You are on page 1of 13

ልባችሁን ቅደዱ

I. የቃሉ ንባብ
ኢዩኤል 2፡12 - 13
አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ
እኔ ተመለሱ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤
አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣውም የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥
ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

II. ጸሎት

III. ነገር ግን መከራችን እጅግ በዛ


a. ዘመናችን እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሆነብን
- ብዙዎች በፍርሃት፣ በድንጋጤ፣ በስጋትና በመጨነቅ ኑሮአቸውን
የሚገፉበት ሆነ፤
- የዚህም ምክንያት፦
o የሰላም እጦት፦
▪ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ጭከና፦ ሰው እርስ በርሱ ተጨካከነ
▪ ሰው በዘርና በሃማኖት በሚያስፈራ ሁኔታ ተከፋፈለ፣
▪ ከቤት ወጥቶ መመለስ ብርቅ ሆነ፣
▪ መፈናቀል፣ ስደት፣ ከዘመድ ካዝማድ መቆራረጥ፣
▪ የደም ምድር ሆነች፣ ደማችን መፍሰሱ አልቆምም አለ፣
o የተፈጥሮ አደጋዎች
o ቸነፈር
o የኑሮ ውድነት፦

o ማህበራዊ ችግሮች፦
▪ ሰዶመኞች፣
▪ ልመና፣
▪ ሴት አዳሪነት፣
▪ ሱስ፤
▪ ትዳር ፈረሰ፦
 ቤተ ሰብም ተበተነ፣
 ህፃናት ደጋፊ አጡ።
▪ የጎዳና ተዳዳሪነት፣
▪ መፈናቀል በዛ፣ ስደት እንደ ዋዛ፣

መልካም የምንለውን ነገር አጣን

ፈራን፣ ተጨነቅን...

IV. ነገር ግን እኛ የእግዚአብሄር በረከት ተካፋዮች...


N.B. የብልጽግና ወንጌል ሰባኪ አይደለሁም

- ሙሴ የእግዚአብሄርን ቃል ስለሚሰሙና ያዘዘውንም ትዕዛዛት


ስለሚጠብቁ ሕዝቦች ሲናገር (ዘዳ. 28፡1- 14)

እግዚአብሄር
o ከምድር አህዛብ ሁሉ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤
o በከተማህ ብሩክ ትሆናለህ፤
o በእርሻህም ብሩክ ትሆናለህ፤
o የሆድህ ፍሬ፣ የምድርህም ፍሬ፣ የከብትህም ፍሬ፣ የላምህም
ርቢ፣ የበግህም ርቢ፣ብሩክ ይሆናል፤
o እንቅብህ ቡቃያህ ብሩክ ይሆናል፤
o በመግባትህ ብሩክ ትሆናለህ፣ በመውጣትህም ብሩክ ትሆናለህ፤
o በአንድ በኩል የመጡብህ ጣላቶች በብዙ መንገድ ከፊትህ
ይሸሻሉ፤
o እግዚአብሔር በረከቱን በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ
ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤
o አምላክህ እግዚአብሄር በሚሰጥህ ምድር ይባርክሃል።
ብሎ ይቀጥላል...

- ማቴ. 6፡ 25 – 26
25
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥
ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል
ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?

ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም


26

በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤


እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

 ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ፦


o የእግዚአብሄር ልጆች ነን፤

ስለዚህም ሲንጠቀልለው፦
ጻድቃን
17
ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው። መዝ. 34፡17

ነገር ግን ብንጮህ ብናለቅስ ነገሮቹ ከድጡ ወደ ማጡ


እየሆነብን ሄደ...

V. ታድያ ለምን የእኛ ኑሮ ከዚህ የተገላቦጦሽ ሆነ? (ለምን


ብለንስ ጠየቅን?)
13
፤ ጌዴዎንም። ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ
ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ። እግዚአብሔር ከግብፅ
አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ። መሳ. 6፡13

ለዚህ ምክንያት፦ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ


ሥራ ሠሩ።

a. ሃጥያትን አበዛን፣ ክርስትና ተደባለቀ


o እኛ በቤተክርስትያን የምናገለግል ሰዎች እንኳን መታለፍ
የማይገባውን መስመር መለየት አቃተን፣
o በእርኩሰት ውለን አደርን ነገር ግን ያለሃፍረት በቆሻሻችን
ታጅለን ወደ መሰውያው ቀረብን፣
o እግዚአብሄርን የሚያሳዝንን ነገር እንደ ቀልድ ተለማመድን
o ነገር ግን ቆይተን ምንም እንዳልተፈጠረ ኑሮአችንን ቀጠልን፦
▪ ንስሃ የለ!!! ፀፀት የለ!!!
o የተሰጠንን ሃላፊነትና አደራ ለክፉ ስራችን ለመጠቀም
አላመነታንም፦
▪ መማለጃን ተቀበልን፦ የብዙ ክርስትያኖች መገለጫ ሆኖአል...
o በቤተ ክርስትያን ውስጥ አገልግሎታችን ብዙ፣ ነገር ግን፦
▪ በስራ ቦታችን አጸያፊ ምስክርነት ያለን፤
o ሰው ለይተን የምንጠላ፣ በዚህ ግብራችንም የምንኩራራ፤

ሃፍረታችን በዛ! እግዚአብሔርን አሳዘንን!

b. ታድያ እግዚአብሄር ለምን አያዝን??? ለምንስ አይለየን???


ምክንያቱም፦
- እግዚአብሔር ሃጥያትን ነፍሱ ትጠላለች፤
- ሃጥያት ደግሞ በሰውና በእግዚአብሄር መሃከል ትለያለች፦
o ስለዚህ ነው ነብዩ ኢሳያስ “በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ
መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ
ሰውሮታል” ብሎ የሚለን፤

ሆሴዕ
- እግዚአብሔር ሃጥያትን እንዴት እንደሚጠየፍ ሰው እንዲረዳም በሆሴዕ
በኩል አንድ ተምሳሌዓዊ ነገርን አደረገ፦
o በዚህ ተምሳሌዓዊ ትይንት፦
▪ ሆሴዕ እንደ እግዚአብሔር
▪ ጎሜር ደግሞ እንደ እስራኤል ህዝብ
እንዲጫወቱ ተደረገ።

o ችግሩ!!! ምድሪቱ ከእግዚአብሄር ርቃ ታላቅ


ግልሙትናን ታደርጋለች።እግዚአብሔር የተሰማውን ቅሬታ
እንዲረዳ ሆሴዕን
▪ ሂድና ጋለሞታ ሴትን አግባ አለው፤
▪ ሆሴዕም ጋለሞታይቱን ጎሜርን ሄዶ አገባ።
▪ ይህች ጋለሞታ ሚስት ሶስት ልጆች ከወለደችለት ቦሃላ እንደገና
ወደ ግልሙትናዋ የምትመለስ ነበረች፤
o እግዚአብሔርም ሆሴዕን ይህች ውሽሞችዋን የምትወደውን
አምነዝራይቱን ሴት ውደድ አለው፤
▪ ከቃሉ እንደምንረዳው ይህች ሴት አምንዝረኛ ብቻ ሳትሆን
የውሽሞችዋም እዳ ነበረባት፤
▪ ስለዚህ ሆሴዕ እዳዋን ከፍሎ ነጻ ማውጣት ይጠበቅበት
ነበረ።
o እዳውን መክፈል ቢቻልም እንኳ፣ እንደዚህ አይነቱን ስው መውደድ
ግን አስቸጋሪ ነበረ፤ ሆሴዕ ግን አደረገው፤
የቤት ስራ፦ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነን ሁኔታን እግዚአብሄር ሲያስረዳ
በሕዝቅኤል 16 ላይ ማየት ይቻላል።

 በዚህም እግዚአብሔር አምላክ እጅግ አዘነ፣ ተቆጣም


▪ ቃሉ ሲናገር ታድያ ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ ይላል፤
▪ ኤፍሬምም እንዳልተገላበጠ ቂጣ ሆነ፤
▪ እንግዶች ጉልበቱን በሉት፣ እርሱ ግን አላወቀም፤
▪ ሽበትም ወጣበት፣ እርሱ ግን አላወቀም፤
▪ ሆሴዕ 7፡8
ኤፍሬም ወደ ብስባሽነት ብፍጥነት እየተቀየረ
ነበረ፣ እርሱ ግን አላወቀም።

- ዛሬም የኛ ክርስትና ከአህዛብ ጋር ተደባለቀ/ወልመካ ሆነ


o ከአብርሃም፣ ከይሳህቅ፣ ከያዕቆብ አምላክ ያስበለጥናቸው ብዙ
ሆነውብናል፦
▪ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” (ዘጸ. 20፡
3፣ ሙሴ “እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን
እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው”፣ (ዘዳ6፡4)
ብሎ ያሳሰበንን ትተን “አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ
እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።” (ዘዳ. 2፡24) የሚሉትን
መለኮታዊ ተዕዛሾች ረስተን ትንንሽ አማልክትን
ማፈላለግ ከጀመርን ስነበተ፣
▪ ክርስቶስን ከሌሎች አማልክት ጋር አደባለቅነው፦
• ገንዘብ አምልኮ ሆነብን፤ በሁለት ሃሳብ አታንክሱ፣ እግዚአብሄር
አምላክ ከሆነ እርሱን ተከተሉ፣ በአል
• ዝና አምልኮ ሆነብን፣
አምላክ ከሆነ እርሱን ተከተሉ
• ክብር አምልኮ ሆንብን፣
• ራሳችንን መውደዳችን ቅጥ አጣብን፤
o በቸርነቱ እንዲጎበኘን እግዚአብሔርን
አጥብቀን አልፈለግንም፣

 ይህን ሁሉ ግን ከሰማይ ሆኖ አይቶዋል፤

▪ ክርስቶስን መምሰል ሲገባን፣ የርሱም ምስክሮች ልንሆን


ሲገባን፣ የአማሌቅ ሰዎችን ፈልገን ተውዳጀን፤

 ከዚያም ተመልሰን እንዘምራለን፣ ራሳችንንም


እናታልላለን።

እግዚአብሄር ከዚህ ይጠብቀን...

እርሱን ከመከተል የሚመለሱትን ሊባርክ እግዚአብሄር


መቼም ቢሆን ለማንም ቃል አልገባም።

የሰለሞን ቤተ መቅደስ እንኳን ይጥለዋል


- ንጉስ ዳዊት ለዚህ ቤተ መቅደስ ስራ ያዘጋጀው (1ኛ ዜና 22)
o 100,000 መክሊት ወርቅ (34,200 ኩንታል)
o 1,000,000 መክሊት ብር (342,000 ኩንታል)
o ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት
o ቁጥር የሌላቸው የዝግባ እንጨቶች
▪ በአጠቃላይ ብር 1.5 ትሪሊየን ይገመታል (USD 26 ቢሊዮን)
▪ የኢትዮጵያ የዚህ አመት በጀት ብር 801 ሚሊዮን ነው።

- እግዚአብሄር በክብሩ የሰለሞንን ቤተመቅደስ ተቀበለ፦


o እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መስዋእትና ሌላውንም
መስዋዕት በላ፦
▪ 22,000 በሬዎችና፣
2ኛ ዜና 7፡5
▪ 120,000 በጎች
o የእግዚአብሄር ክብር ቤቱን ሞላው፤ ካህናቱ ወደ ውስጥ መግባት
አልቻሉም፤
o ሕዝቡ ሁሉ በግንባራቸው ተደፋ፣ ሰገዱም፣ እግዚአብሄርንም
አመሰገኑ፤
2ኛ ዜና 7፡ 1 - 3
o እግዚአብሄርም የተስፋ ቃሉን በህልም ለሰለሞን ሰጠው።

- ነገር ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ (2ኛ ዜና 7፡20)፦


o ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋችሁ ምድር እነቅላችኋለሁ፤
o ይህንንም ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ
▪ በአህዛብም ዘንድ ምሳሌና ተረት ይሆናል፤
▪ እግዚአብሄር ከለዳውያንን አስነሳ፦ የበባቢሎን ምርኮ፤
• ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፣
ከማታም ተኩላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው። (ዕን. 1፡8)
▪ በእዝራና በዘሩባቤል የተገነባውም ቤተ መቅደስ
በሮማውያን ፈረሰ፣
▪ ዛሬ በቤተ መቅደሱ ስፍራ ላይ አል አክሳ (Al-Aqsa) መስጊድ
ይገኛል

ልብ እንበል፦ እግዚአብሄር በኛ የተያዘ ዕዳ


ፈጽሞ የለበትም።

- እንጠንቀቅ፦ እግዚአብሔርን አይዘበትበትም፦


...እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ
10

ይሰጥ ዘንድ ልብን የመረምራል ኵላሊትንም


ይፈትናል። ኤር. 17፡10
VI. እግዚአብሔርን መፈለጋችን ጥያቄ ውስጥ ገባ
a. አምልኮአችንን እግዚአብሄር ጠላ
- ሳንታረም፣ በሃጥያት እየኖርስ፣ ከነቆሻሻችን በእግዚአብሄር ፊት
በአምልኮ እንቅረብን?
o ይህን አይነቱን መስዋእት እግዚአብሔር አይቀበለውም፣

እግዚአብሄር በነብዩ በኢሳያስ በኩል የእስራኤልን ሃጥያት አስመልክቶ


ያለው ለኛም ይሰራል (ኢሳ. 1፡1 – 14)፦
o የመሥዋዕታችን ብዛት ለእግዚአብሄር ምን ይጠቅመዋል? ...፤
o የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ
አያረካውም፤
o የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘውም፤
o የመቅደሱን አደባባይ ሕዝቅኤል 33፡31
መርገጣችንን ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ
አይፈልገውም (ሕዝ. 33፡31) ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም
በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም
o ቍርባናችንና ዕጣናችን ይሰማሉ ነገር ግን
በእርሱ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ
o መባችንና ሰንበታችን ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን
በጉባኤ መሰብሰባችንን ስስታቸውን ትከተላለች።
አይወድም
o በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አይታገስም
(ማቴ 24፡15 …የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥
አንባቢው ያስተውል)፤
o መባቻችንና በዓላቶቻችንን ነፍሱ ጠልታለች፤ ሸክም
ሆነውበታል።

 ልብ እንበል፦ የዳዊት ልብ ሳይኖረን፣ እግዚአብሄርን እንደሚገባው


ሳናከበር፣ ለእግዚአብሄር ክብር
o ዘለልን ብንል, ብናሸበሽብ፦
o ይህ በእግዚአብሄር ዘንድ አጸያፊ ይሆናል።

ከውጭው ነገር የውስጡ ይቀድማል።

 እግዚአብሄር ምህረት ያድርግልን

የቤት ስራ፦ 1ሳሙ 15፡22 / ሆሴ. 6፡8

b. የኤልዛቤል ነብያት በዙ
ዛሬ በእግዚአብሔር ስም የሚተነብዩ፣ ነገር ግን ምኞታቸውን
የሚያሳድዱ ሃሰተኛ ኤልዛብልን የሚያገለግሉ የበዓል ነብያት
በዝተዋል፦
- መልእክታቸው የሚያስት፤
- ትንቢታቸው የማይፈጸም፤
- ኑሮአቸው ውሸት፣
- ተግባራቸው ክፉ፤
- እውነተኛ የእግዚአብሄር ነብያትን የሚጠሉ፦
o የእግዚአብሄር መንፈስ እንዴት ከኔ አለፎ ወደ አንተ መጣ
የሚሉ፤
- የግዚአብሄር ነብያት ሲራቡ፣ ሲሰደዱ፣ ከቁራ ወስደው ሲበሉ፣ እነርሱ ግን
ራሳቸውን በማበልጸግ የተጠመዱ፤
- ክርስቶስን የሚያሰድቡ፣ የሃፍረት ሸክም ክርስትያኖችን
ያሸከሙ፤
- ከእግዚአብሄር የራቁ፣ የጽድቅን መንገድ ያማያውቁ፤
- ከክርስቶስ ጋር ሰዎች የሚታረቁበትን ትልቁን ንስሃ ከሁሉ
አብልጠው የሚረግሙ፣ ካምልኮአቸው ነጥቀው ያወጡት፦
o መጥምቁ ዮሐንስ ከ400 ዓመት የጸጥታ ዘመን ቦሃላ ሲመጣ ንስሃ
ግቡ ብሎ ቢሆንም፤
o ጌታ ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር መንግስተ ሰማያት
ቀርባለችና ንስሃ ግቡ ብሎ ቢሆንም፤
o ሐዋርያው ጴጥሮስ በመጀመርያ የወንጌል መልዕክቱ ንስሃ
ግቡ ኃጥያታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ብሎ ቢሆንም፤
o በራዕይ ከሰባቱ አብያተ ክርስትያናት ለአምስቱ የነበረው
መልዕክት ንስሃ ግቡ የሚል ቢሆንም።
ዛሬ ግን የንስሃን ዋጋን ባዶ አስቀርተውታል፤

የእግዚአብሄር ቁጣ፣ ሲኦል እና የእግዚአብሄር ፍርድ


ስለሚባሉ ነገሮች ማንሳትም፣ መናገርም ማስጠንቀቅም አይፈልጉም።

ስለዚህ የሚያወሩን እየተመቸን፣ እያሳሳቁን ነገር ግን


ወደ ጥፋት ያደርሱናል።

እኛ ደግሞ ተንጋግተን/ተግተልትለን ተከተልናቸው፣ በብዙ ቁጥር


አጀብናቸው።
 እግዚአብሄር ይቅር ይበለን።

እግዚአብሄር መንፈሱን ከኛ ወሰደ፦


- እስራኤል በአክአብ ዘመን እንደተቸገረችው መከራችን አላልቅ አለ፦

VII. መደምደምያ
a. እግዚአብሔር መሃሪ ነው
 ዛሬ ባነበብነው ክፍል (ኢዩ 2፡13B)፦
አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ
እኔ ተመለሱ።
አልፎም...

አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣውም የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥


ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

 አስቀድመን እኛ ከክፉ መንገዳችን መመለስ አለብን፣


 ፍፁም የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ አለብን፣
 ንስሃ መግባትና የአዲስ መንፈስ ህይወትን መኖር አለብን።

ሆሴ. 6፡1
1
፤ ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤
እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።

 ዛሬ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ደምና ስጋ ልንወስድ ቀርበናል፦


o ስለዚህ ልባችንን እንጂ ልብሳችንን አንቅደድ፤
o በተዋረደ መንፈስ፣ በንስሃ ልብ እንቅረብ፤
▪ እግዚአብሔር ይቅር ይበለን፣ ይማረንም፤
▪ ንስሃችን ደግሞ እግዚአብሄርን በማወቅ ይሁን፤

b. የእኛስ የምልጃ አገልግሎት፦


እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባውን እናስታውስ
ዘፍ. 18፡26 - 33
26
፤ እግዚአብሔርም። በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ
ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ።
27
፤ አብርሃምም መለሰ አለም። እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር
ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤
28
፤ ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ
ምክንያት ታጠፋለህን? ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ።
29
፤ ደግሞም ተናገረው፥ እንዲህም አለ። ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?
እርሱም። ለአርባው ስል አላደርገውም አለ።
30
፤ እርሱም። ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ
ቢገኙሳ? አለ። እርሱም ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።
31
፤ ደግሞም። እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ምናልባት
ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም። ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው
አላደርገውም አለ።
32
፤ እርሱም፤ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት
ከዚያ አሥር ቢገኙሳ? አለ፤ እርሱም። ስለ አሥሩ አላጠፋትም አለ።
33
፤ እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፤
አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።

 ዛሬ እንዴት ወደ እግዚአብሔር የሚጮሁ ጥቂት ጻድቃንን


አጣን???
o የምልጃ አገልግሎትን እግዚአብሄር ሰጥቶናል (1 ጢሞ. 2፡1)

 ዛሬ ስጋና ደሙን ስንወስድ ለምድራችንም ንስሃ እንግባ፤


o ሕዝቡ እስካሁን ያለው መከራን ይብቃ ይበል።

 እኛም የክርስቶስ በጎ ምስክሮች አድርጎ ያቁመን፦


ፈቃዳችንን ግን በሙሉ ልባችን በመስቀል
ለሞተልንና እዳችንን ለከፈለለን ለጌታችን
ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ እንስጠው።

VIII. የመዝጊያ ጸሎት


- ከፓስተር መላኩ ጋር በንስሃ ጸሎት እንቀርባለን።
ጌታ ይባርካችሁ!!!

You might also like