You are on page 1of 11

ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ቆሮ.

11፣28
20ኛ ዓመት ቁጥር 4
ታኅሣስ 2009ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን
ጥልቅ ፍቅር ያሳያል። እግዚአብሔር በክፉው ሰይጣን ምክር ተታሎ
በአመጹ ከእርሱ የተለየውን የሰው ልጅ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ

ወቅታዊ መልእክት ታላቅ ዋጋ እንደከፈለልን በማሰብ በፍጹም ልብ ልንገዛለትና ልንከተለው


እንደሚገባ እናስታውስበታለን። ከልደት በዓል ጋር ተያይዞ
ከምናስተውላቸው ታላላቅ እውነታዎች መካከል፡-

ሀ. አውግስጦስ ቄሣር የሕዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ባወጣበት ወቅት


እመቤታችንና ጠባቂዋ ዮሴፍ ይኖሩበት ከነበረው ናዝሬት ገሊላ ወደ
“በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ቤተልሔም ይሁዳ ወጥተዋል። ይህም መሢህ የሚወለደው በቤተልሔም
ወጣች። ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት እንደሆነ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም በሁሉ ነገር ውስጥ
ሆነ። ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ። ዮሴፍም መሥራት የማይከለከለው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ያደረገው
ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ነው። “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ
ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ
ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ። በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን
ወራት ደረሰ፥ የበኩር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ ይወጣልኛል” (ሚክ. 5፣2)።
በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
ለ. ጌታ በበረት መወለዱ ሰዎች ሁሉ ቤታቸውን በእንግዶች ስላስያዙ
በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች
ነበር። እንግዳ ማለት አብሮ ነዋሪና ቋሚ ያልሆነ ማለት ሲሆን ዛሬም
ነበሩ። እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም
ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ልባቸው እንዳይገባ (እንዳይወለድ)
በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው፦
እንግዳ በሆኑ የዓለም ነገሮች መጠመዳቸውን ያሳየናል። በዚያን ዘመን
እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና
የቤተልሔም ነዋሪዎች ለጌታ በራቸውን ባለመክፈታቸውና ቤታቸውን
አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
በእንግዳ በማስያዛቸው እጅግ ታላቅ የሆነ በረከትን አሳጥቷቸዋል። ይህ
ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ
ደግሞ ዛሬ በዚህ ዘመን ለምንገኝ ሰዎች ትልቅ ማስጠንቀቂያት አለው።
በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት
“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ
ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። ክብር እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ
ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ ተጠንቀቁ፤ በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ
አሉ” (ሉቃ. 2፣1-14)። ይደርስባቸዋልና። እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ
ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ
ውድ ወገኖቻችን እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ። ከጌታ ጋር
ሁል ጊዜ ትጉ” (ሉቃ. 21፣34-36)።
በተያያዘ በዓመት ውስጥ ያሉትን በዓላት ስናስብ ብርሃነ መስቀሉ፣ ብርሃነ
ልደቱ፣ ብርሃነ ጥምቀቱ፣ ብርሃነ ትንሣኤው እያልን ነው። ይህም ሐ. የጌታ መወለድ ታላቅ የምሥራች ዜና የተነገረው በሜዳ ላደሩ እረኞች
የጌታችንን የተለየ ባሕርይ፣ ጨለማን ሊያስወግድ የተገለጸ እውነተኛ ነበር። እረኝነት የተናቀ ሥራ ሆኖ ቢገለጽም ሰው የናቃቸውንና የገፋቸውን
(አማናዊ) ብርሃን መሆኑን የሚመሰክርልን ነው። “እኔ የዳዊት ሥርና በመሰብሰብ እረኛ ሊሆን ጌታ ኢየሱስ መገለጹን እንማርበታለን።
ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራእ. 22፣16)።
የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 1
በቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር እየተዘጋጀ በነጻ የሚታደል አዲስ አበባ
ዘሀለወ ምስሌሁ ወልድ ቦቱ ሕይወት 1ዮሐ. 5፣12 ታኅሣስ 2009
መ. የእግዚአብሔር ክብር የሆነው ብርሃን በሌሊት መብራቱ (ሉቃ. ሰ. በአዳም በደል ምክንያት ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት
2፣8-9) የራሱ ትርጉም አለው። ሌሊት (ጨለማ) የሲኦልን ፍርድ ተለያይተው ነበር (ዘፍ. 3፣22-24)። ጌታ በተወለደበት ሌሊት ግን
ሲያመለክት ብርሃን ደግሞ የዘላለም ሞትን መወገድ ያሳያል። ሰውና መላእክት በኅብረት መዘመር ችለዋል። በዚህም ጌታ ሰውንና
በዚህም የጌታ መወለድ በሰው ልጅ ላይ ለ 5,500 ዘመናት ተጭኖ እግዚአብሔርን፣ ሰውንና መላእክትን ያስታረቀ፣ አንድ ያደረገ መሆኑ
የነበረውን የሲኦል ፍርድ መወገድን የገለጠ ብሥራት ነበር። “ነገር ተገልጿል (ኤፌ. 1፣13-18)።
ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው
ሸ. እረኞቹ የጌታ መወለድ የምሥራች በተነገራቸው ጊዜ
ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ በኋለኛው
ለተገለጸላቸው እውነት ታዝዘዋል። “መላእክትም ከእነርሱ
ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን
ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ
የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል። በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ
አየ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው። ሕዝብን እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ
አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል በመከር ደስ ተባባሉ። ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም
እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ በግርግም ተኝቶ አገኙ። አይተውም ስለዚህ ሕፃን
እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። በምድያም ጊዜ እንደ የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ” (ሉቃ. 2፣15-17)። ዛሬም ስለ ጌታ
ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የማዳን ነገር በሚነገረን ጊዜ ሳንዘገይ በእምነት ልብ መቅረብና
የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል” (ኢሳ. 9፣1-4)። ሕይወትን መቀበል ይገባናል (ዮሐ. 1፣44-47)። መላእክቱ
ተወለደልን ሳይሆን ያሉት ተወልዶላችኋል ነው። መላእክቱ ለእኛ
ሠ. የጌታ መወለድ ለሄሮድስ ታላቅ ድንጋጤ ነበር። ይህም በዔድን
በሆነልን ነገር በደስታ ከተናገሩ እኛ ማዳኑን ያገኘን፣ ሕይወትን
ገነት ለአዳም የተገባው ተስፋ (ዘፍ. 3፣15) ፍጻሜ፣ ለዲያብሎስ
የተቀበልን ምን ያህል በሐሤት ልንሞላ ይገባናል?
ደግሞ ትልቅ ፍርሃትና ውድቀት ነበር። “የዲያብሎስን ሥራ
እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ” (1ዮሐ. 3፣8)። ዛሬም የልደትን በዓል ስናከብር በዓሉ በዓመት አንድ ቀን የሚታሰብ
ሕፃን ሆኖ ተወልዶ ገዢዎችን፣ ሥልጣናትን ሊያስፈራ የሚችል እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል። የጌታ ጉዳይ የሕይወትና የሞት ነገር
ሰው አይኖርም። ነገር ግን የሄሮድስ ፍራቻ የጌታ መወለድ የተለየ ያለበት ስለሆነ ዘወትር ስላለንበት ሁኔታ ልናስብ ይገባል። አሁንም
መሆኑን የሚያስረዳን ነው። እርሱ የጌቶች ጌታ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን በእርግጥ ይህ የብርሃን ጌታ በልቤ

የአማልክት አምላክ ነውና ታላላቅ የተባሉ ጠቢባንና ነገሥታት ወደ ውስጥ ተወልዷል ወይ? ብለን ነው። እርሱ ወደ ሕይወታችን ከመጣ
የማይለወጥ ታሪክ አይኖርም። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን
ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜ ያሉት፡- “ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ
አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም
ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥
አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ
ሰብአ ሰገል፡- የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?
ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥
ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና ” (ማቴ.
ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን
2፣1-2) እያሉ ነበር።
ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም
ረ. ጌታ ንጉሥ ሆኖ ሳለ በበረት መወለዱ ትሕትናውንና የተናቁትን ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ
ሊፈልግ መገለጹን ያመለክታል (ማቴ. 19፣10-11፤ ሉቃ. 19፣10)። እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች
በረት ማለት የቆሸሸ የእኛ ልብ ምሳሌ ነው። ጌታ በበረቱ በተወለደ ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ

ጊዜ ነገሥታት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይዘው በመምጣት የበረቱን እንለምናለን። እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ
እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት
የማያስደሰት ሁኔታ እንደለወጡት ሁሉ ጌታም በእኛ ልብ ውስጥ
አደረገው” (2ቆሮ. 5፣21)።
ሲገባ የሕይወታችንን መዓዛና ሽታ ይቀይረዋል (መኃ. 1፣12)።

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 2
ልጁ ያለው ሕይወት አለው 1ዮሐ. 5፣12 አዲስ አበባ
እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ ዘትማልም ወዮም ውእቱ ወእስከ ለዓለም። ዕብ. ታኅሣስ 2009

በምንም እና በማንም የማይሸነፍ አምላካችን እግዚአብሔር ብቻ


ከጉባዔ መድረክ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አባት የሚለውን ቃል የወለደ፣


በሥርዓት ኮትኩቶ ያሳደገ፣ በሥጋና በመንፈስ የአባትነትን ሥራ
የፈጸመ በማለት ይተረጉመዋል።
። ቃሉ የተለያዩ አሳቦችን ሊያመለክት
ኃይለ ቃሉ የተወሰደው ከትንቢተ ኢሳ. 63፣16 ላይ ከሚገኘው
ይችላል። በሥጋ ወላጅ፣ በትውልድ ሐረግ የሚገኝ የቅርብ ወይም
“አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን
የሩቅ ወላጅ (ዘፍ. 17፣4፤ ዮሐ. 4፣12)፤ በሃይማኖት የመጀመሪያ
ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን
ተጠሪ (ዮሐ. 8፣44፣ ሮሜ 4፣11)፤ ሰውን ወደ እምነት ያደረሰ (1ቆሮ.
ነው” ከሚለው ክፍል ነው።
4፣15)፤ የአንድ ዓይነት ኑሮ መሥራች (ዘፍ. 4፣20)፤ አማካሪ (መሳ.
ያ የእምነት አባት፣ ደግ አባት፣ የብዙዎች አባት፣ ለአሕዛብ አባት 17፣10)፤ የአንድ ነገር ምንጭና ምክንያት (ኢዮብ 38፣28፤ ኢሳ. 9፣6፤
ትሆናለህ ተብሎ በዘፍ. 17፣15 የተነገረለት አባት -አብርሃም- ባያውቀን፤ ዮሐ. 8፣44)፤ … ከነዚህ ሁሉ አንዱን ለሚያሟላ አባት የሚለውን ስም
በሕልሙ ከእግዚአብሔር ጋር ታግሎ ያሸነፈው፣ አይሁድ ይህን እንሰጣለን። ከእነዚህ በአንዳቸው ወይም በተወሱኑት ላይ ብቻ ሳይሆን
ጉድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህ? ብለው በሁሉም ላይ በፍጹምነት አባት ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ
የሚመኩበት እስራኤል (ያዕቆብ) እርሱ ባይገነዘብን አንተ ግን አባታችን
ነው።
ነህ ተባለ። ምናልባት እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን አባት ብሎ
መመካትን በአዲስ ኪዳን ጊዜ ቢናገሩ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል
የተገለጠው ፍቅሩ ገብቷቸው ነው ልንል እንችላለን፤ ነገር ግን ይህን ብዙዎቻችን በልጅነት ዕድሜያችን ምን መሆን ትፈልጋለህ? ስንባል
የተነገረው ገና በብሉይ ዘመን ነው። ማንም ላያውቃቸው፣ የምንገልፃቸው ምኞቶች ነበሩን። ያኔ የተመኘነውን እንሁን አንሁን
ላይገነዘባቸው ይችላል፤ ነገር ግን በነፍስም በሥጋም ላይ ሥልጣን ራሳችንን ዛሬ ካለንበት ሁኔታ ጋር በማስተያየት መመዘን እንችላለን።
ያለውን እግዚአብሔርርን እርሱን አንተ አባታችን ነህ አሉት። ዛሬም የልጆቻችንን ምኞት ብንጠይቅ የሚሉን ነገር ይኖራል፤
የአብርሃም የቀድሞ ስሙ አብራም ነበር፤ አብራም ማለት ደግሞ ታላቅ በተለይም ልጆች እነርሱ የሚመኙት ሙያ ባለቤት የሆነ አባት
አባት ማለት ነው። አብራም የሚለው ሥም ታላቅ አባትነቱን እንጂ ቢኖራቸው እጅግ ደስ ይላቸዋል። እከሌ የዶክተር ልጅ ነው፣ እከሊት
የብዙሃን አባትነቱን ስለማይገልጽ ስሙ አብርሃም ተባለ። ይህ ስያሜው የፓይለት ልጅ ናት፣ እከሌ የመሐንዲስ ልጅ ነው ሲባል የሚሰማቸው
ለብዙሃን አሕዛብ አባት እንደሚሆን የሚገልጽ ትርጉም አለው። ስሜት የተለየ ነው። ሆኖም ግን በየትኛውም የሙያ ዓይነት እና ደረጃ
አብርሃም ዘሩ ምድርን እንደሚወርስ የተተነበየለት፣ ተስፋውም
ላይ ቢሆኑም ምድራዊ አባቶች የሥጋ ሞት የሚገድባቸው ናቸው።
በምድራዊ ርስት ብቻ ሳይሆን በሰማያዊ አገርም እንደሚፈጸም የተረዳ
እግዚአብሔር ግን ሁሉ ያለው ደግሞም የማያልፍ አባት ነው።
መሆኑ በዕብ. 11፣8-16 ተገልጾአል። በተጨማሪም በክርስቶስ ኢየሱስ
ላሉ ምዕመናን ሁሉ አባት መሆኑን በገላ. 3፣6-7፤ ሮሜ 4፣1 ላይ
እናያለን። ይህንን አባት ነው አብርሃም ባያውቀን ያሉት፤ አዎ አብርሃም ከላይ የገለጽናቸውን የአባትነት ምሳሌዎች በዝርዝር ስንመልከት አባት
በመልካም አባትነት ሊጠቀስ ይችላል ነገር ግን አብርሃም ምድራዊ ፡-
እንጂ ሰማያዊ አባት አይደለም። አብርሃም ዘመን፣ ጊዜ፣ ዕድሜ ሀ. የአንድ ነገር ምንጭና ምክንያት ነው፡- እግዚአብሔር በኢዮብ
የሚገድበው ሟች ሰው ነው፤ ይገድበዋል። አብርሃም ትሆናለህ
38፣25-28 ላይ እንደተገለጸው የፍጥረት ምንጭና የሕልውናቸው
የተባለውን ተስፋ ተቀባይ ነው እንጂ ተስፋ ሰጪ አይደለም። ጊዜና
ምክንያት ነው። “ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥
ዘመን የማይገድበው በዘመናት ሁሉ ብቻውን አባት የሆነው እርሱ
እግዚአብሔር አባታችን ብቻ ነው። ሣሩንም እንዲያበቅል፥ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥ ሰውም
በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብን ያዘንብ ዘንድ፥ ለፈሳሹ ውኃ
እስራኤል (ያዕቆብ) የእግዚአብሔርን ታላላቅ ሥራዎችን የምናይበት፣ መንዶልዶያውን፥ ወይስ ለሚያንጐደጕድ መብረቅ መንገድን
ከእግዚአብሔር ጋር ታግሎ ያሸነፈ፣ ገና በእናቱ ማህጸን ሳለ ከመንትያ
ያበጀ ማን ነው? በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን
ወንድሙ ጋር ታግሎ ተረከዝ ይዞ የወጣ፣ ብኩርናን እጅግ የሚሻ ሰው
ነበር። ያም ሆኖ ያዕቆብ ሰው እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፤ ሞት ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው?” እያለ የተለያዩ የተፈጥሮ ሁኔታዎችን
ሲመጣ እጁን የሰጠ፣ ምድራዊ ዘመኑ በሞት የተገደበ ሰው ነበር።

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 3
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ዕብ. 13፣8
አዲስ አበባ
አነ ውእቱ ትንሣኤ ወሕይወት፡፡ ዘየአምን ብየ እመኒ ሞተ የሐዩ ወኩሉ ዘሕያው ዮሐ. 11፣25 ታኅሣስ 2009

እያነሣ ይጠይቃል። የዚህ ሁሉ አስገኚና ምንጭ ግን እግዚአበሔር ይሁን እንጂ ያስተማረው እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል አባታችን
ነው። በ ኢሳ. 64፣8 ላይም “አሁን ግን፥ አቤቱ፥ አንተ አባታችን እንደሆነ ነው። ጳውሎስ ልጆቼ ያላቸውን ሁሉ የወለዳቸው በክርስቶስ
ነህ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ነው።
ሥራ ነን” ይላል። አባትነቱም እንደ ምድራውያን አባቶች ሳይሆን
በኢሳ. 9፣6 ላይ እንደተፃፈው ዘላለማዊ ነው። ከላይ አባት ስለሚያሰኙ የተለያዩ ባሕርያት ተመለከትን፣ ምድራውያን
አባቶች አንዱን ወይ ጥቂቱን የአባትነት መስፈርት ቢያሟሉ እንጂ
ለ. አማካሪ ነው፡- “በቤተልሔም ይሁዳም ከይሁዳ ወገን አንድ ጎልማሳ
ሁሉን አያሟሉም፡፡ እግዚአብሔር አባታችን ግን ሁሉንም የአባትነት
ከሌዊ ወገን የነበረ የሚቀመጥበት ስፍራ ሲፈለግ ሚካ የተባለ ሰው
መስፈርት የሚያሟላ ፍጹምና ዘላለማዊ አባት ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ግን
ያገኘዋል። በጠየቀው ጊዜ ከሌዊ ወገን መሆኑን ሲያውቅ ከእኔ ዘንድ
ብቻውን ያለ አማካሪና ረዳት የፈጠረንና በሕይወት የጠበቀን፣
ተቀመጥ አባትና ካህን ትሆነኛለህ፤ እኔም ልብሶችና ምግብህን
ዳግመኛም በሞቱ የወለደን፣ መንፈሱንም በልባችን የላከ እግዚአብሔር
በየዓመቱም አሥር ብር እሰጥሃለሁ አለው። በመጨረሻም ሚካ ሌዋዊ
እርሱ አባታችን ነው። በገላ. 4፣6 ላይ፡- “ልጆችም ስለ ሆናችሁ
ካህን ስለሆነልኝ እግዚአብሔር መልካም እንዲሠራልኝ አሁን
እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ
አውቃለሁ አለ (መሳ. 17፣10)። ይህ ካህን ከእግዚአብሔር የሆነውን
በልባችሁ ውስጥ ላከ” ተብሎ እንደተጻፈም አባ ብለን እንድንጠራው
መልዕክት ይነግረውና ይመክረው ዘንድ ጎልማሳውን በቤቱ
የልጅነት መንፈስን ሰጠን።
እንዲቀመጥ ለመነው። እግዚአብሔር ግን ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ
በምክሩ ግሩም ነው፤ ለዚህም ነው መዝሙረኛው “ኑ ብዙዎቻችን እንመኝ የነበረው በሙያው፣ በስልጣኑ፣ ወይ በሃብቱ
የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር አንቱ የተባለ ትልቅ ሰው ልጅ መባልን ነበር ይሆናል። ነገር ግን የሰማዩ
ግሩም ነው” ሲል የዘመረው (መዝ. 65፣5)። አንዳንድ ጊዜ አባታችን እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡
የጸሐፍያንን ሥራዎች በማንበብ፣ አንዳንዴ ደግሞ የተለያዩ ሰዎችን
በመጠየቅ ምክርን ልናገኝ እንሞክራለን። ከእነዚህ ምንጮች የሚገኝ የሕክምና ሳይንስ እግዚአብሔር ከፈጠረው ሰው አዕምሮ እና ዓለም
ምክር በጥቂቱ ሊጠቅም ይችል ይሆናል። ከሰዎች የምናገኘውን ምክር በተገኘ ጥበብ፣ እውቀት፣ እና ቁስ ለሰዎች የጤና ችግር መፍትሔ
እርግጠኝነቱና አዋጪነቱን መፈተሽ ይገባል። ሁሉን አወቂ የሆነው ይሰጥ ይሆናል። ያም ሆኖ ብዙ ጉድለትና ውሱንነት አለበት፡፡
የእግዚአብሔር አባታችን ምክር ግን ግሩምና እርግጠኛ ነው። አባታችን እግዚአብሔር ግን እውሩን የሚያበራ፣ ጎባጣውን የሚያቀና፣
ሽባውን የሚተረትር፣ ለመካኒቱ ልጅ የሚሰጥ፣ የሞተውን የሚያስነሳ
ሐ. የአንድ ዓይነት ኑሮ መሥራች ነው፡- ዘፍ. 4፣21 ስለ ዩባል ሲናገር አንዳች የማይሳነው ዘላለማዊ ሐኪም ነው።
“እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ ” ይላል።
የእነዚህ ሰዎች ሥራ በገናና መለከትን መያዝ ነበር፤ ዩባልም የዚህ መሐንዲሶች እግዚአብሔር በሰጣቸው አዕምሮና እውቀት መንገድና
ዓይነቱ ኑሮ መስራች በመሆኑ አባት ተባለ። እግዚአብሔር አባታችን ሕንፃ ሊገነቡ ይችላሉ፤ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚያደርስን
ነው ስንል አንዱ ምክንያታችን የሕይወታችን መሥራች ስለሆነ ነው። መንገድ እና የዘላለም ሕንጻ ግን አይደለም። እግዚአብሔር አምላካችን
አዎ! ኑሮአችን ክርስትና ነው፤ ክርስትና ደግሞ የተመሠረተው ግን ከመሐንዲስ ሁሉ በላይ ነው። እርሱ የእኛ አምላክ ግን ብቸኛውን
በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስም የእምነታችን የዘላለም ሕይወት መንገድ የሠራልን፣ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ
ጀማሪና ፈፃሚ ነውና አባታችን ነው (ዕብ. 12፣1-2)። የዘላለም ቤት የሚሆን ሕንጻ ያዘጋጀልን ከመሐንዲስ በላይ የሆነ አባት
ነው፡፡
መ. ሰውን ወደ እምነት ያደረሰ፡- በ 1ቆሮ. 4፣14-15 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ
“እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ የዚህ ዓለም አዋቂዎች አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተፈጠረውን ነገር
ይህን አልጽፍም። በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ መርምረው አዲስ ግኝት ላይ ደረስን ይላሉ። እግዚአብሔር ግን
ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ብቸኛ ፈጣሪ ነው፤ እርሱ
ወልጄአችኋለሁና” ሲል ጽፏል። ይህን በማለቱ ወደ እምነት ያደረሰ ደግሞ አባታችን ነው፡፡
ሰው አባት እንደሚባል ያስረዳል። ጳውሎስ በእምነት የብዙዎች አባት

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 4
ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል ዮሐ. 11፣25
አዲስ አበባ
ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥአ እምኩሎሙ ሰብእ ምውታን 1ቆሮ. 15፣20 ታኅሣስ 2009
“እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥
እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም
ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል
“ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ
ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥
ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም ይላል እግዚአብሔር እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ
አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው። በዚያችም መንገድ እመልሳችኋለሁ” (ኤር. 29፣12-14 )
ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ
ወጣ። ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና፡ - በሉቃ. 8፣42-48 ላይ የምናገኛት ለ12 ዓመት ደም ይፈስሳት የነበረች
ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ሴት ጌታን በሚያጋፉት ብዙ ሰዎች መካከል በፍጹም ልቧ ፈልጋ
ውረድ አለው። ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው። ሁሉም ስለነካችው ኃይል ከእርሱ ወጥቶ የዘመናት ቀንበሯን ሰብሮላታል።
አይተው፡- ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው እግዚአብሔር ከልብ በፈለግነውና በቀረብነው መጠን ይገኝልናል፣
አንጐራጐሩ። ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ ይቀርበናልም (ሉቃ. 7፣37-50፤ ሚል. 3፣1)። “ስለዚህ እልሃለሁ፥
እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት
ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው። ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል” (ቁ. 47)። እግዚአብሔርን
የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤ የሰው ከልብ የምንሻ ከሆነ መሻታችንን በጽኑ እምነት ለራሳችን እንናገር።
ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው ” (ሉቃ. 19፣1-
10)።  “በልብዋ፡- ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ
ትል ነበረችና” (ማቴ. 9፣21)።
ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ እና ባለጠጋ ሰው ነበረ። ስልጣኑ፣ ሆኖም ግን
 “ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ
አንቱ ያሰኘው ንብረቱ፣ በሰው ዓይን ትልቅ መባሉ፣ ስልጣኑ… ጌታን
ለማየት አልረዳውም ነበር። ጌታ ኢየሱስን ለማየት የነበረው ትልቅ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን
መሻትም ስሜ፣ ክብሬ፣ ዝናዬ፣ ሰው ምን ይለኛል? ሳይል እንደ ሕፃን ሮጦ ከዚህ በራብ እጠፋለሁ። ተነሥቼም ወደ አባቴ
ዛፍ ላይ እንዲወጣ አደረገው፤ ጌታን በማየቱም ለክብር በቃ። እሄዳለሁና። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥
ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ
ሰው ልቡን የጣለበት ነገር ይወርሰዋል፤ የወረሰው ነገር ደግሞ ሊያድነው አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ” (ሉቃ. 15፣17-19)።
አልያም ሊያጠፋው ይችላል። “ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ
ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ እኔ በሚል ከፍታ ላይ ተቀምጠን እግዚአብሔርን ወደ ልባችን
አየች ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው ማስገባት አይቻለንም። ስለዚህም ጌታ ወደ እኛ ሲመጣ ከወጣንበት
እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም የእኔነት ከፍታ ወርደን ዝቅ በማለት በትሕትና ልንቀበለው ይገባናል፤
ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው እርሱ የተዋረደ ልብን ይፈልጋልና። “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ” (ዘፍ. 3፣6-7)። የምናየው ነገር ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት
የሚወርሰን ከሆነ የእግዚአብሔርን በረከት እንዳንቀበል ያደርገናል። የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ
አይጠቅምም ብለን ትተነው የወጣነውን ነገር እንደ ገና ወደ ኋላ እያየን ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ
ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔርን ክብር አጥተን እንዳንጠፋ መጠንቀቅ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥
አለብን። “የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፥ የጨው መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው
ሐውልትም ሆነች” (ዘፍ. 19፣26)። ስለዚህ ለእኛ የሚበልጥብን ሁሉን እመለከታለሁ” (ኢሳ. 66፣1-2)።
ትቶ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው። “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ
ጌታ ወደ እኛ ሲመጣ እና ስንቀበለው ሰዎች ሊያንጎራጉሩና ሊቃወሙ
እናንተም ይቀርባል” (ያዕ. 4፣8)።
ይችላሉ፡፡ ሆኖም በተቃውሞ ውስጥም ቢሆን በፍጹም ልብ እርሱን
ሜልኮል ዳዊት ለምን ራሱን እንደጣለ ስላልተረዳች ባየችው ነገር ተወስዳ ለመከተል ውሳኔው የእኛ ነው (ሉቃ. 19፣7)። የዙሪያችንን ተቃውሞና
ንጉሡ ራሱን እንዳቀለለ አድርጋ ናቀችው። በዚህም እግዚአብሔር ወደ
ማንጎራጎር አይተን ወይንም በተለያየም ምክንያት ጌታን በቤታችን
ቤቷ ያመጣውን በረከት አጣች (2ሳሙ. 6፣16-23)። እግዚአብሔርን
ፈልገነው ከቀረብን እንደ ዘኬዎስ ከወጣንበት፣ ከታመንንበት ነገር ላይ ለመቀበል ከቸገረን አልያም ከዘገየን ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችላል።
መውረድ አለብን። እግዚአብሔርን ከልብ መፈለግ ካለን በረከት አለና።
የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 5
አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል 1ቆሮ. 15፣20 አዲስ አበባ
ወናሁ ይእዜ ዕለት ኅሪት ወናሁ ዮም ዕለተ አድኅኖት 2ቆሮ. 6፣2 ታኅሣስ 2009

“እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም


ደጁን ይመታል እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥
በራሴ ጠል፥ በቆንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ክፈችልኝ። ቀሚሴን አወለቅሁ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን
ታጠብሁ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥
ካለፈው የቀጠለ
አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ
እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ምዕ. 8
ከርቤ አንጠበጠቡ። ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ የእስራኤል ሕዝብ እንደሚገባቸው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩና
አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች ፈለግሁት፥ ለኃጢአታቸውም ሥርዓት እንዲያገኙ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት
አላገኘሁትም ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም” (መኃ. 5፣2-6)። ካህናት እንዲቀደሱ አስፈላጊ ነበር። በዚህም መሠረት የአሮንና ልጆቹ
የክህነት ሥርዓት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ማኅበሩን በመገናኛው
ዘኬዎስ በዙሪያው የነበሩትን ሰዎች ማንጎራጎር ሳይመለከት ጌታን ድንኳን ደጅ በመሰብሰብ ተከናወነ። የቀረቡት ሦስት ዓይነት
በቤቱ በመቀበሉ በሕይወቱ ታላቅ በረከት ሆኖለታል። “ኢየሱስም፦ መሥዋዕቶች ነበሩ። እነርሱም፡-
እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን
ሆኖለታል፤ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ሀ. ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን፣
መጥቶአልና አለው” (ሉቃ. 19፣9)። ከልብ የፈልግነው ለ. ለሚቃጠል መሥዋዕት አውራ በግ፣
እግዚአብሔርን ወደ ቤታችን (ሕይወታችን) ሲገባ፡- ሐ. ለቅድስና መሥዋዕት አውራ በግ ናቸው።

 በኃጢአታችንን እንወቀሳለን፣ በደላችንንም እንናዘዛለን (ቁ. 8)፣ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ሕዝብ በክህነት የሚያገለግሉአቸው ካህናት
ይቀቡላቸው ነበር። በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከክርስቶስ መሥዋትነት
 ያለንን ለሌሎች ማካፈል እንጀምራለን (ቁ. 8)። የተነሣ ወደ እግዚአብሔር በሙላት ሊያቀርበን ስለቻለ የንጉሥ ካህናት
 ሕይወታችን፣ ኑሮአችን፣ ትዳራችን፣ … ይፈወሳል፤ ታሪካችንም እንድንባል አስችሎናል። “እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች
ይቀየራል። “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ
ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት
እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ” (1ጴጥ. 2፣5)።
ጋር ይበላል” (ራእ. 3፣20)። ስለዚህ ይህን በረከት ለመቀበል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የካህናት አለቃ፣ ራሱን
የእኔ ብለን ከወጣንበት ከፍታ ፈጥነን እንውረድ፣ ዝቅ እንበል። መሥዋዕት አድርጎ፣ ራሱ መሥዋዕት አቅራቢ በመሆን ከአባቱ ጋር
አስታረቀን፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ካህንነት (አገልግሎት) ብቃት
“…እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን
ሆነን። “ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ግን ጸጋን ይሰጣል…” (ያዕ. 4፣6)።
መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ነብዩ ኤልያስን የተቀበለችው የሰራፕታዋ መበለት ታሪክ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤
አሜን” (ራእ. 1፣5-6)።
የሚያስተምረን ነገር አለ። የጌታን ባሪያ በቤቷ ተቀብላ ጥቂት
በሕይወት ለመቆየት ያላትን የመጨረሻ ነገር ጨክና በማካፈሏ
እግዚአብሔር ሕዝቡ ለእርሱ የተለየ ሕዝብ፣ የተቀደሰ መሥዋዕት
የረሃቡን ዘመን በበረከት ማለፍ ችላለች (1ነገ. 17፣1-24)። የዚህች ሴት
አቅራቢ ካህናት ይሆኑለት ዘንድ ይፈልጋል። “እናንተ ግን ከጨለማ
እግዚአብሔርን መታመን ያስገኘው በረከት ከራሷ አልፎ ለቤቷ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ
(ለቤተሰቧ) ተርፏል። “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ
ይላልና። በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን የተለየ ወገን ናችሁ” (1ጴጥ. 2፣9)። ይህ የታላቁ ጌታ አግዚአብሔር
ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው ካህን (አገልጋይ) የመሆን ዕድል ታላቅ ክብር ስለሆነ የነአሮን
አይጎድልም። እርስዋም ሄዳ እንደ ኤልያስ ቃል አደረገች የመቀባት፣ የመካን፣ የመለየት ሥርዓት ሰባት ቀናት የሚወስድ ነበር።
እርስዋና እርሱ ቤትዋም ብዙ ቀን በሉ” (ቁ 14-15)። ይህም እግዚአብሔርን የማገልገል፣ ለእርሱ የመለየት ነገር ትልቅ
እግዚአብሔር ሲፈልገን መገኘታችን ከራሳችን አልፎ ለቤታችንም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን ያሳያል። በክህነቱ አገልግሎት
ለሌሎችም የሚተርፍ በረከት ያስገኝልናል። የመቀባት ሥርዓት የሚፈጸመው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሕዝቡ
ሁሉ በተሰበሰቡበት ነበር።-

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 6
እነሆ፣ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ፣ የመዳን ቀን አሁን ነው 2ቆሮ. 6፣2 አዲስ አበባ
ወዘሰ ኢየአምን ቦቱ ወድአ ተኮነነ እስመ ኢአምነ በስመ ወልደ እግዚአብሔር ዋህድ ዮሐ. 3፣18 ታኅሣስ 2009
 ሕዝቡ ሁሉ ሲል ነገዶቹን የሚወክሉ የማኅበሩ አለቆች፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናውቅበት፣ የምንጠይቅበት፣
ሽማግሌዎች እንጂ መላው ሕዝብ ላይሆን ይችላል። እጅግ ብዙ የምንመረምርበት ፍጹም ብርሃን የሆነው ኡሪም ቱሚማችን
የሆነውን ሕዝብ በድንኳኑ ደጃፍ መሰብሰብ አስቻጋሪ ሊሆን የእግዚአብሔር ቃል ነው። “ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው ስለዚህ
ይችላልና፣ ደግሞም በእስራኤል ሕግ የነገድ አለቆችና ሽማግሌዎች ነፍሴ ፈለገቻቸው። የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም
የሕዝቡ ወኪል በመሆን በእግዚአብሔር ፊት ይታያሉ፤ አስተዋዮች ያደርጋል። አፌን ከፈትሁ፥ አለከለክሁም ወደ
መላው ሕዘብ እንደቀረበ፣ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንደተቀበለም ትእዛዝህ ናፍቄአለሁና” (መዝ. 118፣129-131)። ቅድስና
ይቆጠር ነበር (ዘጸ. 4፣29-31፤ 34፣31-32፤ ዘኁ. 17፣2-10)። ለእግዚአብሔር የሚለው በግልጽ የሚታይ መታወቂያችን ደግሞ
 መንፈሳዊ ሹመቱ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ፊት በምስክርነት ለእግዚአብሔር መለየት ነው።
የሚከናወን ስለሆነ ሕዝቡ ምስክር ይሆናል፣ ያውቃልም። ሕዝቡ
ደግሞ በእግዚአብሔር የተሾመ፣ የተቀባ መሆኑን በማወቅ ከመታጠብና ከመልበስ ቀጥሎ የሚሆነው ደግሞ ማንም ለራሱ
ሊታዘዙ ይገባል። ሊያዘጋጀውና በሰው ላይ ሊደረግ በማይችል የቅብዓት ዘይት መቀባት
 ሙሴ አሮንና ልጆቹን አቅርቦ በውኃ ያጥባቸዋል። ይህ መታጠብ ይሆናል (ዘጸ. 30፣1-3)። ዘይቱ በአሮን ራስ ላይ ይፈስሳል (መዝ. 133፣1
መላ አካላቸውን ነው፤ ከዚያ በኋላ ለአገልግሎት ወደ መገናኛው -3)። ዘይቱን መቀባት የመሾም ምልክት ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን
ድንኳን በገቡ ቁጥር እጆቻቸውንና እግራቸውን ይታጠባሉ። ደግሞ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ መገለጹን ልብ እንበል።
መንጻቱ፣ መለየቱ አንድ ጊዜ የሚከናወን በዚሁም የሚጸና ነው። በአዲስ ኪዳንም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተቀደሱ
በአዲስ ኪዳንም አንድ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን ክርስቲያኖችም ለአገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ይቀባሉ። “እናንተም
ፈጽመን በመቀደስ የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን (ዮሐ. 13፣9- ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ” (1ዮሐ.
10)። ከዚያም በኋላ በሚኖር ምልልሳችን እግዚአብሔርን 2፣20)።
ስንበድል ንስሐ በመግባት እንነጻለን። “የልጁም የኢየሱስ
ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት ከቁ. 14 ጀምሮ ደግሞ የተለያዩ መሥዋዕቶችን ሙሴ ስለ አሮንና ልጀቹ
የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ሲያቀርብ እንመለከታለን። አሮንና ልጀቹ የኃጢአት መሥዋዕቱ
ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ወይፈን ራስ ላይ እጃቸውን መጫናቸው በምሳሌነት ኃጢአታቸው ወደ
ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ መሥዋዕቱ እንስሳ መተላለፉን ያመለክታል። የወይፈኑ ደም
ነው” (1ዮሐ. 1፣7-9)። በመሠዊያው ላይ ከተረጨ በኋላ ስቡ በመሠዊያው ላይ ይቃጠላል።
ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን በደል ወስዶ ከሰፈር ውጪ
“ሸሚዝም አለበሰው፥ በመታጠቂያም አስታጠቀው፥ ቀሚስም መከራን በመቀበል እንዳዳነን፣ እንደቀደሰን፣ እንዳከበረን ምሳሌ ሆኖ
አለበሰው፥ ኤፉድም ደረበለት፥ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ አስቀድሞ ተገልጾአል። “ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት ወደ ቅድስት
አስታጠቀውና በእርሱ ላይ አሰረው። የደረት ኪስ በእርሱ ላይ የእንስሶችን ደም ያቀርባልና፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ
አደረገ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት” (ቁ. ይቃጠላል። ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን
7-8)። ከመታጠቡ ሥርዓት በኋላ የሚከተለው በተለየ ጥበብ እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። እንግዲህ
የተዘጋጀውን የከበረ ልብስ መልበስ ነው (ዘጸ. 28፣1-29)። በደረቱ ኪስ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ
ውስጥም ኡሪምና ቱሚም ይቀመጣል። ኡሪምና ቱሚም ትርጓሜው እንውጣ” (ዕብ. 13፣11-13)።
ብርሃንና ፍጹምነት ማለት ሲሆን አገልግሎቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ
ማወቂያ (መጠየቂያ) ነው (1ሳሙ. 28፣6)። በራሱ ላይ ባለው ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው አውራ በግ ደግሞ ሙሉ በሙሉ
መጠምጠሚያ ላይ ደግሞ የተቀደሰው አክሊል፣ ቅድስና ራስን ለእግዚአብሔር የመስጠት ነገርን ያመለክታል። “እንግዲህ፥
ለእግዚአብሔር የሚለው ምልክት ይደረግበታል። ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና
ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ
ወደ አዲስ ኪዳን የክህነት አገልግሎት ስንመጣ አማኞች በኢየሱስ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ
ክርስቶስ ደም ከታጠቡ፣ ከነጹ በኋላ የጽድቅ ልብሳቸው ራሱ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም
የተቤዣቸው ጌታ ይሆናል። “ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን
እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ
አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ሮሜ 12፣1-2)። በበጉም ራስ ላይ
በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ እንዲሁ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን ከጫኑበት በኋላ ነው የሚታረደው።
የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ” (ኤፌ. 4፣22-24)። “አሮጌውን ክርስቲያኖች ከኃጢአታችን በመንጻት ለእግዚአብሔር አገልግሎት
ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥ የፈጠረውንም ምሳሌ እንለይ ዘንድ ብቃት የሆነን የእግዚአብሔር በግ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ
እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ነው። የበጉ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ
ለብሳችሁታል” (ቆላ. 3፥9-10፤ ሮሜ 13፣14)።
በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል ዮሐ. 3፣18 የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 7
አዲስ አበባ
ወንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ 1ቆሮ. 1፣23 ታኅሣስ 2009
ሽታ ይሆን ዘንድ ይቃጠላል። “ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ
ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን የጳውሎስ መልእክታት ጥናት
አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር
ተመላለሱ” (ኤፌ. 5፣2)። ካለፈው የቀጠለ የ1ኛ ቆሮንቶስ መልእክት

ለቅድስና በሚታረደው በግ ላይም አሮንና ልጆቹ እጃቸውን ይጭናሉ።


ሐ) የትንሣኤ አካል ሁኔታ (ባሕርይ) (15፣35-58)
ከታረደም በኋላ ሙሴ ከደሙ ወስዶ የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፣ የቀኝ
እጃቸውን አውራ ጣትና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ያስነካቸዋል።
35፡-- “ ነገር ግን ሰው፡- ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ
ቁጥር 35፡
ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።” ፡- ከፈረሱ ከበሰበሱ
† ጆሮ የእግዚአብሔርን ድምፅ ብቻ ለመስማት፣ በኋላ እንደምን ያለ አካል ገዝተው፣ ከመቃብር ሙታን እንደምን
† እጅ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት፣ ይነሣሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል ለማለት ነው፤ (ሕዝ. 37፣3)።
† እግር በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለመሄድ መለየታቸውን ነገሩ የሚያስቸግር ሆኖ ይታየዋልና። ቀድሞ ግሪኮች የነፍስን መኖር
በምሳሌነት የሚያመለክት ይሆናል። ብቻ ያስባሉና ግዙፉን የአካል ትንሣኤ ይክዳሉ። በኋላ አንዳንድ
የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ስለ ክርስትና ትምህርት፣ የሞቱት ነቅተው፣
“ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ የትንሣኤ ሕይወት የቁሳዊ አካል መኖር (መቀጠል) ነው ብለው አሰቡ።
ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በሚቀጥሉት ቁጥሮች ለዚህ ሁለት ነጥቦችን
ረጨው አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም የልጆቹንም ልብስ ያነሣል።
ቀደሰ” (ቁ. 30)። ይህ ደግሞ እነርሱም ልብስ ተክህኖአቸውም
ፈጽመው ለእግዚአብሔር በመለየት የተቀደሱ መሆናቸውን 36፡-- “ አንተ ሞኝ፣ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው
ቁጥር 36፡
አይሆንም፤” ፡- ገበሬ እንኳ የዘራው ዘር ካልፈረሰ ካልበሰበሰ
ያመለከታል። የተካኑበትን በግ ሥጋ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ
አይበቅልም። ይህ የመጀመሪያ ነጥቡ ሲሆን፣ እንዴት ሞት ወደ
ተቀቅሎ ከቅድስናው እንጀራ ጋር አሮንና ልጆቹ ይበሉታል። እነርሱ
ሕይወት መውጣትን ሊሰጥ ይችላል? የሚል ነው። የሚዘሩት ዘር
ከበሉ በኋላ የተረፈው በእሳት ይቃጠላል እንጂ አያድርም። ይህ አስቀድሞ ይበሰብስ የለምን? ከበሰበሰም በኋላ ተመልሶ ሕያው ይሆን
የክህነት ሥርዓት ለሰባት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በእነዚህ ቀናት የለምን? ሕይወት እንዲቀጥል ሞት አስፈላጊ መሆን እንደሚችል የዘሩ
ውስጥ አሮንና ልጆቹ ሌሊትና ቀን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቢለዩ ምሳሌ ያስረዳል (ይጠቁማል)፤ (ዮሐ. 12፣24)። ቅዱስ ጳውሎስ
ይሞታሉ። የእያንዳንዳቸውን ልምድ፣ በኑሮ የሚያዩትንና የሚያውቁትን
ያመለክታል፤ እና ስሜትና ማስተዋል ማጣታቸውን እያጋለጠባቸው
† ሰባት በመድሐፍ ቅዱስ የፍጹምነት መገለጫ ቁጥር ነው። ይህም መሆኑን አስታውስ።
ሰው ለእግዚአብሔር ሲለይ ለአንዴም ለመጨረሻም በፍጹም
የእግዚአብሔር ሊሆን ነው። 37፡-- “ የምትዘራውም፣ ስንዴ ቢሆን ከሌላም ዓይነት የአንዱ
ቁጥር 37፡
ቢሆን፣ ቅንጣት ብቻ ነው እንጂ የምትዘራው የሚሆነውን አካል
† በመገናኛው ደጃፍ ቀንና ሌሊት፤ በወጣትነትና በሽምግልና፣ አይደለም፤” ፡- ሁለተኛ ነጥቡ ይህ ነው።- የሚዘሩት መቼም ቅንጣት
በከፍታና በዝቅታ፣ . . . ሁሉ ቢሆን ከእግዚአብሔር መለየት ብቻ ነው፤ የሚነሣው ግን ሌላ አካል ነው። ማለት የሚነሣው አካል
እንደማይገባ ያስተምራል። ከእግዚአብሔር መለየት ደግሞ ውጤቱ የተዘራው ዘር አካል ነው፣ ሆኖም ልዩ ነው፤ የሚነሣው የታደሰ አካል
ሞት መሆኑን በማስተዋል ለሁላችንም ትምህርትና ማስጠንቀቂያ ሆኖ እንጂ ያው የተዘራው አይደለም። ያ ቅንጣት ወደ አፈር ገብቶ
ይበሰብሳል፤ ከዚያ በኋላ በአዲስ አካል ይበቅላል፣ ይለመልማል።
የተገለጸ ነው። “እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና።
እንግዲህ የትንሣኤ አካል ጠባይ (ባሕርይ) ምንድን ነው? ከአሮጌው
ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና። እኔን ያጣ ግን ራሱን
አካል በቀጥታም ባይሆን ይያያዛል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በትክክል
ይጐዳል የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ” (ምሳ. 8፣35-36)። አንድ አይደለም።
“አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዘውን ሁሉ
38፡-- “ እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል፣
ቁጥር 38፡
አደረጉ” (ቁ. 36)። ካህናቱ እግዚአብሔር የሰጠውን ትዕዛዝ ሁሉ ከዘሮችም ለእያንዳንዱ የገዛ አካሉን ይሰጠዋል።” ፡- ምንም እንኳ ዘሮች
በደስታ ማድረጋቸው እግዚአብሔር የሚሰጠንን ትዕዛዝ (ቃሉን) (ተክሎች) ተመሳሳይ ባሕርይ ቢኖራቸውም' አንዱ ከሌላው የተለየ
በሙሉ መቀበል፣ መፈጸም እንደሚገባ ያስተምረናል። ነው። የተዘራው ዘር በቅሎ ከሚወጣው ተክል ጋር ተመሳሳይነት
ይ ቀ ጥ ላ ል አለው፤ ይሁን እንጂ አዲሱ ቡቃያ የተለየና ፍጹም አዲስ አካል

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 8
እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን 1ቆሮ. 1፣23 አዲስ አበባ
ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወብነ ሕይወት ዘለዓለም 1ዮሐ.5፣21 ታኅሣስ 2009
ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሰጠዋል። አዲሱ የትንሣኤ ሕይወት ወዲያው 44፡-- “ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፣ መንፈሳዊ አካል ይነሣል።
ቁጥር 44፡
የሚሆን አይደለም፤ ነገር ግን አስቀድሞ በተወሰነው ፈቃዱና ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ።” ፡- “ካለ” ሲል፣
በእግዚአብሔር የፈጣሪ ሥራ (የፈጣሪነት ጥበቡ) ላይ የተደገፈ ነው። አለና፣ ማለቱ ነው። “ፍጥረታዊ አካል”፡- የተፈጥሮአዊ ሕይወት
ሁኔታዎችን ይመለከታል። “መንፈሳዊ አካል”፡- በሰው ቁጥጥር ሥር
39፡-- “ ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም፣ የሰው ሥጋ ግን አንድ
ቁጥር 39፡
ሆኖ፣ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ፍጹም ኅብረት ያለው ነው።
ነው፣ የእንስሳም ሥጋ ሌላ ነው፣ የወፎችም ሥጋ ሌላ ነው፣ የዓሣም
“መንፈሳዊና ፍጥረታዊ”፡- የህልውናን ክበባት ወይም ቅርጾች አካላቱ
ሥጋ ሌላ ነው።” ፡- በሥጋ ለባሾች አካላዊ በሕርይ መካከል
በየራሳቸው ገብተው የሚስማሙበትን ያመለክታል። የሚቀበረው
ተመሳሳይነት ቢኖርም' እያንዳንዱ ዝርያ ግን የተለየ ነው፤ ሰው፣
አካል ለዚህ ለምድራዊ ሕይወት የሚሆን ፍጥረታዊ አካል ነው፤
እንስሳት፣ አዕዋፍና ዓሦች የተለያዩ ናቸው። አንድም፡- የሰው ባሕርይ
የሚነሣው ሌላ፣ እርሱም ለመንግሥተ ሰማያት የሚሆን መንፈሳዊ
ከእንስሳው ባሕርይ፣ የእንስሳው ባሕርይ ከሰው ባሕርይ ልዩ ነው፤
አካል ነው።
አካሉ መልኩ። እንዲሁ የወፍ ባሕርይ ከዓሣው ባሕርይ፣ የዓሣው
ባሕርይ ከወፉ ባሕርይ አካሉ መልኩ ልዩ ነው።
እንግዲህ ሰው ከሙታን ሲነሣ ባለ አካል ሆኖ እንዲነሣ እናያለን።
ቁጥር 40 41፡-- “… ሰማያዊ አካል አለ፣ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር
40--41፡ እራቁቱን የሆነ መንፈስ ብቻ መሆኑ አይደለም፣ አካል ይኖረዋል
ግን የሰማያዊ አካል ክብር ልዩ ነው፣ የምድራዊም አካል ክብር ልዩ እንጂ። ይህ የትንሣኤ አካል የአሁኑ ዓይነት ሥጋችን አይሆንም፤
ነው። የፀሐይ ክብር አንድ ነው፣ የጨረቃም ክብር ሌላ ነው፣ መንፈሳዊ አካል ነው። በዚህ ዓለም ላይ የአዳም ልጆች ነንና የተፈጥሮ
የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው፤ በክብር አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ አባታችንን የአዳምን መልክ ለብሰናል፣ ፍጥረታዊም አካል አለን።
ይለያልና።” ሰማያዊ አካላት የተባሉት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት በዚያ ጊዜ ግን እኛ ለክርስቶስ የሆንን ሁሉ የዘላለማዊ አባታችንን
ሲሆኑ፣ ምድራዊ አካላት፡- ተራሮች፣ ባሕሮች፣ ድንጋዮች፣ ወዘተ. የክርስቶስን መልክ እንለብሳለን፣ መንፈሳዊም አካል ይኖረናል።
ናቸው። በአካላት መካከል የተለያዩ ቅርጾች መኖራቸው፣
ለእያንዳንዳቸው በፈጣሪ ተመቻችቶ እንደተሰጣቸው የተለያዩ ቁጥር 45 46፡-- “ እንዲሁ ደግሞ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ
45--46፡
አካላትና የአሠራር ሥልቶች መኖራቸውን ያመለክታል። ስለዚህ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ
በእንዲህ ዓይነት ልዩነት ውስጥ በጣም ትልቅ ኅብረ መልክዕ መኖሩ ሆነ። ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው
ግልጽ ነው። እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያው አይደለም።”፡- ይህን የሚደግፍ
በዘፍ. 2፣7፤ “አዳም ሕያው ነዋሪ ሆነ፤”፡- ሰው ሕያው ነፍስ ያለው
42፡-- “ የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ
ቁጥር 42፡ ሆኖ በመፈጠሩ ይለያል። አሁን በሚገኝበት የኑሮ ቅርጽ በነፍስ የሚገዛ
ይዘራል፣ ባለመበስበስ ይነሣል፤” ፡- እንዲሁ ነው፣ ማለቱ ከላይ አካል ያለው መሆኑ የሰው ባሕርይ ነው። “ኋለኛው አዳም”፡-
ከዘረዘራቸው ምሳሌዎች ጋር ለማስተያየት ነው። የክርስቲያን (ክርስቶስ) የዳኑ ሰዎች አዲሱ ትውልድ ጀማሪ፤ እርሱ (ለእነርሱ)
የትንሣኤ አካል ፍጹም አዲስ ክበብ ሆኖ ከተሰጠው ጋር የተስማማ ሕይወትን ሰጪ መንፈስ ነው፤ (ዮሐ. 5፣21፤ 6፣63)። ይኸውም
ይሆናል። (2ቆሮ. 5፣1-4)። ትንሣኤ ማለት እንደገና መታየት መንፈስ የሚቆጣጠረው (የሚመራው) የሚሆን የሕይወት ባሕርይ
(መገለጥ)፣ ወይም በአዲስ ቅርጸ-አካል ለመንቀሳቀስ እንደገና ወደ ይሆናል። አዳም ሕይወትን የተቀበለ ፍጥረት ነው፤ ኋለኛው አዳም
ህልውና መመለስ ነው። ይህንኑ ሐዋርያው ጳውሎስ በተከታተሉ ክርስቶስ ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ እርሱም መንፈሳዊ
ጥንዶች (ጥምሮች) ምሳሌ ይገልጻል።- የተዘራው ዘር በሕይወት ጊዜ ሕይወትንም ትንሣኤንም ይሰጣል።
አካልንና በመቃብር የተኛውን አካሉን ሊያመለክት ይችላል።
መበስበስ ሊጠፋ የሚችል፣ ወይም ለጥፋት የተጋለጠ ነው። ይህ በነፍስ ሕይወት ሕያው ሆኖ የሚኖር ቀዳማዊ አዳም አስቀድሞ
መሠረታዊ እውነት ነበር ምክንያቱ፣ ግሪኮች ማንኛውንም የትንሣኤ ተገኝቷል። በመለኮታዊ ሕይወት ሕያው ሆኖ የሚኖር ዳግማዊ አዳም
ትምህርት የተቃወሙት። ይሁን እንጂ ሐዋርያው እንዳለው፡- ክርስቶስ ኋላ ተገኝቷል፤ ማለት በዘመኑ ፍጻሜ ተወልዶ፣ በሥጋ
በሚፈርስ በሚበሰብስ ሥጋ ይቀበራል፤ በማይበሰብስ ሥጋ ይነሣል። ተገልጦአልና።
43፡-- “ በውርደት ይዘራል፣ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፣
ቁጥር 43፡
በኃይል ይነሣል” ፡- “ውርደት”፡- (በግሪኩ፣ አቲሚያ)፡- ከዜግነት 47፡-- “ የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው
ቁጥር 47፡
መብቶች ውጭ መሆንን፣ “ድካም” (2ቆሮ. 13፣4)፡- ያም ያለሥልጣን ከሰማይ ነው።” ፡- ይህ እንደገና ዘፍ. 2፣7ን ያመለክታል። “መሬታዊ”፡-
(ያለኀይል) መሆንን (ኢሳ. 14፣10-11)፣ ያመለክታልና ሁለቱም የሬሳ ለመበስበስና ለመጥፋት የተጋለጠ መሆኑን ይጠቁማል። “ከሰማይ”
(በድን) ጠባይ ናቸው። ምሳሌው፡- በስባሽ፣ የተዋረደ፣ ወይም ደካማ ማለት የበላይ መሆኑንና የማይበላሽ፣ የማይጠፋ ማለት ነው።
የሆነውን (ኀጢአት የሚገዛውን ፍጥረታዊ አካል) እግዚአብሔር ሁለተኛው ሰው የተባለ ክርስቶስ ከሰማይ የመጣ ሰማያዊ ነው፤ ሰው
በትንሣኤ የማይበሰብስ፣ የከበረ፣ ብርቱ አካል ሕያው አድርጎ የሆነ አምላክ ነውና።
ሊያስነሣው እንደሚችል ለማሳየት ነው። አንድም፡- ንባቡን
አእምሮውን አጥቶ ይቀበራል፤ ንባቡን አእምሮውን አግኝቶ ይነሣል። ቁጥር 48 49፡-- “ መሬታዊው እንደ ሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ
48--49፡
እንዲሁ ናቸው፣ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 9
ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው 1ዮሐ.5፣21 አዲስ አበባ
ወአልቦ ካልእ ስም በታሕተ ሰማይ ዘይትወሀብ ለእጓለ እመ ሕያው በዘ የሐዩ። የሐዋ.4፣11 ታኅሣስ 2009
እንዲሁ ናቸው። የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን መለከት፡- አንዳንድ ጊዜ በታሪክ ውስጥ የመለኮትን (አምላካዊ)
የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን።”፡- መሬታውያን የሆኑት ጣልቃ ገብነትን ተከትሎ ይመጣል። ለምሳሌ፡- ዘጸ. 19፣16፡19።
ማለት ሰዎች ሁሉ የአዳም ልጅ እንደመሆናቸው፣ የሰው ልጅ ጠባይ በዚያን ጊዜ በክርስቶስ አምነው የሞቱቱ መበስበስን ጥለው ይነሡና
የሆነውን ሙስና መቃብር (ጥፋት) ይካፈላሉ። አዳም የወጣው አዲስ የትንሣኤ አካል (መንፈሳዊ አካል) ይሰጣቸዋል። ከላይ እንደ
(ሥሩ፣ አብነቱ) ከመሬት ነውና (ዘፍ. 3፣19)፤ አካሉ መሬታዊ ነው፣ ተገለጸው፣ ገና በሕይወት ያሉቱም ሳይሞቱ ወዲያውኑ ይለወጣሉ።
ልጆቹም መሬታውያን ናቸው። መሬታዊ አዳምን መምሰልን ገንዘብ ከአምስቱ አዕማደ ሃይማኖት አንዱ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ነውና።
እንዳደረግን፣ ሰማያዊ ክርስቶስን መምሰልን ገንዘብ እናደርጋለን።-
አዳምን መምሰል ዳኅፅ ዘበኀጢአት ሞት፤ ክርስቶስን መምሰል 53፡-- “… ሊለብስ ይገባዋልና።” ፡- የሚበሰብሰው ወደ
ቁጥር 53፡
ሕይወት ጽንዓ ቅድሳት ነው፤ (ቄርሎስ)። ክርስቲያኖች ዝምድናቸው የማይበሰብሰው፣ የሚሞተውም ወደ የማይሞተው አካል መለወጡን፣
በአዲስ ሕይወት ከክርስቶስ ጋር በመሆናቸው ከሰማይ ናቸው። ይህም ሊለብስ ይገባዋል በማለት ልብስ እንደ መልበስ አድርጎ ተናገረ፤
የመጨረሻውን ከሰማያዊው ሰው ጋር አካላዊ መመሳሰልን ተስፋ (2ቆሮ. 5፣4)።
ያረጋግጣል (1ዮሐ. 3፣2)።
54፡-- “ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ
ቁጥር 54፡
50፡-- “ ነገር ግን፣ … ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት
ቁጥር 50፡ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፣ በዚያን ጊዜ፡- ሞት ድል
ሊወርሱ አይችሉም፣ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።” ፡- ከትንቢተ
አይወርስም።” ፡- “ሥጋና ደም”፡- ጠፊውን፣ የሚበሰብሰውን፣ ኢሳይያስ ምዕ. 25 ቁ. 8 የተጠቀሰ ሲሆን፣ እርሱም እንዲህ
ደካማውንና ኀጢአተኛ የሆነውን የሰውን ልጅ ያመለክታል፤ (ዮሐ. ይላል።“ ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ
3፣5፡6)። የሰው የአሁኑ ሟች የሆነው ፍጥረታዊ አካል ስለሆነ፣ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤
ለሚቀጥለው/ለሚመጣው ለአዲሱ ሕይወት ሁኔታ አዲስ ዓይነት እግዚአብሔር ተናግሮአልና።” ይህም የሚሞተው የማይሞተውን
አካል ይፈለጋል። ይህ ሥጋችን፣ ማለት የሚበሰብሰው አካላችን ሲለብስ፡- ሞት በመሸነፍ ባሕር ሠጠመ ተብሎ በነቢይ የተነገረው ነገር
ዘለዓለማዊነትን ከቶ ሊወርስ አይችልም። ሥጋዊ ደማዊ ሰው ያን ጊዜ ይደርሳል፣ ይፈጸማል ለማለት ነው። ስለዚህ ሐዋርያው
መንግሥተ ሰማይን አይወርስምና (ፊልጵ. 3፣21)። የተዋጀው ጳውሎስ ስለ ሞት የመጨረሻ ጥፋት (መደምሰስ) ይናገራል።
የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእርሱ ጋር ለመኖር የማይጠፋ አዲስ አካል የተጠቀሰው ትንቢትም በዚሁ የፍጻሜ ዘመን ሞት ድል ተነሥቶ
መልበስ አለበት (2ቆሮ. 5፣2)። በመጥፊያው ባሕር እንደሚዋጥ ያመለክታል። እንዲሁም ቁ. 26ን
እንደገና ከራእይ 20፣14 ጋር ያስተያዩ።
ቁጥር 51 52፡-- “ እነሆ፣ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን
51--52፡
አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት ቁጥር 55 56፡-- “ ሞት ሆይ፣ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፣ ድል
55--56፡
በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም መንሣትህ የት አለ? የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል
የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።” ፡- ሕግ ነው፤” ፡- አሁን ሞት ገና እየሠራ ነው፤ የመግደል ተግባሩን
እንደቀጠለ ነው፤ መውጊያውን (መንደፊያውን) እንደያዘ ነው።
ምሥጢር” ፡- ሐዋርያው ቀድሞ ምሥጢር የነበረውን በሐዋርያት እርሱም፡- ለሞት አቁስሎ የመግደልን ኀይል የሚሰጠው ኀጢአት
ዘመን ግን በእግዚአብሔር የተገለጠውን ነገር አሁን ይነግራቸዋል። ነው። ሞት እንዲሠለጥንብን ያደረገው ኀጢአት ነው፤ ለኀጢአት
ይህ ከአእምሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ምሥጢር በዘመኑ ለቅዱስ ጉልበት የሆነው ደግሞ ሕግ ነው። ምክንያቱም ሕግ ኀጢአታችንን
ጳውሎስ ተገለጠ፤ በ1ኛተሰ. 4፣15 የተጻፈውን ሊያውጅ ማለት ነው። ገልጦ ያሳየናል፤ ደግሞም በኀጢአታችን ይፈርድብናል፤ (ሮሜ 7፣13)።
“ሁላችን አናንቀላፋም” (ሁላችን የምንሞት አይደለም፤) ሲል፣ ኀጢአት መርዝ የሞላበት የጊንጥ መንደፊያ መስሎ ሞትን ያስመርዛል።
ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ በዚህ ምድር በሕይወት ስለዚህ ሞት ኀጢአትን ይከተላል፤ ወይም የኀጢአት ውጤት ነው።
የሚገኙ ክርስቲያኖች ሞትን ሳይለማመዱ ወይም ሳይቀምሱ፣ ያን ጊዜ ግን (በዘመኑ ፍጻሜ) ሞት መውጊያውን፣ ኀጢአትም ኀይሉን
መቃብርንም ሳያዩ፣ እንደ ዓይን ጥቅሻ ወዲያውኑ እንደሚለወጡና ያጣሉ፤ ስለዚህ ሐዋርያው፡- “ሞት ድል መንሣትህ ወዴት አለ?
አዲስ የማይሞት አካል እንደሚያገኙ ያመለክታል። (ፊልጵ. 3፣21)። መቃብርስ ይዞ ማስቀረትህ ወዴት አለ፣ ወዴት ነው?” እያለ
ሄኖክና ኤልያስን ያስታውሱ። ይጠይቃል። በትንቢተ ሆሴዕ ምዕ. 13 ቁ.14 ላይ ያለው ትንቢት ፍጻሜ
መሆኑንም ጠቅሶ ያመለክታል።
በድንገት በቅጽበተ ዓይን” ፡- ምንም ጊዜ በማይወስድ ክሥተት (ከዊን)
፣ (ለምሳሌ፡- ሞት፣ የዓይን ጥቅሻ፣ ንጥቀት፣ ወዘተ.)። ይህ “የኋለኛው 57፡-- “… በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን
ቁጥር 57፡
መለከት”፡- (የኋለኛው አዋጅ)፡- (ማቴ. 24፣31፤ 1ተሰ. 4፣16) ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።” ፡- በክርስቶስ የተገኘው
የክንውኑ መጨረሻ አይደለም፤ (እንደ ራእ. 8፣2)፤ ነገር ግን ድል ዛሬም እስከ ዳግም ምጽአትም ድረስ ለሚያምኑ ሁሉ የሚሆን
መጨረሻውን የሚያስታውቅ ጥሪ ነው፤ (ቁ. 24)። ፍጹም ድኅነት ነው። አማኞች የክርስቶስን የድል መንሣቱ ፍሬዎች
ተሳታፊ (ተካፋይ) መሆናቸው የተረጋገጠ ስለሆነ፣ ሐዋርያው፡-

የ.መ.ሣ.ቁ. 121024 10
እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋ. 4፣11
አዲስ አበባ
ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ ታኅሣስ 2009
በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ዮሐ. 4፣4
“ለሚሰጠን” በማለት የአሁን ጊዜ ግሥ ሊጠቀም ችሏል። የሞት
መውጊያ ኀጢአት እንደሆነ ሁሉ፣ በሞት ላይ ድልን መጐናጸፍ መሠረቱ የቅዱሳን አባቶች ትምህርት
የይቅርታና የትንሣኤ ሕይወት ተካፋይ (ተሳታፊ) መሆን ነው። ይህ
የአሸናፊነት ድል ከኀጢአት የተነሣ ሕግ ባመጣብን ኩነኔ ላይ፣ በሞትና እግዚአብሔር ከሰማይ በወረደ ጊዜ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል
በመበስበስ ላይ፣ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ አማካይነት የምናገኘው ድል ማርያም ማሕፀንም በአደረ ጊዜ፤ ከርሷም ሥጋን ነፍስን ነስቶ ሰው በሆነ
ነው (ሮሜ 8፣37)። ስለዚህ በምሕረቱና በይቅርታው፣ በጌታችን ጊዜ ከሰማይ ሥጋን ይዞ አልመጣም፤ መለኮቱም ከምድር አልተገኘም፤
በኢየሱስ ክርስቶስ ካሳ፣ በወንጌል ኦሪትን በትንሣኤ ሞትን በጽድቅ ቀዳማዊ አምላክ ነው እንጂ፡፡
ኀጢአትን ድል እንነሣ ዘንድ ድል መንሣቱን የሰጠን እግዚአብሔር እርሱም ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውንም በመፍጠር ማንም
ይክበር ይመስገን። ማን አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ ራሱ ፈጠረው እንጂ፡፡
በዚህ ቁጥር ላይ የኢየሱስን ሙሉ ማዕረጉን አስታውስ።- “ጌታችን ሥጋ በሠራው ሥራ ሁሉ መለኮት አንዲት ሰዓት እንኳን በማናቸውም
ኢየሱስ ክርስቶስ"፡- ለክብሩ ለግርማው ለማንነቱ ትኩረት እየሰጠ ነው። ሥራ ከርሱ እንዳልተለየ እናምናለን ጌታችን መድኃኒታችን ሰው በሆነ ጊዜ
58፡-- “ ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ድካማችሁ በጌታ
ቁጥር 58፡ መለኮቱን ከሥጋ ጋር በተዋሕዶ አንድ እንደ አደረገ እናምናለን፡፡
ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፣ የማትነቃነቁም፣ የጌታም (ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 44፣ ክፍል 1 ፣ ቁጥር 2-4)
ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።”፡-
ማኅበራችን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
“ስለዚህ” በማለቱ ሐዋርያው፡- እግዚአብሔር በኀጢአትና በሞት ላይ 1. ነጻ መንፈሳዊ ጽሑፎችና በፖስታ የሚሰጥ የተልእኮ ትምህርት
ድል መንሣትን ከሰጠን፣ በቀጣይ ተግባራዊ የክርስቲያናዊ ሕይወት መስጠት፣
ልምምድ ተከትሎ መምጣት እንዳለበት ያመለክታል። ለጌታና በጌታ 2. ነጻ መንፈሳዊ ሥልጠናዎችንና ኮርሶችን መስጠት፣
የሆነ ድካም፣ የአገልግሎት፣ የሕይወት ውጣ ውረድ ለከንቱ እንዳልሆነ 3. ነጻ ቅድመና ድኅረ ጋብቻ መንፈሳዊ ትምህርት፣ የምክርና የጸሎት
አገልግሎት መስጠት፣
መረዳት ይገባል። ድካማቸው በሥራ (በተግባር)፣ ቤተ ክርስቲያኗን 4. በተለያየ መንፈሳዊ ችግር ውስጥ ላሉ የምክርና የጸሎት እገዛ
በመገንባት (በማነጽ)፣ ይህም በጌታ ከሆነ፣ በእርሱ ጥበብና ኀይል፤ ማድረግ፣
ሊጠፋ አይችልም፣ ወይም በከንቱ አይሆንም፤ ከቶ አይጣልም። 5. ስብከቶችን፣ መንፈሳዊ ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን ማዘጋጀት፣
የተቀበላችሁት መከራ ዋጋ ላለመቀበል እንዳይደለ ታውቃላችሁና፣
ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት፣ ለጥያቄና አስተያየት፣
በአገልግሎት የሚደክሙት በሥጋው መከራ ተቀብሎ፣ ሞትና ሲኦልን
ድል ለነሣ ጌታ ነውና። በመ.ሣ. ቁ. 121024 ልትጽፉልን
“የምትደላደሉ፣ የማትነቃነቁም፣”፡- ቆሮንቶሶች የአለመረጋጋታቸው ወይንም
ምክንያት ይህ ዓይነት ጠንካራ ማሳሰቢያ አስፈልጐአቸዋል። ዛሬስ ለእኛ
የዚህ ዓይነት ምክርና ማሳሰቢያ አያስፈልግ ይሆን? ኧረ በጣም በስልክ ቁጥር +251 11 835 3433 ልትደውሉልን
ያስፈልገናል። በዚህ ዘመን ትልቁን የትንሣኤ ተስፋ ጨብጠን፣ በእምነት እንዲሁም ጌታ ኢየሱስ በነጻ ተቀበላችሁ በነጻ ስጡ (ማቴ. 10፣8) ባለን
የምንኖር ሁላችን፣ በዚሁ የተደላደለ መንፈሳዊ እርጋታ ልንይዝ ይገባል። መሠረት አገልግሎት የምንሰጠው ያለ ክፍያ ነውና
የቆምንበት መሠረቱ ዐለት ነውና፣ በሐሰት ትምህርት፣ በፈተና፣
በጥርጥር ያለመነቃነቅ (ያለማወላወል) ጸንተን እስከ መጨረሻው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
መጠበቅ ያስፈልገናል። የተንቀሳቃሽ ሒሳብ ቁጥር 1000088480124
“የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።”፡- ጥብቅና ግልጽ የሆነው አገልግሎቱን ለማገዝ ትችላላችሁ።
ትልቁ የትንሣኤ መሠረታዊ ትምህርት ለሁልጊዜም በጌታ ሥራ ውስጥ
የሚበዛልን አነሣሽ ኀይልን ይሰጣልና። አንድም፡- ሁልጊዜ
እግዚአብሔርን ለማገልገል፣ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን ሁልጊዜ የላካችሁልን መልእክቶች ደርሰውናል። አገልግሎታችንን በተመለከተ
የትሩፋት ሥራ አብዝታችሁ ሥሩ፤ ትሠሩ ዘንድ የተዘጋጃችሁ ሁኑ ስለምትሰጡን አስተያየት እግዚአብሔር ይባርካችሁ። በቀጣይም እንደ
ለማለት ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት የመዳንን ወንጌል ለማዳረስ
በምናደርገው መንፈሳዊ ሩጫ አስተያታችሁ ጠቃሚ ነውና ጻፉልን።
… የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም ደግሞም "በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም
በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፣ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን
ይቆጥራችሁ ዘንድ፣ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ" (2ተሰ. 3፣1-2)።
ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።” (2ተሰ.1፣12)።
ይ ቀ ጥ ላ ል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር የተዘጋጀ የድረ-አምባ (website) አድራሻ: www.lidetalemariam.org
የ.መ.ሣ.ቁ. 121024፣ አዲስ አበባ ኢ-ሜይል (e-mail): lidetalemariam@gmail.com 11

You might also like