You are on page 1of 39

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ

በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ


በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቃውንት ጉባኤ
ተገምግመው
በድሬዳዋ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተዘጋጅቶ
በድሬዳዋ ባሉ አድባራት እና ገዳማት ሰንበት
ት/ቤቶች የሚዘመሩ የጥምቀት እና የምስጋና
መዝሙራት

ታኅሳስ ፳፻፲፫ ዓ/ም


የከተራ መዝሙር 28. በጎል በጎል 56. እንዘ ይብሉ

1. ኢየሱስ ሆረ 29. ዮሐንስኒ 57. የኪዳን ጽላት

2. ሖረ ኢየሱስ 30. የዓለምን በደል 58. ይዌድስዋ

3. ወረደ ወልድ 31. እሰይ እሰይ ተወለደ 59. በመኑ

4. እግዚኡ መርሐ 32. ከድንግል ተወልዶ 60. ጽላት ዘሙሴ

5. በወንጌሉ 33. የሰላሙ መሪ 61. ልዑል ውእቱ


34. በዛሬው ጥምቀቱ 62. ውእቱ ሊቆሙ
የጥምቀት አጫጭር መዝሙር 35. አስተርአየ ገሃደ 63. እሳት ጽርሁ
የልደት መዝሙር 64. መሰረተ ዜማ
6. ሶበ መጽአ ቃል 65. ተናገሩ
7. መጽአ ቃል 36. በኮከብ መጽኡ
66. ለሃገሪትነ
8. ሃዲጎ ተስዓ 37. በቤተልሔም ተወልደ
67. ክነፈ ርግብ
9. ሃሌ ሃሌሉያ 38. በጎል ሰከበ
68. ለእመ መሐርከነ
10. ውስተ ማኅፀነ ድንግል 39. አንፈርዐጹ
69. መንክር ግርማ
11. እንዘ ህጻን ልህቀ 40. ይኸው ተወለደ
የቃና ዘገሊላ መዝሙራት 70. አርሴማ ቅድስት
12. አማን በአማን 71. እርሱ እንደ ንብ
13. ዮሐንስኒ ሀሎ 41. በቃና ዘገሊላ 72. የወንጌል ቡቃያ
14. ዮሐንስ 42. ተዓምረ ወመንክረ 73. መድኃኔ ዓለም አዳነን
15. በእደ ዮሐንስ 43. እንዘ ስውር 74. ጊዮርጊስ ኃያል
16. ኧኸ ሃዲጎ ተስዓ የምስጋና አጫጭር 75. ከመ ትባርከነ
17. ወተመሰሉ
44. ንጉሥ ውእቱ ዘለዓለም 76. ገብረ መንፈስ ቅዱስ
18. በመንፈስ የሐውር
45. ንጉሥ ውእቱ 77. ክንፎ ጸለላ
19. በፍስሐ ወበሰላም
46. ሠራዊተ 78. ምስለ ሚካኤል
20. ኢየሱስ ክርስቶስ
47. ዘምሩ 79. ዓይኑ ዘርግብ
21. ነድ ለማየ ባሕር
48. እንተ በምድር 80. መሠረተ ሕይወት
22. ክርስቶስ ተወልደ 81. በበግማድ
49. እመቤታችን
23. ዮሐንስ ክቡር 82. ሶበ መተርዎ
50. ማርያም ተዓቢ
24. ርዕዩከ 83. ወአንተኒ ህጻን
51. ነይ ነይ ማርያም
የጥምቀት ረጃጅም መዝሙር 84. ኀበ ዓምደ ወርቅ
52. መልአከ ሰላምነ 85. ሰባኬ መድኃኒት
25. ጥምቀተ ባሕር 53. ጼና አልባሲሁ 86. ለዛቲ ቤት
26. ግነዩ ለእግዚአብሔር 54. ለተክለሃይማኖት ጻድቅ 87. ሐነጽዋ ለቤተክርስቲያን
27. ጥምቀት ሕይወት 55. ኢትዮጵያ ታበጽሕ 88. ያሬድ ፈልፈለ ማኅሌት
89. አቡነ ኪሮስ 119. ያሬድ ካህኑ 150. ጋሻውን ይዞ
90. ያሬድ ወጠንከ 120. የቅዱሳን በዓት 151. ትንሳኤሽን ያሳየን
ረጃጅም መዝሙር 121. ስምሽን ጠርቼ 152. ተዋሕዶ
91. የሥላሴን መንበር 122. ሥላሴን አመስግኑ 153. ዜና ማርቆስ
92. ኑ በእግዚአብሔር 123. ታማልደናለች 154. እመቤታችን ዋስ ጠበቃችን ነሽ
93. አምላክ ሰው ሆነ 124. ንሴብሖ ለሥላሴ 155. እመ አምላክ ሙሽራ ነሽ
94. እልል በሉ 125. አምላከ እስራኤል 156. ተነግሮ የማያልቅ ነው
95. ይለመነናል 126. አማልደን ስንልህ 157. የኢትዮጵያ አርበኛ
96. ንሴብሖ ለእግዚአብሔር 127. ሰዓሉ ለነ 158. በማኅፀን ቅኔ
97. ኦ ክርስቶስ 128. የቤሩቱ ኮከብ 159. ኦ ቅዱስ ዮሴፍ
98. አንደበቴም ያውጣ 129. ለዓለም ሰበኩ 160. ሶበ ሰማዕነ
99. ከክርስቶስ ፍቅር 130. የብርሃን አክሊል ናት 161. ገብርኤል ኃያል
100. ከወገኔ ጋራ 131. አንቺን የያዘ ሰው 162. የአርባብ አለቃ
101. የመስቀሉ ፍቅር 132. ናና ሚካኤል ናና 163. ዑራኤል ከበረ
102. ደስ ይበለን በጣም 133. ወደ ማደሪያው 164. ዑራኤል መልአከ ብርሃን
103. ደስ ይበለን 134. ማርያም እንወድሻለን 165. ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
104. ድንግል በድንግልና 135. ምሥራቅ ናት 166. ሰላም ለኢትዮጵያ
105. በምን በምን 136. ሞት ነው ረሃብ 167. ገባሬ መንክራት
106. ነይ ነይ 137. ወዳጄ ሆይ 168. ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
107. እመቤቴ የአምላክ እናት 138. ተክለሃይማኖት ተክለ አብ
108. ለማርያም 139. የሕይወትን መዝገብ
109. ትኅትናሽ 140. ውዳሴ ማርያም
110. በጎ መዓዛ 141. ቅዱስ ሚካኤል
111. በችግር ጊዜ 142. በዘባነ ኪሩብ
112. ነዓ ነዓ 143. የያሬድ ውብ ዜማ
113. የስሙ ትርጓሜ 144. ለምኚ ድንግል ለምኚ
114. እልፍ አዕላፋት 145. ቤተክርስቲያንን አንተውም
115. ጻድቃን ሰማዕታት 146. ደስ ይበልሽ
116. ኦ ፍጡነ ረድኤት 147. ይበራል በክንፉ
117. ገድሉ ታምራቱ 148. ኃያል ነህ አንተ
118. ጽኑ ሰማዕት 149. የፍቅር እናት
1. ኢየሱስ ሖረ 7. መጽአ ቃል

ኢየሱስ ሖረ ሀገረ እሴይ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዘይብል(፪)


ዮሐንስ አጥመቆ በማይ (፪) ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር(፪)
መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል(፪)
2. ሖረ ኢየሱስ የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው(፪)

ሖረ ኢየሱስ (፪) 8. ኀዲጎ ተስዓ


እምገሊላ (፫) ኀበ ዮሐንስ
ኀዲጎ ተስዓ ወተስዓተ ነገደ(፪)
ሔደ ኢየሱስ(፪)
ማዕከለ ባሕር (፬) ቆመ ማዕከለ ባሕር(፪)
ከገሊላ(፫) ወደ ዮሐንስ
ትርጉም፡ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላዕክት ትቶ
3. ወረደ ወልድ
በባሕር መካከል ቆመ
ወረደ ወልድ (3)
9. ሃሌ ሉያ
እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት
ሃሌ(፫) ሉያ ሃሌ (፪) ሉያ ሃሌ ሉያ
ትርጉም፡ወልድ ክርስቶስ ሊጠመቅ
ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ
ወደ ወንዝ ወረደ
ሃሌ(፫) ሉያ ሃሌ (፪) ሉያ ሃሌ ሉያ
4. እግዚኡ መርሐ አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደትህ
አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖሰ አብጽሐ
ወበሕየ ዮሐንስ ወበሕየ ፍፁመ ተፈስሐ ትርጉም፡የነበረ በማዕከለ ዓለም ያለ ዓለምን አሳልፎ
የሚኖር ሰማያዊ ክርስቶስ በምድራዊ እጅ ተጠመቀ
ጌታውን መራና ከዮርዳኖስ አደረሰው
በዚህም ዮሐንስ በዚህም በፍጹም ደስ አለው 10. ውስተ ማኅፀነ

5. በወንጌሉ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ማኅፀነ ድንግል


ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ(፪)በማይ ተጠምቀ
በወንጌሉ ያመናችሁ (2)
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳቹሁ (2) ትርጉም፡ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ
በእመቤታችን ማህጸን አደረ በውሃም ተጠመቀ
6. ሶበ መጽአ ቃል
11. እንዘ ህፃን
ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ
ከበቦ(፫) ለማየ ባሕር ነድ ለማይ ከበቦ(፬) እንዘ ህፃን ልህቀ በዮርዳኖስ ተጠምቀ(፪)
በዮርዳኖስ(፬) ተጠምቀ በዮሐንስ(፪)
ትርጉም፡ቃል ከሰማይ ለመናገር በመጣ ጊዜ እሳት
የዮርዳኖስን ባሕር ከበበው ውኃውም የሚሄድበት ትርጉም፡እንደ ህፃን ሆኖ በትንሽ ትንሹ አደገ
ቦታ ጠበበው በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ ተጠመቀ
12. አማን በአማን 18. በመንፈሰ የሐውር

አማን በአማን(፪) በመንፈስ የሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል


መንክር ስብሐተ ልደቱ ካህን ካህን ወነቢይ(፪) ዮሐንስ መጥምቅ
አማን በአማን(፪)
ትርጉም፡ካህን ነቢይ የሆነ ዮሐንስ መጥምቅ ከኃይል
መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ
ወደ ኃይል በመንፈስ ይሸጋገራል
ትርጉም፡እውነት በእውነት የክርስቶስ መወለድ
19. በፍስሐ ወበሰላም
መጠመቅ አስደናቂ ነው
በፍስሐ (፪) ወበሰላም
13. ዮሐንስኒ ሀሎ
ወረደ ወልድ ወልድ ውስተ ምጥማቃት
ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ
20. ኢየሱስ ክርስቶስ
በሄኖን በቅሩበ ሳሌም
ኢየሱስ ክርስቶስ ይወደናል ይጠብቀናል
ትርጉም፡ዮሐንስ በዮርዳኖስ አቅራቢያ
በጥምቀቱ ልጅነት ሰጥቶናል(፪)
በዮርዳኖስ ያጠምቅ ነበር
21. ነድ ለማየ ባሕር
14. ዮሐንስ
ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ
ዮሐንስ(፪) አጥመቆ ለኢየሱስ
ማየ ባሕር ኅበ የሐውር ጸበቦ (፪)
በፈለገ ዮርዳኖስ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ
22. ክርስቶስ ተወልደ
15. በእደ ዮሐንስ
ክርስቶስ ተወልደ እሰይ
በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ
ክርስቶስ ተጠምቀ በማይ
ሰማያዊ (፭) ኢየሱስ ናዝራዊ
ወለደነ ዳግመ እምማይ(፪) ዳግመ(፪)
16. ኧኸ ኀዲጎ ወለደነ ዳግመ እምማይ

ኧኸ ኀዲጎ ተስዓ ኧኸ ወተስዓተ ነገደ ትርጉም፡እሰይ ክርስቶስ ተወለደ እሰይ ክርስቶስ በውሃ
ኧኸ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር ተጠምቆ ዳግመኛ በመንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ወለደን

17. ወተመሰሉ 23. ዮሐንስ ክቡር

ወተመሰሉ ሰብአ ዐይን አባግዐ ላባ ወማይ ዮሐንስ ክቡር ነቢየ ልዑል


ለኀበ አባግዕ (፬) ዘዮም(፪) ወጥምቀት ዐባይ ብእሴ ሰላም (፬) ዘንብረቱ ንብረቱ ገዳም (፪)

ትርጉም፡ውኃን የጠጡ የላባ በጎች ምልክትን አይተው አንድ ትርጉም ፡ የከበረው የልዑል ነቢይ ዮሐንስ ሆይ
እንደሆኑ በጥምቀት አንድሆኑ ለተባሉ ለዛሬዎቹ ምዕመናን መኖሪያው በገዳም የሆነ የሰላም ሰው ነው
ምሳሌ ሆኑ
24. ርዕዩከ የድኩማኖች ብርታት ነው የህሙማን ፈውስ(፪)
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ
ርዕዩከ ማያት እግዚኦ ርዕዩከ ማያት ወፈርሁ(፪)
በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን (፪)
ደንገጹ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ (፬)ኧኸ
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ
አቤቱ ውኆች አዩህ ውኆችም አይተው ፈሩህ (፪)
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ(፪)
ጥልቆችም ተነዋወጡ ውኆችም ጮኹ (፬) ኧኸ
ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ
25. ጥምቀተ ባሕር ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ(፪)
እመቤታችን እናታችን ማርያም
ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ(፪)
የተማጸነሽ ይኖራል ለዘለዓለም(፪)
ሃሌ ሉያ(፬)
ድንግልናሽም ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ
ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች የጌታችን እናት ማርያም ንፅሕት አንቺ ነሽ(፪)
አልችለውም ብላ ወደ ፊት ሸሸች
27. ጥምቀት ሕይወት
ብርሃነ መለኮት በውስጡ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ ጥምቀት ጥምቀት ሕይወት መግቢያ ለገነት
በጥምቀት እንመካለን እንድንበታለን
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ አዝ…
ለልጁ ምስክር ሊሰጥ ፈለገና
በአርባ በሰማንያ ጥምቀት ሕይወት የተጠመቅነው ››
አብም ተናገረ ሆኖ በደመና
ከእግዚአብሔር ልጅነት ›› ›› እንድናገኝ ነው ››
ጌታችን ሲጠመቅ በሠላሳ ዓመት ልጅነት ከሌለ ›› ›› መወለድ በጥምቀት ›› ››
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት ፍጹም አትገኝም ›› ›› የዘለዓለም ሕይወት ››
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
አዝ…
ምሥጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ
በእደ ዮሐንስ ጥምቀት ሕይወት የተጠመቀው ››
እልል በይ ዮርዳኖስ የጽድቅ መገኛ
እንዳይመስለን ፍጡር ›› ወልደ እግዚአብሔር ነው ››
የሕይወት መሰላል ድኅነታችን ለኛ
ዮሐንስ ሲያጠምቀው ›› ›› ሲጠመቅ ክርስቶስ ››
ቀላያት አብርሕት ብዙዎች እያሉ
ዓለም ተቀደሰ ›› ›› ተመታ ዲያብሎስ ›› ››
እንደ ምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ
አዝ…
26. ግነዩ ለእግዚአብሔር
ዮሐንስ እንዲያጠምቅ ጥምቀት ሕይወት ስለፈቀደለት ››
ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር
በደመና ሆኖ ›› ›› አብ መሰከረለት ›› ››
እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም(፪)
መንፈስ ቅዱስ ታየ ›› ›› አረፈ ከአናቱ ›› ››
እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ
ምሥጢረ ሥላሴ ›› ›› ይሔ ነው ትምህርቱ ›› ››
የዓለም ቤዛ ነውና የማሕፀንሽ ፍሬ(፪)
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ካንች ተወልዶ አዝ…
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ(፪)
በድንግልና የወለድሽው ክርስቶስ
ጥንቃቄ አድርገን ጥምቀት ሕይወት ስቶ ከሚያስተን ›› ከኃጢአት ተለዩ ያጠምቅ በውሃ ተጠመቁ ››
መመርመር አለብን ›› ›› ምሥጢረ ጥምቀትን ›› መንግስተ ሰማያት ›› እንዳለች እወቁ ››
ጥምቀት መወለድ ነው ›› ›› እንዳይመስለን ተርታ ››
አዝ…
ወደ ገነት መግቢያ ›› ›› ጋሻ ነው መከታ ››
አምላኩን የሚወድ ያጠምቅ ብዙ ሰው እያለ ››
አዝ…
ጌታውን ለማጥመቅ ›› ዮሐንስ ታደለ ››
ከባሕሮች ሁሉ ጥምቀት ሕይወት ዮርዳኖስ ታደለች ››
አዝ…
በምሥጢረ ጥምቀት ›› ›› ተቀድሳ ዋለች ››
ክርስቶስ ሲጠመቅ ›› ›› ለኛ ተወልዶልን ›› ›› ኮረብታው ይደልደል ያጠምቅ ጠማማውም ይቅና ››
ተደምስሶ ጠፋ ›› ›› ዕዳ በደላችን ›› ›› እያለ የሰበከ ›› እራሱ ነውና ››

28. በጎል በጎል 30. የዓለምን በደል

በጎል በጎል ሰብአ ሰገል(፪) የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ


በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ (፪) ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
ፀሐይ ፀሐይ ፀሐይ ሠረቀ(፪) ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ
ፀሐይ ሠረቀ ክርስቶስ ተጠምቀ(፪)
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ(፪)
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
የእግዚአብሔር መንፈስ ከላይ ወርዶብሽ
የዓለም መድኃኒት ተጠመቀብሽ የሰማዩ ሰማይ የማይችለው ንጉሥ
ድንግል ማርያም ንጽሕት ቅድስት (፪) ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደፈረስ
ከሴቶች ሁሉ በአንቺ አድሮብሻል
ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
እልል እልል ደስ ይበለን (፪)
ዮርዳኖስ ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
ወልድ ተወልዶ ነፃ አወጣን
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
ዮሐንስ አጥምቆ ድል አገኘን(፪)

29. ዮሐንስኒ እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ


መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
ዮሐንስኒ ያጠምቅ(፪) በርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ
በሔኖን(፬) በማዕዶተ ዮርዳኖስ
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሰርት
አዝ… መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
ዮሐንስ ሲያስተምር ያጠምቅ በጫካ በሜዳ ››
ግመል ጸጉር ለብሶ ›› ሆኖ ምድረ በዳ ›› ባሕር ስትጨነቅ ተራራው ሲዘምር
ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር
አዝ…
ዓለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምሥጢር
31. እሰይ እሰይ ቸሩ አምላካችን መድኃኔ ዓለምን
ኑ እናመስግነው በአንድነት ሆነን
እሰይ እሰይ ተወለደ እሰይ እሰይ ተጠመቀ
ከሰማየ ሰማያት ወረደ(፪) 33. የሰላሙ መሪ
ከድንግል ማርያም ተወለደ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ የሰላም የሰላሙ ዳኛ
አዝ… መድኅን ተወለደ ተጠመቀ ላኛ (2)
አዳምን ሊጠራ የመጣ ሙሽራ (2)
እርሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ ቸሩ አምላካችን ›› ››
በገሊላ መንደር ለሰርግ ተጠራ (2)
እርሱ ባይጠመቅ ›› ›› መድኃኒታችን ›› ››
ሰርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ (2)
መች ትገኝ ነበረ ›› ›› ገነት ርስታችን ›› ››
የወይን ጠጅ ሆነ ውሃው ተለውጦ (2)
አዝ… አዲሱ ሙሽራ ሲመጣ እያያችሁ (2)
የዮርዳኖስ ምንጮች ስለምን ሸሻችሁ (2)
ብርሃን ወጣላቸው እሰይ እሰይ ለእውነት ወገኖቹ ›› ››
እናንተ ተራሮች እግር ሳይኖራችሁ (2)
በጨለማ መንገድ ›› ›› እንዲያ ሲሰላቹ ›› ››
እንዴት እንደ ጊደር ሽቅብ ዘለላችሁ (2)
አዝ… ድንግል ማርያም ያስገኘችው ፍሬ (2)
ሕዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ (2)
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ አንድያ ልጁን ››
የዛሬው ጥምቀት ተነግሮ ባዋጅ (2)
እርሱ ወዷልና ›› ›› እንዲሁ ዓለሙን ››
ነፃነት አገኘን በእግዚአብሔር አብ ልጅ (2)
አዝ… 34. በዛሬው ጥምቀቱ
እንደጠል ወረደ እሰይ እሰይ ከሰማይ ወደእኛ ›› በዛሬው ጥምቀቱ እሰይ እሰይ ተነግሮ በአዋጅ ›› ››
ወገኖቹን ሊያድን ›› ›› ከኃጢያት ቁራኛ ›› ነጻነት አገኘን ›› ›› በእግዚአብሔር አብ ልጅ ›› ››
32. ከድንግል ተወልዶ እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ተጠመቀ ኢየሱስ ባሕረ ዮርዳኖስ በቅዱስ ዮሐንስ ተጠመቀ

መጥምቁ ዮሐንስ ምንኛ ታደለ አዝ..


ከነቢያት ሁሉ ስልጣኑ ከፍ አለ
አብ መሰከረለት እሰይ እሰይ በደመና ሳለ ›› ››
ትንቢቱን ሊፈጽም አስቦ ክርስቶስ የምወደው ልጄ ›› ›› ይኼ ነው እያለ ›› ››
ተጠምቆ አዳነን በባሕረ ዮርዳኖስ
አዝ…
ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዛን ለታ
ጌታ በዮርዳኖስ እሰይ እሰይ ሊጠመቅ ሲል ገና ›› ››
ምን ይከፈለዋል ለአምላክ ውለታ
ወደ ኋላ ሸሸ ›› ›› ዮርዳኖስ ፈራና ›› ››
እናታችን ማርያም ምንኛ ታደልሽ
አዝ..
ከአዳም ልጆች አንቺ ተመረጥሽ
እንደ አንበሳ ደቦል እሰይ እሰይ ተራሮች ዘለሉ ›› ›› ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው (3)
ዕፁብ ነው ድንቅ ነው ›› ›› ግሩም ነው እያሉ ›› ›› ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩት ሰግደው (3)

35. አስተርአየ ገሐደ ህፃናት እንሒድ ከልደቱ ቤት (3)


ውሃ ሆኗልና ማር ና ወተት (3)
አስተርአየ ገሃደ (፪)
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ (፪) በሶሪያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ (3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ (3)
36. በኮከብ መጽኡ
41. እንዘ ስውር
በኮከብ መጽኡ (2) ሰብአ ሰገል
ኧኸ ለአማኑኤል (4) ይስግዱ ሰብአ ሰገል እንዘ ስውር እምኔነ ይእዜሰ ክሱተ ኮነ
ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ
ትርጉም ፡ የጥበብ ሰዎች ለአማኑኤል ይሰግዱ ዘንድ
በቃና እኸ(፪) ዘገሊላ ከብካብ ኮነ
በኮከብ እየተመሩ መጡ
ትርጉም፡ጌታችን መድኃኒታችን ከእኛ ተሰውሮ የነበረው
37. በቤተልሔም ተወልደ
አሁን ተገለጠ በቃና ገሊላ ተአምራትን አደረገ
በቤተልሔም ተወልደ (2) አማኑኤል
42. በቃና ዘገሊላ
እምዘርዓ ዳዊት (4) ተወልደ አማኑኤል
በቃና ዘገሊላ
38. በጎል ሰከበ
ዘገሊላ ከብካብ ኮነ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ
43. ማየ ረሰየ ወይነ
ቤዛ ኵሉ ዓለም (2) ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቀለለ ተአምረ ወመንክረ በቃና ዘገሊላ (፪)
የዓለም መድኃኒት (2) ዛሬ ተወለደ ማየ ረሰየ ወይነ(፪)

39. አንፈርአፁ ለምን ትሸሻለሽ አንች ዮርዳኖስ


ወዳንች ሲመጣ የክብርሽ ንጉሥ
አንፈርአፁ ሰብአ ሰገል ረኪቦሙ ህፃነ (2)
ማየ ረሰየ ወይነ
ዘተወልደ ለነ (4) ህፃነ ዘተወልደ ለነ
የዲያብሎስ መዝገብ ከፊትሽ ሲጠፋ
40. እሰይ ተወለደ
በመንግስተ ሰማይ ክብራችን ተስፋፋ
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት ማየ ረሰየ ወይነ
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት
በአንዲት ዕፀበለስ የወጣው አዳም
ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ (3) ተደመሰሰለት የባርነት ስም
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ (3) ማየ ረሰየ ወይነ

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ (3)


የእስራኤል ንጉስ ተወልዷል እያሉ (3)
ሥጋን የለበሰው የማርያም ልጅ 48. እንተ በምድር
ውሃውን ለወጠው ወደ ወይን ጠጅ
እንተ በምድር ስረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ
ማየ ረሰየ ወይነ ሐረገወይን (፪) ድንግል ሐረገወይን
ስሮቿ ያሉ በምድር ቅርጫፎቿ በሰማይ
ከእንግዲህ የማን ልጅ ትሆናለህ ድሃ
የወይን ሐረግ (፪) ድንግል የወይን ሐረግ
መርገምህ ተሽሯል በዮርዳኖስ ውሃ
ማየ ረሰየ ወይነ 49. እመቤታችን ማርያም

እመቤታችን ማርያም ሃገራችንን ጠብቂልን በምልጃሽ


መንፈቅ የምትበልጠው ሕያው ክርስቶስን
ከመናፍቃን ከከሃድያን ከጠላት ሰይጣን ሰውረሽ
በጣም አከበረህ አንተን ዮሐንስን
እንድትጠብቂን በምልጃሽ
ማየ ረሰየ ወይነ

ልብስህ ፀጉር ቢሆን ምግብህም አንቦጣ 50. ማርያም ተዓቢ


እንዳንተ የከበረ ከየትም አልመጣ
ማርያም ተዓቢ እምኵሉ ፍጥረት
ማየ ረሰየ ወይነ ኢያውዓያ እሳተ መለኮት (2)
ማርያም ትበልጣለች ከሁሉ ፍጥረት
የአምላክነት ስራው እጅግ የረቀቀ
አላቃጠላትም የመለኮት እሳት (2)
በገሊላ አውራጃ በቃና ታወቀ
ማየ ረሰየ ወይነ 51. ነይ ነይ ማርያም

አጫጭር የምስጋና መዝሙር ነይ ነይ ማርያም ወላዲተ አምላክ


የጻድቃን እመቤት የመላእክት እኅት
44. ንጉሥ ውእቱ ሁላችሁ እመኗት ከልብ አማላጅ ናትና በእውነት
እናወድሳት እናመስግናት አማላጅ ኪዳነ ምሕረት
ንጉሥ ውእቱ ንጉሠ ሰላም
አምላክነ (፪) መድኃኔዓለም 52. መልአከ ሰላምነ

45. ንጉሥ ውእቱ ዘለዓለም መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል


ሰዓል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ
ንጉሥ ውእቱ ዘለዓለም ክርስቶስ
ቅድመ መንበሩ ለመድኃኔዓለም
ንጉሥ ውእቱ ዘኢይሰዓር መንግሥቱ (2)
53. ጼና አልባሲሁ
46. ሠራዊተ መላእክቲሁ
ጼና አልባሲሁ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ከመ ጼና ስሂን
ሠራዊተ መላእክቲሁ
አልባሲሁ ዘሜላት (2) ዘወረደ ውስተ ገነት
ለመድኃኔ ዓለም (፪) ይቀውሙ (፪)
የመድኃኔ ዓለም አገልጋዮቹ 54. ለተክለ ሃይማኖት ጻድቅ
ይቆማሉ ከፊቱ (፪) አገልጋዮቹ (፪)
ለተክለ ሃይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝኃ ሕማሙ
47. ዘምሩ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ (፪) እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ስጋሁ ወአጽሙ
ዘምሩ ለንጉሥነ ዘምሩ (፪) ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ
እምነ አድባራት ኵሉን ዘተለዓለት በስሙ
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ
ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ 62. ውእቱ ሊቆሙ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ
ውእቱ ሊቆሙ ለመላእክት
ወመልአኮሙ ስሙ ሚካኤል
55. ኢትዮጽያ ታበጽሕ
ልብሱ ዘመብረቅ ዓይኑ ዘርግብ ሊቀ መላእከት
ኢትዮጽያ ታበጽሕ እደዊሃ (2) ሀበ እግዚአብሔር
63. እሳት ጽሩህ
እንዘ ትብል አምላኪየ (2) ነጽረኒ
ወአድኅነኒ አምኃይለ ጸላኢ ወፀር እሳት ጽርሁ ማይ ጠፈሩ (2)
ደመና መንኰራኵሩ ለመድኃኔ ዓለም (2)

64. መሠረተ ዜማ
56. አንዘ ይብሉ
መሠረተ ዜማ ወጠነ (2) ያሬድ ካህን
እንዘ ይብሉ ወይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም
ያሬድ (3) ያሬድ ካህን (2) ጥዑመ ልሳን
አማን በአማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም (2)
65. ተናገሩ
57. የኪዳን ጽላት
ተናገሩ ድንቅ ሥራውንም መስክሩ
የኪዳን ጽላት የተሰወረ መና ያለብሽ
ተአምሩን ለዓለም ንገሩ (2) ድንቅ ሥራውን መስክሩ
ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ (2)
ይኸውም መና (2) የተባለው 66. ለሃገሪትነ
በድንግል ማርያም ያደረው
የእግዚአብሔር አብ ልጁ ነው ለሃገሪትነ ሰላማ ኪያከ ተዓቀብ
አባ ኦ አባ (2) ገብረ መንፈስ ቅዱስ (2) አባ
58. ይዌድስዋ
67. ክነፈ ርግብ
ይዌድስዋ መላእክት (2) ለማርያም
በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ (2)
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አማን በአማን
59. በመኑ በአምሳለ መኑ አማን በአማን (2) ኢየኃልቅ ኪዳንኪ ወላዲተ አምላክ
በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ እንደ ርግብ ክንፍ በብርም እንደተሰራ
እመቤቴ የእኛ አማላጅ አዛኝቱ ጎኖችሽም ሐመልማለ ወርቅ (2)
ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ አንቺ ምሥራቅ ልጅሽም የጽድቅ ፀሐይ ነው እውነት በእውነት
60. ጽላት ዘሙሴ እውነት በእውነት (2) አያልቅም ቃል ኪዳንሽ የአምላክ እናት

68. ለእመ መሐርከነ


ጽላት ዘሙሴ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና
ጸናጽል (2) ጸናጽል ለአሮን ካህን ለእመ መሐርከነ ትሰመይ መሐሬ መድኃኔ ዓለም
61. ልዑለ ውእቱ ወለጻድቃንሰ እምግባሮሙ ትሜሕሮሙ ለጻድቃን

69. መንክር ግርማ


ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር (2)
ሚካኤል (2) ሊቀ መላእክት (2) መንክር ግርማ ኃይለ ልዑል ጸለላ
አማን አማን መላእክት ይዌድስዋ (2)
በሚያስድንቅ ግርማ የልዑል ኃይል ጋረዳት ክንፎ ጸለላ (3)
በእውነት በእውነት መላእክት አመሰገኗት (2) ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ (2)
ክንፉን ጋረዳት /3/
70. አርሴማ ቅድስት
ደስ ይበልሽ ድንግል ሆይ እያላት/2/
አርሴማ ቅድስት (3)
78. ምስለ ሚካኤል
ሰማዕት (2) አርሴማ ቅድስት
ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል ንዒ ሠናይትየ ማርያም
ንዒ (6) እመአምላክ ንዒ ማርያም
71. እርሱ እንደ ንብ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋራ የአምላክ እናት ነይ ማርያም
ነይ (6) የአምላክ እናት ነይ ማርያም
እርሱ እንደ ንብ አውራ ፈረሱ እንደ አሞራ
ጊዮርጊስ (2) ኢትዮጽያን አደራ (2) 79. ዓይኑ ዘርግብ

72. መድኃኔዓለም አዳነን ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ


ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ (2)
መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ 80. መሠረተ ሕይወት
ደስ ይበለን (2) እልል በሉ (2) አዳነን በማይሻር ቃሉ
እናታችን ቅድስት የአምላክ እናት መሠረት ሕይወት ማርያም በረድኤት ነይ
እንስገድላት (2) እንስገድ (2) በእውነት ለአምላክ እናት ምሕረት ቸርነትን ይዘሽ ከሰማይ (2)
ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ ማርያም ድንግል በረድኤት ነይ
ያማልዱናል (2) መላእክት (2) በእውነት በላየኛው ቤት 81. በበ ግማድ
ተዋሕዶ ሃይማኖት እንከን የሌላት
እንከተላት (2) እስከሞት (2) በእውነት ያለ ፍርሐት በበ ግማድ ሥጋሁ መተሩ /3/
ቅዱስ (3) ጊዮርጊስ ሞዖሙ ለፀሩ
73. ጊዮርጊስ ኃያል
82. ሶበ መተርዎ
ጊዮርጊስ ኃያል (2) መስተጋድል
ሶበ መተርዎ ለጊዮርጊስ ፀሐይ/2/ ጸልመ
ገባሬ ተአምር ኮከበ ክብር (2)
አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ /2/ ዬ ዬ ዬ
74. ከመ ትባርከነ 83. ወአንተኒ ሕፃን

ከመ ትባርከነ በመስቀልከ ዘወርቅ (2) ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል፣


ተዋነይ በጽድቅ (4) ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ ዐርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ /2/ ነቢየ ልዑል
84. ኀበ ዐምደ ወርቅ
75. ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው ኀበ ዐምደ ወርቅ (3)


ይኸው ለዘለዓለም ያበራል ስራቸው (2) ተጽሕፈ ስሙ /2/ እስጢፋኖስ ኀበ ዐምደ ወርቅ
85. ሰባኬ መድኀኒት
76. ሚካኤል ሊቅ ሰባኬ መድኀኒት ጎርጎርዮስ አቡነ
ጸሎትከ ትኩነነ ፀወነ
ሚካኤል ሊቅ ልብሱ ዘመብረቅ
ዓይኑ ዘርግብ (4) ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
86. ለዛቲ ቤት
77. ክንፎ ጸለላ ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ለዛቲ ቤት ሐነጻ ወልድ
ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ (2)
87. ሐነጽዋ ለቤተ ክርስቲያን 92. ኑ በእግዚአብሔር
ሐነጽዋ ለቤተ ክርስቲያን፣ ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን (2)
እንተ ተሐንጸት በእደ ካህናት ወተቀደሰት በአፈ ጳጳሳት
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ወተጠምቀት በማይ ዘውኅዘ እምገቦሁ አመ ሕማማቲሁ
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
88. ያሬድ ፈልፈለ ማኅሌት ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን

የሰማዩን መንግስት ርስቱን ለሰጠን


ያሬድ ፈልፈለ ማኅሌት ወቅኔያት ወባሕረ ጥበባት፣
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
እስመ ኮንከ መርሐ ለዘምሮ ለኢትዮጵያ
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
ያሬድ ካህን /2/ ጥዑመ ልሳን
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
89. አቡነ ኪሮስ
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
አቡነ ኪሮስ የአምላክ ባለሟል ቅዱስ ናቸው ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ይኸው ለዘለዓለም ያበራል ሥራቸው ያበራል ይኸው ፍቅርህ የበዛ ነው ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላወድሰው ከጠዋት እስከ ማታ
90. ያሬድ ወጠንከ
በቃዴስ በርሃ ምንም በሌለበት
ያሬድ ወጠንከ ነቢበ አንቀጸ ብርሃን በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
አንቀጸ ብርሃን (5) ወጠንከ አንቀጸ ብርሃን ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት

በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም


91. የሥላሴን መንበር ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ያጣነውን ሠላም ዛሬ አገኘን
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
ድንግል ከመሐል ሚካኤልን ከፊት የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
አዕላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት በእግዚብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት ለምኝልን ለእኛ ኪዳነ ምሕረት
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት 93. አምላክ ሰው ሆነ
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ (3) ሲሉ አምላክ ሰው ሆነ ሰው ሆነ (2)
ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ በድንግል ማርያም ተከናወነ
በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ (2)
የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የቅዱሳን ሕብረት የቅዱሳን ሃገር
የመንፈስ ቅዱስ ፅርሐ ቤቱ
ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን መንበር
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ጽድቅና ርኅራኄ የተሞላ ሰማይ
እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ (3) ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስ ቅዱስ ነው (2) የጸለለሽ
ከሦስቱ አካል ወልደ አምላክ ቃል አብርሃም ይሳስሐቅን ያዕቆብን አስበህ
መጣ ወረደ በገባው ቃል የማልክላቸውን ቃል ኪዳን አስታውሰህ
ተፀንሶ ሳለ ወልድም ከእናቱ ደካማ ለሆንን ሥጋ ሰልጥኖብን
አትመልስ ጌታ የምሕረት ዓይንህን
አልተነጠለም ከሦስትነቱ
ከሰማያት ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን/2/
ተዓምራት አድርጓል ድውይ ፈውሷል በአምላክነቱ
እንዘን እናልቅስ ስለበደላችን/2/
ይህንን ምሥጢር በሉ ግሩም ባይመለከተን አምላከ አብርሃም
ምስጋና አቅርቡ ለዘለዓለም በምሕረት አይኖቹ መድኃኔዓለም
በሥነ ፍጥረት ይታወቃል ባይዘረጋልን አምላከ አብርሃም
የዓለም ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል የፍቅር እጆቹ መድኃኔዓለም
ደስ ይበላችሁ ደስ ይበለን እንበል እልል ሕዝበ እስራኤል ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ
94. እልል በሉ አድኖናልና በሚያስደንቅ ፍቅሩ (2)

እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ ምንም እንኳን ክህደት ቅስፈት ቢበረታ


አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት ስለ አብርሃም ብለህ አልተውከንም ጌታ
እንደ እግዚአብሐር ያለ ማንም የለም በሉ ለቅዱሳን ያለህ ቃልኪዳን ሲጸና
ቀስተ ደመናህን አይተነዋልና
በኃጢአት ባርነት ስንኖር ተገዝተን የእስራኤል አምላክ የማታንቀላፋ/2/
ከቤቱ ስንርቅ ትዕዛዙን አፍርሰን በፍቅርህ ታደገን በሞት ሳንጠፋ /2/
አይቶ ዝም ላለ ጠላቶቹ ሳለን
ውለታው ብዙ ነው ክብር ለእርሱ ይሁን (2) ቃልኪዳንህ ግሩም አምላከ አብርሃም
ምሕረቱ የበዛ መድኃኔዓለም
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን ርስት ጉልታችን አምላከ አብርሃም
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን የህይወታችን ቤዛ መድኃኔዓለም
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም ሳይጸየፍ ጌታ ያደፈ ኃጢአቴን/2/
ምሥጋና ይድረሰው ለመድኃኔ ዓለም (2) ከማጥ ውስጥ አወጣት ታደጋት ሕይወቴን (2)

ሕይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ 96. ንሴብሖ ለእግዚአብሔር


ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ ንሴብሖ (2) ለእግዚአብአብሔር
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋራ (2) ስቡሐ ዘተሰብሐ (2)

ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን እናመስግነው (2)


ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን ምሥጉን ነው የተመሰገነ (2)
ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ (2) ባሕሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የእኛ ሆነ
95. ይለመነናል
ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ወጣን
ይለመነናል አምላከ አብርሃም ሕይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን
ይታደገናል መድኃኔ ዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ ከአለት ላይ ውኃ ፈልቆ የጠጣነው
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ (2) ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግነው
ሕዝቦች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል ሐዋርያት ሁሉ ክረስቶስ ዞረው ያስተማሩት ›› ››
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል ወንጌልህ ብርሃን ነው ›› ›› የዓለም መድኃኒት ›› ››
ዮሐንስ እንዳለ ›› ›› ጥምቀት ለንስሐ ›› ››
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ተጠምቄዋለሁ የጎንህን ውኃ
ሁሉን አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራው ቢበዛ አዝ…
ኃይላችን ጌታ የዓለሙ ቤዛ
ሚካኤል በቀኝህ ክርስቶስ ገብርኤል በግራ ›› ››
97. ኦ ክርስቶስ ቅውማን የሆኑት ›› ›› ሁሉም በየተራ ›› ››
ሱራፌል ኪሩቤል ›› ›› ዓይናቸው የበዛ ›› ››
ኦ ክርስቶስ ኦ አምላክ ብሩህ ነህ
ያመሰግኑሃል አንተን የዓለም ቤዛ
ልቦናዬን አብራው በጥዑም ቃልህ
98. አንደበቴም ያውጣ
አዝ…
አንደበቴም ያውጣ የምሥጋና ቅኔ
የታቦር ተራራ ክርስቶስ የሲና ልምላሜ ›› ››
የአምላኬን ማዳን አይቻለው በዓይኔ
ምነው ሙሴ በሆንኩ ›› ›› አንዳይህ ደግሜ ›› ››
በገባዖን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
የዮርዳኖስ ውኃ ›› ›› በላይህ ሲፈላ ›› ››
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
ዮሐንስን በሆንኩ እንዳይ በተድላ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
አዝ…
ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
ነበልባል ሐመልማል ክርስቶስ ተዋህዶ ሲና ›› ›› የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ
ሙሴ ከሩቅ ሆኖ ›› ›› ተመልክቷልና ›› ›› የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋር
በቀረበ ጊዜ ›› ›› ነገሩን ሊረዳ ›› ››
በዳዊት ምሥጋና በያሬድ ዝማሬ
ለእስራኤል ሾምከው ሁሉን እንዳይጎዳ
ከቅዱሳን ጋራ ስዘምር አብሬ
አዝ… እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ
ሙሴ በበትሩ ክርስቶስ ኤርትራን ሲመታ ›› ››
ተሻገሩ እስራኤል ›› ›› በፍጹም ደስታ ›› ›› አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ያልተደሰቱማ ›› ›› የፈርኦን ሠራዊት ›› ›› ለጣዖት እንድሰግድ ነገስታት ቢያውጁም
እየተሰጠሙ ቀሩ ወደ ኋሊት ሁሉም ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድኃኔዓለም
አዝ…
99. ከክርስቶስ ፍቅር
ትንቢቱ ደረሰ ክርስቶስ የኢሳይያስ ›› ››
ድንግልም ወለደች ›› ›› በመንፈስ ቅዱስ ›› ›› ከክርስቶስ በፍቅር የሚለየኝ ማነው (2)
ምነው ባደረገኝ ›› ›› እንደነ ሰሎሜ ›› ›› መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነው (2)
ጌታዬ ሲወለድ ለማመስገን ቆሜ አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም (2)
እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም (2)
አዝ…
የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሰራው (2) አባ ሕርያቆስ አባታችን
ግንቡ ንጹህ ውሀ መሰረቱ ደም ነው (2) የመስቀሉ ፍቅር ቢገባው
ሳይነጋ ተራምደን እንግባ በጠዋት (2) ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር
ከእመቤቴ ጋራ ሲነጋገር
በደሙ መስርቶ ከሰራልን ቤት (2)
ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር
ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት (2)
የውሃ ግድግዳ የደም መሰረት (2) የምናኔው ጸሎት ልዩ ዕጣን
የዋሻ ሻማ ነሽ እመ ብርሃን
የውሃ ግድግዳ የደም መሰረት (2)
መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን
ይኸው እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት (2)
ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን (2)
100. ከወገኔ ጋራ
ዳዊት በመዝሙር ያነሳሻል
የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል
ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁ
የእግዚአብሔር ሃገር የሚልሽ
በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁ
እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (2)
ምግብና መጠጤ አምላኬ ነውና
ዘውትር አቀርባለሁ ክብርና ምሥጋና ቤተልሔም ስሔድ አይሻለው
ቀራንዮም ስሔድ አይሻለው
ሕዝቦች ተሰብስበው በቤተ ክርስቲያን ፍጹም አትለይም ከልጅ
ስንዘምር ደስ ይላል በአንድነት ሆነን የአንቺስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (2)
በረከት የሞላው ዝማሬው ይገርማል የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (4)
ከዕጣኑ ጋራ ወደ ላይ ይወጣል (2) እመቤታችን አለች ከጎናቸው

ቀሳውስቱ ሌሊት ማኅሌት ሲያቀርቡ 102. ደስ ይበለን በጣም


ከመላእክቱ ጋር ወረብ ሲወርቡ
ደስ ይበለን በጣም ደስ ይበለን
ብርሃንን ለብሰን በደስታ ስንዘምር በረከቱን ለእኛ ስላደለን
ትዝታው ልዩ ነው ኅሊናን ሲሰውር (2)
አዝ…
ራዕይ ነውና ኑ እና ተመልከቱ
በጨለማ ስንኖር ደስ ይበለን በኃጢያት ተከበን ›› ››
ሰዎች ሲዘምሩ እንደ መላእክቱ
የህይወትን ብርሃን ›› ›› ፅድቁን አበራልን ›› ››
የጽጌው ማኅሌት የትንሣኤው ደስታ ወደ ምሥራቅ እንይ ›› ›› ፀሐይ ወዳለበት ›› ››
ልዩ ዝማሬ ነው እንዳይመስለን ተርታ (2) ጨለማው ልባችን ›› ›› ጎህ እንዲቀድበት ›› ››

101. የመስቀሉ ፍቅር አዝ..

የመስቀሉ ፍቅር ቢገባን የግሸኗ ንግስት ደስ ይበለን የአምላክ እናት ደስ ይበለን


እመቤታችንን እናያታለን ሆና ተገኝታለች ›› ›› የሚመኩባት ›› ››
ስምሽን ጠርቼ ›› ›› የምረካብሽ ›› ››
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ጎጆ ማረፊያዬ ›› ›› ማርያም አንቺ ነሽ ›› ››
ነይ ነይ ቤዛዊተ ዓለም
እናቱ ነሽና ለመድኃኔዓለም አዝ…
ፀዓዳ እመቤት ደስ ይበለን ሐመልማለ ሲና ደስ ይበለን ገና ሳይፀነስ ዘመኑ ሳይገባ
የሕዝቅኤል ደጃፍ ›› ›› የሙሴ ደመና ›› ›› ገረድ መሆን ሻተሸ ትንቢቱን አንብባ
የተዋበች ዕንቁ ›› ›› የደጎች አዝመራ ›› ›› ልታያት ናፈቀች ያቺን ቅድስት እናት
በማኅፀንሽ ፍሬ ›› ›› ሕይወታችን በራ ›› ›› ለክብሯ ተገዝታ ውኃ ልትቀዳላት

አዝ… ባሪያ ልሁን አለች ዝቅ አድርጋ ራሷን


መች አወቀችና እናቱ መሆንዋን
የፀሐይ እናቱ ደስ ይበለን ማርያም እመቤቴ ደስ ይበለን ጥቂት ለሚሻ ሰው ያውቃል ብዙ መስጠት
እለምንሻለው ›› ›› እስከ እለተ ሞቴ ›› ›› በማኅፀኗ መቅደስ ሲቀደስ ኖረበት
የልቤ ማረፊያ ›› ›› የዘላለም ቤቴ ›› ››
አንቺ ነሽ ተስፋዬ ›› ›› ዕፀ መድኃኒቴ ›› ›› ሐር ወርቁን ስትፈትል በቤተ መቅደሱ
ማደሪያው እንድትሆን መረጣት ንጉሡ
103. ደስ ይበለን አምላክ አለ በሕሊናው ተስላ የነበረች ምናብ
ደስ ይበለን ደስ ይበለን መሰላል ሆነችው ለአዳም ድህነት ርካብ
አምላክ አለ መሐላችን በጎ መዓዛዋን ውበቷን ወደደ
ምን ይከፈል ለዚህ ስራህ በማኅፀኗ ሊያድር እግዚአብሔር ወረደ
ገናና ነው አምላክ ክብርህ ከኪሩቤል ይልቅ ጀርባዋ ተመቸው
ምህረቱን አይተናልና ንጽሕት ናትና የማትቆረቁረው
አድርሶናል አምላክ በጤና የተዘጋች መቅደስ ከቶ ማትከፈት
ይህችን ዕድሜ ለጨመረልን ታትማ የኖረች የክብሩ ሰገነት
ለንስሐ ጊዜ የሰጠን ማንም አይከፍታትም ጥበብ አላትና
ኃጢአትን ይታገስሃል የእስራኤል ቅዱስ ገብቶባታልና
በቸርነት አምላክ ያይሃል በረቀቀው ጥበብ ድንግል ተቀደስች
ደስታ ነው በሰማያት በሆዷ ቅዳሴን እያስተናገደች
በአንድ ኃጥእ የጽድቅ ሕይወት ጎንበስ አለች ማርያም ውዳሴ ልትሰማ
እልል በሉ የጎበኛችሁ ከቅኔያት ሃገር ከሆዷ ከተማ
በቸርነት አምላክ ያያችሁ 105. በምን በምን
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑት ዝምም አትበሉ በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን
ምሳሌ የላትም (2) ክብሯን የሚመጥን
ድንግል ማርያም ትጸልያለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች የሙሴ ፅላት ነሽ የምሕረት ቃልኪዳን
በድንግል ክብር እንኖራለን
የያዕቆብ መሰላል የአብርሃም ድንኳን
በጽኑ ፍቅር አምላክ ባደለን
የብርሃን መውጫ የኖህ ድንቅ መርከብ
104. ድንግል በድንግልና የመላእክት እኅት የርኅሩኃን ርግብ (2)
ድንግል በድንግልና ፀንሳ
የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር
በድንግልና ትወልዳለች
የዕዝራ መሰንቆ የጌዴዎን ፀምር
ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች
ድንግል እመቤቴ ናት የጻድቃኖች በር 107. እመቤቴ የአምላክ እናት
ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር (2)
እመቤቴ የአምላክ እናት
ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት
የቅዱሳን እናት የዓለም ንግሥት
ለልጅሽም ክብር ውዳሴ
ችላ ተሸከመች መለኮት እሳት
ታቀርባለች ዘውትር ነፍሴ (2)
ብርሃን ትሁነን ጨለማን ገላልጣ
አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ (2) ልቤ ተነሳሳ ተቀኘ ለክብርሽ
በፍጹም ትኅትና ሊያመሰግንሽ
ከማር ይጣፍጣል የድንግል መዓዛ ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን
አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ የታጠረች ተክል እመብዙኃን
ዓለም ሁሉ የዳነው በልጅሽ ነውና
የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት
እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምሥጋና (2)
የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት
106. ነይ ነይ የሰማይ የምድር ንግሥት ናትና
ክብር ይገባታል ዘውትር ጠዋት ማታ
ነይ ነይማርያም ነይ ነይ
ድንግል ሆይ ነይ ነይ አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት
ያን የእሳት ባሕር ከቶ እንዳላይ በምልጃሽ አስቢኝ ኋላ ስራቆት
ያንን የእሳት ባሕር አሻግሪኝ ድንግል ሆይ
በሐመረ ኖኅ የተመሰልሽ
እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ
በአሮን በትር የተመሰልሽ
የምሥራቋ በር (2) ቶሎ ድረሽ 108. ለማርያም

በተራራማው በኤፍሬም ሃገር ለማርያም (2)


እንግዳ የሆንሽ ለኤልሳቤጥ በክብር እንዘምራለን ለዘለዓለም (2)
ነይልኝ ወደ እኔ (2) ካንቺ ጋር ልኑር
አዝ…
ዓለም ከብዶብኝ ተጨንቄአለሁ
ኃዘን በዝቶብኝ ብቸኛ ሆኛለሁ የተዘጋች ደጅ ለዘለዓለም ሕዝቅኤል ብሏል ለዘለዓለም
ንጽሕት ናት በእውነት ›› ›› በፍጹም ድንግል ›› ››
ኧረ ነይ ድንግል ሆይ (2) እጠራሻለሁ
አብነት አድርገን ›› ›› እኛም እርሱን ›› ››
ጥበብ አንቺ ነሽ ለሲሎንዲስ በፍጹም ፍቅር እንዘምራለን (2)
ነይ ብሎ ሚጠራሽ ሱላማጢስ
አትቅሪ ድንግል ሆይ (2) በእጅሽ ልዳሰስ አዝ…

ምሥጢር የገለጥሽ ለሕርያቆስ የዋኅት ርግብ ለዘለዓለም ሰላም አብሳሪ ለዘለዓለም


ፈጥነሽ ያማለድሽ ለቤተ ዶኪማስ የጨለማ ሕይወቴ ›› ›› ብርሃኔን አብሪ ›› ››
ነይልኝ ድንግል ሆይ (2) ልቤ ይፈወስ እማፀንሻለው ›› ›› ድንግል ለነፍሴ ›› ››
አደራ ድንግል አንቺ ነሽ ዋሴ (2)
ድንግል ቀርባለች ጩኸቴን ሰምታ
የኃጢአቴ ገመድ እስሬ ተፈታ አዝ…
አከብራታለሁ (2) ልጇ በእልልታ እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም ያለኝ ፍቅር ለዘለዓለም
አይነገርም ›› ›› አይወሰንም ›› ››
በእርሷ ደስ ይለኛል ›› ›› ሐሴት አደርጋለሁ ›› ›› በፍቅርሽ እሳት ነይ እመቤቴ ልቤ ነደደ ነይ እመቤቴ
ስሟን እየጠራው እዘምራለሁ (2) እናትነትሽን ነይ እመቤቴ ስለወደደ ነይ እመቤቴ

አዝ… አዝ.....

ንዒ ንዒ ስላት ለዘለዓለም ቀንና ሌሊት ለዘለዓለም የሰውስ ጉልበት ነይ እመቤቴ ምን ይረባኛል ነይ እመቤቴ
አትለየኝም ›› ›› ለኔስ ቅርቤ ናት ›› ›› ሰረገላዬ ነይ እመቤቴ መች ያድነኛል ነይ እመቤቴ
እፁብ እፁብ ብለው ›› ›› አመሰገንዋት ›› ›› ከተሰወረው ነይ እመቤቴ ክፉ መከራ ነይ እመቤቴ
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት (2) እድናለሁኝ ነይ እመቤቴ አንቺን ስጠራ ነይ እመቤቴ

109. ትኅትናሽ ግሩም ነው አዝ.....

ትህኅትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም (2) ለስንፍናዬ ነይ እመቤቴ መቼ ልክ አለው ነይ እመቤቴ


እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔዓለም (2) ስለ በደሌ ነይ እመቤቴ እተክዛለው ነይ እመቤቴ
ለአነጋገሬ ነይ እመቤቴ ማጣፈጫ ነሽ ነይ እመቤቴ
አዝ…
ተሰምቻለው ነይ እመቤቴ ድንግል ሆይ ስልሽ ነይ እመቤቴ
ንጽሕት ስለሆንሽ እመቤቴ (2) እንከን የሌለብሽ ›› ›› አዝ.....
የፍጥረታት ጌታ ›› ›› በአንቺ ያደረብሽ ›› ››
የድንግል መመረጥ ›› ›› ዜናው አስገረመን ›› ›› ለመንገዴ ስንቅ ነይ እመቤቴ የረሃቤ መርሻ ነይ እመቤቴ
እሳቱን ታቀፈች ›› ›› የማይቻለውን ›› ›› ለታመመ ሰው ነይ እመቤቴ ነሽ መፈወሻ ነይ እመቤቴ
የተማጸነሽ ነይ እመቤቴ በስምሽ አምኖ ነይ እመቤቴ
አዝ… ማን አፍሮ ያውቃል ነይ እመቤቴ አንቺን ለምኖ ነይ እመቤቴ
ምርኩዜ ልበልሽ እመቤቴ (2) ጥላ ከለላዬ እመቤቴ (2) 111. በችግር ጊዜ
ጋሻዬ ነሽ አንቺ ›› ›› ለእኔስ መመኪያዬ ›› ››
በዓለም እንዳልጠፋ ›› ›› ሕይወቴ መሮብኝ ›› ›› በችግር ጊዜ የምትደርስልን
እንደ ወይን አጣፍጪው ›› ›› ማርያም ድረሺልኝ ›› ›› ስንማጸናት የምትራራልን
እኛም ደስ ይበለን በእመቤታችን
አዝ… እግዚአብሔር ይመስገን የእርሷ ያረገን
የምሥራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ (2) የሁላችን ተስፋ ›› ›› ሰማያዊ መና ጌታን የተሸከምሽ
እሙ ለፀሐይ ጽድቅ ›› ›› ለሁሉ ጠበቃ ›› ›› ንጹሕ የወርቅ መሶብ ድንግል አንቺ እኮ ነሽ
ድንግል የድል አክሊል ›› ›› ድንግል የጽድቅ ሥራ ›› ›› ስዕልሽ ፊት ቆሜ በዓይኔ ሳስተውልሽ
ማርያም መሠላል ነሽ ›› ›› የሁሉ አለኝታ ›› ›› ዕንባየ ፈሰሰ ከልቤ ውስጥ ገብተሸ
110. በጎ መዓዛ በሰርግ ብቻ አይደለም ከልጅሽ ጋር ያለሽ
በዚያ በመከራም መስቀሉ ስር ነበርሽ
በጎ መዓዛ ሽቱዬ ነሽ
አንቺን ከመስቀሉ ማን ይነጣጥላል
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
አምላክ ከአንቺ ጋር ነው ማን ይቃወመናል
በአንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ ፀሐይን እንደ ልብስ የተጎናጸፍሽው
አስራ ሁለት ኮከብ አክሊል የደፋሽው
አዝ....
የሰማይ ጨረቃን በእግርሽ መርገጥሽን
ምሳሌ የለሽ ነይ እመቤቴ ዘመዴ ነሽ ነይ እመቤቴ እኛም እናምናለን ድንግል ሆይ ክብርሽን
ያን ክፉ ዘመን ነይ እመቤቴ ያለፍኩብሽ ነይ እመቤቴ
ምስጋና ለልጅሽ መቆምስ ለአንቺ ነው ብርሃናዊው መልአክ ራጉኤል ነዓ ሥልጣንህ ግሩም ›› ››
አማላጅነትሽን መጽሐፍ የነገረው የሃገር ጠባቂ » » መልአከ ሰላም » »
ተአምርሽ ሲነበብ መልክሽ ሲታደል ተስፋዬ ደብዝዞ » » ጨለማ ሲውጠኝ » »
ትባርኪናለሽ በኪዳን መሐል በረድኤትህ ከበህ » » ብርሃንህን ስጠኝ » »

ሚካኤል በቀኝሽ ገብርኤል በግራ ነዓ ነዓ ዑራኤል ነዓ ነዓ


እልፍ አዕላፍ መላእክት ሆነው ከአንቺ ጋር ነዓ ነዓ ዑራኤል ና ወደ እኛ
እያሸበሸቡ ይዘምሩልሻል ምሕረት ከአምላክህ ለምንልን ለእኛ
እጹብ (2) ብለው ድንግል ያደንቁሻል
ሰውነቴ ደክሞ ዑራኤል ነዓ በደዌ ሲመታ ዑራኤል ነዓ
ነፍሴን ሲያንገላታት » » የኃጢአት በሽታ » »
ተአምሩን በማሰብ » » ጸናው ተማጽኜ » »
112. ነዓ ነዓ ሚካኤል
ዛሬ ዘምራለሁ » » በጸበሉ ድኜ » »
ነዓ ነዓ ሚካኤል ነዓ ነዓ
113. የስሙ ትርጓሜ
ነዓ ነዓ ሚካኤል ና ወደ እኛ
ምሕረት ከአምላክህ ለምንልን ለእኛ የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው
የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደ ሰው
የባሕራንን ጽሕፈት ሚካኤል ነዓ የሞቱ ደብዳቤ ›› ››
እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው
አንተ ስትለውጠው » » ተደሰቴ ልቤ » »
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው
ሚካኤል መሪ ነህ » » ሊቀ መላእክት » »
በኃይልህ ጠብቀን » » አጽናን በእምነት » » ከጉድጓድ ተጥሎ ፍጹም ከሚያስፈራው
ከተራቡ አናብስት ዳንኤልን ያዳንከው
ነዓ ነዓ ገብርኤል ነዓ ነዓ
እኛንም ተራዳን ቸል አትበለን
ነዓ ነዓ ገብርኤል ና ወደ እኛ
ሰይጣን በተንኮሉ መጥመድ ሳይጥለን
ምሕረት ከአምላክህ ለምንልን ለእኛ
የክፉ ሰው ስራው ክፉ ሃሳብ ነውና
ከእሳት ውስጥ ተጥለን ገብርኤል ነዓ ኃይሉ ከበዛበት›› ››
በቅንነት መንገድ ከቶ አይሔድምና
ተስፋችን ፅኑ ነው » » ከላይ ከሰማያት » »
የሞቱን ደብዳቤ ለባሕራን ሲሰጠው
መጣልን ገብርኤል » » ከእሳት መሃል ቆሟል » »
ሚካኤል አጥፍቶ በደስታ ለወጠው
የነበልባሉን ኃይል » » በመስቀል ገስጿል » »
ገና ብላቴና ሳለሁ አንድ ፍሬ
ነዓ ነዓ ሩፋኤል ነዓ ነዓ
ሰው ሁሉ ሲንቀኝ ምሥጋናን ጀምሬ
ነዓ ነዓ ሩፋኤል ና ወደ እኛ
ፀጋዬን አብዝቶ ያበቃኝ ለዚህ ክብር
ምሕረት ከአምላክህ ለምንልን ለእኛ
የሚካኤል አምላክ ይመስገን እግዚአብሔር
ፈታሔ ማኅፀን ሩፋኤል ነዓ ለጭንቅ ደራሽ ሩፋኤል ነዓ 114. እልፍ አእላፋት
ድርሳንህ የሚያስገርም » » ከደዌ ፈዋሽ » »
እንዳበራህለት » » የጦቢትን ዐይን » » እልፍ አዕላፋት ወትእልፊት
የእኛንም ልቦና » » መጥተህ አብራልን » » ቅዱሳን ትጉኃን መላእክት
ነዓ ነዓ ራጉኤል ነዓ ነዓ ቆመው ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ነዓ ነዓ ራጉኤል ና ወደ እኛ ቅዱስ (3) አምላክ በማለት
ምሕረት ከአምላክህ ለምንልን ለእኛ
ኢዮር ራማ ኤረር የመላእክት ሀገር ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል
የሃይማኖት የፍቅር የመላእክት ህብር አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል
እውነት የታየብሽ የመላእክት ክብር
116. ኦ ፍጡነ ረድኤት
እንጽና ሲል ገብርኤል ባለንበት ቦታ
ኦ ፍጡነ ረድኤት (2)
በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ
የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሰማዕት
ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ
ሰላም ላንተ ይሁን ፍጡነ ረድኤት የልዳው ፀሐይ » »
የሳጥናኤል ምኞት እንደ አበባ ረግፎ
በጨካኝ ንጉስ ፊት ቆምክ አደባባይ
ሚካኤል ተሾመ በእምነት ተደግፎ
ታማኝ አገልጋይ ነህ » » ስቃይ ያልበገረህ » »
ሳጥናኤል ወደቀ ፀጋውን ተገፎ
አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሰህ
ቅዱሳን መላእክት በእምነት የጸናችሁ
አዝ…
በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ
ስግደት ዘበፀጋ እንስገድላችሁ የፈጣሪውን ሥም ፍጡነ ረድኤት ስለመሰከረ » »
ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ
115. ጻድቃን ሰማዕታት
የስቃይ መሳሪያ » » ያላዘናጋህ » »
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ
በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ያሉ
አዝ…
ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
የጌታ አገልጋይ ፍጡነ ረድኤት ታማኝ ወታደር » »
የእግዚአብሔር ዓይኖቹ ጻድቃንን ለማየት
ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር
ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ለመስማት
ስቃይ ቢደርስብህ » » በመታገስህ » »
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል ታደርጋለች
ሲወሳ ይኖራል ዘላለም ሥምህ
በምልጃቸው እንመን አናመንታ ባንዳች
አዝ…
ጊዜያዊ መሳሪያ ሳያስፈራራቸው
እሳትና ስለት ሳያሳቅቃቸው ለሰማው ይደንቃል ፍጡነ ረድኤት ያንተ ሰማዕትነት » »
ሰማያዊ ተስፋ ስለሚታያቸው ምሳሌ ይሆናል ለሁሉም ፍጥረት
በመከራ ሁሉ ፀኑ በእምነታቸው ገድልህ ይናገራል » » ክብር እንደተሰጠህ » »
ጊዜ የማይሽረው ምግባር ሃይማኖትህ
ኃጥኡ ነዌ እንኳን በሲኦል እያለ
ስለ ወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ 117. ገድሉ ታምራቱ
እናተማ ጻድቃን በገነት ያላቹህ
ገድሉ ታምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራቹህ
ጣዖትን አዋርዶ የተሸለመው
ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም የተዋሕዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ
የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም አባ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጲያ
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ ነይ ነይ አረመኔው ንጉሥ ነይ ነይ ቢያሰቃይሽም
ንጹሕ ባሕታዊ ጠላት ያስጨነቀ ነይ ነይ ሕይወቴ ክርስቶስ ነይ ነይ ነው ብለሽ ሰበክሽ
የፀጋዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ ነይ ነይ አንገትሽን ለሰይፍ ነይ ነይ አሳልፈሽ ሰጠሸ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ ነይ ነይ ክብርሽም ተገልፆ ነይ ነይ ለዓለም አበራሽ

ደካማ መስሏቸውበአንድ እግሩ ቢያዩት አዝ…


ባለ ስድስት ክንፉ ተክለ አብ የኛ አባት
ነይ ነይ አርአያ ልትሆኚን ነይ ነይ ለኛ ለሁላችን
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ነይ ነይ ፈጽመሽ አሳየሽ ነይ ነይ ታላቅ ተጋድሎሽን
ሌግዮን ሲዋረድ ኀፍረት ተከናንቦ
ነይ ነይ ይህን ዓለም ድል መንሳት ነይ ነይ አቅቶናልና
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው ተክለአብ ነይ ነይ አርሴማ አትለይን ነይ ነይ በእምነት እንድንጸና
መጣው ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ
119. ያሬድ ካህኑ
ኢትዮጲያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት ያሬድ ካህኑ ዘመረ (2)
ዘመረ ያሬድ ዘመረ አምላክን አመሰገነ (2)
የባረከው ውሃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆኗል ጸበል እምነት አዝ…
ኑ እና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
አርያም በማለት ያሬድ ዘመረ ማኅሌት ጀመረ ›› ››
ይሰብካል ተክ ለአብ ዛሬም እንደ ጥንቱ
ዜማውን ከመልዕክት እያስተባበረ
118. ጽኑ ሰማዕት ምስጋና አቀረበ ›› ›› በዜማ መሳሪያ ›› ››
ጸናጽል አነሳ ከበሮ መቋሚያ
ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ አዝ…

አዝ.. በግዕዝ በዕዝል ያሬድ ዘመረ በዐራራይ ዜማ ያሬድ ዘመረ


ከብሉይ ከሐዲስ ምስጢር እያስማማ
ነይ ነይ ቴዎድሮስ አትናስያ ነይ ነይ በስዕለት ያገኙሽ
በዜማው ምልክት›› ›› የአምላክን መከራ ›› ››
ነይ ነይ ብሉይን ከሐዲስ ነይ ነይ ጠንቅቀሽ የተማርሽ
የመስቀሉን ነገር የማዳኑን ስራ
ነይ ነይ በፍጹም ትኅትና ነይ ነይ በእምነት የፀናሽ
ነይ ነይ አርሴማ ልዩ ነሽ ነይ ነይ አምላክ የመረጠሸ አዝ…

አዝ.. ደሙ እየፈሰሰ ያሬድ ዘመረ በጦር ተወግቶ ያሬድ ዘመረ


ሊቁ ማኅሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ
ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው ነይ ነይ ደም ግባትም ከንቱ
በጥዑም ልሳኑ ›› ›› በተሰጠው ፀጋ ›› ››
ነይ ነይ ንብረት ትዳር ሁሉ ነይ ነይ ኃላፊ ውእቱ
ለንጉስ እግዚአብሔር ለአልፋ ኦሜጋ
ነይ ነይ ንግሥት መባልን ነይ ነይ በፍጹም ሳትሻ
ነይ ነይ ዓለምን በመናቅ ነይ ነይ ገባች ወደ ዋሻ አዝ

አዝ…. ድጓ ጾመ ድጓ ያሬድ ዘመረ ምዕራፍ መዋስዕት ›› ››


ምሥጢር ተገልጾለት ከሰማይ መላእክት
የዜማ መሠረት ›› ›› ፈልፈለ ዝማሬ ›› ›› ደርሰሽ አጽናንተሸ አከበርሽኝ
የኢትዮጵያ ኩራት የተዋህዶ ፍሬ ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ

120. የቅድሳን በዓት ድንኳኑ ሞልቶ ሰው ታድሞ


አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
የቅድሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
ምን አቀርባለሁ ብዬ ስጨነቅ
ቤተ ክርስቲያን ናት አንባ መጠጊያችን
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ልቦናን ሚመስጥ መዓዛ ዕጣኗ ያሰብኩት ሃሳብ ደመና ሆኖ
ህሊናን ያድሳል ዝማሬ ድጓዋ ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀር
የመላእክት ዜማ የአዕዋፍ ዝማሬ
በእመ አምላክ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ
እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይዘምሩላታል በአንድነት ተባብረው
ይህች ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ
የሌዋዊው በትር ጸናጽል ከበሮ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ
ወራዳዋን ዓለም የኗቋት በቅድሚያ አውሎ ነፋሱን ባሕሩን አልፋለሁ
የእምነት አርበኞች ያገኟት በፍልሚያ ጠላቴ ደርሶ ቢያገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝ
የገድላቸው ተአምር መንቦግበጊያ መቅረዝ
አላቋርጥም ያንቺን ምሥጋና
የሰማዕታት አክሊል የሥራቸው ደሞዝ
ውለታሽ ድንግል አለብኝና
ከኃጢአት ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ
ክፍዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ
የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሃገሬ
አንቺን መውደዴን አያስተውኝ
መድርሻዬ ይሁን ከመቃብራቸው በአሕዛብ መሐል ስምሽን ስጠራ
ይፈወሳልና ተረፈ አፅማቸው መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
ጠላቴ ደርሶ ቢያገላታኝ
121. ስምሽን ጠርቼ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝ
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ አላቋርጥም ያንቺን ምሥጋና
ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ ውለታሽ ድንግል አለብኝና
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
122. ሥላሴን አመስግኑ
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምሥጋና
ሥላሴን አመስግኑ (2)
ጨለማው ውጦኝ በጠላት ሃገር የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
የዓለሙን መድኅን ወለድሽልኝ ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ከአባቶቼ ርስት ከሃገር ወጥቼ ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
በአሕዛብ ሃገር ስኖር ሸሽቼ ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰገኑት ና ወደ እኛ ሚካኤል (2)
መላእክት በሰማይ ለሚዘምሩለት መላአከ ምክሩ ለልዑል
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል
በሰማይ በምድር እንጠራሃለን ና ወደ እኛ ገብርኤል (2)
ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
በክንፍህ ጥላ እንጠለል
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ና ወደ እኛ ዑራኤል (2)
ሥላሴ አንባዬ ክብሬ ናቸውና
እንደ ቅዱስ ዕዝራ ሱቱኤል
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና
ጥበብን ስጠን ማስተዋል
123. ታማልደናለች ና ወደ እኛ በፈረስ (2)
የልዳው ሰማዕት ጊዮርጊስ
ታማልደናለች (2)
ገድልህን ሰምተን እንፈወስ
ማርያም (2) ቤዛዊተ ዓለም
ና ወደ እና ተክለ ሃይማኖት (2)
ሚካኤል መልአክ ሊቀ መላእክት
ይጠብቀናል ያንተ ጸሎት
ዘአውረድከ (2) መና ከደመና (2)
ፀንተን እንድንቆም በሃይማኖት
ገብርኤል መልአክ አብሳሬ ትስብእት (2)
ዘአብሰራ (2) ለማርያም ንጽሕት 125. አምላከ እስራኤል
ሩፋኤል መልአክ ሊቀ መላእክት
አምላከ እስራኤል ታማኝ ጌታችን
ዘአብርሃ (2) ዓይኑ ለጦቢት (2)
ለአስራኤል ለሙሴ የሆንከው መድኅን
ዑራኤል መልአክ ለዕዝራ ነቢይ (2)
ፈርኦን አንተን ረስቶ በትዕቢት ቢገን
ዘአስተዮ (2) ጽዋዓ ልቡና (2)
ለእስራኤል አርበኛ መረጥከው ሙሴን
ሰሎሞን ይቤላ (2)
ርግብየ ሠናይትየ ሰሎሞን ይቤላ (2) አማላጅ ነው ሚካኤል (2) የአምላክ ባለሟል
ገብረ መንፈስ ቅዱስ (2) ለነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል
ሐዋርያ (2) ዘእስክንድርያ (2)
ፈርኦን እንደገና ልቡን እያጽናና
ተክለ ሃይማኖት (4)
ሲከታተላቸው በፈረስ በፋና
ሐዋርያ (2) ዘኢትዮጵያ (2)
ይመራቸው ነበር ሚካኤል በፋና
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ (2)
ሌሊት በብርሃን ቀኑን በደመና
አዕማደ (2) ቤተክርስቲያን (2)
ፈርኦን እንደገና ልቡ ተጸጽቶ
124. ንሴብሖ ለሥላሴ
ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ
ንሴብሖ ለሥላሴ (2) እስራኤል ተጨንቀው መሄጃቸው ጠፍቶ
ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ (2) አጽናናቸው ሙሴ የአምላክን ሥም ጠርቶ
የእኛ አማላጅ እናታችን (2)
ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን
ነይ ነይ ወደ እኛ እመቤታችን
እጁንም ዘረጋ ከፈለው ባሕሩን
ፈጥነሽ ተገኚ ከመሐላችን
እንደ ግንብ ቆመ ባሕረ ኤርትራ ሠራዊትህ ከበው እነርሱ ያጽናኑን
በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ ዘወትርም ሳትርቀን ሰላምን ለግሰን

በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል 127. ሰአሉ ለነ


ድርሻ የተሰጠህ ሰውን ለማገልገል
ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላአክት
ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማዕታት
የመላዕክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል ኀበ አምላከ ምሕረት ሰአሉ ለነ

በአፎምያ ላይ ሲፎክር ጠላት ለምኑልን ቅዱሳን መላአክት


ፈጥነህ ደረስከው ሊቀ መላዕክት ለምኑልን ጻድቃን ሰማዕታት
እኛን ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት ወደ አምላከ ምሕረት ለምኑልን

ዋስ ጠበቃ ሁነን ሊቀ መላዕክት አንተ የመረጥከውን ማን ይከሳል


ያፀደቅከውን ማን ይወቅሳል
መላአኩ ሚካኤል አማላጃችን ለሚገባው ክብርን መስጠት
እንለምንሃለን እንድጠብቀን ታዟልና በመጻሕፍት
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ ያከበርካቸው ባሪያዎችህን
ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ እናከብራለን ቅዱሳንህን (2)

126. አማልደን ስንልህ ሁሉ መዳንን እንዲይዙ


የሚላኩ የሚያግዙ
አማልደን ስንልህ ስማን እዘንልን ሰርክ በፊትህ እየቆሙ
አጽናን አረጋጋን (2) ገብርኤል የእኛ መመኪያ አባታችን ጥዑም ቅዳሴን እያሰሙ
በምስጋቸውየሚያከብሩህን
እግዚአብሔር እራሱ ክብርን አቀዳጅቶህ እናከብራለን መላእክትህን (2)
ለተልዕኮ እንድትፈጥን ያረገህ የሾመህ
ጤዛ ልሰው ዳዋ ጥሰው
እንደ ሦስቱ ህፃናት አንተን እንደጠሩት
ዋዕይ ቁሩንም ታግሰው
ዛሬም አውጣን ገብርኤል ሆይ ከነፍሳችን ጠላት በየፍርክታው በየዱሩ
ሌጦ ለብሰው እየዞሩ
እምነት አለን እያልን ትተናል ምግባርን
በፅናታቸው የሚያከብሩህን
እባክህን ሊቀ መልአክ እንድናስብ እርዳን
እናከብራለን ጻድቃንህን (2)
መላእክትን ሁሉ ያረጋጋሀቸው
አንተ እኮ ነህ ኃያል መልአክ ፅኑ ቁሙ ያልካቸው እንደሚታረዱ በጎች ሆነው
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው
እኛስ እናምናለን በአማላጅነትህ ስለ ስምህ እየተጠሉ
በተሰጠህ የአምላክ ፀጋ ኃይላችን አንተ ነህ ከአንበሳ ጋር እየታገሉ
የምስራች መልአክ ተብለሀልና በተጋድሎአቸው የሚያከብሩህን
እናከብራለን ሰማዕታትህን (2)
ደስ አሰኘን ደስታን ስጠን ተጨንቀናልና
ከህያው ቃልህ እየጠቀሱ
ኢትዮጵያንም ታደግ ተዋህዶን ጠብቅ
መናፍቃንን ድል እየነሱ
ሊቀ መላእክት በል ቁምልን ሰይፍህንም ታጠቅ በገዛ ደምህ የዋጀሀትን
ቤተክርስቲያንን የጠበቋትን የልዳው ፀሐይ ጊዮርጊስ
በሕይወታቸው ያስደሰቱህን ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ
እናከብራለን ሐዋርያትህን (2)
ሹመቱን ትቶ ተድላውን
128. የቤሩቱ ኮከብ አገለገለ አምላኩን
ሞቶ ተነስቶ መሰከረ
የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ
የጽድቅን ጠላት አሳፈረ
ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ
አልሰግድም ብላ ለጣዖት
በተጋድሎ ጸና ቅዱስ ጊዮርጊስ እውነት መሰከረ ›› ››
አንገቷን ሰጠች ለስለት
ኃያሉ ጊዮርጊስ ›› ›› በሠይፍ ተመተረ ›› ››
የልዳው አንበሳ ›› ›› ጠላት ያልገዛህ ›› ›› ዓለምን ንቃ የመነነች
ሰይጣንን ተዋጋ ›› ›› ጎልማሳው ሥጋህ ›› ›› የነፍሷን ጌታ የፈለገች
ደሟን ስለጽድቅ ያፈሰሰች
አዝ..
ቅድስት አርሴማ ክብርት ነች
ዱዲያኖስ ተቆጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትህን አይቶ ›› ››
ገብረ ክርስቶስ አረጋዊ
ሊቀጣህ ተነሳ ›› ›› በትዕቢት ተሞልቶ ›› ›› ገብረ ኢየሱስ ሰማያዊ
በአንተ ላይ ወገኑ ›› ›› ሰባ ነገሥታት ›› ››
ከምድር ገጽ አንተን ›› ›› ፍጹም ለማጥፋት ›› ›› በፆም በጸሎት ተጋድለው
ጠላት ሰይጣንን ድል ነስተው
አዝ… በክብር ወረሱ ገነትን
ከመበለቷ ቤት ›› ›› ጊዮርጊስ ተዓምር ሰራ ›› ›› የጽድቅ አክሊልን ፀጋውን
ለምፃምን አነፃ ›› ›› ዕውራን አበራ ›› ›› ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
ሰባት አክሊላትን ›› ›› ጊዮርጊስ ተቀበለ ›› ›› የሚላክለት መብረቅ
ስለጌታው ፍቅር ›› ›› በአደባባይ ዋለ ›› ››
ምድራዊ ምግብ ያልቀመሰ
አዝ… ፀጉሩን እንደ ልብስ የለበሰ
ህዝቡ በኃጢአት በረከሰ
ዝክርህን አዘክሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስምህን ለጠራ ›› ››
በአናቱ ቆሞ አለቀሰ
በሥጋም በነፍስም ›› ›› የለበት መከራ ›› ››
ደራጎንን አጥፋው ›› ›› አርቅልን ከእኛ ›› ›› ተክለ ሐይማኖት ሐዋርያ
በዝሙት በኃጢአት ›› ›› ነግሶብናልና ›› ›› ሰባኬ ወንጌል ሃሌሉያ
129. ለዓለም ሰበኩ ህዝቡን በፀጋ ይባርካል
ጸበሉ ድውይ ይፈውሳል
ለዓለም ሰበኩ ወንጌልን
በቃልኪዳኑ የሚያስምር
ጴጥሮስ ጳውሎስ ቅዱሳን
በእውነት ታላቅ ነው የእርሱ ክብር
የፈጣሪን ቃል እያወጁ
ሕይወትን ቀድመው ተወዳጁ ካህነ ልዑል ላሊበላ
የመዳንን ቃል የነገሩ የጽድቁ ዜና ምድርን መላ
ንፁሐን ናቸው የከበሩ በሰማይ አይቶ ሥርዓትን
ድንቅ አድርጎ ሰራው መቅደሱን
ቢያዝን ቢራራ ለምስኪን ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ
ሰጥቶ ጨረሰ ገንዘቡን ቢዝቁት የማያልቅ ፀጋና ሐብት አለሽ (2)

130. የብርሐን አክሊል ናት የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮሬባዊት ዋሻ


የብርሐን አክሊል ናት ድንግል እናታችን የሕይወት ውኃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ
ከሰማይ እያበራች ደስ አለው ልባችን ነበልባል ተዋሕዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል
ፍቅርሽም ሰላምሽም ድህነት ይሁነን ኦ ኦ ጫማውን አውልቆ ከፊትሽ ተደፍቷል (2)
ፍጥረት በሙሉ (2) ፊትሽ ይወደቃሉ
ፀጋሽ ይድረሰን (2) ይሰጠን እያሉ
132. ናና ሚካኤል አዝኛለሁና
አዝ…

የኔ ልብ ምን ጽድቅ አለው አንቺን ለማስተናገድ ናና ሚካኤል ናና (2)


የኃጢአት ጎተራ ነው የተሞላው በስስት አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና
ኧረ እንዴት (2) ድንግል ትኑርበት ኦ ኦ ናና ሚካኤል ናና
አትጸየፍም የኔን ልብ ታሰናዳዋለች
የረዳህ አፎሚያን ሚካኤል ናና ሰይጣን ሲፈትናት ›› ››
ስለ ኃጢኣቴ የኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች (2)
አንተነህ ያዳንከው ›› ›› ባሕራንን ከሞት ›› ››
አዝ.... ለእነርሱ እንደመጣሀ ›› ›› እኔንም ተራዳኝ ›› ››
ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት ሚካኤል ደግፈህ ›› ›› ለመንግሥቱ አብቃኝ ›› ››
ህሊናቸው ይመለስ እንጸልይ ለዚህ ጥፋት አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና
አምላክን ይዛ ነው ድንግል የምትመጣው ኦኦ ናና ሚካኤል ናና
እርሷን ስንመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው (2)
ናና ገብርኤል ናና (2)
131. አንቺን የያዘ ሰው አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱን ሞልቶለታል ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና አምላክ መምጫው ሲደርስ ››
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ገብርኤል አንተ ነህ ›› ›› ያልካት ይበልሽ ደስ ››
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ (2)
ድምጽህን አሰማኝ ›› ›› ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ››
በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና
የምስኪናን እናት የርኁባን ቀለብ ናና ገብርኤል ናና
ለሁሉ መጋቢ ፀጋሽ የማይጎድል
ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሃብ የሚያስጥል (2) ናና ዑራኤል ናና (2)
አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና
አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ
እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ ናና ዑራኤል ናና
የሐዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ
ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና ለዕዝራ ሱቱኤል ›› ››
ጽድቅን አሸተትን የህይወትሽን መዓዛ (2)
ጥበብ አጠጥተህ ›› ›› እውቀትን ስታድል ›› ››
ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ ተገለጠ ክብርህ ›› ›› መልአኩ ዑራኤል ›› ››
ልመናም አልወርድም አልይዝም አቁፋዳ
ድኜ በጸበልህ ›› ›› በዐውደ ምሕረትህ ላይ ›› ›› የምዕመናን ውበት ማርያም ዘውድ አክሊላቸው ›› ››
እኔም ዘመርኩልህ ›› ›› ድንግል አንቺ እኮ ነሽ ›› ›› የመንገድ ስንቃቸው ›› ››
አዝኛለሁና በእንተ ልጽናና ምስክር ነኝ ላንቺ ›› ›› እንደ ነቢያቱ ›› ››
ስጦታ መሆንሽን ›› ›› ለአዳም ልጆች ሁሉ ›› ››
ናና ዑራኤል ናና
አዝ…

ሞገስና ፀጋ ማርያም በጌታ ፊት ያለሽ ማርያም


133. ወደ ማደሪያው ከሰይጣን መሸሻ ›› ›› ዋስ ጠበቃችን ነሽ ›› ››
ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር እንዴት ነበር ያኔ ›› ›› ጌታን ስትወልጂው ›› ››
ምሥጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር የእረኞቹ ደስታ ›› ›› የመላእክት ዝማሬ ›› ››

135. ምሥራቅ ናት
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለው
በዐፀደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ ምሥራቅ ናት (6)
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሳለሁ (2)
ቸሩ መድኃኔዓለም ያንተ እናት
ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ
ስዕለቴን ልፈፅም ላቅርብለት መባ ዳዊቱማ ይላል ›› ይቤሎ ይቤሎ ››
ወደ አደባባዩ በምሥጋና ልግባ (2) እመቤቴ ማርያም ›› የወርቅ ሀመልማል ››

አስር አውታር ባለው በበገና ምሥራቀ ምስራቃት ›› የፀሐይ መገኛ ››


በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምሥጋና ቅድስተ ቅዱሳን ›› ለምኝልንለኛ ››
የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና (2)
ምንም ታጥቦ ጭቃ ›› ቢሆንም ስራችን ››
አሸበሽባለው ድምፄን አሰምቼ
ድንግል አትለይን ›› ጥላ ከለላችን ››
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ
እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ (2) 136. ሞት ነው ረሃብ
በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ ሞት ነው ረሃብ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን
ቤቱ ተገኝቼ በፍፁም ደስታ ኃይሉ በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ (2) ፀጋው በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን
134. ማርያም እንወድሻለን ከአንተ ርቀው ሸሽተው እየሄዱ
ማርያም እንወድሻለን (2) ጠፋባቸው የጽድቅ መንገዱ
ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን በሥጋዊ ጥበብ ሲፈልጉ
ማርያም እንወድሻለን በመታበይ ስንቶቹ አንተን አጡ

አዝ… በተዋህዶ የከበርከው ጌታ


መድኃኔዓለም ሆንክልን መከታ
ድክመቴን አትይ ማርያም በኃጢአት መውደቄን ›› ››
ስንደክም ምኞት ሲፈትነን
ተስፋዬ አንቺ ነሽ ›› ›› እስከ ዕለተ ሞቴ ›› ››
ኃይልን ሰጥተህ በእጆችህ ደገፍከን
ላልከዳሽ ምያለው ›› ›› ከስርሽ ላልጠፋ ›› ››
ገፀ በረከቴ ›› ›› የሕይወቴ ዋስትና ›› ›› የዓለም ሰይፍ በእኛ ላይ ተስሏል
ሥጋችንን ሊቆርጠው አድብቷል
አዝ…
ኃይልን ስጠን እንድናሸንፈው አባታችን ተክለሃይማኖት /2/
ፀጋህ እኛ የእምነት ጋሻችን ነው አማልደን በኃጢያት እንዳንሞት/2/

ሐዋርያት ፀጋህ በዝቶላቸው እንደ መላእክት ክንፍ የተሰጠህ


ስለስምህ ፈሰሰ ደማቸው ሰማዕት ነቢይ አንድም ካህን ነህ
ዛሬም ለእኛ ፀጋህን አብዛልን መምህራችን ሐዲስ ሐዋርያ/2/
እንዳንደክም ፈተና ሲገጥመን አስተምረን የፍቅር ባለሙያ/2/

ጋሻ ሆነህ እንድትመክትልን እንደ ሱራፌል በሰማይ ሲያጥን


ቸር አምላክ ሆይ ወደ አንተ እንጮሃለን በምድር ላይ ረድዕ ሆኖ ማገልገሉን
ቢገጥመንም ችግር ወይ መከራ በተሰጠው ፀጋ ሲያስነሳ ሙታን
አትለየን ጌታ ከእኛ ጋራ ክህነቱ ከአንተ ዘንድ ናት/2/
137. ወዳጄ ሆይ አባታችን ፍታን ከኃጢያት/2/

ወዳጄ ሆይ አንሆ ውብ ነሽ 139. የሕይወት መዝገብ


የታተመች ድንኳን እንከን የሌለሽ
የሕይወትን መዝገብ ቃሉን ያስነበቡህ
የተዘጋች መቅደስ ንጽሕት አዳራሽ
የተዋህዶ አርበኞች ቅዱሳን ዋኖችህ
ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር የድካም ዋጋቸው የእምነታቸው ፍሬ
ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር ያማረ ነውና ምሰላቸው ዛሬ
የልዑል ማደሪያ አማናዊት መቅደስ
ምሥጢሩ ምንድ ነው ድል የማድረጋቸው
ስለ ንጽሕናሽ ምስጋናን እናድርስ
ለሰማያዊ ክብር ለአክሊል ያበቃቸው
ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል የሕይወታቸውን መዝገብ ግለጥና አንብበው
ማኅደረ መለኮት ወላዲተ ቃል መፍትሔ አለውና ገድላቸው የአበው
ያለ ዘርዓ ብእሲ በኅቱም ድንግልና
ድካም ሲበረታ በመንፈስ ስትዝል
አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና
ዙሪያህን ዚከብህ የኃጥአት ማዕበል
ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ ፅናት ትዕግስት አጥተህ እንዳትሰናከል
ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ በጾም ጸሎት በርታ አባቶችን ምሰል
የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሳሺ
ዓለም ኢያሪኮ ቢፍትንም ሥጋህ
ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ
ዲያቢሎስም ቢያሴር ከመንገድ ሊያርቅህ
138. ተክለ ሃይማኖት ተክ ለአብ ልትወድቅ አትችልም ምን ቢያይል ፈተና
ካሰብክ የፀኑትን የተዋሕዶን ፋና
ተክለ ሃይማኖት ተክለ አብ
ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ 140. ውዳሴ ማርያም
አባታችን አማልደን አስታርቀን
ውዳሴ ማርያም እጮሃለሁ
ከፈጣሪ ጋር ከአምላካችን
ድንግል እናቴን እጣራለሁ
በሦስት ቀን ሥላሴን ያመሰገንክ እንደ አባ ኤፍሬም ነይ ባርኪኝ
ከጭንጫ ድንጋይ ውሀን የአፈለቅክ ወድሰኒ ልጄ በይኝ

አዝ..
ውዳሴ ማርያም በሰርክ ጸሎት ላይ ›› ›› ዜማ ስናደርስ ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ
›› ›› ድንግል ትመጣለች ›› ›› በቤተ መቅደስ በቃል ኪዳንህ ሕይወቱ ዳነ (2)
›› ›› የብርሃን ምንጣፍ ›› ›› ከፊቷ ተነጥፏል
›› ›› ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ ›› ›› ያመሰግናታል አዝ…

አዝ.. ከአምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል ክብርህ ያበራል ›› ››


ለጎስቋላው ሰው ›› ›› መጠጊያ ሆኗል ›› ››
ውዳሴ ማርያም አባ ሕርያቆስም ›› ›› ምስጋና ያደርሳል
ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ
›› ›› የቅዳሴው ዜማ ›› ›› ልብን ይመስጣል
ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ (2)
›› ›› በጎ ነገር ልቤ ›› ›› አወጣ እያለ
›› ›› ዳዊት በገናውን ›› ›› እየደረደረ አዝ…
አዝ….
በብሉይ ኪዳን ሚካኤል ከአምላክ ተልከህ ›› ››
ውዳሴ ማርያም የንጽሕናችን ›› ›› መሠረት ነሽና ህዝበ እስራኤልን ›› ›› ነፃ ያወጣህ ›› ››
›› ›› አንቺን ለማመስገን ›› ›› ልቦናችን ይብራ በሐዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ
›› ›› ተፈሥሒ ድንግል ›› ›› ኦ ቤተልሔም በታምራትህ ትፈውሳለህ (2)
›› ›› ከአንቺ ተወለደ ›› ›› መድኃኔ ዓለም
አዝ…
አዝ…..
ባለ መድኃኒት ሚካኤል ያቀተውን ›› ››
ውዳሴ ማርያም ቅዱሳኑ ሁሉ ›› ›› ዙሪያሽን ከበዋል
ፈዋሽ ጸበልህ ›› ›› ሆኖኛል ኃይል ›› ››
›› ›› አባ ጊዮርጊስም ›› ›› ንዒ ድንግል ይላል
እንደ መፃጉዕ ድህነት አገኘው
›› ›› በወርቅ ዙፋን ላይ ›› ›› ተቀምጠሸ ሳይሽ
ፈውሰኸኛል ባንተ ተመካው (2)
›› ›› ልቤ ተሰወረ ›› ›› ድንግል በግርማሽ
142. በዘባነ ኪሩብ
141. ቅዱስ ሚካኤል
በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው
ቅዱስ ሚካኤል (3)
በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ
የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ
አዝ…
ኢሳይያስ ሲያው እጅግ አፈረ
አንተ ስለሆንክ ሚካኤል የአምላክ ባለሟል ›› ›› የተፈራ ነው የተከበረ
ልመናን ፈጥኖ ›› ›› ከአምላክ ያቀርባል ›› ›› የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ
የዋኅ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው ለቅዱስ ስሙ ክብርን ሲሰጡ
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (2)
ያልተደቀሰ ለምጽ ያነደደው
አዝ… እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው
በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና
ደዌ የፀናበት ሚካኤል ባንተ ይድናል ›› ››
ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምሥጋና
በአደባባይህ ›› ›› ምስክር ሆኗል ›› ››
ዙፋንህ ታየኝ ትምክህቴ ሆይ ከጎኔ ነሽ ስልሽ እጽናናለሁ
ስትመሰገን በሰማይ ላይ እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ
ሲያመሰግንህ የተደሰተ
144. ለምኚ ድንግል ለምኚ
ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ
ለምኚ ድንግል ለምኚ (2)
ቅኔ የሞላበት ያንን ሰገነት
ለኃጥአን (3) አይደለም ለጻድቃን
ልቀላቀለው ተመኘው በእውነት
ልዘምርልህ ባይገባኝም አዝ…
ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም
ለምኚ ታላቅ ስጦታዬ ለምኚ አዛኝ ርኅሩኅ ነሽ
143. የያሬድ ውብ ዜማ ›› የጌታዬ እናት ›› ፀጋን የተመላሽ
›› የአምላክ ማደሪያ ›› ለምነሽ አስምሪኝ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ሥጦታዬ ነሽ /2/
›› አማናዊት ጽዮን ›› ከ㙀ኔ አትለይኝ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ /2/
አዝ…
ምድርና ሰማዩ ተአምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለአንቺ ይመስክሩ ለምኚ ኃዘንሽ ኃዘኔ ለምኚ ለእኔ ይሁን ድንግል
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ ›› የተንከራተትሽው ›› በሃገረ እስራኤል
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ ›› ትዕግስትሽን ሳየው ›› ልቤ ይደነቃል
ማርያም ድንግል ረዳቴ ›› የኃዘን ዕንባ ጎርፍ ›› ዓይኔን ይሞላዋል
የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ተአምርሽንም በዓይኔ አይቻለው አዝ…

ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ ለምኚ በቀራንዮ አንባ ለምኚ በዚያ በፍቅር ቦታ

የእግዚአብሔር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ ›› ከእግረ መስቀሉ ስር ›› ከክርስቶስ ጌታ

የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ ›› ለእኛ ተሰጥሻል ›› እናት እንድትሆኚን


የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ ›› ልጆችሽ ነንና ›› ምልጃሽ አይለየን
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ አዝ…
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍጹም አልወድቅም ለምኚ አንደበቴን ጌታ ለምኚ በምሥጋና ሙላው
በፊትሽም እንድቆም ለምሥጋና ›› ደስ ይበልሽ ብዬ ›› እኔም ላመስግናት
ማርያም ልበልሽ በትኅትና ›› አንደበቴን ጌታ ›› በምሥጋና ሙላው
›› ደስ ይበልሽ ብዬ ›› እኔም ላመስግናት
ትውልዱ በሙሉ ለምሥጋና ይቁም
በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 145. ቤተ ክርስቲያን
አዳም ከነ ልጁ በሰማይ በምድር
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሽን ይናገር
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
ሁሉንም በሁሉ በሚሞላው ጌታ 147. ይበራል በክንፉ
ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ
ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
በክብር በሞገስ በፀጋ ተሞልታ
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ (2)
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው (2)
ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ
ወጥመድ ቢዘርጋ በጉዟችን ሁሉ
እንዳልደናፈቅ ጉድባዎቼን ሞልቶ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
ዛሬ ላለሁበት ብርቱ ጉልበት ሆነኝ
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን (2)
ሰው ለመባል በቃው ሚካኤል ደገፈኝ
በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት
በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት
አለው እስከ ዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
ጠላት ዲያቢሎስን ምንም ባያስደስት
የሕይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከእርሱ ጋራ
ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ሕይወት (2)
ተጽፏል በልቤ የሚካኤል ሥራ
ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው
ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር
ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው
ይሰማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሃብት
ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ
ሃይማኖታችን ነው የእኛ ርስት ጉልት (2)
ታላቁን በረከት በልቤ አፈሰሰ
146. ደስ ይበልሽ
ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ
ደስ ይበልሽ (2) አንቺ ንጽሕት ድንግል ደስ ይበልሽ መራኝ ወደ ሕይወት መዳኔን ወደደ
ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የአምላኬን ምስጋና ዘወትር እያሰማኝ
እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ
ሰላም እልሻለሁ ማርያም ድንግል
እንደ ብሥራታዊው እንደ ገብርኤል 148. ኃያል ነህ አንተ
ለአንቺ የተሰጠሸ ሁለት ድንግልና
ኃያል ነህ አንተ ኃያል ደጉ መልአክ ገብርኤል (2)
አንደኛው በሥጋ ሌላው በኅሊና
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አንተ ተራዳን በእውነት (2)
ከዓለም ሁሉ ሴቶች ንጽሕት በመሆንሽ
አዝ…
ሰማያዊ መና የተገለጸብሽ
የልዑል ማደርያ ለመሆን የበቃሽ በዱራ ሜዳ ላይ ገብርኤል ጣዖት ተዘጋጅቶ ገብርኤል
የጌታዬ እናት በጣም ደስ ይበልሽ ሊያመልኩት ወደዱ ›› አዲስ አዋጅ ወጥቶ ››
ሲድራቅ እና ሚሳቅ አብድናጎም ጸኑ
ማርያም ስትጎበኛት ወደ ቤቷ ገብታ
ጣዖቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
ኤልሳቤጥ ዘመረች በመንፈስ ተሞልታ
በማኅፀኗ ያለው ዘለለ በደስታ አዝ..
እኛንም ትጎብኘን ከጠዋት እስከ ማታ
ተቆጣ ንጉሡ ገብርኤል በሦስቱ ሕጻናት ገብርኤል ለሚያስጨንቀኝ ጠላት
ጨምሯቸው አለ ›› ወደ እቶን እሳት ›› ለሚያሳድደኝ አትስጭኝ
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
150. ጋሻውን ይዞ
ከሞት አዳናቸው በእሳት ሳይነኩ
ጋሻውን ይዞ በፈረስ ጋሻውን ይዞ (2)
አዝ..
እንደምን ያምራል ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከእቶኑ ሥር ሆነው ገብርኤል ዝማሬን ተሞሉ ገብርኤል እስጢፋኖስ ሲቀድስ (2)
ገፍተው የጣሏቸው ›› በእሳት ሲበሉ ›› መንፈስ ይወርዳል ከመቅደስ
አልተቃጠለችም ከራሳቸው ጸጉር ገብረ ክርስቶስ ሙሽራው (2)
አዩ መኳንንት የእግዚአብሔር ክብር ጥሎ መነነ ከጫጉላው
ተክለሃይማኖት አባታችን (2)
አዝ..
ቆመ ጸለዩ ለሃገራችን
ናቡከደነጾር ገብርኤል እጁን ባፉ ጫነ ገብርኤል ህጻኑ ቂርቆስ ሰማዕት (2)
ሠለስቱ ደቂቅን ›› ከእሳት ስላዳነ ›› እናቱን መራት ወደ ገነት
ይክበር ጌታ አለ የላከ መልአኩን
151. ትንሣኤሽን ያሳየን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን
ትንሣኤሽን ያሳየን (፪•)
149. የፍቅር እናት የሰላም
ውዲቷ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር
የፍቅር እናት የሰላም (2)
የአባቶች ዘመን ተመልሶ እንድናይ፣
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
አለን ኢትዮጵያ ውስጥ የፍቅር ራእይ፤
በሕይወቴ ውስጥ በኑሮዬ
ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ ትሣኤሽን ያሳየን
ተደላደለ ልቤ
ትቢያሽን አራግፊ ሐዘንሽን ሽረሽ፣
አንቺ አለሽና ከአጠገቤ
ዳግም ትነሻለሽ ሀገሬ እንደ ድሮሽ፣
ምኞቴም ይስመር ድብቅ ህልሜ
ያልታዘዘች ሀገር ለእግዚአብሔር ሥርዐት፣
ልለፍ ወጀቡን ተቋቁሜ
የጌታዬ እናት ነሽ አያጣትምና ዘወትር ፍርሐት፤
ኃይልን ያደርጋል ጸሎትሽ
ትንሣኤሽን ያሳየን
ትላንትም ዛሬም አመስጋኝ ነኝ ከቊጣው አምልጣ ሰላም እንድታገኝ፣
የለም ለነገ የሚያስፈራኝ
ሜዳ ይሆናል ተራራው ሰውና ሰው ታርቆ ኅሊናው ይገናኝ፤

ልጅሽ ስላላ ከእኛ ጋራ ይቅርታ ታላቅ ነው ቍስልን ይሽረዋል፣

እንዴት እቀራለሁ ከመንገዴ ጸብ ግን እስከ ዛሬ እነማንን ጠቅሟል፤


አደራ እናቴ አስቢኝ
ትንሣኤሽን ያሳየን ሥርዐተ ቅዳሴውን ስታከናውን
ጊዜው ቢመሽብህ አቆምክ ፀሐይን (2)
ቂምና በቀልን ለትውልድ ያቈዩ
ድንጋይ ዛፍ ቅጠሉ ሲከተል ተክለ አብን
በማይበርድ እሳት ፍም ኋላ ይጋያሉ። ዐየን ልዩ ተአምር ደብረ ብሥራት ሆነን
ገሥጾ አስቀራቸው ዕፅዋቱን ሁሉ
152. ተዋሕዶ እጅ ነሥተው ቆመው ዛሬም ይታያሉ፡፡ (2)

ተዋሕዶ ሃይማኖቴ 154. እመቤታችን ዋስ ጠበቃችን ነሽ


የጥንት ናት የእናትና የአባቴ
ማዕተቤን አልበጥስም እመቤታችን (2) ዋስ ጠበቃችን ነሽ ለሕይወታችን
ትኖራለች ለዘለዓለም ነፍስና ሥጋዬ ጐስቊለው ሲቈሽሽ ሕይወቴ፤ (2)
ቀድሰሽ አጣፍጪው ድንግል እመቤቴ
የግብጽን ከተሞች በደም ገንብተናል
በመግደል ጽድቅ የለም ሞተን ግን ኖረናል ይሁን ሰውነቴ ሕይወቴ የዶኪማስ ጓዳ (2)
ማዕተብሽን ፍቺ በጥሺ ቢሉኝ በአንቺ አማላጅነት ታጥቦ እንዲሰናዳ
እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ ምግባሬም ጣዕም አጣ መረረ ጨውነቱን አጥቶ /2/
ጴጥሮስ ተሰቀለ ጳውሎስ ተሰየፈ ድንጋይ ነህ ተብዬ ተንቄ እንዳልወረወር /2/
ተዋሕዶ እያለ ኧረ ስንቱ አለፈ እንደ ጨው አጣፍጭው እናቴ ተቀድሼ
ሌሎችም በእሳት በሥቃይ አልፈዋል እንድኖር
ዘመን የማይሽረው ታሪክን ጽፈዋል ይለምልሙ ነፍስና ሥጋዬ በበረከትሽ /2/
ፊተኛ ነንና እንዳንሆን ኋለኛ የልጅሽ አድርጊኝ አረሙን ነቅለሽ
ሕዝቤ ተነቃቃ ተነሥ አትተኛ ወይኑ እንዲለመልም አፍርቶ በረድኤትሽ /2/
ፀሐይ ከጠለቀች እንዳይሆን ጩኸቱ የአማኑኤል እናት በልቤ ንገሽ
የተዋሕዶ ልጆች አሁን ነው ሰዓቱ አልሚልኝ እርሻዬን እናቴ መራሩን ስር ነቅለሽ /2/
ዐይተን እንዳላየን ስንት አሳልፈናል አረም ሆኜ እንዳልቀር መፃተኛው ልጅሽ
የእርሱ ፍቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል መልካሙን ዘር ዝሪ በውስጤ የፍቅርን አዝመራ /2/
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር በአንቺ አማላጅነት መልካም ፍሬን ላፍራ
ይገለጽ ይታወጅ የተዋሕዶ ክብር
155. እመ አምላክ ሙሽራ ነሽ
153. ዜና ማርቆስ
እመ አምላክ ሙሽራ ነሽ /2/
ዜና ማርቆስ (2)
ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ ኧኸ /3/
በጸሎትህ ወድቋል ጠላት ዲያብሎስ
ዐሥራ ሁለት ዓመት ቤተ መቅደስ የኖርሽ
ምርጫህ በማኅፀን ስለ ሆነልህ
የመመረጥ ፀጋ ከጌታ ያገኘሽ
በተወለድክ ጊዜ ሥላሴን ጠራህ
አምላካዊ ምስጢር ዕፁብ ድንቅ ዜና
ተባርከህ መጥተሃል ሄደህ እስክንድርያ
ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና
ኀይሉም አድሮብሃል የማርቆስ ሐዋርያ (2)
በስድስተኛው ወር ተልኮ ገብርኤል
ቃሉን የሰበክህ ምሁር ላይ ስትደርስ
ቤተ መቅደስ ገባ ወደ ንጽሕት ድንግል
ሰዎችን ያሳተው ተሰብሯል ማኮስ
በልዩ ሰላምታ ሰላም ለኪ እያለሽ
ሁሉም ተመልሰው ተዋሕዶ ሆኑ
የክርስቶስ እናት ድንግል ደስ ይበልሽ
የዜና ማርቆስን አምላክ እያመኑ (2)
መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል
ግራርያ ሲሄድ ተክለ ሃይማኖት
ክብር ለአምላክ እናት ይድረስሽ ይሉሻል
ዜና ማርቆስ ጸና በደብረ ብሥራት
በማኅፀንሽ ሊያድር የሠራዊት ጌታ ይሁንልኝ ብለሽ ቃሉን የተቀበልሽ
ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ልዩ ቦታ ድንግል ሆይ እናቴ እጅግ ልዩ እኮ ነሽ
የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ ንጽሕት ሙሽራ ጌታ የታየብሽ
ሰላም ለአንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ ድንግል ለእኛም ይድረስ ፀጋ በረከትሽ
ከፍጡራን ሁሉ አንቺ ስለከበርሽ ማንም አልታደለ ከፍጡር እንደ እርሷ
ገብርኤል ተልኮ ደስታን አበሰረሽ ቅድስት ናትና በሥጋና ነፍሷ፡፡
ምንኛ ድንቅ ነው ድንግል ያንቺ ብሥራት
ጌታን ትወልጃለሽ የሚል ቃልን መስማት

ሥሥት ትዕቢት በልቤ ተሞልቶ


ድረስ ጊዮርጊስ መመኪያችን፤
ጽላትህ ይዉጣ ከመቅደስህ
156. ተነግሮ የማያልቅ ከእኛ ጋር ይዝመት ኀያል ስምህ
ደማችን ሲፈስ በመቅደሳችን
ተነግሮ የማያልቅ ነው ፀጋህ /2/ ጠላት ሲደፍረን በሀገራችን
በጸሎት የተጋህ የሃይማኖት ፍሬ የልዳዉ ሰማዕት እርዳን በብርቱ
ተክለሃይማኖት የእምነት ገበሬ የአበዉ ጋሻ ድረስ ሰማዕቱ
በወንጌል ብርሃን ሕዝቡን የመራኸው ከሳሽ ይደንግጥ ስምህ ሲጠራ
የኃጢአትን ባሕር ከፍለህ ያሻገርከው ቀስቱ ይሰበር ከሰይፉ ጋራ
ኢትዮጵያዊው ሙሴ በመስቀልህ ባርከን ውረድ ከእኛ ጋራ ከትግሉ ሜዳ
ፍሬ እንድናፈራ ንጹሕ ዘር አድርገን ከእጅህ ይቀበል የሞቱን ዕዳ
ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት ትኑር ተከብራ ሃይማኖታችን
ወንጌልን ያበሠርክ ለክርስቶስ መንግሥት ጸንቶ ይቀመጥ ክቡር ቅርሳችን
በጠበልህ እንዳን ባርከው አባታችን ከእኛ ጋራ ሁን በፀር ከተማ
በዕጣንህ መዓዛ ትፈወስ ነፍሳችን ይራድ ከሳሽ በክብርህ ግርማ
ለማጠን የበቃህ የሥላሴን መንበር
ሰይጣን ከቶም አይደርስ በሄድክበት ሀገር 158. በማኅፀን ቅኔ
ለሕሙማን ሁሉ የሆንካቸው ፈውስ በማኅፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
ጠብቀን ተክለ አብ በሥጋም በነፍስ በተራራማ ሀገር በአፍሬም ከተማ
እጅግ የበዛ ነው ትሩፍ ምግባርህ ዮሐንስ ይናገር በረኃ ያደገው
ጸሎትህን ያልተውክ ቢሰበር አንድ እግርህ የእናቱ ማኅፀን የቅኔ ምንጭ ሆነች
ምዕራፈ ቅዱሳን የወንጌል ገበሬ ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለ ቆመች
እኛንም አድነን ከዚህ ዓለም አውሬ በኀሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቅ ሰላምታ
157. የኢትዮጵያ አርበኛ በድንግል ማኅፀን ስላየን ጌታዉን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማን መዝሙሩን
የኢትዮጵያ አርበኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣
ትንቢቱ ሊፈጸም በሆድዋ ሊነግሥ
ፈጥነህ ቶሎ ና በፈረስ፣
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንሥ፤
ጠላት ሰልጥኖ ዙሪያችን ሰፍሯል
ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
የአድዋዉን ድል ዛሬ ናፍቀናል
ተፈጥሮ መች ቻለ? ነቢዩን ለማገድ
ቅጥሯ ሲደፈር የሀገራችን
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
በእናቱ ማኅፀን ድምፁን ሰማና
የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ ገረማት 161. ገብርኤል ኀያል
ልጇ በማኅፀን ቅኔ ሲቀኝባት
ድምጿን ከፍ አደረገች ዓለም እንዲሰማ ገብርኤል ኀያል መልአከ ሰላም መልአከ ብሥራት
መላ መንፈስ ቅዱስ በመዝሙር፣ በዜማ የምታወጣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን
159. ኦ ቅዱስ ዮሴፍ የጽናታቸው ዝና ሲሰማ
ከዚያች ባቢሎን ከሞት ከተማ
ኦ ቅዱስ ዮሴፍ /2/
ሕፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
የድንግል ጠባቂ ታማኝ አገልጋይ
ቆመህ ተገኘህ በመካከላቸው
የድንግል ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ
ታማኝ አገልጋይ
ውሃው ሲዘልል ቢያስደነግጥም
መከራን ታግሠህ ለክብር በቃህ
በጋኖቹ ውስጥ ቢነዋወጥም
የድንግል ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ
ፀንተው ዘመሩ ልጅ እና እናቱ
አይሁድ ሲቃወሙ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ
እጣው ወጣልህ እርሷን ልትጠብቃት
ቂርቆስም ጸና ሞትን ሳይፈራ
ታምነህ የተሰማራህ ቅዱስ ዮሴፍ
አንተ ስላለህ ከእነሱ ጋራ
ሳታወላውል ቅዱስ ዮሴፍ
ይገርማል ይደንቃል ትዕግሥት ጽናትህ አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
የአምላክ ባለሟል ቅዱስ ዮሴፍ አምነው ድልነሱ ያንን መከራ
ሆነህ የተመረጥክ ቅዱስ ዮሴፍ እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ
ልመናህ ይድረሰን ምልጃህ አይለየን ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ
እኔም እንድሆናት ቅዱስ ዮሴፍ ክፉውን ዘመን የማልፍበት
አገልጋይዋ ታማኝ ቅዱስ ዮሴፍ
ጽናትን ስጠኝ ድል ልንሣበት
ተግስት ጽናትህን ለእኔም አስተምረኝ ፡፡

162. የአርባብ አለቃ


160. ሶበ ሰማዕነ
የአርባብ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል
ሶበ ሰማዕነ ዜናከ መጻዕነ ኀቤከ አብሣሬ ትስብእቱ ለቀዳሚ ቃል
መጻዕነ (4) ምሕረት አሰጠን ከአምላክ ልዑል
የእምነትን ፍሬ ጌታ አሳይቶሃል
በሦስቱ ሰማያት በመላእክት ከተማ
ፀጋና በረከት መንግሽቱን ሰጥቶሀል
ሳጥናኤል ተነሥቶ ክሕደትን ሲያሰማ
ቀዳሜ ብፁዓን ዮሴፍ ጻድቅ
በዓለም ያሉትን ሕዝብህን ጠብቅ ጽኑ ብለህ ያቆምክ መላእክትን በእምነት
ታምነህ ተሰደሀል አምላክን ይዘህ እኛንም ጠብቀን አጽናን በሃይማኖት
እንደ ልጅ ታቅፈህ እንደ አባት ታዘህ ቂርቆስ ኢየሉጣን ከነበልባል ያዳንክ
በመታመንህም አምላክ አክብሮሀል በመልካሙ ዜና ድንግልን ያበሰርክ
የሁሉን እመቤት ድንግልን ሰጥቶሀል ተስፋ በቈረጥን በተከፋን ጊዜ
ከመስቀሉ ግርጌ ዘወትር እንድቆም፤
አንተው ድረስልን አውጣን ከትካዜ፤
አንተን ባከበረህ በመድኀኔዓለም፤
ከምግባር ለይቶ በዓለም ፍቅር ስቦ
አልቀርም አባቴ ከመቅደስህ ደጃፍ፤
አበርታኝ በፅናት ለጽድቅ እንድሰለፍ፤ የመስቀሉን ዜና ከልባችን ሰልቦ
ዲያብሎስ በምኞት ሊጥለን ነውና ›› ለሚለምኑህ
ጠብቀን ገብርኤል ከስሕተት ጎዳና ›› ስምህን ስጠራ
ስልጣንህን አምነን የምልጃህን ፀጋ ›› በጣም ሲቸግረኝ
አስታርቀን ስንልህ ዘወትር ስንተጋ ›› በአክናፍህ በረህ
ፈጥነህ ተለመነን ድምፃችንን ስማ ›› ፈጥነህ ድረስልኝ
የአርባብ አለቃ መልአክ ዘራማ ዑራኤል ታምሜ መጥቼ
›› ደጅህ ላይ ስወድቅ
›› ለምነህ አስማርከኝ
163. ዑራኤል ከበረ
›› ሥራህ ረቂቅ
ዑራኤል ከበረ እሰይ እሰይ
›› ፈዋሽ ጸበልህም
ሊቀ መላእክት
›› እኔንም ምሮኛል
የአምላክ አገልጋይ
›› ከጤነኛቹ ሰዎች
ከእመቤታችን ጋር ዑራኤል
›› እኩል አድርጎኛል
አብሮ የነበረ ››
ዑራኤል የዕውቀትን ፅዋ
ወደ ኢትዮጵያ ››
›› ለዕዝራ እንዳጠጣህ
ከእርሷ ጋር የመጣ ››
›› ሁሉን ታሰጣለህ
የጌታ ባለሟል ››
›› ቀርቦ ለለመነህ
መልአኩ ለየውጣ ››
›› ክብርህም ይገለጥ
የጌታ ባለሟል ዑራኤል
›› በምእመናን ፊት
ታማኝ ወታደር ››
›› የአምላክ ባለሟል
ይኸው አማልዶናል ››
›› ሰሚ ነው ጸሎት
ከቸሩ እግዚአብሔር ››
በአንድ ሐሳብ ተስማሙ ዑራኤል
165. ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
በአንድ ልቡናችሁ ››
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
ፍቅርና ምሕረት ››
ልብሱ ዘመብረቅ
እርሱ ያብዛላችሁ ››
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ የወርቅ ልምላሜ (2)
አልፈልግም ሐኪም ዑራኤል
ናና (3) ስለምንህ ቆሜ
ምን ያደርግልኛል? ››
ገብርኤል ሊቀመላእክት
በዑራኤል ጸበል ››
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ለቡናዬ በርቷል ››
ሠለስቱ ደቂቅ ይባርክዎ ለእግዚአብሔር
ስቡሕኒ ውእቱ ልዑልኒ ውእቱ
164. ዑራኤል መልአከ ብርሃን
ብለው ምስጋና አቀረቡ ከእሳቱ ላይ ሆነው
ዑራኤል መልአከ ብርሃን
በሠለስቱ ደቂቅ ናቡከደነፆር ተቈጣ
አማልደን እኛን ከአምላካችን
እሳቱም ነደደ ነበልባሉም ወጣ
ዑራኤል መራሔ ብርሃናት
ግን ኀያል ገብርኤል ሊያድናቸው መጣ
›› የዋህ መልአክ ነህ
ራጉኤል ሊቀ መላእክት
›› ምሕረት ታሰጣለህ
እም ኀበ ላዕሉ ወረደ መብረቅ መብረቅ ሠረገላው መብረቅ
መልአከ ብርሃናት አንሶሳዌ ፋና የቃል ኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
ራጉኤል ና /4/ አማላጅ ነህና የፍጥረቱ ደስታ (፪) ገብረ ሕይወት ጻድቅ
ኮከብ ኮከብ ክብረ ገዳም ኮከብ
ዑራኤል ሊቀ መላእክት
ዓለምን የሚያስንቅ መዓዛው የሚስብ
ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት
አልክ ሥሉስ ቅዱስ (፪) ገብረ ሕይወት ኪሩብ
በዓለም ፈተና በሥቃይ ኵነኔ ስኂን (፪) ፄና ልብሱ ስኂን
ስባዝን ስጨነቅ ስጠበብ ወይ እኔ የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
ዑራኤል የእኔ ኀይል ቆመልኝ ከጎኔ ፡፡ የሚነበብ መጽሐፍ (፪) ገብረ ሕይወት ድርሳን
መቅረዝ (፪) የማኅቶት መቅረዝ
166. ሰላም ለኢትዮጵያ ምድረ ከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዚጊቲው ፈዋሽ (፪) ገብረ ሕይወት ምርኩዝ
ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን (፪)
ይላክልን(፫) ቸሩ አምላካችን 168. ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
ለዓለማት ሁሉ ኢትዮጵያ ተስፋ ነሽ
አይደለሽም ብዙ በቍጥር አንዲት ነሽ ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
ተጠለዪ በእግዚአብሔር ታዛ
ዥንጉርጉርነቱን ነብር አይቀይርም
ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊለውጥ አይችልም
ዘላቂ ሰላም ከእግዚአብሔር ነው
በታላቁ መዝገብ ስምሽ የሰፈረ ይህን ዕወቂ ይህን ተረጂ
የቆየው ድንበርሽ እንደ ተከበረ በልብሽ ጉልበት ለእርሱ ስገጂ
ያኑርሽ ፈጣሪ አንቺን ከፍ አድርጎ በሰይፍ ያልቃሉ ሰይፍ የሚያነሡ
መሃልሽን ገነት ዳሩን እሳት አድርጎ የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሡ
አንቺ ቅድስት እናት የአቤሜሌክ ሀገር በቀል የእርሱ ነው አይደለም ያንቺ
በፀጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ
የጊዮን መፍሰሻ የተመረጥሽ ምድር
ይራቅ፥ ይወገድ የቍስቁልናው
ክብርና ሞገስሽ ይመለስልሻል በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ቀድሞ ያከበረሽ መቼ ይተውሻል? ሰላም ይሁን ሲል ይሆናል ሰላም
ከምድር ነገሥታት አንዳች አትጓጊ ያሳየሽውን ፍቅር አይረሣም
ኢትዮጵያ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሀገሬን
ምግብሽን የሚሰጥ አምላክሽ ታማኝ ነው በየሄድኩበት መጠሪያ ስሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ፀሐይ
ሰላምሽ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ብቻ ነው።
አሁን ይዘርጋ እጅህ ከሰማይ
እንድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
167. ገባሬ መንክራት ብርቱውን ጉልበት ኀይሉን አድክሟል።
ይህን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
ከአንተ በስተቀር መሄጃ የላት
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ
ፀሐይ ፀሐይ ለምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላእክት ወዳጅ (፪) ገብረ ሕይወት ኅሩይ፤

You might also like