You are on page 1of 6

!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ቅዱሱ ከአለም ተሰዶ

እምነትን ከተግባር አዋሕዶ

ባንቺ የዳነው አንቺን ወዶ

አይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የሐዋርያት የጸሎት ቤታቸው

የቅዱሳን ክብር መጠጊያቸው

አረ አንቺ ነሽ ፅዮን ቤታቸው

ዛሬ በአለም ፍቅር የታጠሩ

በዲያቢሎስ መንፈስ የታወሩ

አንቺን ለማጥፋት የሚጥሩ

አረ ብዙ ናቸው ቢቆጠሩ

ታዲያ ወገኖች ምን ይሻላል

በአጥፊው መንፈስ ተከበናል

ለዚህ መጸለይ ይገባናል

ከአምላክ የፅድቅ አክሊል የታደሉ

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያሉ

ስለኛ ድህነት ይማልዳሉ

እንግዲህ በተዋሕዶ ያመናችሁ

አሉ መላዕክት ጠባቂያችሁ

ድንግል ማርያም ናት መከታችሁ

ፈጣሪ አለ አምላካችሁ

ምንም የለ የሚያስፈራችሁ

በተዋሕዶ ይፅና እምነታችሁ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ኆኅተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት

ለጥር 27 /2004 ዓ/ም የተዘጋጀ፡፡

!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የአያት ቅድመ አያት ውርሴ

ተዋሕዶ ኑሪልኝ የዘላለም ቅርሴ

የመቅደስሽን ብርሃን ሕይወቴ ተላብሶ

ለሁለንተናዬ እርካታ ሚሰጠኝ

ለመኖሬ ተስፋ የሚያመቻችልኝ

በዚች አለም ላይ እንዳቺ አላገኝም ሠላም የሚሰጠኝ፡፡

ጆሮ ያለው ይስማ ሲሉኝ እንቴኔ

በአጉል ቅስቀሳቸው ሲያስገቡኝ ኩነኔ

በጸና እምነቴ ላይ ውሃ ሲከልሱ

በኃጢአት በክለው ሕይወቴን ሊያረክሱ

በፍጹም አይችሉም መንፈሴ ቅጡ ነው አንቺን እያጥላሉ እኔን ለሚያቆስሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ኆኅተ-ጥበብ ሰ/ት/ቤት

ለጥር 27/2004 ዓ/ም የተዘጋጀ

!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በወንጌል ቃል ከብሮ መልካም ፍሬ የሚያፈራ


በምግባሩ የታወቀ አለምን በብርሃኑ ያበራ

ለሁሉ ምሳሌ የሚሆን የሚፋጠን ለበጎ ስራ

በርክርስቶስ ክርስቲያን ነው ስሙ ተብሎ የተጠራ

በሃዘንና በደስታ እምነቱን አጽንቱ የጠበቀ

እርሱ ነው ታማኝ አገልጋይ በፈጣሪ የታወቀ

ንፋስ እንደሚወዘውዘው ሸንበቆ ወዲህ ወዲያ ያላለ

ለአምላኩ የታመነ ለውሳኔ ያልቾኮለ እርሱ ነው የክርስቶስ ወዳጅ በቤቱ የበቀለ

እንደ ወርቅ በአሣት በመከራ ተፈትኖ

በሚደርስበት ስቃይ ሁሉ ዋጋ እንደሚያገኝ ተማምኖ

በጽድቅ ስራ የተጋ ከኃጢአት የራቀ ጨክኖ

በሃዘን ጊዜ ጸልዮ በደስታ ጊዜ ዘምሮ

የሚደርስበትን መከራ ሁሉ ለበጎ ነው ብሎ አክብሮ

በሥራው የሚመሰገን ድሮም ይሁን ዘንድሮ

ያለ ክርስቲያን ማን አለ የሚኖር በሁሉም ተከብሮ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ኆኅተ-ጥበብ ሰ/ት/ቤት

ለጥር 27/2004 ዓ/ም የተዘጋጀ


!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አባቶች ሐዋርያት ያቆዩሽ

ቅዱሳን ሰማዕታት የሞቱልሽ

አንቺ በደም የተዋጅሽ

አንቺ በጾም የከበርሽ፡፡

እነ ቅዱስ ቶማስ ቆዳቸው ተገፎ

ቅዱስ ዶስቆሮስም በጅራፍ ተገርፎ

አባታችን ዮሐንስ በሰይፍ ተሰይፎ

ዛሬ ለዚህ በቃሽ ያ ሁሉ ነገር አልፎ

አምላክ የመሰከረልሽ ከሰማያት ወርዶ

ቅዱሷ እምነታችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፡፡


ነገር ግን እማማ ይሔን ሁሉ ዘንግቶ

ታሪኩን ወርውሮ የሰው ታሪክ ይዞ

የመረጠም አለ የጨለማን ጉዞ

እያለ የሌለ ልቡ የታወረ

የቆመ የመሰለው በነበር የቀረ

አርጅታለችና ትታደስ እየለ

በድፍረት ሚናገገር ማስተዋል ያቃተው

አረ ቤት ይቁጠረው በጣም ብዙ ሰው ነው፡፡

ነገር ግን እማማ ደግመሽ ንገሪአቸው

ከአንቺ በቀር እናት ካንቺ በቀር ድህነት ማንም አይሆናቸው

እጅሽን ዘርግተሸ ልጆቼ በያቸው

ድምፅሽን ላልሰሙት ዳግም አለሚያቸው

እናትነትሽን ገልጸሸ በእቅፍሽ አግቢያቸው

ይሔን ሁሉ ብለሽ አልሰማ ያሉትን

የዲያቢሎስ ተገዢ ሆነው በአለም የቀሩትን

ምን ታደርጊዋለሽ በቃ ተያቸው

በኋላ ግን ፍርዱን አምላክ ይክፈላቸው

ትሰሚኝ እንደሆነ እማማ

እነሱ ቢክዱሽም ቢሆኑም ጠማማ

እኛ ላንጠላሽ እኛ ላንክድሽ

ባንቺነትሽ አምነን ልንፀና በቃልሽ

ቃላችን ቃል ይሁን አንሔድም ጥለንሽ

ድሮማ! ድርማ!

በጫካ በዱር በዋሻ እየኖሩ

በፀሐይ ተቃጥለው በውርጭ እየተኮማተሩ

አቆዩሽ ይሔው ለዛሬዋ ቀን በደማቸው

አበው አኖሩሽ አጠሩሽ ባጥንታቸው፡፡

አይ ተዋሕዶ!
የበረከት ስፍራ የድሆች መጠጊያ

ላጣ መጠለያ የቅዱሳን መኖሪያ

የሃዘን መፅናኛ የዝማሬ ቦታ

ሁከት የሌለብሽ ለጭንቀት አሌንታ፡፡

እናም ወገኖቼ በአኩሪ እምነታችን

እንኑር በምስጋና እንድንባታለን

እስከመቼ ድረስ በሐሰት ተነድተን

አረ ይብቃን አረ ይብቃን ወገን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ኆኅተ-ጥበብ ሰ/ት/ቤት

ለኅዳር 24 /2004 ዓ/ም የተዘጋጀ

You might also like