You are on page 1of 1

ጥር ፳፩ ቀን

፳፩.፩ እግዝእትነ ማርያም


ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው፡፡ መትሕተ ፈጣሪ
መልዕልተ ፍጡራን ናትና ፩ም እመ ብዙኃን እግዝእተ ብዙኃን ማለት
ነው። ፩ም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፡፡ ለጊዜው ለእናት አባቷ
ተሰጣለች። ፍጻሜው ለዓለም ተሰጣለችና ፩ም ፍጽምት ማለት ነው።
ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለች። ፍጻሜው ግን
ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ ይዛ ተገኝታለችና
ም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው። በአማላጅነቷ
ምእመናን መርታ መንግሥተ ሰማያት ታገባለችና ማርያም ማር-ያም
ማር በዚህ ምድር ካሉ ምግቦች ያም በገነት ካሉ ፍሬያት የከበሩ የጣፈጡ ምግቦች
ናቸው፡፡ ማርያም ከዚህ ኹሉ ትጣፍጣለች
ትከበራለች ሲሉ ማርያም አሏት። ፩ም ማርያም ማ ማለት ማኀደረ
መለኮት ር ርግብ ይቤላ ያ ያንቅዐዱ ኀቤኪ ኵሉ ፍጥረት ም ምስሓል አሳያትና
ወምስጋድ ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ማርያም ዕረፍቷ ሲቀርብ በተለመደው ጸሎቷ ሐዋርያትን እንዲያመጣላት ጸለየች፡፡
ጌታም ዮሐንስን ከኤፌሶን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን
በደመና ጭኖ አመጣላት፡፡ መጥተው ሰገዱላትና ወደ ተዘጋጀላት
ደናግልም ተሰበሰቡ፡፡ ጌታም እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሉ
ባሕቱ ዘጼነወ እምስሂነ ሳባ፡ ሀብታተ ጸጋኪ ማርያም እስመ እማንቱ
የዘለዓለም ክብር እንደ ምትኼድ ነገሯት፡፡ በደብረ ዘይት ያሉ ደናግልም ተሰበሰብ።ጌታም እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ
መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ዕዉራን በሩ ሐንካሶች ረቱ፣ ለምጻሞች ነጹ::
አጋንንት ከሰዎች ወጡ፡፡ የተለያዩ በሽታ ያለባቸው ኹሉ ተፈወሱ፡፡
አንተን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄኽ
እንዴት እሞታለኹ አለችው፡፡ ያን ጊዜ በሲኦል የሚሠቃዩ ነፍሳትን አሳያትና
ስታዝን ማራቸው አለችው፡፡
አንቺ በትሞችላቸው
እምራቸዋለኹ አላት፡፡ ስለ እነሱስ ፯ ጊዜ እሞታለኹ ብላለች።
ከዚያም ከሚያስደነግጡ በአየርና በባሕረ እሳት ከሚወረወሩ መላእክት
የተነሣ እፈራለኹ አለችው፡፡ ‹‹ወይቤላ እግዚእነ አልቦ ለመኑሂ
ሥልጣን ላዕሌኪ እምኔሆሙ›› እንዲል ትርጕም ««ከእነሱ ባንቺ ላይ
ሥልጣን ለማንም የለውም አላት›› ከዚህ በኋላ በዝማሬ መላእክት
በቃለ አቅርንት መልአከ ሞት ሳይቀርባት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ
ሥጋዋን ቅበሩ ብሎ አሳረጋት፡፡ ስን ነሐ ፲፮ እና ጥር ፳፩ ተመልከት
የበዓሏ መታሰቢያ ጥር ፳፩ ቀን ነው።
ማጠቃለያ፡- እመቤታችን ስለ ኀጥኣን ልሙት ማለቷ ጻዕረ
ሞት ሳያገኛት ነፍሷ ከሥጋዋ መለየቷ ከልጇ ቃል ኪዳን መቀበሏ
ሥጋዋ ከዮሐንስ ጋራ ወደ ሰማይ መነጠቁ ታውፋንያ በሰይፍ
መቀጣቱ ወዘተርፈ ይነገራል፡፡
ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንዘ ድንጋፄ ሞት አልባ፡ በመዐዛ ክርስቶስ ባሕቱ ዘጼነወ እምስሂነ ሳባ ሀብታተ ጸጋኪ ማርያም እስመ
እማንቱ ተውህባ፡ ውዳሴ ዚኣኪ አህጉራተ ዓለም የበባ፡ ወስብሓታተኪ ሰማያት ነበር፡፡
እን ዐርኬ

You might also like