You are on page 1of 2

አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/

ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት


ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

አዲስ አይደለንም ለመከራው ጉዞ


የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋራ ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና/2/

አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/


ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

የአበውን እምነት በአላውያን ፊት


ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት
መስዋዕትነትም ቀርቧል ከፊታችን
እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን/2/

አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/


ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሀድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ከጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክንራችን ነው/2/
አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
አልጠፍቶምና በእሣት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሀድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ለጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው/ 2/
አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
ከተዋህዶ ጋር ስላለ መንፈሱ
እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ
በግፍ ቢገደሉም ክርስቲያኖች ሁሉ
ኦርቶዶክስ አትጠፋም ተነግሯል በቃሉ/ 2/
አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት/2/
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርፃ
ቅርስን ያወረሰች ገዳማት እንጻ
እንግዳ ተቀባይ መንፈሣዊት እናት
ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት
ይህንን አትዘንጉ ተዋህዶ ሀገር ናት

You might also like