You are on page 1of 10

የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

10
www.tlcfan.org 0
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

የሐሰት ነቢያት ሕጎች

ዘዳ.18፥20-22 ላይ በድፍረት እግዚአብሔር ሳይናገረው ስለሚናገር ነቢይ፣ በሌላ ጌቶችና

መሪዎች (አማልክት) ሥምና ግፊት የሚናገር ነቢይ እንዲገደል የሚያዝ የእግዚአብሔር ሕግ እናገኛለን።

ይህ ነቢይ ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑ የሚታወቀው የተናገረው ነገር እንደ ተናገረው ካልሆነ ወይም ካልተፈጸመ

ነው።

ሥም የሌለው ለዔሊ የተገለጠው ነቢይ እውነተኛ ነቢይ እንደ ሆነ እንመለከታለን

ምክንያቱም የተናገረው በሙሉ አንድ በአንድ ተፈጽሟልና ነው። ስለዚህ የነቢይ ቃል የእግዚአብሔር ቃል

ነው እንጂ በመላምት የሰውን ልብ ትርታ እያዳመጡ የሚነገሩት ትንቢት አይደለም። ነቢዮ የተናገረው

ቃሎች ካልተፈጸሙ እግዚአብሔር ይህን ነቢይ እንዳላከው እግዚአብሔር ይህን ነቢይ እንዳልተናገረው

እናውቃለን። በብሉይ ኪዳን ይህ የሐሰት ነቢይ ትንቢቱ ሳይፈጸም ሲቀር የአገልግሎቱም ሆነ የሕይወቱ

ማብቂያው ነበር።

በዘዳግም 13 በሙሉ ስለዚህ ስለ ሐሰተኛ ነቢይ የጠለቀ ትምሕርትና መለኮታዊ ስርዓት

የተሞላ እውቀትን እናገኛለን። በዚያ ስፍራ በዘዳግም ምዕራፍ 18 ካየነው ቃልና ውሳኔ ባሻገር ይህ ነቢይ

በእግዚአብሔር እንዳመጸ ምዕራፍ 13 ላይ ያለው ቃል ያመለክታል። "because he has counseled

rebellion against the Lord your God." በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔር ትኩረቱን ያደረገው ነቢዩ

ተናግሮ ሕዝቡን ሌላ አምላክን እዲያመልኩ ካደረገ የሚለው ሃሳብ ላይ ነው። “2. እንደ ነገረህም ምልክቱ

ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም

ቢልህ፥..” ይህን በቁ. 2 ና 13 ላይ እናገኘዋለን።

ይህን ከዚህ በኃላ በምንመለከተውን የእግዚአብሔር ሕግ ብርሃን የእውነትን እምነት

እንቀበላለን። የእግዚአብሔር ሕግ ሁሉ ከአሥራት በስተቀር ሁሉ እንደ ተሻረ የሚያምኑ ሰዎች ግን

ፈጽመው ሕግንና በሕግ ውስጥ ያለውን እምነት ሊያገኙና ሊረዱት ፈጽመው አይችሉም። የእግዚአብሔር

ሕግ እንደተሻረ የሚያምን እርሱ ከመጀመሪያውኑ ክርስቲያን ነው ለማለት እኔ አልደፍርም። ሕጉ ሕያው

ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ሕጉን ለደቀመዛሙርቱ እንደተረጎመላቸው ሕጉ ሊተረጎምልን ግን የግድ

አስተፈላጊ ነው። ሕጉ በአሁን ዘመንም ሆነ በሚመጣው አለም ሕያው ሆኖ የሚሰራ ነው። ነገር ግን ሕጉን

በተግባር ስናውለው እንደ ብሉይ ኪዳን ዘመን ፊደል በፊደል አይደለም።

www.tlcfan.org 1
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

ሰው ለእግዚአብሔር ሕግ ልቡን ከዘጋ በዚያ ስፍራ ላለው ብርሃን ራሱን ይደብቃል

ወይም በጨረማ ይኖራል። በሕጉም ውስጥ የተሰወረውን ሚስጢር፣ እምነትና ብርሃን ያጣል። ከዚህም

የተነሳ የእግዚአብሔር ሕግ ነፍሱን አይመልስለትም፣ ለመንገዱም ብርሃን አይሆንለትም። ስለዚህም

ጉዞው የጨለማ ጉዞ እምነት የለሽ ይሆናል ማለት ነው።

በጥቅሉ ሰው ሕጉ እንደተሻረ ሲያምን ሕጉን ማጥናትና መመርመር ያቆማል። ይህ የብዙ

የዘመኑ ክርስቲያኖችም ችግር ይህ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህም የተነሳ ብዙዎች ሕጉን በልባቸው ሊጽፍ

ወደ ምድር የመጣውን መንፈስ ቅዱስ ሲያሳዝኑ ይኖራሉ። ከዚህም የተነሳ ከሕጉ ጀርባ የተሰወረውን

ሕይወት ከማግኘት ይጎድላሉ። ይህ ደግሞ እንደ ሕዝበ እስራኤል በምድረበዳ መቅረትን ወደ ርስት ገብቶ

ከመውረስን መጉደልን ያስከትላል።

የእግዚአብሔር ሕግን እይታንና ፍቺን ከኢየሱን ቃል በወንጌል ላይ መመልከትም

እንችላለን። ማቴ.4፥4 ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ቃል ሁሉ የእኛ መኖሪያና ሕይወታችን ነው። ይህ

ከእግዚአብሔር የሚወጣው ቃል 613ቱን ሕግጋት ደግሞም የነቢያቱን ሕግንም የሚያጠቃልል ነው።

ኢየሱስ ራሱ የሚያስተምረው የትምሕርቱ መሰረት ያደረገው የሕይወቱንና የኑሮው መሰረት ያደረገው

ሕጉን ነው። ደግሞም ብዙ ጥቅሶችን ለማስተማር የጠቀሰው ከሕጉ ላይ ነው። ዘዳ.8፥3 ሰው ሕጉ ቢያጠና

እንኳን አሁንም እንደሚሰራ ካላመነ እግዚአብሔር በውስጡ ያለውን ሚስጢር ይደብቅበታል።

እንግዲህ እግዚአብሔር እንደረዳኝና እንደገለጠልኝ መጠን ከዘዳ.13፥1-2 በመነሳት

የሐሰት ነቢያትን ሕግ እንመለከታለን። ይህን በትክክል ከተረዳን ደግሞ ሐሰተኛና እውነተኛ ነቢያትን

የመለየትን እውቀት እንቀበላለን።

“1. በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም

ቢሰጥህ፥ 2. እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን

የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንከተል እናምልካቸውም ቢልህ፥”

አንዳንድ ሰዎች ነቢዮ ያልተናገረው ቃል ሳይፈጸም ሲቀር ነቢዮ ሐሰተኛ ነው በሚለው

ቃል ላይ ያለልክ ያተኩራሉ። ይህም ሃሳባቸው በዘዳ 18 የተመሰረተና ትክክለኛነትም ያለው ነው። ነገር

ግን የነቢያትን ሕግ በጠቅላላው ካላየነው ሙሉ የሆነ መረዳትን ማግኘት አንችልም። ስለዚህም ብዙዎች

በዘዳግም 13 በቁጥር አንድና ሁለት መጀመሪያ ላይ ያለውን ሃሳብ ካለማስተዋል የተነሳ ይስታሉ።

www.tlcfan.org 2
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

ይህም ተአምርና ምልክትን ነቢዮ ማሳየቱን ነው። የተነገረው ሲፈጸም ደግሞ ትክክለኛ

እውነተኛ ነቢይ ነው ካሉ እንደ እግዚአብሔር ሕግ መሰረት አማኞች ይስታሉ። ምክንያቱም

የእግዚአብሔር ሕግ ተዓምርና ምልክትን እንደተናገረው የሚሆንለት ሰው ሁሉ እውነተኛ ነቢይ

አይደለምና ነው። በዘዳግም 13 ላይ ያለው ነቢይ ትምሕርቱን ያመጣው ተዓምራትና ምልክንት ካደረገ

በኃላ ነው። ምልክትና ተዓምር ደግሞ ውጫዊ የሆነ ማረጋገጫ ነው።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ እየተናገረን አንድ ነቢይ ተዓምራትንና ድንቅ እያደረገ

ቢመጣ ነገር ግን ሌሎች አማልክትን እንድታመኩ፣ እንድታገለግሉ፣ በልባችሁ ያልውን ጣኦት

እንድትከተሉና የሥጋችሁን ምኞትና ሃሳብ እንድትከተሉ ቢናገር እርሱ ሐሰተኛ ነቢይ ነው ይለዋል። ዛሬ

ብዙውን ጊዜ ምዕመን የሚታለለው በተዓምራትና ድንቅ ነው። ከዚያ በኃላ የተሰበከውን የሃሰት

ትምሕርት ሁሉ ዝም ብሎ ይጠጣል። የሚነቃው ባዶ ሲሆን ነው። ደግሞም ልናስተውለው የሚገባው

ምድራዊ በረከት ሆነ የሥጋ ፈውስ መቀበል ወደ መንግሥቱ የመግባት ቁልፍ አይደለም ወይም

መግባታችንን አያረጋግጥም። ፈሱን የተቀበለው ሰውም ሆነ ፈውሱን ያመጣው ሐሰተኛ ነቢይ ሁለቱም

በውጭ ሊቀሩ ይችላሉ።

“በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን

አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም፦ ከቶ

አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች (Lawlessness | ሕግ የለሾች) ፥ ከእኔ ራቁ ብዬ

እመሰክርባቸዋለሁ።” ማቴ.7፥22-23

ቃሉ በዘዳግም እንዲህ ብሎ ይቀጥላል፦ ቁጥር.3 “ አምላካችሁን እግዚአብሔርን

በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር

ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስማ።”

በዚህ ስፍራ ደግሞ እግዚአብሔር እነዚህን የሐስት ነቢያትን እራሱ እንደላካቸውና

ተአምራቸውና ድንቃቸው እንዲሆንም የፈቀደው እግዚአብሔር እንደሆነ ያሳየናል። ተዓምርና ድንቅ

ሰሪው እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሲሻው በሐሰተኛ ሲሻው በእውነተኛ ነቢይ ድንቅና ተዓምራቱን

ይሰራል። ይህን በሐሰተኞች ነቢያት የሚደርገው ሥራው የሚያደርገው እኛ አማኞችን ይፈትነን ዘንድ

እንደሆነ እግዚአብሔር ተናገረ።

www.tlcfan.org 3
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

እግዚአብሔርን እንወደው፣ እንታዘዘውና ፍቃዱ ትዕዛዛቱን እንዳደርግ እንደሆነ ሊፈትነን

ይህን የመሰለ አሰራሩን በፊታችን ያሳልፋል ይልካል። እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያብራራዋል፦ ቁጥር 4

“3. አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥

እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።”

በዚህያን ዘመን ከእግዚአብሔር ሌላ ሌሎች አምላኮችን፣ ሃይማኖቶችን፣ ጣዖታትን

እንዲያመኩ የሚፈታተኑ ሐሰተኛ ነቢያቶች አሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እንዳችም እንዲህ አይነት

ስብከት በግልጽ የሰበኩ ነብያቶች አናገኝም። ነገር ግን በዚያን ዘመን ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚደግፉ ብዙ

ሃሳቦችንና ታሪኮችን በቃሉ ውስጥ እናገኛለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፈው የምናገኛቸው ብዙ የነቢያቶች ታሪክ ወይ መቅደሱንና

እግዚአብሔር ወግነው ወይም የሚቀልባቸውን ንጉስ ወግነው ስለሚናገሩ ነቢያት ብዙ ታሪኮችን

እናገኛለን። እውነተኞቹም ሆኑ ሐሰተኞቹ በቃሉ ውስጥ ነቢያት ተብለው ተጠርተው እናገኛቸዋለን።

ማቴዎስ.7፥15 ላይ ኢየሱስ ግን ሃሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንዳሉ ከእነርሱም ልንጠበቅ

እንደሚገባ በግልጽ ይናገራል።

ሐሰተኛ ነቢይ ማለት እንግዲህ የተናገረው የማይሆንለትም ማለት አይደለም። ሐሰተኛ

ነቢይ እግዚአብሔር ሳይልከው ልኮኛል የሚል ደግሞም እግዚአብሔር ሳይልከው እግዚአብሔርን ወግኖ

ሐስት ምስክርን የሚናገር፣ እግዚአብሔር ሳይለው እግዚአብሔር ብሎኛል ብሎ በድፍረት የሚናገር ነው።

ደግሞ ይህ አይነቱ ነቢይ ከአስርቱ ትዕዛዛት መካከል በዘጠነኛውም ይወድቃል። ይህም በሃሰት

አትመስክር የሚለው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር በመካከላችን ታምራትንና

ድንቅ እያደረገ ሕግ የለሽ ስብከት ስለሚሰብከው ከእግዚአብሔር ተልኪያለው ለሚለው ሰው አቋማችን

ዛሬ ምንድን ነው?

ከእግዚአብሔር ያልተላኩ ናቸው ማለት አንችልም። ምክንያቱም ሐሰተኞቹንም ጭምር

የላካቸው እግዚአብሔር ነው። ከላይ በቃሉ እንዳየነው እግዚአብሔር እንደላካቸው ሃላፊነቱ ራሱ

እግዚአብሔር ይወስዳል። ነገር ግን የሚስሩት ታምራት ትላልቅ ሆኖ የሚያስተምሩንና ስለ ቃሉ

የሚመሰክሩልን ምስክር ግን ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። የሚናገሩት ቃል፣ የሚመሰክሩት ምስክር ፣

በዘመናችን የሚወስኑት ውሳኔና የሚናገሩብን ትንቢት የእግዚአብሔር ሕግና ፍቃድ ጋር የሚጻረር ነው።

www.tlcfan.org 4
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

ከእግዚአብሔር ጋር እድንጓዝ እርሱ እንዳለ እሱን እንድንፈልግ፣ ትዕዛዙን እንድናድርግ

፣ እርሱን ወደ መፍራት የሚያመጡን አይደሉም። “ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉም

በጣዖቶቻቸው ከእኔ ተለይተዋልና የእስራኤልን ቤት በልባቸው እይዝ ዘንድ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን

በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ

እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው። ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ

በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ፊታችሁንም

ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ። ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች የሚሆን፥

ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ፥ ስለ እኔ

ይጠይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር በራሴ እመልስለታለሁ፤ፊቴንም በዚያ ሰው ላይ

አደርጋለሁ ምልክትና ምሳሌም አደርገዋለሁ ከሕዝቤም መካከል አጠፋዋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ

ሆንሁ ታውቃላችሁ። ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥

እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ

እንደሚጠይቀውም ሰው ኃጢአት እንዲሁ የነቢዩ ኃጢአት ይሆናል።” ሕዝቅኤል.14 ”ታዲያ ምን

ማድረግ አለብን?

ይህ አይነት የሐሰት ነቢያት ካጋጋታ በእርግጥ የልባችንን ማንነት ሊገልጥ የተገለጠ ታልቅ

ፈተና ነው። እውነት ነው እግዚአብሔር ልባችንን ምን ያሕል በጣኦታት እንደተያዘ አስቀድሞ ያወቀዋል።

የራሳችን ልብ ራሳችንን ያስተናል። ይህም ደግሞ በሆነ ጊዜ በንስሃ ወደ እግዚአብሔር መመልስ ታላቅ

ማስተዋል ነው። ወደ መንግሥቱ ለመግባት ንስሃ ታልቅ ጅማሬ ነው። ደግሞም ዛሬ ከተዓምራት ይልቅ

ከአገልጋዬች አፍ የሚፈሰው ቃል ላይ ትኩረትን ማድረግ ይጠበቅብናል። የእግዚአብሔርን ቃል እና እንደ

እግዚአብሔር ቃል የሚናገረውን ብቻ በልባችን ልናስተናግድና ልንደግፍ ይገባል። በአይን ከሚገባ ነገር

ይልቅ ወደ በጆሮ አልፎ ወደ ልብ በሚገባው ላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ሁላችን አማኞች ይገባናል።

በምድረ በዳ ሕዝበ እስራኤል በዓለ አምሣን ያደረገበት ዋናው ምክንያት እግዚአብሔር

በልባቸው ያለውን ሊፈትን ስለወደደ ነው። “አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን

ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት

በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ። ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት

እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥

አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።”ዘዳ.8፥2-3

www.tlcfan.org 5
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

እስራኤል ሁሉ ከሁለቱ ልዮ መንፈስ ከተቀበሉት ከካሌብና ኢያሱ በቀር በፈተናው ሁሉ

ወደቁ። ከዚህም የተነሳ በፈተናው የወደቁ ሁሉ ከምድረ በዳ ወደ ከንዓን እንዳይዘዋወሩ ተደረጉ።

ስለዚህም በዚያው በምድረ በዳ ወድቀው ቀሩ። ደግሞም የመንግሥቱ ምሳሌ ወደ ሆነችም ከንዓን

ምድር ገብተው እዳይወርሱ እረፍንም እንዳይቀበሉ ተደረጉ። ምንያቱም በፈተና ወድቀዋልና

እግዚአብሔር እንዳይገቡ በቁጣው ማለ። እርሱ ባቀረበልን ፈተና ስንወድቅ ቃል ካወጣ አላውቃችሁም

ካለ አላውቃችሁም ነው። ነገር ግን ቅሬታዎች በድል ነሺዎቹ ኢያሱና ካሌብ ስርዓት ኑሮና በእግዚአብሔር

ሕግ ተገርተው ያደጉት ትውልዶች ግን ገብተው ከነዓንን ወረሱ። ምክንያቱም ልባቸው ከእግዚአብሔር

ቃልና ሕግ ጋር አንድ አድርገው ነበርና ነው።

የዘዳግም 13 ዋና ትምህርት የትክክለኛ ነብይ ማንነት መለኪያ ተዓምርና ድንቅ

አለመሆኑ እንድናውቅ የሚያደርግ ታላቅ ሕግ ነው። ተዓምርና ድንቅ ከእግዚአብሔር በማንም በኩል

ወደ ሕዝብ ሊመጣ የሚችል ነገር እንደሆነም እንድናውቅ ነው። ዋናው የሐሰተኛ ነቢይ መለያው

ከአንደበቱ የሚወጣው ሕግ የለሽ የሐስት ምስክሩ ነው። ሰው ከእግዚአብሔር ቃል በተዓምርና በድንቅ

ሊወሰድ ይችላልን? ሰውስ እግዚአብሔርንና ሕጉ ይወዳል ወይስ ተዓምርንና ድንቅን? ዋናው የትኛውን

ከየትኛው እንደምናስቀድም ማወቅ ነው።

ምልክትና ድንቅ መልካም ነው። ሐሰተኛም ሆነ እውነተኛ ነቢያት ሊያደርጓቸው ደግሞ

ይችላሉ። ዋናው ትኩረት ሊደረግበት የተገባው ግን የሚያስተምሩት ትምህርታቸው፣ ከአንደበታቸው

የሚወጣው ምስክር ቃል፣ እግዚአብሔር ሳይናገር እዛው ቆመው ከመቀጽበት ታሪክ እንደተናገራቸው

በሃሰት ፈጥረው የሚሰክሩት እንደ ጭንቁር የሚባላው ቃላቸው ነው።

ዛሬ በዚህ ዘመን ክርስቲያን ተዓምርና ድንቅ ለማየት ባሕር አቋርጦ ይሄዳል። ነገር ግን

የእግዚአብሔር ቃል ለመማርና ለመስማት መንገድ የሚሻገር ሰው የለም። ተዓምር ያስጨፍራቸዋል ቃል

ግን ይሰለቻቸዋል እንቅልፍ እንቅልፍ ይላቸዋል። ተዓምርና ድንቅ የእግዚአብሔርን ችሎታ ሲያሳይ

በትምህርት የሚገለጥ የእውቀት ቃል ግን የሕይወት መንገድን ይሳያል ሕይወትን ይለውጣል፣ አማኙን

ለበለጠው ክብር ለመንግሥቱ ወራሽነት ያዘጋጃል። ዘዳ.13፥5 “5. አምላክህ እግዚአብሔር ትሄድባት

ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ፥ ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ

ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ያ ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን

ነገር ከመካከልህ አርቅ።”

www.tlcfan.org 6
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

ይህ አይነቱ ሐሰትን የሚያስተምር ነቢይ እንዲገደል እግዚአብሔር ያዛል። ይህም የሰራው

ተዓምር ትክክል ስላልሆነ አይደለም። የሚገደለው ስለ ሕግ የለሽ እግዚአብሔርያዊ ሰላልሆነው

ትምህርቱና ስለ ሃሰት ምስክሩ ነው። እየሱስ ስለ ሃሰተኛ ነቢያት ሲናገር በግልጽ ያመለከተው ሕጉን ነበር።

ማቴ.7፥22-23

“22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ

አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23 የዚያን

ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች[anomia].፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

" (22) Many will say to Me on that day, 'Lord, Lord, did we not prophesy in Your name, and in
Your name cast out demons, and in your name perform many miracles?' (23) And then I will
declare to them, 'I never knew you; depart from me, you who practice lawlessness" [anomia].

አኖሚያ የሚለው ቃል የመነጨው ኖሞስ ከሚለው ቃል ሲሆን ኖሞስ ማለት ደግሞ

ሕግ ማለት ነው። ሕግ የለሽነት በብሉይ ኪዳን ትልቅ ችግር ነበር። ከመስቀሉም በኃላ በአዲስ ኪዳንም

ቢሆን ይህ አልተቀየረም። ሕጉን በራሳችን ሕይወት ስናየው እያንዳዳችን በግላችን ከአሮጌው

ከመጀመሪያው አዳም የወረስነው ማንነታችን ራሱ በሕይወታችን የሐሰትን ትንቢት ሲተነብይ

በውስጣችን ወይም በሃሳባችን ተቀምጦ ያገኘዋለን። ስለዚህ በውስጣችን ያለው ይህ የአሮጌው ሰው

ራሱን የቻለ አሳች ነብይ ነው። ይህ ማንነት ሊገደል ሊሞት ሊሰቀል ይገባዋል። ጳውሎስ ራሱ በሕይወቱ

ውስጥ በማንነቱ ውስጥ ይህ ሕግ የለሽ ሕይወት ገጥሞት ነበር። ሮሜ.ም.6 ና7

“12 እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤ 13

ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን

ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም

የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።”

"I am speaking in human terms because of the weakness of your flesh. For just as you
presented your members as slaves to impurity and to lawlessness [anomia], resulting in
further lawlessness [anomia], so now present your members as slaves to righteousness,
resulting in sanctification."

www.tlcfan.org 7
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

ዮሐንስ ደግሞ ሦስተኛ ምስክር ይሆንልናል፦ 1 ዮሐ 3፥4 “4 ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን

[anomia] ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ [anomia] ነው።”"Everyone who practices sin also
practices lawlessness [anomia]; and sin is lawlessness [anomia]."

ሃጢያት ማለት እግዚአብሔር ያዘዘውን ትዕዛዝ ሕጉን አለማድረግ ወይም አለመታዘዝ

ነው። ሕግ የለሽነት መሆን ደግሞ ሕግ የለም ተሽሯል ብሎ ከእግዚአብሔር ትእዛዛት፣ ፍቃድና ቃል ውጭ

መኖር ፣ ማናገር እና ማድረግ ነው። በጥቅሉ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ በፊቱ መስሎ

እንደታየው ሲኖር ነው። ስለዚህ ሐሰተኛ ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር ሕግና ፍቃድ ውጭ የሚያስተምር፣

ከእውነተኛ የእግዚአብሔር ቃልና ፍቃድ ሰዎችን በተዓምሩና በመገለጡ የሚያርቅ፣ የሚያስት፣ ከታላቁ

የእግዚአብሔር ጥሪ ላይ የሰው ልጆችን አይን በጊዚያዊው በሚታየው ነገር የሚያነሳ ሰው ሁሉ ነው።

“ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፤ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ

እርሱ ጅራት ነው።” ኢሳያስ.9፥15

በሃሰት የሚያስተምር ነቢይ የዘንዶው ጅራት ነው። ስለዚህም በሴቲቱ አዕምሮ ላይ

ያለው 12 የመግዛት ስልጣን አክሊል ጎትቶ የሚጥል። ሰዎች ከመንግሥቱ ግዛት ካለው ሕይወትና

አስተሳሰብ እንዲጎድሉ የሚያደርግ ነገር ነው። “ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር

ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።”ራእይ.12

ሃስተኛ ነብያት የሰይጣን አፈሙዝ ናቸው።

ስለዚህ የሐሰተኛ ነቢይ መለኪያው የሚሰራው ተዓምራትና የሚያስወጣው አጋንት

አይደለም። የሚያስተምረው እግዚአብሔር ቃል ትምህርት እንጂ። ስለዚህ ዛሬ የነቢይነት ፀጋ

የተሰጠንም እንደ እግዚአብሔር ሕግ፣ ፍቃድና ቃል መናገራችን እንዘንጋ። ከቃሉ አትለፍ የሚለውን ከእኛ

ተማሩ እንዳለ ጳውሎስ ከቃሉ እንዳናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን። አለበለዚያ እግዚአብሔር በሕዝቅኤል

ምዕራፍ 14 ላይ እደተናገረ ጊዜውን ጠብቆ በእኛም ላይ ፍርዱን ያመጣል። ስለዚህ ሃሰተኛ ነቢይን

የምናመልጠው ከምንሰማው ነገር በመጠበቅ በምናየው ነገር ከመወሰድ ራሳችንን በመጠበቅ ነው።

የእግዚአብሔር ፈተና የምናልፈውን ሁሉ ለድል ነሺዎች ትምህርት ቤት የበቃን ሰዎች ያደርገናል። ማየት

ምስማትን አይቀድምና ከምንሰማው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባል።

“ለበለጠ እውቀት የነቢያት ሕግ የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ።

www.tlcfan.org 8
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጎች #10

www.tlcfan.org 9

You might also like