መዛርቱ ስለ
ጸሎት ሕይወት ያስተማረውን ቃሉ ይነግረናል፡፡ (ሉቃ. 6*12፤ 11*1-13፤ 18*1-8) በቃል ካስተማራቸውም በላይ ደቀ
መዛሙርቱ ከጌታ የጸሎት ሕይወት አብዝተው ይማሩ ነበር፡፡

4.2 ደቀ መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን

9
የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንን አመሰራረት በምንመለከትበት ጊዜ ደቀ መዛሙርት የቤተ ክርስቲያን የመሰረት ድንጋዮች ሆነው
እናያለን፡፡ (ሐዋ. 6*7፤ 11*26፤ 1 ጴጥ. 2*5) የደቀ መዝሙር ሕይወት ከሚለካበት ሚዛኖች አንደኛው አማኙ ከቤተ ክርስቲያን
ጋር ባለው ግንኙነት ነው፡፡ ጌታ ሲመለከተን የሚያየን በአካሉ (በቤተ ክርስቲያን) ውስጥ ነው፡፡ ደቀ መዝሙርን ከቤተ ክርስቲያን
ውጪ ማየት አንችልም፤ ዛሬም በደቀ መዝሙር ሕይወት ለመኖር የአንድ ማህበር ምዕመናን (ቤተ ክርስቲያን) አካል መሆን
ያስፈልጋል፡፡ (1 ቆሮ. 12*13-18)
4.3 ደቀ መዝሙርና ዓለም

ደቀ መዝሙር በውጭ ባሉት ሰዎች ዘንድ ምሳሌ ያለው ሕይወት ይዞ የመመላለስ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ደቀ
መዝሙር ሊኖርው ስለሚገባው ሕይወት ከዘረዘራቸው ነጥቦች አንደኛው “…በውጭ ባሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር
ሊኖረው ይገባዋል” የሚል ነው፡፡ (1 ጢሞ. 3*7) ሐዋርያው በውጭ ባሉት ሲል ምን ማለቱ ነው? ከቤተ ክርስቲያን ውጭ
በዓለም ማለቱ ነው፡፡ ፍቅራችን በክርስትና ውስጥ ካሉት አልፎ በውጭ ለሚመላለሱት መታየት አለበት፡፡ ደቀ መዝሙርነት
ከዓለም ሸሽቶ መውጣት ሳይሆን፤ በዓለም እየኖርን የጌታን ብርሃን ለጨለማው ዓለም የምናንጸባርቅበት ሕይወት ነው፡፡ (ማቴ.
5*13-16፤ ዮሐ. 17*15፤ ሮሜ 12*2፤ 1 ጴጥ. 3*16)

ምዕራፍ አምስት፡- ደቀ መዝሙር የማድረጊያ መንገዶች

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ፍሬ የሚያፈሩ ክርስቲያኖች ቁጥር ማነሱ የደቀ መዛሙርት ቁጥር ማነሱን ያሳያል፡፡ ለዚህም መነሻ የሆኑ
ሁለት ምክንያቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ደቀ መዝሙርነትን/ተማሪነትንና በዝግታ ማደግን አሻፈረኝ የሚሉ ምዕመናን
መኖራቸው ሲሆን ሁለተኛው ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርትን ስለማታፈራ ወይም አደራረጉን አለማወቋ ነው፡፡ ከዚህ በታች
የተወሰኑትን ደቀ መዝሙር ማድረጊያ መንገዶች እንመለከታለን፡፡
5.1 አንድ ለአንድ

ደቀ መዝሙር በማድረግ ሂደት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ ሌሎች ሐዋርያት ከተጠቀሙበት መንገድ አንዱ አማኞችን በግል
በመያዝ፣ በመጸለይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር መጠቀም ነው፡፡ በዚህ ዘዴ አማኞችን አቅርበናቸው ከሕይወታችን፣
ከትምህርታችንና ከአገልግሎታችን እንዲማሩ ማድረግ እንችላለን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን
ያስተማረበት አንደኛው መንገድ የእርሱን ሕይወት እንዲያዩ በማድረግ ነበር፡፡ በኋላም ሐዋርያቱ ይህንኑ ፈለግ በመከተል ደቀ
መዛሙርትን ሲያፈሩ እናያለን፤ ዛሬም ይህን ፈለግ በመከተል በቃልና በተግባር ሰዎችን እያስተማርን ደቀ መዛሙርትን ማፍራት
እንችላለን፡፡ (ሉቃ. 10*39-42፤ ሐዋ. 18*24-26፣ 28*30-31)

5.2 በክፍል ውስጥ

ደቀ መዝሙር በማድረግ ሂደት ውስጥ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያት በተለያየ ስፍራ ሰዎችን በመሰብሰብ ያስተምሩ ነበር፡፡ ስለዚህ
ዛሬም አማኞችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድ ክፍል ውስጥ በማድረግ በማስተማር ደቀ መዝሙር ማድረግ ይቻላል፡፡ በደቀ
መዛሙርት ሕይወት የእግዚአብሔር ቃል ከፍተኛ ስፍራ አለው ካልን ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርትን ለማዘጋጀት
በምትወሰወደው እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚገባ ማስተማር አለባት፡፡ (ማቴ. 5*1-2፤ ማር. 4*1-2፤ ሐዋ. 19*9)
5.3 በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን
10
ደቀ መዝሙር በማድረግ ሂደት ውስጥ ሌላው ጠቃሚ ነገር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በተለያየ
ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መገኘት አይችሉም፡፡ ለምሳሌ ሙስሊሞች ጌታን አግኝተው ቶሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቀላቀል
ሊከብዳቸው ይችላል ስለዚህ እነሱን ደቀ መዝሙር ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን መልካም ቦታ ነው፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሕይወት ዕድገት እናገኛለን፣ ፀጋችንን ለመጠቀምና ፍሬ ለማፍራት ዕድል እናገኛለን፡፡
ሰዎችን ማስተማር ብቻ በቂ አይደለም፤ ፀጋቸውን እንዲረዱና በአገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም
የቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እጅግ ጥቅም አለው፡፡ (ሐዋ. 5*42፣ 12*12፣ 20*20-21፤ ፊልሞና 1*2)

ምዕራፍ ስድስት፡- ደቀ መዝሙር የምታደርግ ቤተ ክርስቲያን ባሕርያት

በዚህም ዘመን ብዙ ቤተ ክርስቲያናት ደቀ መዝሙር ከማፍራት ይልቅ በብዙ ነገር ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እውነተኛ የክርስቶስ

ደቀመዝሙር የምታፈራ ቤተ ክርስቲያን በምን ትታወቃለች? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች እንደሚሰጡ የታወቀ ነው።

ከዚህ በታች ደቀመዝሙር የምታፈራ ቤተ ክርስቲያን ወይንም በውስጧ በብዛት ደቀ መዝሙር ያሉባት ቤተ ክርስቲያን መገለጫ

የሆኑትን የተወሰኑ ባህሪያትን እንመለከታለን።

ሀ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ ኢየሱስ ማዕከልነትና ሉዐላዊነት በግልጽ የሚታይበት ነው፡፡

ለ/ በቤተ ክርስቲያን የመስቀሉ ማእከልነት ቸል የማይባልበት፤ ይልቁን የመስቀሉ ትሩፋትና የመስቀሉ መንገድ በግልጽ

የሚታወጅበትና የሚኖርበት ነው፡፡

ሐ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና ውጭ የተጠናከረ የግል፣ የቤተሰብና የህብረት የጾም ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ፕሮግራሞች የሚደረጉበት ነው፡፡

መ/ ለቃሉ ስልጣን ያለ ምንም ድርድር የሚገዛ፤ ማንኛውንም ስብከት፣ ትምህርት፣ ትንቢት፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ልምምዶች

በቃሉ ለመፈተሽ/ለማስፈተሽ የሚተጋ፤ ቃሉን በአግባቡ ለመፍታትና ለመተርጐም የሚጠነቀቅ ምዕመን እና አገልጋይ

የሚታይበት ነው፡፡

ሠ/ የአማኞች ሁሉ ክህነት የሚታይበት፣ እያንዳንዱ ምዕመን አስፈላጊነቱ ግልጽ የሆነበትና ሁሉም ምዕመን የሚሳተፍበት፣

ሁሉም ምዕመን በእኩል አይን የሚታይበትና እያንዳንዱ አማኝ ከሌላው አማኝ ጋር የተጠናከረ፣ የተያያዘ እና በአንድነት አብሮ

የሚሰራ ነው፡፡

ረ/ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘና ሚዛናዊ የሆነ የፀጋ ስጦታ አገልግሎት ተግባራዊ የሚደረግበት ነው፡፡

ሰ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እኩል የመንፍስ ፍሬ ጎልቶና ተዘውትሮ የሚታይበት ነው፡፡

ሸ/ የቤተ ክርስቲያን ዋና ተልእኮ በሆነው ሰዎችን ወደ ጌታ ኢየሱስ በማምጣት፣ ደቀ መዝሙር በማድረግ እና ተተኪ አገልጋይ

በማፍራት ላይ አጥብቃ የምትሰራ ናት፡፡

ቀ/ መሪዎች ገንዘብ ስለሚሰጡ፣ ወይም ብዙ ደጋፊና ወገን ስላላቸው፣ ወይም የተማሩ እና የታወቁ ስለሆኑ ብቻ

የማይመረጡበት እንደ ቃሉ ተመዝነውና የሕይወት ጥራት መስፈርቶችን ያሟሉ መሪዎች የሚታዩበት ነው፡፡

11
ምዕራፍ ሰባት፡- ተግባራዊ ተዛምዶ
 ደቀ መዝሙርነት አማራጭ የሌለው የዕድገት መንገድ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምትመሰረተው የደቀ መዝሙር
ሕይወትን በተቀበሉ ምዕመናን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ዕድገት የሚመዘነው በደቀ መዛሙርት ቁጥር እንጂ በቤተ
ክርስቲያን በር በሚገቡና በሚወጡ ሰዎች ብዛት አይደለም፡፡ ስለሆነም አማኞች ሁሉ በዝግታ በማደግ ደቀ መዝሙር
መሆን አለብን፡፡ ለደቀ መዝሙርነት አቋራጭ መንገድ የለውም፡፡ በተጨማሪም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት
በክርስቶስ ኢየሱስ ትምህርትና የኑሮ ጠባይ መኖርን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ (ማቴ. 28*18-20) መጽሐፍ ቅዱስን
መሠረት ያደረጉ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት በትክክል መንገድ ካልተሰጠና በሕይወት ካልተተገበረ እውነተኛ ደቀ

12
መዝሙርነት የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ ስለዚህ ደቀ መዝሙር ማድረጉ ላይ ብቻ ሳይሆን ማተኮር ያለብን በማን
ትምህርት ነው ደቀ መዝሙር እየሆንን ያለነው የሚለውንም መመልከት ያስፈልጋል፡፡
 ክርስትና አልጋ በአልጋ ሁሉ ነገር ምቹ የሆነለት እምነት አይደለም፤ ምክንያቱም አማኝ የሚኖረው የፈጠራትን ኢየሱስ

እንኳን ባልተቀበለች ዓለም ውስጥ ስለሆነ፤  ዓለም ለኢየሱስ አይደለችም ኢየሱስም ለዓለም አይደለም ስለዚህ እሱን

የሕይወታቸው ጌታ ያደረጉ ሁሉ ከዓለም ጋራ በመቻቻል መኖር አይችሉም፡፡ ዓለም ለኢየሱስ መስቀል እንዳዘጋጀች

ሁሉ ለተከታዮቹም መስቀል አላት፡፡  ክርስትና ያለ መስቀል አይሆንም፤ ኢየሱስ እንዳለ ስለ ስሜ የተጠላቹ ትሆናላቹ

በማለት ስለ ስሙ የሚመጣውን መከራ አስቀድሞ ተናገረ፡፡ ዛሬ ዛሬ በስመ ክርስትና በረከት እየተባለ አማኞች ሰማይን

ሳይሆን ምድርን፣ ጌታን ሳይሆን ገንዘብን፣ ወንጌልን ሳይሆን ብልጽግናን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ መስቀል አልባ

ክርስትና በሰፊው ሲሰብኩ ይሰማሉ፡፡ መስቀል ከሌለ ክርስትና የሚባል ነገር የለም፣ ራስን ሳይክዱ ኢየሱስን ማመን

የለም፣ ዓለምን ሳይንቁ ሰማይን መናፈቅ የለም፡፡  መጽሐፍ ቅዱስ ያለመስቀል ደቀ መዝሙርነት እንደ ሌለ ያስረዳል፤
ስለዚህ በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን መስቀሎች ሁሉ እንደ ሙሉ ደስታ በመቁጠር ወደ ደቀ መዝሙርነት
ሕይወት ማደግ አለብን፡፡

 ጌታ የመረጣቸው ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈዋል፣ ሁሉን ትተው ተከትለውታል፣ ስለ እርሱ

በብዙዎች ተጠልተዋል ይሁን እንጂ በአንድ ሌሊት እርሱ ወደሚፈልገው አልደረሱም፡፡ እርሱ አልፎ በተሰጠበት በዚያች

ሌሊት እንኳን ተበተኑ፤ አንዳንዶቹም የማይገባ ድርጊት ፈጸሙ፡፡ (ሉቃ 22*54-62) ደቀ መዝሙር ማፍራት ብዙ ውጣ

ውረድ አለው፤ ደቀ መዝሙርነት በሂደት እንጂ በቅጽበት የሚከናወን አይደለም፡፡ ከዚህ የተነሳ ረጅም ጊዜ እንዲሁም

ብርቱ ጥረትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ለመረዳት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና ባሰለጠናቸው ደቀ መዛሙርት

መካከል የነበረውን ጥብቅ ግንኙነት መመልከት ያግዘናል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ሐዋርያትና ከእነርሱ ጋር

የነበሩት ሌሎች ብዙ ተከታዮች ነበሩ የሚበዙቱ ደቀ መዝሙርነት ከሚጠይቀው ዋጋ የተነሳ በሂደት ተንጠባጥበው

አለቁ፡፡ (ዮሐ. 6*66-69) ደቀ መዝሙር ማፍራት እጅግ ጽናት የሚጠይቅ ስራ መሆኑን በመገንዘብ ቤተ ክርስቲያን

ሳትታክት ደቀ መዝሙር በማፍራት ስራ ላይ ማተኮር አለባት፡፡

የደቀመዝሙር የክለሳ ጥያቄዎች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– እውነተኛ ደቀ መዝሙር ለመሆን ስንጠራ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ትተን ጌታን
እንድንከተል ነው፡፡
2. –––––– አማኞችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ያለብን በክፍል ውስጥ ብቻ ነው፡፡
3. –––––– የደቀ መዝሙር ሕይወት በምንመለከትበት ጊዜ የሕይወቱ ግንኙነት ከቤተክርስቲያን ጋር ብቻ ነው፡፡
4. –––––– ኢየሱስ ወደ ራሱ ሲጠራን ዓለም፣ ኃጢአት፣ ዲያቢሎስ የጫነብንን ቀንበር አውርዶ የራሱን ቀንበር ጫነብን፡፡
5. –––––– ክርስትናን ከመስቀሉ መለየት አይቻልም፡፡
13
ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ
6. የደቀ መዝሙር ምልክቶች ሀ/ ጢሞቴዎስ
7. በግል በመያዝ፣ በመጸለይ፣ በማስተማር ደቀመዝሙር ማድረግ ለ/ ደቀመዝሙር (ተማሪ)
8. የጳውሎስ ደቀ መዝሙር ሐ/ ማርቆስ
9. “ዲሳይፕሎስ” ወይም “ማቴቴስ” መ/ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
10. ቀንበር መሸከም ሠ/ መስቀልና ቀንበር
ረ/ አንድ ለአንድ
ሰ/ መታዘዝ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. የደቀ መዝሙር ጥሪ መስቀል የመሸከም ጥሪ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው?


ሀ/ የራሳችንን ፈቃድና ፍላጎት ትተን ለጌታ ፈቃድ መኖር ማለት ነው፡፡
ለ/ ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተላችንና በቅድስና ሕይወት በመኖራችን ምክንያት ከሰዎች የሚደርስብን መጠላት፣ መገፋት፣ ከስራ
መባረር፣ መሰቃየት፣ መራብና መጠማት እንዲሁም መታሰር ማለት ነው፡፡
ሐ/ ለቃሉ መታዘዝ ማለት ነው፡፡
መ/ ለቤተ ክርስቲያን መታዘዝ ማለት ነው፡፡
12. ወደ እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ለማደግ ከሚደረዱ ደረጃዎች መካከል ትክክለኛው የቱ ነው?
ሀ/ ጐበዞች፣ አባቶች፣ ልጆች ወይም ጠቦት፣ በግ፣ ግልገል፡፡
ለ/ ልጆች፣ ጐበዞች፣ አባቶች ወይም ግልገል፣ ጠቦት፣ በግ፡፡
ሐ/ አባቶች፣ ልጆች፣ ጐበዞች ወይም በግ፣ ግልገል፣ ጠቦት፡፡
መ/ ልጆች፣ አባቶች፣ ጐበዞች ወይም በግ፣ ጠቦት፣ ግልገል፡፡
13. ደቀ መዝሙር ምንድን ነው?
ሀ/ ተማሪ፣ የሚማር፣ ተከታይ ማለት ነው፡፡
ለ/ አስተማሪውን የሚከተል ተማሪ ማለት ነው፡፡
ሐ/ የአስተማሪው እውነተኛ ተማሪ ማለት ነው፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
14. ደቀ መዝሙር ማድረግ ለምን ይጠቅማል?
ሀ/ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑትን ራሳቸውን መመገብ የሚችሉ ክርስቲያኖች እናደርጋቸዋለን፡፡
ለ/ በአማኞች ሕይወት የጠነከረ የፀሎት ሕይወት እንዲኖር እናደርጋለን፡፡
ሐ/ የተሰጣቸውን የአገልግሎት ስጦታ እንዲያውቁና በዛ ላይ እነዲገነቡ እናደርጋለን፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

14
15. የደቀ መዝሙር ሕይወት የሚመዘነው በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ነው፤ የዚህ ግንኙነት
መስመር አውታሮች ምንና ምን ናቸው፡፡
ሀ/ ቃልና ጸሎት ናቸው፡፡
ለ/ ጾምና ጸሎት ናቸው፡፡
ሐ/ አምልኮና ቃል ናቸው፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
16. የደቀ መዝሙር ሕይወት በምንመለከትበት ጊዜ የሕይወቱ ግንኙነት ከምን ከምን ጋር ነው?
ሀ/ ከእግዚአብሔር ጋር፡፡
ለ/ ከቤተክርስቲያን ጋር፡፡
ሐ/ ከዓለም ጋር፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
17. ደቀመዝሙር መታዘዝ ያለበት ለማን ነው?
ሀ/ ለእግዚአብሔርና ለቃሉ፡፡
ለ/ ለቤተ ክርስቲያን፡፡
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
መ/ መልስ አልተሰጠም፡፡

18. እውነተኛ ደቀ መዝሙር ተለይቶ የሚታወቅበት ዓይነተኛ ባሕሪያት የቱ ነው?


ሀ/ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ነው፡፡
ለ/ በፍቅር የተሞላ ነው፡፡
ሐ/ በፍጹም ልቡና ነፍሱ ክርስቶስን የሚከተል ነው፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. አንድ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ሲሆን ምን ዓይነት ጥሪ መቀበሉ እንደ ሆነ የሚያመለክቱ ስድስት የደቀ መዝሙር ጥሪዎች
መካከል ሶስቱን በማብራረት ግለጹ?

20. ደቀመዝሙር የምታፈራ ቤተ ክርስቲያን ወይንም በውስጧ በብዛት ደቀ መዝሙር ያሉባት ቤተ ክርስቲያን መገለጫ

የሆኑትን ሶስት ባህሪያት ጥቀሱ?

15
ትምህርት ሁለት: - የምስክርነት ሕይወት (ወንጌል ስርጭት)

ምዕራፍ አንድ: - የምስክርነት ሕይወት (ወንጌል ስርጭት) ትርጉም


ሰዎች ከዚህ ዓለም ከመለየታቸው በፊት የድነት/ የምስራች ቃል (ወንጌልን) ሰምተው፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል
አዳኛቸው አድርገው በመቀበል የእግዚአብሔርን መንግስት የሚወርሱበትን መንገድ ማስረዳት ወይም መንገር መመስከር
ይባላል፡፡ ምስክርነት በአንደበት የሚነገር አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በሕይወትም የሚገለጥ መልዕክት ነው፡፡ ስለሆነም ኢየሱስ
ክርስቶስ ያድናል ወይም ይለውጣል በማለት የሚመሰክረው ሰው የመለወጡን እውነት በሕይወቱ የሚመሰክር ሊሆን ይገባዋል፡፡
ስለዚህ ምስክርነታችን የአንደበትም የሕይወትም ምስክርነትን አጣምሮ የያዘ ሊሆን ይገባዋል፡፡ (ሉቃ. 24*19፤ ሮሜ 10*14-
17፤ 1 ቆሮ. 15*1-4)
1.1 የምስክርነት ሕይወት (የወንጌል ስርጭት) መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት

1.1.1 ብሉይ ኪዳን

በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው የወንጌል ሰባኪ እግዚአብሔር ነው፡፡ አዳም ኃጢአት ሰርቶ በተሸሸገበት ስፍራ “አዳም አዳም
ወዴት ነህ” (ዘፍ. 3*9) በማለት የፈለገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር የጠፋውን
የሰው ልጅ ይፈልጋል፡፡ በመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “… እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ
በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ይላል፡፡ (ገላ. 3*8፤ ዘፍ. 22*18) እግዚአብሔር
ለአላማው ሰዎችን የሚጠራና የሚልክ አምላክ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጊዜ የተለያዩ ሰዎችን ለዓላማው ይጠራና ይልክ ነበር፡፡
16
ለምሳሌ፡- አብርሃምን (ዘፍ. 12*1-4) ፣ ዮሴፍን (ዘፍ. 45*4-8) ፣ ሙሴን (ዘጸ. 3*10)፣ ነቢያትን (2 ዜና. 36*15-16፤ ኤር.
7*25) በብሉይ ኪዳን እስራኤል በአሕዛብ መካከል የእግዚአብሔር ካህናት እና የተቀደሰ ሕዝብ እንዲሆኑ ተጠርተው ነበር፡፡ (ዘጸ.
19*5-6፤ ኢሳ. 42*5-7) የእግዚአብሔር አላማ በእስራኤል በኩል ዓለምን ሁሉ ለመድረስ ነበር፡፡
1.1.2 አዲስ ኪዳን

በአዲስ ኪዳን በአራቱ ወንጌላትና በሐዋርያት ስራ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማ በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ሀ/ በማቴዎስ ወንጌል 28*18-20 መሠረት
የተሰጠን ትዕዛዝ፡- ወንጌልን መስበክና ደቀ መዝሙር ማድረግ
የወንጌል ስርጭት አካባቢ፡- አሕዛብ ሁሉ
የወንጌል ስርጭት መልዕክት፡- ወንጌል
የወንጌል ስርጭት አፈጻጸም፡- መሄድ፣ማወጅ (መናገር)፣ ማጥመቅ፣ ማስተማር
ለ/ በማርቆስ ወንጌል 16*15-18 መሠረት
የተሰጠን ትዕዛዝ፡- የምስራቹን ወንጌል መስበክ (መናገር)
የወንጌል ስርጭት አካባቢ፡- ዓለም ሁሉ
የወንጌል ስርጭት መልዕክት፡- ወንጌል (የምስራች)
የወንጌል ስርጭት አፈጻጸም፡- መሄድ፣ መስበክ፣ በምልክት መታጀብ
ሐ/ በሉቃስ ወንጌል 24*46-49 መሠረት
የተሰጠን ትዕዛዝ፡- በንስሃ ስለሚገኝ ምህረት ማወጅ
የወንጌል ስርጭት መልዕክት፡- የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ
የወንጌል ስርጭት አፈጻጸም፡- ኃይልን መቀበል፣ መሄድ፣ መስበክ
መ/ በዮሐንስ ወንጌል 20*21-23 መሠረት
የተሰጠን ትዕዛዝ፡- እልካችኋለሁ
የወንጌል ስርጭት አካባቢ፡- ዓለም ሁሉ
የወንጌል ስርጭት መልዕክት፡- የኃጢአት ይቅርታ
የወንጌል ስርጭት አፈጻጸም፡- የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተቀብሎ መሄድ
ሠ/ በሐዋርያት ሥራ 1*8 መሠረት
የተሰጠን ትዕዛዝ፡- ምስክሮች መሆን
የወንጌል ስርጭት አካባቢ፡- ኢየሩሳሌም፣ ይሁዳ፣ ሰማርያ፣ እስከምድር ዳርቻ
የወንገል ስርጭት መልዕክት፡- ወንጌል
የወንጌል ስርጭት አፈጻጸም፡- መሄድ፣ ማወጅ
 ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ተልኮ የጠፋውን የሰው ልጅ ለማዳን ወደ ምድር እንደመጣ፤ እርሱ ደግሞ የጠፋውን
የሰው ልጅ ለማዳን ቤተ ክርስቲያንን ልኳል፡፡ ስለዚህ ወንጌል ስርጭት ከእግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ትልቅ
አደራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለወንጌል ስራ ስትሰማራ በዚህ አገልግሎት ትዕዛዝ የሰጠን ጌታ ኢየሱስ እስከ ዓለም ፍጻሜ
(ሁልጊዜ) ከቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን አብሮ ይሰራል፡፡ (ማቴ. 18*11፤ 28*19-20፤ ዮሐ. 20*21)
1.2 የምስክርነት ሕይወት (የወንጌል ስርጭት) ዓላማ

17
 ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው የእግዚአብሔር ክብር ጐድሎታል፡፡ (ሮሜ 3*23)
 ሰው ሁሉ ይድን ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ (1 ጢሞ. 2*3-4)
 ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ ሊድን (ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ) አይችልም፡፡ (ዮሐ. 3*3-5)
 ሰው ዳግመኛ ለመወለድ ወንጌል መስማት አለበት፡፡ መጽሐፍ “ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ” እንደሚል ያለ ሰባኪ
(መስካሪ) ወንጌል መስማት አይችልም፡፡ (ሮሜ 10*14-15)
 ወንጌል ለሌሎች ሰዎች ለመንገር በምድር ላይ የእግዚአብሔር ወኪል ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ (2 ቆሮ. 5*18-20)
ክርስቲያኖች በግልም ሆነ በማህበር የእግዚአብሔር መልዕክተኞች ናቸው፡፡ (ሐዋ. 20*24)
 የድነት ወንጌል ዓላማው ወደ ሞት የሚነዱትን ሰዎች መታገድ ስለሆነ የሚጠፉትን ለመታደግ የባዘኑትን ለመመለስ
ከክርስቶስ ጋር አብረን ለመስራት መነሳት አለብን፡፡ (ምሳ. 24*11፤ 1 ቆሮ. 3*9)

1.3 የምስክርነት ሕይወት አስፈላጊነት

እግዚአብሔር በምህረቱ ባለፀጋ ስለሆነ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት እንዲሆንልንና በእርሱ
ሞትና ትንሣኤ ድነትና የዘላለም ሕይወት ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር ፈቅዷል፡፡ (ዮሐ. 3*16፤ ሮሜ 5*6-8፤ 2 ቆሮ. 5*21፤
ቲቶ 3*4-7) ስለዚህ ሰዎች የማዳኑን የምስራች ሰምተው ከዘላለም ፍርድና ኩነኔ ይድኑ ዘንድ ይህ የምስክርነት አገልግሎት
(ተልዕኮ) አስፈላጊ ሆኖአል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ለምንድን ነው መመስከር ያስፈለገው የሚለውን እንመለከታለን፡፡
1.3.2 የጌታ ትዕዛዝ ስለሆነ

ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ ይደርሱ ዘንድ የእግዚአብሔር በጐ ፈቃድ ነው፡፡ (1 ጢሞ. 2*3-4) ስለዚህ ይህንን
ፈቃዱን ለማስፈጸም በጌታ የሚገኘውን ጸጋ በሕይወታቸው የተለማመዱ ክርስቲያኖች ሁሉ ሄደው ወንጌልን ወይም የማዳኑን
የምስራች እንዲናገሩ ጌታ አዟል፡፡ (ማር. 16*15፤ ዮሐ. 20*21) እግዚአብሔር ሰዎች የወንጌል ቃል ሰምተው ይድኑ ዘንድ
“ማንን ልላክ? ማንስ ይሄድልናል?” እያለ የጥሪውን ቃል ያሰማል፡፡ (ኢሳ. 6*8) ታዲያ ይህንን የተቀደሰ አገልግሎት ለመፈጸም
እኛም እንደ ኢሳያስ “እኔን ላከኝ እኔ እሄዳለሁ” በማለት ለትዕዛዙ ምላሽ መስጠት ይገባናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወደ
ሞት የሚሄዱትን ታደግ፣ ሊታረዱ የተወሰኑትንም አድን ብሎአልና፡፡ (ምሳሌ 24*11)
1.3.3 የክርስቶስ ፍቅር ግድ ስለሚለን

ማንኛውም በክርስቶስ በመሆን የሚገኘውን ሕይወት ታላቅነት የተረዳና በነፍሱም ይህንን እውነት የተለማመደ አማኝ ሁሉ
የክርስቶስ ልብ ስለሚኖረው ሰዎች ወደ ጌታ ወደ ኢየሱስ እንዲመጡ ከፍተኛ ፍቅር ያድርበታል፡፡ (2 ቆሮ. 5*14)፡፡ ሐዋርያው
ጳውሎስ ስለሰዎች መዳን የነበረውን ፍቅር ሲገልጽ “ብዙ ሐዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ
እውነትን እናገራለሁ፣ አልዋሽም ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል፡፡ በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ
በክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምኩ እንድሆን እጸልይ ነበር” ብሎአል፡፡ (ሮሜ 9*1-3) በዚህ ጥቅስ መሰረት ዘመዶቼ የሆኑት
አይሁዶች ከዘላለም ጥፋት ያመልጡ ዘንድ የእኔ ሕይወት እንደ ካሳ ሆኖ ቢጠፋና እነርሱ ቢድኑ እመርጣለሁ ማለቱ ነው፡፡
ወንጌልን ለማድረስ ያለው ሸክም በአይሁድ ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን ሲገልጽ፣ “ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩ፣ ለጥበበኞችና
ለማያስተውሉ ዕዳ አለብኝ” በማለት የፍቅር ባለ ዕዳነቱን አረጋግጧል፡፡ (ሮሜ 1*14) ለእኛም ይህ ባለ ዕዳነት ተሰምቶን
ከምንም ነገር ይልቅ ሰዎች ድነትን ማግኘት እንደሚገባቸው በማመን በዚህ ፍቅር መመስከር አለብን፡፡
1.3.4 ወንጌልን ላልሰሙት ለማድረስ ብቸኛ መንገድ ስለሆነ

18
ጌታ ኢየሱስም ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ ማድረግ የሚቻለው በእርሱ በኩል እንደሆነ ሲያረጋግጥ “እኔ መንገድና እውነት
ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” ብሏል፡፡ (ዮሐ. 14*6) ይህንን እውነት በማጽናት “እንድንበት ዘንድ
የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (ሐዋ. 4*12) በማለት ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያደርስ ሌላ
አማራጭ መንገድ እንደሌለ ገልጧል፡፡ ስለዚህ ይህንን ብቸኛ የድነት መንገድ ባንነግራቸው ሰዎች መልካም ስራ በመስራት፣
የሀይማኖት ስርዓትን በመፈጸም፣ መላዕክትንና ቅዱሳንን አማላጅ በመጥራት በዚህ አይነት ተግባር ድነትን እንደሚያገኙ
በመገመት በሐሰት ይታመናሉ፡፡ (ቆላ. 2*18-19) ስለሆነም ከዘላለም ሞት የመዳኛው መንገድ አንድ ብቻ ስለሆነ፣ አማኞች ሁሉ
ለጠፉት ሰዎች ይህንን እውነተኛ የጽድቅ መንገድ ልናሳያቸውና ልንመሰክርላቸው ይገባል፡፡ ሰዎች በራዕይ፣ በህልም በመሳሰሉት
መንገድ ጌታ እየተገለጠላቸው ወደ ዘላለም ሕይወት መምጣት ቢችሉም፤ ወንጌል መመስከር ግን በዋናነት የክርስቲያኖች
ኃላፊነት ነው፡፡ በምድር ላይ ይህንን ስራ የምትሰራ ብቸኛ ወኪል ባለ አደራ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ (1 ተሰ. 2*4)
1.3.5 ሽልማት ወይም ፍርድ ስለሚጠብቀን

የምስክርነት ሕይወት የመጨረሻ ግብ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው ያልተቀበሉ ሰዎች፣ ጌታን እንደ ግል
አዳኛቸው እንዲቀበሉና የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ነው፡፡ (ዮሐ. 3*16) ወንጌልን በሕይወታችንም ሆነ በንግግር (በመናገር)
ላልሰሙ ሰዎች ካልተናገርን እግዚአብሔር የሚጠፉትን ሰዎች ደም ከእኛ እጅ ይፈልጋል (ሌላው ቢቀር ዙሪያችን ላሉ ሰዎች
ኃላፊነት አለብን) ፡፡ (ሕዝ. 3*18-19፤ 1 ቆሮ. 9*16) ወንጌልን በሚገባ ከመሰከርን እና አገልግሎታችንን በተገቢው መንገድ
ከተወጣን ደግሞ የጽድቅ አክሊል (ሽልማት) እንቀበላለን፡፡ (ዳን. 12*3፤ 2 ጢሞ. 4*7-8)

ምዕራፍ ሁለት፡- የመስካሪው መልዕክት


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ወጥ የሆነና ሰው ሁሉ እንዲጠቀምበት የተሰጠ መመሪያ ባይኖርንም የመልዕክቱ ይዘት ግን ምን
መምሰል እንዳለበት ግን በግልጽ ተቀምጧል፡፡
2.1 ወንጌል

ወንጌል ማለት ኢንጌሊዮን ከሚለው የዐረማይክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም የምስራች ወይም መልካም ዜና ማለት ነው።

ይህም ዜና በመጀመሪያ ደረጃ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ስጋ ለብሶ ወደ አለም መምጣቱን የሚያበስር ነው። (ሉቃ.

2*10-11፤ ዮሐ. 1*14) በሁለተኛ ደረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ኃጢአት በመስቀል ላይ መከራን ተቀበለ፣ ሞተ፣ በሦስተኛው

ቀን ከሙታን ተነሳ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለላም ሕይወት ያገኛል የሚል ነው፡፡ (1 ቆሮ. 15*3-4) በሶስተኛ ደረጃ

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ዘላለማዊ ተስፋና ዕቅድ መፈፀሙን የሚያውጅ ነው። (ዕብ. 1*1-3) ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ

የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ (ሉቃ. 2*10-11)

2.2 የወንጌል ዋና መልእክት

የወንጌል ዋና መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። ወንጌል ስለ ክርስቶስ እና በእርሱም በኩል

ስለሚገኝ ድነት የሚያስተምር መልካም የምስራች ዜና ነው። የድኅነት (የድነት) ሥራ በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ

ተፈፅሟል፤ የአዋጁ ዋና መልዕክት ይህ የመስቀል ስራ ነው፡፡ (ሐዋ. 2*38፣ 5*30-31፣ 10*43፣ 13*38-39፤ ቆላ. 2*13-14)

19
የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ  የወንጌል ማዕከል ነው። (ሮሜ 1*1-4፤ 1 ቆሮ. 15*1-4) የተለያዩ ነገሮች ተሰብኮላቸው ወደ ቤተ
ክርስቲያን የመጡ ሰዎች ያን ነገር ሲያጡ ተመልሰው ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሳሉ፡፡ ስለዚህ የምስክርነታችን መልዕክት መሆን

ያለበት የመስቀሉ ቃልና የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ (1 ቆሮ. 1*22-23) ወንጌል በምንም አይነት መልኩ ስለ ቅድስት

ድንግል ማርያም፣ መላዕክት፣ ስለ ጻድቃን ሰማዕታት ወይንም ስለ ምድራዊ ነገር (ብልጽግና) አያስተምርም። ወንጌል ስለ

ክርስቶስ ገድል የሚናገር ዜና ነው።

2.3 ወንጌል የተጠራባቸው ስሞች

የእግዚአብሔር ወንጌል (2 ቆሮ. 11*7)፣ የመንግሥት ወንጌል (ማቴ. 4*23)፣ የዘላለም ወንጌል (ራዕይ 14*6)፣ የመዳን ወንጌል
(ኤፌ. 1*13)፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል (ማር. 1*1፤ ሐዋ. 11*20፤ ሮሜ 15*18-19፤ 2 ቆሮ. 4*4)፣ የሰላም ወንጌል (ኤፌ.
6*15)፣ የጸጋ ወንጌል (ሐዋ. 20*24)፣ ቅዱስ ወንጌል (ማር. 16*8)፣ የትንሳኤ ወንጌል (ሐዋ. 17*18)
2.4 የወንጌል ኃይልና ስልጣን

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 1*16 ላይ “በወንጌል አላፍርም አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው ለሚያምኑ ሁሉ
የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና” በማለት ወንጌል ኃጢአተኛውን የማዳን ኃይል እንዳለው ይናገራል፡፡ ስለዚህ ወንጌል ለሰው
ሁሉ መሰበክ አለበት፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ወንጌል ለተለያዩ ሰዎች ተሰብኮላቸዋል ለምሳሌ፡- ለአለቆች (ሐዋ. 18*8)፣ ለካህናት
(ሐዋ. 6*7)፣ ለአገር አስተዳዳሪዎች (ሐዋ. 13*8-12)፣ ለባለስልጣን (ሐዋ. 8*27-38)፣ ለነጋዴዎች (ሐዋ. 16*14)፣ ለዓሣ
አጥማጆች (ሉቃ. 5*10-11)፣ ለቀራጮች (ሉቃ. 5*27-28)፣ ለወታደሮች (ሐዋ. 16*27-33)፣ ለንጉሶች (አገር መሪዎች) (ሐዋ.
24*24-25)፣ ለሴቶች (ዮሐ. 4*7-30)፣ ለሐይማኖት መሪዎች (ዮሐ. 3*1-17)፣ ለሰዎች ሁሉ ይሰበካል፡፡ (1 ጢሞ. 2*4) ወንጌል
የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ በምኩራብ (ሐዋ. 9*20)፣ በወንዝ ዳር (ሐዋ. 16*13)፣ በእስር ቤት (ሐዋ. 16*31)፣ በገበያ ስፍራ
(ሐዋ. 17*17)፣ በቤት ውስጥ (ሐዋ. 20*20-21)፣ በቤተ መንግስት (ሐዋ. 24*24-25)፣ በመርከብ (ሐዋ. 27*1፣ 25)፣
በትምህርት ቤት (ሐዋ. 19*9)፣ በሁሉ ስፍራ በዓለም ዙሪያ (ሐዋ. 1*8) ይሰበካል፡፡

ምዕራፍ ሦስት፡- የመስካሪው ባሕርያት


ወንጌል የሚመሰክረው ሰው ኢየሱስ ያድናል በማለት ከመመስከሩ በፊት የሚከተሉት አበይት ባህሪያት ሊኖሩት ያስፈልጋል፡፡
መስካሪው እነዚህ ባህሪያት ከሌሉት ወንጌል መመስከርን እንደ ስራ (ግዴታ) እንጂ ስለሚጠፉ ነፍሳት ግድ ብሎት አያገለግልም፡፡
3.1 የክርስቶስ ልብ (አእምሮ) አለው

ሐዋርያው ጳውሎስ በ 1 ቆሮ. 2*16 ሲናገር “እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን” ይላል፡፡ ይህ የክርስቶስ ልብ ማለት ምን ማለት ነው
ስንል፤ ኢየሱስ የማያምኑ ሰዎችን ባየ ጊዜ የነበረው ዓይነት አመለካከት ማለት ነው፡፡ “…ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ እረኛ
እንደሌላቸው በጐች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው” (ማቴ. 9*35-38) ከነዚህ ሰዎች መካከል ኢየሱስን
የሚሳደቡና ሊወግሩትና ሊገሉት የሚፈልጉ ነበሩ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ይወዳቸውና ይራራላቸው ነበር፡፡ (ሉቃ. 4*28-29፤ ዮሐ.
5*16) የማያምኑ ሰዎችን (ወንጌልን የሚሳደቡ፣ ክርስቲያኖችን የሚጠሉ) ስንመለከት በክርስቶስ እይታ መመልከት አለብን፡፡
ሰዎች ያንን ሁሉ አመፅ የሚሰሩት የነፍሳቸውን እረኛ ኢየሱስን ስላላወቁ ነው፡፡ እረኛቸውን ቢያገኙ መልካም በጐች መሆን
ይችላሉ፡፡ (ዮሐ. 10*16፤ 1 ጴጥ. 2*25) ጳውሎስም ተመሳሳይ ልብ ነበረው፡፡ (ሮሜ 9*1-3፤ 10*1-3) የተሰጠንን አደራ
መወጣት የምንችለው ሰዎችን ሁሉ ክርስቶስ በሚመለከትበት ሁኔታ ማየት ስንችል ነው፡፡
20
3.2 በእግዚአብሔር ላይ ይደገፋል

ብዙ ክርስቲያኖች ለሌሎች እንዳይመሰክሩ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል ብዙ ጊዜ መስክሬ ማንም ወደ ኢየሱስ አልመጣም
የሚል ነው፡፡ ብዙ መስክረን የጌታን መልዕክት ስላልተቀበሉ መልዕክታችን ውድቅ ሆነ ማለት አይደለም የእኛ ስራ ዘር መዘራት
ነው፤ ዘሩን የሚያበቅለው እግዚአብሔር እንጂ የኛ ሁኔታ አይደለም፡፡ ማንንም እንድንለውጥና እንድናድን አልታዘዝንም፤
የታዘዝነው የምስራቹን ቃል እንድንነግር ነው መለወጥና ማዳን የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ (ሐዋ. 2*47፤ 13*32) ልዩነት ሳናደርግ
ለሁሉም ሰው መመስከር አለብን፤ ብዙ መስክረን በቀላሉ ፍሬ ባይገኝ ተስፋ መቁረጥ የለብንም መጽሐፍ ቅዱስ “ጌታም
ከእነርሱ ጋር ይሰራ ነበር” ስለሚል (ማር. 16*20) እንዲሁም ኢየሱስም “…እስከ ዓለም ፍጻሜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ.
28*20) ስላለን በእርሱ ተስፋ በመደገፍ አደራውን መወጣት አለብን፡፡
3.3 ሸክም አለው

በሐዋርያት ስራና በሌሎች ደብዳቤዎች እንደምንመለከተው ጳውሎስ በአይሁዶች ተሰድቧል፣ በበትር ሦስት ጊዜ ተመቷል፣
አንድ ሲጐድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ተገርፏል፣ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ተወግሯል (2 ቆሮ. 11*24-25) ይህን ሁሉ
አድርሰውበት እርሱ ግን “እነርሱ ከሚጠፉ እኔ ራሴ ከክርስቶስ ተለይቼ መጥፋትን እመርጣለሁ” ይላል፡፡ (ሮሜ 9*3) ለማያምኑ
ሰዎች እንደዚህ ያለ ፍቅርና ሸክም ካለን በብዙ ዋጋ ወንጌልን ለመመስከር እንችላለን፡፡ በወንጌል ስርጭት አገልግሎት ውጤታማ
የምንሆነው ለሚጠፉት ሰዎች እውነተኛ ሸክም እና ዕውቀት ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ (ሉቃ. 15*4፤ ያዕ. 5*20)
3.4 ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ ነው

በሐዋርያት ስራ 1*8 ላይ ያለው “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” የሚለው ቃል በተለይ “ምስክር” የሚለው ቃል ከግሪኩ “ማርቲሮስ”
ወይም በእንግሊዝኛ “ማርታይር” ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፤ ትርጉሙም “የደም ምስክር” ወይም “መስዋዕት”
ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲጠራቸው ስለ እርሱ ምስክር እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን እስከ ሞት ድረስ ዋጋ እንዲከፍሉ ነው፡፡ ዛሬም
የክርስቶስ ምስክር ለመሆን የሚፈልግ ሰው ለተመሳሳይ መስዋዕትነትና መከራ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡ (ማቴ. 5*11-12፤
ሐዋ. 7*54-60፤ 12*1-2፤ 2 ጢሞ. 1*8፤ ዕብ. 11*36-38፤ 1 ጴጥ. 4*14-16፤ ራዕይ 20*4)

ምዕራፍ አራት፡- የምስክርነት መንገዶች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ወጥ የሆነና ሰው ሁሉ እንዲጠቀምበት የተሰጠ አንድ ዓይነት የአመሰካከር ስልትና መመሪያ
የለም፡፡ ቢሆንም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በምስክርነታችን ጊዜ የሚሰጠን የተለያዩ የአመሰካከር ስልትና
መንገዶች አሉት፡፡
ጌታ ኢየሱስ ራሱ ደቀ መዛሙርቱን ለምስክርነት ሁለት ሁለት አድርጐ ሲልካቸው በምስክርነታቸው ጊዜ ይህንን ዘዴ ተጠቀሙ
አላላቸውም፡፡ ቢሆንም ምስክርነታቸውን እየሰጡ ሳለ በእነርሱ ውስጥ የነበረው መንፈስ ቅዱስ በተለያየ ዘዴዎች ሰዎችን ወደ
ድነት ያመጣ ነበር፡፡ የጌታ የኢየሱስን አመሰካከር ልብ አድርገን ስንመለከት የተለያየ የአመሰካከር ስልት ይጠቀም እንደነበር
መገንዘብ እንችላለን፡፡ (ሉቃ. 5*1-10፤ ዮሐ. 3*1-13፤ 4*7-26)
4.1 በቃል (በንግግር) መመስከር

21
ሰዎች ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ በመክፈል ክርስቶስ ኢየሱስ የሰው ልጆች ምትክ ሆኖ
መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን ማወጅ አለብን፡፡ (1 ቆሮ. 15*3-4፤ 1 ጴጥ. 3*18) በቃል (በንግግር) የምስክርነት
አገልግሎት በምናከናውንበት ጊዜ የተለያዩ ስልቶች መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ከእነዚህም ስልቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ለማንሳት
ያህል፡-

4.1.1 በመቀራረብ (ጓደኝነት) በመመስረት

በመቀራረብ ወይም ጓደኝነት በመመስረት ለሰዎች ወንጌልን መመስከር እንችላለን፡፡ ይህም የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም
ለምሳሌ በስራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት፣ በምንኖርበት አካባቢ ከሰዎች ጋር የተለያዩ ቀረቤታዎች በመፍጠር ሊከናወን የሚችል
የምስክርነት መንገድ ነው፡፡ (ሉቃ. 5*1-10፤ ሐዋ. 18*1-4፤ 28*30-31)
4.1.2 አንድ ለአንድ መመስከር

አንድ ለአንድ ማለት በአንድ ጊዜ ለአንድ ሰው መመስከር ማለት ነው፡፡ ይህ ዘዴ አጥጋቢ የሆነበት ምክንያት በማናቸውም ስፍራ
ቢሆን በዚህ ዘዴ በመጠቀም ወንጌልን መመስከር መቻላችን ነው፡፡ ማናቸውም ክርስቲያን ለጓደኛውም ሆነ በተለያየ አጋጣሚ
ለሚያገኘው ሰው መመስከር ይችላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ወይም ሰዎች በሚሰበሰቡበት በሌላ ስፍራ መመስክር ጥሩ ነው፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያንም ሆነ ሰዎች ወደሚሰበሰቡበት ሥፍራ መሄድ አይፈልጉም፡፡ ስለዚህ ወደዚያ ስፍራ
ሄዶ የሚመሰክርላቸው ሰው ይፈልጋሉ፡፡ ይህን ሁኔታ በተመለከተ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት
ያልነበራትንና ከሰዎች ተለይታ የነበረችውን አንዲት ሣምራዊት ሴት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቦ የመዳንን መንገድ እንዴት
እንደነገራት መመልከት እንችላለን፡፡ በተለይ በሆስፒታል እና በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡበት
ምንም መንገድ ስለሌለ ቤተ ክርስቲያን ወደ እነዚህ ሰዎች በመሄድ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት ወንጌል መመስከር
ትችላለች፡፡ (ማቴ. 8*14-15፤ ሉቃ. 19*5-10፤ ማር. 14*3፤ ዮሐ. 1*41-43፤ 3*1-11፤ ሐዋ. 8*26-39፤ 13*6-12)
4.1.3 የጀማ ስብከት

የጀማ ስብከት ማለት በአንድ ጊዜ በብዛት ለተሰበሰቡ ሰዎች ወንጌልን መመስከር ማለት ነው፡፡ ወደ ገበያም ሆነ ወደ አውቶቡስ
ጣቢያ ብንሄድ ክርስቶስን የማያውቁ (እንደ ግል አዳኛቸው ያልተቀበሉ) ብዙ ሰዎች እናገኛለን፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ይህንን መልካም
ዜና በአንድ ጊዜ ለሁሉም መመስከር እንችላለን፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሰዎችን በምኩራቦች፣
በመሰብሰሰቢያ ሥፍራዎች እንዲሁም በሌሎች አንድ ላይ ሆነው በሚከማቹበት ሥፍራ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ይመሰክር
ነበር፡፡ (ማቴ. 5*1-2፤ 13*1-2፤ ማር. 6*2፣56) ሐዋሪያትም የጀማ ስብከት ይጠቀሙ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- ጴጥሮስ (ሐዋ. 2*14-
41)፣ እስጢፋኖስ (ሐዋ. 6*8-15፣ 7*1-53)፣ ፊልጶስ (ሐዋ. 8*5-8)፣ ጳውሎስ (ሐዋ. 13*5፤ 18*19፤ 19*8-9፤ 28*23)
4.1.4 ቤት ለቤት

ቤት ለቤት የወንጌል ምስክርነት ማለት ትንንሽ የሰፈር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖች በማቋቋም በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናት ቡድኖች አማካኝነት ያላመኑ ሰዎችን በመጋበዝ ወንጌል ሰምተው እንዲድኑ ማድረግ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለምሳሌ
ማህበረሰቡ ያገለላቸው ሰዎች፣ ሙስሊሞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ሀብታሞች ወደ ቤተ ክርስቲያን በቶሎ ለመቀላቀል
ስለሚከብዳቸው እነዚህ የጥናት ቡድኖች ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጥሩ ስፍራ ናቸው፡፡ (ሉቃ. 7*36-39፤ 10*38-42፤ ሐዋ.
28*30-31፤ 1 ቆሮ. 16*19፤ ቆላ. 4*15፤ ፊልሞና 1*2)
4.1.5 ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ (ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ፣ ማህበራዊ ድህረ ገጽ)

22
ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የምስራቹን ቃል ለማስተላለፍ እጅግ ጠቃሚ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ሚዲያ በአጭር ጊዜ
በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ወንጌልን ለማድረስ እጅግ ጠቃሚ መንገድ ነው፡፡ ቤተ ክርስትያን ልትደርስባቸው እና የወንጌል
አገልጋዮች ሊገቡ የማይችሉበት ስፍራ ያሉ ሰዎችን በነዚህ ሚዲያ መድረስ እንችላለን፡፡ በተጨማሪም ሰው በቀላሉ ሊረዳው
በሚችል መንገድ ትራክቶችን ወይም መንፈሳዊ በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት በነፃ ማስራጨት አለብን፡፡
4.1.6 የበጎ አድራጎት አገልግሎት

ቤተ ክርስቲያን ከምታከናውናቸው በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎቶች በተጨማሪ የተለያዩ የበጐ አድራጎት ስራዎች መስራት
አለባት፡፡ ለምሳሌ ችግረኞችን በመጐብኘትና በመርዳት፣ እስረኞችን በመጠየቅ፣ በተለያየ ሆስፒታል የተኙትን ህሙማን
በመጠየቅ፣ ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመንከባከብ እንዲሁም አረጋዊያንን በመርዳት ጐን ለጐን የመንጌልን ስራ መስራት ይቻላል፡፡
(ሐዋ. 4*33-35፤ ሮሜ 12*13፤ ገላ. 2*10) የበጐ አድራጎት አገልግሎትን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ጉዳይ ቢኖር
ሰዎች ለርዳታ ብቻ ብለው ወንጌልን በግድ እንዲቀበሉ ማድረግ የለብንም ወይም በጥቅም መደለል የለብንም፡፡
4.2 በሕይወት (በኑሮ) መመስከር

ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድረገው የተቀበሉ አማኞች ሁሉ በምድራዊ ሕይወታቸው፣ በእምነታቸው እና በሌላው

ኖሮአቸው ሁሉ ለማያምኑ ሰዎች ምሳሌ መሆን እንደሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ (ማቴ. 5*13-16፤ 1 ጴጥ.

2*12) አማኞች ሌሎች ወደ ጌታ እንዲመጡ ምክንያት ልንሆናቸው እንደምንችል ሁሉ በጽድቅ የማንኖር ከሆነ ደግሞ ሰዎች

ወደ ጌታ እንዳይመጡ እንቅፋት እንሆናለን፡፡ በአንድ በኩል ወንጌል ይለውጣል ብለን እኛ ግን ሕይወታችን ካልተለወጠ

የምንስብከውን ወንጌል ማንም አይሰማንም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት
በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ..” ነበር ይላል፡፡ (ሉቃ. 24*19) ኢየሱስ በምስክርነት (በቃል) ብቻ ሳይሆን በሕይወትም ብርቱ ነበር፡፡
ስለዚህ መስካሪው ከንግግር ባለፈ በሕይወቱም ኢየሱስን ማሳየት አለበት፡፡ ማንም ሰው በቆሻሻ ብርጭቆ ንጹህ ውሃ ቢሰጠው
እንደማይጠጣ ሁሉ በኃጢአት በተበላሸ ሕይወት ንጹውን ወንጌል ብናቀርብ ማንም አይሰማንም፡፡ (1 ጢሞ. 4*16፤ 2 ጢሞ.
2*21)

ምዕራፍ አምስት፡- ስንመሰክር ልንገነዘባቸው የሚገቡ ነገሮች (መርሆች)

የወንጌል መልእክት ሁልጊዜም ተመሳሳይ ነው፤ ሊለወጥ አይችልም፡፡ ነገር ግን አቀራረባችንና አገላለጻችን እንደ ሁኔታው
ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ስንመሰክር ልንገነዘባቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
5.1 አቀራረብ

የምስክርነታችን ዋና ዓላማ የሚሰሙን (የምንመሰክራላቸው) ሰዎች ኃጢአተኝነታቸውን ተገንዝበው ንስሐ በመግባት ጌታን
በመቀበል ደህንነት እንዲያገኙ ነው፡፡ ስለሆነም የደህንነትን መልእክት ግልጽና ቀላል በሆነ መንገድ ማቅረብ መቻል አለብን፡፡

በወንጌል ምስክርነት ውስጥ የክርስቶስን ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር መናገር ዋናው ነጥብ ሲሆን፣ ይህንን የፍቅር ወንጌል አልቀበል

ላሉ ደግሞ ፍርድ እንዳለ ማሳሰብ የወንጌሉ ሌላኛው ትምህርት መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ኢየሱስ የተለያዩ ሰዎችን
ሲያነጋግር የተለያዩ ቀላል መንገዶችን ተጠቅሟል፡፡ ለምሳሌ ናትናኤልን የእውቀትን ቃል በመጠቀም ወደ ደህንነት አመጣው፡፡
(ዮሐ. 1*47-49) ኒቆዲሞስን ስለ ዳግም ልደት ያለውን ጥያቄ በመመለስ ወደ ደህንነት አመጣው፡፡ (ዮሐ. 3*1-11) ሳምራዊቷን

23
ሴት የአምልኮ ጥያቄዋን በመመለስ ወደ ደህንነት አመጣት፡፡ (ዮሐ. 4*9-42) ጳውሎስም ተመሳሳይ አቀራረብ ተከትሏል፡፡ (ሐዋ.
13*15-17፤ 17*2-3፣ 17*22-23) ሌላው ተጨማሪ ነገር ጥልና ክርክር ሊያመጣ በሚችል ነገር መጀመር የለብንም፡፡ (ምሳ.
15*1፤ 2 ጢሞ. 2*23-25) በመጨረሻ ማወቅ የሚገባን ትልቅ ነገር ቢኖር የምንመሰክራላቸው ሰዎች ሊረዱት የማይችሉትን
አከራካሪ እና ለመረዳት የሚስቸግሩ ስነ-መለኮታዊ አስተምህሮዎችንና ቃላትን መጠቀም የለብንም፡፡
5.2 ልማድ

የምንመሰክርላቸው ሰዎች የተለያዩ ክፉ ልማዶችና ሱሶች ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ ስለሆነም በምንመሰክርበት ጊዜ የሰዎችን
ልማድ መንቀፍ አይገባንም ምክንያቱም ብዙ የምንነቅፋቸው ከሆነ እንደዚያ ሆነው ወደ እኛ ሕብረት መቀላቀል ይከብዳቸዋል፡፡
ሰዎች አጉል የሆኑትን ሱሶች እና ልማዶች በክርስቶስ ኢየሱስ በሚያምኑበትና በቃሉና በመንፈሱ እየበረቱ ሲሄዱ እርግፍ
አድርገው እንደሚተውት ተረድተን፤ ልማዳቸውን በምንመሰክርበት ጊዜ መንካት፣ መንቀፍ፣ ማንቋሸሽ በፍጹም የለብንም፡፡
እንዲሁም የሚያደርጉት ክፉ ተግባር ትክከል እንደሆነ እንዲያስቡም ማድረግ የለብንም፡፡ ከነድካማቸው (ሸክማቸው) ወደ
ኢየሱስ እንዲመጡ መጋበዝ አለብን፡፡ (ማቴ. 11*28)
5.3 ባሕል

ባሕል ማለት ሰዎች አንድን ነገር የሚያደርጉበት መንገድ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ እኛ በጊታር እና በኪቦርድ አምላካችንን
እናመልካልን ሌላው ደግሞ በከበሮ እና በጽናጽል አምላካቸውን ያመልካሉ፡፡ ሰዎች የተለያየ ባሕል አላቸው፤ ስለሆነም
በምንመሰክርበት ጊዜ የሰዎችን ባሕል መንካት፣ መንቀፍ፣ ባሕላቸውን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ነገር መናገር የለብንም፡፡ እኛ
የተጠራነው የኛን ባሕል ሰዎች ላይ ለመጫን ሳይሆን ወንጌልን ለመመስከር ነው፡፡ ወንጌል ባሕልን ሁሉ የሚያልፍ ስለሆነ
በምንመሰክርላቸው ወንጌል ሲለወጡ፤ ከክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ጋር አብሮ የማይሄደውን፤ ለእግዚአብሔር ክብር
የማይሆነውን ባሕል ራሳቸው ሊተውት ይችላሉ፡፡ (ራዕይ 7*9)
5.4 ኃይማኖት

የምንመሰክርላቸው ሰዎች በኃይማኖት ወደ ድነት እንደማይደርሱ ብናውቅም ኃይማኖታቸውን ልንነቅፍባቸው አይገባም፡፡


የአንድን ሰው ኃይማኖት እኛ ባናምንበትም የመንቀፍ ወይም የማጥላላት ሁኔታ ካሳየን፤ ቀጥሎ የምንነግራቸውን ወንጌል
አይሰሙንም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ወደ ኃይማኖት ክርክር ውስጥ እንገባና የምስክርነታችን ዓላማ አቅጣጫውን ይስታል፤ ወደ
አላስፈላጊ ግጭት ውስጥም ሊከተን ይችላል፡፡ በእነርሱ ኃይማኖት ውስጥ ያለውን አንድ መልካም ነገር ይዘን የጎደላቸውን
ክርስቶስ ማሳየት እንችላለን፡፡ (ሐዋ. 17*16-34)
5.5 አውዳዊነት (Contextualization)

አውዳዊነት ማለት የማይለወጠውን (የማይቀየረውን) የወንጌል እውነት ሳይሸቃቅጡና ሳያመቻምቹ ለተለያየ የሰው ባሕልና
አውድ እንዲመች አድርጐ ማቅረብ ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አውዳዊነት በግልጽ ያስተምራል ለምሳሌ ኢየሱስ
ከሰማይ ሆኖ የእግዚአብሔርን ፍቅር አልሰበከም ወደ ምድር በመምጣት እኛን መስሎ እኛ ልንረዳው በምንችለው መጠን ሰው
ሆኖ መጣ፡፡ (ፊሊጵ. 2*6-8) ሌላው የሐዋርያው ጳውሎስ ምሳሌነት ብንመለከት በ 1 ቆሮ. 9*19-23 እንደገለጸው በሁሉ
መንገድ አንዳንዶችን ያድን ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁድ ሆነ፣ ከአሕዛብ ጋር እንደ አህዛብ ሆነ፣ ከደካማው ጋር እንደ ደካማ
ሆኖ ይህን ሁሉ ያደረገው ሰዎችን ለማዳን ስለ ወንጌል ሁሉን አደረገ፡፡ እኛም ወንጌልን ለምንመሰክርላቸው ሰዎች
በኃጢአታቸው ሳንሳተፍ በእነሱ ባህል ውስጥ ወንጌልን ማስተላለፍ እንችላለን፡፡ በሁሉም ባህል፣ ቋንቋ እና ኃይማኖት ኢየሱስን

24
እንዲከተሉ እንድንጋብዛቸው በእግዚአብሔር ተልከናል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ወደ ጌታ የሚመጡ ሰዎች የግድ እኛን መምሰል
የለባቸውም፤ በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 15 የኢየሩሳሌም ጉባዔ ጉዳይ ይህ ነው አሕዛብ የሆኑ ሰዎች ጌታን ለመከተል የግድ
አይሁድ መሆን አይጠበቅባቸውም በራሳቸው ቋንቋና ባህል (አሕዛብ ሆነው) ኢየሱስን መከተል ይችላሉ፡፡ ሰዎች ጌታን
ተቀብለው በራሳቸው ባሕል፣ ቋንቋና አውድ ጌታን መከተልና ማምለክ ይችላሉ የግድ ስታገለግል ሱፍ ልበስ፣ አዳራሽ ስራ፣
በኪቦርድ ብቻ አምልክ፣ እኛን ምሰሉ ሊባሉ አይገባም፡፡ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ቃል ኃጢአት የሆነውን ድርጊት ማስወገድ
አለባቸው፡፡

ምዕራፍ ስድስት፡- የምስክርነት እንቅፋቶች

የተለያዩ የምስክርነት እንቅፋቶች መኖራቸው የታወቀ ቢሆንም በዚህ ትምህርት ውስጥ የተወሰኑትን ለማየት እንሞክራለን፡፡
6.1 ቸልተኝነት

የተጠራንበትን የምስክርነት ሕይወት በሚገባና በተገቢው አኳኋን እንዳንወጣ የሚያደርገን አንዱ ምክንያት ቸልተኝነት ነው፡፡
በቸልተኝነት የእግዚአብሔርን ስራ መስራት ርግማን እንደሚያመጣ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል፡፡ (ኤር. 48*10)
የምስክርነት ሕይወት (መመስከር) እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው ዋናው ነገር ስለሆነ ይህንን ተግባር በትጋት ልናከናውን
ይገባል፡፡ (ቆላ. 3*23-24)
6.2 የእውቀት ማነስ

መጽሐፍ ቅዱስን አለማንበብና የቃሉ እውቀት ማነስ መመስከር እንዳንችል ያደርገናል፡፡ የኢየሱሰ ክርስቶስን የማዳን ወንጌል
ላልደኑ ሰዎች ለመመስከር በክርስቶስ ውስጥ መኖር፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ መኖር አለበት፡፡ (ዮሐ. 15*4፤ ቆላ. 3*16)
የምስክርነት ሕይወት እንዲኖረን፤ ብዙ ፍሬ እንድናፈራ በእግዚአብሔር ቃል ልናድግ ያስፈልጋል ምክንያቱም ለሰዎች
የምንመሰክረው ቃሉን ስለሆነ፡፡ (ሐዋ. 8*4፤ 10*44፤ 14*25)
6.3 የጠላት ተግዳሮት

የምስክርነት ሕይወት ከፍተኛ የጠላት ተግዳሮት ከሚያስነሱ አገልግሎቶች ዋነኛውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ (ማር. 4*14-15፤ 1 ተሰ.
2*18) የጠላት ተግዳሮት በየዘመኑ ሁሉ በወንጌል ስራ ላይ ከፍተኛ ችግርና ስደት እንዳስነሳ መጽሐፍ ቅዱሳችን በሚገባ
ያስገነዝበናል፡፡ (ሐዋ. 8*1፤ 16*19-24) በዚህ ሁሉ ስደትና መከራ ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እያሸነፈና ብዙዎችን
ለእግዚአብሔር መንግስት እንደማረከ እናያለን፡፡ (ሐዋ. 4*1-4) ስለሆነም በጠላት ስልት ሁሉ ላይ በመንቃት የተጠራንበትን
የምስክርነት ሕይወት ተግባራዊ ማድረግ አለብን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የተጠራነው ለመመስከር ስለሆነ፡፡ (1 ጴጥ. 2*9)

6.4 ፍርሃት

ብዙ ክርስቲያኖች ለሌሎች እንዳይመሰክሩ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ፍርሃት ነው፡፡ ስለዚህ ታላቅ እውነት ነግሬው ባይቀበለኝ
ወይም ወንጌል ስመሰክር ጓደኝነታችን ይበላሽ ይሆን፣ ስራዬን አጣ ይሆን፣ ወይም ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን የሚል ፍራቻ ነው፡፡
ኢየሱስ ሲናገር “በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላዕክት ፊት ይመሰክርለታል፤ በሰውም

25
ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላዕክት ፊት ይካዳል” በማለት ተናግሯል፡፡ (ሉቃ. 12*8-9) ስለዚህ ሳንፈራ ምስክርነታችንን
መወጣት አለብን፡፡

6.5 የአማኞች የሕይወት ጥራት (የቅድስና ጉድለት)


ብዙ ክርስቲያኖች ለሌሎች እንዳይመሰክሩ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ የሕይወት ጥራት ጉድለት ነው፡፡ ክርስቶስን የማያውቁ
ሰዎች የሚሰሩትን ኃጢአት እኛም የምናደርገው ከሆነ ለእነርሱ ደፍረን የጽድቅን ወንጌል መናገር አንችልም፡፡ በቅድስና ሕይወት
የማንኖር ከሆነ ለወንጌል እንቅፋት እንሆናለን፡፡ (1 ቆሮ. 15*34)

ምዕራፍ ሰባት፡- የምስክርነት ሕይወት ቁልፍ ነገሮች

ለምስክርነት የሚያስፈልጉ ብዙ ቁልፍ ነገሮች ቢኖሩም ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
7.1 የመንፈስ ቅዱስ ኃይል

የምስክርነት ሕይወት የሁለትዮሽ ተግባር ነው፡፡ የመስካሪው ኃላፊነት አለ የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ አለ፡፡ እግዚአብሔር ከሰጠን
ኃይል በቀር ወንጌልን ለመስበክ ማንም ብቁ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “… እናንተ ግን ከላይ ኃይል
እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ያላቸው፡፡ (ሉቃ. 24*49) የጴጥሮስን ሕይወትና አገልግሎት ስንመለከት በአንዲት
የቤት ሰራተኛ ፊት ሦስት ጊዜ የካደውን ኢየሱስ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተቀበለ በኋላ በብዙ ሺ ሕዝብ መሀል ቆሞ ስለ
ኢየሱስ በድፍረት መሰከረ፡፡ (ሐዋ. 2*1-40) መንፈስ ቅዱስ በምስክርነት ሕይወት ውስጥ የሚከተሉትን ስራ ይሰራል፡-
 ላላመኑ ሰዎች ፍቅር እንዲኖረን ሸክም ይሰጠናል፡፡ (ሮሜ 9*1-2)
 ስንመሰክር የጊዜውን ቃልና ድፍረት ይሰጠናል፡፡ (ማቴ. 10*19-20፤ ሐዋ. 4*8፤ 6*10)
 ወደ ትክክለኛ ሰዎች እንድንሄድ መለኮታዊ ምሪት ይሰጠናል፡፡ (ሐዋ. 8*29፤ 11*12፤ 13*4)
 ሰዎችን ስለ ኃጢአት ይወቅሳል፡፡ (ዮሐ. 16*8)
 የሰዎችን ልብ በመንካት ስለ ኢየሱስ እውነትን ይገልጻል፡፡ (ሐዋ. 2*37)
 ልዩ ልዩ ስጦታን በመስጠት ወንጌሉን በድንቅና በተአምራት ያጸናል፡፡ (ሐዋ. 10*38፤ ማር. 16*20፤ ዕብ. 2*4)
7.2 ፀሎት

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ዓለም ሁሉ በክፋትና በዲያቢሎስ እንደተያዘ ይናገራል፡፡ (1 ዮሐ. 5*19) “… ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን
ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያ ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል” (ማቴ. 12*29)
እንደሚል ትጋት የተሞላበት የምልጃ ፀሎት ለምስክርነት ሕይወት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ መስካሪው የሚጸልይ፣ የሚጾምና
የሚማልድ ሰው መሆን አለበት፡፡ ያልዳኑ ሰዎች ልባቸውን ዲያቢሎስ ስላሳወረው እግዚአብሔር ይህንን መጋረጃ ከልባቸው ላይ
ካላነሳው የወንጌልን መልዕክት መረዳት አይችሉም፤ ስለዚህ ጸሎት ቁልፍ ነገር ነው፡፡ (2 ቆሮ. 4*4፤ ኤፌ. 6*18-19፤ 2 ጢሞ.
2*25-26) በምንመሰክርበት ጊዜ ማስተዋል ያለብን ነገር መንፈሳዊ ጦርነት እንዳለ ነው፤ ይህንንም የምናሸንፈው በጸሎት ነው፡፡
ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ፈውስን፣ አጋንንት ማውጣትንና ወንጌል መስበክን በተያያዘ ሁኔታ ነው
የሚያቀርባቸው ስለዚህ የሀይል አገልግሎት ለወንጌል ስርጭት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ (ማቴ. 4*23፤ ማር. 1*39፤ ሐዋ. 8*5-7፤
19*8-12)

26
7.3 የእግዚአብሔር ቃል

መጽሐፍ ቅዱስ የመልዕክታችን ምንጭና መሰረት ነው፡፡ ስለሆነም የምንመሰክረው ጌታ ኢየሱስ ያስተላለፈውን መልዕክት
ነው፤ ዛሬ ብዙ አማኞች ከመስቀሉ ቃል ፈቀቅ ብለው ዓለም ሊሰማውና ሊያደምጥ የሚፈልገውን ሰው ሰራሽ ትምህርት
እያስተማሩ ነፍሳትን ወደ ደህንነት ከመምራት ይልቅ ወደ ጥፋት እየመሩ ነው፡፡ (2 ጢሞ. 4*3-4) ሰው ተቀበለውም
አልተቀበለውን ቃሉን መስበክ አለብን፡፡ ሰውን ከኃጢአት እስራት የሚፈታ ቃሉ ስለሆነ፡፡ (ሐዋ. 2*41፤ 4*4፤ 8*4፤ 14*25)
ስለሆነም ምንም እንኳን ሰዎች መልዕክታችንን ለማድመጥ የማይፈልጉ ቢሆንም መልዕክታችን በቃሉ ላይ የተመሰረተና
በክርስቶስ የመስቀል ስራ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፡፡ (2 ጢሞ. 4*2) እኛም እንደ መስካሪ የእግዚአብሔርን ቃል መሞላት
አለብን፡፡ (ቆላ. 3*16) ለሚጠይቁን ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጀን መሆን አለብን፡፡ (1 ጴጥ. 3*15)
7.4 አንድነት

ክርስቶስ የተለያየ ቤተ ክርስቲያን የሉትም ያለው አንድ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ የምንሰራው ለአንድ መንግስት ስለሆነ
በፍቅርና በአንድነት መስራት አለብን፡፡ የምስክርነታችን ዓላማ ያልዳኑ ሰዎችን ወደ ጌታ ማምጣት እንጂ ከአንዱ ቤተ ክርስቲያን

ወደ ሌላው ቤተ ክርስቲያን ሰዎችን ማፍለስ ላይ መሆን የለበትም፡፡ ሐዋሪያት በአንድ ልብ እና አሳብ ሆነው ነበር ወንጌልን

የሚመሰክሩት፡፡ (ሐዋ. 2*43-47፣ 4*32) በአንድ ልብ ሆነው ይጸልዩ ነበር፡፡ (ሐዋ. 1*14፤ 24-25፤ 2*42) በመአከላቸው ችግር

ሲፈጠር በሕብረት ተያይዘው ይጸልዩ ነበር፡፡ (ሐዋ. 12*1-17) ለወንጌል አገልግሎት ገንዘብ በጋራ በማዋጣት ይልኩ ነበር፡፡

(ፊልጵ. 4*10-17፤ ዕብ. 10*34) የስህተት ትምህርት ሲመጣ በአንድ ልብ ያወግዙ ነበር፡፡ (ሐዋ. 15) ወንጌል ከምንም ነገር በላይ

አንድነት ይፈልጋል፡፡ (1 ቆሮ. 1*10፤ ፊልጵ. 4*2) ኢየሱስም የምድር አገልግሎቱን ከጨረሰ በኃላ ለደቀመዛሙርቱ የጸልየላቸው

እና ይናፍቅላቸው የነበረ አንድነትን ነበር፡፡ (ዮሐ. 17*20-23)

27
ምዕራፍ ስምንት፡- ተግባራዊ ተዛምዶ
 የወንጌል ጉዳይ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለ፣ የነበርና አሁን ደግም ለቤተክርስቲያን የተሰጠ አደራ ነው። ሆኖም ይህ

ወንጌል በአንድ ልብ፣ እጅ ለጅ ተያይዘን የምንወጣው ታላቅ አደራ እንጂ ጥሪው ለተወሰኑ ወገኖች (ማለትም

ለወንጌላዊያን ወይም በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ለተሰማሩ) ብቻ ሳይሆን ለአማኝ ሁሉ የተሰጠ ነው። ሐዋሪያው

ጴጥሮስ ይህንን እውነት ሲያሰምር “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁ የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ

የተመረጠ ትውልድ … ናችሁ” (1 ጴጥ. 2*9) ስለዚህ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት መመስከር የወንጌላዊ ወይም
የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ምዕመን ኃላፊነት መሆኑን አውቀን ከአካባቢያችን አንስተን
ላልዳኑ ሁሉ ወንጌል ለመመስከር እንነሳ፡፡

 በዚህ ዘመን ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዳይመጡ ትልቅ እንቅፋት የሆነ ነገር ቢኖር አማኞች በሰውና በእግዚአብሔር ፊት
በጐ በማድረግ የክርስቶስን ምሳሌነት በመከተል በኑሮአችን፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ምሳሌ የሚሆን

ሕይወት ባለመኖራችን ነው፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን በግል ሕይወቱም ሆነ በማሕበራዊ ኑሮ የሚንኖረው ሕይወት

በወንጌል ስርጭት ላይ ታላቅ ተጽዕኖ ያመጣል። ወንጌልን ለሌሎችም ስንመሰክር እርስ በእርስ የምንያያዝበት እና

ለአንድ አላማ የምንቆምበት አንደኛው መንገድ ሕይወታችንን እንደ ወንጌሉ ቃል በማስተካከል ነው። በአንድ በኩል

ወንጌል ይለውጣል ብለን እኛ ግን ሕይወታችን ካልተለወጠ የምንስብከውን ወንጌል ማንም አይሰማንም። በሌላ በኩል

ወንጌላዊው በወንጌል ስርጭቱ፣ ሰባኪው በስብከቱ፣ አስተማሪውም በአስተምህሮቱ ያስተላለፉትን እውነት እኛ ደግሞ

በሕይወታችን ኖረን በማሳየት በአንድ ልብ ከሰራን ወንጌል በሚገባ ይሮጣል። ሆኖም ግን አንዱ ያስተማረውን፣ እኛ

ደግሞ በሕይወታችን ካፈረስነው የመያያዝ እና የልብ አንድነት ጎድሏል ማለት ነው። ስለዚህ ከንግግራችን ጐን ለጐን
ለሕይወታችን ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡
 ወንጌል ስለ ክርስቶስ እና በእርሱም በኩል ስለሚገኝ ድነት የሚያስተምር መልካም የምስራች ዜና ነው። ወንጌል

በምንም አይነት መልኩ ስለ መላዕክት፣ ስለ ጻድቃን ሰማዕታት ወይንም ስለ ምድራዊ ነገር (ብልጽግና) አያስተምርም።

ወንጌል ስለ ክርስቶስ ገድል የሚናገር ዜና ነው። በኃጢአት የጠፋውን ሰው ለመፈለግ ሲል ክብሩን ሁሉ ትቶ ከሰማይ

መውረዱን፣ እንደሰው ስጋ ለብሶ ስለ ኃጢአታችን መሞትና መቀበሩን፣ ሞትን አሸንፎ በትንሳኤ መነሳቱን፣ ዛሬ ሰለ

ሰው ይታይ ዘንድ በአብ ዘንድ መቀመጡን ወደፊት ደግሞ የሚያምኑበትን ለመሰብሰብ እንዲሁም በአለም እና

በሰይጣን ላይ ለመፍረድ ዳግም የሚመጣ መሆኑን የሚያወሳ መልካም የምስራች ዜና ነው። እኛም ስንመሰክር

የምንናገርው እውነት ይህንን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ይገባል። ሌላው ወንጌል ላላመኑ ስንመሰክር የሰዎችን ልማድ፣
ባሕል፣ ኃይማኖት ሳንነካ አውዳዊነት በጠበቀ ሁኔታ ወንጌል ማቅረብ አለብን፡፡ ይህ ሲባል ግን የወንጌልን እውነት
በማመቻመች ከኃጢአት ጋር ተስማምተን መኖር የለብንም፡፡ ከወንጌል እውነት ጋር በሚጋጭ ሁኔታ በፍጹም
ከኃጢአት ጋር መተባበር የለብንም፡፡

የምስክርነት ሕይወት (ወንጌል ስርጭት) የክለሳ ጥያቄዎች

28
እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– ምስክርነት (ወንጌል ስርጭት) በአንደበት ብቻ የሚነገር አገልግሎት መልዕክት ነው፡፡


2. –––––– በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው የወንጌል ሰባኪ አብርሃም ነው፡፡
3. –––––– ወንጌልን በሚገባ ከመሰከርን እና አገልግሎታችንን በተገቢው መንገድ ከተወጣን የጽድቅ አክሊል (ሽልማት)
እንቀበላለን፡፡
4. –––––– ኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን ሲጠራቸው ስለ እርሱ ምስክር እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን እስከ ሞት ድረስ ዋጋ
እንዲከፍሉ ነው፡፡ ዛሬም የክርስቶስ ምስክር ለመሆን የሚፈልግ ሰው ለተመሳሳይ መስዋዕትነትና መከራ የተዘጋጀ መሆን
አለበት፡፡
5. –––––– የምስክርነት ሕይወት የሁለትዮሽ ተግባር ነው፡፡ የመስካሪው ኃላፊነት አለ የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ አለ፡፡

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ
6. የምስራች ወይም መልካም ዜና ሀ/ መስዋዕት
7. በአንድ ጊዜ በብዛት ለተሰበሰቡ ሰዎች ወንጌልን መመስከር ለ/ እግዚአብሔር
8. የመጀመሪያው የወንጌል ሰባኪ ሐ/ አብርሃም
9. “ማርቲሮስ” “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” መ/ ወንጌል
10. ታላቁ ተልዕኮ ሠ/ የጀማ ስብከት
ረ/ ማር. 16*16
ሰ/ ማቴ. 28*18-20

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. የምስክርነት ሕይወት (የወንጌል ስርጭት) ዓላማ ምንድን ነው?


ሀ/ ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው የእግዚአብሔር ክብር ጐድሎታል፡፡
ለ/ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ ሊድን (ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ) አይችልም፡፡
ሐ/ ሰው ዳግመኛ ለመወለድ ወንጌል መስማት አለበት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

12. በቃል (በንግግር) የምስክርነት አገልግሎት በምናከናውንበት ጊዜ ከምንጠቀምበት መንገድ ትክክለኛው የቱ ነው?
ሀ/ ኤሌክትሮኒክስ (ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ፣ ማህበራዊ ድህረ ገጽ)፡፡
ለ/ በመቀራረብ (ጓደኝነት) በመመስረት፡፡
ሐ/ አንድ ለአንድ መመስከር፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
13. ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው?
29
ሀ/ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ስጋ ለብሶ ወደ አለም መምጣቱን የሚያበስር ነው።
ለ/ ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀበለ፣ ሞተ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለላም ሕይወት ያገኛል
የሚል ነው፡፡
ሐ/ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ዘላለማዊ ተስፋና ዕቅድ መፈፀሙን የሚያውጅ ነው።
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
14. ከመስካሪው ባሕርያት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የክርስቶስ ልብ (አእምሮ) አለው፡፡

ለ/ ሸክም አለው፡፡

ሐ/ ብዙ ዓመት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቆየ መሆን አለበት፡፡

መ/ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ ነው፡፡


15. መመስከር ያስፈለገው ለምንድን ነው?
ሀ/ የጌታ ትዕዛዝ ስለሆነ፡፡
ለ/ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ስለሚለን፡፡
ሐ/ ወንጌልን ላልሰሙት ለማድረስ ብቸኛ መንገድ ስለሆነ፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
16. የማይለወጠውን (የማይቀየረውን) የወንጌል እውነት ሳይሸቃቅጡና ሳያመቻምቹ ለተለያየ የሰው ባሕልና ወግ
እንዲመች አድርጐ ማቅረብ ምን ይባላል?
ሀ/ አውዳዊነት (Contextualization)፡፡
ለ/ ልማድ፡፡
ሐ/ ባሕል፡፡
መ/ ሃይማኖት፡፡
17. ወንጌል ከተጠራባቸው ስሞች መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የእግዚአብሔር ወንጌል፡፡
ለ/ የቤተ ክርስቲያን ወንጌል፡፡
ሐ/ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፡፡
መ/ የመንግሥት ወንጌል፡፡

18. የወንጌል ዋና መልዕክት ምንድን ነው?


ሀ/ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው።

ለ/ ስለ ክርስቶስ እና በእርሱም በኩል ስለሚገኝ ድነት የሚያስተምር መልካም የምስራች ዜና ነው።

ሐ/ የድነት ሥራ በኢየሱስ በመስቀል ላይ ተፈፅሟል፤ የአዋጁ ዋና መልዕክት ይህ የመስቀል ስራ ነው፡፡


መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ


30
19. ለምስክርነት ሕይወት የሚያስፈልጉ ብዙ ቁልፍ ነገሮች ቢኖሩም ከነዚህ ውስጥ ሶስቱን በማብራረት ግለጹ?

20. የተለያዩ የምስክርነት እንቅፋቶች መኖራቸው የታወቀ ቢሆንም ከነዚህ መካከል ሶስቱን በማብራረት ግለጹ?

ትምህርት ሦስት፡- የዘመናችን የስህተት ትምህርቶችና ልምምዶች

ምዕራፍ አንድ፡- መግቢያ

የዚህ ትምህርት ዋና ዓላማ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚህ ትምህርት ሰለባ የሆኑትን ክርስቲያኖች ወደ ትክክለኛው መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትምህርት እንዲመለሱ እና ክርስቲያኖችም ከዚህ የስህተት ትምህርት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማሳሳብ ነው፡፡

1.1 የስህተት ትምህርትን መቃወም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ

መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውንም ትምህርቶችንና ልምምዶችን መርምረን እንድንቀበል ያዘናል፡፡ (ሐዋ. 17*10-11፤ 1 ዮሐ. 4*1፤
1 ተሰ. 5*20-21) መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስተምረን ጻድቁና እንከን የሌለበት አምላካችን እግዚአብሔር በትንቢተ ኢሳያስ 1*18
ላይ “ኑና እንዋቀስ” በማለት እስራኤልን ሲጣራ እንመለከታለን፡፡ ልውቀሳቹሁ ከማለት ይልቅ እንዋቀስ ማለቱ በድያችሁም
ከሆነ መረጃችሁን አቅርቡና እንነጋገር ማለቱ ነው፡፡ በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ሐዋሪያ ጳውሎስም በተመሳሳይ
ሁኔታ አገልግሎታቸውንና ሕይወታቸውን ሲያስፈትሹ እንመለከታለን፡፡ (ዮሐ. 8*46፤ ገላ. 2*1-2)

የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እውነትን በግልጥ ከመናገር ባሻገር አብላጫው ምንባባት የሐሰት ትምህርትን በመቃወምና በመሔስ
የተጻፉ ናቸው፡፡ ከአዲስ ኪዳን ሃያ ሰባቱ ቅዱሳት መጻሕፍት ሃያ አምስቱ በግልጽ ከሐሰት ትምህርት መጠንቀቅ እንዳለብን
ያሳያሉ፡፡ (ማቴ. 7*15፤ ሉቃ. 21*8፤ ሐዋ. 20*28-30፤ ሮሜ 16*17፤ 2 ቆሮ. 11*3-4፤ ገላ. 1*6-9፤ ፊልጵ. 3*2፤ ቆላ. 2*8፤
ዕብ. 3*12፤ 2 ጴጥ. 3*17፤ 1 ዮሐ. 2*22-26፤ 4*1-3፤ 2 ዮሐ.1*7፤ ይሁዳ 1*17፤ ራዕይ 2*2)

የማንኛውም አገልጋይ ትምህርት፣ ሕይወትና ልምምድ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጠው ከመጽሐፍ ቅዱስ (ከክርስቶስ፣ ከሐዋርያትና
ነቢያት) ትምህርት ጋር ተነጻጽሮ ትክክለኛ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ (ዘዳ. 13*1-3፤ 2 ጴጥ. 3*1-2፤ 1 ዮሐ. 4*1-2፤ ይሁዳ 1*17)
በመጽሐፍ ቅዱስ ከፈተሽን በኋላ ደግሞ ትክክለኛውን ትምህርት ትክክለኛ ሐሰተኛውን ደግሞ ሐሰተኛ ማለት እንዳለብን
የእግዚአብሔር ቃል ያዘናል፡፡ (2 ቆሮ. 4*2፤ ገላ. 2*11-14፤ ኤፌ. 5*11፤ 1 ተሰ. 5*19-22) ከዚህ በተጨማሪም በእግዚአብሔር
ቃል ከመዘንን በኋላ በአስተምህሮ እና በልምምድ ስተው የተገኙትን ሰዎች ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ጊዜ ሰጥተን በፍቅር
ልናቀና፣ ልንመክር፣ ኑፋቄ መሆኑን ልናመለክት፣ እንዲመለሱ መንገድ ልናሳያቸው፣ ልናስመክራቸው፣ ልንጸልይላቸው…መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ዕድሉን ሁሉ በመጠቀም እንዲመለሱ የተገባውን ጥረት ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ (ማቴ. 18*15-18፤ ገላ. 6*1፤ ቲቶ
3*10-11) ከስህተት መንገዳቸው አንመለስም ያሉትን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ በማቆም ሲያስፈልግ ስማቸው
31
በመጥቀስ ማውገዝ እንደሚያስፈልግ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል፡፡ (ሮሜ 16*17፤ 1 ቆሮ. 5*9-13፤ 1 ጢሞ. 1*20፤
2 ጢሞ. 4*14፤ 3 ዮሐ. 1*9)

ከዚህ ባሻገር ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ የተነሱባትን የኑፋቄ ትምህርቶች ታላላቅ ዓለም አቀፍ ጉባዔያትን እንደ ጉባዔ ኒቂያ፤
ቁስጥንጥንያ፣ ኤፌሶንና ሌሎችንም በመጥራት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መዝና ትቃወም፤ አልመለስ ያሉትንም አውግዛ
ከመካከሏ ትለይ (ለሰይጣን አሳልፋ ትሰጥ) እንደ ነበር ታሪክ ምስክራችን ነው፡፡ (1 ቆሮ. 5*5) በእውነት ላይ ሲጨመር ወይም
ከእውነት ላይ ሲቀነስ በዝምታ ማየት መንፈሳዊ ጤናማነትን አያሳይም፡፡ (2 ቆሮ. 13*8)

1.2 ልዩ ወንጌል

“ሌላ ወንጌል” ወይም “ልዩ ወንጌል” በክርስቶስ አማኞች መካከል ሠርጎ እየገባ ላለ የሐሰት ትምህርት የተሰጠ ጥቅል (የወል) ስም
ነው፡፡ የስያሜው መነሾ የተገኘው ከገላቲያ 1*6-8 እና 2 ቆሮ. 11*4 ነው፡፡ የዘመናችን የስህተት ትምህርት የተለያየ ስያሜ
ቢኖረውም ለምሳሌ የእምነት እንቅስቃሴ፣ የብልጽግና ወንጌል የመሳሰሉት ለዚህ ትምህርት ግን ልዩ ወንጌል በሚለው ስያሜ
እንጠቀማለን፡፡

1.3 የሐሰት ትምህርት ምንጭና መንገዱ

ልዩ ወንጌል ጥመት እና ተመሳስሎ የተሰራ ነው ስንል ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፡፡ መበረዙ የሚከናወነው ራሳቸውን ክርስቲያን
ብለው በሚቆጥሩ በመካከላችን ባሉ ሰዎች መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ሐሰት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሲሆን የማታለል
አቅሙ ይቀንሳል፡፡ ከልዩ ወንጌል ጀርባ ያሉት ግን ሐሰተኛ ወንድሞች ብቻ ሳይሆኑ ሰይጣንም ጭምር መሆኑን መዘንጋት
የለብንም፡፡ (1 ጢሞ. 4*1-2፤ 2 ጢሞ. 2*25-26) ልዩ ወንጌል ስንቀበል አብረን ልዩ መንፈስ እንቀበላለን፡፡ (2 ቆሮ. 11*4)
የሐሰት መምህራን ራሳቸው የተታለሉ እና ሌሎችን የሚያታልሉ ናቸው፡፡ (2 ጢሞ. 3*13)

1.4 የሐሰተኞች መለያዎች

የሐሰተኛ መምህራን በርካታ መለያዎች አላቸው፡፡ ከዚህ ቀጥለን የተወሰኑትን እንመለከታለን፡-


 አውድ መጣስ
 ቃሉን ማጣመም
 ግላዊ ራዕይ፣ ሕልምና ትንቢት እንደ ቃሉ ማቅረብ
 ነፍስ ሳይቀርላችሁ ስሙን ማለት
 ራስን ስልጣናዊ አድርጎ ማቅረብ
 ሰው አግንን ትምህርት ማስተማር
 ጆሮ አሳካኪ ትምህርቶች ማስተማር
 ግላዊ ፍላጎትን እና ስግብግብነትን መዕከል ያደረገ አገልግሎት መስጠት

1.5 የልዩ ወንጌል መሠረታዊ ትምህርቶቹ

32
ልዩ ወንጌል የስሕተት ትምህርቶችን በሙሉ የሚያቅፍ ስያሜ እንደ መሆኑ መጠን፤ ሁሉንም የስሕተት ትምህርቶች መዳሰስ
አይቻልም፡፡ ስለዚህም በዘመናችን ካሉ የስሕተት ትምህርቶች መካከል ዋና የሚባሉትን ትምህርቶች እንቃኛለን፡፡

ምዕራፍ ሁለት፡- ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል (የእግዚአብሔር
ቅጂ)

የልዩ ወንጌል መምህራን “ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል” ብለዉ ያምናሉ። “ሰው መንፈስ ነው”
የሚለው ትምህርታቸውን የሚያስተምሩበት ዋና ዐላማቸው ስጋ ለባሹን ሰው “ትንንሽ እግዚአብሔር ለማድረግ” ከሚባዝን
ከንቱ ምናባዊ ቅዠት የተነሣ ነው። እግዚአብሔር ሰውን የራሱ አምሳያ ቅጂ፣ ቁሳዊውን ዓለም የሚገዛ፣ በንግግሩም መፍጠር የሚችል አድርጎ
ፈጥሮታል በሚል እንዲታሰብ ሆኗል። ሰው “እንደ እግዚአብሔር ተፈጥሯል” የተባለው ደግሞ ከሰው ውስጣዊ ማንነት የተነሳ ነው፡፡ በትምህርቱ
የእግዚአብሔር ቅጂ የሚባለው የሰው ማንነት ደግሞ መንፈሱ እንደሆነ ይታሰባል። መምህራኑ መንፈሳችን ከእግዚአብሔር በመወለዱ ልክ እንደ
እግዚአብሔር መሆኑን ያምናሉ፡፡ አንዳንድ የትምህርቱ አራማጆች የሰውን መንፈስ ተፈጠረ ከማለት ይልቅ ከእግዚአብሔር ተወለደ ማለት
ይቀናቸዋል። በተጨማሪም ክርስቲያን ሆነን ኃጢአት ብንሰራም የውስጥ ሰውነታችን ግን ኃጢአት አያደርግም ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልክ
ያለው በመንፈሳችን እንጂ በስጋችን ውስጥ አይደለም በማለት ለስጋ ብዙም ስፍራ አይሰጡም፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን የስህተት ትምህርት
ለመደገፍ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶቸ መካከል፡- (ዘፍ. 1፥27፣ 2፥7፤ ዮሐ. 3፥6፣ 10፥34-35፤ ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥10፤ 1 ዮሐ. 3፥9
ከትምህርቱ ሰፊነት የተነሳ የእነዚህን ጥቅሶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን በዚህ ምዕራፍ ላይ መመልከት ስለማንችል አስተማሪው
በዋቢ ላይ ከተጠቀሱት መጽሐፍት የጥቅሶቹን ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት ይችላል)

2.1 መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ

2.1.1 “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” የማለቱ ነገር (ዘፍ. 1፥26-31)

“መልክ” የሚለው ቃል በዕብራይስጡ “ጼሌም” (tselem – eikon - image) የተባለው ነው፤ ትርጉሙም ሥዕልን ወይም ምስያን
አመልካች ነው። “አምሳል” የሚለው ቃል በዕብራይስጡ “ዴሙት ወይም ዳማት” (demuth – homoiosis - likeness) ሲሆን፤
ቃሉ ከ 25 ላላነሰ ጊዜ በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ውሏል። ትርጉሙም አርዓያ እንደ (በንጽጽር የሚቀርብን) ብለን
መተርጎም እንችላለን።

ዋይኒ ግሩደም ይህን ክፍል ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦

“መልክ” እና “አምሳል” ለሚሉት ቃላት የተሰጠውን የዕብራይስጥ ትርጉም ባየን ጊዜ፤ የመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች ሰው
የእግዚአብሔር አምሳል ነው ሲባል የተረዱት ሰው በብዙ መንገድ እግዚአብሔርን ይወክላል በሚል ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ
እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችን፤ በአምሳላችን እንሥራ” (ዘፍጥ. 1፥26) ያለውን የመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች የተረዱት “እኛን
እንዲመስልና እኛን እንዲወክል ሰውን እንሥራ” በሚል ነው።

በክርስትና ሥነ መለኮት እግዚአብሔርን መምሰል ከሦስት ነገር አንጻር ይተነተናል። እንርሱም፡-

ሀ/ አንደኛው ሰው ከእግዚአብሔር የተካፈላቸውን እንደ ምክንያታዊነት፣ ግብረገባዊነትና ነጻ ፈቃድ ያሉ ባህሪያት ባለቤት እንደሚያመለክት
ተደርጎ ይወሰዳል። ስለዚህም ሰው ከእግዚአብሔር ተካፋይ ባህርያት የወሰደው እንዳለ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ እግዚአብሔር የሚካፈሉ ባህርያት
ብቻ ሳይሆን የማይካፈሉ ባህርያት ባለቤት እንደመሆኑም መጠን፤ እኛ የእርሱ አቻ እና ቅጂ ፈጽሞ ልንሆን አንችልም፡፡
33
ለ/ ሁለተኛው ከሌሎች ፍጥረታት በበለጠ ሰው ከአምላክ ጋር ኅብረት ማድረግ የመቻሉን አቅም እንደሚያመለክት ይረዱታል። ከፍጥረታት ሁሉ
ከእግዚአብሔር ጋር መንፈሳዊ ትስስር የማድረግ አቅም ተሰጥቶት የተፈጠረው ሰው መሆኑን ያመለክታል፡፡
ሐ/ ሶስተኛው ከእግዚአብሔር የተቀበለው ገዢነት በሚል ይፈታል። ስለዚህም ሰው ምንም ፍጡር ቢሆንም፤ በባለአደራነት መንፈስ
የእግዚአብሔርን ዓለም፣ ለእግዚአብሔር ባለ መገዛት እንዲያስተዳድር ኃላፊነትን ተቀብሏል፡፡

2.1.2 ሰው ስጋም አለው

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር ስለፈጠረው ሰው ከምድር የሆነ አካል (ሰውነት) አለው፡፡ ይህ ግዑዝ የሆነውና በሰው
ዓይን የሚታየውና በእጅ ሊዳሰስ የሚችለው የሰው ክፍል ሲሆን ለማይታዩት ነፍስ እና መንፈስ ማደሪያ ነው፡፡ (ዘፍ. 2*7፤ ኢዮ.
19*26፤ ያዕ. 2*26) ስጋ ለእግዚአብሔር መንፈስ ወይም ለሰይጣን መንፈስ ማደሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ (ሉቃ. 13*11፤ 1 ቆሮ.
6*19-20፤ ሮሜ. 6*13) ስጋ ሟችና በስባሽ ነው፡፡ (ዘፍ. 3*19፤ ኢዮ. 34*15) ስጋ ክቡርና ከምናየው ዓለም ጋር ቀጥተኛ
ግንኙነትን የምናደርግበት፤ እግዚአብሔርንም ለማምለክና ለማክበር በቅድስና ልናቀርበው የሚገባ የሰውነት ክፍል ነው። (ሮሜ
12፥1) ስለዚህ ምንም እንኳ ስጋችን የሚሞት ቢሆንም በመጠን ሊኖር (1 ጢሞ. 6፥6፤ 1 ጴጥ. 5፥8) ፣ ለዝሙት ከመሆን ይልቅ
ለጌታ ሊሆን (1 ቆሮ. 6፥13) ፣ ኀጢአት እንዳይነግስበት ልንጠብቀው ይገባናል። (ሮሜ 6፥12) በስጋችን እግዚአብሔርን
ልናከብረው ይገባናል፡፡ (1 ቆሮ. 6፥19) ደግሞም ይህ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፡፡ (1 ቆሮ. 3፥16፤ 2 ቆሮ.
6፥16)

2.1.3 ሰው ነፍስም አለው

“… በአፍንጫም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” (ዘፍ. 2*7) ነፍስ ዘላለማዊ ነው፡፡ (መክ.
12*7፤ ማቴ. 10*28) ከዚህ በተጨማሪ የሰው እኔነት (Personallity) መገለጫ የሆኑት ፈቃድ፣ ስሜት፣ ዕውቀት ማደሪያ ነው፡፡
(1 ሳሙ. 18*1፤ ምሳ. 19*2፤ ማቴ. 26*38፤ ሐዋ. 4*32) ነፍስ የራሷ ማንነትና አካል ያላት ስትሆን፤ ልክ እንደ ሥጋ በድካምና
በኀጢአት ልትያዝ እንደምትችል መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስቀምጣል፡፡ (መዝ. 78፥8፤ ምሳ. 21፥10)

2.1.4 ሰው መንፈስም አለው

መንፈሳችን ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የምናደርግበት ክፍል ነው፡፡ እግዚአብሔርን እንድናመልክና ፈቃዱንም እንድንረዳ
የሚያደርገው ይህ መንፈሳችን ነው፡፡ (ሚል. 2*15፤ ማቴ. 26*41፤ ሉቃ. 2*40፤ ዮሐ. 4*24፤ ሮሜ. 8*16) ሰው የተፈጠረ
መንፈስ አለው፤ የሰው መንፈስ ከመንፈስ ቅዱስ ፈጽሞ ይለያል፤ የእኛ መንፈስ ፍጡር ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ፈጣያችን
እግዚአብሔር ነው። (ኢዮብ 32፥8፤ 33፥4፤ ዘካ. 12፥1) ስለዚህም መንፈስ ስላለን መንፈስ ብቻ ነን አያሰኘንም፤ መጽሐፍ
ቅዱስ ይህን አያስተምረንም። በአዲስ ኪዳንም “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ” (2 ቆሮ. 7፥1) በማለት
መንፈሳችንም ሊረክስ እንደሚችል ነገር ግን ቅድስናን “ፍጹም ገንዘብ” በማድረግ በእግዚአብሔር ፍርሃት መንጻት እንዳለብን
ያስተምረናል።

2.1.5 ነፍስና መንፈስ አንድ ናቸው ወይስ ይለያያሉ

34
አንዳንዶች የሰውን ነፍስ መንፈስ ነው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ነፍስና መንፈስ በየራሳቸው የተለያዩ ናቸው ይላሉ። የነፍስና
የመንፈስን ልዩነትንም ሲያስረዱ፣ ነፍስ የሰውን አእምሮ፣ ስሜትና ፈቃድን የሚያመለክት ሲሆን፣ መንፈስ ደግሞ
ከእግዚአብሔር ጋር በአምልኮትና በጸሎት የሚገናኘውን አመልካች ነው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ነፍስ እና መንፈስን በማለዋወጥ
በተለያየ ስፍራ ይጠቀምባቸዋል፡፡ (ዮሐ. 12*27 ከ 13*21፤ ሉቃ. 1፡46-47፤ ዕብ. 12*23 ከ ራዕይ 6*9) ነፍስና መንፈስ አንድ
ሆኑም አልሆኑም ማስተዋል ያለብን ነገር እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ስጋ ነፍስና መንፈስ አብረው የሚሰሩበት አንድ ሙሉ
ሰው ነው የፈጠረው፡፡ ይህ አንድነት የተዋሃደና ልንነጣጥለው የማይቻል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን የሰውን አንድነት
በሙሉ ማንነቱ እንድንቀበለው ነው፡፡ ሰውን ከፋፍለን ልናይ አንችልም፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወታችን በሁሉም አቅጣጫ ማደግ
አለብን፡፡ (2 ቆሮ. 7*1፤ 1 ተሰ. 5*23) እንዲያው በምሳሌነት ብንጠቅስ፦ ሰው ሲሞት ነፍስና ስጋው ይለያያሉ፤ ነፍሱን ብቻ ሰው
አንልም፤ ስጋውንም ብቻም ሰው አንልም። የሁለቱ በአንድነት መሆን ግን ሰውን ሰው ያሰኘዋል።

2.1.6 ሰው አንዴ ስጋ ሌላ ጊዜ ደግሞ ነፍስ በሚል ቀርቧል

መጽሐፍ ቅዱስ ሰውን አንዴ “ስጋ” ሌላ ጊዜ ደግሞ “ነፍስ” በማድረግ ያቀርባል፡፡ ለምሳሌ፡- እነዚህ ጥቅሶች ሰውን “ስጋ” ወይም
“ስጋ ለባሽ” በማለት ነው የሚያቀርቡት፡፡ (ዘዳ. 5፥26፤ ኢዮብ 34፥15፤ ኢሳ. 40፥6፤ ኤር. 12፥12፤ 25፥31፤ 32፥27፤ 45፥5፤
ሕዝ. 20፥48፤ 21፥4፤ ኢዩ. 2፥28፤ ዘካ. 2፥13፤ ማር. 13፥20፤ ሮሜ 3፥20) እነዚህን ክፍሎች ለሚያነብ ሰው ማለት “ስጋ” ብቻ
ሊመስለው ይችላል ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሰው “ነፍስ” ተደርጎ ቀርቧል፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ይህንን ያሳያሉ፡፡ (ዘፍ. 46፥15፥18፤ ዘጸ. 1፥5፤ ዘኁ. 31፥35፤
ዘዳ. 10፥22፤ ኢያሱ 10፥28፤ 2 ሳሙ. 14፥14፤ መዝ. 107፥9፤ ምሳ. 14፥25፤ ኢሳ. 43፥4፤ ኤር. 52፥29፤ ሕዝ. 17፥17፤ 2 ጴጥ.
2፥14)

ከላይ እንዳየነው፣ ሰው “ስጋ” ተብሎ ተጠርቷል በሌላ በኩል ደግሞ “ነፍስ” ተብሎም ቀርቧል፡፡ እናም እንደ ተፈለገው ሐሳብ
“ስጋ” ፣ “ነፍስ” ወይም “መንፈስ” ተብሎ የሚቀርብበት አግባብ ሊኖር ቢችልም፣ ሰው ሰው ለመሆን ቁሳዊው አካሉ (ስጋ) ሆነ
ቁሳዊ ያልሆነው (ነፍስ/መንፈስ) አካሉ መጣመር አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞቱ ሰዎች እንደሚናገረው ነው
የምንጠራው፡፡ “በወህኒ ለነበሩ ነፍሳት (መንፈሶች)” (1 ጴጥ. 3፥19) ፤ “የታረዱትን ሰዎች ነፍሳት” (ራእይ 6፥9) ፤ “ስለ ኢየሱስ
ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸው ሰዎች ነፍሳት” (ራእይ 20፥4) ሰው ሰው ለመሆን ስጋ፣
ነፍስ/መንፈስ ያስፈልዋል፡፡

2.1.7 “መልክና ምሳሌ” የሰው ሁለንተና ነው!

እግዚአብሔርን የሚመስለው መልክና ምሳሌው የሰውነታችን ሁለንተና [ቊሳዊው ስጋችንና (መንፈሳችንም) ነፍሳችንም
ጭምር] ነው። “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ስጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ” (1 ተሰ. 5፥23) በሚለው ንባብ ውስጥ “ሁለንተናችሁን” የሚለው ቃል
የሰውን ነፍስንም፣ ስጋንም እንደሚያካትት መንፈስን ብቻ እንደማይል ግልጥ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ “ቅድስና ለመንፈስ ብቻ” የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የለም። ስጋም በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ
እንዲገዛ (እንዲመስል) የጸና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አለን። (ሮሜ 6፥11-12፤ 1 ቆሮ. 6፥13-20፤ 1 ጢሞ. 4፥8)

35
እንደ ሦስተኛ ፍሬ ነገር ብንናገር፤ በስጋችንም እግዚአብሔርን እንመስለዋለን ወይ? የሚል ጥያቄ ብናነሳ፤ አዎን ብለን ለመመለስ
እንደፍራለን። (1 ቆሮ. 11፥1) በፍጻሜውም ደግሞ ወደ ፍጹም ሰውነት እንጂ ወደ መንፈስነት አናድግም፡፡ (ኤፌ. 4፥13፤ ቈላ.
1፥28) ሁለንተናችን እግዚአብሔርን ይመስላል፤ ራሱ እግዚአብሔርን ግን አይደለንም። ወደ ፍጹም ሰውነት ብናድግም
እግዚአብሔር ወዳሰበልን፤ እንድንሆንም ወደ ፈቀደልን ምሉእ ሰው-ነት እንጂ መለኮታውያን [ራሱ እግዚአብሔርን] አንሆንም።
እግዚአብሔር ያሰበልንና ያለን ነገር ብቻ እውነትና ትክክል ነው፡፡ (ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥9-10፤ 1 ዮሐ. 3፥2-3)

2.1.8 የእግዚአብሔር ልጅነታችን እስከ መለኮት የሚደርስ ነውን?

ሰዎች ክርስቶስን ይመስላሉ ስንል የአዲስ ኪዳን ምንባባት ይህን አባባል በግልጥ ወስነው አስቀምጠውታል፡፡ (ሮሜ 8፥29፤ ፊል.
3፥21፤ 1 ዮሐ. 3፥2) በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሰው ከእግዚአብሔር ስለ ተካፈላቸው የቅድስና፣ የሕይወት፣
የክብር፣ የገዢነት፣ የጽድቅ፣ የዕውቀትና የግብረ ገብነትን ባሕርይ እንጂ ሰው ፍጹም አምላክ ስለ መሆኑ የሚያመለክቱ
አይደሉም። ከፍጥረታችንም ሰው መሆን እንጂ፤ መለኮት የመሆንም ሆነ ወደዚያ የማደግ አንዳች ምክንያት ወይም ተፈጥሯዊ
ጠባይ የለንም። መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ ረገድ የሚያስተምረን አንዳች ትምህርት የለውም። በዚህ ምድርም ሆነ ከሙታን
ትንሣኤ በኋላ በሚኖረን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጥገኝነት ፈጽመን መላቀቅ አንችልም።

2.1.9 ሰው፤ ሰው ብቻ ነው

እኛ መለኮት መሆን አለመቻላችን ብቻ ሳይሆን፤ ከመለኮት ጥገኝነት መውጣት አይቻለንም። ጌታችን ኢየሱስ ምንም በማያሻማ
መልኩ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና” ብሏል። (ዮሐ. 15፥5)
ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ከሌለን በቀር አንዳችና ምንም ነገር በራሳችን ማድረግ አንችልም። እኛ ግን ያለ እርሱ ዕርቃናችንን ያለን
(ዘፍጥ. 3፥7) ፣ ፍጥረትን አንዳች ማዘዝ የማይቻለን (ዘፍጥ. 3፥17) ፣ ልባችን በክፋት የተሞላ (ዘፍጥ. 8፥21፤ ኤር. 17፥9) ከንቱ
ፍጥረት ነን። (ኢዮብ 34፥14-15፤ መክ. 12፥7) ክብራችንና ግርማችን የእርሱ መልክና አምሳል ስላለብን ብቻ ነው። (ራእ.
21፥26) ከእርሱ ስንለይ እንኳን መለኮት፤ ሰውነትን እንኳ “በወግ” አናሟላም። መጽሐፍ ቅዱሳችን ሰውን በእግዚአብሔር መልክና
አምሳል መፈጠሩን ሲናገር መደብህ መለኮት ነው አይለውም። በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ልዩነት የፈጣሪና የተፈጣሪ መሆኑ ግልጽ
ነው። (መዝ. 86፡8፤ ሕዝ. 28፡2፤ ሆሴ. 11፡9)

ምዕራፍ ሶስት፡- ነገረ ድኅነት (ድነት)


“የልዩ ወንጌል” መምህራን ከሚታወቁባቸው መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ የእውነተኛ ወንጌል ማዕከል በሆነው በክርስቶስ የማዳን ስራ ላይ ወይም
ድኅነት (ድነት) በተመለከተ የሚያስተምሩት ልዩ ትምህርት ነው።

3.1 “መሰይጠን” ና ትምህርቱ

በልዩ ወንጌል መምህራን ዘንድ ልዩ ትኩረት የተሰጠውና “እንደ አዲስና ልዩ መገለጥ” የሚታየው ትምህርት የኢየሱስ ክርስቶስ
ሁለት ጊዜ መሞት ወይም “ሰይጥኗል” ትምህርታቸው ነው። “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጥኗል” የሚለው ትምህርታቸውን
ለማስተማር እንደ ምንጭነት የሚጠቀሙት ታሪክ፤ ሰው በኃጢአት በወደቀ ጊዜ የሰይጣንን ባሕርይ ገንዘቡ አደረገ፤ ዓለምና
የሰው ልጅ በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ ሆኑ ስለዚህ እግዚአብሔር ዓለምን መልሶ በእጁ ለማስገባት ለሰይጣን ቤዛ ከፈለ ይላሉ፡፡
ክርስቶስም ሰውን ለማዳን የሰይጣንን ባሕርይ ገንዘቡ አደረገ እርሱም ሰየጠነ በማለት ያስተምራሉ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሁለት

36
ሞት ሞቷል፤ በመጀመሪያ የስጋ ሞትን ሞቷል፤ ቀጥሎም በመንፈስ ሞቷል። በስጋው ሞተ ሲባል ጌታችን ነፍሱን ሰጠ ወይም ነፍሱ ከስጋው
ተለየች ነው። በትምህርቱ መንፈሳዊ ሞት ከእግዚአብሔር መለየትና ከሰይጣን ጋር በባህሪ ጭምር መተባበር ነው። ከሰይጣን ጋር መተባበርም
የእርሱን ባህርይ በመውሰድ አያበቃም፤ ይልቁኑ በሰይጣን ግዛት ቁጥጥር ስር መውደቅን፣ ብሎም ሰይጣናዊ ባህሪን መካፈልን ጭምር
ያመለክታል። የክርስቶስ ሞት ለሰይጣን የቀረበ መሥዋዕት ነው በማለት የክርስቶስን ሥጋዊ ሞትና መስዋዕትነቱን ፈጽመው
አይቀበሉም። “ተፈጸመ” ብሎ በመስቀል ከተናገረ በኋላ ያልተፈጸመ ሌላ የማዳን ሥራ ነበረው በማለት የመስቀሉን ሥራ
ያክፋፋሉ። ስጋዊ ሞት የብሉይ ኪዳን መሥዋዕታዊ ምሳሌ ብቻ ስለ ሆነ ኃጢአትን ማስወገድ አይችልም፤ ስለዚህ ኢየሱስ
መንፈሳዊ ሞትን በመሞት በሰይጣን እጅ መከራን በመቀበል፤ ለሰይጣን ቤዛ ከፍሎ እኛን ከእርሱ እጅ እንደ ዋጀን አድርገው ነው
የሚያቀርቡት። ከላይ የተጠቀሰውን የስህተት ትምህርት ለመደገፍ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶቸ መካከል ፡- (ማቴ. 27፥46፤ 2 ቆሮ.
5፥21፤ ገላ. 3፥13፤ 1 ጴጥ. 3፥18-19 ከትምህርቱ ሰፊነት የተነሳ የእነዚህን ጥቅሶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን በዚህ ምዕራፍ ላይ
መመልከት ስለማንችል አስተማሪው በዋቢ ላይ ከተጠቀሱት መጽሐፍት የጥቅሶቹን ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት ይችላል)

3.2 ስለ ድኅነት (ድነት) መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮው

3.2.1 የሰይጣን ባሕርይ

ሰይጣን ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን የቅድስና ባሕርይ የሚቃረንና የሚጻረር፣ የመልካምና የጽድቅ ሁሉ ጠላት ነው። ከመጀመሪያው
ኃጢአትን ከራሱ ያመነጨው እርሱ ነው። (ማቴ. 13፥39፤ 1 ዮሐ. 3፥8) እግዚአብሔርን በመዳፈር በትዕቢቱ ውስጡ ተሞላ
(ሕዝ. 28፥13-17) ፣ እርሱና ተከታዮቹ ኃጢአትን ሠርተው ወደ ጥልቁ ወደቁ (2 ጴጥ. 2፥4) ፣ በፍጻሜውም የዘላለም ፍርድ
ተጠብቆላቸዋል፡፡ (ራእ. 20፥10) የጽድቅ ሁሉ ጠላት የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም የማያርፍ ከእግዚአብሔርም ሆነ
ከቅዱስ ቃሉ ጋር አንዳችም ትስስርና ዝምድና የሌለው በሁለንተናው ክፋትን የተመላ ነው። (ሐዋ. 13፥10)

3.2.2 ሰው አልሰየጠነም!

የሰው ልጅ የገዛ መንገዱን በመከተሉ ምክንያት ከታላቅ ክብሩ ወድቋል፣ ረክሷል፣ ኃጥእና በደለኛ ሆናል፣ በበደሉና በኃጢአቱ
ምክንያት ከአምላኩ በመለየቱም ሙት ሆኗል፤ ስለዚህም የእግዚአብሔር ፍርድ አግኝቶታል፡፡ (ኤፌ. 2*1-2) ሰው ኃጢአትን
በመሥራቱ ምክንያት የመጸጸት ባሕርዩን ፈጽሞ አጣ፣ ራሱን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ንስሐ ገብቶ የአምላኩን ፊት
አልፈለገም፣ እንዲያድነው ወደ አምላኩ አልቃተተም፡፡ (ዘፍጥ. 3፥9-15፤ ሮሜ. 3፥11) ይህ ማለት ግን ሰው ሙሉ ለሙሉ
ሰይጣናዊ ባሕርይን ገንዘቡ አደረገ የሚል አስተምህሮ ፈጽሞ የለውም። በውድቀትም ጊዜ እግዚአብሔር ሰይጣንን ኰንኖ ለሰው
ልጅ ግን ታላቅ የመዳንን ዘላለማዊ ኪዳን ሰጥቶታል። (ዘፍጥ. 3፥14፤ 2 ጴጥ. 2፥4)

3.3 ኃጢአትና ሞት ምንድን ነው?

ሰው በኃጢአት ከመውደቁና ከእግዚአብሔር ከመለየቱ በፊት ከእግዚአብሔር ከአምላኩ ጋር ቀጥተኛና ትክክለኛ ግንኙነት
የነበረው፤ ኃጢአትን የማያውቅ፤ በንጽሕና የሚኖርና መኖሪያው ተድላ ኤደን ገነት ነበር፡፡ (ዘፍ. 2*8) ሰው እግዚአብሔር
የሚለውን ባለመታዘዝ በኤደን ገነት የሚገኘውን የዛፍ ፍሬ በበላና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በተላለፈ ጊዜ በኃጢአት ወደቀ፡፡
(ዘፍ. 2*16-17፤ 3*6) ሰዎችም ሁሉ ከዚህ ፍርድ የተነሣ “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ … ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ …
በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች ሆኑ” (1 ቆሮ. 15፥22፤ ሮሜ 5፥14፤ 19) “ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች” ሆንን፡፡
(ኤፌ. 2፥3) ሲፈጠር ሕይወት እንጂ ሞት ያልነበረበት የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ደመወዙን ተቀበለ፡፡ (ሮሜ 6፥23)

37
3.4 መንፈሳዊ ሞት

“የሰው ወገኖች ሁሉ ከአንድ አዳም ተፈጥረዋልና” (ሐዋ. 17፥26) ፣ አዳም ኃጢአትን ባደረገ ጊዜ በአዳም አማካይነት ኃጢአት
ወደ ዓለም ሁሉ ገባ። በኃጢአትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፡፡ (ሮሜ 5፥12፤ 14-15፤
6፥23፤ 1 ቆሮ. 15፥21) በኃጢአት ምክንያት ሰው ሁለንተናዊ ችግር አገኘው፤ ህሊናውና አእምሮ ስለረከሰ የተዛባ ውሳኔ
የሚወስንና የእግዚአብሔርን ዐሳብ ተቃዋሚ ሆነ (2 ቆሮ. 10፥5፤ ቲቶ 1፥15) ፣ ቅድስናን ነቃፊ ሆነ (1 ጴጥ. 1፥16) ፣
ከእግዚአብሔርም በመለየት ምክንያትም [እርሱን ባለመታመን] መንፈሳዊ ሞትንም ሟች ሆነ፡፡ (ማቴ. 8፥22፤ ሉቃ. 1፥79፤
ኤፌ. 5፥14፤ ቆላ. 2፥13፤ 1 ዮሐ. 3፥14) ስለዚህም ዳግም ያልተወለደው የሰው ልጅ በዘላለምና በመጨረሻው ፍርድ ከሰይጣን
ጋር እንደሚቀጣ እንጂ የሰይጣንን ባሕርይ እንደሚወርስ የሚያስተምር አንዳች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም። (ኢሳ. 66፥24፤
ማቴ. 5፥22፤ 7፥23፤ 25፥41፤ 46፤ ማር. 9፥43-44፤ 2 ተሰ. 1፥9፤ ራእ. 20፥13)

3.5 የመዳናችን ነገር

በሰማይም ሆነ በምድር የሚያድነን አንድ አዳኝ ከፍጡር ወገን ስለ ጠፋ፤ እግዚአብሔር የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነ፡፡ (ዕብ.
5፥10) ሊያድነን “በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን” (ኤፌ. 1፥5) ፣
እኛን ወደ ራሱ ያቀርበን ዘንድ (1 ጴጥ. 3፥18) “እግዚአብሔር አብ እኛን ስለ መውደዱ፤ ውድና መተኪያ የሌለው አንድያ ልጁን
በመስጠት በአጋፔያዊ ፍቅር እንዲሁ ወደደን፡፡ (ዮሐ. 3፥16፤ ሮሜ 5፥7-8፤ 1 ዮሐ. 3፥1) “በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት
በኩልም እንዲያው በጸጋው አጸደቀን” (ሮሜ 3፥24) ስለዚህም ለመዳናችን ከመጀመሪያው ያሰበው፤ ደግሞም የፈጸመውና
እንወርሰው ዘንድ በጸጋው እንዲሁ የሰጠን ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

3.5.1 የዳነው ክርስቶስ በስጋው በተቀበለው መከራና ሞት ነው!

ጌታችን ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ ሊያድነን፣ ሊቤዠን፣ ሊዋጀን መጣ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደውና
ሰው የሆነው ከኃጢአት በቀር የሰውን ሁለንተና ገንዘብ በማድረግ ነው። (ሉቃ. 2፥6-7፤ ዮሐ. 1፥14፤ ዕብ. 4፥15) መጽሐፍ ቅዱስ
እግዚአብሔር ወልድ ገና ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ቤዛ ሆኖ ሊሰጥለት የመጣለትን የሰውን (የአብርሃምን) ዘር እንጂ የመላእክትን ዘር
እንዳልያዘ ይመሰክራል። በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለመሻርና በሕይወታቸው ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት
ይታሰሩ የነበሩትን በሙሉ ነጻ ለማውጣት በስጋና በደም መካፈል ብቻ በቂ መሆኑንም መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል። (ዕብ. 2፥14-
17) ከዚህ ውጪ ኢየሱስ የመንፈስ ሞት መሞቱን ወደ ሰይጣንነት መለወጡን ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ መዳናችንን የፈጸመው በመስቀል ላይ ወይም በስጋ ሞቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል። (ሐዋ.
5፥30-31፤ 1 ቆሮ. 15፥3፤ ቆላ. 1፥21-22፤ ዕብ. 10፥10፤ 1 ጴጥ. 2፥24፤ 1 ዮሐ. 4፥2-3)

3.5.2 በደሙ መፍሰስ እኛን ስለ ማዳኑ

በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ክርስቶስ በደሙ መፍሰስ፤ በመስቀል ላይ በሠራልን የቤዛነት ሥራ መዳናችንን ይነግረናል።
(ሐዋ. 20፥28፤ ሮሜ 3፥25፣ 5፥9፤ ኤፌ. 1፥7፤ ዕብ. 9፥14፤ 10፥19፤ 13፥12፤ 1 ጴጥ. 1፥18-19፤ 1 ዮሐ. 1፥7፤ ራእ. 1፥5፤ 5፥9-
10)

38
3.5.3 በመስቀል ላይ እኛን ስለ ማዳኑ

በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም በመስቀል ላይ እኛን ስለ ማዳኑ ይነግሩናል፡፡ (ዮሐ. 3፥14-15፤ 1 ቆሮ. 1፥17፤ ገላ. 3፥13፤
6፥14፤ ኤፌ. 2፥16-17፤ ፊልጵ. 2፥8፤ ቆላ. 1፥19-20፣ 2፥14)

3.5.4 የስጋ ሞቱም አንድ ጊዜ ብቻ (በስጋ) መሆኑ

ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ብቻ በስጋ ሞቱ፤ በመስቀል ላይ በተቀበለው መከራ ብቻ እንዳዳነን ቅዱሳት መጻሕፍት
ይመሰክሩልናል። (ሮሜ 6፥10፤ ዕብ. 7፥27፣ 9፥26-28፣ 10፥10-12፣ 10፥14-18፤ 26፣ 1 ጴጥ. 3፥18) ከዚህ በላይ
እንደተመለከትነው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ አንድ ጊዜ መፍሰስ፣ በሥጋ ሞቱ፣ በመስቀል ላይ በተቀበለው
መከራ ብቻ እንዳዳነን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክሩልናል።

3.6 ጌታችን ኢየሱስ ሰይጥኗልን? ለሰይጣንስ መስዋት አቀረቧልን?

ክርስቶስ ኢየሱስ ያለ ኃጢአት የኖረ፣ በኑሮውም ሁሉ ይህን በማሳየቱ የእግዚአብሔር ልጅና ፍጹም ሰው ተብሏል፡፡ (ሉቃ. 1፥35፤
ሐዋ. 4፥30) እርሱ ቅዱስ ነው ስንል፣ ኃጢአትን አልሠራም ወይም አላደረገም፣ ደግሞም ኃጢአትን የመሥራት ዝንባሌው
ፈጽሞ የለውም፤ ይህንም የአባቱን ፈቃድ ብቻ በመፈጸም አሳይቷል፡፡ (ዮሐ. 8፥29፣ 46፤ 2 ቆሮ. 5፥21፤ 1 ጴጥ. 2፥22፤ 1 ዮሐ.
3፥5)

በቅድሚያ ሰይጣን ቤዛ ለመቀበል ምን ሕጋዊ መብት አለው? የሚለውን መመልከት አለብን። እንደሚታወቀው እግዚአብሔር
ምድርን እንዲገዛ ሥልጣን የሰጠው ለሰው ነው። ይሁን እንጂ ሰው በሰይጣን ምክር ተታልሎ ትእዛዘ እግዚአብሔርን ሲያፈርስ
እንዲገዛው የተሰጠውን ዓለም ይዞ በሰይጣን ስር ወደቀ። ሰይጣንም ሰልጥኖበት የዚህ ዓለም ገዥ ተብሎ ተጠራበት፤ ቢሆንም
በክርስቶስ ላይ አንዳች የለውም፡፡ (ዮሐ. 12፥31፤ 14፥30፤ 16፥11፤ 2 ቆሮ. 4፥4)

3.6.1 ጌታችን ለእግዚአብሔር ብቻ መስዋዕትን ስለ ማቅረቡ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም፣ ቅዱስ፣ ንጹሕና ነውር የሌለበት መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ (ማቴ. 27፥19፤
ሉቃ. 1፥35፤ ዮሐ. 8፥46፤ ሐዋ. 3፥14፤ 2 ቆሮ. 5፥21፤ ዕብ. 7፥26፤ 1 ጴጥ. 1፥18-19፣ 2፥22-23፤ 1 ዮሐ. 3፥5) ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ይህን ቅዱሱን መስዋዕት ወይም ስጋውን ያቀረበውም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለሰይጣን አይደለም። በብሉይ ኪዳን
የሚቀርበው መስዋዕት የሚቀርበው ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር፡፡ (ዘጸ. 30፥12፤ መዝ. 49፥7) እንዲሁ እርሱም ራሱን ያቀረበው
ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ይህንም ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ (ኤፌ. 5፥2፤ ዕብ. 9፥14፣ 10፥12፤ 1 ጢሞ. 2፥6) ታዲያ
ከሰይጣን እጅ ያዳነን እንዴት ነው? በሞት ላይ ስልጣን ያለውን እርሱን በሞቱ በመሻር ነው፡፡ (ቆላ. 2፥14-15፤ ዕብ. 2፥14-15)

ከዚህ ባሻገር በዕለተ ስቅለቱ የነበረውን ሂደት ስንመለከት የክርስቶስን መንፈሳዊ ሞት ወይም መሰይጠንን ፈጽሞ
አንመለከትም። ቢያንስ የተወሰኑ ድርጊታዊ ክስተቶችን በምሳሌነት መጥቀስ እንችላለን፤

ሀ/ “ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.
23፥46) ጌታ ኢየሱስ ነፍሱን ለቅዱስ አባቱ እንጂ ለሰይጣንም ሆነ ለሌላ አሳልፎ አልሰጠም።
ለ/ “እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” (ሉቃ. 23፥43) ይህን ቃል ጌታችን በመስቀል ላይ የተናገረው ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ ወዲያው ልትሄድ ያለችበት ሥፍራው ገነት እንደ ሆነ ተናገረ።
39
ሐ/ “ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት።
ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፦ እናትህ እነኋት አለው።” (ዮሐ. 19፥26-27) ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይም ሆነ ከመስቀል በኋላ
አለመሰይጠኑን በመስቀል ላይ ያከናወናቸው መልካም ሥራዎች ምስክር ናቸው። በመስቀል ላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ እናቱ ግድ
እንዳለው እናስተውላለን።
መ/ “ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።” (ሉቃ. 23፥34) ለመሆኑ ወደ ሰይጣንነት
የተቀየረ ሰው በምን ባሕርዩ ይሆን ይቅርታንና ምሕረትን መለመን የሚቻለው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በመስቀል ላይ
እንኳ በዚያ ሁሉ ሕማም ተከብቦ፣ ቂም አልያዘም፣ አልዛተም፣ አልተሳደበም፣ አልተቆጣም፣ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም...
ምሕረትና ይቅርታን ይለምንና ይማልድም ነበር፡፡ (1 ጴጥ. 2፥22-23)
ሠ/ “የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር
ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ” (ማቴ. 27፥54) የመቶ አለቃውና ከእርሱ ጋር የጌታ ኢየሱስን ነገር ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች
አንዳንዶቹ፤ በዚያ ሥፍራ ይከናወን ከነበረው ነገር አንጻር ያስተዋሉት ነገር የጌታችን ኢየሱስን ኃጢአተኝነት ወይም መሰይጠን
አይደለም፤ ያስተዋሉት ነገር በሆነበት ነገር ሁሉ የታገሰ፣ እንደሚታረድ በግ የተነዳ፣ በነገር ሁሉ መታዘዝን ያሳየና፣ ይታዩ የነበሩት
ታላላቅ ተአምራትም የክርስቶስን ማንነት አጉልቶ እንዳሳያቸው ማስተዋል እንችላለን።
ረ/ “ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።” (ዮሐ. 19፥30) ጌታችን ኢየሱስ
ተፈጸመ በማለት የተናገረው የተላከበትንና የመጣበትን ዋናውን የቤዛነት ሥራውን እንደ ሆነ፣ የመከራው ጊዜ መፈጸሙንና
ዳግመኛ በመከራ የማይያዝ መሆኑን፣ የኃጢአታችንን ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ መጨረሱን፣ ወደ አብ ክብር የሚገባበት ጊዜ
እጅግ እንደ ቀረበ መናገሩን ነበር፡፡ በቀደሙት አገልግሎቶቹ ደግሞ “ጊዜዬ ገና ነው፣ ጊዜዬ ገና አልደረሰም” (ዮሐ. 2፥4፣ 7፥6)
በማለት ተናግሮ በመስቀል ላይ ተፈጸመ ማለቱን ስራው መጠናቀቁን ያሳየናል።

ምዕራፍ አራት፡- ብልጽግና


አብዛኛዎቹ የልዩ ወንጌል አማኞችና መምህራን ቅዱሳት መጻሕፍት ከሚሉትና ከሚናገሩት በላይ ስለ ብልጽግና የሚሉት
አላቸው። ዋና ማጠንጠኛቸውም ምድርና ሁለንተናዋ፣ በውስጧ የያዘችው ሐብት ሁሉ የእነርሱ እንደ ሆነ እጅጉን እርግጠኞች
ናቸው። ይህንም ባስፈለጋቸው ጊዜ እንደሚጠሩትና እርሱንም እንደሚያገኙት ያምናሉ። የአብርሃም በረከትን ወርሰናል ይላሉ።
አብርሃምና ዘሮቹ እጅግ ባለጸጎች እንደ ነበሩ እንዲሁ እኛም ለአብርሃም በተገባው ኪዳን መሠረት፣ እኛም ባለጸጎች እንሆናለን
በማለት መምህራኑ ይከራከራሉ። የጌታ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት ከኃጢአት ማስተሰሪያነት እኩል የብልጽግናችንም ማረጋገጫ
ነው ይላሉ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ድሃ ሆኖ፣ እኛን አበልጽጐናል የሚል ዐሳብ አላቸው። የልዩ ወንጌል መምህራን
ይህን ዐሳብ በተመለከተ ሁለት ተቃራኒ ሃሳቦችን አምታትተው ያቀርባሉ። በአንድ በኩል ክርስቶስ ስለ እኛ ድሃ ሆኖ እኛን ባለጸጋ
አደረገን ሲሉ፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ክርስቶስ በምድር ሲኖር እጅግ ባለጸጋና ቅንጡ ኑሮን ነው የኖረው እኛም እንደ እርሱ እንኖር
ዘንድ ተጠርተናል የሚል እርስ በእርስ የሚቀዋወም ትምህርትን ያስተምራሉ። ሐዋርያትም ሀብታም እንደነበሩ ይሰብኩናል፡፡
በልዩ ወንጌል መምህራን ዘንድ ብልጽግና የእግዚአብሔር በረከት ነው፤ ድህነት ደግሞ የእግዚአብሔር እርግማን ነው፤ ከዚህም ባስ ሲል
ድህነት ኃጢአት ነው ይላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን የስህተት ትምህርት ለመደገፍ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶቸ መካከል፡- (ዘፍ. 12፥ 2-
3፤ መዝ. 34፥10፣ 37፥25፤ ማር. 10፥30፤ ገላ. 3፥14፤ 2 ቆሮ. 8፥9፤ 3 ዮሐ. 1፥2 ከትምህርቱ ሰፊነት የተነሳ የእነዚህን ጥቅሶች
ትክክለኛ ትርጉማቸውን በዚህ ምዕራፍ ላይ መመልከት ስለማንችል አስተማሪው በዋቢ ላይ ከተጠቀሱት መጽሐፍት የጥቅሶቹን
ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት ይችላል)

40
4.1 ዝራ

የልዩ ወንጌል መምህራን አማኞች የእግዚአብሔር በረከት በሕይወታቸው እንዲትረፈረፍ ከተፈለገ በእምነት ዘርን (ሶጦታቸውን) መባ አድርገው
መስጠት ያስፈልጋቸዋል በማለት የመስጠት እና የመቀበልን ስሌት ያስተምራሉ። የልዩ ወንጌል መምህራን ሰዎችን የሚበዘብዙባቸው ዋና
መንገዳቸው ይህ ነው። ስጦታን የሚሰጥ ማንኛውም ሰው በሚሰጠው ልክ እጥፉን እንደሚያገኝ በማሰብ ሊሰጥ ይገባል በማለት
ያስተምራሉ ነገር ግን የዚህ ትምህርት አዋጭነቱ ለሚሰብኩት ሰዎች እንጂ ተስፋ ሰንቀው ለሚሰሙት (ለሚሰጡት) አይደለም።

4.2 ስለ ብልጽግና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ

4.2.1 ብልጽግና በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን እስራኤል የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እግዚአብሔር በምድራዊ ሐብት እንደሚባርካቸው ቃል ገብቷል፡፡ (ዘዳ. 28፥1-8) በዚህ
ቃልኪዳን መሰረት እግዚአብሔር ብዙ ታማኝ ባሪያዎቹን በምድራዊ ሀብት ይባርካቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ ፡- ኢዮብ (ኢዮብ 1፥1-3) ፣ ሰለሞን
(1 ነገ. 3፥11-13) ፣ አብርሃም (ዘፍ. 24፥1፣ 35) ፣ ኢዮሳፍጥ (2 ዜና. 17፥5) ነገር ግን ሁሉም እስራኤላዊ ባለጸጋ አልነበሩም
በመካከላቸው ድሆችም ነበሩ፤ በብሉይ ኪዳን ብዙ ቦታ እንደተገለጸው እግዚአብሔር የድሆችም አምላክ ነው፡፡ (ዘዳ. 15፥11፤ መዝ.
9፥9፣ 12፥5) በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አገልጋዮች መካከል ካህናት እና ነብያት እንኳ ሳይቀሩ ሀብታሞች
አልነበሩም፡፡ (ዘዳ. 10፥9፤ 1 ነገ. 17፥8-9፤ 2 ነገ. 4፥1)

4.2.2 አብርሃማዊው ኪዳን እንዴት ይታያል?

የአብርሃም ኪዳን የሚገኘው በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ነው፡፡ (ዘፍ. 12፥3፣ 18፥18፣ 22፥18 ፤ ገላ. 3፥8፣ 14) ይህ አሕዛብ ሁሉ
በአብርሃም ዘር እንደሚባረኩ የተሰጠው የተሰፋ ቃል ለምድራዊ ብልጽግና ሳይሆን ሰማያዊና መንፈሳዊ በረከት መሆኑን የሚያሳዩ
በርካታ ማስረጃዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን፡፡ በአብርሃም ያገኘነው በረከት መንፈሳዊ በረከት መሆኑን ለመግለጽ
ሐዋርያ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ውስጥ እንዲህ ጽፏል “በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፡፡” (ኤፌ. 1፥3)

ስለዚህም የአባታችን አብርሃም ኪዳን “ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር” (ሉቃ. 2፥32)
እንዲል የኪዳኑ በረከት በክርስቶስ በኩል ያገኘነው የዘላለም ሕይወት እንጂ የሚጠፋው ምድራዊ ሀብት አይደለም፤ ስለዚህም
መዳናችን የተፈጸመውና እኛም እንድንቀበለው የተጋበዝነው ልክ እንደ አብርሃም በእምነት መንገድ እንጂ በሥራችን አለመሆኑን
ሊናገረን ብቻ የተነገረ ቃል ነው። እንደ አብርሃም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የአብርሃም ልጆች በመሆናቸው ከአብርሃም ጋር
ይባረካሉ፡፡ (ገላ. 3፥6-9፣ 29)

4.2.2 ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ ሐብታም (ባለጸጋ) ነበረ?

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜው የተቀማጠለ ኑሮን አልኖረም። ወላጅ እናቱና ዮሴፍ እንደ ሙሴም ሕግ
መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። አንድን ሰው አንድን መሥዋዕት የሚያቀርበው እንዳለው ሃብት መጠን ነው።
በዚህ ክፍል የምንመለከተው ቅድስት ድንግል ማርያም መሥዋዕትን ለማቅረብ ከድሆች እንደ አንዲቱ መመደቧን ነው። (ዘሌ.
5፥7፤ 12፥8፤ ሉቃ. 2፥22-23) ኢየሱስ የተወለደው በቅምጥሉ ቤተ መንግሥት አልነበረም፤ በከብቶች ግርግም እንጂ። (ሉቃ.
2፥7) ከዚህ በተጨማሪ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ወቅት ቀኑን ሙሉ ካገለገለ በኃላ ሲመሽ ሰው ሁሉ ወደቤቱ ሲሄድ እርሱ ግን
41
ረጅሙን ጊዜውን ወደ ሚያሳልፍበት ቦታው ይሄድ ነበር። ደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን ኢየሱስ የሚያዘወትርበት ወይም
የሚያድርበት ቦታው ነበር። (ሉቃ. 21፥37፤ 22፥39፤ ዮሐ. 7፥53፤ 8፥1) ለዚያም ነው “ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት
የለውም” በማለት የተናገረው። (ሉቃ. 9፥58) የራሱ የሚባል ንብረት አልነበረውም፤ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በሰው ውርንጫ
ነበር፡፡ (ማር. 11፥2-3) ፋሲካን ያከበረው በሰው ቤት ነው፡፡ (ማር. 14፥13-14) ስምኦን፣ ዘኬዎስና እነ ማርታ በመሳሰሉት ቤት
እየገባ ያርፍና ይበላና ይጠጣ ነበር፡፡ (ሉቃ. 7፥36፣ 10፥38፣ 19፥1-10) የተቀበረውም በውሰት መቃብር ነበር፡፡ (ማቴ. 27፥57-60)

4.2.3 ስለ ብልጽግና የጌታችን ኢየሱስ ትምህርትና የተገለጠ ኑሮው

ትምህርቱ፦ በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ስለ መንግስተ ሰማይ እና ሲኦል ካስተማረው ይልቅ ስለ ገንዘብ ያስተማረው ይበልጣል፤
ኢየሱስ ሲያሰምር ከተጠቀመባቸው 39 ምሳሌዎች ውስጥ 16 ቱ ስለ ገንዘብ የሚናገሩ ናቸው። ኢየሱስ በትምህርቱ ብዙ
ስለብልጽግና የሚነገሩትን የተሳሳተ ምድራዊ መለኪያዎችና ትምህርቶችን ሁሉ በመገልበጥ ትክክለኛውን ትምህርት አስተማረ፡፡
ለምሳሌ፡- በትምህርቱ ሰዎች ሃብት በማከማቸት ከመደሰት ይልቅ በማካፈልና በመስጠት እንዲደሰቱ አስተማረ። (ማቴ. 19፥21፤
ሉቃ. 6፥38፤ 12፥15-21) ምጽዋት ስንሰጥ እያሰላን፣ ተትረፍርፎ እንደሚመጣ እያሰብን፣ ዋጋችንን ከፍ ከፍ እያደረግን ሳይሆን
በልግስና እንድንሰጥ አስተማረ። (ማቴ. 6፥2) በተለይም ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም ሲል፤ ገንዘብ
የእግዚአብሔር ያህል የመግዛትና ሁለንተናን የመቆጣጠር አቅም እንዳለው አስተማረ። (ማቴ. 6፥24፣ 13፥22) በዝባዥ
ባለጠጐችን ጌታችን ኢየሱስ በግልጥ ተቃወመ። (ማቴ. 19፥21-24፤ ሉቃ. 18፥18-24፤ ማር. 12፥41-44) መሻታችን ምድራዊ
ነገሮች ሳይሆኑ ሰማያዊ ነገሮች እንዲሆኑ ኢየሱስ አስተማረ፡፡ (ማቴ. 6፥19-21፤ ሉቃ. 12፥29-31) ገንዘብን ከመውደድ
እንድንጠነቀቅ አስተማረ። (ሉቃ. 12፥15) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ድኾች በእርሱ ዘመን ብቻ ሳይሆን ወደ ፊትም ሊኖሩ
እንዳላቸው ሲናገር “ድሆችስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥” በማለት ተናግሯል። (ዮሐ. 12፥8)

የተገለጠ ኑሮው፡- እጅግ ድኾች የሆንነውን እኛን በመዛመዱ ጌታችን ኢየሱስ ፍጹም ባለጠግነቱን አሳየ። (2 ቆሮ. 8፥9) ኢየሱስ
ሥጋ ለብሶ በሰው ልጆች መካከል በተመላለሰበት ወራቱ ስራ ፈትና ክፉዎች በበዙባት በናዝሬት ከተማ ለወላጅ እናቱና ለዘመዶቹ ይታዘዝላቸው
እንደ ነበር ተነግሯል፡፡ (ሉቃ. 2፥51) ጌታችን ኢየሱስ በትምህርቱ ቅንጡ ባለጠጐችን ሲነቅፍና ሲወቅስ፣ በተገለጠ ኑሮው ግን
ማንንም ሳይጠየፍ ሕሙማንንና ደካሞችን እየፈወሰና እየረዳ ከድኾች ጋር በመኖር አሳየ። (ማቴ. 4፥23፤ 26፥6-9፤ ሉቃ. 8፥47፤ ዮሐ.
4፥7-30፤ 5፥1-8)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት
ነበር” (ሉቃ. 8፥3) የሚለውን ንባብ አንብበን፤ “ዐምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን
ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል?” እስኪሉ ድረስ በእጃቸው ምንም እንዳልነበረ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ (ዮሐ. 6፥9)

4.2.4 ቅዱሳን ሐዋርያትና ብልጽግና

ሐዋርያት ከመንፈሳዊ የወንጌል አገልግሎት ባሻገር ሥራ ወዳድ ነበሩ። ለምሳሌ ሐዋርያ ጳውሎስ የተጠራለትን የወንጌል አደራ ፈጽሞ ሳይረሳ
የሰው እጅ ላለማየትና ላለመጠበቅ በነበረው የድንኳን መስፋት ሙያ ሥራ ተሰማርቶ በሚያገኘው ገቢ ራሱን ይችል ነበር። (ሐዋ. 18፥2-3፣
20፥33-35) ለዚህ ነው “ሊሠራ የማይወድ አይብላ ያለው” (2 ተሰ. 3፥10) ሐዋሪያት ባለጠግነትን ንቀው፣ ለክርስቶስ መኖርን እንደ ታላቅ
በረከትና ሕይወት ቆጠረው ነበር፤ ደግሞም በባለጠግነት የተቀማጠለም ሕይወት አልነበራቸውም፡፡ (1 ቆሮ. 4፥11-13፤ 2 ቆሮ. 11፥27፤ ሮሜ
8፥35፤ ፊልጵ. 4፥11-12፤ 1 ጢሞ. 6፥6-11) ጴጥሮስ፣ እንድሪያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ዓሣ አጥማጆች ነበሩ፡፡ (ማቴ. 4፥18)
42
ሐዋርያት ስለ ብልጽግና ሊኖረን የሚገባውን ትክክለኛ ትምህርት አስተምረውናል፡፡ ለምሳሌ ገንዘብን መውደድ ከመንግስተ ሰማይ እንደሚያጎድል፣
አማኞች ከገንዘብ ፍቅር ነጻ መሆን እንዳለባቸው፡፡ (1 ቆሮ. 6፥9-10፤ 1 ጢሞ. 6፥8-10) ፣ አማኞች ኑሮዬ ይበቃኛል ማለትን እንዲማሩ
አስተምረዋል፡፡ (ፊሊጵ. 4፥11-13፤ ዕብ. 13፥5) ፣ መሻታችን ምድራዊ ነገሮች ሳይሆን ሰማያዊ ነገሮችን እንዲሆን አስተምረዋል፡፡ (ቆላ. 3፥1-3)
፣ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች ፈተና፣ ስደትና መከራ እንደሚገጥማቸው አስተምረዋል፡፡ (2 ጢሞ. 3፥12፤ 2 ቆሮ. 6፥4-10፣ 11፥23-30፤
ፊሊጵ. 1፥29)

በሐዋርያት ዘመን በአማኞች መካከልም ድኾች እንዳይኖሩና እንዳይጐዱ አንዱ ቤተ ክርስቲያን ወይም በአንድ አገር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በሌላ
አገር ወይም አጠገባቸው ያሉትን ድኾች እንዲረዱ በቀደመችይቱ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ምስክርነትና መንፈሳዊ ውበቷም ነበር፡፡ (ሐዋ. 4፥33-
35፤ ሮሜ 15፥26-27፤ 2 ቆሮ. 8፥1-3፤ ገላ. 2፥10)

4.3 ስለ ዝራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ

ወርቃማው የጌታችን ኢየሱስ የስጦታ መመሪያ ከዝራ በፍጹም ተቃራኒ የቆመ ነው፤ ፈሪሳውያን ስጦታን ይሰጡ ነበር። ጌታችን
ኢየሱስ መስጠታቸውን አልነቀፈም፤ ነገር ግን ይሰጡበት የነበረው መንፈስ እንደ ቅዱስ ቃሉ ትክክል አልነበረም። በስጦታቸው
በእግዚአብሔር ፊት ለመወደድ፣ በሰዎች ፊት ለመከበርና ለታይታ ያደርጉት ነበር። (ማቴ. 6፥2-4) የቀደመችይቱ ቤተ ክርስቲያን
አማኞች ሳይሳሱ በአደባባይ ይሰጡ ነበር፤ ትንሽም ብዙም የሰጠው ከሌላው ጋር እኩል ይከፋፈል ነበር። በአደባባይ አምጥተው
መስጠታቸው የጌታን ሕግ መቃረናቸው አልነበረም። ዋና ዐላማቸው ሰውን ማስደሰት ሳይሆን እግዚአብሔርን ከሚያከብር ልብ
በፈለቀ ደስታ ነበርና። (ሐዋ. 4፥34-35)

ስጦታን ስንሰጥ በአቅማችንና የቻልነውን ያህል ብቻ ነው መስጠት ያለብን፡፡ ፡፡ (1 ቆሮ. 16፥2) እጅግ የበረቱት አማኞች ደግሞ
ከጉድለታቸውም እንኳ አትረፈው ይሰጣሉ፡፡ (2 ቆሮ. 8፥1-3) ስለዚህ መስጠት ካለብን “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን
ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም” (2 ቆሮ. 9፥7) እንዲል፣ ልግስናና ስጦታ ስሌት አልባ
እንጂ በፍጹም አትርፎ ለመቀበል አይደለም። ስጦታችን ለጌታ ያለንን ፍቅርና አክብሮት አመላካች ነው፤ በተጨማሪ መስጠት
አምልኮ ነው፡፡ ሰው እውነተኛ የልብ መለወጥ ሲኖረው ገንዘቡን፣ ጊዜውን፣ እውቀቱን ለጌታ ይሰጣል፡፡

4.4 ድህነት የመረገምና ያለማመን ውጤት ነውን?

በብሉይ ኪዳን ጊዜ የእስራኤል በረከት የተያያዘው እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ጋር ነበር፤ ሕጉን ሲተላለፉ ክፉ ነገር ይገጥማቸው
ነበር፡፡ (ዘዳ. 28፥1-68) ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ሐዋርያቱ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልባቸው
ተገዝተው ቢኖሩም በተለያያ ችግርና ድህነት ውስጥ አልፈዋል፡፡ (1 ቆሮ. 4፥9-13) በተጨማሪም ሀብታሞችም ሆኑ ድሆች
ከክርስቶስ ውጪ ኃጢአተኞች ናቸው፡፡ (ሮሜ. 3፥9-11) አዲስ ኪዳን ድህነትና ባለጸግነት ሁለቱም በየራሳቸው የመርገም ወይም
የበረከት መንገዶች ስለ መሆናቸው አይነግረንም፤ ማጣትን እንደ መርገም ወይም ያለማመን መንገድ አድርጎ አላቀረበም።
(1 ቆሮ. 11፥22፤ 1 ጢሞ. 6፥18-19፤ ያዕ. 2፥5) “ባለጠጋና ድሀ ተገናኙ፤ እግዚአብሔር የሁላቸው ፈጣሪ ነው።” (ምሳ. 22፥2)
እንደሚል እግዚአብሔር አምላክ ድኾች ብንሆንም፤ ባለጸጐች ብንሆንም አምባችንና መጠጊያችን ነው።

4.5 ክርስትያኖች ሀብታም ሊሆኑ አይችሉም ማለት ነው?

43
ፈጽሞ አይደለም! ክርስቲያኖች ሀብታም/ባለጸጋ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በሰጣቸው ችሎታ፣ ሙያ፣
ክህሎት ወይም እውቀት በመጠቀም በትጋት መስራት አለባቸው፡፡ ይህ ፈጽሞ ኃጢአት አይደለም፡፡ ምድራዊ ሀብትን
እንገለገልበታለን፤ እንጠቀምበታለን እንጂ ብልጽግና ከሰይጣን፣ ሃብትም ከዲያብሎስ ነው በማለት በማያመዛዝን ዕይታ
መመላለስ የለብንም። እግዚአብሔር ሃብትን፣ ገንዘብን ይሰጣል፤ ይባርካልም፡፡ (መክ. 2፥25፤ 3፥13) ከእግዚአብሔር እጅ በደስታ
ያልተቀበልነው የትኛውም ሕይወት ትርጉም ሊሰጠን፤ እርካታና ተድላ ሊሆነን አይችልም። ክርስቲያን በእግዚአብሔር ገንዘብ
ላይ የተሾመ ባለአደራ እንጂ ሀብቱ የራሱ እንዳልሆነ ማወቅ አለበት፡፡ (መዝ. 24፥1፤ ማቴ. 25፥14-30፣ 35-40) የቱንም ያህል
ሀብት ቢኖረን መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዓለም ነገር በመጠን፣ በልክ፣ ኑሮዬ ይበቃኛል በማለት እንድንኖር ያስተምረናል፡፡ (1 ተሰ.
5፥6-8፤ 1 ጢሞ. 6፥6-8፤ 2 ጢሞ. 4፥5፤ 1 ጴጥ. 1፥13፤ 4፥8፤ 5፥8) በተጨማሪም ሀብት ወደ ኩራትና ትዕቢት ሊመራ
እንዲሁም እግዚአብሔርን እንድንረሳ ሊያደርግ ስለሚችል መጠንቀቅ አለብን፡፡ (ዘዳ. 8፥12-17፤ መዝ. 62፥10፤ ሕዝ. 28፥5፤
ሆሴ. 13፥6) ብልጽግና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚሰጥ ብናምንም፣ ሳንሠራ ወይም ልንሠራ ሳንወድድ፣ ወዛችንን ሳናፈስስ፣
በማጭበርበር፣ በወንጌል ሽፋን፣ በአገልጋይ ስም፣ በአገልግሎት አስባብ … የግል ኑሮአችንን ለማሟላት ወይም በቅምጥልነት
ለመኖር እንዲያው ዝም ብለን ከሰማይ እንደሚወርድ ነገር፣ ያስፈለገንን ባስፈለገን መንገድ በቃላችን በማዘዝና በመናዘዝ
ለማምጣት አንዳፈርም ወይም አንጠብቅም። እንደ እግዚአብሔር ዐሳብና ፈቃድ፤ ቅዱስ ቃሉም እንደሚያዝዘን ወዝ እያወጣን
እንሠራለን፤ አሥራትን እናወጣለን (ምናልባትም እንደ ብሉይ ኪዳን ብቻ ሳይሆን አትርፈን! አትረፍርፈን!) ፣ የመንግሥትን
ግብር በአግባቡ እንከፍላለን እንጂ አናጭበረብርም … በእነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያበለጽገን፣ ሀብት
እንደሚሰጠንና የእጆቻችንን ስራ እንደሚባርክ እናምናለን። (ዘዳ. 2፥7፤ ምሳ. 14፥23)

ምዕራፍ አምስት፡- በሽታ እና ፈውስ


የልዩ ወንጌል መምህራን ስለ በሽታና መለኮታዊ ፈውስ ብዙ ዐይነት አስተምህሮ ቢኖራቸውም በጥቂቱ ይህን ይመስላል፡፡
ትምህርታቸው በአጭሩ ክርስቲያን መታመም የለበትም፤ በሽታ ሰይጣን በእኛ ላይ ያስቀመጠው ቀንበር እና በሕግ በኩል
የመጣብን እርግማን ነው፡፡ ኢየሱስ የሕግን እርግማን ከላያችን ስላነሳልንና የማዳን ስራ ውስጥ አካላዊ ፈውስ ስላለ ከበሽታ ነጻ
የማንወጣበት አንዳችም ምክንያት የለም ይላሉ፡፡ በተጨማሪም በሽታ ሁሉ የሚመጣው ከሰይጣን መንፈሳዊ ዓለም ነው ስለዚህ
በሽታ መንፈሳዊ እንጂ ስጋዊ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ ሲቀጥልም አማኝ ለበሽታ ሊጋለጥ የሚችልበት አንዱ የተረጋገጠ
መንገድ አሉታዊ ቃል መናገር ነው፡፡ በትምህርቱ መሰረት በሽታ መኖሩን በአእምሮ ማመን ወይም በቃላት መግለጽ ለሰይጣን
ዕድል ይሰጠዋል ተብሎ ይታመናል ስለዚህ የልዩ ወንጌል አማኞች የበሽታ ምልክቶች እያዩ እንኳን ተፈውሻለሁ ብለው
እንዲያምኑና ምንም አይነት ሕክምና እና መድሐኒት እንዳይወስዱ ይደረጋሉ፡፡ ከዚህም ባስ ሲል አካለ-ስንኩልነት የመንፈስ
ቅዱስን ስራ እንደሚያደናቅፍና፤ አማኞች ከ 70 ዓመት በፊት መሞት የለባቸውም በማለት ያስተምራሉ፡፡ የልዩ ወንጌል
መምህራን በአንዱ በኩል አማኝ መታመም የለበትም ይበሉ እንጂ በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ፈውስ ብዙ ያስተምራሉ፡፡ ለፈውስ
በሚል ልዩ ልዩ ሸቀጦችን ከመሸጥ ጀምሮ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌላቸው ልምምዶችን ይከተላሉ፡፡ “ያልተፈወስከው
እምነት ስለሌለህ ነው” የምትለው ቃል የልዩ ወንጌል መምህራን ደጋግመው የሚናገሩት ቃል ነው፡፡ በአገልግሎታቸው
ከእግዚአብሔር ቃል (ወንጌል) ይልቅ ይህ የፈውስ አገልግሎት ትልቅ ስፍራ ይሰጠዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን የስህተት ትምህርት
ለመደገፍ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶቸ መካከል ፡- (ዘጸ. 15፥ 26፣ 23፥25፤ ዘዳ. 7፥15፤ ኢሳ. 53፥5፤ መዝ. 103፥3፤ ገላ. 3፥13፤ 3
ዮሐ. 1፥2 ከትምህርቱ ሰፊነት የተነሳ የእነዚህን ጥቅሶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን በዚህ ምዕራፍ ላይ መመልከት ስለማንችል
አስተማሪው በዋቢ ላይ ከተጠቀሱት መጽሐፍት የጥቅሶቹን ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት ይችላል)

44
5.1 በሽታ ምንድር ነው?

በሽታ፣ ደዌና ሕመም በኃጢአት ምክንያት ወደ ዓለም እንደገባ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ዘፍ. 3፥16፣ 16-17፤ ሮሜ.
5፥14) ከመጀመሪያ ለሰው ልጅ በሽታ እና ሞት የእግዚአብሔር ሐሳብ አልነበረም፡፡ (ዘፍ. 1፥31) እንግዲህ በሽታ ማለት
የሰውን ስጋዊና አእምሮአዊ አካል የሚያጠቃ ስቃይ፣ ድካም፣ ከባድ ሕመም ሲሆን፤ ብዙ ጊዜ የሚታይ አንዳንዴ ለታማሚው
እንጂ ለሌላው የማይታይ አእምሮአዊ ወይም አካላዊ ወይም በጠቅላላው ማኅበራዊ ዋስትናን ማጣት ነው። በመጽሐፍ
ቅዱስ የተጠቀሱ አራት አይነት በሽታዎች አሉ፡፡ እነርሱም፡- የቆዳ በሽታ፣ የአእምሮ (አንጎል) በሽታ፣ ከአጋንንት የሚመጡ
እና ልዩ ልዩ የሰውነት በሽታዎች ናቸው፡፡ (ዘሌ. 26፥16፤ ዘዳ. 28፥22፣ 27-28፤ ማቴ. 4፥24፤ ሉቃ. 7፥21፤ ማር. 1፥34)
ከእነዚህ በሽታዎች ውስጥ የተወሰኑት በስም ተጠቅሰው እናገኛለን ለምሳሌ፡- የአመንዝራ ቁስል (ምሳ. 6፥32-33) ፣
የአይምሮ በሽታ (ዳን. 4፥33) ፣ ፍርሃት፣ ክሳት፣ ዓይንን የሚያፈዝዝ፣ ሰውነትን የሚያማስን ትኩሳት (ዘሌ. 26፥16) ፣ ንዳድ፣
ጥብሳት፣ እባጭ፣ ቋቁቻ፣ ችፌ፣ ዕብደት፣ ዕውርነት፣ ድንጋጤ፣ የዘርህን መቅሠፍት፣ ብዙ ዘመንም የሚኖር ታላቅ
መቅሠፍትና ክፉ ደዌ (ዘዳ. 28፥22፣ 27፣ 59፤ ሉቃ. 7፥21) ፣ በጨረቃ የሚነሳ/ የሚጥል በሽታ (ማቴ. 4፥24፤ 17፥14-15) ፣
ሽባነት/ አንካሳነት (ማቴ. 4፥24) ፣ የሆድ በሽታ (1 ጢሞ. 5፥23) ናቸው፡፡

5.2 በሽታና ፈውስ በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር እርሱን ሲከተሉና ሕጉን ሲታዘዙ ሕዝቡን ከበሽታ እንደሚያድናቸው ተስፋ ሰጥቶ ነበር፡፡ (ዘጸ.
15፥26፤ ዘዳ. 7፥12-15) እንዲሁም እግዚአብሔርንና ሕጉን በማይታዘዝ ሕዝብ ላይ ወይም ኃጢአት ሲፈጽሙ በሽታ እንደ
ቅጣት ይመጣ ነበር፡፡ (ዘሌዋ. 26፥14-16፤ ዘዳ. 28፥20-21፣ 27፣ 58-61፤ ኤር. 24፥10) ነገር ግን እግዚአብሔርን በመፍራት
በጽድቅ እየኖሩም በተለያየ በሽታ እና ስቃይ ውስጥ ያለፉ ቅዱሳን እና አገልጋዮች በብሉይ ኪዳን ዘመን ነበሩ፡፡ (2 ነገ.
13፥14፤ ኢዮብ. 1፥1፣ 2፥7) እንዲሁም አካላቸው ጎድሎም ከነጉድለታቸው እግዚአብሔር ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ (1 ነገ.
14፥4) በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ያለውን የተለያየ በሽታ አገልጋዮቹን/ነብያቶችን እና ባለመድኃኒቶች
(ሐኪሞችን) እየተጠቀመ ይፈወስ ነበር፡፡ (1 ነገ. 17፥19-22፤ 2 ነገ. 4፥32-35፤ ኢሳ. 38፥5-9፤ 2 ዜና. 16፥12፤ 2 ነገ. 20፥5-
7) በብሉይ ኪዳን ዘመን ከመለኮታዊ ፈውስ ባሻገር ልዩ ልዩ የተቀመመ ሽቱ፣ የበለስ ጥፍጥፍ፣ መጻጻ፣ ዘይትና ሌሎችም
ዕፅዋትን ለመድኃኒትነት ይጠቀሙ ነበር፡፡ (ኢሳ. 38፥21፤ ሕዝ. 47፥12፤ ኤር. 8፥22፤ ዘፍ. 50፥2) ሌላው በብሉይ ኪዳን
መጽሐፍት እንደምናየው ለእግዚአብሔር ሕዝብ በሚመጣው የእግዚአብሔርን መንግስት እንጂ ፍጹም የሆነ ሁለንተናዊ
ፈውስ በዚህ ምድር ላይ ተስፋ እንዳልተገባ ግልጽ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ (ኢሳ. 25፥6-8፣ 33፥24፣ 65፥19-20)

5.2 በሽታና ፈውስ በአዲስ ኪዳን

አዲስ ኪዳን በኢየሱስና በሐዋሪያት የፈወስና የተአምራት ስራዎች የተሞላ ታሪክ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በወንጌላትና በሐዋርያት ሥራ
መጽሐፍ ውስጥ የዚህን እውነትነት እንመለከታለን። (ማቴ. 4፥24፣ 8፥16-17፤ ማር. 1፥32-34፤ ሉቃ. 7፥21፤ ዮሐ. 5፥4-9፤ ሐዋ.
5፥16፣ 28፥8) በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ ቅዱሳን እንደማይታመሙ የተገባ ኪዳን የለም። እንዲያሁም የጌታ
አገልጋዮች ሐዋርያት እንኳ ሳይቀሩ በተለያየ ሕመምና ደዌ ውስጥ እንዳለፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል። (ሐዋ. 9፥36-37፤
ፊልጵ. 2፥25-27፤ 2 ቆሮ. 12፥7፤ ገላ. 4፥13-16፣ 6፥11፤ 1 ጢሞ. 5፥23) በተለያየ በሽታዎች ውስጥ እያለፉም ጌታ
ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ እንዲሁም ፈውስና እምነት የተያያዙ መሆናቸውን በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት እንመለከታለን፤

45
እምነታቸውን በራሳቸው እምነት ላይ ሳይሆን በፈዋሹ ኢየሱስ ላይ ያደረጉ ሰዎች ፈውሳቸውን ተቀብለዋል፡፡ (ማቴ. 9፥20-22፣
9፥27-29፤ 15፥28፤ ሉቃ. 17፥19፤ ማር. 10፥51-52) ነገር ግን ለመፈወስ (ፈውስን ለመቀበል) እምነት ሁሉጊዜ ቅድመ ሁኔታ
አይደለም፤ እምነት ሳይኖራቸውም የተፈወሱ ነበሩ፡፡ (ማር. 5፥1-15፤ ሉቃ. 7፥12-15፤ ዮሐ. 5፥5-8፤ 11፥3-44) በአዲስ ኪዳን
መጽሐፍት ወደ ጌታ ኢየሱስ እና ሐዋርያት የመጡ ሕሙማንና ድውያን ሁሉም የተፈወሱበት ታሪኮችን እናነባለን፡፡ (ማቴ.
8፥16-17፤ ማር. 6፥56፤ ሐዋ. 5፥16) በሌላ ታሪክ ደግሞ ሁሉ ሕሙማን እንዳልተፈወሱ እንመለከታለን፡፡ (ዮሐ. 5፥3-6፤ ሉቃ.
4፥25-27፤ 2 ጢሞ. 4፥20) በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንደ ሉቃስ ያሉ ባለመድኃኒተኞች ነበሩ (ቆላ. 4፥14) ፤ የወይን ጠጅና
ዘይትም ለመድኃኒትነት ይውሉ እንደ ነበር የአዲስ ኪዳን ምንባባት ይገልጻሉ፡፡ (ሉቃ. 10፥34፤ 1 ጢሞ. 5፥23) የጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ቤዛነት የተጠናቀቀና “አዲስና ሕያው መንገድ ተመርቆ የተከፈተልን” (ዕብ. 10፥19) ቢሆንም፤ ወደ ተዘጋጀልን
ዘላለማዊ መንግሥቱ ገና ስላልገባን አማኝ ሊታመም የሚችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፤ በአዲስ ኪዳን እንደማንታመም
የተገባልን ኪዳንም የለም። (ሮሜ 8፥18-22፤ ዮሐ. 16፥33፤ 1 ጴጥ. 5፥10፤ ራእይ 21፥3-4)

5.3 የኢየሱስ ተአምራቶችና ፈውሶች

ክርስቶስ ሲመጣ ብዙ ተአምራትንና ፈውሶች እንደሚያደርግ ትንቢት ተነግሮለት ነበር፡፡ (ኢሳ. 61፥1-3) የተነገረውንም ትንቢት
በመምጣቱ ፈጽሞታል፡፡ (ሉቃ. 4፥17-21) የመንግሥቱ ወንጌል፣ ስብከትና ፈውሱ አንድ ላይ የተያያዙ እንጂ የተነጣጠሉ
አልነበሩም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትንና ፈውሶችን የሚያደርገው፤ ብዙ ሰዎችም ከመንግሥቱ ወንጌል ጋር
ለማያያዝ ነበር። (ማቴ. 4፥23-24፤ 9፥35፤ ማር. 1፥21-28፤ 39፤ 2፥2-12፤ ሉቃ. 4፥15፤ 31-40) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የተላከበትና በፈቃዱ የመጣበት ዋና ተልእኮው “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” (ሉቃ. 19፥10) ከሚለው
ንግግሩ እንደምንረዳው፤ ማዳንና የሰው ልጅን ከጠፋበት መመለስ ነው። በዚህ ታላቅና የከበረ መለኰታዊ ሥራ ውስጥ
ተአምራትና ፈውስ የሥራው ማጽኛና ምስክር ሆኖ ቀርቧል። ጌታችን ኢየሱስ ከመንግሥቱ ወንጌል ነጥሎ ተአምራት ለማድረግ
ብቻ ተአምራትን ፈጽሞ አላደረገም። (ማቴ. 4፥3፤ ሉቃ. 23፥8-9፤ ዮሐ. 18፥36) እንዲያውም አንዳንድ ሥፍራዎች ላይ
የመንግሥቱን ወንጌል መስማት ሳይፈልጉ በአለማመን ልባቸውን አደንዝዘው ተአምራት ብቻ ለጠየቁ ወገኖች ፈጽሞ
ተአምራትን አላደረገም። (ማቴ. 12፥38-39፤ ማር. 6፥5-6)

5.4 ጌታችን ኢየሱስ እንዴት ፈወሳቸው?

ጌታችን ኢየሱስ የፈወሰበት መንገድም አንድ ዐይነት ሳይሆን ልዩ ልዩና እንደ ፈቀደው ነበር፡፡ ይኸውም፡-
 በርቀትም በቅርበትም ያሉትን በጩኸት ቃል ወይም በቃል ብቻ፡፡ (ማቴ. 8፥16-17፤ ማር. 9፥25፤ ዮሐ. 4፥50-52)
በተግሳጽ ቃል (ማር. 1፥24-25፤ ሉቃ. 4፥39)
 ጨርቁን የዳሰሱትም ዳኑ፡፡ (ማር. 5፥25-34፤ 6፥56)
 እጅ ይዞ በማስነሣት፡፡ (ማር. 5፥41-42፤ ሉቃ. 8፥54)
 እጁን ጭኖ፡፡ (ማር. 6፥5፤ ሉቃ. 4፥40)
 የተናገራቸውን እንዲፈጽሙ በማዘዝ፡፡ (ሉቃ. 17፥12-15)
 በእጁ ዳስሶ፡፡ (ሉቃ. 5፥13፤ 22፥51) በጣቶቹ በመዳሰስ (ማር. 7፥33)
 በምራቁ ትፍታ ወይም ምራቁን ከጭቃ ደባልቆ ፈወሳቸው። (8፥22-25)

5.5 የሐዋርያት ተአምራቶችና ፈውሶች


46
ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ከማረጉም በፊት “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን
አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ በከንቱ ስጡ።” በማለት የእግዚአብሔርንም መንግሥት
እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ልኳቸው ነበር። (ማቴ. 10፥7-8) የላካቸው ለእግዚአብሔር መንግሥት ሥራና ለፈውስም
ነው። ሁልጊዜም የመንግሥት ወንጌል ሥራ ቀዳሚና ዋነኛው ነው። ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በስሙ
ሥልጣን ፈውስና ተአምራትን አድርገዋል፡፡ (ሐዋ. 8፥5-8) በቅዱሳን ሐዋርያት እጅ ታላላቅ ፈውስና ተአምራት ሲደረጉ፤
ከፈውሱና ከተአምራቱ በፊት ሁልጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ወንጌሉ ይሰበካል፤ በመጨረሻውም ደግሞ ሰዎች
በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያምናሉ፣ ርኩሳን መናፍስት አጋንንት በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ይወጣሉ፣ ሰዎች
ይፈወሳሉ፣ ጠንቋዮች ይዋረዳሉ፣ እግዚአብሔር በታላቅ ፍርሃት ይከበራል፤ ብዙ የሚድኑ ነፍሳትም ይጨመራሉ፡፡ (ሐዋ. 3፥1-
10፤ 9፥33-35፤ 36-43፤ 13፥7-12፤ 14፥8-15፤ 16፥16-18፤ 25-34፤ 19፥11-12፤ 20፥9-12፤ 28፥8፤ 1 ቆሮ. 12፥11፤ 2 ቆሮ.
12፥12፤ ዕብ. 2፥4)

5.6 ሐዋርያት እንዴት ፈወሱ?

የቅዱሳን ሐዋርያት የፈውሳቸው እና የተአምራታቸው ምንጭ ከሞት የተነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወንጌልን
ሲሰብኩ ድውያንን በመፈወስ የሚሰብኩትን ወንጌል እንደ ሚያጸኑ አስቀድሞ ለአሥራ ሁለቱ በኋላም ለሰባው ደቀ መዛሙርት
የተናገረውና ያደረገው ጌታችን ኢየሱስ ነው፡፡ (ሉቃ. 9፥1-2፣ 10፥8-10፤ ዮሐ. 14፥12፤ 2 ቆሮ. 12፥12)

ሲፈውሱም የቃላቸውን ሥልጣን ወይም እምነታቸውን በመታመን አልተጠቀሙም። ሙሉ ለሙሉ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ስምና ሥልጣን በመታመንና በመደገፍ እንጂ። በማናቸውም ዐይነት መልኩ የተአምራቱንና የፈውሱን ክብር ለራሳቸው ሊጠቀሙ
አልፈለጉም፤ ሰዎች ክብርን ሊሰጧቸው ባሉ ጊዜም፤ ወደራሳቸው የመጣውን ማናቸውንም ክብር ተቃውመዋል። (ሐዋ. 3፥12፣
16፤ 14፥11-15)

በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ሥልጣን በመታመን ሐዋርያት የፈወሱበት መንገድ አንድ ዐይነት ሳይሆን ልዩ ልዩ ነበር፡፡
ይኸውም፡-
 “በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም” (ሐዋ. 3፥6)፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል” ብለው በቃላቸው በመናገር፡፡ (ሐዋ.
9፥34)
 ሐዋርያው ጴጥሮስ በጥላው፡፡ (ሐዋ. 5፥15-16)
 ቅዱስ ጳውሎስ በጨርቁ እራፊ፡፡ (ሐዋ. 19፥11)
 በጸሎት ኃይል ፈውሰዋል። (ሐዋ. 9፥40)
 እጅ በመጫን፡፡ (ሐዋ. 28፥8)
 ዘይት በመቀባት፡፡ (ማር. 6፥13)
የመፈወሳቸው ትልቁ ዐላማና ውጤቱ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው፣ “ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ
ሲመላለስ አዩት፤ … ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፤ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ” (ሐዋ. 3፥9፤ 4፥4) ፣
“የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ” (ሐዋ. 5፥14) ፣ “… የጌታም የኢየሱስ
ስም ተከበረ፤ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር …ከአስማተኞችም ብዙዎች
መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት… እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር” ተብሎ በድምቀት
ተገልጧል። (ሐዋ. 19፥17-20)

47
5.7 አማኝ አይታመምምን?

በክርስቶስ ቤዛነት መዳናችን ታውጇል ነገር ግን ፍጹም ባልተዋጀው ዓለም እየኖርን ስለሆነ አማኝ ሊታመም የሚችልበት ብዙ
መንገዶች አሉ። ከእግዚአብሔር አምላክ ጋር ያለን ግንኙነት “ፍጹም የጠራና እንከን የሌለበት” ቢሆን እንኳ ልንታመምና
የማይድን በሽታም ሊያገኘን ይችላል። (2 ነገ. 13፥14) ስለዚህ መታመም በራሱ ብቻውን የኃጢአትና የአሉታዊ ቃል ውጤትም
አይደለም። በሽታ መነሾ ምክንያቱ ብዙ ሊሆን ይችላል።
ሀ/ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከአጋንንት ውጊያ የተነሣ፡፡ (ኢዮብ 2፥6-7፤ 2 ቆሮ. 12፥7)
ለ/ ከኃጢአት የተነሳ ፡፡ (መዝ. 32፥10፤ ያዕቆ. 5፥13-16)
ሐ/ በተፈጥሮና በልዩ ልዩ መንገድ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትና ጌታችን ኢየሱስ በአጋንንትና በኃጢአት ከሚመጣው በሽታና ደዌ ሌላ፤
በሽታ በልዩ ልዩ መንገድ እንደሚመጣ አስተምረዋል። “በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ ብዙዎችንም አጋንንት
አወጣ” (ማር. 1፥34) ልዩ ልዩ የተባሉት ለምሳሌ፡ በተፈጥሯዊ መንገድ ሰዎች ሲያረጁና እጅግ ሲሸመግሉ የሚመጡ በሽታዎች
አሉ፡፡ (ዘፍ. 27፥1፤ 1 ሳሙ. 4፥18) ፣ ከውፍረት የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች አሉ፡፡ (መሳ. 3፥17) ወይም ተገቢውን ጥንቃቄ
ካለማድረግ፣ ንጽሕናን ካለመጠበቅ፣ በተላላፊ የሚከሰቱ በሽታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ በሽታን ካለማመንና ከኃጢአት ጋር
ብቻ ማያያዝ የቅዱሳት መጻሕፍት እይታ ሳይሆን የሰዎች እይታ ብቻ ነው ሊሆን የሚቻለው።

5.8 ስንታመም ምን እናድርግ?

ሀ/ ለፈውስ እንጸልይ፦ የጌታችን ኢየሱስ ስም ዛሬም አዳኝና ፈዋሽ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ እንዲፈውሰን ሳንታክት በእምነት
እንጸልይ፡፡ (ሉቃ. 18፥1፤ ዕብ. 13፥8)
ለ/ ትክክለኛ የፈወስ ስጦታ ካላቸው ጋር እንጸልይ፡- የጸጋ ስጦታዎች ለአካሉ የተሰጡት ቅዱሳንን ለማገልግል ስለሆነ
እውነተኛ የፈውስ ስጦታ ካላቸው ጋር በግልም ሆነ በሕብረት እንጸልይ፡፡ (ያዕቆ. 5፥14-15፤ 1 ቆሮ. 12፥28)

ሐ/ እንታከም፡- የልዩ ወንጌል መምህራን ሕክምናን መከታተል ከክርስትና ጋር ፈጽሞ ተቃራኒ እንደ ሆነ ያስተምራሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ግን ለሕመምና ለደዌ እንደ መፍትሔ ከተሰጡ ነገሮች አንዱ ሕክምናን መከታተል እንደሆነ ወይም መጽሐፍ
ቅዱስ ሕክምናን እንደማይቃወም ከላይ ተመልክተናል። እግዚአብሔር በመድኃኒትና በሕክምና ባለሙያዎች በኩልም
እንደሚሠራ እናምናለን።

መ/ ከነሕመም መቈየት፡-ፈውስንና አካላዊ መዳንን ባናገኝ እንኳ በእርሱ ጸንተን ልንኖር ይገባናል፡፡ (ዮሐ. 15፥1-7) አንዳንዴ
በዚህ ጉዳይ ሌሎችን እየፈወስን ለራሳችን ግን እንደ መውጊያ ሊሰጠን ይችላል። ቅዱስ ጳውሎስ “ፈዋሽና ከሕመም ገላጋይ”
ቢሆንም በተመሳሳይ ችግር ውስጥ አልፏል (2 ቆሮ. 12፥7፤ ገላ. 4፥13-14) “አፍሮዲጡን እንደ ታመመ” ሰምቶ ምንም
አላደረገም (ሐዋ. 19፥11፤ ፊልጵ. 2፥25-27) ፣ “ጥሮፊሞስም ታሞ በሚሊጢን ትቶታል” (2 ጢሞ. 4፥20) ፣ ቅዱስ
ጢሞቴዎስንም ቢሆን ከመፈወስ ይልቅ “የሚያስታግሰውን ነገር” እንዲወስድ ብቻ ነው የመከረው፡፡ (1 ጢሞ. 5፥23) ። አዎን!
እግዚአብሔር አምላክ እንዲህም እንድናልፍ ይፈቅዳል!

48
ሠ/ ሞትም መፍትሔ ነው፡- ይህ ለብዙዎች ከባድና የማይመስል ነገር ቢሆንም፤ ለበሽታ ግን መፍትሔና በተለይ በክርስቶስ
ለዳኑ ቅዱሳን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሄጃ መንገዳቸው ነው። (ፊልጵ. 1፥21-23)

ምዕራፍ ስድስት፡- እምነት፣ አዎንታዊ አዋጅና ጸሎት

እንደ ልዩ ወንጌል አስተምህሮ እግዚአብሔር ራሱ እምነት አለው ብለው ያምናሉ፡፡ እግዚአብሔር ያለ እምነት ምንም ነገር ሊሰራ
አይችልም በማለት ያስተምራሉ፡፡ ይህን አይነቱን እምነት እግዚአብሔር ለቅዱሳን ሰጥቶአቸዋል ስለዚህ ክርስቲያኖች ያላቸው
እምነት እንደ እግዚአብሔር አይነት እምነት ነው፡፡ በተጨማሪም ከእግዚአብሔር ዘንድ ምንም ነገር የሚፈልግ ሰው፤ በእምነቱ
ላይ እምነት ሊኖረው ይገባል ብለው ያስተምራሉ፡፡ እንደ ልዩ ወንጌል አስተምህሮ እምነት ብቻ ሳይሆን፤ ከአንደበታችን የሚወጡ
ንግግሮች ኃይል ስላላቸው ማንኛውንም ነገር በቃል በመናገር (አዎንታዊ አዋጅ) በማወጅ ማግኘት እንችላለን ብለው ያምናሉ፡፡
እግዚአብሔር በመናገር ነገሮችን እንደ ፈጠረ፤ ሰውም በንግግሩ ሊፈጥር ይችላል ይላሉ፤ ስለዚህም አዎንታዊ አዋጆችን እንድናውጅና፤ ምንም
አይነት አሉታዊ ንግግሮችን እንዳንናገር ያስጠነቅቁናል። ከዚህ በተጨማሪ ክርስቲያንም ሆነ ክርስቲያን ያልሆነ ሰው እነዚህን አራት
የእምነት ሕግ መመሪያዎች በተግባር ካዋለ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚፈልገውን ያገኛል ብለው ያምናሉ፡፡ የእምነት ሕግ
መመሪያዎች 1. ተናገር 2. አድርግ 3. ተቀበል 4. አውጅ የሚሉ ናቸው፡፡ (በእንግሊዘኛው 1. Say it 2. Do it 3. Receive it 4.
Tell it በልዩ ወንጌል አማኞችና መምህራን ዘንድ ስለ ጸሎት ሲያስተምሩ የምንፈልገውን ነገር በቀጥታ በቃላችን አማካኝነት
አምነን ማድረግ እንጂ ፈቃድህ ይሁን ብሎ ጸሎትን መጸለይ ኃይማኖተኝነትን እንጂ አማኝነትን አይገልጽም ይላሉ፡፡
እግዚአብሔር ቀድሞውንም ቢሆን በክርስቶስ የመስቀል ስራ ደህንነትን፣ ፈውስን እንዲሁም ብልጽግናን ሰጥቶናል፡፡ የሰጠንን ነገር
ስጠን እንዲሁም የተደረገውን ነገር አድርግ ብሎ መጸለይ የኃይማኖተኝነት ምልክት ነው ይላሉ፡፡ ለእነርሱ ጸሎት ማለት
እግዚአብሔርን መጠየቅ (መማጸን) ሳይሆን እግዚአብሔርን ማዘዝ ነው፡፡ በትምህርቱ ምድር ለሰው ግዛትነት ስለተሰጠች፤ እግዚአብሔር
በዚህ ምድር መሥራት ቢፈልግ የግድ የሰውን ትብብር እንደሚፈልግ ይቆጠራል። በዚሁ አመለካከት እግዚአብሔር ያለ ሰው ልጅ እርዳታ በዚህ
ምድር መስራት ከፈለገ “ህገ ወጥ” ይሆናል፡፡ እኛ ካልፈቀድንለት በስተቀር እግዚአብሔር በዚህች ምድር ምንም ማድረግ አይችልም፤ ለእርሱ ፈቃድ
የምንሰጠውም በጸሎታችን ነው የሚል ትምህርት አላቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን የስህተት ትምህርት ለመደገፍ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶቸ
መካከል ፡- (ዘፍ. 1፥3፤ ምሳ. 6፥2፣ 18፥20-21፤ ማቴ. 12፥37፤ ማር. 11፥ 23፤ ሉቃ. 11፥2፤ ዮሐ. 14፥ 13-14፣ 15፥7፤ ሮሜ.
10፥10፤ ዕብ. 11፥3 ከትምህርቱ ሰፊነት የተነሳ የእነዚህን ጥቅሶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን በዚህ ምዕራፍ ላይ መመልከት
ስለማንችል አስተማሪው በዋቢ ላይ ከተጠቀሱት መጽሐፍት የጥቅሶቹን ትክክለኛ ትርጉም ማግኘት ይችላል)

6.1 ስለ እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ

ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን ማዕከሉ እምነት ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር
ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡” (ዘፍ 1፥1) ሲለን የእግዚአብሔርን መኖር በማመን ሥራውን በመዘርዘር ይጀምራል፡፡ መጽሐፍ
ቅዱስ ስለ እምነት ግልጥና ጥርት ያለ አቋም አለው፤ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እምነት በእግዚአብሔር ላይ በሁለንተና
መደገፍን፣ በእርሱ መተማመንና እርሱን ብቻ ተስፋ ማድረግን የሚያሳይ ነው፡፡ እኛ እግዚአብሔርን ልናምነው፣ ልንታመንበትም
ይገባናል፤ ዳሩ ግን እኛ ባንታመንበት የእኛ በእርሱ አለመታመን ወይም አለማመን የእርሱን ታማኝነት ፈጽሞ አያስቀረውም፡፡
“ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና” (2 ጢሞ 2፥13) ቅዱሳን ሁሉ የሚያድን እምነት

49
ተሰጥቷቸዋል፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን ሁሉ ተአምር የሚሰራ እምነት እንደሌላቸው የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡ (ሮሜ 12፥3፤

ኤፌ 2፥8) ስለ እምነት ስንናገር አስፈላጊ ቁም ነገሮች ማስተዋል ይገባናል እነርሱም፡-

ሀ/ “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፤ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ (ዕብ. 11፥1) በቅዱስ ጳውሎስ
ንግግር እምነት ወደፊት እንዲፈጸም በተስፋ በምንጠብቀውና በማይታየው ነገር ላይ እግዚአብሔር አምላክ እንደሚያደርገው
ማመንን የሚያመለክት ነው፡፡ እምነትና ተስፋ ተያያዥና የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡ ለማመን የተስፋ ምንጭ የሆነውን
እግዚአብሔርን ማመን አለብን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የታመነ ስለሆነ፡፡ እምነት በእግዚአብሔር ላይ ተደላድሎ፤ ተዘልሎ
መቀመጥና ማረፍ ነው፡፡ ስለ ተስፋ ቃሉ እግዚአብሔርን ልንጠረጥረው፣ ልናማው፣ ልንተወው አይገባም፡፡ (ዘዳ. 7፥9፤ ኢሳ.

49፥7፤ ሰቆ. 3፥23፤ ሮሜ 3፥3፤ 1 ቆሮ. 1፥9)

ለ/ ሌላው እውነተኛ እምነት ላመነበት እምነት ምላሽ መስጠትና በመልካም ሥራ መታዘዝ ይገባዋል፡፡ (ዕብ 11፤ ያዕ. 2፥14-17፤
20-24)
ሐ/ ደግሞም “ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም” (ዕብ. 11፥6)

6.1.1 እግዚአብሔር ይታመናል እንጂ አያምንም

መጽሐፍ ቅዱስ ፍጥረት በእግዚአብሔር ሕልውና ተደጋፊና ያለ እግዚአብሔር መደገፍም መቆም የማይችል መሆኑን፤
እንዲሁም እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ፈጽሞ የተለየ ቅዱስና ልዑል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እናም ፍጥረቱ ሁሉ (በተለይም የሰው
ልጅ) በእግዚአብሔር እንዲታመን አጽንቶ ይናገራል እንጂ እግዚአብሔር እንደ ሰው ስለ ማመኑ የሚነግረንን ወይም
የሚያስተምረንን አንዳች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም፡፡ ታማኝ አምላክ ነውና፤ እኛ እግዚአብሔርን እናምነዋለን እንጂ
እግዚአብሔር እንደ እኛ አያምንም፡፡ እምነት በእግዚአብሔር መደገፍና መታመን ከሆነ እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረው
በእምነት ሳይሆን በማንም ሳይደገፍ፣ ያለ አማካሪና ረዳት፣ ከልካይም ሳይኖርበት ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም
በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍት ይህን በሚገባ ይመሰክራሉ፡፡ (ዘጸ. 31፥17፤ 2 ዜና 2፥12፤ ኢዮብ 9፥8፤ መዝ

135፥6-7፤ ምሳ 16፥4፤ ኢሳ. 40፥26-28፤ 43፥13፤ 44፥24፤ ኤር 10፥12፣ 51፥15፤ ሐዋ. 14፥15፤ 17፥24፤ ኤፌ 3፥8-9)

6.2 ቃል ብቻ ማውጣት (አዎንታዊ ዐዋጅ) በእግዚአብሔር ቃል ዕይታ

በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ቅዱሳን ሁሉ ማናቸውም ስራን የሠሩት በቃላቸው ሳይሆን እምነታቸውን በእግዚአብሔር
ላይ በመጣልና በእርሱም ብቻ በመደገፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ተደግፈው የሠሩት አገልጋዮችን ሲያከብር በእርሱ ላይ
ባለመደገፍ በራሳቸው ታምነው ስራን የሰሩትን ሕዝቦች ግን ንቋል፡፡ (ኢሳ. 30፥2-3፤ 12-13፤ ኤር. 7፥8፤ መዝ. 91፥2፣ 14)

አሉታዊ (ተቃራኒ) ንግግሮችን ተናግረው መልካም የሆናላቸው ሰዎች እንዳሉ ቃሉ ምስክር ነው፡፡ (ዘፍ. 34፥30፤ መዝ. 94፥18፤ ዮሐ.

11፥16፤ ፤ ሮሜ. 7፥17) ቅዱሳን የሌላቸውን ነገር እንዳላቸው አርገው ሲያውጁ አንመለከትም፤ እንዲያውም የሎዶቅያ ቤተ

ክርስቲያን ድሀ ሆኖ ሀብታም ነኝ ሲል በኢየሱስ ሲወቀስ እንመለከታለን፡፡ (ራዕይ 3፥17፤ ሉቃ. 9፥10-17፤ ዮሐ. 2፥1-11)
መጽሐፍ ቅዱስ “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህ ሁሉ ይጨመርላችኋል” ይላል፡፡
(ማቴ. 6፥31-33) እነዚህ ነገሮች “የቃል አዋጅ” ውጤቶች አይደሉም፤ እምነታችንን በማመንም የምናገኛቸው አይደሉም!

50
እንዲያውም በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሰውን ቃላት በራሳቸው ኃይል እንደ ሌላቸው ያስተምራሉ፡፡ (ምሳ. 14፥23፤

26፥23፤ 1 ቆሮ. 4፥10-13፤ 1 ተሰ. 2፥18) መጽሐፍ ቅዱስ አዎንታዊ አዋጆችን እንድናውጅ ሳይሆን የሚያበረታታን “ጌታ ቢፈቅድ

ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል” በማለት በጌታ ላይ ብቻ እንድንደገፍ ያበረታታናል፡፡ (ያዕ. 4፥15፤ 1 ቆሮ. 4፥19)

6.3 ጸሎት በእግዚአብሔር ቃል ዕይታ

ጸሎትን ያስተማረን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንጸልይ አዞናል፡፡ (ማቴ. 6፥9-15፤ 21፥22፤ ሮሜ 12፥12፤

ኤፌ. 6፥18፤ ፊልጵ. 4፥6፤ ቆላ. 4፥2) ስንጸልይም ራሳችንን ማዋረድ እንጂ በልባችን መመካት እንደሌለብን አስጠነቀቀን፡፡

(ሉቃ. 18፥9-14) ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱም ጸለዩ ሳናቋርጥ አጥብቀን መጸለይ እንዳለብንም ጻፉልን፡፡ (ሐዋ. 1፥24-25፣ 2፥5፣

3፥1፣ 4፥24-31፣ 8፥2፤ 1 ተሰ. 5፥17-18፤ ዕብ. 5፥7) ስለዚህም እኛ እግዚአብሔርን አማኞች ነን፤ እግዚአብሔር ደግሞ
የምንታመንበትን አምላካችን ነው፡፡ ስለምንታመንበት ጸሎትን ወደሚሰማና ጸልዩ ብሎ ትዕዛዝ ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንጸልያለን፡፡ (መዝ. 65*1-2፤ ኤር. 29፥12-14፤ ማቴ. 6*7-13፤ ዮሐ. 16*23) እግዚአብሔር ያለ ሰው
ልጅ እርዳታ በዚህ ምድር ላይ መስራት ከፈለገ የወደደውን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ከሰው ልጆችና ከፍጥረቱ ሁሉ ተነጥሎ የሚኖር
አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ በላይ ነው በፍጥረቱ አይደገፍም ከፍጥረቱ ይበልጣል፡፡ (2 ዜና. 2*6፤ ኢሳ. 55*8-9፤ ሐዋ.
7*48-50፤ ሮሜ. 11*33-36) እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ማድረግ ከመቻሉ በላይ ሃሳቡን ሊከለክልና ሊያደናቅፍ የሚችል የለም፡፡
(ኢሳ. 43*13፤ ኤር. 32*17፤ ዳን. 4*35፤ ኢዮ. 42*2፤ ማቴ. 19*26)

ምዕራፍ ሰባት፡- ምን እናድርግ


እነዚህ ትምህርቶች ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሾልከው በመግባት ላይ ስለ ሆኑ፤ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሆነ እንደ አማኝ ምን
ማድረግ ይገባናል የሚለውን መጠየቅ ያሻል፡፡ መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም፤ ከእነርሱ መካከል በተወሰኑት
ላይ ትኩረት በማድረግ ሊወሰዱ ስለሚያስፈልጋቸው የወደፊት አቅጣጫዎች እንነጋገራለን፡፡
ሀ/ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መንጋውን የመጠበቅ ኃላፊነት ይወጡ፡፡ (ሐዋ. 20*29፤ ኤፌ. 5*11፤ ፊልጵ. 3*17፤ 2 ተሰ. 2*3-
12፤ 1 ጢሞ. 4*1-6፤ 2 ጢሞ. 4*3-5፤ 2 ጴጥ. 2*1-2፤ 3*3-13፤ ይሁዳ 1*20-21፤ ራዕይ 2*3)
ለ/ ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ/ዶክትሪን ለምዕመኖቿ ማስተማር አለባት፡፡ (ማቴ. 22*23-33፤
ሮሜ 12*3፤ 1 ጢሞ. 4*1-6፤ 2 ጢሞ. 4*3-5፤ ቲቶ 1*9-11)
ለ/ የሐሰት ትምህርትን በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛን እንመዝን፡፡ (ዘዳ. 13*1-5፤ 18*20-22፤ ሐዋ. 17*11፤ 2 ጴጥ. 2*1፤ 1 ዮሐ.
4*1፤ ይሁዳ 1*17)
ሐ/ የተሳሳተ ስነ አፈታት የሐሰት ትምህርት መሰረት መሆኑን እንገንዘብ፡፡ (1 ጢሞ. 1*9-11፤ 4*6፤ 2 ጢሞ. 1*13፤ 2*15፤
4*3፣ ቲቶ 1*9፤ 2*1)
መ/ ከልዩ ወንጌል ጀርባ ያሉት ሀሰተኛ ወንድሞች ብቻ ሳይሆኑ ሰይጣንም ጭምር ስለሆነ በጸሎት ስራውን ማፍረስ አለብን፡፡
(ኤፌ. 6*12፤ 1 ጢሞ. 4*1-2፤ 2 ጢሞ. 2*25-26፤ ያዕ. 4*7)

51
ምዕራፍ ሰባት፡- ተግባራዊ ተዛምዶ

እያንዳንዳችን በቅዱስ ቃሉ ሚዛን ትምህርት ክፋላችንን፤ መድረኮቻችንን፤ ትምህርቶቻችንን፤ ሰብከቶቻችንን፤


ትንቢቶቻችንንና ልምምዶቻችንን ልንመረምራቸውና የእንቅስቃሴ ሰለባ አለመሆናቸውን በልበ ሰፊነት መፈተን መመርመር
አለብን፡፡ እንደዋዛ ባልታሰቡና በማንጠብቃቸው ሰዎችና አገልጋዮች የልዩ ወንጌል ጠባይ እያየን ነውና፤ ምናልባት የሳቱ፣
የተሰናከሉ ወንድሞችና እህቶች ብናገኝ በፍቅር ልናቀና፣ ልንመክር፣ ኑፋቄ መሆኑን ልናመለክት፣ እንዲመለሱ መንገድ
ልናሳያቸው፣ ልናስመክራቸው፣ ልንጸልይላቸው… ቤተ ክርስቲያናዊ እድሉን ሁሉ በመጠቀም እንዲመለሱ የተገባውን ጥረት
ሁሉ ማድረግ ይገባናል፡፡

ሰው ሦስት ነገሮች (ስጋ፣ ነፍስና መንፈስ) በውስጡ የያዘ ፍጡር ነው፡፡ ስለዚህ ነፍሳችንን (መንፈሳችንን) ከስጋችንን ለይተን
ማየት አንችልም፡፡ ሰው መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለሁም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በ 1 ኛ ተሰ.
5*23 እንደሚያስተምረን “መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም ስጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው
ይጠበቁ” እንደሚል ሦስቱን ነገሮች ነጣጥሎ ማየት አይቻልም፡፡

በስጋ የሞተልንና በቅድስና ያዳነን ጌታችን ኢየሱስ የኃጢአትን ኃይል፣ ሲኦልና ዲያብሎስን በሕይወቱና በስጋ መሥዋዕታዊ ሞቱ
ድል ነሥቷቸዋል አሸንፏቸውማል። ስለዚህ በማናቸውም መንገድ የሰይጣንን ባሕርይ አልተካፈለም (አልሰየጠነም)። ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈሱ አልሞተም ስንል ባሕርዩን አይለውጥም ማለታችንም ነው። እንዲህ ያለውን ትምህርት የማይከተል
ሁሉ ጽኑ መርገም አለበት፤ እንዲህ የሚል “ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን” (1 ቆሮ. 16፥22)

ዓለም ከኃጢአት የተነሣ የወደቀ፣ የተበላሸና የተበከለ እንደሆነ እናምናለን በክርስቶስ ቤዛነት መዳናችን ታውጇል፤ ከዚህ ጋር
በተያያዘም እንደማንታመም የተገባልን ኪዳንም የለም። ስለዚህም ብንታመምም ባንታመም ክርስቶስ በሁለንተናችን ጌታና ቤዛ
ነው። ብንፈወስም ባንፈወስም የእርሱ ታማኝነት ጽኑና የማይለወጥ ነው። በአካላዊ ትንሣኤ የሚበልጠውንና ወደር የሌለውን
ሕይወትና ደስታ፤ ባለጠግነትና ክብርን ተስፋ እናደርጋለን አሜን። የሚያድኑና የሚፈውሱ የያህዌ እጆች ዛሬም ሕያውና
የሚሠሩ፤ የሚፈውሱና የሚታደጉ ናቸው። የጌታችን ኢየሱስ ስም ዛሬም አዳኝና ፈዋሽ ነው፤ ነገር ግን ባንፈወስም ብንፈወስም
እንኳ ለእግዚአብሔር ክብርን ከማምጣት፤ ለእርሱም ከመገዛት የሚከለክለን አንዳች ምክንያት የለም።

ብልጥግና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚሰጥ ብናምንም፣ ሳንሠራ ወይም ልንሠራ ሳንወድድ፣ ወዛችንን ሳናፈስስና ስራ ጠልተን
በቅምጥልነት ለመኖር እንዲያው ዝም ብለን ከሰማይ እንደሚወርድ ነገር፤ ያስፈለገንን ባስፈለገን መንገድ በቃላችን በማዘዝና
በመናዘዝ ለማምጣት አንዳፈርም ወይም አንጠብቅም። እንደ እግዚአብሔር ዐሳብና ፈቃድ፤ እንሠራለን፣ እንደክማለን በእነዚህ
ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚባርከን ሀብት እንደሚሰጠን እናምናለን።

የዘመናችን የስህተት ትምህርቶችና ልምምዶች የክለሳ ጥያቄዎች

52
እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– የማንኛውም አገልጋይ ትምህርት፣ ሕይወትና ልምምድ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጠው ከመጽሐፍ ቅዱስ
(ከክርስቶስ፣ ከሐዋርያትና ነቢያት) ትምህርት ጋር ተነጻጽሮ ትክክለኛ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
2. –––––– የአገልጋዮችን አስተምህሮም ሆነ ልምምዶች መርምረን መቀበል የለብንም፤ ስህተት ቢሰሩም እግዚአብሔር
ራሱ ይጠይቃቸው እንጂ የኛ ድርሻ መጸለይ ብቻ ነው፡፡
3. –––––– በሽታ መንፈሳዊ እንጂ ስጋዊ አይደለም፤ በሽታ ሁሉ የሚመጣው ከሰይጣን መንፈሳዊ ዓለም ነው፡፡ ስለዚህ
ክርስቲያን መታመም የለበትም፡፡
4. –––––– ሰው መንፈስ እና የእግዚአብሔር ቅጂ ስለሆነ፤ ቁሳዊውን ዓለም የሚገዛ፣ በንግግሩም መፍጠር የሚችል ነው፡፡
5. –––––– ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ አንድ ጊዜ መፍሰስ፣ በሥጋ ሞቱ፣ በመስቀል ላይ በተቀበለው
መከራ ብቻ አዳነን፡፡

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ
6. ልዩ ወንጌል ሀ/ አዎንታዊ አዋጅ
7. ቃል ማውጣት ለ/ ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ
8. ኖስቲስዝም ሐ/ የአዲሱ አስተሳሰብ እንቅስቃሴ
9. እምነት መ/ ለሐሰት ትምህርት የተሰጠ ስም
10. ሰው ሠ/ ስጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ
ረ/ ዕውቀት
ሰ/ መንፈስ ብቻ

ትክክለኛን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. የሐሰተኛ መምህራን መለያዎች ምንድን ናቸው?

ሀ/ ቃሉን ማጣመም፡፡

ለ/ ግላዊ ራእይ፣ ሕልምና ትንቢት እንደ ቃሉ ማቅረብ፡፡

ሐ/ ራስን ስልጣናዊ አድርጎ ማቅረብ፡፡

መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡


12. ስለ ድኅነት (ድነት) ትክክል ያልሆነው አስተምህሮ የቱ ነው?
ሀ/ ጌታችን ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ ሊያድነን፣ ሊቤዠን፣ ሊዋጀን መጣ።
ለ/ ክርስቶስም ሰውን ለማዳን የሰይጣንን ባሕርይ ገንዘቡ አደረገ (ሰየጠነ)፡፡
ሐ/ ክርስቶስ በደሙ መፍሰስ አዳነን፡፡
53
መ/ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ብቻ በስጋ ሞቱ፤ በመስቀል ላይ በተቀበለው መከራ አዳነን፡፡
13. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ንጹሕና ነውር የሌለበት ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ ራሱን ያቀረበው ለማን ነው?
ሀ/ ለቤተ ክርስቲያን፡፡
ለ/ ለሰይጣን፡፡
ሐ/ ለእግዚአብሔር፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
14. እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችን፤ በአምሳላችን እንሥራ” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ/ ሰው ከእግዚአብሔር የተካፈላቸውን እንደ ምክንያታዊነት፣ ግብረገባዊነትና ነጻ ፈቃድ ያሉ ባህሪያት አሉት።
ለ/ ከሌሎች ፍጥረታት በበለጠ ሰው ከአምላክ ጋር ኅብረት ማድረግ የመቻል አቅም አለው።
ሐ/ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ገዢነት ያመለክታል።
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
15. ስለ በሽታ ትክክለኛው አስተምህሮ የቱ ነው?
ሀ/ በሽታ መንፈሳዊ እንጂ ስጋዊ አይደለም፤ በሽታ ሁሉ የሚመጣው ከሰይጣን መንፈሳዊ ዓለም ነው፡፡
ለ/ በሽታ መኖሩን በአእምሮ ማመን ወይም በቃላት መግለጽ ለሰይጣን ዕድል ይሰጠዋል፡፡
ሐ/ ፍጹም ባልተዋጀው ዓለም እየኖርን ስለሆነ እንደ አማኝ ልንታመምና የማይድን በሽታም ሊያገኘን ይችላል።
መ/ የበሽታ ምልክቶች እያየን እንኳን ተፈውሻለሁ ብለን ማመን አለብን፤ ምንም አይነት ሕክምና እና መድሐኒት መውሰድ
የለብንም፡፡
16. ስለ ብልጽግና ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮው የቱ ነው?
ሀ/ እግዚአብሔር ሃብትን፣ ገንዘብን ይሰጣል፤ ይባርካልም፡፡
ለ/ ሳንሠራ ወይም ልንሠራ ሳንወድድ፣ ወዛችንን ሳናፈስስ ያስፈለገንን ባስፈለገን መንገድ በቃላችን በማዘዝና በማወጅ ብቻ
ለማምጣት አንዳፈርም ወይም አንጠብቅም።
ሐ/ መጽሐፍ ቅዱስ ድህነትና ባለጠግነት ሁለቱም በየራሳቸው የመረገምና ያለ ማመን መንገዶች ስለ መሆናቸው አይነግረንም።
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

17. ስለ ጸሎት ትክክል ያልሆነው አስተምህሮ የቱ ነው?


ሀ/ እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠንን ነገር ስጠን ብሎ መጸለይ እንዲሁም ቀድሞ ያደረገውን ነገር አድርግ ብሎ መማጸን ስህተት
ነው፡፡
ለ/ ጸሎትን ያስተማረን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንጸልይ አዞናል፡፡
ሐ/ ወደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንጸልያለን፡፡
መ/ ስንጸልይም ራሳችንን ማዋረድ እንጂ በልባችን መመካት የለብንም፡፡
18. ስለ እምነት ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮው የቱ ነው?
ሀ/ እምነት በእግዚአብሔር ላይ በሁለንተና መደገፍ ነው፡፡
ለ/ እምነት በእግዚአብሔር መተማመንና እርሱን ብቻ ተስፋ ማድረግን የሚያሳይ ነው፡፡
ሐ/ እውነተኛ እምነት ላመነበት እውነት ምላሽ መስጠትና በመልካም ሥራ መታዘዝ ይገባዋል፡፡

54
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. ከልዩ ወንጌል መሠረታዊ ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ብቻ በመምረጥ የልዩ ወንጌል ትምህርት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን
ትምህርት በማነጻጸር በዝርዝር ግለጹ? (ሰው መንፈስ ነው፣ እምነት፣ ብልጽግና፣ በሽታና ፈውስ፣ ነገረ ድነት)
20. የልዩ ወንጌል ትምህርትን በተመለከተ እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ እንደ አማኝ ምን ማድረግ ይገባናል?

ትምህርት አራት፡- ትምህርተ የመጨረሻው ዘመን


መጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረታት አጀማመር እንዴት መቼና ለምን እንደነበር ቢናገርም በዚህ ብቻ ግን አያበቃም፡፡ የፍጥረታት ፍጻሜ
እንዴትና መቼ እንደሚሆን ይናገራል፡፡ ቃሉ እንደሚያመለክተው የመጨረሻው ዘመን አስተምህሮ መሠረታዊ ሃሳብ
የሚያተኩረው በመጨረሻው ዘመን ክስተት ላይ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ እስከ ኢየሱስ ማረግ
ያለው ጊዜ “የመጀመሪያው ዘመን” ሲባል፤ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ እስከ ፍጻሜ ያለው ጊዜ ደግሞ
“የመጨረሻው ዘመን” ይባላል:: (ማቴ. 13*40፤ ሐዋ. 2*17፤ 1 ቆሮ. 10*11፤ 1 ጢሞ. 4*1-2፤ 2 ጢሞ. 3*1፤ ዕብ. 1*1-2፤
1 ጴጥ. 1*3-5፤ 4*7፤ 1 ዮሐ. 2*18፤ ይሁዳ 1*18) በመጨረሻው ዘመን የሚከናወኑ ብዙ ሁኔታዎች አሉ በዚህ ክፍል እነዚህን
ሁኔታዎች ተራ በተራ እንመለከታለን፡፡

ስለ መጨረሻዉ ዘመን ለምን እንማራለን፡-

ሀ/ የእግዚአብሔር የዘላለም እቅድ አካል ስለሆነ፡፡ (ሮሜ. 8*28-30)

ለ/ እንደ ክርስቶስ ሙሽራ በጽድቅና በቅድስና መኖር እንድንችል፡፡ (ኤፌ. 5*25-27)

55
ሐ/ በክርስቶስን ዳግም ምፃት ጥርጥር እንዳይኖረን ለማድረግ፡፡ (ዮሐ. 14*1-3፤ ፊልጵ. 1*21-26)

መ/ በክርስቶስ ዳግም ምጻት ዙሪያ በሚነሱ የስህተት ትምህርት ዙሪያ ሳይናወጡ ትክክለኛውን ትምህርት ለመማር፡፡ (2 ጴጥ.
3*3-4)
ሠ/ የዘመኑን ፍጻሜ በማወቅ የትንቢቱን ቃል መስማትና መጠባበቅ እንድንችል፡፡ (2 ጢሞ. 3*1-5)

ምዕራፍ አንድ፡- አካላዊ ሞት


ስለ መጨረሻው ዘመን ስናስብ ሁለት ነገሮችን ማሰብ አለብን አንደኛው የዓለም ፍጻሜ ሲሆን ሁለተኛው የሰው ፍጻሜ ነው
ስለ ዓለም ፍጻሜ ከመመልከታችን በፊት ስለ ሰው ፍጻሜ እንመልከት፡፡ ስለ ሰው ፍጻሜ ስናወራ ስለ አካላዊ ሞት መናገራችን
ነው፡፡ ሞት የሚለው ቃል መለየትን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ አታድርግ የተባለውን በማድረግ ኃጢአት በሰራ ጊዜ አካላዊ፣
መንፈሳዊና ዘላለማዊ ሞት እንዳስከተለበት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ አካላዊ (የስጋ) ሞት ማለት የነፍስና የስጋ መለያየት
ማለት ነው፡፡ ከምድር አፈር የተበጀው ስጋ መበስበስን ሲያይ ነፍሱ ደግሞ እስከ ትንሣኤ ቀን ትቆያለች፡፡ (መዝ. 104*29፤ መክ.
12*7፤ ሉቃ. 12*4፤ 2 ቆሮ. 5*1፤ ያዕ. 2*26፤ 2 ጴጥ. 1*13-14)
1.1 አካላዊ ሞት በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን ዘመን አካላዊ ሞት የማይወደድና አስፈሪ ነበር፡፡ (ኢዮብ 10*20-22፤ መዝ. 6*5፤ ኢሳ. 38*9-12) ለሕዝበ
እስራኤላውያን ከመንፈሳዊ ባርኮት በተጨማሪ አብዛኛው የበረከት ተስፋ የተያያዘው ከምድራዊ ባርኮት ጋር ስለነበር ሞት
አስፈሪ ነበር፡፡ (ዘዳ. 28*1-14፤ ኢዮብ 18*14፤ መዝ. 55*4) ሆኖም አንዳንድ ቅዱሳን ከሞት በኋላ ያለውን ሕይወት በተስፋ
ይጠባበቁ ነበር፡፡ (ኢዮብ 19*25-27፤ መዝ. 49*8-15፤ ኢሳ. 26*19፤ ዳን. 12*2) በአዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል
ስራ የተነሳ አካላዊ ሞት የማይፈራ ሆኗል ስለዚህም፡-
 ሞት ድል በመንሳት ተለውጧል፡፡ (1 ቆሮ. 15*54)
 ሞት ለአማኞች ቅጣት መሆኑ ቀርቶ ወደ ክርስቶስ የሚወስደው ድልድይ (መሸጋገሪያ) ሆኗል፡፡ (ማቴ. 10*28፤
ሉቃ. 23*43፤ ፊልጵ. 1*23)
 በሞት ላይ ስልጣን ያለው ዲያቢሎስ ተሽሯል፡፡ (ዕብ. 2*14-15)
 ኢየሱስ በመስቀል ስራው ሕይወትንና አለመጥፋትን (ኢመዋቲነትን) ወደ ብርሃን አውጥቷል፡፡ (2 ጢሞ. 1*10-
11)
 ለአዲስ ኪዳን አማኞች ሞት ሚስጢር መሆኑ አብቅቷል፤ ምክንያቱም ከሞት በኋላ ያለው ሕይወት ግልጽ ሆኖ
ተቀምጧል፡፡ (1 ተሰ. 4*14፤ ፊሊጵ. 1*23)
1.2 አካላዊ ሞት መቼ ያበቃል?

በአዳም ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ላይ ሁሉ እንደመጣ፤ አካላዊ ሞት የሚያበቃው በታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ጊዜ
ኃጢአተኞችን ሁሉ ከተነሱ በኋላ ሞትና ሲኦል የያዙትን ሙታን ከሰጡ በኋላ ወደ እሳት ባህር ሲጣሉ ያን ጊዜ ግን አካላዊ ሞት
ፍጻሜ ያገኛል፡፡ (ራዕይ 20*11-15)

ምዕራፍ ሁለት፡- የመካከለኛው ማንነት (ስርዓት)


56
የመካከለኛው ማንነት ማለት በስጋዊ ሞትና በትንሣኤ መካከል ያለውን ጊዜ የሚያመለክት ነው፡፡ በሞት እና በትንሳኤ መካከል
ነፍስ የምትቆየው የት ነው የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ የመካከለኛው ማንነትን በተመለከተ የሚሰነዘሩ የስህተት ትምህርቶችን
እንመልከት፡፡
2.1 ከአካላዊ ሞት በኋላ መኖር የለም

ከአካላዊ ሞት በኋላ ያለውን ሕይወት የማይቀበሉ አንዳንድ ሰዎች የሙታንን ትንሳኤ ስለማይቀበሉ ከሞት በኋላ ሁሉ ነገር እዛ
ጋር ያበቃል ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ያላመኑ ሰዎች ከአካላዊ ስጋ ሲለዩ ስጋቸው ይበሰብሳል ነፍሳቸው ጨርሳ ትጠፋለች
ይላሉ፡፡
2.2 ነፍስ ታንቀላፋለች

በዚህ ትምህርት መሠረት በሞትና በትንሣኤ መካከል ምንም እንኳ ነፍስ ሕያው ሆና ብትኖርም ምንም አይነት ስሜት ወይም
እውቀት ሳይኖራት በእንቅልፍ (በሰመመን) ውስጥ በመሆን የማትነቃ ትሆናለች በማለት ያስተምራሉ፡፡

2.3 መካነ መጽሔት (ፐርጋቶሪ)

በሮም ካቶሊክ ትምህርት መሰረት በመካከለኛ ማንነት ሁኔታ ከኃጢአታቸው በንስሃ እና በስጋ ነጽተው በፍጹምነት ያሉ ሲሞቱ
በቀጥታ ወደ መንግስተ ሰማይ ሲሄዱ እስከ ፍጻሜ ድረስ በመንፈስ ያልነጹ አማኞች ሲሞቱ ደግሞ ነፍሳቸው (መንፈሳቸው)
ወደ ነፍስ መታጠቢያ ስፍራ (ፐርጋቶሪ) በመሄድ ምድር ላይ በሚደረግላቸው ጸሎት፣ ምጽዋት የመሳሰሉት ተግባር ወደ

መንግስተ ሰማይ ለመሄድ በዛ ትነጻለች ብለው ያምናሉ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ከዚሁ ጋር

የተመሳሰለ ትምህርት አለ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሙታን ነፍስ ከስጋ ከተለየ በኃላ እስከ ምጽአት

በማረፊያ ቦታ እንደሚቆይ እንጂ በቀጥታ ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ታምናለች፡፡ ለዛ ነው

ለሞቱ ሰዎች ፍትሐት፣ አርባ፣ ሰማንያ፣ ሙት አመት የመሳሰሉት ተግባር የሚደረገው፡፡

2.4 ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት

ከላይ የተመለከትናቸው ትምህርቶች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ይቃረናሉ፡፡ በመካከለኛው ማንነት ጊዜ ነፍስና ስጋ
ከተለያዩ በኋላ ስጋ ወደ አፈር ተመልሶ መበስበስን ሲያይ ነፍስ ግን ከስጋ ሞት በኋላ ህያው ሆና ትኖራለች፡፡ ጳውሎስ ከሞት በኋላ
ስላለው ነገር ሲናገር “ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ” ይላል፡፡ (ፊልጵ. 1*23) ኢየሱስም ከአጠገቡ ለተሰቀለው ወንጀለኛ
“እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” (ሉቃ. 23*43) በማለት ከሞት በኋላ ህያውነት መኖሩን ያረጋግጣል፡፡ ከስጋ
ሞት በኋላ በሕያውነት መኖር እንዳለ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያስተምሩናል፡፡ (ሉቃ. 19*31፤ ዕብ. 12*23፤ ራዕይ
20*13)

ስለዚህ ከስጋ ሞት በኋላ የአማኞች ነፍስ ወደ ገነት በመሄድ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት በማድረግ ደስታ ስታገኝ የማያምኑ
ሰዎች ነፍስ ግን ወደ ሲኦል ትሄዳለች፡፡ (ማቴ. 10*28፤ ሉቃ. 16*19-26፤ ዮሐ. 11*25፤ 2 ቆሮ. 12*4፤ ራዕይ 2*7) ነፍስና ስጋ
ከተለያዩ በኋላ ሰዎች የዘላለምን ሕይወት ለማግኘትም ሆነ ከኃጢአታቸው ለመንጻት የሚያስችል ሁለተኛ ዕድል ይኖራቸዋል

57
ብለን እናምን ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለሰዎች አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱም በኋላ ፍርድ
እንደተመደበባቸው” ይናገራል፡፡ (ዕብ. 9*27)
2.4.1 ሲኦል

ሲኦል እንደ አውዱ ወይም ቃሉ እንደሚገኝበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከሁለት በላይ የሆኑ ትርጉሞች አሉት፡፡ ትርጉሞቹንም
ብንመለከት፡-

ሀ/ ሲኦል የኃጢአትን ስርየት ያልተቀበሉ ወይም ያላገኙ ኃጢአተኞች ከሞት በኋላ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበት ስፍራ
ነው፡፡ (ዘዳ. 32*22፤ መዝ. 9*17፤ ምሳ. 5*5፤ 7*27፤ 9*18፤ ማቴ. 11*23፤ ሉቃ. 16*23፤ ራእይ 1*18) ከዚህ ባሻገር ጥልቁ
በመባልም የተጠቀሰበት ሥፍራ አለ፡፡ (ሉቃ. 8*1፤ ራእይ 9*1-11፤ 17*8፤ 20*1-3) ይህም ኃጥአን የሚከማቹበት ሥፍራ ነው፤
በሁለቱም ሥፍራ የሚቆዩ ነፍሳት መጨረሻቸው ገሃነመ እሳት እንደ ሆነ አዲስ ኪዳን ያስተምራል፡፡ (ራእይ 20*12-13)

ለ/ ከዚህ በተያያዥነት “ቄቤር” የሚለው የዕብራይስጡ ቃል የሞተ ሥጋ የሚቀበርበትን የመቃብር ሥፍራም ሊያመለክት
ይችላል፡፡ (ዘፍ. 23*4፤ 50*5፤ ዘጸ. 14*11፤ 1 ነገ. 13*31፤ ኢዮብ 17*13፤ ኤር. 26*23፤ ሆሴ. 13*14) በአዲስ ኪዳንም
መቃብር ከሲኦል በተለየ ቃል አገላለጥ መገለጡን እንመለከታለን፡፡ (ማቴ. 23*29፤ 27*52፤ ሉቃ. 11*47-48)

ሐ/ ሲኦል አፈ ታሪክ ሳይሆን ነገር ግን ተጨባጭ እውን ስፍራ ነው። ይህ ቦታ ኃጥአን የሆኑት ማለቂያ የሌለው ዘላለማዊ ቁጣ

የሚያገኙበት ነው። እየታወቃቸው ስሜታዊ፣ አዕምሮአዊና አካላዊ ስቃይ የሚጋፈጡበት ነው። በተጨማሪም በዚህ ስፍራ
የተወሰኑት የወደቁ መላዕክት (አጋንቶች) በዘላለም እስራት እስከታላቁ ፍርድ የሚጠበቁበት ስፍራ ነው፡፡ (2 ጴጥ. 2*4፤ ይሁዳ
1*6) በመጨረሻም ከታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ በኃላ ሞትና ሲኦል በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ይሰጡና ወደ እሳት ባህር
ይጣላሉ፡፡ (ራዕይ 20*13-15)

2.4.2 ገነት

አማኞች ከሞቱ በኃላ የሚሄዱበት ስፍራ “ገነት” ሲባል፤ እሱም “የአብርሃም እቅፍ” በመባል ይታወቃል፡፡ (ሉቃ. 16*22-26)

የፃድቃን መንፈስ ገነት ተብላ ወደምትጠራው የእረፍት ቦታ በመሄድ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት በማድረግ በሰላምና በደስታ
እስከ ትንሳኤ ጊዜ የሚኖሩበት ስፍራ ነው፡፡ ገነት ከምናስበው በላይ እጅግ አስደናቂና ከአዕምሮ በላይ የሆነ ቦታ ነው፡፡ (ሉቃ.
23*43፤ 1 ቆሮ. 2*9፤ 2 ቆሮ. 12*4፤ ራዕይ 2*7)

ምዕራፍ ሦስት፡- የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መመለስ (ምጽዓት)

በመጨረሻው ዘመን ከሚከናወኑ ሁኔታዎች ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ዋናውን ስፍራ ይይዛል፡፡
3.1 እርግጠኝነቱ

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር አገልግሎቱ ፍጻሜ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ተናገረ “እኔ ባለሁበት እናንተም ደግሞ እንድትሆኑ
ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” (ዮሐ. 14*3) በማለት ስለ ዳግም መመለሱ አስረግጦ ተናገረ፡፡ ኢየሱስ ዳግመኛ
እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል፤ ኢየሱስ ስለ መመለሱ በግልጽ ተናግሯል፡፡ (ማቴ. 24*1-51፤ 26*64)

58
መላዕክት ተናግረዋል፡፡ (ሐዋ. 1*9-11) ሐዋርያት በስብከታቸው፣ በትምህርታቸውና በመልዕክቶቻቸው በሰፊ ገልጸዋል፡፡ (1 ቆሮ.
15*23-24፤ ፊልጵ. 3*20፤ 1 ተሰ. 4*15-18፤ 5*23፤ 2 ተሰ. 1*6-10፤ 1 ጢሞ. 6*13-16፤ ዕብ. 9*28፤ 2 ጴጥ. 1*16፤ 3*4-
12፤ ራዕይ 1*7-8፤ 3*11፤ 22*12-13 ) ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ለክርስቲያኖች ሁሉ የተባረከ
ተስፋችን ነው፡፡ (ቲቶ. 2*12-14) ስለዚህ የክርስቶስን መመለስ በጉጉት መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ (1 ቆሮ. 16*22፤ ራዕይ 22*20)
3.2 መቼ ይመጣል?

ኢየሱስ ክርስቶስ “መቼ ትመጣለህ” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ “የሰው ልጅ የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት ከእግዚአብሔር
አብ በቀር ማንም አያውቅም” በማለት ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን እንደማናውቅና ማወቅ እንደማንችል ገልጾልናል፡፡ (ማቴ.
24*3-35፤ ማር. 13*32-33) ኢየሱስ የሚመጣበትን ቀን ባናውቅም ነቅተን፣ ተጠንቅቀን፣ ተግተን፣ እየጸለይን በናፍቆትና
በጉጉት እንድንጠብቅ ግን ተነግሮናል፡፡ (ማቴ. 24*42-44፤ ማር. 13*32-33፤ ሉቃ. 12*40፤ 1 ተሰ. 5*2፤ ቲቶ. 2*12-13፤ ዕብ.
10*25፤ ያዕ. 5*7-9)
3.3 ዳግመኛ የሚመጣው ማን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስረዳን ዳግመኛ የሚመጣው ለሰው ልጆች ኃጢአት በመስቀል ላይ የሞተው፤ ሞትን ድል አድርጐ ከሦስት
ቀን በኋላ ከሞት የተነሳው፤ ደግሞም ዳግመኛ እንደሚመለስ ተስፋ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ (ዮሐ. 14*3፤ 21*22፤ ሐዋ.
1*11፤ 1 ተሰ. 4*16) ኢየሱስ ዳግም የሚመጣው በአካል እንጂ በመንፈስ አይደለም፡፡ (ማር. 24*30፤ ሐዋ. 1*11፤ ራዕይ 1*7)
3.4 ጌታ ኢየሱስ የሚመጣባቸው ሁኔታዎች

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሁለት መልኮች ወይም ገጽታዎች አሉት እነዚህም ስውርና ግልጽ አመጣጡ ወይም
ለቤተ ክርስቲያንና ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሚል በሁለት ይከፈላል፡፡
3.4.1 ስውር አመጣጡ (ለቤተ ክርስቲያን መምጣቱ)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስውርና ባልተጠበቀ ሰዓት በመላዕክትና በታላቅ ክብር ታጅቦ ለቤተ ክርስቲያን ይገለጣል፡፡ የሞቱ
አማኞች በትንሣኤ አካል ተነስተው በምድር የምንኖር ቅዱሳን የለበስነውን ስጋ በቅጽበት ዓይን ተለውጦ ጌታን በአየር ለመቀበል
እንነጠቃለን፡፡ ይህ ስውር የክርስቶስ አመጣጥ ይባላል፡፡ (1 ቆሮ. 15*51-54፤ 1 ተሰ. 4*16-17)
ሀ/ ሁኔታው
 በቶሎ (በቅርብ)፡፡ (ራዕይ 22*7-12)
 እንደ ሌባ፡፡ (1 ተሰ. 5*2፤ ራዕይ 16*15)
 በድንገት (ባልታሰበ ሰዓት)፡፡ (ማቴ. 24*44)
ለ/ ምክንያቱ
 አማኞችን ለመውሰድ፡፡ (ዮሐ. 14*2-3)
 ያንቀላፉ (የሞቱ) አማኞች ትንሣኤ እንዲያገኙ፡፡ (1 ቆሮ. 15*22-23፤ 1 ተሰ. 4*15-17)
 በቅዱሳን ዘንድ ሊከብር የሚያምኑት እንዲገረሙ፡፡ (2 ተሰ. 1*9-10)
 አማኞችን ከታላቁ መከራ ለማዳን፡፡ (1 ተሰ. 1*9-10፤ ራዕይ 3*10)
 ለእያንዳንዱ አማኝ እንደ ስራው ብድራትን ለመክፈል፡፡ (1 ቆሮ. 4*5፤ 2 ቆሮ. 5*10፤ 2 ተሰ. 1*6-7)
3.4.2 ግልጽ አመጣጡ (ከቤተ ክርስቲያን ጋር መምጣቱ)

59
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በንጥቀት ከወሰዳቸው አማኞች ጋር በመሆን በታላቅ ክብር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እያየው ይመጣል፤
ይህ ግልጽ አመጣጡ (ከቤተ ክርስቲያን ጋር መምጣቱ) ይባላል፡፡
ሀ/ ሁኔታው
 እየታየ፡፡ (ዘካ. 12*10፤ ሐዋ. 1*11፤ ራዕይ 1*7)
 በደመና፡፡ (ማቴ. 24*30)
 በራሱና በአባቱ ክብር፡፡ (ማቴ. 25*31)
 በእሳት ነበልባል፡፡ (2 ተሰ. 1*6-7)
 በኃይልና በብዙ ክብር፡፡ (ማቴ. 24*30)
 ከመላዕክቱ እና ከቅዱሳን ጋር፡፡ (ማር. 8*38፤ 1 ተሰ. 3*12-13፤ ይሁዳ 1*14-15)
 የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ ሆኖ፡፡ (ራዕይ 19*11-16)
ለ/ ምክንያቱ
 የክርስቶስን ተቃዋሚ ለመሻር፡፡ (2 ተሰ. 2*8)
 የአርማጌዶንን ጦርነት በድል ለመፈጸም፡፡ (ዘካ. 14*4-5፤ ራዕይ 16*12-16)
 እስራኤል ለማዳን፡፡ (ዳን. 12*1፤ ማቴ. 24*21-31)
 አመጸኞችን ለመበቀል (በአሕዛብ ለመፍረድ)፡፡ (ማቴ. 25*32፤ 2 ተሰ. 1*8፤ ይሁዳ 1*14-15)
 ሺህ ዓመት በምድር ላይ ለመንገስ፡፡ (ዳን. 7*13-14፤ ራዕይ 11*15፤ 20*4-6)

3.5 የጌታ የኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ምልክቶች

ምንም እንኳን ኢየሱስ ዳግመኛ የሚመጣበትን ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ በቀር ሌላ ማንም ባያውቀውም ነገር ግን ኢየሱስ
ክርስቶስ የመምጫው ጊዜ መቃረቡን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ነግሮናል፡፡ (ማቴ. 24*1-44፤ ማር. 13*5-29) ዋና ዋናዎቹ
ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
3.5.1 በዓለም ላይ (ከቤተ ክርስቲያን ውጭ) የሚታዩ ምልክቶች

 ጦርነትና የጦርነት ወሬ መሰማት፡፡ (ማቴ. 24*6)


 የሕዝብ በሕዝብ የመንግስት በመንግስት ላይ መነሳት፡፡ (ማቴ. 24*7)
 የሎጥና የኖህ ዘመን ምልክቶች መታየት፡፡ (ሉቃ. 17*26÷30)
 የምርምርና የዕውቀት መብዛት፡፡ (ዳን. 12*4)
 ከዓመጽ የተነሳ የብዙ ሰዎች ፍቅር መቀዝቀዝ፡፡ (ማቴ. 24*12)

3.5.2 በተፈጥሮ ላይ የሚታዩ ምልክቶች

 ረሃብ፣ ቸነፈርና የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መሆን ይህም ሁኔታ እየጨመረና እየተባባሰ መሄዱ፡፡ (ማቴ. 24*7፤
ማር. 13*8)
 በሰማይ ላይ የሚሆኑ የሚያስፈሩ ነገሮችና ምልክቶች መታየት፡፡ (ማቴ. 24*29-30፤ ራዕይ. 6*12-13)
3.5.3 በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚታዩ ምልክቶች
60
 ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በኢየሱስ ስም መምጣትና ብዙዎችን ማሳት፡፡ (ማቴ. 24*5)
 ሐሰተኛ ነብያትና ሐሰተኛ አስተማሪዎች መነሳትና በእነርሱም ታላላቅ ምልክቶችና ድንቆች መደረግ፡፡ (ማቴ. 24*24፤
1 ጢሞ. 4*1-3)
 የሚያስጨንቅ ዘመን መምጣትና ስለዚያ ዘመን የተሰጡ ምልክቶች መፈጸም፡፡ (2 ጢሞ. 3*1-5)
 ወንጌል በዓለም ዙሪያ መሰበክ፡፡ (ማቴ. 24*9-14)
3.5.4 በእስራኤል ላይ የሚሆኑ ምልክቶች

 እስራኤላውያን ከተበተኑበት ሁሉ ወደ ምድራቸው መሰብሰባቸው፡፡ (ኤር. 31*10፤ ሕዝ. 36*24፤ 37* 21)
 የእስራኤል መንግስት መመስረትና የአሕዛብ ዘመን ፍጻሜ መቃረብ፡፡ (ሉቃ. 21*24)
 ምድረ በዳ የነበረው የእስራኤል ምድር መለምለም፡፡ (ሕዝ. 36*8-11)
3.5.5 የምልክቶቹ አገልግሎት

 አማኞች የጌታ የኢየሱስ ዳግም ምጽዓት እንደደረሰ አውቀው በመዘጋጀት እንዲኖሩ፡፡ (ማቴ. 24*32-33፤ 25*1-13)
 አማኞች በጌታ ስራ በመጠመድ እንዲኖሩ፡፡ (ማቴ. 24*45-51)
 አማኞች በጸሎት በመትጋት እንዲኖሩ፡፡ (ሉቃ. 21*36)
 አማኞች ሊሆኑ ካሉት መጥፎ ነገር እራሳቸውን በመጠበቅ እንዲኖሩ፡፡ (2 ጢሞ. 3*10-14፤ 1 ጴጥ. 4*7-11)

ምዕራፍ አራት፡- ንጥቀት


አማኞች ጌታ ኢየሱስን በአየር ለመቀበል ከምድር ወደ አየር የሚያደርጉት ጉዞ መነጠቅ ይባላል፡፡ (1 ተሰ. 4*15-17) በዚህ ስውር
በሆነው የጌታ የኢየሱስ ዳግም መመለስ ጊዜ የፊተኛው ትንሳኤ ተካፋዮችና በዚያን ጊዜ በምድር ላይ በሕይወተ ስጋ የሚገኙ
አማኞች ሁሉ በአንድነት ሆነው ኢየሱስን በአየር ለመቀበል በደመና ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በሕይወተ ስጋ በምድር ላይ የሚገኙ
አማኞች በቅጽበት በመለወጥ በክርስቶስ አንቀላፍተው እንደተነሱት ሁሉ የማይበሰብስ አካል ይለብሳሉ፡፡ (1 ቆሮ. 15*51-52)

4.1 ንጥቀት መቼ ይሆናል?

በመሰረቱ ስለ ጌታ ምጽዓት እንጂ ስለ መነጠቅ ወይም ንጥቀት መቼ ሊከሰት እንደሚችል የተነገረ ምልክት በመጽሐፍ ቅዱስ

ውስጥ የለም፤ ስለዚህ ንጥቀት ዛሬ ሊሆን ይቻላል በማለት እንደ ልባሞቹ ቆነጃጅት ተዘጋጅተን መኖር አለብን። (ማቴ. 25*1-
13)

4.2 የመነጠቅ ልዩ ባህሪያት


 ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ለመውሰድ በደመና ይመጣል፡፡ (1 ተሰ. 4*16-17)
 በክርስቶስ አምነው የሞቱ (ያንቀላፉ) ቅዱሳን በከበረ አካል ይነሳሉ፡፡ (1 ተሰ. 4*16)
 በምድር ላይ ያሉ ቅዱሳን በድንገት በቅጽበት ዓይን በከበረ አካል ይለወጣሉ፡፡ (1 ቆሮ. 15*51-52)
 ሁለቱም ጌታን በአየር ለመቀበል በደመና ይነጠቃሉ፡፡ (1 ተሰ. 4*17)
61
 ሁሉም ክርስቲያኖች አይነጠቁም ያልተዘጋጁ (በጽድቅ የማይኖሩ) አይሄዱም ልዩነት ይሆናል፡፡ (ማቴ. 24*40-41)
 ከንጥቀት የሚቀሩ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ በማለፍ በጭንቅ (በመሰዋትነት) ይድናሉ፡፡ (ራዕይ 6*9-
10)
4.3 ከመነጠቅ በኋላ የሚከተሉት ይከናወናሉ

 የሙሽሪት (የቤተ ክርስቲያን) እና የሙሽራው (የክርስቶስ) መገናኛ ጊዜ ወይም የበጉ ሰርግ ግብዣ ይሆናል፡፡ (2 ቆሮ.
11*2፤ ራዕይ 19*7-9)
 አማኞች ሁሉ በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ይቀርባሉ፡፡ (ሮሜ 14*10፤ 2 ቆሮ. 5*10) ይህ የፍርድ ወንበር አንድ አማኝ
በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ስለ ሰራው ስራ ብድራት የሚቀበልበት ወይም ስራው ተቃጥሎ ያለ ብድራት የሚቀርበት እንጂ
የሚኮነንበት ወይም ወደ ሲኦል የሚገባበት አይደለም፡፡ (1 ቆሮ. 3*12-15፤ 2 ተሰ. 1*6-7፤ ራዕይ 22*12)
 ቅዱሳን ለሰባት ዓመት ከክርስቶስ ጋር ይቆያሉ፡፡ (ዳን. 9*26-27፤ ራዕይ 11*3)
 ከሰባት ዓመት በኋላ ከክርስቶስ ጋር በምድር ለመንገስ ይመጣሉ፡፡ (ራዕይ 20*4)

ምዕራፍ አምስት፡- ታላቁ መከራ


ታላቁ መከራ የሚባለው እንደዚህ ያለ መከራ ከዚህ በፊት ሆኖ ስለማያውቅና ከዚህ በኋላም ስለማይሆን ነው፡፡ የመከራው ቀኖች
ባያጥሩ ኖሮ ስጋ የለበሰ ሰው ሁሉ ባልዳነም ነበር፡፡ (ማቴ. 24*21-22) ከዳንኤል ሰባተኛ ሱባኤ ውስጥ የመጨረሻው ሦስት
ዓመት ተኩል “የታላቁ መከራ” ጊዜ ነው ዓለም ሁሉ የዚህ መከራ ተካፋይ ቢሆንም እንኳን ይህ መከራ በዋናነት የእስራኤል
መከራ ነው፡፡ (ኤር. 30*7) ቤተ ክርስቲያን ይሄ መከራ አያገኛትም ምክንያቱም ከመከራው በፊት ኢየሱስ መጥቶ ይወስዳታል፡፡
(ሉቃ 21*36፤ ሮሜ 5*9፤ 1 ተሰ. 1*9-10፤ 5*9፤ ራዕይ 3*10)
5.1 ታላቁ መከራ የተሰየመባቸው ስሞች

በመጽሐፍ ቅዱስ ይህ የመከራ ዘመን በተለያዩ ስሞች ተጠቅሷል እነርሱም የመከራው ቀን (ኤር. 30*7፤ ዳን. 12*1) ፣ የጌታ ቀን
(ሐዋ. 2*20፤ 1 ተሰ. 5*2) ፣ የሚመጣው ቁጣ (ኢሳ. 26*20፤ 1 ተሰ. 1*9-10፤ ራዕይ 6*16-17) ፣ የኋለኛው ዘመን (ሕዝ.
38*8፤ 1 ጢሞ. 4*1) ፣ የዓለም መጨረሻ (ማቴ. 13*39)
5.2 የታላቁ ዘመን ምን ያህል ነው?

በዳንኤል 9÷26-27 መሠረት የመከራው ዘመን ለአንድ ሱባዔ እንደሚቆይ ይናገራል ብዙ ሰዎች እንደሚስማሙበት አንድ ሱባዔ
ሰባት ዓመት ነው ስለዚህ ታላቁ መከራ ለሰባት ዓመት ይቆያል፡፡
5.2.1 የዳንኤል ሰባኛ ሱባዔ

በነብዩ በዳንኤል ትንቢት መሠረት ኢየሩሳሌምን ለማደስ ትዕዛዝ ከሚወጣበት ጊዜ አንስቶ፣ የእስራኤል ኃጢአት ፈጽሞ
እስከሚሰረይበትና የዘላለም ጽድቅ እስከሚጀመርበት ጊዜ ያለው የጊዜ ርዝመት ሰባ ሱባዔ ወይም 490 ዓመት ነው፡፡ (ዳን.
9*24-25) ከዚህ ጊዜ ውስጥ 69 ሱባዔ ወይም 483 ዓመት ጌታ ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ተፈጽሞአል፡፡ (ዳን. 9*26) አንድ ሱባዔ ገና
ወደፊት ይቀራል፡፡ በ 69 ኛውና በ 70 ኛው ሱባዔዎች መካከል የቤተ ክርስቲያን ዘመን ገብቷል፡፡ (ማቴ. 21*43፤ ሐዋ. 15*14፤
ሮሜ 11*25) ይህ ዘመን፡-
 የእስራኤል መንግስት ከእስራኤል ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያደርግ ሕዝብ የተሰጠችበት ዘመን ነው፡፡ (ማቴ 21*43)

62
 የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ በእስራኤል ላይ ድንዛዜ የሆነበት ዘመን ነው፡፡ (ሮሜ 1*25)
 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ የሚወስድበት ዘመን ነው፡፡ (ሐዋ. 15*14)
 ለብሉይ ኪዳን ነብያት ተሰውሮ የነበረና፣ በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ዘመን ነው፡፡ (ኤፌ. 3*5-6)
ይህ ዘመን አብቅቶ ቤተ ክርስቲያን ስትነጠቅ፣ ተቋርጦ የነበረው የዳንኤል ሰባኛ ሱባዔ ይቀጥላል፡፡ በዚህ የመጨረሻ ሱባዔ ውስጥ
የእግዚአብሔር እቅድ ትኩረት እንደገና በእስራኤል ላይ ይሆናል፡፡ ይህ ሰባኛ ሱባኤ ( 7 አመት፣ 42 ጊዜ 2 ወራት፣ 1260 ጊዜ 2
ቀናት) ታላቁ መከራ ይባላል፡፡ (ዳን. 9*27፤ ራዕይ 11*2-3፤ 12*6)

5.3 በታላቁ መከራ ዘመን ጊዜ ምን ይሆናል?

የታላቁ መከራ ዘመን ሰባት ዓመት መሆኑን ተመልክተናል ይህንን ሰባት ዓመት ለሁለት ከፍለን እንመለከታለን፡፡
5.3.1 የመጀመሪያው ሶስት ዓመት ተኩል የመከራ ዘመን

በዚህ የመጀመሪያ ሦስት ዓመት ተኩል የሚከተሉት ነገሮች ይሆናሉ፡-


ሀ/ የሁለቱ ምስክሮች መነሳት (ራዕይ 11* 3-12)

በታላቁ መከራ መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር ልክ እንደ ኤልያስ እና ሙሴ ታላላቅ ተአምራት የሚያደርጉ ሁለት ምስክሮች
ያስነሳል፡፡ በአገልግሎታቸው ብዙ ሰዎች ይድናሉ አገልግሎታቸውን እንደጨረሱ በአውሬው ይገደላሉ፤ ሬሳቸው ለሦስት ቀን
ተኩል በአደባባይ ይጣላል ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከሞት ተነስተው ጠላቶቻቸው እያዩ ወደ ሰማይ ይወጣሉ፡፡
ለ/ የሐሰተኛው ክርስቶስ መገለጥ (2 ተሰ. 2*3-8፤ ራዕይ 13*1-10)

በመጀመሪያ ሦስት ዓመት ተኩል ከሚሆኑት ነገሮች መካከል ሌላው የሐሰተኛው ክርስቶስ መገለጥ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን
መነጠቅ ለሐሰተኛው ክርስቶስ መገለጥ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ምክንያቱም ከልካይ መንፈስ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር
ስለሚሄድ (በሙላት) ስለማይኖር፡፡ (2 ተሰ. 2*7)
የሐሰተኛ ክርስቶስ ማንነት ስንመለከት፡-

 በመከራው ዘመን ወደ አመራር በመምጣት ከእስራኤል መንግስት ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ያደርጋል፡፡ (ዳን. 9*27) ይህ ቃል
ኪዳን ለእስራኤል ከሚያስገኝላት መብቶች መካከል ቤተመቀደሷን መስራትና በዚያም እንደ ቀድሞው ስርዓትዋ
መስዋዕትንና ቁርባንን ማቅረብን ይጨምራል፡፡ (ዳን. 9*27፤ ማቴ. 24*15፤ 2 ተሰ. 2*4)
 ከሰይጣን በሆነ ተአምራዊ አሰራር ከሞተ በኋላ ሕይወት ያገኛል፡፡ (ራዕይ 13*3፤14) ትልቅ ስልጣን ያገኛል፡፡ (ራዕይ
13*2)
 በሰይጣን ኃይል ተአምራትን፣ ምልክቶችን፣ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋል፡፡ (2 ተሰ. 2*9-10)
 ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ በማድረግ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይቀመጣል፡፡ (ዳን. 11*36፤ ማቴ. 24*15፤
2 ተሰ. 2*4)

ሐ/ ሐሰተኛው ነብይ

ሐሰተኛው ነብይ በሰባተኛው ሱባዔ ውስጥ በዓለም የታሪክ መድረክ ላይ የሚገለጸው ሁለተኛው ሰው ነው፡፡ (ራዕይ 13*11-12)
እርሱም፡-
 በሐሰተኛው ክርስቶስ ስልጣን ይሰራል፡፡ (ራዕይ 13*12)

63
 ምድር ሁሉ ለክርስቶስ ተቃዋሚ እንዲሰግድለት ያደርጋል፡፡ (ራዕይ 13*12)
 እሳትን ከሰማይ እስኪያወርድ ድረስ ታላላው ተአምራትን ያደርጋል፡፡ (ራዕይ 13*13)
 ለክርስቶስ ተቃዋሚ ምስል እንዲሰሩ አሕዛብን ያነሳሳል የተሰራውም ምስል እስትንፋስ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ (ራዕይ
13*15)
 ሰዎች የክርስቶስን ተቃዋሚውን ስም ወይም የስሙ ቁጥር ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት (666) በክንዳቸው ወይም
በግንባራቸው እንዲቀበሉ ያደርጋል፡፡ (ራዕይ 13*16-17)

5.3.2 የሁለተኛው ሦስት ዓመት ተኩል የመከራ ዘመን

በታላቁ መከራ የሁለተኛው ሦስት ዓመት ተኩል ከሚሆኑ ነገሮች መካከል፡-


 በእስራኤልና በሐሰተኛው ክርስቶስ መካከል የነበረው ስምምነት ይፈርሳል፡፡ (ዳን. 9*27)
 የእስራኤል የስደት፣ የሽሽትና የመከራ ዘመን ይሆናል፡፡ (ራዕይ 12*1-17)
 የጥፋት እርኩሰት በተቀደሰ ስፍራ ይታያል፡፡ (ዳን. 9*27፤ ማቴ. 24*15፤ 2 ተሰ. 2*3-4)
 ሐሰተኛው ክርስቶስ ራሱን ከፍ በማድረግ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ይላል፡፡ (2 ተሰ. 2*4)
 የእስራኤል መከበብና በአሕዛብ መረገጥ ይሆናል፡፡ (ዘካ. 14*2፤ ራዕይ 11*2)
 እስራኤል ፊቷን በንስሐ ወደ አምላኳ ትመልሳለች፡፡ (ዘካ. 12*10፤ ሮሜ. 11*26)
5.3.3 በታላቁ መከራ ዘመን የሚድኑ ሰዎች

በታላቁ መከራ ዘመን በሁለቱ ምስክሮች ብዙ ሰዎች ይድናሉ፡፡ (ራዕይ 11*3-10) ከዚህ በተጨማሪ ከነገድና ከቋንቋ ሁሉ
144,000 የዳኑ አይሁዶች ለአሕዛብ የክርስቶስን ወንጌል ይሰብካሉ፡፡ (ማቴ. 24*14፤ ማር. 13*10፤ ራዕይ 7*4-17) እነዚህ
ሰዎች ውሸት በአንደበታቸው የማይገኝ ለወንጌል ቀናኢዎች ናቸው፡፡ (ራዕይ 14*5)
5.3.4 አርማጌዶን ጦርነት

ታላቁ መከራ የሚደመደመው በአርማጌዶን ጦርነት ነው ይህ ጦርነት በእስራኤል ሀገር አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ይደረጋል፡፡
(ራዕይ 16*16) የዓለም ነገስታት ሁሉ ይካፈሉበታል፡፡ (ዘካ. 14*2) ነገስታቱን ለጦርነት የሚያስከትቷቸው ርኩሳን መናፍስት
ናቸው፡፡ (ራዕይ 16*13-14) ጦርነት የሚካሄደው በአንድ በኩል በምድር ነገስታቶችና በመሪያቸው በክርስቶስ ተቃዋሚ ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በተከታዮቹ በኩል ነው፡፡ (ዘካ. 14*3፤ ራዕይ 19*19) ጦርነቱ በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣትና ድል አድራጊነት ይፈጸማል፡፡ (ዘካ. 14*4-5፤ 2 ተሰ. 2*8፤ ራዕይ 19*20-21)

ምዕራፍ ስድስት፡- ትንሣኤ


መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሁሉ በአዳም ምክንያት እንደሚሞትና እንዲሁም ደግሞ ሰው ሁሉ በክርስቶስ ሕያው እንደሚሆን
ያስተምራል፡፡ የሙታን ሁሉ ትንሣኤ በአንድ ጊዜ አይሆንም መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩና ተራ በተራ የሚሆኑ ትንሣኤዎች እንዳሉ
ያስተምራል፡፡ (ኢሳ. 26*19፤ ዳን. 12*13፤ ዮሐ. 5*28-29፤ ሐዋ. 24*15፤ 1 ቆሮ. 15*20-24፤ 1 ተሰ. 4*14-16፤ ራዕይ 20*13)

64
6.1 የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ

በትንሣኤ ቅደም ተከተል መሰረት የመጀመሪያውን ስፍራ የሚይዘው የክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡ ክርስቶስ ለሞቱት ሁሉ በኩራት
ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፡፡ የትንሣኤ በኩር ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ (1 ቆሮ. 15*20) የክርስቶስ ትንሣኤ የክርስትና እምነት መሰረት
ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ የሚከተሉት ውጤቶች ተገኝተዋል፡-
 ሞት በክርስቶስ ላይ ስልጣን ላይኖረው ክርስቶስ ድል አድርጐ ተነስቷል፡፡ (ሮሜ 6*9-10)
 ንስሐ እና አዲስ ሕይወት አግኝተናል፡፡ (ሐዋ. 5*30-31፤ 1 ጴጥ. 1*3-5)
 ሊመጣ ካለው ፍርድ አምልጠናል፡፡ (ሐዋ. 17*31፤ ሮሜ 5*9፤ 1 ተሰ.1*9-10)
 በእርሱ የሚያምኑ ክርስቶስ እንደተነሳ እነርሱም በትንሣኤ አካል ይነሳሉ፡፡ (ሮሜ 6*4፤ 8*11፤ 1 ቆሮ. 6*14፤ 2 ቆሮ.
4*14)
 የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጁ ሆኗል፡፡ (ራዕይ 1*18)
6.2 የቅዱሳን ትንሣኤ

ከጌታ ኢየሱስ ቀጥሎ በሁለተኛ ተራ የሚነሱት የእርሱ የሆኑት ናቸው፡፡ የቅዱሳን ትንሣኤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
እንደሚከተለው ተገልጻ E ል፡- “የፃድቃን ትንሣኤ” (ሉቃ. 14*14) ፣ “የሕይወት ትንሣኤ” (ዮሐ. 5*28-29) ፣“ፊተኛው
ትንሣኤ” (ራዕይ 20*6) በቅዱሳን ትንሣኤ የሚከተሉት ይሆናሉ፡-
 ኢየሱስን በማመን የሞቱ ቅዱሳን ከመከራው ዘመን በፊት የማይበሰብሰውንና ክቡር የሆነውን የትንሣኤ አካል በመልበስ
ከሞት በመነሳት ይነጠቃሉ፡፡ (1 ቆሮ. 15*51-54፤ ፊሊጵ. 3*21፤ 1 ተሰ. 4*15-18)
 በአዲስ አካል ሆነው በበጉ ሰርግ ላይ በምድር እንደሰሩት ስራ ሽልማት ይቀበላሉ፡፡ (ሉቃ. 14*14፤ 1 ቆሮ. 3*14፤
2 ጢሞ. 4*8፤ ራዕይ 2*7)
 በትንሣኤ አካል በምድር ላይ ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ይነግሳሉ፡፡ (ራዕይ 20*4)
6.3 የኃጥአን (የማያምኑ) ትንሣኤ

ይህ የኃጥአን ትንሣኤ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ዘመን ይኖሩ የነበሩ በኃጢአታቸው ንስሐ ሳይገቡ የሞቱ ሰዎችን ሁሉ
የሚያጠቃልል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን የኃጥአን ትንሣኤ በተለያየ ቋንቋ ይገልጸዋል፡፡ “የውርደትና የዘላለም ጉስቁልና”
(ዳን. 12*2) ፣ “የፍርድ ትንሣኤ” (ዮሐ. 5*28-29) ፣ “ሁለተኛው ሞት” (ራዕይ 20*6)
የኃጥአን ትንሣኤ ክርስቶስ ከቅዱሳን ጋር ወደ ምድር ከመጣና ሺህ ዓመት ከነገሰ በኋላ ይሆናል በኃጥአን ትንሣኤ የሚከተለው
ይሆናል፡-
 በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔርን እንደ ቃሉ ያልተከተሉ፣ ሌላ አማልክትን ያመለኩ እና የተከተሉ፣
ለክርስቶስ ወንጌል ተገቢ ምላሽ ባለመስጠት በኃጢአታቸው ጸንተው የኖሩት ላይ የኃጢአት ደመወዝ የሆነውን
ዘላለማዊ ሞት ይቀበላሉ፡፡ (ሮሜ 6*23)
 ከፍርድ በኋላ ለሰይጣንና ለመላዕክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡ (ራዕይ 20*12-15)
 ሰይጣንና መላዕክቱ፣ ሐሰተኛው ክርስቶስ፣ ሐሰተኛው ነብይ እና በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ያሉ ስማቸው በሕይወት
መጽሐፍ ያልተጻፉ ሰዎች በሙሉ የእሳት ባህር ወይም ሁለተኛው ሞት ይጠብቃቸዋል፡፡ (ዳን. 12*2፤ ራዕይ 19*20፤
20*12-15)
6.4 የትንሣኤ አካል ምን ይመስላል?
65
የትንሣኤ አካል የሚጨበጥና የሚዳሰስ ሲሆን ነገር ግን የሚታየው ነባራዊው ዓለም የማይዘው ሕመምና ሞት የማያውቅ፤
የከበረና የማይበሰብስ ሰማያዊ አካል ነው፡፡ (ሉቃ. 24*36-40፤ ዮሐ. 20*19-27፤ 1 ቆሮ. 15*53-54፤ 2 ቆሮ. 5*4-5)

ምዕራፍ ሰባት፡- የሺህ ዓመት መንግስት

ሺህ ዓመት የሚለው ቃል ሚሊኒየም ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አንድ ሺህ ዓመት ማለት ነው፤ ቃሉ
የመጣው ከራዕይ 20*4-5 ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ከመጣ በኋላ በክብር ዙፋን ላይ ይቀመጣል ያን ጊዜ የአንድ
ሺህ ዓመት መንግስት በመባል የሚታወቀው ዘመን ይጀምራል፡፡ (ዳን. 7*13-14፤ ማቴ. 19*28፤ 25*31፤ ራዕይ 20*4-6)

7.1 የሺህ ዓመት መንግስት አስተዳደሩ(የመንግስቱ ዜጐች/ተካፋዮች)

የሺህ ዓመት መንግስት የሚመሰረተው በምድር ላይ ነው፡፡ (ዘካ. 14*1-9፤ መዝ. 72*8-19፤ ኢሳ. 42*4፤ 65*20፤ ኤር. 23*3-6፤
ዳን. 2*35-45) የመንግስቱ ማዕከል ኢየሩሳሌም ትሆናለች፡፡ (ኢሳ. 2*3) የዚህ የሺህ ዓመት መንግስት ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ይሆናል፡፡ (ዳን. 7*14) ኃጢአት ይቀጣል ፍጹም ሠላምና ፍትህ በምድር ላይ ይሆናል፡፡ (ኢሳ. 11*3-5፤ 65*20) ሐዋርያትና
ሌሎች ቅዱሳን በዚህ መንግስት ውስጥ የተለያየ ኃላፊነቶችን ይቀበላሉ፡፡ (ኤር. 30*21፤ ኢሳ. 32*1፤ ማቴ. 19*28፤ ሉቃ.
19*11-27) በዚህ ሺህ ዓመት መንግስት በምድራዊ አካላቸው ሆነው ከታላቁ መከራ የተረፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም
በትንሣኤ አካል ከክርስቶስ ጋር አብራ ትገዛለች፤ እንስሳት እንኳ በስምምነት ይኖራሉ፡፡ (ኢሳ. 11*8-9) ሰይጣን ለሺህ ዓመት
ስለሚታሰር በምድር ላይ ፍጹም ሰላም ይሆናል፡፡ (ዘካ. 9*10፤ ኢሳ. 9*7፤ ራዕይ 20*3)
7.2 መንፈሳዊ ባህሪው

የሺህ ዓመት መንግስት የጽድቅ፣ የሰላም፣ የመንፈሳዊ ንጽሕና ዘመን ይሆናል፡፡ (ኤር. 23*5-6፤ ሕዝ. 36*24-26) ውኃ ባህርን
እንደሚከድን ምድርም እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለች፡፡ (ኢሳ. 2*3፤ 11*9) ፍጥረት ከጥፋት ባርነት ነጻ ይወጣል፡፡ (ሮሜ
8*19-22)

ምዕራፍ ስምንት፡- የመጨረሻው ፍርድ

እግዚአብሔር ጻድቅ ፈራጅ ስለሆነ ሰዎች ሁሉ ፍርዳቸውን ለመቀበል በታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ፊት ይቀርባሉ፡፡ (ራዕይ 20*11-
12) በዚህኛው ፍርድ ጊዜ “የሕይወት መጽሐፍ” የተባለ አንድ መጽሐፍና “መጻሕፍት” የተባሉ ሌሎች መጻሕፍት ይከፈታሉ
ሰዎች ፍርዳቸውን የሚቀበሉት በሁለቱ መጻሕፍት መሠረት ነው፡፡
8.1.1 የሥራ መጽሐፍ፡- የሰው ልጆች ሁሉ እንደ ስራቸው መጠን ፍርድ ይሰጣቸዋል፡፡ (ማቴ. 7*22-23፤ 25*32-41)
8.1.2 የሕይወት መጽሐፍ፡- በሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ያልተገኘ ሁሉ ወደ ሁለተኛው ሞት ይሄዳሉ፡፡ (ፊልጵ. 4*3፤
ራዕይ 20*12-15፤ 21*27)
8.2 ፈራጅ ማን ነው?

66
እግዚአብሔር አብ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ስለሰጠው ፈራጁ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ (ማቴ. 25*31፤ ዮሐ.
5*27፤ ሐዋ. 10*42፤ 2 ጢሞ. 4*1)
8.2.1 የሚፈረድባቸው እነማን ናቸው?

በመጨረሻው ፍርድ የሚፈረድባቸው፡-


ሀ/ መላዕክት ይፈረድባቸዋል፡- በእግዚአብሔር ላይ ያመጹት መላዕክት ሰይጣንን ጨምሮ ይፈረድባቸዋል፡፡ (1 ቆሮ. 6*3፤ 2 ጴጥ.
2*4፤ ይሁዳ 1*6፤ ራዕይ 20*1-3፤ 10)
ለ/ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኙ፡- በክርስቶስ ኢየሱስ ሳያምኑ የሞቱ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ላይ ያልተጻፈ ሰዎች በሙሉ
ይፈረድባቸዋል፡፡ (ዳን. 12*2፤ ዮሐ. 3*18፤ ራዕይ 20*12)

ምዕራፍ ዘጠኝ፡- ዘላለማዊ ኹነት


ከታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ በኋላ ዘላለም ይጀምራል፡፡ ዘላለም ሁለት ዓይነት ገጽታ አለው፡፡ እርሱም የጻድቃን የመጨረሻ ሁኔታ
እና የኃጥአን የመጨረሻ ሁኔታ ናቸው፡፡
9.1 የጻድቃን የመጨረሻ ሁኔታ

“ጻድቃን” የሚለው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ያንቀላፉትን የብሉይም ሆነ የአዲስ ኪዳን አማኞችን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
እነዚህ ቅዱሳን ወደ መንግስት ሰማይ ይሄዳሉ፡፡
9.1.1 ጻድቃን በመንግስተ ሰማይ (አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር)

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር አሁን የምንኖርባት ዓለም እንደምታልፍ እና አዲስ ሰማይና ምድር እንደሚሆን ይናገራል፡፡ (ኢሳ.
65*17፤ 2 ጴጥ. 3*13፤ ራዕይ 21*1)
ሀ/ አዲስ ሰማይና ምድር (ቅድስቲቱ ከተማ) ምን ትመስላለች

 በእግዚአብሔር ክብር የተሞላች ናት፡፡ (ራዕይ 21*11-23)


 ኢየሱስ መብራቷ ስለሆነ ሌላ ብርሃን አያስፈልጋትም፡፡ (ራዕይ 21*23)
 ከተማይቱ አስራ ሁለት በሮች አሏት፡፡ (ራዕይ 21*12-13 )
 መሠረቷ ከውድና ከከበሩ ድንጋዮች የተሰሩ ሲሆኑ የከተማይቱ መንገድ በሚያንጸባርቅ ንጹሕ ወርቅ የተሰራ
ነው፡፡ (ራዕይ 21*18-21)

ለ/ የቅዱሳን ሕይወት በዘላለም መንግስት

 ስቃይ፣ ለቅሶ፣ ጩኸት፣ ሐዘን፣ መከራ፣ ረሃብ በዚያ የለም፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፡፡
(ኢሳ. 25*8፤ ራዕይ 7*17)
 ከብዙ መላዕክት ጋር በደስታ እግዚአብሔርን እያመለኩና እያገለገሉ በዕረፍት ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ (ራዕይ 4*9-
10፤ 22*3)
 ሁሉ ነገር ለቅዱሳን ይሆናል፡፡ (ራዕይ 21*7)

67
9.2 ሽልማቶች (አክሊል)

አማኞች በመጨረሻው ቀን የሚቀበሉት ሽልማት በመጽሐፍ ቅዱስ አክሊል በመባል ይጠራል፡፡ (ራዕይ 3*11)
9.2.1 የማይጠፋ አክሊል፡- በሚገባ በመታገል ራሳቸውን በቅድስና በመግዛት እንደሚገባ ለሚመላለሱ የሚሰጥ፡፡
(1 ቆሮ. 9*24-26)
9.2.2 የደስታ (የድል) አክሊል፡- ነፍሳትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት በመመስከር ለሚያመጡ የሚሰጥ፡፡ (ዳን. 12*3፤
1 ተሰ 2*19-20)
9.2.3 የጽድቅ አክሊል፡- የተሰጣቸውን አገልግሎት በሚገባ ለሚጨርሱ የሚሰጥ፡፡ (2 ጢሞ. 4*8)
9.2.4 የክብር አክሊል፡- የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሚገባ ለሚመሩ ለታማኝ አገልጋዮች የሚሰጥ፡፡ (1 ጴጥ. 5*2-4)
9.2.5 የሕይወት አክሊል፡- ስለ ጌታ ኢየሱስ መስዋዕት ለሆኑ ቅዱሳን የሚሰጥ፡፡ (ራዕይ 2*10)
9.2.6 ሌሎችም ልዩ ልዩ ሽልማቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

9.3 የኃጥአን (የማያምኑ ሰዎች) የመጨረሻ ሁኔታ


ኃጥአን ከነጩ ዙፋን ፍርድ በኋላ ወደ ገሃነመ እሳት (የእሳት ባህር) ይሄዳሉ፡፡
9.3.1 ገሃነመ እሳት

ገሃነመ እሳት ለሰይጣንና ለመላዕክቱ የተዘጋጀ ነው፡፡ (ማቴ. 25*41) ኃጥአን (የማያምኑ ሰዎች ነፍስ) እየታወቃቸው ስሜታዊ፣

አዕምሮአዊና አካላዊ ስቃይ የሚጋፈጡበት እና ቀንና ሌሊት ለዘላለም የሚሰቃዩበት ስፍራ ነው። (ማቴ. 25*46፤ ሉቃ. 16*23፤

ራዕይ 20፡10) ጥልቅ ሐዘን፤ ዋይታና ጥርስ ማፏጨት የሚገለፅበት ቦታ ነው። (ማቴ. 13፡ 42) ይህ ቦታ ትሉ ፈፅሞ

የማይሞትበትና እሳቱም የማይጠፋበት ነው። (ኢሳ. 33*14፤ ማቴ. 3*12፤ ማር. 9*42-48)
ሀ/ የኃጥአን ሕይወት በገሃነመ እሳት
 ከእግዚአብሔር ተለይቶ ለዘላለም እየተሰቃዩ መኖር፡፡ (ማቴ. 25*41)
 ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት በሆነበት ስፍራ ለዘላለም እያለቀሱ መኖር፡፡ (ማቴ. 8*12፤ 25*41)
 በማይሞቱ ትሎች እና በማይጠፋ እሳት ለዘላለም መሰቃየት፡፡ (ማር. 9*47-48)
በመጨረሻም ዘመን ከሚሆኑት ነገሮች አንዱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ነው፡፡ እስከ አሁን እንደተመለከትነው
በመጨረሻው ዘመን የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም እንደሚከተለው ቅደም ተከተል ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡
 የቤተ ክርስቲያን ዘመን እስከ ክርስቶስ ምጽዓት ይቀጥላል፡፡
 ክርስቶስ በድንገት (ባልታሰበ ሰዓት) ይመጣል፡፡
 ቅዱሳን በሙሉ ከሞት ይነሳሉ፤በሕይወት ያሉትም አማኞች (ቤተ ክርስቲያን) በሙሉ በቅጽበት ይለወጣሉ፡፡ በአንድነት
ጌታን ለመቀበል በደመና ይነጠቃሉ፡፡ ከጌታ ጋርም በሰማይ ይቆያሉ፡፡
 የቤተ ክርስቲያንን መነጠቅ ተከትሎ የታላቁ መከራ ዘመን በምድር ይሆናል፡፡
 በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ክርስቶስ በግልጽ እየታየ ይመጣል፡፡ የአርማጌዶንን ጦርነት በድል ይፈጽማል፡፡ ሰይጣን
ለሺህ ዓመት ይታሰራል፡፡
 ክርስቶስ በምድር ላይ ለአንድ ሺህ ዓመት ይነግሳል፡፡
 በሺህ ዓመት መጨረሻ ሰይጣን ከእስራት ይፈታና ለጦርነት ይሰለፋል፡፡ በክርስቶስ ድል ይነሳል፡፡

68
 ከዚያ የኃጥአን ትንሣኤ ይሆንና በመጨረሻው ፍርድ ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡
 በመጨረሻም በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የቅዱሳንን የዘላለም ኑሮ ይሆናል፡፡

ኢየሱስ እሞታለሁ ብሎ ከሞተ፣ ኢየሱስ እነሳለሁ


ብሎ ከተነሳ፣ ኢየሱስ አርጋለሁ ብሎ ካረገ፣ ኢየሱስ
እመጣለሁ እንዳለ ይመጣል !!!!! ማራናታ ጌታ
ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና፡፡

ምዕራፍ አስር፡- ተግባራዊ ተዛምዶ

 በመሰረቱ ስለ ጌታ ምጽዓት እንጂ ስለ መነጠቅ ወይም ንጥቀት መቼ ሊከሰት እንደሚችል የተነገረ ምልክት በመጽሐፍ

ቅዱስ ውስጥ የለም፤ አሁን ሊሆን ይቻላል ወይም ነገ። ስለዚህ እንደ ሐዋርያት ሁላችንም ንጥቀት በእኛም ዘመን

ሊከሰት ይችላል ብለን ነው መኖር ያለብን። ወገኖች ሆይ፣ ጌታችን ሲመጣ በደመና ለመቀበልና ለመነጠቅ
ተዘጋጅተናልን? መለከት ሲነፋ፣ ድምጹን ሰምተው የሞቱ ቅዱሳን ከመቃብር ሲወጡ፣ በትንሣኤ አካል ጌታን ለመቀበል
በአየር ሲነጠቁ፣ እነርሱን ተከትለን በአየር ለመነጠቅ ራሳችንን እያዘጋጀን ነውን? ጌታን ለመቀበል በቅድስናና በጽድቅ
እየተመላለስን ነውን ወይስ እንደምድር ሰዎች ተስፋ እንደሌላቸው በምድራዊ ነገር ብቻ ተጠምደን አለን? ጌታችን
ሲመጣ ሳይነጠቁ የሚቀሩት የምድር ወገኖች ዋይ ዋይ ይላሉና፤ ጌታችን ሲመጣ ሳንነጠቅ እንዳንቀር ሁሌ የተዘጋጀ
ሕይወት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ “የክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም መምጣት በድንገትና ባልታሰበ ሰዓት ይሆናል” የሚለው ትምህርት
እምነታችንን አጥብቀን እንድንይዝና ተዘጋጅተን እንድንኖር ያደርገናል፡፡

 ዛሬም በርካታ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ዳግመኛ መመለስ ዙሪያ ያልተገባ አመለካከት አላቸው አገሬ በሰማይ ነው በማለት አሁን
የሚኖሩበትን ዘመን ወሳኝነት ቸል ይላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የምድር ቆይታችንን እና አሁን ያለብንን ሃላፊነት ምንም እርባና
እንደሌለው አድርገን እንድንቆጥረው አይፈልግም፡፡ ይልቁኑ ይህንን ጊዜ ለእርሱ ታማኝ ሆነን የምንዘልቅበት፣ በቅድስና የምናድግበት፣
በዓለምም የእርሱ ምስክሮች የምንሆንበት እንደሆነ እንድናየው በምድር አስቀምጦናል፡፡ የጌታን ዳግመኛ መመለስ እና የመጪውን
ዘመን በረከቶች በምንጠባበቅበት ወቅት በምድር ላይ ያለንን ኃላፊነት እየተወጣን መሆን አለበት፡፡ አማኞች በሙሉ በክርስቶስ ወንበር
ፊት ቀርበን በምድር ላይ ስለሰራነው ስራ የምንሸለምበት ወይንም ስራችን የሚቃጠልበት ስለሚሆን ዛሬ ቀን ሳለ ሽልማት ለመሸለም
ተግተን መስራት አለብን፡፡

 መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስተምረን በምድር ሳለን መከራ እንዳለብን ነው ያስተማረን። ይህ ሥጋ እስከሚዋጅበት ጊዜ ድረስ
በዚህ ሥጋ እስከኖርን ድረስ የውድቀት መዘዞች፣ ጠንቆችና ውጤቶች ይፈራረቁበታል። በሽታና ሞት በዚህ ዓለም
እስካለን ድረስ እንደ ማንኛውም ሰው ሊያገኘን ይችላል፡፡ እንደ ሰው ልንታመም እንችላለን፤ ጌታ መጥቶ ካልተነጠቅን

69
በቀር እያንዳንዳችንም በየተራችን እንሞታለን። በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ በፍጹም ጤንነት፣ ህመምና ደዌ፣
ሞትና መበስበስ በማይሆንበት የትንሣኤ አካል ለዘላለም እንኖራለን አሁን ግን በወደቀ ዓለም ውስጥ ስላለን
እንደማንኛውም ሰው ልንታመም፣ ልናዝን፣ ልንቸገር፣ እንችላለን፡፡ ይህንን አውቀን መኖር አለብን፡፡ ፍጹም ፈውስ ቃል
የተገባልን በዘላለም መንግስት ብቻ ነው፡፡ በዘላለም መንግስት ውስጥ ስቃይ፣ ለቅሶ፣ ጩኸት፣ ሐዘን፣ መከራ፣ ረሃብ
በዚያ የለም፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፡፡

የመጨረሻው ዘመን የክለሳ ጥያቄዎች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– የሰው ልጅ የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት ከእግዚአብሔር አብ በቀር ማንም አያውቅም፡፡


2. –––––– ኢየሱስ ዳግም የሚመጣው በመንፈስ እንጂ በአካል አይደለም፡፡
3. –––––– አማኞች ሁሉ በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ይቀርባሉ፡፡
4. –––––– በትንሣኤ ቅደም ተከተል መሰረት የመጀመሪያውን ስፍራ የሚይዘው የክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡
5. –––––– ቤተ ክርስቲያን በታላቁ መከራ ውስጥ ታልፋለች፡፡

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ

6. የመካከለኛው ማንነት (ስርዓት) ሀ/ ገነት


7. የአብርሃም እቅፍ ለ/ ነፍስ መታጠቢያ ስፍራ
8. ሚሊኒየም ሐ/ በስጋዊ ሞትና በትንሣኤ መካከል ያለው ጊዜ
9. አክሊል መ/ አንድ ሺህ ዓመት
10. መካነ መጽሔት (ፐርጋቶሪ) ሠ/ የፍዳው ዘመን
ረ/ ሽልማት
ሰ/ ሲኦል

ትክክለኛን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. ኃጢአተኞች ከሞት በኋላ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበት ስፍራ ምን ይባላል?
ሀ/ ሲኦል፡፡
ለ/ መንግስተ ሰማይ፡፡
ሐ/ ገነት፡
መ/ ገሃነመ እሳት፡፡
12. ስለ መካከለኛው ማንነት (ስርዓት) ትክክል የሆነው አስተምህሮ የቱ ነው?
ሀ/ ከአካላዊ ሞት በኋላ መኖር የለም፡፡
70
ለ/ ከስጋ ሞት በኋላ የአማኞች ነፍስ ወደ ገነት በመሄድ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት በማድረግ ደስታ ስታገኝ የማያምኑ ሰዎች
ነፍስ ግን ወደ ሲኦል ትሄዳለች፡፡
ሐ/ ነፍስ በእንቅልፍ (በሰመመን) ውስጥ በመሆን የማትነቃ ትሆናለች፡፡
መ/ ነፍሳችን (መንፈሳችን) ወደ ነፍስ መታጠቢያ ስፍራ (ፐርጋቶሪ) ትሄዳለች፡፡
13. ኢየሱስ ክርስቶስ የመምጫው ጊዜ መቃረቡን የሚጠቁሙ ምልክቶች መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ጦርነትና የጦርነት ወሬ መሰማት፡፡
ለ/ ረሃብ፣ ቸነፈርና የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መሆን፡፡
ሐ/ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በኢየሱስ ስም መምጣትና ብዙዎችን ማሳት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
14. የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሁለት መልኮች ወይም ገጽታዎች ምንና ምን ናቸው?
ሀ/ ስውር አመጣጡ (ለቤተ ክርስቲያን መምጣቱ)
ለ/ ግልጽ አመጣጡ (ከቤተ ክርስቲያን ጋር መምጣቱ)
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው።
መ/ መልስ አልተሰጠም፡፡
15. አማኞች ጌታ ኢየሱስን በአየር ለመቀበል ከምድር ወደ አየር የሚያደርጉት ጉዞ ምን ይባላል?
ሀ/ ታላቁ መከራ፡፡
ለ/ ንጥቀት፡፡
ሐ/ ሚሊኒየም፡፡
መ/ ትንሳኤ፡፡
16. በታላቁ መከራ ዘመን ምን ይሆናል?
ሀ/ ሁለቱ ምስክሮች ይነሳሉ፡፡
ለ/ ሐሰተኛው ክርስቶስ ይገለጣል፡፡
ሐ/ ሐሰተኛው ነብይ ይገለጣል፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
17. በመጨረሻው ፍርድ የሚፈረድባቸው እነማን ናቸው?
ሀ/ መላዕክት ይፈረድባቸዋል፡፡
ለ/ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኙ፡፡
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
መ/ መልስ አልተሰጠም፡፡
18. ስለ መጨረሻው ዘመን ትክክለኛው ቅደም ተከተል የቱ ነው?
ሀ/ የቤተ ክርስቲያን ዘመን - ንጥቀት - ታላቁ መከራ - ሚሊኒየም - ዘላለም
ለ/ ንጥቀት - ታላቁ መከራ - ሚሊኒየም - የቤተ ክርስቲያን ዘመን - ዘላለም
ሐ/ ሚሊኒየም - ታላቁ መከራ - የቤተ ክርስቲያን ዘመን - ንጥቀት - ዘላለም
መ/ ታላቁ መከራ - ሚሊኒየም - ንጥቀት - የቤተ ክርስቲያን ዘመን - ዘላለም

71
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. ከመጨረሻው ዘመን ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ብቻ በመምረጥ በዝርዝር ግለጹ? (ሞት፣ የመካከለኛው ማንነት
(ስርዓት)፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መመለስ (ምጽዓት)፣ ንጥቀት፣ ታላቁ መከራ፣ ትንሣኤ፣ የሺህ ዓመት መንግስት፣
የመጨረሻው ፍርድ፣ ዘላለማዊ ኹነት)

20. ኢየሱስ ክርስቶስ የመምጫው ጊዜ መቃረቡን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ነግሮናል፡፡የእነዚህ ምልክቶች አገልግሎት
(ጠቀሜታ) ምንድን ነው?

72
ትምህርት አምስት፡- መለኮታዊ ስርዓት

ምዕራፍ አንድ፡- መለኮታዊ ስርዓት


እግዚአብሔር በቤተሰብ፣ በቤተክርስቲያን እና በመንግስት መዋቅር ውስጥ መለኮታዊ ስርዓትን አስቀምጧል፡፡ መለኮታዊ
ስርዓትን መንፈሳዊ ስልጣን በማለትም መጠቀም እንችላለን፡፡ መለኮታዊ ስርዓት ከገባንና በሕይወታችን መተግበር ከቻልን ብዙ
ችግሮቻችንን ማስወገድ እንችላለን፡፡ በዚህ ዘመን በቤተሰብ፣ በቤተክርስቲያን እና በመንግስት አካባቢ ለሚታዩ ችግሮች አንዱና
ዋንኛው ምክንያት መለኮታዊ ስርዓት እየተዛባ (እየጠፋ) መምጣቱ ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍቃዱን የሚፈጽመው በመለኮታዊ
ስርዓት ውስጥ ነው፡፡

1.1 ትርጉም

መለኮታዊ ስርዓት ማለት የእግዚአብሔር እቅድ ተፈጻሚነት ያገኝ ዘንድ እግዚአብሔር በቃሉ የደነገገው የአሰራር ስልትና ደንብ
ነው፡፡ ሰፋ አርገን ስንመለከተው እንደታዘዘው፣ እንደተቀመጠውና እንደተጻፈው ማከናወን (መስራት) ማለት ነው፡፡ መለኮታዊ
ስርዓት በነገር ሁሉ የመምራት፣ የመፍረድ፣ የመግዛት፣ ማንኛውንም ነገር በትክክል ለማድረግ ከእግዚአብሔር ለሰው የሚሰጥ
ስልጣን ነው፡፡ በሌላ በኩል ትዕዛዝ የመስጠትና እንዲታዘዙትም የማድረግ ወይም ማንኛውንም ነገር የማድረግ እግዚአብሔር
የሰጠው ስልጣን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ስልጣን የተሰጠዉ አካል የተሰጠውን ስልጣን የሚለማመድበት ወይም የሚያስፈፅምበት
ክልል መለኮታዊ ስርዓት ይባላል፡፡

1.2 መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት

የመለኮታዊ ስርዓት ፅንስ ሀሳብ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን በስፋት ተገልጾ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-

1.2.1 መለኮታዊ ስርዓት በብሉይ ኪዳን

ብሉይ ኪዳንን ስንመለከት እግዚአብሔር ከፍጥረት አጀማመር ጀምሮ መለኰታዊ ስርዓትን ሲደነግግ፤ የሰው ልጅ ደግሞ
ባለማቋረጥ ይህንን ስርዓት ሲያበላሽና ቅጣት ሲቀበል እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡-
 በዘፍጥረት መጽሐፍ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድር በፈጠረ ጊዜ ፍጠረትን በስርዓት ሲያስቀምጥ እንመለከታለን፡፡
(ዘፍ. 1፡2-4)
 መለኰታዊ ስርዓትን ጠብቆ እግዚብሔርን እንዲያገለግል በኤደን ገነት የተቀመጠው የተቀባው ኪሩብ መላዕክ ወደ
ሰይጣንነት የተቀየረው በእግዚአብሔር ስልጣን ላይ በማመጽ መለኰታዊ ስርዓትን ባለመጠበቁ ነበር፡፡ (ኢሳ. 14*12-
15፤ ሕዝ. 28*13-17)
 በራሱ ያልተሳካለትን መለኰታዊ ስርዓትን የማፍረስ ተግባር ወደ አዳምና ሔዋን ይዞ ሲመጣ እንመለከታለን፡፡ (ዘፍ.
3*1-6) በዘፍጥረት መጽሐፍ የተቀመጠውን የአዳምና የሔዋን ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር አምላክ አዳምን
ከፈጠረ በኋላ በኤደን ገነት መለኰታዊ ስርዓትን ሲያስቀምጥ እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን በኤደን
ገነት በመሾም በመለኰታዊ ስርዓት ስር መሆኑን፤ መታዘዝን እና ለስልጣን መገዛትን እንዲማር መልካሙንና ክፉን
ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ በማለት ሲያስጠነቅቀው እንመለከታለን፡፡(ዘፍ. 2*16-17) የሰው ውድቀት የጀመረውም
ልክ እንደ ሰይጣን፤ አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረግ በመለኰታዊ ስርዓት ላይ በማመጹ ነው፡፡ (ዘፍ. 3*6)
73
 እግዚአብሔር ስለ ታቦቱና የማደሪያው ድንኳን አሰራር “በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሰራ ተጠንቀቅ”
በማለት ለሙሴ ሲነገረው እንመለከታለን፡፡ (ዘጸ. 25*40፤ 26*30) የሚሰራበትን እቃዎችና ቀለም እንኳን ሳይቀር
የመረጠው እግዚአብሔር ነበር፡፡ እግዚአብሔር መለኮታዊ ስርዓት ተጠብቆ እንዲሰራ ይፈልግ ነበር፡፡
 የአሮን ሁለቱ ልጆች ናዳብና አብዩድ መለኮታዊ ስርዓቱን በመተላለፍ በእግዚአብሔር ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ
እሳት ስላቀረቡ እሳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ እንደበላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ (ዘሌ. 10*1-2)
እግዚአብሔር ሌላ እሳት በማቅረባቸው ብቻ ሳይሆን የቀጣቸው፤ አገልግሎቱን በተመለከተ አሮን ዋናውና ቀዳሚው
ሲሆን ልጆቹ ናዳብና አብዩድ እርሱን ለመርዳት የተቀመጡ ናቸው፡፡ ለብቻቸው እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር በፍጹም
አላዘዘም፡፡ በዘሌዋውያን ምዕራፍ ስምንት ብቻ 12 ጊዜ አሮንና ልጆቹ በሚል የተጠቀሰ ሲሆን ልጆቹ አሮንን እንዲረዱ
እንጂ ለብቻቸው እንዲያቀርቡ አላዘዘም፡፡ እነርሱ ግን መለኰታዊ ስርዓትን በመጣስ ከአባታቸው አሮን ፍቃድ ውጪ
ለማገልገል ሲነሱ እንደተቀሰፉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
 ማርያምና አሮን የሙሴ ታላቅ ወንድም እና እህት ሲሆኑ በቤት ውስጥ ለእነርሱ መታዘዝ ሙሴ የሚገባው ሲሆን
በውጪ ባለው የእግዚአብሔር ስራ ግን ዋናው ሙሴ ነበር፡፡ እህትና ወንድም መለኮታዊ ስርዓቱን በመጣስ ሙሴን
በተቃወሙት ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ በማርያም ላይ እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ (ዘኁ. 12*1-16)
በተመሳሳይ ሁኔታ በሙሴ ስልጣን ላይ የተነሱት ቆሬ፣ ዳታንና አበሮን ተመሳሳይ ቅጣት ሲደርስባቸው እንመለከታለን፡፡
(ዘኁ. 16*1-35)
 ዳዊት መለኰታዊ ስርዓቱን በመጣስ በሌዋውያን መምጣት የሚገባውን የቃል ኪዳኑን ታቦት በአዲስ ሰረገላ አድርጐ
በበሬዎች ለማምጣት ሲሞክር፤ በሬዎቹ በፋነኑ ጊዜ ዖዛ እጁን ዘርግቶ መንካት የሌለበትን ታቦት ሲነካ እንደተቀሰፈ፤
ዳዊትም በድጋሚ መለኮታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በሌዋውያን ሲያስመጣ ታቦቱ በሰላም ወደ ከተማ እንደመጣ መጽሐፍ
ቅዱስ ይነግረናል፡፡ (2 ሳሙ. 6*1-17፤ 1 ዜና. 15*12-13) ስለዚህ አገልግሎትን በተመለከተ ዋና ቁም ነገር እግዚአብሔር
ምን አደረግን ብቻ ሳይሆን የሚመለከተው እንዴት አደረግን የሚለውንም ይመለከታል ወይንም ያደረግንበትን መንፈስ
ብቻ ሳይሆን የሚመለከተው መለኮታዊ ስርዓቱን ጠብቀን ማድረጋችንንም ይመለከታል፡፡
 ንጉስ ዖዝያን ታላቅ በሆነ ጊዜ ልቡ እንደታበየ እና መለኰታዊ ስርዓትን በመጣስ ካህናት ብቻ የሚሰሩትን ስራ ወደ
መቅደስ ገብቶ ካላጠንኩ ባለ ጊዜ በእግዚአብሔር እንደተቀጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ (2 ዜና. 26*16-21)
 የእስራኤል የመጀመሪያ ንጉስ ሆኖ የተሾመው ሳኦል መለኰታዊ ስርዓቱን ጠብቆ ከመምራት ይልቅ የራሱን መንገድ
ተከትሎ ያልተገባውን የካህን ስራ ለመሰራት ሲሞክር ንግስናውን እንዳጣ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ (1 ሳሙ.
13*9-14) እግዚአብሔር ንግስናውን ወስዶ “እንደ ልቤ” ላለው ለዳዊት ሰጠው፡፡ ምንም እንኳን ዳዊት ባለማወቅ
መለኰታዊ ስርዓትን የተላለፈበት ወቅት ቢኖርም በብዙ ቦታ መለኰታዊ ስርዓትን በመጠበቅ ከእርሱ በኋላ ለተነሱ
ነገስታት ሁሉ እንደ ምሳሌ እየተጠቀሰ የቀጠለ ንጉስ ነበር፡፡ (1 ሳሙ. 24*4-6፤ 26*9-11፤ 2 ሳሙ. 1*14፤ ሐዋ.
13*22)
 በብሉይ ኪዳን የነበሩ አብዛኛው ነገስታት፣ ነብያት፣ ካህናት መለኰታዊ ስርዓትን ባለመጠበቅ ሕዝቡን ወደ ጥፋት
በመምራት ለውድቀት ቢዳርጉትም በዛው ልክ ደግሞ መለኰታዊ ስርዓቱን በመጠበቅ ሕዝብን በመልካም የመሩ
ነገስታት፣ ነብያትና ካህናት ነበሩ፡፡

1.2.2 መለኰታዊ ስርዓት በአዲስ ኪዳን


74
ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሲጽፍ “ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በስርዓት ይሁን” ይላል፡፡ (1 ቆሮ. 14*40)

ቀጥሎም ሰለ እግዚአብሔር ባህሪ ሲናገር “እግዚአብሔርስ የሰላም (የስርዓት) አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና

በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው፡፡” (1 ቆሮ. 14*33) ይላል፡፡ የምናገለግለው እግዚአብሔር የስርዓት አማላክ

ስለሆነ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ነገር መለኮታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በስርዓት እንዲሰራ ይፈልጋል፡፡ መለኮታዊ ስርዓትን

በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ተጠቅሶ የምናገኘው ሲሆን ተመሳሳይ ትርጉምን ይዞ እናገኘዋለን፡፡ (ቆላ. 2*5፤

1 ጢሞ. 3*14-15፤ ቲቶ 1*5) መለኮታዊው ስርዓት ሲዛባ ክፍፍል፣ ግጭት ፀብና መለያየት ይፈጠራል፡፡ በአዲስ ኪዳን የተወሰኑ

የመለኮታዊ ስርዓት ምሳሌዎችን እንመልከት፡-

 መጽሐፍ ቅዱስ በስላሴ አካላት መካከል መለኮታዊ ስርዓት እንዳለ በግልጽ ያስተምራል፡፡ አንዱ ሌላውን ሲልክ፤
እንዲሁም አንዱ ሌላውን ሲታዘዝ እንመለከታለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለአብና ለወለድ ይገዛል (በአብና በወለድ ተልኮ
መጥቷል)፡፡ (ዮሐ. 14*15-16፤ 14*26፤ 15*26፤ 16*7፤ 16*13-14) ኢየሱስ ክርስቶስ ለአብ ይታዘዛል (የአብን ፍቃድ
ይፈጽማል)፡፡ (ሉቃ. 22*42፤ ዮሐ. 4*34፤ 6*38፤ 5*30፤ 17*21፤ 1 ቆሮ. 11*3) ሁለት አይነት መገዛት አለ፡፡
አንደኛው ከስራ ክፍፍል የተነሳ መገዛት (Functional Subordination) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከማንነት የተነሳ
(Ontological Subordination) መገዛት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄኛው መገዛት የስራ ክፍፍልን የሚያሳይ እንጂ መበላለጥን
የሚያሳይ አይደለም፡፡ አንዱ ለሌላው ይገዛል ማለት አንዱ ከሌላው ያንሳል ማለት አይደለም፡፡ ሦስቱም የስላሴ አካላት
የእግዚአብሔር ማንነትና ባሕርያት በሙላት አላቸው አብ ፍጹም እግዚአብሔር ነው ወልድ ፍጹም እግዚአብሔር ነው
መንፈስ ቅዱስ ፍጹም እግዚአብሔር ነው፡፡ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ መበላለጥና መተናነስ የሚባል ነገር
የለም፡፡
 መለኮታዊ ስርዓትን በቃልም በተግባርም ያስተማረ ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 23 ቁጥር 3 ላይ

ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ ስለ መለኰታዊ ስርዓት ሲያስተምር እንዲህ ሲል ገልጿል፡፡ “ስለዚህ
ያዘዝኋችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁም ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ስራቸው አታድርጉ” ይላል፡፡ ለምን
የሚያዟቸውን ማድረግ እና መጠበቅ እንዳለባቸው ሲገልጽ “ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል”
በማለት ይገልጻል፡፡ (ማቴ. 23*2) ኢየሱስ በተለያየ ስፍራ መለኮታዊ ስርዓትን ሲያስተምር እና ሲተገብር
እንመለከታለን፡፡ (ማቴ. 17*24-27፤ 22*21፤ ማር. 14*60-62)
 ሌላው ስለ መለኮታዊ ስርዓት የሚገልጽ ጥሩ ምሳሌ የምናገኘው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6 ላይ ነው፡፡ ሐዋርያው
ጴጥሮስ በምግብ ማደል አሠራር ላይ ለተነሳው ችግር ሲመልስ እንዲህ ነበር ያለው፡- “እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን
ለማገልገል እንተጋለን” (ሐዋ. 6*4) ሰይጣን በሐዋሪያት የተጀመረውን የወንጌል ስራ በማሳሰር፣ በማስፈራራትና
በተለያየ መንገድ ሊያስቆመው ስላልቻለ በሌላ መንገድ ሲገለጥ እናያለን፤ እግዚአብሔር ስራውን የሚሰራው
በመለኰታዊ ስርዓት ውስጥ እንደሆነ ስለገባው፤ በአማኞች መካከል ክፍፍል በመፍጠር ሐዋርያት ስብከትና ጸሎት
ትተው ምግብ እንዲያከፋፍሉ በማድረግ ሌላ ጥሪ የሌላቸውን ሰዎች ወደ አገልግሎት በማምጣት የተጀመረውን
የወንጌል ስራ መለኮታዊ ስርዓቱን በማበላሸት ለማስቆም ሰይጣን ያቀደውን ዕቅድ ጴጥሮስ ስለገባው
“የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም” በማለት የሰይጣንን ዕቅድ ጴጥሮስ
ሲያበላሽ እንመለከታለን፡፡ (ሐዋ. 6*2)

75
 እንዲሁም በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 19 ላይ የመለኮታዊ ስርዓት አስፈላጊነት በግልጽ እንመለከታለን፡፡ ስልጣን
ያልተሰጣቸው የካህናት አለቃ የአስቄዋ ልጆች አጋንንትን ለማስወጣት የኢየሱስን ስም ሲጠቀሙ ክፉው መንፈስ
መልሶ “ኢየሱስን አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ እናንተስ እነማን ናችሁ” በማለት እንዳሸነፋቸው
መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ (ሐዋ. 19*13-16)
 በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 እንደተገለጸው ሐዋርያ ዮሐንስ ሰባቱን ደብዳቤዎች ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
መላዕክት (መሪዎች) እንዲጽፍ ነበር የተነገረው፡፡ (ራዕይ 1*20) የኤፌሶን መሪ “ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ
ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ” (2*2) በማለት ሲሞገስ በተቃራኒው በትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን
መለኮታዊ ስርዓት ተበላሽቶ ነበር፡፡ ኤልዛቤል ነብይ ነኝ ብላ ተቀምጣ የስህተት ትምህርት በማስተማር ብዙዎችን
ታስት ስለነበር የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መሪ ሲነቀፍ እንመለከታለን፡፡ (ራዕይ 2*20)
 ሐዋርያት በትምህርታቸው ስለመለኮታዊ ስርዓት ብዙ አስተምረዋል፡፡ (ሐዋ. 23*4-5፤ 1 ቆሮ. 16*10-11፤ 1 ጢሞ.
5*17፤ ፊልጵ. 2*29፤ ዕብ. 13*17)

1.3 መለኮታዊ ስርዓትና ስልጣን

መለኮታዊ ስርዓት ስልጣንን የሚያንጸባርቅ በመሆኑ ስለ ስልጣን ማወቅና መረዳት ይኖርብናል፡፡ ስልጣን ስንል ስልጣን ሰጭና
ስልጣን ተቀባይ አለ፡፡ በመለኮታዊ ስርዓት ስልጣን ሰጪው እግዚአብሔር ሲሆን ተቀባዩ ግን በጌታ የተመረጠ ሰው ነው፡፡ አንድ
ግለሰብ የተቀበለው ስልጣን ከፍ ባለ ቁጥር ኃላፊነቱና ተጠያቂነቱ በዚያው መጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ መለኮታዊ ስርዓት
የሚዘረጋው ስልጣን ባለው ሰው በኩል ነው፡፡ (ዘጸ. 25፡1፣25፤ 1 ቆሮ. 10፡1-11፤ ኤፌ. 2፡20)

1.4 ስለ መለኮታዊ ስርዓት ትክክል ያልሆኑ አመለካከቶች

በዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት የተሳሳቱ አመለካከቶች (ጽንፎች) አሉ፡፡ በአንድ በኩል ምዕመኑና አገልጋዩ እኩል ነው
በመካከላችን ምንም ልዩነት የለም በማለት እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ስጦታ አድርጐ የሰጠውን አገልጋዮችን የመናቅና
ያለመታዘዝ ለአገልጋዮች ስፍራ ያለመስጠት ነገር ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ
አገልጋዮች የስልጣን ማዕከል ራሳቸው በመሆን የተለየ ክብርና አምልኮ ከምዕመኑ በመቀበል በተጨማሪም የሚያስተምሩት
ትምህርት ብቻ ሳይሆን ልምምዳቸውም በእግዚአብሔር ቃል እንዳይፈተሽ ጸጥና ዝግ ብሎ ምዕመኑ እንዲቀበላቸው በስልጣን
ቃል በማዘዝ ለእነርሱ ትምህርትና አካሄድ ላይ (ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ቢሆኑም እንኳን) ጥያቄ ማንሳት መንፈስ ቅዱስን እንደ
መቃወም፣ የተቀባውን እንደ መንካት፣ ሲከብድም የእግዚአብሔርን ቁጣ (መቅሰፍትን) እንደመጋበዝ ስለሚቆጠር
አስተምህሮታቸውን እና ልምምዳቸውን በወደዱት መንገድ ያለምንም ተጠያቂነት ያስኬዱታል፡፡ ሁለቱም የተሳሳቱ
አመለካከቶች ናቸው፡፡

1.4.1 አገልግሎት ለማን የተሰጠ ነው?

በመለኮተዊ ስርዓት ውስጥ ልንጠይቀው የሚያስፈልገው የመጀመሪያ ጥያቄ በመጽሐፍ ቅዱስ አገልግሎት ለማን የተሰጠ ነው?
የሚለውን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፡፡ (ዘጸ. 19*5-6፤ ዘዳ. 7*6፤ መዝ.
135*4) ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ደግሞ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን በሙሉ በማፍሰስ ምንም ዓይነት ምድራዊ ስራ

76
ከመስራት ተቆጥበው እግዚአብሔርን ለማገልገል የተመረጡና የተለዩ ሌዋውያን፣ ካህናት፣ ነብያት፣ ነገስታት ነገሩ፡፡ (ዘጸ. 28*1፤
መሳ. 4*4-5፤ 1 ሳሙ. 16*13)
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ በ 1 ጴጥ. 2*9 እንዲሁም በራዕይ 1*6 እንደምናየው በጌታ በኢየሱስ አምነው ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም
የተወለዱ ሁሉ ለአገልግሎት ተመርጠዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን የክህነት አገልግሎት ለሌዊ ነገድ የተወሰነ ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን ግን
አማኞች ሁሉ ለክህነት አገልግሎት ተመርጠዋል፡፡ ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር የተወሰኑ ሰዎችን ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት
አይለይም ማለት አይደለም፡፡ ለተለየ አገልግሎት የተመረጡና የተጠሩ ለቃሉና ለጸሎት የሚተጉ ሐዋርያት፣ ነብያት፣ እረኞች
ወንጌላውያንና አስተማሪች የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ናቸው፡፡ (ኤፌ. 4*11-13) እነዚህ ከጌታ ዘንድ ልዩ ጥሪ የደረሳቸው ናቸው፡፡
(ማር. 16*20፤ ሐዋ. 1*17፤ 13*1-3)

1.4.2 አገልጋዬችን ማክበር

በቤተ ክርስቲያን የሚደረጉ አገልግሎቶች በሙሉ በመከባበር በመቀባበል ላይ የተመሰረቱ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፍ ቅዱስ
ያስተምራል፡፡ የቤተ ክርስቲያን መረዎች የተከበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ
ስጦታዎች ስለሆኑ ልናከብራቸው፣ ልንታዘዛቸው እና በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ልንከባከባቸው እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ
ያዘናል፡፡ (ሮሜ. 15*24-25፤ 1 ቆሮ. 9*8-14፤ 1 ተሰ. 5*12-13፤ ፊልጵ. 2*29፤ ዕብ. 13*17) መጽሐፍ ቅዱስ “በመልካም
የሚያስተዳድሩና ሽማግሌዎች ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት እጥፍ ክብር ይገባቸዋል” (1 ጢሞ. 5*17)
እንደሚል አገልጋዮቻችንን በፍቅርና በአክብሮት መያዝ አለብን፡፡ የአገልጋዮች ክብራቸው የተመሰረተው ባላቸው የጽድቅ
ሕይወት፣ ታማኝነት፣ ቤተ ክርስቲያንን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመምራታቸው እና ለአገልግሎት በመትጋታቸው ነው፡፡

1.4.3 አገልጋዮች ሲያጠፉስ?

አገልጋዮች በትምህርታቸው በልምምዳቸውና በሕይወታቸው ላይ ግልጽ ስህተት ፈጽመው ሲገኙ መለኮታዊ ስርዓቱ ተጠብቆ
እንደ እግዚአብሔር ቃል መጠየቅ እንዳለባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ጻድቁና እንከን የሌለበት አምላካችን
እግዚአብሔር በትንቢተ ኢሳያስ 1*18 ላይ “ኑና እንዋቀስ” በማለት እስራኤልን ሲጣራ እንመለከታለን፡፡ ልውቀሳቹሁ ከማለት
ይልቅ እንዋቀስ ማለቱ በድያችሁም ከሆነ መረጃችሁን አቅርቡና እንነጋገር ማለት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ
“ራሱንና ትምህርቱን ለትችት አጋልጦ” ምናልባት አይሁድ እርሱን የሚከሱበት ምክንያት ካላቸው ብሎ “ከእናንተ ስለ ኃጢአት
የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንኩ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም” (ዮሐ. 8*46) በማለት ተናግሯል፡፡ ራሱ እውነት
የሆነ ጌታ ይህን ያህል ራሱን ዝቅ ካደረገና አይተነው መርምረነው ቀምሰነው እንድንከተለው ከፈቀደ፤ የየትኛውም አገልጋይ
ትምህርታቸውና ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ቃል መፈተሽ አለበት፡፡ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ የተነጠቀው ሐዋሪያ
ጳውሎስም በተመሳሳይ ሁኔታ አገልግሎቱንና ሕይወቱን ሲስፈትሽ እንመለከታለን፡፡ (ገላ. 2*1-2) የተቀባው ንጉስ ዳዊት
ሲበድል፣ ሲስትና ሲያጠፋ …. ነብዩ ናታን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በመሄድ ሲገስጸው እናያለን፡፡ (2 ሳሙ. 12*7-13)
እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ጳውሎስ ሐዋርያው ጴጥሮስን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄደ ባየ ጊዜ በሁሉ ፊት ሲገስጸው
እንመለከታለን፡፡ (ገላ. 2*14) እግዚአብሔር የቀባውን አገልጋይ ማክበር እግዚአብሔርን ማክበር ስለሚሆን ጥሩ ነው፡፡ አገልጋዩ
ደግሞ ሰው መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀምበትም ቢሆንም ሰው ስለሆነ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ (ዘኁ. 20*8-
13) ሲያጠፋ ጥፋቱ በግልጽ ሊነገረውና ሊገሰጽ ይገባል፤ ይህ ጽድቅ እንጂ እግዚአብሔር በቀባው ላይ በድፍረት መናገር
አይደለም፡፡ (1 ጢሞ. 5*19-20) ይህም ቢሆን ግን ማስተዋል ያለብን እግዚአብሔር የስርዓት አምላክ ስለሆነ የምናደርገውን
ሁሉ እንደ ቃሉ በፍቅርና በብዙ ጸሎት ማድረግ ይገባል፡፡ (ማቴ. 18*15-18፤ ገላ. 6*1፤ 1 ጢሞ. 5*1-2) በቤተክርስቲያን ውስጥ
77
ቡድንተኝነት፣ አድመኝነት፣ መፈንቅለ ስልጣን በፍጹም አይሰራም፡፡ ይህ እግዚአብሔር የሚጸየፈው የስጋ ስራ ነው፡፡ (ምሳሌ
6*16-19) እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ሰው በአመጽ፣ በሴራ፣ በአድማ ካለበት ስፍራ ለማውረድ መሞከር የቤተክርስቲያን
ባለቤት የሆነውን ኢየሱስን መጋፋት ነው፡፡ (ሐዋ. 9*4-5፤ 20*28፤ ኤፌ. 5*23፤ 1 ጴጥ. 5*4)

1.4.4 ለአገልጋዮች መታዘዝና መገዛት እስከ ምን ድረስ ነው?

ቤተ ክርስቲያን አንዱ ሌላውን የሚያገለግልበት ስፍራ እንጂ አንዱ በሌላው ላይ አለቃና ጌታ ሆኖ የሚሰለጥንበት ስፍራ
አይደለም፡፡ የጌታ ኢየሱስን ሕይወትና ትምህርት መሰረት በማድረግ አገልጋዮች ማገልገል አለባቸው፡፡ (ማቴ. 20*20-28፤ ማር.
10*35-45፤ ሉቃ. 17*10፤ ዮሐ. 13*4-17) የኢየሱስን ፈለግ የተከተሉትም ሐዋርያት አገልግሎትና ትምህርት ስንመለከት

እንዲሁ ያንኑ ሲያደርጉ እንመለከታለን፡፡ (ሐዋ. 20*25-38፤ 1 ቆሮ. 15*9፤ ገላ. 5፥13፤ ፊልጵ. 2*3-4፤ 1 ጴጥ. 5*1-4) ሌላው
ማወቅ ያለብን አገልጋዮች ከጽድቅ መንገድ ሲወጡና ቤተክርስቲያንን ወደ ተሳሳተ መንገድ ሲመሩ ዝም ማለትና እንዲያውም
ከእነርሱ ጋር መተባበር የአመጽ ተካፋይ መሆን ነው፡፡ (ኤፌ. 5*11) መጽሐፍ ቅዱስ በመልካም ምሳሌ የሚመሩትን አገልጋዮች
“ምሰሉአቸው” ሲለን (ዕብ. 13*7) እንደ ዲዮጥራጥስ ያሉትን መሪዎች ደግሞ “አትምሰል” ይላል፡፡ (3 ዮሐ. 1*11)

1.4.5 “የቀባኋቸውን አትዳስሱ”

በመዝ 105*14-15 ላይ የተጠቀሰው “የቀባኋቸውን አትዳስሱ” የሚለው ቃል ብዙዎች እንደሚያስተምሩት “ሲሳሳቱ


አለመውቀስ ሲያስቱ ተው” አለማለት አይደለም፡፡ ቃሉ የተነገረው ለልዩ ሕዝብነት ተመርጠው ለነበሩ እስራኤል ሕዝብ ነው፡፡
(ዘፍ. 12*17-20፤ 20*3፤ 26*11፤ 1 ሳሙ. 12*13፤ መዝ. 9*5) የመነገሩም ምክንያት ለእስራኤላውያን የብርታትና
የማደፋፈሪያ ቃል ሲሆን ከግብጽ ምድር ወጥተው ወደ ከነዓን ሲሄዱ በዙሪያቸው ላሉ አሕዛብ እንዳይነኳቸው የተነገረ
ማስጠንቀቂያ ቃል ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመን ካህንም፣ ነቢይም፣ ንጉስም ሊሆን በእግዚአብሔር የተቀባ አንድ የላቀ ስብህና
ባለቤት የሆነ ሰው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ (ሉቃ. 4*17-19፤ ሐዋ. 10*38-39) ይህ ጌታ ምድራዊ
አገልግሎቱን ጨርሶ በክብር ሲያርግ ቅባቱን ከሙሉ ኃይሉና ኃላፊነት ጋር በአዲስ ኪዳን ምዕመናን ሁሉ ላይ አፈሰሰው፡፡ (2 ቆሮ.
1፥21፤ 1 ዮሐ. 2*20፣27) እርግጥ ነው እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸውን (የቀባቸውን) አገልጋዮች ማክበርና መታዘዝ
የማይሻሻል፣ ለድርድር ሊቀርብ የማይችል ዘመን፣ ታሪክ፣ ባህል ዘለል መርህ ነው፡፡ ነገር ግን “የቀባኋቸውን አትዳስሱ” የሚለውን
ቃል ያለ ስፍራው በመጥቀስ ቅዱሳንን ማስፈራሪያ ማድረግ ትክክል አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አገልጋዮችን እንድንታዘዝ እና
እንድናከብራቸው ብቻ ሳይሆን፤ የሚያስተምሩትንና የሚሰብኩትን እንድንመረምር ሕይወታቸውንና ልምምዳቸውን በቅዱስ

ቃሉ እንድንፈትን ሙሉ መብትን ይሰጠናል፡፡ (ዘዳ. 18*21-22፤ 1 ተሰ. 5*19-22፤ 1 ዮሐ. 4*1-3)

ምዕራፍ ሁለት፡- መለኮታዊ ስርዓት ክልሎች (ግዛቶች)


መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ጎልቶ የሚታይ የመለኮታዊ ስርዓት ትርጉም የግዛት ክልል መሆኑን የመለኮታዊ ስርዓት ትርጉም ላይ
አይተናል፡፡ የግዛት ክልል ስንል ሦስት አይነት ናቸው እነርሱም፡- የእግዚአብሔር ፣ የመላዕክትና የሰው የግዛት ክልል ናቸዉ፡፡

2.1 እግዚአብሔር የሁሉ የበላይና የስልጣን ሁሉ ምንጭ ነው


78
እግዚአብሔር የሚታየውና የማይታየው አለም ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት ስለሆነ ሉአላዊ ገዢ ነው፡፡ ስለዚህም በሚታየውም አለም
ላይም ሆነ በማይታየውም አለም ላይ ያለ ስልጣን ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔር ነው፡፡ (2 ዜና. 20*6፤ መዝ. 115*3፤ ዳን. 2*20-
22፤ 4*35፤ ማቴ. 28*18-20) አዲስ ኪዳንም በቀጥታ ስልጣን ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደሆነ በማያሻማ ሁኔታ አጥብቆ
ይነግረናል፡፡ (ሮሜ. 13*1) ጲላጦስ ኢየሱስ ክርስቶስን “ልሰቅልህ ስልጣን እንዳለኝ ወይም ልፈታህ ስልጣን እንዳለኝ
አታውቅምን?” ባለው ጊዜ ይህንም ለማድረግ “ከላይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ ምንም ስልጣን ባልነበረህም” በማለት
መልሶለታል፡፡ (ዮሐ. 19*10-11)
ስልጣን የእግዚአብሔር ዙፋን መሰረት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከዙፋኑ ይወጣል፤ ዙፋኑም በስልጣኑ ላይ የተመሰረተ
ነው፤ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የፍጥረት ዓለሙ ሕግና ሥርዓትም የሚጠበቀው በእግዘአብሔር ስልጣን ነው፡፡ (ዕብ. 1*3)
ስለዚህ ጠቅለል አድርገን ስናስቀምጠው የስልጣን ሁሉ ባለቤትና ምንጭ በሰማይም በምድርም እግዚአብሔር ነው፡፡

2.2 የመላዕክት የመንፈሳዊ ስልጣን ክልሎች

ከፍጥረታት መካከል ለመላዕክት እና ለሰዎች እግዚአብሔር ስልጣንን እና ሀላፊነትን እንደሰጠ እናያለን፤ መላዕክት የስልጣንና
የሀላፊነት ደረጃ አላቸዉ፡፡ (ዳን. 10*13) መላአክት፣ ዙፋናት፣ ጌትነት፣ አለቅነት፣ ስልጣናት ተብለው ተገልፀዋል፡፡ (ቆላ. 1*15-
16) መላዕክት የብርሀንም ይሁኑ የጨለማ መላእክት የእግዚአብሔር ፍጥረት እንደመሆናቸው በስራ ክፍፍል እና በመንፈሳዊ
ስልጣን ተዋረድ ፣ በግዛታቸዉ ውስጥ ተግባራቸውን ይፈፅማሉ፡፡

2.3 የሰዉ የመንፈሳዊ ስልጣን ክልሎች

እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እና በምሳሌው ከፈጠረው በኋላ ሲባርከው እናያለን፡፡ ማለትም ሰው በእግዚአብሄር ስልጣን ስር
ሆኖ ምድርን ማለትም የባህርን ዓሶች ፣ የሰማይን ወፎችና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ እንዲገዛ ስልጣን ተሰቶታል፡፡
(ዘፍ. 1*28-29)

ምዕራፍ ሦስት፡- በምድር ላይ የእግዚአብሔር ወኪል ባለስልጣናት


በበሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች በምድር እየበዙ ሲመጡ እግዚአብሔር ለአህዛብ ነገስታት ስልጣን በመስጠት ያስተዳድር ነበር፡፡ (ኢሳ.
44*28፤ ዳን. 4*25-26) የቃል ኪዳን ሕዝቡን ደግሞ ህግን በመስጠት ለነገስታት (ለፈራጆችና ለአለቆች) ፣ ለካህናት እና
ለነብያት ስልጣን በመስጠት ይመራቸውና ያስተዳድራቸው ነበር፡፡ (ዘዳ. 16*18-20፤ 17*8-21፣ 18*14-22) በአዲስ ኪዳን
ደግሞ ከዚህ በታች እንደምንመለከተው በምድር ላይ የእግዚአብሔር ወኪል ባለስልጣናት ለሆኑት ቤተሰብ ፣ ቤተክርስቲያን ፣
መንግስት (ማህበረሰብ) መንፈሳዊ ስልጣን በመስጠት ዘላለማዊ እቅዱን በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

3.1 የቤተሰብ ስልጣን


3.1.1 የባል ስልጣን

በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የቤተሰብ ኃላፊና አስተዳዳሪ ባል ነው፡፡ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነ ባልም የሚስት ራስ ነው፡፡
(ኤፌ. 5*23) በፍጥረት መጀመሪያ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የትዳር ጓደኛ ሲያዘጋጅለት ገዢ ወይም ተገዢ ሳይሆን የሚመች
ረዳት መፍጠሩን ስለገለጸ፤ በጋብቻ ግንኙነት መካከል ባል አባወራነቱ ለክርስቶስ እየተገዛ የክርስቶስ እንደራሴ ሆኖ ቤቱን በፍቅር
79
እንዲያስተዳድር እንጂ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን እንዲሆን አይደለም፡፡ ባል ለሚስት ራስ ነው የሚለው መለኮታዊ ስርዓትን
እንጂ የበላይነትም ሆነ የበታችነትንም አያሳይም፡፡ (1 ቆሮ. 11*3) ሴቶችና ወንዶች ተደጋጋፊ ናቸው፡፡ (1 ቆሮ. 11*11-12)
በክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን መካከል ባለው ንጹሕ፣ የማይለወጥ፣ እውነተኛ፣ መሥዋዕታዊ ፍቅር ምሳሌ ባል ሚስቱን ተለዋዋጭ
ባልሆነ ስሜት፣ በሁኔታዎች ላይ በማይመሰረት ፍቅር ምንጊዜም ሊወድዳት ይገባል፡፡ (ኤፌ. 5*25-33፤ ቆላ. 3*19፤ 1 ጴጥ.
3*7) ከእግዚአብሔር በተቀበለው ቤተሰብን የመምራት፣ የመጠበቅ፣ የመንከባከብ ተልዕኮ መሰረት፤ ራሱ በክርስቶስ ጌትነት ሥር
እየተገዛ ሚስቱንና ቤተሰቡን በፍቅር፣ በእውቀት፣ በጥበብና በማስተዋል ሁለንተናዊ አመራር በመስጠት መምራት ይኖርበታል፡፡
በዚህ መሰረት ሚስቱን መንከባከብ፣ መጠበቅና መመገብ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔርና በቅዱሳን ፊት የገባውን ቃል
ኪዳን እያሰበ በሁሉም አቅጣጫ ሊታመንላት ለራሱ ዋጋ እንደሚሰጥ ሁሉ አካሉ የሆነችውን ሚስቱን ሊያከብር ይገባል፡፡ (ሚል.
2*14-16፤ ኤፌ. 5*30፤ 1 ጴጥ. 3*7)

3.1.2 ሚስት ለባሏ መገዛት አለባት

ሚስት በትዳሯ ውስጥ እውነተኛ የእግዚአብሔር በረከቶች እንዲለቀቁ ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሁሉ ራሷን
ለባሏ በፍቅር ማስገዛት ይጠበቅባታል፡፡ (ቆላ. 3*18፤ 1 ጴጥ. 3*5-6) ይህ ሲሆን ሁለት ነገሮችን ማጤን ይኖርባታል፡፡
የመጀመሪያው ነጥብ ባልና ሚስት ተፈጥሯዊ እኩልነታቸው በምንም መንገድ የማይገሰስ መሆኑን ማስተዋል ሲሆን፤ ሁለተኛው
ነጥብ ደግሞ እኩልነቱ እግዚአብሔር በሁለቱ ጾታዎች መካከል ያስቀመጠውን ልዩነት የማያፋልስ መሆኑን ነው፡፡
ስለዚህ መጽሐፍ እንደሚል ሚስት ባሏን ማክበር (ኤፌ. 5*33፤ 1 ጴጥ. 3*12) ፣ መውደድ (ቲቶ 2*4) ፣ ልታደርግለት
የሚገባትን ነገር ሁሉ በደስታ ማድረግ (1 ቆሮ. 7*3) ፣ በታማኝነት ጸንታ መኖር (ሮሜ 7*2-3) ፣ ራሷን ማለትም ውስጣዊም
ይሁን ውጫዊ ንጽህናዋን ነቅታ መጠበቅ (1 ጴጥ. 3*1-4) ፣ ቤቷን በመልካም ማስተዳደር የምትጥር ልባም ሴት ልትሆን ይገባል፡፡
(ምሳ. 14*1፤ 19*14፤ 31*10-31፤ ኢሳ. 66*13)
አንዳንድ ባሎች ለእግዚአብሔር ቃል የማይታዘዙ፣ የተሰጣቸውን የቤተሰብ ሀላፊነት የማይወጡ፣ አለምን የሚወዱ፣ ግዴለሽ
ሊሆኑባቸው ቢችሉ እንኳን ሚስቶች እንደ እግዚአብሔር ቃል በቅድስና በመኖር ለባሎቻቸው የህይወት ምስክርነትን እየሰጡ፤
ባሎች የእግዚአብሔርን ቃል እንኳን ባይሰሙ በሚስቶቻቸው ህይወት እንዲማረኩ በማድረግ ለባሎቻቸው ሊገዙ ይገባል፡፡
(1 ጴጥ. 3*1-2)

3.1.3 ልጆች ለወላጆቻቸዉ መገዛት አለባቸዉ

ወላጆቻችንን ማክበር

እናትና አባትን የማክበር ትዕዛዝ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ልንፈጽመው የተገባ ያልተሻረ መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው፡፡ (ዘጸ. 20፡
12፤ ኤፌ. 6፡1-3) እንግዲህ ማክበር የሚለው ቃል መገዛትን፣ መታዘዝን፣ ስፍራ መስጠትን፣ ትኩረት መስጠትን፣ ቅድሚያ
መስጠትን፣ መስማትን፣ ጥንቃቄ ማድረግን የመሳሰሉ እውነቶችን የያዘ ቃል ነው፡፡ ወላጆቻችንን እንዴት ነው የምናከብረው፡-

ያለምንም ምክንያት ማክበር ወላጆቻችንን ሰካራም ቢሆኑ፣ ድሃ ቢሆኑ፣ ያልተማሩ ቢሆኑ፣ አካለ ጎደሎ ቢሆኑ፣ በሽተኞች
ቢሆኑ መከበር አለባቸው፡፡ (ዘፍ. 9፡20)

ወላጆቻችንን አለመናቅ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ወላጆቻችንን ባዋረድንና በናቅን ቁጥር የምናዋርደው እነርሱን
ብቻ ሳይሆን እንድናከብራቸው የተናገረንን እግዚአብሔርን ነው፡፡ (ሮሜ 13፡7)
80
ለወላጆቻችን መታዘዝ ለወላጆች መታዘዝ ማለት የቃሉ ባለቤት ለሆነ ለጌታ መታዘዝ ነው፡፡ (ምሳ. 6፡20፤ ኤር. 35፡18፤ ኤፌ. 6፡
1፤ ቆላ. 3፡20) በዚህ ጉዳይ አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ወላጆቻችን ኃጢአት የሆነ ነገር ቢያዙን እንዲሁም በዋናነት ጌታን ተው
ቢሉን እንዴት እንታዘዛለን? ጌታ ደግሞ ያልታዘዝንባቸው ምክንያቶች አይቶ የሚፈርድ አምላክ ስለሆነ ቀጥታ እርሱን
እንድንተውና ኃጢአት እንድናደርግ በሚያዙን ትዕዛዝ ከቃሉ ውጭ ስለሆነ ከእነርሱ ጎን አይቆምም፡፡ ነገር ግን ምላሻችንን
በፍቅር፣ በአክብሮትና በማሳመን ማቅረብ ይገባል፡፡

ወላጆቻችንን ማስደሰት ወላጆቻችንን ማስደሰት ማለት ለሀዘናቸው ምክንያት ከሚሆን ነገር እየራቅን ለደስታቸው ምክንያት
የሚሆኑ ነገሮችን ዕለት ዕለት መፈለግና ማድረግ ነው፡፡ (ዘፍ. 27፡4፤ ምሳ. 23፡24-25)

የወላጆችን ምክር መስማት ወላጆቻችን ከእኛ የተሻለ የሕይወት ተሞክሮ ስላላቸውና እንደ ወላጅ ለእኛ የተሻለ ነገር
ስለሚያስቡ ምክራቸውን መቀበል አለብን፡፡ (ምሳ. 1፡8-9፣ 13፡18)

ወላጆችን ማመስገንና መባረክ በሕይወታችን ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ልናመሰግናቸውና ልንባርካቸው የሚገባን እናትና
አባቶቻችንን ነው፡፡ (ምሳ. 30፡11)

ስለ ጥፋታችን ይቅርታ መጠየቅ እነርሱን በማሳዘን የበደልንበት ብቻ ሳይሆን እንደ ቃሉ በትክክል ባለማክበራችን፣
ባለመታዘዛችን፣ ባለማስደሰታችን፣ ባለመጦራችን፣ ለእነርሱ ትኩረት ባለመስጠታችን በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ይቅርታ
መጠየቅ እና መካስ አለብን፡፡ ወላጆቻችን በሕይወት የሌሉ ከሆነ ደግሞ በአምላካችን ፊት በደላችንን በመናዘዝ ይቅርታ መጠየቅ
አለብን፡፡

ለወላጆቻችን ስጦታ መስጠት ወላጆቻችንን ደስ ከምናሰኝበት መንገድ አንዱ የተለያዩ ስጦታዎችን እንደ አቅማችን መጠን
መስጠት ነው፡፡ (ዘፍ. 27፡3)

በወላጆቻችን መልካም ቃል መባረክ የሰው ልጅ በሕይወቱ አጥብቆ ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ በረከት ነው፡፡ እግዚአብሔር
እኛን ለመባረክ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ የወላጆቻችን የበረከት ቃል ነው፡፡ (ዘፍ. 27፡38፤ ዕብ. 7፡7)

ወላጆችን የማክበርና የመታዘዝ ውጤቶች

በረከትን እንቀበላለን፡፡ (ዘፍ. 9፡26-27)፣ ዕድሜን ያረዝማል፡፡ (ዘጸ. 20፡12፤ ኤፌ. 6፡1-3) መከናወንን ያመጣል፡፡ (ዘዳ. 5፡16፣ ኤፌ.
6፡3)፣ መልካም ዘርን እናጭዳለን፡፡ (ገላ. 6፡7)

ወላጆችን የአለማክበር፣ መናቅና አለመታዘዝ ውጤቶች

እርጉም ያደርጋል፡፡ (ዘፍ. 9፡25፤ ምሳ. 26፡2)፣ ባርያ (ተገዥ) ያደርጋል፡፡ (ዘፍ. 9፡25)፣ ዕድሜን ያሳጥራል (ዘጸ. 20፡12፤ ኤፌ. 6፡
2)፣ ክፉን ያመጣል፡፡ (ዘዳ. 5፡16፣ ኤፌ. 6፡3)፣ ቅጣትን ያመጣል፡፡ (ዘጸ. 21፡17፤ ዘሌ. 20፡9፤ ምሳ. 30፡17)፣ ክፉ ዘርን ያሳጭዳል፡፡
(ገላ. 6፡7)

81
ልጆች ወላጆቻቸውን መታዘዝ ያለባቸው ጌታን እያሰቡ መሆን አለበት እንጂ ጭንቅ ጭንቅ እያላቸው መሆን የለበትም፡፡
ለወላጆቻቸው መታዘዝ ተገቢና ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ ልጆች ወላጆቻቸውን በማክበር ፣ በመገዛትና እግዚአብሔርን በመፍራት
በምድር ላይ ረጅም ዕድሜና መልካም ነገር ያገኛሉ፤ በአጠቃላይ መንፈሳዊ እና ምድራዊ በረከትን ከእግዚአብሔር ማግኘት
ይችላሉ፡፡ (ኤፌ. 6*1-3፤ ቆላ. 3*20) ልጆች እናት እና አባቶቻቸውን ካላከበሩ በመለኮታዊ ስርዓት ላይ ያምፃሉ፤ አንዳንድ
አመፀኛ ልጆች የወላጆችን ተግሳፅ አይሰሙም እስከ መሳደብና ማዋረድ ይደርሳሉ እንደነዚህ አይነት ልጆች በራሳቸው ላይ
እርግማንና ፍርድን ያመጣሉ፡፡ (ዘዳ. 27*16፤ ምሳ. 13*1፤ ማቴ. 15*4) ልጆች የወላጆችን ምክር መስማት አለባቸው፤ ወላጆች
የሚያዙአቸውን ሁሉንም መፈፀም ባይችሉ እንኳን ማክበር ግን ይጠበቅባቸዋል፡፡ (ምሳ. 23*22፤ ዘሌ. 19*32)

3.2 የቤተክርስቲያን ስልጣን


በሰማይና በምድር ስልጣን ያለው ጌታ የቤተክርስቲያን ራስ ስለሆነ ለቤተክርስቲያን ስልጣን ሰጥቷል፡፡ የቤተክርስቲያን ስልጣን
ስንል ቤተክርስቲያን በጠላት ሀይል ላይ፣ ወንጌልን ለመስበክ እና የቤተክርስቲያን ምዕመናንን የመቅጣት (የመገሰፅ ፣የማረም ፣
የመቅጣት፣ ከህብረት የማባረር) ስልጣን ማለት ነው፡፡
3.2.1 የቤተክርስቲያን ስልጣን በጠላት ሀይል ላይ

ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊው አለም ላይ ስልጣን አላት፡፡ ይህም ስልጣን የምትጠቀመው በጠላት ሀይል ላይ (በአጋንቶች) ስልጣን
ላይ ነው፡፡ ክርስቲያን ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ በዲያቢሎስ ላይ ስልጣን አለው፤ ስራውንም ማፍረስ ይችላል፡፡ የተሰጠንን
ስልጣን ካወቅን ሰይጣን ከእግራችን በታች የተጣለ ነው፡፡ (ሉቃ. 10*19፤ ሮሜ. 16*20፤ ያዕ. 4*7) የጨለማው ገዢ
ቤተክርስቲያን ይዋጋታል ነገር ግን አይችላትም፡፡ (ማቴ. 11*12፤ ኤፌ. 6*12) እግዚአብሔር ለክርስቲያን የጠላትን ስራ ሁሉ
የሚያፈርስበት ስልጣን ሰጥቶታል፡፡ ስልጣናችንም የኢየሱስ ስምና ደም ነው፡፡ (ሐዋ. 4*7-10፤ ፊሊጵ. 2*9-11፤ ራዕይ 12*11)

3.2.2 ወንጌልን የመስበክ (ሰዎችን የማዳን ስልጣን)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለጴጥሮሰ የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ “በምድር የምታስረዉ ሁሉ በሰማይ የታሰረ
ይሆናል በምድር የምትፈታዉ ሁሉ በስማይ የተፈታ ይሆናል” ብሎ ስልጣን ሲሰጠዉ እናያለን፡፡ (ማቴ. 16*19) ይህ ስልጣን
ወንጌል የመስበክ ስልጣን እና ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲገቡ የማድረግ ስልጣን ነው፡፡ (ሐዋ. 2*14-41)
ለጴጥሮስ የተሰጠው ስልጣን በኋላም ለቤተክርስተያን ተሰጥቶአል፡፡ (ማቴ 28*19-20) ይህ ስልጣን ወንጌልን የመናገር፣
አጋንንትን ማውጣትና በሽተኞችን መፈወስ ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ (ማቴ. 10*1፤ ማር. 3*15 ሉቃ. 9*1-2፤ 10*19)

3.2.3 ቤተክርሰቲያን አባላትን የመቅጣት ስልጣን

ቅዱሳን በጽድቅ እንዲኖሩና በስርዓት እንዲመላለሱ የእግዚአብሔር ቃል ያዛል፡፡ (2 ተሰ. 3*11-12) ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ
የሚመላለሱትንና በጽድቅ የማይኖሩትን ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስልጣኗን ተጠቅማ ከጥፋታቸው እንዲመለሱ እና
እንዲታረሙ መምከር፣ መገሰጽና መቅጣት ያስፈልጋል፡፡ (ማቴ. 18*15-18፤ 1 ቆሮ. 5*3-5፤ 1 ተሰ. 5*14፤ 1 ጢሞ. 5*20)

3.2.4 የቤተክርሰቲያን ቅጣት አላማ

82
መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተክርስትያን ቅጣት አላማ ሀጢያት የሰራን ክርስቲያን ከክፉ መንገዱ በንስሐ እንዲመለስ ለማድረግ ነው፡፡
(ማቴ. 18*15) የማይታዘዘውን ለማሳፈር ነው፡፡ (2 ተሰ. 3*14) ወደ ሌሎች ቅዱሳን እንዳይዛመት እና ሌሎችም በተመሳሳይ
ኃጢአት እንዳይኖሩ ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ (1 ቆሮ. 5*6፤ ገላ. 5*8፤ 1 ጢሞ. 5*20) በመጨረሻ ቤተክርስትያን ሀጥያትን
ካልቀጣች የጌታ ስም በአህዛብ ፊት ይሰደባል፡፡ (ሮሜ 2*24፣ 1 ቆሮ. 6*6) ቤተክርስትያን በደለኛውን ክርስትያን ከቅጣት በኋላ
ማፅናናት እና ይቅር ማለት አለባት፡፡ (2 ቆሮ. 2*6-8፣ 7*8-11) ቤተ ክርስትያን በኃጢአት ተገኝተን ስትቀጣን ወደ ሌላ ቤተ
ክርስትያን መሄድ ወይንም የቤተ ክርስትያንን ቅጣት አልቀበልም ማለት የቤተ ክርስትያን ባለቤት የሆነውን ኢየሱስን መቃወም
ነው፤ የትም ቤተ ክርስትያን ብንሄድ በንስሐ እስካልተመለስን ድረስ እግዚአብሔር በሚመርጠው መንገድ ይቀጣናል፤ የዘራነው
ዘር የትም ብንሄድ ይከተለናል፡፡ (ገላ. 6*7)

3.2.5 ቅጣት መቀጣት የሚገባቸው እነማን ናቸው?

ሀ/ የስህተት ትምህርት የሚያስተምሩ፡፡ (1 ጢሞ. 1*20፤ 6*3-5፤ 2 ዮሐ. 1*10-11)


ለ/ በቅዱሳን መካከል መለያየትን የሚያመጡ፡፡ (ሮሜ 16*17፤ ቲቶ 3*10-11)
ሐ/ ቅዱሳንን በድሎ የቤተ ክርስቲያን ምክርና ተግሳጽ የማይሰማ፡፡ (ማቴ. 18*15-18)
መ/ ስራፈት የሆነ እና ያለ ስርዓት የሚመላለስ፡፡ (2 ተሰ. 3*6-10፣14-15)
ሠ/ አመንዝሮች፡፡ (1 ቆሮ. 5*1-2፣ 11-13)

3.3 የመንግሰት ስልጣን

የመንግስት ስልጣን ስንል በማህበረሰብ ላይ የተሾሙ ባለስልጣናት ስልጣን ማለታችን ነው፡፡ ቤተ ክርስትያን የማህበረሰቡ አካል
ስለሆነች ሁሉም ስልጣን ከእግዚአብሔር ስለሆነ ለመንግስት ስልጣን መገዛት አለባት፡፡ ባለስልጣናት ሁሉ የተሾሙት
በእግዚአብሔር ነው ስለዚህ ለመንግስት ስልጣን መገዛት አለብን፡፡ ለመንግስት ስለልጣን ባንገዛ በራሳችን ላይ ፍርድን እናመጣለን
ምክንያቱም መንግስት ስርዓትንና ፍትህን ለማስፈን ሰይፍ ታጥቋል፡፡ (ሮሜ 13*1-5፤ 1 ጴጥ. 2*13-17፤ ቲቶ 3*1)
ክርስቲያኖች ለመንግስት የሚገባውን ግብርን መክፈል አለብን ምክንያቱም አገር የምትተዳደረው ከሕዝብ ከሚሰበሰብ ግብር
ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለመንግስት መስጠት ያለብንን ለመንግስት ለእግዚአብሔር መስጠት ያለብንን ለእግዚአብሔር እንድንሰጥ
አዟል፡፡ (ማቴ. 17*24-27፤ ማር. 12*13-17፤ ሮሜ 13*6-7)
ቤተክርስትያን በሀገር ላይ በስላም ለመኖርና ወንጌል ለመስበክ እንድትችል ለሕዝብና እና ለመንግስት በልመና እና በምልጃ ወደ
እግዚአብሔር መፀለይ አለባት፡፡ (1 ጢሞ. 2*1-2) በተጨማሪም በኅብረተሰብ ውስጥ ፍትህ ሲጓደልና አመጽ ሲበዛ ቤተ
ክርስቲያን እውነትን በአደባባይ የመንገር እና የመምከር ኃላፊነት አለባት፡፡ (ማቴ. 14*6-12፤ ማር. 6*17-28)

3.3.1 ክርስቲያኞች እስከምን ድረስ ለስልጣን መገዛት አለባቸው

ክርስትያኖች መንግስት ለእግዚአብሔር ስልጣን እንዳይገዙ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚቃረን ነገር እንዲያደርጉ ካዘዘ
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔርን ቃል ማክበር እርሱንም ብቻ መታዘዝ አለብን፡፡ (ዘጸ. 1*17፤ ዳን. 3*1-30፤
6*1-28፤ ሐዋ. 5*29) ነገስታት ሁሉ ፍፁም እና መልካም መሆናቸውን መፅሐፍ ቅዱስ አይነግረንም፤ እንዲያውም አንዳንድ
ነገስታት በሚያስፈራ አውሬ ተገልፅዋል፡፡ (ሉቃ. 13*32) ክርስትያኖች ዋጋ ቢያስከፍለንም ስለ ክርስቶስና ወንጌል በመንግስት

83
መከራን ለመቀበል የተዘጋጀን መሆን አለብን፡፡ (ማር. 13*9) ስለዚህም ቤተክርስትያን ለእውነት በመቆም የመንግስትን ስህተት
ፊት ለፊት መቃወም አለባት፡፡ (ማር. 6*18፤ ሐዋ. 23*3)

3.3.2 ክርስቲያኞች እስከምን ድረስ ፖለቲካ ዉስጥ መሳተፍ ይችላሉ

ክርስትያኖች በተለያየ የመንግስት ኃላፊነት ቦታ ላይ በመመደብ ሕዝብንና አገርን ማገልገል ይችላሉ፡፡ በተሰማሩበት ዘርፍ
ራሳቸውን በኃጢአት ሳያረክሱ ትጉህ ሠራተኞች መሆን አለባቸው፡፡ (ዳን. 6*5፣ 22፤ አስቴ. 10*3፤ ማቴ. 14*1፤ ሉቃ. 7*5፤
23*50-51) ክርስትያኖች በቤተ ክርስቲያን ስም የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት አይችሉም፡፡ ነገር ግን ስለ ነፃነት፣ ፍትህ፣ ሰላም
እንዲሁም የሕዝብን ችግር ለመፍታት እና መልካም አሰተዳደር ለማስፈን ከማንኛውም ማህበረሰብ ጋር የፖለቲካ ፓርቲ
ማቋቋምና በስላማዊ መንገድ መታገል ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖች የአለምን ሀይል (ጦር መሳሪያ) በመጠቀም ወንጌል
መስበክና ፍትህን ማምጣት አይፈቀድላቸውም፡፡ (ሉቃ. 9*54-56፤ ዮሐ. 18*36፤ 2 ቆሮ. 10*4 )

ምዕራፍ አራት፡- ሥልጣንን የሚያዛቡ አመለካከቶች

 በወደቀው አለም ውስጥ ስለምንኖር፡፡ (ሮሜ 3*23)


 ከበላይ ባለስልጣን ጋር መፎካከር፡፡ (ዘኁ. 12*1-10)
 የበላይ ባለስልጣን ድካም ማጉላት፡፡ (ዘፍ. 9*20-29)
 የገንዘብ ፍቅር ለበላይ ስልጣን እንዳንገዛ ያደርጋል፡፡ (ዮሐ. 12*1-8 )
 ክርስትያን በቤተ ክርስትያን ውስጥ የተለየ ራዕይ ሲያመጣ አንድነትን እና ስልጣንን ያናጋል፡፡ (1 ቆሮ. 1*10)
 ያልተሰጠን ስልጣን መመኘት እና ለማግኘት መሞከር፡፡ (2 ሳሙ. 15*1-6)
 የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅ፡፡ (ሮሜ 13*1-5 )
 ዘረኝነት ማለትም ለራስ ብሔር ማድላት፡፡
 ባህል፡- ከእግዚአብሔር ስልጣን ተዋረድ በተለየ ሁኔታ ስልጣን የሚተገበርበት ባህል፡፡

ምዕራፍ አምስት፡- ተግባራዊ ተዛምዶ

 መለኮታዊ ስርዓት መዛባት ዛሬ ለቤተሰብ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለአገረ ትልቅ ተግዳሮት ሆኗል፤ ይህም የአደባባይ

ሚስጥር ነው፡፡ ዛሬ ያለነው ክርስቲያኖች “ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በስርዓት ይሁን” (1ቆሮ. 14*40) የሚለውን

84
አምላካዊ ጥሪ/ግብዣ የዘነጋንበት በትኩረትም የማናስተምርበት ወቅት ላይ ነን። መለኮታዊ ስርዓት ቸል የተባለበት

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ መለኮታዊ ስርዓት ወደ ጎን የተተወበት ጊዜ ላይ ነን። ከዚህም የተነሣ ቤተሰብ፣ ቤተ

ክርስቲያንና አገር በብዙ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከየትም ስፍራ ይልቅ በቤተ ክርስቲያን መለኮታዊ ስርዓት

መመለስ አለበት፡፡ እንዲህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋን ትወጣለች። ለደከሙት ማረፊያ፣ ለባዘኑት አምባ፣ ሕይወት

ትርጕም ላጡ ትርጕም ማግኛ፣ ለተራቡ ምግብ፣ ለተጠሙ የሕይወት ውሃ መመንጫ ትሆናለች። የተፈራች

የተከበረች በችግር ጊዜ በኅብረተሰቡ ዘንድ ለመፍትሔ የምትፈለግ ተናፋቂ ትሆናለች። እግዚአብሔር ለቤተሰብ፣ ለቤተ

ክርስቲያንና ለአገር መለኮታዊ ስርዓትን ይመልስልን፡፡

 በአሁኑ ጊዜ በርካታ ምእመናን እና አገልጋዮች ለቤተ ክርስቲያን ስልጣን ለመገዛት ስንቸገር ይታያል፡፡ ግልጽ በሆነ ኃጢአት

ተገኝተን እንኳን ንስሐ መግባት አንፈልግም፤ የወደቅንባቸውን ጉዳዮች በመረዳት በእውነተኛ ንስሓና ተሐድሶ ወደ

እግዚአብሔር ከመመለስ ይልቅ እንደ መፍትሄ የምንወስደው ቤተ ክርስቲያን መቅየርን ነው፡፡ ነገር ግን ንስሐ ሳንገባ ቤተ

ክርስቲያን ብንቀይር ከተጠያቂነትና ከፍርድ አናመልጥም። ቤተክርስትያን በደለኛውን ክርስትያን ከቅጣት በኋላ
ማፅናናት፣ ይቅር ማለትና ወደ ትክክለኛው ነገር መመለስ አለባት፡፡ የቤተክርስትያን ቅጣት አላማ ሀጢያት የሰራን
ክርስቲያን ከክፉ መንገዱ በንስሐ እንዲመለስ ለማድረግ እንጂ ቂም በቀል መወጫ መሆን የለበትም፡፡
 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለስልጣናት ይገዛ ያለው እራሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለባለስልጣናት
ሊገዛ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ባሪያ ያልተቀበለ እግዚአብሔርን እንዳልተቀበለ ይቆጠራል፡፡ የእግዚአብሔርን
ወኪሎች ቃል እየናቅን የእግዚአብሔርን ቃል ልንሰማ አንችልም፡፡ ለእግዚአብሔር ስልጣን ከተንበረከክን ለወኪሎቹም
ስልጣን ልንገዛ ይገባናል፡፡ የእግዚአብሔርን ወኪሎች ስልጣን አለመቀበል ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነው፡፡
የእግዚአብሔርን ወኪሎች ስልጣን ችላ ብሎ ለእግዚአብሔር ቀጥታ ስልጣን ለመገዛት የሚፈልገው አዳማዊ
ባህሪያችንን መሆኑን አውቀን በማስወገድ ለእግዚአብሔር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለስልጣን መገዛትን መለማመድ
ይገባናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስልጣንን የተቀበሉ ሰዎች እንደሚገባ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ካልተወጡ የስራውና
የስልጣን ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ስልጣናቸውን ይወስዳል፡፡ እነርሱም በስራቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት
ተጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡ እግዚአብሔር የናቃቸው መሪዎች እንደ ንጉስ ሳኦል በሕዝቡ ዘንድ የተናቁ ይሆናሉ፡፡ ይሁን
እንጂ መሪዎችን በጉልበትና በአመጽ ካሉበት ስፍራ ለማውረድ መሞከር የስጋ ስራ ነው፤ ስለዚህ ከእንዲሁ አይነት
የአመጽ ተግባር እራሳችንን መጠበቅ አለብን፡፡

የመለኮታዊ ስርዓት የክለሳ ጥያቄዎች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– ባል ለሚስት ራስ ነው የሚለው መለኮታዊ ስርዓትን እንጂ የበላይነትም ሆነ የበታችነትንም አያሳይም፡፡


2. –––––– መንግስት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚቃረን ነገር እንድናደርግ ቢያዘን ለምሳሌ ወንጌል አትስበኩ ቢለን
ለመንግስት ስልጣን መገዛት አለብን፡፡
3. –––––– ባሎች ለእግዚአብሔር ቃል የማይታዘዙና አማኝ ካልሆኑ፤ ሚስቶች ለባሎቻቸው ሊገዙ አይገባም፡፡

85
4. –––––– በቤተክርስቲያን ውስጥ ቡድንተኝነት፣ አድመኝነት፣ መፈንቅለ ስልጣን በፍጹም አይሰራም፡፡ ይህ
እግዚአብሔር የሚጸየፈው የስጋ ስራ ነው፡፡
5. –––––– አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ስጦታዎች ስለሆኑ ልናከብራቸው፣ ልንታዘዛቸው እና
በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ልንከባከባቸው ይገባል፡፡

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ

6. የቤት ራስ ሀ/ ቤተሰብ፣ ቤተክርስቲያን፣ መንግስት


7. እግዚአብሔር ወኪል ባለስልጣናት ለ/ ሚስት
8. ናዳብና አብዩድ ሐ/ ከእግዚአብሔር ለሰው የሚሰጥ ስልጣን ነው
9. የአዲስ ኪዳን ካህናት መ/ ባል
10. መለኮታዊ ስርዓት (መንፈሳዊ ስልጣን) ሠ/ አማኞች ሁሉ
ረ/ መላዕክት
ሰ/ ሌላ እሳት

ትክክለኛን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. በአዲስ ኪዳን አገልግሎት ለማን የተሰጠ ነው?

ሀ/ ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ብቻ፡፡


ለ/ ለአማኞች ሁሉ፡፡

ሐ/ ለፓስተሮች ብቻ፡፡
መ/ ለነቢያት ብቻ፡፡

12. በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ልጆች ለወላጆቻቸው በመታዘዝ ምን አይነት በረከት ያገኛሉ?


ሀ/ በምድር ላይ ረጅም ዕድሜ፡፡
ለ/ መልካም ነገር ሁሉ፡፡
ሐ/ መንፈሳዊ እና ምድራዊ በረከት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
13. የስልጣን ሁሉ ምንጭ ማን ነው?
ሀ/ እግዚአብሔር ነው፡፡
ለ/ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
ሐ/ አገልጋዮች ናቸው፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
86
14. በምድር ላይ የእግዚአብሔር ወኪል ባለስልጣናት እነማን ናቸው?
ሀ/ ቤተሰብ፡፡
ለ/ ቤተክርስቲያን፡፡
ሐ/ መንግስት (ማህበረሰብ)፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
15. ክርስቲያኞች በፖለቲካ ዉስጥ ስላላቸው ተሳትፎ ትክክል የሆነው አመለካከት የቱ ነው?
ሀ/ ክርስቲያኖች የአለምን ሀይል (ጦር መሳሪያ) በመጠቀም ወንጌል መስበክና ፍትህን ማምጣት ይችላሉ፡፡
ለ/ ክርስትያኖች በቤተ ክርስቲያን ስም የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት ይችላሉ፡፡
ሐ/ ክርስትያኖች በተለያየ የመንግስት ኃላፊነት ቦታ ላይ በመመደብ ሕዝብንና አገርን ማገልገል ይችላሉ፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
16. የቤተክርስቲያን ስልጣን ስንል ምን ማለታችን ነው?
ሀ/ ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊው አለም ላይ ስልጣን አላት፡፡
ለ/ ቤተክርስተያን ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ የመስበክ ስልጣን ተሰጥቷታል፡፡
ሐ/ ቤተክርስተያን አባላትን የመቅጣት ስልጣን ተሰጥቷታል፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
17. ሥልጣንን የሚያዛቡ አመለካከቶች የትኞቹ ናቸው?
ሀ/ በወደቀው አለም ውስጥ ስለምንኖር፡፡
ለ/ ከበላይ ባለስልጣን ጋር መፎካከር፡፡
ሐ/ የበላይ ባለስልጣን ድካም ማጉላት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
18. የቤተክርስተያን ቅጣት መቀጣት የሚገባቸው እነማን ናቸው?
ሀ/ የስህተት ትምህርት የሚያስተምሩ፡፡
ለ/ በቅዱሳን መካከል መለያየትን የሚያመጡ፡፡
ሐ/ አመንዝሮች፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. የመለኮታዊ ስርዓት ፅንስ ሀሳብ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን በስፋት ተገልጾ እናገኛለን፡፡ ከብሉይ ኪዳን አንድ ከአዲስ ኪዳን
አንድ ምሳሌ ስጡ፡፡

20. የቤተክርሰቲያን ቅጣት አላማ ምንድን ነው? ሁለቱን ብቻ ግለጹ

87
ትምህርት ስድስት፡- ወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን

ምዕራፍ አንድ፡- መግቢያ


የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን “እነሆ በጨለማ የተቀመጠ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገር ጥላ
ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው፡፡” (ማቴዎስ 4÷16) ተብሎ በተጻፈው የወንጌል ቃል መሠረት እግዚአብሔር በፓስተር
ዳንኤል መኰንን ልብ ውስጥ ባስቀመጠው ራዕይ አማካኝነት በ1987 ዓ.ም ተጀምራ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመላው
ኢትዮጵያና ከኢትዮጵያም ውጭ ባሉ የአለም ሀገራት ውስጥ በማሰራጨት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህም ሂደት ከፍተኛ ተግዳሮቶችን
በማለፍ በርካታ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ለመመስረት በቅታለች፡፡

1.1 የራእይው መወለድና በሥራ መተርጐም (ከሐዋሪያ ዳንኤል መኰንን)

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ 1989 ዓ.ም ከቤተሰቦቼ ጋር በመስከረም ወር በአሜሪካን ሀገር ሳለሁ፤ ጊዜው በአንዳንድ ጉዳይዎች
ላይ የእግዚአብሔርን ፊት የምሻበት ሳምንት ነበር፡፡ በዚህ ሰሞን እግዚአብሔር እንዳስለመደኝ አንድ መለኰታዊ ድምጽ ወደ እኔ

88
መጣ፡፡ ድምጹም “የወንጌል ብርሃን ተብሎ የሚጠራ አገልግሎት አቋቁም” የሚል ነበር፡፡ ስለ ሰማሁት የጌታ ድምፅ ለባለቤቴ
ካካፈልኩ በኋላ ሁለታችንም ከሁለት ዓመት በላይ በጉዳዩ ስንፀልይ ቆይተን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር Jan 1, 1992 የአሜሪካን
መንግስት ትርፍ አልባ ለሆኑ ድርጅቶች (Non profit) ባወጣው መመሪያ መሠረት አገልግሎቱ በዋሽንግተን ዲሲ ተመዝግቦ
ሕጋዊነትን አገኘ፡፡

የወንጌል ብርሃን አገልግሎት ስንጀምር በወቅቱ ያወጣነው የአገልግሎቱ መመሪያ እንደሚጠቁመን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን
በሚኖሩበት በየትኛውም ሀገር በመዘዋወር ወንጌልን መስበክ፣ ሴሚናር ማዘጋጀት፣ መሪዎችን ማሰልጠንና ማንኛውም የሚዲያ
ውጤት የሆኑ ማቴሪያሎችን ማሰራጨት ላይ ያተኰረ ነበር፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1992 ዓ.ም በሐምሌ ወር የአሜሪካን የአየር ሁኔታ በጋ በነበረበት ወቅት በጊዜው በኢትዮጵያ
ክርስቲያኖች ኅብረት የተዘጋጀውን ዓመታዊ ኮንፍረንስ ለመካፈልና አገልግሎትም ለመስጠት ከቤተሰቤ ጋር ወደ ቺካጎ ከተማ
በአውሮፕላን ተሳፍረን ሄደን በጉዞ ላይ እንዳለን ስብሰባው እግዚአብሔር የሚገኝበትና የሚሠራበት እንደሚሆን መንፈስ ቅዱስ
ይመሰክርንል ነበር፡፡ በስብሰባው አንድ ምሽት አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለው መንፈስ ቅዱስ “ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለህ”
የሚል ድምጽ አሰማኝ፡፡ በመድረክ ላይ እንዳለሁ ለጉባኤው ከጌታ የሰማሁትን መልዕክት አካፈልኳቸው፡፡ በጊዜው በስብሰባው
ላይ የነበሩት ወዲያው ወደ ኢትዮጵያ የምንሄድ መስሎቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ ዝግጅት የሚያስፈልገውና ታላቅ ውሳኔ
ስለ ነበር ከባለቤቴ ጋር ብዙ መፀለይና የሰማነውን ድምጽ ከጌታ መሆኑን በተለያየ መንገድ ማረጋገጥ ነበረብን፡፡

ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የወንጌል ብርሃን በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በኢትዮጵያ አገልግሎቱን
በማቀጣጠል ለአብያተ ክርስቲያናትና ለምዕመናን ብዙ በረከት ሆኖአል፡፡ በተለይ በዓመት ሁለቴና ሦስቴ ወደ ኢትዮጵያ
በመመለስ በተለያየ ክፍል ሀገር የጀማ የወንጌል ስብሰባዎችን በማድረግ የእግዚአብሔር የፈውስ እጅ እየተገለጠ አስገራሚ
ታአምራቶችና ድንቆች እየሆኑ ለብዙ ሰዎች መዳን ምክንያት ሆኖአል፡፡

በመጨረሻም ጸሎታችንን በማጠናከር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ኅዳር 28, ቀን 1998 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ሲሆን
በ 2000 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ወስነን ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ በዚህ ሁሉ የከበደን ዕድሜያቸው ሰባትና ዘጠኝ
የሆኑን ልጆቻችን ይዘን መምጣቱ ነበር፡፡ ብዙ ዓይነት ጥያቄዎች በአምሮችን ይመላለሱ ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ኑሮና ሕይወት
ይለምዱት ይሆን? የሚስማማቸው ትምህርት ቤት እናገኝ ይሆን? ወ.ዘ.ተ

ይሁንና በውሳኔያቸው ፀንተን የመመለሳችን ጊዜ ሲደርስ አባል የነበርንበት ቤተ ክርስቲያን (የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ
ክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ) ባደረገልን የገንዘብ አስተዋጽኦ ቁሳቁሳዊ ዝግጅት አድርገን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነሐሴ
2000 ዓ.ም ልጆቻችንን ይዘን ቀደም ሲል በተቋቋመችው የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል አዲስ አበባ ገባን፡፡ የአዲስ
አበባ ወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አጀማመር ከዚህ ራዕይ ጅማሬ ጋር አብሮኝ እያገለገለ ካለው በፓስተር ሠለሞን መንገሻ
ይገለፃል፡፡

1.2 የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አጀማመር (ከፓስተር ሰለሞን መንገሻ)

የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን በ 1990 ዓ/ም በታህሳስ ወር ውኃ ልማት ጀርባ የአሁኑ ቺቺኒያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ
ከአንዲት ክርስቲያን እህት በተከራየነው ቤት በይፋ ተጀመረ፡፡ ሲጀመር ሐዋሪያ ዳንኤል መኰንን የያኔውን አገልጋይ የዛሬውን
መጋቢ ሠለሞን መንገሻን ራዕያቸውን በማካፈል በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ተቀብለው አገልግሎት እንዲጀመርና ቤተ ክርስቲያን

89
እንድትተከል ተደረገ፡፡ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተከላ ጐን ለጐን ከመንግስት ፈቃድ ማግኘት ዋና ጉዳይ በመሆኑ ይኸው ጉዳይ በመጋቢ
ሰለሞን መንገሻ አስተባባሪነት ጉዳዩን በመከታተል በዚሁ በ 1990 ዓ/ም የካቲት 25 ቀን ከመንግስት ፈቃድ ተገኘ፡፡

1.2.1 መንፈሳዊ እንቅስቃሴ

በዚህ ቺቺኒያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ረቡዕና ዓርብ ብቻ ፕሮግራም በመጀመር የጸሎትና የአምልኮ ፕሮግራም ያለ ምንም
ድምጽ ማጉያና የሙዚቃ መሣሪያ ተጀመረ፡፡ ከዚያም አንድ የቦክስ ጊታር በመግዛት አምልኮውን ማካሄድ ነበረብን፡፡ በዚህ ጊዜ 12
ሰዎች እስከ ነሀሴ ድረስ ጌታን የተቀበሉ ነበሩ፡፡ በዚህ ቤት እስከ ነሐሴ 1990 ዓ/ም ብቻ ነው የቆየነው፡፡ በመስከረም ወር 1991
ዓ/ም በኖርዌጂያን ሚሽን አጠገብ ያለውን ግቢ በመከራየት መስከረም 6 ቀን ረቡዕ 1991 ዓ/ም በዚያን ቦታ አገልግሎት ሲጀመር
በዚያ ቀን ብቻ 8 ሰዎች ጌታን ተቀበሉ፡፡ ከ 1991 – 1993 ዓ.ም ነሐሴ ድረስ የ 3 ዓመት እንቅስቃሴን ስንመለከት በየጊዜው
ሰዎች እየዳኑና የእግዚአብሔር መንግስት እየሰፋች ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር መንግስት በብዛት ተጨምረዋል፡፡ በ 1993 ነሐሴ
ወር መጀመሪያ ሐዋሪያ ዳንኤል መኰንን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጠቅልለው አዲስ አበባ በመግባታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ
እድገት በሪቫይቫል ታጅቦ አገልግሎቱን በስፋት ማካሄድ ቀጠለ፡፡ ከ 1994 1997 ዓ.ም ድረስ ሪቫይቫል በኃይል የተነሳበት ወቅትና
ጊዜ ስለነበር በዓመት ሁለት ጊዜ የውኃ ጥምቀትና በዓመት 1 ጊዜ የደቀ መዝሙር ምርቃት ይካሄድ ነበር፡፡ በአንድ ዓመት ወደ
ከ 1000 በላይ ነፍሳት ሲድኑ ከነዚህ መካከል 750 ሰዎች ውሃ ጥምቀት ይወስዱ ነበር፡፡ 500 ደግሞ ደቀ መዝሙር ይመረቁ ነበር፡፡
በዚህ ጊዜ ብቻ ብዙ ሰዎች ተፈውሰዋል፤ ተጐብኝተዋል፣ ብዙ ነፍሳት ድነዋል፣ ብዙ ሰዎች ከአጋንንት እስራት ተፈተዋል፡፡

በዚህ ሁሉ የረዳንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ዛሬ የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሶስት አጥቢያ
ቤተክርስቲያን (አዋሬ፣ አየር ጤና፣ አያት)፣ በምስራቅ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ስምንት አጥቢያ ቤተክርስቲያን (ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሂርና፣ መሰላ፣
መጣቀሻ፣ ዶባ፣ አሰበ ተፈሪ፣ መቻራ)፣ አስራ ስምንት ወንጌል ስርጭት ጣቢያ (ታችኛው መጣቀሻ፣ ጨፌ፣ ጬማ፣ ገንደ አዲ፣
ጋራቁፋ፣ ገንደ መምሬ፣ ወሌንሶ፣ ደበሶ፣ አሮጌ ገበያ፣ አደስ፣ ጎልያ፣ ኡቴ፣ ሉጮ፣ ሚጨታ፣ ካራሚሌ፣ ወላርጊ፣ ኩፋካሳ፣ ገንደ
ጃርሶ)፣ በምስራቅ ሸዋ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አራት አጥቢያ ቤተክርስቲያን (አዳማ ልዩ ዞን፣ አዳማ ስላሴ፣ ሰፈረ ሰላም፣ መቂ)፣ ሁለት ወንጌል
ስርጭት ጣቢያ (መቶ አምስትና ቆቃ) በደቡብ እና ምዕራብ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሶስት አጥቢያ ቤተክርስቲያን (ሻሸመኔ፣ አዋሳ፣ ወልቂጤ)
ያላት ሲሆን ከ 20,000 በላይ ምዕመናን ሲኖራት በዚህ ሁሉ የረዳን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ
ጊዜያት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን 56 ለሚጠጉ አገልጋዮችን በመጋቢነት፣ በአስተማሪነትና
በወንጌላዊነት የአገልግሎት ስልጣን ሹመትን የሠጠች ሲሆን ከዚህም ውስጥ አራት ሴት ፓስተርና ወንጌላዊ ይገኛሉ፡፡

1.2.2 የማህበረሰብ አገልግሎት

ከዚህ ጐን ለጐን 180 የሚጠጉ ልጆችን በማስተማር፣ ወደ 20 ለሚጠጉ ወጣቶችን መንጃ ፈቃድ በማውጣት፣ ለእህቶች
የእንጀራ መጋገሪያ ፕሮጀክት በመክፈት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን በማሳጠርና በማጐልበት፣ ቤቶች ለፈረሱበቸው
ደካሞች ቤታቸውን በማደስና ለችግረኞች በየጊዜው ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ሠርታለች፤ አሁንም እየሰራች ትገኛለች፡፡

1.3 የራዕይ መግለጫ

ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ፤ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ መለኰታዊ ሥርዓትን በማራመድ ሁለንተናዊ አገልግሎት ለመስጠት የታጠቀ
ትውልድ ማስነሳት፡፡

90
1.4 ራዕይው በሥራ የሚተረጐምባቸው መንገዶች የተልዕኮ መግለጫ

1.4.1 የደህንነትን ወንጌል ከመስበክና ከማስተማር ባሻገር አማኞች የደቀመዝሙርነት ሕይወት እንዲኖሩና የክርስቲያን ባለአደራነትን እንዲረዱ
በማድረግ በሥራ እንዲተረጐሙ ማደፋፈርና ፍሬያማ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት፡፡
1.4.2 ደቀ መዝሙር አድራጊዎችን በማሰልጠን ከታዳጊ ክርስቲያኖች ጋር መለኮታዊ ስርዓትንና አባታዊ ግንኙነትን በመፍጠር ለበለጠ
ኃላፊነት ማዘጋጀት፡፡
1.4.3 አማኞች በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ አካሄድ እንዲኖራቸው በቃልና በስራ ብርቱ የሆነ ምሳሌነትን
መስጠት፡፡
1.4.4 የሰው ፍላጐት መንፈሳዊ እንደመሆኑ ሥጋዊም ስለሆነ በሕጻናት፣ በወጣቶች፣ በአረጋውያን፣ መበለትና እና ሌሎች ዙሪያ ምግባረ ሰናይ
አገልግሎት መስጠት፡፡

ምዕራፍ ሁለት፡- መተዳደሪያ ደንብ

2.1 መቋቋም

የኢትዮጵያ ወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን በየክልሉ አቅም እንደፈቀደ ወንጌልን ለሕዝቡ ማድረስ የምትችልበት
መንገድ ሁሉ መንግስት ለዚሁ ዓላማ በሰጣት ሕጋዊ መብት በመጠቀም ታቋቁማለች፡፡

2.2 ስያሜና አርማ

2.2.1 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተቋቋመው ማህበር “የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን” /Gospel Light International
Church/ በሚል ከዚህ ቀጥሎ “ቤተ ክርስቲያን” ተብሎ ይጠቀሳል፡፡
2.2.2 የቤተክርስቲያኒቱ ዓርማ በዓለም ካርታ /ሉል/ ላይ መስቀል፤ ከመስቀሉ ላይ ነበልባል እና መጽሐፍ ቅዱስ ያለበት ሲሆን
ምስሉና ትርጓሜው ከታች እንደተመለከተው ይሆናል፡:

2.2.3 የዓርማው ትርጓሜ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

ሀ/ መስቀሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን የከፈለውን መስዋዕትነት ያመለክታል፡፡


ለ/ መጽሐፍ ቅዱሱ ቤተ ክርስቲያኒቷ በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ ላይ የተመሰረተች መሆኗን ያመለክታል፡፡
ሐ/ የእሳት ነበልባሉ ቤተ ክርስቲያኒቷ በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ሥጦታዎች የምታምን መሆኗን ያመለክታል፡፡
መ/ የዓለም ካርታ /ሉል/ ቤተ ክርስቲያኒቷ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማድረስ ተልእኮ ያላት መሆኑን ያመለክታል፡፡

91
ምዕራፍ ሦስት፡- የእምነት መግለጫ

3.1 መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይና አዲስ ኪዳን) በምልዓት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ታምናለች፡፡ እንዲሁም
ሊታመንበት የሚገባው በሰው እምነትና ሕይወት ላይ የመጨረሻ ስልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት እርሱ ብቻ መሆኑን
ታምናለች፡፡ (1ቆሮ. 1*22፤ 2ጢሞ. 3*16፤ ሮሜ 15*14፤ ዮሐ. 3*6፤ 1ቆሮ. 10*11)

3.2 እግዚአብሔር

ዘላለማዊ የማይወሰን፤ ፍጹም፤ የማይለወጥ፤ ራሱን በሦስት አካል በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ በሚገለጥ በአንድ አምላክ ታምናለች፡፡ (ዘፍ.
1*26፤ ዘዳ. 6*4-5፤ መዝ. 89(90)*2፤ መዝ. 138(139)*7-12፤ መዝ. 146(147)*5 ኢሳ. 40*28፤ ሚልክ. 3*6፤ ዮሐ. 17*11)

3.2.1 እግዚአብሔር አብ

እግዚአብሔር አብ በፍቅሩ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በገባው ቃል ኪዳን መሠረት የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ በልጁ
በኢየሱስ ክርስቶስ ደኅንነት እንዳዘጋጀ እርሱን ተቀብለው ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን
እንደሰጣቸው ታምናለች፡፡ (ዘፍ. 17*1፤ ዘጸ. 3*15፤ 6*2-5፤ ኢሳ. 63*16፤ 1ቆሮ. 8*6፤ ኤፌ. 4*6)

3.2.2 እግዚአብሔር ወልድ


ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ልጅ መሆኑን፣ በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ ፍጹም ሰውና ፍጹም
አምላክ መሆኑን፣ ኃጢአት ያልሰራ መሆኑን፣ ሰውን ለመዋጀት ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ራሱን ቤዛ አድርጐ በመስቀል ላይ መሞቱን፣
በሦስተኛው ቀን ከሞት መነሳቱን፣ በክብር ማረጉን ለእኛም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት መኖሩን፣ የቤተ ክርስቲያናችን መሥራችና ራስ መሆኑን፣
ደግሞም ለፍርድ እንደሚመጣ ታምናለች፡፡ (ዘፍ. 3*13፤ ኢሳ. 53*5-6፤ ማቴ. 28*6፤ ሉቃ. 1*35፤ ዮሐ. 1*1-14፤ 19*34፤ ሐዋ.
17*31፤ 2ቆሮ. 5*18-21፤ ኤፌ. 5*23፤ 1ጢሞ. 3*16፤ ዕብ. 1*8፤ 4*5፤ 7*25፤ 9*12፤ 13*8፤ 1ጴጥ. 2*22)
3.2.3 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ምልዓተ አካል እንዳለውና መለኮት መሆኑን፣ ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ እንደሚወቅስ፣ በምዕመናን
ውስጥ አድሮ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው፣ እንደሚያጽናናቸው፣ የቅድስና ኑሮ ለመኖር እንደሚያስችላቸው፣ ለአገልግሎትም ኃይልንና
የፀጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጣቸው ታምናለች፡፡ ዛሬም ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚጠመቁና በልዩ ቋንቋ (ልሳን) እንደሚናገሩ
ታምናለች፡፡ (ዘፍ. 1*2፤ ዮሐ. 7*37-39፤ ሐዋ. 2*3-4፤ 8*14-17፤ 10*45-46፤ 19*6-7፤ 1ቆሮ. 12*10፤ 14*4-5)

3.3 ደኅንነት (አዲስ ፍጥረት)


ሰው በመጀመሪያ ያለ ኃጢአት መፈጠሩን ታምናለች፡፡ ይሁን እንጂ ሰው በፈቃደኝነቱ ኃጢአት ላይ በመውደቁ ምክንያት የኃጢአት ባሕርይ ይዞ መወለዱን
እንዲሁም በኃጢአቱ ተጸጽቶና ንስሃ ገብቶ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው የመስቀሉ ሥራ በማመን በፀጋ ብቻ እንደሚድንና እንደሚጸድቅ ዳግመኛ በመንፈስ
ቅዱስ በመወለድ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሆን፣ በክርስቶስ መንፈሳዊ በረከትና የዘላለም ሕይወትን እንደሚያገኝ ታምናለች፡፡ (ዮሐ. 12*13፤ 3*4-8፣
16፤ ሐዋ. 13*38-39፤ ሮሜ 3*20-26፤ 10*9-10፤ ኤፌ. 2*8-9)

92
3.4 መለየትና ቅድስና

ምዕመናን ከዓለማዊነትና በዓለም ከሚገኙ ከንቱ ነገሮች ተለይተው ለእግዚአብሔር ክብር በኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ ኑሮ መኖር እንደሚገባ ታምናለች፡፡ (ዮሐ.
17*15፤ 2ቆሮ. 6*14-18፤ ሮሜ 12*1-2፤ 1ጴጥ. 2*9፤ 1ዮሐ. 2*9፤ 2*15-16፤ ዕብ. 12*14፤ 1ተሰ. 4*3፤ ቲቶ 2*11-14)

3.5 የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት


የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የምዕመናን ሁሉ ተስፋ መሆኑንና በምጽዓት ጊዜ በሕይወት ያሉና ከሙታን የሚነሱ ምዕመናን ጌታን በአየር እንደሚቀበሉ ከዚያም
በኋላ ለዘለዓለም በደስታ ከእርሱ ጋር እንደሚኖሩ ታምናለች፡፡ (ማቴ. 24*44፤ 24*30-31፤ ዮሐ. 14*3፤ ሐዋ. 1*11፤ 1ተሰ. 4*13-18፤ 1ዮሐ. 2*28)

3.6 ቅዱሳን መላዕክት

ቅዱሳን መላዕክት ሕያዋን መሆናቸውን፣ በእግዚአብሔር ፊት እንዳሉ፣ ቅዱሳንን እንደሚያገለግሉና ጌታ ሲመጣ አብረው እንደሚገለጡ ታምናለች፡፡ (1ነገ.
19*5-7፤ ማቴ. 1*20-22፤ 2*13፤ 28*28፤ ሉቃ. 1*11-20፤ 16*22፤ 1ተሰ. 4*16፤ ራዕይ 1*14፤ 14*10)

3.7 ሰይጣን
ሰይጣን እርኩስ መንፈስ መሆኑን፣ የጥፋት ሁሉ ምንጭ በእግዚአብሔር መንግስትና ዕቅድ ላይ ያመጸ ሐሰተኛ አባት መሆኑን፣ በመጨረሻም ከተከታዮች ጋር
ወደ ተዘጋጀለት ወደ ገሃነመ እሳት እንደሚጣል ታምናለች፡፡ (ዘፍ. 3*1-5፤ ኢሳ. 14*12-15፤ ዮሐ. 8*44፤ 2ቆሮ. 11*14፤ 1ጴጥ. 5*8፤ ራዕይ 2*10፤
20*10)

3.8 ፍርድ

ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻም በክብር በሚገለጥበት ጊዜ በክርስቶስ አዳኝነት ያመኑ (ጻድቃን) ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም በመንግስተ ሰማይ እንዲያርፉ
ሲፈርድላቸው በክርስቶስ አዳኝነት ያላመኑ (ኃጥአን) በገሃነም ለዘለዓለም እሳት ውስጥ እንዲጣሉ እንደሚፈረድባቸው ታምናለች፡፡ ሰይጣንና መላዕክቱም
በእሳት ባሕር ውስጥ እንደሚጣሉ ታምናለች፡፡ (ማቴ. 25*31-46፤ ሉቃ. 13*23-30፤ 16*19-30፤ ራዕይ 7*9-17፤ 20*10-15)

የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች

3.9 የውኃ ጥምቀት


የውኃ ጥምቀት መከናወን ያለበት ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ንስሃ ገብተው ከክርስቶስ ጋር መነሳታቸውን ለዓለም የሚያረጋግጡበት፣
የሚመሰክሩበትም መሆኑን ታምናለች፡፡ የጥምቀት ሥርዓት በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ ጠልቆ (ተቀብሮ) በመውጣት
መልክ ይፈጸማል፡፡ (ማቴ. 18*19-20፤ ሐዋ. 2*38፤ 8*34፤ ሮሜ 6*1-8፤ ቆላ. 2*12)
3.10 የጌታ እራት

በሕብስትና በወይን ጭማቂ የሚዘጋጀውን የጌታ እራት የጌታችን ስቃይና ሞት እንደገናም መመለሱን የሚያሳስበን ሲሆን እርሱ እስኪመጣ ድረስ
በአማኞች መደረግ ያለበት ሥርዓት መሆኑን ታምናለች፡፡ (ሉቃ. 22*19-20፤ 1ቆሮ. 11*23-26፤ 2ጴጥ. 1*14)

93
3.11 ሕፃንን ለጌታ ስለመስጠት

ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትን ለጌታ አሳልፎ በመስጠት ታምናለች፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ሕፃናቶቻቸውን በሕዝብ ፊት ይዘው በመቅረብ ሥርዓተ
ባርኰት ያስፈጽማሉ፡፡ (1ሳሙ.1*25-28፤ ማቴ. 19*14-14፤ ሉቃ. 2*27፤ ማር. 10*13-16)

3.12 ጋብቻ

በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚፈጸም እግዚአብሔር የቀደሰው የሁለት ተቃራኒ ጾታዎች አንድነት መሆኑን ታምናለች፡፡ (ዘፍ. 2*20-
24፤ ማቴ. 19*3-9፤ ማር. 10*2-12፤ 1ቆሮ. 7*39፤ ኤፌ. 5*22-23)

3.13 ክህነት
ቤተ ክርስቲያኒቱ በመመሪያዋ የተዘረዘረውን መሥፈርት ያሟሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን መተዳደሪያ ደንቡን በመከተል በኤፌ 4*11
የተዘረዘረውን መሠረት በማድረግ የክህነት ሹመት ትሰጣለች፡፡

3.14 ቀብር መፈጸም

አማኞች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትፈጽማለች፡፡

ምዕራፍ አራት፡- የቤተ ክርስቲያን ዓላማ


ቤተ ክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫዎችን መሠረት አድርጋ የተቋቋመችው ለሚከተሉት ዓላማዎች ነው፡፡
4.1 የእግዚአብሔርን ቃል በሙላት መስበክና ማስተማር፡፡ (ማቴ. 4*23፤ ኤፌ. 4*12-13፤ 5*2 ፤2ጢሞ. 4*1-2
4.2 ሰዎች ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት እንዲያውቁና አምነው እንዲድኑ በዚህ በኩል የሚገኘውን ዘላለማዊ ሕይወት በምልዓት
እንዲያገኙ ማበረታታት፡፡ (ማቴ. 9*35፤ 2ጢሞ. 4*1-2፤ 1ዮሐ. 5*11-12)
4.3 የክርስቲያኖች እምነትና ታማኝነት እንዲጠነክር ለጸሎት፣ ለምክርና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት አማኞችን ማደራጀት፡፡ (ማቴ.
9*35፤ ሐዋ. 1*14፤ 2*1-2፤ 1ዮሐ. 5*11-12)
4.4 ቤተ ክርስቲያኗ በሐዋርያት፣ በነቢያት፣ በመጋቢ፣ በአስተማሪና በወንጌላውያን አገልግሎት ስለምታምን ለዚህ አገልግሎት የተጠሩ ሰዎች
አገልግሎታቸውን በሙላት እንዲሰጡ ማበረታታት፡፡ (ሐዋ. 13*1-4፤ ኤፌ. 4*11፤ 1ቆሮ. 12*28)
4.5 በአብያተ ክርስቲያናትና በወንጌል አማኞች መካከል አንድነትና ሕብረት እንዲኖር ጥረት ታደርጋለች፡፡
4.6 ስለ ሰዎች ሁሉ፤ ስለ መንግስትና ስለ ባለሥልጣናት ሁሉ ልመና፤ ጸሎትና ምልጃ ማድረግ፡፡ (1ጢሞ. 2*2)
4.7 በሥነ ምግባር የታነጸ ብቁ ዜጋ ማፍራት፡፡
4.8 የልማት ድርጅት በማቋቋም መንግስትና ሕዝብን የሚጠቅሙ የልማት ሥራዎች መስራት፡፡
4.9 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ከዚህ በላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የቤተ ክርስቲያኒቱን ዓላማዎች የማስፈጸም ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡

ምዕራፍ አምስት፡- የቤተ ክርስቲያን ተግባራት


5.1 ጽሑፍ፣ ጀማ ስብከት፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ኦዲዮ ቪዲዮ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት ማሳተምና ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ መጠቀም፡፡
5.2 የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም የአገልግሎት ጥሪ ያላቸውን ለወንጌል ሥራ ማሰልጠን፡፡
94
5.3 የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም ወንጌልን ማሰራጨትና ማስተማር፡፡
5.4 በጸሎት፣ በገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ከሚመለከታቸው ጋር በአንድነት መሥራት፡፡
5.5 መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚረዱ የትምህርት መረጃዎችንና ማስተማሪያ መጽሐፍትን እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት
መሣሪያዎችን በማዘጋጀት ማሰራጨት፡፡
5.6 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ከዚህ በላይ የተመለከቱትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ተግባርና ኃላፊነቶች ወደ ተግባር የመለወጥ
ሙሉ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ምዕራፍ ስድስት፡- ቤተክርስቲያንና ፖለቲካ


6.1 ቤተ ክርስቲያኗ ለኃይማኖት ተግባር ብቻ እንድትውል ተቋቁማለች፡፡ ስለሆነም ትርፍ አልባ ከፖለቲካ ነፃ የሆነች ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ
በምንም ዓይነት መንገድ የሀገሪቱን ሕግና የፖለቲካ ይዘት የሚተች ወይም ሊያዛባ የሚችል ጽሑፍ አታሰራጭም፡፡
6.2 ቤተ ክርስቲያኗ በምንም ዓይነት ለመመረጥ፣ ለመምረጥ ወይም የፖለቲካ ዘመቻ ለሚያደርጉ ግለሰቦች ድጋፍ አትሰጥም፡፡
6.3 ቤተ ክርስቲያኗ ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎችና መሰል የፖለቲካ ሁኔታዎችን አታስተናግድም፡፡
6.4 የዚህች ቤተ ክርስቲያን ዋና ዓላማ መንፈሳዊ ተልዕኮ በመሆኑ የማናቸውንም የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብና ርዕዮተ ዓለም አታሰራጭም፡፡
6.5 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀገሪቱ ሕጎች በሚፈቅደው መሰረት በሀገር ጉዳይ ላይ
ያላትን ሐሳብ ለመንግስት ታቀርባለች፡፡
6.6 የቤተ ክርስቲያን አባላት በግላቸው በፖለቲካ ውስጥ የሚያደርጉት ማንኛውም ተሳትፎ ቤተክርስቲያንን አይወክልም፡፡

ምዕራፍ ሰባት፡- አባልነት


ሀ/ በጌታ በኢየሱስ በማመን በእምነት ደህንነትን የተቀበለ/ች ወይም የተለወጠ ክርስቲያን መሆን አለበት/ባት፡፡ (ዮሐ 1*12-14፤ ሐዋ. 23*8-
42፤ ኤፌ. 2*8-10)
ለ/ የቤተ ክርስቲያኒቱን የእምነት አንቀጽና መተዳደሪያ ደንብ አምኖ/ና የተቀበለ/ች መሆን አለበት/ባት፡፡
ሐ/ በዚች ቤተ ክርስቲያን ደህንነትን ያገኘ/ች ከሆነ የመጀመሪያውን የድነት ትምህርት የተካፈለ/ች እና የተጠመቀ/ች መሆን አለበት/ባት፡፡
መ/ ከሌላ ቤተ እምነት የሚመጣ/የምትመጣ አማኝ፤ የተለወጠ/ች ክርስቲያን የአባልነት ቅጹን በፈቃደኝነት ከሞላ/ች በኋላ በመጋቢው
አቅራቢነት በሽማግሌዎች ጉባዔ ከተወሰነ በኋላ የተጠየቀውን በማሟላት አባል ይሆናል/ትሆናለች፡፡
7.1 የአባልነት መብት

7.1.1 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ በልዩ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር ሁሉም አባላት እኩል መብት አላቸው፡፡
7.1.2 አባላት እንደ ጸጋቸው እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን ያገለግላሉ፡፡
7.1.3 አባላት ሥጋዊ/መንፈሳዊ የሆነ ችግር ሲገጥማቸው፣ በኃዘንም ሆነ በደስታ ቤተ ክርስቲያን አቅሟ እንደፈቀደላት እርዳታ
ታደርጋለች፡፡
7.1.4 የቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡
7.1.5 ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል፡-
ሀ/ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዓላማና ተልዕኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ማናቸውንም አይነት ሥራዎች የመስራት፤
ለ/ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትሰጠውን አገልግሎት እኩል የማግኘት፤ መብት አለው፡፡

95
7.1.6 ማንኛውም አባል ቤተ ክርስቲያኒቱ የተቋቋመችበትን ዓላማ በግልጽ ተቃርኖ ወይም የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና
በሚያሰጋ መልኩ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ በአባልነት መብቶች መጠቀም አይችልም፡፡

7.2 የአባላት ግዴታ

7.2.1 ማንኛውም አባል የቤተ ክርስቲያኒቱን ራዕይ፣ የእምነት አንቀጽና አስተምህሮ መቀበልና መተግበር ይኖርበታል፡፡
7.2.2 የቤተ ክርስቲያኒቱን ስብሰባዎች መካፈልና ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ፣ የመንፈስን አንድነትን ማስጠበቅ፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠ
ትምህርት መጽናት፣ ከሀሰተኛ አሠራር መጠበቅ፡፡
7.2.3 በገንዘብና በመንፈሳዊ ስጦታ የክርስቶስን አካል ማነጽና መገንባት፡፡
7.2.4 ማንኛውም አባል ቤተክርስቲያኒቱ ከተቋቋመችበት ዓላማ ጋር የሚጻረር አካሄድ ሲታይበት ከቤተክርስቲያኒቷ
የሚሠጠውን ምክር፤ ተግሣጽን፤ የሥነ ሥርዓት እና ሌሎች ውሳኔዎችን በጸጋ መቀበል ይኖርበታል፡፡
7.2.5 ማንኛውም አባል የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት የመንከባከብና የሚጠበቅበትን አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
7.3 አባልነት ስለሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች
7.3.1 አንድ አባል፡-
ሀ/ ሲሞት ወይም
ለ/ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እንዲሰናበት ሲወሰን ወይም
ሐ/ በራሱ/ሷ ፈቃድ በጽሑፍ ሲ/ስት/ጠይቅ፤
መ/ የቤተ ክርስቲያኗን ደንብ ሲስት፣ ሲተላለፍና የሞራል ውድቀት ወይም የእምነት ግድፈት ወይም የአስተምህሮ (ዶክትሪን)
ሥህተት ወይም የሥህተት አሰራር ሲገኝበት/ባት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላምና አንድነት የሚያናጋ ድርጊት ሆን ብሎ
ሲፈጽም/ስትፈጽም ሲገኝ/ስትገኝ ተመክሮ/ራ ተዘክሮ/ራ የማይመለስ/የማትመለስ ከሆነ አባልነቱ/ቷ ይቋረጣል፡፡ (ማቴ.
18*15-17፤ 1ቆሮ. 5*1-5፤ 2ቆሮ. 2*5-10)

7.3.2 ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሳያሳውቅ/ሳታሳውቅ ለተከታታይ ሦስት ወራት አባል ከሆነባት/ከሆነችባት አጥቢያ
ቤተክርስቲያን የራቀ/የራቀች ወይም በአጥቢያዋ የማይገኝ/ የማትገኝ አባል አሳማኝ ምክንያት ለአጥቢያዋ
ሽማግሌዎች ጉባዔ አቅርቦ/ባ ተቀባይነት ካላገኘ/ች በስተቀር የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባልነቱ/ቷ ቀሪ ይሆናል፡፡
በአባልነት መብቶች መጠቀም አይችልም፡፡ ሆኖም የአጥቢያዋ ሽማግሌዎች ጉባዔ ጉዳዩን መርምረው በሚሰጡት
ውሳኔ አባልነቱን መልሶ ማግኘት ይችላል፡፡

ምዕራፍ ስምንት፡- አመራር


ቤተክርስቲያኒቱ በሚከተለው መልኩ የተዋቀረች ናት

96
8.1 ጠቅላላ ጉባዔ፡- እስከ ሦስት መቶ አባላት ያሉት አጥቢያዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ተወካዮች ይኖራቸዋል፡፡ እነርሱም የአጥቢያ
ዋና ፓስተርና ከሽማግሌዎች መካከል የሚወከል አንድ አባል ይሆናል፡፡
8.2 የሥራ አመራር ቦርድ፡- የሥራ አመራር ቦርድ ሐዋርያውን ጨምሮ 7 አባላት ይኖሩታል፡፡ ሐዋርያው የቦርዱ ሰብሳቢ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ቦርዱ
ምክትል ሰብሳቢውን ይመርጣል፡፡ ዋና ጸሐፊው ድምጽ የመስጠት መብት ሳይኖረው የቦርድ ጸሐፊ ሆኖ ይሰራል፡፡
8.3 የሐዋሪያው ተግባርና ኃላፊነት፡- የቤተክርስቲያኒቱ ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያኒቱን ራዕይ ማንም ሳይኖር ከእግዚአብሔር ዘንድ
ተቀብሎ ለመስራች አባላት ራዕዩን ያካፈለና ለዚህም ስራ እግዚአብሔር የሾመው የህይወት ዘመን አገልጋይ ሲሆን
ሥልጣኑና ተግባሩም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
 ሐዋርያው በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኗ ተጠሪና አገልጋይ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱን እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፤
ያስተባብራል፤ ያደራጃል፡፡ የአጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ሕብረት፤ የሐዋርያው ቢሮ፤ ሲኖዶሱንና ሚዲያ ኮሙኒኬሽንን በበላይነት
ይመራል፡፡
 ሐዋርያው የቤተ ክርስቲያኗ የእድሜ ልክ አገልጋይ ነው፡፡
 ለቤተ ክርስቲያኗ የሚያስልጓትን አገልጋዮች ይመርጣል፤ ሹመት ይሰጣል፤ የሥነ ሥርዓት እርምጃም ይወስዳል፤ ይሽራል፡፡
 ሐዋርያው ምዕመኑን በአጠቃላይ እንዲሁም ሽማግሌዎችን፤ መጋቢዎችን፤ ወንጌላውያንን፤ አስተማሪዎችን፤ ነቢያትን፤ ሐዋርያትንና
የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን ለመጠበቅ፤ ለማጽናናት፤ ለማስተማር፤ ለመምከር የጠፋውን ለመፈለግ ምሳሌ ለመሆን ይተጋል፡፡
(ኤር 3÷15፤ ዮሐ 21÷15,17፤ ሐዋ 20÷28፤ 1ጢሞ 4÷11-13) በቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት ትምህርት ላይ በሚነሱ አከራካሪ
ነጥቦች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
 የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አንድነትና ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋግጡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሐዋርያ
የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ዓይነት እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ሐዋርያው ቢያንስ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ
በመጥራት ለጉዳዩ እልባት መሥጠት ይኖርባቸዋል፡፡
 አዲስ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን በበላይነት ያደራጃል፤ ለሐዋርያው ቢሮ አቅርቦ የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን
አባል ያደርጋል፡፡ ለቦርድና ለጠቅላላ ጉባዔው ያሳውቃል፡፡
8.4 የሐዋርያው ቢሮ፡- የሐዋርያው ቢሮ ተጠሪነት ለሐዋርያው ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
 ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አገልግሎቶችንና አገልጋዮችን ይመራል፡፡
 አገልጋዮችን በረዳት አገልጋይነት ወይም በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ያሰማራል፤ የክህነት ሥልጣን /ordination/ ይሰጣል፤ የዲሲፕሊን እርምጃዎችን
ይወስዳል፤ ያሰናብታል፡፡

97
 ከመንፈሳዊ ሥራ ጋር በተያያዘ ቋሚነት ያላቸው ፖሊሲዎች ለምሳሌ ጋብቻ፤ አባልነት ወዘተ… በመንደፍ በጋራ ስምምነት ሥራ ላይ ይውላል፡፡
 ማንኛውም የዶክትሪንና የመንፈሳዊ ትምህርቶችን ማዘጋጀትና እንደ እግዚአብሔር ቃል ባልሆኑ ትምህርቶችና አሰራሮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
 በመጽናናት አገልግሎት ሥር የሚመራው መንፈሳዊ አገልግሎቶችንና ሥርዓትዎችን ይከታተላል፡፡
8.5 የሲኖዶስ ጽ/ቤት፡- በአገሪቱ ውስጥ በምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብና በመሐል አገር አምስት ሲኖዶስ በማቋቋም አጥቢያ አብያተ
ክርስቲያናትን ታደራጃለች፡፡ እያንዳንዱ ሲኖዶስ በሲኖዶስ አስተባባሪ የሚመራ ይሆናል፡፡ የሲኖዶሱን ስራ በበላይነት የሚመራው የሲኖዶሱ
አስተባባሪ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተመርጦ በሐዋሪያው ሹመት የሚጸድቅ ይሆናል፡፡
8.6 የሽማግሌዎች ጉባዔ
የሽማግሌዎች ጉባዔ ማለት በ1ኛጢሞ 3 እንደተገለጠው በሙሉ ጊዜ አገልግሎት በመጋቢነት፣ በምክትል መጋቢነት የተሰማሩትንና በትርፍ
ጊዜያቸው ለማገልገል የተመረጡትን የሚያካትት ነው፡፡
8.6.1 የሽማግሌ ምርጫ
የቤተ ክርስቲያኒቱ ሽማግሌዎች በዋና መጋቢው የሚመረጡ ሲሆን በአገልግሎቱ ላይ ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሽማግሌዎች በምርጫው ላይ ሙሉ
ተሳትፎ ይኖራቸዋል፡፡ ሽማግሌዎች መጋቢው በሚያደርገው ምርጫ ሃሳብ መስጠትና እጩዎችን መጠቆም ይችላሉ፡፡ መጋቢውና ሽማግሌዎች
የተሰማሙባቸውን እጩዎች ለቤተ ክርስቲያኒቱ በማቅረብ መጋቢው ሹመት ይሰጣል፡፡

8.7 የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት


በመሠረቱ የቤተ ክርስቲያን መሥራችና ራስ የሆነው ጌታ ኢየሱስ እንደ ሆነ ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል፡፡ በወንጌል ብርሃን ቤተ

ክርስቲያን የአጥቢያ አመሰራረት የሚከተለው ይዘት ይከተላል፡፡


8.7.1 በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች ወንጌልን የማሰራጨትና የመስበክ ኃላፊነት አለበት፡፡
8.7.2 ይህ የመመስከርና የምስራቹን የማብሰር አገልግሎት በወንጌላውያን አስተባባሪነት ምዕመናንን የሚያሳትፍ ሆኖ በቅርብ ወዳሉ
ወረዳዎችና ከተሞች የሚዛመት ይሆናል፡፡
8.7.3 ይህን አሰራር ሌሎች ተመሳሳይ እምነት ያላቸውን ቤተ እምነቶች ምዕመን በማይነካ የቅዱሳንን አንድነት በማይጐዳ ሁኔታ መካሄድ
ይኖርበታል፡፡
8.8 የሥርጭት ጣቢያ
የስርጭት ጣቢያ የምልጃ ጸሎት የሚካሄድበት ወደ ጌታ የመጡ ሰዎች የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትና የቅርብ ክትትል የሚደረግበት ስፍራ
ነው፡፡ ምንም እንኳ የሥርጭት ጣቢያ በመባል ቢታወቅም ቢያንስ የአንድ ወንጌላዊ ቢሮ የሚገኝበትና በሳምንት አንድ ጊዜ የወንጌል ስርጭት
ወይም የጸሎት ስብሰባ ይካሄድበታል፡፡ የሥርጭት ጣቢያው አንድ ሳምንታዊ ፕሮግራም የሚኖረው ሲሆን ፍሬያማ ሲሆንና የተሳታፊዎች ቁጥር
ከሃምሳ በላይ ሲሆን በሐዋሪያው ቢሮ ውሳኔ ‘‘የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን’’ ስያሜ ይሰጠዋል፡፡

ምዕራፍ ዘጠኝ፡- የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን (ክህነት) መንፈሳዊ ሥልጣን ስለመስጠት


(Ordination)
9.1 አንድ አገልጋይ የሐዋሪያነት፣ የነቢይነት፣ አስተማሪነት፣ የወንጌላዊ እና የመጋቢ ሹመት የሚቀበለው ጠቅላላ የወንጌል ብርሃን ጉባዔ
ሲያምንበትና ሲያጸድቀው በሐዋሪያው ቢሮ ያቀረበውን መሥፈርት ሲያሟላ ነው፡፡
9.2 አንድ አገልጋይ ሹመት ከመቀበሉ በፊት የጥሪውን እውነተኛነት፣ ስጦታውና ችሎታው በቤተ ክርስቲያኗ የሽማግሌዎች ጉባዔ ፓስተሮች
የልዩ ልዩ አገልጋዮች መሪዎች ሁሉ ሊታመንበት ይገባል፡፡
9.3 የሽማግሌዎች ጉባዔ በፓስተሮች ለምዕመናን ስለ አገልጋዩ ጥሪ እውነተኛነት ስለ ፀጋው ስጦታ የሚያውቁትንና በመንፈስ የተረዱትን
ይገልጻሉ፡፡
98
9.3 አገልጋዩ ሹመት ለመቀበል ግለሰቡ መለኰታዊ ጥሪ እንዳለው ከምዕመኑ ሦስት አራተኛው እንዲያምንበት ያስፈልጋል፡፡
9.4 አገልጋይ ሲሾም ሐዋሪያው ለመገኘት በቻሉበት ቦታ ሁሉ ሹመቱ ይሰጥና መገኘት ባልቻሉበት በሐዋሪያው በሚወከለው ሰው ፊት
ይሾማል፡፡

9.5 ታዳጊ አገልጋይዎች (Junior Ministers)

ታዳጊ አገልጋይ ማለት የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ጥሪ እንዳለው አምኖ ለሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ለቤተ ክርስቲያን በጽሑፍ ያመለከተ ወይም በቤተ
ክርስቲያን ዋና መጋቢ በኩል ጥሪ አቅርባለት በሙከራ ጊዜ ላይ ያለ ማለት ነው፡፡ ይህ/ች/ ግለሰብ ምንም ዓይነት የአገልግሎት ሥልጣን መጠሪያ
ሳይሰጠው/ጣት/ (በኤፌ 4÷11 የተዘረዘረው) ‘‘ታዳጊ አገልጋይ’’ በሚል ስያሜ ከፓስተሩ ወይም ሹመት (Ordination) ከተቀበሉ አገልጋዮች
ስር ሆኖ የሚያገለግል ነው

ምዕራፍ አስር፡- ከሌላ ቤተ እምነት መጥተው የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ለመሆን
ጥያቄ ስለሚያቀርቡ ግለሰቦች
10.1 ከሌላ ቤተ እምነት በሆነ ምክንያት ተነጥለው የሚወጡ ክርስቲያኖች በወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ጥላ ስር መሆን ቢፈልጉ
ጥያቄአቸውን በጽሑፍ ለሐዋሪያው ቢሮ (ለአጥቢያው መሪ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10.2 የደብዳቤዎች ይዘት የሚከተለውን ሃሳብ የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
10.2.1 ስማቸውን እድሜያቸውንና ሙያቸውን በመዘርዘር ያቀርባሉ፡፡
10.2.2 ከነበሩበት ቤተ እምነት የወጡበትን ምክንያትና አብረው ለመኖር ያደረጉትን ጥረት በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡
10.3 የሐዋሪያው ቢሮ (የአጥቢያው መሪ) ደብዳቤአቸውን ከተመለከተ በኋላ ለሚቀርባቸው የወንጌል ብርሃን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን
እንዲያጠናና እንዲከታተል በአደራ ይሰጠዋል፡፡
10.4 በጥናቱ ላይ የሚካተቱ ሃሳቦች፡፡
10.4.1 ተለይተው የወጡበትን ቤተ እምነት መሪዎች ማነጋገርና ስለ ግለሰቦች የሚሰጡትን ምስክርነት መረዳትና ማወቅ
10.4.2 በሁለቱ ወገኖች መካከል አለመስማማት ተፈጥሮ ከሆነ ሁለቱን ወገኖች ማስታረቅ የሚቻል ከሆነ አብረው የሚቀጥሉበትን ሁኔታ
ማመቻቸት
10.4.3 የቤተ እምነቱ መሪዎች ግለሰቦች ወደ ወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ቢገቡ የሚሰማቸውን መጠየቅና መረዳት

ምዕራፍ አስራ አንድ፡- የቤተ ክርስቲያኒቷ የገቢ ምንጭ


የቤተ ክርስቲያኒቷ የገቢ ምንጭ ከአስራት፣ ከመባ፣ የሃገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው እና ሃይማኖታዊ መሰረት በጠበቀ ሁኔታ ከሚቋቋሙ
የገቢ ማስገኛ ተቋማት፤ እንዲሁም ከተለያዩ ስጦታዎችና ዕርዳታዎች ነው፡፡

ምዕራፍ አስራ ሁለት፡- በወንጌል መጽናናትና መረዳዳት ሕብረት


ቤተ ክርስቲያን ከምታከናውናቸው በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎቶች መካከል፤ አንዱና ዋነኛው በሆነው የወንጌል ስርጭት ስራ
ውስጥ፤ ህብረቱ በጐ ተጽዕኖ በመፍጠር ከቤተ ክርስቲያን ጐን በመሆን፣ በርካታ አገልግሎቶችን በመስጠት ይገኛል፡፡ የሕብረቱ
ዓላማም ክርስቲያኖች በግልም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታቸው፣ ደስታም ሆነ ሐዘን ሲያጋጥማቸው፣ ወንጌልን ማዕከል ያደረገ
99
የእርዳታና የድጋፍ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን
ችግረኞችን፣ ወላጅ አልባ ሕጻናት፣ አረጋዊያን መርዳት ነው፡፡ ይህንንም የሕብቱን ዓላማ ለማስፈጸም በማሰብ፤ በወቅቱ ዘርፈ
ብዙ ተግባራትን ለማከናወን ከሕብረቱ ምስረታ ጀምሮ፤ አንድ ቢሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከፍቶ በእንቅስቃሴ
ላይ ይገኛል፡፡ የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፤ በወንጌል መጽናናትና መረዳዳት ሕብረት፣ ከፍ ብሎ በተገለጸው ዓላማና ግብ
የተቋቋመ ሲሆን፤ ይህንኑ ዓላማ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመፈጸም፤ የቤተ ክርስቲያን አባላት በሙሉ በአባልነት ከመመዝገብ
ጀምሮ ሌሎች ኃላፊነቶችን በመውሰድ ሊሰሩና አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

12.1 የገቢ ምንጭ

በወንጌል መጽናናትና መረዳዳት ሕብረት የገቢ ምንጭ


 የአባላት መዋጮ
 የአባላት ልዩ ስጦታ
 የቤተ ክርስቲያን ስጦታ
 ለጋሾች ሥጦታ (አልባሳት፤ ቁሳቁስ…..)
 ከሕብረቱ የአገልግሎት ዘርፎች የሚገኙ የተለያዩ ገቢዎች ናቸው

ተግባራዊ ተዛምዶ
 ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ሲገልጻት ወደ ባህር የተጣለች መረብን ወይም በእርሻ መልክ መስላታል (ማቴ.
13*36-37፤ 47)፤ ይህ ማለት ወደ ባህር የተጣለ መረብም ሆነ እርሻ መልካም ነገር ብቻ ሳይሆን መጥፎም ነገር
ይኖርበታል፤ ወደ ባህር የተጣለ መረብ ዓሣ ብቻ ሳይሆን ጊንጥም ሌላም የባህር እንሰሳ ይይዛል፤ እንዲሁም እርሻ ስንዴ
ብቻ ሳይሆን አረምም በውስጡ ያበቅላል፡፡ ወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያንም ልክ እንደ መረብ እና እርሻ
በውስጧ የተለያዩ ሰዎች ስለምትይዝ ፍጹም የሆነች ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ ስሌለች፤ በትንንሽ ችግሮች
100
(ምክንያቶች) ከቤተ ክርስቲያን መልቀቅ (መራቅ) የለብንም፡፡ ችግሮች እንኳን ቢፈጠሩ በፍቅር ልንነጋገር፣ ልንመካከር፣
ልንወቃቀስ… ቤተ ክርስቲያናዊ እድሉን ሁሉ በመጠቀም ችግሩን ለመፍታት መሞከር አለብን እንጂ ሌላ
አለማዊ/ምድራዊ መፍትሄ መፈለግ የለብንም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቡድንተኝነት፣ አድመኝነት፣ መፈንቅለ ስልጣን
በፍጹም አይሰራም፡፡ ይህ እግዚአብሔር የሚጸየፈው የስጋ ስራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያስቀመጣቸውን አገልጋዮች
(መሪዎች) በአመጽ፣ በሴራ፣ በአድማ ካሉበት ስፍራ ለማውረድ መሞከር የቤተክርስቲያን ባለቤት የሆነውን ኢየሱስን
መጋፋት ነው፡፡
 የቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮግራሞች መካፈልና ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ፣ የመንፈስን አንድነትን ማስጠበቅ፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ
በተሰጠ ትምህርት መጽናት፣ ከሀሰተኛ አሠራር መጠበቅ ከእያንዳንዱ አባል ይጠበቃል፡፡ ቤታችን ውስጥ ተቀምጠን በተለያየ
ሚዲያ ( ቲቪ፣ ሬዲዮ፣ ኢንተርኔት ወ.ዘ.ተ) መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን መከታተል ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ትልቅ
ጠቀሜታ ቢኖረውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አባል ሆነን የምናገኘውን ትልቅ ጥቅም ግን ሊተካ አይችልም፡፡ ስለዚህ
አንድ አማኝ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮግራሞች መካፈልና ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ አለበት፡፡
 ማንኛውም አባል ቤተክርስቲያኒቱ ከተቋቋመችበት ዓላማ ጋር የሚጻረር አካሄድ ሲታይበት ከቤተክርስቲያኒቷ
የሚሠጠውን ምክር፤ ተግሣጽን፤ የሥነ ሥርዓት እና ሌሎች ውሳኔዎችን በጸጋ መቀበል ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔር
ለቤተ ክርስቲያን ስልጣን ስለሰጠ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀችው ስርዓት ውስጥ ገብቶ መተዳደርና በስርዓት ለመኖርና
ተጠያቂ ለመሆን ራስን ማቅረብ አለብን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን መቃወም እና ለቤተ ክርስቲያን ስልጣን አለመታዘዝ
ስልጣን ሰጪውን ክርስቶስን መቃወም ነው፡፡
 የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የገቢ ምንጭ ከአስራት፣ ከመባ እንዲሁም ከተለያዩ የፍቅር ስጦታዎችና ዕርዳታዎች ነው፡፡
ስለዚህ እንደ ቤተ ክርስቲያን አባልነታችን ለአስራታችን ታማኝ መሆን አለበን፡፡ ካለን ገንዘብ ለወንጌል አገልግሎት መስጠት
በረከት ከመሆኑም ባሻገር እኛ በምንሰጠው ገንዘብ የእግዚአብሔር መንግስት ወንጌል ይሰፋል፣ ድሆች ይረዳሉ፣ መማር
የማይችሉ መማር ይችላሉ፡፡ እንደ አባልነታችንም የሰጠነው ገንዘብ ምን ላይ እንደዋለ የማወቅ መብት አለን፡፡ ቤተ
ክርስቲያንም በአመት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ለአባላቶቿ ሪፖርት ማድረግ አለባት፡፡

ወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የክለሳ ጥያቄዎች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. –––––– ወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለኃይማኖት ተግባር ብቻ እንድትውል ተቋቁማለች፡፡ ስለሆነም ትርፍ አልባ ከፖለቲካ ነፃ
የሆነች ናት፡፡
2. –––––– የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው፡፡
3. –––––– ከሌላ ቤተ እምነት በተለያየ ምክንያት የሚወጡ ክርስቲያኖች በወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አባል መሆን በፍጹም
አይችሉም፡፡
4. –––––– የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አባላት በግላቸው በፖለቲካ ውስጥ የሚያደርጉት ማንኛውም ተሳትፎ ቤተክርስቲያንን
አይወክልም፡፡
5. –––––– ማንኛውም አባል ቤተ ክርስቲያኒቱ የተቋቋመችበትን ዓላማ በግልጽ ተቃርኖ ወይም የቤተ ክርስቲያኒቱን
ህልውና በሚያሰጋ መልኩ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ በአባልነት መብቶች መጠቀም አይችልም፡፡

101
ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

ሀ ለ
6. መስቀሉ ሀ/ ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን የከፈለው መስዋዕትነት
7. መጽሐፍ ቅዱሱ ለ/ በደስታ/ሐዘን ጊዜ የእርዳታና የድጋፍ አገልግሎት
8. የእሳት ነበልባሉ ሐ/ እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ
9. የዓለም ካርታ /ሉል/ መ/ ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ትውልድ
10. በወንጌል መጽናናትና መረዳዳት ሕብረት ሠ/ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማድረስ ተልእኮ
ረ/ አማኞች ደቀመዝሙር ማድረግ
ሰ/ የመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ሥጦታዎች

ትክክለኛን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ/ የደህንነትን ወንጌል መስበክና አማኞች ደቀመዝሙር ማድረግ፡፡

ለ/ ቤተ ክርስቲያኗ የፖለቲካ ዘመቻ ለሚያደርጉ ግለሰቦች ድጋፍ መስጠት፡፡

ሐ/ ከክርስቲያኖች ጋር መለኮታዊ ስርዓትንና አባታዊ ግንኙነትን መፍጠር፡፡

መ/ በሕጻናት፣ በወጣቶች፣ በአረጋውያን፣ መበለትና እና ሌሎች ዙሪያ ምግባረ ሰናይ አገልግሎት መስጠት፡፡
12. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የራዕይ መግለጫ ምንድን ነው?
ሀ/ ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ትውልድ ማስነሳት፡፡
ለ/ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ ትውልድ ማስነሳት፡፡
ሐ/ መለኰታዊ ሥርዓትን የሚያራምድ ትውልድ ማስነሳት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
13. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የተቋቋመችበት ዓላማዎች ምንድን ናቸው?
ሀ/ የእግዚአብሔርን ቃል በሙላት መስበክና ማስተማር፡፡
ለ/ አገልግሎት የተጠሩ ሰዎች አገልግሎታቸውን በሙላት እንዲሰጡ ማበረታታት፡፡
ሐ/ በሥነ ምግባር የታነጸ ብቁ ዜጋ ማፍራት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
14. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ተግባር መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የሀገሪቱን ሕግና የፖለቲካ ይዘት የሚተች ወይም ሊያዛባ የሚችል ጽሑፍ ማሰራጨት፡፡
ለ/ ጽሑፍ፣ ጀማ ስብከት፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ኦዲዮ ቪዲዮ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት ማሳተምና ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በመጠቀም
ወንጌልን ማሰራጨት፡፡
ሐ/ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም የአገልግሎት ጥሪ ያላቸውን ለወንጌል ሥራ ማሰልጠን፡፡
102
መ/ የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም ወንጌልን ማሰራጨትና ማስተማር፡፡
15. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ከአባላት ግዴታ መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የቤተ ክርስቲያኒቱን ራዕይ፣ የእምነት አንቀጽና አስተምህሮ መቀበልና መተግበር ይኖርበታል፡፡
ለ/ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠ ትምህርት መጽናት፣ ከሀሰተኛ አሠራር መጠበቅ አለበት፡፡
ሐ/ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስብሰባዎች መካፈልና ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ አለበት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
16. የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን በወንጌል መጽናናትና መረዳዳት ሕብረት ዓላማው ምንድን ነው?
ሀ/ የቤተክርስቲያንን አባላት ደቀመዝሙር ትምህርት ማስተማር፡፡
ለ/ የተለያዩ የወንጌል ስርጭት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፡፡
ሐ/ ክርስቲያኖች በግልም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታቸው፤ ደስታም ሆነ ሐዘን ሲያጋጥማቸው ወንጌልን ማዕከል ያደረገ የእርዳታና
የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
17. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የገቢ ምንጭ ምንድን ነው?
ሀ/ አስራት፡፡
ለ/ መባ፡፡
ሐ/ ከተለያዩ ስጦታዎችና ዕርዳታዎች ነው፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
18. የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን (ክህነት) በተመለከተ የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛው ትምህርት
የቱ ነው?
ሀ/ የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የሐዋሪያነት፣ የነቢይነት፣ አስተማሪነት፣ የወንጌላዊ እና የመጋቢነት ፀጋ ትቀበላለች፡፡
ለ/ አገልጋይ ሹመት ከመቀበሉ በፊት የጥሪውን እውነተኛነት፣ ስጦታውና ችሎታው በቤተ ክርስቲያኗ የሽማግሌዎች ጉባዔ መሪዎች ሁሉ
ሊታመንበት ይገባል፡፡
ሐ/ አገልጋዩ ሹመት ለመቀበል ግለሰቡ መለኰታዊ ጥሪ እንዳለው ከምዕመኑ ሦስት አራተኛው እንዲያምንበት ያስፈልጋል፡፡
መ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ
19. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በተመለከተ በክፍል ውስጥ የተማራችሁትን ግለጹ?
20. የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ከእምነት መግለጫ ውስጥ አራቱን በዝርዝር ግለጹ? (ለምሳሌ፡- መጽሐፍ
ቅዱስ፣ ደኅንነት (አዲስ ፍጥረት)፣ የጌታ እራት)

103
ዋቢ መጻሕፍት
 መለሰ ወጉ (ዶ/ር) ፤ መስቀል አልባ ክርስትና፡፡ አዲስ አበባ፡- ፋር ኢስት ትሪዲንግ፣ 2007 ዓ.ም፡፡

 መርዓዊ ንጉሴ (መጋቢ) ፤ ለላቀ የሕይወት ስርዓት ከጌታ ዘንድ የተለቀቀ ቱንቢ፡፡ አዲስ አበባ፡- አሳታሚው

አልተጠቀሰም፣ 1998 ዓ.ም፡፡

 መልሳቸው መስፍን (ዶ/ር) ፤ ቤተ ክርስቲያን፡፡ አዲስ አበበ፡- አንድነት አታሚዎች፣ 2007 ዓ.ም፡፡

 ሙላቱ በላይነህ (ዶ/ር) ፤ የአገልግሎት ተግዳሮትና መፍትሔዎቻቸው፡፡ አዲስ አበባ፡- አሳታሚው አልተጠቀሰም፣ 2009

ዓ.ም፡፡

 ሰለሞን አበበ ገብረ መድኅን ፤ የደነበረው በቅሎ፡፡ አዲስ አበባ፡- ርኆቦት አታሚዎች፣ 2007 ዓ.ም፡፡

 ሳሙኤል ሳላቶ (መጋቢ)፤ መሰረታዊ ክርስትና አጠቃላይ አስተምህሮ፡፡ አዲስ አበባ፡- እሌኒ ማ.ቤ.ኃ.የተ.የግ..ማ፣ 2009

ዓ.ም፡፡

 ሳሙኤል ሳላቶ (መጋቢ) ፤ ታላቅ ብድራት ያለው ሕይወትና አገልግሎት፡፡ አዲስ አበባ፡- እሌኒ ማ. ቤ.ኃ የተ የግ.ማ.፣

2009 ዓ.ም፡፡

 ሽመልስ ረጋ (ተርጓሚ) ፤ ይህች ዓለም ምን ትሆናለች?፡፡ አዲስ አበባ፡- አሳታሚው አልተጠቀሰም፣ 1998 ዓ.ም፡፡

 በልሁ ደለለኝ (መምህር) ፤ ደቀመዝሙር፡፡ አዲስ አበባ፡- ሶላር ማተሚያ ቤት፣ 2006 ዓ.ም፡፡

 በልሁ ደለለኝ (መምህር) ፤ ደቀ መዝሙርና የተልዕኮ ሕይወት፡፡ አዲስ አበባ፡- ሶላር ማተሚያ ቤት፣ 2006 ዓ.ም፡፡

 ቢኒያም በፈቃዱ (መጋቢ) ፤ ለመከሩ ሰራተኞች፡፡ አዲስ አበባ፡- ሰለሊአም፣ 2016 ዓ.ም፡፡

 ቤንናያ እና ሙሳ ሲይ ፤ እናንተም በረከት ትሆናላችሁ፡፡ አሳታሚው አልተጠቀሰም፣ 2001 ዓ.ም፡፡


104
 ተስፋ በዳሳ (ዶ/ር) ፤ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት፡፡ አዲስ አበባ፡- ባርኮት አታሚዎች፣ 2006 ዓ.ም፡፡

 ተስፋ ወርቅነህ (ዶ/ር) ፤ የስብከተ አዘገጃጀትና አቀራረብ፡፡ ቴክሳስ፡- የኢትዮጵያ አቀራረብ ክርስቲያኖች ሕብረት ቤተ

ክርስቲያን፣ 2007 ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ መስፍን፤ ሂዱና ደቀ መዝሙርት አድርጓቸው፡፡ አዲስ አበባ፡- ኤስ.አይ.ኤም፣ 2009 ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ ሮበሌ፤ የትምህርተ ስላሴ መሰረታውያን፡- መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ምክንዮአዊ ትነታኔ፡፡ አትላንታ

ጆርጂያ፡- ተስፋ ዐቃብያን ማህበር፣ 2010 ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ ሮበሌ እና ምንሊክ አስፋው ፤ በእምነት መኖር፡፡ አዲስ አበባ፡- ተስፋ ዐቃብያን ማህበር፣ 2010 ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ ሮበሌ ፤ ከእምነት እንቅስቃሴ መምህራን ትምህርት ተጠበቁ፡፡ ሚሽገን፡- ተስፋ ዐቃብያን ማህበር፣ 2011

ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ ሮበሌ ፤ የእምነት ወይስ የክህደት እንቅስቃሴ? አትላንታ፣ ጆርጅያ ፡- ተስፋ ዐቃብያነ ክርስትና ማህበር፣ 2016

ዓ.ም፡፡

 ተስፋዬ ሮበሌ ፤ ዶክትሪን አስፈላጊ ነውን?

 ተኩ ከበደ (መጋቢ) ፤ የቅዱሳን በአየር መነጠቅ፡፡ አዲስ አበባ፡- ፋር ኢስት ትሬዲንግ፣ 2005 ዓ.ም፡፡

 ተካልኝ ነጋ (ዶ/ር) ፤ የጸሎት-የንግድ ቤት? አዲስ አበባ፡- ርኆቦት አታሚዎች፣ 2010 ዓ.ም፡፡

 ታምሩ ዘለቀ ፤ የትንቢት መንፈስ፡፡ አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን፣ 1985 ዓ.ም፡፡

 ኃይሉ ቸርነት (ዶ/ር) ፤ ደቀመዝሙር፡፡ 2003 ዓ.ም፡፡

 አበራ አባይ (ዶ/ር) ፤ የቤተ ክርስቲያን ተከላና እድገት፡፡ አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነመለኮት ሴሚናሪ፣

2008 ዓ.ም፡፡

 አቤንኤዘር ተክሉ (ዲያቆን) ፤ የእምነት እንቅስቃሴ፡- የዛሬይቱ ቤተክርስቲያን ፈተና፡፡ አታሚው አልተገለጸም፣ 2010

ዓ.ም፡፡

 ኢያሱ ፈረንጅ (ዶ/ር) ፤ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፡፡ አዲስ አበባ፡- ሮሆቦት አታሚዎች፣ 2007 ዓ.ም፡፡

 አድያምሰገድ ወልደማርያም ፤ መሰረተ አስተምህሮ፡፡ ምኮሎራዶ፡- አሳታሚው አልተጠቀሰም፣ 2009 ዓ.ም፡፡

 አድያምሰገድ ወልደማርያም ፤ የኤፌሶን መጽሐፍ ጥናት፡፡ አዲስ አበባ፡- ማንኩሳ ማተሚያ፣ 2011 ዓ.ም፡፡

 ዘለቀ በኃይሉ ፤ የብልጽግና ወንጌል ወደ ገሃነም የሚመራ የተለየ ወንጌል፡፡ አዲስ አበባ፡- ማተሚያ፣ 2012 ዓ.ም፡፡

 ዘሪሁን ታከለ ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አጠቃቀም፡፡ ያልታተመ፣ 2005 ዓ.ም፡፡
105
 የተሐድሶ ጥሪ (መመርመር-መመለስ-መታደስ) ፤ አዲስ አበባ፡- 2007 ዓ.ም፡፡

 የወንጌል ስርጭትና መንፈሳዊ መነቃቃት፡፡ አዲስ አበባ፡- የኢተዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን፣ 1985

ዓ.ም፡፡

 ዳንኤል መኰንን (መጋቢ) ፤ የክርስትና እድገት (ክፍል አንድ እና ሁሉት)፡፡ አዲስ አበባ፡- አሳታሚ አልተጠቀሰም፣ 1997

ዓ.ም፡፡

 ዳንኤል መኰንን (መጋቢ) ፤ ደቀ መዝሙርነት፡፡ አዲስ አበባ፡- ሊቶ ማተሚያ ቤት፣ 1990 ዓ.ም፡፡

 ገብሩ ወልዱ ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው፡፡ አዲስ አበባ፡- አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ 1987 ዓ.ም፡፡

 ጋዲሳ አዱኛ ፤ የመጨረሻ ዘመን፡፡ አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ሴሚናሪየም፣ 2008 ዓ.ም፡፡

 ፀጋዬ አበበ፤ የብሉይ ኪዳን አሰሳ፡፡ አዲስ አበባ፡- አሌሉያ አታሚዎች፣ 2001 ዓ.ም፡፡

 21 ቀን ሀገር አቀፍ የጾምና ጸሎት ወቅት የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች፡፡ በኢትዮጵያ ኒው ሚሊኒየም 2000 ፕሬየር ቼይን

የተዘጋጀ፣ 2006 ዓ.ም፡፡

 መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ 1954 ዓ.ም፡፡

 መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ቀላል አማርኛ፤ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፣ 1980 ዓ.ም፡፡

 https://tgstat.com/channel/@tehadso/58

 https://www.facebook.com/643433682339861/photos/1592680944081792

 https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%8C%E1%88%8D

የዘመናችን የስህተት ትምህርቶችና ልምምዶች የግርጌ ማስታወሻ (footnote)

1. የእምነቱ ዋና አደራጅ የኾኑትም ኬኔት ሔጌንም እንዲህ ይላሉ፦ “ Man is a Spirit who possesses a soul and lives
in a body.” (Hagin,Kenneth E.; “Man on Three Dimension” Vol. 1 of the spirit, soul and body series
18th printing; Tulsa; Kenneth Hagin Ministries; 1994. pp. 8.
2. opeland, Following the Faith of Abraham, 1989, Tape #01-3001
3. Copeland, The Force of Love, 1987, Tape #02-0028.
4. Kenneth Copeland, "Believer's Voice of Victory" broadcast on TBN, recorded 7/9/87
5. Now we are in christ Jesus; 1980, fort worth : KCP publications, pp. 16-17
6. The End Time Manifestation of the Sons of God, Audio Tape 1, Sides 1 & 2).
7. Zoe: The God Kind of Life, pp. 35-36, 41.
8. Hank Hanegraff, Christianity in Crisis, pp. 116
9. Paul Crouch, “Praise the Lord” broadcast on TBN, recorded 7/7/86

106
10. Benny Hinn, Trinity Broadcasting Network, 1 November 1990 እና Our Position In Christ", Tape #
A031190 -1.
11. Charles Lee Feinberg, The Image of God; July 1972; by Dallas Theological Seminary. pp. 237
12. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 29
13. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 148
14. Charles Lee Feinberg, The Image of God; July 1972 by Dallas Theological Seminary. pp.237
15. Kenyon, Hidden man, pp. 47
16. ኢሴክ ደብሊው ኬንዮን፤ New creation Realities (የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች)፤ ዓ.ም እና አሳታሚው

ያልተጠቀሰ፤
17. Frederick K. C. Price, "Identification #3" (Inglewood, CA: Ever Increasing Faith Ministries, 1980),
audio tape #FP545, side 1.
18. Kenneth Copeland, What Happened From the Cross to the Throne, (Fort Worth, TX: Kenneth

Copeland Ministries, 1990) audiotape #02-0017 side 2 tape.ወይም በአማራጭነት ይህንን ሊንክ በመጫን

ይህንኑ ትምህርት ማስተማሩን መመልከት ይቻላል፤


http://www.kcm.org/studycenter/articles/seasonal/power_of_resurrection.html.
http://www.creflodollarministries.org/public/bible/article.aspx?id=18, retrieved 10 september 2008.
እንዲሁም Benny Hinn, Our Position In Christ, Part 1 (Orlando, FL: Orlando Christian Center, 1991),
videotape#TV-254.
19. Covenant of Blood; 1987; Kenneth Copeland Publications Fort Worth; እና What Satan Saw on the
Day of Pentecost; February 1983 በሚለው ስብከቱም ይደግመዋል።
20. Kenneth Hagin, The Name of Jesus,(1979) PP. 29-30.
21. Charles Capps, Authority In Three Worlds, pp. 212-213.
22. Kenyon, E.W. 1999. The Bible in the Light of our Redemption: Basic Bible Course. Lynnwood, WA:
Kenyon’s Gospel Publishing Society. pp.303
23. Kenneth E. Hagin, The Name of Jesus, (1979),pp. 31. ቤን ሂንም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ አስተምህሮ አለው፤
Benny Hinn TBN December 15, 1990.
24. Kenneth Copeland, Believer's Voice of Victory (television program), TBN, 21 April 1991.
25. Kenneth E. Hagin, The Name of Jesus, (1979), pp. 29.
26. ኢሴክ ደብሊው ኬንዮን፤ New creation Realities (የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች)፤ ዓ.ም እና አሳታሚው
ያልተጠቀሰ፤ ገጽ 196፣ 200 እና 204።
27. Kenneth copeland “Jesus –our Lord of Glory; Beliver’s voice of victory, April 1983, p. 3
28. John Piper, The Passion of Jesus Christ: Fifty Reasons Why He Came to Die (Wheaton: Crossway,
2004).
29. Kenneth Copeland, God's Miracle Plan for Man, p. 36.
30. ተካልኝ ነጋ፤ የጸሎት ንግድ ቤት - ጆሴፍ ፕሪንስ የተናገረውን ጠቅሶ እንደ ጻፈው ገጽ 213።
107
31. Kenneth E. Hagin, Authority of the Believer, Tulsa: Kenneth Hagin Ministries, 1967. ትርጉም፦ ፀሐይ
ታደሰ(ፓስተር)፤ 1996 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት። ገጽ 50፤ ክሬፍሎ ዶላርም በተመሳሳይ መንገድ
“ምርጥ ምርጡ ለእኛ ነው” ይለናል፤ (Maximizing Your God Given Potential", May 18, 2003)
32. Kenneth Copeland, Prosperity: The Choice Is Yours, 4
33. John Avanzini, "Was Jesus Poor?" Believer's Voice of Victory, July/August 1991, 6-7; cf. Believer's
Voice of Victory (tv program), TBN, 20 January 1991, and Praise the Lord, TBN, 1 August 1989.
እንዲሁም ክሬፍሎ ዶላርም ተመሳሳይ ትምህርት አለው፤ (Creflo Dollar Crusad e, February 9, 1999).
34. (Was Jesus rich? - Swanky messiah not far-fetched in Prosperity Gospel by JOHN BLAKE, The
Atlanta Journal-Constitution, Published on: 10/22/06.) 

35. ግርማዊ፤ የብልጽግና ወንጌል፤ ገጽ 78-80። ከዚህም ባሻገር ኦራል ሮበርትስ፣ ኬነት ሄገንና ክሬፍሎ ዶላር “ጌታ ኢየሱስና
ሐዋርያት የነጠጡ ሃብታም ነበሩ” ብለው በግልጥ ያስተምራሉ።
36. ኢሴክ ደብሊው ኬንዮን፤ New creation Realities (የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች)፤ ዓ.ም እና አሳታሚው
ያልተጠቀሰ፤ ገጽ 161
37. የኬኔት ኮፕላንድ “የስኬት ፎርምላዎች”፤ ግርማዊ፤ የብልጥግና ወንጌል።ገጽ 82፤ መቶ እጥፍ ስለ ማግኘት
የሚቀርበውን የፈጠራ ወሬ (hundredfold hoax) ጆን ኢቫንዚኒን “የሚተካከለው” ያለ አይመስልም፤ (John
Avanzini, Praise-a-Thon, TBN, 5 November 1990.)
38. Charismatic Chaos, pp. 285.
39. Benny Hinn; TBN, November 6, 1990
40. ኢሴክ ደብሊው ኬንዮን፤ New creation Realities (የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች)፤ ዓ.ም እና አሳታሚው
ያልተጠቀሰ፤ ገጽ 31
41. ዝኒ ከማኹ ገጽ 116-117
42. ቤን ሂን እንደ ጂም ቤከር ተመልሻለኹ ካለና ወደ እምነት እንቅስቃሴ ትምህርት ከተመለሰ በኋላ ከተናገረው ስብከቱ
የተወሰደ።
43. ኢሴክ ደብሊው ኬንዮን፤ New creation Realities (የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች)፤ ዓ.ም እና አሳታሚው
ያልተጠቀሰ፤ ገጽ 121
44. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ገጽ 104-105
45. ሕንጸት፤ ሰሎሞን አበበ (“መለኮታዊ ፈውስ” በማለት ከጻፈው ርእስ)፤ ታኅሳስ 2010 ቁ.10፤ አዲስ አበባ፤ ርኆቦት
አታሚዎች።ገጽ 6

108
የደቀመዝሙር የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

6. እውነት
7. ሐሰት
8. ሐሰት
9. እውነት
10. እውነት

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. ሠ
7. ረ
8. ሀ
9. ለ
10. ሰ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

109
11. ለ
12. ለ
13. መ
14. መ
15. ሀ
16. መ
17. ሐ
18. መ

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19.
ቀንበር ለመሸከም ተጠርቷል፣ መስቀል ለመሸከም ተጠርቷል፣ ሁሉን ትቶ ኢየሱስን ለመከተል ተጠርቷል፣ ራስን
ለማዋረድ ተጠርቷል፣ ለመታዘዝ ተጠርቷል፣ ለመመስከር ተጠርቷል
20.
ሀ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ ኢየሱስ ማእከልነት፣ ሉዐላዊነትና ልይትነት በግልጽ የሚታይበት ነው፡፡

ለ/ የመስቀሉን ማእከልነት ቸል የማይባልበት፤ ይልቁን የመስቀሉን ትሩፋትና የመስቀሉ መንገድ በግልጽ የሚታወጅበትና የሚኖርበት

ነው፡፡

ሐ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና ውጭ የተጠናከረ የግል፣ የቤተሰብና የህብረት የጾም ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ፕሮግራሞች የሚደረጉበት ነው፡፡

መ/ ለቃሉ ስልጣን ያለ ምንም ድርድር የሚገዛ፤ ማንኛውንም ስብከት፣ ትምህርት፣ ትንቢት፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ልምምዶች

በቃሉ ለመፈተሽ/ለማስፈተሽ የሚተጋ፤ ቃሉን በአግባቡ ለመፍታትና ለመተርጐም የሚጠነቀቅ ምዕመን እና አገልጋይ

የሚታይበት ነው፡፡

ሠ/ የአማኞችን ሁሉ ክህነት የሚታይበት፣ እያንዳንዱ ምእመን አስፈላጊነቱ ግልጽ የሆነበትና ሁሉም የሚሳተፍበት፣ ሁሉም

ምዕመን በእኩል አይን የሚታይበትና እያንዳንዱ አማኝ ከሌላው አማኝ ጋር የተጠናከረ፣ የተያያዘ እና በአንድነት አብሮ የሚሰራ

ነው፡፡

ረ/ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘና ሚዛናዊ የሆነ የፀጋ ስጦታ አገልግሎትን ተግባራዊ የሚደረግበት ነው፡፡

110
ሰ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እኩል የመንፍስ ፍሬ ጎልቶና ተዘውትሮ የሚታይበት ነው፡፡

ሸ/ የቤተ ክርስቲያን ዋና ተልእኮ በሆነው ሰዎችን ወደ ጌታ ኢየሱስ በማምጣት፣ ደቀ መዝሙር በማድረግ እና ተተኪ አገልጋይ

በማፍራት ላይ አጥብቃ የምትሰራ ናት፡፡

ቀ/ መሪዎች ገንዘብ ስለሚሰጡ፣ ወይም ብዙ ደጋፊና ወገን ስላላቸው፣ ወይም የተማሩ እና የታወቁ ስለሆኑ ብቻ

የማይመረጡበት እንደ ቃሉ ተመዝነውና የሕይወት ጥራት መስፈርቶችን ያሟሉ መሪዎች የሚታዩበት ነው፡፡

የምስክርነት ሕይወት (ወንጌል ስርጭት) የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. ሐሰት
2. ሐሰት
3. እውነት
4. እውነት
5. እውነት

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. መ
7. ሠ
8. ለ
9. ሀ
10. ሰ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. መ

111
12. መ
13. መ
14. ሐ
15. መ
16. ሀ
17. ለ
18. መ

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. የመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ ፀሎት፣ የእግዚአብሔር ቃል፣ አንድነት

20. ቸልተኝነት፣ የእውቀት ማነስ፣ የጠላት ተግዳሮት፣ ፍርሃት

112
የዘመናችን የስህተት ትምህርቶችና ልምምዶች የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. እውነት
2. ሐሰት
3. ሐሰት
4. ሐሰት
5. እውነት

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. መ
7. ሀ
8. ረ
9. ለ
10. ሠ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. መ
12. ለ
13. ሐ
14. መ
15. ሐ
16. መ
113
17. ሀ
18. መ

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19.

1. ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል፣ 2. ነገረ ድኅነት (ድነት)፣ 3. ብልጽግና፣ 4. በሽታ እና ፈውስ፣ 5.
እምነት በተመለከተ የልዩ ወንጌል ትምህርቱም ሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትምህርት የመለሱትን ከኖቱ ጋር በማነጻጸር ይታረም፡፡
20.

ሀ/ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መንጋውን የመጠበቅ ኃላፊነት ይወጡ፡፡ (ሐዋ. 20*29፤ ኤፌ. 5*11፤ ፊልጵ. 3*17፤ 2 ተሰ. 2*3-
12፤ 1 ጢሞ. 4*1-6፤ 2 ጢሞ. 4*3-5፤ 2 ጴጥ. 2*1-2፤ 3*3-13፤ ይሁዳ 1*20-21፤ ራዕይ 2*3)

ለ/ ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ/ዶክትሪን ለምዕመኖቿ ማስተማር አለባት፡፡ (ማቴ. 22*23-33፤
ሮሜ 12*3፤ 1 ጢሞ. 4*1-6፤ 2 ጢሞ. 4*3-5፤ ቲቶ 1*9-11)

ለ/ የሐሰት ትምህርትን በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛን እንመዝን፡፡ (ዘዳ. 13*1-5፤ 18*20-22፤ ሐዋ. 17*11፤ 2 ጴጥ. 2*1፤ 1 ዮሐ.
4*1፤ ይሁዳ 1*17)

ሐ/ የተሳሳተ ስነ አፈታት የሐሰት ትምህርት መሰረት መሆኑን እንገንዘብ፡፡ (1 ጢሞ. 1*9-11፤ 4*6፤ 2 ጢሞ. 1*13፤ 2*15፤
4*3፣ ቲቶ 1*9፤ 2*1)

መ/ ከልዩ ወንጌል ጀርባ ያሉት ሀሰተኛ ወንድሞች ብቻ ሳይሆኑ ሰይጣንም ጭምር ስለሆነ በጸሎት ስራውን ማፍረስ አለብን፡፡
(ኤፌ. 6*12፤ 1 ጢሞ. 4*1-2፤ 2 ጢሞ. 2*25-26፤ ያዕ. 4*7)

114
የመጨረሻው ዘመን የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. እውነት
2. ሐሰት
3. እውነት
4. እውነት
5. ሐሰት

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. ሐ
7. ሀ
8. መ
9. ረ
10. ለ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. ሀ
12. ለ
13. መ
14. ሐ
15. ለ
16. መ
17. ሐ
18. ሀ

115
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19.
ስለ (ሞት፣ የመካከለኛው ማንነት (ስርዓት)፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መመለስ (ምጽዓት)፣ ንጥቀት፣ ታላቁ መከራ፣
ትንሣኤ፣ የሺህ ዓመት መንግስት፣ የመጨረሻው ፍርድ፣ ዘላለማዊ ኹነት) የመለሱትን ከኖቱ ጋር በማነጻጸር ይታረም፡፡
20.
የምልክቶቹ አገልግሎት
 አማኞች የጌታ የኢየሱስ ዳግም ምጽዓት እንደደረሰ አውቀው በመዘጋጀት እንዲኖሩ፡፡ (ማቴ. 24*32-33፤
25*1-13)
 አማኞች በጌታ ስራ በመጠመድ እንዲኖሩ፡፡ (ማቴ. 24*45-51)
 አማኞች በጸሎት በመትጋት እንዲኖሩ፡፡ (ሉቃ. 21*36)
 አማኞች ሊሆኑ ካሉት መጥፎ ነገር እራሳቸውን በመጠበቅ እንዲኖሩ፡፡ (2 ጢሞ. 3*10-14፤ 1 ጴጥ. 4*7-11)

የመለኮታዊ ስርዓት የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ


116
1. እውነት
2. ሐሰት
3. ሐሰት
4. እውነት
5. እውነት

ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. መ
7. ሀ
8. ሰ
9. ሠ
10. ሐ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. ለ
12. መ
13. ሀ
14. መ
15. ሐ
16. መ
17. መ
18. መ

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19.
የመለኮታዊ ስርዓት ፅንስ ሀሳብ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን በስፋት ተገልጾ እናገኛለን፡፡ ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ
ኪዳን የመለሱትን ከኖቱ ጋር በማነጻጸር ይታረም፡፡
117
20.
መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቤተክርስትያን ቅጣት አላማ ፡-
 ሀጢያት የሰራን ክርስቲያን ከክፉ መንገዱ በንስሐ እንዲመለስ ለማድረግ ነው፡፡ (ማቴ. 18*15)
 የማይታዘዘውን ለማሳፈር ነው፡፡ (2 ተሰ. 3*14)
 ወደ ሌሎች ቅዱሳን እንዳይዛመት እና ሌሎችም በተመሳሳይ ኃጢአት እንዳይኖሩ ለማስጠንቀቅ ነው፡፡
(1 ቆሮ. 5*6፤ ገላ. 5*8፤ 1 ጢሞ. 5*20)
 በመጨረሻ ቤተክርስትያን ሀጥያትን ካልቀጣች የጌታ ስም በአህዛብ ፊት ይሰደባል፡፡

የወንጌል ብርሃን ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የክለሳ ጥያቄዎች መልሶች

እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ

1. እውነት
2. እውነት
3. ሐሰት
4. እውነት
5. እውነት
118
ከ “ሀ” ወገን ለሆኑት ትክክለኛውን መልስ ከ “ለ” ወገን ፈልጉ

6. ሀ
7. ሐ
8. ሰ
9. ሠ
10. ለ

ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ

11. ለ
12. መ
13. መ
14. ሀ
15. መ
16. ሐ
17. መ
18. መ

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ

19. የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በተመለከተ የመለሱትን ከኖቱ ጋር በማነጻጸር ይታረም፡፡

20. የወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ በተመለከተ የመለሱትን ከኖቱ ጋር በማነጻጸር ይታረም፡፡

119

You might also like