You are on page 1of 38

መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

መሠረተ ሃይማኖት
ሁለተኛ ክፍል

ነገረ ክርስቶስና
ነገረ ሰብእ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/


ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመንበረ ፓትርያርክ (ዓለም አቀፍ)
የሰንበት
ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀ 2015 ዓ.ም

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

(ማውጫ)
ምዕራፍ አንድ - ነገረ ሰብእ ፩
፩.፩ እግዚአብሔር ሰውን አክብሮ ስለመፍጠሩ ፪
፩.፩.፩ በእጁ እንደ ሠራው ፪
፩.፩.፪ በአርአያውና በአምሳሉ እንደ ፈጠረው ፪
፩.፩.፫ የሁሉ ገዢ እንዳደረገው ፫
፩.፪ ሰይጣን በእባብ ተሰውሮ አዳም እና
ሔዋንን አታሎ ዕፀ በለስንማስበላቱ ፫
፩.፪.፩ አዳምና ሔዋን መቀጣታቸው ፬
፩.፪.፩ የአዳምና ሔዋን ንስሓ ፭
፩.፪.፪ እግዚአብሔር ሊያድናቸው ቃል
መግባቱንና (ማዳኑ) ፮
ምዕራፍ ሁለት - ነገረ ክርስቶስ ፱
፪.፩ የእመቤታችን ታሪክ በጥቂቱ ፲
፪.፩.፩ ስለ ልደቷ ፲፩
፪.፩.፪ ስለ ዕድገቷ ፲፩
፪.፩.፫ ስለ ዮሴፍና ስለጠባቂነቱ ፲፪
፪.፩.፬ ጌታን ስለ መፅነሷ ፲፪
፪.፩.፭ ጌታን ስለመውለዷ ፲፫
፪.፩.፮ ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ስደት ፲፭
፪.፪ የጌታ መጠመቅ ፲፮
፪.፪.፩ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ፲፮
፪.፪.፪ በዮርዳኖስ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን
ስለማጥመቁ ፲፮
፪.፪.፫ የምሥጢረ ጥምቀት መመሥረትና ሰው
በ፵ እና በ፹ ቀን ስለመጠመቁ ፲፰
፪.፪.፬ ጥር ፲፩ - በዓለ ጥምቀት ፲፰
፪.፪.፭ ጠበልና ጠበልን ስለመጠበል ፲፰
፪.፫ የጌታ መጾምና በዲያቢሎስ መፈተኑ ፲፱

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፬ በደብረ ታቦር ጌትነቱን ስለመግለጡ


(በዓለ ደብረታቦር) ፲፱
፪.፭ ስቅለቱና ትንሣኤው ፳
፪.፭.፩ ሆሣዕና ፳፩
፪.፭.፪. የይሁዳ ክሕደት ፳፪
፪.፭.፫ የጌታ መንገላታት ፳፫
፪.፭.፬ የጌታ መሰቀል፣ መሞት፣ መቀበርና
የዕለተ ዓርብ ተአምራት ፳፫
፪.፪.፭ የጌታ ትንሣኤ ፳፮
፪.፮ ዕርገቱና በዓለ ሃምሳ ፳፯
፪.፮.፩ ዕርገቱ ፳፯
፪.፮.፪ መንፈስ ቅዱስን ስለመላኩ ፳፯
፪.፯ ዳግመኛ የሚመጣ ስለመሆኑና ስለ ትንሣኤ ሙታን ፳፰
፪.፰ ሰውን ስለማዳኑ ፳፱
የማጠቃለያ ጥያቄ ፴፩
ዋቢ መጻሕፍት ፴፪

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ምዕራፍ አንድ
ነገረ ሰብእ

የምዕራፉ ዓላማ
ልጆች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• እግዚአብሔር ሰዉን እንዴት እንደፈጠረው ያውቃሉ።


• የሰዉ ልጅ በማወቅ ሰውን ያከብራሉ።
• የሰይጣንን ክፉ ሥራ ይረዱታል ከክፉ ሥራውም ይርቁበታል።
• የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ ያውቁበታል።
• የኢየሱስ ክርስቶስን አበይት በዓላት ይረዱበታል።

ቁልፍ ቃላት

• እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክ


• ደመ ነፍስ ሥጋ የሚንቀሳቀስበት መንፈስ

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

፩. ልጆች እግዚአብሔር ሰውን እንዴት እንደፈጠረው ተናገሩ?


፪. ልጆች መታዘዝ ማለት ምን ማለት ነዉ? ባንታዘዝ ምን እንሆናለን?
፫. ልጆች አዳም መች ተፈጠረ?

፩A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

በቃል የሚጠና ጥቅስ

‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ


የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል››
መዝ፲፰፥፩

፩.፩ እግዚአብሔር ሰውን አክብሮ ስለመፍጠሩ


ልጆች እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በመልኩ እንደምሳሌው ከምድር አፈር አበጅቶ
የሕይወትን እስትንፋስ በመስጠት ክቡር አድርጎ ፈጥሮታል። ከሌሎቹ ፍጥረታት
ይልቅ የሰው ልጅ ክቡር ፍጥረት መባሉ እግዚአብሔር በግብር /በእጁ ከምድር
አፈር አበጅቶ ፈጥሮታልና በተጨማሪ በአምላኩ መልክና አምሳል በመፈጠሩ ነው።
፩.፩.፩ በእጁ እንደ ሠራው
እግዚአብሔር ፳፪ቱን ሥነፍጥረት ከፈጠረ በኋላ ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ
በዕለተ ዓርብ ፈጥሮታል፦
• ፲፬ቱን በነቢብ/ በቃሉ በመናገር
• ፯ቱን በአርምሞ/ ሳይናገር እና
• አዳምን በገቢር በመሥራት ፈጥሮታል።

፩.፩.፪ እርሱን አስመስሎ እንደፈጠረው


“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር።” ዘፍ፩፥፩፮
እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እርሱን አስመስሎ ፈጥሮታል።
• ይህም እንደ እርሱ ሕያው ፣ ነባቢ እና ለባዊ አድርጎ መፍጠሩን ያሳያል። ሰው
ሕያው ነው እንደ እንስሳት ሳይሆን ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ ሕያዊት ነፍስ
አለችው ማለት ነው።
• ሰው ነባቢ ነው ስንል ቃል አለው ይናገራል ሃሳቡን መግለጽ ይችላል ማለት ነው።
• እንዲሁም ሰው ለባዊ ነው ስንል አስተዋይ ልቦና አገናዛቢ አእምሮ አለው ማለት
ነው። እነዚህም ሦስቱም በአንዲት ነፍስ የሚገኙ ግብራት ናቸው። ስለዚህም
የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት የሚያሳይ ምሳሌው ሰው ነው።

፪A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

እነዚህም ሦስቱም በአንዲት ነፍስ የሚገኙ ግብራት ናቸው። ስለዚህም


የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት የሚያሳይ ምሳሌው ሰው ነው።

፩.፩.፫ የሁሉ ገዢ እንዲሆን አደረገው


ሰውን እግዚአብሔር ከፈጠረው በኋላ ምድርን እንዲሞላ እንዲገዛ የባሕርን ዓሦችና
የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ እንዲገዛቸው ሥልጣንን
ገዥነትን ሰጥቶታል። ስለዚህም የምድር አራዊትን እንስሳትንና የሰማይ ወፎችን
ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ እነርሱም እንደጠራቸው ስማቸው ያው ሆነ።
- “ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥
ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም
ሁሉ ግዙአቸው።” ዘፍ፩፥፳፰

፩.፪ ሰይጣን በእባብ ገላ ተሰውሮ አዳም እና ሔዋንን በማታለል


ዕፀ በለስን ማስበላቱ ?
አሳች የሆነው ሰይጣንም አዳምና ሔዋን በእርሱና በወደቁት ሠራዊቱ ፋንታ
የእግዚአብሔርን ስም ለመቀደስ ክብሩንም ለመውረስ በመፈጠራቸው በመቅናት
የልጅነት ክብራቸውን ለመንጠቅ በእባብ ገላ ተሰውሮ ወደ ገነት ገባ። እባብ ኩሩ
ነበረችና እርሷን በመደለል ተሰውሮ ወደ ገነት ገባ በዚያም አዳምን በቅድሚያ
ፈጣሪውን ሲያመሰግን አገኘው። እርሱንም በከንቱ ውዳሴ ሊጥለው ከምድር
ገዥነቱ ውጭ ያልተሰጠውን የሰማይ ገዥነትን ጨምሮ “የሰማይና የምድር ገዥ
የሆንክ አዳም ሆይ እንደምን አለህ” በማለት ቀረበ። ነገር ግን አዳም “ሰላምታህን
ለይ! እኔ የምድር ብቻ ገዥ ነኝ” ስላለው ትቶት ሄደ። በመቀጠልም ወደ ሔዋን
በመሄድ “የሰማይና የምድር ንግሥት የሆንሽ ሔዋን ሆይ ሰላም ለአንቺ ይሁን”
በማለት እርሷን በመሸንገል የተሳሳተ ጥያቄና ሃሳብ በማቅረብ በእግዚአብሔር
እንዳይበሉ ከታዘዙት የእነርሱም ታማኝነት ከሚፈተሽበት ትእዛዝ ፈቀቅ በማለት
አስቀድሞ የተከለከሉትን ዕፀ በለስ በመጎምጀት ቀጥፉ እንቢ ከማይላት ከአዳም ጋር
ተመገቡ። በዚህም ምክንያት ጸጋቸው ተገፈፈ፣ ተራቆቱ፣ ሃፍረት ተሰማቸው፣
የእግዚአብሔርን ድምጽ ሲሰሙም ተሸሸጉ፣ ፍርኃትም ከበባቸው፣ ከንስሓም ይልቅ
እርስ በእርስ ተካሰሱ። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ጋር እንዲህ አጣላቸው።

፫A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፩.፪.፩ አዳምና ሔዋን መቀጣታቸው


አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን የሞት ሞትን ትሞታላችሁ የሚለውን ቃል
ባለመቀበል ይልቁኑ የሰይጣንን ቃል በመቀበል፣ ትእዛዙን ስለጣሱ ለፍርድና
እርግማን ተጋለጡ። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ቃሉ ስለማይታጠፍ አስቀድሞ
አስጠንቅቋቸው ነበርና እውነተኛም ዳኛ ስለሆነ እና ስለማያዳላም ነው።

ሥዕል ፩ ፡ ሰይጣን በእባብ ገላ ተሰውሮ አዳም እና ሔዋንን እንዳሳታቸው

፬A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ስለዚህም እግዚአብሔር እባብን፣ ሔዋንን እና አዳምን ረገማቸው። እባብ


ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይቶ የተረገመ ሆነ፤ በሆዱም የሚሳብ አፈርንም የሚበላ
ሆነ። ሔዋንም በጭንቅ የምትወልድ፣ ባሏ የሚገዛት፣ ፈቃዷም ወደ ባሏ ሆነ።
አዳምም ከእርሱ የተነሳ ምድር ተረገመች በድካምም ከእርሷ የሚበላ እናም ከአፈር
ተገኝቷልና ወደ አፈር የሚመለስ ሟች ሆነ። ሁለቱም ገነትን ከመሰለ ቦታ ተባረሩ። ዘፍ ፫፥፯

ሥዕል፪፦ አዳም እና ሔዋን ከገነት ሲወጡ


፩.፫ የአዳምና ሔዋን ንስሓ
አዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን የመሰለ ጌታ ገነትን ያህል ቦታ በማጣታቸው
እጅግ አዘኑ። አዝነውም አልቀሩ ንስሓ ገቡ። ቀኖቻቸውንም በውኃ ውስጥ ለ፵ ቀን
በመጸለይ ለመቆየት ወሰኑ። በውኃው ውስጥ ሱባዔ እንደያዙ ውጤቱም ምሕረት
እና ከእግዚአብሔር መታረቅ እንደሆነ የተረዳው ዲያብሎስ ግን በ፴፰ ኛው ቀን
ቅዱስ ገብርኤልን ተመስሎ ከሱባኤያቸው ሊያቋርጣቸው ወደ እነርሱ ሄደ። ሄዶም
“እግዚአብሔር ምሯችኋልና ከውኃው ውጡ” አላቸው።
ሰይጣንም “እግዚአብሔር ምሬሃለሁ እያለ እምቢ ማለት የከፋ በደል ነው” ቢለውም
አልወጣም። በዚህ ጊዜ ወደ ሔዋን ሄዶ ለአዳም ያለውን ቢነግራት ‹‹ምሕረት
ለማግኘት አይደለምን ሱባኤ መያዛችን›› ብላ ፈጥና ወጣች አዳም ግን “አልወጣም!”
አለ።
፭A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

አዳም ሔዋንን እንዲጠብቃት ታዞ ነበርና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከማፈርስ ሱባኤ


ባፈርስ ይሻላል ብሎ ወጣ። ሰይጣንን ተከትለውትም ወደ ገነት አቅራቢያ ደረሱ።
እዛም ጋር ሰይጣን አወቃችሁኝን እኔ ያሳትኳችሁ ዲያብሎስ ነኝ አላቸው። እነርሱም
ደነገጡ አዳምም እንደሞተ ሆነ። ከዚያም ምግብ የሚያመጡለትን የገነትን አእዋፋት
ድምጽ ሰምቶ ተከትሎ ከገነት ደጃፍ ሲደርስ ሰይጣን ይህ ሰውዬ ብሎ በድንጋይ
ሲመታው ወደቀ ሌላም ድንጋይ ሲጭንበት እግዚአብሔር እንደድንኳን አደረገለትና
በዛ ወድቆ ቆየ። ሲነቃም የፈሰሰ ደሙን ከፍራፍ ጋር አድርጎ መስዋዕት አሳረገ።
እግዚአብሔርም ሁለተኛ ደምህን እንዳትሰዋ፤ ይልቁኑ ወደ ፊት እንደሚያድነው
ተስፋ ሰጠው። ይህንም ተስፋ አድርገው እየኖሩ አዳምና ሔዋን ከብዙ ዓመታት
በኋላ ልጆችን ወለዱ።

፩.፫.፩ እግዚአብሔር ሊያድናቸው ቃል መግባቱ


አዳምና ሔዋን ንስሓ መግባታቸውን መጸጸታቸውን ተከትሎ “ከአምስት ቀን ተኩል
በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” ሲል ቃል ኪዳን ገባለት። አዳም ከእኛ እንደ
አንዱ ሆነ ያለውና እርሱ የተባለ ከእመቤታችን የተወለደ ጌታ የሰይጣንን ራሱን
እንደሚቀጠቅጥም ነገራቸው።

የተግባር ልምምድ

ተማሪዎች በዚህ ምዕራፍ የተማራችሁትን ታሪክ ለቤተሰቦቻችሁ


ተናገሩ።

፮A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የክለሳ ጥያቄዎች

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል ካነበባችሁ በኋላ ትክክል የሆነውን


ዓረፍተ ነገር ‹‹እውነት›› ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ‹‹ሐሰት›› በማለት
መልሱ።

፩. የሰው ልጅ በሥላሴ አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት ነው።


፪. እግዚአብሔር በገነት ከፈጠራቸው አትክልቶች መካከል ዕፀ በለስን እንዳይበሉ
የከለከለው የሞት ሞት እንዳይሞቱ ነው።
፫. አዳምና ሔዋን ዕፀ በለስን በመብላታቸው ከእግዚአብሔር ተጣሉ።
፬. እግዚአብሔር ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን
ገባለት።
፭. እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር የፍጥረት ሁሉ ገዥ አድርጎ ነው።

፯A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ከላይ የተሰጠውን ሥዕል ቀለም በመጠቀም አቅልሙ!

፰A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ምዕራፍ ሁለት
ነገረ ክርስቶስ

የምዕራፉ ዓላማ
ልጆች ይህንን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ

• ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን መወለዱን ያውቃሉ።


• እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን ያውቃሉ።
• የኢየሱስ ክርስቶስን ከልደት እስከ ዳግም ምጽአቱ ያለውን ታሪክ
ያውቃሉ።
• በጾምና በጸሎት ፈተናን ማሸነፍ እንደሚቻል ይረዳሉ።

ቁልፍ ቃላት
• ስዕለት፦ መልካም የሆነ ነገር እንዲገጥመን ከእግዚአብሔር ጋር
የሚደረግ ቃልኪዳን
• ታሳድፍብናለች ፦ ታቆሽሽብናለች
• በበፍታ ፦ ጨርቅ
• ምሴተ ሐሙስ ፦ የሐሙስ ምሽት

የማስጀመሪያ ጥያቄዎች

፩.ልጆች የእመቤታችን እናትና አባት ስማቸው ማን ይባላል ?


፪. ልጆች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠመቀው ሰው
ስሙ ማን ይባላል ?
፫. ልጆች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሲጠብቃት የነበረዉ
አባት ማነው?

፱A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

በቃል የሚጠና ጥቅስ

‹‹እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትዉልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል።


ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነዉ!››
ሉቃስ ፩፥፳፮

ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ


ክርስቲያናችን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እና አበው ሐዋርያትን አብነት (ምስክር)
አድርጋ የምታምነው፣ የምታስተምረው፤ ከጽንሰቱ እስከ ዳግም ምፅአቱ ያለውን
ታሪክ የምንማርበት ክፍለ ትምህርት ነው።

• ኢየሱስ ማለት አዳኝ፥ መድኃኒት ማለት ሲሆን፦


• ክርስቶስ ማለት ደግሞ መሲሕ ፥ንጉሥ ማለት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ለክርስትና እምነት መሠረቱም


ይህን ማወቅ እና ማመን ነው።
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን
ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” ዮሐ ፲፯፥፫

፪.፩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታሪክ በጥቂቱ


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ተስፋ
የተፈጸመባት የጌታችን የአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ናት።
ስለእርሷም መማር የጌታችንን የማዳን ሥራ የበለጠ ግልጽ ያደርግልናል። ልዑል
እግዚአብሔር የድኅነታችን ምክንያት ትሆን ዘንድ ያስቀረልን ዘር እርሷን ነውና ።
ነቢዩ ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም
በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን” ሲል አስቀድሞ እንደተናገረ (ኢሳ ፩፥፱)።

፲A
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽሕት ከሆነች ከእርሷ ተወልዶ ነውና ያዳነን፤
ትምህርተ ክርስቶስን ለመማር ከፅንሰት መጀመር ፥ስለ ቅድስት እናቱ እና ስለድንቅ
ልደቱ ማወቅ የተገባ ነው:: ስለዚህ አስቀድመን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም
ጥቂት እንማራለን።
ስለ መፀነሷ
“ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ
ዘለለ፤በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት ፥በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ
አለች።አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።”
አለቻት። ሉቃ ፩፥፵፩-፵፪ እመቤታችንም
“እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ
ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።” በማለት ተናገራለች። ሉቃ ፩፥፵፰-
፵፱
የእመቤታችን የስሟ ትርጉም፦
• ማርያም ማለት የብዙዎች እመቤት ማለት ነው።
• ሌላው ማርያም ማለት መርህ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው። ምእመናንን
እየመራች ወደ መንግሥተ ሰማያት ታስገባለችና።
• አንድም ፍፅምት ማለት ነው ። በሥጋ በሕሊና ንፅህት ናትና
• ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው።

፪.፩.፩ ስለ መወለዷ
እመቤታችን የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና የስእለት ልጅ ናት። እነርሱ ለ፴
ዓመታት ልጅ በማጣት ከኖሩ በኋላ በስዕለት የተገኘች የእናትና አባቷ ደስታ የሆነች
እመቤታችን ናት። የተወለደችውም በሊባኖስ ተራራ በግንቦት ፩ ዕለት ነው። ዕለቱ
‘ልደታ ለማርያም’ ተብሎ ይከበራል።

፪.፩.፪ ስለ ዕድገቷ
እመቤታችን ከእናት ከአባቷ ጋር ለ ፫ ዓመታት ከኖረች በኋላ በብፅአታቸው
መሠረት እንደ ስዕለታቸው ለቤተ መቅደስ ተሰጥታ በመልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል
መጋቢነት፣ በቅዱሳን መላእክት ሞግዚትነት በቤተ መቅደስ አድጋለች። ወደ ቤተ
መቅደስ የገባችበት ቀን ታኅሣሥ ፫ ሲሆን ‘በዓታ ለማርያም’ ተብሎ ይከበራል።

፲፩
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ሥዕል ፫ ፡ እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገባ


፪.፩.፫ ስለ ዮሴፍና ስለጠባቂነቱ
እመቤታችን እስከ ፲፭ ዓመቷ ድረስ በአጠቃላይ ለ፲፪ ዓመታት በቤተ መቅደስ
ከቆየች በኋላ አይሁድ እንደሌሎች ሴቶች የሴቶች ልማድ ያለባት መስሏቸው
በሰይጣንም አነሳሽነት ቤተ መቅደሱን “ታሳድፍብናለች” ብለው ከቤተመቅደስ
እንድትወጣ በማለታቸው ሊቀ ካህኑ ስለእርሷ ጸልዮ በእግዚአብሔር አመላካችነት
ለዘመዷ ለአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ እንዲጠብቃት በአደራ ተሰጥታዋለች። እስከ ጌታ
ስቅለት ድረስ ለ፴፫ ዓመታት በአረጋዊው ዮሴፍ ቤት ኖራለች።

፪.፩.፬ ጌታን ስለ መፅነሷ


እመቤታችን በአረጋዊው ዮሴፍ ቤትም ስትኖር ሳለ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት
ኤልሳቤጥን መጥምቁ ዮሐንስን እንደምትወልድ ባበሰራት በስድስተኛው ወር ለአዳም
እግዚአብሔር የሰጠው ቃል ይፈጸም ዘንድ መልአከ ብስራት ወደ እርሷ ተላከ።

፲፪
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

መጀመሪያ ውኃ ልትቀዳ በወጣችበት፣ ቀጥሎም በዮሴፍ ቤትሳለች ሊያበሥራት


ቢገለጥም እንደ እናታችን ሔዋን ሰይጣን በመልአክ ተመስሎ እንዳያሳስታት የነገሩን
እውነተኝነት ለማረጋገጥ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳለች። መልአከ ብስራት ቅዱስ
ገብርኤልም ለሦስተኛ ጊዜ በዚያ ተገልጦ ጌታን እንደምትወልድ አብስሯታል።
በዚህም የእርሷም ክብር፥ ንጽሕናና አስተዋይነት ተገልጧል። ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ
ክስተቱን እንደሚከተለው ገልጦታል።
“መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ጌታ ከአንቺ
ጋር ነው፤አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም ባየችው ጊዜ
ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።መልአኩም
እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
እነሆም፥ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። ”ሉቃስ
፩፥፳፰-፴፩ እመቤታችንም ይሁንልኝ ብላ የመልአኩን ቃል በተቀበለች ጊዜ አካላዊ
ቃል በመንፈስ ቅዱስ ግብር በማሕፀኗ ተጸንሷል። ይህም መጋቢት ፳፱ ቀን
የተፈጸመ በመሆኑ ዕለቱ ‘በዓለ ጽንሰት’ ተብሎ ይከበራል።

፪.፩.፭ ጌታን ስለመውለዷ


እመቤታችን ጌታን ከፀነሰች በኋላም የዘመዷ ኤልሳቤጥን በስተርጅና መጽነስ
መልአኩ በነገራት መሠረት ልትጠይቃት ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ
ሄዳለች። ከዚያም ለሦስት ወራት ቆይታ ተመልሳለች። የመውለጃዋ ወራትም
ሲደርስ የሕዝብ ቆጠራ ነበርና ወደ ቤተልሔም ከጠባቂዋ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና
ከሰሎሜ ጋር ተጉዘዋል። በዚያም ሳሉ በእንግዶች ማረፊያ ስፍራ ስላልነበራቸው
በከብቶች በረት በድንግልና ጌታችንን ወልዳለች። (ሉቃ ፪፥፯)

በግርግምም የነበሩ እንስሳት የተወለደው ሕፃን ጌታቸው መሆኑን አውቀው ወቅቱ


የብርድ ወራት ነበርና በትንፋሻቸው አሙቀውታል። እረኞችም መላእክት የልደቱን
የምሥራች አሰምተዋቸው እንደተለዩአቸው ፈጥነውም በመውጣት ማርያምንና
ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አግኝተዋል። ያዩትንም ሁሉ ወደ ሕዝቡ ሂደው
ገልጠዋል። እኛም ክርስቲያኖች የጌታ ልደት ዓለም ሁሉ ደስ የተሰኘበት እለት
በመሆኑ በየዓመቱ ታኅሣሥ ፳፱ ‘በዓለ ልደት’ ብለን በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ
ሥርዓት እናከብረዋለን።

፲፫
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ሥዕል ፬ ፡ የጌታችን ልደት

፲፬
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፩.፮ ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ስደት


ምንም እንኳ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ አዳምና ልጆቹ
በተስፋ ይጠብቁት የነበረና የልደቱ ዜናም ፍጥረትን ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም
የይሁዳ ገዥ የነበረው ንጉሥ ሔሮድስ ግን ለተወለደው ሕፃን ሊሰግዱና በፊቱ
ስጦታን ሊያቀርቡ የሰብአ ሰገልን መምጣት ተረድቶ ሕፃኑ መንግሥቱን ሊነጥቀው
የመጣ ምድራዊ ንጉሥ አድርጎ በማሰቡ ሊያስገድለው ፈለገ። የጌታ መልአክ
በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና
እናቱንም ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።”ማቴ
፪፥፲፫ አረጋዊው ዮሴፍም በታዘዘው መሠረት መልአኩ እየመራው ወደ ግብጽ ብሎም
ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል። በሀገራችን ኢትዮጵያም በታላላቅ ቦታዎች አርፈዋል።
ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ በስደት ቆይተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከስደት
የተመለሱበት እለትም በየዓመቱ ኅዳር ፮ ቀን ይከበራል።

ሥዕል ፭ ፡ የእመቤታችን ስደት ከተወደደ ልጇ ጋር

፲፭
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ነገረ ክርስቶስ
፪.፪ የጌታ መጠመቅ
ጌታችን ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ አዳም ልጅነትን ባገኘበት ዕድሜ ልጅነት
የሚገኝበትን ምሥጢረ ጥምቀትን ሊመሠርትልን፣ እንዲሁ የዕዳ ደብዳቤያችንን
ረግጦና አቅልጦ ይደመስስልን ዘንድና ትንቢቱም ይፈጸም ዘንድ በዮርዳኖስ
በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ ተጠምቋል። ሲጠመቅም ምሥጢረ ሥላሴ ተገልጧል።
አብ በደመና ተናግሯል፣ ወልድ በዮሐንስ እጅ ተጠምቋል መንፈስ ቅዱስም በርግብ
አምሳል በወልድ ራስ ላይ ወርዷል።

፪.፪.፩ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ


መጥምቁ ዮሐንስ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ከካህኑ ዘካርያስና
ከቅድስት ኤልሳቤጥ የተወለደ ሲሆን ጌታችንን ንጉሥ ሄሮድስ ሊገድለው
ባሳደደው ጊዜ አባቱን በመቅደስ ገድለውበታል። እርሱም ወደ በረሃ ከእናቱ ጋር
ከተሰደደ እና እናቱ ቅድስት ኤልሣቤጥ ካረፈች በኋላ በዚያው በበረሃ አንበጣና
ማር እየተመገበ አድጓል። ልብሱም ቆዳና የሚታጠቀውም ጠፍር ነበር። ስለ
እርሱም ነብዩ እንደተናገረው እንዲሁም አባቱ እንዳመላከተው የጌታችንን
መንገድ ሊጠርግ በእግዚአብሔር ታዝዞ የንስሐ ጥምቀትን ያጠምቅ ነበር።
“እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል እናንተም
የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል የምትወዱትም የቃል ኪዳን
መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል” ት. ሚል ፫፥፩
“ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥መንገዱን ልትጠርግ በጌታ
ፊት ትሄዳለህና፤እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት
ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤”ሉቃ ፩፥፸፮- ፸፯
“ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤
ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።” ማቴ ፫፥፬

፪.፪.፪ በዮርዳኖስ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ስለማጥመቁ


ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን አጥምቋል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በሄደ ጊዜ ዮሐንስ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል
አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ብሎ ሊከላከለው ፈልጎ ነበር። ጌታችን ግን “አሁንስ

፲፮ A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት


እና ተጠመቀ። ማቴ ፫፥ ፲፬-፲፭

ሥዕል ፮ ፡ የጌታችን ጥምቀት


ጌታ በተጠመቀ ጊዜ ቀድሞ በነበረው ዘመን በግልጥ የማይታወቅ የነበረው የሥላሴ
ምሥጢር በገሃድ (በግልጥ) ታውቋል። ምክንያቱም እግዚአብሔር አብ ከላይ
ከሰማይ ሆኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፤ እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በእርሱ ላይ ሲወርድ ታየ።

ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ መጠመቁ ስለ ተለያዩ ምክንያቶች ነው። ከነዚህም


መካከል
• ምሥጠረ ጥምቀትን ቀድሶ ሊመሠርትልን ፣
• ተጠምቆ አርአያ ሊሆነን ፣
• በፍጡሩ እጅ በመጠመቅ ትሕትናን ሊያስተምረን ፣
• በአዳም በደል ምክንያት ያጣነውን ልጅነት ሊመልስልን ነው የሚሉት ይጠቀሳሉ።
“ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ

፲፯A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ” ማቴ


፫፥፲፮
“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል” ፩ኛ ጴጥ፫፥፳፩

፪.፪.፫ የምሥጢረ ጥምቀት መመሥረትና ሰው በ ፵ እና በ፹ ቀን ስለመጠመቁ


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን በተግባር እንደመሠረተልን ከላይ
በቀረበው ክፍልተምረናል። ጌታችን ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ መምህር “እውነት
እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት ሊገባ አይችልም” ዮሐ፫፥፭ ሲል ያስተማረውን ትምህርት መሠረት
በማድረግ ሕፃናትን ወንዶች በ፵ ቀን ሴቶች በ፹ ቀን እንዲጠመቁ ይደረጋል።
በ፵ እና በ፹ ቀን መደረጉ የብሉይ ኪዳንን ሥርዓት ተከትሎ ነው። ይህም አዳም
በተፈጠረ በአርባ ቀኑ ሔዋንም በተፈጠረች በሰማንያ ቀኗ ወደ ገነት የመግባታቸው
ምሳሌ ነው።
“በተፈጠረባት ምድር ለአዳም ኣርባ ቀን ከተፈጸመለት በኋላ ይገዛትም ይጠብቃትም
ዘንድ ወደ ገነት ኣስገባነው። ሚስቱንም በሰማንያ ቀን ኣሰገባናት።” ኩፋሌ ፬፥፱

፪.፪.፬ ጥር ፲፩ - በዓለ ጥምቀት


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው ጥር ፲፩ ቀን በመሆኑ
በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ እጅግ በደመቀ ሥነ ሥርዓት ይከበራል። ከበዓሉ
ዕለት አስቀድሞ በዋዜማው ከተራ ይባላል ታቦታት ከመንበራቸው ተነስተው
በካህናት ፣ በሰንበት ተማሪዎች እና በምእመናን ታጅበው ለበዓሉ ማክበሪያ
በጥምቀተ ባሕር በተዘጋጀላቸው ድንኳን ያድራሉ። ሌሊቱን ሙሉ ለበዓሉ
የተዘጋጀው ስብሐተ እግዚአብሔር (ማኅሌት) እና ቅዳሴ ከተከናወነ በኋላ ጠዋት
በማለዳ በተዘጋጀው መጠመቂያ ካህናቱ የቡራኬ ጸሎት አድርሰው ምእመናንን
ይረጫሉ። ከዚያም ዝማሬ እና ትምህርት ከቀረበ በኋላ ታቦታቱ ወደ መንበረ
ክብራቸው ታጅበው ወደ ወጡበት ቤተመቅደስ ይገቡና የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።

፪.፪.፭ ጠበልና ጠበል ስለመጠበል


በጥምቀተ ባሕር የሚከናወነው ጸበልን መረጨት (መጠበል) የጌታችንን ጥምቀት
በሚታይ ምሳሌ ለመግለጽና ከበዓሉ በረከት ለማግኘት ነው። ይህ ዓይነት ጥምቀት

፲፰ A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ከእግዚአብሔር ልጅነትን ለማግኘት የምንጠመቀው ጥምቀት አይደለም። የልጅነት


ጥምቀት የምትከናወነው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ይህ ግን በየዓመቱ ይከናወናል።

፪.፫ የጌታ መጾምና በዲያቢሎስ መፈተኑ


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ዕለቱን
ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ በዚያ ፵ ቀንና ሌሊት በጾም በሱባኤ ቆይቷል።
ይህም አብነት (ምሳሌ) ይሆነን ዘንድ እና ጾምን ሊባርክልን ነው። ከገዳም ከወጣ
በኋላም በሰይጣን ተፈትኗል። ጌታችንን ሊፈትነው ሰይጣን ዲያብሎስ ያቀረባቸው
ጥያቄዎች፦

• ከገዳም ሲወጣ ተርቦ ነበርና ይህንን ድንጋይ ዳቦ አድርግና እንብላ (የስስት


ፈተና) ማቴ ፬፥፲፩
• ወደ ተራራ ጫፍ ከወጡ በኋላም መላእክት ስለ አንተ ይታዘዛሉና ከዚህ ተራራ
ራስህን ወርውር ( የትዕቢት ፈተና)
• ዓለምን እና በዓለም ያለውን ሀብት አሳይቶ ብትሰግድልኝ ይህንን ሁሉ
እሰጥኃለው። (የፍቅረ ነዋይ ፈተና) የሚሉ ሲሆኑ

ጌታችን የቀረቡለትን ፈተናዎች ሁሉ በጥበብ አልፎ ማለትም ስስቱን በትዕግስት፣
ትዕቢቱን በትህትና፣ ፍቅረ ነዋዩን በጸሊዐ ነዋይ (የዓለምን ንብረት በመጥላት) ድል
አድርጎ በመጨረሻም ሂድ አንተ ሰይጣን ለአምላክህ ብቻ ስገድ ተብሎ ተጽፏል
ሲል አሰናብቶታል። በዚህም ከሰይጣን የሚመጣብንን ፈተናዎች በጾም እና በጸሎት
ማሸነፍ እንደምንችል አስተምሮናል።

፪.፬ በደብረ ታቦር ጌትነቱን ስለመግለጡ (በዓለ ደብረታቦር)


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት መካከል
ጴጥሮስን ዮሐንስን እና ያዕቆብን ይዞ ታቦር ወደ ተባለ ረጅም ተራራ ወጣ።
በዚያም የመለኮቱን ምሥጢር ገለጠላቸው ልብሱ በምድር ላይ ያለ አጣቢ
ሊያነጣው እስከማይችል ድረስ ነጭ ሆነ። ከእርሱ የሚወጣውን ብርሃን ለመቋቋም
አልተቻላቸውምና ሐዋርያትም በግንባራቸው ተደፉ። በመካከላቸውም ሙሴ እና
ኤልያስ ተገልጠው ከጌታችን ጋር ሲነጋገሩ ሰሟቸው። በዚህም ጊዜ ከላይ “ብሩህ

፲፱A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ደመና ከሰማይ መጥቶ ጋረዳቸው የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው እርሱን


ስሙት”የሚል ቃል መጣ።ማቴ ፲፯፥ ፭
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ዕለት (ነሐሴ ፲፫) ‘በዓለ ደብረ ታቦር’ በሚል
ከጌታችን የማዳን ሥራ ጋር በተገናኘ ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል
አንዱ አድርጋ በድምቀት ታከብረዋለች። በዓሉ የቡሄ በዓል ተብሎ የሚጠራ ሲሆን
በአብነት ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች እና ሕፃናት በናፍቆት የሚጠብቁት በዓል
ነው።

ሥዕል ፮ ፡ የጌታችን በደብረ ታቦር መገለጥ

፪.፭ ስቅለቱና ትንሣኤው


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዚህ ዓለም ሰው ሆኖ የመጣው በአዳም
ምክንያት በሰው ልጆች የደረሰው ፍዳና መከራ ያበቃ ዘንድ ስለሰው ልጆች ሁሉ
ቤዛ ለመሆን ነው። ሐዋርያትን ከእርሱ ጋር ከዋለበት እየዋሉ ብዙ ትምህርትን
እንዲሁም የክህነት ሥልጣንን ከሰጣቸው: በኋላ ወንጌልን እንዲያስፋፉ አዝዞአቸዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ክርስቲያኖች ልንፈጽማቸው የሚገቡ እንደ ጥምቀት፥ ጾም፥
ጸሎት ፥ ምጽዋት ያሉ ተግባራትን እየፈጸመ እና ወንጌልን እየሰበከ ብዙ ዓይነት

፳A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

በሽታና ጉዳት የነበረባቸውን እየፈወሰ ከቆየ በኋላ በአይሁድ ክፋት ምክንያት


ተሰቅሎ እንዲሞት ፈረዱበት። ከስቅለቱ በፊትም የበዛ መከራን አድረሰውበታል።
ይህ በክርስቶስ የደረሰ መከራ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በምን ያህል ፍቅር
እንደሚወድ የተገለጠበት ነው። ከዚህ በሚከተሉት ክፍሎች ከዕለተ ሆሣዕና ጀምሮ
እስከ በዓለ ትንሣኤ ድረስ ባለው ሰሞን የተከናወኑ ዐበይት ድርጊቶችን በቅደም
ተከተል እንመለከታለን።
“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”ዮሐ
፲፭፥፲፫

፪.፭.፩ ሆሣዕና
በዓለ ሆሣዕና በሊቃውንት ዘንድ ‘ የዘንባባ በዓል’ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሆሣዕና
ማለት ‘አሁን አድን’ ማለት ነው። በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያና
በውርንጫይቱ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሕዝቡ በእልልታ ልብሳቸውንና
ዘንባባ እያነጠፉ ‘ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና
በአርያም እያሉ ተቀብለውታል።

ሥዕል ፰ ፡ በዕለተ ሆሣዕና ጌታ የተቀመጠባት አህያ


እና ልብሳቸውን ያነጠፉ ዘንባባ የያይዙ ሰዎች

፳፩A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ይህንንም ታሪክ መሠረት በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከሌሊት ጀምሮ ዕለቱን


የተመለከቱ ዝማሬዎችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባትን በማንበብ በቅዳሴ እና
በአደባባይ ሥርዓተ ዑደት በየዓመቱ ከትንሣኤ በፊት ባለው እሑድ በድምቀት
ታከብረዋለች። ለምእመናንም ከበዓሉ በረከት ይሳተፉ ዘንድ ዘንባባ የሚታደል ሲሆን
ምእመናን በግንባራቸው በማሰር ቀለበት በመሥራት በጣቶቻቸው ያጠልቃሉ።

፪.፭.፪. የይሁዳ ክህደት


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረጋቸው በጎ ሥራዎች በሽተኞችን
በመፈወሱና ምግብ አበርክቶ በማብላቱ ምክንያት ብዙዎች ስለተከተሉት አይሁድ
በምቀኝነት ተነስተው በእርሱ ላይ አንዳች ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜን ይፈልጉ
ነበር። በበዓለ ሆሣዕና የነበረው የሕዝቡ ድጋፍ ያበሳጫቸው የአይሁድ አለቆች ጌታ
ተሰቅሎ ይሞት ዘንድ ተስማምተው ባሉበት ከጌታ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ
የነበረው ይሁዳ ሰይጣን በልቡ ገብቶ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ በማሰብ ለአይሁድ
አለቆች ጌታን አሳልፎ ሊሰጣቸው በምትኩም ፴ ብር ሊከፍሉት ተስማማ።
ይህ ዕለት ከሆሣዕና ቀጥሎ ባለው ረቡዕ ዕለት ሲሆን ይህንን በምሥጢር እንዲያዝ
ተስማምቶ ምንም እንዳላደረገ ወደ ጌታችን ሄዶ በምሴተ ሐሙስ የሕጽበተ እግር
እና የቁርባን ሥርዓት ተሳታፊ ሆኗል። ሐሙስ ማታም በጌቴ ሴማኒ የጸሎት
ሥፍራ ሳሉ የአይሁድ አለቆችና ጭፍሮቻቸው ጌታን ለመያዝ ሰይፍና ጎመድ
ይዘው በይሁዳ እየተመሩ መጥተዋል ይሁዳም ለአይሁድ አለቆች ‘የምስመው
እርሱ ነው፤ ያዙት’ ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበርና መጥቶ ‘መምህር ሆይ፥
ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው’ በዚያም አይሁድ ይዘው ወደ ሊቀ ካህናት ቀያፋ
ዘንድ ወሰዱት። ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷልና በዚህ ሰሞን እርስ
በእርሳችን ሰላም ባለመባባል የይሁዳን የክህደት ሥራ እናስባለን።

- “በዚያ ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት


አለቆች ሄዶ ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? አላቸው
እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።”ማቴ ፳፮፥፲፭-፲፮
- “የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ
ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር ።” ማቴ
፳፮፥፳፬

፳፪A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፭.፫ የጌታ መንገላታት


ጌታችን ተይዞ ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ከተወሰደ በኋላ የካህናት አለቆች እና ሽማግሌዎች
የሞት ፍርድ ይፈረድበት ዘንድ የሐሰት ምስክሮችን በብዛት ቢያቀርቡም ለሞት
የሚያበቃ አንድም በደል ሊያገኙበት አልተቻላቸውም። ክስ አድርገው ካቀረቡት
መካከልም [ራሱን የአግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ይናገራል] የሚል ሲሆን ሊቀ
ካህናቱም ‘ስለሚመሰክሩብህ ምላሽ አትሰጥምን በውኑ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ
ነህን ’በማለት ቢጠይቀው ጌታችንም ‘አንተ አልህ’ አለው። በዚህ ጊዜ ቀድሞውኑ
ምክንያት ይፈልግ የነበረው ሊቀ ካህናት ልብሱን ቀድዶ ‘ተሳድቦአል እንግዲህ
ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን
ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም፦ ሞት ይገባዋል ብለው መለሱ። በዚያን ጊዜ በፊቱ
ተፉበት፤ ከሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፈ መትተው ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ
ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን አሉ።”ማቴ ፳፮፥፷፭-፷፮

በመንገድም እያንገላቱ ወደ ጲላጦስ ወሰዱት ጲላጦስም ከመረመረው በኋላ ምንም


በደል ባያገኝበትም ግን ሰቅለው ይገድሉት ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው። በዚያን ጊዜ
የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ
ወደ እርሱ አከማቹ። ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥ ከእሾህም አክሊል
ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ
ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ አሾፉበት፤ተፉበትም መቃውንም ይዘው
ራሱን መቱት። ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት
ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

ቤተ ክርስቲያናችን ይህን የጌታ መከራ በማሰብ በየዓመቱ ከዕለተ ሆሣእና ጀምሮ


እስከ በዓለ ትንሣኤ ድረስ ያለውን ሳምንት ‘ሰሙነ ሕማማት’ በማለት ሰይማ
የጌታን ሕማሙን የሚያስታውስ ልዩ ልዩ ሥርዓት ሠርታ ታከብራለች።

፪.፭.፬ የጌታ መሰቀል፣ መሞት፣ መቀበርና የዕለተ ዓርብ ተአምራት


አይሁድ ጌታችንን እያንገላቱ እንዲሰቀልበት ባዘጋጁት ጎልጎታ በተባለ ሥፍራ
ሲደርስም መራራን ሐሞት ይጠጣ ዘንድ አቀረቡለት፤ ጌታም ቀምሶ ሊጠጣው
አልወደደም። እጅግ ብዙ ወንጀልን ከሠሩ ወንበዴዎች መካከልም ሰቀሉትና

፳፫A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ልብሱንም በዕጣ ተከፋፈሉ። በዚያ የሚያልፉ መንገደኞች ሁሉ ራሳቸውን እየነቀነቁ


ይሰድቡት ነበር። ሌሎችን የሚያድን ራሱን ማዳን አይችልምን? እያሉም ተዘባበቱበት
የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነስ ለምን አያድነውም? በማለት ይሳለቁ ነበር። አብረውት
ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ ‘አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም
እኛንም አድን ብሎ ሰደበው።’ በቀኝ ተሰቅሎ የነበረው ግን መልሶ ‘አንተ እንደዚህ
ባለ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለአደረግነውም የሚገባንን
እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም’
በማለት ገሠጸው። ወደ ጌታም ዘወር ብሎ ‘ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ
አስበኝ’ባለ ጊዜ ጌታችንም ‘እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ’
በማለት የሕይወት ቃልን አሰማው።

ከዚህም በኋላ ከቀኑ ፮ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ሁሉ
ጨለማ ሆነ ። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጌታ ‘ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ’ ብሎ በታላቅ
ድምፅ ጮኸ። ትርጉሙም ‘አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?’ ማለት ነው።
ከመካከላቸውም አንዱ በሰፍነግ ወይም ሸምበቆ የተሞላ መራራ መጠጥን አጠጣው
ከዚያም ጌታችን በታላቅ ድምጽ ‘አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ ብሎ
ነፍሱን ሰጠ። ከጭፍሮች መካከልም አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወዲያውም ደምና
ውኃ ወጣው።

ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሳለ ልዩ ልዩ ተአምራት ተፈጽመዋል ከነዚህም መካከል


• የፀሐይ መጨለም፥
• የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ቦታ መቀደድ፥
• የዐለቶች መሰንጠቅ እና
• የሙታን መነሳት ይጠቀሳሉ።

ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የስቅለት ዓርብን ይህንን የጌታችንን መከራ በማሰብ


በጾም እና በሥግደት በልዩ ሥርዓትም ስትዘክረው ትውላላች። የጌታችን ጥንተ
ስቅለት ቀን መጋቢት ፳፯ ነው።

፳፬A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ሥዕል ፱ ፡ ጌታችንን ወደ መቃብር ሲያወርዱት

፳፭A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፪.፭ የጌታ ትንሣኤ


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት
ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በሥልጣኑ ከለየ በኋላ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ
ነፍሳትን ነጻ አውጥቷል። ቅዱስ ሥጋውንም የአርማትያሱ ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ
በበፍታ ገንዘው በአዲስ መቃብር አሳርፈውታል። ጌታችን አስቀድሞ እንደተናገረም
በሦስተኛው ቀን ሞትና መቃብርን ድል አድርጎ ተነሥቷል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
የጌታን ሕማማት ስታስብ ያሳለፈችውን የሐዘን ሳምንት ከዓርብ ማታ ጀምሮ እስከ
ትንሣኤው ድረስ ያለውን ጊዜ በደስታ ታከብረዋለች። ይህም ጌታችን በሲዖል ያሉ
ነፍሳትን ነጻ ማውጣቱን ዲያብሎስን ማባረሩን እና በሞቱ ሞትን ድል ማድረጉን
በመዘከር ነው። “እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና
እዩ።”ማቴ ፳፰፥፮
• “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ
በዚህ የለም።”ሉቃ ፳፬፥፭

ሥዕል ፲ ፡ የጌታችን ትንሣኤ

፳፮
A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፮ ዕርገቱና በዓለ ሃምሳ


፪.፮.፩ ዕርገቱ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ለአርባ ቀናት ያህል
ለሐዋርያት እየተገለጠላቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት እና ስለቤተ ክርስቲያን
ሥርዓት እያስተማራቸው ቆይቶ ከትንሣኤው በኋላ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ
አርጓል።
‘ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም
ቀኝ ተቀመጠ። ማር ፲፮፥፲፱

፪.፮.፪ መንፈስ ቅዱስን ስለመላኩ


ጌታችን ባረገበት ዕለት ለሐዋርያት ኃይልን የሚሠጥ አጽናኝ መንፈስ እንደሚልክላቸው
ቃል ገብቶላቸው ነበር እና ከሙታን ከተነሳ በ፶ኛው ካረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ
ቅዱስን ልኮላቸዋል። ይህም ዕለት በዓለ ሃምሳ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሁሉም
በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በእያንዳንዳቸው ላይ
ወረደ፤ ወንጌልን ለዓለም ይሰብኩ ዘንድ ኃይል እና ፅናትን የሚሰጥ መንፈስን
ተቀበሉ ብዙ ቋንቋ ተገለጠላቸው። ይህም በቋንቋ ልዩነት ምክንያት የክርስቶስን
ትምህርት ሕማም ብሎም የማዳን ሥራ ሳይሰሙ የሚቀሩ ሰዎች እንዳይኖሩ ነው።
• “ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው
ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።” የሐዋ ፪፥፮
• “እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?” የሐዋ ፪፥፰

፳፯A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ሥዕል ፲፩ ፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ

፪.፯ ዳግመኛ የሚመጣ ስለመሆኑና ስለ ትንሣኤ ሙታን


የጌታችን ዳግመኛ መምጣት ‘ዳግም ምጽአት’ ተብሎ በግእዝ የሚጠራ ሲሆን
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኋለኛው ዘመን በታላቅ መለኮታዊ ግርማ
በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በክብር ዙፋን ላይ ተቀምጦ በጻድቃን እና በኃጥአን ላይ
ለመፍረድ ይመጣል። የዚህች ዓለም ፍጻሜም ይሆናል። ስለ ዳግም ምጽአቱ ዕለት
ከፈጣሪ በቀር ማንም ማን የሚያውቅ እንደሌለ ጌታ ሐዋርያት ስለመምጣቱ እና
የዓለም መጨረሻ ዕለት በጠየቁት ሰዓት ነግሯቸዋል። በዚያን ጊዜ የሞቱ ሁሉ
ይነሣሉ ጻድቃንን በቀኝ ኃጥአንን በግራ ያቆማቸዋል። መልካም የሠሩ ‘እናንተ
የአባቴ ቡሩካን’ የሚል የሕይወት ቃል፥ ኃጢአትን ያደረጉ ደግሞ ‘እናንተ እርጉማን’
የሚል የወቀሳ ቃል ይደርስባቸዋል። መልካም የሠሩ የእግዚአብሔርን መንግሥት
ሲወርሱ ኃጥአን ግን ለዲያብሎስ እና ለጭፍሮቹ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም ይላካሉ።

፳፰A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

፪.፰ ሰውን ስለማዳኑ


አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፈው የፈጣሪያቸውን ቃል ከመስማት
ይልቅ የፍጡርን ቃል ሰምተው አትብሉ የተባለውን ዕፀ በለስ በመብላታቸው የሞት
ፍርድ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ተላለፈ። በነፃነት ይኖር ዘንድ የተፈጠረ የሰው ልጅ
ነፃነቱ ተገፈፈ የዲያብሎስ ባሪያ ሆነ። ይህን የሰው ልጅ ጉስቁልና የተመለከተ
እግዚአብሔር አምላካችን ከ5500 ዘመን በኋላ አንድ ልጁን ልኮ እንደሚያድነው
ለአዳም ቃል ገባለት። የሰው ልጅ ይህንን የተስፋ ቃል ሲጠባበቅ ቆይቶ ጊዜው
በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁን ከሰው ወገን ንጽሕት ድንግል ከምትሆን
ከድንግል ማርያም ይወለድ ዘንድ ወደ ምድር ላከው። ሰማያዊ ጌታ የሁሉ ገዢ
ሲሆን ይወለድበት ዘንድ ዓለም ሥፍራን ነሳችው። በበረት ውስጥ ተወለደ እንደሰው
ልጆች ተመላለሰ በ፴ ዘመኑ ተጠምቆ ልጅነትን የምናገኝባትን ጥምቀትን መሠረተ
የዕዳ ደብዳቤያችንን ደመሰሰ ሕማም እና መከራን ተቀብሎ በመስቀል ተቸነከረ
የመስቀልን ሞት ሞቶ ዲያብሎስን አስወገደ ሲኦልን በርብሮ ሞትና መቃብርን ድል
አደረገ። ከዚህም በኋላ እንደ ትእዛዙ ለኖሩ ሃይማኖታቸውን ለጠበቁ ዋጋቸውን
ይሰጥ ዘንድ በግርማ መለኮት ይመጣል።
- “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል
ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።” ራእይ ፳፪፥፲፩

የተግባር ልምምድ

ተማሪዎች በዚህ ምዕራፍ የተማራችሁትን ታሪክ ለቤተሰቦቻችሁ


ተናገሩ።

፳፱A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የክለሳ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል ካነበባችሁ በኋላ ትክክል የሆነውን
ዓረፍተ ነገር ‹‹እውነት›› ትክክል ያልሆነውን ዓረፍተ ነገር ‹‹ሐሰት››
በማለት መልሱ።

፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ያድን ዘንድ ያለ አባት


ተወለደ (ሰው ሆነ) ?
፪. ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት ሥፍራ ዮርዳኖስ ይባላል።
፫. ኢየሱስ ማለት አዳኝ መድኃኒት ማለት ነው።
፬. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ዳግመኛ ለፍርድ ይመጣል።
፭. ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ግዜ ፀሐይ ጨልማለች።

፴A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

የማጠቃለያ ጥያቄ
የሚከተሉትን ጥያቅዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።

፩.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሠራት መልአክ ስሙ ማን ነው?


ሀ. ቅዱስ ገብርኤል ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል
ለ. ቅዱስ ሚካኤል መ. ቅዱስ ራጉኤል
፪.ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠመቀው ማን ይባላል ?
ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ ሐ. ቅዱስ ጳውሎስ
ለ. ቅዱስ ዮሐንስ መ. ቅዱስ ማርቆስ
፫.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው በስንት
ዓመቷ ነው ?
ሀ. በ፲፪ ዓመቷ ሐ በ፫ ዓመቷ
ለ በ፲፭ ዓመቷ መ እንደተወለደች
፬.ጌታችን በመስቀል ሳለ የታዩ ምልክቶች
ሀ ዐለቶች ተሰነጣጠቁ ለ. ሙታን ተነሱ
ሐ. መጋረጃ ለሁለት ተሰነጠቀ መ› ሁሉም መልስ ነው።
፭.ማርያም ማለት
ሀ‹ መርህ ለመንግስተ ሰማያት ለ‹ ልዕልት
ሐ‹ የብዙሐን እናት መ. ሁሉም መልስ ነው።

በ “ሀ” ስር ያሉትን በ “ለ” ስር ካሉት ጋር በመስመር አዛምዱ።


ሀ ለ
፩. የአርብ ፍጥረት ሀ. እግዚአብሔር
፪. ፈጥሮ የሚገዛ ለ. ያማረ ፍጥረት
፫. መጸጸት ሐ. ዘላለማዊነት
፬. ሥነ-ፍጥረት መ. አዳም
፭. ሕያዉ ረ. ንስሓ መግባት

፴፩ A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት


መሠረተ ሃይማኖት ሁለተኛ ክፍል ነገረ ክርስቶስና ነገረ ሰብእ

ዋቢ መጻሕፍት
፩. መጽሐፍ ቅዱስ
፪. የኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ
፫. መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት
፬. ገድለ አዳም

፴፪A

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

You might also like