You are on page 1of 8

እንኳን ወደ ቅዱስ ቲቶ ምድብ ዝግጅት

በደኅና መጣችኹ

+
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!

ፕሮግራም መሪ: - ዕፀገነት


ሥነ ጽሑፍ - ጽንሰት
መቅደስ እና ዳዊት
ወረብ ቅንዋት
ማርያም ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመባህርይ ፀዓዳ
እስመ በእንቲሃ ወበ እንተ አዝማዲሐ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ መስቀል
ይቤ ከመ አድህኖሙ አዳምሃ አቤልሃ አብርሃምሃ ይስሃቅሃ፣ ወያዕቆብሃ
ወባዕዳነ ነቢያት ዕለ ከማሆሙ ዐቀቡ ህግየ ከመ በላዕሌሆሙ እሰብክ
እስከ ለአለም አለም።

ማርያም ተሐቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባህርይ ፀአዳ


እስመ በእንቲአሐ ወበእንተ አዝማዲሃ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ መስቀል ይቤ
መድኃኔዓለም
ትርጉም:- ማርያም ታበራለች ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባህርይ ውስጥ
እንደ ነጭ እንቁ በአዳም ባህርይ ውስጥ
እርሷን ደስ ይበላት ብሎ ስለወገኖቿ ተሰቀልኩ አለ በእንጨት መስቀል ላይ
መድኃኔዓለም።
ውይይት
ዶር ግርማ እና ቤዛ
ሥነ ጽሑፍ - ደብረ ታቦር
✝ በደብረ ታቦር ✝

በደብረ ታቦር /፬/


ለሙሴ ወኤልያስ ታያቸው ምሥጢር /፪/

ዮሐንስ ያዕቆብ ጴጥሮስም ባሉበት


ሙሴና ኤልያስ በተጋበዙበት
አምላካዊ ክብሩን ኢየሱስ ገለጠ
በፊታቸው ድንገት መልኩ ተለወጠ
አዝ.....
ሙሴና ኤልያስ የታደሉ ናቸው
ብርሃነ መለኮት ማየት መቻላቸው
ከሕያዋን ዓለም ወደዚህ በመምጣት
ከሔዱ በኋላ ጥለውት ንቀውት
አዝ.....
ቀኑ በመድረሱ ሳይጎድል ከቁጥሩ
የሚገለጽበት አምላካዊ ክብሩ
ክብሩን ተመልካቾች እንዲሆኑ ጠራ
እነ ኤልያስን ከነ ጴጥሮስ ጋራ
አዝ.....
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

You might also like