You are on page 1of 2

ደቂቀ ነቢያት

መልዕክታቸውና የአገልግሎት ዘመናቸው


ምዕራፍ ስምንት መጽሐፍ ሶፎንያስ
ምዕራፍ አሥራ መጽሐፍ ኢዩኤል
በእዮቤል በላይነህ

ለደርሱ ጌታቸው
አዲስ አበባ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ( ABC ) 2013
ምዕራፍ ስምንት ሶፎንያስ
መግቢያ
ሶፎንያስ ከንጉስ ሕዝቅያስ ቤተስብ የተወለደ ነብይ ነው። ( 716-686 ዓ.ዓ) ሶፎንያስ ትንቢት የተናገረው ዘመዱ በሆነ
ንጉሥ ዘመን ነበር ማለት ነው።ሶፎንያስ አገሩ የት እንደሆነ አይናገርም። ከንጉሥ ቤተሰብ ስለሆነ ደግሞም ኢየሩሳሌምን
በሚገባ ስለሚያውቃት ምናልባት የየሩሳሌም ነዋሪ ሳይሆን አልቀረም።
የስሙም ትርጓሜ " እግዚአብሔር ከልሏል " ማለት ነው።
ወቅቱ
የሶፎንያስ መጽሐፍ የሚጀምረው ሶፎንያስ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ይናገር በመግለጥ ሲሆን ኢዮስያስ በይሁዳ ላይ
የነገሠው ከ 640 - 609 ዓ.ዓ ነው። ሶፎንያስ ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሰባቸው በነዚያ 31 ዓመታት መካከል ትንቢት እንደተናገረ
ይታስባል።
መቸት ( ሁኔታው)
ሶፎንያስ ከይሁዳ ነገስታት መካከል ከሆነው ከህዝቀያስ ቤተስብ የተወለደ ሲሆን ያገለገለበትም ዘመን ከነዚሁ ጥቂቶች
ከሚባሉ የይሁዳ ነገሥታት መካከል በሆነው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ነው።
ሶፎንያስ ትንቢት በሚነገርበት ጊዜ ሕዝቡ እውነተኛ አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር ደግሞም የውሸት አማልክት
በሚያምልክበት ወቅት ነበር ማለት ይቻላል። ይህ ወቅት አሶር እየተዳከመ ነበርና ይሁዳ በአሶር ምክንያት ያጣችውን ነፃነቶች
እንደገና ያገኝበት ወቅት ነበር።
ጥቅልል ሀሳብ
የሶፎንያስ ስለ እግዚአብሔር ቀን የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን ስለዚህ የተሰፍውንና የፍርድ ስዕል በግልፅ አድርጎ ያሳያል። በዚህ
ክፍል በመላው ዓለም ላይ ስላለው የእግዚአብሔር ሀይልና ሥልጣን ጠንከር ያለ አትኩሮት ስጥቷል። የፍርዱ ምክንያቶች
በሌሎች 1, ስለማህበራዊ ፍትህ መጓደል
2, ስለ ሥርዓት ተኮር ሃይማኖተኛነት
3, ስለጣዖት አምልኮ ናቸው።
የሶፎንያስን መጽሐፍ በምናንበት ጊዜ ሁሉ የእግዘያአብሔርን ተግ
ትክክለኛ መንፈሳዊ ለውጥ የሚመጣ ስህታችውን ከሚቀበሉ ተግሳጽን የሚቀበሉ ነው። በሰፎንያስ ዘመን ለነበሩት ካህናት
እንደሆነ ሁሉ ለአሁን ዘመን አገልጋዮችና መጋቢያን የሚሰራ ጉዳይ ነው።
መልዕክቱ
መጽሐፍ ሶፎንያስ ነብይ ብሎ ባይጠራም የጌታ ቃል ወደ እርሱ መጣ በማለት ትክክለኛ ነብይ እንደነበር ይጠቁመናል።
ሶፎንያስ መልዕክቱን የሚጀምረው በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ በማወጅ ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያጠፋል
በማለት ነው።
እግዚአብሔር ነብያትን የተጠቀመባቸው ሕዝቡን ወደ ንስሐ እንዲጠሩለትና ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ዕቅዱን
እንዲያበስሩለት ነው። የሶፎንያስ ትንቢትም ዓላማ ይሁዳ መቼ በማን እንዴት እንደሚጠፋ ማሳየት አይደለም። ይልቁንም
የእርሱ ዋናው ነጥብ ጥፋት በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ቁጥጥር ስር እንደሆነ በእርሱ ዓላማና ፈቃድ ሊሆን እንደሚችል ማሳየት
ነው።
ፍርድ በአሕዛብ ሀገሮች ላይ
እግዚአብሔር የምድር ሁሉ አምላክ በመሆኑ ፍርድም ምድርን ሁሉ የተመለከተ ነው። የጌታ ቀን በእስራኤል ላይ በሚሆን
ፍርድ ሊጀመር ይችላል እንጂ በዚያ አይቆምምወደ ዓለም ሀለ የሚተላለፉ ነገር ነው። ከቅጣቱ ማምለጫው መንገድ ወደ
እግዚአብሔር ንሰሀ በመመለስ ነው።
ፍርድ በእየሩሳሌም ላይ ( 3:1-8)
ሌላው ሶፎንያስ " ስለምፃተኛው ከተማ " መናገር ይጀምራል ይህች ከተማ የእግዚአብሔር ሕግና ትዕዛዝ አልቀበልም ብላ
ነበርና በመጨረሻው የእግዚአብሔር ፍርድ ላይ ከፍት ሁሉ ላይ ይመጣል። ምክንያቱም እየሩሳሌም ክፍ ስለነበረችና በዚሁ
የፍርድ መርሃ ግብር ውስጥ ትከታታለች።
የደነዘዘ መንፈስ
የቆመ ሁልጊዜ የማይንቀሳቀስ ነገር አደገኛ ነው። መንፈሳዊ ድነዛዜ ስንፍና ከመሆን ያለፈ ሲሆን መንፈሳዊ ድንንዛዜ በነገሰበት
ልብ ውስጥ እግዚአብሔር ምንም ማድረግ የሚል አስተሳስብ አለ። መንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ ያሉ ሰዎች የእግዚአብሔር
ፈቃድ እና ሃይል በሕይወታቸው እንደሚገለጥ አያስቡም። ይህን መንፈሳዊ ድንዛዜ ለማስወገድ መፍትሔው ዘውትር በመንፈስ
በእግዚአብሔር ፊት መጸለይ ብቻ ነው።
የእግዚአብሔር ፍርድ በባዕድ መንግሥታት ላይ
እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ ከምድር ገጽ ያጠፋል የሚለው የሶፎንያስ መግቢያ ንግግር አስደንጋጭ ንግግር ነው።
በመጨረሻ የሚሰራው ነገር ሁልጊዜ ትክክል እሳቤ ላይ ነው የምናረፈው። ከዚህ የተነሳ መረዳታችን ሊደብረልን የሚችሉ
ነገሮች
1, እግዚአብሔር የምድር አምላክ እንደሆነ ማስታወስ ወይም ማሰብ ነው። በሁሉም ሀገሮች የሚሆኑ እርሱ ያውቃል።
2, በልባችን ውስጥ ሊቀመጥ የሚገባው እጅግ በጣም ጠቃሚ የሀነው ነገር ደግሞ የእግዚአብሔር አጠቃላይ እቅድ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ደግሞ የሚነግረን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሁሉ ወደራሱ የመመለስ ዓላማ እንዳለው ነው።
ምዕራፍ አሥራ ኢዮኤል
መግቢያ
ነብዩ :- መሀፀፍ ቅዱስ ሰለአዩኤል የሚነገረው ጥቂት ነገር ሆኖ ያባቱሜል ልጅ እንደሆነ ከሚነገረው ባሻገር የየት ሀገር
ተወላጅ እንደነበረም ምንም አይገልጽንም። የስሙ ትርጓሜ እግዚአብሔር አምላክ ነው የሚል ነው። የኢዮኤል ትንቢት ትኩረት
የሚያድርገው በኢየሩሳሌም ዙሪያ መሆኑ ስለመቅደሱ በቂ ዕውቀት እንደነበረው አመልካች ነው።
ወቅቱ
ኢዩኤል ትንቢት የተናገሩበትን ወቅት ለመናገር የሚያስችለን ዘመኑን ወይንም ደግሞ ባገለገለበት ወቅት የነበረውን ንጉሥ
ወይም ገዚ ስም አይነግረንም
ኢዮኤል የነበረበት ዘመን የሚያስችል ከሚሰጡን ፍንጭ ይሰጠናል።
1, አንዱ ፍንጭ ውሳኔ መስጠት የሚችል ኢየሩሳሌም ያልነበረበና ሽማግሌ የአመራሩን ውሳኔ የሚሰጡትን ሥራ ይሰሩ
ነበር።
2, ኢዮኤል ስለመቅዱስ ደግሞ ስለሚናገረው ወቅቱ መቅደሱና የመቅደሱ የነበረበት ወቅት እንደነበር ያመልክታል።
3, ስለበእዳን መንግሥታት የተናገረው ትንቢት ነው።
ሁኔታው
ኢዩኤል መልዕክቱን የተቀበለው ታላቅ የአንበጣ መንጋ የይሁዳን ምድርን ካጠፉ በሗላ ነበር። ኢዮኤል ይህን ክስተት
የእግዚአብሔር ቀን ምን ያህል ታላቅ እና አስፈሪ ሊሆን እንደሚችል እንደገላጭ ምሳሌ አድርጐ ይጠቅመታል። ስለዚህ ኢዮኤል
ሕዝቡን ንስሐ እንዲገቡ እና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዲቀደሱ ያሳስብቸዋል።
ኢዮኤል ስናንብ ማስተዋል ያለብን ነገር በአሁን ጊዜ የተከስተን አስደንጋጭ ሁኔታ በመውሰድ ወደፊት ሊመጣ ያለን
ክስተት ለመጠቆም ይጠቀምበታል።
መልዕክቱ
የአንበጣ ወረርሽኝና የእግዚአብሔር ቀን ( 1:1 -2:17)
ኢዮኤል እንዲተንብይ የተጠራው ታላቅ የሆነ የአንበጣ ወረርሽኝ ምድሪቱን ከመታ በሗላ ነው። እዮኤል ይህንን ክስተት
ሕዝቡን ከዚህ የከፋ አደጋ ሊመጣ እንደሚችል ለማስጠንቀቂያ ይጠቀምበታል።
የኢዮኤል ትንቢቱን የሚጀምረው አድምጡ በማለት ነው በዕብራይስጥ ይህ ቃል የመስማት እና የማስተዋል ወይም
የማገናዘብ ትርጉም ነው ያለው።
የእግዚአብሔር ቀንና የዝግጅት ጥሪ ( 2:1-17)
በአበንጦች መቅሰፍት ምክንያት የደረሰው ጉዳትና ጥፋት አንድ የሚስተላለልፍው መልዕክት በኖር ወደፊት ሊመጣ ስላለ
ቀን ማመልከትና የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማስተላለፍ ብቻ ነው። ኢዬኤል ሊመጣ ያለው የጌታ ቀን አሁን ከገጠማቸው ችግር
በእጅግ የከፋ ነው የሚሆነው ይላቸዋል።
ከወቅቱ ስቃይ እፎታይን ስለማግኘት ( 2:18-27)
ለኢዮኤል የንስሃ ጥሪ በእግርጥ ተገቢ ምላሽ ተግኝቷል። እግዚአብሔር የድርቁንና በአንበጦች ምክንያት ያደረሰውን ገዳት
እንደሚያስቀር ተስፋ ይሰጣል። ምድሪቱ የእግዚአብሔር እንደሆነች እርሱም ለምድሪቱ መልካም እንደሆነ ይናገራል። (2:18)
ስለ ኢዬኤል ለመበስክ
የግል ምልክታ አንዱ ስለ አማራር ጥበብ ከኢዪኤል የምንወስደው ትምህርተ ዋና በሆኑ ክስተቶች ላይ አትኩሮትን
ማድረግ ነው። ኢዩኤል ያጋጠመውን ክፉ ነገር ለማሰብ የሚከብድ ነው።
ማህበረሰብን ወደ ንስሐ ማምጣት
ክርስቶስን አንድ ግል አዳኝ አድርጎ የመቀበሉና የማመኑ ውሳኔ የግል ነው። ያንን ማንም ለእኛ አያደርግልህም ደግሞም
እንዳናደግርግ ሊያስቆመንም አይችልም።
ኤክስከርሰስ ( ከዋና ርዕሰ ጉዳይ ወጣ ባለ መልኩ)
ኢዩኤልና የበዓለ ሀምሳው ቀን
ኢዩኤልንና የብሉይ ኪዳንን ትንቢት በትክክል መረዳት የበዓለ ሀምሳ ቀን ከግለሰቦች በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በዘለለ
መልኩ ታላቅ ፋይዳ ያለው ከስስት እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል ። የመንፈስ ቅዱስ መምጣትና የኢየኤል ትንቢት ፍፀሜን
ማግኘት መጀመሩ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሰዮናዊነት ተልዕኮ የጌታን ስም ሊድነት ወደሚጠሩ ሁሉ መተላለፉን ይመላክታል።

You might also like