You are on page 1of 6

Hi selam ehitina wendimoche endemin koyachu yih

kelay letenesaw tiyake yetesete mabrariya nw ebakachu


betigist anbibut geta yibarkachu
ጥያቄ፦በውኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ስጋና ደምን

ነስቷልን?

ማብራሪያ
ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በስጋና በደም ተካፍሏልን?” ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ
መጽሐፍ ቅዱሳችን “አዎን! ተከፍሏል!” ሲል ከመመለሱ ባሻገር፤ ‹‹ይህን እውነት አለመቀበል በራሱ፥ ክርስቶስን
ከሚቃወመው ዲያብሎስ የሚመንጭ›› መሆኑን አበክሮ ያስተምረናል፡፡ አብረን ቃሉን እንመርምር፥

በመጀመርያ ደረጃ አንደ አካል “ሰው” ሊባል የሚችለው ምን ምን ሲያሟላ እንደሆነ ከመሰረቱ ካጠናን፥ በቀላሉ የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስን በስጋና በደም፥ እኛን ይወክል ዘንድ መካፈሉንና ፍጹም ሰው መሆኑ ላይ ጥያቄ አናነሳም፡፡ እንደ
እግዚአብሔር ቃል አንድ አካል “ሰው” ሊባል የሚችለው “ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ” ሲኖረው ነው፡፡ ይህንም መጽሐፍ
ቅዱሳችን “የሰው ሁለንተና” ሲል ይጠራዋል፥

· “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ *መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም (spirit and soul
and body)* ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” 1 ተሰ 5፥ 23፡፡

ይህ ክፍል የሚያስተምረን፥ አንድ አካል ሰው ሊባል የሚችለው “ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ” ብቻ ሲኖረው በመሆኑ
‹‹ሁለንተናችሁ›› የተቀደሱ ይሁኑ ሲል ሐዋርያው እንደጻፈልን ነው፡፡ በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን ‹‹ሁለንተና››
የሚለው ቃል የግሪኩን “ኾሎክለሮሽ ὁλόκληρον, 3648 holokleros” የሚለውን ቅጽል (Adjective) የወከለ ሲሆን፥
የሁልጊዜ ትርጓሜውም “ሙሉ በሙሉ የሆነ (complete in every part)” ማለት ነው፡፡ ከዚህ ክፍል በመነሳትም፥ የሰው
ሁለንተና ወይንም ሙሉ አካል “ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ ነው” ብንል የተደላደለ መሰረት አለን፡፡ (ተወዳጆች ሆይ፥ በዚህ
ትምህርት ዙሪያ በእናንተው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ፥ ሰፊ ተደማጭነት ካላቸው አስተማሪዎች መካከል፥ “ሰው
ምንድን ነው?” በሚል ርዕስ ዶክተር ማሙሻ ፈንቴ ያስተማረውን ትምህርት እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ
https://www.youtube.com/watch?v=M8rE9x1IhX4)፡፡ በተጨማሪም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፥ የሰው ሁለንተና
ማለትም “ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ” ከእንስሳት “ሥጋ” ጋር አንድ አለመሆኑን፥ “ሥጋ ሁሉ አንድ” አይደለም በማለት
አጽንኆት ሰጥቶ በቆሮንጦስ መልዕክቱ ላይ አስፍሮልናል፥
“እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል፥ ከዘሮችም ለእያንዳንዱ *የገዛ አካሉን* ይሰጠዋል። *ሥጋ ሁሉ አንድ
አይደለም*፥ የሰው ሥጋ ግን አንድ ነው፥ የእንስሳም ሥጋ ሌላ ነው፥ የወፎችም ሥጋ ሌላ ነው፥ የዓሣም ሥጋ ሌላ ነው።”
1 ቆሮ 15፥ 38-39፡፡

ሐዋርያው እንደጻፈልን አምላካችን እግዚአብሔር፥ ፍጥረታትን ሲፈጥር የእያንዳንዱን ፍጥረት ዘር፥ ከየወገኑ እየለየ
የራሱን አካል እንደሰጠ እንማራለን፡፡ ይህም ማለት፥ የሰው ዘርና አካል ከሌሎች እንሳስትና ፍጥረታት ዘርና አካል ጋር
ፈጽሞ አንድ አይደለም፡፡ የሰው ሥጋ ብቻ አይደለም ከሌሎች እንስሳት የሚለው፥ ይልቁንም እንስሳትም ጭምር
እንደየወገናቸው ዕርስ በዕርስ የተለያየ ሥጋና አካል ነው ያላቸው፡፡ ክርስቶስም ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋና ደም
ካልተካፈለ፥ ከመሰረቱ “ሰው” ሊባል አይገባውም፡፡ ምክንያቱም አንድ አካል ሰው ሊባል የሚችለው “ሥጋ፣ ነፍስ፣
መንፈስ” ሲኖረው ነው፡፡ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋና ደም ሳይካፈልና የሰውን ዘር ሳይዝ፥ “ሥጋ፣ ነፍስ፣
መንፈስ” ቢኖረውም እንኳ +ሰው+ ሊባል አይገባም፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሥጋ ሁሉ አንድ”
አይደለም ይለናልና፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ “ሰው” መሳይ “ሌላ ዓይነት ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ ያለው የሰው ዘር”
እንዳለ በአንድም ስፍራ አያስተምረንም፡፡ በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ክብር ይግባውና ከድንግል ማርያም
የእኛኑ ሥጋና ደም ተካፍሎ፥ የሰውን ዘር በመያዝ “ሰው” ሊባል ችሏል፥

“የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ
በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ *ሰው ነበረ*፡፡”
ሐዋ 2፥ 22፡፡

ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆኑን ይህ ክፍል ያስረዳናል፡፡ ለዛም ነው ቅዱስ
ዳዊት አስቀድሞ በትንቢት መንፈስ ክርስቶስ ሰው እንደሚሆን በቅኔ ዝማሬው የመሰከረው፥

“መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም *ሥጋን አዘጋጀህልኝ* የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት


አልሻህም።” መዝ 40፥ 6፤ “መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም *ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ*” ዕብ 10፥ 5፡፡

በዚህ ክፍል የሰውን ልጅ ወደ ፍጽምና የሚያበቃ፥ የኃጢአት ማስተሠረያ የሆነ፥ ብቃት ያለው የሚቃጠል መስዋዕት
በእግዚአብሔር ፊት ካለመገኘቱ የተነሳ፥ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ መወሰኑን ነው
የሚያስተምረን፡፡ “ሥጋን አዘጋጀህልኝ” የሚለውን አገላለጥ አንዳንድ ግለሰቦች ከድንግል ማርያም በስጋና በደም
አልተካፈለም ለማለት ሲጠቅሱት ይታያል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ክፍል “ሥጋ” የሚለው ቃል “የሰውን ሥጋ” የወከለ በመሆኑ
“ጌታችን ኢየሱስ የሰውን ዘር” እንጂ የሌላ ፍጥረትን የሥጋ ዘር አልያዘም፥ “ይህም ወንጌል *በሥጋ* ከዳዊት ዘር ስለ
ተወለደ (ስለ ኢየሰስ ክርስቶስ)” ሮሜ 1፥ 2-3፡፡ በተጨማሪም የዕብራውያኑ ጸሐፊ፥ የቅዱስ ዳዊትን የትንቢት ቃል
በተብራራ መልኩ አስፍሮልናል፡፡ ከዚህም የተነሳ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የሰውን ዘር በሥጋና ደም
ተካፍሎ በመያዙ “የሰው ልጅ” እያለ ራሱን ሊጠራ ችሏል፥

“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው *የሰው ልጅ* ነው” ዮሐ 3፥13

“ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ *የሰው ልጅም* በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።” ማር 14፥ 62፡፡
ይህም ብቻ አይደለም ከላይ ለማየት እንደሞከርነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን የሰው ልጅ እያለ የሚጠራው
በሁለንተናው “ፍጹም ሰው“ በመሆኑ ነው፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍት ጌታችን ኢየሱስ ሥጋ፣ ነፍስ፣ መንፈስ ያለው ፍጹም
ሰው መሆኑን ስፋት ባለው ምስክርነት ያስተምሩናል፥

ክርስቶስ ሥጋ አለው፥ “ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን *ሥጋ* ለመነው። ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ።
ዮሴፍም *ሥጋውን ይዞ* በንጹሕ በፍታ ከፈነው” ማቴ 27፥ 58-59፡፡

ክርስቶስ ነፍስ አለው፥ “*ነፍሴን* ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል፡፡ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ
ከእኔ ማንም አይወስዳትም።” ዮሐ 10፥ 17-18፡፡

ክርስቶስ መንፈስ አለው፥ “ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ *በመንፈሱ*
አዘነ በራሱም ታወከ፡፡” ዮሐ 11፥

ክርስቶስ አንዳንዶች እንደሚሉት “ሰው መሳይ ሌላ ዓይነት ሰው” አይደለም! ክርስቶስ በሥጋና በደም ባለመካፈል፥
የሰውን ዘር ያልያዘ ሰው መሳይ ትያትረኛ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ሥለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል፥ አምላካዊ ልዕልናና
ግርማ እንደተነጠቀበት እንኳ ሳይቆጥር፥ ሰው እስከመሆን ድረስ ራሱን ዝቅ ያደረገ፥ እውነተኛ የፍቅር ተምሳሌት ነው፡፡
በመጽሐፍም ቅዱስ ዮሐንስ “ቃልም ሥጋ መሰለ” ሳይሆን ያለው “ቃልም ሥጋ ሆነ” ነው (ዮሐ 1፥ 12)፡፡ ይህም
የሚያስተምረን እግዚአብሔር ወልድ ፍጹም ሰው መሆኑን ነው፥

እርሱ በእግዚአብሔር *መልክ* ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
ነገር ግን *የባሪያን መልክ* ይዞ *በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ* አደረገ፥ በምስሉም *እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን
አዋረደ*፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊል 2፥ 6-8፡፡

የሁላችን አባት እግዚአብሔር አንድ ልጁን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲልከውና ፍጹም ሰው ሲሆን፥
ከአምላካዊ ልዕልናው ከአባቱ ጋር ከነበረው እኩልነት እንደተነጠቀበት እንኳ አልቆጠረውም፡፡ በዚህ ክፍል ቁጥር 6 ላይ
“በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ” በሚለው ሀረግ ላይ ‹‹መልክ›› የሚለው የአማርኛ ቃል የኢንግሊዘኛውን “the
*form* of God” የሚለውና የግሪኩን “ሞረኽፍ μορφή, 3444 morphe” የሚለው ቃል የወከለ ነው፡፡ የሁልጊዜ
ትርጓሜውም “ባሕርይ፣ ተፈጥሮዊ ማንነት, shape; nature” የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ኢየሱስ በማንነቱ ወይንም
በባሕርይው እግዚአብሔር መሆኑን ያስተምረናል፥ “እርሱ በባሕርዩ (nature) አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዝአብሔር ጋር
መተካከልን ሊለቀው እንደሚገባ አድርጎ አልቆጠረውም፤” (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በዚሁ ክፍል
ዐውድ ላይ ክርስቶስ ሰው ሲሆን በባሕርይው ልክ እንደኛ ፍጹም ሰው መሆኑን ቁጥር 7 ላይ ያስተምረናል፥ “ነገር ግን
የባሪያን መልክ (the form of a servant, ሞረኽፍ μορφή, 3444 morphe ባሕርይ፣ ተፈጥሮዊ ማንነት) ይዞ በሰውም
ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ”፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍት ክርስቶስን አምላክ ነው የሚሉን በባሕርይው (በማንነቱ) አምላክ
በመሆኑ እንደሆነ ሁሉ ክርስቶስን ሰው ነው የሚሉን በባህርይው (በማንነቱ) ሰው ስለሆነ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከመንበረ
ጸባኦት ስላወረደውና ሊገለጥ ስለማይችለው ስለክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር እግዚአብሔር ይሄን ጥልቅ በእነዚህንና መሰል
ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ላይ በመመርኮዝ ነው “ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ፥
ፍጹም ሰው ነው” የምንለው፡፡ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው ቢሆንም ጌታችን፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በሰውነቱ”
የመለኮት ሙላት ተገልጦበት የሚኖር አንድ አካል መሆኑን መስክሯል፥
“በእርሱ *የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት* ተገልጦ ይኖራልና። (For in him dwelleth all the fulness of the
Godhead (θειότης– Deity, Divine) bodily.”

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ሆኖ መወለዱን በተመለከተ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እስካሰፈረልን እውነት
ድረስ መሄድ ተገቢና ርቱዕ ጎዳና ነው፡፡ ከድንግል ማርያም ሲወለድ ክርስቶስ በስጋና በደም መካፈሉን መጽሐፍ ቅዱሳችን
ያስተምረናል፥

“እንግዲህ ልጆቹ *በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ*፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም
ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ *በሥጋና
በደም እንዲሁ ተካፈለ*።” ዕብ 2፥ 14፡፡

በዚህ ክፍል “ልጆቹ” የሚላቸው፥ ወንድሞች ብሎ ሲጠራቸው ያላፈረባቸውን “የሰውን ዘር” ነው፡፡ እነዚህ ልጆች
የተባሉት ደግሞ ፍጹም ሰው መሆናቸውን የሚነግረን ቃሉ *በሥጋና በደም በመካፈላቸውን* በማሳየት ነው፡፡ ይህም ብቻ
አይደለም፥ እነዚህ ሰዎች “በሞት ፍርኃት” የተያዙ መሆናቸውን ይነግረናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጌታችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሞቼ ብሎ ሲጠራቸው ያላፈረባቸው ሰዎችን ወክሎ፥ ሞትን በሞት ይሽረው ዘንድ “በሥጋና
በደም ተካፈለ”፡፡ በዚሁ ክፍል ዐውድ ቁጥር 15 ላይ “በሥጋና በደም ተካፈለ” የሚለው ሐሳብ፥ የዕብራውያኑ ጸሐፊ
“የሰውን ዘር መያዝ” መሆኑን ያስረዳናል፥

የአብርሃምን *ዘር ይዞአል* እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። (For verily he took not on him the nature of
angels; but he took on him the seed of Abraham.) ዕብ 2፥ 15፡፡

ተዋዳጆች ሆይ፥ የዕብራውያኑ ጸሐፊ እንደጻፈልን ጌታችን ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሲወለድ፥ በሥጋና በደም
በመካፈል የአብርሃምን ዘር መያዙን ያስተምረናል፡፡ በዚህ ክፍል ልብ የምንለው የአንድን አካል፣ የአንድን እንስሳ፣ የአንድን
ፍጡር፣ እንዲሁም መላዕክትን ዘር መያዝ የሚቻለው “በየወገኑ ካለው አካል በመካፈል” ብቻና ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ለዛም
ነው ቃሉ “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላዕክትን አይደለም” የሚለን፡፡ ይህም ማለት ክርስቶስ ከድንግል
ማርያም በስጋና በደም ሳይካፈል *የሰውን ዘር በመያዝ ሰው ሊባል* አይችልም፡፡ ጌታችን ግን በርግጥም ከቅድስት ድንግል
ማርያም ሥጋና ደምን በመካፈል (በመንሳት) ፍጹም ሰው በመሆኑ በእግዚአብሔር ፊት እኛን ሊወክለን ችሏል፥

“ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መስዋዕትን ሊያቀርብ *ከሰው ተመርጦ* ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ *ስለ
ሰው ይሾማልና*” ዕብ 5፥ 1፡፡

“በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ *እኛ ቀዳሚ* ሆኖ ገባ።” ዕብ 6፥ 20፡፡

በእነዚህ ሁለት ክፍሎች ሊቀ ካህናት ሰዎችን በእግዚአብሔር ፊት ወክለው፥ የመካከለኛነት አገልግሎትን የሚፈጽሙት
“ከሰው መካከል በመመረጥና በመሾም” መሆኑን ያስረዱናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
በሥጋና በደም ያልተካፈለና የሰውንም ዘር ያልያዘ ቢሆን ኖሮ፥ እኛን በእግዚአብሔር ፊት ወክሎ “ሊቀ ካህናችን” ሆኖ
ማገልገል ባልቻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ ሰማያዊቷ ድንኳን ስለ እኛ ቀዳሚ” ሆኖ መግባቱን ቃሉ
ይመሰክርልናል፡፡ ከያዘውም የሰው ዘርና ከለበሰውም ሥጋ የተነሳ፥ እንደእኛው የሚደክም፣ የሚራብ፣ የሚጠማ፣
የሚተኛ፣ የሚነሳ፣ የሚያለቅስ፣ የሚያዝን፣ የሚደሰት… በመሆኑ ድካማችንን ሁሉ ስለሚያውቅ ሊራራልን ችሏል፥
“ከኃጢአት በቀር *በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ* ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
ዕብ 4፥ 15፡፡ (“ሥጋን ለበሰ” የሚለው አገላለጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፥ ሐዋ 2፥ 17፤ ማቴ 24፥ 22፤ ሉቃ 3፥ 3-6፤ ሮሜ
3፥ 20፤ 1 ቆሮ 1፥ 29፤ ገላ 2፥ 16)፡፡

ተወዳጆች ሆይ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከድንግል ማርያም በሥጋና በደም ሳይከፈል ቢቀርና የሰውን ዘር ባይዝ ኖሮ፥
ድካማችን ሊያውቅና ሊራራልን እንደማይችል ተረዳችሁን? ደግሞስ ሰው ያልሆነና ሥጋችን ያልተካፈለ በእግዚአብሔር
ፊት ሊወክለን ከቶ እንደማይችል አወቃችሁን? አንዳንድ ግለሰቦች ከድንግል ማርያም በሥጋና በደም መካፈሉን ማመን
“ድንግል ማርያምን እንደማምለክ” ስለሚቆጥሩት ያለምንም መደላድል፥ ይህን መሰረተ እምነት ሲክዱ እንመለከታለን፡፡
እንደ እውነቱ ግን ድንግል ማርያም “እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤” ስትል የተናገረችው፥
የሰማይና የምድር ሁሉ ፈጣሪ፥ ፍጥረታትን ደጋፊና አሳላፊ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ፥ ሰው ሆኖ ይወለድ ዘንድ
እርሷን በመምረጡ ምክንያት፥ መሆኑን መስክራለች፥ “ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ
ነው።” (ሉቃ 1፥ 48-49)፡፡ ከዚህ በመነሳት ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ፥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ፥ ከኃጢአት ባርነት እኛን ለማዳን፤ ከሞትና ከሲኦል ፍርሃት ሊያወጣን፤ የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ፤
ሰው ሆኖ እኛን ለመወከል ከድንግል ማርያም በስጋና በደም ተካፈለ፡፡ ይህችንም ድንግል ባሰብን ጊዜ “ድንግል ሆይ ብጽሂት
ነሽ” ባንላትም፤ “ጌታን የወለደችው ድንግል ብጽሂት ናት” እንላለን፡፡ ይህም ደግሞ፤ ለድንግል ማርያም የሚሰዋ
አምልኮም፣ ስግደትም፣ እልታታም … አይደለም፤ ይልቁንም እርሷ በቃሉ እንደመሰከረችው፥ በእርሷ ታላቅ ነገርን
ያደረገውን ጌታ እናከብራለን እንጂ!

በሌላ ጽንፍ፤ አንዳንድ ግለሰቦች “ከድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋና በደም ከተካፈለ አዳማዊ የውርስ
ኃጢአት አለበት ማለት ነው?” ሲል ስጋታቸውን ይናገራሉ፡፡ ከሉቃስ ወንጌል የምንማረው ትምህርት ግን፥ ከዚህ ሥጋት
የወጣ ሆኖ ነው የምናገኘው፥

“መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ *መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል* ስለዚህ ደግሞ
ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” ሉቃ 1፡-35፡፡

ይህ ክፍል “ቃል ስጋ በሚሆንበት” ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሥራ እንደነበረው የሚናገር ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ምንድን
ነው ብንል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን የሚለውን “ይጸልልሻል” ቃል ይጠቁመናል፡፡ ይህ ቃል የግሪኩን “ኢፒሽኬዞ
ἐπισκιάζω 1982 – episkiazó” የወከለ ሲሆን፤ የሁል ጊዜ ትርጓሜውም “መሸፈን፣ መከለል፣ መጠቅለል –
overshadow, envelop” ማለት ነው (ይህ ቃል ጥቅም ላይ ከዋለባቸው ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ያነጻጽሩ
ማቴ 17፥ 5፤ ሐዋ 5፥ 15)፡፡ ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ስጋና ደምን በመክፈል፣ በአባቶች በኩል
ከሚመጣው አዳማዊ የውርስ ኃጢአት የመከለልና ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስ ይወለድ ዘንድ ሥራን መስራቱን እንረዳለን፡፡
አንዳንድ ወገኖቻችን በዚህ “ይጸልልሻል” በሚለው ቃል ግር የሚሰኙ ካሉ፡- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ላይ፤ “መጸለል” የሚለውን ቃል በአድራጊ ግስ ሲተረጎም “ማጥለል፣ ማጥራት፣ ጥሩ
ማድረግ” ማለት እንደሆነ በገጽ 654 ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡ ለዛም ነው የልዑል ሐይል“ይጸልልሻል” ካላት በኃላ “ስለዚህ
ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” በማለት ክርስቶስ ፍጹም ሰው ሆኖ ሲሆን፥ በውርስ
ከሚተላለፈው አዳማዊ ኃጢአት ንጹህ ሆኖ ስለሚወለድ “ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ” ተብሎ ይጠራል ያላት፡፡
ተወዳጆች ሆይ፥ የሁላችን መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ በስጋና በደም መካፈሉንና በዚህች ምድር መገለጡን
አለመቀበልና አለማመን፥ ከዲያብሎስ የሚመነጭ ትውልድ ገዳይ፥ መርዘኛ ኑፋቄ መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ
እንዲህ አስፍሮልናል፥

“የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ *ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን* መንፈስ ሁሉ
ከእግዚአብሔር ነው፥ *ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን* መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤
*ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው*፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።” 1 ዮሐ 4፥
2-3፡፡

እንግዲግ ምን እንላለን? ቃል ሥጋ የሆነው ከድንግል በመወለድ እንጂ፥ አንዳንዶች እንደሚሉት ሰማያዊ ሥጋ ይዞ፥
ከድንግል ማህጸን በማደር አይደለም፡፡ ቃሉ የሚለን “ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” እንጂ “ቃልም ሠማያዊ ሥጋ ይዞ ነበረ”
አይለንም፡፡ እግዚአብሔር የነበረው ቃል ነው ከድንልግ በመወለድ ሥጋ የሆነው ነው፡፡ ለዛም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ (ሰው ሆኖ) እንደመጣ አለማመን ከዲያብሎስ ነው በማለት አጽንኆት ሰጥቶ የጻፈልን፡፡ ይህ የክርስትናችን
መሰረተ-እምነት ከመሆኑ ባሻገር ከዲያብሎስ የሆኑ አስተምህሮችን የምንለይበት የእምነታችን መመዘኛ ነው፡፡ ጌታችንም
“እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ” ሲል አንዳአችስ እንኳ አልዋሸም፥ በርግጥም እርሱ የዳዊት ሥርና ዘር ነው፥ ስሙ ብሩክ
ይሁን። አሜን።

ተባርካቿል

You might also like