You are on page 1of 2

ጥር 4, 2014 ዓ.


አዳማ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።


በአሁኑ ሰዓት ያለው በግቢ ጉባዔያት ያለው የቋንቋ አገልግሎት ላይ የሚነሳው ችግር ለመፍታት በሚደረግ ጥረት
ታሳቢ ይደረጉ ዘንድ ይገባቸዋል ብየ የማስባቸው ነጥቦች።

1. ሰው የበላውን ነው የሚል አባባል በሩቅ ምሥራቅ ሰውች ዘንድ የሚነገር አባባል አለ።በቅደስት ቤተ
ክርስቲያን ትርጓሜም ተጠቅሷል ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋሰው የሰው ልጅ በሕጻንነት ያልነበረው
የሐጢያት ፍትወት እያደገ ለመምጣቱ አንዱ ምክንያት የሚመገበው ምግብ ለውጥ እንደሆነ በዚህ
ምክንያት ጾም ማለት ከምግብ ብቻ መከልከል ሳይሆን ምግብም አለመለዋወጥም መሆን እንዳለበት
አባቶች የሚናገሩት ። ስለዚህ ሰው የበላውን ነው የሚለውን እንያዝና ጥያቄ እናንሳ ብርቱካን የበላ ሎሚ
ሎሚ ያገሳልን? አንዳንድ ጊዜ ሰው እንዴት እንደዚህ ያስባል ብለን እንገረማለ? ክርስቲን ሆኖ እንዴት
እንደዚህ የወረደ ሀሳብ ያነሳል? ያው መልሱ የሚሆነው የበላውን ነው? ማለትም የተነገረውን
የተተረከለትን ነው የሚያውንጸባርቀው። ሰለዚህ አንድ ሰው የሚበላውን ማስተው ካልቻልን አሊያም
ከዚያ የተሻለ በመጠንም በአይነትም ምግብ አቅርበን ማዕዛውን መቀየር ካልቻልን ለምን ብርቱካን
ብርቱካን አላገሳህም ልንለው አንችልም። ምንም እንኳ ሰው ቀምሶ መትፋት ይችላል የሚል አምክንዮ
እንዳለ ብናውቅም ነገ ርግን መትፋት ያልቻሉ ሰወች ዙሪያ እየተነጋገርን ስለሆነ ማለቴ ነው። ማሳያወች
እናንሳ
 “ጃኖ የአማራ ነው” የሚለውን ሀሳብ ይዘን በኦሮሞና በገዥው መደብ የነበረውን ጦርነት
ስንመለከት ተቀናቃኝ ሀይሎች ከሆኑ እኔ በምን ምክንያት ነው ጃኖ ምለብሰው አይ የአማራ
አይደልም ወይም ኦሮሞም እንደዚህ የይነት ልብስ(ጃኖ) አለው የሚለው ሀሳብ ማዓዛውን
የማያጠፋ ሌላ ምግብ ስለሚሆን ጥያቄ ማንሳትቱ የሚጠበቅ ነው?
 ሰንደቅ ዓላማ የሌለበት ጉባዔ ባለማየቴ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዘመኔ ለዩ ቀኔ ዛሬ ነው
 ለምን ድራማ ሲሰራ በኛ በዓል አይሰራም የሚሉት ጥያቄወች ከቋንቋ አገልግሎት ጋር ተደብለው
መታየታቸው ውጤት አያመጣም ባይ ነኝ?
2. መዋቅርህን ጠብቀህ ማገልገል አለበህ የሚለው ሀሳብ ኣንዴት ማሰረዳት መቻል አለብን የሚለው ደግሞ
ሁለተኛው ነጥብ ነው ? እንደ ሀሳብ ከመዋቅርን በፊት ትያቄዎች ቢመለሱ መልካም ይሆናል ባይ ነኝ?
ብርሃናችሁ በዓለም ይብራ የሚለው ሲተረጎም ።በዓለም ላይ ሁሉ የራሱ የሆነ ብርሃን አለው የእናንተ
ብርሃን ከሆሉ በላይ አብርቶ እንደ ፀሐይ ሁኖ የራሱን ትንሽ እንደ ጧፍ ጭል ጭል የምትል ብርሃን
በመመልከት ምን ያደርግልኛል ብሎ ብሎ እንዲጥላት ነው።የያዝከው አይጠቅምህም ከማለት ይልቅ
የራስን ብርሃን አጉልቶ ማሳየት የተሻለ ነው። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው የቤተ ክህነት ታሪክ ነው
የኢ/ቤ/ክህነት 50 ዓመት ታሪክ አለው ቤተ ክርስቲናችን ግን ሺህ ዓመታት ስለዚህ ከመዋቅር በላይ ናት
ማለት ነው ። ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያን ያለ ምድራዊ መዋቅር የነበረችበት ዘመን አለ ማለቴ አይደለም
አሁን የምናውቀውን መዋቅር ማለቴ ነው። ስለዚህ ቢቻለን መዋቅሩን ከሀይማኖቱ ኣንዲያስተባብር ጥረት
ማድረግ አሊያ ሀይማኖቱን እንዳይጥል መሰራት ያስፈልጋል ለምሳሌ በ 5 ኛ ው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ
ኢትዮጵያ የመጡ ቅዱሳን ከነበረው የቢዛንታይን መዋቅር ወደ እኛ መዋቅር ሲመጡ ለመንፈሳዊ ህይወት
የተሻለን መምረጣቸው እንደሆነ ስለተገነዘቡ ነው።
እነዚህ ልጆች የመናፍቃን እራት ይሆናሉ ከዚህ መዋቅር ከተለዩ የሚል ሀሳብ ይነሳል ትክክልም
ነው ስለዚህ እንዴት እናስረዳ። አንድ ታሪክ ላንሳ አንድ ተነሳሂ(ንስሃ የሚገባ ሰው)ንስሃ አባቱ ፊት
ቀርቦ ኃጢያትህን ተናገር ሲባል በጣም ፈራሁ ይላል? እውነት ነው መናዘዝ በጣም
ያስፈራል(መፍራት ከሌለው ምኑን ተጋድሎ ሆነ፣ እርሃብ ከሌለ ጾም ምንድን ነው እንዴሉ)
እርሳቸውም መልሰው በፊትህ እሳት አለ ቁምበት ብልህ ትቆምበታለህ ይሉታል አይ እፈራለሁ
ያቃጥላል ይላቸዋል የቆምክበትን መሬትስ ትፈራዋለህ አሉት እርሱን እንኳ አልፈራውም
ይላቸዋል ።እሳታዊ ከሆነ መለኮት መሬታዊ የሆንኩ እኔ እሻልሃለሁ እና አትፍራ እውነት ነው ህጻን
ሳለን የምንፈራውን መሬት አሁን አንፈራውም ነገርግን ምንም ብንፈራው ከእሳት ይሻለናል።
ምንም እንኳ ይህ መዋቅር ጥንቅቅ ያለ ጥቅም ሰጥቶሃል ባንልም ከልኦች መዋቅር ግን ይሻልሀል
የሚል አረዳድ መፍጠር ይገባል። ያኛ ሙሉነት ለማሳየት ብዙ ርቀት መጓዝ ጥቅሙ ያን ያሃል
ነው። ስለዚህ እስከ ጉድለታችን እንደምንሻል ማሳየት ማቻል አለብን። አጼ ኃይለ ሥላሴ
የተናገሩት የሚባለው አባባል ገላጭ ይመስለኛል። ታስረው በነበረበት ጊዜ አቡነ ተ/ሃይማኖት
እንዴት ነወት ብለው ሲጠይቋቸው “ካለፈው ብሶብኛል ከሚመጣው ይሻለኛል ” ይህ አነጋገር
ምንም እንኳ ክፍተት ቢኖር ከሌላ መዋቅር ይሻላል የሚለውን ማሳመን ይሻላል።
ጥር 4, 2014 ዓ.ም
አዳማ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን።

በመሆኑም እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት የበሉትንም ለማጥፋትም ሆነ የያዙትን መብራት ለማስጣል የሚችል ስራ
ይጠበቅብናል ባይ ነኝ ምንድን ነው እርሱ ከተባለ ልዩ ልዩ ፍላጎት የሚያካትትው ሃሳብ እንዳለ ሁኖ ትምህርተ
ክርስትና መግቢያ ተብሎ የሚሰጠው ኮርስ ስለ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ህይወት ግሎባላይዜሽን የመሳሰሉትን
ከታሪክና ቋንቋ አንጻር ለሁሉም የግቢ ጉባኤ አባልት ትምህርቱ ቢሰጥ መልካም ነው።
ልዩ ልዩ ፍላጎት የሚለውም አማረኛ ተናጋሪው ኦሮመኛ ቋንቋን እንዲማር ማገዝን ኦሮመኛ ተናጋሪውም አማርኛ
እንዲማር ማስቻል ድረስ የሚያድግ መሆኑንን መገንዘብ ተገቢ ነው?

መቁረጥ ሆነ መቀጠል ስናስብ እነዚህን ታሳቢ ብናደርግ ተገቢ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

You might also like