Professional Documents
Culture Documents
04.
04.
4
www.tlcfan.org 0
መለከት #4
ቀናተኛ አምላክ ነኝ
“5. በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት
በልጆች ላይ የማመጣ 6. ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ
ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።”
ዘጸ.20፥1-3, ዘዳ.5፥9
እግዚአብሔር በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት
በልጆች ላይ የማመጣ ሲል ለማስፈራት ወይም ማለት ስላለበት የተናገረው ቃል አይደለም። እግዚአብሔር
ቀናተኛ አምልክ ስለሆነና እንዳለውም በትውልድ ላይ ይህንን ትዕዛዙ በማያደርጉ ትውልዶች ላይ ፍርዱን
እንደተናገረው ስለሚያመጣ ነው። “እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።” ዮሐ.15፥23-25 ኢየሱስ
ይህን ያለው መዝሙረ ዳዊት ላይ በከንቱ ይጠሉኛል የተባለው ይፈጸምባቸው ዘንድ ነው።
እንግዲህ ይህን እውነት በደንብ በቃሉ መሰረት ከተመለከትን ሕይወታችንን በቃሉ መሰረት
መርምረን ከእርሱ ጋር መንገዳችንን እናስተካክላለን። ይህን የምናደርግ ከሆንን ደግሞ እግዚአብሔርን
ደስ እያሰኘነው እንዳለንና እንደምንወደው እንድናውቅ እወዳለሁ። በአንጻሩ ደግሞ ይህን እርሱ
የማይወደውን እያደረግን ከሆነ እርሱን በከንቱ እየጠላነው ነው። ይህ ከሆነ በቶሎ ንስሃ እንግባ።
www.tlcfan.org 1
መለከት #4
“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥
ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ
አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ “ ዘጸ 20
www.tlcfan.org 2
መለከት #4
“ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥” ፊሊ.2፥10
የተሳለው መልካቸውስ ትክክለኛ መልክ ነውን? ይህን ታሪክ ያጠና ሰው የሚመልሰው ቀላል
ጥያቄ ነው። ያለየነው እግዚአብሔር በምስል ስለን ስንመስለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እየተላለፍንና
በከንቱ እርሱን እየተጠላነው በትዕዛዙ ላይም እያመጽን ነው። ይህንን ሕሊናችሁ ወይም በውስጣችሁ
የተተከለው የእግዚአብሔር ሕግ ይፍረድ። ሮሜ.2 ጳውሎስ ኢየሱስ በስጋ ለሚያውቁት፣ በአይናቸው
ላዮት፣ በእጃቸው ለዳሰሱት እንዲሁም ቁጭ ብለው በጆሮዋቸው ለሰሙት ሰዎች እርሱ ወደ አባቱ ካረገና
ለጳውሎስም በደማስቆ በክብር ከተገለጠለት በኋላ እንዲህ ብሎ ያስተምራል።
“ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ
እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።”
2.ቆሮ.5፥16
www.tlcfan.org 3
መለከት #4
የጌታ ቃል ፍጹም የሆነ የሰው ልጆች ሃይል ነው። ዛሬ ግን ቃሉን ጥለን እንጨቱንና ነሃሱን
እንደ እስራኤል ልጆች እያመለክን እንገኛለን። እነርሱ ጌታ ረድቷቸው ሰባብረው ከእግዚአብሔር ጋር
ተጣበቁ እርሱን ብቻ ታዘዙት እኛስ? መስቀል ሃይላችን ነው ተብለን የተማርንና ያመንን ካለን እንግዲህ
በዚህ ቃል መሰረት ራሳችንን እናርም። መስቀል ሳይሆን ሃይላችን የመስቀሉ ቃል ሃይላችን ነው።
www.tlcfan.org 4
መለከት #4
ስለዚህ አስተውሉ የገና ልደት በዓል፣ የስቅለት በዓልን ፋሲካን በዓላት እንደ ቃሉ ሳይሆን
እንደ ሃይማኖትና ወግ ስርዓት ልናከብር ስንጥር የእግዚአብሔርን ሕግጋት እንተላለፋለን
እግዚአብሔርንም እናሳዝናለን። እንድናደርግና እንድንጠብቃቸው የተሰጡን የእግዚአብሔር በዓላት
አሉን በእነርሱ ላይ ግን መጨመር ወይም መቀነስ ፈጽሞ አይገባንም።
ዛሬ ባለንበት ዘመን በቃሉ ያልታዘዝነው ማንኛውንም ነገር ምሳሌ በአቢያተ ክርስቲያን ሆነ
በቤታችን አናድርግ። በቃሉ የተመሰሉትንም የተቀመጡትንም ቢሆን እንደተመሰሉበትና እንደተሰጡበት
አላማ ልንማርባቸው መሆኑን ማወቅ አለብን። ስለዚህ ልናመልካቸው፣ በፊታቸው ልንሰግድ፣ ሻማ
ልናበራላቸው፣ ድግስ ልንጥልላቸው፣ እንዲማልዱና እንዲደርሱልን እንድንለምናቸው፣ ፈጽሞ
እግዚአብሔር በቃሉም ሆነ በሕጉ አላዘዘንም። እግዚአብሔርን ወይስ ሃይማኖትን እናስደስት? ሰውን
ወይስ እግዚአብሔር? ምርጫው የእናንተ ነው። ይህ ጳውሎስ የተሻረው ያለው የሃይማኖተኛ ሰዎች
ወግና ልምምድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስርዓት እንጂ በእግዚአብሔር ቃልና ሕግ ውስጥ ምንም አይነት
ይህን አድርጉ የሚል ቃል ፈጽሞ ተጽፎ አናገኝም። ስለዚህ ከቃሉ ውጭ የሆነውን ሁሉ ከእለት እለት
ልምምዳችን እናስወግድና ከእግዚአብሔር ጋር እንወግን እርሱን ብቻ ደስ እናሰኝ። ሮሜ.8፥7-8
ከአሮጌው ኪዳን ጋር አብረው ፍጻሜን ያገኙ ሕግጋት አሉ። ነገር ግን ተፈጸሙ ማለት ተሻሩ
ማለት አይደለም። እነርሱንም አሁን ደግመን ልናደርጋቸው ፈጽሞ አያስፈልግም። ምክንያቱም በኢየሱስ
በኩል የተሻለና የከበረ ኪዳንን ትዕዛዝን ስለተቀበልና በኢየሱስ ስራ በኩል የተፈጸሙ ስራዎችና ሕጎች
ስለሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል ለሃጢያት ስርየት በግ አናርድም። በጉ ተቀይሯል ሕጉ ግን አሁንም አለ።
አሁን እጣን አናጥንም ነገር ግን የእጣን ሕግ አሁንም አለ። በአዲሱ ኪዳን እጣን ወደ እግዚአብሔር
በሚደረግ የምስጋናና የምልጃ ጸሎት ተቀይሯል። ይህን ወደፊት ወደ እግዚአብሔር ሕግጋቶች በትምህርት
እየዘለቅን ስንገባ በዝርዝር የምንመለከታቸው ይሆናል። ስለዚህም ነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ
ተፈጸመ ያለው። መስቀሉ የብዙ ነገሮች ፍጻሜና ጅማሬ ነው።
www.tlcfan.org 5
መለከት #4
www.tlcfan.org 6