You are on page 1of 5

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሕሳስ 21 የሚከበሩ

ዓመታዊና ወርኃዊ ክብረ በዓላት


ወርኃ ታሕሳስ ፦ ኃሰሰ(ሲተረጎም ፈለገ) ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ሰብዓሰገል የጌታችንን
ልደት ለማየት ሽተዉ በቤተልሔም ድንግል ማርያም እቅፍ ዉስጥ እስኪያገኙት መፈለጋቸውን
ሚያመለክት ስያሜ ነዉ።

መነኩሴ፦ ማለት ለእግዚአብሔር ሲል ዓለምን ፍላጎቷን የናቀ ለእግዚአብሔር ፍቅር ሲል ሰውን


ላለማሳዘን ወደ ገዳም(በረሃ) በስርዓት ገብቶ በፆምና በፀሎት የሚተጋ/የምትተጋ ለስብከተወንጌልና ዝክረ
ቅዱሳን ቀናዒ የሆነና በእዉቀት በጉልበቱ ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በአበዉ ጳጳሳት የተሾመ ማለት
ነዉ::
፩. ኖላዊ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ሰብስባ ከምታከብራቸው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዓላት መካከል ፩ዱ የሆነዉ ኖላዊ በመባል የሚታወቀውና ጌታችን በበግ ጠባቂ (እረኛ) አምሣል የተገለጠበት ዕለት ታሕሳስ
፳፩ ነው ።

"ኖላዊ" ማለት ጠባቂ፣ እረኛ ማለት ነዉ። አዳም ከክብሩ ዝቅ ባለና በተዋረደ ጊዜ ቸር መድኃኒታችን ክርስቶስ
ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በቤተልሔም በግርግም ተወለደ፤ በእረኞችና መላእክትም ምስጋና
መድኀኒትነቱን ገለጠ። እረኛም ነፍሱን ለበጎቹ አሳለፎ እንደሚሰጥ ክርስቶስም ለኛ ወገኖቹ በመስቀል ዋጋ ከፍሎ አዳነን።
እረኛ በጎቹን ከተኩላ( ከጠላት) እንደሚያስጥል ጌታችንም ከዲያብሎስ ባርነት ማስጣሉን ቤተክርስቲያን በልዮነት
የምታስብበት እንዲሁም

“ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።”

— መዝሙር ፸፱[፹]፥፩ እያለች የልደቱን ዋዜማ ምታደርስበትና ምታመሰግንበት ልዮ እለት ናት።

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”

— ዮሐንስ ፲፥፲፩

አሜን የቸር አምላካችን ጠባቂነት እስከዘላለሙ አይለየን።


ስዕል: ኖላዊ ሔር እግዚእነ/ ቸር እረኛ ጌታችን
፪, እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጥር እና ሰኔ ፳፩ መሠረት በማድረግ በየወሩ ፳፩ የእመቤታችን መታሰቢያ ይታሰባል። በወርኃ ታሕሳስም ለአባ ይስሐቅ
ጻድቅ መገለጧ ይታወሳል። ቤተክርስቲያንም እመቤታችንን "ከፍጡራን በላይ፤ ከፈጣሪ በታች" ብላ ታመሰግናታለች።
የተወዳጅ ልጇ ክርስቶስ ቸርነት የእመቤታችንም በረከት እስከዘላለሙ ሲጠብቀን ይኑረ።

ስዕል: ጥንታዊ የእመቤታችን የግድግዳ ላይ ስዕል

፫, በርናባስ ሐዋርያ

ቅዱስ በርናባስ ምንም በትውልዱ እሥራኤላዊ ቢሆንም ተወልዶ ያደገው በቆዽሮስ ነው:: እስከ ወጣትነት ጊዜውም የቆየው
እዚያው ነው::የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የመሆኑ ዜና ሲሰማ ግን ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ መድኅን ክርስቶስን
ተመለከተ:: ጌታውንም ሊከተል በልቡ ቆረጠ:: የፈጠረን ሁሉን ሚያውቅ ክርስቶስም እንዲጠቅም አውቆ: የመጀመሪያ
ስሙ "ዮሴፍ" ሲሆን "በርናባስ" ያለው መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው:: ትርጉሙም "ወልደ ኑዛዜ-የመጽናናት ልጅ" እንደ
ማለት ነው:: ስሙንም ቀይሮ አስከተለው:: ከ72ቱ አርድእትም ደመረው::ቅዱስ በርናባስ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ
ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር: ቀጥሎ ደግሞ ቅዱስ ማርቆስን አስከትሎ ብዙ አሕጉራትን አስተምሯል። ቅዱሱም ከብዙ ትጋት
በሁዋላ በዚህች ቀን አረማውያንና አይሁድ ገድለውታል(ሰማዕትነት ተቀብሎ አርፏል):: ቅዱስ ማርቆስም ገንዞ ቀብሮታል::
ስዕል: ቅዱስ በርናባስ

፬, አባ ይሥሐቅ ጻድቅ ( ግብፃዊ )


ይህ ቅዱስ በመካከለኛው ዘመን ሐያላን ርዕሰ መነኮሳት አባ እንጦንስ እና አባ ጳዉሊ ከተነሱባት ምድረ ግብጽ የነበረ ገዳማዊ
ነው:: የዚችን ሃላፊ ዓለም ከንቱ ዉዳሴና ክብርን ንቆ ከሰው ርቆ መንኖ ለብዙ ዘመናት በገዳም ሲኖር ምኞቱ አንዲት ብቻ
ነበረች:: እመቤታችንን በአካል መመልከትን ይፈልግ ነበር(አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ/ ብርሃንን የተሞላ ፊትሽ
ይገለጥል፣ይታየኝ እንዳለ የመልክዓ ማርያም ደራሲ)::የገዳሙ ጠባቂ በመሆኑ መነኮሳት ሲተኙ መቅደሱን ከፍቶ በድንግል
ማርያም ስዕል ፊት ይጸልይ: ይሰግድ: ያነባ ነበር:: እንዲህ ለ7 ዓመታት ስለ ተጋ ድንግል እመ ብርሃን ልመናውን ሰማች::
በዚህ ዕለትም ከፀሐይ 7 እጅ ደምቃ ወደ እርሱ መጣች:: ደንግጦ ሲወድቅ አነሳችው:: በታሕሳስ 23ም ዐረፈ::
የእመቤታችን አማላጅነት የአባ ይሥሐቅም በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ስዕል: አባ ይሥሐቅ ለእመቤታችን እንደሰገደላት

ማጠቃለያ
ቤተክርስቲያን ከማንም እና ከምንም ነገር በላይ አምላክ ፈጣሪ ብላ እግዚአብሔርን ታመልካለች

ቅድስት ድንግል ማርያምን አመ አምላክ (አምላክ እናት) ብላ ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን
ፃድቃን ሰማዕታትን ደሞ እግዚአብሔር እንዳከበራቸዉ መጠን ታመሰግናቸዋለች።

ጥያቄዎች

1. ኖላዊ ማለት ምን ማለት ነዉ?


2. ለእመቤታችን ወር በገባ በ፳፩ መታሰቢያዋ እንዲሆን መነሻ የሆኑት ወራት የትኞቹ ናቸዉ?
3. በርናባስ ምን ማለት ነዉ?

You might also like