You are on page 1of 6

ድንግል ማርያም የውርስኃጢያት ይመለከታታልን

ድንግል ማርያም የዘርኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው
የሚከተሉትንሶስት ነጥቦች እንመለከታለን
፩.አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት [ጥንተ አብሶ ] እንደሌለባት አስረግጠው
ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል
፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ
«እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ስዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር» ኢሳ፩፤፱ ዘር የተባለች ዓለም
የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት ድንግል ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን ክታቡ
«የአብራሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም » እብ፩፤፲፮
በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳያስም
እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት እመቤትችንን ነው አምላካችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ለይቶ
በንጽሐ ስጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከስጋዋ ስጋ ከነፍስ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን
ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት፡፡
፩.፪ ነብዩ ዳዊት « የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና
ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብይ ወገንሽን የአባትሽን
ቤት እርሺ ንጉስ ውበትሽን ወዶአልና» መዝ፵፬፤፱-፲፩ መቼም ማንም ሊከራክር
ቢወድ ከእመቤታችን በላይ ለሌላ ይህ ቃል ገላጭ በምንም መልኩ አያስከድም ይልቁንም በማስተዋል ላነበበው ድንግል
ማርያምን የሚገልጽ ጥልቅ ትምህርት ማግኘት ይችላል ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ደርባ ደራርባ የተባለው ደግሞ ንጽሓ
ስጋ ላይ ንጽሓ ነፍስ ንጽሃ ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ
ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን
ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ
የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ፩፤፩ ንጉስ የተባለ ልጇ እይሱስ ክርስቶስ
ሲሆን ውበትትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው
፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን «ወዳጄሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም» መኃ፬፤፯
ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ
አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹህ ነው ብሎ አመስግⶈታል
፪. የቅዱስ ገብርኤል
ብስራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ (የዘር ኃጢአት )እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል
ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ክፍለን ማየት እንችላለን
" ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው አንቺ ከሴቶች መካከል
የተባረክሽ ነሽ" ሉቃ ፩፣ ፳፰ ግሩም ከሆነው የመልአኩ የምስጋና ቃል ወላዲተ አምላክ ኃጢአት የሚባል ጨርሶ
እንደማያውቃት ሶስት ጥልቅ የሆኑ መልእክቶችን እንመልከት
፪.፩" ጸጋ የሞላብሽ ሆይ"
እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት እመቤታችን
ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው "ሁሉ የእግዚአብሔር ክብር
(ጸጋ)ጎሎአቸዋል" ሮሜ፫፤፳፬ እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል
የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሰሩ አይደለም ነገርግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው
"ኃጢአት ባልሰሩት ላይ እንኳን ሞት ነገሰ "ሮሜ፭፤፲፬ ተብሎ የተጻፈው
ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ
የሞላብሽ ተባለች ? ይህ በርግጥም እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ
የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊትነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ
ሳይሆንለት ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ
አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው
፪.፪ ከሴቶች መካከል
ሁለተኛው ነጥብ ድንግልማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት
በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ
ሌሎች የሰው ልጆች መጽሓፍ ቅዱስ ሲገልጽ " ልዩነት የለም ሁሉ ከበደል በታች ናቸው" ሮሜ፫፤፳፪ ይላል ስለእመቤታችን
ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት
ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም ወላዲተ አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ።
እመቤታችን ከብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም
የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን? አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም
ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽህይት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ
፪.፫ የተባረክሽ ነሽ
በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ
የሚለው ኃይለቃል ነው በጣም የሚገርመው በዚሁ ተመሳሳይ ቃል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም በተመሳሳይ ስፍራ ምስጋና
ቀርቦለታል "አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው"ሉቃ፩፤፵፪
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለንና እመቤታችንም የተባረክሽ ነሽ ጌታም የተባረከ ነው የሚል ተምሳሳይ ምስጋና
ቀርቦላቸውል ይህ ማለት ሁለቱንም የጥንቱ መርገም እንደማይመለከታቸው ያመልክታል የበረከት ተቃራኒ መርገም ነው
ስለዚህም የተባረክሽ ነሽ ማለት መርገም የሌለብሽ ነሽ ማለት ሲሆን ጌታ ደግሞ የተባረከ ነው ሲባል መርገምን የሚያርቅ
ማለት ነው። ልዩነቱን ልብ እንበል እምቤታችን የተባረክሽ ስትባል ከእናቷ ማህፀን ጀምሮ ልጇ ከምርገም ጠበቃት ማለት
ሲሆን እርሱ ግን የተባረከ ነው ሲባል ለባህሪው መርገም የማይስማማው ከሌሎች መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው።
በአጠቃላይ ድንግል ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም
እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከስጋዋ ስጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለምሆን ያዘጋጃት
በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል
3.እመቤታችን ድንግል
ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት የጌታችንን ንጹሐ ባህሪውን መዳፈር ነው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ስጋና ነፍስን ከሰማይ ይዞ
አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባህሪይ ተዋሕዶ ነው። ይህን በተመለከተ ቅዱስ
ጳውሎስ እንዲህ ይላል"እንግዲህ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት
ላይስለጣንያለውንእንዲሽር - እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን
አይደለም''ዕብ 2፤14-1 5 እንግዲህ ጌታ ሰው ሲሆን ስጋንም ነፍስንም ከድንግል ማርያም ከነሳእርሷ ደግሞ
መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታ ኃጢአትያለበትን ስጋ ተዋሐደ
ልንል ነውን?እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለትነው ምክንያቱም ደፍረው ጌታን ኃጢአት
አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና " ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛእናውቃለን" ዮሐ 9፤24
እኛስ ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ስጋ እንደነሳ እንመሰክራለን እንደ
እውነተኞቹ አባቶቻችን ጌታችን ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ
መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን " ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ ከመአንስት እለ እምቅድሜኪ
ወእምድሬኪ አላ በቅድስና በንጽሕና ስርጉት አንቲ"ትርጉም"ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድመው ካንችም በኋላ
እንደ ነበሩ ሴቶች አደፍ ጉድፍን የምታውቂ አይደለሽም በቅድስና በንጽሕና ጸንተሽ ኖርሽ እንጂ"ቅዳሴ ማር 5፤42
መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት
መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ
ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
መንገድ ከጌታችን ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና ጌታ ከእመቤታችን መርገም
ያለበትን ስጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል። ይቆየን
፩. የድንግል ማርያም ሥጋ
የውርስ ኃጢአት ወይም የጥንተ አብሶ ፍዳ አለበት ከተባለ ክርስቶስ ከርሷ
ሲወለድ ኃጢአት የወረሰውን ሥጋ ወሰደ ሊባል ነው ይህ ማለት ደግሞ በመጽሐፍ
ቅዱስ አስተምሮ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ነው ምክንያቱም ለኢየሱስ
ክርስቶስ ባሕሪይ ኃጢአት ፈጽሞ አይስማማውምና ኃጢአት የነካውን ሥጋ
ተዋሐደ ከተባለ መለኮት ኃጢአት ይስማማዋል እንደማለት ነው ይህ ደግሞ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ክህደት ነው ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ
ቅዱስ ንባቦች መመልከት ይቻላል
«ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞት የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ
ያለ» ዕብ ፯፤፳፮
«ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደኛ ተፈተነ…………» ዕብ ፬፤፲፭
«ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለኛ ኃጢአት……»፪ቆሮ፭፤፳
፪. የድንግል ማርያም ሥጋ
የጥንተ አብሶ ፍዳ ወይም የውርስ ኃጢአት አለበት ማለት የክርስቶስን የማዳን
ስራ አለመቀበል ነው ። ምክንያቱንም ከዚህ እንደሚከተለው ማብራራት
ይቻላል ። ጌታ ከድንግል ማርያም መርገም ያለበትን ሥጋ ከነሳ ክብር ምስጋና
ይግባውና መርገም ባለበት ሥጋ መርገምን አራቀ ማለት በጭራሽ አያስኬድም። ይህ
ደግሞ አለም እንዲድን የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበትም ምክንያት
ከንቱ ሊሆን ነው ። የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበት ምክንያትኮ ሰው
ሁሉ የመረገም የእዳ የበደል ተጠያቂ ስለነበር ንጹሕ የሚያድን በመጥፋቱነው።ለዚህም ነው በነብዩ
ኢሳያስ እንዲህ ተብሎየተነገረው «እግዚአብሔር አየ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ ሰውም እንደሌለ
አየ ወደ እርሱ የሚማልድም እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም ስለዚህም የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት
ጽድቁምአገዘው» ኢሳ፶፱፡፲፮ አዎን እግዚአብሔር ያጣው ንጹሕ ሆኖ ስለ ሌላውየሚማልድ ካሳ ቤዛ የሚሆን
ሰው ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእዳ ከበደል በታች ስለነበሩ ንጹሕ መረገም የሌለበት ጠፋ ስለዚህም በንጹሐ ባህሪው
ጌታ ንጹሕ ስጋን ተዋህዶ ወደ እኛ መጣ ።ነብዩ የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ማለቱ እርሱ እራሱ ሰው ሆኖ
አዳነን ማለቱ ነው ። እርሱ በባህሪው ኃጢአት ስለማይስማማው ኃጢአት የሌለበትን ሥጋ ለመዋሐዱ
ምንም ሊያከራክር አይችልም ።መርገም ያለበት መርገም ያለበትን ማዳን ቢችል ኖሮ ከብዙ ነብያት አንዳቸው
አለምን ማዳን በተቻላቸው ነበር። የድንግል ማርያምን ንጽህና በጥቃቄ ከተረዳን ነገረ ድኅነትን እንዳናፋልስ
ይረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ አትናትዮስ ሐዋርያዊ ስለጌታ ሰው መሆን ሲገልጽ ስለእመቤታችን ንጽሕና
አስረግጦ የተናገረው «ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ ኢተአምር ብእሴ በስጋ ዘፈጠሮ ለእርሱ ወወለደቶ
ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም
ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ ዘእንበለ ትካዝ ።» ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡ ፲፱ትርጉም
« ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው የአራስነት ግብርም
አላገኛትም ያለድካም ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላውምን አለብሰው ሳትል
አሳደገችው» ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን «ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ ኢተአምር ብእሴ በስጋ
ዘፈጠሮ ለርእሱ ወወለደቶ ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም
ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ ዘእንበለ ትካዝ ።»
« ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው የአራስነት ግብርም አላገኛትም ያለድካም
ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው» ሃይማኖተ
አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡፲፱ትርጉም ማብራሪያውን በቀጣዩ ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናትዮስ ካስተማረው ትምህርት
እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ ለማድረግም የሚከተሉትን
ነጥቦች መመልከት ይቻላል
1.ያለ ኃጢአት
ከሚለውቃልወላዲተ አምላክ ጌታን ምንም ምን ኃጢአት ሳያገኛት እንደወለደችው ያስረዳናል
2.ያለምጥ የአራስነት ግብርም
ሳያገኛት ከሚለው ደግሞ ሌሎች ሴቶች በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት በምጥ በአራስነት የሚወልዱ ሲሆን
እረሷ ግን ከመርገመ ከእዳ ከበደል የተለየች በመሆኗ ምጥና አራስነት አልነበረባትምይህምከመላአ
ኩየምስጋና ንግግር ተስማሚነትያለውነውቅዱስ ገብርኤልሲያበስራትከላይ ከተጠቀሱት የመርገም ምልክቶች
እመቤታችን የተለየች መሆኗን ሲያስረዳ «አንች ከሴቶት መካከል የተባረክሽ ነሽ » ሉቃ 1 ፡ 28 በማለት
አመሰግኖአታል።ለመሆኑ እርሷ በሌሎች ሴቶች ያለ የመርገም ፍዳ ካለባት ከሌሎች ሴቶች መለየቷ ምን
ላይ ሊሆን ነው ?ስለዚህ እመቤታችን የመርገም ፍዳ ይመለከታታል በሎ ማስተማር ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ የራቀ
ትምህርት ነው ማለት ነው ። ውላዲተ አምላክ የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ቅዱስ አትናትዮስ ብቻ ሳይሆን
በርካታ ቅዱሳን አበውም መስከረዋል ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድንግል ማርያም የጥንተ አብሶ ፍዳ
እንደማይመለከታት ስያስረዳ እንዲህ በማለት በሚደንቅ ንግግር እንዲህ ይላል « ከመገባሪ ጠቢብ ሶበ ይረክብ ግብሮ
ዘይትጌበር ይገብር እምኔሁ ንዋየ ሰናየ ከመዝ እግዚእነ ሶበ ረከበ ሥጋሃ ቅዱስ ለዛቲ ድንግል ወነፍሳ ቅድስት ፈጠረ ሎቱ
መቅደስ ዘቦቱ ነፍስ » ሃይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡14 ትርጉም « ጥበበኛ ንጹህ አፈር ባገኘ ጊዜ ጥሩ እቃ እንደሚሰራበት
ጌታችንም የድንግልን ንጹህ ሥጋዋን ንጹህ ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ይዋሃደው ዘንድ ነፍስ ያለውን መቅደስ ሰውነቱን
ፈጠረ » መቼም የቀናች የተረዳች ርትዕት የሆነች የተዋህዶ ምዕመን ሆኖ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የማያውቅ አለ ማለት
ይከብዳል ምንም በማያሻማና ግሩም በሆነ አገላለጽ ሊቁ እነዳስቀመጠልን አምላክ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነው
ምንም ምን እንከን ከሌለው ሰውነቷ ነው ሊቁ የእመቤታችንን ነፍስና ሰጋዋን በንጹሕ አፈር መስሎታል በዚህ አገላለጹ
ከሰው ወገን ተመርጣ ለአምላክ እናትነት የበቃች መሆኗን አስረዳን ምክንያቱም የሰው ሁሉ ተፈጥሮው ከአፈር ነውና ።
ወላዲተ አምላክ እንደሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ ከአፈር ቢሆንም ቅሉ ሊቁ እንደተናገረው « ንጹሕ አፈር » የሚለው አገላለጽ
በሰዎች ከደረሰ አዳማዊ መርገም የተለየች መሆኗን ያስረዳናል ቅዱስ ኤፍሬምም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ዘር
ያልተዘራባት እርሻ በማለት በንጹሕ እረሻ መስሎአታል ልበ አምላክ ዳዊትም« እንደ ዝናብ በንጹሕ እርሻ ላይ ……..
ይወርዳል » መዝ 71 ፡6 በማለት ጌታን በዝናበ ሕይወት እመቤታችንን ደግሞ አረም ተዋስያን በሌሉት ንጹሕ መሬት መስሎ
ትንቢት ተናግሮአል ይህም ምንም ተፈጥሮዋ ከሰው ወገን ብትሆንም የኃጢአት አረም ህዋስ ያልነካት ንጽህት
ዘር መሆኗን ያስረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በንጹሕ አፈር የመሰላት ። ሊቁ በመቀጠልም « ንጹሕ ስጋዋን
ንጹሕ ነፍሷን ባገኘ ጊዜ » በማለት የወላዲተ አምላክ ነፍሷ ስጋዋ ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ ንጹሕ ቅዱስ መሆኑን ይመሰክራል
ባገኘ ጊዜ አለ እንጂ ሊዋሐደው ሲል አነጻው አላለም ሰለዚህም እውነተኞች ቅዱሳን አበው በጥንቃቄ የመሰከሩትን
የእመቤታችንን ንሕጽና ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊያስተባብል አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
እንዳስተማረን « እኛ ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰብክላችሁ
የተረገመ ይሁን » ገላ 1 ፡ 8 ባለው መሰረት ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊሽረው ወይም ሊለውጠው አይችልም ቢሞክር እንኩአን
የተለየ የተረገመ ነው ቅድስት ቤተክርስትያን የምትመራው ቀደምት ቅዱሳን ባስተማሩን እውነተኛ ትምህርት እንጂ
አዲስ ዛሬ የሚፈጠር ምንም የለም ስለዚህ ከአንዳንድ የዘመናችን ሰዎች የተሳሳተ ትምህርት ብንሰማ እነሱ
የተለዩ ይሆናሉ እንጂ የሰማይ መልአክ ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን የቤተክርስትያን አስተምሮ አይለወጥም
ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 48 ቁጥር 31 ስለ እመቤታችን ንጽህና
ሲመሰክር እንዲህ ይላል « ኢያእመረ እስመ ዘተፈጥረት እምነ ጽቡር ጽሩይ ትከውን መቅደሶ
ለእግዚአብሔር »ትርጉም « የእግዚአብሔር መቅደሱ ማደርያው ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር
(ዘር)የተፈጠረች መሆኗን አላወቀም » ታላቁ የቤተክርስትያን አባት ቅዱስ ኤራቅሊስ ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው አረጋዊ
ካህን ዮሴፍ ለእመቤታቸን አገልጋይ ሆኖ የታጨለትን ምሥጢር በተረጎመበት ክፍል ነው ።በእርግጥ አረጋዊ ዮሴፍ
ለእመቤታችን ለምን እንደታጨ አላወቀም ነበር እርሷም ትንቢት የተነገረላት ሱባዔ የተቆጠረላት አምላክን
በድንግልና ጽንሳ በድንግልና የምትወልድ ከመርገመ አዳም ከመረገመ ሔዋን የተለየች መሆኗን አላወቀም ነበር።
ነገሮችን መረዳት የጀመረው መልአኩ ካረጋጋው በኃላ የተለያዩ ምልክቶችን አይቶ ነው ።ሊቁም ይህንን ሲያስረዳ
« የእግዚአብሔር መቅደሱ ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር የተፈጠረች መሆኗን አላወቀም « ይህም አገላለጽ ወላዲተ
አምላክ ስትፈጠር ጀምሮ ንጽህት ቅድስት መሆኗን ያስርዳል ዮሴፍ ማንነቷን ከማወቁ በፊት እንደማናቸውም አንስት
ከአዳማዊ እዳ በደል ያልተለየች ሴት መስላው ነበር ሁሉን የተረዳው ቆይቶ ነው ድንግል ማርያም ግን ሊቁ እንደተናገረው
ተፈጠሮዋን በተመለከተ « ከንጹህ አፈር « በማለት ንጽሐ ጠባይዋ ያላደፈባት ያልጎደፈባት ገና በማህጸን አጥንት ሰክቶ
ሲፈጥራት በንጸህና የጠበቃት ስለሆነች ከንጹህ አፈር የፈጠራት በማለት ተናገረ ። ድንግል የአምላካችን አማናዊት
መቅደስ ናት እንደ ደንግል ማርያም የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነ ማንም የለም በሌሎቹ ሁሉ ቢያድር በጸጋ ነው
በእመቤታችን ግን በኩነት ሰው በመሆን በተዋህዶ ነው ያደረባት ስለዚህም አማናዊት መቅደስ ናት ።የእግዚአብሄር
መቅደስ ደግሞ በእውነት ንጹሕ ነው ኃጢአት የማይስማማው ንጹሐ ባህርይ የሆነ መለኮት ንጹህ ማደርያንይፈልጋልና ።
ከሊቁ ከቅዱስ ኤራቅሊስ ንግግር ልናስተውለው የሚገባን መሰረታዊ ነጥብ አለ ይህም ድንግል ማርያምን በንጽህና ፈጠራት
አለ እንጂ ከፈጠራት በሁኃላ አነጻት አላለም አንዳንድ አደናጋሪዎች ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባትና አዳማዊ
መርገም በብስራተ መልአክ ጠፋላት እያሉ ለማሳሳት ይሞክራሉ ይህ ግን አላዋቂነት ነው ቅዱሳን አበው በመንፈስ
ቅዱስ እየተመሩ ያስተማሩትን ትምህርት ማስተባበል ነው ደግሞስ መርገም በብስራተ መልአክ
የሚጠፋ ከሆነ መላእክት ያበሰሯቸው ሁሉ መርገመ አዳም መርገመ ሔዋን ጠፍቶላቸዋል ማለት ነው ?
ይህስ ከሆነ የአምልክ መውረድ መወለድ ሰው መሆን ሰጋውን መቁረስ ደሙን ማፍሰስ ለምን አሰፈለገው ? በክርስትና
አስተምሮ መሰረት የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ
ከምሥጢረ ድህነት ጋር የተያያዘ ነው ስለዚህም ነው ስለእርሷ የምንናገረውን ነገር ልንጠነቀቅ የሚገባን ።ሊቁ
ቅዱስ ኤራቅሊስ ከንጹህ አፈር ተፈጠረች ማለቱ የሚጠቁመን ሌላ ነጥብ ደግሞ በጥንተ ተፈጥሮ ስንመለከት ከአፈር በቀጥታ
የተፈጠረ አባታችን አዳም ብቻ ነው ሌሎቹ አዳማዊያን መሰረታቸው አፈር ቢሆንም የተፈጠሩት በውልደት ነው
ድንግልን ግን ከንጹህ አፈር ተፈጠረች አላት ይህም ምሳሌ ነው በቁሙ አፈር ንጹህ እና ቆሻሻ ተብሎ አይደለም ነገር ግን በዚህ
አገላለጽ በአፈር የተመሰለ የሰው ልጆች ሰውነት ነው በቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ እንደተባለ
«አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ » ዘፍ 3 ፡19 ከሌሎች የአፈር አይነቶች ተለይቶ ተዋስያን በሌሉበት በንጹህ አፈር
የተመሰለ መርገመ አዳም መርገመ አዳም ያልነካው የእመቤታችን ሰውነት ነው ምንም እንኳን አምላክን ብትወልደውም እንደ
ሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ እንደ አዳማዊያን ከአፈር ነውና ሰለዚህም ቅድስት ቤተክርስትያን የእውነተኞቹን
ደጋግ አበው ምስክርነት ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር አስተባብራ ወላዲተ አምላክ መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ
የሌለባት የጥንተ አብሶ ፍዳ የተለየች መሆኗን አበክራ ታስተምራለች እውነት ከምድር በቀለችጽድቅና ሰላም
ተስማሙ መዝ 84፤10 እውነት ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ዮሐ 14፤7 እውነት የበቀለባት
ምድር ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡ጽድቅና ሰላም የተስማሙበት በጌታችንልደት ነው፡፡
-አዳም የተገኘው መርገም ካልደረሰባት ምድር ነው/ ከበደል በፊት ማለት ነው/ ምድር መርገም የደረሰባት
በልጅዋ በአዳም በደል ነው፡፡ አዳም የተገኘባት ቀዳማዊቷ ምድር መርገም እናዳላገኛት ሁሉ ዳግማዊቷ ምድር
ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደችልን ድንግል ማርያምም እዳ መርገም/ጥንተ ብሶ/ አልደረሰባትም/
አላገኛትም/፡፡አስቀድማ በደል/ጥንተ አብሶ/ነበረባት ካልን ጌታ ከተገኘባት ዳግማዊቷ ምድር አዳም
የተገኘባት ቀዳማዊቷ ምድር ትበልጣለች ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ አዳም ተካሰ ተዋጀ ወደቀድሞ ክብሩ
ተመለሰ ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በደል ከሌለባት ምድር የተገኘው አዳም በደል " ካለባት " ከእመቤታችን
ድንግል ማርያም ከተገኘው ከዳግማዊው አዳም ከጌታ ኢየሱስ " ይበልጣል "/ሎቱ ስብሃት/ ማለት ነው፡፡ይህ
ከሆነ ደግሞ " ያነሰው " ጌታ " የበለጠውን " አዳምን ሊያድነው " አይችልም " ፡፡ ስለዚህ ሀጢአት ከሌለባት
ከመቤታችን የተገኘው ዳግማዊው አዳም በደል ያለበትን ቀዳማዊ አዳም በደሙ ከንጽህይት ቅድስት ተወልዶ አድኖታል
አሜን፡ « ቀዳማዊ አዳም ወዳግማዊ አዳም » ቀዳማዊ አዳም የሚባለው ከምድር አፈር የተፈጠረው ሰው ነው ፡፡
« እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው ፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ
ያለው ሆነ ፡፡» እንዳለ ፡፡ ዘፍጥ 2፤7 ፡፡ ዳግማዊ አዳም የተባለው ደግሞ በተለየ አካሉ ከሰማይ ወርዶ. በማኅጸነ
ድንግል ማርያም አድሮ. ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ የተወለደው የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፡- « አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ( በኵር ሆኖ )
ተነሥቷል ፡፡ በመጀመሪያው ሰው ( በቀዳማዊ አዳም ) ሞት መጥቷል“. በሁለተኛው ሰው( በዳግማዊ አዳም
በክርስቶስ ) ትንሣኤ ሙታን ሆነ ፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በክርስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ . . . መጽሐፍ
እንዲህ ብሏል. የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ ፤ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ
ነው ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ሥጋዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም ፡፡ የመጀመሪያው
ሰው ከመሬት የተገኘ መሬታዊ ነው ፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ ነው፡፡ » በማለት ገልጦታል፡፡
1 ኛ ቆሮ 5፤5 ፡፡ ከዚህም የመጀመሪያው ፍጡር ሁለተኛው ፈጣሪ. የመጀመሪያው ከምድር ሁለተኛው ከሰማይ መሆኑን
እንረዳለን ፡፡ እንግዲህ የሚያንሰው ቀዳማዊ አዳም ከመጀመሪያው ንጽሕት ከነበረች መሬት ተፈጠረ እያልን የሚበልጠውን
ዳግማዊ አዳም ከመጀመሪያው ንጽሕት ካልነበረች. በጥንተ አብሶ አድፋ ጐድፋ ከነበረች ከድንግል ማርያም ተወለደ
ማለት ክርስቶስን ከአዳም ማሳነስ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡«ብሥራተ ገብርኤል ወፅንሰት፡፡ »
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እመቤታችን በመጣ ጊዜ ፡- « ደስ ያለሽ.
ጸጋንም የተመላሽ ሆይ. ደስ ይበልሽ ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ፤ ከሴቶች ተለይተሸ አንቺ የተባረክሽ ነሽ ፡፡»
በማለት አመስግኗታል፡፡ ሉቃ 1፤8 ፡፡ ከእርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ ማንም አልነበረም
፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን
ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል « ጸጋን የተመላሽ ሆይ » አይላትም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐዶሎ ያሰኝባት
ነበርና ፡፡ ከላይ እንደገለጥነው እነ ኢሳይያስን ጽድቃቸውን የመርገም ጨርቅ ያሰኘባቸው ጥንተ አብሶ ነው፡፡ የቅድስናን
ሥራ እየሠሩ « ሁላችንም እንደ ርኵስ ሰው ሆነናል ፤ » ያሰኛቸው ይኽው ነው ፡፡ ኢሳ 4፤6 እነ ኤርምያስንም ፡- «
ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም፡፡ ስንዴ ዘሩ እሾህንም አጨዱ ፤ » አሰኝቷቸዋል፡፡ ኤር 2፤3፡፡ እመቤታችን ግን
ከመጀመሪያው ንጽሕት ቅድስት በመሆኗ « ጸጋን የተመላሽ ሆይ ፤ » ተብላለች፡፡
አንዳንዶች፡- ለእመቤታችን ጥንተ አብሶ የጠፋላት መልአኩ ባበሠራት ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ ይህም አባባላቸው
ሁለት ጥያቄዎችን ያስነሣል፡፡ 1 ኛ ፡- ከዚህ በፊት መልአክ ያበሠራቸው ማኑሄናሚስቱ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
ለምን ጥንተ አብሶ አልጠፋላቸውም; መሳ 3፤2 ሉቃ 1፤8 ፤ 2 ኛ ፡-
ጥንተ አብሶ የሚጠፋው በብሥራተ መልአክ ቢሆን ኖሮ አካላዊ ቃል ከሰማይ ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው
መሆን . መከራ መቀበልና በመስቀል ላይ መሞት ለምን አስፈለገው; በልዑል መንበሩ እንደተቀመጠ እልፍ አዕላፋት
ወትእልፊተ አዕላፋት መላእክትን ልኮ በብሥራት ብቻ ጥንተ አብሶን አያጠፋም ነበር; አንዳንዶች ደግሞ « ጌታ
በተፀነሰ ጊዜ በዚያ ቅጽበት ነው የጠፋላት ፤ » ይላሉ፡፡ ይህም ፡- «ጌታ የመጣው ጥንተ አብሶን እንዴት አድርጐ
ለማጥፋት ነው; » የሚል ጥያቄ ያስነሣል ፡፡ መልሱም « በመስቀል ላይ በሚፈጽመው ቤዛነት በሚከፍለው መሥዋዕትነት
ነው፤» የሚል ይሆናል ፡፡ እንግዲህ እመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚሉ ከሆነ «እርሷም በጥንተ አብሶ
እንደተያዙ እንደማናቸውም ሰው ናት፤ » ማለታቸው ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ እንደማናቸውም ሰው በመስቀል ላይ
በሚፈጸም ቤዛነት ብቻ ከጥንተ አብሶ ትድን ነበር እንጂ ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት ሊሆን አይችልም፡፡
« ሰው አይደለችም ወይ;» ነቢዩ ኢሳይያስ ፡- « በትር ከእሴይ ሥር ትወጣለች. አበባም ከእርሷ ይወጣል፤»
በማለት ስለ እመቤታችንም ስለ ጌታም ትንቢት ተናግሯል፡፡ ኢሳ 01.1 ፡፡ የበትር ምሳሌነት ለእመቤታችን ሲሆን የአበባ
ምሳሌነት ደግሞ ለጌታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዚህ ትንቢት ላይ ተመሥርቶ ፡- « ትወጽእ በትር እምሥርወ ዕሴይ.
ወየዐርግ ጽገ. ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ይእቲ. ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ ፤ አምሳሉ ዘወልድ ዘኀደረ ላዕሌሃ. ቃል
ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ፤ ከነገደ ዕሴይ በትር ትወጣለች. አበባም ከእሷ ይወጣል. ይህችውም በትር የማርያም አምሳል ናት
፤ ከእርሷ የሚወጣውም በትር የወልድ ምሳሌ ነው፤ የአብ አካላዊ ቃል በማኅጸኗ አድሮ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን
ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው ሁኖ ከእርሷ ተወለደ፤ » ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም ቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረን የእመቤታችን የዘር
ሐረግ (የዘር ቅጂዋ) ከዕሴይ ወደ ዳዊት ወደ ሰሎሞን . ከዚያም ሲወርድ እስከ አልዓዛር .ከዓልዓዛር ደግሞ ሴት ልጁ
ወደምትሆን ወደ ቅሥራ. ከቅሥራም ወደ ኢያቄም የደረሰ ነው፡፡ በእናቷ በኵል ደግሞ ከሊቀ ካህናቱ ከአሮን ወገን ናት፡፡
በመሆኑም ከሰው ወገን የተወለደች ሰው ናት፡፡ በዘመናችን ኤች አይ ቪ ኤድስ ከእናት ወደልጅ በሳይንሳዊ መሳሪያ
እንደማይተላለፍ ሁሉ እመቤታችንም በናቷ ማህጸን ሳለች ጥንተ አብሶ እንዳይተላለፍባት መንፈስ ቅዱስ በአምላካዊ ጥበቡ
ለጌታ ማደሪያ ስለመረጣት ከጥንተ አብሶ ጠብቋታል፡፡ ካቶሊኮች፡- ጥንተ አብሶን የሸሹ መስሏቸው « ሰው አይደለችም .
ኃይል አርያማዊት ናት » እያሉ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ይኽንን የካቶሊኮች አመለካከት የሸሹ መስሏቸው «እንደማናቸውም
ሰው ጥንተ አብሶ የነበረባት ሰው ናት፡፡ » ይላሉ ፡፡ የሁለቱም « ከድጡ ወደ ማጡ » ነው ፡፡ የሁለተኛዎቹ አስተሳሰብ «
ከሰው ወገን የተወለደች ሰው እስከሆነች ድረስ. የሰው ልጅ ተብላ እስከተጠራች ድረስ የግድ ጥንተ አብሶ ነበረባት ያሰኛል ፤
» የሚል ነው፡፡ ይህም አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ይኽውም ፡- « የሰው ወገን . የሰው ልጅ ለመባል የግድ የጥንተ
አብሶ መኖር ያስፈልጋል ወይ; » የሚል ነው ፡፡ እንዲህስ ከሆነ ቀዳማዊ አዳም ከመበደሉ በፊት ለምን ሰው ተባለ; መርገመ
ሥጋን መርገመ ነፍስን ያጠፋ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ለምን የሰው ልጅ ተባለ; ያሰኛል፡፡ መናፍቃኑ እነደሚሉት ቢሆን
ኖሮ፡-
እነ ኢሳይያስ « እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ ፤» እያሉ አይመኩባትም ነበር፡፡ እነ ሰሎሞንም « አልብኪ ነውር »
እያሉ አያመሰግኗትም ነበር፡፡ እነ ቅዱስ ኤፍሬም « አክሊለ ምክሕነ. ወጥንተ መድኃኒት. ወመሠረተ ንጽሕነ ፤ » እነ
አባ ሕርያቆስም ፡- « ወኢረከበ ዘከማኪ፤ » አይሏትም ነበር፡፡ ስለዚህ ብርሃኑን ከጨለማ በጐውንስንዴውን ከእንክርዳድ
ለይተን አባቶቻችን ባቆዩልን ልንጸና ያስፈልጋል፡፡ ነገሩ የእውቀት ብቻ ሳይሆን የእምነት ነውና፡፡ የዕውቀት ሰዎች ሁለት
ዓይነት ናቸው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ እውቀታቸውን በትህትና ይዘው በእምነት የሚኖሩ ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ግን በእውቀታቸው
ሲታበዩ በጥርጥር ማዕበል የሚመቱ . በኑፋቄ የሚለዩ . በክህደት የሚወድቁ ናቸው፡፡ ትእቢት ዲያቢሎስ የተያዘበት አሽክላ
ነው፡፡ በንስሐ የማይመለሰው ለዚህ ነው፡፡ ዲያቢሎስ የትዕቢት እንጂ የእውቀትም የሥልጣንም ችግር አልነበረበትም፡፡ እነ
አርዮስ. እነ ንስጥሮስ. እነ መቅዶንዮስም የትዕቢት እንጂ የእውቀት ችግር አልነበረባቸውም፡፡ ነገር ግን እውቀታቸውን ለክፋት
ተጠቀሙበት ፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜ ለሚነሡ መናፍቃንም መጥፎ አብነት ሆኑበት፡፡ ስለዚህ ከዚህ እንዲሠውረን
ተግተን ልንጸልይ ይገባናል፡፡ ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት . የንጽሕተ ንጹሐን . የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን የድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን ፡፡ ድንግል ማሪያም የአዳም ሐጥያት አለባት ካልን ጌታ ኢየሱስ ክብር ለሱ ይሁንና
የአዳም ሀጢያት አለበት እያልን ነው /ሎቱ ስብሃት/ ምክንያቱም ቆሻሻ ባሊ ውስጥ የተጨመረ ንፁ ውሀመቆሸሹ
ስለማይቀር…… ቸር ይቆየን አሜን

You might also like