You are on page 1of 2

የ ሆሳዕና መዝሙራት

1. አጫጭር መዝሙራት
1. ወአንተኒ ህፃን ነብየ ልኡል /፬/
አርኩ ለ መራዓይዊ ትሰመይ /2/ ነብየ ልዑል /፪/

2. ኢትዮጵያ ታበፅእ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሄር


እንዘትብል አምላክየ/2/ ነፅረኒ ወአድህነኒ እምሃይለፀራህ ወፀር/፪/

3. እንዘ ዪብሉ ወዪዜምሩ በልሳን ዘ እያረምም


አማን በ አማን /2/ መንግስተ ስላሴ ዘለአለም /፪/

4. ማህደረ መለኮት /፪/


ማርያም እመ ብዞሃን /፪/

5. አማን በ አማን /፬/


መንግስተ ስላሴ ዘለአለም /፬/

6. ንጉስ ውእቱ ንጉሰ ሰላም /፪/


አምላክነ/፪/መድሃኒአለ /፪/
ንግስት ይእቲ ንግስተ ሰላም /፪/
ማርያም/፪/ኪዳነምህረት /፪/
ልኡል ውእቱ ልኡለ መንበር /፪/
ሚካኤል/፪/ ልኡለ መንበር/፪/

2.እረጃጅም መዝሙራት

1, ንሲብሆ
ንሴብሆ/፪/ለእግዚአብሔር
ስቡሃ ዘተሰብሓ/፪/
እናመስግነው/፪/እግዚአብሄርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ/፪/
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ኦነ
ከ ባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ህይወት የሚሆነን መና ነው ምግባችን
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ዪክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ንው የ አለሙ ቤዛ
ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ኣምላክ ኑ እናመግን
ሰዎች ደስ ዪበለን ህይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፉ ተመልሷል
2. ሰላምሽ ዛሬ ነው
ሰላምሽ ዛሬንው እየሩሳሌም
ወደአንች መቷልና አምላክ ዘለአለም/፪/
ሆሳእና በአርያም እያሉ ዘመሩ ህፃናት በእየሳሌም
አንቺ ቤተልሄም የ ዳዊት ከተማ
የ ህዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2/
ሆሳእና እያሉ አመሰገኑት
በእየሩሳሌም አሉ ህፃናት/፪/
ኪሩበል መንበሩን የሚሸከሙት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድሃኒት/፪/
የ እየሱስን ህመም ደናግልም ኣይለው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው /፪/

You might also like