You are on page 1of 2

ልጅህንም ወደ እኛ ሰደድከው ከአንተ ዘንድ በሥውር በኅቡእ አንተን ለማግኘት ሰው፣

ሳይለይ መጣ ከአንተ ሳይነቃነቅ ሄደ። በምድር አይወጣም አይዋኝም ስለማይቻለው።


ከወላጁ ጋር ሳለ በሰማይ ከአባቱ ጋር ተቀመጠ ለአንዳፍታ ለሰዓት ለዓይን ጥቅሻ ያህል፣
ከላይ ሳይጎድል ከታች ሳይጨመር ወረደ። ማንም ሊመረምር ሊገነዘብ አይችል።
ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቁጥር ፴-፴፩ ለማወቅ ይከብዳል ነገር ሁኔታውን፣
የሚያቃጥል እሳት በአብ እና በወልድ መካከል ያለውን።
ሥጋን ተዋሐደ፣ ሕያውና ቅዱስ የሚሆን መንፈስህ፣
ገብርኤል ተልኮ ብሥራት ሳይናገር፣ ጥልቅነቱን ያውቃል ስለ መለኮትህ።
ዜናው ሳይሰማ የመምጣትህ ነገር፣
እረኞች ሳያዩህ በግርግም ተኝተህ፣ የተዋሕዶን ነገር ከእርሱ ተምረን ነው
የሰው ልጅ ሳትባል ከድንግል ተወልደህ፣ የአንድነት ሦስትነት ምሥጢርን ያወቅነው።
ለአንዳፍታ እንኳ አይጠፋም እኩልነታችሁ
አንደበት የሆንከው ኢሳይያስ ሲናገር፣ ከቶ አይበተንም ይኽ አንድነታችሁ፣
ሰማዮችን ቀደህ ውረድ ይልህ ነበር። ደርሶ እንደማይለይ የግብራችሁ ነገር፣
ከአንተ ሌላ ማንም ሰውን መች ረዳው፣ ማንም አልነገረን ከመንፈስህ በቀር።
የገዛ ክንድህ ነው መድኃኒት ያመጣው።
ሁ ሉ ን ሳ ት ደ ክ ም ት ሸ ከ መ ዋ ለ ህ ፣
ዳርቻ ፍጻሜ የሌለህ አምላክ ነህ፣ ለ ሁ ሉ ሳ ታ ጎ ድ ል ት መ ግ በ ዋ ለ ህ ፣
ማንም የማያውቅህ ማንም ሰው ያላየህ። ደግሞም ዝም ሳትል ሁሉን ታስባለህ፣
ያገኘህም የለም ደግሞም የሚያገኝህ። በጎ ቅን አሳቢ ቸር አምላክ አንተ ነህ።
መንግሥትህ አያልቅም አይሻርም ኃይልህ። ለሁሉ ስትሰጥ ካንተ አንዳች አይጎድልም፣
አያልቅ አይጨረስ ገናንነት ክብርህ፣ ሁሉን ስታረካ አንተ ግን አትነጥፍም፣
ከቶ አይሠወርም የአንተስ ጌትነትህ። ለ ሁ ሉ ያ ለ ህ ን ት ተ ው ለ ታ ለ ህ ፣
አንተን የሚያውቅ የለም ከራስህ በስተቀር አንተ ሳትቀበል የምትሰጥ ጌታ ነህ።
ለአንተ ግን ግልጽ ነው አባት ሁሉም ነገር። ክቡር ነህ ዘላለም ባዕድ የማይሰጥህ፣
አንተ ፈጣሪ ነህ ማንም የማያዝህ።
ጥንት እና ዳርቻ በፍጹም የሌለህ፣
ለ ሁ ሉ ፍ ጻ ሜ አ ን ተ ት ሰ ጣ ለ ህ ።
ሁሉ ስላንተ ነው በሁሉ ስፍራ አለህ፣
ከልዑላን ይልቅ እግዚአብሔር ልዑል ነህ።
በአንድ ልጅህ መምጣት ያፈረን ጎበኘህ፣
በይቅርታህ ብዛት የራቁትን ቀርበህ።
ከራቁት ሩቅ ነህ ስውር በመሆንህ፣
በአንተ ተሠውሯል ገናንነት ኃይልህ።
በውስጥም በውጪም በሁሉ ቦታ አለህ፣
ሁሉን ቻይ ነህና አንተን በአንተ ጋርደህ።

የወለድከው ልጅህ ስለ አንተ ነገረን፣


እርሱ ነው ዜናህን ለእኛ ያደረሰን።
እንዳንተ እንደ አባቱ አንተ እንደከበርከው
ልጅህም እንዲሁ ዘላለም ክቡር ነው። እግዚአብሔር ልጅህን ወደኛ ሰደድከው፣
ስለ ወልድ ነገር የአንተን አባትነት፣ ከአንተ ጋር እያለ ከአንተ ሳትለየው።
የሰማን ከአንተ ነው ምስክርን በእውነት። ሁለንተናው ሲኖር አንተ ካለህበት፣
ለአንተም ለልጅህም ስግደት ይሰገዳል፣ ሳ ይ ለ ይ ህ መ ጣ እ ኛ ካ ለ ን በ ት ።
እኩል ነው ክብራችሁ መበላለጥ የታል። በምድር ከእናቱ ጋር አብሯት እየኖረ፣
በአብ እና በወልድ በእናንተ መካከል፣ ከአባቱ ጋር ደግሞ በሰማይ ነበረ።
ዕለት ሰዓት የለም መቅደም መከታተል። ከሰማይ ሳይጎድል ሳያንስ ከቁጥር፣
አባት በመሆኑ አብ ከልጁ አይበልጥም፣ ከታች ሳይጨመር ወረደ ወደ ምድር።
ልጅም በመሆኑ ወልድ ከአብ አያንስም። መምህረ ወንጌል አምላኩ ለጴጥሮስ፣
ለዓለም መድኅን የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ፣
ከሰማይ የወረድክ ረጅም ፈትል ነህ፣ መልክ ረጋፊ ነው ዕድሜም ታይቶ ጠፊ፣
ምድር በመምጣትህ ከአብ ያልተለየህ። ወንድሜ አትታለል እኅቴ አትስነፊ።
ይኽ ምሥጢር ታላቅ ነው ከሁሉ በለጠ፣ ተወለደ ብቻ ብንለው አይበቃም፣
እግዚአብሔር በሥጋ አሜን ተገለጠ። ለመዳን ካልቀረብን ከእስር አንፈታም።
ሥ ጋ ዊ ፍጥረት ን ሁሉ ን የ ፈ ጠ ረ፣
የ ፍ ጥ ረ ታ ት ጌ ታ በ ማ ኅ ፀ ን ኖ ረ ። ያለ ዋጋ ሰጥቶን መመገብ ካቃተን፣
የሚያቃጥል እሳት ሥጋን ተዋሐደ፣ ሰዎች የፍርድ ቀን ማምለጫም ቃል የለን።
ሥውር የማይታይ ገሐድ ተወለደ። ድግስ ተደግሶ ሰው ቤት ከተጠራን፣
እንበላ የለም ወይ ማዕድ እያነሳን።
ያን የጠራንን ሰው ጥሪውን አክብረን፣
ከቀረበው ምግብ አብረን እንቆርሳለን።

በመድኃኔዓለም ቤት ሁልጊዜ ድግስ ነው፣


ሁሉም ሰው ተጋብዞ በዪው ግን ጥቂት ነው።
የአብርሃም ልጆች ነን ብለው የተመኩት፣
አይሁድ መልስ አጥተዋል ጌታን ያናገሩት።
አባታችን ብቻ ማለት በቂ አይደለም፣
እንደ አብርሃም ሁኑ ብሏል መድኃኔዓለም።
ደፍረን ብንናገር እኛም ተመክተን፣
ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶልናል ብለን፣
ለብቻው አይጠቅምም ስላወራን አንድን፣
ለሥጋው ለደሙ በእምነት ካልቀረብን።
ብርሃን ተጎናጽፎ መኖር የሚቻለው፣
በግርግም ተኝቶ ጨርቅ ጠቀለለው። ቃል ገብተን እንውጣ እውነት ነው እያልን፣
እንደ አምላክነቱ ሁሉን እየሠራ፣ ከቁርባኑ ሳንወስድ የታል መዳናችን።
በምድር ክርስቶስ እንደ ሰው ተጠራ። ክርስቶስ ሲወለድ ስጦታ ላመጡት፣
ወርቅ እጣን ከርቤውን ይዘው ለቀረቡት፣
ታላ ቅ የ ም ስ ራ ች በ ዳዊ ት ከ ተ ማ ፣ ጌታ ተቀብሏል የእጅ መንሻቸውን፣
ከእግዚአብሔር መላእክት ለእረኞች ተሰማ። ስጦታውን ሳይንቅ ከሰው የመጣውን።
ክርስቶስ የሚባል መድኃኒት ተወልድዋል፣
ሄዳችሁ አግኙት በግርግም ተኝትዋል። የ ኛ ን ም ዝ ማ ሬ የ ኛ ን ም ም ስ ጋ ና ፣
ዛሬም ይቀበላል የእጅ መንሻ ነውና።
በማለት ተናግረው ምስራች አብስረው፣ እ ኛ ም እ ን ቀ በ ል ከ ቅ ዱ ሱ ቦ ታ ፣
ወደ ሰማይ ወጡ እረኞቹን ትተው። ሥጋ ወደሙ ነው የእግዚአብሔር ስጦታ።/፪/

የመላእክቱን ቃል ሰምተው የተረዱ፣


ቤተ ልሔም ድረስ ወልድን ሊያዩት ሄዱ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንደ መላእክቱ ቃል ግርግም የደረሱት፣ አብርሃም ሰሎሞን
ዮሴፍን ድንግልን ጌታንም አገኙት። ታኅሣሥ ፳፱/፳፻፬ ዓ.ም።
የማይመረመር ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፣
ወልድን ለማግኘት ነው እዚህ የመጣነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ባለበት፣
አ ብራ ት ገ ኛ ለ ች ድ ንግ ል ማ ር ያ ም በ እ ው ነት ።

የታመነ ቃል ነው መቀበል ያለብን፣


ክርስቶስ ተወልድዋል ኃጢአተኞች ሊያድን።
ለእኔም ለአንተም ለአንቺም ለሕፃናቱም ነው፣
ወልድ ሥጋ ለብሶ ምድር የወረደው።
ኢሳይያስ ተናግሯል እንዳንጠፋ በዓለም፣
ያለ ዋጋ ብሉት ይኼን ሥጋ እና ደም።

You might also like