You are on page 1of 4

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

አማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው?


ሀ.እግዚአብሔር ብርሃን ነው
ለ.እግዚአብሔር ፍቅር ነው
#ሐ.እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው
መ.እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው
እንሆ፥ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ዅሉ
ኾኗል፥ትርጓሜውም፦እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ የሚል ነው።
የማቴዎስ ወንጌልን (1,;;,23 )
የነብያት ትንቢት ፍጻሜ የሆነውን ጌታችንን ሳያይ ሞትን እንደማይቀምስ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ የነበረ ሰው ማን ነው?
ሀ.ቀነናዊው ስምዖን
ለ.ስምዖን ጴጥሮስ
#ሐ.አረጋዊው ስምዖን
መ.ሲሞን መሥርይ(መሠርይ)
እንሆም፥በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፥ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር ጻድቅና ትጉህም
ነበረ፥መንፈስ ቅዱስም በርሱ ላይ ነበረ።
በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።
በመንፈስም ወደ መቅደስ ወጣ ወላጆቹም እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ፥
ርሱ ደግሞ ተቀብሎ ዐቀፈው እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ።
ጌታ ሆይ፥አኹን እንደ ቃልኽ ባሪያኽን በሰላም ታሰናብተዋለኽ
ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤
ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።
#የሉቃስ_ወንጌል (2,;; 26_ 32)
የሰውነት መብራት የሚባለው የአካል ክፍል የትኛው ነው?
ሀ.ልብ
ለ.ልቦና
#ሐ.ዓይን
መ.አዕምሮ
የሰውነት መብራት ዐይን ናት።ዐይንኽ እንግዲህ ጤናማ ብትኾን፥ሰውነትኽ ዅሉ ብሩህ ይኾናል
ዐይንኽ ግን ታማሚ ብትኾን፥ሰውነትኽ ዅሉ የጨለመ ይኾናል።እንግዲህ ባንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከኾነ፥ጨለማውስ እንዴት
ይበረታ!
የማቴዎስ ወንጌል 6÷ 22_23
ከሚከተሉት አባባሎች መካከል በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረው የትኛው ነው?
ሀ.«ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ»
ለ.«ስለ እኔና ስለወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል»
ሐ.«የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና»
#መ.ሁሉም መልስ ይሆናሉ
«ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቷል፡ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል»ያለው ማን ነው?
ሀ.ፊሊጶስ
ለ.ጲላጦስ
#ሐ.ሄሮድስ
መ.አርኬላዎስ
በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥
ለሎሌዎቹም፦ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው ርሱ ከሙታን ተነሥቷል፥ስለዚህም ኀይል በርሱ ይደረጋል አለ።
ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና
የማቴዎስ ወንጌል( 14÷ 1_3)
«የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም»ያለው ማን ነው?
#ሀ.ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለ.ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ.ልጇ የታመመችባት ከነናዊት ሴት
መ.ይሁዳ
ርሱ ግን መልሶ፦የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገ፟ባ፟ም አለ።
ርሷም፦አዎን ጌታ ሆይ ቡችሎችም እኮ ከጌታዎቻቸው ማእድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦አንቺ ሴት፥እምነትሽ ታላቅ ነው እንደ ወደድሽ ይኹንልሽ አላት።ልጇም ከዚያች ሰዓት ዠምሮ ዳነች።

የማቴዎስ ወንጌል (15÷ 26_28)


ልጆቿ በክርስቶስ ቀኝ እና ግራ እንዲቀመጡላት የለመነችው ማን ናት?
ሀ.የያዕቆብ እና ዮሳዕ እናት
ለ.የጴጥሮስ እና እንድርያስ እናት
#ሐ.የያዕቆብ እና የዮሐንስ እናት
መ .የማርታ እና የማርያም እናት
በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋራ እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ ርሱ ቀረበች።
ርሱም፦ምን ትፈልጊያለሽ፧አላት።ርሷም፦እነዚህ ኹለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝኽ አንዱም በግራኽ በመንግሥትኽ እንዲቀመጡ እዘዝ
አለችው።
የማቴዎስ ወንጌል ።(20÷20 _21)
የጌታችን ደቀመዛሙርት ምን በማድረጋቸው ነው ፈሪሳውያኑ ቀርበው«ደቀመዛሙርትህ እንደ ሽማግሎች ወግ ስለምን
አይሄዱም»ያሉት?
ሀ.ስላልጾሙ
ለ.ሰንበትን ስላላከበሩ
#ሐ.እጆቻቸውን ሳይታጠቡ ስለበሉ
መ.ብሉይ ኪዳን አያስፈልግም ስላሉ
ደቀ መዛሙርትኽ ስለ ምን የሽማግሌዎችን ወግ ይተላለፋሉ፧እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት።
የማቴዎስ ወንጌልን (15÷2)
ወደ ኤማሁስ በሚሄዱበት ጊዜ ሁለት ሐዋርያት ስለምን እየተነጋገሩ ነበር?
#ሀ.ስለ ኢየሰስ ክርስቶስ ማንነት
ለ.ክርስቶስ በምሳ ስላስተማረው ትምህርት
ሐ.ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ እየተመካከሩ
መ.መልስ የለም
ርሱንም የካህናት አለቃዎችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው።
እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው ርሱ እንደ ኾነ ተስፋ አድርገን ነበር ደግሞም ከዚህ ዅሉ ጋራ ይህ ከኾነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን
ነው።
ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን
የሉቃስ ወንጌል (24 ÷20_22
በይሁዳ ምትክ ከዐሥራ አንዱ ጋር የተቆጠረው ሐዋርያ ማን ነው?
ሀ.ማቴዎስ
ለ.ሉቃስ
#ሐ.ማትያስ
መ.ቀለዮጳ
ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋራ ተቈጠረ።
የሐዋርያት ስራ ( 1÷26 )
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረታቦር ተራራ አምላክነቱን በገለጠ ጊዜ የነበሩት ሦስት ደቀመዛሙርት እነማን
ነበሩ?
ሀ.ቅዱስ ጴጥሮስ፣ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ እንድርያስ
ለ.ቅዱስ ፊሊጶስ፣ቅዱስ በርተሎሚዎስ እና ቅዱስ ታዴዎስ
#ሐ.ቅዱስ ጴጥሮስ፣ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ ዮሐንስ
መ.ቅዱስ ናትናኤል፣ቅዱስ ስምዖን እና ቅዱስ ማርቆስ
ከስድስት ቀንም በዃላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
የማቴዎስ ወንጌል ( 17 ;;1)
በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው የሐዲስ ኪዳን ሰማዕት ማን ነው?
#ሀ.ቅዱስ እስጢፋኖስ,
ለ.ቅዱስ ያዕቆብ
ሐ.ቅዱስ ለንጊኖስ
መ.ቅዱስ ጴጥሮስ
እስጢፋኖስም ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።
የሐዋርያት ስራ (6÷8)
ክርስቶስ በተሰቀለበት ዘመን ሊቀ ካህናት የነበረው ማን ነው?
ሀ.ሐና
#ለ.ቀያፋ
ሐ.ሰጲራ
መ.ሐናንያ
በዚያችም ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከነርሱ አንዱ፦እናንተ ምንም አታውቁም
ሕዝቡም ዅሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል (11÷49_50)
በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃዎች የሕዝብም ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥
የማቴዎስ ወንጌል (26÷3)
ከሚከተሉት የቅዱስ ጳውሎስ መልዕካታት ውስት ስለ ካህናት አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልፀው የትኛው ነው?
ሀ.ለቲቶ የተላከው
#ለ.ለጢሞቴዎስ መጀመሪያ የላከው
ሐ.ወደ ኤፌሶን ሰዎች የላከው
መ.ወደ ገላቲያ ሰዎች የላከው
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት ከተማ ማን ናት?
ሀ.ገሊላ
#ለ.ቤተልሔም
ሐ.ናዝሬት
መ.ቃና
ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰዶ፟፦ኺዱ፥ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ ባገኛችኹትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ
አላቸው።
የማቴዎስ ወንጌል (2÷8)
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው---
#ሀ.መንግስተ-ሰማያት የእነርሱ ናትና
ለ.መጽናናትን ያገኛሉና
ሐ.ምድርን ይወርሳሉና
መ.እግዚአብሔርን ያዩታልና
በመንፈስ ድኻዎች የኾኑ ብፁዓን ናቸው፥መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። የማቴዎስ ወንጌል (5÷3)
ነባቤ መለኮት በመባል ሚታወቀው ወንጌላዊ ማን ነው?
ሀ.ቅዱስ ማቴዎስ
ለ.ቅዱስ ማርቆስ
ሐ.ቅዱስ ሉቃስ
#መ.ቅዱስ ዮሐንስ
እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ ------------- መንፈስ አልሰጠንምና
#ሀ.የፍርሃት
ለ.የግብዝነት
ሐ.የሐሰት
መ.የጥላቻ
እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና።
እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ነገር ግን፥እንደእግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል ዐብረኸኝ
መከራን ተቀበል
2 ኛ ጢሞቴዎስ 1÷7_8
አገልጋዩ አናሲሞስን ምሕረት አድርጎ እንዲቀበለው ቅዱስ ጳውሎስ ደብዳቤ የላከለት ሰው ማን ነው?
ሀ.በርናባስ
ለ.ጢሞቴዎስ
#ሐ.ፊሊሞና
መ.ቲቶ
የእምነትኽም ኅብረት፥በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ዅሉ በማወቅ፥ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለኹ
የቅዱሳን ልብ ባንተ ሥራ ስለ ዐረፈ፥ወንድሜ ሆይ፥በፍቅርኽ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቻለኹና።
ስለዚህ፥የሚገ፟ባ፟ውን አዝኽ ዘንድ
በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥
ይልቁንም እንደዚህ የኾንኹ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው፥አኹንም ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስር የኾንኹ፥ስለ ፍቅር እለምናለኹ።

ወደ ፊሊሞና (1÷ 6_9)


ከሚከተሉት ውስጥ ምሳሌያዊነት የሌለው ታሪክ የትኛው ነው?
ሀ.የጠፋው ልጅ
ለ.የቀራጩና የፈሪሳዊው
ሐ.የጠፋው በግ
#መ.የሰማርያዊቷ ሴት

You might also like