You are on page 1of 3

ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ትባላለችን?

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ትባልለችን ? የሚለውን ከማየታችን በፊት
ስለቤዛነት ትርጉም እንመልከት።
1.ቤዛ፦ ቤዛ የሚለው ቃል በሁለት መልኩ ሊተረጎም ይችላል።የመጀመሪያው ስርወ ቃሉን ወይም ግሱን
መሥረት አድርጎ በመተንተን የሚገኝ ትርጉም ሲሆን ሁለተኝእው ደግሞ በአገባብ ደረጃ የሚሰ/ተው
ትርጉም ነው።
ቤዛ ሥረወ ቃሉ “ቤዘወ” ቤዛ ሆነ፣ አዳነ ማለት ሲሆን ቤዛ የሚለው ቃል ትርጉምም በቁሙ ዋጋ፣ካሳ
፣ለውጥ፣ምትክ፣ኃልፊ፣ ዋቢ ፣ማስጣል፣ከጭንቅ ከባርነት ማውጣት ለውጥ መስጠት ማለት ሲሆን
በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ቤዛ ማለት የተያዘን ወይም የተወሰደን ለማስመልውስ የሚከፈል ዋጋ፣ካሳ፣ዋጋ
በመክፈል ወይም ራስን በመተካት የተወሰደን ማስመለስ መሆኑን የሥነ ቋንቋ መዛግብት ያስረዳሉ።
ከዚህ በተጨማሪ የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚያትቱት ቤዛ የሚለው ቃል አገባባዊ ፍች ትርጉሙን
ስለ፣ ፈንታ፣ ምክንያት የሚል ሁኖ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ንባብን መሠረት አድርገው ሙያውንና ትርጉሙን
ሲያስረዱ “እሜጡ ንፍስየ ቤዛ አባግዕየ” ንፍሴን ስለ በጎቼ እሰጣለሁ (ዮሐ 10፥14-15) ዐይን ቤዛ
ዐይን፣ወስን ቤዛ ስን፣በዓይን ፈንታ ዓይን፣በጥርስ ፈንታ ጥርስ(ዘዳ 22፥13)፣ቤዛ ይስሐቅ፤ በይስሐቅ
ፈንታ(ዘፍ 22፥13) በማለት ቤዛ የሚለው ስለ፣ስለ ፈንታ ብለው ተርጉመዋልና ፣ተሰቅለ ቤዘነ ስለእኛ
ምክንያት ተሰቀለ
ለምሳሌ ፦ ጫማ፣ዣንጥላና ጋሻን እንመልከት። ጭእማ እግራችንን እሾህ እንዳይወጋው እንፋት
እንዳይመታው ስለ እግራችን ቤዛ ሆኖ የቀረበ ነው ። ጭእማችን ያልቃል ፣ይቀደዳል ያረጃል እግራችንንም
ከጉዳት ይጠበቃል።ይህም የሚያመለክተው ጫማው ለእግራችን ቤዛ መሆኑን ነው። ዣንጥላና ከጠላት
ጦር የምንከላከልበት ጋሻም እንደዚሁ ነው።እንግዲህ እነዚህን ትርጉሞች በአግባቡ መረዳትና መገንዘብ
የእመቤታችንን ቤዛነት ለመረዳት መንገዱን ይጠርጉልናል።
አንድ ሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን ቤዛ ትባላልች ? ቤዛ የሚለውን ቃል ትርጉም
ማወቅና መማር አለበት።
ከላይ በምሳሌ እንድናየው የክርስቶስን ቤዛነት ከፍጡራን ቤዛነት ጋር ማምታታት የለበትም።ይህ ግልጽ
እንዲሆን የባሕርይ እና የጸጋ ቤዛነት ምስጢር /ትርጉም እንመልከት።
1.እግዚአብሔር በባሕርይው ቤዛ ተብሏል።እግዚ አብሔር የባሕርይ ቤዛ ስንል ሰጭ ወይም ነሽን የሌለው
፣የማይጨመርበት የማይቀነስበት ሆኖ ከሰወች ምንም ምን ሳይፈልግ የሰውን ልጆችን በነፍስም በሥጋ
ለማዳን ለማዳን ከብዝኃ ፍቅሩ የተነሳ ራሱን በእምነት መስዋዕት ለማድረግ በመስቀል ላይ የከፈለው
አምላካዊ የቤዛነት የሚገለጽ ነው።ብመሆኑም የባሕርይ የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ ወልድ በተልየ አካሉ ሥጋና ነፍስን ነስቶ
የፈጸመልን ሥራ የቤዛነት ሥራ ስትለው በእርሱ ቤዛነት ምክንያት የተገኘውን ድኃነት ደግሞ የቅድስት
ሥላሴ ማዳን ነው ትላለች ።ይህንን የአምላክ ሥራም(የባሕርይ ቤዛነት) ለፍጡር አትሰጥም ወይም
ሰጥታም አታውቅም።
2.ቤዛ የሚለው ቃል በጸጋ ለፍጡራን ለሰው ልጆች ተገልጾ እናገኛለን።
የጸጋ ቤዛነት ማለት ሰጭም ሆነ ነሽ(ባለቤት) ያለው የሚጎድልበት የሚጨመርበት የራስ ያልሆነ ማለት
ሆኖ በእግዚአብሔር አምነው ለታመኑት ቅዱሳን በእርሱ ፈቃድ ሁነው እንደኖሩበት ቤዛ ተብለውም
እንዲጠሩበት የሚሰጥ አምላካዊ በረከት ነው።
በዘመናችን ትውልዱ በአዕምሮ “ፍጡር ቤዛ ይባላልን” ብሎ ይጠይቃል የዚህ መሥረታዊ ጥያቄ መልሱ
ይሆናል፣አይሆንም ይባላል፣አይባልም የሚል ቁንጽል የግል ሀሳብ መስጠት ሳይሆን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው
ነይስ አይደለም የመጽሐፍት ምስክርነት ነውን? መጽሐፍት በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ? የሚለውን ጥያቄ
በመተየቅ በቅን ልቡናመፈልግ እና መረዳት ይኖርበናል። መሆኑን እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ “አምላክን
መሆንና መባልን” “ብርሃን መሆንና መባልን” ፈራጅ መባልና መሆንን ፣መድኃኒት መባልንና መሆንን
ለፍጡር በጸጋ የሜጥ( የተፈቀደ) ነው። ቤዛም ለፈጣሪ ሲሰጥ “የባሕርይ”ለፍጡር ሲሰጥ ደግሞ
“የጸጋ”መሆኑኑ መረዳትና መገንዘብ አለብን።
ለምሳሌ፦ ለቀ ነቢያት ሙሴ በግልጽ ቤዛ ተብሎ እንገናኛለን።
“ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው” ብለው የካዱት ይህን ሙሴን በቁጥቋጦ በታየው በመላእኩ
እጅ ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው /ሐዋ 7፥35/ በማለት እስራኤልን ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍከው
መጽሐፍህ ደምስሰኝ በማለት በእስራኤል ዘሥጋ ፈንታ እኔን አጥፋኝ ማለት ስለእነርሱ ቤዛ ሁኖ
በአማላጅነቱ በተደጋጋሚ አድኗቸዋል።
ከዚህ በላይ እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቃል በምንረዳው ፍቱር በጸጋ “ቤዛ ሆኖም”
ተብሎም መጠራት እንደሚችል ነው።ይህም ሆኖ ግን ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች መሠረት ቅዱስ ሙሴ
በጸጋም ቢሆን “ቤዛ ብቻ እንጅ የዓለም ቤዛ ሊባል አይችልም”ለምን ካልን ቅዱስ ሙሴ ቤዛ ሁኖ ከጊዜአዊ
መከራ ሥጋ የታደጋቸው የዓለምን ሕዝብ በሙሉ ሳይሆን እሥራኤል ዘሥጋን ብቻ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ እስራኢላውያን በተደጋጋሚ ሲበድሉ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል ወደ እግዚአብሔር
ሲመለሱ እግዚአብሔር አዳኝ ያስነሳላቸው ነበር። ይህንንም በተመለከተ መጽሀፍ እግዚአብሔር
የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሳላቸው መሣ 3፥9
በማለት ይገልጻል። እንዲህ አይነት በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትቅሶች አሉ።እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ
አስተምህሮወች ፍቱራን ቤዛዎች ተብለው ሊጠሩ አይገባም ለሚሉ መናፍቃን ደገኛ ምላሽ ናቸው።
ስለዚህ ከዚህ አንጻር ስንመለከት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ የሰው ልጅ/ዘር/
በሙሉ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ነጻ ወጥተን ሀብተ ሥጋንና ሀብተ ንፍስን ገንዘብ አድርገው በፍጹም
ነጻነት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ትክክለኛ ምክንያት ሁና ንጽህናዋን ጠብቃ የተገኘች ምክንያተ
ድኂን ስለሆነች “ቤዛዊተ ዓለም ” ትባላለች።ይህንን ስንል ግን የክርስቶስን የባሕርይ ቤዛነት አዳኝነት
የምትተካ አይደለችም ።
እስኪ የበለጠ እንድንረዳውና እንድንገነዘበው ቤተ ክርስቲያናቸን አቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን
በዛዊተ ዓለም የምትልበትን ምክንያቶች እንመልከት።
1.የሰውን ዘር ተክታ ፍጽምት ንጽሕት/ቅድስት መሆኗ
አዳምና ሔዋን እጸ በለስን በልተው ባሕራይቸው ተጎሳቆሎ የሰው ዘር በሙሉ ከገነት ተባሮ በኃጢአት
ውስጥ በዚህ ዓለም መኖር ጀመረ።በዚህ ሰዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሰው ዘር ተገኝታ
ነገር ግን የሰው በደል መርገም ኃጢአት ሳያገኛት ቅድስት፣ንጽሕት ቡርክት ሆና በመገኘት የአምላክን እናት
በምሆን ለድኅነት ምክንያት በመሆኗ እመቤተቻንን ቤዛዊተ ዓለም እንላታለን።
ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ “በእንተ ምርያም ተዐጽወ ኆኅተ ገነት ወበእንተ ማርያም
ድንግል ትርኅወ ለነ ዳግመ” -ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከጀተልን።
በማለት ሄዋን ባለመታዘዝ ያዘጋችውን ገነት እመቤታችን በመታዘዝ እንዳስከፈተችልን ያስገነዝበናል።
ሊቁ ሰማዕት ዮስጢኖስ እመቤታችንና ሔዋንን እያነጻጸረ ሲጽፍ “ሔዋን ድንግል ስትሆን የእባብን ቃል
ፀንሳ አለመታዘዝንና ሞትን ወለደች ፤ማርያም ድንግል ስትሆን በእምነት ተመልታ ለመልአኩ የምሥራች
ቃል በመታዘዝ እባብን የሚያጠፋውንና በእርሱ ያመኑትን ከሞት የሚታደጋቸውን ሕጻን ጸነሰች “በማለት
እመቤታችንን የዳግሚቷ ሔዋን ምትክ ለማለት ቤዛዊተ ዓለም የምንል መሆናችንን መገንዘብ ተገቢ ነው።
2. ምክንያተ ድኂን መሆኗ
እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን የበደልው ሰው የሞተውም ሰው ነውና ሰው መሆን ነበረበት ምክንያቱ
ደግሞ የበደለው ሰው ነውና ከሰው ወገን ንጹህ ሆኖ የሰውን በደል የሚክስ ሰው ያስፈልግ ነበር። ይህንን
ለማድረግ ደግሞ የሰው ልጅ በሙሉ በመርገምና ኅጢአት ውስጥ ስለነበር ይህንን ማድረግ አይችልም ነበር።
በዚህ መሥረታዊ ምክንያት አምላክ ሰው ሆኖ በአዳም ላይ የወደቀውን መርገም --------- ስላስፈለገው
ከሰው ወገን ለእርሱ እናትነት ንጽህት ፣ቡርክት ቅድስት እናት ታስፈልገው ነበር።እርሷም በቅድስና አጊጣና
ተውባ የተገኘች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች። ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው ፍጹም
ሥጋችንን ተዋሕዶ ነውና ለዚህ ደግሞ ጌታችን መልአኩን ልኮ ፈቃዷን በጠየቃት ጊዜ “ይኩነኒ” ብላ
ዓለምን ወክላ በመቀበሏ ምክንያት አምላክ ፍጹም ሰው እንዲሆን ምክንያት ሁናለች። ይህ ደግሞ በመገረ
ድኅነት ትምሕርት መጀመሪያ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን
አፍስሶ አዳነን ስንል ይህንን ሥጋና ደም ከየት የመጣ ነው? ካልን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን
ነስቶ መወለዱ ያስገነዝበናል። ስለዚህ ዕለምን ለማዳን በተደረገ አምላካዊ የድኅነት ጉዞ ውስጥ ማለትም
አምላክን ከመፀነስና ከመውለድ ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ በተፈጸመው ድኅነት ምክንያተ ድኂን ምክንያት
ድንግል ማርያም በጸጋ “ቤዛዊተ ዓለም” እንላታለን።
ሊቁ ቅዱስ አምብሮስ ፦ በአዳምና በሄዋን ምክንያት ሥጋ ለባሽ በሙሉ ከገነት ወጣ በድንግል ማርያም
አማላጅነት ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኘ ፣ሔዋን የሰው ዘር በሙሉ እናት ናት ማርያም ግን የድኅንነት እናት
ናት። ይላል።
ሊቁ አባ የሮኒመስ(ጀሮም) “ሞት በሔዋን ምክንያት ገባ ሕይወት ደግሞ በማርያም” በማለት ጠቅለል
አድርጎ እመቤታችን ሕይወት ያመጣች መሆኗን ይገልጻል። እግዚአብሔር ዓለሙን ያዳነው እርሷን
ምክንያት አድርጎ ሥጋና ነፍስን ከእርሷ ነስቶ ነውና ይህ ደግሞ የርሷን ቤዛዊተ ዓለምነት በግልጽ
ያስገነዝባል።
3.የዓለምን መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷ።

You might also like