You are on page 1of 6

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ነገረ ማርያም
ምዕራፍ አንድ
ነገረ ማርያም ትርጉም
ነገረ ማርያም ከሁለት ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም

ነገር፡- የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የአንድን ትምህርት መገለጫ አጉልቶ የሚያሳይ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ማርያም፡- ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠ ክቡር ስም ነው፡፡

ነገረ ማርያም ሲል በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በኩል ለሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጠውን ሁሉ (እናትነቷ ዘላለማዊ
ድንግልናዋን ንጽህናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷንና ክብሯን) የምንማርበት ትምህርት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ማርያም በሚል መጠሪያ የተጠሩ እመቤታችንን ጨምሮ 8 ያክል ሰዎች ተጠቅሰዋል፡፡ እነርሱም እንደሚከተለው
ተጠቅሰዋል፡፡

1/ ማርያም እህተ ሙሴ፡- ይህች እናት የሙሴ እህት ስትሆን ሙሴ ወደባህር ከተጣለ ጊዜ ጀምሮ እስራኤላውያን የኤርትራን ባህር እስከ
ተሻገሩበት ጊዜ ድረስ ብሎም እስከ ቃዴስ በረሐ የተጓዘች በኋላም በቃዴስ በረሐ ያረፈች እናት ናት፡፡

• ዘፀ 2፣4-8 እህቱም የሚደረግበትን ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐበኘው ነበር፡፡


• ዘፀ 15፣20-21 ነብዩቱ ማርያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፣ ዘፀ 12፣1-15 በለምጽ ስለመመታቷ
• ዘፀ 20፣1 ማርያምም በዚያ ሞተች በዚያም ተቀበረች፡፡፣ ዘዳ 24፣9

2/ ማርያም እህተ አልአዛር፡- ማርያም እንተ እፍረት ትባላለች ጌታን የናርዶስ ሽቱ ቀብታዋለችና ዮሐ 12፣1-3፣ ዮሐ 11፣1 ከጌታ እግር ስር
ተቀምጣ የሚያስተምረውን ቃል በመስማቷ ጌታችን መልካም እድልን መርጣለች ብሏታል፡፡ ሉቃ 1 ዐ፣39-42

3/ መግደላዊት ማርያም፡- ጌታችን ሰባት አጋንንት ያወጣላት ናት፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ወቅት በመስቀሉ አጠገብ ነበረች፡፡ ሉቃ 8፣43 ፣
ማቴ 27፣55-56፣ ዮሐ 19፣25 ከሁሉ አስቀድማ የክርስቶስን ትንሳኤ ለማየት ታድላለች ማር 16፣9

4/ የእዝራ ልጅ የዬቴር ልጅ ማርያም፡- ከስሟ በስተቀር የተጠቀሰ ታሪክ የላትም 1 ኛ ዜና 4፣17

5/ የቀለዮጵያ ሚስት ማርያም፡- የታናሹ የያዕቆብና የዮሳ የዮዳም የስምኦንም እናተ ናት፡፡ ማር 15፣40 ወንጌላዊው ማቴዎስ ሁለተኛይቱ
ማርያም ብሎ ይጠራታል፡፡ ማቴ 27፣61 ማቴ 28፣1 አንዳንዴ ከአራቱ ልጆች በአንዱ እናትነት ትጠራለች ማር 15፣47 ፣ማር 16፣1 ሉቃ
24፣10 የእመቤታችን ዘመድ ናት ማር 6፣3 ዮሐ 19፣25

6/ የማርቆስ እናት ማርያም፡- የወንጌላዊው ማርቆስ እናት ናት ሐዋ 12፣12፡፡እርም የሐዋርያው የበርናባስ ወንድም ሚስት ናት ማለትም
በርናባስ የማርቆስ አጐት ነው ቆላ 4፣10፡፡ ጽርሀ ጽዮን/የፅዮን አዳራሽ/ተብላ የምትጠራው ለሐዋርያት ፀጋ መንፈስ ቅዱስ የወረደው በዚህች
እናት ቤት ነው ሐዋ 12፣12 ሐዋ 20፣19-26 1፣12

7/ ማርያም ባዎፍልያ፡- ይህች የዘብድዮስ ሚስት የሁለቱ ሐዋርያት የያዕቆብና የዮሐንስ እናት ናት፡፡ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው
ወደ ክርስቶስ ቀርባ ለልጆቿ ስልጣን ጠይቃለች፡፡ ማቴ 20፣20 በክርስቶስ መስቀል አጠገብ ከሌሎች ሴቶች ጋር ነበረች ማቴ 27፣55፡፡

1 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ


8/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡- ከላይ የጠቀስናቸው ሰባቱ ማርያሞች ምንም እንኳ ይህ መጠሪያ ቢሰጣቸውም
ቅድስና፣ንጽህና፣ድንግልጽ እንደ እመቤታችን የፈጸመ የለም፡፡ እንዲሁም ለጌታችን እናትነት እርሷተመረጠች፡፡ ሉቃ 1፣21 ‘’የድንግሊቱም
ስም ማርያም ነበር’’፡፡

የስመ ድንግል ማርያም ትርጓሜ

ማርያም የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ማሪሃም /ሚርያም/ ሲሆን ትርጉሙም እመ ብዙኃን /የብዙዎች እናት/ ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ማርያም የሚለው ስም የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንተ በሚስጥራዊ ዘይቤ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፡፡

ሀ/ ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት፡- ወደ መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ከሕገ
እግዚአብሔር እና ከፀጋ እግዚአብሔር የወጣው ከፀጋ እግዚአብሔርም የተራቆተው አዳም ወደ ቀድመ ክብሩ እንዲመለስ ምክንያተ ድኅነት
የሆነችው ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ናትና ወደ መንግስተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ትባላለች፡፡ የእመቤታችንንን አማላጅነት ተስፋ
ሳያደርግ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት የሚቻለው የለምና፡፡

ለ/ ማርያም ማለት ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፡- እመቤታችን ለጊዜው ወላጆቿ መውለድ ባለመቻላቸው በሰው ዘንድ ተንቀው ተዋርደው
እነርሱም አዝነው የኖሩ ስለነበረ ታላቅ ሀብትና ፀጋ ሆና ተሰጥታለች፡፡ ፍጻሚው ግን አማላጅነቷን አውቀው ቃል ኪዳኗን አምነው
ለሚመጡ ምእመናን ሁሉ ሀብትና ፀጋ ሆና ተሰጥታለች፡፡ ይህም “እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፡፡” በሚለው የመልአኩ ንግግር ታውቋል፡፡
ሉቃ 1፣28-30

ምክንያቱም፡- ከፀጋ እግዚአብሔር ተራቁቶ በእግረ አጋንንት ይቀጠቀጠ የነበረው አዳም ፀጋው ተመልሶለት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ
ያደረገው በእመቤታችን በኩል ነውና፡፡ ‘’አዳም ከገነት በተባረረ ጊዜ ተስፋው አንቺ ነሽ’’ ብሎ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ያመሰገነው ለዚህ
ነው፡፡ እንዲሁም በእግዚአብሔር ወልድ የባህርይ አምላክነት የሚያምኑ ምእመናን አምላካዊ ፀጋውንና ሀብቱን ለማግኘት መሰረት
የሚያደርጉት ወላዲተ አምላክ ድንግል ምርያምን ነው፡፡ እመቤታችን ለዚህ ሁሉ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ያበቃት ምንድን ነው ቢሉ የአምላክ
እናት ሆና መመረጧ ነው፡፡ መዝ.131፣13 ፣ ሮሜ 5፣18

እንድም ይህ እንዴት ነው ቢሉ፦

# መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ
ተጽፎአልና።

# ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል፣
እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7፥14)

# ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር


የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።

# አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ"
ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።

# አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ
ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው። "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ
ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።

ማርያም ማለት ስጦታ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በእናትነት ሰጥቷታልና ዮሐ 19፣26
2 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ
ሐ/ ማርያም ማለት ፍፅምተ ስጋ ወነፋስ ማለት ነው፡- በድንጋሌ ስጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም በስጋም በነፍስም ፍጹም ንፅሂተ፣ቅድስት፣ድንግል ናት ማለት ነው፡፡

መ/ ማርያም ማለት መልዕልተ ፍጡራን መትህተ ፈጣሪ / ክፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች/ ያለች ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር አክብሮና አልቆ የፈጠራቸው ሰውንና መላእክትን ነው፡፡

- እመቤታችን ከፍጡራን በላይ ስንልም ከሰው ልጆችም ሆነ ከመላእክት የምትልቅ የምትከብር ማለታችን ነው፡፡
- እመቤታችን ድንግል ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ በፍጹም ተዋሕዶ ዓለምን ለማዳን
ምሕረቱን የገለጠባት እም መሐሪ በመሆኗ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራ በላይ ከእርሷ በቀር ማንም የለም፡፡
 በተጨማሪም ቅዱሳን አባቶች ከመላእክት እንደምትበልጥ ‹‹ጸጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ . . . ዓይኖቻቸው ብዙዎች
ከሆኑ ከኪሩቤልና ክንፎቻቸው ስድስት ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፡፡ . . . የእሳት ነበልባልን
ተሸከምሽ›› (ቅዱስ ያሬድ)
 ከሰው ልጆም እንደምትበልጥ ‹‹ከቅዱሳን ክብር የእመቤታን ክብር ይበልጣል አካላዊ ቃልን ለመቀበል በቅታ ተገኝታለችና
መላእክት የሚፈሩትን . . . ›› ቅዱስ ኤፍሬም በረቡዕ ውዳሴ ማርያም

ሠ/ ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን / የብዙዎች እመቤት/ ማለት ነው

የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር ከእርስዋ በመወለዱ እምቤታችንም የብዙዎች እመቤት ሆነች፡፡ ሮሜ 5፡፡ እመቤት ማለት በአንድ ቤተሰብ
መካከል አስተዳዳሪና ኃላፊ የሆነች ታላቅ ሴት ማለት ነው፡፡ እንዲዚሁም በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ያመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ
በክርስቶስ አንድ ቤተሰብ በመሆናቸው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እመቤታቸው ናት፡፡

ረ/ ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነው፡፡

አምላክ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆኖ፤ መለኮት ከትስብእት ተዋሕዶ ስለተገለጠባ ለሰው የመዳኑ ምክንያት ናትና፤ የሰውን ልመና ወደ
እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወደ ሰው በማድረስ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ፣ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለደች
ታሰጣለች፡፡

 አንድም ማርያም የሚለው ቃል የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፡፡

ማር + ያም

ማር፡- በምድር ካለ ነገር ሁሉ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን ነውና

ያም፡- በገነት የጻድቃን ምስጋና

እናም በምድር ያሉ ቅዱሳንና በገነት ያሉ ጻድቃን ስምሽን ሲጠሩ ለአፋቸው ይጥማቸዋል ለልባቸው ደስ ያሰኛቸዋል ሲሉ ማርያም ተባለች፡፡
አንድም ቃሉ የእብራይስጥ ነው በእብራይስጥ ማሪሃም ይላታል፡፡

ማሪ፡- እመቤት ማለት ሲሆን

3 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ


ሃም፡- ብዙሃን ማለት ነው

ማሪሀም፡- የብዙሀን እመቤት ይሆናል፡፡

አንድም ማሪያም የሚለው ሆሄ ሲተነተን ማ፡- ማህደረ መለኮት.. የመለኮት ማፊረያ

ር፡- ርግብየ ይቤላ ሰሎሞን …የሰሎሞን ርግብ (መሀልይ 6፣9)

ያ፡- ያንቅሀዱ ሀቤኪ ሁሉ ፍጥረት..ፍጥረት ሁሉ ወደ አንቺ ያንጋጥጣሉ

ም፡- ምስሀል ወምስጋድ ወመስተስርየ ሀጥያት . . . ለሚሰግዱላት ለሚያከብሯት ኃጥያት ታስተስርያለች፡፡

ከብዙ የእመቤታችን መጠሪያ ስሞች በከፊል

 ሰአሊተ ምህረት፡- ምህረት የምትለምን


 እመ ብዙሃን ፡- የብዙሃን እናት ዮሐ 19፣27
 እመ ብርሃን፡- የብርሃን እናት
 ቤዛዊት ዓለም፡- የዓለም ቤዛ
 ኪዳነ ምሕረት፡- የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጣት
 መልእተ ውዳሴ፡- ውዳሴ የበዛላት
 ምክሆ ደናግል፡- የደናግል መመኪያ
 ማህደረ መለኮት.. የመለኮት ማፊረያ
 አቁራሪተ መአት፡- መአትን የምታርቅ ወዘተ. . .

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘር ሀረግ

በኢየሩሳሌም አካባቢ በቅዱስ ጋብቻ ተወስነው የሚኖሩ ጴጥራቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ልጆች የሌላቸው መካን ሲሆኑ
ሀብታቸውን የሚወርስ ልጅ ባለመውለዳቸው ያዝኑ ነበር፡፡ ከእለታት በአንዱ ቀን ስለሀብታቸው ብዛት በሰፊው ከተወያዩ በኋላ ጴጥርቃ
በተስፋ መቁረስ ጥሜት እህቴ ሆይ ይህ ሁሉ የሰበሰብነው ገንዘባችን ምን እናድርገው የሚወርሰን ልጅ የለንም ምክንያቱም አንቺ መካን ነሽ
እኔ ደግሞ ከአንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ ቴክታም እጅግ አዝና ጌታዬ ሆይ አምላከ እስራኤል እኔን ልጅ ቢነሳኝ አንተም
እንደእኔው ትቀራለህን ከሌላ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንዲህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንደማላስበው አምላክ
ያውቃል አላት፡፡

ይህንን ተነጋግረው ሌሊቱን ህልም አልመው አደሩ ሲነጋም ቴክታ ለጴጥርቃ ትናንት ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ
ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስም ሲዋለዱ ሰባተኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ
አለችው፡፡ ጴጥርቃም ይህን ሰምቶ ህልሙን ለማስፈታት ወደ ህልም ፈቺ ዘንድ ሄዱ ህልም ፈቺውም እግዚአብሔር በምሩቱ አይቷችኋል
ሰባት እንስት ጥጆች መውለዳችሁ ሲወልዱም ማየታችሁ ሰባት ሴቶች ልጆች ትወልዳላችሁ ሰባተኛዋ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች

4 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ


ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አላቸው፡፡ ባልና ሚስቱም ይህነ ቃል ተቀብለው ወደ
ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ቴክታም ፀነሰች ሔመንን ወለደች፣ ሔመንም ዴርዴን ወለደች፣ ዴርደም ቶናን ወለደች፣ ቶናም ሲካርን ወለደች፣ ሲካርም ሴትናን
ወለደች ፣ ሴትናም ሔርሜላን ወለደች፣ ሔርሜላም ማጣትን አግብታ ከአንስት ዓለም ተመርጣ የአምላክ አያት ለመሆን የበቃችውን
ቅድስት ሐናን መስከረም ሰባት ቀን ወለደች፣ ሐናም በሥርአት አደገች ለአካለ መጠን ስትደርስም ከቤተ መንግስት የተወለደን ክቡር ጻድቅ
የሆነውን ኢያቄም የሚባል ሰው አገባች፡፡

በዚህም በተቀደሱ እናቶችና አባቶች የዘር ሀረግ አልፈው የመጡት ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና እግዚአብሔር ለድህነት ዓለም
የመረጣት ቅድስት ድንግል ማርያም በነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት 1 ቀን 5485 ዓ.ዓ በሊባኖስ ተራራ ተወለደች፡፡ በሊባኖስ ተራራ
መወለዷም በመሀልየ መሀልይ ዘሰሎሞን 4፣8 ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ የሚለው ትንቢት ይፈጸም
ዘንድ ነው፡፡

 የእመቤታችን የዘር ሐረግ ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢያቄምና ሐና ድረስ በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል ስትወርድ
እንደመጣች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይመሰክራሉ፡፡
 ይህም ከአዳም ልጆች በሴት በኩል
 ከኖኅ ልጆች በሴም በኩል
 ከአብርሃም ልጆች በይስሐቅ በኩል
 ከያዕቆብ ልጆች በይሁዳና በሌዊ በኩል
 ከዳዊት ልጆች በሰሎሞን በኩል በተመረጡና በተቀደሱ አባቶችና እናቶች በኩል በጥበበ እግዚአብሔር
ስትወርድ ከመጣች በኋላ
 ከቤተ ሌዊ ከነገደ አሮን ከካህናቱ ወገን ከሆነች ከቅድስት ሐና
 ከነገደ ይሁዳ ከነገሥታቱ ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም እንደምትወለድ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረ፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ምንም እንኳን በአዳማዊ በደል ከተያዙ ሰዎች መካከል የተገኘች ብትሆንም ከጥንተ አብሶ
(ከአዳማዊ በደል፣ መርገም) ነፃ ናት፡፡

5 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ


6 ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ቡሩክ ኃይሌ

You might also like