You are on page 1of 8

የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

9
www.tlcfan.org 0
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

የእግዚአብሔር ቅባት ሕግ

ይህ ካለፈው ቁ.8 እትም የቀጠለ ነው። የኢየሱስን መቀባት ከማየታችን በፊት ስለ ቅባት

ልንገነዘባቸው የሚገቡ ሃሳቦች አሉ። አንዱ የእግዚአብሔር ቅባት ዘይት አስራር ነው። በዘጸ.30፥23-25

ላይ የቅባቱ አሰራር በዝርዝር ተጽፏል። በማደሪያው ድንኳን ውስጥ ያሉ እቃዎች በሙሉ ለእግዚአብሔር

የተለዮ ይሁኑ ዘንድ በዚህ በልዩ መልኩ በተዘጋጀው ዘይቱ ይቀቡ ነበር። (ቁ. 26-28). አላማውን ሲናገር

በዘጸ.30፥30 እንዲህ ይለናል፦ “በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ቀድሳቸውም።

አንተም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሁንልኝ”

ስለዚህ ቅባት ሁል ጊዜ ከመቀደስ፣ ከመለየትና ከአገልግሎት ጋር እንደተያያዘ እንደሆነ ከቃሉ

እንመለከታለን። ክርስቶስ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ መሲሁ ሲሆን የቀባ ማለት ነው። ኢየሱስ ለምን

የተቀባ ተባለ? እንዴትስ ተቀባ? ኢየሱስ በቅብዓ ዘይቱ ሲቀባ የሚናገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስም በቃሉ

ውስጥ አናገኝም። ታዲያ ተቀባ የሚለው ለምንድን ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ዮሐንስ በውሃ

አጥምቆታል ቅብዓ ዘይት በላዮ ላይ አላፈሰሰበትም። መልሱን ለማግኘት ቃሉን መመርመር ይገባናል።

በብሉይ ኪዳን ጥምቀት ነበር። ኢየሱስ ወደ ምድር ሳይመጣ ጥምቀት በመርጨት ወይም

ሙሉ በሙሉ በማስጠም ይፈጸም ነበር። በዕብ. 9፥10 ላይ "ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም " ይናገራል። ግሪኩ

ቃል ( ጥምቀት ብሎ ያስቀምጠዋል። ጻፎችና ፈሪሳዊያን ደቀመዛሙርትን ስለዚህ ጥምቀት

ወይም መታጠብ በኢየሱስ ፊት ከሰዋቸውም ነበር። “ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ

ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥ ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፥

ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ።”

(ማር.7፥3, 4). የተቀበሉት ከብላት በፊት እጅ መታጠብ የሚጠቀሙትን እቃ ከመጠቀማቸው በፊት

በውሃ ማስነካት ወይም ማጠብ. . .ወዘተ ነበረባቸው።

ይህ ለእነርሱ የቅባት ውሃ ነበር። “ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥

በውኃም አጠባቸው።”(ዘሌ.8፥6), ከለምጽ የነጹትም በውሃ ይረጩና ይታጠቡም ነበር። “የነጻውም ሰው

ልብሱን ያጥባል፥ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ

ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።” (ዘሌ. 14፥8). በዚሁ በመጠመቅ

ሕግ በነብዮ ትዕዛዝ ንዕማን ከለምጹ ነጽቷል “ኤልሳዕም፦ ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ ሥጋህም

ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።” (2 ነገ. 5፥10)

www.tlcfan.org 1
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

ሌላ ደግሞ በቃሉ ውስጥ የቅባት ደም ወይም የመርጨት ደም ደግሞ አለ።

በዘሌ.8፥30 “ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና

በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም የልጆቹንም ልብስ

ቀደሰ።” በዘጸ.29፥1,20 “እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግባቸው ነገር

ይህ ነው፤. . . አውራውንም በግ ታርደዋለህ፥ ደሙንም ትወስዳለህ፥ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥

የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ

ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ትረጨዋለህ።” በአሮንና ልጆቹ ላይ ይህ ደም መረጨቱና መቀባቱ

የእግዚአብሔርን መስዋዕት ለማቅረብ፣ እርሱን ለመስማትና ለመታዘዝ የስልጣን ብቃት ነበር። ይህ

የደም መቀባት ወይም መርጨር ከያሕዌ ጋርም የቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ በሕዝቡ ላይም ይረጭ ነበር።

“ሙሴም ደሙን ውስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፦ በዚህ ቃል ሁሉ እግዚአብሔር

ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ አለ።” ዘጸ. 24፥8

ሥስተኛውና የትምህርታን ክፍል የሆነው ቅባት የዘይት መቀባት ነው። ይህ ቅባት አሰራሩም

ሆነ ጥቅም ላይ የሚውለው በአሮንና በልጆቹ ሥራ ላይ ብቻ ነው። ዘይቱ ራሱን የቻለ ለካህናት ብቻ

የተሰጠ አስራር አቀማመም አለው። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዳዊት በሳሙኤል ሲቀባ ኤልሳ በኤልያስ

ሌሎች ነገስታቶች ሲቀቡ በዚህ ካህናቶቹ በሚያዘጋጁት ቅባት ነው ማለት ፈጽሞ አይቻልም። ሁሉም

የተቀቡት ግን በወይራ ዘይት ነው።

ይህ በአሮንና በልብሱ ላይ የሚፈሰው ዘይት ከዳስ በዓል ጋር ፣ የማይሞተውን አካል

ከመልበስ ጋር፣ ከመጨረሻው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጋር የሚያያዝ ነው። ይህም በአዲሱ አቁማዳ

አዲሱን ዘይት/ ወይን እንደ መሙላት ማለት ነው።

ሌላ ልንዘለው የማይገባ ቅባት ወይም ጥምቀት አለ። ይህም የእሳት ጥምቀት ነው። ይህንን

ጥምቀት መጥምቁ ዮሐንስ አስተምሮናል። ማቴ. 3፥11, "እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤

ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ

ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤" በሐዋ. 2፥3, "እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች" ከሚለው ቀን አንስቶ

የጀመረ ነው። ነገር ግን መያዢያው እንጂ ሙላቱ እንዳልነበረ ሐዋርያቶች አስተምረውን አልፈዋል።

“ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።” 1.ቆሮ.2፥22፣ ኤፌ 1:፥14

www.tlcfan.org 2
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

የእሳት ጥምቀት ወይም ቅባት በበዓለ አምሣ የተገለጠ ነው። ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ

የብሉ ኪዳን ጥላ በዘጸ.20፥21 ላይ አለው። ይህም እግዚአብሔር ሕጉን ለመስጠት በእሳት የወረደበት

ቀን ነው። ወደ እሳቱ ውስጥ ገብተው ለመጠመቅ ሁሉ እድል ተሰጥቷቸው ነበር። ነገር ግን ስለ ፈሩ ይህ

ወደ ሐዋርያት ዘመን ተሸጋግሯል። በሐዋርያት ዘመን ደግሞ ይህ እሳት ሲመጣ ሙሉውን በአንዴ ሁሉ

አማኝ አልተቀበለም። የእሳት ቅባት ወይም ጥምቀት የሚገናኘው እሳት ከሆነው ከእግዚአብሔር ሕግ

ጋር ነው። “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ በሴይርም ተገለጠ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ ከአእላፋትም

ቅዱሳኑ መጣ፤ በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።”ዘዳ.33፥2

ስለዚህም የእሳት ቅባት ወይም ጥምቀት አላማ እግዚአብሔር የሚናገረውን ሕግ ስምቶ

ለመታዘዝ ብቃትን ለመስጠት ነው። ይህም ሲሆን የእግዚአብሔር ሕግ በሚሰማው ሰው ልብ ላይ

ከመጻፉ የተነሳ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሄዳል ወይም ይኖራል። ይህም በመንፈስ እንጂ “እንደ ሥጋ

ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ” ነው። ሮሜ.8 ይህ እሳት ደግሞ ሌላም አላማ

ነበረው። ይህም ገለባውን፣ ሥጋዊ ወይም አዳማዊ ማንነታችን ከላያችን ላይ ማቃጠል ነው። ይህም ወደ

ልጁ መልክ እንለወጥ፣ እንድንነጥርና የልጁን መልክ በላያችን እንድናብለጨልጭ ነው።

ዕብራውያን 6፥2 ላይ "ስለ ጥምቀቶችና" በማለት ጥምቀት ብዙ እንደሆኑ ይነገረናል።

ስለዚህ ከላይ እንዳየነው መሰረት የቃል ስህተት ሳትሆን በጥቂቱ የተለያዩ ጥምቀቶች እንዳሉ ከቃሉ

ተመልክተና። የሆኖ ሆኖ ግን መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጥምቀት እንዳለ ይነግረናል። (ኤፌ. 4፥5). ስለዚህ

ይህን ቃል መረዳት ያለብን መርህ አካል አንድ እንደሆነ በውስጡ ሦስት ክፍሎች እንዳሉት እንዲሁ

ጥምቀት አንድ ሲሆን በውስጡ ሦስት ክፍሎችን ይዟል። 1 ቆሮ. 12፥12-14.

ጥምቀት መንፈስ ቅዱስን በተለያየ መልኩና መጠን ለእያዳዳችን ያከፋፍለናል። በመንፈስ

ቅዱስ ወይም በዘይት መቀባት ግን ከዚህም ያለፈ ነው። ይህ ኢየሱስም ሆነ ካህናቱ የተቀቡት ቅብዓ

ዘይት ለመንፈስ ቅዱስ መገኘትና ሥጦታዎች ከመቀበል ባሻገር ከስልጣንና ከሥራ ጋር የተያያዘ ነው።

ኢየሱስ በሦስት በተለያየ ወቅት ተጠምቋል። ይሁንና ይህ ጥምቀት እኛ እንደምነገምተው

አይነት ጥምቀት አይደለም። እያንዳዱ የኢየሱስ ጥምቀቶች በመቀጠል መለኮታዊ አዋጆች ታውጀዋል።

ኢየሱስ በውሃ ሲጠመቅ "እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ

ነው አለ። (ማቴ. 3፥17).

www.tlcfan.org 3
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

ሁለተኛው ጥምቀት በቀርሜሊዬስ ተራራ ኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ ፊት ሲለወጥ

ሲያደርግ የተፈጸመ ነው። “በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም

እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።. . .እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦

በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።” (ማቴ. 17፥5).

ኢየሱስ ከዚህ ሰዓት አንስቶ ስለ ሚቀበለው መከራ ይነግራቸውና ያመለክታቸው ጀምር።

"ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤

እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።" (ቁ. 12), እንዲሁን

መጥምቁ ዮሐንስ እንደተሳቀየ ማለት ነው። ይህ የኢየሱስ የደም ጥምቀት ወይም መቀባት ነው። ይህም

በሕጉ በዘጸ. 29፥21 የተጻፈውን ሊፈጽም ነው። ይህም አሮንና ልብሱ በደም ስለ መረጨትና መንጻት

የሚናገረውን ሕግ ነው። ስለዚህ በተራራው የኢየሱስ ልብስ ነፃ። ይህ እውነተኛ ሊቀ ካህን ለመሆን ብቃት

የሚሰጥ መለኮታዊ ሕግ ነው። ኢየሱስ ይህን የደም መቀባት ወይም መረጨት ሕግ በመፈጸሙ ይህን

ብቃት የሊቀ ካህንነት ብቃት ከእግዚአብሔር ተቀብሏል። እግዚአብሔር ይንን ለማስረገጥ ከሰማይ እንደ

ውሃው ጥምቀቱ ቀን ቃሉን አውጇል።

ኢየሱስ ይህን የሊቀ ካህን ስፍራ በመውሰዱ የሰው ልጆችን ሁሉ ሃጢያት ለማስተሰረይ

የሚያስችለውን ሥልጣንና ሥራ ተቀብሏል። የሦስተኛው ጥምቀቱ ወደ ሰማይ አርጎ በአብ ቀን ሲቀመጥ

ነው። “ከመላእክትስ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም

ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው?. . . ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ

እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል?” ዕብ.1:5 ይላል።

ስለዚህ ኢየሱስ እኛ የምንሄድበትን አዲስ መንገድ መርቋል። እራስ በሚሄድበት መንገድ

አካል ይሄድ ዘንድ ግድ ነው። ስለዚህም ነው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ሲጽፍ "በሚመጡ ዘመናትም

በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ

ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።" (ኤፌ. 2፥6). ይላል። በሌላ

አባባል ኢየሱስ ወደ ሰማያዊ ስፍራ እንደገባ እኛም አካሉ እንደመሆናችን መጠን ከእርሱ ጋር ወደ ሰማያዊ

ስፍራ ገብተን በእርሱ ውስጥ እኛም ከእርሱ ጋር ተቀምጠናል። ይህ ማለት ግን በተግባር አይፈጸምም

ሁሉ ተጠናቋል ማለት አይደለም። አንዳዶች ይህን ቃል ካመኑና በአፋቸው ደጋግመው ከተናገሩት ብቻ

ሁሉ የሚሆን እና የሚጠናቀቅ የሚምሰላቸው አሉ። ይህ ከእውነት እና ከእርሱ ሃሳብ የራቀ ነው።

www.tlcfan.org 4
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

ማንም ሰው አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ሙሉ ስልጣን ወይም ዙፋን የያዘ የለም።

ይህን ግን አሁን ሁሉን እደያዘ የሚቆጥር ግን ሰነፍ ደናግል የሆነና ልቡን ባዶ ምኞት የሞላ ሰው ብቻ

ነው። ይህ ደግሞ አደጋ አለው። ምክንያቱም አማኞች ለዚህ ክብር የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት ከማድረግ

ይገድባቸዋልና ነው። እምነት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚወጣ ቃል ሁሉ ላይ የተመሰረተ እንጂ እኛ

የምንፈልገውን ከቃሉ ነቅሰን በማውጣት የምናምነው አይደለም። ማቴ4:፥4

የኢየሱስን ሙሉ ሥልጣን መካፈል ከፈለግን የኢየሱስን ፍለጋ ልንከተል ይገባል። እነዚህ

ሦስቱ የቅባት አይነቶች ከእግዚአብሔር ሦስቱ በዓላት ጋርም የሚያያዙ ናቸው። እነዚህም የእግዚአብሔር

በዓላት ፋሲካ፣ በዓለ አምሣ እና የዳስ በዓል ናቸው። እነዚህን በሌላ ትምህርቶች ላይ እንዳየነው የሦስቱ

መንፈሳዊ እድገቶች ምሳሌም ናቸው። መኪና መንዳት ለማይችለው ልጃችን የቱንም ያህል ብንወደው

የመኪና ቁልፍ አንስተን እንደማንሰጠው ሁሉ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን የመንግሥቱን

ሥልጣን ፣ቁልፍ ሆነ ዙፋን ለማንም ሕጻን እና ላልበስለ አዋቂ ዝም ብሎ አሰጠውም።

ስለዚህም በፋሲካ በዓል የእድገት ደረጃ ላይ የቀሩ ሰዎች ፈጽሞ ይህን እድል እያገኙም።

እንዲሁም ደግሞ በበዓለ አምሣ እግዚአብሔር ከመስማት ይልቅ ሰውም መስማት የመረጡና ወደ

ዲኖሚኔሽን ድንኳናቸው ከእግዚአብሔር ድምፅና ሕግ ሸሽተው የሮጡ ሁሉ ከምድረ በዳው መጥተው

ወደ መንግሥቱ ስልጣንና ክብር እረፍት ውስጥ ከመግባት ይጎድላሉ። ነገር ግን ይህ ልጅነታቸው ከእነርሱ

እንደማይወስድባቸው በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

በዓለ አምሣ ግን በመጠኑም ቢሆን አማኙ የቅባት ሥልጣን የሚቀበልበት የአንድ አማኝ

የመንፈሳዊ የእድገት ወይም የጉዞ ደረጃ ነው። በዚህ የእድገት ደረጃ ብዙዎች ከመንፈስ ቅዱስ ቅባት

የተነሳ ብዙ የእግዚአብሔር መንፈስ ስጦታዎችንም ይቀበላሉ። ነገር ግን በዚህ ዘመን ብዙ መውደቅና

መነሳት፣ እምዲሁም ማበላሸት ይኖራል። ሕዝበ እስራኤል በምድረ በዳ እንደተፈተነ ብዙዎች በተቀበሉት

ስልጣንና ስጦታ ይፈተናሉ። (ዘዳ.8:፥2) አንዳዶች ለራሳቸው ጥቅምና ለራሳቸው ሞገስን ለማግኘት

የተሰጣቸውን ስልጣን ሲጠቀሙ በስልጣኑን ሌሎችን በምታትና በማፍረስ ሕይወት ላይ ይቀራሉ።

ሉቃ.12 ነገር ግን በምድረ በዳ ከስህተታቸው ተምረውና በመንፈስ ተመርተው በመታዘዝ ሕይወት

የተሰጣቸውን ሥልጣን እንደሚገባ አክብረውና እንደ እግዚአብሔር ፍቃድና ሃሳብ ብቻ ተጠቅመው ድል

የሚነሱ አማኞች ሁሉ እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ቁልፍ ብቃትን ይጠጣቸዋል። እነርሱም በመንግሥቱ

ዘመን ከእርሱ ጋር ይገዛሉ ደግሞ ይነግሳሉ። ራእይ. 20፥6 ሙሉ ስልጣንንም ከእርሱ ይቀበላሉ።

www.tlcfan.org 5
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

እነዚህ በአስሩ ደናግል መጽሐፌ ላይ ያስቀመጥኳቸው ልባሞቹን ደናግልና በመጨረሻዋ

ዘመን ቤተ ክርስቲያን በሚለው መጽሐፌ ላይ ደግሞ ያሉትን ድል ነሺ አማኞችን እንደ እነርሱ አይነት

ባሕሪ ያላቸውን አማኞች ሁሉ የሚያመለክት ነው። ድል የሚነሱ ብቻ ለመንግሥቱ ስልጣን፣ ቁልፍና

የመጨረሻው ቅባት ለመቀበል ብቁ ይሆናሉ። “ጌታም አለ፦ እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው

ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው? ጌታው መጥቶ እንዲህ

ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው። እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። ያ ባሪያ

ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም

ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ ከሁለትም

ይሰነጥቀዋል እድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።”ሉቃ.12፥42-44 ይህም መሰንጠቅ ከድል ነሺዎች

ተለይቶ ፍርዱን ከማይታመኑ ጋር መቀበሉን እና ለመንግሥቱ ሥልጣን ብቁ አለመሆኑን ያመለክታል።

አሁን በበዓለ አምሣ ዘመን ልምምድ ብዙዎች እንገኛለን። አንዶዶች ድል ነሺዎች የዳስ

በዓልን በመለማመድ ላይም ይገኛሉ። በበዓለ አምሣ ሥር ስንሆን ጌታ እስኪመጣ ይዘገያል ብለን እንደ

ፈለግን በሕይወታችንና በሰዎች ሕይወት የምናደርግ ከሆነ፣ የእርሱን ሎሌዎችና አገልግዬች ይመታ፣

ይበላም፣ ይጠጣም ደግሞ በተለያየ ነገር ይሰክር ቢጀምር እድሉ ከማያምኑት ጋር ይደረጋል።

ኢየሱስ በደም፣ በውሃ፣ በመንፈስና በእሳት ተጠምቋል ብንል እንደ ቃሉ ፈጽሞ

አልተሳሳትንም። እኛም ሁላችን በእርሱ ውስጥ ሆነን በመንፈስ እነዚህን ጥምቀቶች ተጠምቀናል።

በቅዱስ ቅባትም ተቀብተናል። ነገር ግን በሕይወታችን በግል ልምምዳችን ግን እንድንኖረው

እግዚአብሔር ከእያንዳዳችን ይጠብቅብናል። ለምሳሌ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር ክብር

መገኛ ለመድረስ ከአደባባይ እንጀምራለን በዚያ አደባባይ ደምና ውሃ እናገኛለን። ከዚያም በመቀጠል

በመጋረጃው አልፈን ወደ ቅድስት ስንገባ በዚያ ደግሞ የወርቁን መቅረዝ ዘይት ተሞልቶ ሲያበራ

እናገኛለን። የመጨረሻው ክፍል ቅድስተ ቅዱሳን ስንገባ ደግሞ የእሳቱን አምድ እናገኛል። ስለዚህ በዚህ

መልኩ እኛም ኢየሱስ ተከትለን በመረቀልን መንገድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንገባለን። በእያንዳዱ ክፍል

ያሉትንም ጥምቀቶች መርጨቶች ሆነ መቀባት ፈጽመን ወደ ክብር፣ ሥልጣንና መንግሥቱ እንገባለን።

“በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው

ብቻ አይደለም። መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። የሚመሰክሩት

መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።”1ዮሐ 5

www.tlcfan.org 6
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #9

www.tlcfan.org 7

You might also like