You are on page 1of 3

አኮቴት ለማርያም

መንፈሳዊ የግጥም መድብል


አትርሳኝ

ዓለም በእጄ መስላኝ፤ ራሴን እረሳሁ፣

ማን እንደፈጠረኝ፤ ለደቂቃ ዘነጋሁ፡፡

በላሁኝ፣ ጠጣሁኝ፤ ዘለልኩኝ፣ ጨፈርኩኝ፣

ዘላለም ህያው ነኝ፤ ብዬ እያሰብኩኝ፡፡

ንፁህ የለበስኩ ለት፤ ያጫፈሩኝ ሁሉ፣

ገንዘቤ እያለ፤ “ከጎንህ ነን” ያሉ፣

አጥቼ ስመክን፤ ከፊቴ ዞር አሉ፡፡

ለሰላምታ ዘጉኝ

ሁሌ ያፌዛሉ፣

“አንተ ማን ነህ” እያሉ፡፡

እውነትም አሰብኩኝ፤ እኔ ማን ነኝ ብዬ፣

ወዴትስ ነኝ ብዬ፡፡

ኑሮ እንደ ጋን ከብዶኝ፤ ዓለም ስትጥለኝ፣

ተስፋዬ ተሟጦ፤ ህይወቴ ሲመረኝ፡፡

ወደ’ርሱ ቀረብኩኝ፣

ከደጁ ላይ ስደርስ፤ አንገቴን ደፋሁኝ፣

ከደጁ ሳይጥለኝ፤ ብሶቴንም ሰማኝ፣

የፀፀቴን ዜማ፤ እንዲህ ሲል አዜምኩኝ፡-

እባክህ አምላኬ፤ አንተው ይቅር በለኝ፣

ሰው ሁሉ እየጠላኝ፤ ፊቱን እየነሳኝ፣

ይምቱኝ ይደብድቡኝ፤ አንተ ግን አትርሳኝ፡፡

† † †
እስኪ ልጠይቅህ…፡-

ሉቁምና ደጅህ፣

እስኪ ልጠይቅህ፡-

ምን ቢረቅ ነው ፍቅርህ?

“…ሸክም የከበዳችሁ

ኑ ላቅልልላችሁ…”

ብለህ ያልከን አምላክ፣

ቤዛ ልትሆን ለኛ መስቀሉን ተሸከምክ፡፡

የማያስጠማውን የህይወትን ውሀ

ልትሰጠን ፈቅደህ፣

አንተ ግን ስለእኛ፤ የሀሞት ቆምጣጤ

መራራውን ጠጣህ፡፡

የምንሰራበት እጆችን የሰራህ፣

በሰጠኸን እጆች በጥፊ ተመታህ፡፡

እስኪ ልጠይቅህ፡-

ምን ቢረቅ ነው ፍቅርህ?

You might also like