You are on page 1of 2

እግዚአብሔር እንዴት ሊባርከን ይችላል ?

19፤ዕሺ፡ብትሉ፡ለኔም፡ብትታዘዙ፥የምድርን፡በረከት፡ትበላላችኹ፤ 20፤እምቢ፡ብትሉ፡ግን፡ብታምፁም፥ሰይፍ፡
ይበላችዃል፤የእግዚአብሔር፡አፍ፡ይህን፡ተናግሯልና፦ ት ኢሳ 1 ፥ 19

እግዚአብሔር እንዴት ክፉ ስራችንን ሊባርክ ይችላል ? አይገናኝም የእግዚአብሔር በረከትና ክፉ ስራ ! ።


የእግዚአብሔር ስራ ማዳን እና ፈውስ ነው ፤ ክፉ ተግባራችንን ባረከው ማለት አከሸፈው ወይም ደግሞ እንደ ማኑሔ
የሞት ደብደዳቤ ቀየረው ማለት ነው ። ነገር ግን እኛ ክፉ ስንሰራ እግዚአብሔር እንዲያከሽፍብን አንፈልግም። ስለዚህ
የእግዚአብሔር በረከት ቀርቶ የሰይጣን እርግማን በዛ ክፉ ተግባራችን ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ ፈቅደናል ማለት ነው ።

ለምሳሌ ስርቆትንን እንይ ። የተሰረቀን ነገር እግዚአብሔር አይባርክም ፤ ሊባርክም ከቶ አይችልም ፤ ውሸትን ይናገር
ዘንድ ሰው አይደለም እርሱ ! ። የተንኮል ነገር ፈጽሞ አይስማማውም ። ህብረት የለውም ከጨለማ ስራ ጋር በቃ! ።
ያንን የተሰረቀ ነገር ባረከው ማለት ግን ያ የተሰረቀን ነገር ለባለቤቱ መለሰው ማለት ነው ! ይሄ ነው የእግዚአብሔር
ቡራኬ !። ቅን ፣ ደግ ፣ ገር ማድረግ ። በእርግጥ የተሰረቀ ባይሆን ኑሮ ያንን ነገር እግዚአብሔር ሲባርከው ደግ ፣ ቅን ፣
ገር ስለሚሆን ይስማማል ለተጠቃሚው ! ይትረፈረፋል ፣ ሰላም ፣ ጤና ፣ ደስታ ፣ ፍቅር ፣ በረከት ድህነት ይሰጣል።
አሁን ግን የተሰረቀ ነው ፤ ደግሞም እንዲመለስ የሰረቀው ሰው "ሌባው " ስለማይፈልግ የእግዚአብሔርን ቡራኬ
ከልክሏል ማለት ነው! ፤ ስለዚህ ያንን ነገር ክፉው ነው የሚረግመው ። እንዲያሳምም ፣ እንዲያሰቃይ ፣ እንዲያደኸይ
፣ እንዲያከስር ፣ እንዲያበሳጭ ፣ እንዲያሳዝን .. በአጭሩ ወደ ጥፋት እንዲወስደው አጥፊው ይረግመዋል ። የሰረቀው
ሰው ያንን ነገር ሲጠቀም ህመም ወይም እርግማን ይሆንበታል ማለት ነው ። ምርጫችን ነው ። ክፉን በሚፈልግ
ክፉው ይመጣበታል። ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል ። አነሆ እሳትንና ውሀን በፊትህ አደርጋለሁ እጅህን ወደ ወደድከው
ስደድ ፤ ተብሏልና።

ሳኦል የአህዛብን ምርኮ በተጠቀመ ግዜ

አንድ ወታደር የምርኮ ንብረት በወሰደ ግዜ እርም እንደሆነባቸው

ለምሳሌ ዝሙት፤ አንዴት ሴት ከባለቤቷ ተደብቃ ከአንድ ሰው ጋር ዝሙት ለመፈጸም ብትመኝ ፤ እግዚአብሔር ይሄንን
ግንኙነታቸውን ፈጽሞ አይባርክም ። በዚህ ጊዜ ይህን ግንኙነታቸውን እርሱ ባረከው ማለት ፤ ይህን ስራ እንዳይሰሩ
ከለከለ ማለት ነው ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነችና ይህን የረከሰ ስራ ፣ የስጋ ፈቃድ
የሚፈጸምበትን ፤ ራስ ወዳድነት የነገሰበትን ፣ ከስነ ምግባር ውጪ የሆነ ክፉ ተግባር እንድትሰራ እግዚአብሔር ተባባሪ
ከቶ ሊሆን አይችልም ፣ አንድም በገዟ ባሏ ላይ የሚፈጸም በደል ነውና ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ስራ ጋራ ምንም ህብረት
አይኖረውም !። እነርሱም ይህ ግንኙነት እንዲፈርስ ስለማይፈልጉ ፤ የእግዚአብሔርን ቡራኬ በዚህ ተግባራቸው
ውስጥ ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ከልክለዋል ማለት ነው። ክብር እና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁንና ፤ እነሆ በደጅ
ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምጼን ቢሰማ ቢከፍትልኝም ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱ ጋራም እራት እመገባለሁ ያለውን
አምላክ የልባቸውን በር እግዚአብሔር ተግባሮታቸውን እንዲባርክላቸው ሊከፍቱለት አልወደዱም ማለት ነው። ያ
የሁለቱ ሰዎች ግንኙነት ለክፉ ነው ወይም የሁለቱ ሰዎች ግንኙነት በራሱ ክፉ ነው ። ስለዚህ አጥፊው በቀላሉ
ይረግመዋል ማለት ነው ። ክፉ ሀይል በግንኝነታቸው ውስጥ ስላለ በቀላሉ እርግማን ወደ ሰዎቹ ህይወት ዘልቆ
ይገባል ማለት ነው ፤ እግዚአብሔር ይማረን !። በመሆኑም የህይወት ዘመናቸውን አልፎ ተርፎም ወደ ትውልድ
ሊሸጋገር የሚችን ክፉ የእርግማን ሀይል በዛ ግንኙነት እነዛ ሁለት ግለሰቦች ይሸምታሉ ማለት ነው ።

እንደዚሁ ሰው በሀጢአት ኑሮ ውስጥ የእግዚአብሔርን በረከት መጠበቅ አይኖርበትም ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን


በረከት ፈልጎ የከለከለው ነገር ወይም እምቢ ያለው ነገር ስለሆነ። ማንኛውም ከእግዚአብሔር ትእዛዛት ውጪ የሆኑ
ክፉ ተግባራት በሚፈጸሙበት ግዜ ክፉው ሀይል ህይወታችንን ሊረግም በቀላሉ ሊገባ ይችላል ። የምናደርገው
ተግባር ክፉ ከሆነ ፤ ወደ ህይወታችን ዘልቆ ሊገባ የሚችል በረከትን የሚከለክል ክፉ የእርግማን ሀይል በውስጡ
እንዳለ በዚህ ልንገነዘብ ይገባል!። ከመጽሀፍ ቅዱስ በበረከት ውስጥ ያለፉትን ብንመለከት አብርሀም ትልቅ ምሳሌ
ነው !። በ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደምናገኘው አብርሀም በእግዚአብሔር ፊት እንደሚመላለስና ፍጹምም እንደሚሆን ፤
ማለትም የእግዚአብሔርን ትአዛዛት ሙሉ በሙሉ እንደሚፈጽም በግንባሩ ወድቆ ሰግዶ ስላረጋገጠ ከእግዚአብሔር
ታላቅ በረከትን ተቀብሏል ፣ ሚስቱም ዘሩም ተባርኳል። ኦሪ ዘፍ 17 ፣ መጽ መቃ 36 ፥ 3
በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የእርግማን ሀይል ወደ ህይወታቸው ዘልቆ ከገባባቸው መካከል ደግሞ ሳኦል ትልቅ ምሳሌ
ነው ። ለእግዚአብሔር አልታዘዝም ወይም ደግሞ ክፉ ነገር እፈጽማለሁ ባለበት ጊዜ የሚያስጨንቅ ክፉ መንፈስ
እየመጣ ያሰቃየው ነበርና። ቅዱሱ ዳዊትም በገና እየደረደረ ያባርርለት ነበር።

የጠፋው ልጅ ታሪክ ( ክፉ ተግባር እጽማለው ወይም ደግሞ ፍቅር ከሆነው የእግዚአብሔር ትእዛዛት እንወጣለን
ካላችሁ እራሳችሁን ከእቅፉ እንደለያችሁ ቁጠሩት ፤ ራሳችሁን ለክፉ አጋልጣችሁ ነው የሰጣችሁት !። እነሆ ከኔ
የሚቆረጥ ዛፍ ሁሉ ይደርቃል ወደ እሳትም ይጡሉታል፤ እሳቱ በምድርም በሲኦልም ነው!። እግዚአብሔርን ማጣት
ሲኦል ማለት ስለሆነ።

ስጡ ይሰጣችኋል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር !።

ፍጹም መልካሙ ሚያዚያ : 2012

You might also like