You are on page 1of 2

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

/በመድረኩ ላይ ዩኒፎርም የለበሱ የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች የክብ ግማሽ ቅርፅ ይዘው ይቆማሉ ከመሃል ላይ የጌታን ስነ-
ስቅለት ያሚያሳየው ስነ- ስዕል ይቀመጣል ሦስት ወንዶች ልጆች ይቆማሉ አንደኛው ሙሉ በሙሉ በስነ -ስዕሉ ይሸፈናል
(ጌታን ሆኖ የሚሰራው ማለት ነው ከአጠገቡ አንዲት ሴት ትቀመጣለች እመቤታችን ሆና ይምትሰራዋ ማለት ነው
ሁለቱም ሙሉ ለሙሉ በሥነ-ስዕሉ ይሸፈናሉ) ሁለቱ ዳርና ዳር ይቆማሉ (ፈያታዊ ዘየማንና ፈያትዊ ዘፀጋ) ከፈያታዊ
ዘየማን አጠገብ አንድ ወንድ ልጅ ይንበረከካል (ወንጌላዊው ዮሐንስ) ከዚያም ዩኒፎርም ለብሰው ግማሽ ክብ ይዘው
የቆሙት አባላት ብቻ የሚከተለውን መዝሙር ይዘምራሉ፡-

ዩኒፎርም የለበሱት፡-

ምድረ ጎለጎታ ምድረ ቀራንዮ /2/

ጌታ ተሠቃየ ተሠቀለ ወዮ

ከሁለት ወንበዴ መሃል ለመሃል

አምላከ እስራኤል ጌታ ሲሰቀል

አንደኛ ወንበዴ እንዲ ይለው ነበር

ፈያታዊ ዘፀጋ፡-

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆንክ አምላክ /2/

እራስህም ድነህ እኛንም ባዳንክ /2/

ፈያታዊ ዘየማን፡-

አንተ ወንድሜ ሆይ አሁንም አትፈራም

እኛስ ለዚህ በቃን ብንነሳ ሰላም

ይሔ ቅዱስ ሰው ግን ኃጢአት የለበትም

አንተ ኢየሱስ ሆይ ኋላ ስትመጣ

ነፍሴ ከሥጋዬ በራ ስትወጣ

በክብር መንግስትህ ህይወት እንዳላጣ

ጌታ፡-

አንተ ወንድሜ ሆይ እልሃለው በእውነት /2/

ዛሬ ከእኔ ጋራ ትሆናለህ ገነት /2/

ዩኒፎረም የለበሱት፡-

ምድረ ጎለጎታ ምድረ ቃራንዬ /2/

ጌታ ተሠቃየ ተሠቀለ ወዮ

ጌታም አዘቅዝቆ ዮሐንስን ሲያየው


እናቴን ጥራት ብሎ በፅኑእ አዘዘው

ስቃይ መከራውን እንድትመለከተው /ዮሐንስ ይሔዳል/

ዮሐንስም ሔዶ እናቱን አመጣት

ስትወድቅ ስትነሳ እሾኽ እየወጋት

እያለቀሰች ቆመች በልጇ ፊት

/ዮሐንስ የእመቤታችንን ስነ-ሥዕል ይዞ ይመጣል ከጌታ ሥነ-ስዕል አጠገብ ያስቀምጣል ከውስጥ የሚከተለውን መዝሙር
በሚያሳዝን ድምፅ ትዘምራለች/

እመቤታችን፡-

አንተን ለመሸሽግ በርሃ መጓዜ

አብሬህ መዞሩ ማልቀስ መተከዜ

ልጄ መልስልኝ ይሔው ነው ደሞዜ /2/

ዩኒፍሮም የለበሱት፡-

ጌታም በአይኖቹ እናቱን እያያት

እያለቀሰ እንዲ ብሎ አላት

ጌታ፡-

አይዞሽ እናቴ ሆይ ፍፃሜ ነውና

ልጅሽ እንዲሆንሽ ዮሐንስ ያውና

ዮሐንስ ውሰዳት እናትህ ናትና

ዩኒፎርም የለበሱት፡-

ምድረ ጎለጎታ ምድረ ቃራንዮ /2/

ጌታ ተሠቃየ ተሠቀለ ወዮ /2/

/የሚለውን መዝሙር አዝማቹን ብቻ እየደጋገሙ እየዘመሩ መጋረጃው ይዘጋል/

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

በአንተነህ አስረስ (ፅሑፍ ፋሲል ኪዳኔ)

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ -ክርስትያን ኆኅተ- ጥበብ ሰ/ት/ቤት

You might also like