You are on page 1of 11

መዝሙር

እኛ እዘምራለን

እኛ እዘምራለን ጥላት ይጨነቃል

የ ደሥታቸዉ ምንጩ ከወደየት ነዉ ይላል

የ ሠላም መፍሠሻ አንችነሽ ደሥታችን

የ መሥቀል ሥር ሠነድ ማሪያም እናታች

በልባችን ደሥታ ፊታችን የበራው

ሥለ ሠንሠለቱ ልጅሽ ሠብሮልን ነው

ሞት መሻገሪያችን ድልድይ ከመከረው

የምሥራቅ ልጅ ጽሐይ የእኛ ትንሣኤ ነው

የመድሐኒት መዝገብ የቁሥላችን ጤና

ከርዕሥቱ እንዳጎድል በተሥፋ እድንፀና

ልጁን ደሥታ ለሚል የደሥታ ምንጭ ሁና

ሐዘን በዕርሧ እርቋል ሥላዘኑት አዝና

የሊቀ ካሕናቱ የክርሥቶሥ እናት

አሡ ዝናብ ሢሆን እሧ ደመና ናት

ሢጠብቅ እረኛ ሢርበን በግያል ነው

አልፋ ና ኦሜጋ የድንግል ልጇነዉ

ፅዋ የያዘው

ፅዋ የያዘው በቀኝ እጁ

ሁሌ ይራራል ለወዳጁ
ኡራኤል መጣ እረዳቴ

ጥበብ ሊሞላ በአደበቴ

በቤቱ እድኖር የመረጠኝ

ጋሻ መከታ ለኔ የሆነኝ

እኔም ተፅናናሁ በምልጃህ /2/

ጎኔ ይቆማል ሥጠራው/2/

ዉሥጤ ሢዳከም ሢባክን

ኡራኤል ብዬ ሥማፀን

ልቤን ያድሣል ብሎ ፅና/2/

አፊን ይሞላል በምሥጋና/2/

የጌታዉን ደም የረጨው

ለዓለም ልዩ ነው ውለታው

በኡራኤል እጅ ተቀብቶ/2/

የኪዳን ስፍራ ታዬ በዝቶ/2/

የ እውቀትን ፅዋ ያጠጣኸኝ

ለእዝራ ሡቱኤል የረዳኸኝ

እኔንም እርዳኝ በ ምልጃህ/2/

አገልጋይ ልሁን ለ ክብርህ/2/

ሊቀ መልአክ

ሊቀ መላዕክት ኡራኤል አባት

ሊቀ መላዕክት ኡራኤል አባት


ፀበልኅም ያድናል በ እውነት

በምልጀህም ያመኑ በሙሉ ባንተ ይድናሉ

ዑራኤል መልዐክ ያንተ ድንቅ ሥራ

አይመረመርም

ጥልቅ ነው ምህረትህ

ማዳንህ ዘለዓለም

ቸርነትህ ብዙ

ምልጃህም ፈጣን ነው .

ፀጋውን አድለንለ እኛለምናም ነው

ኡራኤል መላክ ማዳንህን ሰምቼ

ሥምህን ጠርቼዓለሁ

አላሣፈርከኝም

ባንተኮርቻለሁ

መንገዴም አንተነህ

የግልህ አድርገኝ

ከሐጢያት ፈላፃ እኔንም ጠብቀኝ

ኡራኤል መላክ ለእዝራ ሡቱኤል

እውቀትን አጠጠው

በፅዋ ብርሐን

ደሙን እደረጨው

ሠላምን ልታሠፍን
ዐዓለም ዕደዞርክ

ማዳንህ ተገልጦ በ ዓለም ተነገረ

እንደ እግዚአብሔር ያለ

እደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና/2/

እልል በሎ ቁሙ ለምስጋና/2/

በባሕር ተከፈለ ዕሥኪታይ መሬቱ

ፈርኦን ወደቀ አልሠራ ም ትምክቱ

ደካሞቹም ፀንተው ተራመዱ

ሐይለኞቹም ይሕው ተዋረዱ

የእያሪኮ ቅፅር የማይደፈረው

ይሄው ፈራረሠ የሠው ልጅ ሳይነከው

ሐይለኞቹ ምቢበረታቱብን

እፀናለን በእርሡ ተደግፈን

የተወረወረው የጥላታችን ጦር

ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሑኖ እግዚአብሔር

ለሥላሤ ይድረሥ ምሥጋናችን

ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን

ባህርላይ ሢራመድ ሞገሥ ዓለው እሱ

በግርማው ሢነሣ ፀጥ ይላል ንፋሡ

የድንግል ልጅ እኛ ምናመልከው

መድሐኒዓለም የለም የሚሳነው


ተዋሕዶ

ተዋሕዶ ሃይማኖቴ

የጥንትነሽ የእናት ናአባቴ

ማሕተቤን አልበጥሥም

ተኖራለች ለዘለዓለም

የግብፅን ከተሞች በደም ገንብተናል

በመግደል ፅድቅ የለም ሙተን ግን ኖረናል

ማዕተብሽን ፍቼ በጥሽው ቢሉኝ

እኔሥ እሥከ አንገቴ ዉሠዱት አልኩኝ

ጴጥሮሥ ተሠቀለ ጳውሎሥ ተሠየፈ

ተዋሕዶ እያለ እረ ሥንቱ አለፈ

ሌሎችም በእሣት በሥቃይ አልፈዋል

ዘመን የማይሽረው ታሪክን ፅፈዋል

ፊተኛነን ና እንዳን ሆንኀ ለኛ

ሕዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ

ጅብ ከሔደ ውሻ እዳይሆን ጮኸት

የተዋሕዶ ልጆች አሁን ነው ስዓቱ

አይተን እዳላየን ስንት አሳልፈናል

የሱፍቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል

አሁን ግን ይበቃል ዝምተው ይሠበር

ይገለጥ ይታወጅ የ ተዋሕዶ ክብር


ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱሥ ሚካኤል ወዳጅነህ ለሁሉ

ዛሬም ቁመሀል በኪዳንህ ላሉ

ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ

ምራኝ መንገዱን እዳይመሽ ልድረሥ ካ አባቴ

እዴት ይገፋል ጎዳ ነው ያላንተ ዕርዳታ

ጥሜን ቁረጠው በበትርህ ጭጨውንምታ/2/

ተጠመጠመ ጥላቴ በእሣት ሠንሠለት

የጌታ መላዕክት ሚካኤል በሠይፍ ቆርጦበት

የለም በቦታው ሥመለሥ አጥቼዋለሁ

የሚረዳኝን ተሽሞ አይቼዋለሁ/2/

ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሐል

ሥለ ረዳኸኝ ዳንኤል እጅግ ወዶሀል

ይለዋወጣል ባህሩ አንተ ሥትመጣ

እግዚአብሔ ይገስ ዲያብሎስ መድረሻ ይጣ/2/

አለኝ ትዝታ በቤትህ በልጅነቴ

ስትሳሳልኝ እያየሁ ፀንቷል ጉልበቴ

ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ

አንተን ለሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ/2/


በ ፍቅር ተስቦ

በ ፍቅር ተስቦ ወረደ ለኛ ሲል

የ ፍቅሩን ፍጻሜ ገለጠው በመስቀል

ለ እኛ ያላረገው ከቶ ምን አለ ና

አፋችን ዝም አይበል እናቅርብ ምሥጋና

ደስ ይበለን ሠማያትን ቀዶ

ታላቁ ዓባታችን

የዘመናት ንጉስ

ኢየሡሥ ጌታችን

የ ኤፍራታው ሕጻን

በዳዊት ከተማ

ተወልዶ ማደሩን

ምስራች ተሠማ

ደስ ይበለን ወረደ ወደ ምድር

ሠላሙን ሊሰጠን

ሠላም ለእናንተ ይሁን

ብሎ ሊሠብክልን

በ መስቀል ተሠቅሎ

እኛን የተቤዤን

ከሲኦል እስራት

በ ፍቅሩ የፈታን
ሃሌ ሉያ ምስጋና በሠማይ

ምሥጋና በምድር

ሁሉን ቻይ ለሆነው

ለቸሩ እግዚአብሔር

ሃሌ ሉያ ለእርሡ

ለነፍሣቸን ጌታ

ዝማሬን እና ቅርብ

ከ ጧት እስከ ማታ

መራሒ ብርሐን

መራሒ ብርሐን ረድኤት ሕ የበዛ

ወደ ግብፅ ሥትሔድ ድንግል ልጇ ይዛ

አብረሕ የተራዳሕ መልዓከ ልዑል

የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ኡራኤል

አበው ሠባሠገል ኡራኤል

ከምሥራቅ ሢመጡ " "

ኮከብ የመራ " "

አመሐ እንዲሠጡ " "

ሕይወቴን አቅናልኝ " "

ከሐጢያት ዓውጣና " "

በብርሐን ምራኝ በፅድቁ ጎዳና

ፈጥነኸ የምትደርሥ ኡራኤል


ሥምሕን ለጠራ " "

ፅወዓ ልቦና " "

ያጠጣሕ ለእዝራ " "

ጥበብ መንፈሣዊ " "

በውስጥህ እዲዘራ " "

ብርሐናዊ መላክ ልቦናዬን አብራ

ለ ሔኖክ የገለጥክ ኡራኤል

የ ረቀቀ ሚሠጥር " "

በ ገፀ ሰማይ ላይ " "

የ ፊደላት ቁጥር " "

ማሥተዋል አግኝቼ " "

በፍቅር እድሞላ " "

ምልጃህ አይለየኝ ሑንልኝ ከላ

አምላክ ስ ለሰው ልጅ ኡራኤል

ቀራኒዮሢሠዋ " "

ደመ መለኮትን፡፡፡፡፡፡፡፡

በብርሐን ፅዋ፡፡፡፡፡፡፡፡

ተቀብለ ሕረጭተሕ፡፡፡

ዓለምን የቀደሰክ፡፡፡፡፡፡፡

ለምሥጋና አንቃን፡፡፡፡፡

በነግህ ና በሠርክ፡፡፡፡
ጧትና ማታ

ዑራኤል ብርሃና

ኡራኤል ብር ሐና

ኡራኤልብርሐና/4/ለኢትዮጲያ/2/ብርሐና ለኢትዮጲያ

እንለምንሐለን ወድቀን ከፊትህ

እየተማጸንን በሥነ ስዕልህ

ስለሚገልፅብህ እዚአብሔር ሀይሉን

በቅድመ እግዚአብሔር ቁመህ አማልደን

ለኤትዮጺያ/2/ብርሐና ለኢትዮጲያ

መራሒ ብርሐን ከሳቴ ሚስጢር

ከሞት ወደ ሕይወት የምታሻግር

ከመላዕክት ሁሉ አንተ ተመረጥክ

በብርሐን ፅዋ ደሙን ተቀበልክ

ለኢትዮጽያ/2/ብርሐና ለኢትዮጲያ

ለጥበብም ሠዎች መረ ኮከባቸው

እስከ ቤተልሔም መርተሕ ያደረስካቸው

ዛሬም ልጆችህን አስገባን ከዕርዕስቱ

አፅናን አረጋጋን እንዳንቀር በከቱ

ለኢትዮጲያ/2/ብርሀና ለኢትዮጺያ

የክርስቶስን ደም ስትረጭ በምድር ላይ

ቃለ ማህለቅትህ ተሠማ እስከ ሠማይ


እንደ ቅዱስ ሔኖክ እንደ እዝራ ሱቱኤል

ሠማያዊ ካህን ባርከን ኡራኤል

ለኢትዮጲያ/2/ብርሐና ለኢትዮጲያ

ለድንግል ማሪያም መንገድ የመራሐት

በስደቷም ወራት ቀርበህ የረደሐት

ኢትዮጲያም ስትደርስ ነበርክ ከርሷ ጋራ

የረገጥሐትን ምድር ኢትዮጲያን አደራ

ለኢትዮጲያ/2 /ብርሐናለኢትዮጲያ

You might also like