You are on page 1of 28

21 May 2023

ጥሪየን እንዴት አውቃለሁ?


How do I know my Calling?
በእግዚአብሔር መጠራት
በሕይወታችን ልዩ ልዩ ጥሪዎች ደርሰውን ያውቃሉ። የጠሪዎቹና የጥሪዎቹ ዓላም መለያየት
ብቻ ሳይሆን የጥሪውም መንገድ የተለያዬ ነው።
አንድ የማናውቀው ሰው ትፈለጋለህ ቢለን ቀድሞ ወደ አይምሮአችን የሚመጣው
ለምንድን ነው የምፈለገው? ማን ነው የሚፈልገኝ የሚል ነው።
ልጅ በነበርኩ ጊዜ ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እጅግ ደክሞኝና እርቦኝ ቤት
የምደርስበት ሰአት እርቆኝ እየመጣሁ እያለ ሰፈር ስደርስ ሰዎች መንገድ ላይ አቁመውኝ
ትፈለጋለህ አሉኝ። ለምን ስላቸው ዝም ብለህ ግባ አለኝና የያዙት ቶዮታ መኪና ውስጥ
አስገቡኝ፤ ይዘውኝ ወደ አንድ የጥንት ቤተመንግስት ነገር አስገቡኝ። እኔ ብቻ ሳልሆን
ሌላም ልጅ ከእኔ በእድሜ የሚልቅ አለ።
የተፈለኩት በጥሩ ምሳና በጥሩ መጨወቻ ሊያስደንቁኝ (surprise) ሊያደርጉኝ አይደለም።
ሰፈራችን አንድ በባለስልጣናት የሚዘወተር ምግብ ቤት ነበረ። በዘመኑ እጅግ ተፈሪ
የነበረው አስተዳዳሪ ምሳ የሚበላው እዛ ቤት ነው። የእኛ ቤት ከዚህ ምግብ ቤት ፊትለፊት
ነበረ።
መኪናቸውን አቁመው በሚበሉበት ጊዜ የመኪናው ሎጎ ጹሁፍ TOYOTA የሚለው ተነቀሎ
አጡት። በዚህ ጊዜ እዚያ ሰፈር ያለ ልጅ ሁሉ እየተጠራ ወደዚያ ማዕከል ተወሰደ። ጥሪው
ለሹመትና ሽልማት አይደለም።
ያልወሰድነውን እዳ ለመክፈል ነው፤ ያለየነውን ለመመስከር ነው፤
እኛን ጫማችንን አስወልቀው እግራችንን ገልብጠው ከገረፉን በኋላ ሌሎችን እንድንጠራ
ይዘውን ወጡ። ይህ ጥሪ የመከራ ጥሪ ነው። የግርፋት፤ የድብደባ ጥሪ ነው።
የእግዚአብሔር ጥሪ ምንድን ነው?
አዎ እግዚአብሔር ይጠራል። ጥሪው ለማን ነው?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ
ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Rom 8፡28 And we know that all things work together for good to them that love God, to
them who are called according to his purpose.
ለምንድን ነው?
ጥሪው ለዓላማው ነው?
የጥሪው አላማ ክብሩንና መንገስቱን ማካፈል ነው።

1
21 May 2023

1 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡11-12 ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር


እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ
እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና።
እግዚአብሔር እየጠራን ያለው ወደመንግስቱና ወደ ክብሩ ነው።
መጥሪያ ካርዱ ወንጌል ነው።
2 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡14 ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት
በወንጌላችን ጠራችሁ።
ለጥሪው ምላሽ የሚሰጥ ከጌታ ጋር አብሮ የነግሳል፤ አብሮ ይከብራል።
የሉቃስ ወንጌል 16፡16 ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር
መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።
ይህ አንዳንዶቻችን የምንግደረደርበት ወንጌል ሊሎቹ በኃይል የሚገቡበት ነው።
ዛሬ የሰማዩን ጥሪ ቸል ማለት የለብንም። ጥሪው የቅጣት አይደለም፤ የሞት አይደለም፤
የእዳ አይደለም
የክብርና የንግስና ነው።
ጥሪያችን የምድር ቆይታ ዘመን አላማችንን እውን ማድረጊያ ነው።

ሰዎች ራሳቸውን እንዳውቁ የሚጠዩቋቸው ዋና ዋና ሁለት ጥያቂዎች አሉ።


1 ኛ. እኔ ማን ነኝ? የማንነት ጥያቄ፤ ካልተመለሰ የማንነት ቀውስን ያመጣል። ይህም
ራስን ወደመጥላት ሲከፋም ራስን ወደማጥፋት ያደርሳል።
2 ኛ ለምን ተፈጠርኩ? የሕይወት አላማ ጥያቄ፤ ካልተመለሰ የሕይወት መዘባረቅን፤
የመኖር ትርጉም ማጣትን፤ ተስፋ መቁረጥን ወይም ደግሞ እውነተኛ ላልሆነ አላማ ራስን
መሸጥን ያስከትላል።
በሚቀጥሉት የተወሰኑ ሳምንታት ይህን ትልቅ ጥያቄ የሚመልሰውን እርዕሰ ጉዳይ
እንመለከታለን።
ጥሪያችንን እና የሕይወታችን አላማ ሳናውቅ ደስተኛ የሆነ፤ ድፍረት ያለው፤ በእምነትና
ተስፋ የተሞላ ሕይወት መኖር አንችልም።
እግዚአብሔር ፈጥሮን ለምንና እንዴት እንደምትኖሩ ራሳቹሁ ጨርሱት ብሎ አልተወንም።
አምላካችን የተፈጠርንበትን አላማና ጥሪያችንን ሊያስታውቀን ፈቃደኛ ነው።
የተፈጠርንበትን አላማ እንደአጠቃላይ፤ ጥሪያችንን በግል ማወቅ ከእግዚአብሔር ጋር
ለመኖር ቁልፍ ነው።
የክርስትና ሕይወታችንን ጣፋጭ፤ መኖራችንን ትርጉም ያለው ያደርገዋል።

2
21 May 2023

የእግዚአብሔርን ረዴት በቀላሉ እንድናገኝ፤ እግዚአብሔርን እንዲመራን፤


እንዲያቀርብልን፤አብሮን እንዲሆን ለመጠየቅ እምነትና ድፍረት እንዲኖረን ያስችላል።
ብኩንና አባካኝ ሕይወትን ከመኖር ይጠብቀናል። ብኩንና አባካኝ ስንል የተሰጠንን ሕይወትና
መልካም እድሎች ሁሉ ወጥነት ላለው አላማና ግብ የማናውል መሆንን ነው።
ሁልጊዜ ባተሌ(busy) ነገር ግን እዚህ ግባ የሚባል ተጨባጭ ውጤት የሌለን ያደርገናል።
ውጤታማ ነን ብንል እንኳ በሰዋዊ መለኪያ እንጅ በአምላካዊ ሚዛን ስለማይሆን ጊዜአዊና
ከንቱ ይሆናል።
እግዚአብሔራዊ አላማና ጥሪ ከአሁኑ ዘመን እስከዘላለም እንድናተርፍበት ተደርጎ በአምላክ
የተቀየሰ ነው። በእርሱ ከተሳካን ስኬታችን የአሁን ብቻ አይሆንም። እንዲያውም በአሁኑ
ዘመን መለኪያ ያልተሳካን፤ የከሰርን ሊመስል ይችላል።
ጳውሎስ እግዚአብሄር ለሕይወቱ የያዘለትን አላማና ጥሪ በተረዳ ጊዜ ይሮጥበት የነብረውን
መንገድ አቆመ፤ በዘመኑ ማህበረሰብ ዘንድ አንቱ የተባለበትን ሁሉ እርግፍ አድሮጎ ተወ።
እግዚአብሔር ካዘጋጀለት የዘላለም አሳብ ጋር ለመሰለፍ ስጋንና ደምን ሳያማክር የልዑል
አምላክን ጥሪ ተቀበለ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡3 እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ
ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና።
4 እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ። ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ
የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ።
5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥
ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤
6 ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ
ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ።
7 ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ።
8-9 አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ
እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥
ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት
ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥
በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤

ጳውሎስ እኔ እግዚአብሔር ነህ ያለኝን ነኝ፤ ሌላ ልሆን አይገባም፤ ሌላ ልሆን አልችልም።


ታደርጋለህ ያለኝን አድርጋለሁ፤ ሌላ ግብ እና ሌላ አላማ አይኖረኝም። የሚል ቆራጥና
ጨካኝ አቋም ነበረው።

3
21 May 2023

ወደ ገላትያ ሰዎች 1፡14 ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ


በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር።
15-16 ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር
በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ
በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥

እንደጳውሎስ አይነት አቋም ካልያዝን መንፈሳዊ ሕይወታችንና እለታዊ ኑሮአችን እየቅል


ይሆናል። የተጣመሩና የሚደጋገፉ አንድ አካልና አንድ አምሳል መሆን ሲገባቸው
እንዲያውም አንደኛው የአንደኛው እንቅፋት ይሆናል።
ከዚህም የተነሳ ከጌታ ጋር ያለን ህብረት ጥልቀት የሌለው ይሆናል። ከሁለት በኩል
ስለምንጎተት በቂ የትኩረት ኃይል አይኖረንም።
በዙሪያችን ያሉ ነገሮችና ሁኔታዎች ለመንፈሳዊ ሕይወታችን እድገት የማያገለግሉ፤
በመንፈሳዊ ሕይወታችን እድገትና መሻሻል ላይ ድርሻ የሌላቸው ይሆናሉ።
ለምሳሌ ሥራን ብንወስድ
የሕይውቱን ጥሪ ያልተርዳና ለዚያ ጥሪ ምላሽ ያልሰጠ ሰው ሥራው ከሌሎች የሕይወቱ
እንቅስቃሲዎች ጋር ያለው ግንኙነት የላላ ይሆናል። የቀኑ የስራ ሰአት ሲያልቅ ሥራን
ተሰናብቶት ወደሌላ የሕይወቱ ጉዳይ ይሄዳል። ማለዳ ደግሞ እንደምንም ሃይሉን አሰባስቦ
ወደ ሥራ ይገባል።
እንዲህ ላለ ሰው ሥራ ሌላ፤ ቤተክርስቲያን ሌላ፤ ወዳጅ ሌላ ይሆንበታል።
የሕይወት ጥሪውን ለይቶ አውቆ ምላሽ በመስጠት ያልተሰለፈ ሰው የሕይወቱን ጉዳዮች
ሁሉ የሚያይዘውን ዋና ነገር ባለመያዙ ነገሩ ሁሉ ብትንትን ያለ ይሆናል።

ጥሪ ምንድን ነው?
ጥሪ እግዚአብሔር አስቀድሞ ( አለም ሳይፈጠር) ወደ አዘጋጀልን ሕይወትና የሕይወት
አላማ እንድንገባ የሚደረግ ግብዣ ነው።
ለሰው ሁሉ እጅግ ዋና ከተባሉ ክስተቶች ሁለቱ የተወለደበት ቀንና የሕይወት አላማውንና
ጥሪውን ያውቀበት ቀን ነው።
የሕይወት አላማና ጥሪ በሰው የሚገኝ እንጅ በሰው የሚዘጋጅ አይደለም።
የአንድ ሰው የሕይወት ጥሪ በሉአላዊ አምላክ ሉአላዊ ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ነው።
ሉአላዊ አምላክ ማለት የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ፤ በፈለገው መንገድ የማንንም
ፈቃድ ሳይጠቅ የሚያደርግ ማለት ነው።
ይህን መረዳት ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ነው። ያልከው ይሁን ብሎ ተስማምቶ የልዑል
አምላክን እርዳታና ይሁንታ የሚያገኝ ሕይወት ለመምራት ይረዳል።
4
21 May 2023

የሌሎችንም ጥሪ ለማክበርና ለመቀበል ይጠቅማል።


የሰው ምርጫና የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት
እነዚህ ሁለት ነገሮች ሁልጊዜ ያወዛግባሉ። የእግዚአብሔር ልዓላዊነትን ከሰው ነጻ ምርጫ
ጋር ማነጻጸር እግዚአብሔርንና ሰውን በኩል መድረክ ላይ አቁሞ ማወዳደር ነው።
የአምላአክን ፍጹም የሆነ ነጻ ፈቃድ ከፍጡር ጋር ማሰተያየት አንችልም።
እርሱ የሁሉ ምንጭና ባለቤት ስለሆነ በፈጠረው ላይ የፈለገውን የማድረግ ሙሉ መብትና
ስልጣን አለው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡20 ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን
ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን?
የሰው ነጻ ፈቃድ በራሱ አለም የተገደበ ነጻ ፈቃድ ነው። የአምላክ ፈቃድ ግን ሁሉን አለም
የሚጠቀልል ፈቃድ ነው።
የሰው ነጻ ምርጫ በጊዜና በቦታ የተገደበ ነው። ስለሆነም ጊዜና ቦታ ሲያቆሙ ያቆማል።
የእግዚአብሔር ምርጫና ፈቃድ ዘላለማዊ ነው። በዘላለማዊ ክልል ውስጥ ያለ ነው።
ስለሆነም የሰው ነጻ ፈቃድ የተገደበ ነጻ ፈቃድ እንጅ ወሰንና ገደብ የሌለው ነጻ ፈቃድ
አይደለም። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ወዶና ፈቅዶ መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችለው
በገደብ ውስጥ ሆኖ ነው።
ለምሳሌ ሰው አልሞትም ማለት አይችልም። እስከሚሞት ድረስ ግን በምድር እንዴት
መቆየት እንደሚፈልግ መምረጥ ይችላል። ይህን እንኳ ማለት የሚችለው የእግዚአብሔር
እቅድና አላማ የማይነካ ከሆነ ነው። እግዚአብሔር ለሌላ ወገን ያለውን ፈቃድ የእኛ ነጻ
ፈቃድ የሚነካ ከሆነ በእግዚአብሔር ይጣሳል።
አምላካችን እግዚአብሔር ልዑአላዊ ስልጣኑ በፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ ነው።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29፡11 አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ
ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት
የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
12 ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ ኃይልና ብርታት
በእጅህ ነው ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው።
13 አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ፥ እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና
እናቀርባለን።
እዚህ ላይ አስደናቂ ጥበብ እንማራለን። እግዚአብሔር በሉዐላዊነቱ የወደደውን ሁሉ
ማደረግ የሚችል አምላክ መሆኑን መረዳት ብቻ በቂ አይደለም።
ዳዊት እንገዛልሃለን እንዳለ መገዛት ያስፈልጋል።
እግዚአብሔርን ማምለክ ማለት መንገዱን ፈቃዱን መከተል፤ የሰራውን ሁሉ በምስጋና
መቀበል ማለት ነው።
5
21 May 2023

የፈቃድ ሁሉ ምንጭ አብ ነው
የሐዋርያት ሥራ 1፡7 እርሱም፦ አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና
ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤
እዚህ ላይ ጌታችን መዳህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውነቱ ያልተሰጠው ድርሻ እንደሆነ
የሚያመላክት ነው።
የዮሐንስ ራእይ 4፡10-11 ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥
ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ
ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም
ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለፈቃዱ በፈቃዱ ፈጥሮታል። ባለሙሉመበት ነው። ባለቤት
ነው።
ለዚህ እውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን ሕይወትን መስጠት አምልኮ ነው። ምስጋናና ውዳሴ
ምንጫቸው ይሄ ነው።

እግዚአብሔር የያዘልህ ሃብት መክፈቻው ምንድን ነው?


እግዚአብሔር አምላክ የያዘልን ሃብት አለ። አብርሃምን ሲጠራው ይህን ነግሮታል።
ኦሪት ዘፍጥረት 12፡1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም
ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
ኦሪት ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን
አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ
ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
የእግዚአብሔር ቃል ለእኛም የተያዘ በረከት እንዳለ እንዲህ ይነግረናል።
1 ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና
ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት
6
21 May 2023

ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት
በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል
ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
ጥሪ ቁልፍ ነው!
አንድ ሰው ጥሪውን ሲያገኝ እግዚአብሔር አለም ሳይፈጠር ለእርሱ ያዘጋጀለትን ሁሉ
የሚያገኝበትን ቁልፍ አግኝቶአል።
2 ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥
ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤
ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
የዘላለም ሕይወት፤ በምድር የምንሆነውና የምናደርገው፤ በዘላለም የእግዚአብሔር አጀንዳ
ውስጥ ያለን ስፍራ ሁሉ በአምላክችን አስቀድሞ የተሰወሰነ ቢሆንም መግቢያው ግን ጥሪ
ነው።
ጥሪና የጸጋ ስጦታ የተለያዩ አለመሆናቸውን ተመልክተናል። ጸጋን መረዳት ወደ ጥሪያችን
ዘልቀን ለመግባት እጅግ ስለሚረዳን በሚቀጥለው የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጦታ
እንመለከታለን።
ጸጋን ምን እንደሆነ በሚገባ ተረድተን ጸጋውን በሕይወታችን መቀበል ስንችል ባለጸጋ
እንሆናለን።
ጸጋ የበዛለት እንሆናለን።

ጥሪንና ጸጋን መረዳት


ጥሪ በእግዚአብሄር ምርጫ ላይ የተመሰረተ ነው። አንድ ሰው የእግዚአብሔር ጥሪ
የሚመጣለት ከሰውየው ተፈጥሮአዊ ማንነት ተነስቶ፤ ወይም እምቅ ችሎታው ታይቶ፤

7
21 May 2023

ወይም ወደፊት ምን እንደሚሆን ታውቆ የዚያን ሰው ድብቅ አቅም ለመጠቀም


አይደለም።
ትንቢተ ኤርምያስ 1፡5 በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ
ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።
ለኤርምያስ ያለው አስገራሚ ነው። በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ማለቱ ሁለት ነገሮችን
ያስገነዝበናል። አንተ የእኔ እቅድና የእኔ ንድፍ ውጤት ነሕ። ገና ወደ እናትህ ማህጸን
ሳትመጣ ማን እንደምትሆንና ምን እንደምትሆን አቅጀሃለሁ። ለዚህ ሥራ የምትገጥም
እንድትሆን ታስበሃል።
በማህጸን እያለህ ገና ክፉና ደግ ሳታደርግ ለዚህ ስራ ለይቸሃለሁ። ስራህን አይቼ ሳይሆን
እንዲሁ በሉዓላዊነቴ ለዚህ ስራ ልይቼሃለሁ። አሁን ደግሞ ለአህዛብ ነብይ እንድትሆን
አድርጌሃለሁ።
ስለዚህ አንተ እኔ ነህ ያላልኩህን ነኝ አትበል።
ትንቢተ ኤርምያስ 1፡6 እኔም። ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና
እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ።
7 እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ። ወደምሰድድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥
የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና። ብላቴና ነኝ አትበል።
ጥሪና ጸጋ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፍላጎት መተግበሪያዎች ናቸው።
 ጥሪ እግዚአብሔር ወደወሰነው ውሳኔ ግብዣ ሲሆን፤ ጸጋ ደግሞ ለዚያ መብቂያ
ነው።
ለዚያ መብቂያ ነው ስንል ለመጠራት መብቃታችን ሆነ የተጠራንበትን ሆነን ለመገኘት
ምክንያቱ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው ማለታችን ነው።
እግዚአብሄር ጸጋውን የሚሰጠው ለተጠሩ ነው። የጠራቸውም በጸጋ ነው። የሚጠራቸው
የመረጣቸውን ነው። ሁሉም መመረጥም፤ መጠራትም፤ የተጠሩትን መሆንም በጸጋ ነው።
እንግዲያውስ ጥሪን መቀበል ጸጋን መቀበያ መንገድ ነው።
ጸጋ ማለት ያለ ዋጋ ከእኛ አስትዋጾ ሳይኖር (ስራ ሳይታከልበት) ማለት ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡4 ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን
ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።
5 እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ።
6 በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።
7 እንግዲህ ምንድር ነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን
አገኙት፤

ጥሪና የጸጋ ስጦታ የማይለያዩ ናቸው።


8
21 May 2023

ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


ጸጋ ከእርሱ የሆነ የእኛ የሚሆንበት፤ በጸጋ የእኛ በሆነው መልሶ እርሱ የሚከብርበት ስርዓት
ነው።
ዳዊት ይህን በመገንዘቡ ዘምኑን በከንቱነትና በድህነት አልጨረሰም።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29፡14 ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም
የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ
ማን ነው?
ይህን የዘላለም የሕይወት መንገድ ጳውሎስ ቁልጭ ባለ መንገድ አስቀምጦታል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡36 ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም
ክብር ይሁን፤ አሜን።

አስቀድሞ የመታውቅ አስደናቂ ምስጢር


ስድስቱ የፍጻሜ ሂደቶች
የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ በምናጠናበት ጊዜ ሰው እግዚአብሔር አምላክ ወደያዘለት
የክብር ፍጻሜ እንዲደርስ የተቀየሰለት መንገድ ወይም ሂደት አለ። እነዚህ ሂደቶች
የሚከተሉት ናቸው።
አስቀድሞ መታወቅ፤ መመረጥ፤ አስቀድሞ መወሰን፤ መጠራት፤ መዳን (መጽደቅ)ና መክበር
ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ
ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
30 አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን
ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።
2 ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም
እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ
ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
10-11 አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን
ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል
ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።
ኤፌሶን 1፡4-14 ይነበብ
በኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ላይ አስደናቂ እውነቶችን እንረዳለን
1 ኛ. መመረጥና መጠራታችን የተመሰረተው በሰዎች ውሳኔና ድርጊት ላይ ሳይሆን
ሁሉን አዋቂ በሆነው በእግዚአብሔር ምክር እንደሆነ
9
21 May 2023

2 ኛ. ይህ ውሳኔ የተወሰነው በፍቅር እንደሆነ። ማለትም እግዚአብሔር ይህን ውሳኔ


በሚወስንበት ጊዜ ፍጹም የሆነው የአምላክ ፍቅር እንደነበረ
3 ኛ. ያደረገውን ሁሉ ያደረገው የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ እንደሆነ። ይህ ማለት
መወሰናችንና መመረጣችን ከእኛ በተገኘ አንዳንች ነገር ሳይሆን እንዲሁ እንደሆነ
4 ኛ. ወንጌል ለተመረጡት የመዳን ወንጌል እንደሆነ

 ጥሪ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ሕይወትና ክብር


እንዲመጡ የሚደረግ ግብዣና ነው። ብለናል።
ምርጫ፦እግዚአብሔር ከብዙሃን መካከል የእርሱ እንዲሆኑ የፈለጋቸውን ግለሰቦች ወይም
ቡድኖች ለይቶ የሚወስድበት መንገድ ነው።
ስለሰው ፍጻሜ በምናይበት ጊዜ በተለይ መመረጥ፤ መውሰን መጠራት የሚሉት የመጸሐፍ
ቅዱስ ቃሎች እጅግ የተያያዙና ለመረዳት የሚከብዱ ናቸው።
የእግዚአብሔር ምርጫና ጥሪ መነሻው ሁለት ነገር ነው ።
 አንደኛው የእግዚአብሔር omnipotent love ነው። ወደርና ልክ የሌለው ፍቅር ነው።
መጥቶም የሞተው እስከመጨረሻው ስለወደደን ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 13፡1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት
ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ
ወደዳቸው።
ኦሪት ዘዳግም 7፡7 እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ
በዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤
8 ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥
ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ
አዳናችሁ።
እላይ እንዳየነው እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠበት ምክንያት በቁጥር ከሌላው ህዝብ
ብዙ ሆነው፤ ወይም ብርቱ ሆነው ወይም የሚወደድ ነገር ተገኝቶባቸው አይደለም።
እንዲያውም እስራኤል የዚህ ተቃራኒ ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 9፡25 እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥
ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ
26 እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር
ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
እግዚአብሔር በጎነትን የሚያደርግላቸው ለራሱ ደስ ስለሚለው ነው።

10
21 May 2023

ኦሪት ዘዳግም 28፡63 እግዚአብሔርም በጎ ያደርግላችሁ ዘንድ ያበዛችሁም ዘንድ ደስ ይለው


እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል፤
ትወርሱአትም ዘንድ ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ።
 ፍቅሩ ጽንፍ እንደሆነ ሁሉ እውቀቱም እንዲሁ ነው። የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር
የመረጣቸውን አስቀድሞ እንዳወቃቸው ያስረዳል።
1 ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:1-2 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ
አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም
ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም
ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
1Pet 1:1 Peter, an apostle of Jesus Christ, to the strangers scattered throughout Pontus,
Galatia, Cappadocia, Asia, and Bithynia,
2 Elect according to the foreknowledge of God the Father, through sanctification of the
Spirit, unto obedience and sprinkling of the blood of Jesus Christ: Grace unto you, and
peace, be multiplied.
ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ
ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
የሐዋርያት ሥራ 2፡23 እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ
ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።
Acts 2፡23 Him, being delivered by the determinate counsel and foreknowledge of God, ye
have taken, and by wicked hands have crucified and slain:
እግዚአብሔር አምላክ በሁሉን አዋቂነቱ ማን ጌታ ኢየሱስን እንደሚቀበልና ማን
እንደማይቀበል አስቀድሞ አውቆአል። አስቀድሞ ያወቃቸው ምን እንደሚሆኑና ምን
እንደሚያደርጉ አስቀድሞ ወስኖአል።
እግዚአብሔር አንዳንዶች እንዲጠፉ አንዳንዶች ደግሞ እንዲድኑ ወስኖአልን?
እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሁሉ የሚያደርገው ከባሕሪው በማይጻረር መልኩ ነው።
እግዚአብሔር ጻድቅና እውነተኛ ነው። እግዚአብሔር ቅንና ንጹህ አምላክ ነው።
ኦሪት ዘዳግም 32
4 እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤
መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤
የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥
እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።
የመረጣቸውን ሰዎች እግዚአብሔር ይጠራል። የመረጣቸው ሰዎች የተመረጡት በእርሱ
አምላካዊ ፍቅር ስለተወደዱና በእርሱ አምላካዊ እውቀት ስለታወቁ ነው።

11
21 May 2023

እግዚአብሔር አምላክ የሚጠራቸው አስቀድሞ ያወቃቸውን ነው ብለናል።


የእግዚአብሔር እውቀት ምሳሌ
ክዋክብትን ሁሉ በስማቸው ያወጣቸዋል
ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡13 የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው
ማን ነው?
14 ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን
አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?
25 እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።
26 ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው?
ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤
በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
Isa 40
26 Lift up your eyes on high, and behold who hath created these things, that bringeth
out their host by number: he calleth them all by names by the greatness of his might, for
that he is strong in power; not one faileth.
ወደ ዕብራውያን 1፡3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ
ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
ጽንፈ አለም ምን ይመስላል? ምንስ ያክላል የሚለውን ለመገመት የሚከተለውን ሳይንሳዊ
መረጃ እንመልከት
እርቀት
የጽንፈ አለም እርቀት በብርሃን አመት ይለካል
አንድ የብርሃን አመት 9.46 ትሪሊዮን ኪሎሜትር ነው።
መታየት የሚችለው አጸናፈአለም እርቀት
በጸሐይና በመሬት መካከል ያለው እርቀት 150 million km ነው።
እኛ ያለንበት ጋላክሲ milky-way የሚባለው ከ 200 እስከ 400 ቢሊዮን ክዋክብትን እንደያዘ
ይገመታል።
ከነዚህ ክዋክብት መካከል ጸሐይ አንዷ ናት። ጸሐይ ከመሬት ያላት እርቀት 150 ሚሊዮን
ኪሜ ሲሆን በዚህ ጋላክሲ ውስጥ እስከ 100000 የብርሃን አመት እርቀት ያላቸው ክዋክብት
አሉ።
የራሳቸው የሆኑ ፕላኔቶች ያሏቸው 3200 ክዋክብት በኛ ጋላክሲ ይገኛሉ። የእኛዋ ኮከብ
ጸሐይ ፕላኔቶች እንዳሏት ማለት ነው።
በአጠቃላይ
12
21 May 2023

የክዋክብት ብዛት በጽንፈ አለም


በሚታየው አለም (observable universe) ውስጥ ሁለት ትሪሊዮን ጋላክሲዎች እንዳሉ
ይገመታል። በእኛ ጋላክሲ በሚልክ ወይ እንኳ ብናየውና በትንሹ በአንድ ጋላክሲ ውስጥ
100 ቢሊዮን ክዋክብት አሉ ብንል
200 ቢሊዮን ትሪሊዮን ክዋክብት አሉ ማለት ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ስለእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት ሲነገርን እነዚህን ሁሉ በየስማቸው
ያሰማራቸዋል ይላል።
እግዚአብሔር ኢዮብን ምን እንዳለውው ስንመለከት የበለጠ እንደነቃለን። እግዚአብሔር
አምላክ ክዋክብት እንዳሉ ብቻ ሳይሆን የሚያውቃቸው የሚያሰማራቸውም እርሱ ነው።
መጽሐፈ ኢዮብ 38
31 በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥
ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን?
በአዲሱ መደበኛ ትርጉም
31“ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጕም፣
ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን?
32 ማዛሮት የተባለውን የከዋክብት ክምችት በወቅቱ 38፥32 ወይም በወቅቱ የሚወጣ
የንጋት ኮከብ ልታወጣ፣
ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ?
33 የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ?
ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?

ትንቢተ አሞጽ 5፡8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮከብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ
ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች
ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥
እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው ስንል ከዚህም ሁሉ ይልቃል።
ወደ ዕብራውያን 4፡13 እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና
የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔር እውቀትና ጥበብ በእኛ ውስን እውቀትና ጥበብ
በመለካት ምርጫውንና ውሳኔውን መመዘን አንችልም።
እጅግ ደስ የሚለው ነገር የእግዚአብሔር ምርጫና ውሳኔ ልክ እንደ እግዚአብሔር የጸና
ነው። አይሻርም አይለወጥም።
13
21 May 2023

ዛሬ የእግዚአብሔርን ምርጫና ውሳኔ ተረድተን ልባችን በእርሱ ሊያርፍ በመረጥንበትና


በተጠራንበት ጸጋ ደስ ሊለን በደስታና በምስጋና እግዚአብሔርን ልንከተለውና ልናገለግለው
ይገባል።

ጥሬዬን እንዴት እለያለሁ?


How I know my place?
ይህ ጥያቄ እንዲህ ቢቀመጥ ደግሞ ሌላ ጥሩ አሳብ ያጭራል። ስፍራዬን እንዴት
አውቃለሁ።
ጥሪ ስንል ለአንድ አላማ ተለይቶ መውጣትን የሚያሳይ ሲሆን ስፍራ ስንል ደግሞ
በእግዚአብሔር እቅድና አላማ ውስጥ የተሰጠንን ድርሻ፤ በሰዎች መካከል የተሰጠንን ቦታ
አመላካች ነው።
1. አጠቃላይ የሰውን ሕይወት አላማ መረዳትና መቀበል ነው።
እግዚአብሔር የአላማና የዕቅድ አምላክ ነው። የለአላማ የፈጠረው ፍጥረት የሚሰራው ስራ
የለም። ሁሉን ነገር ለአላማው አቅዶና አስቦ ያደርጋል። ይህን ደግሞ ለሰው ልጆች
መግለጥና ማሳወቅ ይፈልጋል።
14
21 May 2023

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡11 እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥
አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።
የፈቃዱ ምክር ማለት የእርሱ አላማ ማለት ሲሆን አስቀድመን የተወሰንን ማለት ደግሞ
የእርሱ እቅድ ማለት ነው።
እግዚአብሔር ያለመው ነገር አለ። ለዚያ እኔና እናንተን አስቀድሞ ወሰነን።
 የሰው ልጅ ሕይወት አላማ ምንድን ነው?
መጀመሪያ ይህ ጥያቄ ሳይመለስ የግል ሕይወት አላማ ጥያቄ ሊመለስ አይችልም።
እግዚአብሔር ሰውን ለምን ፈጠረው የሚለውን ለእስራኤል ከተናገራት ቃል መረዳት
እንችላለን
ትንቢተ ኢሳይያስ 43፡1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥
የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም
ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
በዚህ ስፍራ አንተን የፈጠርኩህ፤ ከዚያም የሰራሁህ፤ ከዚያም የተቤዥሁህና የጠራሁህ የእኔ
ስለሆንክ ነው ይላል።
ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሔር ነው። ይህ መሰረታዊ መረዳት ለሁላችንም እጅግ
አስፈላጊ ነው። እኔ የእግዚአብሔር ነኝ። አንተ የእግዚአብሔር ነህ። አንች የእግዚአብሄር
ነሽ።
ቀጥሎ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ስንመለከት ደግሞ እግዚአብሔር ለምን ፈጥሮ፤
ሰሮቶና አብጅቶ የእራሱ እንዳደረገን ይናገራል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:6-7 ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፦ አትከልክል፤
ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን
ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።
በስም መጠራት ማለት ቃልኪዳናዊ ትስስርን አመልካች ነው። ሚስት በባሏ ስም
እንደምትጠራ ለክብሩ የተፈጠረው ህዝቡም በእግዚአብሔር ስም ተጠርቶአል።
ሰራትና መደረግ ከምን ጋር እንደሚገናኝ አዳም ክላርክስ እንዲህ ይላል

I have formed him - ‫ יצרתיו‬yetsartiv. I have given him that particular


form and shape which are best suited to his station in life.
ለሕይወት ዘመኑ ቆይታ የተመቸ እንዲሆን አድርጌ የተለዬ ማንነትና ቅርጽ እንዲኖረው
የሰራሁት
I have made him - ‫ עשיתיו‬asithiv. I have adapted him to the
accomplishment of my counsels and designs.
ያድረኩሁት የሚለው የእኔን ምክርና የእኔን እቅድ መፈጸም እንዲችል አድርጌ ያዘጋጀሁት
ማለት ነው።
15
21 May 2023

ይህን ሁሉ ያደረገው ለአንድ ፍጻሜ ነው። ያ ፍጻሜ ክብሩ ነው።


እግዚአብሔር የፈጠረን፤ የሰራንና ያደረገን ለክብሩ ነው።
የተፈጠርከው ለእርሱ ደስታና ክብር ነው።
የአንተ ደስታና ክብር ያለው ለእርሱ ደስታና ክብር በመኖር ውስጥ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ስለጌታ ኢየሱስ ሲናግር እንዲህ ይላል።
ወደ ዕብራውያን 10፡7 በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል።
ስለአንተም የተጻፈ የሕይወት መጽሐፍ አለ። በዚያ እንደተጻፈ ፈቃዱን እንድታድረግ
ተወልደሃል።
መዝሙረ ዳዊት 139፡16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
 በዚህ ዘመናችን እግዚአብሔርን በሕይወታችን የምናከብረው የሰጠንን ስራ በመፈጸም
ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 17፡4 እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤

እኛ ደስ ያለንን ሳይሆን እርሱ የሰጠንን ስራ በምፈፍጸም ነው እግዚአብሔርን


በሕይወታችን ማክበር የምንችለው።
የወደድነውን ሳይሆን የታዘዝነውን ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለብን።
እርካታችን የእርሱን ፈቃድ መፈጸም መሆን አለበት
የዮሐንስ ወንጌል 4፡34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ
አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
John 4፡34 Jesus saith unto them, My meat is to do the will of him that sent me,
and to finish his work.

2. አንተ እንድትሰራው አስቀድሞ የተዘጋጀልህ ሥራ አለ።


ሥራ ፈላጊ እንጅ ሥራ ፈጣሪ መሆን አያስፈልግህም። የተዘጋጀልህ ስራ አለ ያን ማግኘት
ነው ያለብሕ።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ
ኢየሱስ ተፈጠርን።
በሞራልም በተግባርም መልካም እንድናደርግ እግዚአብሔር ያዘጋጀው መስመር አለ።

16
21 May 2023

በዚያ መወሰን ያስፈልጋል።


1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡17 ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ
ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ።
እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ
1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:20 እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ
ይኑር።
3. ስፍራ ተዘጋጅቶልሃል
የምትሰራው ስራ ብቻ ሳይሆን የት ሆነህና መቼ እንደምትሰራ ስፍራና ጊዜ ተዘጋጅቶልሃል።
ስፍራ ስንል አካላዊና መንፈሳዊ ስፍራ ነው።
አካላዊ ስፍራ ስንል የት አገር የትኛው የተለዬ ቦታ፤ በየትኛው አጥቢያ ቤተክርስቲያን
ማለት ነው።
መንፈሳዊ ስንል በክርስቶስ አካል ላይ የትኛው ብልት ነህ? በአካሉ ያለህ ስፍራ ምንድን ነው
ማለታችን ነው።
1 ቆሮንቶስ 12፡ 12-27
4. ስጋችንን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገን ማቅረብ

የእግዚአብሔርን ደስታና ክብር መፈጸም የምንችለው በእግዚአብሔር መሰዊያ ላይ


ሰውነታችንን ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገን ማቅረብ ስንችል ነው። ለእግዚአብሔር
መስዋዕት ሆኖ የቀረበ እንስሳ የእግዚአብሔር ነው።

ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡1 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን


እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ
ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ
የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
ለራሳችን ደስታና ለራሳችን ክብር እንጠቀምበት የነበረውን ሰውነታችን ለእግዚአብሔር
አገልግሎት ማቅረብ አለብን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 6፡13 ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ
ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት
እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ
የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
ወደንና ፈቅደን ባልሰጠነው እግዚአብሔር አይጠቀምም። ስለዚህ እንደተሰዋ መስዋዕት ይሄ
አንተ እንደምትወድ አድርገው። ወደምትወደው ምራኝ ማለት አለብን።
እግዚአብሔር አምላክ ጠርቼህ ነበር እምቢ አልክ ብሎ ሊፈርድብን አይፈልግም። ስለሆነም
እሽ የምንልባቸውን መነገዶች ዘርጎቶልናል።

17
21 May 2023

5. በአይምሮ መታደስ መለወጥ


ዳግመኛ ልደት የሚለውጠው መንፈሳችንን ብቻ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 3፡5 ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥
ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ
አይችልም።
6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
የአሁኑን አለም ባህል፤ አስተሳሰብ፤ እይታ፤ እሴት እንደያዝን ወደ እግዚአብሔር ጥሪ
መግባት ይቸግረናል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጥሪ ለዚህ አለም አስተሳሰብ ሞኝነት
ነውና።
ንጽረተ አለማችን መቀየር፤ ሕይወትን ከዘላለም አንጻር መመልከት ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር ስለሁሉም ነገር የሚለውን መረዳትና መቀበል አስፈላጊ ነው።
የአስተሳሰብ ለውጥ ሳይኖር የሕይወትን አላማ ማግኘት ከባድ ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም
የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ
እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Rom 12፡2 And be not conformed to this world: but be ye transformed by the
renewing of your mind, that ye may prove what is that good, and acceptable, and
perfect, will of God.
ይህ እንዴት ይሆናል?
 የፈቃዱ እውቀት
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡10 የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት
የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፤
Col 3፡10 And have put on the new man, which is renewed in knowledge after the
image of him that created him:
 አሮጌውን ትቶ አዲሱን መልበስ
ብዙ ሰው ካወቀ በኋላ በአሮጌው መኖርን ምርጫው ያደርጋል።
ኤፌሶን 4፡20 እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤
21 በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤
22 ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን
ሰው አስወግዱ፥
23 በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥

18
21 May 2023

24 ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን


አዲሱን ሰው ልበሱ።
6. ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የጠበቀ ሕብረት ይኑርህ
ጌታ ኢየሱስን መቀበል የእግዚአብሔር ልጅነትን ያስገኛል። በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ
ስፍራን ያስይዛል። ጌታ በተደጋጋሚ እርሱ በመጣ ጊዜ ታድርጋላችሁ፤ ትረዳላችሁ፤
ትችላላቹህ ብሎ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረው ሰው እግዚአብሔር ወደያዘለት ስፍራ
መግባት የሚችለውና ማድረግም የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ስለሆነ ነው።

ኦሪት ዘጸአት 31፡1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


2 እይ ከይሁዳ ነገድ የሚሆን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ
ጠርቼዋለሁ።
3 በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም
የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፤
እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን ነገር ማወቅም ሆነ ማድረግ የመንፈስ ቅዱስን እረዴት ፈላጊ
ነው። በሰው እወቀትና ጥበብ ልንደርስበት አንችልም።
ለምሳሌ እኔ በልጅነቴ የማነበውም የምሰማውም ስለሶቬት ሕበረት ወጣቶች፤ ስለ እነዩሪ
ጋጋሪ ነበር። ምኞቴና ፍላጎቴ ሳይንቲስት መሆን ነው። ከሳይንስም ውስጥ የህዋ ሳይንስን
ማጥናት።
በምንም ታምር ዛሬ እያድረኩ ያለሁትን ያኔ ልረዳው አልችልም፤ ልቀበለውም አልችልም።
1 ቆሮንቶስ 2፡7 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን
የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር
እንናገራለን።
8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ
የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤
9 ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው
እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
10 መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ
እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።
የሚያሳውቀንም የሚያሰማራንም እርሱ ነው
የሐዋርያት ሥራ 13፡2 እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦
በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።
3 በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።
መንፈስ ቅዱስ
19
21 May 2023

1. በልብ ብርሃን
2. በልባችን ውስጥ ከፍተኛ ፍላጎትና መሻት በመስጠት
3. በህልምና ራዕይ
4. በማረጋገጫዎች ይመራናል።

የጥሪ አይነቶች
የጥሪ አይነቶች ስንት ናቸው?

 አጠቃላይ የተመለሱ ጥሪ (General Call)፡ እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ


ክርስቶስ እንዲያምኑና ንስሃ እንዲገቡ ለአለም የሚያደርገው ጥሪ ነው።

የማቴዎስ ወንጌል 22:14 የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

የሐዋርያት ሥራ 17:30 እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው


ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤

 2 ኛው ጥሪ ለመንግስቱና ለክብሩ መጠራት ። ወይም የዘላለም ሕይወት ጥሪ ነው።


እግዚአብሔር ለአለም ሁሉ ያደረገውን ጥሪ የሚቀበሉ ለዘላለም መንግስት ክብር
ተጠርተዋል። በክርስቶስ ኢየሱስ ላለ ሕይወት ተጠርተዋል።

1 ተሰሎንቄ 2፡11-12; 2 ጢሞ 1፡9-11 ሮሜ 8፡ 29 -30 (Romans 1:6; 1


Corinthians 1:9)

 በክርስቶስ የቤዛነት ሥራ ተሳታፊ ለመሆን መጠራት (2 Corinthians 5:18-20;


Ephesians 4:1).
 ለተለዬ ሥራ ወይም አገልግሎት መጠራት ለምሳሌ as prophets, apostles,
pastors, teachers, etc. (Ephesians 4:11-12; 1 Corinthians 12:4-11).
 ለተለዬ ሁኔታ ወይም ወቅት መጠራት: .መከራን ፈተናን ስደትን ለመቋቋም
መጠራት (Philippians 1:29; Hebrews 11:8-16; 1Pet_4:13).

ለምንም ነገር የተጠራሁ እንደሆነ እየተሰማኝ አይደለም ምን ላድርግ?


20
21 May 2023

o ጥሪህ ገና ግልጽ ሆኖ ባይታይህም እግዚአብሔር ለአንተ ፍጻሜ ተስፋ


ይዞልሃል። (Proverbs 3:5-6; Jeremiah 29:11)
o እግዚአብሄር ያለአላማ እንድትኖር አላደረገህም። your existence has purpose
o በእርግጠኝነት ለመንግስቱና ለክብሩ ተጠርተሃል። ቤቱ ያለከው ለዚህ ነው።
ማንኛውም ጥሪ እንድታደርገው የሚጠበቀው ለጠራህ እግዚአብሔር እንደሚገባ መኖር
ነው።
ሁሉም ጥሪ መለየትን ይጠይቃል። ለእግዚአብሔር እንደሚገባ የምትኖረው
ለእግዚአብሔር በመለየት ነው። 1 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡11-12 ወደ መንግሥቱ
ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና
እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ
ሆንን ታውቃላችሁና።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡1 እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት
መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤
 ይህ ለአገልግሎት መለየት ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 1:1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ
አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።
 ይህ ደግሞ ለሕይወት መለዬት ነው
2 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡17-18 ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ
ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት
እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።
oየአንተን የተለዬ ተልዕኮ ባትረዳ እንኳ መርዳቱ ወደአንተ እስኪመጣ ድረስ በተገለጠው
የእግዚአብሔር ፈቃድ በእምነት ተመላለስ። ለሰው ሁሉ መልካም እያድረክ እግዚአብሔርን
እያከበርክ በእምነት ተሰማራ።
መዝሙረ ዳዊት 37፡3 በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥
በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
4 በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
5 መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም
ያደርግልሃል።
o ቀጣዩን ጥሪህን እንድታውቅ ጥሬየን እንዴት አውቃለሁ በሚለው ትምህርት ላይ
የተዘረዘሩትን እያደርግህ በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ እዚህ ላይ የተጠቀሱትን እየጠበቅህ
ቀጥል።
ቀጣይ
ጥሪየን ማግኘቴን ወይም ጥሬየን እየፈጸምኩ መሆኔን እንዴት አውቃለሁ?
በጥሪ እና በስራ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

21
21 May 2023

ጥሪየ ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዴት አውቃለሁ?


ጥሪያችን ከእግዚአብሔር መሆኑን እርግጠኛ መሆን እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። በተለይም
የተለዬ ስራ ለመስራት ወይም ለተለዬ ጊዜና ሁኔታ ራስን ለመስጠት እየተዘጋጀን ከሆነ
ስለጥሪያችን እርግጠኛ መሆናችን ለቀጣይ ጉዞአችን እጅግ ወሳኝ ነው።
ከይመስለኛል ወደ እርግጠኛነት ካልተሸጋገርን ፈተናዎችንና ተገዳሮቶችን ተቋቁመን የቤት
ስራችንን መወጣት አንችልም።
አንዳንድ ጊዜ ጥሪ እከሕይወት መስዋዕትነት ሁሉ ይጠይቅ ይሆናል። ጥሪውን የተቀበለው
ከእግዚአብሔር እንደሆነ እርግጠኛ ያልሆነ ሰው ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ይከብደዋል።
ሐዋርያት ሥራ 20፡24 ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን
አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ
ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።
ጥሪያችን ከእግዚአብሔር መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለመረዳት
o ጥሪህ ከእግዚአብሔር ቃልና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚስማማ መሆኑን
አረጋግጥ
22
21 May 2023

ቃሉን የሚቃራን ከእግዚአብሔር ባህሪይ ጋር የማይስማማ ነገር እንድታደርግ እግዚአብሔር


አይጠራህም። የእግዚአብሔርን ቃል እያጠናህና እየጸለይክ ጥሬዬ ይሆንን ብለህ እየጠየቅህ
ያለሁ ነገር ከእግዚአብሄር አላማና ከእግዚአብሔር መርህ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ፈትን።
 ጥሪህ ከስጦታህና ከውስጣዊ ፍላጎትህ (passions) ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን
መርምር።እግዚአብሔር አምላክ ለጥሪህ የሚያስፈልግህን የተለየ ተስጥኦ፤ ችሎታ፤
ክህሎትና የማድረግ ፍላጎት ሰጥቶሃል።
ኦሪት ዘጸአት 31፡1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
2 እይ ከይሁዳ ነገድ የሚሆን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ
ጠርቼዋለሁ።
3 በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእዚአብሔርን
መንፈስ ሞላሁበት፤
o ጥሪህ ፍሬ እያፈራና ለሌሎች በረከት እየሆነ መሆኑን አረጋግጥ። የእግዚአብሔር
ጥሪ ሁሉ ለሌች በረከት ይሆናል። ለእግዚአብሔር ክብር ያመጣል።
o የእግዚአብሔር ጥሪ አንተን ማዕከል ያደረገ አይደለም። የምትጠራው ለሌሎች
ነው። ከእነርሱ የሚመጣ ግብረ መልስ በተላክበት ስፍራ ላይ መሆንህን አመላካች ነው።
ግብረ መልስ ማለት ለእነርሱ ጥያቄ መልስ ያለህ፤ መፍትሄና መጽናናት የምታመጣ መሆንህ
o የእግዚአብሄር አብሮነትና ምሪት መኖሩን አረጋግጥ። እግዚአብሔር ለጠራህ ነገር
እግዚአብሔር አብሮህ ይሰራል።
ጥሬየ ሰዎች ከእኔ ከሚጠብቁት የተለዬ ቢሆንስ?
( መጠራቴን ባይቀበሉ ወይም ጥሬየን ባይርዱስ?)
የሐዋርያት ሥራ 7፡25 ወንድሞቹም እግዚአብሔር በእጁ መዳንን እንዲሰጣቸው
የሚያስተውሉ ይመስለው ነበር፥ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።
ስዎች ከእኛ የሚጠብቁትን በተመለከት በተለይም ከእኛ ጥሪ የራቀ መጠበቅ ካላቸውና ይህ
ጠበቃቸው ከመስመር የሚያስወጣን ከሆነ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ አለብን።
1. ተጠሪነታችን ለእግዚአብሄር መሆኑን መገንዘብ
የሐዋርያት ሥራ 5፡29 ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ
ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
ጥሪ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ጉዳይ ነው። የፈጠረን፤ የተፈጠርንበትን አላማ
ያዘጋጀልን፤ የዋጀንና ለተለዬ ስራ የጠራን እግዚአብሔ ነው። ለጠራን ሥራ
የሚያስፈልገውን ስጦታና ችሎታ የሰጠን እርሱ ነው። መስማትም መታዘዝም ያለብን
እርሱን ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 5፡34 እኔ ግን ከሰው ምስክር አልቀበልም፥ እናንተ እንድትድኑ ይህን
እላለሁ እንጂ።

23
21 May 2023

የዮሐንስ ወንጌል 5፡41-42 ከሰው ክብርን አልቀበልም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር


በራሳችሁ እንደ ሌላችሁ አውቃችኋለሁ።
2. ጥሪህን ለሌሎች በአክብሮትና በግልጽ አካፍላቸው። ለአንተ ቅርብና አስፈላጊ ለሆኑ
ጥሪህን አካልፍል። ለቤተሰብህ፤ ለውዳጆችህ፤ ለቤተክርስቲያንህ፤ ለመንፈሳዊ
መሪህ።
እንዴት ጥሪህን እንዳወቅ፤ እንዴት በጥሪህ ለመኖር እንደወሰንክ መግለጽ ትችላለህ።
ከእነርሱ የሚመጣውን ጥያቄና መልስ አስተያዬት መስማቱ መልካም ነው።
ጥሪን ለማሳወቅ መታዬት ያለባቸው ዋና ዋና ነጥቦች
 ለማን ነው የማሳውቀው፦ ለእስራኤል ሽማግሌዎች ( ሙሴ)
 መቼ ነው የማሳውቀው፦ ዮሴፍ ገና በልጅነቱ ለወንድሞቹ አለግዜው

ነህምያ፦
መጽሐፈ ነህምያ 2፡12 በሌሊትም ተነሣሁ፥ ከእኔም ጋር አያሌ ሰዎች ነበሩ፤
እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም
አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ
አልነበረም።

13 በሸለቆውም በር ወጣሁ፥ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጕድፍ መጣያው በር


ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን
ተመለከትሁ።

14 ወደ ምንጩም በርና ወደ ንጉሡ መዋኛ አለፍሁ፤ ተቀምጬበትም የነበረው


እንስሳ የሚያልፍበት ስፍራ አልነበረም።

15 በሌሊትም በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትሁ፤ ዘወርም ብዬ በሸለቆው


በር ገባሁ፥ እንዲሁም ተመለስሁ።

16 ሹማምቱ ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤


ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹማምቱም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት
ለሌሎች ገና አልተናገርሁም ነበር።

17 እኔም፦ እኛ ያለንበትን ጕስቍልና ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት


እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ፤ አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና
የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ አልኋቸው።

18 የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል


ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።

24
21 May 2023

19 ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ ባሪያውም አሞናዊው ጦብያ፥ ዓረባዊውም ጌሳም


በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፥ ቀላል አድርገውንም፦ ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድር
ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን? አሉ።

20 እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን


እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት መታሰቢያም
የላችሁም አልኋቸው።
o ነህምያ ጥሪ የመጣለት ስለኢየሩሳሌምና በዚያ ስለሚኖሩ አይሁድ በሰማ ጊዜ
ነው።
o መጀመሪያ ነገር መጾምና መጸለይ ነው
o ሶስተኛ የነገሩን እውነተኛ ነገር መሬት ላይ ያለውን እውነታ እርሱ ራሱ
መረዳት ነው።
o አራተኛ ለአለቆች ያዬውን ጥፋትና መከራ እነርሱ እንዲገነዘቡ ማድረግ
o አምስተኛ ለዚህ ስራ እግዚአብሔር እንዴት አብሮት እንዳለ ማሳየት ነው
 ምን ያህል ነው የማሳውቀው፦ ሙሴ
ሙሴ ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔር ጥሪ የገባው ቢሆንም እግዚአብሔር ሊልከው
የተገለጠለት ግን በሽምግልና እድሜው ነው።
ኦሪት ዘጸአት 3፡15 እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ ለእስራኤል ልጆች
እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ
የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥
እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
ኦሪት ዘጸአት 3:16 ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፦ እግዚአብሔር
የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ፦ መጐብኘትን
ጐበኘኋችሁ፥ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
17 ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ
ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር
ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ በላቸው።
ለሰዎች ጥሪያችንን ስናካፍል መለኮታዊ አብሮነቱን የተረዳንባቸው ማረጋገጫዎች
ያስፈልጉናል።
 ነህምያ ጥበቃና አቅርቦት
 ሙሴ ድንቅና ታምር

25
21 May 2023

መሾምና መቀባት
ጥሪያችን ያለእኛ ምንም አስተዋጽኦ በእግዚአብሔር ነጻ ምርጫ ወደ ተመረጥንበት የከበረ
ሕይወትና ፍጻሜ የሚደረግ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ
አይጸጸትምና።
መወሰንም መጠራትም መመረጥም የእግዚአብሔር ጸጋ ውጤቶች ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡5 እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ
ቅሬታዎች አሉ።
ከሰው የሚጠበቀው ምላሽ መስጠት ብቻ ነው።
ለእግዚአብሔር ውሳኔና ጥሪ ከምስጋናና መሰጠት ጋር ምላሽ ስንሰጥ እግዚአብሔር ወደ
ተወሰነልና ስፍራና ወደተወሰነልን ጸጋ ያስገባናል።
ይሾመናል፤ ለተሾምንበት ስፍራ ሃይልን፤ ጥበብን፤ አቅምን የሚሰጠንን ጸጋ ይሰጠናል።
ለሕይወት ይቀባናል፤
2 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡21 በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን
እግዚአብሔር ነው፥
1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡20 እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም
ታውቃላችሁ።
1John 2፡20 But ye have an unction from the Holy One, and ye know all things.
1 ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡27 እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ
ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ
ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥
እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
( ይህ ቅባት የምንኖርበት ቅባት ነው)
ለቤት ስራችን ይቀባናል።
1 ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡12 ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል
የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤
ለተጠራንበትና ለተሾምንበት ስፍራ የሚሆን ኃይል ( ቅባት) እግዚአብሔር በአደራ
ይሰጠናል።

26
21 May 2023

1Tim 1፡12 And I thank Christ Jesus our Lord, who hath enabled me, for that he
counted me faithful, putting me into the ministry;
ኃይል የሰጠኝን የሚለው ቃል፡ 1743 endunamoo en-doo-nam-o'-o ሲሆን የተገኘው (from 1722 and
1412; to empower:--enable, (increase in) strength

) dunamoo doo-nam-o'-o ብርታት ጥንካሬ ችሎታ ማለት ነው። ኢንዱናሞ ሲሆን


ብርቱ፤ ጠንካራ፤ አቅም ያለው ማድረግ ማለት ነው።

ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ለተለዬ አላማ የጠራቸውንና ሐዋርያት


ብሎ የሾማቸውን ኃይልን ሳትቀበሉ አትውጡ ብሎ የኃይሉን ሚስጢር አብርቶላቸዋል።
የሉቃስ ወንጌል 24፡49 እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ
ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።
Luke 24፡49 And, behold, I send the promise of my Father upon you: but tarry ye
in the city of Jerusalem, until ye be endued with power from on high.
የሕይወታችን ስኬታማነትና ውጤታማነት በእነዚህ ሁለት ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው
1 ኛ መጠራታችን ሁለተኛ endowed መደረጋችን።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡9 ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን
የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ
እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤
10-11 በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
12 ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን
በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን
አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ
ዘንድ እንለምናለን።
ከዚህ የተነሣ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር የፈቃዱን
ዕውቀት በመንፈሳዊ ጥበብና መረዳት ሁሉ ይሞላችሁ ዘንድ ስለ እናንተ
መጸለይና መለመን አላቋረጥንም፤ 10 የምንጸልየውም ለጌታ እንደሚገባ
እንድትኖሩና በሁሉም ደስ እንድታሰኙት ነው፤ ይኸውም በመልካም ሥራ ሁሉ
ፍሬ እያፈራችሁ እግዚአብሔርን በማወቅ እያደጋችሁ፣ 11 ታላቅ ጽናትና
ትዕግሥት ይኖራችሁ ዘንድ፣ እንደ ክቡር ጕልበቱ መጠን በኀይል ሁሉ
እየበረታችሁ፣ ደስ እየተሰኛችሁ፣ 12 በቅዱሳን ርስት በብርሃን ተካፋዮች
ለመሆን ያበቃንን 1፥12 ወይም ያበቃችሁን አብን እንድታመሰግኑ ነው። (አዲሱ
መደበኛ ትርጉም)
ይህ ከእግዚአብሔር ሲሆን
ከእኛ ለጥሪው የእሽታ ምላሽ ለኃይል ስጦታው ደግሞ ታማኝነት ያስፈልጋል።

27
21 May 2023

ጳውሎስ ለጥሪው ከደምና ስጋ ጋር ሳይማከር ሙሉ በሙሉ ፍጹም የሆነ ምላሽ አደረገ።


የተሰጠውንም ኃይል ደግሞ ለተሰጠበት አላማ አሟጥቶ በመጠቀም ታማኝ ሆነ።
ዛሬ እግዚአብሔር ላሰማራን ነገር ሁሉ የሚሆንን ኃይል ይሞላብናል።
እግዚአብሔር በፍጹም ክርስትና ሕይወታችንንም ሆነ የቤት ስራችንን በራሳችን ብቃት
እንድናደርገው ሸክም አልሰጠንም።
ይህን ብንማር ሁላችንም መልካም ነው።
እግዚአብሔር እኛን በኃይል ሲያስታጥቀን የተሰጠንን ኃይል ለተሰጠን አላማ በሰጠን
እውቀት፤ ጥበብ፤ ጊዘና አካል የቻልነውን ያህል መጠቀም ያስፈልጋል።

28

You might also like